ye_abrsh | Unsorted

Telegram-канал ye_abrsh - 💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

-

የአብርሀም ተክሉ ግጥሞች ቻናል ለአስተያየት @Abrham_teklubot ይጠቀሙ

Subscribe to a channel

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ሰላም የምወዳችሁ በአብሮ ቆይታችን እየተደሰታችሁ እንደሆነ አምናለው ።

ግጥሞቼን ስለምትታደሙልኝም አክብሮቴ የላቀ ነው እስኪ ስራዎቼን ሼር በማድረግ ቤተሰባችንን እናብዛ ።

🙏🙏🙏🙏
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ፀሎተ ገና

ፊኛ...ማንነቶች
ማንም ...እየነፋ
የሚወጥራቸው
ለገባሽ ሆዳቸው
የሚዘላብዱ ...
በመላ አካላቸው...
እግዜር ሰርቶ...ሰርቶ
ሰይጣን የነፋቸው
የደም ጅረት መኋል ...ሀሴት የሚያደርጉ
ምድር ቋያ ስትሆን ...
አየር ተወጥረው ፥ ሰማይ የሚያረግዱ
ነጥረው...
ነ
ጥ
ረ
ው
ነጥረው
ቀን የጎደለ ቀን ...በሳር የሚጎዱ
ለእስላም ...ለክርስቲያን
ለሴት ወይ ለወንዱ
ከማንቧቸር ሌላ ፥ ምንም ያልፈየዱ
ንፍፊታም ፊኞች .... ለገና ይፈንዱ !!!

#አብርሃም_ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

#ድኩም_ምርጫ

ሰው ሲኖረው እንጂ ፥ ነብስ ሲዘ'ራበት
ብቻውን ኦና ነው ፥ተክል እና ዳገት
ሰው ነው ያገር ጥንሱ
ሰው ነው ያገር ዳሱ
ሀገር የት ይቆማል ፥ ሰብ እያፈረሱ ?

ብዬሽ እንዳልነበር
ብል በልቶት ጭንቅላት
አልቅት ጎጠኝነት ፥ ተጣብቶን ለቅጣት
ማዘን ተጠይፈን
ከገቢሩ ዘለል ፥ አዳም ላወረሰን ፥ የሰውነት ቅንጣት
ከሰው ሰው መረጥን
ከጣትም ልዩ ጣት !!

ፐ !!!
#ም_ይ_ም_ና

#አብርሃም_ተክሉ
ጳጉሜ / 4/ 2013 ከምሽቱ 3:00
አዲስ አበባ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ወደው አይስቁ

የውልሽ..... አንቺዬ
በታዳሚያን ፊት ፥ አንዱ ወግ አዋቂ
ዲስኩር ሲሰካካ
እራሱን ኮርኩሮ ፥ አንቺም እንድትስቂ
አላውቃት
አታውቀኝ
የነቀዘ ሰብል ፥ መች እኔን ሊደንቀኝ
ከሁሉም አጣላኝ ፥ አምላክ ሊታረቀኝ
ብሎ ክትክት አለ...በሳቁም ገደለኝ ።

በኔና በሱ ቤት
ድንግል ጎልማሳ አገር ፥ በእድሜዋ ማምሻ
በደባ ተደፍራ
ወልዳ ታርፍ ዘንዳ
አምሮቷ እያደገ
ሽታ እየነቀሰ ፥ በህዝብ እየሰፋ
ተስፋ ተገዝግዞ ፥ ሰበዙ ሲለፋ
ቀዩ ሰው ሲጠቁር
ጥቁሩ ሰው ሲከፋ
እንደ ሁሉ አገርሽ
እንደ እንደልቡ
ሁሉ እንደሞላለት
የጭንቅን አቀበት
በመታበይ ጉልበት
ለመውጣት ማሰቡ ፥ በራሱ ይደንቃል
ድሮስ ሹማምንቷ
የልመና ስንዴ ፥ መቼ በልቶ ያውቃል ?

አብርሃም ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ መልካም በአል ይሆንላችሁ ዘንድ ምኞቴ ከልብ❤️ ነው

☪☪☪ ኢድ ሙባረክ ☪☪☪

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_Teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

#__ቁዝም....

የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ
እኩል አይታይም
ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ።

እያረፋፈደ
የሚገለጥ ሰማይ
ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ
ጨክኖ መጨከን የተለማመደ
የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ
ነጋ...ነጋ ...ባዩ
ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ።

ወ
ረ
ደ
መአቱ
ክንትው ....አለ ስንቱ
ሺ ዘመን ቢኖሩ ...
ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ
የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ
ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ
ክ
ፋ
ቱ
ይገርማል !!!

በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ
ፅልመት ያው....ፅልመት ነው
ተገባም ....ተወጣ
ሁሉን ይጋርዳል
ከነጭ ጥርስ ኋላ
የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል
እውነት የሚመስል
ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል
የተወለደም ዘር
ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል
ቀመሩ ያልገባው
ልቡ የታወረ
ኗሪ እንደ ደረጃው
ለእግሩ ጧፍ ያነዳል
ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ...
ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል
እንዲ ነው ክፉ ቀን
ይሄ ነው ጨለማ
ይህ ነው ሰንካላ እድል
እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል
ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል
ይህ ነው እርኩስ ወራት
ይህ ነው ብላሽ እድል
ምንም ማለት ማቃት
ምንም ማድረግ መሳን
ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል
ዳሩ ቀን ሲጎድል
ቀን ሲጥል ቀን እንጂ
ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ?
የት ችሎስ ይፈርዳል !!!

#አብርሀም_ተክሉ

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

#ያኔ_ነበር_እንጂ

በሀያኛው ዘመን ፥ በተቃጠለዉ
ሚጠብሰው ሳያጣ ፥ የሚያቃጥለዉ
ካንዱ ቤት ፥ አንዱ ቤት ፥ እያካለበዉ
ተፈጃጁ ብሎ ፥ ባላገሩን ሁሉ ፥ ማን እሳት ሰጠዉ ?

#አብርሀም_ተክሉ

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

የከናፍር እድሜ

በሽርፍርፍ ሰአት
በቀን ግርዶሽ ጥላ
ጣት ያቆላለፈ
የእርምጃዎች ኬላ
አይን ውስጥ ሰው ፍለጋ
ልብ ተስፈንጥሮ ጎድኑን ሲወጋ
ትንፋሽ ተመጋግቦ
መጣጋት ተስቦ
ገቢር መደምድሙ
ከንፈር እና ከንፈር የመሰላለሙ
ፓ..........................መጣሙ
መች እንዴት ይረዳል ...
ሳያቅፉ
ሳይስሙ ።


አብርሀም ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ትላንት
ሀገር ወዳድ ጅግና
እፍኝ መሬቷን ባዕድ እንዳይረግጠው
ሰላቶና ባንዳ
የፈጨው ብርጭቆ እግሩን እየላጠው
በቆመህ ጠብቀኝ ...
የቆመን አጨደው ።

ድልም ተቀዳጀ
አርበኛ ዘ ሀገር
በጦር በጎራዴ
በምንሽር ጓንዴ
በድንጋይ በዱላ
በቋጥኝ በቢላ
የሚወድቅ ወደቀ
የሚሞት ተቀላ

ወራሪም ተቀጣ
አህጉር ነፃ ወጣ !


ዛሬ...
በሰሜን ኤርትራ በሙሉ ሻለቃ ከነሜካናይዙ
በምዕራብ ሱዳን....ከነ ኮተት ጓዙ
ዘልቆ ገብቶ ባገር ህዝቤን እያመሰው
አድዋን ሻቢያ ይዞት እያተራመሰው
አማን ኢማን ብሎ ሲረጋ ወንበሩ
ነገን ላየ ዜጋ ያስፈራል ነገሩ ።

አብርሀም ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

#ዝክረ_ቫለንቲኖ

በሮማኖች...አገር
ይሄውልሽ #ውዴ...በፊት ድሮ ድሮ
ሴት ሴቱን ሲከተል ፥ በዘቡ ተማሮ
ንጉስ... #ክላውዲዎስ
ለክተት ዘመቻ....
#ልጄን #ሚስቴን...በሚል ስስት እያነቀው
እንዴት ነው ጦረኛ ፥ ላገር የሚወድቀው ?
ብሎ ስለራደ...
ተባእቱን ሁላ.... ከተራክቦ አገደ
አሻፈረኝ ያለ .. #ሰማዕቱ_ቄስም
በንጉሱ ፈቃድ ስለተናደደ
#እስከተቀላበት...ህይወቱ እስካለፈ
በሚስጥር ፥ ስንቱን ጥንድ ፥ አጋብቶት አረፈ
እናም ዛሬ ዛሬ.......ባገርሽ ፣ ባገሬ
ቀይ....ቀዩ #ነገር ......እየተማገደ
ቫለንቲኖን ማሰብ ....ስለተለመደ
ምን ከኔ ባትኖሪ...
የት እንደሆንሽ እንኳን ፥ ባይጠረጠርም
ግራ ጎኔን #ለራት...ለደስታው ባልቀጥርም
እስክትመጪ ድረስ
#በቀይ ደምቄ........ቤቴን አሸብርቄ
አንቺ መናፈቄ
አስቤሽ መዝለቄ
በ ከማን አንሼ...እንዲያው ለነገሩ
ከማላውቀው አገር ፥ የነበሩት አባት ፥ እንዲህ ሲዘከሩ
ለማላውቅሽ አንቺ
#happy_valentine ...
የተባለ ምኞት ፥ ምኑ ላይ ነው #ነውሩ?

" #Happy_valentine_my_Love "
( #ባለሽበት_ቦታ 💕💕💕💕💕💕)

✍ አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)

2012

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ባልቀረ

ቅንጣት ዘሩን ውጦ ፥ ጨቅላ የሚያፈልቀው
ከመቼ ወዲያ ነው
የሴት ልጅ አከላት ፥ በመስጠት ያለቀው ?
በ90 አመቱ ፥ ስጋው ተሸብሽቦ ፥ ዘሩ ያላረጠው
ከመቼስ ወዲያ ነው
የወንድ ልጅ መቅኔ
ለሴት በማደግደግ ፥ ወዙ የሟጠጠው ?
ከመቼስ ጀምሮ
የጥንዶች ፍንጠዛ ፥ መሬት የከበዳት ?
እንዲያውም ተመቻት
አፈር ባፈር ዝላይ ፥ ኩርማኗን ይዞታ ፥ ለቤት አስወደዳት
አንቺ እንካ....በመደብ
እንቺ እንካ...በቁሙ
እንቺ እንካ ቀን በቀን
እንቺ እንካ በሌቱ
ለሰው ልጅ ፣
ለእፅዋት ፣
ላዋፍ ፣ ለአራዊቱ
የመጀባበቱ
ስንክሳር ቢበዛው
አልጋቤት ቢወደድ...
ምግብ እና መጠጥ ፥ ሰማይ ቢንተራስም
እቀምስ ላለው ጃል ...ኑሮ ባያቀምስም
ፍቅር እርካሽ ነው...
ከመዋደድ በቀር ፥ ወረት አይዳብስም
ዝም ብሎ መዋደድ
ከሚወዱት መክረም ፣
በፍቅር መታከም
በውድ መታረም ፣
እድሜን ማነባበር
ዘር ሀረግ መከመር
እንዲያ ነበር አዳም ፥ መሆን የሚገባው !!!
ስራውን ወጥሮ
እሾሁን ላጣሪው ፥ መተው እንዲረባው ።
እርሻውን መረሽረሽ
ከብቶቹን ማስባባት
ሚስቱን ማቀማጠል
ለዶሮዎች ጥሬ... ለፍየሎች ቅጠል
ጭድና ገለባ ... ለቡሬ እና መጋል
ካዳረሰ ኋላ
መልካም ሚስቱን አቅፎ ፥ ሰውነቷን ማጋል
ውሀ...ውሀ እያሉ ፥ ተጣምሮ መጠማት
አካል አወዳጅቶ ፥ በገላ መቃዳት ፥ በገላ መጠጣት
ተያይዞ መርካት... ለታመኑት መውጣት
እንዲህ ነበር መልኩ
እድሜና ክራሞት
አያዉቁን ፈትፍቶ ... አያውቁት ከመሞት ።


✍ አብርሃም ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

አይንሽ

ኮከብ የፈሰሰው
ጋላክሲ የወረሰው...ጠረፍ ይመስለኛል
አይንሽን እያየው...
ከባህር ነብስሽ ውስጥ ፥ መጥፋት ያሰኘኛል

አሳ ነው አካሌ
ባንቺ ተንቦራጭቆ ፥ ሲርቅሽ የሚሞት
መሳቅሽ ወተት ነው ፥
መከፋትሽ ሀሞት
ነይልኝ አለሜ
የቀን መዋለ ዜና ፥ የዕኩለ ሌት ህልሜ ።

አብርሃም ተክሉ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

~~~ አትነካኪኝ ይቅር ~~~

ገጣሚ ፦ አብርሃም ተክሉ

ለቅንብሩ ፥ ሙሌ ዛይን አመሰግናለው🙏


@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ክቡራት እና ክቡራን የግጥም ጥዋዬ እድምተኞች በመጀመሪያ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በመቀጠል እስከዛሬ ስለነበረን ቆይታ እያመሰገንኩ ነገንም አብረን እንደምዘልቅ በማመን ለተሻለ ጥንስስ ይረዳን ዘንዳ እስከዛሬ ከታደማችሁት የግጥም ጥዋ የተሰማችሁን ማንኛውም ግላዊ አስተያየት ለመቀበል ዝግጁ መሆኔን ስገልፅ በደስታ ነው ።
❤️ አንብቡ
❤️አድምጡ
❤️ተመሰጡ
❤️ኮምቱ
❤️የወደዳችሁትን ለምትወዱት አጋሩ ( ባጭሩ ሰው ጥሩ 😊)

ምን ይጨመር ?

ሀሳቦቻችሁን በ 👉 @Abr_sh ላይ እቀበላለው ።

💠 ለምትሰጡኝ ሀሳብ እና አስተያየት በሙሉ ግን ምስጋናዬ የቀደመና ከልብ ነው 🙏🙏🙏

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

...... #ትንሳኤ .......

መድኔ....ስለኔ አከላቱ ደምቷል፣
የበደሌ ሸማ በሞቱ ተገፏል፣
እነሆ ...ተነስቶ ለዘላላም ነግቷል ።
፨፨፨
ሀጢያተኛው እኔ... ከነ ግሳንግሴ
የጥፋቴ ጋሪ ፥ ከብዶ ለፈረሱ
ሳያወላክፈኝ..... ፊዳ ሆኖ እርሱ
በእድፋም ገላ ፥ ክንዱን መንተራሴ
ሞቴን ቢሞትልኝ ፥ነፃ ወጣች ነብሴ።

#ክበር _ተመስገን!!

✍ አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu
@Abrham_Teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

#ብረት_መዝጊያ

በደባል እየኖርሽ...መዋጮ ተጋርተሽ
ከደም ወዝ ጨልፈሽ የወር ክራይ ከፍለሽ
የራስሽ ቤት ሳይኖር
እንጀራ ለማብሰል....ቋንጣ መዘልዘያ
መጅሊስ ለመፈረሽ ...አልጋ ለመዘርጊያ
ባል አገባሽ አሉ .....ባለ ብረት መዝጊያ
ይሁና........
በመንግስት ኮንዶሚንየም ....በሰው ሰረገላ
ከህዝብ ተነጥቆ ....በተሰራ ጥላ
ከተኮናተርሻት የብቻሽ ሰቀላ
እንደ ውሎሽ ውሎ መብልሽን ሊበላ
ወዶ ገብ ባልሽ
ከእጅ እና እግሩ በቀር ጣማ ያጣ ሌላ
ከየት ወጣው ብረት?
የት አገኘ መዝጊያ?
መቃን የሚደፍን....ቅጥር መሸጎሪያ?
....
እንጃ.....😉😉


✍ #አብርሀም_ተክሉ

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ንቅለ ጉልቻ

ያልባረከው ትዳር ... ሲጋፈጥ መዘዙ
አወይ እባብ ...ጣሙ
ካልተገዳደሩ
መች ይወጋል መርዙ...
ይመስገን አደቤ
አንችን አየው ከይሲ ፥ ታዘብኩሽ በብዙ ።

ካዝማዴ ተጣላሁ ፥ ተፋታሁ ከስጋ
ነብስ አባቴ ሳይቀር ፥ በእጁ ጆሮ ዘጋ
ጩኸቴን ቀምተሽ ፥ አነባሽ በነጋ
እራሱ ገረፈ ... እራሱ ተናጋ
በሚል አጭር ስንኝ እውነቴ ተለጋ ።

አበምኔት ያረገሽ ፥ ወዳጅ ግትልትሉ
የጠላሽ ይጠላ ፥ የረገምሽው ይሙት ፥ ሲሉ ተከተሉ
ባልሽ አፈር ይብላ
ድንጋይ ይንተራሰው
ብላችሁ ፀልዩ ፥ ስትይ የሰማሰው
ሲሞት እንዳይገድሽ... አገር ምድሩን ማሰው
የኔ ያልኩት ሁሉ ፥ መደፋት ሲደርሰው
ወዝና ስጋዬ እየተሞዠቀ ፥ ጅማት ሰጠሁ ለሰው
ከደም ጠፈጠፌ ፥ አገሬው ደረሰው
እንዲህም ሆኖ ግን ...
ለምነው ማትሞተው ... ይለኛል አላፊ
እላለሁ መልሼ ፥ ለዚህ ተላላፊ
ቀኑ ያልደረሰ
ሰው ለሞት አይወድቅም ፥ እንኳንስ ለጥፊ
ታሪክ ለድምቀቱ...
ማሰለፍ ይወዳል ፥ አጥፊውን ከጠፊ ።

ከለታት ባንዱ ቀን
እገሌ ከገሊት ፥ ተጋብተው ነበረ
ሲኖሩ ሲኖሩ ፥ እሷ ስትወደው ፥ ይገፋት ነበረ
ትላንት የነበረ ፥ ዛሬ በቀን ሻረ ፥ በለት ተቀየረ
እንዲህ ሆነች እሷ ፥ እሱም እንዲህ ቀረ
ያባብላል ወራት
የገንፎ ላይ ስንጥር ፥ የጎን ላይ ውጋት
ሁነሽኛል መቼም
ለግፍሽ እርግጫ ፥ ለበቀልሽ ቼቼ
አልጥልሽም ከቶ ፥ ባንቺ ቀን ታግዬ ፥ በሸንጎሽ ሞግቼ
ድሌን እሽታለው ... እሳት ላይ ተኝቼ
ምሳሩ ቢበዛ ፥ እውነቴን ላይበጥስ ፥ አምናለሁ በርትቼ
እስከቀኔ አልፋለው ፥ ቀኜ ሲዝልብሽ ፥ ግራዬን ሰጥቼ ።

ይሄም ሆኖ ግና...
አይንሽ ደም ለውሶ ፥ አንዴ ሰክረሽ ለኔ
ጎንጉነሽ ጎንጉነሽ ፥ ግፍና ኩነኔ
ያዘዘልሽ አልቆ ፥ ያዘዘው እስኪደርስ
እንባና ለቅሶዬ ... ገደል ልብሽ ላይደርስ
ሸለል በይ ካብ ለካብ
ተሳቢ ... በዲቡ
እስኪጥልሽ እጄ ... እስኪክሰኝ ፀቡ ።

አብርሃም ተክሉ

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ዝክረ ቫለንቲኖ

@Abrham_teklu

Читать полностью…

💡 የአብርሃም_ቤት ⛺️

ተጋበዙልኝማ ይሄን ❤️ የወዳጄን ❤️ በኩር ልጅ
#ሰው_ፍቅር_ናፍቆት ( ዳግም ሄራን ) በተገኘበት ይነበብ !!!

@Abrham_teklu

Читать полностью…
Subscribe to a channel