ye_adis_kidan_hiwot | Unsorted

Telegram-канал ye_adis_kidan_hiwot - የአዲስ ኪዳን ህይወት

670

በመወለድ ከእግዚአብሔር የተካፈልነውን ህይወት መግለጥ! @adiskidanbot

Subscribe to a channel

የአዲስ ኪዳን ህይወት

መንፈሳዊ ውጊያ


1ኛ ጢሞቴዎስ 6
12፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።

ከክርስቶስ የመስቀል ሥራ በኋላ ያለነው የአዲስ ኪዳን አማኞች፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰርቶ ከጨረው ሥራ የተነሣ ለድል ሳይሆን ከድል፣ ለአሸናፊነት ሳይሆን ከአሸናፊነት፣ ለበረከት ሳይሆን ከበረከት፣ ለጤንነት ሳይሆን ከጤንነት የምንኖር፣ ለዓለምና ለሀይማኖት የመጨረሻ ግብና ምኞት የሆነው ሁሉ ለእኛ መነሻችን የሆነልን ነን።

መንፈሳዊ ውጊያ ብለን ስንልም፣ ''አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው'' እንደሚል ቃሉ፣ በክርስቶስ ድል ያልተነሱና ያልተገፈፉ አለቅነትና ሥልጣናት የሉምና የክርስቶስ አካል ከመሆናችን የተነሣ ያገኘነውን ድል ለማስጠበቅ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ለብሰን፣ ባመነው እውነት ላይ በመጽናት የምናስጠብቀው ድል እንጂ እንደ አዲስ የምናሸንፈው ውጊያ የለም!

አንተ የታመምክ አይደለህምና ጤነኛ ለመሆን አትዋጋም! ይልቁኑ በመገረፉ ቁስል የተፈወስክ ነህና በዚህ እውነት ላይ በመጽናት ጤንነትህን ታስጠብቃለህ! ከድል እንጂ ለድል አትኑር!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ቅድስና

ቅድስና መለየት ነው! በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ከጨለማው ስልጣን በመለየት ወደ ልጁ የፍቅር መንግሥት፣ ሀጢአትና ሰይጣን ከሚገዛበት ክፉ ከሆነው ዓለም በመለየት በክርስቶስ ለእግዚአብሔር ተገኝተናልና ቅዱሳን ነን!

በብሉይ ኪዳን የመቅደስ ዕቃዎች ቅዱስ የተባሉት ለመቅደስ አገልግሎት ስለተለዩና እግዚአብሔር አድሮበት የነበረው ቦታ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው!

ቅድስናን ገልጦ መኖር ብዙ ሰው እንደሚያስበው አትንካ፣ አትቅመስ በሚል የህግ ትዕዛዝ ተተብትቦ መኖር ሳይሆን ''የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ በአዕምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ'' እንደሚል ቃሉ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ፣ ባወቅነው እውቀት አዕምሮን እያደስን መኖር ነው!

የቅድስና ተቃራኒም ሀጢአት ሳይሆን ከዓለም ጋር ተመሳስሎ መኖር(Commonness) ነው! ዓለም የሚያወራውን አለማውራት፣ ዓለም ነገሮችን በሚያይበት መንገድ ነገሮችን አለማየትና አለማድረግ ቅድስናን ገልጦ መኖር ነው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ክብር የመጣሉ ጉዳይ


የዮሐንስ ወንጌል 17
22-23፤ እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።


በአዲስ ኪዳን ክብራችን ሆኖ የተቆጠረልን እራሱ እግዚአብሔር የከበረበት ክብር ነው!

መጽሐፍ፣ የጠራቸውን አጸደቃቸው፣ ያጸደቃቸውንም አከበራቸው ብሎ ነገረን እንጂ በሉ ስትዘምሩ ክብራችሁን ጣሉ አላለንም! ለእግዚአብሔር ምስጋናው መክበራችን ነው እንጂ ክብሬን ጥዬ፣ ዝቅ ብዬ፣ ተዋርጄ እዘምራለው ማለታችን አይደለም!

ከብረካል ሲባል አሜን እያልኩ ስዘምር የምጥለው ክብር የለኝም! ክብሬ ክርስቶስ ነው !

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

እግዚአብሔር ያለው ይሆናል....ብቻ አይባልም!


በምድር ህይወታችን እግዚአበሔር በክርስቶስ ሰርቶ የጨረሰው ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚያስችለው፣ ''እግዚአብሔር ያለው ይሆናል'' ብሎ መቀመጥ ሳይሆን እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ በመስቀል በሰራው ሥራ ያለውን ያንን ደግሞ መናገር ነው!

እግዚአብሔር ትወርሳላችሁ ብሎ ያለውን ማርና ወተት የምታፈስን ሀገር ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ አስራ ሁለት ሰላዮችን ላከ! ትወርሳላችሁ የተባለውን የበረከት ምድር የወረሱት ግን፣ አስራ ሁለቱ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ከግብፅ ሲያወጣቸው የተናገራቸውን ያንን ብቻ የተናገሩት ሁለቱ ካሌብና ኢያሱ ነበሩ!

እወጃ (confession) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል፣ በግሪክ ሆሞሎጊዮ(Homologeo) የሚል ቃል ሲሆን ''ተመሳሳይ ነገር መናገር'' የሚል ትርጉምን ይዟል። እግዚአብሔር በክርስቶስ ለእኛ ያለውን ያንን ደግመን እየተናገርን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንኖረዋለን!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ከፍላጎት ያለፈ አቅራቦት!

መጽሐፍ፣ ''ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን'' ይላል! እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በክርስቶስ ውስጥ ያየልን ርስትና በመስቀል ሥራውም ያፈሰሰው ጸጋ ከፍላጎት ያለፈና የተትረፈረፈ ነው!

ጴጥሮስ በክርስቶስ ቃል መረቡን ሲጥል፣ መረቡን የበጠሰና የእርሱም ሆነ የጓደኞቹ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ የበዛ፣ ከፍላጎትና ከጥያቄያቸው ያለፈ አደገኛ አቅራቦት አገኛቸው! ክርስቶስ ሁለቱን ዓሣና አምስቱን እንጀራ ሲያበዛም፣ አምስት ሺህ ሰዎች (ሴቶችና ህጻናት ሳይቆጠሩ) በልተው፣ አስራ ሁለት መሶብ ተረፈ!

ወዳጄ፣ በዓለም ካለው ሀጢአት እጅጉን የላቀ ጸጋ፣ ከፍላጎት ያለፈ አቅርቦት በክርስቶስ ተሰጥቶናል! ጽዋችን ሞልቶ የተረፈ፣ በረከታችን የተጨቆነ ነው! መትረፍረፍ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ሁሉን እንችላለን!

ወደ ፊልጵስዩስ 4
13፤ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።

ክርስቶስ፣ አብን ለእኛ የተረከ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ነጸብራቅ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ማንነታችንን ገልጦ ያሳየን መስታወታችን ነው! በዚህም፣ በእርሱ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ብቻ ሳይሆን ለእኛ ለአማኞች ሁሉ መቻሉን አየን!

''ይህ ለእግዚአብሔር ቀላል ነው'' አትበል! የተፈለገው ለእግዚአብሔር መቅለሉ ሳይሆን የአንተ ቀሎክ መኖር ነው! በመሰረቱ፣ አንድ ወንድማችን እንዳለው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ከባድም ቀላልም ነገር የለም! ከባድና ቀላል የሰው ቋንቋ ናቸውና!

ወዳጄ፣ ሁሉን መቻል ምንጫችን ከሆነው ከእግዚአብሔር የተካፈልነው ማንነት ነው እንጂ በአነቃቂ ንግግር የሚመጣ የአዕምሮ ውጤት አይደለም! ሁሉን መቻል ተሰቶኛል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ብልጥግና!

1ኛ ቆሮንቶስ 1
4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤

5-6፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።

ጳውሎስ፣ በቆሮንጦስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተክርስትያን፣ ''በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመናችሁ የተነሣ በነገር ሁሉ፣ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ ባለጠጋ ተደርጋችኋል!'' ብሎ አለ!

ወንጌል ያበለጥጋል! ወንጌል አያበለጥግም ብሎ ማለት ዉኃ ውስጥ ገብተህ ሳትረጥብ እንደ መቅረት ነው!

ብዙ ሰው በገንዘብ አቅጣጫ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መንካት ስለማይፈልግ፣ አዲስ ኪዳንን የመንፈሳዊ በረከት(ጽድቅ፣ ቅድስና፣ ክብር፣ ልጅነት) ብቻ አድርጎ ለማስቀመጥ ይሞክራል። በአዲስ ኪዳን፣ ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች በመደረግ፣ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ጽድቅና ቅድስና ልጅነትና ክብር ለእኛ ቢሆንም መንፈሳዊ በረከትን ባገኘንበት በዝያው በክርስቶስ የመስቀል ሥራ የአብርሀም ዘር በመሆን በአብርሀም በረከት ተባርከን የምድርም ባለጠጎች ተደርገናል!

ወዳጄ፣ ሰማይ ቤት ስትሄድ ታርፋለህ፣ ትበለጥጋለህ እያለ ለሞት ከሚያዘጋጅህ ትምህርት ፈጥነህ ራቅ! ሰማይ ቤት የሚነዳህ መኪና እንደሌለህ ላስታውስህ! መዝሙረኛው፣ ''እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ የሚያሳጣኝም የለም'' ብሎ ያለው ለምድር ህይወቱ እንጂ ለሰማይ አይደለም! አባቴ ባለጠጋ ነው፣ እኔም በብልጥግናው እኖራለው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የእግዚአብሔር ስጦታ


የዮሐንስ ወንጌል 14
15-16፤ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ #ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ (* አጽናኝ ማለት በግሪክ ቋንቋ ጰራቅሊጦስ ማለት ነው)


በአሮጌው ኪዳን፣ ሰዎች እንኳን ሀጢአት ሰርተው፣ ሀጢአት ባይሰሩ እንኳን መንፈስ ቅዱስ ለተወሰነ ዓላማ አንዴ በእነርሱ ላይ ይገለጥና መስራት የፈለገውን ሰርቶ ይሄድ ነበርና፣ ዳዊት፣ ''ቅዱሱ መንፈስህን አትውሰድብኝ'' ብሎ ጸለየ።

በአዲስ ኪዳን ግን መንፈስ ቅዱስ ተመላላሽ ጎብኚ ሳይሆን ለዘላለም በእኛ ያደረ መንፈስ ነውና ''መንፈስህን አትውሰድብኝ'' አይባልም!
መንፈስ ቅዱስን እኛ ጋር የሚያቆየው መልካም ሥራችን ሳይሆን ልጅ መሆናችን ብቻ ነውና!

መጽሐፍ፣ ''ቅዱሱን መንፈስ አታሳዝኑ'' አለ እንጂ ''ይወሰድባችኋል'' አላለም! መንፈሰ ቅዱስ፣ ለጥቅማችን ለዘላለም በእኛ አድሯልና ስንደክም እራሱ የሚያዝነው በእኛ ሳይሆን ለእኛ ነው! ይህንን ዘላለማዊ ወዳጅ ተደሰቱበት፣ ተጠቀሙበት!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

እግዚአብሔር መልካም ብቻ ነው!


ወደ ዕብራውያን 13
8፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

እግዚአብሔር አይለወጥም! በዚህም በመጀመርያ ሰውን ሲፈጥር ለሰው የነበረው በጎና ፍጹም ፈቃድ ዛሬም ያው ነው! እግዚአብሔር ሰው ደስ ተሰኝቶ ይኖርበት ዘንድ ለሰው የፈጠረውን ቁሳዊ ዓለም ተመልክቶ ''መልካም ነው'' ብሎ አለ! የሰው በሀጢአት ከእግዚአብሔር መለየት፣ እግዚአብሔር ለሰው ያለውን መልካም ፈቃድ አልቀየረም!

እግዚአብሔር አይቀየርምና ዛሬም ሰው በመለኮታዊ ጤንነት እንዲኖር፣ በእግዚአብሔር አቅርቦት ተደላድሎ እንዲመላለስ፣ ለነፍስ ሀዘን ከሚሆን ተለይቶ እራሱ እግዚአብሔር የሚኖረውን አስደሳች ህይወት ይኖር ዘንድ በጎ ፈቃዱ ነው!

ላለመፈወስ፣ እግዚአብሔር ስሙንም ሆነ ማንነቱን መቀየር አለበት! ምክንያቱም ለእስራኤል ልጆች ተገልጦ ''እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ'' ብሏልና! እግዚአብሔር ደግሞ ሊቀየር አይቻለውምና ለሰው ልጆች ሁሉ የልቡ ሀሣብ በክርስቶስ መገረፍ ያቀረበው መለኮታዊ ጤንነት ነው!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

አንድ ነን!


ኦሪት ዘጸአት 19
12፤ #ወሰንም ለሕዝቡ በዙሪያው አድርግላቸው፦ ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤

ወደ ኤፌሶን 2
18፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።

የብሉይ ኪዳን ሕግ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ወሰንን ያበጀና ሰውን ወደ እግዚአብሔር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ያራቀ ነው!

አሁን በክርስቶስ የመስቀል ሥራ የተመረቀልን አዲስ ኪዳን ግን ወደ አብ የገባንበትና ከክርስቶስ ጋር አንድ የሆንበት ድንቅ ህይወት ነው! ዛሬ እግዚአብሔርን ሩቅ አስቀምጦት፣ በብዙ ጸሎትና ልመና እንድትፈልገው እያደረገ ያለው ሀይማኖት ነው እንጂ ወንጌል አይደለም!

ወዳጄ፣ በመዝሙር'' ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርቤ የሆነው'' ብለህ ስታበቃ መልሰ ''እፈልግሀለው'' አትበል!! እግዚአብሔር ሳንፈልገው ተገኝቶልናልና በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ምንም ርቀት የለም! አንድ ሆነናል!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ጽዮን ተራራ

ወደ ዕብራውያን 12
21፤ ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ፡ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤


በብሉይ ኪዳን የኖረና ሕግን የተቀበለው፣ ለእግዚአብሔርም ቅርብ ነው ተብሎ የሚታሰበው ሙሴ፣ እግዚአብሔር ሕጉን ሲሰጥ የነበረውን የሲና ተራራን ልምድ ሲናገር፣ ''እጅግ እፈራለው ደግሞም እንቀጠቀጣለው'' ብሎ ነው።

አሁን በክርስቶስ ሥራ ከማመናችን የተነሣ የደረስነው መደንገጥና መንቀጥቀጥ፣ ፍርድና ኩነኔ ወደሞላበት ሲና ተራራ ሳይሆን ድፍረትና ሰላም፣ ጽድቅና በመንፈስ የሆነ ደስታ ወደ ሞላበት ጽዮን ተራራ ነው! ተራራ ቀይረናል!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ልብሰ ተክህኖ


ልብሰ ተክህኖ፣ በብሉይ ኪዳን የመቅደስ አገልግሎት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው።

ሰማይንና ምድርን በአንደበቱ ቃል የፈጠረው፣ ቀይ ባህርን በአፍንጫው ትንፋሽ የከፈለው፣ እልፍ አዕላፍ መላዕክት ሳያቋርጡ የሚያመልኩት ትልቁ እግዚአብሔር፣ አሮን ስለሚለብሰው ልብስ አስቦ፣ ልብሱ ስለሚሰራበት ጨርቅና ቀለም፣ ልኬትም ሆነ ስለ እያንዳንዱን እቃ በተራራ ላይ ለሙሴ በማሳየት፣ እኔ እንዳልኩህ ብቻ አድርገህ ሥራው በማለት ለልብሱ ሲጠነቀቅ የምናየው፣ ይህ ልብስ፣ በብሉይ ኪዳን የተገለጠ የክርስቶስ ጥላ ስለሆነ ነው!

ይህ ልብስ በራሱ ቅዱስ የሆነና ለባሹንም ቅዱስ የማድረግ አቅም ያለው፣ ለአሮንም፣ መግባቱና ድፍረቱ የሆነ ልብስ ነው! አሮን ልብሱን እስከለበሰበት ጊዜ ድረስ፣ ልብሱ ላይ ያለው እያንዳንዱ ነገር ይቆጠርለታል!

መጽሐፍ፣ ክርስቶስን ለብሳችሁታል ይላልና ክርስቶስ መግባታችንና ድፍረታችን ነው! እግዚአብሔር ደህንነታችንን፣ ሰላማችንን፣ ጤንነታችንን፣ ብልጥግናችንን በተመለከተ ሁሉን በክርስቶስ ላይ ሰራና ክርስቶስን አለበሰን! አሁን ክርስቶስን ለብሰነዋልና ሙሉ ነን!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የአብርሃም ዘር

ኦሪት ዘፍጥረት 13
2፤ አብራምም #በከብት_በብርና_በወርቅ እጅግ በለጠገ።

ኦሪት ዘፍጥረት 26
12፤ ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፤ እግዚአብሔርም ባረከው።

13፤ #ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ፥ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመረ ይበዛ ነበር፤

14፤ #የበግና_የላም_ከብትም_ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፤ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።

ወደ ገላትያ 3
14፤ የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ #የአብርሃም_በረከት_ወደ_አሕዛብ_በኢየሱስ #ክርስቶስ_ይደርስላቸው_ዘንድ።

በአዲስ ኪዳን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመናችን የተነሣ፣ የአብርሃም ዘር ተደርገናል! ከዚህም የተነሣ የአብርሃም በረከት ደርሶናል!

የአብርሃም በረከት ደግሞ መንፈሳዊ ሳይሆን ምድራዊ በረከት ነው! ለዚያም ነው መጽሐፍ፣ አብርሃም በብር፣ በከብትና በወርቅ እጅግ በለጠገ ብሎ የሚለን! በአብርሃም በረከት የተባረኩትንም የአብርሃምን ዘሮች ስንመለከት በረከታቸው ቁሳዊ ነው!

መጽሐፍ የአብርሃም ዘር ናችሁና በአብርሃም በረከት ተባርካችኋል ብሎ ሲለን የዓለም ወራሽ ናችሁ እያለን ነው! እግዚአብሔር በዓለም ያለውን ሀብት ሰጥቶናል!

ወርቅና አልማዝ እግዚአብሔርን አይጠቅሙትም! ሰው ይደሰትበት ዘንድ ነው የሰራቸው! በዚህ የበረከት ዶፍ ተደብድበናል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

አለመጥፋት

1ኛ ጴጥሮስ 1
3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት #በእግዚአብሔር_ኃይል #ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

ብሉይ ኪዳን፣ በሕጉ መጽሐፍና በእስራኤላውያን መካከል የተደረገ ኪዳን ነውና የመጽሐፉን በረከት ለመብላት የመጽሐፉን ትዕዛዛት ሁሉ መጠበቅ ግድ ይላቸው ነበር!

አዲሱ የጸጋው ኪዳን ግን በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገና ደህንነታችንን የማስጠበቁ ሀላፊነት በትክሻችን ላይ ያረፈበት ሳይሆን በአንድ ወገን እግዚአብሔር፣ በሌላ ወገን ደግሞ ክርስቶስ ቆሞ፣ ሥራችን ሳይሆን ሥራው ታይቶ ለዘላለም ተቀባይነት ያገኘንበት ኪዳን ነው!

የደህንነት(ያለመጥፋት) ዋስትናዬ ሥራዬ ሳይሆን ጠባቂዬ የሆነው የመለኮት ሀይል ነው! አሁን በአዲስ ኪዳን፣ ሊቀጣኝ ስህተቴን ጠባቂ ሳይሆን እንዳልጠፋ እኔን ጠባቂ እግዚአብሔር ነው ያለው!

ጻድቅ አይጠፋም!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ወንጌል!


ወደ ሮሜ 1
11፤ #ትጸኑ_ዘንድ_መንፈሳዊ_ስጦታ #እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤

12፤ ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።

13፤ ወንድሞች ሆይ፥ #በሌሎቹ_አሕዛብ #ደግሞ_እንደ_ሆነ_በእናንተም_ፍሬ_አገኝ #ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

14፤ ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤

15፤ ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ #ወንጌልን_ልሰብክ #ተዘጋጅቼአለሁ።

የሮሜ ቤተክርስትያን፣ ጳውሎስ ያልተከላት፣ በአካል ተገኝቶም አገልግሎባት የማያውቅ፣ ነገር ግን ሊያያት የሚፈልግ ቤተክርስትያን ነች!

ጳውሎስ፣ በሮሜ ያለችውን ቤተክርስትያን ማየት የሚፈልግበትን ምክንያት ሲናገር፣ "መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ"ብሎ ነው! ከዚህም የተነሣ ትጸናላችሁ አላቸው! የመጽናታቸው ውጤት ደግሞ በሌሎች አህዛብ ዘንድ እንደሆነው እናንተም ፍሬ ታፈሩ ዘንድ ነው ብሎ አላቸው!

በመጽናት ፍሬ እንዲያፈሩ የሚያደርጋቸውን መንፈሳዊ ስጦታ እንዴት አድርጎ እንደሚያካፍላቸው ሲናገር፣ እጅ ልጭንባችሁ ሳይሆን ወንጌል ልሰብክላችሁ ተዘጋጅቻለው ብሎ ነው!

ወዳጄ፣ በአንድ ቀን እጅ መጫን የሚመጣ መንፈሳዊ እድገትም ሆነ ጽናት ብሎም ፍሬ የለም! ይህ ሁሉ ያለው ወንጌልን በመስማት ብቻ ነው! ወንጌል ደግሞ ስለ ልጁ፣ በልጁም ስለ አንተ ነው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ዋጋ!

የዮሐንስ ራእይ 22
12፤ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ #ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።

Revelation 22
12 'Behold, I am coming quickly, and My #reward is with Me, to render to every man according to what he has done.

ብዙዎች ከላይ ያስቀመጥኩትን ቃል ጂምናስቲክ እያሰሩ ቃሉ የማይለውን እንዲልላቸው ሲሞክሩ ይታያል! ይህ ቃል፣ ብዙ ሰው የጌታን ዳግም መምጣት ሲያስብ እንዲፈራ የሚያደርግ ቃል ሳይሆን ቤተክርስትያን የተባረከ ተስፋዋን በሀሤት እንድትጠብቅ የሚያደርግ ድንቅ ቃል ነው!

በዚህ ቃል ውስጥ ልብ ልንለው የሚገባን ጉዳይ፣ ይህ ቃል ሙሽራው ክርስቶስ፣ ሙሽሪት ለሆነችው ለቤተክርስትያን የላከላት መልዕክት መሆኑን ነው! አንድ ሙሽራ ሙሽሪትን ሊወስድ ሲሄድ፣ በትልቅ ደስታና ፍቅር እንጂ በብዙ ቁጣና በቀል እንዳልሆነ ሁሉ ፣ ሙሽሪትም ሙሽራዋን ስትጠብቅ በብዙ ሳቅና ናፍቆት ነው!

በዚህም ክርስቶስ፣ ''ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ'' ብሎ ሲል ለቤተክርስትያን ይዞ ስለሚመጣው ሽልማትና አክሊል እንጂ ስለ ቁጣና ፍርድ አለማውራቱን እንረዳለን! ለዚህም በአማርኛው ትርጉም ላይ ''ዋጋ'' ተብሎ የተጠቀሰው ቃል በእንግሊዘኛው ''reward'' ወይም ''ሽልማት'' የሚል ትርጉም መያዙን ማየት ከበቂ በላይ ነው። የምንጠብቀው ሙሽራችን ሽልማትና አክሊል ይዞልን የሚመጣ አፍቃሪ እንጂ ቁጣና ፍርድ ይዞብን የሚመጣ ክፉ አይደለምና ደስ ይበለን!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ጰራቅሊጦስ

የዮሐንስ ወንጌል 14
15-16፤ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤


መንፈስ ቅዱስ እንደ ክርስቶስ የሆነ ሌላኛው አጽናኝ ነው! ክርስቶስ በምድር ሳለ ሰዎችን እያጽናና የነበረበት ብቸኛው መንገድ፣ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ሊያጽናና የወረደበት መንገድ ነው!

ክርስቶስ እንደ ሀበሻ አጽናኝ ከንፈር እየመጠጠና ናፕኪን እያቀበለ ሳይሆን የሞተ ካለ እያስነሳ፣ የታመመ ካለ እየፈወሰ መፍትሔ ሆኖ ነበር ሲያጽናና የነበረው!

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ የህይወትህ አቅጣጫ፣ ክርስቶስ በመስቀል ሰርቶ የጨረሰውንና ርስት አድርጎ የሰጠህን እውነት እያሳየህና አካል እያለበሰው ያጽናናካል እንጂ ድንኳን ጥሎ እያስለቀሰክ ተስፈኛ አድርጎህ አይደለም!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የተሰጠህን አትጠብቅ!

ኦሪት ዘኍልቍ 6
24፤ እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
25፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤
26፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።
27፤ እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።


ይህ ከላይ ያስቀመጥኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ በአዲስ ኪዳን የፕሮግራም መዝግያም ሆነ የበረከት ቃል ሊሆን ፈጽሞ አይችልም! ምክንያቱም፣ ሁሉም በክርስቶስ የእኛ ሆነዋልና!

አንድን ተደላድሎ በመቀመጫ ላይ የተቀመጠን ሰው፣ ተቀመጥ ብለህ እንደማትለው ሁሉ፣ አንድን በክርስቶስ በማመን በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የተባረከንና የእራሱ የክርስቶስን ሰላም ያገኘን የእግዚአብሔርን ልጅ፣ ተባረክ ብሎ ማለትና እግዚአብሔር ሰላሙን ይስጥህ ብሎ ማለት አለማስተዋል ነው! ምክንያቱም ሰማይ ያስቀረብን ሰላምም ሆነ በረከተ የለም! የእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ የእኛ ሆኗል!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

እጅጉን ይበልጣል!

በድንጋይ ላይ የተቀረጸውና የሚገድለው የፊደል አገልግሎት፣ የተሻረውና የኩነኔ፣ እንዲሁም በእንስሳት ደም የተመረቀው የብሉይ(የሕግ) አገልግሎት በክብር ከሆነ፣

በልብ ላይ የተጻፈውና ህይወት የሚሰጠው የመንፈስ አገልግሎት፣ ጸንቶ የሚኖረውና የጽድቅ አገልግሎት፣ እንዲሁም በእንስሳት ደም ሳይሆን ክቡር በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተመረቀው አዲሱ የጸጋው አገልግሎት እንዴት አብዝቶ በክብር አይበልጥም?

በአዲስ ኪዳን የተሰጠን ህይወት እንደ ብሉይ ኪዳን በባርያ በኩል የተገለጠ ሳይሆን በልጅ በኩል የመጣ ነውና እንደ ባርያ ሳይሆን አባ አባት እያስባለን ልጅ አድርጎ እያኖረን ያለ ክቡር ህይወት ነውና አቅልለን ከእነ ሙሴ መንደር አናውለውም! ጸጋ ከፍ ያለ መልዕክትና ከፍ ያለ ህይወት ነው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ተወደናል!

የማቴዎስ ወንጌል 3
17፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡ አለ።

ክርስቶስ፣ አብ እርሱን በወደደበት ፍቅር እንደወደደን ነግሮናልና ሰማይ ተከፍቶ፣ ''በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው'' ተብሎ የመጣው ድምጽ በአዲስ ኪዳን የእኛ ቃል ሆኗል!

ከእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም እርሱ ለእኛ ካለው ፍቅር ሊለየን የሚችል አንዳች የለም! ዮሐንስ በወንጌሉ ውስጥ እራሱን ሲጠራ፣ ''ክርስቶስም ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር'' ብሎ ነው! ይህ ግን ክርስቶስ ከሁሉም የበለጠ ዮሐንስን መውደዱን ሳይሆን ዮሐንስ ከሌሎቹ በተሻለ መልኩ ስለተወደደበት ፍቅር መገለጡ እንዳለው ነው የሚያሳየው! ለእግዚአብሔር ባለህ ፍቅር በመደገፍ እንደ ጴጥሮስ በራስህ ሥራ አትመካ! ይልቁን የተወደድክበትን ፍቅር በማወቅ ስር ስደድ! ምክንያቱም መጽሐፍ፣ '' እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እንወደዋለን'' ብሎ ስለሚል!

ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጆችና ደስ የተሰኘብን ውድ ልጆቹ ነን! ዋጋችን ክርስቶስ ነውና!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

መንፈስ ቅዱስ

በብሉይ ኪዳን አንድ ሊቀ ካህናት በመቅደስ ሲያገለግል፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያውቅ ዘንድ፣ ኡሪምና ቱሚም የተባሉትን ሁለት ድንጋዮች በደረት ኪሱ ውስጥ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል።

ክርስቶስ፣ ''እርሱ ለእኔ ካለው ወስዶ ይነግራችኋል፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል'' በማለት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነገረን! በዚህም፣ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መንፈስ ለሆነው ትክክለኛ ማንነታችን የሚመሰክርልን የአዲሱ ኪዳን ኡሪምና ቱሚም ሆነ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የጌቶች ጌታ

የዮሐንስ ራእይ 5
9-10፤ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፡ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

Revelation 5
10 And made them #kings and priests to our God, And they reign on earth."

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ''የሰማይ ሰማያት ለእግዚአብሔር ናቸው፣ ምድርን ግን ለሰው ልጅ ሰጠ'' ብሎ ይናገራል! በዚህም፣ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ያመልከው ዘንድ ሳይሆን ''ምድርን ግዟት'' በተባለው ቃል መሰረት፣ የእግዚአብሔርን አይነት ህይወትና አገዛዝ በተፈጠረለት ቁሳዊ ዓለም ላይ ገልጦ ይኖር ዘንድ ነው!

የምድር ገዢ ወይም ጌታ ሰው ነው! አዳም ከእግዚአብሔር በመለየት ይህን ስልጣኑን ለሰይጣን ቢሰጥም፣ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ፣ ይህ ስልጣን ተመልሶልናልና የምድር ጌታ ተደርገናል!

አሁን፣ ክርስቶስ ኢየሱስን የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉስ ብለን ስንል ጌቶችና ነገሥታት እኛ ስንሆን እርሱ ደግሞ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉስ ነውና ጌታችንና ንጉሳችን ነው! ባለስልጣናት ተደርገናል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

ከልጁ ጋር!


የማቴዎስ ወንጌል 6
33፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ክርስቶስ፣ ''ይህ ስለ ብዙዎች የሀጢአት ይቅርታ የሚፈሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው'' ብሎ ያለውን ደሙን በመስቀል ከማፍሰሱ በፊት፣ ''አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን ጽድቅና መንግሥት ፈልጉ፣ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል'' ብሎ አስተማረ።

አሁን ያለንበት አዲሱ የጸጋው ኪዳን ደግሞ ከፈሰሰው ከክርስቶስ ደም የተነሣ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅና መንግሥት እኛ ጋር የደረሰበት ኪዳን ነውና አሁን ይጨመራል የተባለው ላይ ነን! ይጨመራል የተባለው ደግሞ ቁሳዊ ነገር ነው! እግዚአብሔር አባታችን ከሁሉ የሚበልጠውን ልጁን እንዲያው ሰጥቶናልና ከልጁ የሚያንሰውን ሁሉ ለጥቅማችን እንዲያው ከልጁ ጋር ሰጥቶናል!

እግዚአብሔር ከሁሉ የሚበልጠውን ልጁን ሰጥቶናል ብለን ከልጁ የሚያንሰውን ቁስ ከለከለን ብሎ ማለት እግዚአብሔር ከልጁ ይልቅ ቁስን ይወዳል ማለት አይሆንብንም? እግዚአብሔር ቁሳዊ ነገር ሁሉ ይኖረን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ነው!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

በልቡ ላይ


በሊቀ ክህነት ልብስ ላይ ባለው የደረት ኪስ፣ የአስራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስም የተቀረጸባቸው አስራ ሁለት የተለያዩ ዕንቁ ድንጋዮች ይገኛሉ! እነዚህ ዕንቁ ድንጋዮች፣ የእስራኤል ልጆች ስም ተቀርጾባቸዋልና የእስራኤልን ልጆች በመወከል በሊቀ ካህኑ ልብ ላይ ይቀመጣሉ።

የአዲሱ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ኢየሱስ ነውና በሥራው ያመነው እኛ ሁላችን፣ ከእርሱ ርቀን ሳንሆን ለእርሱ ዕንቁ ሆነን በልቡ ላይ በፍቅር ተደላድለን ላንወድቅ ተቀምጠናል!

መገኛችን ልቡ ላይ ነውና በሰው(በሌላ መካከለኛ) ወደ እርሱ አንቀርብም፣ እርሱም በሰው አይመልስልንም! በቀጥታ የልቡን ሀሣብ የምናውቅበት ስልጣን ተሰጥቶናል! ክርስቶስም፣ ''በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ'' አለ እንጂ ''ለበጎቼ ሌሎች በጎቼ ይሰሙላቸዋል'' አላለም! የእረኛችንን ድምጽ በመስማት እንደግ!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የእግዚአብሔር ስጦታ!

የዮሐንስ ወንጌል 3
16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን #እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

በብሉይ ኪዳን፣ ሕግ ከሰው ጠባቂ ነውና ሰው ለእግዚአብሔር ሊያደርገው ስለሚገባው እያንዳንዱ ነገር ሲያወራ፣ በአዲሱ በጸጋው ኪዳን ግን፣ ጸጋ ጽድቅንና ቅድስናን ብሎም ቤዛነትን ስጦታ አድርጎ ለሰው ስላቀረበ፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ በመስቀል ሰርቶ ስለጨረሰው እያንዳንዱ ሥራ ያወራል!

በአዲስ ኪዳን ድርሻዬ ምንድነው? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል! በአዲስ ኪዳን የተተወልህ ድርሻ፣ መቀበል፣ አሁንም መቀበል፣ ከዚያም መቀበል ብቻ ነው! ምክንያቱም፣ ክርስቶስ አንተን ወክሎ ለእግዚአብሔር መቅረብ ያለበትን ሁሉ አቅርቧልና አሁን ስጦታው በነጻ ይፈሳል!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

በድል መመላለስ


መጽሐፈ ኢያሱ 6
4፤ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።

5፤ ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱንም ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል።

የኢያሪኮ ቅጥር የፈረሰው በፈረጠመው በእስራኤላውያን ጡንቻ ሳይሆን ካህናት ከተሸከሙት ታቦትና ከነፉት ቀንደ መለከት የተነሣ ነው!

ቀንደ መለከት አንድ እንስሳ ሲሞት ነው የሚገኘው! ዮሐንስ፣ ክርስቶስን በማየት፣ ''የዓለምን ሀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ''ብሎ አለው። ቀንደ መለከቱን መንፋት ከበጉ ሞት የተነሣ የተገኘውን ድል መናገርና ማወጅ ነው!

በአዲስ ኪዳን ማስተርያችን
በመሆን የተገለጠው እውነተኛ ታቦታችን ደግሞ ክርስቶስ ነው!

ከድልና በድል መመላለስ ያለው ታቦቱን በመሸከም(ክርስቶስን በማላቅ) እና ቀንደ መለከቱን በመንፋት(በክርስቶስ ሞት ያገኘነውን ህይወት በማወጅ) ነው!


ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የክርስቶስ አካል

ወደ ኤፌሶን 5
29-30፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

Ephesians 5
30 For we are members of his body, of his flesh, and of his bones.

በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ያመነ ሁሉ፣ የክርስቶስ አካል ማለትም የክርስቶስ ሥጋና አጥንት ሆኗል!

መጽሐፍ፣ ማንም የገዛ ሥጋዉን የሚጠላ የለም ብሎ ይላልና በክርስቶስ ፊት አለመወደድ አንችልም! የእርሱ አካል ስለሆንን የሚንከባከበንና የሚመግበን ራስ እንጂ አጥፍታችኋል በማለት የገዛ ሥጋውን ቆርጦ የሚጥል ራስ የለንም!

ክርስቶስ ይንከባከበናል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

እግዚአብሔር ይሰጣል ይሰጣልም!

እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ ብሎ ያለው አንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ፣ በብዙ መከራ ውስጥ ያለፈ ኢዮብ የሚባል ሰው ነው!

የእግዚአብሔር መተርጎምያ ደግሞ ኢዮብ ሳይሆን አብን ያየውና የተረጎመልን እንዲሁም የአብ ትክክለኛ ነጸብራቅና የባህሪው ምሳሌ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው!

ክርስቶስ ደግሞ ሲሰጥና ደጋግሞ ሲሰጥ እንጂ የሰጠውን መልሶ ሲነሳ አይቼ አላውቅም! ህይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣው አለ እንጂ ልሰርቃችሁ መጣው አላለም!

እግዚአብሔር ቸር ነው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

የእግዚአብሔር ቸርነት

ወደ ሮሜ 2
4፤ ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?

ወደ ንስሐ የሚመራው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ ቸነፈር አይደለም!

👉ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ ነበርና በንሰሐ መንፈስ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለው ብሎ ያለው ክርስቶስ ቁጣንና ቅጣትን ይዞ ቤቱ ስለገባ ሳይሆን ፍቅርና ጸጋ ሆኖ ከእርሱ ጋር ስለተቀመጠ ነው!

እግዚአብሔር ንስሐ ትገባ ዘንድ በሽታም ሆነ ወረርሽኝ፣ የመሬት መንቀጥቀጥም ሆነ የመኪና አደጋ አይልክብህም! በመሰረቱ በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ የሆነና ለነፍስ ሀዘን የሚፈጥር አንዳች ነገር የለም!

እግዚአብሔር ቸር ነውና ቸርነቱ ብቻውን በአዕምሮ ወደ መታደስ ንስሐ ያመጣካል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…

የአዲስ ኪዳን ህይወት

አንድ ነን!

አሁን በአዲስ ኪዳን፣ ክርስቶስ የሆነ ቦታ፣ ቤተ ክርስትያን ደግሞ ከክርስቶስ ተለይታ የሆነ ቦታ ለብቻዋ አይደለም ያለችው! መጽሐፍ ምን አለ?

1ኛ ጴጥሮስ 2
4፤ በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥

5፤ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

የዮሐንስ ወንጌል 15
5፤ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

ወደ ኤፌሶን 1
22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።

23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።

መጽሐፍ፣ ክርስቶስን ሕያው ድንጋይ ብሎ በጠራበት ተመሳሳይ ቋንቋ አማኞችን ሕያዋን ድንጋዮች፣ ክርስቶስን ግንድ ብሎ ባለበት ቃል አማኝን ቅርንጫፍ፣ ክርስቶስን ራስ ብሎ ባለበት ቋንቋ አማኝን አካል ብሎ ጠራ!

ግንድ ውስጥ ያለው ተመሳሳይ ሕይወት ነው ቅርንጫፍ ውስጥ ያለው! በራስ ውስጥ ያለው ተመሳሳይ ሕይወት ነው አካል ውስጥ የሚፈሰው!

በክርስቶስ ውስጥ ያለው በሙሉ በእኔ ውስጥ አለ! አንድ ነን!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot

Читать полностью…
Subscribe to a channel