የድካም ምንጭ በሰውነት ውስጥ ሳይሆን በአእምሮ ውስጥ ነው. ከምታስበው በላይ ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ።
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ፍቅር ሰላም የነፍስ እጅግ የንጹህ መልክ ነው!
ሰላም የሕይወት ውበት ነው። የፀሐይ ብርሃን ነው!
የልጆች ፈገግታ፣ የእናት ፍቅር፣ የአባት ደስታ ፣የቤተሰብ አንድነት ይህ የሰው ልጅ ፣ እድገት የፍትሃዊነት ድል
የእውነት ድል ነው። የህይወት ውበት!!
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ጊዜ ቁስልን ይፈውሳል!
በጊዜ ውስጥ ምንም ነገር አይታይም ፣ ግን አመጣጡ ራሱ ጊዜው ነው!
ጊዜ ለሁሉም የታወቀ ነው ! ለመግለጽ እና ለመረዳት ከባድ ነው። ሳይንስ ፣ ፍልስፍና ፣
ሃይማኖት እና ሥነ ጥበባት የጊዜ ልዩነት ፍቺ ቢኖራቸውም የመለኪያ ሥርዓቱ በአንጻራዊ
ሁኔታ ወጥነት ያለው ነው። ለዛሬ ለቅዳሚታችን ስለ ጊዜ የተነገሩትን አንዳንድ ሀሰቦች እንይ
ጊዜ ምንድን ነው? ሀሳብ ለማሰላሰል ያህል።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው
ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው” ይላል። ይህንን ሐሳብ የጻፈው በጥንት ዘመን የኖረው
ጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን፣ ለመወለድና ለመሞት ብሎም ለመገንባትና ለማፍረስ እንዲሁም
ለመውደድና ለመጥላት ጊዜ አለው።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ ደግሞ ይህን ያስቀምጣሉ።
ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነዉና በጊዜህ ሁሉ
ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት
አይምሰልህ።
ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም
በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።
ሬይ ከሚንግ የተባለው ልብ ወለድ ጸሃፊ በ1920 ስለ ጊዜ ሲጽፍ " ሁሉ ነገር በአንድ ጊዜ
እንዳይፈጸም የሚያደርገው ነገር....ጊዜ ነው ።
ጊዜ የለም ፣ ግን ነገሮች ወደ አንድ ጊዜ ይሄዳሉ!
ጊዜው ሮጠ አመቱ በፍጥነት አለቀ እንላለን ምን ማለታችን ይሆን? ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
አንድ ደግ ተኩላ ለበግ'‹‹ቤታችንን አትጎበኙልንም?››ወይ ብሎ ጠየቀ
በጉም'‹‹ ቤታችሁ ሆዳችሁ ውስጥ ባይሆን ኖሮ እንጎበኝላችሁ ነበር›› በማለት መለሰ፡፡
︵‿ካህሊልጂብራን︵‿︵
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
«... "እኔም እኮ እንደሱ ቅቅል ነው ያዘዝኩት እንዴት ቅልጥም የለውም የኔ" እያለ እየተጨቃጨቀ ነው የሆነ ሰውዬ ፊት ለፊቴ 😂😂😂
ሶዬ ቡና ጠጥቼ መረቅ የሚመጣልኝ ነኝ
እኮ ዋናው የውስጥ ዲፕሎማሲህን ማጠናከር ነው
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ቦርጫምነትሽን ፡ አምኜ ፡ ተቀብዬ ፡ ኖሬያለሁ ።
"አንተኮ ፡ ለስንግ ፡ የምትመች ፡ ነህ !" ስትይኝ ፡ ፈገግ ፡ ብያለሁ ። ‘ሙግት ፡ እንደ ፡ ከሳሹ ፡
ሥጋ ፡ እንደጠባሹ’ ፡ ብዬ ፡ ያለተለተው ፡ ሰውነትሽን ፡ ታቅፌ ፡ አድሬያለሁ ።
‘ምንም ፡ ብቀጥን ፡ ጠጅ ፡ ነኝ!’ ፡ ብዬ ፡ የጠጅን ፡ ግብር ፡ ከፅዋው ፡ አስጎንጭቼሻለሁ ።
‘ምን ፡ እያልኳት ፡ ምን ፡ ትላለች’ን ፡ ተለማምጅ ፡ ለምጀሽ ፡ ኖሬያለሁ ።
አንቺ…
"የሚጣፍጥ ፡ ምግብ ፡ ሲርብ ፡ የበሉት ፡ ነው ።" እያልሽ ፡ ስጋሽ ፡ ከነብስሽ ፡ ለየሽ ። ‘የማታ
፡ አፍ ፡ ከጋን ፡ ይሠፋል!’ ፡ ብልሽ ፡ አሻፈረኝ ፡ ማለትሽ ፡ ለከቱን ፡ መቆጠብ ፡ ተሳነው?
‘የቸገረው ፡ ዱቄት ፡ ከነፋስ ፡ ይጠጋል!’ ፡ ኾነብሽ ። ዓመታት ፡ ቢቆጠሩም – የት አለሽ?
ስልሽ ፡ "እዚህ ፡ አለሁ!" ፡ የምትይ ፡ ብትኾኝም ፡ ‘ሽማግሌ ፡ የትናንቱን ፡ ጎበዝ ፡ የማግስቱን
፡ ልጅ ፡ የዕለቱን ፡ ሲያልሙ ፡ ያድራሉ!’ና ፡ አልፈርድብሽም ።
‘ አንድ ፡ ወሬኛ ፡ ያወራውን ፡ አንድ ፡ ሺህ ፡ ፈረሰኛ ፡ አይመልሰውም!’ ፡ እንዲሁም ፡ ‘ሲዞሩ ፡
መኖር ፡ ፅድቅ ፡ ሲመኙ ፡ በመኖር ፡ ወርቅ ፡ አይገኝም!’ና ፡ ሒጂ ፡ እልሸለሁ ።
አጀብ ፡ ነው!
“ በቅሎ ፡ ሽንቷን ፡ አጠራ ፡ ብላ ፤ እፍረቷን ፡ አሳየች ። ”
እንዲሉ…!
ሕምም…!
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ዛሬ በተለይ አሁን ያንተ ስጦታ ነች!
ሕይወትህን መቆጣጠር ጀምር። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዕጣ ፈንታን ወሳኙ አንተ
መሆንህን ወስን። የራስህን ሩጫ መሮጥ ጀምር።
የነፍስ ጥሪህን ተከተል በመጨረሻም ሁል ጊዜ ከፊትህና ከኋላህ ያለው በሙሉ ውስጥህ
ካለው ጋር ሲነፃፀር ምንም አለመሆኑን ተገንዘብ።
ሕይወት ባላቸው ነገሮች ሁሉ ዘንድ ያለውን ውበት ማጣጣም ችላ አትበል።
ዛሬ በተለይ አሁን ያንተ ስጦታ ነች።።
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
"ሰላምን ለማምጣት ትዕግሥት፣ ጥበብና ከፍተኛ ጽናትንም ይጠይቃል" በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አንድነት ሲኖር የተሻለ አቅም መፍጠር ይቻላል።
አገር ፀንታ የምትቆመው ቅንነትና ሰፋ ያለ ዕይታና አንድነት ሲኖር ነው‼️ሰላምን ለማምጣት ትዕግሥት፣ ጥበብና ከፍተኛ ጽናትንም ይጠይቃል።
ፍቅር ሲኖር አንድነት ስምምነት ይኖራል‼️ ሰላም ሲኖር ሰዎች የተረጋጋ ሕይወት ይኖራል።
በአንድነት ሲታሰብ መደጋገፍ ይበለፅጋል። መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ በየአንዳንዱ ግለሰብ ሲኖር እና ሲታይ አንድነትን ይፈጥራል።
የሐሳብና የተግባር አንድነት ሲኖር ነው የአገር የሚለወጠው ለእውነተኛ አንድነት የሚያበቃንን መተሳሰብ ሲኖር አንድነት ሲኖር ጠንካራ ሰላም ይፈጠራል።
አንድነት ሲኖር ደግሞ መተማመን ይበልጥ ይጎለብታል
ፍቅርና አንድነት ያብዛልን 🙏
●------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ለውብ ቀን
ቅን መሆን በራሱ ውበት ነው።
ውበት የመልክ ማማር 😍 ወይም ቁንጅና 😘 አይደለም የሰው ልጅ ውበቱ ልቡ ❤️ ላይ ነው መልካም ስብእና እና ቅን ልብ ❤️ ያለው ሁሉ ውብ 😍 ነው
#ውብ_ቀን
●------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ይህን ስታይ ብዙ ምክንያት ልትሰጥ ተችላለህ ለሷ ግን ምክንያት አያሻትም
ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች አንዱ ማፍቀር ❤️ ነውና አፍቅር ❤️ ውደድ 😘 ያለህን ትሰጣለህ‼️
ውብ ቀን
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ለውብ ቀን
ህይወትህን በሰው ሚዛን ስትሰፍረው አይሞላልህምና! ስኬትህን በራስህ ሚዛን መዝነው በሰውሚዛን ከመዘንከው ሚዛን አይደፋልህምና ደስታህን
በራስህ መስፈሪያ ስፈረው በሰው ሚዛን ስትሰፍረው አይሞላልህምና።
ውድቀትህን በራስህ አይን እየው በሰው አይከተመለከትከው ጉድጓዱ ይበልጥ ይርቅሃልና።
የራስህን ህይወት በሌላ ሰው እይታ ከተመለከትከው ፈጽሞ እርካታ አይኖርህም ህይወትሀን ከሰው ጋር እያነጻጸርክ የምትኖርከሆነ እርካታ የሌለው ኑሮ እየኖርክ ነው።
ምክንያቱም በንጽጽር ህይወት ውስጥ ሁሌም የሚበልጥህ አታጣምና።
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
አራቱ ቀናት ለማርታ….ክፍል አንድ
.
( አቢ ጌቱ )
.
እንደ ድንገት ነው አፈፍ ያደረጋት። እንደ ድንገት! አንድ ቀልብ የለለው የታክሲ ሹፌር ቀልብ የሌላት ታክሲ ሲያበር ፣ ላይዋ ላይ ሊወጣባት ለትንሽ ነው የሳታት። ይሄ ሰው አዳናት እንጂ
የመኪና አደጋ ሰለባ ነበረች። በአካባቢው የነበሩ መንገደኞች “ሲጢጥ!” የሚለውን የፍሬን ድምጽ ሲሰሙ ያበቃላት መስሏቸው ተጯጯሁ። ወዲያው ምንም አለመሆኗን ሲያውቁ ፊታቸውን አዙረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ማርታ ለደቂቃዎች እንደመደንዘዝ ካለች በኋላ ግንባሯ ላይ ጠዘጠዛት። መኪናው የገጫት ነበር መሰላት። ደምቶ ይሆን በሚል ደጋግማ ነካችው። ከማበጥ ውጭ ምንም አልሆነም። <<ምንም አልነካሽም። ስጎትትሽ ከእኔ ጋር ተጋጭተን ነው።>> አላት ጎርነን ባለ ድምጽ። ደንገጥ ብላ አየችው። እስከዚህ ጊዜ ድረስ ከጎኗ ሰው መኖሩን አላስተዋለችም ነበር። ቀስ በቀስ የሆነው ሁሉ ሲገለጥላት ያተረፋት እሱ መሆኑን ተረዳች።
<<ወይኔ! አንተ ነህ ያተረፍከኝ? በፈጣሪ ስም! በጣም አመሰግናለሁ>>
<<አይዞሽ ተረጋጊ…>>
<<….የሞትኩ ነበር የመሰለኝ። በስመአብ!!... አመሰግናለሁ…>> ምን ማለት እንዳለባት ግራ
ገብቷት ተቅበዘበዘች።
<<ተረጋጊ! የኔ እናት! እና ደግሞ አመሰግናለሁ አትበይኝ። ምስጋና ከኪስ አይገባም!>>
...የበለጠ ግራ ተጋብታ ተመለከተችው። ብዙ የተለበሰ ግን ደግሞ በቅርቡ ስለታጠበ አዲስ የሚመስል ቀይ ጃኬት እና ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ ለብሷል። በእሷ የእድሜ ክልል እንደሚሆን ገመተች። <ምስጋና ከኪስ አይገባም ማለት ምን ማለት ነው?...ዘንድሮ ደግሞ ሰው ሁሉ
ጥቅመኛ ነው።> አለች በልቧ።
ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ላይ ናት። የእጅ ሰአቷን ተመለከተች።አንድ ሰአት እየሆነ ነው። በታክሲ መንቀሳቀስ ስለሰለቻት ወክ ለማድረግ ወስና ነው ይህ የገጠማት። ውሳኔዬ ስህተት ይሆን ስትል አሰበች። ሕይወቷን ያተረፈው ወንድ አሁንም አብሯት አለ።
በፈገግታ እና በሀዘን መሀል ሁኖ (ጭፍግግ ያለ ፈግግታ እያሳየ)<<…አንቺን አድናለሁ ብዬ ህይወቴን ላጣ ነበር።>> አላት። ወደ እግሩ ተመለከተች ፤ እያነከሰ ነው። <<ገብቶኛል። ባታተርፈኝ በህይወት አልኖርም ነበር። ግን ምን እንደምልህ አላውቅም። በቃ በጣም ነው የማመሰግነው።>> <<ምስጋና ከኪስ አይገባም አልኩሽኮ! አልሰማሽኝም እንዴ? >> <<ምን አይነት ሰው ነህ? እንደዛ ይባላል እንዴ?...ገንዘብ ልትጠይቀኝ እንዳይሆን? >> <<ሰርቼ የምበላ ሰው ነኝ...ገንዘብ አልፈልግም>>
<<እና ምንድን ነው የምትፈልገው?>> ትኩር ብሎ ተመለከታትና በስሱ ፈገግ አለ።
ነጭ ግን በስርአት ያልተደረደሩ ጥርሶች ብቅ ብለው ጠፉ። <<ምንድን ነው?>> አለችው <<መኪናውን እንዴት አላየሽውም ነበር? ፊትለፊትኮ ነው የመጣው…>> <ሐሳብ ውስጥ ስለነበርኩ ነው።>> ጸጥ አላት።
<<እና ምንድን ነው የፈለከው?>>
<<የምጠይቅሽ ነገር ግራ ሊያጋባሽ ይችላል። ግን ካደረኩልሽ አንጻር ይገባኛል ብዬ አስባለሁ።>>
ሊጀናጀናት እየሞከረ ስለመሰላት ተኮሳተረች። ክፉ አጋጣሚዎችን ለግል ጥቅም ማዋል የከንቱ ሰዎች መገለጫ እንደሆነ ታምናለች። በዚያ ላይ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለችም። የትኛዋ ሴት ናት ከሞት ለትንሽ ባመለጠችበት ቅጽበት ሌላ ጨዋታ የሚያምራት? <<የምፈልገው ከነገ ጀምሮ በቀን አንድ አጭር ታሪክ እየጻፍሽ እንድታስነብቢኝ ነው። ሶስት
ታሪኮች ይበቁኛል። ሶስት ቀናት ብቻ ነው የማስቸግርሽ።>> አላት። <<እ? የምን ታሪክ?>> <<አጭር ልብወለድ።>> ጸጥ አለችው። መጀመርያ ገንዘብ ሊጠይቃት ወይ ሊጀናጀናት መስሏት ፈርታ ነበር። አሁን በጠየቃት ነገር ግን የበለጠ ፈራችው። የፍቅር ታሪክ ጽፈሽ ትሰጪኛለሽ ነው ያላት። የቱ ጤነኛ ነው እንደዚህ ሊል የሚችለው? ከእብድ ጋር እያወራች አለመሆኑን ለማረጋገጥ አካባቢዋን ዞር ዞር ብላ ቃኘች።
በመገረም የሚያያኝ ሰው ካለ ብላ
ነበር። ምንም የተለየ ነገር የለም።
<<ምን አይነት ነገር ነው የምታወራው? ስምህ ማን ነው?>> <<ሰኢድ እባላለሁ>> እጁን ዘረጋላት።
<<እኔ ደግሞ ማርታ።>> ጨበጠችው። ጤነኛ መሆኑን የመዘነችበት ፈተና በውስጧ ፈገግ አስባላት።
<<እየውልህ ሰኢድ…በመጀመርያ እንደ ኢትዮጵያዊነታችን መልካም ነግሮችን ዝም ብለን ለሰዎች እናደርጋለን እንጂ ክፍያ አንጠይቅም። ታክሲ ውስጥ ለትልቅ ሰው ወንበር ስትለቅ
ታስከፍላለህ?>> <<በአላህ! ምን አይነት ሰው ነሽ? እንዴት አስከፍላለሁ?>>
<<እና ታድያ ለምንድን ነው እኔን የምታስቸግረኝ? ደግሞ አበረኸኝ እየመጣህ ነው ወይስ በዚህ ነበር የምትሄደው?>> <<የምሄደው እንኳን ወደ ሽሮ ሜዳ መስመር ነበር። ክፍያ አይጠየቅም ያልሽው ግን
አያስኬድም።>>
<<ማለት?>>
<<መልካምነት ኢትዮጵያ ውስጥ ያን ያህል ዋጋ አይሰጠውም ማለት መልካምነት በራሱ ዋጋ የለውም ማለት አይደለም።>> <<ዋጋ የለውም እያልኩህኮ አይደለም። ግን እኔ ቢኖረኝና በፈቃዴ የሆነ ነገር ባደርግ ጥሩ
ነበር…ያንተ መጠየቅ እንግዳ ነገር ነው። ደግሞ የጠየከኝ ፈጽሞ የማልችለውን ነገር ነው!
ከይቅርታ ጋር እያስፈራኸኝ ነው! እብድ አይደለህም አይደል? ጤነኛ ነህ ኣ?>> ጥያቄዋ ለራሷም ገረማት። እብድ ቢሆን እብድ ነኝ ሊላት ነው?
<<ጤነኛ ነህ ወይ ነው ያልሺኝ? ቅድም መኪናው ሳይመጣ በፊት ጤነኛ ነበርኩ። አሁን እግሬን አሞኝ እያነከስኩ ነው። ጥቂት ደግነት ለመስራት ባልሞክር ኑሮ ጤነኛ እሆን ነበር።
አንቺም እንደዚህ የሚያስፈራ ወጣት ጋር አታወሪም ነበር።>> ልትናገር የነበረው ነገር ጠፋት።
<<እና ጥያቄዬን ትቀበያለሽ? …ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀናት…በቀን አንድ ታሪክ…>> << ሰውዬ እኔኮ ደራሲ አይደለሁም!>> ተበሳጨች።
<<በጣም ይቅርታ በቃ አትከተለኝ። ከዚህ በላይ ልናወራ አንችልም።>> <ራሴን ማረጋጋት
ባለብኝ ሰአት ለምንድን ነው ከሱጋር የማወራው?>> ራሷን ጠየቀች።
<<…ጥሩ! እሄዳለሁ ፤ ከመሄዴ በፊት ግን ይሄንን ነገር አስቢው… ቤቴ መድሃንያለም ስለሆነ በዚህ መንገድ ሳላልፍ አልውልም። ዛሬ ግን ፒያሳ የእህቴ ሰርግ ነበር። ከእህቱ ሰርግ የማይገኝ ምን አይነት ሰው ነው ትይ ይሆናል። ነገር ግን በዚህ ሰአት እዚያ ሰርግ ቤት ውስጥ
ብሆን ኑሮ የሚፈጠረውን አስቢው። ጭንቅላትሽ ከመኪናው ጎማ ስር ይሆን ነበር። እናትሽም በመርዶ ነጋሪ ይደወልላቸዋል። በስልክ የልጅን ሞት መስማት ምን ያህል ከባድ ነው?
እየተብከነከኑ መሬት ላይ ይንከባለላሉ።ልጄን! ልጄን! እያሉ። ፊታቸው በእንባ ተሸፍኖ ደረታቸውን እየደቁ እሪ ይላሉ። አባትሽም በህይወት ካሉ ቅስማቸው ይሰበራል። ከዛሬዋ ቀን
ጀምሮ ግማሽ ነብሳቸው ሰማይ ቤት ትሆናለች። በህይወት መኖራቸው ይቆማል። እህት እና ወንድሞች አልያም ልጆች ካሉሽ ምን እንደሚሆኑ አስቢ….በተለይ ሴት ልጅ ካለሽ…>>
በመብረቅ የተመታች ያህል ከላይ እስከታች ሰውነቷ ሲሰነጠቅ ተሰማት። የሴት ልጇ ፊት በአይምሮዋ ድቅን ሲልባት ሰውነቷ ተንዘፈዘፈ። ከእሬሳዋ ፊት ልጇ እየተንፈራፈረች ሲታያት
አንዳች ቅዝቃዜ ከጭንቅላቷ ጀምሮ እስከቁርጭምጭሚቷ ድረስ ሰቅዞ ያዛት።
<<ሃሎ!..እናቱ>> እየሰማችው አልነበረም...ወረቀትና እስክርቢቶ ከኪሱ አውጥቶ ስልክ ቁጥሩን በፍጥነት ጻፈ።
<<ሐሳብሽን ከቀየርሽ …ነገ በዚሁ ሰአት እዚሁ እንገናኝ…ደውይልኝ>>
…መሽቷል። መኪናዎች የፊት መብራታቸውን አብርተው ውርውር እያሉ ነው። እያነከሰ ሲሄድ አይኗን ቡዝዝ አድርጋ ተመለከተችው።። ነገሩ ሁሉ ህልም መሰላት። ሁሉም ነገር እንደ ህልም የፈጠነና ድብዝ
ምናለ ከዚ ሀገር 🇪🇹 ውልቅ አድርጋችሁኝ እዛ ሀገር ጥልቅ ብታደርገኝ ብሎ የሚያፀልይ ነው… አሜሪካ🇺🇸 ውስጥ ካሉ የማክዶናልድ በርገር 🍔 መሸጫ ሱቆች ብዛት በላይ የህዝብ ላይብረሪዋች 📚📘 ይበልጣሉ…
ችግሩ ግን እዚ ምንድነው… ቤተ_መፀሀፍትም 📚 ማክዶናልድም 🍔 አለመኖራቸው ነው‼️ … የትኛው ጫፍ ላይ ነን ግን ምእራባውያን ጥንቸል🐇 ቢሆኑ እኛ ኤሌ ነን ይሄ ጥንቸሏን ለማሳፈር እንደፈጠራችሁት የጥንቸል እና የኤሊ ተረክ አይደለም… ምን ያህል ተጎታች እና ተሳቢ እንደሆን ለማሳያ የተቀመጠ ምሳሌ ነው ‼️
…
እኛ ጋር ቢያንስ በየ ቤተ-መፅህፍቱ 📚📘 ዙሪያ ገብ የተከፈቱ የጫትና የመጠጥ 🍷🍻🥃 ቤቶች ይበልጣሉ
በዚ ከአቻችን ከምንላት አሜሪካ ጋር መወዳደር እንችላለን…
👉 ይታይሀል 👀 ቁልቁለቱ… 🔽እንደ አንድ ሀላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ ሆኜ… ኋላ ቀርነታችን ሳስበው እና ለኋላ ቀርነቴ
አመርቂ አሳማኝ አበረታች ምክንያት ስሰጠው እነሱ እየሄዱ እኛ እየተመለስን ይመስለኛል እላለሁ‼️
…
ከተወለድኩ የማውቀው ያገሬ ህዝብ ድህነትን በመሳሪያ ሲዋጋው ነው እንደዛ ነው አንዴ ማሸነፍ ሚቻለው❓
💥 ህዝብ መሀል ቦንብ 💣 የሚወረውር እንጂ ሚጠቅም ሀሳብ 💡 ሚሰነዝር የለም …
💥 ሰው ለምን እንደማይገባው ሁሌም ይገርመኛል ሁሉም ስለታጠቀ የሰለጠነ ሀገር የመሰረተ ያለ ይመስለዋል አንድም ሀገር በዚህ መንገድ ሄዶ አልሰለጠነም እርስ በእርሱ ተባልቶ ተጠፋፋ ሀገር አፈረሰ እንጅ‼️
።።።።።።።
●----------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
እንዳትጣሉ ነው የዘወትር ሙከራ/ዬ በሁለት ጥይት አይደለም በሦስትም ልመታ ብዬ ነው የቆረጥኩት።
የፈጣሪንም ጥይት ጨምሮ። ቀላል መስሎሀል መሀል መሆን❓ ቀላሉማ ፅንፍ መያዙ ነው።
ትክክለኛው ፅንፍማ ሁለት species ቢሆን ነበር። በኒያንደርታል እና ሳፒያኖች
አይነት።
📌 ግን ነገሩ እንደዛ አይደለም። በተመሳሳይ መሀል ያለ የባህል ልዩነት እንዴት ፅንፍ መያዝ ይቻላል❓
📌 በጣም መጠላላት እየፈለጋችሁ አለመቻላችሁ አይደል የሚያሰቃያችሁ❓
📌ትርክታችሁ ይዋጋል እናንተ ግን ተጋብታችኋል።
ተዋልዳችኋል። የወለድከው ልጅ በእናቱ በኩል የእናቱን አባት መምሰሉን እየጠላህ ግን ልጅህን እየወደድክ እንዴት ቁርጠኛ ጦርነት ማድረግ ትችላለህ❓
.
💠 ሁለት ፈልፈሎች ሊጣሉ ሲል ተዉ ትላለህ❓።
👉 ከቻልክ ሁለቱንም ትመክራለህ። እንደ ጤነኛ መንግስት ጤነኛ ህግ ካለህ አጥፊውን ከአልሚው ለይተህ ትቀጣለህ።
👉 አባታዊ ከሆንክ ሁለቱንም ትኮረኩማለህ።
👉 ይህ ሁሉ ካልሰራ ግን "በቃ ተደባደቡና ይለይላችሁ" ብለህ
ትተዋቸዋለህ።
💥 ከመሀል ትወጣለህ። ተደባድበው እንደ አቅማቸው ቦታቸውን አውቀው
ይከባበራሉ።
👉 ከዚህ በኋላ "ተው" ብሎ መምከር ስለሰለቸ የሚቀጥለው ሂደት እሱ
ይመስለኛል። ከመሰለኝ ደግሞ ነው‼️
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
💥 በቃ እኛ… ምንም ነገር ላይ የሰላ አስተያየት እና ትንታኔ መስጠት… ባህል አርገናል…‼️
🔹 ከ #ፖለቲካ ወደ ➡️ #ወሲብ
🔹 #ከወሲብ በብርሀን ፍጥነት ስለ #እምነት…
🔹ከ #እምነት… ወደ #አመፅ
ትንተና…
🗯 አንድ ሰው በነዚህ ጉዳዬች ላይ ረጃጅም ትንተናና ፣ትልተላ ከሰጠ… ቆም ብለን ማሰብ ያስፈልጋል…🤔
👉 ላይ ላዩን እየጋለብን ነው ወገን… … እንግዲያው ቼ በለው ወገን እኔ ራሴ በዚህ አንድ አመት ያልጻፍኩት 📝 ያልተነተንኩት አጀንዳ የለም እኮ በስማም ተበላሽቼ የለ እንዴ…?
🔴 የረባ መረጀ እንኮ የለኝም እኮ ‼️ 🔴
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
በዚህ ዓለም ውስጥ ፍቅርን ለማግኘት አንድ መንገድ ብቻ አለ - መጠየቅን አቁም እና ፍቅርን መስጠት ጀምር ምስጋናን ተስፋ ሳታደርግ።
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ቁራሽ ዳቦ፣ አንድ ብርጭቆ ውሀና አካልህን የምትሸፍንበት ልብስ ካለህ ድሀ ነኝ አትበል-_-_-_-_
በአንድ ወቅት አንድ መርከበኛ ባህር ውስጥ ለሃያ አንድ ቀናት ይጠፋል። ህይወቱ ከተረፈ በኋላ ከዚህ ሁኔታ ምን ተምረህ መጣህ ተብሎ ሲጠየቅ " ከዚህ ክስተት የተማርኩት ትልቅ ነገር ንፁህ ውሀና በቂ ምግብ ካለህ ምንም ነገር ማማረር እንደሌለብህ ነው በማለት መልሷል።
"ህይወት በአጠቃላይ አንድ ጉርሻ ምግብና አንድ ጉንጭ ውሀ ናት።
ከዚህ ውጭ ያለው ሁለ ትርፍ ነው"የሚል አባባል አለ።
ዮናታንስዌፍት በበኩሉ "በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ ዶክተሮች የአመጋገብ ፤ የእረፍትና የደስታ ዶክተሮች ናቸው ብሏል ። ስዌፍት ይህን አስተያየት የሰጠበት ምክንያት ውፍረት የአንድ ሰው ንቃተ ህሊና የሚያቀጭጭ የሚወገዝ በሽታ ነው። በሌላ በኩል እረፍት ፣ ሚዛናዊነት ና ደስታ - የአእምሮ ፣ የልብና የነፍስ ማርኪያ ናቸው ።
--------- °°° 🔥 °°---------°°🔥°°--------
ሼር > @ye_esatu_wegoch
@yene_eyta
ከዛሬ ነገ ይሻላል በማለት መኖርን የምንመርጥ ለምንድ ነው? በይሆናል ተሥፋ ተሞልተን ወይስ ዛሬን መጠቀም ሥላቃተን? እነዚህን ጥያቄ ግላዊ በማድረግ ወደውስጥ መመልከት ቢቻል በማንኛውም አይነት የኑሮ ደረጃ ከፍ በማለት ህይወትን መቃኘት ይቻላል ይህ ደሥታን መሥጠት ፡ ፍላጎትን ማሟላት ፡ ስሜትን ማርካት የሚችል ከሆነ ፡፡
ነገን በመናፈቅ ዛሬ እስከተቀመጥን ድረስ ህይወታችንን ከማጉደል ተግባር እንዳልተቆጠብን ይሠማኛል ፡፡ ይህን በማድረግም በሚደርስብን የሞራል ሀላፊነት ልናመልጥ አይገባንም ፡፡
ፍርሀት በዛሬ ላይ ነግሶ ተስፋ ቢሥነት ከተወለደ የተቀኘው ህይወት ያለ ቅኝቱ ሲያቃስት ውድቀት ይንሰራፋል ችግር በዛሬ ላይ መሠረቱን ያንፃል መዋተትና መጎተት መቀመጥና መገፋት ይህ ሁሉ ይከተላል ይህ ሳይሆን የትላንትናዋን ዛሬ በመተው በትላንቷ ነገ ዛሬ በአዲስ ማንነት ሁሉን በመተው ቆምኩ ከአሹሐማው ህይወት ወደ አለቱ ቤቴ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ዛሬ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
🦋…………አንድ ተናጋሪ ተነሳና "እስቲ ደግሞ ስለነፃነት ንገረን" አለ እሱም መለሰ
✏️️…………በአምባገነን ገዢያቸው ፊት ራሳቸውን አሳንሰው እንደሚሽቆጠቆጡትና አጋድሞ ሲያርዳቸው ጭምር እንደሚያወድሱት ባሪያዎች በከተማይቱ መግቢያና በየጓዳችሁ ተደፍታችሁ ለገፃ ነፃነታችሁ ስትሰግዱ አይቻለሁ ። አዎ! በየመቅደሱ ጓዳና በየምግቡ ጥላ ስር ሆነው ከእናንተ መሃል በጣም ነፃ የሚባሉት ሰዎች ጭምር ነፃነታቸውን እንደቀንበር ተሸክመውና እንደ እግር ብረት አጥልቀውት አይቻለሁ ። ልቤም በውስጤ ደምቷል ።
✏️………ነፃ የምትሆኑት ነፃነትን የመፈለግ ሃሳብ እንኳን የማያፈናፍን ጭነት ማሰርያ ሲሆንባችሁና እንደ አላማና ግብ ቆጥራችሁ ስለ ነፃነት መናገር ስታቆሙ ብቻ ነውና ። ነፃ የምትሆኑት ቀኖቻችሁ ደንታ ቢስ ፣ ሌሊቶቻችሁ ደግሞ ፍላጎትና ችግር የሌለባቸው ሲሆኑ አይደለም ። እነዚህ ነገሮች ሕይወታችሁን ሲከቡትና እናንተ ግን ተገላልጣችሁ እርቃናችሁን ሆናችሁ ከበባውን በጣጥሳችሁ ከእነሱ በላይ ከፍ በምትሉበት ግዜ ነው ።
✏️………ነፃ ለመውጣት ከላያችሁ አራግፋችሁ የምትጥሉት ነገር የገዛ ራሳችሁን ማንነት ስብርባሪዎች እንጂ ሌላ ምንድንነው? የምታስወግዱት ኢ-ፍትሃዊ የሆነን ሕግ ከሆነ ያ ሕግ በየግንባራችሁ ላይ የተፃፈው በእናንተው በራሳችሁ እጅ ነው ። የሕግ መጽሐፍቶቻችሁን በሙሉ ብታቃጥሉ እንኳ ልታስወግዱት አትችሉም ። ባሕር ሙሉ ውሃ እያንቆራቆራችሁ የዳኞቻችሁን ግንባር ብታጥቡ እንኳ ልትፍቁት አትችሉም ። ከዙፋን ላይ የምታስወግዱት አምባገነንነትን ከሆነ በቅድሚያ በራሳችሁ ውስጥ የተተከለው(ያለው) ዙፋን መውረዱን አረጋግጡ ።ምክንያቱም አምባገነን መሪ የሚያስተዳድረው በራሳቸው ነፃነት ላይ አምባገነን የሆኑትን በገዛ ክብራቸው ላይም ሃፍረት የሆኑትን ነውና ። ነፃዎቹንና ክብራቸውን የሚጠብቁትንማ ሊመራቸው (ሊያስተዳድራቸው) አይችልም ።
✏️………የምታስወግዱት ደንታ-ቢስነትን ከሆነ ያ ደንታ-ቢስነት እናንተው ያመጣችሁት እንጂ በእናንተ ላይ የተጫነባችሁ አይደለም ። የምታስወግዱት ፍርሃትን ከሆነ የዚያ ፍርሃትU መኖርያ በእናንተው ልብ ውስጥ እንጂ በምትፈሯቸው ሰዎች እጅ ውስጥ አይደለም ። በእውነቱ ነገሮች ሁሉ የምትፈልጉትንና የምትፈሩትን ፣ የምትጠሉትንና የምትወዱትን የምታሳድዱትንና የምትሸሹትን ሁሉ በከፊል ይዘው ያለማቋረጥ የሚንቀሳቀሱት በእናንተነታችሁ ውስጥ ነው።
✏️…………እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ የሚንቀሳቀሱት እንደ ብርሃንና እንደ ጥላ አብረው ሆነው ነው ። ጥላው እየደበዘዘ ሲጠፋ ከኋላ የሚንቀረፈፈው ብርሃን ለሌላኛው አዲስ ብርሃን ይሆናል ። በተመሳሳይ ሁኔታም የእናንተ ነፃነት ማሰሪያውን ሲፈታ ለሌላኛውና ከፍ ላለው ነፃነት ማሰሪያ ይሆናል ።
{…………"የኻሊል ጂብራን ምርጥ ስራዎች………
………… ትርጉም…"ግርማ ለማ"……………………
………… ገፅ………210 - 212 ……………………}
🍂🍂ለዓለም እደበቀለ አበባ ዋሉልኝ!!!🍂🍂
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
አንዳንዱ ግልጽነት ስትለው ክፍትነት ይመሥለውና የማይባለውን ሲል ታገኘዋለህ።
ሌላው ተናጋሪነት ማለት ለፍላፊነት እየመሠለው ባገኘው ርእስ ዙሪያ ሲቦጠረቅ ታገኘዋለህ
.
ይሄኔ "ሽጉጥ በኖረኝ" ትላለህ‼️
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም በጤና አደረሰን::
በአሉን የሰላም የጤና የፍቅር የመተሳሰብ ያርግልን!!!!
የሕይወት ደረጃ ላይ ከደረስን ያሰብነውን ካሳካን በኋላ እንደሰታለን ብለን እናስባለን፦
ነገር ግን ያሰብንበት ደረጃ ላይ ስንደርስ ያለምነውን ደስታ ከማጣጣም ይልቅ ሌላ አዲስ ልንደርስበት ልናሳካው የሚገባ ነገር እናስቀምጣለን።
እንዲህ እያልን ሙሉ ሕይዎታችንን አዳዲስ መዳረሻዎችን እያስቀመጥን እንሄዳለን ይህ የሰው ልጅ ባህሪ ነው።
ደስታ ከጅምሩ ይዘነው የምንነሳው እንጂ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሰን የምናገኘው አይደለም።
ዛሬም የኛ ሂወት ነውና ባለን ነገር እየተደሰትን የሌለንን ለማሟላት የህይወት ጉዟችንን እንቀጥል
ስለዚህ ጥዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ባለን ነገር በመደነቅ ፣ በመደሰት ፣ በመርካት ምስጋና አቅርበን ደስተኛ ህይወት መኖር እንችላለን። ባለህ ነገር ተደሰት
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
የጠበቅነው ለመማር ነበር፤ የተማርነው ግን መጠበቅን ነው‼️
ስታስተውለው 🤔 የሚያመው ይበዛል ይህ ሁሉ ግን ለበጎ ይሆን❓🤔ወይስ ክፋት ነግሷል 🤔።
ክፋትስ መንገሱ ለበጎ ይሆን❓🤔
መልካሙን ማሰብ 🤔 ይሻላል ውብ 😍 ቀን ይሁንልን 🙏 ።
●------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ሕይወት ብዙ መልክ አላት በአካል አትወሰንም በተሰጠህ ፀጋ እንጅ።
ሌሎችን መምሰል ከፈለክ ቶሎ ተስፋ ትቆርጣለህ ብኩን ሆነህ እንዳትቀር በተሰጠህ ፀጋ ተደሰት ካልሆነ የበይ ተመልካች ሁነህ መቅረትህ ነው።
በረከትን ቁጠር
●-------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ፍቅረኞችን ❤️ ሸፍነህ አትለያያቸውም‼️ በየትም ቀዳዳ ተፈላልገው ይገኛሉ‼️
ማን ነበር ካንድ ወንዝ ይቀዳሉ ምናምን ሲለኝ የከረመው
●------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
“ሑ ላ ች ኁ ም _ ተ ቀ ባ ዮ ች _ና ች ሑ ና . . .”
_
« . . . ሲሰጡ ስስት የማያውቁ የማያማቸው ደስታን የማይፈልጉ ለደግነታቸው ትኩረት
የማይሰጡም ኣሉ።
.
እዚያ ማዶ ባለው ሸንተረር ላይ ያሉ ኣረንጓዴ እፅዋት ማራኪ መዐዛቸውን ያለ ስስት ወደ
ህዋው እንደሚተነፍሱት ሑሉ እነዚህኞቹም የሚሰጡት በሰፊው ነው . . .
.
ፈጣሪም በእነዚሕ ሰጪዎች እጅ በኩል ይናገራል። ከዓይኖቻቸው ጀርባም ሖኖ በፈገግታ ወደ
ምድር ያያል . . .
በተጠየቃችሑ ጊዜ መስጠት መልካም ነው። ነገር ግን ሳትጠየቁ መስጠት እንዳለባችሑ
ተገንዝባችሑ መስጠት የተሻለ ነው . . .
ደፍሮ የማይለምን ተቀባይን መፈለግም እጁን ዘርግቶ ለሚጠባበቀው ከመስጠት የበለጠ
ደስታ ኣለው . . .
.
ደግሞስ የምትነፍጉት ነገር ኣላችሁን ? ያላችሑ ነገር በሙሉ ኣንድ ቀን መሰጠቱስ
ይቀራልን ?
.
እናንተ ተቀባዮችም ብትሖኑ ሁላችሁም ተቀባዮች ናችሑና የማመስገን ጫና ኣይሰማችሑ።
ኣሊያ በራሳችሁም ላይ ሖነ በሚሰጣችሑ ላይ ቀንበር ትጭናላችሑ . . . »
_
# ካህሊል_ጂብራን
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
እኔ አዳም እሷ ሄዋን… የያኔዋ ሄዋን ገብጋባ አልነበረችም ያሁኖቹ እኮ እየበሉ ሚርባቸው እየጠጡ ሚጠማቸው… ናቸው ያኔ ግን ሄዋን የጣፈጣትን ቀምሳ… ይሄማ… ጣፋጭ ነው አዳሜ ቅመሰው ብላ አጎረሰችው
… ይሄ ፈረንጆቹ ፖስቲቭ ቲንከር እንደሚሉት ቀና አሳቢ ለመሆን አደለም… ያው ሰብአዊነት ከዛ አደል ሚጀምረው… እና ብቻዋን ልትበላ❓ ኧረ በስመአም አታረገውም
…… ከዛ በላች ጣፈጣት ከጣፈጣት ወዲያ አቀመሰችው አለቀ ሌላው
እንተወው …የተረፈውን እስኪበቃችሁ ታውቁታላችሁ‼️ ስለመታውቁት ላውራ ስላልሰማችሁት ልናገር ልብ ስላላቹት አጢኑት‼️
…
አያችሁ… ከዛን ወቅት ጀምሮ ነው እንግዴ ሚስት ለባልዋ ማጀት ጉድ ጉድ ብላ ማብላትና ማጉረስ የጀመረችው ስናመሰጥር መሆኑ ነው…
…
ከዛ እንግዲህ ወደዚህ ስንመጣ… አዳም… ለሄዋን ባልዋ ነው ወንድምዋ የሚል ጥያቄ እናነሳለን…🤔 ይሄ ጥያቄ ያስወግዛል ሆኖም ወልደዋል ስለዚህ ባል እንበለው
… አዳም ለልጁ አቤልና ቃየልስ አጎት ነው አባት የሚያስብል ሌላ ጥያቄ እናነሳለን❓ … ኧረ ይሄም ያስወግዛል… ግን አባትም አልነው አጎት ዋናው ማመኑ ነው…‼️
…
አዳም ሽማግሌ ሳይልክ ሄዋንን ካገባ… ሰርግ ሳይደግስ ሄዋንን ከጠለፈ እኔ ከማን በለጥኩ እና ነው እሷ ከማን በልጣ ነው ጥሎሽ ለሷ… በቀደምት አባቶቻችን ዘንድ ያልነበረ ባህልና ወግ ከየት አመጣን❓
… የሚኒሊክን ሻሽ ፊፊቲ ሴንት ወሰደው… የባላገሩን ጋርሶ ባላቶሊ በላን ከምንል ይሄስ ባህላችን መች እና እንዴት መጣ ለምን አንልም…
አይ እኛ ፑሽኪን ሲሆን በአያቱ የኛ ነው ብለን ግግም እናንተ ቱትሲዋች ወደ ሀገራችሁ ኢትዬጵያ ሂዱልን ብለው ሁቱዋች ገጀራ ሲያነሱ… ማን የኛ ይበላቸው…
…
የሚከብደንን ካላደረግን የሚቀለንን ብናረግ ጥቅም የለውም… ሁለት ያለው አንዱን ለባልንጀራው ይስጥ የሚለውን ትዛዝ ማንም ሳያከብር… በየመንገዱ ላለ የኔ ቢጤ ቁራጭ መወርወሩ አጉል መመፃደቅ ነው…።
…
ሎተሪ ሲቆርጥ ሰባት ሚልየኑ ከደረሰኝ ለሚካኤል… አንዱን ሚልየን እሰጣለሁ አለኝ… ደሞ ሚካኤል ያንተ ገንዘብ ምን ያረግለታል አልኩት እዛ ብትሰጥ ማን እንደሚበላው ታውቃለህ አልኩት አላስጨረሰኝም አውቃለው ምናቃቸው ይበሉታል አለኝ ኧረ ለተቸገሩት መቶ መቶ ብር ሰጥቼ ጨርሰዋለው አለኝ…
አደንደዛም አታርግ አልኩት ከቻልክ ለ አምስት ሰው ሁለት ሁለት መቶ ሺህ ብር ስጣቸው… ካልሆነ ለአስሩ አካፍላቸው መቶ መቶ አልኩ… ተስማማ ሲደርሰው
እንደዛ ካደረገ አበጀ…
ግን አይደርሰውም… ሎተሪ ማለት እንደ ላዳ ሾፌር ያልቀጠርከውን ሰው መጠበቅ ማለት ነው
…
አጉል ፅሁፍ ነው የፃፍኩት ኣ❓
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
የኔ ሚስት እኔን እምታየኝ እንደ አምላኳ ነው❓ እንዴት እንዴት❓❓
ሲሞላላት ዞር ብላም አታየኝ አለሁ የለሁ ተናደድኩባት ግድ የላት… ሲቸግራት ስትፈልገኝ እንዲ አድርግልኝ ብላ ልምምጧ አይጣል… … ኧሃ ኧሃ… ……
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
በህይወት ያለን ጎሽ… ስጋውን መካፈል ዋጋ ያስከፍላል… መጀመሪያ ጎሹን ጥሎ አርዶ ነው መካፈል‼️ ደግሞ ከአንበሳ 🦁 ጋር ለመጣላት… አንበሳ 🦁 መሆን ያስፈልጋል…
ተራ ፍየል 🐐 እየተነሳ ና ወንድ ከሆንክ አንበሳን 🦁 የሚል ከሆነ… ከባድ ችግር ነው ያለው ማለት ነው‼️
…
#ለማንኛውም …
👉 በተለይ የኛ ሰው የሚለው አያጣም… ገንዘብ 💸 ሲኖርህ… ዳንጌቦ (ሙጠምጢም 😂) እኮ ነው ይልሀል
👉 ከሰው ለየት ያለ የማገናዘብ 🤔 አቅም ካለህ ያ መተተኛ አባቱ አብሾ አጠጥተውት እኮ ነው…ይልሀል
👉 ተመችቶህ ሞላ ስትል… ምፅ እንትናም ሊሞት ⚰ ሲል እንዲህ ነበር ድንቡሽ ቡሽ ያለው…
…
💠 ስትሰራ በርታ 💪 የለም ❌ … 🙅♂
👉 ያዋጣል ብለህ ነው ይሆንልሀል ግን… ከዚህ ግን ይሄ አይሻልም…❓❓
ሀሳብ ማንም ይሰጥሀል እንካ በዚህ ገንዘብ 💸 ይሄን ተውና ያንን ጀምር የሚልህ ግን የለም ‼️
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛
ወደ ቤት 🏘 ስትገባ ጥቁር ድመት 🐈 መንገድህን 🛣 ካቋረጠች አለቀልህ ቤት 🏘 ጉድ ይጠብቅሀል ማለት አይደለም 🙅♂
💥 አንድ የቤት እንስሳ… ካንተ ፊት እንዳለፈች አስብ ድመቷ 🐈 ግን አንተ
ስታቋርጣት በጣም ተስፋ ቆርጣ ነበር ይሄን አይነት ሰው አቋርጦኝ ቤት ደህና ነገር አይጠብቀኝም ብላ ነበር ‼️
●---------------------๑۩۩๑-----------------●
┏━ •• •🔥• •━━ • •🔥 ••🔥 ━┓
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
ሼር➢ @ye_esatu_wegoch
┗━ ••🔥 • • •━━ 🔥••• •🔥•━┛