yebezigetmoch | Unsorted

Telegram-канал yebezigetmoch - የግጥም መንደር

1655

የጥበብ መጀመሪያ ...... getem bech@

Subscribe to a channel

የግጥም መንደር

?❤️‍🩹 መድኃኒት❤️‍🩹🥹

ክፍል ፩

✍በቤዛዊት የሴት ልጅ ✍

የስልኩ ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ ተናደድኩ...... ያቋረጡኝ ምን ከመሰለ ህልም ነበር። የህይወቴ የመጨረሻዋ ስኬቴ ናት አምላኬ እሷን የሰጠኝ ዕለት እውነት በዓለም ላይ ሾሞኛል ማለት ነው። "ባሮክ ባሮክ" ጩኸቷማ እህቴ ነበረች ወደ ቆጡ መውጫ መሰላል ላይ ሆና የምትጠራኝ። "ተነስ ኧረ እንዳትበቅል" አለችኝ። ብበቅል ደስ ባለኝ እሷን እያሰብኩ ጥርሴ ቢረግፍ ጸጉሬ ቢሸብት አልኮነንም ነበር።

እንደ ምንም ተነስቼ ወረድኩኝ። ምሳ ቀርቧል የእህቴ ቆንጆ ሽሮ እንጀራው ላይ ራስ ሆኖ ይታያል ተጣጥቤ ከማዕዱ ተቋድሼ ወደ ጓደኛዬጋር ሄድኩኝ።
ባሮክ እባላለሁ በኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ከተመረኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል እንደማንኛውም ወጣት የመንግስት ስራ ባይኖርኝም ለራሴ ባመስነፍ ከአንድ ሞል ላይ አንዲት ልጅ ቀጥሬ ቡና ጠጡ እየሰራሁ ነው። አብሮ አደጌም ሳሚም የራሱ የስፖርት ቤት ከፍቶ እየሰራ የሚገኝ የቅባት ልጅ ነው። ከሁለተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ተምረን ያደግን ልጆች ነን። አሁንም ወደ እሱ ነው የምሄደው። ገና ስደርስ ሽሮ በልቶ የሚያድረው ህዝቤ ይሄን ብረት እየገፋ ነበር የተጨማደደ ፊቴን ፈገግ አድርጌ ወደ ሳሚ ቢሮ ገባሁ።
"እ ብሮ ቆየህ እኮ" ገና እንዳየኝ ሳሚ ተናገረ።
"ምን ከመሰለ ህልም ላይ እንደተነሳሁ ብታውቅ እንዲህ ባላልክ" አልኩት ሰላም ብዬው እየተቀመጥኩ።
"ቅዠታም ደግሞ አገረሸብህ" አለኝ ፋይሉን እየከተተ።
"የምሬን ሳም በአሁኑ እኮ ሳገባት ነው ያየኋት" አልኩት ውስጤ ያለውን ደስታ ከፊቴ እያስነበብኩት።
"ቆይ ለምን ሱባኤ አትይዝላትም እንዴ ተቆጣጠረችህ እኮ" አለኝ የባከንኩ የመሰለው አብሮ አደጌ።
"ሳምዬ ብትቆጣጠረኝማ እየበተነ ያለው በረከቴ በሰበሰብኩት የተዘጋው በሬ በተከፈተልኝ እውነት እንዴት ውብ ሆና ስታየኝ እንደነበር በተለይ የምወደው ጥርሷ ብልጭ አድርጋ ስታሳየኝ እኮ....." አቋረጠኝ።
"ተነስ ባክህ እንሂድ" አለኝ። ተናደድኩ ተኮሳትሬ ቀድሜው ወጣሁኝ። መኪና ውስጥ እየሄድን ዝም አልኩኝ ዕቃቃውን እንደተቀማ ህፃን እጄን አጣምሬ በመስኮቱ ወደ ውጪ እያየሁ ነበር እንደማላወራው የተረዳው ሳሚ ሙዚቃውን ከፈተው።

🎧🎧🎧🎧🎧
ኤፍሬም እኔን የጠየቀኝ ይመስል ስለ ውበቷ የዘፈነልኝ የሚመስለኝን የምወደውን ሙዚቃ ነበር
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶

ዞሬ አየሁት እና ፈገግታዬን ሰጠሁት። "ኧረ ወንድሜ ለአንተ ብዬ ነው አልነገርካት ነገር ልጅቷ በየት ትወቀው ሁሌ እየተያዩ መሳቅ በአይን መሸኛኘት ይጎዳሃል። በህልምህ አትቃዥ ንገራት" አለኝ አፍ ሆኖ የሚነግርልኝ ይመስል። እኔም ሌላ ክርክር ውስጥ ላለመግባት የወሬውን ርዕስ አስቀይሬ ስለ ምንሄድበት ስራ ማውራት ጀመርኩ። ከደቂቃዎች በኋላም የምንገባበት ህንጻ ጋር ደርሰን መኪናውን ፓርክ እያደረግን እኔም ሳሚም የደነገጥነው። ህልሜ ናት......

ክፍል ፪ይቀጥላል

❤️‍🩹🥹መድኃኒት አዲስ ተከታታይ ታሪክ ❤️‍🩹🥹

በማንበብ አስተያየት ስጡ ወዳጆቻችሁን ጋብዙ!
/channel/yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ህይወት ሁሉ ጊዜ ሁለት አማራጭ አላት አንዱ
ምን አባሽ ብሎ ጥሎሽ ሲሄድ አንዱ ደሞ ምን
አባቴ ልሆንልሽ ምን ጎደለብሽ ብሎ ይመጣል ..

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ፅናት ወዳንቺ የሚወስደኝ ከሆነ እስኪበቃሽ ድረስ ፀንቼ ጠብቅሻለው ።❤💔😔

Читать полностью…

የግጥም መንደር

• ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

• አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

• ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ

• ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

• ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

• ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

• ፀዳ በል፡፡ በደንም ልበስ፣ ፏ በል!

• ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

• አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

• በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

• ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

• የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናር

• ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

• ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

• ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

• የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

• ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል

✋🌹 በቸር ያውላችሁ ✋🌹

✍ @yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

@yebezigetmoch ❤💔
💋🙈🥺

😞 ትዝታዬ😞

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ወጣሁኝ ከቤታችን ወደ ተለመደው ቦታችን አብረን ወደታየንበት ሳቅሽ ሳቄ ከሆነበት ሰውን ረስተን በፍቅር የሰከርንበት❤ ህልም ያለምንበት ተኳርፈን ከታረቅንበት ከቦታችን ደረስኩኝ😒ቁጭ አልኩኝ......
ማኩረፊያዬ 💋 ቦታው ልክ እንደ እኛ ተለውጧል እኔ ልሙት! ብታይው ትገረሚያለሽ❤️🤌.....

❤ቤዛዊት የሴት ልጅ❤

💬💬💬💬
💬🐷🐷🐷💬
💬 በመጥፋታችን ይቅርታ 💬
💬💬💬💬
😳
🙏
👖
👟👟
Join ❤👏 👌👌🌹🌹🌹

Читать полностью…

የግጥም መንደር

አደራ ጠርጥሪኝ

ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ

እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
....ማለቱን ካበዛሁ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ


አደራ......
/channel/yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

በሰዎች ለመወደድ ብዙ ዋጋ እንከፍላለን፤ ሰዎች ደግሞ አይን የሚጥሉት ወይ አጥብቀው የሚወዱት ጠንካራ የሆነ ሰውን ነው። ማንም ደካማን አይወደውም፤ እንዲሁ የሚወድህ ፈጣሪ ብቻ ነው።

ወዳጄ ጠንካራ መሆን ከፈለክ ራስህን አክብረው፣ ራስህን ከነ ድክመትህ ውደደው እና የህይወትህን ትልቁን አላማ እወቀው እሱ ላይ አተኩር ከዛ ሰዎሰዎይች አንተ ላይ ያተኩራሉ፤ እሱኮ ጠንካራ ነው አላማ አለው ብለው ይወዱሀል፤ ሳታስበው ድንቅ ማንነት ገነባህ ማለት ነው!

/channel/yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

አዲስ ነገር ዛሬ ማታ🖤 🙏💥💥💥💥

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ይሄ ቀን ለኔ ነው በል! 💪

እንዴ ላንተ ባይሆንማ በተኛህበት ትቀር ነበር፤ ስንቶች በተኙበት ቀሩ? ስንቶች በዚህ ለሊት ከመሬት በታች በመቃብር አደሩ? ለምን መሰለህ? ቀናቸው እንዲሆን ፈጣሪ አልፈቀደማ! እኛ ግን ተፈቅዶልናል ዛሬ የኛ ነው!

ታላቅ ሰኞ ተመኘንላችሁ

Читать полностью…

የግጥም መንደር

በሀገራችን እንዲሁም በመላው አለም የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለ1442ኛው ዓመተ-ሂጅራ የኢድ አልአድሃ~አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!🧡

EID MUBARAK 🕌
የግጥም መንደር🤲🤲🤲🕋🕋🕋

Читать полностью…

የግጥም መንደር

❤❤❤ተስፋ🍁🍁🍁
🥀 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
በቤዛዊት የሴትልጅ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ክፍል ስድስት
🥀🥀🥀🥀ከቦሌ አየርመንገድ ገብተን መጠበቅ ጀመርን ስልኳ ጠራ "ውዴ ወረድሽ" አለች ዮዳሄ። "እሺ ስትወጪ ታይኛለሽ" አለችና ዘጋችው መልሳ ወደ እኔ ዞራ " ከባሏ ጋር ነው የመጣችው ይቺ ጉድ" አለችኝ። ለምን እንደሆነ አልገባኝም ልቤ በሃይል ትዘል ጀመር።ወንድነቴ ጉልበቴ ተነነ "ደግሞ ፍቅረኛዬ ነው ብዬ አስተዋውቅሃለሁ እንዳትዘላብድ" አለችኝ። " ለምን እንዴ እህህ" የምላት ግራ ገባኝ "ደነዝ በእኔ ብቸኝነት ስለሚከፋቸው ነዋ የእሷ ባል ወንድሜ ነው የኔን ሰርግ ለማየት የሚናፍቅ ነው ስለዚህ ለትንሽ ጊዜ እስኪሄድ እናስመስላለን ድንጋይ ታካብዳለህ እንዴ" አለችኝ። የስድብ ሰይጣኗ ተነስቶባት። "እሺ ግን.." አላስጨረሰችኝም "መጡ መጡ እጄን ያዘኝ ማሬ" ብላ ትወናውን በይፋ አስጀመረች እጄ በመዳፏ መሃል ሲሆን ደግሞ ልቤ ጉሮሮዬ ጋር ደረሰች። እሷ ግን ምንም አልመሰላትም ፈገግ ብላ የሚመጡትን ጥንዶች ማየት ጀመረች እኔ ግን እሷን እያየሁ ነበር። "አታፍጥ እነሱን ተመልከት" አለችኝ። ፈገግ ብዬ ወደሚመጡት እንግዶች እኔን እንደ ፍቅረኛ የሚተዋወቁኝ እኔም እንደ ቤተሰብ የማውቃቸው ጋር አይኔን ወረወርኩ።

ጠላታችሁ ክው ይበል ልቤን በጦር የተወጋሁ ይመስል ክው ድርቅ አይኔን ፍጥጥ አድርጌ የዮዳሄን እጅ ለቀኩኝ። እሷም ፈገግ እያለች "ድንጋይ እርጥብ ነሃ" እያለች አጉረመረመች። እኔ ግን ድንጋይ ብሆን ፈጣሪን የማመሰግንበት ሰው ሆኜ ግን በማየቴ የማማርርበትን ነገር አይቼ ነው። ሰናይት ናት የለቀቀኝ እጇ በሌላሰው ተይዞ የልጄ እናት እንድትሆን የጓጓሁላት በሌላ እጇ ልጅ ይዛ በሆዷም አዲሱን ህፃን እየጠበቀች አየኋት። ሳላውቅ በቀኝ አይኔ ብቻ እንባዬ ፈሰሰ ወዲያው ሞዥለቅ አድርጌ ጠረኩት "ዮ ዬ ኬኳ" ሰናይት ከዮዳሄ ጋር ተቃቀፈች።"ሰውየው ይኸው" አለች ዮዳሄ እኔ ላይ እየጠቆመች። "ኧረ ዮ" ሰናይት አላስተዋለችኝም ይሁን አውቃ እንደማያውቀኝ ሰው ልታቅፈኝ ወደእኔ ቀረበች እኔ ግን በሌላ ገላ ውስጥ የተዋሐደው በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ያለው ሰውነቷ የአጋም እሾህ መስሎ ታየኝ እጄን ሰነዘርኩላት መራቄ ስለገባት እጄን ጨብጣ አብሯት ከመጣው ባሏ ስር ተሸጎጠች ዮዳሄ በእንባ ከወንድሟ ጋር ተቃቀፈች እና "ፍቅር እሱ ወንድሜ ነው እሷ ሚስቱ ነች ማኪ ደግሞ ልጃቸው" አለችኝ ደስ የሚል ዜና መስሏት በፈገግታ "እንኳን ደህና መጣችሁ" ብዬ ወደ መኪናዬ ሻንጣቸውን እየገፋሁ ከነፍኩ። የብስጭት የንዴት እሳት ውስጤ ሲቀጣጠል ይሰማኛል። ስናፍቃት የኖርኩት ሰናይትን ሳገኝ በደስታ ጮቤ የምረግጥ መስሎኝ እንዳገኛት ጸልዬ ነበር ግን አሁን ደስታ የለም እኔ ጋር።

እንደምንም እየነፍስኩ በሩን ከፍቼ ገባሁ ዮዳሄ ከአጠገቤ እነ ሰናይት ከኋላ ተቀመጡ "ደከመሽ እንዴ" ዮዳሄ ጠየቀቻት። "አይ አልደከመኝም" አለች ሰናይት በመስታወቱ እኔን እያየችኝ። የዮዳሄ ወንድምም "ሳትተኛ ነው የመጣችው" አለ እጇን ጠብቆ አርጎ እየያዘ "ለምን አትተዛዘሉም ደነዞች" አልኩኝ በልቤ መልሼ ፈገግ አልኩ ዮ የምትሳደበው ስድብ እኮ ነው ብዬ። "እና አዲስ ፍቅር እንዴት ነው" አለች የኔ ጠላት ሰናይት። ዮ ለመመለስ አፏን ስትከፍት ቀደምኳት " የረከሰ የማይሰጥ ፈጣሪ ይመሰገን በከበረ ፍቅሯ አክብሮኛል ዕድለኝነት ደስታ ተስፋ ልዩ ጣዕም አለው ሁሌም አዲስ ፍቅር" ብዬ በአንድ እጄ መሪውን እንደያዝኩ በአንድ እጄ የዮዳሄን እጅ ያዝኩ። "ስለአንተ ብዙ ብላኛለች ግን ከተባለልህ በላይ ነህ" አለችኝ ነገረኛዋ ሰናይት።" የእሷ ፍቅር ነው ከፍ ያደረገኝ የሞላኝ ይመሰገን" አልኩኝ። ዮዳሄ በመልሴ ደንግጣ ምልሷን ውጣለች። "ፍቅር እኔን እዚህ ጋር አውርደኝ እና ሜካፕ ልሰራ አንተ ቤት አድርሰኻቸው ተመለስ" አለችኝ እና ልትወርድ ስትል እየተንቀጠቀጥኩ እጇን ስሜ ተለየኋት። እነ ሰናይትን ቤት አድርሼ እንደ ጭራቅ እያረገኝ ወደ ዮዳሄ ጋር መብረር ጀመርኩ። ላንቃት ልገላት....ማን ልኳት እንደሆነ ልጠይቃት......አላውቅም


❤❤❤ይቀጥላል💙💙💙💙ይቀጥላል💙💙💙💙

❤❤❤❤ተስፋ ❤❤❤❤❤

✍️በቤዛዊት የሴትልጅ ✍️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
📭 @yebezawit2 📬
ለአስተያየት 👆👆 ይጠቀሙ
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
የእኔ አይነቱ ተስፋ ቢስ ተስፋ ቢሰጠውም ይቀማል
🥀የለውማ የእሱ አይደለም🥀🥀🥀🥀.
🥀🥀#🥀🥀

Читать полностью…

የግጥም መንደር

❤❤❤ተስፋ🍁🍁🍁
🥀 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
በቤዛዊት የሴትልጅ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ክፍል ስድስት
🥀🥀🥀🥀ከቦሌ አየርመንገድ ገብተን መጠበቅ ጀመርን ስልኳ ጠራ "ውዴ ወረድሽ" አለች ዮዳሄ። "እሺ ስትወጪ ታይኛለሽ" አለችና ዘጋችው መልሳ ወደ እኔ ዞራ " ከባሏ ጋር ነው የመጣችው ይቺ ጉድ" አለችኝ። ለምን እንደሆነ አልገባኝም ልቤ በሃይል ትዘል ጀመር።ወንድነቴ ጉልበቴ ተነነ "ደግሞ ፍቅረኛዬ ነው ብዬ አስተዋውቅሃለሁ እንዳትዘላብድ" አለችኝ። " ለምን እንዴ እህህ" የምላት ግራ ገባኝ "ደነዝ በእኔ ብቸኝነት ስለሚከፋቸው ነዋ የእሷ ባል ወንድሜ ነው የኔን ሰርግ ለማየት የሚናፍቅ ነው ስለዚህ ለትንሽ ጊዜ እስኪሄድ እናስመስላለን ድንጋይ ታካብዳለህ እንዴ" አለችኝ። የስድብ ሰይጣኗ ተነስቶባት። "እሺ ግን.." አላስጨረሰችኝም "መጡ መጡ እጄን ያዘኝ ማሬ" ብላ ትወናውን በይፋ አስጀመረች እጄ በመዳፏ መሃል ሲሆን ደግሞ ልቤ ጉሮሮዬ ጋር ደረሰች። እሷ ግን ምንም አልመሰላትም ፈገግ ብላ የሚመጡትን ጥንዶች ማየት ጀመረች እኔ ግን እሷን እያየሁ ነበር። "አታፍጥ እነሱን ተመልከት" አለችኝ። ፈገግ ብዬ ወደሚመጡት እንግዶች እኔን እንደ ፍቅረኛ የሚተዋወቁኝ እኔም እንደ ቤተሰብ የማውቃቸው ጋር አይኔን ወረወርኩ።

ጠላታችሁ ክው ይበል ልቤን በጦር የተወጋሁ ይመስል ክው ድርቅ አይኔን ፍጥጥ አድርጌ የዮዳሄን እጅ ለቀኩኝ። እሷም ፈገግ እያለች "ድንጋይ እርጥብ ነሃ" እያለች አጉረመረመች። እኔ ግን ድንጋይ ብሆን ፈጣሪን የማመሰግንበት ሰው ሆኜ ግን በማየቴ የማማርርበትን ነገር አይቼ ነው። ሰናይት ናት የለቀቀኝ እጇ በሌላሰው ተይዞ የልጄ እናት እንድትሆን የጓጓሁላት በሌላ እጇ ልጅ ይዛ በሆዷም አዲሱን ህፃን እየጠበቀች አየኋት። ሳላውቅ በቀኝ አይኔ ብቻ እንባዬ ፈሰሰ ወዲያው ሞዥለቅ አድርጌ ጠረኩት "ዮ ዬ ኬኳ" ሰናይት ከዮዳሄ ጋር ተቃቀፈች።"ሰውየው ይኸው" አለች ዮዳሄ እኔ ላይ እየጠቆመች። "ኧረ ዮ" ሰናይት አላስተዋለችኝም ይሁን አውቃ እንደማያውቀኝ ሰው ልታቅፈኝ ወደእኔ ቀረበች እኔ ግን በሌላ ገላ ውስጥ የተዋሐደው በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ያለው ሰውነቷ የአጋም እሾህ መስሎ ታየኝ እጄን ሰነዘርኩላት መራቄ ስለገባት እጄን ጨብጣ አብሯት ከመጣው ባሏ ስር ተሸጎጠች ዮዳሄ በእንባ ከወንድሟ ጋር ተቃቀፈች እና "ፍቅር እሱ ወንድሜ ነው እሷ ሚስቱ ነች ማኪ ደግሞ ልጃቸው" አለችኝ ደስ የሚል ዜና መስሏት በፈገግታ "እንኳን ደህና መጣችሁ" ብዬ ወደ መኪናዬ ሻንጣቸውን እየገፋሁ ከነፍኩ። የብስጭት የንዴት እሳት ውስጤ ሲቀጣጠል ይሰማኛል። ስናፍቃት የኖርኩት ሰናይትን ሳገኝ በደስታ ጮቤ የምረግጥ መስሎኝ እንዳገኛት ጸልዬ ነበር ግን አሁን ደስታ የለም እኔ ጋር።

እንደምንም እየነፍስኩ በሩን ከፍቼ ገባሁ ዮዳሄ ከአጠገቤ እነ ሰናይት ከኋላ ተቀመጡ "ደከመሽ እንዴ" ዮዳሄ ጠየቀቻት። "አይ አልደከመኝም" አለች ሰናይት በመስታወቱ እኔን እያየችኝ። የዮዳሄ ወንድምም "ሳትተኛ ነው የመጣችው" አለ እጇን ጠብቆ አርጎ እየያዘ "ለምን አትተዛዘሉም ደነዞች" አልኩኝ በልቤ መልሼ ፈገግ አልኩ ዮ የምትሳደበው ስድብ እኮ ነው ብዬ። "እና አዲስ ፍቅር እንዴት ነው" አለች የኔ ጠላት ሰናይት። ዮ ለመመለስ አፏን ስትከፍት ቀደምኳት " የረከሰ የማይሰጥ ፈጣሪ ይመሰገን በከበረ ፍቅሯ አክብሮኛል ዕድለኝነት ደስታ ተስፋ ልዩ ጣዕም አለው ሁሌም አዲስ ፍቅር" ብዬ በአንድ እጄ መሪውን እንደያዝኩ በአንድ እጄ የዮዳሄን እጅ ያዝኩ። "ስለአንተ ብዙ ብላኛለች ግን ከተባለልህ በላይ ነህ" አለችኝ ነገረኛዋ ሰናይት።" የእሷ ፍቅር ነው ከፍ ያደረገኝ የሞላኝ ይመሰገን" አልኩኝ። ዮዳሄ በመልሴ ደንግጣ ምልሷን ውጣለች። "ፍቅር እኔን እዚህ ጋር አውርደኝ እና ሜካፕ ልሰራ አንተ ቤት አድርሰኻቸው ተመለስ" አለችኝ እና ልትወርድ ስትል እየተንቀጠቀጥኩ እጇን ስሜ ተለየኋት። እነ ሰናይትን ቤት አድርሼ እንደ ጭራቅ እያረገኝ ወደ ዮዳሄ ጋር መብረር ጀመርኩ። ላንቃት ልገላት....ማን ልኳት እንደሆነ ልጠይቃት......አላውቅም


❤❤❤ይቀጥላል💙💙💙💙ይቀጥላል💙💙💙💙

❤❤❤❤ተስፋ ❤❤❤❤❤

✍️በቤዛዊት የሴትልጅ ✍️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
📭 @yebezawit2 📬
ለአስተያየት 👆👆 ይጠቀሙ
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
የእኔ አይነቱ ተስፋ ቢስ ተስፋ ቢሰጠውም ይቀማል
🥀የለውማ የእሱ አይደለም🥀🥀🥀🥀.
🥀🥀#🥀🥀

Читать полностью…

የግጥም መንደር

💙💙💙ተስፋ 💙💙💙
ክፍል አራት
በቤዛዊት የሴትልጅ
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

አራት ኪሎ እንደደረስኩ መኪናዬን ከአንድ ጥግ አቆምኩ እና ወደ ተቆጭዋ እመቤት ደወልኩ ጠራ ደገመ "ምን ይሻልሃል በእናትህ ቆሚያለሁ እኮ" አለች የእውነት ጩኸቷ አጠገቤ ያለች ነው የመሰለኝ። "ደርሻለሁ " አልኳት ስልኩ ተዘጋ ወዲያ የመኪናዬ የኋለኛው በር ተከፈተ ሳምሶናይቷን ወርውራ ተቆጭዋ እመቤት ተቀመጠች። "ወደቢሮ ውሰደኝ" ትዕዛዝ ሰጠች እኔ ግን ቢሮዋን አላውቅም እና ዝም አልኳት። "ደነዝ ቶሎ ውሰደኝ" ስድብ ምርቃቷ ነው መሰለኝ። "አላውቀውም ቢሮሽን" አልኳት "ኡ ምኑ ነህ በእናትህ እሺ ወደ ሳርቤት ውሰደኝ" አለች እና የሚጮህ ስልኳን አነሳች። ረጅም ሰዓት ከማውራቷ ብዛት ምላሷ የሚያልባት ነው የሚመስለኝ። "በዚህ ጋር ታጠፍ" ብላ ወደ አንድ ቅያስ ጠቆመችኝ። ከህንፃው ጋር እንደደረስን አቆምኩላት "ና ተከተለኝ" ብላ ወረደች። የእውነት ለእሷ እያዘንኩ ከመኪና ወርጄ ተከተልኳት ገና ከቢሮው ስንገባ አንዲት ሴት ሮጣ መጥታ "ውስጥ ሆነው እየጠበቁሽ ነው ጠረጴዛው ላይ ያልሽኝን ፅፌ አስቀምጫለሁ" አለች እኩሏ እየተራመደች። እሷ ምንም ሳትመልስ ወደ አንድ ክፍል ገባች አብሪያት ገባሁ ከቦርጫም እስከ ኮሳሳ ክብ ጠረጴዛው ላይ ተሰይመዋል "ደህና ዋላቹ" ቦርሳውን እያስቀመጠች ሰላምታ ሰጠች ትርፍ ወንበሩ ላይ ተቀመጥኩ። "የዛሬው ዕለት ለድርጅታችን ጥሩ ነገርን የማጣ እና የአክሲዮን ሽያጮቹም ትርፍ ያገኙበት ነው........." እሷ ስታወራ እንቅልፍ ይዞኝ ጠፍቷል እኔ እንደዚህ በሚሊዮን የሚንቀሳቀስ ካፒታል አይቼ ሰምቼ አላውቅምና ወደ እንቅልፌ አለም ሄጄ ተሰወርኩ " አንተ ብሽቅ" የሚል ድምፅ ከእንቅልፌ አነቃኝ። አይኔን አሸት አድርጌ አየኋት ልጅቷ ብቻዋን ተቀምጣለች። "አለቀ እንዴ" አልኳት። "ምን አለ ውለታ ብትውልልኝ" አለችኝ ደነገጥኩ የሰው ዕርዳታ የምትሻ አትመስልም ስለገንዘብ ታወራለች ስለ ህክምና ስለ ህግ በአገኘኋት አጋጣሚ የታዘብኳት ነገር ነው። "ምን ልታዘዝ" አልኳት። መነፅሯን አውጥታ ጠረጴዛው ላይ እያስቀመጠች "ዮዳሄ እባላለሁ የዚህ ድርጅት ከፍተኛ ሼር ነኝ ያው በቤተሰቦቼ ስም ቢሆንም እኔ ነኝ አሁን የምሰራው ከዚህ በተጨማሪም የአባባ እርሻ የመድሃኒት አስመጪ እና ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አስተዳድራለሁ በማኔጅመንት እና በፋርማሲ የመጀመሪያ ድግሪ አለኝ። ከዛ ባለፈ ደግሞ የዕርዳታ ተቋም አለኝ በትንሹ...." ልጅቷ ስታወራ እኔ አፌን ከፍቻለሁ። "እና አሁንም ጊዜ የለኝም እንድታግዘኝ የምፈልገው በሹፌርነት ብቻ ሳይሆን አማካሪዬ እንድትሆን ሰዎች የስራ ጫናዬን አይተው ሊያጭበረብሩኝ ይሻሉ እና እንደ አማካሪ አጠገቤ ብቻ እንድትገኝ ነው ገንዘብ እከፍልሃለሁ" አለች አይኖቼን እያየች። "ዕውቀት የሚባል እኮ የለኝም" አልኳት እንዴት ይሄ ሁሉ ነገር ለምትሰራ እና ብዙ ትምህርት ለተማረች የኔ አይነቱ መሃይም ምን ሊጠቅማት ይችላል። "ደነዝ መማር የማይወድ ህዝብ ብቻ....እኔ የፈለኩት አብረኸኝ እንድትገኝ ነው እንጂ እንድታግዘኝ አይደለም" ኧረ ስድብ አልኩ። ያለ ፍርሃት መሃይም ስትለኝ ደነቀኝ ከተቀመጠችበት ተነስታ እንድከተላት በአይኗ ተናግራ ከስብሰባው ክፍል ወጣን። ከኋላዋ እየተከተልኳት ስንት የጭንቅላት ብሎኗ ቢፈታ ነው ክብር የሚባል የሌላት እያልኩ አየኋት። አለባበሷ አቋሟ ፍክት ማለቷ እንደ ጠዋት ፀሐይ ተወዳጅ ያደርጋታል ስድቧን እና ጥድፊያዋን ላየ ደግሞ የሰባት ሰዓት ፀሐይ ሆና ተንገበግባለች። አንዱን ቢሮ ከፍታ ገባች እኔም እንደ ጥላው ተከትያት ገባሁ። "ይሄ የኔ ቢሮ ነው አክሲዮን ሲሆን ከብዙ ምሁራን ጋር ነው የምንሰራው ስለዚህ ለአለባበስህ ለንግግርህ መጠንቀቅ አለብህ ቅርፅህንም አስተካክል" ተፀይፋ አየችኝ። "የምን ቅርፅ ክብ ልሁን" አልኳት። "ጂም መስራት ጀምር ራስን ጠብቅ" ወንበሩ ላይ ተለጥጣ ተቀመጠች "ሜካፕ ተሰራ" ከተቀመጥኩበት ወንድነቴ ተነክቶብኝ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ እና ቁልቁል ተመለከትኳት አንጋጣ አየችኝ ቁልፉን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩላት " መጀመሪያ ክብርን እና ስርዓትን ተማሪ ጨርቅ ከምትለቅሚ ድግሪ ከምትሰበስቢ መጀመሪያ ሰው ሁኚ ስርዓት....." በሩ ተበረገደ።

☺️☺️☺️☺️☺️ይቀጥላል☺️☺️☺️☺️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱
🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊
🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈
ተስፋ

Читать полностью…

የግጥም መንደር

❤️❤️ተስፋ ክፍል ሶስት❤️❤️❤️
ከሰዓታት በኋላ ይቀጥላል

Читать полностью…

የግጥም መንደር

"ደስታ በዙሪያህ የምትጠብቀው ነገር አይደለም,
አንተ ራስህ የምትፈጥረው ነገር ነው."
@yebezigetmoch 😍
join 💗

Читать полностью…

የግጥም መንደር

በስህተት የ5ብር ካርድ ወደ ስልኬ ልከው
ማንም ሳይጠይቀኝ ለባለቤቱ መልሻለሁ 😁😋

Читать полностью…

የግጥም መንደር

" የናፈከኝ ለታ"

ብዙ አለም ኣላውቅም
ብዙ አለም ኣልኖርኩም
ጊዜን ካንተ ጋራ
ቁጥር ኣልሰፈርኩም
ግን......የናፈከኝ ለታ
አይንህ ከአይኔ ሲያርፍ
አቅሜን እንዳሳጣኝ
በከንፈርህ መሳም
ልቤ እንደከዳኝ
በእቅፍህ አለም
ሚወስደኝ አታሎ
ደስታ እንደ ሞት ነው ወይ
እራሴን አስጥሎ
እኔ አላውቅም.......
ነብስ ድረስ ሚዘልቅ
ፍቅር ይሰማኛል
የናፈከኝ ለታ
ሰከንድ ያድርብኛል
ትዝታን እየካበ
አንተን አንተን እያለ
እኔን ይንደኛል
ማሰቤስ የታለ
ሸመትከው በፍቅርህ
ሸከፍከው በጀርባ
ልቁረጥ ያሉት ፍቅር
ለምለም ነው ሚረባ
የናፈከኝ ለታ........
አንተ አደርስበት
ጥልቅ ነው ስሜቱ
በሌለህበት
እልፍ ነው ፍሰቱ
ናፍቆትህ ትንግርቱ
.
.
.
💋💋💋🌹🌹🌹❤️❤️❤️🤌🤌🤌
@yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

የፍቅር ደብዳቤ

👩‍❤️‍💋‍👨.... ፍፁም አይቼ የማላውቀው ዓለም የማላውቀው ስሜት ካንቺ ጋር በመሆኔ የሚሰማኝ ብቻ መንፈሴ ትረካለች ፍፁም ደስተኛ እሆናለሁ.....❤
@yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

💔 መቆየት ለፈለገው ልብህን
መሄድ ለፈለገው ደግሞ መንገዱን
ዘርጋለት‥
🌹💋😍

Читать полностью…

የግጥም መንደር

አለሌ ነበርኩ ። ከህንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ። የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም አልቆጠርኳቸውም እንጂ።

ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው ።ሆቴሏ ሸጎጥ ያለች ሰዋራ ስፍራ ነች ፤ ከመኖርያዬም እሩቅ ነች ።

አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም ። ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ ።

ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል ፤ በእርግጥ መስኪ የምትባለው ትንሽ ተለቅ ትላለች ።
ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን ፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን ፣ ነፍፍ ቺክ ስለማመላልስ ይሆን ፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ
አትስቅልኝም አትኮሳተርብኝም ።

ፊቷ አልሰጥም።።ን ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው። መስኪ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም ተመሳሳይ ነው ።

ክላሴ ውስጥ አጭሼ ፣ ጠጥቼ ፣ ባልጌ ሹልክ ብለን በጓሮ እንሄዳለን ። በሌላ ቀን ሌላ ቺክ ይዤ እመጣለሁ ፣ ካልጠረረብኝ ቺክ አልገርብም ።

ሁሉንም እንደሙዳቸው እና እንደፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ ።
ላጤነቴ በነፃነት ታየው አልታየው ብዬ ሳልሳቀቅ ለመባለግ አግዞኛል።

ጓደኞቼ ሁሉ ሲያገቡ ፤ ቤተሰቦቼ የአታገባም ውትወታ የበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅኩ ።

ባገኘኋት በሁለተኛ ቀን ለመቾመስ በት በት አልኩ አልተሳካልኝም ።
በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል ምነው አለቺኝ

እርጋታሽ ደስ ይላል አልኳት

ውስጤ እንደላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ አለቺኝ ። ይሆናል ግን ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል አልኳት ከንፈሯን ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ አይነት አለቺኝ

በነገራችን ላይ

አንተም ረጋ ያልክ ነክ አለቺኝ... ስስቅ ። ውስጥህ ወዲ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ አለችኝ ።

ይሆናል አልኳት

ሶልያና የበዛ እርጋታ አላት ፥ እርጋታዋ ይረብሸኛል ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው የሚሰጠኝ።

አብሪያት የምሆነው እስከምደክላት ብቻ ነበር።

ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ ። ሲኒማ እጋብዛታለሁ ፤ ትያትር ትጋብዘኛለች ከንፈሯ ጋ ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ

በጭራሽ የወሲብ ወሬ ለማውራት አታመችም ። ወሲብ ነክ ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም።ወሲብ ነክ ወሬ ካወራሁ ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም።

መንፈሳዊ ጉባኤ ትጋብዘኛለች። ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ ።

ቀልቧን ለመግዛት መንፈሳዊ መፅሃፍ እያነበብኩ ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እውቀት አለኝ ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ ወሬው ሲጥማት አያለው።

ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ ።

ከሌሎች ስለተለየች ይሆን ፣ እንደምፈልገው
አለመሆኗ ይሆን ፣ የምፈልገውን ስላልሰጠቺኝ ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች።

ውሎዋን ስራዬ ብዬ እከታተላለሁ ። ካልተደዋወልን ይታወቀኛል ። እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ ። ሳላገኛት የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ ።

ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ ። በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ ። ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ

የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ የምቀመጭላቸው ቺኮች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን ቀየርኩ ።

የትላንት የውድቀት መንገዳችንን ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል ።

አሁን ፈልጌ መፅሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እፆማለሁ ጉባኤ እከታተላለሁ ።መንፈሳዊ ጉዞ እሄዳለሁ ። ከሶሊያና ጋ እንፋቀራለን። የትላንት መንገዴን አልተረኩላትም ለዛሬው ማንነቴ ግን ማሃንዲሷ እሷው ናት ።

ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት። የትላንት ህይወቴን እንዴት አሁን እንደማልወደው ። ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሃሳብ አልሰጥም ያ ዘመን ያሳፍረኛል።

ሶልያና አንድ እለት ስትፍነቀነቅ መጣች ምነው ስላት እቴቴ ስራ አገኘች አለቺኝ የት ስላት ባንክ

በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው። ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን ሁሉ ነገሯ ስለሆነች ይሆን ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች።

ምን እንደምትሰራ አላውቅም ። በትምህርት ብዙ ያልገፋች ስለሆነች የት እና ምን ትሰራለች ብዬ አልጠየኩም ፤ እሷም ስራ ነች አልመጣችም ፣ ስራ ቀረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሰራ ነግራኝ አታውቅም ።

በጥንጡም በግዙፉም ወሬዎቾ መሃል እቴት ሳትል አትውልም ።

የድሮ ስራዋስ ስላት ። ውይ የድሮ ስራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ አለቺኝ።

ስለ እኔ እንደነገራቻት እና እንደወደደቺኝ የነገረቺኝ እለት እንዴት ደስ እንዳለኝ ።

ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ ። ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ ። ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ ስትለኝ ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት ።

እንደ እሷ ቆንጀ ነኝ ግን ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ ።

ማመን አልቻልኩም

ክው

ድርቅ አልኩ

የላከችልኝ ፎቶውን አገላብጬ አየሁት ፤ አልቀየር አለ ። የማራኪ ሆቴል አስተናጋጅ መስኪ የሶሊያና እናት ናት ፤ ሁለት አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ ።

ውስጤ ታወከ ።

ያ ሴት አውል አብርሃም ፤ ያ በየጊዜው ለቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሴቶችን የሚያጋድመው ፣ የሚያጨሰው አብራሃም ፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብራሃም ፤ የአንድ ልጇ ሶሊያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል??

ትላንቴ ተከተለኝ። እግዜር በተፀፀትንበት ትላንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ ??

የማደርገው ጠፋኝ ። ጠፋሁ ። አንዳንድ ትላንት ትላንት ላይ ብቻ አይቆምም።
© Adhanom Mitiku

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ህይወት ትርጉም የሚኖራት አንተ እስካለህ ድረስ ነው፤ አንተ ከሌለህ እኮ ያ ለቤተሰቡ የሚያስበው፣ ለሚወዳቸው ዋጋ የሚከፍለው ጠንካራው ሰው የለም ማለት ነው።

መጥፎ ስሜት ሊሰማህ ተስፋ መቁረጥ ሊፈታተንህ ይችላል፤ ወዳጄ አንተ መበርታት ያለብህ ለራስህ ብለህ ብቻ አይደለም፤ በዙሪያህ ፈጣሪ ላስቀመጣቸው ስጦታዎችህም ስትል ነው!
/channel/yebezigetmoch
❤️🌹🌹🌹❤️❤️❤️

Читать полностью…

የግጥም መንደር

🍃🍃ተስፋ 🌱🌱🌱
ደራሲ 📖ቤዛዊት የሴትልጅ🖊

❤️ክፍል ሰባት❤
.
.
.
.
.
ሀዘኔን ደስታዬ ያካፈልኳት ህይወቴን የሰጠኋት ሰናይት ዛሬ የኔ አይደለችም ጭራሽ የውሸት ድራማ ውስጥ በእሷ አለም ላይ ተገኝቻለሁ። ባያት ብዬ ስናፍቅ የኖርኩ እኔ ከንቱ አፍቅሪ ከፊቴ ሳያት እጅጉን ዘገነነኝ። መኪናውን አቁሜ ወደ ዮዳሄ ጋር ገባሁ።
      ሁለተኛ ፎቅ ላይ ካለው የውበት ሳሎን በሩን በርግጄ ገባሁ ሁሉም አፈጠጠ። ሴቶቹ በእሳት ይለበለባሉ ሌሎቹ ፊታቸውን እጅ እና እግራቸው ይታሻሉ። በአይኔ ሳማትር ዮዳሄ ጆሮዋ ላይ ኤርፎን አድርጋ ከሰው መሃል ተነጥላ ተልይታለች እና አላየችኝም። እኔም ሄጄ እጇን ያዝኩት በርግጋ ከዓለሟ ወጣች። "ምንድነው አንተ ደነዝ" አለች ቃል ሳይወጣኝ ጎትቻት ወደ መኪናው ወሰድኳት በጣም ደንግጣለች መደንገጧ እኔን ሊያረጋጋኝ አልቻለም። "ስሚ ህይወቴን እንዳልኖር ነው የመጣሽው ወይስ እንድሞት ነው ማነሽ....ከእኔ ምንድነው የምትፈልጉት" እንደ ክረምት መብረቅ አምባረቁባት። "አትጩህብኝ ምንድነው የምትዘላብደው ማነህ እና ነው ከአንተ የምፈልገው" ከእኔ ድምፅ በላይ ድምጿ ገነነ ፊቷ እያየሁት ጉበት መስሏል። "ሰናይት" ጠራኋት። "ምን ትሁን " አልተረጋጋችም። "ትሰሚኛለሽ ድሮም ስትቅለሰለሺ መጠርጠር ነበረብኝ የዋህ መስለሽ ነው የሰራሽልኝ ደግሞ ሰናይት ጓደኛዬ....." ተበሳጭቼ በቆመችበት ጥያት ሄድኩ።

       ያንን ጊዜ እያሰብኩ ስንከፍ ከእናት አባቴ ቤት ደረስኩ የወትሮ ብስጭቴ ከፊቴ ላይ ያነበቡት ቤተሰቦቼ ዝምታን መርጠዋል እኔም ክፍሌ ገብቼ ከወንድነቴ ጋር እየታገልኩ ወደ ውስጤ አለቀስኩ። ስልኬ በተደጋጋሚ ይደወላል ዮዳሄ ናት። እንዴት ነው የተዋወቅነው አውቃ ነው የመጣችው ግራ ገብቶኛል። የፅሁፍ መልእክት  ገባልኝ ከፈትኩት .."ለእኔ ጥሩ ነገር አይገባኝም አውቃለሁ። ላደረክልኝ ነገር አመሰግናለሁ አንተ ደነዝ።ልትሰማኝ ከፈለክ ወይ ልታወራኝ ከፈለክ ለአንተ ዝግጁ ነኝ" ይላል። ውስጤ የሆነ ነገር ተጎምዶ የወደቀ መሰለኝ የረሳሁት ነገር ያለ ይመስል ንዴቴ ተኖ ስለ ዮዳሄ ማሰብ ጀመርኩ። ደወልኩላት...... "ደነዝ እወነት የሰው ንዴት እኔ ላይ ትወጣለህ" አለችኝ። የኔን ቃል ሳትጠብቅ ፈገግ አልኩኝ ወደ ልቤ ደም እያዘራሁ "ተንኮልሽ ነው ቀድመሽ ብትነግሪኝ ደስ ባለኝ።ለእኔም ጥሩ ነገር አይገባኝም ግን ይሄም አይገባኝም።" አልኳት ድጋሜ ህመሜ አገርሽቶ።"የምትለው እኮ አልገባኝም ሰናይት ማናት" አለችኝ። ክው አልኩ እንዴት እንግዳዋን አታውቅም አልኩኝ። "እባክህ እናውራ ያለህበት እኔ እመጣለሁ" አለችኝ። ያለ መጠን ዝቅ ማለቷ የሌለባትን ትህትና ብታሳይ ይበልጥ ከልቤ ጠረጠርኳት መልሴን ሳልሰጣት ስልኩን ዘጋሁት። የዮዳሄ ግራ መጋባት እኔንም አወዛግቦኛል። ሰናይት ለእሷ የወንድሟ ሚስት ለእኔ ደግሞ የህልሜ እመቤት ነበረች ብቸኛዋ የልቤ ንግስት ህይወትን መኖርን ያወኩባት ሰው አድርጋኝ አውሬ ያደረገችኝ ከሰውተራ ቀላቅላ ከሀዘን መጋዘን የከተተችኝ ብቸኛዋ ህመሜ ናት። ቀኑን የምናፍቃት ለሊቱን የማለቅስላት የኔዋ ሰናይት የሌላ ናት የኔዋ ህልሜ የሌላ እውን ናት። እንባዬ በጉንጬ ቦይ ሰርቶ ይዘረገፋል ድጋሜ መልእክት ገባልኝ ዮዳሄ ናት "እባክህን ለዛሬ ብቻ ከጉድ አውጣኝ አንተን ነው ቤተሰቤ የሚጠብቀው ከቅዠት አለም አትክተተኝ አታሳፍረኝ እከፍላለሁ" ብላ ነበር። አሰብኩት የምወዳት የአይኗ የብርሃኑ ፍላፃ ጨለማዬን የሚያበራው ዛሬ ሊያጨልምብኝ በአንድ ገበታ የተቋደስን ተለያይተን ልንቀርብ። ምን አማረሽ ብዬ ላቀማጥላት የምሻ አፍቃሪዋ ተመልካች ልሆን አልሄድም ብዬ ስልኬን ዘጋሁ። መከፋቴ አይደለም ወደአለሜ መምጣቷ ማዕበሉን አስጀመረው። ድጋሜ መልእክቱ ገባልኝ "እናቴ አይኖቿ ከበሩ ላይ ነው አንተ መድሃኒቴ ወይም በሽታዬ ነህ ምርጫው የአንተ ነው" ይላል ደነገጥኩ። ግን ደግሞ አልሄድም አልችልማ ተነስቼ ወደ መስኮቱ ተጠግቼ ቆምኩኝ .....መድሃኒት እና በሽታ  ሁለት ምርጫ አለኝ ምንም አለመምረጥም መብቴ ነው።


     🫀🫀🫀ይቀጥላል....🫀🫀🫀
🍃🍃🍃🍃🍃ተስፋ🍃🍃🍃🍃🍃
💑አዲስ ተከታታይ ድርሰት👫
በቤዛዊት የሴትልጅ💛
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ሜሎሪና
ስምውር ጥበብ
@yebezigetmoch 🖤

Читать полностью…

የግጥም መንደር

፡ ለምንድን ነው እምሰማው ሁሉ ሙዚቃ አንቺን እሚያስታውሰኝ?…ለምንድን ነው ጐዳናው የአንቺን ጠረን ብቻ የሚያስታውሰኝ?…ለምንስ ነው አብዝቼ እማስብሽ?…በጥያቄ ላይ ሌላ ጥያቄ…ኡፍ…አንዳንዴ ግን ለካ የእውነት ይደክማል…❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ቀጣዩን ክፍል ይጠብቁ🙏🙏🙏 🤗🤗💛

Читать полностью…

የግጥም መንደር

ነበር ወይ የገባሽው ቃል
ሌላ ስትለምጅ በአንዴ የሚጣል
ልቤ አልቻለም አምኖ ሊቀበል
ሰማው አፍሽ በሌላ ሲምል

እውነት ግን እነዛ የገባናቸው ቃላቶች የት ሄዱ ሁሉም ውሸት ነበር ማለት ነው የሚገርመኝ እኮ እስትንፋሴ ነህ ነበር የምትይኝ እስትንፋስ ይቃረጣል እንዴ ከተቋረጠ ሞተሻል ማለት ነው ።

መልሽልኛ በቃ ይሄው ነው ቃልሽ ብርሃን አለሜ ከድቅድቅ ጨለማ ያወጣኸኝ ንጉሴ የምትይኝ እየዘበትሽብኝ ነበር እግርሽ ተነስቶ ሲሄድ እኮ እየቀለደ ነበር የመሰለኝ ያ'ሁሉ ሽንገላ ለምን አስፈለገ ታድያ ?.....

አሃሃሃሃ
በቃ ልሂድ የኔ ሲሳይ
ደስ ካለሽ አዲስ ቀን ባይ
........ስንለያይ.......

በቃ ሄድኩልሽ ዳግመኛ ላልመለስ አይንሽን ላላይ እያንዳንዷን ትዝታዬን ልቀብር ላንቺ ደስታ ለመኖር ደስታሽ እኔን ማጣት ከሆነ ምን አደርገዋለው በቃ ሄድኩልሽ

አሃሃሃሃ
ከ ደመና ልቃ በልጣ
ለኔም ፀሐይ እስቅትወጣ

ልክ ነኝ ተገፍቶ የወደቀ የለም ይነሳል ገፍቶ የተነሳ ግን የለም ሁሌም ይወድቃል የተዘበተበት ይነሳል የተዋረደ ይከበራል የተናቀ ይከበራል የ'ኔ ቀን ደሞ ትመጣለች አትዘገይም !

በይ ቻው........ሸኝኝ አበባዬ.....ሄድኩኝ አሜን ብዬ

✍️ የማርያም
@yebezigetmoch
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

Читать полностью…

የግጥም መንደር

❤❤❤ተስፋ🍁🍁🍁
🥀 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
በቤዛዊት የሴትልጅ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ክፍል አምስት
🥀🥀🥀🥀🥀



"ዮድዬ ቃል መጣ" አለች በሩን የበረገደችው እንስት እየተርበደበደች።"እሺ" አለ ዮዳሄ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ እኔ እየተጠጋች። እንስቷ ለቃ ወጣች። "እሺ ይቅርታ እባክህ አትሂድ" አለችኝ ወደ እኔ ይበልጥ ተጠግታ። ከፀግሯ እስከ አገጯ ድረስ አየኋት በጎበዝ ጠራቢ የተጠረበ ይመስላል የፊቷ ቅርፅ። ሁለት እጄን በሚለሰልስ እጇ ያዘቻቸው....ልቤ...ት.ር.ት.ር ስትል ይሰማኝ ጀመር የልቤ ድለቃ ልብሴ ላይ የሚታይ መሰለኝ። አይኖቿን በአይኖቼ አተኩሬ እያየሁ በሩ ተከፈተ። የዮዳሄ ድንጋጤ አስደነገጠኝ በሌላ ዓለም ውስጥ ያለን አስመስላ ነበር እጄን የለቀቀቸው። የገባሁ መልከመልካም ወጣት አየኝ አየሁት ፈገግ አለ ፈገግ አልኩ። "ዮ እኔን በእሱ" አለ። ዮዳሄም "ድንጋይ ራስ ነህ እንዴ በር ማንኳኳት ከማታውቅ ጋር እንዴት ነው የዘለኩት" አለችው ወንበሯ ላይ በኩራት እየተቀመጠች። የሚሆነው ባይገባኝም ዝምታን መርጬ ቆሚያለሁ " እንዳልሆንኩ አሳምረሽ ታውቂያለሽ ደግሞም ማነው እኔን የሚተካ ብዬ ጓግቼ ነው የገባሁት ሳየው ግን...."። ዮዳሄ ከመቀመጫዋ ተነስታ ፊቷ የጋለ ብረት ምጣድ መስሎ ከወጣቱ ፊቱ ቆመች እና "ስማ አንተ የተጎመደ ማንጎ እሱ ከአንተ ጋር አይወዳደርም ልቡ ፍቅር ስብዕናው ሰውነት ነው ገባህ እንደአንተ ቆሻሻ አልሞላውምና ትንሽነትህን ይበልጥ አታሳየኝ ሳላዋርድህ ከቢሮዬ ውጣ" አለች በሩን እየጠቆመችው። ወጣቱም "ትለምኚኛለሽ ዮ" ብሎ በትዕቢት ሊወጣ ሲል መንገዱን ዘጋሁበት። ወንድነቴ አስገደደኝ። "ስማ ወጣቱ ከዚህ በኋላ አጠገቧ እንዳትደርስ ንግስቲቱን አንድ ዝንብ ቢያርፍባት እንኳን ከአንተ ራስ አልወርድም" አልኩት እና የዮዳሄን እጅ አጥብቄ ያዝኩት እና እንዲወጣ በአይኔ ጠቆምኩት ደም መስሎ ወጣ። እኔና ዮዳሄም ተያይዘን ቆመን ቀረን። ትንሽ እንደቆየሁ ግን ክብሬን ነክታ ልወጣ እንደነበር ትዝ አለኝና እጇን ለቀኩት እሷም ከጎኔ ራቅ አለች።በሩ ጋር ስደርስ "አመሰግናለሁ " አለች ስድብ የለመደችዋ እመቤት። ዞሬ አየኋት አየችኝ "ከአንቺ አንደበት" አልኳት። "ይቅርታ ለቅድሙ" አለችኝ። ገረመኝ ይበልጥ "ስድብ እኮ ነው ያንቺ ተስጥኦ" አልኳት። ቀጠል አድርጌም "በቀላሉ አልፋታሽም ሆዴ እየጮኸ ነው" አልኳት። ሰዓቷን አየችና "እሺ እንብላ" ብላ ጃኬቷን እና ቦርሳዋን ይዛ ቀድማኝ ወጣች። "ደነዝ" አልኩኝ። ደስ አለኝ ስድቧ እሷ ላይ ውበት አለው።

ከሆቴሉ ገብተን አስተናጋጁ ሜኑ ይዞ መጣ "ፓስታ በእንጀራ" አልኩት። "አንተ ጥርብ ምኑ ነህ...ለእኔ ሩዝ ለእሱ ፓስታ በአትክልት" አለችውና ሜኑውን መለሰችው። "ካልተሳደብሽ አትችይም እንዴ" አልኳት። "ውስጤ ሲያር እኮ ነው ካልተሳደብኩ ቂም እይዛለሁ ተረዳኝ" አለችኝ። "ፍቅረኛሽ ነው" አልኳት። ተከዘች አይኖቿ እንባ አረገዙ ጥያቄዬ ስህተት መስሎ ታየኝ ግን እንድትተወው አልፈለኩም "ቃል ፍቅረኛዬ ብቻ አይደለም እጮኛዬ ነው የዛሬ ወር እንደምንጋባ ነበር የማውቀው ግን ምን ዋጋአለው ብዙ የሆንኩለት ፍቅር እንደ ባቢሎን ግንብ ፈረሰ አመድ ሆነ በሳቅ የደመቀ ፊቴ በሃዘን ጠቆረ እኔ እና እሱ አብረን ከሆንን ሰባት ዓመት ሆኖናል ለሚያውቀን ሰው የምንጋባ እንጂ የምንለያይ አንመስልም ምን አለፋህ ጥላዬ ሆነልኝ ሁሌ ነገሬ ነው ብዬ ብዙ ሆኜለታለሁ እጅግ ከማፍቀሬ ብዛት አግኝቼው ስንለያይ አለቅሳለሁ ሰርጌን እንደ ትንሳዔ ነው የምናፍቀው። ቤተሰብ አወቀው ወደዱት የተማረ አርቆ አስተዋይ ጎበዝ ነው ብለው ደስ አላቸው ግን ተሳስተናል። እሱ ባለትዳር እና የሶስት ሴት ልጆች አባት ነው ሚስቱ ደግሞ....." መቆጣጠር ያቃትን እንባዋን ዘረገፈችው በጣም ደነገጥኩ። "በቃ ተይው" አልኳት። "የድርጅታችን ፅዳት ሰራተኛ ነበረች" ጨረሰችው ቃሉን። ሽባ ሆንኩኝ። እኔ ሰባት ሰባት መገጣጠሙ ገርሞኝ በእሷ የሞቀ ፍቅር የኔን የሞቀ የሰኒን ናፍቆት እያሰብኩ ነበር። "ይቅርታ" ብላ ተነስታ ወደ መታጠቢያው ሄደች።
ስትመለስ ነገሩን ለመለወጥ ስለሌላ ታሪክ እያወራሁ ማሳቅ ጀመርኩ። ልጅቷ ቀልድ አትፈጅም ትስቃለች ያውም ከልቧ ተፍነክንካ። የይቅርታ ግብዣውን ተቀብዬ ምግብ በልተን ወጣን ልብሴ የደበራት የስድብ እመቤትም ልብስ ገዝታ አሸከመችኝ አዘነጠችኝ እና "ዛሬን እና ነገ እረፍት አድርግ ነገ ማታ ትልቅ የእራት ግብዣ አለ ግብዣው የኤስዋይ ድርጅት ትርፋማነት ምክንያት በማድረግ ነውና ዘንጠህ ካለሁበት መጥተህ ትወስደኛለህ" አለችኝ ከመኪናው ልትወረድ ቀበቶውን እየፈታች። "ማረፉንስ ተይው ትጠሪኛለሽ" አልኳት ሳቅ አለችና "ደነዝ እስክጠራህ እረፍት አድርግ አመሰግናለሁ" ሳቀች። "ያንቺ ደነዝ አደረግሽኛ" ብዬ "እሺ ቻው" ብያት ከመኪናው ወርዳ ወደትልቁ የቤቷ ግቢ ስትገባ እኔም ወደ እናቴ ቤት ነገን እያሰብኩ የሁኔታዎች በአንድ ጊዜ መቀየር እያጤንኩ ተመለስኩ። ቤት ስደርስ ለእናት አባቴ የሆነውን እንደህልም ስተርክ አፋቻውን ከፍተው እየሰሙኝ ነበር ከልብ ስብራቴ በኋላ ረጅም ሰዓት አውርተን አናውቅም እና የእምዬን የተስፋ ፀዳል ሳየው የአባቴን የስስት አይን ስመለከት ዮዳሄ ለእኔ የተላከች መልአክ መሰለችኝ። መኝታዬ ላይ ጋደም ብዬ ሳለሁ ስልኬ መልእክት ገባለት ከፈትኩት እብዷ ናት "ቤት ገባህ" የሚል ነበር። ለምን እንደሆነ ሳላውቅ ፈገግ አልኩና ደገፍ ብዬ ደወልኩላት ጠራ ደገመ ተነሳ....."አንተ እርጥብ ቴክስት አታውቅም" ከመነሳቱ ..."የአንቺስ ለጉድ ነው ስድቡ" አልኳት። "ወሬ ገባህ ወይ" አለችኝ። "አዎ ገባሁ" አልኳት። "በል ጠዋት ከቤት መጥተህ ቦሌ ትወስደኛለህ ሰው እንቀበላለን" አለች ተኮሳትራ " ብያለሁ እኮ እንደማላራፍ" አልኳት። "ሾካካ ብንቀራረብ እንኳን አለቃህ ነኝ እና እንዳታረፍድ" ስልኩ ጆሮዬ ላይ ተዘጋ። እኔም አርፌ ተጠቅልዬ እንቅልፌን ተኛሁ።

ማለዳዬን በምስጋና ጀምሬ በእናቴ ቁርስ እና በአባቴ ምርቃት ደምድሜ ከቤቴ ወጣሁኝ። የዮዳሄ በር ላይ እንደደረስኩ እሷም ተጣድፋ ወጣችና ወደ መኪናው ገባታ እኔንም ማጣደፍ ጀመረች። "ከቦሌ እኔን ቢሮ አስገብተህ እንግዳዬን እዚህ ታመጣታለህ ከዛ ቢሮ መጥተህ ወደ ባንክ ሄደን ከዛ ስንመለስ ፀጉርቤት ትወስደኛለህ።" አለች ስልኳ ላይ ለብዙ ሰው መልእክት እየላከች። በመስታወቱ አየኋት እና "መጀመሪያ እንግዳሽ ጋር እንሂድ" አልኳትና በስሱ የኤፍሬምን ሙዚቃ ከፍቼ የመኪናዬን ፍጥነት ጨምሬ ወደ እንግዳዋ ጋር ቦሌ አየርመንገድ ደረስን። የሆነው እና የተፈጠረው ግን ሌላ ነው.......🥀🥀🥀🥀🥀


💙💙💙💙ይቀጥላል💙💙💙💙

❤❤❤❤ተስፋ ❤❤❤❤❤

✍️በቤዛዊት የሴትልጅ ✍️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
📭 @yebezawit2 📬
ለአስተያየት 👆👆 ይጠቀሙ
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
የእኔ አይነቱ ተስፋ ቢስ ተስፋ ቢሰጠውም ይቀማል
🥀የለውማ የእሱ አይደለም🥀🥀🥀🥀.
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

Читать полностью…

የግጥም መንደር

❤❤❤ተስፋ🍁🍁🍁
🍁🍁🍁በቤዛዊት የሴትልጅ🍁🍁🍁

🎉ክፍል ሶስት🎉


.........ትከሻዬ ላይ ድንጋይ የተቀመጠ ይመሰል መሬቱ ላይ ተዘረፈጥኩ። አባቴም ወደ እኔ ሲጠጋ በዝምታ ነበር የማየው "ምነው ልጄ" አለኝ። የልቤን ስለሰጠኝ ባለማቀፌ "ስትወጣ ትጠቀማታለን ብለን እኮ ነው" አለኝ የመኪናዋን ቁልፍ እንድወሰድ እጁን ዘርግቶልኝ። ሰኒ ከሄደች በኋላ ሰው ማየት አስጠልቶኝ ነበር መማር መስራት አንገሽግሾኝ ነበር እና ምን ይሻላል ብለው ቤተሰቦቼ ሲጨነቁ ነው የማይችሉ ይመሰል መኪና ግዙልኝ ያልኩት ከየት እንዳመጡት ባላውቅም መኪናዋ ፊቴ ቆማለች በተስፋዬ ዕለት።
በእንባ አባቴን አቅፌ ቁልፌን ተረከብኩ።ህይወት ቀጠለች መንጃ ፍቃድ አወጣሁ። በመኪናዬ የግል ስራዬን ጀመርኩ ትራንስፖርት ሰርቪስ እየሰጠሁ እንደምንም ከሰው ጋር ለመቀራረብ እየጣርኩ ነው። ዛሬም አጎና አካባቢ መኪናዬን አቁሜ የእጅስልኬን እየነካካሁ ያልተቆለፈ በሩን በርግዳ አንዴት ሴት ገባች። በደንጋጤ አፈጠጥኩባት። "ምን አይነት ጉድ ነው በፈጣሪ አንተን በመጠበቅ ልሙት እንዴት" ቦርሳዋን እየቆፈረች ተናገረች። የምመልስላት ጠፋኝ "ይሄ ህዝብ ግን..." አለመንቀሳቀሳችን ገብታቷ ቀና አለች ስታየኝ ክው ብላ መነፅሯን አወጣች እና "ያ ነፈዝ ነው የላከህ" አለችኝ። "የወራሽው አንዱም አልገባኝም" አልኳት። የእውነትም መዋከቧን እንኳን ለመረዳት ተወዛግቢያለሁ። "አንተ ቆይ ማነህ?" አለች ፈጣጣዋ እንስት። "አንቺ ማነሽ" አልኳት ፊቴ ባለው መስታወት እያየኋት "ስታስጠላ" አለችኝ። ይሄን ነው መሸሽ አልኩ በልቤ። ስልኳን አውጥታ ቁጥር መታች እና ደወለች። "አጎት ሹፌሩ ማንን ነው የላከው" አለች። የቅምጥል ልጅ ነሽ በልቤ ተናገርኩ። "እንዴ የእኛ መኪናን ይዞ የመጣ እኮ አለ" አለች። ቀስ ብላ ስልኩን ከጆሮዋ አወረደች እና አየችኝ ዝም አልኳት። "ይቅርታ ወንድም ከስብሰባ ስለወጣሁ ነው ተቻኩዬ" አለችኝ ለመውረድ እየተጠጋች "ቤቴን ቀወጥሽው እኮ ወዴትነሽ ላድርስሽ" አልኳት። ማፈሯ ስለገባኝ። "አይ በእግሬ እሄዳለሁ" አለች። "ታክሲ በሚጋፋ ህዝብ ተሳልቀሽ እንዴት በእግር ትሄጃለሽ" አልኳት። "አይገርምህም ምንም ቢሆን ከእነሱ ጋር አታወዳድረኝ እንዴት እንደደነቀኝ ታክሲውን ሊያነሱት ነው የሚመስሉት መተሻሸት መተዛዘል መነካካት መቆሸሽ................." ጆሮዬ እስኪደማ ድረስ ለፈለፈች እና ዝም አለች። "ቤት አያስወሩሽም እንዴ" አልኳት። "እሺ ወደ ካዛንቺስ ውሰደኝ" አለችኝ። ቀበቶዬን አድርጌ መኪናዬን ወደፊት መንዳት ጀመርኩ። የልጅቷ የማያቋርጥ የስልክ ጥሪ የእሷ መለፍለፍ ጭንቅላቴን አዙሮት ካለችኝ ቦታ ደረሰን። "ይኸው እመቤት" ዞሬ አየኋት። "አመሰግናለሁ" ብላ ከቦርሳዋ የመቶ ብር ኖቶችን ሳትቆጥር ሰጠችኝና ወረደች። "ይሄ ሁሉ ምነው" አልኳት በመስኮቱ አንገቴን አውጥቼ። ለነገሩ ይገባኛል የማያልቅ ወሬዋን መስማቴ ሌላ ክፍያ ያስጨምራል። ህዝቡ እያለች ስታጣጥል ጠላ እና ሽሮን ስታሳንስ ታግሼ መስማቴ በራሱ ሽሮ በእኔ ላይ የምታነሳው ጦርነት እንዳለ ግልፅ ነው እሱን ለመመከት ብር ያስፈልጋል እና ያንሰኛል። ልጅቷ ተመልሳ መጣችና የስልክ ቁጥር መፃፊያው ላይ አድርጋ ስልኳን ሰጠችኝ። ስልኬን መፈለጓ ገባኝ። ፃፍኩላት "ስራ ከፈለክ እደውልልሀለሁ" አለች በትዕቢት። "ደውይ" አልኳትና በቆመችበት ጥያት ሄድኩ። ዛሬ የቀን ገቢዬን ስላገኘው ወደ ሰፈራችን ተራራ አቀናው እና ቁጭ ብዬ ህመሜን ማስታመም ጀመርኩ። ፈገግ አልኩኝ። ሰናይት ዳገት መውጣት ስለማትችል ስታናደኝ የምቀጥራት ከፍታ ቦታ ነው ልቧን እስክተፋ ድረስ ነበር የማስኬዳት ግን ደግሞ ታሳዝነኝ እና በጀርባዬ ላይ አሳርፋታለው።የሆነ ቀን ነው ከሜክሲኮ ወደ ቄራ አብረን እየመጣን ሰኒን የሆነ ወንድ ሲጠቅሳት አየሁ እሷን ሳያት በረጅሙ ሳቀች በጣም ተናደድኩ ቅናት ፊቴን አገረጣው። ዝም ብያት ጥያትሄድኩኝ። እየሮጠች ተከተለችኝ እኔ በጣም ስራመድ እሷ ስትሮጥ ልቧ ውለቅ እስክትል አሯሯጥኳት እና ደክሟት ስትቆም "እንዲህ ነው በአንቺ የምደክመው" አልኳት። ለነገሩ እኔ በእሷ ነገር የምደክመው በየቀኑ ሳይሆን በየሰከንዱ ሳስባት ውዬ አድሬ ሳገኛት ድክም እላለሁ ይበልጥ በፍቅሯ ወድቄ እታመማለሁ እኔጃ ሰባት ቀን ሰባት ዓመታት ይመስሉኛል ያለየነው የዓለም ታሪክ የለም ታሪካችንን አስቀምጠናል። አወይ ሰናይት ሄደች ቢባል ማንያምናል አንድ ሳንሆን እኮ አንድ ናቸው ተብለን የተጠረጠርን ነን።እኔ የእሷ ታማሚ
ስልኬ ጮኸ።ድሮም ከሞቀ ትዝታ ወደ ቀዘቀዘችው ዓለም የሚመልሰኝ አላጣም ብዬ አነሳሁት። "አንተ ደነዝ አራትኪሎ ነኝ ቶሎ ና" ስልኩ ተዘጋ። ጎሽ እንዲህ ነው ደውሎ መስደብ ዝም ብዬ በትዝታዬ ዳግም ልመሰጥ መረከቤ ላይ ወጣሁ ዳግም ስልኬ ጠራ " የትደረሰክ" ገና ከማንሳቴ ጥያቄ። "የኔ እመቤት ተሳስተሻል" አልኩ በስልኩ ውስጥ ሆና ለምትቆጣው። " አንተ የቅድሟ ሴት ነኝ ስራ አትፈልግም" ጠየቀችኝ። "በቁጣ ነው እንዴ ማስተርስሽን የያሽው" ብዬ " እሺ መጣሁ" ብዬ ቀድሜ ስልኩን ዘጋሁት የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ግልፅ ነው። ኧረ ቁጣ ኧረ ስድብ የነገዬን ብር ካሸከመችኝ ነገ ቤቴ ነው የምውለው እያልኩ የሰኒን ትዝታ ከከፍታው ቦታ ሰቅዬው መኪናዬን አስነስቼ መንገዴን ቀጠልኩ። ይቀጥላል.........

✍️✍️ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ✍️✍️

🎉🎉 አዲስ ለመሆን ዛሬ ነው ዕለቱ🎉🎉

ተስፋ❤❤❤
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

Читать полностью…

የግጥም መንደር

🍃🍃ተስፋ 🌱🌱🌱
ደራሲ 📖ቤዛዊት የሴትልጅ🖊

❤️ክፍል ሁለት❤
.
.
.
.
.
ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ሞቴ ነበረች ሳስበው ራሱ አንዳች ነገር ልቤን ይወጋዋል። ከሰኒ ጋር ስድስት ቀናት ደስታዬ ነበሩ። ሰባተኛዋ ግን መጥፊያዬ። ከምሰራበት ቦታ ወጥቼ አይኗን ለማየት ነበር በጥድፊያ ወደተከራየችው ቤት ያቀናሁት።ስደርስ ግን በሩ ዝግ ነው።በዚህ ሰዓት እሷ ቤት መሆን ነበረባት እያልኩ ግቢ ውስጥ ያለችውን ለሰኒ የምትቀርበውን ተከራይ ቤት አንኳኳሁ። "አቤት" የሚል ድምፅ ከውስጥ ተሰማኝ። ከበሩ ራቅ ብዬ ቆምኩኝ። ሲጢጥ ብሎ በሩ ተከፈተ።"ደህና ዋልሽ እሙዬ" አልኳት። እሙዬ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ እናት ናት። ሰኒን እንደ ታናሿ ነው የምታያት እና አከብራታለሁ። "ሰላም ነው" አለችኝ አንድ እጇን ዘርግታልኝ ለሰላምታ። እኔም እጄን ሰንዝሬ ሰላምታዋን ተቀበልኩ። "ሰኒ እኮ ስልኳ ዝግ ሆነብኝ አልገባችምም" አልኳት የሰኒን ቤት እያሳየኋት። "ጠብቀኝ" ብላ ወደቤት ተመልሳ ገባች። ፊቷ ላይ ያየሁት መከፋት አስደንግጦኛል። ተመልሳ መጣች ስትመጣ ግን በእጇ ወረቀት ይዛ ነበር የመጣችው። "ይሄን እንድሰጥህ ነግራኝ ነው" አለችኝ። መነጨኳት እና ከፈትኩት ጥቅጥቅ ያለ ፅሁፍ ነበር።ቃል በቃል ነው የማስታውሰው ከእነ ስርዓተነጥቡ።
ሚኪዬ ይሄ ወረቀት ሲደርስህ እኔ እርቂያለሁ።ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ግን ሳትሰለች አንብበው።ሚኪዬ እኔ እና አንተ አንድ ላይ የሆነው የእኔን መልስ ሳትጠብቅ ነበር።የዛን ቀን ጉንጭህን የሳምኩት ስስትህ እና መውደድህ አይሎብኝ እንጂ አፍቅሬህ አልነበረም።ለአንተ የሆነ ከልቤ የሚሰጥህ ፍቅር አልነበረኝም። ደስታህን ሳይ እና ለእኔ ያለህ ነገር እንደማይለወጥ ሲገባኝ በዝምታ አብሬህ ቀጠልኩ ግን እኔ ለሶስት ዓመታት ስጠብቀው የነበረ እጮኛ ነበረኝ።እጮኛዬ ለእኔ ነፍሴ ነው። ሰው ባልነበረኝ ጊዜ ተገኝቶ የታየ እና ከልቡ የሚወደኝ ነው። አንተን ላለማሳዘን አንተን ላለማስከፋት እና ልብህን ላለመስበር ነው ከጎንህ የሆንኩት። አሁን የምንለያይበት ጊዜው ደርሶ ርቄ ሄጃለሁ ለዓመታት ስናፍቀው የነበረው የውጭ ፕሮሰስ ተሳክቶልኝ ወደሚናፍቀኝ እና ወደማፈቅረው እጮኛዬ እቅፍ ውስጥ ገብቻለሁ። እንደማትጎዳ እና እንደማታዝን ተስፋ አለኝ ምክንያቱም ከቀናት ያለፉ ትውስታዎች የሉም ደግሞም ቶሎ እርሳኝ እና ሌላ ህይወት ጀምር። እንደ ቀልድ ባሳለፍናቸው ጊዜያት ሁሉ ደስተኛ ነኝ። ብቸኝነት እንዳይሰማኝ ተጠንቅቀህልኛል እና መልካም ሴት እንድትገጥምህ እመኛለሁ።አንተን እና ፍቅርህን በመበደሌ ይቅርታ አድርግልኝ ቻው ሰናይት.....

ወረቀቱን ጭምድድ አድርጌ እመዬን አየኋት። "ሚኪዬ ይሄ እንዳይመጣ ብዙ ብያታለሁ ለአንተ በማሰብ ነው እሷም እንዲህ ያደረገችው" አለችኝ። ሰው ለሰው የሚያስበው መርዙን በልብ ውስጥ እያስቀመጠ ነው።እንባዬን ወደ ውስጥ እያፈሰስኩ ከግቢ ወጥቼ ዝም ብዬ መሄድ ጀመርኩ እሷ እንደ ራቀችው እኔም ከትዝታዬ ከህልሜ ለመራቅ ሸሸሁ። ግን አልሆነም ጭንቀት አዙሮ ይጥለኝ ጀመር ፍቅር የሚሉት በሽታ ከእኔ አልፎ ቤተሰቤን አስጨነቀ ለወራት ጸበል ገብቼ ተጠመኩ ግን እሷ ያሰረችኝን እሷ ናት የምትፈታው እና በጸበል ተፅናናሁ እንጂ አልተፈወስኩም። ታዲያ ለወራት ቤተሰቦቼ እላይ እታች ብለው ሲሰቃዩ ብቻዬን ጸሎት አደረኩ።የእነሱ ስቃይ እንዲበቃ የእኔን ቁስል እንዲሽር ተማፀንከለ። በቃ አስረሳኝ እሷን ልጥላት እሷን ልርሳት ብዬ ተማፀንኩት። ባልረሳትም ዛሬ የምረግጠውን መሬት አውቀዋለሁ። ቤተሰቦቼም ስራ ባይሉኝም ወጥቼ ስገባ ምግብ ስበላ ትንሽ ፈገግ ካልኩ ትልቁ ደሞዛቸው ነውና ለእነሱ ስል ግድ እንገዳገዳለሁ። መቃብር ስፍራው ጋርም የምመጣው ለዚህ ነው የልቤን ስነግራቸው ያደምጡኛል። ሚስጥሬን ይጠብቃሉ ተነስተው አይሸሹም ቦታዬ እነሱ ጋር ባይሆንም ግድ እሄዳለሁ አይገፉኝማ። ይኸው ሰኒ እጄን ከለቀቀች ሁለት ዓመት ተቆጥሯል።እኔም መኖር ካቆምኩ አመታት ተቆጥረዋል።ዛሬ ግን ወስኛለሁ ከተቀመጥኩበት የመቃብር ሃውልት ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ እና አየኋቸው። "ሚኪያስ እየሄደ ነው ዳግም ወደዚህ የሚመጣው ሲሞት ነው ሰው ለመሆን ወስኛለሁ ቦታዬን አገኘዋለው" ብያቸው በሃዘን አየኋቸው። ልለያቸው ነው ሁሉንም ተመልክቼ የመቃብር ስፍራውን ለቅቄ በኩራት በእልህ ወደ ቤቴ ገሰገስኩ። ስራ መጀመር እና ወጥቼ መግባት አለብኝ። ከጓደኞቼ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እና መዝናናት ይኖርብኛል። ምክንያቱም ካቆምኩበት መቀጠል ባልችል እንደ አዲስ መነሳት ግን እችላለሁ።ከጭንቅላቴ ጋር እየተወያየሁ የግቢያችን በር ከፍቼ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁ። ስገባ ግን ያልጠበኩትን ነገር አየሁ ቆሞ እኔን በፈገግታ የሚያየኝን አባቴን አፍጥጬ አየሁት። ፊቱ ላይ ካለው የቆዳ ሽብሽብ ላይ የሚነበብ ነገር ፈለኩኝ ግን የለም ውስጤ ይላወስ ጀመር።

👫ይቀጥላል....💑
🍃🍃🍃🍃🍃ተስፋ🍃🍃🍃🍃🍃
💑አዲስ ተከታታይ ድርሰት👫
በቤዛዊት የሴትልጅ💛
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

Читать полностью…
Subscribe to a channel