የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት እና የዩኒቨርስቲ ምደባ ሌሎችንም ትክክለኛና ወቅታዊ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ኢትዮ students የሚለውን ክሊክ በማድረግ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
Читать полностью…HinDhufaa
Fikadu Gemeda
Adola makane iyesus
Join our yuotube channel and Telegram channel
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
Watch "April 14, 2021" on YouTube
https://youtu.be/_BMyKResQNg
✍ መግባቢያ ቋንቋዬ
********************
በቋንቋ ህመም ፣ በብሄር ስቃይ
በነገድ ደዌ ፣ እንዳልሰቃይ
ኢየሱስ ዋጅቶኝ ፣ ከነዚህ ሁሉ
አይገባኝ አለ ፣ ብሄሬ ሲሉ
ቋንቋዬ ሲሉ
ነገዴ ሲሉ
ዘሬ ማንዘሬ ፣ ጎሳዬ ሲሉ
ለአለም አዝኖ ፣ ላለም የሞተው
ላንዱ ራርቶለት ፣ አንዱን የማይተው
ለኔ ኢየሱስ ነው ፣ የሆነኝ ወገን
የእግዚአብሔር ልጅ ፣ ያደረገኝ ዘር
ለኔ ኢየሱስ ነው ፣ የነፍሴ ስንቋ
ከእግዚአብሔር ጋር ፣ ያግባባኝ ቋንቋ
✍ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ እንጂ በእንግሊዝኛ አይግባባም!!
#ሄኖክ_አሸብር
❓ይህንን ያውቃሉ❓
👉የሚቀጥለው እና ወደ ኋላ ሊነበብ ይችላል "Do geese see God"
/channel/yeeiyesu 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ውድ እህት እና ወንድሞች
ሰላማችሁ ይብዛ!
ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ዛፍ ሥር አይጠለሉ:: ለመብረቅ አደጋ ያጋልጣል:: ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ ለሌሎችም ያጋሩ::
@yebirihan_lijoch
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-ዘጠኝ
...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደምንም ተረጋግቼ አንድ ስርቻ ጋር ተሸጎጥኩ አሁንም ፀጥታው እንደቀጠለ ነው ይመስለኛል ጆሯቸውን ቀስረው በድጋሜ የኔን ድምፅ እየጠበቁ ነው ማንም ከተቀመጠበት የተነሳ የለም...በዚህ ሰዓት ከተደበኩበት ቦታ ቀስ ብዬ በጥንቃቄ ተነሳሁ ልወጣ በሩ አካባቢ ስደርስ ሰውዬውም ሊወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሩ ተነሳ ወዲያውኑ ወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ ይባስ ብሎ ሰውዬው ሊወጣ ብሎ ወደሗላ መለስ አለ የጠረጠረው እንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝ "በቃ ከዚህ በሗላ ማምለጥና መትረፍ አይታሰብም" ብዬ ለራሴ ነግሬ ጭንቅላቴን ጉልበቴ መሀል አስገብቼ የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ እዛው በቃረቀርኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ከዛም እንደምንም ድፍረቴን ሰብስቤ ፍራቻዬን ተቋቁሜ ከአንገቴ ቀና ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ጋር አልነበረም በጣም ግራ ገባኝ ሲራመድ እንኳን ኮቴ አልተሰማኝም ነበር አሁን የባሰ ጭንቅ ሆነብኝ ሰውዬው ከየት እንደሚመጣ ለመገመትም ከበደኝ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተደበኩበት ተነስቼ ቅድም ውስጥ ያለውን ነገር እመለከትበት ወደነበረው የመጋረጃው ሽንቁር ተጠጋሁ ሁለቱ ሴቶች እንደነበሩት ናቸው በአርምሞ ሆነው የሮቤልን አካል ይመገባሉ ቀና ብለው እንኳን አይተያዩም ነበር ግን ከዛ አረመኔ ሰውዬ የተሻለ የተስተካከለ የፊት አቀማመጥ እና ጤናማነት ይታይባቸዋል በድንገት አይኔ ተወርውሮ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ሁለት የህፃናት ፎቶ ላይ አርፎ ቀረ "እነዚህ ብላቴናዎች ማን ሊሆን ይችላሉ" ብዬም አሰብኩ በድጋሜ በዛች ሽንቁር ዙሪያ ገባውን መቃኘት ጀመርኩ በድጋሜ አንድ ፎቶ ተመለከትኩ አንዲት መልከ መልካም እናት በጨርቅ የተጠቀለለ ልጅ አቅፋ ከሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ቆማ ያሳያል በእርግጥም ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ አሁን ያለንበት ቦታ ነው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር "ህፃን ታቅፋ ፎቶ ላይ ያለችው ሴት ማን ልትሆን ትችላለች" ብዬ ራሴን ጠየኩ ዳሩ መላሽ ባላገኝም በድጋሜ አይኔን ወርወር አድርጌ ሌላ ነገር ማየቴን ቀጠልኩ ፎቶዎቹ በአጠቃላይ ጥቁርና ነጭ ቀለመሸ ያላቸው ናቸው...አይኔን ግድግዳው ላይ ሳንከባልል አንድ መልከ ሸጋ ብላቴ ያለበትን ፎቶ ተመለከትኩ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቢከብድም ገዳዩ ሰውዬ ይሆን እንዴ ብዬም አሰብኩ ግን የማውቀውን የፊቱን ገፅታ እና አቀማመጡን ሳስበው ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችል ደመደምኩ ግን እነዚ የፎቶ ስብስቦች ያለ ምክንያት እንዳልተሰደሩም ተገንዝቤያለሁ በድንገት በዕድሜ ጠና ያለችው ሴትዮ ተነስታ ስመለከት ወደነበረው መልከ መልካሙ ብላቴና ፎቶ ጋር ጠጋ ብላ በእጆቿ እየዳበሰች በስስት አይን እየተመለከተች ድምፅ ሳታሰማ የእንባዋን ጎርፍ በጉንጯ ላይ ታወርደዋለች ከዛው ሌላኛዋ ሴት ተነስታ ከሗላ በኩል እቅፍ አርጋ የፊቷን የግራ ክፍል ጀርባዋ ላይ አስደግፋ ዝም ብላ አብራት ቆመች ከደቂቃዎች በሗላም ሴትየዋ ማልቀሷን አቆመች ወደነበሩበትም ተመለሱ ግን አሁንም ፊቷ አልተፈታም ነበር ሁለት እጆቿን በእልህ ጨብጣ ከንፈሯን ነክሳ በፍጥነት መተንፈስ ጀመረች ምን ሆነች ሳይባል በድንገት ተነስታ የክፍሉን ዕቃ አመሰችው በዚ ጊዜ ሰውዬው ድምፅ ሰምቶ ሊመጣ ይችላል ብዬወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ አሁን ንግግር ጀምረዋል "እባክሽ እባክሽ ተይ ተረጋጊ" ትላለች በዕድሜ አነስ የምትለዋ "ልጄን ልጄን ልጄን በሉብኝ አንድዬን የአይኔን ማረፊያ የፈጣሪዬን ስጦታ በሉብኝ" እያለች ድምፇን ከፍ አርጋ አምርራ ታለቅሳለች "ራስሽን አትጉጂ እባክሽን ተረጋጊ መድሃኒትሽን መውሰድ አለብሽ እንዲ መሆን የለብሽም የባሰ ታስጨንቂዋለሽ" አለቻት "ማነው ሚጨነቀው" ብዬ ወዲያውኑ ራሴን ጠየኩ "ሴትየዋ ልጄን በሉብኝ ብላ ነው ምታለቅሰው በሉብኝ ማለት ደግሞ ገደሉት ይመስለኛል እና ስለየትኛው ሰው እና ስለየትኛው ልጅ ነው እንደዚ ካየሽ ይጨነቃል" የምትለው ብዬ ከራሴ ንግግር ጀመርኩ የዚህ ቤተሰብ ውስብስብ ታሪክ ይበልጥ ዘልቄ እንዳውቃቸው አጓጓኝ ግን መሞትም እንዳለ አልዘነጋሁትም በድጋሜ ከተደበኩበት ተነስቼ ወደመጋረጃው ሽንቁር አመራሁ አሁን ፀጥታው ተመልሶ ነግሷል ሴትዬዋ መሬት ላይ ተኝታለች በዕድሜ አነስ የምትለው ደግሞ በተኛችበት ፀጉሯን እየደባበሰች ታፅናናታለች የሴትየዋ ጉዳት ከባድ እንደነበር መገመት ቀላል ነው ልጇን ምንም ያርጉት ምንም በብዙ ተጎድታለች ሰው ነችና አሳዘነችኝ አነስ የምትለዋ ሴት መድሃኒቱን እንድትውጥ አድርጋ አረጋጋቻት እዛው ቆሜ በመጋረጃው ሽንቁር እየተመለከትኩኝ ሳለ በድንገት በሩ ተከፈተ ስዞር...................,.....
...............ይቀጥላል.................
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-ሰባት
...የሚሆነውን ሳስበው አንቀጠቀጠኝ ለማየትም ለመስማትም ሰቀጠጠኝ...በድን የመሰለኝ የሮቤል አካል መንቀሳቀስ ጀመረ እንደ ማሳልም ሲያረገው ከአፉ ደም ይረጫል ይሄን ባየ ጊዜ ያ ሰው ይበልጥ ደስ አለው ከሚሰማው ጫጫታ ይልቅ ይሄ ለሱ ደስታ ሰጥቶታል ጠጋ ብሎ አይን አይኑን እደተመለከተ ፈገግ ይላል በሌላ በኩል ሮቤል በለዘበ እና በቀሰስተኛ ድምፅ "እርዱኝ አድኑኝ ይላል" ይሄን መመልከት ለኔ እጅግ በጣም ከባድ ነው የማደውን ነገር ማመን አልቻልኩም እጄን አፌ ላይ አድርጌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ አቅም ቢኖረኝና ከዚ አረመኔ ሰው ባስጥለው ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ ነገር ግን አልችልም...ሰውዬው አሁንም ዋይታ በሞላው የሰዎች ጫጫታ በደስታ እና እረፍት የተሰማው በሚመስል መልኩ ይንቀሳቀሳል የዘይቱን መፍላት እየተመላለሰ ይመለከታል ለምን እንደጣደው ባይገባኝም ብቻ አስፈርቶኛል...ሮቤል ሙሉ ለሙሉ ሰውነቱ በደም ተጨማልቋል ከቅንድቡ ትንሽ ከፍ ብሎ በስለት የተቆረጠ የሚመስል ቁስል አለ ይመስለኛል እኔ የተመለኩት ያ የተሰበረ መስታወት ሮቤል ለማምለጥ ሲል የሰበረው እንደሆነ ተረዳሁ ሳሩ ላይ የተመለከትኩት ደም ደሞ ከመስኮቱ ከወደቀ በሗላ ለማምለጥ በደረቱ የተሳበበት እንደሆነ ገባኝ ሁኔታዎቹን ከሮቤል መጥፋት ጋር ማመሳሰሌ ትክክል ነበርኩ ይሄን ሁኔታ ቅድስቴ አለመመልከቷ ለሌሎቻችን በህይወት መቆየት ምክንያት ነው...ብትመለከት ኖሮ ራሷን ማረጋጋት ስለማትችል ሁላችንም እንጠመድ ነበር...ሮቤል አሁንም ድምፁን እያሰማ ነው አረመኔው ሰውዬ ደግሞ እየደነሰ...እንቅስቃሴው ሁሉ ግራ ነው ጨፈረ ለማለት እንኳን አያስደፍርም...ከደቂቃዎች በሗላ የዘይቱን መፍላት አረጋገጠ ከዛም እየሳቀና እንደ ጭፈራ የሚያረገውን እንቅስቃሴ እያሳየ ወደ ሮቤል ተጠጋ ሁለት ተለቅ ያሉ ጥቋቁር ቀበቶ መሳይ ማሰሪያዎችን አንስቶ አንዱን ደረቱጋ አንዱን ደሙ ታፋው ጋር አድርጎ ከጠረጴዛው ጋር ሮቤልን የፊጥኝ አሰረው...የሮቤልን ስቃይ ለመረዳት ሮቤልን መሆን አልነበረብኝም ህመሙ አብዝቶ አመመኝ ስቃዩ አሰቃየኝ ወዲያውኑ ትሪ መሳይ በሆነው ነገር ካመጣቸው ስለቶች መሀል ሁለቱን አንስቶ ወደሰማይ እየተመለከተ ማፋጨት ጀመረ የዘይቱ መፍላት እኔ እስካለሁበት ቦታ ድረስ ሲፍለቀለቅ ይሰማል ብቻ እንደማስበው አይሁን ብዬ አምላኬን ተማፀንኩኝ..."እርዱኝ አድኑኝ እርዱኝ አድኑኝ" እያለ ሮቤል የማይደርስለትን አዳኝ ይጣራል አረመኔውም ሰውዬ አንድ ጣቱን አፉ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ለሮቤል በምልክት ያሳየዋል ነገር ግን ሮቤል የሚረዳውን ሰው ከማያገኝበት ስፍራ መጣራቱን ይቀጥላል በዚ ግዜ ሰውዬው አብዝቶ ይናደድና ሲያፋጭ የነበረውን ስለት ከፍ ሲያረገው አሁን ካሁን አንዳች ቦታ ላይ ወጋው ስል ከፍ ካደረገበት እጁን ሳይመልስ በንዴት የተለዋወጠው ፊቱ ወደ መጀመሪያ ገፅታው ተመልሶ በተረጋጋ ስሜት ሆኖ አሁንም አንድ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ይነግረዋል...ከዛ ከጋለ ስሜት ውስጥ መውጣቱ ለኔ በጣም ግራ ነው ሰውዬው በጣም አጠራጣሪና አወዛጋቢ በሆኑ ነገሮች ነው የተሞላው...ዶክተሮች የሚጠቀሙበትን የህክምና ጓንት ከአንዱ መሳቢያ አውጥቶ እጆቹ ላይ አጠለቀ በመሃል የከፈተው ዋይታ ፀጥ አለ እሱም እዛው የቆመበት ቦታ ለይ ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሎ ቆመ ሰከንዳት አልፈው ደቂቃዎች ተቆጠሩ እንደዛው ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሉ እንደቆመ...በዚ ሰዓት ሮቤል አንዳች ድምፅ ቢያወጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰላሰል ጀመርኩ ይሄን እያሰብኩኝ ሳለ የቅድሟ ድመት እየጮኸች ወደክፍሉ ስትገባ ከቆመበት ተስፈንጥሮ መጥረቢያውን አንስቶ ወገቧን ብሎ ለሁለት ከፈላት ከቅድሙ ይልቅ አሁን አፌን አጥብቄ ያዝኩ ሰውዬው እዛው ድመቷ የሞተችበት ቦታ ላይ በድጋሜ ፀጥ ብሎ ቆሟል አይኑ እንኳን አይርገበገብም ከደቂቃዎች በሗላ የዋይታው ድምፅ ጀመረ መጥረቢያውን ትከሻው ላይ አድርጎ እያፏጨ መንቀሳቀስ ጀመረ ትንሽ ተንፈስ አልኩኝ ምን ሲያቀብጠኝ ወደዚ ክፍል እንደመጣሁ አላውቅም እዛው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ የሚሆነውን ብጠብቅ ይሻለኝ ነበር...መጥረቢያውን የነበረበት ቦታ ላይ አስቀምጦ ድመቷን ከወደቀችበት አንስቶ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተታት ያደረገውንም ጓንት አውልቆ ከድመቷ በድን ጋር አብሮ ጣለው ከዛም አዲስ ጓንት ለማድረግ ወደ መሳቢያው ተጠጋ አውጥቶም በዋይታው እየተንቀሳቀሰ ማድረግ ጀመረ ከዛም ከተሰጡት የዶክተሮች ጋውን አንዱን አንስቶ ለበሰ ከዛም ፈገግ እያለ እየቆለፈ ራሱን በራሱ መመልከት ጀመረ በጣም ደስ ያለው ይመስላል እጁን ኪሱ ከቶ ወደዛ ወደዚ መንጎራደድ ጀመረ ጓንት ወዳወጣበት መሳቢያ በድጋሜ ሄዶ መነፅር አውጥቶ አደረገ አሁን የባሰ ፈገግ አለ የሚያረገው ነገር ትንሽም ቢሆን ከፍራቻዬ አውጥቶ በአግራሞት ዝም ብዬ እንድመለከተው አደረገኝ ደረቱን ነፍቶ አሁንም መንጎራደዱን ቀጠለ ነገር ግን ሙዚቃው በድጋሜ ፀጥ አለ እሱም ባለበት ቦታ እጁን ኪሱ እንደከተተ ቆመ እኔም እቺ ደቂቃ እስክታልፍ አፌን አፍኜ ያዝኩኝ ነገር ግን ሮቤል.......
...............ይቀጥላል................
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-አምስት
...በሆስፒታሉ የመግቢያ በር ላይ የቆመ ሰው ተመለከትን እጅግ በጣም ከመደንገጣችን የተነሳ የነበርንበትን ክፍል በር ሳንዘጋ እየተጯጯህን ወደ ውስጥ ገባን አንድ ላይ ተጠባብቀን የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርን ለደቂቃዎች ቢሆንም መብራቱ አልጠፋም ግን ብዙም አልቆየም ነበር ወዲያውኑ ጠፋ አሁን ፍራቻችን የባሰ አየለ...ከእስትንፋሳችን በቀር የሚሰማ አንዳችም ድምፅ የለም ግን ትንሽ እንደቆየ ከድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ልዝብ ያለ የእርምጃ ድምፅ እና መሬት ላይ የሚጎተት የስለት ድምፅ ተሰማ አሁን ሆስፒታሉ ውስጥ ከኛ ሌላ ሰው እንዳለ እርግጠኛ ሆንኩኝ በመሃል መብራቱ መልሶ በራ ከመፍራታችን የተነሳ መብራቱ ሲበራ እንኳን ደንግጠናል...እርምጃው ቀጥ ብሎ ግን መብራቱ ብዙም ሳይቆይ ጠፋ የሆስፒታሉ በር መግቢያጋ ያለው ብቻ ነበር የሚበራው ለዛም ነው መሰለኝ ወለሉ ላይ የሰው ጥላ ይታየኛል...ጥላው መንቀሳቀስ ጀምሯል እነ ባርሳ ማልቀስ ጀምረዋል እኔ ግን ጥላው ምን እንደሆነ ለመመልከት ከክፍል መውጫ ወደሆነው በር ዝግ ባለ እና ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ መጠጋት ጀመርኩ "ሜርሲ የት ነው ምትሄጂው" አለኝ ባባ በሹክሸካ ድምፀት ከሱ ቀጠል አርጋ "ነይ ተመለሺ" አለችኝ ባርሳ...ሽሽሽሽ ተረጋጉ ያለውን ሁኔታ ለመመልከት ነው አልሄድም አልኳቸው ግልፅ የሆነ እይታ ባይኖረንም ውጪ ከሚበራው መብራት የሚገባው ወጋገን በጥቂቱ ብርሃን ሆኖናል...ጥላው እየቀረበ መጣ እኔም ወደ በሩ መጠጋት ጀመርኩ ያለሁበት የድንጋጤ ስሜት ነው መሰለኝ የእግሬ ህመም ብዙም አልተሰማኝም...አሁን በሩ ጋር ደርሻለሁ አንገቴን ወደ ውጪ አስግጌ ስመለከት አንዳች ነገር የለም የሆስፒታሉ መብራት በድጋሜ ፏ ብሎ በራ በዚ ጊዜ በፍጥነት ወደ ውስጥ ተመለስኩኝ እነ ባርሳ እዛው ቦታ ላይ ቁጭ እንዳሉ ነው "ምንድነው እዚ ውስጥ ያለው ነገር" አለችኝ ቅድስቴ በተረጋጋ ድምፅ "እስካሁን ምንም ያየሁት ነገር የለም ግን ከኛ ውጪ የሆነ ሰው እዚ ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል ለማንኛው እናንተ ተረጋጉ እኔ ሁኔታው አጣራለሁ" አልኳቸው ሶስቱም በእሺታ አንገታቸውን ነቀነቁ እኔም መለስ ብዬ ያለውን ነገር ለመመልከት በድጋሜ ከክፍሉ ወጣሁ ሁሉም ክፍሎች ዝግ ናቸው ኮሪደሩም ቢሆን ባዶ ነው ግን ከክፍሎቹ ሁላ አንዱ ክፍል ገርበብ ብሏል ቀስ ብዬ እየተራመድኩኝ ገርበብ ወዳለው በር መጠጋት ጀመርኩኝ ጀርባዬን ግድግዳው ላይ አስደግፌ የጎን ነበር ስራመድ የነበረው ግራ ቀኜን ለመመልከት እንዲመቸኝ...ክፍሉ በር ላይ ደረስኩ እስከተከፈተበት ድረስ ስመለከት ምንም አልታየኝም ግራ ቀኜን አየሁና ወደ በሩ እጄን ሰደድኩ ግን ምንም አልነበረም አንገቴን ወደ ውስጥ አስገብቼም ተመለከትኩ አሁንም ባዶ ነው ግን አንዳች ነገር ቀልቤን ሳበው በደም የተጨማለቀ መጥረቢያ ተመለከትኩ እንደገመትኩትም ያ ሰው በዙሪያችን ነው ያለው ማንነቱን ለመለየት በድፍረት ወደ ውስጥ ገባሁ መጥረቢያው ወዳለበት ተጠግቼ ስመለከት በውስጥ በኩል ሌላ በር አለ መጥረቢያውን ትቼ ወደ ውስጠኛው በር አመራሁ ሆስፒታሉ አሰራሩ በጣም ውስብስብ ነው ወደ ውስጠኛው በር እንደተቃረብኩ ያልጠበኩትን ነገር ተመለከትኩ ወለሉ ላይ ወደ ውስጥ የሚያስገባ መንገድ ተመለከትኩ መስኮት የሚመስል መዝጊያ አለው ወለሉ ላይ በርከክ ብዬ ስመለከት ወደታችኛው ክፍል የሚወስድ በደም የተጨማለቀ ደረጃ ተመለከትኩ በጣም ደነገጥኩኝ ያ ሰው አዳኝ ሰውዬ መኖሪያው እዚ እንደሆነ ተሰማኝ በመሀል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ አሁን ካለሁበት ቦታ መሄድ ስላለብኝ ለደህንነቴም ስለሚያሰጋኝ የመጣሁበትን በምናቤ ስዬ ግድግዳውን እየተደገፈኩ ከክፍል ለመውጣት ሙከራ ጀመርኩ ግን ሳልጠብቀው እጄ የሰው አካል ላይ አረፈ.............
............ይቀጥላል ...............
#ውዴ_እርቃኑን_ያምራል
**
አብ ፊት ሲያዞርበት ፣ እኔ አፍጥጨ ያየሁት
አይኔን እና ልቤን ፣ መስቀል ላይ የጣልኩት
ሲገረፍ ደስ ያለኝ ፣ ሲሰድቡት የሳ'ኩት
ሲወጉት ከልቤ ፣ ሀሴት ያደረኩት
የ'ሾህ ጉንጉኑን ሳይ ፣ ስቦርቅ የዋልኩት
ሲተፉበት ጊዜ ፣ ታድያለሁ ያልኩት
መች ወድጄ ሆነና.........እነሱ እኮ ናቸው
በሚስማር ፣ ችንክረው
በጦር ፣ ጎኑን ወግተው
በጥፊ ፣ መትተው
እሾሁን ፣ ጎንጉነው
ገላውን ፣ ገርፈውት
ደም በደም ፣ አርገውት
ልብሱን ቀደውበት ፣ ያለ ልብስ ሲገኝ
በፍቅር እያየኝ ፣ ላንተ ስል ነው ሲለኝ
የሱ እርቃን ሲገለጥ
የኔ እርቃን ሲሸፈን ፣ ስለብስ ታወቀኝ
ያኔ የጠላሁት.......
ወጥቶ የመጣው ፣ ከአባቱ እቅፍ
የኔን ሀጥያት ወስዶ ፣ የኔን እድፍ ሲያድፍ
እርቃኑን አይቸው ፣ ፍቅር ይዞኝ እርፍ
ታድያ እኔ ምን ላድርግ........እነሱ እኮ ናቸው
ፊቱ ላይ ፣ ሲተፉ
ተሳልቀው ፣ ሲፅፉ
እግሮቹ ፣ ሲነቁ
ፌዘኞች ፣ ሲስቁ
ተጠምቶ ፣ ሲጨነቅ
በደሙ ፣ ሲጠመቅ
ኮምጣጤ ፣ ሲያጠጡት
አሳቅለው ፣ ሲሰቅሉት
ልብሱን ቀደውበት ፣ ያለ ልብስ ሲገኝ
በፍቅር እያየኝ ፣ ላንተ ስል ነው ሲለኝ
የሱ እርቃን ሲገለጥ
የኔ እርቃን ሲሸፈን ፣ ስለብስ ታወቀኝ
ያኔ የጠላሁት..........
ወጥቶ የመጣው ፣ ከአባቱ እቅፍ
የኔን ሀጥያት ወስዶ ፣ የኔን እድፍ ሲያድፍ
እርቃኑን አይቸው ፣ ፍቅር ይዞኝ እርፍ
እናማ ምን አልኩኝ..........
ከእልፍ የመረጥኩት ፣ ልብን ይማርካል
ፍቅሩ ያንበረክካል ፣ ይራራል ይምራል
በደም ተለውሶ ፣ ውዴ እርቃኑን ያምራል
የ'ሾህ አክሊል ደፍቶ ፣ ውብ ነው ውዴ እርቃኑን
ስለኔ የወጉትን ፣ እዩትማ ጎኑን
እዩማ ፣ እጆቹን
እዩማ ፣ እግሮቹን
እዩ ቆንዳላውን ፣ አስውቦታል ደሙ
ፈውሴ ሆኖልኛል ፣ ፍቅር መታመሙ
ዝርግፍ ጌጥ ሳይኖረው ፣ ዝርግፍ ጌጤ ሆነ
ውዴ እርቃኑን ሆኖ ፣ እርቃኔን ሸፈነ
ግን በደንብ ስማኝ........እርቃኑን ነው ስልህ
አንተን ሊያለብስ እንጂ ፣ ልብስ አ'ቶ እንዳይመስልህ
እስከ እግሩ ድረስ ፣ የለበሰ ነው
ወገቡን በወርቅ ፣ የታጠቀ ነው
የራሱ ጠጉር ፣ እጅግ የነጣ
እግሮቹ እንደ ናስ ፣ ግሎ እንደወጣ
ድምፁ እንደ ውሆች ፣ ፊቱ እንደ ፀሐይ
የ'ሳት ነበልባል ፣ አይኖቹን ለሚያይ
ማንም ሰው ቢሆን ፣ በክብሩ ሲያየው
በፊት ለፊቱ መቆም አይችልም
እንደሞተ ሰው ፣ ይወድቃል እንጂ
እንኳን ጠላቱ ወዳጁ አይቆምም
እና ምን ልልህ ነው............
ከእልፍ የመረጥኩት ፣ ልብን ይማርካል
ፍቅሩ ያንበረክካል ፣ ይራራል ይምራል
በደም ተለውሶ ፣ ውዴ እርቃኑን ያምራል
እኛን ጽድቁ ሊያደርግ ፣ ኃጢአት የሆነበት
ይህ ነው ያንተ ያንቺ ፣ ይህ ነው የኔ ውበት♥♥♥
/channel/yebirihan_lijoch
😍😍 የዕድል ጨዋታ እንጫወት እርሶ ብቻ የራሶትን ስም አልያም የፍቅረኛዎን ስም የመጀመሪያ ፍደል አንዴ ብቻ በመንካት የሚፈጠረውን ነገር ይመልከቱ 😍😍
Читать полностью…Watch "ፀሎቱ New Protestant Dirama by ARIEL literature team 2013 YHBC" on YouTube
https://youtu.be/6gER7MmXR-0
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-ሶስት
፡
...ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ "ይመስለኛል ይሄ ታካሚ ድንገተኛ አደጋ ደርሶበት ነው የመጣው" አለች "በምን ልታውቂ ቻልሽ ብዬ" ጥያቄዬን ቀጠል አድርጌ እየጠየቋት "የህክምና ካርዱ ላይ የታካሚው ስም የለበትም የመድሃኒት መዘዢያውም ላይ እንዲሁ" ብላ መለሰችልኝ "ቀንስ አልተፃፈበትም" አልኳት በውስጤ የማስበው አንዳች ነገር ስለነበር ክፍሉ ወውስጥ ወዳለው ወደ አንዱ ጠረጴዛ እያመራች የመድሀኒት ማዘዣ ወረቀቱን እየተመለከተች "ቀኑ ትላንት ነው ወደዚ ስፍራ የመጣው ሰዓቱ ግን የለም" ብላ መለሰችልኝ የራጅ ወረቀት ከጠረጴዛው ላይ አንስታ ከፍ አርጋ እየተመለከተች "ግን ታማሚው አብዛኛው የሰውነት ክፍሉ ያን ያህል አልተጎዳም ግን የሗላ የጭንቅላት ክፍሉ ላይ የአጥንት መሰንጠቅ ይታያል ከሆነ ነገር ጋር እንደተጋጨ ወይም በሆነ ነገር እንደተመታ ገምታለው" ብላ ስለ ራጅ ምሰስሉ አብራራችልኝ የጭንቅላት የሗላ ክፍሉ ስትል ጫካ ውስጥ የተመለከትኩት የቅድስት ጓደኛ የአወዳደቅ ሁኔታ ውስጤ ብልጭ አለብኝ እሱ ሊሆን እንደሚችልም አሰብኩ "ግን እዚ ማን ሊያመጣው ይችላል" ብዬም እራሴን ጠየኩ ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ ነበርና "ምን አለሽኝ" አለችኝ ቅድስቴ "አይ ምንም እንዲሁ ከራሴጋ እያወራሁ ነው ብዬ መለስኩላት ከደቂቃዎች በሗላ እነ ባርሳ መጡ "ምነው ቆያቹ" አለች ቅድስቴ ባባም ቀበል አርጎ "ቶሎ ማግኘት አልቻልንም ለዛ ነው አሁን ሜርሲ እንዴት ነሽ" አለኝ "ደህና ነኝ አሁን ምንም አልልም" በማለት እንዳይጨነቁ ደህና ነኝ አልኩኝ እንጂ ክፉኛ እያመመኝ ነው ቅድስቴ መድሃኒቶችን መዘጋጀት ጀምራለች ግን በመጠራጠር ስሜት ሆና ደግማ ቁስሌን ተመለከተችው "ራጅ ብትታዪ መልካም ነው ሜርሲዬ" አለችኝ "እንዴ ለምን" ብዬ በጥያቄ መለስኩላት "የአናትሽ በስጋ የሸፈነው ክፍል ክፉኛ በወጋሽ ነገር ተቀዷል በዚህ ሁኔታ አጥንትሽም ሊነካ ይችላል" ብላ መለሰችልኝ ባለችው ነገርም ተስማማሁ የተኛሁበትንም አልጋ እየገፉ ወደ ክፍሉ ማምራት ጀመርን በሩ ላይ የተፃፉትን እያነበብን ነበር ፍለጋችን ከተወሰኑ ክፍሎች በሗላ አገኘነው ወደ ውስጥም ዘልቀን ገባን ግን ምንም አልነበረም ባዶ ክፍል ነበር ባየነው ነገር ሁላችንም ግራ ተጋባን "ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ" አለ ባባ "አዲስ ሆስፒታል ነው እንዴ?" አለች ባርሳ ከባባ ቀበል አርጋ "በቅርብ ቀን የተሰራ የራጅ ውጤት እኮ አሁን ተመልክቻለሁ ግን እንዴት ላይኖር ቻለ" አለች ቅድስቴ ግራ በመጋባት ስሜት ሆና "ቁስሉ ንፋስ ስለሚገባበት በቃ መሰፋት አለበት" አለች ቀጠል አርጋ ከዛ ክፍል ወጥተን መጀመሪያ ወደነበርንበት ክፍል ማምራት ጀመርን ሆስፒታሉ ሲበዛ ነጭ ነው ፍሎረሰንት በሚባለው የአንፖል አይነት እጅግ ደምቋል እይታው ራሱ ትንሽ ህመምን ያቀላል ፈፅሞ ሰላም ይሰጣል ወደነበርንበት ክፍል ዘልቀን ገባን የህክምና ጓንቷን አድርጋ በደረቴ ከነ ባርሳ ጋ ሆነው አስተኙኝ ከዛም ህክምናውን ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ፈፀመችው ከዛም አገችው "አሁን ከኢንፌክሽን ነፃ ነሽ" አለችኝ "በቃ እሺ ከዚ አካባቢ በፍጥነት እንውጣ" አለ ባባ አዎ ብለው እነ ቅድስቴ በሀሳቡ ተስማምተው እኔን ደግፈው አነሱኝ እራሴን ችዬ መሄድ እንደምችል ነገርኳቸው እና የተኛሁበት አልጋ ላይ ቁጭ አልኩኝ እነሱ እዛው ባለሁበት ሆኜ ወደ መኪናው ሄዱ ከአልጋው ተነስቼ እየተራመድኩ ወደ መስኮቱ አመራሁ መጋረጃውን ገለጥኩት መስታወቱ ተሰብሮና በደም ተጨማልቆ ነበር ሲመስለኝ የሆነ ሰው ለማምለጥ በዚ በኩል ወድቋል በተሰበረው መስታወት ውስጥ አንገቴን ወደ ውጪ አውጥቼ ስመለከት ሳሩ በደም ተለውሷል የሆነ ሰው እየተንፏቀቀ እንደሄደበት አይነት ምልክት አለው አንገቴን ወደ ውስጥ መልሼ መስኮቱን በመክፈቻው ከፍቼ ቀስ ብዬ ወጣሁ የደሙንም ምልክት እየተመለከትኩ ወደፊት አመራሁ ማን እንደሆን እንጃ ብቻ ክፉኛ የተጎዳ ሰው ነው ከሆነ እርምጃ በሗላ ደሙ ላይ ተለቅ ያለ የጫማ ምልክት ተመለከትኩ እዛው ባለሁቡት ቆምኩኝና አይኔን አሻግሬ ወደፊት ሰደድኩት ከአንድ ስፍራ ላይ ሲንፏቀቅ ይፈስ ከነበረው ደም ይልቅ ብዙ ደም ፈሿል ሳሩም የተረጋገጠ ይመስላል ከዛ ከተጎዳው ሰው ሌላ ሌላም ሰው ነበር ... መሬት ራሱን እያንፏቀቀ ይሄድ የነበረው ሰው በድንገት ጠፋ እርምጃዬን ቀጠል አደረኩኝ አንዳች ምልክት አልነበረም ግን ከትንሽ እርምጃ በሗላ የተንጠባጠበ የደም ጠብታ ተመለከትኩ እሱን ተከትዬ መሄድ ጀመርኩ ዞር ብዬ ስመለከት ከሆስፒታሉ እየራኩኝ ነው ግን ለመመለስ አልፈለኩም እርምጃዬን ቀጠልኩ የደሙን ጠብታ ተከትዬ ስጓዝ ከአንድ ጫካ አጠገብ ደረስኩ አሁን እርምጃዬን ገታሁት ነገር ግን የደም ጠብታው እንደ ቀጠለ ነው ከጫካው መግቢያ ላይ አንድ ነጭ ነገር ተመለከትኩ ወደ ውስጥ ብዙም ያልገባ ስለነበር ለመመልከት ተጠጋሁ የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር............
..............ይቀጥላል......,........
━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት እና የዩኒቨርስቲ ምደባ ሌሎችንም ትክክለኛና ወቅታዊ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ኢትዮ students የሚለውን ክሊክ በማድረግ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
Читать полностью…HinDhufaa
Fikadu Gemeda
Adola makane iyesus
Watch "April 14, 2021" on YouTube
https://youtu.be/_BMyKResQNg
✍ የኔ መገረሚያ
*****************
ከኔ ባልጀመረ ፣ በኔ በማይቀጥል
የሕይወት ስጦታህ ፣ የማዳንህ ፍቅር
እኔ ያላሰብኩህ ፣ የአብ ቀመር ስሌቴ
በ'ሳት የተፈተንክ ፣ ወርቅ የሆንክ እምነቴ
አንተ አይደለህም ወይ ፣ በአብ መግቢያ ደጄ
እንዳምንህ ያመንከኝ ፣ ተወዳጅ ወዳጄ
አቤት ፍቅርህ ሲገርም ፣ አቤት አንተ ስትገርም
እያልኩኝ ስትደንቀኝ ፣ እያልኩኝ ስገረም
ለኔ መገረሚያ ፣ ካንተ ውጭ የለም
እንዴት ይገርመኛል ፣ ያልኖርኩበት አለም
አንተ ነህ አለሜ ፣ ብርቄ የምትበርቀኝ
ሌላ ማን ይታየኝ ፣ ተቀምጬ በአብ ቀኝ
በክብርህ ክብር ልክ ፣ ካንተ ጋር ቁጭ ብየ
ከጸሐይ በላይ ነው ፣ ሁሉም እይታየ
ሰርክአዲስ ም'ረትህ ፣ ሰርክ እያስደመመው
ውስጤ ባለኸው ነው ፣ ውስጤ 'ሚገረመው
#ሄኖክ_አሸብር
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል ሀያ
....ሰውዬው ነበር እሱ ነገር ግን አልተመለከተኝም ነበር...ወደ ውስጥ ሲገባ ውጪ ላይ አንዳች የረሳው ነገር ያለ ይመስል ወደሗላ እየተመለከተ ነበር እኔም ይሄን ቅፅበት ተጠቅሜ ተደብቄ ወደ ነበረበት ስርቻ ተመለስኩ ግን ወደ ውጪ ሲመለከት የነበረው ሰውዬ ወዲያውኑ ከውስጥ አንዳች ነገር በልቡን የሳበው ይመስል በፍጥነት ዞረ ይመስለኛል ስደበቅ ያሰማሁት ኮሽታ ነው...ለደቂቃዎች በአፍንጫው እያነፈነፈ ቤቱ ውስጥ የገባውን እንግዳ ነገር ማሰስ ጀመረ ቅርቤ ስለነበር ይበልጥ ሰውዬውን መመልከት ቻልኩኝ ሁለቱም አይኖቹ ትክክል አይደሉም አቀማመጣቸውም ይለያል ከአይኖቹ ይልቅ አፍንጫውን አብዝቶ ይጠቀምበታል ነገር የአይኑ ብሌኖች ምስል ይከስቱ አይከስቱ እንጃ...በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰውዬውን እየተመለከትኩት ሳለ በዕድሜ አነስ የምትለዋ ሴት "ለምን እዚጋ ቆም አንድዬ" አለችው በማይገባ ቋንቋ የሆነ ነገር ብሎ መለሰላት "ምንም የለም ሁሉም ሰላም ነው እናትህ እንደ ድሮው ፀጉርህን ልታበጥርልህ ነው ና ወደ ውስጥ እንግባ" አለችው እያባበለችና የሚወደውን ነገር እየነገረችው እሱም በሃሳቧ ተስማምቶ እቅፍ አርጓት ወደ ውስጥ ገቡ...ውስጤ ለሰውዬው እንደ ማዘን አረገው በሆነ አንዳች ክፉ ክስተት እና ገጠመኝ ለዚ እንደተዳረጉ ለማሰብ ሰከንድ አልፈጀብኝም "ብቻ ከዚ በፊት መልካም ቤተሰቦች የነበሩ እሱም መልኩና አስተሳሰቡ ልቡም ጨካኝ ሳይሆን ሩሩህ ሰው ነበር" እያልኩኝ ከራሴ ጋር ስለ ሰውዬው መነጋገር ጀመርኩ ከዛም ከተደበኩበት በጥንቃቄ ተነስቼ ከኔ ቀጥሎ የሚከሰተውን ትዕይንት ወደሚያሳየኝ የመጋረጃ ሽንቁር ተጠጋሁ ወዲያውኑ ትልቋ ሴትዮ ባለመደገፊያ የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጣለች እሱ ደግሞ አነስተኛ ወንበር ላይ ጀርባውን ሰጥቷት እግሯ መሃል ተቀምጧል በያዘችው ማበጠሪያ ሉጫ ፀጉሩን ወደሗላ በማበጠሪያ ታስተኛዋለች አንዳች አትናገርም ቃልም አይወጣትም ነገር ግን ከአይኗ የሚፈሰው እንባ ከእልፍ ድምፅ አልባ ቃላት የበለጠ ይናገራሉ በሚወርደው የእንባዋ ቦይ ላይ ብዙ ብሶቶቿ እና ችግሮቿ በግልፅ ይነበባሉ ፊቷ እንኳን እንደሚያለቅስ ሰው አልተኮማተረም አልተጨማደደም የማትናገረው ውስጧ ሚብሰለሰል እያደር ሚበላት ግን የማታከው አንዳች ነገር እንዳለ አሰብኩኝ..."አንዳንዴ ጥፍር ደርሶ የማያከው ቆዳ ስጋና አጥንትን አልፎ ከውስጥ የሚበላ ክፉ እከክ" አለ አልኩኝ ለራሴ ደሞም ልክ ነበርኩ በሴትየዋ ሁኔታ ከገባሁበት ሰመመን ስነቃ ሳላስበው ጉንጬ በእንባ ርሷል በጣም ደነገጥኩኝ ግራም ተጋባሁኝ እንዴት ሊሆን እንደቻለም ለራሴ ገረመኝ ግን በቃ ሆነ ልቤ እና አይኔ ተስማምተው በአንድነት አዘኑ በእንባዬም ገለፁት..."ግን የእውነትም እጅግ ያሳዝናሉ አንጀትም ይበላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ስጋ ይበላሉ እዚህ ቤተሰብ ላይ የተከሰተው አንዳች ክፉ ገጠመኝ ምን ሊሆን ይችላል እንዴትስ ሊሆን ቻለ" እያልኩኝ ራሴን መጠየቄን ተያያዝኩትን ከራሴ ንግግር ተመልሼ በድጋሜ አይኔን በመጋረጃው ሽንቁር ወደ ውስጥ ሰደድኩት ትልቋ ሴትዮ ፈትል የሚመስለው ነጭ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ተንጋሏል ከፊት ያለው የፀጉሯ ክፍል አልፎ አልፎ ጥቁር ጣል ጣል ብሎበት የተለየ ውበት ሰጥቷታል ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ማበጠሯን ተያይዛዋለች አነስ የምትለዋ ሴትዮ ግን ሰውዬውን ካስገባች በሗላ ደግሜ አልተመለከትኳትም ከነሱጋ አለመሆኗ ቢያስገርመኝም "ለምን" ብዬ ምጠይቀው ሰው የለ ግን ከአይኔ መሰወሯን አልወደድኩትም ውስጤ ተረብሿል... ነገር ግን ቀልቤ አሁንም እናትና ልጁ ላይ ነው...ከዛም እሱ በተራው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ ውሃና የእግር መታጠቢያ አምጥቶ ቀስ እያለ አጠባት ከዛም ቅባት ነገር ይመስለኛል አነስቶ ከእናቱ ትይዩ ባለው የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጦ በእርጋታ ያሻት ጀመር እሷም ፈገግ እያለች አይን አይኑን ትመለከተዋለች ነገር ግን አሁንም አይኗ ከማንባት አልቦዘኑም ነበር ያለመታከት ያነባሉ የእግር ጣቶቿን አንድ በአንድ እያረገ ዘና እንድትል የተቻለውን ይጥራል ደግሞም ከተቀመጠበት ተነስቶ ጉንጯ ላይ ሚንከራተተውን እንባ በመዳፉ ጠርጎ ግንባሯን ይስማታል...ምን አለ አንዳች ነገር ተከስቶ ወደ ቀድሞው በመለስኳቸው ብዬ ተመኘሁ...እዚ ቦታ ላይ ከዚ በላይ መቆየት እንደሌለብኝ ግልፅ ነው ቶሎም ተመልሼ ጓደኞቼን ከዚ አካባቢ ይዤ መሄድም እንዳለብኝ ግልፅ ነው...የውስጡን ትዕይንት ከምከታተልበት የመጋረጃ ሽንቁር አይኔን አንስቼ ወደ በሩ ስዞር አነስ ምትለዋ ሴትዮ................
...............ይቀጥላል...............
Join and share us
👇👇👇👇👇👇👇
━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-ስምንት
...በድጋሜ "እርዱኝ አድኑኝ" ብሎ ድምፅ አወጣ በዚ ሰውዬው ቡታጋዙ ላይ ተጥዶ የነበረው የሚፍለቀለቅ ዘይት ከመቅፅበት አንስቶ ከፊቱ ጀምሮ እስከ እግሩ ድረስ ደፋበት ሮቤል አምርሮ ክፉኛ ጮኸ ግን ድጋሜ አልጮኸም ነበር ለዘላለሙ በዛው አሸለበ...ይሄን መቆጣጠር አልቻልኩም በዘይት የተጠበሰው የስጋው ሽታ ወደኔ ሲመጣ አጥወለወለኝ ሊያስመልሰኝም ዳዳሁ በብዙ ተፈታተነኝ...እንዳጋጣሚ ሰውዬው ለምን እንደሁ እንጃ ከክፍሉ ወጣ እኔም የሱን አለመኖር ጠብቄ ሚተናነቀኝን አስወጣሁት ከአንድ ደቂቃ በሗላ ሶስት ነጫጭ ሳህን አምጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ምንም አልገባኝም የሩቤል አስክሬን ድርቅ ብሏል አንደበቱ ሊጮህ እንደተከፈተ በዛው ስላሸለበ አልተዘጋም ይሄ ሁሉ ነገር ሲደረግ አይኔን ገልጬ ማየቴ ራሴን እንደ ጨካኝ እንዳይ አድርጎኛል በሌላ በኩል ደግሞ ይሄን ሁላ ትዕይንት መቋቋሜ መልሶ ለራሴ ይደንቀኛል ሰውዬው አሁንም ከዘፈኑ እኩል እየተንቀሳቀሰ ሚከውነውን ይከውናል አንድ ተለቅ ብሎ ስፋት ያለው የሚያብለጨልጭ ስለታም ቢላ እና አነስተኛ ቢላ ይዞ ወደ ሮቤል በድን ተጠጋ ሊሆን ያለውን ማሰብ ለኔ ከባድ ነበር ይህ ከገመትኩት በላይ ክፉና አረመኔ ነው ሰው መባል ሁሉ የለበትም ሰይጣን ስጋ ለብሶ እንጂ...ሰውዬው መለስ ብሎ አነስ ያለ ወንበር ይዞ ወደ በድኑ ተመልሶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ ከዛም በትንሿ ቢላ አስክሬኑን መክፈት ጀመረ ለሚመለከተው የሚያክም እንጂ የሚበልት አይመስልም ዘየት በደንብ ያገኘውን የሰውነት ክፍል እየመረጠ መቁረጥ ጀመረ የቆረጠውንም የሰው ስጋ ባመጣቸው ሳህኖች ላይ እያስተካከለ መደርደር ጀመረ...ሲለው ደግሞ መሀል መሀል ላይ ከሚቆርጠው ስጋ እየቀመሰ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ይደነቃል ይሄን መመልከት ምነኛ አለመታደል ነው ግን ከቤት ወደዚ የመጣሁበትን ቀን አምርሬ ጠላሁት ሲበዛም ረገምኩት...ሰውዬው አሁንም እየቆራረጠ ነው ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱን ሳህኖች አንስቶ ከክፍሉ ወጣ ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ተመልሶ አንደኛውን ሳህን ይዞ ወጣ እኔም የሚሄድበትን ለመመልከት ብዙ ሳይረቅ ወደ በሩ ተጠጋሁ ሆስፒታሉ ውስጥ ከሚገኝ አንዱን በር ከፍቶ ሲገባ ተመለከትኩት የከፈተውንም በር ሳይዘጋ ወደ ውስጥ አመራ እርምጃዬን አጥፍቼ ያለውን ነገር ለመመልከት ወደ ውስጥ ገባሁ ግን ክፍሉ ባዶ ነበር በጣም ደነገጥኩኝ ወጥመድም መሰለኝ እዛው በቆምኩበት በድንጋጤ እያለከለኩ ተዟዟርኩኝ ግን ማንም አልነበረም የት እንደተሰወረ ግራ ሆነብኝ ነገር ግን የቆምኩበት ወለል እስካሁ ከረገጥኩት የወለል ድምፅ ይለያል ግድግዳ እና ጣሪያ ላይ ሲያማትር የነበረው አይኔን ቁልቁል ወደ ወለሉ ወረወርኩት እውነትም የቆምኩበት ወለል የተለየ ነበር ከላዩ ላይ ወረድኩና በጉልበቴ በርከክ ብዬ ጆሮዬን ላዩ ላይ ደቀንኩና ማዳመጥ ጀመርኩ በጣቶቼም ቆረቆርኩት ከሰማሁት ድምፅ በመናሳት ከታች የሆነ ክፍል እንዳለ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ ውስጥ ያለውን ነገር ገብቶ ለመመልከት ወሰንኩኝ ከዛም ወለል መሳይ በሩን ለመክፈት መታገል ጀመርኩኝ ግን ብዙም አድካሚ አልነበረምና ተከፈተልኝ ቁልቁል ስመለከት ውስጡ ብዙም ብርሃን አልነበረውም ቢሆንም ግን የመመልከት ሀሳቤን አላስቀየረኝም ቀስ ብዬ እግሬን ከደረጃው ላይ አሳረፍኩ በአንድ እጄ በሩን ይዤ በጥንቃቄ ቁልቁል መውረድ ጀመርኩ አልፎ አልፎ ከሚታይ ወጋገን በቀር ክፍሉ ጨለማ ነው እቃ ነገር ጥዬ እራሴ ላይ ወጥመድ እንዳልሆን በጥንቃቄ መራመድ ጀመርኩ ወደፊት በተጠጋሁ ቁጥር ብርሃን እየበዛ መጣ ትንሽ እንደተራመድኩ የሚሳሳቁ የሰዎች ድምፅ ተሰማኝ "ያ ክፉ ሰው ብቻውን አልነበረም ሌሎች የሚያግዙት ሰዎች" አሉ አልኩኝ ለራሴ እርምጃዬን ጠብቄ ወደፊት መሄዴን ቀጠልኩኝ ጨዋታቸው ደርቷል ምን እንደሚባባሉ ግልፅ ባይሆንም ሳቃቸው ግን ይሰማል በነሱ ሁኔታ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ በድንገት ሳላስበው በእግሬ መሬት የነበረ ጣሳ ረገጥኩኝ የፈጠረው ድምፅ ለተንኮል ከፍ ያለ ነበር የደራው ጨዋታቸው እና የሞቀው ሳቃቸው በአንድ ጊዜ ፀጥ አለ በር ሲከፈት ያለው ድምፅ ተሰማኝ የሆነ ሰው ነገሩን ለማጣራት እየመጣ ይመስለኛል እንደዚ ባሰብኩ ጊዜ ከአካባቢው መራቅ ነበረብኝና የሆነ ጥግ ላይ ተደበኩ ግን ማንም አልመጣም ነበር በድጋሜ ቀስ ብዬ ወደፊ ተጠጋሁ ቅድም ሲከፈት የሰማሁት በር ይመስለኛል ከፊት ለፊት ክፍት ሆኖ ይታየኛል ጨዋታው በድጋሜ ደርቷል እየቀረብኩኝ ስሄድ ድምፃቸው ግልፅ እየሆነ መጣ ከእርምጃዎች በሗላ ወደ ክፍቱ በር ደረስኩ አንገቴን አስግጌ ውስጡን ስመለከት የተቀዳደና በደም የመነቸከ ነጭ መጋረጃ ተመለከትኩ ሰዎቹም ከመጋረጃው ጀርባ እንዳሉ ተረዳሁ ቀስ ብዬ ተጠጋሁና በቀዳዳው መመልከት ጀመርኩ ሰውዬው ጀርባው ለኔ ሰጥቶ ነው የተቀመጠው በሱ በስተቀኝ በኩል ተለቅ ያለች አሮጊት ትታየኛለች ከሷ ሴትዮ በመቀጠል ደግሞ ከሁለቱም በዕድሜ ምትበልጥ ሴት ከሱ ፊት ለፊት ተቀምጣለች በድንገት አይኔ የሚመገቡት ነገር አረፈ እሱን ባየው ጊዜ ሳላስበው ድምፅ አወጣሁ..............
..................ይቀጥላል...............
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚አስራ-ስድስት
...ልቤ ስንጥቅ እስኪል ድረስ ድንጋጤዬ ከባድ ነበር ነገር ግን ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌ ምንም ድምፅ ሳላሰማ ፀጥ አልኩኝ...የነካሁት አካል በደም የተጨማለቀ መሰለኝ ይቀዘቅዛል ቀስ ብዬ ወደ ነበርኩበት ቦታ ለመመለስ እጄን በጥንቃቄ ከነካሁት አካል ላይ አነሳሁ ከዛ ወደሗላ ማፈግፈግ ጀመርኩ ትንሽ እንደተጠጋሁ መብራቱ ቦግ ብሎ በራ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ድንጋጤዬ ከመጠን ስላለፈ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ በጭለማ ዳብሼ የነካሁት በደም የተጨማለቀው ገላ የሮቤል ነበር...ድምፄ ከተሰማ በሗላ ወዳለሁበት የሚራመድ ፈጠን ያለ እርምጃ ተሰማኝ ከገባሁበት ድንጋጤ ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ምደበቅበትን አንዳች ስፍራ እንዳለ አይኔን እያማተርኩ ማሰስ ጀመርኩ ከፊት ለፊቴ የዶክተሮች ጋውን በብዛት የተሰቀለበትን ቦታ ተመለከትኩ እርምጃዬንም ፈጠን አድርጌ ከጋውኖቹ መሃል ተደበኩኝ ወደኔ ይመጣ የነበረው ያ እኔ የምፈራው ሰው ነበር በሩ ላይ ቆሞ ግራ ቀኙን ማማተር ጀመረ መጥረቢያውንም ከተቀመጠበት ስፍራ አንስቶ ያዘው ክፍሉ ውስ መዘዋወር ጀመረ ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ወደ ጋውኖቹ ትኩር ብሎ መመልከት ጀመረ እጅግ በጣም ጨነቀኝ አፌን በእጆቼ እፍን አድርጌ ደብዛዬን ለማጥፋት ፀጥ አልኩኝ ግን ከበስተሗላዬ ከሁለት የገመድ መስቀያ አለፍ ብሎ የነበረው መስቀያ ምን እንደነካው እንጃ ወደቀ ፀጥታውም በአንዴ ታወከ ከጋወኑ በታች የነበሩ ፕላስቲኮች እና ብረት ነክ ዕቃዎች ተንጫጩ ወደኔ በርቀት ሆኖ ሲመለከት የነበረው ሰው አሁን መጠጋት ጀመረ ምንም ማድረግ የማልችልበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሁ ተረዳሁ ለማምለጥ ምንም አይነት አጋጣሚ ሊፈጥር እንደማይችል ደመደምኩ ሰውዬው አብዝቶ ወደኔ ተቃርቧል በመሃላችን ያለው ልዩነት የሶስት ገመድ መስቀያ ብቻ ነበር መጥረቢያውን እያንፏቀቀ አንዱን መስቀያ አለፈ ከጋውኖቹ መሀል ላይም ቆሞ ዙሪያ ገባውን ቃኘ በድጋሜ አንደኛውን መስቀያ አልፎ ወደኔ እጅግ ተቃረበ በመሃላችን የአንድ መስቀያ ልዩነት ብቻ ቀረ መላ አካላቴ መርገፍገፍ ጀመረ ተውረገረገ አይኖቼን ከድኜ ሞቴን መጠባበቅ ጀመረኩኝ እያወቁ መሞት ምንኛ ከባድ ነው ግን አስተውያቸው የማላውቃቸው እነዛ የሰላም ቀናት አብዝተው ናፈቁኝ ሰውነቴ በላብ እና በደም ተጨማልቋል አይኔን ጨፍኜ ሞቴን ብጠብቅም ገዳዬ ግን ዘገየ ምን እንደተፈጠረ ለመመልከት አይኔን ገለጥኩኝ ሰውዬው የተመለከተኝ ይመስል ወደኔ አቅጣጫ እያየ መጥረቢያውን ከፍ አድርጎ በሁለት እጆቹ ያዛው እርምጃው ትንሽ ወደኔ አስጠጋና ለሰከንዳት ያህል ፀጥ ብሎ ቆመ በድንገት አዲት ድመት ድምፇን ከፍ አርጋ ጮኻ ከወዳደቁት ጋውኖች መሀል ተስፈንጥራ ወጣች ወዲያውኑ እኔን ትቶኝ ወደሗላው ተመለሰ ነፍሴም ተረጋጋች ነገር ግን ሰውዬው ከክፍሉ ውስጥ አልወጣም ይብሱኑ ክፍሉ ውስጥ ያለውን ተለቅ ያለ ጠረጴዛ አየጎተተ ወደ መሃል አመጣው ከዛም ስለት ያላቸውን መቆራረጫዎች ተለቅ ባለ ብራማ መልክ ባለው አራት ማዕዘን ትሪ መሳይ ነገር ላይ አድርጎ አመጣ...የሚያደርገው ነገር እጅግ ግራ ያጋባል ከዛም ወደበሩ ጋር ጠጋ ብሎ የሮቤልን በድን አካል ጠረጴዛው ላይ አደረገው ሊያረግ ያሰበውን ሳስበው ሆዴ ተላወሰ ሊያስመልሰኝም ቃጣው ፈጥኜ እጆቼን አፌ ላይ አደረኩኝ መስኮቱ አጠገብ ካለው መሳቢያ ውስጥ ቆየት ያለ ሞዴል ያለው ቴፕ አውጥቶ ውስጡ ያለውን ካሴት በመዳፉ መታ መታ አድርጎ አድርጎ ከተተው ከዛም ግራ የሚያጋባ ግጥም የሌለው በጩኸት የተሞላ ድምፅ ጀመረ ዋይታ ይበዛዋል ለሰሚው በጣም ይጨንቃል ግን እሱ በደስታ ይንቀሳቀስበት ነበር ፊቱ የጤነኛ ሰው መልክ የለውም ከአፍንጫው ጀምሮ እስከ ጆሮው ድረስ ተቀዶ የተሰፋ ቁስል ይታየኛል አንደኛው አይኑ የአይን ኳሱ የለውም የግራ ጆሮው በከፊል ተቆርጧል ፊቱ በእሳት የተለበለበ ነው ሚመስለው የእጅ ጣቶቹ ላይ ጥፍር የሚባል የለባቸውም የጭንቅላቱ ፀጉር መሃል መሃሉ ባዶ ነው በአደጋ እንደዚ የሆነ ይመስላል ይሄን ሁሉ ነገር የምመለከተው ለጆሮ በማይመቸው የሰቀቀን ድምፅ በሆነው ዋይታ ሲደንስ ነው ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ከክፍሉ ከአንዱ ጥግ ተለቅ ያለ ድስት አንስቶ ውሃ በዛ ያለ ዘይት ጨምሮበት ቡታጋዝ ለኩሶ ጣደው የሚያረገውን ሁሉ እየደነሰ ነበር ሚከውነው ግን ያልጠበኩት እና ያስደነገጠኝ አንዳች ክስተት ተፈጠረ...............
...............ይቀጥላል.................
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ-አራት
...በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች አደጋ ደርሶበት ወደዚ ሆስፒታል መጥቶ ነበር ግን ለምን ህክምናውን ሳይጨርስ ወጣ? ማንስ ሊያስወጣው ቻለ? ዶክተሮቹስ የት ሄደው ነው? የሚሉ መልስ አልባ ጥያቄዎች አይኔን ጫማው ላይ ተክዬ ሳለ ውስጤ ይመላለሱ ነበር ከጫማው ትንሽ ተስፈንጥሮ አንድ ግራ ሚያጋባ ነገር ተመለከትኩ ለማየትም እንዲያመቸኝ ወደፊት እየተጠጋሁ ሳለ ባርሳ "ሜርሲ" እያለች ስጠራኝ ተሰማኝ እኔ ያለሁበት ስፍራ ከመጡ የሚፈጠረውን ስሜት ስለማውቀው ቶሎ ወደ ሆስፒታሉ ተመለስኩ እግሬ ቢያስነክሰኝም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደነሱ ሄድኩኝ ሳያቸው ሶስቱም ፊት ላይ አንዳች ልዩ ነገር ይታየኛል "የት ሔደሽ ነው?" አለች ሜርሲ በንዴት ስሜት ውስጥ ሆና የሷን ጥያቄ መመለስ ሳልጀምር ቅድስቴ ተከተለች "በቅጡ እንኳን የረባ ህክምና ሳታገኚ ምንድነው ሚያዞርሽ" አለችኝ በጣም ደነገጥኩት "ምን የተፈጠረ ነገር አለ" ብዬ ጥያቄዬን ቀጠል አደረኩኝ "የመኪናችንን ጎማ ማን እንደሆነ እንጃ በሆነ ነገር ወግቶታል" አለ ባባ ወዲያውኑ ያ ሰው ነበር ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ያለው "የመንደሩ ነዋሪ መሆን አለበት ማለትም ያ አንቺ ከምታስቢው ሰውዬ ሌላ" አለ ባባ እንዴት እንደዚ ማለት እንደቻለ ጥያቄ ፈጥሮብኛል ሆኖም ግን ምንም አላልኩትም ነበር...መልስ ሳልሰጣቸው ወደ መኪናው እያነከስኩኝ ሄድኩ እነሱም ከሗላዬ ተከተሉኝ የሗላው ጎማ ነበር የተወጋው...የቆምንበት ስፍራ ከአስፓልቱ ወረድ ብሎ ስለነበር አፈርማ ነው ግን መኪናው ዙሪያ ምንም አይነት የእግር ኮቴ የለም ከእኛ ውጪ...ከኛ መኪና ትንሽ ተስፈንጥሮ የሆነ ነገር ተመለከትኩ እያነከስኩኝ ተጠጋሁ "ምንድው ሜርሲ" አለችኝ ባርሳ የማየውን ነገር እስካረጋግጥ ድረስ ምንም አላልኳትም ነበር ግን ከእኛ ሌላ እዚ አካባቢ የቆመ መኪና እንዳለ ይሰማኛል እኛ ከቆምንበት በተቃራኒ አቋቋም የሆነ መኪና እንደነበር ያስታውቃል...ግን ሙሉ ለሙሉ ከአስፓልቱ ወርዶ አልቆመም ነበር በአንድ ጎን ያሉት ጎማዎች ናቸው አፈሩ ላይ ያረፉት አሁንም የጎማውን ቅርፅ ወዳየሁበት በጥንቃቄ መመልከት ጀመርኩኝ ይመስለኛል መኪናው ለኛ መኪና ጀርባውን ሰጥቶ ነው የቆመው አቅጣጫው ደሞ እና በቆምንበት ነበር...አተኩሬ ስመለከት የሰው የእግር ኮቴ አለ ኮቴውን እየተመለከትኩ ተጠጋሁ ብዙ ዱካ የለውም ከአምስት እርምጃ በላይ አልተራመዳም ታዲያ ወደመኪናችን እንዴት ሊደርስ ቻለ የሚለው ጥያቄ ውስጤ እያሰላሰልኩ ያለፍኳቸውን የእግር ዳና ድጋሜ እየተመለከትኩ ሳለ አስፓልቱ ላይ የእግር ዱካ ተመለከትኩ ይህ ሰው ካቆመው መኪና እስኪያልፍ ብቻ ነው የተራመደው ከዛ በአስፓልቱ ተራምዶ ወደ መኪናችን ይደርሳል አሁን ጥርጣሪዬ እውነት እየመሰለ ነው...እነ ሜርሲም የማየውን ነገር ሲያዩ የሆነ ነገር እንደተገለጠላቸው ያስታውቃሉ ወዲያው የመኪናው የፊት ጎማ ወዳረፈበት ተጠጋሁ ሲገባና ሲወጣ ይመስለኛል በዛ ያለ ዱካ ይታያል "ያ ሰው አሁንም እየተከታተለን ነው አልተወንም" አልኩኝ "ምነው እግራችንን በቆረጠው ባንመጣስ" አለች ባርሳ እጅግ ተበሳጭታ "አሁን ማማረሩን ትተን ከዚ አካባቢ የምንሄድበትን መንገድ እንፍጠር መዋከቡ ዋጋ ቢስ ነው" አለች ቅድስቴ የማልጠብቀውን የእርጋታ ስሜት እያሳየች "ልክ ብለሻል" በማለት ባባ በሀሳቧ ተስማማ "ትርፍ ጎማ አልያዝክም" ብዬ ባባን ጠየኩት በጭንቅላቱ ንቅናቄ አለመያዙን ነገሮኝ ቀጠል አርጎ "ጎሚስታ ቤት ነው ያለው ኔትወርክ እንኳን ቢኖር ብደውል ይልኩልኝ ነበር" አለ "እና ዛሬ እዚ ልናድር ነው" አለች ባርሳ በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን ገለፅኩላት ቢመራትም ትዋጠው ምንም ምርጫ የለንም እዚ ባናድር መልካም ነበር ግን አለማደር አንችልም...ሰዓቱ ተጉዞ ወደ አመሻሹ እየተቃረበ ነው ከመኪናው ውስጥ ምግብና አልባሳት ይዘን ወደ ሆስፒታሉ ውስጥ ተመለስን እኔ ከታከምኩበት ክፍል ፊት ለፊት ገባንና ማስተካከል ጀመርን እኔም ልብሴን ለመቀየር ወደ ሻንጣዬ ሄድኩኝ ለአይን ያዝ ያዝ ማረግ ጀምሯል ባባ መብራት ካለ ብሎ ሲሞክር ምንም የለም "መቆጣጠሪያው ጋ አይቼ ልምጣ" ብሎ ባባ ወጣ "ተጠንቀቅ አባቴ" አለች ባርሳ በስስት እያየችው ይሄን ጊዜ ቅድስቴ አይኗ እንባ አረገዘ የባሰ እንዳይከፋት ብዬ ምንም አላልኳትም እኔም ልብሴን ቀያይሬ ተቀመጥኩ ባባ ተሳካለት መሰለኝ መብራቱ በራ "የስ" አሉ ቅድስቴና ባርሳ እኔም ፈገግ አልኩኝ ወዲያውኑ ምግቡን አቀራረቡት ባባም መጣና ለመመገብ ተዘጋጀን በሩን ዘጋንና መመገባችንን ጀመርን አሁን ምሽቱ ጀምሯል ነፍሴ እየተጨነቀች ነው...እየተጨዋወትን መመገባችንን ቀጠልን ግን መብራቱ ጠፋ በጣም ደነገጥን ሁላችንም ፀጥ አልን የሆስፒታሉ አንዱ ክፍል በሃይል ጓ ተደርጎ ተዘጋ በጣም ደነገጥን ግን መብራቱ ወዲያውኑ መጣ ውጪ ያለውን ነገር ለመመልከት ሁላችንም ተነስተን በሩን ከፍተን ወጣን ግን አንዳች አልነበርም ወዲያውኑ ድጋሜ መብራቱ ጠፋ ግን ባሁኑ ብዙ አልቆየም ከመቅፅበት መጣ ደግሞም ጠፋ ድጋሜ ሲበራ ግን................
ይቀጥለል.........
“በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤”
— ኤፌሶን 1፥3 (አዲሱ መ.ት)
ብዙ ሰዎች በማህበረሰቡ ባለው አስተሳሰብ መሠረት በኑሯቸው የሆነ ነገረ ስሳካለቸው፣ ስቀናቸው፣ የሆነ የሚጠብቁት ነገር ቀኝ ስይዝላቸውና መልካም የሆነላቸው ስመስላቸው ተበርኬያለሁ ተበርኬያለሁ ተባርኬያለሁ... ይላሉ። በሕይወታቸውም መልካም እድል እንደገጠማቸው በመቁጠር ደስተኞች ይሆናሉ። [ግዜያዊ ውስን አላፊ መሆኑንም ባለማስተዋል ራሳቸውን ለተሰጡበት ነገር ይጥላሉ።]
ሐዋሪያው ጳውሎስ ግን በዚህኛው ክፍል ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆን ተብሎ ስለሚሰጠው ዘላለማዊ በረከት (መባረክ) ይነግረናል። ይሄኛው አይነት መባረክ ማህበረሰብ ወለድ አስተሳሰብ፥ በዚህች ጎስቋላ ምድር ስለምናግበሰብሰው ብልጽግና፥ ሰዎች በተለያዩ መንገድ ጥረው ግረው ስለሚያመጡትና ስኬት ብለው የሚጠሩት አይነት አይደለም፤ እንደ ቸርነቱ መጠን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለኃጢኡም ለጻድቁም ስለምሰጠውም በረከት አይነትም አይደለም። በሰማያዊ ስፍራ ስለመባረክ እንጅ።
ጸሐፍው በሰማያዊው ስፍራ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ስለምሆነው መንፈሳዊ በረከት ስነግረን የእኛን ምንምነትንና የባራክውን ገደብ የለሽ ስልጣን ጭምር ይነግረናል። በረከቶቹም [ኤፌሶን 1V4-14]፦ መመረጥ፥ መወሰን፥ ልጅ መሆን፥ ቤዛነት፥ የኃጢአት ስርየት፥ ጥበብ፥ ማስተዋል፥ በመንፈስ ቅዱስ መታተም ናቸው። እነዚህ ዘላለማዊና መንፈሳዊ በረከቶች እንደመሆናቸው በግዜ የማይገደቡ ኢወስንና የማያልፉ ናቸው።
አዎን! በመንፈሳዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ባርኮናል፤ ከዚህ በኋላም ልባርከን ያስቀረው በረከት የለም። እኛም ለመቀበል ያስተረፍነው ባታም የለም።
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
━━━━━━━━━━━━
➠ TITLE: "ለምን ከሳህ"
➠ GENRE: New Teaching
➠ Quality: 360pHD
➠ SIZE: 70.0 Mb
➠ TIME: 36:18
➠ CHANNEL @yekebere
━━━━━━━━━━
➠share link: t.me/yebirihan_lijoch
Watch "ፀሎቱ New Protestant Dirama by ARIEL literature team 2013 YHBC" on YouTube
https://youtu.be/6gER7MmXR-0
Watch "New_oromic_song_singer_Araru_Robe_2020_Adola l_woyu_Subscribe,share and lik our YouTube channel" on YouTube
https://youtu.be/Cn0W65AsbJ4
🚷የጠፋው ሬሳ🚷
📚ክፍል አስራ ሁለት
...በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች ነገር ሆነው እንደው ብዬም ተጨነኩኝ ባባ ይቁነጠነጣል ምን እንደሚያደርግ ፈፅሞ ግራ ገብቶታል ግን ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱም መጡ ባዩኝ ጊዜ በጣም ደነገጡ ባርሳም ወደኔ እየመጣች "ምንድነው ሜርሲ ምን ሆንሽብኝ" አለች ምንም መልስ አልሰጠሗትም ቅድስቴም እኔን አይታ "ከዚህ ቦታ አሁኑኑ ተነስተን መሄድ አለብን አንድ በአንድ ከማለቃችን በፊት" አለች ትዕዛዝ የሆነ ንግግር ቁጣም ቀላቅላበት "አሁን ተረጋጉ መጀመሪያ ሜርሲን ወደ ሀኪም ቤት እንውስዳት" አለ ባባ ድንኳኖቹን እየነቃቀለ እነ ባርሳም ሌሎች ዕቃ በማዘገጃጀት እያገዙት...ቅድሚያ እኔን ወደ መኪናው ወሰዱኝና እነሱ እየተመላለሱ ዕቃዎቹን ጫኑ ከደቂቃ በሗላ ጉዞ ጀመርን በተቀመጥኩበት የጋቢና መስኮት በኩል ፊቴን መስታወቱ ላይ ተደግፌ አይኔን ወደ ውጪ ልኬ ያንን ክፉ ጫካ እየተመለከትኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ እጅግ በጣም ሰፊ ቦታ የያዘ ውስጡ ጨለማ የሆነ ጫካ ነው ከዚ ስፍራ በሰላም መውጣታችን እጅግ ድንቅ ነው..."አይዞሽ የኔ ጓደኛ ምንም አትሆኚም" አለች ባርሳ በእጇ ትከሻዬን እየነካች እሺታዬን በአንገቴ ንቅናቄ ገለፅኩላት ጉዟችን ለረጅም ደቂቃዎች ፀጥታ የተሞላበት ነበር ሁላችንም የድንጋጤ ስሜት ላይ ስለሆንን ይመስለኛል ከግማሽ በላይ ለሆኑ ደቂቃዎች ጉዞ በሗላ አንድ የድሮ ሆስፒታል ተመለከትን ታፔላው እንኳን የለም ነበር በሽተኛም ሆነ ዶክተር በዙሪያው አይታይም ባዶ ነበር መኪናችንን ከመግቢያው ትየይዩ አድርገን አቆምናት "እዚሁ ጠብቁኝ" አለ ባባ ከመኪናው እየወረደ ውስጡ ገብቶ ያለውን ነገር ቃኝቶ መግባት እንደምንችል ነገረን እነ ባርሳ ቀድመው ወርደው በጥንቃቄ ከመኪናው አወረዱኝና መሸከም የሚለው ቃል በሚገልፀው ድጋፍ ደግፈውኝ ወደ ውስጥ ገባን ፍፁም ፀጥ ያለ ስፍራ እርገግጠኛ ነኝ ከኛ ሌላ በዚ ሆስፒታል ውስጥ የለም ባባ ከኛ በፊት እየተራመደ ወዴት መሄድ እንዳለብን እየመራን ነው ከጥቂት እርምጃ በሗላ ከአንድ ክፍል በር ላይ ቆመ ወደ ውስጥም እንድንገባ ምልክት ሰጠን ገባንም ወዲያው ክፍሉ ውስጥ ካለው አልጋ ላይ አስተኝተውኝ መድሀኒት መፈለጉን ተያያዙት በነገራችን ላይ ቅድስቴ የህክምና ተማሪ ነች "አይዞሽ ሁሉም ሰላም ይሆናል አለ ባባ ከዛም ቅድስቴ በደረቴ መተኛት እንዳለብኝ ነግራኝ ለሶስት ገለበጡኝ የጭንቅላት ቁስሌን ለማከም እንዲመቻት...ከዛም ቁስሉን ለመመልከት ፀጉሬን ስትገለጥ ቁስሌ ላይ ተጣብቆ ኖሮ እጅግ አመመኝ ግን ህመሙን ጨክኜ ያዝኩት ከዛም ፀጉሬን መቁረጥ ጀመረች ባርሳ ከፊት ለፊቴ ካለው ወንበር ላይ ሆና አይዞሽ እያለች ታበረታኛለች አሁን ቅድስት ቁስሉን ለመመልከት ግልፅ ሆነላት መሰል መሰፋት አለበት አለች በሰለለ ድምፅ ሆኜ "እንደዚ አይሆንም እንዳታደርጊው" አልኳት "የጭንቅላትሽን ክፍተት ቶሎ ካልሸፈነው ወደ ሌላ ኢንፌክሽን ሊቀየር ይችላል እዛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አሁን ላይ እንፍጠን" አለች ባርሳ ጭንቅላቷን በመነቅነቅ በቅድስቴ ሀሳብ መስማማቷን ገለጸች "ግን እርግጠኛ ነሽ ይሄን ማረግ ትችያለሽ?" አለ ባባ እርግጠኛ ለመሆን እየጠየቀ "በኔ ተማመን ምንም አይፈጠርም" አለች ባባም ተስማማ እኔም ውስጤን አሳመንኩትና ተዘጋጀሁ የዶክተሮቹን ጓንት አድረገችና በሆነ ፈፃሽ ቁስሌን ማጠብ ጀመረች በትንሹ የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል "አቃጠለሽ እንዴ" አለችኝ ቅድስቴ "በትንሹ" ብዬ መለስኩላት "ሰውነትሽ እየደነዘዘ ነው ማለት ነው" ብላ መለሰችልኝ "እንደዚም ቢሆን ግን ማደንዘዣ ያስፈልገናል" አለች ቅድስቴ በቁራጭ ወረቀት ላይ የሆነ ነገር ፅፋ "ይሄን መድሃኒት ፈልጉ" አለቻቸው እነ ባባን "ከየት" አለች ሜርሲ ግራ በመጋባት "ከክፍሎቹ አንዱ የመድሃኒት ማከማቻ መሆኑ አይቀርም ፈልጉና አምጡ" ብላ ትዕዛዝ ሰጠች እነሱም ተቀብለው አብረው ወጡ ከዛ ጫማዬን ፈትታ የእግሬን ቁስል መመልከት ጀመረች "የወጋሽ ነገር ብረትነት አለው" ብላ ጠየቀችኝ "እሾህ ነው መሰለኝ አላስተዋልኩትም" ብዬ መለስኩላት "ለማንኛውም ለጥንቃቄ ቲታነስ መወጋት አለብሽ" አለችኛና መድሃኒቷን ማዋሃድ ጀመረች "ከዚ ክፍል የጠፋ ወይም ህክምናውን ሳይጨርስ የወጣ ሰው አለ " አለችኝ በጣም ግራ ተጋብቼ "በምን አወቅሽ" ስላት የህክምና ካርዱ እና እዚ ያሉት መድሃኒቶች የሱ ናቸው" ብላ መለሰችልኝ "ስሟ ማን ይላል" ብዬ ጠየኳት እሷም እያነበበች ድንጋጤ በሚመስል መልኩ ግንባሯን አጨማደደች "ምነው" አልኳት...
................ይቀጥላል...............
Join us share
━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───