😔ግር ያላት ነብስ😔
ክፍል2⃣2⃣
ተመለስኩ ለሳሪ የሆነውን ሁሉ ነገርኳት ሳሪ የምትገርም ሰው ናት እንደ እናቴ እንጂ የእንጀራ እናቴ አትመስለኝም ትረዳኛለች ሳጠፋም ትቆጣኛለች ጥሩ እናት ና ልጅ ወጥቶናል እነ ማርኩን አስጠናቸዋለሁ አጫውታቸዋለው በትርፍ ጊዜአችን አባቢ እና ሳሪ እኔና እነ ማርኩ ጊቢ ውስጥ ኳስ እንጫወታለን በቃ ሰላም ያለው ቤተሰብ ሆነናል ። የገ ፍርድ ቤት ቀጠሮ አለን ማህሌት የሚሰጣትን ፍርድ ለማወቅ በጣም ጓግቻለሁ ።
ሳሪ ግን እንዳልጨነቅ ብላ ነገ ፍርድ ቤት አትሄጂም አለችኝ በዛ ላይ ብሔራዊ ፈተና ደርሷል ማጥናት ነው ያለብሽ ብላኛለች ሳሪን ማስቀየም ስለማልፈልግ ባልደሰትም ተቀብያታለሁ ጠዋት ቁርስ በልተን አባቢ ና ሳሪ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ እኔ እነማርኩን ማጫወቱን ተያይዤዋለሁ ከዛ ደግሞ ጥናቴን በጣም ቆይተው እነ ሳሪ መጡ ቡና አፍልቼ ምሳ ሰራርቼ ነበር የጠበኳቸው መን ተባለ ብዬ በጥያቄ አጣደፍኳቸው የተለያዩ ነገሮች ተነስተው ምስክሮች እንዲቀርቡ ተብለናል የስልኩን ማስረጃም የዛን እለት ነው ምናቀርበው አሉኝ ።
እሷስ አልኳቸው እሷማ አንድም ወንጀል እንዳልሰራች አይኗን በጨው አጥባ ስትከራከር ነበር አቤት እንባዋስ አለ የአዞ እንባማ መገለጫዋ ነው እኮ አልኩት ሁለቱም ፈገግ አሉ ምሳ በልተን ቡና አጠጥቻቸው ለማጥናት ወደ ክላሴ ለመግባት ተነሳው እንዴ ሩሀ ሳልነግርሽ ጓደኛሽም ፍርድ ቤት መጥታ ነበር ምን ናዙ አልኳቸው አዎን አሉኝ ለምስክርነት እንደምትቀርብም ተስማምታለች አሉኝ በጣም ደስ አለኝ ።
ሰሞኑን ከክላስ ወጥቼም ቶሎ ወደ ቤት አልመለስም ላይብረሪ ነው ማሳልፈው በነገራችን ላይ ጀሚላ ትምህርት አቁማለች ምክንያቱም የ6 ወር እርጉዝ ናት ይቅርታ ጠይቄአት ታርቀናል ቤተሰቦቿ ተደፍራ ሳይሆን በራሷ መስሎአቸው ከቤት አባረዋታል ሳሪ ደግሞ ነግሬአት እኛ ቤት እንድትገባ አባቢን ልታማክረው ወስናለች ለጊዜው ግን ቤት ተከራይተን እዛ ናት ሳሪ ምግብ እየሰራች ትወስድላታለች እኔም ሄጄ አብሪአት አሳልፋለሁ ዛሬ ከክላስ ወጥቼ ቀጥታ እሷ ጋር ነበር የሄድኩት እዛው ቡና አፍልቼላት ሳሪ ያመጣችላትን ምግብ አብረን በልተን ክርስቲያን መሆን እንደምትፈልግ ነገረችኝ ደስታዬን አትጠይቁኝ እዛው ፀለይኩላት አብረን ቸርች ሄድን ቀኑ አርብ ነበር እዛም አገልጋዮች ነበሩ ተፀለየላት በቅርቡ የደህንነት ትምህርት እንደምትጀምር ተነግሮን ወደ ቤት ሄድን ስንደርስ አባቢ እና ሳሪ አብረው ቁጭ ብለዋል ገና ስታየን እችሁት እንደውም እሷ ናት ጀሚላ አለችው ተዋወቃትና ተቀመጥን አባቢ እዚህ እንድትኖር መስማማቱን ነገሩን በጣም ደስ አለኝ ጌታን መቀበሏን ስነግራቸው ሁለቱም ተደሰቱ አባቢ የምታገለግልሽ ሞግዚት አመጣልሻለሁ አትሳቀቂ ቤትሽ ነው የምትፈልጊውን ሁሉ ጠይቂ አላት እንዴት ደስ ይላል የሚገርም ምሽት አሳልፈን ፀልየን ተኛን በጠዋት ሄጄ ልብሶቿን አመጣሁላት አሁን እሷም ደስተኛ ናት ሚሊ በጠዋት ደወለልኝ ሰላምታ ተለዋውጠን ዛሬ በጊዜ ነይ እነ ናዙ ቤት ሰርግ ስላለ በቲም ሄደን አንድ አንድ ስራ እናግዛቸዋለን አለኝ ምን የምን ሰርግ አልኩት እኔ እንጃ ወንድሟ ምናምን ሲባል ነው የሰማሁት ለማንኛውም በጊዜ ነይና አብረን እናያለን አለኝ ምን..... ልዑል ሊያገባ ነው ቀወጥኩት ሳሪ ልታረጋጋኝ ብትሞክር የማይሆን ተስፋ ነው የሰጠሽኝ መጀመሪያም እጮኛ ባትኖረው በዚህ በአጭር ጊዜ ሊያገባ አይችልም ብዬ አበድኩባት ጀምስም ሳሪም እንዴት ያረጋጉኝ ቀወጥኩት ተረጋጊ እሱ ላይሆን ይችላል ደግሞስ እግዚያብሔር ካልፈቀደ ምንም ማድረግ አይቻልም አሉኝ ምንም መረጋጋት አቃተኝ በአንዱ ሲሳካልኝ በአንዱ አዝናለሁ ሁሌ ለስቃይ የተፈጠርኩ ደግሞ እዛ ቤት ድርሽ አልልም አልኳቸው ለምን ጠንካራ ሴት መሆንሽን ማንም ያውቃል እንዴት በአንዴ ትሰበሪያለሽ ለአንቺ እልህም ከሆነ ተገኝተሽ ምንም እንዳልሆንሽ ማሳየት አለብሽ አሉኝ ምን አማራጭ አለኝ ሳሪ አሳምራ አዘጋጀችኝ ሆሆሆሆሆ ሙሽራ ሳልሆን ለስራ ነው ምሄደው ብያት ወደ ቸርች ሄድኩ አንድ ላይ ተሰባስበን ነው ወደ ነናዙ ቤት ምንሄደው ሁላችንም ተገኝተናል ወደ እነ ናዙ ቤት እየሄድን ነው.........
..............ይቀጥላል..............
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ 😔
ክፍል2⃣1⃣
....ስልኩ ጠራ አላነሳም ደጋግሜ ደወልኩ ሊያነሳ አልቻለም ልዑል በጣም ተቀየሞኛል ማለት ነው በጣም ከፋኝ ሳሪ በራሷ ስልክ እንድደውልለት ሰጠችኝ ትንሽ ቆይቼ ደወልኩ ወዲያው አነሳ ሄለው ልዑል አልኩት አቤት አለኝ ልዑሌ እንዳስቀየምኩህ አውቃለሁ ግን ላገኝህ እፈልጋለሁ አልኩት ለምንድነው ምታገኚኝ አለኝ እንድናወራ ፈልጋለሁ አልኩት እኔና አንቺ ምንም ምናወራው ጉዳይ የለም ብሎ ስልኩን ዘጋብኝ በጣም አዘንኩ ሳሪ አረጋግታኝ ተደብሬ ዋልኩ ለምን ለናዙ አትደውይም አለችኝ ተስማምተን ደወልኩላት ወዲያው አነሳች ናዙ ሰው ምን ይለኛል ባይ ናት ባትፈልግም ታወራኛለች ሀይ ናዙ አልኳት ሀይ አለችኝ ሰላም ነሽ አልኳት ይመስገን አለችኝ ናዙ ተቀይመሽኛል አይደል አልኳት ፀጥ አለች እሺ ላገኝሽ ፈልጋለሁ ስላት ምነው ችግር ገጠመሽ እንዴ አለችኝ ማለት አልኳት ያው አንቺ ሰውን በችግርሽ ጊዜ ብቻ ነው የምትፈልጊው አለችኝ በጣም ተናደድኩ አራሴው ስልኩን ዘጋሁት ሳራ ምነው ሩሀ እንዴት ትዘጊባታለሽ ብላ ተቆጣችኝ በቃ የመሰለኝን በሰአቱ ስላልኳት እንዴት እንዲህ ትለኛለች ደግሞ ትንሽ ነገር እንደሚያናድደኝ እያወቀች የባሰ ተናደድኩ በቃ ተረጋጊ ሁሉም ይቅር አለችኝ ።
ዛሬ ቅዳሜ ነው እንደተለመደው ቲማችን ሚሰበሰብበት ቀን ነው ተዘገጃጅቼ ሰአት ገና ስለነበር በእግሬ ወክ እያደረኩ አንድ ቦታ ትዝ አለኝ ልዑል የሆነ ቀን ወደ አንድ ቦታ ወስዶኝ ሲደብረው እና አልፎ አልፎ እንደሚያዘወትርበት የነገረኝ መናፈሻ ቢጤ አለ እዛ አይጠፋም ብዬ መገስገስ ጀመርኩ ትንሽ ውስጥ ለውስጥ ያስገባል እየሄድኩ በሞተር ሚሊዮንን አገኘሁት ሞተሩን አቁሞ እንዴ እዚህ ሰፈር ምን ትሰሪአለሽ አለኝ አይ እዚ ተንተባተብኩ እዚህ ሰፈር አክስቴ አለች አንተስ ምን ትሰራለህ አልኩት በጥርጣሬ አይን እያየኝ የብሩክቲ ቤት እዚጋ ነው አለ ብሩክቲ ማለት ፍቅረኛው ናት ነው ጥሩ ነው አልኩትና ለመሄድ አንድ እርምጃ ተራመድኩ አንቺ ግን እርግጠኛ ነሽ አክስት አለሽ እዚህ ሰፈር አለኝ አናደደኝ ምን አገባህ በአንተ ቤት የአንተን ፍቅረኛ ለማግኘት የመጣው መስሎህ ነዋ መች ስራ አጣሁ በዚህ ባህሪህ እንዴት እስከአሁን ልወድህ ችላለሁ አልኩት ከሆነ ጥሩ ነው አለኝ ጉረኛ ትቼው መንገዴን ቀጠልኩ ገና እየቀረብኩ ስመጣ የወንዙ አወራረድ ሰላም አለው አልፌ ከሚያማምሩት ተፈጥሮን ቁልጭ አርገው ከሚያሳዩት ልዑል ይቀመጥባቸው ከነበሩ ዲንጋዮች ላይ ተቀመጥኩ ንፋሱ የዛፎቹ ሽውታ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ሰዎች እንቅስቃሴ የወንዙ አወራረድ እንዴት ልግለፀው አቤት ግን የእግዚአብሔር ስራ እንዴት ይገርማል እነዚን ያማሩ ፍጥረቶች ያበጃጀህ አምላክ ስምህ ይባረክ እያልኩ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ፎቶ ማንሳት ለራሴም መነሳት ጀመርኩ እንደ ድንገት ከኋላዬ አንቺ አለኝ ሚሊ ሂድ ቆሌህ ይገፈፍ ምን ትሰራለህ አልኩት አንቺስ አክስቴ ምናምን ብለሽ ይሄን የመሰለ ቦታ ብቻሽን ትኮመኩሚያለሽ አለኝ እንሂድ አይባልም አቤት እንዴት አባቱ ያምራል እያለ ወገቡን ይዞ በአይኑ ይቃኝ ጀመር ከሩቅ ከንፁ ዲንጋይ ውስጥ ጥርት ያለ የምንጭ ውሀ ይፍለቀለቃል ወንዙ አወራረዱ አንተ ተከትለኸኝ ነው አልኩት እና በኔ ምክነያት እራሷን ብታጠፋስ ብዬ ጫካ ያለ መስሎኝ ነበር ምን ጫካ ገነት በይው አለኝ ደፋር እኮ ባንተ ምክኒያት ደረቅ አታፍርም አልኩት ምን ያሳፍረኛል ብሎ አጠገቤ ተቀመጠ አንቺ ግን ማን አሳይቶሽ ነው አለኝ ምን አገባህ አልኩት ድምፁ ሁሉ ቀፎኛል ጭራሽ በኔ ምክኒያት ይላል እያሰላሰልኩ ብሽቅ ብያለሁ በዚህ ቅፅበት ልዑል መጣ ገና እንዳየን ድርቅ ብሎ ቀረ ፊቱ ተቀያይሮ ለመመለስ ዞረ እየሮጥኩ ተከተልኩት መኪናውን ወደ ሚያቆምበት ነበር እየሄደ ያለው ልዑል በናትህ አዳምጠኝ አንተን ለማግኘት ነው እዚህ ድረስ የመጣሁት አልኩት ነው እንዴ ቆመና ትንሽ አታፍሪም ቢያንስ ቦታ አትቀይሩም አለኝ 😳😳 ልዑል በእውነት እንዳሰብከው አደለም ድንገት ተከትሎኝ ነው የመጣው ጌታን ብዬህ እንዴት ላስረዳህ አልኩት ይሄን የህፃናት ወሬሽን መስማት አልችልም አለኝ መኪናው ውስጥ ገብቶ እየለመንኩት ሄደ ሚሊ ከኋላዬ ቆሟል ምንድነው ሩሀ ተረጋጊ አለኝ ዞርበልልኝ በአንተ ጦስ ነው ይሄ ሁሉ ማን ተከተለኝ አለህ አልኩት ይቅርታ እኔ ይሄን መች አሰብኩ ሩሀ ወይ እኔ አስረዳዋለሁ በቃ ተረጋጊ አለኝ መጀመሪያ ለራስህ ተረዳ ብዬው መሄድ ጀመርኩ ተከትሎ አስቆመኝ ሩሀ ቸርች ሰአት አልፏል እልክሽን ትተሽ በሞተር እንሂድ ይሄን ሁሉ መንገድ እስከታክሲ ሊመሽብሽ ሁሉ ይችላል አለኝ አማራጭ ስላልነበረኝ አብረን እስከ ቸርች ሄድን ስንደርስ ጨርሰው እየወጡ ነው ሰላም አልናቸው እስከዳር ለካ ለሁለት በሞተር አለማቹን ስትቀጩ ነበር አለች ሁሉም ሳቁ ናዙ እያየኋት ተለዋውጣ ሄደች እቺ ልጅ እሷ ናት ወንድሟ ነው የወደደኝ ሆሆሆ ምን አማራጭ አለኝ የባሰ ነገሩን አበለሻሽቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩ..........
...............ይቀጥላል............
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ😔
ክፍል2⃣0⃣
.....እሺ አሁን እነሱ ቤት ልሂድ እኛ ቤት
ከራሴ ጋር ስከራከር ደረስን ሁላችንም ተሰነባብተን መለያየት ጀመርን ናዙ ሻንጣዋን ይዛ ወደ አንድ ታክሲ ገባች የዚህን ያክል ትቀየርብኛለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ግን ምን ሆና ይሁን ቢያንስ ምክነያቴን ለምን አትነግረኝም በምንድነው ራስ ወዳድ የሆንኩት እኔም ወደ ቤት ተመለስኩ እቤቱ ልክ ማሚ እንዳለች ጊዜ ሞቅ ሞቅ ብሏል በነገራችን ላይ የመንታ እህትና ወንድሜ ስም የሱ ማርኮን የሷ ማርካን ነው እንደስማቸው ይማርካሉ አባቢ ጋቢ ለብሶ ከነሱ ጋር እየተጫወተ ሳሎን ነበር ሳሪ ደግሞ ቡና እያፈላች በትንሹ አጠገቤ ነህ የሚለውን የተከስተን መዝሙር ከፍታ ቤቱን ሞቅ አድርጋዋለች ። ገና እንደገባሁ በፈገግታ ነበር የተቀበሉኝ ወንድምና እህቴም ጥምጥም አሉብኝ ቆይታዬን ጠይቀውኝ የሚጣፍጥ ምግብ በልቼ እየተጨዋወትን ነው የሳሪ ቡና አንደኛ ነው ። የነ ማርኪን እድሜ ጠየኩ 11 አመታቸው ነው ቆይ እንዴት ብዬ ታሪኩን ጠየኳቸው እናቴ ከኔ በኋላ እናቴ በደረሰባት አደጋ ማህፀኗ እንደተጎዳ እና መውለድ እንደማትችል ሲነገራት ሳራ የአባቴ ወንድም ቤት ተጠግታ ትኖር ነበር ልክ እኔ እነ ናዙ ቤት እንደገባሁ ከዛ ወንድ ልጅ የመውለድ ፍላጎት ስለነበራቸው እናቴ ሆን ብላ ከአባቴ ጋር አቀራረበቻቸው ካረገዘች በኋላ ልጁን ወስዶ እንደሚያባራት ድንገት የሰማችው ሳራ ከሀገሩ ለቃ ጠፋች ልጆቹ ተወልደው 2 አመት ሲሞላቸው በህይወት እንዳሉ ደብዳቤ እና ፎቶአቸውን ላከችለት እያደጉ በሄዱ ቁጥር ፎቶ ትልክለት ነበር ደግም ገና ወጣት ቆንጅዬ እኮ ናት ብቻዋን ተቸግራ ከአቅሟ በላይ ሲሆን አድራሻዋን ልካለት ሄዶ አይቷት በደንብ እንደተቀራረቡ ቤት ሰርቶላት ስራ አስጀምሯትም እንደነበረ ነገረኝ እሺ ማህሌትንስ አልኩት አሷማ የመጀመሪያ ሰሞን እንደ እናትሽ ስትንከባከብሽ ላንቺ ብዬ ሳልወዳት ነበር ሚስቴ ሁኚ ያልኳት እሷ ግን ንብረቴን በስሟ እንዳዞርላት ሁሌ ስትጨቀጭቀኝ ብሞት 3ቱ ልጆቼ ምን ላይ ይወድቃሉ ብዬ የሀሰት ወረቀት አሰርቼ አዙሬልሻለሁ አልኳት ከዛ የእውነት ያዞርኩ መስሏት እገልሀለው ከቤቴ ውጣ ልጅህን ልገላት ነበር ሚስትህን የገደልኳት እኔ ነኝ ይሄን ሁሉ ሰክራ ቀባጠረች ሙሉውን በስልኬ ቀዳሁት ልትገለኝ ሽጉጥ ስታወጣ ንብረቱን እንዳላዞርኩ ስነግራት ምን አማራጭ አላት በመዳኒት አሳስራ አስቀምጣኝ ልታስፈርመኝ ብዙ ሞከረች ግደይኝ እንጂ መቼም አላዞርልሽም ብያት በዛቻ እያለች አንቺ ደረስሽልኝ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ በጣም አለቀስኩ ሳራ እንደምንም አረጋጋችኝኟ አሁን እኮ አልፏል እኔም ያለ እድሜዬ እነዚህን ልጆች ሳሳድግ መከራና ስቃይ ደርሶብኝ እናትና አባትሽን እየረገምኩ ነው የኖርኩት እነሱ ወንድ ልጅ ለማግኘት ብለው ከትምህርቴ ከህልሜ አሰናከሉኝ ግን ዛሬ በይቅርታ ከአባትሽ ጋር እየኖርኩ ነው እሷም ፍርዷን ታገኛለች አባትሽ እንደነገረኝ መውለድ አትችልም በርግጥ እንዲ መሆኗ አያስደስትም ገን ስራዋ ይከፍላታል ብላ አፅናናችኝ ትንሽ አረፍኩ ማስረጃም ስላለን ይፈረድባታል ተረጋጊ ብላ የተከስተን መዝሙር እየደጋገመች ውስጤን ሰላም ሞላችው ።
ከሁን ቤታችን ሰላም ሰፈነ ማታ ማታ ፀሎት አስጀመረችን አባቴም ወደ መንፈሳዊነት እየተመለሰ ነው እነ ማርኩ የሚያካፍሉን ቃል የሚገራርም እራሴን ታዘብኩ ያስመልካሉ ቤታችን ቸርች በሉት ልክ እንደ በፊት ክርስቲያን ጎረቤቶቻችን ይመጣሉ አብረን እንፀልያለን እኛ ቤት ያሳልፋሉ ከአባቴ ሸሽተው የነበሩ ወንድሞቹ ዘመዶቹ እንደ ድሮው መምጣት እኛ ጋር መሰነባበት ጀምረዋል። የናፈቀኝ የቤታችን ሰላም ተመለሰ ግን ናዙ ልዑል እነ አባባ ንግስቴ በጣም ናፍቀውኛል ትምህርት ቤት እንደ በፊት በቻዬን በታክሲ መሄድ ጀምሬአለሁ እነ ሚሊን እዛው አገኛቸዋለሁ ወሬው ሰላምታው ሁሉ ስለ ፍቅረኛው ሆኗል በተለይ እኔ ካለሁ ስለሷ እንጂ አይወራም ሰሞኑን የነናዙ ናፍቆት ሊገለኝ ነው ትካዜ አብዝቻለሁ ሳራ የሰሞኑን መከፋቴን አይታ ጠየቀችኝ ሁሉንም ነገርኳት የምናሳልፈውን ስለ ሚሊም ስለነ ናዙም ከልዑል ጋር ስለ ነበረን ቀረቤታም ነገርኳት ግን ያለጥፋቴ ዘጉኝ አልኳት አፅናንታኝ ትንሽ አሰበችና ግን እኮ አስቀይመሻቸዋል አለችኝ እንዴት አልኳት እንደነገርሽኝጰከሆነ ልዑል ይወድሻል ምን ደነገጥኩ እሱ እንዲ እየሆነልሽ እየተንከባከበሽ አንቺ የማይፈልግሽ ሚሊ ስር ስር ትያለሽ ማገናዘብ ጀመርኩ እሷ ታወራለች እኔ ስላለሁ እና መሄድሽ አስጨንቆት በማታ ክፍላቹ አንኳኩቶ መጣ ናዙም እንደነገርሽኝ ከሆነ ስራዋ አብራቹ እንድትሆኑ ትፈልጋለች ፍቅራቹ ጨመረ ስትልሽ ወንድሜ አደል ሰትይ ከፋቸው እሷ መልሳ ስለ ሚሊ ስትጠይቅሽ ተንሰፈሰፍሽ እሱ online ሲገባ ፕሮፋይልሽ ሚሊ ነው ከዚ በላይ በምን ታስከፊያቸው ጭራሽ ናዙን ያላሰቡትን ሰለቸኋቹ አሁን እህትና ወንድሜም ስለመጡ ወደ ቤት እመለሳለሁ አልሻት ታዲያ በችግርሽ ሰአት እነሱ ቤት ከርመሽ አሁን ሰላም ሲሆን በኩራት ወደ ቤት እመለሳለሁ ስትያት ልጅቷስ ምን ታድርግ በጣም አስቀይመሻቸዋል ።
ወይ ሚሊዯን ጭንቅላቴን ደፍኖት አይኔን አውሮት በየት በኩል ይሄን ላስተውል ልዑል እኮ እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም አልኳት ድሮ እንዴት ይነግርሻል ሴት መቅረብ ይፈራል እያልሽ እንዴት ይሄማ ይከብደዋል በይ ደውይለት ና ተገናኝታችሁ አውሩ አለችኝ ግን ፈራለሁ ምን ልበለው አልኳት አሁን ላወራህ ፈልጋለሁ ብቻ በይው ከተስማማ ስትገናኙ ምትይውን እኔ እነግርሻለሁ አለችኝ ተስማምተን ደወልን ስልኩ ጠራ..........
..........ይቀጥላል...........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ😔
-------------""""""""""""""""--------------
ክፍል 1⃣8⃣
ማመን አልቻልኩም እንዴት መጠርጠር አቃተኝ የዚህችን አውሬ ስራ ነይ ተንበርከኪ አማራጭ አልነበረኝም ያለምንም ርህራሄ እንደምትገለኝ አውቃለሁ ሞትን ፈርቼ አደለም ለአባቴ መኖር ግን እፈልጋሁ ተንበረኩላት እስከዛሬ የታገስኩሽ በትንሹም ስላዘንኩልሽ ነበር አያያዟ እንዴት እንደሚያስፈራ በሰው ላስገድልሽ የነበረውም እራሴ ማድረግ ስላቃተኝ ሳይሆን አንቺ ስለሆንሽ ነበር ከእምባ ውጪ ምንም መናገር አልቻልኩም የጀመርኩትን ሳልጨርስ እንደምትሸኘኝ አውቃለሁ ደግሞ ለፍልፌ ጣጣዬ ለናዙ ቢደርሳትስ ስሚ እናትሽም ስላሳዘነችኝ በወሬ ላለያያቸው ሞከርኩ ግን እሷ በተቀናበረ ፎቶ እንኳን አሳይቻት አያደርገውም ትለኝ ነበረሸ ሰምታኝ ቢለያዩ አንቺም እናት አታጪም ነበር ግን አልሰማ ስላለች በመርዝ ደፋዋት ምን አንቺ አውሬ እናቴን የገደልሻት አንቺ ነሽ እንደ አብድ አረገን አው ጠረጥር ነበር ስሄድ ጤነኛ የነበረችው ከቸርች ስመለስ ድንኳን አጋጠመኝ አንድ ቀን እንደምደርስበት አውቅ ነበር አልኳት እንባዬ አየወረደ ናዙም አብራኝ ታለቅስ ነበር ሳቀች ይሄን የጠንቋይ ሳቋን ምን ልታመጪ ከ5 ደቂቃ አታልፊም እኮ በሉ በሉ መልክት አላቹ የምነግርላቹ ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ ንሰሀ ምናምንም ግቡ እንደ ጥላ ትዞረናለች ከማን ልጀምር ከሷ ከሳሳቋ ሊያስመልስ ይደርሳል እኔማ ለምጄው ብሔራዊ መዝሙር ነው ሚመሰለኝ ናዙ ላይ ደቀነችባት ናዙ እየተንቀጠቀጠች ነው ከኔ ጀምሪ እሷን ተያት አልኳት የኔ ደፋር ጥሩ ብላ ግንባሬ ላይ ደቀነችው ናዙ የሆነ ነገር እያረገች ነው ማህሌት ወደ እኔ ወደ ጎን ዞራ ጀርባዋን ሰጥታታለች ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ናዙ እባክሽ አትግደይን እባክሽ እዘኚልን መኖር እንፈልጋለን ብላ ለመነቻት ናዙ እየጮኸች ነው ሰው እየለመነ ይጮሀል የእልህ ልመና ቆይ ገንዘብ ንብረት ነው ምትፈልጊው አው ይሄን ቤት በጣም እፈልገዋለሁ አለች በኩራት እኔ ተጠልቼ ተገፍቼ ጎዳና ነው የደኩት ፍቅር ምናምን ሚባል ነገር አላውቅም ያኔ እናትሽ ከትምህርት ቤት ስትመለስ በአለባበሴና በመቆሸሼ ትሳለቅብኝ ነበር ተምራ ምታመጣውን በሙሉ ለራሴ እንደማደረገው ያኔ ነው የወሰንኩት ግድግዳ ተደግፋ ያልተጠየቀችውን ትቀባጥር ጀመር ግን አሁን አልምራቹም ብላ ወደ ሰይጣንነቷ ተመለሰች አምጥታ ሽጉጡን ግንባሬ ላይ አረገችው ጌታ ሆይ በደል ሀጢያቴን ስለኔ በፈሰሰው በልጅህ ደም ይቅር በለኝ አልኩ በልቤ በዛው ቅፅበት እጅ ወደላይ የሚል ድምፅ ተሰማኝ የጨፈነውን አይኔን ስከፍት ሽጉጡን አዞረችው 4ፖሊስ ልዑልና ጓደኛው ነበሪ መሳሪያውን ጣይው ተባለች ያሁሉ ሞገስ ጠፍቶ ኩምሽሽ ብላ መሬት አደረገችው አቤት የኔ ጌታ ከሞት አተረፈኝ እኔና ናዙ ከ1ሰአት በላይ ከተንበረከክንበት ተነስተን ልዑል ላይ ተጠመጠምን እሷን በካቴና ሁለት እጇን ጠፈሩአት ናዙ ሙሉ ንግግራን በስልኳ ቀድታዋለች ለልዑል መኪና ብቻ ይዞ እንዲመጣ ቀድመን ደውለን ነበር ናዙ ሳታስነቃ ደውላ እባክሽ አትግደይን ብላ ቅድም የጮኸችው ልዑል እንዲሰማ ነበር እንደ እኔ እልህ ቢሆን ሞቼ ነበር መቼም ምትያዝ ማይመስላት ማህሌት እየተሸማቀቀች ተይዛ ሄደች ።
ተሯሩጠን አባቴን ሆስፒታል ወሰድነው በምግብ እንደተጎዳ እና ምንም ፈሳሽ በውስጡ እንደሌለ ነገሩን በጉሉኮስ ትንሽ ነብሱ እየተመለሰ ነው ።
ፖሊስ ጣቢያ ሄደን ክስ መሰረትንባት ከ3ሳምንት በኋላ ፍርድ ቤት ቀጠሮ አለን አሁን አባቴ በደንብ አገግሟል ።
ደውሎ አይቻቸው የማላውቀውን 1ወጣት ሴት እና ሁለት መንታ ልጆች አስመጣ እያለቀሰ ይቅርታ ጠየቀኝ ልጆቹ እንደሆኑ አሷ እናታቸው ናት አለኝ በጣም ደስ አለኝ መንታ ወንድምና እህት አገኘው እሷንም ተዋውቄአት ሳራ ትባላለች በጣም ወጣት ናት ደግሞ ስታምር አባዬ አልተቻለም እሷ ስለመጣች ናዙ ቤት እንሂድ ብላ ጨቀጨቀችኝ ተስማምተን ሄድን ልክ በሩን ከፍተን ስንገባ የማየውን ማመን አልቻልኩም........
...........ይቀጥላል...........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ😔
-----------""""""""""""""-----------
ክፍል 1⃣6⃣
......ገባሁ ናዙ ሁሌ እንደምታዘወትረው በረንዳው ላይ ናት አንደኛ መናደዴ ሁለተኛ ልዑል አለመኖሩ አስገርሟት ሩሀ ምነው አለችኝ ምንም ብዬ ቆምኩ ተናደሻል እኮ አለችኝ አይ ዝም ብዬ ነው ብዬ ንዴቴን ለመደበቅ ፈገግ አልኩ ልዑልስ አለችኝ ምን አውቃለሁ አልኳት ምን እንዲ እንደሚያደርገኝ አላውቅም ከማን ጋር መጣሽ አለችኝ ከነሱ ጋር አልኳት ግራ በመጋባት እነማ አለችኝ ልዑልና ልጅቷ ብታያት እንዴት እንዴት እንደሚያረጋት አልኳት ቆይ ቆይ ልዑል በር ላይ አውርዶሽ ከሌላ ሴት ጋር ተመለሰ አለችኝ እንዴ እሷ ደግሞ ምን አናደዳት አዎን አልኳት ምን እኮ ልዑል አዎን በቃ በቀደም የነገረን ትሆናለች ደብሮኛል እንግባ አልኳት ቆይ ቆይ የጀሚላስ ነገር አለችኝ እየነገርኳት ገብተን መክሰስ በልተን ሳሎን ከነ አባባ ጋር ተቀምጠናል ልዑል ያለመደበትን አምሽቶ መጣ ሁሉንም ሰላም ብሎ ተቀመጠ ንግስቴ ምነው ልጄ እንዲ ምታመሸው አለችው ለስብሰባው ከመጡት እንግዶች ጋር ነበርኩ አለ እኔና ናዙ ወዲያው ተያየን ግራ ገብቶት እሱም አየን ናዙ ምን እንዳናደዳት ተነሺ እንተኛ ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች እኔም ስልኬን ከቻርጅ ነቅዬ ተከተልኳት ልዑል ተከትሎኝ መጣ ሩሀ ብሎ አስቆመኝ ይኸውልሽ ቅድም ካየሻት ልጅ ጋር ምንም የለንም ሀገሩን አስጎብኘኝ ብላ ደረቀች እንዳየሻት ፈጣጣ ናት እምቢ ማለት ከብዶኝ ነው ምን አገባኝ አልኩት ደና እደር ብዬው ሄድኩ እንደገባሁ ናዙዬ ምኑም አደለችም ብዬ ተጠመጠምኩባት እሷም ደስ ብሏት በምን አወቅሽ አለችኝ እራሱ ነገረኝ አልኳት ቆይ ምን እንዲ ያረገኛል እራሴን ታዘብኩት ናዙስ ምን ትለኛለች በቃ እንተኛ ተባብለን ፀልየን ተኛን .....
..........ይቀጥላል ..........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
ነገሩ ድሮ ነዉ...ሁለት የግሪክ ሰዎች ደሴት ላይ መኖርን አጥብቀዉ ይመኙ ነበር፡፡
የሆነ ደሴት ላይ ጠንካራ ሰዉ ሆነዉ ህይወታዉን በራሳቸዉ መምራት የሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ህልም ነበር፡፡ ሁለቱም አዲስ ደሴት በማግኘታቸዉ እቃቸዉን ይዘዉ ወደደሴቱ ሄዱ፡፡
አንደኛዉ ሰዉ ትንሽ ጊደር ይዞ ወደ አዲሱ ደሴት ተቀላቀለ፡፡
ከዛ መኖር ተጀመረ፡፡ ጊደር የሌለዉ ያለዉን “ግን አንተ ምን ሊሰራልህ ነዉ የቤት እንስሳ እዚህ ይዘህ የመጣኸዉ” ይለዋል፡፡ ባለጊደሩ ስፖርት ሲሰራ ጊደሩን እየተሸከመ ነበር...
ጊደር ተሸክሞ ይሮጣል፡ ይዘላል፡ ብቻ የማይሰራዉ ስፖርት አልነበረም! ጊደሯ እያደገች ሄደች
ሰዉየዉ ግን እሷን ተሸክሞ ስፖርቱን እየሰራ ነበር፡፡ ከአመት በኋላ ጊደሯ ትልቅ መሆኗን ያየዉ ሌላኛዉ ሰዉ ሊያነሳት ቢሞክር አልቻለም
ይሞክራል ወድቃል...በቃ አልቻለም፡፡ ባለጊደሩ ግን ችሎታዉን ወደላይ ጨመረዉ!
ትላንት ያለሳደግነዉንና የናቅነዉን ስራ ዛሬ የበይ ተመልካች ሆነን ከመቅረት በስተቀር ምንም አይጠቅመንም፡፡
“ወይኔ! ይሄኮ ገና ከገጠር ሲመጣ አዉቀዋለሁ! አሁን ከተማዉን ተቆጣጠረዉ!” ብሎ ታሪክ መዘከር እራስን ማድከም ነዉ፡፡
ትላንት ሳንንቅ ያሳደግነዉን 'የተጣለ ቢዝነስ' ዛሬ ትልቅ ካምፓኒ ብናደርገዉ አድናቂዎቻችን የትየለሌ ናቸዉ፡፡ ትላንት ግን አልነበሩም ወይም ዳር ላይ ሆነዉ እንቆቅልሽ እየተጫወቱ ይሆናል!
ቁም ነገሩ አንድ ነዉ፡ ትንሽ የምንለዉን ስራ እንስራ፣ እናሳድገዉ
በተረፈ የተለመደ 'አበሻዊ ወሬ' ሲመጣ ‘ጆሮ ዳባ ልበስ...አልሰማህም!’ ብለን መኖር!
------- @yebirihan_lijoch ------
------- @yebirihan_lijoch -------
.
#ጨረቃና_ጸሃይ_አይወዳደሩም!
የራስህን ሕይወት በፍፁም ከማንም ጋር አታወዳድር። ምክንያቱም ብሎ የሚያስቀምጥል ነገር እራስህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆንክ #ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ #ቅናት ነው የሚሆነው። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው ። ጨረቃና ጸሃይ አይወዳደሩም ሁለቱም በጊዜያቸው ደምቀው ያበራሉ ።
🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾
------ @yebirihan_lijoch ------
------ @yebirihan_lijoch ------
ለጥያቄና አስቸያየት @KTCOJ
#ተብሎ_ቢሰበክ
ዘፍጥረት ላይ እንደምናውቀው
ዮሐንስ ኢየሱስን እንዳጠመቀው
ኢዮብ ባለትዕግስቱ እንዳየ መከራ
ሙሴ ፅፎልናል ዘፀአት ላይ በተራ
ኤልሳ ወደ ላይ በሰረገላ ተነጥቆ
እጥፍ ቅባት ገባ በኤልያስ ውስጥ ዘልቆ
ባለራዕዩ ዮሴፍ ታልፎ ሲሰጥ
ይሁዳ ነበር እርሱን የሚሸጥ
አቤል ቃየልን በቅናት ተነሳስቶ
ጨፍጭፎ ገደለው በስለቱ ወግቶ
ጠቢቡ ሰለሞን ፍርድ ሲሰጥ አርቅቆ
ከፍሎ ሰጣቸው ልጁን አሰንጥቆ
ከሃዲው ዮሐንስ ኢየሱስ እንዳለው
ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ነው የካደው
ተብሎ ቢሰበክ በአሁኑ መሰረት
አሜን ሚል እንጂ ሚል የለም ስህተት
------==================------
| መፅሐፍ ቅዱስን አንብቡ |
------==================-------
#ገጣሚ_ቃባታ(KB)
👇👇👇JOIN IT👇👇👇
@yebirihan_lijoch
👇👇ሌላ ግጥም ከፈለጉ👇👇
✍ #ለስፍራ
******************
ጫማ ለመግዛት፤ መስዋዕት ያደረገ እግሩን ቆርጦ
ለአይኑ ውበት መነፅር ሸምቶ ፤አይኑን ግን ሽጦ
በሌለ እግር የእግር ጫማ ምን ረብ አለው?
በሌለ አይን የአይን ማስዋቢያ መነፅር ጥቅሙ ምንድነው?
.......................አይታየኝም ፋይዳው?
ዋጋ የከፈለበት ጥቅሙን ሳያውቀው፤
ለትርፍ እየሰራ ዋና ግን የሌለው፤
ያስደሰተ መስሎት እጅግ አሳዝኖት፤
ለነገው እየሰራ ነገውን ግን እረስቶት፤
እንዲሁ ሚባክን እየሰራ መስሎት።
እየሰራ ግን ሳይሰራ የሚኖር ብዙ ነው
ለስፍረው የሚሆነውን ለመግዛት ስፍራውን ሚሸጠው
እንዲሁ ሲባክኝ......ሲባክን.... ሚኖረው::
ስፍራ እያለው በሌለው ስፍራ፤ ስፍራ ላይ ተቀምጦ ስፍራውን የረሳ
የስፍራ ምርጫ በሌለበት፤ ኋላ ስፍራ አቶ እንዳይረሳ
ምናልባት ካስተዋለ ፤ካሸለበበት እንቀስቅሰው ሳይረፍድ አንዲነሳ
✍kabata (KB)
🎸🎸🎸🎸JESUS🎸🎸🎸🎸
.
✝✝ #ተፈፀመ ✝✝
እንድኖር ከህግ በላይ ህይወትን ሰቶኝ
መስቀል ላይ አምጦ በፀጋው አፈራኝ
የእዳ ፅፈቴን ደምስሶ
ስጋውን ስለህይወቴ ቆርሶ
ደሙን ስለእኔ አፍስሶ
እንካችሁ ብሎ ስለእኔው ሃጥአት እኔን አጉርሶ
ከጌተሰማኒ ጎልጎታ መስቀል ተሸከመ
'ህ' ብሎ መስቀል ላይ እያዘገመ
ሞቴን ሞቶ ገደለው ብሎ ተ.ፈ.ፀ.መ።
✍ ቃባታ(KB)
.
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
✍ ማነው የገደለህ?
**************
ከአባትህ እቅፍ ፣ የወጣህ ከጉያው
ልጁ በመሆንህ ፣ ያላነስክ እኩያው
በእግዚአብሔር ዘንዳ ፣ እግዚአብሔር የነበርክ
ያልነበረን አለም ፣ በ"ይሁን" የፈጠርክ
የማይታይ አምላክ ፣ ምሳሌ የሆንከው
ሁሉንም በስልጣን ፣ ቃልህ የደገፍከው
ለስጋ ለባሹ ፣ ስጋ ሆነህ መጣህ
ማንነቱን ላጣው ፣ ማንነትህን አጣህ
ራስህን ባዶ አ'ርገህ ፣ የባርያን መልክ ይዘህ
በደዌ ለመድቀቅ ፣ ለመስቀል ሞት ታዘህ
ሞቶ የተለየህ ፣ ሞቶ ቀሪ እንዳይሆን
ልትፈልገው ወደህ ፣ ለሰው ሰው ስትሆን
አለምን ለማዳን ፣ በእንጨት የሰቀለህ
አባትህ ነው እንጂ ፣ አንተን ማን ገደለህ
ወደህ ሞተህ እንጂ ፣ የቱ ጀግና ገ'ሎህ
እንኳንስ ሊይዝህ ፣ ማን ሊጠጋ ደፍሮህ
ከኃጢአተኛው ጋር ፣ ሆነና ጉዳይህ
የበዳይ ፍቅር ነው ፣ መስቀል ላይ ገዳይህ
የሰው ሞት ሆነና ፣ ለሞት የደገሰህ
ሞት የማይዝህን ፣ ሟች ወታደር ያዘህ
ትወደኛለህ!!
#ሄኖክ_አሸብር
. ፀጋው በለጠ
ዘማሪ ዮሐንስ በላይ
New Amazing Live Worship
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
✅ @yebirihan_lijoch ✅
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Watch "ፀሎቱ New Protestant Dirama by ARIEL literature team 2013 YHBC" on YouTube
https://youtu.be/6gER7MmXR-0
"ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም፤ ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም፤ ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም፤ ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም፤ እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም። #ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ፡፡"
.
[[ ☞ ዶ/ር ምህረት ደበበ ]]
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉት ሌላ ፕሮግራሞች ካሉ #comment ላይ ያስቀምጡልን። #ከልቦለዱ ጎን ለጎን የምናስኬደውን programe
Читать полностью…ይህንን ምስል በsocial ሚድያችን ላይ profile picture በማድረግ የኢየሱስ ዳግም መምጣትን እንስበክ። እንዲሁም ለወዳጆቻችን #share በማድረግ እናጋራ።
#ኢየሱስ_ይመጣል
#ኢየሱስ_ይመጣል
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
😔ግር ያላት ነብስ😔
_'""""""""""""""""______
ክፍል 19
......የማየውን ማመን አልቻልኩም ሙሉ የቲማችን ልጆች ሰርፕራይዝ ብለው ጮኹብኝ የነናዙ ቤት በጣም ተውቧል ለካ ዛሬ ልደቴ ነው 20 አመት ሞላኝ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ልዑል አረጋግቶ የልደት ኮፍያ አደረገልኝ ደስታም ሀዘንም ይሰማኛል እንባ ተናነቀኝ እማ ባለመኖሯ እነ ልዑልን ናዙን ሁሉንም ጓደኞቼን ስለሰጠኝ ደግሞ ደስ አለኝ ብቻ ደስ በሚል ሁኔታ ልደቴ ተከበረልኝ ሁሉንም አመሠገንኳቸው አርት ቲማችን ነገ ለአገልግሎት መንገድ ልንሄድ ነው ሁሉም ወደ የቤቱ ሄደ ናዙዬን አመሠግናለሁ በጣም አልኳት እኔን አታመስግኚኝ ልዑል ባለቀ ሰአት ደውሎ ይዘሻት ነይ ነው ያለኝ የሱ ሀሳብ ነው ብላ ፈገግ አለች ልዑሌ በጣም አመሠግናለሁ አልኩት ምንም አደል ሩሀዬ አለኝ ግን እንዴት አወክ ቀኑን አልኩት የሆነ ቀን እንደ ቀልድ ጠይቄሽ ነግረሽኝ ነበር በቁም ነገር ያዝከው ይገርማል እናንተ ልጆች የንግስቴ ድምፅ ነው ናዙ እነ ማሚ መጡ ብላ ወጣች እንደ ገቡ ሰላም ብለናቸው ተቀመጥን ልጄ እንኳን ለ20 አመት አበቃሽ አለኝ አባባ አሜን አልኩት ንግስቴም ቀሪ ዘመንሽ ይባረክ ብላ መረቀችኝ እንዲሁ ስንጨዋወት አምሽተን እኔና ናዙ ነገ መንገደኛ ስለሆንን እንተኛ ተባብለን ገባን ሻንጣችንን ማዘጋጀት ጀመርን ስለ ልደቴ ሁኔታ እያወራን እየተሳሳቅን የክፍላችን በር ተንኳኳ በሩን ከፈትኩት ልዑል ነበር ምነው ልዑሌ አልኩት ቻው ሳትይኝ ልትሄጂ ነው እንዴ አለኝ ኸረ አልነበረም ምነው ግን ባልልህስ አልኩት የሚለውን ለመስማት አይ ምንም ብሎኝ ለመሄድ አንድ እርምጃ ተራመደ እንዴ ልዑል ብዬ እጁን ይዤ አስቆምኩት ምነው በቀረብኝ ለምን እንዳስቆምኩትም አላውቅም ወይ አዳዬ ዝም ተባባልን ወዲያው ናዙ መታ ገላገለችኝ እናንተ ምን እየተንሾካሾካቹ ነው ሰሞኑንማ ፍቅራቹ ጨምሯል አለች እሰይ አይ ናዙ እንዴ ከአባቴ ልጅ በፊት ያገኘውት ምርጥ ወንድሜ አደል እንዴት አይጨምርም አልኳት ናዙ እያየዋት ፊቷ አዘነ እሺ ደና እደሩ ብሎ አቀርቅሮ እርሱም ወደ ክላሱ ገባ ልጆቹ ምን ሆኑ ናዙ የጀመርነውን ልብስ መክተት ትታ ተጠቅልላ ተኛች ናዙዬ ምን ሆንሽ አልኳት ዝም አለችኝ ነገሩ ግር እንዳለኝ ገባት መሰለኝ ቆይ ሚሊን አሁንም ትወጂዋለሽ አለችኝ በቃ የሚሊ ስም ሲጠራ ፈገግታ በፈገግታ ነው ምሆነው አዎ ናዙ ምን አለሽ አውታቹ ነበር እእእእ እንደ ጅል ሆንኩባት ተመልሳ ተኛች ደግሞ እኮ አላፍርም የቴሌግራም ፕሮፋይሌ የሚሊ ፎቶ ነው እዲሁ ጋደም ብዬ መጠቀም ጀመርኩ ልዑል online ላይ ነበር እንቅልፍ የለም እንዴ ብዬ ፈገግ ያለች ስቲከር ላኩለት ወዲያው ወጣ ልጆቹ ሰለቸዋቸው እንዴ ምን ሆኑ ግራ ገብቶኝ ተኛው ስነቃ ናዙ ለባብሳ ሻንጣዋን ጨርሳ ተዘገጃጅታ ጨርሳለች አይኔን እያሻሸው ናዙ ምን አለ ብትቀሰቅሺኝ አልኳት ይልቅ ቶሎ በይ ብላኝ ወጣች ፊቴን ታጥቤ ለባብሼ ወጣሁ ናዙ የራሷን ሻንጣ ብቻ ይዛለች እኔም እየጎተትኩ የራሴን ይዤ ወጣሁ ንግስቴ ቁርስ ቢ እንጂ የኔ ልጅ አለችኝ አይ በቃኝ ግን ልዑልስ አልኳት እሱማ ጠዋት ገና ከመንጋቱ ነው የወጣው አለችኝ ውጪ የቲማችን ልጆች በሙሉ በመኪና እየጠበቁን ነው ሁለቱንም ተሰናብቼ መርቀውኝ ወጣሁ ናዙ ቀድማኝ ትሄዳለች ናዙ አስቆምኳት ምነው ምን አድርጌሽ ነው አልኳት ምንም አለችኝ ናዙ እንደምሰለቻቹ አውቃለሁ የእናት ልጅ ከሚሸከመው በላይ ተሸክማቹኛል ግን አሁን አባቴም ስለተሻለው ሳራም ወንድምና እህቶቼም ስለመጡ ወደ ቤት እመለሳለሁ በእውነት አላስቸግራቹም እንድሄድ መናገር ከከበዳቹ እረዳቹአለሁ አልኳት ናዙ እያየኋት ፊቷ ቲማቲም መሰለ በጣም ራስ ወዳድ ነሽ ብላ ጥላኝ ወደ መኪናው ገባች ሁሉም እየዘመሩ እየጮሁ መኪናውን በአንድ እግሩ አቆሙት ገባሁ ሚሊ አጠገብ ማንም አልነበረም አጠገቡ ተቀመጥኩ እዙ መምጣቴንም አላስተዋለም ግራ እንደገባኝ ነው ለልዑልም ለናዙ ያልኳትን በሙሉ text አደረኩለት ምንም አልመለሰም እኛም ደረስን የምንቆየው ለ3ቀነ ነው ምሳ በልተን ተዝናንተን ሁላችንም ወደ ሩማችን ሄድን ናዙ እንኳን ልታናግረኝ ልታየኝ ፈቃደኛ አደለችም እስከዳር ሰው እኮ ናቸው ሰልችተውሽ ነው ማን እንደ እናት ላ አባባሰችብኝ መረረኝ እንደ ህፃን ሁሉ ነገር ያስለቅሰኛል ሁለት ቀን ተደብሬ አሳለፍኩ አገልግሎቱ ግን የተሳካ ነበር በሶስተኛው ቀን ቁርስ ልንበላ ተሰብስበን የሚሊን ስልክ ዝም ብዬ ተቀበልኩት የምታምር ቆንጅዬ ልጅ ፎቶዎቿ በብዛት አሉ አጠገቤ ስለተቀመጠ ሚሊ ማነች አልኩት በቀስታ ኦኦ ቅድስት ትባላለች የአሁን እጮኛዬ የወደፊት ሚስቴ አለኝ ስልኩን ይዤ እጄ ተንቀጠቀጠ ወድያው ተደወለ enatye ይላል ስሙ እንደውም እሷ ናት ብሎ ተቀብሎኝ ሊያወራት ሄደ ደረቄ ቀረሁ ።
በቃ ከአቅም በላይ ታመምኩ እንደምንም ዛሬን አሳልፌ ጠዋት ወደ ሀገራችን ጉዞ ጀመርን እስከዳር አይ ወንድ ጉድ ሰራሸ አደል ወሬዋ ሁሉ ቅስም ሰባሪ ነው ስንደርስ ወዴት እንደምሄድም አላውቅም እነ ናዙ ጋር የማይታሰብ ነው እቤት ደግሞ ያለ ነሱ አልችልም በተለይ ናዙ እንዴት ያለሷ እንቅልፍ ይወስደኛል ያሳለፍነውን እያሰብኩ እንባዬ መቆም አልቻለም ኢቺ ደግም አጠገቤ ተቀምጣ በነገር ትወጋጋኛለች ውይ ስቃዬ በዛ አንድ ደስታ አጊንቼ ለምን ቀጣይነት እንደማይኖረው ግራ ነው የገባኝ በዚህ ሁሉ ቀን አንድም ቀን ልዑል አልደወለልኝም ናዙም ፊት ነስታኛለች እሺ ምን ማድረግ አለብኝ ምክነያታቸው እንኳን አልገባኝም ።
እሺ አሁን እነሱ ቤት ልሂድ እኛ ቤት.......
.............ይቀጥላል.........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ😔
ክፍል 1⃣7⃣
...... ተኛን ምንም መተኛት አልቻልኩም ልዑል ግን ለምን በቁም ነገር ነገረኝ አይ የታዘብኩት መስሎት ይሆናል ወዲያው በስልኬ text ገባ ሳይ ልዑል ነው ። ልጁ አልተኛም እንዴ ሩሀ አላመንሽኝም እንዴ ይላል ምን ልመልስለት ደግሞ እንቅልፍ እስኪነሳው ምን አሳሰበው አይ የኔ ነገር ማንም ባላረገው ነገር ስሙ እንዲጠፋ አይፈልግም ውይ አራሴው ጠይቃለሁ እራሴው መልሳለሁ ብተኛስ
አንድ ነገር ብንን አረገኝ ናዙም ደንግጣ ተነሳች ሰውነቴ በላብ ተጠምቋል ናዙ ምነው ውዴ ቅዠት ነው? ምን ሆንሽ? አለችኝ አላውቅም ናዙ መጥፎ ህልም አየሁ አባቴ ጋር ጠዋት መሄድ አለብኝ ናዙዬ አልኳት ። እሺ አብረን እንሄዳለን ተረጋጊ በቃ ብላ አረጋጋችኝ ጠዋት 12:ሰአት ሲል ተነስተን ወደ እኛ ቤት ሄድን በሩን አንኳኩተን ዘበኛችን አቶ ተሻገር በጣም ጥሩ ሰው ናቸው ገና ሲያዩኝ አገላብጠው ሳሙኝ የኔ ልጅ ስታገቢ ረሳሽን አሉኝ ምን ማነው ያገባው እኔ አልኳቸው ናዙም ግራ ተጋብታ አየቻቸው እናስ እትዬ ማህሌት የለ ሰርግ አግብተሽ አባትሽ ላይ ጨክነሽ እንደቀረሽ ነግረውኛል የአባት ነገር መቼም መታመማቸውን ሰምተሽ አላስችል ብሎሽ ነው አደል ምን አባቴ ታሟል እየተሰባበርኩ የቤቱን በር ከፍቼ ገባሁ ናዙም እየተከተለችኝ ነው የፈረደበት እንባዬ እንደ ጉድ ይወርዳል ደጓ የእንጀራ እናቴ ማነው በሬን ሚሰብረው እያለች መጣች አባቴስ አልኳት እንባዬ እየፈሰሰ ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ ይሄን የሰይጣን አሳሳቅ ጀመረችው ሊሞት መስሎሽ ነው የመጣሽው ጠልተሽው የሄድሽው ቤት አጓጓሽ እያለች ደጋግማ ትስቃለች ስሚኝ እኔ እንደአንቺ ለጥቅም ህሊናዬን የሸጥኩ ሰው አደለሁም ናዙ ስልክ ተደውሎላት ወጣች ምን እኔን ነው ጥቅም ፈላጊ ያልሽው አንቺ ማትረቢ ጩኸቷ አያምጣው ነው ናዙ ተመልሳ መጣች ጭቅጭቃችን እየተባባሰ ነው ናዙ ለምን ተረጋግታቹ አታወሩም አለችን ጨንቋታል ወደ መደርደሪያው ሄዳ ቆመች አሁን ምን ፈልገሽ መጣሽ ገንዘብ ከሆነ ልስጥሽና ቤቴን ለቀሽ ውጪ አለች ቤቴን ቤቴን ነው ያልሽው ምስኪኗ እናቴ ላቧን ጠብ አርጋ የሰራችውን ቤት ቤቴ ስትይ አታፍሪም አንቺ እርኩስ ደግሞ ተገላግዬሽ ነበር አለችኝ አባቴን እኔን ልትገይኝ እንደነበር ገለሽውስ ቢሆን አልኳት ምን እንዲ እንደሚያናግረኝ እንጃ ማህሌት አፍጥጣ ከማየት በቀር መናገር አቆመች አጠገቧ ያለው የመፅሀፍት መደርደሪያ ላይ ተደግፋ ፀጥ አለች እየሮጥኩ ወደ ላይ ወጣሁ የአባቴን መኝታ ቤት ከፍቼ ገባሁ አባቴ አልጋ ላይ ተዘርሮ ያቃስታል መተንፈስ እንኳን አይችልም እያለቀስኩ እጆቹን ያዝኩት ከስቶ አጥንቱ ይታያል ገና እንዳየኝ እንባው ፈሰሰ ምንም መናገር አልቻለም ናዙ ለልዑል ስልክ ደወለችለት መኪና ይዞ እንዲመጣ አባ አናግረኝ ያንተ መኖር እኮ ይጠቅመኛል አባ እባክህ አናግረኝ እሱ እንባውን ማፍሰስ ቀጥሎአል በፊት ስኳር ያመዋል ክትትል ሚያረግበት ወረቀት ሳሎን አለ መደርደሪያው ውስጥ ናዙን እንድታመጣ ልኬያት እኔ ጋቢ ማዘገጃጀት ጀመርኩ ጋቢ አለባብሼው ናዙ ስትቆይብኝ ወደ ሳሎን ወረድኩ ።
ናዙ ተንበርክካለች ማህሌት ጀርባዋን ሰታኝ ቆማለች ናዙ ምነው አልኩ የያዘችውን ሽጉጥ ወደ እኔ አዞረችው...............
.........ይቀጥላል......
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
😔ግር ያላት ነብስ😔
------------""""""""""""""""-----------------
ክፍል 1⃣5⃣
ተስማምተን ተኛን ጠዋት እንደተነሳን ለጀሚላ ደወልኩላት ሀይ ጀምስ ሰላም ነሽ ---
አለሁ ውዴ ምነው በጠዋት አለችኝ
አይ ስጨናነቅ ለsis ያጋጠመሽን ነግሬአት ላውራት ብላ ነው ከቻልሽ እናግኝሽ አልኳት ።
ምን አንቺ ያምሻል ለምን በጥሩንባ አስፓልት ላይ አላወጅሽልኝም?
ጩኸቷ ጆሮ ይበሳል ደንግጬ ደርቄ መስማት ጀመርኩ ላውድ ላይ ስለሆነ ናዙም ደንግጣለች ሲበዛ ባለጌ ነሽ ሰው ነሽ ብዬ ሚስጥሬን ብነግርሽ ይሄኔ ልዑል ላልሽውም ነግረሽዋል አትረቢም በቃ የስድብ አይነት በጠዋቱ ናዙ ተናዳ ስልኩን ነጠቀችኝ ይኸውልሽ የኔ እህት ሩሀ እንደማንም ወረኛ አደለችም አሳዝነሻት ስትጨናነቅ ጨቅጭቄአት ነው የነገረችኝ ደግሞ እህቷ ነኝ ለኔ እንጂ ለማንም አልተናገረችም አለቻት ስልኩን ዘጋችብን በሁለታችንም ግራ ተጋባን ምነው በቀረብን ናዙ አልኳት
ተያት ባክሽ አትጨናነቂ አለችኝ በዚህ መሀል ልዑሌ በሩን አንኳኳ እናንተ አትወጡም በጊዜ መሄድ አለብኝ አለን እሺ ጨርሰናል ብለነው በቶሎ ለባብሰን ወጣን ።
ዋው ልዑሌ በጣም አምሮበታል ልክ እንደ ናዙ ቆንጅዬ ነው በዚ ግርማ ሞገሱ ሙሉ ልብስ ለብሶ ናዙ ነይ ከረቫቴን አስተካክይልኝ አላት እየሳቀች ከፈለክ ሚስት አግባና አሷ ታለባብስህ አለችው ነይ በናትሽ አትቀልጂ ቸኩያለሁ ይላታል አልሰማ አለችው ሆን ብላ እኔ እንዳስተካክልለት ብላ ነው ገብቶኛል እሱ ስለሚያፍር እኔን ማለት ከብዶታል እንደውም ሩሀ ታስተካክልልህ ብላው ሄደች የደነገጥኩትን ድንጋጤ አትጠይቁኝ እሱም እንደደነገጠ ፊቱ ያሳብቅበታል እምቢ ማለት ስለከበደኝ እየፈራው እንደገና አሰርኩለትእና ወደ ሳሎን ሄድኩ ናዙ የለችም ንግስቴ እንዴ እናንተ ሰአት ሄደባቹ ኑ በሉ ቁርስ ብሉ አለችን አባባም የኔ ልጅ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲ የዘነጥከው አለው እፎይ ለካ ለኔ ብቻ አደለም ተመስገን ፈገግ አለና ዛሬ እኮ ነው ከውጪ ለሚመጡት ሰዎች የፋብሪካችንን ሪፖርት ማቀርበው እንደውም ብትገኝ ደስ ይለኛል አባ አለው አባባም አይ ልጄ አሁን ማረፍ ነው ምፈልገው አንተ አለህልኝ ግን ልጄ ያለ እድሜህ ይሄን ጫና አሸክሜህ የራስህን ህይወት ችላ አትበል ወጣት ብትሆንም ለትዳር መዘጋጀት አለብህ ሲለው እንደማፈር ብሎ ይሽኮረመማል ንግስቴም ልክ ነው ስማ እሺ በሉ ቶሎ ቶሎ ብሉ አለችን ልዑል ግን ጥሩ ልጅ ነው እኔ በሱ እድሜ ብሞት ፋብሪካ አላስተዳድርም ሆሆ በወጣትነቱ እስረኛ ለዚህም ነው ከሴት ጋር ማውራት ሚፈራው ማለት ነው በሀሳብ ተመስጬ ቀረሁ ሩሀ ደጋግሞ ሲጠራኝ እንደመንቃት አልኩኝ ንግስቴ ምነው የኔ ልጅ ያልተመቸሽ ነገር አለ አለችኝ ተከዝሽ እኮ አለችኝ አይ እማ አልኳት እማ ስላልኳት በደስታ ልትሞት ነው የምር እናቴን ነው ምትመስለኝ አባባም ለምን ታስቢያለሽ ቤተሰባችን እኮ ነሽ ሚቸግርሽ ነገር ካለ ጠይቂን ይኸው ወንድም እና እህትሽም አሉ አይዞሽ አለኝ ውይ ደስ ሲሉ በእርግጥ እንደዛ አላሰብኩም ግን ከጎኔ ሰው እንዳለ ተሰማኝ እንዴ ናዙስ ግን ጥላን ሄዳ ነው አለ ልዑል እየሳቁ የመቼውን እናንተ ልጆች ዛሬ ምን ሆናቹአል ሁለታቹም ምትደናበሩት ሆሆሆሆ ብላ ንግስቴ ፈገግ አለች እንሂድ በቃ ብሎኝ ደብተሬን ይዞልኝ ተነሳ አምጣው ልያዘው ስለው ተይው እኔ ይዛለው እኔም ተው እኔ ልያዝ አባባ ኸረ አትገባበዙ ረፈደ እኮ ሲለን ልዑል ቀድሞኝ ወጣ በሩን ከፍቶ አስገባኝና ለራሱም ዞሮ ገብቶ መኪናውን አስነሳ ለረጅም ደቂቃዎች ዝም ተባባልን ጭራሽ እንደማይተዋወቅ ሰው በሆዴ አይ ናዙ እብድ የሆንሽ ልጅ ከረቫቱን አስተካክይ ባትለኝ እንዲ ደንግጬ ቀር ነበር ልዑሌ ሩሀ ግን እያጠናሽ ነው ተፈታኝ እኮ ነሽ አለኝ ።
አይ ልዑሌ እናንተ ቤት ከመጣሁ ነው እኮ ሰላም ያገኘውትም በፊትማ ምኑን አጠናውት አሁንም ክፍል ከመከታተል ባለፈ እንደ በፉቱ ማጥናት ከብዶኛል አልኩት ።
ቅድም እንደዛ ሊያየኝ ያፈረ ልጅ በአንዴ ተቆጣ ሩሀ ትቀልጃለሽ እንዴ በፊት በጣም ጎበዝ እንደነበርሽ ናዙ ነግራኛለች እና አሁን ለምን ትኩረት አትሰጪም ለጥናትሽ በእርግጥ እረዳሻለው የደረሰብሽን ተቋቁመሽ ፀንተሽ መኖርሽ ራሱ ያስገርማል ትልቅ ቦታ ደርሰሽ ማየት ነው ምፈልገው አለኝ ።
እሺ ልዑሌ አመሠግናለሁ አልኩት ልዑል በጣም ጎበዝና ጠንካራ ተማሪ እንደነበረ አባባ ነግሮኛል ለዚህም ነው በዚህ ወጣትነት የአባቱን ንብረት ሚያስተዳድረው ።
ትምህርት ቤት አደረሰኝ ና ቻው ብዬው ወረድኩ ወደ ክላስ ስገባ ጀሚላ የለችም አርፍዳ ትመጣለች ብዬ ብዙ ጠበኳት አልመጣችም ሆሆሆ የዚህን ያክል አስከፍቻት ነው ምን ይሻለኛል ።
እረፍት ሰአት ደርሶ ከነ ሚሊጋ ምንሰባሰብበት ቦታ ሄድኩ ሁሉም አሉ ሠላም አልኳቸውና ተቀመጥኩ ውይይት በመሀል ቀልድ ሳቅ ተጀመረ እኔ ግን ተክዣለሁ ሁሉም እየተጨዋወቱ ነው ጀሚላ አዝናብኛለች በእኔ ቤት ጥሩ መስራቴ ነው እኮ ።
ሚሊ ሩሀ ምን ሆነሽ ነው ደብሮሻል አለኝ ሁሉም ትኩረታቸውን ወደ እኔ አረጉ አይ ምንም ብዬ ተነስቼ ሄድኩ ሚሊ ተከትሎ አስቆመኝ ሩሀ ምን ነካሽ የምር ስትስቂ እንጃ ስትተክዢ አያምርብሽም አለኝ አይ ሚሊ ምንም ይልቅ ተመለስ ወደ ክላስ ልገባ ነው አልኩት ካልነገርሽኝ ብሎ ደረቀ ጭራሽ ላንተም ነግሬ ላባብሰው ሆሆ በቃ ከጓደኛዬ ጋ ተጣልቼ ነው ተመለስ አልኩት እኔ ላስታርቃቹ ማናት አለኝ አትሰማም ሂድልኝ ብዬ ጮኹኩበት አይ እኔ እኮ ሲከፋሽ ደስ ስለማይለኝ ነው አለኝ
አይደል እስከዛሬው ስታስከፋኝ አልነበርክ በቃ ተወኝ ብዬው ሄድኩና ክፍል ገባሁ ወይኔ ጉዴ ይቅርታ ብሎኝ ያለፈውን ማንሳት ምን ይሉታል ምን አይነት ሰው ነኝ እራሴን ታዘብኩት ኡፍፍፍፍ እየሮጥኩ ተመልሼ ሄድኩ ሁሉም አሉ ሚሊ የለም ሚሊስ ስላቸው ወደዛ ታጠፈ አሉኝ ሄድኩ አቀርቅሮ ዲንጋይ ላይ ተቀምጧል ሚሊ በጣም ይቅርታ አጥፍቻለሁ አልኩት ችግር የለውም አለኝ በጣም አዝኗል ።
ሚሊ በጌታ በእግዚአብሄር አልኩት እሺ አልተቀየምኩሽም ብሎ ፈገግ አለ ታርቀን ወደ ክላሴ ገባሁ ክላስ አልቆ ከጊቢ ወጣው ልዑል ዘገየብኝ ተማሪ ሁሉገብቶ አልቋል በቃ በእግሬ ልሒድ ብዬ መንገዱን ካጋመስኩ በኋላ ከሩቅ እየመጣ አየሁት መኪናውን አቆመልኝ ገቢናው ውስጥ ሴት አለች እራሴ ከፍቼ ከኋላ ገባሁ ሩሀዬ ተዋወቁ ሊያ ትባላለች አለኝ የሆነች ቀበጥ ነገር ኦው ሩሀማ ስምሽን ነግሮኛል ብላ እየተቀናጣች ጨበጠችኝ ምን እንዳናደደኝ እንጃ ሚጡዬ ማነሽ ሩሀማ ለምን በታክሲ አናሳፍርሽም አለችኝ ልዑል እንዴ አይሆንም ቤት ነው ማደርሳት አላት ኦው ለነገሩ ብትጠፋስ ልክ ነህ እያናደደችኝ ነው እኔ ህፃን ነኝ እንዴ ምጠፋው አልኳት አይ ያው ገና ተማሪ ነሽ ብዬ ነው አለችኝ እቤት በር ላይ አወረደኝና መኪናዋን አዙሮ ሄዱ እየተናደድኩ ወደ ቤት ገባሁ ....
.............ይቀጥላል..........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------
አስተማሪ ታሪክ
✳️✳️✳️✳️✳️✳️
አካባቢው የከተማው የወርቅ፣ የብርና የዳይመንድ ውጤቶች የሚሸጡባቸው ሱቆች የሞሉበትና ጎብኚዎች ከየአለማቱ የሚጎርፉበት አካባቢ ነው፡፡ ይህ አካባቢ በዚህ አይነት ንግድ ሲታወቅ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ብዙ አመታት ውስጥ አልፎ አልፎ የተለያዩ የስርቆት፣ የሌሊት ዝርፊያና በእኩለ ቀን አይን ያወጣ ቅሚያ ይሰማል፡፡
አንድ ቀን ግን ከአነዚህ ሱቆች በአንደኛው ሱቅ ከዚህ በፊት በፍጹም ተከናውኖ የማያውቅ ድንገተኛ ነገር ሆነ፡፡ በአንድ ሌሊት ቁጥራቸው ሶስት የሚሆኑ ሌቦች በአንደኛው ሱቅ ጣሪያ ፈልቅቀው በመግባት አንድን ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ነገር አደረጉ፡፡ በሱቁ ውስጥ የነበሩትን ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ የሆኑትን ጌጣጌጦች ሰርቀው የመሄዳቸው ነገር በማንኛውም ሰው የሚገመት ቢሆንም ያንን ግን አላደረጉም፡፡ በምትኩ ግን ያደረጉት በጣም ውድ የተባሉ ጌጣጌጦች ላይ ያለውን ዋጋ በማንሳት በጣም ርካሽ ዋጋ ባላቸው ጌጣጌጦች ጋር ለጠፉ፡፡ በተቃራኒውም በጣም ርካሽ ዋጋ ያላቸውን የጌጣጌጦች ዋጋ በማንሳት በውዶቹ ላይ ለጠፉ፡፡ ይህንን የመሰለ የዋጋ ቀውስ ካደረጉ በኋላ አንድም እቃ ሳይሰርቁ ቀስ ብለው እንደገቡ በማያስታውቅ መልኩ ወጡ፡፡
ምሽቱ ነግቶ የሱቁ ባለቤት ሱቁን ሲከፍት ምንም የጎላና የሚታይ ለውጥ ስላላየ ቀኑ እንደተለመደው ስለመሰለው ላይ ላዩን ቃኝቶ በዚያን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ለሚጀምረው አዲስ ሰራተኛ አደራ ብሎ ተጣድፎ ወደ ግል ጉዳዩ ይወጣል፡፡ ብዙ ደንበኞችን በማስተናገድ የታወቀው ይህ ሱቅ ብዙም ሳይቆይ ሽያጩን አጧጧፈው፡፡ አንዳንድ ገበያተኞች ገና እንደገቡ አይናቸው ውድ ዋጋ የተለጠፈበት ላይ ይተከላል፡፡
አንደኛው ባለሃብት ፍቅረኛውን ለማስደሰት በጣም ውድ የተባለውን ጌጥ ለመግዛት መጥቷል፡፡ በሱቁ ውስጥ ግን እጅግ በጣም ርካሽ የተባለው እቃ ላይ ነው ውድ ዋጋ የተለጠፈበት፡፡ ስለሆነም እነዚህን ውድ መሰል ርካሽ ጌጦች ሰብስቦና ብዙ ዋጋ ከፍሎ ይወጣል፡፡
ሌላዋ ገበያተኛ ከጓደኞቿ ለየትና በለጥ ማለቷን የምታሳየው እነሱ መግዛት የማይችሉትን ውድ ጌጣ ጌጥ በማድረግ ስለሆነ፣ ረጅም ጫማዋን አድርጋ በጥንቃቄ እየተራመደች ገባችና ረጃጅም ሰው ሰራሽ ጥፍሮች በተሰካኩበት ጣቶቿ ውድ ውዱን ጌጣ ጌጥ ጠቆመችና ሰብስባ ገዝታ ሄደች፡፡ የተደረገውን የዋጋ መሰባጠር ግን አላስተዋለችውም፡፡
እነዚያ ሌቦች በሌሊት ገብተው ከፈጠሩት የዋጋ መዛባት የተነሳ እነዚህ ነጋዴዎች ዋጋ ሊሰጣቸው ከሚገባቸው ነገር ላይ አይናቸውን አንስተው ያን ያህል ዋጋ ሊሰጣቸው የማይገባቸውን ነገሮች ላይ ትኩረታቸውን ጣሉ፡፡ በውጤቱም፣ ለከበረውና ብዙ ትኩረትና ዋጋ ሊሰጥ የሚገባውን ነገር ችላ ብለው፣ ለተራና ለማይገባው ነገር ብዙ ዋጋ ሰጡ፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በእኛም ዘንድ ይሄ ይስተዋላል ብዙ ትኩረት መስጠት የሚገባን በዋጋ የማንተምናቸው ሀብቶች አሉን።
------ @yebirihan_lijoch ------
------ @yebirihan_lijoch ------
✍ የኔ መገረሚያ
*****************
ከኔ ባልጀመረ ፣ በኔ በማይቀጥል
የሕይወት ስጦታህ ፣ የማዳንህ ፍቅር
እኔ ያላሰብኩህ ፣ የአብ ቀመር ስሌቴ
በ'ሳት የተፈተንክ ፣ ወርቅ የሆንክ እምነቴ
አንተ አይደለህም ወይ ፣ በአብ መግቢያ ደጄ
እንዳምንህ ያመንከኝ ፣ ተወዳጅ ወዳጄ
አቤት ፍቅርህ ሲገርም ፣ አቤት አንተ ስትገርም
እያልኩኝ ስትደንቀኝ ፣ እያልኩኝ ስገረም
ለኔ መገረሚያ ፣ ካንተ ውጭ የለም
እንዴት ይገርመኛል ፣ ያልኖርኩበት አለም
አንተ ነህ አለሜ ፣ ብርቄ የምትበርቀኝ
ሌላ ማን ይታየኝ ፣ ተቀምጬ በአብ ቀኝ
በክብርህ ክብር ልክ ፣ ካንተ ጋር ቁጭ ብየ
ከጸሐይ በላይ ነው ፣ ሁሉም እይታየ
ሰርክአዲስ ም'ረትህ ፣ ሰርክ እያስደመመው
ውስጤ ባለኸው ነው ፣ ውስጤ 'ሚገረመው
#ሄኖክ_አሸብር
✍ #ያልተነበበ_ገፅ
ክርስትናን ኖሮ ላጣጣመው
ሁሌም ያልተነበበ ገፅ ነው
በዛ ተብሎ የማይጎድል
አረጀ ተብሎ የማይጣል
ከረመ ተብሎ ማይለመድ
ረዘመ ተብሎ የማይገመድ
መቼም ተነቦ ተቀምሶ የማያልቅ
አዲስ ሆኖ ጣፍጦ የሚዘልቅ
ክርስትናን ኖሮ ላጣጣመው
ሁሌም ያልተነበበ ገፅ ነው
#kabata_H
✍ የተወደደ
**
እንደበደሌ እንዳልከፈለኝ ፣ ያወኩኝ ጊዜ እንደራራልኝ
የወደደኝን የወደድኩት ለት ፣ የሚጠሉኝን መውደድ ሆነልኝ
ለካ ያለምክንያት የተወደደ ፣ ብዙ የተማረ እንዲያው ተወዳጅ
የኢየሱስ ፍቅር ልቡን የነካው ፣ እየጠሉትም ይሆናል ወዳጅ
ተማርኩኝ ያለ አይበቀልም ፣ ተወደድኩ ያለ ጥላቻ አያውቅም
ፍቅርን ከእግዚአብሔር የተካፈለ ፣ ከየት ያገኛል የመጥላት አቅም
እኔ እንጃ!!
#ሄኖክ_አሸብር
#Easter
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
. #ተነስቷል
ተሰርቆ አይደለም ፤ ሬሳው በደቀመዛሙርቱ
በእውነትም ተነስ፤ ሄዷል ወደ አባቱ
ይህ ነው ቃላችን ፤ የማይሻር እውነት
ኢየሱስ ተነስቷል ፤ አልተገታም በሞት!!!
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
. ፀጋው በለጠ
ዘማሪ ዮሐንስ በላይ
New Amazing Live Worship
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
✅ @yebirihan_lijoch ✅
✅ @yebirihan_lijoch ✅
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
#ጊዜ …
•
ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች።
ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ ሀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን።
በከረጢትዋ ውስጥ ያሉት ፈርጦች አንድ ባንድ፣ አንዳንዴም ካንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ።
ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም። ድህነት የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም።
•
#ምንጭ :- የተቆለፈበት ቁልፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ
በቅንነት ሼር በማድረግ አዳርሱ
@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch
እኔ የማወራው ነገር ሁልጊዜ
1 እውነት
2 ሕይወት
3 መንገድ
እኔ ግን ገብቶኛል የዘላለም ሕይወት መስጠት የሚችል ማን እንደሆነ
ስለሕይወት ትርጉም ትንሽ ልበላችሁ።
ከጦጣ አልመጣሁም ወይም ከዝንጀሮ ሳይንስ እንዲህ ያምናል አሁንም ዘንድሮ። ፈላስፋም ይሰብካል እግዜር የለም ብሎ ካላየው አላምንም አሳዩኛ ብሎ ።የእኔ ሕይወት እንዲህ ነው በእምነት ነው የምኖረው ሳላይ ያመንኩትን አምኜ ነው የማየው። እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከቃሉ የሁሉ መሰረት ኢየሱስ ብቻ ነው።
እስከሞት ብቻ ሕይወትን ካሰላህ እውነቱን ልንገርህ አንተ ሰው ተበላህ😭
ሕይወት ስለማይቆም ከሞትንም በኋላ ከምድር ተሻግረን ዘላለማዊ የሆነውን ክርስቶስን እናስላ።
አስተያየት ➡➡➡ @KTCOJ ቻናሉን ይቀላቀሉ @yeeiyesus