yebirihan_lijoch | Unsorted

Telegram-канал yebirihan_lijoch - የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

3717

#የብርሃን_ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ አላቸው። ኢየሱስም ይህን ብሎ ሄደ። ዮሐ 12 ÷36 ይህ መንፈሳዊ የቴሌግራም channel ነው። 👉 @yebirihan_lijoch Youtube channel https://youtube.com/channel/UCtp5XBjV0p6Mw0BX1Nmu81w 🌍 LOCATION 👉 ADOLA WOYU

Subscribe to a channel

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

የተመቻችሁን ይበልጥ የወደዳችሁትን ምረጡ

የዳኛ ድምፅ
#ምድብ_A.......30%
#ምድብ_B……..30%

Like ነው የሚለያችሁ እስከ ነገ ጠዋት 3:00 ብቻ ነው like ሚታየው

ምርጫችሁን 👇

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

#እንዲህም_ይፃፋል 👏👏👏👏👏👏👏

#ምድብ_A

ያንተ ፍቅር ደቀነኝ
የራኩትን ስትቀርበኝ
ትርጉማለው ጌታ
መዋለህ ጎልጎታ
ስለ ኃያሉ ፍቅርህ
ምላሽ አጣሁልህ
እርሱ አልሰሰተም ሲሰጠኝ እራሱን
በመስቀል ተሰቅሎ ሲያፈስ ደሙን
ክብሩን ለተወልኝ ክብሬን የምሰጠው
ለሞተልኝ ጌታ ለሱ ነው ምኖረው

በደም ነው የገዛኝ ዋጋየ ትልቅ ነው
የዚህ አለም ስሌት ፍፁም ማይመጥነው
ታዲያ እንዴት ልርሳ ያለብኝን ዕዳ
ቀድሞ የከፈለልኝን እኔ እንዳልጎዳ
ሞት የሚገባኝ ሳለው
ሞቴን በሂወት ቀየርከው
ውዳሴ ይፈልቃል ዛሬም ካንደበቴ
በደሙ ላነጻኝ ለመድሀኒቴ
ዛሬን አየው እየሱስ ጌታዬ
ክበር ንገስ ይኸው ምስጋናዬ

ወደዚህ መምጣትህ በምክንያት እኮነው
ለኔ ለጠፋሁት ህይወት ለመሥጠት ነው
በምህረትህ ታነሳለህ
በፍቅርህ ትደግፋለህ
እውነተኛ ወዳጅ አጣሁኝ እንዳንተ
ነፍሱን አሳልፎ ስለኔ የሰጠ
ደስ ይለኛል እኔ ሁሌም ባንተ ጌታ፤
ያደረከው ሳስብ የዋልከዉ ዉለታ
አረሳውም ውዴ የፋሲው አዳር
የተገለፀበት ለኔ ያለህ ፍቅር

መዳኔ በዋጋ ከፎሎ ከባለጋራዬ
ዳበቢሎስን አስመለጠኝ!
ማነሽ ይሉኛል ሰዎች እርስተውኝ
ግራ እስካጋባ እንዲ ለውጠኸኝ
ሳስበው ደነቀኝ የትናንት ህይወቴን
ለውጠኸው ጌታ መላ ማንነቴን
አይቀልብኝም መገኘትህ
ከኔጋ መዋል ማደርህ
አባብሎ የሚያስተኛ አባት
ለኔ እንዳንተ ማነው ልቤ ያረፈበት

ያኮራል የእሱ መወኔ
ኢየሱስ ይመሰገን አለው አለኝ፡፡
የማይንቀሳቀስ የዘላለም ነዋሪ
የማይዋሽ የተናገረውን አክባሪ።
አንድ እውነት አለ ሁሉን ጉድ ያስኘ
ከሞት የሚያድነው ከበረት ተገኘ
ምህረትህ ገርሞኛል ሌላ ምን እላለሁ
ወድደህ ስላዳንከኝ አመሠግናለሁ
የሞቴን ቀጠሮ የጥፋቴን ሰአት
በእጆቹ ሸሽጎ ጌታዬ አሳለፋት
ከአሁን በኀላ እኔ ጴንጤ ነኝ
ምን እንደነካኝ ሳላውቅ ያኔ ጌታ አገኘኝ
አፅናኝ ነህ ለሃዘኔ አማላጅ ነህ ለፀሎቴ
ውዱ ስጦታዬ እስትንፋስ ህይወቴ
ዶሮ ሳይጮህ 3 ጊዜ የካድኩህ ያኔ
ዶሮ ሳይጮህ አመሰግንሀለው መድህኔ


እንዳላለቅስ እንባ እንዳይወጣ ከዓይኔ
በመስቀል ሞቶ አዳነኝ መድህኔ!!
በደም ነው የገዛኝ ዋጋየ ትልቅ ነው
የዚህ አለም ስሌት ፍፁም ማይመጥነው
ንጋት ተጀምሮ ሰአታት ሲሄዱ ቀኑ ሲሆን ማታ
ልነሳ ልዘጋጅ ጌታን ልጠብቀው እያልኩ ማራናታ
የዚህ አለም ኑሮ በጣም ሰልችቶናል፤
መቼነዉ ምትወስደን የሱስ ናፍቀኸናል።

#ምድብ_A

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Ina degmo 4 sinign yetsafachu yemiwesedew yemechereshawochu 2 sinign Bicha new

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ምድብ B abalat be english tsufet yetetsafutin gitimoch wede amrign bemelewex yitebaberun

natisho
ribk
teketel
natiyopia yitebaberun

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ምድበ B yibekachiwal ke 28 bewala yalew ayikatetim

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Cimari 3 dekika bicha tolo belu

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Zigiju nachu??? ምድብ

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Chawetawn yeminichawetew be budin sihon ina ashenafi lehonut team degmo mecheresha lay 1 mirx axer yalech liboled mulu shilimat alew….ahun silechawetaw kemenagere befit chawetawn kejemerin bewala lela sew indayigeba be midibachu comment bota lay simachun tsafu

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

አሁን #online ላይ ያላችሁ 1 menfesawi chaweta inichawet bezawm tilik sira iniseralen inaa fikadegna yehone #like yadrgi

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ኡሪም ምርጥ ታሪክ ያለው ፣ ምርጥ ሃሳብ ያለው አስተማሪ ልቦለድ በቅርብ ቀን በዚህ channel ይጠብቁ።

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Yemecheresha kifil silehone nege new yeminilekew muluwun

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ 😔

........ክፍል2⃣8⃣.......

.....እያጋመስኩት ነው እንግዲ የጊቢ ተማሪ ከሆንኩ 4ዓመታት ተቆጠሩ ለእረፍት ስመለስ በናፍቆት አገኛቸዋለሁ የጀምስም ልጅ በጣም አድጓል የልጇ አባት አጎቷም እንደሞተ ሰማሁ የወንድሙ ልጅ ልጅ አባት ከመባልማ ይሻለዋል በነገራችን ላይ ጀምስ ጥሩ ዘማሪ ወጥቷታል ስትዘምር የተቀረፁ ምስሎችን ምናምን ትልክልኛለች እነ ማርኩም የሀይስኩል ተማሪ ሆነዋል ሳሪ ደግሞ አሁንም ነብሰ ጡር መሆንዋን ነግራኛለች ናዙዬ ትምህርቷን አጠናቃ በነርሲንግ ስራ ጀምራለች ጀምስም እዛው የግል ኮሌጅ ትምህርቷን እየተከታተለች ነው እኔም እዚሁ ትምህርቴንም አገልግሎቴንም በአግባቡ እየተከታተልኩ ነው ከልዑል ጋር ስልክ አላነሳህም አልደወልክም ወይ እሱ ደግሞ text አትመልሺም በሚል ተራ ምክኒያት መጣላት የተለመደ ነው ግን ደግሞ ወዲያው ነው ምንታረቀው ሰሞንን ግን ያለወትሮው ጠፍቷል ስልኩ በጭራሽ ዝግ ነው ቢቸግረኝ እነ ሳሪን ጠየኳቸው ኸረ ሰላም ነው ግን ቢዚ ሆኖ ይሆናል ይሉኛል ለማመን ተቸግሬአለሁ ናዙ ደግሞ ጭራሽ ስልኬን አታነሳም ኦንላይን ላይም ካለች እኔ ስገባ ትወጣለች ንግስቴም አባባም ማንም ስልኬን አያነሳም ሰዎቹ ምን ሆነዋል እውነት ልዑል እኔ ላይ አስችሎት እንዲ ይጠፋል አሁን ደግሞ የፈተና ሰሞን ነው ምንም ማንበብም አልቻልኩም ።

አሁንስ ግራ አጋቡኝ አባቴም ረጅም ሰአት ያወራኝ የነበረው ስራ ቢዚ እንዳረገው ወዲያው ይዘጋብኛል ሁሉም ስለ ልዑል ሳነሳ አይሰማም ኔትዎርኩ ነው ሄለው ... ሄለው ይቆራረጣል እያሉ ስልኩን መዝጋት ተያይዘውታል በቃ ማበዴ ነው ምን እንደሚሰማኝ እንዴት ልንገራችሁ ማያ በዚህ ሁሉ ጊዜ ከአጠገቤ አልጠፋችም እሄዳለሁ በቃ አልኳት ሁሉም የዶርም ጓደኞቼ ሩሃ ምን ነክቶሻል በዚህ በፈተና ወቅት እንዴት ነው ምትሄጂው ተረጋጊ ምንም አይፈጠርም ይሉኛል እኔ ግን የመጣው ይምጣ እሄዳለሁ የሚል አቋም ላይ ነኝ ለአባባ ደወልኩለት ነገ ልመጣ ነው አልኩት የኔ ልጅ አይሆንም ተረጋጊ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ፈተናሽ እንዳለቀ መጥቼ እወስድሻለሁ አለኝ ልዑልስ ብዬ አለቀስኩበት ልዑል ደህና ነው ተረጋጊ ልጄ ያኔም ቃል ገብተሽልኛል የሱና የአንቺ ነገር ትምህርትሽን በማይጎዳ መልኩ ተባብለናል እና ለምን ጠፋ ቆይ አላሳዝናችሁም አልኩት እንደተረበሸ ያስታውቅበታል ተረጋጊ ልጄ በይ ደህና ሀኚ ብሎኝ ስልኩን ዘጋብኝ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ ማበድ ነው የቀረኝ እነ ማያ ሊያፅናኑኝ ቢሞክሩም ማንም የውስጤን አያውቅም ወዲያው ናዙ ደወለችልኝ ሩሃ በጣም ይቅርታ ስልክሽን ስላላነሳው አለችኝ ልዑል ምን ሆኗል የት ነው ያለው ብዬ ጮኹኩባት ምንም አልሆነም ግ ን ስብሰባ ላይ የው 15 ቀን ከውጪ እንግዶች ጋር አላለችም ናዙ ህፃን መሰልኩሽ ልዑልን እኮ አቀዋለው ለኔ 5ደቂቃ አጥቶ ነው የማይደውለው ለምን ትሰብሪኛለሽ እውነቱን ንገሪኝ አልኳት ዘጋችብኝ እኚ ሰዎች ሊገድሉኝ ነው መሰለኝ እቅዳቸው ምርርር ብሎኛል ነገ ፈተና ይጀመራል በድን እንዴት መፈተን ይችላል በድን ሆኜአለሁ .....

...........ይቀጥላል...............

💐💐 ተባረኩ 💐💐
-------------"""""""""""----------------

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

...............ክፍል2⃣6⃣................

ቅዳሜ ውጤት ይለቀቃል ተብለናል ሰሞኑን ቤት ነው በብዛት ምውለው የሌለ ተጫጭኖኝ ተኝቼ ነበር የክፍሌን በር በርግዳው ገባች ሳሪ ሩሀ ሩሀ' ደንግጣለች ምነው ሳሪ ብዬ እኔም በፍጥነት ከአልጋዬ ወረድኩ ጀምስ ምጧ መጣ መሰለኝ የአባትሽ ስልክ አይሰራም መኪና ይዞ እንዲመጣ አለችኝ ከምሽቱ 1ሰአት ሆኗል ምን እናድርግ በኔም ብንሞክርለት አይሰራም እሺ ወይ ለልዑል ደውይ አለችኝ ወዲያው አባቢ በር ሲያስከፍት ሰማን እየሮጥኩ ወጥቼ ነገርኩት ተሯሩጠን በመኪና ይዘናት ሆስፒታል ይዘናት ሄድን ገና ናት ብለውን በብርድ ጠወለግን ከምሽቱ 3 ሰአት ሆነ ሳሪ ምትበላው ነገር ስለሚያስፈልግ ሄጄ ገንፎ ምናምን ላምጣ እናንተ እዚሁ ሁኑ አለችን ኸረ አይሆንም አባቢ ያድርስሽ አብራቹ ሂዱ እኔ እዚህ ሆናለሁ አልኳቸው ባትስማማም አባቢ በግድ ይዟት ሄደ እኔ በብርድ እየተብረከረኩ ነው የጀምስ የሲቃ ድምፅ በጣም ይጨንቃል በዛ ላይ የኔ ታናሽ ናት በዚህ እድሜዋ አንድ ነገር ብትሆንስ በጣም ፈርቻለሁ ወዲያው ነርሷ መጥታ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ደም ሚሰጣት ሰው አለ አለችኝ እኔ አለው ብዬ ተከትያት ሄድኩ አዝናለሁ ደማቹ አንድ ነው ግን ኪሎሽ ለመስጠት አይሆንም አለችኝ እኔ ምንም አልሆንም እሷ ትሙትልሽ ብዬ ጮኹኩባት ታዲያ ወንጀል ነው እኔን ያስቀጣኛል አንቺም በሽታ ላይ ትወድቂያለሽ አለችኝ የመጣው ይምጣ አታሳዝንሽም ያለ እድሜዋ ትሙት ብዬ አለቀስኩባት አንቺ ያምሻል መኖር አትፈልጊም ? ሌላ ሰው ካለ ደውለሽ ጥሪ እንጂ አይሆንም አለችኝ አባቢ ጋ ደወልኩ ስልኩ አይሰራም የሳሪ ደግሞ ይጠራል አታነሳም ደጋግመን ሞከርን ምንም ለውጥ የለም ዶክተሩ ኸረ አፍጥኑት ልጅቷ እየደከመች ነው አለን ።

ምንም አማራጭ ሲያጡ ከኔው ለመውሰድ ተስማሙ አስደግፈውኝ ደምስሬን መፈለግ ጀመሩ 4:ሰአት ይሆናል ወዲያው ልዑል ደወለልኝ ነርሷ አንስታ ሰጠችኝ ሰላም አለኝ ደና ነሽ የሆነ ነገር እየረበሸኝ ነው የት ሆነሽ ነው አለኝ እ እንትን እእ እቤት ነኝ አልኩት ተንተባተብኩ የምርሽን ነው አለኝ ማለቴ ሆስፒታል አልኩት ምን ምን ተፈጥሮ አለኝ ጀምስ ምጥ ይዟት ነው አልኩት የት ነው አለኝ ቦታውን ነገርኩት እና ስልኩ ተዘጋ አፍጥነው በናትህ እየመጣ ይሆናል አልኩት ደምስሬ ቢፈለግ ጠፋ አንቺ ምግብ አትበይም እንዴ ኪሎሽ እንዲ ሆኖ ደምስር እስኪጠፋ አለኝ ልጁ በምን ተአምር እንደመጣ የማዋለጃ ክፍል አጠገብ ነው ያለነው ትንሽ ቆይተው ነርሷ ይዛው መጣች ምን እንደነገረችው ባላውቅም አንቺ ያምሻል ለኔ አትደውይም ነው እኔ ስለ አንቺ አያገባኝም የሌለ ተናዷል እኔን አስነስተው ተሱን ደምስር መፈለግ ጀመሩ ምንም አልተቸገሩም ወዲያው አጊንተው እየወሰዱ ነው በዚህ መሀል አባቢና ሳሪ መጡ ደሙ እየተሰጣት ነው ግን ስለ ደከመች ቀዶ ጥገና ሊደረግላት ነው ሳሪ ለቅሶውን ተያይዛዋለች አይዞሽ ምንም አትሆንም ብንላትም መረጋጋት አልቻለችም ዘላለም ጭንቅ አያጣኝም ከሰአታት በኅላ ነርሷ መልካም ዜና አሰማችን ጀሚላ ወንድ ልጅ ተገላግላለች እስከ ጠዋት ትነቃለች አለችን ኡፍ ሳሪ ከለቅሶ ወደ እልልታ ገባች ሳሪ ልዑልና አባባን ወደ ቤት ሂዱ አለቻቸው ሁለቱም አንሄድም ብለው ደረቁ እሺ እስክትነቃ ተብሎ አባባና ልዑል አባቢ መኪና ውስጥ ሳሪ እና እኔ የልዑል መኪና ውስጥ አረፍ አልን ጠዋት 12 ሰአት እኔና ሳሪ ተነስተን ስንወጣ ነቅታለች ትንሽ ክትትል ይደረግላታል ህፃኑን ከሙቀት ክፍል አመጡት የሚያሳዝን ህፃን ነው አባባና ልዑልም መተው አይተውት በረከት ማለትም የጀምስ ሞግዚት ናት ቁርስ ይዛልን መጣች አሷ አብራት ሆና እኛ ካፌ በልተን ምናምን በዛ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ነው 9ሰአት ሲል ውጤት ተለቋል የኔ አምላክ ጥሎ የማይጥል በከፍተኛ ውጤት አለፍኩ እነ ሚሊም እስከዳርም አቤት በደስታ ልንሞት ነው ጀምስ ሰኞ ነው ወደ ቤት ምትገባው ተብለን ቅዳሜን እና እሁድን አሳልፈን ሰኞ ወደ ቤት ገባች ልጇን በጭንቅ ተወልዷልና ያቤፅ አልነው እነ ማርኩም ልጅ ስላገኙ ደስተኛ ሆነዋል ጀምስ ከወለደች ሳምንት አለፋት አሁን መንቀሳቀስም እየጀመረች ነው እየተንከባከብናት ናዙም አብራኝ ነው ቤት ከኔ ጋር ምታሳልፈው ።

ቀውጢ ፕሮግራም አዘጋጅተን እነ ንግስቴን እቤት ጋበዝናቸው ያው ደስ በሚል ሁኔታ እሁድን አሳለፍን ።
ሰሞኑን ደሞ የጊቢ ምድብ ይነገረናል አሁንስ ባር ባር አለኝ.....

........ይቀጥላል...........

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦

⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ጥያቄና መልስ ልንጀምር ስንቶቻችሁ ዝግጁ ናችሁ??

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

..... ክፍል 2⃣3⃣ ......

ወደ እነ ናዙ ቤት እየሄድን ነው የሚሰማኝን ስሜት እንዴት ልግለፅላቹ አልቅሺ አልቅሺ ነው ሚለኝ ስንደርስ የመዝሙር ድምፅ ሰፈሩን ቀውጢ አድርጎታል በሩ ላይ ከ10 በላይ መኪናዎች አሉ ገብተን ተቀመጥን ናዙም ልዑልም አይታዩኝም አባባ መጥቶ ተጫወቱ ብሎ ሁላችንንም ሰላም ብሎን ናዙን ሊጠራት ወደ ቤት ገባ ጊቢው ሰው በሰው ነው ጫጫታ ነው ዘመድ አዝማድ ተሰብስቧል ጌታ ሆይ ህልም ነው በለኝ እውነት ልዑል ሲያገባ ላይ ነው እዚ የጎለትከኝ እየተብሰለሰልኩ ነው ናዙና አባባ መጥተው ናዙ ሁላችንንም ሰላም ብላን አብራን ተቀላቀለች ምን እናግዝ ሲላት ሚሊ ምንም ሁሉም አልቋል አለችው ምግብ መጣልን በህብረት መብላት ሲያስደስት በተለይ የኛ ቲም ፍቅር በፍቅር ነው የምንሆነው አባባም ንግስቴም ምን ይጨመር ተጫወቱ እንክብካቤው በዛ በነገራችሁ ላይ ሙሽራውን ተዋወቃችሁት አለን አባባ ሁሉም አይ አሉ ምነው እኔም ባላወኩት እያልኩ በሆዴ ንግስቴ ናዝሪ ሂጂ እንጂ ጥሪአቸው ሚዜዎቹንም ይተዋወቁ ጓደኞችሽ አደሉ እንዴ የማያውቁትን ሰው ነው ነገ የሚያጅቡት አለቻት ልትጠራቸው ሄደች እውነት እምባዬ ጠብ አለ ባላየው ይሻለኛል ኡኡ ብዬ ብጮህም ደስ ይለኛል ልዑል በዛ ግርማ ሞገሱ ከሶስት ወንዶች ጋር እየመጣ ነው ተነስተሽ ሂጂ ሂጂ ይለኛል ደረሱ አንዱ ሀይ ያፌት እባላለሁ በሰርጌ ዋዜማ ስለተገኛቹ ደስ ብሎኛል የናዙ የአጎት ልጅ ነኝ ከአሜሪካ ሰርጌን እዚህ ለማድረግ ነው የመጣሁት አላለም ወይኔ ጉዴ አፌ ቁርጥ ይበልልህ ብዬ ልጠመጠምበት ምንም አልቀረኝም ሁላችንም ጨበጥነው እሰይ ጌታ ሆይ ውለታህ በዛብኝ የኔው ልዑል ሚዜ እንጂ ሙሽራ አይደለም በቃ እግዚያብሔር ሀዘኔን በአንዲት ቅፅበት በደስታ ቀየረው አራቱም ተቀላቀሉን መጨዋወት መሳሳቅ ተጀመረ በወሬ መሀል ሩሐ ምናምን ሲሉኝ የሰማው ያፌት ማለቴ ሙሽራው እንዴ ሩሀ እሷ ናት አለው ወደ ልዑል እያየ የኔ ቀበጥ ናዙ እንዳኮረፈችኝ ረሳችው መሰለኝ አዎን ተዋወቃት እንጂ እንዴት ናት ጓደኛዬ አለችው ዋው ከጠበኳት በላይ ናት ወንድሜ ምርጫህን አድንቄልሀለው ብሎ እርፍ ግማሹ እርስ በእርስ በወሬ ተጠምዷል 20 አናልፍም ወሬው ና መዝሙሩ ጩኸቱ አንድ ላይ ገበያ በሉት እንደገና ተነስቶ ሰላም አለኝ እግዚያብሔር ይስጠወና ታዲያ በሰርጌ ዋዜማ ማንም እንዲኮራረፍ አልፈልግም ይቅርታ ተጠያየቁ አለን ናዙም አዎን ጥሩ ሀሳብ ቶሎ በሉ ብላ አሽቃበጠችለት ተገኝቶ ነው እንዴ እግሩ ስርም ብወድቅ እሱ ብቻ ይቅርታ ያርግልኝ እንጂ አልተግደረደርኩም የምር እግሩ ላይ ልወድቅ ስል ቀና አድርጎ አቀፈኝ እነዚ እብዶች ጊቢውን በጩኸት አጥለቀለቁት ናዙዬም እቅፍ አርጋ ሳመችኝ እኔ ደግሞ ነከስኳት አቤት ሰላም የሀናን አንተ አይደለህም ወይ የሚለውን መዝሙር ከፍተን ጊቢውን በአምልኮ በጠበጥነው የቸርቻችን ፓስተሮች ሽማግሌዎች አንድ አልገሩም ነበር በቃ የእሁድ አምልኮ በሉት ከዝማሬ በኋላ ቃል ፀሎት 2 ሰአት ሲል ነገ ሰርገኛም አደለን ወደ የቤታችን ለመሄድ መሰነባበት ጀመርን እኔን ደግሞ ልዑል ያፌት እና ናዙ በልዑል መኪና እስከ ቤት አደረሱኝ ቻው ብያቸው ልወርድ ስል ልዑሌ ጠዋት ስንት ሰአት መጥቼ ልውሰድሽ አለኝ ኸረ ታመራለህ እንዴ መጀመሪያ ሽማግሌ ላክ አልኩት ሁሉም ሳቁና አንቺ የምሬን ነው ሲለኝ በቃ ተዘጋጅቼ ስጨርስ ይደወልልሀል ብዬው ተሰናብቻቸው ወደ ቤቴ ገባሁ ከጊቢ አስከ ቤት የሮጥኩት ሩጫ ያልተሰባበርኩ ሳሎኑን በርግጄ ገባሁ ሳሪ ና ጀሚላ የተለያየ ሶፋ ላይ ጋደም ብለዋል ምነው ብለው ሁለቱም ደንግጠው ተነሱ ኡኡ ብዬ እየጮሁኩ አቀፍኳቸው ከልዑል ጋር እኮ ታረቅን ብዬ ቀወጥኩት የምር ብለው ሁለቱም አበዱ ከዛ ደንግጠው ፀጥ አሉ ምነው ብዬ ዞር ስል አባቢ ከኋላዬ ቆሟል እኔም ፀጥ አልኩ ለካ መኝታቤት ነበር እኔ የሌለ መስሎኛል ጩኸቴን ሰምቶ ነው የመጣው ማነው ልዑል ብሎ ኮስተር አለና የያዘውን መፅሀፍ ጠረጴዛው ላይ ወረወረው ።


ከዛ ተቀመጠ ቆሜ አጆቼን ማንቋቋት ጀመርኩ መልሽሺልኝ እንጂ ብሎ ጮኸ እንዲ ሲቆጣ ከተወልድኩ አይቼ አላውቅም የሩሀ ወንድም ነው ባለፈው ሆስፒታል የወሰደህ አልኩት ከት ብሎ ሳቀና መጥቶ አቀፈኝ ምነው አባ ስለው እጠረጥር ነበር ከተሻለኝ በኋላ አንዳንዴ በመኪና ስዞር ለሁለት የካፌዎች በር ላይ ምናም አዘውትሬ ሳያቹ ገመትኩ ግን የኔ ልጅ ትምህርትሽን በማይጎዳ መልኩ ይሁን ደሞ ልጁን እተማመንበታለሁ የልጅ በሳል ነው ከአቶ መሳፍንት ጋር ልታዛምጂን ነዋ የኔ ጀግኒት አለኝ በደስታ ተጠመጠምኩበት በይ የሚቀጥለው እሁድ እዚ ትጠሪውና በደንብ ይተዋወቀኝ ምሳ እንጋብዘዋለን ጓደኛሽንም ጥሩ እህት ናት ያለችው እነሱን በማግኘትሽ በዕውነት እግዚያብሔር አድሎሻል በጭራሽ አታስከፊአቸው አለኝ እሺ አባ ብዬ እሱም ተመልሶ ተቀመጠ ጀምስን እንድትንከባከባት እቤታችን የመጣች ልጅ አለች እሷ ቡና እያፈላች ነው ልብስ ልቀይር ብዬ ወደ ላይ ወጣሁ እነ ማርኩ ክፍል ስገባ ተኝተዋል እንዲሁ ስሜአቸው ክፍሌ ገባሁ ልብሴን ቀያይሬ ልዑል text ሲፅፍልኝ ደወልኩለት አረጅም ሰአት አወራን አባቢ ያለኝን ነግሬው እሱም በጣም ተደስቷል በቃ ሳሎን ልሂድ እየጠበቁኝ ነው አንተም እረፍት አድርግ ብዬው ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ ሳሎን እራት ተበልቶ ቡና ጠጥተን ፀልየን ተጨዋውተን ተኛን እኔስ ምኑን ተኛሁት ከመች መች ነጋ እያልኩ ነው ያውም ልዑል መጥቼ ወስድሻለሁ ብሎኝ ስልኬን ሳይ ገና 8:ሰአት ነው ለመተኛት እየሞከርኩ ነው .......

.......ይቀጥላል........

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

#እንዲህም ይፃፋል 👏👏👏👏👏👏

#ምድብ_B


ነብሱን እስከ መስጠት እኛን የወደደን
የዘላለም ወጃጅ ኢየሱስ አለልን
አለው እኔ በኔ ሳይሆን በርሱ ምርጫ
የመኖረ ምክንያት ሆኖልኝ ፀጋው ብቻ
ይሄ ነው አምላኬ እንድሁ የወደደኝ
በአንድያው ልጁ መርጦ ያጸደቀኝ
በቃሉ ተጠርታ የተፈጠረች ምድር
ሰሪዎ ሲወለድ መች ቻለች ማሳደር
በግጥም በመዝሙር በእጄም ሆነ ባፌ
ለሱ ልቀኝለት በሱ ነው ማረፌ
ይቅርታ ይቅርታ ልድገመው ይቅርታ
እንደውም ያንሰኛል ጠዋት እና ማታ

እንደ ጥላቴ እቅድ ቢሆን ኖሮ
አልኖርም ነበር ዘንድሮ
ሲጠጉ ወዳንተ ወደ ደረትክ
በነው ይጠፋሉ ሀሳብና ጭንቀት
እርሱ ብርሃን ነው ላሉ በሞት ጥላ
የሀጥያጥያተኞች ወዳጅ ጠበቃ ከለላ
እርሱ ለሰላሙ ፍፃሜ የለውም
እርሱ ፃዲቅ አምላክ እንከን አያውቀውም
ሌላ ህይወት በፍፁም አይሆንም
ሰወች እንመነው ያለሱ አይሆንም
እርሱ ከወደደን ከነ በደላችን
ለምን እንራቀው አይሂድ ከደጃችን

ዝም በይ ብሉኝ ዝም የማልልው
ውለታው ብዙ አለብኝ ቆጥረ የማልጨርሰው
መች ሳላዉቅ ቀርቼ የተደረገልኝ
ቃላት አጣሁ እንጂ የልቤን ሚገልፅልኝ
እና ምን እላለሁ ከማመስገን በቀር
ቢወራ አያልቅም ቢዘመር ቢዘመር
ተናግሬው አያልቅ የጌታዬ ፍቅር

በሞትህ ሞተን ገለህ ህይወትን የሰጠሄኝ
እርግማነን ሽረህ ፅድቅን ያለበስከኝ
አቦ ልክ ብለሃል እግዚአብሔር ይባርክህ
ጸጋውን አብዝቶ ፊቱንም ያብራልህ
የኔ አምላክ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ዘለዓለምን ፈጠራ በወዘላለም የምትኖር

እስኪ ልንገራችሁ አንደ ስሙኝማ
ዘመኑን እንዋጀው ሕይወት ሳንቀማ
አንተ ያልሰማክ ስማ ይሄ ቃል ላንተ ነው
ሳይረፍድ አስገባው ጌታ በደጅህ ነው
በሩ ሳይዘጋ ሙሽራውም መቶ
ፋኖሱ ይሞላ ጋዙ ተዘጋጅቶ
በሩም ቶሎ ይከፈት ሙሽራችን ሳይሄድ
እሱ ነው ብርሃን እውነት እና መንገድ
በሉ ተዘጋጁ አለም ጊዜዋ አልቋል
ውዱ ሙሽራችን እየሱስ ይመጣል


#ምድብ_B

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

eyalek nw tinish dekika bicha tagesu

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ahun hulunm gitim andi lay adrge orderd adrge lekewalew….

Yedagna dimtsi ke 30%
Ye like bizat demo 70% yihonal malet new ina yashenefe demo 🎁 alew

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ምድበ A yibekachiwal ke 28 bewala yalew ayikatetim

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Ye ምድብ A & ምድብ B abalat be english tsufet yetetsafutin gitimoch wede amrign bemelewex yitebaberun

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Beka inijemiralen bemidibachu giximun be 3 dekika wsx laku yifxen 3tu dekika kaleke waaa…..

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Hulet ayinet chaweta yeminichawet yihonal….

1, yemejemeriyaw be group hulet hulet sinign iyawaxan 1 gixim metsaf new..
#Rule
Gitimu menfesawi mehon alebet
Yetetsafewn gixim azegajuna hulum betesexew dekika wusx yerasu group comment bota wsx yiposital….ye group meposechiyawn ine lekilachiwalew ahun le 5 dekika yakil hulachum 2 sinign Bicha gixim tsafu azegaju kezan ine group comment place siposit hulachum be groupachu yazegajachutin tilikalachu

Tereditachiwal aa yalkutin??

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

Bemejemeria 2 bota inikafelina inijemiralen ina hulet midib inawxa inaa

ምድብ A
ምድብ B

Yefelegachihutin midib mirexu comment lay yemerexachihutin tsafu

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

ክፍል 3⃣0⃣

እራሴን ሳትኩ ለስንት ሰአት እንደተኛሁ ባላውቅም ስነቃ እራሴን የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ተኝቼ አገኘሁት በመጀመሪያ ደብዘዝ ያለ ነገር ብቻ ነበር ሚታየኝ በደንብ አይኔ ሲገለጥ ሳሪ ፊትለፊቴ ቁዝም ብላ ተቀምጣለች አይኔ መከፈቱን ስታይ ሩሃ ነቃሽ ብላ ወደ ውጪ ወጣች ነርሷን ይዛት መጥታ ካወራችኝ በኋላ ምን ሆኜ ነው አልኳት አይዞሽ እራስሽን ስተሽ ነበር አሁን ደህና እየሆንሽ ነው እረፍት አድርጊ አለችኝ ሳሪ ልዑል ጋ ውሰጂኝ አልኳት ነርሷ አይሆንም ትንሽ አገግሚ በምግብ መጎዳት እና አእምሮሽ በጣም መጨናነቁ ነው እራስሽን እንድትስቺ ያደረገሽ ስለዚ እረፍት አድርጊ አለችኝ ባይዋጥልኝም ምን አመጣለሁ እሺ ምን ሆኖ ነው እንደዚ የሆነው አልኳት ጀምስን ትምህርት ቤትም ቸርችም ያደርሳት የነበረው እሱ ነው እናም ዘማሪ መሆኗን ሀይማኖት መቀየሯን ቤተሰቦቿ ሲሰሙ ልዑል ባልዋ መሰላቸው ያቤፅንም ትምህርት ቤት አብረው ስለሚያደርሱት ታላቅ ወንድሟ እቤትም ወደ ሀይማኖቷም እንድትመለስ ብዙ ለመናት እናቷም አባቷም ተለመነች አልሰማ ስትላቸው ሀሳባቸውማ ልዑልን ገለውት ሲቸግራት እቤታቸው ምትመለስ ነበር የመሰላቸው ከዛም ሆን ብለው መኪና እያሽከረከረ በከባድ መኪና ገጩት እናም የአንቺ አምላክ አሁን ባይነቃም የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ ነግረውናል ተረጋጊ አለችኝ እሺ ጀምስስ አልኳት ትመጣለች እቤት ምሳ ልታመጣ ሄዳ ነው አለችኝ ደግሞ ልዑል ላይ ጉዳት ያደረሰው ወንድሟ መሆኑ ተረጋጥጦ እስር ቤት ይገኛል አለችኝ እኔም ከቆይታ በኋላ ወደ ጤንነቴ ተመለስኩ ልዑልን ካየሁት እስከሁለት ሳምንት ምንም ለውጥ አላመጣም ነበር ከሁለት ሳምንት በኋላ ነቃ በመጀመሪያ እስኪያገግም በክራንች ወር ምናምን ተንቀሳቀሰ አሁን ወደ ሙሉ ጤንነቱ ተመልሷል ሳሪም ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች አባቢ ሁለት ሴት ሁለት ወንድ ሆነለት ሁላችንም ደስተኛ ሆነናል ያው ይሄም ክረምት ተገባዶ ወደ ጊቢ ልመለስ ነው ጀምስም እንደራሷ ዘማሪ ልታገባ ነው ናዙ ደግሞ ታላቋ እያለ በሚል እኔ ትምህርት እስክጨርስ እየተጠበቀ ነው እጮኛዋ ዘላለም ይባላል እየደወለ ኸረ አንቺ ልጅ አየር አትያዢ ቶሎ ተምረሽ ውጪ እናግባበት ይለኛል ገና ተመርቄ 9 አመት ቆያለሁ እያልኩ አበሽቀዋለው ልዑል የወደፊት ቤቱን ማሰራት ጀምሯል ተንቀባርሬ እየተማርኩ ነው እንደ ጠላትም እንደ ማህሌትም ሀሳብ ሳይሆን እነደ እግዚያብሔር ቸርነት ዛሬም አለሁ ።


እናም ትምህርቴን ጨርሼ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተመርቄአለሁ እቤት ቀውጢ ፕሮግራም ተዘጋጀልኝ ከማያ ጋርም እንደዋወላለን ልዑል በዝምንድና ምናምን ሚባል ነገር አያውቅም በተመረኩበት ሙያ ስራ ጀምሬያለሁ 1 አመት ሞላኝ ስራ ከጀመርኩ እናም በህይወቴ የምጓጓለት የሰርጌ ቀን እሁድ ነው ናዙ ሚዜዬ ብትሆን ደስ ይለኝ ነበር ግን እሷም በወንድሟ ሰርግ ቀን ልትሞሸር ነው እነ ንግስቴ ሴት ልጃቸውን ሊሸኙ የወንድ ልጃቸውን ሚስት ሊቀበሉ ዝግጅት ላይ ናቸው በነገራችሁ ላይ ልዑል አብረን ምንኖርበትን ቤት ሰርቷል እዛ መኖር ከጀመረም ሰነባብቷል ቢሆንም ግን ሰርጋችን የሚሆነው ተወልዶ ባደገበት ቤተሰቦቹ ቤት ነው እነ አባቢም እኔን ለመዳር መላው ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ ቤታችን ቀውጢ ሆኗል የታናሽ ወንድሜ ስም ናቲ ነው አሱም እያደገልን ነው ሳሪ የእንጀራ እናት ሳትሆን ልክ እንደወለደችኝ የኔ ነገር አይሆንላትም እናቴ አብራኝ ብትኖር እንዲ አድጌላት ላገባ መድረሴን ብታይ ምን ነበር ግን እግዚያብሔር በስራው ትክክል ነው ማያ ለኔ ሚዜ ለመሆን ከሀገሯ መጥታለች አስከዳር እና ጀምስም ከቲማችን ልጆች እነ ቤዚ የሚሊ እጮኛ ቅድስቴም ሚዜዎቼ ናቸው ሚሊም አስከዳርም ትምህርት ጨርሰው ሰራተኛ ሆነዋል እናም እግዚያብሔር ሲያከብር የባለስልጣን ሰርግ እስኪመስል በምወዳቸው ሰዎች ተዳርኩ ናዙዬም በአንድ ቀን ከምርጧ ጓደኛዬ ጋር አገባሁ ለ1ሳምንት እነ ንግስቴ ጋር ነበርን ከዛ ወደ ቤታችን የምንገባ ቀን የኔም የልዑሌም ቤተሰቦች ተገኝተው ወደ አዲሱ ቤታችን መርቀው አስገቡን እግዚአብሄርን አያመሰገንኩ ከውዱ ባሌ ከልዑል ጋር አብረን መኖር ከጀመርን 1አመት ከ 1 ወር ተቆጠረ በዚህ ላይ ወንድ ልጅ ወልጄ 4ወር ሆኖኛል ያው እናቴ ሳሪ ጋ ነው የታረስኩት አሁን ወደ ቤት ተመለስኩ ልጃችን የአብ ቃል ልዑል ይባላል የሳሪን ታናሽ እህት አምጥታልኝ ከኛ ጋር ትኖራለች ልዑሌ ባል የሚለው ቃል አይገልፀውም በእኝክብካቤ እና በፍቅር ነው የሚያኖረኝ ልጃችንንም ከእናት በላይ ነው ሚንከባከበው ቲማችን አሁንም አለ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔርን እያመገንን በሰላም እየኖርን ነው ።

_ተፈፀመ_
THE END

ህይወት ይቀጥላል ...............

💐💐 💐💐
💐💐 🙏ተባረኩ🙏 💐💐



━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ግር ያላት ነብስ የመጨረሻ ክፍል #ዛሬ ማታ 2:30 ይጠብቁ። አጨራረሱን እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለው።

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

.............ክፍል 2⃣9⃣ ..........



በድን ሆኜአለሁ በምናብም ይሁን በደመነብስ ምንም ሳይገባኝ ፈተናው አለቀ ልሄድ ወስኜአለሁ ሁሉም እኔ ካልደወልኩ አይደውሉም የልዑል ወሬም የለም ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመለስኩ እቤት ስሄድ ሳሪ ሶፋው ላይ ጋደም ብላ ቲቪ እያየች ነበር ልመጣ ነውም አላልኳቸውም ሳሪ እንዳየችኝ ደንግጣ ከተኛችበት ተነሳች ጀምስ ቤት የለችም መሰለኝ ሩሃዬ ምነው ጠቋቆርሽ ብላ አቀፈችኝ ምንም አላልኳትም የፈረደበት እንባዬን ለቀኩት አባቢም ከመኝታ ቤቱ እየመጣ መሰለኝ ገና ሲያየኝ ደርቆ ቀረ የኔ ልጅ ምነው መጣሁም ሳትዪ ደሞ ምነው ከሳሽብኝ ልጄ አለኝ ከሳሽ ጠቆርሽ ምን ያደርግልኛል ልዑል ጋር ውሰዱኝ አልኳቸው ሁለቱም ተያዩ ምን ዝም ያስብላቹአል ልዑል የት ነው ጮኹኩባቸው ለእንባዬ ልክ አልነበረውም ስለ ልዑል ቀርቶ የጠላቴንም ክፉ ዜና መስማት አልፈልግም ሁለቱም በዝምታ አንዴ እኔን አንዴ መሬት መሬቱን ያያሉ ለምን አትነግሩኝም ልዑል የት ነው ድጋሚ ጮኹኩ አባቢ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ተቀመጪ መጀመሪያ ከዛ እንንገርሽ እስቲ ነይ ተቀመጪ ብሎ እጄን ጎተት አረገኝ በጩኸት ቆሌውን ገፈፍኩት ተወኝ የት እንዳለ ንገረኝ መቀመጥ ብችልማ እዛው እቀመጥ ነበር የት ነው ልዑል አልኳቸው ሰለቻቸው መሠለኝ ሁለቱም ትተውኝ ተቀመጡ ። ተዉት እንደዉም ብዬ እንደ እብድ እየከነፍኩ ወጣሁ አባቢ እየተከተለኝ መጣ ይዞ ሊያስቆመኝ ሞከረ በፍጥነት እየተራመድኩ ጥዬው ታክሲ ይዤ እነናዙ ቤት ሄድኩ እንደገባሁ ሳሎን ውስጥ ሰራተኛቸው ብቻ እያፀዳዳች ናት ሩሃማ ምነው መች መጣሽ ብላ ደነገጠች ልዑልስ አልኳት ሁኔታዬ ወደ ህመም እየወሰደኝ ሰማይ ምድሩ እየዞረብኝ ነው
ንገሪኝ ልዑልስ አልኳት እኔ እንጃ እዚ ከመጣ ወር ያልፈዋል አለችኝ እየተንተባተበች እሺ እነናዙስ አልኳት በዚህ መሀል አባባ መጣ እንዳየሁት አባባ ልዑልስ አልኩት ፊቱ አዘነ እግሩ ስር ወድቄ አለቀስኩበት ተነሽ ለጄ አዝኗል ድምፁን አስለመለመው ነይ እሺ አለኝ ተከተልኩት በረንዳው ላይ ወንበር ሰጥቶ ተቀመጪ አለኝ ንዴቴን አትጠይቁኝ አልቀመጥም ልዑል የት ነው ቆይ አላሳዝናቹም እሺ ልንሄድ ነው ሹፌሩን ልጥራው አለኝ ደውሎ ጠራው መሰለኝ ቆይቶ መጣ አብረን ሄድን አምላኬ ሆይ ምን ልታሰማኝ ይሁን ፍርሀት ፍርሀት እያለኝ ነው ደረስን ጉድ በሉ ሆስፒታል ነው የመጣነው ወደ ውስጥ ስንገባ ናዙን እንድ ክፍል በር ላይ አየኋት እነአባባን ጥያቸው ወደ እሷ ሮጥኩ አፈችኝ ናዙ ልዑልስ በለቅሶ ብዛት ራሴን ያዞረኛል አይኔን ማርገብገብ እንኳን አቅቶኛል ወደ ውስጥ ከፍቼ ስገባ ሰውነቴን ነዘረኝ ልዑል አልጋው ላይ ተዘርግቷል ጭንቅላቱ ታሽጓል ግሉኮስ ተደርጎለት እንዳልነቃ ያስታውቃል በለቅሶ ክፍሉን በጠበጥኩት ናዙ ልታረጋጋኝ ብዙ ሞከረች እጆቼም እግሮቼም ተብረከረኩብኝ ድሮም ታምሜያለሁ እራሴን ሳትኩ ......

.......... ይቀጥላል........

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

............ክፍል 2⃣7⃣...........

.......ሰሞኑን ደሞ የጊቢ ምድብ ይነገረናል አሁንስ ባር ባር አለኝ ግን ደግሞ ዩንቨርስቲ የመግባት ጉጉቱም አለ እናም ምድብ ተነገረን እስከዳር መቀሌ ሚሊ ጂጂጋ እኔ ደግሞ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ደረሰን ሁሉም በኔ መሄድ እንደከፋቸው ያስታውቃሉ ግን ግድ ስለሆነ ደስተኛ ለመምሰል ይሞክራሉ በቃ ሰሞኑን እየከፋኝ ነው ደግሞ መለስ እልና ያንን ሁሉ መከራና ችግር በእግዚያብሄር አልፌ የምን ፍርሀት ነው ብዬ አስባለሁ እና ነገ ባህር ተጓዥ ነኝ ልዑልና አባባ ናቸው አብረውኝ የሚሄዱት ከቸርች የአገልግሎት መሸኛ አፅፌ አዘጋጅቼአለሁ እና እነ አባባን እና እነ ንግስቴን ለመሰናበት እነ ናዙ ቤት ከልዑል ጋር እየሄድን ነው ሩሀዬ እንዳይከፋሽ እሺ በተቻለኝ አቅም ከናዙ ጋር እየመጣሁ አይሻለሁ ደግሞ ቶሎ የ fellow ህብረት አጠያይቀሽ ለመቀላቀል ሞክሪ አለ አደል ከመንፈሳዊነት የሚያርቁ ብዙ ነገሮች አሉ በዛ ላይ መጥፎ ጓደኞች ካጋጠሙሽ ለመጥፋት ቅርብ ነው በፀሎት በርቺ ትምህርትሽ ላይ ትኩረት አድርጊ በቃ ምክር ትጠላላቹ ተዘከርኩ ለጉድ እቤት ደርሰን የሽኝት ፕሮግራም በሉት ናዙዬ ቀውጢ ፕሮግራም አዘጋጅታለች ተወዳጁ ቲማችን ሁሉም ተሰባስበዋል እስከ 1 ሰአት እነ ናዙ ቤት አሳለፍን እነ ንግስቴን ተሰናበትኳቸው የናዙ እና የንግስቴ ለቅሶ ለዘላለም ምሄድ አስመሰሉት እኔም ተረበሽኩ ልዑል የምን ሻንጣ እንደሚጭን እንጃ ከቤት እያወጣ መኪናው ውስጥ ይጭናል እስከ በረንዳው አወጡኝ እና ናዙ እጄ ላይ ብር አስራልኝ ስማኝ እያለቀሰች ገባች በቃ ይቅናሽ በሰላም ተሳክቶልሽ ወደ ሀገርሽ ይመልስሽ ብለው አባባም ንግስቴም መረቁኝ በቃ እንሂድ ብሎኝ ወደ መኪናው ገባን ከኋላ ሁለት ትልልቅ ሻንጣዎች አሉ አንተ የምን ሻንጣ ነው አልኩት ይዘሽው ምትሄጂው ልብስ ነው ከናዙ ጋር ነው የገዛነው አለኝ አንተ ያምሀል አሜሪካ ነው እንዴ ምሄደው አልኩት ፈገግ አለና ይሁና ደግሞ ላንቺ ምን አለበት አለኝ እሺ አልኩት እሺ አንዴ ብቻ አይንሽን ጨፍኚ አለኝ ጨፈንኩለት አንገቴ ላይ የሚያምር ወርቅ ነበር አሰረለኝ በጣም ያምራል አመሰግናለሁ አልኩት የራስ ሰው አይመሰገንም አለኝ በዚህ አላበቃም አሁንም ከኪሱ ትንሺዬ ሳጥን አውጥቶ ቀለበት አሰረልኝ እስክሞት እጠብቅሻለሁ አለኝ እኔም አልኩት እቤት አድርሶኝ በጠዋት መጣለሁ ብሎኝ ተመለሰ እቤት ሁሉም ከፍቶአቸው በዝምታ ተውጠዋል ሳሪማ ቆዝማለች በናታቹ እኔን አትረብሹን እናንተ ቢያንስ አንዳቹ ለአንዳቹ አላቹ እኔ ግን ብቻዬን ነው ምሆነው ስለዚህ በደስታ ሸኙኝ አልኳቸው ሁሉም ስጦታ ሰጡኝ አመስግኛቸው ትንሽ ተጫውተን ተኛን ።


ጠዋት በጊዜ ተነስቼ ለባብሼ ልዑል የመጣቸውን ሻንጣዎች እቤትም የተዘጋጀልኝን ሁሉ አዘገጃጅቼ ወጣሁ አባባም ለባብሶ ተዘጋጅቷል በልዑል መኪና ነው ምንሄደው ሳሪ ቁርስ አብልታን ጀምስም መክራኝ እያለቀሱ እየረበሹኝ ነው ከጠዋቱ 2:46 ይላል ስልኬ አባባ እሱን ተንው ብሎ ሌላ ስልክ ሰጠኝ አመስግኜው በዚህ መሀል ልዑልም መጣ እነ ማርኩንም ሁሉንም ተሰናብቼ ጉዞ ወደ ባህር ዳር በሰላም ደረስን ሆቴል ክላስ ይዘን ከኔ ጋር 5 ቀን ቆዩ ቆይ ትመዝገብ ሲሉ ቆይ ዶርም ትያዝ ሲሉ እኔ እዛው ጊቢ እውልና መጥተው ይወስዱኛል እንግዲ ከኔጋር አይኖሩ ተሰናብተውኝ ሊመለሱ ነው አሁን አምርሬ እንደ ህፃን አለቀስኩ በዚ መሀል የተዋወኩአት ማያ ምትባል ልጅ ብዙም ጠልቄ አላወኩአትም ቢሆንም በጣም ትሁት ናት አንድ ዶርም ነን እሷን ወንድሟ አድርሷት ወዲያው ተመልሷል አፅናንታኝ እንደምንም እያሳዘንኩአቸውም ቢሆን ለመመለስ ተገደዱ ።

እንግዲህ የጊቢን ህይወት ከተቀላቀልኩ 6ወር ከ12 ቀን ሆኖኛል በመሀል ናዙና ልዑል መተው አይተውኝ ተመልሰዋል የ software የኢንጂነሪንግ ተማሪ ነኝ ከማያ ጋር ላይብረሪ እናሳልፋለን ፌሎም አብረን ነው የምንሄደው በፌሎ ከብዙ ልጆች ጋር ተግባብተናል እንደውም አገልገሎት ጀምረናል ደስ የማይሉም ደስ የሚሉም ነገሮች እያጋጠሙኝ የነ ልዑል የነ አባባ የሁሉም ናፍቆት ቢኖርም ችዬው
እያጋመስኩት ነው .......


............ይቀጥላል ............

---------------"""""""""""""""""-------------
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

............ክፍል2⃣5⃣..............

...አጠገቧ ስለ ፈተናው አላወራም እናም የማይደርስ የለም ዛሬ ሰኞ ነው ኢንትራንስ ልንፈተን ነው ፍርሀቴን አትጠይቁኝ በጠዋት ሳሪ የሚገርም ቁርስ ሰርታ እንደ ህፃን ልጅ እያጎረሰችኝ በላሁ ልዑል የመኪናውን ክላክስ አጮኸልኝ ያው ስልክ ተይዞ አይገባም የታወቀ ነው የመፈተኛ ማቴሪያሎቼን ብቻ ይዤ ወጣሁ አባቢም ጀምስም ሳሪም ይቅናሽ ብለው ሸኙኝ አየሩ ደመናማ ነው ብርዱ ና ድንጋጤው አንድ ላይ እያብረከረከኝ ነው መኪናውጰውስጥ ገብቼ ሰላም አልኩት እሺ ተፈታኟ የረሳሽው የገር የለም እንሂድ አለኝ አዎን አልኩት ኡፍ እንዲ ፈርቼ አላውቅም መኪናው ውስጥ የሳሚን ሁል ጊዜ መልካም የሚለውን መዝሙር ከፍቷል በዝምታ ተዋጥኩ ሩሀዬ ፈርተሻል እንዴ አለኝ አዎን በጣም አልኩት እንዴ ጠንከር በይ እንጂ እራስሽን ነፃ አርጊ ለዛሬ ነው የፈራሽው ስታይው ይቀልሻል አለኝ በትንሹም ቢሆን እየተረጋጋው ነው ትምህርት ቤት ደረስን ኡፍፍፍፍ በቃ ቻው አልኩት በቃ በጊዜ መጣልሻለው አትጨናነቂ እሺ አለኝ እሺ አልኩት በቃ መልካም ፈተና አለኝ መልካም ቀን ብዬው ወረድኩ ያው ተፈትሼ ገባሁ ሁሉም እንደእኔ ፈርተዋል ማለት እኔ የማውቃቸው ጓደኞቼ የሚገርማቹ ከጠበኩት በላይ እግዚአብሔር ረዳኝ በብዛት ያጠናሁት ነው አንዳንዱ ቢከብድም ዞሮብኝ ተፈትኜ ወጣሁ ኡፎፎፎፎይ በጣም እንደፈራሀለት አደለም የነገና የእሮቡንም አንተ ከኔ ጋር ሁን እያልኩ ጓደኞቼን አውርቻቸው ስለፈተናውም ያው አመል አይለቅም ቲማችን ምንሰበሰብበት ቦታ ስሄድ ሁሉም አሉ በጣም ስለናፈቁኝ ሁሉንም ተጠምጥሜ ሰላም አልኳቸው ትንሽ አውርተን ተሰነባበትን ከጊቢ ስወጣ ልዑል እየጠበቀኝ ነው እእእ እንዴት ነበር አለኝ አሪፍ ነው ብዬ ፈገግ አልኩለት ዋናው አለመጨናነቅሽ ነው የኔ እናት አለኝ ባይገርምህ በጣም ነው ሚቀለው ስለው ጉረኛ እስቲ እስከመጨረሻው እናይሻለን አለኝ ምን ታካብዳለህ አልኩት እሺ እማዬ ናፈቀችኝ ብላለች እቤት እንሂድ አለኝ እኔም በጣም ነው የናፈቀችኝ አባባም ናዙም ግን አንቆይም እቤት ይጠብቁኛል አልኩት ለሳሪ በሱ ስልክ ደውዬ እነ ናዙ ጋ እየሔድኩ ነው ቶሎ ነው ምመለሰው ልሂድ አልኳት ሳቀችና እሺ የኔ ልዕልት ቶሎ ተመተሺ ስለፈተናው ስትመጪ ትነግሪኛለሽ አለችኝ እሺ አልኳት በነገራችን ላይ በፊት ማስፈቀድ ምናምን ሚባል ነገር አላውቅም ልዑል ነው ያስተማረኝ የሚሄድበትን ወይ ለንግስቴ ወይ ለአባባ ሳይናገር በተአምር አይወጣም አሁንም ደውይላት ያለኝ እሱ ነው ከሁሉ በላይ የማደንቅለት ስነ ስርአቱን እና ለመንፈሳዊነት ያለውን ቦታ ነው በሁሉ ነገር ሲሪየስ የሆነ ሰው ነው በስራ ይጠመድ እንጂ ስለ መፅሀፍ ቅዱስ ሲያወራኝማ ከራሱ እንደማይናገር ያስታውቃል እንደሱ አይነት ወንዶች ቢበዙ ምኞቴ ነው እቤት ደረስን ንግስቴም አባባም አሉ ሁሉንም ሰላም ብዬአቸው ተጫውቼ ቤት ይጠብቁኛል ብዬ ተነሳሁ ናዙ መጣች ወዴት ወዴት እንደውም ከኔ ጋር ነው ምታድሪው እኔ ሰመጣ ነው ለመሄድ የተነሳሽው አለች እውነት ነገ መጣለሁ አልኳት አልፈልግም እዚሁ ካልሆንሽ ብላ ሙጥኝ አለች ልዑል ግን አይሆንም ናዙ ነገ አመጣታለው ቤት አልቆይም ብላ ሳትገባ ነው የመጣችው ደሞ ከፈተናዋ በኋላ ብዙ ጊዜ አላቹ አላት ባትፈልግም ልዑል ሲያመር ስለምትፈራው አኩርፋ ወደ ክፍሏ ሄደች ልከተላት ስል ተያት ዘላለሟን ህፃን ናት ሳሪ ታዝናለች ይሄኔ እየጠበቀችሽ ነው እንሂድ አለኝ ወደ ቤት አደረሰኝ ካልገባህ ብዬ ስለምነው አይሆንም አማች ቤት ዝም ብሎ አይገባም አለኝ ነው እንዲ ከሆነ እኔም አልመጣም አልኩት እህህህህህ አንቺ እኮ ሴት ነሽ እንደውም ስትቀሪ ነው ሚደብራቸው ደግሞም ቤትሽ ነው አለኝ ሂድ እዛ የሆንክ የወጣት ሽማግሌ ብዬው ወርጄ ገባሁ እነ ማርኩ ገና ከበር ስገባ ተጠመጠሙብኝ ቤቱ እንደተለመደው ሞቋል ስለፈተናው ጠይቀውኝ ነገርኳቸው


በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው አለቀ ውይ አሁን ግልግል ነው ደስ ሲል ልዑል የኔን ፈተና መጨረስ አስመልክቶ ሀሙስን ከናዙ ጋር ሲያዝናናን ዋለ ደስ ሲል አሁን ቲማችን እንደ ድሮው መገናኘት ጀምረናል ዛሬ ሚሊ በናታቹ አንድ ነገር ተባበሩኝ አለን ምን አልነው ነገ የቅድስቴ ልደት ነው እስከዳር የብሩክቲ አለችው አዎን አለን ያው ቅድስቴም ብሩክቲም ስሟ ነው እና ነገ አብረን ሰርፕራይዝ እናድርጋት አለን ተስማማን እንደተስማማነውም ፏአድርገን አከበርንላት በናታቹ ደስ ስትሉ እኔንም አቀላቅሉኝ አለችን ናዙ ኸረ ደስ ይለናል አለቻት ከኛ ጋር ማጥናት ጀምራለች አሁን ትምህርት ተዘግቶ ሁሉም እረፍት ላይ ነው በፊት ዩኒቨርሲቲ የሄዱት የቲማችን ልጆች መጥተዋል በቃ ተሰባስበን የሚገራርሙ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀን ክረምቱን አሳለፍን አሁን ደግሞ ውጤት ሊለቀቅ ነው ተብለን መንቆራጠጥ ላይ ነን ግን ለአመታት ከልዑል እኚን ከመሰሉ ቤተሰቦቼ ከቲማችን ከናዙ ከነዚ ሁሉ ሰዎች ተለይቼ ልኖር ነው? ውይ ሲጨንቅ ቅዳሜ ውጤት ይለቀቃል ተብለናል ..........

............ይቀጥላል.................

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

😔ግር ያላት ነብስ😔

........... ክፍል 2⃣4⃣..............

ለመተኛት እየሞከርኩ ነው ግን ብታምኑም ባታምኑም ሳልተኛ ሰአቱ 11:45 ይላል ።ህፃን እንኳን እንዲህ አይሆንም ተነስቼ ሻወር ወሰድኩ 12 ሳት ሲሆን ሳሪ እንደማልተኛ ስለምታውቅ መጣች ፀጉሬን በፓየስትራ አሳመረችልኝ ቀሚስ መርጣልኝ እራሴን እስክጠራጠር ድረስ አስዋበችኝ እየተንቆራጠጥኩ ሚሊ ደወለ በቲም እንሂድ መኪና ተዘጋጅቷል አለኝ አይ ሚሊ እኔ ከነልዑል ጋር ነው ምሄደው አልኩት ነው ከአሁኑ ካድሽን አለኝ አይ ሚሊ ማለት ስለው ኸረ ስቀልድ ነው በቃ እዛው እንገናኝ ብሎኝ ተሰነባበትን ከዛም ለልዑል ደወልኩለት እየመጣው ነው አስጠበኩሽ እንዴ አለኝ አይ ቀስ ብለህ ና አልኩት እሺ በቃ ጠብቂኝ አለኝ ስልኩን ዘግቼ ወደ ሳሎን ሄድኩ ሁሉም ሲያዪኝ ፈገግ አሉ አባቢ እንዴ የኔ ልጅ በሰው ሰርግ እንዲ ያማርሽ በራስሽስ ሰርግ እንዴት ልትሆኚ ነው አለኝ ሁሉም እንጃላት ብለው ሳቁብኝ እህህህ እንዳላወልቀው አልኳቸው እሺ ላድርስሽ እንዴ አለኝ አባቢ አይ ልዑል እየመጣ ነው አልኩት ወዲያው ደወለልኝ እንደውም መጣ ብዬ ቦርሳዬን ይዤ ተነሳው ኸረ እንዳትወድቂ በዚ ጫማ አቤት መንገብገብ ብላ ሳሪ አበሸቀችኝ ሆሆሆ ሰዎቹ አበዱ እንዴ ዘበኛችንም እንዴ ወዴት ነው እንዲ ተሞሽረሽ ኸኸኸኸ ዛሬ ነብሷን ይማርና እትዬን መሰልሽ በውበት ሚደርሳት አልነበረም አለኝ የኔ ደግ እናት መቼም አልረሳትም ምን አለ ብትኖርልኝ ቁጣዋ ፍቅሯ የሆነ ቦታ ስወጣ በግድ ምግብ ምታበላኝ ነገር ብቻ ብዙ ብዙ ነገሯ ከጊቢ ስወጣ ልዑሌ መኪናውን ተደግፎ ቆሟል አቤት ውበት እንዴት ልግለፅላቹ አንተ አንተ ነህ ወንድምህ ነው ሚሞሸረው አልኩት አንቺስ በቃ በዚሁ ልውሰድሽ እንዴ አለኝ አደል ሲያምርህ ይቀራል አልኩት ግንባሬን ስሞኝ የመኪናውን በር ከፈተልኝ ገባሁ በሩን ዘግቶ ዞሮ ገባ የባጥ የቆጡን እያስቀባጠረኝ ደረስን ከትናንቱ በደመቀ ሁኔታ ሰፈሩ ተውቧል የባለስልጣን ሰርግ ነው ሚመስለው አብረን ወደ ውስጥ ገባን የኔ ልዩዎች የቲማችን ልጆች ሳሎኑን በአንድ እግር አቁመውታ ገና ሲያዩን ተጮኹ እብዶች ሁሉንም ሰላም አልኳቸው ናዙ አንቺ ምንድነው እንዲ ማማር አለችኝ አስከዳር ደግሞ የው ከአንድ ጉድጓድ ይቀዳሉ አይደል ሚባለው በወንድምሽ ወጥታ ነዋ አለቻት ጨዋታው ሳቁ ጦፏል አጃቢ የተባለ በሙሉ ከኛ ጋር ተሰብስበን እየቀወጥነው ነው ዳግም የቸርቻችን ምርጥ ዘማሪ ነው እሱ ያዘምራል እኛ እናመልካለን ወደ ሙሽሪት ቤት ልንሄድ ነው ዋው ሙሽራው ከነ ሚዜዎቹ ደምቋል ናዙ አንቺ እነ አባባን አናገርሽ አለችኝ ውይ አላገኘዋቸውም አልኳት ጊቢው ወከባ ብቻ ስለሆነ ያሉበት ወሰደችኝ ንግስቴ እየሳመችኝ እልልታውን አቀለጠችው አባባንም ሰላም በዬው የነናዙ አጎቶችች አክስቶች ሁሉም አሉ ሰላም ብያቸው ተመለስኩ አንቺ የምን እልልታ ነው ስላት አቃጠርኩልሻ አማቻቸው ልትሆኚ እንደሆነ አለችኝ አንቺ ያምሻል ጤና የለሽም አልኳት እየሳቀች ሄደች ብቻ ደስ በሚል ሁኔታ እሁድን ሰርገኛ ሆነን አለፍን በጣም ስለመሸ አኔና አስከዳር ከናዙ ጋር ልናድር ነው ለዚህም አባቢን ደውዬ ንግስቴ አስፈቀደችልኝ እኔ ትናንትም ስላልተኛው ድካሙም ተጨምሮ እንቅልፍ እንቅልፍ እያለኝ ነው ከእስከዳር ጋር የናዙ ክላስ ገብተን ተኛን ክላስ መሄድ ስላለብኝ በጠዋት ወደ ቤት ለመሄድ ተነሳሁ ገና 12: ሰአት ነው ንግስቴን ነግሬአት ፈቅዳልኝ ወደ ቤት ሄድኩ ሰአት ገና ነው ብዬ እንደ ቀልድ አልጋዬ ላይ አረፍ ባልኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ ድንገት ስነቃ 8:ሰአት ሆኗል ስልኬ የmiss call መአት ናዙ ያፌት ልዑል እስከዳር ያልደወለ ሰው የለም እንዴ ተነስቼ ፊቴን ታጥቤ ለልዑል ደወልኩለት እንዴ ምን ሆነሽ ነው በሰላም ነው አንደኛ ሳትነግሪኝ ሄድሽ ሁለተኛ ትምህርት ቤት ልወስድሽ ደጋግሜ ብደውል ስልክ አታነሺም አለኝ ተኝቼ እንደነበር ነገርኩት ክላስ በመቅረቴ ጮኸብኝ ቀወጠው ሳላውቅ እኮ ነው እንቅልፍ የወሰደኝ አልኩት ትእዛዝ አይሉት ቁጣ እሺ አሁኑኑ ላይብረሪ ሄደሽ አንድ አንድ ነገሮችን ለማየት ሞክሪ አንቺ ፈተና ደርሶ ትቀልጃለሽ ውይ ቀወጠው በቃ እሺ ብዬው ስልኩን ዘጋሁት ሳሎን ስወርድ ሳሪ እና ጀምስ ፊልም እያዩ ነው አንቺ እንቅልፋም ሀሳብሽን ጥለሽ ትተኛለሽ አለችኝ ጀምስ ደግሞ ሩሀ ፈተና ደርሷል መቅረት አልነበረብሽም አለችኝ ባክሽ ይኸው ላይብረሪ ልሔድ ነው ልዑል ጮኸብኝ አልኳት ሁለቱም ስቀው እሰይ ለጌታም ጌታ አለው በይ ሂጂ አሉኝ።


ሰሞኑን ጥናቱን ተያይዤዋለሁ ልዑልም ጥናት ላይ ትኩረት እንዳደርግ ስለሚፈልግ በቀን አንዴ ቢደውልልኝ ነው ትምህርትም ዘግተን 12ኞች ጥናት ላይ ነን በብዛት ተፈታኞች ስለሆንን ቲማችንም መገናኘት አቁመናል ከእሁድ ውጪ ቸርች ድርሽ የለም ግን ይናፍቀኛል ግን ደግሞ ክርስቲያን በሁሉ ነገር ብርቱ መሆን አለበት በትምህርቱም በአገሎግሎቱም ስለዚህ ለሁሉም ጊዜ አለው ብዬ በማጥናት ተመስጫለሁ ።


በነገራችን ላይ ማህሌት ምስክሮች ቀርበው ከእናቴ ሌላም የ3 ሰዎች ህይወት ማጥፋቷ ተሰጋግጦ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባታል አንድ አንዴ እነ ሳሪ ምግብ ይዘው ይጠይቋታል አንድ ቅዳሜ ከነሱ ጋራ ሄጄ ምነው በመርዝ ልትገሉኝ ነው ተሰብስባቹ የመጣቹት አለችን አሁን እንኳን አትማርም ከተፈጠርኩ የክፋትን ጥግ በሷ አየው የፍቅርን ጥግ ደግሞ በክርስቶስ ለነገሩ በክርስቶስ ስለማታምን ፍቅርን ታውቃለች ብዬ አልገምትም እሷ ራሷን አፍቃሪ ገንዘብ አምላኪ ናት ።

እና ሰኞ ፈተና እንጀምራለን እኔም በርትቼ እያጠናሁ ነው ዛሬ ቅዳሜ ነው ግን እንደበፊት ቸርች የለም አይገርምም ከነገ በኋላ ተፈታኝ ነኝ አምላኬ በአጠናሁት እንደሚረዳኝ አምናለሁ ከሁሉ በላይ አባቴም ሳሪም ልዑልም እንዲያፍሩብኝ አልፈልግም ጀምስ ደግሞ 8ወር ሞልቷታል የሷ አለመፈተን በጣም እያሳሰበኝ ነው እንዲከፋት ስለማልፈልግ አጠገቧ ስለ ፈተናው አላወራም.......

........ይቀጥላል........

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
⇨ @yebirihan_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

🙏ተባረኩ🙏
-------------"""""""""""""""""""-------------

Читать полностью…

የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

#comment ላይ #ኢየሱስ_ይመጣል ብላችሁ Pp ያደረጋችሁ የእናንተ #gift ነው

Читать полностью…
Subscribe to a channel