yegetaserawit | Unsorted

Telegram-канал yegetaserawit - የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

1852

የጌታ ሠራዊት ሳምንታዊ ፕሮግራም ሐሙስ አርብ የፀሎት ጊዜ የትምህርት ጊዜ ቅዳሜ የኦንላይን ወንጌል ስርጭት እሁድ የአንድነት የስነጽሁፍ እና የምስክርነት ጊዜ ሁሉም ማታ 3:30 ላይ ይጀምራል ካሰኞ እስከ ሰኞ ከቃኑ 11:30 ላይ ጥያቄ እና መልሰ ፕሮግራም ይኖረናል https://t.me/eyubibleteachings

Subscribe to a channel

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Kudusan tslot gibu 🥰🤗🙏

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

👉🌹ፍቅሬ እንደተጠበቀ ነው ።
ዘማሪት አዲስአለም
!!!🌹👈

የኔን ጉዳይ አጥብቆ የያዘው የእግዚአብሔር  እጅ ነው ። ታግዬ ነገሩን ከእሱ እጅ አላወጣውም ጉዳዩን በራሴም direct አላረገውም ማለቴ ..ነገሩን በእጅ ጥምዘዛ ወይም እግዚአብሔርን የተለያዩ ቃላቶችን ከሽኜ አላሳምነውም እሱ የሚሰራውን ስለሚያውቅ ።  ነገር ግን ...." እንጀራህን በውሃ ፊት ላይ ጣለው ከብዙ ቀንም በኃላ ታገኘዋለህ " እንደሚል እንደ እግዚአብሔር  ቃል  እጁ ላይ አቆየዋለሁ ።  እንደዛ ከሆነ አይበላሽማ ..... ከብዙ ቀን በኃላ ግን አምሮና ተውቦ ክብሩን ጌታ ብቻቻቻቻ በሚወስድበት መንገድ ማንም ይሄንን ነገር አኔ አረኩላት በማይልበት መንገድ ብቻውን ሰርቶ ጨርሶ ያለቀለት ነገር ያስረክበኛል  !! .....  ዛሬም ብዙ  የጌታን ጣልቃገብነት የሚፈልጉ ጉዳዮች ያሏችሁ ወገኖቼ ከሰው ጋር ወይም ከራሳችሁ ጋር አትታገሉ    (  " መሰዊያው ስር  ታገሉ " ) እግዚአብሔር ያኔ በራሱ አደራረግ  ያገኛችኋል !!!

የንፋስ  መንገድ እንዴት እንደሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ እንዲሁም ሁሉን የሚሰራውን የእግዚአብሔርን ስራ አታውቅም  ( መክ - 11 - 5 )

ፍቅሬ እንደተጠበቀ ነው ።
ዘማሪት አዲስአለም !!!
              
ይህንን መልዕክት ሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ መልካም ተግባሮትን ያሳዩ
ቅዱሳንንም አድ በማድረግ ትጉልን

ኢየሱስን እንሰብካለን ✍️
✍️💜💜❤️❤️💜❤️✍️
📡📡ይቀላቀሉን📡📡
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ነው በድል ተመለሱ😘

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

#ሚሽናችንን ጀምረናል ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ወደ ኦሞ ወንጌልን ይዘን እንዘልቃለን
👉ያው መጀመሪያ የጂንካ ቡና😂
👉ነገ በለሊት ጉዞአችንን ወደ ዳሰነች እንቀጥላለን።
👉ጌታ በነገር ሁሉ በብዙ ፍሬ እንዲባርከን እና በጸጋው እንዲረዳን ጸልዩልን።
👉ወንጌል ይቀጥላል።
#የጌታ_ሠራዊቶች #yegetaserawitoch
#Evangelist_eyu

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

በእየሱስ ስም ታበረኩ ፀጋ ይብዛለችሁ ቡሩከን ናቹሁ መልካም ምሽት ይሁንለችሁ

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

YaLeNa YeMiNor endeMuse LikoAchewAL.Bertu God is with you

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Kudusan tslot gibu 🥰🤗

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

👉 እግዚአብሔር ነገሮችን የምንለውጥበትን ጉልበት ብቻ ሳይሆን የሚሰጠን፥ የማይለወጡትን ነገሮች የምንታገስበትን ፀጋም ጭምር ይሰጠናል፡፡

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ!

ማቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴³ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
⁴⁴-⁴⁵ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
⁴⁶ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
⁴⁷ ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
⁴⁸ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።

በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ!

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ኢየሱስ ይባላል
የማለዳ ጸሎት ጀምሯል ኑ ተቀላቀሉ
/channel/+OMezYinWzFtlNmI0

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

amen tebareku kidusan melkam adar🙏❤️

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

:
:

🛑   #የዘላለም_ሕይወት ከእግ/ር ዘንድ የተሰጠን #ሽልማታችን ሳይሆን #ስጦታችን ነው

✍️  ሀለችንም እንደምናውቀው #ለሰራ ሰው #የምሰጠው_ስጦታ ሳይሆን ሽልማት ነው ። ምክንያቱም ለሰራ ወጤቱ #ሽልማት ወይም #ደምዎዝ መሆኑ ግዴታ ነውና ።  #ስጦታ ግን የምሰጠው ከፍቅር ጋር እና ፍቅርን ለመግለፅ ተብሎ #ላልሰራ #ላልደከሜ ይሰጣል ። ብሰጠውም እንኳን ተጨብጭቦለት ይገባዋል ተብሎ ሳይሆን ሳይገባው ግን ይገባዋል ተብሎ #ስለፍቅር ይሰጠዋል ። 

✍️ ስለዝህ እኛ #የዘላለምን_ሕይወት ልንሸለም  ምን ያህል መልካም ሥራ ሰራን ??
✍️ እንድህ #ያልሰራን ከሆነ በምኑ ነው #ሽልማታችን ምሆነው ??? ያልሰራ ይሸለማልን ??
✍️ ታድያ #ስላልሰራን እንግድህ እግዚአብሔር ስሰጠን እንዴትስ ሰጤን ?

♦️ እውነቱን ብናወራ እኛ እንኳን #ሰራችን ተብሎ እንድንመካበትም ሰርተዋል ምባልልን #ኃጢአት ብቻ ነው እንጅ አንዳች #ፅድቅ የለንም ። #ፅድቅ አለን ምንለውም እንኳን እንደመርገም ጨርቅ  ተቆጥሮልን ። #ኃጢአትን ብቻ በመስራት የኃጢአት ሽልማት ወይም ደምዎዝ የምገባን ነበርን ።

(( ሮሜ 3፥23))
“ሁሉ #ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”

♦️ ነገር ግን እግዚአብሔር ገለባበጠውና የምገባን ሞት ስሆን እርሱ ግን በጸጋው ብቻ የዘላለምን ሕይወት ስጦታ ሰጠን ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን #የዘላለም_ሕይወት ነው።”
  (( ሮሜ 6፥23))
“እግዚአብሔርም #የዘላለምን_ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።”
  ((1ኛ ዮሐንስ 5፥11))
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

#የዘላለም_ሕይወት_በክርስቶስ እየሱስ ቤዛነት  ለሚናምን  ከእግዚአብሔር የተሰጠን #ስጦታው ነው እንጂ ስለሰራን  ስለ መልካም  ስራችን የተቀበልን #ሽልማታችን አይደለም🙅።

🛑 ይህም #የዘላለም_ሕይወት የዘመን ብዛት ወይም ወደፍት ከሞትን ቦኅላ የምናገኘው ነገር( something) እና ወደፍትየምንጀምረው #የሕይወት_ስርዓት ወይም የዘመን ብዛት ሳይሆን #የዘላለም_ሕይወት የሆነ #ማንነት (person) ነው እርሱም #የእግዝአብሔር_ልጅ_እየሱስ_ክርስቶስ_ነው።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 👇👇👇
“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”
  — ዮሐንስ 10፥10👆👆👆
🛑ስለዝህም እንዲህ ማለት እችላለው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ #የዘላለም_ሕይወት ሰጭ እና ራሱ #የዘላለም_ሕይወት ነውና። እናም #የዘላለም_ሕይወት በርሱ ውስጥ ነው ከእርሱ ዘንድ እና እንድሁም በርሱ #የዘላለም_ሕይወት አለ። እርሱ #ያለው_ሕይወት አለው #እርሱ_የለለው_ሕይወት የለውም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።👆👆👆👆👆
🛑 እናም ይህ ይህ #የዘላለም_ሕይወት ከእግዚአብሔር የተሰጠን #ትልቁ_ዋስትናችን ነው ። #የዘላለም_ሕይወት የለለው ዋስትና አለው ።
🛑 በተጨማርም ይህ #የዘላለም_ሕይወት የዘላለም የሆነ ሕይወት  እንጂ በእኛ ሁነታ እና ከስንፍናችን የተነሳ ሰሞናዊ ወይም ወቅታዊ ሕይወት ልሆን የማይችል የእግዚአብሔር ልዑላዊ የሆነ ለኛ የተሰጠን የርሱ ስጦታችን ነውና ስለዝህ ከእኛ ምጠበቀው ይህንን #ስጦታ በእኛ ሁነታ እና በእኛ አቋም ሳይሆን #በራሱ_አቋም_ብቻ የሰጠን የዝህ #ስጦታ ባለበት እርሱን #እግዚአብሔር ማመስገን እና ስለዝህ #ስለተሰጠን ስለዘላለም ሕይወት መመስከር ይህ ማለት ለሎችም ይቀበሉ ዘንድ መስበክ ይገባናል 🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
… 
²⁰ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም  ሕይወት ነው:: ፀጋ ይብዛላቹ 🙏🙏❤️

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Ameen Ameen 🙏 🙌 🙏 🙌

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ የሚፈልግ ?🤔

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው!

ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
³² ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
³³ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
³⁴ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
³⁵ አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።
³⁶ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።

በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም!

ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ! ስለዚህ ምስክሩን ተቀብላሃል/ተቀብለሻል?

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/idu-mchs-azx

Or open Meet and enter this code: idu-mchs-azx

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

😍መዝሙር 28:6-9❤️
6 የልመናዬን ቃል ሰምቷልና፣
  እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።🙌

7 እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤
  ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤
ልቤ ሐሤት አደረገ፤
  በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

8 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤
  ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

9
#ሕዝብህን_አድን፤ ርስትህንም #ባርክ
#እረኛ_ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።

1፦
#ሕዝብህን_አድን፤(አሕዛብ የነበርን በክርስቶስ ሕዝብ ሆነናል እግዚአብሔርም በልጁ በኢየሱስ አድኖናል )🙌


2፦
#ርስትህንም_ባርክ፤(እግዚአብሔር ለአብርሃም አሕዛብ በዘርህ ይባረካሉ እንዳለው እኛም በዚያ የተስፋ ቃል በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ባለ በረከት ሁሉ ተባርከናል)🙌


3፦
#እረኛ_ሁናቸው( ነፍሱን እስከ መስጠት ድረስ ኢየሱስ እወነተኛ እረኛ መሆኑን አሳይቶናል ስለዚህ እርሱ እውነተኛ እረኛችን ነው። )

4፦
#ለዘላለሙም_ዐቅፈህ_ያዛቸው።(በማይጥሉ እጆቹ በማይለወጥና በማይቀየር ቃል ኪዳኑ ተይዘናል ደግሞ ኢየሱስ አልተዋችሁም(አልጥላችሁም) ብሎ ቃል ገብቶልናል እስከ ዘላለም የማይተወን የማይጥለን አምላክ አለን።🙌

🗨️ ዳዊትን እግዚአብሔር የልቤ ሰው ስለው ልክ ነው።❤️

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

💚💚 ብታቁሙ ይበጃችኋል 💚💚
        ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️



በእጌታ ፀጋ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው የሚያገለግሉ አገልጋዮች ላይ በፀጋቸውና በማንነታችው ያልተገባ ንግግር የምታደርጉ ሰዎች
#ብታቆሙ አይሻላችሁምን ?
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ግድ የለም ያሻችሁን በሉዋቸው
ፀባችሁ ከእነርሱ ሳይሆን ከጌታ ጋር መሆኑን አትርሱ  ማንም ወዳጁን ቢጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው አመፀኞችን ይቃወማል

“ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 3፥15

ታዲያ የአገልጋዮችን ፊት ለምን ትጠላለህ አገልግሎታቸውንስ ስለ ምን ታንቋሽሻለህ?

በመሠረቱ ማንንም የማንንም ማንነት ሟንቋሸሽ ሆነ መልካም ስዕብና ማበላሸት አይችልም ❗️❗️

ምናልባት ይህንን ድርጊት በዕብሪተኝነት አንድ አካል አደረገው ማለት የተነገረበት አካል  የተናጋሪው ንግግር ነው ማለት አይደለም 💚👈

እንኳን አደረሳችሁ ይትብዬ
3ኛ አመት እንወድሃለን 💚👈

From yasin fujeta fujeta fb

   
ይህንን መልዕክት ሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ መልካም ተግባሮትን ያሳዩ
ቅዱሳንንም አድ በማድረግ ትጉልን

💚💚💚💚💚💚💚💚
✍️ኢየሱስን እንሰብካለን ✍️
✍️💜💜❤️❤️💜❤️✍️
📡📡ይቀላቀሉን📡📡
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

#ጌታ ረድቶን #ጂንካ ገብተናል።
#ሚሽናችንን ጀምረናል ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ወደ ኦሞ
👉ያው መጀመሪያ የጂንካ ቡና😂
👉ነገ በለሊት ጉዞአችንን ወደ ዳሰነች እንቀጥላለን።
👉ጌታ በነገር ሁሉ በብዙ ፍሬ እንዲባርከን እና በጸጋው እንዲረዳን ጸልዩልን።
👉ወንጌል ይቀጥላል።
#የጌታ_ሠራዊቶች #yegetaserawitoch
#Evangelist_eyu

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ወይ ተንበርከክ ወይም ተንጠራራ

ስለፀሎት አንዲ እውነት ተማርኩኝ
ተንበርክከህ የሰቀልከውን ተንጠራርተው አያወርዱትም!.... Wow Wow ምን አይነት አባባል ነው እስቲ ደግመን እንበለው
ተንበርክከን የሰቀልነውን ተንጠራርተው አያወርዱትም
ነገር ግን ምንም ያህል ተንጠራርተህ ብትሰቅል በቀላሉ ያወርዱታል። ለምን? b/c ከተንጠራራክ ነገርህን የምትሰቅለው በቁመትህ ልክ ነው ስትንበረከክ ግን ነገርህን የምትሰቅለው ሀያሉ እግዚአብሔር ጋር ነው። ከሱ እጂ ማን ሊነጥቅ ይችላል? እርሱ ኤልሻዳይ ነው ሁሉን ይችላል።

ይህንን ተገንዝበን ብንደክምም በእርሱ ፊት እንውደቅ እርሱ ነገሮቻችንን ያቀናልናል። ይሄንን ፀጋ ያብዛልን🙏


ለወዳጃቹ አጋሩለት
@YIKRTAYEE          yiso

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ሰላም ሰላም ! ሰንቶቻችሁ ናችሁ ድሮ የተከፈተ Telegram  ግሩፕ እንደምሸጥ የምታውቁት!
  
በወቅታዊ ባለው የግሩፕ ሽያጭ መቀነስ ምክንያት የቆዩ ግሩፖችን የምገዛበት ዋጋ ላይ ማስተካከያ አድርጊያለሁ 🤚
በዚህም መሠረት :
✅2023Jun Feb Mar Apri May💵
✅2022 -
✅2021 -
✅2020 -
✅2019 -
✅2018 -

በእነዚህ ዓ.ም ውስጥ የተከፈተ ማንኛውም group ካላችሁ አናግሩኝ 🙌
-እኔ የምፈልገው የተከፈተበት ቀን እንጂ የግሩፑን አባል ብዛት አይደለም “0” ፣ “100” member ዋጋው ተመሳሳይ ነው🙏

📥ግሩፕ ካላችሁ እንግዛችሁ inbox

     @Deraba07
      
     @Buyerbnl

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/tbz-bmgh-jsm

Or open Meet and enter this code: tbz-bmgh-jsm

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

✍የአማኞች ስኬት ከምድር ከፍታዎች ያለፈ ነው።የሰኬታችሁ መለኪያ እስከ ባለጠግነት ወይም እስከ ዝነኝነት መሆን የለበትም።እንደ ክርስቲያን ሩጫችሁ በምድር ላይ የሚያበቃ አይደለም መዝገባችሁ በሰማይም ነው።በምድር ለሰማይ በመስራት በሰማይ ብድራት የሚሆናችሁን ሽልማት መስራት ጥበብ ነው።

𝐊𝐢𝐧𝐠𝐝𝐨𝐦 𝐨𝐟 𝐆𝐨𝐝 𝐜𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ነው ተቀላቀሉን እናም ቤተሰብ ይሁኑ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ አሜን።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ኢየሱስ ይባላል
የማለዳ ጸሎት ጀምሯል ኑ ተቀላቀሉ
/channel/+OMezYinWzFtlNmI0

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

✍️🌏🗣እውነተኛ እረኛ🌏 ✍️
ለጥቂት ጊዜ እስቲ አስብ
በምትኖረው ሁለእንተናዊ አኗኗር ውስጥ ሁሉ ለራሱ እንጂ ለአንተ የሚያስብልህ ይኖራል ብለህ ሁሉ ካመንክ ራስህን ትጎዳለህ።
ከእምነት አንፃር ቃልህን ሳታጎድል፣ እምነትህም ሳትሸርፍ፣ ጉዞህን ቀጥል አንጂ፦ ይህ ከአንተ የሚጠበቅና ለአንተ ፅኑ ሰላምህ ነው።


እስቲ በጋራ ወደ አንድ የገበያ ማዕከል በፁሑፍ ጉዞ  አብረን እንጓዝ ፣
በያንዳንዱ በሚሸጡ ግባቶችና ግብይት ውስጥ ነጋዴው፦ ና እኔ ጋ ግዛ ይልሀል እንጂ ለአንተ ይጠቅምሀል በፈለከው ቦታ የተሻለውን ግዛ ብሎ አይሰድህም፦ ያለውን ቅራቅንቦ ሆነ ብርቱ እቃዎቹ እንዲሁም ነቀዝ የበላው እህሎቹ እንኳን ቢሆን እያሳሳቀህ ካሰፈለገም የመላእክት ስም በየ ተራ እየጠራ፣ በእግዚአብሔርም እየማለ ምን ይህ ብቻ አባቴ ወይም እናቴ ትሙት እያለ ይምልልሀል፦
ይህ ሁሉ መሀላ ለምን ካልከኝ ያንተውን አስር ብር፣ መቶ ብር ፣ ሺህ ወይም ሚሊዮን ብርህን ለመቀበል ነው።
ብቻ ግን እየማለለህ ካሰበው ደረጃ አድርሶህ ልትሸምተው ያለውን ዕቃ ጠቅልሎ ይሰጥሃል።

በያንዳንዱ በምንኖረው ኑሮ ይህ ነው ሚስተዋለው 🗣

እያልኩህ ያለው ነገር ተረዳኽኝ?
በሕይወትህ ውስጥ ኢየሱስ ብቻ ለአንተ ፍፁም መልካም ነው።
ለዚህም 👉“ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”
  — ኤርምያስ 29፥11

🌏🌏🌏ታዲያ🌏🌏🌏🌏
🌏🌏🌏ማነው እረኛ 🌏🌏🌏
በጥቅሉ ከእንደዚህ አይነት የሸቀጥና የንግድ ሴራ ወጥቶ ለመንጎቹ እረኛ የሚሆነውን ማን ነው?
የግል ጥቅሙ ያልሳበው፣ ለቢሮው ወንበሩ ያላጎባደደ፣ ለእውነተኛ ጥሪ እና አግልግሎት የቆመ ማን ይሁን?

👉 በስውር በኪስ የሚወሸቅለት ቢጎድል አገልግሎቱን የሚረግም ስንቱ ይሁን?
👉 ለካፌና ለሆቴል ጋባዦቹ እንደ ማዕድን ፈላጊ፣ ለተቸገሩትና ለታመሙት እንዲሁም ለታረዙት ተሸሻጊ ፣ ቤቱ ይቁጠረው ።
👉 ክርስቶስ ለሠዎች ሁሉ ያፈሰሰው የቤዛነት ደሙ ከእርሻውና ከማሳው ያመጣው ይመስል የአገልጋይነት ሽፋን በመልበስ እንደ ፈረኦን የእግዚአብሔር ህዝብን የሚይዝ ስንቱ ነው?

በተለይም ፣ በመንፈስ ቅዱስ አሰራር  በቤተክርስቲያን ባለራዕይ በሚነሱበት ወቅት የተለያዩ የአለም አመክንዮ በማቅረብ ባለራዕዩ ለማደናቀፍ መሞከር፣

ሠዎች የሀጢዓት ባሪያ እንዲሆኑ ማሳየትና የንስሀ እንዲሁም ነፃ አለማስወጣት፣
👉ከይቅር ባይነት ይልቀ ድንጋይ ወርዋሪነት የሚቀናቸው፣

(# አብዛኛው ክርስቲያን እና አገልጋይ በተሠጠው ስልጣን ሰይጣን አስጩሆ ማስወጣት ቢቀለንም  በሃጢአት ለደከሙትና ነፃ መውጣት ለሚገባቸው ግን እጁ ጭኖ ለመፀለይ የሚከብደን ስንቶቻችን እንሁን?

🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏
በዚህ ሁሉ አይዞአችሁ ❤️ኢየሱስ❤️ አለ እርሱም፣🌏
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ የሚሰጥ 🌏🌏🌏🌏🌏
የሕይወትህን ቤዛ ፣ የማይሸነግልህ፣ የማይክድህ፣🌏 ሁሉንም ነገር ያሸነፍክበት፣ ሁሉንም ነገር የምትችልበት፣
👉👉👉👉👉👉❤️ኢየሱስ❤️ 👈👈👈👈👈🌏
🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌏


🗣ኢየሱስና አለም🌏  በተሰኝው ከወንድም ✍️ ያሲን ፉጀታ✍️ የጹሑፍ ስራ የተወሰደ Ⓒ

🎮ይህንን መልዕክት ሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ          እና
ቅዱሳንንም ወደዚህ በመቀላቀል በጋራ ወንጌል እንስራ🗣

🌎🌍🌏ክርስቲያን ሚዲያ🌍🌎🌏
📡ኢየሱስን እንሰብካለን ✍️
✍️💜💜❤️❤️💜❤️✍️
📡📡ይቀላቀሉን📡📡
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv
/channel/a1acmntv
                

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Ameen Ameen birukii nash imaa geta abzito yibrkishii❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Ameen Ameen Ameen 🙏🙏🙏🙌🙌🙌🙌

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

https://www.facebook.com/share/v/1AeCLr5QbM/

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

"ሰላሜ ኢየሱስ ሰላሜ
እረፍቴ ኢየሱስ እረፍቴ"

የመዝሙር ግብዣ🤗
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/Yahweh_Poem

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ!

ማቴዎስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።
²⁵ ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።
²⁶ ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።

³⁶ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
³⁷ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
³⁸ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
³⁹ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
⁴⁰ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
⁴¹ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
⁴² ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
⁴³ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል! ስለዚህ መልካሙ ዘር እንሁን !

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel