yegetaserawit | Unsorted

Telegram-канал yegetaserawit - የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

-

Subscribe to a channel

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

Tselot gibu yetawodadachu

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ስለዚህ፣ “የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ” ተብሎ ተጽፎአል፤ የኋለኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። ነገር ግን በመጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፤ ከዚያም በኋላ መንፈሳዊው መጣ። የመጀመሪያው ሰው ከምድር የተገኘ ምድራዊ ነው፤ የኋለኛው ግን ከሰማይ ነው። ከምድር የሆኑት እንደ ምድራዊው ናቸው፤ ከሰማይ የሆኑትም እንደ ሰማያዊው ናቸው። የምድራዊውን ሰው መልክ እንደ ለበስን፣ የሰማያዊውን ሰው መልክ ደግሞ እንለብሳለን።

1 ቆሮንቶስ 15:45-49

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

መዝሙር 41
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።
² እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም።
³ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
⁴ እኔስ፦ አቤቱ፥ ማረኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት አልሁ።
⁵ ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ መቼም ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ።
⁶ እኔን ለማየት ቢገባ ከንቱን ይናገራል፤ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም።
⁷ በላዬ በመተባበር ጠላቶቼ ሁሉ ይሾካሾኩብኛል፥ በእኔ ላይም ክፋትን ያስባሉ።
⁸ ክፉ ነገር መጣበት፤ ተኝቶአል ከእንግዲህ ወዲህ አይነሣም ይላሉ።
⁹ ደግሞ የሰላሜ ሰው የታመንሁበት እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
¹⁰ አንተ ግን አቤቱ፥ ማረኝ፥ እመልስላቸውም ዘንድ አስነሣኝ።
¹¹ ጠላቴ እልል አይልብኝምና ስለዚህ እንደ ወደድኸኝ አወቅሁ።
¹² እኔን ግን ስለ ቅንነቴ ተቀበልኸኝ፥ በፊትህም ለዘላለም አጸናኸኝ።
¹³ ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። አሜን አሜን።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ሰዎችን እና መናፍስትን የሚለያቸው አካላቸው ብቻ አይደለም መኖሪያቸውም ጭምር ነው ፣ ሰማያት ለመናፍስት ምድር ደግሞ ለሰዎች ተፈጥረዋል ።

ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

ኢሳይያስ 45:18

በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ምድር የተፈጠረችው የሰው መኖሪያ እንድትሆን መሆኑን በግልፅ ተናግሯል ። መናፍስት በምድር የሚኖሩ አይደሉም ለሥራ ተልከው ከመምጣት ውጪ መኖሪያቸው ከምድር ውጪ ነው ። መላዕክት ምድር ላይ የኖሩበት ዘመን ነበር ፤ ነገር ግን ከቦታቸው የለቀቁ ስለሆኑ ቅጣታቸውን እየተቀበሉ ነው ።

የሥልጣን ስፍራቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘላለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ በጨለማ ጠብቆአቸዋል።

ይሁዳ 1:6

እነዚህ በዘፍጥረት 6 የተጠቀሱት መኖሪያቸው ሰማያት ሆነው ሳለ ወደ ምድር ወርደው ከሰው ሴት ልጆች ጋር አብረው የኖሩ እና ልጆችን የወለዱ የወደቁት መላእክት ናቸው ። ከዚህ ምንረዳው መናፍስት ቋሚ መኖሪያቸው ሰማይ እንደሆነ ነው ፣ ሰዎች ደግሞ ምድር ቋሚ መኖሪያቸው ነው ። ከውድቀት በኋላ ግን ሰዎች በሞት ከምድር መለየት የማይቀር ስለሆነባቸው በድካም ምድርን በሞት ሲሰናበቱ የሚሄዱበት ስፍራ ነበር ፣ ያ ስፍራ ደግሞ ያለው ከምድር በታች ሲኦል (Hades) ነው ። ክፉ ሰዎች የሚሰቃዩበት እና ፃድቃን የሚፅናኑበት ሥፍራ በትልቅ ገደል ከመለየቱ ውጪ አንድ ስፍራ ነበር ።

ከሁሉም በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንደማይችሉ፣ እዚያ ያሉትም ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ፣ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጎአል።

ሉቃስ 16:26

ነገር ግን ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ የፃድቃን መኖሪያ ከምድር በታች ሳይሆን በሰማይ እንዲሆን ተደረገ ።


እኛ ግን አገራችን በሰማይ ነው፤ ከዚያ የሚመጣውንም አዳኝ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን፤

ፊልጵስዩስ 3:20

ኢየሱስ ወደ እኛ ይመጣል አልያም እኛ ወደ እርሱ እንሄዳለን ፣ ንጉሳችን በሰማይ ስለሆነ አገራችን በሰማይ ነው ። ይሄ ግን ምድር የሰዎች መኖሪያ መሆኗን የሚክድ አይደለም ፣ ሰማያት የሰዎች መኖሪያ ሳይሆን የመናፍስት መኖሪያ በመሆኑ ሰዎች ከሞት በኋላ ወደ ሰማይ ሲሄዱ በሰማያት ከሰዎች መፈጠር በፊት ያልነበረ አዲስ ነገር እንዲኖር የግድ ነው ።

በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው።
ዮሐንስ 14:2

ሰማያት ቀድሞውን የተፈጠሩት ለመናፍስት ስለሆነ ፣ ሰዎችን ለመቀበል ዝግጅት ያስፈልገዋል ፣ ኢየሱስ ሰማያት ከሰዎች መኖሪያ ጋር የማይገናኙ እንደሆኑ ስለሚያውቅ በምድር ሰዎች የሚያውቁትን ቁሳዊ (material) የሆነ ነገር በዚያም ሂደው እንዲያገኙት ይፈልጋል ። መላእክት እንደሰዎች ለቁሳዊ ነገሮች ብዙም ቦታ የላቸውም ፣ አፈጣጠራቸው ከቁሳዊ ነገር ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም ፤ ሰዎች ግን አፈጣጠራቸው ከቁሳዊ አካል ጋር አብረው የሚሄድ ስለሆነ ከሞቱ በኋላ ባዕድ የሆነ ዓለም ውስጥ እንዳሉ እንዳይሰማቸው በምድር በነበሩበት ዘመን የሚነኩትን እና የሚዳስሱትን ዓለም እንደሚለማመዱ ፣ በሰማያዊ ስፍራ ደግሞ ከዚያ እጅግ አብልጦ በውበት የሚሻል የሚታይ ፣ የሚነካ ፣ የሚዳሰስ እና የሚራመዱበት ዓለም ተዘጋጅቷል ። ሰማያት ቀድሞው ለመናፍስት የተዘጋጁ ናቸው ። ኢየሱስ ስፍራን ሊያዘጋጅልን የሄደው የመናፍስት መኖሪያ እና የእኛ መኖሪያ የተለያየ በመሆኑ ነው ፤ እንደዚያ ባይሆንማ ቅዱሳን በሞት ወደ ሰማይ ሲሄዱ ከ ሱራፌል እና ከኪሩቤል ፣ ከተለያዩ የመላእክት አይነቶች ጋር ወስዶ ይደባልቃቸው ነበር ። ሰማይ ለሰዎች መኖሪያ የተዘጋጀ ስፍራን ስለያዘ የሰዎች መኖሪያ ነው ልንል አንችልም ፣ በሚመጣው ዓለም ሰዎች የሚኖሩት በምድር ነው ።

ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያዪቱ ምድር ዐልፈዋልና፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።

ራእይ 21:1

እኛ ሰዎች እራሳችንን ከመናፍስት ጋር ለማመሳሰል መሞከር የለብንም ፣ መናፍስት ሥፍራቸውን ሲለቁ እንደተቀጡ ፣ ሰዎችም ለራሳቸው ሌላ ስም መስጠት በእግዚአብሔር ፊት የሚያስጠይቅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው ። በሰው ማንነት ላይ የሚነዙ የስህተት ትምህርቶች እንዲኖሩ አንዱ ምክንያት የሆነው ቁሳዊ የሆነውን ነገር ከመንፈሳዊው ተቃራኒ እንደሆነ አድርጎ መቁጠር ነው ብዬ አስባለሁ ። ቁሳዊ የሆነ ዓለም ከተፈጥሮአዊ ዓለም በፊት የነበረ መሆኑን አለማስተዋል መንፈሳዊውን ዓለም በተሳሳተ መንገድ እንድንረዳ ያደርገናል ።

በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ። በዚያው ቃል ደግሞ አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር፣ ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።

2 ጴጥሮስ 3:6-7

አሁን ያሉት ሰማያት እና ምድር ሆነ ቀድሞው የነበረው ዓለም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቁሳዊ የሆነውን ነገር መያዛቸው ሲሆን አሁን ያለው ዓለም ተፈጥሯዊ በመሆኑ ቀድሞ ከነበረው የተለየ ሆኗል ። ስድስት ሺህ አመታት ያለፈው ዓለም ተፈጥሯዊው እንጂ ቁሳዊው አይደለም ። መንፈሳዊ ለመሆን መንፈስ መሆን አያስፈልግም ፣ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ነው ።

ፍጥረታዊ አካል ይዘራል መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ።

1 ቆሮንቶስ 15:44

መንፈሳዊ አካል ያለው ሁሉ መንፈስ አይደለም ፣ መንፈስ የምንላቸው ቁሳዊ አካል የሌላቸውን ነው ፣ ክርስቲያኖች ደግሞ በትንሳኤ የሚቀበሉት መንፈሳዊ አካል ቁሳዊ አካል ነው ፣ እሳት ወይም ንፋስ አንሆንም ። መንፈስ የሚለውን ቃል መፅሐፍ ቅዱስ ለመጠቀም የመረጠበት ምክንያት ቃሉ እራሱ ትርጉም የያዘ ስለሆነ ነው ፣ መንፈስ ምንድነው ?? ተብለህ ብትጠየቅ መልሱን ከዛው መንፈስ ከሚለው ቃል ማግኘት ትችላለህ ። ንፋስ በእብራይስጥ "ሩዋክ" በግሪክ ደግሞ "ኒዩማ" የሚል ቃል ነው ፣ ይሄው ቃል ነው መናፍስትን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለው ። እግዚአብሔር እራሱን ጨምሮ መናፍስት የሆኑትን ለመግለጽ ከሰዎች ቋንቋ የሚጠቀማቸው ፣ እንደ ንፋስ ፣ እሳት ፣ እስትንፋስ ፣ ብርሃን ፣ ቃል ፣ ወዘተ ... ቁሳዊ ያልሆነ አካል ያላቸው መሆናቸውን ለማሳየት ነው ፣ ከእነዚህም ቃላት አጠቃላይ መናፍስትን ለመጥራት የመረጠው ነፋስ የተጠራበትን ቃል (ሩዋክ / ኒውማ) ነው ፣ ይሄም ሰዎችን በራሳቸው ቋንቋ ለማስረዳት ነው ። ንፋስ የማይዳሰስ እንደሆነ ሁሉ መናፍስት ደግሞ እንደዚሁ የማይዳሰሱ ናቸው ። መፅሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮአዊ ሆነ ቁሳዊ የሆነውን ዓለም ከ ሰማያዊው ዓለም የተለየ እንጂ ያነሰ ወይም የወረደ አድርጎ አያሳየንም ። ሰማያት ሆነ ምድር የእግዚአብሔር ጥበብ መገለጫዎች ናቸው ። ቁሳዊ ነገርን ወደ መኖር ያመጣው እግዚአብሔር ነው ፣ ለወደፊት የማይኖረው ተፈጥሯዊው እንጂ ቁሳዊ የሆነው አይደለም ። እግዚአብሔር መንፈሳዊ የሆነውን ዓለም በትክክለኛው መንገድ መረዳት እንድንችል ይርዳን ።

ተባርካችኋል 🙏

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

1ኛ ቆሮንቶስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።
² ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
³ ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።
⁴ ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል።
⁵ ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።
⁶ ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።
⁷ ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት።
⁸ ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና።
⁹ ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና።
¹⁰ ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል።
¹¹ ነገር ግን በጌታ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም።
¹² ሴት ከወንድ እንደ ሆነች እንዲሁ ወንድ ደግሞ በሴት ነውና፤ ሁሉም ከእግዚአብሔር ነው።
¹³ በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን?
¹⁴-¹⁵ ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥ ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።
¹⁶ ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ፥ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም።
¹⁷ ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም።
¹⁸ በመጀመሪያ ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፥ በአንድ በኩልም አምናለሁ።
¹⁹ በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት እንዲገለጡ በመካከላችሁ ወገኖች ደግሞ ሊሆኑ ግድ ነውና።
²⁰ እንግዲህ አብራችሁ ስትሰበሰቡ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም፤
²¹ በመብላት ጊዜ እያንዳንዱ የራሱን እራት ይበላልና፥ አንዱም ይራባል አንዱ ግን ይሰክራል።
²² የምትበሉባቸውና የምትጠጡባቸው ቤቶች የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ማኅበር ትንቃላችሁን አንዳችም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።
²³ ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤
²⁴ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
²⁵ እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
²⁶ ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።
²⁷ ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት።
²⁸ ሰው ግን ራሱን ይፈትን፥ እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤
²⁹ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና።
³⁰ ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል።
³¹ ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤
³² ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።
³³ ስለዚህ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ ለመብላት በተሰበሰባችሁ ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
³⁴ ማንም የራበው ቢኖር ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ በቤቱ ይብላ። የቀረውንም ነገር በመጣሁ ጊዜ እደነግጋለሁ።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።

መዝሙረ ዳዊት 143 : 10

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት በአቋረጥን መጠን እራሳችንን ከዓለም ጋር እያገናኘን ነው!


1ኛ የጴጥሮስ 4:7
ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፥

1ኛ የጴጥሮስ 1:13
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።

ምሳሌ 25:28
ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።

ራእይ 2:4
ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፡ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
5:እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።


እንመለስ 🥺

@marii_dubbi_waaqa
@dhalootaa_hidhate

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ዕብራውያን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³-¹⁴ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ፦ በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤
¹⁵ እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ።
¹⁶ ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤
¹⁷-¹⁸ ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤
¹⁹ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤
²⁰ በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

👉የእግዚአብሔር ቃል ማለት ቅዱሳት መፃህፍት
ማለት አይደለም።

“እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤”
  — ዮሐንስ 5፥39

👉ቅዱሳት መፃህፍት ህይወት ወደሆነው
ወደ ክርስቶስ የሚጠቁሙን እና የሚመሰክሩልን
እንጂ በውስጣቸው ህይወት የለም።

👉መፃህፍት ወይም scripture ማለት በግሪኩ
ሲተረጎም ዶክመንት ማለት ነው።
👉የእግዚአብሔር ቃል ማለት የእግዚአብሔር
ድምፅ ማለት ነው፤ይህም ማለት ይሰማል፣ይንቀሳቀሳል
በውስጡ ህይወት እና መንፈስ አለው።
👉ብዙ ፈላስፎች ቅዱሳት መፃህፍን አንብበው
ነገር ግን ህይወት ስላልገባቸው የክርስቶስን ህልውና
እና አዳኝነት ክደው አልፈዋል።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/zek-hxbw-hkm

Or open Meet and enter this code: zek-hxbw-hkm

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

♦️ ነፋስ ይመጣል ብለህ ፈርተህ መዝራትን አትተው ይልቁንስ ማልደህ መሬትህ ላይ ዘርህን ዝራ::

- ከዘራኸው ውስጥ ጥቂቱ በንፋስ ቢወሰድም እንኳ ማጨድህ አይቀርም...ካልዘራህ ግን አታጭድም!!!

“ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም።”
— መክብብ 11፥4

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

🥞🥞የዕለት_እንጄራ🥞🥞 (  8 / 4 /2016 ዓ.ም)

🟥 #ጸጋና_እውነት ግን #በኢየሱስ_ክርስቶስ ሆነ።

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ #ቃልም ሥጋ ሆነ፤ #ጸጋንና_እውነትንም ተመልቶ በእኛ #አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው #ክብሩን አየን።
¹⁵ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ #ስለ_እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
¹⁶ እኛ ሁላችን #ከሙላቱ_ተቀብለን #በጸጋ ላይ #ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
¹⁷ #ጸጋና_እውነት ግን #በኢየሱስ #ክርስቶስ ሆነ።


መልካም ቀን 🙋🙋

@Essube23@Essube23🙏

👇👇👇ይቀላቀሉን ቴሌግራም  ቻናላችንን እና የመወያያ ግሩፓችንን👇👇
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ
/channel/Gosphelofchrist
/channel/Gosphelofchrist
"""""""""""""___
/channel/yekiristos_wongel
/channel/yekiristos_wongel
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ኢየሱስ ኢየሱስ ብላቹ ስሙን ጥሩት እስክ

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

https://youtu.be/wJebqfuiqmE?si=BCHFfuKxjIkxtlso

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
²³ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
²⁴ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/aae-ijab-wqf

Or open Meet and enter this code: aae-ijab-wqf

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

⚠️"ዛሬን ለሰይጣን ነገን ደግሞ ለእግዚአብሔር አትስጡ"

ዘጸአት 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
¹⁴ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው።

🗣🕊እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚያደርገውን ማዳን የሚታዩበት ቀን ይሁንላችሁ ❗️
🔴ትላንት ዛሬ ላይ ያስጨንቃችሁን ለዘላለም የሚያጠፋበት ቀን ይሁንላችሁ ❗️
☑️🕊እግዚአብሔር ሆይ እንዴየ እምነቱ አሜን ላሌ ሁሉ ይሁንለት ❗️

               ተባርካችኋል
              እወዳችኋለሁ

                            ✍እስራኤል ኢዮብ
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
╭══•|❀:✧♡๑✧❀|: ══╮
  🪴 ለህይወት እንመካከር 🍀
╰══•ೋ•๑♡๑♡✧• ══╯
/channel/ProDr_Boanerges
/channel/ProDr_Boanerges
/channel/ProDr_Boanerges

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም!
=============================

ዮሐንስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።
¹⁹ ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
²⁰ ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።
²¹ ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ስለ ስሜ ያደርጉባችኋል።
²² እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።
²³ እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።
²⁴ ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።
²⁵ ነገር ግን በሕጋቸው። በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
²⁶ ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
²⁷ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ።

ዮሐንስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
³³ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።

አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ!

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

🚨 መንፈሳዊ አካል እና ቁሳዊ አካል
(spiritual body and physical body)

በዚህ ዘመን ብዙ በመንፈሳዊ ዓለም እና በሚታየው ዓለም ላይ ስላሉ ነገሮች የሚሰጡ የተለያዩ ሀሳቦች አሉ ፣ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው ወይስ አይደሉም ብለን ከመረመርን ግን አብዛኞቹ አመለካከቶች ጉድለት ያለባቸው ናቸው ።
መንፈሳዊ ዓለም እና ቁሳዊ ዓለም የሚል ክፍፍል መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የለም ፣ መፅሐፍ ቅዱስ ዓለማትን የሚከፍለው በሁለት ነው ፣ የሚታዩ ዓለማት እና የማይታዩ ዓለማት በሚል ይታወቃሉ ። መንፈሳዊ ዓለም የሚባል ነገር በመጀመሪያ አልነበረም ፣ ተፈጥሯዊ የሆነው ነገር ወደ መኖር ሲመጣ የቀረው ተፈጥሯዊ ያልሆነው መንፈሳዊ ዓለም ተባለ ።

በመጀመሪያ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ

ዘፍጥረት 1:1

እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማያትን እና ምድርን ሲፈጥር መንፈሳዊ ዓለም እና ተፈጥሮአዊ ዓለም አይደለም የፈጠረው ፣ ሰማያትንና ምድርን እንጂ ። ሰማያት የተባሉት የ መናፍስት መኖሪያ ሲሆኑ ምድር ደግሞ የሰዎች እና የእንስሳት መኖሪያ ነበረች ። እነዚህን ዓለማት የሚታዩ እና የማይታዩ ዓለማት ብለን ልንከፍል አንችልም ፤ ምክንያቱም ቁሳዊ ዓለም ተፈጥሮአዊ ዓለም ማለት ስላልሆነ ።
ስለዚህ በዘፍጥረት 1:1 ላይ የተፈጠረው ሰማያት(heavens) እና ምድር ወይም ቁሳዊ ዓለም (physical / material world ) ነበር ማለት ነው ።

ሚታዩት ዓለማት እና ማይታዩት ዓለማት እንዴት ሊከፈሉ ቻሉ ?? የሚታየው ዓለም የመጣው ከማይታየው ዓለም እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል ።

ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።

ዕብራውያን 11:3

የሚታየው ዓለም የሚታየው ለማን ነው ?? ለሁሉም ፣ የማይታየው ዓለም የማይታየው ለማን ነው ?? ለ ተፈጥሯዊ አይን ። የማይታየውን ዓለም ማየት የማይችሉት ተፈጥሯዊ እይታ ያላቸው ፣ በተፈጥሮአዊ ብርሀን የሚያዩ ፍጥረታት ሁሉ ናቸው ። ስለዚህ የማይታየውን ዓለም የማይታይ ዓለም ያስባለው ተፈጥሮአዊ(Natural) የሆነው ነገር እንጂ ቁሳዊው(physical) የሆነው ነገር አይደለም ። በእርግጥ ቁሳዊ ነገሮች በተፈጥሮ ስርዓት ኡደት (natural phenomenon) ስለገቡ ከመንፈሳዊው ዓለም ውጪ ሆነዋል ።

ተፈጥሯዊ አካል እና ቁሳዊ አካል ልዩነት አላቸው ?? አዎ በትክክል የሚታወቅ ልዩነት አላቸው ። ቁሳዊ አካል ምድር ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ (ከስድስቱ ቀናት በፊት) እስካሁን ያለ ወደፊትም በሚመጣው አዲስ ምድር የሚቀጥል ነገር ነው ፤ ነገር ግን ተፈጥሮአዊ አካል ምድር ከጥፋት ውሃ በኋላ ድጋሚ በተፈጥሮአዊ ስርዓት ውስጥ ገብታ ስትሰራ የጀመረ እና ይሄ የተፈጥሮ ስርዓት ሲያበቃ የማይቀጥል ጊዜያዊ ነገር ነው ።

ተፈጥሯዊ ስርዓት ምንድነው ??

ተፈጥሮአዊ ስርዓት ማለት ከጊዜ ጋር አብሮ የሚሄድ የማያቋርጥ ለውጥ ፣ ግንባታ ፣ ጥፋት ፣ ሕይወት ፣ ሞት ወዘተ ... ያለበት ስርዓት ማለት ነው ። ተፈጥሮአዊ የሆነው ስርዓት ቁሳዊ የሆኑ ነገሮች በሆነ ኡደት ውስጥ ሲገቡ የሚፈጠር ነው ። ለምሳሌ ፦ ድንጋይ ቁሳዊ አካል ነው ፤ ነገር ግን ተፈጥሮአዊ አካል ግን አይደለም ። ድንጋይ ቁስ ቢሆንም ከጊዜ ውጪ ስላልሆነ የተፈጥሮአዊው ዓለም አካል ነው ። ድንጋይ ወደ ሰማይ ብትወረውር ፣ ፍጥነቱን(velocity) እና ተመልሶ የሚወድቅበትን ጊዜ(time) ፣ የሄዱበት ርቀት(distance) መለካት ስለምትችል ያንን ድንጋይ የተፈጥሮአዊው ዓለም አንድ አካል አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ ፣ ተፈጥሮአዊ አካል ካልከው ግን ልክ አይደለህም ።

ተፈጥሯዊ አካል ማለት ፣ በጊዜ ውስጥ ያለ ማቋረጥ ለውጥን የሚያስተናግድ እና ያ ለውጥ ከተቋረጠ ሞተ የሚባል አካል ነው ።
ቁሳዊ አካል ማለት ደግሞ የሚዳሰስ ፣ የሚነካ ፣ በተፈጥሯዊ የመንካት የስሜት ሕዋስ ሊታወቅ የሚችል አካል ማለት ነው ። በዚህም መሰረት ተፈጥሯዊ አካል ቁሳዊ አካል ነው ፤ ነገር ግን መንፈሳዊ አካልም ቁሳዊ አካል ሊሆን ይችላል ።

እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና

ሉቃስ 24:39

ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ያለው አካል መንፈሳዊ አካል እንደሆነ ይታወቃል ፣ አማኞች በትንሳኤ የሚቀበሉት መንፈሳዊ አካል የትንሳኤን አካል ነው ፤ ሆኖም ግን ኢየሱስ በዚያ መንፈሳዊ አካል እንኳን ደቀመዛሙርቱ ሊነኩት እንደሚችሉ አሳይቷቸዋል ። ከዚህ መረዳት የምንችለው መንፈሳዊ አካል ማለት ተፈጥሯዊ ያልሆነ እንጂ ቁሳዊ ያልሆነ ማለት እንዳልሆነ ነው ።

ተፈጥሯዊ የሆነው ስርዓት ቁሳዊ የሆነውን አካል ከመንፈሳዊው ተቃራኒ እንደሆነ አድርገን እንድናስብ አድርጎናል ። መንፈስ(a spirit) ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ መንፈሳዊ ማንነት ያለው ማለት ነው የሚል መልስ የሚሰጡ ሰዎች የሳቱት ነገር ይሄ ነው ። መንፈስ የሚለውን ቃል እና መንፈሳዊ የሚለውን ቃል አጥርተው መለየት የማይችሉት ቁሳዊ ነገር መንፈሳዊ ያልሆነ እንደሆነ አድርገው ስለሚረዱ ነው ። መንፈሳዊው ዓለም ማስተናገድ የማይችለው ተፈጥሯዊ አካልን እንጂ ቁሳዊ አካልን አይደለም ፤ ምክንያቱም ሥጋ እና አጥንት ያለው ሰው አሁን በሰማይ በአብ ቀኝ ስለተቀመጠ ።

መንፈስ ማለት ምን ማለት ነው መንፈሳዊስ ??

መንፈስ ( spiritual being ) የምንለው ምን አይነት ማንነት(person) እንደሆነ ኢየሱስ ገልፆልናል ። መናፍስት ነን የሚሉ ሰዎች ከኢየሱስ ምስክርነት የተሻለ የማንን ምስክርነት እንደሚያምኑ አይገባኝም ። ኢየሱስ በሉቃስ 24:39 ላይ ከተናገረው ተነስተን መንፈስ የምንላቸው እነማንን እንደሆነ መመልከት እንችላለንን ።


See My hands and My feet, that it is I Myself! Feel and handle Me and see, for a spirit does not have flesh and bones, as you see that I have.

Luke 24:39

ኢየሱስ መንፈስ እንዳልሆነ ለማስረዳት ያቀረበው ማስረጃ መታየት እና መነካት መቻሉን ነው ፣ በተፈጥሮአዊ አይናቸው እንዲያዩት እንጂ በራዕይ ወይም በመገለጥ እንዲያዩት አይደለም እዩኝ ያላቸው ፣ በዙሪያቸው የሚያዩትን ቁስ አካል እንደሚያዩት ኢየሱስን ማየት እንደሚችሉ ያሳየበት መንገድ ነው ፣ እንዲነኩት የጋበዛቸው ደግሞ በዙሪያቸው ያሉትን ቁሳዊ አካላት መንካት እንደሚችሉት እርሱንም መንካት እንደሚችሉ ሊያሳያቸው ነው ። ከዚያም መንፈስ ሥጋ እና አጥንት እንደሌለው ነገራቸው ፣ ሥጋ እና አጥንት እንዳለው በማየት እና በመንካት ማረጋገጥ መቻላቸውን እንረዳለን ። በዚያም ማመን ስለ ከበዳቸው ኢየሱስ መብላት የማያስፈልገው ሆኖ ሳለ ከተጠበሰ ዓሳ ቁራሽ ተቀብሎ በፊታቸው በላ ። በዚህ ደግሞ ሊያሳያቸው የፈለገው እነርሱ ከቁሳዊ አካል ጋር መነካካት እንደሚችሉ እርሱም እንደዚያ እንደሆነ ሊያሳያቸው ነው ። የትንሳኤ አካል ተፈጥሯዊ አካል ባይሆንም ቁሳዊ አካል እንደሆነ በዚህ ማረጋገጥ እንችላለን ።

መናፍስት የምንላቸው ኢየሱስ በሰጠን ማብራሪያ መሰረት በእውነተኛ አካላቸው ሲመጡ በተፈጥሮአዊ አይን የማይታዩየማይዳሰሱ እና ከቁሳዊ አካል ጋር መነካካት የማይችሉ የሆኑ
ማንነቶች ብቻ እንደሆኑ እንረዳለን ።

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

https://vt.tiktok.com/ZSNgbT7d7/

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

𝚃𝚑𝚎𝚛𝚎 𝚒𝚜 𝚙𝚘𝚠𝚎𝚛 𝚒𝚗 𝚝𝚑𝚎 𝚗𝚊𝚖𝚎 𝚘𝚏 𝚓𝚎𝚜𝚞𝚜

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ሰላም ለእናንተ ይሁን😃😃😃😃😃✨✨✨✨✨✨✨💫💫💫💫💫💫

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

"መስቀል የእግዚአብሔር ፍቅር ያረፈበት ቦታ ነው። በእግዚአብሔር እይታ መስቀል የሰማይ ፍቅርና የሰማይ ፍትህ የተገናኙበት፣ የተስማሙበት ቦታ ነው።"

   __Alistair Begg

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ሰላም ቅዱሳን የጌታ እየሱስ ፀጋ ይብዛላችሁ ዛሬ ምሽት ልዩ የፀሎት ግዜ ለታመሙ በተለያየ ጥያቄ ውስጥ ላሉ እፀልያለሁ የፀሎት መስመር +251930325200
ከነብይ ፍፁም ጋር

፨ ለሚያምን ሁሉም ይቻላል ፨

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ክፍል አንድ
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
#ጸጋ_እና_እውነት_የተገለጠው_ራሱ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው።

📖 ጸጋ እና እውነት በሙላት የተገለጠው ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣው አንድያ ልጁ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም ዘመናት በፊት መለኮታዊ ቃል ነበረ፤ ቃልም ደግሞ በሥጋ እንደተገለጠ ይናገራል።
📖 "ቃልም ሥጋ ሆነ" ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ አምላክነቱን እንደተጠበቀ ሆኖ እራሱን ዝቅ በማድረግ ሰው መሆኑን የሚያስረዳ ሐቅ ነው፤ ፊል.2፥6-8።
📖 መጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት ጅማሬ ከተረከበት ዘመን አንስቶ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት ድረስ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ቃል አድርጎ ሲገልጠው እናያለን፤ ይህ ቃል በፍጥረት ጅማሬ የጀመረ ሳይሆን ለጅማሬዎች ሁሉ መጀመሪያን የሰጠው ጅማሬ የሌለው ዘላለማዊ መለኮት እና አምላክ ነው።

📖 አምላክ በስጋ ውስጥ ማደር ለምን አስፈለገ?

ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ይሆንና ለእኛም በመሞት በጽድቅ ስራውን ይፈጸም ዘንድ፤ ከእግዚአብሔር ጋርም ያስታርቀን ዘንድ ነው፤ በተጨማሪም ከአባታችን ዘንድ የተሰጠ ድንቅ ሰማያዊ ስጦታ ነው።

#ጸጋ_እና_እውነት_የተገለጠው_ራሱ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው

መጥምቁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ክብር ሲገልጥ ከእኔ የሚበልጥ እና የሚሻል ክብር እንዳለ ተመልክቶአል። ይህ የሚሻል እና የሚበልጥ ክብር ጸጋን እና እውነት ተሞልቶ የመጣው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

#የጸጋው_አካል_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው

📖📖📖ይቀጥላል📖📖📖

/channel/abundant_grace_church

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ

@eyesus15

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

ባሳለፍነው ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ከካሪቢያንና ከፓሲፊክ የተውጣጡ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነትን ከአውሮፓ ህብረት ጋራ #ሳሞዋ በምትባል ሀገር በፈረሙ ወቅት አገራችን #ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት ተቀማጭነታቸው ብራሰልስ በሆኑ አምባሳደር አማካኝነት #በፊርማ_አጽድቃለች፡፡ ይህ #አደገኛ_ይዘቶች ያሏቸውን አንቀጾች የያዘው ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ከሚቀጥለው #ጥር ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
 
ይህ የትብብር ስምምነት በውሥጡ የያዛቸውን አስራ ሁለት ዋና ዋና አደገኛ ይዘቶችን ጠቅልለው የሚይዙ የተወሰኑ ሀሳቦች ለመጥቀስ ያህል ፡-
 
ሀ) የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጥሱ አንቀጾች በግልጽ መቀመጣቸው፣
 
ለ) ግብረሰዶማዊነት፣ የጾታ መቀየርና፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት መሆኑ፣
 
ሐ) ግብረሰዶማዊነት በርካታ ቀውሶች ማለትም በአካል፣ በሥነልቦናና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትልና ለሀገር ደህንነትም አደጋ መሆኑ፣
 
መ) የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን የሚንድ መሆኑ፣
 
ሠ) የሀገራችንን ሀይማኖት፣ባህልና እሴቶች የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶችን እንድንቀበል በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በእርዳታ ስም የምንገደድበትና ለዘመናዊ ባርነት ወይንም ቅኝ አገዛዝ ታልፈን የምንሰጥበት መሆኑ፣
 
በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት መሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡
 
በተጨማሪም ከተጠበቀው ውጭ ሀገራችን ይህንን ስምምነት በመፈረሟ የተጋረጠብንን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊ የሆኑ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም መንግስት ትኩረትን እንዲሰጠው ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡
 
በመሆኑም ይህ የመንግስት ውሳኔ እንደገና ተጠንቶ ውሳኔው እንዲቀለበስ ማለትም ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ማስተካከያ እስኪደረግበት ድረስ ወይንም እጅግ አደገኛ የሆኑት አንቀጾች ተነቅሰው ወጥተው የማንቀበላቸው መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ (Submission of an Interpretive Declaration) እስከምንችል ድረስ የምንወዳት ሐገራችን ኢትዮጵያ #ፊርማዋን_በመሰረዝ_ከስምምነቱ ራሷን እንድታገልል በሐገራችን ከፍተኛው የሥልጣን አካል ለሆነው ለተከበረው #የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤትና ለሐገሪቱ መሪ #ለክቡር_ጠቅላይ_ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በታላቅ አክብሮት እጅግ አስቸኳይ ጥሪን እናደርጋለን፡፡

የፊርማ ማሰባሰብ ሂደቱን ለመደገፍ ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ።

👉 https://keap.page/gq193/.html

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

መዝሙር 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
² ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።
³ ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።

❤መልካም ቀን💚

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
╭══•|❀:✧♡๑✧❀|: ══╮
  🪴 ለህይወት እንመካከር 🍀
╰══•ೋ•๑♡๑♡✧• ══╯
/channel/ProDr_Boanerges
/channel/ProDr_Boanerges
/channel/ProDr_Boanerges

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

⚜️ ትልቅነት ምስጢሩ ቀላል ነው....እርሱም ፀሎት ነው!!!

“ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥”
  — ሉቃስ 18፥1

📣 ፀልዩ ፀልዩ ፀልዩ

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ሠራዊቶች

እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ !
=====================

ኤፌሶን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥
² ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።
³ ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤
⁴ የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ፥ ይልቁን ምስጋና እንጂ።
⁵ ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።
⁶ ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።
⁷ እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤
⁸ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
⁹-¹⁰ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤
¹¹ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥

Читать полностью…
Subscribe to a channel