yeilmkazna | Unsorted

Telegram-канал yeilmkazna - ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

11338

Subscribe to a channel

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ኢድ ሙባረክ!

እንኳን አደረሳችሁ!

አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

🔘 ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🟢 حكم ربط أرجل الذبيحة

لا يجوز!!!
لأن فيه تعذيب للذبيحة وزيادة الألم فيها!!! ......

🎙 الشيخ صالح الفوزان حفظه الله


🟢 በእርድ ጊዜ የታራጁን እንስሳ እግር ማሰር!!!

❌ ይህ ተግባር የተከለከለ ነው።
ምክንያቱም እንስሳውን ይበልጥ ህመምና ስቃይ ይጨምርበታል። እንስሳውን ከሚገባው በላይ ማሰቃየትና መቅጣትም ነው።

እንስሳው በታረደ ጊዜ መወራጨቱ በራሱ የተወሰነ ህመሙን ይቀንስለታል። ከህመሙ እረፍትን እንዲያገኝ ይረዳዋል።

🎙 ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን حفظه الله

🔆 እስልምና ውብ የሆነ እዝነትን እያስተማረህ ጨካኝ አረመኔ አትሁን!!! 🔆


#أبو_عبد_الله_الكريري
@ibnuljezeriy

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

📢 ምርጥ ፕሮግራም 👍

📋 በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ቁርኣንን ለማኽተም የሚረዳ ፕሮግራም 👇

📆 ዙልሒጃ 01 : ከፋቲህ - አል ዒምራን
📆 ዙልሒጃ 02 : ከኒሳእ - ማኢዳህ
📆 ዙልሒጃ 03 : ከአንዓም - ተውባህ
📆 ዙልሒጃ 04 : ከዩኑስ - ኢስራእ
📆 ዙልሒጃ 05 : ከከህፍ - ኑር
📆 ዙልሒጃ 06 : ከፉርቃን - ፋጢር
📆 ዙልሒጃ 07 : ከያሲን - ሐዲድ
📆 ዙልሒጃ 08 : ከሙጃደላህ - ናስ
📆 ዙልሒጃ 09 : ፆም ፣ ተክቢራ ...
📆 ዙልሒጃ 10 : የዒድ ቀን 🎈🎁🎈

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️

📮 የማመልከቻ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
🛍 ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶👇
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

☘ የጠዋት ስንቅ ለቀልብ ❤️

{ الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ ۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَجِّ ۗ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّهُ ۗ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ }

«ሐጅ (ጊዜያቱ) የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን (እንዲሠራ) ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡ ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡»

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️
🌐 በኦንላይን 📱ለመመዝገብ :👇
@FurqanOnlineQuran
@FurqanOnlineQuran
⭕️ የtelegram ግሩፓችን :👇
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🔖ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት


بسم الله الرحمن الرحيم
فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها

ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል

" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል

🔹ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!

🔸መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል

☄ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል

[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]

"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"

🔸እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል

[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77

" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"

አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል

(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)

" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1

(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)

“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1

▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው
ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው

▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:-

☄ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ!
ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!

💥 ውድ የአሏህ ባሮች

አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:-

▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣

▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣

▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣

▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው

☄ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::
በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል
እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል

☄እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች

▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው።
ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት

☄" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "
አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር

(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)

" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!

✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም


@ዛዱልመዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

💢ቁርአን በመሀፈዝ ላይ ብዙ
    ሰዎች ሚሳሳቱባቸው ነገሮች📖.

📌ቁርአን መሀፈዝ ላይ የምንሳሳትባቸው
     ብዙ ስህተቶች ያሉ ቢሆንም ይህ ግን
     ቁርአኑን እየሀፈዝነውም ሆነ ሀፈዘን
     ከጨረስነውም ቡሀላ የምንወድቅባቸው
     ዋና የሚባሉት ስህተቶች ናቸው :

1⃣ቁርአኑን ስንቀራው አለማስተንተንና
     ትርጉሙን ለመረዳት አለመሞከር።


⏺አዎ ማስተንተንና ትርጉም መረዳቱ
    ስተማማኝ ሂፍዝ ለመሀፈዝ የሚረዳ
    ነገር ከመሆኑም ጋር ቁርአን የመውረዱ
    ዋነኛው ግቡና አላማውኮ ለፍዙን ብቻ
    ለመቅራትና ፊደሉን ለመሀፈዝ ሳይሆን
    እንድናስተነትነውና እንድንረዳውኮ ነው.

2⃣መጀመርያ የሀፈዝነውን በደንብ
     ሳናጠናክር አዲስ ለመሀፈዝ
     መቸኮል ወይም እየሀፈዝን
     የምናልፋቸውን ሙራጀዐ
     አለማድረግ.

⏺ያ ጀመዐ የምንሀፍዘውን ጥርት
     አድርገን አለመሀፈዛችን ወይም
     የሀፈዝነውን ሙራጀዐ ማድረግ
    መተዋችን የሀፈዝነውን እንድንረሳው
    ትልቅ ሰበብ ነው ስለዚህ የምንሀፈዘውን
    ጥርት አድርገን በማሰማትና ከዚያም
    ቡሀላ ሙራጀዐ በማድረግ ላይ እንጀግን። .

3⃣ቁርአን ሀፍዘን ከጨረስን ቡሀላ
     በምንሀፍዝበት ጊዜ የነበረንን
     ወኔ ወርዶ ሙራጀዐ ላይ ከመበርታት
     መዘናጋትና መታከት .

⏺ያ ጀመዐ ቁርአንኮ ሁሉም ሙስሊም
     አጅርን ፈልጎ ዘወትር የሚቀራው
     የማይጠገብ ጣፋጩ የአላህ ንግግር
     እንጂ እንዲሁ ተሀፍዞ የሚተው ነገርኮ
     አይደለም .

4⃣የምንሀፍዘው ሂፍዝ መጠን
     አለመገደብና የመሀፈዣ ጊዜ
     አለመለየት .


⏺አዎ ስንሀፍዝ አቅማችንን አመጣነኘጥነን
     ሂፍዛችንን ካልገደብነውና የምንሀፍዝበት
     የተወሰነ አንዲት ወቅት ከሌለን አእምሯችንን
     ይበታትንብናል ብዙም ሳንጠቀም እንዲሁ
     ጊዜያችንም ያልቅብናል.

5⃣ስንሀፍዝ የትኩረት ማነስና ወሬ
     እንዲሁም ጨዋታ ማብዛት

⏺አዎ ቁርአን በምንሀፍዝበት ወይም
     በሙራጀዐ ሰአት ከቁርአኑ ውጪ
     በሆኑ ነገር በስልክ ከጓደኛ በማውራትና
     መሰል ነገሮች መወጠር ለረጅም
     ሰአት ተቀምጠንም ምንም ሳንሀፍዝና
     ሙራጀዐ ሳናደርግ እንድንነሳ ሰበብ ነው .

6⃣ሲተሀፈዝም ሆነ ሙራጀዐ ሲደረግ
      ተጅዊዱን ሳይጠብቁ በጣም
      የፈጠና አቀራር መቅራት .

⏺ስንሀፍዝ በጣም እየፈጠንን መቅራታችንኮ
     ቶሎ እንድንይዘው አያደርገንም ቶሎ
     የሚያዝልን ትኩረት ሰጥተን ተረጋግተን
     እያስተነተንን ደጋግመን ስንለው እንጂ።.

አላህ ተግባሩን ይስጠን።

📮 ወደ ጉሩባችን ለመቀላቀል 👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

እስኪ አድ አድ አድ አድ አድ አድ አድ አድርጉ

ይህን ቅዝቅዝ ያለ ግሩፕን  አንቀሳቅሱት ባረካላሁ ፊኩም
Add- ------------------🎁🎁🎁🎁🎁🎁
Add------------------👍👍👍👍👍👍
Add------------------☘☘☘☘☘☘
Add------------------🎈🎈🎈🎈🎈🎈
Add------------------🌼🌼🌼🌼🌼🌼
  
🎁 በርቱ  አብሽሩ☕️

👇አብሽሩ ተሳተፉ አድ አድርጉ 👇

✅ ወደ መልካም ነገር የጠቆመ አጅሩ እንደ ሰሪው ነው።

Add...Add....Add....Add....Add...
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ፈታህ ❌
ፈታ❌
ፈተሀ ❌

*ፈትሀ*✅ فتحة✅

ደማ❌ ዱማ ❌

*ዶመህ* *በዷድ* ✅ ضمة✅

ኪስራ ❌

*ከስራ* ✅ كسرة✅

ፈትሀቴን ❌ ፈትህተይን❌

*ፈትሀተይን* ✅ فتحتين✅

ዶመቴን❌ ዶማተይን ❌

*ዶመተይን* ✅ ضمتين✅

ከስረቴን❌ከስራተይን❌ ኪስተረይን ❌

*ከስረተይን* ✅ كسرتين✅

ሠቂራ❌ ሰጊራ ❌

በ ሷድ, በገይን = *ሠጊራ* ✅ صغيرة✅

ስኩን❌❌❌
ሱክና❌❌❌

*ሱኩ...ን* ✅ سُكون✅

ሺዳ❌ ሸዱ❌

*ሸደህ*✅ شدة✅

*በዚህ መሠረት ያለዉን ችግር አስወግዱ*

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

📖| ቁርአን እና 20 ስኬቶቹ |✨
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
✅:ለአእምሮ ሰላም መፍትሔ ነው ፡ ፡
✅:እውቀትን ያስጨብጣል ።
✅:ለስነ ምግባር ምክንያት ነው ፡ ፡
✅:ልብን ንጹህ ያደርጋል ።
✅:የሰዎች ፍቅር ያጎናጽፋል ።
✅:የአላህን ፍቅር ያስገኛል ።
✅:ስኬትን ያመጣል ።
✅:በራስ መተማመንን ያላብሳል ።
✅:ላልታወቁ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል ።
✅:መልካም ስራ መስራት ድፍረት ያመጣል ።
✅:አንድን ሰው ከጀሀነም እሳት ይጠብቀዋል ።
✅:አንድን ሰው ከቀብር ቅጣት ይጠብቃል ።
✅:አንድን ሰው ከመፍራት ይጠብቃል ፡ ፡
✅:አንድን ሰው ቆሻሻ እንዳይሆን ይጠብቃል ፡ ፡
✅:አንድን ሰው ከምቀኝነት ይጠብቃል ።
✅:አንድን ሰው ከመናፍቃን ይጠብቃል ።
✅:አንድን ሰው ከውድቀት ይጠብቃል ፡ ፡
✅:አንድን ሰው ሁልጊዜ ወደ አላህ ከልሆነ እንዳያለቅስ ይጠብቃል ፡ ፡
✅:አሉታዊውን ወደ አዎንታዊነት ይቀየራል ፡ ፡
✅:የጀነት ትልቁ ቁልፍ ነው ፡ ፡

🍃:ቁርአንን በየቀኑ እንድናነብ ፣ ከቁርአን ጋር እንድንሰራ አላህ ይርዳን ৲

┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📖
┊  ✿ 🍃
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

☘⛅️ የጧት ቲላዋ ግብዣ 🌤☘

☘ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
🌀/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

📮 የምስራች 👇

📢 ዛሬ አንድ ሳምንታዊ ፕሮግራም እንጀምራለን። በዚሁ በፉርቃን የቁርአን ቻናል

#ይወቁ_ይሸለሙ
🎁🎈🎁🎉🎈🎊🎁

እየተማሩ እና እያወቁ የሚሸለሙበት ሳምንታዊ ውድድር

🛍 አሸናፊዎች የሚሸለሙበት ልዩ ውድድር

🌘 ከምሽቱ 1:00 ይለቀቃል ይጠብቁን ኢንሻአሏህ

💎 ጆይን እያደረጋችሁ👇 ለወዳጅ ዘመድም እየጋበዛችሁ

/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

💎ዛሬ አንድ ኸይር ነገር ላመላክታችሁ!!
.......
📌 ብዙ እህት ወንድምና እህቶች ቁርኣን አልቀሩም❗️ ፣ ወይም አቀራራቸው የተስተካከለ አይደለም‼️
⭕️ ታዲያ ለነዚህ እህትና ወንድሞቻችን አንደርስላቸውም ⁉️

✅ እንዲያውስ ይህን ግሩፕ
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school
ጆይን እንዲያደርጉ እናድርግ ፣ #ሼር አድርገንላቸው ከስህተታቸው ቢታረሙ ሙተን እንኳን ቢሆን አጅሩ ይደርሰናል እሱ ያስተማረውም ሰው አጅር ለኛ ይደርሰናል።

⭕️ አድ አናድርጋቸው። /channel/furqan_school

➺ ያ ጀማአ Add አድ አድርጉ ወደ ኸይር እንጣትራ ባረከላሁ ፊኩም 🌹🌹🌹

ኸይርንስራ ትንሽ ናት በለን እንተዉ

🌹አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ አድ አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ አድ አድ አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ አድ አድ አድ አድ
/channel/furqan_school
🌹አድ አድ አድ አድ አድ አድ አድ እያደረግን ወንድም እህቶችን ወደ ኸይር ነገር እናምጣቸው!!!

🌟 አድ ለምታደርጉ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ!

♻️/channel/furqan_school
♻️/channel/furqan_school
♻️/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🔖ቁርአንን መሳም ውሳኔው⚠️

📮 ቁርአንን መሳም እንዴት ይታያል? ይህ ተግባር ቢድአ ነው ወይስ ሱና ቁርአን መሬት ላይ ሲወድቅ አንስተን መሳም እንዲሁም አንዳድ ሰዎች እንደሚያረጉት ቀርተው ከጨረሱ ቡሀላ መሳም⁉️

ቁርአንን መሳም ቢድአ ነው አንድ ሰው ቀደምት ሰለፎች ሰሀባዎች ያልሰሩት ያልተገበሩት ነገር እንዲሰራ በዲን የለለን ተግባር እንዲፈጥር አይቻልለትም። ቀደምት ሰለፎቻችን ከኛ በበለጠ በዲን ላይ ➷አዋቂዎች ጥንቁቆች ናቸው፣ ይህን ተግባር አልሰሩም፣ ይህ አዲስ ፈጠራ ተግባር ነው።

👤
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ

☘ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
🌀/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

☘⛅️ የጧት ቲላዋ ግብዣ 🌤☘

☘ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
🌀/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🔺ቁርኣንን መተው የተለያዩ አይነቶች አሉት!!!

ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-

➊ ,ቁርኣንን መተው ማለት፣ ከመስማትና በርሱ ከማመን እንዲሁም ወደርሱ ከመጠጋት መራቁ ነው።

❷ , በቁርኣን ከመተግበር መራቅ፣ ቢያነበውም ቢያምንበትም ሀላልና ሀራም በሚያደርገው ነገር ላይ ተግባሪ ሆኖ አለመቆም ቁርኣንን ከመተው ነው።

➌ , በመሰረታዊም ሆነ በቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች በቁርኣን ከመዳኘት መራቅ ቁርኣንን ከመራቅ ነው።
እንዲሁም እርግጠኛነትን አያስይዝም፣ ማስረጃዎቹም ቃል ብቻ እንጂ እውቀትን አያስጨብጡም ብሎ ማመን ቁርኣንን ከመራቅ ነው።

➍ , ሲያነቡት አለመገንዘብና አለማስተንተን ተናጋሪው በሚናገረው ምን እንደፈለገበት ለማወቅ ጥረት አለማድረግ ቁርኣንን ከመራቅ (ከመተው) ነው።

➎ ,በቁርኣን መታከምን መተው፣ በርሱም ለጠቅላላ የልብ በሽታ መድኃኒትነትን መተውና ለህክምና ከርሱ ውጭ ባለ ነገር ላይ መድኃኒትነትን መፈለጉ በርሱ ከመታከም መራቁ ቁርኣንን ከመተው ነው።

ይህ ሁሉ የላቀው አላህ እንዲህ በማለቱ ውስጥ ይካተታል:-

﴿وَقالَ الرَّسولُ يا رَبِّ إِنَّ قَومِي اتَّخَذوا هذَا القُرآنَ مَهجورًا﴾ الفرقان ٣٠

«መልእክተኛውም “ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት” አለ።»
📚[አል ፉርቃን 30]አል ፈዋዒድ 82

Share👇🏻👇🏻
↷⇣🌹⇣↷
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🎉 تكبيرات العيد للشيخ الفاضل المبارك أبي مالك صابر بن عبود اللحجي رحمه الله تعالى

የዒድ ተክቢራ በታላቁ ሼኽ ሷቢር ቢን ዑቡድ አል-ለሕጂ አላህ ይዘንለት።

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

«በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
1️⃣ የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

2️⃣ መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::

3️⃣ የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"

4️⃣ አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።

5⃣ በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::

አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!»

©: ኡስታዝ ጣሃ አሕመድ

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

♻️ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፦
"ከቀናት ውስጥ አላህ ባሮችን በብዛት ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት እንደ #ዓረፋ ቀን አንድም ቀን የለም፤ እነሆ እሱ [አላህ] ይቀርብና #እነዚህ_ምን_ፈልገው_ነው? በማለት ስለእነሱ መልአክቶች ላይ #ይፎክራል" ይላሉ።

📕 ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል።

Te»/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

عظموا الله بتكبيره في أيامكم هذه، وأفضله
ما جاء عن الصحابة، وهو أنواع:


🔹منها: الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله والله أكبر، الله أكبر ولله الحمد.

🔹ومنها: الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر كبيرًا.

🔹 ومنها: الله أكبر كبيرًا ، الله أكبر كبيرًا ، الله أكبر وأجلُّ ، الله أكبر، والله الحمد.

🖋الشيخ صالح العصيمي

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

الله اكبر الله اكبر الله اكبر ، لا إله إلا الله

الله اكبر الله اكبر ولله الحمد

كبِّروا ليَبْلُغَ تكبيركم عَنَانَ السَّمَاءِ ..

كبروا فإن الله عظيمٌ يستحق الثنآء

الشيخ .د #ماهر_المعيقلي

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🔅እርስዎስ❓❓

በኦንላይን በቀጥታ በሚሰጠው የቁርኣን ትምህርት ፕሮግራም ብዙዎች ተመዝግበው በመማር ላይ ይገኛሉ።

1⃣ #ነዞር (ከአሊፍ ጀምሮ ቁርኣንን ለማኽተም)
2⃣ #ቲላዋ (አቀራርን በተጅዊድ ህግ ማስተካከል)
3⃣ #ሒፍዝ (ቁርኣንን በቃል መሸምደድ)

⏰ ታዲያ ጊዜው አለፎኛል ብለው እንዳይጨነቁ... በፉርቃን ሁሌም ምዝገባ አለ‼️ ሁሌም ትምህርት አለ‼️

🔍በኦንላይን ፕሮግራሙ ለመመዝገብ ከዚህ በታች👇 ያለውን Username በመጫን በውስጥ መስመር ያናግሩን 👇

📎 @FurqanOnlineQuran

🌀 ይህን መልዕክት ለሌሎችም በማሰራጨት እርስዎም የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ‼️

🔆 ያሰራጨ አጅሩ እንደሰሪው ነው❕
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
© ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

☘ የጠዋት ስንቅ ለቀልብ ❤️

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️
🌐 በኦንላይን 📱ለመመዝገብ :👇
@FurqanOnlineQuran
@FurqanOnlineQuran
⭕️ የtelegram ግሩፓችን :👇
/channel/furqan_school
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🍀 መሳጭ ቲላዋ 🍀

🌸ቁርአን የልብ መርጊያ ለደረቀ ልብ ማረስረሻ🌸

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️
🌐#በኦንላይን📱 ለነዞር ፣ ለተጅዊድ እና ለሒፍዝ ለመመዝገብ :👇
@FurqanOnlineQuran
⭕️ የtelegram ግሩፓችንን :👇ይቀላቀሉን
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ህይወት ከቁርኣን ጋር ምንኛ ያማረ፣ የተረጋጋና የጣፈጠ ነው።

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

#ይወቁ_ይሸለሙ

እየተማሩ እና እያወቁ የሚሸለሙበት ሳምንታዊ ውድድር

👉 ይህን በመንካት የተጅዊድ ትምህርታዊ ቪድዮ ይመልከቱ

👉 ቪድዮውን ካዩ በኋላ ከታች ያሉትን ጥያቄዎች ቪድዮው ስር ካለው ኮመንት መስጫ ቦታ ላይ ይመልሱ።

👉 ትክክለኛ መልስ ለመለሱ #ሶስት አሸናፊዎች ሽልማቱ ይበረከታል።

📮 ጥያቄዎቹ 👇

1⃣- ቪድዮ ላይ ያለው ትምህርት ስለምንድን ነው ?

2⃣ - ስንት አይነት የሚፈቀድ የአነባብ አይነት አለ ?

3⃣ - የሚከለከለው የአነባብ አይነት ምንድን ነው ?

4⃣ - ወስሉል ጀሚዕ ምን ማለት ነው ?

⭕️ መልሱን ቪድዮው ስር ካለው ኮመንት መስጫ ቦታ ላይ ማስቀመጥ አይርሱ

⏰ የመመለሻ ሰአት ከአሁኑ ምሽት 1:00 እስከ ነገ ከቀኑ 6:00 ድረስ ብቻ
ቪድዮ ለማየት 👇

🌐 በቴሌግራም
/channel/furqan_school/9133

🌐 በፌስቡክ
https://fb.watch/f5XnFY-Hrt/

የአሸናፊዎች እጣ ነገ ይወጣል ! ኢንሻአሏህ

☘ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🔅እርስዎስ❓❓

በኦንላይን በቀጥታ በሚሰጠው የቁርኣን ትምህርት ፕሮግራም ብዙዎች ተመዝግበው በመማር ላይ ይገኛሉ።

1⃣ #ነዞር (ከአሊፍ ጀምሮ ቁርኣንን ለማኽተም)
2⃣ #ቲላዋ (አቀራርን በተጅዊድ ህግ ማስተካከል)
3⃣ #ሒፍዝ (ቁርኣንን በቃል መሸምደድ)

⏰ ታዲያ ጊዜው አለፎኛል ብለው እንዳይጨነቁ... በፉርቃን ሁሌም ምዝገባ አለ‼️ ሁሌም ትምህርት አለ‼️

🔍በኦንላይን ፕሮግራሙ ለመመዝገብ ከዚህ በታች👇 ያለውን Username በመጫን በውስጥ መስመር ያናግሩን 👇

📎 @FurqanOnlineQuran

🌀 ይህን መልዕክት ለሌሎችም በማሰራጨት እርስዎም የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ‼️

🔆 ያሰራጨ አጅሩ እንደሰሪው ነው❕
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
© ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

🌹سورة الكهف

🎙خليفة الطنيجي
📚ሱረቱ'ል ከህፍ

💎የተረጋጋና አስተወሎት የሚያሰርፅ ቂርኣት💎


▷ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል :- አንድ አማኝ #ቁርአንን ማንበብ ባበዛ ቁጥር ቀልቡ ይበራል፣ መተናነሱ ይጨምራል፣ ቁርአን ተፅእኖ ያሳድርበታል (ይገሰፃል)። ነገር ግን (ከቁርአን) ዝንጉ የሆነ አካል በዚህ ቁርአን ምንም አይጠቀምም።
📚"كلمــات رمضانـية ١٤٤٠هـ"


◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
⭕️ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ⭕️
🌐#በኦንላይን ለመመዝገብ :👇
@FurqanOnlineQuran
⭕️ የtelegram👇ይቀላቀሉን
/channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ታላቅ የምስራች
------
ወሎ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ አዳሪና ተመላላሽ የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

⭕️ አጂብ ‼️....

☝️ ተመልከቱ ይህን ቃሪእ ፣ አሏህ ሁለት አይኖቹን ወስዶበት ግን በብሬል ቁርኣን ቀርአንን ተምሮ ሀፍዞ በዚህ መልኩ በሚያምር አቀራር ሲቀራ ተመልከቱ ‼️

🚫 እኛስ ... ሁለት አይን እያለን ፣ሙሉ አካል አሏህ ሰጥቶን— ከቁርኣን ግን ርቀናል ❌

🔺 እርሱ ማስተዋሉን ይስጠን ...

Join : 👇 Share ... Share....👇
🌀 /channel/furqan_school
🌀 /channel/furqan_school

Читать полностью…

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

አተርፍ ባይ...

🔅የቁርኣን ቃላትን ከዐረብኛ ውጪ ባሉ ፊደሎች መፃፍ ክልክል ሆኖ ሳለ ቁርኣንን ለመማር ለማስተማር በሚል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ቁርኣንን በሌላ ቋንቋ የሚፅፉ ብዙዎች ናቸው።
🔅ለሰለምቴ/አዲስ ወደ ኢስላም ለገቡ ወገኖችም ይሁን ሳይማሩ ዕድሜያቸው ለገፋ ሰዎች ቁርኣንን በሌላ ቋንቋ እየፃፉ የሚያስተምሩና እንደ ኣየተል-ኩርሲይ ወዘተ ያሉ ልዩ ትሩፋት ያላቸው አንቀፆችን በአማርኛ፣እንግሊዘኛ፣ኦሮሚኛም ይሁን በሌሎች ከዐረብኛ ውጪ ባሉ ፊደሎች እየጻፉ የሚሸጡ፤ ይህንንም የሚያሳትሙ ሰዎችና ድርጅቶች በሙሉ ለዲናቸው ሲሉ (አላህን ፈርተው) ከዚህ ሊታቀቡ ይገባል!።
🔅ስለዚህ የፈጀውን ያክል ጊዜ ፈጅቶ ቁርኣኑ በወረደበት ፊደል፣ ነቢዩ ﷺ እና ሰሓባዎች ባስተማሩበት መልኩ፣ ቀደምት ሙስሊሞች እንደተማሩት በዐረብኛ ፊደላቱን አጥንቶ ከዛም በየደረጃው ቃላትን እያጣመሩ፤ ለጀማሪ በተዘጋጁ መጽሐፍት እየታገዙ መቅራትና መማር ይገባል።
🔅ከላይ የተባለው ሁሉ የቁርኣንን የዐረብኛውን ቃል እራሱን በሌላ ፊደል መጻፍን በተመለከተ ነው እንጂ የቃላቱን ትርጉም ዕውቀትና ብቃት ባለው ሰው ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎሙ (መፈሰር) የተፈቀደና ለመላው የሰው ልጆች የቁርኣንን መልዕክት በሚገባቸው ቋንቋ ከማድረስ አንጻር ተፈላጊና ተወዳጅም ነው።
🔅ነገር ግን ማንኛውንም የትርጉም ስራ ለመስራት ሁለቱን ቋንቋዎች በሚገባ ማወቅና በሁለቱ ቋንቋዎች መካከል ሊኖር የሚችልን የንግግር ዘይቤ ልዩነት ከግምት ውስጥ ባደረግ መልኩ የትርጉም ስራውን ማስኬድ እንዲሁም ወደ ሌላ ቋንቋ የተተረጎመውን ቁርኣን ሳይሆን የቁርኣን መልዕክት ማለት (ብሎ መሰየም) ይገባል።

💥ቁርኣንን በሌላ ፊደል ከመጻፍ ይጠንቀቁ! ቁርኣን ከአላህ ዘንድ የወረደው በዐረብኛ ቋንቋ ነው። ከነቢዩ ﷺ ዙሪያ የነበሩ ሰሓባዎችም የጻፉት በዐረብኛ ቋንቋ እና ፊደል ብቻ ነው።

﴿نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ١٩٣ عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ١٩٤ بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ١٩٥﴾ [الشعراء: 193-195]
ከአስጠንቃቂዎች ትሆን ዘንድ ቁርኣንን ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ ታማኙ መንፈስ ጂብሪል (ከአላህ ዘንድ) ልብህ ላይ አወረደው።” (አሽ-ሹዐራእ 193-195) ።

✍ጥቅል መልዕክት ለማስተላለፍ ያመች ዘንድ "ቁርኣን የህይወት ብርሃን" ከሚለው መፅሀፍ ተቀንጭቦ የተዘጋጀ።

ዛዱል መዓድ

Читать полностью…
Subscribe to a channel