""እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::""
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቱአ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ:እነሆ በዚ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው:በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው ::ከዚ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ "ማርያም" ብለው አወጡላት::የእመቤታችን ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና:-""ማ"" ማለት ማህደረ መለኮት: ""ር"" ማለት ርግብየ ይቤላ: ""ያ"" ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት:""ም"" ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስትሥራየ ኃጥያት ማለት ነው::አንድም "ማርያም" ማለት ልዩ ከጣዖት:ክብርትእምፍጥረታት:ንጽህትእምሃጥያት:መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው:ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ተፈስሂ ቤተ ይሁዳ ወተሃሠዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው::አንድም "ማርያም" ማለት መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው:ይህስ እንዴት ነው ቢሉ:እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሱአም በፍቅሩአ:በጣዕመ ፍቅሩአ የሰውን ሁሉ ኃጥያት:ክፋት ፍቃ ከልጁአ ከወዳጁአ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አሉአት::አንድም ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሄር ወሰብእ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ውብህት(ስጥውት) ማለት ነው::አንድም ማርያም ማለት መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ማለት ነው።አንድም እየተባለ የስሟ ትርጉም ቢዘረዘር የክረምት ዝናም ቀለም ቢሆንና ምድርና ሰማይ ወረቀት ቢሆኑ መግለጽ አይቻልምና..
ይቆየን!!!
በይቅርታውና በቸርነቱ ተመልክቶ ለ እመቤታችን የልደት በዓል ያደረሰን አቤቱ ክብር ምሥጋና ለእርሱ ይሁን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን!!!
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
ሰኞ
ማዕዶት / ፀአተ ሲኦል
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ማለፍ ማለት ነው።ይህችውም ጌታችን በትንሣኤውነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮለማስገባቱ መታሰቢያ ናት።በዚህች ዕለትበጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደንቅ ብርሀን ፣ከሞት ወደ ሕይወት ፣ከሲኦል ወደ ገነት፣ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን።ዮሐ.፲፱÷፲፰ ሮሜ.፭፥፲-፲፭
ማክሰኞ
ቶማስ
ይህች ዕለት ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትሆን ዘንድ "ቶማስ" ተብላ ትጠራለች ።የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጥ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም ።በመጣ ጊዜም ሌሎች ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት "ካላየሁ አላምንም" ብሎ ነበር ።በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን ድጋሚ ለሐዋርያት ተገለጠ።ቶማስም ጌታን አይቶ ማመኑ ፣ ጊታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይነገርበታል። ዮሐ.፳፥፳፬-፴
ረቡዕ
አልዓዛር
በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ሥልጣን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርን አይተው ሕዝብ በጌታችን ማመናቸው ይታሰብበታል።ዮሐ.፲፩፥፴፰-፵፮
ሐሙስ
የአዳም ሐሙስ/ አዳም
በዚህች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ 'አምስት ሺህ አምስት መቶ አመት ' ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ " ብሎ የገባለትን ኪዳን የተሰጠውን ተስፋ እንደተፈጸመና ከነ ልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ መግባቱን ፣መመለሱን እናስባለን። ሉቃ.፳፬፥፳፭-፵፱
ዓርብ
ቤተክርስቲያን
በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ አክብሮ እንደመሠረታት ይዘከራል።ይህም በዋናነት ስለ ሰውነታችን ቤተክርስቲያን ነገረ ግን ሰለ ሦስቱም የቤተክርስቲያን ትርጉም መሆኑ ልብ ይለዋል። ማቴ.፳፮፥፳፮-፳፱ ሐዋ.፳፥፳፰
ቀዳሚት ሰንበት
ቅዱሳት አንስት
ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ላገለገሉት፣ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት ፣ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብር ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት ፣ በትንሣኤውም ጌታችንን ከሁሉ ቀድመው ለማየት ለበቁት ሴቶች "አንስት" መታሰቢያ ትሆን ዘንድ "ቅዱሳን አንስት" ተብላ ትጠራለች። በዚህችም ዕለት ስለ ቅዱሳን አንስት ይዘከራል፣ ይሰበካል።
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
ዳግም ትንሣኤ
በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መገለጡን ፤የትንሣኤውን ምሥጢር ለሦስተኛ ጊዜ ለሐዋርያት ተገልጦ ሰላምን የመስበኩ እና ሥልጣንን የመስጠቱ ነገር ይታሰባል።
ይቆየን!!!
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
ትንሣኤ ክርስቶስ
ስለ ክርስቶስ መነሣት አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፡፡ ይህም ዳዊት "ይትነሣዕ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጉየዩ ጸላዕቱ እምቅድመ ገፁ" እግዚአበሔር ያነሣ፣ ጠላቶቹም ይበተኑ፣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ፡፡ መዝ. 67፡1 "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመዘንቃህ እምንዋም ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ" እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደኃያል ሰው ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ መዝ. 77፡65
በደቂቀ ነቢያት፡- በሠኑይ ዕለት ይቀስፈነ ወበሠሉስ መዋዕል ይሠርየነ ወየሐይወነ አመሣልስት ዕለት ይትነሣእ ወንቀውም ምስሌሁ፡፡ በኦሪት አንበሳ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ዕርግ እምንዝኅትከ እየተባለ በብሉይ በሐዲስ በብዙ ዓይነት ተነግሯል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ ተነሣ ማለት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ዝም ብሎ ድንጋዩ እንደ ተገጠመ ተነሥቶ ሄደ፡፡ ከዚያ በማርቆስ ወንጌል እንደተጻፈው ሴቶች ወደ መቃብሩ ሂደው "መኑ ይከሥትለነ" "ድንጋዩን የሚገለብጥልን ማነው?" ሲሉ መላእክት አነሱላቸው፡፡ /ማር. 16፡1-8፤ ማቴ. 28፡1-8 ሉቃ. 24፡1-10 ዮሐ. 20፡1/
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክታቡ "ክርስቶስ ላንቃላፉት በኵር ሆኖ ተነሥቷል፡፡" ይላል ይህም ማለት መጀመሪያ ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሣ እሱ ነው፡፡ ሌላ ገና አፈር ሆኖ ለመነሣት ዕለተ ምጽአትን ይጠብቃል "ተነሥአ እግዚእነ ከመይምሐረነ በተንሥኦቱ እንከሰ ዳግመ ኢይመውት" ከእንግዲህ ወዲያ ሁለተኛ አይሞትም" እነ አልአዛር ቢነሱ ተመልሰው ሞተዋል፣ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃሉ፡፡
ጌታችንና እመቤታችን ግን ተመልሰው አይሞቱም እንዲህ ያለው ትንሣኤ ዘጉባኤ ይባላል፡፡"ቀደመ ተነሥኦ እምኲሉሙ ሙታን" ከሙታን አስቀድሞ ተነሣ የተባለው ስለዚህ ነው፡፡ እስከ አሁን ሁለቱ ብቻ ናቸው ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሡት፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ ሊታይ የሚገባው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ ማርያም መግደላዊነት ቀርባ ልትነካው ባሰበች ጊዜ ገና ወደ አባቴ አላረኩምና አትንኪኝ ብሎ እንደነገራት በዮሐንስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ የዚህ ዋና ትርጉሙ ጌታችን ሴት እንዳትነካው /ንቆ/ ሳይሆን ማርያም መግደላዊት የሚያርግ መስሏት ስለነበር ገና 40 ቀን እቆያለሁ ለማለት ነው፡፡
ወንጌላዊው ዮሐንስ በሌላ ምዕራፍ "አኅዛ እገሪሁ ወሰገዳ ሎቱ" እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት ይላል፡፡ አሁንም በዚሁ ምዕራፍ 20 ቁጥር 24 "ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም ምልክት ከእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ማለቱን ያስረዳል፡፡ በእርግጥ ቶማስ ጌታ ከሙታን ተነሥቶ በዝግ ቤት ገብቶ ለቀደ መዛሙርቱ ሰላም ለእናንተ ይሁን ሲላቸው አልነበረም በዚህም ምክንያት ተጠራጥሮአል፡፡
ጌታ ደግሞ ለምን ተጠራጠርክ ካልዳሰስኩህ አላምንም ብለሃል፡፡ በልና የተወጋው ጎኔን እይ፤ የተቸነከረው እጄን ተመልከት፡፡ ብሎ እንዲዳስሰው ፈቀደለት፡፡ ቶማስም ሲዳስስ እሳተ መለኮት ቀኝ እጁን አቃጠለው፡፡
"እግዚእየ ወአምላኪየ" ፈጣርዬ አምላኬ አምላኪየ "መዳሰሱ ሲያይ" እግዚእየ ማቃጠሉን ሲያይ አምላኪየ አለ፡፡ ይኸንን "እግዚእየ ወአምላኪየ" ያለውን ወስዶ በሃይማኖተ አበው "አንተ ቀዳማዊ ወአንተ ዳኅራዊ" አንተ መጀመሪያ አንተም መጨረሻ ነህ ብሎ ተርጉሞታል፡፡
ይህች ገቦ መለኮት የዳሰሰች እጅ ሳትሞት ሕያዊት ሆኖ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ትኖራለች፡፡ ጥር 21 ቀን የአስተርእዮ ዕለት በዓሉ ይከበራል፡፡ ይህ ታሪክ የሚገኘው መጽሐፈ እንድልስ በሚባለው ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድም "ይትፌሣሕ ሰማይ ወትተሐሰይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ኅምዝ" ያለው ትሑታኑ ደቂቀ አዳም ልዑላኑ መላእክት ጌታ አስታረቃቸው ሁሉም ደስ አላቸው ማለቱ ነው ሰማያውያንና ምድራውያን በክርስቶስ አንድ ሆኖአልና፡፡ "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ" "ምድርም በክርስቶስ ደም ተቀድሳ የክርስቶስን ትንሣኤ ታከብራለች"፡፡
አንድም ያመኑ ምዕመናን ሁሉ በክርስቶስ ደም ነጻ ወጥተው በዓለ ትንሣኤን ያከብራሉ መጽሐፍ ለግዕዛን ሰጥቶ መናገሩ የተለመደ ነው፡፡
"ትባርኮ ምድር ለእግዚአብሔር" ምድር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች ይህ ማለት ማኅበረ ምዕመናን እግዚአብሔር ያመሰግኑታል ማለት ነው፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር በመቆየት ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ ሞትን ድል ነስቶ ተነሥቶልናል፡፡
ዕለተ ኅሪት
ዕለተ ኅሪት ተብላ በኢሳይያስ የተጠቀሰችው በዘመነ ብሉይ ዕለት ኅሪት ዕለተ ፄዋዌናት፣ ኅሪት አላት "ወሶበይበዝኅ አወጽአከ ለትፍስሕት" እንዲል፣ በሰባ ዘመን ትወጣለችሁ የሚለው ቃል ተስፋ ሰምተው ስለ ነበር ዕለተ ኅሪት አላት ዕለተ መድኃኒት፣ ዕለተ ሚጠት፣ ከፋርስ ከባቢሎን ሰባዘመን ኑረው የተመለሱበት ስለሆነች፡፡"
ዕለት ኅሪት በዘመነ ሐዲስ ዕለተ ጽንስ፣ ዕለተ መድኃኒት ዕለተ ልደት፣ዕለት ኅሪት ዕለተ ሥቅለት፣ ዕለተ መድኃኒት ትንሣኤ ዕለት ኅሪት ተስፋ ያለው ንስሐ የሚገባበት፣ ዕለተ መድኃኒት ዳግም ንስሐውን ጨርሶ ሲወጣ፣ ለበጎ ሁሉ የሚሆን እንጂ በጥቂት የሚወሰን አይደለም፡፡
ነፍሳት ከሲኦል የወጡ መቼ ነው?
ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ዓርብ በሠርክ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ሰበከሎሙ ግዕዛነ" "ነጻነት አወጃላቸው" ይላል፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ "ሰላም ለኵልክሙ" "ሰላም ለእናንተ ይሁን" እንዴት ሰነበታችሁ? አስታረቋችሁ ሲላቸው ነው፡፡ አዳም የተቀጠረች የድኅነት ዕለት ዛሬ ናት ተንሥኡ ለጸሎት ሲል ነፍሳትም ምስለ መንፈስከ አሉ፡፡
ጌታም "እለውስተ ጽልመት ጻኡ ወእለ ውስተ ሲኦል ተከሠቱ ወርእዩ ብርሃነ" "በጽልመት ውስጥ ያላችሁ ውጡ፣ በሲኦል ያላችሁ ተገለጡ ብርሃንም አዩ" ብሎ እልፍ ፀሐይ ቢገባበት የማይለቅ የሲኦልንም ጨለማ ብርሃነ መለኮቱን ነዛበት ያኔ ጨለማው ለቀቀ የዚያን ጊዜ ወጐዩ ዓቀበተ ሥጋ መናፍስት /አጋንንት/ በዚህ ጊዜ ነፍሳትን የተቆራኙ አጋንንት ሸሹ፣ እለ ውስተ ሲኦል ጻኡ፤ ወእለ ውስተ ጽልመት ተከሠቱ ብሎ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት አገባቸው፡፡
በዚያ በሲኦል ሳሉም "ነፍሶሙ ለጻድቃን ውስተ ዕደ እግዚአብሔር" እንዲል "ያድነናል ብለው እንደነቢያት እንደአብርሃም፣ ያሉ አበው ዕደ እግዚአብሔር እንደ አጐበር እንደ ድንኳን ሆኖ ይጠብቃቸው ነበር እንጂ እንደ ኃጥአን ስቃይ መከራ አይጸናባቸውም ነበር፡፡"
ፊያታይ ዘየማን ደግም "አንተ ትቀድሞ ለአዳም በዊአ ውስተ ገነት" "አንተ አዳምን ቀድመህ ወደ ገነት ትገባለህ" ብሎት ነበርና እሱ ተቀድሞ ሲገባ፣ አዳም ከእነ ልጆቹ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘአውረሰነ መንግሥቶ ሰማያዊተ ሰማያዊት መንግሥቱን ላወረሰን ለአግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እያሉ ገብተዋል፡፡
በዕለተ ዓርብ ስንት ታምራት ታይቷል?
በዕለተ ዓርብ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ የታዩት ታምራት ሰባት ናቸው፡፡ በሰማይ ፀሐይ ጨለማ ሆነ፣ ጨረቃ ደም ሆነች፣ ከዋክብት ረገፉ በምድር አዕባን ተፈተቱ፡፡ መቃብራት ተከፈቱ፡፡ አምስቱ ምእት ቢጽ ሙታን ተነሡ፤
የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ፡፡ "ወወጽአ ሕሩይ መልአክ እማዕከለ ኲሎሙ መላእክት እንዘ ይእኅዝ ሠይፎ ከመያጥፍኦሙ ለአላውያን፣ ወሶበ ከልአቶ ምሕረቱ ለአብ ወኂሩቱ ለወልድ ሜጠ ዝኩ መልአክ ሠይፎ ክሱተ ወዘበጦ ለመንጠላዕተ ቤተ መቅደስ ወሰጠጦ ወከፈሎ ለክልኤ፡፡"
መልአኩ ላጥፋቸው ቢለው ተውካጠፋኋቸውማ እኔ አጠፋቸዋለሁ አይደል? ብሎ አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ከለከሉት፣ መልአኩ ተናድዶ ሰይፉን ሲወረውረው የቤተ መቅደሱን መጋረጃ ለሁለት ከፈለው ብሏል፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ፤
ለምን 450 ጊዜ እግዚኦ ይባላል?
በዚሁ ዕለት በአራት መዓዘን እየዞርን 450 ጊዜ ምሕላ እናደርጋለን፣ ምሕላ የምናደርገውም አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የአዳም ልጆች በሲኦል ሆነው አቤቱ ይቅር በለን ብለው የለመኑትን ለማስታወስ ነው ከምሕላው በኋላ በወይራ እየተጠበጠቡ የንስሐ ስግደት እንደየ አቅሙ ይሰጣል፡፡ ከምን የተነሣነው ቢባል የክርስቶስን መከራ እንቀበላለን፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለናልና፡፡ የኛን መከራ ተቀብሎ እንዳዳነን እሱ የተቀበለውን መከራ እንቀበላለን፣ እንገረፋለን፣ አላውያን ነግሥታት፣ አላውያን መኳንንት፣ ሃይማኖታችሁን ካዱ ቢሉን ቢገርፉን እንገረፋለን በሰይፍ ቢመቱን፣ ቢሰቅሉን፣ መከራውን በጸጋ እንቀበላለን፡፡ ለማለት ነው፡፡ "ወዘኢጾረ መስቀለ ሞትየ ኢይጸመደኒ" እንዳለ ያለ ነው፡፡ እሱ የተቀበለው መከራ ተቀበሉ ተብሎ ታዟልና፡፡
በዕለተ ዓርብ ንሴበሖ ለእግዚአብሔር የሚባለው ለምንድነው?
በስቅለት፣ ዓርብ ማታ ከእግዚኦታ /ምሕላ/ በኋላ ንሴብሖ ይባላል፡፡ ምክንያቱም እስራኤል በምድረ ግብጽ 215 ዘመን በባርነት ቀንበር ሲገዙ ከነበሩ በኋላ በሙሴ መሪነት የኤርትራን ባሕር ስላሻገራቸው "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ" እያሉ አመስግነውታል፡፡ እኛ ደግሞ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት ስለአገባን "ንሴብሖ" እያልን እናመሰግነዋለን፡፡
ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ከተባለ በኋላ እግዚአብሔር ይፍታህ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር ይፍታህ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር ይፍታህ የሚባልበት ምክንያትም ካሣ ከተፈጸመ ወዲያ፣ ልጅነት የተመለሰ፣ ነጻነት የተገኘ ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ስለሆነ ነው
"ሴትን አይቶ የተመኛት አመነዘረ" ብሏል፡፡ እንኳንስ ከወንድ ሚስት መድረስ አይቶ የተመኘ በደለ፣ በማለት የኦሪትን ሥርዓት እየፈጸመው ሄደ፤
ይቆየን!!!
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ፫
ረቡዕ
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አመዘጋገብ መሠረት በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ነገሮች ተፈጽመዋል፤
አንደኛ የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
ሁለተኛ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
ሦስተኛ ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹ሲኒሃ ድርየም›ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌእሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማቷል፡፡
ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡
‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤››በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች››እንደሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ይሁዳ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ፡፡ ይህ ታሪክም በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ በሚከተሉት ምዕራፎች ተመዝግቦ እናገኛዋለን፤ ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምንይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡
ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡
ይቆየን!!!
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
ውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ
ተደስቷል፡፡ «ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደ ሆነ
አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ
ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡
የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲዖል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ
ሶ የፈጠረ አምላክ ተራቆተ፡፡ ጸጋውን ለዕሩቃን የሚያለብስ አምላክ ልብሱን ተገፍፎ ዕራቁቱን ቆመ፡፡ ጨለማን ለብሶ ጨለማን ተንተርሶ ይኖር የነበረውን ሰው መልሶ ብርሃን ያለብሰው ዘንድ የብርሃናት ጌታ፣ የጸጋ ሁሉ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገፈፈ፤ ተራቆተ፡፡
የሲኦል ወታደሮች የሆኑት አጋንንት የሰውን ልጅ ጸጋ ገፍፈውት ነበርና ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ በሰጣቸው ሰዓት ወታደሮች ልብሱን ገፍፈውታል (ማቴ 27¸27)፡፡ የሰው ልጅ ለቀረበለት ምርጫ የሰው ምላሽ ዘራፊው፤ ገራፊው ወንበዴ በርባን እንዲፈታለት ነበር፡፡ ‹‹አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኅበ ዘፈቀድከ! እነሆ እሳትና ውኃን አቅርቤልሃለሁ፣ እጅህን ወደ ፈቀድከው ስደድ›› ሲባል የሰው ልጅ እጁን ወደ እሳት ሰደደ፡፡
7. #ርግዘተ ገቦ (ጎንን መወጋት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ጎኑን በስለታም ጦር መወጋቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ርግዘት›› የሚለው ቃል ረገዘ- ወጋ ከተሰኘ የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ገቦ ማለት ደግሞ ጎን ማለት ነው፡፡ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ፣ በግራና በቀኙ ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ነበር፡፡ ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር ጭናቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ አይሁድ ጲላጦስን በለመኑት መሠረት ጭፍሮቹ የሁለቱን ወንበዴዎች ጭን ጭናቸውን ከሰበሩ በኋላ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ሲመጡ ፈጽሞ እንደሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፡፡ ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ስለወጋው ወዲያው ከጎኑ ደምና ውኃ ፈሰሰ (ዮሐ 19¸33)፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ያደርገው ዘንድ ሞተ፤ የሰው ልጅ በዘለዓለማዊ ሞት ተይዞ ነበርና፡፡ ትልቁ ሞት በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ በጌታችን ሞት ግን ሞት ራሱ ድል ተነሣ፡፡ የሞት መውጊያ በሆነ ኃጢአት የሞተውን ሰው ለማዳን ጎኑን በጦር ተወጋ፡፡ በሰው ልቡና ተተክሎ የነበረውን ኃጢአት ከነሥሩ ነቅሎ ስለጣለው ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?›› ተባለ፡፡ የሞት መውጊያው ኃጢአት ነበርና (1ቆሮ 15¸54-55፤ ኢሳ 25¸8፤ ሆሴ 13¸14)፡፡
ከተወጋው የጌታችን ጎን ደምና ውኃ መፍሰሱም የእግዚአብሔርን ልጅነትና የዘለዓለምን ሕይወት አጥቶ የነበረው ሰው ልጅነቱና ሕይወቱ እንደተመለሰለት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ምክንያቱም ከጎኑ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቆ ልጅነትን፣ ደሙንም ጠጥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛልና (ዮሐ 3¸5፤ ዮሐ 6¸54)፡፡
8. #ተአሮተ_ድኅሪት (ወደ ኋላ መታሠር)፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እጆቹን ወደኋላ የፊጥኝ መታሠሩን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተአሥሮት›› የሚለው ቃል አሠረ (ሲነበብ ይላላል) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አሠረ ማለት ነው፡፡ ‹‹ ድኅሪት ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተድኅረ- ወደኋላ አለ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ በሰጠባት በዚያች ዕለትና ሰዓት ሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች እጁን የኋሊት አሥረው መሬት ለመሬት ጎትተውታል፡፡ አፍገምግመውታል (ዮሐ 18¸12)፡፡
በኃጢአት ሰንሰለት የኋሊት ታሥሮ ጠላት ዲያብሎስ የሚያፍገመግመውን የሰው ልጅ ለማዳን፣ ሰውንም ከኃጢአት እሥራት ይፈታ ዘንድ ሲል መድኃኔዓለም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ የኋሊት ታሠረ፡፡
#አምሥቱ_ቅንዋተ መስቀል
_______~___________
መድኃኒታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረባቸውን ጠንካራ የብረት ችንካሮች (ምስማሮች) የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ቅንዋት›› የሚለው ቃል
ቀነወ- ቸነከረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ መስቀል ማለት ደግሞ የተመሳቀለ እንጨት ማለት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች
9 #ሳዶር ፣
10 #አላዶር ፣
11 #ዳናት ፣
12 #አዴራ ፤
13 #ሮዳስ ይባላሉ፡፡
እነዚህም የአምሥቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌዎች መሆናቸውን አበው ያስተምራሉ፡፡
ሐዋርያው ቶማስ ከትንሣኤ በኋላ ወንድሞቹ ሐዋርያት ስለ ትንሣኤው በነገሩት ጊዜ ‹‹የችንካሩን ምልክት በዓይኖቼ ካላየሁ፣ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላስገሁ፣ በእጄም የተወጋውን ጎኑን ካልዳሰስኩ አላምንም›› ማለቱ በብረት ቀኖት በመቸንከሩ ነበር (ዮሐ 2ዐ¸25)፡፡ መድኃኒታችን በኃጢአት ቀኖት (ምስማር) ተይዞ የነበረውን ሰው ለማዳን በብረት ቀኖት ተቸነከረ፡፡
እንግዲህ አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ድሀ ያይደለ ጌታ፤ ፍጡር ያይደለ የፈጠረውን ሥጋ ገንዘብ ያደረገ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ብሎ ተናቀ፡፡ የሕማም ሰው፤ ደዌንም የሚያውቅ ሆነ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፡፡ ሕማማችንንም ተሸከመ፡፡ ይህም የሰውን ልጅ ለማዳን ማለትም እኛን ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰንና ከሕማመ ሥጋ ከሕማመ ነፍስ ሥቃይ ያሳርፈን ዘንድ ነው፡፡ ቁስለ ኃጢአታችንን ያደርቅልን ዘንድ ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፡፡ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ስለ በደላችን ደቀቀ፡፡ ሊያረጋጋን ተጨነቀ፡፡ ሊያሣርፈን ተሠቃየ፡፡ አፉንም አልከፈተም፡፡
የእግዚአብሔር የመሥዋዕቱ በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ መልካምን እንጂ ግፍን አላደረገም ነበር፡፡ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ወሰብእ ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ በተመረመረ ጊዜ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም፡፡ በፈቃዱ ነፍሱን ስለ እኛ መሥዋእት አደረገ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሥጋውን ቆረሰልን፣ ደሙንም አፈሰሰልን (ኢሳ. 53¸1-13፤ ዮሐ. 10¸18፤ ዮሐ. 19¸30፤ 1ኛቆሮ. 5¸7)፡፡ በዚህ የተቀደሰው ሳምንት ይህንን የጌታን ውለታና የድኅነት ሥራ እናስተውል፡፡
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር፡፡
ግብሐት :-ማህበረ ቅዱሳን ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ
📢ዐውደ ምሕረት🎤
" #ሰሞነ ሕማማ "
ሰሞን ማለት ሳምንት ማለት ነው::ሕማማት የሚለው ቃል ደግሞ “ሐመ፤ ታመመ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን የጌታችንና የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና ሞቱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ በሌላም በኩል ይህ ሳምንት ከአዳም እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ የነበሩ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት የአምስት ሺህ አምስት መቶ የመከራ፣ የፍዳና የኩነኔ ዘመን መታሰቢያ ስለሆነ የሕማማት ሳምንት የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ እንደዚሁም ይህ ሳምንት “ቅዱስ ሳምንት” ይባላል” ከሌሎች ሳምንቶች ሁሉ የተለየ የከበረ ነውና፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሳምንት በእያንዳንዱ ዕለት ስለ ፍጹም ፍቅር የተከፈለ የመሥዋዕትነት ሥራ ስለ ተሠራበት፣ የሰው ልጆች ደኅንነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኀኔዓለም ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆኖ ነፍሱን ስለ ካሠልን “ቅዱስ ሳምንት” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም “የመጨረሻ ሳምንት” ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሙዓለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን ኢየስስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል የሚያዘክረውን ምዕራፍ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብና በመጸለይ ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ ያሬድ በመጨረሻው ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈጸመውን ነገረ መስቀል በተመለከተ ያዘጋጀውን መዝሙር ይዘምራሉ፤ አብዝተው ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፣ ስብሐተ ነግህ አይደረስም፣ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፣ ጸሎተ አስተስርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት ነው፡፡ ሕማምና ሞት የማይገባው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞት ለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንት ለእኛ ቤዛ ሆኗል፡፡ “ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዓመፀኞችም ጋር ተቆጠረ፡፡ እርሱ ግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም፡፡” /ኢሳ.53÷4-12/ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለው የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘከር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ ዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር በኀዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙነ ሕማማት አስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡
ለሀሳብ ለአስተያየት ለጥቆማና ለጥያቄዎቻችሁ @YeawedMeherte ይጠቀሙ
የሰሙነ ሕማማት ሳምንታት ስያሜዎች
ሰኞ(ሰኑይ)
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ኾኖ በዚህ ዓለም ሲመላለስ በሆሣዕና ማግሥት ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አከናውኗል፤ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል (ማቴ. ፳፩፥፲፪-፲፯፤ ማር. ፲፩፥፲፯፤ ሉቃ. ፲፱፥፵፭-፵፮)፡፡ በቅዱስ ማቴዎስ አገላለጥ ‹‹በማግሥቱ ተራበ›› የሚል ቃል እንመለከታለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔርለዘለዓለም አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤››ይላል (ኢሳ. ፵፮፥፳፭)፡፡ በቅዱስ ወንጌል በመጀመሪያ ቃል እንደ ነበር፤ ያ ቃል ቀዳማዊ እንደ ኾነ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ነበር፤ ያም ቃል እግዚአብሔር እንደ ኾነ ተጽፏል (ዮሐ. ፩፥፩-፪)፡፡ ጌታችንም በመዋዕለ ትምህርቱ ሲያስተምር፡- ‹‹የእኔስመብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፤ ሥራውንም እንፈጽም ዘንድ ነው፤›› ሲል ተናግሯል (ዮሐ. ፬፥፴፬)፡፡ ታዲያ ጌታችን ለምን ተራበ?
ሰማያውያን መላእክት እንዳይራቡ አድርጎ የፈጠረ፤ እስራኤልን ገበሬ በማያርስበት፣ ዘር በሌለበት፣ ዝናብ በማይጥልበት ምድረ በዳ የመገበ፤ ድኅረ ሥጋዌ በአምስት አንጀራና በሁለት ዓሣ ከአምስት ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችን የመገበ ጌታ ‹‹ተራበ›› ተብሎ ሲነገር እጅግ ይደንቃል፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመኾኑ አልተራበም አንልም፡፡ የጌታችን ረኃብ የድህነት (የማጣት) አይደለም፡፡ የክርስቶስ ረኃቡ የበለስ ፍሬ ሳይኾን የሃይማኖትና የመልካም ሥነ ምግባርን ፍሬ የሻ መኾኑን ለማጠየቅ ‹‹ተራበ›› ተባለ፡፡ ‹‹በለስ ብሂል ቤተ እስራኤል እሙንቱ››እንዲል፡፡ ጌታችን የፈለገውን ባለማግኘቱ ጉባኤ አይሁድን ረግሟል፡፡ በአይሁድ ጉባኤ የነገሠውን ኃጢአት፤ በበለስ አንጻር መርገሙን ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹በአንጻረ በለስ ረገማት ለኃጢአት፤ በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማት›› ብሏል፡፡
እስራኤልም በአንድ ወገን የተጠበቀባቸውን ፍሬ ባለማፍራታቸው ተረግመዋል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እስራኤል ከፍቅር ይልቅ እርግማን እንዳገኛቸው፤ አሕዛብ ደግሞ የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው ያመኑበትን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጁ ለመኾን መብቃታቸውን ሲመሰክር እንዲህ ይላል፤ ‹‹አሕዛብ አስተጋብኡ ጽጌሬዳበኂሩቱ ወሶኩሰ ተርፈ ኀበ አይሁድ ዘውእቱ ሕፀተሃይማኖት፤ አሕዛብ በእግዚአብሔር ቸርነት አበባሰበሰቡ፤ በአይሁድ ዘንድ ግን እሾኹ ተረፈ፡፡ ይኸውምየሃይማኖት ጉድለት ነው፤›› ብሎ ተርጕሞታል፡፡ እሾኽ የእርግማን፤ አበባ የእግዚአብሔር ጸጋ ልጅነት ምሳሌ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! ዛሬ ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይኾን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ለንስሐ የሚገባ ፍሬአድርጉ፤›› ይለናልና እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገውን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ እናፍራ (ማቴ. ፫፥፰፤ ገላ. ፭፥፳፪)፡፡ ጌታችን በዳግም ልደት ሲመጣ ከሰው ልጅ ሃይማኖት መገኘቱ አጠራጣሪ እንደ ኾነ ተናግሯል፡፡ ‹‹የሰው ልጅወደዚህ ዓለም ሲመጣ ሃይማኖት ያገኝ ይኾንን?››ሕይወታችንን በአምላካዊ ሥልጣኑ የቃኘ አምላክ ለፍርድ በመጣ ጊዜ የእምነት ፍሬ አፍርተን እንዲያገኘንና ዘላለማዊ መንግሥቱን እንዲያወርሰን የጽድቅ ሥራ ለመሥራት እንትጋ፡፡
ይቆየን!
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ
ተፈሣሕ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
የዓቢይ ጾም ፰ ኛ ሳምንት
ሆሣዕና
‹ሆሣዕና› የሚለው ቃል ‹ሆሼዕናህ› ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲኾን፣ ትርጕሙም ‹እባክህ አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ‹‹አቤቱእባክህ አሁን አድን፤ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፡፡ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፻፲፯፥፳፭-፳፮)፡፡ የሆሣዕና በዓል ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አዕሩግም ሕፃናትም ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣየተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡
በሌላ አገላለጽ ይህ በዓል ‹የጸበርት እሑድ› (Palm Sunday) ይባላል፡፡ ታሪኩም የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ኾኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ሣራ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ዅሉን ቻይ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብጻውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ፣ እንደዚሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ወደ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት፣ ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አዕሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እግዚአብሔር አመላክቷቸው ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል (ሉቃ. ፳፪፥፲፰)፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ዘንባባ በመያዝ እግዚአብሔርን እንዳመሰገኑ እኛ እስራኤል ዘነፍስም ዘንባባ (ጸበርት) በግንባራችን በማሰር በዓሉን እናከብራለን፡፡ በዕለተ ሆሣዕና አዕሩግና ሕፃናት ‹‹ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል›› እያሉ ዘምረዋል፡፡
ይህ ዅሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲኾን፣ በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታችንን ‹‹ደቀ መዛሙርትህን ገሥፃቸው››ነበር ያሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ፡- ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉድንጋዮች ይጮኻሉ›› በማለት ሕያዋን ሰዎች ብቻ ሳይኾኑ ግዑዛን ፍጥረታትም እርሱን እንደሚያመሰግኑ አስረድቷቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያን የሕዝቡን ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ በማድረጋቸው በዕለተ ሆሣዕና ዘንባባ ይዘው ይዘምሩ የነበሩ ጭምር በዕለተ ዓርብ ‹‹ይሰቀል!›› እያሉ በጌታችን ላይ ጮኸዋል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በነቢዩ ዘካርያስ፡- ‹‹እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ኾኖበአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፤›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጽሟል (ዘካ. ፱፥፱፤ ማቴ. ፳፩፥፬፤ ማር. ፲፩፥፩-፲፤ ሉቃ. ፲፱፥፳፰-፵፤ ዮሐ. ፲፪፥፲፭)፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መኾኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲኾንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡
መድኃኒታችን ክርስቶስ መላእክት በዕለተ ልደቱ ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል፤በምድርም ሰላም ለሰዉ ዅሉ ይሁን›› እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው (ሉቃ. ፪፥፲፫)፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም ‹‹ሰላሜን እሰጣችኋለሁ›› ብሎ አስተምሮናል (ዮሐ. ፲፬፥፳፯)፡፡ ሰላሙን የሚሰጥበት ዕለት መቃረቡን ለማመልከት ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፡፡ በሌላ በኩል በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፤ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ፣ ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ አምላክ መኾኑን አስተምሯል፡፡
ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የኾነው ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደ ተቀመጠ ዅሉ ዛሬም ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት አድሮ የሕሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፡፡ እርሱ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅምና (መዝ. ፶፥፲፯፤ ኢሳ. ፷፮፥፪)፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜአችን ሳትጠልቅ በእምነት እግዚአብሔርን እንፈልገው፡፡ ሰላሙን ይሰጠን ዘንድም ንስሐ ገብተን ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› እያልን እናመስግነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ምንጭ፡- ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም፡፡
ሆሣዕና
ሆሣዕና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን ሲሆን በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘመር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።
አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካርያስእንደተነገረው
‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’
ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናገሮ ነበር። ሲመጣም
‘‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።ቀንደ መለከትም እየነፉ፣ - እዩ ነግሦአል አሉ።’’
በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ፣ ምዕራፍ ፱፣ ቁጥር ፲፫ ።
የሆሣዕና በዓል የቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፯ ቁጥር ፳፮) በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይታደላል። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚጠቅሱት የቅዱስ ማቴዎስ(ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩–፲፯)፤ የቅዱስ ማርቆስ(ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፩–፲)፣ የ[ቅዱስ ሉቃስ]] (ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፱–፴፰) እና ፤ የ[[ቅዱስ ዮሐንስ] (ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፲፪–፲፭) ወንጌላት ይነበባሉ ።
በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም ለክብር የተሸከመችው አህያ ናት። ጌታን የተሸከመችው አህያ ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጎላታል። አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ እንደበድባት ነበር፡ ነውም። ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ። ኢየሩሳለሌም ሲደርስ ከገጹ ብርሃን የተነሣ ከተማዋ ብርህት ሆነች፡፡ ሕዝቡ የሆነውን ሊያዩ ወጡ፡፡ ሕፃናት ፀሐይ ስትሰግድለት መላእክት ከበው ሲያመሰግኑት አይተው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የሰሌን ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል፡፡ ሆሣዕና ማለት በልዕልና ጸንቶ የሚኖር መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ
ለሔዋን
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
ልደታ እግዝእትነ ማርያም
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት የንጽሕት የውድስት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ነገር እንዲህ ነው
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር:እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን:አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት:እሱአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው:እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች::
ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት::እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ:ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች: እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች:እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ::
ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው:
ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት:ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሃምሌ 30 ዕለት ነው::
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ:ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና):እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት:የሃናም የአጎቱአ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቹአ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት:እርሱአም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት:አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን:እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሱአ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
“አሁን ግን #ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን #ተነሥቶአል።”
— #1ኛ_ቆሮንቶስ 15፥20
"ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓብይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሃ ወሰላም፡፡"
" #መልካም_የትንሣኤ_በዓል "
ዐውደ ምሕረት የእናንተ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በዓለ ፋሲካ
በብሉይ የነበረ በግ ምሳሌ በብሉይ ኪዳን በጉ ዓመት የሆነው፤ ቀንዱ ያልከረከረ፤ ጥፍሩ ያልዘረዘረ፤ ዓመት የሞላው ጠቦት አይታችሁ ከ10 እስከ 14 ቀን በመዓልቱ በሁለት እጅ ብርሃን፤ ከሌሊቱ በአንድ እጅ ጨለማ ሰውት፡፡ ስትሰውትም ሰባት፤ አሥር፣ አሥር ሁለት ሆናችሁ ሰውት ብሎአቸዋል፡፡
በጉ ቀንዱ ያልከረከረ፤ ጥፍሩ ያልዘረዘረ መሆኑ፤ ጌታም ምክንያተ ኃጢአት የለበትምና ነው፡፡ ደሙን ስትቀቡት "ወሶበ ርእየ መልአከ ሞት ደመ በግዕ ለበወ ሞተ እግዚእ ፈርሐ ወኢቀርበ" እንዲል "ይህ የክርስቶስ ምሳሌ ነው ሲለው ነው፣ አባር ቸነፈሩ ከእስራኤል ቤት እንዳይገባ ይሆናል"፡፡ ደመ በግዑን ያየ መልአከ ሞትም እስራኤልን እያለፋቸው መሄድ ጀመረ፡፡ የግብጻውያን በኩር፣ ይገድላል፡፡ ያ የክርስቶስ ምሳሌ በመሆኑ የደመ በግዑ የደም ምልክት ያለው ቤት ሞት አይገባውም፡፡ በደመ ክርስቶስ የተዋጀ፣ በደመ ክርስቶስ መዳኑን ያመነ ሰውም ሞተ ነፍስ አያገኘውም፡፡ ላቱ እስከ ምጽአት የሚነሱ መምህራን፣ ጸጉሩ የመንፈስ ቅዱስ፣ ስለሀብቱ ብዛት፣ ቀንዱ የሥልጣነ እግዚአብሔር፣ ዓይኖቹ የነቢያት ምሳሌ ናቸው"፡፡
በዚህ ዕለት በተለይ በምዕመናን የሚፈጸም ሌላ ድርጊት አለ፡፡ ይኸውም ዳቦ ይጋገራል፣ ንፍሮ ይነፈራል፣ ይኸ ልማደ ሀገር ቢሆንም የተቻለው ዓርብንና ቅዳሜን ያክፍል፣ ያልተቻለው ቅዳሜን ብቻ ያክፍል ብሏልና፡፡ ለአክፍሎት የሚስማማን ምግብ የሚጾም ሰው እንዳይደክም "ጉልባንን" አብዝቶ ይበላል፡፡
ጾሙን የጀመረው "ያዕቆብ እኁኁ ለእግዚእነ" የጌታ ወንድም ያዕቆብ ነው፡፡ ይኸውም የጌታ ትንሣኤን ሳላይ አልበላም በማለት ጀምሮታል፡፡ ጌታ ከተቀበረ በኋላ ሐዋርያት እህል እንብላ አሉ፡፡ "ያዕቆብ በሦስት ቀን እነሳለሁ" ብሏል አይሆንም ቢላቸው እንግዲያስ እኛም እንጹም ብለው ጹመዋል፡፡ እኛም ያንን ይዘን እንጾማለን፡፡
ቅዳሜ ሥዑር
እስከ ምሴተ ሐሙስ ወይም እስከ ሐሙስ ማታ ጌታ የኦሪትን ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ መስዋዕተ ብሉይን፣ ሥርዓተ ብሉይ አሳልፎ ላም፣ በግ፣ ፍየል እንዳይሰዋ ከለከለ፡፡ መስዋዕቱን በስንዴና በወይን አድርጎ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ አይሁድ ቅዳሜን ያከብሩ እሑድን ይሽሩ ነበር፡፡ ስለዚህ ቅዳሜን ብቻ ሳይሆን መላ የኦሪት በዓል ተሽሮ በዚያ ተተክቷል፡፡
ለምሳሌ፡- በበዓለ መጥቅዕ ቅዱስ ዮሐንስ መስከረም 1 ቀን ከገባ
በሠርቀ ወርኅ ልደተ ክርስቶስ
በበዓለ መጸለት በዓለ ጥምቀት
በበዓለ ፍሥሕ ስቅለተ ክርስቶስ
በበዓለ ፋሲካ በዓለ ትንሣኤ
በበዓለ ሠዊት በዓለ ጰራቅሊጦስ
በጾመ አስቴር ጾመ ረቡዕ
በጾመ ዮዲት ጾመ ዓርብ
በጾመ ሙሴ ጾመ እግዚእነ
በቅዳሜ ዕለተ እሑድ ተክከቶበታል፡፡ስለዚህ ነው ተሻረ ያሰኘው፡፡
ስለዚህ ነው ተሻረ ያሰኘው፡፡ ቅዳሜ የምትቆጠረው ከዐሠርቱ ቃላት ነው፡፡ እንዴት ተሻረች ይባላል የሚል ካለ? "አክበር ሰንበቶ ስለ በማለቱ እሑድን ተካ እንጂ ከዓሠርቱ ቃላት አልጎደለም፡፡ አንድ ምሳሌ ጥቀስ አንድ ሰው አንድ ብር ተበድሮ ይሄዳል ተመልሶ የሰጠኝ እንደሆን ጎደለ ያሰኛል? ወይም ብሩ ጎደለ ይባላል አይባልም፡፡" እንደዚሁም በቅዳሜ ፈንታ እሑድን ተካባት እንጂ አላጎደላትም "ሠለስቱ ምእትም" "ወሠዓራ ለሰንበተ አይሁድ ወሠርዐ ህየንቴሃ ዕለተ እሑድ ቅድስት" ስለ ቅዳሚት ፈንታ እሑድን ሠራ መላው በዓል ተተክቶበታል ማለት ነውሰው ግን በልማድ እሺ አይልም፡፡ በሕንጻ መነኮሳት ዓመት እስከ ዓመት ጾም እንድትጾም አዘውባታል፡፡ "ወኢይደሉ ይጹሙ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት እስከ ዕርበተ ፀሐይ አው እስከ ስድስቱ አው እስከ ሰብዓቱ ሰዓት" በቀዳሚት ሰንበት እስከ ዕርበተ ፀሐይ ወይም እስከ ስድስት ወይም እስከ ሰባት ሰዓት በልቶ ቤተ እግዚአብሔር ሲያገለግል ይደር ተብሎ ተሠርቷል፡፡"
ሠለስቱ ምእትም በሃይማኖተ አበው "ኢይደልዎሙ ከመያጽርኡ ተገብሮ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከመአይሁድ፡፡"
ክርስቲያኖች በዕለተ ቀዳሚት እንደ አይሁድ ሥራ መፍታት አይገባቸውም፡፡ ጌታችንም ሲያስተምር ደቀ መዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው ሲበሉ ፈሪሳውያን "ርኢ ዘይገብሩ አርዳኢከ ዘኢይከውን ገቢረ በዕለተ ሰንበት" ደቀመዛሙርቶችህ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ሊደረግ የማይገባውን ሲያደርጉ አታይምን" ብለው ቢጠይቁት ጌታም ሲመልስ ለምን ነው እሸት አሽተው ቢበሉ የምትፈርድባቸው? "ሶበሰ ተአምሩ ምንት ውእቱ ዘይቤ ምፅዋተ አባደር እመሥዋዕት እምኢኰነንክምዎሙ ለእለ ኢይኤብሱ እስመ እግዚአ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው" "ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፡፡ያለው ምን እንደ ሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ሐዋያትን ባልኮነናችኃቸው ነበር" የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና ብሎአቸዋል፡፡ ማቴ. 12
ቀጥሎ ደግሞ እነሱ መንገድ አይሄዱም ጌታ ግን "ወበውእቱ መዋዕል ወፈረ ኢየሱስ በሰንበት ማዕከለ ገራውኅ" በዚያው ወራት ኢየሱስ በሰንበት ከእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄደ እሸት ይቀጥፉ ነበር፡፡ ማቴ. 2፡23
በዮሐንስ ወንጌል "አኮ ዘይሥዕር ሰንበተ ባሕቲቶ ዓዲ አባሁ ይሬስዮ ለእግዚአብሔር..." ሰንበትን ስለሻረ ብቻ አይደለም ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስለ አለ... ወኢያብኡ ጾረ ክቡደ ውስተ ኀዋኅዊሃ ለኢየሩሳሌም በነፍስክሙ /ኤርምያስ/ ያለውን ይዘው በሰንበት አይሸከሙም፡፡
ጌታ ግን ሰላሳ ስምንት ዘመን የታመመውን መጻጉዕን "ንሣዕ ዓራተከወሑር" "አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" አለው፡፡ አልጋው የብረት ነው፡፡ አልጋውን ተሸክሞ ሄዷል፡፡
ጌታ ሠዓሬ ሰንበት የተባለበትን ዕለት አከብራለሁ ማለት ያው የአይሁድ ረዳት መሆን ነው፡፡ "ይከውንኬ ገቢረ ሠናይ በሰንበት" በቀዳሚት ሰንበት በጎ ሥራ መሥራት ይገባልን፡፡ "ሠናይ" እርሻ ብሎታል፡፡ ወአትሐተ መትከፎ ከመይትቀነያ "ይትጌበራ" ያለውን ሠናይት አላት፡፡ አንዳንድ ደግሞ ቅዳም ሥዑር የተባለው ዲያብሎስ የተሻረበት ነው በማለት የሚናገሩ አሉ፡፡ የዲያብሎስ መሻር ከዚህ ጋር የሚገናኝበት የለም፡፡ ዲያብሎስ የተሻረ ዓርብ ዕለት ነው፡፡ ወተርፈ ውሳጤ ነፋሳት ዘኢይክል ያንቀልቅል ወዲያና ወዲህ ማለት ዲያብሎስ አቅቶት ተሰቅሎ የዋለ ዓርብ ዕለት ነው እንጂ ቅዳሜ ዕለት አይደለም፡፡
ካህናት ቤተ ምዕመናን እየዞሩ ለምን ቄጤማ ያድላሉ?
ካህናት በቅዳሜ ሥዑር ነግህ /ጧት/ በየቤቱ እየዞሩ ቄጤማ /ግጫ/ የሚያድሉበት ምሳሌ አለው፡፡ ማየ አይኅ በወረደ ጊዜ መርከቢቱ እየተንሳፈፈች አራራት ላይ አረፈች፡፡ ኋላ ኖኅ ርግብን ላካት ግጫ ይዛ መጣች፡፡ የምሥራች ውሃው ደረቀ ስትል፡፡ ያ ቀደም ብሎ የተላከው ቁራ ከዚያው ቀረ የሰይጣን ምሳሌ፣ ርግብ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ፣ ግጫው፣ ውሃው ጐደለ ና ከመርከብ ውጣ ብላ ሰጠችው፡፡ እኛ ደግሞ የምሥራች መርገመ ኃጢአት ተሽሮ፣ ሞተ ነፍስ ጠፍቶ፣ ባሕረ እሳት ተከፍሎ፣ ነፍሳት ገነት ገቡ፣ ሰው ከፈጣሪው ጋር ታረቀ፣ ዲያብሎስ ተሻረ፣ "ገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ" እያልን ቄጤማ ይዘን የምሥራች እንናገራለን፡፡
ገብረ ሰላመ
ገብረ ሰላመ ማለት ሰባቱ መስተ ጻርራንን አስታረቀ ማለት ነው ሰባቱ መስተጻርራን የተባሉት ሰውና እግዚአብሔር፣
ሰውና መላእክት፣
ሕዝብና አሕዛብ፤
ነፍስና ሥጋ፣ እነዚህ ለ5500 ዘመናት ተለያይተው ይኖሩ ነበር፡፡ "ወነሠተ ዓረፍተ እንተ ጽልእ በሥጋሁ" አባቱን መሰተጻርራን አስታረቀ ሲል "ገብረ ሰላመ" ሰላምን አደረገ አለ፡፡ ሰውና እግዚአብሔር በአዳም ምክንያት ተጣልተው ስለነበር፡፡ ሰውና መላእክትም መላእክት ነፍሳትን ወደ ገነት አያገቡም ነበር ወደ ሲኦል እንጂ፤ ወደ ገነት የሚገባ አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን የጻድቅ ነፍስ መላእክት በይባቤ ይዘዋት ወደ ገነት ሲገቡ በመዓዛ ገነትን ትለያለች፡፡
ሕዝብና አሕዛብ "ኢይባእሞአባዊ ወአሞናዊ" "ሞአባዊእና አሞናዊ አይግባ" ባለው መሠረት ከአብርሃም ልጆች በቀር ቤተ መቅደስ አያስገቡም ነበር፡፡ አሁን ግን "ዘአምነ ወዘተ ጠምቀ ይድኅን" የአመነና የተጠመቀ ይዳን ብሎ ለመላው ለአዳም ልጅ ድኅነቱን ሰጥቷል፡፡
ነፍስና ሥጋ ዲያብሎስ ነፍሳትን በሲኦል ተቆራኝቼ እኖራለሁ ሲል ከሲኦል አወጣበት፡፡ ሥጋም አበስብሼ አስቀራለሁ ብሎ ነበር፡፡ ጌታ አምስት መቶ ቢጽን አስነሳበት፡፡ "ተነሥአ እግዚእነ ከመይምሐረነ በተንሥኦ ሥጋቲነ" እንዲል የእኛን ትንሣኤ በእሱ ትንሣኤ አስረዳን፡፡
እንኳን ለ ፳፻፲፫ ዓ.ም የስቅለት በዓል አደረሳችሁ!!!
ዕለተ ዓርብ
ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕለት ዕለተ ዓርብ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ በክርስቲያኖች ዘንድ በጾምና በስግደት በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በመጀመሪያ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተሰቀለው ትንቢቱን ለመፈጸም ነው፡፡ ሙሴ "ስቅልተ ትሬእያ እስራኤል ለሕይወትከ ቅድመ አዕይንቲከ ወኢትትአመና"
"እስራኤል ሆይ ሕይወትህ /ክርስቶስ/ በዓይኖችህ ፊት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ታየዋለህ፡፡ ግን አታምነውም፡፡" /ዘዳግ. 28/
ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስም "መጽአ ከመ በግዕ ይጠባሕ ወከመ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርጾ ከማሁኢከሠተ አፍሁ በሕማሙ በቅድመ እለ ይረግዝዎ፤ ወበ ኃጢአተ ሕዝብየ በጽሐ እስከ ለሞት፣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ" አኮ በመልአክ ወአኮ በተንባል አላ ለሊሁ እግዚእ መጽአ ወአድኀነነ ተብሎ በሰፊው ተናግሯል፡፡ ጥቅሶቹ ብዙ ናቸው፡፡ ኢሳ. 53፡1-6
ነቢዩ ዳዊትም "አገቱኒ ከለባት ብዙኃን፣ ወአዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን" ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ ወኆ ለቁ ኵሎ አዕጽምትየ" "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም" እንዳለው፡፡ 6666 ጊዜ በገረፉት ጊዜ አጥንቱ ተቆጥሮዋል፣ ይኸ አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ነው፡፡ 6666 ጊዜ ለመገረፉ ግብረ ሕማማት ይገልጻል፡፡ መዝ. 21/22 ቁጥር 17-18
ክርስቶስ ለምን ሞቱ በመስቀል ሆነ? ከመስቀል በሌላ ማዳን አይችልም ነበር ወይ? ቢባል በዘመኑ የነበረው የበደለኛ አገዳደል ሥርዓት እንደየሀገሩ ሁኔታ የተለያየ ነበር፡፡
ለምሳሌ የሮማውያን ሥርዓታቸው መስቀል ነው፡፡ የአይሁድ "ውግረተ ዕብን" ነበር፡፡ የባቢሎናውያን እሳት አንድዶ እዚያ መክተት ነው፡፡ ፋርስ ለአንበሳ መጣል ነው፡፡ ጌታም በሮማውያንም ሥርዓት ተሰቅሎ ሞተ፣ ለዚህም ራሱ ጌታ ሞቱ በመስቀል እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ ዮሐ. 3፡14፡፡
ባይሰቀል፣ ጎኑ ባይወጋ ማይ ለሕጽበት፣ ደም ለጥምቀት ባልተገኘ ነበር፡፡ ብለው መምህራን ተርጉመዋል፡፡ አይ፣ በውግረትም ደሙን አይታጣም ብለው ትንቢትን ለመፈጸም ተሰቀለ ብሎ አስታርቀውታል እንጂ፡፡ የአይሁድ ሥርዓት በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው፡፡ ጌታ የተሰቀለው በሮማውያን ሥርዓት ነው፡፡
"ኲሉ ሰቁል ዲበ ዕፀመስቀል ርጉም ውእቱ" "ሠርቶ ቀምቶ የተሰቀለ ሰው የተረገመ ነው" ትላለች ኦሪት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "ወፆረ መርግማ ለኦሪት" አለ፡፡
ርጉም ተብሎ የአዳምን መርገም ለማጥፋት በአዳም የተፈረደው ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ከመርገመ ነፍስ አዳነው፡፡ "ወሠዓረ መርገመ እምኔነ" ከእኛ መርገመ ኃጢአትን ደመሰሰ፣ አጠፋ ያለው ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ክርስቶስ ከተሰቀለ፤ ልጅነት ከተመለሰ ወዲህ ወደ ሲኦል መውረድ ቀርቷል፡፡ ይህም ዮሐንስ አፈወርቅ ገልጦታል፡፡ "እንከሰ ኢንወርድ ታሕተ አላ ፈድፋደ ንተልዎ ለዘፈጠረነ ወንበውእ ኀበ ቦአ ሐዋርያነ ህየ ንበውእ ኵልነ" ይላል፡፡ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፋልን የተባለው አምኖ፣ ተጠምቆ፣ ጥሩ ሥራ ከሠራ ወደታች መውረድ የለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡
ቀድሞ በዘመነ ብሉይ መልካም ሥራ ቢሠሩም እነ አብርሃም ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ሁሉ በሲኦል ነበሩ፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ አጠፋ የሚለው ስለዚህ ነው፡፡
"ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በሞትየ ወበመስቀልየ" ቀሌምንጦስ፤
"ወለትከ" የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ገድለ አዳም ገጽ 105፡125፡፡ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ገጽ 54፡8
ቀደም ብሎ እንደተገለጸው "ከመይሥዓር መርግማ ለኦሪት" በተባለው መሠረት አዳም ተርግሞ ነበር ወይ? ሲባል መልሱ አዎ ነው፡፡
ከገነት ሲኖር "ይችን ዕፅ የበላህ እንደሆነ ትመውት ሞተ" ሞትን ትሞታለህ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል ያገኝሃል ነው ያለው፡፡ "ወአልበሶሙ አእዳለ ማዕስ" ያብርሃን የነበረው፣ እንደብርሌ፣ እንደ ብርጭቶ ንጹሕ የነበረው እሾኽ እማይወጋው፣ እንቅፋት የማይመታው፣ እማያደማው፣ ብርድ የሌለበት የነበር በኋላ መርገም ሲያድርብት እሾክ የሚወጋው፣ እንቅፋት የሚመታው፣ ብርድ የሚሰማው ልጅነት የሌለው ቁርበት አለበሰው፡፡
እሱ ባይረገም፣ ወደ ምድር ባይወርድ፣ በዘፍጥረት 1፡28 "ብዙ፣ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም" ብሎ ነበረ አዳም ባያጠፋ ኑሮ ሰው እንዴት ሊበዛ ይችል ነበረ ቢሉ? ይኸማ መጀመሪያ አዳም በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘ እንጂ ከሴት አልተገኘም፡፡ ሔዋንም ያለ ወንድ በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘች እንጂ ሴትና ወንድ ተገናኝተው አልተፈጠሩም፡፡ ባይበድሉ በሥልጣነ እግዚአብሔር ወንድም በአዳም አምሳል፣ ሴቱም በሔዋን አምሳል በሥልጣነ እግዚአብሔር እየተባዛ፣ ዕፀ ሕይወትን እየበላ ሺህ ዘመን ሲሞላው መንግሥተ ሰማያትን ሊገባ ተፈጥሮ ነበር፡፡
እንግዲህ ለአዳም ዕፅዋትን ሰጠው፤ አንዱ የሚመገበው በመዓዛው ይጠግባል ሁለተኛው ሕግ ሊጠብቅለት ይችን ዕፅ አትብላ ብሎ፤ ሦስተኛው ሺህ ዘመን ኑሮ ያን ሲበላ ተሐድሶ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ፈጥሮት ነበር፡፡
ይኸንንም ሰሎሞን ገልጦታል "እግዚአብሔርሰ ኢገብረ ሞተ አላ ረሲአን ሰብእ አምጽእዎ በቃሎሙ ወዓርከ አምስልዎ" እግዚአብሔር ጥንቱን ሲፈጥረው ሞት እንዲሞት እንዲቀበር ወደሲኦል እንዲወርድ አልፈጠረውም፡፡ ሕጉን እንዲጠበቅ ሺህ ዘመን በሕይወት እየተቀመጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ተፈቅዶ ነበር፡፡ "ኢትብልዑ እምዕፅ" ይችን እንጨት አትብሉ ያለውን የዘነጉ አዳምና ሔዋን ሞትን፣ መቃብርን፣ ስበው ጎትተው አመጡት፡፡ "ወአርከአምስልዎ" ወዳጅ አስመሰሉት አለ ወዳጅ እንዳይለይ እንዳይለይ አደረጉት፡፡ ቀጥሎ ልጆቻቸውን፣ ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ ገልጦታል፡፡ "ወሶበ ኵነኔ ኃጢአት ወጽአ እምላዕለ አሐዱ ብእሲ ተቀሰፈ ባቲ ኩሉ ፍጥረት" ሮሜ. 5፡12፡፡
ከአንዱ አዳም የተገኘች ኃጢአት ሁሉን /መላውን/ አደረሰች፣ ከአንድ ዛፍ በተቈረጠ ጨንገር ብዙ ሕፃናት እንደሚገረፋ ኃጢአትም ከአዳም ተገኝታ ሁሉን ያዘች፡፡ መባዛት በዘር በሩካቤ የሆነው ከመርገም በኋላ ነው፡፡ በገነት ሳሉ ወንድና ሴት መሆናቸው አይተዋወቁም፡፡ አዳም እኔ ብቻ ነኝ ሲል ረዳት እንድትሆነው ፈጠረለት እንጂ በዘር በሩካቤ ሊገናኙ አይደለም፡፡ ለምን ተባዙ አለ በሥልጣኑ ያበዛቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ሁሉን አንድ አንድ ጊዜ ነው የተናገረው "ለታብቁል ምድር" አለ ይኸ መሬት ሁል ጊዜ ታበቅላለች፡፡
"ለያብርኁ ብርሃናት" አለ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ፣ ከያለበት ሲያበሩ ይኖራሉ፡፡ "ለታውጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት" ሲል አዞ፣ ጉማሬ አንድ ጊዜ ሲባዙ ይኖራሉ፡፡
ይቆየን!!!
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ፬
ሐሙስ
ጸሎተ ኀሙስ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚሁ ዕለት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም ለሐዋርያት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ የነበረው ሐሙስ ነው፡፡ ከአይሁድ ጋራ በበዓል በጾም እንዳንገናኝ የኒቅያ ጉባኤ በድሜጥሮስ ቀመር፤ እንዲሁም የአውሻክር ሰዎች በአውሻህር፣ በባሕረ ሐሳብ በዚሁ ሁሉ ወስነውታል፡፡ "እመቦ ዘይጸውም ጾሞሙ ለአይሁድ ወያከብር በዓሎሙ ለአይሁድ ይሰደድ እምክርስቲያን"
"የአይሁድ ጾማቸውን የሚጾም፣ በዓላቸውንም የሚያከብር ካለ? ከክርስቲያንነት ይወገድ /ይባረር/ ብሏል ሰለስቱ ምዕት በሃይማኖተ አበው"
በዚሁ ዕለት በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 26፡26 እንደተገለጸው ጌታ ክቡር ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት ሰጥቷል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ቁርባን የሚለው በዕለቱ ተለውጧል ወይ? ወይስ አልተለወጡም?
በሌላ በኩል ጌታችን ለሐዋርያት የሰጣቸው "ሥጋዬ" ብሎ ሲሆን ይህ አማናዊ ነው ወይ? እንዴት ከመሰቀሉ በፊት "ሥጋዬ" ብሎ ሊሰጣቸው ቻለ? የሚሉ እንዳሉ ጥያቄ ሰምቼአለሁ፡፡
መልሱ ግልጽና አጭር ነው፡፡ ይኸውም አማናዊ ነው፡፡ ነገ በቀራንዮ የሚሰቀል "ዝውእቱ ሥጋየ ወዝውእቱ ደምየ" "ነገ በመስቀል የሚሰቀል ሥጋየ ይህ ነው፣ ነገ ኲናተ ሐራዊ የሚያፈሰው ደሜ ይህ ነው" ብሎ አክብሮ፣ ለውጦ ትኩስ ሥጋ፣ ትኩስ ደም አድርጎ ሰጣቸው፡፡ ስለፈሩ "ጥዒሞ አጥዓሞሙ" አይዟችሁ አትፍሩ ብሎ ቀምሶ ሰጣቸው፡፡
ጌታ ሳይቀበል አቀበሎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ ዛሬ የሚቀድሰው ካህን አቀብየ ሳልቀበል ልውጣ ባለ ነበርና፣ ተቀብሎ ያቀብል ለማለት ለአብነት፣ የሠራው ሁሉ ለእኛ ነው፡፡
"እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ" "ለእግዚአብሔርየሚሳነው የለም"፡፡ እግዚአብሔር ይህ ሥጋየ ነው ሲል ውሸት ነው አይባልም፡፡ የተናገረውን ሁሉ ማመን አለብን፣ ጥያቄው ሳይሰቀል ለምን ሥጋየ ነው አለ ነው፣ ነገር ግን ነገ የሚሰቀለው ሥጋዬ ይህ ነው ሲል ተለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ሆነ ማለቱ እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ያ የዕለተ ሐሙስም ሆነ ዛሬ ካህናት የሚያቀርቡት መሥዋዕት አማናዊ ሥጋውና ደሙ ነው፡፡
ጠያቂዎቹ እንደምሳሌ አድርገው የሚያቀርቡት ጌታ ከመሰቀሉ በፊት ሥጋውና ደሙ ተበልቷል ወይስ አልተበላም እንዴት ጌታ ሳይሰቀል ሥጋው ተበላ የሚል ጥያቄ ነው፡፡
መልሱ፣ ነገ የሚሰቀለው ሥጋየ ይኸ ነው፣ ነገ የሚፈሰው ደሜ ይኸነው ሲል ቃሉ ለወጠው፤ ሥጋና ደሙ አደረገው፡፡ እኛ አምነን እንቀበላለን እንጂ አይደለም አይባልም፡፡ እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ አምነን መቀበል አለብን፡፡ እሱ ይህ ሥጋየ ነው ይህ ደሜ ነው እያለ አይደለም የሚል ካለ ሐሰተኛ ይሆናል፡፡ "እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር" እሩቅ ብእሲ ቢሆን ኖሮ አይሆንም ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ያለው ሁሉ ይሆናል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም በዕለተ ሐሙስ ሐዋርያት የታጠቡት ኅፅበት ስለ ትሕትና ወይስ ስለ ጥምቀት የሚል ጥያቄ አለ፤ ይህም፡-
ሐዋርያት የታጠቡት ጥምቀት ነው፡፡ "እመ ኢሐጸብኩከ እገሪከ አልብከ ክፍል ምሳሌየ" "ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም" ሲል መልሶለታል፡፡ ዮሐ. 13፡7 ዕድል ፈንታ የለህም ማለት ልጅነት አታገኝም ማለት ነው፡፡
ጥምቀት እንዳንል ካሣ አልተፈጸመም የሚል ሐሳብ ካለ አስቀድሞ አጥቦ ወዲያው ሥጋና ደሙን ሰጣቸው፡፡ ዛሬ መጀመሪያ ሕፃኑን እናጠምቀዋለን፤ ኋላ ሜሮን ተቀብቶ ሥጋውና ደሙን ይቀበላል፡፡ ይኸ "ተሰዕሎተ ቢንያም" የሚባል ጥሩ አድርጐ ጽፎታል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያት መቼ ተጠመቁ ቢባል በሕጽበተ እግር ጊዜ ነው፡፡ ይህም "አልብከ ክፍል" "ዕድል ፈንታ የለህም" ባለው ይታወቃል፡፡
ለጊዜው ሐዋርያት ዕግራቸው ብቻ እንደታጠቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ግማሹ አካላቸው ታጥበውስ እንዴት ጥምቀት ሆኖ ሊቆጠር ቻለ ቢሉ? ያማ "ዘይውህጥ ርዕሶ" ብለው ሠለስቱ ምዕት የሕጻኑን ራስ በሚውጥ ባሕር ብቅ ጥልቅ ብቅ ጥልቅ አድርጉ ብለው በጥልቅ ባሕር፣ በማዕከላዊ ባሕር፣ በንዑስ ባሕር የተጠመቀ እንደ ሆነ ነው ብለው ጽፈው የለ፡፡ "ዘይውህጥ ርዕሶ" የሚጠመቀውን ሰው በፈሳሽ ወንዝ ብቅ ጥልቅ ብቅ ጥልቅ አድርገህ ታወጣዋለህ፡፡ ጴጥሮስ መላ አካላቴን እጠበኝ ባለበት ሰዓት ጌታ አይፈቀድልህም ያለው ይህ ለምንድነው ቢባል? እግሩን የታጠበ ሰው ሌላው ሊታጠብ አይፈልግም፡፡ አንዱ የሰውነት አካልህ ካጠብኩህ መላ ልጅነት ይሰጥሃል፡፡ ማለት ነውና በትልቁ ባሕር፣ በትንሹ ባሕር፣ በጳጳስ ቢጠመቁ አንድ ነው፡፡ "አሐቲ ጥምቀት" "አንዲት ጥምቀት" /ኤፌ. 4፡4/፡፡
አንዳንዴም ሐዋርያት የተጠመቁት በውሃ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ለዚያም እንደ ማስረጃ የሚጠቅሱት መጥምቁ ዮሐንስ በማቴዎስ ወንጌል የንስሐ ጥምቀት በሚያጠምቅበት ጊዜ "እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳት ያጠምቃችኋል" ማቴ. 3፡11 ያለውን ይጠቅሳሉ፡፡
ለዚህ መልስ የሚሰጠን በግብረ ሐዋርያት ጴጥሮስ ሲናገር "ንስሐ ግቡ፣ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ የሚለው ነው፡፡ /የሐዋ. 2፡38/
ሐዋርያት ሲያጠምቁ ቋንቋ ይገለጽላቸው ነበር መንፈስ ቅዱስ ያድርባቸው ስለነበር ተጠቀሰ እንጂ የሐዋርያትን መጠመቅ አያስመለክትም፡፡ ከዚሁ ባልተለየ መልኩ አብሮ የሚታየው ኦሪት አለፈች፤ ወንጌል ተተካች የሚባለው መቼ ነው ቢሉ ከልደቱ እስከ ጥምቀቱ ከጥምቀቱ እስከ ዕለተ ሐሙስ ከዕለተ ሐሙስ እስከ ትንሣኤ ባለው ሰዓት ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲያስተምር እሷን ወደ ወንጌል እየሳበ ቆይቷል፡፡መስዋዕትዋን የሻረው በዕለተ ሐሙስ ነው፡፡ በግ ይሰዋ ነበር፤ ቀርቷል መስዋዕትዋን አሳለፈው፣ የበሉትን ምግብ ከሆዳቸው በግብር አምላካዊ አጥፍቶ አማናዊ ሥጋውን አማናዊ ደሙን ሰጣቸው፡፡ ሌላው በየስፍራው ሲያስተምር አሳልፎታል፡፡
ዐሠርቱ ቃላት ብቻ አላለፉም፡፡ ሌሎች ሥርዓቶች ግን አልፈዋል፡፡ የወንድምን ሚስት ማግባት ቀርቷል፡፡ የበግ፣ የላም፣ የዋኖስ የዕጉለር ግብ፣ መስዋዕትና ይህን የመሰለ ሁሉ ቀርቷል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ኦሪት ለምን አለፈች ይባላል? "ጌታ በወንጌል ኢመጻእኩ እስዓሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት አላ ከመእፈጽሞሙ" "ኦሪትንና ነቢያትን ሊሸራቸው አልመጣሁም፣ ልፈጽማቸው እንጂ" ብሎአልና አላለፈችም የሚሉ አሉ፡፡ "ኢመጻእኩ ከመእስዓሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት" ማለት፤ ኦሪት፣ ነቢያት የተናገሩትን ላስቀር አልመጣሁም፣ ይወርዳል ይወለዳል፣ ብለው የተናገሩትን ሁሉ ልፈጽም ነው የመጣሁ፣ ማለት እንጂ ኦሪት አላለፈችም ለማለት አይደለም፡፡
"የውጣ" የተባለው ዐሠርቱ ቃላት ነው፡፡ ይኸውም እነሱ አልተሻሩም፡፡ኦሪት አለፈች የሚያሰኘው በግ፣ ላም መሠዋት፣ የወንድም ሚስት ማግባት፣ እጃቸው እስኪላጥ መታጠብ፣ ይህን የመሳሰለ ሁሉ አልፏል፡፡ ከአሥሩ ቃላት በቀር ሁሉም አልፏል፡፡ ዐሠርቱ ቃላት ግን በወንጌል እንኳንስ ነፍስ መግደል፤ ወንድሙን የሰደበ ይፈረድበታል፡፡ ሲል ፈጽሞ እያበለጠው ሄደ፣ "አትዘሙ" ያለውን "ኲሉ ዘርእያ ለብእሲት ወፈተዋ ዘመወ"
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ፪
ማክሰኞ
በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፳፰፤ ፳፭፥፵፮፤ ማርቆስ ወንጌል ፲፪፥፲፪፤ ፲፫፥፴፯፤ በሉቃስ ወንጌል ፳፥፱፤ ፳፩፥፴፰ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማክሰኞ ዕለት የሚነገሩ ትምህርቶችን ይዘዋል፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ ‹የትምህርት ቀን› ይባላል፡፡ ክርስቲያን የኾነ ዅሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ሲኾኑ፣ ጥያቄውም፡- ‹‹በማን ሥልጣንእነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህማነው?›› የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማከናወኑን ተከትሎ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን››ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡
ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ አሳብ ስለሚያውቅ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስከምድር?›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ኹኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ነው›› ቢሉት ‹‹ለምንአላመናችሁበትም?›› እንዳይላቸው፤ ‹‹ከሰው ነው››ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት፣ እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ስለፈሩ ‹‹ከወዴት እንደ ኾነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው፡፡ ይህን ጥያቄ መጠየቃቸውም እርሱ የሚያደርጋቸውን ተግባራት ዅሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነበር እንጂ፡፡
ዛሬም ቢኾን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊኾኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ‹‹ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገርይመልሱልናል?›› በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን አሳባችን ከዓለም ዘንድ ተቃራኒ ነገር እንደሚጠብቀን ለመረዳት ‹‹ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው›› የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልንም ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡
ይቆየን!!!
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
#የሰሞነ_ሕማማት_ ሥርዓቶች
በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈፃፀም መዛግብት አገላብጠን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
#አለመሳሳም
በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክረቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንሰቀለው ፤እንግለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ስላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሳምንት የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ አይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ እኔ የምስመው እርሱ ነው ያዙት ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም ተንኮል የተሞለበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን ስላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት የይሁዳም ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኽው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ስርወ መሰረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል፡፡ ይቀጥላልም፡፡
#ሕፅበተ_እግር (እግር ማጠብ)
ጌታ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ህይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ እለተ እናንተ ለወንድማችሁ እንዲሁ አድርጎ ለማለት የደቀ መዛሙርቱን አግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረኩ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብጹዓን ናችሁ፡፡ ዮሐ 13፡16-17 በማለት ትህትናውን አሳይቷል ጌታ በዚህ እለተ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ አርአዬን ሰጥቻችኋለሁ እናንተም የወንድማችሁን እግር ታጥቡ ዘንድ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል አለ ደቀ መዛሙርቱም ማንይሆን አሉ፡፡ ጌታም ህብስት ቆርሼ፣ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ደንግጠዋል ይሁዳን ማመልከቱ ነበር ለጊዜው አልገባቸውም፡፡ ጌታችን መዳኃኒታችን የሐዋርያቶቹን እግር በማጠብ ትሕትናን ካስተማረቸው በኋላ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሰጣቸው የኦሪትን መስዋዕት የሻረው እና መስዋዕተ ሐዲስን የሠራው በዚሁ እለት ነው፡፡
#አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ በዓል/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከዓርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታቸን ያዕቆብ እና ዩሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡ ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዋስ አውሳብዩስ የተባሉ ጸሀፍተ ሐዋርያት በስሙነ ህማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደ ማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኽው ነው፡፡ ቅዳሜ ይበላል ማለት ግን ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ በልቶ እንደ ማስቀደስ እና በልቶ እንደመቁረብ ይቆጠራል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮችም ይህንኑ ትውፊት ሲከውኑ አያሌ ዘመናት ተቆጥሯል፡፡
#ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጀና የጸሎት ሐመስ እለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብጽ ተሰደው በሚነጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካው ሊጥ እያጋገሩ ቂጣ መብላት ንፎሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን እንዲሁም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውሃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ስርዓት በእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹን የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ስርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
#ጥብጠባ
በሰሙነ ሕማማት እለተ የዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ቀን ከስገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጠባው የሚደረግለት ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸማ በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ
ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ህዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኃላ ሰርሆተ ህዝብ (የህዝብ መሰነባበቻ) ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል እያንዳንዱን ምዕመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ የጌታን ግርፋት ያስተውሳል፡፡ ማቴ 26፡26 ማቴ 19፡1-3
#ቄጠማ (ቀጤማ)
በቀዳም ስዑር ቀሳውቱን ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ አዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመኑም ለቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ እለት ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የ
#አሥራ_ሦስቱ ሕማማተ መስቀል
በሰሙነ ሕማማት ጠቅለል ባለ መልኩ የምናስባቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት አሥራ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡ ለክርስቲያኖች እነዚህን ሕማማተ መስቀል ማወቅና ዘወትር ማሰብ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
#1_ተኰርዖተ_ርእስ (ራስና በዘንግ መመታት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በዘንግ መመታቱንና መቀጥቀጡን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተኰርዖት›› የሚለው ቃል ኩርዐ -
መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ርእስ ደግሞ ራስ ማለት ነው፡፡ አገረ ገዥው ጲላጦስ ‹‹እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› ብሎ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፎ ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች አሳልፎ ሰጥቶት ነበር፡፡ በአይሁድ ሕግ የተገረፈ አይሰቀልም፤ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም፡፡ እርሱ ጲላጦስ ግን ከገረፈው በኋላ፣ የበደል በደል፣ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው (ማቴ 27¸24፤ ማር 15¸15፤ ሉቃ 23¸25፤ ዮሐ 18¸39)፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ የእሾህ አክሊል ጐንጉነው ራሱ ላይ ደፍተውበታል፡፡ ራሱንም በዘንግ መትተውታል (ማር 15¸19)፡፡ የሰው ዘር ከአዳም ጀምሮ በጠላቱ በዲያብሎስ በተጐነጐነ የኃጢአት እሾህ ራሱ ተይዞ ነበርና ይህንኑ ለማስወገድ ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ የሆነ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ ተንኮል የተጐነጐነ አክሊለ ሦክ እንደ ዘውድ ደፋ፡፡ በሲኦል ወድቆ በዲያብሎስ ተረግጦ ራሱ የሚቀጠቀጠውን የሰውን ልጅ ለማዳን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱን በመቃ ተቀጠቀጠ፡፡ ከራሱ ላይ በሚወርደው ደም ፊቱ ተሸፈነ፡፡
#2ተፀፍዖ_መልታሕት (በጥፊ መመታት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጃቸው በደም፣ ጣቶቻቸው በበደል በረከሰ በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተፀፍዖ›› የሚለው ቃል ፀፍዐ በጥፊ መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡
መልታሕት ደግሞ ፊት ጉንጭ ማለት ነው፡፡
ጌታችን ለሊቀ ካህናት ቀያፋ እውነትን መናገር እንደ ስድብ ተቆጥሮበት መላልሰው ፊቱን በጥፊ መትተውታል፡፡ ፊቱንም በጨርቅ ሸፍነው ‹‹ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማነው? ትንቢት ተናገርልን›› እያሉ ዘብተውበታል፡፡ በጠላት ዲያብሎስ እጅ ወድቆ በነፍሱ ይቀለድበትና ይንገላታ የበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ብሎ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ ወድቆ ተጐሰመ፤ ተንገላታ፤ በጥፊም ተመታ (ማቴ 27¸27)፡፡ ጲላጦስ አሳልፎ ከሰጠው በኋላም አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ አኑረው ቀይ ልብስ አልብሰው ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን›› እያሉ እየተሳለቁበት በጥፊ መትተውታል (ዮሐ 19¸2-4)፡፡ አላወቁትም እንጂ እርሱ በመንግሥቱ ሽረት፣ በባሕርዩ ሞት የሌለበት የዘለዓለም አምላክ ነው፡፡
3 #ወሪቀ_ምራቅ (ምራቅ መተፋት)፤
ርኩሳን አይሁድ በብርሃናዊው የክርስቶስ ፊት ላይ በሚያስጸይፍ ሁኔታ ምራቃቸውን እንደተፉበት የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ወሪቅ›› የሚለው ቃል
ወረቀ ካለው ግእዛዊ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም እንትፍ አለ፣ (ተፋ) ማለት ነው፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ (ምዕራፍ 5ዐ¸6) ‹‹ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኩም›› ተብሎ እንደተነገረ እየዘበቱበት ምራቃቸውን ተፉበት (ማቴ 27¸29-3ዐ፤ ማር 15¸19)፡፡ በኃጢአት የቆሸሸውን የሰውን ሕይወት ለማጥራት የመጣው ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፋበት፡፡ በሥራው ከገነት ተተፍቶ፤ ተንቆ፤ ተዋርዶ የነበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ ጌታችን ያለ ኃጢአቱ ተተፋበት፤ ተናቀ፤ ተዋረደ፡፡ እንኳን በአምላክ ፊት በሰው ፊት እንኳን መትፋት እጅግ ያስነውራል፡፡ እርሱ ግን የኃጢአታችንን ነውር ከእኛ ሊያጠፋ ነውር የሆነውን ምራቅ ተቀበለ፡፡
4 #ሰትየ ሐሞት ( መራራ ሐሞት መጠጣት)፤
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሳለ ተጠማሁ ባለ ጊዜ መራራ ሐሞት መጠጣቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ሰተየ›› ማለት ጠጣ ማለት ነው፡፡ ሐሞት የሚለውም አሞት ተብሎ በቁሙ ይተረጐማል፡፡ በመዝሙር 68 ቁጥር 21 ላይ ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ ነቢዩ ዳዊትን ትንቢት ያናገረ የነቢያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ‹‹ተጠማሁ›› ባለ ጊዜ ሆምጣጤ ተሞልቶበት ተቀምጦ ከነበረው ዕቃ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡ ውኃ አጠጡኝ ቢላቸው በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፡፡ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም (ማቴ 27¸34)፡፡ ጌታችንም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ (ማቴ 27¸48፤ ማር 15¸36፤ ሉቃ 23¸36፤ ዮሐ 19¸29)፡፡
ቢጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ ውኃ የሚሰጥ አምላክ፤ የተጠማችውን ነፍስ የሚያረካ ጌታ፤ ለዘለዓለም የሚፈልቅ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሚያድል ፈጣሪ በተጠማ ጊዜ የፈጠረውን ውኃ እንኳን የሚያጠጣው የሚያቀምሰውም አላገኘም (ኢሳ 55¸1)፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ በቃዴስ በረሃ ኳትነው ለነበሩ አባቶቻቸው ከሰማይ መና አውርዶ የመገባቸው፤ ከአለት ላይ ውኃ አመንጭቶ ያጠጣቸው ክርስቶስ በተጠማ ጊዜ ቀዝቃዛ ውኃ ነፈጉት (ዘዳ 16¸1-2ዐ፤ 1ቆሮ 1ዐ¸3)፡፡ የዝናማት፤ የባሕርና የውቅያኖስ ጌታ በውኃ ጥም ተቃጠለ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሲኦል በረሃ ወድቀው በሕይወት ውሃ ጥም የተቃጠሉትን ነፍሳት ለማርካት ሲል እርሱ ተጠማ፡፡ በኃጢአት ወድቀው፣ በበደል ረክሰው፣ በነፍሳቸው ተጐሳቁለው፣ መራራ መከራን የሚቀበሉትንና ምረረ ገሃነም አፉን ከፍቶ ሆዱን አስፍቶ የሚጠብቃቸውን ሁሉ ለማዳን መራራ ሐሞትን ቀመሰ፤ ሆምጣጣውንም ጠጣ፡፡ የመረረውን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማጣፈጥ የመረረውን መጠጥ ተቀበለ፡፡
5 #ተቀሥፎ_ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀርባው እስኪላጥ ያለ ርኅራኄ የመገረፉን ነገር የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተቀሥፎ›› የሚለው ቃል ቀሠፈ- ገረፈ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ ዘባን›› ደግሞ ጫንቃ፣ ትከሻ፣ ጀርባ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጠው የተገረፈ አይሰቀልም፡፡ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም ነበር፡፡ ጲላጣስ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን አስገረፈው፡፡ ከደሙ ንጹሕ ነኝ ብሎ ከታጠበ በኋላ ክርስቶስን ያለ ኃጢአቱ በመግረፍ ለአይሁድም አሳልፎ በመስጠት ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› እንዲሉ የታጠበ እጁን መልሶ አቆሸሸው (ማቴ 27¸28፤ ማር 15¸15፤ ዮሐ19¸1)፡፡
መድኃኒታችን መንፀፈ ደይን ወድቆ በእግረ አጋንንት ተጠቅጥቆ በእሳት አለንጋ የሚገረፈውን የሰው ልጅ ለማዳን ሲል ጀርባውን ለግርፋት ሰጠ፡፡ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገረፈ፡፡ አይሁድ አገረ ገዥያቸው ጲላጣስ ላቀረበላቸው ምርጫ ይፈታላቸው ዘንድ ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣውን ክርስቶስን ሳይሆን ራሱን እንኳን ከምድራዊ ወህኒ ማውጣት ያልቻለውን ወንበዴውን በርባንን መረጡ፡፡ መገረፍ ይገባው የነበረ በርባን ተለቀቀ፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ ‹‹ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ›› (በኢሳ 5ዐ¸6) ተብሎ እንደተነገረ ጀርባውን ለገራፊዎች አሳልፎ ሰጠ፤ ጽሕሙንም ተነጨ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የሰው ልጅ ከሚያድነው አምላክ ይልቅ የሚገርፈውንና የሚዘርፈውን ወንበዴ መርጦ ስለተገኘ ነው፡፡
6 #ተዐርቆተ_ልብስ (ከልብስ መራቆት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስስቶስ ልብሱን መራቆቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተዐርቆተ›› ማለት ታረዘ፤ ተራቆተ ማለት ነው፡፡ ፀሐይና ከዋክብትን ብርሃን አልብ
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን
«ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡
ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ
ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው።
ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ
ማረን» ማለት ነው።
ትስቡጣ
የዚህን ቃል ምንጭ እና ትርጉም እስካሁን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ በቅብጡ ግብረ ሕማማትም የለም፡፡ምናልባት ቃሉ ወደ እኛ ሲመጣ ውላጤ ገጥሞት ይሆናል፡፡
፦አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ»
ማለት ነው፡፡
፦አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው።
፦አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
ምንጭ፦የ ሙሀዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ዕይታዎች
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል"የተባለው ተፈፀመ
ት.ዘካ 9÷9
ይህ በነቢዩ ዘካሪያስ አስቀድሞ በትንቢት የተነገረ አማናዊ ቃል የተፈፀመው በኢየሩሳሌም ከተማ ደብረ ዘይት አቅራቢያ ቤተ ፋጌ በምትባል መንደር ነው::ጊዜው በግምት 2000ዓመት ገደማ ይሆናል::ከተማዋ በደስታ ታምሳለች የኢየሩሳሌም ከተማ በተለያዮ ጊዜያት ልዮ ልዮ ነገስታት በሰረገላ ተቀምጠው ጎብኝተዋታልች፣ገስተዋታል የዛሬው ግን ልዮ ንጉሥ ነው ስለ ፍቅር ሲል የእሳት ሰረገላውን ትቶ አህያን የመረጠ አበ ትህትና(የትህትና አባት)መድኃኒት የሆነ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::ሕዝቡም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው አስቀመጡት፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ማቴ 21÷1-17 ከፊትና በኋላ ያሉት ብዙ ሰዎችም “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ሆሳዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው ሕዝቡም እንዲ ማለታቸው አቤቱ አሁን አድን ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት የተናገረውን ንግግር ሲገልጡ ነው ።አህያይቱ ተሰርቃ ከነ ልጆ ከነ(ውርንጭላዋ) ታሰረች ነበር ያሰራት ሰው ሌባ ነወ የሌላ ሰው ንብረት እንደ ንብረቱ አድርጎ ከደጃፉ አስሯታልና ሌባው በቤቱ ያቆያት 5ቀን ተኩል ነው" የማታ የማታ እውነት ይረታ" እንዲሉ አበው እውተኛ ፈራጅ በወጣ ጊዜ አህያዋ ከእስራቷ እንድትፈታ አደረገ ::አህያዋ ና ውርንጫላዋ አዳምና ልጆቹ ሲሆኑ ሌባው ዲያቢሎስ ነው: በአሰት ንግግር እግዚአብሔርን ከመሰለ አምላክ ገነት ከምታክል ቦታ ለይቶ ለ5ቀን ተኩልያክል ጊዜ በሲዖል አስሮናል::
5500 ዘመን ሙሉ በእግረ አጋንንት ተይዘን ሰንጨነቅ መድኃኒት ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም አልደረሰልንም ነበርና ስለዚህ በደስታ ተሞልተው የሆሳዕና አሉ ::
ለምን በአህያና በአህያ ወርንጭላ ላይ ተቀመጠ ቢሉ?
✝እናቲቱ አህያ የብሎይ ውርንጭላይቱ የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ናቸው በሁለቱ መቀመጡ ኦሪትን እንዳልሻረ ወንጌልንም እንደሰጠ ሲያጠይቅ አንድም እናቲቱ አህያ ሸክም የለመደች ነች አዲሲቱ ውርንጫይቱ ግን ሽክም ያለመደች የቤተ አሕዛብና የቤተ እስራኤል ምሳሌ ናቸው::ኦሪት ከባድ ወንጌል ግን ቀሊል ናትና አንድም ሕግ የለመዱና ሕግ ያለመዱ እዝቦች ናቸውና:: አንድም አህያ በወለደችሁ ታርፋለች እንዲሉ ኦሪትም በወንጌል ታግዛ ጸንታለችና ነው::ሌላው
👉ፋረስና በቅሎ ለጦርነት ይሁላሉ አህያ ግን አትውልም ጥንት ነቢያት ክፉ ትንቢትና ክፎ ወሬ ይዘው ሲመጡ ማቅ ለብሰው ትቢያ ነስንሰው በፈረስ ወይም በበቅሎ ተቀምጠው ወደ ከተማ ይባሉ መልካም ዜናና ትንቢት ይዘው የመጡ እንደሆነ ደግሞ በአህያ ላይ ተቀምጠው ይመጣሉ ሕዝቡም መቀመጫቸውን አይቶ መልካም ዜና እንዳመጡ ተረድቶ በደስታ ይበቀላቸው ነበርና ጌታችንም መልካም የድኅነት ዜና ሆኜ መጣው ሲል ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በአህያ ላይ ተቀመጠ::
👉በአህያ ተቀምጦ እንደሚመጣ በኦሪት የተነገሩ የኢሳይያስና የዘካሪያስን ትንቢት' ለመፈጸም ነው::(ትንቢቱን ለመፈጸም) ዘካ9÷9
👉ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና እንዳለ ትዕትናን ለማስተማር ማንንም አትናቁ ሲል ማቴ11÷29 ዮሐ13÷1
👉በፈረስና በበቅሎ ያለን ሰው ማንም አይደርስበትም በአህያ ያለን ሰው ግን በቶሎ ይደርሱበታል ስለዚህ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የእሩቅ አምላክ አይደለሁም ከፈለጋችሁን በቅርብ ታገኙኛላችሁ ለማለት በአህያ ተቀመጠ ኤር 23÷23
🌴ሕዝቡ የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው🌴
🌿- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል (የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምትሰጥ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው)
🌿- ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው ይህንኑ አርአያ አድርገን እኛም እንዲሁ እናደርጋለን
"እነሆ ዛሬ እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የሰራትን ቀን ይህች ነችና ሐሴትን እናድርግ " መዝ 117 (118) ÷ 24....ይቆየን
እንደ አህያይቱ እኛም ከእስራታችን ሁሉ ተፈተን የሰላም ባለቤት የሆነውን መዳኃኔ ዓለም ክርስቶስን በልባችን ከተማነት የምናሳድር እውነተኛ ክርስቲያኞች ያደርገን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ለዘለዓለሙ አሜን❤️
ሀሳብ ጥቆማ ጥያቄና አስተያየታችሁን @YEAWEDIMERITE ላይ አድርሱን።
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ
ርእየ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
የሆሣዕና ሥርዓት
የሆሣዕና ሥርዓት አከባበር ከመቼ ጀምሮ ነው ቢባል ከመጀመሪያው ጳጳስ ከአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ጀምሮ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ /ዕለት/ ሊቃውንቱ ማኅሌተ እግዚአብሔር ቆመው አድረው፣ ከቅዳሴ በፊት "ወበልዋ ለወለተ ጽዮን" "ለጽዮን ልጅ ንገሯት" እያሉ ቤተ መቅደሱን ወይም ቤተ ክርስቲያኑን በዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በመዞር፣ ሥርዓተ ዑደቱን ይፈጽማሉ፡፡ ምስባክ ይሰበካል፤ ወንጌል የአራቱ ወንጌላውያን ለዕለቱ ተስማሚ የሆነ ከየምዕራፉ ይነበባል፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፡፡ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ አመሰግነዋልና ያንን ለመፈጸም ነው፡፡
ሰሌን እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል፤ ክርስቲያኖችም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በየዓመቱ "ሆሣዕና በአርያም" እያሉ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፡፡
በዚህ ዕለት ለምን ልዩ ጸሎተ ፍትሐት ይፈጸማል?
በዚህ ዕለት ጸሎተ ፍትሐት የሚፈጸመው በሰሙነ ሕማማት በሚገኙ ዕለታት ለሙታን፣ ፍትሐት ስለማይደረግ ነው፡፡ ካሣ የተፈጸመው ጌታ ተሰቅሎ ነፍሳትን ከሲኦል ነጻ ካወጣ በኋላ ስለሆነ፤ ከዚያ በፊት ካሣ አልተፈጸመምና፡፡ ይኸውም በሰሙነ ሕማማት ለሙታን ፍትሐት እንዳይደረግ ካልዕ ሰላማ በግብረ ሕማም መጽሐፍ ስለአዘዘ፤ በዚህ ምክንያት የሆሣዕና ዕለት ጸሎተ ፍትሐት ይፈጸማል፤ እንጂ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ለሞተ ሰው ጸሎተ ፍትሐት አይደረግለትም፡፡ በሆሣዕና ዕለት የሚደረገው ጸሎተ ፍትሐት ለዚህ ተብሎ ነው፡፡
አሁን ያለነው ድርጊቱ /ካሣ/ ከተፈጸመ የዛሬ 1970 ዓመት ነው፡፡ ይህ ዛሬ እንዴት እንደ አዲስ አድርጎ ሊፈጸም ይችላል? የሚል ካለ ያማ ጌታ የሠራውን ሥራ ሁሉ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሥሩ ተብሎ የለ? ሥሩ ማለት እናንተ ስታልፉ /ስትሞቱ/ ልጆቻችሁ ይሰሩ ማለት ነው፡፡
ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ
ኢየሱስ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!
ኦ እግዝትየ ፍትህኒ እም/ እማዕሠሩ ለሰይጣን እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን ባርክኒ ቀድስኒ ወአንጽሕኒ በከመ ባርኪዮ ለቅዱስ ኤፍሬም ፍቁርኪ ።
በረከተ ፍቁር ወልድኪ ወአቡሁ መንፈስቅዱስ ይኅድር በላዕሌየ አሜን!