yenetay | Unsorted

Telegram-канал yenetay - የኔታ

-

አብነቱን በአብነት እናስቀጥለው

Subscribe to a channel

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን

መቅደስ

✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
👉 @YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን

ተሰመይኪ

✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
👉 @YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ከተራ #ዘኢትዮጵያ
_______1
#ሐሳቢ ያልቅ ሆናል እንጂ ሐሳብ አያልቅም! ስለዚህ ሀሳብ ቦይ እስካገኘ ድረስ ፈሶ
የማያልቅ ወንዝ ነው ። ይልቁኑ መነሻቸው በምድር የማይታወቁ ገነታዊ የሆኑ ወንዞች ለዚህ
ጥሩ ማሳያዎች ናቸው።
ሀገራችን ሁል ጊዜ የጥምቀት በዓልን ምክንያት አድርጋ ዋዜማውን ማለትም ጥር 10 ቀንን
" ከተራ " ብላ ታቦት ከመንበሩ አንስታ ድንኳን ወደ ተተከለበት የታቆረ ፣የተከተረ፣የተገደበ
ውኃ ወዳለበት ሥፍራ ይዛ በመሄድ በልልታና በግርግርታ በድምቀት ከምዕመኞቿ ጋር
ታከብረዋለች ። ኢያሱ 3÷3
#ይህንንም ማድረጓ አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ መጥቶ
ያጥምቀኝ ሳይል ወደ ባሪያው ወደ ዮሐንስ በትሕትና ሄዶ መጠመቁን ለማሰብ ነው።
የትሕትና አባት ! ይህን በማድረግ ባያስተምረን ኖሮ ዛሬ ካህናቱ ቤታችን መጥተው
ያጥምቁን ባልን ነበር። ከተራ የቃሉ ትርጉም መገደብ ፣ በአንድ ቦታ መርጋት (ለፈሳሽ
ነገር)፣ መታቆር ፣መቆም ወይም ማቆም የሚል ነው።
ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ " እነሆ ውኃ ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው? " ብላ
ከተጠመቀችበት ጊዜ አንስቶ ይህው ዛሬ ድረስ ምሥጢረ ጥምቀትን በሚገባ ለልጆቿ
ስታስተምርና ሥርዓቱንም ስትፈጽም ኖራለች ። ወደ ፊትም ትኖራለች። # ሐዋ 8÷36
#ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የጥምቀትን በዓል ማክበር የጀመረችሁ በኩረ ጳጳሳት ዘኢትዮጲያ
የሚባሉት " ፍሬ ምናጦስ" ወይም ሕዝቡ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ ፊደል ቀርጾ ንባብ አደላድሎ
የድንቁርናን ጽልመት ገፏልናልና ብለው " አቡነ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን " /የሠላም አባት
ብርሃንን የሚገልጥ / እያሉ ይጠሯቸው በነበሩት በመጀመሪያው ታላቅ ጳጳሳችን ትዕዛዝና
መመሪያ ነበር።
ከዛ በመቀጠል እነ አፄ ገብረ መስቀል፣ እነ አፄ ናዖድ እና አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የመሳሰሉት
ቅዱሳን ነገሥታት ይህ ደገኛ የጥምቀት በዓል በአደባባይ እንዲከበር አድርገውታል።
ዛሬ ዛሬ እነዚህን የመሰሉ ቅድስናን ከንግሥና አስተባብረው የያዙ መሪዎችን በማጣቷ
ባህሏን ፣ወጓን፣ ሃይማኖቷን ፣ትውፊቷ ፣ሥርዓቷን በአደባባይ ወጥታ እንዳታከብር ጫና
እያሳደሩባት ትገኛለች።
#እርሷ ግን ተስፋዋ እግዚአብሔር ነውና ዛሬም ወደ ዮርዳኖስን መውረዷን አላቆመችም ።
አንድነት ይዛለች ፣ ፍቅር ከትራለች ፣ ሠላም ጸንሳለች መለያት እንዳያጨነግፋት፣ አጥንት
ቆጣሪነት እንዳይበትናት እንጠንቀቅላት።
ይህ ሀገራዊ ከተራ ከመንፈሳዊ ክትረት ምሳሌነት አልፎ በየ ቤታችን መብራትና እራት ሆኖ
የሚመጣ የብልጥግናችን ቀንዲል ነው። ከተራውን ከተራ ነገሮች ሁሉ ወጥተን በአንድነት
የምንረጨው ጥሩ ውኃ ያድርግልን። # ሕዝ 36÷25
"ሃይማኖት፣ ብሔር፣ዘር የማይለኝ ሰናይ ከተራ... #ዓባይ !"
ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
10/2013ዓ.ም

Читать полностью…

የኔታ

ሥርዓተ ማኅሌት ዘኅዳር ሚካኤል

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
(ሥርዓተ ነግሥ)

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ፡ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመ ትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ፤ ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ

አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ ኢዜነዎ ለሰማይ፤ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ ወተከለ ፫ተ ዕፀ ህይወት በዲበ ምድር።

ነግሥ

ጎሣዐ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤ አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ ወአንተኑ ለ፳ኤል ዘአውረድከ መና።

ወረብ

አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ/፪/
ወአንተኑ ለ፳ኤል መና ዘአውረድከ/፪/

ዚቅ

አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ወርእየቱ ከመ ተቅጻ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤ አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ ዘትረ ኮክሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ።

መልክአ ሚካኤል

ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤ ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ።

ወረብ

ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን/፪/
በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ/፪/

ዚቅ

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ፤ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሠፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።

ወረብ

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር/፪/
ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/

መልክአ ሚካኤል

ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ፤ በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ፤ ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ፤ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ

ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ/፪/

ዚቅ

ረሰዮ እግዚኦ ለውእቱ ሚካኤል፤ እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን።

ወረብ

እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል/፪/
እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ/፪/

መልክአ ሚካኤል

ሰላም ለሕንብርትከ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤ ነግኃ ነግኅ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤ በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤ ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ።

ወረብ

"በገዳም"/፫/ ዘሴሰይኮሙ/፪/
ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ/፪/

ዚቅ

ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤ ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤ በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርባዐ ዓመተ፤ ወሴሰዮሙ መና ኅብስተ፤ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መስፈርተ።

ወረብ

ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር/፪/
በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ ለ፳ኤል አርብዐ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/

መልክአ ሚካኤል

አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤ ለለ፩ ፩ ዘበበክፍሉ፤ ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ

ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤ ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ።

ወረብ

ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ/፪/
ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት/፪/

አንገርጋሪ

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤
ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።

አመላለስ

ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/
ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ/፬/

ዘሰንበት

ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለእረፍተ ዚአነ ከመ ናእብያ ወናክብራ ለዕለተ ሰንበት መላእክተ ሰማይኒ ወኵሉ ፍጥረት እለ ውስተ ሲኦል እለ ውስተ ደይን የአዕርፉ ባቲ እስመ ቀደሳ አዕበያ ወአልአላ በዕለተ ሰንበት መኑ ከማኪ ስቡሕ እግዚኦ ውስተ ቅዱሳን መንክር ስብሐቲከ እግዚኦ ወትረ እሴብኀከ።

አመላለስ

መንክር ስብሐቲከ/፪/
እግዚኦ ወትረ እሴብኃከ/፬/

ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ

👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa

ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነጽጌ "፬ኛሳምንት" "ጥቅምት፳፩
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተነግሥ)
💐💐💐🌹🌹🌹🌺🌺🌺
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ፡ሃሌ ሉያ ሃሌሉያወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ሃሌሉያ ሃሌሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፡ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ሃሌሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡በአሐቲ ቃል።

🌸መልክአ ሥላሴ🌸

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

🌸ዚቅ🌸

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን ፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳንሐረገወይን፤
ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ፡፡

🌸ማኀሌተ ጽጌ🌸

ትመስል እምኪ ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለምብርህተ፤ ካዕበ ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ
ዕረፍተ።

🌸ወረብ🌸

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም
/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

🌸ዚቅ🌸

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእም ኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

🌸ወረብ🌸

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ/፬/
ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኲኖ ማኅደረ ለመንፈስቅዱስ/፪/

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ስብሐተ ፍቅርኪ ማርያም ኩሎ አሚረ፤ በልሳነ ኩሎ ይጸጊ ወኢይፈርህ አባረ፤ ዘያረጥብ የብሰ ወያየብስ ባሕረ፤ እስመ ብኪ ጠለ ተአምር እንተ ርደቶ ነጸረ፤ ጌድዎን ኀበ ሰፍሐ አምሳለኪ ፀምረ ።

🌸ወረብ🌸

ስብሐተ ፍቅርኪ ማርያም ኩሎ አሚረ በልሳነ ኩሎ ይጸጊ ወኢይፈርህ አባረ/፪/
እስመ ብኪ"ጠለ ተአምር"/፪/ገባሪተ ኃይል/፪/

🌸ዚቅ🌸

ወዓዲ በትር እንተ ሠረፀት ወጸገየት ወፈረየት፤ ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ ፀምር ዘጌዴዎን፤ ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል።

🌸ዓዲ ዚቅ🌸

ስብሐተ ማርያም ይነግር አፉየ፤ ወኩሉ ዘሥጋ ይባርክ ለስማ ቅዱስ፤ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።

🌸ዓዲዚቅ🌸

ስብሐተ ለማርያም ንፌኑ፤ ይእቲ ለመለኮት ክዳኑ ።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸
🌸 (በላይ ቤት የሚባል)🌸

ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ፤ ወዘመነ ፍኔ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ፤ ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፤ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ፤ ፀቃውዓ መዓር ቅድው ወሀሊብ ፀዓዳ ።

🌸ዚቅ🌸

ይቤሎ ኢዩኤል ለንጉሥ፤ ናሁ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም፤ ያንጸፈጽፍ መዓር እምአድባር፤ መያሕመለምል አውግር።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽ ሕ ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

🌸ወረብ🌸

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተመቅደስ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
/፪/

🌸ዚቅ🌸

ንዒ ርግብየ ሰላማዊት ንባብኪ አዳም ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ እሞሙ ለሰማዕትወእኅቶሙ
ለመላዕክት አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቊ ባሕርይ ዘይኀቱ ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ ወለኪኒ ይሰግድ
ውእቱ።

🌸ወረብ🌸

"ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ" እምዕንቍ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ/፪/

🌸ዚቅ🌸

ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት።

🌸ሰቆቃወ ድንግል🌸

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ ለወልድ
ኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ ለክብረቅዱሳን በከመ ይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤ እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

🌸ወረብ🌸

በከመ ይቤ "ኦዝያን"/፪/ለክብረ ቅዱሳን/፪/
እም ግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ(፪)

🌸ዚቅ🌸

ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ
ለወልድየ ለክብረቅዱሳን

🌸ዓዲ ሰቆቃወ ድንግል🌸

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደክምኪ፤ ሶበኒ የሐውር በእግሩ
ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።

🌸ዚቅ🌸

ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስእን ሕፃንኪ፤ ያንቅዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ፤ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ፤ እስከ ትጸውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ።

🌸መዝሙር በ ፮ ነገሥት ቤት🌸

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት፤ ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጎታትማ፦ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ነአኩቶ ለዘፀግወነ
ሠናይቶ።

🌸ዓራራት🌸

በጊዜሁ ኃለፈ ክረምት በጊዜሁ ቆመ በረከት እግዚአ ለሰንበት አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ።

🌸ዕዝል🌸

ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኩሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለዘቀደሳ ለሰንበት ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት።

🌸ሰላም🌸

ሐረገ ወይን በል አመ ፫ ለዝ
ዝማሬ ፦ ትብሎ መርዓት በል
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ጥቅምት ስምንት የማኅሌተ ጽጌ ሁለተኛው(፪) ሳምንት።
ማኅሌተ ጽጌ ጥቅምት 7
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

ነግሥ
(የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
✝✝✝✝✝✝✝
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤
ንወድስ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፣ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፩. ነግሥ (ለአፉክሙ )
ሰላም፡ ለአፉክሙ፡ ዘማዕፆሁ፡ ሰላም፤
ጽጌያቲሁ፡ ሥላሴ፡ ለተዋሕዶ፡ ገዳም፤
መንገለ፡ አሐዱ፡ አምላክ፡ ንዋየ፡ መጻኢ፡ ዓለም፤
ወልጡ፡ አምልኮትየ፡ በጸጋክሙ፡ ፍጹም፤
እምአምልኮ፡ ጣዖት፡ ግሉፍ፡ አሐዱ፡ ድርኅም።

ዚቅ
ለሥሉስ፡ ቅዱስ፡ ጥዑም፡ ቃሎሙ፤
ናርዶስ፡ ጸገየ፡ ውስተ፡ አፉሆሙ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፪. ተፈሥሒ ድንግል (ማኅሌተ ጽጌ )

ተፈስሒ፡ ድንግል፡ ዘኢተአምሪ፡ ብእሴ፤
ዘጸገይኪ፡ ለነ፡ አሐደ፡ እምነ፡ ሥላሴ ፤
እንዘ፡ ትዘብጥ፡ ከበሮ፡ ቅድመ፡ አዕላፈ፡ ኤፍሬም፡ ወምናሴ፤
ለተአምርኪ፡ ትነግር፡ ውዳሴ፤
ማርያም እኅቱ ለሙሴ፡፡

ወረብ

ተፍሥሒ፡ ድንግል፡ ዘኢተአምሪ፡ ብእሴ፡ ዘኢተአምሪ፤
ዘጸገይኪ፡ ለነ፡ አሐደ፡ እምነ፡ ሥላሴ፡ እምነ፡ ሥላሴ፡ ዘጸገየኪ፡ ለነ፤

ዚቅ

በህየ፡ ማርያም፡ እኅቱ፡ ለሙሴ፡ በዕብራይስጥ፤
በይባቤ፡ ዘበጠት፡ ከበሮ፤ በዝየ፡ ማርያም፡ ቅድስት፤ በሥምረተ፡ መለኮት፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፫. እንበለ ትሣረር

እንበለ: ትሣረር: ምድረ: ገነት: ወሥነ: ጽጌያት: ያስተርኢ፤
በኅሊና: ሥሉስ: ዘሀሎ: ተአምርኪ: በቋዒ፤
ኦ: መዋዒት: እመ: አምላክ: መዋዒ፤ ንዒ: ንዒ: እምርእሰ: ኤርሞን: ንዒ፤ ከመ: ትንስቲዮ: ለጸላዒ: ሕዝበኪ: ገፋዒ፡፡

ወረብ

ኦ: መዋዒት: እመ: አምላክ: ንዒ: ንዒ: እመ: አምላክ

እምርእሰ: ኤርሞን: ንዒ: ለፀላኢ: ለፀላኢ: ከመ: ትንሥቲዮ /፪/

ዚቅ
ዘእንበለ፡ ይትፈጠር፡ ሰማይ፡ ወምድር፤ ወዘእንበለ፡ ትሣረር፡ ምድረ፡ ገነት፤ ሀለወት፡ ስብሕት፡ ቅድስት፡ ወቡርክት፡ ይእቲ፡ ማርያም፤
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፬. እንዘ ተሐቅፊዮ

እንዘ ፡ ተሐቅፊዮ ፡ ለሕጻንኪ ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ ፡ ወቀይሕ፤
አመ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ቦእኪ ፡ በዕለተ ፡ ተአምር ፡ ወንጽሕ፤
ንዒ ፡ ርግብየ ፡ ትናዝዝኒ ፡ እምላህ፤ወንዒ ፡ ሠናይትየ ፡ ምስለ ፡ ገብርኤል ፡ ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ፡ ከማኪ ፡ ርኅሩኅ ፡፡

ወረብ
ንዒ፡ ርግብየ፡ ንዒ፡ርግብየ፡ ምስለ፡ ሚካኤል፤
ወንዒ፡ ሠናየት፡ ወንዒ፡ ሠናይትየ፡ ምስለ፡ ገብርኤል፡ ፍሡሕ፤

ዚቅ

አንቀጸ፡ አድኅኖ፡ ረሰያ፤ ኀደረ፡ ቃል፡ ኀበ፡ ሠምረ፡ አብ፤
ወይቤላ፡ ንዒ፡ ርግብየ፡ ሠናይትየ፤ አግአዚት፡ ንባብኪ፡ አዳም፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፭. ክበበ ጌራ ወርቅ

ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ጽሩይ ፡ እምዕንቈ ባሕርይ ፡ ዘየኃቱ፣
ዘተጽሕፈ ፡ ብኪ ፡ ትእምርተ ፡ ስሙ ፡ ወተዝካረ ፡ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ፡ ማርያም ፡ ለጊዮርጊስ ፡ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ፡ ኵሎ ፡ ታሰግዲ ፡ ሎቱ፣
ወለኪኒ ፡ ይሰግድ ፡ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ዘየኃቱ፡ ጽሩይ፡ እምዕንቈ ባሕርይ፤
ማርያም፡ አክሊለ፡ ጽጌ፡ ለጊዮርጊስ፡ ቀጸላ፡ መንግሥቱ፡፡

ዚቅ
በወርቅ፡ ወበዕንቊ፡ ወበከርከዴን፤
ሥርጉት፡ ሥረጉት፡ በስብሐት፤
ወነገሥት፡ ይትቀነዩ፡ ለኪ፤
ትርሢተ፡ መንግሥቱ፡ አንቲ፡ መድኃኒቶሙ፡ ለነገሥት፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
፮. ስብሐት ለኪ (ሰቆቃወ ድንግል )

ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ አብ፡ ፈናዊ፤
ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ ወልድ፡ ተፈናዊ፤
ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ማኅየዊ፤
ቃለ፡ ስእለትነ፡ በአዕዛነ፡ መንፈስ፡ ጽልዊ፤
ወዲበ፡ ዛቲ፡ ማኅሌት፡ ሰላመ፡ ከዓዊ፡፡

ወረብ፦

ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ አብ፡ ፈናዊ፡ ስብሐት፡ ለኪ ፤
ስብሐት፡ ለኪ፡ ማርያም፡ በስብሐተ፡ ወልድ፡ ወመንፈ፡ስ ቅዱስ ፤

ዚቅ

ስብሐት፡ ለኪ፡ ኦ፡ ወላዲተ፡ እግዚአ፡ ኲሉ፡ አኰቴት፡ ወክብር፤
ለአብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ይእዜኒ፡ ወዘልፈኒ፡ ወለዓለመ፡ ዓለም፡ አሜን፤
ወልድኪ፡ ሣህሎ፡ ይክፍለነ፤ ሰአሊ፡ ለነ፡ ቅድስት።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ናሁ እግዚእ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ተሰመይኪ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ኮንኪ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ከመ ከብካብ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ንጽሕት ወብርህት
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ጥቅምት ስምንት የማኅሌተ ጽጌ አንደኛው ሳምንት።
ማኅሌተ ጽጌ መስከረም 30

ነግሥ
(የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ
ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤
ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።

፩ ነግሥ ( ለኵልያቲክሙ)
ሰላም፡ ለኵልያቲክሙ፡ እለ፡ ዕሩያን፡ በአካል፤
ዓለመክሙ፡ ሥላሴ፡ አመ፡ ሐወፀ፣ ለሣህል፤
እምኔክሙ፡ አሐዱ፡ እግዚአብሔር፡ ቃል፤
ተፈጸመ፡ ተስፋ፡ አበው፡ በማርያም፡ ድንግል፤
ወበቀራንዮ፡ ተተክለ፡ መድኃኒት፡ መስቀል ፡፡

ዚቅ
ወኃይዝተ፡ ወንጌል፡ የዓውዳ፡ ለቤተክርስቲያን፤
እም፡ አርባዕቱ፡ አፍላጋት፤ እንተ፡ ትሰቀይ፡ ትእምርተ፡ ለለጽባሑ፤
እማቴዎስ፡ ልደቶ፡ ወእማርቆስ፡ መንክራቶ፤
እም፡ ሉቃስ፡ ዜናዊ፡ ተሰምዮ፡ ወእም፡ ዮሐንስ፡ በግዓ፤
ወዘንተ፡ ሰሚዓ፡ ትገብር፡ በዓለ፡ በፍግዓ።

፪ ጽጌ አስተርአየ
ጽጌ፡ አስተርአየ ፡ ሠሪጾ፡ እምዐጽሙ፤
ለዘአምኃኪ፡ ጽጌ፡ ለገብርኤል፡ ምስለ፡ ሰላሙ፤
ወበእንተዝ ፡ ማርያም ፡ ሶበ ፡ ሐወዘኒ ፡ ጣዕሙ፤
ለተአምርኪ ፡ አኀሊ፡ እሙ፤
ማኅሌተ፡ ጽጌ፡ ዘይሰመይ፡ ስሙ፡፡
ወረብ
መዓዛ፡ ጣዕሙ፡ ለተአምርኪ፡ ሶበ፡ ሶበ፡ ሐወዘኒ፤
ወበእንተዝ፡ ማርያም፡ አሐሊ፡ ለተአምርኪ፡፡

ዚቅ
ሃሌ፡ ሉያ፡ ሃሌ፡ ሃሌ፡ ሉያ፤
ናሁ፡ አስተርአየ፡ ጽጌ፤
መርዓቱኒ፡ ትቤ፡ ወልድ፡ እኁየ ፡ ይምዕዝ ፡ ከርቤ፤
ናሁ ፡ አስተርአየ ፡ ጽጌ፤
ዕንባቆም ፡ ነቢይ ፡ ግብረ፡ ምግባሩ፡ ለወልድ፡ አንከርኩ፡ ይቤ፤
ናሁ ፡ አስተርአየ፡ ጽጌ፤
ንጉሠ ፡ ሰላም፡ ክርስቶስ፤
ዓቢይ፡ ልዕልናከ፡ ወመንክር፡ ስብሐቲከ፡ ለዕረፍት፡ ሰንበተ ፡ ሠራዕከ፡፡

፫ እንዘ ተሐቅፊዮ
እንዘ ፡ ተሐቅፊዮ ፡ ለሕጻንኪ ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ ፡ ወቀይሕ፤
አመ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ቦእኪ ፡ በዕለተ ፡ ተአምር ፡ ወንጽሕ፤
ንዒ ፡ ርግብየ ፡ ትናዝዝኒ ፡ እምላህ፤
ወንዒ ፡ ሠናይትየ ፡ ምስለ ፡ ገብርኤል ፡ ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ፡ ከማኪ ፡ ርኅሩኅ ፡፡
ወረብ
እንዘ፡ ተሐቅፊዮ፡ ለሕጻንኪ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ፡ ወቀይሕ፤
አመ፡ ቤተ፡ መቅደስ፡ ቦእኪ፡ በዕለተ፡ ተአምር፡ ወንጽሕ፤

ዚቅ
ንዒ፡ ርግብየ፡ ወንዒ፡ ሠናይትየ፤ እንተ፡ ሐዋርያት፡ ይሴብሑኪ፤
መላእክት፡ ይትለአኩኪ፤ ፃዒ፡ እምሊባኖስ፡ ሥነ፡ ሕይወት፡፡

፬ ሰዊተ ሥርናዩ
ሰዊተ፡ ሥርናዩ፡ ለታዴዎስ፡ ወለበርተሎሜዎስ፡ ወይኑ፤
እንተ፡ ጸገይኪ፡ አስካለ፡ በዕለተ፡ ተከለኪ፡ ዕደ፡ የማኑ፤
ማርያም፡ ለጴጥሮስ፡ ጽላሎቱ፡ ወለጳውሎስ፡ ሰበኑ፤
ብኪ፡ ምውታን፡ ሕያዋነ፡ ኮኑ፤
ወሐዋርያት፡ መላእክተ፡ በሰማይ፡ ኮነኑ፡፡

ወረብ
ማርያም፡ ለጴጥሮስ፡ ጽላሎቱ፡ ጽላሎቱ፡ ወለጳውሎስ፡ ሰበኑ፤
ወሐዋርያት፡ መላእክተ፡ መላእክተ፡ በሰማይ፡ ኮነኑ፡፡

ዚቅ
ኦ፡ መድኃኒት፡ ለነገሥት፤ ማኅበረ፡ ቅዱሳን፡ የዓውዱኪ፤
ነቢያት፡ የአኵቱኪ፡ ወሐዋርያት፡ ይዌድሱኪ፤
እስመ፡ ኪያኪ፡ ኃርየ፡ ለታዕካሁ፡ ከመ፡ ትኩኒዮ፡ ማኅደረ ፤
መላእክት፡ ይኬልሉኪ፡ ጻድቃን፡ ይባርኩኪ፡ አበው፡ ይገንዩ፡ ለኪ፤
እስመ፡ ኪያኪ፡ ኃርየ፡ ለታዕካሁ፡ ከመ፡ ትኩኒዮ፡ ማኅደረ፡፡

፭ ክበበ ጌራ ወርቅ
ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ጽሩይ ፡ እምዕንቈ ባሕርይ ፡ ዘየኃቱ፣
ዘተጽሕፈ ፡ ብኪ ፡ ትእምርተ ፡ ስሙ ፡ ወተዝካረ ፡ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ፡ ማርያም ፡ ለጊዮርጊስ ፡ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ፡ ኵሎ ፡ ታሰግዲ ፡ ሎቱ፣
ወለኪኒ ፡ ይሰግድ ፡ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ፡ ጌራ፡ ወርቅ፡ ጽሩይ፡ ዘየኃቱ፡ እምዕንቈ፡ ባሕርይ፤
ማርያም፡ አክሊለ፡ ጽጌ፡ ለጊዮርጊስ፡ ቀጸላ፡ መንግሥቱ፤

ዚቅ
ውድስት፡ አንቲ፡ በአፈ፡ ነቢያት፤ ወስብሕት፡ በሐዋርያት፤
አክሊለ፡ በረከቱ፡ ለጊዮርጊስ፤
ወትምክህተ፡ ቤቱ፡ ለእሥራኤል፡፡

፮ በስመ እግዚአብሔር (ሰቆቃወ ድንግል)
በስመ፡ እግዚአብሔር፡ ሥሉስ፡ ሕጸተ፡ ግጻዌ፡ ዘአልቦ፤
ሰቆቃወ፡ ድንግል፡ እጽሕፍ፡ በቀለመ፡ አንብዕ፡ ወአንጠብጥቦ፤
ወይሌ፡ ወላህ፡ ለይበል፡ ዘአንበቦ፤
ከማሃ፡ ኀዘን፡ ወተሰዶ፡ ሶበ፡ በኵለሄ፡ ረከቦ፤
ርእዮ፡ ለይብኪ፡ ዓይነ፡ ልብ፡ ዘቦ።

ወረብ
ከማሃ፡ ኀዘን(፪)፡ ወተሰዶ፡ ኀዘን፤
ርእዮ፡ ለይብኪ፡ ዓይነ፡ ልብ፡ ዘቦ፡ ዓይነ፡ ልብ።

ዚቅ
እወ፡ አማን፡ እምውሉደ፡ ሰብእ፡ አልቦ፤
ምንዳቤ፡ ወግፍዕ፡ ዘከማኪ፡ በውስተ፡ ኵሉ፡ ዘረከቦ።
++++++++++++++

መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ትዌድሶ፡ መርዓት፤ እንዘ፡ ትብል፡ ነዓ፡ ወልድ፡ እኁየ፡ ንፃእ፡ ኃቅለ፤
ትዌድሶ፡ መርዓት፤ ንርአይ፡ ለእመ፡ ጸገየ፡ ወይን፡ ወፈረየ፡ ሮማን፤
ትዌድሶ፡ መርዓት፤ አሠርገወ፡ ሰማየ፡ በከዋክብት፡ ወምድርኒ፡ በስነ፡ ጽጌያት፤
ትዌድሶ፡ መርዓት፤ እስመ፡ ውእቱ፡ ወልድ፡ ዋሕድ፡ እግዚአ፡ ለሰንበት፤
ትዌድሶ፡ መርዓት፡ ወትብሎ፤ ወልድ፡ እኁየ፡ ቃልከ፡ አዳም፡፡

አመላለስ
ትዌድሶ፡ መርዓት፡ ወትብሎ፤
ወልድ፡ እኁየ፡ ቃልከ፡ አዳም።

ሰላም
ናሁ፡ አስተርአየ፡ ጽጌ፤ መርዓቱኒ፡ ትቤ፡ ወልድ፡ እኁየ ፡ ይምዕዝ ፡ ከርቤ፤
ናሁ፡ አስተርአየ፡ ጽጌ፤ ዕንባቆም፡ ነቢይ፡ ግብረ፡ ምግባሩ፡ ለወልድ፡ አንከርኩ፡ ይቤ፤
ናሁ፡ አስተርአየ፡ ጽጌ፤ ንጉሠ፡ ሰላም፡ ክርስቶስ፤
ዓቢይ፡ ልዕልናከ፡ ወመንክር፡ ስብሐቲከ፡ ለዕረፍት፡ ሰንበተ ፡ ሠራዕከ፡፡
+++

ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመድዎ በዚህ 👇ሊንክ ያስተዋውቁልን !
❖❖ ሐመረ ኖኅ ❖❖
❖💚═ @ORTHOTEK ═💚❖
❖💛═ @ORTHOTEK ═💛❖
❖❤️═ @ORTHOTEK ═❤️❖

Читать полностью…

የኔታ

✝መስቀል ክፍል ፯ (የመጨረሻ ክፍል)✝

✝በመስቀል ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች ክፍል ፫✝

✝ጥያቄ፦

ኢየሱስ ክርስቶስን የገደለውን መስቀል አናከብርም።እርሱን ማክበር ጠላትን መውደድ ነወ።ጣኦት ማምለክ ነው።(ፀረ ማርያሞች)

✝መልስ፦
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉን ማክበር እንደሚገባን ሲነግረን "ለሁሉም እንዲህ አላቸው። በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።" ሉቃ 9 : 23 ያውም አምላካችን ዕለት ዕለት ተሸከሙት በማለት ገልጾልናል።

✝ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስም ለገላትያ ሰዎች የላከው መልእክቱ " ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። ገላ.6 : 14 በማለት የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልን በጣም ማክበር እንደሚገባን ነገረን

✝ታዲያ መናፍቃን ዘወትር ሰውን ከእመቤታችንንና ከቅዱሳን ፣ከመላእክት እንዲሁም ለቅዱስ መስቀሉ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ይህን ይናገራሉ። ይህንንም ሐዋርያው ሲያጸናው " ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። "ፊልጵ 3 : 18-19 ብሎ በመልእክቱ አስቀምጦልናል ።

እግዚአብሔር አምላክ በመስቀሉ ባርኮ ቀድሶ ለክብር ያብቃን!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ።አሜን!!!

ጥያቄ እና አስተያየት ለማስቀመጥ
☞ @Benyaa_s
ወይም
☞ @Mulexa

ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመድዎ በዚህ 👇ሊንክ ያስተዋውቁልን !
❖❖ ሐመረ ኖኅ ❖❖
❖💚═ @ORTHOTEK ═💚❖
❖💛═ @ORTHOTEK ═💛❖
❖❤️═ @ORTHOTEK ═❤️❖
መስከረም ፳፻፲፬ ዓመተ ምሕረት
ሐመረ ኖህ ©

Читать полностью…

የኔታ

የተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን መቼ ዐውቀዋለሁ? ብዬ ስለው፤ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አሉልህ ብሎ ይለኛል። ወደ ምሥራቅ ስሄድ፥ የደብረ አሚን ተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ቤተ ክርስቲያን ዐየሁ። ከቤተ ክርስቲያኑ ደረጃ ላይ ሦስት መነኰሳት አገኛለሁ። ሁለቱ ይይዙኝና አንደኛው እንደ ቱቦ ባለ ነገር ሲያጠምቀኝ ዐየሁ።
አረ ለቀቅሁኝ ለቀቅሁኝ እያልሁ የምጮኽ ይመስለኛል። በሕልሜ ስጮኽ ድምፄ ተሰምቷቸው ሴትዮይቱ ዳጃፉን ቆፍቁፈው (ቆርቁረው)፥ ምን ሁነህ ትለፈልፋለህ? አሉኝ። ለፈለፍሁ? አልዃቸው። አዎ አሉኝ። ኧረ ሕልም ታይቶኝ ነው አልኋቸው።
ወዲያውም ተክለሃይማኖት ከዚህ ሀገር አለ ወይ? አልዃቸው። አዎን አሉኝ። ወዴት ናቸው? ብዬ ብላቸው፥ ወደ ጸሐይ መውጫ ናቸው ያሉት ቅርብ ናቸው ብለው አሉኝ። ጠበል
አላቸው ወይ ብዬ ብላቸው አዎን አለ፤ ማንም የክፍለ ሀገር ሕዝብ እየመጣ የሚድንባቸው ናቸው። በጋዜጣም ተጽፏል አሉኝ። እንግዲያስ ማለዳ እንዲያሳዩኝ አልዃቸው።

ማልዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውኝ ሲመጡ፥ ከቅጽረ ጊቢው ልገባ ስል፤ ከቤተ ክርስቲያኑ (ፊቴ) . . . ፊት ለፊት ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ዐየሁ። መሄድ አቅቶኝ ተጎንብሼ ከትከሻዬ ላይ ትልቅ ሸክም የተሸከምኩ የመሰለኝ ሰው፤ ቀስተ ደመናውን እንዳየሁ፥ ሸክሙ ወርዶ ከጀርባዬ ሲወድቅ ተሰማኝ። ምን ዕቃ ጣልሁ? ብዬ ወደ ኋላዬ ዘወር ብል፥ ባዶ ሆነ። ከዚያ በኋላ ትከሻዬን ስለ ለቀቀኝ ቀና አልሁ። ቤተ ክርስቲያ ሄጄ ተሳልሜ በመስቀል አማተብሁ።
በስመ አብ ብዬ ለመጸለይ በቃሁ። የዕለት ውዳሴ ማርያም መጽሐፈ ጎልጎታ ደገምሁ። ከዚህ በኋላ ወደ ጠበሉ ገባሁ። ባዩህና አሰፋ ከየት እንደ መጣሁ ጠየቁኝ። ከጎንደር አልኋቸው። አስታማሚ የለኝም ብዬ ብነግራቸው፥ በነጻ ትጠመቃለህ ማደሪያ ፈልግ ተባልሁ። እሺ ብዬ ተጠመቅሁ። ምንም ሳያስጮኸኝ አንደበቴም ሕሊናዬም ተመለሰልኝ።

ከሴትዮይቱ ቤት እያደርሁ ሰባት ቀን በተከታታይ ተጠመቅሁ። ሴትዮይቱም
እንዳልከብዳቸው ራሴን ስለቻልሁ ማደሪያ ቤት ስጡኝ ብዬ እነባዩህን (እንባዬን)
ለመንኋቸው። ለሰባት ቀን ብቻ ከአዳሹ ግባ አሉኝና ገባሁ።
ሰባት ቀን ተጠመቅሁ። እነሱም ውጣም አላሉኝ። ጠበሉን ስለወደድሁት እንደ ሱባኤ አድርጌ ጸሎት እያደረግሁ ተጠመቅሁ። ጤናዬን ካገኘሁ አገሬ አልሄድም ብዬ እስከ አሁን አለሁ። ከሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ጀምሮ፥ እስከ ዛሬ የካቲን ፫ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. ድረስ እዚሁ ጠበል ቤት እየተጠመቅሁ፤ በቤተ ክርስቲያንም እያገለገልሁ አለሁ። ልብሴም ጉርሴም አባቴ ተክሃይማኖት ሁነውኝ እስከ አሁን አለሁ።

ምንጭ :- ምክሖን ለደናግል Mkhon Ledenagil

Читать полностью…

የኔታ

ልደት እግዝእትነ ማርያም ከአበው አንደበት በጥቂቱ

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ

✍ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ
ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ
ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ
እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ
ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ”

(ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) ፡፡

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ

✍ “ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ
ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ
ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ
እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ
ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ”

(ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር)፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን በመኃልይ

✍“ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት” (ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ) (መኃ.፬፥፲)፡፡

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ

“ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ
በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ
ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ
ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ”

(ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል)፡፡

✍ “ተፈሥሐት ምድር ወሰማይ አንፈርዐጸ
በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውጽኡ ሠርጸ
ተአምረ ሕይወት ማርያም ዘአልብኪ ቢጸ
እስከ ፈርሀ መልአከ ሞት ወሰይጣን ደንገጸ
ዜና ልደትኪ ነጐድጓድ እስከ (ውስተ) ሲኦል ደምፀ”
(በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሽ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤ ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤ መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ) ፡፡

አባ ሕርያቆስ በ ቅዳሴ ማርያም

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነዝ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እም ሐና ወኢያቄም ተወለደች"
(ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነሽ አይደለሽም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ)

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን

ታቦት

✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
👉 @YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ውድ የ የኔታ ተከታታዮች

ለረጅም ጊዜ በጉጉት እየጠበቃችሁት ተቋርጦ የቤተክርስቲያናችን ዕንቁ ሀብት የሆነው አብነት ትምህርታችን ተጀመረ ሁላችንም በመማር

ኑ አብነቱን በአብነት እናስቀጥለው!!!

Читать полностью…

የኔታ

ስለ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉ ተአማኚነት ያላቸው ይትባህሎች

፩. #አስታራቂነት ፡-ነብርና አንበሳ አይስማሙም፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ሥር ግን ነብርና አንበሳ ተስማምተው ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ለመታረቅ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለማስታረቅ የሚሄዱ ሽማግሌዎች ‹አቦን ሆነን መጥተናል› ይላሉ፡፡

፪. #የአቦ_ጠበል ፡- አንድ ሰው እየተመገበ ቢያንቀው ‹የአቦ ጠበል› እያልክ ውኃን ሦስት ጊዜ ጠጣው ይባላል፡፡
፫. #የአቦ_ብቅል ፡- አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታ ስሙ ቢጠራና በአካባቢው የሚያውቀውን ሰው ቢያጣ የጠራው ሰይጣን ሊሆን ስለሚችል ‹‹የአቦን ብቅል እፈጫለሁ› በል ይባላል፡፡

፬. #የአቦ_መገበሪያ ፡- አንድ ሰው አንድን ነገር አጥፍቶ ተሠውሮ እንደማይቀመጥ ለመግለጥ ‹‹የአቦን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይውላል›› ይባላል፡፡

፭. #አቦ_ሰጥ ፡- አንድ ሰው የማያውቀውን ነገር በግምት ሲናገር ‹አቦ ሰጥ› ይባላል፡፡

፮. # በአቦ_ይዤሃለሁ ፡- አራዊት የቤት እንስሳትን እንዳይበሉባቸው ገበሬዎች ‹በአቦ ይዤሃለሁ› ብለው ይገዝቷቸዋል፡፡

፯. #የአቦ_መንገድ ፡- በሰሜን ሸዋ መራኛ አካባቢ ባሉ ሕዝቦች ዘንድ ‹የአቦ መንገድ› የሚባል ብሂል አለ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሚዳ ከሚገኘው የአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ጥቂት ጊዜ ቆይተዋል ይባላል፡፡ በኋላ ከዚያ ገዳም ሲወጡ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የት ሊሄዱ ነው›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹እርሱ ወደ መራኝ›› ብለው መለሱላቸው፡፡
ከተማው ‹‹መራኛ›. የተባለው በዚህ ምክንያት ነው ይባላል፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው መድረሻውን በውል ሳያውቀው መንገድ ሲጀምር መንገዱ ‹የአቦ መንገድ› ይባላል፡፡

፰. #የአቦ_ቁራ ፡- ሰይጣን በቁራ ተመስሎ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓይናቸውን ሊያወጣ ስለመጣ በጎ ነገር የያዘ መስሎ የሚመጣ ክፉ ሰው ‹የአቦ ቁራ› ይባላል፡፡

፱. #በአቦ_በሥላሴ ፡- በሕዝቡ ብሂል ውስጥ ከሥላሴ ጋር ተያይዘው ብዙ ጊዜ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ‹በአቦ በሥላሴ› ሲባል አጥብቆ መለመን ነው፡፡ በሕዝባዊ መዝሙሮችም ውስጥ ‹በአምስት አቦ ናቸው በሰባት ሥላሴ› የሚል ሐረግ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
❤ስለ አቡዬ  ሌሎች የሚያውቋቸው ይት ባህሎች ካሉ ይጨምሩበት!

#የጻድቁ እረድኤት አይለየን...አሜን!

#ምንጭ :- ከሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሁፍ የተቀነጨበ

Читать полностью…

የኔታ

ውድ የሐመረ ኖኅ ተከታታዮች እንኳን ለ ፳፻፲፬ ማኅሌተ ጽጌ ፍጻሜ አደረሳችሁ!!!

ሥርዓተ ማኅሌት ዘተፈጸመ ጽጌ
"፮ ኛሳምንት" ኅዳር ፭
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተነግሥ)
🌹🌹🌹
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ፡ሃሌ ሉያ ሃሌሉያወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ሃሌሉያ ሃሌሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፡ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ሃሌሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡በአሐቲ ቃል።


🌸ነግሥ🌸

ሰላም፡ ለኵልያቲክሙ፡ እለ፡ ዕሩያን፡ በአካል፤ ዓለመክሙ፡ ሥላሴ፡ አመ፡ ሐወፀ፣ ለሣህል፤
እምኔክሙ፡ አሐዱ፡ እግዚአብሔር፡ ቃል፤ ተፈጸመ፡ ተስፋ፡ አበው፡ በማርያም፡ ድንግል፤ ወበቀራንዮ፡ ተተክለ፡ መድኃኒት፡ መስቀል ፡፡

🌸ዚቅ🌸

ዛቲ: ይእቲ: እኅተ: ትጉኃን: መላእክት፤ ወለተ፡ ኄራን፡ ነቢያት፤
እሞሙ፡ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ፡ ለጻድቃን፡ ወሰማዕት።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ኢየኃፍር፡ ቀዊመ፡ ቅድመ፡ ስዕልኪ፡ ወርኃ፡ ጽጌረዳ፡ አመ፡ ኃልቀ፤
ዘኢየኃልቅ፡ ስብሐተኪ፡ እንዘ፡ እሴብሐኪ፡ ጥቀ፤ ተአምርኪ፡ ማርያም፡ ከመ፡ አጠየቀ፤ ጸውዖ፡ ስምኪ፡ ያነሥእ፡ ዘወድቀ፤
ኃጥአኒ፡ ይሬሲ፡ ጻድቀ፡፡

🌸ወረብ🌸

ኢየኃፍር፡ ቀዊመ፡ ቅድመ፡ ስዕልኪ፡ ወርኃ፡ ጽጌረዳ፡ አመ፡ ኃልቀ፤
ዘኢየኃልቅ፡ ስብሐተ፡ ስብሐተ፡ እንዘ፡ እሴብሐኪ።

🌸ዚቅ🌸

እለ፡ትነብሩ፡ ተንሥኡ፤
ወእለ፡ ታረምሙ፡ አውሥኡ፤
ማርያምሃ፡ በቃለ፡ ስብሐት፡ጸውዑ፤ ቁሙ፡ ወአጽምዑ፡ ተአምረ፡ድንግል፡ ከመ፡ ትስምዑ፤ ጸልዩ፡ ቅድመ ስዕላ፡ ለቅድስት፡ ድንግል፤ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

እንዘ፡ ተሐቅፊዮ፡ ለሕጻንኪ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ፡ ወቀይሕ፤ አመ፡ ቤተ፡ መቅደስ፡ ቦእኪ፡ በዕለተ፡ ተአምር፡ ወንጽሕ፤ ንዒ፡ ርግብየ፡ ትናዝዝኒ፡ እምላህ፤ ወንዒ፡ ሠናይትየ፡ ምስለ፡ ገብርኤል፡ ፍሡሕ፤ ወሚካኤል፡ ከማኪ፡ ርኅሩኅ፡፡

🌸ወረብ 🌸

እንዘ፡ ተሐቅፊዮ፡ ለሕጻንኪ፡ ጽጌ፡ ፀዓዳ፡ ወቀይሕ፤
ንዒ፡ ርግብየ፡ ምስለ፡ ገብርኤል፡ ወንዒ፡ ሠናይትየ፡ ምስለ፡ ሚካኤል።

🌸ዚቅ🌸

ይዌድስዋ፡ ትጉኃን ይቄድስዋ፡ ቅዱሳን፤ ሰሎሞን፡ ይቤላ፡ ርግብየ፡ ሠናይት፤ ጳውሎስኒ፡ ይቤላ፡ ደብተራ፡ ፍጽምት፤ ዳዊትኒ፡ ይቤላ፡ ስምዒ፡ ወለትየ፡ ወርእዪ ወአጽምዒ፡ ዕዝነኪ።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ሶበ፡ ዴገነኪ፡ አርዌ፡ በሊዓ፡ ሕጻንኪ፡ ዘኀለየ፤ በዘትሠርሪ፡ ገዳመ፡ ወታፈጥኒ፡ ጐይየ፤
አመ፡ ጸገይኪ፡ አክናፈ፡ ከመ፡ ዮሐኒ፡ ጸገየ፤ ብእሲተ፡ ሰማይ፡ ማርያም፡ ዘትለብሲ፡ ፀሐየ፤ ተአምረኪ፡ ጸሐፈ፡ ዮሐንስ፡ ዘርእየ፡፡

🌸ወረብ🌸

አመ፡ አመ፡ ጸገይኪ፡ አክናፈ፡ ከመ፡ ዮሐኒ፤
ተአምረኪ፡ ጸሐፈ፡ ዮሐንስ፡ ዘርእየ፡ ዘርእየ፡ ተእምረኪ፡፡

🌸ዚቅ🌸

በሊዓ፡ ሕጻናት፡ ሶበ፡ ኀለየ፡ ሄሮድስ፡ አርዌ፡ ሰማይ፤ ዘምስለ፡ ዮሴፍ፡ አረጋይ፤ ነገደት፡ ቍስቋመ፡ ናዛዚተ፡ ኃዘን፡ ወብካይ፤

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ጽሩይ ፡ እምዕንቈ ባሕርይ ፡ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ፡ ብኪ፡ ትእምርተ፡ ስሙ፡ ወተዝካረ፡ ሞቱ፤
አክሊለ፡ ጽጌ፡ ማርያም፡ ለጊዮርጊስ፡ ቀጸላ፡ መንግሥቱ፤
አንቲ፡ ኵሎ፡ ታሰግዲ፡ ሎቱ፤
ወለኪኒ፡ ይሰግድ፡ ውእቱ፤

🌸ወረብ🌸
ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ ጽሩይ፡ ክበበ፡ ጌራ ወርቅ፡ዘየኃቱ፡ እም፡ ዕንቈ፡ ባሕርይ፤
አክሊለ፡ ጽጌ፡ ማርያም፡ ቀጸላ፡ መንግሥቱ፡ ለጊዮርጊስ፡ መንግሥቱ፡ ለመፍቀሬ፡ አምላክ ፡፡

🌸ዚቅ🌸

አክሊሎሙ፡ ለሰማዕት፤
ተስፋ፡ መነኮሳት፤
ሠያሚሆሙ፡ ለካህናት፤
ነያ፡ ጽዮን፡ መድኃኒት።

🌸ማኅሌተ ጽጌ🌸

ኅብረ፡ ሐመልሚል፡ ቀይሕ፡ ወፀዓድዒድ፤አርአያ፡ ኮሰኮስ፡ ዘብሩር፤ ተአምርኪ፡ ንጹሕ፡ በአምሳለ፡ ወርቅ፡ ግቡር፤
ተፈጸመ፡ ናሁ፡ ማኅሌተ፡ ጽጌ፡ ሥሙር፤ አስምኪ፡ ቦቱ፡ ንግሥተ፡ ሰማያት፡ ወምድር፤ ከመ፡ በሕጽንኪ፡ ያሰምክ፡ ፍቁር ።

🌸ወረብ 🌸

ናሁ፡ ተፈጸመ፡ ተፈጸመ፡ ናሁ፡ ማኅሌተ፡ ሥሙር፡ ተፈጸመ፡ ናሁ፤
አስምኪ፡ ቦቱ፡ አስምኪ፡ ቦቱ፡ ንግሥተ፡ ሰማያት፡፡

🌸ዚቅ🌸

ሃሌ ሃሌ፡ ሉያ፡ ሃሌ፡ ሉያ፤
ጥቀ፡ አዳም፡ መላትሕኪ፡ ከመ፡ ማዕነቅ፤ ይግበሩ፡ ለኪ፡ ኮሰኮሰ፡ ወርቅ፡፡

🌸 ሰቆቃወ ድንግል🌸

ተመየጢ፡ እግዝእትየ፡ ማርያም፡ ሀገረኪ፡ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ፡ በግብጽ፡ ከመ፡ ዘአልብኪ፡ ቤተ፤
በላዕሌኪ፡ አልቦ፡ እንተ፡ ያመጽእ፡ ሁከተ፤ለወልድኪ፡ ዘየኃሥሦ፡ ይእዜሰ፡ ሞተ፤ በከመ፡ ነገሮ፡ መልአክ፡ ለዮሴፍ፡ ብሥራተ።

🌸ወረብ🌸

ተመየጢ፡ ተመየጢ፡ እግዝእትየ፡ ማርያም፡ ሀገረኪ፤
ወኢትጎንድዪ፡ በግብፅ፡ በግብፅ፡ ከመ፡ ዘአልብኪ፡ ቤተ፡፡

🌸ዚቅ🌸

ሃሌ፡ ሉያ፤ ተመየጢ፡ ተመየጢ፡ ሰላመ፡ ሰጣዊት፤ወንርዓይ፡ ብኪ፡ ሰላመ፡ ምንተኑ፡ ትኔጽሩ፡ በእንተ፡ ሰላመ፡ሰጣዊት፤እንተ፡ ትሔውፅ፡ እምርኁቅ፡ ከመ፡ መድበለ፡ማኅበር፤ሑረታቲሃ፡ ዘበስን፡ ለወለተ፡አሚናዳብ።

🌸መዝሙር 🌸

ሃሌ (በ፮) ክርስቶስ፡ ሠርዓ፡ ሰንበተ፡ ክርስቶስ፡ ሰንበተ፡ ወጸገወነ፡ ዕረፍተ፡ ከመ፡ ንትፈሣሕ፡ ኅቡረ፤አዕጻዳተ፡ ወይን፡ ጸገዩ፡ ቀንሞስ፡ ፈረዩ፡ ሰሎሞን፡ ጥቀ፡ ኢለብሰ፡ ከመ፡ አሐዱ፡ እምእሉ።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
ሐመረ ኖኅ !!!

Читать полностью…

የኔታ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የማኅሌተ ጽጌ ፫ ሳምንት ሥርአተ ማኅሌት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ስምዓኒእግዚኦጸሎትየ፤ሃሌሉያ ሃሌሉያ ወይብጻሕቅድሜከገዓርየ፤
ሃሌሉያሃሌሉያወኢትሚጥ ገጽከእምኔየ፡፡
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌሉያ(፪)
እመ ዕለተአጽውአከፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌሉያሃሌሉያለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡
ሃሌሉያዘውእቱብሂል፡፡ንወድሶለዘሀሎእግዚአብሔርልዑል፡፡
ስቡሕወውዱስዘሣረረኵሉ ዓለመ በአሐቲቃል፡፡

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
መልክአሥላሴ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤
ለወልድሰላም ወለመንፈስቅዱስ ሰላም፤ ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም ፤
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያትሰላም፤
ለሰማዕታትሰላም ወለጻድቃንሰላም።

ዚቅ
ሃሌሉያሃሌሉያሃሌሉያንፌኑስብሐተ፣
ለዘአክበረነቢያተ፤ንፌኑስብሐተወለዘኀረየ ሐዋርያተ፣ ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአፍቀረ ካህናት፤ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአጥብዐ ሰማዕታተ፤ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአጽንዐ መነኮሳተ ፤ ንፌኑ ስብሐተ እለዔሉ አድባራተ፤ ንፌኑ ስብሐተ ንበሎ ኩልነ ፤
አቢተነ አንተ

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ማኅሌተጽጌ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤
ለዕረፍትዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ)ኪዳን፤
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተብርሃን፤
ብኪይትፌስሑ ዘገነተጽጌጻድቃን፤
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

ወረብ

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍትዘኮንኪ ትእምርተኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ

ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ማኅሌተጽጌ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
እንዘተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ ወንዒ
ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ

ዕፀጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን፤ ይብልዋ ቅድስተቅዱሳን፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ወይቤላ መልአክ
ተፈሥሒ ፍሥሕት፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ማኅሌተጽጌ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድውእቱ፡፡

ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
"አክሊለ"/፪/ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ

ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ
ንጹሐን ብርሃን ቅዱሳን።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ማኅሌተጽጌ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ለተአምርኪ ማርያም ኃጥእ ውእቱ ዘአስተቶ፤ከመ ስብሐቲሁ ኢይርአይ እስመ ጽጌኪ አዕተቶ፤
ለተአምርኪሰ እንዘ ይነግር ረድኤቶ፤ ቦ ዘፈለሰ ኃዲጎ ብእሲቶ ፤ ወቦገዳመ ዘተግህሠ መኒኖ መንግሥቶ።

ወረብ

ቦ ዘፈለሰ "ኃዲጎ ብእሲቶ"/፪/ብእሲቶ ኃዲጎ/፪/
ወቦ ገዳመ ዘተግህሠ መኒኖ" መንግሥቶ"/፪/
መናኔ መንግሥት/፪/

ዚቅ

ትዕግስትኪ ፈድፋደ እምትዕግሥተ ኢዮብጻድቅ፤
ወእማርቆስ ዘቶርማቅ ፤ወገብረክርስቶስ መርዓዊ
ተወካፌ ሕማም መጽዕቅ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ሰቆቃወድንግል
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፣ ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ ተአወዩ
በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ዚቅ

አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤
አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤ ወለመላትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ
ሐፍ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
መዝሙር
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑመሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ ወሰማይ ወምድረ ዘእንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪዘ ከማከ ፥ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ

ወመኑመሐሪዘከማከ/፪/
ወኩሉይሴፎኪያከ/፬/

ዓራራይ

በኩሉ ጊዜ ወበኩሉ ሰአት በኩሉ ሌሊትወበኩሉ መዓልት እግዊ አለ ሰንበት አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥት ከምድረ ጽጌ አሠርጎከ።

ዕዝል

ልዑል ውእቱ እምልዑላን መሐሪ ውእቱ ዘየአርፎ ለዓለም ጻድቅ ውእቱ ወይባርክ ጻድቃነ ጠቢብ
ውእቱ ይመይጥ ስሑታነ ሠርዓ ሠንበተ ለዕረፍት አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
👉 @Benyaa_s
👉 @Mulexa
ሐመረ ኖኅ!!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት

ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ

ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ሰዋስው
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ደብተራ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ዘመድ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውዳሴ ማርያም ዘቀዳሚት
ናስተበጽዕ
ውድ የ የኔታ ተከታታዮች
ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ተከታታዮች ይጠቀሙ
👉 @YENETAY
👉 @YEAWEDIMERITE
👉 @Mulexa
የ ዐውደ ምሕረት እህት ቻናል
የኔታ
አብነቱን በ አብነት እናስቀጥለው !!!

Читать полностью…

የኔታ

ውድ የ የኔታ ተከታታዮች እንኳን ደስ አላችሁ!!!!

ለረጅም ጊዜ በጉጉት እየጠበቃችሁት ተቋርጦ የቤተክርስቲያናችን ዕንቁ ሀብት የሆነው አብነት ትምህርታችን ተጀመረ

ኑ አብነቱን በአብነት እናስቀጥለው

Читать полностью…

የኔታ

ውድ የሐመር ኖኅ ተከታታዮች
እንኳን ለመጀመሪያው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ አደረሳችሁ!!!

የመጀመሪያው ሳምንት የጽጌ ማኅሌት
👇👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

የኔታ

✝መስቀል ክፍል ፯ (የመጨረሻ ክፍል)✝

✝በመስቀል ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች ክፍል ፫✝

Читать полностью…

የኔታ

#ዜና ዕረፍት !
____~_____
አዲስ አበባ በሚገኝው በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እስከ ሥጋዊ ሕይውታቸው ፍጻሜ ድረስ በጠበል ቤት ሕሙማንን በማጥመቅ ፈውሰ ጸጋ የነበራቸው እና በቅንነት ከ35 ዓመት በላይ ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ ሰኞ ግንቦት 16 ቀን በድንገት ታመው ሆስፒታል ከሄዱ በኃላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ለሊት ለረቡዕ አጥቢያ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።

እግዚአብሔር አምላክ የአባታችንን ነፍስ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እቅፍ ያኑርልን ከዚህ ቀጥለን አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ በአንድ ወቅት እንዴትና ለምን ወደ ደብራችን ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እንደመጡ የሰጡትን ምስክርነት እናስነብባችኋለን
#መምሬ_ብሩ_ታከለ ( #ገ/ሥላሴ )

ጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቡ አውራጃ አዲስ ዘመን ወረዳ መኖሪያ ቦታ ጎድንዲት ኪዳነምሕረት፥ ሥራ ቅስና ጎድንዲት ኪዳነምሕረት ማገልገል (አገልጋይ)። በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. በወርኃ መስከረም ወር በገባ በ፳ ቀን ታመምሁ። የሕመሙ ዓይነት እንደ ልክፍት አድርጎ ይጥለኝ ነበር።
ሲጥለኝ አይታወቀኝም ነገር ግን ሊጥለኝ ሲል በገሀድ ቁመቱ እንደ ምሰሶ የረዘመ ጥቁር ሰው ይታየኛል። ያ ሰው ይመጣና ከትከሻዬ ላይ ይሰቀላል (ይቀመጣል)። በዚህ ጊዜ ኑህያዬን (አእምሮዬን ) አላውቀውም። ሲጥለኝ በየቀኑ ሆኖ በሦስት ሰዓት፣ በመዓልትና በስድስት ሰዓት፣ በዘጠኝ ሰዓት ቀድሼ በመጣሁበት ሰዓት ይጥለኝ ነበር። ሌሊት በሰው ተመስሎ ከበላዬ ተጭኖ ስለሚያድር፥ ራሴን አላውቅም ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፥ ከአመመኝ ጊዜ ጀምሮ፥ ዳዊት መድገም የለም፣ ውዳሴ ማርያም ትቻለሁ፣ መቀደስ ማስቀደስ፣ ቃለ እግዚአብሔር መሳተፍ አልችልም ነበር። የደዌው መነሻ፥ በቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ እኔ በጸሐፊነት መምሬ በላይ ገላዬ በግምጃ ቤት አገልግሎት እንሠራ ነበር። ቤተ ክርስቲያቱ የሣር ስለ ነበረች፥ በቆርቆሮ አሠርተን፣ ቅጽር አስቀጽረን፣ መንበር አሠርተን ከወጪ ቀሪ ገንዘብ ነበር። ያን ቀሪ መቶ ሃምሳ ስድስ ብር መምሬ በላይ ገላዬ ስለ በላው፤ ካህናቱና ምእመናን ገባኤ አድርገው፥ ጸሐፊም ተቆጣጣሪም ስለ ነበርሁ፥ የሒሳብ መዝገቡን አቅርብ ተብዬ አቀረብሁ። መቶ ሃምሳ ስድስ ብር ጉድለት ተገኘ። አገሬው . . . . (ጉባኤው) ክፈል ቢለው እንቢ ስላለ፥ በዳኛ ተከሶ ከፈለ። በኋላም አገሬው እርሱን ሽረናል፤ በግምጃ ቤትነት መምሬ ብሩ ይሠራልናል ብለው
በሌለሁበት መረጡኝ። ጸሐፊነቱና ተቆጣጣሪነቱን ለቄስ አጠና ከበደ ሰጡት። በግድ ተረከብ ብለው የግጃ ቤትትነት ሥራውን ተረከብሁ።

#ከዚያ ይዤ . . . ስሠራ፥ መምሬ በላይ በዚሁ ምክያት ቂም ይዞ፥ ከቤተ ክርስቲያን ስወጣ መዝጊያ እየዘጋሁ ሳለ፤ በጨለማ ተከልሎ በዱላ ማዥራቴን መታኝ። ከቅድስቱ የመቆሚያ ሰሌን ላይ ወደቅሁ። ከዚያ በኋላ የሆንሁትን አላውቅምና አብረውኝ የቀደሱት ደጀ ሰላም ገብተው የነበሩት ቀረብንሳ ብለው ዲያቆን ጠጋ ፈረድን እንዲፈልገኝ ላኩ። ቢያየኝ ከዚያ ወድቄ ራሴን ስቼ አገኘኝ። እሪ ብሎ ያሉት ሁሉ ተሰብሰው መጡ።
ተጯጩኸው አገሬው ሰምቶ ቄስ በላይን ያዙት። ቢጠየቅ አዎን መትቼዋለሁ ብሎ ለገበሬ ማኅበሩ ሊቀ መንበር ገለጠ። እኔን በቃሬዛ ተሸክመው፥ ሕይወቴን (ራሴን) ሳላውቅ፤ የመታኝንም ቄስ በላይን ይዘው፥አዲስ ዘመን ከሊቡ አውራጃ አስተዳደር አቀረቡን። ተጠይቆ ያንኑ ለገበሬ ማኅበር
ሊቀመንበር የሰጠውን ቃል ሰጠ። እርሱ ወደ እሥር ቤት ተላላፈ። እኔም ወደ ሐኪም ቤት ተወሰድሁ። ወር ያህል በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ስረዳ ቆይቼ አልሻል ስላለኝ፤ በጎንደር ክፍለ ሀገር ካለው ቼቼላ ሆስፒታል ገባሁ።

#ሁለት ሳምንት ሆስፒታል ተኛሁ። የጭን መርፌ፣ የትከሻ መርፌና የሚዋጥ ኪኒን ተደረገልኝ (ተሰጠኝ)። አልፎ አልፎ ነብሴን (ራሴን) ባውቅም የሚጥለኝ ደዌ ሲመጣብኝ ግን ሊሻለኝ አልቻለም። ከዚህ በኋላ ጠበል ይሻልሀል ብለው ሊቦ ጎዮርጊስ ተወሰድሁ። እዚያ ተስፋ ሳላገኝ ቀረሁ። ጎንድ ተክለሃይማኖት ጠበል ሄድሁ፥ እዚያም ተስፋ አላገኘሁም። ዙሬ ተመልሼ ደብረ ታቦር አውራጃ ሕክምና ይሻላል ብለው ከደብረ ታቦር ሆስፒታል ወሰዱኝ።
ምርመራ ተደርጎልኝ አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ተወስዶ ካልዳነ ከዚህ ልንረዳው አንችልም ተብየ ተሰናበትሁ። ከዚያ ተመልሼ ቤቴ ገባሁ። በገባሁ በአምስት ቀኔ ቤተ ዘመዶቼ ተስፋ ቆርጠው አይድንም ብለው ተዉኝ። ከዚያ በኋላ ከዘመድም ከባዕድም ብዬ ለማምኜ፥ ሞቴን ሞት ያድርገው ብዬ መቶ ሠላሳ ብር ይዤ አዲስ ዘመን መኪና ተሳፍሬ ባሕር ዳር ደስኩ። ከመኪና ወርጄ ለምሳ ስንዘጋጅ ሕመሙ ተነሥቶብኝ ጣለኝ። ዘመድ ተመስሎ አንድ ሰው ደገፈኝ። ትንሽ ነብሴን ሳውቀው፥ ያው ደግፎ የያዘኝ ሰው የት ልትሔድ ነው? ብሎ ጠየቀኝ። አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ነው የምሄደው አልሁት። እኔም አብሬህ እሄዳለሁ፥ ዘመዶች ከሆስፒታሉ አሉኝ፤ አስታምሜ እመልስሃለሁ አለኝ። እውነት መስሎኝ ዘመድ አርድጌው ደግፍና ከመኪናው ስቀለኝ (አሳፍረኝ) አልሁት። ገድፎ አሳፍሮኝ ቡሬ በዓሥር ሰዓት ደረስን። አውታንቲው መኝታ ፈልጉና አልቤርጎ እደሩ ብሎን ወረድን። ከወረድን በኋላ ያሰው ዘመድ አለኝ የማሳድርህ ቦታ አለ ብሎ ወደ በረሐ ይዞኝ ሄደ።

#ከዚያ በረሐ እንደ ደረስን፥ ከዚህ ነው የምተኛው አለኝ። የዚያን ጊዜ ሊዘርፈኝ እንዳሰበ ዐወቅሁና ስደነግጥ አእምሮዬን ስቼ ወደቅሁ። በነጻ እንድታከም ከገበሬ ማኅበር ያወጣሁትን
ደብዳቤና አንድ መቶ ብር በአንድ ላይ አሥሬ የያዝሁትን ወሰደብኝ። ሕመሙ ጋብ ብሎ አእምሮዬ እንደ ተመለሰ ሳውቀው፥ ሰውየውም ጠፋ ኪሴም ባዶ ሆነ። ከዚያው በጨለማ ውስጥ ሳለቅስ አደርሁ። ምነው ብትገድለኝ ከምሰቃይ ብዬ ወደ ፈጣሪዬ አለቀስሁ። የጎጃም ጅብ አጠገቤ እየመጣ ይጮኻል፥ ግን ሳይበላኝ አደርሁ። ሲነጋ ወደ ቡሬ ከተማ ገባሁ። የተሳፈርሁበት መኪና የት እንዳለ ብጠይቅ ሄዷል ተባልሁ። ከዚያ ወዲያ ሳለቅስ አንድ ብርም ሁለት ብርም ብሎ ሕዝቡ በአዘኔታ ሰጠኝ። ዓሥራ ሦስት ብር አገኘሁ። ያንኑ ዕለት መኪና ተሳፍሬ አዲስ አበባ ከቀኑ ዓሥር ሰዓት ሲሆን ገባሁ።
#አውቶቢስ ተራ ከመኪና እንደወረድሁ ኑህዬን . . . (አእምሮዬን) አላወቅሁም። አንድ አዛውንት ሽማግሌ ደግፈውኝ ቆይተው ቆይተው፥ አእምሮዬ ሲመልስልኝ ከየት ነው የመጣኸው? ብለው ጠየቁኝ። ከጎንደር ነው አልኋቸው። ዘመድ አለህ ብለው ቢጠይቁኝ፥ ዘመድ እንኳ የለኝም። ነገር ግን ከሀገሬ ሳለሁ የማውቃቸው አንድ ቄስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አሉና የአማኤልን ቤተ ክርስቲያ ያሳዩኝ አልኋቸው። ሰውየውም ወስደው አሳዩኝ። የማውቀውንም ቄስ አገኘሁት። መምሬ ጸዳሉ ይልማ ይባላል። ቄሱም የመጣሁበትን ምክያት ጠየቀኝ። ስለታመምሁ ለሕክምና ነው የመጣሁት ማደሪያ ፈልግልኝ አልሁት። የንስሐ ልጁ ስዕለ ማርያም የምትባል ዘንድ ወስዶ፥ እባክዎን ይህንን ሰው ያሳድሩልኝ፤ ነገ*አማኑኤል ሆስፒታል እወስደዋለሁ አለ። በዚህ ሁኔታ ሴትየዋ ቤት ሰጥተውኝ ከዚያ አደርሁ።

#ሌሊት_ተኝቼ በሕልሜ፥ ሀገር ቤት የማውቀው መኰንን የሚባል ቀይ ሰው፤ የቤተ ክርስቲያን መቋሚያ ይዞ፥ አንተ ተክለሃይማኖት ተጠመቅ እንጂ፥ ይህ ሐኪም ምንም እይሠራልህም ብሎ ይለኛል።

Читать полностью…

የኔታ

 ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel