yetumim_lijoch | Unsorted

Telegram-канал yetumim_lijoch - 🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

-

🎛🎚🎹🎙Anchor Studio🎙🎹🎚🎛 🎙 Track 🎙 Cover 🎙 Album 🎙 Promotion 📽 Video clip 🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹 🎹📌📍 Shashemene 📌📍🎹 🎹 📞 +2519 70 60 95 82 🎹 🎹 📞 +2519 25 31 51 64 🎹 🎹🎼🎧🎤🎸🎻🎷🎺🥁🎧🎼🎹 🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹

Subscribe to a channel

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

. ተወደናል
Saris Area Christian
Student | New Song
⏰7:00Min 📥32.2MB
🔰ወንጌል ክርስቶስ ነው🔰
Share 📲 Share 📲 Share
▷ @yetumim_lijoch ◁
▷ @yetumim_lijoch ◁
△Join Us△

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

😊ለፈገግታ😊
አንዲት ክርስትና በደንብ ያልገባት ሴት ነበረች የኑሮ ውድነት በጣም አሰቃይቷት በቃ መረረኝ ልጆቼን እንዴት ላኑር እኔስ በምን ልኑር ኢየሱስ ኢየሱስ እያልኩ ከሰኞ እስከ ሰኞ ቸርች እየሄድኩ በረሀብ እንለቅ ጠንቋይ ጋር ሄጄ እልባት ማግኘት አለብኝ ትልና ወደ ጠንቋዩ ቤት ትሄዳለች ምንድነው ችግርሽ ብሎ ከጠየቃት በኋላ የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍልሽ ነው ምትፈልጊው? አዎ
ሀብታም መሆንስ? ኸረ በደንብ ዋናው እሱ አይደለ በይ ነገ ግንባረ ቦቃ አውራ በግ ይዘሽ ትመጪአለሽ ያ ካልሆነ ልጆችሽ ይሞታሉ የሚል ሰቅጣጭ ነገር ተናገራት የኔ ጌታ እኔ በግ የምገዛበት አቅም ቢኖረኝ ምን አንተ ጋ አስመጣኝ
ልጆቼንስ ከረሀብ ለማዳን መስሎኝ
እንኳን ለሞት እንቅፋት እንዳይነካቸው የሚጠብቅልኝ ኢየሱስ ይሻለኛል ሆሆሆሆሆሆ እያለች ወደ ቤቷ ገብታ ንሰሀ ገባች እላቹአለው የኛ ጌታ ጥቅምም ከኛ አይፈልግም ምህረቱም ብዙ ነው እንዲሁ ሳንከፍል ንፁህ አየር ያስተነፍሰናል በገንዘባችን መጠን አልወደደንም ክብር ለታረደው በግ ።
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንላችሁ🙏
✍AksanAdane

━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

. የተሰጠኝ ስም
ኢየሩሳሌም || New Song
⏰7:29Min 📥46.2MB
🔰ወንጌል ክርስቶስ ነው🔰
Share 📲 Share 📲 Share
▷ @yetumim_lijoch ◁
▷ @yetumim_lijoch ◁
△Join Us△

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

ከእርሶ ጋር በዚህ ጊዜ እናሳልፋለን
፦
➠ ተከታታይ ኣዲስ ትምህርት
➠ተከታታይ ልብ አንጠልጣይ መንፈሳዊ ልብወለድ
➠ የተለያዩ አዳዲስ ዝማሬዎችን
➠ አዝናኝ ቁም አዘል ታሪኮች
➠ እንዲሁም ሌሎች ፕሮግራምችን አሰናድተን እንቀርባለን አብሮነታችሁ አይለየን።

አድሚን ለማናገር ➠ @wunuye95 ላይ ይጠቀሙ

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

የዘማሪ ቢኒያም መኮንን ሙሉ አልበም
👇👇👇👇👇

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

ዘማሪ ሸዋዬ ዳምጤ
🕒7:42min 💾-1.8MB
🎷መዝሙር ግብዣ🎷
💁‍♂💁‍♂ ተጋበዙልን

@Christ_progeny_tube
@Christ_progeny_tube

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

📜📜ተከታታይ ትምህርት📜📜


#አምስቱ #የፍርድ #አይነቶች❤️

#ክፍል #አምስት #፭

📌2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

5) #በኢየሱስ #ባላመኑ #ሙታን #ላይ #የሚፈረድ #ነው።

👉ፍርዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላመኑ ላይ ነው
👉የፍርዱ አይነት ሁለተኛው ሞት ነው
👉ጊዜው የሺው አመት መንግስት ፍፃሜ ላይ
👉ቦታው ታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት ነው

(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 20)
----------
11፤ 👉ታላቅና ነጭ ዙፋንን👈 በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም።

12፤ 👉ሙታንንም👈 ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።

13፤ ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።

14፤ ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር 👉ሁለተኛው ሞት👈 ነው።

15፤ በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም 👉በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።👈

♦️አማኝ ለፍርድ በነጩ ዙፋን ፊት አይቀረብም።

✍️ " እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 5:24 , 6:37- 40, 10:27-31

✍️ ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር
ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች ሁለቱ 4ኛው እና 5ኛው የፍርድ አይነቶች በክርስቶስ አምነው የዳኑትን እውነተኛ አማኞች አይመለከታቸውም

📌 በ 4ኛው እና በ5ኛው ፍርዶች መካከል ያለወን ልዩነት ልናስተውል ይገባል። ልዩነቶችም ይህን ይመስላሉ፦

👉4ኛው ፍርድ Vs 👉 5ኛው ፍርድ
ማቴ 25:31-46 ራዕ 20:11-15

1) ከሺ አመት መንግስት 1) ከሺ አመት መንግስት
በፊት በኃላ

2) በጎች እና ፍየሎች 2) ሙታን አንድ ወገን
የተባሉ ሁለት ወገኖች ብቻ ናቸው።
አሉ።

3) ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ጋር 3) ስለመምጣት የተጠቀሰ
በመምጣት የሚፈረድ ጥቅስ የለም።
ነው።

4) ፍርዱ የሚፈፀመው 4) ከፍርዱ በፊት ሰማይ እና
ምድር ላይ ነው። ምድር ከፊቱ ይሸሻሉ።

5)ስለ መጻሕፍት 5) መጽሐፉ እና መጽሐፍት
የተጠቀሰ ነገር ተከፈቱ ይላል።
የለም።

6) ትንሣኤ የለም 6) ትንሣኤ አለ ሙታንም ሁሉ
ይነሳሉ።

7) ከፍርድ የተረፉት ወደ 7) በሙታን ሁሉ ላይ
ሺው አመት መንግስት ይፈረዳል ሁሉም ወደ
በመግባት በምድር ላይ እሳት ባህር ይጣላሉ
ለሺ አመት መደበኛ ኑሮ ይህም ሁለተኛው ሞት
ይኖራሉ። ነው።


📌 ቅዱሳን ልብ ሊሉት የሚገባ፦

👉 በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ በብዛት የጻፈውን አማኝ ሽልማት የሚቀበልበትን የፍርድ ወንበር (Bema) እና በክርስቶስ ያላመኑ ሙታንን በሚመለከተው በነጩ ዙፋን ፍርድ መካከል በቅዱሳን መካከል ግራ መጋባት እና አለመለየት ይስተዋላል። መጽሐፍትን ስናጠና ግን ሁለቱም በጣም የተለያዩ ናቸው።

📌ስለዚህ የእግዚአብሄር ልጆች፦

➡️ከዘላለም ጥፋት በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በእምነት ብቻ እንደዳንን አውቀን
➡️የመዳናችን ግብ የሆነውን ሽልማት የሚያስገኘውን የእምነት ሩጫ በትዕግስት እየሮጥን
➡️ከማናቸውም መዳናችንን ከሚያጠራጥር የትምህርት ንፋስ ራሳችንን እየጠበቅን
➡️በዚህ እምነት እግዚአብሄር አባታችን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እያከበርን እንኑር ጥሪያችን ነው።

📌 2 ቆሮንቶስ 13:14
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

🍁ተፈፀመ።🍁


━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

📜📜ተከታታይ ትምህርት📜📜


❤️#አምስቱ #የፍርዶች #አይነቶች❤️

#ክፍል #አራት #፬

✍️ ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር
ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች ከዚህ በኃላ ያሉት ሁለቱ 4ኛው እና 5ኛው የፍርድ አይነቶች በክርስቶስ አምነው የዳኑትን እውነተኛ አማኞች አይመለከታቸውም

📌2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

4) #ባልተነጠቁ #በምድር #በሚኖሩ #ላይ ነው።

ምክንያት፦ የመንግስት ወንጌልን ባለማመን እና
እስራኤላውያንን የማጥፋት ሙከራ
ጊዜ፦ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በክብር ሲገለጥ
ማቴ 25:31-33, ዘካ 14:5
ቦታ፦ በኢዮሳፍጥ ሸለቆ ( አርማጌዶን)
ኢዮኤል 3:2,12...,ራዕ 16:16

ውጤት፦
♦️ የመንግስት ወንጌልን ያመኑ ወደ
ሺው አመት በረከት ይገባሉ ። ማቴ 25:31-32

♦️ የመንግስት ወንጌልን አናምንም
እስራኤላውያንን እናጠፍለን የሚሉት
ፍርድ= ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ ።
ራዕ 19:21

✍️ ይህ ፍርድ ከአማኞች ጋር ግንኙነት የሌለው እና አማኞች ከተነጠቁ ከ ሰባት(7) አመት በኃላ የሚፈፀም ፍርድ ነው።

✍️ ፍርዱ በዋናነት ባልተነጠቁ እና የመንግስት ወንጌል አናምንም እስራኤልንም እናጠፋለን በሚሉት አህዛብ (የአውሬው= የአውሮፓ ህብረት እና ጦር) ላይ የሚፈፀም ነው።

✍️ ይህ አራተኛው ፍርድ ከ አምስተኛው(5) የነጬ ዙፋን ፍርድ እንደሚለይ ልብ ልንል ይገባል።

📌 ማቴዎስ 25:31-33
31፤ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤
32፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥
33፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።

📌 መዝሙር 96፡13
ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

📌 ዘካርያስ 14:5 = ማቴ 25:31-33
የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፤ 👉አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።👈

📌 ዘካርያስ 14 :12-13 = ራዕ 19:17-21
፤ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
13፤ በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፤ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል።

📌 ራእይ 1፡7
እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።

📌 1 ተሰሎንቄ 5:9
፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።

✍️ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


...............ይቀጥላል........

✅ @yetumim_lijoch
💬 @jossy_j
👉Admin📩 @wunuye1995
#share #share

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
— ዮሐንስ 11፥25

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

📜📜ተከታታይ ትምህርት📜📜

❤️ #አምስቱ #የፍርድ #አይነቶች❤️

#ክፍል #ሁለት(፪)

2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

2) ሁለተኛው የፍርድ አይነት #በአማኝ #ስጋ ላይ
👉ምክንያት፦ #የተገለጠ #ሀጥያት
👉 ቦታ፦ በምድር ላይ
👉 ጊዜ፦ አማኙ በህይወት በምድር ሲኖር
👉ውጤት፦ አማኙ በተለያየ መንገድ በስጋው
ይገሰጻል ይህም ለአማኙ ጥቅም ነው።

✍️አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ በምድር ላይ በዋጋ የተገዛ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሲሆን የሰማይን ሕይወት እንዲገልጥ እና የክርስቶስ የጽድቁ እና የቅድስናው መገለጫ ለመሆን ተጠርቷል። ነገር ግን በዚህ ደካማ ስጋ ምድር ላይ ሲኖር መድከሙ የማይቀር ነው በሚደክምበትም ጊዜ በሕብረት ንስሃ በድካሙ ሊራራለት ከሚችለው እና ጸጋና አቅምን ከሚሰጠው ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር መጨረስ ይችላል።

✍️ነገር ግን አንድ ክርስቲያን ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር በንስሃ መጨረስ አቅቶት ቤተመቅደስነቱን ረስቶ በተገለጠ ሃጥያት ውስጥ ቢገኝ እና የጌታውንም ስም ቢያሰድብ #በስጋው ጌታ #ይገስጸዋል ፍርድንም ይቀበላል።

✍️1 ጢሞቴዎስ 5 (1 Timothy)
24፤ የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ ነው ፍርድንም ያመለክታል፥ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤

1 ቆሮንቶስ 3 (1 Corinthians)
16፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
17፤ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።(1 Corinthians 3
17: If any man defile the temple of God, him shall God destroy; for the temple of God is holy, which temple ye are.)

✍️1 ቆሮንቶስ 5 (1 Corinthians)
1፤ በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።.......
3-4፤ እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥
5፤ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።

✍️1 ቆሮንቶስ 11 (1 Corinthians)
30፤ ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል።
31፤ ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤
32፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።

✍️ገላትያ 6 (Galatians)
7፤ አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
8፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና

✍️ዕብራውያን 12 (Hebrews)
7፤ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
8፤ ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
9፤ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
10፤ እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን::

ይቀጥላል......

✅ @yetumim_lijoch
💬 @jossy_j
👉Admin📩 @wunuye1995
#share #share

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

ውዶች በቅርብ ቀን አዲስ ተከታታይ ትምህርት እንጀምራለን አብሮነታችሁ አይለየን

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

➠ ተከታታይ ኣዲስ ትምህርት

°°°°__መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው?__°°°°

°°°°__ምዕራፍ 1__°°°


[[[_°ክፍል-2°_]]]


የመጽሐፍስ ይዘት

ይህ ታላቅ መጽሐፍ ተጽፎ ለመጠናቀቅ 1500 ዓመታትን የፈጀ፣ ከ40 በላይ ጸሐፊያንን ያሳተፈና በተለያዩ ብዙ ቦታዎች የተጻፈ ቢሆንም በሚያስደንቅ ሁኔታ ማዕከላዊ መልዕክቱ አንድ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያዘጋጀው የዘለዓለም ሕይወት ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን  ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት ቅድመ ዝግጅት ሲሆን አዲስ ኪዳን ደግሞ የእርሱን መምጣት እውን መሆን የሚያበስር ነው፡፡
ብሉይ ኪዳን የፍጥረትን አጀማመርና የጥፋትን ውሃ ከተረከ በኋላ እግዚአብሔር አብራም የተሰኘ የመስጴጦምያ (Mesopotamia) ሰው ስለመጥራቱና ከዚህም ሰው እስራኤል የተባለ ሕዝብ ስለመገኘቱ ይተርክልናል፡፡ የአብራም መጠራት መሲሁ ኢየሱስ ወደ ምድር ይመጣ ዘንድ የመጀመርያው ዝግጅት ነበር፡፡ በዘፍጥረት 26፡2 ላይ እግዚአብሔር “የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ” የሚል ቃል ኪዳን ለአብራም ገብቶለት ነበር፡፡ ይህ ቃል ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደተፈጸመ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሯል (ገላትያ 3፡16)፡፡ የተቀረው የብሉይ ኪዳን ክፍል በአብዛኛው የሚያተኩረው እግዚአብሔር ከሕዝበ እስራኤል ጋር በነበረው ግንኙነት እንዲሁም ስለመሲሁ መምጣትና ስለሌሎች ብዙ ጉዳዮች በተተነበዩ የነቢያት ትንቢቶች ላይ ነው፡፡

አዲስ ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ በትምህርቶቹ እንዲሁም ከእርገቱ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ባደረጓቸው ነገሮችና ባስተማሯቸው ትምህርቶች ላይ ያተኩራል፡፡ ጠቅለል ባለ ሁኔታ የአዲስ ኪዳን መልዕክት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ማስተማሩን፣ ማንነቱን የሚያረጋግጡ ብዙ ተዓምራትን ማድረጉን፣ መከራን መቀበሉን፣ ስለ ሰው ልጆች ኃጢዓት ሲል በመስቀል ላይ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መነሳቱን፣ ለደቀ መዛሙርቱ መታየቱን፣ ወደ ሰማይ ማረጉን፣ ለሁሉም እንደየሥራው ሊከፍል ወደ ምድር ተመልሶ እንደሚመጣ፣ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ለነዚህ ነገሮች ምስክሮች መሆናቸውንና የዘለዓለም ሕይወት የሚገኘው በእርሱ በማመን ብቻ መሆኑን የሚናገር ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት የሥነ  ጽሑፍ ስልት የተከተለ መጽሐፍ አይደለም፡፡ ሕግ፣ ትረካ፣ ቅኔ፣ ትንቢት፣ መልዕክት፣ አቡ ቀለምሲስ፣ ወዘተ. የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ የሥነ  ጽሑፍ ዓይነቶች በውስጡ ይገኛሉ፡፡

💥የመገለጥ ትርጉም

የተለያዩ ኃይማኖቶች ስለመገለጥ የየራሳቸው የሆነ አመለካከት አላቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሙስሊሞች ቅዱስ ቁርአን “የተገለጠበትን” ሁኔታ ተንዚል ወይም ናዚል በማለት ይጠሩታል፡፡ ተንዚል ማለት “ከላይ የወረደ መገለጥ” ማለት ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረው ክርስቲያናዊ አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ የወረደ መገለጥ ነው የሚል ሳይሆን የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት (በመመራት) የጻፉት ቃል ነው የሚል ነው፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎቹ የነበራቸውን እውቀት፣ ባህልና ቋንቋ እንዲጠቀሙ መንፈስ ቅዱስ ፈቅዷል፡፡

ክርስቲያኖች የሚያምኑት ከላይ የወረደው የእግዚአብሔር መገለጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ መሆኑን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን በሰው ልጆች ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ የተገለጠ በጽሑፍ የቀረበ ግልጠተ-መለኮት ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ንግግር ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆች ለእግዚአብሔር ሐሳብ የሰጡትንም ምላሽ በውስጡ አካቷል፡፡ ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በውስጡ የያዘ መጽሐፍ ነው ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው በተለያዩ ዘመናት የተደረጉ የሰው ልጆች ታሪኮች በውስጡ የሚገኙት፡፡

በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “የእግዚአብሔር ቃል” (ሎጎስ) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ይህም እግዚአብሔር በሙላት ራሱን የገለጠው በእርሱ በኩል መሆኑን ያሳያል፡፡

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” (ዮሐ. 1፡1-3)

እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረበት ሕያውና ዘላለማዊ ቃሉ ሰው ሆኖ በመምጣት ከሰው ልጆች ጋር በምድር ላይ ኖረ፤ የእግዚአብሔርንም ማንነት በሙላት ገለጠ፡፡ ይህ መገለጥ ተሠግዎ (Incarnation) በመባል ይታወቃል፡፡ ተሠግዎ ማለት “ሥጋ መሆን” ማለት ነው፡፡
“ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን፡፡” (ዮሐ. 1፡14)

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃል በመሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ መግለጥ ይችላል፡፡ እርሱ የእግዚአብሔር የመጨረሻው ታላቅ መገለጥ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ላይ ይናገራል (ቆላስይስ 2፡9 ጢሞቴዎስ 3:16 ቆላስይስ 1፡15-16 ዮሐንስ 14፡7-10)
ከመሲሁ ስሞች መካከል አንዱ “አማኑኤል” የሚል ሲሆን ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ኢየሱስ ከመወለዱ ከ700 ዓመታት በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግሮ ነበር ፡-

“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” (ኢሳ. 7፡14)

ክርስትና እግዚአብሔር ከንግግር ባለፈ መንገድ ራሱን ለሰው ልጆች እንደገለጠ ያስተምራል፡፡ ይህም አንድያ ልጁን ወደ ምድር በመላክ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃል የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በማይለካ ፍቅር፣ በማይለካ ፅድቅ፣ በማይለካ ቅድስና፣ በማይለካ እውነተኛነትና በማይለካ ይቅር ባይነት የእግዚአብሔርን ማንነት በትክክል አሳይቶናል፡፡ በእርሱም በኩል እግዚአብሔርን አይተነዋል፡፡ በስሙ የሚያምኑ ሰዎች የእርሱን ማንነት በሕይወታቸው ውስጥ እውን ሆኖ ያገኙታል፡፡ የክርስትና አስደናቂና አስደሳቹ ገጽታም ይህ ነው፡፡ 


................ይቀጥላል...............


━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

👆👆👆👆👆👆👆
ለፕሮፋይሎ የሚሆኑ ጥቅሶቸ

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

. የተሰጠኝ ስም
ኢየሩሳሌም || New Song
⏰7:29Min 📥4.1MB
🔰ወንጌል ክርስቶስ ነው🔰
Share 📲 Share 📲 Share
▷ @yetumim_lijoch ◁
▷ @yetumim_lijoch ◁
△Join Us△

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

➠ ተከታታይ ኣዲስ ትምህርት

°°°°__መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው?__°°°°

°°°°__ምዕራፍ 1__°°°


[[[_°ክፍል-1°_]]]

መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ሰዎች፣ በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ ቦታዎች የተጻፉ በቁጥር 66 የሚያክሉ የተለያየ ርዝማኔ ያላቸውን መጻሕፍት በውስጡ ይዟል፡፡ ሁለት ታላላቅ ክፍሎች ሲኖሩት እነዚህም ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን በመባል ይታወቃሉ፡፡ ብሉይ ኪዳን በዋናነት እግዚአብሔር  ከሕዝበ እስራኤል ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን ይናገራል፡፡ የተለያዩ ሕዝቦች ታሪኮች በውስጡ የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ታሪኮች የተጻፉት ህዝቦቹ ከእስራኤል ጋር ከነበራቸው ግንኙነት አኳያ ነው፡፡  አዲስ ኪዳን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ክርስቲያኖች የተጻፈ ሲሆን ቤተክርስቲያን በመባል ስለምትታወቅ ማሕበረሰብ ይናገራል፡፡ የመጀመርያውን ምዕተ ዓመት የታሪክ ዘመን ይሸፍናል እንዲሁም ስለመጨረሻው ዘመን ይተነብያል፡፡ ብሉይ ኪዳን 39 አዲስ ኪዳን ደግሞ 27 መጻሕፍትን በውስጣቸው ይዘዋል፡፡
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት በእብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን በአራማይክ ቋንቋ የተጻፉ ጥቂት ክፍሎችም በውስጡ ይገኛሉ፡፡ አዲስ ኪዳን የተጻፈው “ኮይኔ” ወይም “የአሌክሳንደርያ ዘዬ” በመባል በሚታወቅ የግሪክ ቋንቋ ዘዬ ነው፡፡ ይህ የግሪክ ቋንቋ ዘዬ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን የሜድትራንያን አካባቢ ሕዝቦች መግባብያ (Linguafranka) ነበር፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የተተረጎመው የሰብዓ ሊቃናት የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ (Septuagent) ይህንኑ የግሪክ ቋንቋ ዘዬ የተከተለ ነበር፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ 1,189 ምእራፎችና 31,103 ቁጥሮች አሉት፡፡ የቁጥሮቹ ብዛት በተለያዩ ትርጉሞች ውስጥ በትንሽ መጠን ከዚህ ከፍ ወይም ዝቅ የሚልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ እነዚህ አከፋፈሎች በቀዳሚያን ጽሑፎች ውስጥ የማይገኙ ቢሆኑም ነገር ግን በመካከለኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የኖሩ አይሁድና ክርስቲያን ሊቃውንት መጽሐፉን በቀላሉ ለማንበብ እንዲያመች በማሰብ በዚህ መልኩ ከፋፍለውታል፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1227 ዓ.ም. የካንተር በሪ ሊቀ ጳጳስ የነበረው እስቴፈን ላንግተን ለመጀመርያ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን በምዕራፎች ከፋፈለ፡፡ በ 1382 ዓ.ም. የታተመው የዊክሊፍ የእንግሊዘኛ ትርጓሜ ይህንን አከፋፈል በመከተል በምዕራፎች የተከፋፈለ የመጀመርያው መጽሐፍ ቅዱስ ለመሆን በቃ፡፡ በ 1448 ዓ.ም. አይዛክ ናታን ቤን ካላኒመስ የተሰኘ አይሁዳዊ ረቢ ብሉይ ኪዳንን በቁጥር የከፋፈለ ሲሆን በ 1555 ዓ.ም. ደግሞ ሮበርት ኤስቲን (እስቴፋነስ) የተባለ ሰው አዲስ ኪዳንን በቁጥር ከፋፍሏል፡፡ እነሆ የነዚህ ሰዎች መልካም ጥረት ዛሬ በእጃችን የሚገኙትን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮፒዎች በቀላሉ ተነባቢ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

✍️መጽሐፍ ቅዱስ በማን፣ መቼና የት ተጻፈ?

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፉት መጽሐፍ እንደሆነ ክርስቲያኖች ያምናሉ፡፡ እነዚህ ጸሐፊያን በተለያዩ ቦታዎችና ዘመናት የኖሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ እድሜያቸው፣ ዕውቀታቸው፣ ሥራቸው እንዲሁም በማሕብረሰባቸው ውስጥ የነበራቸው ደረጃ የተለያየ ነበር፡፡ ከጸሐፍቱ መካከል አብዛኞቹ ስሞቻቸው  ከጻፏቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ተያይዘው ተጠቅሰዋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ለመጠናቀቅ 1,500 ዓመታት ያህል ፈጅቷል፡፡ የመጀመርያው ጽሑፍ የተከተበው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1400 ዓ.ዓ. አካባቢ እንደሆነና የመጨረሻው ክፍል ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ90 ዓ.ም. አካባቢ እንደተጻፈ በአብዛኞቹ ምሑራን ዘንድ ይታመናል፡፡
የዚህ እድሜ ጠገብ መጽሐፍ ልዩ ልዩ ክፍሎች በተለያዩ ሦስት አህጉራት፣ ማለትም በኢስያ፣ አውሮፓና አፍሪካ ውስጥ ተጽፈዋል፡፡


................ይቀጥላል...............


━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
⇨ @yetumim_lijoch
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በቻናላችን ስናቀርብ የነበረው ፕሮግራም በመቋረጡ እጅግ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ከአሁን ቡኋላ እጅግ ባማረ አቀራረብ ፕሮግራማችንን ወደ እናንተ እናቀርባለን። እስካሁን በትዕግስት ለቆያችሁን ለጠበቃችሁን አክብሮታችን እጅግ የላቀ ነው።

ከእንግዲህ ወዲህ ጊዜያችንን ከእርሶ ጋር እናሳልፋለን 😊

°°°°°°____ ብሩክ ኖት____°°°°°

Admin➠ @wunuye95

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

🏤🏤🏤🏤
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/v3pb5ufFlZ0yMWE0
👆👆👆👆👆👆👆👆
✳ የሙዚቃ መሳሪያዎችን እኛ ጋር መማር የምትፈልጉ በሙሉ ከታች ባሉት ስልኮች በመደወል መመዝገብ እንደምንችሉ ልንገልፅ እንወዳለን ።
➠ 0933128558
➠ 0925315164
👆👆

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

የማይቀርበት ቀጠሮ 📌🔖🖇📎💡

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

🙇ከኖሩማ ኑሮ ካንተ ጋራ🙇
🙇በችግርም ቢሆን በመከራ🙇
😭ከተያዘ እጄ ባንተ እጄ😭
😭ህይወቴ ሰላም ነው የሚመች😭

የኔ ነገር ሰው የማይዘጋው ሆሆ
ሰው የማይከፍተው ሆሆ
ሁሉ በእጁ ነው🙇
የኔ ነገር መጀመሪያዬ አሄሄ
መጨረሻዬ አሄሄ
በሱ አይደል ወይ🙇

✍ ...... ተስፋ_hope🙇

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

. ይህ ነው ፀሎቴ
ይስሃቅ ሰዲቅ | Live Worship
🕑-6:26Min◦💾-5.5MB
🔰ወንጌል ክርስቶስ ነው🔰
Share 📲 Share 📲 Share
▷ @zema_sink ◁
▷ @zema_sink ◁
△Join Us△

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

📜📜ተከታታይ ትምህርት📜📜

❤️#አምስቱ #የፍርዶች #አይነቶች❤️

#ክፍል #ሶስት(፫)

✍️ ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር
ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች የመጀመሪያወቹ ሶስቱ ብቻ አማኞችን የሚመለከቱ መሆኑን ነው።እነዚህም
1) በአማኝ የእድሜ ዘመን ሃጥያት
2)በአማኝ ስጋ(እኔነት)
3)በአማኝ ሥራ ላይ የሚፈረዱ ፍርዶች ናቸው።

📌2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

3, #በአማኝ #ሥራ ላይ የሚፈረድ ፍርድ ነው

👉ፍርዱ ፦በአማኝ ሥራ ላይ ነው
👉ጊዜው፦ ቅዱሳን ሁሉ ስንነጠቅ
👉የፍርዱ ቦታ፦ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር(Bema)
ፊት ነው።
📌አንባቢያን የፍርድ ወንበር እና የነጩ ዙፋን ፍርድ መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩን ልብ ሊሉ ይገባል፦

♦️የፍርድ ወንበር(Bema) አማኞችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን
♦️የነጩ ዙፋን ፍርድ ያላመኑ ሙታንን ብቻ የሚመለከት የመጨረሻው ፍርርድ ነው።

👉የፍርዱ ውጤት ፦#ሽልማት #መቀበል ወይም
#ሽልማት #አለመቀበል

✍️ቅዱሳን ሁሉ የዳኑት እና ከእግዚአብሔር ቁጣ ያመለጡት በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ በእምነት እና በጸጋው ብቻ እና ብቻ ነው።

✍️የጸጋው ሀይል ግን ከእግዚአብሔር ቁጣ ማዳን ብቻ ሳይሆን ሀጥያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን በማስካድ በዚህ ዘመን በጽድቅ፣ በቅድስና እና እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር እና ሽልማትን (ደሞዝን) ከጌታ ኢየሱስ እንድንቀበል ያደርገናል።

✍️ጌታ በቤዛነት ስራው ከቁጣ አድኖ ደግሞ በእኛ ሆኖ መልካም ስራን በመስራት ራሱ በእኛ በሰራው ስራ ግን ሽልማቱ ለእኛ መሆኑ ያስደንቃል ያስገርማልም።

📌1ቆሮ 3፡11-15
----------
11፤ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

12፤ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ
👉በወርቅ ቢሆን
👉 በብርም
👉 በከበረ ድንጋይም

👉በእንጨትም
👉 በሣርም ወይም
👉 በአገዳ ቢያንጽ፥
የእያንዳንዱ 👉ሥራ👈 ይገለጣል፤

13፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም 👉ሥራ👈 እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።

14፤ ማንም በእርሱ ላይ 👉ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤👈

15፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ 👉እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።👈

📌1 ቆሮንቶስ 4
5፤ ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።

📌ሮሜ14:10)
" አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? 👉ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና👈።"

📌2ቆሮ 5:10)
" መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ 👉በሥጋው👈 የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን 👉በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።👈"

📌2 ጢሞቴዎስ 4
8፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።

👉ስራችን ,ኑሮአችን እና ንግግራችን እንደቃሉ ከሆነ ሽልማት ከጌታ ዘንድ አለን። ጌታ ኢየሱስም ከሽልማት ጋር እንደሚመጣም ነግሮናል።
📌የዮሐንስ ራእይ 22:12)
" እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ 👉ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ(reward) ከእኔ ጋር አለ።👈"

📌ራእይ 22
20፤ ይህን የሚመሰክር፡— አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ፡ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
21፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።


ይቀጥላል........

✅ @yetumim_lijoch
💬 @jossy_j
👉Admin📩 @wunuye1995
#share #share

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

📜📜ተከታታይ ትምህርት📜📜

❤️ #አምስቱ #የፍርድ #አይነቶች❤️

#ክፍል #አንድ(፩)

2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

✍️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአዲስ ኪዳን አምስት( 5 ) የተለያዮ ፍርዶች ይገኛሉ። ይህን በአግባቡ መረዳት ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እንዲኖረን ከማስቻሉ በተጨማሪ ለእግዚአብሄር ያለን እይታንም ያስተካክልልናል ብዬ አምናለሁ። የትኛው ፍርድ ይመለከተናል የትኛው ደግሞ አይመለከተንም ሚለውን ማወቅ የጸና መሠረት ላይ ተደላድለን እንድንኖር ይረዳናል።

✍️ ሀይማኖቶች ስለ ፍርድ የሚያስተምሩት እና የሚያምኑት ሰው ሁሉ ያመነም ሆነ ያላመነ አንድ ላይ ተነስተው እግዚአብሔር ፍርድን ያስተላልፋል ይላሉ። ይህ የሐይማኖቶች አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ስለሌለው ወደ መጽሀፍ ቅዱስ እውነት በትህትና ልብ እንመለስ። ይሁዳ 1፡17

ይሁዳ 1 (Jude)
17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤

❤️ የፍርዶችን ልዩነት ለመረዳት ፦
1) የፍርዱ ዓይነት/ምክንያት
2) ፍርዱ የሚፈረደው በማን ላይ ነው
3) ፍርዱ የሚፈረድበት ጊዜ
4) ፍርዱ የሚፈረድበት ቦታ
5) የፍርዱ ውጤት

1,የመጀመሪያው ፍርድ

👉የፍርዱ አይነት ፦በአማኝ የእድሜ ዘመን ሀጥያት
ላይ ነው
👉ጊዜው ፦ በ30 ዓ.ም የዛሬ ሁለት ሺህ አመት
👉 ቦታ ፦ በቀራንዮ( በጎልጎታ) መስቀል ላይ
👉ፍርዱን የተቀበለልን ኢየሱስ ነው
👉የፍርዱ ውጤት ለእኛ ከእግዚአብሄር ቁጣ መዳን ነው።

✍️ ዮሐንስ 19 (John)
17፤ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ።
18፤ በዚያም ሰቀሉት፥

✍️ 1 ጴጥሮስ 2 (1 Peter)
24፤ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤

✍️ 1 ጴጥሮስ 3 (1 Peter)
18፤ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤

✍️ ገላትያ 3 (Galatians)
13፤ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤

✍️ ዕብራውያን 10 (Hebrews)
10፤ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።........
14፤ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።

✍️ ሮሜ 4 (Romans)
7፤ ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤
8፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።

✍️ ዕብራውያን 10 (Hebrews)
18፤ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።

✍️ መዝሙር 103 (Psalms)
10፤ እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።......
12፤ ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ።

✍️ 2 ቆሮንቶስ 5 (2 Corinthians)
21፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

✍️ ሮሜ 8 (Romans)
1፤ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።

✍️ ሮሜ 8 (Romans)
33፤ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

✍️ የዮሐንስ ወንጌል 5:24)
" እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ 👉ወደ ፍርድ አይመጣም👈።"

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


................ይቀጥላል...........

✅ @yetumim_lijoch
💬 @jossy_j
👉Admin📩 @wunuye1995
#share #share

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

ምን እከፍልሀለው ደስ አሠኝተኸኛል •
በከበረ ስፍራ አስቀምጠኸኛል
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
🌹 @Fiker_QUOTE 🌹
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

Читать полностью…

🎹 ANCHOR PRODUCTION 🎬

🍂የፈሪሳውያን 50 ምልክቶች


ክፍል-3


4. ፈሪሳዊያን እንደ መነኑ ሰዎች ብቸኞች ናቸው


የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች በተለያየ ደረጃ ባህታዊነትን እና ጾምን ይለማመዳሉ። አንዳንዶቹም ከትዳር ጓደኞቻቸው ጋር ፍትወተ ሥጋን ከመፈጸም ይቆጠባሉ። ነገር ግን ክርስቲያን በንደዚህ አይደለም ቅዱስ የሚሆነው። የትክክለኛ ሰው ምልክቱ እና ራሱን ሥርዐት የሚያሲዘው ከምግብ እና ከፍትወተ ሥጋ በመቆጠብ ሳይሆን ምላሱን በመቆጣጠር ነው (ያዕቆብ 3፡2)። በተጨማሪም አስተሳሰባችንን እና ዐይኖቻችንን መቆጣጠር አለብን።
ኢየሱስ በጥሩ ምግብ መደሰት ይችላል። በዚያን ጊዜ "በላተኛ" ነው ይሉት ነበር (ሉቃስ 7፡34)። መጀመሪያ የሠራው ተአምር ሠርግ ላይ ተጨማሪ የወይን ጠጅ መፍጠር ነበረ! የኢየሱስ መጀመሪያ ተአምር 'መንፈሳዊ' የሚባሉ ለምሳሌ የሞተን ማስነሳት የመሳሰሉ ሊመስለን ይችላል። ይህን ያደረገበት አንደኛው ምክንያት ወደ ምድር የመጣው ውጫዊ የሆኑ 'አትንኩ፣ አትቅመሱ' የሚሉ የሃይማኖት ትምህርቶችን ለማውደም ስለነበረ ነው።

ስለ ጾም ጊዜአቸው በረቀቀ መንገድ የሚያወሩ ክርስቲያኖች አግኝቻለሁ። እነዚህም ሰዎች ሲናገሩ "በቅርብ ጊዜ በ21 ቀን ጾም ላይ ሳለሁ ጌታ የሰጠኝን የከበረ ቃል ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ" ይህንን እና የመሳስሉትን ቃላት ይጠቀማሉ። ዋናው ዓላማቸው ስለ 21 ቀን ጾማቸው ሰውን ማስደነቅ ነው። ሌላቹ ቃላቶች ሁሉ ሁለተኛ ናቸው። ኢየሱስ ግን ስለጾማችን ለሌሎች እንዳንናገር ነግሮናል። ፈሪሳዊያን ግን በባሕታዊነታቸው ይኮሩ ነበር። በእርግጥ በክርስትና ኑሮ ምግብ ፤ መኝታ እና የፍትወተ ሥጋ ጉዳይ ላይ ሥነ ሥርዓት ያስፈልጋል። ቢሆንም ስለእነዚህ ጉዳዮች ለሌሎች መንገር ወይም መመካት አያስፈልግም።

5. ፈሪሳዊያን በጥቃቅን የሌሎች አድራጎቶች ላይ ሂሣዊ ትንታኔን ያበዛሉ

"ፈሪሳውያንም አይተው። እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት።" (ማቴዎስ 12፤2)

በእስራኤል ሕግ መሠረት ሰዎች በእርሻ ውስጥ ሲያልፉ ጥራጥሬ ቀጥፈው መብላት የተፈቀደ እንደሆነ ፈሪሳዊያን ያውቁ ነበር። እዚህ ላይ ጥያቄአቸው ለምን በሰንበት ቀን 'ሥራ' ተሠራ ነበር። ፈሪሳዊያን በጥቃቅን የሌሎች አድራጎቶች ላይ ሂሣዊ ትንታኔን ያበዛሉ። በማቴዎስ 15፡2 እንደምናየው ለምንድን ነው ደቀመዛሙርቶችህ ከታላላቆቻችን እንደተማርነው ሥርዓት መሠረት እጃቸውን የማይታጠቡት ብለው ኢየሱስን ጠየቁት ። ፈሪሳዊያን ጥቃቅን ጉድለቶችን አማኞች ላይ ለማግኘት ሁልጊዜ ይከታተላሉ።
የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ሆናችሁ ከላይ የተጠቀሱትን የምታደርጉ ከሆነ ቤተ ክርስቲያናችሁ በፈሪሳዊያን የተሞላ ሊሆን ይችላል። ይህም የሚሆነው የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች አኗኗር የቤተክርስቲያን ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ነው። ይህንንም በዮሐንስ ራእይ ምእራፍ 2 እና 3 ላይ እናያለን። ነገር ግን ሽማግሌዎቹ ከፈሪሳዊነት ነጻ የሆኑ ቢሆኑ አብዛኛው የቤተ ክርስቲያን ሰዎችም ከፈሪሳይዊነት ነጻ ይሆናሉ።

6. ፈሪሳዊያን የሚኖሩት ሕግን በመከተል ነው

"እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት።" (ማቴዎስ 12፤10)

ፈሪሳዎያን ሕግ ተከትለው ነው የሚኖሩት። የኢየሱስን ሕይወት ተከትለው አይኖሩም። አስቂኝ የሆነው ሕጋቸው በሕመም ላይ ያለ ሰው በሰንበት ቀን ከህመሙ ለመፈወስ መሻትን ይከለክላል። እነዚያ ፈሪሳዊያን ኢየሱስን "ይከሱትም ዘንድ" ነበር ይህን ጥያቄ የጠየቁት። ዛሬም ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ራሳቸው ያወጡዋቸውን ጥቃቅን ደምቦች የጣሰን ሰው ለማውገዝ ይቸኩላሉ። ለፍጥረት ሁሉ ሕግን ሰጪ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ያልሰጠውን ሕግጋት ቤተ ክርስቲያን ላይ ማውጣት የእግዚአብሔርን ቦታ እንደመውሰድ ነው፤ ይህም "የጸረ ክርስቶስ መንፈስ ነው" (2 ተሰሎንቄ 2፡4)። ይህን የሚያደርጉ በመጨረሻም እንደነዚያ ፈሪሳዊያን ከሰይጣን ጋር አብረው "የወንድሞቻችን ከሳሽ" ይሆናሉ (የዮሃንስ ራእይ 12፡10) ።

7. ፈሪሳዊያንን ለአድራጎት የሚገፏፏቸው ቅናት እና ጥላቻ ናቸው

" ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት " (ማቴዎስ 12፡14)

ሰው ላይ ያላችሁ ቅናት መግደል ላይ ላያደርሳችሁ ይችላል። ሆኖም ለግድያ የመጀመሪያው እርምጃ ቅናት እና ጥላቻ መሆናቸውን አትዘንጉ። የቃየንም አካሄድ ይኸው ነበር፡ ቅናት... ጥላቻ... ግድያ።
ፈሪሳዊያን ማድረግ የማይችሉትን ብዙ ስላደረገ እና በሰዎች ዘንድ ዝናን ስላተረፈ ፈሪሳዊያኑ ኢየሱስ ላይ ይቀኑ ነበር። ስለኢየሱስ ጥቂት እውቀት የነበረው ጲላጦስ እንኳን ፈሪሳዊያን ኢየሱስ እንዲሰቀል የፈለጉት ከቅናት የተነሳ መሆኑን አስተውሎ ነበር (ማቴዎስ 27፡18)።

ሰው ላይ ቅናት ሲኖራችሁ በአነጋገራችሁ እና በአኳኋናችሁ ይታያል። ከእናንተ የተሻለ በሚሰብክ፤ የበለጠ ሀብት ባለው ወይም እናንተ የሌላችሁ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ባለው ሰው ላይ ትቀኑ ይሆናል። ይህም ሲሆን ይህን ሰው ለመንቀፍ ጥቂት እንከን መፈለግ ቀላል ሆኖ ታገኛላችሁ። ይህ ስው ሲወድቅ ለማየትም ትጓጓላችሁ። የፈሪሳዊያን ሃይማኖት የቃየን ሃይማኖት ነው።

8. ፈሪሳዊያን ተጠራጣሪዎች ስለሆኑ ሰዎች ላይ መልካም አመለካከት የላቸውም

"ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።" (ማቴዎስ 12፤24)

ፈሪሳዊያን በጣም ተጠረጣሪዎች ስለሆኑ እና ሁሉም እንደእነሱ ራስ ወዳድ ስለሚመስላቸው ሰዎች የራሳቸው ጥቅም ሳይኖርበት ሌሎችን ብቻ ለመርዳት ይሠራሉ ብለው አያምኑም። ፈሪሳዊ ከሆናችሁ ሰዎች መልካም ነገር ያሚያደርጉበትን ምክንያት በመጥፎ ታጤናላችሁ። በተጨማሪም ሌሎች የተደሰቱበትን ነገር ትተቻላችሁ።


ይቀጥላል...




━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨ @christ_progeny_tube
⇨ @christ_progeny_tube
⇨ @christ_progeny_tube
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

Читать полностью…
Subscribe to a channel