ነብይ ስምዓን ሪቄ
🇪🇹ሊያጠፏት የተነሱ ሁሉ ያፍራሉ🙏የጉብኝት ዘመን ይመጣል🇪🇹🇪🇹
ነሀሴ 01/2013 ዓ/ም የመጣ መልዕክት
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
“በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።” ኤርምያስ 17፥7
👉እርሱ ስለተስፋ ቃሉ ታማኝ ነው።
👉ስለኢትዮጵያ እናመንዋለን የታመነ ነው።
👉የተስፋ ቃሉ ስለማይለወጥ እናንተ የጠፋችሁ አይደላችሁም። 🇪🇹🇪🇹
ነብይ መስፍን ንጉሴ
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ #ልባችሁ_አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
…
²⁷ ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። #ልባችሁ_አይታወክ_አይፍራም።
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
ሐዋርያት 20፥28
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር መንገሻ ጥላሁን ከእግዚአብሔር ቃል በ1ጢሞ 3:1-13 እና ኦሪ ዘኁ 27:15 ባለው ክፍል በመመስረት ቤተክርስቲያንን የሚመሩ ሽማግሌዎች የሚመረጡበት መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት አካፍለውናል።
.......................................................................
"ሙሴም እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።" ኦሪ ዘኁ 27:15-16
የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደ መንጋ ነው የሚመራው ያሰወፈልገዋል። ስለዚህ ሕይወቱ በቃልህ ፈቃድ የሚመራ በፊታቸው ሲገባ ሲወጣ የሚያዩት በሕይወት አካሄዱ ምሳሌ የሚሆን መሪ ስጣቸው
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
ሐዋርያት 20፥28
👉በ1 ጢሞ 3:1-13 ባለው ክፍል መሰረት በክርስቶስ ደም የተዋጀችን ቤተክርስቲያንን የሚመሩ መሪዎች መስፈርት
1.የአገልግሎት ፍላጎት ያለው 1ጢሞ 3:1
ፍላጎቱን በሰዎች ልብ የሚያስቀምጠው እግዚአብሔር ነው።
“ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።”
— ፊልጵስዩስ 2፥13
2.ክርስቲያናዊ ባሕሪ ያለው 1ጢሞ 3:2
ለአገልግሎት ካለው ፍላጎት በተጨማሪ ከአገልግሎቱ ጋር የሚስማማ ሕይወት ያለው ለአገልግሎቱ የሚመጥን ሕይወት ያለው
3.በአገልግሎት ሕይወቱ የተመሰከረለት 1ጢሞ 3:2
👉በመልካም የተመሰከረላቸው
“ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ” ሐዋርያት 6፥3
👉ለማስተማር የሚበቃ
“ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።” ቲቶ 1፥9
4.በቤተሰብ ሕይወቱ የተመሰከረለት
የራሱን ቤት በአግባቡ ሊያስተዳድር የሚችል
" ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?" 1ጢሞ 3:4-5
5. በማህበራዊ ሕይወቱ የተመሰከረለት 1ጢሞ 3:7
“በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥7
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#በእግዚአብሔር_ልጅነት_ውስጥ_ያሉ_በረከቶች
በፓስተር ዳዊት ላምቤቦ
በእሑድ የአምልኮና የቃል ጊዜ ፓስተር ዳዊት ለምቤቦ በእግዚአብሔር ልጅነት ውስጥ ያሉ በረከቶች በሚል ርዕስ ድንቅ ቃል አካፍሎናል።
* ምንም እንኳ ሰው ዕድሜው ያረጀ ቢሆን ኢየሱስን ሲቀበል ዳግም ይወለዳል (ልጅ) ይሆናል።
# በእግዚአብሔር ልጅነት ውስጥ ያሉ በረከቶች ምንድናቸው?
፨ በእግዚአብሔር ልጅነት ውስጥ ያሉ ሁለት ሊነሱ የተገቡ ጥያቄዎች :-
ሀ . በልጅነት ውስጥ ያሉ ረከቶች ምንድናቸው? የሚል እና
ለ . በረከቶችን የሚያበላሹስ ነገሮች ምንድናቸው? የሚሉ ናቸው።
ሀ. በልጅነት ውስጥ ያሉ በረከቶች:-
1. የጸጋውን ባጠግነት ማየት:- (ኤፌ 2:5)
*. ከእርሱ ጋር አስነሳን
*. ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን
*. ከእርሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ አስቀመጠን
*. በክርስቶስ ደም አቀረበን
*. በእርሱ ሥራ ወደ ሰማይ አስገባን። የሚሉ በረከቶች የጸጋውን ባለጠግነት ማየት ጋር ተያይዘው የሚነሱ በረከቶች ሲሆኑ ሌሎችም ብዙ በረከቶች ይነሳሉ...
2. አባ አባ ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ ተቀበልን:- (ሮሜ 8:15)
*. ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ሲገባ የኃይል መንፈስ ወደ እኔነት ይገባል
*. የሰው ልጅ በጠላት እጅ ሲወድቅ ይ መንፈስ ይከፈላል።
*. በዚህ ልጅነት ውስጥ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ማግኘት እንደሚቻል የማወቅ ጥበብ።
3. ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን መጠራት:- (1ኛ ዮሐ.2:9)
*. ወደ ብርሃን መጠራት እና በዚህ ብርሃን ውስጥ በዘላለማዊነት መኖር።
ለ. ልጅነትን (በረከትን) የሚያበላሹ ነገሮች
1. ጥላቻ
2. ኃጢአት
3. ዓለምን መውደድ
በነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅነት ውስጥ ባሉ በረከቶች ውስጥ መኖር ይሁንልን🙌❤️🙌!!!
አሜን!!!
“አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።”
መዝሙር 46፥1-2
በፓስተር ጌቱ አያሌው
እግዚአብሔርን የመጠጋት ዓመት #2
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ የቤተክርስቲያናችን ዋና መጋቢ በሆኑት በፓስተር ጌቱ አያሌው በኩል የእግዚአብሔርን ቃል የተካፈልን ሲሆን እግዚአብሔርም በቃሉ በኩል ለሚቀጥለው ዘመን ለሕዝቡ ድንቅ የሆነ መልዕክት ተናግሯል።
" አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።"
፨ ዳዊት ይህንን መዝሙር የዘመረበት ዋናው ጉዳይ በእሥራኤል ላይ በተለይም ሁለት ዓይነት ፍርሃት ያንዣብብ ስለነበር ሲሆን
1. በተፈጥሮ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎች ፍርሃት
ምሳሌ፦ የምድር መናወጥ....
2. በዙሪያዋ ያሉ የተለያዩ የነገሥታት ሠራዊት ፍርሃት
ምሳሌ፦ ኢያቡሳውያን...
- ስለዚህ ከዚህም የተነሳ የተቀቡ የዘመኑ አገልጋዮች (መዘምራን፥ ካህናት ነቢያት...) የእግዚአብሔርን መልዕክት በተለያየ መንገድ (ድምፅ) ሲያመጡ በሕዝቡ ላይ የነበረው ታላቅ ፍርሃት ይወገድ ነበር።
- አሁን በዚህ ዘመን ብዙዎቻችን ከእግዚአብሔር ወጥተን በብዙ ፍርሃት ተይዘን እንገኛለን። በፍርሃት እንድንያዝ ችግር (ምክንያት) የሆኑብን ነገሮች፦
ገንዘብ፥ ኑሮ፥ ዝናን የመሳሰሉትን ማሳደድ ሲሆን
የሚሻለን ግን ወደ እግዚአብሔር መጠጋት ነው።
- እግዚአብሔር ደግሞ ለሚጠጉት ጽኑ መጠጊያ ነው። መዝ.48:3፥ መዝ:91
* በኢየሱስ ያመኑ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የመጠጋት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
እግዚአብሔርን መጠጋት ማለት ምን ማለት ነው?
1. በእግዚአብሔር ህልውና (በአብሮሆቱ፥ በመገኘቱ) ውስጥ መኖር ማለት ነው።
. ዘዳ. 33:26-29
# አንዴ እግዘብሔርን መጠጋት ከጀመርክ ቀጥሎ ምን መጠጋት እንዳለብህ እርሱ ያሳይሃል።
2. የእግዚአብሔርን ሕያው ቃል በማኖር፥ በማሰላሰል...በራሱ በቃሉ ውስጥ መኖር ማለት ነው።
. ዮሐ. 15:7, ኢያሱ. 23:6-8
#የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ወደ ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያስጠጋናል።
3. ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደረት (ልብ) ተጠግቶ የእግዚአብሔርን ሀሳብ (ድምፅ) መስማት ነው።
. ዮሐ.13፥23-26
# ከኢየሱስ ደረት (ልብ) የሚወጡ ሕይወታቸው ሌሊት ይሆንባቸዋል።
፨ የሕይወት ትልቁ ደስታ የጌታን ድምፅ መስማት ነው። ይህም ድምፅ ሊሰማ የሚችለው ወደ እርሱ ደረት (ልብ) በመጠጋት ነው። ወደዚህ የተጠጉ ሁሉ ጥሩ ራዕይ፥ ጥሩ መንፈስ ከዚህ ይቀበላሉ። እነ ዳዊት፥ እነ ዳንኤል ከዚህ ተካፋይ የነበሩ ግሩም ምሳሌዎቻችን ናቸው።
- እኛም ከዚህ ከአዲሱ ዓመት (2014 ዓ.ም) ጀምሮ ለቀጣይ ዘመናችን ሁሉ ወደ እርሱ (ወደ ኢየሱስ) ደረት መጠጋት ይሁንልን 🙌🙏🙌..!
አሜን!!!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#የጋብቻና_የቤተሰብ_ሳምንት_በድል
#ተጠናቋል
=========================
ከሐምሌ 21 -25 /11 /2013 የጋብቻና የቤተሰብ ሳምንት በቤተክርስቲያናችን ነበረን።
መጋቢ ይመስገን ሞላ በእግዚአብሔር ቃል ቅድመ ጋብቻና ድረ ጋብቻን ያስተማረን ሲሆን ፦
ለቤተክርስቲያናችን የጋብቻ አማካሪዎችም ስልጠና ተሰቷቸዋል ።
*ላላገቡ ወጣቶችም የጋብቻ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን
ሀምሌ 25 እሁድ ከ9:00 ጀምሮ በነበረን የጋብቻና የቤተሰብ ፌስቲቫል ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ዝግጅቶችም ቀርበዋል።
የቤተክርስቲያናች መጋቢ ጌቱ አያሌውም
*በጋብቻ ለተጣመሩ ባለትዳሮች
*ላላገቡ ወጣቶች
*እንዲሁም በጋብቻ ህይወት ውስጥ ሆነው ልጅ ለሌላቸው ባለትዳሮች ሁሉ በስፋት ፀለየዋል።
በመጨረሻ ፕሮግራም ላይ በጋብቻ 30 -60 ዓመት ለቆዩ ሰርቸፍኬት፣ሜዳልያ በመስጠት ታላቅ በዓል አድርገን በምስጋና ፈጽመናል ።
ይህንን ያህል ዘመን በጋብቻ በመኖር ለዛሬው ትውልድ ምሳሌ ስለሆናችሁን እናመሰግናለን እግዘብሔር ዘመናችሁን ይባርክ።
#ክርስቲያናዊ_ኑሮ
አገልጋይ በረከት ዋቤሎ
“በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤”
ፊልጵስዩስ 4፥8
የፊልጵስዩስ ሰዎች
👉በጥሩ መንፈሳዊ ዕድገት
👉በመልካም የክርስቲያናዊ ኑሮ
👉የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል በማገልገል የተሰሰካላቸው ናቸው።
ነገር ግን ክርስቲያናዊ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችሉ ተግዳሮቶች በፊታቸው እንደተደቀነ ይነግራቸዋል።
እነዚህም ተግዳሮቶች:-
1. በመካከላቸው ያሉ ስብከታቸው ጤናማ ሰባኪዎቹ ግን ጤናማ ያልሆነ ዓላማ ያላቸው ናቸው።
"......እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ።
ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።" ፊሊ 1:15-18
ስለ ክርስቶስ ያወራሉ ነገር ግን ዓላማቸው ጤናማ አይደለም። በቅንነት ሳይሆን በክፋት ቅናት ሁከትና መለያየትን ለመፍጠር ለክፉ ምኞታቸው ማሳኪያ ፈልገው ይሰብካሉ።
2.በክርሰወቶስ ውስጥ ያለው በክርስቲያኑ ውስጥ ሲጠፋ
"...ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤
እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።....." ፊል 2:1-11
3.በመለየት ከመኖር ይልቅ በመደባለቅ መኖርን የመረጡ መሆናቸው
“በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤”
ፊል 2፥14-15
4.የክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም መፈለጋቸው
“ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።” ፊል 2፥21
5.የመስቀሉ ጠላቶች መብዛታቸው
"ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።" ፊል 3:18-19
6.ኑሮዬ ይበቃኛልን ያልተማሩ ቅዱሳን መብዛታቸው
“ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።”
ፊልጵስዩስ 4፥11
👉ዛሬም በክርስቶስ ውስጥ ያለው በእኛ በውስጣችን እንዲኖር ክርስትናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉትን በመረዳትና ነቅተን ሕይወታችንን መጠበቅ እንድንችል የፀጋ ሁሉ አምላክ ይርዳን አሜን!🙏🙏
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#ለእግዚአብሔር_ክብር_ማገልገል
ዮሐ.17:1-4
“.......እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤” ዮሐንስ 17፥1-4
፨ በእሑድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንድማችን ፓስተር ጌትነት ከአማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን "ለእግዚአብሔር ክብር ማገልገል" በሚል ርዕስ ድንቅ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል።
፨ አገልግሎታችን ሊመሠረትበት/ሊቃኝበት/ሊቆምበት የሚገባው ዋናው አስተሳሰብ ይኼ መሆን አለበት።
፨ አስተሳሰባችን በእግዚአብሔር ቃል ካልተቃኘ ሁለት ነገሮች ይበላሻሉ፦
1. ንግግራችን እና
2. ድርጊታችን
# ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው(ራሱ እንደተናገረው) እኛን ለማገልገል ነው። በመሆኑም አገልግሎቱን በሚገባ ፈጽሞታል።
# ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛው አገልጋይ ነው።
፨ አገልግሎትን በተለይ ለሁለት ነገር መፈለግ የለብንም፦
1. ለጥቅም መግኛ
2. ክብር መፈለጊያ (ለራስ ክብር)
# አገልግሎት ለወደደን፥ ለጠራን፥ ላከበረን፥ ለእርሱ ክብር ብቻ የምናገለግለው ሥራ ነው።
# ለዚህም ነው መጥመቁ ዮሐንስ "እርሱ ሊልቅ (ከፍ ሊል) እኔ ግን ላንስ ይገባል" አለ።
# አገልግሎትን መፈጸም ማለት ደግሞ እግዚአብሔርን ማክበር ነው።
፨ እግዚአብሔር በእኛ የሚከብረው የሚከተሉትን ነገሮች ስናደርግ ነው፦
1. አገልግሎታችንን ስንፈጽም። ዮሐ. 17:1-4
2. በቅድስናና በጽድቅ ስናገለግል። ሉቃ:1:74
3. በተሰጠን ጸጋ ማገልገል። 1ኛ ጴጥ.4:10
4. በትጋት ማገልገል ነው
# ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎቱን በታማኝነት እንዳገለገለ እኛም በትጋት አገልግሎታችንን ፈጽመን እና እግዚአብሔርን አስከብረን እንድናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን🙌❤🙌!
አሜን!!!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#እንደተቀበልን_ፀጋ_መጠን_እናገልግል
"ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ #እያንዳንዳችሁ_የጸጋን_ስጦታ_እንደ_ተቀበላችሁ_መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤" 1ጴጥ 4:10
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ሰንበቶ ባሼ የኢትዮጲያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕረዝዳንት በ1ጴጥ 4:10-11 ባለው ክፍል በመመስረት እንደተቀበልን ፀጋ መጠን እናገልግለ በሚል ርዕስ ድንቅ ቃል አካፍለውናል።
"ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።"
1ጴጥ 4:11
እያንዳንዱ ክርስቲያን በተቀበለው ፀጋ እንዴት ማገልገል አለበት
👉ምንድነው የተቀበልነው ፤ ምንድነው የተሰጠን
👉ምንም ያልተቀበለ ምንም ያልተሰጠው የለም
አገልግሎታችን ለክብሩ እንጂ ለክብራችን አይደለም ስለዚህ #እንዴት_እናገልግል
1. #እንደተቀበልነው_ፀጋ_መጠን
"እያንዳንዳችሁ_የጸጋን_ስጦታ_እንደ_ተቀበላችሁ_መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ" 1ጴጥ 4:10
ማቲ 25:14-30 እንደአቅማቸው መክሊት ተሰጣቸው በተሰጣቸው ልክ ተጠየቁ አምስት ለነገደም ሁለት ለነገደው የተሰጣቸው ምላሽ ተመሳሳይ ነው አንተ ታማኝ በጎ ባሪያ
2.#እንደ_እግዚአብሔር_ቃል
"ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤" 1ጴጥ 4:11
3. #የሚያገለግል_ቢኖር #እግዚአብሔር_በሚሰጠኝ_ኃይል ነው በማለት ያገልግል
በራሳቹ አትመኩ
ሉቃ 17:7 -10 “እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።”
👉ምንድነው የተሰጠን ፀጋ በተሰጠን ፀጋ ምን እያደረግንበት ነው።
እንደተቀበልነው ፀጋ መጠን በታማኝነት ማገልገል እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን🙏🙏
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#አገልግሎትህን_ፈጽም!
በወንጌላዊ አበራ ጉንታ
" አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ #አገልግሎትህን_ፈጽም።"
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
......................................................................
፨ ይህ መልዕክት ጳውሎስ ከመሰብሰቡ (ወደ አምላኩ ከመሄዱ) በፊት ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ ያስተላለፈው አደራን የተሸከመ ምክር ነው።
ጳውሎስ ይህን ምክር ለጢሞቴዎስ ሲያስተላልፍ በዘመኑ ብዙ ሰዎች አገልግሎትን ይጀምራሉ ነገር ግን አይፈጽሙም ነበር። እንዲሁም በመልካም ይጀምራሉ አጨራረሱ ግን የማያምር ብዙ አገልጋዮች ነበሩ። ይህ ነገር በዚህ ዘመንም አንገብጋቢው ጉዳይ ነው።
፨ አገልግሎት ሰሞናዊ ትጋት አይደለም!
#አገልግሎትን_እንዴት_ልፈጽም?
1. ሁሉም ቢተው አንተ ግን ፈጽም። 2ኛ ጢሞ. 1:15
1.1. ሰዎች አንተን ቢተው ፈጽም። 2ኛ ጢሞ. 1:15, ማር.14:50
1.2. አገልግሎትን ራሱን ቢተው ፈጽም። ይሁዳ ስለ ብርና ወርቅ አገልግሎቱን ተወ
*. አገልግሎትን የሚተው ሰዎች ሰውን ከሰው ያጋጫሉ።
2. ጊዜው ቢመችም ባይመችም አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞ.4:2
*. ሰዎች በኑሯቸው ጊዜያቸውን የሚመች እና የማይመች ጊዜ ብለው ስለ አገልግሎት መድበዋል።
#የሚመች ጊዜ
- ትምህርት የሌለ ጊዜ
- ሥራ የሌለ ጊዜ
- ችግር የሌለ ጊዜ
- ተቀባይነት ያለበት ጊዜ
# የማይመች ጊዜ
- የመከራ ጊዜ
- የእሥራትና የግርፋት ጊዜ
- የስደትና የውርደት ጊዜ
- ወገን የማጣት ጊዜ
እነዚህን እና እነዚህን የመሰሉ ነገሮች ሁሉ በሰውኛ ተከፋፍለው ቢቀመጡም አገልግሎት ግን በጊዜውም አለጊዜውም ሊፈጸም ይገባል።
3. የተሰጠህን (ከጌታ የተቀበልከውን) አገልግሎት ፈጽም። ቆላ.4:17
- በአንተ ውስጥ የተቀመጠውን ወይም የሚሰማህን መክሊት ለመፈጸም ትጋትን ማሳየት
- በተሰጠን ጸጋ ማገልገል እንጂ ያልተሰጠንን መሆን አንችልም
- እግዚአብሔር እጃችን ላይ ባለው ጥቂት ነገር ይሰራል።
4. መከራን በመቀበል አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞ.4:5
- ጳውሎስ ጢሞቴዎስን መከራ ተቀበል ሲል እሱ ራሱ በመከራ እያለፈ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ሌላውን ሰው ሲመክሩ ራሳቸው ያላለፉበትን እና የሌሉበትን ሕይወት ይመክራሉ።
- ክብርን ብቻ እየፈለግን አገልግሎት አይሆንም። 2ኛ. ቆሮ1:12
- የምናገለግለው በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በራስ ጥበብ፥ ዕውቀት አይደለም። ይህንን ስንረዳ የእግዚአብሔር ጸጋ ይጨመርልናል። ጳውሎስ ይህንን አገልግሎት በአደራ ሲሰጥ በምስክር ፊት ነበር። ይህም ምስክር በሕያዋንና በሙታን ፊት ሊፈርድ ባለው በኢየሱሰ ፊት ነበር።
፨ ምስክርነት ያለውና ምስክር ያለው አገልግሎት ፈጽመን እንድናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን!
አሜን🙌❤️🙌!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#ልጅነታችንን_እናክብር
ፓስተር ኢያሱ ሰለሞን
“የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ” 1ኛ ዮሐንስ 3፥1
“ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።” ሮሜ 8፥17
እግዚአብሔር በክርስቶስ አምነው ወደ እርሱ የመጡትን ከምንም በፊት ልጆች አድርጓቸዋል። ልጅንት በወንጌል እውነት በማመን ያገኘነው ማንነታችን ነው።
ልጅነት በእግዚአብሔር መንገስት ውስጥ የመጨረሻው ማዕረግ ነው። ከእግዚአብሔር ልጅነት ስልጣን በላይ አይታደግም።
ልጅነታችን ከቀለለብን ልጅነት ካላረካን መንፈሳዊ የጤንነት ችግር ገጥሞናል ማለት ነው።
ለምንድነው ልጅነታችንን ማክበር ያለብን?
1.የማይተካ ስለሆነ በሌላ ነገር የማይገኝ የማይካስ ስለሆነ
በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘው ልጅነት በሌላ በምንም መንገድ አይገኝም።
ከእግዚአብሔር ካልመጣ በሌላ በምንም ነገር አይገኝም።
“የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ” 1ኛ ዮሐንስ 3፥1
2.በእግዚአብሔር የመሰማት እድል ያገኘነው በልጅነታችን ስለሆነ ነው
“...በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።” 1ዮሐ 5:13-15
" እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።" ገላ 4:5-6
በእግዚአብሔር ዘንድ የመሰማት ዕድል ያገኘነው በልጅነታችን ነው።
ልጅነታችንን እናክብር ልጅነታችንን ጠብቀን እንኑር
3. ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የማድረግ ዕድል ሰጥቶናል
"...በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። " ኤፌ 2:11-22
በእግዚአብሔር መገኘት:ህልውና ውስጥ መኖር የልጅነት መብታችን ነው።
4.ወራሾች አድርጎናል
“ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።” ሮሜ 8፥17
ልጆቹ ከሆንን ወራሾች ነን ምድር ለእኛ የእንግድነት ቤታችን ነው። ምድር ለዘለዓለሙ የምንዘጋጅበት ስፍራ ነው።
ወራሽ ያደረገን ልጅነታችን ነው። የምንወርሰው እግዚአብሔርን መንግስቱን ነው።
በክርስቶስ ስራ/በፀጋው/ ያገኘነውን የእግዚአብሔር ልጅነት ስልጣን አክብረን እንዲሁም ጠብቀን መኖር እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን ። አሜን🙌🙏🙌
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
“እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1
#ልጅነት
በፓስተር ዮሴፍ(ጆሲ)
፨ በእሑድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንድማችን ፓስተር ዮሴፍ ስለ ልጅነት ድንቅ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል መልእክት ከ2ኛ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 2 ያስተላለፈበት ጊዜ ነበር።
- ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በክርስቶስ ኢየሱስ እንዲበረታና በታማኝነት እንደተሾመ ሁሉ ቀጣዩንም አገልግሎት ለታማኝ አገልጋይ እንዲሰጥ ያዘዋል።
- ጢሞቴዎስ በአያቱ በእናቱ እና በራሱ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ (ፍሬ) የሚታይበት ልጅ ከመሆኑም ባሻገር የዘለዓለም ሕይወት የሚገኝበትን መጽሐፍት በማንበብ ትልቅ ቁመና የነበረው ልጅ ነው።
እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን የዳንን ሰዎች ልጅ የሆንነው ሐዋርያት ወይም ነቢያት መተውልን ሳይሆን ኢየሱስ ራሱ ደርሶልን (መቶልን) ነው። ስለዚህ የተሰጠን የደህንነት እና የልጅነት ክብር ለዘለዓለም ነው።
# የጢሞቴዎስ መጽሐፍ የተጻፈው፦
1. ቤተክርስቲያንን ከስህተት ትምህርት ለመጠበቅ
2. የአካልነትዋን መዋቅር ለማሳየት እንዲሁም
3. በእግዚአብሔር ቤት ልጅ ሆነው በሥርዓት የሚኖሩትን እና የማይኖሩትን ለማሳየት ነው።
፨ ልጅነት የሚገኘው በመወለድ ነው።
ልጅነትና ውሎ
-ማንም በጽድቅ መንገድ ወደ ልጅነት ከመጣ በረከሰና በተዋረደ ቦታ ሊውል አይገባም። ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2:20 ላይ የከበረውን ከተዋረደው ለይቶ እንዲይዝ ያዘዋል።
ኤልሳቤጥ ዕድሜዋ ከማርያም እጅግ ከፍ ያለ ቢሆንም በማርያም ሆድ ውስጥ የነበረው ጽንስ መድኃኒት እንደሆነ ስለገባት ውሎዋን ከማርያም ጋር ማድረግን መረጠች።
እንዲሁም ሔዋን ነገሯ የተበላሸው ውሎዋን ከአዳም ጋር ማድረግ ሲገባት ከእባብ ጋር ንግግር ማድረግ እና መዋል የጀመረች ቀን ነበር።
ዛሬም የእግዚአብሔር ጸጋ ተሰጥቶን የልጅነት ሥልጣን ተሰጥቶን ውሎአችን እንደ ልጅነታችን ካልሆነ ችግር ውስጥ ነን ማለት ነው።
፨ ብዙ ጊዜ መፍራት ያለብን ውድቀትን ሳይሆን ውሎን ነው። ምክንያቱም ውድቀትን የሚያመጣው ውሎ ሊሆን ይችላልና።
- ሶምሶን ከውሎው የተነሳ በደሊላ ወደቀ
- ሰለሞን ከውሎው የተነሳ ለአማልክት ሰገደ
- ደግሞም ዳንኤል አዋጅን በመቀየር ከጸሎት (ከውሎው) የተነሳ ለንጉሡ ሕልሙንም ፍቺውንም ገለጠ።
ውሎአችን እንደ እግዚአብሔር ልጆች የተቃኘ ይሁን
እግዚአብሔር ይርዳን🙌🙌🙌!
አሜን!!!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
#ሀዋሳ_የሕይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን
#ዓመታዊ_ኮንፍራንስ
“አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።” መዝሙር 46፥1
በሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከነሀሴ 12 - 16/2013 ዓ/ም ዓመታዊ ኮንፍራንስ ይካሄዳል።
👉ረብዕ ከ10: ሰዓት ጀምሮ የመክፈቻ ፕሮግራም
👉ሀሙስና አርብ ከጠዋት 3:00- 6:30 ፤ ከሠዓት ከ8:00-11:30 የአገልጋዬች የትምህርት ጊዜ
👉ቅዳሜና እሁድ ቀኑን ሙሉ ኮንፍራንስ
👉ከሀሙስ እስከ እሁድ 11:30 እስከ 2:00 የፀሎት ጊዜ
በፕሮግራሞቹ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ሁላችሁም በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa
እሑድ 20/10/2013
በፓ/ር መንገሻ ጥላሁን
መንፈስ ይሙላብን
" መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤"
ኤፌ. 5:18
- ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ተጉዞ ከአማኞች ጋር ሲገናኝ የጠየቀው የመጀመሪያው (ዋናውና ወሳኙ) ጥያቄ ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር።
"...ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን?"አላቸው። እነርሱም። አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት።"
የሐዋርያት ሥራ 19:2
- ጳውሎስ መልሳቸውን ሲያውቅ ያደረገው ነገር እጁን ጭኖ መጸለይ ነበር እነርሱም መንፈስ ቅዱስን ተሞልተው ትንቢትን ተናገሩ።
"ለአንድ አማኝ ከደንነቱ ቀጥሎ ሊለማመደው የሚገባው ነገር ቢኖር የመንፈስ ቅዱስን ሕይወት ልምምድ ነው!"
ስለዚህ ጳውሎስ በኤፌሶን እስር ቤት ሆኖ የጻፈው ትዕዛዝ መሰል ግን ወሳኝ መልዕክት "መንፈስ ይሙላባችሁ!" ነው።
-እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ በሁለት ነገሮች ሰዎች ሲሞሉ በተሞሉት ነገር ቁጥጥር ውስጥ እንደሚሆኑ ያሳያል:-
1. በወይን ጠጅ (ለጥፋት ሊዳርግ ይችላል)
-ኖህ የወይን ጠጅ በጠጣ ጊዜ ዘፍ. 9:20
- ሎጥ የወይን ጠጅ በጠጣ ጊዜ ዘፍ 19:33
2. በመንፈስ ቅዱስ ( ለመልካም ሕይወት ብቻ)
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሰው ሕይወቱ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ውስጥ ይሆናል። ለዚህም መጽሐፍ ሲናገር "በመንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው" ይላል።
መንፈስ ቅዱስ፦
1. የእግዚአብሔር ኃይል ነው
፨ ያለንበት ዘመን ኃይል የሚያስፈልግበት ዘመን ነው።
፨ዘመኑ የፍጻሜ ዘመን ነው።
፨ዘመኑ አስጨናቂ ዘመን ነው
ስለዚህ ሰው (ክርስቲያን)የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሊሞላ ይገባል።
-ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲወራ እንዲያው ዝምብሎ የመዝናናት ጉዳይ ሳይሆን ኃይል በመሞላት የአሸናፊነት ጉዳይ ነው።
"እግዚአብሔር ማሸነፍን አዞልናል!"
-የመጨረሻውን ዘመን አስጨናቂ ጊዜ ማለፍ የሚቻለው በመጨረሻው ዘመን/ቀን በሚፈሰው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው።
2. የመገለጥ መንፈስ ነው
- ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲሞላ በሕይወቱ ሰማያዊ ዕውቀትና ጥበብ መገለጥ ይጀምራል
- አዳዲስ መንፈሳዊ ልምምዶች መገለጥ ይጀምራሉ 1ኛ ቆሮ. 2:9
-መንፈሳዊ ነገር በመንፈስ ውስጥ ይገለጣል፤ የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት መዝገብ በእርሱ ውስጥ ነውና። ቆላ. 2:3
- መንፈስ ቅዱስ ከስጦታዎች ጋር ይመጣል። 1ኛ ቆሮ. 12:4-12
3. ድካምን የሚያግዝ መንፈስ ነው።
ሮሜ 8:26&27
-ሸክማችን ከላያችን ያነሳል ቀንበርን ሰብሮ ያቀልልናል።
- ፈውስ ይሆናል።
Watch "በልዑል መጠጊያ ውስጥ ስትኖር ||ክፍል ሁለት|| ድንቅ ትምህርት በፓስተር ጌቱ አያሌው|YHBC Tube|" on YouTube
https://youtu.be/8aylPzMQihY