" የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።"
ሮሜ 14:17
በዶ/ር እንዳለ ሰብስቤ
« ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።»
ማቴዎስ 24፡4-5
በእሁድ የቃልና አምልኮ ጊዜ ዶ/ር እንዳለ ሰብስቤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከማቴዎስ 24፡4-5 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ በድንቅ ሁኔታ ያካፈሉን ሲሆኑ በዕለቱም ለ39 ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር ቤት መጨመርን በማስመልከት የጸሎት እና የቡራኬ ጊዜ ተካሂዷል።
# የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት የእግዚአብሔር አገዛዝ፥ አስተዳደር (ራሱ እግዚአብሔር የሚያስተዳድርበት መንግሥት ማለት ነው)።
👉 መጥምቁ ዮሐንስም ይሁን ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የአገልግሎታቸው ፍሬ ሀሳብ የእግዚአብሔር መንግሥት መጥታ በመካከላቸው እንዳለች ይናገሩ ነበር።
👉 የእግዚአብሔርን መንግሥት "አሁን ያለውና የሚመጣው" በሚል በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል።
# የፍጥረት ሥርዓት ተቀይሮ (በእግዚአብሔር ሥርዓት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ሲፈጠር) የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንግሥት በሙላት ተገለጠች ማለት ነው። 1ኛ ቆሮ. 15
# ደቀ መዛሙርቱ አሁን ባለችው የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሆነው ገና በሙላት ለምትገለጠው የእግዚአብሔር መንግሥት አብዝተው ጥያቄን ያነሱ ነበር።
# ደቀመዛሙርቱ ከሚጠይቁት ጥያቄዎች በከፊል
1. መምጫው መች ይሆናል? (ጊዜ)
2. የመምጫው ምልክት ምንድነው? (ሁኔታ)
# ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው መምጫውን ከአብ በቀር ማንም እንደማያውቅ እና ነገር ግን ዘወትር ተዘጋጅተን መጠበቅ እንዳለብን ነው።
# ተዘጋጅቶ ለመኖር፦
1. ማንም እንዳያስተን መጠንቀቅ ያስፈልጋል
ማቴ. 24:4 እና ቁ.4
# ሠይጣን ወደ ተዘጋጁትጋ ሲመጣ የመጀመሪያው አመጣጥ በማሳት ነው። ነገር ግን ወደ ማንምጋ ሲመጣ መጥፎ መልክ ይዞ አይመጣም። ይዞ የሚመጣው መልክ የሐዋርያትን፥ የነቢያትን፥ የወንጌላውያንን እና የሌሎች አገልጋዮችን መልክ ይዞ ይመጣል።
ማቴ.7:45-23
👉 ብዙዎች የሚስቱት የተግሳጽ ቃል ስለማይፈልጉ ነው።
#ሐሰተኞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የመግባት መብት አለን ብለው ከሚያነሷቸው ነጥቦች፦
1. በስምህ ትንቢት ተናግረናል
2. በስምህ አጋንንትን አስወጥተናል
3. በስምህ ብዙ ተአምራት አድርገናል የሚሉ ሲገኙበት ነገር ግን ከጌታ ጋር የምንተዋወቀው በምናደርገው ብዙ ተአምራት ሳይሆን በምንኖረው ሕይወት ነው።
#የእግዚአብሔር_መንግሥት ሥርዓት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠበቅበት ሕይወት ነው።
👉 ትክክለኛ ክርስቲያን ሁሉንም ነገር ፈትኖ (መርምሮ) ይቀበላል። የማይፈትን ክርስቲያን አስቸጋሪ የሕይወት ሕፃንነት ውስጥ ነው።
2. በባህሪ መዘጋጀት
ማቴ. 24 እና 25
# በዚህ የመዘጋጀት ሕይወት ውስጥ ሁለት ነገሮች ሊነሱ ይችላሉ። ታማኝነት እና ልባምነት።
#ታማኝነት፦ ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረው የተቀበለውን አደራ በተገቢው ሲይዝና ሲያስፋፋ እና ለእርሱም በሚገባ መንገድ ስንገዛ ነው።
👉ቤተክርስቲያን በታማኞች እንጂ በሰካራሞች መሞላት የለባትም።
👉 ምዕመን ማለት ለክርስቶስ ታማኝ የሆነ ማለት እንጂ የቤተክርስቲያን አባል ማለት አይደለም።
# በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታማኝነትን በፍቅር ልናደርገው ይገባል። ይህ ፍቅር በሦስት ሞዴል ሊከፈል ይችላል።
1. የቀራጮች ሞዴል ፍቅር። ማቴ. 5:45
2. የቤተሰብ.. ሞዴል ፍቅር። ማቴ. 5:47
3. የእግዚአብሔር ሞዴል ፍቅር። ማቴ:48
👉 ስለዚህ በእግዚአብሔር ቤት ፍቅር ውስጥ ታማኝነት፥ እኩልነት (ፍትህ) አለ።
#ልባምነት፦ ይህ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ የሚያደርግ ማለት ነው። ማቴ 7:24
👉 ሕይወታችንን በዓለት ላይ መሥራት ልባምነት ነው። ምክንያቱም በዓለት ላይ መሥራት የሚቻለው ቃሉን ሰምቶ ከማድረግ የሚመጣ ነውና።
3. ምርታማና ውጤታማ መሆን
ማቴ. 25:14
👉 በተሰጠን ጸጋና አገልግሎት ትርፋማ መሆን ያስፈልጋል።
# ከላይ በተሰጠን (ተዘጋጅቶ በመኖር ውስጥ ያለውን)መልዕክት ማለትም ማንም እንዳያስተን፥ በባሪ መዘጋጀት እና ምርታማና ውጤታማ ሆነን አሁን ባለችው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ማለፍ እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን!
...🙌❤️አሜን❤️🙌!..!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
መንፈሳዊ ውጊያ
👉"የገሃነም ደጆች የማይችሉሽ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን"
"ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።"
ማቴ.12:22-30
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ጌቱ አያሌው "የገሃነም ደጆች የማይችሉሽ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን" በሚል ርዕስ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ከማቴዎስ ወንጌል 12: 22-30 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል። በዕለቱም 21 ወንድሞችና እህቶች ጌታን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሲሆን የጌታ እራት መታሰቢያ በጋራ ወስደናል፡ ፡ ጌታ ሰለሰጠን ድንቅ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን፡ ፡
፨ በዚህ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ኃይለኛ" የሚለው ሰይጣንን ሲሆን ነገር ግን የኃይለኛው ኃይለኛ ራሱ ጌታ ኢየሱስ መሆኑንም በተዘዋዋሪ መረዳት ይቻላል።
፨ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ በአጋንንት እስራት ውስጥ ያሉትን ነጻ ማውጣት ነው።
፨ በዚህ ክፍል ውስጥ ቁጥር 26, 27 እና 28 ላይ ኢየሱስ ኃይማኖተኛ ነን ለሚሉ ሦስት ወሳኝ ጥያቄዎችን አንስቷል እነሱም፦
1. "ሰይጣን የራሱን መንግስት ካፈረሰ እንዴት መንግሰቱ ትጸናለች?"
2. "እንዴት ሰይጣን ሰይጣንን ያወጣል?"
3. "እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል የማስወጣ ከሆነ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸዋል?" የሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎችን ቢጠይቅም ትክክለኛ ደቀ መዝሙር ስላልነበሩ ተገቢውን መልስ ማወቅ አልቻሉም።
# "የገሃነም ደጆች" የሚለው ሀረግ የክርስቶስን መንግስት የሚዋጉትን እና የዓለምን የክፋት ኃይል የሚያመለክት ነው።
# የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አካል የሆነ ሰው እጁን በደዌ እና አጋንንት ያደረበት ሰው ላይ ሲጭን የማስወጣት እና የመፈወስ ኃይል ተቀብሏል ማለት ነው።
# ቤተክርስቲያን ከዓለም ኅብረት፥ ከርኩሰት ነገር...ተለይተው የሚሰበሰቡባት የክርስቶስ ማህበር ናት።
# መንፈሳዊ ውጊያን የሚዋጉ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ የሚያሳዩ ሦስት ነገሮች፦
👉1. ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ የተለወጠ ልብ እና የታደሰ አዕምሮ ያላቸው የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብቻ ናቸው። ሮሜ.12:1-2።
# ደቀ መዝሙር ማለት፦ ክርስቶስ የተገለጠለት፥ የክርስቶስን እውነተኛ ቃል (ትምህርት) የተማረ እና የሚማር ማለት ነው።
ማር.3: 13-15
👉 ኃይለኛውን የሚበዘብዙ
1.1. በኢየሱስ የተወደዱ
1.2. የኢየሱስን ድምጽ የሰሙ
1.3. ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሄዱ
1.4. ከኢየሱስ ጋር የኖሩ
1.5. ኢየሱስን የሚሰብኩ
1.6. እጃቸውን በድዊዮች ላይ የሚጭኑ እና
1.7. አጋንንትን በስሙ የሚያወጡ ናቸው።
👉2. በእግዚአብሔር ኃይል እና መንፈስ የተሞሉ እና የእግዚአብሔር ጣት አብሯቸው የምትሰራ ናቸው።
፨ መንፈሳዊ ውጊያን መዋጋት የሚቻለው የእግዚአብሔርን ኃይልና መንፈስ በመሞላት እንጂ ኃይማኖታዊ በመሆን አይደለም።
👉3. የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር የሚለብሱ/የሚያነሱ ናቸው።
# ኃይለኛውን ለማሰር እና መንፈሳዊውን ውጊያ ለመዋጋት እንነሳ ጌታ ኢየሱስም ይረዳናል።
ሃሌሉያ!
🙏❤️አሜን❤️🙏!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#መንፈሳዊ_ውጊያ
በአገልጋይ አዲሴ ቀልብሰው
#እሁድ_የቃልና_የአምልኮ_ጊዜ
"እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።.."
ያዕቆብ 4: 1-12
፨የያዕቆብ መልዕክት በተለይም ምዕራፍ 4 የተጻፈበት ጊዜ ሐሰተኞች የበዙበት ጊዜ ስለነበር ቅዱሣንን ለመመለስ ነው።
፨ የያዕቆብ መልእክት መንፈሳዊ ውጊያ ባልበሰሉት ዘንድ ምን እንደሚመስል ያሳያል።
# መልዕክቱ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ሦስት ነገሮችን ያሳያል:-
1. # በሰዎች መካከል ያለን ጦርነት (በወንድማማች መሀከል በተለይም በክርስቲያኖች መካከል ያለን ጦርነት)
👉 በደሃና በሀብታም መሀከል ያዕቆ.2:1-9
👉 በአሠሪና ሠራተኛ መሀከል ያዕቆ.5:1-6
👉 በአስተማሪዎች መካከል ያዕቆ. 3
👉 በሃሜት ምክንያት 4: 11-12
2. ባልበሰሉት መካከል (በውስጥ ልባቸው) ያለ ጦርነት:-
👉 የብዙ ጦርነቶች መነሻ ውስጣዊ ጦርነት ነው ሲሆን ለምሳሌ- ምኞት
- ራስ ወዳድነት
- የሥጋን ድምጽ መስማት
3. ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ጦርነት
👉 እግዘብሔርን ትቶ ዓለምን መውደድ
# ሰው በሰላም ለመኖር ከፈለገ ከሦስት ነገሮች ጋር ኅብረት አለመፍጠር ይጠበቅበታል።
# ዓለም፦ ከእግዚአብሔር ህልውና መለየት
# ሥጋ፦ ከአሮጌው አዳም የተወረሰ ማንነት
# ዲያብሎስ፦ ተሳዳቢ ማንነት
# ክርስቲያን ለአንዴና ለመጨረሻ ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ ነው። ዕብ.10:10
፨ በመንፈሳዊ ውጊያ ሊረዱን የሚችሉ ሦስቱ የያዕቆብ ምክሮች፦
#1. ለእግዚአብሔር መገዛት። ያዕቆ. 4:7
#2. ወደ እግዚአብሔር መቅረብ። ያዕቆ. 4:8
#3. በጌታ ፊት ራስን ማዋረድ። ያዕቆ. 4:9-10
፨👉 በሚገጥመን መንፈሳዊ ውጊያ ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ነገሮችን መቃኘት ይሁንልን!!
❤️🙏አሜን🙏❤️!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#ንጹህ_አምልኮ_ምንድነው?
በፓስተር እንዳልካቸው ተፈራ
"አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።"
ያዕቆብ 1:26-27
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ በፓስተር እንዳልካቸው ተፈራ "ንጹሕ አምልኮ ምንድነው?" በሚል ስለ ትክክለኛው አምልኮ በያዕቆብ 1: 26-27 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ አካፍለውናል።
# እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ እና እንደ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል "ንጹህ አምልኮ ምንድነው?" ለሚለው ጥያቄ
1. ንጹህ አምልኮ አንደበትን መግታት/መግራት ነው።
👉 ማንም "ጤነኛ ነኝ" የሚል ሰው በተፈጥሮው አንደበቱን የሚገራ ነው። በተጨማሪም ክርስቲያን ሲኮን ደረጃውን ይጨምራል። ምክንያቱም አምልኮ በንግግር ስለሚገለጽ ያልተገታ/ያልተገራ አንደበት አምልኮን ያቆሽሻልና። ይህ ማለት ደግሞ ሰው ጌታን ሲቀበል ልቡ ይለወጣል ማለት ነው።
፨ በሳይንስ የተደገፈ ማስረጃ ይኑር አይኑር ባይታወቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግን ልብና አንደበት ግንኙነት እንዳላቸው ያሳያል። ሉቃስ 6:45፥ መዝ. 19:14
2. ችግርተኞችን መርዳት። ያዕቆብ 1:27
# ወላጆች የሌላቸውንና ባልቴቶችን መጠየቅ/መርዳት። ይህ ንጹህና በተግባር የሚታይ አምልኮ ነውና።
3. በቅድስና መኖር። ያዕቆብ 1:27
# ከዚህ ዓለም ዕድፍ ራስን መጠበቅ።
፨ ከላይ እንደተጠቀሰው "ንጹህ አምልኮ ምንድነው?" ለሚለው ጥያቄ ሦስት ነጥቦች የተጠቀሱ ሲሆን "እንግዲህ ምን ማድረግ አለብን?" የሚል ጥያቄ መፈጠሩ አይቀርምና ምላሽ የሚሆነን ደግሞ:
1. አንደበትን መግራት አለብን። ያዕቆብ 3:6-10
2. ችግረኞችን እንርዳ።
#ሀ. ከግል ቤተሰቦቻችን እንጀምር ። 1ኛ ጢሞ. 5: 8
#ለ. የእምነት ቤተሰቦችን እንርዳ። ገላ. 6:10
#ሐ. ሕዝባችንን ሁሉ እንርዳ። ኢሳ. 1:10
፨ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ከሰጠ እኛም ራሳችንን ለወንድማችን ልንሰጥ ግድ ይለናል።
# ዮሐ 3:16 ላይ የተጻፈው ቃል በ1ኛ ዮሐ. 3:16 በተግባር እንድንፈጽመው ያሳያል።
3. በቅድስና እንኑር። ያዕቆብ 2:1-5።
፨ እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው በይበልጥ ቅድስናን ነውና የተቀደሰውንና ንጹህ የሆነውን አምልኮ እንድናቀርብለት እግዚአብሔር ይርዳን!
🙌❤አሜን❤🙌!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
" በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"
ትንቢተ ሚልክያስ 3:10
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንጌላዊ አብራሃም ሴባ በሚልኪያስ 3:7-12 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍሎናል።
# አሥራትንና መባን አለመስጠት ከእግዚአብሔር ሥርዓት ፈቀቅ ማለት ነው።
፨ ወደ እግዚአብሔር ከምንመለስበት መንገድ አንዱ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር በመስጠት ነው።
# መስረቅ ማለት የአንድን ግለሰብ ንብረት ያለ ፈቃዱ መውሰድ ብቻ ሳይሆን የግለሰቡን ነገር ያለ ፈቃድ ራስጋ ማቆየትም ስርቆት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ለእግዚአብሔር የሚገባውን እኛጋ ካቆየን ሰርቀነዋል ማለት ነው።
ሀ. #አሥራትን በአግባቡ አለመስጠት ምንን ያመጣል?
1. #እርግማን: እርግማን ደግሞ፦
- ተሸናፊ ያደርጋል
- ስኬትን እንዳናገኝ ያደርጋል
- ወደ ፊት እንዳንሄድ ያደርጋል
፨ ባለ መስጠት የመጣ እርግማን በመስጠት ብቻ ይለቃል።
2. #ሰማይን ይዘጋል: ሰማይ ሲዘጋ ደግሞ
- ራዕይ የለም
- ሕልም የለም
- ሰላም የለም
-እኛና እግዚአብሔር አንገናኝም ማለት ነው።
3. #ፍሬ ያጠፋል:
- ነነገርን ሁሉ ፍሬ እንዳይኖረው ያደርጋል።
4. #ፍሬ ያረግፋል:
- የደረሰ ነገር ሁሉ ይረግፋል (ይጨነግፋል) ማለት ነው
ለ. #አሥራትን በአግባቡ ለሚሰጡ ሰዎች ምን ይሆናል?
1. በረከት ይሆናል
2. ሰማይ ይከፈታል
3. ነቀዙ ይገሰጻል
4. የእግዚአብሔር ስም በእሱ ላይ ይፈራል (ይከብራል)።
#እግዚአብሔር ለቤቱ በአግባቡ ሰጪዎች ያድርገን።
...🙏አሜን🙏....!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#የክርስቲያን_የደስታውና_የስኬቱ_ምንጩ_ምንድ_ነው?
#ፓስተር_ጌቱ_አያሌው
“ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል፤ ” ፊል 4፥18
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ጌቱ አያሌው የክርስቲያን የደስታውና የስኬቱ ምንጭ ምንድነው? በሚል ርዕስ በፊሊ 4:10-20 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል።
እስረኛ የሆነ ነገር ግን የደስታው ምንጭ ከውስጡ የሚወጣ ሰው ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ
ይህንን መልዕከት የፃፈው ለማመስገን ነው ነገር ግን እኔ የእናንተን ስጦታ ፈላጊ አይደለሁም አስባችሁ ስለላካችሁ አመሰግናለሁ። በሕይወቴ ስለጉድለት ስለማጣት አላወራም።
👉"በተሰሎንቄ እንኳ ሳለሁ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ያስፈለገኝን ሰዳችሁልኝ ነበርና።
በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም።" ፊል 4: 16-17
👉“ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቼአለሁ።” ፊል 4፥18
#የክርስቲያን_የደስታውና_የስኬቱ_ምንጭ
➽የክርስቲያን የደስታው ምንጭ ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወቱ ማዕከል ማድረግ ነው።
“ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።” 2ኛ ቆሮ 6፥10
እንዲኖርህ የምታስበው ሁሉ የደስታህ ምንጭ ሊሆን የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትህ ማዕከል ሲሆን ብቻ ነው።
ኢየሱስ የህይወታችን ማዕከል ከሆነ ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል ማለት እንችላለን።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወትን ጥያቄ የሚሞላ ሙላት ነው።
የዚህ መፃፍ ዓለማ የክርስቲያን የመኖር ዓላማውና የሕይወት ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ለመግለፅ ነው።
➽የክርስቲያን የደስታው ምንጭ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እርሱ ሲመለስ ነው።
“እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።” መዝ 17፥15
የእግዚአብሔርን ቃል በልቡ ሰውሮ በአዕምሮ ማሰላሰል ነው የስኬት ምንጭ
“አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።”
መዝ 119፥11
ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወታችን ማዕከል አድርገን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል ማለት እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን።🙏🙏
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
መዝሙር 85:8
''እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።''
#New Coming video Clip
#Wudase Worship Team
#ሰላም ለኢቲዮጲያ💚💛❤
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#መንግሥተ_ሰማይ
(የእግዚአብሔር መንግሥት ዛሬ እና ነገ)
" ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።"
ማቴ 4:23
" ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።"
ማቴ. 5:10
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ኢያሱ ሰለሞን "የእግዚአብሔር መንግሥት ዛሬ እና ነገ" በሚል ርዕስ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4: 23 እና ምዕራፍ 5: 10 እንዲሁም ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በማጣቀስ ድንቅ የሆነ መልዕክት አካፍለውናል።
# የማቴዎስ ወንጌል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በስፋት ከሌሎች ወንጌላት ይልቅ የተጻፈበት ነው።
# የእግዚአብሔር መንግሥት ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሲነሳ አንዱና የመጀመሪያው እንዲሁም ዋናው ጉዳይ ራሱ እግዚአብሔር ነው። ራዕይ 21:3
#👉 የእግዚአብሔር መንግሥትን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን
1. ዛሬ (አሁን ባለንበት ዓለም ያለው) የእግዚአብሔር መንግሥት እና
2. ነገ (በሙላት ሊገለጥ ያለው) የእግዚአብሔር መንግሥት።
#ሀ. የዛሬው የእግዚአብሔር መንግሥት
# በዚህ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ጥያቄ ሁሉ ላይመለስ ይችላል። አንዳንዱን ነገር ሰው የማያውቀው እና እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀው ነው።
👉 ይህቺ መንግሥት በሙሉ ሳይሆን በከፊል የተገለጠች ናት።
# ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ሆኖ አገልግሎቱን ገና ሊጀምር አከባቢ መጥመቁ ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እያስተማረ እና ሰዎችም ንስሐ ይገቡ ዘንድ እያወጀ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን ኢየሱስ መገለጥ ሲጀምር የዮሐንስ አገልግሎት እየቀነሰ መጣ። ይህ ማለት ለዋናው እና ለሚመለከተው አካል አገልግሎቱን አስረከበ ማለት ነው። በተጨማሪም ዋናው ትኩረት ኢየሱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱ አንድ ጥያቄ ኢየሱስን እንዲጠይቁት አደረገ። "የሚመጣው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ..." የሚል ሲሆን ኢየሱስም በቂ መልስ እንደሰጠ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
👉ሉቃስ 7:18-23
# "የእግዚአብሔር መንግሥት የት ነው?" ከተባልን የምናሳየው ሥፍራን፥ ሀገርን፥ ቦታን...ወዘተ ሳይሆን የእግዚአብሔር አገዛዝ፥ ሥርዓት እና ሥራውን ጠንቅቀን ልናውቅ ግድ ይላል።
👉 ማቴ 5: ቁ21፥ ቁ 27፥ ቁ 33 እና ቁ 43..
# ኢየሱስም ሆነ ከእርሱ ጋር እና በኋላም የተነሱት ሐዋሪያት ትምህርታቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነበር።
# ይህንን የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዴት እናውቃለን?
👉 የእግዚአብሔር መንግሥት ሕገ መንግሥቱ በእጃችን ያለ ሲሆን ዋንኛው የምንዳኝበት የሕገ መንግሥቱ መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል (መጽሐፍ ቅዱስ) ነው።
#ለ. ሊገለጥ ያለው የእግዚአብሔር መንግሥት
👉 በሙላት እና በፍርድ የምትገለጥ ናት።
# የእግዚአብሔር መንግሥት በክብር እና በኃይል የምትገለጥበት ዘመን አለ። እስከዚያው ድረስ ግን ቤተክርስቲያን በዚህ መልኳ ትቀጥላለች። አንድ ቀን ግን በትክክለኛዋ መልኳና ገጽታዋ ትገለጣለች።
👉 ራዕይ 7:13-17
ራዕይ 21: 1-4
# ስለዚህ በምንኖርበት ሕይወት ሁሉ በዚህችኛዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ እየተዘጋጀን መኖር ይጠበቅብናል። ለዚህም እግዚአብሔር በኃይሉ ይርዳን!
...አሜን 🙏❤️🙏...!!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ሕዝቅኤል 12፥28
#መንፈሳዊ_ውጊያ
በወንጌላዊ (ዶ/ር) ተስፋዬ በላቸው
"#በሰው_ልማድ_ምንም_እንኳ_የምንመላለስ_ብንሆን፥ #እንደ_ሰው_ልማድ_አንዋጋም!"
2ኛ ቆሮ. 10:3
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንጌላዊ (ዶ/ር) ተስፋዬ በላቸው #መንፈሳዊ_ውጊያን በሚል ርዕስ 1ኛ ቆሮ 10:3 እና ከሮሜ 13:11 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል፡ ፡
፨ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናይ ከዘፍጥረት ምዕራፍ 3 እስከ ራዕይ ምዕራፍ 20 ድረስ ሙሉ በሙሉ ጦርነትን (ውጊያን) እንመለከታለን።
፨ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ሲሆን እሱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ የተዋጋበት ጦርነት ነው።
፨ በብሉይ ኪዳን ዘመን ጦርነት የሚጀምሩት የእሥራኤል ጠላቶች እንጂ ሕዝበ እሥራኤል አልነበረም።
# የብሉይ ኪዳን ሦስት የውጊያ ልምምዶች:
1. ቅድመ ጦርነት (ከውጊያ በፊት)
2. በጦርነት ወቅት እና
3. ድኅረ-ጦርነት (ከውጊያ በኋላ)
# 1. ቅድመ ጦርነት: በብሉይ ኪዳን ከውጊያ በፊት ያለው ልምምድ ሕዝበ እሥራኤል ራሱን ይቀድስ የነበረበት ልምምድ ነበር።
# 2. በጦርነት ወቅት: ይህ ልምምድ ደግሞ በውጊያ ወቅት የእግዚአብሔር ታቦት አብሯቸው ይሆን ነበር።
# 3. ድኅረ-ጦርነት: ከውጊያ በኋላ ድሉ የእግዚአብሔር ስለሆነ ሕዝቡ በምሥጋና ተሞልቶ ይዘምር የነበረበት ዓይነት ልምምድ ነበር።
# እግዚአብሔር ሲዋጋ:
1. የሕዝቡን የሥጋና የደም ጠላቶች ይዋጋ።
2. ሰው ካልታዘዘው ራሱን (ሰውየውን) ይዋጋል።
3. በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል (የመለኮታዊ) ተዋጊነት ያደርጋል።
# ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረ ጊዜ በመሞት መሸነፍ በሚመስል መልኩ ተዋግቶ በትንሣኤው ዓለምን አሸነፈ።
👉# በኢየሱስ ያመነ ሁሉ በመንፈሳዊ ውጊያ ማለፍ ግድ ይለዋል።
👉# በዓለም ውስጥ መኖራችን ራሱ ውጊያ ውስጥ እንድንሆን ያደርገናል።
👉# የሰይጣን ማንነት በራሱ ውጊያ ውስጥ እንድንሆን ያደርገናል።
# መንፈሳዊ ውጊያ ማለት ምን ማለት ነው?
👉 መንፈሳዊ ውጊያ ማለት ከጠላታችን በተቃራኒው መቆም ማለት ሲሆን ጠላታችን:
1. ዲያብሎስ
2. ሥጋና ደም የለበሰ ወንድማችን ነው።
👉 መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ነን ስንል በሚታየው በገሃዱ ዓለም እንዳለው ሳይሆን:
1. የብርሃንን ጋሻ ለብሰን መሆን አለበት።
2. በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳን የሰውን ሀሳብ ማፍረስ ሲቻል።
3. ለውጊያው ኃይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲመጣ።
# አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ እንቅልፍ ላይ ከሆነ መንፈሳዊ ውጊያን መዋጋት አይችልም።
የሐዋ. 20:7-12
# መንፈሳዊ እንቅልፍ ማንቀላፋት ማለት ለመንግሥተ ሰማይ ትኩረት አለመስጠት ማለት ነው።
# ስለዚህ እንድንነቃ እና ድል እንድናደርግ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
1. የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ (ማጥናት)
2. በክርስቶስ የሆነልንን ነገር ማወቅ ይጠበቅብናል።
# እግዚአብሔር በቃሉ ሙላት አድርጎን እና በክርስቶስ የተደረገልንን ሥራ አውቀን ሁልጊዜ እንደ ወታደር ነቅተን መንፈሳዊ ውጊያችንን እስከ መጨረሻው እንድንፈጽም ይርዳን!
❤️❤️❤️🙏አሜን🙏❤️❤️❤️!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#መንፈሳዊ_ውጊያ
በፓስተር ብርያን
" በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና"
1ኛ የጴጥ. 5:8
# አንድ ክርስቲያን በየዕለቱ ሦስት ጠላቶችን እየተፋለመ ይኖራል።
1. ዓለም
2. ዲያብሎስን እና
3. ሥጋ
# እነዚህን ውጊያዎች አሸንፈን ከሄድን እያደግን እንሄዳለን። እየተሸነፍን ከሄድን ግን እየደከምን እንሄዳለን። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች አሸንፈን መኖር ከፈለግን
. በእምነት ወደ ጸጋው መግባትና
. በደህንነት በኩል የተገኘልን የጸጋ ሕይወት ውስጥ መግባት ይጠበቅብናል።
# በክርስቶስ ጸጋ ውስጥ ካለን ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
*. አሁን እንደተወለዱ ሕጻናት የቃሉን ወተት መመኘት። 1ኛ ጴጥ. 2:2-3
*. ክርስቶስን ወደ መምሰል ሕይወት ማደግ አለብን። ኤፌ. 4:1-3
# ከላይ ያየናቸው ነጥቦች እጅግ ወሳኝ ሀሳቦች ቢሆኑም ክርስቲያን ግን ትልቁ ተግዳሮት ማደግን አይፈልግም። በዚህ ውጊያ ውስጥ ለሰይጣን ትልቁ ድል ደግሞ አንድ ክርስቲያን ሁልጊዜ ሕጻን እንደሆነ እንዲቆይ ማድረግ ነው።
ይህ ማለት ደግሞ ሁልጊዜ ያ ክርስቲያን ሥጋዊ ነው ማለት ሲሆን የሰይጣን አሸናፊነት ማረጋገጫ ነው።
፨ አንድ ክርስቲያን "አደገ!" ከተባለ ጠንካራ ምግብ ተመጋቢ ነው ማለት ነው።
👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ በዕድሜ ያረጁ ነገር ግን በእምነታቸው ሕጻናት የሆኑ ብዙዎች ናቸው። 1ኛ ቆሮ. 3:1
👉 በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 ላይ የተጻፈው በቀጥታ መንፈሳዊ ውጊያን ተዋግተው ለሚያሸንፉ ክርስቲያኖች የተጻፈ ነው።
# መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ኢየሱስ የተሰጠን ስጦታችን ሲሆን ቤተክርስቲያን ባለ አገልግሎት የሚያገለግሉ አምስቱ የአገልግሎት ዘርፍ አገልጋዮች ይህንን ስጦታ በጥበብ ካልያዙ ቤተክርስቲያንን ከማሳደግ ይልቅ እንድትቀጭጭ ያደርጋታል።
# በሕይወታችን መንፈስ ቅዱስ የሚለንን ነገር አጣርተን መስማት ከቻልን ግን እያደግን እንሄዳለን። ስለዚህ አገልጋዮች በተሰጣቸው ጸጋ እርስበርሳቸው ሊደማመጡ እና ሊግባቡ ይገባል።
👉 በ1ኛ ቆሮ 3 ላይ እንደተጻፈው የጳውሎስ ምክር በመጨረሻው ቀን የፍርድ ሂደት የሚከናወነው በተገነባው መሠረት ላይ የተመረኮዘ ስለሚሆን መሠረታችን በጽኑ አለት ላይ ሊሆን ይገባል።
# እግዚአብሔር ራሱ በራሱ ጸጋ ውጊያውን አሸንፈን የምንሄድ ሰዎች ያድርገን!
....🙌❤️አሜን❤️🙌....!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
የመስጠትና የመቀበል ስሌት
በፓስተር በኃይሉ በራሶ
" የፊልጵስዩስ ሰዎች ሆይ፥ ወንጌል በመጀመሪያ ሲሰበክ፥ ከመቄዶንያ በወጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን #በመስጠትና_በመቀበል_ስሌት ከእኔ ጋር እንዳልተካፈለች እናንተ ደግሞ ታውቃላችሁ፤"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:15)
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ከአማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በፓስተር ኃይሉ በራሶ "የመስጠትና የመቀበል ስሌት" በሚል ርዕስ በፊልጵስዩስ 4: 10-20 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል።
# በመንፈሳዊው ዓለምም የመስጠትና የመቀበል ሥርዓት ከሚጠበቀው በላይ ይሰራል። ነገር ግን አሁን በዚህ ዘመን ባለችው ቤተ ክርስቲያን ጎልቶ የሚታየው ሥርዓት የመስጠት ሳይሆን የመቀበል ሥርዓት ነው።
፨ ከወንጌል አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሁልጊዜ ጳውሎስ የመቄዶንያን ቤተ ክርስቲያን ያነሳል። በዋናነት ደግሞ የሚያነሳት ከመስጠት ጉዳይ ጋር ነው።
# ጳውሎስ የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን ስለመስጠት ሲያስተምር በዋናነት የሚያነሳው የመቄዶንያን ቤተ ክርስቲያን ነው። 2ኛ ቆሮ. 8:1
# ሰዎች መስጠትን ሲያስቡ አብሮ ሊነሳ የሚገባው ጉዳይ የ'ጸጋ' ጉዳይ ነው። ያለ እግዚአብሔር ጸጋ ማንም መልካም ነገር አይችልም።
# ለመቄዶንያ ቤተ ክርስቲያን የነበራት ጸጋ፦
1. እላያቸው ላይ ከነበረው ችግር/ተግዳሮት ይልቅ ደስታቸው የበዛ/የላቀ ነበር።
- ከደረሰብን መከራና ችግር ይልቅ እግዚአብሔር በውስጣችን ያፈሰሰው ደስታ እጅግ የላቀ ነው።
2. ከድህነታቸው ጥልቀት ይልቅ በልግስናቸው የሚታወቁ ናቸው። 2ኛ ቆሮ. 8:2
- እንደ አቅማቸው ብቻ ሳይሆን ከአቅማቸው በላይ አብዝተው የሚሰጡ ናቸው።
2ኛ ቆሮ. 8:3
3. ለመስጠት የሚለምኑ ናቸው። 2ኛ ቆሮ. 8:4
- ቅዱሣንን ለመርዳት በሚደረግ አገልግሎት የሚለምኑ ነበሩ።
4. ራሳቸውን ለጌታ የሰጡ ናቸው። 2ኛ ቆሮ. 8:5
- ራሱን ለጌታ የሰጠ ሰው ምንም ቢሆን ለጌታ ሊሰጥ አይሳሳም።
# ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ብዙ ነገር ስለ መቄዶንያ ሰዎች ከተናገረ በኋላ ስለራሳቸው ስለ ቆሮንቶስ ሰዎች " በእናንተ ላይ ትምክት አለኝ!" ይልና ደግሞ ሲናገር "እባካችሁ የመቄዶንያ ሰዎች ወደ እናንተ በመጡ ጊዜ አታሳፍሩኝ" ይላቸዋል። ይህን ያለበት ምክንያት በስጦታ ጉዳይ የመቄዶንያ ሰዎች ወደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ የቆሮንቶስ ሰዎች በመስጠት ከመቄዶንያ ሰዎች ወርደው እንዳይገኙ ስላሰበ ነው። አስቀድሞ ጳውሎስ ስለ መቄዶንያ ሰዎች ልግስና በደንብ ነግሯቸዋልና። 2ኛ ቆሮ. 9:4
# የምንቀበለው ነገር ስሌት የሚለካው በምንሰጠው መጠን ስለሆነ ከምንቀበለው ይልቅ አብዝተን ሰጪዎች እንድንሆን እግዚአብሔር በጸጋው ይርዳን
... አሜን🙏❤🙏...!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
➲https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
➲https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
'እኔ ሰጥቻለሁ እናንተስ?"
በፓስተር አበራ ጉንታ
"ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?"
1ኛ ዜና 29:14
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ አምልኮ ፓስተር አበራ አበራ ጉንታ "እኔ ሰጥቻለሁ፤ እናንተስ?" በሚል ርዕስ ስለ መስጠት ድንቅ መልዕክት ለጉባኤው አስተላልፈዋል።
# አንድ ክርስቲያን ስለ መስጠት ሲያስብ ቶሎ ወደ አዕምሮው ሊመጣ የሚገባው ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ለእግዚአብሔር መስጠትን ነው።
# ሰው ከመስጠቱ በፊት አስቀድሞ ማወቅ ያለበት የሚሰጠው ነገር/ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የሰውየው ማንነት ራሱ ለእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
፨ ቅዱሱ መጽሐፍ የሚለን "#እኛ ራሳችን ወይም ዓለምና ሞላው የእርሱ ነውና።"
መዝ . 50:12
፨ እንዲሁም በሐጌ መጽሐፍም ሲናገር "ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው" ይላልና።
ሐጌ. 2:8
# ያፈሩት ንብረት ቀርቶ ራሳቸው ለእግዚአብሔር መሆናቸውን የዘነጉ ሰዎች እንዲሁም እግዚአብሔር እንደ ዳዊት ከመሬት ያነሳቸው ሰዎች ዛሬ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መልሰው መስጠት ከብዷቸው ተቅበዝባዥ ሆነዋል።
# እህታችን ሐና ግን ከእግዚአብሔር የተቀበለችውን (ሳሙኤልን) መልሳ ለእግዚአብሔር በመስጠት የታወቀች ትልቋ ምሳሌያችን ናት።
# ሀብታችንን (ያለንን) ለእግዚአብሔር ከምንሰጥባቸው መንገዶች በጥቂቱ፦
1. #አሥራት: ከአሥር አንዱ የእግዚአብሔር ነው።
2. #በኩራት: ከምናገኘው የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ነው።
3. #መባ: ደስ ያለንን ለእግዚአብሔር ቤት የምንሰጠው ነው።
4. #ምጽዋት: ራሳቸውን መርዳት ለማይችሉ የሚንሰጠው ስጦታ ነው።
5. #የፍቅር ስጦታዎች: እግዚአብሔርን ስለምንወድ እና ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የምንሰጣቸውን የፍቅር ስጦታዎችን ያመለክታል።
፨ ከላይ የተጠቀሱት እንደ ዋና ቢታዩም ራሳችን የእግዚአብሔር ከመሆናችን እና ያለን ነገር ሁሉ ከእርሱ የተቀበልነው ከመሆኑ የተነሳ የምንሰጠው ነገር ሁሉ በፍቅር እና ያለ ማንም ቀስቃሽነት ሊሆን ይገባል።
# እግዚአብሔር አምላክ በፍቅሩ ብዛት ነክቶን ያለ ማንም ቀስቃሽ ወደን እና ፈቅደን ሁልጊዜ ሰጪዎች እንድንሆን ይርዳን!
#ሁሉ ከእርሱ፥ በእርሱ እና ለእርሱ ነውና ለዘለዓለም ክብር ይሁንለት!
🙏አሜን🙏!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#የሚበልጥ_ደስታ
በፓስተር መንገሻ ጥላሁን
“ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።” ኢሳ 9፥3
የሰው ሁሉ መውጣት መውረድ ድካም መዳረሻው ደስታን ማግኘት ነው። ሰው ምንም እንኳ ደስታን ሊያገኘው የሚጥረው ቢሆንም ሰው ደክሞ ከሚያገኘው የሚበልጥ ደስታ እግዚአብሔር አዘጋጅቷል። ይህ ደስታ ከራሱ የሚወጣ ደስታ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የደረሰ ደስታ ነው።
" ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል። "
መክብብ 8:15
፨ የሰው ልጅ በሕይወቱ ውስጥ ደስታ አስፈላጊውና መሠረታዊው ነገር ሲሆን ሰው በሰራው እና በለፋው ነገር ውጤቱን አይቶ መደሰት አምላካዊ ፈቃድ ያለበት ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ሳንደክም ከራሱ የሚመጣ እና ከሁሉ የሚበልጥ ደስታን አዘጋጅቶልናል።
፨ ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ700 ዓመተ ዓለም ስለዚህ ደስታ በትንቢቱ ተናግሯል። ይህም ደስታ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
👉 እግዚአብሔር በክርስቶስ እንድናገኘው የሰጠን ደስታ በማግኘት በማጣት በሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ደስታ ሳይሆን እንዲሁ ራሱን ኢየሱስን ወደ ውስጣችን ስንጋብዘው የምናገኘው እውነተኛ ደስታ ነው።
ሉቃስ 2:8-11
👉 ጌታ የሚፈልገው እኛ በምናገኘው ነገር ተደስተን እንድንኖር ሳይሆን ራሱ (እሱ በሚሰጠን ደስታ) ብቻ ተደስተን እንድንኖር ይፈልጋል።
# ከጌታ የምንቀበለው ደስታ ምን ዓይነት ነው?
1. የሚበዛ ደስታ ነው። መዝ. 4፡7-8
2. የማይወሰድ ደስታ ነው። ዮሐ. 16:22
3. በመከራ ውስጥ የሚያስዘምር ደስታ ነው። የሐዋ. 5:41, 1ኛ ተሰ. 1:6, የሐዋ.13:52
4. ፍጹም የሆነ ደስታ ነው። ዮሐ.16:24
# ክርስቶስ የሚበልጥ ደስታችን ነውና በዚህ ደስታ ውስጥ ለዘላለም መኖር ይሁንልን🙏❤🙏!
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#የክርስቲያን_ስኬት
"እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ
➽የተመረጠ ትውልድ፥
➽የንጉሥ ካህናት፥
➽ቅዱስ ሕዝብ፥
➽ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።"
1ጴጥ 2:9-10
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንጌላዊ ሀርኪሶ ሀዬሶ የክርስቲያን ስኬት በሚል ርዕስ ከ1ጴጥ 2 : 9 - 10 ባለው ክፍል በመመስረት ድንቅ ቃል አካፍሎናል።
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#የክርስቲያን_ስኬት_እና_ደስታ!
"የማይተካውን በምንም አልተካም!!"
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ነቢይ ተመስገን አየለ የጌታን ቃል ያካፈለ ሲሆን "የማይተካውን በምንም አልተካም!" በሚል ርዕስ ድንቅ እና ትንቢታዊ የሆነውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
" ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር.....።"
ዘጸአት 33:9-18
# እሥራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ በተጓዙበት ምድረ በዳ ሁሉ የእግዚአብሔርን ተአምራዊ እጅ አይተዋል።
# ቀን በደመና እና ሌሊት በእሳት አምድ ሲመራቸው እንደነበር ከራሳቸው በላይ ሌላ ምስክር የለም!
# ሲራቡ መና በልተው ሲጠሙም ከአለቱ ጠጥተዋል።
፨ ነገር ግን ተርቦ ከእጁ የበላ ሕዝብ፥ ተጠምቶም ከእጁ የረካ ሕዝብ በማይረባ ሁኔታ የማይተካውን ጌታ በሚተካ ነገር ለመለወጥ ፈለገ። በወርቅና በብር ጌጣጌጥ ምስል አምላኩን ለማስመረር ፈለገ።
፨ ሙሴም የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ራሱን እንዲለይ ቁርጥ እና አቋምን የሚጠይቅ የውሳኔ ጥያቄ ለሕዝቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም በሙሴ በኩል ሕዝቡን እንዲወስን አስጠነቀቀ። እግዚአብሔርም የወሰኑትን ለማወቅ ሕዝቡን በሙሴ በኩል ማርና ወተት ወደምታፈልቀው ምድር ወደ ከነዓን እንደሚገቡ ቃል ገባ።
የሚገርመው ነገር ግን ሙሴ ለእግዚአብሔር የመለሰው መልስ ሲሆን እሱም "ዋናው ነገር የሚበላና የሚጠጣን ነገር መውረስ ሳይሆን የማይተካው የእግዚአብሔር አብሮነት ከእነርሱ ጋር እንዲሆን ነበር።
👉 በዘመናችን እግዘብሔር ብዙ ነገር ሊሰጠን ሊያቀርብልን ይችላል ነገር ግን ሁሉ ዳግም ሊተካ የሚችል ነው። የእኛ ምርጫ መሆን ያለበት ግን አስቀድመን የማይተካውን ራሱን እግዘብሔርን መፈለግ ነው።
አስቀድመን የማይተካውን ራሱን እግዚአብሔርን መፈለግ ይሁንልን!!
አሜን🙏!!!!!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#የታላቅ_እምነት_ምልክቶች
ወንጌላዊ ፀጋአብ በቀለ
ማቴ 15 :25-28
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ወንጌላዊ ፀጋአብ በቀለ "የታላቅ እምነት ምልክቶች" በሚል ርዕስ በማቴ 15:25-28 ባለው ክፍል በመመስረት ድንቅ ቃል አካፍሎናል።
➾የክርስትና ጅማሬ በእምነት ነው፣ ኑሮውም በእምነት ነው የምናጠናቅቀውም በእምነት ነው።
ያለ እምነት ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት አይቻልም። መጽሐፍ ቅዱስ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንደማይቻል ይናገራል።
“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።” ዕብ 11፥6
የተለያየ የእምነት ዓይነቶች እንዳሉ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
➲የሌለ እምነት “እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ #እምነት_የላችሁም? አላቸው።” ማር 4:40
➲የጎደለ እምነት “እርሱም፦ እናንተ #እምነት_የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ” ማቴ 8፥26
➲ታላቅ እምነት:- በአዲስ ኪዳን ለሁለት ሰዎች ብቻ የተጠቀሰ የእምነት ዓይነት
👉“ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ #ትልቅ_እምነት አላገኘሁም።” ማቴ 8፥10
👉“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ #እምነትሽ_ታላቅ_ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።” ማቴ 15፥28
➢እምነት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ነው።
#ታላቅ_እምነት_ምልክቶቹ ምንድናቸው?
1. የአካባቢውን መንፈስ ሰብሮ መውጣት የሚችል
2.ያለፈን የኋላ ጎታች ታሪክ አስትቶ ወደ ፊት መሄድ የሚችል
3.ጌታን ባየነው ዓይን ችግርን/ሁኔታን ማየት የሚያስችል
➽ከማግኘት መቀበል ስሌት ባለማግኘት አንተን ወደ ማምለክ እሻገራለሁ ። ሀዘኔ ከላዬ ባይነሳ የጠበቅኩት ባይሆን አመልካለው። የታላቅ እምነት ምልክቱ ይሄ ነው።
"እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።" ማቴ 15:23
“እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።” ማቴ 15፥25
➲ታለቅ እምነት የሚወለደው በታላቅ ተግዳሮት ፊት ለፊት ነው።
“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።” ማቴ 15፥28
በሕይወት ጨለማው ሲጠክር ነገሮች ሲዘጋጉ ተግዳሮቶቻችን ሲያይሉ እምነታችን ወደዚህ ወደ ታላቅ እምነት ሊያድግ ነው ብለን እግዚአብሔርን ማምለክ ይኖርብናል።
ዛሬም ባቃተን መካከል በጎደለው መካከል በታላቅ እምነት መቆም ይሁንልን።
🙌❤🙏አሜን
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#ከቅዱሳንና_ከቤተክርስቲያን_የጠፋች_እንቁ
ፓስተር ጌቱ አያሌው
“አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፤ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።
ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።” ዘዳ 10:20-21
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ጌቱ አያሌው በዘዳ 10:20-21 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ "ከቅዱሳንና ከቤተክርስቲያን ስለ ጠፋች እንቁ 'እግዚአብሔርን መፍራት' ድንቅ ቃል አካፍለውናል።
👉እግዚአብሔርን መፍራት ከቅዱሳንና ከቤተክርስቲያን የጠፋች ዕንቁ ናት።
እግዚአብሔርን መፍራት የአንድ አማኝ የህይወቱ እንቁ ነው። እግዚአብሔርን መፍራት የሌለበት አምልኮ፣ አገልግሎት ከነፍስ የተለየ ሰጋ ነው።
“አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፤ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።” ዘዳ 10፥20
እግዚአብሔርን መፍራት ከእርሱ ጋር መጣበቅ የአንድ አማኝ የሕይወቱ ልምምድ ነው።
👉እግዚአብሔር ከግብፅ ከባርነት ቀንበር ነፃ ላወጣው ሕዝብ የሰጠው አንድ መርሆ በሕይወቱ ዘመን እግዚአብሔርን መፍራትና እርሱን ማክበር ዋናው ሕግ ይሆነው ዘንድ ነው
“አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ ➢አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ
➢እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥
➢ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት።” ዘዳ 6 :1-2
ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ከመሰናበቱ በፊት የነገራቸው ይህ ነው። በምትገቡባት በዚያች ምድር እግዚአብሔር እንድትጠብቁ የሰጠኝ ትዕዛዝ እግዚአብሔርን እንድትፈሩና ትዕዛዙን እንድትጠብቁ ነው።
➢ #ያዳነ_ከባርነት_ቀንበር_ነፃ_ያወጣህ #አምላክ_ከአንተ_ምን_ይፈልጋል?
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ
➾አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥
➾በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥
➾አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥
➾በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው?”
ዘዳግም 10፥12-13
እግዚአብሔርን መፍራት የሌለበት አገልግሎት ከንቱ ነው
ምሳ 1:7 ፣ምሳ 30:1፣ ኢዮ 28:12-28
በዓለም ላይ ትልቁ ጥበብ ትልቁ ዕውቀት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሌላው ከምድር በታች የሚቀር ነው።
ታላላቆችን ማክበር :የእግዚአብሔር ትዕዛዝን መጠበቅ እግዚአብሔርን ከመፍራት ውስጥ ይወጣል።
➽ #እግዚአብሔርን_መፍራት_ማለት_ምን_ማለት_ነው?
1. የእግዚአብሔርን የቅድስናውን፣ የፍርዱን፣ የኃይሉንና የክብሩን ማንነት አውቆ ለስሙ የሚገባውን ክብርና አምልኮ መስጠት ማለት ነው።
ዘዳ 4:24፤ ዕብ 12:28-29፤ መዝ 33:8፤ መዝ 96:4-9
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ምስጋናውም ብዙ ነው።
2. ለእግዚአብሔር ስልጣንና ፈቃድ በመገዛት የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝና በመጠበቅ መኖር ነው
ዘፍ 22:9-18 "......የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።
➢ ለሰማነው ለእግዚአብሔር ቃል ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው እግዚአብሔርን መፍራት።
3. እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን ነገር መምረጥና በእርሱ ሀሳብ ለመወረስ በፊቱ መዘርጋት ነው።
“እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም አፍ እጠላለሁ።”
ምሳሌ 8፥13
“ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው።”
ምሳሌ 22፥4
➾ እግዚአብሔር መፍራት ከሚያስገኙልን በረከቶች ➢እግዚብሔር መጠጊያና መታመኛ ይሆንልናል።
እግዚአብሔርን የሚፈሩ አንዳች አያጡም።
“የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።” መዝሙር 34፥9
➢እግዚአብሔርን የሚፈሩ ረጅምን እድሜ ይኖራል።
“ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።” መዝሙር 91፥16
➲"አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥
➾መብራት አብርታ
➾ቤትዋንም ጠርጋ
➾እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ፦ የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።" ሉቃ 15:8-9
➽ዛሬ ቤታችንን እንጥረግ ፣መብራታችንን እናብራ የጠፋብንን እንቁ አጥብቀን እንፈልግ
ከቤታችን የጠፋው ከአገልግሎታችን የጠፋውን እንቁ የሆነውን እግዚአብሔርን መፍራት እንፈልግ።
🙌❤🙏አሜን
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw
#እግዘብሔርን_መፍራት
" እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው...." መዝ 33:18
"የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ሚፈሩት ያያሉ!"
በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ አምልኮ ወንጌላዊ ሰለሞን ገበየሁ "የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ሚፈሩት ያያሉ!" በሚል ርዕስ ድንቅ እና ወሳኝ ለጊዜው አስፈላጊ የሆነውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
መዝሙር 33:18
" እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው...."
# እግዚአብሔርን እየፈራን ስንኖር አንዳንድ ጊዜ አንገታችንን የሚያስደፉ እና የማይመቹ ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ለዚህም ነው አሳፍ በጽድቅ መንገድ እየሄደ ሳለ በአንድ ወቅት "በኃጢአተኞች ቀናሁ" አለ። ነገር ግን ወዲያው ፈጥነው እንደሚጠፉ አወቀ።
፨ ለምንድነው የእግዚአብሔር ዓይኖች እርሱን በሚፈሩት ዙሪያ የሚሆኑት?
1. ከሞት ሊያድናቸው
# ዓለም ስለማትመች ከተለያዩ ምድራዊ መከራዎች ቅጥር ለመሆን የእግዚአብሔር ዓይኖች እርሱን በሚፈሩት ዙሪያ ይሆናሉ።
2. በረሃብ ዘመን ሊመግባቸው
# እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች እግዚአብሔር ካልታሰበ ቦታ/ነገር ይመግባቸዋል።
# እግዚአብሔርን የሚፈሩና የማይፈሩ ሰዎች ምልክት፥ መገለጫ እና መታያ፦
1. እግዘብሔርን የማይፈራ ሰው ምልክት፦
ሀ. ክፉና ጨካኝ ይሆናል
ሉቃስ 18:2-3
ለ. ህሊና ቢስ ይሆናሉ
1ኛ ጢሞ. 1:19
# ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ቢያነብ ቢያነብ በህሊናው እግዚአብሔር እንዳለ ያውቃል።
2. እግዘብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ምልክት፦
ሀ. ጠቢባን ይሆናሉ
ምሳሌ 1:7
፨ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
ለ. በጽድቅ እና በቅድስና ይኖራሉ።
1ኛ ሳሙ. 12:18
፨ በጽድቅና በቅድስና ስንኖር እግዚአብሔር ራሱ ከሰማይ ይመሰክርልናል።
ሐ. ለራሱና ለልጆቹ ተከምራትን ያኖራል።
2ኛ ነገሥት 4:1
፨ ስለዚህ እግዘብሔርን በመፍራት ውስጥ ብዙ በረከት ይገኛል። ለእኛም ደግሞ እርሱን በመፍራት በሚገኝ በረከት ውስጥ ማለፍ እንዲሆንልን እግዚአብሔር በጸጋው ይርዳን።
አሜን🙏❤🙏!!
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa