yhbchawassa | Unsorted

Telegram-канал yhbchawassa - ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

-

“ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ፦ እኔ እሞታለሁ፤ #እግዚአብሔርም_መጎብኘትን_ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል።” ዘፍጥረት 50፥24

Subscribe to a channel

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/K_FROhdGdy0

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#አገልግሎት
#እኛ_የእግዚአብሔር_የእጅ_ሥራ_ነን
አገልጋይ ደረጀ ባዩ

📖 “እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።"
ኤፌ 4:1-13

#በእሁድ_የቃልና_የአምልኮ_ጊዜ የጌታን ቃል ያካፈለን ወንድም ደረጀ_ባዩ_ሲሆን "#እኛ_የእግዚአብሔር_የእጅ_ሥራ_ነን" በሚል ርዕስ ስለ አገልግሎትና ስለ ተጠራንበት ሕይወትና ምክንያት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከኤፈሶን ምዕራፍ 4:1-13 ያለውን ክፍል መሠረት በማድረግ ድንቅ መልዕክት አካፍሎናል።

# ይህ የኤፌሶን መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ላይ ያለውን ክፍል ጳውሎስ ከመናገሩ እና ከመለመኑ በፊት ቀድም ብለው በተጻፉት ምዕራፎች ውስጥ የመንበርከክ ሕይወት እንደነበረው ያሳያል።

፨ ለቤተክርስቲያን ከተጻፈው ከጳውሎስ ድንቅ መልዕክቶች ውስጥ አንዱ የኤፌሶን ቤተክርስቲያን መልዕክት ነው።

* እግዚአብሔር በኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ላይ እንደተገለጸው በዘመን ፍጻሜ ሊያደርግ ያሰበው ሰማይንና ምድርን አቀራርቦ እና አንድ አድርጎ በክርስቶስ መጠቅለል ነው።

* በኤፌሶን 2: 14 ላይ ሲናገር የጥልን ግድግዳ አፍርሶ አንድ አዲስን ሰው መፍጠርን ነው። ይህቺም አዲስ ሰው ቤተክርስቲያን ናት።

* እንዲሁም በኤፌሶን ምዕራፍ 3:10 ላይ ደግሞ በቤተክርስቲያን በኩል የጥበቡን ሥራ መግለጥ ነው። በመጨረሻም እነዚህን ሁሉ ከተናገረ በኋላ ጳውሎስ ስለ አለቆችና ሥልጣናት መልዕክት ያስተላልፋል።

#_የጳውሎስ_ሦስት_ልመናዎች

1. የመንፈስ አንድነትን መጠበቅ ኤፌ.4:3

፨ ጳውሎስ እነዚህን ልመናዎች በሰባት "አንዶች" አጥብቆ ይለምናል። በቅድሚያ ግን "በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።" ይልና እነዚህን ከቁጥር 4-6 ይዘረዝራል፦

- አንድ ተስፋ
- አንድ አካል
- አንድ መንፈስ
- አንድ ጌታ
- አንድ ኃይማኖት
- አንዲት ጥምቀትና
- አንድ አምላክን ይገልጻል።

👉 አንድነታችን መሠረታችን ነው!!

፨ አጋንንት የማይወደው ነገር ቢኖር አንድነት ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ዓለም በብዙ መንገድ የተከፋፈለችና በመለየት (በፍቺ) የተሞላች ናት። ይህንንም ሁኔታዋን ሰይጣን አዲስ ሰው ወደ ሆነችው ወደቤተክርስቲያን ሊያስገባ ሥራውን በረቀቀ መንገድ ያከናውናል። ለዚህም ነው ጳውሎስ አንድነታችንን እንድንጠብቅ እና በትጋት እንድናገለግል የሚለምነው።

# ይህንን_አንድነት_እንዴት_እንጠብቅ?

- በትህትና
- በየዋህነት
- በትዕግሥት
- በፍቅር
- በሰላም

2. በክርስቶስ ወዳለው ፍጹም ሙላት (ሰው) አዳጊዎች መሆን። ኤፌ. 4:13

- እውነትን በፍቅር እየያዝን እና እየገለጥን ወደ ክርስቶስ ማደግ።

- በፍጹም እድገትን አለማቆም።

3. በተሰጠን ጸጋ አገልጋዮች እንድንሆን። ኤፌ.4፡7

- እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን በተሰጠን ነገር ላይ ትኩረት ሰጥተን እናገልግል

# "ጸጋው ለምን ተሰጠን?" ከተባለ
“ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።” የሚል ቃል ስለተሰጠን ነው።
ኤፌሶን 4፥12-13

፨ በተጠራነው መጠራት መኖር እና ማገልገል ይሁንልን!!

...🙏❤🙏አሜን🙏❤🙏...!!!
ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን
#የፌስቡክ_ገፃችንን_ይወዳጁ_ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/QKJt7I4ZKnY

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/ywcjhTaO0kY

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/qcMZTqImFyY

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

''ለእግዚአብሔር መንግሥት ዓላማ የሚኖሩ እጆች!"
በአገልጋይ አዲሴ ቀልብሰው


የሐዋ. 20:33-35


"ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።

የሐዋ.20:33-35

# በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ አገልጋይ አዲሴ ቀልብሰው "ለእግዚአብሔር መንግሥት ዓላማ የሚኖሩ እጆች" በሚል ርዕስ በሐዋ 20 ፡33-35 መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል፡ ፡

# ከላይ የተጠቀሰውን የመልዕክቱን ርዕስ ማጠናከር የሚችሉ ሦስት ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ የጌታን ቃል አካፍለዋል።

1. የሚሠሩ (የሚያገለግሉ) እና የሚጸልዩ እጆች

፨ እጅ የሌላቸው ሰዎች እጅግ እንደሚቸገሩ ለማወቅ ብዙም አያስቸግርም።
እግዚአብሔር እጅን የሰጠን እንድንሰራበት ሲሆን ሰውን ከፈጠረ በኋላ በዔድን ገነት ሲያስቀምጠው እንዲሰራበትም ጭምር ነው። ዘፍ.2:15

👉 እግዚአብሔር ራሱ የተገለጠበት መንገድ አንዱ ሥራ ነው። ምክንያቱም በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ፈጥሮ (ሰርቶ) አሳየ። ዘፍ.1:1

# በሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍም እንዳየነው ከጳውሎስ የምንማረው እጆቹ እንደሚሰሩ እንጂ ለማንም ባለመሰራቱ ምክንያት ዕዳ ሆኖ አይደለም።

👉 እጆቹ ለተፈጠሩበት(ለእግዚአብሔር መንግሥት) ዓላማ ይኖሩ ነበር።

# እሱ በሚያደርገው ነገር ሁሉ እጆቹ በትጋት የሚያደርጉ ሲሆን በተለይም አንዱ ጸሎት ነበር።

👉 የቅዱሳን እጆች የሚጸልዩ ናቸው። 1ኛ ነገሥ. 8:22,38፥ ኢዮብ 11:13-15፥ ዘፀ. 17:10-13 እና 1ኛ ጢሞ. 2:8

፨ እጃችን እየሠራ እና እየጸለየ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲስፋፋ ያግዛል። ይህ ማለት በተዘዋዋሪ እየሠራን ሌሎችን ልናግዝ (ልንረዳ) ይገባል።

2. በሥራ እንጂ በምኞት የሚኖሩ አይደሉም።

፨ ጳውሎስ የዚህን ዓለም ሸቀጥ የሚመኝበት ልብም፥ ዓይንም፥ ጆሮም እንዲሁም እጅም አልነበረውም። ፊልጵ. 3: 8-12። ምክንያቱም የዚህን ዓለም ነገር የሚመኝበት ነገር እውነቱ የበራለት'ለት ከዓይኑ ቅርፊት ወድቆለት ነበር። በዓለም እየኖረ ለእግዚአብሔር የኖረ ታማኝ ባሪያ ነበር። ስለዚህ ከዚህ የተነሳ ምኞቱም ጉጉቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር።

👉 ምኞት፦ ማለት እግዚአብሔር በሰጠን ነገር አለመርካት ማለት ነው። ዘፀ. 20:17

3. ትጉህ እጆች ናቸው እንጂ ሰነፍ እጆች አይደሉም!

፨ በድካምና በጥረት መሥራት መልካም ነው። 2ኛ ተሰሎ. 2:8

👉 ጳውሎስ ራሱ እየደከመ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያሰፋ እና ያገለግል ነበር።

👉 ስንፍና ኃጢአት ሲሆን ሰነፍ ደግሞ ሳይሰራ መብላትን የሚወድ ነው።ምሳ. 24: 30-34

👉 ችግራችንን ማሸነፍ የምንችለው በጸሎት ብቻ አይደለም። በጸሎትና በሥራም ጭምር እንጂ!!

ለሥራ ያለን አመለካከት

# የሥራ ትንሽ እና ትልቅ እንዳለው መቁጠር!

ለምሳሌ ሀ)፦ ሸክላ ሰሪ፥ ቀጥቃጭ...የመሳሰሉት ሥራዎች የተናቁ ናቸው ብሎ መቀበል። የሚገርመው ደግሞ ሰውን ከአፈር የሰራው እግዚአብሔር ራሱ ሸክላ ሰሪ መሆኑን አለማወቅ። ምክንያቱም ሰው ከአፈር የተሰራ ሸክላ ነውና!!

ለ)፦ ግብርናን መሥራት ያልተማረ ሰው ሥራ ብሎ መረዳት። ኢየሱስ ሲናገር "እውነተኛው የወይን ግንድ እኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው!" ይላል። ይህ ማለት እግዚአብሔር በገበሬ የተመሰለው ትክክለኛ ሰራተኛ ስለነበር ነው። ከዔደን ገነት ጀምሮ የተፈጠሩ ሥራዎች በሙሉ የእርሱ ድንቅ የሥራ ውጤቶች ናቸውና።

# እግዚአብሔር እጆቻችንን ለመንግሥቱ ዓላማ እንዲኖሩ ያድርጋቸው!!

...❤️❤️❤️🙏አሜን🙏❤️❤️❤️...!!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#እግዚአብሔርን_ደስ_የሚያሰኝ_መሥዋዕት!
በነቢይ ተመስገን አየለ

ሮሜ 12: 1-11

" እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።"
ሮሜ 12:1

# በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ነቢይ ተመስገን አየለ #እግዚአብሔርን_ደስ_የሚያሰኝ_መሥዋዕት!" "በሚል ርዕስ ድንቅ ቃል አካፍለውናል።

# በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ በሐዋሪያት ሥራ ውስጥ ጳውሎስ አሳዳጅ እንደነበር ይታወቃል። ይህም አሳዳጅነት ከላዩ ላይ የተገፈፈው በደማስቆ መንገድ ላይ በተገለጠ ታላቅ ብርሃን ሲሆን የሮሜ መጽሐፍንም የጻፈው ከዚህ በኋላ ነው። ይህ ብርሀን ከበራለት በኋላ 13 መጽሐፍትን ጽፏል።

# ጳውሎስ ስለ ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት ሲናገር አጥብቆ በመለመን ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፡

1. አንድ አማኝ ሙሉ ለሙሉ ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ መሆን አለበት።

- ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ገንዘቡን፥ ጊዜውን፥ ንብረቱን ለእግዚአብሔር መስጠት አይከብደውም።

👉 ምድራችን የምትለወጠው ራሱን ለእግዚአብሔር በሰጠ ሰው ነው።

👉 ጳውሎስ ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ስለነበር መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ሊሰራ አልከበደውም።

2. በልብ መታደስ የተለወጠ (ይህንን ዓለም የማይመስል) መሆን አለበት?

👉 "ልበ ንጹሐን እግዚአብሔርን ያዩታል!"
👉 ሰው ልቡ ተበላሽቶ ሊዘምር ሊሰብክ ይችላል።

- ልብ ጤነኛ ሲሆን አካል በመሉ ጤነኛ ይሆናል

👉 ልብህ አጠገብህ ላለው ሲመች ለእግዚአብሔር ትመቻለህ ማለት ነው።

# ቃየልና አቤል ሁለቱም መስዋዕት ይዘው ቢቀርቡም እግዚአብሔር ግን ወደ አቤልና ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ። የቃየልንን ግን አልተቀበለም። ምክንያቱም ልቡ የተበላሸ ነበር።

3. አጠገባችን ያለ ሰው አስፈላጊ እንደሆነ ማሰብ

# የተለያየን ብልቶች ብንሆንም አንዳችን ለሌላችን አስፈላጊ ነን።

👉 አንዱ ያለ ሌላው ምንም ነው!

👉 የትጋትን እና ከልብ የመሥራትን ፍላጎት እግዚአብሔር የሚወደው ነው። ልባችን ለዚህ የተነሳሳ መሆን አለበት።

እግዚአብሔር ወደሚፈልገው መሥዋዕት ውስጥ መግባት ይሁንልን!!!

...❤❤❤🙏 አሜን🙏❤❤❤...!!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#የክርስቶስ_መከራ_እና_የትንሣኤው_ኃይል"
በፓስተር ዳዊት ላምቤቦ

"መልዕክተኛ ስለሆንኩኝ ተረኛ ነኝ!"

"ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።
እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።" ማር. 16:1-20

በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ዳዊት ላምቤቦ "የክርስቶስ መከራና የትንሣኤው ኃይል" በሚል ርዕስ ድንቅ መልዕክት አካፍለዋል።
# የኢየሱስ ተከታዮች (ደቀመዛሙርት) ከኢየሱስ ሞት እና ከትንሣኤው በኋላ በተለያየ ሀዘን፥ ተስፋ መቁረጥ እና የልብ ስብራት ውስጥ ቢገኙም ኢየሱስ ግን ድጋሚ በመገለጥ መልዕክተኛ እንደሆኑ እና መሄድ ወዳለባቸው ቦታዎች እንዲሄዱ ነግሯቸዋል።

# በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይ ኪዳን ሳምሶን ናዝራዊ (የተለየ) ሲሆን ወደ ፍልስጤማውያን መንደር መውረዱ መልዕክተኛ ስለነበር ነው። መጨረሻው ያላማረው የተላከበትን ጉዳይ አለመተግበሩ እንጂ ከጅማሬው መልዕክተኛ ነበር።

# መልዕክተኛ እግዚአብሔር ከላከው እና ወዴት እንደሚሄድ ካወቀ በፍጹም ሳይፈራ ካለበት ሁኔታ እና ወደሚሄድበት ቦታ ይወጣል።

# ጌታ ኢየሱስ ተከታዮቹን ከምን ከምን አወጣቸው?

1. ካለማመን አወጣቸው

2. ከጥንካሬያቸው(ግትር ከሆኑበት)፥ ከቅዠታቸው እና ከነቀፌታቸው አወጣቸው

3. ተስፋ ከቆረጡበት አወጣቸው

# ሐዋሪያቱ ከኢየሱስ ሞት በኋላ የተነገራቸውን የተስፋ ቃል እስኪረሱ ድረስ በተለያየ ሀዘን፥ ተስፋ መቁረጥና ጭንቀት ወድቀው ነበር።

👉 ሰይጣን አንዱ እና ትልቁ የውጊያ ስልት መልዕክተኞችን የተነገራቸውን የተስፋ ቃል ማስረሳት ነው። ከሐዋርያቱም አዕምሮ የተነገራቸውን የኢየሱስን ዳግም ከሞት መነሳት አጥፍቶ ነበር።

👉 መልዕክተኛ መሆናይን ሲገባን ካለንበት ቅርቃር እንወጣለን!

# ስለዚህ ኢየሱስ ካሉበት እንዲወጡ፦

👉 ውስጣቸው እንዲቃጠል አድርጎ ዓይናቸውን አበራ።

👉 በተዘጋ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን አለ።

# ዛሬም ጌታ ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገው እንደ ንቁ መልዕክተኛ የተነገረንን የተስፋ ቃል አጥብቀን እንድንይዝ እና በተገቢው መንገድ መልዕክቱን እንድናስተላልፍ ነውና እግዚአብሔር በጸጋው ይርዳን።

❤️❤️❤️🙏አሜን🙏❤️❤️❤️!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

"እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ #መጽሐፍ_እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
#መጽሐፍም_እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥"
1ቆሮ 15 : 3-4
https://youtu.be/yfyn1NtrCAo

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/NGki4aCsaIM

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/Fal61AWz9M8

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/TZpybWxcUo8

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/DBWc0_BdzOI

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#የእግዚአብሔር_መንግሥት
በፓስተር ዮሴፍ በቀለ
እሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ


" ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።"
ማቴ. 13:44-47

# በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብቻ በማቴዎስ ወንጌል ወደ 34 ጊዜ እንደ ተጠቀሰ ይነገራል።

# የእግዚአብሔር መንግሥት ጠቅልሎ የያዘው፦
፨ ንግሥናውን
፨ አገዛዙን እና
፨ ሕዝቡን የያዘ ነው።

# የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው ለአይሁድ አማኞች ነው። ምክንያቱም፦
👉 ዓለም በሙሉ በሮም አገዛዝ ውስጥ ስለነበር
👉 በገዛ ሀገራቸው ሙሉ ሥልጣን ተወስዶባቸው ስለነበር ነው።

# አይሁድ የሉዓላዊነት ጥያቄ ስለነበረባቸው ስለ መንግሥት መመለስ በተደጋጋሚ ኢየሱስን ይጠይቁት ነበር።

# ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማይ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ስለነበር ከትንሣኤ በኋላ አርባ ቀን በምድር ቆየ።

# የትንሣው ጉልበት/ኃይል የሚገለጥበት ዋናው መንገድ በቤተክርስቲያን በኩል ነው። ለዚህም ኢየሱስ ለቤተክርስቲያን ሥልጣንን ሰጥቷታል።

# ማቴዎስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በተለያየ መንገድ የገለጠ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ "በእርሻ ውስጥ የተሰወረች መዝገብ/ሀብት ትመስላለች" በማለት ገልጿል።

በማቴዎስ 19:16-22 ላይ አንድ ባለጠጋ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ ሰው የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ማድረግ የሚጠበቅበትን ነገር ሲጠይቀው ኢየሱስ ተገቢውን መልስ ሲሰጠው እና ሰውየውም በኩራት ሁሉን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እንደጠበቀ ያስረዳ ነበር። ኢየሱስም ያለውን ሽጦ ለድሆች እንዲሰጥና እንዲከተለው ሲነግረው ግን እያዘነ ሄደ። ምክንያቱም ለእሱ የእግዚአብሔር መንግሥት ጉዳይ ካለው ሀብት በታች ስለተቆጠረ ነው። ነገር ግን እውነቱ ከዚህ በፍጹም የተለየ ነው።

👉 በሕይወታችን መፍራት ያለብን የከበበንን ምርጥ ነገር ነው። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዳይበልጥብን ነው። ምድራዊ ሰዎች ሀሳባቸው ምድራዊ ነው።
ፊልጵ 3:19

ኢየሱስ ያዳነን ተራ ነገር ሰጥቶን ሳይሆን ነፍሱን እርቃኑን በመሆን ሰጥቶን ነውና ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር መንግሥት በሚያበቃን ቁመና ላይ መሆን ይገባናል።

ፈጽሞ የማይገባንን ነገር ጌታ ግን " አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።" በማለት መንግሥቱን ሰጠን።
ሉቃስ 12:32

ይኸንን ከተቀበልን ደግሞ አጥብቀን መያዝ፥ መወሰን እና መከተል ይገባናል።

#በብሉይ ኪዳን ስለ መንግሥቱ ጉዳይ ዳንኤል ወደ አንበሳ ጉድጓድ እስከመውረድ የወሰነ ሲሆን በዚህም ውሳኔ መጨረሻው ድል የእሱ እንደሆነ አሳይቷል። እንዲሁም ኖህ ለ120 ዓመት ሙሉ መርከብ ሲሰራ አንድ ሰው አልተቀበለውም። ነገር ግን የማይታየውን ተረድቶ በእምነት መርከብ አዘጋጀ። በጽናት ስለ መንግሥቱ ጉዳይ እንደ ሞኝ ተቆጥሮ በድል ተወጥቷል።

👉 እኛም ደግሞ ፍጹም የሆነው መንግሥት እስኪመጣ በዚያች ውብ ከተማ ከበጉ ጋር ለዘላለም ለመኖር በውሳኔ፥ በጽናት መኖር ይሁንልን!

...🙌❤️አሜን❤️🙌...!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#የእግዚአብሔር_መንግሥት

በፓስተር መንገሻ ጥላሁን

#የሚበልጠውን_መፈለግ
ማቴ. 6:24-33

“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
ማቴዎስ 6፥33

# በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በቃል ያገለገሉን ፓስተር መንገሻ ጥላሁን ሲሆኑ "የሚበልጠውን መፈለግ" በሚል ርዕስ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6: 24-33 እና ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በማጣቀስ ድንቅ የሆነ መልዕክት ያካፈሉን ሲሆን በመጨረሻም ሁለት አዳዲስ ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተጨምረዋል።

➽ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅ ትኩረት የሰጠው ጉዳይ ቢኖር የእግዚአብሔር መንግሥት ጉዳይ ነው። ማር. 1:15

➽ አጠቃላይ የአዲስ ኪዳን (ወንጌላት) መጽሐፍት የተሞሉት በእግዚአብሔር መንግሥት ትምህርት ጉዳይ ነው።

➽ ከትንሣኤ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ በትኩረት ይናገር የነበረው ሀሳብ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ጉዳይ ነበር። የሐዋ. 1:1-4

➽ ለነፍሳችንና ለሰውነታችን ከመብልና ከመጠጥ እንዲሁም ከልብስ የሚበልጥ ነገር ያስፈልጋል። እሱም #የእግዚአብሔር_መንግሥት ጉዳይ ነው። ሉቃስ 12:32

➽ የመንግሥቱን ክብር በእኔ ሕይወት ሊያደርግ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኗል። ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን!" የሚለውን ጸሎት ያስተማረው።

➽ አሁን ያለችው የእግዚአብሔር መንግሥት በእኔ ሕይወት ውስጥ ነች።

➢ ዛሬ የሕይወታችን ቅድሚያ ፍለጋ ምንድነው? አስቀድመን የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቅ ልንፈልግ ይገባል።

#የእግዚአብሔርን_መንግሥት_መፈለግ_ማለት_ምንድው?

1. የእግዚአብሔርን ሕይወቱን መፈለግ ነው።

ሀ. የእግዚአብሔርን አስተዳደር፥ አገዛዙን፥
ሕልውናውን ገዥነቱን፥ አዳኝነቱን፥ ባርኮቱን ሁሉ እና ራሱን እግዘብሔርን መፈለግ ነው።
እግዚአብሔር በመጀመሪያ መፈለግ ይፈልጋል ዘዳ 4:29 ፤ ዘፀ 13:2
➲ “ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤” ማቲ 10:37

ለ. ደግሞም የራሱን የእግዚአብሔርን ጽድቅ መፈለግ ነው።

የእግዚአብሔር ባርኮቱን የምናገኘው በእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። ይህም ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት የሚያቆመን የራሱ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። ይህም ጽድቅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጧል። በእግዚአብሔር ፊት ያለፍርሃት እንድንቆም ድፍረት ያገኘንበት ነው።
“...በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤” ፊሊ 3:9
“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” 2ኛ ቆሮ 5፥21

2. የእግዚአብሔርን ሰላምና ደስታ መፈለግ ነው።
“የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” ሮሜ 14:17
➢ የእግዚአብሔር መንግስት ወደ ህይወታችን ሲገባ ወደ ህይወታችን ይዞ የሚመጣው የእግዚአብሔር ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ነው።
ነፍስን፣ መንፈስንና ስጋን የሚያሳርፍ ሰላምና ደስታ
የሐ 14:27፤ ኢሳ 9:7፤ መዝ 4:7-8


3. የእግዚአብሔር መንግስቱንና ጽድቁን ስንፈልግ ፈውስና ነፃነት ይሆንልናል።
የመንግስቱ ወንጌል የኃይል ወንጌል ነው።
“ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።” ማቴ 4፥23
➲ የመንግሥት ወንጌል ሲሰበክ ነፃነት፥ መፈታት፥ መፈወስ ይሆናል። ሉቃ. 4:17-19, ማቴ. 12:28

👉 አስቀድመን የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ሁሉ ከልብ መፈለግ ይሁንልን!!

...🙏❤አሜን❤🙏...!

የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#አገልጋይና_አገልግሎት

📖 “የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።”
ዮሐንስ 12፥26።"

# በእሁድ_የቃልና_የአምልኮ_ጊዜ የጌታን ቃል ያካፈለን #አገልጋይ_በረከት_ዋቤሎ ሲሆን "አገልጋይና አገልግሎት" በሚል ርዕስ ስለ አገልጋይና አገልግሎት እንዲሁም ማንን እና እንዴት ማገልገል እንደሚገባን በማሳየት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 12:26 ያለውን ክፍል መሠረት በማድረግ ድንቅ መልዕክት አካፍሎናል። በዕለቱም በአስደናቂ ሁኔታ 50 ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተጨምረዋል።

# በክፍሉ ላይ እንደሚናገረው የሚያገለግለው ካለ ራሱ ኢየሱስ መንገድን እንደሚያሳይ ነው። ይህም ማለት፦

ሀ. አገልጋዩ ፈጥሮ (ከራሱ) አያገለግልም
ለ. እያገለገለ ከቆየ ኢየሱስ ባለበት ከእርሱ ጋር ይኖራል።
ሐ. ኢየሱስን ካገለገለ አባቱ (አብ) ያከብረዋል። ወይም ደግሞ ከልዑል እግዚአብሔር ክብር ይጠብቀዋል ማለት ነው።

#ምን_ዓይነት_አገልጋይ_መሆን_አለብን?

1. #የአገልግሎታችን_ማዕከል_ኢየሱስ_ማድረግ_አለብን።

* ኢየሱስን ስናገለግል አገልጋዩም ሕዝቡም ማዕከል ሊሆኑ አይገባም። የአገልግሎቱ ባለቤት ራሱ ኢየሱስ እንጂ።

* ልክ እንደ መጥመቁ ዮሐንስ "ኢየሱስ" ብሎ አገልግሎት የጀመረ ሰው የአገልግሎቱ ማዕከልና መዝጊያ ኢየሱስ ሊሆን ይገባል።

* ዮሐንስን በጠየቁት ጊዜ "የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ እኔ አይደለሁም" ብሏል። ምንም እንኳ የሰዎችን ትኩረትና ቀልብ የመሳብ ዕድል በእጁ ቢኖርም የኢየሱስን ባለቤትነት አልወሰደም።

# በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የኢየሱስን ባለቤትነት ከተናገሩት በጥቂቱ፦

፨ ራሱ ዮሐንስ
- " እኔ ስለ ብርሃን ልመሰክር የመጣሁ ነኝ እንጂ ራሴ ብርሃን አይደለሁም ብሏል። ዮሐንስ 1:5

፨ ማርያም
- የወይን ጠጁ ባለቀ ጊዜ እና ተጨንቀው ሳለ ማርያም የሰዎች ትኩረት ወደ እሷ እንዳይሆን በፈለገች ጊዜ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ!" ስትል ወደ ኢየሱስ መራች። ዮሐንስ 2: 5

፨ ኒቆዲሞስ
- ይህ ከፈሪሳዊያን ወገን እና የአይሁድ አለቃ የነበረ ሰው ነው። ነገር ግን ከራሱ አለቅነት ይልቅ ከተያዘበት ጥያቄ ለመላቀቅ ከነበረበት ፍላጎት የተነሳ ገና በሌሊት ወደ ኢየሱስ በመምጣት ሊማር የወደደ ሰው ነው። ደግሞም የኢየሱስን ማንነት የተናገረ ሰው ነው። ዮሐንስ 3: 1-2

፨ ሳምራዊቷ ሴት
- ከአይሁድ የበላይነት የተነሳ ቀና ብላ እንኳ መሄድ ያልቻለችውን ሳምራዊት ሴት በውሃ ጉድጓድ አጠገብ አግኝቷት ታሪኳን ሲቀይር የራሷን ነገር ረስታ ስለ እርሱ ልትመሰክር ወደ ከተማ ሮጠች።
ዮሐንስ 4: 28-30

፨ ሰላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበረው ሰው።
- ይህ ሰው ትክክለኛ ፈውስ የቱጋ እንዳለ ሲያውቅ ስለ ኢየሱስ አዳኝነት በግልጽ ተናገረ። ዮሐንስ 5:11

በእውነት እኛ በግ ነን? አዎ በእርግጥ በጎቹ ነን። ነገር ግን የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ በግ አይደለንም። እርሱ ኢየሱስ ብቻ ነው!

“ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።”
ዮሐንስ 1፥46

👉 በሩም በጉም ኢየሱስ ነው!!

* አገልጋዮች (ሰባኪዎች፥ ዘማሪዎች፥ ነብያት፥ አስተማሪዎች...) ምንም አይደሉም። በእነርሱ የሚሰራው ኢየሱስ እንጂ።

👉 ውሃ የሌለበት ብርጭቆ ጥምን እንደማያረካ ወይም ጥይት የሌለበት ጠብመንጃ ምንም እንደማያመጣ ሁሉ ኢየሱስ የሌለበት አገልጋይና አገልግሎት እንዲሁ ነው።

👉 ሌላ የሚጀምር፥ የሚቀጥልና የሚጨርስ የለም ኢየሱስ ብቻ ጀማሪ ማዕከልና መደምደምያ ነው።

👉 እውነተኛ አገልግሎትና መባረክ ራስን ዝቅ ማድረግና ኢየሱስን ብቻ ማጉላት ነው።

2. #የአገልግሎታችን_መለኪያ_እነዚህ_ይሁኑ

ሀ. #ትሁት_መሆን። ዮሐንስ 13

- ትህትና በእጅ እግር መያዝ ነው።
- መሬት ተቀምጦ ወንበር ላይ ያለውን ማስተናገድ ነው።
- ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ ማየት ነው።

ለ. #እግዚአብሔርን_ማመን።
ዮሐንስ 14

- እግዚአብሔር አባት እንደሌላቸው ልጆች እንደማይተወን ማመን ነው።
- አጽናኝ እንደሚልክልን ማመን ነው
- አሜን ማለት ነው
- አገልጋይ አምኖ ይሰብካል ይጸልያል...

ሐ. #ፍሬ_ይኑረን። ዮሐንስ 15

- ፍሬ የሌለው ነገር ጥቅም የለውም።
- ፍሬ እንደሌለን ካወቅን ለማፍራት ከግንዱ ጋር እንጣበቅ
- ብዙ ለማፍራት መበስበስ ያስልጋል።

መ. #ዋጋ_እንክፈል። ዮሐንስ 16

- አገልግሎት ዋጋ መክፈል ነው። በጥፊ መመታት፥ መረገጥ፥ መታሰር፥ መደብደብ፥ መሞትም ነው። ስለ ወንጌል ሲሉ በአገልግሎታቸው አባቶቻችንም ይህን ተቀብለዋል።
- ያለን ነገር ማጣት ነው

ሠ. #ተቀብሎ_መቀበል።
ዮሐንስ 17

- የመቀበያ ሥፍራ መድረክ ሳይሆን ጓዳ ነው።
- ተንበርክከን የተቀበልነውን ቆመን እንሰጣለን።

👉 ትኩረታችን ኢየሱስ ብቻ ይሁን!!!

...🙏❤🙏አሜን🙏❤🙏...!!
ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን
#የፌስቡክ_ገፃችንን_ይወዳጁ_ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

ሕዝብን አበዛ
ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ
የምስጋናና የመከር በዓል

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#አገልግሎት

📖 “ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”
2 ዜና 29፥11

#በእሁድ_የቃልና_የአምልኮ ጊዜ የጌታን ቃል ያካፈለን የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ #ፓስተር_አበራ_ጉንታ ሲሆን "#ለአገልግሎት_ተጠርተናል" በሚል ርዕስ ስለ አገልግሎት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከ2ኛ ዜና 29: 1-11 እና ከ1ኛ ጴጥሮስ 2:9-10 ያለውን ክፍል መሠረት በማድረግ ድንቅ መልዕክት አካፍሎናል። በዕለቱም 20 ወንድሞች እና እህቶች ጌታን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ተቀብለዋል።

# በ2ኛ ዜና እንደተገለጸው ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚነገርለት ነገር ብዙ ቢሆንም በጥቂቱ፦

👉 ሕዝቅያስ በይሁዳ ምድርን ተሐድሶን ያመጣ ንጉሥ ነበር።

👉 ከሰለሞን በመቀጠል ብዙ ክብርና ብልጽግናን ያገኘ ታላቅ ሰው ነበር።

👉 እግዚአብሔር ሰውን ለአገልግሎት እንደሚመርጥ ጠንቅቆ ያወቀ ሰው (ንጉሥ) ነበር።

# በ1ኛ ጴጥሮስ ላይም የተገለጸው ቃል ለተበተኑት እና በምጻት ምድር ለሚኖሩ የእግዚአብሔርን በጎነት እንዲናገሩ የተመረጡ እንደሆነ ቃሉ ይናገራል።

፨ በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የመረጠን እንድናገለግለው ነው።

👉 ሜልኮል በናቀችው ጊዜ ዳዊት እግዚአብሔር ከአባቷ ቤትና ከእሥራኤል ይልቅ እንደመረጠው ነግሯታል።
2ኛ ሳሙኤል 6:21

👉 ኢየሱስ የተናቁና ማንም የማይመርጣቸውን ሰዎች መርጦ የራሱ ደቀመዛሙርት አድርጓቸዋል።

👉 ጳውሎስም እግዚአብሔር ሊጠቀምባቸው ሲወድ ምን ዓይነት ሰዎችን እንደሚመርጥ ተናግሯል። 1ኛ ቆሮንቶስ 1:26-29

👉 እንዲሁም ጳውሎስ ስለ ራሱ መመረጥ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 1:12 ላይ እና በኤፌሶን 3:8-9 ላይ በድንቅ ሁኔታ ገልጿል።

# የመረጠንን_ጌታ_እንዴት_እናገልግል?

# እግዚአብሔር ማንም ቁጭ ብሎ ተመልካች እንዲሆን አይፈልግም። እናም በተሰማራንበት መንገድ ሁሉ እንድናገለግለው ይፈልጋል። እንዴት?

1. እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት በመኖር

# ይህ ማለት ግብዝነት፥ ማስመሰል...የሌለበት ሕይወት መኖር። ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብዝነትን ይጸየፋልና።

# አገልግሎት ራስን መስጠት ነው። አንዳንድ ሰው አገልግሎት ማለት አደባባይ ቆሞ መስበክ፥ መዘመር...ብቻ ይመስለዋል። ነገር ግን ራስን ለሌላው መስጠት ከአገልግሎት ክፍሎች አንዱ ነው።

👉 ሰዎች የሚያውቁን መልዕክት እኛው ነን። 2ኛ ቆሮ 3:2

፨ በማቴዎስ ወንጌል 5:13-16 ባለው የተራራው ስብከት ኢየሱስ
" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ!"
" እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ!" ብሏል። ስለዚህ ሕይወታችን እንደ ጨው እና ብርሃን ሊሆን ይገባል።

፨ እንዲሁም “ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።” ይላል። ቆላስይስ 4፥6። እንደዚሁም የሚበራ ነገር ለራሱ እየተቃጠለ ለሌላው እንደሚያበራ ሁሉ ክርስቲያንም ለሌላው ሲኖር ራሱን እየሰጠ ነው።

👉 ክርስቲያን እውነተኛ ቃሉን እየሰበከ ያበራል።

2. ባለን ነገር (በተሰጠን ጸጋ) እናገልግል።

“እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤”
ሮሜ 12፥6

በብሉኪዳን ዘመን፦
- የእሥራኤል ሕዝብ በተጨነቀ ወደ ሙሴ ሲጮህ እና ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ሲጮህ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴን ወደ እርሱ ከመጮህ ይልቅ በእጁ በያዘው በትር ወደ መፍትኼ እንዲሄድ (እንዲጠቀም) አድርጓል።

- ዳዊት ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ቢታመንም ጎልያድን የዘረረው ግን በእጁ ላይ በነበረ ወንጭፍ ነው።

- ጌዴዎን በወይን መጥመቂያ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ሲያናግረው እርሱ ግን እንደማይችል እና ከሁሉ ታናሽ እና ደካማ እንደነበር ይናገራል። ነገር ግን እግዚአብሔር "በዚህ በጉልበት ሂድ!" አለው ምድያምንም እንደ አንድ ሰው መታ። በእጁ የነበረው ነገር በጉልበቱ መሄድ ብቻ ነበርና።

በአዲስ ኪዳን ዘመን፦
- ብዙ ሕዝብ በነበረበት እና ምድረ በዳ በሆነ ሥፍራ ምንም የሚበላ ነገር በሌለበት ቦታ ደቀመዛሙርቱ ሕዝቡ ምግብ ወዳለበት እንዲሄድ ፈልጎ ሲጎተጉቱት እርሱ ግን "እጃችሁ ላይ ምን አለ?" አላችሁ። ከብላቴናውም ሁለት ዓሣና አምስት እንጀራ ብቻ ነበር። ያንኑ ወስዶ ባረከ እና ለዚያ ሁሉ ሕዝብ ሰጠ።

👉 እኛ ያለንን ስለማናውቅ እንጂ እግዚአብሔር የሚፈልገው እጃችን ላይ ያለውን እንድንጠቀም እና እንድናገለግልበት ነው።

# ለማገልገል_ምን_እናድርግ?

1. እግዚአብሔር ለአገልግሎት እንደመረጠን እንወቅ

2. የጨውና የብርሃን ሕይወትን እንኑር

3. ባለን (በተሰጠን) ለማገልገል እንዘጋጅ (እንወስን)

# በተሰጠን ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማገልገል ይሁንልን!

...🙏❤🙏አሜን🙏❤🙏...!
ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን
#የፌስቡክ_ገፃችንን_ይወዳጁ_ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#ማመስገንና_መናገር
በዶክተር አንተነህ ታየ


📖 "እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
መዝሙር 105:1-2

# በእሁድ_የቃልና_የአምልኮ_ጊዜ የጌታን ቃል ያካፈለን አገልጋይ ዶክተር አንተነህ ታየ ከ"Sendme Global Mission" ሚኒስትሪ ሲሆን እግዚአብሔርን ስለማመስገን እና ስለ እርሱ መናገርን አስመልክቶ "ማመስገንና መናገር" በሚል ርዕስ ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር 105:1-2 ያለውን ክፍል አካፍሎናል።

፨ በሕይወታችን እግዚአብሔር ተአምር የሚያደርግባቸው መንገዶች እጅግ ብዙ ቢሆኑም በሚከተሉት ሁለት መንገዶች ግን የበለጠ የእግዚአብሔርን ተአምራት ይገልጣሉ።

1. ማመስገንና መናገር
2. የሰራውን ሥራ ማወጅ ናቸው።

፨ ይህ በመዝሙር 104(105):1-2 የተጻፈው ታሪክ የተጨመቀ እና አጠር ብሎ የተቀመጠ የእሥራኤል ታሪክ ነው።

# እግዚአብሔርን ማመስገን ማለት ተአምራቱን ማሰብ ማለት ነው። የተጠራነውም የእግዚአብሔርን ተአምራት እንድናስብ ነው።

# በኢዮብ መጽሐፍ ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር ሲነጋገር "ቁም! የእግዚአብሔርን ተአምራት አስብ!" ብሎታል። ኢዮብ 37:14

# በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ተአምራት እያሰበች እና የሕይወት ታሪኳን እያስታወሰች በወለደች ቁጥር አስደናቂ ስሞችን ለልጆቿ ታወጣ የነበረች ድንቅ ሴት አለች። ልያ (የያቆብ ሚስት)ናት። ዘፍ.29:31-35

- ሮቤል= እግዚአብሔር መከራን ያያል
- ስምዖን= እግዚአብሔር ይሰማል
- ሌዊ= እግዚአብሔር ምርኮን ይመልሳል
- ይሁዳ= እግዚአብሔርን ማመስገን

👉 እግዚአብሔር የሠራልንን ነገር ስንቆጥር (ስናስብ) እግዚአብሔር መከራችንን ያያል። ስለዚህም ያደረገልንን እንድናስብ ይፈልጋል። ሸለቆ ውስጥ ያለ ሰው ቢሆን እንኳን እግዚአብሔር ያደረገለትን ነገር ሲያስብ ተአምር ይሆንለታል። ለዚህ ማሳያ ሌላኛው ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌዴዎን ነው።

#ጌዴዎን በወይን መጥመቂያ ውስጥ ሆኖ "አባቶቻችን የነገሩን ተአምራት ወዴት አለ?" እያለ ሲያስብ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አንተ ጽኑ እና ኃያል...!" ብሎ ጠራው። አልፎም በጌዴዎን ጥቂት እንጎቻ የእግዚአብሔር ኃይል ተጨመሮበት የጠላት ድንኳን ተገለባበጠ። ይህም የሆነው በጌዴዎን ማንነት ሳይሆን በእግዚአብሔር ተአምራታዊ ጉብኝት ነው።

👉 እግዚአብሔር በእኔ ላይ ስለተደመረ ለእኔ ጉልበት ይጨምራል።

# ኢየሱስም ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው። " ያደረኩላችሁን ነገር ታስተውላላችሁን?" ዮሐ.13:12። እግዚአብሔር በሕይወታችንን ያደረገውን ነገር የምናስብ ስንቶች ነን? ኢየሱስኮ እኛን ከማግኘቱ በፊት ወዝ ያልነበረን፥ ሐዘንተኞች... ነበርን። መጽሐፍ ሲናገር፦ “....በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።” ይላልና።
ኢሳይያስ 61፥3

2. የሰራውን ሥራ ማወጅ (መናገር)

# የእርሱን ነገር እንድናውጅ የከበረ ሥራ ተሰጥቶናል። ይህም የኢየሱስን ጌትነት ለዓለም ሁሉ ማወጅ ነው። ኢየሱስ የሌለው ተስፋ የለውም። በኢየሱስ ውስጥ ዘላለማዊ ተስፋና ሕይወት አለ። ስለዚህ ይህ ዘመን ወንጌልን የምናውጅበት ዘመን እንደመሆኑ ሥራችንን ተግተን ልንሰራ ያስፈልጋል።
#_ለምንድነው_ወንጌልን_መሥራት_ያለብን?

1. ሁላችንም ተልከናል። ማቴ.28:19-20

👉 እግዚአብሔር ሁልጊዜ አብሮት መሆን የሚፈልገው ወንጌልን ከሚሰራ ሰው ጋር ነው።

2. የቤተክርስቲያን ተፈጥሮዋ ስለሚያስገድዳት ነው።

፨ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረችው ሚስዮናዊት ሆና ነው።

" እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ!"
" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ!"

👉 ብርሃንም ጨውም ሁለቱም የተፈጥሮ ነገሮች ናቸው አገልግሎታቸውንም በሥርዓቱ የሚያከናውኑ ነገሮች ናቸው። እንዲሁም ቤተክርስቲያንም ለተፈጠረችበት ዓላማ ልትኖር ይገባታል።

3. የንጉሥ ካህናት ስለሆንን ነው።

👉 የንጉሥ ካህናት የሆንነው እና ከጨለማው ወደ ሚደነቅ ብርሃን የተጠራነው የንጉሡን በጎነት እንድንናገር ነው።

4. የቤተክርስቲያንን ሥርዓት የምናደርግ ሁላችን (የጌታን ራት ተካፋይ የሆንን በሙሉ) ወንጌልን እንድንናገር ስለምንገደድ ነው።

👉 ጌታ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ሞቱንና ትንሣኤውን እንድንናገር እንገደዳለን።

# እግዚአብሔር ያደረገልንን ነገር በመናገርና በማወጅ እንዲሁም በማሰብ የሚመጣ ተአምራት ሁሉ ያግኘን!

...🙏❤🙏አሜን🙏❤🙏...!
ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን
#የፌስቡክ_ገፃችንን_ይወዳጁ_ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/ETKVqj-n9rA

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/-gfrbINWW7Y

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#ለሥራ_ከመትጋት_አትለግሙ!"
"ዘመንንና ትውልድን የተሻገረ ኑሮ መኖር የሚቻለው እንዴት ነው?"
በዶ/ር እሸትአየሁ ክንፉ
«ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤» ሮሜ 12 ፡ 11

“ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።” ዳን. 6:28

እሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ዶ/ር እሸትአየሁ ክንፉ "ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ" በሚለው ርዕስ ሥር "ዘመንንና ትውልድን የተሻገረ ኑሮ መኖር የሚቻለው እንዴት ነው?" በሚል የተዘጋጀውን ድንቅ መልዕክት አካፍለዋል።

#ኑሮ እና የኑሮ ሁኔታ በየዘመናቱ የሚነሱ ሐሳቦች ሲሆኑ አሁን እኛ በምንኖርበት ዘመን እና በዳንኤል ዘመን የነበረው የኑሮ ሁኔታን አንድ የሚያደርገው የኑሮ ሁኔታ በየጊዜው የሚነሣ ትልቅ አጀንዳ ሲሆን ዳንኤልን ግን ለየት የሚያደርገው በተለያዩ ነገሥታት ዘመን ኑሮው ምንም ሳይሆን የተቃናን ሕይወት ማሳለፉ ነው።
ዳንኤል 6:28

#የክርስቲያን ኑሮ ዕድል ፈንታው የተሻለ እና የተቃና ቢሆንም አብዛኛው ክርስቲያን ግን በዚህ ሕይወት አያልፍም።

# እግዚአብሔርም ሆነ አንድ አማኝ የተቃና ኑሮ እና ሕይወት ለክርስቲያኑ እንዲሆንለት ይፈልጋሉ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሚሰጠው ዕውቀት ማጣት የተነሳ ይህ ሕይወት የለም።

# ዳንኤል በነገሥታት መካከል የተቃና ኑሮ መኖር ተቻለው። ምክንያቱም የዳንኤል ሕይወት የተጣበቀው ከእግዚአብሔር ጋር ከመሆኑ የተነሳ የሚጠበቅበትን ሥራ በአግባቡ ይሰራ ነበርና።

👉 የዳንኤልን ሕይወት ምን አሳካው (ምን አቃናው)?

1. ዳንኤል መለየትና መምረጥ ያውቅ ነበር

#ዳንኤና እነዚያ ሦስቱ ወጣቶች የቀረበላቸውን ሁሉ ከመብላት ይልቅ መርጠው ቆሎ መብላትን ፈለጉ እንዲህም ተፈትነው ከእግዚአብሔር ጋር ከመሆናቸውም የተነሳ ጮማ ከበሉት ይልቅ ፊታቸው ያበራ ነበር።

👉 ነገሮችን መርጠው ያደርጉ ነበር

2. ዳንኤል ክብርን ለእግዚአብሔር ብቻ ይሰጥ ነበር

#ንጉሡ ሕልምን አለመና ሕልሙ ሲጠፋበት ተቆጥቶ የሕልም ፈቺዎችን ማስጨነቅ ሲጀምር ዳንኤል ግን በአምላኩ ታምኖ "ሚስጥርን የሚገልጥ በሰማይ አለ!" አለና ሕልሙንም ፍቺውንም ለንጉሡ ገለጠ። ንጉሡም ከደስታ የተነሳ ዳንኤልን ሲያሞግሰው ዳንኤል ግን ክብርን ለአምላኩ ነበር ያመጣው።

👉ስለሚገጥመው እና ስለገጠመው ነገር ሁሉ ክብርን ለእግዚአብሔር ብቻ ያመጣ ነበር።

3. ዳንኤል የሥራም የአምልኮም ሰው ነበር።

#ንጉሡ ዳርዮስ ከንግሥናው በኋላ ሹመትን ሲያደርግ ዳንኤልንም ሾሞት ነበር። ዳን.6:1-2። በተሾመበት ቦታ ሁሉ ምንም ዓይነት ስህተት እና በደል ሊገኝበት አልተቻለም። ምክንያቱም የታመነ ነበርና።

👉 ዳንኤል የሚሠራውን ያውቅ ነበር።ዳንኤል 6:4

#ዳንኤል የሚሠራውን ከማወቁ የተነሳ ማንም ከአምላኩ ጋር እንዳይገናኝ የሚል አዋጅ በወጣበት ጊዜ እንኳ "የእኔ ሥራ በምንም ዓይነት ሁኔታ አይቀርም/አይቀየርም" በሚል አቋም መስኮቶችን ወደ ምስራቅ በመክፈት ተንበርክኮ አብዝቶ ይጸለይ ነበር።ምክንያቱም ሥራው መጸለይ ነበር።

👉 እግዚአብሔር የተሰጠንን ሥራ በትጋት እንድንሠራ እና የተቃና ሕይወትን እንድንኖር ይፈልጋልና በትጋት እንድንሠራ መንፈሱ ያግዘን!

...❤️❤️❤️🙏አሜን🙏❤️❤️❤️...
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

''ኢየሱስን ማመን የመገለጥ ጉዳይ ነው! "
በፓስተር ደረጀ ፊሊጶስ

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
ዮሐ.1፥1

በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ ፓስተር ደረጀ ፊሊጶስ "ኢየሱስ መገለጥ ነው( የመገለጥ ጉዳይ ነው)!" በሚል የተዘጋጀውን ድንቅ መልዕክት አካፍለዋል።

# በእኛ አረዳድ "በመጀመሪያ" በሚል ቃል ውስጥ ያለው የሆነ ፍጥረት ሳይሆን የነበረው ቃል ነው።

# ከዮሐንስ በፊት ሦስት የወንጌላት መጽሐፍት ስለ ኢየሱስ የጻፉ (የገለጡ) ሲሆን

👉 ማቴዎስ፦ "የአይሁድ ንጉሥ"
👉 ማርቆስ፦ "አገልጋይ"
👉 ሉቃስ፦ ደግሞ "የሰው ልጅ ነው" በማለት የገለጡት ሲሆን
👉 ዮሐንስ፦ ግን ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ፥ አገልጋይና የሰው ልጅ ብቻ እንዳይደለ እና መጀመሪያ ከሚል መረዳት አልፎ ሄዶ የነበረ "ቃል" እንደሆነ ያየ ሰው ነው።

#ዮሐንስ እንደሌሎቹ ወንጌላዊያን ስለ ኢየሱስ ከሩቅ (በመላ ምት) የተረዳውን ለመግለጥ የሞከረ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ጉያ በመጠጋት እውነትን የገለጠ ሰው ነው።

# በዚህ ዘመን እግዚአብሔር የሚፈልጋት ቤተክርስቲያን በመገለጥ የተሞላችን ቤተክርስቲያን ሲሆን እኛም ይኸን ክፉ ዘመን ማለፍ የምንችለው ወደ ኢየሱስ በመጠጋት እና እውነትን በማወቅ ብቻ ነው።

#በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለት "በመጀመሪያ" የሚል ቃል ሲኖር አንዱ በዘፍጥረት 1:1 እና ሌላኛው በዮሐንስ 1:1 ላይ የተጠቀሰው ነው።

# የመጀመሪያው (የዘፍጥረት 1:1) "በመጀመሪያ" የተገለጠው ለሙሴ ሲሆን የዚህ መገለጥ ባለቤት ሙሴ ነው። ሙሴ ደግሞ የፍጥረትን ጅማሬ አየ

# የሁለተኛው (የዮሐንስ 1:1) "በመጀመሪያ" ደግሞ የተገለጠው ለዮሐንስ ሲሆን ዮሐንስ ያየው ግን ከፍጥረት ጅማሬ አልፎ በመሄድ የነበረውን ኢየሱስ አየ። የሚገርመው ነገር ዮሐንስ በጌታ ቀን በመንፈስ ሆኖ ያየው መገለጥ ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የሚመጣውን ኢየሱስን (አልፋ እና ዖሜጋ) የሆነውን ጌታ ነው።

👉 ከላይ የተጻፈው የሁለቱ ሰዎች የመገለጥ ሁኔታ ልዩነቱ በሰፊው የሚታይ ቢሆንም አንድ የሚያደርጋቸው ትልቁ ነገር ግን ሁለቱም ነገሮችን በመገለጥ ማየታቸውና ሁለቱም ስለ እግዚአብሔር መንግስት ጉዳይ መሆኑ ነው።

👉 ዮሐንስ በመንፈስ ሆኖ ሳለ የሮማውያን ወታደሮች አስረውት እሱ ግን በመገለጥ ሰማይ ነው ያለው። ራዕይ 4:4።

# በመገለጥ የሚኖሩ ሰዎች ከሁኔታ በላይ ይኖራሉ። ደግሞም እውነተኛ ነብያቶች ኢየሱስን እና ኢየሱስን ብቻ ያወራሉ።

# ሁልጊዜ በመንፈሱውስጥ እና በመገለጥ ውስጥ ያኑረን።

...🙏❤🙏 አሜን🙏❤🙏...!

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

በእርሱ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።” ዮሐ 3:14
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
2ኛ ቆሮ 5፥15
#ኢየሱስ_ስለኃጢያታችን_ሞቷል
#ሊያፀድቀንም_ተነስቷል
ፓስተር ጌትነት በቀለ

በሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በድምቀት ተከብሯል።
ፓስተር ጌትነት በቀለ በዮሐ 3:14-15 ባለው ክፍል መሰረት በማድረግ ድንቅ ቃል አካፍለውናል።
“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።”
ዮሐንስ 3፥14-15
➽ኢየሱስ ክርሰወቶስ የሞተልን የዘላለም ሕይወት ሊሰጠን ነው።
ኢየሱስ ስለኃጢያታችን ሞቷል ሊያፀድቀንም ተነስቷል
👉ኢየሱስ ሞቱን እና ትንሳኤውን በቀጥታ ያገናኘው ከዘላለም ሕይወት ጋር ነው
➽የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ዓላማው እኛ ሕይወቱን ለሰጠን ለእርሱ እንጂ ለራሳችን እንዳንኖር ነው።
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
2ኛ ቆሮ 5፥15
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

"መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥" 1ቆሮ 15:3-4
ፓስተር ጌቱ አያሌው
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!!

#Share ♻️ Join ♻️ #Share
@YHBCHawassa

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

''የክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት እና በሞቱ የተገኙ በረከቶቻችን"
በአስተማሪ ሃርኪሶ ሃዬሶ

" በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።"
ዘፍ. 3:15

በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ አስተማሪ ሃርኪሶ ሃዬሶ "የክርስቶስ መከራና የትንሣኤው ኃይል" ውስጥ የሚካተተውን "የክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞትና በሞቱ የተገኙ በረከቶቻችን" በሚል የተዘጋጀውን ድንቅ መልዕክት ለጉባኤው አካፍለዋል።

# የክርስቶስ በመስቀል ላይ የመሞት ምክንያቶች፦

1. የዲያብሎስን አናት (ጭንቅላት) ለመቀጥቀጥ ነው።
ዘፍ. 3:15 «በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።»
ሮሜ. 16:20 «የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል።» እና ራዕይ 12:9

2. እርግማንን ወደ በረከት ለመለወጥ ሞተ።
ገላ. 3:14 «የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።» እና ዘዳ. 21:23, ቆላ. 2:13-15

3. ሰውን ከሰው እና ሰውን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ሲል ሞተ።
ኤፌ. 2:14-16, ሉቃ. 23:12

👉 ሰውን ከሰው ለማስታረቁ ትልቅ ምሳሌ የሚሆነን ሄሮድስን ከጲላጦስ ያስታረቀ መሆኑ የኢየሱስ ሞት አሸናፊነት እንዳለበት ያሳያል።

# በክርስቶስ የመስቀል ሞት ያገኘናቸው ሁለት በረከቶች፦

1. በሞቱ ቅዱስ አደረገን፥ (አነፃን፥ አጠበን ጽድቅን አለበሰን።)
ዕብ. 10:10-13

👉 እየኖርን ያለነው ሕይወት ክርስቶስ ያጸደቀን ሕይወት እንጂ ለመጽደቅ የምንኖርበት ሕይወት አይደለም።

2. ምህረት እና ይቅርታን አግኝተናል።
ሉቃ. 23:34

👉የመስቀሉ ሞት ከሰጠን በረከት አንዱ ምህረት ነው። 1ኛ ጴጥ. 2:10

# እግዚአብሔር አምላክ በተደረገልን የመስቀል ላይ በረከቶች የምንኖር ፥ የምናመሰግን እና በማስተዋል የምንመላለስ ሰዎች ያድርገን!

...🙌🙏❤️አሜን❤️🙏🙌...!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#የክርስቶስ_መከራና_የትንሣኤው_ኃይል
#መከራውን_እንካፈል
በአገልጋይ በረከት ዋቤሎ

" ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።" ሮሜ. 8:17

በእሁድ የቃልና የአምልኮ ጊዜ አገልጋይ በረከት ዋቤሎ የጌታን ቃል ያካፈለ ሲሆን በሚያዚያ ወር ከተዘጋጀው ርዕስ (የክርስቶስ መከራና ትንሣኤ) ውስጥ"መከራውን እንካፈል!" በሚል ርዕስ ድንቅ መልዕክት አካፍሎናል።

# የተቀበልነው የእግዚአብሔር መንፈስ (ስልጣን) አባ አባ የምንልበት የልጅነት እና የሚመጣውን ክብር የምንቀበልበት ብቻ ሳይሆን የሚመጣውን የክርስቶስን መከራ የምንቀበልበትም መንፈስ ጭምር ነው።

👉 የተጠራነው በሥልጣን ያስተማረውን፥ ከእጁና ከአፉ የወጡትን ፈውሱን ለመካፈል፥ ያበዛውን እንጀራ ለመካፈል፥ ድንቅና ተአምራቱን እያየን ለማድነቅ ብቻ ሳይሆን የተጠራነው በመከራውም አበረነው ሆነን ለመካፈልም ጭምር ነው የተጠራነው።

👉 ክርስትና በጎ እና መልካም ነገሩ ብቻ ሳይሆን መስቀል(መከራ፥ስቃይ፥ቀራንዮ እና ልቅሶ) የሚልም የሕይወት ገጽታ አለው።

👉 ኢየሱስን እየገደሉት የሰቀሉት ሲሆን በወቅቱ መንግሥትም ሆነ ቤተመቅደስ እሱን ከመደገፍ ተቆጥበዋል።

# ኢየሱስ በአይሁድ ህግ መሠረት እንደ ወንጀለኛ የተቆጠረበት ሁኔታ ከመፈጠሩ የተነሣ በመከራው ጊዜ ሁሉም ትተውት የሸሹበት ወቅት ነበር። ደቀመዛሙርቱ ሳይቀር በመከራውና በሞቱ ጊዜ ጥለውት የሄዱበት ጊዜ ነበር። ምክንያቱም ከኢየሱስ ጎን ሆኖ መጋፈጥ እጅግ ዋጋ የሚያስከፍልበት ሁኔታ ነበር። ነገር ግን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያልተጠበቁ እና በራሳቸው ወስነው መከራውን አብረው ለመካፈል የወሰኑ ሰዎች ታይተውም ነበር። ከእነዚህም ውስጥ፦

1. ኃጢአተኛዋ ማርያም። ማቴ. 26:12
ውድ ሽቶ እግሮቹ ላይ በማፍሰስ

2. በቤቱ ኢየሱስን የጠራው ግለሰብ። ማቴ. 26:18
ለፋሲካው እራት ቤቱን ለኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ለቀቀ።

3. ኢየሱስ በወደቀበት በኢየሩሳሌም ጎዳና ውሃ ያጠጡት ሴቶች።

4. መስቀሉን ተቀብሎ ያገዘው የቀሬናው ስምዖን። ሉቃ. 23:26
"እኔ ምን አገባኝ ብሎ መሄድ ይችል ነበር። ነገር ግን የኢየሱስን መስቀል በመሸከም መከራን መካፈልን መረጠ።

5. የክፉው ወንበዴ መልካም ምስክርነት።
ሉቃ. 23:39-42
መስቀል ላይ ሆኖ ስለ ኢየሱስ ንጽሕና በመመስከር መከራውን መካፈል ፈለገ።

6. ሁሉ ከተበተኑ በኋላ እዚያው (የስቅለቱ ቦታ) የቀሩ ሴቶች። ዮሐ. 19:25

7. ባለጠጋው (ሀብታሙ) ዮሴፍ። ማቴ. 27:57-60። የመቃብር ብታን በመስጠት።

# እነዚህ ሁሉ የኢየሱስን መከራ በመካፈል የክርስትናን ሙሉ ትርጉም የሰጡ ሲሆን አንዳንዶቹ ግን ለአጭር ሰዓት አብረውት ሆነው በጥቂቱ ለመጸለይ አብረውት መትጋት አቃታቸው። በጌቴሴማኒ የጸሎት ጊዜ በእንቅልፍ ይቸገሩ ነበር።

# ኢየሱስን የተቀበልነው፦

👉 ገሊላን (የታምራቱን ነገር) ብቻ ሳይሆን ጎልጎታንም (መከራውንም) ጭምር ለመቀበል ነው።

👉 ልንድንበት፥ ልንከብርበት ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን የሚመለከት የትኛውንም ስቃይ ልንቀበልም ጭምር ነው።

# የክርስትና ጣዕሙ በመከራ ውሰጥ ማለፍም ነውና መከራውንም ጭምር አብረን እንድናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን!

...🙏❤️አሜን❤️🙏...!
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/Hawassa-Yehiwot-Birhan-Church-748303915231037/
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
➲/channel/YHBCHawassa
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

https://youtu.be/gF0btVl8QKw

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#ባርኮቴን_ስቆጥረው_ዘምር_ዘምር_ይለኛል።
አቤንኤዘር እግዚአብሔር ረዳኝ
የትናንቱን ካሻገረረኝ ለዛሬውስ ምን አሰጋኝ
ለነገውም እሱ አለኝ
Getayawkal & Biruktawit
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
/channel/YHBCHawassa

Читать полностью…

ሀዋሳ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

#የተገለጠው_ማንነቴ
#Share ♻️ Join ♻️ #Share
/channel/YHBCHawassa

Читать полностью…
Subscribe to a channel