zakiiir12 | Unsorted

Telegram-канал zakiiir12 - ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

-

❤️ልብን እንድታፈቅር ላደረገ አላህ♡ ♡ምስጋና የተጋባ ይሁን!!! አላህ ሀላሉን ይወፍቀን አሚን🙏 ለአስተያየታችሁ👉 @Fiamanillah2

Subscribe to a channel

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ፆምን የሚያበላሹ ስምንት ነገሮች
★★★★★★★★★★★★★★

1 ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ፆም ግዴታ የሆነብን ሰዎች በረመዷን ቀን ላይ ወሲብ ከፈፀምን ይህን ቀን ማካካስና መቶበት ይኖርብናል። ያለፈንን ቀን ለማካካስ አንድ ባርያ ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል። ይህን ማድረግ ካልቻልን ሁለት ወር በተከታታይ መፆም ይኖርብናል። ይህንንም ማድረግ ካልቻልን ስልሳ ድሆችን መመገብ ይኖርብናል።

2 ሆንብሎ የዘር ፈሳሽን ማፍሰስ

3 ሆንብሎ መብላት መጠጣት

4 የምግብ መርፌ መወጋት ፆም ያበላሻል። ምክኒያቱም ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ተመሳሳይ ነውና።

5 ደም መለገስ (መሰጠት): ፆመኛ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ብዙ ደም ፈሶት እንዲያገግም ደም ቢለገሰው ፆሙ ይበላሻል።

6 የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም

7 የዋግምት ደም መፍሰስ: ደም በራሱ ጊዜ ከአካል ከፈሰሰ ፆም አያበላሽም። ለምሳሌ የነስር ደም ወይም ደግሞ ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈስ ደም

8 ጣታችንን ወደ ጉሮሯችን በማስገባት ሆንብለን እንዲያስታወከን ብናደርግ ፆማችን ይበላሻል። ሳናስበው በድንገት ቢያስታውከን ግን ፆማችን አይበላሽም።
ምንጭ ፦ 【ኑበዝ ፊ ሲያም" በሸይኽ ኡሰይሚን)
★★★★★★★★★★★★★★★★
የአህመዲን ጀበልን ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉና መረጃዎችን በቴሌግራም ያግኙ።
★ T.me/ahmedin99

T.me/Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

🍂 ለእህቶች አስፈላጊ ትምህርት!

✔ ሙስሊም ሴት ለመፆም ብላ ሀይድን የሚያስቀር ኪኒን መዋጥ ይፈቀድላታል?

✔ ሙስሊም ሴት በሀይድ ግዜ ምን አይነት ኢባዳ ማድረግ ትችላለች?


||
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.
እንኳን ለ1442ኛው የታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
የአላህ እዝነቱ ሆኖ ለተከበረው የረመዷን ወር ፆም ደርሰናል። በነገው እለት ማክሰኞ ሚያዚያ 5 የረመዳን ወር ፆምን አንድ ብለን እንጀምራለን::ይህ ትልቅ እድል በኛ አቅም የገጠመን ሳይሆን በአላህ መልካም ፈቃድ መሆኑን አውቀን ሁላችንም ምስጋና ማድረስ ይኖርብናል፣ አልሃምዱሊላህ!
ከረመዷን እስከ ረመዷን በአለማችንም በሀገራችንም ብዙ ጉዳዮች ተስተናግደዋል። በሰው ልጆች ላይ በጎ ለውጥን ያመጡ እና ተስፋን የሚሰጡ ሂደቶች አልፈዋል። በተቃራኒው የሰው ልጆችን ህይወት ያከበዱ፣ እርስበርሳቸው ያጋጩ እና ነገን ተስፋ ማድረግ ያከበዱ ሂደቶችም አልፈዋል። ሀገራችንም ከዚሁ የተለየች አይደለችም።
ባለፈው ረመዷን ኑረውን እስከአሁን ያሻገርናቸው በጎ ፀጋዎችን ጠብቀን፣ በዚህ ረመዳን የሚኖሩንን የፆምና ኢባዳ እድሎች እንደትልቅ እድል ተጠቅመን የምናሳልፍው የፆም ወር እንዲሆንልን እመኛለሁ።
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉና ለችግር የተጋለጡትን በማገዝ ላይ አደራ እላለሁ። በአቅራቢያችን የሚገኙ የተቸገሩትን ሁሉ በኢፍጣርና ሱሁር ሰአት እንድናስባቸው፣ እንድናግዛቸውም እንድንበረታ ለማስታወስ እፈልጋለሁ።
ከመጅሊስ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙን ችግሮች በዚህ ረመዷን ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ተስፋው ወደ እምነት እንዲቀየር ሁሉም በየዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ። መንግስትም ከግማሽ የቀረው ድጋፉ ካልተጠናከረ ወደሁዋላ የሚመለሰው ሂደት ሁላችንንም የሚያስከፍለን ዋጋ ቀላል አለመሆኑን በመረዳት የመፍትሄው አካል ሊሆን ይገባል። ሙሉ ሂደቱን ለረመዷን ክብር በሚመጥን መመካከርና መተጋገዝ መንፈስ እንድንመራው አደራ እላለሁ።
በድጋሚ ረመዳን ሙባረክ
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
ሻዕባን 30/1442

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ
======================
①) ለራሷ ጹማ ውላ፣
②) ማታ ለማፍጠሪያ ደፋ ቀና እያለች ምግብ አዘጋጅታ፣
③) ከተፈጠረ በኋላ የተመገበበትን እቃ አጥባ፣
④) ተራዊሕ ሰግዳ፣
⑤) ለሌሊት የሰሑር ምግብ አዘጋጅታ፣
⑥) አሁንም እቃ አጥባ፣
⑦) ልብስ አጥባ፣
⑧) ቤት ወልውላ፣
⑨ቁርኣን እየቀራች፣
⑩) ልጆችን ተንከባክባ…፣
ረመዷንን በከፍተኛ ልፋት የምታሳልፍ
√ እናት (ማማዬ)፣
√ እህት፣
√ ሚስት፣
√ ሴት ልጅ… ትልቅ ክብር ይገባቸዋል።
አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።
የቻላችሁ ሰዎች ትንሽ እንኳ አግዟቸው።»

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው!
በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳደረሱን በተሚዝ አካባቢ ያለው የጨረቃ መጠባበቂያ ማእከል ውጤት ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ሆኖም ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4/2013 የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማክሰኞ ደግሞ ረመዳን 1 ይሆናል። ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋ መግለጫ በመጠበቅ ላይ ነው።
ነሲሓ ቲቪ መላውን ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያለ አላህ ተውበትና መልካም ስራን እንዲያገራልን እንለምነዋለን። ረመዳን ሙባረክ!!
ነሲሓ ቲቪ
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ከደራሲያን አለም ፔጅ
አስባችሁታል ......
#ልጁ ከስር እባብ መኖሩን አያውቅም...ልጅቷ ልጁ ላይ ድንጋይ እንደተጫነበት አታውቅም።
*
# ልጅቷ:- "ልወድቅ ነው ወደ ላይም መውጣት አልቻልኩም ምክንያቱም እባቡ ይነክሰኛል... ለምን እሱ ጉልበቱን አጠንክሮ ወደ ላይ አይጎትተኝም?!"
*
# ልጁ:- "በጣም እያመመኝ ነው በምችለው አቅም ሁሉ ወደ ላይ ልጎትታት እየሞከርኩ ነው... እሷ ግን ለመውጣት ለምን አትሞክርም?!" ይላል።
*
# ሽረኛው እባብ በመሃል እየሸረበ ያለውን አላወቁም፤ እርሷም የተጫነበትን አላወቀችም፤ እባቡ ግን አንዳቸው ሌላቸውን እንዳይረዳዱ ስውር ስራውን እየሰራ፤ ተሰውሮ መርዙን እየረጨ ነው።
*
# ሰው ምን ያህል ጫና ውስጥ እንዳለ አንረዳም። ሌላም ሰው አንተ ያለህበትን ህመም አይረዳልህም። ስለዚህ ሌሎችን ከመውቀስ በፊት ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት መሞከር፣ ራሳችንን በሌላው ሰው ቦታ አርገን ማሰብ ያስፈልጋል።
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ሱብሃነክ ያረብ
ምን ልበላት የችህን ልባም ሴት
ማሻ አላህ🙏👉 @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

𝐁𝐫𝐢𝐝𝐠𝐞𝐫 𝐖𝐚𝐥𝐤𝐞𝐫 Walker ይባላል። የ6 ዓመት ልጅ ነበር። አንድ ተናካሽ ውሻ ወደ የ3 ዓመት እህቱ እየተምዘገዘገ ሲሮጥ ያያል። እህቱን በጀርባው ሸሽጎ ከፊት ራሱን አስቀደሞ የጀርመን ዝርያ ካለው አስፈሪ ውሻ ጋር ግብግብ ገጠመ። ውሻው አልማረውም።
ሰውነቱ ላይ 90 ያህል ንክሻና ቡጭሪያ አደረገበት። እህቱን ግን ጫፏ ሳይነካ ማዳን ቻለ። እናም ሚዲያወች ቀርበው ጠየቁት ከሁለት አንዳችን መሞት ካለብን መሞት ያለብኝ እኔ ነኝ ምክንያቱም እኔ ላጣት የማልፈልጋት አህቴ ናትና ሲል መለሰ።ለዚህ ጀብዱ እና አባባሉ የአለም የቦክስ ምክርቤት ( 𝐖𝐁𝐂 ) July,9 የእለቱ የአለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዬን እንዲባል አድርጎታል። ይህም በየዓመቱ የሚታሰብ ነው
By-Mohammed Ali

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

እንኳን ደስ አላችሁ!
| *አስደሳች ዜና ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ* |
¦ አፍሪካ አካዳሚ ¦
የትም ቦታ በመሆን ፕሮግራሙን ይተከታተሉ
አፍሪካ አካዳሚ ከአፍሪካ ቲቪ ጋር በመተባበር ልዩ ዲናዊ የርቀት ትምህርት ስልጠና
*"ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት"*
በሚል ርዕስ ሥልጠና (6) ማዘጋጀቱን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው
ሁሉም ሙስሊም ማወቅ ያለበት
[ *ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት*]
*በክቡር ሼኽ ሓሚድ ሙሳ*
የሚቀርብ
*ፕሮግራሙን ለየት የሚያደርጉ ነገሮች፡*
ያለ ምንም ክፍያ የነፃ ስልጠና!
የፕሮግራሙ ጊዜ ለ ቀናት ብቻ የሚቆይ ነው።
*አቀራረቡ*
በየቀኑ ለ1 ሰዓት ብቻ የሚቀርብ ሲሆን፣
ፕሮግራሙን ካጠናቀቁ ነፃ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።
በየቀኑ ትምህርቱን መረዳትዎን ለመገምገም ጥያቄዎች የሚቀርቡ ይሆናል።
ትምህርቶቹን በፈለጉት ጊዜ በቪዲዩ፣ በድምፅ እና በፅሁፍ PDF ሊከታተሉ ይችላሉ።
ሥልጠናው የሚጀመርበት ቀን፡
*ቅዳሜ ረጀብ 22/ 1442 ሒጅሪ*
(March 6/ 2021 እ'ኤ'አ')
ይሆናል።
*የኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት ኮርስ መመዝገቢያ ቅፅ*፡
[ http://bit.ly/3cBMfED ]
ከተመዘገቡ ቡኋላ ወደ አፍሪካ አካዳሚ ሥልጠና ለመግባት ይህን የቴሌግራም ሊንኩን ይጫኑ፤
/channel/Africa_Academy1
ጊዜዎን በዚህ ልዩ ፕሮግራም ያሳልፉ፣ በአሏህ ፍቃድ በጣም አንገብጋቢ እና በጣም አስፈላጊ ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት ተረድተው ይመረቁ።
ለሌሎችም እንዲደርስ የፕሮግራሙን ማስታወቂያ SHARE ያድርጉ

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ሸር ያድርጉ ወገንዎን ያንቁ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በመንገድ ላይ ሲጓዙ ህፃናት ይዘው ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ ሰዎችን በአይነ ቁራኛ መከታተል አጠራጣሪ ነገር ከተመለከቱ አስቁሞ መጠየቅ ከአቅም በላይ ከሆነ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ ፖሊሶች ማሳወቅ።
ልጅ ይዘን ከቦታ ቦታ ስንዘዋወር በመንገድ ላይ ሰዎች ቢጠይቁን ተገቢውን ምላሽ በተገቢው መንድ ከማስረጃ ጋር እንመልስ እንጂ አንበሳጭ ዞሮ ዞሮ ጥቅሙ ለራሳችን ነው።
ነገሩ ከባድ ቢሆንም ከልጅ መጥፋት አይብስም እና እንተግብረው።
ኸይር ፈላጊ
ሸር ያድርጉ ወገንዎን ያንቁ
# challenge_ልጄን_ጠብቅልኝ_ልጅህን_እጠብቅልሃለሁ

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

# ጁምዓ ነው ወዳጆቼ
እስቲ ለታመሙብን ፈርጦች ዱአ እናድርግላቸው።
ሸይኽ ሙሂዲን{የፈትህ መስጂድ ኢማም ወደር የሌላቸው ፈቂህ}
ሸይኽ ሰዒድ ዩሱፍ መንሱር{ የፈትህ እንቁ አሊም የአለም ውበት}
ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን{ የፈትህ ሙፈሲር የአለም ኩራት}
ኡስታዝ ኢድሪስ አህመድ{የፈትህ ኮከብ የወጣት ተምሳሌት}
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ{የፈትህ ወኔ የኡማው ውበት}
ለሌሎቹም ቤት ለሚቆጥራቸውም ሁሉ አላህ ምህረትን ያልብሳቸው ከበሽታውም ይፈውሳቸው።
አላህ ሆይ ለታመሙብን፣
ወንጀላቸውን አብሰህ
ካሉበት መረድ ፈውሰህ
ራህመትህን አፍስሰህ
እውቀታቸውን አድሰህ
ከተከፋባቸው አውፉታን ለግሰህ
ጠላታቸውን አርክሰህ
ከኛጋር መስጂድ መልሰህ
አኑራቸው ኡምርን ጨምረህ
አሚን አሚን በእዝነትህ!
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ምንም የሌለው ድሀ ወንድ ሷሊህ ሚስት ካለችው ከማንም በላይ ሀብታም ነው።ረሱል ﷺ አላህ ሷሊህ የሆነችውን ለወንድሞቼ ሷሊህ የሆነውን ለእህቶቼ ይወፍቃችሁ ጥሩ ትዳር ይስጣችሁ ደስተኛ ህይወት ይወፍቃችሁ አሜን።
___➾join ይበሉ __
👉 @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ጌታዬ ሆይ!ነፍሴን የሚያጠፉ ከባድ ሰሜቶችን ሁሉ በእዝነትህ አስወግድልኝ ፣ ከአቅሜ በላይ የሆነን ነገርም አትጫንብኝ ።

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

# ምርጥ_ምክሮች
ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም
# በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!
ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ # ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!
ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
#ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ
ዝም በል ማለት # አትናገር ማለት አይደለም
ሌሎችን ለመስማትም # ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም
በሰዎች # ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!
አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም
# ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!
ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
# ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ
ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ # ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ውደድ ማለት እንጂ!
ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም
ምንም # ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!
ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም
ምንም ቁም ነገር # ሳትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!
ብቸኛ አትሁን ማለት # ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም
ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ
ሁን ማለት እንጂ!
እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት
አይደለም # ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!
አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም
# ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!
ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም
ሌሎችን # አትናቅ ማለት እንጂ!
ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም
# አምሮብሃል ማለት እንጂ!
አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም
# ብልህ ሁን ማለት እንጂ
ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም
# ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ
ከወደዱት ሼር ላይክ ያድርጉ @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

የሰው ልጅ በራሱ የሰው ልጅ ላይ በጨከነበት ጊዜ እንስሳቶች እርስ በርሳቸው ሲረዳዱ ስታይ ክብር የነበረው የሰው ልጅ ዛሬ ላይ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ትረዳለህ። @Zakiii12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

🔴 ጁምዓ
‏قال ﷺ :

"أفضل الأيام عند الله يوم الجمعة"

قال المحدث الألباني : صحيح

📚السلسلة الصحيحة - رقم : 1502

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው»

ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ "ሰሂህ" ብለውታል።

📚 [አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1502]

‏قال ﷺ :

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً"

قال المحدث الألباني : حسن

📚السلسلة الصحيحة - رقم : 1407

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በጁምዓ ለሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።»

ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሀሰን " ብለውታል።

📚 [አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1407 ]
★★★★★★★★★★★★★★
የፍቅር እስከ ጀነትን ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።ለሌሎችም ያጋሩ።
★ T.me/Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️
========================
1) አንድ ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16 መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20 ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

አላህ ያግዘን።
|| @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ረመዷንን በምን አይነት ሁኔታ ለማሳለፍ አስባችኋል
ከማን ጋር? የት ሃገር?
በበኩሌ የአላህ ፈቃዱ ከሆነ የዘንድሮውን የረመዷን ጾም በብዙ ምክንያት ከወትሮው በተለዬ መልኩ የማሳልፍ ይሆናል።
ለአስተያየትዎ
@Fiamanillah2

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

ረመዳን ሙባረክ!

የታላቁ የረመዳን ፆም ማክሰኞ 1 ብሎ እንደሚጀመር ተገለፀ!

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን

በሳኡዲ አረቢያ ዛሬ እሁድ ሚያዝያ 3/2013/ አፕሪል 11/2021 የረመዳን ወር መግቢያ አዲስ ጨረቃ ሊታይ ባለመቻሉ ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4 የሻዕባን 30 እንደሚሆን እና የረመዳን የመጀመሪያ ቀን ማክሰኞ ሚያዝያ 5 መሆኑ ታውቋል!

የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ሸሪኣ ፍርድ ቤት ዛሬ ምሽት እና ሰኞ ምሽትን የረመዳን ወር መግቢያ አዲስ ጨረቃ መውጣቱ እንዲጠባበቅ ህዝበ ሙስሊሙን አሳስቦ ነበር::

ነገ ሰኞ የሻዕባን የመጨረሻ 30ኛ ቀን እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ረመዳን ሙባረክ!

አላህ ሃቁን ጠብቀው የሚፆሙት ያድርገን!
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

አላህ በሰላም አድርሶ በሰላም ያስጨርሰን
መጪው ረመዳንን በምን መልክ ለማሳለፍ አስበዋል
ነብዩ ሰዐወ ረመዳን ሲደርስ ስነምግባራቸው ይበልጥ ይጨምራል ቁርዐን ይቀራሉ ለሊት በብዛት ይሰግዳሉ ዱዐ ያደርጋሉ ተራዊህ ለብቻቸውም በጀመዐም ይሰግዳሉ ወዘተ እኛ ደሞ የሳቸውን ፈለግ ብቻ በመከተል ረመዳናችንን በሰላም እናሳልፍ ከኺላፍ ነፃ እንሁን ዐውፍ እንባባል

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ ይደረጋል...

የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ፈተናው በ 2ሳምንት ውስጥ ታርሞ መጠናቀቁን እና ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ወይም ከነገ ጀምሮ በ8181 እንዲጠባበቁ ጠቁመዋል።

የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ከ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 2,2013ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

ለበለጠ መረጃ
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

Faysal Ahmed Yimam ▶ የኡስታዝ ኻሊድ ክብሮም ወዳጆች ጉሩፕ

ሾስማን ኦንላይን የተሰኘ ድርጅት ለጉሌድ ኢብራሂም የስራ እድል ሰጥቶት፣
በቅርብ ለሚያከናውነው ጋብቻ የሰርግ ወጪውን እንደሚሸፍንለት ቃል
ገብቶለታል።
ጉሌድ ባጃጅ ውስጥ 3መቶ 50ሺህ ረስተው ለወረዱ እናት መመለሱ የሚታወስ
ነው። ለዚህ ታማኝ ወጣት በጎፈንድሚ ከአስርሺ ዶላር በላይ እንደተሰበሰበለት
ተነግሯል። በገንዘብ እጦት የዩኒቨርሲቲ ውጤት አምጥቶ ያቋረጠውን ትምህርት
በክልል መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንደሚቀጥል ቃል ተገብቶለታል።
አርዓያነት ባለው ተግባሩ በርካቶች ጉሌድን አመስግነውታል፣ ሸልመውታል።
(ምንጭ፦ ኡስማኖቪች)
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

"የተከበረ ቢሆን እንጂ ሴትን አያከብርም
የተዋረደ ቢሆን እንጂ ሴትን ልጅ አያዋርድም"
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)


"ለሴቶች ደግ መልካም ሁኑ" ረሱል ﷺ
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

የሠው ሀቅ አትፈልግ የራስህን ታጣለህና!!!
ዛሬ ሌላ ታሪክ ተሰራ
ድንቅ ታማኝነት ይህ ታማኝ ወጣት የባጃጅ ሹፌር ያሳፈራትን ግለሰብ
ጅጅጋ 04 ቀበሌ ሪል ቢሲዲሞ ክሊኒክ አድርሶ ተመለሰ። በደቂቃዎች
ውስጥ አካባቢው በሀዘን ድባብ ተዋጠ አንዲት ታካሚ ባጃጅ ላይ 300
000 ብር ጠፋኝ አለች። ሰው አስተዛዘናት........ከግማሽ ሰአት በኋላ
ከላይ የሚታየው ታማኝ ወጣት ገንዘቡን ይዞት ከች አለ። እኔ የገረመኝ
በዛሬ ጊዜ የዚህ አይነት ወጣት መገኘቱ ነው።
©hairu
የሀገር ውስጥ እና የአለም ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይህን የtelegram ገፅ ይቀላቀሉ፡፡ @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ ወንድም እና እህቶች
ትንሽ ህመም እንዳጋጠመኝ ሰምታችሁ ለተጨነቃችሁ በሙሉ
ሰሞኑን ትንሽ ህመም አጋጥሞኝ የነበረ ቢሆንም በአላህ ፈቃድ በአሁኑ ወቅት ጥሩ ለውጥ አለኝ አልሐምዱሊላህ !
እንዳመመኝ ሰምታችሁ ለተጨነቃችሁ ፣ በዱዓም ስታግዙኝ ለነበራችሁ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ
አሁን ላይ ከህመሙ እያገገምኩኝ ሲሆን በመልካም ሁኔታ ላይ እገኛለው አልሐምዱሊላህ

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
አልሀምዱሊላህ👍

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

▫️በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት

1, ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም።
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ፡-
«በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፉን እንደተሸከመ አህያ ነው» (አህመድ 1/230 ዘግበውታል)

በሌላም ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፡-
«ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርክ» (ቡኻሪ 394 ሙስሊም 851 ዘግበውታል)

2, በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል መሸጋገር አይፈቀድም።

ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው
«ተቀመጥ ሰውን አስቸገር» ብለውታል።
በዚህም ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያዳምጥን ማዘናጋት ይፈጠራል። ኢማሙ ግን የሰዎችን ተከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ሚንበሩ የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል።

3, ሁለት ሰዎችን በመለያየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

«የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል» (ቡኻሪ 910 ዘግበውታል)

--------------------------------------
🔗 @Zakiiir12
--------------------------------------
💬 @Zakiiir12
--------------------------------------

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

💜 ከእንቅልፍ መነሳትህ
አላህ ተውባ ልታደርግ ሌላ ቀን
ሰጥቶህ ነው እንጂ… የትላንትናውን
ወንጀል እንድታሟላው አይደለም ።

መልካም ቀን🥰

➧ @Zakiiir12 || #share

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

የተከበረው # የረጀብ ወር ሊገባ የአንድ ሳምንት እድሜ ቀርቶታል። ለታላቁ # የረመዳን ወር ደግሞ ሁለት ወር ከአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ ቀርቷል።
በረጀብና በሻዕባን ወር ለረመዳን ዝግጅት የሚደረግበት ጊዜ ነው። በረጀብ ወር ዘር ይዘራል፤ በሻዕባን ወር ውሃ ይጠጣል በረመዳን ደግሞ ካፈራነው ፍሬ የምንቋደስበት ይሆናል። ለረመዳን የሚሆኑ ስራዎችን የምናቅድበት ጊዜው አሁን ነው።
አላህ ያድርሰን! @Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ታሪክ ተመዝግቧል
ሀናን ፈድሉ
በሁለት ዘርፍ ተሸላሚ የሆነች ሲሆን፥
በፋርማሲ የት/ር ዘርፍ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ከዩኒቨርሲቲው
አጠቃላይ አንደኛ በመሆን በከፍተኛ ማዕረግ የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን
በቅታለች
3.98 አስደናቂ የመመረቂያ ውጤት በማስመዝገብ
ያኮራችን እህታችን ሀናን ፈድሉ ቀሪ ህይወትሽ የከፍታ ይሆንልሽ እንላለን

ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
@Zakiiir12

Читать полностью…

ፍቅር እስከ ጀነት ቁ.1

በተለይ # ለሴት እህቶቻችን # ጠቃሚ_ምክር !
ሴት እህቶቻችን በታክሲ ዉስጥ "ሿሿ" በሚባል የሌብነት አይነት በየቀኑ ማለት በሚቻል ደረጃ እየተዘፉ ስለሆነ ለሕብረተሰቡ አሳውቁ።
1. ረዳቱ የትነሽ / ናቹ? ሲል የሚሔዱበትን ቀድሞ አለመናገር፣
2.ገቢና አስገብተው "የበሩ ጎማ ለቀቀ አስተካክይው" ሲሉ አለመተባበር፣
3. አጠገብሸ ያስቀመጡት ሰው የእነሱ ተባባሪ ስለሆነ ስልክ ቁጥር በስልክሸ ያዥልኝ ስትባይ አለመተባበር፣
4. ሶስት ወይም አራት ሆነው ተነጣጥለው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ሲያጋጥሙ ጥንቃቄ ማድረግ፣
5. የታክሲዉ ታፔላ እንዲሁም ታርጋው የተሸፈነ ከሆነ መጠራጠር፣
6. ከጎንሽ የተቀመጠው ተሳፋሪ ኮቱን በእጁ ይዞ እጁን ሸፍኖ የሚቁነጠነጥ ከሆነ ጥንቃቄ ማድረግ፣
7. ታክሲው እየሄደ ጋቢና ከሌላ ሰው ጋር ተቀምጠሽ የጋቢናው መስታወት ክፍት ሆኖ ረዳቱ በደጅ በኩል ሲያዋራሽ ጥንቃቄ ማድረግ፣
ሼር ብታደርጉት ብዙ እህቶችን ከዘረፋ ታድናላችሁ። @Zakiiir12

Читать полностью…
Subscribe to a channel