ኮምቦልቻዎች ለጎዳና ላይ ኢፍጧር ያዘጋጁትን ቲሸርት እጅግ በጣም
ወድጄዋለሁ
"ሙስሊም ነኝ ሶላቴ ህይወቴ " ይላል !!
እሁድ ሚያዚያ 9 ይካሄዳል
የደሴው ሚያዚያ 7 ነው::
በነገራችን የሶላት እና የሂጃብ ጉዳይ ልክ እንደ ጁምዓ ሶላት በአዋጅ እና
በህግ ቋሚ መፍትሄ እስኪሰጠው ድረስ ትግላችን ይቀጥላል !
/channel/EthioomahTvchannle
ٓ
٭ لَقَدۡ مَضَی مِنۡ شَهۡرِڪُمۡ عَشۡرُهُ ٱلأُوَلۡ!
የመጀመሪያዎቹ የረመዿን አስር ቀናት አልፈዋል። በመካከለኛዎች አስር ቀናት በር ላይ እንገኛለን። የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት መጥተው ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት የመጀመሪያዎቹን አስር ቀናት በምን ሁኔታ እንዳሳለፍንና ቀጣዮቹን በምን ሁኔታ ለማሳለፍ እንዳሰብን ቆም ብለን ራሳችንን እንገምግም። እስካሁን በመልካም ያሳለፈ ሰው የሥራ ማማር በመጨረሻው ነውና እስከ መጨረሻው ይበርታ። የተዘናጋ ካለ ግን ራሱን ገምግሞ ባለፈው አላህን ምህረት ጠይቆ በቀጣዮቹ ቀናት ለመጠቀም ራሱን ያዘጋጅ። እድሚያችን አጭር ናትና አንዘናጋ!
ٱلشَّيۡخصَالِحُ بۡنُ فَوۡزَانۡ ٱلفَوۡزَانۡ
||
t.me/MuradTadesse
ረመዳን 1 ፣
ረመዳን 2 ፣
ረመዳን 3 ፣
ረመዳን 4 ፣
ረመዳን 5 ላይመለሱ ሄደዋል !
መልካም ከነበሩ ጨምርባቸው ፣
ካልነበሩ እንደገና ጀምር ‼
#ውድድሩ ከተሰጠህ ግዜ ጋ ነው።
Umer Yassin
🛑 ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች
📌 ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን
📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን
📌 ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን
📌 ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን
📌 ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን
📌 ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን
📌 በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል
📌 መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል
📌 ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል
📌 የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን
📌 ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል
📌 ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን
📌 ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን
📌 ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን
📌 በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን
📌 ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን
📌 የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም
📌 ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።
አላህ ያግራልን
ይህን ጽሑፍ ግን አንብባችሁታል⁉️
=======================
(እስኪ ካላነበባችሁት አንብቡትና ተገረሙማ!)
||
✍ «ማታ ከሥራ ወደ ቤት ከጓደኛዬ ጋር እየተመለስን ሰባተኛ አካባቢ እንደደረስን አጋጣሚ መንገድ ተዘጋግቶ ነበርና ጓደኛዬ ስልኩን ለመጎርጎር ከኪሱ ባወጣበት ቅፅበት አንዱ ላቦሮ(ሌባ)ጠብቆ መነተፈውና ሮጠ!
ወዲያው ዳር ይዘን ወርደን ልንከተል ስንል ተሰለበብን! ጓደኛዬም ተወው እንሂድ አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን! ደሞኮ ላቦሮ አይመስልም!አለባበሱ ምናምን የሌለ ነው!ስልኩ Huawei P50Pro ነው በሰአቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አልገባም ነበር!ስልኩ ከተለቀቀ ገና ወር ከምናምኑ ነው እሱ ኦርደር አድርጎ ነው በ90,000 ሺ ብር የመጣለት!
ከ5ደቂቃ በኃላ ስልኬን ተቀበለኝና ደወለ!በመጀመሪያው ጥሪ አላነሳም በ2ተኛው ጥሪ ላቦሮው አነሳው!ጓደኛዬም ስልኩን እንደማያገኘው ስላወቀ
"አንድ ነገር ልንገርህ?"አለው ላቦሪቲ ቀጥል ቀጥል ሰአት የለኝም አለችው!
"ይሄውልህ የኔ ወንድም ስልኩን የምትመልስልኝ ከሆነ እንደራደር" አለው! ጆሮው ላይ ዘጋበት!!
ድጋሚ ደውለን አነሳው"ያልከኝን እከፍላለው እንደራደር ነው ያልኩህ ስልኩን አትዝጋው ሲለው ላቦሪቲም "እንዳታስቡት" አለው!!!
"እሺ እንግዲያውስ ልንገርህ አዳምጠኝ ስልኩንየገዛሁት በ90,000ሺ ብር ነው ወላሂ፤የምምልልህ እንድታምነኝ ነው አንተ ባለማወቅ በሁለት ሺ እና በሶስት ሺ ብር ትሸጠዋለህ ስለዚህ አደራህን ስልኩን ከ80,000 ሺ እና ከ75,000 ብር በታች እንዳሸጠው ቢያንስ ይሄን ሽጠህ ከዚህ #ባለጌ_ስራ ተላቀቅና ትንሽዬም ቢሆን ራስህን የሚቀይር ስራ ጀምርበት"ብሎ ሶስቴ አደራ ብሎት ስልኩን ዘጋው!!
በ3ተኛው ቀን ላቦሮው በሌላ ስልክ እኔጋ ደወለ!ሰላምታ ተለዋወጥንና ማን ልበል ስለው?
"ባለ ስልኩ ነህ"አለኝ የትኛው ስልክ ስለው? "ባለፈው ስልክ የወሰድኩብህ ልጅ ነኝ"አለኝ "አዎ አዎ ነኝ" አልኩት
"የት ነህ?"አለኝ አሁን ያለሁት መርካቶ ነው አልኩት በቃ ስልክህን እሰጥሀለሁ መጣው"ሲለኝ እረ እኔልምጣ ብሮ አልኩት "አይ እኔ የሆነ ሱቅ አስቀምጥልህና ትወስዳለህ እሺ ስንት ልቀጣ?ስለው "ችግር የለውም እናወራለን" ብሎኝ ዘጋው!
ወዲያው ጓደኛዬ ጋር ደውዬ ነገርኩት ማመን አልቻለም! በድጋሚ ደወለና እዚህ ቦታ አስቀምጬልሀለው" አለኝ "እሺ እኔ ስንት ላስቀምጥልህ አልኩት "አይ ምንም ግን መልዕክት አስቀምጬልሀለው"አለኝ!
ወዲያው ያለን ቦታ ሄደን ስልኩን ተቀብለን መልዕክቱን ስናነበው "ይቅርታ ወንድሜ በጣም አመሰግናለሁ! በችግርና በታናሽ እህቴ ህመም ምክንያት ነው እዚህ ስራ ላይ የገባሁት ከቻልክ ግን እህቴን ማሳከሚያ ብር ስጠኝ" ይላል!!
እኛም እያዘንና እየተደሰትን ወደ ስራ ቦታ ተመልሰን ሻይ ቡና እያልን ደወልንለት!ጓደኛዬ አወራው "እኛ ምንም አናደርግህም፣በፈለከው እምልልሀለው፣ እህትህንም ታሳክማለህ፣ስራም ከፈለክ እኔጋ መስራት ትችላለህ" አለው!!
በጣም እንደፈራ ያስባንንበታል ግን "እሺ" ብሎን ዘጋው!
በማግስቱ ደውሎ የት ልምጣ?አለንና መርካቶ ጠራነው #ተገናኘን!የምር በጣም ደነገጠ! አቅፈን ሰላም አልነው!
መኪና ውስጥ አስገባነው እንዲረጋጋም ነገርነው!!
የሚፈልገውን ነገር ጓደኛዬ ጠየቀው"እህቴን ማሳከሚያ ብር ስጠኝና ስራ እናንተ ፈልጋቹልኝ እየሰራውእከፍላለሁ!አለንና #መርሀባ ተባብለን የወጪ ሰጥተነው እንሸኝህ ስንለው "አይ አያስፈልግም አለንና ከመኪና ወረደ!!
ይህ የሆነው ከ3ቀናት በፊት ነው ዛሬ እራት ጋብዘነው እህቱን ዘይረን ማሳከሚያ ብር ሰጥተነው ስራም ጓደኛዬ ጋር መጥቶ እንዲሰራ አመቻችተንለት ተለያየን።»
(የጻፈው ወንድም ዐብዱ-ል-ዓዚዝ ነው።)
@Zakiiir12
ዶ/ር ዛኪር ለልጄ ሚስት ፈልጉ እያለ ነው‼
=============================
✍ ብዙዎቻችሁ በዓለም አቀፍ ደረጃ በንጽጽር ዳዕዋዎቹ የምታውቁት ዶ/ር ዛኪር ናይክ፤ ዛሬ ከ3 ሰዓታት በፊት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ልጥፍ፤ በዳዕዋ ሥራ ላይ ለተሰማራው ለልጁ ለፋሩቅ ዛኪር ናይክ ሚስት የምትሆን ልጅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
ዶ/ር ዛኪር በልጥፉ ላይ ባያያዛቸው ሁለት ገጽ ጽሑፎች፤ በመጀመሪያው ገጽ የሚፈልጋትን ልጅ መስፈርት የዘረዘረ ሲሆን፤ በሁለተኛው ገጽ ደግሞ ስለ ራሱ ልጅ ዝርዝር መረጃ አስፍሯል።
እንደ ዶ/ር ዛኪር ያለ ታዋቂ ሰው ልጅ ሚስት በቀላሉ ማግኘት ይችላል ተብሎ የሚገመት ቢሆንም፤ በአደባባይ በዚህ መልኩ ማፈላለጉ ግን አግራሞትን ያጭራል።
He is Dr Zakir Naik's son. It's very easy for him to find a good woman. But what I don't understand is why searching his spouse through social media?
እንዲህ አይነት ነገር በሸሪዓችን ያለውን ብይን (ሑክም) በውል ባላውቅም፤ መስፈርቱን ተመልክታችሁ የምታሟሉ የገጼ ተከታታዮች ካላችሁ ሳትቀደሙ እንዲትቀድሙ ብዬ ነው ያጋራኋችሁ¡ ያው እጨነቅላችሁ የለ!
በወላጅ አባታችሁ (በወልያችሁ) በኩል ሲቪያችሁን በተቀመጠው አድራሻ ማስገባት ትችላላችሁ¡
ለማንኛውም ዶ/ር ዛኪር ሆይ! እንኳን ልፈለግህ በዘረዘርከው መስፈርት መሠረት
If I see this girl I will marry her¡ so I wouldn't tell you¡
ጉድ'ኮ ነው እናንተዬ! እንደት አይነት ዘመን ላይ ደረስን?
★
በነገራችን ላይ ካላመናችሁኝ ፖስቱን በዚህ ሊንክ ግቡና ተመልከቱ።
ፌስቡክ Blue Badge የሰጠው የራሱ ኦፊሲያል ገፅ ነው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=425359428952756&id=100044361072708
*
አላህ መልካሟን ሴት ይወፍቀው ወንድማችንን ፋሩቅ ዛኪር ናይክ!
❥:::::::::::የአሹራ ፆም:::::::::::❥
👉ከአሹራ ቀን በፊት አንድ ቀን አስቀድሞ መፃም የተወደደ ተግባር ነው። ትልቅ ምንዳንም ያስገኛል። የአሹራ ቀን ብቻ ነጥሎ ከሚፃም ሰውም የተሻለ ይሆናል።
✅ አብደላህ ኢብኑ አባስ ስራው አላህ ይውደድለትና እንዲህ አለ። የአላህ መልእክተኛ የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው ተባሉ። እሳቸውም፦ የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከኖርን ዘጠነኛውንም ቀን አስቀድመን እንፃማለን አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ከመድረሳቸው በፊት ወደ አሄራ ሄዱ።
📚(ኢማሙ ሙስሊም ሰግቦታል)
✅ ይህን በተመለከተ ኢማሙ ሻፍእይ፣ ባልደረቦቻቸው፣ ኢማሙ አህመድ፣ ኢስሀቅና ሌሎችም ኡለማዎች የዘጠነኛውና የአስረኛው ቀን በተከታታይ መፃም ይወደዳል ብለዋል። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ አስረኛውን ቀን ፁመውታል። የዘጠነኛው ቀን ግን ደርሰው ባይፃሙትም ከኖርኩ እፃመዋለሁ ብለው ነይተውታልና።
የ አሹራ ጾም👇👇👇#ነገ
የዘጠነኛው ቀን = ሮብ ኦገስት 18/2021
የአስረኛው ቀን = ሀሙስ ኦገስት 19/2021
የአስራ አንደኛው ቀን = ጁምዓ ኦገስት 20/2021
ይሆናል አላይ የወፍቀን አላህ ይወፍቃችሁ መልከቱን በፍጥነት #ሼር በማድረግ ሌላዉን ያስታዉሱ 👇👇
/channel/Zakiiir12
ዒድ ሙባረክ‼
===========
አላህ መልካም ሥራችንን ይቀበለን። ዒዱን አቅመ ደካሞችን፣ ህመምተኞችንና የቲሞችን በመርዳት እንዲሁም ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ እናሳልፈው።
የዛሬዋን ሰኞ ዙልሂጃ 9 (አረፋ) የፆምን ሁሉ አላህ ይቀበለን
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹የአረፋን እለት የፆመ ሰው ያለፈውን የአንድ አመትና
የሚመጣውን የአንድ አመት ወንጀሉን ያስምርለታል ብየ እከጅላለሁ›› ማለታቸው
ተዘግቧል። (ሙስሊም)
የነገዋ ቀን በዱኒያ ላይ ካሉ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀን ናት፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከፍተኛ
ቁጥር ያለውን ሙስሊም ከጀሃነም እሳት ነጅ የሚልበት ቀን ነው፡፡ በዚህች
በተቀደሰች ቀን አላህ የወፈቃቸው በአረፋ ተራራ ላይ ቆመው አላህን ሲማፀኑ
ይውላሉ፡፡ ከሃጅ ስነ ስርአት ውጪ ያለው በቢሊዬን የሚቆጠር ሙስሊም ደግሞ
ቀኑን በታላቅ ኢባዳ፣ በፆም፣ በዚከር፣በዱዓ፣በሰደቃ ባጠቀቃላይ በመልካም
ስራዎች ተጠድሞ ያሳልፈዋል፡፡
ይህ ውድ ቀን ሁላችንም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ለወንጀላችን ምህረት
የምንጠይቅበት፣ ከእሳት ነጅ እንዲያወጣን አልቅሰን የምንማፀንበት ፣ ሃገራችንን
እና አለማችንን ሰላም እንዲያደርግልን የምንለምንበት፣ ላስጨነቀን ሁሉ ነገር
መፍትሄ ለማግኘት አላህን የምንማጸንበት ቀን ነው፡፡
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) " በላጩና ምርጡ ዱዓ በዐረፋ ቀን ውስጥ የተደረገ ዱዓእ ነው"
ብለዋል ፡፡ (ቲርሚዚ እንደዘገቡት)
እራሳችንንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን እንዲሁም አጠገባችን ያሉ ሙስሊሞችን
የነገዋን የአረፋ ቀን በፆም እና በኢባዳ እንዲያሳልፉት እናስታውሳቸው
እናበረታታቸውም!
የነገን የአረፋ ቀን ፆመን ከእሳት ነጅ ከሚባሉት፣ወንጀላቸው ከሚማርላቸው እና
በዱኒያም ሆነ በአኼራ ስኬታማ ከሚሆኑት አላህ ያድርገን!!
@Zakiiir12
ተወዳቹ የዙል ሒጃህ ⑩ ቀናት‼======================(ያለፈውን የረመዷን ወር ሳትጠቀምበት አልፎብሃል? በወንጀል ጨቅይተሃል?)||✍ ስለ ተከበሩት ውድ የወርሃ ዙል ሒጃህ የመጀመሪያ አስርት ቀናት ትንሽ እንተዋወስ።"وليال عشر" ماذا بعد هذا القسم يا صديقي؟ እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች «በአስሩ ሌሊቶች» በማለት ታላቁ ጌታችን አላህ ምሎባቸዋል። ወንድሜ ሆይ! ከዚህ መሃላ በላይ ስለነዚህ ቀናት ታላቅነት ምን ማሳያ ይምጣ⁉️إنها فرصة تصحيح المسار مع الرب الكريم مقبلة فلا تكن لها من المدبرين. እነዚህ ቀናቶች ለወንጀል መታበሻ ጥሩ አጋጣሚዎች ናቸውና ሳታባክን በአግባቡ ተጠቀምባቸው። العشر فرصة لعلاج الأمراض القلبية فرصة للتقرب والتحبب لله الواحد الأحد. እነዚህ ቀናቶች ለቀልብ በሽታ ሕክምና፣ ወደ አንዱ አምላካችን አላህ ለመቃረብ እንዲሁም እርሱ ዘንድ ለመወደድ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው።في العشر من ذي الحجة ابكِ على خطيئتك ووجه قلبك لخالقك وتمنى على الله العفو والعافية.በነዚህ አስርት የዙል ሒጃህ ቀናት በወንጀልህ አልቅስ፣ ፊትህን ወደ ፈጣሪህ አቅጣጭ፣ አላህ ይቅር እንዲልህና ነፃ እንዲያወጣህ ተማጸን። تجتمع في هذه الأيَام أهمّ العبادات؛ حيث تجتمع فيها الصَلاة، والصِيام، والصَدقة، والحج. በነዚህ አስርት ቀናቶች ውስጥ አሳሳቢ የሆኑት ቁልፍ የዒባዳህ አይነቶች ይሰባሰባሉ። ሶላት፣ ጾም፣ ሰደቃና ሐጅ!في العشر طهر قلبك من كل دخيلة ونقيصة طهر قلبك من أسباب الذنوب هي فرصتك أنت فلا توليها الأدبارበነዚህ ቀናቶች ወደ ቀልብህ የገባውን ወንጀል አስወጣ፣ ታዘህ ላላሟላኸው ይቅርታ ጠይቅ፣ ወደ ወንጀል ከሚያዳርሱ መንገዶች ራቅ፣ ይህን አጋጣሚ ተጠቀምበት እንጅ ፊትህን እንዳታዞር።أرهقتك الذنوب ،ضيعت رمضان ،ها هي ( عشر ذي الحجة )منحة ربانية ..ወንጀልህ በዝቶ ተብትቦሃል፣ ረመዷንን በአግባቡ አልተጠቀምክበትም፣… لتبدأ صفحة جديده مع الله فرغ نفسك في هذه الأيام، وخفّف من الاشتغال بالدنيا، واجتهد؛ فإنها والله أيام معدودة، ما أسرع أن تنقضي، وتُطوى صحائفها.يبدأ صيام العشر الأوائل من ذي الحجة يوم الأحد ١١ يوليو ٢٠٢١ .. وذكر وفقك اللهየእስካሁኑን ህይዎትህን ተወውና ላለፈው ወንጀልህ አላህን መሃርታ ጠይቀህ ለወደፊቱ ከአላህ ጋር ያለህን አዲስ የህይዎት ምዕራፍ ጀምር።እነዚህ የተገደቡ አስርት ቀናቶች ብቻ ስለሆኑ ከዱንያ ጉዳዮች ቀነስ አድርግና በቁርኣን፣ በሶደቃ፣ በሶላት፣ በዚክር፣ በጾምና በመሳሰሉት መልካም ሥራዎች ላይ ተጠመድ።አላህ እኔንም እናንተንም ለሚወደው ተግባር ይግጠመን።|| @Zakiiir12
Читать полностью…እንዲህ አይነት ደስ የሚል ልጅ አላህ ይስጣችሁ።
♠
በነገራችን ላይ ⑤ አመት አልሞላውም!
አንደበቱ ሲጣፍጥ ግን!
ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ… ደስ ሲል!
ደግሞ ትርጉሙን የተረዳው ይመስል የሌለ ተመስጦ ነው የሚቀራው!
ወላጆች ልጆቻችሁን ገና በለጋነታቸው ከቁርኣን ጋር አስተዋውቋቸው።
«አሁን ፈታ ይበሉ!፣ ማጨናነቅ ነው!…» የሚባለውን ነገር ተውት። ፈታ ማለትን የምንመለከትበት መነፅር ነው ስለተንሸዋረረ እንጅ ቁርኣንን በለጋነታቸው ማስተማር ማጨናነቅ አይደለም። ኋላ ሲያድጉ ይጠቅማቸዋል።
ከወዲሁ አጠናክሯቸው!
||
t.me/zakiiir12
🎉ውብ ጁምአን ከነሱናው ተመኘሁላችሁ!
የጁምዐ ሱናዎች👇
👉ገላን መታጠብ
👉ሱረቱል ካህፍ ን መቅራት
👉በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት ማውረድ
👉ሰደቃ መስጠት
👉ንፁህ ልብስ መልበስ
👉 ሲዋክ (ጥርስን ማፅዳት)
👉መስጂድ በጊዜ መገኘት
👉ዳዓ እና ኢስቲግፋር ማድረግ
👉የጁሙዓ ኩጥባን ማዳመጥ
﷽ {إنّ اللهَ وملائكتَهُ يُصَـلُّونَ على النبي يا أيها الذين آمنوا صَلُّوا عليه وسلِّمُوا تسليما} اللهم صلِ و سلم على نبينا محمد ﷺ
•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•┈
🕋 የተባረከ ጁምዓ
#ሼር👇
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
Tᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ➤@zakiiir12👈
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ነገ ከጾማችሁ‼
===========
①) የሸዋልን ጾም ያልጨረሰ ወይም የረመዷን ወር ቀዿ ያለበት ካለ ይጹም።
•
②) ቀኑ ሐሙስ ስለሆነ ሐሙስን መጾም ደግሞ ሱን'ና ስለሆነ ይህንንም አብሮ ያስብ።
•
③) ቀኑ የወርሃ ሸዋል አጋማሽ (15ኛ ቀን) ስለሆነ «አያመ-ል-ቢዽ» ከሚሰኙት የወሩ ሦስት ቀናት መካከል አንዱ ነውና እርሱን መጾም ደግሞ ሱን'ና መሆኑን አስቦ ይጹም።
«በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ» እንዲሉ በአንድ ቀን ጾም ከነየታችሁ ሦስቱንም ማሳካት ትችላላችሁ።
♠
በአጋጣሚ ለመጾም የማያስችል ምክንያት ቢኖራችሁ እንኳ፤ ይህን መልዕክት ለሌላው ሰው በማመላከት የርሱን የጿሚውን ያክል ምንዳ ማገኘት ትችላላችሁ፤ ከርሱ ምንም ሳይቀነስበት። ወደ ኸይር ነገር ከማመላከት ነውና ሼር በማድረግ ሌሎችን አስታውሱ!
ምናልባትም መልዕክታችሁን አይቶ አስታውሶ የሚጾም ብዙ ሰው ሊኖር ይችላል።
@Zakiiir12
. ☞ ስጦታ እና ትዳር በኢስላም ውስጥ፡-
ስጦታ ለትዳር ማጣፈጫ ቅመም ሲሆን ሚስቶች ደግሞ ስጦታን የመውደድ ልዩ ተፈጥሮአዊ ባህሪ አላቸው፡፡ ባል ለሚስቱ ስጦታ ሲሰጣት ኢስላማዊ በሆነ መልኩና አላህን የሚያስደስት ሲሆን ይበልጥ ለትዳር ማማር ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡
@Zakiiir12
@Zakiiir12
የሂጅራ ባንክ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
Beeksisa Qaxarri hoji Baanki Hijraa
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/895574457450379/posts/1702890536718763/
እናንተ ሶላት ለማሰቆም ስትሞክሩ አቁመው የነበሩ ይጀምራል!!
ከቻላችህ ከትምህርት ቤት ፎርፈው ሺሻ ቤት እና መጠጥ ቤት የሚገባውን
ትውልድ አድኑት!!
# መስገድ#ወንጀል#አይደለም !!
المفتاح هو الصلاة
مفتاح حل جميع المشاكل هو الصلاة. أول صلاة في اليوم صلاة الصبحي في الجلسة الصباحية. ابدأ يومك بالصلاة ، ما الذي لم يحل ، ما هو ليس سهلا ، ما هو الصعب؟ المفتاح هو الصلاة.
"الصلاة خير من النوم" "الصلاة خير من النوم"
"الصلاة خير من النوم" "الصلاة خير من النوم"
ቁልፉ ሶላት ነው
የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ ሶላት ነው። የቀኑ የመጀመሪያው ሶላት በቀኑ የንጋት ክፍለጊዜ ላይ የሚገኘው የሱብሂ ሰላት ነው። ቀንህን በሶላት ጀምረህ፤ ምን የማይፈታ፣ ምን የማይቀል፣ ምን የሚያስቸግር ጉዳይ ይኖራል? መፍቻ ቁልፉ ሶላት ነው።
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”
#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ
ፆመኛ ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ ከፊል ነገሮች
፣
① ሀሜት፣ውሸት ፣ነገረኝነት እና ማንኛውንም አሉባልታ ወሬዎች
ፆመኛ የሆነ ሰው እነዚህን ሊጠነቀቅ ይገባዋል እነዚህን ነገሮች ካልተጠነቀቀ እየተራበ እና እየተጠማ ያለው በከንቱ ነው ማለት ነው ።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ በለዋል
"የውሸት ንግግርን እና በእሱ መስራትን ያልተወ ሰው ምግብ እና ፆም በመተዎ ለአላህ ጉዳይ የለውም" [ቡኻሪ 6057]
፣
② ውዱ በሚያደርግ ግዜ በአፍንጫው ውሃ ሲያስገባ(እስቲንሻቅ ሲያደርግ) በደንብ አለመሳብ
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም "ፀመኛ የሆንክ ግዜ ሲቀር በአፍንጫህ በደንብ ውሀን ሳብ" ብለዋል [ሱነን አቢ ዳውድ 2366]
ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው ውሃን የውዱ ግዜ በአፍንጫ በደንብ ወደ ውስጥ በመሳብ ማስገባት ሱና ነው ግን የፆም ግዜ ክልክል ነው ምክያቱም በደንብ ውሃውን ከሳብን ወደ ጉሮሯችን መግባቱ ስለማይቀር ነው በፆም ግዜ የተከለከለው።
፣
③ አብዛሀኛውን ወይን ብዙውን የቀን ክፍል መተኛት ለፆመኛ ጥሩ አይደለም ምክኒያቱም ውድ የሆነውን ግዜ ያለምንም ኢባዳ እንዲያልፍ ያደርግበታል (እንቅልፍም ኢባዳ አይደል ላላችሁኝ አዎ ግን መባል የያዘው ሁሉም በልክ ይሁን ነው)
ታላቁ ዐሊም ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
"ለፆመኛ በሶላት፣አላህን በማውሳት(በዚክር)፣በዱአና ቁራኣን በመቅራት (ግዜውን ሊያሳልፍ) ይገባዋል። ሰው በፆመ ግዜ ነፍሱን በተለያየ ኢባዳ ካላመዳት ይህ ለሱ ይገራለትል። (ግን በተቃራኒው ነፍሱን)
በስንፍና እና ረፍት(እንቅልፍ) በማብዛት
ከሆነስ ያላመዳት እሄንኑ ስንፍናውን እንጅ ሌላን አይለምድም (ሁኔታው እንዲህ ከሆነች) የፆመ ግዜ በእርሱ ላይ መልካም ስራ እና ዒባዳዎች ይከብዱበታል" [መጅሙኡል ፈታዋ ወረሳኢል 19/171]
፣
④ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ሚስቱን መሳም ይህም በፆም ሰአት ሊጠነቀቁት የሚገባ አደጋ ነው።
ኢብኑ አብዲል በር (ረሂመሁላህ)
"ሚስቱን ከመሳም የተነሳ ፆም የሚያበላሽ ነገር የሚመጣበት ለሆነ ሰው መሳምን(ይፈቀዳል) ያለ (ዐሊም) አንድንም አላውቅ" ይላሉ [አት-ተምሂድ 5/114]
ስለዚህ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ከንደዚህ አይነት ድርጊት እራሱን ሊቆጥብ ይገባዋል
አላህ ፆማቸውን ከተቀበላቸው ያድርገን
፣
⑤ ፉጡርን ማዘግየት ብዙ ሰዎች ፀሀይ ተገባ በሗላ ፉጡርን የሚያዘገዩ አሉ አንዳዶች አዛንኳ እየተደረገ ከሶላት በሗላ ካልሆነ እንጅ የማያፈጥሩ አሉ ይህ ስህተት ነው። ፀሃይ መግባቱ ከተረጋገጠ ፉጥርን ማቻኮል ሱና ነው። ነቢዩ(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ "ሰዎች ፉጡርን እስካቻኮሉ ድረስ ከመልካም ነገር አይወገዱም" 【ቡኻሪና ሙስሊም】
፣
IbnuMuhammedzeyn
፣
✍ወንድማችሁ ኢበኑ ሙሀመድዘይን
ትርጉሙን ላላችሁኝ ጭብጡን ይሄው፦
ልጄና ባለቤቱ አንዳቸው ለሌላቸው አጠናካሪ ሆነው ለሌሎችም ቅናቻ ምንጭ ይሆኑ ዘምድ ጥሩ ጸባይ ያላት መልካም ሴት ለልጄ ፋሩቅ ሚስት እፈልጋለሁ።
ከታች ያሰፈርኳቸውን መስፈርቶች የምታሟላ ተገቢ ልጅ አለችኝ የሚሉ አባት ከሆኑ ምላሽ ይስጡኝ።
ዋና ዋና መስፈርቶች፦
①) በቁርኣንና በትክክለኛ ሐዲሥ መሠረት እስልምናን የምትተገብርና ግደታዋን በአግባቡ የምትወጣ፣
②) ከክልክል (ሐራም) ድርጊቶች የታቀበች፣
③) በተቻለ መጠን ተወዳጅ ሱንና ድርጊቶችን የምትተገብር፣
④) ደግ፣ የተቀደሰችና የመልካም ስነ ምግባር ባለቤት፣ ትሁትና ርኅሩኅ የሆነች፣
⑤) ለዳዕዋና ኢስላማዊ አስተምህሮን ለማሰራጨት ተነሳሽነቱ ያላት፣
⑥) በዳዕዋ እንቅስቃሴዎች ባሏን ለማገዝና ለማጃገን ሙሉ ፈቃደኛ የሆነች፣
⑦) ቀለል ያለና ያልተንደላቀቀ ህይዎትን ለመኖር ፈቃደኛ የሆነች፣ በአላህ ፈቃድ ልጄና ባለቤቱ የተመቻቸ ህይዎት እንዲኖሩ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ነገሮች እንደፈለጉት አላመች ቢሉ፤ ለአላህ ሲሉ ምቾታቸውን መስዋእት ለመክፈል የግድ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
⑧) እንግሊዝኛ አቀላጥፋ መናገር የምትችል፣
⑨) በሃገረ ማላይሲያ ለመኖር ፈቃደኛ የሆነች፣
*
ተጨማሪ ግደታ ያልሆኑ ተመራጭ መስፈርቶች፦
①) የቁርኣን ዐረብኛን የምታውቅ፣
②) ዳዒያህ የሆነች፣ እስልምናን ሙስሊም ላልሆኑና ለሆኑ የምታስተላልፍ፣
③) በየትኛውም ኢስላማዊ የጥናት መስክ የባችለር ድግሪ ያላት፣
④) ቁርኣን የሐፈዘች፣
⑤) ከኢስላማዊ ተቋም ጋር ንቁ ግንኙነት ያላት፣
⑥) የበርካታ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ዳዒዎችን ትምህርት ያዳመጠች!
╔═══════════════╗
የረሱል ኒካህ ዕለት
══════════════
የሙሽሪት እና የሙሽራው አጎቶች ተሰባስበው ወጉን ሊጀምሩ እርስ በርስ እየተያዩ ነው። የሙሽራው አጎት የሆነው አቡ ጣሊብ ከመሐል ብድግ ብሎ ቆመ።
ስፍራው ላይ የታደሙት ሰዎች አቡ ጣሊብ ለመናገር እንደቆመ ሲረዱ ፅሞናን አሰፈሩ። አቡ ጣሊብም ንግግር ጀመረ፦ "የኢብራሂም ዝርያዎች እና የኢስማዒል ፍሬዎች ያደረገን ጌታ የክብርነት ቤቱ ጠባቂያዎች እና የጎብኚዎቹም ተቀባይ ስላደረገን ጌታችንን እናመሰግናለን። በመቀጠል ይህ የወንድሜ ልጅ ምንም እንኳ ደሃ ቢሆንም ከመካ ቁረይሽ ወጣቶች ብታነፃፅሩት ብጤ የሌለው ሲሆን በልግስናም፣ በትህትናም፣ በክብርም ማንም አይስተካከለውም። ባለ ፀጋነት እንደሆን የቀን ጥላ ማታ ጠፊ ነው። ልጃችን ልጃችሁን የከጀለ ሲሆን ልጃችሁም ልጃችንን ከጅላለች እና የሻችሁን የመህር ተመን ወስኑ ከፋዩ እኔ ነኝ" ብሎ የሽምግልና ሂደቱን አስጀመረ።
የሙሽሪት አጎት እሷን ወክሎ ሊድራት ከተሰየመበት መንበር ተቀምጦ እንዲህ አለ፦ "ባወሳኋቸው ፀጋዎች ሁላ ለጌታችን ምስጋና ይገባው። የመላው አረብ በላጮች ስላደረገንም እያመሰገንን እናንተም በኑ ሀሺሞች የዐረብ ሁላ ቁንጮ መሆናችሁን እንመሰክራለን። እኛም ከናንተ በሚያስተሳስረን የዝምድና ገመድ ለመተሳሰር ከጅለናል" ብሎ ሽምግልናውን ተቀበለ።
ንግግሩን ቀጠለ። በስፍራው ወደታደሙ የቁረይሽ ነገዶች ፊቱን አዙሮም፦ "እናንተ የቁረይሽ ነገዶች ሆይ! እኔ ኸዲጃ ኹወይሊድን ለሙሐመድ ዐብዱላህ የዳርኩ ስሆን እናንተም ምስክር ሁኑ" ብሎ ለኸዲጃ የአለማቱን ክብረት ሸለማት።
ይኼኛው የረሱል (صلى الله عليه وسلم) ሰርግ ቢያመልጠንም ነገ በአኪራ በጀነት እልፍኞች ውስጥ የሚደገሰውን ሰርጋቸውን
"ንፁህ ልብ ብዙ ትጎዳለች ትሰበራለች
ነገር ግን ጥላቻን በፍፁም አታውቅም!"
ሀገራችን ውስጥ ከልብ ያፈቀረ ከልብ ይጎዳል ይባላል ግን ሀሰት ነው!
አላህ ሶብሩን ይጨምርለታል እንጂ መቼም አይጠላም! ከልብ የተፋቀሩ ልቦች ይቃረናሉ፣ይሰዳደባሉ፣ይላቀሳሉ ነገር ግን መቼም አይለያዩም!
ይህ ነው ሀላሉ በሸሪዐው መሰረት የተጣመሩ ልቦች እስከተፋቀሩ ድረስ አይለያዩም!
ሀላሉን ይወፍቀን
በዱዐ አትርሱኝ
@Zakiiir12
ዒድ-ሙባረክ!
እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሰን!
ቀናት ቀናቶችን እየወለደ የተከበሩት አስርቱን የዙልሂጃ ቀናቶች አገባደን እነሆ
ለኢዱ ደርሰናል:: አልሐምዱሊላህ
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከእስልምና ማዕዘናት መካከል አንዱ የሆነው የሐጅ
ስነ ስርዓት የሚከናወንበት በውስጡ ብዙ አስተምህሮቶችን የያዙ ታሪካዊ
ክስተቶችን አቆራኝቶ የያዘ ታላቅ በዓል ነው፡፡
የሐጅ ስነ ስርዓት በዘንድሮ አመት በድጋሚ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በ60ሺህ
ምዕመናኖች ብቻ ተገድቦ ቢከናወንም ከመላው አለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ
ሙስሊሞች ወደ ቅዲስቲቷ መካ በማምራት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን
የሚፈፅሙበት ስነ ስርዓት ነው፡፡
በዚህ ስነ ስርዐት ላይ በዋናነት ከምንቀስማቸው ትምህርቶች መካከል
አንድነትን፣ እኩልነትን፣ ታጋሽነትን፣ ታዣዥነትን፣ መስዋትነትን፣ በአላህ ላይ
መወከልን ፣ መተሳሰብን እና አለምቀፍ ወድማማችነትን ነው፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ለአንድ አላማ፣ በአንድ ቦታ፣ በአንድ አይነት
አለባበስ፣ በአንድ አይነት የአምልኮ ተግባር የሚሰባሰቡበት ፤ ዘረኝነት እና ቁሳዊ
መበላለጥ በእስልምና ቦታ የሌለው መሆኑን በተግባር የሚገለፅበት ስነ ስርዓት
ነው፡፡
የነብዩላህ ኢብራሂም አንድዬ ልጃቸው የሆነውን እስማኤልን ለመስዋትነት
እንዲያቀርቡ ታዘው የጌታቸውን ትዕዛዝን ተቀብለው ለመፈፀም መንቀሳቀሳቸው
የታዛዥንትን ጥግ ሲያስተምሩን፣ ባለቤታቸው ሀጀራ ደግሞ በበርሃ ላይ ነብዩላህ
ኢብራሒም ጥለዋቸው ሲሄዱ "አላህ አዞህ ከሆነ እሱ አይተወንም አላህ
በቂያችን ነው" በማለት የተወኩልን ጥግ ያሳዩበት ድንቅ አስተምህሮቶችን
የምንዘክርበት በዓል ነው ኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል፡፡
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሰው ልጆች እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩል
መሆናቸውን በዘር፣በቀለም፣በብሄር እና በውጫዊ መገለጫዎች የማይበላለጡ
መሆኑን በተግባር የምንማርበት፣ እኩልነትን ብቻ ሳይሆን በዓሉ የሁሉም የደስታ
ቀን መሆን ስለሚገባው በኡዱሂያ እርድም ከሚታረደው እርድ አንድ ሶስተኛውን
ለሚስኪኖች እና ለአቅመ ደካሞች እንድንለግስ፣ማህበራዊ ትስስራችን ይበልጥ
ይጠናክር ዘንድም ሌላውን አንድ ሶስተኛ ለጎረቤቶቻችን፣ለዘመድ አዝማድ እና
ለሌሎች እንድናካፍል የታዘዝንበት ድንቅ የአንድነት እና የመተሳሰብ በዓል ነው፡፡
የዘንድሮን በዓልን ስናከብርም ከበዓሉ ጋር የተሳሰሩትን አስተምህሮቶች በተግባር
አስተንትነን በህይወታችን ተግባራዊ የምናደርግበት፣ በችግር ላይ ያሉ
ወገኖቻችንን የምናስታውስበት እና የምናግዝበት፣ለሃገራችን ሰላም እና
መረጋጋትም ከልባችን ዱዓ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ለማስታወስ
እወዳለሁኝ፡፡
በድጋሚ የኢዱ ቀን የደስታ፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ መልካም
ምኞቴ ነው
ኢድ ሙባረክ
@Zakiiir12
ነገ ሰኞ ሀምሌ 12/2013 የዐረፋ ቀን ነው።
★★★★★★★★★★★★★★
★ T.me/Zakiiir12
🔴 የአላህ መልክተኛ [ﷺ] «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢአት ያስምራል።» ብለዋል። ሙስሊም ዘግበውታል።
ኢማም አል—ሙናዊ [ረሒ] እንዲህ ብለዋል: ‐ ገና ያልተከሰተውን «የመጪውን ዓመት ኃጢኣት» ያስምራል ሲባል ምን ማለት ነው?: —
❶ በመጪው ዓመት ከኃጢኣት ይጠብቀዋል ማለት ነው።
❷ ለመጪው ዓመት ኃጢኣቱ ማሰረዣ የሚሆን ምንዳ ይሰጠዋል ማለት ነው።
ወይም
❸ ሰውየው በህይወት ቆይቶ ኃጢኣት ቢሰራ እንኳን ይሰረዝለታል ማለት ነው።»
ፈይዱል ቀዲር ቅፅ 4፣ ገፅ 230
መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምክንያት እንሁን።
💚ትንፋሻችንን ለሌላው ማጋራት
ስስታምነታችንን ለመቀነስ ያጎለብተናልና
ልባችንን ለናንተም ገር አድርገናል!
ልብ አላቸው ለምትሏቸው ልባችንን አጋሩልን!😊
@alem_alhub
ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሰኔ 01 ቀን 2013 E.C እና ሰኔ 02 ቀን 2013 E.C በ http://portal .aau.edu.et በመጠቀም የኦንላየን ምዝገባ እንድታከናውኑ እያሳሰብን፡
1. በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኔ 19 እና ሰኔ 20 2013 E.C
2. የገጽ ለገጽ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 E.C
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ
የሚከተሉትን መረጃዎች በ www. aau.edu.et ስለሚገኙ ከወዲሁ እንድትጠቀሙባቸውና አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
1. ምዝገባችሁን ከወዲሁ እንዴት ማከናወን እንዳለባችሁ፤
2. የተመደባችሁበትን የዩኒቨርሲቲ ካምፓስ መኝታ ቤት ቁጥር እንዴት ማወቅ እንደምትችሉ፤
3. ለአንደኛ ሰሚስተር ትምህታችሁ የምትጠቀሙባቸው በዩኒቨርስቲው የተዘጋጁ ሞዱሎችን ለማግኘት፤
4. በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ በምትቆዩበት ግዜ ማወቅ ስላለባችሁ የአካዳሚክ እና ሌሎች ደንቦችና መመሪያዎች፤
አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት @Zakiiir12
🖤ትዝታ
(ያስሚን)
አንተማ ሄደሃል የኔን ልብ በመስበር፣
የ ትዝታን አለም ባትሰጠኝ ኖሮ፣
ምን ያፅናናኝ ነበር?
'ደረቴ ላይ መተኛትሽ ሰላሜ ነው!' እንዳላልክ፤ ያለኔ ከመኖር መሞት እንደሚበጅህ እንዳልነገርከኝ፤ የዝምታዬ ለቅሶ በጩኸት ሲፈነዳ ግን ኮበለልክ። ርቀህ ሄድክ፤ ፍቺ ይሉትን አለም፣ መራራቅ የተሰኘውን የሞት ጣእም አሳየኸኝ። ግን አልጠላህም፣ ለዛም ነው ከሰርጋችን አንስቶ ያሳለፍናቸው የኋሊት እየደገምኩ ራሴን የማፅናናው።
ይብላኝ እንጂ ላንተ! ትዝታዬንም እኔንም በመራቅ ህመም ለገዛኸው፤ እኔ ግን አልሀምዱሊላህ ከአሁኑ አለም ተሰናብቼ የትዝታ አለምን አግኝቼዋለሁ። ያ ፍፁም ደስታ፣ ካለምንም ሀዘን የሰፈረበት ቦታ ላይ አሁኔን ሰውቼ ትናንቴ ላይ ቆሜ ቀርቻለሁ።
'ሀያቲ በልተሻል?'
'ስጠብቅህ አልበላሁም'
'ማን ስለሆንሽ ነው ስለኔ ምታስቢው? ምትወጂኝ ከሆነ ራስሽን ውደጂልኝ' ኮስተር ብለህ ስታወራ እንዴት እንደምታምረኝ። የኔ አለመብላት ይጨንቅህና ከደረትህ ሸጉጠኸኝ ፀጉሬን እየደባበስክ ታጎርሰኛለህ! አሁንስ? በትዝታችን ጠልቄ ከእህል እንደራቅኩ ብታውቅልኝ ምናልባትም 'ሀያቲ' እያስባለህ ታቅፈኝ ነበራ? ምን አርጌህ ነው እንዲህ በአንዴ የጠላኸኝ? እኔ ግን አላህዬ ያውቅብኛል እሱ ዘንድ ካንተ ሌላን እስከማላወሳ ድረስ መውደዴን፤ ፍቅሬ በመፅሀፍ ቢደረስ በስርአቱ እንደማይገለፅልኝ፤ በሞቴ ደጃፍ ያንተን ፈገግታ ማየቴ ጣእረሞትን እንደሚያስረሳኝ፤ መሻቴን ሁሉ ላንተ አንድ ፈገግታ መሰዋት እንደሚቀለኝ፤ ነፍሴ በእጁ የሆነው ጌታ ብቻ ሊረዳው ሚችለው ያህል ልቤን ሞልተሃል።
እስትንፋሴ ድምፅ ቢኖረው አንተን ብቻ እስከሚል ድረስ መውደዴ፤ መራራቅ ይሉትን ከሞት የገዘፈ ሞት አሳየኝ። ሳቄን ነጠቀኝ፤ ልቤ ነበርክና የሰውነቴን መሪ ፍርክስክሱን አውጥተህ 'እንለያይ!' በሚል አጭር ልብ ሰባሪ ቃል ተለያየን። አልሀምዱሊላህ! አልጠላሁኽም፤ አሁንም ትናፍቀኛለህ። ከእቅፍህ ተጋድሜ ፈገግታህን ማየት እናፍቃለሁ። ለዛም ነው ከሀዘን ድባቴ ወደ 'ትዝታ' ምሽግ አምልጬ የገባሁት። አንተ ያልታደልከውን ትዝታችንን እየቃኙ መደሰትን ያለማንም ተቀናቃኝ አግኝቼዋለሁ።
አላዝንም፤ ከኔ ላይ አይደለም አንድ፣
የምድርን ሴት ሁላ ብትደርብ ፍቅርህ ይገዛኛልና ይቅርታዬ ያንተው ነው። እወድሀለሁ፤ በቃላት ሳይሆን በልብ ተግባቦት፣ በአይን መልእክተኝነት የሚደርስ ፍፁም ሰላማዊ ፍቅር፤ ፍፁም ጥልቅ መውደድ ላንተ ብቻ አለኝ። ያም ነው ልቤን ወግተህ ስትጨርስም፣ ይቅር በለኝ ብዬ እኔው ይቅርታ እንድጠይቅህ ሚያረገኝ!
ይቅር በለኝ ጓዴ! ከልቤ ብቻ አንተን መውደዴ እንዳሳነስኩህ እንዲሰማህ እንዳደረገህ ይገባኛል፤ ግና የኔ ደነዝ እኔ አቅመ ቢስ ነኝና፤ ልቤም ደንዳና ነውና ያንተን ያህል ከሩህ የሚፈልቅ ማፍቀርን አልቻለም!
አውፍ በለኝ ሆዴ! እያንዳንዷን ውሎህን እና ደህንነትህን ከመጠየቄ ባለፈ አተነፋፈስህን ልጠይቅህ አልቻልኩም! ለድክመቴ ሁላ አፉታህን!😔
ይቅርታህን ሆዴ ፍቅሬ ስላነሰ፤
ከልቤ ላይ አልፎ ነድዶ ስላልጬሰ፤
ልቤ ትንሽዬ፣
አቅም የላት ምግባር በብዙ ማትወድ፤
አህዋልህን እንጂ እስትንፋስ ማትለምድ፤
አንተንትህ ክዷት ሲኮበልል ጥሎ፤
ሌላን ማለት አትችል ቃላትን አቻኩሎ፤
ይቅርታን ብቻ ነው፣
በፈገግታህ ናፍቆት ሰውነቷ ዝሎ!
#ያንተው 'ሀያቲ'💚
@Zakiiir12
"ኒካህ ለማሰር መስፈርቱ ወልይ እንጂ ገንዘብና እድሜ አይደለም! ሀቢቡና ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ከአኢሻ (ረ.ዐ) በዕድሜ ይበልጡ ነበር ከእናት ኸዲጃ(ረ.ዐ) ደግሞ ያንሱ ነበር!ከባልተቤቶቻቸውም ጋር ምግብ ሳይቀምሱ ውለው ያድሩ ነበር!!! ግና ሙሀባቸው ተነግሮ አያልቅም እንደነሱ የሚዋደድምአልነበረም!!
የኛ ደሞ ከነሱ በተገላቢጦሽ ገንዘብና እድሜ የምንመለከት ሲሆን የወልይ ጉዳይ አያሳስበንም!
ሱና የምንከተል ከሆነ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ መስፈርታችንን እናርም!!!
@Zakiiir12