በመላ ሀገራችን ዛሬ የሚጀምረውን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች በያሉበት ቦታ መልካም ዕድል እንመኛለን።
መልካም ፈተና ይሁንላችሁ ይቅናቹ 🫶
የአሹራ ፆም
ሙሐረም 10 ነብዩላህ ሙሳ(ዓ.ሰ) ከአንባገነኑ የፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነው::
ይህን ቀን አንድ ቀን ቀደም ተብሎ ሙሐረም 9 አልያ ሙሐረም 11ን በማስከተል መፆም
ይወደዳል::
የፊታችን እሁድ የሙሀረም ወር ዘጠነኛው ቀን ነው - ረሱል ስለ አሹራ ፆም ሲናገሩ "ምናልባት
ለሚቀጥለው አመት በህይወት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም እፆማለሁ ብለዋል (ሶሒሁ ሙስሊም
1134)
ሙሐረም 10 የአሹራ ቀን ዕለተ ሰኞ ነው:: ይህን ቀን መፆም የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ)
"የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል (ሶሒሁ
ሙስሊም 1163)
ቤተሰባችንንም ሌላውንም ይህን መልዕክት እናስታውስ!
@Zakiiir12
«#ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም !
ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።
ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።
በዚህም፦
👉 1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤
👉 45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤
👉 100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤
👉 የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።
(ማስታወሻ ፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)
ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።»
©: ቲክቫህ
👉ለመልካም ነገር እንጠቀምበት
@Zakiiir12
ከተከበሩት የዙልሒጃ 10ቀናቶች ውስጥ የመጀመሪያው ቀን ላይ እንገኛለን
በነዚህ ውድ ቀናቶች የኢባዳዎች ሻኛ በሆነው በዱዓም ልንበረታም ይገባል
አላህ ሆይ:-
ኢማናችንን እንድትጨምርልን እንማፀንሃለን፣ እድሜያችንን ባርክልን፣
የአካላችንን ጤንነት ጠብቅልን፣ ሲሳይችንን አስፋልን፣
ጌታችን ሆይ
ጥርት ያለች ተውበትን ከመሞታችን በፊት ወፍቀን፣ በምንሞትበት ወቅትም ሸሃዳ
ግጠመን፣ ከሞትንም ቡኃላ ምህረት አድርግልን፣ በሂሳብ ወቅትም ጉድለታችንን
እለፍልን፣
ኢላሂ
ከእሳት ቅጣትህ ጠብቀን፣ ጀነትህንም ወፍቀን፣ በመጨረሻም የተከበረውን
ፊትህን ለማየት የምንበቃ አድርገን
አሚን
ወንድሜ ሆይ ‼
ለሴት ልጅ ምን ያህል ክብር አለህ ❓❓
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
የአንድን ማህበረሰብ የስልጣኔ እምርታ ከሚወስኑ ትላልቅ ነገሮች መካከል ለሴት ልጅ ያለው ቦታ ዋነኛው መሆኑ ነው ።
ሴት ልጅ ማን ናት ❓ ምንድን ናት ❓
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➖ እናትህን ➾ ስታይ ከ እግሯ ስር ያለውን ጀነት አስታውስ
አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡፡ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና፣ አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ ከሰዎች ሁሉ በበለጠ ጓደኝነቱን ወይም ግንኙነቱን ልጠብቅለት የሚገባ ማን ነው? አላቸው፡፡
እሳቸውም፡ ‹‹እናትህ›› አሉት፤ ከዚያስ? አላቸው፤ ‹‹ከዚያም እናትህ›› አሉት፤ ከዚያስ? አላቸው፤ ‹‹አሁንም እናትህ›› አሉት፡፡ ለአራተኛ ጊዜ፡ ከዚያስ? አላቸው፣ ‹‹ከዚያማ አባትህ ነው፡፡›› አሉት፡፡ (አል ቡኻሪ 5626 / ሙስሊም 2548)
➖ ባለቤትህን ➾ ስታይ "ከእናንተ በላጩ ለባለቤቱ ምርጥ የሆነው ነው" የሚለውን አስታውስ...
እናታችን ዓኢሻ(ረ.ዐ)፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡-
‹‹በላጫችሁ ለቤተሰቦቹ መልካም የሆነው ነው፡፡ እኔ ለቤተሰቦቼ መልካማችሁ ነኝ፡፡›› (አል ቲርሚዚ 3895)
➖ ሴት ልጅህን ➾ ስታይ በመጪው ዓለም ከእሳት ከለላ እንደምትሆንህ አስታውስ...
ዑቅበቱ ኢብኑ ዓሚር(ረ.ዐ) ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡
‹‹ሦስት ሴት ልጆች ኖረውት፤ ስለነርሱ ትዕግስት አድርጎ፣ ጥሮ ግሮ ከላቡ ውጤት ያበላቸው፣ ያጠጣቸውና፣ ያለበሳቸው ሰው፣ የትንሳኤ ቀን ከእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል፡፡›› (ኢብኑ ማጃህ 36
የመልእክተኛህን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)
አደራህን አትዘንጋ ‼️
➖ "የሴቶችን ነገር አደራ
➷➷➷➷
. 📌 "ሴትን ልጅ አያከብርም
የተከበረ ቢሆን እንጂ ❗️
📌 ሴትን ልጅ አይንቅም
የተረገመ ቢሆን እንጂ‼ ብለዋል ።
➷➷➾➾➾➾➷➷➷➾➾➷➾➷➾➷
አንተ ውድ ወንድሜ የአላህ ባሪያ ሆይ ስማኝማ አንድ ያልተገነዘብከው ነገር አለ‼️
📌 የቅርብ ዘመድ ባትሆንም፣
➖ ረዳት የሌላትን ደካማ ሴት መርዳትና ማገዝ ልዩ ክብርና ደረጃ የሚሰጠው መሆኑን እስልምና አጽንኦት ሰጥቶታል፡፡
➖እሷን ለመርዳትና ለማገዝ መሯሯጥ አላህ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው ተግባር መሆኑን በመግለጽ አነሳስቷል፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
➖ ‹‹ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና
➖ የችግረኞችን ጉዳይ ለመፈፀም የሚሯሯጥ ሰው፣ ልክ በአላህ መንገድ ላይ ትግል እንደሚያደርግ፣ ሌሊት ተነስቶ ሳይታክት እንደሚሰግድና፤ ጾሞ እንደማያፈጥር ሰው ነው፡፡›› (አልቡኻሪ 5661 / ሙስሊም 2982)
ኢስላም
➖ ሴት ልጅ ልዩ ትኩረት እንዲቸራቸው አድርጓቸዋል
➖ ሴት ልጅን እጅግ በጣም አክብሯታል ።
ስለዚህ አንተ ማነህ እና ነው በሷ ላይ የበላይነት የሚሰማህ ❓
ሴት ልጅ አዛኝ እንጂ ደካማ አይደለችም ። በእዝነቷ ስትታዘዝህ እራስህን ቆልልህ እንደ ክፉ ንጉስ አትሁንባት ።
ወንድሜ ሆይ አንድ ምክር ልምከርህ ‼️
እሷን ስትፈልጋት ለዱንያ ሃብት ማካባቻ
ሳይሆን ለትዳርህ ታማኝ
ለልጆችህ ሷሊህ እናት
ላንተ አላህን አስተዋሽ እንድትሆንህ ምረጣት ።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት‼️
====================
✍ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።
እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 E.C. ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 E.C. ድረስ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 E.C. ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 E.C.
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 E.C.
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 E.C.
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014
መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014
ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 በቅጣት ግንቦት 1 /2014
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11
መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014
ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14
የጀማዓህ ተቀባዮችን ዝርዝር በውስጥ ላኩልኝ።
➧. #ዛሬ_ለሊት_ረመዳን_27_ለሊት_ነው !!
✅. አብዛሃኛው ኡለማዎች ለይለተል ቀድር የሚከጀለው በዚህ ለሊት እነደሆነ ይገልፃሉ!!
አደራህን ወንድሜ አንቺም እህቴ አንሳነፍ እንበርታ እንጠንክር እስኪ በተቻለው አቅም በቁርኣን በሶላት እናሳልፍ አላህ ለይስሙላ ኪሚሰሩት ሳይሆን የሱን ፊት ከጅለው የሚቀሩት የሚቆሙት ያድረገን አሚን!
የለይለተል ቀድርን ደረጃ ከሚገልጹ ነገሮች ውስጥ:-
1/ቁርኣን የወረደው (መውረድ የጀመረው) በዚህች ሌሊት መሆኑ
2/ አሏህ ሱብሓነ ወተዓላ ሌሊቷን "ለይለተል ቀድር" (የውሳኔና የተከበረች ሌሊት) ብሎ መሰየሙ
3/ የተከበሩ እና ቅዱስ የሆኑ መላኢኮች በዚህች ሌሊት በብዛትና በተደጋጋሚ የሚወርዱ መሆናቸው
4/ በዚህች ሌሊት የሚሰራ ዒባዳ ከአንድ ሺ ወር (ከ83 ዓመት) ዒባዳ የሚበልጥ መሆኑ
5/ በቀጣዩ አመት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች በሙሉ የሚወሰንባት ሌሊት መሆኗ
6/ አሏህ ሱብሓነ ወተዓላ ይህችን ሌሊት ሰላም ብሎ መሰየሙና ለሙስሊሞች ሰላም የሆነች ሌሊት መሆኗ
7/ አሏህ ሱብሓነ ወተዓላ ይህችን ሌሊት በተመለከተ አንድ ሙሉ የቁርኣን ሱራ ማውረዱና ወዘተ የዚህችን ሌሊት ደረጃ ገላጮ ናቸውና እኛም ዒባዳዎችን በማብዛት ከሌሎች ሌሊቶች ልንለያት ይገባናል👌🏻
اللهم وفقنا ليلة القدر.
واعف عنا وعافنا وأصلح شأننا وشأن أمتنا.
واغفر لنا ولوالدينا ولمشاينا وأحبابنا.
🔸ያረብ፥ የኡመቱን ቀልብ በሐቅ ላይ አንድ አድርገው ወደ አንተ መንገድ የሚጣሩ ሰዎችንም አግዛቸው ተሳስቶ ከማሳሳትም ጠብቃቸው በለይለተል ቀድርም መልካሙን ሁሉ ክተብልን! መመለሻችንም ጀነት አድርገው ከእሳትም ጠብቀን
"አሚን"
የረመዳን 27ተኛ ለሊት
★★★★★★★★★★★
በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ83 ዓመት ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ ሰሀባዎች ውስጥ፥ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም ለይለተል-ቀድር የረመዳን 27ተኛ ለሊት ላይ ናት ይሉ ነበር!
ይህች ለሊትም ዛሬ ማክሰኞ ምሽት ላይ ናትና እንበራታ!
👉. ሁላችሁም ለአላህ ብላችሁ በዱዓችሁ አትርሱኝ ለአላህ ብላችሁ ዱዓ አድርጉልኝ አላህ ይቀበላችሁ ይቀበለን ለይለተል ቀድርንም ይወፍቀን አደራ በዱዓ🤲🤲 #ወንድማችሁ_ማህሙድ_አሰን_አሊ‼
❀ـــــــــــــ🍃🌸🍃ــــــــــــ❀
🌹. @Muslim_negn
🌻. @Muslim_negn
🦋............🍃🌹🍃..........🦋
🛑 ተሀጁድና ተራዊሕን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች
📌 T.me/ahmedin99
📌 ኢማሙ ለሱጁድ አትአቲላወህ ሱጁድ ወርዶ ሳለ ሩኩዕ ያደረገ መስሎት ሩኩዕ የወረደና "ኢማሙ፥ አላሁ አክበር" ብሎ ሲነሳ መሳሳቱን ያወቀ ሰው ከሩኩዑ ፈጥኖ በመነሳት ኢማሙን መከተል ብቻ ነው የሚጠበቅበት፣ለብቻው የቲላወህ ሱጁድ አድርጎ(ወርዶ) መመለስ አይፈቀድለትም
📌 ኢማሙ ሩኩዕ ወርዶ ሳለ ወደ ቲላወህ ሱጁድ የወረደ መስሎት ሱጁድ የወረደና ኢማሙ "ሰሚዐልላሁ..." ሲል ሰምቶ መሳሳቱን ያወቀ ሰውም ፈጥኖ ከሱጁዱ ተነስቶ ሩኩዕ አድርጎ ኢማሙን መከተል ነው የሚጠበቅበት
📌 ኢማሙ ሲቀራ ስለ ጀነት ወይም ስለ ጀሀነም ስንሰማ አላህን ከረሕመቱ መጠየቅና ከቅጣቱ ጠብቀኝ ማለት ይቻላል፣ግን ያለ ድምጽ ነው መሆን ያለበት፣እንዲሁም ስለ አላህ ትልቅነት ስንስማ "ሱብሓነ-አላህ" ይባላል
📌 ኢማሙ ከሩኩዕ በኋላ ቁኑት እያደረገ ደርሶ ሰላትን የተቀላቀለ ሰው ልክ ኢማሙ ስያሰላምት ተነስቶ ፣እንደ ኒያው ሁለት ረክዓ ወይም ደግሞ ዊትር ብቻ ከሆነ መስገድ የሚፈልገው አንድ ረክዓ መስገድ ይጠበቅበታል
📌 በላጩ ተራዊሕም ተሀጁድም መስገድ ነው ሁለቱን መስገድ ላልቻለ ሰው ተሀጁድ መስገድ አጅሩ ይበልጣል፣እየቻለ ሁለቱንም የተወ ሰው ትልቅ ዕድልን በማስመለጡ ኸሳራ ላይ ወድቋል
📌 በአንድ ሌሊት ተራዊሕም ተሀጁድም መስገድ እንደ ሚቻል የሚያሳይ ንግግር ከታላቁ ሰሓቢይ (ዑመር ኢብኑል-ኸጣብ) እና (አነስ ኢብኑ ማሊክ) رضي الله عنه عنهما ተዘግቧል
ያለ በቂ ማስረጃ "ቢድዓ" ነው የሚሉ ሰዎች ከመልካም ስራ አያርቁህ/ሽ
📌 የመጨረሻ 10 ሌሊቶችን ረዘም ያለ ሰላት እየሰገዱ ማሳለፍ ቁጭ ብሎ ቁርኣን ብቻ እየቀሩ ከማሳለፍ ይበልጣል። በሌላ ነገር ከማሳለፉ ግን በቁርኣን ማሳለፉ ይበልጣል
📌 ለይለተል-ቀድር ወቅቱ የሚጀምረው የዕለቱ ጸሐይ እንደጠለቀች ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ ሱብሒ ተሰግዶ ነው
በመሆኑም የለይለተል-ቀድርን ትሩፋት ለማግኘት በተሀጁድና በተራዊሕ ወቅት ብቻ ጥረን ሌላውን ወቅት ችላ ልንል አይገባም
📌 ሙሉ ኢዕቲካፍ መግባት ላልቻለ ሰው ኢዕቲካፍን በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ብቻ ማድረግም ይቻላል
📌 ወደ ተራዊህና ተሀጁድ ሲሄዱ ንፁህ ሆነው ፣ንፁህ ልብስ ለብሰው ፣ሽቶ ተቀብተው(ለወንዶች ብቻ) መሆን አለበት
አላህ ለይለተል ቀድርን ከሚታደሉ ያድርገን!
ዛዱል መዓድ
በድር እውነት ከሐሰት የተለየበት ታላቅ ክስተት
ረመዳን 17 የዋለ ታሪካዊ የድል ቀን!
የመካ ሙሽሪኮች የጭቆና በትራቸውን መዘርጋት የጀመሩት የአላህ መልዕክተኛ
ሰዎችን ወደ ኢሰላም መጥራት በጀመሩበት ቅፅበት ነበር። የሰው ልጆችን
በሰብዓዊነታቸው የተቸራቸውን የማሰብና የማመን ነፃነት መንጠቅ የሁሉም
አምባገነኖች ሁነኛ ባህሪ ነው። የመካ ሹማምንትም የፈለጉትንና የመረጡትን
ማመን በጀመሩ ንፁሀን ላይ ‹‹የእኛን እምነት ተከተሉ! እኛ የምናስበውን አስቡ!››
በሚል ትዕቢት አቅመ ደካሞች ላይ የጭቆና ቀንበር ጫኑ። እስራት፣ ድብደባ፣
ከማህበራዊ ህይወት ማግለል ወዘተ ‹‹የፈለግነውን በነፃነት የማመን መብት
አለን›› ባሉ ንፁሀን ላይ ያሳረፉት የግፍ አለንጋ ነበር።
ከእምነታቸው እንዲመለሱ፣ የያዙትን ጎዳና እንዲለቁ የሰው ልጅ ሊሸከመው
የማይችለውን የስቃይ ዶፍ አዘነቡባቸው። በደሉ ሲበረታ፣ ጭቆናው ሲያይል
የአላህ መልዕከተኛ (ሰዐወ) እና ባልደረቦቻቸው እምነታቸውን በነፃነት
ወደሚያራምዱበት አገር ተሰደዱ - ሀብትና ንብረትን፣ ዘመድ አዝማድና
የትውልድ መንደርን ጥሎ የእምነት ነፃነትን በመሻት የተደረገ ቅዱስ ጉዞ!
በትዕቢት የተሞሉት የመካ ሹማምንት ግን በበደል አለንጋ ገርፈው ያባረሯቸው
ንፁሀን አሁንም በነፃነት እንዲኖሩ አልፈቀዱም።ሰላም የሚሹ ንፁሀንን
ለመበጥበጥ ተንኳሽ እጃቸው ከመካ መዲና መዘርጋቱን ቀጠለ፡፡ ሙእሚኖች
በስደት ዓለም ጥለው የወጡትን ሐብት ንብረታቸውን ለማስመለስ ካደረጉት
ጥረት ጋር ተደምሮ ሊያጠቃቸው የመጣውን ኃይል ለመመከት ይዘጋጁ ጀመር፡፡
ጭቆናው አንገብግቧቸዋልና ነፃነታቸውን ለማስከበር የትግል መሰናዶ ማድረግ
ጀመሩ - በዚያ በተቀደሰው የረመዳን ወር!
የሰው ልጅ በራሱ ላይ ድል ሲቀዳጅ፣ ነፍሱን በቁጥጥሩ ስር ሲያውል ውጫዊ
ጠላቱን በቀላሉ መርታት ይችላል። በራስ ላይ ድል መቀዳጀት፣ ነፍስን በቁጥጥር
ስር ማዋል ግን ብዙ ትግልን ይጠይቃል። ወርሀ ረመዳን ለዚህ ታላቅ ትግል
ስኬታማነት ምቹ የሆነ ምህዳር ያለው ወር ነው።
ስጋ በርሀብ መዳከሙ፣ ነፍስ ከእኩይ ተግባራት ስንቅ መታቀቧ፣ የሰው ልጅ
ጠላት የሆነው ሸይጣን መታሰሩ እና ማህበረሰቡ ውስጥ የሚሰፍነው የመልካም
ስራ ተነሳሽነት ተደማምረው የሰው ልጅ ራሱን ድል እንዲያደርግ ነፍሱን በማረቅ
ተገዢው እንዲያደርጋት ያስችላል።
በዚሁ የረመዳን ወር ከራስ ጋር የሚደረገውን ትግልና አስፈላጊውን ቅድመ
ዝግጅት ያደረጉት የአላህ መልዕክተኛና ባልደረቦቸቸው የማይነጥፍ ፅናት
ታጥቀው የጌታቸውን እርዳታ ተማምነው ጨቋኛቸውን ለመርታት ዘመቱ። በዚሁ
የረመዳን ወር 17ኛው ቀን ከጨቋኛቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋጠሙ። በዳይና
ተበዳይ፣ እውነትና ሀሰት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ተፋለሙ። የዓላማ ፅናት፣
የአሸናፊነት ስነ ልቦና ከወኔ እና ብርታት ጋር የታጠቁት ሶሀቦች ምንም እንኳ
ቁሳዊ ስንቃቸው አናሳ ቢሆንም ለእምነት ነፃነትና ጭቆናን ለማስወገድ
ያደረጉትን ትግል በድል አጠናቀቁ። ታሪክ የበድርን ዘመቻ በተምሳሌትነት
እንዲቀር አደረገው።
በድር ዘውታሪ ተምሳሌትና የማይነጥፍ አብነት ነው። ጭቆና ምንም እንኳ ገዝፎ
ቢታይም ፅናትና ብርታትን በተላበሱ ተበዳዮች የተባበረ ክንድ የሚናድ መሆኑን
ያስተምረናል፡፡ ወርሀ ረመዳን የድል ወር መሆኑን ያውጅልናል። በድር ታጋዮች
በራስ ላይ ድልን በመቀዳጀት፣ ነፍስን በመግራት፣ ትዕግስትን በመማርና ፅናትን
በመላበስ ጭቆናን በፍትህ ለመተካት ባደረጉት ትግል ድል የተቀዳጁበት የታሪክ
ገጠመኝ ነው።
@ Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
@Selam_Aleyk_TUBE
«ምነው ጥሪዬን አክብሬ ተገኝቼ በነበር!» አስብሎኛል ይህ ህብረታችሁ‼
አማራ ክልል እንዲህ ለጌታቸው የተደፉ ሙስሊሞች መኖሪያም ነው‼
አስገራሚ ቪድዮ ከዛሬው የደሴው ኢፍጣር‼
================================
(ይህን የሺዎች ድምፅ በማሰራጨት ለሚመለከተው ሁሉ እናድርሰው)
||
①) የመጅሊስ ምርጫ በአጭር ጊዜ ይካሄድ።
②) በሴኪዩላሪዝም ሽፋን በሶላትና ሒጃብ ምክንያት ሙስሊሞችን ከትምህርት ማቀብ ይቁም‼
♠
መጀመሪያ ቪድዮውን ስመለከት ኢትዮጵያ ውስጥ ሁላ አልመሰለኝም ነበር።
ለካ ያውም አማራ ክልል ውስጥ በአዝሃሩ-ል-ሐበሻ ወሎ ደሴ ከተማ ኖሯል።
ይመቻችሁ‼
||
t.me/MuradTadesse
የስልክ አጠቃቀማችንን እናሳምር !
ሣይታሰብ ሊመጣ የሚችለውን ሞት እናስታውስ! ነገ ሟቾች ነን!
ጨለማውን ቀብር እናስታውስ !
አጠገባችን ማንም፣ ምንም ሣይኖር አሏህ ፊት መቆም አለ !
የማይቻለው ና ከባድ የሆነው የእሳት ቅጣት አለ !
ከዚህም ጋር ፣ ሐራም ነገርን በመመልከትና በመስማት ደስተኛ ህይወትን መግፋት በፍፁም አይታሰብም ! በአምላክህ ላይ አመፀኛ እየሆንክ ደስታን እጎናፀፋለሁ ማለት ቂልነት ነው!
አሏህን እንፍራ !
ስልኮቻችን የተከለከሉ ነገሮችን መስሚያ ና መመልከቻ ከሚሆኑ ከነ አካቴው አለመጠቀሙ ይሻላል !
#መሀመድሲራጅ
❤️አልወድህም አፈቅርሃለሁ💋
ባሏን ሁልጊዜም እንደምትወደው ትነገረው ነበር፤ ሆኖም እንደቀልድ ይወስደው ስለነበር በጣም አዝና አንድ ቀን፡- እንደምወድህ ስነግርህ ለምንድነው የምትስቀው😄 ብላ ጠየቀችው፡፡
ባሏም እንድህ አለ፡- እንደምትወጂኝ ሳይሆን እንደምታፈቅሪኝ ስለማውቅ አፈቅርሃለሁ ከማለት ይልቅ እወድሃለሁ ማለቱን ማዘውተርሽ ስለሚገርመኝ ነው ብሎ መለሰላት፡፡ 😒
ልጅቷም ጭንቀት እና ሃዘን የተሞላበት ፊቷን ወደ ፈገግታ ቀይራው😁 ኦ… የኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሃለሁ አለችው፡፡ 😍
ባሏም፡- የኔ ውድ አንድ ለየት ያለ ነገር እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ
ልጅቷም፡- ምን?
ባሏም፡- ማታ ቤት ስትገቢ እናትሽን አመስግኚልኝ 🙏
ልጅቷም፡- እሺ… ግን በምን ምክንያት?
ልጁም፡- በሕይወቴ መጥታ ደስታን የሰጠችኝኝ ነገ ደግም የትዳር አጋሬና የልቤ መርጊያ አንቺን ስለወለደች ነው፡፡ ብሎ መለሰላት ደስ አይሉም?? በአሏህ!!!
#ጥሩን ለጥሩ ነው አላህ የኸለቀው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Join us 👇👇
@Zakiiir12
🔴 የአረፋ ቀን ፆም!
ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦
﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾
“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
📌 ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
📌 ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
📌 ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
📌 በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት
📌 ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።
📌 ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።
በፊት ስለ ነሺዳ ስናነሳ በርካታ እህት ወንድሞች እነዚህ ሰለፊዮችና መድኸሊዮች ኡማውን ከፋፈሉት እያሉ ይኮንኑን ነበር። ግቢ ሳለሁ ከአስር በላይ ክፍሎች ያሉት ስለ ነሺዳ ተከታታይ የሆነ ረጃጅም ጽሑፍ ስጽፍ አስታውሳለሁ።
ይሄው ዛሬ ላይ ብዙው ሰው ስለ ነሺዳና መንዙማ ምንነት በግልጽ እየተረዳን ይገኛል። ዑለማዎች በግልጽ መናገር ጀምረዋል። የዘመኑ ወጣቶች ነሺዳ ብለው የሚያወጧቸው ነገሮች ብዙዎቹ የዘፈን ማስታገሻ ናቸው የምንለው በምክንያት ነው።
💝ቅዠት ነው ወይስ ፍቅር?
በተራመድኩ ቁጥር የማገኝሽ የመሰለኝ፣
በተነፈስኩ ቁጥር የምቀርብሽ የመሰለኝ፣
በፍጥረተ አለሙ መገኘት እርገጠኛ ከሆንኩት ያለፈ እንደምንዋሀድ ያመንኩት፣
ቅዠት ለክፎኝ ወይስ ፍቅር?
@In_Life_S
ሰበር‼
======
✍ በዛሬው ዕለት በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ የሸዋልን ጨረቃ ለመመልከት ጥረት ቢደረግም ልትታይ ስላልቻለች፤ ነገ ዕለተ እሁድ ሚያዚያ 23, 2014 E.C. የወርሃ ረመዿን 30ኛ ቀን ሲሆን ሰኞ ሚያዚያ 24, 2014 E.C./ ሸዋል 01, 1443 H.C. የዒደ-ል-ፊጥር በዓል ይሆናል።
እንኳን አደረሰን! አላህ ወንጀላችንን ሁሉ ምሮ መልካም ሥራችንን ይቀበለን!
BREAKING NEWS | The Crescent for the month of Shawwal 1443 was NOT SEEN today, subsequently:
Monday, 2nd May 2022 will be the day of Eid Al Fitr
The month of Ramadan 1443 will complete 30 days tomorrow
||
t.me/MuradTadesse
🛑 ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ውስጥ ላለ ብቻ አይደለም
የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች...የዚች ለሊት ትሩፋት አይለፋችሁ። በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል።በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛትም አትዘንጉ። ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ላይ ላለ ብቻ አይደለም።
ብዙ ሰው መስጂድ ካልሄደ ይሄን ምንዳ የሚያገኙ አይመስለውም። ይህ ስህተት ነው! ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው በኢባዳ ላይ መሆናችን ነው። ለቻለ እና አቅሙ ላለው ሰው ግን የተወዳጁን ነብይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና(ፈለግ) ለመከተል መስጂድ ላይ ብንሆን ይመረጣል፣ ይወደዳል። ካልቻልን ባለንበት ቦታ ስራ ላይ የሆነም በስራው ላይ እቤቱ የሆነም በቤቱ በኢባዳ ልንበረታ ይገባል!
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን!
የረመዷን ወርቃማ 10 ቀናቶች
★ T.me/ahmedin99
🔅የወራቶች ሁሉ አለቃ የሆነው ረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶቹ ደግሞ የወሩ ቀናቶች ቁንጮ ናቸው፡፡በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የምትገኘዋ ለይለቱልቀድር ደግሞ የቁንጮዎች ቁንጮ ናት፡፡
🔅አስሩን ቀኖች (ሌሊቶች) በሙሉ ለይለተል-ቀድርን በማሰብ በዒባዳ ያሳለፈ ያለምንም ጥርጥር ለይለተል-ቀድርን ያገኛል።
🔗ቡኻሪይና ሙስሊም ከእናታችን ዓኢሻ
እንደዘገቡት ነቢዩ ﷺ"የረመዷን 10 ቀኖች ሲገቡ መቀነታቸውን ያጠብቁ ነበር፣ ለሊቱንም በሙሉ በዒባዳ (በሰላት) ያሳልፉ ነበር፣ ባለቤቶቻቸውንም (ለዒባዳ) ይቀሰቅሱ ነበር" ብለዋል፡፡
🔅ጅምርና መነሻ ላይ ሁሉም እኩል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮች የሚለኩት ግን በፍጻሜያቸው ነው፡፡ እስከመጨረሻው ታግሶ ስራውን አሳምሮ ያጠናቀቀ ይሸለማል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሳነፈና ያበላሸ ግን ሽልማቱን በማጣት ወይም ከዛም በከፋ ነገር ሊቀጣ ይችላል፡፡
🔅የረመዷን የመጨረሻ 10 ቀናት ላይ ይበልጥ ኸይር ስራ ላይ ልንተጋና መጨረሻችን ያማረ እንዲሆን ጥረት ልናደርግ እንጂ ልንዘናጋና ልንሰላች በጭራሽ አይገባንም፡፡
🔗ኢብኑል-ጀውዚይ እንደሚሉት"ፈረስ እንኳ የእሽቅድድም ሜዳ ላይ የመጨረሻው ዙር ላይ ሲደርስ ኀይሉን አሟጦ ተጠቅሞ ሌሎች ፈረሶችን በመቅደም ከግቡ ላይ ቀድሞ ለመድረስ ይጥራል" ፣እነሆ ከፈረስ በላይ እንጂ በታች ልንሆን ፈፅሞ አይገባምና እኛም ወደ ጀነት በሮች በመልካም ስራ ልንሽቀዳደም ይገባናል፡፡
🔅የረመዷን የመጀመሪያ አስርቶች ላይ ከነበረን የተሻለ ንቃትና ትጋት ሊኖረን ይገባል።
🔅ሰራተኛ ስራውን ሲያጠናቅቅ የሚያገኘውን ደመወዝ በማሰብ የስራውን ድካም ተቋቁሞ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርገው ሁሉ እኛም የአላህን ውዴታና ጀነትን በማሰብ ነፍሲያችንን በማሸነፍ መልካም ስራ ላይ ልንበረታ ይገባናል፡፡ ሁኔታዎች ለመልካም ስራ የማያግዙበት ወቅትና ቦታዎች ላይ ሁሉንም ተቋቁሞ ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግና አላህ እንደሚፈልገው ሆኖ መገኘት ደረጃው ለዲን ብሎ ወደ ነቢዩﷺ የመሰደድ ያክል ነው፡፡
💥ኢዕቲካፍ በመግባት ከዓለማዊ ጉዳዮች ርቆ፣ ከዱንያ ግርግርና ወሬዎቿ ተነጥሎ፣ ዒባዳ ታስቦ፣ የተለያዩ የአምልኮ ተግባራትን መፈፀም እዚያው ለመዋልና ለማደር ጠቅሎ መስጊድ መግባት ማለት ነው፡፡ የቻለ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፤ ያልቻለ የተመቸዉን ቀን መርጦ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፡፡ ኢዕቲካፍ ነፍስን ያጠራል፣ ዉስጥን ያፀዳል፡፡ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ የፈለገ ሰው ረመዷን 20 ቀን (ምሽቱ 21) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መስጊድ ይገባና ነገ ዒድ ሲባል ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ ይወጣል፡፡
💥"የሰው ልጅ ሆይ:- የተወለድከው ብቻህን ነው፣የምትሞተውም ብቻህን ነው፣ ቀብርም የምትገባው ለብቻህ ነው፣ ለምርመራ አላህ ፊት የምትቆመውም ለብቻህ ነው፣ጀነትም ይሁን ጀሀነም የምትገባው ለብቻህ ነው!" ታዲያ ነገ የምትድንበትን ኸይር ስራ ለብቻህ መስራት እንዴት ይከበድሃል?!?
🔅ዛሬ ዱኒያ ላይ መስፈርቱን ያሟላ መልካም ስራ ከሰራን ነገ ኣኺራ ላይ በጀነት ስናርፍ ድካሙን በሙሉ እንረሳዋለን! ከዛም አልፎ የከፈልነውን ዋጋ እንንቃለን!
💥በወርቃማ አስርቱ ቀናት፣
1/ ኢዕቲካፍ በመግባት
2/ ቁርኣን
3/ ለራሳችንም ለሌሎችም የተለያዩ ዱዓዎችን በማድረግ በተለይም (አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) የሚለውን ዱዓ ማብዛት
4/ ዚክር በማብዛት
5/ ሰደቃ
6/ ለሊቱን ሙሉውን -እስከ ሱሑር- በሰላት ብቻ ማሳለፍ የቻለ ይህን በማድረግ ይህን ያልቻለ ደግሞ ለሊቱን ከፋፍሎ በዚክር፣በዱዓእና በኢስቲግፋር እንዲሁም የቻልነውን ያክል ረዘም ያሉ 2/2 ረክዓ ሱንና ሰላቶችን በመስገድ ልናሳልፍ ይገባናል፡፡
አላህ ያግዘን ለይለቱል-ቀድርንም ይወፍቀን "ኣሚን"
✍ ኡስታዝ አሕመድ አደም
🔹🔸🔹🔸🔹
የአህመዲን ጀበልን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያጋሩ
T.me/ahmedin99
መልካም ዜና‼
===========
በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
🛑 ዳግም እንገናኝ ይሆን...?
የፆምና የምህረቱ ወር ረመዳን ቀጣይ አመት ምህረቱንና በረካውን ይዞ ዳግም ሲመጣ ምድር ላይ በህይወት ያገኘን ይሆን!? ወይስ ሞት ወስዶን ከምድር ስር ቀብር ውስጥ በስብሰን?!
ይህ ረመዳን የመጨረሻችን ሊሆን ይችላል። እንግድነቱን ጨርሶ ሊሰናበትን ውስን ቀናት ብቻ ቀርተውታል። በተቀሩት ቀናት ሀቁን እንጠብቅለት።
ምስል:- የጎዳና ላይ ኢፍጣር በደሴ
📌 T.me/ahmedin99
መገን ወሎ‼
ዐረብ ገንዳ መስጅድ ስሰግድ ድምጹ ደስ የሚለኝን ልጅ በዛሬው የደሴው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ያሰገደበት ቪድዮ ደረሰኝና ሰማሁት።
አላህ ይጨምርላችሁ‼
||
t.me/MuradTadesse
የማኅበራዊ ትስስር ገጾችንና ማንኛውንም አጋጣሚ ኢስላማዊ ዳዕዋን ለማሰራጨት ተጠቀምበት።
اجعلوا حساباتكم منابر للدعوة
️قالﷺ:
ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
{بلغوا عني ولو آية}.رواه البخاري
«አንድት አንቀፅ እንኳ ብትሆን ከኔ (የሰማችሁትን ለሌሎች) አድርሱ።»
في الحديث تكليف وتشريف وتخفيف:
بلغوا: تكليف
عني: تشريف
ولو آية: تخفيف.
በዚህ ሐዲሥ ላይ ትዕዛዝ፣ ልቅናና ማቅለል አለበት።
√ "አድርሱ" ሲሉ ትዕዛዝ ነው፣
√ "ከኔ" ሲሉ ልቅና ነው፣
√ "አንድትን አንቀፅ እንኳ" ሲሉ ኢስላማዊ ዳዕዋን ለማስፋፋት የግድ ኩቱቡ ሲታ የጨረስክ መሆን እንደማይጠበቅብህና የምታውቃትን ማስተላለፍ እንዳለብህ ስለሚያመላክት ማቅለል ነው።