zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ግልጽ እኮ ነው…😂😂😂

• እና ስታስበው ቅዱስ ዮሐንስ፣ እንቁጣጣሽ፣ መስቀል፣ ገና፣ ጥምቀት እና ፋሲካን ደስ ብሎህ ልታከብር ፈለግክ። 😂😂 ኢሬቻና መውሊድ መሰለህ እንዴ? በል እባክህ አትቀልድ። ኧረ ይሄ ቀላል ነው የከብት እርዱ ቀረ፣ ቅርጫ ቀረ ብለህ ማዘን ማለት ጥጋበኝነት ነው። የሰው እርዱ በቀረልህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የኦሮሙማው ዕርድና…!

"…በሀገር ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያዊ ኦሮሙማው በወሎ ዐማራው ዳንኤል ክብረት ያዋርደዋል። አፈር ከደቼ ያስበላዋል። ጃርት፣ ጁንታ፣ ጃውሳ እያለ እንዲሰድበው ያስደርገዋል። ዳንኤል ዐማራ ነው ነገር ግን ከዐማራና ከትግሬ፣ ከኦርቶዶክስ በቀር ኦሮሞን፣ ጴንጤና እስላምን እንዲያዋርድ አይፈቀድለትም።

"…አሁን ደግሞ አራዳው ኦሮሙማ በሆዳቸው የወደቁ፣ የዐማራነት ሥነ ልቦናቸው የተሰለበ ሦስት ዐማሮችን ከፊት አሰልፎ አንዱ የሀገር ውስጡን ሕዝብ አፈር ደቼ ሲያበላ፣ ሁለቱ ደግሞ አንዱ ኤርትራን፣ ሌላኛው ደግሞ ሱማሌን እንዲጋፈጡ ተደርገዋል። አይጀመርም እንጂ ጦርነቱ ሲጀመር ደግሞ አበባው ታደሰና የዐማራ ተዋጊና አዋጊዎች ይዘምታሉ። ይሞታሉ። አይ ኦሮሞ።

"…የሚገርመው ሦስቱም ዐማሮች ብቅ የሚሉት ሕዝብ ለማስለቀስ፣ ለማስጨነቅ፣ ከሃገራት ጋር ጦርነት ለመግባት፣ ሃገሮችን ለማዋረድ ነው የሚልካቸው። የባንኩ ገዢ የጎጃም ዐማራው የሞጣው ተወላጅ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ብቅ አለና የዶላር ምንዛሬ ሰማይ እንዲነካ፣ ሕዝቤ እሪ እንዲል አስደረገው። በአባቱ ሰሜን ሸዋ፣ በእናቱ የወልቃይት ዐማራ ጎንደሬውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አፅቀ ሥላሴን አመጣና ግብፅንና ሶማሊያን ዋ ወየው ብለህ ጓ በል አሰኘው። ከዚያ ትውልዱ የማይታወቀው የአየር መንገዱ ሓላፊ መስፍን ጣሰው ብቅ አለና ኤርትራን ቀድሞ በማበሳጨት፣ ማኮሰስ ወደ ግብግብ እንድታመራ አደረጋት። ሦስቱም ዐማራዎች እንደ ኮንዶም…

"…ኦሮሙማስ…? አባቴ እነሱማ ኮሬ ነጌኛ፣ ሸኔና ኦነጋቸውን አደራጅተው ያግታሉ፣ ያርዳሉ፣ ይዘርፋሉ። ከዚያ በደንብ አስለቅሰውህ የኮንደሚንየም ቁልፍ ይሰጡህና ጮጋ ያሰኙሃል። ቶማስ ጃጀው፣ ስዩም ተሾመ፣ ጌትነት አልማው…

• ኧረ ፍራሹን እየረዳችሁ… ትንሽ ነው የቀረኝ። የአንዱ ዋጋ 3500 ብር ብቻ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከግማሽ አልፈናል

"…የሚፈለገው ፍራሽ 1200 ፍራሽ ነው። የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር ነው። እንደምንም ገፍተን ከግማሽ በላይ የሆነ ፍራሽ መግዣ አግኝቻለሁ። በተለይ አሜሪካን ሀገር ያላችሁ፣ በካናዳ፣ በአውሮጳ ያላችሁ ከተባበራችሁ እስከማታ እንሞላዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ሱማሌና ግብፅ ሊወሩን ነው አሁን መስሚያዬ ጥጥ ነው። መተማ ከተማን ፋኖ ስለያዘው ጎንደር ላይ ህፃን ልጅ አርዶ አጀንዳ ማስቀየስ፣ ይሄን ዘግናኝ የደም ግብር የለመደ ሰይጣናዊ መንግሥት በሰላማዊሰልፍ ለመጠየቅ የወጡትን የጎንደር ነዋሪዎች አናት አናታቸውን በርቅሶ መግደል፣ ወደ ኤርትራ የሚበረው በረራ መቋረጥ ወዘተ የጀመርነውን ከግብ ከማድረስ አያግደንም። አቢይ አሕመድ የኦርቶዶክሳውያን ዓመት በዓል ሲመጣ የእናቱ የወይራ ጢስ ጠንቋይ ያንቀዠቅዠዋል። ከጨለማ ፊት ለፊት ብርሃን ሆነን እንጋፈጣለን። እነርሱ የሚጨልሙትን ብርሃን እኛ እናበራዋለን። የሞቱትን ነፍስ ይማር።

"…ዐቢይ አሕመድ ከዐማራ ክልል ተሸንፎ ቢወጣም ብዙ ህጻናትን አርዶ፣ ብዙ ሴቶችን ደፍሮ፣ በበሽታ በክሎ ነው። ለወታደሩ የተሰጠው ሥልጠና ዐማራ ለኦሮሞ አልገዛ አለ። እኛ ሥልጣን ስንይዝ ተቃወመን፣ እናም በሉት ተብለው እንደገቡ ነው የሚነገረው።

"…ጎንደር ከተማ የማንቂያ ደወል ተደውሎላታል። በኦሮሚያ የነበረው አጋች ኃይል በስፋት ገብቶላታል። ተዘልለው ተቀምጠው ነበርና ኦሮሙማው ቆረጣጥሞ ይበላታል። የአማች ቦለጢቃ ከሚመጣው መዓት አያተርፋትም። መፍትሄው ጅብ ብልፅግናን በልቶ መቀደስ ብቻ ነው።

"…ኧረ…ኧረ የማይመለከተኝን ቦለጢቃ እየተበጠረቅኩ ሥራዬን ተዘናጋሁ። ይሄን ወንድም ካሊድ የላከላቸውን የጠነባ ፍራሽ ራሱ ሌላ በሽታ ነውና አይጠቀሙም። እናቃጥለዋለን። አፈሩ ትል በሰውነታቸው እንዲያፈራ አድርጓል እና በአዲስ እንቀይርላቸዋለን።

• በርቱ፣ ስጡ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይ የቀጠለ… ✍✍✍ አብቅቷል። ጠግባቹሃል። ኦሮሞ አይገዛንም ስላለቹ ዋጋችሁን አየሰጠናችሁ ነው። ሰለዚህ እኛን ያልተባበረ ዐማራ ይረሸናል። እናም ብረሽንህ ማንም አይጠይቀኝም። ስለዚህ ተዘጋጅ አለኝ።

"…እኔም ከመደናገጤና ከመረበሸ የተነሳ የምሞትም ከሆነ ቢያንስ አንዱን አውሬ ይዤ መሞት አለብኝ ብየ ወሰንኩና በእጄ ላይ ከገዋኔ ኪስ ካለ ከእስክርቢቶ ወጭ ምንም አልነበረም። ግን በእሱም ቢሆን ለመውጋት መሞከሬ አይቀርም ነበር። ግን በጣም የሚያሳዝነው እንደዚህ ዐማራ የተባለ ሳናጠፋ አንሄድም ሲል ከጎኑ ሁለት የዐማራ ሚኒሾች ይሰሙ ነበር። ከዚያ የመጨረሻ ኑዛዜዬን ልናገር ብዬ እባክህ ለናንተም ቢሆን በነጻ አክማለሁ። ከአካውንቴ ያለውንም ያለኝ ብር አሰጥሃለው ልጅ አለኝ አትግደለኝ ስለው አሺ 40ሺ ብር አምጣ አለኝ። አይ አሁን አልያዝኩም በአካውንት እልካለሁ አልኩ። እሽ 10:00 ሰዓት ላይ ከመኮድ ጀርባ የሆነ ዛፍ አለ ከዛ እጠብቀሃለሁ። 40 ሺ ብር ታመጣለህ ካለሆነ መጥቼ አንተንም ክሊኒኩንም ነው የማቃጥለው አለኝ። እኔም በደስታ እሽ ብየ እኔም ነፍሴ ተረፎ ሁሉንም ነገር ትቸ ሕይወቴን ይዤ ወደ አዲስ አበባ ተሰደድኩ። ነበር የሚለው።

"…ሁሉም ዐማራውም፣ ኦሮሞውም፣ ትግሬውም፣ አፋር ሱማሌውም፣ ደቡቡም ወዳ አዲስ አበባ በመሰደድ የሚድን ይመስለዋል። መዳኛው ራስ ወዳድነትን ትቶ፣ ለሥልጣን፣ ለዝና፣ ለሀብት ብሎ መንሰፍሰፍ፣ መንገብገቡን ትቶ በአንድነት ቆሞ መታገል ብቻ ነው። አበቃ። በተለይ ጎንደር አሁንም ከማነቆው መውጣት አለባት። ሌላው ዐማራ ለነፃነት ሲታገል ጎንደር ከተማዋ ብቻ ዳተኛ ሆና በጊዜው በጎንደሬዎቹ በእነ ጋሻው መርሻና በእነ ጣሂር መሀመድ የቱሪዝም ድግስ ስትጨፍር ነበር የከረመችው። በወቅቱ ጎንደር ማንነቷንና ባህሏን በሚቀሙ ሌቦች መዳፍ ስር እንደነበረች ቢያውቁም ጉዳዬም አላሉትም ነበር። ወይም ጭራሽ አላወቁም ነበር። እነ ጣሂር ጎንደርን ሲያስጨፍሯት ሲያስደልቋትና እናትዋ ጎንደር ሲያስብሏት የነበሩት ሁሉ ዛሬ ጎንደርን የሉም። ስኳድ መልካሙ ሹምዬ የብልፅግና ባለሥልጣን ሆኗል። የወልቃይት መሬት አራሹ ጋሻው መርሻ የፖስታቤት ምክትል ነው። እነ ቶማስ ጃጃው የሉም ከኦሮሙማ ቀለብ እየተሰፈረላቸው ዐማራን ጎንደርንም እየተሳለቁባት እየሳቁባትም ነው። አገኘሁ ተበሻገር፣ መላኩ አለበል አንዳቸውም የሉም። ጭራሽ አቢይ አህመድ አያሌው መንበር ያመሰገናትን አዳነች አበቤን ለጎንደር ከንቲባነት ሹሜያታለሁ ብሎ አረፈው። ሌላው ጋር ፋኖ ብልፅግናን ሲያጸዳ ጎንደር ነው ከንቲባው የአጎቴ ልጅ ነው። እንትኑ እንትኔ ነው ብሎ እሹሩሩ ብሎ ብልፅግናን ጎንደር ላይ አቀማጥሎ የያዘው፣ ይዞም ያስቀመጠው። ዛሬም አልረፈደም። ከእነ ደመቀ ዘውዱ እስከእነ መላኩ አለበል አገነሁ ተሻገር እስከ አብይ አህመድ የተዘረጋውን ኔትወርክ አነፍንፎ ካልደረሰበትና ካልበጣጠሰው ጎንደር ደም እንባ ሲያለቅስ ይኖራል።

"…እንደው ለደንቡ ያህል ርእሰ አንቀጻችን እንዳይቀር ብዬ ነው እንጂ እኔ ዛሬ የቀበሮ ሜዳ ስደተኞች ፍራሽ ልብስ ማሰባሰብ ሥራ ላይ ነው የምውለው። የ1 ፍራሽ ዋጋን በ3,500 ብር ነው የያዝነው። በዶላር፣ በፓውንድና በዩሮ ከሆነ በቶሎ ይሞላል። እያሰባችሁ፣ በውስጥ መስመር የምትችሉትን ቃል የገባችሁትን የፍራሽ ብዛትና ስማችሁን እያስቀመጣችሁልኝ እንጠብቅ። ከምር ከአሁኑ ብዙ ፍራሽ እያገኘሁ ነው። ፍራሹን እንደጨረስኩ በቀጥጥታ ለህፃናቱ ዩኒፎርም፣ ደብተርና እስራስ፣ ቦርሳም ወደማሰባሰቡ እገባለሁ። የሞተችዋን ሕፃን በአብርሃም፣ በይስሀቅና በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን።

• 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ቃላችሁን ስጡ። እኔም ወዲያው የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁ። አመሰግናለሁ። ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ሌሊት አምሽቼ ተኝቼ ሰላምታ ካቀርብኩ በኋላ እንዴት እንቅልፍ እንደወሰደኝ ሳይታወቀኝ በተቀመጥኩበት ተኝቼ አሁን ገና መንቃቴ ነው። ዳይ ወደ ሥራ። እንቅልፋም ዘመዴ። ዳይ ዳይ… ፍጠን።

"…ለደንቡ ያህል ርዕሰ አንቀጻችንን በፍጥነት አዘጋጅቻለሁ። እሷን አቀርብላችሁና በቀጥታ ወደ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ሄደን የጀመርነውን የቅድስና የበጎ ተግባር ሥራችንን ላይ ወደ መረባረቡ እናተኩራለን። ፍራሹን መለመን ሳልጀምር ከወዲሁ እየተገባደደ ነው።

• እህሳ… ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አንሶላ~ 2400  ተሳክቷል። ተሟልቷል።

"…በ5 ሰው የአዲስ ዓመት መቀበያ ግብዣን መሰናዶ በተመለከተ ሰንጋ፣ ፍየል፣ ቅቤ፣ ማገዶ፣ ለስላሳና ውኃ፣ ድንኳን፣ እንጀራን፣ ሽንኩርት በርበሬን 5 ቅን ልቦች አሟልተው አስደስተውናል። ልብ በሉ አቶ ወርቁ አይተነውን ጨምሮ አምስት ሰዎች ብቻ ናቸው ይሄን ያሳኩት። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከአዲስ ዓመት ግብዣ ቀጥሎ የሄድነው ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ ፍራሽ ወደሟሟላት ነበር። ለብርድልብሱ 40 ኢትዮጵያውያን 1200 ውን የሚፈለግ ብርድልብስ የአንዱ ዋጋ በ600 ብር የተተመነውን ነው 40 ሰዎች ብቻ ያሟሉት። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከብርድ ልብሱ በኋላ ደግሞ በቀጥታ የሄድነው የአንዱ አንሶላ ዋጋ 500 ብር ወደሆነው 2400 አንሶላ ወደመግዛቱ ነበር። እሱንም ጠዋት ጀመርን። ምንም ውትወታ ሳላደርግ፣ ዋይዋይ ሳልል፣ ሳላለቃቅስ፣ በቴሌግራሜ ብቻ በለጠፍኩት መልእክት ተስበው 129 ኢትዮጵያውያን ተረባርበው አሳክተውታል። አሁን ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ያሉ ቀን የጣላቸው የዐማራ ስደተኞች የአንዱ ዋጋ 600 ብር የሆነ ብዛቱ 1200 ብርድልብስና የአንዱ ዋጋ 500 ብር የሆነ ብዛቱ 2400 አንሶላ በአንድ ቀን ተሳክቷል። ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ነገ ብዛቱ 1200 የሆነ ዋጋው 3500 ብር የተተመነውን ፍራሽ ተረባርበን ካሟላን በቀጥታ የምንሄደው ወደ ህፃናት ተማሪዎች ዩኒፎርም ከነሸራ ጫማው፣ ቦርሳ፣ ደብተር፣ እርሳስና እስኪሪብቶ ወደ ማሟላቱ ዘመቻ እናልፋለን። ባለፀጋው አቶ ወርቁ አይተነው በወሮ ሊሊ ተጀምሮ የነበረውን ትምህርት ቤት እንደሚያጠናቅቁ ቃል በመግባታቸው ህፃናት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለባቸው። ስለዚህ ከፍራሹ ቀጥሎ በዚህ የህፃናት ትምህርት ጉዳይ ላይ በተለይ ጎንደሬ ባለሃብቶች እንደ አቶ ወርቁ አይተነው ብታግዙኝ ደስ ይለኛል። እናንተ ባታግዙኝም ግን እኔ የቴሌግራም ጓደኞቼን ይዤ አሳካዋለሁ። አዛኚቷን አሳካዋለሁ። ግን ጎንደሬዎችም እርዱኝ። አለን ዘመዴ ብትሉኝ ደስ ይለኛል።

• በመቀጠል አንሶላውን ተረባርበው ያሳኩልኝን የልብ ወዳጆቼን ስምዝርዝር ከነአሟሉት የአንሶላ ብዛት ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ይኸው አስቀምጬላችኋለሁ።

1.አንተነህ~ 300
2.ዳኛቸው~ 200
3. ጌታሰው~ 112
4. ፌቨን~   105
5.መላኩ~   100
6.ቅድስት~ 100
7.ሮማን ~  100
8.አስካለ~  100
9.ሥርጉት~ 80
10.አይናለም~ 60
11.ገ/ማርያም~ 60
12. ሙሌ~  50
13.በላይነሽ~ 48
14.ወይንሸት~ 48
15.አስራት~  40
16.ሳሚ~  30
17.ሸዋፀሐይ~ 28
18.ዘውደነሽ~ 28
19.ፀሐይ~ 29
20.ኃ/ሥላሴ~ 29
21.ፍሰሃ~  25
22~ ክንፈ~   24
23.ታምር ዳኜ~24
24.ሕይወት~  24
25.እሙ~      24
26.ሰላም~    24
27.ሳሚ~      24
28.በኃይሉ ~  22
29.መዓዛ~  20
30.ትርሲተ ማርያም~ 20
31.ወለተ ተንሣኤ~ 20
32.ብርቄ~    20
33.ኤርሚ~  20
34.ዓመተሥላሴ~ 20
35አእምሮ~  20
36.ሲሳይ~   20
37. የትናየት~ 18
38.የኔነሽ ~ 15
39.እነ ዮርዳኖስ~ 15
40.ያሬድ~ 12
41ቤቲ~ 12
42.መዓዛ መሐመድ~ 11
43.መስፍኔ~ 10
44.ሰሎሞን~ 10
45.መሲ~ 10
46.በየነ ~10
47.ወ/ሥላሴ~ 10
48.ዮሐንስ~ 10
49.ብሥራት~ 10
50.ያረጋል~ 10
51.ፀጋ~ 10
52.እቱ~ 10
53.ቬሮኒካ~ 10
54.ዴቭ~ 10
58.ያልታየወርቅ~ 10
59.ወ/ማርያም~ 8
60.ጋሻው~ 6
61.ብዙነሽ~ 6
62.ቤቲ~  6
63.ደሬ~ 6
63.አዚቲ~ 6
64.ይርጋለም~ 5
65..ሰለሞን~ 5
66.ገነት~ 5
67..ኃይለልዑል~ 5
68.ሀብቱ~ 5
69.ተስፋነሽ~ 5
70.ደረጄ~ 5
71.ኃ/ማርያም ~ 5
73.ደሳለኝ~ 4
74.ሊሊ~ 4
78.ሉላ ~ 4
79.ዳግም~ 4
80.ብርሃን~ 4
81.በላይ~ 4
82.ዘካርያስ~ 4
83.ጥሩነህ~ 4
84. እህተ ገብርኤል~ 3
85.ሰጠኝ~ 3
86.ፍጹም~ 3
87.አንቴ~ 3
89.ቅድስት~ 3
90.ወ/ጻድቅ~ 3
91.ኩኩ~ 3
92.ኤልሣ~ 2
93.ፅጌድንግል~2
94.ተመስገን~ 2
95.ጌታመሳይ~ 2
96.ክ/ሚካኤል~ 2
97.ክ/ማርያም~ 2
98.በጸሎት~ 2
99.ኤልሳ~ 2
100.ቤቲ~ 2
101.ደረጄ~ 2
103.ኃይሉ~ 2
104.ደሳለኝ~ 2
105.ኖላዊ~ 2
106.ምስጋናው~ 2
107.ዓይናዲስ~ 2
108.ዝናቧ~ 2
109.መልካመ~ 2
110.ወንዲ~ 2
111.ግርማ~ 2
112.ታዲሻ~ 2
113.ኑርልኝ~ 2
114.ወ/አማኑኤል 1 
115.ብሩክ~ 1
116.ዮሐንስ~ 1
117.አብርሃም~ 1
118.ጽዮን~ 1
119.ኃይሉ~ 1
120.አስናቀ~1
121.አስቤላ~ 1
122.ሃና~ 1
123.ሔኖክ~ 1
124.ዋሴ~ 1
125.ሃኒ~ 1
126.ኃ/ገብርኤል~ 1
127.ዐቢይ~1
128.ዮሲ~ 1
129.ፀጋዬ~1

"…እነዚህ ናቸው ለእነዚያ ምስኪን እናቶቻችን 2400 አንሶላ ተረባርበው ያሟሉት። አያችሁ በጥቂት ሰው ሺዎችን መደገፍ እንደሚቻል? ያለ ኮሚሽን፣ ያለ ኮሚቴ፣ ያለ ቲክቶክ፣ ያለ ማስታወቂያ፣ ያለ ሰበካ፣ ያለ ቲፎዞ፣ ያለ ልምምጥ፣ ያለ ተማጽኖ፣ ያለ ውሎ አበል፣ በነፃ፣ በፍቅር መሥራት፣ ለሚልዮኖች መድረስ እንደሚቻል? አዎ ይቻላል። ነገ ደግሞ እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ ፍራሹን ተረባርበን ስናሟላ እንውላለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ነገ ሱማሌን በተመለከተ፣ ብልፅግና ለጎንደር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዐማራና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ጭምር ስላዘጋጀው ሰቅጣጭ፣ ስሜት ገዳይ፣ አሳባጅ ዕቅድ በርዕሰ አንቀጽ መልክ ለማዘጋጀት ሓሳብ ነበረኝ። ነገር ግን ይሄ የጀመርኩትን መፈጸም ስላለብኝ ላላደማው ነገር ለኳኩፌ ላለመተው ስል አልፈዋለሁ። መጪውን አዲስ ዓመት ዐማራ በመከራም ውስጥ ቢሆን በደስታ ተረጋግቶ እንዳያሳልፍ ስላዘጋጀው ወጥመድ ብፅፍ ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ትኩረቴን ወደጀመርኩት ለማድረግ እገደዳለሁ። ፍራሹም፣ የተማሪዎቹም የትምህርት መርጃ መሳሪያዎቹ ከተሟሉልኝ በመሃልም ቢሆን ልጽፈው እና ላፈርሰው እችላለሁ።

"…ጎንደር ላይ ደስታ፣ ሃሴት ስፈጥር ጎንደር ላይ ዘግናኝ፣ ዘግናኝ የአህዛብ ድርጊት መፈጸም ከዲያብሎስ ነው። ከዚህም በላይ ገና እንሰማለን። የኦርቶዶክሳውያን በዓል እየመጣ አይደል? የተለመደ ነው። ለጎጃምን በሴት ህፃን፣ ለጎንደር ሌላ ህፃን፣ ወሎም፣ ሸዋም እስከ መስቀል በዓል ድረስ ገና አቢይ ጉድ ያሳየናል። በግፍ ለታረደች ሕፃኗ ሰልፍ የወጣ የጎንደር ሕዝብ የተጨፈጨፈው ለምክንያት ነው። ሐበሻ ከጥንት የለመደውና ያስለመደው የአዲስ ዓመትን በተስፋን የመለወጥ ተስፋውን ለማጨለም ታቅዶ በለቅሶ እንድናሳልፍ ፈርዶብን ነው። የእኔ ጎንደር ጎንደር ማለት ራሱ መነቃቃት መፍጠሩም ያበሳጨዋል። የፈለገ ቢሆን ግን በፋኖ ትግል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። እስከአሁን የተኛው እየተገረፈ ሳይወድ በግዱ ይነሣታል። የአማች ፖለቲካም ይፈርሳል። ዐማራ ያሸንፋል።

"…ነገ ፍራሹን ለሟሟላት እንዘጋጅ። በተለይ ዳያስጶራዎች ተረባረቡበት። ፍራሹም ቢሆን ትንሽ ነው የሚቀረን። በጣም ትንሽ። አያምልጣችሁ። ደግሞም እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ። ይፍቀድልን። አሜን።

"…የሚገርመው እስከአሁን ቄሶች፣ ሼኮች፣ ጳጳሳት፣ ኡስታዝ ፓስተሮች፣ ሰባኪያነ ወንጌል አላየሁም። የራሳቸው ጉዳይ። ሙዳይ ምፅዋቱም እየሳሳ ነው። ለነገሩ ከራሳቸው አልፎ ለደሀ የሚራሩበት ጊዜም አይደለም። የሆነው ሆኖ እኛ ግን እንበርታ።

• ሻሎም…! ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የብርድ ልብስ ሪፖርት…

"…የሚያስፈልገው የብርድ ልብስ ብዛት 1200 ነበር። 5 መጠባባቂያ ይዤ ማለት ነው። የአንዱ ብርድ ልብስ ዋጋ 600 የኢትዮጵያ ብር ነው። ስንት ዶላር፣ ዩሮ፣ ወይ ፓውንድ እንደሆነ አላውቅም። የሆነው ሆኖ ግን እስከአሁን ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ ሰዎች እያንዳንዳቸው አቅማችን ይችላል የሚሉትን በማዋጣት በቀበሮ ሜዳ ጎንደር የብርድ ልብሱ መግዣ አዋጥተው አጠናቅቀውታል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ለብርድ ልብስ መግዣ የሚሆን ያበረከቱ ደጋግ ሰዎች በቁጥር 40 ናቸው። አርባ ሰዎች ናቸው 1205 ተፈናቃዮችን ብርድልብስ ያለበሱት። እያንዳንዳቸው የሚችሉትን ያህል የገዙትን ብርድ ልብስ ብዛትም አያይዤላችኋለሁ። ልብበሉ 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለ50 ሰው ጌጡ ማለት ይሄ ነው። በቁጥር 40 የሆኑ ሰዎች ናቸው የስደተኞቹን ብርድ ለብስ የዘጉት። ይሄን በብር ስናሰላው 1,205×600= 724.197 ብር ነው የመጣው። ወዳጄ እጅህን ለመፍታት መመረጥ፣ እግዚአብሔር መፍቀድ አለበት። እነሆ የተፈቀደላቸው ይህን አድርገዋል። እነርሱም…

      ስም           ብዛት
1.ሆቤ ተስፋዬ~ 120
2.ቲጂ ~              83
3.አቤል~             83
4.ከፍያለው~        83
5.ምሥራቅ ~        83
6.ጋሽ ኃይሉ ~      83
7.ቢኒ ከለንደን ~   80
8.ሎዛ ~              60
9.ፍርዬ~              50
10.ሰሎሞን          40
11.ገኒ~               33
12.የዓለም ልጅ~   30
13.ሃይማኖት ~      30
14.ተክለ መስቀል~ 30
15.ሳሚ ከአዲስ አበባ~ 30
16.ዴቭ ሪች ~              30
17.መሰረት ከቤሩት ~    30
18. ኤልሳ በቀለ~          28
18.ሙሉ ~                    20
19. ትሪስተ~                 20
20.ማይክ ከሰውዝ አፍሪካ ~ 16
21.ወንዴ ~                         16
22.የኔነሽ ካናዳ~                  15
23.ስንታየሁ ከደቡብ አፍሪካ ~ 15
24.ወለተ ወሀና ~                   14
25.ሂሩት ከሊባኖስ ~               10
26.አበባ ከአሜሪካ ~              10
27.ገዛኸኝ ~                          10
28.ቤዛ ~                              10
29.ገነት ~                               8
30.ወድነህ~                            8
31.ሄኖስ ~                              5
32.አሜን ዳኒ~                        5
33.መክሊት~                         5
34.ቤዛ ~                              2
35.ጌታመሳይ ~                     2
36.ክንፈ ~                            2
37.እንዳወቅ~                       2
38.ምስጋናው~                      2
39.ሳሙኤል~                       1
40.ወለተ ሰንበት~                 1

"…ብርድልብሱን ያሟሉ ዘንድ እግዚአብሔር የፈቀደው ለእነዚህ ደጋግ ቅን ልብ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ብርድልብስ መግዢያ ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ። አለቀ። ተፈጸመ፣ ተጠናቀቀ። እግዚአብሔር ይመስገን። የሚቀረኝ አንሶላና ፍራሽ ነው። እሱላይ ተሻሙ።

• የ1 ብርድ አንሶላ ዋጋ 500 ብር ነው።
• የአንድ ፍራሽ ዋጋም 3500 ብር ነው።

"…የስደተኞቹ መከራ፣ ሰቆቃ፣ ከሰውነታቸው የሚወጣው ትል ያሳቀቃችሁ ወገኖች የምትችሉትን ያህል አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል አንሶላና ፍራሽ ለመግዛትና ከወደቁበት አፈር ላይ ለማንሣት ተረባረቡ። በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓውንድ በጣም ብዙ ነው። ዳያስጶራ ግድየለህም ተሳተፍ። አንሶላው ላይ እንረባረብና እሱን እናጠናቅቀው። አንድ አንሶላ በ500 ብር አባዝታችሁ የምትችሉትን ቃል መግባት ትችላላችሁ።

• 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ቃላችሁን ስጡ። እኔም ወዲያው የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁ። አመሰግናለሁ። ፍጠኑ።

• ለአንሶላው ደግሞ ስንት ሰው ይሆን የሚያስፈልገው አምላኬ። ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የፋኖ ዜና የሚኖረኝ፣ ርእሰ አንቀጽም የሚጻፈው ከማክሰኞ እስከ አርብ ድረስ ብቻ ነው። እሱም ቢሆን እንደ ድሮው ዋይ ዋይ እሪሪ ቁቁቁ ኡኡኡም የለበትም። በቃ ለስለስ ያለ አንጀት አርስ፣ አናት ቀዝቀዝ የሚያደርግ ለጋ ቅቤ የመሰለ ዜና ብቻ ነው የማቀርበው። አለቀ።

"…አሁን የዐማራ ትግል ከባዱን ማዕበል፣ ወጀብ፣ ሞገድ እያለፈ ነው። እየተሻገረም ነው። የተጸነሰው የነጻነት ልጁ ሊወለድ ከጫፍም ደርሷል። ጩኸቱም የምጡ ድምጽ ነው። ህመሙም የምጥ ህመም ነው። የምጥ ህመም ደግሞ ጩኸቱ እርግጥ ይረብሻል፣ ቀበቶ ያስፈታል፣ ማርያም ማርያም ያስብላል፣ ለተመልካች ለሰሚ ይጨንቃል እንጂ እንደ ራስ ምታት፣ እንደ አሜባ፣ ወስፋት፣ ኮሶ የመሰለ የበሽታ የሆድ ቁርጠት፣ አይደለም። በቃ ልጅ ሊወለድ ነው። ደምም፣ ውኃም ቢፈስ፣ ልጄን፣ እናቴን፣ ውይ እህቴን የእኔ ደም ይፍሰስልሽ ተብሎ ደረት የሚያስደቃ፣ የሚያስለቅስ አይደለም። ምጥ ነው። ልጁ ሲወለድ ጠብቆ ምጡን እርሺው ልጁን አንሺው ማለት ብቻ ነው።

"…ይልቅ ለመልሶ ግንባታ ከወዲሁ ተዘጋጁ። በወለጋ በኦሮሚያ ወላጆቻቸው የታረዱ የትየለሌ የዐማራ ሕፃናትን ለማሳደግ፣ ለማስተማር ተዘጋጁ፣ በኦሮሙማው እና በትግርሙማው የወደሙ አብያተ ክርስቲያናትና ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታል ጤና ጣቢያዎችን መልሶ ለመገንባት ተዘጋጁ። እኔ የምዘጋጀው ለእሱ ነው። ድሉ ወዶ ሳይሆን በግዱ አፈር ልሶ፣ ደቼ በልቶ ይመጣታል። ለነገው ዛሬ መስጠትን ልመዱ።

"…መርዳት አሁን ጎንደር በቀበሮ ሜዳ ስደተኞች ጀምረናል። የምትችሉትን በውስጥ ጻፉልኝ እና የባንክ አካውንታቸውን ውሰዱ። ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ ነው አሁን የምፈልገው።

• 1 ፍራሽ በ3500 ብር
• 1 ብርድልብስ በ600 ብር
• አንሶላ በ500 ብር

• ቀጥሎ እስከአሁን ስንት ሰው እንደለገሰ እለጥፍላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።” ምሳ 19፥17  …“ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና።” ምሳሌ 22፥9  …“ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፤ ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።”
ምሳ 28፥27 "…እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና። ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፥ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን። ምሳ 3፥ 26-27

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:05 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ በሚገኙ ስደተኞች ካምፕ ነው የምናመሻው። በዚያም እያለቅስንም፣ እየሳቅንም አብረን እያወጋን እናመሻለን። 

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/mmnEIicMuZQ

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እልልልል እያላችሁልኝ።

"…ይሄን ፍራሽ አቃጥለን በአዲስ ፍራሽ እንተካዋለን።

ፍራሽ

ዝናሽ ከቤሩት ~ 2000 ዶላር
60 ፍራሽ
ሀይል ጊዮርጊስ ~ 1000 ዶላር
30 ፍራሽ


ብርድ ልብስ

ከፍያለው~ 83
ሃይማኖት ~ 30
ሂሩት ከሊባኖስ ~ 10
ስንታየሁ ከደቡብ አፍሪካ  ~ 15
አበባ ከአሜሪካ ~ 10
ገዛኸኝ ~ 10
ወለተ ወሀና ~ 14
ሳሙኤል ~ 1
ክንፈ ~ 2

• አንሶላ
ሳሚ ሲያትል~ 30
ፍሰሃ ከሊቨር ፑል~ 25
መዓዛ ~ 20
ያሬድ ከአሜሪካ~ 12
መስፍኔ ከአሜሪካ~ 10
ሰሎሞን ~ 10
ጋሻው እስራኤል ~ 6
ክንፈ ሚካኤል ከናዝሬት፣~ 2
ዋሴ ~ 1 አንሶላ

"…እግዚአብሔር ይስጥልኝ። አግኝታችሁ አትጡ። ቃላት የለኝም። እንዲያው ዝም፣ ጭጭ ብቻ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዘመቻ ፍራሽ ተጀምሯል
ያዙ እንግዲህ ሻሞ…

"…የድምፅ መልእክቴን ሰምታችሁታል። የሚያናድድ፣ የሚያበሳጭ ነገር ባልናገርም ነገር ግን የሆኑ ሰዎች 😡 ብው ብላችሁ ትታዩኛላችሁ። ምህረቱን ይላክላችሁ። እኛ ግን ሥራ ላይ ነን። እንቀጥላለን።

"…አንድ የተባረኩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ዶክተር ፍራሹን በተመለከተ ባህርዳር ላይ ያለ ግሬስ የሚባል ፋብሪካ አለ የሥራ አስኪያጁ ስልክ አልሠራ ስላለኝ ነው ከዚያው በፋብሪካ ዋጋ እንዲገዛ እናደርጋለን ብለው ተስፋ ሰጥተውኛል። የአንሶላና የብርድልብስም የምታውቁ አገናኙኝ። እኔ እማፀናቸዋለሁ።

የሚያስፈልገው የፍራሽ ብዛት 1200
                የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር

የሚያስፈልገው የብርድ ልብስ ብዛት 1200
                የአንዱ ብርድልብስ ዋጋ 600 ብር

የሚያስፈልገው የአንሶላ ብዛት 2400
                  የአንዱ አንሶላ ዋጋ 500 ብር

"…ከላይ መርጣችሁ ልባችሁ የፈቀደውን ለሟሟላት ጀምሩ። ጻፉልኝ። የባንክ አካውንታቸውን እሰጣችኋለሁ። እስከማታ ድረስ እስከ መረጃ ቲቪ ነጭነጯን ከዘመዴ ጋር ድረስ ከጨረስን መልካም በቀጥታ ወደ ተማሪዎች ዩኒፎርም እንሄዳለን። ካልጨረስን ግን በነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ ዋይዋይ ስል አመሻለሁ ማለት ነው።

"…1…2…3 ጀምሩ…✍✍🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጀመሪያ ትሉን እናጠፋለን…

"…ትሉ የመጣው ከመኝታው ንፅሕና ጉድለት ነው። 3 ዓመት ሙሉ አፈር ላይ መተኛት ያመጣው ነው። የሕክምና ባለሙያዎች ትሉ በዝንብ የሕይወት ዑደት ያለ የዕጭ ደረጃ ነው ይላሉ። በሕክምና በሽታው Myiasis ወይም "ዱቅንዱቅ" ተብሎ የሚጠራ ሲኾን ሕክምናውም ዕጩ በአለበት አካባቢ ዙሪያውን ቫዝሊን በመቀባት አየር በማጣት እንዲሞቱ ማድረግ አሊያም ነቅሶ ማውጣት፤ እንዲኹም በጣም የቆሰለ ከኾነ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር መድኃኒት መጠቀም ይቻላል ነው የሚሉት። በዋነኝነት ግን መሬቱን ሲሚንቶ መለሰን፣ ፍራሽና የፕላስቲክ ምንጣፍ ማንጠፍ፣ ንፁሕ ጽዱ ከባቢን መፍጠር።

"…እኔ ዛሬ ያሰብኩት መጀመሪያ መኝታቸውን ማስተካከል ነው። ቅድሚያ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ ካሟላንላቸው በኋላ መሬቱን ሊሾ ለማድረግ አልቸገርም። ቅድሚያ ግን በእናቶቻችን፣ በአባቶቻችንና በሕፃናቱ ሰውነት ውስጥ የሚራባውን ትል ማጥፋት ይኖርብናል። ትሉን ለማጥፋት ደግሞ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብሱን ማሟላት አለብን። ባለ ፋብሪካ ወይም በጅምላ የሚያከፋፍል ነጋዴ ካለ ብትጠቁሙኝ መልካም ነው።

"…ፍራሽ የሚፈልገው የሰው ብዛት፣ የሚፈለገው የፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ ብዛት ከነዋጋው ጭምር ከቀበሮ ሜዳ ኮሚቴዎች ደርሶኛል። እሱን ነው የማቀርብላችሁ። በግል፣ በቤተሰብ፣ በማኅበር መግዛት ትችላላችሁ። ይሄን ነገር አንድ በካናዳ፣ በአሜሪካ፣ በእስራኤል፣ በኢትዮጵያ፣ በአውስትራሊያ፣ በደቡብ አፍሪካና በአውሮጳ የሚገኝ ባለፀጋ ሀብታም ጎንደሬም ሊዘጋላቸው ይችላል። ጎንደሬው አያገባኝም ቢል እኔ ሐረሬው ለጎንደር ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለምኜ ማሟላት አያቅተኝም። እነታማኝ በየነ፣ አበበ በለው፣ ጎንደር ኅብረት፣ ስኳድ እያሉ እኔ በቁማቸው ትል ለሚበላቸው ወገኖቼ በመለመኔ አላፍርም።

• ዋጋ ልለጥፍ ነኝ። ለመረባረብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ። ዘካ 7፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተናግሬ ሳልጨርስ…

"…ለአዲስ ዓመት በዓላቸው ፈታ ብለው ስቀው እንዲውሉ ግማሽ ሚልዮን ብር ጠዋት ያስገባላቸው ያደግ ሰው አሁን ደግሞ ዘመዴ ለህጻናቱ ትምህርት ቤት የሚጎድለውን ንገረኝ። እኔ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ቆርቆሮ ገዝቼ አሠራላቸዋለሁ ብሎ አስደስቶኛል ብቻ ሳይሆን በረዶ እንደፈሰሰበት ሰው አደንዝዞ አስቀርቶኛል።

"…ጋሼ ኧረ በሚልዮኖች የሚቆጠር ብር ሊያስወጣህ ይችላል ብለውም ታዲያ ይሄ ሁሉ ሕፃን መሃይም ሆኖ ይቅር እንዴ? የራሱ ጉዳይ ያስወጣኝ። አንተ ብቻ ወጪውን በባለሙያ አሠርተህ አስልክልኝ እኔ ማቴሪያሉን ገዝቼ እልካለሁ ብሎኛል። በቅርቡ አልቆ ትምህርት መጀመር አለባቸው ብሎኛል።

"…እኔ ዘመዴ ገና ለገና በነገ ዕለት ምሽት በመረጃ ቴሌቭዥን ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው መርሀ ግብሬ ላይ ድንጋይ ተሸክሜ ሕዝብ እለምናለሁ ብዬ ዕቅድ የያዝኩት ሰውዬ ዛሬውኑ ተሳክቶልኝ የምሆነው ጠፍተኛል። የባንክ ደብተራቸውን ሳልለጠፍ በጥቂት ሰዎች ልገሳ ብቻ ዓለሜን እያየሁ ነው። በእውነት ከእኔ በላይ በዚህ ምድር ማን ዕድለኛ አለ?

• አሁን ቆይ ላልቅስ…? ወይስ ልሳቅ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

461 ፍራሽ ቀረኝ።

"…እስከ አሁን ጎንደር በቀበሮ ሜዳ ትል የፈላባቸውን ህፃናት ለመታደግ፣ በዓሉንም በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ አቅጄ እግዚአብሔርን አጋዥ፣ ወላዲተ አምላክን አማላጅ፣ እናንት ጓደኞቼን ተስፋ አድርጌ ተነሥቼ ብዙዉን አሳክተናል።

"…እስከአሁን በተደረገው ርብርብ ከጎንደር ነኝ ያለ ባለፀጋ አልገጠመኝም። ከጎጃም ዐማራ አቶ ወርቁ አይተነው ለበዓላቸው ሰንጋ፣ ፍሪዳ፣ የሚጠጣ ውኃና ለስላሳ ሁሉ አሟልቶ ግማሽ ሚልዮን ብር አብርክቷል። 5 መቶ ሺ ብር ማለት ነው። አቶ ወርቁ ይሄን ብቻ ሳይሆን ስዊድን ሀገር ያለች አንዲት ሊሊ የተባለች እህት ጀምራላቸው በአቅም ማነስ ምክንያት ቆሞ የነበረውን ትምህርት ቤት አቶ ወርቁ አይተነው ገንዘብ ሳይሆን ማቴሪያል በማቅረብ የተጀመረውን ፈጽሜ፣ ቁሳቁሶቹን አሟልቼ አስረክባለሁ ብል በደስታ ጮቤ አስረግጦኛል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ቀጥሎ በትናንትናው ዕለት ደግሞ እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ እናንተ 1200 ብርድ ልብስ እና 2400 አንሶላ ተረባርባችሁ አሳክታችሁላቸዋል። የሚቀረን ፍራሽ ነው። ፍራሹን ካሟላን በሕፃናቱ ገላ ላይ የሚርመሰመሰውን ትል አጠፋን ማለት ነው።

"…አሁን የምፈልገው 1200 ፍራሽ ሲሆን ይሄን ቁጥር ለመሙላት 461 ፍራሽ ብቻ ነው። በዶላር፣ በዩሮና በፓውንድ ሀገር የሚገኙ ልበ ቅኖች ቢረባረቡ ይሕቺ ቀሪዋ ምንም ማለት አትሆንም ነበር። በርቱ እንበርታ ናሳካዋለን።

• የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር ነው። እንረባረብ። ይሄን እንደፈጸምን ደግሞ አቶ ወርቁና ወሪት ሊሊ በሚያሠሩት ትምህርት ቤት ለምናስተምራቸው ሕፃናት ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ቦርሳ፣ ሸራ ጫማ፣ ካልሲ፣ እስራስና እስኪሪብቶ እናሟላላቸዋለን። አዛኜን እናደርገዋለን።

• አግኝቶ ከማጣት ይሰውራችሁ። ጎንደሬዎችም ተንቀሳቀሱ። ቀስቅሱም። ዳይ ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይድረስ ለኮሎኔል አደይ ርስተይ ተስፋይ…!

"…ለህወሓት ወታደር ሆነው ለትግራይ መገንጠል ውድ የወጣትነት ዘመንዎን ከደርግ ጋር ሲፋለሙ ከርመው በመጨረሻ ወደ አሜሪካ ከተሰደዱ በኋላ ወልቃይቴ፣ ጎንደሬም፣ ዐማራም፣ አንዳንዴ ደግሞ ኢትዮጵያዊት የሚሆኑት አደይ ኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ ሆይ፤ ግድየሎትም ሱማሌም ይዝመቱ፣ ጓደኛዎ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የብልፅግናው ሰው ተነካብኝ ብለው የእኔንም ፎቶ ይዘቅዝቁ። እሱ ችግር የለውም። እንደው ግን እርስዎ የምር እውነተኛ ዐማራ ከሆኑ ግን እስቲ እዚያው ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ላይ ኮሎኔል ደመቀ መኮንን ጭምር ከወልቃይት አፈናቅሎ፣ ቤታቸውን ቀምቶ ያባረራቸውን የዐማራ ተፈናቃዮች፣ ከላይ በቪድዮ የሚመለከቱትን መካሮኒ የሚያካክል ትል ከሰውነተቻው የሚወጣውን የዐማራ ሕፃናትን ይርዱ። ልጅ ካልዎትና ዐማራ ከሆኑ ብዬ ነው እንዲህ ያልኮት እንጂ ትግሬ ከሆኑ አላስገድዶትም።

"…አደይ ኮሎኔል ርሰተይ ተስፋይ ወልቃይቴዋ ሆይ የጎንደር ዐማራን ባይረዱም ግን እኔ መራታው የሐረርጌው ቆቱ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን አስተባብሬ ይኸው ጠብ እርግፍ እያልን ነው። ማርያምን እኛ ግን አሳምረን እንረዳቸዋለን። ሰሊጣሞች ኧረ ተንቀሳቀሱ።

• ከግማሽ አልፈናል። እግዚአብሔር ይመስገን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርእሰ አንቀጹን እንዳነበባችሁ እያየሁ ነው። የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን ያልከፈትኩት በውስጥ መስመር ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ፍራሽ የሚገዙትን ፍራሽ ብዛት እና የባንክ ሒሳብ ደብተሩን እየጠየቁኝ፣ እኔም ለእነሱ እየላኩ፣ ከዚያ ደግሞ ስማቸውን በወርቃማው መዝገብ እየመዘገብኩ ነው የቆየሁት።

• እግዚአብሔር ይመስገን። 1200 ፍራሽም እየተሻሙበት ሊያልቅ ነው። በርእሰ አንቀጹ ላይ እየተወያያችሁ እስከዚያው ይሄን የጎንደር ዐማራ የቀበሮ ሜዳ ስደተኞችን አኗኗር የሚያሳይ ቪድዮ እያያችሁ በውስጥ መስመር ይሄን ችግር ለመቅረፍ ለሚደረገው ርብርብ እጃችሁን ዘርጉ። በግድ ነው። ግድ።

• ብዛት 1200 ፍራሽ
• የአንዱ ዋጋ 3500 ብር

👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ቃላችሁን ስጡ። እኔም ወዲያው የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁ። አመሰግናለሁ። ፍጠኑ።

"…ጀምሩ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ከፊታችን ሁለት ዓበይት የኦርቶዶክሳውያን በዓላት አሉ። መስከረም 1 እንቁጣጣሽ፣ የአዲስ ዘመን መለወጫ፣ አዲስ ዓመት፣ ቅዱስ ዮሐንስ። ቀጥሎ ደግሞ መስከረም 16 የመስቀል ደመራ፣ በማግስቱ መስከረም 17 መስቀል። ይሄ የታወቀ ነው። የአቢይ አህመድ አገዛዝ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ደግሞ ይሁነኝ ብሎ ቋሚ ሥራው አድርጎ የያዘው ደግሞ ከግራኝ አሕመድ ወረራ ወዲህ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በኢትዮጵያ ታሪክ የሰው ልጅ በዘግናኝ ሁኔታ እየታረደ ለአጋንንቱ የደም ግብር ሲያቀርብ ነው የምናየው። በወያኔ ጊዜ አንድ ሰው ሲሞት መግለጫ ያወጡ ቁጣቸውንም ይገልጹ የነበሩ ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሆኑ ሌሎች ይሄን በዘመነ አቢይ የምናየውን የሚልዮን ሰዎች ጭፍጨፋም ባላየ ባልሰማ ነው የሚያልፉት። ትንፍሽ አይሏትም። እኛም ዘግናኝ ዘግናኝ የአቢይ አገዛዝ ግድያዎችን እየተለማመድን መጥተን መደንገጥ እየተውን ነው። እነሱ ግን ሥራ ላይ ናቸው።

"…በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ማለት ለእኛ ለኢትዮጵያው ያን ልዩ ሥፍራ ያለው ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቢፈጽመውም ባይፈጽመውም አዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ ላይ መለወጥን ይመኛል፣ ያቅዳል። ከሱስ ለመላቀቅ፣ ትዳር ለመያዝ፣ የትምህርት፣ የሥራ ወዘተ ዕቅዶችን ብቻ በአዲስ መንፈስ በመነቃቃት በተስፋ ተሞልቶ ይጠብቃል። የመስቀል በዓልም እንደዚያው ነው። ጉራጌ ዓመት ሙሉ የሠራውን ይዞ ሀገር ቤት ገጠር የሚገባበት ወቅት ነው። በዓለ ልደትም፣ በዓለ ጥምቀትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ እርካታ የሚገኝባቸው በዓላት ናቸው። የስቅለትና የትንሣኤ በዓላትም እንደዚያው። አስተውላችሁ ከሆነ ግን አህዛቡ አቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ለመጣ ወዲህ እነዚህ የኦርቶዶክሳውያን በዓላት በኀዘን፣ በልቅሶ ነው የሚያልፉት። በዓላቱ በቀረቡ ቁጥር አገዛዙ ለአእምሮ የሚቀፍ ዘግናኝ፣ ሰቅጣጭ ግድያዎችን፣ ጭፍጨፋዎችን በመፈጸም የሕዝቡን ተስፋ ለማጨለም ይዳክራል። አጋንንታም።

"…ለዚሁ ሁሉ ከኢትዮጵያውያን ባሕል ያፈነገጠ፣ በአሸባሪዎቹ በእነ አይኤስ፣ ቦኮሐራም እና አልቃይዳ ዘንድ እናያቸው የነበሩ አሰቃቂ ግድያዎች ስፖንሰር የሚሆናቸው አረመኔ አገዛዝ አግኝተው ከሠለጠኑብን 6 ዓመታት አለፉ። እነዚህ በውጭ ሀገር አሠልጥኖ ያስገባቸው አራጆችም በመላ ኢትዮጵያ ከተሠማሩም ቆዩ። አራጆቹ በፋኖ ሲማረኩም የፋኖ አማኝነት ስለተነገራቸው ምንም አይደነግጡም። እንዲያውም ፋኖ የኪስ ገንዘብ ሁሉ ሰጥቶ፣ አብልቶ፣ አጠጥቶ ሁላ ነው የሚሸኛቸው። ከዚያ ጎንደር፣ ከዚያ፣ ጎጃም፣ ከዚያ ወሎ፣ ከዚያ ሸዋ እየሄዱ ያርዳሉ። ለዚህ መፍትሄው ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተነሥቶ ሥርዓቱን ታግሎ መቀየር። በአቢይ አሕመድ አገዛዝም ላይ ፍፁም ጨካኝ አረመኔ ካልሆነ በቀር ዘግናኝ ግድያው ይቀጥላል። ድሉም ይዘገይበታል።

"…ለምሳሌ በጎንደር የሚፈጸመውንና የተፈጸመውን እንይ። ጎንደር ከተማውን የሚያስተዳድረው ማነው? ራሱ የዐማራ ብልጽግና፣ ሚሊሻውና ፖሊሱ ከመከላከያ ጋር ያሉት ጎንደር ከተማ ነው። ፋኖ ከከተሞች ወጥቷል። እና እዚያ ብልፅግና በሚያስተዳድረው ከተማ ውስጥ የሚያግቱት ከራሱ ከሥርዓቱ አጋቾች በቀር ማን ሊሆን ነው? ማንም ሊሆን አይችልም። ገዳዮች እዚያው ከተማው ውስጥ ነው የሚኖሩት። ለመዝረፍ፣ ለማገት፣ ለመግደል የሚጠቀሙት የመንግሥት መኪና ነው። እና እንዲህ ከሆነ ወደማን አቤት ልትል ነው። ይሄን አረመኔ ሥርዓት በአንድ ልብ ተነሥተህ ካልታገልከው ተራ በተራ ቀስበቀስ ታልቃታለህ። በተራኪ አራስ ደፍሮ፣ ሕፃን አግቶ የሞያርድ ዐማራ የለም። ለዚህ ቀፋፊ፣ አረመኔያዊ ሥራ ሠልጥነው በአገዛዙ የገቡ ኮሬ ነጌኛዎች አሉ።

"…ደግነቱ መንግሥት አለ ብለው በአማች ቦለጢቃ የቆረቡ ጎንደሬ ዐማሮች ትናንት የሚያምኑት መንግሥታቸውን ዱላ ቀምሰውት አይቻለሁ። አራጁን አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፍ ፍትህ ሊጠይቁ ሆ እያሉ ሲሄዱ ራሱ አራጁ በጥይት እሩምታ በመሃል ጎንደር አርከፍክፎ አጨዳቸው። ረፈረፋቸው። የፈለገ ብትነጠፍለት፣ ብትታመንለት አራጁ የሚረካው ሲያርድህ ነው። እነዚያ በጎጃም የ7 ዓመት ሕፃን ተደፍራ ተገደለች ብለው በቀን 13 ዜና የሠሩ የመንግሥት ሚዲያዎች ትናንት የሉም። እነ ያሬድ ያያ፣ እነ በቀለ ወያም ትንፍሽ አላሉም። ስኳድ ድምፁ አልተሰማም። ምክንያቱም የተፈለገው የሕዝብን ስሜት መግደል ስለሚፈለግ ነው።

"…ዳንኤል ክብረት አንዴ ሲናገር ሕዝብ ምርር ሲለው ራሱ ፋኖዎችን ይዋጋል፣ ውጡልን ይላል ነበር ያለው። ለዚህ ነው አሁን ከዐማራ ባህልና ሃይማኖት ተቃራኒ የሆነ የሰው ልጅ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ያለው። ለዓይን የምታሳሳ ሕፃን የሚያርድ የዐማራ ፋኖ የለም። የሚያርድ አህዛብ ግን ነፍ ነው። የትየለሌ ነው። በጎንደር በባህርዳር በዋና ዋና የዐማራ ከተሞች አገዛዙ ጦርነት መግጠም ይፈልጋል። ከተሞችን ለማውደም፣ ለማድቀቅ ውጊያ ይፈልጋል። ይሄን ፍላጎቱን ያላሟሉለት ፋኖዎች ናቸው። ጎንደር ላይ ተዋግቶ የፋሲል ግንብን ማውደም ይፈልጋል። ፋኖ ግን እምቢ አለ። ደብረ ብርሃን ላይ ተዋግቶ ፋብሪካዎች እንደ ትግራይ ቢወድሙ ደስታው ነው። ፋኖ ግን በጥበብ የአገዛዙን ፍላጎት ማሟላት አልፈለገም። ስለዚህ ከተማው ውስጥ ፋኖ ከሌለ ወንጀል የሚሠራው ራሱ ከተማዋን የሚያስተዳድር አካል ነው ማለት ነው። የዛሬውን የጎንደር ከተማ መግለጫ ስናይ የሚጠቁመን "የምትወዷትን ከተማችሁን" ከእኛ ጋር ሆናችሁ ካልጠበቃችሁ ለሚደርሰው ውድመት አያገባንም የሚል ነው የሚመስለው። "…የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የሰው ሃብት እና ንብረት ዘርፈው ለመክበር የቋመጡ  ኃይሎች ከተማውን ለመዝረፍ የተሰለፋ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከመንግሥት ጎን በመቆም የምትወዷትን ከተማችሁን ከአጋችና ከዘራፊ ቡድን እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን" ነበር ያለው።

"…ባሳለፍነው ሳምንይ የኢትዮ ኒውሱ በለጠ ከሣ ከባሕርዳር የደረሰኝ የሃኪሞች ሰቆቃ ነው በሚል አንድ መረጃ አጋርቶ አይቼ ነበር። መከላከያ ተብዬው በዐማራ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ይፈጽም ዘንድ ፈቃድ አግኝቷል። አይጠየቅምም። ለጋዜጠኛ በለጠ ካሣ የደረሰውን መረጃ እንደወረደ ላቅርብላችሁ።

"…ሰላም በሌ። ባህር ዳር ላይ የገጠመኝን ጉድ ላካፋልህ ስለፈለኩ ነው። ስሜ ለጊዜው ይቆይ አስፈላጊ ከሆነ እነግርሃለው። እኔ የጤና ባለሙያ ሃኪም ነበርኩ። ባህር ዳር አንድ የግል ክሊኒክ ነው የምሠራው። እና የመንግሥት ኃይሎች በድንገት እያለፋ ነበር። በሩ ክፍት ስለነበርና እኔም ገዋን ለብሼ ስላዩኝ ወደ ክሊኒኩ ገቡ።  ከዚያ የሚታከሙ ፋኖዎች የታሉ? ጥቆማ ደርሶናል አሉ። አይ የሉም አልኳቸው። ገብተው አዩ። ባጋጣሚ ወጣት ታካሚ አልነበረም። ከዛ ፋኖን አክምሃል ተጠቁመናል አለኝ። እኔ እኮ ሠው የሆነን በሙሉ ነው የማክመው። ይሄን ሁሉ ዓመት የተማርኩትም የሰው ልጅን ሁሉ ሳላዳላ ላክም ነው አልኩት። ከዚያ ውጭ ላለው ጓደኛው በኦሮሞኛ ካወራ በኋላ፣ ሁለቴ በጥፊ ከመታኝ በኋላ ክላሹን እየነካካ "አንተ የት ነበርክ አልሠማህም እንዴ? አለኝ። በዚህ መሃል የማክማቸው ሰዎች ግማሹ በልመና ግማሹ እኛን ግደለን ሃኪሙን ተወው የሚሉ ትልልቅ እናትና አባቶች ሲጠጉን እኔን ወደውጭ ጎትቶ አውጥቶ የሆነ ጓዳ የሚመስል በረንዳ ያለው ቤት አሰገብቶ "ስማ አለኝ እኛ የዐማራን ወጣት ሳናጠፋ፣ ሴቶችን ደፍረን፣ በሽታ አስይዘን ነው የምንወጣው። ጌዜው የኛ ነው። የእናንተ ጊዜ …👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።” ሉቃ 6፥38

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአንሶላው ነገር…

"…ተመስገን 2400 አንሶላውን አሁን ገና ጨረስኩ። ስልኬ ጋለ፣ ደነዘዘ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ ለብቻዬ ሁላችሁንም እያስተናገድኩ ዋልኩ። የመጨረሻዋን 11 ፍሬ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ጠቅልላ ወስዳ ገላገለችኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…የሰጣችሁትን ሰዎች ሁሉ ስማችሁንና የሰጣችሁትን አንሶላ ብዛት ስጽፍ፣ የባንክ አካውንቱን ስልክላችሁ ነው የዋልኩት። የሰጪ የለጋሾቹን ስም ዝርዝራችሁን ከቻልኩ ዛሬ ሌሊት እለጥፍላችኋለሁ። አስደሳቹና እንዳልደክም ያደረገኝ ደግሞ ሁላችሁም በላኩላችሁ ቅፅበት ብሩን ልካችሁ ሪሲቱን መልሳችሁ የምትልኩልኝ ነገር ያስደስታል። ያኮራልም። እግዚአብሔር ይስጣችሁ።

"…ነገ ደግሞ ወደ ፍራሽ ነው የምንሄደው። ያን የገማ ፍራሽ አስግደን ንፁሕ ፍራሽ ነው የምንገዛላቸው። አሁን ቃል የምትገቡ ለፍራሽ መግዢያው ቃል ግቡ። አንዳችሁም ስለ ብርድልብስና አንሶላ እንዳታወሩብኝ። በቃ ከፍራሹ በኋላ ደግሞ ወደ ተማሪዎች ዩኒፎርም፣ ጫማ፣ ደብተር፣ እስራስ፣ እስኪሪብቶና ቦርሳ ነው የምናመራው። መጀመሪያ ፍራሹ ይለቅ።

"…የምፈልገው የፍራሽ ብዛት 1200 ነው። የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 የኢትዮጵያ ብር ነው። በተለይ ከሀገር ውጭ ያላችሁ 1ሺ$፣ 500$ 200$ እና 100$ ብትሰጡ በአጭሩ ያልቅልን ነበር። 10ሺ ዶላር ያልጻፍኩት የሚሞክር የለም ብዬ ነው። ግን እኮ ማን ያውቃል። ይኖር ይሆናል።

"…አሁን ዓይኔን መክፈት እያቃተኝ ስለሆነ ልሰናበታችሁ ነው። ቁርስ የበላሁ ነኝ። እስኪ ምሳም፣ ራትም ካለ ጠይቄ ልብላ። ማርያምን፣ አዛኜን እጅግ ደስ ብሎኛል። እናንተንም ደስ ይበላችሁ። ፍራሽ ይቀጥላል… በቀበሮ ሜዳ ያሉ ስደተኞች ጎደለን ያሉትን በሙሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እናሟላላቸዋለን። የሌሎችም ይቀጥላል።

• እስቲ ለእግዚአብሔር እልልልልልል በሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እግዚአብሔር ይመስገን። የብር ድልብስ ሪፖርት ላቀርብ ነኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ የዕረፍት ቀኔ ነው። ዕለተ ሰኞን ለእኔ የዶርዜ ማርያም በሏት። የእሁድ ጩኸቴን፣ መወራጨቴን፣ ላቤን፣ ልፍለፋዬን ዕለተ ሰኞን በማረፍ ላካክሰው ከወሰንኩ እነሆ ዛሬ ሁለተኛ ሳምንት ሆነኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ሆኖም በጎንደር በቀበሮ ሜዳ ላሉት ወጎኖቻችችን የጀመርነውን ሥራ በቶሎ ጨርሰን ለሌሎቹ በደብረ ብርሃን፣ በወሎ፣ በደቡብ ለሚገኙ እንደርስ ዘንድ የጀመርነውን መጨረስ ስላለብን በመሃል የደረስንበትን ላስታውሳችሁ ብቅ እላለሁ።

"…እንደሚታወቀው አቶ ወርቁ አይተነው ትልቁን ሸክማችንን አቅልሎልኛል። ግማሽ ሚልዮን ብር በመለገስ መጪውን አዲስ ዓመት ተፈናቃይ ስደተኞቹ ደስ ብሏቸው እንዲውሉ ሰንጋውን፣ ፍየሉን፣ ውኃና የለስላሳ መጠጡን ለግሶልናል። አንድ ባልና ሚስቶች አምስት ኩንታል ማኛ የሆነ ነጭ ጤፍ አቅረበውልናል። ወድሜ ጆኒ ቅቤውንና ማገዶውን ችሏል። ማባያ፣ ሚጥሚጣ፣ በርበሬ፣ ሽንኩርቱ ሁሉ በአንድ ወንድም ተችሏል። ድንኳን፣ ወንበር፣ የኩሽና ዕቃም በአንድ ወንድሜ ተችሎ ብሩ ገቢ ሆኗል። በ6 ሰው የግብዣው ነገር ተጠናቅቋል።

"…አሁን የሚቀረን እነዚያን ህጻናቱን ትል የሚያወጣባቸውን የመኝታቸውን ጉዳይ በአዳዲስ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ መቀየር ነው። እሱን እየተረባረባችሁበት ነው። የደረስኩበትን ቀጥዬ እለጥፍላችኋለሁ። እሱን እንደጨረስን ትምህርት ቤታቸውን አቶ ወርቁ እኔ እፈጽመዋለሁ ስላለ እኛ ደግሞ ለተማሪዎቹ ሕፃናት ዩኒፎርም፣ ጫማና ካልሲ፣ ቦርሳ፣ ደብተር፣ እርሳስና እስክሪብቶ እናሟላላቸዋለን። በቅድሚያ ግን የጀመርነውን እንፈጽማለን።

"…ይሄን በቶሎ እንደጨረስን በቀጥታ ከጳጉሜ 1-5 በደብረ ብርሃን፣ በወሎ፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአፋር የሚገኙትን ሌላው ቢቀር ሰንጋ በማቅረብ እንጎበኛቸዋለን። የዚያ ሰው ይበለን።

• የምትችሉትን ጻፉልኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እስከ አሁን…

"…412 አንሶላ፣ 260 ብርድልብስ፣ 170 ፍራሽ ተችሏል።

"…ዝናሽ ከቤሩት ~ በ2000 ዶላር 60 ፍራሽ፣
ኃይል ጊዮርጊስ ከካናዳ ~ በ1000 ዶላር 30 ፍራሽ፣ ኖሐ ከአሜሪካ በ1000 ዶላር 30 ፍራሽ ብዙ በመግዛት ይመራሉ። የሰፈሬ ልጆች ቢኒ ከደጃች ውቤ ከሀገረ ለንደን 80 ብርድልብስ ከፌ የደጃች ውቤ ከሜሪላንድ 83 ብርድልብስ ችለውኛል። አንተነህ ከለንደን በ150 ሺ ብር ለ300 አንሶላ መግዣ ለግሷል። ሳሙኤል 1 ብርድልብስ፣ ሃኒም 1 ብርድ ልብስ ለግሰዋል። እግዚአብሔር ለሁላችሁ ይስጥ።

የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር ነው
የአንዱ ብርድልብስ ዋጋ 600 ብር ነው
የአንዱ አንሶላ ዋጋ 500 ብር ነው።

"…በጎንደር በቁማቸው ትል በላቸው ወገኖች እርዱ። አንዳንድ ቪ ዶላር፣ አምስትም ሦስትም ሺ ዶላር፣ አቅም ያላችሁ እጃችሁን ዘርጉላቸውና በትል ከመበላት ታደጉአቸው።

• እንዲሰጥህ ስጥ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እልል በሉልኝማ…

• እስከአሁን ያገኘሁትን ልንገራችሁማ። 

ከአንሶላ ልጀምር…

አንሶላ… 3 ወዳጆቼ ገዝተዋል።

አንተነህ ከለንደን ~   300
ሰለሞን ፈለቀ ባህርዳር ~ 5
ሃኒ ~ 1
ድምር = 306

ብርድ ልብስ
• ቢኒ ከለንደን ~ 80 ብርድልብስ
• አሜን ዳኒ~ 5
ድምር=  85

ፍራሽ
• ኖህ አሜሪካ በ 1000 ዶላር
34 ፍራሽ
• ዶር ወዳጄ ሽመልስ~ 10
አመሊታ~ 10
ቲጂ ~ 20
ብርሃነ መስቀል ~4
ኤልሳ~6
ድምር 80 ፍራሽ


• ይቀጥላል። የብርድልብስና የአንሶላ ፋብሪካውን ባለቤቶች አግኝቻለሁ። እነሱንም ቀጥቼ፣ አስቀንሼ አግዛለሁ። በዚያ ላይ ጎንደሬዎች ናቸው። አከተመ

• እንረባረብ…🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የ 39 ደቂቃ የድምፅ መልእክት ናት። ሰብሰብ ብላችሁ አድምጡልኝማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አንድ ሺ አመስጋኝ እግዚአብሔር ይመስገን ካላለ በቀር ወደ ሌላ ሥራ እንደማልገባ ይታወቃል። ዛሬ እኔም ነጋ አልነጋ እያልኩ ሌሊት ነው የተነሣሁት። እናንተም በጊዜ ነው 1ሺውን ምስጋና የሞላችሁት። እንግዲህ ከምስጋናው ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ዛሬው አጀንዳችን ነው።

"…የዛሬው አጀንዳችንም ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ነው የሚወስደን። እነዚህ በምሥሉ ላይ የምታዩአቸው የጎንደር ዐማራ ሕፃናት በቁማቸው የትል መፈልፈያ የሆኑ ሕፃናትን የመታደግ ዘመቻ ላይ ነው ተሰልፈን የምንውለው።

"…ለስደተኞቹ 50 ሎሚ ለ 1 ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ግን ጌጡ ነው እንደሚባለው ሁሉ ሲያዩት ለአንድ ሰው የሚከብደው ለብዙ ሰው ይቀለዋልና በዚያ መንገድ ችግራቸውን ተረባርበን እንፈታዋለን።

"…እኔ ለራሴ እንጂ የማልሆነው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለአባቶቼ ገዳማውያን፣ ለስደተኞች፣ ለተቸገረ፣ ለተጨነቀ ሰው ለምኜ አፍሬ አላውቅም። እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ተዘጋጁ። የእርዳታ አሰጣጡን ቀጥዬ እጽፍላችኋለሁ። በተለይ፣ በዶላር፣ በዩሮ፣ በዲናር፣ በፓውንድ የምትሰጡ ሰዎች የብዙዉን ቀዳዳ ትሸፍናላችሁ። ለመስጠትም እኮ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ። በተለይ ሕፃናት ልጆች ያላችሁ አግኝቶ ከማጣት ፈጣሪ ይጠብቃችሁ።

• የእኔዎቹ ዝግጁ ናችሁ አይደል…? አንድ 100 ያህል ሰው ፈቃደኝነቱን ካሳየኝ ማብራሪያዬን እቀጥላለሁ። አያችሁ እግዚአብሔር ሲፈቅድ በቴሌግራም ጽሑፍ ብቻ ያለምንም ጩኸት እግዚአብሔር ሥራውን ሲሠራ…?

• ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ለነገ እነዚህን አስፈላጊ ቁሳቁሶች ለጎንደር ለቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ለሟሟላት እያሰባችሁ ተዘጋጅታችሁ እደሩ።

"…በህፃን በዐዋቂዎቹ ገላ ውስጥ የሚርመሰመሰውን ትላትል ለማጥፋት መሬቱን በሲምንቶ እንቀይረዋለን። ፍራሽም አንሶላም እናሟላላቸዋለን። ጽዱ አካባቢ ስንፈጥር ትላትሉ ይጠፋል። አለቀ።

"…ህፃናቱ ትምህርት ቤቱ ከተሠራላቸው ይማራሉ። ሲማሩ ደግሞ መሃይም ሆነው አይቀሩም። ለዚህ ደግሞ ለሁሉም ሕጻናት የትምህርት መርጃ መሣሪያ እናሟላላቸዋለን።

"…ነገጠዋት የእያንዳንዱን ዋጋ እጽፍላችኋለሁ። ለአንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ወጪም እጽፍላችኋለሁ። እናንተ መሻማት ነው። መረባረብ ነው።

"…ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸውን ቁሳቁሶች በፋብሪካ ዋጋ የሚሸጥልኝ ካገኘሁ እመርቀዋለሁ። አገናኙኝ፣ ወይ ደግሞ ጠይቁልኝ። አደራ፣ አደራ። አደራ። በማርያም።

• ፍራሽ
• ብርድ ልብስ
• አንሶላ
• ደብተር
• እስክሪፕቶ
• እስራስ
• ሸራ ጫማ
• ዩኒፎርም
• ሲሚንቶ
• አሸዋ
• ቆርቆሮ

"…ይሄን ወዳችሁ ሳይሆን በግዳችሁ በነገው ዕለት ተረባርባችሁ የምታጠናቅቁት ይመስለኛል። ኮሚቴ የለ፣ ጎፈንድሚ የለ፣ አንበሳ አውርዱልኝ የለ። በቃ በጥቂት እግዚአብሔር በፈቀደላቸውና በተመረጡ ሰዎች ይጠናቀቃል። ደኅና እደሩልኝ። የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አልጨረስኩም ገና ምኑ ተነካና…

"…ወደ ዋናው አጀንዳችን እየተንደረደርኩ ነው። የሕጻኗ የመራቢያ አካል ለለሚታይ ሙሉ ፊልሙን አላሳያችሁም። ነገር ግን ይሄ በፌስታል ውስጥ የምታዩት መኮሮኒ የሚያካክል ትል ከሰውነቷቸው ውስጥ ተለቅሞ፣ ሰውነታቸው ተቀድዶ የሚወጣ ትል ነው።

"…አፈር ላይ ስለሚተኙ፣ ፍራሽ ብርድልብስ ስለሌላቸው ነው። መሬቱን በሲምንቶ ቀጭን ፍራሽም ብንገዛላቸው ከዚህ ሁሉ ስቃይ ይድናሉም ይወጣሉም።

"…ማርያምን ጎንደር ሰው አጥታ የሰው ደሃም ሆና አይደለም። ዕድሜ ለመላኩ ተፈራ እሱን ሽሽት ከሁሉ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ ከሀገር የወጣው የተሰደደው ጎንደሬ ነው። ነገር ግን ማን ያስተባብረው? ማን ይሰብስበው። የጎንደር አክቲቪስቱም ሲበዛ ራስ ወዳድ ጉረኛም ነው። በቤቱ ያለውን ገመና ሳይሸፍን በውጭ በሌላ በማያገባው የሚደክም ጉረኛ ይበዛዋል። ያ ሆኖ ነው እንጂ ጥቂት ጎንደሬዎች ለዚህ በቂ ነበሩ።

፩ኛ፦ ለተማሪዎቹ ትምህርት ቤት ያስፈልጋቸዋል። የተጀመረ ትምህርት ቤት አለ እሱን አጠናቅቅላቸዋለሁ። ወንበር፣ ሰሌዳ ሳይቀር አሟላላቸዋለሁ።

፪፦ 3,500 ሕፃናት ሙሉ ዩኒፎርም፣ ሸራ ጫማ፣ ደብተርና ቦርሳ እገዛላቸዋለሁ። ይሄንም አደርገዋለሁ።

፫ኛ፦ መሬቱን ሲሚንቶ፣ መኝታቸውን ፍራሽና አንሶላ ብርድልብስም እንዲኖራቸው አደርጋለሁ። ወላዲተ አምላክ ትረዳኛለች አደርገዋለሁ። አሁን ከእነዚህ ላይ 1 ሚልዮን ብር ይሠረቃል? ይወሰዳል? ነውር ነው።

"…ለጎንደር እኔ ዘመዴ ብቻዬን እበቃታለሁ። ሾተላይዋን እነቅለዋለሁ። መርገምቶቿን አርቃለሁ። የጎንደር ዐማራን ስንፍናም ለዓለም እገልጠዋለሁ። እወቅሳቸዋለሁ። በጭቃ ዥራፌ እዠልጣቸዋለሁ።

• ተራ በተራ እያሟላን እንሄዳለን። እግዚአብሔርም ይረዳናል። ልጁን የሚወድ ከእኔ ጎን ይቆምና የእነዚህን ህፃናት ሰቆቃ ያስወግዳል።

• አዛኜን አላለቅስም።

Читать полностью…
Subscribe to a channel