በማዕተብ ቀናችን መሃል።
"…በጎንደር ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች እናንተ ያደረጋችሁላቸውን ሰምተው በደስታ ጮቤ እየረገጡ ነው ተብሏል። ዕድሜ ግማሽ ሚልዮን ብር ፎጭ አድርጎ አውጥቶ ሰንጋና ሙክቶቹን ገዝቶ ለሰጠው ለባለሀብቱ ለጋሽ ወርቁ አይተነው፣ ዕድሜ ለእነ ጆኒ፣ ዕድሜ ነጭ ማኛ ጤፍ ለገዙት፣ ዕድሜ ሽንኩርት በርበሬ መግዢያውን ለሰጡት፣ ዕድሜ ድንኳን፣ ወንበር ተከራይተው ከአፈር ላይ አንስተው ወንበር ላይ ላስቀመጧቸው በጎ አድራጊ የእኔ ወዳጆች። አሁን ተፈናቃዮቹ ደስተኞች ናቸው።
"…ጤፉ ተገዝቶ፣ ተፈጭቶ ተዘጋጅቷል። በርበሬው፣ ማገዶው፣ ቅቤው፣ ቅመማ ቅመሙ፣ ማገዶው ተገዝቶአል። አሁን ተፈናቃዩ ሁሉ ደስታ በደስታ ሆኗል ተብሏል። 2400 አንሶላ፣ 1200 ብርድልብስ፣ 1200 ፍራሽ እንደተገዛላቸው ሰምተውም በቁማቸው በትል ከመበላት መዳናቸውን ሲያስቡት የሌለ መደሰታቸውን ነው የተነገረኝ። ደስ ሲል።
"…አሁን ደግሞ ህፃናቱ ማይም ሆነው እንዳይቀሩ እነዚህ አግኝተው ያጡት ሕፃናት መማር እንዳለባቸው ወስኜ የትምህርት መርጃ መሣሪያቸውን ለማሟላት ደፋ ቀና በማለት እገኛለሁ። ትምህርት ቤቱን ወሮ ሊሊ የጀመረችውን አቶ ወርቁ አይተነው እኔ አጠናቅቅላቸዋለሁ ብሏል። አሁን እኔ ከደብተር፣ ከእስኪሪብቶና ከእስራስ በፊት እንደ ሳጥንም ያገለግላቸው ዘንድ የተማሪ ቦርሳ ልገዛላቸው ልመና መጀመሬን ሰምተው ህፃናቱ በደስታ እየቦረቁ ነውም ብለውኛል። እስከአሁን ከሚያስፈልገኝ 3,300 ቦርሳ ውስጥ 1,047 ቦርሳ መግዣ አግኝቼ የሚቀረኝ 2,253 ቦርሳ ብቻ ነው። 100$ 12, 100 ፓውንድ 14 ፍሬ ቦርሳ ይገዛል። በ500$ 60 ቦርሳ የገዙልኝም አሉ።
"…የለገሳችሁት ሳንቲም አንዲቷም ያለቦታዋ አትውልም።
• በማዕተብ ቀናችን እስቲ የተወሰነ ቦርሳ እንረባረብ። ማነህ የህፃናት ወዳጅ? አለሁ በል እስቲ።
ጥያቄ ነው…?
"…እስቲ የባለ ማዕተብ ሙሽሮችን ብቻ ፎቶ ላኩልኝና የሆነ ነገር ልበልበት። እናንተም በሉበት። እስቲ ማዕተቧ የሚታይ ባለማዕተብ ሙሽሬት ፎቶ ላኩልኝ።
• ፍጠን ባለ ማዕተብ።
ማዕተቤ…!
ተዋሕዶ ሃይማኖቴ፣
የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ።
ማዕተቤን አልበጥስም፣
ትኖራለች ለዘላለም።
"…ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።” ምሳ 6፣ 20-22
• ይትአለ ማዕተብህ…?
• የትአለ ማዕተብሽ…?
"…መልካም
"…የሚጠበቀው አንድ ሺ አመስጋኝ አመስግኖአል። እግዚአብሔር ይመስገን። ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ለረጅም ዓመታት እያሰብን የመጣነውንና በየዓመቱ በወርሀ ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ ሰይመን እያሰብን የምንውለውን "የማዕተብ ቀንን" በተመለከተ አጠር ያለች መልእክት የተላለፈበት ርእሰ አንቀጽ ነው።
"…ርእሰ አንቀጹ ከተለጠፈ በኋላ የፎቶ መላኪያው ሰንዱቅ ሳጥን ይከፈታል። ከዚያ ባለማዕተቦች ከነማዕተባችሁ የተነሣችሁትን ፎቶ በመላክ ማዕተባችንን ለመላው ዓለም እንገልጠዋለን። እነመሰክራለንም።
• ዝግጁ…?
912 ላይ ደከመኝ…!
"…ነገ የማዕተብ ቀን ነው። በዚህ ቀን እንደተለመደው የቴሌግራም ገጻችን የፎቶ ማስቀመጫ ሳጥኑ ይከፈታል። ማዕተባችንን አንገታችን ላይ አስረን ለዓለሙ ሁሉ እንገለጣለን። በዚያውም እግረመንገዳችንን ለጀመርነው በጎንደር በቀበሮ ሜዳ ተፈናቅለው ለፈሰሱ ለምታዩዋቸው የሚያሳዝኑ ምስኪን ሕጻናት መጀመሪያ ቦርሳቸውን ከዚያ እስራስና እስኪሪብቶ፣ ደብተራቸውንም እንገዛላቸዋለን።
• ላልሰማ አሰሙ። ነገ እናሳካዋለን። የነገ ሰው ይበለን። ደኅና እደሩልኝ።
421 ደርሰናል…!
"…ለግል ጉዳዬ ከቤት ወጣ ብዬ ወደ ቤት አሁን ገና መመለሴ ነው። ባለሁበት ቦታ ሆኜም ገባ እያልኩ ቃል የሚገቡትንና የባንክ አካውንቱን ለሚጠይቁኝ ሁሉ በተቻለ መጠን እሰጣቸው ነበር። አሁን የኢትዮ ቤተሰብ የዕለተ ሐሙስ ዝግጅታችን ሰዓትም እየደረሰ ስለሆነ ወደቤት እየተመለስኩ በግርድፉ እስከአሁን የተቻለውን ቦርሳ ስቆጥር በግርድፉ 421 ቦርሳ ደርሷል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ርብርቡ በጣም ደስስ ይላል። አይቻልም ብሎ ነገር እኔ ጋር የለም። አልጀምር እንጂ ከጀመርኩ ሳላደማ አልመለስም። መፋታት ብሎ ነገር አላውቅም። በተለይ 100 ዶላር የ10 ሕፃናት ቦርሳ ይገዛል። 100 ፓውንድ የ10 ሕፃናት ቦርሳ ይችላል። አቅም ያላቸው አይገቡም እንጂ አቅም ያላቸው ቢገቡ በቶሎ ያልቅ ነበር።
"…ከደብተሩ በፊት ቦርሳውን ያስቀደምኩበት ምክንያት አለኝ። የሚኖሩት ድንኳን ውስጥ ስለሆነ ቦርሳው እንደ ሳጥንም ያገለግላቸዋል ብዬ ነው። እንደእናንተ ቤት ልጆች ሳሎኑ ላይ አያዝረከርኩትም። ለዚያ ብዬ ነው። ቦርሳውን ከገዛንላቸው በኋላ ደብተሩም፣ እርሳሱም፣ እስኪሪብቶውም እዚያው ውስጥ ይቀመጣል። እንበርታ። ላልሰማ አሰሙ።
"…ከ3,300 – 421 = 2879 ይቀራል። አዛኜን ይህቺ ደግሞ ምን አላት?
• እንበርታ…!
መልካም…
"…በርእሰ አንቀጻችን ላይ አስተያየት እንሰጥና በቀጥታ ወደ ቀበሮ ሜዳ ጎንደር እንሄዳለን። በዚያም ቦርሳ፣ ደብተር፣ እርሳስ፣ እስኪሪብቶ፣ ዩኒፎርም ዛሬውኑ ሰብስበን እንዘጋዋለን።
"…ነገ ደብረ ብርሃን ተፈናቃዮች ስላናገሩኝ ለእነሱ የበዓል መዋያ ሰንጋ እናሟላላቸዋለን። በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ለተፈናቃይ ሙስሊም አባቶቼና እናቶቼም ለብቻቸው እንደ እምነታቸው ሰንጋ ቢፈልጉ አልያም ፍየል፣ በግም ገዝቼ አንበሸብሻቸዋለሁ። ተዘጋጁ።
"…በቅድሚያ ርእሰ አንቀጹ ላይ አንድ 20 አስተያየቶችን እንቀበልና በቀጥታ ወደ ቦርሳ ግዢው እንገባለን። ቦርሳው ከተገዛ በኋላ በቦርሳው ውስጥ ስለሚቀመጠው ደብተር፣ እስራስና እስኪሪብቶ እናወራለን።
• የአንድ ቦርሳ ዋጋ በዝቅተኛው 1 ሺ ብር ነው የያዙት። እናንተ የስንት ተማሪ ቦርሳ እንደምትችሉ ብቻ ጻፉልኝ። ከዚያ እኔ በውስጥ የባንክ አካውንታቸውን እጽፍላችኋለሁ።
• ቦርሳውን እህቴ እሙ ከአሜሪካ ከሚያስፈልገው 3,300 ተማሪ መሃል የ10 ተማሪዎችን 10 ሺ ብር በመላክ መግዛት ጀምራለች። አሁን የሚቀረን የ3,290 ተማሪ ቦርሳ ነው ማለት ነው። ምን አላት…?
"…👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና በኋትስአፕ ወይም በቴሌግራም የውስጥ መስመር ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የቦርሳ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ1,000 የኢትዮጵያ ብር አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። ዛሬ የጎንደር ቀበሮ ሜዳን ፋይል ዘግተን ወደ ደብረ ብርሃን፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ወዳሉ ተፈናቃዮች የበዓል ሰንጋ ወደማሟላቱ ፊታችንን እናዞራለን።
"…እስቲ ደግሞ ተሻሙና ልቤን በደስታ አቅልጧት። 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
ETHIOPIA |~ በትኩረት ይነበብ
"…ከዛሬ ከነሐሴ 30/2016 ጀምሮ ርእሰ አንቀጼን ስጽፍ መግቢያው ላይ ኢትዮጵያን፣ መዝጊያው ላይ የስሜን ማኅተም እና ወሩን፣ ቀኑን፣ ዓመተ ምሕረቱን እንደ ድሮው እንደ ፌስቡክ ዘመኔ መጻፍ እጀምራለሁ። ሻሎም…! ሰላም…! ም ተመልሳ መጥታለች። አዲስ የጨመርኩት ድርጅቱ/አሸበርቲው እና አስነቀልቲው የሚለውን ተጨማሪ መንግሥትና ተቃዋሚዎች የሰጡኝን የማእረግ ስሞቼን ነው። ይሄ ይታወቅልኝ።
"…እኔና የቴሌግራም ቤተሰቦቼ የዘንድሮውን የ2016 ዓም ማብቂያ የ2017 ዓም መግቢያ መሸጋገሪያ ድልድይ የሆነችውን አጭሯን 13ኛ ወራችንን ወርሀ ጳጉሜን እስከዛሬ ከምናደርገው ፎቶ የመለጠፍ ተግባር በዘለለ በተለየ መልኩ ነው ለማክበር የተዘጋጀነው። ዘንድሮ በየዓመቱ በምንዘክራቸው በእያንዳንዷ ዕለታት ቁምነገር፣ የጽድቅ ሥራም እየሠራን ነው የምንውለው። በእያንዳንዷ ዕለት በታወቁና ሊያገኙኝ በሚችሉ የስደተኛ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሰንጋ እናቀርብላቸዋለን። እናደርገዋለን። ብቻ የምታውቋቸው ኮሚቴዎች እንዲደውሉልኝ አድርጓቸው። ማርያምን፣ አዛኜን አደርገዋለሁ። እናደርገዋለን።
"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ አብዛኛዎቻችሁ የዓመት በዓል ዝግጅት ስለሚኖርባችሁ በተለይ ሴቶቹ በኩሽና ሥራም፣ በገበያም፣ በቤት ጽዳት ዝግጅት፣ በማዕድ ቤት ሥራ ስለምታሳልፉ ለማንበብ ጊዜ ስለማይኖራችሁ ሌላው ቢቀር ርእሰ አንቀጹን በድምጽ ላደርግላችሁ እሞክራለሁ። በእጅ እየሠሩ በጆሮ ቢያዳምጡ ወጡም የሚያር አይመስለኝም። መልካም ነው አይደል…?
"…መልካም… በቴሌግራም መንደራችን የምንገኝ እኔና ጓደኞቼ እንደ ኃጢአታችን ብዛት፣ እንደሰውነታችን ክፋት ሳይሆን በቸርነቱ የቸርነቱን ሥራ ሠርቶልን፣ በምህረት ዓይኖቹም ዓይቶን፣ ልክ እንደ አምና ካቻምናው ዘንድሮም ዕድሜ ለንስሀ ዘመን ለፍስሐ ሰጥቶን በፈቃደ እግዚአብሔር የወርሀ ጳጉሜን ቆይታችንን በነገው ዕለት "የማዕተብ ቀንን በማሰብ በታላቅ ተጋድሎ እንውላለን። የዘንድሮው ጳጉሜን የምናከበረው ከፎቶ የዘለለ ነው። የተግባር ሥራ የምንሠራበት ነው። ጳጉሜን ስታልቅ ደግሞ መስከረም 1/2017 ዓም አዲስ ዓመት ይመጣል። ቅዱስ ዮሐንስ፣ እንቁጣጣሽ። መጬውን አዲስ ዓመት ለመቀበል ዛሬ አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እንገኛለን። እናም በወርሀ ጳጉሜን ባሉት ፭ ቀናት እኔና ጓደኞቼ በእያንዳንዱ ቀናት ለቀናቱ ስያሜ በመስጠት በቀናቱም ቸርነት፣ ምጽዋት በማድረግ፣ ድሆችንና አግኝተው ያጡ በሰው ሠራሽ ፖለቲካዊ ችግር ሰለባ የሆኑ ተፈናቃይ ስደተኞችን በግሩም ሁኔታ ማኅበራዊ ሚድያውን ባጥለቀለቀ መልኩ ደስ እያለን አስደስተናቸው እናልፋለን ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። ቀናቱ አምስት ናቸው። እነርሱም…
፩፥ ጳጉሜን ፩ የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜን ፫ የፊደል ገበታ ቀን።
፬፥ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማና
፭፥ ጳጉሜን ፭ የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፮፥ ጳጉሜን ፮ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የስጦታ ቀን ናቸው።
"…ርዕሰ አንቀጽ"
"…ከታላቅ ይቅርታ ጋር ከነገ ጳጉሜን አንድ ጀምሮ ምንም አይነት አዲስ አጀንዳ ከየትኛውም ስፍራ ተፈብርኮ በበተን እኔ ዘመዴ አልቀበልም። አላስተናግድምም። ነገ የምትጀምረዋን የኢትዮጵያ አጭሯን ወር፣ ለአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ ድልድይዋን ወርሀ ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ በእንዲህ መልክ ልናሳልፍ ወስነናል።
•••
ስለዚህ ከነገ ጳጉሜን ፩ ጀምሮ በመንደራች በመሃል ድንገት አንገብጋቢ፣ አስፈላጊ የሆነ ወሳኝም የሆነ ሰበር የድል ዜና ካልሆነ በቀር ሌላ እዬዬ፣ ለቅሶ፣ ሙሾ እኔም የማላቀርብ፣ የማላወራ፣ የማላወጋ፣ ወደ እናንተም የማላደርስ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ። የሚወራም፣ የሚነገርም ካለ እንፈጣጥመዋለን። ከነገ ጀምሮ ግን የምናወራው…
፩፥ ጳጉሜን ፩ የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜን ፫ የፊደል ገበታ ቀን።
፬፥ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማና
፭፥ ጳጉሜን ፭ የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፮፥ ጳጉሜን ፮ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የስጦታ ቀን።
• ጳጉሜን ፩ ፥
"…የተዋሕዶ ልጆች አንገት በሙሉ በአንገት ማዕተብ ክር ያሸበርቃል። የመስቀል ዓይነት በፌስቡክና በቴሌግራም ቻናሎች ይጥለቀልቃል። በዕለቱ ፌስቡክም ሌላ ወሬም እስኪያጣ ድረስ እንዲያ እናደርጋለን። የፎቶ ማስቀመጫ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቄም በዓመት ለአምስት ቀናት ይከፈታል። ዕለቶቹን በተመለከተ የሚያወሱ ፍቶ ግራፎችም ይለጠፋል። ሌላ ፎቶም አይለጠፍበትም። እናንተ ተዘጋጁ፣ ማዕተብ የሌላችሁ ከወዲሁ ግዙ፣ ግዙናም እሰሩ። በዚሁ ቀን በማዕተብ ቀን ቢቻል ለሁለት ለሦስት መጠለያ ካምፖች፣ ካልቻልን ለአንድ መጠለያ ካምፕ ሰንጋዎች እንገዛለን። ተዘጋጁ።
• ጳጉሜን ፪ ፥
"…የክብረ ክህነት ቀን ነው። በዚያ ቀን ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለካህናት አባቶቻችን፣ አክብሮታችንን የቻልን በአካል እየሄድን፣ ያልቻልን በስልክ እየደወልን ፍቅራችንን የምንገልጽበት ዕለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት፣ ቡራኬ የምንቀበልበት፣ ለበዓሉ የሚሆን የልጅነት ስጦታ የምንሰጥበትም ዕለት ነው። እኔም አደርገዋለሁ። እናንተም አድርጉት። በዚህም ቀን ቢቻል ለሁለት ለሦስት መጠለያ ካምፖች፣ ካልቻልን ደግሞ ለአንድ መጠለያ ካምፕም ቢሆን ሰንጋዎች እንገዛለን። ለዚህም ተዘጋጁ።
• ጳጉሜን ፫፥
"…የፊደል ገበታ ቀን። አከተመ የዚያን ዕለት ቴሌግራምም ሆነ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፊደላት ሲያሸበርቅ የሚውልበት ቀን ነው። የዚያን ዕለት ልብሱ ሁሉ የፊደል ገበታ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን በሁሉ ሰው ስንነበብ እንውላለን። በመላው ዓለም በምትኖሩበት ምድር ላይ በየትኛውም ስፍራ የከበረው የግዕዝ፣ የአማርኛ ፊደላችን ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቆት ይውላል። በዚህም ቀን ቢቻል ለሁለት ለሦስት መጠለያ ካምፖች፣ ካልቻልን ደግሞ ለአንድ መጠለያ ካምፕም ቢሆን ሰንጋዎች እንገዛለን። ለዚህም ተዘጋጁ።
• ጳጉሜን ፬ ፥
"…የሰንደቅ ዓላማ የክብር ቀን፦ በዚህ ዕለት በትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓትና በኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ ኦህዴድ ኦነግ ብልጽግና ቡችሎች የሚዋረደውን፣ የሚቃጠለውን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ከፍ አድርገን እያውለበለብን ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀን የምንውልበት ዕለት ነው። በዚህም ቀን ቢቻል ለሁለት ለሦስት መጠለያ ካምፖች፣ ካልቻልን ደግሞ ለአንድ መጠለያ ካምፕም ቢሆን ሰንጋዎች እንገዛለን። ለዚህም ተዘጋጁ።
• ጳጉሜን ፭ ፥
"…ዘንድሮ ጳጉሜን 5 ስለሆነች ዕለቱን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ከሱሶች ሁሉ የመላቀቂያና፣ የመገላገያ ለአቅመ ደካሞችም የስጦታ መስጫ ቀን አድርገን አስበን እንውላለን። ይሄ ዕለት ማብራሪያም ዝርዝርም አያስፈልገውም። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስናስብ በዚህ ዕለት በገጠር በከተማ፣ በጭቃ፣ በሸክላ፣ በእምነበረድ፣ በሳር በቆርቆሮ፣ በዋሻ ያለችውን የቅድስት እናት ቤተ ክርስቲያናችንን ፎቶዎች በመለጠፍ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አሸብርቀን እንውላለን። በዚሁ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እያከበርነ በዚያውም ከተጣባን ሱስ ለመገላገል እንጸልያለን፣ እነ ሲጋራ በአደባባይ ይረገጣሉ። አልኮል፣ ጫት፣ ሺሻና ሀሺሽም ይወገዳሉ፣ ይረገማሉ። ከዝሙት እንሸሻለን። በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዘመን ዘመነ ማቴዎስን እንቀበለዋለን፣ እንቀላቀለዋለንም። 👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።” ሉቃ 6፥38
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የፍራሹ ሪፖርትና የነ ዝግጅት።
"…2,400 ውን አንሶላ የገዙልኝ 129 ወዳጆቼ ናቸው። የአንዱን አንሶላ ዋጋ በ500 ብር አስበው ነው የገዙልኝ። 1,200 ውን አንሶላ የገዙልኝ 40 ወዳጆቼ ናቸው። የአንዱን ብርድልብስ ዋጋ በ600 ብር አስበው ነው የገዙልኝ። ከበድ ይል የነበረው ፍራሹ ነበር። 1,200 ውን ፍራሽ የገዙልኝ 179 ወዳጆቼ ናቸው። የአንዱን ፍራሽ ዋጋ በ3,500 ብር ዋጋ አስበው ነው የገዙልኝ። 5 ሰንጋ በሬ፣ 5 ፍየል የገዛልኝ፣ ውኃ፣ ለስላሳውን ሁሉ በግማሽ ሚልዮን ብር ወጪ የሸፈነልኝ አንድ ሰው ነው። አቶ ወርቁ አይተነው። አቶ ወርቁ አይተነው ይሄን ብቻ አይደለም ቃል የገባልኝ ወሮ ሊሊ የጀመረችውን ትምህርት ቤት ማቴሪያሉን ብቻ ገዝቶ ሊያጠናቅቅልኝም ነው ቃል የገባልኝ። ስንት ሚልዮን እንደሚያስወጣው መድኃኔዓለም ይወቅ። ቅቤ ከነ ማገዶው አንድ ሰው፣ አምስት ኩንታል ጤፍ የተባረኩ ባልና ሚስቶች፣ በርበሬ፣ ሽንኩርት አንድ ሰው። ድንኳን፣ ወንበር፣ ድስት፣ ሰሀን ኪራዩንም አንድ ሰው ነው የቻለልኝ። ይሄን ሁሉ ዝግጅት ያሟሉልኝ 353 ወዳጆቼ ብቻ ናቸው። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…መጽሐፍ እንዲህ ይላል። “…እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።” ማቴ 20፥16። የቴሌግራም ጓደኞቼ 300 ሺ ያለፉ ናቸው። ሁሉም ወዳጆቼ ናቸው ማለት አይደለም። ሁልጊዜ እንደምለው የእኔ ምርጥ የምላቸው ተገልጸው እግዚአብሔር ይመስገን ብለው የማያቸው ከሁለት ሺ የማይበልጡ፣ እንዲሁም በተለያየ ምክንያት የጠዋት ጠዋቱን የእግዚአብሔር ሰላምታ የማይመልሱ፣ ነገር ግን ከእኔ ቤት የማይለዩ ሦስት ሺ ቢኖሩም፣ እሰከ መቶ ሺህ የሚደርሱ አንባቢዎች አሉኝ። ከዚህ ውስጥ ስህተቴን ፈልገው ካገኙ ጠብቀው ሊወቅጡኝ አሰፍስፈው የሚጠብቁኝ ሲሆኑ ሌሎች ለመንግሥት ወሬ የሚቃርሙ፣ ቀሪዎቹ ቁጥር ብቻ ናቸው። “የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።” ማቴ 22፥14 ተመረጡ፣ ተጠሩ እንጂ በበዛ አይደለም። ስትመረጥ፣ ሲፈቀድልህ አንድ ሆነህ ሺውን ታሳድደዋለህ። “አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና ከእናንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።” ኢያ 23፥10።
“… እመን ብቻ እንጂ አትፍራ።” ማር 5፥36። በጉዳዩ ልመንበት እንጂ መመሪያዬ ይሄ የጌታ ቃል ነው። አልፈራም። ባለመፍራቴም ሁሌ አሸናፊ ነኝ። ፍርሃት የምለው የውጊያ፣ የቦክስ፣ የጥፊ አይደለም። ለድሆች፣ ለአብያተ ክርስቲያና፣ ለገዳማትና ለገዳማውያን ቀኝ ትከሻዬን ሸክኮኝ ከእግዚአብሔር ጋር አደርገዋለሁ ብዬ ከተነሣሁ አደርገዋለሁ። ጌታዬና አምላኬ መድኃኒቴም ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈጽምልኛል። ዘወትር ሁል ጊዜ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት እመምህረት እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምም ትቀድምልኛለች። እናም አፍሬ አላውቅም። ወደፊትም አላፍርም።
"…ተመልከቱ በዚህ ሁሉ ክብሩን የሚወስደው እግዚአብሔር ነው። ያለ ኮሚቴ፣ ያለማስታወቂያ፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ ሳይኖር፣ አርቲስቶች፣ ሯጮች፣ ዘፋኞች፣ ኮሚዲያን ሳይሳተፉበት። ጳጳሳት፣ ሼኮች፣ ሰባክያን፣ ፓስተሮችና ዘማርያን ሳይኖሩት፣ የውሎ አበል፣ ኮሚሽን፣ የነዳጅ ሳይቆረጥ፣ በመሃል ሳይነካካ፣ ጣልቃም የሚገባ ሳይኖር፣ በቴሌግራም ጽሑፍ፣ በቴሌግራም መልእክት ብቻ ይህን ከባድ ዕቅድ ማሳካት የተቻለው እግዚአብሔር ፈቃዱ ስለሆነ ብቻ ነው። ታነብባለህ፣ ታለቅሳለህ፣ ያለህን ታበረክታለህ። አለቀ። ገንዘብ ይበላብኛል፣ ዘመዴ ይቀሽብብኛል የለ በቀጥታ ከባለቤቱ ጋር ነው የማገናኝህ፣ በእኔ በኩል 05 ሳንቲም አያልፍም። ጎፈንድሚ የለም። አንበሳ ማውረድ የለ። በቀጥታ ከባንካቸው ጋር ማገናኘት። አከተመ።
"…ነገ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶቹን ማሟላት እንጀምራለን። ዕለቱን ከጨረስን ጨረስን ካልጨረስን ግን ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በየሀገሩ በመጠለያ ውስጥ ላሉት ሰንጋ እንገዛና ከበዓሉ በኋላ ተመልሰን እናጠናቅቅላቸዋለን። እንደ እኔ ግን ጸሎታችሁ ይርዳኝ እና ነገዉኑ እናጠናቅቃለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በዝርዝር የሚያስፈልጉትን የትምሕርት መርጃ ቁሳቁሶችን ከነዋጋቸው አቀርብላችኋለሁ። ደብተር በደረዘን፣ እርሳስ እስኪሪብቶም እንዲሁ። ዩኒፎርም፣ ሸራ ጫማም ቢሆን ከነካልሲው ዋጋቸውን አቀርብላችኋለሁ። የነገ ሰው ይበለን። እደግመዋለሁ ቢልዮን ብር ቢኖረው ያልተፈቀደለት ሰው አይሰጥም። አለቀ።
"…ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ከዚህ በታች ያሉትን 179 ለፍራሹ መግዣ ሰጥተው 1200 ፍራሽ የአንዱን ዋጋ በ3500 ብር ገዝተው ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ በተይም ህፃናትን በትል ከመበላት ያዳኑትን ወዳጆቼን ስም ዝርዝር ከነ ገዙት የፍራሽ ብዛት አስቀምጥላችኋለሁ። አንብባችሁ ስትጨርሱ ሁላችሁም በታማኝነት አንድ አቡነ ዘበሰማያትና አንድ ሰላምለኪ አድርሱላቸው። ጸልዩላቸው።
"…ለቀበሮ ሜዳ ጎንደር ተፈናቃዮች የፍራሽ ለጋሾች ስም ዝርዝር።
①.ዝናሽ ከቤሩት~ 2ሺ$ 60
②./ጊዮርጊስ~1ሺ$ 30
③.ኖህ 1ሺ$ 30
④.ግርማ 1ሺ$~30
⑤. ወለተ 1ሺ$~ 30
⑥. ጆኒ 1ሺ$~ 30
⑦.ኃ/ኢየሱስ 1ሺ$~ 30
⑧. ፋንታነሽ~ 30
⑨.ፍቅረ ሥላሴ~30 (ነፍስ ይማር)
10.አሳዬ~23
11.እነ ዮናስ~20
12.ቲጂ~20
13.ኤልሳ~20
14.ምሥራቅ~20
15.የትናየት~20
16.ሂረተ ሥላሴ~17
18.ብሩክ~17
19.መሳይ~ 17
20.ሰሎሞን~17
21.ዓለም~17
22.ማኅሌት~17
23.ያሬድ ቨርጂንያ~15
24.እነ ትእግስት~15
25.ሮማን~12
26.ወላንሳና ሲሳይነሽ~14
27..ዶር ወዳጄ ሽመልስ~ 10
28.አመሊታ~10
29.ዓለም~10
30.ገብርሽ~10
31.ሰገዱ~10
32.አቤል~ 10
33..ኤልሲ~10
34.ተፈሪ~10
35.ተገኝ~10
36.ፀሐይ~10
37.ኤልሳቤጥ~10
38.መሳይ~10
39.ማርታ~10
40.ዜድ እና አስቱ~10
41.ዮሐንስ~10
42.ግሩም~10
43.ይበቃል~10
44.ተመስገን~10
45.መንግሥቱ~10
46.ተስፋዬ~10
47.ዳኒ~10
48.ሙሴ~10
49.ሳህለ ሥላሴ~7
50.መልአክ~7
51.ኢዩ~7
52.ግርማይ~7
53.ኤልሳ~6
54.ፍሬ~6
55.ኒቆዲሞስ~6
56.ሊዲያ~6
57.ፅጌ~6
58.ኃ/ማርያም~6
59.እህታበዝ~6
60.አልማዝ~6
61.ጌትነት~6
62.ሰርኬ~6
63.ማኅፀንተ~6
64.አበባው~5
65.መከተ~5
66.ፍሬ~5
67.ፀደይ~5
68.ተመስገን~5
69.አትንኩት~5
70.ወልደ ክርስቶስ~5
71.ፌውዛን~5
72.አሜን~5
73.ዳንኤል~5
74.ብርሃነ መስቀል~4
75.ዘመናይ~4
76.ቤትሄል~4
77.ኢዮብ~4
78.ብሩክ እና ቃል~4
79.ወ/ሰንበት~4
80.ኢያሱ~4
81.ሳምራዊት~4
82.ዮናታን~4
83.ስዩም~4
84.ወ/አማኑኤል~4
85.ማሜ~4
86.ፋንታዬ~4
87.ሰላም ከኤርትራ~4
88.ማርታ~4
89.መዓዛ ድንግል~4
90.ኤልያስ~4
91.ዳዊት ዓለሙ~3
92.መዓዛ ድንግል~3
93.ዳዊት~3
94.ደረጀ~3
👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍
እልልልልልታ ለእግዚአብሔር…!
"…እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው። ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ ጠብቃቸው፥ ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው። መዝ 28፥ 7-9
“…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3
"…የፍራሹ ጉዳይ ተዘጋ። ዘውዲቱ ከቤሩት በ2000 ዶላር በመስጠት 60 ፍራሽ በመግዛት የጀመረችውን አቶ ግርማይ የተባሉ ዕድለኛ ሰው በመጨረሻ 1998 ደርሶ መጥተው ሁለት ፍራሽ ቢቀረኝም እሳቸው 7 ፍራሽ በመግዛት ይፈለግ ከነበረው 1200 ፍራሽ ላይ ሁለቱን ሞልተው አምስቱን ለመጠባበቂያ ይዘን 1205 አምስት ፍራሽ ግዢ ተጠናቅቋል።
"…አልጨረስኩም። የህጻናት ተማሪዎቹ የትምህርት ቁሳቁስ ይቀረኛል። እሱን እንደጨረስኩ የጷግሜ በረከታችንን ጀምረን በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙ ቀን የጣላቸውን የቻልነውን በዓሉን ሰንጋ ጥለን እናደምቅላቸዋለን። ተስፋ እንሞላቸዋለን።
• እልልልልልል በሉና እግዚአብሔርን አመስግኑልኝ። ቆይቼ እመለሳለሁ። መላቀቅ የለም። ደብተር፣ እርሳስ፣ እስኪሪፕቶ፣ ቦርሳ፣ ሸራጫማ፣ ለመግዛት ተዘጋጁ።
144 ፍራሽ ቀረኝ…!
"…የነብርን ጭራ አይዙም። ከያዙም አይለቁም። ኢዩኤል በ1ሺ ዶላር 30 ፍራሽ ሲገዛልኝ፣ ወሮ ዓለም በ500 ዶላር 17 ፍራሽ ሲገዙልኝ ሌሎችም ተረባርበው አሁን የቀረህ 148 ፍራሽ ነው ይለኛል ሒሳቤ። 148 ፍራሽ ምን አላት?
"…ዐውቃለሁ ወቅቱ ወጪ የሚበዛበት ሰዓት ነው። የልጆች የትምህርት ቤት፣ እንቁጣጣሽ፣ መስቀል፣ ተደራርበው መጥተው ወገብ ቁምጥ በሚያደርግ ወጪ ሰንገው የሚይዙበት ወቅት ነው። ዐውቃለሁ። እኔም ባላየ ባልሰማ ማለፍ እችል ነበር። ግን አልቻልኩም።
"…ከሕፃናት ገላ ላይ በቁማቸው ትል ሲረግፍ እያየሁ እንዴት ልተኛ? የወለደ ያውቀዋል። በመሰረቱ አምሽቼ ተኝቼ አርፍጄ ነበር የምነሣው። አሁን ግን አምሽቼ እተኛለሁ ጥቂት ተኝቼ ወዲያው እነሣለሁ። ማርያምን እንቅልፍ አያስተኛም። አግኝታችሁ አትጡ። ስንትና ስንት ሀብት የነበራቸው ቤተሰቦች ያለ ፍራሽ አመድ ላይ ራሳቸውን ሲያገኙ አስባችሁታል? ምንም በማያውቁት ጉዳይ በአንዴ የደሀ ደሀ ሲሆኑ ምን እንደሚሳማቸው አስቡ። ነግ በእኔ ነው። አግኝቶ ከማጣት ይሰውራችሁ።
"…አሁንም ልክ እንደነ ኢዩኤል እንደነ ወሮ ዓለም እግዚአብሔር የባረካችሁ 1ሺ ዶላር፣ ወይም 500$ አልያም 100$ ዶላር ብትልኩላቸው 1ሺው 30 ፍራሽ፣ 500ው 17 ፍራሽ፣ 100 ዶላሩ 3 ፍራሽ አሳምሮ ይገዛላቸዋል።
"…አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። …በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም። ራእይ 14፥ 1-3
• ለተፈናቃዮቹ አሁን 144 ፍራሽ ይፈለጋል። 144… ማነህ የእግዚአብሔር ወዳጅ? አለሁ በል…!
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ለጎንደር የቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች የፍራሽ ጉዳይ ለማጠናቀቅ ከጫፍ መድረሴን ስገልጽላችሁ በደስታ ነው። 1200 ፍራሽ ለመግዛት ተነሥቼ አሁን የቀረኝ የ244 ፍራሽ መግዣ ብር ብቻ ነው። እሱን ለሟሟላት ደግሞ ጥቂት ሰዎች 1ሺ ዶላር ቢለግሱ 30 ፍራሽ፣ ጥቂት ሰዎችም 500 ዶላር ቢለግሱ ይቀላል። በቶሎም ያልቃል።
"…ለምሳሌ እስከአሁን ከፍተኛ ብር አውጥተው 210 ፍራሽ የገዙልኝ ሰዎች በቁጥር 6 ናቸው። 1ኛ.ዝናሽ ከቤሩት በ2ሺ$ 60 ፍራሽ ስትገዛልኝ፣ 2.ኃ/ጊዮርጊስ~ በ1ሺ$ 30 3.ኖህ በ1ሺ$ 30፣ 4.ግርማ በ1ሺ$~ 30፣ 5.ወለተ በ1ሺ$ 30፣ 6. ጆኒ በ1ሺ$~ 30 ናቸው። እስከ አሁን 144 ሺ ሰዎች በፍራሽ መግዛቱ ላይ ተሳትፈዋል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
"…ፍራሹን ከጨረስን ጨርሼ ሌሎቹን ቀሪ ለህፃናቱ ወደሚያስፈልገው የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ እዞርና እሱን ከጨረስኩ በኋላ ደግሞ በቀጥታ ወደ ደብረብርሃን፣ ወሎ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ትግራይ ወዳሉ ተፈናቃዮች ለበዓል መዋያ ሰንጋ ወደመግዛት ፊቴን አዞራለሁ።
"…በ5ቱ የጳጉሜ ዕለታት ተፈናቃዮች በአዲስ ዓመት እንኳ ለአንዲት ቀን ደስ ብሏቸው እንዲውሉ ለማድረግ እንዘጋጅ። እውነት ነው ዘመኑ ጨለማ ነው? አዎ ጨለማ ነው። ነገር ግን ጨለማውን ዓለም ብርሃን ሆነን ማብራትም ይቻለናል። “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።” ማቴ 5፥14 ነው የተባለነው። እኛ ብርሃን ብቻ አይደለንም።“እናንተ የምድር ጨው ናችሁም።” ማቴ 5፥13። ተብለናል። ዓልጫውን ዓለም የማጣፈጥ አቅምና ፀጋም የተሰጠው ለእኛ ነው።
"…ወገኔ እነዚህ ሕፃናት ያወደሟትን ኢትዮጵያ መልሰን የምንገነባትም እኛው ነን። መስጠትን ከወዲሁ እንለማመድ። በሉ ቀሪዋን ፍራሽ ወደማሟላቱ እንሸጋገር።
•1 ፍራሽ 3500 ብር ነው። 224 ፍራሽ እፈልጋለሁ።
“…ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ያጠፋና ይጨርስ ዘንድ ጥርሶቹ ሰይፍ መንጋጎቹም ካራ የሆኑ ትውልድ አለ።” ምሳ 30፥14
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ማዕተብና ሙሽሪት…
"…ጥሎብኝ ሀብት፣ ዝና፣ ዕውቅና ያላቸው ሰዎችን አንገት ማየት እወዳለሁ። አትሌቶቹን ሳይማ ደስታዬን አትጠይቁኝ። በእምነታቸው ምክንያት ማዕተብ የማያስሩትን አልቀወምም። ኦርቶዶክስ ነን ብለው ሌጣ የአንገት እርቃን የሚያሳዩትን ግን ኢደብሩኛል። ኃይለ ማርያም ተብሎ አንገቱ ሌጣ ሆኖ ሳይ እሳቀቃለሁ። ለሴቷም እንደዚያው። በተለይ ሙሽሮችን ሳይ ወንዱ በሸሚዝም ሊሸፈን ስለሚችል ዓይኔ የሴቷ ሙሽሪት አንገት ላይ ነው ፈጥኖ የሚያርፈው። ብዙ ሙሽሮች በፕሮቶኮሎቻቸው፣ በሚዜዎቻቸው ግፊት የሠርጋቸው ዕለት ማዕተባቸውን ይበጥሳሉ። ለፎቶ አያምርም ተብሎ ነው አሉ የሚበጠሰው ማዕተቡ። ወይ ደግሞ ሴቷ እምቢ ማዕተቤንማ በጥሼ አህዛብ አልመስልም ብላ በአቋሟ ከፀናች እንግዲያውስ ማዕተቡ በስሱ ይታሰር፣ አልያም በጡቶችሽ ጋር አልፎ እንብርትሽ ስር ይደበቅ ብለው ይሸፍኑታል። ለአንገት የተባለው ለእንብርት እንዲሆን ይፈረድበታል።
"…የሠርጓ ዕለት በማዕተቧ አፍራ የበጠሰች፣ የሰይፍ ዕለትማ ሳትጠየቅ ነው የምትበጥሰው። የሠርግ ፎቶ ቋሚ ነው። ፎቶው በታየ ቁጥር አብሮ የሚታይ ምስክር ነው። እንዴት በዚህ ሕዝብ ሁሉ የጓብቻው ተቋም ምሥረታ ዕለት በሚያይበት ዕለት ምስክር የሚሆነን ማዕተባችንን እንበጥሳለን? ክህደት ነው። ነውርም፣ ኃጢአትም ነው። ፕሮቶኮሏ በጥሺ ስትልሽ "አንጀትሽ ይበጠስ" ብለሽ ወሽመጧን በጥሺው። በእምነት ድርድር የለም።
"…አንዳንድ ሙሽሪቶች ማዕተብ ውበቴን ያጠፋዋል ሲሉ ይሰማሉ። በአንጻሩ ሜካፕ ተለቅልቀው ቫምፓየር፣ ቡልጉ፣ ጭራ ቀረሽ ሆነው ለመታየት አያፍሩም። በደህናው ጊዜ ቆንጅዬ፣ ኡሙንዱኖኢሹ ቦንቦሊኖ ውብ የሆነች ልጅ ሠርጓ ላይ ተገኝቼ በሳቅ ነው የፈረስኩት። የመድኃኔዓለም ያለህ። የተረበሸ ከተማ፣ የፈረሰ ሰፈር መስላ በሠርጓ ዕለት አስደነገጠችኝ። ሌሎች ደግሞ አሉ። ሳውቃት አይነ ግቡ ያልሆነች ለሠርጓ ዕለት ልዕልት ተናኘወረቅን መስላ የምትከሰት። እሷ እንኳ ይሆን። ሲነጋ ባሏ ማነሽ ካላላትና የትናንትናዋን ልጅ አምጫት ካላላት መብቷ ነው።
"…ብዙ ጊዜ ከጋብቻ በፊት ወንዶች የሚሸወዱትም በሜካፕ ጉዳይ ነው። ሴቶቹ 5 ሰዓት የፈጀ ዝግጅት አድርገው ቦይ ፍሬንዳቸው ጋር ይሄዳሉ ከዚያ ፍሬንድ ደስ ይለዋል። ከዚያ ይጋባሉ። ከዚያ ሜካፑ ይቀራል። ከዚያ ወንድየው ይፈረጥጣል፣ ያማግጣልም። ራሳችንን ሆነን እንገኝ። ከጋብቻ በፊት ልዕልት፣ ከጋብቻ በኋላ ድብኝት አንምሰል። ውበት ይጠበቅ። ግን አይብዛ ለማለት ነው። የሦስት ብር ማዕተብ ክር ማሰር እንቢ ብለሽ ስንት ሺ ብር ነው አሉ ሜካፑ? ውድ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። እሱን ተለቅልቆ እኛን ማዛግ ደግም አይደል። ደግሞ ሰደብከን በሉ አሏችሁ። መቼም እኔ ነገር ይገንብኛል።
"…ማዕተባችን በክር የታሰረ የእንጨት መስቀል ነው። የወርቅ፣ የብር ሀብሉ መዕተብ ሳይሆን የሀብታችሁ መግለጫ ነው። የክሩን ማዕተብ ሳደርግ የልብስ ክር ይይዝብኛል፣ ከመኝታዬም ላይ የብርድልብስ፣ የነጠላ፣ የጋቢም ጥጥ ይሰበስብብኛል በማለት የክር ማዕተብ ትተው ወርቅና ብር የሚያደርጉ አሉ። ይሄ ትክክል አይደለም። ማዕተብክን አድርግ። የአንተ ኢንቨስተርነት ሳይሆን የሦስት ብሯ ማዕተብ ክርህ ናት የምትፈለገው። እሷን አድርግ።
"…ኧረ ደግሞ እንዲህ የሚሉ አሉ? ለምንድነው ማዕተብ የማታስሪው፣ የማታስረው? ተብለው ሲጠየቁ "እኔ የማዕተብ ክር የማላስረው ቅጫም ስለሚይዝብኝ ነው። ተባይም ያፈራብኛል ይላሉ። ይህንና ይህን የመሳሰለ ምክንያት በመደርደር በክር የታሠረ ዕፀ መስቀል ማዕተብ ለማድረግ ምክንያት የሚሰጡ፣ የሚደረድሩም አሉ። የሹራብ ክር፣ ሻርፕና ልብስ ለብሰው እየሄዱ በአልርጂ ምክንያት አላስርም የሚሉም አሉ። ክር አንገቴ ላይ አያምርምብኝም፣ ኋላቀር የሆንኩ፣ ከዘመናዊነትም የተጣላሁ ፋራ ሰገጤ የሆንኩም ይመስለኛል የሚሉም ሜካፓም፣ የሜካፕ ቆንጅዬዎችም አሉ።
"…እናት ለቅጫም፣ ለቅማሉ መፍትሄው መታጠብ ነው። ቶሎ ቶሎ መታጠብ። አበክሮ የግል ንፅሕናን መጠበቅ ነው። የክር ማዕተብ አያምርብኝም ለሚሉም ይሄ እኮ የፋሽን ውድድር አይደለም። የቁንጅና መለኪያም አይደለም። ማዕተብ መሳርን ከሃብትና ከቁንጅና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። በጣም በቀላል ቁስ የከበረን ማዕተብ ማሰር ግድ ይላል። ሃብትን ለማሳየት ሠርጉ፣ የራት ግብዣው መች አነሰ? ማዕተብ ማሰር በቀላል ነው ግን የሚከበረው በክር ብቻ ሲታሰር ነው። ማዕተብ። በተለይ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ውድድር ላይ አንገታቸው ላይ ማዕተቡን ሳየው የሌለ ሙቀት፣ ኩራት፣ ደስታ ነው የሚሰማኝ።
"…እነ ኢቢኤስ ማዕተብ ያሰረ ጋዜጠኛ የማይቀጥሩት፣ አንዳንድ የፊልም ፕሮዲዩሰሮች አክተርስ ሲመርጡ ማዕተብ አስበጥሰው የሚመለምሉት፣ የሙስሊም ሂጃብ የለበሰችዋን ዜና አንባቢ ፈቅደው ማዕተብ ያሰረችዋን በጥሺ ያለበለዚያ ትባረሪያለሽ የሚሉት በማዕተቡ ላይ ያለውን ኃይል ስለሚያውቁት ብቻ ነው። ሌላ ምንም ምክንያት የለም። አንተም፣ አንቺም የትም ቢሆን የትም ማዕተብሽን እንዳትበጥስ፣ እንዳትበጥሺ።
ተዋሕዶ ሃይማኖቴ፣
የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ።
ማዕተቤን አልበጥስም፣
ትኖራለች ለዘላለም።
"…ሙሽሮች የታል ፎቶአችሁ…?
"ርእሰ አንቀጽ"
ጳጒሜን ፩ |~ የማዕተብ ቀን።
*~★★~*
"…ዛሬ ጳጒሜን ፩ ነው። እኔና የቴሌግራም ጓደኞቼ ይህን ቀን የማዕተብ ቀን ብለን ሰይመን በዕለቱ ማዕተባችንን እና ሰማእታቱን እያሰብን መዋል ከጀመርን አስር ዓመት ሊሞላን ጥቂት ዓመታት ይቀሩናል። ከእኛ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ በቅርቡ ደግሞ የዐማራ አክቲቪስቶችም ጳጉሜን ከፋፍለው ለየዕለቶቹም ስያሜ ሰጥተው ማክበር ከጀመሩ ቆይተዋል። እናም እኛም እንደ ቀዳሚነታችን በዛሬ ዕለት ጳጉሜን ፩ የማዕተብ ቀን ብለን በሰየምነው በዚህ ዕለት ስለ ማዕተባችን ሥናወጋ፣
የማዕተብ ቀንን እያሰብን፣ ደግሞም ማዕተባችንን እያጠበቅን፣ በጎ የበረከት ሥራም እየሠራን፣ እንዲሁም ማዕተባቸውን እንዳሰሩ፣ ሳይበጥሱ፣ ሳይክዱ በክብር የተሰዉ ሰማእታት ወንድም እህቶቻችንም እያሰብን፣ እየዘከርን እንውላለን። እናመሻለንም። በመሃል ደግሞ የቀበሮ ሜዳን የተፈናቃይ ልጆች ቦርሳ ስንገዛ፣ ጎዶሎአቸውንም ስንሞላ እንውላለን። በቀር ውሎአችን ስለማዕተባችን ብቻ በማውሳት ይሆናል። ፌስቡክ ስለማልጠቀም የፌስቡክን መንደር ሁናቴ አላውቅም እንጂ የቲጂ መንደራችን ግን በባለማዕተቦች ማዕተብ ነው አጥለቅልቀን የምንውለው።
"…ይህ በእንዲህ እንዳለ ርእሰ አንቀጹ ተነቦ ካለቀ ሰዓት ጀምሮ የፎቶ መላኪያ ሰንዱቁንም እከፍተዋለሁ። ስለዚህ እንደተለመደው ለዛሬ ባለማዕተቦች አንገታችሁ ላይ ያለውን ማዕተብ ፎቶ አንስታችሁ፣ መላክ፣ መለጠፍም ተፈቅዷል። ይቻላልም ማለት ነው።
እናም ወዳጄ ማዕተብክን፦
• ተማሪም ሁን አስተማሪ
• ወታደርም ሁን ወዛደር
• አርቲስትም ሁን ካራቲስት
• አትሌትም ሁን ፓይለት
• ሯጭም ሁን አሯሯጭ
• ወጣትም ሁን ሽማግሌ
• ወያላም ሁን ሹፌር
• ኢንቨስተርም ሁን መናጢ ደሀ
• አናጢም ሁን ግንበኛ
• ዶክተርም ሁን ኢንጂነር
• ጤነኛም ሁን በሽተኛ
• ቀጭንም ሁን ወፍራም
• ረጅምም ሁን አጭር
• ጠንካራም ሁን ደካማ
• ባለሥልጣንም ሁን ሥልጣን አልባ
• ማናጀርም ሁን ዘበኛ
• ዓረብ ሃገርም ሁን አውሮጳና አማሪካ
• ጨረቃም ላይ ሁን ውቅያኖስ ላይ
• ፋራም ሁን አራዳ
• አስመጪም ሁን ላኪ
• አምራችም ሁን ነጋዴ
• ቀዳሽም ሁን አራሽ፣ ተኳሽ
• ወንድም ሁን ሴትም ሁኚ
• ቆንጆም ሁኚ ፉንጋ
• ሞዴልም ሁኚ ወደል
"…ብቻ የሆናችሁትን ሁኑ፣ ያሻችሁም ቦታ ኑሩ። አንገታችሁ ሌጣ ባዶ አይሁን። ማዕተባችሁን እሰሩ፣ እሰሩ እንጂ እንዳትበጥሱ። እንዲህች ብላችሁ ለሆዳችሁ ብላችሁ እንዳታስበጥሱ። እንዲያውም የባሰ እንዳይፈታ፣ እንደይቆረጥ፣ እንዳይበጠስ አድርጋችሁ አጥብቃችሁ እሰሩት።
"…ማዕተባችን ውበታችን። የማንነታችን መግለጫም ነው። ክብራችን፣ ኩራታችንም ነው። አንገትህ ላይ ያለው ማዕተብህ አንተ ስለራስህ ሳትናገር ማንነትህን መስካሪ መታወቂያ ፓስፖርትህ በለው። እኔ ክርስቲያን ነኝ ብለህ መናገር ሳይጠበቅብህ ማዕተብህ ብቻ እሱ፣ እሷ፣ እነሱ የተዋሕዶ ልጆች ናቸው ብሎ ጮሆ ይናገርልሃል።
"…እናም ስማ ወዳጄ፥ ከሌሎች ለመመሳሰል ብለህ፣ እንደ ዘመኑ ዘመናዊ ሆኜ ልኑር ብለህ፣ ጓደኞቼን፣ ሥራዬን፣ ቢዝነሴን እንዳላጣ ብለህ፣ ብለሽ፣ እንጀራዬ እንዳይቀር፣ ሆዴም እንዳይጎል ብለህ፣ ብለሽም ማዕተብህን እንዳትበጥስ። እንዳትበጥሺ።
"…ባለማዕተብ ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ልጅ ሆኖ መወለድ እኮ መመረጥ ነው። መታደልም ነው። አይደለም እንዴ?
"…የእኔ ማዕተቤ ይኸው። የታል የእናንተ ማዕተብ? እስቲ አንገትህ ይታይ? አንገትሽም ይታይ?
ጳጉሜን ፩
የማዕተብ/የሰማእታት ቀን
"…ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።” ምሳ 6፣ 20-22
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
አሁን ደግሞ ወደ ልመናዬ ልመለስ…
"…በእንተ ስማ ለማርያም ስለ እመቤታችን ብላችሁ አንድ ቦርሳ በአንድ ሺብር፣ ከቻላችሁ 12 ቦርሳ በ100 ዶላር ግዙልኝ። በእናታችሁ፣ በአባታችሁ።
"…421 ደርሶ ነበር እኔ ወደ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን የሄድኩት። አሁን ተመልሻለሁ። አስቲ ቃል የተገባ መልእክት ካለ ለቅሜ ልንገራችሁ። ዳይ የሰማ ላልሰማ ነግሮ ዛሬ ቢያንስ ሺውን ቦርሳ ለህጻናቱ ገዝተን ደስታ እንፍጠርላቸው። በማርያም ተረባረቡ። እንረባረብ።
• የሚፈለገው ቦርሳ ብዛት 3300
• የአንዱ ዋጋ 1000 ብር
👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን ቦርሳ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ1000 አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ወይም ከእንቅልፌ ስነቃ የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና ትልኩላቸዋላችሁ።
• እንበርታ። በረከቱ አያምልጣችሁ።
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉YouTube
https://www.youtube.com/live/-tN3NRNsG5k?feature=shared
👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v5dr3ud--ethiobetesebmedia.html
👉 Facebook.com/ethiobeteseb
👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb
"…ሻሎም ! ሰላም !
ዘመቻ ቦርሳ ተጀምሯል
"…ቀን ጨልሞባቸው፣ ዕድል ለጊዜው ጠምሞባቸው፣ የፖለቲካ ሰለባ ሆነው እንደ ሌሎች ሕፃናት ተረጋግተው ከቤተሰብ ጋር ተረጋግተው መማር ባይችሉም እነዚህ ሕፃናት ከራብ ጋር እየታገሉም ቢሆን የግድ መማር አለባቸው። እኔ በትምህርት አምናለሁ።
"…ትል እንዳይበላቸው ካደረግን፣ የመኝታ ቁሳቁሳቸውን ካሟላን። ወለሉን ሲሚንቶ፣ የፕላስቲክ ምንጣፍም ካነጠፍንላቸው። የጤና መድኅናቸው በሊሊ በኩል ከተሟላላቸው እኛ ደግሞ እነዚህ ሕጻናት መማር አለባቸው ብለን የትምህርት መርጃ መሣሪያ ልናሟላላቸው ይገባል። አሁን ከቦርሳ ጀምረናል።
"…ከቦርሳ እጀምርና እሱን ተረባርበን ከዘጋነው በኋላ የኢትዮ ቤተሰብ ሳምንታዊ የዩቲዩብ ዝግጅታችን ካለቀ በኋላ ደግሞ ቀሪዎቹን ወደሟሟላት እንሄዳለን። ቦርሳው ከተገዛ የሚቀጥለው ቦርሳው ውስጥ የሚገባው የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ነው። ቅድሚያ ለቦርሳው። የአንዱ ቦርሳ ዋጋ 1ሺ የኢትዮጵያ ብር ነው። በ100 ዶላር 12 ቦርሳ፣ በ100 ፓውንድም 14 ቦርሳ፣ በ100 ዩሮም እንደዚያው ከ10 በላይ ቦርሳ መግዛት ይቻላል። ከተረባረብን በአጭር ሰዓት ውስጥ እንዘጋዋለን። እስከአሁን።
"…ሮሚ USA~60 ፀዳለ ማርያም ከUK~14 እሙዬ ከUSA~10 ቢኒያም ከGR~10 ዲን ዳኒ ከኢትዮጵያ~1 ሀ/ገብርኤል~1 ታምራት~1 በአጠቃላይ 97 ቦርሳ ችለዋል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እስከአሁን አንድም ከአቶ ወርቁ አይተነው በቀር አንድም ባለሀብት አልተሳተፈም። ዕሁድ ዕለት በመረጃ በቴቪ እኔ ከተናገርኩት በቀር በየትኛውም ሚዲያ አልተነገረም። ፌስቡክ ላይ የጻፈ አንድም ሰው አላየሁም። ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ ላይ ትንፍሽ ያለም የለም። በቴሌጌራም ገፄ ላይ ብቻ በምጽፈው መልእክት ነው በጥቂት አንባቢዎቼ ሥራው እየተሠራ ያለው። አንድም ጳጳስ፣ ካህንና ሼክ ሲሰጥም አላየሁም።
• ጀምሩ …
👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ታዲያ እኛ ደስስ ሲለን ሌላ የሚከፋው እንዳይኖር ጉረቤቶቻችን፣ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች በዓሉን አዲሱንም ዓመት በደስታ ይቀበሉ ዘንድ ያለንን እያካፈልን እንውላለን። በበዓሉ ዕለት ቢያንስ ቢያንስ ቅቤ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ዶሮና እንቁላል እናበረክትላቸዋለን። በዚህም ቀን ቢቻል ለሁለት ለሦስት መጠለያ ካምፖች፣ ካልቻልን ደግሞ ለአንድ መጠለያ ካምፕም ቢሆን ሰንጋዎች እንገዛለን። ለዚህም ተዘጋጁ።
"…በቅድሚያ ግን ዛሬ በጎንደር በቀበሮ ሜዳ ላይ ለተፈናቃይ ስደተኞች የጀመርነውን ልገሳ በድል እናጠናቅቃለን። ከዚያው ጎን ለጎን የደብረ ብርሃን፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በትግራይ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ የሚገኙ የሕጋዊ ተፈናቃይ ኮሚቴዎችን አገናኙኝ። ሰምታችኋል ጓደኞቼ ተዘጋጁ። ደግሞም እናደርገዋለን። አባቴ ይሙት እናደርገዋለን። ይሄን መልእክት የጻፍኩት ለጓደኞቼ መሆኑ ይሰመርበት። መንገደኞችን አይመለከትም። አከተመ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ድርጅቱ ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
"አሸበርቲው እና አስነቀልቲው"
ነሐሴ 30/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ እግዚአብሔርን የሚያመሰግነው የመንደሬ ነዋሪ ስለበዛ በፍጥነት 1ሺ ሰው በቶሎ ሞልቷል እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ቀጥሎ በቀጥታ ጊዜ ሳናጠፋ የምናልፈው ወደ "ርእሰ አንቀጻችን" ነው። የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ቅመም ናት፣ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ናት፣ የማንቂያ ደወልም ናት። የምሥራች ነጋሪም ናት አንቧት።
"…ከዚያ በፊት ግን በጀርመን ያላችሁ የሞባይል ካርዴን የምትሞሉ ወንድም እህቶች የስልክ ካርዴ ማለቁን ሳበስር በታላቅ ድፍረት ነው። የ20 ብርም ሆነ የ30 ብር የላይካ ካርድ ገዝታችሁ ቁጥሩን በኋትስአፕ ፎቶ አንስታች ትልኩልኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ። በጀርመን ለ lycamobile የሚሆን ካርድ እፈልጋለሁ። አሁን ራሱ ሰሞኑን ለምትሰሙት የምስራች ስደዋወል ጆሮአቸው ላይ ነው ጢው፣ ጢው፣ ጢው ብሎ የዘጋው። ሰምታችኋል ጀርመኖች። ፍጠኑ።
"…ሌላው ትናንት ከደቡብ አፍሪካ ስለ ደብተርና እስኪሪብቶ ያናገሩኝ ሰው እባክዎ ስልክዎን ሳልይዘው ስላመለጡኝ ከተቻልዎት ይደውሉልኝ። አርስዎ እስኪደውሉ እስክሪብቶና ደብተር ማሰባሰቡን ወደ ኋላ አዘገየዋለሁ።
"…መልካም አሁን ወደተለመደው ጥያቄአችን እንመለስ። ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ? ለማንበብ 15 ለአስተያየት 15 ደቂቃ እሰጥና በቀጥታ ወደ ዛሬው ዝግጅታችን እንገባለን።
• ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
95.ዳዊት~3
96.መላኩ~3
97.ሜሮን~3
98.ተ/ማርቆስ~3
99.ህይወት~3
100.ተ/ጻድቅ~3
101.ህብስት~3
102.ሳሚ~3
103.ፍሬህይወት~3
104.ዘሪሁን~3
105.ዳን~3
106.ታዴ~3
107.ሰላማዊት~3
108.ጌታ~3
109.ራሄል~3
110.ፈንታሁን~3
111.አደራጀው~3
112.ፍስሀ~3
113.ሚሚ~3
114.ናታን~3
115.ቴድ~3
116.ግዛቴ~3
117.ዘሪሁን~3
118.ፀዳለ ማርያም~3
119አንተነህ ካሣ~3
120.ዳኜ~3
121.ሮቤል~3
122.መላኩ~3
123.ገነት~3
124.አዲሱ~2
125.ልዩ~2
126.ሙሉሸዋ~2
127.ወ/ገብርኤል~2
128.ዮዲት~2
129.ቢኒ~2
130.ፀዳለ~2
131.ምንቱ~2
132.አገኘሁ~2
133.ክፍለ ኢየሱስ~2
134.ዳንኤል~2
135.መቅዲ~2
136.ፋንታሁን~2
137.ትእግስት~2
138.ወለተ ይሐንስ~2
139.ዳዊት~2
140.በሚካኤል~2
141.ክርስቲያን~2
142.የአምላክ~2
143.ሙሉቀን~2
144.ሱራፌል~2
145.ግዛቸው~2
146.ብርሃን~2
147.አብርሽ~2
148.ሀ/ወልድ~2
149.አዳሙ~ 2
150.ታምራት~2
151.ክህነት~ 2
152.ዳንኤል~2
153.ሳምሶን~2
154.ዳኜ~2
155.አፈወርቅ~2
156.ሰሎሞን~2
157.አንተነህ~2
158.ሰናይት~2
159.አስቤላ~1
160.ዝናሽ~1
161.ጌታቸው~1
162.ሀብቴ~1
163.ናቲ~1
164.ሜሪ~1
165.ሀብታሙ~1
166.አብነት~1
167.ብርቱካን~1
168.ዳንኤል~1
169.Ti~1
170.ዘሪሁን~1
171.ዳንኤል~1
172.ማርዮ~1
173.ሚልካ~1
174.ሀብታሙ~1
175.ሕይወት~1
176.ሀብታሙ~1
177.እሱባለው~1
178.ጸዳለ~1
179. ሄኖክ~1
1200 - 1200+ 5= 1205።
"…ወቅቱ ብዙ ወጪ የሚወጣበት ጊዜ ነው። ሁለት ዓበይት በዓላት እንቁጣጣሽ እና መስቀል። የልጆች የትምህርት ቤት ወጪ በራሱ ናላ የሚያዞርበት ወቅት ነው። በውጭ ያሉትም ቢሆኑ ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰብም የሚረዱበት ወቅት ነው። ይሄን ሁሉ ከባድ ኃላፊነት ተሸክማችሁ ለእነዚህ በሰቆቃ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች መድረሳችሁ በራሱ ያስመሰግናችኋል። በእውነት በጎዶሎአችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይሙላላችሁ። አግኝታችሁ አትጡ። የሰው ፊት አያሳያችሁ። ከነ ልጆቻችሁ ለመከራ አይዳርጋችሁ።
• የነገ ሰው ይበለን። ደኅና እደሩልኝ።
"…ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው አይደል?
"…አዎ አሁን ደግሞ ከጳጉሜ አንድ እስከ ጳጉሜ አምስት በሌላ የበረከት ተፈናቃዮችን ተስፋ ወደ መሙላት፣ ወገን እንዳላቸው ወደ ማሳየት ለመግባት ቢያንሥስ ለክርስቲያን ሙስሊሙ አዲስ ዐመትን ሰንጋ በማረድ፣ ከበቆሎና ከፉርኖ ዱቄት ምግብ አውጥተን እንጀራ፣ ያውም ለምለም እንጀራ፣ ሀጫ በረዶ የመሰለ ማኛ ጤፍ የጤፍ እንጀራ፣ ሲያሻቸው በቀይ ወጥ፣ ሲያሻቸው በአልጫ፣ አልያም ቁርጥ እየበሉ እንዲውሉ ለማድረግ ወደማደርገው ዘመቻ ከመንቀሳቀሴ በፊት የቀበሮ ሜዳን ጉዳይ ብንዘጋው ምን ይመስላችኋል። ሥራዎች ላይ ወደ
• የሚቀረው ለሕፃናቱ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ማቅረብ ብቻ ነው።
• እህሳ ሠራዊቶቼ ዝግጁ…?
33 ፍራሽ ቀረኝ…!
"…ጥንባታም አላለኝም። 😂😂😂 አይ እስኳድ። አሁን የዙም ሚቲንግ ላይ ዘመዴ የፌክ መግለጫውን አጋልጦ ጉድ አድርጎናል ብለው እየቦጨቁኝ ነው ስኳዶች። እኔም እየቀዳኋቸው ነው ገብቼ። 😂😂… ይሄ የምትሰሙት የትናንት የእነ አያሌው መንበር የቲክቶክ ውይይት ነው። ጎንደሬ ነን የሚሉት። እኔ ደግሞ የሀረርጌ ቆቱ ምርጥዬ የአራዳ ልጅ መራታ የምሥራቅ ሰው ነኝ የምለው። አያሌው መንበር ብአዴን ያውም የአገኘሁ ተሻገር ቱርጁማን ነው። በዚያ ላይ ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ጎንደር አጠቃላይ ፀረ ዐማራ። ስኳዶች በጎንደር ይምላሉ፣ በጎንደር ይሸልላሉ፣ በጎንደር ይዘፍናሉ፣ በጎንደር ስም ይዘርፋሉ። ቁጥራቸውም 15 አይሞላም። በስም ሁላ ይታወቃሉ። ሌባ ሁላ።
"…እኔ ቀበሮ ሜዳ ያሉትን ተፈናቃዮች ጓደኞቼ እንዲረዱ የጠየቅኩት የጎንደር ዐማራ ህፃናት በቁማቸው ትል ከሰውነታቸው ሲለቀም ስላየሁ እንቅልፍ አጥቼ ተጨንቄ ነው። ጎንደሬ ነኝ ባይዋ መማር አለባቸው ከነዚህ ትል ከሚያሰቃያቸው የጎንደር ዐማራ ሕፃናት ላይ 1 ሚልዮን ብር ስትሰርቃቸውማ አበድኩ። ጭራሽ ጎንደር ላይ ጴንጤ፣ አዋሳ ላይ እስላም ሆኖ አሁን እምነት የለሽ የሚባለው ጓደኛው ማማ ትሬሳ ብሎ ሲያሞካሻት ስኳዱ ፍፁም ጨካኝ፣ ፀረ ዐማራ መሆኑን አረጋገጥኩ። እናም በብዕሬና በአንደበቴ ልፋለማቸው ቆርጬ ተነሣሁ።
"…ጎንደሬ ነኝ ባዮቹ እነ ስኳድ እያዩ ዝም ያሏቸውን እኔ የሐረርጌው ቆቱ ዓለሙን አስተባብሬ ችግራቸውን ልቀርፍ ከጫፍ ስደርስ እነሱ ጎጃምና ጎንደርን ለማጣላት፣ ዘመዴና መረጃ ቲቪን ለመስደብ፣ እስክንደርን ለማንገሥ ለሚከፍቱት የጣና ቴሌቭዥን መዋጮ ተሻማብን፣ የሐሰት መግለጫውን በፋኖ ስም ብናወጣ አከሸፈብን ብለው ጓ እያሉብኝ ነው። ጭራሽ ከሱዳን የመጡ ስደተኞች ናቸው አላለም አያሎ መንባሩ…
• ጎበዝ 33 ፍራሽ ነው የቀረኝ። ዝጉልኝ።
198 ቀረኝ…!
• 2400 አንሶላ ተችሏል።
• 1200 ብርድልብስ ተችሏል።
• 1200 ፍራሽ እፈልጋለሁ። አሁን የሚቀረኝ 198 ፍራሽ ብቻ ነው።
• መሙላቱ እንደሁ አይቀር እንበርታ። አፈር ላይ እየተኙ ከሰውነታቸው ውስጥ ትል የሚራባባቸውን የጎንደር የቀበሮ ሜዳ ሕጻናት ለመታደግ የቻላችሁትን ሁሉ አድርጉ።
• 198 ፍራሽ ምን አላት? …አልሰሙም እንጂ ቢሰሙ አንድ የወልቃይት የሰሊጥ ነጋዴ ይሸፍናት ነበር። እነሱ አልሰሙም ተብሎ እኛ አናቋርጥም።
• እንበርታ…!
ግልፅ እኮ ነው… 😂
"…ፋሲካ ሲቃረብ በቤተ መንግሥት ያለው ኦነግ በአሩሲ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በጎንደር፣ በወለጋ ኦርቶዶክሳውያንን መርጦ አረደ። በናዝሬት አካባቢም ካህናቱን አረደ። ኦርቶዶክሱ በሙሉ ደነገጠ፣ ተንጫጫ፣ በጫካ ያለው ኦነግ ደግሞ ዝቋላ አየር ኃይሉ አጠገብ መነኮሳቱን አረደ። ጨፈጨፈ፣ ከታትፎም ገደላቸው። አዳሜ ጭጭ፣ ምጭጭ፣ ጮጋ አለች። የገዳ ሥርዓት እንዲህ ነው። ያርድሃል። ብልትህን ቆርጦ ግንባሩ ላይ ሰክቶ አስፈሪነቱን፣ ጭካኔውን ያሳይሃል። ይሄን ታዲያ እነ በላይ በቀለ ወያ፣ እነ ሀብታሙ አያሌው የዲሞክራሲ ሥርዓት ነው ብለው በቲክቶክ ይሰብኩሃል።
"…አሁን ደግሞ የቤተ መንግሥቱና የጫካው ኦነግ ተናብበው ለአዲስ ዓመት፣ ለእንቁጣጣሽ፣ ለቅዱስ ዮሐንስ፣ ለዘመን መለወጫ በተለይ ለኦርቶዶክሳውያኑ በዓላት ምንም ዓይነት የእርድ ከብት፣ ዶሮ፣ በግ፣ እንቁላል፣ ቅቤ፣ አይብ ሽንኩርት በኦሮሚያ ክልል አልፎ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ አድማ መጥራታቸው ተነሰምቷል። ባንክ ሁላ አይሠራም። ጉራጌም ለመስቀል ሀገሩ በደስታ እንዳይገባ ከወዲሁ የጫካው ኦነግ መመሪያ ተቀብሎ ክስታኔን ማረድ፣ ካህናትን ሁሉ መግደል ጀምሯል። የመስቀል በዓል ካለፈ በኋላ ግን ለእሬቻ ድምቀት ሲባል ሁሉ ነገር ይከፈታል። አይዟችሁ። ልመዱት። ቻሉት።
"…ለኢሬቻ የሚሄዱ ግን መብታቸው ነው ብሏል። የአሩሲው እስላም ኦሮሞ የሸዋ ሰላሌውን ኦርቶዶክስ ኦሮሞ አርዶ፣ አግቶ ዘርፎ፣ አብያተ ክርስቲያናቱን አውድሞ፣ ካህናትን መቅደስ ውስጥ አርዶ ጨርሷል። የሚሳበበው በሸኔ ነው። ኦነግ እስላማዊ ኦሮሚያን ለመፍጠር የሚታገል ድርጅት ነው። አቢይ እስላም ነው። ሶማሌ ላንድንና ኦሮሚያን በማዋሃድ አልያም ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና በመስጠት ለአዲሲቱ ኦሮሚያ ወደብ እየተበጀላት ነው። ምእራባውያኑና ኤምሬትም እየደከሙበት ነው።
"…የሚገርመው ከአዲስ አበባ አገልግሎት የሚያቀርበው የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪ ነው። ገበሬው ምርቱን አውጥቶ ካልሸጠ የሚጎዳው እሱ ነው። ቅጠል የሚሸጠው ኦሮሞ ሳይቀር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው። ከዐማራ እኩል ያደኸዩታል፣ ያርዱታል፣ ያወድሙታል። የኦሮቶዶክስ በዓላትን ጠብቆ መታረድ፣ መታገት፣ በዓሉን በድንጋጤ፣ በኀዘን ማሳለፍ ከተጀመረ 6 ዓመት ሞላን።
"…አዳሜ የኮሪደር ልማት እያልሽ ጨፍሪ፣ ከርስቶሽ ነቅሎ ለጅብ የሰጠሽን አረመኔ ልማታዊ መንግሥት እያልሽ አጨብጭቢ፣ ጊዮርጊስ፣ ቅድስተ ማርያም፣ ጎላ ሚካኤል፣ እስጢፋኖስ፣ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዘተ በዘዴ ያለ ምዕመናን አስቀርተው ባዶ አድርገዋቸው አረፉት። አቃጣሪ፣ አሽቋላች ካህናትና ዲያቆናትም ውኃ ሊበላቸው ነው። ጳጳሳቱና የቤተ ክህነቱ ሰዎች ብቻ ናቸው ደሞዝ የማይቋረጥባቸው። ቤተ ክርስቲያን ያለ ምዕመናን ባዶ ናት። ምንም ናት። እናም አሁን በስተመጨረሻ በዓታ፣ ግቢ ገብርኤል ያለ ምእመናን ይቀሩ ዘንድ የአጥቢያው ሕዝብ ድራሹ እንዲጠፋ ተፈርዶበታል። አብይ አሕመድ ሆይ በደንብ ቀጥቅጠው። ለብልበው በእሳት፣ ሱሪውን ዝቅ አድርገህ በሳማ በለው ይሄን አልሰማ ያለ ሕዝብ።
"…ኧረ እኔ አሁን ስለዚህ ጉዳይ ምን አገባኝ? እንዲሁ አላስችል እያለ እጄን ስለሚበላኝ ነው እንጂ ምን አገባኝ? ወዳጄ እኛ የጀመርነውን ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ለሚገኙ ስደተኛ ተፈናቃዮች ፍራሽ ለመግዛት የምናደርገውን ርብርብ እንቀጥላለን።
• ብዛት 1200 ፍራሽ
• የአንዱ ዋጋ 3500 ብር
👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የፍራሽ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ3500 አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ወይም ከእንቅልፌ ስነቃ የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና ትልኩላቸዋላችሁ።
• አመሰግናለሁ። መልካም የአድማ ሳምንት ይሁንላችሁ።