zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝ 68፥31 …“…በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።” መዝ 72፥9 …“አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” መዝ 74፥14

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ዳይ ወደ ቀደመው ኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን እንመለስ። ወደ ኢትዮጵያዊው ማንነታችን እንመለስ። ይሄ ዘመን የጣለውን ካዛንችስና ፒያሳ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ ለእኔም አምጪ ለአንቺም ጠጪ የሚለውን ዘመን የወለደው ነቀርሳ የሆነ “ካህን መሳይ” ክብረ ክህነት አዋራጅ እርሱን እርሱት። እርሱን ተዉት። እርሱን አትስሙት። የእኔ ካህን ይሄኛው ነው። ቀን እያረሰ ሰዓት ሲደርስ ከነ አፈሩ ቅዳሴ የሚገባው። እሱ ነው የእኔ ካህን። መተተኛ፣ አጋንንት ሳቢው እሱ የእኔም የእናንተም፣ የማንም ካህን አይደለም። ቤተ ክርስቲያኔም አታውቀውም። እሱ አጭበርባሪ ነው። ሌባ ነው። ነጣቂ ተኩላ ነው። ልብሱ ነጭ፣ አነጋገሩ ምላጭ፣ ከወደ ዕድሜው የሚቀጭ ነው። የእነ ፓስተር ዮናታን፣ የኢዩ ጩፋ፣ የእነ እስራኤል ዳንሳም ጓደኛ ነው። በፍጹም እኔን አይወክለኝም። ባለ ሽቶው፣ ባለ ድራፍት ባለ ውስኪው፣ ኮማሪት ቤት፣ ባለጌ ወንበር ይዞ እንደ ጋን ፣እንደበርሜል አምቡላውን ሲጋት፣ የጋለሞታ ጭን ሲያሻሽ የሚውለው እሱ ካህኔ አይደለም። ጠንቋይ ነው እሱ።

"…ወዳጄ የካህን ያለህ የሚባልበት ዘመን ይመጣል ከተባለው ከዚያ ዘመን አያድርሰን። ዛሬ የናቅከውን፣ ያቀለልከውን፣ የሰደብከውን፣ ያላከበርከውን እውነተኛ ካህን ነገ ድንጋይ ተሸክመህ፣ በእንብርክክ፣ በእንፉቅቅህ ብትሄድ አታገኘውም። መቃብሩ ላይ ሄደህ ይፍቱኝ አባቴ የምትልበት ዘመን ይመጣል። እስከዚያው ሰላም ለሃገራችን፣ ሰላም ለተዋሕዶአችን፣ ሰላም ለሁላችን። ክብር ለካህኔ ለነፍሴ አገልጋይ ሃይማኖቴን ላጸናልኝ አባቴ። ክብር ለአንተ። ክብር ለእናንተ። ቆይቼ እመለሳለሁ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ጸልይልኝ አባ አክሊለ ገብርኤል ብለህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከጥንት እስከዛሬ ከክብር፣ ልቆ ከመገኘት እና ከነጻነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው

የእኔ አስተያየት…

፩ኛ፦ ነው ብሎ ። አራት ነጥብ ቢኖረው።

፪ኛ፦ እንደ ሌላው ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ስታወራ በቁቤ በአፋን ላቲንና በእንግልጣር ቢጻፍ መልካም ነበር። ግን አልሆነም። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲባል ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያ ሲል ለከረመ አካል ከባድ ነው።

"…ጦርነት ሲመጣ በአማርኛ ብቻ መፎከር፣ መቀስቀስ፣ መዘመር አይነፋም። በኦሮሚኛም፣ በትግርኛም ቢፎከር ሸጋ ነው ለማለት ነው። የእንግሊዝኛው ቢቀር ቶሎ በቁቤም ጻፉት ለማለት ነው። ከመስከረም አንድ ውጪ ስለ ቦለጢቃ አላወራም እልና እጄን የሚበላኝ ነገርስ…?

"…በነገራችን ላይ ቦርሳውን 792 ቀርቶኛል። ሊያልቅ ነው ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የምሥራች ሪፖርት…!

"…የበዓል 5 ሰንጋ፣ 5 ፍየል ከነ ውኃ ለስላሳው በአቶ ወርቁ አይተነው ተችሎ፣ በወልደ ገብርኤል እና ትርሲተ ሚካኤል 5 ኩንታል ጤፍ፣ ቅቤው እና ማገዶው በጆኒ፣ ሽንኩርቱ፣ ማገዶው ሁሉ ተችሎ፣ ሽንኩርት፣ ጨው በርበሬው ሳይቀር ተችሎ፣ ድንኳን፣ ወንበሩ ሁሉ ተዘጋጅቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። የበዓል ዝግጅቱ በቀበሮ ሜዳ ጎንደር ጡፏል በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ካምፕ በተስፋና በሌላ የምሥራች ዜናዎችም ተሞልተዋል። የሚደንቀው የዐማራ የሞራል ከፍታው ነው። ተፈናቃዮቹ ለእነሱ ለምኜ ከገዛሁላቸው ሰንጋዎች መሐል አንድ በሬና አንድ ኩንታል ጤፉን በራሳቸው ፈቃድ ከተፈናቃይ ስደተኞቹ ካምፕ ውጪ ለሚገኙና በጎንደር ከተማ በቀበሌ ዘጠኝ ሸዋ ዳቦ አካባቢ ለሚገኙ የአእምሮ ውስነንት ያለባቸው "ካለን እናክፍል" ለሚባል ድርጅት ተረጂዎች ያላቸውን አካፍለዋል። የዐማራ ስብእነናው፣ የሞራል ከፍታው ይገርመኛል። ማካፈል ከአማኝነት ባሕሪ የሚመጣ ነው። በትምህርት ብቻም የሚገኝ ፀጋ አይደለም። ለመስጠት፣ ለማካፈል ከመስጠት፣ ከማካፈል ቅመም መሠራት አለብህ።

"…በቁማቸው ትል የፈላባቸውን ሕፃናት ትሉን ለማስወገድ መሬቱን ሊሾ፣ የፕላስቲክ ምንጣፍና ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ፍራሽና ብርድ ልብስ ያስፈልግ ነበር። መጀመሪያ ሁለትም ሦስትም ሆነው ቢለብሱት ተብሎ 1,200 ብርድ ልብስ ያስፈልግ ነበር እሱ ወዲያወረ ተችሏል። ከዚያም 2,400 አንሶላ ያስፈልግ ነበር እሱም በፍጥነት ተችሏል። 1,200 ፍራሽም ያስፈልግ ነበር እሱም ተችሏል። ፋብሪካ አነጋግሬአለሁ በጅምላ አከፋፋዮች ሒሳብ እንሸጥልሃለን ብለውኛል እግዚአብሔር ይመስገን። የሚቀረው ፍራሹን ለማንጠፍ ሲሚንቶ አሸዋና ጠጠር ያስፈልጋል። ምክንያቱም ፍራሹ አፈር ላይ ከተነጠፈ ተመልሶ ወዲያው ስለሚበላሽ ማለት ነው። እሱን መጨረሻ ላይ ጥቂት ሰዎች ገዝተው የሚፈጽሙት ተግባር ነው የሚሆነው። ደግሞም ቀላል ነው።

"…ከዚህ ሁሉ በመጨረሻ የሚያስፈልገው ሕፃናቱ ማይም ሆነው እንዳይቀሩ ትምህርት ቤት ማሠራት ነበር። እርሱን ደግሞ በሀገረ ስዊድን የምትኖር ወሮ ሊሊ የምትባል የእነ እቴጌ ምንትዋብ ጎንደሪት ልጅ ጀምራው በአቅም ማጠር ምክንያት ተቋርጦ ነበር። የተቋረጠውን የጎጃም ባለሀብቱ የበላይ ዘለቀ ልጅ አቶ ወርቁ አይተነው "ዘመዴ ትምህርት ቤቱን እኔ ሠርቼ አጠናቅቄ አስረክብህሃለሁ" ብሎ ነው በደስታ ያሰከረኝ። ለአቶ ወርቁ ጨምሮ ጨማምሮ እግዚአብሔር ይስጠው። የጎንደር ባለሀብቶች ዝምታ ግን አስገርሞኛል። የመድኃኔዓለም ያለህ። የትምህርት ቤቱ ነገር ከተያዘ ቀሪ የሚያስፈልገው ለተፈናቃይ ተማሪዎቹ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች ማሟላት ነው። እሱንም የእናንተን ኪስ ተማምኜ በድፍረት ጀምሬዋለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር አጠናቅቀዋለሁ።

"…እኔ ቅድሚያ የሰጠሁት ለቦርሳ ነው። ብዙዎች "ዘመዴ ለምን ግን ቦርሳው ቀደመ? ደብተርና እስኪሪብቶ ብታስቀድም አይሻልም ነበር" ብለውኝም ነበር። እኔም የመለስኩላቸው ደብተርና እስኪሪብቶውን አስቀድሜ ብገዛላቸው ሕፃናቱ ደብተርና እስክሪብቶውን የት ያስቀምጡታል? ላስቲክ ድንኳን ውስጥ አንድ ፍራሽ ላይ አራትና አምስት ሆነው እየተኙ ደብተሩን የት ያደርጉታል? በየቤታችሁ የሚያደክማችሁ የተዘርከረከውን የልጆች ደብተርና እስራስ መሰብሰብ አይደለም እንዴ? ቤት ላለው ነው መጀመሪያ ደብተር የሚገዛው። ለተፈናቃይ ሕፃናት መጀመሪያ መግዛት ቦርሳውን ነው። ምክንያቱም ቦርሳው ከተገዛ አገልግሎቱ ብዙ ነው። ቦርሳው በትምህርት ቤት የትምህርት መርጃ መሣሪያ መያዣ ቦርሳ ሆኖ ሲያገለግል በመኖሪያ ድንኳናቸው ደግሞ ደብተር፣ እርሳስ፣ እስኪሪብቶ ሁሉ ሸክፎ እንደ ሳጥን ሆኖ ይይዝላቸዋል። ለዚያ ነው ቦርሳ ይቅደም ያልኩት።

"…የሚያስፈልገው ቦርሳ አጠቃላይ 3,300 ነበር። እሱን ከትናንት ወዲያ ጀምሬው ትናንትን ትንፍሽ ሳልል ውዬ ዛሬ የደረሰበትን ልነግራችሁ ነኝ። እስከ አሁን ለ2,336 ሕፃናት ቦርሳ የሚገዙልኝ ደጋግ ቅን ልብ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን አግኝቻለሁ። በሚገርም ሆኔታ በዚህ የጎንደር ተፈናቃዮች ጉዳይ የእስላሞች ተሳትፎ ምንም ሆኖ ነው ያገኘሁት። እኔ ግን ክርስቲያን ብሆንም በመጠለያው ውስጥ ላሉት እስላሞች አንዲት ነገር አላጓድልም። ከሙክቱም ከሁሉም አንዲት ነገር አላቋርጥም። ገርሞኛል ግን ማርያምን። ሳልናገረው ባልፈው ይቆጨኝ ነበር። ደግሞም በደንብ እናገረዋለሁ። ፕሮቴስታንቶች የማውቃቸው ጥቂቶች ተካፍለዋል። ሌላው ግን ዝም ነው ያለው። ከእስላሞቹና ከፀረ ዐማሮቹ እኩል የጎንደር ባለሀብቶች ለገዛ ወገናቸው አንዲት ፍራሽ ለመግዛት አቅም፣ ወኔ ማጣታቸውም አሳፍሮኛል። ይሄ መረገም ነው። ማርያምን መረገም ነው። አንዳንዶችማ እንኳን ሊሰጡ ሌሎች ለሰጡት ፎቶዬን ዘቅዝቀው ሁላ ሲሰድቡኝ ነው የሚውሉት። አንድ ሚልዮን ብር ከእነዚህ ትል ከላያቸው ላይ ከሚፈልቀው ተፈናቃይ ቀርጥፋ የበላቸው የቲክቶከሯ መማር አለባቸው ጠበቃ ሁላ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። የቲክቶክን የዘረፋ ስልት ብትንትን አድርጌ ሰሞኑን በዚያው በቲክቶክ እመጣበታለሁ። እነ መማር አለባቸው እንዴት ከስኳድ ጋር ሆነው ይሄን የዋሕ ሕዝብ እንደሚግጡት አሳያችኋለሁ። ጠብቁኝ።

"…አሁን ከ3,300 የሚፈለግ ቦርሳ ውስጥ የ2,336 ቦርሳ ገዢ አግኝቼ አሁን የሚቀረኝ የ964 ሕፃናት ቦርሳ ብቻ ነው። እንደነገርኳችሁ ቦርሳው ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ ተማሪዎች ቤት ቤት በድንኳናቸው ውስጥ እንደ ሳጥን ትምህርት ቤት እንደ ቦርሳ የሚያገለግላቸው ቦርሳ ነው። ይሄንንም ከእናንተ ጋር እንደማሳካው ቅንጣት ታህል አልጠራጠርም። ቦርሳውን እንደጨረስኩ በቀጥታ የምዞረው ወደ ተማሪዎቹ ዩኒፎርም ማሟላት ነው። ቦርሳና ዩኒፎርም ከገዛንላቸው ደብተርና እርሳሱን ደግሞ አዳሜና ሔዋኔ ወደህ ሳይሆን በግድህ ታሟላታለህ። በግድህ አልኩህ። እና ላታሟላ ነው? ተኗኗርናታ…!

"…እኔ ዘመዴ በሕይወቴ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር እንዳለ ያረጋገጥኩበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። አሁን በዚህ በቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ጉዳይ። ይሄን ጉዳይ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክ፣ በፌስቡክ ሳልጮኸው፣ ኮሚቴ ሳላቋቁም። ታዋቂም፣ ዐዋቂም ነን የሚሉ ሰዎች ሳልለማመጥ፣ ሳልለምን፣ ሳላካትት። ስብሰባ፣ ውይይት ሳላደርግ፣ ደጅም ሳልጠና፣ አትሌት፣ አርቲስት፣ ሞዴል፣ ሯጭ፣ ነጋዴ ወዘተ ብዬ ሳልለማመጥ። እግዚአብሔርን ይዤ፣ ዘወትር ከአንደበቴ የማልለያትን ድንግል ወላዲተ አምላክ እመ ምሕረት እመቤቴ ማርያምን ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ ብዬ፣ ተማጽኜ፣ የቅዱሳኑና የእናንተን ጸሎት አጋዥ፣ ረዳት አድርጌ በቴሌግራም ጽሑፍ ብቻ በጥቂት ሰዎች ተሳትፎ የሺ ሰዎችን ችግር ሲቀረፍ ያየሁበት ጊዜ በመሆኑ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር እንዳለ አረጋግጫለሁ። ይሄን ድል፣ ስኬት እንደማየት ምን የሚያስደስት ነገር አለ? ምንም።

"…በቴሌግራም ገፄ ላይ 360 ሺ ሰዎች አሉ። ይገኛሉም። ነገር ግን ሁሌ እንደምለው ይሄ ሁሉ ሰው ማለት ወዳጄ ነው፣ በምናገረው፣ በማወራው ሁሉ የሚስማማ ነው ማለት አይደለም። መጽሐፍ እንዲል የተጠሩ ብዙዎች የሚገቡት ግን ጥቂቶች ናቸው። ሁል ጊዜ መጸለይ ከተመረጡ ምርጥ ጥቂቶች ውስጥ እንደሚደበን ነው። የተጠራ ብዙው ሳይሆን የተመረጠ ጥቂቱ ነው ተአምር የሚሠራው። ዓለም በወንጌል የተከደነው በ12 ሐዋርያት ነው። ከሙሉ እስራኤል ሕዝብ የተመረጡት 12 ሐዋርያት፣ 36 ቅዱሳት አንስት፣ 72 አርድዕት፣ በአጠቃላይ 120 ቤተሰብ ነው። ከሚልዮን እስራኤላዊ ተጨምቆ የተገኘው 120 ሰው ብቻ ነው። በእኔም ፔጅ ላይ…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132 ፥ 8-9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘመነ መንደር
ለበለፀገ ሀገር

ተመስገን ከጎጃም
ዝናሽም ከጎንደር
ወለዬው አቢቹ ከአባጅፋር ሰፈር
ከጎንደር ስኳዱ አገኘሁ ተሻገር

በአንደነት መከሩ
እየመሰከሩ ለዓለም ነገሩ
ለዘመነ ሀገር
የበለፀገ መንደር

• ጥቅሱን የጻፈው ግን መሰሪ ተንኮለኛ ነገር ነው። 😂😂😂 ወሎዬው ዳንኤል ከሆነ የጻፈው ቅኔው ይገባኛል። ወይ ቅኔ። ጉድ እኮ ነው። ሁሉም ደግሞ ሳቅ ብለው ነው የተነሱት።

የአሩሲዋን እመቤት
አዳነች አበቤንም ከፎቶው አላስገቧት

• እየገጠማችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"… ጳጉሜን ፪ ፦ የፊደል ገበታ ቀን…። "

• ኢትዮጵያዬ … እ…ም… ጷ  !!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጳጉሜን ፪፦ የፊደል ገበታ ቀን

"…ኩራታችን፣ መመኪያችን፣ በኢትዮጵያ ከቀሩን አንድ ከሚያደርጉን ተቋማት መካከል አንደኛው እና ዋነኛው ሀብታችን የኢትዮጵያ አየር መንገዳችንም ዕለቱን የፊደል ቀናችንን ሳያውቅ በስህተት፣ አውቀውም በድፍረት ሊሆን ይችላል ብቻ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እሱ ባወቀ ፊታቸውን ፀፍቶ አንደበታቸውንም ከፍቶ የፊደል ገበታ ቀናችንን ተቀላቅለው ባየን ጊዜ እጅጉን ደስስ አለን።

"…እባካችሁ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌስቡክ ገፅ በመሄድ በአስተያያት መስጫ ሰንዱቁ ውስጥ እናመሰግናለን በሉልኝ።

• ክብር ለአባቶቻችን…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጳጉሜን ፪፦ የፊደል ገበታ ቀን

• ላቲኖች… ባለቁቤዎች ሳትማረሩ እየተማራችሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እናመሰግናለን…🙏

"…ጳጉሜን ፪ ፦ የፊደል ገበታን ቀን አስበን ስንውል "ዕውቀት ይስፋ፣ ድንቊርና ይጥፋ፣ ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ በሚለው መሪ ቃል መፈክራቸው የሚታወቁትና የፊደል ገበታን በማዘጋጀት ለመላው ዓለም ያስተዋወቁት አብዬ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋንም መዘንጋት የለብንም።

• እናመሰግናለን አባታችን።

• ነፍስ ይማር።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እኔ ግን እላለሁ ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !
                                                
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "

"…ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት።+49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው። 

¶ ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••

ሻሎም !   ሰላም ! 

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው፥አስነቀልቲው
ጳጉሜን 2/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

ETHIOPIA | ~ ጷጉሜን የፊደል ገበታ ቀን።

"…ስለ ኢትዮጵያ ሲነሣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም አብራ ትነሣለች። ትወሳለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና ኢትዮጵያ ማለት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ የሆነው ሁሉ ምንጩ ቤተ ክርስቲያን ናት። የፊደል፣ የቋንቋ፣ የሥነ ጥበብ፣ የኪነ ሕንፃ፣ የዜማ፣ የሥነ ጽሑፍ ወዘተ መገኛ፣ መፈጠሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት።

"…ይህን መሰል ምስክርነት ሲሰጥ የሚያኮርፍ፣ የሚናደድ፣ የሚከፋ፣ የሚበሳጭ፣ አረፋ የሚደፍቅ ኢትዮጵያዊ የተፈጠረው ከዓድዋ ጦርነት ድል ማግሥት ነው። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ሲባል መበሳጨት የመጣውም ከዚሁ የዓድዋ ድል ማግሥት ነው። ከዓድዋ ድል ማግሥት ወዲህ እንደ ሀገር ኢትዮጵያ፣ እንደ ነገድ ዐማራ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና አማኞቿ ቂም ተይዞባቸው፣ ፖሊሲ ተቀርጾባቸው፣ በጀት ተመድቦባቸው መጥፋት አለባቸው ተብሎ ነው የተወሰነው። ምክንያቱም ደግሞ የዓድዋ ድል ነው።

"…የዓድዋ ድል የዓለምን የፖለቲካ ምሕዋር የቀየረ ድል ነው። ነጭ የሰው ዘር አይሸነፍም ተብሎ በሰዎች አዕምሮ ሁሉ እንዲቀረጽ የተደረገውን ማኅተም የፋቀ፣ የቀየረ ሁናቴ የተፈጠረው፣ ጥቁሮችም ነጮችን ማሸነፍ ይቻላል የሚለውን አስተሳሰብ ለመላው ዓለም ሕዝብ ያሳየ ድንቅ ተአምር የተፈጸመበት ነው የዓድዋ ድል። የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው። አንዱ ከአንዱ አይበልጥም። አንዱ አንዱን ጨፍልቆ መግዛት አይችልም። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠው ድንበር፣ ሀገር፣ ባህር፣ ወሰን አለው። በተሰጠው ሀገር ውስጥ ባሕሉን፣ ሃይማኖቱን እያከበረ፣ እየጠበቀ፣ እያበለፀገ መኖር አለበት የሚለውን አስተሳሰብ የያዘችዋ ኢትዮጵያ ይሄን የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት በጋሻና ጦር ብቻ በመግጠም ምርጥ የአውሮጳ ጀነራሎች በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ታግዘው የመሩትን ጦርነት በድል የተወጣችው ኢትዮጵያ ቂም የተያዘባትም ከዚያው የዓድዋ ድል ማግሥት ነው። አሃ ለካስ ጥቁርም ነጭን ማሸነፍ ይችላል እንዴ የሚል የአሸነፋኒትን ሥነ ልቦና በመላው ዓለም ለሚገኙ በቅኝ ግዛት ስር ይማቅቁ ለነበሩ ሕዝቦች የድል ጮራን የፈነጠቀ ነበር የዓድዋ ድል። ኢትዮጵያ ለሌሎች አብርታ እርሷ ግን ጥርስ ተነከሰባት። የጨለማውንም ዘመን ይኸው ብቻችንን እንጋፈጠው ጀመር።

"…ከዓድዋ ድል በኋላ የኢትዮጵያ የማሸነፏ ምስጢር ምንድነው ተብሎ ሲመረመር ከብዙ ምክንያቶች መሐል በዋነኝነት የተገኙት ሦስቱ ሆነው ተገኙ። ከነገድ ዐማራው፣ ከሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ከቋንቋ አማርኛ ቋንቋ፣ ከስም ኢትዮጵያ የሚለው ስም መጥፋት አለበት ተብሎ ተወሰነ። እነዚህን ለማጥፋት፣ ለማኮሰስ፣ ለማኮስመን ደግሞ በውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት እንደማይቻልም ተወሰነ። የከበረውን ማዕድን አልማዝን ብረት አይቆርጠውም ይባላል። አልማዝን የሚቆርጠው አልማዝ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። እንደዚሁ ኢትዮጵያን ለማቀጨጭ፣ ተዋሕዶንም ለማጥፋት፣ ዐማራንና አማርኛን ለማዳከም ብረት የሆነ አካል አይቻለውም። ስለዚህ በራስ ልጆች፣ በኢትዮጵያውያኑ እነዚህን ማጥፋት፣ ማዳከም ይቻላል ተብሎ ነው ተወስኖ ወደ ሥራ የተገባው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አሁን በዐማራ ክልል እየተደረገ ባለው ጦርነት እንኳ ረዘም ያለ ጊዜ መከላከያው ከፋኖ ጋር የሚዋጋው በውስጡ የዐማራ ተዋጊዎች ሲኖሩ ነው። ዐማራ ከሌለበት ጦሩ ጎመኔ ነው። ወዲያው ነው የሚታጨደው። ዐማራን የሚያሸንፈው ዐማራው ብቻ ነው። የዐማራ አድማ ብተና፣ የዐማራ ሚሊሻ፣ የዐማራ ፖሊስ፣ የዐማራ ፌደራል ፖሊስ፣ የዐማራ ተወላጅ ሆኖ መከላከያ ውስጥ ያለ ነው አሁን በመጠኑም ቢሆን ለዐማራ ፋኖ እንቅፋት የሆነው።


"…ለቤተ ክርስቲያንም እንዲሁ ያፈርሷት ዘንድ ነጭም፣ ጥቁርም ፓስተር እንዳይቻለው ስለሚታወቅ በራስ ልጅ ነው መናድ የተጀመረው። የፕሮቴስታንት እምነት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በቀጥታ ኢንቨስት የተደረገው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ላይ ነው። ከቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ምክንያቶች ያኮረፉ፣ ሆዳቸው የበለጠባቸው፣ በንጽሕና ጉድለት፣ በቀኖና ጥሰት የወጡ ልጆቿን፣ ሊቃውንቶቿን ይዘው ነው ውጊያ ጦርነት የገጠሟት። ከዓድዋ ድል በኋላ በዓድዋ ጦርነት ወቅት በወቅቱ የባንዳ ልጆችንና የልጅ ልጆችን በሙሉ ወደ ምዕራባዊው ዓለም በመውሰድ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ አማርኛ ትርክት እየጋቱ፣ እያጠጡ አሳደጉ። አሳደጉና አስመርቀው፣ አብቅተው መልሰው ወደ ኢትዮጵያ ላኩአቸው። አልማዝ ኢትዮጵያውያን ሀገር አንድ የሚያደርገውን የዘውድ ሥርዓት ገርስሰው ጣሉ። ዐማራ ጨቋኝ ነው ብለው ጭፍጨፋ ጀመሩ፣ እስከአሁንም ጭፍጨፋው ቀጥሏል። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶም የእነዚሁ ሰለባ ሆነች። አማርኛ ቋንቋም እንዲሁ እንደምታዩት ከኢትዮጵያውያን አእምሮ ለማጥፋት መከራ ፍዳቸውን ይበላሉ። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም የዚሁ ሰለባ ነው።

"…ቤተ ክርስቲያን ዘር፣ ቀለም፣ ሳትለይ እንደ ዶሮ ሁሉን ከክንፎቿ በታች አስጠልላ መያዟ ለዓድዋ ጦርነት ተሸናፊዎች የእግር እሳት ስለነበር አንዴ በአረቦቹ በኩል፣ ሌላ ጊዜ በሚሽነሪዎቹ በኩል በሁለቱም በኩል የገቡት ፍዳዋን እያሳዩአት ይገኛሉ። ዛሬ የወሀቢ እስላምም ሆነ የፕሮቴስታንቱ ዓለም በጋራ የሚዘምቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ ግዙፍና ጠንካራ መርከብ ሆና የሚገጩአትን ሁሉ እንደ ትናንሽ ማዕበሎች እየቆጠረች ተቋቁማ ከዚህ ደረሰች እንጂ እንደ ተነሣባት ወጀብ፣ እንደ ሱናሚ ማዕበሉ ቢሆን ኖሮ በተገለባበጠች፣ በተሰባበረች ነበር። ግን በደመ ክርስቶስ በዓለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነች ሰይጣን የፈለገ ቢደክም ሊያጠፋጥ አይቻለውም።

“…እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።” ማቴ 5፥14 ነው የተባልነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደመ ክርስቶስ ላይ የታነፀች ስለሆነ ሊያጠፏት አይቻላቸውም። እኛ ቃሉን ሰምተን ቃሉን የምንተገብር፣ እንደ ቃሉ የምንኖር ነን። እኛ "…ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል የተባልን ልባሞች ነነ። ቃሉን ሰምተን የማናደርግ ሰው እና ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን አይደለንም። ሃይማኖት ተብለው በምዕራቡ ዓለም በአሸዋ ላይ የታነጹት ሁሉ ዛሬ በእምነት የት እንደደረሱ እያየን ነው። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ። ማቴ 7፥ 24-27 ተብሎ በተነገረው መሠረት የምዕራቡ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዴት ዓይነት አወዳደቅ እንደወደቀች ሁሉም ምስክር ነው። በአሜሪካ የፕሮቴስታንት የካቶሊኮችን አብያተ ክርስቲያናት እየገዙ በመውረስ ላይ የሚገኙት ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። በአውሮጳ ታላላቅ ካቴድራሎች ሆቴልና የምሽት ክበብ ሆነው አይወድቁ አወዳደቅ ወድቀዋል። ያን የእነሱን ውድቀት ነው ወደ እኛ ለማምጣት የሚላላጡት። ሁሉም ግን መርከቧን ተላትመው የሚመለሱ ሚጢጢዬ ማዕበል ናቸው። መርከቢቷን ቢያነዋውጹአት ነው እንጂ አይሰባብሩአትም፣ አያሰምጡአትም። 👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ሕዝብም ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል፥ እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም እንሄዳለን።” ሚክ 4፥5 “…እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።” መዝ 33፥12 “…እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ።” መዝ 150፥6

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

1,097 ቦርሳ ቀረኝ።
በማርያም ጸልዩልኝ🙏

"…አዛኜን እመ አምላክን እሞላዋለሁ። ብዙዎቻችሁ እነ እገሌ፣ አትሌት እገሌና እገሊት፣ ዘፋኝ እገሌና እገሊት፣ እገሌ የተባለው ባለሀብት ለምን አይሰጡም ብላችሁ ስትጨነቁ አያለሁ። አርቲስቱም ቢሆን የእኔ ሀብት ሕዝቤ ነው የሚለው እኮ ካሴቱን መሸጥ ሲያምረው ነው። እንጂማ ዘፋኙ መጨረሻ ላይ እንዲሁ ተለምኖለት፣ በጎፈንድሚ አይደል የሚቀበረው። ለልጆቹ ሀብት ትቶ የሚሄድ ዘፋኝ ከስንት አንዱ እኮ ነው። አትጨቅጭቋቸው። ጎንደር ጎንደር እያለ ዘፍኖ ከበላ፣ የበላይ ልጅ ነኝ እያለ የዕለት ጉርሱን ከሞላ በቂው እኮ ነው። አትጨቅጭቁአቸው።

"…ባለሀብቱም ቢሆን ለአንድ ሰሀን ምሳ 10 ሚልዮን ብር ፎጭ፣ ሆጭ አድርጎ ሲያወጣ ዓይታችሁ አትደነቁ። ወዶ ነው ተገዶ እንጂ። ቪትሳም ሁላ እንዲህ ዓይነት የበረከት ሥራ ላይ አብዶ ነው የሚሳተፈው። አላበደም።

"…ቦሌ መድኃኔዓለምን፣ መርካቶ አውቶቡስ ተራ ቅዱስ ሚካኤልን የሠራው ዲታ አይደለም። ሀብታም ኢንቨስተር አይደለም። ደሀው ነው የሠራው። ምስኪኑ ነው ያሳነጸው። ቅጠል ሻጯ፣ ጠላ ጠምቃ፣ ልብስ አጥባ በላቧ ጽዳት ሠርታ ያመጣችው ናት የሠራቸው። ጭቃ ረግጦ፣ በመንግሥት ደሞዝ፣ ከሸቀጥ ሱቁ ከፍሎ፣ አረብ ሀገርና አሜሪካ ኩላሊታቸው እየፈረጠ ደም ተፍተው በላባቸው ያመጡ ምስኪኖች ናቸው ያሠሩት። ዛሬም የኢትዮጵያ ገዳማት እና አድባራት የሚረዱት በማዳም ቤት ቅመሞች፣ በካናዳ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮጳ በሚኖሩ ምስኪን ዝቅተኛ ገቢ ካላቸውና ጥቂት ሀብታቸውን እግዚአብሔር ከባረከላቸው ሰዎች ነው። ስለ እነሱ እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ዛሬ ቲክቶክ እገባ ነበር። ነገር ግን በቴሌግራም የጀመርኩትን በቴሌግራም ልጨርሰው ብዬ ነው መርሀ ግብሬን የዘለልኩት። በጽሑፍ ብቻ ድንግልን ይዤ አሳካዋለሁ።

• የተፈቀደላችሁ ስጡ። ቆይቼ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማችንን የክብር ቀን አስበን የምንውልበት ቀን ነው። ነገ የቴሌግራም መንደራችን በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማችን ተጥለቅልቆ ይውላል።

• ማርያምን ኢትዮጵያማ ታሸንፋለች…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:10 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ በሚገኙ ስደተኞች ካምፕ ነው የምናመሻው። በዚያም እያለቅስንም፣ እየሳቅንም አብረን እያወጋን እናመሻለን። 

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/sqGQeWriBOA

• Mereja TV: https://mereja.tv

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

ETHIOPIA |~ ጳጒሜን 3 የክብረ ክህነት ቀን

"…በዛሬው ርእሰ አንጻችን ደግሞ ካህናት አባቶቻችንን እና ክህነት እያነሳን፣ እያወደስን፣ እያመሰገንም እንውላለን። ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ካህናቱን ባወደሰበት፣ በመረቀበት ቃል ነው አበው ካህናትን እና ቅድስት ክህነታቸውን እያከበርን በነቢዩም ቃል እኛም እየመረቅናቸው የምንውለው። "…አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው። መዝ 132፥ 8-9 እንዲል እኛም እንላለን አሜን ጽድቅን ይልበሱ። ረጅም የአገልግሎት ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን እያልኩ ስለ ካህኔ መጻፍ እጀምራለሁ።

"…የእኔ ካህን ይህ ነው። ከላይ በምሥሉ ላይ ያያችሁት። አራሽ፣ ቀዳሽ፣ ተኳሽ። ለፍጥረት ዓለሙ ሰዎች ሰዎች በሥጋ እንዳይራቡ አርሶ የሚያበላ ጠንካራ ትርፍ አምራች ገበሬ ነው። ለነፍሳችን ምግብ፣ ለሰማያዊው ቤታችን የሚሆነን ምግበ ነፍስ ቃለ እግዚአብሔርን በልባችን የሚዘራም የነፍሳችን ስንቅ አምራች ነው። ሀገር፣ ድንበር እንዳይደፈር፣ ሃይማኖት እንዳይረክስ ደግሞ በጦርነቱ ጊዜ ተኳሽ፣ ቀንዳሽ ብሎም ሕይወቱን ለሀገሩ አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ የሚያልፍ ነው። የእኔ ካህን እንዲህ ነው። ሌጦ ቆዳ ፍቆ፣ ብራናውን ዳምጦ፣ ቀለም በጥብጦ፣ ብዕሩን ስሎ አእምሮውን ተጠቅሞ በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጽፎ፣ ደጉሶ፣ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ፣ አሳንጾ። የቀን የዘመን መቁጠሪያ ካላንደሩን አዘጋጅቶ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያኔን ከምስረታዋ ጀምሮ ያለ ዕረፍት፣ ያለድካም በታላቅ ትጋት አገልግሎ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስም ከወራሪ ጠላት፣ ከመናፍቃን ሠራዊትም ጠብቆ፣ ያቆየለኝ ካህኔ ነው።

"…ከህኔ የጥንቱ የጥዋቱ። ሲያወራ አነጋገሩ ጎልዳፋ፣ ሲታይ ልብሱ አዳፋ፣ ከወደ ዕድሜው ግን የገፋ፣ ዘለግ ያለ ረጅም ዓመታትን በጤና የሚኖር፣ ዕድሜ ጠግቦ የሚያርፈው እሱ ነው ካህኔ። ልብሱ፣ ጠረኑ፣ ዕጣን፣ ዕጣን የሚሸት፣ መዓዛው ከሩቅ የሚያውድ፣ ቃል ከአንደበቱ ሲያወጣ የሚፈውስ፣ ምክሩ የሚያሳርፍ፣ ቁጣው የሚመልስ፣ ተግሳፁ የሚያንፅ፣ በእኔና በእናንተ በማናችንም ላይ ቢዝነስ የማይሠራ፣ ረግጦ ያልገዛን፣ ያላዋረደን። አውቅልሃለሁ ብሎም ያላታለለን፣ ወደ ሕይወት መንገድ፣ ወደ ጽድቅ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ብቻ የመራኝ እሱ ነው የነፍሴ ንጉሥ ካህኔ የነፍሴ አገልጋይ።

"…ከህጻንነቱ ወራት ጀምሮ እውቀትን ሽቶ፣ ፈልጎ፣ ከእናት አባቱ ከቤተሰብ ጉያ ወጥቶ፣ ከዘመድ አዝማድ፣ ከቀዬው፣ ከሰፈሩ፣ ከደብር ከአድባሩ፣ ከመንደሩም ርቆ፣ ከተራበ ውሻ ጋር ታግሎ፣ በረሃ ለበረሃ ተንከራትቶ፣ ጥፍሮቹ በእንቅፋት፣ ሰውነቱ በእሾህ፣ በጋሬጣ ተቀዳዶ፣ ተበሳስቶ፣ ከትግራይ ጎጃም፣ ከጎጃም ጎንደር፣ ከጎንደር ወሎ፣ ከወሎ ሸዋ ቆላና ደጋ ወይና ደጋ በረሃም ወርዶ። ወለጋ፣ አሩሲ ጅማ፣ ጋምቤላ አፋር፣ ኦጋዴን ጎዴ ድረስ በባዶ እግሩ፣ በባዶ ሆዱም ተንከራቶ፣ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ የዕውቀት፣ የእውነት፣ የጽድቅ ሻማዋ እንደበራ እንዲቀጥል ያቆየልኝ እሱ ነው ካህኔ። አመሰግነዋለሁ።

"…በየሊቃውንቱ ደደጃፍ ተንከራቶ፣ ዕወቀት ምድራዊ፣ ዕውቀት ሰማያዊውን ሸምቶ፣ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ቀኖናና ዶግማዋ ሳይሸራረፍ ለትውልድ እንዲተላለፉ ያደረገልኝ ታማኝ አገልጋይ ካህኔ ነው። ከዋዜማ ቁመት የጀመረ፣ ሰዓታት ማኅሌቱን የሚያሳምር፣ በጸሎተ ኪዳኑ የሚፈውስ፣ ቀድሶ የሚያቆርበኝ፣ ወንጌል የሚያስተምረኝ፣ የሚባርከኝ፣ የሚቀድሰኝ፣ እያወቅኩ በድፍረት፣ ሳላውቅ በስህተት የሠራሁትን ኃጢአት እግዚአብሔር ይፍታህ ብሎ ከኃጢአት ማሰሪያ በተሰጠው ሥልጣን የሚፈታኝ፣ እሱ ነው ካህኔ፣ የልተነካካ ድንግል፣ ያላፈረሰ፣ ያልረከሰ፣ ያልተልከሰከሰ፣ በየመጠጥ ቤቱ፣ ቡና ቤቱ ራሱን ያልሰየመ፣ ታማኝ የሚስቱ ባል ቅዱሱ አገልጋይ እሱ ነው ካህኔ። ጸልይልኝ አባ።

"…ቢታመም፣ ቢርበው፣ ቢጠማው፣ ቢታረዝ፣ ቢያጣ ቢነጣ፣ ቢገረጣ ቅር የማይለው። ደሞዝ ባይከፈለው የማይከፋው። ለምኖ አዳሪው። በ40 ቀኔ ያጠመቀኝ፣ የሥላሴ ልጅነትን የሰጠኝ፣ ሥጋ ወልደ አምላክን ያቆረበኝ፣ ደግሞም በእጆቹ የባረከኝ፣ የቀደሰኝ፣ ለእኔ አማላጄ ከፈጣሪዬም መገናኛ ድልድዬ እሱ ነው ሳወድሰው የምውለው የምታዩት ካህኔ ነው። ለተዋሕዶ ሃይማኖቴ መቀጠል፣ ከዚህም ለመድረሷ በብርቱ የታገለ፣ በነፍሱ ተወራርዶ ፀበ አጋንንትን ታግሶ፣ ግርማ ሌሊቱ ሳያስፈራው ራብና ጥምም ሳይበግረው፣ ዝቅ ብሎ ባት፣ ከፍ ብሎ አንገት የሚቆርጡ የአላውያን፣ የአህዛብ ሰይፍ ሳያስቆመው፣ ሳይሰቅቀው፣ ዘመን የዘመን እኩሌታውን በሙሉ በትምህርት አሳልፎ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኔን ያቆየልኝ ታማኝና ለዘመናት ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታ ያለብኝ ለእኔ ፕሮፌሰሬ፣ ደብተራዬ ዶክተሬ፣ ሳይንቲስቴ አባቴ፣ ካህኔ ይህ ነው።

"…የእኔ ካህን ነጋዴ አይደለም። ቃሉን አይሸቅጠም። እግር አያረዝምም። የባንክ ዕዳ አይሰርዝም። የፈውስ አገልግሎት ብሎ ድራማ አይሠራም። ስልክ ቁጥር እና የፌስቡክ ፕሮፋይል በቃሉ አጥንቶ በመናገር ተአምር ሠራሁ አይልም። ውኃ ወደ ወተት፣ ውኃ ወደ ደም ለወጥኩ ብሎ አያጭበረብረኝም። ካህኔ የነፍሴ አገልጋይ አባቴ በምድር ያለ ሰማያውያን መላእክትን የሚመሰስ ፀጋን የተሞላ አስደናቂ ፍጥረት ነው። ስታቅፉት፣ ትከሻውን ስትሰሙት ጠረኑ ዕጣን፣ መዓዛው የሚያውድ ነው ነው የእኔ አባት የእኔ ካህን።

"…ፀበል ሲያዩት ውኃ እንዲመስል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶቼም ሲያዩዋቸው ሰው ይመስላሉ። ፀበል ውኃ ቢመስልም የእግዚአብሔር መንፈስ የተመላ ነውና ሲፈውሰን ይኖራል። ካህኔም እንደዚያው ነው። ምድራዊ መልአክ እኮ ነው የእኔ ካህን። የሥላሴን ልጅነት እንዳገኝ ያጠምቀኛል፣ ስታመም ያጠምቀኛል፣ ያስተምረኛል፣ በኀዜኔ ያጽናናኛል፣ ስጣላ፣ ስቀያየም ያስታርቀኛል። ሲጨንቀኝ ያረጋጋኛል፣ ተስፋ እኮ ነው ካህን። በደስታዬ እለት በሠርጌ ዕለት ይባርከኛል፣ ስታመም ጸልዮ፣ ስሞት እያለቀሰ ፈትቶ ይቀብረኛል። ይሄነው የእኔ ካህን።

"…ካህኔ እንደኛ ሰው ቢመስልም በምድር ላይ ያለ ሰማያዊ መልአክ ነው። ከፍጥረት ዓለሙ ሁሉ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ የተሰጠው ብቸኛው ፍጥረት ካህኔ ብቻ ነው። ማንንም የማሰርና የመፍታት ሙሉ ሰማያዊ ሥልጣን የተሰጠው ለእኔ ለካህኔ ለተዋሕዶ ወታደር ለእርሱ ብቻ ነው። በየዕለቱ የማይደክም፣ ለዘመናት በቤተ መቅደሱ ተገኝቶ ያለ እረፍት ዕለት ዕለት ሲዘምር፣ ሲያዜም፣ ጸናጽሉን እየጸነጸለ፣ በመቋሚያው እያሸበሸበ፣ ከበሮ እየመታ፣ እየቀደሰ፣ እያወደሰ፣ ወንጌል ፈትፍቶ ሲያጎርሰኝ የኖረው ከህኔ ነው። እናም ዛሬ አንተ፣ አንቺ፣ እናንተ ሁላችሁ ካህኔን አክብሩልኝ። የራቃችሁ በስልክ ደውላችሁ ተባረኩ። በቅርብ ያላችሁ በአካል ቀርባችሁ ተባረኩ። ለበዓሉ፣ ለመጪው አዲስ ዓመት፣ ለዘመን መለወጫው ለቅዱስ ዮሐንስ እንኳን አደረሰህ በሉት። ይሄን በፎቶ ከተቻለ በቪድዮም ማየት እፈልጋለሁ። አድርጉት።👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ጨምቄ ያገኘሁት ነፍስ ያለው ሰው ቁጥሩን መጨረሻ ላይ እነግራችኋለሁ። የሚበዙቱ ግን መስጠት እየፈለጉ እጅ ያጠራቸው እንዳሉ መዘንጋት የለበትም።

"…በመጨረሻም ዛሬ እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ ባለን ሰዓት ስናወጋ የምናመሸው ስለ ክብረ ካህነት፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው። በዚህ መሐል እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ጓደኞቼ ቀሪዋን 964 ቦርሳ መግዣ ትሰጡኝ ዘንድም ድንጋይ ተሸክሜ እለምናችኋለሁ። 100 $ 12 ቦርሳ ነው የሚገዛው፣ 200$ 24፣ 300$ 36 ቦርሳ ይገዛል። ገንዘቡ ሓላፊ ጠፊ ነው። ያላችሁ ሰዎች በተለይ 500 ም 1ሺም አርጋችሁ ብትሰጡልኝ በቀላሉ ተዘጋ ማለት ነው። ይሄን ከማሟላት ደግሞ 80 ሰዎች 100$ ቢያወጡ፣ 40 ደጋጎች 200$ ዶላር ቢያወጡ፣ 26 ሰዎች 300$ ዶላር ቢሰጡ 964 ቱም ቦርሳ ተዘጋ ማለት ነው። ዶላር ዶላር የምለው የእኔ ዕዳ ተሸካሚ የሚበዛው ከወደ አሜሪካ ስለሆነ ብቻ ነው። ካናዳ ሳስቷል። አውስትራሊያማ ጭራሽ የለም። ከአውሮጳ በአሁኑ እንግሊዞች እጃቸው ሲፈታ አይቻለሁ። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድ፣ ስዊድን ወዘተ ከጥቂቶች በቀር የዳር ተመልካች ይበዛዋል። ፍታ እጅህን፣ ተረባረብ፣ እርዳ። ቦርሳውን እስከማታ ጨርሼ ማታ ዩኒፎርሙን እጀምራለሁ። የነከስኩትን ሳላደማ የምለቀው ሞቼ ነው ቆሜ። እህዕ…

"…1 ቦርሳ 1ሺ የኢትዮጵያ ብር ነው። 100 ዶላር 12 ቦርሳ ይገዛል፣ 100 ፓውንድ 14 ቦርሳ ይገዛል፣ 100 ዩሮ ስንት እንደሚገዛ እናንተው ድረሱበት። ማነው አግተው ላጡ የጎንደር ሕፃናት አንድ ቦርሳ በመግዛት ተስፋቸውን የሚያለመልም? አግኝታችሁ ከማጣት ፈጣሪ ይሰውራችሁ። እደግመዋለሁ፦

• ብዛት 964 ፍራሽ
• የአንዱ ዋጋ 1ሺ ብር

👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የፍራሽ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ1ሺ ብር አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ቃላችሁን እመዘግብና የስደተኞቹን ሕጋዊ የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና ትልኩላቸዋላችሁ። በRIA የምትልኩ ለዐማራ ሲሆን እምቢ ስለሚሏችሁ፣ ሀገር ቤት ላለ ቤተሰብ ልካችሁ ቤተሰብ ሊያስገባላችሁ ይችላል።

• አመሰግናለሁ። መልካም የክብረ ክህነት ቀን ይሁንላችሁ።

• ዘመቻ ቦርሳ 964 ይፋፋም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አመስጋኝ ቁጥር ሞልቷል። ቀጥሎ እንደተለመደው እንሄድ የነበረው ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው። ዛሬ ግን ርእሰ አንቀጻችን ከአጭር የምሥራች በኋላ ቢቀርብ ብዬ ተመኘሁ። ተመኘሁናም የምሥራቹን ልነግራችሁ ወሰንኩ።

"…ድንኳን ውስጥ እንደ ሳጥን፣ ትምህርት ቤት ደግሞ እንደ ቦርሳ ያገለግላቸው ዘንድ ለ3300 ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ጥርሴን ነክሼ ማሰባሰብ የጀመርኩት ቦርሳ አሁን ስንት እንደቀረኝ ልነግራችሁ ነኝ። ትናንት ትንፍሽ ሳልል ውዬ ዛሬ እስቲ ልንገራችሁ ብዬ ነው። በዙያውም ተረባርበን ቀሪውን እናሟላለንም ብዬ ተስፋ ስለማደርግም ጭምር እሱንበላስቀድም ብዬ ነው።

• እስቲ ገምቱ ስንት ቦርሳ የቀረኝ የመስላችኋል? አንድ 100 ሰው እንደገመተ የምሥራቹን እለጥፍላችኋለሁ።

• 1…2…3…ገምቱ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዓይኔ መቼም አያርፍ እኔ ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የሞተችው የሕፃን ፌቨን እናት መስላኝ እንደፈረደብኝ ከምኔው ጥቁር ልብስ አወለቀች፣ ባለፈው ቤት ተሠርቶ ተሰጥቷት ነበር። አሁን ደግሞ ሁለተኛ ቤት ልትቀበል ነው ወይ? ፍትሕ ፍትሕ ብላ የጮኸችው ቤት እስኪሰጣት ደረስ ነው ወይ ብዬ ከምር ልጠይቅ ነበር። እሷ መስላኝ ማለት ነው።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ስለቀበሮ ሜዳ ሕፃናት የቦርሳ ጉዳይ አልተነፈስኩም። ምክንያቱም ደስስ ስላለኝ። ነገ ምሽት ከነጭ ነጯን ከመረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ በፊት ዩኒፎርማቸውን እጀምርና ከዚያ እስራስ፣ ደብተር እና እስኪሪብቶውን መለመን እጀምራለሁ። የነገ ሰው ይበለን።

"…ነገ ጳጉሜን ፫ የክብረ ክህነት ቀን ነው። ካህኔ ነገ ሲከብር ይውላል። በዚያውም ቅዱስ ሩፋኤል ነው። በዚያ ላይ የካህኑ መልከ ጸዴቅም በዓል ስናከብር እንውላለን።

"…ለንስሀ አባቶቻችሁ እየደወላችሁ ፍቅራቸውን ግለጹላቸው።

• ሻሎም…! ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከሱማሌና ግብፅ የወረራ ዜና በፊት ነው…!😂

ኦነግ በአማርኛ መፈክር ሲያሰማ…
እስቲ አንደዜ አብራቹ በሉ…! 😂😂😂

• ካሲልጣን ኢናባራሌን…!✊✊✊
• አቢዪ ሌባ ኖ…!✊
• ነፍጠኛ ሌባ ኖ…! ✊
• የፈረስ ሌባ ኖ…! ✊
• ያታሪክ ሌባ ኖ…! ✊
• የሃገር ሌባ ኖ…! ✊
• የማሬት ሌባ ኖ…! ✊
• ናፍጣኛ ላማኝ ኖ…! ✊
• ለሊመና ማጣቹ፣ ዛሬ ሃገራቺን ቲፋለማላቹ…!✊
• ወዳቹም፣ ጠላቹም፣ ከኦሮሚያ ቲዋጣላቹ…!✊
• ወደ ጎንዶር ትገባላቹ…! ✊
• ወዳ ቆማጤ ቲመለሳላቹ…! ✊
• ከአሂያቹ እናባሪራቻለን…!
• አንዲም ንቢረት ይዛቹ መውጣት አይችሉም…!
• ከሃገራቺን አንድ ሳንቲም፣ ያላቆማጤ፣ ያለ አሂያ ምንም ዪዛቹ አቶጡም…!✊
• ለራሳቹ ቲዋጣላቹ…!✊
• በሰላም ሃጋራቺን ሊቀቁ…! ✊
• ኢኛ ኦሮሞ ወዳጂ ናን ቢሌን ኢናንቴን አስገባናቹ፣ ኢናንቴን ኢያበላን፣ ኢያጠጣን፣ ኦሮሞ ሲፈናቄል፣ ቲደሰታላቹ፣ ኦሮሞ ሲሞት ቲጨፋራላቹ፣ ኢንደዚ አብሯቺን መኖር አንቺሊም…!✊
• ኢናንቴ ለራሳቹ የሚትሞቱበት ጉድጓድ ኢየቆፈራቹ ኖ…! ✊
• ሁላቹም ወደ አሰር ሺ/አስር ሚሌየን ኦሮሚያ ዊስጢ ናቹ። ኦሮሞን ማጥቃት አትቺሉም።


• ብልጽግና ወዳ ጎንዶር…!✊
• ብልጽግና ወዳ ጎንዶር…!✊
• አዳ ቢሊሲማ ኦሮሞ አቃፊ ኖ…!😂😂

• ኡፍ ማርያምን ደከመኝ…! እናንተ ቀጥሉ…! አግዟቸው። አይ ኦሮሞ አለ አራጁ አቢይ…!

"…በነገራችን ላይ ይሄን ነገር ደጋግማችሁ ስሙት። ሆድ ያባውን ሰልፍ ያወጣዋል የሚባል አባባል አለ። ይሄ እንደዋዛ ስቃችሁ ብቻ የምታልፉት ነገር አይደለም። ደጋግማችሁ ስሙት።

"…አይ አማርኛ ነፍስ ነገር እኮ ነሽ…! እምጷ አማርኛዬ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የአባ ካሤን ልጅ ያለ አይመስለኝም።

"…ኧረ ምን አገባኝ ደግሞ። ወደ ጀመርነው ወደ ፊደል ገበታ ቀናችን እንመለስ። ይሄ ዓይኔ ገና ብዙ ጣጣ ሳያመጣብኝ አይቀርም።

• ክብር ብራና ዳምጠው፣ ቆዳ፣ ሌጦ ፍቀው፣ ቀለም በጥብጠው የራሳችንን ፊደል ፈጥረው ቀርጸውም ላቆዩሉን አባቶቻችን።

የዘመነ ካሤ መንደር
ለበለፀገ ሀገር

"…ብለህ አንብብ አሉህ ደግሞ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጳጉሜን ፪፦ የፊደል ገበታ ቀን።

"…የተከበረው የኢትዮጵያ ፊደል አማርኛ ቋንቋችን በሀገረ እስራኤል የምርጫ ቅስቀሳ ሁላ ይደረግበታል።

• የተገረማችሁበትን ፎቶ ላኩልኝማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጳጉሜን ፪፦ የፊደል ገበታ ቀን

"…የፎቶ መላኪያ ሰንዱቁን ከፍተን እንቀውጠው አይደል? ፊደል በፊደል ነው የምናደርገው።

• 1…2…3…ጀምሩ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

• ጷግሜን ፪ የፊደል ገበታ ቀን

• ርእሰ አንቀጻችን በብዙ ሺ ሰዎች መነበቡን የቴሌግራም ካምፓኒያችን በሰሌዳ ላይ ሪፖርቱ እየነገረን ነው። ከርእሰ አንቀጽ ንባብ ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ከእኔ እናንተ ወደምትሞሉበት እና በጎደለው ሓሳቤ ላይ እናንተ የተሟላ ሓሳባችሁን ስትፈልጉ ሳሳ፣ ወፈር፣ ቀጠን፣ ስትፈልጉ ጮክ ብላችሁ ግን በጨዋ ደንብ አስተያየት ወደምትሰጡበት መድረክ ነው።

"…በርእሰ አንቀጼ ላይ በጻፍኩት ሓሳብ ቅር የሚለው ካለም በጨዋ ደንብ ለዓይን በማይቀፍ ትችት ሊያገጣብረኝ ይችላል። ፈቅጄለታለሁ። በጻፍኩት ርእሰ አንቀጽ ግን ቅንጣት ታህል አይሰቀጥጠኝም። ሃላስ።

"…የሚያስጠላው አንብቦ ዝም ማለቱ ነው። አትፍሩ፣ አትሸማቀቁ። አትሽኮርመሙም። የራሴ የምትሉትን የሚሰማችሁን ሓሳብ ተንፍሱ። ወይ Like አታደርጉ፣ ወይ ሓሳብ አትሰጡ ዝም ብሎ በቤቴ ውስጥ መጎለት፣ ያለ ሥራ መርመጥመጥም ያስጠላል። ኢደብራልም። በፊደልህ አትፈር፣ በማንነትህም አትሸማቀቅ። የዓረብ ዲቃላና የዓረብ ገረድ፣ የምዕራባውያኑ አሽከሮች በተውሶ ዕቃ ደፍረው ደረታቸውን ነፍተው ሲፎልሉ አንተ ባለቤቱ ለምን ዝም ትላለህ። ተንፍስ፣ ሓሳብ ስጥ። ወዳጅም ጠላትም ያንብበው። እንደ ኢድሪስ ሁኑ። ተመልከት ኢዲሪስ የሚሰጠውን ኮመንት።

"…እኔን ለማመስገን ብለህ ብዕርህን አታንሣ፣ ቦታ አታጣብ። ዘመዴ ብራቮ፣ አንበሳ፣ ድኩላ፣ ዝሆን ቀበሮ ብለህ በዱርና የዱር እንስሳ ማዕረግ ስታመሰግነኝ አትገኝ። ሞራል እንዲሆነኝ አንተም ከእኔ ምስጋና ውጪ አእምሮህን ተጠቅመህ የሆነ ነገር በል። የጋን ውስጥ መብራት አትሁን። ዐዋቂዎች ፈርተው ዝም ስላሉ እኮ ነው ስሙን አስተካክሎ ለመጻፍ ሦሰዓት ከዐርባ ሰባት ደቂቃ ከሠላሳ ሁለት ሰከንድ የሚፈጅባቸው እነ ዮኒ ማኛ ሲበጠረቁብን የሚውሉት። ጻፍ። ነግሬሃለሁ።

"…1…2…3…✍✍✍ ጀምሩ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እርግጥ ነው አሁን አሁን እንደሚታየው ለቤርቤረሰቦች ሁሉ ባንዲራ ሰፍተው ሰጥተዋል። ቤርቤረሰቦችም ከኢትዮጵያ በላይ የሀገረንት ስሜት እንዲሰማቸው ማገዶ እየፈጁባቸው ነው። በክልሎች የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዳይታይ እየተደረገ ነው። በፕሮቴስታንት ቸርች መድረክ ላይ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ የእስራኤል፣ የእንግሊዝ፣ የጃፓን፣ የጀርመን ወዘተ ባንዲራ በክብር ይሰቀላል። ካላመናችሁ ፈልጋችሁ እዩ። በስብሰባ ማዕከላት ውስጥ ሰንደቅ ዓላማችን መታየት ካቆመች 6 ዓመት አለፈው። በኦሮሚያ በትግራይ ጭራሽ የለም። በኦሮሚያ ከቤተ ክርስቲያን ጎልላት፣ ከካህናት ጥንግድርብ፣ ከአባቶች ጃኖ፣ ከእናቶች መቀነት፣ ነጠላ፣ የአንገት ልብስ ላይ ሳይቀር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተፍቋል፣ ተሰብስቦ ተቋጥሏል። ይሄን ያደረገችው አሜሪካ ወይ እንግሊዝ ቢሆን ብረቶች ናቸው አልማዝ እኛን መቁረጥ አይችሉም ነበር። ነገር ግን በአልማዞቹ ኢትዮጵያውያን በኩል መጡ። መጡና አልማዙ አልማዙን ይቆርጠው ጀመር።

"…አማርኛን፣ የግዕዝ ፊደልን ለማጥፋት ላቲንን ጀርመን ሀገር ቀርጸው ለኦሮሞ ሰጡት። ሲዳማም፣ ሌሎችም አማርኛን እንዳይጠቀሙ እያደረጉ ለማጥፋት መከራ ፍዳቸውን እየበሉ ነው። በአማርኛ ዕቃ ሊገዛህ የሚመጣውን ዕቃ እንዳትሸጥለት የሚል ደንቆሮ ማይም ፓስተር በቀለ ገርባ በአማርኛ መመሪያ ሲሰጥ ያየነውም በዚሁ ዘመን ነው። ዐማራ አታግቡ፣ እኛ የኦሮሞ ሴቶች እያለን ለምን ዐማራ ታገባላችሁ። በቶሎ ፍቱና አግቡን ያሉት የፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ የፓስተር በቀለ ገርባና የሀጂ ጃዋር መሀመዱ ኦፌኮ የሴቶች ሊግ ነው። በእኛ አካባቢ ክርስቲያን ቀና ብሎ ከሄደ አንገቱን በሜንጫ ነው። ኦሮሞና እስላም አንድ ነው። ኦሮሞ ሆኖ እስላም ካልሆነ በለው ተብሎ የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ የታጨዱት እዚያው ኦሮሚያ ውስጥ ነው። እናም አልማዙ አልማዙን ለመቁረጥ አየተላላጠ ነው።

"…አሁን በትግራይ የቀረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ላይ ያለ ኢትዮጵያ ስም እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ናቸውው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ታላቅ ስም የአሜሪካው ሰላይ አባ ሰራቂ ብርሃን፣ የእንግሊዙ ወንድኛ አዳሪ አቶ አሮን ቀይረውታል። "የትግራይ ኦርቶዶክስ ብለው ቀይረው የዓድዋ ድል ተሸናፊዎችን ፕሮጀክት አሳልጠዋል። አሁን ግን በትግራይ መዓቱ እያንዣበበ ስለሆነ የኢትዮጵያ ጠላቶችን፣ የቤተ ክርስቲያን አፍራሾችን ሊያደቃቸው ይችላል። ህወሓት ለሁለት መከፈሏ የእውነት ከሆነ ኢትዮጵያ ትድናለች። ኦሮሞም ትግሬን አይቶ ነው የኦሮሞ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካልሆንኩ ብሎ ዊኒጥ ዊኒጥ የሚለው።

"…እናት ዓለማችን፣ ሽልማት ጌጣችን መኩሪያ መመኪያያችን የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዓድዋ ድል ተሸናፊዎች እና በዓድዋ ድል ተሸናፊ ባንዳ የልጅ ልጆች አማካኝነት እንዲህ የምትታመስበት ምክንያት ግልጽ ነው። ቤተ ክርስቲያን ታቦት ተሸክማ ሕዝብ አስተባብራ ዘምታ የወራሪን አከርካሪ ስለሰበረች ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት…

• ነፃነት ከነክብሩ፥
• ሙሉ ትምህርት፥
• ሕግን ከነ ሥርዓቱ፥
• አንድነት ከነጀግንነቱ፥
• ኪነ ጥበብ በየዓይነቱ፥
• ሥነ ጥበብ በየመልኩ፥
• ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርስ፥
• ሰንደቅ ዓላማን ከነ ክብሩ፥
• ስም ከነምልክቱ ከነ ትርጉሙ፥
• አገር ከነ ዳርድንበሩ፣ ከነፍቅሩ፥
• ዜማን ከነመሳሪያው ከነምልክቱ፥
• ሥነ ጽሑፍ ከነጠባዩ፣ ከነሙያው፥
• እምነት/ ሃይማኖትን ከነፍልስፍናው፥
• ፍጹም ቋንቋን ከነፊደሉ፥ ከነቁጥሩ ከነትውፊቱ፦

… ፈጥራ፣ አዘጋጅታና አሳድጋ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ያበረከተች የምሥራቅ አፍሪካ አብሪ ኮከብ ናት። እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እናቴ የኮሎኒያልዝምን ቅስም የሰበረች የጥቁር ህዝብ ሁላ በኩራት፣ በጀግንነት፣ በወኔ፣ ቀና ብሎ መሄድን ያሳየች የይቻላል መንፈስም ናት።

"…የኢትዮጵያ ጌጥ፣ የሀበሻ ሁሉ መኩሪያ ነው ሀ ሁ የፊደል ገበታችን። ክብርና ምስጋና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይድረሳትና ልጆቿ አበው ብራና ፍቀው፣ ቀለም በጥብጠው፣ አእምሮአቸውን ተጠቅመው ይኸው እኛንም በዓለም ላይ የራሳቸው ፊደል ካላቸው ሀገራት በቀዳሚው ተርታ ላይ እንድንመደብ አደርገው አስቀመጠውናል። ያለ ድጋፍ በራሱ የሚቆም ፊደል ባለቤቶች አድርገው አንደኛ አደረጉን። ክብር ለአባቶቻችን።

"…ሀበሻ ሆኖ በኢትዮጵያ ፊደል የማይጠቀምና የማይኮራ ሰው የለም። ሀበሻ ሆኖ በአማርኛና በግዕዝ ፊደላት የሚሸማቀቅ፣ የሚያፍር፣ የሚንበጣረር ካለ እሱ ሶዬ ወይ የባንዳ የልጅ ልጅ ነው ወይም ደግሞ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ የጠላት ቅጥረኛ ነው። እኛ ግን በፊደላችን እንኮራለን። ከፍከፍም እንለን።

"…ብዙዎች የፊደል ገበታችንን አሳምረው ይጠቀሙበታል። የአማርኛ ቋንቋን ለመቃወም ራሱኑ የአማርኛ ቋንቋን አሳምረው የሚጠቀሙ ጥቂቶች አይደሉም። እየጠሉት የፊደል ገበታውን የሚጠቀሙ ሰዎች ደግሞ በጣም ያስቁኛል ያሳዝኑኛልም። ስንት ዓይነት ሰው አለ መሰላችሁ ቆንጅዬ የዐማራ ሚስት በአማርኛ ጀንጅኖ፣ አማላጅ በአማርኛ ልኮ አግብቶ ትዳር መሥርቶ፣ ዐማራዋን ቆንጆ እሷን ታቅፎ እየተኛ፣ ቆንጅዬ ቆንጅዬ ልጆችን አከታትሎ በላይ በላዪ አስወልዶ እየኖረ ሲነጋለት ጠዋት ሚድያ ላይ ቀርቦ ዐማራንና አማርኛን ሲሳደብ፣ ሲራገም የሚውል ስንት ዓይነት ሰው አለ መሰላችሁ።

"…እነ ጃዋር መሀመድ ሀብታምና ታዋቂ የሆኑት አማርኛን አቀላጥፈው በመናገራቸው ነው። በአማርኛ ቅኔ በመዝረፋቸው ነው። እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል፣ እነ ግርማ ጉተማ፣ እነ ፀጋዬ አራርሳ አማርኛን ከዐማራው በላይ አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው። በዚህም ደግሞ ተጠቀሙ እንጂ አልተጎዱም። ነገር ግን ሰዎቹ በተፈጥሮአቸው ምቀኞች ስለሆኑ፣ የበታቸኝነት ስለሚያጠቃቸው የኦሮሞው ህዝብ አማርኛን አውቆና ተምሮ በመላ ሀገሪቱ ተዘዋውሮ በፈለገው የሥራ መስክ ተቀጥሮ እንዳይበላ በካቴና አስረውታል። እነሱ ግን እንዳሻቸው ሆነው ይኖራሉ።

"…ተወደደም ተጠላም አማርኛ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ የሥራ ቋንቋ ይሆናል። ላቲንን ለላቲኖቹ  እንመልስና ክብር ለሚገባው ለኢትዮጵያው የፊደል ገበታ ክብርን እንስጥ።

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ወ ው ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ
ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ
ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ

"…ይሄ ነው የእኔ ፊደል። ያልተሠረቀ፣ ያልተበረዘ። የማንነቴ መገለጫ። ወዳጄ የሰው ወርቅ እኮ አያደምቅ። መኩራትስ በራስ ነው። ማን እንደራስ ወርቅ? ክብር ለአባቶቻችን። ከብር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን። እኔ ዘመዴም በፊደል ገበታ ቀን የቀደመ መሃላዬን ዛሬም አስታውሼ እደግመዋለሁ።👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…1ሺው አመስጋኝ ገና በጠዋቱ ሞልቶ አልፋል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…በመቀጠል ደግሞ ዛሬ ጳጉሜን ፪ ቀን የፊደል ገበታ ቀንን በተመለከተ የሚጮህ ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችኋለሁ። ከርእሰ አንቀጹ በኋላ ዛሬ የተቀበል የግጥም መርሀ ግብርም ስላለን ግጥም እየገጠምን ፈታ፣ ዘና እያልን እንውላለን። የጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ ወገኖቼም የህፃናቱ የቦርሳ መግዢያ ከፍ እያለልኝ ነው። 3300 ቦርሳ ለመሙላት ከግማሽ በላይ አልፌአለሁ። በመሐል በመሐል ስለ ተፈናቃዮቹ ልመናዬን እየቀጠልኩ የዛሬውን መርሀ ግብራችንን በደማቅ ሁኔታ እናሳልፋለን።

"…ወዳጅም ጠላትም ይደነግጥ ዘንድ ዝግጁ ናችሁ ስል እናንተም ጮክ እያላችሁ "አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ" በማለት ድብልቅልቁን አውጡልኝ።

• ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመርሀ ግብር ለውጥ

"…የእስከ ዛሬው የወርሀ ጳጉሜን የቀናት ስያሜአችን እንደሚከተለው የነበረ ሲሆን በተደጋጋሚ ይሰጥ የነበረውን አስተያየት በቸልተኝነትና በስንፍና፣ በመዘንጋትም ምክንያት ሳላርመው ቀርቻለሁ። ከነገ ጳጉሜን ሁለት ጀምሮ ግን መርሀ ግብራችንን እናስተካክለዋለን። የእስከዛሬው፦

፩፥ ጳጉሜን ፩ የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜን ፪ የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜን ፫ የፊደል ገበታ ቀን።
፬፥ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማና
፭፥ ጳጉሜን ፭ የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን፣ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያ እና ለአቅመ ደካሞች የስጦታ ቀን ብለን ነበር የምናከብረው። አሁን ግን ከነገ ጀምሮ በየዓመቱ ጳጉሜን ፪ የምናከብረውን የክብረ ክህነት ቀን ወደ ጳጉሜን ፫ እንወስደዋለን። ጳጉሜን ፫ ከቅዱስ ሩፋኤል በዓል በተጨማሪ የካህኑ መልከ ጼዴቅ መታሰቢያ በዓል ዕለት ነው። ስለዚህ ጳጉሜ ፪ እና ፫ ቀናትን አዘዋውረን በሊቀ ካህኑ መልከጼዴቅ የመታሰቢያ ዕለት ስለ ክብረ ክህነት ብንዘክር የሰመረ ይሆናል። "የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር… እንዲል።" የሚል ምክረ ሓሳብ በማግኘቴ ከነገ ጀምሮ ይኸው ተግባራዊ ይሆናል።

፩፥ ጳጉሜን ፩ የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜን ፪ የፊደል ገበታ ቀን።
፫፥ ጳጉሜን ፫ የክብረ ክህነት ቀን።
፬፥ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማና
፭፥ ጳጉሜን ፭ የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን፣ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያ እና ለአቅመ ደካሞች የስጦታ ቀን

"…ነገ በመላው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን የአማርኛ ፊደል ያያችሁበት ቦታ ሁሉ ፎቶ አንስታችሁ ትልካላችሁ። ታዲያ የሕፃናቱን ቦርሳ እንዳትረሱ። አደራ።

• 1 ቦርሳ 1ሺ ብር ነው።
• 100$ 12 ቦርሳ ይገዛልኛል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የብዙዎች መልእክት ነው።

"…ዘመዴ RIA በሚባለው የገንዘብ መላኪያ በኩል ወደ ተፈናቃዮቹ የባንክ አካውንት ገንዘብ ለማስገባት ሄደን የገንዘብ መላኪያ ድርጅቱ አይቻልም እያለን ነው። ምክንያት ስንጠይቅም ወደእዚህ ሒሳብ ቁጥር ማስገባት የሚቻለው የገንዘብ መጠን ጣሪያው ደርሷል። ከዚህ በላይ መላክ አይቻልም እያለን ነው። ከአንድም ሁለት ቦታ ሄደን ሲስተሙ ዘግቶታል ነው የሚሉን ምን ተሻለን እያሉኝ ነው?

"…በእኔ በኩል ሪያ እርያ ሆኖ ካስቸገረ መፍትሔው ሌላ አማራጭ የገንዘብ መላኪያዎችን መጠቀም ነው። ሀገር ቤት ለዘመድ ልኮ ከባንክ ወደ ባንክ ማስተላለፍም አንዱ አማራጭ ነው። ብዙዎችም እንደዚያ እያደረጉ ነው። Ria ሄጵ ስላለ ግን የተፈናቃይ ሕፃናቱ ተስፋ አይጨልምም። እንረባረባለን። እናሟላላቸዋለን።

"…የቦርሳ ግዢው ቀጥሏል። አሁን እንኳ ሦስት ሰዎች ማለትም አቶ MG~ 35 ቦርሳ፣ ገብረ ሥላሴ~24 ቦርሳ፣ ፍቅርተ ማርያም ከለንደን~ 10 ቦርሳ ገዝተውልኛል።

• እንበርታ…!

"…50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ለ50 ሰው ግን ጌጡ ነው። ይሄን ሳላሳካ ሌላ ሥራ አልጀምርም። አከተመ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel