"ርእሰ አንቀጽ"
"…ዛሬ መስከረም 2 ነው። ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ዓመተ ምሕረቱም 2017 ዓም። በዚህ ዓመትም ፈጣሪ በሰጠን ፀጋ እና ዕድሜ ተጠቅመን በተሰጠን መክሊት ልክ በአንዱ አስር እጥፍ ትርፍ እያተረፍን እንኖርበት ዘንድ፣ ልክ እንደ አምና ካቻምናው ዘንድሮም ተሰፍሮ፣ ተለክቶ፣ ተሰፍሮና ተቆጥሮ ለሁላችንም እኩል በእኩል ያለምንም አድልኦ 365 ቀናት ተሰጥተውናል። እሊህ 365 ቀናትን እንደ ዓመታዊ በጀት ቁጠሩት። በጀቱን በአግባቡ ተጠቅሞ፣ አትራፊ ሆኖ መገኘት የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው።
"…እንግዲህ ለዘንድሮ ዓመት ከተያዘልን 365 ቀናት ውስጥ አንደኛውን ቀን ትናንት ቆርጥመን በልተን ዘሬ ሁለተኛውን ሃም፣ አኝ አድርገን እየበላን ቀኑን ልናገባድድ ነው። ነገ ደግሞ ሌላኛው መስከረም 3 የተባለ እልል ያለ ቀን ታጥቦ፣ ታጥኖና ተቀሽሮ ሰንዳ ሰንዳ እያለ አፍጥጦ እየጠበቀን ነው። ሦስት አትሉልኝም። ከተሰጠን ዓመታዊ በጀት ላይ 2 ቀን ቆርጥመን ስንበላ የሚቀረን 363 ቀን ይሆናል። ሁለቱን ቀን በኪሣራ በዋዛ ፈዛዛ አሳልፈን ከሆነና ነገም እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ የምናሳልፋት ከሆነ አለቀለን ማለት ነው። ኪሣራ በኪሣራ ነው የምንሆነው። እናም በጀታችን እንዴት እና በምን አግባብ እንጠቀም በሚለው ላይ ነው አተኩረን መንቀሳቀስ ያለብን።
"…እኔና ባለቤቴ በሀገር ቤት ሳለን ጳጉሜን ላይ አንድ ልማድ ነበረን። ዓመታዊ ዕቅድ የማውጣት ልማድ። የባንክ ደብተራችንን እናመጣና ከፊታችን ዘርግተን እናስቀምጠን ቀሪ ሒሳባችንን እናየዋለን። ቀጥሎ ከዚያ ተነሥተን የምናደርገው ነገር ቢኖር የሥራ ዕቅድ ማውጣት ነው። መስከረም ግሸን ላይ፣ ህዳር አክሱም፣ ታህሳስ ቁልቢና ቅዱስ ላሊበላ፣ ር ጥምቀት ላይ፣ ለአቢይ ጾም፣ ለትንሣኤ ወዘተ እያልን የሥራ ዕቅድ እናወጣለን። አውጥተን ስናበቃ እንዴት አድርገን ነው ሌት ተቀን ሠርተን እዚህ አካውንት ላይ በሚታየው የገንዘብ መጠን ላይ ተጨማሪ ገንዘብ የምናመጣው ብለን እንወያያለን። ባለፈው ዓመት እንተገብረዋለን ብለን ከስንፍና፣ ከዳተኝነት ደግሞም ጊዜም፣ አቅምም ከማጣት የተነሳ ያልፈጸምናቸውንም ከልሰን እንገመግማለን፣ ከዚያ በዚህኛው ዓመት ውጤታማ ለመሆን ወጥረን እንሠራለን።
"…ሁላችሁም እያያችሁኝ በግሸን ማርያም፣ ቁልቢ ገብርኤል፣ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ሞንታርቦ ይዤ፣ አውቶቡስ ላይ ተሰቅዬ፣ እንደ እብድ እየጮህኩ ፖስተር ግዙኝ፣ የመዝሙር ካሴት ፣ መጽሐፍና ቪሲዲ ግዙኝ እያልኩ እጮህ የነበረው ያንን ዓመታዊ ዕቅዴን ለማሳካት ስል ነበር። "ዘመዴ አንተ እኮ የተከበርክ፣ የተፈራህ ሰባኬ ወንጌል ነህ፣ አንተ ዐውደ ምሕረት ላይ ቆመህ የምትመሰክር ትልቅ ሰው ነህ፣ እንዴት እንዲህ ወርደህ እየጮህክ ትሠራለህ? እንዴት እንደመብረቅ እየጮህክ ሰው እያደነቆርክ ትደክማለህ? የሚሉኝ አርብ ለጉባኤ ክፍለ ሀገር ሄደው ቅዳሜና እሁድ ሰብከውና ዘምረው፣ የአበል ገንዘብ ተቀብለው ሕይወታቸውን የሚገፉ ኩሩ የመድረክ ባልንጀሮቼም ምክራቸውን ባልቀበለውም ይመክሩኝ ግን ነበር። ሲመክሩኝ ቆይተው አዲስ አበባ ስንደርስ የምንሰጥህ ብር አበድረን የሚሉኝ ነበሩ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ከክፍለ ሀገር ሰበካ አበል በተጨማሪ በኋትስአፕ እና በቫይበር፣ በኢሞና በሚሴንጀር ሆዴ፣ ማሬ እያሉ የዓረብ ሀገር የማዳም ቅመሞችንም፣ በአውሮጳ፣ በአማሪካ፣ በካናዳና በአውስትራሊያ የሚኖሩ ባልፈላጊ እህቶችን ልብ በማቅለጥ ከዚያ በሚያገኙት ገቢ ዓመታዊ ዕቅዳቸውን የሚያወጡም ነበሩ። ከዚህ ይልቅ የእኔ በስንት ጣዕሙ። ላቤን ጠብ አድርጌ ነበር ወጥሬ የምሠራው።
"…በዚህ መልኩ ላቤን ጠብ አድርጌ ሠርቼ፣ ፍልውኃ ምትኩ እስቱዲዮ እስከ መንፈቀ ሌሊት እየቆየሁ፣ ቤተሰብ ተኝቶ እኔ እየሠራሁ ሌሊት እንደ ጅብ እየኳተንኩ ነበር ፏ ሽር ብትን ብዬ እኖር የነበረው። ሱቆቼን ወያኔ በልማት ስም አፈራርሳም እንኳ እኔ ዘመዴ እጅ አልሰጠሁም ነበር። እንዲህም ለፍቼ ለፍቼም ጎዶሎ ቀኖች ግን ነበሩ። እኒያም ጎዶሎ ቀናት በቸርነቱ እየተሞሉ እሻገራቸው ነበር። ያለ ዕቅድ የሚንቀሳቀስ ሰው ያለ ኮምፓስ እንደሚንቀሳቀስ መርከበኛ ያለ ነው። አዎ አሁኑኑ የባንክ ደብተርዎን ይግለጡትማ። መልካም ገለጡት እንበል። በባንክ ሒሳብ ደብተርዎ ላይ ስንት ብር ነው ተቀማጭ ያልዎት? ይመልከቱት። ምን ወጪ ቀንሼ፣ ምን ተጨማሪ ሥራ ብሠራ ነው እዚህ ብር ላይ አሴት የምጨምረው ብለው ያስቡ። ያስቡና ወረቀት ላይ ይጻፉት። ከዚያ ወዲያውኑ ወደ መተግበር ይግቡ። ውጤቱን ያዩታል።
"…እኔ ሻይ አልጠጣም ነበር። አሁንም አልጠጣም። ቡና አልጠጣም ነበር አሁንም አልጠጣም። ኮካኮላ፣ ፔፕሲ የሚባሉ መጠጦች በአፌ አልቀምስም ነበር። አላጨስም፣ አልቅምም፣ ቢራ ከአንድ ቡትሌ አላልፍም። እሱንም በስንት ወር አንደዜ ነው። ወይን ጨዋታ ባለበት አንድ ብርጭቆ። የእኔ መጠጥ ውኃ ነው። ወተት፣ እርጎ ነፍሴ ነበር። ያኔ ሁሉም ርካሽ ነበር። አላስፈላጊ ወጪ የለብኝም። ሥራ ቦታዬ ስሄድም፣ ስመጣም በእግሬ ነበር የምሄደው። ልብስ አያልቅብኝም፣ ጫማም እንደዚያው፣ በዚህም ወጪ ብዬ አልባክንም። እኔ ልጆቼና ቤቴ እንዳይጎድልባቸው ብቻ ነበር የምደክመው። የተማሪ ዩኒፎርም መኖር ደግሞ ዋነኛው ወጪ መቆጠቢያ ነበር። ጫማ ነው ግፋ ቢል የሚያስወጣኝ። እሱም ቢሆን በደጉ ግዜ ነው። ውኃ 30 ብር፣ መብራት 50 ብር ቆጠረ ብዬ ኤሌክትሪክ ልጨብጥ በምደረስበት ዘመን ማለት ነው። ጤፍ 600 ብር ገባ ብለን ምን ሊውጠን በሚባልበት ዘመን ማለት ነው። ሲሚንቶ ቁምጣው 200 ብር፣ ብረት ርካሽ፣ ብሎኬት 75 ሳንቲም፣ አንድ መኪና አሸዋ 3ሺ ብር በነበረ ጊዜ ነው የማወራችሁ። አዎ ካልደነስኩ፣ ካልጨፈርኩ፣ ካልቀበጥኩ በቀር፣ ደባል ሱስ ከሌለብኝ በቀር ገንዘብ ይያዛል። እንደ ውሻ የሴት እግር እያየህ የምትልከሰከስ ከሆነ ግን አለቀልህ። ገንዘብህን ብቻ ሳይሆን መቅኔህም፣ ሐሞትህም፣ ጂስምህም ነው ፈስሶ የሚያልቀው።
"…የማወራው ይገባችኋል አይደል? እኔ ከቤተሰብ የወረስኩት ሀብት የለኝም። ስለዚህ አፈር ደቼ መብላት ነበረብኝ። እንደዚያም ነው ያደረኩት። መኪና የሚገዛ ብር እያለኝ መኪና አላማረኝም። በእግሬና በታክሲ እየሄድኩ ነው በወቅቱ ቤት የሠራሁት። የእኔ ጓደኞች መኪና ነበራቸው። እስከአሁን ግን ቤት ይኑራቸው አይኑራቸው አላውቅም። መሥሪያ ቦታዬ ከቤቴ 3 ፌርማታ ሆኖ ሳለ እኔ ምን ይሁነኝ ብዬ ነው መኪና የምገዛው? ለጉራ ካልሆነ በቀር። እናም የሚቀድመውን እናስቀድም። ቁጥብ፣ ራሳችንን የምንገዛ እንሁን። የሲጋራ፣ የድራፍት፣ የጫት ወጪ ሲያዩት ቀላል ነው። በዓመት ስትመቱት ነው ኡኡ አሽቃሩ፣ አሽቃሩ ብላችሁ የምትጮሁት። በዚያ ላይ የፔንሲዮንና የቤርጎ ወጪን ደምሩት፣ ምቱት በዓመት። ናላችሁ ነው የሚዞረው።
"…እናም ወዳጄ ዓመታዊ ዕቅድ አውጣ፣ ያወጣኸውን ዕቅድ እስከቻልክ ድረስ አስኪደው፣ ቀሪውን ፈጣሪ ይጨመርበት። ሜካፕ የማታበዛ፣ አርቴፍሻል ያልሆነች ጓደኛና ሚስት ካገኘህ ደግሞ አንተ ሎተሪ እንደወጣልህ ቁጠረው። በፊልም ላይ ያየችውን በአካል ካልኖርነው የምትል ጓደኛ ካገኘህ ሞትካት። የጋን ታናሽ ወንድም፣ ውሸታም፣ በዚያ ላይ ሱሰኛ ሱሳም ጓደኛ ካገኘሽ እና ከእሱ ጋር ለመኖር ከወሰንሽ በጊዜ የሬሳ ሣጥን በቅናሽ ገዝተሽ በቅርብ ማስቀመጥ ነው። የእኔዋን ባለቤቴን ሂሩቴን ስጠብሳት የማውቀው አንድ ሹራብ ነበራት፣ ተጋብተን ሁላ ቤት ቤት ውስጥ ትለብሰው ነበር። ያ ሹራብ በስንት ዘመኑ መጨረሻ ላይ መወልወያ ሆኖ ነው የተገላገልነው። አታምኑኝም እኔና ሉሌ…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ።” ኢሳ 35፥3
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
አዲስ ዓመት በቀበሮ ሜዳ…
"…የእኔን ታማኝ ተናካሽ ውሻውን የሀረርጌ ቆቱ የመራታው ዘመዴን ጥሪ ሰምቶ ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ግማሽ ሚልዮን ብር በለገሰው በባለ ሀብቱ በአቶ ወርቁ አይተነው ብር ለተፈናቃዮቹ የተገዙት ሰንጋና ፍየሎች ከተፈናቃዮች ካምፑ በሰላም ደርሰዋል። አንድ ሰንጋም ሌላ ቦታ ለሚገኙ ካለን እናካፍል ለተባለ ለአረጋውያንና ህፃናት አእምሮ ህሙማን ማዕከል አስረክበዋል።
"…ተፈናቃዮቹ ለነገው በዓል ድንኳኑን ተከራይተዋል። ወንበሩ ሁሉ እየተዘጋጀ ነው። የወጥ መሥሪያ የኩሽና ዕቃዎች፣ ምግብ መመገቢያ ሰሀኖች በሙሉ ተከራይተው ቀበሮ ሜዳ ደርሰዋል። ነጭ ማኛ እንጀራው በሙሉ ተጋግሯል። የሚጣው ውኃው ተራግፏል። በቀበሮ ሜዳ ነገ ተፈናቃዮቹ አዲሱን ዓመት በደስታና፣ በሐሴት፣ በተስፋም ያከብሩታል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ይሄ ሁሉ እንዲሳካ ላደረጋችሁ ለእናንተ ለቴሌግራም ጓደኞቼ ቃልም የለኝ። በጽሑፍ ብቻ አምናችሁኝ በመቶ ሺዎችን ሳትሰስቱ ላበረከታችሁ ለእናንተ ቤታችሁ በበረከት ይሞላ። ጤና፣ ዕድሜ፣ ሀብቱን ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣችሁ። አግኝታችሁ አትጡ። በተለይ ልጆቻችሁን ይዛችሁ አትቸገሩ። መከራ አያግኛችሁ።
"…ነገ ደግሞ በዓሉን ከቀበሮ ሜዳዎች ጋር አብረን እናሳልፋለን። እስቲ ሰጪዎቹን ሁሉ እናንተም መርቁልኝ። በእናታችሁ መርቁልኝ።
👆⑤ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ይሄ ሁሉ ሌብነት፣ ዘረፋ፣ ሰው ማገት፣ ዘግናኝ ግድያና ግፍ፣ ጭፍጨፋም ሁላ የዐቢይ አሕመድ ሥርዓት የወለደው ነው። አንተ በእሱ ስታለቅስ እሱ ኮሪደር ልማት ብሎ በቀለም እና በመብራት ያበደ፣ ያሸበረቀ ከተማ በቶፕ ቪው የድሮን ቀረጻ እያሳየህ በአይንህ ላይ ቁማር እየተጫወተ፣ ኧረ ሞትን ስትለው መሞት ብርቅ ነው እንዴ እያለ እያላገጠብህ ትኖራለህ። አዎ አቢይ አሕመድ ያለፉትን ዓመታት በዚህና በዚያ በመሳሱሉት አሰቃቂ ዜናዎች አየሩን እየሞላ ነው ከዛሬ የደረሰው። ለአቢይ አሕመድ የሴራ አጀንዳ ደርሶ አየሩን መሙላት የተለመደ ተግባር ነው። ቲክቶክ ላይ ሲንቶኮተኩለት የሚውሉ ማይም ቲክቶከሮች፣ ዩቲዩበርና ፌስቡከሮች ስላሉትም ሼም አይሸምመውም። አቢይ አሕመድ ሚልዮን ትግሬ ጨፍጭፎ የጠየቀው ስለሌለ ይሄ መንገድም አዋጭ ሆኖ ስላገኘው ዘንድሮም በ2017 ዓም በደንብ ይሠራበትና ቀጣይ ተጠቂ የማኅበረሰብ ክፍል ተራውን ይጠብቅና ሰቆቃው በአዲስ አጀንዳ ይጀምራል። ተረኛዎቹ የጦር አውድማዎች፣ የሰቀቀን ዜና መስሚያ ክልሎች ዐማራ እና ኦሮሚያ እንዳሉ ሆነው የሱማሌ ክልል በዋነኝነት፣ ደቡብ በተጠባባቂነት ይወድሙ ዘንድ የተፈረደባቸው ይመስላል። ይህ ነው ያለፉት 6 ዓመታት የአብይ አመድ ትሩፋት። ይሄን አረመኔ ሥርዓት ለመለወጥ አትንቀሳቀስና እግዚአብሔር ላይ ጣትህን ስትቀስር ኑር። የፋኖ መንገድ ብቻ ነው ብቸኛው መዳኛህ። ነገርኩህ።
"…እኔ ዘመዴም ያለፈው ዓመት 2016 ዓም ዘመነ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ስለነበረ እንደ ነጎድጓድ እያጓራሁ፣ ሾተላዩን ሁሉ የእሳት ብዕሬን እየተፋሁ ስቆማምጠው ከርሚያለሁ። ዓመቱ ለእኔ የድል ዓመት ነበር። ቀና ቀና ብለው በብልጠት የዐማራን ትግል ለማጠልሸት ዊኒጥዊኒጥ ለማለት የሞከሩ ሚሳኤሎችን በፀረ ሚሳኤል ሱፐር ሶኒክ ሚሳኤሎች ሳመክን፣ ሳከሽፍ ኖሬአለሁ። ወላ እስክሳታ መቺ፣ ወላ ዶፍተር፣ ወላ ጋዜጠኛ፣ ቦለጢቀኛ የቀረኝ የለም። አለሁ አለሁ ባይ የማኅበራዊ ሚዲያ እብዶችን አደብ ያስገዛሁበት፣ ፊታቸው ከስሎ ጥቀርሻ ያስዋጥኩበት ዓመት ነበር ያለፈው የእኔ 2016 ዓም። ዘንድሮም ብስቦኝ እቀጥላለሁ። በ2017 ዓም ዘመኑ ዘመነ ማቲዎስ ነው። ማቴዎስ ገፀ ሰብ ነው። የሰው ምሳሌ የሆነ ስለሰው ልጅ በትረካው የጀመረ ነው ማቴዎስ ወንጌላዊው። ማቴዎስ ወንጌላዊ ነው። የምሥራች ነጋሪ ነው። እኔም ዘንድሮ ሰው ሰው ለሚሸቱ የምሥራቹን አብሠራሁ፣ የሰው ፀር ሾካካ፣ ቃጥራ፣ ሌባ፣ አጭበርባሪ፣ ዋሾ፣ ቀጣፊ፣ አስመሳይ፣ ባንዳ ባንዳውንሁል ግን እሰብረዋለሁ። እንደ አማኝ ለሃይማኖቴ፣ እንደ ዜጋ ለሀገሬ በብዕሬ እና በምላሴ የራሴን አስተዋጽኦ በማድረግ ልክ እንደ አምና ካቻምናው ዘንድሮም ፀረ ሰው ኃይሎችን በሙሉ ያለምሕረት፣ ያለ ሰቀቀን ልፋለማቸው ዝግጁ መሆኔን ለመግለፅ እወዳለሁ። የዐማራ ፋኖን ትግል በሴራ ለመጥለፍ የሚሞክር ማንም ይሁን ማንአባቱ አልፋታውም። ደሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ እል ዘንድ የረዳኝ አምላኬንም አመሰግነዋለሁ። እናንተም አመስግኑልኝ። የዳዊት ጠጠር ሆኜ ጎልያዶችን አጋድማቸው ዘንድ፣ በሸረኞች፣ በሴረኞች ላይ አምቦ ውኃ ሆኜ ሓሳባቸውን፣ ሴራቸውን እበታትን ዘንድም ፈጣሪዬ እንዲረዳኝ ትጸልዩልኝ ዘንድም እማጸናለሁ። የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትን አግዝ ዘንድ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችንም አጽናና ዘንድ እግዚአብሔር እንዲያበረታኝ እንዲፈቅድልኝም ጸልዩልኝ። 2017 ዓም ፀረ ሰው የሆኑ ጋግርታም የኢትዮጵያ ነቀርሳ ሾተላዮች ሁሉ ተወግደው ለማየት ያበቃን ዘንድም በጽናት እንታገል። መጪው ጊዜ ለታጋዮች ብሩህ ነው። ለዳተኞች ግን ጨለማ ሲኦልም ነው።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
መስከረም 1/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍
"…የዐማራን ተማሪዎች በጦርነት ማግደህ፣ ለፈተና የሚሄዱትን ገድለህ፣ ሰብስበህ ወታደራዊ ካምፕ አስገብተህ ሕፃናት ተማሪ ሴቶችን ደፍረህ፣ ያን ሁሉ ፈተና ተቋቁመው የተፈተኑትንም በዜሮ ዘርረህ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዳያልፉ አድርገህ፣ በኦሮሚያ በኢፋ ቦሩ በአዳሪ ትምህርት ቤት ቻይንኛና ዓረብኛ ጭምር በልዩ ሁኔታ የምታስተምራቸውን የኦሮሞ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ፣ ትግሬዎቹ እንዳይከፋቸው ከቀለሚኖ ጥቂት ትግሬ ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ አሳልፈህ ስታበቃ ብራኑ ነጋ የጣላቸውን የእግዚአብሔር ቁጣ ነው ብትል ማን ይሰማሃል? ብርሃኑ ነጋንና አቢይ አህመድ በትምህርትና በተማሪዎች ላይ የሚፈጽሙትን ጄኖሳይድ በቀልድ፣ በፉተታ፣ በፉገራ እያሾፍክ እያሳለፍክ ያ አላህ፣ ያ ረቢ ምን በድለንህ ነው ግን፣ እመቤቴ ማርያም ኧረ አማልጂን። መድኃኔዓለም ምን አጥፍተን ነው ብትል ፈጣሪ በአንተ ከመሳቅ ውጪ ምንም ያደርግልህ ዘንድ አይችልም።
"…አገዛዙ በፈጠረው አርቴፊሻል ሰው ሠራሽ ራብ ምክንያት ጠኔ እያዳፋህ በፈጣሪ ላይ ማጉረምረም ዋጋ የለውም። እግዚአብሔር የቤት ኪራይ አይጨምርም። የመኪና ነዳጅ ተመን አያወጣም። ትራንስፖርት ላይ ዋጋ፣ የሕዳሴ ግድብ ተመርቆ በማግሥቱ ለኬንያና ለሱዳን በቅናሽ ለአንተ ለባለቤቱ፣ ደሞዝህን አዋጥተህ ግድቡን ለሠራኸው ሶዬ በ300% እጥፍ በመብራትና በውኃ ላይ ታሪፍ አይጨምርም። እግዚአብሔር ማዳበሪያ አያከፋፍልም። ግብር እና ታክስ በአናትህ ላይ አይቆልልም። እግዚአብሔር ዩኒቨርሲቲ እንዳትገነባ፣ ተማሪ እንዳትቀበል አያደርግም። እግዚአብሔር ሰላሌ ሜዳ ላይ መኪና ሙሉ ጎጃሜና ጎንደሬ በኦሮሞ ቄሮ አሳፍኖ በሰው ሚልዮን ብር አስከፍሎ አይለቅም። እየለየን ጎበዝ።
"…ባለፈው ዓመት በ2016 ዓም ከአዲስ አበባ አምቦ፣ ወልቂጤ፣ አዋሳ፣ ደጀን፣ ደብረ ብርሃን፣ ናዝሬትና ሐረር መስመር እንዳትንቀሳቀሱ፣ እንዳትነግዱ፣ ዘመድ እንዳትጠይቁ ያደረጋችሁ ማነው? ከቤታችሁ፣ ከመንገዳችሁ አግቶ ጫካ ወስዶ የደፈራችሁ፣ ሚልዮን፣ መቶ ሺህ ብሮችን አግቶ የተቀበላችሁ፣ ያቆረቆዛችሁ ማነው? እግዚአብሔር ነው እንዴ? የቦሌ አውሮጵላን ጣቢያን እንደ መርካቶ መነኻሪያ በሰው ያጥለቀለቀው እግዚአብሔር ነው እንዴ? አውቶቡስ በምድር እንዳይሠራ የፈረደበት አላህ ነው እንዴ? አይደለም ከልካዩን በስሙ ጥሩት። በስሙ ውቀሱት፣ ክሰሱትም። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይቅር። ባለፈው ዓመት የልብ ድካም፣ የጨጓራ ህመም፣ የደም ማነስ፣ የራስ ምታት ያመጣባችሁ፣ ሪህ፣ ጉበት፣ ኩላሊት ያሳመማችሁ፣ ትን ብሏችሁ ከሞት የተረፋችሁትም በመንግሥቱ፣ በአገዛዙ ነው ማለት አይደለም። እሱ ተፈጥሮ ነው። ይሄ ስትታገቱ ደንግጣችሁ፣ ስትፈናቀሉ በርግጋችሁ በዚያ ምክንያት በተፈጠረ የልብ ህመም፣ የደም ግፊት ክልትው የምንለው ካልሆነ በቀር በተፈጥሮ የሚመጣን ህመም በመድኀኒት፣ በሃኪም፣ በጸበል ልትቆጣጠረው ትችላለህ። ደግሞም ቀንህ ካልደረሰ የሚስተካከልም ነው። አርቴፍሻሉን የእነ አቢይን ህመም ግን በፈጣሪ ማሳበቡ አይጠቅምም።
"…እግዚአብሔርን የምትከሰው ዝናብ ሲከለክልህ ብቻ ነው። በወቅቱ ዝናብን ማዝነም የፈጣሪ ተግባር ነው። ወቅት ጠብቀህ ማረስ ያንተ ፈንታ ነው። የዘራኸውን ማጽደቅ ግን የፈጣሪ ሥራ ነው። የጸደቀውን ተንከባክበህ ማሳደግ፣ ያደገውን፣ ለፍሬ የበቃውን፣ ማረም፣ መኮትኮት፣ ማጨድ፣ መውቃት፣ ወደ ጎተራ ማስገባት፣ ማስፈጨት፣ ማቡካት፣ መጋገር፣ የተጋገረውን አመስግነህ እንክት አድርገህ መብላት የአንተ ፈንታ ነው። ማዳበሪያ ከተከለከልክ አገዛዙን እንጂ እግዚአብሔርን መውቀስ ልክ አይደለም። ዝናብ ሲቀርብህ በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ ወድቀህ ተነሥተህ ፈጣሪን ተማጽነህ ይመለስልሃል። ማዳበሪያ ከልክሎህ የጠየቅከው መንግሥት "የጅራፍ ፖለቲካ" ብሎ ሲያሾፍብህ ምንሽርህን ወልውለህ ለለውጥ ካልተነሣህ በቀር በራብ ነው የምታልቃት። ጅሎ ፈጣሪ ማዳበሪያ አቅራቢ ድርጅት አይደለም ዝናብ አቅራቢ እንጂ። እናም አንተ ራስህ ተንቀሳቅሰህ የምትለውጠውን ለውጥ ዓመት ተወዝፈህ፣ አገዛዙን ፈርተህ በፈጣሪ ቁጣ፣ በእሱ ጭካኔ እንደመጣ ቆጥሮ መቀመጥ ስንፍና ነው፣ ሰገጤነትም ጭምር ነው።
"…አገዛዙ በራብ የሚገድለው አለ። በማፈናቀል የሚገድለውም አለ። በጦርነት የሚገድለውም አለ። አቢይ ትግሬን በራብና በጦርነት እምሽቅ አደርጓል። ዐማራ ከኦሮሚያ፣ ከመተከል በገፍ ታርዶ በግሬደር ሁላ ተቀብሯል። አሁን በክልሉ ጦርነት ገጥሞ በትንቅንቅ ውስጥ ይገኛል። አፋር ደቅቋል። ትንፍሽ አይላትም እንጂ ጉራጌ እየታረደ ነው። እየታገተ ገንዘብ ለኦሮሞ ቄሮ በገፍ እያፈሰሰ ነው። ደቡብ እየተገደለ ነው። በፓስተሮቹ እየተቀለደበት መጫወቻ እየሆነ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ሃኪሞችና መምህራን ደሞዝ መቀበል ካቆሙ ቆዩ። እና ለዚህ ደሞዝ መቆም ፈጣሪ ምን አገባው? ፈጣሪ የደሞዝ በጀትህን የሚይዝበት ቋት የለውም። ደሞዝ የሚከለክልህ፣ የሚያስቀርብህ ሕዝብ የመረጠኝ መንግሥትህ ነኝ የሚለው ብልፅግና እንጂ ፈጣሪ አይደለም። ይሄም በእግዚአብሔር ቁጣ መደብ ውስጥ መካተት የለበትም ባይ ነኝ።
"…800 ሺ ተማሪ ፈትነህ፣ 3ሺ ተማሪ አሳልፈህ ስታበቃ በፈጣሪ ማማረር ጅልነት ነው። የቲክቶክ ቪድዮ እየሠራህ ብርሃኑ ነጋ ላይ ስትቀልድ፣ ስታሽሟጥጥ ብትውል ብታድር ለጊዜው ላይክና ሼር ታገኝ እንደሁ እንጂ ምንም አባክ አታመጣም። ብራኑ ነጋ በኢትዮጵያ ተማሪዎች በተለይም የዐማራውን የተማረ የሰው ኃይል አጥፍቶ ደንቆሮ፣ ማይም ዐማራ ይፈጥር ዘንድ በዓላማ ተልእኮ ተቀብሎ የሚሠራ፣ ከወያኔም ጠብ ያልነበረው፣ በኤርትራ በረሃ ዐማሮችን ይዞ ኢትዮጵያን ነፃ አወጣለሁ በሚል ሰበብ ሞኝ ዐማሮችን ኤርትራ በረሃ ወስዶ ቆርጥሞ የበላ፣ የገደለ፣ ያስረሸነ፣ ፀረ ዐማራ የኦነግ፣ የሻአቢያና የወያኔ አሽከር ነው። በኢትዮጵያ የተማሪዎች የዕውቀት ርሸና፣ ጄኖሳይድ ለመፈጸም የተላከ ሀሳዊ አረመኔ ነው። በብልፅግና የመሻገር ቀን እሱ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመሻገሪያ ድልድዩን ሰብሮ ሲያላግጥብህ እያየህ አምላኬ ምን በድዬህ ነው ብትል አምላክህ አይሰማህም። እና ይሄም የፈጣሪ ቁጣ ነው እንዴ? ምህላና ሱባኤ እንያዝ ብትል ቲክቶክ ላይ 3 ሺ ሰው ቢሰማህ እንጂ ፈጣሪማ ጭራሽ አይሰማህም። ይሄን ሰው ሠራሽ ጄኖሳይድ በጆክ፣ በቀልድ፣ በድራማ፣ በኮሜዲ ሳይሆን በነፍጥ ነው አናፍጠህ የምትቀይረው። አለቀ።
"…በራኑ ነጋ የጣለውን ብራኑ ጁላ ያነሣዋል ወዳጄ። ፈጣሪ ጣለኝ አትበል። የጣለህ ብራኑ ነጋ ነው። ፈጣሪ ያንሣኝ አትበል። ብራኑ ጁላ ተንሰፍስፎ በጉጉት አቅፎ ያነሣሃል። ብራኑ ነጋ ጣለኝ፣ ምን ሠርቼ ልበላ ነው አትበል። ብራኑ ነጋ የጣለህን አንተ ሰገጤውን ብራኑ ጁላ አንሥቶ፣ ጦላይ ወስዶ አሠልጥኖ ያብቃቃሃል። ሥራም አሣርም ይሰጥሃል። ስትፈልግ ወለጋ ተልከህ በጫካው ሸኔ ትበላለህ፣ አልያም ዐማራ ክልል ሄደህ ዕድለኛ ከሆንክ ትማረካለህ፣ አልያም ትቆረጠማለህ ወይም ደግሞ ለቀይ ባህር ከኤርትራ፣ ለወደብ ከሱማሌያ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ትፈሳፈሳለህ። የወደቅከው ለተለየ ዓላማ፣ ለመስዋዕትነት ተፈልገህ ነውና በፈጣሪ አትማረር። አጠገብህ የዘፈዘፈህ ብራኑ ነጋ እያለ የምን ወደ መንበረ ጸባኦት ወደላይ ማንጋጠጥ ነው? ደፋር።
"…በኢትዮጵያ ካለህ በፈጣሪ ላይ ማንጎራጎርህን ትተህ ይልቁኑ ፈጣሪን አምላኬ ሆይ እርዳኝ፣ ጉልበትም ሁነኝ፣ ይሄን ፀረ ሰው፣ ፀረ ሀገር የሆነ አረመኔ አገዛዝ እፋለመው ዘንድ ብርታት ሁነኝ፣ ድልን አደርግ ዘንድ…👇③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ዘመን ተቀየረ፣ ዘመነ ዮሐንስ ሂዶ በዘመነ ማቴዎስ ተተካ። ዘመነ ዮሐንስ ተራውን ጠብቆ ከዘመነ ሉቃስ በኋላ ዳግም ይከሰታል። የዘንድሮው ይህን ርእሰ አንቀጽ ከምናነብ ሰዎች መካከል ዕድሜ ሰጥቶን ለዚያ ዕለትና ዓመት ከደረስን ዘመነ ዮሐንስ ዳግመኛ ይመጣና እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገረን እንባባላላን። ዳግም ደግሞ የማይመጣው፣ እንደሞተም ሰው በመታሰቢያ መዝገብ ውስጥ ብቻ ሰፍሮ የሚቀረው፣ ተመልሶ መጥቶ የማናየው፣ የማንኖርበት ታሪክም ሆኖ የሚቀረው ይሄ ያሳለፍነው 2016 ዓመተ ምሕረት ነው። ልክ እንደ 2015፣ 14፣ 13፣ ወዘተ ያለፈው ዓመት፣ የዛሬ 2 ዓመት፣ የዛሬ 300 ዓመት እየተባለ ነው የሚጠራው። ትናንት የኖርንበት 2016 ዓም ራሱ ከዛሬ ጀምሮ ያለፈው ዓመት መባል ጀምሯል። አዎ 2016 ዓም የተባለ ዓመተ ምህረት በሕይወታችን ውስጥ ዳግመኛ ላይመለስ ለ2017 ዓመተ ምሕረት ም አስረክቦን ሄዷል፣ አልፏልም።
"…መጪውን የአዲሱን ዓመት 2017 ዓምን ምን አሰብን፣ እንዴት አሳለፍን ብለን ስለ እሱ ከማውጋታችን በፊት ስለ 2017 ዓም መባቻ፣ ወንጌላዊና ዘመኑን እንዴት በቀላሉ ማስላት እንደሚቻል ጥንታዊቷ፣ ሐዋርያዊቷ፣ ብሔራዊቷ፣ ቀኖናዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀምራ አዘጋጅታ የሰጠችንን የዘመን አቆጣጠር ባሕረ- ሓሳብ ወይም አቡሻኽሩን መሠረት በማድረግ ወንድሜ ጋዜጠኛ ጴጥሮስ አሸናፊ ካዘጋጀው ጦማር ላይ በማካፈል እናንተም ትጠቀሙበት ዘንድ እንደሚከተለው በቀላሉ ማስላት የምትችሉበትን ዕውቀት በማካፈል ማየት እንጀምራለን።
"…ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለው 5500 ዘመን ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) ሲሆን፣ ከክርስቶስ መወለድ እኛ እስካለንበት ያለው ዘመን ደግሞ ዓመተ ምሕረት ይባላል። የኹለቱ ድምር ዓመተ ዓለም ይባላል።
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት ➕ ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ)
= 2017 ➕ 5500
= 7517
ወንጌላዊ፦ በየ4 ዓመቱ አንድ ጊዜ የሚሾም ማለት ነው፡፡
ወንጌላዊ = ዓመተ ዓለም ➗ 4
= 7517 ➗ 4
= 1879 (ቀሪ 1️⃣ )
1879፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡ አንድ አራተኛ (1/4) ማለት ነው።
= 7517➖ ( 4 ✖1879)
= 7517➖ 7516
= 1
ቀሪው '1️⃣‘ ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '1️⃣' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ (2017) ማቴዎስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ይባላል።
"…በሌላም በኩል ዓመተ ምሕረቱንም ለ4ቱ ወንጌላውያን ብናካፍለው የዘመኑን ወንጌላዊ ማወቅ እንችላለን። 2017 ➗ 4 = 504 (ቀሪ '1️⃣' ) ቀሪው ' 1 ' በመሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ እንደሆነም በዚህ ይታወቃል።
ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር = (ዓመተ ዓለም ➕ መጠነ ራብዒት) ➗ 7
= (7517➕ 1879) ➗ 7
= 9396 ➗ 7
= 1342 ቀሪ 2
ቀሪው '0️⃣ 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1️⃣' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው ''2️⃣ ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3️⃣ 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4️⃣'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5️⃣ 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6️⃣ 'ከሆነ እሑድ መባቻ ይሆናል።
"…በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው ''2️⃣ ' ስለሆነ ዕለተ ቀመር ረቡዕ ይሆናል ወይም አዲሱ ዓመት 2017 ዓም መባቻ መስከረም አንድ ቀን በዕለተ ረቡዕ ይውላል ማለት ነው። ዘንድሮ ዕለተ ቀመር ጥንተ ዮን (ዖን) ከተባለችው ረቡዕ ጋር መገጣጠሙ ነው። ሥነ ፍጥረት የተጀመረባት እሑድ ጥንተ ዕለት፣ ዘመን አቆጣጠር የተጀመረባት ማክሰኞ ጥንተ ቀመር እንዲሁም ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩባት ዕለተ ረቡዕ ጥንተ ዮን (ዖን) ትባላለች።
በተመሳሳይ ፤
መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል
ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል
ኀዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል
ታኅሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል
ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል።
"…በዚህ መሠረት የ2017 ዓ/ም መስከረም 1 ቀን ረቡዕ ስለሚውል በተመሳሳይ ሚያዝያ 1 ቀንም ረቡዕ ይውላል ማለት ነው። የዚህ ዓመት ጳጉሜን 5 በዋለበት ዕለት የቀጣይ ዓመት በዓለ ልደት (ገና) ይውላል። ይህም ማለት የ2016 ዓም ጳጉሜን 5 ማክሰኞ ቀን ስለምትውል የ2017 ዓ.ም በዓለ ልደት (ገና) ማክሰኞ ታኅሣሥ 29 ቀን ይውላል ማለት ነው። በተመሳሳይ በ2017 ዓም መስቀል መስከረም 17 ቀን አርብ፣ ጥምቀት ጥር 11 ቀን እሑድ፣ ጾመ ነነዌ የካቲት 3 ቀን ሰኞ፣ ዐቢይ ጾም የካቲት 17 ቀን ሰኞ፣ ስቅለት ሚያዚያ 10 ቀን አርብ፣ ትንሣኤ ሚያዚያ 12 ቀን እሑድ፣ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 1 ቀን እሑድ፣ ዕርገት ግንቦት 21 ቀን ሐሙስ የሚውሉ ይሆናል።
"…አዳም የተፈጠረው በዕለተ ዓርብ ነው። ከ40 ቀን በኋላም ወደ ገነት እግዚአብሔር አስገባው። አዳምም የእግዚአብሔርን ሕግ እየጠበቀ 7 ዓመት ከ1 ወር ከ17 ቀን በገነት ተቀመጧል። ከዚያ በኋላ አትብላ የተባለውን እጸ በለስ ስለበላ ተፈረደበት። አዳምም ንስሓ በገባ ጊዜ እግዚአብሔር ከ5500 ዘመን በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ተስፋ ሰጠው። የአዳም ልጆችም ይህን ይዘው ጌታ ሰውን ለማዳን የሚመጣበትን ጊዜ በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት እየቆጠሩ ይኖሩ ነበር። የዘመን ቁጥር የተጀመረበት ምክንያቱም ይህ ነው።
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤
"…ዓለም ከተፈጠረ በ5500 ዘመን በዘመነ ዮሐንስ መጋቢት 29 እሑድ ቀን በ 3:00 ሰዓት ተጸነሰ፤ ዓለም ከተፈጠረ በ5501 ዘመን ወይም በ1 ዓመተ ምሕረት በዘመነ ማቴዎስ ታኅሳስ 29 ቀን ማክሰኞ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ተወለደ። በ5531 ዘመን ወይም በ31 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ ጥር 10 ቀን ለ11 አጥቢያ ማክሰኞ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ተጠመቀ። በ5533 ዘመን ወይም በ33 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ነሐሴ 13 እሑድ ቀን በቀትር ጊዜ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት በደብረ ታቦር ገለጠ። በ5534 ዘመን (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 22 ቀን እሑድ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (ሆሣዕና)። በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 26 ቀን ሐሙስ በሠርክ ጌታችን መስዋዕተ ኦሪትን በመስዋዕተ ወንጌል የተካበት ነው። በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 27 ቀን ቀትር በ6:00 ሰዓት ተሰቅሎ በ9:00 ሰዓት ነፍሱን ከሥጋው ለይቶ ሠርክ በ11:00 ሰዓት የተቀበረበት ነው። በ5534 ዓ.ዓ ( በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 29 ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት ነው። በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ ግንቦት 8 ቀን በ 3:00 ሰዓት ያረገበት ነው። ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው ዘመን በዓመተ ፀሐይ ሲቆጠር 7516 ዓመተ ዓለም ነው። …👇 ① ከታች ይቀጥላል✍✍✍
“…ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።” ዕብ 13፥16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
እነ ጃል ወያ እነ ጃል ያያ
ይሄን አያዩም አይሰሙም ኦያያ
"…ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው። ወንጀሉ የተፈጸመው በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባ ቦራ ዞን በዳሪሙ ወረዳ ቤና 3ተኛ ተብላ በምትጠራ መንደር ነው። አሰቃቂውን የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ደግሞ በምሥሉ ላይ የሚታየው አህመድ ኡስማን የተባለው ግለሰብ ነው።
"…ወንጀለኛው አሕመድ ኡስማን አሰቃቂውን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ የፈጸመው ሰኔ 29/2016 ዓም ወላጅ እናቱን፣ እህቱን እና የ8 ወር ጨቅላ የሆኑ መንትያ የእህቱን ልጆች በቤት ውስጥ አስገብቶ፣ በሩን በላያቸው ላይ ቆልፎ ዘግቶ በእሳት ተቃጥለው ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጎ ነው።
“አህመድ ወንጀሉን ለመፈጸም ያነሣሣው ከወላጅ እናቱ የጠየቀውን የገንዘብ ብድር ባለማግኘቱ በዚያ ቂም በቀል ይዞ ነው ብሏል መርማሪ ፖሊስ። እናት፣ እህት እና የ8 ወር ዕድሜ ያላቸው የእህቱ መንትያ ልጆች ሕይወታቸው ማለፉን ጨምረው ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ነሐሴ 28/2016 ዓም በዋለው ችሎት አሕመድ ኡስማን በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። አበቃ።
"…ይሄ ወንጀል የተፈጸመው ባህርዳር ቢሆን አስባችሁታል? እነ ጃል ወያ፣ እነ ያያ፣ እነ ማኚቲ ያቀልጡት ነበር እነ ሮሚቲ።
"…የግብዳ ፈላው ተብታባው ሞገስ ዘውዱም ይሄኔ ስንት ፀረ ዐማራ ተንታኝ አምጥቶ ዋይ ዋይ ባለ ነበር።
• ፍትህ ለኦሮሞ ሟቾች።
ፎሊሱ ግን…
• በጎማው ለምንድነው መሬቱን የሚደበድበው?
• ቪድዮ ቀራጩ ፊት ያለው ሰውዬስ ለምንድነው እንደ ፊልም ዳይሬክተር ለደብዳቢው ፎሊስ አቁም የሚል የእጅ ምልክት ሲሰጠው ፎሊሱ ከት እንደተባለ አክተር መሬት መደብደቡን ያቆመው?
• ብቻ እንደ ዕድል ሆኖ የእኔ ዓይን ችግር አለበት እንጂ ቪድዮው እንኳ በጣም ያሳዝናል። ሲያዩት ያማል፣ ያስደነግጣልም። "ዱቴ" አለ እኮ ሞተች ማለት ነው።
• መንሱሬ ባለ ሽቶው ሰምቶ ይሆን?
• ፍትሕ ለልጅቷ።
"…እኔምለው ያ የሱማሌና የግብጽ ወረራ ጉዳይ ከምን ደረሰ…? …አይበለውና እነሱም አያደርጉትም እንጂ ሱማሌና ግብፅስ ቢሆኑ ተሳክቶላቸው ቢመጡ እንዲህ የሚደፍሩ ይመስላችኋልን…?
Читать полностью…👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ብልጦ ህወሓት ጫት አደንዛዥ ዕፅ እንደሆነ ስለምታውቅ በዘመኗ በአቶ ገብሩ አሥራት የትግራይ አስተዳደር ዘመን ጫት መቀሌ እንዳይገባ በሕግ አግዳ የትግሬን ወጣት ከሱስ ለመታደግ ሞክራ ነበር። የሂዊ ክፋቷ ግን በሌላው ክልል የሚገኝ ወጣት ጫታም እንዲሆን ነበር ያደረገችው። በትግራይ ስለ ልቅ ወሲብ የሚያወሩ መጽሔቶች፣ የፖለቲካም ጋዜጦች እንዳይገቡ አድርጋው ሌላው የኢትዮጵያ ወጣት ጋለሞታ፣ ወንድኛ አዳሪ እንዲሆን ነበር የፈረደችበት። የጎጃም ባህርዳርና ጎንደር እንፍራንዝ ሁላ ጫት ቃሚና አምራችና ሻጭ ሁላ አድርጋ አጀዘበችው። የዐማራ ጫታም ደግሞ ብታዩት ሲያስጠላ። ልምድ ስለሌለው ሲቅም ከነ እንጨቱ ነው አሉ። አንደ ዳቦም በሻይ እያማገ ሲበላው ልታገኘው ትችላለህ ብሎኛል አንዱ የድሮ ቃሚ። ከምር ጫትና ዐማራን አስቡትማ። ምን የመሰለ የዶሮ አይን የመሰለ ጠላና የመኳንንት ጠጅ እያለለት ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ዐማራ፣ ትግሬ ጫት ሲበላ፣ ሲያመነዥግ። ቱ…! ማርያምን አያምርበትም። ክፋቷ ደግሞ ህወሓት በትግራይ ጫት ከልክላ አልኮሉን ፈቅዳ የትግሬ ወጣት በዳሽን ቢራና በጊዮርጊስ ቢራ የመቀሌን ወጣት የጠላ ጋን አስመስላው አረፈችው። የትግራይ ወጣት ከጫት ቢርቅም ከአንቡላው ግን አልራቀም። ያለነው አንድ ኮንዶሚንየም ላይ ስለሆነ ጉዳቱ የጋራም አይደል? አዎ እንደዚያ ነው። በትግራይ ውኃ ጠፍቶ በበቢራ እጃቸውን ሲታጠቡ በዓይኔ በብረቱ አይቼ አውቃለሁ። ጫትም ቢራም ጋለሞታ ነው የሚያደርጉት።
"…ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከዐማራ ክልል ጫት ሲወገድ፣ ሲቃጠል አይተን ነበር። ከጫት የራቀ ትውልድ ሲፈጠር ጠያቂ ተመራማሪ፣ አእምሮው ብሩህ ይሆናል። ለቤተሰቡም፣ ለሀገር ለመንደሩም ሳይቀር ይራራል። ነፃነትን ይመኛል። ነፃ ለመውጣት ይጥራል፣ ይታገላል። ጫት የተወ ትውልድ ንፁህ አዕምሮ፣ ንፁህ ልብስም ይኖረዋል። ንፁሕ ጠረንም ይኖራል። አፉ አይሸት፣ ልብሱ አይሸት። ሚስቱን ቢስም፣ ልጆችን ቢያቅፍ አይሸክክ፣ አይደብር። እናም ወጣቱ ከጫት ከራቀ በሀገር ግንባታውም ተሳታፊ ይሆናል። በመይምና ሀ ገደሉ ካድሬም አይመራም። የሆነ ሰሞን ወደ ትግራይም ጫት ወደ መቀሌ እንዳይገባ ሲያደርጉ አይቻለሁ። በጣም ደስስ ይላል። ይደገፋልም።
"…የሆነ ወቅት በኮሮናው ሰሞን በኦሮሚያም ፖሊሶች በኮሮናው ምክንያት በግለሰብ ቤት የተጠራቀመ ነው የተባለ ጫት አስወጥተው ሲያስወግዱም አይቻለሁ። ይሄም ይበረታታል። የሆነ ሰሞን ጃዋር መሐመድም በኮሮናው ምክንያት መቃም ካቆመ ወዲህ ሞትን ፈርቶ ከምህረተ አብ የበለጠ ሰባኪ ሆኖ ታይቷል። ጫት በሳኒታይዘር አይጸዳ? ምን ያድርጉት? በሰሜን ሸዋ የሚገኙ አንዳንድ ነፍጠኞችም የሸዋን ወንድ ሁሉ የማጀት ድመት አድርጎ አኮላሽቶ ያስቀረባቸውን አጅሬ ጫት አደንዛዡን ዕፅ የፍየሎችን ምግብ ነው በማለት በገፍ ሲያስወግዱና ሲያቃጥልም አይቻለሁ።
"…የዐማራ ወጣት እንኳ የባነነው የውሻና ፈረስ ቁማር ያቆመ ጊዜ ነው። የጫት እርሻ መንጥሮ፣ የጫት ነጋዴዎችን የዠለጠ ጊዜ ነው። ቀደም ብለው ነቅተው የዐማራ ፋኖን ያደራጁ ፋኖዎች ብዙ ወጣት የተቀላቀላቸው ቁማር ቤትን በዐዋጅ ካስዘጉ በኋላ ነው። በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር በወሎ ይሄን ዐዋጅ ተከትሎ ወጣቱ ከቁማር ቤት ወደ ነፃነት ሜዳው ተምሟል። አዎ ሱስ ገዳይ ነው። ሱስ ቁልቁል ይቀብርሃል። ሱሳም ባል ሚስቱ ለሠርጓ ቀን ተሠርታ ያሰረችውን ሻሿን ከጠጉሯ ላይ አትፈታም። ገንዘብ የለማ። ሚስቱ የቆሸሸ ቀሚስ፣ የተቦጨቀ ጫማ አድርጋ ነው ከጓደኞቿ በታች የምትቀረው። ሱሳም ባል አያኮራም፣ አያስፈራም፣ የተናቀ ቀትረ ቀላል ውቃቤቢስ ነው። ሱሳም ባል አንገት ያስደፋል። ሱሳም ሴትም እንደዚያው ናት። ሱሳም ሴት ማይም ናት። ሱሳም ሴት የወንድ ሁሉ መጫወቻ ናት። ሱሳም ሴት ክብሯን በአደባባይ ታዋርዳለች።
"…ሱሳሞች ወላጆቻቸው አይኮሩባቸውም። ማኅበረሰቡ እምነት አይጥልባቸውም። ሱሳሞች ይናቃሉ፣ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናሉ። ሱሳሞች አያስቀድሱም፣ አይጾሙም፣ አይጸልዩም። ሱሳሞች አኗኗራቸው እንደ አሳማ ነው። ቀና ብለው አይሄዱም። ሱሳም ወጣት በሰፈር ውስጥ ከታየ ዶፍ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ የመጣ ይመስል መንደርተኛው ሁሉ የተሰጣ ልብስ ይሰበስባል። ዶሮ ካለ ይጠብቃል። ሱሳም አዋራጅ ነው። አስበኸዋል ቆንጅዬ ሴት ሆኗ፣ ሥራ ኖሯት ሺ ሻ ቤት ሱሰኛ ሆኗ የማንም ወንድኛ አዳሪ ስሜት ማራገፊያ ስትሆን? ከምር ሱሳምነት ይውደም።
"…ሱሰኛ አባት ልጆቹ ይጫጫሉ፣ ይራባሉ፣ ይጠማሉ፣ ዐመዳም ቀጫጫ፣ ሲምቢሮ ይሆናሉ። ቅጫማም፣ ፎሮፎራም ሁላ ይሆናሉ። የሱሳሞች ልጆች በትምህርት ውጤታቸውም ዝቅተኛ ውጤት ያመጣሉ። በመጨረሻም የሱሳም ልጆች ወንዱ ዘራፊ፣ ሴቷ ሴተኛ አዳሪ ይሆናል። ሱሳም አባት የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ ነው። ኤትአባክንስና አንተ የሞትክ ሙትቻ። የቤትህን መብራት አጥፍተህ፣ የቤተሰብህን ሕይወት አጨልመህ ለውጭ ሰው የምታበራ አንተ ከንቱ የሆንክ ፍጥረት በቶሎ ተመለስ። አንተ ከውጭ ቁርጥህን እየቆረጥክ፣ የጣመ የላመ እየበላህ አንተን ብላ ሚስትህ የሆነች ስትራብ፣ ልጆችህ ሲራቡ ምንአባህ ነው የሚሰማህ አንተ ደነዝ? ሚስትህን ገረድ፣ ባልሽን አሽከር ያደረግሽ ነውራኛ በቶሎ ተመለሽ። ሱስህንም ተው። ሚስትህን ፀጉሯን አስተኩስ፣ አልብሳት፣ አሰማምራት፣ ከጓደኞቿ፣ ከእድርተኞቿ፣ ከማኅበርተኞቿ እኩል አድርጋት። ሰምተኸኛል? ልጆችህን ጎብኝ፣ አብላቸው፣ አጠጣቸው። አባት ሆኗቸው። አልብሳቸው፣ ትምህርታቸውን ተከታተል። በሚቀጥለው ዓመት ራስህን ለመለወጥ አሁን ይሄን ጦማር እያነበብክ ወስን። ማርያምን ወስን። ተለወጥ አባቴ፣ ወንድሜ። ተለወጭ እህትዓለሜ። ለውጥ አሁኑኑ። የትኛውንም ሱስ ተው። ያለፈውን የሱስ ዘመን እርገም። ለርእሰ አንቀጼ ጫትን ጠቀስኩ እንጂ ሱስ የሆኑ ሁሉ በዚህ መልኩ ይነበቡልኝ። እኔ ደግሞ ጥሎብኝ አለሳልሶ መምከር፣ ማስተማር ብሎ ነገር አይመጣልኝም። የሐረርጌ ልጅነቴ ለዚህ የዳረገኝ ይመስለኛል። ሱሳም ስትፈልግ ሰልፍ ጥራብኝ እንጂ እኔ የምነክርህ በዚህ መንገድ ነው። አለቀ። ስትፈልግ ስማኝ፣ ሳትፈልግ ተግማማ። ለደንታህ ነው።
"…ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፥1114
“…የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።” 1ኛ ጴጥ 4፥3
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ድርጅቱ ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
"አሸበርቲው አስነቀልቲው"
ነሐሴ ጳጉሜን 5/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…ዛሬ ጳጉሜን ፭ ከሱስ ሁሉ የምንላቀቅበትን ዕለት ስናስብ፣ ስንዘክር፣ ቃል ስንገባ፣ ስንወስን የምንውልበት ዕለት ነው።
"…ለዚህ ርዕስ የሚሆን ሱሰኞች ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩብኝን ጠጠር ያለ ርእሰ አንቀጽ ጽፌ አዘጋጅቼ ላቀርብላችሁ ነኝ። እናንተስ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
"…አንድ ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ። "ዘመዴ የቀበሮ ሜዳን የተማሪዎች ዩኒፎርም አሰባስበህ እስክትጨርስ ድረስ እንዲህ ዓይነት ነገር ባትጽፍስ ይለኛል። እኔም ለደንታው ነው ብዬ ምክሩን ጥሼ ጽፌዋለሁ። ለተፈናቃዮቹ የቀረኝ ዩኒፎርም ብዛት ትንሽ ነው። በዚህ ምክንያት ተናድዶ አልረዳም የሚል ለደንታው ነው። ሲፈልግም በአናቱ መተከል ይችላል። እኔ ግን ጽፌዋለሁ። እናንተስ ለማንበብ፣ አንባችሁም የመሰላችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ?
•,እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…? 😂😂
ልናገባድደው ነው…!
"…በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቅለው ለሚገኙ ህፃናት ተማሪዎች የደብተር መያዣ ቦርሳውን ጨቅጭቄአችሁ አስገዝቼአችሁ። አቶ ቴዎድሮስ መለስ ከስዊድን የተማሪዎቹን ሙሉ ደብተር፣ እስራስና እስኪሪብቶ ዘግቶላቸው በደስታ በቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሬ ላይ አስለቀሰኝ፣ የቀረኝ የተማሪ ደንብ ልብስ ነበር። እሱንም አሁን ነግሬአችሁ ጀምሬው ነበር።
"…የመረጃ ቲቪዎቹ የቀድሞ መሥራቾች ወሮ መሲና ሶል በ2ሸ$~ የሦስት መቶ 342 ተማሪዎች ዩኒፎርም በመግዛት የጀመሩትን፣ የአማሪካ አስተናጋጄ ወሮ ሕይወትና ልጇ ዘላለም ብሩክ ከነቤተሰባቸው የ150 ተማሪ፣ ቴዲ ከስዊድን~ የ142 አቢሲንያ~ የ130፣ ንጉሤ~ የ91፣ እህትዓለሜ~የ100 ተማሪ፣ ዜና ሥላሴ~የ24 ቲጂ~የ24፣ ጥበቡ~የ20፣ ቲጂ~የ17 አጥላባቸው~17፣ መብራቴ~15፣ ቶማስ~14፣ ወልደ አማኑኤል~13 ኧረ ደከመኝ። እፎይ ቆይ ትንሽ ልረፍ። አይኔ ቦዘዘ፣ እንባ አቀረረ እኮ።
"…ለማንኛውም በዚህች አጭር የልመና መልእክት ብቻ ለ1,321 ተማሪዎች የሚሆን ዩኒፎርም መግዢያ አግኝቻለሁ። ከጠቅላላው 3,300 – 1321= የ1979 ተፈናቃይ ምስኪን ሕፃናት የተማሪ ደንብ ልብስ መግዢያ ይቀረኛል። ምን አላት። በተለይ እንደ ወሮ መሲ 2 ሺ ዶላር የሚሰጥ ከተገኘ፣ 1ሺ$፣ 500ም$፣ 2መቶና 1መቶ ዶላር የሚሰጥ ከተገኘ እስከ ነገ ድረስ የምንዘጋው ይመስለኛል። "…100 $ የ17 ተማሪዎች ዩኒፎርም ይገዛል።
• ዘመቻ 1,979 ይፋፋም…!!!
አራት ነጥቧ እዚህ ጋር ተስተካክላለች።
"…ትችቴ ቀላል ይመስላል። ነገር ግን ለሚገባው ከባድ ነው። እዚህ ፌስቡክ ላይ ጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት፣ ባለ ሥልጣን ሆነው በአማርኛ መልእክት ሲያስተላልፉ ሳይ አይኔን እንቅፋት ነው የሚመታኝ። አንድ አማርኛ አስተካክሎ የማይጽፍ ጋዜጠኛ ጋዜጠኛ ነኝ ሲል ያስቀኛል። ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጪው ኦሮሞ ላይ በነፍስ በሥጋው ጢባጢቤ ከተጫወተበት ነገር አንዱ ላቲን ቁቤ የተባለ ፊደል አምጥቶ አናቱ ላይ እንደ ቂቢ የመረገበት ነው። ዐማራና አማርኛን ጎዳሁ ብሎ ኦሮሞን ኪሣራ ላይ ነው የጣለው። ለምሳሌ፦
"…ለምሳሌ ይሄን የአቢይን ልጥፍ ብቻ ተመልከቱ። አማርኛው ዘርዘር ተደርጎ ተጽፎም 5 መስመር ሲፈጅ ቁቢቲ ግን ደብል ደብል ሆና እንደ ሞላ የታክሲ ተሳፋሪ ተደራርባ ታጭቃ ተጽፋ 9 መስመር መኘነው የፈጀችው።
"…ወያኔ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ለመነጠል ብላ በሠራችው ሴራ ዛሬ ኦሮሞ ሁለት መስመር ደብዳቤ ለመጻፍ አራት ሉክ፣ በአማርኛ 100 ገጽ የሚፈጅ መጽሐፍ 700 ገጽ እየፈጀ በሰው በጉልበት፣ በቀለም፣ በወረቀት ላይ ኦሮሞ ቢልዮን ብር እንዲከሰክስ አድርጎታል። ወያኔ ግን ያው በግዕዝ ፊደል እንደ አማርኛው ነው የምትጠቀመው። ኪሣራ…
"…ኧረ እኔ አሁን እዚህ ላይ ምንአገባኝ። ይልቅ የቀበሮ ሜዳ አጭር ሪፖርት ላቅርብና ምሽታችንን የተማሪዎቹን የደንብ ልብሶች በሟሟላት ደስ እያለን እናሳልፍ።
• ይሄን እርሱት ተዉት ይልቅ ጠብቁኝ የምሥራች አለኝ።
"…የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀናችንን ስናስብ የምንውልበት መርሀ ግብራችን በይፋ ተጀምሯል።
"…የፎቶ መላኪያ ሰንዱቁም ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ክፍት ነው። ተምነሽነሹበት። መንደሩን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማም አጥለቅልቁት።
• ክብር እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ላልካዱት፣ ላላዋረዱት ለዐማሮች።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
መልካም…
"…ይጠቅማችሁ እንደሁ ብዬ በማሰብ የእኔ የዘመዴን ዓመታዊ ዝርዝር የሥራ ዕቅዴን በርዕሰ አንቀጽ መልኩ ልጽፍላችሁ ነኝ።
• አላችሁ አይደል?
• በማይካድራ ቤት፣ ንብረትም ነበራቸው። ዝርዝሩን በሰፊው ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። አሁን ግን ሁሉን አጥተው ቀበሮ ሜዳ ነው ተፈናቅለው ያሉት። ሌሎች አባታቸው ያረፈ ልጆች ያሳድጋሉ። አግኝቶ ማጣትን የመሰለ ክፉ ነገር የለም።
"…ክፋቱ ደግሞ ይሄ ታዳጊ ልጃቸው የስኳር ታማሚ ነው። በየሰዓቱ ይርበዋል። ይጠማዋል። ጭንቁ ነገር እሱን ማብላት ነው። የሚያደርጉት ቢያጡ በጎንደር ከተማ ልመና ላይ ተሰማርተው የሰው እጅ ያያሉ። አግኝታችሁ አትጡ። ማጣትን በልጅነቴ ስለቀመስኩት ጭንቀቱን አሳምሬ ነው የማውቀው።
"…ባለፈው ዕሁድ እኔን በእኚህ እናት ቦታ ተክቼ ሳስበው በመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶች አስለቀሱኝ። እንባዬን ያዩ አንድ አባት ከሀገረ እንግሊዝ ጻፉልኝ። በየወሩ እኔ 50 ፓውንድ ተቆራጭ ላድርግላቸው፣ ልጁም ይታከም፣ ያማረውንም ይብላ አሉኝ። ደስም አለኝ። ሌላ አንዲት እህት 50 ፓውንድ ከዚያው ከእንግሊዝ በየወሩ ለመስጠት ቃል ገባች። መልሼ አላገኘኋቸውም እንጂ ሁለት ሰዎችም 50፣ 50 ዶላር ቃል ገብተው ነበር። ይሄን ሲያነቡ ይመጣሉ ብዬም አምናለሁ።
"…የሆነው ሆኖ ኮሚቴዎቹን እኚህን እናት ፈልጉአቸውና የምሥራቹን ንገሩልኝ፣ የባንክ ደብተር ካላቸውም ስጡኝ፣ ከሌላቸውም አውጡልኝ ብዬ ላኩኝ። እናትም ሲፈለጉ ጠፉ። የጠፉትም ልመና ወጥተው ነበር። የኋላ ኋላ ተገኙ። ተነገራቸውም። እሷቸውም ደስም አላቸው።
"…አሁን ከላስቲክ ቤት ወጥተው አነስተኛ ቤት ጎንደር ላይ ይከራያሉ። ለልጆቻቸው ቀለብም ይገዛሉ። እኚህን አግኝተው ያጡ የጎንደር ዐማራ እናት ከልመናም፣ የሰው ፊት ከማየትም አዳንናቸው ማለት ነው። በእውነት ወላጅ እናቴን የደረስኩላት ያህል ነው የተሰማኝ። ከምር ከተባበርን የብዙ ምስኪን ተፈናቃዮችን ሕይወት መቀየር እንችላለን።
• በማርያም ለጋሾቹን መርቁልኝ። 🙏🙏🙏
"…15 ሺ ሰው ርእሰ አንቀጹን ማንበቡን እያየሁ ነው። እስከ አሁን ብው😡 ብሎ የሚናደድ ሰው ብጠብቅ፣ ብጠብቅ ላይ አልቻልኩም። ተናዳጆቹ ምነው ጠፉብኝሳ። ምንአልባት ከአሁን በኋላ ይመጣሉ ብዬ ተስፋ ላድርግ እንጂ የሚበሳጭብኝ አጥቼ በጣም እየተቸገርኩ ነው። ምን ባደርግ ይሻለኛል?
"…ለማንኛውም ተራው የእናንተ ነው። እናንተ ደግሞ ሓሳባችሁን የምትሰጡበት። ጎንደር ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃይ ሕፃናትን የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በመግዛት 2017 ዓምን በተስፋ ሙሉአቸው። 100 ዶላር 17 ተማሪዎችን ያለብስላችኋል።
• አስተያየታችሁን እየኮሞኮምኩ ምሽቴን አድምቄ አሳልፋለሁ። ጀምሩ…✍✍✍
👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ክንድህን ዘርጋልኝ ብሎ መነሣት ብቻ ነው የሚያዋጣው። አዎ እንዲያ ብሎ ሱሪውን ታጠቆ፣ ቀበቶውን አጥብቆ የተነሣው የዐማራ ፋኖ ብቻ ነው በትክክለኛው ምህዋር ላይ ያለው። በዱላ፣ በቆመህ ጠብቀኝ፣ በክላሽ የጀመረው ትግል ዛሬ ሞርታርና ዲሽቃ፣ ዙ 23 ጭምር እስከመታጠቅ የደረሰው በዚያ መንገድ ሂዶ ነው። አሁን ወረዳ፣ ቀበሌ፣ ዞንና ከተሞችን ተቆጣጥሮ እስከ ማስተዳደር የደረሰው፣ በምርጫ የማይለቅ፣ በጸሎትም፣ በጠበልም የማይለቅ፣ በሰበካም፣ በንግግርም የማይሰማን አረመኔ አገዛዝ ማስለቀቂያ ምሱን አጅሬ የፋኖ ስላገኘው ነው። የነፃ መውጫ መንገዱ የፋኖ መንገድ ብቻ ነው። የፋኖ መንገድ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ሰው የሆኑትን የዘመኑን አውሬዎች በሙሉ ያስተነፍሳቸዋል። ያጸዳቸዋልም። በአንድ ዓመት ከዚህ የደረሰው የዐማራ ፋኖ ትግል በሚቀጥለው ዓመት የሚደርስበትን ቁጭ ብሎ ከዳር ቆሞ ከመጠበቅ ጠጋ ብሎ መሳተፍ ነው።
"…እናም ዘመንህን የምታሳምረው አንተው ነህ። የአንተን ዘመን የሚያሳምርልህ ሌላ ኃይል የለም። ባለሁበት ሀገር በሀገረ ጀርመን ቀደምት አባቶቻቸው በሠሩት ሲስተም ዘመናቸውም፣ ሀገራቸውም አምሮላቸው እንዴት እንደሚያስቀኑ አትጠይቁኝ። እነሱም ዓለም የሚያውቀው የጨለማ፣ የሰቆቃ፣ የውድመት ዘመንን አሳልፈዋል። ጀርመኖቹ የፈራረሱ ከተሞቻቸው ዛሬ ለላንቲካ፣ ለቅርስ፣ ለታሪክ ከሚታዩቱ በቀር የሉም። በባቡር ከጀርመን ወጥቼ ወደ ጀርመን መግባቴን ማንም ሳይነግረኝ፣ ጽሑፍ ሳላነብ የማውቀው በቤቶቹ ውበት፣ በመንገዶቹ ጥራት ነው። በጀርመን ለዓይንህ የሚታይ በቀንም ቢሆን ብርሃን ይበዛል። የመብራት ብርሃን አይደለም። የፀሐይም አይደለም። ቤቶቹ፣ መንገዱ፣ ሰፈሩ ሁሉ የብርሃን ቀለም የተሞሉ ናቸው። ይሄ የሆነው ጀርመኖቹ ወጥረው ሠርተው፣ የሕግ የበላይነትን አስከብረው፣ ሁሉም ሰው ከሕግ በታች መሆኑን አምነው፣ ተማምነው የማይነቃነቅ ብረት የሆነ ሲስተም ዘርግተው ነው። በጀርመን ጥንብዝ ያለ ሰካራም፣ በሐሺሽ የጀዘበም፣ አዕምሮውንም የሳተ ዕብድ ጫፍህን አይነካም። ይሁነኝ ብሎ ከስንት አንድ ወንጀለኛ ቢኖርም በጀርመን ግን የታዘብኩት ይሄንን ነው። እብዱም፣ ሰካራሙም አዕምሮ ውስጥ የሕግ የበላይነቷ ታትማ ስህተት አታሰራውም። ታስታውሰዋለች። በጀርመን ማን ሰደበህ ሳይሆን ማነው እጁን የሰነዘረብህ ተብለህ ነው የምትቀጣው። ህፃናት አረንጓዴ መብራት ሳይበራ ውልፍት አይሉአትም፣ እናት የባቡር ትኬት ሳይኖራት ልጇን በነፃ ይዤ ሸውጄ እሄዳለሁ ብትል ለፖሊስ አሳልፎ የሚሰጣት የራሷ ልጅ ነው። በጀርመን የደንብ ልብስ የለበሰ ፖሊስ የምታየው አልፎ አልፎ ነው። በጀርመን ሁሉም ዜጋ የፖሊስን ሥራ በንቃት የሚሠራ ነው። እንጂ 1ሚልዮን ትግሬ ጨፍጭፎ ሲያበቃ ፈገግ፣ ፈካ፣ እያለ ትግሬዎቹን ራሱ ሰብስቦ ፀባይ ካላሳመራችሁ ሌላ እልቂት እንዳልጨምርባችሁ ተጠንቀቁ እያለ የሚያስጨበጭብ ደፋር ዘና ብሎ የሚኖርበት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።
"…እናም ወዳጄ አንተ ሳትለወጥ ዘመኑ አይለወጥብህ። ዘመኑን ውብ ማድረግ የምትችለው ራስህ ነህ። ዘመኑን ግማታም፣ ጨለማ፣ ሸታታ፣ ክርፋታም የምታደርገውም አንተው ነህ። ባቄላ ስትቆረጥም ውለህ ገማኝ፣ ሸተተኝ ብሎ ነገር አይሠራም። ቅድሚያ አንተ እንደ ሻማ ለመሆን ወስን፣ ለነገ ትውልድ ካሰብክ ዛሬ አንተ ሻማ መሆን አለብህ። ሳትንቀሳቀስ ለውጥ የለም። መሬት መሬት አቀርቅረህ እየሄድክ ሚስት አታገኝም። ባልም አይገኝም። ቀና በል፣ ዞር ዞር በል። አካባቢህን ቃኘት አድርግ። ያለ ሰላም ሥራ የለም። ተዘዋውረህ ካልነገድክ፣ ካልተማርክ እድገት የለም። ከጳጉሜን 1 እስከ መስከረም 17 የእሬቻ ዋዜማ ድረስ በኦሮሚያ መኪና ማንቀሳቀስ፣ ተዟዙሮ መነገድ፣ ምግቤት፣ የሸቀጥ ሱቅ፣ ባንክና ትራንስፖርት መሥራት አትችልም የሚልህን ደደብ ታግለህ አፈር ደቼ ካላበላህ በቀር በቁምህ ሟምተህ ነው የምታርፈው። ደናቁርት የሆነ የጋርዮሽ ሥርዓት የሆኑ ቡድኖች በደደቡበት ሀገር አብረህ አትደድብ። ተንቀሳቀስ። ይሄን ኋላቀር ፀረ ሰው አስተሳሰብ ይዞ የሚንቀሳቀሰውን ድባቅ ምታው። ደምስሰው። አለበለዚያ 2017 ዓመተ ምሕረትንም እንደ 2016 ዓም ስታማርር፣ ስታለቅስ ነው የምታሳልፍ። ዘመኑን ቀይረው። ውብ አድርገው። ፀረ ሰው ኃይሎችን ጉልበት አሳጣቸው። ተማሪዎች በብራኑ ነጋ ሙድ መያዝ ትታችሁ ወይ ለለውጥ ተንቀሳቀሱ አልያም በብራኑ ጁላ ስር ታቅፋችሁ የጦስ ዶሮ በመሆን ለመዋጥ ለመሰልቀጥ ተዘጋጁ። አታሹፉ።
"…ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት እልል ብለህ ንገሥብን ብለህ ማንነቱን ሳትመረምር፣ ከየት መጣ ማነው? እንዴት ነው? የት ነው? ሳትል በፈቃድህ አናትህ ላይ ያወጣኸው አቢይ አመድ መጀመሪያ በሶማሊያ ክልል ካህናት አርዶ፣ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥሎ፣ አውድሞ፣ ዜጎችን ጨፍጭፎ ነው ሥራ የጀመረው። ያኔ ወያኔ የተባለ የጦስ ዶሮ ስለነበር በእሷ ይሳበብ ነበር። ከዚያ ቀጠለና በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ በከታ፣ በአሸዋ ሜዳ የደቡብ የጋሞ እና የወላይታ ተወላጆችን ያለከልካይ ጨፈጨፈ፣ አጸዳ፣ አወደመ፣ በሰሜን ሸዋ አጣዬን አቃጠለ፣ አወደመ፣ በኦሮሚያ ሙሉ ዐማራና ኦርቶዶክስን፣ በወለጋ በተለየ መልኩ የወሎ እስላም ዐማሮችን ጨፈጨፈ። በመተከል ዐማራና አገው በግሬደር ተቀበሩ፣ በሲዳሞ ሳይቀር የሲዳሞ ጴንጤ ዐማራና ጉራጌን አረደ፣ አወደመ። በወለጋ ሙሉ ቀበሌ ሰው ጨፈጨፉ፣ ቀጥሎ የዐማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማሳገት በየዩኒቨርስቲው ጎበዝ ተማሪዎችን ከፎቅ ገፍትሮ መግደል፣ ብጥብጥ በማስነሳት በፖሊስ በማስደብደብ ሙሉ የዐማራ ተማሪዎች ከትግራይና እና ኦሮሚያ ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ ተደረገ።
"…የአቢይ አህመድ አገዛዝ በግልጽ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጣልቃ በመግባት ለማፍረስ ተንደፋደፈ፣ የጨረቃ ጳጳሳትን ሾመ፣ በሻሸመኔ ምእመናንን በገጀራ፣ በጥይት በመቅደሱ ጨፈጨፈ፣ በዓለምገና፣ በአሰበ ተፈሪ፣ በሐረር ኦርቶዶክሳውያን ታረዱ፣ መነኩሴ መውገር፣ ቄስ በአደባባይ በጥፊ በመምታት የክህነትን ክብር ለማሳጣት ለዓለም ሁሉ አሳየ። ቀድሶ፣ አቁርቦ ወደ ቤቱ የሚሄድ አረጋዊ ካህን በድንጋይ ቀጥቅጦ በመግደል ጭካኔን ለዜጎች አስተማረ። ሲጠቀምባቸው የቆያቸውን ጳጳሳት ሀገር ቤት እንዳይገቡ ከለከለ፣ ከአየር መንገድ አንጠልጥሎ በመጡበት አዋርዶ መለሰ፣ ሥልጣኔን በኃይል እቀማለሁ የሚል ከመጣ በቀን ውስጥ መቶ ሺዎችን አርዳለሁ ብሎ በቴሌቭዥን ለመቶ ሃያ ሚልዮን ዜጎች ዐወጀ፣ በኦሮሚያ ዜጎች መቱን በመደዳ ታርደው አየን፣ የዝቋላ ገዳም አባቶች በአቢይ ሸኔ አራጆች ተከታትፈው ታርደው አየን።
"…የክፍለ ሀገር አገር አቋራጭ መኪኖችን ማቃጠል፣ ቀጥሎ ሾፌሮችን ማገት፣ ቀጥሎም ሾፌሮችን አነጣጥሮ መግደል በኦሮሚያ ፋሽን ሆነ፣ ሕፃናትን ማሳገት፣ ሕፃናትን ማረድ፣ ሕፃናትን ደፍሮ መግደል ወዘተ የመሳሰሉ ዘግናኝ አረመኔያዊ ወንጀሎች ከአቢይ አሕመድ ሥርዓት ጋር አብረው መጡ። ትግሬ የሆነ ሰው ከነ ነፍሱ በቁሙ በመተከል ጫካ የአቢይ አህመድ ወታደሮች ሲያቃጥሉት ታዩ። ድርጊቱን ያወገዙ ሁሉ ታሰሩ፣ ፓትርያርኩም ተወገዙ፣ በእነ ታዬ ቦጋለ፣ በእነ ስዩም ተሾመ፣ በእነ ቶማስ ጃጀው፣ በእነ ዳንኤል ክብረት ተሰደቡ። ተዋረዱም። ጴንጤው ናትናኤል መኮንን ማይም ቢሆንም በጋርድ እንዲንቀሳቀስ የተደረገው በአቢይ ዘመን ነው።👇④ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍
"…ዘመናት ሲቆጠሩ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው። ሁልጊዜም ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር ጳጒሜን 6 ትሆናለች። ይህ እንዴት ሆነ? 3ቱ ዓመታት (ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ) 365 ቀናት ከ6 ሰዓት ይይዛሉ። ስለዚህ የሦስቱ ዓመታት የ6 ሰዓታት ጥርቅም 18 ይሆናል። ዘመነ ሉቃስ ተገባዶ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር 18+6=24 ሰዓት (አንድ ቀን) ይሆናል። ስለዚህ በየአራት ዓመቱ ጳጉሜን 6 ትሆናለች። በፈረንጆቹ leap year ይሉታል እሱም February ወር 29 ቀናትን ይይዛል። በእኛ መጠነ ራብዒት ማለትም ዘመነ ዮሐንስ የሚውልበት ነው።
"…ቀደምት አባቶች ጳጒሜን 7 ቀናትን የምትይዝበት ዓመት እንዳለ ጽፈው አስቀምጠዋል። ይህም በ600 ዓመት አንዴ ይከሰታል። በቀን በ24 ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 0.4 ሰከንድ አለ። ሪና መዐልትና ሪና ሌሊት የሚል ሌላም ስሌት አለ። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አንድ ዓመት 365 ቀናት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይንም 365 ቀናት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው። ስለዚህ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ተጠራቅሞ ጳጒሜን 7 ያደርጓታል። ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ማለት ነው። የ5 ዓመት 30 ካልዒት የ10 ዓመት 60 ካልዒት ነው። 60 ካልዒት ደግሞ 24 ሰከንድ ነው። የ100 ዓመት 240 ሰከንድ ወይም 10 ኬክሮስ የ200 ዓመት 20 ኬክሮስ፣ የ300 ዓመት 30 ኬክሮስ፣ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፣ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፣ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ። 60 ኬክሮስ 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ይሆናል።ስለዚህ በ600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጒሜን 7 ይሆናል። እንዲህ እንዲህ እያለ ዘመን እየተቆጠረ እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ትውልድ እየተፈራረቀ ይቀጥላል። ጊዜን ማስቆም፣ ዘመንን ማቆም አይቻልም።
"…ያለፈው ዓመት ምን ዓይነት አሻራ ጥሎብን አለፈ? ባለፈው ዘመን ምን በጎና መጥፎ ኩነት ተፈጸመ ብለን መገምገም ለወደፊቱ ዘመን እንዴት ካለፈው ስህተት ተምረን እናልፍ ዘንድ ጠቃሚ ይሆናል። በዘመናት ውስጥ ያየን እንደሆነ ሁሉም ሰው በየዘመናቱ ያሳለፈው የደስታና የመከራ ታሪክ ስላለው የሚያወራው አያጣም። ገሚሱ 2016 ዓም የስኬት፣ የደስታ፣ የሐሴት ዘመኔ ነበር፣ በልጅ፣ በትዳር፣ በሀብት፣ በጤና፣ በሥራ የተባረኩበት ዓመተ ምሕረት ነበር። ስስቅ፣ ስደሰት፣ ሳመሰግን ነው ያሳለፍኩት የሚልና በእውነትም በዚህ መልክ ያሳለፉም ይኖራሉ። አሉም። እነርሱ 2016 ዓመተ ምሕረትን በማይረሳ የደስታ፣ የብርሃን፣ የሐሴት፣ የስኬት መዝገብ ውስጥ መዝግበው ነው ሲያስታውሱት የሚኖሩት። ለምን ሆነላቸው ብሎ የሚቀናው ሰይጣን ብቻ ነው። እንኳን በደስታ አሳለፋችሁ።
"…ሌሎች ደግሞ አሉ። ያለፈው ዓመት ሲኦል ሆኖባቸው የነበር፣ ምድር ተከፍታ ብትውጠን፣ ተራሮች ቢጫኑን፣ ሰማይ ቢከደንብን፣ ከዚህ መከራ፣ ከዚህ መዓት፣ ከዚህ ሁላ ጭንቅ ማነው የሚያወጣን? ብለው ዓመቱን በሙሉ በፍርሃት፣ በስጋት፣ በልቅሶ፣ በዋይታ፣ በጥም፣ በራብ፣ በህመም ያሳለፉ። አሉ ዛሬ ላይ ቆመው ያለፈውን ዓመት ሲያስታውሱት ፍርሃት የሚሰማቸው፣ ጭንቀትም የሚታይባቸው፣ ሲያስቡት እና ሲያስታውሱት እንኳ አሁን እንዳለ እንደሆነም ቆጥረው የሚዘገንናቸው የትየለሌ ሰዎች አሉ። ዓመታት ለሰው ልጆች ጫፍና ጫፍ በቆመ ሚዛን ላይ ሆነው ነው የሚታዩት። ያለፈው ዓመት ለአንዱ ብርሃን፣ ለሌላው ጨለማ ሆኖ ነው ያለፈው።
"…መልካም አስተዳደር፣ ጥሩ መንግሥት ሲኖርህ፣ ፍትሕ የነገሠችበት፣ ሕግ የሁሉም የበላይ በሆነበት ሀገር ስትኖር ዓመታቱ ብሩህ ናቸው። ዓመቱ ለምን አለቀ ብለህ ትቆጫለህ። መጪውንም ዓመት እንዳለፈው ዓመት ውብ ሆኖ እንዲያልፍ ትጥራለህ። ሰው በተፈጥሮው አንድ ቦታ እንደ ከብት ታጥሮ መኖር፣ መቀመጥ አይፈልግምና ነፃ ፍጡር ስለሆነ ተዘዋውሮ መሥራት፣ መዝናናት፣ በሀገሩም ልቡ ከፈቀደበት፣ ለጤናው፣ ለኑሮው ይስማማኛል ብሎ ባሻው ሥፍራ በሚኖርበት ሀገር ዓመታቱ ብሩህ ናቸው። ካሊፎርኒያ ያልተመቸው ሰው ኒውዮርክ ልሂድና ልኑር ማለት መብቱ በሆነበት ሀገር፣ የጸጥታ ችግር ችግር በማይሆንበት ሀገር ስትኖር ነው ከምኔው 7፣ 8 ዓመት የሞላኝ ብለህ ያለፉትን ዓመታት እንደ ትናንት የምትቆጥረው። ይሄ በሀገሬ ይታሰባል ወይ ነው ጥያቄው። በጭራሽ። በቀበሮ ሜዳ፣ በደብረ ብርሃንና በጃራ፣ በትግራይ መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ዜጎች ሌሊቱ የአንድ ዓመት ያህል ነው የሚረዝምባቸው። ቀኑም እንደዚያው። በሙስና ብር፣ በታገተ ሰው ገንዘብ ሽቶ እየተራጨ የሚኖር ሌባ ዘራፊ ወንበዴና እነሱ እኩል አይደለም ሌትና ቀኑን የሚያሳልፉት።
"…የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተት፣ በረዶ፣ ውርጭ፣ ዶፍ ዝናብ፣ ደርቅ፣ ወረርሽኝ ወዘተ ሲከሰት በመንግሥት ልትማረር አይገባም። እርግጥ ነው በደጃፋችሁ ያለውን ቱቦ መዘጋጃ ቤቱ ባለ ማስተካከሉ በሚመጣ የጎርፍ አደጋ መዘጋጃ ቤቱ ሊወቀስ ይችል ይሆናል። የተፈጥሮ ደደጋን አደጉ፣ ሰለጠኑ፣ በቴክኖሎጂ መጠቁ፣ በሀብት ደረጃቸውም ላይ ደረሱ የሚባሉ ሀገራትም ቢሆኑ ሊቆጣጠሩትና ሊያስቀሩት አይቻላቸውም። የፈጣሪን ቁጣ በጸሎት ካልሆነ በቀር በወታደር፣ በበጀት፣ በባለሙያ አትመልሰውም። የጃፓንን ሱናሚ፣ የአሜሪካን ቶርኔዶ በየትኛውም የሰው ልጅ ሥልጣኔና በየትኛው በጀት ነው የምትመልሰው? ቁጣው እስኪበርድ ከመጸለይ በቀር ምንም መፍጠር አትችልም። ዓባይ ወንዙ ሞልቶ ሱዳንና ግብጽ ቢጥለቀለቁ፣ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ኦሮሚያ፣ አፋርና ሱማሌ ቢጥለቀለቁ፣ መቶ ሺ እንስሳት፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ቢሞቱ፣ ንብረት፣ የሀገር ሀብት፣ ሰብል፣ መሰረተ ልማት ቢወድም በማን አባክ ታሳብባለህ? በማንም፣ በማንም አታሳብብም። ተፈጥሮ ነው። አለቀ።
"…በህወሓት ጥጋብ፣ በአቢይ አሕመድ ድንቁርና 1 ሚሊዮን ትግሬ ጭፍጭፍ ሲደረግ ግን ይሄ የፈጣሪ ቁጣ ነው ተብሎ መውሰድ ኃጢአትም ወንጀልም ነው። በኦሮሚያ ዘር ለይቶ መግደል፣ ማፈናቀል፣ ነፍሰጡር እናት ማረድ፣ አርዶ ጽንሱን መብላት ይሄ የፈጣሪ ቁጣ ነው ተብሎ ቁጣህን አብርደው የሚል ክሊፕ በመልቀቅ የሚታለፍም አይደለም። በጣትህ መሬቱን በስተህ በቆሎ በምትዘራበትና ምርት በምታፍስበት ወለጋ ላይ ራብ ተከሰተ ሲባል ስትሰማ ይሄ የእግዚአብሔር ቁጣ አይደለም። ጎተራ ሙሉ እህል አቃጥለህ፣ አራሽ ገበሬውንም፣ ጥማድ በሬውንም አርደህ በልተህ ምርት ጠፋ፣ ምርት ቀነሰ ብለህ እግዚኦ ብትል ይሄ የፈጣሪ ቁጣ አይደለም። ይሁነኝ ብለህ ሁከት፣ ጦርነት ጭረህ፣ አምራቹን ኃይል የምርት ግብዓት ከልክለህ መሬቱን ጦም አሳድረህ ስታበቃ፣ ጤፍ ኩንታሉ 30 ሺ ብር ገባ ብለህ ደረት እየደቃህ ብታለቃቅስ ይሄም የእግዚአብሔር ቁጣ አይደለም። የአቢይ አሕመድን ወንጀል፣ የአገዛዙን ድክመት፣ የአስተዳደን ማይምነት በፈጣሪ ቁጣ ማሳበብ ራሱ ሰገጤነት ነው። አገዛዝ የፈጠረውን በፈጣሪ የምታላክክበት ምክንያት የለም። ወንጀሉን የፈጠረ፣ የፈጸመ፣ ያስፈጸመ እገሌና እገሊት የሚባሉ ተጠያቂዎችን አስቀምጠህ የምን ፈጣሪን መውቀስ ነው። ቀልደኛ።👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በጤና አሸጋገረን አሸጋገራችሁ። መልካም በዓል።
"…ሁለት ነገር አሰብኩ። አሰብኩና ልጽፍላችሁ ወደድኩ። እዚህ ባለሁበት ሀገር የራሴ አዲስ ዓመት የለኝም። የለንም። እንቁጣጣሽ በሀገር ቤት ቀረ። ልጆች ትምህርት ቤት፣ ሚስት ሥራ፣ እኔም እንደዚያው። ምንአልባት ማታ ሁሉም ደክሞት ካልመጣ ለደቂቃዎች አብሮ ራት መብላት ቢኖር ነው። እንጂ ሌላ አታስቡ። ልጅና ቤተሰብ ያለው እንደምንም ሸውዶ ያልፋል። ከዚህ የሚከፋው ደግሞ በብቸኝነት የሚገፋው ወገኔ ነው። መሄጃ ከሌለው ዩቲዩብ ከፍቶ መቆዘም ነው።
"…እናም ዛሬ በርእሰ ዐውደ ዓመትን በተመለከተ ከድፎ ዳቦ ጋር፣ ከጠላ፣ ከጠጁ ከውኃው እየተጎነጫችሁ የምታነቡት ርዕሰ አንቀጽ ልጽፍላችሁ ወደድኩ። ዛሬ ጦም ስለሆነ ቁንጣን አያስቸግራችሁም፣ ሞቅም አይላችሁም ብዬ ነው።
"…ሌላው ዛሬም በቀበሮ ሜዳ ለተማሪዎቹ የጀመርነውን የዩኒፎርም ማሰፋት መርሀ ግብራችንን እንቀጥላለን። ጾም ስለሆነ ለማሰብ፣ ለመወሰንም ይመቻችኋል ብዬም ነው። 100 $ 17 ልጆች አልብሶ ተማሪ ያረጋቸዋል። ተስፋቸውንም ያለመልማል። 100 ዶላር፣ መቶ ዩሮ፣ መቶ ፓውንድ ሸክም ያቀላል። እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ርእሰ አንቀጹን እያነበባችሁ ተሳተፉ። ቃልም ግቡ። እኔ እመዘግባለሁ። በጣም ትንሽ ነው የቀረን።
"…እህሳ ጎዶኞቼ ፈቃደኛም፣ ዝግጁም ናችሁ? ዛሬ ስለ ዘመን መለወጥ ልጽፍላችሁ ነው የፈልግኩት። ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
• አንድ መቶ ያህል ሰው ዘመዴ ዝግጁ ነነ ካለኝ በኋላ እለጥፍላችኋለሁ።
የቀበሮ ሜዳ ሪፖርት…
"…ሁሉ ተሟልቶ፣ ሁሉ ተዘጋጅቷል። ሰንጋዎቹም ተገዝተዋል። 4ቱ ለቀበሮ ሜዳ፣ አንዱ ለአብረን እናካፍል ለአዕምሮ ህሙማን ድርጅት ተበርክቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። የሚቀረን የ3,300 ተማሪዎች ዩኒፎርም ነው። ከዚህ ላይ እስከአሁን በትክክል ደጋግሜ ስቆጥረው ውዬ የ1,494 ተማሪዎች ለመግዛት ቃል ተገብቷል። የሚቀረን የ1,806 ተማሪዎች ዩኒፎርም ነው።
"…ሌላም የምሥራቾች ከቀበሮ ሜዳ እየሰማሁ ነው። የጎንደር ከተማ አስተዳደርም ሆነ የጎንደር ከተማ ሕዝብም በተሠራው ሥራ ደስተኞች መሆናቸውን እየሰማሁ ነው። ልጃቸው በስኳር ህመም የሚሰቃየው እናትም ቃል የገቡት ብሩን ልከውላቸው ነገ የፈለጉትን ያህል አውጥተው በስኳር ህመም ምክንያት የሚራብባቸውን ልጅም ሆነ ራሳቸውን፣ ቀሪ ልጆቻቸውንም በበቃኝ መመገብ እንዲጀምሩ፣ ህክምናውንም መከታተል ይጀምራል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ነገ ዐውደ ዓመት ነው። ነገን እረፍት እንወስድና የቀረውን ለማሟላት ከበዓል በኋላ ወደ ልመናዬ እመለስና የቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮችን ችግር እንዘጋለን። ሪፖርትም በይፋ እናቀርባለን። 1 ዩኒፎርም 700 ብር ነው። በ100$ 17 ዩኒፎርም ይገዛል። ያልረዳችሁ እርዱ። ከበዓል በኋላም ቢሆን ተሳተፉ። የኃጢአተኞች ሁሉ አለቃ ሆኜ ሳለሁ ሁሉ የተከናወነለት፣ ለምኖም የማያጣ እንደ እኔ እንደ ዘመዴ እንደ ሥላሴ በራሪያው የድንግል አሽከር እንደ እኔ እንደ የሀረርጌው ቆቱ እንደመራታው ዘመዴ፣ ባለማዕተቡ የምሥቅ ሰው ዕድለኛ የሆነ ግን ማን አለ?… ማንም የለም ባይ ነኝ። ስላላሳፈራችሁኝ ክበሩልኝ። ለምስኪኖች እንደደረሳችሁ ለእናንተም በጠራችሁት ጊዜ ሁሉ ፈጣሪ ይድረስላችሁ። በልጆቻችሁ ፊት አግኝቶ ከማጣት ይሰውራችሁ።
• መልካም ዐዲስ ዓመት።
የታሉ እነ ፍትህ ለፌቨን…!
"…ይቺ ኦርቶዶክሳዊት ሰንበት ተማሪ ልጅ ሰሞኑን ከ4 ቀናት በፊት ነው ጀቤቷ ወጥታ ታፍና ተወስዳ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ የተገኘችው።
"…ይህችን ኦርቶዶክሳዊት ታዳጊ ልጅ የገደሏት ሰዎች ደፍረው ጭምር፣ ዓይኗንም በሹካ ወጋግተው አፍስሰው እንደሆነም ተነግሯል። ግን ዐማራ ክልል ስላለሆነ ወንጀሉ የተፈጸመው አንድም ጃል አክቲቪስት ትንፍሽ አላለም።
"…አኬሩ የሆነ ቀን፣ የሆነ ጊዜ መገልበጡ አይቀርም። ግን መርጦ ማልቀስ ቢቀር ለማለት ነው።
• ዱላው ጎማ ነው አይደል?
"…ይሄ ቀፋፊ ነገር ዐማራ ክልል ቢሆን፣ ያውም ከዐማራም ክልል ጎጃም፣ ፖሊሱም ከነገደ ዐማራ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በማኅበራዊ ሚድያውም ሆነ በእነ ኢቲቪ ፋና ቴቪ ምን ይፈጠር ነበር ብላችሁ ትገምታላችሁ?
• OMN,KMN, ወዘተ ምን ይሉ ነበር?
• እነ ጃል ወያስ፣ ጃል ያያ፣ ጃል ሀፍታሙ፣ እነ ጃል ማኚቲስ፣ ጃልቲቲ ሮማንቲቲስ ምን ብለው ቲክቶኩን ይቀውጡት ነበር?
• አህመዲን ጀበል፣ ሙጂቦ፣ የሴቶች ጉዳይ፣ የእስልምና መጅሊስ፣ በቅርቡ ገሌ የገቡ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ የስልጤ ሙስሊሞች፣ ፕሮዎች ምን ይሉ ነበር?
• ኤርሚያስ ዋቅጅራና ገመድ አፍ ተብታባው የግብዳ ጩጬ አራስ መሳዩ አኞ ሞገስ ዘውዱስ ምን ብለው ይተነትኑት ነበር?
"…ዮናስ ቬጋስ የሻማ ማብራት፣ አዳነች አቤቤ ኮንዶሚንየም ትሰጥ ነበርን? ለልጅቷ አዝናለሁ ድርጊቱ ግን እንኳንም ጎጃም አልተፈጸመ።
"…ግንባሩና ባልደራስ ሁሉ ዘመነ ካሤ እኚኚ ይሉ ነበር። ብቻ መቺውም፣ ተመቺዋም እንኳንም ኦሮሞ ሆኑ። ቦታውም እንኳንም ኦሮሚያ ሆነ። እንቁጣጣሽ ይረበሽ ነበር።
"…ሁሉንም ዐማራ ላይ ጓ የሚሉ አክ እንትፍ ስቶችን ተዟዙሬ ሳይ ፀጥታ ሲያበዙ፣ ዝም ጭጭም ሲሉ ባይ እንዲያውም ልጅቱና ፖሊሱ ተጠቃቅሰው አጀንዳ ለመስጠት ድራማ የሚደርሙ ሁላ ነው የመሰለኝ። እደግመዋለሁ ይሄ ወንጀል እንኳንም ጎጃም ያልተፈጸመ፣ አያሌው መንበር ራሱ አረፋ እየደፈቀ ከች ይል ነበር።
• የምትደበደበው ልጅ ወንድ ቢሆንስ፣ መመታቷን እንጂ በምን እየተመታች እንዳለ የማያገናዝብ ሰው ፍልጥ መስሎት ይደነግጥ ይሆናል፣ እናም ተመቺዋ ወይም ተመቺው ከውስጥ የጎማ አለንጋው መከላከያ አድርጎ ቢሆንስ፣ የሚሉ ጨካኞችም ገጥመውኛል። ዱላው ግን ከምር ጎማ ነው?
• ፍትሕ ለእሕታችን፣ ለእናታችን። ምን አገባህ በለኝ አሉህ ደግሞ።
መልካም…
"…የዛሬውን መብረቅ ነጎድጓድ የመሰለ፣ ሱሰኞች ላይ የሰነዘርኩትን የጭቃ ዥራፍ ርእሰ አንቀጽ አንብበው ሲጨርሱ ብዙ ሱሰኞች ብው ብለው ይበሳጩብኛል፣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠሩብኛል፣ ሺሻ ቤት ያላቸው ቲክታከሮችም ፎቶዬን ዘቅዝቀው ቡቺ ቡቺ ብለው ይዝረከረኩብኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ስኳድም አኩርፎ ይሄ ተሳዳቢ ምናምን ይለኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን ወፍ የለም። ሙንኦኖነው? በሰላም ነው?
"…ለማንኛውም የአንድ 50 ያህል ሰዎችን አስተያየት እቀበልና ወደ ሌሎች ዜናዎቻችን እንሄዳለን። የቀበሮ ሜዳ ልጆቻችንን የጀመርነውንም ጉዳይ ወደ ማታ ላይ እንረባረብበታለን።
"…አትፍሩ፣ አትሽኮርመሙ፣ እናንተስ ስስ እንዴት እያደረጋችሁ ነው? …ሱስ አፈር ከደቼ ያበላቸው፣ ከሰውነት ተራም ያወጣቸው ሰዎችስ የሉምን? በመጪው አዲስ ዓመት አንተ ሱሰኛው ምን ወሰንክ? እስቲ ተንፍስ…!
• 1…2…3…ጀምሩ…
"ርእሰ አንቀጽ"
ETHIOPIA| ~ ለሚሂኢኢኢ ፍየሊት ጫታም ትውልድ የጦመርኩት ነው።
"…ዛሬ ጷጉሜን ፭ ከሱስ ለመላቀቅ የውሳኔ ሓሳብ የምናጸድቅበት ቀን ነው። በዚያውም ከዚሁ የውሳኔ ሓሳብ የማጽደቅ ጎን ለጎን ደግሞ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን ካለን አካፍለን አረጋውያንን የምንረዳበት፣ የምንጎበኝበትም ቀን ነው። እናም ለዛሬ ከሱሶች ሁሉ ቀፋፊ ስለሆነው የጫት ሱስ ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ደግሜ እለጥፍላችኋለሁ። ሲጋራም፣ ሃሺሽ ሺሻ፣ ካቲካላ ዝሙትም ያው ነው።
"…ጦማሩን እያነበባችሁ በሳቅ ፍርፍር እንዳትበሉ ተጠንቀቁ። እያጓራችሁም ሰው አትረብሹ። ለጫታሞች ግን SHARE በማድረግ ተባበሩዋቸው። ከምሳ በፊት ካነበባችሁት የምግብ ፍላጎታችሁን ሊዘጋ ስለሚችል ባታነቡት፣ ከምሳ በኋላም ከ30 ደቂቃ በኋላ ብታነቡት ይመከራል። ዘጋኝ፣ ዘጋኝ፣ ዘጋኝ እንዳትሉ ብዬ ነው።
"…ዛሬ አመስጋኙ ሁሉ ዘግይቷል። ምክንያቱም ደግሞ ሲመስለኝ በፎቶው ላይ የሚታየው የጫት፣ የሺሻና የሰካራሞች ፎቶ ስለሚያስደነግጥ ይመስለኛል። ይቀፍፋል ግን የግድ ማየት፣ ማንበብ ይጠቅማል። በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ለጫትና ለጫታም አግዛችሁ የሚሰድበኝ አይጠፋም። ስትፈልግ ለምን ጧ አትላትም ኬሬዳሽ…እኔ ደስ እያለኝ እንዲህ እጦምረዋለሁ።
"…ጫት ማለት የኢትዮጵያን ወንዶች በሙሉ ወንድነታቸውን ሰልቦ ቀምቶ ሰንርቆ ስንትና ስንት ጀግና ጀግና ወንዶችን እንደ ለማዳ ድመት ፍራሽ ለፍራሽ ሲያንደባል፣ ሲያንከባል የሚኖርረ ወኔ ሰላቢ፣ አነፋራቂ አደንዛዥ ዕፅ ነው። ጫት በክርስትናም ክልክል ነው። በእስልምናም ሃራም ነው።
"…ጫት ማለት የስንቱን ጀግና ወንድ መቀመጫውን ሳይቀር ክው ብሎ ደርቆ የተላገ፣ የተፋቀ የጣውላ እንጨት አስመስሎ በማሽላ እርሻ ውስጥ እንደተሰቀለ የግሪሳ ወፍ ማስፈራሪያ አሻንጉሊት በባዶ ሜዳ በነፋስ ጭምር እየታገዘ ሲወዛወዝ እንዲኖር አድርጎ እያዋረደ ያለ አደገኛ አደንዛዥና አጀዛቢ መርገምትም የሆነ ዕፅ ነው።
"…ጫት ጥንቱን የተፈጠረው ለፍየል ምግብነት ነበር። የፍየልን ፈንታ የተፈጥሮ ምግቧን ነው የኢትዮጵያ ሰው በግፍ በአደባባይ መንግሥት ባለበት ሀገር ቀምቶ የወረሰው። ወርሶ መች በዚያው ቀረ? ለቅርብ ጎረቤት ሀገራት ለየመን፣ ለጅቡቲና ለሱማሌ በእርጥቡ፣ ለአማሪካና ለአውሮጳ ለአውስትራሊያና ለአረቦች ደግሞ ጫቱን አድርቆ፣ ወቅጦ፣ ፈጭቶ በዱቄት መልክ አሽጎ እየላከ በመአብቸብ ስንቱን ስደተኛ ያጀዘበ ዕፅ ነው። ክቡር የሆነው የሰው ልጅ የፍየልን ምግብ በግፍ ቀምቶ በመብላቱ ተዋረደ፣ ክብሩንም አጣ፣ ዓይኑ ፈጠጠ፣ ጥርሱም ገጠጠ፣ ሻገተ፣ ገማ፣ ከረፋ፣ ሸተተም፣ ረገፈ። እንቅልፍ ያጣ ፈጣጣ ጀዝባ ፍጡርም ሆኖ ቀረ። ጀዝባ።
"…ጫታሞች ሲበዛ አልቃሾች ናቸው። ደግሞም በባዶ ቤት የሌለ ህልመኛም ጭምር ናቸው። ጫታሞችን በምርቃናና ሺሻ ቤት ተቀምጠው በአንድ ጊዜ ቢልጌትስንና አላሙዲንን ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው እያረኩ እንዲያስደስቱም የሚገፋፋቸውም ይኸው ወስዋሽ ሰይጣናም የሆነ ዕፅ ነው። በጫት ምርቃና የተደረሰ የፊልም ድረስት፣ የዘፈን ግጥምና ዜማ እንዲሁ በማሽተት ይታወቃል። ዜማው ዝሙት ነው፣ በትዳር ላይ ማማገጥ የበዛበት ፊልም ካያችሁ የጫት ምርቃናና የሺሻ አጫጫሿን ቀዮ ገላ እያየ በምርቃና ለሃጩን ያዝረከረከ ህልመኛ ደረሲ የደረሳቸው የድርሰት ውጤት መሆናቸውን ማወቅ ይገባል። ጫታም ደራሲ ካለ ዝሙት፣ ካለማማገጥ ሌላ አይታየውም። ይሄ ዝሙታም።
"…ጫት የሱሳ ሱሶች ሁሉ ሰብሳቢ ማግኔትም ነው። ጫት ሲጋራንና ሐሺሽን ያስከትላል። ከዚያም ለጨብሲ ብሎ ካቲካላ አምቡላን አረቄንም የሚስብ ማግኔት ነው አጅሬ ጫት። ጫት ቀላል አይምሰልህ። አዳሜ እና ሔዋኔ ሁሉ ይሄን ሁሉ የሱስ መዓት በላዩ ላይ እንዲከምር እና እንዲግፍ፣ የሱስ ጎተራም እንዲሆን ያደርገውና ከዚያ ሱሰኛው ሁሉ በየጎዳናው ሲያስመልስ፣ ከስልክ እንጨትና ከፖሊስ ከመንገደኛ ጋር ሲጋጭ፣ በሌባ ሲበረበር፣ ከቱቦ ሲደፋ፣ ክብሩን አጥቶ እንዲኖር ሲሚያደርግ፣ ከጋለሞታም ጭን ስር ሳይወድ በግዱ እንዲወሽቅ፣ በዝሙት ጦር እንዲወጋ የሚያደርግ አደገኛ ዕጽ ነው። በተለይ ለክርስቲያን ጫት አዋራጅ ነው። ግማቱም አይጣል። ክርፋቱ።
"…የጫት ሱሰኛ የሆነ ወንድና የሆነች ሴት ታመው ለሀኪም ምርመራ ሰገራ አምጡ ቢባሉ እንኳ የገዛ ሰገራ አይኖራቸውም። ሰገራ የላትም። ቢኖረውም በመከራ፣ በስቃይ፣ በስንት ምጥ ነው የሚመጣው ይላሉ የጫት ሱሰኞቹ። የጫት ሱሰኛ የሆነ ግለሰብ ከአንተ ቀድሞ መጸዳጃ ቤት ከገባ አንተ ያለህ ምርጫ እርምህን አውጥተህ ኮንትራት ታክሲም ጠርተህ፣ ራቅ ያለ ጫካ ወይም ከመኖሪያ ቤትህ ብትሄድ ይቀልሃልም ይላሉ። ጫታም መጸዳጃ ቤት ገብቶ 4 ሰዓት ሙሉ እንደ ወላድ ሴት የሌለውን ካካ እንዲኖረው በመመኘት እንደ ወላድ ሴት ሲያምጥ ለመኖር በራሱ ላይ የፈረደ፣ ራሱንም ለመከራና ለምጥ ፍርድ አሳልፎ የሰጠም ጉደኛ ነው። ጫታም ሰው "የወንድ ምጣም" ነው ይላሉ። ጫታሞቹ።
"…ጫታምን ሰው አፉ እንዲከረፋ፣ እንዲሸት፣ እንዲገማ፣ እንዲጠነባ ያደርገዋል። የጫታም ሰውን አፍ እንደፈነዳ ሽንት ቤት ቁጠሩት። ቁናሱ አይጣል ነው። ጫታም በጫት ጥርሱ እንዲቦሮቦር እና ለጥርስ ህመም እንዲጋለጥ ያደርገዋል። ጫታም ሰው ከሰው መሃል ጮክ ብሎ ማውራት እንኳ አይችልም። ገርልፍሬዱንም ሆነ ያገባትን ሚስቱን ከንፈሯን መሳምም አይችልም። የራሱን ልጆችም ሆነ የሌላ ሰው ልጅ ዓይቶ መሳም፣ ማድነቅም አይችልም። በአፉ መጥፎ ጠረን ምክንያት ሲሳቀቅ ይኖራል። ጫት የ40 ዓመቱን ጎልማሳ ጎሮምሳ ከ30 ኪሎ የቀለለ ገለባ ያደርገዋል።
"…ጫታም ሰው መውለድም ማስወለድም አይችልም። ነገርየው አይታዘዝለትም ይላሉ በዘርፉ ብዙ ያጠኑ የመራቢያ አካላትን እንቅስቃሴ የሚያጠኑ ባለሙያዎች። የጫታም ሚስት ጫታም ባሏ አጠገብ ተኝታ ስትቃጠል ነው የምታድረው። ስትነድ ነው የምታድረው ይባላል። ሞቷላ። እንደ አጋጣሚ፣ እንደ ዕድል ሆኖ በድንገት ቢያስወልድ እንኳ ልጆቹ የራብ ማስታወቂያ፣ ሚስቱ ጎስቋላ ነው የምትሆነው ይላሉ። ምክንያቱም ሱሰኛ ነዋ። የጫታም ሰው ትዳር አይጸናም። ጫታም ሥራ ጠል ደካማም ነው። ሐሞቱም የፈሰሰ፣ ወንድነቱ የተሰለበ ነው። ስለሀገር ፍቅርም፣ ስለ ሚስት ፍቅርም ደንታ የማይሰጠው ወኔው የተሰለበ ነው። ጫት መግዣው ውድ ስለሆነም ጫታም ሰው በተፈጥሮው ሌባ ነው የሚሆነው። ባለ ሥልጣን ጫታም ሀገር ይሰርቃል። ወጣት የቤት ዕቃ ሰርቆ ይሸጣል፣ የሚሰረቅ ሲያጣ ማጅራት ይመታል። አዎ ለሱሱ ሲል ይሰርቃል፣ ይዘርፋል፣ ይገድላል። ጽንፈኛው ቄሮ ሰምተሃል !!
"…የተማረ ጫታም ደግሞ አይጣል ነው። በቢሮው አይገኝ። የሰዓት ሌባ ነው። ፀሐይ ከበረታ ስብሰባ ላይ ናቸው ብሎ የሀገር ሰዓት፣ የሀገር እድገት የሚሰርቅ ሌባ ነው። ሱፍና ከረባት አጥልቆ፣ V8 ቱን እያሽከረከረ በየስርቻው በየጉራንጉሩ የአይሬ ሰዓት እያለ እየተወሸቀ፣ ሲርመጠመጥ፣ ቀትረ ቀላል ባለ ሥልጣን፣ የቢሮ ሓላፊም ይሆናል። ጫታም ዳኛ ፍርዱ ጠማማ ነው። ጫታም ትራፊክ መራታ ዘራፊም ነው። ጫታም በቃ ጫታም ነው። አለቀ። 👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፥1114
“…የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።” 1ኛ ጴጥ 4፥3
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች
አጭር የምሥራች ሪፖርት
1ኛ፦ 5 ~ ኩንታል ጤፍ ተችሏል።
2ኛ፦ 5 ~ ሰንጋ ተችሏል።
3ኛ፦ 5 ~ ፍየል ተችሏል።
6ኛ፦ ውኃ፣ ለስላሳ በሙሉ ተችሏል
7ኛ፦ ቅቤ፣ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ጨው፣ ቅመማ ቅመሙ፣ ማገዶው ሁሉ ተችሏል። ተዘጋጅቷልም።
8ኛ፦ ድንኳን ኪራይ፣ የወንበር፣ የወጥ መሥሪያ ድስቶችና ሰሀኖች ተችለዋል። አዝማሪ ሁላ አይቀርም የበዓሉ ዕለት። ደስ ብሏቸው እንደ ሀገራቸው በዓል ያሳልፋሉ። ይሄ ለበዓሉ ነው። ለእንቁጣጣሽ፣ ለአዲስ ዓመት። ድፎ ዳቦ ቄጤማ ሁሉ አልቀረም ሲዘጋጅ።
9ኛ፦ 1200 ብርድልብስ ተችሏል።
10ኛ፦ 2400 አንሶላ ተችሏል።
11ኛ፦ 1200 ፍራሽ ተችሏል
"…ይሄ ለመኝታቸው ነው። አፈር ላይ ከሚተኙ፣ በትል ከሚበሉ ብዬ እናንተን ለምኜ ነው ያሟላላችሁልኝ። በጣም ነው ደስ ያለኝ። ቀጥሎ ለተማሪዎቹ ያሰብኩት ነው።
11ኛ፦ ትምህርት ቤት። ሊሊ ጀምራው የቆመውን ግማሽ ሚልዮን ብር አውጥቶ ለበዓሉ ሰንጋ የገዛላቸው አቶ ወርቁ አይተነው እኔ አስፈጽመዋለሁ በማለት ዘግቶታል።
12ኛ፦ 3,300 የተማሪ ቦርሳ ተችሏል
13ኛ፦ለ3,300 ተማሪዎች ደብተር
14ኛ፦ለ3,300ተማሪዎች እርሳስ
15ኛ፦ለ3,300 ተማሪዎች እስክሪብቶ ጎንደሬው የአፄዎቹ ልጅ አውሮጳ ስዊድን የሚኖረው ወዳጄ አቶ ቴዎድሮስ መለስ በሙሉ ዘግቶታል።
"…አሁን የሚቀረው ለ3,300 ተማሪዎቹ የሚሆን የደንብ ልብስ ነው። መለመን ጀምሬአለሁ። የአንዱ ዩኒፎርም ዋጋ 700 ብር ነው። 100$ 17 ይችላል። ተረባርበን እንፈጽማት። ደግሞም እንችላለን።
👉🏿 +4915215070996 የእጅ ስልኬን ሴቭ አድርጉና በኋትስአፕ ወይም በቴሌግራም ቃል የገባችሁትን ጻፉልኝ። እኔም የባንክ ቁጥራቸውን እሰጣችኋለሁ።
"…ዘመቻ 3,300 የደንብ ልብስ ማሰባሰብ በይፋ ጀምሬአለሁ። ተቀላቀሉኝ።
ታርሟል…!
"…በትናንትናው ዕለት የቴሌግራም ጥቆማዬም ሆነ በምሽቱ የመረጃ ተለቭዥን የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ ቢስተካከል ብዬ በቅን ልቦና ተነሣስቼ ወደ ላይ ተንጠራርቼ ለብልፅግናው ሊቀመንበር ያቀረብኩት የማስተካከያ ሓሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ተረስቶ የነበረው የአፋን ኦሮሚፋው የላቲን ቁቤው መልእክት ተጨምሮ ታትሟል። ፈረንጆቹ ቅር እንዳይላቸው ነው የእንግልጣር አፉ የተረሳው? 😂
"…ቆይቶም ቢሆን በላቲን በቁቤ አፍ ኢትዮጵያ ተጽፋለች። ከትናንቱ የይታረም መልእክቴ የሚቀረው፣ ያልታረመው አረፍተ ነገሩን "በ አራት ነጥብ መዝጋትና። ያው እንደ ሌላ ግዜው በእንግልጣር አፍ መጻፉ ብቻ ነው።
"…የሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የፌስቡክ ገጽ ላይ የሀገሪቱን ብሔራዊ ቋንቋ ሆሄያቱንም ሆነ ሥርዓተ ነጥቡን 👉🏿 ። ፣ ፤ ፡ ወዘተ በተገቢው መንገድ ያለመጠቀም ያስገምታል። ይስተካከል።
"…በላቲኑ መልእክት ላይ አረፍተ ነገሩ የተዘጋው 👉🏿 . ነው። ለላቲኑ ሥርዓተ ነጥብን ጠብቆ ለአማርኛ 👉🏿 ። መንፈግ ልክ አይደለም። ይሄ እኔ አሁን የምተቸው ነገር ለእነ ስዩም ተሾመ፣ ለእነ ዮኒ ማኛና ለእነ ጉማ ሰቀታ ሊገባቸው አይችልም። በፍጹም አይገገባቸውም። የምጽፈው መልእክቴንም የማስተላልፈው ለሚመለከታቸው ነው። አንድ የሀገሩን ቋንቋ ሥርዓተ ፊደል የማያውቅ ጠቅላይ ሚንስትር አለ ቢባል የሚያሳፍረው እኔንም ጭምር ነው። እነ ሪፖርተር፣ የቀድሞዎቹ አዲስ ነገር ጋዜጦች፣ አዲስ ዘነመንም አርታኢዎች አሏቸው። ቶፕ ቪው ቀረጻ የሚሠሩ የካሜራ ባለሙያ እንደሚቀጥሩት ሁሉ ፊደሉን የሚያርሙ ባለሙያዎች መቅጠር አይጎዳም።
"…ፀሎት አይባልም ጸሎት እንጂ፣ ጸሐይ አይባልም ፀሐይ እንጂ መንግስት አይባልም መንግሥት እንጂ፣ በጭካኔው እኔ ስለ ናቅሁት አቢይ ብዬ እጽፈዋለሁ እንጂ አቢይ አይባልም ዐቢይ እንጂ።
• ቆይቼ እመጣለሁ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
ETHIOPIA |~ ጳጉሜን ፬ የሰንደቅ ዓላማ እና
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።
"…ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያን ሁለቱም አንድ ናቸው። ድርና ማግ። የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎችም ናቸው። ይሄን ማለት ሌላውን ማበሳጨት አይደለም። ሌላውም ታሪክ ጠቅሶ በራሱ መንገድ የራሱን ነገር የመግለጽ መብቱ የተጠበቀ ነው። አትበሳጭ። አትናደድ። አንተም አለኝ የምትለውን መረጃና ማስረጃ እየጠቀስክ ጻፍ፣ መስክር፣ ተናገር። መብትህ ነው።
"…በዘመነ ፌስቡክ የጀመርኩት የወርሀ ጳጉሜን ዕለታቱን ሰይሞ ሲያስቡ መዋል ይኸው ከመንደረ ፌስቡክ ተባርሬ ወደ መንደረ ቴሌግራም ስመጣም ሳይቋረጥ መከበር ቀጥሏል። እንደ መርሀ ግብራችን መሠረት ዛሬ ጳጉሜን ፬ አስበን የምንውለው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ዓላማችንን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው። እናም ዛሬ ቴሌግራማችን በሁለቱ ምሥሎች ተጥለቅልቆ ይውላል ማለት ነው። ከዋሻ እስከ ካቴድራል፣ ከገጠር እስከ ከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ፎቶዎች ይለጠፋል፣ የአጥቢያችሁ፣ የደብራችሁም ፎቶ ይለጠፋል። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀሚስ፣ ሻሽ፣ ነጠላ፣ ጃኖ፣ ጥንግ ድርብ፣ ኩታ እና ኮፍያ ጭምር ይወጣል፣ ይገለጣል፣ ይለጠፋልም።
"…በኢትዮጵያ ምድር ሁለቱም ሲዋረዱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይዋረዳሉ። ሁለቱም ሲሰደቡ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይሰደባሉ። ሁለቱም ሲናቁ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይናቃሉ። ሁለቱም ሲቃጠሉ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይቃጠላሉ። በሥጋ ይቃጠላሉ፣ አንጀታቸውም እርር ድብንም ይላል። መንፈሳቸውም ይታወካል።
"…በኢትዮጵያ ምድር ሁለቱም ከተደበቁበት፣ ከወደቁበትና ከተጣሉበት ሲነሱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይነሳሉ ከፍከፍም ይላሉ። ሁለቱም ሲከበሩ ኢትዮጵያውያን አብረው ይከበራሉ። በየሄዱበትም መንገድ ይከፈትላቸዋል፣ ወንበርም ይለቀቅላቸዋል። ሁለቱም ሲወደዱ ኢትዮጵያውያንም አብረው ይወደዳሉ። ሁለቱም ሲወደሱ፣ ሲዘመርላቸውም ኢትዮጵያውያንም ሁሉ አንጀታቸው ቅቤ ይጠጣል። ህሊናቸው ያርፋል፣ መንፈሳቸው ይረካል። ልቦናቸውም ሀሴት ያደርጋል። የደስታ ዕንባም ያነባል።
"…የሰንደቅ ዓላማ ክብር፣ ፍቅር የሚገባህ በባዕድ ሀገር ተቀምጠህ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በሰማይ ላይ ሲበር ድንገት ስታየው ነው። በየአውሮፕላን ጣቢያው በትኬት መሸጫ ቢሮዎች ተርታ ስታየው ነው፣ በኦሎምፒክ እና በአለም ሻምፒዮና የስፖርት ውድድር ላይ አትሌቶቻችን አሸንፈው በቴሌቭዥን መስኮት ለብሰውት ሲሮጡ ስታየው ነው፣ በባዕድ ሀገር እናቶች፣ እህቶች፣ አባቶችና ወንድሞች፣ ኢትዮጵያውያንም፣ የውጭ ሀገር ዜጎች ድንገት ለብሰውት ስታየው አቤት የምታደርገውን ነው እኮ የሚያሳጣህ። ያቁነጠንጥሃል።
"…በውጭ ሀገር ብቸኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። ካለችበት የስደት ሀገር በቀኝ በኩል ከመቅደሱ ከታቦቱ ፊት፣ በውጭ በሕንፃው ላይ፣ በሰንደቅ ዓላማ መስቀያው ላይ በክብር ታየዋለህ። ኤምባሲዎችም ስሜት አይሰጥም እንጂ አምባሻው ያለበትን ይሰቅሉታል። የሐበሻ ሆቴሎች፣ የሐበሻ ሱቆች፣ ሰንደቅ ዓላማችን በግልፅ የሚታዩባቸው ስፍራዎች ናቸው። አውርድ፣ አንሳ፣ አውልቅ፣ ላቃጥለው የሚል ቄሮ ስለሌለበት እሱን ስታይም እንዲሁ ልቦናህ በሐሴት ይሞላል። በሀገር ቤት ሳለ ቅደሴ የማያስቀድስ ሁሉ በውጭ ሀገር አስቀዳሽ ነው። በሀገር ቤት አልጋው ላይ ተኝቶ እንደሬሳ እንደ አስከሬን ተኝቶ ከቤተ ክርስቲያን በድምጽ ማጉያ በሚሰማ ጸሎት ላዩ ላይ የሚቀደስበት ሰውዬ በውጭ ሀገር ቤተ ክርስቲያን ፍለጋ 4 ሰዓት መኪና ነድቶ፣ ባቡርና አውቶቡስ ተሳፍሮ፣ ተንከራቶ ሄዶ ነው የሚያስቀድሰው።
"…በሀገር ቤት የምንንቀው እንጀራ እንኳን እንደ ሃሺሽ ሱሰኛው መሆናችን የሚታወቀው ኢትዮጵያን ለቅቀን የወጣን ጊዜ ነው። ለዚህ ነው ጤፍ ባይገኝ እንኳ ስንዴ እና ሩዝ አቡክተው በሥጋ መጥበሻ ጋግረው እንጀራ የሚመስል ቂጣ ለመብላት መከራ የሚበሉት። ወዳጄ እነ ሩዝ በውጭ ሀገር የጎጃምና የአድአ ነጭ የማኛ ጤፍን አስንቀው ነው የሚያስደምሙህ። የፈለገ ቢሆን ግን ጤፍን አይተኩም። የኢትዮጵያውያን ጤና መሆን ያሳሰበው አቢይ አህመድ ቢልጌትስን ጋብዞ ጤፍን በስንዴ ካልተካሁ ብሎ ሲፎገላም ታይቷል። ስንዴ።
"…ሁለቱም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደርጋሉ። ያስማማሉ። ያኮራሉ። ያዋድዳሉ። ያፋቅራሉ። በአንድነት በአንድ ዓላማ ጥላም ሥር ይሰበስባሉ። በትግራይ ይሄን መንፈስ ወያኔ ሰብራዋለች። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በትግራይ በባንክ እና በአየር መንገዱ ሮጲላ፣ ጠያራ ላይ ብቻ ነው የቀሩት። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ አየር መንገድ። በቀር እነ አባ ሰራቂ መናፍቅ ከትግራይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለውን ስም ፍቀው በትግራይ ተክተዋል። ኦሮሞም እንደ ትግሬ ኢትዮጵያ ከሚለው ስም እና ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለመነጠል እየተፍጨረጨረ ነው። እናም ዛሬ ሁለቱንም ስናከብር እንውላላለን። ሰንደቅ ዓላማችንንም፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንንም ከፍ ከፍ አድርገን ስናከብር እንውላለን። እኛይ ይሄን በማድረጋችን አንተ ልትበሳጭ፣ አረፋ ልትደፍቅ አይገባም። ለምን ይነስርሃል?
"…ዛሬ በመሃል በመሃል ቀበሮ ሜዳዎችን የጎደላቸውን ዩኒፎርም እያሟላን እንውላለን። የአንዱ ተማሪ ዩኒፎርም ዋጋ 700 ብር ነው። ይህን ርዕሰ አንቀጽ እያነበቡ ስንት ተማሪ ፏ ሊያደርጉ እንደሚችሉ እያሰቡ ይቆዩን። የቦርሳው አልቋል። ደብተርና እርሳስ፣ እስኪሪፕቶውን አቶ ቴዎድሮስ የተባለ ነፍጠኛ ጎንደሬ ወዳጄ ዘግቶታል። የቀረውን እያሟላን እንውላለን። 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና በኋትስአፕ አልያም በቴሌግራም ላይ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የደንብ ልብስ ብዛት የአንዱን ዋጋ በ700 ብር አባዝታችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ቃላችሁን እመዘግብና የተፈናቃይ ስደተኞቹን ሕጋዊ የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና በዚያ ትልኩላቸዋላችሁ። በRIA የምትልኩ በጎ አድራጊዎች እርያ ለዐማራ ሲሆን እምቢ ስለሚሏችሁ፣ ሀገር ቤት ላለ ቤተሰብ ልካችሁ ቤተሰብ ሊያስገባላችሁ ይችላል። አመሰግናለሁ። መልካም የሰንደቅ ዓላማ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን ይሁንላችሁ። ዘመቻ የተማሪ ደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) 3,300 ይፋፋም።
"…ነገ ጳጉሜን 5 ደግሞ በመላው ዓለም የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን የሆን በሱስ የተጠቃን ሱሰኞች ከሱስ ለመላቀቅ የምንወስንበት ዕለት ነው። ሲጋራ ይረገጣል። ጫት ይረገጣል። እነ ሺሻ ይጣላሉ። ድሆች ይረዳሉ ይጠየቃሉ። ኢትዮጵያና ሰንደቅ ዓላማዋም፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ሁለቱም ይነሣሉ። ከፍ ከፍም ይላሉ። ሩቅ ባልሆነ ጊዜ በቅርቡ ይነሣሉ። ይነሣሉ አልኩህ ይነሣሉ ነው። ክብራችን፣ ማንነት ጌጣችን፣ ሞገሶቻችን ናቸውና ሁለቱም ዛሬም ነገም ወደፊትም ይከብራሉ። ከፍ ከፍም ይላሉ። ይህ ለምን ሆነ? የሚል፣ የሚናደድ ካለ እርሱ ኢትዮጵያዊ አይደለም። እርሱ ባንዳ የባንዳ የልጅ ልጅ ነው። አከተመ።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጳጉሜን 4/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።