😂😂😂 🙏🙏🙏✍✍✍
"…ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም፦ እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ። ማቴ 13፥ 24-30
"…አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ሉቃ 12፥ 1-2 “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” ሉቃ 8፥17
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
በ462 እንሰነባበት
እሱ፦ ሰላም ዘመዴ። የአንድ ዩኒፎርም ዋጋ ስንት ነው?
እኔ፦ 700 ብር።
እሱ፦ ስንት ቀረ…?
እኔ፦ 595
እሱ፦ አንድ የፈጣሪ እርዳታ የሚያስፈልገው ችግር አለብኝ። አምላኬ እንዲረዳኝ፣ እንዲሰማኝ ለአባቶች እንዲጸልዩልኝ ንገርልኝ። እኔ የ95 ተማሪዎችን ዩኒፎርም እችላለሁ። አለ። እኔም የባንክ አካውንቱን ላኩለት። ወዲያው በሞባይል ባንኪንግ ልኮ ሪሲቱን ላከልኝ።
እኔ፦ እሱ ችግር ያለውን ስለነገረኝ ከምር ደንግጫለሁ። ነገር ግን ደግሞ ችግር የተባለው ለእግዚአብሔር ከባድ አይደለም። ይሄን መልእክት ያነበባችሁ ቤተሰቦቼ አንድ አቡነ ዘበሰማያት እና ጸሎተ ማርያም በታማኝነት ጸልዩለት። እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
"…የአሜሪካው ወዳጄ ዳዊት ደግሞ ልተኛ ስዘጋጅ የ18 ተማሪ እችላለሁ አለኝ። አንድ ፍቃዱ የሚባል ወንድም ከአውስትራሊያ ደውሎ 20 መዝግብ አለኝ። አሁን የቀረኝ የ462 ተማሪዎች ዩኒፎርም ነው።
• የዛሬውን የእረፍት ቀኔን በዚህ መልክ ደስስ ብሎኝ አሳልፌአለሁ። ከእንቅልፌ ስነሳ ምንአልባትም ሞልቶ ሊጠብቀኝ ይችላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ለማንኛውም…
• ደኅና እደሩልኝ የነገ ሰው ይበለን።
766 ይቀረናል…!
"…የምናለብሰው 3,300 በጎንደር ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃይ ሕፃናት ተማሪዎችን ነው። እስከአሁን ለ2,534 ተማሪዎች የሚያለብሱልኝ ጓደኞችን አግኝቻለሁ። የሚቀረኝ ለ766 ምስኪን ተፈናቅለው በካምፕ ለሚኖሩ ተማሪዎች ብቻ ነው።
"…ሰኞ ሰኞ የዕረፍት ቀኔ ነው። በዕረፍት ቀኔ ደግሞ ይኸው አንጀት አርስ የሆነ፣ ከህሊና ተጠያቂነት የሚያድን፣ የዜግነት ግዴታዬንና ሓላፊነቴን እየተወጣሁ እንዲሰማኝ የሚያደርግ ሥራ እየሠራሁ ደስስ ብሎኝ የዕረፍት ቀኔን እያሳለፍኩ ነው።
"…እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ በ…👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬን መዝግቡትና በኋትስአፕ ወይም በቴሌግራም ላይ፤ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የዩኒፎርም ብዛት የአንዱን ዋጋ በ700 የኢትዮጵያ ብር እያባዛችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ።
"…ዛሬ የ500 ልጆች እስኪቀር ብለምን ሰሞኑን ደግሞ እንደምንም ለምኜ እሞላላቸውና ወደ ደብተር፣ እስራስና እስክሪብቶ መለመን እሄዳለሁ ማለት ነው። 100$ 17 እና ከ17 በላይ ተማሪዎችን ያለብስልኛል። እየለመንኳችሁ ነው። ብሊስ…🙏🙏🙏
• እንበርታ…👏👏👏
የቀበሮ ሜዳ ሪፖርት…
1ኛ፦1200 ብርድ ልብስ ተችሏል።
2ኛ፦2400 አንሶላ ተችሏል።
3ኛ፦1200 ፍራሽ ተችላል።
4ኛ፦3300 የትምህርት ቤት ቦርሳ ተችሏል።
5ኛ፦ በሊሊ በኩል የተጀመረውን ትምህርት ቤት አቶ ወርቁ አይተነው ለማጠናቀቅ ቃል ገብቶልኛል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"… አሁን የሚቀረኝ የተማሪዎቹ ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ እስራስና እስኪሪብቶ ብቻ ነው። ደብተር፣ እስኪሪብቶ እና እስራስን በተመለከተ በስዊድን የሚኖሩ የጎንደር ተወላጅ አቶ ቴዎድሮስ የተባሉ ወንድም እስከ 300 ሺ ብር የመደቡልኝ ሲሆን ቀሪውን እኛው እንሞላላቸዋለን።
"…አሁን እየለመንኩ ያለሁት ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ 3,300 ሕፃናት ተማሪዎች ዩኒፎርም ለማልበስ ነው። እስከአሁን ከ3,300 ዩኒፎርም የ2,124 ተማሪዎች ዩኒፎርም መግዣ አግኝቼ የሚቀረኝ የ1,176 ተማሪዎች ዩኒፎርም ብቻ ነው። ይሄ ደግሞ በጣም ቀላል ነው። ከባዱን ዳገት ወጥቼ ሜዳውን በመጋለብ ላይ ነኝ።
"…አንዱ የተማሪ ዩኒፎርም የተሰላው በ700 የኢትዮጵያ ብር ነው። ለዚህም 168 ሰዎች አንድ አንድ ዩኒፎርም እናሰፋለን ብለው 700 ብር ቢያዋጡ እንኳ የቀረውን 1176 ዩኒፎርም ዘጉት ማለት ነው። ከምር ቀላል ነው። ለጋሶቹ በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓውንድ የሚለግሱ ከሆነ ደግሞ ዕዳው ይቀልልናል። ለምሳሌ 69 ሰዎች ብቻ 100 ዶላር ቢለግሱ የተማሪዎቹ ዩኒፎርም ተዘጋ። 🙏
"…እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ በጠዋት እዚሁ ጀርመን ሀገር ዳርምሽታት የሚኖሩ ወ/ሮ ትእግስት ዓለሙና ባለቤታቸው ደውለውልኝ ምንዛሬውን ባናውቀውም በትንሹ በዶላር አስበነው በ500 ዩሮ ከ85 በላይ ተማሪዎችን እንደሚያለብሱልኝ ነግረው ቀኔን ብሩህ ነው ያደረጉልኝ። ዕለተ ሰኞ የዕረፍት ቀኔን ለወገኖቼ እለምንበታለሁ።
• በአዛኚቷ 1176 ዩኒፎርም ተባብራችሁ ግዙልኝ…🙏 እጠብቃችኋለሁ።
"…የስኳዱ መሪ ዶፍተር ምስጌ ለአዲሱ ጣና ቴሌቭዥን ገንዘብ ወደሚሰበሰብበት ቤት ወደ ጠሽ ሚኪ ሚዲያ ሂዱ ባለን መሠረት እኔም ገንዘብ የሚረዱ ሰዎች ይዤ መሄድ። አብረውኝ ከሄዱት መካከል ወሎዬዎች፣ ጎንደሬዎች፣ ሸዋና ጎጃም፣ አገዎችም ነበሩ። እናም ቦታ ቦታ ይዘን ተቀመጥን።
"…እሸቱ ገጠሬው እና ሚስቱ ፔይንኪለር ከጀርመን ተሰይመዋል። ፔይንኪለር ወዳጄን፣ የምወደውን፣ የማከብረውን ወንድሜን ልጅ ተድላ መላኩን ምን እንዳስነካችብኝ እንጃ የልጅ ተድላ ቲክቶክ አድራጊ ፈጣሪ ሆናለች አሉ።
• ኪሩቤል ባለ ከበሮውም በዚያው አለ። የሚገርመው ኪሩቤል ባለ ከበሮውም ከትግሬ ልጆች ወልዶ ትግሬዋን ሚስቱን ያቀወሰ ወንድማችን ነው። ዛሬ ደግሞ የስኳድ ቴሌቭዥን ገንዘብ ሰብሳቢ ሆኖ ከች ብሏል። ሚኪም ሁለት ልጅ ከትግሬ ወልዷል። እስክንድር ነጋም እንዲሁ ትግሬ ናት ሚስቱ፣ የእስክንድር ገንዘብ ያዥ ዶክተር አምሳሉም እንዲሁ ሚስቱ ትግሬ ናት። 😂 ሞኙ ዐማራ ዐማራ ነን ለሚሉ ገንዘቡን ለፋኖ ብሎ ይሰጣል፣ ገንዘቡን የሰበሰቡት ዐማሮች ሚስቶች ዳውን ዳውን ዐማራ እያሉ ብሩን ቆጥረው የት እንደሚያደርሱት አቡነ አረጋዊ ይወቁላችሁ። ታቦተ ጽዮን ትመስክር።
"…ለማንኛውም ጣና ቴሌቭዥንን ለመርዳት ይዤአቸው የሄድኩት ጎጃሜዎችና የአገው ዐማሮች "ምነው? ምነው? ምነ ዘመዴ? ምን አደረግንህ ብለው እዝን ብለው ነቅለው ወጡ። እኔ መች እንዲህ ይሆናሉ ብዬ ገመትኩ። ይቅርታ ወንድሞቼ።🙏 ብሊስ🙏
"…እኔ ግን እላለሁ ይሄ ማፍያ ስብስብ ያን የተከበረ ባለማዕተብ ጎንደሬ አይወክልም። አንዳቸውም የጎንደሬነት መልክና ስብዕና የላቸውም። ጎንደርና ጎጃም አንድ ናቸው። እኔ የማምነው፣ የምመሰክረውም ይሄንን ነው። ይሄ ቲክቶክ ላይ ገንዘብ የሚሰበስብ ማፍያ ቡድን ስንቱን የሸዋ ልጅ ቤተሰብ እንዳስገደለ በመረጃ እመጣበታለሁ።
• እየኮመታችሁ…!
"…ስኳድ ምስጌ "ለፀረ ጎጃም ፀረ ዐማራው ጣና ቴቪ ፈንድ ወደ ሚሰበስበው ) ጋሽ ሀሺሽ የጁንታ ባል ሚኪ ቤት እንሂድ እያለ ነው። እንሂድና ጉድ ላሳያችሁ እንዴ…?
"…የሚገርመኝ ጥያቄ ግን አለ። ለምንድነው የትግሬ ሚስት ያገቡ አካላት ፀረ ዐማራ ፋኖ የሚሆኑት? ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው።
• እስክንድር ነጋ ~ ሚስት ትግሬ
• ዶር አምሳሉ ገንዘብ ያዥ~ ሚስት ትግሬ
• ሚኪ ሚዲያ~ የልጆቹ እናት ትግሬ
• አበበ በለው~ ወላጅ እናት ከየት ናቸው ነው ያላችሁኝ።
• ሃብታሙ አያሌው~ ባለቤቱ ከየት ትሆን?
"…ብቻ ገራሚ ነገር ነው። ለማንኛውም እንሂድ ወይ…? እንሂድና ሰዎች ላስተዋውቃችሁ…?
መልካም…
"…ስላልገባኝ ካልደበራችሁ የሆነ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ነበር። የምሽት የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብራችን እስኪጀምር የሆነ ቪዲዮ አሳይቼአችሁ ሓሳብ እንድትሰጡበት ፈልጌ ነበር። ትንሽ መረር የሚል ቪድዮ ነው። ሕፃናት፣ ነፍሰጡሮች፣ የደም ግፊትና የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች እንዲያዩት አይመከርም።
"…ልጠይቅ…?
• አቤ ሙንኦኖኖ…?
"…የጣና ቲቪ ሼር አለው እንዴ? ተው አቤ። ተው። ተው እረፍ። እኔ በጣም ነው የምወድህ። የማከብርህም። ተው እረፍ።
"…ወያኔንም፣ ኦነግንም አትስደብብን ብለን ጳጳስ፣ ቄስ ሁላ ልከንበት መክረነዋል አላለም። ከኦነግና ከወያኔ ጋር እየተታኮሰ፣ እየተገዳደለ ሲያበቃ እኔ ዘመዴን ወያኔን አትስደብብን አላለም ጋሽ አበበ በርሄ። 😂😂
"…እነ አበበ በለው ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር ተጠቃቅሰው መረጃ ቲቪን በሆያ ሆዬ አዋክበው ሊያፈርሱ ዳከሩ። እኔ ዘመዴ ደግሞ ራሳቸውን እነዚህን የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ከሀዲዎችን ሰባበርኳቸው። ታሪኩ ይኸው ነው።
"…በተረፈ ፋኖዎች ወጥተው ዘመድኩን ተሳስቷል፣ ሀብታሙ አያሌውን፣ እስክንድር ነጋን፣ አበበ በለውን፣ ምስጋናው አንዷለምን ከነካህብን እንቀየምሃለን፣ እናስቀይምሃለን ብለዋል የምትለውንም ቀደዳ አልሰማህም። እኔ ማንንም እንደምተቸው፣ እንደምሸነቁጠው እኔንም ማንም ሊተቸኝ፣ ሊሸነቁጠኝ መብት አለው። መብቱም ነው።
"…ታዲያ ስትተቸኝ የመልስ ምት እንዳለ እንዳትዘነጋ። ስታስነጥሰኝ እኔም መልሼ እንደማስነጥስህ ማወቅ አለብህ። እገሌ ወእገሌ ብሎ ነገር የለም። ትችትህ ትክክል እስካልሆነ ድረስ እኔም ልክ አስገባሃለሁ።
"…ብሩክ ይባስ በቀደም ዕለት በአንድ ፋኖ ሲያስደብኝ ነበር። አበበ ጢሞም ዋይ ዋይ ሲልብኝ ነበር። ሁለቱንም ንቄ የተውኳቸው እፉዬ ገላ ሆነው ስለታዩኝ ነው።
"…በቀደም አርበኛ ሰሎሞን አጣናው ደውሎልኝ ነበር። ከምር ትልቅ ሰው ነው። ዘመዴ እንዲህ ብሏል ብለው ነግረውት እሱን ለማጣራት ነበር የደወለልኝ። ክርስቲያን፣ ባለ ማዕተብ ስለሆነ ወሬ ሲነግሩት አልተቆጣም። ወደ እኔ ደወለ። ተነጋገርን። እኔ እንዲህ እንዳላልኩ ነግሬው ብዙ አውርተን ተለያየን መፍትሄው ይሄ ብቻ ነው።
• አይዞኝ አቤ። ገጥመናል ገጥመናል ነው። ቻለው።
ተቀበል…!
"…አቢይ አህመድ እንደ ትግሬና እንደ ዐማራዎቹ ባይገድላቸውም ኦሮሞዎቹንም ጢባጢቤ ተጫውቶባቸዋል የሚሉ አንዳንድ መተርጉማን አሉ። አቢይ እንዴት ተራ በተራ ቁማር እንደበላቸው እንመልከት።
"…ጀዋር መሀመድ። አቢይ ማይም ነው ብሎ እምቡር እምቡር አበዛ። በገመድ አስሮ ጥጃው ጃዌን ለቀቀው። ጃዌ ሃገር አልበቃው ብሎ ሲቦርቅ ገመዱን አሳጠረበትና በደረቅ ሱፋጭ ፀጉርን ላጭቶ ዘብጥያ ወረወረው። ጃዊ ተንፍሶ ወጣ። ምርጫ ቀረበለት እንደ ሃጫሉ ከአፈር ትቀላቀላለህ ወይስ ትፈረጥጣለህ። ጃዌም አለ። ኧረ ልፈርጥጥበት ብሎ ነካው። ወደ ሀራሬ ሳይሆን ወደ ናይሮቢ።
"…ፓስተር በቀለ ገርባ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል ብሎ ለጃዋር ተገረደ። በአማርኛ ለሚጠይቃችሁ ዕቃ አትሽጡም አለ። ፈነዳ። በመጨረሻም በሱፋጭ ተላጭቶ ዘብጥያ ገባ። ኦሮሞን ኦሮሞ አይገድለውም ብሎም ምርጫ ሰጠው። ፍርጣ፣ ወይም ደፍት? ነካው በቄ። ነካው ወደ አማሪካ።
"…ኦነጉን ሌንጮ ለታን ደግሞ አርቆ ሳዑዲ አረቢያ ለከው። እዚያ ዱቅ ብሎ አለሙን እየቀጨ ሀገር ሰላም ሆነለት። ሲቆይ አብይ አህመድ ድንገት አንደኛውን ሌሊት ሲያይ ባደረው ህልም ላይ ውቃቢው የኦሮሞ ወዳጆቹን ሙልጭ አድርጎ ማጥፋት እንዳለበት ይጠቁመዋል። ከዚያ ወደ ሥራ ገባ። ለአሜሪካ ፍሬንዶቹ ልልከው ነኝና አዋርዱልኝ ብሎ አሜሪካ አምባሳደር አድርጎ ላከው። አሜሪካም ቅሌቱን አንብባ ጥፋ ከዚህ አለችው። ሌንጮ ጨረቃ ላይ ዱቅ። ሬድዋን እንዳይበጠብጠው ከኢሱ ጋር ተጠቃቅሶ አስመራ ዓመት ሙሉ የቁም እስር እንዳሰረው ማለት ነው።
~ ቀጀላ መርዳሳ~ ጨረቃ ላይ
~ ዳውዳ ኢብሳ~ አልጋ ላይ (ዳይፐር)
~ በቴ ኡርጌሳ~ ወደሰማይ ቤት ሸኘው
~ ከማል ገልቹ~ አርሰህ ብላ ብሎ ወደ ገጠር…
~ ዲማ ነገዎ… ከሀገር እንዳይወጣ አድርጎ ጨረቃ ላይ
• የዘነጋሁት ካለ ጨምሩበት
ተቀበል…!
"…በኮሪደር ልማቱና በወንዝ ዳር ልማት ስም በአጭር ቀን ትፈርሳላችሁ ተባልን የሚሉ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪ ድምጾችን እየሰማሁ ነው። ጎንደርም፣ ዲላና አዋሳ፣ ደብረ ዘይትም እንዲሁ ዋይ ዋይ የሚሉ አሉ።
• አዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ሙሉ በሙሉ፣ ትምህርት ቤቱ ሁላ ይነካል እየተባለ ነው። በካሳንቺስ መነሃሪያ የሚተርፍ የለም።
• ፈረንሳይ ለጋሲዮን በጫካ ቤተመንግሥቱ ፕሮጀክት ምክንያት እስከ መስከረም 20 ድራሽ አባታችሁ ይጥፋ መባላቸው እየተነገረ ነው።
• ከሽሮሜዳ እስከ መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ድረስ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የተወሰኑቱ በኮሪደር ልማት የተወሰኑቱ ደግሞ ወንዝ ዳር በርቀት ላይ ቢኖሩም በወንዝ ዳር ልማት በሚል እንደሚያፈርሱ ተነግሯቸዋል ተብሏል።
"…ብቻ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30 ድረስ ብዙ ክፍለ ከተሞች ድራሻቸው ጠፍቶ መሬቱ አበባ ይተከልበታል ተብሏል።
• የሚነሡት ሰዎች የት ነው የሚያርፉት…? የቀበሌ ቤት ውስጥ ያሉ፣ ደባሎችስ ምን ይውጣቸው ይሆን…?
• ያለ ወረቀት በቃል ብቻ መጥቶ ተነሥ ብሎ መንገር ማለትስ ምን ማለት ነው?
• የማይፈርሰው የትኛው ሰፈርና ከተማ ነው?
• ኦሬክሶቹ ግን ምን አስበው ነው…?
ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!
✍️✍️✍️…በአዜብ ወርቁ
"…የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አይቼ ሳልመረምር አስተያየት ብሰጥ ሚዛናዊ አልሆን ይሆናል፣ እሳሳት ይሆናል በሚል ከማዘን በስተቀር ምንም አላልኩም ነበር፣ አሁን ግን ለልማት ድንገት መፍረስ የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት።
"…የማወራው ስለአንድ ሰው ታሪክ ነው፣ ተቆጥሮ ህዝብ ስለሚባለው፣ ሀገር በማቅናት ውስጥ ማህበረሰብ በመስራት ውስጥ አስተዋጽኦ ስላለው አንድ ሰው ነው።
የሕይወት ታሪኩ እንዲህ ነው ...
"…ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ በግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቶ ከራሱ አልፎ ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ስር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሑፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሠርቶ ኑሮውን መሰረተ።
"…12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣ የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሠራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ ዐዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል። ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለራሱ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል።
"…ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ። “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ። ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል።
"…የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ። እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለሕግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ ዓይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም። ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትእዛዝ ሰጥተው ሄዱ።
"…መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው።
• ለምን?
~ ለጫካ ፕሮጀክት ልማት።
• መቼ?
~ እስከ መስከረም 20።
"…ተሰብሳቢው ደነገጠ። “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የዕለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ።
• ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል??
"…በየቤቱ ያለ እቅድ፥ ያለ ኑሮ... ለቅሶ፣ ጽኑ ታማሚ፣ ሰርግ፣ አራስ፣ የደረሰች ነፍሰጡር....ቤቱ ይቁጠረው። ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል? ምንድነው ጥድፍድፉ? ልማት ታስቦ እንደሆነም እኮ በረጅም ጊዜ እቅድ ላይ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሊቀመጥ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሰው ነው።
"…ነዋሪው እንዴት ይነሳ? ወዴት ይሂድ የሚለው እንጂ ትግበራ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ለነዋሪው በቀናት ውስጥ ትነሳለህ ብሎ በቃል መንገር እንዴት? ሰው ያነሰ ቅድሚያ ነው የሚሰጠው? ልማቱ ለሰው ነው አይደል??
"…ይህ ቤተሰብ የመራ፣ ሀገር ያቀና፣ ስንቱን ያስተማረ፣ የዳረ፣ አስታሞ በክብር የቀበረ፣ የተጣላን አስታራቂ የሐገር ሽማግሌ፣ አልጋ የያዘ መንቀሳቀስ፣ መንቃት የማይችል፣ ፈጣሪው ጋ እስኪሄድ ቀኑን የሚጠብቅ አረጋዊ እስከ መስከረም 20 ይነሳ ቤቱ ይፈርሳል ተባለ።
"…እንዴት ይሄድ? የት ይሂድ? በኖረበት ሰፈር ባቋቋምው እድር፣ በሚወደው አብሮ በኖረው የሰፈር ሰው ላይሸኝ? የሀገር ትርጉም ሲነገር “አባት የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል” አልተባለም ነበር እንዴ? እና ለአባት የሚለቅሰበት፣ ለቅሶ የሚቀመጡበት ሀገር የለም??
"…ልማት ማንም አይጠላም፣ ማማር፣ መታደስ ማንም አይጠላም። የሰው ልጅን ግራ ሲያጋባ ለድንገተኛ ስጋት ሲዳርግ፣ ሰው ሁሉ የኔስ ተራ መቼ ይሆን እያለ በጭንቀት እንዲኖር ሲገደድ፣ ክብርን ሲነካ፣ ሰውነትን ሲያፈርስ ግን አዎን ልማት ይጠላል!!
"…ይሄን ጽሑፍ የምታዩ የልማት ደጋፊ ነን ባዮች ኮመንት ላይ መጥታችሁ፣ "እና ሀገር አይልማ? ሀገር ሲለማ አይናችሁ የሚቀላ፣ የልማት አደናቃፊዎች" ትሉ ይሆናል። እውነቱ ግን የልማት አደናቃፊ እናንተ ናችሁ።
"…እንደግፈዋለን የምትሉት ልማት በሰዎች እንዲጠላ፣ ሰው እንዲያለቅስበት፣ የምትታትሩ ዛሬን እና ሆዳችሁን ብቻ የምታዩ፣ ከሆዳችሁ ውጪ ሌላ ነገር የመደገፍ አቅም የሌላችሁ ሰባራ ሸንበቆዎች የልማት ጠላቶቹ ናችሁ።
"…ድንገት እንደ ሱናሜ አደጋ ቤታችሁ የፈረሰባችሁ ወገኖቼ፡ እስቲ ተናገሩት እንዴት ሆናችሁ? እንዴት አለፋችሁት?
"…እስቲ እውነተኛ ታሪካችሁን፣ ስሜታችሁን፣ ትኩስ ትዝታችሁን አጋሩን ታሪክ ይጻፍ። ለሚመለከተው አካልም ሰውን ሳያፈርስ፣ ቤት አላልኩም ሰውን ሳያፈርስ ሰዉም ተቀብሎት ሊሠራ እንደሚችል ትክክለኛ ጥቆማ እና ድጋፍ ይሁነው። በማለት አዜብ ጦማሯን ትቋጫለች።
• አዜብ ወርቁ ተዝብቷን በዚህ መልኩ ገለጸች። ተነፈሰችም። እናንተስ ምን ትላላችሁ…? ከ10 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።
"…ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆ 3፣ 22-23 “…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…በቃኝ ስለደከመኝ አልመለስም።
"…ቅድም 462 ዩኒፎርም ቀረኝ አይደል ብዬ ነግሬአችሁ ልተኛ ስል ዓይኔ አላርፍ ብሎ የመልእክት ሳጥኔን መጎብኘት። 300$ የሚል መልእክት ማየት። እንቅልፌ ብን ብሎ መጥፋት። ወዲያው በድፍረት ወደማላውቀው ስልክ መደውል። ሴት ናት ባለ 300$ ላሯ፣ አወራኋት። አመሰገንኳት፣ መዝግቤ ተለየኋት። ስልኩን ስዘጋው እዚያው ስልኩ አጠገብ ከደቡብ አፍሪካ ወዳጄ ጎጄ 20 ዩኒፎርም ብሎ መጻፍ። ከዚህ በላይ አልታመማትም፣ የመልእክት ሳጥኔንም አልከፍታትም ብዬ አምላኬን አመስግኜ ይህቺን ጽፌላችሁ ወደ መኝታ።
• አሁን የቀረኝ 391 ዩኒፎርም ብቻ ነው ለማለት ነው። በሉ ደኅና እደሩልኝ።
የ595 ተማሪዎች ቀረኝ…!
"…ከቀጨኔ መድኃኔዓለም በታች የሚገኘው አፄ ልብነ ድንግል ትምህርት ቤት በ1975 ዓም በወር የሚያስከፍለው በክፍል ቁጥር ልክ ነበር። አያቴ ሦስተኛ ክፍል በወር 3 ብር መክፈል አቅቷቸው ከትምህርት ቤቱ ተባረርኩ። እናም ሊስትሮ ጀመርኩ። ታሪኩ ረጅም ነው የሆነ ቀን የትምህርት ቤቱ ገንዘብ ያዥ ወሮ ፍቅርተ ማርገጃው ጋር ጠራችኝ። ሄድኩኝ። በአያቴ ላይ የደረሰውን አግኝቶ ማጣት ስለምታውቅ ነገ ጠዋት ትምህርት ቤት እንድትመጣ አለችኝ። ለአያቴ ስነግራቸው ሂድ አሉኝ። ሄድኩኝ።
"…ተማሪዎች ወደ ክፍል እስኪገቡ ጠብቄ እያላበኝ ወደ ተጠራሁበት ክፍል እየሄድኩ ሳለ አሁን የአፋር ክልል ባለ ሥልጣን ሔሬ ሐመዱ፣ መኮንን ጥበበ፣ ታዬ ኃ/ገብርኤል ከቢሮ ሲወጡ አገኙኝ። ተቆጡኝ። ለምን ከትምህርት ቤት ቀረህ ብለው ጓ አሉብኝ። ምን ብዬ ላስረዳቸው? ዝም ብዬ እንደቆምኩ ቲቸር ፍቅርተ እኔ ጠርቼው ነው ብላ ነገረቻቸው። ተንሾካሸኩ። ነው እንዴ ብለው ሊሄዱ ሲሉ ሄሬ ዳይሬክተሩ ቢሮ ገብቶ ወጣ። ያሳየኝን ፍቅርና ፈገግታ አልረሳውም።
"…አስፈሪው፣ ኮስታራው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ቲቸር ደምሰው ፊት ቀረብኩ። አንድ የነተበ ቁምጣ፣ የአያቴ አሮጌ ትልቅ የተቀደደ ሹራብ አድርጌ፣ ባዶ እግሬን ከአስፈሪው ዳይሬክተር ፊት ቆምኩ። ፍቅርተ እና ደምሰው ብዙ መክረው ወደ እኔ ዞሩ። እንዲህም ተባልኩ። ከዛሬ ጀምሮ በእዚህ ትምህርት ቤት እስከ 8ተኛ ክፍል ድረስ አትከፍልም። ከአንተ የሚጠበቀው ጠንክሮ መማር ብቻ ነው። ተማሪዎች እንዳይሰሙ። ምስጢር ጠብቅ። ደብተርህን ክረምት ሊስትሮ እየሠራህ አሟላ። በተረፈ ሳትሳቀቅ ተማር። ተስፋ ያለህ፣ ጎበዝ ልጅ ነህ። መባከን፣ በልጅነትህ መክነህ መቅረት የለብህም ብለው የመማር ዕድል ሰጡኝ መምህራኖቼ። እኔም ያለሰቀቀን ተማርኩ። በየወሩ የትምህርት ቤት ክፍያ ያላሟላችሁ ውጡ ተብሎ የስም ዝርዝር ሲጠራ መጀመሪያ እኔ እንደሆንኩ ዐውቀው ተማሪዎች ዞር ብለው አፍር የነበርኩት ዘመዴ ውርደቱ ቀረልኝ። ቪላ ቤት ውስጥ እየኖሩኩ ሦስት ብር ለትምህርት ቤት መክፈል ያቃተኝ እኔ ዘመዴም ደረቴን ነፍቼ መማር ጀመርኩ። ስድብ፣ ውርደት ራቀልኝ። ዕድሉን የሰጡኝን ቲቸር ደምሰውን እና ቲቸር ፍቅርተንም አላሳፈርኳቸውም በአቅሜ ይኸው ጥሩ ዜጋ ለመሆን ዘወትር እጥራለሁ።
"…የራሴን ድርጅት ከመሰረትኩ በኋላ መጀመሪያ መበቀል የጀመርኩት የትምህርት ቤት መክፈል ያቃታቸውን ተማሪዎች እየፈለግኩ ማስተማር ነበርኩ። አሁን አንድ ባለ ሥልጣን የሆነ ሰው ዩኒቨርስቲ ድረስ አስተምሬ፣ በመንግሥት ሚዲያ ውስጥ ጎምቱ ጋዜጠኛ የሆነ ልጅ እንዲሁ አስተምሬ፣ ሌሎች ብዙ ልጆችም በአቅሜ ሌሎችንም አስተባብሬ በማስተማር ብድሬን መልሻለሁ። ቲቸር ደምሰውን እና ቲቸር ፍቅርተንም ለበዓል ደውዬ መመረቅ ጀምሬአለሁ። እንዴት ደስ እንደሚለኝ አትጠይቁኝ።
"…ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ በድህነት መማርን ከእኔ በላይ የሚያውቀው የለም። በልጅነት ከፊደል ጋር መቆየት እንዳትባክኑ ያደርጋችኋል። ለዚህ ነው 5 ወይ 10 ልጆችን እንዲማሩ አግዝ የነበረውን አሁን ደግሞ ጎንደር ላይ 3300 ተማሪዎችን ከትምሕርት እንዳይርቁ ለማድረግ በትበት የምለው። እኔ የሐረር ልጅ ነኝ። ያስተማሩኝ መምህራን ቤርቤረሰቦች ናቸው። ዛሬ ጎንደር ላይ እነዚህ ልጆች ላይ የምደክመው ጎንደሬ ስለሆንኩ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ነው። ጎጃሜው ወርቁ አይተነውን ከልቤ ነው የማመሰግነው። ትምሕርት ቤቱን ሊሠራላቸው ቃል ስለገባልኝ። የሚፈለገው ማቴሪያል ዝርዝር ደርሶኛል እሱን ለእሱ እልካለሁ፣ እሱም ዕቃውን ገዝቶ ያቀርባል፣ ትምህርት ቤቱም ይሠራል፣ ይጠናቀቃል። ታዲያ እኔ ዕድለኛ አይደለሁምን?
"…አሁን አግኝተው ላጡት ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ ተማሪዎች የምፈልገው የደንብ ልብስ 3,300 ነበር። እስከ አሁን ብዙም ሳልደክም እናንተ የቴሌግራም ጓደኞቼን ብቻ በጦማር ልባችሁን አውልቄ፣ ዝቅም ከፍም አድርጌ፣ ወትውቼ የ2,705 ተማሪዎችን ዩኒፎርም ችላችሁልኛል። የሚቀረኝ የ595 ተማሪዎች ዩኒፎርም ብቻ ነው። 595 ብቻ።
"…እነዚህ ሕፃናት ፈልገው ባልተወለዱበት ነገድ፣ ዐማራዊ ማንነታቸው ምክንያት ነበር ከወለጋ፣ ከመተከል፣ ከሽሬ፣ ከማይካድራ፣ ከሱዳን ጭምር ተፈናቅለው በአንድ ቀን ጀምበር ባዶ ቀርተው ሜዳ ላይ የተበተኑት። ሕፃናቱም፣ ወላጆቹም ሊሰማቸው የሚችለውን ስቃይ፣ ህመም፣ ጭንቀት የእነሱ እንዳለ ሆኖ እንደ እኔ በልጅነቱ በድህነት ያደገ በሚገባ ያውቀዋል። በደህና ቤተሰብ ውስጥ ያደጋችሁ ላይሰማችሁ ይችላል። አስባችሁታል በልጅነቴ እግዚአብሔር በቴቸር ደምሰው እና በቲቸር ፍቅርተ በኩል ባይጎበኘኝ፣ ባይታደገኝ ዛሬ ምን ልሆን እንደምችል ፈጣሪ ብቻ ነበር የሚያውቀው። ሌላው ቢቀር እነዚህን ሕፃናት ከትምህርት እንዳይርቁ ማድረግ ይኖርብናል።
"…35 ደጋግ ሰዎች 100$ ዶላር ቢያዋጡ 595ቱ ዩኒፎርም ይሞላል ብዬ አምናለሁ። ተወደደም ተጠላም የነከስኩትን ሳላደማ፣ የጀመርኩትን ሳልፈጽም፣ የነብሩን ጅራት ይዤ የመልቀቅ ልምድ የለኝም። ይሄንንም አሳካለሁ። ኮሚቴ የለው። ታዋቂ ሰዎች፣ አርቲስቶችና ዩቲዩበር፣ ቲክቶከሮች፣ ጋዜጠኞች አልተሳተፉበት፣ በሚዲያ፣ በፌስቡክ፣ በቲክቶክ ዋይ ዋይ አልተባለበት፣ በቴሌግራም ብቻ ያለ ድምጽ በጽሑፍ ብቻ ግቤን እየመታሁ ነው። ኮሚሽን የለው፣ አበል የለው፣ ገንዘቡ በእኔ በኩል አያልፍ። ቃል ትገባለህ የኮሚቴ የባንክ ቡክ እሰጥሃለሁ፣ ከዚያ በቀጥታ ታስገባለህ። በላው፣ ነከሰው ብሎ ነገር የለው። አከተመ።
"…ወቅቱ ከባድ ነው። ኑሮ የተወደደበት ዘመን ነው። በዚያ ላይ መስከረም ነው። መስከረም ኪስ የሚራገፍበት ወር ነው። ሁለት ታላላቅ በዓል፣ እንቁጣጣሽና መስቀል፣ የትምህርት ቤት የልጆች ወጪ፣ ዘመድ አዝማድ የሚረዳበት፣ ጉራጌ ለመስቀል ወደ ሀገር ቤት የሚገባበት ወቅት ነው። በመስከረም በኢኮኖሚ የሚመታው ወላጅ የሚያገግመው ጥቅምት አልፎ ከህዳር ጀምሮ ነው። እንዲህ ሆኖ ነው እንግዲህ እናንተ የእኔን ቴሌግራም አንብባችሁ የእነዚህን ተፈናቃዮች አንገብጋቢ የተባለ ችግር ለመቀረፍ የተረባረባችሁት። በእውነት ከእኔ በላይ ዕድለኛ ማን አለ?
• ቀሪዋን 595 ዩኒፎርም እየሞላችሁ ደኅና እደሩልኝ።
~ዘጠኝ መቶ ቤት ገባን
እግዚአብሔር ይመስገን
• የሚቀረን ብዛት 992 ፍራሽ
• የአንዱ ዋጋ 700 ብር ነው
"…በቀደመው መልእክቴ ለ3,300 የጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ለማልበስ የ2,124 ተማሪዎች ዩኒፎርም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ አሟልተውልኝ የሚቀረኝ 1,176 ዩኒፎርም መግዢያ ነው ብዬአችሁ ነበር። ጋሽ ኃይሉ ከአማሪካ የሰጡኝ 300$ የ51 ተማሪ ሲገዛልኝ ሌሎች ሁሉ ተረባርበው የ2308 ተማሪዎች ሲሟላልኝ አሁን የ992 ተማሪዎች ዩኒፎርም ቀርቶኛል።
"…ይህ የእኔ የዘመዴ 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልክ ነው። ስልኬን መዝግቡትና በኋትስአፕ ወይም በቴሌግራም ላይ፤ ስማችሁንና ቃል የገባችሁትን የዩኒፎርም ብዛት የአንዱን ዋጋ በ700 የኢትዮጵያ ብር እያባዛችሁ ቃላችሁን አስቀምጡልኝ። እኔም ወዲያው በፍጥነት ቃላችሁን እመዘግብና የተፈናቃዮቹን ሕጋዊ የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁና ብሩን በቀጥታ ትልኩላቸዋላችሁ። በRIA የምትልኩ ለዐማራ ሲሆን እምቢ ስለሚሏችሁ፣ ሀገር ቤት ላለ ቤተሰብ ልካችሁ ቤተሰብ ሊያስገባላችሁ ይችላል።
"…በእረፍት ቀኔም ለወገኔ እየሠራሁ ነው። ይህን በመሥራቴ መብራትና ውኃ አይቆጥርብኝ፣ ስትራፖ አይዘኝ፣ ትንፋሼ አይቆራረጥ፣ ላብ አያልበኝ፣ በቃ በቴሌግራም ገጼ ላይ ጻፍ፣ ጻፍ ማድረግ። ከዚያ ቪድዮውንና ፎቶውን አይቶ የሚወጣ ሳይሆን መልእክቱን አንብቦ የተረዳ፣ የገባው እግዚአብሔርም የፈቀደለት ቤተሰቤ ልቡ የፈቀደውን ሰጥቶ የበጎ ሥራው ተሳታፊ ይሆናል ማለት ነው። ተሳተፉ። አትለፉት።
• 100 $ ~ የ17 ተማሪ ዩኒፎርም ያለብሳል።
• ዘመቻ ዩኒፎርም 992 ይፋፋም።
"…አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ሉቃ 12፥ 1-2 “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” ሉቃ 8፥17
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ምሽት 2:05 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ትዊተር 👉Twitter: https://x.com/MerejaTV
• በራምብል 👉 Rumble: https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 YouTube: https://youtu.be/vkuVwmi6BFs
• Mereja TV: https://mereja.tv
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሻሎም… ሰላም…!
"…ሚኪ ቤት ስገባ…
"…ስኳድ ምስጌ ሂዱ ባለን ማስታወቂያ መሰረት ወደ ሚኪ ቤት ኮተት እያልኩ መሄድ። እዚያ ሚኪ ቤት ስገባ ማንን ቲክቶክ ላይ ተጥዶ ባገኝ ጥሩ ነው? ከምር አታምኑኝም በቀጥታ ያገኘሁት ከራሳ ሰሜን ሸዋ ከቀለጠው የጦርነት ሜዳ መሃል 😂😂 ተረጋግቶ ተቀምጦ ቲክቶክ የሚጠቀመውን የእስክንድር ደንገጡር፣ ሻለቃ መከታው ማሞ የሚመራው የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ የሆነውን ኢንጂነር ፋኖ አዶናይ አበበን።
"…አይገርምላችሁም? በቀለጠ ጦርነት መሃል ለእስክንድር የፖለቲካ ሓላፊ ኢንተርኔት ተፈቅዶለት ቁጭ ብሎ ከሚኪ ጦሽ ጋር ስለ ፀረ ዐማራው፣ ፀረ ጎጃሙ ስኳድ በእስክንድር ነጋ በኩል ሊከፍቱ ስለሚላላጡበት ጣና ሚዲያ እየመከረ ነው። ኢትዮ 360 እንዳከሰራቸው በዚህ ነው ያወቅኩት። ሀብታሙም፣ አበበ በለውም በሚፈለገው መጠን ወደፊት አላራመዱትም። እነ ስኳድ ምስጌን፣ እነ እስኬውንም አላኮሩም። ስለዚህ በእነ ፔይንኪለር እና በእነ እሸቱ ገጠሬው ፊት አውራሪነት እነ አዶናይ በስመ ጎንደር ሸዋን ለማሾቅ ቆዳ ቀይረው ብቅ። አሁን ምስክርነቱን ሰምተን እንመለሳለን።
• አዶናይ ማለት ከእስኬው ጋር የገጠር ቤርጎ ቁጭ ብላ ቲክቶክ የምትጠቀመዋ ናት። ያው ፍልሚያ ላይ አይደል ያለነው። መግጠም ነው እንግዲህ። መግጠም ነው።
• እየኮመታችሁ…!!
ቪድዮ ፩
"…ሸዋ ሳሲት በሚባል ቦታ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚያስተዳድረው የሻለቃ መከታው ማሞ ልጆች ካምፕ አድርገው የተቀመጡበት ስፍራ ላይ ድንገት የኦሮሙማው ጦር ይገባባቸዋል። እስክንድር የገዛው የመከታው ጦርም ወደ ኋላ ያፈገፍጋል። የመከታው ጦርም ከጦሩ ጋር መሸሽ ያልቻሉ 15 ቁስለኞችን ጥለዋቸው ነበር የሸሹት አሉ። የኦሮሙማው ጦር በደረሰ ጊዜም እነዚህን ሸሽተው ማምለጥ ያልቻሉ የመከታው ልጆችን ይይዙና ያለ ርህራሄ ይረሽኗቸዋል። መረሸን ብቻ ሳይሆን ቀርጸው በቲክቶካቸው ይለቁታል። (እኔም ከዚያው ነው ያገኘሁት) ምርኮኛና ቁስለኛ መረሸን በዓለምአቀፍ ሕግ የጦር ወንጀል ይመስለኛል። ብቻ ይሄን ቪድዮ ያዙልኝ።
ቪድዮ ፪
"…ሰሜን ወሎ ነው። የዐማራ ፋኖ በወሎ ከብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ጋር ውጊያ ይገጥማል። ገጥሞም ይሸነፋል። የኦሮሙማው የጁላ ሠራዊትም እንደ ልማዱ ይማረካል። መማረኩ ብቻ ሳይሆን ፍሪዳም፣ ሰንጋም ታርዶለት፣ ጠጅ ተጥሎ፣ ጠላ ተጠምቆለት፣ ሻወር እየወሰደ፣ ያማረ ጽዱ ልብስም ተቀይሮለት፣ በመከላከያ እያለ የማያገኘውን ምግብ እየበላ በሸነና እያለ ፈታ ብሎ በእንክብካቤ ይኖራል።
"…እኔምለው ግን ፋኖ ገንዘብ፣ ስንቅ ተርፎት ነው? እጸድቅ እንደሁ ብሎ ነው? እንዲራሩለት ነው? ፋኖ ተተኳሽ አለው? ሠራዊቱ ጠግቦ በልቶ አድሮ ነው? የኦሮሙማው ጦር ፋኖን ቢማርክ በዚህ መልክ ነው የሚይዘው? ታሞ ሆስፒታል የተኛን ፋኖ አውጥቶ በመኪና ጭንቅላቱ ላይ ሄዶ የሚጨፈልቅ፣ ፋኖ አከማችሁ እያለ ሃኪሞችን ለሚረሽን የገዳይ አገዛዝ ወታደር እንዲህ ልነጠፍልህ ማለት፣ አብልቶ፣ አጠጥቶ፣ የተለመነ ዶላር፣ የገበሬ ቀረጥ የኪስ ገንዘብ ሰጥቶ መስደድ ፌር ነው ወይ? ከምር ብዙ ጥያቄ ነበረኝ ጠፋኝ። ምን ልጠይቅ ነበር በናታችሁ? ቆይ ሳስታውስ እጠይቃችኋለሁ።
•አትማርክም እንጂ ሱማሌ ብትማርክ እንዲህ…
"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6። “…ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።” መዝ 65፥5
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ተቀበል…
"…ከአንድ የመሸጋገሪያ ሙዚቃ በኋላ አንድ አድርስልኝ የተባልኩትን ማስታወቂያ ለቅቄላችሁ ለዛሬ እንሰነባበታለን።
• መርዞ ና…!😂
ተቀበል…!
"…ፈጣሪም እያየህ ለምን ዝም አልክ እንዳይለኝ ይሄን ጎምቱ የዐማራ ትግል መሪ ዶፍቶሩን ነኝ ባይ እስቲ አሁን ደግሞ አማርኛ ላስተምረው…
• ዶፍቶርዬ…
• ስራ አይባልም ሥራ እንጂ
• ህዝብ አይባልም ሕዝብ እንጂ
• ሶሎሞን አይባልም ሰሎሞን እንጂ
• አጣናው ወይስ አጠናው? ?? ይህን አላውቅም።
• ብሄርተኛ አይባልም ብሔርተኛ እንጂ
• አማራ አከራካሪ ነው ዐማራ፣ ኣምሓራ የሚሉም አሉና። እሱን አላርምህም። ሌላውን ግን ከአንድ ዶፍቶርነቱ 12 ዓመት ከፈጀበት ስኳድ አይጠበቅም። የሕዝብህን ቋንቋ ጠንቅቀህ ሳታውቅ እንዴት ነው የእነ ጌታ አስራደ አለቃ የሆነከው። በእውነት ልክ አይመስለኝም። ግን ደግሞ አያገባኝም። አማርኛህን ብቻ ካስተካከልክ ለእኔ በቂዬ ነው። ✍✍
~ በዚያውም 65 ሺ ዶላራቸውን መልስ።
ጉድ በል ጎንደር
አማርኛ መምህር መጣልህ ከሐረር …ማለት አሁን ነው። እንዲህ እንዲህ እያልኩ አስተነፍሳችኋለሁ። ዐማራን እንደማትወክሉም አሳያችኋለሁ።
• ከፈንድ ስብሰባው መልስ እንጠብቅህሃለን። እውነት ጎንደር ስኳድ አይደለም። ስኳዶቹማ በስም ይታወቃሉ። ይዠለጣሉም። 😁
• ደግሞ አንተን ሳርምህ የጎንደር ሕዝብ አማርኛ አይችልም አለኝ ብለህ በጎንደር ፋኖ ስም መግለጫ አውጥተህ በአበበ በለውና በሀብታሙ አያሌው ሰበር ዜና ብለህ አሰድበኝ አሉህ…? 😂 …አድማጭ ተመልካቾችም እያያችሁ ዝም አትበሉ። የዐማራ ፋኖ መሪውን ዶፍቶር አማርኛውን አርማችሁ ዐማራ አድርጉት። 😂
"…ተቀበል ይቀጥላል…!
ተቀበል…!
"…የኦሮሞ ብልፅግና ሲፈልግ ከሻአቢያ፣ ሲያሻው ከሱዳን፣ በል ሲለው ከሶማሊያ፣ ደስ ሲለው ደግሞ ከግብፅ ጋር ማንንም ሳያማክር በሃላል ይሠራል። ይሄን እንደ መብትም ያየዋል። ደግሞም መብቱ ነው።
"…መልካም… ታዲያ ያው የኦሮሞ ብልፅግና ከሻአቢያ ጋር ሲታረቅም፣ ሲጣላም ለዐማራ አላማከረም። ከኦነግም ጋር ታንዛኒያ ድረስ ሂዶ ሲደራደር ለዐማራ አላማከረም። ከግብፅ ጋር ሲጣላም፣ ሲታረቅም ዐማራን አላማከረም። ከወያኔ ጋር ሲጣላ አጋዥ ፈልጎ ለዐማራ ከነገረ ዐማራን ካማከረና ትግሬና ዐማራን ደም አቃብቶ ሲያበቃ ከወያኔ ጋር ሲታረቅ እንኳን ሊያማክረው ጭራሽ ዐማራን ድራሽ አባትክ ይጥፋ ነበር ያለው። ሃቅ።
"…አሁን የምር ይሁን የፌክ ወያኔ ለሁለት ተከፍላለች። ሻአቢያና የኦሮሞ ብልፅግናም የተጣሉ መስለው እየታዩ ነው። የአቢይ ብልፅግና ከጌታቸው ረዳ ጋር የመሥራት ፍላጎት አለው የሚሉም አሉ። መብታቸውም ነው።
"…የሆነው ሆኖ የእኔ ጥያቄ አሁን የዐማራ ፋኖ ከሻአቢያም ጋር ይሁን፣ ከትግሬ ጋር፣ ከሱዳኑ ሃሚቲ ጋርም ይሁን ከሌላ ኃይል ጋር ተነጋግረው ቢሠሩ፣ ቢታገሉ ኃጢአቱም፣ ወንጀሉም እምኑ ላይ ነው? ለዐማራ ሲሆን ክልክል፣ ለብልግና ሲሆን የተፈቀደ የሚሆነው ለምንድነው? ስላልገባኝ ነው። ጀስት ጥያቄም ነው። የገባችሁ እስቲ መልሱልኝ…!
• ብሊስ… ብሊስ…
መልካም…
"…የደራሲ አዜብ ውርቁን ጦማር በ10 ደቂቃ ውስጥ 3 ሺ ሰው አንብቦታል። አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። ቶሎ ቶሎ ሓሳባችሁን ስጡበትና ወደ ዕለቱ የተቀበል የመሰንቆ ግጥም መርሀ ግብራችን እናልፋለን።
• እየኮረደራችሁ…😂
መልካም…
"…አሁን ደግሞ ሳምንታዊው የግጥም፣ የቅኔ ማዕበል የሚፈስበት የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን እስኪደርስ የደራሲ አዜብ ወርቁን ምርጥ ዕይታ የሚያሳይ ግሩም የሆነ ጦማር እጋብዛችኋለሁ።
• የፈራረሰው 😂 የኮሪደር ልማት ፎቶ አዜብ ወርቁን አይመለከትም። የቶፕ ቪው፣ የመብራት ቀረጻው የኮሪደር ልማት የእነ ቶሎቶሎቤት ግድግዳው የሌማት ትሩፋት የሆነው የእነ ደርምሴ ድርምስምስ ፎቶው የራሴ ምልከታ ነው። ሆኖም ግን አዜብ ጦማር ላይ ጥድፊያውን ለማሳየት ስለፈለግኩ ነው ፎቶውን መለጠፌ። እንጂ አዜብን አይመለከታትም።
"…የአዜብን ጦማር ካነበባችሁ በኋላ እናንተም የምታውቁትን የልማት ተነሺነት ገጠመኝ እንድታወጉንም ትመከራላችሁ። እንዲህና እንዲያ እያልን ቅዳሜ ከሰዓታችንን ውብ አድርገን የቴሌግራም መንደራችንን በሳቅ፣ በእንባና በለቅሶ፣ በደስታና በሀዘን ሰው ሰው የሚሸቱ መርሃ ግብሮችን አያሳየን ፈታ ስንልበት እናመሻለን።
• ለምጠይቃችሁ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ስትረባረቡ ሳይ እኔም የመጻፍ አፒታይቴ ይከፈታል። ዝም ስትሉ ግን ሰው የሌለ ስለሚመስለኝ እኔም ጮጋ በል በል ያሰኘኛል።
• አላችሁ አይደል?
"…ጣና ቴቪን እንርዳ… 😁
"…አዝማሪው ግን ነገ ቅዳሜ ከሰዓት አይሻልም ነበር…?
• ዳሩ እኔ ምን አገባኝ…?
• ተቀበል… ግጥም ስጡት ለአዝማሪው።