የመሰናበቻ… ስለ ሁለት ነገር መጣሁ፦
"…አደጋው ከባድ ነው ብለው ኢኮነሚስቶች ሲያስጠነቅቁ ስለሰነበቱበት እና በአገዛዙ ካድሬዎች እና በአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን የእንኳን ደስ አላችሁ የምሥራች ዜና ሲበሠር የከረመውን የብር የመግዛት አቅምን መዳከም በተመለከተ ጥቅምና ጉዳቱን የዘርፉ ባለሙያዎች ይተንትኑት ዘንድ ለእነርሱ ትተን እኔ ግን ከከባዱ ፍልሚያ ማግስት ከእረፍት እስክመለስ ድረስ ለአሁን የመጨረሻዬ የሆነውን ጦማር በዚህ መልክ እለጥፍላችኋለሁ። በዛሬው ጦማሬ የኮሎኔል ጌታሁን መኮንንን የመጨረሻ ማረፊያ ስፍራ እና በኮሎኔል ጌታሁን እና በፋኖ ኮማንዶ ሳሙኤል ባለድል መካከል ተፈጠረ ተብሎ የተሰራጨውን ወሬ በተመለከተ የሁለቱን ሰዎች የስልክ ልውውጥ ትሰሙት ዘንድ ወደ እናንተ አቅርቤላችሁ እንለያያለን።
መረጃ፦ ፩
"…በቅድሚያ የኮረኔል ጌታሁን መኮንንን በተመለከተ ትናንት ለመከላከያ እጅ መስጠቱን ከስፍራው ያለ ለጊዜው ስሙን በሚዲያ የማልገልፀው የሁላችንም ወዳጅ የሆነ ተወዳጅ ወንድም የላከልኝን መረጃ እንደወረደ ማቅረቤን የመረጃው ባለቤት አስታውሶ ዛሬ ደግሞ ሌላ አዲስ መረጃ ልኮልኛል። ትናንት ከአራት ጠባቂዎቹ ጋር ሆኖ ከመከላከያዎቹም ጋር በስልክ ተገናኝቶ እጁን ሊሰጥ ወደ ሊበን ከተማ ለመሄድ መንገድ ጀምሮ እንደነበር እና ሽማግሌዎችን አሻፈረኝ በማለት እጁን ለመከላከያ ለመስጠት ስለተለየን ያን ምክንያት በማድረግ ነበር እጅ ሰጠ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሼ የነገርኩህ በማለት አስታውሶ ነገር ግን ከእኛ እንደተለየ እንደ ድንገት መንገድ ላይ ምን ሓሳቡን እንዳስቀየረው ሳይታወቅ ከመከላከያዎች ጋር ይድረስ አይድረስ፣ ይገናኝ አይገናኝ ሳይታወቅ "ሓሳቡን ቀይሮ ወደ ጃዊ አካባቢ ሄዷል የሚል መረጃ ደርሶን ቆይቷል። አሁን ግን ነገሮች ተለዋዋጭ ቢሆኑም ተለዋጭ ነገር ካለም መልሼ እስክነግርህ ድረስ ለጊዜው ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ለእስክንድር ነጋ ድጋፍ ከሰጠውና በአመለ ሸጋው ፋኖ ደረጀ ከሚመራው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ መግባቱም ተነግሯል። የተለየ ነገር ከተሰማ ብቻ በዚህ ጉዳይ እመለሳለሁ። ደግሞ መከላከያዎች አስረው ፈትተው ለምን ለቀቁት ምናምን እያላችሁ እንዳታዝጉኝ አደራ። ይሄን በተመለከተ እነ አበበ በለው፣ የጎንደር ስኳድ፣ ጎጤና እነ ጌትነት አልማው ይተነትኑላችኋል። ስለእሱ አይመለከተኝም።
መረጃ፦ ፪
"…ሁለተኛው መረጃ ፋኖ ሳሙኤል ባለድልን በተመለከተ ይሆናል። ሰሞኑን ሳይወለድ የሞተውና የጨነገፈው የእስክንድር ነጋው አዲሱ የጨበራ ጩሮራ ምርጫን መክሸፍ ተከትሎ በጎንደር ፋኖ ላይ ክፍፍል ለመፍጠር በሚመስል መልኩ በብዙ በደከሙት በእነ ዶ/ር ምስጋናው አንዷለም እና ሙሉነህ፣ በግንቦቴዎች፣ በግንባሩና በሠራዊቱ ግሪሳዎች መሪነት በኮማንዶ ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ላይ የተቀናጀ የስም ማጥፋት ዘመቻም ተከፍቶበት አይቻለሁ። ዘመቻው ልክ አርበኛ ፋኖ ሜጀር ጄነራል ውብአንተን ዘመቻ ከፍተው ሕይወቱ የተቀጠፈበትን መንገድ ይመስላል።
"…ውባንተ ከመሞቱ እና ከመሰዋቱ በፊት መጀመሪያ ስሙን ነበር ያጠፉት፣ ዘመቻ ከፋቾቹ ደግሞ በሀብታሙ አያሌው፣ በሀብታሙ በሻህ እና በሀብታሙ በቀለ ጉደታ የሚመራው የቲክቶክ ሠራዊት ነበር። ይሄ ሠራዊት ነበር ቅድሚያ የስም ማጥፋት በውባንተ ላይ የከፈተበት። አርበኛ ፋኖ መሳፍንት በበላይ ጠባቂነት የሚያዙት እና አርበኛ ፋኖ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው የጎንደር ዕዝ ደግሞ መግለጫ ጭምር ነበር ጽፎ በኢትዮ 251 ውስጥ ይሠራ ለነበረው ጋዜጠኛ ሙላት አድህኖ በመላክ ያንን መግለጫ በማንበብ ብቻ ሳይሆን መግለጫውን ለውይይት በማቅረብ በመረጃ ቲቪ ላይ በማሠራጨትም ስሙን አጥፍተው አዋክበው፣ አዋክበው ለሞት ያበቁት። በዚያው መንገድ ነው አሁንም ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ላይ የተቀናጀ ዘመቻ የከፈቱት።
"…በፋኖ ሳሙኤል ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ለየት የሚያደርገው በዘመቻው ላይ ሳሚ የሚደግፈውን የአቶ አሰግድን ግሩፕ ኮሚቴ ሁላ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ የዋን ዐማራዎቹ እነ አኪላና ዘርዓ ያዕቆብም ጭምር ለሳሚ "ቃየን" የሚል የወንድም ገዳይነት መጥፎ ብያኔ ያለው ስም ሰጥተው ሲጨፈጭፉት እንደነበርም መመልከቴ ነው። አርበኛ ጋሽ አሰግድ በደረሰበት ውክቢያ አገዛዙ እጅ ሲወድቅ እንዴት እንደወደቀ የሚያውቁት ዋን ዐማራዎች በሳሙኤል ባለድል ላይ የከፈቱት ዘግናኝ ዘመቻ ግን የማልደብቃችሁን ግርምት ፈጥሮብኛል። ዋን ዐማራዎች ዐማራ ነኝ ብለው እስከተነሡ ድረስ ለሚያነሡት መከራከሪያ ጣልቃ ገብቼባቸው የማላውቅ ቢሆንም በዚህኛው ግን በድፍረት ልክ አደላችሁም ልላቸው ወደድሁ። ለምሳሌ ከፋኖ አመራሮች መካከል ጋሽ አሰግድ እኔ ራሴ ተጋብዤ በተገኘሁበት አንድ የስልክ ውይይት መድረክ ላይ አኪላ የሚረዳኝ ልጅ ነው ብሎ የመሰከረለትን፣ ገንዘብ እንዲያስተባብር የፈቀደለትን ሰው እኔ ምንም አስተያየት ልሰጥበት አልችልም። ነገር ግን አኪላም ባለበትና አቶ አሰግድ በነበረበት አንድ መድረክ ላይ የተናገርኩትን ሁላቸውም ያስታውሱታል። አሁን ግን እነ አኪላ በኮማንዶ ሳሙኤል ባለድል ላይ የከፈቱት ቅጥያጣ የጥላቻ ዘመቻ፣ ከፖለቲካ ቅማንቴው፣ ከኦሮሙማው ፀረ ዐማራ ቡድን ጋር ስምም ሆኖ ስላገኘሁት የመጀመሪያውን ልክ አይደላችሁም የሚለውን የጭቃ ዥራፌን መልእክት አንሥቼ በስሱ ልዠልጣቸው ወደድኩ። ልክ አይደላችሁም።
"…ውባንተ ይገደል ሲል የከረመው የእነ ሀብታሙ አያሌው ገረድ ሳሚ ቅማንቴው በቲክቶክ መንደሩ በከፈተው ቤትም ውስጥ አሁንም ስለ ሳሚ ባለድል መገደል፣ መወገድ አንሥተው ሲወያዩ የነበረውን ውይይትም ለታሪክ ቀድቼ አስቀርቼ በእጄ ይዤዋለሁ። መጀመሪያ ውባንተ፣ ከዚያ አሰግድን፣ ከዚያ ዘመነን መግደል ይፈልግ የነበረው አደገኛ ግሩፕ ውባንተን በመግደል አሰግድን በማዋከብ አገዛዙ እጅ ላይ እንዲወድቅ ካደረገ በኋላ በቀጥታ የግድያ ዘመቻውን የከፈተው በዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ከሣሴ ላይ ነበር። ዘመነ ካሤን በቀላሉ መድፈር እንደማይቻል ካዩ በኋላ ደግሞ ፊታቸውን በቀጥታ ወደ ምሬና ወደ ባዬ ከማዞራቸው በፊት በቅድሚያ ወደ አርበኛ ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ለይ ነበር። በዚህ ዘመቻ ላይ ተደብቀው ከርመው የነበሩት እነ ወንድም አያሌው መንበር ሁላ ናቸው ወደ አየር ሞገዱ የተመለሱት። እኔ ሳሚን አላውቀውም። እየተነሣበት ያለው ማዕበል ግን ወዴት እንደሚያመራ ስለሸከከኝ የግድ ጣልቃ ለመግባት ተገድጃለሁ።
"…ሳሙኤል እየተከሰሰ ያለው እነ አኪላ በከሰሱበት የትግሬነት ማንነት ላይ ሁላ ነው። በሸዋ የዐማራ ፋኖ ከምዕራብ ትግራይ ይውጣ ብሎ ሲታገል የከረመውን ሰሎሞን ወልደገሪማን አጨብጭቦ የተቀበለው ቡድን አሁን ሳሚን ከመሬት ተነሥቶ ማንነቱን ትግሬ አድርጎ ስሎ ነው ዘመቻ የከፈተበት። እንዲያውም ክፍለጦሩን ራሱ የዓድዋ ክፍለጦር ብሎ የሰየመው ሳሚ ትግሬ ስለሆነ ነው ሁላ ብለው የሚናገሩ ሰዎችን ሰምቻለሁ። መነሻቸው ደግሞ ኮረኔል ጌታሁን ወደ አርበኛ ባዬ ጋር ልለፍ ብሎ መንገድ ሲጀምር አታልፍም ብሎ መንገድ የዘጋበት ሳሚ ነው የሚል ክስም አቅርበውበት ነው ዘመቻውን የከፈቱበት። ኮረኔል ጌታሁን ሲያለቅስ ነው ተብሎ የተለቀቀውን ቪድዮም እኔም "ቢያለቅስ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ነው፣ ከውርደት ጋር አይያያዝም ብዬ ማቅረቤም ይታወቃል።👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
በመጨረሻም…!
"…በጎጃም ዐማራ ፋኖ በጎጃም የሥራ አመራር ሓላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ ሳለ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ ማስረሻ ሰጤና እስክንድር ነጋ ከእናት ድርጅቱ ገንጥለው አስወጥተውት እናት ድርጅቱም በአንድ ቤት ሁለት አባወራ የለም። ንብረት አስረክብ፣ እጅህንም ስጥ ብለው ቢጠይቁት ሞቼ ነው ቆሜ ብሎ በሚዲያ እንዲፎክር ካደረጉት በኋላ በመጨረሻ በቁጥጥር ስር ሊያውለው የተንቀሳቀሰውን በጎጃም የዐማራ ፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት ሠራዊቱ ለጎጃም ፋኖ እጁን ሰጥቶ ነበር።
"…ኮረኔል ጌታሁን በሽማግሌ ግፊት ለመደምሰስ ከጫፍ ደርሶ ቢድንም አስቀድሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ለእነ ዘመነ እጅህን ከምትሰጥ እና ከምታዋርደን ሽጉጥህን ጠጥህ ሙት ቢሉትም እሱ ግን ጋሾላ ገዳም ውስጥ ከተወሰኑ ተከታይ ፋኖ ልጆቹ ጋር ቆይቶ ነበር። ሰው ቢላክበትም እምቢኝ ብሎ ቆየ። ልጆቹም ተበትነዋል። ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዐማራ ፋነለ በጎጃም እጅ ሰጥተው ተቀላቅለዋል። እሱ ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ግን አራት አጃቢዎችን ይዞ ወደ ሊበን ከተማ ወጥቷል። በይፋም እጁን ለመከላከያ ሰጥቷል።
"…ሀብቴ ወልዴ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ እስክንድር ነጋ በአርበኛ አሰግድ መኮንን በመከላከያ እጅ መውደቅ ሲሳለቁ፣ ኮረኔል ጌታሁንን ሲያጀግኑ፣ ሲያሞግሱ ቢቆዩም ኮረኔሉ ግን ጎመን በጤና ብሎ እጅ መስጠቱ ተሰምቷል። አበበ በለው፣ ሀብታሙ አያሌው አጀግነው አጀግነው ሰውዬውን አስበሉት። አለቀ በቃ።
• ጎጃም ጎጄ መለኛው ግን አንደኛ…!!
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር አሁን ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ተከታተሉን።
• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/Xx7nJiC45FQ
• ሻሎም… ሰላም…!
"…ከዓመት በፊት "እያናፈጠልን ነው" ብሎ አመስግኖኝ ነበር ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው። እኔ መቼም ወዳጅ አይበረክትልኝ በዚያ ላይ ሲያመኝ ጤና የለኝ አይደል? 😂 ቋሚ ወዳጅም ቋሚ ጠላትም የሌለኝ እኔ ዘመዴ ይኸው ዛሬ ደግሞ አለቃው እስክንድርን ጨምሮ ሁላቸውን አሯሩጬ በጭቃ ዥራፌ አናፍጣቸው ጀመር። ከምር እያናፈጥኳቸው ነው አይገልጸውም።
• እኔ ማለት ዘመድኩን ነቀለ ነኝ (አባ ንቀል)
ፋኒት ትእግስት ጫኔ…💪
"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም በግዛቱ ውስጥ የጠላትን ተልእኮ አንግበው፣ ከዐማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ውጪ ያሉትን የማጥራት ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል። በአንድ ቤት አንድ አባወራ በሚለው ዐማራዊ ይትበሃል መሰረት የዐማራ ፋኖ በጎጃም በጎጃም ውስጥ ሆነው በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ወደዱም፣ ጠሉም፣ በግድም በውድም ወደ አንድ ይመጡ ዘንድ መመሪያ አውርዶ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምሯል። እንዲያ ሲሆን ተጠያቂነቱም ከፍ ይላል።
"…በዚሁ መሠረት የጎጃም ፋኖ ከድርጅቱ የመልቀቂያ ሕጋዊ ደብዳቤ ሳይደርሰው፣ የድርጅቱን ንብረት፣ የጦር መሣሪያና የሰው ኃይል ይዞ በሀብታሙ አያሌው፣ በማስረሻ ሰጤና በእስክንድር ነጋ ሰበካ የጎጃም ፋኖን ከድቶ ድርጅት ቀይሬአለሁ ያለውን ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተንቀሳቅሶ አሁን የበዛው ሰራዊቱ ወደ እናት ድርጅቱ ተመልሶ ኮረኔሉ በጫካ ሆኖ በሽምግልና ተይዟል። ይሳካል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።
"…ሌላው ዜና ደግሞ ጠዋት የነገርኳችሁ የጋዜጠኛ ወግደረስ በጎጃም ፋኖ ቁጥጥር ስር መዋል ነው። ለመላው የዐማራ ፋኖ ከሕዝብ ከተሰበሰበው ዶላር ላይ በእስክንድር ነጋ እየተከፈለው በጎጃም የእስክንድር የምናብ ሠራዊት እና ለሀብታሙ አያሌው ቅዠት ኢትዮ 360 በጎጃም ምድር ቋሚ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል የነበረውን ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን የዐማራ ፋኖ በጎጃም በቁጥጥር ስር አውሎታል። ወግደረስን በቁጥጥር ስር ያዋለችው ደግሞ ፋኒት ትግስት ጫኔ ትባላለች። ዛሬ ጠዋት 1:15 አካባቢ ፈለገ ብርሃን አልጋ ቤት ውስጥ እያለ ነው ከእናት ድርጅቷ ከጎጃም ፋኖ አመራሮች በተሰጣት ትእዛዝ መሰረት ፋኒት ቲጂ ፋኖዎቿን አስከትላ ቀጨም ያደረገችው። አሁን የሀብታሙ አያሌውና የእስክንድር የመረጃ ምንጭ ከስሩ ከሰመ ማለት ነው።
• ብራቮ ቲጂ 👏👏👏 ብራቮ ጎጄ መለኛው
👆ከላይኛው ይቀጥላል…✍✍✍ "…የዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ዓላማ ይህ በሆነበትና ዐማራው በኢትዮጵያዊቱ ላይ ጥያቈ ያነሳ ይመስል እስክንድር ግን አንጠልጥሎት የሚዞረው ጉዳይ የመኖር መብት የተነፈገው የዐማራ ሕዝብ ያነሳውን የኅልውና ጉዳይ ሳይሆን የግንቦት ሰባት ፀረ- ዐማራዎች የዐማራን የኅልውና ጥያቄ ወደ ዜግነት ጉዳይ አውርደው በዐማራው መቃብር ላይ የዜግነት ፖለቲካቸውን ሊያራምዱ የሰጡትን “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል መፈክር ነው። በዚህ መፈክር መሰረት ለዐማራ ኢትዮጵያዊነት ከሆነ እድገት በኋላ የሚደርስበት ግብ ወይም መዳረሻ ነው።
"…በሌላ አነጋገር ዐማራው ዛሬ ላይ በእስክንድር አሳዳጊነትና ሞግዚትነት ጉዞ ላይ ስላለ የደረሰበት ግብ ወይም መዳረሻ የለውም። እስክንድር ነጋ ዐማራውን እንደዚህ ታሪክ የሌለውና ኮምፓሱ የጠፋበት መርከብ ለማድረግ ይኼን ያህል ርቀት የሄደበት ምክኒያት የምታወቀው “በኢትዮጵያዊነት ስታገል” ስለነበር ዐማራ መባል፣ በዐማራ መታገል እንደማነስ መስሎ ስለሚሰማውና እንዳይተወው በዐማራ ላይ ካልተረማመደ በስተቀር ከሥልጣን መድረስ እንደማይችል መስሎ ስለተሰማው ነው።
"…ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ከ ያ ትውልድ የተማሪ ፖለቲከኞች የተወረሰው ኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ሳትሆን በምኒልክ ቅኝ ግዛት የተሰባሰቡ ነጻ የነበሩ የአፍሪካ አገሮች የተሰባሰቡባት ኢምፓየር አድርጎ የማየት አባዜ ነው። እስክንድር “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ሲልም ይቺን በያ ትውልድ አእምሮ ኢምፓየር ሆና የተፈጠረችውን የነጻ አገሮች ስብስብ መሪ ከሆንሁ በኋላ ኢትዮጵያ ወደምትባል አገር አሳድጌ መዳረሻዬ አደርጋታለሁ እያለን ነው። እብደት ካልሆነ በስተቀር በዚህ የእስክድንር እንቶ ፈንቶ የሚስማማ ፋኖ ሊኖር አይችልም።
• ማጠቃለያ!
"…የፋኖ የኅልውና ተጋድሎ በአንድ ማዕከል ስር እንዲሰበሰብ ለማድረግ እሠራለሁ የሚል አካል ቢኖር የመጀመራያውና ቀዳሚው ተግባሩ መሆን ያለበት የፋኖ አንድነት እንዳይሳካና ሐዲዱን እንዲስት እያደረገ ያለው (The elephant in the room) እስክንድር ነጋ መሆኑን ዕውቅና ሰጥቶ ለጉዳዩ ዘለቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል።
"…በእኔ በኩል እስክንድር ነጋን በተመለከተ የሚታየኝ አንድ አማራጭ ብቻ ነው። እስክንድር ነጋ የፋኖ የኅልውና ተጋድሎ ችግር የሆነው የሥልጣን ፍላጎቱ ከቁጥጥር ውጪ አድርጎት ኅሊናው ሊወቅሰው ወደማይችል ግብዝ ፍጡር የለወጠው በመሆኑ ነው። ሆኖም ግን ዐማራው እያደረገ የሚገኘው የኅልውና ተጋድሎ በመሆኑ እስክንድር የኅልውና ተጋድሎው መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ ከሥልጣን ሽሚያና የዐማራውን ድምጽ ከፋኖ ከመጫረት ለጊዜው ገለል ብሎ እንዲቆይና የኅልውና ተጋድሎው መቋጫ አግኝቶ የፖለቲካ መድረክ ሲከፈት በፈለገው ፕሮግራምና ፓርቲ ስር ለምርጫ ድል ለዲሞክራሲውን ይዞ ቢወዳደር የተሻለ እንደኾነ፤ እስከዚያ ድረስ ግን በሞያው ተወስኖ አለኝ የሚለውን ተሰሚነት በመጠቀም የፋኖን የኅልውና ተጋድሎ እንዲረዳ ማግባባት የሚል ነው።
"…ከዚህ ውጭ የእስክንድር ጉዳይ ተለይቶ እልባት ሳይሰጠው ፋኖን አንድ ለማድረግ መሞከር በትግሉ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ከማድረስ ውጭ ዘላቂነት ያለው መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል መታወቅ አለበት። ነገር ግን የግል የስልጣን ፍላጎቱን ለማርካት ቆርጦ በተነሳው በእስክንድር ነጋና በተቀረው የኅልውና ተጋድሎ በሚያደርገው የአማራ ፋኖ መካከል መጠላለፍ ሳይፈጥር ሕዝብዊ ተጋድሎውን ወደፊት ማራመድ ይቻላል የሚል ሓሳብ ያለው ሰው ቢኖር ለመስማት ዝግጁ ነኝ። አበቃሁ!
• ተጻፈ በአቶ አቻምየለህ ታምሩ (ዐማራ ነው)
• አቅራቢ…
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
• ዐማራ አቀፍ የፋኖ አንድነት ለምን ከሸፈ? የሚፈለገው የፋኖ አንድነትስ እንዲመጣ ምን ሊደረግ ይገባዋል?
"…በየጠቅላይ ግዛቱ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶች አነሳሽነት እና በቅን አሳቢ ዐማራዎች ግፊት የዐማራ ፋኖን ወደ አንድ የተማከለ አደረጃጀት ለማምጣት በርካታ ጥረቶችና ሙከራዎች ተደርገዋል። ሆኖም ግን ጥረቶችና ሙከራዎች ሁሉ አንድ መሰረታዊ ችግር አለባቸው። ጥረቶቹና ሙከራዎቹ የተደረጉት በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ጣልቃ እየገባ ልዩነትና አለመግባባት እንዲሰፍን ያለ እረፍት የሚሠራ ችግር ጠማቂ ኃይል እንደሌለ በመቁጠርና የፈጠረውን ችግር በማለባበስ ነበር። “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” እንዲሉ በፋኖዎች መካከል የተፈጠረውን ችግር ምንጭ (root cause) በድፍረት ሳይመረምሩ በየጠቅላይ ግዛቱ ወገን ለይተው የየራሳቸው አደረጃጀት የመሰረቱትን ፋኖዎች እንዲሰበሰቡ በማድረግ ብቻ ዘለቄታ ያለውና እንደ ብረት የጠነከረ አንድነት ያለው የተማከለ የዐማራ አደረጃጀት እንዲፈጥሩ ማድረግ አይቻልም።
"…በየጠቅላይ ግዛቱ የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች አንድ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ጠላት እንዲተያዩና በጦር እንዲፈላለጉ በተደረጉበት ሁኔታ ከላይ የተንጠለጠለ መሪ በመሰየም የዐማራ ፋኖ አንድነት ሊመጣ አይችልም። በመሆኑም ዐማራ አቀፍ የፋኖ አንድነት ለመፍጠር በየጠቅላይ ግዛቱ በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች መካከል ጠንካራ ወንድማዊ አንድነት እንዳይፈጠርና በጠላትነት እንዲፈላለጉ ያደረጋቸው አካል መታወቅና መለየት አለበት።
"…የዐማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ የነበረው አሰግድ መኮንን ከይዞታው ከእስከንድር ነጋ ጋር በሚሠሩ ፋኖዎች ተባሮ ይንከራተት በነበረበት ወቅት መሆኑን ይመራው የነበረው ዕዝ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ይቻላል። በማኅበራዊ አውታሮች ሲዘዋወር ባዳመጥነው የአርበኛ አሰግድ ድምጽም አሰግድ በእስክንድር ነጋ በሚታዘዙ ፋኖዎች የደረሰበትን በደል እንባ እየተናነቀው በዝርዝር ሲናገር ሰምተነዋል።
"…መሪ ለመሰየም የተሰባሰቡ የየጠቅላይ ግዛቱ የፋኖ አዛዦች ይህን ችግር ተጋፍጠው መፍትሔ ማስቀመጥ ሲገባቸው ልክ ወንድማዊ ስምምነት በመካከላቸው ያለ ይመስል የፋኖ መሪ ለመሾም መስፈርት ዘርግተው ገመድ መጓተትና ምርጫ ለማድረግ ጥቆማ ውስጥ መግባት አልነበረባቸውም። ይልቁንም ሸዋ ላይ እስክንድር ነጋ የፈጠረው ችግር ምንድን ነው? ብለው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ቢሞክሩ ኖሮ ዛሬ ላይ በአርበኛ አሰግድ መኮንን ላይ የደረሰው መከራ ላይደርስ ይችል ነበር። በርግጥ የሸዋው ጎልቶ ስለወጣ እዚህ ላይ ተነሳ እንጂ እስክንድር ነጋ በረገጠው ምድር ሁሉ ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ በጎጃም፣ በጎንደርና በወሎም የፋኖን አንድነት እያመሰው ነው።
"…በአጭሩ መሪ ለመሰየም የተሰባሰቡ የፋኖ አዛዦች በየጠቅላይ ግዛታቸው አንድ ላይ መቆም ሳይችሉ ወይንም በጠላትንት እየተያዩ ወይም እንዲተያዩ ሚሊዮኖች እያፈሰሰ የሚሠራ ኃይል በመካከላቸው እያለ በዐማራ አቀፍ አደረጃጀት አንድ ላይ መቆም እንደማይችሉ ማሰብ ነበረባቸው። ምርጫ ተብየው ተሳክቶላቸውና አንድ ሰው መሪ አድርገው የመረጡ ቢሆን ኖሮ በመካከላቸው እንዲፈጠር የተደረገው በጠላትነት መተያየት በእርቅ ባልተፈታበት ሁኔታ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በወሎና በጎንደር የተደራጀውን ውሕዱን ፋኖ ማን ሊመራው ነበር? የሸዋውን ዕዝ የሚመራው አሰግድ ወይስ መከታው? የጎንደርሩንስ? የወሎውንስ? የጎጃሙንስ? ብለው አርቀው ሳያስቡ ዐማራ አቀፍ የፋኖ እውነተኛ አንድነት ለማምጣት መሞከራቸው ትልቅ ስህተት ነበር።
"…በጉባዔ አንድ ሰው በመሪነት ስለተሰየመ ብቻ ጎራ ለይተው በጠላትነት እንዲፈላለጉ በተደረጉ የየጠቅላይ ግዛት አደረጃጀቶች መካከል የሰፈነው ጠላትነት ተንኖ ሊጠፋ አይችልም። በጠላትነት የሚፈላለጉ ቡድኖችን እርቅ ሳያወርዱ አንድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ውጤቱ አንዱ አንዱን ጥሎ ማለፍ ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ አንድነት ሊያመጣ አይችልም። በፋኖዎች ዘንድም የሆነ ይሄ ነው።
"…በአጭሩ በፋኖዎች ዘንድ ተገቢው ክብደት ተሰጥቶት ብቻውን ተለይቶ መታየት የነበረበትና ከፍ ብሎ ለታዩት ችግሮች ሁሉ መንስዔ የሆነው የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ሳይፈታ የፋኖ አንድነት ሊመጣ አይችልም። እስክንድር ነጋ እንደ ፋኖ አንድነት ዋናው የችግር ምንጭ ታይቶ የፈጠራቸው ችግሮች ቅድሚያ መፍትሔ እስካልተሰጣቸው ድረስ የአንድነት ጥረት ውጤቱ ወደፊትም ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ነው።
"…እስክንድር የዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ችግር የሆነው በፋኖዎች መካከል በሚፈጥረው መከፋፈል ብቻ አይደለም። ይልቁንም በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ እስክንድር ነጋ የሚባል አንድ ለዐማራ የኅልውና የሚጋደል የፋኖ አዛዥ ተደርጎ መቅረቡ ጭምር ነው። እስክንድር ሕዝባዊ ግንባር፣ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ወዘተረፈ እያለ የፈጠራቸውና ከሱ በስተቀር ሌላ መስራች አባል የሌላቸው የውሸት ድርጅቶች ባለቤት መሆኑ ብቻ ሳይሆን የኋላ ታሪኩና በዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ ሊያራምደው በሚሞክረው ፀረ ዐማራ እሳቤው ጭምር ተመዝኖ እንደየ ጠቅላይ ግዛቶቹ የፋኖ አዛዦች አንዱ ተደርጎ መቆጠር አልነበረበትም።
"…እስክንድር በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ላይ ያደረሰው ጥፋት ሁሉ ወደ ጎን ተብሎ እንደ አንድ የፋኖ መሪ ይቆጠር ቢባል እንኳን ለእውነተኛ ፋኖዎች ፍትሐዊ አይሆንም። እስክንድር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከዐማራው ማኅበረሰብ የሰበሰበ፤ የላቀ ገንዘብ እየከፈሉ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን እየገዙ ተጫዋች ሲያዘዋውሩ እንደሚውሉ የአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦች በየጠቅላይ ግዛቱ ከተሰባሰቡ የፋኖ አደረጃጀቶች ግለሰቦችን በረብጣ ብር እየገዛ ሲያዘዋውር የሚውል፤ በዐማራ ሕዝብ ትግል ስም የሰበሰበውን ገንዘብ የዐማራ ልጆች በሚከፍሉት መስዕዋትነት የሚሠራውን ገድል እየገዛ ያናወዘውን የሥልጣን ወልፉ ለማርካትና የዐማራን መስእዋትነት የሰልጣን መወጣጫና መፈንጫ አድርጎ የሚቆጥር በፍቅረ ሥልጣን የተለከፈ ሰው ነው።
"…እስክንድር የሥልጣን መዳረሻዬ ናት በሚላት ኢትዮጵያ ያነገበውን ርዕሰ መንግሥትነት ከዐማራ የኅልውና ተጋድሎና ከዐማራ በላይ በማድረግ ሌት ተቀን ሲያላዝኑለት የሚውሉ የብዙ ምላሶችና ጆሮዎች ባለቤት የሆነ ግለሰብ ነው። እነዚህ የእስክንድር መጠቀሚያ የሆኑ ምላስና ጆሮዎች ለኅልውና ተጋድሎ ተብሎ ከተሰባሰበው/ከሚሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ ቀለብ እየተሰፈረላቸው በየቀኑ ሲያቀርቡ የሚውሉት አቢይ አሕመድ በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚወርደውን መከራና ፍዳ ሳይሆን እስክንድር ነጋ በየቀኑ የሚነሳውን ፎቶና ተንቀሳቃሽ ምስል እያሳዩ እስክንድር መዳረሻው ለሆነችው ኢትዮጵያ ምን ያህል ከፈጣሪ የተሰጠ መሪ እንደሆነ በትወናና በመወድሰ የታበጀ የእስክንድር አምልኮ ነው።
"…ከእስክንድር ጋር ለውድርድር ቀረቡ የተባሉት እውነተኛ የፋኖ መሪዎች ደግሞ በዓላማ ከሚከተላቸው የድኃ ገበሬ ልጅ ውጭ ምንም የሌላቸው፤ በትክሻ ወይም በአህያ የተያዘ በሶ፣ ቆሎና ጥሬ እየበሉ፣ በወጣ ገባው አስቸጋሪ የአገራችን መልክዓ ምድር ሲወጡና ሲወርዱ የሚውሉ ምስኪኖች ናቸው። የሥልጣን ወልፉን ለማርካት ለእሱ የሚሠሩ ምላስና ጆሮ፤ እንዲሁም ለፍላጎቱ ማስፈጸሚያ የፋኖ ዕዝ ጭምር የሚገዛበት ረብጣ ገንዘብ ያለውን ግለሰብ ምንም ከሌላቸው ከወሎ፤ ሸዋ፤ ጎጃምና ጎንደር የፋኖ አዛዦች ጋር በአንድ መለኪያ መስፈር፤ እውነትኛ የፋኖ አዛዦችን ከፍ ባለ መለኪያና ፍትሐዊ ባልሆነ ሚዛን እየሰፈሩ፤ እስክንድርን ግን በጣም ዝቅ ባለ ልኬት በመመዘን
መልካም…
"…የምስጋናው ፍጥነት እያስገረመኝ፣ እያስደነቀኝም ነው። 1ሺ ሰው ከምኔው አመስግኖ እንደሚሞላ ሳይም አምላኬን ደጋግሜ እያመሰገንኩትም ነው። በእውነት እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ሌላው በምስጋና መሃል ፀያፍ ቃል መጠቀም፣ መሳደብ፣ አዲስ አጀንዳ ጣልቃ ማስገባት፣ እኔን ጭምር ማመስገን፣ ማወደስ ያስቀስፋል ባልኩት መሠረት እንደምትመለከቱት በምስጋና መሃል ጣልቃ የሚገባ ሰው ጠፍቷል። የሚጻፈው ቃል በሙሉ እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ሆኗል። በእውነት መታደል ነው። ይሄ ሁሉ ሕዝብ በየቀኑ እግዚአብሔር ይመስገን እያለ ሲያመሰግንና ለምስጋና ሲጋፋ ማየት ምንኛ መታደል ነው? አመስጋኞች በረከታችሁ ይደርብኝ።
"…ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ የተጻፈው በእኔ አይደለም። በማን እንደተጻፈ ሰዓቱን ጠብቆ ይቀርብላችኋል።
"…ከዚያ በፊት ግን አሁን ከዐማራ ፋኖ በጎጃም የደረሰኝ ሰበር መረጃ አለ። ይኸውም በጎጃም የግንቦት7፣ የባልደራስ፣ ግንባሩና ሠራዊቱ የሚባሉት የእስክንድር ፍልፈሎች እየጸዱ መሆኑን ነው። ኮረኔል ጌታሁን ከወንድሙ ከዘመነ ጋር ይገናኛል፣ የግንቦቴዎችን ህልምም ይቀጫል የሚል ተስፋ ነው የሰጡኝ።
"…በዛሬው ዕለት ደግሞ የዐማራ ፋኖ በጎጃም በምሥራቅ ጎጃም አካባቢ የሠፈረውን ደርዘን አይሞሌ የእስክንድር የዶላር ሚሊሻን እጅ ለማሰጠትና ንብረት ለመረከብ ክፍለጦር ተልኮ ዘመቻ መጀመሩን ሰምቻለሁ።
"…በሌላ በኩል ጎጃም ተቀምጦ ለሀብታሙ አያሌው፣ ለ360 የዘገባ ሥራ ሲሠራ የከረመው የቀድሞው የባልደራስ የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ፣ የዓለም ብርሃን ሃይማኖት የጦር አደራጅ፣ የግንባሩና የሠራዊቱ አሁንም ሳይወለድ የሞተው የእስክንድር ድርጅት የፕሮፓጋንዳ ሓላፊ የነበረው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ለጎጃም ፋኖ እጅ መስጠቱ ተነግሯል።
• መጣሁ…
ክቡራን ደንበኞቼ ሆዬ… ስላችሁ ወዬ አላችሁ? 😁
"…እህሳ… እኔ አስነቀልቲው ዘመዴ እንዴት ነኝ…?ብፌውስ እንዴት ነው? " …በእኔ በኩል ምን ጎደለ? ምንስ ልጨምር? ምንስ ልቀንስ…?
• እየኮመኮማችሁ ነው…?
"…መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጻችን በ18 ሺ ሰው ተነብቦ ወደፊት ይናደዳሉ ተብለው የሚጠበቁት እንዳለ ሆኖ እስከ አሁን ባለው የቴሌግራም ካምፓኒ መረጃ ላይ 4 ሰው ብቻ ብው 😡 ብሎ መናደዱን ነው የካምፓኒው ሪፖርት የሚያሳየኝ። እናም ተራው የእናንተ ነው። አትፍሩ ደፈር ብለን እንነጋገር። ካለመናገር ደጃዝማችነት ሁላ ይቀራል እኮ። አይደለም እንዴ። ህመሙን ያልተናገረ በሽታው የትአባቱ ይገኝለታል። ይሉኝታ፣ ምናምኑን ወዲያ አሽቀንጥረህ ጣልና በጨዋ ደንብ ተወያይ፣ ተንፍስም።
• 1…2…3…✍✍✍ ጀምሩ
"…እስክንድርን እጠይቃለሁ። ሲጀመር የምታወጣውን መግለጫ አስቀድመህ ለዛራ ሚዲያ ለእስታሊን ሀወይ የምትልከው በሚስትህ ወገን የኢሮብ ትግሬ ስለሆንክ፣ አንተም እንደሚባለው በአባትህ ወገን የተንቤን ትግሬ ስለሆንክ ነው ወይ? እንዴት ነው ነገሩ እስቲ አስረዳን። ስትናበቡ ግን ታስቀናላችሁ። አሁን እስቲ ትግሬ በዐማራ ፋኖ ውስጥ ምን ይሠራል? ጥፋ ከዚህ። ቴዎድሮስ የርዕዮት ሚዲያው፣ ስታሊን የዛራው ሁሉም እኮ የትግሬን ጉድ፣ የህወሓትን ፀእረ ሞት፣ የመቀሌን በወንጀል መጥለቅለቅ፣ የትግሬን መራብ መዘገብ ትተው እንደ ጆፌ ዐሞራ የዐማራ ፋኖ ላይ ነው የተዘፈዘፉት። እሽሽ ጥፉ ከዚህ። የምን በዐማራ ፋኖ ትግል ላይ ማፍጠጥ መለፋደድ ነው? ጥፋ አልኩህ ምደረ ቀላዋጭ ምድረ ገገማ ሁላ። አሁን ዐማራው አዚሙ ተገፎለታል፣ የሱዳኑ ትብትብ ወልቆለታል። በራሱ ኮተቶቹን አራግፎ ወደፊት ይስፈነጠራል። ጥፋ ብዬሃለሁ።
"…እስክንድር ሾተላይ ነው። የአዲስ አበባን ዐማራ ሲያደዝዝ ቆይቶ በመጨረሻ ለኦህዴድ ኦነግ አሳልፎ የሰጠ ይሁዳ ነው። አዲስ አበቤ የሚባል አዲስ ማንነት ፈጥሮ የአዲስ አበባን ዐማራ ያጀዘበ፣ ያጃጃለ፣ ያደነዘዘ፣ ከዚያም ለዘንዶ አሳልፎ ሰጥቶ የሄደ ነው። እስክንድር መዐሕድን ያፈረሰ፣ ቅንጅትን ያፈረሰ፣ የልደቱ አያሌውን ስም ከሲሳይ አጌና ጋር በፕሮፓጋንዳ ድራሽ አባቱን ያጠፋ ሰው ነው። እስክንድር የዐማራን ድልና ነፃነት አጨናጋፊ ፀረ ዐማራ ፀረ ዲሞክራሲ ሾተላይ የሆነ ግልሰብ ነው። እስክንድር ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ አምስት የፖለቲካ ድርጅት የቀፈቀፈ የፖለቲካ ኢንኪዩቤተር ነው። የአምስቱም ፕሬዘዳንት ሆኖ ድርጅቶቹን በትግሬና በፖለቲካው ቅማንቴ ሞልቶ ያጨነገፈ ፀረ ዐማራ የፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ኤጀንት የዐማራ ነፃነት ሾተላይ ነው።
"…እስክንድር ዐማራው በተበጣጠሰም መልኩ ገንዘብ እያዋጣ ወደ ዐማራ ፋኖ ይላክ የነበረውን ገንዘብ እንደ ግንብ፣ እንደ ግድብ ሆኖ መሃል ገብቶ እንደ ደንቃራ ምንጩን ያደረቀ ዘንዶ ነው። የዐማራ ኢኮኖሚ እንዳይንቀሳቀስ ሰቅዞ የያዘ፣ ዐማራ ላይ ተቀምጦ ከዐማራ እየበላ ዐማራን እያደቀቀ ያለ ስግብግብ ሆዳም ግለሰብ ነው። እስክንድር በፈጠረው ስግብግብነት ምክንያት ወደ ዐማራ ክልል የሚላክ ብር አሁን የለም። በዚህ ምክንያት የተነሣ ከጦርነቱ ሌላ የሚላክ ብር ስለሌለ ኢኮኖሚው ደቅቋል። የዳያስጶራ በሚልከው ብር እምነት እንዲያጣ ያደረገ ከሃዲ ነው። ፋኖዎች ዕድሜ ለመከላከያ ይበሉ እንጂ እንደ እስክንድርማ ቢሆን ኖሮ ባዶ እጃቸውን በቀሩ ነበር። አዎ እስክንድር በጋሽ አሰግድ ላይ የማሾፍ ቅንጣት ታህል ሞራል የለውም። እንዴት ወደ ገብ የቃሊቲ ደንበኛ በአቶ አሰግድ የማሾፍ ሞራል ይኖረዋል?
"…የእስክንድርስ ይሁን ሀብታሙ አያሌው እንዴት በጋሽ አሰግድ መያዝ ዙሪያ ያሾፋል? መቀመጫዬ ላይ ቡጉር ወጣብኝ ብሎ ሞትን ሸሽቶ ወደ አሜሪካ የፈረጠጠ አንድ ቡጉንጃም በምን ሞራሉ ነው አቶ አሰግድን ለምን ሽጉጡን አይጣጣም ነበር ብሎ የመለፋደድ ወኔና ሞራል የሰጠው? ኪንታሮት አሜሪካ አስገብቶት ጀግና ያደረገው ሰው እንዴት በሌላ ሰው ላይ ሞትን ለመፍረድ ደፈረ? የመቀመጫ ኪንታሮት ጉሉኮስ በአፉ የከተተበት፣ መተንፈስ አቅቶት ኧረ በፈጠራችሁ አሜሪካ ውሰዱኝ ያለ ግለሰብ በምን ምክንያት ነው እንዲህ ወንድ ወንድ ለመጫወት ያማረው? ደቡብ አፍሪካ እወስዳችኋለሁ ብሎ 49 ሚልዮን ብር ከዜጎች ከበላው ትግሬ ጋር ሠርቷል ተብሎ የሚከሰሰው ሀብታሙ አያሌው እንዴት ነው እንዲህ አፉን በአቶ አሰግድ ላይ ሊከፍት የቻለው? ከእንግዲህማ ማርያምን ይብስብኛል።
"…በአሰግድ ጉዳይ ከተነገሩ መግለጫዎች በጄነራል ተፈራ ማሞ የተሰጠውን ሓሳብ ነው የምስማማው። በምሬ ወዳጆ፣ በባዬና በዘመነ፣ በኢንጂነር ደሳለኝ ሓሳብ ነው የምስማማው። አሰግድ እጅ ቢሰጥ እንኳ እስክንድር እንደ ጠላት ሊዘምትበት አይገባም። ፈሪ፣ ቦቅቧቋ፣ እንደ ቄራ ከብት እጁን አንከርፍፎ ሲታሰር ሲፈታ የኖረ ሰው እንደ ወንድ፣ እንደ ጀግና በወንዶች በጀግኖች ላይ ሊቀልድ፣ አፉንም ሊከፍት አይገባም። ነውር ነው። ታሞ የተነሣ ፈጣሪውን ረሳ ማለት እኮ ይኸው ነው። በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ሳታወጣ እንዴት በጓደኛህ፣ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ለማውጣት ትላላጣለህ? አያምርብህም። ትቀፍፋለህ።
"…እስክንድር ከመጣ በኋላ የፋኖ ገንዘብ ደርቋል። ኮቴ መናና እግረ ደረቅ፣ ሰላቢ ስለሆነ ለፋኖ እርዳታ ቆሟል። እስክንድር ሸዋ በመግባቱ፣ መከታውን በመጠጋቱ ለመከታው ግሩፕ እስከ 30 እና 60 ሚልዮን ብር ይልኩ የነበሩ የሸዋ ሰዎች ለመከታው እስክንድር ይርዳህ ብለው በራቸውን ዘግተውባታል። በእስክንድር ጦስ በመከታው ስር ያሉ እንዴት እንዴት ያሉ ጀግኖች ስንቅ አጡ መሰላችሁ። እነዚህን ረጂዎች ለእነ ደሳለኝ ቡድን ራሱን ሪፎርም አድርጎ ሲመጣ ለመርዳት ዝግጁ ናቸው ሲባልም ሰምቻለሁ። አከተመ። እስክንድር ከመጣ በኋላ ጎጃም እርስ በእርሱ ለማዋጋት ብዙ ርቀት ሄዷል። ተጉዟልም። ጎጄ መለኛው ግን ነገሩን በአባት በአያቶቹ ጥበብና ብልሃት ፈትቶታል። እስክንድር ከመጣ በኋላ ጎንደር ለሁለት ተከፍሏል። ሰሞኑን ደግሞ ለሦስት ይከፈላል። የሀብቴና የጋሽ መሳፍንት አንድ ላይ፣ የባዬና የሳሚ አንድ ላይ ሲሆኑ፣ እነ ዶክተር ምስጋናው፣ እነ ሙሉነህ ኢዩኤል፣ እና የጎንደር ኅብረቶች፣ ፋፍዴኖችም የሚመሩት ቡድንም ከእነ አርበኛ ባዬ ተገንጥለው ይወጡና ከእነ ሀብቴ ጋር ይቀላቀላሉም ተብሏል። ከዚያ ውባንተ እንዴት እንደተገደለም ወለል ብሎ ይገለጽላችኋል። ወሎም ለሁለት ይሰነጠቃል። ኮሎኔሉ ከእስክንድር ጋር ይለጠፋል። ምሬ ወዳጆ ከጀግኖቹ ጋር ብቻውን ይቆማል። ስለዚህ የእስክንድር ጦስ ዐማራን ትንሽ ይንጣል። ግን የስኒ ማዕበል ስለሆነ በቀላሉ ይቆማል። ይረጋጋል። የዐማራ ፋኖም ያሸንፋል።
"…ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሐባው እንዲህ አለ። እስክንድርን የመረጥነው እኮ ደቡብ ጎንደሮቹ እነ ፋፍዴን ዘመነ ካሤን በሰኔ 15ቱ ጉዳይ ስለሚጠረጥሩት ነው። ስለዚህ እሱን ዞር አድርገን እስክንድርን ለአንድ ወይም ሁለት ወር መሪ አድርገን ብንመርጠው የሚል ሓሳብ ስለቀረበ ነው አለ። እኔም አልኩኝ። በሰኔ 15 ጉዳይ ዘመነ ካሤ ተጠርጣሪ ነው። ተጠርጣሪ ደግሞ ወንጀለኛ አይደለም። ኮሎኔል ፋንታሁን ግን በሰኔ 15 ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነህ፣ ገድለሃል፣ አስገድለሃል ተብለህ ነው የታሰርከው። እና ጎንደሬዎቹ እንዴት አንተን ቀጥተኛ ነፍሰ ገዳይ የተባልክን አምነው በጥርጣሬ የሚወራበትን ዘመነን ሊከሱት ቻሉ። ይሄ የማይመስል ነገር ነው። እንዴት ኮሎኔልን ያክል ማእረግ ይዞ፣ በዚያ ላይ ዕድሜው ሰድሳዎቹ ቤት የሆነ ሰው፣ በዚያ ላይ የተከበረ የእስልምና አማኝ የሆነ ኮረኔል ይዋሻል? እንዴት ያልተመረጠን ምርጫ ተመርጧል ብሎ ይዋሻል? በጣም ነውር ነው። ትልቅ ሰው የጠፋበት ዘመን።
"…ደቡብ ጎንደሮቹ ፋፍዴኖች እነ ምስጋናው አንዱአለም የፈለጉት እስክንድርንና ዘመነን አናጭተው ከዚያ ፋኖ ሲበጠበጥ በቃ ሁለቱም አይሆኑም ገለልተኛ የተማረ ሰው ይምጣ ብለው ፕሮፌሰር ጌታ አስራደን ማምጣት ነበር የፈለጉት። ተበሉ። ከሸፈባቸው። እነ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው ደግሞ የፈለጉት እስክንድርና ዘመነ ሲናጩ በቃ ሁለቱም ይረፉ እና ጄነራል ተፈራ ማሞ ይምራው ብለው የወሎ ልጅነታቸውን ተጠቅመው ጀነራሉን ወደፊት ለማምጣት ነበር ሴራ ሊጎነጉኑ የከረሙት። አሁን ሁለቱም ከሽፎባቸዋል። እኔ የማናቸውም ደጋፊ አይደለሁም። ነገር ግን ከውባንተ ቀጥሎ አሰግድ ላይ የዘመቱት ገዳይ ኃይሎች…👇ከታች ይቀጥላል✍✍✍
"…በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት። 1ኛ ቆሮ 5፥ 12-12
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ቅድም የሆነ ጓደኛዬ የኢትዮ 360 ዋ ጄሪ በጎንደር ሰልፍ አለ እያለች ነው ዘመዴ ይለኛል። የምን ሰልፍ እለዋለሁ። አሁን እያወራች ነው ስማት ይለኛል። ዘልዬ ገባሁና መስማት ጀመርኩ። በመሃል በቀጥታ ሥርጭቱ ላይ ልቅሶ ሰማሁ።
"…በሉኝ አባቴ፣ በሉኝ እያለ የሚያለቅስ ሰው የለቅሶ ድምጽ ነው። ኮሜንታተሮች አስተያየታቸውን ያጎርፉት ጀመር።
• ልዩ ከጀርባ ያለውን ድምጽ አጥፊው
• ኧረ ድምፅ ይሰማል?
• ድምፅ ገብቶባችኋል የሚለው በዛ። አይ አምላኬ ይሄን ልታሰማኝ ነው የመጣሁት አልኩና መጠበቅ ጀመርኩ። ልቅሶው ቀጥሏል። ኋላላይ ጄሪም አለች። ልዩ ድምፅ ይሰማል። አጥፊ። ሀብታሙ ቀጠለ ማይኬን ዘግቻለሁ። ለካስ የኮለረኔሉን ለቅሶ እያሰሙት ነበር ለሀብታሙ።
"…በመጀመሪያው ቀን እንደ ትናንት ኮረኔሉን የሌለ አስፎከሩት… አስፎከሩት። አሸለሉት። በቃ ጎረረ።
"…መሸ ነጋ፣ ሁለተኛም ቀን ሆነ… ኮረኔሉ እየዬ አለ አሉና ቪድዮ ቀርጸው ድምፁን በተኑበት። ከምር ኮረኔሉ አሳዘነኝ። አንጀቴን ነው የበላኝ። እዚህ ስህተት ውስጥ የከተቱት ግን እነ እስክንድር ነጋ፣ ሁለቱ የኡጋንዳ ስደተኞች፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ብሩክ ይባስና ማስረሻ ሰጤ ናቸው።
"…ሰውየው በማልቀሱ ግን አልፈርድበትም። ሥጋ ለባሽ አይደለ? ደግሞ ያመኑት ሁሉ ሲከዱት ምን ያድርግ። ሞት ወደ አንተ ሲመጣ የምትሆነውን አታውቅም። ክርስቶስ ኢየሱስም እኮ ፈራ ተብሎ አይነገርም፣ አይገለጽም እንጂ ሎቱ ስብሃት ክብር ይግባውና የሰውን ሥጋ መዋሐዱን፣ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን በምንማርበት ክፍል ሰው ለመሆኑ አንደኛው "በጌቴሴማኒ አባት ሆይ ቢቻልህስ ይህቺ ፅዋ ከእኔ ትለፍ ማለቱ ነው" እናም የኮረኔል ማልቀስ ሰው መሆኑን ነው የሚያሳየው። ፈሪ ሁላ ፈሪ እያለ አሰግድን ሲሰድብ የከረመ ዛሬ ምን ሊል ነው?
• ቆይቼ ለመሰናበቻ እመለሰላሁ።
ብሩክ ይባስ ሆድ ሲያስብሰው…
"…ብሩክ ይባስ ኢትዮ 360 ላይ እያለ በሠራው ስህተት ብላክ ሜል ያደረገው ሀብታሙ አያሌው ጢባጢቤ የሚጫወትበት ሰው ነው ብሩክ ይባስ። መቼም ብሩኬ ላይ በስሱም እንኳ ስጽፍበት እጄ እየተንቀጠቀጠ ነው። ምን ላድርግ ከነጀግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ ሆኖ ተገኘና መውቀጤ ግድ ሆነ።
"…እነ ብሩኬ ኮሎኔል ጌታሁንን ጋር ደውለው አስፎከሩት። እጅ አትስጥ አሉት። የፖለቲካው ቅማንቴና የአገው ሸንጎ፣ ኦሬክስና ቲጄክሶችም እንዴት ተደርጎ አሉ። ኮለኔሉን ጀግና ዘመነን ፈሪ አድርገው ፎከሩ። አሽላሉ።
"…እስክንድር ነጋ ከሕዝብ የለመነውን ገንዘብ ወስዶ ምኒልክ ሳታላይት ቲቪ ብሎ በከፈተው ጣቢያም ብሩኬና ሀብታሙ አያሌው ቀርበው "ፍረዱ እስቲ፣ አያችሁት ዘመነን፣ አያችሁት ጥጋቡን፣ የሕዝባዊ ሠራዊቱን አባል ኮሎኔልን እጅህን ስጥ አለው እኮ ብለው ጓ አሉ። ፈነጩ፣ ተወራጩ። ኮሎኔሉም አይሆኑ ሰዎች ተጠግቶ አይወድቁ አወዳደቅ ወደቀ።
"…እንዲህ የፎከው ኮሎኔል፣ እንዲህ ያስፎከሩት እነ ሀብታሙ፣ እነ እስክንድር በስተ መጨረሻ ኮሎኔሉን ምን አስደረጉት። በቀጣይ ቪድዮ እመለሳለሁ። እስከዚያው ሀብታሙና እስክንድርን እየረገማችሁ ጠብቁኝ።
• በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ…! ወጥር ጎጄ። 💪✊💪
የጥያቄ መልስ ነው።
"…በእነ እስክንድር ጉዳይ ግንባሩን ብዬ ናላውን ያዞርኩት ለአንዱ አቀሳሳሪ ጠያቂዬ እንዲህ አልኩት። ባለፈው እሁድ ዕለት እኮ በነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእኔ ጋር ቆመው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የሁለት ደቂቃ የህሊና ጸሎት እንዲያደርግላቸው አስደረግኩ። ይኸው ከእሁድ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ መርሀ ግብሩ በተደገመ ቁጥር ይታያል። እኔ ያንን ሳስደርግ አቢይ አሕመድ አልተነፈሰም፣ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አልደነገጠም፣ ፑቲን የኀዘን መግለጫ መልእክት አልሰደደም፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ቃለ ምዕዳንና የማጽናኛ መልእክት አልጻፉም ነበር። እኔ ይሄን ሳደርግ አንተ የአሁኑ ጠያቂዬ ያኔ የት እንደነበርክ ፈጣሪህ ይወቅልህ። በአንተ ቤት ተበጥርቀህ፣ እኔንም አቀሳስረህ መሞትህ ነው። ለማንኛውም ተቀድመሃል።
"…ፖለቲካ ላልከው ግን በወለጋ በአንድ ቀን የተጨፈጨፉት 3ሺ ዐማሮች፣ በጉምዝ ቀበሌ ሙሉ ተገድለው በግሬደር የተቀበሩ ዐማሮች የአሁኑን የገዜ ቀበሌ የጎፋውን አደጋና ከአደጋው በኋላ የቤርቤረሰቦችን ርብርብ የተጨፈጨፉት ዐማሮች ከላይ ከሰማይ ቤት ሆነው ሲሰሙና ሲመለከቱ ምነው እኛም እንዲህ እንዲታዘንልን የተስፋዬ ቤልጂጌና የታገሰ ጫፎ ዘሮች የጎፋ ሰው በሆን ሳይሉ ይቀሩ ብለህ ነው።
"…አንቶኒዮ ጉተረዜ፣ ፑቲን፣ አሜሪካ ሁላ እኮ አዘኑ። ያኔ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በግፍ በፓርላማው ላይ በኦሮሞ ለተጨፈጨፉ 3ሺ ዐማሮች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ሲጠይቅ የከለከለው ጨካኙ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንኳ እንደሰው ሰያለቅስ ለዘመዶቹም የ3 ቀን ብሔራዊ የኀዘን ቀን ሲያውጅ አየነው። ፀረ ዐማራው፣ ፀረ ኦርቶዶክሱም ተስፋዬ ቤልጂጌም እንደ ሰው ጭንቅላቱን ይዞ ሲያለቅስም አየሁት።
"…በአደጋው የሞቱትን ወገኖቻችንን ግን ነፍሳቸውን ይማርልን። አሜን።
“…የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።” ኢሳ 50፥4
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
• ይሄ ከባድ ነው።
"…አንድ ጋዜጠኛ ያውም ከደጀን ጎጃም የተገኘ ጋዜጠኛ። ከቅዱስ ሲኖዶስም በላይ ሆኖ የቅድስና ማእረግን ሲሰጥ ካየህ በቀጥታ ጸሎት ነው ማድረግ ያለብህ። እንዲህ ዓይነቱ አጋንንት በጾምና በጸሎት፣ ስግደት ጨምረህበት ያለ ግርማ መቁጠሪያ በማልቀስ ጭምር ካልጸለይ አይፋታህም።
"…ወግደረስስ ጎጃም ስላለ በቁጥጥር ስር አውለው አሁን ጠበልም፣ ምክርም ሰጥተው ያስተካክሉታል። ጌጥዬ እንዴት ይስተካከላል? ከማዶ ሀብታሙ አያሌው ዶላር እየላከ፣ አጠገቡ መከታው ማሞ በምስኪን ፋኖ እያስጠበቀ፣ ቅዱስ ጻድቅ እስክንድርን ዜና መዋዕሉን የሚከትብ ጋዜጠኛ ሸዋ አስቀምጠው ወይ ጻድቃኔ ማርያም ጠበልም ቢሆን በጊዜ ሳይወስዱት ቀርተው ይኸው ጌጥዬ ለቀቀ።
"…ሸዋ ቁጭ ብሎ የትውልድ ሀገሩ ጎጃምን ጓዳ ጎድጓዳ ስም እየጠራ ሲዘግብ ነው የሚያስቀኝ። ኔትወርክ በተዘጋ ጊዜ እንኳ ጌጥዬ ኢንተርኔት ሲጠቀም አይሳቀቅም። ድሮን ይመታኛል ምናምን የለም። ምክንያቱም የባሕታዊ ቅዱስ ጻድቅ እስክንድር ነጋ ጸሎት ከድሮን እይታ ይሰውረዋልና ነው።
"…ለማንኛውም የጻድቁ ቅዱስ እስክንድር ነጋ ጸሎት የመከታውን ጦር ይረዱ የነበሩትን የሸዋ መኳንንት አስቀረ። የፈረንካ ሰንዱቃቸውን ቆለፉ። መከታው ስንቅና ስንቅ እንዲጠርርበት አደረገ፣ አስደረገ። በአጠቃላይ የሸዋ የመከታው ጦር በአንድ እስክንድር ጦስ ሚልዮን ደጋፊዎቹን አጣ።
"…ከባድ ነው። በእነ መከታው የደረሰ መረገም በሀብቴና በኮሮኔል ፈንታሁንም ሙሀባውም ላይ ይድረስ አሜን። የኮቴ መናናው እስክንድር ነጋም መርገምት በላያቸው ይደር።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የተሰኘው የመረጃ ቴሌቭዥን የእሁድ ምሽት መርሀ ግብሬ በቴሌቭዥን እና በቲክቶክ ወደ እናንተ እስኪደርስ ድረስ እንዲህና እንዲህ እየዛግን እንቆያለን።
• አስነቀልቲው ዘመዴ ነቀለ አባ ንቀል ነኝ።😂
"…ድሮ ድሮ የሠራኸው ግፍ በልጅ ልጅ፣ ወይም በልጅ፣ ወይ ቆይቶ ነበር የሚደርሰው። አሁን ግን በጣም ፈጣን ነው። 5ጂ በሉት። ግፍ ትሠራለህ ወዲያው ያናፍጥህሃል። በአናትህም ይተክልሃል።
"…የጋሽ አሰግድን በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ፣ መጀመሪያ አሰግድን ሊገድሉት ሲያሳድዱት የነበሩት ሀብታሙ አያሌው፣ መከታው ማሞና፣ ፋኖ ሀብቴ ወልዴ፣ እንዲሁም እስክንድር ነጋ ሲያሾፉበት፣ ለምን ጥይት አይጣጣምና አይሞትም ነበር እያሉ ሲያላግጡበት ነበር የከረሙት። ከእነዚህ አላጋጮችም መሃል ጎጃም ተቀምጦ ለሃብታሙና ለእስክንድር ይሠራ የነበረው ወግደረስ ጤናው አንዱ ነበር። ወግደረስ በፌስቡኩ እንዲህ ብሎ ነበር የጻፈው።
"...ንጋትና ጉድ እያደረ ይጠራል!!"
"አባ ዳምጠውም" እጅ ሰጥቷል።
በሃቀኛው የፋኖ አደረጃጀት ላይ ያ ሁሉ ዘመቻና ወከባ፣ ከማንና ለምን እንደሆነ ህዝቤ ሆይ ዛሬ የገባህ ይመስለኛል።
ዕውነት፤ዕውነት እላችኋለሁ፤ኪዳነምህረትን እኛ ግን እናሸንፋለን!!!!
ድል ለሃቀኛው ፋኖ!
"…እንግዲህ ወግደረስ ጤናው በመከላከያ እጅ ባለው በዕድሜም፣ በልምድም አባቱ በሚሆነው ጋሽ አሰግድ መኮንን ላይ ባሾፈ፣ እስክንድር ጽፎ የሰጠውንም መግለጫ በድምጽ አንብቦ ለዛራ ሚዲያ ለስታሊን ገብረ ሥላሴ በሰጠ በአምስተኛ ቀኑ ዛሬ በዕለተ እሑድ በሆቴል ቤት አልቤርጎ ውስጥ በፋኒት ትእግስት ጫኔ በቁጥጥር ስር ውሎ ገበያ ለገበያ እንደ ሌባ ሲያዞሩትና እኔን ያየህ ተቀጣ ሲያስብሉት ውለው በመጨረሻም ወደ ማረፊያ ስፍራ ወስደውታል።
"…ወዳጄ ዘንድሮ ግፍ አትስራ፣ ግፍ አትናገር። በልጅ ልጅህ፣ በልጅህ ሳይሆን በራስህ ላይ ነው የሚደርሰው። 5G በለው። ብራቮ ጎጄ ጎጄ መለኛው። ይቀጥላል… ✍✍✍
"…ዘመድኩን ነቀለ ነኝ (አስነቀልቲው) አባ ንቀል ከራየን ወንዝ ማዶ። 😂😂😂
"…መልካም… ርዕሰ አንቀጹ ከ13 ሺ ሰዎች በላይ እንደተነበበ የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት እያመለከተኝ ነው። እስከአሁን ከዚህ ልጥፍ በኋላ የሚጨመሩትን ሳይጨምር ወደ 10 ሰዎች አካባቢ ብው😡 ብለው በርዕሰ አንቀጹ መናደዳቸውን እያየሁ ነው። መቶ ሁለት መቶ የነበረው ተናዳኝ ወደ 10 እና 11 መውረዱም ትልቅ እመርታ ነው። ይሄ ለእኔ የአሸናፊነት ምልክቴም ነው።
"…በዐማራው ሊቅ ምሑር በአቻምየለህ ታምሩ ጦማር ላይ አነሰ ይምትሉት ካለ ጨምራችሁ፣ በዛ የምትሉት ካለም ቀንሳችሁ አስተያየት ለመስጠት ተዘጋጁ። ታዲ አስተያየት ስትሰጡ አዲስ ገቢዎች ሌላ ቦታ እንደለመዳችሁት አቦሬ አፋችሁን እከፍታለሁ ብትሉ እቀስፋችኋለሁ። ተቃውሞም ካለ በጨዋ ደንብ ይቅረብ። ሰምታችኋል።
• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍
ትይዩ ሊሆኑ ወደማይችሉበት ሚዛን እንዲቀመጡ እንደማድረግ ነው።
"…በአጭሩ እስክንድር እንደ ፋኖ አዛዥ ግምት ውስጥ ገብቶ እየተወዳደረ ያለው ያለውን የሚዲያና የገንዘብ ሞኖፖል በመጠቀም እንጂ በፋኖነት፤ ፋኖን በማደራጀት ባደረገው ጉልህ አስተዋጽኦና ጀብድ አይደለም። በስተመጨረሻም የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለኹ ብሎ ያወጀው ከሕዝብ የሰበሰበው መጠቀሚያ ገንዘብ ስላለው፣ ዝና አለኝ ብሎ ስለሚያስብ፣ በየቀኑ ስለሱ በሚያላዝኑ ተከፋይ ምላሶችና ጆሮዎች በመመካት እንጂ መልምሎ ባሰለጠናቸው ተዋጊዎች፣ ባደራጃቸው የፋኖ ብርጌዶችና በሰጠው በሳል አመራር ተመዝኖ አይደለም።
"…የምናውቀው የፋኖ ተጋድሎ ከተጀመረ ወዲህ እስክንድር ከጀምሩ ጀምሮ ይህንን ሁሉ በሕዝብ ገንዘብ የገዛውን የምላስና ጆሮ ተጎታች ጭኖ ሲንገታገት የከረመው የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት እንጂ ለዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ሊያውለው እንዳልሆነ ግልጽ ነበር። ለዚህም ነበር እውነተኞቹ የፋኖ አዛዦች የድኃ ገበሬ ልጅ እየመለመሉና እያሰለጠኑ የፋኖ ብድርጌዶችና ዕዞችን ለመመስረት ሲወጡና ሲወርዱ እስክንድር ግን የዐማራ የፋኖ መሪነት ጉዳይ አጀንዳ ሲሆን ከእውነተኛ የፋኖ አዛዦች ጋር በፍትሐዊ ሚዛን ሊቀመጥ እንደማይችል ስለሚያውቅና ከዐማራ ፋኖ መሪነት ያነሰ ሥልጣን ለመቀበል ዝግጁ ባለመሆኑ በማናቸውን መንገድ የፋኖ መሪ ለመሆን የገንዘብ፣ የጆሮና ምላስ ኃይሉን ሲያደራጅና ሲያሰማራ የከረመው።
"…ጊዜው ሲደርስም ያደራጀውን የጆሮና የምላስ ኃይል በማንሰሳቀስና ከሕዝብ በሰበሰበው ገንዘብ ደንገጡር በመግዛት እውነተኛ ፋኖዎች የፋኖ መሪ ለመሆን መሟላት አለባቸው ባሏቸው መመዘኛዎች ዙሪያ ያካሄዱት ጉባዔ ያለ ውጤት መበተኑን ተከትሎ የመላው ዐማራ ፋኖ መሪ ነኝ ብሎ መግለጫ አወጣ። ሳይመረጥ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ ሲል ያወጣው ይህ መግለጫው የእስክንድርን የስልጣን ጥም በግልጽ ያሳየ ጉዳይ ነው። እስክንድር የዐማራ ትግል የኅልውና ተጋድሎ ነው ብሎ የሚያምን ቢሆን ኖሮ በኅልውና ተጋድሎው ስማቸው ከፊት የሚጠቀሱ ከአራት በላይ የፋኖ ዕዞች የዐማራ ፋኖ ጠቅላይ መሪ ለመሆን መሟላት ስላለባቸው መስፈቶች እያደረጉት የነበረውን ስብሰባ አቋርጠው ሲወጡና ራሳቸውን ከሒደቱ እናገልላለን ሲሉ፤ አንድም የፋኖ ዕዝ ከሒደቱ እንዳይወጣ ብሎ ጊዜ ተወስዶ ንግግሩ እንዲቀጥልና ያላግባባቸው ችግር እንዲፈታ ጥረት ያደርግ ነበር እንጂ ራሱን ሳይመረጥ የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር።
"…ምን ይኼ ብቻ! የአማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ በእስክንድር ምክንያት ከከሸፈ በኋላ አብዛኞዎቹ የፋኖ አደረጃጀቶች ሂደቱ አይወክለንም ብለው ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ የዐማራው ኅልውና ትግል ግድ የሚላቸው በውጭም በውስጥም የሚኖሩ ዐማራዎች ሁሉ በተፈጠረው ሁኔታ ብስጭታጨውን በተለያየ መንገድ እንደገለጹ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚሰጡትን አስተያየቶች መመልከቱ ብቻ በቂ ነው። በዚህ ሁኔታ አንድ ለዐማራው ትግል ቀናዊ ነኝ፣ ሓላፊነት ይሰማኛል የሚል አካል ቢኖር አንድ ሆነው ይወጣሉ ብሎ በጉጉት ለሚጠብቀው ሕዝብ ማድረግ የነበረበት ወደ አንድነት ለመምጣት የተሞከረው ድካም ባለመሳካቱ አዝኖ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቆ አንድነቱ ወደፊት ይሳካ ዘንድ ከሁሉም ጋር በወንድማማች መንፈስ በትጋት ለመሥራት ቃል ይገባ ነበር እንጂ ሳይመረጥ ራሱን ሹሞ በሕዝብ ላይ አይሰይምም ነበር። እስክንድር ግን ለዐማራው ካለው ንቀትና በሥልጣን ጥም መታወር የተነሳ የዐማራውን ጩኸትና ተቃውሞ እንደ ወፎች ዜማ ቆጥሮት እነ ዐቢይ እንደሚያደርጉት ዐይኑን በጨው አጥቦ በዲሞክራሲ አግባብ ተመርጫለሁ ብሎ የፋኖ መሪነቱን አወጀ።
"…እስክንድር ራሱን መሪ አድርጎ ሲሾም የሚታየው ድል ለዲሞክራሲ የሚለው ሕዝባዊ መዋቅር በተዘረጋበት አገር የሚታሰብ መፈክሩ እንጂ የዐማራ የኅልውና ተጋድሎ አይደለም። የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ የሚለንም በዚህ ጭንቅላቱ እያጭበረበረ ነው። ሆኖም ግን የኅልውና ተጋድሎ አደረጃጀት ትልቅ ጥበብና ጥንቃቄ፣ ሀቀኛነት፣ ከራስ በላይ የሆነ ዓላማ መያዝ፣ መግባባትና ወንድማማችነት የሚጠይቅ እንጂ በዚህም በዚያም አማታትቶና ማጅራት መትቶም ቢሆን “በድል ለዲሞክራሲ” ተመርጫለሁ ተብሎ የሚታወጅበት አልነበረም። እስክንድር ግን ትኩረቱ ሥልጣኑ እንጂ የዐማራ የኅልውና ጉዳይ ስላልሆነ ይህ ሊታየው አይችልም።
"…እስክንድር የዐማራን የኅልውና ተጋድሎ እያወከው የሚገኘው ከላይ በቀረበው ተግባሩ ብቻ ሳይኾን የኅልውና ተጋድሎውን ዓላማና ግብ በማሳት ጭምር ነው። ከአሁን በኋላ በሚደረግ የኅልውና ተጋድሎው ማናቸውም እንቅስቃሴ በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ቅዱስ ዓላማ፣ መርኅና ግብ ላይ ጥርት ያለ አቋም ያስፈልጋል። ይህ ጥርት ብሎ አለመቀመጡ ለዐማራ ኅልውና የሚጋደሉ ፋኖዎች በእስክንድር ነጋ ፀረ- ዐማራ “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ዝባዝንኬ ዙሪያ ድምጽ ለመስጠት እንዲቀመጡና ጉዳዩን የዐማራ አጀንዳ እንዲያደርጉት አድርጓቸዋል።
"…እስክንድር ነጋ ቀለብ የሚሰፍርላቸው ምላስና ጆሮዎቹ፤ ዐማራ ነኝ ማለት የሚቀፋቸውን የግንቦት ሰባት ጉግ ማንጉጎች፤ የእስክንድር ነጋን “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል ፀረ- ዐማራ ዝባዝንኬ ማዘውተራቸው ለምን ይሆን ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሲጀመር “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለው ፀረ- ዐማራ ማጭበርበሪያ የተፈለሰመው በእስክንድር ነጋም አይደለም። ማጭበርበሪያውን የፈለሰሙት የፋኖን ተጋድሎ ለመጥለፍ የተሰለፉ አሜሪካን አገር የሚኖሩ የምናውቃቸው የግንቦት ሰባት ጉግ ማንጉጎች ናቸው።
"…እነዚህ ጉግ ማንጉጎች በፋኖ በኩል በቀጥታ የዐማራን ተጋድሎ መጥለፍ ሳይቻላቸው ሲቀር ማጭበርበሪያውን ለእስክንድር ነጋ በማቀበል የዐማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ተሰማሩ። ለዚህም ነው ፀረ- ዐማራዎቹ የግንቦት ሰባት ኃይሎች ያቀበሉትን ፀረ- ዐማራ መፈክር እንደራሳቸው ሆኖ “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” እያለ ሲጃጃል በሚውለው እስክድር ነጋ ላይ ተሳፍረው የሙጥኝ የሚሉት። በአጭሩ ፀረ- ዐማራው የግንቦት ሰባት ኃይል በእስክንድር ነጋ ላይ እንደ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ የሰፈረው “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለውን መፈክራቸውን አንጠልጥሎ ስለሚዞርላቸው ነው።
"…የዐማራ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በፋኖነት በመደራጀት እየተጋደለ ያለው ዐማራ በመሆኑ ብቻ በአቢይ አሕመድ አረመኒያዊ የጭካኔ አገዛዝ የዘር ማጥፋት ጦርነት ስለታወጀበት እንጂ በኢትዮጵያዊነቱ ጥያቄ ስላነሳ ወይም ከኢትዮጵያ ለመገንጠል አይደለም። ዐማራው የሚጋደለው የዘር ማጥፋት ያወጀውን የአቢይ አሕመድ አረመኔያዊ የጭፍጨፋ አገዛዝ አስወግጄና የኅልውና አደጋውን ቀልብሼ፣ ለሁሉ እኩል የሆነ መንግሥታዊ መዋቅር ተዘርግቶ፣ ዐማራውም እንደ ሕዝብ በኢትዮጵያ መንግሥታዊ ሥልጣን ውስጥ በእንደ ብአዴን ዓይነት ባንዳ በምስለኔ ሳይሆን በቀጥታ የመንግሥት ተጋሪ የምሆንበት መንግሥታዊ ሥርዓት እንዲዘረጋ ነው። ስለ ዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ዓላማ ከፋኖዎች የምንሰማው ቃል በቃልም ባይሆን ይህንን ነው። 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም… የሀብታሙ አያሌው፣ ለዐማራ ፋኖ በተዋጣ ብር ደሞዝተኛ ሆኖ ለኢትዮ 360 ለሀብታሙ አያሌው ቅጥረኛ፣ የእስክንድር ነጋ በጎጃም የስለላ መዋቅሩ መሪ፣ የዓለም ብርሃን ጦረኞች የጦር መሪ፣ የግንቦት ሰባት፣ የግንባሩም፣ የሠራዊቱም አፈ ቀላጤ ሆኖ ሲሠራ የነበረው የጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው በቁጥጥር ስር መዋልን በተመለከተ ቆይቼ እመጣበታለሁ።
"…ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን በቁጥጥር ስር ያዋለችው ፋኒት ትግስት ጫኔ ናት። ጠዋት 1:15 አካባቢ ፈለገ ብርሃን አልጋ ቤት እያለ ነው ቀርጨም ያደረገችው። ትልቁ የሀብታሙ አያሌው የመረጃ ምንጭ ከስሩ እንዲከስም እየተደረገ ነው። ሸዋ መከታው ስር የሚገኘው ጎጃሜው የእስክንድር አምላኪ፣ ፍርዬ ኢንተርኔት በነፃ ሰጥታ እንዲደሰኩር የፈቀደችለት ጋዜጠኛ ጌጥየ ያለው ነው የሚቀረው። እርሱም አይቀርለትም። ይቀጥላል። ብራቮ ጎጄ። ጎጄ መለኛው። 😂💪💪🏿👌✊
"…አሁን በጉጉት በሚልዮኖች በጉጉት ወደሚጠበቀው ወደዛሬው "ርዕሰ አንቀጻችን" ብንሄድ ምን ይለናል? የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ የጻፈው እንደኔ የሐረርጌ መራታ ቆቱ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት እየተባለ የሚጠራ ለእኔ ደግሞ ወዳጄ የሆነ ጎምቱ ዐማራ ነው። ዛዲያስ እናንተስ ይሄን በራሱ በዐማራው ተወላጅ የተጻፈን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
• አንድ 100 ያህል ሰው ዝግጁ ነነ ይበል እስቲ?
“…የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።” ገላ 5፥12
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የኀዘን መግለጫ
ከዐማራ ፋኖ በጎጃም
ከዐማራ ፋኖ በጎንደር
ከዐማራ ፋኖ በወሎ እና
ከዐማራ ፋኖ በሸዋ እዝ የተሰጠ የኅዘን መግለጫ፣
"…በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በመሬት ናዳ በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው አዳጋ የዐማራ ፋኖ በጎጃም፣ የዐማራ ፋኖ በጎንደር፣ የዐማራ ፋኖ በወሎና የዐማራ ፋኖ በሸዋ እዝ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እንገልጻለን፡፡
"…ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን እየተመኘን መላ ኢትዮጵያዊያንን በማኅበራዊ ቀውስ፣ ኢኮኖሚያዊ ድቀትና ፖለቲካዊ ዝቅጠት የዳረገውን የብልፅግና ነውረኛ ሥርዓትን ቀብረን የዐማራንና ሌሎች ጭቁን ሕዝቦችን ነፃ በማውጣትና ነፃ እያወጣን የምንገኝ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በወሎና በጎጃም የምንቀሳቀስ ነጻ አውጪ የፋኖ ኃይሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያስፈልገው ሁለንተናዊ ድጋፍ በአብሮ መኖር መርህና ባህል በሚያምነው ሕዝባችንና በድርጅታችን ስም ከጎናችሁ መሆናችንን በአክብሮት እንገልጻጻን፡፡
"…በዚህ አጋጣሚ ለትግላችን አጋሮች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የስቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የግል ባለሀብቶች ለተጎጂ ቤተሰቦች ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም
ዐማራ በቁርጥ ቀን ልጆቹ ነጻነቱን ያውጃል !
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ ከአሰግድ ቀጥሎ ዘመነ ላይ ሲረባረቡ ሳይ ፍሬን ይዣለሁ። ሰዎቹ በዘመነ አያቆሙም። ዘመነን አሳልፈህ ከሰጠሃቸው ቀጥሎ ምሬ ጋር፣ ከዚያ ባዬ ጋር፣ ከዚያ ሳሙኤል ባለ ድል ጋር መሄዳቸው አይቀርም። ለዚህ ነው ለጊዜው ከዘመነ ጎን መሆን ትክክል የሚሆነው። አለቀ።
"…አሁን ሳሙኤል ባለ ድል ላይ ዘመቻ ከፍተዋል። ሳሙኤል ላይ ዘመቻ የከፈቱት። ሳሙኤል ኮሎኔል ታደሰን ጥያቄ በመጠየቁ ነው ለምን ተጠየቀ ብለው ዘመቻ የከፈቱበት። ኮሎኔል ታደሰ እስር ቤት ሲገባ ሻምበል ነበር። ከእስር ቤት ሲወጣ ኮሎኔል ነኝ እያለ ራሱን ማስተዋወቅ ጀመረ። ይባስ ብሎ ድርጅቱ ሳያዘው እስክንድርን እጩ ይሁን ብሎ በፋፍዴንነቱ ድጋፍ አሳየ። እነ ሳሚ፣ ባዬና ሠራዊቱ ደግሞ የመርህ ጥያቄ አንሥተው የኮረኔሉን ድምጽ ፉርሽ አድርገው አመከኑበት። ስለዚህ ፋፍዴንም አበደ። እስክንድርም አበደ። ኤርትራ አስመራ የተቀመጠውም አንዳርጋቸው ጽጌ አበደ። ሀብታሙ አያሌውም አበደ። በቃ የሆነው ይሄ ነው። ለዚህ ነው ትናንት እንግሊዝ ሀገር ያለው ቅማንቴው ሳሚ ግሩፕ ከፍቶ ሳሚ ባለ ድል ይገደል ሲል ያመሸው። ቅማል ቅጫምህን ግደል ዝተቴ።
• ለዛሬ በቃኝ፣ ለነገ ግን እያየሁ እጨምራለሁ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በጥዋት ሄጄ ነበር። ጸሎት ሥነ ሥርዓቱ አልቆ የፈረደበት ስልኬን አወጣሁና የምስጋና ጥቅሱን ለጠፍኩት። እናም አንድ ሁለት ሰዓት ያህል ሰው ቀስ እያለ አንድ ሺ እስኪሞላ ድረስ ቢያመሰግን እስከዚያው ባቡር ውስጥ ሆኜ ርዕሰ አንቀጹን እጽፋለሁ ብዬ ነበር። ነገር ግን በ10 ደቂቃ ውስጥ 370 ሰዎች በምስጋና አጠለቀለቁት ፔጄን። ዞር ብዬ ስመለስ 600 ደርሷል። 30ኛው ደቂቃ ላይ 1ሺ ሞልቶ አረፈው። እግዚአብሔር ይመስገን። ከዚያ እኔም ባቡሬ ውስጥ ሆኜ እንደ ነገሩ የሆነች ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጀሁላችሁ።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጼ ጋሽ አሰግድ ላይ የዘመተውን የእስክንድር ሠራዊት አፈር ከደቼ ማብላት ነው። ጭራሽ እኔው ራሴ ያስተዋወቅኩት ሉሲ ድንቅነሽ የቴሌግራም ፔጅ የመከታው ካልሲ አጣቢ፣ የእስክንድር በቀቀን ሆኖ ከች አይል መሰላችሁ። እሱን ለብቻው ራሱን በቻለ ርዕሰ አንቀጽ ራቁቱን እናስቀረዋለን። ለዛሬ ግን ጋሽ አሰግድ ላይ የተዘመተውን ዘመቻ እበቀልለታለሁ። እንዳይነሣ አድርጌ ነው ድባቅ የምመታው።
"…መግለጫው እስክንድር አሰግድ ላይ ያወጣው መግለጫ ሲሆን ዛሬም መግለጫው የተላከው ለዓድዋው ትግሬ ለወየንቲቲው ወለይ ስታሊን ገብረ ሥላሴ ነው። 😂😂😂 እንዴት እንደሚናበቡ ሳይሆን እንዴት እንደሚፋቀሩ ሁላ ነው የምትደመሙበት።
"…እናሳ እነዚህ ከንቱ ብኩኖች የዘሪትን ቆሼ ቁሩምቡሼ ፕሮፓጋንዳ በርዕሰ አንቀጻችን ላይ በማንበብ ፕሮፓጋንዳውን አፈር ከደቼ ለማብላት ዝግጁ ናችሁ?
• አንድ 200 ያህል ሰው እስቲ "ዘመዴ ዝግጁ ነነ" ይበል። እዚያው የምታፍደውን አፋህድ ምኑ አፋዳ ነው በጌታቸው። 😂
በመጨረሻም…
"…የእነ ሀብታሙ አያሌው የጎጃም ሕዝባዊ ሠራዊት እጅ በመስጠት። ወደ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ተጠቃለለ። ትግላችን በዶላር አይጠለፍም አለ። ጎጃም አያይዞም መሪያችን ዘመነ ካሤም ነው አለ።
• አሁን ማስረሻ ሰጤ የት ነው ያለው ነው ጥያቄው። ምክሬ የአንድም ሰው ነፍስ አይጥፋ። በመስቀል፣ በሼክና በቄስ አልመለስ፣ አንድም አልሆን ያለውን በሳማ እየገረፉም ቢሆን አንድ ማድረግ ግድ የሚልበት ዘመን ነው የመጣው። ዘመነ ካሤ በመምራቱ በኩል የአቅም ማነስ ካሳየ እሱንም ቢሆን በንግግር አውርደህ መቀጠል ነው አማራጩ።
"…በአንድ ቤት ግን አንድ አባወራ ብቻ ነው ደንቡ። አንድ ዐማራ፣ አንድ ፋኖ። አከተመ። ይሄ የጎጃም ልምድ ወደ ሸዋ፣ ወደ ወሎና ወደ ጎንደርም ሊሸጋገር ግድ ይለዋል። አፄ ቴዎድሮስ አሁን ነው የሚያስፈልጉት።
"…የዐማራ ሕዝብ በኢኮኖሚ እየደቀቀ ነው። እንደ አሜባ የተከፋፈለ የፋኖ አደረጃጀት አያስፈልግም። በፍጥነት አንድ ሆነህ ታገል። እምቢ ያለውን መንግል። ጦርነቱም ከዐማራ ክልል ይውጣ፣ ይነቀል። አዎ በዝቷል። ይበቃል።
• የሚሻለው እንዲህ አንድ መሆን ነው። አከተመ።
"…የበፊቶቹ ሃዲጎች ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጂራ፣ ሀፍታሙ አያሌው፣ ብሩኬ እንኳ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብላ ነው። ኦነግና የሂዊ አክ እንቲፍስቶች ኮረኔን ጌታሁንን አጦዙት። አይዞህ በርታም ብለው አጀገኑት። ዘመነ ካሤ ላይ ብቻ ሳይሆን እንደ ሕዝብ ጎጃምን ነጥለው በፕሮፓጋንዳ ደበደቡት። አስደበደቡት።
"…የእምቧይ ካቡን ፕሮፓጋንዳ የሚያውቀው ጎጄም ለወንድሙ ለኮረኔል ጌታሁን በሰላም እጅህን ስጥ አሉት። የኦነግ ሚዲያ ድጋፍ አያዋጣህምም አሉት። ኮረኔል ግን እኔ የፍየል ወጠጤ አይደለሁም። ልምድ ያለኝ ኮረኔል ነኝ አላደርገውም አለ። እነ ሀብታሙ አያሌውም በርታ ወንድ የእናቱ ልጅ ብለው ጃስ አሉት። ቆሰቆሱት።
• ቆይቶ ምን ሆነ? እመለስበታለሁ። ጠብቁኝማ።
ወደ ኋላ "ጋላ"
"…ኮሎኔል ጌታሁን የጎጃም ዐማራ ፋኖ ነበር። እንደ ብዙዎች የዐማራ ፋኖዎች ሰው ነውና ስህተት ይሠራል። በጀግንነትም እንዲሁ። ነገር ግን ኡጋንዳ ያሉ ሁለት ጋዜጠኞች እባብ ሆነው ቀርበው አሳሳቱት።
"…ለመኴ የተወሰነ ብርም ሰጡትና ለእስክንድር ነጋ ገብር፣ መሪዬ ነው በል አሉት። በሬ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ ሆነበት ኮሎኔሉ። አጠገቡ ካለው ከሚያውቀው ከወንድሙ ከዘመነ ይልቅ ሩቅ ያለው የማያውቀው የፖለቲካ ኢንኩዩቤተር እስክንድር ነጋ በለጠበት።
"…እነ ሀብታሙ አያሌውና ብሩክ ይባስ እየደወሉ፣ ግንቦቴዎችም አለንልህ በርታ እያሉት፣ ማስረሻ ሰጤ አዲስ አበባ እየጨፈረ ኮሎኔሉን ዘመነ ያቅትሃል ወይ ግጠመው እያለ አጦዘው። እስክንድርም የምተማመንበት ጦሬ ነው እያለ ደሰኮረ።
"…ደካማ መስሎ ለበዛ ትችት ተጋልጦ የከረመው ዘመነ ካሤም ካለፉት አንድ ወራት ወዲህ ቆራጥ በላይ ዘለቀን ሆኖ ተገለጠ። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ነው ያለው እንዲል ዐማራ በጎጃምም አንድ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ብቻ ብሎ "ኮሎኔሉን አስራችሁ አምጡልኝ" ብሎ ሠራዊቱንም አዘዘ። ኦሬክሶችና ትግሬክሶች ሳይቀሩ ዘመነን ተቃውመው ተንጫጩ፣ እነ ሀብቴም ወደ ጎንደር ና ሽሽ እኛ ጋር ተደበቅ ቢሉትም የጎንደር ፋኖዎችም አላላውስ አላሳልፍ አሉት።
"…እነዚህ ግምቦቴዎች ኮሎኔሉንና ሠራዊቱን ከኦሮሞ ጋር ለማጣላት "ወደፊት ፋኖ፣ ወደ ኋላ ጋላ" እያስባሉ ቪድዮ ቀርጸው በተኑበት። ይሄ እንግዲህ ጎጃምን ከኦሮሞ ለማቀሳሰር ነበር። ሀብታሙ አያሌው ፈጣሪ ይይልህ።
"…ውብአንተን አዋክበው ገደሉት። ዝም ተባሉ። አሰግድን አዋክበው አሳልፈው ሰጡት። አሁን ደግሞ ዘመነ ካሤ ላይ በስፋት ዘመቱ። ጎጄ ግን ምኑ ሞኝ ነው ክላልኝ አለ። ቀጥለው ምሬና ባዬ ላይ መዝመታቸው አይቀርም ነበር።
• በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ።
"…ርዕሰ አንቀጹን ካነበቡት 15 ሺ ሰው መካከል 9 ግለሰቦች በርዕሰ አንቀጹ 😡 ብው ብለው መናደዳቸውን እንደምትመለከቱት የቴሌግራም ካምፓኒ እየገለጸልኝ ነው። ድሮ ድሮ 100 እና 200 ሰዎች ነበር የሚበሳጩብኝ። አሁን ግን እየቀነሱ ተቸግሬአለሁ። ምንአልባት ከዚህ ልጥፍ በኋላ ግርር ብለው ይመጡ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
"…ለማንኛውም እስከ ምሽት ድረስ መንገድ እየሄድኩ ኮመንታችሁን ልኮምኩም። 1…2…3…ጀምሩ ✍✍✍