zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደተለመደው ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ አመስጋኝ በፍጥነት ሞልቶ እንዲያውም አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ያው እንግዲህ ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ተለመደው ርእሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርእሰ አንቀጻችንም እንደተለመደው ሲያወያየን፣ ሲያነጋግረን፣ እንዲውል አድርጌ እያዘጋጀሁት ነው። ከእናንተ የሚጠበቀው ከርእሰ አንቀጹ በኋላ የእናንተ ተሳትፎ ነው። ሓሳብ ማፍለቅ፣ መነጋገር፣ በጨዋ ደንብ መወያየት የቤታችን ጠባይ ነው። በሌላ ቤትና መንደር የሚታይ ጋጠወጥ እና መደዴ ነውረኛ ፀያፍ ቃል ተጠቃሚ ኮማች ስለማይሰተናገድ የቤታችን ውበቱ በሁሉ ዘንድ የሚታይና የሚወደድ ነው። ይሄን ጠላትም ይመሰክራል።

"…እኔና ጓደኞቼ ከእውነት ጋር ተጣብቀን፣ እውነትን መስክረን፣ አጀንዳ አፍላቂ፣ አምራችና አከፋፋይ እንጂ አጀንዳ የሚራገፍብን የአጀንዳ ወደብ እንዳይደለን አስመስክረናል። ቢያንስ ቢጠፋ፣ ቢጠፋ አንድ አምስት ከእውነት ጋር የሚቆርቡ ሰዎችን ሳላፈራ አልቀርም። እውነት መራራ ናት፣ ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ናት።

"…እህሳ… ጓደኞቼ እንደ ኮሶ የመረረውን፣ ሲሰሙት የሚያንገሸግሸውን እውነት ስንወያይ ለመዋል ፈቃደኛ ናችሁ?

• ዝግጁ ናችሁ ወይ አላልኩም? ፈቃደኛ ናችሁ ወይ…? ( ብቻ ተመልከቱልኝ። ልብም በሉ መልእክቱን ሳያነብ፣ ጥያቄው ሳይገባው አዎ ዝግጁ ነን የሚልም አይጠፋም) ሳያነብ የሚመልሰውን በዚህ ነው የማጣራው። መሳሳቱን 😁 ኢሞጂ እገልጽለታለሁ። እናንተም ከቀልባቸው እንዲሆኑ 😁 ፈገግ በሉባቸው።

• እደግመዋለሁ ፈቃደኛ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በላያና ያያ የልብ ባልንጀራሞች ናቸው። በላይ በአባቱ ኦሮሞ በእናቱ የዓድዋ ትግሬ ሲሆን እሱ ግን ምርጥ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ ነው። ሁለቱም ግን በብልፅግና በድንገት ታሰሩ።

"…በላያ የታሠረው ባህርዳር ነው። ለምን ባሕርዳር እንደሄደ አይጠየቅም። ምክንያቱም መቀሌም፣ ሞላሌና ባሌም መሄድ የዜግነት መብቱ ነውና። የሆነው ሆኖ በላያ በባህርዳር ለምን እንደታሠረ፣ በምን ወንጀል እንደተከሰሰ፣ ለዓመት ለቀረበ ጊዜ በዚያ በዘብጥያ ቆይቶ፣ በመጨረሻ እንዴትና በማን ትእዛዝ እንደተፈታ ሳናውቅ ተፈትቶ ይኸው 24/7 ቲክቶክ ላይ ሆነ ውሎና አዳሩ።

"…ያያም ታስሮ ተፈቷል። ለምን እንደታሠረ አልነገረንም። ብቻ ተሥሮ ተፈታ። ያያ ጎንደርን እንደኔው ሞቼ ነው የምወድሽ ነው የሚላት። በስኳድ የመልማዮች ዓይን ውስጥ ይግባ አይግባ አላውቅም። ያያ ፏ ብሎ ከኢንቬስተር በላይ ያለ ሰቀቀን በሸገር የሚኖር ፀጋው የበዛለት ወንድም ነው።

"…ሰሞኑን ስኳድን አንቄ ስይዝ ሊነሣ ተሞክሮ የነበረውን አዋራ ታስታውሳላችሁ። ዶር ምስጋናው በቅርብ እከፍታለሁ ብሎ ላወጀው የስኳድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ከወዲሁ እነ ቲክቶከሪት መማርን ማዘር ትሬዛ ብሎ በፌቡ ላይ መለጠፉን ሳይ መማርን ለሚቀጥለው ዝርፊያ እያመቻቿት እንደሆነ ነው የታየኝ።

"…በእነሱ ቁማር መማር ጎንደሬ ናት። ሞጣ ጎጃሜ። መማርን ለማንገሥ ሞጣን ማሳነስ፣ ማዋረድ፣ በጎጃሜነቱ ማሸማቀቅ ነበር የተፈለገው። አልተሳክቶም። አሁን ሞጣን 6ሺ ሰው Live ያየው ጀመር። አንደበቱን ቢገታ ደግሞ ከዚህ በላይ ውጤታማ ይሆን ነበር። የምትቀርቡት ምከሩት።

"…ስኳድ ወደ ባሕርዳር ብዙ ወጣት ማስገባት፣ መረጃ ቲቪን 360ንና (ዘመድሁን በቀለን) እንዳይደመጡ ማድረግ ያስፈልጋል ያለው ድሮ ነበር። የ360 ተሳክቷል። የዘመዴ ግን ሲያምርህ ይቀራል።

• አዛኜን ብቻዬን አፈራርሳችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እነ ያያ ዘልደታ ያሬድን እጠይቃለሁ…

"…የዐማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የሠጠው መግለጫ
አግባብነት የለውም። ወንጀለኛውን ገድላችሁ አሳዩን። ሰቅላችሁ አሳዩን ስትል ከምን የሕግ አግባብ ተነሥተህ ነው ብዬ አልጠይቅህም። ሕፃናትን የሚደፍሩ ሁሉ ይገደሉ ማለት አግባብ ነው። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት የአሁኑ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በሰበር ዜና "ህፃናትን የሚደፍሩ የሞት ቅጣት ይበየንባቸው" ብለው ተናግረዋል መባሉን እያነበብኩም ነበር። በማንኛውም መመዘኛ ሕጻናትን ደፍሮ፣ ገድሎ ተደራራቢ ወንጀል የሠራ ወንጀለኛ ከሞት ፍርድ ሌላ መኖር የለበትም ከሚሉት ወገንም ነኝ።

"…የእኔ ጥያቄ የሚመጣው ይሄን በባሕርዳር ፖለቲካዊ ድራማ ለመሥራት የተተወነን አጀንዳ የሴትየዋን እንባ የሌለው ልቅሶ ብቻ ዩቲዩብ ላይ አይተህ እንዴት የተጎጂ ወገንን ቃል፣ ክርክር ሳትሰማና ሳትሰሙ እንዲህ ዓይነት አይን ያወጣ ፍርደ ገምድልነት ሊወጣህ ቻለ? አንተ ደጋግመህ እንደምትፖስተው ጎንደር ሞቼ ነው የምወድሽ እንደምትለው በብአዴን ስኳድ ተጠልፈህ በጎጃም ጎንደር የስኳድ የዘቀጠ ፖለቲካ ውስጥ  ተዘፍቀህ ነው ወይ?

"…ያያ እኔ የምጠይቅህ? ዳኞቹን ሕግ ጠቅሰህ የሞገትክበትን ጽሑፍ ማን ሰጠህ አልልህም። ነገር ግን ይህች የፍርደኛው ልጅ ባለቤት ደግሞ ዛሬ በሚዲያ ቀርባ ያለችውንስ ስትሰማ አንተም እንደ አይንህ ብሌን የምትሳሳላቸው እና የምትወዳቸው እናት አሉህና ምን ይሰማህ ይሆን? የአንተን የተሸፈነ በደልና ኃጢአት የሸፈነልህ አምላክ በእውነት እንዴት ይታዘብልህ ይሆን። ያውም በሴት…? ተው ያያዬ…😁

"…እኔ ዘመዴ የስኳድ ኦሮሙማው ዐማራን የማባላት፣ ጎጃምና ጎንደርን የማቃቃር ግም ቦለጢቃ ማርያምን አዛኜን ድባቅ እመታዋለሁ። አፈርሰዋለሁም።

• ቆይቼ የይግባኝ ባይዋን ቃል አጠር አድርጌ እለጥፋለሁ። ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄም ለሟቿ ሕፃን ታዝኖ ነውን?

"…ትውልደ ጉራጌዎቹ እነ ቹቹ፣ እነ እማማ ሮማን ከወልቃይት ናፋቂ ሰነ30 ዎቹ ትግሬዎችና ከጎንደሩ ፀረ ጎንደር ፀረ ዐማራው ስኳድ ጋር ተሰብስበው እንዲህ አረፋ እየደፈቁ ጎጃምን እንደ ሕዝብ የሚወርዱበት ከምር ለሟቿ ሕፃን አዝነው ነውን?  ጎጃም የቲክቶክ ጉራጌዎችን ምን ቢያደርጋቸው ነው? ከኦሮሙማው ሥርዓት በላይ እንዲህ የሚወርዱበት?

"…ሕፃን ፌቨን ተደፍራ እንዳልሞተች የሕፃኗ አክስት ዛሬ በሚዲያ ቀርበው ሀገር ይፍረደኝ ብለዋል። በዚህ አጋጣሚ የሌሎችንም ተበዳዮች ድመፅ ለመስማት በመፍቀድህ ኢዮሐ ሚዲያ ልትመሰገን ይገባል።

"…በሉ እነ ያያ ዘልደታ በኪዳነምሕረት በዓል ከመሸሸግ ወጣ ብላችሁ እስኪ ድምጻችሁን አሰሙ። ጠበቃው፣ ዳኛው ይገደል ያላችሁ ስኳዶች እስቲ ወጣ በሉና ይህቺንም ሴት ስሟት።

"…አያችሁ ከሕፃኗ ሞት ይልቅ ዘመቻው ጎጃም ላይ ነው የምለው ለዚህ ነው። ሞጣ ቀራንዮ የተዘመተበትም ጎጃሜ ስለሆነ ብቻ ነው። ሞጣ በሚናገራቸው አሰቃቂ ቀልዶች ሲስቅ የከረመው መንጋ ሁላ በዚያ ቀን ሞጣ ያን ነውር፣ ፀያፍ ቃል ተናገረ ብሎ የዘመተበት በሌላ ምክንያት አይደለም። ትግሬው ፓስተር ኤድመንድ የምን ሰብአዊነት ያውቃልና ነው ሞጣን የሚከሰው? ነገርየው ሌላ ነው። ሞጣ ላይ ያዘመታቸው የሞጣ ጎጃሜነት ብቻ ነው። አለቀ።

"…እኔንም ድርቅ አድርጎ ወደዚህ አጀንዳ ስቦ ያስገባኝም ይሄው ነው። ቁማሩን ኦሮሙማው ቢበላውም የዚህ ዘመቻ አቀጣጣይ አቃጣሪ ራሱ ዐማራ ነኝ ባይ መንጋ መሆኑን ሳይ ደግሞ ይበሰጨኛል። እንዲያው በማንም ቲክቶከር መነዳት አይሰለችምን? እቪ ይሄንንስ ምን ትሉታላችሁ? 

"…እኔ ግን እላለሁ። ጎጃሜ ግን ከምርም ቡዳ ነው። ይሄን አረመኔ የኦሮሙማ አገዛዝ ቆርጥሞ በልቶታል ማለት ነው። ቡዳው ጎጃሜ በማርያም አነካክትልኝማ። አስጓራው። አድቅቀው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርእሰ አንቀጻችንን 14 ሺህ ሰው አንብቦት 1 ሰው ብቻ ብው 😡 ብሎ መናደዱን የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት ያሳየናል። አንድ ሰው ብቻ መናደዱ ደግሞ ቆይቶ የሚባንነው ስለሚበዛ ነው። የእኛ ሰው ልማዱ ነው። ለማመስገን መቸኮል፣ ለመርገም መቸኮል። ለመመረቅ መቸኮል፣ ለማልቀስ መቸኮል፣ ለመተቸት መቸኮል ልማዱ ነው። ደግሞ እኮ ቶሎ ነው የሚረጋጋው።

"…በርእሰ አንቀጹ ላይ የየራሳችሁን አስተያየት ስጡና ወደ ቀጣዩ አጀንዳ የማፍረስ ሥራ እንሄዳለን።

• ማስታወሻ … አንዳንድ እያደረግኩ ያለሁት ነገር ሳይገባችሁ ወይም ገብቷችሁም ቢሆን የቀጠራችሁኝ ይመስል ስለ ሌላ ነገር ጻፍልን፣ ስለዚህ መስማት አንፈልግም የምትሉ አፈ ጣዲቆች ሥነ ሥርዓት ግበሩ። እንዲህ የሚል ሃስማሳይ ቀጣፊውን እቀስፈዋለሁ። እኔ አጀንዳ ሰጪ፣ አጀንዳም አፍራሽ እንጂ ለአንተ አጫጭር ዜና አቅራቢ ነጋዴ አይደለሁም። ሰምተሃል።

"…ዳይ ወደ እናንተ ልብ አድርስ፣ አንጀት አርስም ወደሆነው አስተያየታችሁ እንግባ። 1…2…3… „ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…እኔ አሁን ለማየት የጓጓሁት ቁማርተኛው ኦሮሙማው አገዛዝ የአፄ ምኒልክን ሃውልት ለማንሣት ምን ዓይነት አጀንዳ ፈብርኮ፣ እነማንን ለሙሾ አውራጅነት አዘጋጅቶ እንደሚያሰማራ ብቻ ነው። ማንን ገድለው፣ ወይም ቀደም ብሎ የሞተ ሰው ፈልገው ዘግናኝ፣ ለአእምሮ የሚከብድ እውነተኛ የወንጀል ተግባር በመንግሥታዊ የመገናኛ ብዙሃን አስለፍፈው፣ የአጀንዳውን ተቃዋሚም፣ በቄስ በሼክም በኩል ሼም አስይዘው እንደሚያፈርሱት ነው። ይሄኛው አጀንዳ በእነ ያሬድ ያያ ዘልደታ የማኅበራዊ ሚዲያ ፊትአውራሪነት ሕዝቡን በሙሉ ወላድ የሆነውን ሁሉ አንጀቱ የሚንሰፈሰፍበትን የወንጀል ድርጊት ፈጽመው "የጎንደር የባህል ልብስን በደም ነክረው፣ ፊልም ሠርተው፣ በትወና አላቅሰው፣ አላቅሰው፣ ባልሠራው ወንጀል ጎጃምን እንደ ሕዝብ አሰድበው፣ የአፄ ቴዎድሮስን ሴባስቶፎል መድፍ ያለምንም ኮሽታ በጨለማ አንዳነሡት (ሃውልቱ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ይመለስ አይመለስ የታወቀ ነገር የለም።") የምኒልክን ሃውልት እንዴት አድርገው ያነሡት ይሆን። ይኸው እነ ያሬድ ያያ ሌላ ትወና ላይ ተጥደው የእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አጥሩ፣ ሱቆቹ እየተናዱ፣ እየፈረሱ ነው አሉ። ማን ይተንፍስ?

"…እኔ የሚያስፈራኝ ቀጣይ የሚያመጡት አጀንዳ ነው። አጀንዳው የብዙሃንን ስሜት ቀፍድዶ እንዴት እንደሚይዝ ገብቷቸዋል። ማን ማን ምን ሲያይ እንደሚያለቅስም ገብቷቸዋል። ተቃዋሚ እንኳ ቢኖር እንዴት በራሱ በአገዛዙ ተቃዋሚ በነበሩ ሰዎች የውግዘት ናዳ እንደሚያስወርዱበትም አይተዋል። ለምሳሌ ሞጣ ቀራንዮ ኋላ ላይ ሊያሸንፋቸው በራሱ ጋጠወጥነት እና ያላታረመ፣ ያልተገራ ምላስ ነጥብ ጥሎላቸው አዋክበው እንዴት ድራሽ አባት እንደሚያጠፉም ተምረውበታል። (በነገራችን ላይ ሞጣ ከእድሜው ጋር የማይሄድ የብልግና ቃላቶችን ትቶ በሥነ ሥርዓት ተዘጋጅቶ ፖለቲካ ቢሠራ ብዙዎቹን ይቦንሳቸዋል" ሞጣን በተናገረው ስድ ቃል ሳይሆን በጎጃሜነቱ ብቻ እሱን ለማሳደድ፣ እነ ትግሬው ፓስተር ኤድመንድ ሁላ፣ እነ መንሱር ጀማል ሁላ እንዴት እንደዘመቱበት ታይቷል። ሞጣም ከስህተቱ ተምሮ ንስሀ ገብቶ ከዐማራ ጎን ቆሞ፣ የዐማራን ጨዋነት በጠበቀ መልኩ ከእንግዲህ ይንቀሳቀሳል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። እናም አልቃሻ፣ ሳያላምጥ የሚውጥ ሳይመረምር የሚፈርድ መንጋ እንዳለ ስለተረዱ ከእንግዲህ በደንብ ተዘጋጅተው ነው አደገኛ እና  ከባድ የታሪክ ስህተት ለመሥራት የሚከሰቱት ብዬም እጠብቃለሁ።

"…ይሄ ብቻ አይደለም። እንዲያውም አሁን ሌላ እልቂት ለባህርዳር እንደተዘጋጀላትም እየሰማሁ ነው። ይሄን ሕዝብ እንባ የሚያራጭ የወንጀል ድርጊት ለፖለቲካዊ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ያዋለውና አረመኔዋን አዳነች አበቤን ሽንት ቤት የሌለው ቁልፍ ሰጥታ "ማዘር ትሬዛ፣ እቴጌ ጣይቱን ሆና የተወነችበትን ፊልም ወደ ባሕርዳር በመውሰድ እዚያው ባሕርዳር በጦርነት መሃል ሰልፍ እናደርጋለን በማለት የጎንደር ስኳድ ሥልጣኑን ተጠቅሞ ብጥብጥ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሰምቻለሁ።

"…በቲክቶክ አደገኛ የሆነ አንድ ከባድ የታወቀ የቲክቶክ እስኳድ ያለው ካርሎስ ቀበሮ የተባለው የባህርዳር ሚልዮነር አሁን ደግሞ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በአክቲቪስት ሰጡ ብርሃኔ የሚመራ የብልፅግና አክቲቪስት ግሩፕ ጃካራንዳ ሆቴል ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸው፣ ለሕፃን ፌቨን ሰልፍ ለማዘጋጀት ቲሸርት እያሳተሙ ነው ተብሏል። ይህ ድርጊት እልቂት የሚያመጣ ነው ተብሎ ለብልጽግና ቢነገርም "ጎጃሜ ለምን አይጨራረስም" የሚል ምላሽ መሰጠቱ ነው የተነገረው። ምጥንቓቅ። በመጨረሻም የጎንደር ተወላጅ ነው የተባለ ኃይሉ ማንአለ የተሰኘ ጸሐፊ ይሄን የአጭር ቀን ተውኔት እንዴት በብልፅግና አሸናፊነት በድል እንደተጠናቀቀ የጦመረውን ጦማር ለርእሰ አንቀጽ የተገባ ነው በማለት አቅርቤላችኋለሁ። አንብቡትና አስተያየታችሁን ስጡት። የእኔ ዋና ዓላማ እንደ መንጋ የማይነዳ፣ የሰማው ሁሉ የማያስለቅሰው፣ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ትውልድ ማፍራት ነው። ወደ ንባቡ።

መድፈርን በመደፈር
Hailu Menale

አጀንዳው ተዘጋ....

1. ቀደም ባሉት ቀናት በዐማራ ክልል ያሉ የተግባቦት (communication) ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ሰልጥነው መሰማራታቸው በርካታ ሰዎች ሲናገሩ ሰማን።

2. ቅዳሜ ነሐሴ 11/12/2016 ዓ.ም በጥዋት አሰቃቂ ወንጀል በፌክ ስም በተከፈተ አካውንት ተለቀቀ። ድርጊቱ የተገለፀበት መንገድ እንኳን የሰውን ልብ የሰይጣንን ልብ ይሰብራል። 

3. ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ በዚያው ቅፅበት አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጎልተው የሚታወቁ ሰዎች ተቀባበሉት።

4. በዚያው ቀን ከምሳ ሰዓት በፊት (ከመጀመሪያው መረጃ በተወሰነ ሰዓቶች ልዩነት ማለት ነው)  ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ አወጣ ተብሎ የመንግሥት ሚዲያዎች ተቀባበሉት። ( ቀኑ ቅዳሜ በዛ ላይ በዛች ቅፅበት መግለጫውን መቸ እደተቋም ተወያይተው ጽፈው ለሚዲያ ላኩት ብለን መጠየቅ ይኖርብን ይሆንንንንንንንንንንን.....)

5. ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ማኅበራዊ ሚዲያው በዚህ አጀንዳ ተጠመደ። ነገሩን አጉልተው ሊያሳዩ የሚችሉ በርካታ ቪዲዮዎች በበርካታ ሰዎች እየተሠሩ መለቀቅ ጀመሩ። አጀንዳው ዋና የገቢ መሰረቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ለሆነው አካል ፈጣሪ ከሰማይ ያወረደው መና ሆነ።

6. ነገሩ እየጋለ ይሄድ ዘንድ ከስር ከስር ግብአት የሚሆኑ መግለጫዎች ከተለያዩ ተቋማት እየተሰጡ በመግሥት ሚዲያ ይለቀቃሉ። (ዐማራ ፖሊስ፣ ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ የዳኞች ማኅበር.... ባለሙያዎች ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡ ተደረገ....

7. በሁለተኛ ቀኑ በአሚኮ ዶክመንታሪ ተሠርቶ ተለቀቀ። (ስለ አንድ ጉዳይ ዶክመንታሪ ለመሥራት ምን ያክል ጊዜ ይወስዳል የሚለውን በሙያው ያለ ሰው ይንገረን)

8. እናት በየሚዲያዎች እየቀረበች የተፈፀመውን ወንጀል መጀመሪያ ተፅፎ በተለጠፈው መልኩ አስተጋባች። እዚህ ላይ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች የሰጠቻቸውን ቃለ መጠይቆች ቢያዩአቸው ደስ ይለኛል ...እኔ በሙያው ጨዋ የሆንሁት የሆነ የተሰማኝ ነገር አለና።

9. ለእናትየዋ ድጋፍ በተለያየ መልኩ ተጀመረ ....ገንዘብ ማሰባሰብ ተቋማት የሥራ እንስጥሽ ጥሪ ....

10. አጀንዳው በጣም ጡዞ ብሔር ተኮር እዲሆን ተደረገ። ይህ ብቻ አይደለም ጎጃምን ለብቻው ለይቶ የሚያወግዝ ቡድንም ተፈጠረ።

11. በዚህ መሀል የመንግሥት ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን እየሰጡት ነው። ከስር ከስር ያራግቡታል። Etv ብቻውን በ 5 ቀን ውስጥ 10 ዘገባ ሠርቷል። ታዋቂ ሰዎችም እንዲሁ ....

12. በዚህ መሃከል የአፄ ቴዎድሮስ አሻራ የሴባስቶፖል ሃውልት ምንም ኮሽ ሳይል ከቦታው ተነሣ። የሃውልቱን መነሳት ቪዲዮ ቀርፆ የለቀቀ ሰው ቢኖርም ዘወር ብሎ ያየው የለም። ይህ ሀገራዊ ታሪክን ማጥፋት ነውና ሀገርንም ሕዝብንም መድፈር ነው። የበለጠ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የተሸፈነበት አጀንዳ ነው። የህፃናት መደፈር እኮ ትንሽ ትልቅ፣ ሀብታም ደሀ ባለሥልጣን ... ሳይል የሁሉም ዜጋ ጉዳይ እንጅ የአጀንዳ መሸፈኛ አይደለም። እህት ወይም ሴት ልጅ የሌለው አለን? በሱ ቢደርስ ህመሙ የማይሰማው ድንጋይ ልብ አለን? እናም መድፈርን በመደፈር መሸፈን የበደል በደል አይሆንምን? ወደፊት የምኒሊክን ሃውልት ለማንሳትም ምን ዓይነት አጀንዳ ይፈጠር ይሆን? ያው መነሳቱ አይቀርም ብየ ነው ....አዎ አይቀርም።👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

👆② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በዚህ ዓለም 64 ዓመት ኑራ ጥር 21 ቀን ያረፈችው የእመቤታችን የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ…

"…ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው። ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ 2ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል። በ3ኛ ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት። ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከኀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ። እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሣኤዬን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ? አላቸው። አግኝተን ቀበርናት አሉት። ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስም መልሶ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት። ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው። የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው። ለበረከትም ተካፍለውታል።

"…በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን ዓይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ16ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አሁንም በትህትና እጠይቃለሁ።

"…ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን" ሲባል ምን ማለት ነው? የማይካደው ነገር ሕፃና ሞታለች። አሟሟታን በተመለከተም የሃኪም ማስረጃ ተያይዟል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አይቶ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኖበታል። የደረሰውን ግፍ ክልሉ በክልሉ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዶክመንተሪ ሠርቶ ለሕዝብ ቀደም ብሎ አሠራጭቷል። እናስ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች በምን የሞራል እና የሕግ መሠረት ነው በአንድ ክልል ውስጥ የተፈጸመን የሕግ ውሳኔ አጣጥላ "ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን" ልትል የቻለችው? በቃ ብአዴን የዐማራ ክልልን ማስተዳደር ካቆመ ዓመት አለፈው ብላ በሽሙር መናገሯ ይሆን እንዴ?

"…የለም የለም በአዲስ አበባ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ፣ ቤተሰቡ የተበተነ፣ ሱቁ ፈርሶበት የቀወሰው በአዳነች አቤቤ ፍርደ ገምድልነት እና የፍርድ ቤት ትእዛዝን በአፍጢሙ በመድፋት አይደለም ወይ? ምን ማለት ነው? በቃ ዐማራን አጠገባቸው የሚገረድላቸውን አገኘሁ ተሻገር፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ዣንጥራርን እንኳ ባያከብሩ ትንሽ እንኳ ሼም አይቆነጥጣቸውም እንዴ?

• በእነ ያያ ዘልደታ የቲክቶክ ጩኸት ፍትህ ሲዳጥ፣ ሲጨፈለቅ እንደማየት የሚያስጠላ ነገር የለም። አሁንም ቢሆን የህፃና አሰቃቂና የግፍ አሟሟት በሚገባ ከፖለቲካ ነጋዴዎች ባሻገር በባለሙያ ይመርመር። ይመርመር፣ ይመርመር።

"…የወሃቢይ እስላምም አጀንዳውን ይዞ ከች ብሎልሃል። የሽሪአ ሕግ አሁኑኑ እያለልህ ነው። እነ አልጀዚራም ግራቀኙን ሳያዩ ዘለው እንደገቡበት እየሰማሁ ነው።

• ደፈር ብለን በጨዋ ደንብ እንወያይ። አመሰግናለሁ። 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄም አልገባኝም…!

"…በቅድሚያ የህፃኗ ወላጅ እናት እንኳን ደስስ አለሽ። ነገር ግን በሟች ህፃን ፌቨን የግፍ ግድያ ምክንያት በኦሮሞ ብልፅግና ሠራዊትና በደጎንደር የሰሊጥ ብር ስኳድ እየተሠራ ያለውን ፖለቲካዊ ግልሙትና አጥብቄ እቃወማለሁ።

"…የባሕርዳር ፖሊስ የሚጠበቅበትን ፈጽሟል። የዐማራ ክልል ፍርድ ቤት የሚጠበቅበትን ፈጽሟል። ከ25 ዓመት በላይ ሞት ይፈረድበት ብሎ ለማመልከት በሩ ዝግ አይደለም። ወንጀለኛውም ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው። እናም ነገርየውን ፖለቲካዊ አድርጎ ማጯጯህ ተገቢ አይደለም።

"…በአዲስ አበባ ብቻ ተደፍረው በየቤቱ አልጋ ላይ ውለው እየማቀቁ ላሉ ህፃናት እንዲህ ዓይነት እንክብካቤ ይደረጋል? ተደፍረው የተገደሉና በየቦታው ለሚንከራተቱ ወላጆች ተገቢው ፍርድና ካሣስ ይሰጣል? ሚዲያው አጯጩሆ፣ አክቲቪስቱ ዋይዋይ ለማይሉላቸው በየቤቱ ላሉ ፍትሕ ፈላጊዎችስ ምን ታስቧል? …ምነው እሷን ባደረገኝ ብለው የሚመኙ ልባቸው በኀዘን የተሰበሩ እናቶችን ማሰቡም መልካም ነው።

"…ለማንኛውም ከሁሉም ከሁሉም ሰገጤዋ ስኳድ የአያሌው መንበር ምልከታ እና መልእክት የነገሩን መሄጃ እና መዳረሻ፣ ማጠንጠኛ መንገድም አሳይቶኛል። ባህርዳር… ጎጃምና ጎንደር።

• ቀጥሎ የሟች ሕፃን ሔቨንን ይህክምና ውጤት እለጥፍላችኋለሁ።

• ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ…!🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዛሬ ብዙ ሴራ ላፈርስ ነኝ ካልደበራችሁ ልቀጥል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍

"…ስቋጨው እኔ ዘመዴ ሞጣ አምላኬን ሲሳደብ፣ እምነቴን ሲያንቋሽሽ ዝም ብዬ ሳየው ከርሜ ዛሬ ላይ ይሄን የተለመደ ክፍት አፉን ከፍቶ ነውር ቃል ተናገረ ብዬ ከምደረ ገጽ ይጥፋ ማለት አልችልም። አሁን የተከፈተበት ዘመቻ በግሉ ላይ ያነጣጠረ ሆኖ ከተጎዳም ሲሰድበው፣ ሲያዋርደው የኖረው ፈጣሪው እንደፈረደበት ነውም የምቆጥረው። የሞጣን አፀያፊ ነውረኛ ተግባር ያወገዙ ሰዎችንም አልቃወምም። ሊወገዝም ይገባዋልና። ነገር ግን ሞጣን ፈጣሪ በሠራው ኃጢአት ይቅር አይለውም ብዬም አላምንም። እምመክረውም ንስሐ እንዲገባ ጭምር ነው። ሞጣ የፈለገ ቢሣደብ ለሰዎች አዛኝ፣ ስስ ልብ ያለው፣ እንባውም ቅርቡ የሆነ፣ ርኅራሄም የጠፋበት ሰው አይደለም። በሊቢያ በረሃ የታሠሩ፣ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለይ ቁጭ ብሎ ሲረዳም፣ የብዙዎችንም እንባ ሲያብስም አይቻለሁ። በትዳሩም ላይ ወስላታ ሆኖ በአደባባይ ነውር ሲሠራም አልታየም። ሞጣ ከአፉ ብልግና በቀር ሰው ላይ የሚደርስም አይመስለኝም። እናስ ፈጣሪ ይህን ጥቂት ሰዋዊ ምግባሩን አይቶ አይምረውም ማለት እንዴት ይሆንልኛል? አስመሳይ አንሁን። ሞጣን ፈጣሪ አይምረውም የሚል ወደፊት ብቅ ይበል።

"…ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።" ሞጣን ለመክሰስም፣ ለመወንጀልም እስቲ ከሞጣ የተሻለ ንፁሕ፣ ሞራል ያለው ሰው ወደፊት ይምጣ? ጻድቁ ና። ደፋሪው ራሱ እኮ ነው አሁን አየሩን ያጨናነቀው።

"…እኔ ግን እላለሁ። ለሞጣም ይሄንን በደሉን ትምህርት ያድርግለት። ለወለዳቸው ልጆቹ ሲል ፈጣሪ ምሕረት ይላክለት። ወደ ቀልቡም ይመልሰው። ለንስሐ ሞት ለሥጋወ ደሙ ያብቃው። አብዝቼ እጸልይለታለሁ። እየሰደብከኝ፣ እኔንና ባለቤቴን፣ ልጆቼን ሁሉ እያዋረደም ቢሆን እኔ ግን እጸልይለታለሁ። ይሄን ስላልኩ እኔን መስደብ፣ ማዋረድ ብታቆም ግን ሞጣ ሆይ አለቅህም። ሰምተሃል።

• ይኸው ነው ስለሞጣ ያለኝ አቋም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተጠየቅ…

"…ዘመዴ… ተጠየቅ ተብያለሁ። ተጠየቅ… እስቲ ወንድ ከሆንክ ስለ ቲክቶከሩ ሞጣ ቀራንዮ ወይም በመዝገብ ስሙ አቶ ማማሩ አዳሙ መንግሥቴ አንተ ብቻ ነህና ዝም፣ ጮጋ፣ ጭጭ ያለው የሆነ ነገር በል። አንዳች ነገር ተናገር? የሚሉ ነፍ የትየለሌ ወሬ ናፋቂ ነገር አቀሳሳሪ ጠያቂዎች በውስጥ መስመር በቤቴ ጓዳ ጎድጓዳ ውስጥ ሲርመሰመሱ እያየሁ ነው።

"…እኔም ተናገር ብላችሁ ከወተወታችሁኝማ በስሱ ሳይሆን እናንተ እኔ የምጽፈውን ለማንበብ ዝግጁ ከሆናችሁ አስረግጬ ነዋ የምነግራችሁ። እኔኮ ዘመዴ ነኝ። ዘመዴ መራታው የምሥራቁ ሰው ቆቱው የሐረርጌ ዘመዴ ነኝ። የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ።

• እናም የጠቢቡ የሰሎሞን ፍርድ የሆነ እርግጡን ልንገራችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ፩

"…በሰሞኑ ብልፅግና በቀል ስኳዳዊ አጀንዳ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያው በኩል በቲክቶክ፣ በፌስቡክ እና በዩቲዩብም ቢሆን ፍጥጥ ብለው አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆነው በአንደባባይ የተገለጡትን ቲክቶከሮችና ፌስቡከሮች አስቲ ግለጧቸው?

"…በአገዛዙ ተቀርጾ የተሰጣቸውን አጀንዳ ተሸክመው የሚዞሩ የአጀንዳ ኩሊዎች፣ ደርሰው አዋራ የሚያስነሱ፣ ማር የሆነ አጀንዳ ላይ የሰፈረን ሕዝብ የገማ አጀንዳ አስቀያሽ ጭሳቸውን አጭሰው ማር ከሆነው አጀንዳ ላይ ለማባረር የሚደክሙ፣ በአገዛዙ ተፈቀደላቸው ቦይ ብቻ የሚፈስሱ፣ የመጫወቻ ሜዳ ላይ የሚጫወቱ፣ መሙን ሳይለቁ የሚሮጡ። በተከፈተላቸው ቀዳዳ የሚሾልኩ የአዞ እንባ እያነቡ የኢትዮጵያ እናቶችና ሴቶችን አንጀት እየበሉ በእንባ የሚያራጩ፣ ኀዘን መከራቸውን፣ ራባቸውን በሆያሆዬ ለማስረሳት ከሚሯሯጡ አጭቤዎች መካከል ማንን ታዘባችሁ?

• ሁሉም ስለሚያነበው በድፍረት ትዝብታችሁን ግለፁላቸው።

• 100 ሰው አስተያየት ከሰጠ በኋላ ሌላ ጥያቄ አስከትላለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቶ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ያው ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ ለየት ያለ እና የእናንተን ተሳትፎ የሚጠይቅ አጠር ብላ ወፈር፣ ደልደል ያለች ጥያቄአዊ ርዕሰ አንቀጽ ናት።

"…እህሳ… ለጠያቂ ርዕሱ አንቀጽ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሐምሌ ፲፭ ዕረፍቱ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ (ከ306-373 ዓም) … ታሪኩ ከላይ ይነበብ።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።”ራእ 6፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የፍርደኛውን ባለቤት ደግሞ እንስማት

"…ፌቨን የሞተችው ግቢ ውስጥ ባለ እንጨት ዥውዥዌ ስትጫወት ወድቃ ነው። (እህቷ መስክራለች) …አሸዋ አፏ ላይ ተደረገ የተባለው የአቡነ በትረማርያም እምነት ነው።… በሰዓቱ ባለቤቴ ቤት ውስጥ ፊልም እያየ ነበር። ፖሊስ የሄቨን እህት እና ጓደኞች ህፃናትን የምስክርነት መረጃ አጥፍቶብናል። …መርማሪ ፖሊሱ ህፃን ሄቨን ዥውዥዌ ስትጫወት ወድቃ መሞቷን ነግሮኝ ባለቤቴም አከራይና በጊዜው በቦታው ስለነበረ ብቻ መታሰሩንና ቶሎ እንደሚለቀቅም ነግሮኝ ነበር።

"…ሕፃን ሄቨን በማንም አልተደፈረችም። ጫማዋም እኛ ቤት አልተገኘም። ወሸት ነው። …ባለቤቴ ጋር ከተጋባን 10 ዓመት አልፎናል። አንድም ክስ ኖሮበት አያውቅም። ሁሉም ውንጀላ ሀሰት ነው። ባለቤቴ ንፁህ ነው። …ባለቤቴ የተፈረደበት በተፅዕኖ ነው። …በምላጭ ተተልትላለች የተባለው ውሸት ነው። አሜን ሀኪም ቤት ነው የሴራው ጠንሳሽ። ሀኪም ቤቱ የፎረንሲክ ምርመራ ክፍል የላቸውም።

"…የሕፃን ሄቨን እናት ለልጇ ፍትሕ እንደምትጠይቀው ሁሉ እኔም ለባለቤቴ ፍትሕ ጠይቃለሁ። …ይግባኝ ጠይቀን ይግባኛችን ተቀባይነት አግኝቶ በሂደት ላይ ነን። የ10 ዓመት ባለቤቴ በፍፁም እንደዚህ አያደርግም። ደግሜ ደጋግሜ የምናገረው ሕፃን ሄቨን ተደፍራ አልሞተችም። የ7 ዓመት ሕፃን ልጅ አባት የ7 ዓመት ሕፃን አይደፍርም። …ባለቤቴ በግልፅ ተጣርቶ ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ከዚህ በላይ ቢፈረድበት እንደሚባለውም ቢሰቀልም አይከፋኝም። እውነታው ግን ፍርዱ ትክክል አይደለም።

"…አሜን የአጥንት ስፔሻሊቲ ነው ስህተት የሠራው። የሄቨን እናት አይደለችም የተሳሳተችው። ፍርድ የተሰጠው በአሜን ሀኪም ቤት ምክንያት ነው። የፈለገ ሕይወት ሆስፒታል እና የአሜን ሀኪም ቤት የምርመራ ውጤት አንድ ላይ በድጋሚ ታይቶ ባቀረብነው ይግባኝ መሰረት ፍትሕ ይሰጠን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቀጣዩ የደቦ ፍርድ…

"…ኦሮሙማው በጋዜጠኞቹ፣ በቲክቶከር፣ በዩቲዩበርና በፌስቡከሮቹ አማካኝነት በመጨረሻ ሲሸነፍ ሩዋንዳ አድርጎን እንደሚያልፍ ምልክት እያሳየን ነው።

"…አረመኔ፣ ጨካኝ፣ ሺዎችን በደቂቃ ከንግድ ሥራቸው፣ ከቤታቸው በግሬደር ላያቸው ላይ እየናደች ሀገር አልባ ያደረገች፣ በፈረሱና በወደሙ መኖሪያ ቤቶችና ሱቆች ሥፍራ ላይ አበባና ችግኝ የተከለችን የአዳነች አበቤን የትናንት የጽሕፈት ቤት መልእክቷን መመልከቱ በቂ ነው። "ፍርድ የተሰጠበትን ጉዳይ ላለፈው አንድ ዓመት ፍትሕ አጥታ የተሰቃየች" በማለት የክልሉን የፍትሕ ውሳኔ አፈር ከድሜ አስግጣ እሷ ነገ የምትቀማትን ቤት ቁልፍ ሰጥታ ቀሽም ቦለጢቃ የሠራችን ከንቲባ ተብዬ ድፍረትም አይተናል። እና ነገ ያሳስበኛል።

"…ተመልከቱ ይሄ ልጅ በስካር መንፈስ ፌስቡክ ላይ የሆነ ኮመንት ይሰጣል። ከዚያ የሚያውቁት ቤቱ ሄዱለት። ከቤቱም አውጥተው የደቦ ፍርድ ሰጡት። ፍርዱ ደግሞ የተሰጠው በLive የቲክቶክ ፍርድ ቤት ነው። ቀጥቃጮቹ ፖሊሶች አይደሉም። ደንብ አስከባሪዎችም አይደሉም። በቃ ቲክቶከሮች ናቸው።

"…ይሄ ልጅ በኮመንት ምክንያት ፖሊስ ቢይዘው አይመታውም ባይባልም እንዲህ Live እየቀየረፀ ቤተሰብ ሰብስክራይብ አድርጉ እያለ አይወግረውም። ልጁ ይከሰስ ተብሎ ፍርድ ቤት ቢቀርብ ዳኛው በሉ ውገሩትና ልቀቁት አይልም። ቲክታከሮቹ ግን…👊

"…ልጁ Live ሲቀጠቀጥ፣ ሲወገር ተመልካቹ በለው፣ ግደለው ይል ነበር። በቃ ዳኛ ሆነ ማለት ነው። ይቅርታ ቢጠይቅም እንኳ የሚፈለገው፣ እጅግ ተቆርቋሪና ተወዳጅ የሚያደርገው ልጁን መውገር ነውና ቀጠቀጡት። ይሄ ነገር ነገ በሁሉም ቤት ይገባል። በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት መሞት ከማልቀስ ይልቅ ዛሬ በዚህ ጎሽ ያላችሁ ሁሉ ነገ በወንድሞቻችሁ ታገኙታላችሁ።

•ጎበዝ እንረጋጋ ከእብዱ አገዛዝ ጋር አብረን አንበድ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ልጠይቅ ነኝ…?

"…ከትናንት ጀምሮ የሟች ሕፃን ፌበንን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በጎጃም የዐማራ ፋኖ እየተቀጠቀጠ የነበረውን የጁላ ጦር ለማጽናናት ሲባል ፍርድ የተሰጠበትን ወንጀል አዋራውን አራግፎ አምጥቶ ለፕሮፓጋንዳ ሥራ አውሎታል በማለት ሙግት ከጀመርኩ በኋላ ዛሬ ስለ ሕፃኗም ሆነ ስለወንጀሉ የሚያነሣ ሰው ፈልጌ አጣሁ።

"…ያን መቼ እንደተዘጋጁበት የማይታወቅ ድራማ በደም በተነከረ የጎንደር የእቴጌ ምንትዋብ ባሕላዊ ልብስ ተይዞ ሕዝብ ያላቀሱበት ቲያትር የቴዎድሮስን መድፍ ከቦታው ለማስነቀል ነበርን? በቃ የሕፃኗን እናት ነገ ላለመንጠቃቸው ዋስትና የሌለውን የኮንዶሚንየም ቁልፍ ለመስጠት ነበርን?

"…ትናንት የጎጃምን ሕዝብ እንደ ሕዝብ እየሰደቡ፣ ደረት እያስደለቁ፣ እንባ ሲያራጩ የነበሩት አክ እንትቪስቶች አንዳቸውም የሉም። አብሯቸው ያላለቀሰንና "ይሄ ነገር እንዴት ነው?" ብሎ የጠየቀን ሁላ "በልጅህ ደርሶ እየው፣ ቲክቶኩን እናዘጋ፣ ፈልጋችሁ ውገሩት እያሉ የደቦ ፍርድ ይፈርዱ የነበሩ ሁሉ ከወዴት ተደበቁ?

"…በቃ የሕፃኗ ፍትሕ በአንድ የኮንዶሚንየም ቁልፍ ተቋጨ ማለት ነው? በቃ? ያ ሁሉ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ሲያሰድብ የነበረ፣ ጎጃምና ጎንደርን ለማቃቃር ስኳድ ሲጎፈላባት የነበረ አጀንዳ አበቃ ማለት ነው?

"…በቃ ወንጀሉን የቲክታክ ላይ ሸቃላዎች ሸቅለውበት፣ የአንበሳ መዓት አስውርደውበት፣ ሕዝቡን ግጠውበት፣ ልጅቷን እርዱ ብለው ባንካቸውን ሞልተውበት ጨረሱ ማለት ነው? ይሄ ነውር ነው።

"…የት አሉ? መንጋውን እንባ አራጭተው ድራማ ሲሠሩ የከረሙት? በቃ ሺዎችን በጭካኔዋ ያፈናቀለችዋን የአሩሲዋን እመቤት አዳነች አቤቤን ጻድቅ ለማስመሰል ነበር ዘመቻው…?

• በቃ ለዚሁ ነው…? ምነው ረጭ አላችሁ…? እናንተም ደረት ደቂዎች፣ ሳታላምጡ ዋጮች፣ ግራቀኝ ለማየት ትእስት የሌላችሁ የት ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

13. የእናትየዋ ደህንነት ተደጋግሞ ተነሳ ...የወንጀለኛው ቤተሰቦች እንደሚያሳድዷት… በዛ ምክንያት ሥራዋን፣ ቤቷንና ከተማውን እንደለቀቀች በሰፊው ተስተጋባ…ከበደል ላይ በደል....የሕዝቡን ቁጣ አጋለው።

14.ከፍትሕ ሂደቱ ጋር ተያይዞ በጠበቃው፣ በሀኪሙ፣ በዳኞች፣ በወንድምየው ...ላይ በፍትህ ፈላጊው ዘማች የደቦ ፍርድ ተሰጠ። ያልተገባ አስተያየት ሰጥቷል የተባለ ወጣት ክፉኛ ተደብድቦ ደብዳቢዎቹ በጀብደኝነት  ወንጀላቸውን ቪዲዮ ቀርፀው አየር ላይ አዋሉት። ፍትሕ ፈላጊው ዘማችም እሰይ አለ። የፍትሕ አካላትም ደግሞ ባላየ አለፉት።

15. ቅዳሜ በፌክ ስም የተጀመረው ዘመቻም ረቡዕ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ለእናትየዋ የቤት ቁልፍ በመስጠት ተደመደመ። (በሂደቱ የእናትየዋንና የከንቲባዋን የፊት ገፅታ ንባብ ለባለሙያዎች) ትቻለሁ። ስጦታውን ሳይ ለጉዳቷ ድጋፍ፣ ...ሽልማት ወይስ…ክፍያ ብየ ለራሴ ጠየቅሁ። ግን መልስ አላገኘሁም። ምንም ይሁን ምን ዋናው እሷ ማግኘቷ ነው።

16. ለ 5 ቀናት በርካታ ተዋንያን የተሳተፉበትና ሚሊዮኖች የተመለከቱት በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ትራጀዲ ሲትኮም ብዙ አስተምሮን፣ እናትየዋን ጨምሮ በርካቶችን ጠቅሞ፣ ጥቂት ግለሰቦችን ጎድቶ (ጉዳታቸው ግን በቀላሉ የማይጠገን እጅግ ከባድ) ተጠናቀቀ። አዎ ተጠናቀቀ… ከነገ በኋላ ሁሉም ይረሳዋል… የሚያስታውሰው አንድስ እንኳ የለም ከተጎጅዎች በስተቀር።

17. በሂደቱ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ወንድም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ሀኪም ... እና ሌሎች ምን አልባት ከተወነጀሉበት ነገር ነፃ ከሆኑ ለማገገምና ስማቸውን ለማደስ ረዥም ጊዜ ይወስድባቸዋል። ሙሉ ለሙሉ ላይመልሱትም ይችሉ ይሆናል።

18. የተፈጠረው የጎጥና የብሔር አጀንዳ ቀድሞ ከነበረው ጋር ተዳምሮ ወደ ከፋ ችግር የሚያንደረድር ብዙ ሕዝባዊ ስብራቶችን ይፈጥራል። ፈጣሪ ያግዘን ....

መውጫ

- ይህ የኔ የግል ምልከታ እንደሆነ ይሰመርበት.... አዎ የሰነበተውን ሁነት የተመለከትኩበት ግላዊ አረዳድ ነው።

- የሴቶች በተለይ የሕፃናት መደፈር ጎልቶ የወጣ ወንጀል ነውና የአጀንዳ መሸፈኛ ሳይሆን የነገን ሀገራዊ ዕጣ ፈንታ በማሰብ ወንጀሉን መቆጣጠር በሚያስችል መልኩ የሕግ ድንጋጌዎች ተሻሽለው ወደተግባር እንዲገቡ የሁላችንንም ርብርብ ያሻል።

- ፍትሕ ይፀና ዘንድ በሕግና በሥርዓት ይጠየቅ እንጅ ፍትሕን ለመጠየቅ ፍትሕን መደፍጠጥ ተቃርኖ መሆኑ በጠያቂውም በተጠያቂውም ዘንድ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል።

- የሕፃን ፌቨን ጉዳይ በሚመለከተው አካል በደንብ ተጣርቶ ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጥ። የተዛነፈ ፍትሕ ካለ ይስተካከል። ያላግባብ የተጎዳ ካለ ይካስ። የሷ ፍትሕ ማግኘት ለልጆቻችን ደንነት ዋስትና ነው።

- ቃላት ስጠቀም ወይንም ሀሳቤን የገለፅሁበት መንገድ የሚያስቀይመው አካል ካለ በፈጣሪ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ፍትሕ ለሁሉም ! በማለት ጸሐፊው ሓሳቡን ይቋጫል።

"…እኔም ይሔን አጀንዳ የተቀላቀልኩት ለዚህ ነው። ወንጀሉን በግልፅ በማውገዝ ነገር ግን የአገዛዙን ሴራም ማክሸፍ ስለምፈልግ ነው። በዚህ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የእነ አቡበከር የወሃቢይ እስላም ቡድን ስለ ሸሪአ ሕግ መወትወት ጀምሯል። ይሄን ደግሞ እነ ያሬድ ያያና ኦርቶዶክሳውያን ነን የሚሉ በሙሉ ሳያውቁት እየገቡበት ነው። ለወንጀለኛ ጠበቃ አያስፈልግም ሁላ እኮ ነው የሚሉት።

"…የሚያሳዝነው ነገር የሁሉም አጀንዳ ማራገፊያ፣ ሳያላምጥ አራጋቢው ኦርቶዶክሳዊ ነኝ የሚለው ማዕተብ በደረቱ ያንጠለጠለው መሆኑ ነው። ከ95% በላዩ ኦርቶዶክሳዊ ነው። ቲክቶከር በለው፣ ዩቲዩበር፣ ፌስቡከር፣ ኦርቶዶክሳዊው ነው። ሁለቴ አያስብም። ብቻ  እንዴት ሰብስክራይበር እንደሚያገኝ፣ ወዲያው ደግሞ የእርዳታ አኩፋዳ ኮሮጆዋቸውን ይዘው ለልመና፣ በሰው ኅዘን አንበሳ አውርደው ለመሸቀል መጣደፍ ላይ ናቸው። በእውነት ያሳዝናል። ልብ ይስጣችሁ። ወንጀሉን አታውግዙ ሳይሆን ወንጀሉን አጣሩ። አትቸኩሉ። አትጣደፉ ለማለት ነው።

• ዛሬም አልጨረስኩም። ይሄን ፓርት ስቀጠቅጠው ነው የምውለው።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው፣ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደተለመደው የልቤ፣ የአንጀቴ፣ እንደቤተሰቤ የማያቸው ተናፋቂ የሆኑም የዘወትር ወዳጆቼ የሆኑ 1ሺ ጓደኞቼ አብረውኝ እግዚአብሔርን አመስግነዋል። በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ከሚከታተሉኝ ጥቂቶች በቀር የእኔ ትክክልኛ የማይቀየሩ የቴሌግራም ወዳጆቼ ቁጥርም እነዚሁ አመስጋኝ ጓደኞቼ ብቻ ናቸው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ቀጥሎ ደግሞ እንደተለመደው የምንሔደው ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርእሰ አንቀጻችንም ትናንት በኅዘን ለተጎዳች አንዲት የጎንደር እናት ሽንት ቤት ይኑረው አይኑረው የማይታወቅ የኮንዶሚንየም ቁልፍ በመስጠት የአፄ ቴዎድሮስን አደባባይ በማፍረስ፣ የሰባስተተፎልን ሃውልት በመንቀል በድል በኦሮሙማው የተጠናቀቀውን ቁማር በተመለከተ ነው የምሄድበት። ምሽትም በቲክቶክ ሁላ ልንወያይበት እንችላለን።

"…እህሳ ዝግጁ ናችሁ? እንደተለመደው እስቲ ዝግጁ ነነ ዘመዴ ብላችሁ አጥለቅልቁልኝማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻም…

"…ኦሮሙማ ቁማሩን በላው።

     "…እስኳድንና ቲክታከሮችን ከፊት በማሰለፍ ጎጃምን በማሰደብ ፍርድ ያገኘን የወንጀል ታሪክ በማጯጯህ ጎንደር ጎጃም ሲያባብሉ ከርመው ተጠቃች ለተባለች የጎንደር ልጅ የኮንዲሚንየም ቤት ቁልፍ በመስጠት እነ አያሌው መንበርን ጮቤ በማስረገጥ ማኖ ካነካኳቸው በኋላ በጨለማ በአጼ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ ያለውን አፄ ቴዎድሮስ ያሠሩት የሴባስቶፎል መድፍ የመታሰቢያ ሃውልት በክሬን ተንጠልጥሎ ምንም እና ማንም ኮሽ ሳይል ከሥፍራው አንሥተውታል። ሃውልቱ ለጊዜው ይነሣ ለዘላለሙ የታወቀ ነገር የለም።

"…ስኳድ የሚለውን ነግቶ ሰምቼው ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሟች ፌቨን አወት ግርማ የሃኪም የምርመራ ውጤት እነሆ እንካችሁ።

"…የህፃኗን የሞት ምክንያት በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ነው የሚለው የህክምና ምርመራ ውጤቱ። ስለዚህ የህፃኗን የወንጀል ድርጊት ሰፋ አድርጎ በድጋሚ ቢታይ ሕጉ ይከለክላል ወይ…?

"…እነ ያሬድ ያያ ዘልደታ ምን አይተው አጀንዳውን እንዳጯጯሁት ቢነግሩን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። እነ ኤልያስ መሠረት ምን ይዘው ነው እንዲህ ዋይዋይ ያሉት? ከምር መስከን ያስፈልጋል።

"…ለእኔ ጎጃምና ጎንደር አንድ ነው። አንድ የጎጃም ተወላጅ የሆነ ዐማራ ጎንደር ላይ ወንጀል ቢሠራ ወንጀሉን የሠራው በግል ፍርድ ያገኛል፣ ይወቀሳል እንጂ እንዴት ሙሉ ጎጃም ይሰደባል? አንድ ጎንደሬም ጎጃም ላይ እንዲሁ ወንጀል ቢሠራ ግለሰቡ በግል ይጠየቃል፣ ይወቀሳል እንጂ እንዴት ሙሉ ጎንደር ይሰደባል።

"…በግፍ የተገደለችው ህፃን አሟሟት ግን በድጋሚ በደንብ ቢጣራ ሌላም ወንጀለኛ ስቦ ሳያመጣ አይቀርም ባይ ነኝ። ፍትህ የሕዝብ ገንዘብ መዥረጥ እያደረጉ በመስጠት የግል ፖለቲካን በመሥራት አይረጋገጥም።

"…በኦሮሚያ ሽመልስ አብዲሳ በሸኔ የተደፈሩ ወንዶች አሉ ያለው ምን አይነት ፍትህ አገኙ? አዲስ አበባ ላስቲክ ዘርግተው የሚያድሩ ህፃናትን የደፈሩት ምን ፍትሕ ተሰጣቸው። ዜጋ ከሆነ ሁሉም ዜጋ እኩል ነው። እነዚያ የፖለቲካ ትርፍ ስለማያስገኙ ቤትም የሚዲያ ሽፋንም አያገኙም ማለት ነው አይደል?

"…ስለ ሟች ሕፃን ፌቨን ክብረ ንፅህናም ያወራል የህክምና ወረቀቱ። ባለሙያዎች አስተያየት ስጡበት እስቲ።

• ደፈር ብለን በቅንነት እንወያይ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በጨዋ ደንብ እጠይቃለሁ…

"…የህች ህፃን ልጃችሁ አይደለችም? የት ሄደ? ሀገሬ አይደለም ባሕርዳር? መኖር አልችልም ማለት ነው? ለእናንተ እኮ ነው ያገለገልኩት? ላቤን ጠብ አድርጌ፣ እኔ ጎንደር ተወልጄ ባድግም ሀገሬ ነው። እና የት ሄዳችሁ? የት ሄዳችሁ እናቶቼ ፍረዱኝ። አብዛኛው በእርግጥ ተሸፋፍኖ ለማስቀረት ጥረት ይደረግ ስለነበር የባሕር ዳር ሕዝብ አብዛኛው የሰማ አይመስለኝ። እና የት ሄዳችሁብኝ። ፍረዱኝ። ፍረዱኝ። አሁን ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ ነው።

"…ሀገሬ አይደለም ባሕርዳር? መኖር አልችልም ማለት ነው? ለእናንተ እኮ ነው ያገለገልኩት? ላቤን ጠብ አድርጌ፣ እኔ ጎንደር ተወልጄ ባድግም ሀገሬ ነው። ዋናዋ የነገር ማጠንጠኛዋ ሰበዝ ያለችው እዚህ ጋር ነው። ይህቺን ስሰማ፣ የሴቲቱ አለመረጋጋትን ሳይ እዚህ ጋር ነው የስኳድ ፖለቲካ የሸተተኝ። "መልሳ ደግሞ "የባሕር ዳር ሕዝብ አብዛኛው የሰማ አይመስለኝም"

"…የክልሉ መንግሥትማ ሰማ እኮ። ሰማና በሀገሪቱ የመጨረሻውን የፍርድ ውሳኔ ሰጠ። 25 ዓመት ፈረደበት። እና ከዚህ በላይ ሕጉ የማይፈቅድለትን ከየት አምጥቶ ይፍረድ? በዚህ ጉዳይ የሕግ ባለሙያዎች የሰጡትን አንድ ቪድዮ ቆይቼ አሳያችኋለሁ።

"…የሟች ሕፃን ፌቨንም የህክምና የምርመራ ውጤት ደርሶኝ አይቼዋለሁ። ህፃኗ መደፈሯን አላረጋገጠም። ክብረ ንጽህናዋም አልተገሰሰም ነው የሚለው። እሱንም እለጥፈዋለሁ። ትንሽ ቢብራራልን ብዬ ነው።

"…ይህቺ ግን "…ሀገሬ አይደለም ባሕርዳር? መኖር አልችልም ማለት ነው? …እኔ ጎንደር ተወልጄ ባድግም ሀገሬ ነው።" የምትለዋን ሀረግ ይዛችሁ እንደ ሕዝብ ጎጃም ላይ ከተከፈተው የስድብ ዘመቻ ጋር አነጻጽራችሁ አስረዱኝ። ስኳድ አጀንዳ ስቦ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ማሰደብስ ጥሩ ነው? የሟች አባትም ካለበት ቢናገር ጥሩ ነው።

• ደፈር ብለን እንወያይ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኔ ዘመዴ ሞጣን በተመለከተ ያለኝን አቋም በተጠየቅኩት መሠረት ምለከታዬን አስቀምጫለሁ። እስከ አሁን አቋሜን ካነበቡ መካከል 5 ሰዎች 😡 ብው ብለው ከመናደዳቸው በቀር እስከዚህም ጓ ያለ ሰው አላየሁም።

• ይሄ የእኔ የዘመዴ አቋም እና ምልከታ ነው። የእናንተንም አቋምና ምልከታ አከበርላሁ። ለማንኛው ቀጥሎ የተወሰነ ሓሳብ በዚህ ጉዳይ ላይ በጨዋ ደንብ እንሰጥና ወደ ሌላ ርእሰ ጉዳይ እናልፋለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሞጣን በተመለከተ ለተጠየቅኩት
የእኔ የዘመዴ መልስ…

"…መቼም በዚህ የቲክቶክ መንደር ያለ ነዋሪ ከተወሰኑና በጣት ከሚቆጠሩ የመንደሩ አክተሮች መካከል ሞጣ ቀራንዮ ወይም በመዝገብ ስሙ ማማሩ አዳመ መንግሥቴ የተባለን ቲክቶከር የማያውቅ የለም። እኔ ደግሞ የሞጣ ፕሮግራም ማጣፈጫ ቅመሙ ነኝ። እሱና የከለኗ ትእግስት ብሪጅስቶን እኔን ካልሰደቡ፣ ካላዋረዱ መርሀ ግብራቸውም አያምር፣ አየሰምርላቸውም። እኔም ሞጣን እንዲሁ እዝናናበት ነበር።

"…ሰሞኑን ሞጣ ቀራንዮ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ በግፍ፣ በጭካኔ በተገደለችዋ ህፃን ልጅ ላይ የተለመደውን "ጥራዝ ነጠቅ፣ ግበረገብነት የጎደለው፣ አፀያፊና ሊሰሙት የማይታገሱትን ዘግናኝ ቃላቶችን"  በመጠቀም መናገሩን ተከትሎ በዚሁ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች፣ ከልጁ ጋር በቲክቶክ ሲረጋገጡ በከረሙ ባላንጣዎቹ አማካኝነት የልጁን ቲክቶክ ለማዘጋት ሲረባረቡ እያየሁ እየታዘብኩ ነበር። ዘማርያን እና ኡስታዞች ሁላ አልቀሩም ሲረባረቡ።

"…እኔ ግን እጠይቃለሁ። ከምር ሞጣ ያንን የተለመደ ቀፋፊ ጋጠወጥ አረመኔ ንግግሩን የዚያን ዕለት ብቻ ነው የሰማችሁት? ሞጣ ከዚህ ባለፈ እግዚአብሔር አምላክን፣ እየሱስ ክርስቶስን፣ አላህን፣ ሙስሊምና ክርስቲያኖችን፣ ሲሰድብ፣ ሲሞልጭ፣ ቅዱሳት መካናትን፣ ታቦታቱን ሲያዋርድ፣ በቅዱስ ገብርኤልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ሙድ ሲይዝ፣ በቅድስት አርሴማ ላይ ሲሳለቅ፣ ሲያላግጥ፣ ካህናትን፣ መነኮሳትን፣ ገዳማዊ ሕይወትን ጭምር አፈር ከደቼ ሲያስግጥ ሴቶቹ መቀመጫቸውን ወጥረው፣ ጡታቸውን አገፍጥጠው፣ ስለ ጭንና ጡት፣ ስለ ወሲብ ሲያወራ አፋቸውን ከፍተው ሲሰሙት አልነበር ወይ የከረሙት። እና ዛሬ ምን እውነት ምን አዲስ ብልግና፣ አዲስ ነውር ነገር ተናግሮ ነው በዚህ ልክ አዋራ የተነሣው? አልገብቶኝም።

"…ሞጣ ጎጃምን ገጀጀ እያለ የራሱን ሀገር የሚሰድብ፣ ዐማራን ከትግሬና ከኦሮሞ ነፃ አውጪ በላይ የሚያዋርድ፣ ጀግናው በላይ ዘለቀን፣ አርበኛ ዘመነ ካሤን፣ የዐማራ ፋኖን፣ የሚያዋርድ፣ አገውን በይፋ የሚሰድብ፣ ሆኖ ሳለ አሁን በነውረኛው ሞጣ ሰበብ ሞጣ የተወለደው ጎጃም ነው ተብሎ በጎጃም ላይ በዚህ መጠን መዝመትስ ሌላ ነገር ከጀርባ እንዳለ አያስጠረጥርም ወይ? ልጁን ለይቶ መስደብ የአባት ሆኖ ሳለ ልጁ የተወለደበትን ሀገር አፍ አውጥቶ በጅምላ ለማዋረድ መላላጡ የፋኖን ትግል ያስቆማል ወይ? ሞጣ ማለት የትግሬን ሕዝብ፣ የዐማራን፣ የኦሮሞን፣ የጉራጌን ሕዝብ ወዘተ በድፍረት ለዓመታት ሲሰድብ የኖረ፣ ሲያዋርድ የኖረ መሆኑ እየታወቀ፣ ነገር ግን ትግሬው፣ ዐማራ ኦሮሞው አብሮት እየሳቀ፣ እየተሳለቀ የምናየው አይደለም ወይ? አምላኩ፣ ማንነቱ ሲሰደብ አብሮት ሲስቅ፣ ሲደበር፣ ፈጣሪው ሲሰደብ ሲያሽካካ፣ የሞጣን ስድብ በቲክቶኩ እየለጠፈ እንጀራ ይበላ የነበረ መንጋ ሁላ ድንገት ዛሬ ብድግ ብሎ ጻድቅ ጻድቅ በመጫወት የሚቃወመው ስለ እውነት ያ የሰውየው የብልግና ንግግሩ ብቻ አስቆጥቶትና ተናድዶ ነው? ሰብአዊነት ተሰምቶት ነው ወይ? እኔ በበኩሌ አይመስለኝም።

"…ዮኒ ማኛ፣ እማማ ሮማን፣ ኢዳብ፣ ወዘተረፈ የሚባሉ የቲክቶክ ባለ ዛሮች እንዲየው ከሞጣ ተሽለው፣ ሰብዓዊነትም፣ ሥነ ምግባርም ኖሮአቸው ነው ያውም የዘመቻው ፊትአውራሪ ሆነው ዋይ ዋይ ብለው የተነሡት? አይመስለኝም። ለሞጣ እየሞገትኩ አይደለም። ሞጣን ሰው ባያዋርደው ፈጣሪ ቀን ይቆጥረለታል፣ ወይም ደግሞ ፈጣሪ መሃሪ ነውና ይምረዋል። እኔ በበኩሌ ስለሞጣም ሆነ ስለሌላው ክፉ አልመኝም። እኔ አምላኬ ያስተማረኝ “ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ሉቃስ 23፥34 ብሎ ነው። እኔ እያዋረደ። ልጄን ድፈሯት እያለ ከብሪጅ ስቶን ጋር እያወጀብኝ እንኳ ምህረት ነው የምለምንለት።

"…ባለፈው እንደተናገርኩት ጉዳዩ ፖለቲካ ነው። ድብን ያለ ፖለቲካ ነው። ፖለቲካው ሲበዛ ደግሞ አረመኔውን ወንጀል መጠራጠር እንጀምራለን። የጉዳቱ ተጠቂ የሆነችው ልጅ በራሱ የምትሰጣቸው ቃለመጠይቆች እርስ በራሳቸው እ ተጋጩብኝ ነው። ከኀዘን ብዛት ባትረጋጋ ይሆናል ብዬ ባስብም ነገርየው ግን ከዚያም የዘለለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ነገርየው የትግሬ፣ የቅማንት፣ የጎንደር፣ የጎጃም እና የኦሮሞ ፖለቲካ ሆኗል። የተጠቂዋ ልጅ እናት "እኔ ከጎንደር ስለመጣሁ ጎጃም መኖር የለብኝም ማለት ነው?" ብላ ኢንተርቪው መስጠትዋን ሳይ ምን እየተደረገ እንደሆነም አመላካች ነው።

"…እርግጥ ነው ወንጀሉ ሲበዛ አፀያፊ ነው። ዘግናኝም ነው። ነገር ግን ፖለቲካ ሊሠራበት የተሄደበት መንገድ ይደብራል። እኔ የጎንደሩን ስኳድ መቀጥቀጥ ስጀምር፣ የጎጃም ፋኖ የትራንስፖርት እቀባ ዐዋጅ ዐውጆ በጎጃም ምድር መንግሥት መሆኑን ሲያስመሰክር፣ ወንጀሉ ተፈጽሞ፣ በሀገሪቷ ሕግ መሠረት የመጨረሻው ቅጣት ተወስኖበት ማረሚያ ዘብጥያ ያለን ሰው፣ ፍርዱ የካቲት ላይ ተፈርዶ መንፈቅ የሞላውን ጉዳይ አሁን አምጥቶ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ለማሰደብ መጣጣር አስቂኝ ነው።

"…አባ አብዲ የተባለ ኬንያ የተሰደደ ዐማራ ጠል የኦሮሞ ቲክቶከር ሳይቀር የዚህ ዘመቻ ተሳታፊ ሲሆን በእውነት ነው የተደመምኩት። በግፍ የሞተችው ሕፃን ወላጅ አባት ትግሬ መሆን ደግሞ የሟች እናት ከጎንደር ባላረጋግጥም (ቅማንት ናት) የሚሉ አሉ ጎጃም ላይ ለሚደረገው ዘመቻ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎችን ድጋፍም አግኝታለች። በኦሮሚያ ምድር የዐማራ ሕፃናት እንደ ሳር ሲታጨዱና ሲጨፈጨፉ ቅሽሽ ያላላቸው የኦሮሞ አክቲቪስቶች አሁን ዐ"በግፍ የሞተችዋን፣ በአረመኔያዊ ሁኔታ የተገደለችዋን" ህፃን አስታከው ቲሸርት ሁላ አሠርተው ኅዘን በዘመቻ መቀመጣቸው ያስገምታል። የወንጀል ድርጊቱ ይወገዛል። አውጋዦቹ ግን… ?????

"…አንድ ሰው እያየሁ ነበር። የወንጀል ድርጊቱ በፋና፣ በዋልታ፣ በኦቢኤን፣ በደረጀ ሀብተወልድ፣ በኢቲቪ ሲቀርብ አይቶ መፈክር አሠርቶ ብቻውን ድርጊቱን ተቃውሞ አደባባይ ባነር ይዞ ይወጣል። ሕፃናትን መግደል ትውልድ መግደል እንደሆነ ነው ባነሩ ላይ ያለው ጽሑፍ የሚያሳየው። ከዚያ ፖሊሶች መጡ። መጡና መሰለፍ አትችልም ብለው እያገጣበሩ ይዘውት ሄዱ። ቪድዮው አለኝ። ማረሚያ ቤት ተፈርዶበት ያለ ወንጀለኛ ይግባኝ መጠየቅ፣ ጠበቃ ማቆም መብቱ ነው። አገዛዙ ከፈለገ አውጥቶ መግደልም መብቱ ነው። ነገር ግን አገዛዙ በግፍ በተገደለች ሕጻን ላይ ድራማ መሥራቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ወንጀሉ ያሳዝናል እና ቆም ብሎ ማሰቡ ተገቢ ነው።

"…ነጥቦቹን ስናገጣጥም። ከፊት የተሰለፉትን የድምጻችን ይሰማ የወሃቢይ ኃይላትን ስመለከት መዝግቡልኝ በቅርቡ በኢትዮጵያ የሽሪአ ፍርድ ቤት ይቋቋም ይባልልሃል። ይሄ ያልገባቸው የተዋሕዶ ልጆች እና የቅድስት ልደታው ያሬድ ያያ ግንባር ቀደም ሆኖ "ገድላችሁ አሳዩን" ብሎ ሲማጸን ነበር። በሌላ በኩል ቅማንቴው የጎንደር ስኳድ በአገዛዙ ውስጥ ባለው የሥልጣን መዋቅር ተጠቅሞ በሰብአዊነት ስም አንጀት የሚያራራ አጀንዳ አምጥቶ ለማምለጥ ሞክሯል። በፍጹም በሕፃን ሔቨን አሰቃቂ ግድያ ተሸፍኖ ማለፍ፣ ማምለጥ ብሎ ነገር የለም። የወንጀል ድርጊቱን ስኳድ እንዲመራው፣ ጎጃምና ጎንደርን እንዲያቃቅርበት መፍቀድም የለብንም። ለእናትየው ቤት መሰጡትን እደግፋለሁ። ደስም ይለኛል። ነገር ግን አሁንም ነገርየው ፖለቲካ መሥሪያ ሊሆን አይገባም። ልጆቻቸው ተደፍረው፣ ሞተው ሜዳላይ የቀሩ። ወንጀለኞቹ በነፃ ተለቀው አሁንም የሚፎክሩባቸው ሰዎች የሉም ወይ? ሌሎቹስ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በዐማራ ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው እናቶች መኖሪያ ቤት ይሰጣቸዋል ወይ? 👇ከታች ① ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ፪

"…መልካም። እኔን ከሚከታተሉኝ 300 ሺ ሰዎች አንድ መቶ ያህል ሰው በዚህ መጠን መንቃቱን፣ መባነኑን ካወቅኩ እጅግ አትራፊ የሓሳብ ነጋዴ ነኝ ማለት ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ዛሬ በፅሞና እስከ ፍጻሜው ድረስ ከተከታተላችሁኝ መጨረሻ ላይ እናንተው ራሳችሁ አገዛዙ እንዴት አጀንዳ እንደሚፈበርክና የፈበረከውንም አጀንዳ እንዴት አድርጎ በጅምላና በችርቻሮ እንደሚያከፋፍል ትደርሱበታላችሁ።

"…አጀንዳ ተፈብርኮ በእነማን በኩል እንደሚከፋፈል፣ እንደሚቸረቸር ካወቃችሁ ደግሞ ሌላ ጊዜ የበግ ለምድ የለበሰውን ተኩላ ከመለየት ይጠቅማችኋል ማለት ነው። ገባችሁ… ኣ…? …መልካም ወደ አሁኑ ጥያቄ አመራለሁ።

• ለዐማራ ተብሎ ተመርቶ በሚከፋፈል አጀንዳ ላይ ከአጀንዳው አከፋፋዮች መካከል ፀረ ዐማራ አቋም ይዘው ከፊት መስመር ከሚሰለፉት አጀንዳ አከፋፋዮች መካከል ዋናዋናዎቹን በስም ጥቀሱና ብሔራቸውንም አብራችሁ ግለፁ እስቲ። በድፍረት አውሩ። በድፍረት።

"…የተፈበረከውን ፀረ ዐማራ የሆነ አጀንዳ ተቀብለው እንደወረደ የሚያከፋፍሉት ሌሎች ነገዶች ሆነው ሳለ ያንን መርዝ ቅብ አጀንዳ ሳያላምጡ እንደወረደ የሚቀጎርሱ የዐማራ ነገድ አባላት ነን ባዮች እስከአሁን ያልነቁ "እከደከን ማንችሎት ከወንድ በላይ አበጀን" የሆኑ ሰገጤ የዐማራ ቲክቶከሮች፣ ፌስቡከርና ዩቱዩበሮችን እስቲ ጥቀሷቸው። በዚያውም እንወቃቸው።

"…100 ሰው አስተያየት ከሰጠ በኋላ ሦስተኛው ጥያቄ ይቀጥላል። ዥልጥ ዐማሮችን፣ የጠላታቸውን አጀንዳ አራጋቢዎችን እስቲ እንወቃቸው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ከላይ በመግቢያችን ላይ እንደተገለፀው የዛሬው ርእሰ አንቀጸችን የሚሆነው የእናንተን በነገሮች ሁሉ መባነን እና ነቄ መሆናችሁን ለማወቅ እና ሌሎችም ይህን ንቃታችሁን በግላጭ እንዲያዩና እንዲያውቁት የሚያደርግ ርዕሰ አንቀጽ ነው።

"…ለመሆኑ ሰሞኑን የዐማራ ፋኖ በጎጃም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ገደብ ካወጀ እና ዐዋጁንም ተከትሎ ሕዝቡ ዐዋጁን ተቀብሎ ከዳር ዳር ተግባራዊ ካደረገው በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያው ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ዘንድም ሆነ በመንግሥታዊው የመገናኛ ብዙኀን ሳይቀር ይሄን የጎጃም ዐማሮችን ተጋድሎ ለመቀልበስ ሲባል በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዪቲየብ፣ በቴሌግራም ሳይቀር አጀንዳውን ለማስቀየር ሲባል ተፈብርከው ስለተሰራጩና ዋይዋይ ስለሚባልባቸው ጉዳዮች እና ደረት አስደቂ አጀንዳ ፈጣሪዎች ምን ታዘባችሁ…?

"…የእናንተን ምልከታ፣ ማወቅ ስለፈለግኩ ነው። ጻፉ፣ ጻፉ፣ ጻፉ። ወዳጅ ጠላትም ያነበው ዘንድ ጻፉ፣ ጻፉና ለአጀንዳ ፈብራኪዎቹ ነቄነታችሁን አሳዩ።

• አስባችሁ ምልከታና መረዳታችሁን አሳምሮ ለመጻፍ 10 ደቂቃ ብቻ እሰጣችኋለሁ። ከ10 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።

• 1…2…3 ጀምሩ ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሐምሌ 15 ዕረፍቱ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ (ከ306-373 ዓም) … ታሪኩ ከላይ ይነበብ።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ

"…ሀገሩ ሶርያ የያዕቆብ ዘንጽቢን ደቀመዝሙርም ነው፡፡ ያዕቆብ ዘንጽቢን ለአውግዞተ አርዮስ ወደ ኒቅያ ሲሄድ አስከትሎት ሄዶ ነበር፡፡አርዮስን አውግዘው ሃይማኖት መልሰው ካደሩበት ሌሊት ዓምደ ብርሃን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ብርሃኑ በዓለሙ ሞልቶ ራዕይ አየ፡፡
ባለቤቱን ግለጽልኝ ብሎ ቢያመለክት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው የሰውን ልቦና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና እንዲህ ባለ አርአያ አየኸው ለመርዳት ቂሣርያ ሄደ፡፡ በወቅቱ በወርቅ ወንበር ተቀምጦ በወርቅ አትሮንስ የወርቅ ወንጌል አዘርግቶ ኩፋር ጠምጥሞ ካባ ላንቃ ለብሶ እጀታው የወርቅ የሆነ የወርቅ መነሳንስ ይዞ ሲያስተምር አገኘው፡፡ ወተሐዘቦ ልቡ ለኤፍሬም ከመሥጋዊ ውእቱ ይላል፦እርሱ መሆኑን ተጠራጠረ አራት ነገር አይቶ ይረዳል፡፡

"…መጀመሪያ ከአፉ ነጸብራቅ እሳት እየወጣ ያያል። እሳቱ ሕዝቡን ሲዋሓዳቸው ያያል ትምህርቱ ነው፣ ሶስተኛ ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ ስታርፍበት ያያል። አራተኛ ስሙን ያውቃል ሀገሩን ሳይጠይቅ ኤፍሬም ሶርያዊ ኤፍሬም ለብሐዊ ብላችሁ ጥሩልኝ ከማዕዘነ ቤተክርስቲያን ባንዱ ቆሞ ይጸልይላቹሀል ብሎ አስጠራው። እያደነቀ ቀርቦ የባስልዮስ ቋንቋ ለኤፍሬም የኤፍሬም ቋንቋ ለባስልዮስ ተገልጾላቸው ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አሰናብቱኝ ልሂድ አለው። ልትኖር እንጂ ልትሄድ አምጥቶሀልን ብሎ ሕዝባዊ ነው ቢሉ ዲቁና ዲያቆን ነው ቅስና ሹሞ ከሀገር ስብከቱ ሀገር ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡

"…ባስልዮስ ይህን መልበሱ ስለ ክብረ ወንጌል ነው፡፡ ዛሬ ካህናት አክሊል ደፍተው ካባ ላንቃ ለብሰው ሥጋውን ደሙን እንዲያከብሩ እንዲለወጡ እሱ ግን በውስጡ የሚለብሰው ማቅ ነበር። ለብሐዊ የተባለው ሞ ብረሌ መርጠብ ብርጭቆ ኩዝ ካባ እየሠራ ሽጦ የዓመት ልብሱን የዕለት ጉርሱን እያስቀረ ሌላውን በእመቤታችን ስም ይመጸውት ስለነበረ ነው። እመቤታችንን ከመውደዱ የተነሳ የእመቤታችን ምስጋናዋ እንደሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው እንደ ውኃ ጠጥቼው ረክቼው እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር። የሹትን መግለጽ ለመንፈስ ቅዱስ ልማዱ ነውና ገልጾለት እልፍ ከአራት ሺህ ደርሶት ደርሷል። አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋኪ እስኪል ድረስ ጸሎቱም ከወንጌለ ሉቃስ ወበሳድስ ወርኀን፣ ጸሎተ እግዝእትነን አውጥቶ 64 ጊዜ ይደግም ነበር።

"…ከጊዜያት በአንዱ ዕለተ ሰኑይ ጊዜው ነግህ ነው። የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል የብርሃን ድባብ ይዘረጋል። ከዚያ ላይ ሁና "ሰላም ለከ ኦ ፍቅርየ ወፍቁረ ወልድየ ኤፍሬም" ትለዋለች ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድስኒ ትለዋለች እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራውያን ሰማያውያን መላዕክት ምድራውያን ጻድቃን ሰማዕታት አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት። "በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ" መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለህ ተናገር አለችው፡፡ ባርክኒ ይላታል በረከት ወልድየ ወአበሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኀድር በላዕሌከ ትለዋለች። ተባርኮ እንዳጸናው ቀለም ሰተት አድርጎ አመስግኗል። ስታስደርሰውም በሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች። ምስጋናውም የሰባቱ ዕለታት ውዳሴ ማርያም ነው። ዜማውን ቅዱስ ያሬድ ደርሶታል። በያዘችውም መስቀለ ብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው አርጋለች። እሱም የበለጠ ሲያገለግላት ኑሮ በዚህ ዕለት በሐምሌ 15 አርፏል። ለቅዱስ ኤፍሬም የተለመነች ድንግል ማርያም ለኛ ለኃጢአተኛ ልጆቿ ትለመነን። የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በረከቱ ይደርብን። አሜን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel