መልካም…
"…የእኔን ሓሳብ የሆነው ርዕሰ አንቀጼን 5 የ😡 የመበሳጨት፣ የመብገን፣ የመናደድ፣ የመጨስ፣ የመቃጠል፣ የማረር ፊት ካሳዩ ደንበኞቼ በቀር ከ10 ሺ ሰው በላይ ማንበቡን ቴሌግራም ሪፖርቱን በገጼ ላይ ገጭ አድርጓል። 😡 ይሄን ፊት ከዚህ በኋላም በብዛት አይ እመለከትም ይሆናል።
"…ለማንኛውም አሁን ተራው የእናንተ ተራ ነው። እናንተ ደግሞ ከእኔ የቀረ፣ የጎደለ ካለ ጨምራችሁ፣ ከእኔ የበዛ፣ የተረፈ ካለ ቀንሳችሁ የእናንተን ሓሳብ የምታስኮመኩሙን ሰዓት ነው። ቤቱ ለባለጌ አይመችም። ተቃውሞም ካለ በጨዋ ደንብ ይስተናገዳል። ስድብ ያስቀስፋል።
• 1…2…3…ጀምሩ…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…አሁን አሁን ዐማራው ተራራው የማንንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያውቅም ቱሪናፋ ሁላ አጀንዳ እየቃረመ ከመቀበል ራሱ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ጋግሮ ወደ መስጠት፣ ወደ መለገስ፣ ወደ ማከፋፈል ተሸጋግሯል። ይሄ ደግሞ በእጅጉ ጠቅሞታል። እስከ ዛሬ ድረስ የትግሬ ነፃ አውጪም ሆነ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮች የአለቃቸውን የሲአይኤን የአጀንዳ አፈበራረክ፣ አዘገጃጀትና አተራረክ በጅምላና በችርቻሮ አዘጋጅተው ስለማከፋፈል የሚያስረዳውን ማንዋል እያነበቡ ዐማራውን በራሱ ጉዳይ መፍትሄ እንዳያመጣ እነሱ ፈብርከው በሚሰጡት አጀንዳ ተወጥሮ በላይ በላዩም አጀንዳ እየከመሩበት በአካልም፣ በመንፈስም ሲበታትኑት ኖረዋል።
"…የዐማራ አንቂዎች አይደለም በተቋም፣ በፓርቲ ደረጃ ተፈብርኮ የተበተነ አጀንዳ ይቅርና በዮኒ ማኛ፣ በመስፍን ደበሌ፣ በሞጣ ቀራንዮ፣ በናትናኤል አንደግምም ወይ፣ በስዩም ተሾመ፣ በቶማስ ጃጀው፣ በጌትነት አልማው፣ በስታሊን እና በአሉላ ሰለሞን ወዘተረፈ ተራ የፖለቲካ ፓርቲ ገሌ ጋለሞቶች ተዘጋጅቶ ለሚበተን አጀንዳ ጎጋዎቹ የሚያቀረሹትን ቅርሻት ተቀብሎ ነጠላ ዘቅዝቆ፣ እንደ መንደር ኃይለኛ ሴት ወገቡን በእጁ ጥርቅም አድርጎ ይዞ እንጥሉ እስኪያብጥ፣ ልቡ እስኪፈነዳ ድረስ ቆሞና ተቀምጦ ምላሽ ለመስጠት ይጋጋጥ ነበር። ያነዜ ዐማራ አጀንዳ ለመፍጠር፣ ለማቀበልም አልታደለም ነበር።
"…አሁንስ? አሁንማ አባቴ ዐማራው ሲሳይ አጌና የሚባል ገሌ ጋዜጠኛ እስከነ መኖሩም አያውቅ። ናቲ አንደግምም ወይ ቢጨንቃት የጌታ ልጅነቷን መስክራ የጴንጤ መዝሙር ወደመጋበዝ መውረዷን እንኳ አልሰማም። ሞጣን ለመደበሪያ፣ ጊዜ ለማሳለፊያ፣ እነ ቶማስ ጃጀውን ሙድ ለመያዣነት ይጠቀምበት ካልሆነ በቀር አባከና የሚላቸው ዐማራ የለም። አሁን የነፃ አውጪዎቹ አክቲቪስቶች በሙሉ በኦሮሚኛና በትግርኛ የሚሰማቸው ቢያጡ ልመናም፣ ቅፈላም፣ እዬዬም፣ ጮቤም መርገጥ ሲያምራቸው ልፈፋቸው በአማርኛ ሆኗል። ትኩረት ለመሳብ፣ አጀንዳ ለመስጠት የሚጋጋጡት በአማርኛ ብቻ ሆኗል።
"…በፊት በፊት የዐማራ ጠላቶች ዐማራን ምን ዓይነት አጀንዳ ወርውረንለት እናስለፍልፈው፣ እናዘናጋው፣ እናተራምሰው ብለው ነበር የሚፍጨረጨሩት። አሁን ግን ወፍ የለም። በፊት በፊት ጃዋር መሀመድ እንዲህ አለ፣ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ብሎ አቀረሸ፣ አዳነች አቤቤ በዚህ ወጣች፣ አቢይ አህመድ በዚህ ገባች፣ ዳንኤል ክብረት እንዲያ ጻፈ፣ የሆነ አረብ ሀገር ያለ ገገማ እንዲህ አለ ለሚለው ሁሉ ዐማራው የራሴ የሚለውን ምላሽ ይዞ በፌስቡክ፣ በቲክቶክ፣ በዩቲዩብ እና በቴሌግራም ተሰይሞ ይንጠራወዝ፣ ሲንተከተክም ውሎ ያድር ነበር። አሁን ግን የፈለገ አጀንዳ ቢወረወር አባከና የሚለው ዐማራ የለም። ወላሃንቲ አለ ትግሬ።
"…ዳንኤል ክብረትም ኃይሉን አሟጥጦ ጨረሰ። አቢይ አሕመድም እጅ እጅ አለ ቸከ መነቸከ። በቴሌቭዥን፣ በራዲዮ፣ በጋዜጣ አጀንዳ ተፈብርኮ ቢወጣ በጣቱ የሚነካው ሳይሆን ዞር ብሎ የሚያየው ዐማራ ሁላ ነው የጠፋው። በፊት በፊት ሥራ ፈት የነበረው ዐማራ አሁን ሥራ ላይ ስላለ ለመንደሬዎች ወሬ ቦታ፣ ጊዜ መስጠት አቁሟል። ምንም ዓይነት ሥራ የሌለው፣ በምድር ላይ እየተካሄደ ያለውን ጉዳይ የማያውቅ፣ መረጃም የሌለው አዲስ መጪ ዐማራ ነው አሁን በዚህ ጊዜ ለቲክቶክ ወሬ፣ ለፌስቡክ አጀንዳ ጆሮ ሰጥቶ የሚንከላወሰው። ይነስም ይብዛ፣ በእውቀትም ይሁን በስሜት አሁን ሁሉም ዐማራ እንደየአቅሙ አጀንዳ ሰጪ ሆኗል።
"…በፊት በፊት ትግሬ የትግሬ ዘፋኞች ብቻ ነበሩ ስለትግሬ፣ ስለተጋሩ፣ ስለትግራይ የሚዘፍኑት። ዐማራው ወይ በእነሱ ዘፈን ይጨፍራል አሊያም በቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ያብድ ነበር። በፊት በፊት የኦሮሞ ዘፋኞች ስለኦሮሙማ፣ ስለኦነግ፣ ስለ አባገዳና ስለ ገዳ ሥርዓት ዘፈን አውጥተው ራሱ ዐማራውን የሚሰድብ፣ የሚያንቋሽሽ ዘፈን አውጥተው ለገበያ ሲያቀርቡ ትርጉሙ ሳይገባው ከኦሮሞ በላይ አዋራ ያጨስ የነበረው ዐማራው ነበር። ቢያንስ ስለ ጎንደር፣ ስለ ጎጃም፣ ስለ ሸዋ ስለ ወሎ፣ ስለ ቴዎድሮስ፣ ስለ በላይ ዘለቀ፣ ስለ ሚኒልክ ደፍሮ ይዘፍን ነበር እንጂ የዐማራ አርቲስቶች እንዲህች ብለው ስለ ዐማራነት እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ አይዘፍኑም ነበር። ምክንያቱም እነ ግንቦት 7 ዐማራ በዐማራነቱ እንዳይኮራ ዐማራ ዐማራ ነኝ ካለ ከከፍታው ይወርዳል። እንደ ትግሬና ኦሮሞ መውረድ የለበትም። ዐማራ የሚያምርበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል ነው ብለው በሱዳን አስማት ጠፍረው ይዘውት ስለነበር ነው።
"…አሁንስ? አሁንማ ምኑ ይጠየቃል? ቀረርቶው፣ ፉከራው፣ ሽለላው ሳይቀር ምድሪቱን አጥለቅልቆታል። ከቀደምቶቹ ጩጬ ሚጢጢዬ የትግሬ እና የኦሮሞ የዘር ዘፋኞች ግዙፉ ዐማራ ከኋላቸው ተነሥቶ ቀድሞ ከፊት ጉብ ብሎ አርፎታል። ዳኜ ዋለ፣ ፋሲል ደሞዝ፣ ተመቸ ንጉሥ፣ መሃሪ ደገፋው፣ ተዋቸው አዳነ፣ ሞላ ሰጥአድርጌ ወዘተ እናንተም ጨምሩበት። ዘረገፉታ። በፊት ለኢትዮጵያ ያዥጎደጉዱላት የነበረውን ጥበብ አሁን እነርሱም እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ለራሳቸው፣ ለወገናቸው ለዐማራው ያፈሱት ጀመር። ልክ እንደ ዓባይ እንደ ወንዛቸው ያንቆረቁሩት ጀመር። ዋሸሁ እንዴ?
"…በፊት በፊት ዐማራ ነኝ ለማለት ዐማራው ይሳቀቅ፣ ያፍር፣ ይሽኮረመም ነበር። አሁን ደረቱን ነፍቶ ነው ዐማራ ነኝ የሚለው። ትግሬ ጁንታ ሲባል ቀውጢ ፈጥሮ ለምን ጁንታ እባላለሁ ብሎ እሪሪ ሲል ነበር። ዐማራው ጃውሳ ሲባል አዎ ጃውሳ ነኝ ምንአባህ ታመጣ ብሎ ድራሽ አባቱን አጠፋው። አዎ የአሁኑ ዐማራ ይለያል። የአሁኑ ዐማራ በጀግኖቹ ልጆቹ ምክንያት ቀና ብሎ፣ ኮራ ቀብረር ብሎ አንተ ማነህ? ሲባል ዐማራ ነኝ ብሎ በሙሉ ልቡ በድፍረት ይናገራል። ዐማራነት አብቧል። ዐማራነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ኩራት ወደ መሆን፣ ተስፋ ወደ መሆን ተሸጋግሯል። ራሳቸውን ደብቀው የነበሩ ሁላ አሁን ዐማራ ነኝ ሲሉ ቅሽሽ አይላቸውም። ጋዜጠኛ እና አርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው እና እነ አበበ በለው እንኳ ዕድሜ ለዐማራ ፋኖ በአደባባይ ዐማራ ነን ወደ ማለት ተሸጋግረዋል። ይሄ ታላቅ ድል ነው ለዐማራ።
"…ዐማራነት የታማኝነት፣ የፅናት፣ የአይበገሬነት፣ የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት፣ የአማኝነት፣ የሁሉን ቻይነት፣ የታጋሽነት፣ የጥንካሬ፣ የውበት፣ የድፍረት መገለጫ ሆኗል። ከዜሮ ተነሥቶ ሂሮ መሆን ከፈለክ ከዐማራ ተማር። ከባዶ እጅ ከመውዜር ከምንሽር ተነሥቶ ዲሽቃ ሞርታር እስከመታጠቅ፣ ከትንሽዬ ስብስብ ክፍለጦር እስከመመስረት መድረስ እንዲህ በቀላል የሚታይ አይደለም። ሌባ ነው። ዘራፊ ዘራፊ ቀማኛ ነው። ደመሰስነው፣ አጠፋነው የተባለው ዐማራ ይኸው በቀን አስሬ፣ አንዴ አዲስ አበባ፣ ሌላ ጊዜ ባህርዳር፣ ደግሞ ደሴ፣ ከዚያ ጎንደር ያሰባስባቸዋል። ምክንያቱም ዐማራ ነዋ።
"…እኔ የኦሮሞዎቹን ፔጅ እከታተላለሁ። የትግሬዎቹንም እንደዚያው። የዐማራው ትግል ትግሬዎቹን ማልቀሻ እንኳ ምክንያት ነው ያሳጣቸው። በትግራይ ፋኖ የለም፣ ሻአቢያ የለም። ቢኖርም ጫፍ ላይ ነው። ነገር ግን በትግራይ ሴቶች ይደፈራሉ፣ ይታገታሉ፣ ይሰወራሉ፣ ይገደላሉ። አሁን በትግራይ የህወሓት ፖለቲካ ብልሽትሽቱ ወጥቶባታል። ራበኝ፣ ጠማኝ፣ አትድፈሩን፣ አትግደሉን በሚሉ ሰልፈኞች ተሞልቷል። ለዐማራ እንኳን አጀንዳ ሊሰጡ በራሳቸው እጃቸው ላይ የፈነዳው አጀንዳ ናላቸውን አዙሮታል። የኦሮሞዎቹም እንደዚያው ነው። በፊት በፊት ኦሮሞዎቹ የሚያወሩት በኦሮሚኛ፣ የሚጽፉት በላቲን ነበር። አሁንስ። ኧረ የምን ላቲን። እህሳ የሚቀሽሩት በአማርኛ…👇ከታች ይቀጥላል✍✍✍
“…ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም። ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። …ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።ሕዝ 7፥ 25-27
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የጉድ ሀገር…
"…ኦቦ ቀጄላ መርዳሳ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሊቀ መንበር (ኦነግ) የኦሮሞ ቅኝ ገዢ ናት ብለው ከቅኝ ገዢዋ ኢትዮጵያ ነፃ ለመውጣት የሚታገለው ነፃ አውጪ ድርጅት ፕሬዘዳንት ነው። የኦነግ ማለት ነው።
"…ፀረ ኢትዮጵያ አቢይ ታዲያ ይሄን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፕሬዘዳን ካለበት በባትሪና በእግር ፈረስ አፈላልጎ አግኝቶ አምጥቶ የኢትዮጵያ ባሕል እና ስፖርት ፕሬዘዳንት አድርጎ ይሾመዋል። ባንዲራው የኦርቶዶክስ ነው አላምንበትም ብሎ በድፍረት የሚናገር ሰው አምጥቶ ይሾመዋል።
"…ይሄ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ነፃ ለማውጣት የሚታገል ሰው ነው እንግዲህ አሁን ብሪክስ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሰበሰበ የሚገኘው። 😂😂😂
• አይ ኦሮሞ አለ አቢይ…
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍"…ተረኛው ዝናብ ሆነ። እያስገመገመ መጣ። ሰውየው ላይ ዶፉን አወረደ። ለቀቀው። ሰውየውም ኮፍያውን እንደ ጥላ ተጠቅሞ፣ ልብሱን በላዩ ላይ አጣብቆ፣ እግሩን እንዳይወድቅ ተጠንቅቆ፣ አለፈው ልብሱን ሳያወልቅ። ማባራቱ አይቀርምና ዝናብዬ ሆዬም አባራ። ሰውየውም ልብሱን ሳያወልቅ መንገድ ጀመረ።
"…ተረኛ ልብስ አስወላቂ ፀሐይ ሆነች። እንደ ነፋስም በጉልበት፣ እንደ ዝናብም በማበስበስ፣ በዱላ ልብሱ እንደማይወልቅ ዐውቃ ተረድታለች። እናም በራሷ ጥበብ በዘዴ ልብሱን ማስወለቅ ጀመረች። መጀመሪያ በስሱ ፀሐይ ሙቀቷን ለቀቀች። ሰውየው ራሱን፣ ጭንቅላቱን ሲያልበው ኮፍያውን አወለቀ። ቀጥላም ሙቀ ን ከብርሃን ጋር በተን አድርጋ መርጨት ጀመረች። ሰውየው እየሞቀው መጣ። መጀመሪያ ካፖርቱን፣ ከዚያ ኮቱን፣ ከዚያ ሸሚዙን እያለ ቀስ በቀስ ማውለቅ ጀመረ። ፀሐይም ውድድሩን አሸነፈች። ሳትላተም፣ ሳታበሰብስ በስስ ሙቀት ብቻ በፍቅር ልብሱን አስወለቀች።
"…ዐማራ የወያኔንም የኦሮሞ ብልጽግናንም ልብስ አስወላለቅ አይቷል። ተምሯልም። ከሁሉም ትምህርት ወስዷል። አዎ እንደ ፀሐይ ነው መሆን ያለበት። ሙቀት እየረጨ በገዛ እጁ ጨርቁን ጥሎ እንዲወጣ ነው ማድረግ ያለበት። መከላከያ ከዐማራ ክልል ሟምቶ ይወጣል። ማድረግ ቢችል ዐማራን ከፋፍሎ መውጣት ነው። ወልቃይትን አበጣብጦ፣ ፀለምት ላይ ከትግሬ ጋር ጦርነት ከፍቶ፣ ራያን ከወሎ አባልቶ፣ አገው ሸንጎና ቅማንት አናክሶ፣ ግዙፉን ክልል አራት አምስት ቦታ ቆራርጦ እወጣለሁ ቢል ነው። ይሄም ለብልጽግና አያዋጣውም። ዐማራ እና ብርሌ አንድ ናቸው። ብርሌ ከነቃ ይሆናል ዕቃ? አይሆንም። ዐማራም እንደዚያ ነው አሁን።
"…የእኔን ተዉት እስቲ እናንተ መስክሩ፣ ተናገሩም። አጅሬ የኦሮሞ ብልፅግና በበበድኑ በብአዴን በኩል ለዐማራ ሰላም ማምጣት ይችላልን? እንደኔ እንደኔ ከዐማራ ፋኖ በቀር አይደለም ለዐማራ ለኢትዮጵያ ራሷ ሰላም የሚያመጣ ሌላ አንድም አካል የለም። አበደን የለም።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጼ ስለ ሰላም ነው የሚያወራው።
"…ሰላም እንዲህ ቀልድ መች ሆነችና? ትግሬው አበባው ታደሰ ዐማራን አንገት ሳያስደፋ ከምኔው እሱ አንገቱን ደፋ? አይ የዐማራ አምላክ። እጹብ ድንቅ እኮ ነው።
"…በቅርቡ ደግሞ ዐማራን አንገቱን ሊያስደፉት የተነሡት አሥራት ሴንቸሪ ሞል እና በላይነህ ክንዴ አንገታቸውን ይደፋሉ። የታቦት ሽያጭ እና የመተት ገንዘብ እና ሀብትም ድራሹ ይጠፋል። ሰከላ ያለው በሰንሰለት ታስሮ የሚማቅቀውም የአበባው ወንድም ከአጋንንት እስራት ይፈታል።
• ወደ ርዕሰ አንቀጹ እንሂድ።
“…ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 48፥22
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሁድ ምሽት በመረጃ ተለብዥን በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው መርሀ ግብራች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ልክ ከምሽቱ 2:15 ሲል ወደ እናንተ ይቀርባል።
~ በዛሬው ዝግጅታችን ፦
• የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር በውጭ ሀገር ባለ ሙሉ ሥልጣን ተወካይና የድጋፍ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የግንባሩንና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሰማዕታት ስም የተሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ ለሚድያዎች ያላኩትን ደብዳቤ እንመለከታለን።
• ሌላው በአዲስ አበባ ከተማ በዓድዋ ዜሮዜሮ አዳራሽ የሐሙስ ዕለቱን የዐማሮቹና የጄነራሎቹን ስብሰባ በተመለከተ እንወያያለን።
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=N_Q5irXlcSk
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
👆ካይኛው የቀጠለ✍✍✍ …እኛን ጨፍጭፈው አፈረሱን። መከላከያን ያፈረሱት እነዚህ ናቸው። ሕዝቡን የኦሮሞ ኃይል ሸኔ ሊወርህ መጣ ብለው መንገድ አዘግተው ጨፈጨፉን። ማጭድና ዱላ ይዞ ሕዝብ መንገድ ዘግቶ አስጨፈጨፉን። በመሬት ወደ ክልሉ መግባት ሲያቅተን በአንድ ሌሊት 18 ቦይንግ አውሮጵላን አዘዞ ላይ አሳርፌ ሠራዊቱን በአየር አመላልሰን ነው ያሸነፍናቸው። የጎንደርን አሮጌ ቅርስ ፋኖ ሊያወድመው መጥቶ ያደነው እኛ ነን። እንዲዚያ አርገን ነው የክልሉን መንግሥት ያተረፍነው። አሁን የክልሉ መንግሥት በዞንና በቀበሌ ደረጃ እግሩን የተከለው እኛ ተዋግተን ስለደመሰስንለት ነው። አሁን ፋኖ የሚባል ኃይል መሬት ላይ የለም። የሎጀስቲክ፣ የመረጃ ግኑኝነቱ ተበጣጥሷል። ከሕዝቡ ጋር ያለው ግኑኝነት ተቋርጧል። እርስ በእርሱ እንዳይተማመንም አድርገነዋል። አሁን አለ ቢባል ምሥራቅ ጎጃም ላይ አንድ 10፣ ጎንደር ሸዋም ላይ እዚያም እዚህም ያሉ ጥቂት፣ ወሎ ላይም ምሬ ጋር ያሉ አንድ 20 ቢቀሩ ነው። ስለዚህ የሌለን ፋኖ እንደ ዐማራ ተቆርቋሪ ተቋም የምትመለከቱት ካላችሁ እርማችሁን አውጡ። አይ ፋኖ አለ የምትሉ ከሆነ ግን እኛን ከክልሉ አውጡን። (ወደው አይሰቁ ሆነ እኮ)
"…የዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተበድያለሁ ካለ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ነው ማቅረብ ያለበት። ጥያቄው ትክክል ነው ጥያቄው የቀረበበት መንገድ ነው ስህተቱ። ጦርነት የሚያስመልሰው ጥያቄ የለም። በጦርነቱ እርስ በእርስ ተጨራርሰናል። የዚህ ጦርነት ምንጩ የውስጥ ችግር ነው። መጀመሪያ ዐማራ መቼ እርስ በእርሱ ይከባበራል? ዐማራ መሪዎቹን መቼ አክብሮ ያውቃል? በሕዝብ የተመረጡ መሪዎቹን እነ ዶር አምባቸውን የገደለው ማነው? ዐማራ መች ይደጋገፋል? መች እርስ በእርሱ ይረዳዳል? እንዲያውም እኛ እንደ ዐማራ ሰላማችንን ራሳችን አደፍርሰን ሌላውንም ኢትዮጵያዊ ሰላም አሳጥተነዋል። ለምሳሌ ተደጋግሞ ዐማራ ተከቧል ሲባል ይሰማል? እሺ ማን ከበበው? ማንም አልከበበውም። ፈጠራ ነው። ይልቅ መሪ ያጣሁት ለምንድነው ብለህ ቁጭ ብለህ ምከር። ተወያይ? ምን ሆኜ ነው? ምን ነክቶኝ ነው ብለህ ራስህን ጠይቅ።
"…አሁን ላይ ዐማራ ማለት በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ምንም የማያመጣ ጨዋ፣ ጉረኛ እና ብረት ወልዋይ ጠብአጫሪ ተደርገን ነው የተቆጠርነው። የሚረዳንም እናጣለን። ማነው የሞተውን ወያኔ ከመቃብር አውጥቶ ወደ ዐማራ እያመጣ ያለው? አንተ ራያን ያዝ እኔ ይሄን እይዛለሁ እያለ ወያኔን እያመጣ ያለው ማነው? ማነው አሁን ከግብፅ ጋር እየተነጋገረ ያለው? ፋኖ ነኝ የሚለው ኃይል አይደለም እንዴ? ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እየሠራ ያለውን ፋኖን እየደገፋችሁ ራያ ተይዟል ብትል ማን እንዲዋጋልህ ነው የምትፈልገው? የራያ ይገርማችኋል እኛ ባለን መረጃ በቅርቡ ፋኖ ቆቦን ያስይዘዋል። የዐማራ ክልል ኢኮኖሚው ደቅቋል፣ ግብር መሰብሰብ አልተቻለም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለሠራተኛ የሚከፈል ገንዘብ የለም። ቱሪስት የሚባል ከቆመ ዓመት ሊሞላ ነው። ሥራ አጥነቱ ተንሠራፍቷል። ክልሉ ወደ ኋላ እየቀረ ነው። ለዚህ ሁሉ ድክመቱ የራሳችሁ ነው ብለዋል ትግሬው የዐማራ ወኪል ጄነራል አበባው ታደሰ።
"…አዲስ አበባ አላስገባ አሉን ስትሉ ነበር። መጀመሪያ እስቲ በሰላም ግቡ። ባህርዳር በሰላም ሳትገባ ስለምን አዲስ አበባ ነው የምታወራው? ጎንደር በሰላም ገብቶ የሚወጣ አለ እንዴ? ተበታትነህ አታሸንፍም። ወደዳችሁም ጠላችሁም በዚህ ጦርነት እርስ በእርሳችን እየተበላላን ነው። ለጠላቶቻችን ምቹ ሁኔታ የፈጠርነው እኛው ዐማሮች ራሳችን ነን። የሚገርመው ይህ ሁሉ ሲሆን እንዴት እረፉ የሚል አንድ የሃይማኖት አባት ይጠፋል? እንዴት ምሁራን የሃገር ሽማግሌዎችስ ይጠፋሉ?
"…የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያላቸው፣ በሩቅ ሆነው የሚያቀጣጥሉ እኛን የመተቸት ሞራል የላቸውም። እቆረቆርለታለሁ የሚሉት ሕዝብ ካለ ሀገር ገብተው አብረው ነው መታገል ያለባቸው። የዐማራ ሕዝብ ችግር ላይ ነው ካሉ ወደ ሀገር ገብተው ከዐማራ ሕዝብ ጋር ችግሩን መካፈል ነው ያለባቸው እንጂ ውጪ ሀገር ሆነው የሀገር ውስጥ ችግር መፍታት አይችሉም። ፋኖ 4 ኪሎ እገባለሁ ሲል እውነት መስሎት ያላመነው ሰው አልነበረም። የብዙ ሕዝቦች ፍላጎት ባለበት ሀገር በጠመንጃ ሥልጣን መያዝ አይቻልም። መንግሥት የድርድር በሩን አልዘጋም። እንመካከር እያለ ነው። የምንግሥትን ጥሪ አክብሮ መደራደር ነው የሚበጀው። የመደራደሪያ ቦታ መምረጥ የመንግሥትና የፋኖ ጉዳይ ነው። ስለሱ እኛ ሓሳብ አንሰጥም። አያገባንም። ግን የሰላም በሩ አልተዘጋም። ሌላውን ደቡብ አፍሪካ፣ ሌላውን ዛንዚባር ተደራድሮ እኛን እንዴት ይላሉ ቦታ መምረጥ መብታቸው ነው። የፈለጉበት ቦታ መደራደር ይችላሉ። (የተደመሰሰ ኃይል ምን ድርድር ያስፈልገዋል? ለ10 ሰው የምን ድርድር ነው?) ብሎ የጠየቀ ሰው ግን አልነበረም። እናንተ ግን ብድግብሎ ከመሬት ተነሥቶ 4 ኪሎ እገባለሁ የሚለውን ወፈፌ ሁላ እረፍ በሉት። ከድርድሩ በፊት ግን በቅድሚያ አንድ ሁኑ በማለት የትግሬው ተወላጅ አበባው ታደሰ ዐማሮቹን ገስጸዋል። እነዚህ ውጭ ተቀምጠው ታብታብ አድርጉ የሚሉትን ታብታብ አታድርጉ፣ ሼርም፣ ላይክም አታድርጉ ብለዋል። (እኔ ነው?)
"…በመጨረሻም አቦይ አበባው ታደሰ ከምሳ ሰዓት በፊት በዛሬው ስብሰባ ችግር እንቀርፋለን፣ ችግሩን የመቅረፍ ሙሉ ሥልጣን አለኝ ሲል የነበረው ሶዬ ከምሳ በኋላ እነዚህን የተነሡ ሓሳቦችን እኔ ልፈታ አልችልም። ጥያቄአችሁን በተደራጀ መልኩ ሰንጄ ለመንግሥት እና ባሕርዳር ለሚዘጋጀው የሳለም ኮንፈረስ ላይ እናቀርብላችኋለን ብሎ አርፎታል። ጠዋት እኮ ሙሉ ሥልጣን አለኝ። እኔ በራሴ መወሰን እችላለሁ። እናንተ ብቻ ከምር ሃቅ ሃቋን፣ (ነጭነጯን ላለማለት ነው) ተናገሩ ብለህ እኮ ነበር ያለው ሰው ግን አልነበረም። ትግሬው አበባው ቀጠለ።
"…ፋኖ ከወያኔ ጋር የሚያደርገውን ደባ ማቆም አለበት።
"…በመጨረሻም ዛሬ የቀረቡ መፈታትም ያለባቸው የእናንተ ጥያቄዎች በማለት ጥያቄዎቹም ሲጠቃለሉ ይህን ይመስላሉ በማለት ዘርዝሮ አስቀመጠ።
፩ኛ፦ ሕገ መንግሥቱን በተመለከተ
፪ኛ፦ የይገባኛል ጥያቄን
፫ኛ፦ የአስተዳደር በደልን
፬ኛ፦ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ስላለ መገፋትን
፭ኛ፦ የመልማት ጥያቄን
፮ኛ፦ የፖለቲካ ግፍ የሚለው በጥያቄ መልክ መያዙን ነገሮ እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንፍታቸው ለሚለው ደግሞ 2 አማራጭ አቅርቧል። በክላሽ ነው በጠረጴዛ ዙሪያ? በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት፣ በድርድር፣ በሰላም ከሆነ እናንተ አመቻቹ እኔ ለመንግሥት አቀርባለሁ በማለት ንግግሩን ቋጭቷል።
"…የፊታችን ሰኞ ከየወረዳው የተመረጡ ካድሬዎች የሚገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ በባህርዳር ተዘጋጅቷል። ከሐሙሱ ስብሰባም ላይ 30 ሰዎች እንደሚሄዱም ተነግሯል። ስብሰባው ለ2 አበይት ጉዳዮች እንደሆነም ወፌ ጠርጥራለች። አንደኛው ብአዴንን ማፍረስ ሲሆን ብአዴንን አፍርሰው ክልሉን በመከላከያ አስተዳደር ስር ለማድረግ ነው ያሰቡት ብዬ እገምታለሁ ነው የምትል ወፌ። ትራንስፖርትና የምግብ ወጪውን የሴንቸሪ ሞል ባለቤት እነ አሥራት፣ እነ ካሳሁን ባይካ እና እነ በላይነህ ክንዴ እንደሚሸፍኑ አዘጋጁ አቶ ያያ አዲስ ባለሀብቶቹን እዚያው አነጋግሮ በጉባኤው ላይ አብሥሯል። ለወጪው ችግር የለም አሥሩ አለ፣ አሥሩ፣ በላይነህ አለ እንሸፍናለን ብለዋል በማለት ተናግሮ ጉባኤው በጭብጨባ አጽድቆታል።
• ባህርዳሮች እንደምን አላችሁ? የዐማራ ፋኖ በጎጃሞች እንደምን አላችሁ።
• እህሳ… እንዴት አያችሁት የዤኔራሉን ዲስኩር…?
መልካም…
"…ለምስጋና የምጠብቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል ማለት ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የሐሙሱ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ የዐማሮቹ ስብሰባን የመራው የትግራዩ ተወላጅ የአበባው ታደሰ የማጠቃለያ ንግግር ነው። ንግግሩን ነው የጻፍኩላችሁ።
"…በዐማራ ክልል ያለው ሕዝብ ይሄ በዚህ ስብሰባ ላይ የተባለው ነገር ስለማይደርሰው ዛሬ ምሽት በመረጃ ቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት በሚቀርበው መርሀ ግብሬ ላይ አቀርበዋለሁ። እስከዚያው ወደ አቦይ ታደሰ ልጅ ዲስኩር እንግባ…!
"…የመጨረሻውን የአቤክስን የመዝጊያ ዲስኩር ለማንበብ፣ አንብባችሁም አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?
"…ቀጥሎ መድረኩን የሚረከበው ይሄ በአባቱ ትግሬ በእናቱ የዋግ ኽምራ ተወላጅ ልጅ የሆነ ፀረ ዐማራ ከሃዲ ንግግር ነው። ወላጅ አባቱ በድርቅ ምክንያት ከትግራይ ተሰድዶ መጥቶ የሞተ ሰው አስከሬን በጨረታ በመገነዝ ይተዳደር የነበረው የአቶ ታደሰ ልጅ አበባው በፋኖ ላይ ዐማሮቹን ሰብስቦ ያስታወከውን ትውከት ነው የማቀርብላችሁ።
"…በዐማራ ጥላቻ ያበዱትን በበታችነት ስሜት የተጠቁትን ሁሉ ሰብስባ በዐማራው ላይ ዘፍዝፋ ዐማራውን እንዲበቀሉላት ካደረገቻቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነው አበባው። ሦስቱም ዐማሮችን ሰብስበው መድረኩን የመሩት ሙሉ ዐማራ ያለመሆናቸው ገራሚ ነው።
"…ጄነራል አበባው ታደሰ ወሎ፣ ጄነራል በላይ ስዩም፣ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ፣ ዛዲግ አብርሃ፣ ጌታቸው ረዳ፣ አቢይ አህመድ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ደመቀ መኮንን፣ ዋለልኝ መኮንን፣ በለጠ ሞላ፣ የሱፍ መሀመድ፣… ወዘተረፈ… ብዙ ታዋቂ ሰዎች ከወሎ መሆናቸው ይደንቀኛል።
"…ወሎ የንጉሥ ሚካኤል፣ የምሬ ወዳጆ፣ የእነ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባውም ሀገርም ናት።
"…ጌታቸው ረዳ ከትግራይ ጀነራሎች ጋር አቢይ አህመድ ስካይላይን ሆቴል አልጋ ይዞ ወጪያቸውን ሸፍኖ ወልቃይት እና ራያን ለመቆጣጠር የሚችሉበትን መንገድ እየመከሩ ነው ተብሏል። በድኑን ብአዴን አሜሪካ ልከው ራያን እንዳስያዙት ሁሉ አሁን ደግሞ በእነዚህ ፀረ ዐማራ ፖለቲካ ወለድ የአገው ሸንጎዎች አማካኝነት ሕዝቡን በስብሰባ አጀንዳ ወጥሮ ሰኔ 30 ን ሊያጨናብርበት የተዘጋጀም ይመስላል። ዐማራ ግን ነቅተህ ጠብቅ።
"…ለማንኛውም የዕለት 10 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዜዬ ላይ ስለሆንኩኝ የትናንቱን አባ እናፀዳቸዋል፣ እንደመስሳቸዋለን፣ የዛሬውን የፋኖና የመንግሥት አስታራቂ ሽማግሌ አበባው ታደሰን ዝብዘባና ንቀት በነገው ዕለት አቀርብላችኋለሁ።
• የነገሰው ይበለን።
የሐሙሱ ስብሰባ
ክፍል ፯
"…ከኮሚሽነር ዘላለም ቀጥሎ ከመድረክ የመናገር ዕድል የተሰጠው ለብርጋዴር ጀነራል በላይ ስዩም ሆነ። የአገው ሸንጎ ነው የሚባለው ጄነራሉ ጨለማ ፊቱን ይዞ ፀረ ዐማራ ትውከቱን ማስታወክ ጀመረ። "እንደማመጥ። አለ ብለን ነበር ያቆምነው። የዋግኽምራው የወያኔ ቅጥቅጥ በዐማራ ስም ዐማሮቹን ወደ ማሸማቀቁ ገባ።
"…እንደማመጥ። የሰከነ ውይይት ያስፈልጋል። እናንተ ምንድነው የምታወሩት? መከላከያ በዐማራ ክልል እያደረገ ያለው በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ነገር በተፈጸመ ጊዜ ያደረገውን ነው አሁን እያደረገ ያለው። ፋኖ መከላከያን አግዟል የሚባለውም ተረት ነው። ፋኖ እንዲያውም ትግሬዎቹ በሰሜን ዕዝ ላይ እንደፈጸሙት ነው በሠራዊታችን ላይ የፈጸሙት። አርደውናል፣ ከድተውናል፣ ሸኔ መጣልህ እየተባለ የተቀሰቀሰው ዐማራ እኮ ነው፣ በደጋ ዳሞት፣ በጅጋ፣ በሉማሜ፣ በፈረስ ቤት፣ በደምበጫ፣ በሰሜን ሸዋ በአረርቲ፣ በሸዋሮቢት፣ ጃውሳው ያረደን። ጫማችንን አውልቀን በተቀመጥንበት እኮ ነው በሰላም ሀገር ያረዱን። የጨፈጨፉን። ትግሬዎቹ እንዲያውም እንደ ጃውሳው አላደረጉንም። እነዚህ እርድ ነው ያደረጉን። እንደማመጥ።
"…እኛ ከትግራይ ጦርነት ወጥተን ዐማራ ክልል እስቲ አረፍ እንበል ብለን በተቀመጥንበት ያረደንን ፋኖ ነው የምታሞግሱት? ጦርነቱን የጀመሩን እኮ እነሱ ናቸው። መከላከያ በዐማራ ተከድቷል። ይሄ ከሕግ መንግሥቱ አሠራር ውጭ በጉልበት ነው 4ኪሎ የምገባው የሚለውን ሽፍታ ኃይል ለምን መከታችሁት ነው የምትሉን? እኛ ጣልቃ ባንገባ እኮ ክልሉ ዜሮ ሆኖ ነበር። እኛ ገብተን፣ ጃውሳውን አጽድተነው ነው ክልሉ አሁን 99% ከጃውሳ ነፃ የሆነው። ክልሉም ሥራ የጀመረው እኛ ገብተን ተዋግተን ስላሸነፍነው ነው። አሁን ጃውሳውን ድራሽ አባቱን አጥፍተነዋል። ብትንትኑን አውጥተነዋል። ጃውሳ አሁን እንዳለ አይቆጠርም። የለም። እኔ በበኩሌ መከላከያ ከዐማራ ክልል ይውጣ የሚለውን ነገር በደስታ ነው የምቀበለው። ምክንያቱም በዐማራ ክልል የምንገዳደለው ጠላት በሰጠን ሴራ ምክንያት ስለሆነ ብንወጣ ደስ ነው የሚለኝ።
"…ጃውሳ ማለት እኮ የባለሀብቶችን ገንዘብ የሚሠርቅ፣ ትምህርት ቤት የሚያወድም፣ ጤና ጣቢያ የሚዘርፍ፣ የሚያቃጥል አሸባሪ ነው። ይሄንን አሸባሪ ቡድን ነው እናንተ ጀግና፣ የአባቶቹ ልጅ ወዘተ እያላችሁ እያቆለጳጰሳችሁ የምትደግፉት። መጀመሪያ እንግባባ። እንግባባ አለና ሕዝቡን በሳቅ ያፈረሰ ንግግር አደረገ። "እኛ አሁን የተቸገርነው እኮ፣ ሕዝቡም የተቸገረው ፋኖ ተብዬው መግባባት አቅቶት እርስ በራሱ እየተጣላ እኛ መሃል እየገባን እየገላገልን ነው ያለነው። በቶሎ እናንተ ልጆቻችን ናቸው ካላችሁ በጊዜ ካላስታረቃችኋቸውና ከጫካ ወጥተው ወደ ሰላማዊ ህይወት ካልተመለሱ ሊተላለቁላችሁ ነው። በእነሱ መተላለቅ ሕዝቡ እንዳይጎዳ ይልቅ እናንተ አሁን ማድረግ ያለባችሁ በአስቸኳይ ሽማግሌ ተመርጦ እኛም ይቅር ብለናቸው በዕርቅ ነገሩን መዝጋት ነው። ሕዝቡ በልቡ በሳቅ ፈረሰ።
"…ቀጠለ የሸንጎው ጄነራል። ፋኖነት ፋብሪካ እያወደሙ፣ ልማት እያደናቀፉ፣ ባለሀብት ገንዘብ እየዘረፉ ነው እንዴ? እንዲህ ዓይነት ፋኖነት የለም። ሌላው የክልሉ አመራሮችም፣ የክልሉ ፖለቲከኞችም ተጠያቂዎች ናቸው። ፋኖ 4 ኪሎ እገባለሁ ስላለ ፋኖን ደግፈው ክልሉን ሽባ ያደረጉት አንደኛ ተጠያቂዎችም ናቸው። በአጠቃላይ አመራሩ ልፍስፍስ፣ ሽባ፣ አቅመቢስ ናቸው። አንዴ ከብልፅግና ጋር ሌላ ጊዜ ከፋኖ ጋር ሆነው የሚሠሩ ይበዛሉ። ተዉ እነዚህን ልጆች በጊዜ አርቋቸው ስንል፣ ጠመንጃ እየወለወሉ ነው በጊዜ መላ በሉ ስንል ራሳቸው ናቸው ጭራሽ እየደገፉ፣ እየሸለሙ እዚህ መከራ ውስጥ የከተቱን። አሁን ሕዝቡ ተሰቃየ፣ ሕዝባችን አለቀሰ፣ አሁንማ ፋኖ ነን ባዮቹ ሲመጡ ሕዝቡ " እነኚህ ዝንጀሮዎች መጡብን ኧረ ድረሱልን እያለ እየወተወተን ነው የተቸገርነው። እንጀራችንን ደፍተውት ስለሄዱ ልጆቻችንን ምን እናብላ እያሉን ነው። እስኪ ለገበሬ ሕዝባችን እዘኑለት። በዚህ የኑሮ ውድነት ያንን ሁሉ ጃዊሳ ሕዝቡ መግቦ ማኖርስ እንዴት ይቻላል? እናንተ እኮ እዚህ ያላችሁት በሙሉ ከዚያ ሸሽታችሁ የመጣችሁ ናችሁ። ልጆቻችሁ እዚያ የሉም። እናም እባካችሁ ሽማግሌ ሁኑና በእርቅ እንመልሳቸው አለ ጀነራሉ። ከሕዝቡ ግን "ደምስሰን አጥፍተናቸዋል ካልክ በኋላ የተደመሰሰውን ከየት አምጥተን ነው የምንመልሰው?" ብሎ የጠየቀ አልነበረም። ጃውሳ እርስ በእርሱ ከተፋጀ መከላከያ ምን አገባውና ነው እንዳይፋጁ መሃል ገብቶ ለማስታረቅ የሚሞክረው? ምንዓይነት መቀዣበር ነው የምታወራው ጄኔራሉ ያለ አንድም ሰው አልነበረም።
"…በላይ ስዩም ሲናገር ትግሬው አበባው ታደሰ እና ኮሚሽነር ዘላለም ስሙኒ አክለው በእፍረት ይንቆራጠጡ ነበር። ይህ የሆነው እንግዲህ በሻይ እረፍት ለአለቆቻቸው ደውለው አለቆቻቸው ጨዋታውን ቀይሩት። ዐማራውን አስበርግጉት። ፊት አትስጡት። ቆፍጠን በሉ ተብለው ስለሆነ ነው የሚሉት ወፎቼ። ከጀነራል በላይ ስዩም ቀጥሎ ዋና ሰብሳቢው ትግሬው የወዲ ታደሰ ልጅ አገው ሸንጎው የምርኮኛው የብርሃኑ ጁላ ምክትል በዐማራ ስም መድረኩን ተቀበለ።
"…10 ሺ ሰው እንዳነበበው እመለስና በዚህ ጀነራል ሓሳብ ላይ ሓሳብ እንድትሰጡ አደርግና የመጨረሻውን የትግሬውን የአበባው ታደሰን ድንፋታ አስነብባችኋለሁ። ወደ ንባቡ…
የሐሙሱ ስብሰባ
ክፍል ፮
"…ዶክተር አረጋ ተናግረው እንደጨረሱ አበባው ታደሰ ስብሰባችን ይቀጥላል አሁን ለሻይ እረፍት እንውጣ በማለት የጋለውን የስብሰባ ስሜት አቀዘቀዘው በማለት ነበር የቀደመውን የስብሰባ ሂደት ያቆምነው። አሁን ካቆምንበት እንቀጥላለን።
"…በሻይ እረፍቱ ወቅት እነ አበባው ለብቻቸው ዞር ብለው አየርም ትእዛዝም ተቀብለው ቆይተው ነው የተመለሱት። ከሻይ እረፍቱ በኋላ በቀጥታ ሰብሳቢ ተደርጎ የተሾመው የትግሬ ተወላጁ አበባው ታደሰ ዐማራ ሆኖ ንግግር ማድረግ ጀመረ። ጠዋት ስብሰባው ሲጀመር ዛሬና ነገ ለሁለት ቀን ነው አድምተን የምንወያየው ብሎ የነበረው አበባው አሁን ከሻይ እረፍቱ በኋላ ግን "በቃ ዛሬውኑ ጠቅልለን እንጨርሳለን" በማለት እንቅጩን ተናገረ። የዐማሮቹን፣ የነፍጠኞቹን ድብደባ አልቻለም ማለት ነው።
"…የጎንደር ፋኖዎች ባወጡት መግለጫ ላይ የጠቀሱት ቃል አለ። "የብልጽግና ካድሬዎች ያልቻሉትን የዐማራ ትግል በኢትዮጵያ ስም የተቋቋመው የመከላከያ ሠራዊት ጄኔራሎች ሊቀለብሱት አይችሉም።" ያሉት ቃል በትክክል የሚገለፀው በትናንቱ ስብሰባ ላይ ነበር። አንድ ጄኔራል እንዴት የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ካድሬ ይሆናል? ሀገርን የሚጠብቅ ሠራዊት እንዴት ግብር ከፍሎ በሚያስተዳድረው የሆዱ ጌታ የሆነ ሕዝብ ላይ ይዘምታል? የፈለገ ጥቅም ቢኖር፣ አልማዝ ዕንቁ ወርቅ ቢሰጠው እንዴት አንድ ጄኔራል የፖለቲካ ፓርቲን ሰዎች ወደ ንግግር ሂዱ፣ ተስማሙ፣ እኛ ድንበር እንጠብቅላችሁ፣ ገበሬው ይረስ፣ ነጋዴው ይነግድ፣ ተማሪም ይማር ወዘተ ብሎ ገለልተኛ በመሆን ጫና ይፈጥራል እንጂ በማያገባው በማይመለከተው በሕዝብ የመብት ጥያቄ ላይ ገብቶ እንደ ሚልሻ፣ እንደ ፖሊስ መንደር ለመንደር ይርመጠመጣል? ከቻለ የሕዝብን ድምፅ ሰምቶ አንባገነኑን ገልብጦ ሥልጣን ለሕዝብ ማለት ሲችል እንዴት በየከተማው ሕዝብን እየሰበሰበ ብልፅግናን ስሙት፣ ተከተሉት፣ ተገዙለትም እያለ የካድሬ ሥራ ሲሠራ ይውላል? ቱ ማፈሪያ ሁላ። ለነገሩ ለደንታው ነው።
"…ከሻይ መልስ ማጠቃለያ ይስጡ ተባለና በአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳይ ለተነሡ ጥያቄዎች ኮሚሽነር ዘላለም መልስ መስጠት ጀመረ። ለኮሚሽነሩ ከቀረቡት ወሳኝ ጥያቄዎች መካከል እኛ ዐማሮች በአዲስ አበባው የቤት ለቤት ፍተሻው እየተዘረፍን ነው። ፖሊሶች ወርቅ፣ ብር፣ የሞባይል ስልክ፣ ላፕቶፕ እየዘረፉን ነው። የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንኳ የላቸውም። የፈለጉትን ሰው ወስደው አስረው በገንዘብ ተደራድረው እየፈቱ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በዐማራ ክልል ሆኖ ሳለ፣ እንደገናም ተጠርጣሪ ተብለው የሚያዙት ዐማሮች እንኳ ወይ በክልላቸው፣ አልያም እዚሁ አዲስ አበባ መታሠር ሲገባቸው ለምንድነው አዋሽ አርባ፣ አፋር ክልል ወዘተ ሄደው የሚታሰሩት? ለምንድነው በባለሀብቶች መጋዘን የሚታሠሩት? እናንተ እንዲያውም ጫና አለባችሁ ለሚለው ጥያቄ ነበር መልስ ለመስጠት የተሰየመው።
"…ዐማራ ነኝ በዐማራ ኮታ ነው በፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ያለሁት የሚለው ኮሚሽነር ዘላለም የተነሡትን ጥያቄዎች በሙሉ አንዳቸውንም ሳያምን "በመሸምጠጥ" መልስ መስጠት ጀመረ። "በፍጹም ጥያቄአችሁ ትክክል አይደለም። በዐማራነቱ ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ አንድም ከአዲስ አበባ ውጪ የታሰረ ዐማራ የለም። እርግጥ ነው በዓመት ከ33 በላይ ኢቨንቶች አሉ። ለእነዚህ ዝግጅቶች እንደ መንግሥትም የወረደ እኛም ተነጋግረንበትና ያመንበት ነገር አለ። ይኸውም መታወቂያ የሌላቸው ዐማሮችም ሆኑ፣ ኦሮሞ ትግሬ ደቡብ፣ ከጃውሳውም፣ ከሸኔም ጋር ግኑኝነት ያላቸው ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በዚያውም የሀገር ኢሜጅ ያበላሻሉ፣ (በቆሻሻነታቸው) ችግርም ይፈጥራሉ ተብሎ ስለሚገመት መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች ይታሰሩ፣ ስብሰባው ባለቀ ጊዜ ግን ይለቀቁ የሚል አካሄድ ስላለ መታወቂያ የሌላቸውን በጊዜአዊ የማቆያ ጣቢያ አቆይተን እንለቃለን እንጂ አዋሽ አርባ የምንልከው የለም።
"…ይሄ በፍተሻ ወቅት ፖሊስ ይዘርፋል የምትሉት ግን ልክ አይደለም። ይሄ ተቋሙን ማጠልሸት ነው። አንድ ሀገር ያለ ተቋም አይኖርም። እናም ልክ አይደለም። ጫና አለባችሁ ላላችሁት ምንም ዓይነት ጫና የለብንም። እኔ በምመራው የፖሊስ ተቋም ማንም አያዘኝም። ይሄ ድብደባ፣ ዘረፋ፣ ጥፍር ነቀላ፣ ቶርቸር የምትሉት ነገርም አንዲት ነገር የለም። ከፈለጋችሁ ኮሚቴ አቋቁሙና ወስጄ አስጎበኛችኋለሁ። እንዲህ ዓይነት ነገር ከለውጡ በኋላ ቀርቷል። በፍጹም እንዲህ ዓይነት የጠላት ወሬ እንዳታምኑ ወዘተ በማለት ንግግሩን ጨረሰ። ዐማራውን ለማስፈራራት ጠርተውት ሲያበቁ መልሰው ራሳቸው ተንበጫብጨው አረፉት። አይ ፋኖ የሥራህን ይስጥህ።
"…ከኮሚሽነር ዘላለም ቀጥሎ ከመድረክ የመናገር ዕድል የተሰጠው ለብርጋዴር ጀነራል በላይ ስዩም ሆነ። የአገው ሸንጎ ነው የሚባለው ጄነራሉ ጨለማ ፊቱን ይዞ ፀረ ዐማራ ትውከቱን ማስታወክ ጀመረ። "እንደማመጥ። የሰከነ ውይይት ያስፈልጋል። እናንተ ምንድነው የምታወሩት? በማለት ለምቦጩንና የሚያስፈራ ቀፋፊ ፊቱን በመዘፍዘፍ ነው የጀመረው። እንደማመጥ…
"…ይሄንኛውን ልጥፍ 10 ሺ ሰው አንብቦ በኮሚሽነር ዜድ ላይ ሓሳብ ከሰጠን በኋላ ወደ ቀጣዩ ወደ ጄኑ ሓሳብ እንመጣለን። ኢቀጥላል…
መልካም…
"…14 ሺ ሰው አንብቦታል። ወደ ቀጣዩ ውይይት ከመሸጋገራችን በፊት ቅድሚያ የዶር አረጋ ይርዳውን አስተያየት እና ጥያቄ እንዴት እንዳገኛችሁት አካፍሉን እስቲ? እንዴት አገኛችሁት…?
• ጥቂት ሓሳብ ስጡበትና ወደ ቀጣዩ ውይይት እንሸጋገራለን።
መልካም…
"…ዘወትር የክርስቶስ ኢየሱስን የትንሣኤውን ዐዋጅ ያውጅ ዘንድ የምንጠብቀው አንድ ሺ ሰው ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ዛሬም የተለየ ራሱን የቻለ ርዕሰ አንቀጽ አይኖረንም። የሚኖረን ትናንት ያቋረጥነውን የዓድዋ ዜሮዜሮ የጀነራሎቹና የዐማራ ወኪል ነን ባዮቹን ፍጥጫ በተመለከተ የጀመርኩትን ወደ እናንተ በማድረስ ነው። ዛሬም እዚያው ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ነው የምንውለው።
"…ይሄንን የስብሰባ ድምጽ ቀርጸው በማውጣት የላኩልኝን ባለሀብት እያመሰገንኩ ነገር ግን ባለሀብቱ የጠንቋይ ልጅ ጠንቋይ ስለሆኑ የጭቃ ጅራፌ አይዘላቸውም። ለጠንቋይ ምህረት የለኝም። ቀድሞውኑ መረጃውን ስጠኝ አላልኩም። ቢሆንም ግን እኔ መረጃውን ሰጥቼ እንዴት እሰደባለሁ ማለት አይቻልም። መረጃው ሌላ ነውርህ ሌላ። መረጃውን እንድትሰጥ ያደረገህ የንፃሃኑ የዐማራ ልጆች ደም ነው። አንተ ቤተኛ ስለሆንክ እንደማትፈተሽ አድርጎ አስገብቶ ለእኔ አሠራህ። አለቀ ይሄው ነው። ጠንቋያም። ዝጋ። 😂
"…ትናንት ያቆምነው የወሎው የወይዘሮ ስሂን ትምህርት ቤት ፈርጥ የወልድያው የሼህ አላሙዲን የልጅነት ጓደኛ እና የሥራ ባልደረባ ኢንጅነር ዶክተር አረጋ ይርዳው የመናገር ዕድል አግኝተው ለመናገር ጉሮሮአቸውን እንደጠራረጉ ነበር አይደል ያቆምነው? ዛሬ ከዚያው ካቆምንበት እንጀምራለን።
"…እህሳ ጃዊሳ ዝግጁ ናችሁ…?
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ነው። ቃለ መጠይቁ በአማርኛ ነው። ማን ጫነባቸው? እንጃ አባታቸው? ወደው አይስቁ አሉ። ጠላቴ የሚሉትን ዐማራ በአማርኛ ያሙታል። እንዲያውም ሰሞኑን ትግሬዎቹ እነ ስታሊን፣ እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ የኦሮሞ አክቲቪስቶች የእስክንድር ነጋ እና የሻለቃ መከታው ደጋፊ ሆነው ተከስተው ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ነው። ሐሙስ ዕለት እነ አበባው ታደሰ ፋኖ እርስ በእርስ እየተዋጋ ነው የሚለውን ሟርት ዛሬ መከታውና አሰግድ በጦርነት ተጋጠሙ ብለው ጮቤ እስከመርገጥ ደርሰዋል። እስክንድር እንዲያሸንፍ ሱባኤ ሁላ ይዘዋል። በሳቅ ሊገድሉኝ ነው።
"…እነ የኦነግ አክቲቪስቶች ትኩረት አጥተው በስቃይ ላይ ናቸው። ፋኖ መከላከያን ማረከ ሲባል በማግስቱ እንደምንም የመንደር ጎረምሳ ሰብስበው መከላከያን ማረክን ብለው ይለጥፋሉ። በአማርኛ። የዐማራ አድማ ብተና እና የዐማራ ሚልሻ ወደ ፋኖ ተቀላቀለ ሲባል መንጋ የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና አረቄ የጨረሰው የኦሮሞ ሚልሻ አሰልፈው ኦነግን ተቀላቀሉ ይላሉ። ስለ ፋኖ በተወራ ቁጥር ኦነግ ሸኔ በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ይላሉ። አቢይ ወለጋ ላይ ተጸዳድቶ ሲወጣ ተደብቀው አገኘሁ ተሻገር ባህርዳር ሲሄድ ፋኖ የት አለ ብለው እሪሪ ይላሉ። ማፈሪያ ሁላ።
"…አዎ ዐማራ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን የለበትም። እገሌ ታሰረ፣ እገሌ ተፈታ ብሎ ዋይ ዋይ ማለት የለበትም። በሆነ ቦታ የተጣሉ ፋኖዎችን አጀንዳ አድርጎ አጋግሎ ማቅረብም ልክ አይደለም። በዐማራ ጉዳይ የጥል ሰበዝ መዝዛችሁ አጀንዳ ለማድረግ የምትጥሩ የዐማራ ልጆች ብትጠነቀቁ መልካም ነው። የከፋ ደረጃ የደረሰ እና አደጋ የሚፈጥር፣ ሕዝብ ጣልቃ ገብቶ እንዲፈታው የሚደረግ ጉዳይና ችግር ካልገጠመህ በቀር ችግሩን ሁሉ አደባባይ አታውጣው። በውስጥ ጨርሰው። የራስ እግርና እግር በሚጋጭበት ምድር ላይ ሁለት ፋኖዎች ክፉ ደግ ተነጋገሩ ብሎ ነገር ማጋጋል ደግ አይደለም። ይሄ ሊታረም ይገባል። የሆነው ሆኖ ፋኖ ልዩነቱን በንግግር፣ በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በጥፊ በካልቾ፣ በድንጋይ በክትክታም ቢሆን ፈትቶ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የለም። ከዚህ ካለፈም በጥይት ተፈታትሾ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የለም። አሁን የዐማራ ትግል የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት፣ የብልፅግና፣ የወያኔ አክቲቪስቶች እና የብአዴን ካድሬዎች የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብለው ለሀጫቸውን እያዝረከረኩ በመጎምጀት ከሚጠባበቁት በቀር ወፍ የለም። አይቆምም።
"…ገዱ አንዳርጋቸው፣ ይልቃል ጌትነት ስለ ዐማራ ጉዳይ ከማሲንጋ ጋር ተነጋገሩ። ተወያዩ እሱ አጀንዳህ ሊሆን አይገባም። ገዱ አንዳርጋቸውም፣ ይልቃል ጌትነትም ለደንታቸው ነው። የፋኖ እንቅፋት ሆኖ የከረመ ሁላ አሁን ፋኖ ሊያሸንፍ ሲል ግርር ብሎ መጥቶ ከፊት ልሰለፍ ቢል ማን ይሰማዋል? ብልፅግና ፕላን ቢ፣ ፕላን ሲ ብሎ ላስቀመጠው አጀንዳ መፍትሄው ያለው መሬት ላይ፣ ምድር ላይ ባሉት ጀግኖች እጅ እንጂ በቦሌ አየር መንገድ ሰተት ብለው ወጥተው ሲያበቁ አሁን የዐማራ ጠበቃ ነን በሚሉ ግለሰቦች አይደለም። አጀንዳ አታድርጉት። ጉልበት ሲኖርህ ወዳጅህ ይበዛል። ከዋርካ ስር መጠለል የማይፈልግ አለ እንዴ? ጨፈቃ ሆነህ ማን ይቀርብሃል? እንቦጭ፣ እንባጮም ሆነህ ማን ይጠጋሃል? ግዘፍ፣ ዝግባ፣ ዋርካ ሁን ያኔ አይደለም አማሪካ አውሮጳና አፍሪካም ከስርህ ይደፋሉ።
"…የወያኔም አጀንዳ ግንቦት 30 አለፈ። ሰኔ 30ም ደረሰ። ዐማራም ግን ሥራ ላይ ነው። አጀንዳ መቀበል ድሮ ቀርቷል። ቢያንስ ቢያንስ ዐማራው ቢፈዝ እንኳ እኔ የሐረርጌው መራታ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ አልፈዝም። የአየሩን አጀንዳ ሰጪ ሁላ ራሴ አጀንዳ እሆነዋለሁ። እነ ጂጂን፣ ግንቦቴና ግንባሩን ብቅ እያልኩ እንደ ጠበል አስለፈልፋቸዋለሁ። መሬት ላይ ሁከት ለመፍጠር የተዘጋጁትን አየር ላይ አጋንንቶች ራሴ አጀንዳ ሆኜ ስለ እኔ ብቻ እንዲያወሩ አድርጌ አዘገያቸዋለሁ። ዘመድኩን ጋላ ነው፣ ዘመድኩን ቆቱ ነው። ዘመድኩን ሌባ ነው። ዘመድኩን አጭበርባሪ ነው። ዘመድኩን ከዐማራ ትግል ይውጣልን ወዘተ ብለው ቀንና ማታ ሌሊቱን ሁሉ እንዲለፈልፉ፣ ስሜን እያነሱ ከመሬቱ ትግል እጃቸውን እንዲያነሱ አደርጋቸዋለሁ። ዐማራ እስኪያሸንፍ የአየሩን የዐማራ አጋንንት እኔ ጠርንፌ ሽባ አድርጌ እይዘዋለሁ። ጠንካራ አጀንዳ ከፈጠሩ በየሳምንቱ ማክሰኞ ማክሰኞ፣ ጠንካራ አጀንዳ ካልፈጠሩ ደግሞ በ15 ቀን አንድ ቀን ብቅ እያልኩ በቲክቶክ መንደር ቀውጬው አረጋግቼአቸው እመለሳለሁ። እናም ዐማራ በዚህ በኩል እንዳያስብ። በእኔ በወዳጁ ይኩራ።
"…እኔ ለዐማራ ጥብቅና የምቆመው ወድጄና ፈቅጄ ነው። ግንቦቴዎችን፣ ግንባሩና ሠራዊቱ ነን ባዮችን፣ ሂዊና ኦኔ፣ ብልፄም እኔን ቢሰድቡኝ ነው። ቢወርዱብኝ ነው። ሌላ ምንም አቅም የላቸውም። ሌባ ሁላ። ዐማራ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን በጭራሽ የለበትም።
"…ብልጽግና በቀይ ቦኔት ያልቻለውን የዐማራ ፋኖ ነጭ ሻሽ በጠመጠሙ ቄሶች፣ ነጭ ቆብ ባጠለቁ ሼሆች፣ ነጭ ጺም ሪዝ ነጭ ሽበት በወረራችው ሽማግሌዎች አይፈታም። አይንበረከክም። ተወደደም፣ ተጠላም ብልፅግና ለፋኖ እጁን ይሰጣል። እመኑኝ ፋኖ ያሸንፋል። ዐማራ ወደ ሥልጣን ይመጣል።
• ይህን አልክ ብሎ የሚከፋ ካለ በአናትህ ተተከል በሉልኝ። አደራ አደራ እንዳትረሱት ንገሩልኝ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ፣
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም…
"…ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አንድ ሺ ሰው ከአንድ ሺም አልፏል። ስለእውነት በቴሌግራም መንደር የእኔ ትክክለኛ ወዳጆች ከአንድ ሺ ወይም ከሁለት ሺ አይበልጡም። የእኔ ትክክለኛ ወዳጆች የጋራ አምላካችንን ስሙን ጠርተው እግዚአብሔር ይመስገን ብለው መልስ የሚሰጡኝ ብቻ ናቸው። ቁጥራቸው ራሱ የተመጠነ ነው። እኔ እነዚህን ወዳጆቼን ይዤ ተአምር ሁሉ መሥራት እችላለሁ።
"…አንድ ሺ አመስጋኝ እስኪሞላ ድረስ ቁጭ ብዬ ስማቸውን እያነበብኩ አብሬ አመሰግናለሁ። ከምስጋና ሌላ ሌላ አጀንዳ የሚጽፈውን እያጸዳሁ አብሬ እቆያለሁ። አሁን አሁንማ አመስጋኞቹን ከምር በስም ሁላ እያወቅኳቸው እየመጣሁ ነው። የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለቱን አመስጋኞች ❤️❤️❤️ በልብ ቅርጽ ፍቅሬን የምገልጽላቸውማ እስኪነጋ ድረስ ነው የሚናፍቁኝ። ሁሉንም የቤተሰብ ያህል እየቆጠርኳቸው ነው። 100 ሺ ሰው ምስጋናውን አይቶት አመስጋኙ ግን 1ሺ ሲሆን ድንቅ ነው የሚለኝ። አዲስ አበባ ችግር እንዳለ ቢገባኝም ሌላው ግን አይገባኝም። አንዳንዴ የማውቃቸው የለመድኳቸው ስሞች ሳያመሰግኑ ሲቀሩ ሳይ ምንሆነው ይሆን እስከማለት ሁላ እደርሳለሁ። ማርያምን እውነቴን ነው።
"…ከምስጋናው ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ምንድነው? አዎ ወደ ርዕሰ አንቀጻችን። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ አጀንዳን ይመለከታል። አጀንዳ። ቀኝ ትከሻዬን ሲሸክከኝ የምጽፈውን ታውቃላችሁ አይደል? እሱኛውን አጻጻፍ ተጠቅሜ ነው ዛሬ የምጽፍላችሁ። እህሳ እናንተስ ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመጨመር ዝግጁ ናችሁ?
• አንድ 100 ያህል ሰው እስቲ ዝግጁ ነነ ይበል። ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
ያልገባኝ ነገር…
"…የዘንዶው አማካሪ ዳንኤል ክብረት ፋኖ እንደ ዐሞሌ ጨው ሟምቶ ጠፍቷል አላለም ነበር ወይ?
"…ትግሬው አበባው ታደሰ፣ በላይ ስዩምም ፋኖ ጠፍቷል። ደምስሰነዋል። የቀሩት ጎጃም ላይ አንድ 10፣ ሸዋም አንድ 10፣ ወሎ አንድ 20 ፍሬ ነው። ብልፅግና ተመልሶ እግር ተክሏል፣ እንዲያውም እነ ፋኖ እርስ በእርሳቸው እየተጣሉ እንዳይገዳደሉ እኛ መሃል ገብተን እየጠበቅን ነው።
"…አረጋ ከበደም የክልሉን 97% ከፋኖ ነፃ አውጥተን መደበኛ አስተዳደሩን መልሰናል አላለም ወይ። ፋኖ እጅ ሰጥቷል፣ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሷል አላሉም ወይ…?
"…ታዲያ ዛሬ ጋሽ ሽጉጤን ጠጥቼ እንደ አጼ ቴዎድሮስ እዚህችው ፍግም ብዬ እሞታለሁ ባዩ ጋሽ ኡዞ አገኘሁ ተሻገር እና ቀንድ አውጣው ከየት አምጥተው ነው ይሄን ሁሉ አለመቻል የሚያወሩት? የዐማራ ተማሪዎች ተምረውስ የት ሊደርሱ? ታፍነው፣ ተደብድበው፣ አዲስ አበባ መግባት አትችሉም ተብለው፣ በጅምላ ረፍርፈው የጣሏቸውን የት ረስተው ነው ዛሬ ስለተማሪዎች መጨነቅ የጀመሩት? አይ ኡዞ… ታስቁኛለሽ እኮ።
"…በድሮን ጨፍጭፈህ፣ ሠራዊት አዝምተህ አውድመህ፣ አርደህ፣ ገድለህ ያላሸነፍከውን፣ ያላስቆምከውን የዐማራ ትግል "የትኛው የሃይማኖት አባት መጥቶ ነው የሚያስቆምልህ? በጥፊ የተጠናገሩት አባት? ወይስ የታረዱት የሃይማኖት አባቶች ናቸው ፋኖ ጋር ሄደው የሚያስታርቁህ? የምን እርቅስ ነው? የምን ድርድር? ከተደመሰሰ ፋኖ ጋር የምን ድርድር ነው?
"…በቃ አትዘብዝቡ። አልቻላችሁም እናም እጅ ስጡ፣ በፈቃደኝነትም ለፍርድ ቅረቡ። ህወሓትን አስገብተን፣ ወያኔን አስመጥተን ዐማራን ዳግም እናንበረክከዋለንም ብላችሁም አታስቡ። አበደን ተሸንፋችኋል። ስልጣኑን ለዐማራ ፋኖ ልቀቁ። ከዚያ ውጪ ሰላም ኢንጂሩ።
• ማኔ ቴቄል ፋሬስ …
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ሰላም የመንፈስ ፍሬ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ላይ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።” ገላ 5፥22 በማለት ነው ሰላምን የሚገልጻት። ሰላም የመንፈሳውያን፣ የደስተኞች፣ ፍቅር የበዛላቸው፣ ትእግስተኞች፣ በቸርነት በበጎነት፣ እምነት ያላቸው ሰዎች በየውሃትና ራስን በመግዛት ልምምድ ውስጥ ያሉ ሰዎች ገንዘብ የሚያደርጓት ናት። እነዚህ አይደለም ምድራዊ ሰማያዊ መንግሥቱን ወራሾች ናቸው።
"…ዓለም ዛሬ ሰላም የሚለውን ቃል የሚያውቀው በጽሑፍ ብቻ ነው። በአመጸኞች አንደበት ሰላም ስትጠራ ራሷ ሰላም ይገርማታል። ይደንቃታልም። ሰላም የሚገኘው በመንፈስ ፍሬ ውስጥ ለተካተቱ ብቻ ነው። ሰላም በዜና ስለተነገረ፣ ወርክሾፕ፣ ስብሰባ፣ ሲምፖዚየም ስለበዛ አትመጣም። አትገኝምም። ሰላምን በሥጋ ሥራ ልምምድ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞችም ሆኖ ሃይማኖተኞች ሲፈነዱ ይውሉአታል እንጂ፣ ሲፈርጡ ይከርሟታል እንጂ አያገኟትም። ሰላም ልክ እንደ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አትሸወድም። አትፎገርምም። ሰላም መሃሙድ ስለዘመራት፣ ይልማ ሃይሉ ስለዘመራት፣ በቅዳሴና በአዛን ስለወተወቷት አትመጣም። በሥጋ ሥራ ውስጥ ያለ ሰላምን አያገኛትም። ይሄንንን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይገልጠዋል።
"…የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው። እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ገላ 5፥ 19-21
"…እና ይሄ ዲምላይታም ሜካፓም ወሴ ዝሙታም መንግሥት ነው ሰላምን የሚያመጣው? ርኩሰቱ ምድሪቱን የሞላው፣ መዳራቱ ጌጥ እስኪሆን የሚታየው፣ ካገኘው ወንድ ጋር የሚተሻሽው ወሴ፣ የጣኦት አምልኮን የብሔራዊ በዓል ለማድረግ በጀት የመደበ፣ ሟርተኛ፣ የለ ጥል ሀገር መምራት የማይችል፣ ክርክሩ አዝግ፣ 40 ቢልየን ችግኝ በሁለት ሺ ገበሬ በሦስት ቀን እተክላለሁ የሚል ቡትርፍ ቀዳዳ፣ ቅንዓቱ ለከት የሌለው፣ ቁጣው በማረድ የሚገለጽ፣ አድመኛ፣ መለያየትን በሕገ መንግሥት አንቀጽ ሰጥቶት የሚፎገላ፣ ምንፍቅና ሃይማኖቱ የሆነ፣ ምቀኛ፣ መግደል እንጀራው የሆነ፣ የሰካራም ስብስብ እየዘፈነ፣ እያቅራራ፣ እየሸለለ ሰላም ሰላም ቢል ማን ይሰማዋል? ማንም።
"…አዲስ አበባም ካድሬ ሰብስበህ፣ የፓርቲህን አባላት ሰብስበህ፣ መክረህ፣ ዘክረህ፣ በሕዝብ የተጠሉ፣ ከሕዝብ ተደብቀው ሸሽተው አዲስ አበባ የተሸጎጡ ጉደኞችን እየቀለብክ ሰብስበህ ሰላም ሰላም ብትል አልተገናኝቶም። ሕዝብ ሁሌ ሾርት ሚሞሪያም አይሆንም። ሕዝብን አንዴ፣ ሁለት ሦስቴ ግፋ ቢል እስከ አስር ጊዜ ልታታልለው ትችላለህ። እሱንም በመሃል እንደ ወያኔ አስቀያሽ አጀንዳ እያመጣህ ማለት ነው። ቅንጅቶችን ዘብጥያ ወርውረህ በማግሥቱ ዓባይን ልገድብ ነው ብለህ ሕዝቡን ከዓባይና ከቅንጅት ዓባይ ይበልጣል ብሎ እንዲረሳቸው እያደረግክ ከሆነ ነው እንጂ እንደ አቢይ አሕመድ ሺ ሰው ጨፍጭፈህ ስታበቃ አረንጓዴ አሻራ፣ ቀይ ባሕር፣ ሕንድ ውቅያኖስ ብትል ማንም አይሰማህም። ገተት።
"…ሐሙስ ዕለት አዲስ አበባ በትግሬው አበባው ታደሰ የሰበሰብከውን ካድሬ ሰኞ ዕለት ባህርዳር ድረስ አረቄያሙን አገኘሁ ተሻገርን ይዘህ ሄደህ ስለ ሰላም ስትለፋደድ ብትውል ወፍ የለም። ሰካራም እንኳን ሰላም ቤት አይሠራም። ቤት ቢሠራ እንኳን በጊዜ አይገባም። መለስ ዜናዊን ሲያመልክ ያረጀን ሰውዬ፣ ለኃይለማርያም ደሳለኝ አሽከር፣ ለአቢይ አህመድ ገረድ የሆነ ሰውዬ ስለ ሰላም አውርቶ የዐማራ ሕዝብ አንጀት ሲላወስ እግዚአብሔር ያሳያችሁ። በድኑ ብአዴን መገረድ እንጂ ስለሰላም የትአባቱ ያውቅና ነው ሰላም ሰላም የሚለው? ሰላምን የሚያውቃት አርነት የወጣ፣ ነፃ የሆነ ሕዝብ ብቻ ነው። ሰላም በወሬ አይገኝም።
"…ባህርዳር ዙሪያ ጦርነት፣ ጎጃምና ደቡብ ጎንደር የቀለጠ ውጊያ ላይ ሆኖ አበባው ታደሰ አንገቱን ደፍቶ የሚያደርገው አጥቶ፣ አረጋ ከበደ ማድያቱ ጆሮ ግንዱን አልፎ፣ ቡቶክስ በሜካፕ ተቀብቶም ከ30 ደቂቃ በኋላ አጽመ ርኩሳን መስሎ እንደ ሬሳ፣ እንደ አስከሬን በድን ሆኖ የሚመራው ክልል የምን ሰላም ነው የሚሰብከው? ሰላም በወሬ አይመጣም። አክቲቪስቶች ስለ አክተቨሰቱ፣ ጋዜጠኞች ዶክመንተሪ ስለሠሩ ሰላም የለም። ሰላም ሰላማውያን ሰዎችን ነው የምትፈልገው። ሰላምን የሚያመጧት ሰላማውያን ብቻ ናቸው።
"…ለምሳሌ ትግሬን ተመልከት። ፕሪቶሪያ ሰላምን፣ ናይሮቤ ሰላምን አላመጣለትም። ውጊያ ያቆመው ጥይትና ተዋጊ ስለጨረሰ ነው። ቀለብ ስለጨረሰ ነው። ስንቅና ትጥቅ ሳይኖረው እንዴት ይዋጋል? አሁን ትንሽ ስንቅ፣ ጥቂት ቀለብም፣ ኦሮሙማም አግዝህሃለሁ ስላለው ጦርነት እየጎሰመ ነው። ግን አያዋጣውም። ኦሮሙማን አምኖ ወደ ጦርነት መግባት ትግሬን ከምድረ ገጽ ቢያጠፋው ነው እንጂ ምንም አይጠቅመውም። ትግሬ ሰላሙን ያጣው በገዛ ልጁ በወያኔ አማካኝነት ነው። ወያኔ እስካለች አይደለም ትግሬ ኢትዮጵያም፣ አይደለም ኢትዮጵያ ምሥራቅ አፍሪካ ሰላም አያገኝም። ወያኔ አእምሮው ከዲሽቃና ከባዙቃ ጥይት የተሠራ ነው። ስለዚህ ወያኔ እያለ ሰላም የለም።
"…ብአዴን የወያኔ ልጅ ነው። ኦህዴድ የወያኔ ልጅ ነው። ኦነግም እንደዚያው፣ ወላጅ አባትን ፀረ ሰላም እያልነው ልጆች ሰላማውያን ሊሆኑ አይችሉም። ልጆች ሁሉን የተማሩት ከወላጃቸው ከወያኔ ነው። ወያኔ ከሃዲ ነው። ብአዴንና ኦህዴድ ሲክዱህ አትደነቅ። ለምን ትደነቃለህ? ልጅ አባቱን ነው የሚመስለው። መርከብና አውሮጵላን ኮንዶሚንየም በቁሙ የሠረቀ ወያኔን ረግመህ ኦህዴድን በሌብነት፣ ብአዴንን በሰሊጥ ስርቆት ለምን ታማዋለህ? የሌባ ልጅ ሌባ ነው።
"…ወያኔ ያለ ጦርነት በሕይወት መኖር አትችልም። የወያኔ ልጆችም እንደዚያው። አሁን ለብልጽግና ሀገር በሙሉ ሰላም አድርገህ ብትሰጠው ብልፅግና በሰላም ሀገር፣ ሰላማዊ ሕዝብን መምራት፣ ማስተዳደር አይችልም። ብልፅግናም የወያኔ ልጅ ነውና ያለ ቀውስ መኖር አይችልም። በሌባ ታጅቦ፣ በዘራፊ ታጅቦ፣ በገዳይ፣ በአጋች ታጅቦ ነው ብልጽግና መኖር የሚችለው። ፀብ ያለሽ በዳቦን ሰላም ብትሰብከው፣ ብትነግረውም ሰላምን አያውቃትም። የሚሞትለት የደሀ ልጅ እስካለ ድረስ ደንታውም አይደለም። መፍትሄው ሰላምን የመንፈስ ፍሬ ልጆች ዐማሮቹ በፍቅር ማምጣት አለባቸው። በፀሐይ ሙቀት አይነት ፍቅር ሰላምን ለሕዝቡ ማምጣት አለባቸው።
"…አንድ ሰው ነው አሉ። ኮፍያ ባርኔጣ በራሱ ላይ ደፍቶ፣ ካፖርት፣ ኮት፣ ሸሚስ አጥልቆ በመንገድ ሲሄድ ፀሐይና ነፋስ፣ ዝናብ ሆነው ተወራረዱ አሉ። የዚህን ሰው ልብስ እኔ አስወልቅ፣ እኔ አስወልቅ ብለው ነው የሚወራረዱት። ውርርዱ መደቡ ስንት ብር እንደነበር አልተገለፀም። ብቻ ተወራረዱ። እናም እነ ጨረቃ፣ እነከዋክብት፣ እነ ደመና ታዛቢ ሆነው ውድድሩን መመልከት ይጀምራሉ። የመጀመሪያው ሞካሪ አጅሬ ነፋስ ሆነ።
"…ነፋስ ሆይ እየተወረወረ መጥቶ እንደ ብርሃኑ ጁላ ጦር ሰውየው ላይ ይላተማል። ሰውዬው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ዐላወቀም "የዛሬው ነፋስ ደግሞ ምንድነው?" እያለ ካፖርቱን ቆልፎ፣ በአንድ እጁ ባርኔጣውን አጥብቆ ይዞ፣ ወደፊት አላስኬድ ያለውን ነፋስ በግንድ ተከልሎ ልብሱን እንቅ አድርጎ ይዞ የነፋሱን ትግል አመለጠው ታግሎ።👇 ከታች ይቀጥላል። ✍✍✍
መልካም…
"…ላለፉት 50 ቀናት የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤውን ዐዋጅ፣ እና የዕርገቱን ምስክርነት ስናውጅ ከርመናል። ሃምሳውን ቀን እንደ አንድ ቀን ቆጥረን ስናመሰግን ከርመናል
እነሆ ዛሬ ደግሞ ከበዓለ ጰራቅሊጦስ ማግስት የሚጀምረውን ጾመ ሐዋርያት በፍቅር ጀምረናል። የዘንድሮው ጾመ ሐዋርያት እንደ ጾመ ማርያም በጣም አጭር ነው። ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን እንጾመ ዘንድ ከታዘዝናቸው ሰባቱ አጿማትም አንደኛው ስለሆነ እነሆ ጾማችንን አንድ ብለን ጀምረናል።
"…ከዛሬ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ዓመት በዓለ ትንሣኤ ድረስም እንደተለመደው ጠዋት ጠዋት ከአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ድርሳናት፣ የአዋልድ መጻሕፍት፣ ወይም ከሊቃውን ቃል መርጠን እግዚአብሔር ይመስገን በማለት ሥራችንን እንጀምራለን። እንደ ዜጋ ስለ ሀገራችን እንደ አማኝ ስለ ሃይማኖታችን በገባን መጠን ሓሳብ እየሰጠን እሱ እስከፈቀደልን ድረስ እንቀጥላለን።
"…ቢያንስ ቢያንስ በእኔ ፔጅ የእግዚአብሔርን ስም በትክክለኛው ፊደል መጻፍ የጀመሩ ሺዎችን አፍርቻለሁ። እግዜር፣ እዚያር፣ እዚጋቤር፣ እእግዚያብሄር፣ እ/ር፣ እግ/ር ወዘተ ብለው ይጽፉ የነበሩ አማኞችን በትክክል "እግዚአብሔር" ብለው እንዲጽፉ አስደርጌአለሁ። ቀላል መስሎሃል አዳሜ። ይሄም አንዱ አገልግሎት ነው። ደግሞም ይሄን አደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ቢረዳኝ እኮ ነው። ጠዋት ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ እኔ ፔጅ ላይ መጥቶ እግዚአብሔርን ማመስገን ሱስ የሆነበት ስንት ሰው አለ መሰላችሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ቀጥሎ የምንሔደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ርዕዘ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ? የሚለው ጥያቄም ይከተላል? ደብለቅለቅ ስታደርጉትም አንጀቴ ይርሳል።
• ዝግጁ ናችሁ?
መልካም…
"…አንድም በኢሞጂ እንኳ የተበሳጨ ሰው ሳላይ እስከአሁን 11ሺ ሰው ርዕሰ አንቀጹን ማንበቡን የቴሌግራም ሰሌዳ ይጠቁማል። ከርዕሰ አንቀጹ በኋላ ወደ እናንተ ትዝብት አስተያየት ነው የምሔደው።
"…በአሁኑ ወቅት ባለሀብት ተብለው የአዲስ አበባን መሬት ተቀራምተው ለኦሮሙማው አገዛዝ የገንዘብ ምንጭ የሆኑትን የዐማራና የኦሮሞ ባለሀብቶችን የሀብት መጠን ሰሞኑን እመለስበታለሁ። ለአሁኑ ለሸኔ 45 ሚልዮን ብር ለፋብሪካው ደኅንነት ሰጥቶ የዐማራ ፋኖን ግን መከላከያን እየቀለበ መከራ ስለሚያበዛበትም የዐማራ ባለሃብት ሰሞኑን በሰፊው እንመለስበታለን። ወንድሙን በመተት ሽባ አድርጎ እንዳይሞት ተንከባከቡልኝ ወንድሜ ከሞተ ሀብቴ ይጠፋል ስለሚለው ፋኖ አሳዳጅ ጠንቋይ ቀላቢም በሰፊው እንመለስበታለን፣ የሰሜን ሸዋን ታቦት፣ ቅርስ ጨፍጭፎ ስለጨረሰውም አሁን የአቢይ የገቢ ምንጭ ስለሆነ የጠንቋይ ልጅ ባለሀብት ተብዬ ዘራፊም በዝርዝር እንመጣበታለን።
"…አሁን የእነሱ ይቆየን እና የትግሬ ልጁ የኦቦይ ታደሰ ልጅ የጄነራል አበባውን ዲስኩር እንዴት አያችሁት? ይሄ የስብሰባ ውሎ በኋላ በሳምንታዊው ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው መርሀ ግብሬ በቴሌቭዥን እስካቀርብላችሁ ድረስ አስተያየታችሁን እየኮመኮምኩ እጠብቃችኋለሁ።
• 1…2…3…ጀምሩ…!
የሐሙሱ ስብሰባ
የመጨረሻ ክፍል
"…ከጀነራል በላይ ስዩም ቀጥሎ ዋና ሰብሳቢው ትግሬው የወዲ ታደሰ ልጅ አገው ሸንጎው የምርኮኛው ኦሮሞ የብርሃኑ ጁላ ምክትል በዐማራ ስም መድረኩን ተቀበለ።
"…በመጀመሪያ የመከላከያ ተግባር ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን መጠበቅ ነው በማለት እንደከሱቀደሙ ተናጋሪ እንደ ጄነራል በላይ ስዩም ለወያኔ ሕገ መንግሥት ጥብቅናውን በማሳየት ነው ንግግሩን የጀመረው። በሕገ መንግሥቱ መሠረት በተቀመጠው ሰላማዊ መንገድ እንጂ ሥልጣን የሚያዘው እንዲሁ በጉልበት ማንም ተነሥቶ ሥልጣን መያዝ አይችልም። ይሄን ማድረግ የሚቻለው እኛ በሕይወት ከሌለን ብቻ ነው። በሕይወት እያለን አይሞከረም።
"…አሁን እናንተ ፋኖ እያላችሁ የምትጠሩት፣ የምታወድሱት ለእኛ የሽፍታ፣ የወንበዴ፣ የዘራፊ፣ የቀማኛ ስብስብ ነው። እኛ የምናምነው እንደዚያ ነው። አይ ፋኖ ሽፍታ አይደለም፣ ዘራፊ አይደለም የምትሉ ካላችሁ ደግሞ ልታሳምኑኝ ይገባል። እንተማመን። እናንተ መስመር ቀየራችሁ ትሉናላችሁ። መስመር አልቀየርንም። እንደዚያ አትበሉን። እዚህ ላይ በደንብ እንግባባ። ቆይ እኔ አበባው ነኝ ወይ የክልሉን መንግሥት እግሬ እስኪንቀጠቀጥ ቆሜ የመረጥኩት? ምን አገባኝ። ይሄን ልፍስፍስ መንግሥት ብላችሁ፣ ምራን ብላችሁ ከምትመርጡ ደህና ሰው አትመርጡም ነበር? የእኛ ሥራ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠን ሥልጣን መሰረት በድንበር አካባቢና በክልሎች ውስጥ ችግር ሲፈጠር ጣልቃ ገብቶ ሕገ መንግሥቱን ማስከበር ብቻ ነው። እያደረግን ያለነውም እንደዚያ ነው። አንዴ ወደ ጦርነት ከተገባ ደግሞ ጦርነት ጦርነት ነው በቃ። በድሮን ተዋጋ፣ በክላሽ ተዋጋ፣ በሚግ አትዋጋ ብሎ ነገር፣ ብሎ ምርጫም የለም። በተገኘው ነው የምንዋጋው። አለቀ። እንዲያውም ዐማራ ክልል እኮ ታንክ ይዘን አልገባንም። ድሮኑን ተዉት መከላከያ እኮ ከዚያ በላይ አውዳሚ መሣሪያ የታጠቀ ተቋም ነው። ዐማራ ላይ እሱን መች ተጠቀምን? አልተጠቀምንም። ይሄን የምናደርገው እኛ ኃላፊነት ስላለብን፣ ስለሚሰማን ብቻ ነው።
"…እንደ ነገርኳችሁ ፋኖ ሽፍታ ነው። በጉልበት ሕገ መንግሥቱን መቀየርም ሆነ መንግሥት መለወጥ አይቻልም። ሥልጣንን በኃይል መንጠቅም አይቻልም። ከምርጫ ውጪ ሥልጣን ላይ መውጣት አይታሰብም። ፋኖ ሽፍታ ነው። በዚህ መግባባት ላይ መድረስ አለብን። መጀመሪያ ፋኖ ሽፍታ ነው በሚለው እንስማማ። ወያኔ ያሸነፈችው በዘር ነው። የወያኔ ጀነራሎች ዘረኞች ስለሆኑ ወያኔ ስታኮርፍ ከያሉበት ተነሥተው ሄደው ትግራይ ገብተው ተወሽቀው ተዋግተው አሁን ላሉበት በቅተዋልና እኛም ልክ እንደ ወያኔ ባህርዳር ግቡ ነው የምትሉን? አንተም እንደ ወያኔ ዘረኛ ሁን ነው የምትሉኝ? አላደርገውም። እኔ የኢትዮጵያ ጀነራል ነኝ። እናንተ ስታሳድጉኝም ዘረኛ አድርጋችሁ አይደለም ያሳደጋችሁኝ። እኔን ያሳደጋችሁኝ ኢትዮጵያዊ አድርጋችሁ ነው። ስለዚህ ከኢትዮጵያዊነት ወርጄ እንደ ወያኔ ዘረኛ አልሆንም። ወደ ባሕርዳርም አልሄድም። የማስፈጽመውም ተልእኮ በብሔሬ ሳይሆን በተቋሜ ነው።
"…የዐማራ ምሁራን ያላቸው ባዶ ፉከራ ብቻ ነው። በዚህ ባዶ ፉከራውም ራሱን እያዋረደ ነው። (ትግሬው አበባው ነው እኮ እንዲህ የሚለው) በቁጥር ብዙ ነን እያሉ መፎከር መፍትሄ አያመጣም። መደረጃት ነው መፍትሄ የሚያመጣው። እኛ የዐማራ ክልል ፖለቲከኞችን ደጋግመን መክረናቸው ነበር። አይሰሙም። ከዚህ በላይ የዐማራ ልዩ ኃይል አታሰልጥኑ ብለን መክረናቸው ነበር። በየወረዳው፣ በየቀበሌው ፋኖ እያላችሁ አታሰልጥኑ፣ አታስታጥቁ፣ በኋላ ይኼው ያለልክ የተንከባከባችሁት መልሶ ይዞርባችኋል፣ ይበላችኋል ብለን ብንነግራቸው እምቢ ብለውን ይኸው ያልነው አልቀረም በሏቸው። ፖለቲከኛው በሙሉ አሁን እኛ ስር ተጠልሎ ነው የሚንቀሳቀሰው።
"…እኛ እኮ እናውቃለን። አሁን ፋኖ ነኝ የሚለው ሽፍታ ሰነዱ የሚያሳየው 4 ኪሎ መግባት ነው ነው የሚለው። አራት ኪሎ በዚህ መልኩ በጉልበት መግባት ግን አይቻልም። ማንም ይሁን ማን የፈለገ ደካማ መንግሥት ቢሆን 4 ኪሎ መግባት የሚችለው ሕዝብ በድምፁ የመረጠው መንግሥት ብቻ ነው። ሕዝብ የመረጠው ከሆነ ንፍጣም መንግሥት ቢሆን እንኳ ንፍጣሙን የመረጠው ሕዝብ ስለሆነ ንፍጣሙን መንግሥት መቀበል ግድ ነው። እናንተ በደንብ ተረዱ። የፋኖ አካሄድ ከማንም ጋር አያኖርም። ፕሮፓጋንዳው ሁሉ አደገኛ ነው። ዐማራ አንደኛ ስለሆነ ሁሉንም በለው ነው የሚለው። ዐማራ ኦርቶዶክስ ደሴት ናት እያለ የሃይማኖት ችግር እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው።
"…ፋኖ የምትመለምሉ፣ ፋኖ የምትረዱ፣ የምትደግፉ ተጠንቀቁ። ለፋኖ ንገሩ። አራት ኪሎ እገባለሁ የሚለው ምኞት እንደማይሳካም ንገሩት ብሎ አረፈው። አበባው በጠዋቱ ስብሰባ ወቅት በአራቱም አቅጣጫ ካለው ፋኖ ጋር ተደዋውለን "ሕዝቡ ምን እንደሚል ሰብስባችሁ ጠይቁና ንገሩን" ስላለን ነው የሰበሰብናችሁ። ስለዚህ እናንተ ለፋኖ በዚህ መንገድ 4 ኪሎ እንደማይገባ ንገሩት ብሎ አረፈው። እናንተ ከፋኖ ጋር የምትደዋወሉ ከሆነ እናንተው ንገሩት እንጂ እኛማ በየትኛው ኔትወርክ ደውለን እንነግረዋለን ያለ ግን አልነበረም።
"…ትግሬው አበባው ታደሰ ቀጠለ…ቅድም ፋኖን 99% ደምስሰን አጥፍተነዋል ብሎ ከተቦተረፈ በኋላ እዚያው መድረኩ ላይ ጠረጴዛው ላይ የተኛውውን ሸንጎ ወንድሙን ጀነራል በላይ ስዩምን የጎሪጥ እያየ። ፋኖ ማለት የመረጃ መዋቅር አለው። የፕሮፓጋንዳ አደረጃጀት አለው። የፋይናንስ ምንጭ አለው። የስለላ አቅምም ፈጥሯል። በጊዜ መላ ካላበጀንለት እንደሀገር ለመቀጠል እንኳ ፈተናውን ያከብደዋል። ይሄ ብቻ አይደለም። ፋኖ በአደረጃጀቱ "ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ደሴት ናት ብሎ የተነሣና ሌሎችን ያገለለ ነው። ይሄም ሌላው አደጋ ነው ማለት ሲጀምር ተሰብሳቢው በአንድ ድምጽ በጭብጨባ ቀውጦ አስቆመው። የፈለገህን ቀባጥር በሃይማኖት አትግባ ነው መልእክቱ የሕዝቡ ጭብጨባ። አበባው መልሶ እንደማማጥ፣ እንደማመጥ አለ። ፋኖ እኮ ከመንግሥት ጋር የሚጠጋጋ ባለሀብት በክልሉ እንዳይሠራ እየተደረገ ነው። ስለዚህ ይሄ ነገር ለዐማራ ሕዝብ ከባድ ነው። እንደማመጥ።
"…እኔ የታጠቁ ኃይሎችን በ4 ነው የምከፍላቸው። አንደኛው ሽፍታ ነው። ሽፍታ የነበሩ፣ ነፍሰ ገዳይ የነበሩ፣ በጎንደር አካባቢ ሀገር ያስለቀሱ፣ በሽፋ፣ በዳንሻ፣ በወገራ፣ ዳባት አካባቢ እስቲ ሕዝቡን ሄዳችሁ ጠይቁት፣ እነዚህን አሁን የፋኖ መሪዎች የተባሉትን ቢያገኛቸው በቤንዚል ነው አቃጥለን ጠብሰን የምንገላቸው የሚለው። ማንም አይፈልጋቸውም። የሽፍታ አለቃ ያለውን በስም ሳይጠቅስ ቀጠለ። ቀጠለናም እንዲህ አለ። "…የክልሉ መንግሥት ይሄንን ሰውዬ ከሽፍትነት ጫካው አምጥቶ ሸለመው። ፖሊስ ስለገደለ። መከላከያ ስለገደለ። ሕዝብ ዘርፎ ስለገደለ ሸለመው። እኛ ግን አታድርጉ ብለናቸው ነበር። ማንይስማን? ይኸው ዛሬ ራሳቸው ላይ መጣ። አሁንም ይሄ ሽፍታ ዛሬ እንኳ ካለበት አካባቢ እዚያው ጎንደር ሌላ ስፍራ ቢሄድ ሰንበሌጥ አዘጋጅቶ ሊያቃጥለው ነው የሚፈልገው። እናም እኛ አሁን እናንተን የምንለምነው ሕዝቡ ያንን ሽፍታ ቢገድለው ሌላ ትርምስ ስለሚፈጠር ነው ነገሩ በእርቅ ይፈታ እያል ያለነው።
"…ሁለተኛው የታጠቀ ኃይል ሚሊሻውን እና ልዩ ኃይሉን አባብለው የወሰዱት ናቸው አለ። እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች የአመፅ አድማሱን አሰፉት። በተለይ የልዩ ኃይል የነበሩት የውጊያ ልምድም ስላላቸው ከጦርነቱም በላይ መንገድ እየዘጉ ለመከላከያው ስንቅና ትጥቅ እንዳይደርስ በማድረግ ራሳቸውን በራሳችን በሀገር ሀብት አደራጅተው👇 ከታች ይቀጥላል✍✍✍
"…በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው" ሐዋ 2፥1
"…መንፈስ ቅዱስ… እግዚአብሔር ነው። አጽናኝ ነው። የሚያረጋጋ ነው። ምሥጢር ገላጭ ነው። አስደሳች ነው። ከኃጢአት የሚያነጻ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ነው።
"…መንፈስ ቅዱስ… እግዚአብሔር ነው። መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ ነው። መንፈስ ቅዱስ የሚያረጋጋ ነው። መንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ገላጭ ነው። መንፈስ ቅዱስ አስደሳች ነው። መንፈስ ቅዱስ የሚከፍት ነው። መንፈስ ቅዱስ ማስተዋልን የሚሰጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከኃጢአት የሚያነጻ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ነው።
~ እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ።
መልካም…
"…የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ሓላፊው የዋግ ኽምራ የሰቆጣው የሌተናል ጀኔራል በላይ ስዩምን በዐማሮች ላይ በዐማራ ፋኖም ላይ የሰጠውን አስተያየት ከ11 ሺ ሰዎች በላይ ማንበባቸውን የቴሌግራም ካምፓኒያችን ሪፖርት እያመለከተኝ ነው። ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው በጀነራሉ ሓሳብ ላይ የእናንተን አስተያየት ነው።
"…በነገራችን ላይ ይሄ ጀነራል ታማኝ የትግሬ አገልጋይ ነበረ። ሕወሓት ድንገት አልበለጽግም ብላ በተሳፈጠች ጊዜ የሰሜን ዕዝን በመምራት የትግሬ ነፃ አውጪዋን ከሻአቢያ ጋር የወቀጣት ሰውዬም ነው። የኤርትራ ወታደሮች የትግሬ ሴቶችን እየደፈሩ ነው። የትግሬን ሀብትም እየዘረፉ ነው የሚል ስብሰባ በመቀሌ እየመራ በስብሰባው ላይ አዎ እናውቃለን፣ የባዕድ ሀገር ወታደሮች ባይገቡ ጥሩ ነበር። እኔ ራሴ ሳያቸው ይደብረኛል። የሆነው ሆኖ ለሻአቢያ መግባት ተጠያቂው ህወሓት ነው ብሎ በመናገሩ ሻአቢያ ለአቢይ አህመድ " እኛ እየረዳንህ ይሄ የትግሬ ድቅል የሆነ ጀነራል እኛን እየኮነን ነው። ስለዚህ መላ በለው ብለው ሲነግሩት ወዲያው ነው ከሥልጣን አንሥቶ ከትግራይ ያራቀው።
"…ጄነራል በላይ ስዩምም ተናድዶ በቤቱ ተቀመጠ። በዐማራ ስም በኮታ ጀነራል ከሆኑት እና ካሉት የአገው ሸንጎ ሰዎች መካከል ተደማጩ በላይ ስለሆነ ሌላ ነገር እንዳይፈጥርብኝ በማለት አቢይ አህመድ ለአዲስ ዓመት በድንገት ቤቱ በግ ይዞ በመሄድ እዚያው አሳርዶ በመብላት እዚያው ላይ ሹመት በመስጠት አፉን ለጉሞ በይሉኝታ አስሮ ዛሬ ይኸው ዐማራውን እንዲሳደብ አድርጎ አስቀረው። የሆነ ነገር በሉት እና ወደ ትግሬው አበባው ታደሰ ድንፋታ እናልፋለን።
• ቪድዮው ጁንታው ተሸንፎ በመቀሌ የተደረገ ስብሰባ ነው።
መልካም…
"…እንደምታዩት እንደምትመለከቱትም የቴሌግራም ገፄ በዚህች ደቂቃ ውስጥ 15ሺ ሰው በላይ አንብቦታል። ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ የየት አካባቢ ዐማራ ነው በማለት ለጠየቅኩት ጥያቄም ሁለት አካላት የተለያየ መረጃ አቅርበዋል። ኮሚሽነር ዘላለም ኦህዴድ ሲሆን ወለጋ ደምቢዶሎ አካባቢ ከአማራ ቤተሰብ የተወለደ ነው። በቂ ሌሎች ዝርዝሮች አሉ። ይህ ይብቃህ ያሉኝ ያሉ ሲሆን የእኚህን ሰው መረጃ የሚቃረንና ከቤተሰቦቹ ጠይቄ አረጋግጬ ነው ያገገኘሁት ያሉኝ ሌላ የዐማራ ተወላጅና በሙያቸው ጋዜጠኛ የሆኑ ወዳጄ እንዲህ ብለውኛል።
"…ኮሚሽነር ዘላለም አዲስ አበባ የተወለደ አባቱ የላስታ መዳጌ የሆነ ነው። ዘላለም ዲቃላ በመሆኑ በዐማራ ጥላቻ ያበደ ሰው ነው። ዐማራን የሚያስገድሉት ዲቃላዎችና የማንነት ቀውስ ውስጥ የገቡ ሰዎች ናቸው።
የአዲስ አበባውን የዐማራ ስብሰባ የመሩት በሙሉ የላስታና የዋግኽምራ የትግሬ ዲቃላዎች ናቸው በማለት አስረግጦ ነግሮኛል።
"…ነገሩ ከምር ይገርማል። ከዘላለም ቀጥሎ ንግግር ያደረጉት አበባው እና በላይ ንግግራቸውን ብትሰሙት ፀረ ዐማራነታቸው ፍጥጥ ብሎ ነው ወጥቶ የሚታየው። በኮሚሸነሩ ላይ ሓሳባችሁን ጣል ጣል አድርጉና ወደ ቀጣዩ እንሸጋገራለን።
• እመለሳለሁ…
"…ቀጥሎ የሚናገረው ከአበባው አጠገብ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ነው። የትግሬው አበባው ታደሰና የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ሓላፊው ሌተናል ጀኔራል በላይ ስዩም ሰዓታቸውን ጠብቄ አቀርባለሁ።
• መጀመሪያ የዜድን ዲስኩር እንስማ…
የሐሙሱ ስብሰባ
ክፍል ፭
"…በዚህ መሃል የወልድያው ተወላጅ፣ የሼህ አላሙዲን ጓደኛ ዶር አረጋ ንግግር ለማድረግ ዕድል ስለተሰጣቸው ተነሡ። ትግሬው አበባባው ታደሰም ዓይኑን አፍጥጦ ወደታች መመልከቱን ቀጠለ… አረፍ እያልኩ እቀጥልላችኋለሁ። መጣሁ። በማለት ነበር ትናንት ያቆምኩላችሁ። ዛሬ ካቆምኩበት እንቀጥላለሁ።
"…ከአቶ አረጋ በፊት አንድ እኔ የአዲስ አበባ ዐማራ ነኝ ያለ ወጣት በግድ "ይቅርታ ማይክ ይሰጠን፣ ማይክ ይሰጠን" በማለት ዕድል እንዲሰጠው ጠይቆ ዕድሉ ከተሰጠው በኋላ በሚገርም ወኔና ቁጣ ተናግሮ ነበር። እኔ በአባቴም፣ በእናቴም ዐማራ ነኝ። ጥርት ያልኩ የአዲስ አበባ ልጅም ነኝ። እኛ አሁን የተቸገርነው የማንም ሆዳም፣ የማንም ቀፈታም ሆዱን አንዘርጥጦ በደሀ ላይ በሚጫወት ነጋዴንኝ ተብዬ ነው። ከቲማቲም አንፃር እንኳ ዋጋ ቆልሎ ፍዳችንን የሚያበላን ባለሀብት ተብዬ ነጋዴ አይደለምን? በማለት ሲናገር እነ በላይነህ ክንዴ፣ እነ አሥራት ሴንቸሪ በብስጭት ይንቆራጠጡ ነበር። ወደ ዶር አረጋ ንግግር እንግባ…
"…ዶር አረጋ እንዲህ አሉ። በቅድሚያ ስለተሰጠኝ ዕድል አመሰግናለሁ። እኔ እንኳ በተለያዩ መድረኮች ላይ መናገር አልወድም። አልፈልግምም። ዛሬም የምናገረው ካሜራ የለም ስለተባለ ብቻ ነው። ወደ አስተያየቴ ስገባ " አሁን ያለው የሀገሪቷ ችግር የፖለቲካ ችግር ነው። እኔ የወልድያን ስታዲየም የሠራሁት እናንተ ምሽግ እንድታደርጉት ሳይሆን የወልድያ ሕዝብ እንዲጫወትበት ነው። በዚያው አካባቢ ትምህርት ቤት የገነባሁት የሀገሬ ልጆች እንዲማሩ፣ እንዲበቁ፣ ለሀገር የሚጥቅሙ ዜጎች እንዲያፈሩበት ነው እንጂ እናንተ ምሽግ እንድትሠሩበት አይደለም። ወታደር እንዴት ትምህርት ቤት ላይ ይሠፍራል? እንዴት ትምህርት ቤት ላይ ምሽግ ይቆፍራል? ከ 1890 ትምህርት ቤቶች በላይ ወድመዋል። ከትግራይ ጋር በነበረው ጦርነት ተነቅሎ የተወሰደው የዐማራ ትምህርት ቤት የሚታወቅ ነው። መረጃው አለን አሁንም ትምህርት ቤቶችን ካምፕ ያደረገው ማነው? እናንተ ራሳችሁ ናችሁ። ይሄ ተገቢ አይደለም በማለት ዐማራን እያወደመ ያለውን ትግሬውን ጀነራል አበባው ታደሰን ፊትለፊት ሞገቱት።
"…አሁን አበባው ታደሰ አጠገቡ ካሉት ጋር ተንሾካሸከ። ነገርየው መስመር እየሳተ መምጣቱንም ተመለከተ። ከሕዝብ ወገን ተብለው የገቡ ተናጋሪዎችም በብልፅግና አደረጃጀት ወደ ስብሰባው ገብተው ለብልፅግና የሚጠቅም ነገር ይናገራሉ ሲባል ጭራሽ ጉባኤው አገዛዙን አፈር ከደቼ የሚያበላው እየሆነ መጣ። መጀመሪያ ላይ ነው የእነ ሙጂብ አሚኖ እስላሞች የጉባኤውን መንፈስ ይረብሹና ዐማራውን ቅዘን በቅዘን አድርገው ዱካካም ያደርጉታል ተብሎ ታስቦ የነበረው። ነገር ግን ከጎንደር የመጡት የዳንኤል ክብረት ኔትወሮኮች "አሁንስ በዛ፣ ባይበላስ ቢቀር ብለው የእነ ሙጂብን እስላሞች እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው በመናገራቸው እነ ትግሬው አበባው ታደሰ ጉዳዩ ወዳልተፈለገ መስመር ከመግባቱ በፊት በአጭሩ አስቁሞ ተገላገለ። ብዙዎቹ ካድሬ ሆነው ገብተው እዚያው የእግዚአብሔር መንፈስ የለወጣቸው ይመስላል።
"…ዶክተር አረጋ ተናግረው እንደጨረሱ አበባው ታደሰ ስብሰባችን ይቀጥላል አሁን ለሻይ እረፍት እንውጣ በማለት የጋለውን የስብሰባ ስሜት አቀዘቀዘው።
"…ከሻይ እረፍት መልስ ምን ይፈጠር ይሆን…? ቆይቼ እመለሳለሁ።
"…ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” ሐዋ 1፥ 9-11
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።