zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ያው እንደፈረደብኝ ደግሞ ልመጣ ነኝ…!

"…እኔ ዘመዴ፣ አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ መራታው ዘመዴ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር አሸበርቲው ዘመዴ ይሄን ፀረ ክርስቶስ፣ ፀረ ኢትዮጵያ መንጋ ልወጥረው በቲክቶክ መንደራችን እየሄድኩ ነውና ላልሰማ አሰምታችሁ ዘጭ ብላችሁ ጠብቁኝማ።

"…ለሳቅ ለፈገግታ፣ ደግሞም ለቁም ነገር
መሄድ መገኘት ነው ከዘመዴ ተክቶክ መንደር በልልኝ አንተው…

• የአቦን መገበሪያ የበላችሁ ሁላ እየለፈለፋችሁ ኮፍያና አበባ ይዛችሁ ጠብቁኝማ…😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሆነ ጊዜ ነው አሉ…

"…መምህሩ ዐውደ ምህረት ላይ ቆመው ይሰብካሉ። በስብከታቸውም መሃል "…የአቦን መገበሪያ የበላ ሳይጠይቁት ይለፈልፋል" በማለት ነው አሉ ታሪክ ጠቅሰው የሚሰብኩት። ኋላ ላይ ብድግ አለ ኣ አንዱ ተሰባኪ ምእመን። ብድግ ብሎ ቆሞ እጁን እየወዘወዘ መምህሩን እንዲህ አለ አላቸው አሉ።

"…መምሬ አሁን ያስተማሩት ትምህርት ልክ አይደለም። ለምሳሌ እኔ የጌዮርጊስን መገበሪያ በልቻለሁ። ይኸው እስከአሁን ግን አለፈለፍኩም" በማለት ሙግት ጀመራቸው አሉ።

"…መለሱለታ መምሩ። "…እና አሁን ምን እያደረገህ ነው? ማንስ ጠይቆህ ነው የምታወራልን? ዥል… አሉት አሉ።

"…ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ… ቆይቼ እመለሳለሁ። …ስደበኝ አሉህ ደግሞ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ።” መዝ 84፥7

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኔ ዘመዴ ሰፍሬ፣ ቆጥሬ፣ ለክቼ በዓይነት በዓይነቱ አጀንዳ እሰጣለሁ እንጂ ምን አጣሁ ብዬ ነው ከአንተ ዘንድ አጀንዳ የምቀበለው? ሃኣ…!

"…የሚወራ የማይወራ አለ። የተገኘው ሁሉ አይወራም። አይነገርም። የአንተን የወሬ ሱስ ለማርካት ብዬ ከየትም ለቃቅመህ እየቃረምክ የምታመጣውን ወሬ ሁሉ በዚህ ሚልዮን ሰው አፍጦ በሚጠብቀው በተከበረ ፔጄ ላይ አምጥቼ እንድለጥፍልህ አትፈልግ። ሰገጤ ሁላ…

"…እኔ የትግሬዎቹንም ሆነ የኦሮሞዎቹን ፔጅ በንቃት ነው የምከታተለው። የምንቀው ፔጅ የለም። የዙም ስብሰባ ሲደረግ በሌላ ሀገር መስመር በአሜሪካም ስልኬ ገብቼ እሳተፋለሁ። በትግርኛም ሲያወሩ፣ ሲመክሩ፣ በኦሮሚኛም ሲመካከሩ ተገኝቼ እሰማለሁ። ለዐማራ ይሄን አጀንዳ ጋግረን እንስጥ ብለው ሲመክሩ እሰማቸዋለሁ። እናም አቡኩተው የጋገሩትን ወሬ ለአዳሜ አሻምተው ሲያደነዝዙት እኔ ጋር ወፍ የለም።

"…በነገራችን ላይ ከአንዳንድ ዥልጥ ፀረ ዐማራ የዐማራ አክቲቪስት ነኝ ባይ ገተቶች ለየት የሚያደርገኝ እኔ ዘመዴ ትግርኛ ባልናገር መስማቴ፣ ኦሮሚኛ መስማቴም መናገሬ ነው። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ለዐማራ አጀንዳ የሚሆን ነገር በአማርኛ ነው የሚበትኑት። ለውሻ አጥንት እንደመወርወር በሉት። ከዚያ ይሄ ገብሴ ግራ ቀኝ ሳያይ የተወረወረለትን አጥንት ተሸክሞ መጥቶ አንተኑ መልሶ ያዝግህሃል። ፔጅህንም ያግማማል፣ ያጠነባል።

"…አሁን አሁን ግን በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብም ሆነ በቴሌግራም እየመጡ ያሉ እሳት የላሱ ዐማሮችን እያየሁ እየተደመምኩባቸው እገኛለሁ። ሴቶቹንም፣ ወንዶቹንም ቆሜ እያጨበጨብኩላቸው ነው። አይሳደቡ፣ አይጮሁ፣ አይናደዱ፣ አይፈሩ፣ አያፍሩ ንቅንቅ ሳይሉ ከዕውቀትና እውነት ጋር ድባቅ ሲመቱ እያየሁ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ ነው። በርቱ ግፉበት።

•እናም ዘመዴ ስለዚህ ነገር ጻፍ አትበለኝ። ሰምተሃል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በምሥሉ ላይ የምታዩአቸው ሴት የኬንያ የፓርላማ አባል ናቸው አሉኝ። ባለፈው ሳምንት የኬንያ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ የተቃወመውን የታክስ ጭመራ ሕግ ደግፈው የነበሩ የፓርላማ አባል ናቸውም አሉኝ። "ሕጉ ከጸደቀ የዳቦ ዋጋም አሁን ካለው በእጥፍ ይጨምርብናልና አደራ ሕጉን ከሚቃወሙት ወገን ሁኚልን ብለው የመረጧት ዜጎች ደውለው ወትውተዋት ነበር አሉ።

"…ሴትዮይቱም እሺ ብላ፣ ሰምታቸው ነበርም አሉ። ኋላ ምን እንደነካት አይታወቅም በፓርላማ "ሕጉ ይጽደቅ" ከሚሉት ወገን ቆማ እንደ ኢትዮጵያ የፓርላማ ተመራጮች እጇን ወደላይ ቀስራ አውጥታ ሕጉ ይጽደቅ ዘንድ ደግፋ ድምፅ ሰጠች አሉ።

"…መቼም የመረጠኝ ሕዝብ ገጠሬ ነው ደግሞስ ምንአባቱ ያመጣል? ለዚህ አንድ ሚሊሻ ለሚበቃው አፈር ሕዝብ ብላ እንደ ኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት ሳትታበይ አልቀረችም። እናም ኬኒያ ናይሮቢ ግርግር ስለበዛ፣ ከግርግሩ ዞር ብዬ ገጠር ዘመዶቼ ጋር ሄጄ ልሰንብት ብላ የፓርላማ ደሞዟን እንደያዘች ወደ ትውልድ መንደሯ ቪ8 መሂናዋን እያሽከረከረች፣ መነጥሯን ሰክታ ነው ጆሌ መስላ ሄደች አሉ።

"…ድሮ ድሮ የባርላማ አባል መጣ ሲበል ዴየስስ የሚለው የአካባቢው ነዋሪም የሴትዮይቱ ጣቷን ቀስራ ሕጉን መደገፍ ቀድሞ ሰምቶ ኖሯል ሴትየዋ ስትመጣ ቤተሰቦቿ፣ አብሮአደግ ጓደኞቿ፣ ዘመድ አዝማድ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ተሰብስቦ ጠበቃት። ጠበቃትና በምታዩት መልኩ በድንጋይ ቀጥቅጦ "ምንአባሽ ቀረኝ ብለሽ ነው የመጣሽ?" ብለው ውሻ አድርገው መለሷት ነው ያሉኝ።

"…እናንተ አካባቢ ተመርጦ ባርላማ የገባው ማነው? የአባይ አራጅ መከላከያ ወደ ክልላችሁ ገብቶ ቤተሰቦቻችሁን እንዲያርድ እጁን አውጦ ፈቃድ የሰጠውን ሰው ታውቁታላችሁ? ደግሞ እንደ ኬንያውያን ክፉ ነገር አታስቡ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬውንም ርዕሰ አንቀጽ ወደ 13 ሺ ያህል ሰዎች እንዳነበቡት እያየሁ ነው። ቀጣዩ መርሀ ግብር ደግሞ የእናንተ አስተያየት የሚኮመኮምበት ሰዓት ነው። እስቲ እናንተ ደግሞ በጎደለ ሞልታችሁ አስደምሙን።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…እነ ጫላ የከተማውን ሙሉ ህንጻ ግራጫ በግራጫ ጫ በ ጫ ቀለም በመቀባት፣ በየህንፃዎችም ላይ የቡና ቤት መብራት በመሰቀል፣ በማንጠልጠልም፣ ራሳቸው ካሜራ ፊት በቀረቡ ቁጥርም እንደ ከተማዋ ግራጫ በግራጫ ቀለም ተቀብተው አድገናል፣ ተለውጠናል እንደሚሉት ያለ አይደለም እድገት ማለት። እንደዚያ አይደለም። አንድን ሰፈር፣ ወይም አንድን አውራ ጎዳና በቀለም በማዥጎርጎር እና የቡና ቤት መብራት በመሰቃቀል እንዴት እንደ ሀገር አድገናል፣ ተለውጠናል ተብሎ በድፍረት ዜና ይሠራል?

"…እኔ በስደት በጊዜአዊነት በተጠለልኩበ አጎት ሀገር በጀርመንም ሆነ በመላው አውሮጳ፣ በአማሪካም የዲም ላይት ሲበራ የማየው በዓመት አንድ ጊዜ የገና በዓል ሲቃረብ ብቻ ነው። ያኔ ክረምቱም ከበድ ስለሚል፣ ጨለማውም ስለሚያስፈራ፣ ድብርት፣ ጭንቀትም ብዙ ሰው ስለሚያጠቃ፣ በተለይ ከፈረንጆቹ የገና በዓል አንደወር ቀደም ብሎ እና ከገና በዓል በኋላ ለአንድ ወይም ለሁለት ሳምንታት በሁሉም የገጠር ከተማዎች ሳይቀር በህንጻዎች፣ በቪላ ቤቶች፣ በመንገዶች ላይ ሁሉ መብራት ይሰቀላል፣ ይበራልም። መብራት ማብራት ብቻ አይደለም ሰዉ ሁሉ ሲበላ፣ የፈላ ወይን ሲጠጣ ያመሽና የክረምቱ ጨለማ የሚፈጥርበትን ድብርቱን አራግፎ ወደ መኝታው ይሄዳል። ከዚያ ውጪ አንዳንድ ቦታ እንዲያውም የኤሌክትሪክ ኃይል ለመቆጠብ ሲባል የድልድይ ላይ መብራት ራሱ ሲያጠፉ ነው የማየው።

"…ያብለጨለጨ ከተማ ውስጥ ያለ ሥራ መቀመጥ እንዴት የእድገት መለኪያ ይሆናል? ፋብሪካዎች በኃይል እጦት ሥራ ባቆሙበት ሀገር ፒያሳና አራት ኪሎ አካባቢ፣ ሜክሲኮና ሳርቤት አደባባይ ላይ መብራት ቦግ አድርጎ አብርቶ እንዴት አደግን፣ ተለወጥን ይባላል? ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎች የሚያቀርቡት ምግብ በማጣታቸው ምክንያት በሚቀጥለው ዓመት ተማሪ ለመቀበል እንቸገራለን ብለው በይፋ በሚያውጁበት ሀገር እንዴት ነው የፒያሳ መብራት የሀገር እድገት መለኪያ የሚሆነው? እነ ካኑን እና ዳንኤል አሞካቺን አምጥቶ በፓርክ መብራት ላይ አስደንሰህ ስታበቃ ኢትዮጵያ አድጋለች ብለህ ስለ ተናገርክ፣ ፕሮፓጋንዳም ስለ ሠራህ አይኤምኤፍ ገንዘብ አይለቅልህም እኮ። እነ ካኑ በሀገራቸው ቅንጢ ፓርክ የነበሩ ስፍራዎች አሁን የሸረሪት ድር አድርተው እያየን እኛ ባለ ሾርት ሚሞሪያም ናችሁ ስለተባልን ብቻ በእነሱ ሰበካ በቃ አድገናል ልንል ይመስላቸዋልን?

"…በአንድ ሀብታም ቤት የተቀጠረ ዘበኛ እንኳ ከደሞዙ ባሻገር ለሆዱ ፍርፋሪ አያጣም። ማደሪያም አይቸግረውም። የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁናቴ እኮ ከሀብታም ቤት ዘበኛ ኑሮ ጋር እንኳ የማይነፃፀር የሰቆቃ ሕይወት የሚገፋው ሕዝብ እኮ ነው። አዳነች አበቤ በቀለምና በመብራት ባሸበረቀችው ከተማ ውስጥ ማደሪያ አጥቶ ባዶ ሆዱን የሚዞር ሕዝብ፣ ማደሪያ ቢኖረው እንኳ በቤት ኪራይ ናላው ዞሮ ጨርቁን ሊጥል የደረሰ ሕዝብ እንዴት ነው በፒያሳ መብራት አድገናል ብሎ ጮቤ የሚረግጠው? የአንድ ነት ፓርክ ምግብ ይሆናል ወይ? እንጦጦ ፓርክ ዳቦ ይሆናል ወይ?

"…ራስህን፣ ቤትህን፣ ግቢህን፣ ሰፈርህን፣ አካባቢህን፣ ቀበሌህን፣ ወረዳህን፣ ክፍለ ከተማህን፣ ከተማህን የሚቀይረው እኮ ገቢህ ነው። አንድ ሰው ሥራ እና ገቢ ሲኖረው መጀመሪያ ራሱን ይቀይራል። መጀመሪያ ጭቅቅቱን ያራግፋል፣ በማጣት ጊዜ በሥራ አጥነቱ ወራት ተቀይሮ የማያውቀውን ከመሄድ፣ ከመጓዝ ብዛት ጥንባት፣ ክርፋት፣ ሽታ ያመጣበትን፣ ከማኅበረሰቡም ጋር ያቃቃረውን በመጥፎ ጠረኑ ያስወቀሱትን እነ ጫማ፣ እነ ካልሲ፣ እነ የውስጥ ግልገል ሱሪን፣ እነ ሸሚዝ፣ ኮትን ሁሉ ይቀይራል። ለብብቱ ዶደራንት፣ ለፀጉሩ ቅባት፣ ለልብሱ ሽቶ ይገዛል። በራሱ ላይ ኢንቨስት ያደርጋል። ይሄ የሚሆነው ታዲያ ከተማረ፣ ሥራ ከሠራ ብቻ ነው። ባይማርም ግን ገበሬም ቢሆን ካላረሰ፣ ምርጥ ዘር ማዳበሪያም ሳታቀርብለት ፉሉስ ሊኖረው አይችልም። በባዶ ሜዳ ሥራ አጥ እንደ አሸን በፈላበት ምድር ላይ በፒያሳ መብራት ብቻ አደግን ብለን መበጥረቁ ማንን ያሳምናል? ውኃ ከመጣች አንድ ወር ሆናት ብሎ እንደፈነዳ ሽንት ቤት የሚሸት፣ የሚጠነባ ሰው አዳነች አቤቤ ፋውንቴን አጠገብ ቆሞ አድገናል ሲል ከዚህ በላይ ማፈሪያነት ከየት ይመጣል?

"…አንድ ሰው አነሰም በዛም ገቢ ሲኖረው ከራሱ አልፎ ቤቱንም ይቀይራል። እንደ አቅሙ ማለት ነው። ቆርቆሮ፣ ኮርኒስ፣ ወንበር አልጋ ሁሉ ይቀይራል። አንድ ሰው ሥራ ካለው ነው ቅድመ አያቱ የተወለዱበት፣ ከዚያ አያቱ የተወለዱበትን፣ ከዚያም አባቱ ተወልዶ አድጎ እሱ የተወለዶ ያረጀበትን እና የሀገር ቅርስ ለመሆን መስፈርት እያሟላ ያለውን የዘመናት ትውልድ አሳዳጊ የሆነ አልጋ፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ እንኳ ሊቀይር የሚችለለው ገቢ ሲኖረው ነው። አሁን በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ይሄን የሚያስደርግ ገቢ ያለው አለ ወይ ነው ጥያቄው። ቤቱን የቀየረ ሰው ግቢውን ይቀይራል፣ የሰፈሩ ሁሉ ሰው ገቢ ያለው፣ ሥራ ያላቸውም ከሆነ ሰብሰብ ብለው ሰፈራቸውን ስለማሰማመር ይነጋገራሉ። ተነጋግረውም ሰፈራቸውን ፏ ሽር ብትን ያደርጉታል። በአንዳንድ ኮንዲሚንየሞች አካባቢ የሚታይ ነው። ሰፈሩ ሲቀየር ደግሞ የቀበሌው ነዋሪ ገቢው ከጨመረ ቀበሌው፣ ከሕዝቡ የሚገኘው ገቢ እየጨመረ ሲመጣ ሌባ የመንግሥት ሓላፊዎች ከሌሉ ከተማው፣ ከዚያም ሀገሩ ሁሉ ውብ ይሆናል። እንዲያ ሲሆን ሕዝቡም ልማቱን በላቡ፣ በጥረቱ ያመጣው ነውና ይንከባከበዋል። ይሄ ነገር በአንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገር ተደራሽ ከሆነ ደግሞ እንደ ሀገር ጠቀሜታው ከፍ ይላል። አለበለዚያ እድገቱም፣ ለእይታ የሚሠራው ሥራ ሁሉ በአንድ ከተማ ላይ ብቻ ከሆነ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል።

"…ለምሳሌ እንውሰድ። አሁን እነ አቢይ አሕመድ የጨበሬ ተስካር ምርጫ ተብዬዋ እየደረሰች ስለሆነ ይሄን ሾርት ሚሞሪያም ያሉትን ሕዝብ በቀለም፣ በዲም ላይት መብራት ሊያጭበረብሩት ይፈልጋሉ። በሀገሪቱ ውስጥ የቀለጠው ጦርነት፣ የኑሮ ውድነት አናቱ ላይ የወጣው ሕዝብ እንዳይበላቸው ከተማን በመብራትና በቀለም በማብለጭለጭ በቶፕ ቪው ቀረጻ ሊሸውዱት ይሞክራሉ። ይሄ ማለት እሳት የላሱ የቡና ቤት ባለቤቶች ሥራ ነው። የቡና ቤት ባለቤቶች ዋነኛ ሥራቸው ደንበኛው በደንብ እንዲጠጣ ሜካፓም ሴቶችን፣ አጭር ቀሚስ  አስለብሰው በፊትህ ላይ ያሯሩጡብሃል። እንድትሰክር ደግሞ ዲጄው ሞንታርቦውን እስከ መጨረሻው ይከፍተውና በመጠጡ ብቻ ሳይሆን በሙዚቃው ናላህ፣ አንጎልህ፣ ማሰቢያህ እንዲበጠበጥ ያስደርጋሉ። መብራቱ ብልጭ ድርግም ሲል ደግሞ ቅዥብርብር ይልብህና ራስህን ትጥላለህ። ገነት የገባህ ሁላ ይመስልሃል። ሲኦል እንደነበርክ የምታውቀው እንኳ የስካሩ አንጎበር ሲለቅህ እና ጨለማው በብርሃን ሲተካ ነው።

"…አዲስ አበቤም እንደዚያው ነው እየሆነ ያለው። ጭራሽ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማቱ ባለበት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ መዝጋት የለባቸውም የሚል ሕግ ሁላ አውጥታለች ነው የሚባለው። መብራቱም ፖሊሱም ያለው አራት ኪሎና ፒያሳ የኮሪደር መብራቱ ጋር ነው። የኮሪደር መብራቱ ጋር ደግሞ ፎቶ እየተነሡ የሚያመሹት በኩራዝ እና ፋኖስ አድገው አሁን በዲሞግራፊ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩና የሰፈሩ ባለ ጊዜዎች ናቸው። የንግድ ድርጅቶቹ ሌሊቱን አምሽታችሁ ሥሩ ተብለው ተገደው ወደ ቤታቸው አምሽተው ሲገቡ መብራት በሰፈራቸው የለም እና ለዘረፋ ይጋለጣሉ። እድገት በግድ፣ በዐዋጅ እኮ አይመጣም። 👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6።

"…አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል በተመቱ ጊዜ፥ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥ አንተ በሰማይ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው።

"…አንተን ስለ በደሉ ሰማይ በተዘጋ ጊዜ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ ባስጨነቅሃቸውም ጊዜ ከኃጢአታቸው ቢመለሱ፥ አንተ በሰማይ ስማ" 1ኛ ነገ 8፥ 33-35

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከታላቁ ገዳም ከደብረ ሊባኖስ ስር ከበታቹ የሚገኘው የይሰበይ ደብረ ብፁዓን አቡነ ሀብተ ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት ቆሞስ አባ ተክለ ብርሃን ትናንት ዓርብ ሌሊት ለዛሬ ቅዳሜ አጥቢያ በእኩለ ሌሊት ጫገል ደብረ ሊባኖስ ከሚገኘው የገዳሙ ዘይት መጭመቂያ ቤት ኦነግ ሸኔ አፍኖ እንደወሰዳቸው ተነግሯል።

"…ቆሞስ አባ ተክለ ብርሃንን ያገታቸው አጋቹ ኦነግ ሸኔ የገዳሙን አበምኔት አፍኖ ወደ ሙገር አካባቢ እንደወሰዳቸውም የተነገረ ሲሆን፤ በተሰጠ ቀነ ገደብ ውስጥ ገዳሙ 15 ሚልዮን የኢትዮጵያ ብር ከፍሎ ማስለቀቅ እንደሚችልም ለገዳማውያኑ በምርጫ መልክ እንደተነገራቸውም ተነግሯል። አስራ አምስት ሚልዮን ብር መክፈል ካልተቻለ ያው እንደተለመደው… ለዳንኤል ክብረት እና ለአቢይ አህመድ የሰኔ ግብር…

"…የሚገርመው ነገር ከወር በፊት በዚያው ገዳም የሚያገለግሉ ሌላ አባት እንዲሁ ታግተው የነበረ ሲሆን የንስሀ ልጆቻቸው እና ወዳጆቻቸው ተሯሩጠው ከዚያም ከዚህም ብለው ፈልገው የተጠየቁትን አምስት ሚልዮን ብር ከፍለው እንዳስለቀቋቸውም ተነግሯል። አየተበለፀገ ነው። ደግነቱ በገዳም የሚኖር የለም እንጂ ለገዳም አበምኔት ያውም ለአረጋዊ ለመነኩሴ 15 ሚልዮን የተጠየቀ ለጳጳስና ለፓትርያርክ ቢሆን ስንት ብር ሊጠይቁ ነበር? አጋቾቹ ግን ፓስተርና ሼክ የማያግቱት 😂😂 ለምን ይሆን ብዬ ልጠይቅ አልኩና ከአፌ መለስኩት። እየታገትነ፣ እየታገታችሁ።

"…የኮሪደር ልማቱ እንዴት ነው? ያምራል አይደል?

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከወሎው የብአዴን ቡድን ጋር በኃይለኛው ለመምከር በዚያውም የብአዴንን የኃይል ሚዛን ከጎጃምና ከጎንደር ዐማሮች ነጥቆ በወሎ ለሚገኙ መሰረተ ኦሮሞ ለሆኑ ለወሃቢይ እስላም ዐማሮች በመስጠት ያኛውን ክርስቲያን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ዐማሮች ይበዙበታል የሚለውን በአዴን በማቀጨጭ ለማክሰም እና ምክክር የሚደረግበት ምስጢራዊ ጉባኤ ለማድረግ፦

"…እንደገናም አሁን ያለው የፋኖ እንቅስቃሴ ፀረ እስላም መሆኑን በመንገር ትግሉን የሃይማኖት ቅርጽ በመስጠት ቀደም ሲል ፀረ ፋኖ ሆኖ የተዋቀረውን የወሃቢይ እስላም ቡድን ለማጠናከር፦

"…ከባህልም፣ ሃይማኖት፣ ሥነ ልቦናም ጭምር ከሌላው የዐማራ ግዛቶች የተለየና በጭቆና ያለ ከትግሬና ከዐማራ ይልቅ ለኦሮሞነት የቀረበ በመሆኑ ወሎ ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን የተጀመረውን ሂደት ለማጠናከር ሲል አቢይ አሕመድ ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ጠዋት የጎን ቁጥሯ ET-ARM በሆነች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮጵላን በልዩ በረራ ወደ ኮምቦልቻ ለመሄድ መዘጋጀቱ ነው ወፎቼ የሚናገሩት።

"…ለብልጽግና ሰዎች አቢይ ወደ ወሎ ቤተ አምሓራ መናገሻ ከተማ ወደ ደሴ የሚሄድበት ምክንያት ነው ተብሎ እንደ ሽፋን የተነገረው፦

1ኛ፦ ገበታ ለሀገር የሚለውን የሐይቅ ዳር ኘሮጀክት ወደ ታላቁ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በማምጣት በዚያም የመሰረት ድንጋይ ለመጣል፥

2ኛ፦ የደሴ ከተማ አስተዳደር ያሠራውን አስፓልት መንገድ እና እንዲሁም በአዲስ መልክ የተሠራውን የአውቶቡስ መነሃሪያ ለመመረቅ
 
3ኛ፦ በባለቤቱ ስም የተሰየመውን ዝናሽ ታያቸው ዳቦ መጋገሪያ ቤት ለመመረቅ ነውም ብለዋል ወፎቼ።

"…በደሴ 7ተኛው ንጉሥ ይመጣል ተብሎ አስፓልቱ እየታጠበ፣ የሸገሩ የዲም ላይት ቦለጢቃም ደርቶ ደሴ በባዶ ሆዷ ሽርጉድ እያለች ነው ተብሏል።

• በቀጣይ ገበታ ለሀገር ደብረ ሊባኖስ… ወይ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹን 12 ሺ ሰው አንብቦት አንድ ሰው ብቻ በኢሞጂ 😡😡😡 ብው ማለቱን ከማየቴ በቀር የአብዛኛው አንባቢ ስሜት መልካም ይመስላል። ለማንኛውም በርዕሰ አንቀጹ ላይ የሚጨመር ጨምራችሁ፣ የሚቀነስ ቀንሳችሁ፣ በተለይ ተቃዋሚ ካለ በጨዋ ደንብ ሳይሳደብ ርዕሰ አንቀጼን መቃወም አፈር ደቼም ማብላት ይችላል። እኔ ዲሞክራት አሸበርቲ ነኝ።

• እንደኔ ተናገሩ ተንፒሱም። ተንፒሱና በጤና ለሽሽ ብላችሁ ኑሩ። ተንፒሱ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ያደርጋል። መናፍቅም፣ ፅንፈኛ የወሃቢ እስላምም ስለሆነ ይሄን ያደርጋል። ዥልጥ፣ ዥል አራጁ ይሄን በማድረጉ በዓላቱ ደምቀው እንዳይውሉ በማድረጉ ይህን በማድረጉ በሌላው ቤተ እምነት በፀረ ኦርቶዶክሳውያኑ ዘንድ ጮቤ ይረገጣል። ሃይማኖቷን ያጠፉ ያህልም ደስታ ይሰማቸዋል።

4ኛ፦ ከአማራው ጋር ለሚያደረገው ጦርነት ወጣቱ መከላከያውን እንዲቀላቀል፣ ሕዝቡም ድጋፍ እና ቀለብ እንዲሰፍርለት ሲፈልግ።
            

"…ለትግራዩም ጦርነት ያደረገው እንዲሁ ነው። መጀመሪያ ወለጋ ውስጥ ዐማሮችን ስብሰባ ጠራ። እዚያው ስብሰባው ላይ ረሸናቸው። የፋና ቴሌ ቭዥን ጋዜጠኞች ሳይቀር ቦታው ድረስ ሄደው ዶክመንተሪ ሠሩ። አቢይ ያልተገኘበት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ። ከብቶቹ የብአዴን ሰዎች ወያኔ ነው ወለጋ ውስጥ ዐማራውን ያስፈጀው የሚል ትርክት እንዲነገራቸው ተደረገ። አስታውሳለሁ ከወሎ ደሴ የመጣች ወፍራም፣ ግብዳ፣ ጥቁር ሴትዮ እንባዋን መንታ መንታ እያፈሰሰች አለቀሰች። ሌሎችም ዐማሮች አሁንስ በዛ ብለው ፓርላማውን ቀወጡት። አቢይ ከጀርባ ሆኖ ከዳንኤል ክብረት ጋር ይስቃል። ዜናው ደጋግሞ በቴሌቭዥን ታየ፣ ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው ብለው ካድሬዎቹ አጓሩ። ወጣቱ ወደ መከላከያ እንዲጎርፍ የዐማራ አክቲቪስቶች ሁሉ ወተወቱ። ሰንጋ በሬ፣ በሶና ድርቆሽ ተዘጋጀ፣ አቢይ ኢትዮጵያውያንን በዐማሮች ሞት አሰልፎ ትግራይ ዘመተ። ትግሬንም አደቀቀ። አለቀ።

"…አቢይ በእሱ ቤት ለሁሉም ኢትዮጵያ የሰለም ሰው ነው። ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ነው የሚታገለው። ሌላው ታጋይ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ነው ብሎ ሰብኮ የሚፈልገውን ድጋፍ እንዲቸሩትና እንዲያምኑት ጭምር ከፋኖ ጋር መደራደር እፈልጋለሁ፣ ጥሯቸውና እንነጋገር ምናምን ብሎ ወሬውን በተለያየ ሚዲያ ያቀልጠዋል። የአቢይ ፍላጎት ግን ሌላ ነው። ዐማራውን በአስር እና አስራ አምስት ሚሊዮን ቁጥሩን ማውረድ ስለሆነ የእውነት ድርድር መደራደር አይፈልግም። የድርድር ሰው መስሎ ለሁሉም ባስወራ ማግሥት በጀርባ ይሄድና ፋኖው ሞኝ መስሎት ድርድሩን እንቢ እንዲል ንጹሃን ዐማራዎችን ፈልጎ ታይቶ በማይታወቅ ዘግናኝ ሁናቴ ይጨፈጭፋቸዋል። ያኔ ፋኖ የሚታገልለትን ሕዝብ ስለሆነ አቢይ የጨፈጨፈበት ድርድር የሚለውን ቃል ራሱ መስማት አይፈልግም። በእውነቱም ከሆነ ኀዘን ላይ ላለ ሰው የሚያበሳጭ ስለሆነ አቢይም ይሄንኑ ዐውቆ ስለሚያደርገው ፋኖ ይቆጣል። የኢትዮጵያም ሕዝብ የአቢይን ሴራ በቅጡ ስለማይረዳው፣ በቀላሉም ስለማይገባው ፋኖን በማውገዝ እንዴት አይደራደርም በማለት ልጁን፣ ገንዘቡን፣ ድጋፉንም ሁሉ ለዐቢይ ያዘንባል ብሎ ይጠብቃል። ተሳክቶለት ድጋፉን ካገኘም መሰሪ እባቡ አቢይም በሚያገኘው ድጋፍ ዐማራን በሻሻ ማድረጉን ይቀጥላል። እንዲህ እያለ ጊዜ ካገኘ፣ ዘመኑ ከረዘመ ሀሉንም ክልል ተራ በተራ በሻሻ ያደርጋል።

5ኛ፦ ኢሬቻ ሲቃረብ
        
"…አቢይ አሕመድ የኢሬቻን በዓል አምልኮ ባእዱን ከተቀበረበት መቃብር ጎትቶ አውጥቶ ሰይጣንን ማምለክ መብቴ ነው እንደሚሉት እንደ ምዕራባውያኑ ሀገራት በኢትዮጵያም አምልኮ በእድ ብሔራዊ በዓል ያደረገ ከይሲ ሰው ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከተሠራው የሰይጣን ማምለኪያ በምንም የማይለየውን የእነ ጠቋርን አምልኮ እልል አስብሎ ኦሮሞን አደባባይ ውሎ ያሳደረ ነው። አውሬው ይሄን የሚቃወሙትን ሰዎች ከፀረ ኦሮሞኖት ጋር አያይዞ እየፈረጀ ባእድ አምልኮን ብሔራዊ የኦሮሞ በዓል ለማስደረግ ከጫፍ የደረሰ ከይሲ ሰው ነው። አቢይ በቀጣይ በጫካ ያሰማራቸው ሸኔዎች ወንድ ለወንድ ሲጋቡ መብታቸው ነው ቢል የሚቃወም ሼክም ሆነ ቄስ ጳጳስ አይኖርም። የኦሮሞን ባህል የሚቃወም ይታረዳል፣ ይታገታል፣ ይጨፈጨፋል። ስለዚህ አውሬው በግድ ሰዉን ያስገብራል። 666 ማለት እኮ ይሄው ነው።

"…አቢይ አህመድ ከእነ በላይ መኮንን ጋር በመመካከር የኢሬቻ በአል መቼ ይሁን ለሚለው የኦርቶዶክስ በዓል በዋለ በሳምንቱ እናድርገው ብለው ወሰኑ። በመስቀሉ ላይ ጣኦት ለማቆም፣ በዓሉን ለማደብዘዝ ነው የመስቀሉ ጠላቶች ይሄን የወሰኑት። ከነሀሴ መመጀመሪያ ጀምሮ ስለ ኢሬቻ መድረስ ሚዲያው ሁሉ ያለመታከት እንዲሰብክ፣ እንኳን ለመስቀልና ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ የሚሉ ነውረኛ ድምጾችን በማጯጯህ የርኩሰት ቃል ከቅዱሱ መስቀል ጋር ይሰበካል። የኢሬቻ ማክበሪያው ቦታ ራሱ መስቀል ደመራው በተለኮሰበት አደባባይ ላይ መልሶ ጣኦት እንዲከበር ይደረጋል። ነጮቹ የወደዱት ይሄንን ነው። ያለምንም ሚሽነሪ ሰይጣኒዝምን የሚያስፋፋ አገዛዝ ማግኘታቸው ሎቶሪ እንደወጣላቸው ሁላ ነው የሚቆጥሩት። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል። “…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥” ማቴ 24፥15

"…ታዲታ የመስቀል ከመድረሱ በፊት ካህናትን በማረድ  እንዲደበዝዝ ካደረገ በኋላ በተቃራኒው ደግሞ የኦሮሞ የዋቄፈና አማኞች የኢሬቻን በዓል የኦርቶዶክስ ካህናትን ጭፍጨፋ በማሰብ የኢሬቻ በአላቸውን በታላቅ ድምቀት አክብረው እንዲውሉ ይደረጋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖንሰር ያደርጋል። በመስቀል በዓል የተከለከለው ባንዲራ በኢሬቻ በዓል የኦነግ ሁሉ ተይዞ ይወጣል። በመስቀል በዓል ሰላም ለኢትዮጵያ ብለው የዘመሩ አማኞች በፖሊስ ዱላ ሲቀጠቀጡ በኢሬቻ በዓል አቢይ ሌባ መሮ ጀግና የሚሉ ወጣቶች አንደኛ ደረጃ ዜግነታቸው ተከብሮ በእንክብካቤ ይሸኛሉ። የመስቀል በዓል ኮስምኖ የኢሬቻ በዓል ደምቆ ይውልለታል ማለት ነው። እነ አቢይም ወደፊት ኦሮጵያ የምትታወቅበትን ትልቁ በአል ኢሬቻ ይሆናል መሥራታቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው።

"…አሁን ዐማራ ራሱን ማዘጋጀት አለበት። ምክንያቱም
      
1ኛ፦ በቅርቡ ኦሮሞ ሰልፍ ይኖረዋል።
2ኛ፦ ፓርላማም ደርሷል።

"…ዘንድሮ በአሜሪካ የሀጫሉን ሙት ዓመት ሰበብ በማድረግ የኦሮሞ ሙሁራን እና ተራው ሕዝብ በተለየ መልኩ ሲመክር እና ከፍተኛ ፖለቲካ ሲሠራ እንዲውል ተወስኗል። ስለዚህ በሀጫሉ ሞት ምክንያት የሀጫሉ ገዳይ አቢይ አሕመድ በሙት ዓመት በዓሉ ፖለቲካ ለመሥራት አስቧል። ገዳዩ አቢይ ዘማች ወታደርና ጦር እንዲሁም የሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ተፍተፍ እያለም ይገኛል። እናም በዚህ ምክንያት በሀጫሉ ሞት ምክንያት እነ ጃዋር አህመድ ዐማራውን ተጠቃቅሰው እንዳስፈጁት ሁሉ አሁንም የሚታረዱ ዐማሮች ይኖራሉ እና መጠንቀቁ አይከፋም። ከሰልፉ በፊት ንፁሐን የሚታረዱ ከሆነ ለሙት ዓመቱ ድምቀት መሆኑንም ዕወቁ። ኦሮሞ የገደለውን ሃጫሉን ዐማራ ነው የገደለው ብለው ሊያስለቅሱት ሁላ ይችላሉ።
       
"…ሰሞኑን በባህርዳር እርቅ ከፋኖ ጋር እያለ እየጨፈጨፋቸው ያሉት ንፁሐን ግን እየተገደሉ ያሉት ፓርላማው በሚቀጥለው ሳምንት ስለሚሰበሰብ ነው። አቢይ ከስብሰባው በፊት የሚጨፈጭፋቸውን ትናንት ከሜክሲኮ ቄራ ድረስ ቀለም እና ዲምላይት መብራት የሰካበትን አስፓልት በማሳየት አደብዝዞታል። ዘግናኙ የዐማራ የሰሞኑን ግድያ በቶፕ ቪው ቀረጻ በአንድ ምሽት ዜና ዝም፣ ረጭ አስደርጎታል። አጎቷ የታረደባት ልጅ አዲስ አበባ ግን አሳመራት ትልሃለች። ዘመዶቹ፣ ቤተሰቦቹ ተፈናቅለው ጎዳና ላይ የፈሰሱበት ጎረምሳ የፒያሳ መብራት ቦግ አለ ብሎ ይደመማል። ውኃ ከጠፋች አንድ ወር ሆኖበት የጠነባ፣ የሸተተ፣ የገማ ሰውነቱን ይዞ ፒያሳ የአዳነች ፋውንቴን ጋር ከነ ጥንባቱ ፎቶ የሚነሳ ጉደኛ ሕዝብ እኮ ነው ያለን።…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከምስጋናው ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ርዕሰ አንቀጿ ዛሬም ሰናፍጭ የበዛባት እንደ መተሬ ኮሶም ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ተደርጋ ነው የተዘጋጀችው።

"…አቢይ አሕመድ ንፁሐን ዐማሮችን የሚያርደው መቼ መቼ እንደሆነ የምታሳይ አይን ገላጭ ርዕሰ አንቀጽ ነው። በተለይ ሟች፣ ታራጅ፣ ተፈናቃይ ዐማሮች የምትታረዱበትን፣ የምትሞቱበትን፣ አቢይ የሚገድላችሁን ቀን፣ ኦሮሙማው መቼ እንደሚሰዋችሁ የሚጠቁም ርዕሰ አንቀጽ ስለሆነ በጥሞና እንድታነቧት ትጋበዛላችሁ።

"…ውኃ ከጠፋ ወር ሆኖት ሰውነትህ፣ ሰውነትሽ ሸትቶ ነገር ግን የአዳነች አበቤ የፒያሳ ፋውንቴን አጠገብ ፎቶ የምትነሣው ዐማራ አንድ ጊዜ አረፍ ብለህ መቼ እንደምታረድ፣ አባትህ ገበሬው መቼ እንደሚጨፈጨፍ የሚጠቁመውን ርዕሰ አንቀጽ አንብብና የኮሪደር ልማቱን ፋውንቴን ወደ ማድነቁ ትመለሳለህ። መብራት ከጠፋ ሳምንት አለፈው እያልከኝ የኮሪደር ልማቱን መብራት እያደነቅክ ትልክልኛለህ። ዥልጥ።

"…ለማንኛውም እንደተለመደው ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጎረምሳው ልጄ ወደቤት ሲገባ ዘወትር እንደሚያደርገው ለሰላምታ ወዳለሁበት ክፍል ብቅ ብሎ ሥራ ላይ ከሆንኩ በዓይኑ፣ ሥራ ከሌለኝ ሰላም ብሎኝ የመሄድ ልምድ አለው።

"…ዛሬም እንደልማዱ መጥቶ ገባ ብሎ እኔ ብቻዬን በኢትዮ ቤተሰብ አየር ላይ ስለፈልፍ ያየኝ እና ተመልሶ ወጥቶ ይሄዳል።

"…ቆይቶ ተመልሶ መጥቶ ፎቶ ያነሣኛል። አንሥቶኝም ይሄድና መርሀ ግብሩን ስጨርስ "አባባ አይተኸዋል ግን ላብህን? በማለት ፎቶውን በቴሌግራም ይልክልኛል።

"…አምላኬ ሆይ እንዲህ ላቤን አፍስሼ፣ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ጩሄ በብዙዎች ተሰድቤ፣ ተረግሜ ሳይቀጥሩኝ ጥብቅና የቆምኩላቸውን የዐማራ ፋኖዎችን ትግል ለድል አብቅተህ ታሳርፈኝ ዘንድም ስለ እናትህ ብለህ ትለመነኝ ዘንድ፣ ጸሎት ምኞቴንም ትፈጽምልኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬው መርሀ ግብራችን እንዲህና እንዲያ እያለ ከዚህ ደርሷል። የቲክቶክ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስም እንዲህና እንዲያ እያልን አብረን እንቆያለን።

• እያረሳችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

“…መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።” 1ኛ ቆሮ 2፥15 … “…አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።” መዝ 141፥3 አሜን…🙏🙏🙏

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመብራት ታሪፍ ነገር

"…በዓለም ላይ ዝቅተኛው የመብራት ታሪፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ ከዓለም ጋር እኩል ለመሰለፍ  የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን" «መብራት ኃይል»

እነሱ:- የነዳጅ ዋጋ ኬንያ ላይ፣ የወኃ ዋጋ ጅቡቲ ላይ፣ የኢንተርኔት ዋጋ ኤርትራ ላይ፣ የመብራት ታሪፍ በዓለም ላይ ውድ ነው። ከዓለም እኩል ለመሆን የዋጋና የታሪፍ ጭማሪ እናደርጋለን። አዳዲስ የግብር ዓይነቶች ማለትም እንደ ፕሮፐርቲና የተሽከርካሪ ታክስ ያሉትን ሁሉም ሀገራት ስለሚያስገብሩ እናንተም ትገብራላችሁ

እኛ:- ኬንያ ውስጥ አማካይ ዝቅተኛ ግብር የማይከፈልበት የደሞዝ መጠን 111.5 ዶላር ወይም 6438 ብር ነው። የገቢ ግብር ደግሞ አራት እርከን ብቻ ያለው ሲሆን ዝቅተኛው የደሞዝ ግብር የሚጀምረው ከ10% ነው። ከፍተኛው የደሞዝ ግብር ደግሞ 32.5 % ሲሆን በዶላር 2326 ወይም በብር 132,558 በላይ የሚያገኝ ሠራተኛ ላይ ይጣላል። 

"…ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛው ግብር የማይከፈልበት ደሞዝ 600 ብር ወይም 10.5 ዶላር በታች ሲሆን 10% ይከፈልበታል። ከፍተኛው የደሞዝ ገቢ ግብር 35 % ሲሆን ደሞዝህ ከ10,000 በላይ ወይም 175.4 ዶላር ከሆነ ደግሞ 35% ትገብራለህ። ቫት፣ ቲኦቲና ወዘተን ሳይጨምር ማለት ነው።

"…ከኬንያና ከዓለም ልምድ በመቅሰም የመብራት፣ የውኃ፣ የፕሮፐርቲ ታክስና የተሽከርካሪ ግብር በመጨመር ከዓለም ጋር እኩል እንዳደረጋችሁን ሁላ የደሞዝ እድገት፣ የገቢ ግብርና ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንንም በልምድ ልውውጡ አካታችሁ ከዓለም ሕዝብ ጋር እኩል አድርጉን ያሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ናቸው። እኔም ለጊዜው ስለዚህ ጉዳይ ባወራ ይሻለኛል።

• እናንተስ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሰላም ሰላም ጎደኞቼ…🖐

"…የኬንያ ባርላማ ተመራጭ ሴትዮ የመወገር ጉዳይ በርዕሰ አንቀጽ መልክ ጥፌላችሁ በዚያው ጠፋሁ አይደል?

"…ጀነራል ጻድቃንን በተመለከተ የሰማሁት ዜና እውነት ይሁን ውሸት ለማረጋገጥ ብዬ አዎ ወደ ትግራይ ክልል እና የዐማራ ክልል የሰላም ካውንስል ቢሮ ሰዎችን የጓዳ የኋላ የጀርባ ታሪክ ለማጥናት ወደ ዐማራ ክልል ሄጄ ነው የጠፋሁት። ይሄ ይታወቅልኝ። አደራ መዝግቡልኝ።

"…የጀነራሉም ጉዳይ አድካሚ ነው የሆነብኝ። ስለ ጀነራል ጻድቃን የመከላከያ ሚንስትሯ ኢንጅነር አይሻ ናቸው የሚያውቁት ተብዬ ነበር። ሚንስትሯን እንደ ዶር ኦላና በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም። የጻድቃንም የኢንጅነርም ስልክ ደግሞ የለኝም።

"…የሆነው ሆኖ እላላጣለሁ፣ ማገዶ እጨርሳለሁ እንጂ የሰማሁትን ለማጣራት የጀመርኩትን መንገድ እስኪያልበኝ ድረስ እሄድበታለሁ። ወፎቼም ይሠማራሉ። የሰላም ካውንስሉን እንኳ አጥቤ የማሰጣበት መረጃ ነው ያገኘሁት። በተለይ ወልቃይቶች ተጠንቀቁ። አትዘናጉ።

"…እኔምለው በርዕሰ ርዕሰ አንቀጼ ላይ የነገርኳችህ የኬንያ ባርላማ ተመራጭ ሴትዮ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታዋ ምን ሆነ ይሆን?

• ማስጠንቀቂያ፦ እንዲህ ዓይነት ግምኛ ነገር ከጎረቤት ሀገር እንዳትኮርጁ አደራ። አደራ በሰማይ አደራ በምድር።

• ቆይቼ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።” 1ኛ ዮሐ 4፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ዘወትር እሁድ ምሽት በመረጃ ተለብዥን በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው መርሀ ግብራች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ልክ ከምሽቱ 2:10 ሲሆን ወደ እናንተ ይቀርባል።

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=0ESdYUvKz0A

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍  "…አሁን ይህቺ አዲስ አበባን በመብራት ኒውዮርክና ዱባይን አስንቃለች የሚለው የብልፅግና ሰበካ ብዙም ሳይቆይ ሌላም ጣጣ ያመጣበታል። በሌሎች ክልሎች ምንም ሳይሠራ በፒያሳና በ4ኪሎ ብቻ በተሰቀለ መብራት ብቻ እንደ ሀገር አድገናል በማለት ይሄን ነገር ደጋግሞ በሬድዮና በቴሌቭዥን ፕሮፓጋንዳ መሥራቱ ሥራ አጡን ኢትዮጵያዊ በሙሉ ለምን በሊቢያ በባህር ሄጄ የአሸባሪ ሰይፍ ይበላኛል? ለምን ወደ ሳውዲ ልሂድ ብዬ ቀይ ባህር፣ አውሮጳ ልሂድ ብዬ የሜዲትራንያን ባህር ይበላኛል? ለምን በሞያሌ በኩል ኬንያ ደብቡ አፍሪቃ ድረስ በእግሬ ልሂድ ብዬ ጉዞ እጀምራለሁ? ለምን እንደ ዱባይ፣ እንደ ኒውዮርክ ወደሆነችዋ አዲስ አበባ አልሄድም በማለት ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ይጎርፋል። ያንጊዜ አዲስ አበባ ሲመጣ የጠበቃትን ኒውዮርክ እና ዱባይ ያገኛል ወይ? መልሱልኝ። የትግሬ ለማኝ የኔቢጤ የበዛው፣ የዐማራ ተፈናቃይ የተከማቸው፣ የሀረርጌ የተራበ ኦሮሞ የተከማቸው፣ የደቡብ ልጆች የታጨቁት አዲስ አበባ በጌታ ሰው በአቢይ አሕመድ ኒውዮርክና ዱባይን አስንቃለች ተብሎ ስለተሰበከ ነው። ባለአደራው የሚባለው ልጅን ፔጅ ስትከታተሉ የችግሩን መጠን ትረዳላችሁ።

"…በኬንያም ልክ አቢይ አሕመድ ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ያስገነባው እንደ አንድነት እና እንጦጦ ፓርክ ያለ መናፈሻ ተሠርቶ ነበር። የራበው ኬንያዊ በመናፈሻው ገብቶ አየር እንዲበላም ተሰብኮ ነበር። ቤት የሌላቸው ኬንያውያንም በመናፈሻው ገባ ብለው እንቅልፋቸውን ለጥጠው ይወጡ ዘንድ ተሰብከው ነበር። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚደፍሩት ሬስቶራንቶችም በዚያ መናፈሻ ውስጥ ነበሩ። በቀደም ዕለት ለተቃውሞ የወጣው የራበው፣ የጠማው የናይሮቢ ሕዝብ ግን ያው በቪድዮው ላይ እንደምታዩት እሳት ለቆበት መናፈሻ ፓርኩን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ዐመድነት ቀይሮታል። ቅድሚያ ለጤና፣ ቅድሚያ ለትምህርት፣ ቅድሚያ ለዳቦ ያለው ሕዝብ ፓርክና መናፈሻ ዳቦ አይሆኑንም በማለት በደቂቃዎች ውስጥ አውድሞታል። እናም ራበኝ፣ ሥራ አጣሁ፣ ቤቴ ፈረሰ፣ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ አጣሁ፣ የት ልድረስ? ኧረ የውኃ፣ የመብራት ያለህ! ተቸገርኩ ኧረ ኡኡኡ ብሎ ለሚጮህ ሕዝብ መናፈሻ ሠርቼልሃለሁ። ናና ተዝናና፣ ባይበላስ፣ ባይጠጣስ ቢቀርብህ ብለህ ስታሾፍበት የሆነ ቀን፣ የሆነ ሰዓት ላይ እንዲህ ጉድ ይሠራሃል።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እግዚአብሔርን የማመስገን ፍጥነታችሁ ገርሞኛል። አስደምሞኛል። እግዚአብሔር ይመስገን። እንደ እኔ እድለኛ እኮ የለም። ጠዋት ጠዋት ሺዎች እግዚአብሔር ይመስገን ብለው እንዲያመሰግኑ ምክንያት በመሆኔ እንደኔ እድልኛ ማን አለ። አሁንማ ለብዙዎች እንደ ሱስ ሆኗል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ለዛሬ ያዘጋጀሁላችሁ ፓርክና ኮሪደር ልማትን በተመለከተ ነው። ሥራ አጥ በበዛበት፣ ፋብሪካዎች ሥራ ባቆሙበት፣ መብራትና ውኃ ሕዝቡ ተቸግሮ በሚናውዝበት ምድር፣ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪ የምናቀርበው ምግብ ስለሌለን በሚቀጥለው ዓመት ተማሪ ለመቀበል አንችልም በሚሉበት በዚህ ጊዜ ከተማ ቀለም ቀብቶ፣ ፒያሳና ሜክሲኮ አራት ኪሎ ላይ የቡና ቤት መብራት ሰቅሎ አድገናል ማለት እንዴት ይቻላል? ብሎ የሚጠይቅ በጣም ትሁት ሲበዛ ጨዋ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ነው ያዘጋጀሁላችሁ።

"…በኬንያ ናይሮቢ የራበው ሕዝብ የአንደነት ፓርክ፣ የእንጦጦ መናፈሻን የመሰለ ስፍራ በደቂቃ ውስጥ ምን እንዳስመሰለውም ርዕሰ አንቀጼ ይዳስሳል። እናሳ ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?

• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኦሮግሬዎች ምንድነው የሚሉት መሰላችሁ…

"…የቄሮ ትግል ኬንያ ገብቷል ነው የሚሉት። ከራስ በላይ እጅ አጣምሮ እዬዬው ራሱ ከነ ምልክቱ አልቀረም።

"…እኔ ዘመዴ በቀደም ዕለት ቀኝ ትከሻዬን ሸክኮኝ በጻፍኩት ርዕሰ አንቀጼ ላይ ምን ብዬ ነበር።

"…በትግራይ 1ሚልዮን ትግሬ ጨፈጨፈ የሚባለው የኦሮሞው ጄነራል ባጫ ደበሌ ማዕረጉን አውልቆ በቀጥታ አቶ ተብሎ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በአምባሳደርነት ተላከ።

"…ቄሮን ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ አድርጎ እነ አምባቸውን፣ እነ ጄነራል አሳምነውን ከአቢይ አሕመድ ጋር ተጠቃቅሶ ያስገደለው፣ በሚልዮን ኦርቶዶክሳውያን በኦሮሚያ መታረድ፣ መጨፍጨፍ፣ አቢያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣ መውደም፣ በባዶ እጅ ከመሬት ተነሥቶ በዘረፋ ቢልየነር የመሆንን ጥበብ እንደ ሥራ ያስተዋወቀው ወንጀለኛው ጃዋር መሀመድ ካልጠፋ ሀገር ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተሰደደ…

"…በኢንጂነር ስመኘው ግድያ እጁ እንዳለበት የሚነገረው አቶ የኦህዴዱ ብርሃኑ ፀጋዬ ጅቡቲ በአምባሳደርነት ተመደበ…

"…የሻሸመኔው የኮሮጆ ሌባ አባ ቁጥሬ ትውለደ ትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ ገብረ ኪዳን የኢጋድ ዋነኛ ሰው ሆኖ ተመደበ…

"…የዊልያም ሩቶ ከአቢይ ኋላ መጥቶ በምዕራባውያኑ እንደ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መታየት፣ መወደስ፣ ፈረንካ በፈረንካ መሆን…ወዘተ ቢበሰጫቸውና ቄሮን ቢያሰማሩት ይፈረድባቸዋልን?

"…ትግሬዎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ። በራያ ሰልፍ አለ የምትሉ አቁሙ። ባታቆሙ ግን ውርድ ከራሴም አሉ። ሰልፍ እንዳለም ራሳቸው አውርተው፣ ሰልፍ ከልካይ መሆናቸውንም ራሳቸው አውርተው፣ ጭራሽ ዘመድኩን ፔጃችንን ስለምትከታተል ንገራቸው አላሉኝም። 😁 …አይ የትግሬ ጥጋብ እኮ ግርም ነው የሚለኝ። እኔ ዘመዴማ ስትጨፈጨፍ እዘግብልሃለሁ፣ ስትራብም፣ ስትጠግብም እዘግብልሃለሁ። ከዐማራ ጋር ግን ፈልቶብሃልና ሥራህ ያውጣህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆ 3፣ 22-23 “…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ብአዴን የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ጠለምት እንዲገቡ መስማማቱ ተነግሯል። በዚህም ምክንያት የዋልድባ መነኮሳት ሌላ ዙር አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተሰምቷል።

"…የሰኔ 30ን መቃረብ ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሃይማኖት መሪዎች ጭምር የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ከመደረጉ ጎን ለጎን የብልፅግናው አገዛዝ እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አመራሮች በአክሱምና በሽሬ ከተሞች በተደጋጋሚ በመገናኘት ወደ ጠለምትና ወልቃይት በሚገባበት መንገድ ዙሪያ ከስምምነት መድረሳቸውም ነው የተነገረው።

"…ይሄንኑ የህወሓትንና የኦሮሞ ብልፅግናን ስምምነት ተቀብሎ በአግባቡ በመተግበር ያስፈጽም ዘንድ በድኑ ብአዴን የተስማማ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎችን ጨምሮ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ አንባሳደሮች ያሉበት ቡድን አኩስም ከተማ መግባቱም ተሰምቷል።

"…የዐማራ ሚሊሻዎች ሱዳን የያዘቻቸውን የኢትዮጵያ ግዛቶች በማስለቀቅ መሬታቸውን አስመልሰው የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ጦርም ወደ ሶማሊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ጦሩን ማስገባቱ ተሰምቷል። ብልፅግና የሱዳን ኃይሎች ያቀረቡትን ስሞታ የሰማ ቢሆንም ጦሩ እንደ ብራና በመወጠሩ እስከአሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ለሱዳን አለመስጠቱም ተነግሯል።

"…በወልቃይት ጉዳይ ወያኔ ያዝ ብታደርግልን እና የፋኖን ኃይል ካዳከምን በኋላ ወልቃይትን አሳላፈን ብንሰጥ አይሻልም ወ? በማለት አሮጌው ብአዴን አለቆቹን ኦሮሞዎቹን መጠየቁ፣ መማጸኑ የተሰማ ሲሆን የኦሮሞ ብልጽግናና በብአዴን ውስጥ አሁን ኃላፊነት የተሰጣቸው የወሎ የወሀቢያ እስላም አመራሮች "አይሆንም እንዲያውም አሁን ወልቃይትም፣ ጠገዴና ራያን ህወሓት ብትወስድ ጥሩ ነው። እኛም በፋኖ ለማሳበብ ያመቸናል" የሚል መከራከሪያ ማቅረባቸውም ተሰምቷል።

• እንግዲህ እየተጨፋጨፋችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው…የቀጠለ…✍✍✍ "…አሁን ፓርላማው እስኪያልፍ ቁጠሩ ብቻ የሚታረዱ ዐማሮችን ብዛት። በፓርላማው ላይ የኢትዮጵን ሕዝብ ወክሎ ልክ እንደ ኬኒያ ኑሮ አቃተን፣ ከበደን፣ ታክስና ቀረጥ፣ ቫት ይቀንስ፣ ነዳጅ ለምን፣ ኑሮ ተወደደ፣ ሥራ አጥ ጨመረ ብሎ የሚጠይቅ ባይኖርም ምንአልባት የሚጠይቅ አይጠፋም ተብሎ ስለሚታሰብ ከወዲሁ ሰዉ በዘግናኝ፣ በዘግናኝ ግድያዎች እንዲደነዝዝ ይደረጋል። አገዳደሉም የሚሰቀጥጥ ይሆናል። ከዚያ ድንዙዙን ፓርላማ ሰብስቦ፣ በጭካኔ አረመኔያዊ ግድያ የደነዘዘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ "ቃል በገባነው መሠረት የኮሪደር ልማቱን አቀላጠፍንልህ፣ ዘንድሮ 7 ቢልዮን ችግኝ ልንተክል ነው እንኳን ደስ ያለህ" በማለት አስጨብጭቦት ይወጣል። ታዘቡኝ፣ ቱ ምንአለ በሉኝ የሚሆነው ይሄው ነው። ተመካክረው ስለሚሠሩ አሁን ሸኔው ድምፁን አጥፍቷል።

"…ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የዐማራው ጦርነት መዘጋት፣ መቋጨት አለበት ብሎ ብልጽግና የኦሮሞ ወጣቶችንና በጴንጤ ፓስተሮች ሰበካ የተነዱ የደቡብ ልጆች፣ በአፈሳና በፈቃደኝነት በአውሮጵላን፣ በመሂና፣ በኮንኮላታ፣ በእግር ጭምር ወደ ዐማራ ክፍል በገፍ እያስገባ እነሱም ነው። ነፍስ ይማር።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አቢይ ንጹሃን ዐማራዎችን የሚገድልበት ወይም የሚጨፈጭፍበት ግዜ መቼ ነው…?

"…በፊት በፊት ወደ መንበረ ሥልጣኑ በመጣ ጊዜ አቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ውስጥ በዐማሮች ላይ ጭፍጨፋ የሚፈጽመው ኢትዮጵያንን ሁሉ ሸውዶ፣ ነጮቹ ግን ይሁነኝ ብለው ድንቁርና መሃይምነቱንም እያወቁ ለኋለኛው ጥቅማቸው ሲሉ ምንም ሳይሠራ፣ የአላባና ጠምባሮ፣ የኮተቤና የገዳም ሰፈር ልጆች እንኳ ሳያውቁት ከመሬት አንሥተው የኖቤል ሽልማት ሸልመው ዝነኛ አድርገውት በነበረ ጊዜ አሁን እንዲህ ካካ እንደነካው እንጨት ተጸይፈው ላይጠሩት በየቦታው ኢትዮጵያን ወክሎ ለስበሰባ፣ ለውይይት፣ ለጉብኝት በጠሩት ጊዜ ከሃገር ሲወጣ የእሱን እግር መውጣት ተከትሎ ግድያ፣ ጭፍጨፋ ይፈጸም ነበር። የቡራዩ፣ ከታ፣ አሸዋ ሜዳው፣ የመተከል፣ የወለጋው፣ የከሚሴ፣ የአጣዬው ወዘተን እዚህ ማንሳት ይቻላል።

"…አቢይ አሕመድ ገዳይ አረመኔ ተግባሩ ተነቅቶበት፣ ውሸታም፣ አቅመቢስ መሆኑ ተገልጦበት እንኳን ለግብዣ ሊጠሩት የደቡብ ሱዳንና የጅቡቲ ሚጢጢዬ መንግሥታት እንኳ ተጠይፈውት ወደ አዲስ አበባ ለጉብኝትም፣ ለስብሰባም መምጣት ካቆሙ ወዲህ ግን ሀገር ውስጥ እያለ አቢይ አህመድ መቼ መቼ ዐማሮችን እንደሚጨፈጭፍ፣ የደም ግብርም ለአምላኩ፣ ለፈጣሪው ለዲያብሎስ እንደሚያቀርብ በስሱ ለዛሬ በርዕሰ አንቀጻችን እንመለከታለን።

1ኛ፦ የፓርላማ ስብሰባ ሲቃረብ፦

"…አረመኔ አራጁ ልቡሰ ሥጋ ጋኔሉ አቢይ አህመድ የፓርላማ ስብሰባ በቀረበ ጊዜ ስብሰባው ከመድረሱ ጥቂት ሳምንታት በፊት ዘግናኝ ግድያዎችን፣ ጭፍጨፋዎችን በዐማሮች እና በዐማራ እንስሳት ላይ ሳይቀር ይፈጽማል። አቢይ ይህንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ የሚፈጽመው የመከላከያ ልብስ ባለበሳቸው የኮሬ ነጌኛ አራድ ቡድኖች እና አልያም በኦነግ ሸኔ ስም በሚያሰለጥናቸው ነፍሰ በላ የራሱ ቅልብ አራጅ ቡድኖች አማካኝነት ነው። የፓርላማ ስብሰባ በቀረበ ቁጥር የዐማራን መታረድ እንደ ጉድ ትሰማላችሁ። ሰሞኑን በወለጋ፣ በጅማ፣ በጎጃም፣ በወሎ እና በሰሜን ሸዋ የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ ማዳበሪያ ለመቀበል ከተማ የሄዱና በእርሻ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ገበሬዎችን ከነበሬዎቻቸው አይን፣ አይናቸው ላይ ተኩሰው የሚገድሉት፣ ከእስር ቤት አውጥተው በአደባባይ የሚረሽኑት በሚቀጥለው ሳምንት አቢይ በፓርላማ ስብሰባ ስላለው ነው።

"…አቢይ አሕመድ የፓርላማ ስብሰባ ሲደርስ በፓርላማው ውስጥ ከሕዝብ እንደራሴዎቹ የተለያዩ ፈታኝ ጥያቄዎች ለምሳሌ የነዳጅ መጨመር፣ የቤት ኪራይ መናር፣ የምግብ ነክ ምርቶች ዋጋ ሰማይ መንካት፣ ስለ ሕገወጥ እስር፣ ግድያ፣ ስለ ትምህርት መዝቀጥ፣ ስለ ሥራ አጥነት መስፋፋት ወዘተ የሚል ጥያቄ እንዳይመጣበት ሲል አቅጣጫ ለማስቀየስ ሲል ያው ዘሩ እንዲጠፋ የተፈረደበት በሞቱ የትግሬ ነፃ አውጪዎችና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ጮቤ የሚረግጡበት የፈረደበትን ዐማራ በባትሪ ፈልጎ ዕጣ የወጣበትን ዐማራ ወይ በድሮን አልያም በታንክ እና በክላሽ፣ ወይም ደግሞ ወታደሩ ቤት ለቤት ገብቶ በሳንጃ በካራ በማረድ አረመኔያዊ ተግባሩን ይፈጽማል። ይሄ አንደኛው ነው።

"…በነገራችን ላይ አቢይ አህመድ መሃይም ስለሆነ ድንገት ለሚጠየቅ ጥያቄ መልስ መስጠት አይችልም። አለመማሩ ጎድቶታል። አቢይ አሕመድ ፓርላማ ላይ ለሚጠየቀው ጥያቄ ጥያቄዎቹ ቀደም ብለው ተሰብስበው ተሰጥተውት፣ ሁለት ሳምንት ሙሉ እንደ ቲያትረኛ፣ እንደ ፊልም ባለሙያ መልስ አጥንቶ፣ በቃሉ ሸምድዶ አክቲንግ ሠርቶ ነው የሚመጣው። እንጂ ወዲያው ለሚጠየቅ ጥያቄ መልስ የለውም። አቢይ አሕመድ ጋዜጠኛ ጠርቶ እንደ መሪ ቃለመጠይቅ አድርጎ አያውቅም። አቢይ አሕመድ ጋዜጠኛ ጠርቶ ራሱ አውርቶ፣ የሚፈልገውን መልእክት፣ ነቆራም ሆነ ዛቻ ተፍቶ፣ ራሱ አውርቶ ራሱ ስቆ፣ ራሱ ጠይቆ፣ ራሱ መልሶ፣ ራሱ አድንቆ ይፈጽማታል እንጂ አንድም ጋዜጠኛ አስቀምጦ ፈታኝ ጥያቄ ተጠይቆ እሱም መልሶ አያውቅም። ሰይፉ ፋንታሁን እና ሶልቴክም መዝናኛ ጥያቄ አስቀድመው አጥንተው አንዴ ሠሩት እንጂ አቢይ አሕመድ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ፊት ቀርቦ የመናገር ወኔም፣ ድፍረትም፣ በዚያ ላይ ዕውቀትም የለውም።

2ኛ፦ ኦሮሞ ለሆነ ጉዳይ ሰልፍ የሚወጣ ከሆነ

"…ሌላው አቢይ አህመድ ዐማራን የሚያርደው ጽንፈኛው የኦሮሞ ኃይል አቢይ አህመድን የሚደግፍ ሰልፍ እንዲወጣ ዝግጅት ካለ ወይም ሌላ አቢይ የሚፈልገው ብቻ የሆነ የሚወጡት ሰልፍ ካለ ንጹሃን ዐማራዎች ይገደላሉ። ይህ ከሆነ በኋላ ጽንፈኛው ኦሮሞ ደግሞ አቢይን ለማወደስ በሰልፉ ላይ ላንቃው እስኪላቀቅ ድረስ እየጨፈረ የአቢይ አህመድን ፎቶ በባነር አሠርቶ አቢቹ ኮ፣ አቢቹ ኬኛ ሺ ዓመት ግዛን፣ አቢቹ አንደኛ፣ በአቢይ የመጣ በዓይናችን መጣ እያለ ሰልፍን አሙቆ የአቢይን ፍላጎት ሲያረካ ይውላል። በሀሰት ትርክት የኦሮሞን ጡት እና እጅ ቆርጧል የሚሉትን ዐማራን አቢይ አሕመድ ቀደም ብሎ ከሰልፉ በፊት ገድሎ፣ ጨፍጭፎ ካሳያቸው ብቻ ነው ኦሮሞ ፈንጥዞ ሰልፍ የሚወጣው። ይሄን ልብ ብላችሁ ታዘቡ።

"… አጅሬው አቢይም ይህን ስለሚያውቅ የሰልፉ ቀን ሲቃረብ ንጹሃን ዐማራዎችን ቦታ አጥንቶ፣ ባላሰቡበት ሁኔታ ውስጥ ያርዳቸዋል። ሀገር አማን ብለው ለገበያ ተሰብስበው ሲገበያዩ፣ ወይ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ሰንበቴ ውለው ጽዋ ይዘዉ ሲመለሱ፣ ወይ ማዳበሪያ ለመውሰድ ቀበሌ ሲሰበሰቡ፣ እንዲህም እንኳን ቢያጣ ቢያጣ በየቤቱ ገብቶ ፈልጎ ይጨፈጭፋቸዋል። ያኔ የኦሮሞ ጽንፈኛም በደስታ አዲስ የሚገዛ ገንዘብ ያለው አዲስ የባህል ልብሱን ገዝቶ፣ ገንዘብ የሌለውም ያለችውን በእንዶድም ቢሆን ፈትጎ አጥቦ ለብሶ የሰልፉ ቀን ኢሾ እያለ በደስታ ሰልፉን ያሞቃል። አቢይም ከሰለፉ የሚፈልገውን ትርፉን ያገኛል ማለት ነው። ለኦሮሞ ዐማራን በማስጨፍጨፍ እሱ በኦሮሞ ዘንድ ታማኝነቱን ይገልጻል።

3ኛ፦ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአደባባይ በዓላት ሲደርሱ

"…ይሄ ዋነኛው ነው። የአቢይ አሕመድ መንፈሱ የሚረበሸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአደባባይ በዓላት ማለትም እንደ መስቀል እና ጥመቀት ያሉ በዓላት ሲቃረቡ ግድያ ይጀምራል። የመስቀልና የጥምቀት በዓላት ከመድረሳቸው በፊት የሳዲስቱ የፌደራል ፖሊስ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል የሚመራው የፌደራል ፖሊስ ተቋም "አሸባሪዎች ተያዙ፣ ይሄን ያህል ፈንጂና ቦንብ በቁጥጥር ስር ዋለ፣ መጪውን የመስቀልና የጥምቀት በዓል ላይ ሁከት ለመፍጠር፣ ደም ለማፍሰስ ሲሉ ያዝኳቸው፣ አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ በማለት ያስወራል። ይሄኔ ሕዝቡ ለመስቀልም፣ ለጥምቀትም ሳልወጣ አርፌ በቤቴ ለምን አልቀመጥም በማለት ተሸብሮ ከቤቱ ይቀርለታል። ዋና ፍላጎቱም ይሄው ነበር። ይሄ ዜና ለኢድና ለአረፋ፣ በዓል ዜናው አይሠራም። አሸባሪም አይኖርም። ማሸበር የሚፈለገው ኦርቶዶክስን ስለሆነ ነው ዜናው የሚሠራው።

"…ከሽብር ዜናው በተጓዳኝ ጫካ ካለው ፕላን B ሸኔ ጋር በመመካከርም ወይ በራሱ በሸኔ ታጣቂ አልያም በብራኑ ጁላ መከላከያ ተብዬው እንደ ሸኔ ዊግ ጠጉር አድርጎ በከተሞች አቅራቢያ ያሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ወይም ገዳማት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ካህናትን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲታረዱ ያስደርጋል። ያም ዜና በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት እንዲሠራጭ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት የኦርቶዶክሳውያን በዓላት ድባቡ የሞቀ የደመቀ እንዳይሆን ያስደርጋል። ምእመንም በፍራቻ ከቤት በመዋል፣ ከቤት በመቅረት በፍራቻ፣ በስጋት፣ በጭንቀት፣ ወይም በመሰደድ በዓላቱ ደምቀው እንዳይከበሩ…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።” ኢሳ 40፥31

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጀምረናል ገባ ገባ በሉ።

"…ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ከሀገረ ማርያም (ሜሪላንድ) እና እኔም ዘመዳችሁ ከአጎት ሀገር ጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ በየሳምንቱ በዕለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርበውን መርሀ ግብር አሁን ጀምረናል

አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…
Subscribe to a channel