zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በዓለም ላይ ሰላም ሳይኖራት የሰላም ሚንስትር መሥሪያ ቤት ያቋቋመችው ብቸኛዋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት። እናም ይሄው ቀልደኛ የብልፄ መሥሪያ ቤት በኢትዮጵያ የጠፋውን ሰላም በማራቶን ሩጫና በቀበሌ ኮንፍረንስ አመጣዋለሁ እያለ ነው።

"…በውኑ ሰላም የቀረ ደሞዙ በሚቆረጥበት በካድሬዎች የጎዳና ላይ ሩጫና የቀረ ማዳበሪያ፣ ስኳርና ዘይት በሚከለከልበት በቀበሌ የሴፍቲኔት ኮንፍረንስ ስብሰባ ይመጣል? ይገኛል? ይሰፍናልን?

"…የሮጡትም አዘጥዝጠው ላብበላብም ሆነው፣ ትርፉን ቲሸረት አግኝተው ወደ ቤታቸው ገብተዋል። ሴፍቲኔቶችም ከቤተ ክርስቲያን ቀርተው፣ እንቅልፋቸውን በአዳራሽ ለጥጠው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። ሰላም በዚህ መልኩ ትመጣለች ወይ?

"…ሁለት መኪና ሙሉ ተማሪ ኦሮሞዎች አግተው ወስደው፣ መውሰድ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ ተማሪ 700 ሺ ብር በባንክ ከፍላችሁ መውሰድ ትችላላችሁ በሚባልበት ሀገር፣ ይሄንኑ ዜና አንድም ጋዜጠኛም ሆነ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይዘግቡት መመሪያ ወርዶ እንደተራ ነገር በሚቆጠርበት ሀገር ሰላም፣ ሰላም ቢባል እንኳን ሰላም ወሮ ሰላማዊት እንኳ ትሰማለች፣ ትመጣለችስ ወይ?

"…ሰላም በዲስኩር፣ ሰላም በድራማ፣ ሰላም በቲያትር፣ ሰላም በፊልም፣ ሰላም በሙዚቃ፣ ሰላም በኮንፈረንስ፣ ሰላም በሩጫ፣ ሰላም በፉገራ፣ ሰላም አራጅ አሳራጁ አቢይ አህመድ እያለ፣ አጨብጫቢ ለምን ብሎ የማይጠይቀው እንቅልፋሙ ፓርላማ እያለ፣ አትልፉ አይመጣም። ሰላም ገዳይ ሥርዓት እያለ አትመጣም። ትፈራለች። ትደነግጣለችም።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሉ ጎዶኞቼ ለማንኛው ነገ ዕለተ ሰንበትም፣ በዚያውም ሰኔ 30ም ነው። ከረሳችሁት ላስታውሳችሁ ብዬ ነው።

"…ደግሞ ግርርም እንዳይላችሁ ሥርዓተ ቅዳሴውም በቤተ ክርስቲያን ነው የሚፈጸመው።

• ሌላው ደግሞ አዝማሪ አቡዱ ኪያር አዲስ ዘፈን አውጥቷል እንዴ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኔምለው ጀርመንና አርጀንቲና ለአፍሪካ ዋንጫ አለፉ ወይስ ወደቁ…? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ምንአለ ሰላምን ብትሰብክ? ይለኛል… መለስኩለታ… የማንም ንፍጣም ከመሬት ተነሥቶ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ እንደ በግ አጋድሞ፣ እንደ ዶሮ ጨምቆና አንቆ ያለሕግ የማንም ወጠጤ ቦዘኔ አዋርዶ ከሚገድልህ ራስህንም ቤተሰብህንም ተደራጅተህ እና ታጥቀህ ተከላከል። እየፎገላ ሊያርድህ የሚመጣን ሰገጤ የሰው መቶ ኩንታል ገተት ፋራ መክተህ፣ አናት አባቱን ብለህ አንክተው፣ ከበረታብህ ጥለህ ውደቅ፣ አልያም ጥለህ እለፍ ብሎ እንደ መስበክ ያለ የሰላም ሰባኪነት ከየት አባክ እንዲመጣልህ ትፈልጋለህ? ሰላምን ለማያውቅ ደንቆሮ አራጅ መድኃኒቱ ይሄ ነው ብሎ ከማስተማርስ ውጪ ሌላ ምን ዓይነት ስብከት እንዲሰበክለት ነው የሚፈልገው። አዛኜን ከእኔ በላይ የሰላም ሰባኪማ የለም።

ረስቼው…

"…ቤተ ክርስቲያን ከነ ካህኑና ምእመኑ መስጊዱንም ከነ ሼሁና ሙኢመኑ፣ የደረሰች ነፍሰጡር አርዶ ጽንስ የሚበላ፣ ሰው እያገተ ሚልዮኖችን የሚለቅም፣ ለእንስሳት እንኳ የማይራራን አረመኔ ሴቶችን የሚደፍር፣ የሚጨፈጭፍም፣ ሕጻናትን አራጅ አሳራጅን አሸባሪ መክቶም አንክቶም አናቱን ብሎ ፈርክሶ ራስን መከላከል "ጽድቅ" ነው። የሀገርን ነቀርሳ መንቀል ጻድቅ ያደርጋል፣ ሃውልት ሁላ ይቀረጽለታል።

• እህዕ…ሚልኢላል ኢሄ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በፍልስጤማውያን፣ በበርማውያን፣ በሶሪያ፣ በሊቢያና በየመን፣ በኢራቅም፣ በሱዳንም በደረሰው ውድመት፣ ጭፍጨፋ እንደ አንድ ክርስቲያን አዝናለሁ። ይሰማኛልም። እውነቱን ለመናገር ግን ኀዘኔ ከሌሎቹ ጋር ሲነፃፀር በኢትዮጵያ አስላም የዐማራ ወገኔ ላይ ከደረሰበት ኀዘን አይበልጥብኝም።

"…በኢትዮጵያ ምድር አንድ ፓስፖርት የሚጋሩ ዜጎች በዜግነት ቢሉ አንድ የሆኑ የአንድ ሀገር ልጆች በአገዛዝ ሴራ ምክንያት እንዲህ መንደር ሙሉ እስላም በማንነቱ ብቻ ተለይቶ ሲጨፈጨፍ እያየሁ "ፍልስጤም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብዬ የአዞ እንባ አላነባም። ከምር ይሄ አስመሳይነት ነው። ፍልስጤማውያን ራሱ ቢሰሙን አዛኜን ያፍሩብናል። ይስቁብናልም።

"…አሁን በኢትዮጵያ እስላም ስለሆንክ ከአራጆች ሰይፍ አትድንም። ዐማራ ከሆንክ ሃይማኖትህ፣ ኦርቶዶክስ ከሆንክ ደግሞ ማንነትህ አያድንህም። ወላ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ሲዳማ ወዘተ ሁን ለደንታህ ነው። ኦርቶዶክስ ከሆንክ ትገደላለህ፣ ትታፈናለህ፣ ትሰወራለህ። ትታረዳለህ። አለቀ። ዜና አይሠራልህ፣ ጭራሽ "እንኳንም ሞትክ ፀሐይ እንዳይመታው ለአስከሬንህ ዛፍ ነው የምተክልልህ ትባላለህ። እናም ወዳጄ መጀመሪያ ማንነትህን አድን። እሱን አስቀድመው።

• ፀቡ እንደዚያ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ዐማራ ከሆንክ መጀመሪያ ከሁሉ አስቀድመህ በኢትዮጵያ ውስጥ በማንነትህ ምክንያት ተለይተህ የዘር ጭፍጨፋ እንደተፈጸመብህ፣ አሁንም እየተፈጸመብህ እንዳለ እና ለወደፊቱም ከአሁኑ ከወዲሁ ዋጋ ከፍለህ ካላስቆምከው በቀር ይኸው የዘር ጭፍጨፋ በከፋ መልኩ እንደሚፈጸምብህ እመን። ያመነ ነው የሚድነው። ይሄ ሥልጣኑ፣ ገንዘቡ እና ዝናው ይቆይህ ከድል በኋላ ይደርሳል። መጀመሪያ ለምን እና ለማን እንደምትታገል ዕወቅ ተረዳ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹ ከ11 ሺ ሰው በላይ በዚህች ደቂቃ ውስጥ እንዳነበበው ቴሌግራም እያሳየን ነው። ከዚህ በኋላ እንጃልኝ እንጂ እስከአሁን በኢሞጂም ቢሆን 😡 የተናደደና የተቆጣ አንድም ሰው አላየሁም። ቢቆጡም ግን እኔ ኬሬዳሽ…

"…ቀጥሎ ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። በጨዋ ደንብ ሓሳብ ስጡ። በጨዋ ደንብ ሞግቱ። ሄጵ ብዬ እሳደባለሁ ብትል ግን እቀስፍሃለሁ። እኔ ምንም አይቀርብኝ የወሬ ጠኔ የሚደፋህ፣ በአናትህም የሚተክልህ አንተኑ ነው። አይደለም እኔን እርስ በእርስም በጨዋ ደንብ መሟገት እንጂ ስትሰዳደብ ባገኝህ አጠናግሬ ነው ጠፍጥፌ የምቀስፍህ። ተናግሬአለሁ።

• በሉ 1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ወጣ በሚል የምከሰስበት ወንጀል የለኝም። ወዳጄ አንደዜ ከሁሉ ጋር ከተነካካህ በኋላ አረማመድህ፣ አበላልህን አነጋገርህ ሁላ በጥንቃቄ የተሞላ ነው መሆን ያለበት።

"…አንተ "የዐማራ ሕዝብ ጄኖሳይድ አልተፈጸመበትም" ብለህ ለእስክንድር ነጋዋ ገንዘብ ያዥ ለወሮ ሕይወት በተናገርከው ቃል እሷም አንተንና እስክንድር ስትጣሉ ጠብቃ በሀብታሙ አያሌው በኩል ድምፁን ለቅቃ በነበረ ጊዜ የጨሰውን አቧራ ታስታውሳለህ። ያ እንደምንም አልፎ ቀጥሎ ደግሞ ሰሞኑን ከጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው ጋር ባደረግከው ቃለመጠይቅ ላይ "ህወሓት ልትወረን ብትመጣም እንኳ እኛ ዐማሮች ጥይት አንተኩስባትም" ብለህ በተናገርከው ንግግር ብዙ አዋራ እንዴት እንደ ጨሰ የምታስታውሰው ነው። ህወሓት ብትመጣ እኮ ቅድሚያ በጎንደር እና በወሎ በኩል አልፋ ነው። አንተ ጎጃም ተቀምጠህ ወልቃይት፣ ራያ እና ጠለምት እየተኮሰች ብትመጣም እኛ አንተኩስባትም ማለት ምን ማለት ነው? በቀደም ራያ አላማጣ ስትገባ እንኳ 50 ሺ ዐማራ ያፈናቃለችው ህወሓት ጎንደር ስትገባማ ስንት መቶ ሺህ ዐማራ እንድታፈናቅል ነው የፈለገው ይሄ ልጅ። ይሄ ዐቋም የሙሉ የጎጃም ፋኖ ነው እንዴ? በማለት ሌላው ዐማራ መደንገጡን ለአንተ መቼም አልነግርህም። እናም ወንድሜ ለንግግርህ ልጓም ብታበጅለት መልካም ነው። ይሄን የምነግርህ ካለን ቀረቤታና ወዳጅነት በመነሣት ጭምር ነው።

"…በሰሞነኛው ከኢኤምኤስ ጋር ባደረግከው ቃለመጠይቅም ላይ እንደ ድንጋይ ደርቄ የቀረሁበትን ጉዳይ ነው ለኢዜማ ግንቦት ሰባቱ ሚዲያ የሰጠኸው። አለቃህና ወንድምህ የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊው ጠበቃ አቶ አስረስ ዳምጤ ለግዮን ሚዲያ "በጎጃም አንድ የፋኖ አደረጃጀት እንዳለ ገልጾ፣ የእነ ማስረሻና የእነ እስክንድር ነጋን አካሄዳቸውን አበሻቅጦ፣ ገስጾ የሰጠውን ቃለመጠይቅ አዳምጠን ሳናበቃ አንተ በአናቱ መጥተህ ከህዝባዊ ሠራዊቱ ጋርም ወደ አንድነት ልንመጣ ነው ብለህ ቃልህን ስትሰጥ ደርቀን፣ ፈዝዘን ነው የቀረነው። አንድነቱን ጠልቼ አይምሰልህ። ስለ ሕግ፣ ስለ መርህ ነው እያወራሁህ ያለው። የአንተን ቃለ መጠይቅ ተከትሎም የእነ ሀብታሙ አያሌውን እና የግንባሩን ሰዎች በቲዩተር መንደር ጮቤ ስታስረግጥ ዋልክ። እኛ በጎንደርም፣ በጎጃምም፣ በሸዋም፣ በወሎም ያለው መኖርም ያለበት አንድ የፋኖ አደረጃጀት ነው ብለን የምንሞግት ሰዎችን ደግሞ የሌለ አንገት አስደፋኸን። ይሄ ከመቸኮል እንደሚመጣ ባውቅም አካሄድህ ግን እየሸከከኝ መምጣቱን ሳልደብቅህ አላልፍም። ይሄን እንድታውቅልኝ ይሁን። የሸከከኝ ደግሞ የአንተ ተደጋጋሚ ፋውል መሥራት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ጠበቃ አስረስና እርበኛ ዘሜ የሚመሩትን የጎጃም ፋኖን አካሄድ ለመመርመር እና ለመሞገት ቀኝ ትከሻዬንም እየበላኝ፣ እያሳከከኝ ስለመጣም ጭምር ነው። ይሄንም ሳልደብቅህ አላልፍም።

"…ተመልከት አያያዝ ባለመቻላችሁም ይሁን በስንፍናችሁ ኮሎኔል ጌታሁንን የመሰለ ጀግና ታጋይ ከጎጃም የዐማራ ፋኖ ወጥቶ የእነ እስክንድር ሠራዊት የሚባለው ጋር እንዴትና ለምን ተቀላቀለ? እናንተ እነ አስረስ፣ እነ ዘሜ፣ የአመራር ስፍራውን ከያዛችሁ በኋላ የጎጃም ዐማራ የዕለት በዕለት የድል ዜና ለምን ተቀበረ? ተዳፈነም ሁላ? በጎጃም ነፍስ ያላቸው የዐማራ ፋኖዎች እየተገለሉ፣ ዞር እየተደረጉ የዐማራ ልዩ ኃይል የነበሩ ፖሊሶች ትናንት መጥተው በተሠራ የፋኖ አደረጃጀት ላይ ለምን ተሹመው ትግሉን ገደሉት? ቀበሩትም? አፈና፣ እገታ፣ ባለሀብቶችን ማማረር ለምን በጎጃም ምድር በዛ? በአጠቃላይ በጎጃም ብቻ አይደለም በመላው ዐማራ የዐማራ ፋኖ ትግል ተጠልፎ ባይኮላሽም የሚያዘገየው ነገር ግን እየተስተዋለ ነውና በጊዜ ይታረም። ሰው እያገቱ አዲስ አበባ ቤት ሠርተው ቤተሰቦቻቸውን ያሸሹ የፋኖ አለቆችን በጊዜ መንጥራችሁ ለዩ። ብልጣብልጥነት አያሻግርም። አያራምድምም።

"…ለኢኤምኤስ በሰጠኸው ቃለመጠይቅ ምክንያት አዲሱ የዐማራ አደራጅ ኮሚቴ አንተን እንደቀጣህ፣ ከሰብሳቢነትህም አውርዶህ እንደነበር ዐውቃለሁ። በኮሚቴው ፊት ቃልህን ስትሰጥም አደባባይ የዋለን ተቀርጾም ለሕዝብ የተላለፈን ቃልህን ለመካድ ያደረግከውም ሙከራ ትክክል አልነበረም። በኋላ ላይ ግን በማስረጃ ሲሞግቱህ አምነህ ይቅርታ መጠየቅህን ብቀበለውም ከእንግዲህ ግን በአንተ ቃልአቀባይነት እንብዛም የድሮው መተማመኔ ይኖራል ብዬም አላስብም። እኔማ ሲመስለኝ "እናንተና እነ ማስረሻ አልተጣላችሁም። እናንተና እነ እስክንድርም አልተጣላችሁም። ዐውቃችሁ የተጣላችሁ መስላችሁ፣ ታጋይ ወጣቶቹን ለመዋጥ፣ ለመደምሰስ እና ለማጥፋት ድራማ የሠራችሁ ሁላ እስኪመስለኝ ድረስ ነው የተጠራጠርኳችሁ። የእስክንድር ሕዝባዊ ሠራዊት ገና እኮ ወደፊት ስለ ሠራዊቱ ይጠየቃል ተብሎ በኮሚቴ ደረጃ ወንድማችን ነው ሳንገፋው፣ ሳናርቀው አቅርበነው አሳትፈን እናወያየው የተባለውን ግሩም ዐማራዊ ሓሳብ ተቀብለን አክብረነው ተደምመንበት ሳለ፣ የእስክንድር ነጋን ሠራዊቱ ስለሚባለው ከፋፋይ ጠንቀኛ ቡድን ካልጠፋ ሚዲያ ያውም ራስህ በምትዘውረው በግዮን ሚዲያ ቃልህን መስጠት ስትችል እንዴት ለግንቦት 7 ለኢዜማ ሚዲያ ወጥተህ ትበጠረቃለህ? ከምር ይሄ አስደንጋጭ ነው። ብዙ የሚደግፏችሁን ሰዎች ሁላም አንገት ያስደፋም የማይደገም ስህተት ነው።

• ቀጥሎ ደግሞ ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው የምለው አለኝ። ወደ አንተም ልምጣ።

"…ምናላቸው ሆይ አንተ ጎምቱ ጋዜጠኛ ነህ። እንደ አንጋፋ ባለሙያነትህ ከትግል ሜዳ የሚመጡ ቃለመጠይቆችን በሙሉ እንደወረደ ባታቀርብ ብዬ እማጸንሃለሁ። ካቀረብክም ደግሞ ሞግት። ማርሸት ወያኔ ላይ አንተኩስም ሲልህ ዝም ጭጭ ሳይሆን ለምን? ብለህ ማፋጠጥ ነው ያለብህ። ዝም ጭጭ ካልክማ አንተም ያው የወያኔ ናፋቂ ነህ ማለት ነው። በተለይ እንደ ወጣት ማርሸት ዓይነቱን እንዳመጣለት ሳይጠነቀቅ ቃለመጠይቅ የሚያደርግን ጀብደኛ ወንድም የግድ መቅረብ ካለበት በደንብ ታይቶ ለሕዝብ ቢቀርብ መልካም ነው ባይ ነኝ። ልጁ ልጓም ሊበጅለትም ይገባል። በዚህ ዘመን አንድጊዜ ከአፍህ ቃልህ ካመለጠ፣ አመለጠ ነው። እናም ጥንቃቄ ባይለይህ መልካም ነው እላለሁ። ደውዬልህም አውርቼሃለሁ።

"…ሲጠቃለል። እገሌ ሰብሳቢ፣ እገሌ ምክትል። አቶ እስክንድር የውጭ ጉዳይ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ አማካሪ፣ እነ መስከረም አበራ፣ እነ ዮሐንስ ቧያለው አማካሪ ምናምንትስዬ ተብሎ የተሰራጨው ዘገባ እኔ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እንዳለኝ መረጃ ሀሰት ነው። ከአራቱም ጠቅላይ ግዛት ተወካዮችም የተሰጠም አይደለም። ይሄ ሆን ተብሎ ለተንኮል የተሰራጨ፣ ወይም ደግሞ የሕዝቡን ስሜት ለማወቅ ይሄ ምኞት ያለው አንደኛው የፋኖ አደረጃጀት ያወጣው ሊሆን ይችላል ባይ ነኝ። ዘገባው የወጣው በዘመነ የቅርብ ሰዎች ከሆኑት አካላት የሚዲያ ስም ጠቅሰው ያወጡት ሲሆን ይሄ ደግሞ የተንኮል ድር መነሻ ምንጩ የሚያመራው ወደ እናንተ ወደ የእነ ጠበቃ አስረስ እነሰ ወደ እነ ፋኖ ማርሸት ግሩፖች ነው ማለት። እደግመዋለሁ። በሴራ ቦለጢቃ አትበልጡኝም። አቡክቼ እጋግራችኋለሁ። አስምሩበት። ደግሞም አልፋታችሁም።…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደተለመደው ዛሬም የአመስጋኙ ቁጥር ያመሰግን ዘንድ ከሚጠበቀው ቁጥር በላይ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። እንግዲህ ከምስጋናው ቀጥሎ በቀጥታ የምናልፈው ወደተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል ማለት ነው።

"…እናም ጎዶኞቼ ለዛሬም እንደተለመደው በወንድ አቅሜ በስተእርጅና በትበት ብዬ እጥር፣ ምጥን ያለች ለወዳጅ ማንቂያም፣ ማስጠንቀቂያም ጭምር የምትሆን አጭርዬ፣ ድንክ የሆነች ጥፍጥ፣ ምጥን ብላ በጥቂት መስመሮች የተሰደረች፣ የተቀመመች፣ የተቀነበበችም ቆንጅዬ ኡሙንዱኖኢሹ የሆነች ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችኋለሁ።

"…እኔ እኮ ቀኝ ትከሻዬን ሲሸክከኝና በልበል ሲለኝ ካልተነፈስኩት ጤናም የለኝ። እናንተስ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ማንበብ ብቻ ሳይሆን ካነበባችሁ በኋላ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?

• እስኪ አንድ 100 ሰው ዝግጁ ነነ ይበል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዘንድሮ ቁርጥ ነው።

ገና ገና… ያሸዋል ገና
ገና ገና…  ያሸዋል ገና

"…አበደን ዘንድሮማ ቁርጥ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሄዳችሁ እዩ። ውሸት ነው በትግራይ ውስጥ አንድም የፈረሰ ፋብሪካ የለም። ወታደሮቼ ማንንም በጅምላ አልጨፈጨፉም። የመምህራንን ሕይወት አሻሽላለሁ። የኮሪደር ልማቱ የማደጋችን ምልክት ነው። በመንግሥት ደረጃ አንድም ሌባ የለም። ሲሲቲቪ ካሜራ በመንገድ መብራት ላይ ተክለናል። በሰብአዊ መብት አያያዝ በኩል የመከላከያና ፌደራል ፖሊሶች ምስጋና ይገባቸዋል። ከታጠቀ ኃይል ጋር እኛ ለንግግር ዝግጁ ነን።

"…ለአባቶቼ ፤ ለታላላቅ ወንድሞቼ ምክር ቢጤ ልለግሳቸው። በቅርቡ አንዳንድ ቦታ ላይ "መፈንቅለ መንግሥት እናካሂዳለን" ብለው አንዳንድ አባቶቻችን ውይይት ያደርጋሉ። መፈንቅለ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይሳካም። እኛ ወታደሮች ነን መፈንቅለ መንግሥት እንዳይሳካ አድርገን ነው ተቋማት የሠራነው።

"…ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አንዴ ተሳካ የዛሬ 50 ዓመት። ከ50 ዓመት በኋላ ብዙ የሚረቡና የማይረቡ ሙከራዎች ነበሩ አልተሳኩም። አሁን ጭራሽ አይሳካም። ለወንድሞቼና ታላላቆቼ ምክር መስጠት የምፈልገው ጊዜ አታባክኑ፣ የወዳጆቻችንን ሀገር ገንዘብም አታባክኑ፣ ገስት ሀውስም አታጣቡ አይሳካም። በግጭት፣ በጦርነት፣ በሽፍታነት፣ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ መያዝ ማለት ብሎን እንደ ተበላበት ጥርስ ማለት ነው። የሚሽከረከር እንጂ የማይሻገር። በተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ምክር ስንለግስ ቀለል አድርገው የሄዱ ሰዎች በኋላ ዋጋ ይከፍላሉ።"

"…የፓርላማ አባላት የጠየቁት ሌላ። እርሱ የሚመልሰው ደግሞ ሌላ። ስገምት ግን በቅርቡ "የመፈንቅለ መንሥት ሙከራ ከሸፈ" የምትል ዜና አስነግረው በገፍ የሚታሰሩ ጀነራሎችና ታላላቅ ሰዎች የሚኖሩ ይመስለኛል። ተወደደም ተጠላም ግን ዐማራ ያሸንፋል። በቅርቡም አገዛዙ ይፈርሳል።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ናዝሬት ከተማ ነው አሉ። አሮሬቲና ቶርበን ኦቦ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ የከተማው አስተዳደር ከ1,500 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ሕገ ወጥ ናቸው በሚል ሰበብ ለማፍረስ አፍራሽ ግብረ ኃይል ይዞ ከች ይላል አሉ።

"…ነዋሪዎቹም በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ እኛም ላይ ሊፈጽሙ ነው እንዴ ብለው ደነገጡ አሉ። ሕዝቡ መንግሥት ቤት ማቅረብ ሲያቅተው መሬቶቹን ከአካባቢው አርሶ አደሮች ገዝተው ከ2005 ዓም ጀምሮ መብራት፣ ውኃ ሁሉ ገብቶላቸው፣ ለከተማ አስተዳደሩም ግብር እየከፈሉ የቆዩ ናቸው።

"…ከዚህ በፊትም እንዲሁ አፍራሽ ግብረ ኃይል መጥቶ  ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቅርበው ጉዳዩ በይደር እንዲታይ ተወስኖላቸው ነበርም ተብሏል። እናንላችሁ ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማ አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀ ወታደርና ፎሊስ ይዞ ቤቶቹን እንደለመደው ሊያፈርስ ይመጣል። ሕዝቡም መጪውን ክረምት የት ልንወድቅ ነው? በማለት ተቃውሞ ያሰማሉ።

"…እንደ አዲስ አበባ ሕዝብ ላፍርስህ ስልህ እሺ ነው እንጂ የምን እንደ ኬኒያ ሕዝብ ተቃውሞ ማሰማት ነው? ያለው ደደቡ የኦሮሞ ብልፅግና አገዛዝ አንዲት ነፍሰጡርን ጨምሮ 7 ንፁሐን ሰዎችን አናት አናታቸውን በጥይት ፈረካክሶ ረፍርፎ በመግደል ብዙዎችንም አቁስሎ ሌሎችንም እየወገረ ወደ ዘብጥያ ማውረዱ ተነግሯል።

"…ሰዉም እንደ አዲስ አበባዎችማ ዝም ብለን በጅብ አንበላም። የኦሮሞ ብልጽግና ገድሎ ጨርሶን ነው እንጂ ቤታችን አይፈርስም እያሉ ነውም ሲሉ አገዛዙም ነገም ከተቃወሙኝ ለሌላው ክልል መጥፎ ትምህርት ስለሚያስተምሩብኝ በማለት ከዚህ የበዛ ሕዝብ ለመግደል እየዛተ እንዳለ ነው የሚሰማው። ገዳይ ወታደሮች ተጠያቂ እንደማይሆኑም እንደተነገራቸውም ተሰምቷል። መፍትሄው ፋኖነት ብቻ ነው። የሞቱትን ነፍስ ይማር።

• እየተገደላችሁ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹን ወደ 14 ሺ ሰው ማንበቡን እያየሁ ነው። ወደፊት ቁጥሩ ከፍ እንደሚል ተገማች ቢሆንም እስከአሁን ባለው ቁጥር 16 ሰዎች 😡ብው ብለው በኃይለኛው መቆጣታቸውንም እየተመለከትኩ ነው። ዋናው ማንበባቸው ነው። አንብበውም መናደዳቸው ተፈጥሮአዊ ነው።

"…እንግዲህ ይሄ የእኔ ምልከታ ነው። እኔ ምልከታዬን በጨዋ ደንብ፣ በግልጽ አማርኛ እንዳቀረብኩ በቀረበው ሓሳብ በርዕሰ አንቀጹ ላይ የተለየ ሓሳብ አለኝ የሚል ካለ በጨዋ ደንብ ይስተናገዳል፣ ሁላችንም እናነብለታለን ማለት ነው። ተራው የእናንተ ነው።

• 1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እርግጥ ነው ጄነራሉ ኢህዴን ነበሩ። የአንድ ሰው የኋላ ታሪኩን ይዞ መመርመር ጉዳት የለውም። ከወያኔ ከገንጣይ አስገንጣይዋ ጋር አብረው የኢትዮጵያ መንግሥትን የወጉ ወንበዴ የሚል ስምም የተሰጣቸው ነበሩ። ከኢህድን ወደ ብአዴንም የተቀየሩ ሰው ነበሩ። ብአዴን ሆነው ሳለ በዐማራ ላይ የደረሰውን በደል፣ የዘር እልቂት፣ መፈናቀል የእሳቸው ድርጅት ነበር ይፈጽም ያስፈጽም የነበረው። መለስ ዜናዊ ካሰመረው አርቴፊሻል የዐማራ ክልል ዐማራ ውጪ ስሚገኙ ዐማሮች አይመለከተንም ብለው እነ በረከት ስምዖን ፀረ ዐማራ ሕግ ሲያጸድቁም እሳቸው ብአዴን ነበሩ። ወልቃይት፣ ጠለምት፣ ራያ፣ ደራና መተከልም እነ ጄነራል ተፈራ ማሞ አቅም፣ ጉልበትም በነበራቸው ሥልጣኑም በእጃቸው በነበረ ጊዜ ዐማራ የተነጠቃቸው ናቸው። እነ ወልቃይት በቀድሞው ኢህዴን በአሁኑ ብአዴን አዴፓ መሪነት የተዘረፉ የዐማራ ርስቶች ናቸው። ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን መለስ ዜናዊ ህክምና ከልክሎ ሲገድላቸው ጀነራሉ የመለስ ዜናዊም አገልጋይ ነበሩ። ዕድሜ ዘመናቸውን ዐማራ ሲሰቃይ፣ ሲገደል፣ ሲሰደድ ቆመው ያዩ የነበሩ ሰውም ናቸው። አሁን በቅርቡ ለህክምና ወደ ውጭ እንዳይሄዱ የተከለከሉት ጀነራል ተፈራ አሁን አገዛዙ ሊያስራቸው ሲዘጋጅ ወደ ጫካ በመግባታቸው ከመሞት መሰንበት ነውና በዚህ ልንደነቅ አይገባም። ታስረው ከሚማቅቁ ታግለው የበደሉትን ሕዝብ ቢክሱ እንደ ንስሐም ይቆጠርላቸዋል ብዬ ነው የማስበው።

• ስጋቴን ላስከትል እና ነገሬን ልቋጭ

"…ጄነራል ተፈራ ማሞ በሁለት የሀገር ውስጥ፣ እና በሦስት የውጭ ጠላቶች እንዳይጠለፉ እሰጋለሁ። ዘመዴ አትስጋ ብትኝም መስጋቴን ግን አልተውም። በሀገር ውስጥ ጄነራሉ በሳልሳዊው ብአዴን፣ እንዲሁም በግንቦት ሰባት እንዳይጠለፉ እሰጋለሁ። ጄነራሉ በዐማራ ፋኖ ትግል የዐማራ ፋኖ ትግል ሲጎመራ ከመታሰር ብለው ሸሽተው ወደ ጫካ ገብተው ትግሉን በስመ ጀነራልነት ጠልፈው የአንድነት ኃይሎች ነን ለሚሉት ፀረ ዐማራ ድርጅቶች እና ለፌክ ኢትዮጵያኒስቶች እጅ መንሻ አድርገው እንዳያቀርቡትም እሰጋለሁ። የጀነራሉ በግንቦት ሰባት አባልነት ተጠርጥረው፣ በዚያው በግንቦት ሰባት አቀናባሪነት የወያኔን መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ሊገለብጡ ነበር ተብለው ከእነ ጀነራል አሳምነው ጽጌ ጋር አብረው ታስረው የነበሩ መሆናቸውም መዘንጋት የለበትም።  ጀነራል ተፈራ ለሁለተኛ ጊዜ በሰኔ 15 ቱ ጉዳይ ተጠርጥረው ባህርዳር በታሰሩም ጊዜ የአቢይ አሕመዱ ወዳጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባህርዳር ድረስ ሄዶ ጀነራሉን ሲጠይቅ በወቅቱ በግንቦት ሰባት ስም ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ የዐማራ ልጆች አንዳርጋቸው ላይ በእስር ቤቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ፣ ጀነራል ተፈራ ልጆቹን ለመቆጣት ሲሞክሩ፣ "ዝም በል አንተ። ይሄ ነፍሰ በላ በኤርትራ ምድር ያደረገንን የምናውቅ እኛ ነን፣ አንተ ከዚህ ከፀረ ዐማራ ሰውዬ ጋር ሆነህ እኛን ልትቆጣን አትችልም" በማለት ዝም እንዳሰኟቸውም ሰምቻለሁ። እናም ትግሉ በዚህ መንገድ እንዳይጠለፍ ብሰጋ አይፈረድብኝም።

"…አንዳርጋቸው ጽጌ በአሁን ሰዓት ከሕጋዊ ባለቤቱ ውጪ የወለዳትን ልጁንና ሁለተኛ ሚስቱን ይዞ አስመራ እንደከተመ እና በዚያ እንዳለ ወፎቼ እየነገሩኝ ነው። አስመራ የተቀመጠው የፋኖ ውክልና አለኝ በማለት እንደሆነም ሰምቻለሁ። ነጥቦቹን በሙሉ ዐውቃቸዋለሁ። በተለይ በጎንደር እና በአንዳንድ የዐማራ አካባቢዎች በፊት ግንቦት 7 የነበሩ ቡድኖችን የፈረንካ ሰቀቀናቸውን እያሟሉ የፋኖ አንድነት እንዳይመጣ እየበጠበጡ ያሉ ኃይሎች ትግሉን በእጃቸው ለማስገባት ሲጥሩም አያለሁ። እናም ሣልሳዊው ብአዴን እና ሻአቢያ በቅንጅት አብረው እየሠሩ በጎንደር በኩል በወልቃይት ኮሎኔል ደመቀን፣ በወሎ በኩል ደግሞ ጀነራል ተፈራን ይዘው አይንቀሳቀሱም ብሎ አለመጠርጠርም አይቻልም። ኤርትራም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ፖለቲካ የድርሻዋን ለማንሣት ስትል በዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ተሳትፎ አታደርግም ማለትም አይቻልም። ኢትዮጵያ በጦርነት መድቀቋ ለኤርትራ ቶንቦላ ሎተሪ እንደወጣለት ነው የሚቆጠረው። አንዳርጋቸው ደግሞ ለሻአቢያ የእድሜ ልክ ቅጥረኛ የሆነ ሰው ነው። እናም ጀነራሉ ከግንቦቴዎች እና ብአዴኖች ጋር ባላቸው ወዳጅነት የተነሣ እንዳይጠለፉ መመኘት እና መስጋት በምንም ዓይነት መንገድ ስህተት አይሆንም። (ብአዴንን ትርፍ አንጀት ማለታቸውን ሳልዘነጋ ነው)

"…የጀነራሉ ወደ ፋኖ መቀላቀል ከመጠን በላይ ጮቤ ያስረገጣቸውን አካላት ሳይም የሆነ የሚሸክከኝ ነገር ቢፈጠር እርሱም መጥፎ ሚልኪ አይሆንም። የሀብታሙ አያሌው እንዲህ ነገሩን ማጋጋል ጀነራሉ የት ሄደው ይሆን? ያረፉት ማንጋር ነው? የግንቦቴዎችና የፈረሰው የእስክንድር ነጋ ግንባሮችም በኃይለኛው ጮቤ መርገጥ ነገሩን እንድጠራጠረው ቢያደርገኝ አይፈረድብኝም። እንደ እኔ ዓይነት የቀረበለትን ምግብ ሁሉ አጋብሶ የማይበላ ሰው፣ እንደ እኔ የጎረሰውን ምግብ ሳያላምጥ የማይውጥ ሰው፣ እንደ እኔ የመጣለትን መረጃ ሁሉ ዜና አድርጎ የመቀበል ልማድ ያሌለው ሰው፣ እንደ እኔ ነገሮችን ግራ ቀኝ በማየት አስሬ ለክቶ አንዴ የመቁረጥ ባህል ያለው ሰው፣ እንደወረደ የማይወርድ ሰው፣ እባብ ሳይ ኖሬ በልጥ ብበረይ፣ ብደነግጥ አይፈረድብኝም። ደግሞም ለበጎ ነው። መመርመር፣ መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ ነው የሚባል።

"…የሆነው ሆኖ ለጀነራሉ ጊዜ መስጠት ተገቢ ነው። በቀጣይ እቅዳቸውን መስማትም ተገቢ ነው። ባለቤታቸው ወሮ መነን ኃይሌም ሳትታሰር ታሰረች ብሎ ማራገብም ልክ አይደለም። የአንዳርጋቸው ጽጌን ኤርትራ መቀመጥ፣ የእነ ገዱ አንዳርጋቸው እና ኢንጅነር ይልቃል በስቴት ዲፓርትመንት አካባቢ ተፍተፍ በትበት ማለት፣ የእነ ስታሊን ነገርየውን ማጯጯህ፣ የኢትዮ ፎረም ጮቤ መርገጥ፣ የብአዴን ሰዎች ግልጽ የአቦን መገበሪያ እንደበላ ሰው ሳይጠየቁ መለፍለፍ፣ የግንባሩና የሠራዊቱ ሰዎችና ልሳናትም ያለቅጥ መፎግላት ነገሩን በአንክሮ፣ በተዘክሮ መመልከቱ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ቢያይል፣ ቢበዛ እንጂ ምንም ክፋት አይኖረውም። ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዮሐንስ ቧያለው፣ ወዘተረፈን ከወሎ ብአዴንነት ጋር እያያዙ ነገር መሥራትም ዴየግ አይደለም።

"…የሆነው ሆኖ የጄነራሉ ፋኖን መቀላቀል እሰየው፣ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ልክ እንደ እስክንድር ነጋ ፋኖን ሲቀላቀል ጮቤ እንደተረገጠው ያለ ስሜት ቢሰማም፣ ፈንጠዝያን በልክ፣ ኳስ በመሬት አድርጎ ነገሮችን በመናበብ እየተመለከቱ መንቀሳቀስ ግን ወሳኝ ነገር ነው። እስክንድር ነጋን በስማችን አትደራደርም ያሉት ፋኖዎች ጀነራል ተፈራ ያንን ክፍተት እንዲሞሉ ብአዴን ልኳቸው ከሆነም ትክክል አይመጣም ብሎ ለመሟገት መዘጋጀት የግድ ነው። እኔ የማምነው አሁንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኙ ብአዴን እንደሆነ ነው። ብአዴንን በድን ብለን ዘወትር ብንሳለቅበትም እየቆየ እየገባኝ የመጣው ነገር ቢኖር ብአዴን ስር የሰደደ የኢትዮጵያ ነቀርሳ መሆኑን ነው። የመድኃኔዓለም ያለህ ይጫወቱት የለ እንዴ ቦለጢቃውን። ሀገር ለማዳን አይደለም እንጂ አልቅት አይደሉ እንዴ? ጥብቅ እንደ ማስቲሽ፣ እንደ ሙጫ። የምንከሰው በኦሮሞ ስም የተጎለተውን ጨቅላ አቢይ አሕመድን ሆነ እንጂ የብአዴን ሚናም ቀላል ነው ብዬ አላምንም። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በቤቴ አመስጋኙ በእጥፍ ጨምሯል። እግዚአብሔር ይመስገን፣ ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ፈዋሽ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ነው በወንድ አቅሜ በስተእርጅና ተፍተፍ ብዬ ያዘጋጀሁላችሁ።

"…ነገ የሚሆነው አይታወቅም እና ልሙት ልኑርም አላውቀውም እና በጀነራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ የተሰማኝን ደስታ እና የሚሸክከኝንም ሽከካ ነው በዛሬው ርዕሰ አንቀጼ ላይ በስሱ ያዘገጀሁላችሁ።

• እናንተስ እንደተለመደው ሰናፍጭ በልኩ፣ ቃሪያና በርበሬው ከጥሩ ብርዝ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበላችሁን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ፣ አንብባችሁም በጨዋ ደንብ አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?

• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።” መዝ 20፥2

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኔየምለው ሸዋፈራሁ ደግሞ ከምኔው ፐሰተረ…? 😂 እውነትም ያረፈደ አራዳ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይ ኤልያስ መሠረት…

(የግለሰቡን ስም እና ይኖርበት የነበረውን ከተማ አስቀርቼዋለሁ)። ምን ማለት ነው? በቃ እኮገደሉት። የሟችን ስም እና ከተማ መደበቁ ምን እንዳይቀር ነው? ይሄኔ ሟች ትግሬ ቢሆን እስከ ቅድመ አያቱ ትበጠረቅ ነበር።

• እኔ ግን ስገምት ከተማውን ባለውቅም ሟች ግን የታረደው ዐማራ ይመስለኛል። የሰውየውን የሟቹ ስምና ፎቶ ያላችሁ ላኩልኝ እና እኔ ነገ በመረጃ ቲቪ ነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ እዘክረዋለሁ።

• ግፉን መዘገብህ ራሱ ግን ያስመሰግንህሃል። ይሄንንስ ማን አየበት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ሰምቻለሁ ግን ምን ይጠበስ…?

"…ከደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተነሥተው ወደ ቤተሰብ ለመመለስ መንገድ የጀመሩ ተማሪዎች ሰላሌ ሲደርሱ ታፍነው ተወሰዱ። በእያንዳንዱ ተማሪ ቤተሰብ 700 ሺ ብር ከፍሎ ልጆቹን መረከብ ይችላል ተብሎም ዜና መሠራቱን ሰምቻለሁ። የትግሬ እና የኦሮሞ ተማሪዎች ሲለቀቁ ሌሎች ወደ ጫካ መወሰዳቸውንም ሰምቻለሁ። ትምህርት ሚንስቴርም፣ የብልፅግናው አገዛዝም ጉዳዩን ቢሰሙም የታገቱት የፈረደባቸው ዐማሮች ስለሆኑ ዐማራ ተጠሪም ስሌለው ምንም እንደማየመጡም ሰምቻለሁ። እና ተማሪ ማገት በኦሮሚያ ሥራ እንደሆነ አታውቁም እና ነው አልሰማህም ዘመዴ የምትሉኝ። ከዚህ ግፍ ለመዳን ነው እኮ ታገል የምትባለው።

"…አልሰማህም እንዴ ዘመዴ? በሳኡዲ አረቢያ በስደት የሚኖሩ የዐማራ ሙስሊሞችን በዚያው በስደት የሚኖሩ የኦሮሞ ሙስሊሞች አረዷቸው እኮ ያላችሁኝንም ሰምቻለሁ። እና ምን ይጠበስ በወለጋ 3ሺ እስላም ዐማራ ማረድ የተለማመደ፣ በዚያም የተለከፈ፣ ልቡሰ ሥጋ የኦሮሞ የወሃቢያ እስላም ምን እንዲያደርግልህ ነበር የጠበቅከው? ዥሎ አይደለም ሳኡዲ አረቢያ፣ አይደለም ኦሮሚያ እዚያው በክልልህ መጥቶ አጋድሞ እያረደህ አይደለም እንዴ? ንገሩኝ ባይማ አትሁን።

"…በኦሮሚያ ታገትን፣ ታረድን፣ ወዘተረፈ አይሠራም። ሥራ ነው። አገዛዙ በዐዋጅ ያላጸደቀው ሥራ። በራስ አቅም በጀት የሚጀመር የወጣት ቄሮዎች የፈጠራ ሥራ ነው። የሚበረታታ የሚደገፍ ሥራ ነው። እናም ምኑ ነው የሚያስደንቅህ። በመከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ የሚደገፍ ሥራ እኮ ነው። እና ገንዘቡ ከየት መጥቶ ይመስልሃል ሴተኛ አዳሪ ለአንድ አዳር ሁለት ሚልዮን ብር የሚጫረቱት። ሞኞ። የኦሮሚያ የአፈና ልምድ አድጎ ለትግራይም መትረፉ እየተነገረ ነው። ትግሬ ኦሮሚያ ውስጥ አይታገትም። ዓድዋና መቀሌ ላይ ግን… 

• ላለመታገት ታገል። ሰምቼሃለሁ ልልህ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጸሎት ምህላው፣ ሱባኤ ዱአው እንደለ ሆኖ ከፈጣሪ ጋር ለዐማራ ብቸኛው የመዳኛ መንገዱ ይሄ ነው።

"…የዘር ቦለጢቃው በኢትዮጵያ ምድር በሕግ እስኪታገድ ድረስ ዐማራም ልክ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ሁን። እነርሱ ለልጆቻቸው ጭምር ዘረኝነትን በእናት ጡትና በጡጦ መልክ ሰጥተው ሲያስድጉ ጭብጨባ፣ እነርሱ እንደ ስለት ልጅ ባዩት ነገር ላይ ሁሉ ተቸንክረው የእኔ ነው ኬኛ እያሉ ሲያለቅሱ ማባበል፣ ዐማራው ከመሸ ነቅቶ ራሱን ለማዳን በትበት ሲል እርግማን አይሠራም። ለትግሬና ለኦሮሞ ቅድሚያ ለዘራቸው ከሆነ መፈክሩ ለዐማራው ሲሆን ምንሼ ነው?

"…ለአራሱ፣ ለጨቅላው ዐማራ ሳይቀር ዐማራነትን ከነ መዳኛ መንገዱ አሳየው። አስቀጽለው። ሃቅ ስለሌለው የእነዚያ የክፋት ብሔርተኝነት እየደከመ፣ እየሳሳ፣ እየተነነ ነው የሚሄደው። የአንተ ብሔርተኝነት ሌላ አማራጭ ከማጣት የመጣ፣ መገፋት፣ መጨፍጨፍም፣ መሰድም የወለደው ሃቅ ስለሆነ እየጎመራ፣ እያበበ ነው የሚሄደው። ዐማራነትን አስቀድም። ትድናለህ።

• እየመከርኩህ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።” ኢያ 7፥13

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ ✍✍✍ "…አድማጭ ተመልካቾቼ ገና ምንም ሳይወሰን ይሄ ከታች የምለጥፍላችሁ የሥልጣን ክፍፍል ተሠርቶ አስቀድሞ ለደጋፊ ፌስቡከሮች እና ለደጋፊ አፍቃሬ ብአዴን ደጋፊ ሚዲያዎችም ተላከ። እነርሱም ዜናውን አስቀድመው አንጫጩት። እኔም የተለጠፈውን መልሼ ልለጥፍላችሁ እና እስቲ እናንተ ፍረዱ። ይሄን የምለጥፍላችሁን ያገኘሁት ከጊዮን ዐማራ ሚዲያ ነው። ፊደላቱንም አላረምኩም። ዐማራ ሆነው የጻፉትን እኔ የሐረርጌው ቆቱ ምን በወጣኝ እና አርማቸዋለሁ። ደግሞ ጉድ በል ጎንደር የአማርኛ መምህር መጣልህ ከሀረር ብለው ይተርቱብኝ እንዴ?,አላደርገውም። ከማንኛው አንብቡት። አንብቡትና ፍረዱ።

ሰበር ዜና❗️

የአማራ ፋኖ አደረጃጅት በአንድ አደረጃጀት ተዋቀረ !
///////
አርበኛ ዘመነ ካሴ ---- የአማራ ፋኖ ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ሰብሳቢ
ታላቁ እስክንድር ነጋ ---- የአማራ ፋኖ ውጭ ጉዳይ ጉዳይ ግንኙነት እና ምክትል ሰብሳቢ
ፋኖ ሃብቴ ወልዴ ---- የአማራ ፋኖ ሎጀስቲክ መምሪያ ሃላፊ
ፋኖ ማስረሻ ሰጤ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ሎጀስቲክ መምሪያ
ዋርካው ምሬ ወዳጆ ---- የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ጉዳይ ሃላፊ (ጦር መሪ)
ፋኖ አሰግድ መኮነን ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ወታደራዊ ሀላፊ (ምክትል ጦር መሪ)
ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ ---- ምክትል የውጭ ጉዳይ አማካሪ እና ፓለቲካ ዘርፍ
ፋኖ መከታው ማሞ ---- የአማራ ፋኖ ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ
ፋኖ ፈንታሁን ሞሐባው ---- የአማራ ፋኖ መረጃና ደህንነት ሃላፊ
ፋኖ በየነ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል መረጃና ደህንነት ሃላፊ
ፋኖ ማርሸት ፀሐዩ ----- የአማራ ፋኖ ሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ ሃላፊ
ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤና ----- የአማራ ፋኖ ምክትል ህዝብ ግንኙነት
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው -----የአማራ ፋኖ የውጭ ግንኙነት ጉዳይ አማካሪ
አቶ ኢንጂነር ይልቃል፣ አቶ ዩሐንስ ቦያሌው እና ወ/ሮ መስከረም አበራ ----- የአማራ ፋኖ አጠቃላይ አማካሪ ይሆናሉ ተብሏል።

ማሳሰቢያ:- ይህ ዘገባ "በጃዊሳ ሚዲያ" የተሰራ ሲሆን ዋናውን መግለጫ በቅርቡ የምንዘግብ መሆኑን እና የቦታ ቅይይር እንዲሁም የአደረጃጀት ለውጥ ካለ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል። ለጊዜው በዚህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን እና በቀጣይ ያልተካተቱ የፋኖ አመራሮችን እና ሌሎች ወደፊት መምጣት ያለባቸውን ጀግኖች ጨምሮ ሲጠቃለል አጠቃላይ መግለጫ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀት ስያሜ ጋር የሚሰጥ ይሆናል።

አንድ መሆናችን በእጅጉ የሚያስደስት ሆኖ ቅሬታ ሊፈጥሩ ይችላሉ ከሚባሉት አንድ አንድ ነገሮች ሊጠኑ እንደሚገባ እናምናለን። በተለይ እንደ አንድ የአማራ ፋኖ ታጋይ የብአዴን አመራሮችን ወደፊት የማምጣቱ ጉዳይ በደንብ ሊታሰረበት ይገባል።

ብአዴኖች በትክክል የአማራ ፋኖ ትግል አላማው ገብቶቸው ከሆነ በንስሃ ተመልሰው ለህዝብ መሬት ወርደው መስዋትነት መክፈል አለባቸው የሚል ሃሳብም እናንፀባርቃለን። ያም ሆኖ ይህ ከድል ማግስት ሁሉም ባጠፋው ጥፋት ልክ እስኪቀጣ ድረስ ለአማራ ፋኖ ወሳኝ ከሆነ አይደለም ከብአዴን ጋር ከሰይጣን ጋር አብረን እንሰራለን።

በዚህ ጉዳይ ትግሉን ወደ ኃላ የሚጎትቱ አካላት የሚፈጠሩ ከሆነ ከድርጅቱ በቀጥታ እንደሚሰናበቱ መጥቀስ እንፈልጋለን። ከዚህ በላይ ደስታ በዚህ ትግል ውስጥ እንደሌለና ይህንን ካበሰርን በኃላ ነገ እንኳ ብንሞት የማይፀፅተን መሆኑን እየገለፅን አንድነታችን የሚያስደስታችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🙏 …ሹመቱን በማስመልከት እስከዚህ ድረስ ያለው ጦማር ሾልኮ እንዲወጣ ያደረጉት የሆኑ አካላት ሓሳብ ነው።

"…ለማንኛውም ስብሰባው አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተቋርጧል። ለምንና እንዴት እንደ ተቋረጠ፣ በማን ምክንያት እንደተቋረጠም አስፈላጊ ሲሆን በቴቭዥን ሁላ እመጣበታለሁ። የሆነው ሆኖ የዐማራ ፋኖ ትግል እየወደቀ እየተነሣ፣ እየተንፏቀቀም፣ እየተንከባለለም ቢሆን ከማሸነፍ በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። ዳግማዊ ብአዴን በፋኖ በኩል ይከሰታል ብዬም አላምንም። ጥንቃቄ ግን እጅግ አስፈላጊ ነው።

"…እግዚአብሔር ካለ ደግሞ ሰሞኑንም የምንሰማቸው የምሥራቾችም ይኖራሉ። ወያኔ እንኳ መረጃው ደርሷት ሠራዊቷን ከራያ ማስወጣት መጀመሯም ደንቆኛል። እኔ የዐማራ ፋኖ ትግል በወያኔና በብልጽግና በኩል አደጋ ይገጥመዋል የሚል ስጋት የለኝም። ብአዴን ግን ነቀርሳ ነው። ጋንግሪን ነው። እሱ ግን ያሰጋኛል። ቢያሰጋኝም ቢያዘገይ እንጂ አያስቀረውም። ለማንኛውም ይህ እየተካሄደ ያለውን ነገር ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካልት ቀርበው የነገሩን ፍጻሜ እስኪያሳውቁን ድረስ ርዕሰ አንቀጹን እየኮመኮማችሁ ጠብቁን።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የዐማራ ፋኖን ወደ አንድ አደረጃጀት ለማምጣት እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን የሚያሳልፉ፣ ከጎንደር ሁለቱን የፋኖ አደረጃጀቶች፣ ከሸዋም ሁለቱን የፋኖ አደረጃጀቶች፣ ከጎጃም አንዱን የፋኖ አደረጃጀት፣ ከወሎም አንዱን የፋኖ አደረጃጀት ሰብስበው፣ ፋኖዎቹም ሰው መርጠው ልከው፣ በጉዳዩ ላይ በብዙ እየደከሙ ነው። ከእነዚህ አደረጃጀቶች ሌላም ጣልቃ ገቡ እስክንድር ነጋም ቢሆን ሠራዊት አለኝ በማለት ለክፍፍል በር እየከፈተ በመሆኑ እስክንድር ያለው ሠራዊት "ወደፊት የሚታይ ሆኖ" ለአሁኑ ግን ራሱ እስክንድር ይሳተፍ ተብሎም እሱም ከዐማራነት ሳይገፋ በአንድነቱ ላይ ተሳታፊ ሆኖ እየመከረ ነው። እኔ እስከማውቀው እና እየተከታተልኩት እስካለው ድረስ በብዙ ጉዳዮችም ላይ ተስማምተው ፍጻሜውን በድል ለመቋጨት በብርቱም እየጣሩ እንደሆነ ነው የማውቀው።

"…ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙዎቻችሁ የጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸውን የትናንት የፌስቡክ ልጥፍ እና የዐማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ የፋኖ ማርሸት ፀሐዩን ለEMS የተባለ አፍቃሬ ግንቦት ወኢዜማ ለሆነ ስብስብ የሰጠውን ቃለመጠይቅ አድምጣችሁ ያን ተከትሎም ዛሬ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ በተበተነው የፋኖ አመራሮች ስምዝርዝር ምክንያት መንደሩ ትርምስምስ ሲል ባይ ጊዜና ወደ እኔ ወደ ዘመዴም ቤት በጓሮ በር " ዘመዴ ይሄን ጉዳይ ሰመተኸው ወይስ ዓይተኸው እንደሁ ንገረን" በማለት ወትዋቼ በመብዛቱ ምክንያት ይሄን ርዕሰ አንቀጽ አጠር፣ ለስለስም አድርጌ ለመጻፍ ተገደድኩ።

• የምጀምረውም ይሰማኛል ብዬ በማመን ለወዳጄ ለፋኖ ማርሸት ፀሐዩ ወንድማዊ ምክር ቢጤ በመስጠት ነው።

"…በአንተ ጫማ ውስጥ ቆሜ ልመክርህ አይዳዳኝም። በዚህ ዕድሜህ በታንክና በድሮን ፊት ቆመህ ነገ ትሞት ዛሬ ሳታውቅ አንድ ውድ ሕይወትህን ለሕዝብህ ለመስጠት ቆርጠህ የወጣህን ጀግናም አክብሮቴ ከፍ ያለ እንደሆነም ራስህ ምስክር ነህ። ዛሬ ግን የሸከከኝን ነገር ልነግርህ፣ በዚያውም ወንድማዊ ምክሬን ልመክርህ ወደድኩ። ብትቀበል እሰየው፣ ባትቀበል ግን እኔ ከህሊና ዕዳ ነፃ ነኝ። ድገም፣ ድገም የሚያሰኘኝ ነገር ካልገጠመኝ በቀርም ደግሜ አልጽፍም። እናም በቅንነት ትቀበለኛለህ ብዬ ይሄን ግልጽ ምክር ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ለጠፍኩት።

"…መፍጠንህ ለተንኮል እስካልሆነ ድረስ እንብዛም ችግር የለውም። አንተ አሁን በታሪክ አጋጣሚ የአንድ ትልቅ ሕዝብ ያውም የዐማራ፣ ብሎም የጎጃም የእነ በላይ ዘለቀ ልጆች የተሰባሰቡበት የዐማራ ፋኖ በጎጃም የዐማራ ነፃ አውጪው ድርጅት ቃልአቀባይ አድርጎ ፈጣሪ የመረጠህ ሰው ነህ ብዬ ነው የማምነው። በተለይ መጀመሪያ አንተን ከመላው የዐማራ ሕዝብ ጋር ያስተዋወቀህ ከዶቼቬሌው ጋዜጠኛ ከነጋሽ አህመድ ጋር ያደረከው ቃለመጠይቅ እንደሆነ ይታወቃል። ፈታኙን፣ መስቀለኛውን፣ ነጥብ አስጣዩን የጎምቱው ጋዜጠኛ የነጋሽ መሀመድን ከባድ ቃለመጠይቅ ጠያቂውን ራሱን በማስደመም በድል መጨረስህ የሚረሳም አይደለም።

"…ማርሸት ኦንዲሜ ሆይ… አንተ በዐማራ ትግል የቆየህ፣ ለእኔም እንዳጫወትከኝ ከዓባይ ሚዲያ እስከ አሻራ ሚዲያ፣ አሁንም እስከ ጊዮን ሚዲያ ድረስ ያለህን ሱታፌና አበርክቶም የማውቅ ሰው ነኝ። በብዙ ምክንያት ሳላደንቅህም አላልፍ። በብዙዎች ልቦና ውስጥ ግን አይደለም አንተን አጠቃላይ "የዐማራ ፋኖ ማለት ይሄነው" ያስባለው ሥራህ ግን ያ ቃለመጠይቅህ ነበር ማለት እችላለሁ። ይሄ የእኔ የግል ግምገማ ነው። አሁንም የምመኘው ከከፍታህ እንዳትወርድ ነው። በዚያው በጀመርከው በዚያኔው ቃለ መጠይቅ ወቅት በነበረህ የዕውቀት፣ የመረዳት እና የማስረዳት ፀጋህ ቆይተህ ዕድሉንም በሚገባ ተጠቅመህ አሁንም በዚያው መጠን በከፍታ እንደትንቀሳቀስ ነው ይህን ጦማር መጻፌ። ከደከምክ፣ ከዛልክ ደግሞ አረፍ በል። ቦታውንም ለሌላ ለአዲስ፣ ለትኩስ ዐማራ ልቀቅ እንጂ የዐማራ ፋኖን ትግል ውርድ በሚያደርግ አቋም ላይ አትገኝ።

"…ማንም ደፍሮ የማይመክርህን ምክር እኔ ወንድምህ ዘመዴ በሁሉ ሰው ፊት ልመክርህ ነኝ። ልመክርህ ነኝ እናም ጮጋ ብለህ ስማኝ። በእንቁላሉ ጊዜ በቀበቶ፣ በሳማ፣ በልምጭ፣ በአለንጋ፣ በጎማሬ ካልተቀጣህ በበሬው ጊዜ የሚጠብቅህ ስቅላት ብቻ መሆኑን ዕወቅ። የሰው ልጅ የሆሳዕና እሁድ አንግሶህ በዕለተ አርብ የሚሰቅልህ ነው። ሚያዚያ 29 ለኢህአዴግ፣ ሚያዚያ 30ም የኢህአዴግን ቲሸርት ለብሶ ለቅንጅት ድጋፍ የሚወጣ ጉደኛ ሕዝብ ነው። አንተ ብቻ እንደ ትልቅ ሰው ብቻ ሳይሆን እንደ ልባም ትልቅ ሰው ሁን። ለደወለልህ ቲክቶከር፣ ለደወለልህ ፌስቡከራም፣ ዩቲዩበራም ሁሉ ቃልህን አትስጥ። ለደወለልህ ሴትም፣ ሰውም ሁሉ አትበጥረቅ። የድርጅት ምስጢር በድፍረት፣ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ለማንኛውም መንገደኛ አሳልፈህ አትስጥ። የግል ስሜትህን፣ የግል አቋምህን፣ የግል፣ መረዳትህንም ጭምር አንተው ለራስህ በራስህ አፍነህ ያዝ እንጂ ጎጃም የሚያስበው እንዲህ ነው እንዴ? የሚያሰኝና ሌላውን ዐማራ የሚያሳስብ፣ አንገት የሚያስደፋ ሥራ አትሥራ። ሰው አታጠራጥር። የራስህን ሓሳብ የድርጅት አታድርግ። ይሄን ስልህ ጓ የሚሉ አፍቃሬ ብአዴኖች ሊንጫጩ እንደሚችሉ ባምንም፣ በዚህም ምክንያት ቲክቶክ ላይ ሲንተኮቶኩ የሚውሉና የሚያድሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ ባምንም ለደንታቸው ነው። ኬሬዳሽ።

"…ታስታውሳለህ የባልደራሷ፣ የግንባሩና የሠራዊቱ ገንዘብ ያዥ ወሮ ሕይወት እንዴት ቀርባ በስልክ እንዳናዘዘችህ? ሕይወት እንዴት፣ በማን በኩል እንደቀረበችህም ያስረዳኸኝ ዕለትም ይሄንኑ ቃሌን ነግሬሃለሁ። ስልክ በተደወለልህ ቁጥር የደወለልህ ሰው ሁሉ አትመን። ደዋይ ሊቀርጽህ እንደሚችል አስብ። እኔ የማደርገው እንደዚያ ነው። እኔ ዘመዴ ማንም ይደውልልኝ ማንም ተጠንቅቄ ነው የማወራው። ያ ሰው እንኳ ባይቀርጸኝ የቴክኖሎጂ ነገር ስለማይታወቅ ሌላ ሦስተኛ ወገን ጠልፎን በመሃል ቁጭ ብሎ እየቀረጸ ሊያዳምጠኝ ይችላል ብዬ ስለማምን በስልክ የማወራው ሁሉ በአካል የማወራው፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌቭዥን የማወራውን ነው። ወይም በቴሌግራሜም የምጽፈውን ጭምር ነው። ቀርጸውኝ ቢያወጡት እንኳ ሰሚው ሕዝብ እና ይሄ ምኑ ነው ምስጢር? ዘመዴ ሁሌ የሚበጠረቀው አይደል እንዴ? ብሎ እኔ ምላሽ ሳልሰጥ ሕዝቡ እንዲሞግትልኝ ነው የማደርገው። አማላይ ሴቶች ይደውሉልኛል። አላግጬባቸው ነው የምሸኛቸው። ርቃናቸውን ቪድዮ፣ ፎቶ ተነሥተው ይልኩልኛል። በብሎክ አጠናግሬ ነው የምሸኛቸው። ፓርቲ ቤት፣ ጭፈራ ቤት፣ ሰካራሞች ጋር አልገኝም። እንደ ጠላቴ ብዛት ባልጠነቀቅ አይቀርልኝም ነበር። በምህረቱ ተሸፍኜ እንጂ ኃጢአተኛ መሆኔ ግን እንዳይረሳ።

"…ለምሳሌ እኔ በሰው ሀገር ነው ያለሁት። ስልኬም፣ ኢሜይሌም፣ ቴሌግራሜም፣ ኋትስአፔም፣ ቫይበሬም ጭምር እኔ ላውራበት፣ ልጻፍበት እንጂ የሚከታተለው፣ የሚገመግመው፣ የሚያየው ሌላ አካል የለም ብዬ አላምንም። ያውም አሸባሪ ተብዬ የተፈረጅኩ እኔ ካልተጠነቀቅኩ ማን ይጠንቀቅልኝ ትላለህ። ማንም ሰው ስልክ ሲደውልልኝ ስልኩን አነሳለሁ። ገፊ ጥያቄዎችን ዐውቃቸዋለሁ። ለሐሜት፣ ለነገር ፍለጋ፣ ነጥብ ላማስጣል የሚሰነዘር ጥያቄንም ዐውቀዋለሁ። ጠያቂው ፓትርያርኩም ቢሆኑ፣ ጳጳስም ቄስም ቢሆኑ፣ የልብ ጓደኛዬም ቢሆን ዝም ብዬ አልበጠረቅም። ለመመታት ተመቻችቼም አልገኝም። ይህን ማድረጌ ደግሞ ሲበዛ ጠቅሞኛል። እኔ ዘመዴ ብዙ ጊዜ እኔን ጠላት ባደረጉ ሰዎች የምከሰሰውና የምወቀሰው እኮ እኔው ራሴ አስሬ ለክቼ አንዴ በቆረጥኩት እና አደባባይ ባወጣሁት ቃሌና ጽሑፌ ነው እንጂ በድብቅ ተቀርጾ👇… ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” አሞ 3፥3

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እርፍ…

"…እስኪ ገምቱ እንዲህ ያለውን ምክር የሚመክረው ግን ዳንኤል ነው ቆሌው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፤ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፤ ለሰላም ሰው ቅሬታ አለውና። በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፤ የኃጢአተኞች ቅሬታ ይጠፋል። መዝ 37፥ 35-38

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዘለሰኛ…

እንኳን ክላሽ ይዤ መውዜር ዲሞፍተር
ዘንድሮስ ቁርጥ ነው በወንጭፍም ቢሆን
መግጠሜም አይቀር"

"…ከፊትም… ከኋላም ጫፉ እኮ አይታይም። ትግሉ ሕዝባዊ ነው። የጥጋብ ትግብል አይደለም። የመቅበጥ ትግልም አይደለም። ትግሉን የፈጠረው ለዘመናት ተጠራቅሞ ጫንቃውን ያጎበጠውን ሸክም ለመገላገል ሲል በቁጣ ተነሥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ ከዜሮ ከምንም ተነሥቶ የተፈጠረ የትግል ውጤት ነው።

• አዛኜን ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…የጀነራሉ ፋኖን መቀላቀል በትክክለኛው ያልተጠለፈው፣ ያልተቀባባው፣ ፅዱ፣ ነጭ ወረቀት፣ ሃቅ በሆነው የዐማራ ፋኖ አዲሱ የትግል መሠረት ከሆነ፣ ብአዴናዊ፣ ወያኔያዊ፣ ግንቦቴያዊ፣ ሻአቢያዊ፣ ግንባሩና ድዱ፣ አገጩአዊም ካልሆነ ለዐማራ ፋኖ ትግል አሸወይና ነው። ወደ ፋኖ የሚቀላቀለው የዐማራ አድማ ብተናም ጄነራሉ ጫካ ስለገቡ ብቻ እሳቸውን ተከትሎ ጫካ ይገባል ማለት ሳይሆን ከጀነራሉ ጫካ መግባት ጋር ተያይዞ ወደ ፋኖ የሚቀላቀልበት የራሱ አስገዳጅ ሁኔታም ስለተፈጠረበት ጭምር ከጫካ መግባት ይቀራል ብዬ አላምንም። የዐማራ አድማ ብተናው ወርሀዊ ደሞዙ እስከዛሬ 17,000 ሺ ብር ይታሰብለት የነበረ ሲሆን አሁን ግን ለምን ከእኛ የተለየ ይከፈለዋል የሚለው የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት ተቃውሞ መሠረት፣ በዚያውም ላይ በገንዘብ ምንጩ ማረጥ ምክንያት የዐማራ አድማ ብተናም ልክ እንደ መከላከያ ሠራዊቱ 3,000 ሺ ብር ደሞዝ ይከፈለው ተብሎ መወሰኑ ራሱ ለዐማራ ፋኖ እንደ ቶምቦላ ቁጠሩት። በጄነራል ተፈራ ጫካ መግባት ላይ የአድማ ብተናው ደሞዙ መፈጥፈጥ በራሱ አድማ ብተናውን ይበትነዋል። ብአዴንም ያርፋል ብዬ አላስብም። አሁን የዐማራ ፋኖ ማድረግ ያለበት ብዬ የማስበው ወደ ዐማራ ፋኖ ትግል የመጣ ይምጣ፣ የተቀላቀለም ይቀላቀለው፣ ፋኖ ዓላማውን አስረድቶ፣ አሳውቆም በአዲሱ የፋኖ የትግል አቅጣጫ መሰረትም አጥምቆ በዚያ በአዲሱ የፋኖ እምነት እና አስተሳሰብ እየመሩ ማንቀሳቀስ እንጂ ብአዴን የነበረ ሰው ሲመጣ ብአዴን፣ ግንቦቴ የነበረ ሰው ሲመጣ ግንቦቴ፣ ብልግና የነበረ ሲመጣ ባለጌ ሆኖ በዚያው የብልግና ሀሳቡ የፋኖን ትግል ለመምራት የሚሞከር ከሆነ ይሄ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። የመጣ ይምጣ፣ የመጣውን ሁሉ አለመግፋት። መቀበል። መግፋትም አይቻልም። ነገር ግን የመጣው ቢመጣ፣ ስምም፣ ገንዘብም፣ ዝናና ማዕረግ ዕውቀትም ቢኖረው መመራት እና መገዛት ያለበት ግን በአዲሱ የዐማራ ፋኖ የጥመቀት ባህል መሠረት መሆን አለበት ባይ ነኝ። አሮጌውማ አሮጌ ነው አልፏል።

"…በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። ማር 2፥ 21-22

"…በተረፈ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ሟቹ አገዛዝ የትየለሌ አጀንዳ ነው የሚፈበርከው። ታገቱ፣ ተገደሉ፣ ሰልፍ ወጡ ወዘተ ነፍ አጀንዳ ነው ያለው። በዐማራ ክልል ብልፅግና ፈርሷል። በየቦታው ወይ በብሄር፣ ወይ በሃይማኖት አጀንዳ ሊፈጥር ይችላል። የዐማራ ግን አይኑን ከእንቁላሏ ላይ ሳይነቅል አጀንዳው ፋኖነት ብቻ መሆን ነው ያለበት ባይ ነኝ። በየቦታው መጯጯህ የለበትም። ንቁ፣ ተጠራጣሪ፣ መርማሪ፣ ብልህ ዐማራ ነው መፈጠር ያለበት። አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን የለበትም። ደግሞም ዐማራ ከማሸነፍ ውጪ ሌላ አጀንዳ የለውም። ሊኖረውም አይገባም። ተጯጩሆም፣ በጥፊ፣ በካልቾ፣ በእርግጫም ተጎሻሽሞም ቢሆን አንድነቱን ፈጥሮ ወደፊት ብቻ መሄድ ነው የሚያዋጣውም ባይ ነኝ እኔ። እናም ዘመዴ ይሄን አለኝ ብለህ የምትከፋ ካለህ ግን ከይቅርታ ጋር ምንም ልረዳህ አልችልም እና አንድ ጊዜ በአናትህ ተተከል። ሚልኢላል ኢሄ…😁

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ስለ ብዙ ምክንያቶች ስል በሰሞነኛው የጀነራል ተፈራ ማሞ የዐማራ ፋኖን የመቀላቀል ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቤ ዝምታን መምረጤ ይታወቃል። አሁንም ቢሆን ከአቅም በላይ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ እና ተናገር፣ ተናገር የሚያሰኘኝና ያ ቀኝ ትከሻዬንም የሚሸክከኝ ነገር ካላስቸገረኝ በቀር እንደወትሮው ሁሉ በጉዳዩ ላይ እንዲች ብዬ የታወቀውን ዝርግፍ ነጭ ነጯን ሓሳቤን አልሰጥም። ብዙ ቃልም አልተነፍስም። ይሄ ማለት በቃ ዝም ጭጭ ብዬ እቀራለሁ ማለትም አይደለም። መነሻ ምንጫችሁ ከግግጂጂ የሆናችሁና በዚህ ጉዳይ ላይ እንድናገር ደጋግማችሁ የምትወተውቱኝ ሰዎች እያየሁ ነውና ለሀራራችሁ ስል የዛሬውን በስሱ ወርውሬላችኋለሁና የወረወርኩላችሁን አጥንት ይዛችሁ እሱን እያኘካችሁ ተፋቱኝ።

"…ጄነራሉ የዐማራ ፋኖን በመቀላቀላቸው ምንም ዓይነት ተቃውሞም የለኝም። ማርያምን አዛኜን ነው የምላችሁ ምንም ዓይነት ተቃውሞም የለኝም። የጄነራሉ ፋኖን መቀላቀል ጥቅሙ ቢበዛ እንጂ ክፋቱ ስለማይታይ ተቃውሞ የለኝም። አይደለም አንድ ስመ ጥር ጎምቱ ልምድ ያለው የዐማራ ጀነራል ይቅርና ይሄን የአሁኑን የዐማራ የህልውና ትግል ዐማራ ነኝ ያለ ሁሉ እንዲቀላቀለው አይደል እንዴ የዘወትር ውትወታዬ? ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ድረስ መጮሄስ ለምን ሆነና? የልዩ ኃይል ወታደሮች፣ የመከላከያ ኮሎኔሎች፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና የመንግሥት ሠራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ ሚሊሻዎች፣ ሴቶች፣ ገበሬዎች እስላም ክርስቲያን ሳይል የዐማራ ፋኖን የመቀላቀል ውዴታ ሳይሆን የግዴታ ግዴታ ነው መሆን ያለበት ብለን መወትወት ከጀመርን እኮ ቆየን። እንዲያውም ጀነራሉ እስከአሁን ለምን ዘገዩ ተብለው ካልተጠየቁ በቀር ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል በሚለው በደስታ መቀበሉ የተገባ ነው። እንዲያውም ወደፊት አሁን በፋኖ ትግል ላይ አሻራውን ያላሳረፈ ዐማራ ዐማራነቱ ጥያቄ ውስጥ እስኪገባ ድረስ ሕግ ሁላ መውጣት አለበት የምል ሰው ነኝ እኮ እኔ ዘመዴ። እናም ከዚህ የተነሣ ይሄን ጮማ የሆነ ዜና ሰምቼ የምቃወምበት ምንም ምክንያት የለኝም። በዚህ በኩል ስጋት አይግባችሁ። ይህን ማለቴ ግን ጥያቄ የለኝም ማለት አይደለም። ጥያቄው መቼ ነው መቅረብ ያለበት የሚለው ቢያከራክረን ነው እንጂ ወሳኝ ወሳኝ መታለፍ የሌለባቸው ጥያቄዎችማ ይኖራሉ። እሱ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው።

"…እኔ በበኩሌ ጄነራሉ መቼ ፋኖን እንደተቀላቀሉ፣ ተቀላቅለው አሁን የት እንዳረፉ ጭምር ቀደም ሲል ነው የማውቀው። ዜናውን በሰበር መልክ ከሠሩት አካላት አስቀድሜ ነበር የማውቀው። መቼ ወደ ፋኖ እንደሄዱ፣ ለምንስ ብለው እንደሄዱ ጭምር አሳምሬ ነው የማውቀው። ከኦሮሙማው አገዛዝ የተደገሰላቸውን ድግስ ከውስጥ ካሉት ወዳጅ ጓደኞቻቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ራሳቸውን እንዴት ተዘጋጀላቸው ከተባለው ወጥመድ እንዳስመለጡ ጭምር ነው የማውቀው። የመጨረሻ ማሪያፋ ምሽጋቸው ሳይደርሱ አስቀድሞ የጠፋ፣ የጎደፈ ስማቸውን በሰበር ዜና በመጠገን በእስክንድር ያጡትን ቅቡልነት ዳግም ለመጠገን የተሄደበትን መንገድ ግን እቃወማለሁ። አሁን እንኳ ጀነራሉ አስተማማኝ ሥፍራ ነው ያሉት ስለተባለ የዜናው መውጣት፣ መራገብም ስጋቴን ይቀንስዋል። እሳቸው እደርሳለሁ ብለው ከተነሡበት ስፍራ ሳይደርሱ ዜናው መሠራቱ ነበር ያስደነገጠኝ። ዝም ያስባለኝ።

"…እኔ የማምነው፣ የምጠብቀውም የፋኖ ትግል እንደሆነ በግለሰቦች ላይ የተመሰረተ፣ የተንጠላጠለም አይደለም። እኔ የማምነው የፋኖ ትግል መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ያለው ቅዱስ ትግል ነው ብዬ ነው የማምነው። የፋኖ ትግል አስነሺው ራሱ እግዚአብሔር ነው ባይም ነኝ። ፈጣሪ የሀገሪቱን አምባገነኖች ሊያስተነፍስበት፣ የዓለማችንን ነውረኛ የአምባገነን መሪዎች ደጋፊ፣ ስምሪትም ሰጪና ተንከባካቢ መንግሥታትን ሊያሳፍርበት፣ በዚያውም ለዘመናት የተጠራቀመውን የዐማራን በደል ሊክስ፣ እንባውንም ሊያብስ፣ የደረሰበትንም የግፍ የዶፍ ዝናብ ያስቆም ዘንድ ፈጣሪ ወዶና ፈቅዶ ጊዜው ሲደርስ ያስነሣው ነው ብዬ ነው የማምነው። ብዙ ሰው ይሄን ለማመን ሲቸገር ባይም ለእኔ ግን እውነቱ ይሄው ነው። ይሄን እግዚአብሔር ለሕዝቡ እፎይታ ለማምጣት ሲል በፈቃዱ ያስነሣውን ሕዝባዊ የኅልውና ትግል ግን ተፃራሪ፣ ፈታኝ ሁነት አይፈጠርበትም ማለት አይደለም። ይፈጠራልም። እነ ብአዴን፣ እነ ግንቦት 7፣ እነ ግንባሩና ድዱ፣ እነ ኦሮሙማ፣ እነ ወያኔና ሻአቢያ፣ እነ አማሪካና አውሮጳ፣ አረቡና ሌላውም ጭምር ዝም ይላሉ ብዬም የማስብ ሞኝ አይደለሁም። ፍላጎቶች ይኖራሉ። ግን የዐማራ ፋኖ ይሄን ሁሉ ሸፋጭ አሸንፎ ነጥሮ ይወጣል ብዬ የማምን ሰው ነኝ። ፈተናማ እንኳን ለፋኖ ለክርስቶስ ራሱ መች ቀረለት?

"…ላለፉት 12 ወራት የዐማራ ፋኖ ያለምንም የጦር ጀነራል መሪነት፣ የጦር መሣሪያ ክላሽና ተተኳሽ ትጥቅ አቅርቦት፣ በባዶ እጅ በጥቂት ፋኖዎች ቁርጠኝነት፣ ከዐማራ የልዩ ኃይሉ በወጡ ፖሊሶች፣ እኔ እስከማውቀው ቁጥራቸው ከ4 በማይበልጡ ኮሎኔሎች፣ አብዛኛው ከተሜ፣ ጠመኔ ሲጨብጥ በኖረ አስተማሪና ብዕር ሲጨብጥ በኖረ ተማሪ፣ በንግድና በእርሻ ሥራ ይተዳደሩ በነበሩ ዐማሮች፣ ወጣት ሴቶችና ወንዶች፣ ከዩኒቨርሲቲ በሄዱ ኢንጂነር፣ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ተጋድሎ ነው ይሄን በድሮን፣ በጀት፣ በታንክና በባንክ፣ አቅርቦቱ ከፍ ያለ፣ ስንቅና ትጥቁ ከራሱ ከዐማራው ግብር ላይ በሚቆረጥ በጀት የተደራጀን የፈርዖን፣ የናቡከደነጾር፣ የኔሮን ቄሳር የሆነ የፋሽስት አረመኔ የኦሮሙማ አገዛዝ መክተው እንኩትኩቱን ያወጡት፣ ገትረውም የያዙት እነሱ ናቸው። ይህ የሆነው ደግሞ የዐማራ ሕዝብ የሚታገልበት ሃቀኛ ምክንያት ስላለው ፈጣሪም ስለረዳው እንጂ ጀነራል ጦሩን ይመራ ስለነበር አይደለም። ደግሞም ለመታገያ ሃቅ ያለው አካል በየትም ቢሆን አሸናፊ ነው።

"…የጄነራሉ ወደ ፋኖ የመቀላቀል ጉዳይ በዜና ሲነገር ምንም ጥርጥር የለውም የፋኖ ትግል ዓለምአቀፍ ትኩረት ይስባል። ያገኛልም። ምንም ጥርጥር የለውም ጄነራሉ ያደራጁት፣ አስቀድመውም የሚያውቁትና በአገዛዙ ተጠርንፈው አሁን ዐማራን እየወጉ የሚገኙትና በዐማራ የአድማ ብተና ውስጥ ያሉ፣ የዐማራ የልዩ ኃይሉ አባላትም ቀላል የማይባሉቱ ሌላ አስገዳጅ የመኮብለያ ምክንያትም ተጨምሮበት የጀነራሉ ወደ ፋኖ ትግል መቀላቀል ግን እነሱን ወደ ፋኖ ትግሉ ይስባል ተብሎ መጠበቁ እውነት ነው። ተመልከት ዓላማህን፣ ተከተል አለቃህን አይደል ከነአባባሉስ? ደግሞም የትኛውም ጦርነት ወይ በእውቀት፣ አልያም በዘልማድ በድፍረት ነው የሚመራው። ጀግናን የሚፈጥረው ጊዜና ሆኔታ ነው። በሁለቱም የሰው ጉዳት አለ። በእውቀት የሚመራው በጉልበት ከሚመራው የተሻለ የወገን ጉዳት ግን ይቀንሳል። ውትድርና ጥንትም፣ አሁንም ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው። ጀነራል ሆነህ እንደ ወያኔው ጀነራል ምግበ ዓይነት ደደብ ከሆንክ ብቻ በሰው ማዕበል በ21ኛው ክፍለ ዘመን አዲስ አበባ ልግባ ብለህ ከመቀሌ ተነሥተህ ጥቁር አስፋልት ላይ እየተግተለተልክ በድሮን ሕዝብህን አስጨፍጭፈህ ሚልዮን ትግሬ የምታስበላው። አልያም እንደ ዐማራ ልጆች ከባዶ ተነሥተህ ቀስ በቀስ እየዘመንክ አስተማማኝ ድል ወደ መጎናጸፍ የምትሸጋገረው። እናም የጄነራል ተፈራ ማሞ አሁን ወደፋኖ መቀላቀላቸው ለፋኖ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙን ይበልጣል ብሎ ማሰቡ እና መመኘቱ ይበልጣል። 👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።” ሉቃ 9፥62

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel