መልካም…
"…እንደተለመደው እግዚአብሔር ይመስገን ባዩ ሕዝብ ቁጥሩ ሞልቶ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። ያው እንደሁል ጊዜው ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን እንደ ጥቅሱ የዐማራን ሸለቆ ሁሉ ከፍ የሚያደር፥ ተራራውና ኮረብታ የመሰለውን ሁሉ ዝቅ የሚያደርግ፣ ጠማማውንም የሚያቀና፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል ብሎ ዐማራውንና የዐማራውን ትግል የሚደግፉትን ሁሉ በተስፋ የሚሞላ መራር እውነት የያዘ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ” ኢሳ 40፥4
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ዛሬ ተጀምሮ ዛሬ የሚያልቅ አልሆነም። ስጽፈው ራሱ እየተቃጠልኩ፣ በተስፋ እየተሞላሁ የጻፍኩት ስለሆነ ብዙ አናግሮኛል። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚያልቅ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ከእኔ ርዕሰ አንቀጽ እንደ መንደርደሪያ ተነሥታችሁ እናንተም በራሳችሁ እይታ ልታዳብሩትም ትችላላችሁ። የዛሬው ርዕሰ አንቀጼም እንደ ወትሮው ሰናፍጭ የበዛበት፣ መተሬም፣ እንቆቆም ያለበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የበዛበት ርዕሰ አንቀጽ ነው። ሰብሰብ ብላችሁ የምታነቡት ነው።
"…እኔ ርዕሰ አንቀጼን ቋጭቼ ወደ እናንተ ለትችት እስከመጣው ድረስ እስከዚያው በእዚህ ቁርስና ምሳ እራትም በሆነ የፋኖዎች አቋም እየተደመማችሁ ቆዩኝ። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ተአምር እየተሠራም ነው።
• ወደ ኩሽናዬ ተመልሼ ርዕሰ አንቀጹን ልቀምምላችሁ አይደል? 😂 እስኪ እናንተም ለምሳም ለእራት ለቁርስም የሚሆናችሁን ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችሁ እስክመጣ ድረስ እነዚህን የእሳት ላንቃ የሆኑ ነበልባል የዐማራ ፋኖዎችን ሞራል እየሰጣችሁ፣ አጋርነታችሁን እየገለጻችሁላቸው፣ እየመረቃችኋቸውም ጠብቁኝ።
"…አንዳንድ ቦታ ኔትወርክ ስለተለቀቀ መልእክታችሁን ያነብቡታልና በማርያም ሞራል ስጡአቸው። 🙏🙏🙏
"…የነገ ርዕሰ አንቀጼ ነው።
"…በአርበኛ ዘመኔ ካሴ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ይመሰገናል፣ ይበረታታል፣ ደግሞም ከእኔ ከምሥራቁ ሰው ከሐረርጌው ቆቱ ከመራታው ዘመዴ ከሥላሴ ባርያ ከድንግል አሽከር ከባለ መዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ ከነፍጠኛ ወዳጁ ከአክሊለ ገብርኤል ተጨማሪ ነጭ ነጯን የሆነ ወንድማዊ ማር ማር የምትል የጭቃ ዥራፌን ምክር እሰጣለሁ። አርበኛ ማርሸት ፀሐዩን አመሰግናለሁ። ድርጅቱንም የዐማራ ፋኖ በጎጃም ከምክር ጋር አከብረዋለሁ። የነገ ሰው ይበለን።
"…በአንጻሩ በሻለቃ መከታው እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጋራ የሚተዳደረውንና የሚመራውን የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ፋኖን መከታውን ጨምሮ በውስጡ ስላሉት ወንድሞች ስል የማርያም መንገድ የሚሰጥ የጭቃ ዥራፌን ምክር እና ጥቆማም እሰጣለሁ። መቼ ነገ ጠዋት በርዕሰ አንቀጼ ማለት ነው።
"…የጎጃማ ዐማራ ፋኖዎች የሕዝባችሁን አስተያየት ስለሰማችሁ ሰምታችሁም ማስተካከያ ስላደረጋችሁ በታላቁ የዐማራ ሕዝብ ስም ሳመሰግናችሁ ቅሽሽ አይለኝም። ያውም ቆሜ ነው የማጨበጭብላችሁ። ቀሪ ጎዶሎአችሁም እንዲሁ ይሰተካከላል ብዬም አምናለሁ።
"…ሻለቃ መከታው እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም አብራህ የተቀመጠችውንና በሕግ ያልተሰጣትን የዐማራ ፋኖ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ይመስል የሌለ ከፋፋይ አጀንዳ እያነሳች ሕዝብ ላይ ምታስታውከውን በመደዴነትም በሸዋ ሕዝብ ላይ ቅርሻቷን እንድታቀረሽ የቴሌ ኢንተርኔት አሰጥታችሁአት የምታስለፈልፋትን የአጣዬ ወረዳ በርግቢ አካባቢ ተወላጇን በትግል ስሟ ፋኒት ባርች ወይም በመዝገብ ስሟ መቅደስ አድማውን በተመለከተ እሷን እንደ ተናግሮ አናጋሪ በመቁጠር ልክ እንደ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የግል ትችቴን አቀርባለሁ። መቼ? ነገ ጠዋት።
• ማርያምን አዛኜን ዐማራ ግን ድብን አድርጎ ያሸንፋል…!
ግሩም ነው…!
"…ለመጀመሪያው ጥያቄ ማለትም "አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…? ለሚለው ጥያቄ አንድም የሳተ ሰው ሳይኖር ፋኖ በማለት መልሷል።
"…ቀጥሎም በሁለተኛ ደረጃ ለቀረበው "የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ነው ካልን፣ የኦነግ ሸኔም ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው…? ለሚለው ጥያቄም እንደ ቀደመው ጥያቄ አንድም የሳተ ሰው ሳይኖር በብዙ ሰው የሚደንቅ ተሳትፎ ዐማራ በማለት ተመልሷል።
"…አሁንም እጠይቃለሁ… ወያኔን የሚመራው፣ መሪውንም የሚመርጠው ትግሬ ከሆነ፣ ኦነግ ሸኔንም የሚመራው መሪውንም መሪ ሁነን ብሎ የሚመርጠው ኦሮሞ ከሆነ ፋኖን ለመምራት የፋኖን መሪም መምረጥ፣ መሾም፣ መሻርም ጭምር ያለበት ማነው?
• አንድ 100 ሰው ✍✍✍
በጥያቄ እንጀምር…?
"…አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…?
"…መዘብዘብ የለም። ጥያቄው ቀላል ነው ብሎ መናቅም የለም። መጎረር፣ መፎከርም የለም። ከዚህ ምላሽ በመቀጠል ወደ ሌላ ጥያቄ እና መልስ ስለምንሄድ ያለምንም ገተታ መልሱን ብቻ ቁጭ።
"…እደግመዋለሁ… አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገዶች (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…?
~ 100 ሰው ✍✍✍
“…እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።” ኢሳ 30፥26
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ከዝክር መልስ…
ከጥያቄ 1 - 26
"…ዛሬ ደስ ብሎኝ ነበር ያመሸሁት። በሀገረ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጅ ከዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን የሐምሌ ሥላሴን አከበረን። ኢትዮጵያን ነው ያስታወሰኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ከመኝታ በፊት ግን ይህን ልበል። እንግዶቼን ከሸኘሁ በኋላ አስቀድሞ ወጣ በተባለው በፈተናው ጉዳይ ዘመዴ ይሄ የለጠፍከው ያልተፈተኑት ነው የሚል ሓሳብ ሰጪ በዝቶ አግኝቻለሁ። ጥያቄው የማኅበራዊ ሳይንስ ቢሆንም ከሰብጀክት ኮድ በስተቀር አይመሳሰልም። ለምሳሌ፦ ፔጅ ነምበር፣ ቡክሌት ኮድ፣ ምርጫ ኮድ በአጠቃላይ ጥያቄው ገና ያልተፈተኑት ነው የሚልም አስተያየት እያየሁ ነው። አይ እገሌ ነኝ ይሄንን በእገሌ ዩኒቨርሲቲ ፈትኜዋለሁ የሚሉም ታይተዋል።
"…የሆነው ሆኖ እኔን ምን አስጨነቀኝ? ምንስ አጨቃጨቀኝ? ተማሪዎቹ ቀድመው ተፈትነውት ከሆነ እሰየው ቀድመው ያልተፈተኑት እና ወደፊት የሚፈተኑት ከሆነም ከሆነም እሰየው፣ የተፈተኑት ከሆነ እንዲያውም ክለሳ ይሆንላችኋልና ለምን ሙሉውን አልለጥፍላችሁም ብዬ በማሰብ ሙሉውን ለጥፌላችኋለሁ። ተማሪዎች ቀድመው የተፈተኑት ከሆነ መልካም ነው መልሰው ቢያጠኑት ምናቸው ይጎዳል? ምንም። ያልተፈተኑት ከሆነም አገዛዙ ተሰርቆ ወጥቶበት ከሆነ ይጠነቀቅበታል። አለቀ። ተማሪዎች ግን አጥኑ። ሳትዘናጉ ወጥራችሁ አጥኑ።
• ደኅና እደሩልኝ።
"…ቀጥሎ የምጽፈው ርዕሰ አንቀጽ ለፍሮፌሰር ብራኑ ነጋ ተቋም ለሆነው ለትምህርት ሚንስቴር ነው። ይሄ በስሱ አለፍ አለፍ አድርጌ የለጠፍኩት ፈተና የእናንተ ተቋም ለመጪው ረቡዕ ያዘጋጀው የፈተና ወረቀት ነው ወይ? ከሆነስ አስቀድሞ ተበትኗል እና ለማስተካከል ምን አስባችኋል? ካልሆነም በመረጣችሁት መንገድ አትጨነቅ አትሰብ በሉኝ ለማለት ስል ይህን ርዕሰ አንቀጼን ቀጥዬ እለጥፋለሁ።
• ፌክ ከሆነ ግን እለፉት።
መልካም…
"…ይጠበቅ የነበረው 1ሺ አመስጋኝ በቶሎ ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ሰሞኑን በነገርኳችሁ መሠረት ዛሬ በቤቴ ከባባድ እንግዶች ይመጡብኛል። እኔና ቤተሰቤም የቅድሥት ሥላሴን፣ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስንና ቅዱስ ጴጥሮስን፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዝክር በአንድነት ልንዘክር ተፍተፍ እያልን ነው። እናም ዛሬ ሰፊ ርዕሰ አንቀጽም ሆነ ዛሬ ማታ በመረጃ ተለቭዥን ነጭነጯን ከዘመዴ ጋር አይኖረንም። በፈረንሳይኛ ዛሬ ዘኬ ለቀማ ላይ ነኝ ማለት ነው። ገባችሁ ኣ…?
"…ለማንኛውም ግን በዐማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በይፋ ሳይነሣ በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተነሣውን የኢንተርኔት እገዳ አስመልክቶ የቅድመ ጥንቃቄና አንዳንድ መልእክቶችን…
"…የፊታችን ሐምሌ 10 የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ፈተናን በተመለከተ ለትግሬና ለኦሮሞ ተማሪዎች አስቀድመው መልሱን ሠርተው ይዘጋጁ ዘንድ ነው ተብሎ የወጣን ሙሉ የፈተና ወረቀት ለልጃቸው ደርሶ ነገር ግን ድርጊቱን ተቃውመው ሕዝቡም መንግሥትም ድርጊቱን አውግዘው ያርሙም ዘንድ ከአንድ ለነፍሳቸው ካደሩ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለ ማዕተብ ቤተሰብ የተላከልኝን ሙሉ የሒሳብ የፈተና ወረቀት በተመለከተም ለትምህርት ሚንስቴርና ለኢትዮጵያው አገዛዝ ጥቆማ ከነምልክቱ ለመስጠት ብቅ ለማለት እሞክራለሁ።
"…አገዛዙ ስህተቱን የሚያርም ከሆነ በተመቸው መንገድ ያሳውቀኝ። ዝም ጭጭ ብሎ ባላየ ባልሰማ ለማሳለፍ የሚሞክር ከሆነ ግን ዛሬ እስከ ማታና እስከ ነገ ጠዋት የማያሳውቀኝ ከሆነ ትግሬና ኦሮሞ ብቻ ፈተናውን የሚሠራበት ምክንያት የለም ብዬ ዐማራ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጉራጌና ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ጉምዙ፣ ጋምቤላው ሁሉም ተዘጋጅተው ይገቡ ዘንድ ሙሉውን የፈተና ወረቀት ለመለጠፍ እገደዳለሁ።
• እንግዶቹ ሳይመጡ አጭሯን ርዕሰ አንቀጽ ልጻፍላችሁ አይደል? 😂
"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ ጽፌ ከለጠፍኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ወርሀዊው የማኅበር ጸሎት ስፍራ ነበር የሄድኩት። የቴሌግራም መንደር የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም ክፍት አድርጌ ነው እኔ ስልኬን ዘግቼ የጸሎት መርሀ ግብሬን ስከታተል ያመሸሁት።
"…ከጸሎት መልስም ከካህናት አባቶቼና ከወንድም እህቶቼ ጋር ስጫወት አምሽቼ ከሁሉም ጋር ከተለያየን በኋላ ነው ቆይቼ ወደ ቴሌግራም መንደሬ የገባሁት። ወደ መንደሬ ስገባ እማመይ ድረሽ መንደሩ በአስተያየት ጨቅ ብሎ ነው የጠበቀኝ። አንድም ሳይቀረኝ ሙሉ በሙሉ ነው አስተያየቶቹን ያነበብኳቸው።
"…ግንባሩና ሠራዊቱ ቲክቶክ ላይ በአፋቸው የሚጸዳዱ የሴትና የወንድ ክፍት አፎችን እንደለመዱት ወደ እኔ የቴሌግራም መንደር ልከው የለመዱትን ጥንባታም፣ ግማታም፣ ክርፋታም፣ ሸታታ የተለመደ አሳቃቂ የስድብ ናዳ የሚያወርዱ ልማደኞች እንደሌላው ቤት መስሏቸው በለመዱት መንገድ ወደ ቤቴ መጥተው ቤቴን ቁናስ በቁናስ ሊያደረጉ የሞከሩ ጥቂት ክፍት አፎችን በማግኘቴ እነሱን ከቤቴ ጠራርጌ ወደ ጋርቤጅ ከትቼ ነው ገና አረፍ ማለቴ ነው። እንዴት ናችሁልኝ? እንዴት አመሻችሁ?
"…ደፈር ብሎ መነጋገር መጀመሩ አስደስቶኛል። የዛሬው አብሪ ጥይት ነው። ስስ የጭቃ ዥራፌም ነው። ወፈር ያለው የጭቃ ዥራፌ እንደ ሁኔታው እየታየ ወደፊትም ይቀጥላል። በድፍረት በእውነት እና በእውቀት መወያየት ያጸድቃል። ገነት ነው የሚያስገባው።
"…እኔ አይስክሬም ነጋዴ ወይም ሻጭ አይደለሁም። እኔ ኮሶ ነጋዴ ነኝ። መቅመቆ መተሬ ሻጭ። ስታነበው ሱሩር ይልሃል። ይቀፍሃል። ያንገሸግሽሃል። እንደምንም እያንዘረዘህ፣ እያንቀጠቀጠህ ጨክነህ መጨለጥ ነው።
• ደና ናቹ…?
👆ከላይኛው የቀጠለ… በዚህኛው በኩል ደግሞ ይሄን ነፍሰ ገዳይ አረመኔ ሥርዓት ለመንቀል ለሕይወታቸው ሳይሳሱ በድንጋይና በዱላ ሳይቀር ፊት ለፊት ከጠላት ጋር እየተናነቁ የአገዛዙን ሠራዊት እያባረሩ ትጥቅ የሚማርኩ ጀግኖችን ስናይ ደግሞ ተስፋችንን ይበልጥ ያለመልመዋል። እንኳን አሁንና አድማ ብተናው፣ ሚሊሻው ግልብጥ ብሎ ወደ ፋኖ ትግል እየገባ፣ እንኳን አሁን እና ኮሎኔል ጄነራሉ ወደ ፋኖ ትግል እየተመመ ይቅርና በፊትም ቢሆን ገና በጨቅላ በልጅነት ጊዜ በፋኖ ትግል አፍሬ አላውቅም። ይደፈርሳል። ከዚያ ደፍርሶም ይጠራል። ገፈቱ፣ አተላው ይወገድ እና ንጹሑ የጠራቀው ፋኖ ያቸንፋል። አለቀ። ይሄው ነው።
"…ሁለት ሦስት እንቁራሪቶች በጩኸት በሚረብሹት ውቅያኖስ ውስጥ ስንትና ስንት ፀጥ ብለው ሥራቸውን የሚሠሩ ግዙፍ ግዙፍ ሻርኮችና ዓሣ አንበሪዎች እንዳሉ ማወቅ ተገቢ ነው። እንዴት ሰው ከኦሮሙማውና ከትግርሙማው አክቲቪስት እኩል እንዲህ ወርዶ በራሱ መሪዎች ላይ ይደነፋል? እናም ወዳጆቼ በእንቁራሪቶች ጩኸት አትረበሹ ለማለት ነው። እንቁራሪታም…
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አንድ ሰሞነኛ ጀብዱ ላጫውታችሁ። ሰሞኑን ነው። 10 መኪና ሙሉ የሰለጠነ የብራኑ ጁላ መከላከያና የአቢይ አህመድ ሪፐብሊካን ጋርድ ከባህር ኃይልና ከኮማንዶ ጋር ተሰባጥረው በአንድነት የተዘጋጁ ልዩ ኦፕሬሽን ሠሪ ናቸው የተባሉ ወታደሮችን የያዘ ጦር ለተባለው ልዩ ኦፕሬሽን ወደ አንድ የፋኖ ቀጠና እየተመመ ይሄዳል። ያ የፋኖ ሠራዊትም እየተመመ ወደ ቀለበቱ ውስጥ የሚመጣውን ጦር ጠብቆ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር ይደመስሰዋል። ፋኖዎቹ ሦስቱን መኪና ወታደር ይቀብሩና የ7ቱን መኪና አስከሬን ግን ሕዝቡን ቅበሩ ብለው ያዝዛሉ። ሕዝቡም በጡሩንባ ወጥቶ ወታደሮቹን ከነቀዩ ቆብ ልብሳቸው እያለቀሰ ቀበራቸው። ተተኳሽ ጥይት፣ በግመል፣ በአህያ፣ በበቅሎም ተግዞ አላልቅ ነበር ያለው። ሁሉ ነገር በፎቶም፣ በቪድዮም ተቀርጿል። ነገር ግን ለአንዳቸውም የሚዲያ አካላት አልተላከም። ፕሮፓጋንዳም አልሠሩም። ሃቀኛ ሠራተኛ እንዲህ ነው። አይለፈልፍም። እወቁኝ፣ እዩኝ፣ ተመልከቱኝም አይልም።
"…ሰሞኑን በጎጃም እና በጎንደር የተደረገ አንድ ከፍተኛ ሰቅጣጭ የሆነ የጦርነት ቪድዮ እያየሁ ነበር። በጦርነቱ ላይ በተፈጸመ ተጋድሎ ምክንያት በፋኖ ኃይሎች የተጨፈጨፉ የአገዛዙን የመከላከያ ሠራዊት አባላት እያየሁ ነበር። የፋኖ ኃይሎቹ ከድል በኋላ በአስከሬኖቹ ዳር ቆመው ሲያለቅሱ ሁላ ነው ያየሁት። ለአንድ አቢይ አህመድ ለተባለ እብድ ሰው ብለው እንደ ጭዳ እየተጨፈጨፉና እያለቁ ስላሉ የኦሮሞና የደቡብ ወጣቶች ቆመው ሲያለቅሱ ነው ቪድዮው የሚያሳየው። "ጨርሱን፣ ግደሉን፣ ግደሉን" የሚሉና ከወገብ በታች ተጎምደው የሚያቃስቱ፣ በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ የሚቃትቱ ነፍሳትን እያየሁ መፈጠሬን ነበር የጠላሁት። ከጎረቤት ሀገር ጠላት ጋር፣ ከውጭ ከመጣ ወራሪ ጋር አይደለም ጦርነቱ። ጦርነቱ ከራስ ሕዝብ ጋር፣ ከራስ ወገን ጋር ነው። እናም ዘግናኝ ነው። ይሄን ጀብዱ የሚፈጽሙ የዐማራ ፋኖዎች ግን ሚዲያው አያውቃቸውም።
"…በዚያው ልክ የበሰሉ የዐማራ ፋኖ ትግል የገባቸው፣ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ ያልሆኑ የዐማራ ሚዲያዎችንም እያየሁ ነው። የማይሞቃቸው የማይበርዳቸው። በግንቦት ሰባት፣ በባልደራስ፣ በግንባሩና በሠራዊቱ ዝባዝንኬ ላይ ሓሳብ የማይሰጡ፣ እንደ ዋቅጅራ ልጅ፣ እንደ ስታሊንና ሀብታሙ የመሳሰሉ የሰይጣን ጥንቸሎችን ለመያዝ የማይሯሯጡ ጎበዝ የዐማራ ሚዲያዎችን እያየሁ ነው። ሥራ ብቻ ላይ የተጣዱ። ይሄ ራሱ የዐማራ ፋኖ የደረሰበትን ከፍታ የሚያሳይ ነው። ቆሜ ነው የማጨበጭብላቸው። አከበርኳችሁ። መከታውን እንግደለው፣ አሰግድን ድፋው፣ ዘመነን አስወግድ፣ ሀብቴ ድራሹ ይጥፋ፣ ምሬ እንደዚህ ነው የማይሉ። ትግሉ የገባቸው። የጠላትን አጀንዳ የማያስፈጽሙ። በወሬ የሌለ ፍሬ የማይለቅሙ። የአባቶቻቸው ልጆችን እያየሁ ነው። ዝንፍ እንዳትሉ አንበሶቼ።
"…የዐማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ከዐማራው ይልቅ ለምን አማሪካ፣ ብርሃኑ ጁላና ብአዴን እነ ህወሓት ሁላ እንደፈለጉት አልገባኝም። የብልፅግና አክቲቪስቶችም በአንድነቱ ላይ ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ እየተጉ ነው። አንድነቱ ባይጠላም በእርግጥ ለአንድነቱ እንቅፋት እየሆኑ ያሉ በጣት የሚቆጠሩ በእነ ሀብታሙ አያሌው በኩል የሚዘወሩ አደረጃጅቶችም እንዳሉ እሙን ነው። በእነ ሀብታሙ በኩል ብቻ ሳይሆን በጎጃም በእነ ማርሸት በኩልም በዚህ በዘመነ ቴክኖሎጂ ጊዜ ድምፁ እንደሚቀዳ እየታወቀ ሆን ተብሎ ለጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው ከፋፋይ መረጃ መስጠት ለምን እንደተፈለገም የሚያወረቁት ሴራውን የፈጠሩ አካላት ናቸው። እንደ ምናላቸው ዓይነት ጎምቱ ጋዜጠኛም ለፋኖ የማይጠቅም የወረደ ተርኪ ምርኪ መረጃ መለቃቀም እና እንደነ ሀብታሙ አያሌው የፋኖ ትግል ውስጥ ገብቶ ማቡካካትን ለምን እንደመረጠ አላውቅም። ሀብታሙ አያሌው ሸዋን፣ ወሎን፣ ጎንደርና ጎጃም ላይ ራሱ ዘልቆ ገብቶ እያተራመሳቸው ነው። ምንአላቸው ደግሞ የሰፈሩን ልጅ ይዞ ሀብታሙን ለመገዳደር እየታተረ ነው። በሀብታሙና በምናላቸው፣ በግዮን ቲቪና በኢትዮ 360 ፉክክር ፋኖዎች በሁሉም እየታዘቡ ይስቃሉ።
"…በቅርበት እንደማውቀው በአንድነት ጉዳይ ሰፊ ሥራ እየተሠራበት ቢሆንም ልዩነቱን በማስፋት በጎጣቸው እና በአካባቢያቸው ለመወሸቅ የሚሠሩ ታጋይ መሳይ ብዙ ባንዳዎችም ተፈልፍለውም እየታዩ ነው። ፀቡ ባለፈው እንደገለጥኩት በፋኖ አደረጃጀት አለመስማማትና ሁሉም የመሪነት ሥፍራውን ቦታ ለመያዝ መሽቀዳደም ላይ ነው የተጠመደው። አሁን ላይ የብርሃኑ ጁላን ሠራዊት ከመመከት ባለፈ በአንድነቱ ላይ እየመከሩ ቢሆንም ልዩነቶች እየሰፉ ስለመጡ በዚህ ከቀጠሉ እመኑኝ በቅርቡ እርስ በእርስ ይጣለዙና ትልቁ ዓሣ ትንሹን ዓሣ ቀርጥፎ በመብላት አሸናፊ ሆነው ለመከሰት ይላላጣሉ። ይሄ አስፈሪ ነው። መካሰሱ፣ ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከሚቢያው ላይ ቁምቢጥ ልበል ባዩም በዝቷል።
"…ወደ ሰሞነኛው የአንድነት ጉባኤ ስንመጣ የዋቅጅራ ልጅ እንደሚያወራው አይደለም። ሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ተገናኝተው ተሰባስበዋል። ሕግም አውጥተዋል። በሕጉም ላይ ቃል በቃል ተናብበው አስተያየትም፣ እርማትም ሰጥተው ቃላቸው እንደፊርማ ተቆጥሮ ተመዝግቦ አልፎ ጸድቋል። ከዚያ ወደ ጥቆማ ነው የተሄደው። የሚጠቆመው ሰው ከተጠቆመ በኋላ በሥሩ ስላለው የኃይል አሰላለፍ፣ ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያ፣ የእዝ፣ የብርጌድ ብዛት፣ ወዘተረፈ ማስመዝገብ አለበት። እናም በዚህ መሠረት ነው ስምም ሆነው ወደ ምርጫው የገቡት። የመጀመሪያውን ዕጩ ተመራጭ ሻለቃ ዝናቡ ጠቆመ። የጠቆመውም አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ነበር። ከጥቆማው በኋላ በሕጉ መሠረት አርበኛ ዘመነ ካሴ ስለሚመራው ጦር አጠቃላይ መረጃ ከነጦር መሣሪያው ዘርዝሮ አቀረበ። አለቀ። የዘመነ እንደተሰማ ቀጣዩ ጥቆማ እና ተጠቋሚ ቀረበ። የተጠቆመው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነበር። መልካም በሕጉ መሠረት ስለምትመራው ጦር፣ ስላለህ የኃይል ብዛት፣ ከነጦር መሣሪያህ አቅርብ ተባለ። እስክንድር አላቀርብም አለ። አንተን ሳንገፋህ ወደዚህ ኅብረት ያመጣንህ ለዐማራ ስንል ነው። እናም በጨበጣ ማለፍ የለም። የምትመራውን ጦር አስጽፍ ተባለ። በስንት ውትወታ ኮሎኔል ጌታሁን የእኔ ነው። ጎጃም ጋር ማስረሻ አለ። ጎንደርና ወሎም አለኝ አለ። ጎንደር የት? ወሎስ እነማን ብለው አፋጠጡት። አልናገርም አለ። እገሌ ጋር ሁለት ስናይፐር፣ አንድ ሞርታር አለኝ ሲል ጉባኤው በሳቅ ፈረሰ። በቃ ስብሰባው ተቋረጠ። እርግጥ ነው ከወሎ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባው፣ ከሸዋ መከታው፣ ከጎጃም ኮሎኔል ጌታሁን፣ ከጎንደር እነ ጋሽ መሳፍንት፣ የማከብረው ሀብቴም ወደ እስክንድር ነው የሚያደሉት። በጉዳዩ ላይ የፋፍዴን እና የቀደመው ጎህልማ ቡድን፣ የፒለቱካው ቅማንት እና የፖለቲካው አገው ሸንጎ፣ ግማሽ ኦሮሞ የሆኑቱ የሸዋ ሰዎችም፣ የዜጋ ፖለቲካ አራማጆችም አንድ ያለን ተስፋ እስክንድር ነው በማለት ከእስኬው ጋር እየተንደፋደፉ ነው። ግን በብዙ ምክንያት አይሳካላቸውም ባይ ነኝ።
"…እስክንድር መሪ መሆን አይችልም። እስክንድር ከዳር ያደረሰው አንድም ድርጅት የለም። እስክንድር የተማረ ሰው ፀር ነው። እስክንድር ሁል ጊዜ ሁላችን በገነባንለት ስሙ ላይ ተንጠላጥሎ ድርጅት ከመሠረተ በኋላ ገንዘብ በመሰብሰብ ወደ ድርጅቱ የተማሩ ሰዎች፣ መርህ ይከበር የሚሉ ሰዎች አጠገቡ እንዲደርሱ አይፈልግም። እስክንድር ነጋና አቢይ አሕመድ ለእኔ ተመሳሳይ ባሕሪ ነው ያላቸው። አቢይ አሕመድም በዙሪያው የሚሰበስበው አቅመ ቢስ ደካሞችን ነው። እሱ ሲናገር የሚያጨበጭቡ። ስድስት ዓመት 👇ከታች ይቀጥላል…
መልካም…
"…ምስጋናችን ሰፍቷል። አመስጋኙም በዝቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋናው በኋላ በቀጥታ የምንገባው እንደተለመደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…ትናንት በክብርት ባለቤቴ ትዕዛዝ ሁላችን የቤተሰቡ አባላት በቤት ሥራ ተጠምደን በማምሸታችን ምክንያት እንደወትሮው ርዕሰ አንቀጻችን ሊቀርብ አልተቻለም። የእናንተ ርዕሰ አንቀጽ ይቀራታል እንጂማ የ30 ዓመት ባለቤቴን ትእዛዝ አልሽራትም። እንደዚያ ብዬ ነው ከግድግዳ ግድግዳ እንደ ፌንጣ እየዘለልኩ መስታወት ሳጸዳ ያዋልኩት። አቤት እንዴት እንደመረቀችኝ። አይነገርም። በሚስታችሁ መመረቅን የመሰለ ነገር የለም። ባረከችኝ በሉት።
"…ዛሬ ከድካም አገግሜ፣ እስትራፖው ለቅቆኝ😂 እንደምንም ተከስቻለሁ። በዛሬው ርዕሰ አንቀጼ እነዚህን ወንድሞቼን የጭቃ ዥራፌን አንስቼ እየሸነቆጥኩ፣ መራር ኮሶ፣ መተሬ ሰናፍጭ የበዛበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ሸንቆጥ፣ ብትት፣ ነቃ የምታደርግ ጦማር በርዕሰ አንቀጽ መልክ ላቀርብላቸው ወደድኩ። ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ምክር ልመክራቸውም ፈለግኩ። ደግሞስ ምክር ነው ምንአባታቸው ያመጣሉ? ምንም ምንም አያመጡም።
"…እ… እንዴት ነው ምን ታስባላችሁ? ልምከራቸው ልተዋቸው። ባላየ ባልሰማ ልዝለላቸው? እናንተስ ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?
• ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
"…በካቶሊክና በፕሮቴስታንቶች የፕሮሞሽን ብዛት ስለተሸፈነው ጥንታዊውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በተመለከተ እንዴት ያለ ክሽን ጥፍጥ ያለ ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጅቼ ነበር መሰላችሁ።
"…ሰሞኑን እንግዶች ስለሚመጡ መኖሪያ ቤታችን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ይጽዳ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ከክብር ቀዳማዊት እመቤት እሜይቴ ሚስት ቀጭን ትእዛዝ ስለወረደ እኔም ከቤተሰቡ በአቅሜ እሠራው ዘንድ የቤቱን መስታወት የተባሉ ጉዶች አፀዳ ዘንድ የወደቀብኝን ዕጣ አንሥቼ እንደ ወፍራም ወደል ዝንጀሮ ከጣሪያ ጣሪያ ከግድግዳ ወደ ግድግዳ ስዘል ቆይቼ ገና አሁን መሬት መንካቴ ነው። የማዳም ቅመሞች ድካም፣ የሚስቶች፣ የእህቶችም የቤት ጽዳት ድካምን ዛሬ አይደል እንዴ ያየሁት። የመድኃኔዓለም ያለህ።
"…አሁን ደግሞ የወደቀብኝን ዕጣ ጉዳይ ጨረስኩ ስል ቤተሰቡ አድሞ አዬ ወዴት ወዴት በል በል የምን ስልክ ላይ መጣድ ነው? አባው አልጨረስክም። አሁን ደግሞ የቤቱን ደረጃና የቤቱን ምንጣፎች ታጸዳ ዘንድ ሁለተኛው ዕጣ የወደቀው አንተ ላይ ነው። እናም ፅዳቱን የሚያግዝህ ማሽን ቢሆንም ሥራው ግን የሚጠብቀው አንተኑ ነው ተብዬ ወደዚያው ልነካው ነው።
"…ዛሬ ብዙ የምሥራች፣ ቁንጥጥ፣ ልምዝግ የሚያደርግም ጦማር ለማዘጋጀት በትበት ብዬ መጣም፣መጣም ዝግጁ የነበርኩ ቢሆንም የቤተሰብ ጉባኤው ፍርድ ግን አላላወሰኝም።
"…ዳይ ወደ ጥግረራዬ… ጊዜ፣ ፋታ ካገኘሁ እመለሳለሁ። እስከዚያው በፋኖ ፍቅር የወደቀው የወለይ ስታሊን እና የዐማራ ፋኖ ቃለ የስብሰባ ጉባኤ ያዥ ሆኖ የተከሰተው የባለአደራው፣ የባልደራሱ የአዲስ አበቤው የእስክንደር ነጋ የአማሪካ ተወካይ የነበረው ኤርሚ ኤል ዋቅጅራን ዘገባ እየሰማሁ ልጠግረር። 😂😂😂
• 🖐🖐🖐
መልካም…
"…እስከአሁን ርዕሰ አንቀጹ በ17 ሺ ሰው መነቡብን እያየሁ ነው። ቆይቶ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ እስከ አሁን በርዕሰ አንቀጹ የተበሳጨም ሰው 😡 አላየሁም። ከርዕሰ አንቀጹ ቀጥሎ የሚቀርበው ደግሞ ርዕሰ አንቀጹን ተከትሎ ከእኔ የጎደለው የሚሞላበት፣ የበዛው የሚቀነስበት የእናንተው ሓሳብ የሚንሸራሸርበት መድረክ ነው።
"…ዛሬ ከወትሮው ከተለመደው ሰዓታችን 1 ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርበው የዕለተ ሐሙሱ የኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ ዝግጅታችን እስኪደርስ ድረስ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ሓሳብ እየሰጠን እንቆያለን።
• 1…2…3…ጀምሩ…!✍✍✍
“…ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤” ኢሳ 40፥4
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ከዚህ የመሸጋገሪያ መልእክት በኋላ እንመለሳለን… 😂😂😂
"…ባንዲራው የሰይጣን ነው ብለው ለባንዲራው ደሙን የሚያፈሰውን ሶዬ ባንዲራው ላይ አስቁመው አስካዱት። ይሄ ባንዲራ የሰይጣን ባንዲራ ነው" በል አሉት ኦነግ ሸኔውም ግጥም አድርጎ ይሄ ባንዲራ የሰይጣን ባንዲራ ነው ብሎ አረጋገጠላቸው። ይሄ ባንዲራ አያሻግርም፣ ይሄ ባንዲራ አያበለፅግም😂 ይሄ ባንዲራ ሀገር አጥፊ ነው በል አሉት ሸኔውም አለላቸው።
"…በመጨረሻው ዘመን ቤተሰብ ለቤተሰብ አንዳንዴ ይጣላል የተባለው እውነት ነው ለካ። የራስህ ጉዳይ…
• ቆይቼ ተመልሼ እመጣለሁ…
መልካም… ወደ ሁለተኛው ጥያቄ እናልፋለን።
"…ለመጀመሪያው ጥያቄዬ "አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ አዳኝም ጠባቂም ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…? ለሚለው ጥያቄ መቶ ሰዎች ይመልሱልኝ ብዬ ብጠይቅም በደቂቃዎች ውስጥ ከ400 በላይ ሰዎች በድፍረት፣ በወኔ፣ በእውነት እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው መልሱ ፋኖ ነው በማለት መልሰዋል። ግሩም ነው። ዕጹብ ድንቅ ነው።
• ሁለተኛውን ጥያቄ እቀጥላለሁ።
"…አሁንም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ (የነገድ አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ከሆነ፣ የኦነግ ሸኔ ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው እንላለን…?
• ይሄንንም ሳትዘበዝብ፣ ሳትቸከችክ፣ ሳታንዛዛ መልስልኝ።
• ከአንድ 100 ሰው መልስ በኋላ ከች እላለሁ።
"…እደግመዋለሁ። "…የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ነው ካልን፣ የኦነግ ሸኔም ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው…?
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ይሄ ሩቅ ዓባይ ማዶ አይደለም። ተከዜም፣ ራስ ደጀንና መተማ፣ ቋራም አይደለም። ደምበጫም፣ አዲስ ዘመን፣ ነፋስ መውጫ፣ ደብረታቦር ጋይንትም አይደለም። የዋግሹሞቹ ሀገር ላስታ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎም አይደለም። እዚህ ነው አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ሸዋ ክፍለ ሀገር። አዎ እዚሁ ቅርብ ነው።
ከጥንት እስከ ዛሬ ቃሉን የጠበቀ
ፋኖ ነው ዘላለም ሱሪ የታጠቀ
"…ይሄ የምታዩት የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ነው። ዐማራ በታሪኩ በመንግሥት ላይ ተቆጥቶና አኩርፎ ነፍጥ ሲያነሣ ይሄ ዘመን ዘመነ አቢይ የመጀመሪያው ነው። ዐማራ ዳር እስከዳር "መዳኛችን ነፍጣችን" ብሎ ሲወስንም ይሄ ዘመን የመጀመሪያው ዘመን ነው። ያውም ማነቆ ባንዳዎች፣ ሆዳም ዐማሮች፣ የጠላት ቅጥረኞች፣ ሾተላይ ሰላዮች በውስጡ ተሰግስገው፣ በላዩም ተከምረው ተጣብቀውበት ሁሉን ጣጥሎ ከባዶ እጅ፣ ከድንጋይና ሽመል ተነሥቶ እንዲህ ዘጭ ያለው በአንድ ዓመት ውስጥ ነው። ይሄ በአንድ ዓመቱ እዚህ ቁመና ላይ የደረሰው የዐማራ ነገድ እንደ ትግሬ ነፃ አውጪዋ ወያኔና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪው ኦነግ ከ50 እና 60 ዓመት ጀምሮ ብሎ አለማሰቡ ይሻላል። ይሄኔ በምሥራቅ አፍሪካ ራሱን የቻለ ልዕለ ኃያል ነበር የሚሆነው።
"…የዐማራ ትግል አሁን ቁርጥ ሆኗል። አደረጃጀቱም በመንግሥት ቁመና ነው እየተደራጀ ያለው። በስመ ፋኖ መንቀሳቀስ። መዘባረቅ አይቻልም። ፋኖ ባለቤት አለው። የ10 ኛ ክፍል ወዳቂ እና መውደቂያ፣ ገዢ ያጣ ፖለቲካ ይዞ የሚዞር የቦለጢቃ ነጋዴ ሁላ በስሙ የሚነግድበት አይደለም። ሸዋ እንዲህ የሆነ ጎጃም፣ ጎንደር፣ እና ወሎን ማሰብ ነው። መንደሩ ሁሉ ወታደራዊ ሥልጠና ላይ መሆኑም አስደሳች ነው።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
ከዝክር መልስ…
ከጥያቄ 27 - 60
"…ዛሬ ደስ ብሎኝ ነበር ያመሸሁት። በሀገረ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጅ ከዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን የሐምሌ ሥላሴን አከበረን። ኢትዮጵያን ነው ያስታወሰኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ከመኝታ በፊት ግን ይህን ልበል። እንግዶቼን ከሸኘሁ በኋላ አስቀድሞ ወጣ በተባለው በፈተናው ጉዳይ ዘመዴ ይሄ የለጠፍከው ያልተፈተኑት ነው የሚል ሓሳብ ሰጪ በዝቶ አግኝቻለሁ። ጥያቄው የማኅበራዊ ሳይንስ ቢሆንም ከሰብጀክት ኮድ በስተቀር አይመሳሰልም። ለምሳሌ፦ ፔጅ ነምበር፣ ቡክሌት ኮድ፣ ምርጫ ኮድ በአጠቃላይ ጥያቄው ገና ያልተፈተኑት ነው የሚልም አስተያየት እያየሁ ነው።
"…የሆነው ሆኖ እኔን ምን አስጨነቀኝ? ምንስ አጨቃጨቀኝ? ተማሪዎቹ ቀድመው ተፈትነውት ከሆነ እሰየው ቀድመው ያልተፈተኑት እና ወደፊት የሚፈተኑት ከሆነም ከሆነም እሰየው፣ የተፈተኑት ከሆነ እንዲያውም ክለሳ ይሆንላችኋልና ለምን ሙሉውን አልለጥፍላችሁም ብዬ በማሰብ ሙሉውን ለጥፌላችኋለሁ። ተማሪዎች ቀድመው የተፈተኑት ከሆነ መልካም ነው መልሰው ቢያጠኑት ምናቸው ይጎዳል? ምንም። ያልተፈተኑት ከሆነም አገዛዙ ተሰርቆ ወጥቶበት ከሆነ ይጠነቀቅበታል። አለቀ። ተማሪዎች ግን አጥኑ። ሳትዘናጉ ወጥራችሁ አጥኑ።
• ደኅና እደሩልኝ።
መልካም…
"…የለጠፍኩትን የፈተና ወረቀት በተመለከተ ሌሎችም መምህራን ያደረሱኝ ሲሆን። ይሄ የፈተና ወረቀት የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች የተፈተኑት የፈተና ወረቀት ነው። እናም አሁን በመጪው ሳምንት የሚፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ የሚፈተኑት አይደለም የሚሉ መረጃዎች ደርሰውኛል።
"…ምስጋና በቀጥታ የስልክ መስመር ጭምር ደውላችሁ እኔ ራሴ ፈተናውን በኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ክልል ወዘተረፈ ፈትኜዋለሁ ብላችሁ መልሳችሁ ለላካችሁልኝ ይሁን። ልጃችሁ ይዞት መጥቶ አይሆንም እውነት ከሆነም መንግሥት እርምት ይውሰድበት ብላችሁ ጥያቄውን ለላካችሁልኝ ቤተሰቦች ይሁን።
"…የሆነው ሆኖ የፈተና ወረቀቱ ቀደም ብሎም ይውጣ አይውጣ ጉዳዩ ላሳሰባችሁና ለተጨነቃችሁ በሙሉ እንደ ዜጋ ነገሩ አሳስቦን ጥያቄውን ሳነሣና ለውይይት ሳቀርብ ፈጣን ምላሽ ለሰጣችሁኝ ወንድም እህቶቼ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለማንኛውም እኔ ወደ ወደ ዘኬ ለቀማዬ ልመለስ ቢሆንም ፈተና ወረቀት የተባለው ቢሆንም፣ ባይሆንም ብታጠኑት አይጎዳችሁም እና እኔ እንደሚከተለው አድርጌ ለጥፌላችኋለሁ።
• ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ተፈተኑ። መልካም የፈተና ሳምንት ይሁንላችሁ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
፩
• የኢንርኔት መለቀቅን በተመለከተ።
"…50 እና 60 ሚልዮን ሕዝብ በሚኖርበት የዐማራ ክልል ውስጥ ዓመት ሙሉ ኢንተርኔት ዘግቶ ጦርነት ሲያካሂድ፣ የዘር ማጥፋት ሲፈጽም የከረመው የኦሮሙማው አገዛዝ ሰሞኑን በእሜቴ ፍርዬ ታምሩ በኩል ከፓርላማው ዘንዳ ቀርቦ በዐማራ ዘንድ ብከስርም በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ግን ትርፍ በትርፍ ሆኛለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይሄው ትርፋማ ሆኛለሁ ብሎ የተቦተረፈው የፍርዬው ቴሌኮም ካምፓኒ ነው ታዲያ በዛሬው ዕለት በተመረጡ የዐማራ ክልል ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍት ማድረጉን ያወጀው። ይሄን በማስመልከትም የዐማራ አንቂዎች ስጋታቸውን፣ ጥቅምና ጉዳቱንም ጭምር አስመልክተው አጭር የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል። ተጠቀሙበት።
ሀ፦ ጥንቃቄ እና አደጋው
፩ኛ፦ አንዳንድ የዐማራ ወጣት ፋኖዎች ልክ እንደ እንደ እስክንድር ፋኖ እንደ ፋኖ ባርች ሌላኛውን ፋኖ ለመስደብ፣ ለመከፋፈል እና ሰሞኑን የተራገበውን የብልፅግና ሰዎች የሚጮሁበትን የምኞት የክፍፍል ዜና በስፋት በቲክቶክና በፌስቡክ ጭምር በቪዲዮና እና በፎቶ ጭምር ቁርቋሶውን ቢያሰፋልን ብለው በማሰብ በዚያውም የወጣቶቹን ማንነትና መገኛ ስፍራ፣ አደረጃጀት ወዘተ በማነፍነፍ የመሪዎችን መገኛም ለማወቅ ሊሆን ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ ተብላችኋል።
ለ፦ ጥቅሙ እና መልካም አጋጣሚው
፩ኛ፦ አገዛዙ ለተንኮሉም ይሁን የኪሳራው ጉዳት አሳስቦት የከፈተውን ኢንተርኔት መላው የዐማራ ሕዝብ ደግሞ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ቶሎ ቶሎ መረጃ እንዲለዋወጥበት ይደረግም ተብሏል። ለምሳሌ እንደ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ዓይነቱን መልእክት ተለቭዥን ለሌለው ለሁሉም የዐማራ ሚሊሻና አድማ ብተና አባላት እንዲደርስ ማድረግ
፪ኛ፦ በአገዛዙ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን ቶሎ ቶሎ ለታማኝ ሚዲያዎች በመላክ ወዲያው ግን የኢንተርኔት አጠቃቀምን በራስ ላይ ማዕቀብ በመጣል ጭምር ገደብ መጣል ያስፈልጋል ተብሏል።
፫ኛ፦ ከወትሮው በተለየ መልኩ የፋኖ አባላት ስልክ እንዳይጠቀሙ መጠርነፍ፣ መከልከል። ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ፣ ለፍቅረኛ ወዘተ ለመደወል መሯሯጥ ቢቀርም ተብሏል። ወዳጄ ፋኖ ድምጽህን አጥፋ። እንደ እነ ፋኖ ባርች በመንግሥት የተፈቀደልህን የመከፋፈል ፈቃድ ይዘህ ኢንተርኔት ላይ ተጥደህ አትደስኩርም ተብለሃል።
"…የማትሪኩን የፈተና ወረቀት በተመለከተ ከ30 ደቂቃ በኋላ ሓሳቤን በመረጃና በማስጃ እሰድላችኋለሁ። መጀመርታ ይሄኛውን ተጠቀሙበት።
• ቆይቼ እመለሳለሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"…እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን። ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።
…በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። 2ኛ ቆሮ፥ 13፥ 9 -14
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…ያለምንምንም ተናዳጅ 😡 ሰው እስከአሁን ርዕሰ አንቀጻችንን 14 ሺ ሰዎች ማንበባቸውን የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት በግድግዳዬ ላይ ተለጥፎ ይታያል። ይሄን ከለጠፍኩ በኋላ 😡😡😡 ብው ያሉ ሰዎች ቢግተለተሉ አይገርመኝም። የሚጠበቅም ነው።
"…እንግዲህ ቀጥሎ ደግሞ እስከ መኝታችን ሰዓት ድረስ የእናንተ ሓሳብ የሚደመጥበት ሰዓት ነው። ርዕሰ አንቀጹ ላይ ጎደለ የምትሉት ነገር ካለ መጨመር መብታችሁ ነው። የበዛ ነው የምትሉት ካለም መቀነስ መብታችሁ ነው። እኔ የታየኝን፣ የመሰለኝን ጽፌአለሁ። እናንተም እንደዚያው።
"…እንደ ማሳሰቢያ በዚህ ርዕሰ አንቀጽ ላይ ጥቅማችን ተነክቷል። በደል ደርሶብናል የምትሉም ካላችሁ ደግሞ በጨዋ ደንብ መወያየት፣ መሞገትም የተፈቀደ ነው። በተለይ የግንባሩ፣ የሠራዊቱ፣ የግለሰቦች ፍቅር ከትግሉ በላይ እንደ አምልኮ የተጠናወታችሁ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን መግለጽ ትችላላችሁ። የቦርኮ ስድብ ግን አልታገስም። ቦዘኔ ጥግህን ያዝ። አልያም ክፍት አፍህን እከፍታለሁ ብትል አጠናግሬ አሳርፍህሃለሁ። ሰምተሃል።
"…ይሄ ስስ፣ ቀጭን የጭቃ ዥራፌ ነው። ጸሎቴ ተሰምቶ ተናግሮ አናጋሪ ካገኘሁ ግን ከዚህ የባሰ፣ ወፈር ያለ ርዕሰ አንቀጽ እንደምንም ብዬ በትበት ብዬ ላዘጋጅላችሁ እሞክራለሁ።
• 1…2…3… ጀምሩ…✍✍✍
✍✍✍
👆ከላይኛው የቀጠለ… ሙሉ ሲጠራቸው አቤት፣ ሲልካቸው ወዴት የሚሉ ሰዎችን ነው የሚሰበስበው። ሲሾማቸው እሺ፣ ሲሽራቸው እሺ የሚሉትን ነው የሚሰበስበው። እስክንድርም እንደዚያው ነው። በብዙዎች ተስፋ የተጣለበትን ባልደራስን እኮ ያፈረሰው አቅም ያላቸውን ዶክተሮች፣ ምሁራን ድራሽ አባታቸውን አጥፍቶ የተራ አስከባሪ፣ ሊስትሮና የጥበቃ ሰዎችን ሰብስቦ ነው አፈር ከደቼ ያበላው። በባልደራስ ስም በአሜሪካ የተሰበሰበ ዶላር እዚያው አሜሪካ ነው ቀልጦ የቀረው። የተራ አስከባሪ የባልደራስ አባላት፣ ሊስትሮዎች ይሄን ሊጠይቁ አይችሉማ። ኦዲት ሳይደረግ ነው ተቀርጥፎ የቀረው። እስክንድር ሸዋ ላይም እንደዚሁ ነው ያደረገው። መጀመሪያ ሁሉንም በአራቱም የፋኖ ግዛት ዚሮ ተመለከተ። ገመገመ። የኃይል ሚዛናቸውን፣ የሰው ሀብታቸውንም ገመገመ። አማኞቹን በመሀላ ቀፈደደ፣ ምርጫውን ግን ሸዋ ከመከታው ጋር አደረገ። መከታው እንደ እስክንድር ፈጣሪውንም ያከብር አይመስለኝም። የመከታውን ስስ ብልት እስኬው በደንብ ነው ያገኘው።
"…እስክንድር ገንዘቡ በእጁ፣ ፕሮፓጋንዳውን በሀብታሙ አያሌው በኩል አድርጎ ኢትዮጵያኒስቱን በእነ አበበ በለው ታጅቦ በሸዋ አሰግድና መከታው እንዳይስማሙ፣ እንዳይታረቁ አድርጎ ሽብልቅ ገባላቸው። እስክንድር በደረሰበት ስፍራ ሁሉ ድሮኗ ከእስክንድር ኋላ የሚሄድ ወሳኝ ዐማራ እየበታተነች ስትገድል ኖራለች። ደብረ ኤልያስ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ የተካሄደው በእስክንድር ነጋ ምክንያት ነው። በሸዋም እንደዚሁ። እስክንድር ኢንተርኔት ይጠቀማል። የአገዛዙ ስጋት የለበትም። እስክንድር እነ ባርች የተባሉ የ10ኛ ክፍል ወዳቂ፣ የአረብ ሀገር ተመላሽ ህመምተኛ ከአጠገባቸው አድርገው ሸዋ ላይ ክፍፍል ይፈጽማሉ። በእነ አቶ አሰግድ ጋርም ጥፋት የለም እያልኩ አይደለም። ጥፋቱ ግን በንግግር የሚፈታ እንጂ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚያስነሣም አይደለም። የሆነው ሆኖ እስክንድር የፋኖን ትግል ቢያዘገየው እንጂ ሊያስቆመው አይችልም።
"…አሁን ጉዳቱ ለእነ መከታው ጦር ነው። የመከታው በግል ከእስክንድር ነጋ ጋር መጣበቅ የመከታውን ጦር ዓለምአቀፍ የሸዋ ተወላጆችን ድጋፍ አሳጥቶታል። መድኀኒት፣ የሴት ታጋዮች የንፅህና መጠበቂያ ቁስ ሳይቀር ይረዱ የነበሩት አሁን ቀጥ አድርገዋል። ለአቶ አሰግድ አግዘው አይደለም ያቆሙት። የእስክንደር ነጋ ሴራ ስለገባቸው ነው ያቆሙት። የመከታው የጦር አዛዦችም ለመከታው አማራጭ እያቀረቡ ነው። ወይ ከእኛ ወይ ከእስክንድር ብለውት አጣብቂኝ ውስጥ ከትተውታል። የእስራኤል የስለላ ቡድን ድጋፍ እንዳለው የሚነገርለት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባለው ቡድን ከእስክንድር ነጋ ጀርባ መኖር ደግሞ እስክንድር የገንዘብ ምንጩ ይነጥፍበታል ተብሎ እንደማይገመት የሚናገሩም አሉ። እስክንድር ገንዘብ እስካለው ድረስ ትንቢት የተነገረልኝ የፋኖ መሪ ነኝ ባዩ እስክንድር ነጋ የፋኖን ትግል ማተራመሱን ይቀጥላል። ሰሞኑን አይታችሁ እንደሆነ የኦሮሞና የትግሬ አክቲቪስቶች፣ የግንቦቴና የግንባሩ ሰዎች ሳይቀር ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸው። የመከታው ጦር የሚባለው የአቶ አሰግድ መኖሪያ ነው የተባለን ቤት ወርረው በቪድዮ ተቀርጸው የለቀቁት ምስል እስክንድር ነጋ ሁሌ ዙሪያው የሚያሰፍረው ጋጠወጥ መደዴ መረን የለቀቁ፣ የዐማራን ስብዕና የማይወክሉ ግለሰቦችን እንደሆነ ነው። እኔ መከታውን ጨምሮ እነ አቤ ጢሞን፣ እነ ዮናስን የመሰሉ ሰዎች እንዴት እንዲህ ዓይነት ጋጠወጥ ወጠጤዎች መሪ ሆነው እንደተቀመጡም ገርሞኛል።
"…ዳግማዊ ቴዎድሮስ ነኝ፣ በጳጳስ ተቀብቼ ነግሻለሁ፣ ትንቢት የተነገረልኝ ቀጣዩ ንጉሥ ነኝ የሚሉ ቅዠታም ድንባዣም አእምሮቢስ ሰገጤዎችን በዚህ ትግል ውስጥ ማየቱም እንብዛም አይገርመኝም። በተለይ የታላቁ እና የታናሹ እስክድር አጠቃላይ የዐማራ ፋኖ መሪ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ ብሎ የሙጥኝ ማለት በፋኖ ውስጥ ቀውጢ እየፈጠረ ነው። ይሁን እሺ አንግፋው ብለው ቢያቀርቡትም አንጃ ለመፍጠር ከመወተርተር አልቦዘነም። በጎጃም ማስረሻ ሰጤን እና በወሎ የኮለኔል ሞሀባውን ክንፉ በመዘወር የሥልጣን ግብግብ እንዲያደርጉ የሚገፋፋው ደግሞ ሀብታሙ አያሌው ነው ተብሏል። የእነ ዘመነ ካሴ ድክመት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ሀብታሙም የወሎ ዐማራ ነኝ በማለት የሸዋ የቱለማ ኦሮሞዎችን በእነ መከታው በኩል በማስተባበር፣ አሰግድንና መከታውን በማመታት፣ በመጨረሻ አሰግድን በማስገበር እስክንድርን ይዘን ወደፊት መምጣት አለብን ነው የሚሉት። ገና አራት ኪሎ ሳንገባ ካላነገሣችሁኝ የሚል የሥልጣን ጥም ያለባቸው አንድ አንድ ሰዎች ቢያስቸግሩንም ግን ዘመዴ ሙት አሳምረን እናሸንፋለን የሚሉኝ ፋኖዎች መኖራቸውን ሳይ ደግሞ ተስፋዬ ሺ እጥፍ ይለመልማል።
"…የእስክንድር አካሄድ አይሳካም። እኔ ሲመስለኝ በሻዋ ጠንካራ ዲሲፒሊን ያለው እስከአሁንም አድፍጦ ሲሠራ የነበረ፣ እዩኝ፣ እዩኝ የማይል አዲስ ግርማ ሞገስ ያለው ጦር ይፈጠራል። በቅርቡም ሁሉንም ውጦ ሰልቅጦ ወደ አንድ የሸዋ አደረጃጀት ያመጣቸዋል። አሁን ራሱ በመከታውም በአሰግድም ጦር ስር ያሉት ታጋዮች ከነ ብርጌዳቸው ወደዚያ የፋኖ አደረጃጀት ለመግባት ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የመከታውም ጦር ከመከታው ይለያል። የማውቀውን ነው የምነግራችሁ። የአሰግድም ጦር እንደዙያው። መስማማት፣ መነጋገር፣ መወየያት፣ ልዩነትን መፍታት የማይችል የዐማራ ፋኖ ትግልን አያሻግርም። ትግሉ የህልውና ትግል ነው። በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለም አይደከም። እየወደቀ፣ እየተነሣም ይሻገራል። የሚገርመው በጎንደር ሁለት አይነት የፋኖ አደረጃጀቶች ቢኖሩም ውጊያ ሲመጣ ሁለቱም ልዩነታቸውን ትተው አንድ ላይ ሆነው ነው የሚታገሉት። የሚዋደቁት። ይሄ ማለት ጠንካራ፣ ቅን፣ እውነተኛ ሽማግሌ ቢኖር ጎንደር አንድ ይመጣል። ሸዋም እንደዚያው። እንደ እስክንድር አይነት እኔ ካልመራሁ ባይ የዳያስጶራ ገንዘብና የኢትዮጵያኒስቱ ካምፕ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ ካምፕ የሆነ ሰው እያለ ግን ትግሉ ይዘገያል። ይዘገያል እንጂ ድሉ እንደሁ አይቀርም።
"…የሚያናድደው ነገር እስክንድር እና እነ ሀብታሙ አያሌው ከሥልጣን ጥም የተነሣ ባይበጠብጡ ኖሮ በዚህ ክረምት ወደ አንድ መጥተው በጋራ አመራር የተሳካ ኦፕሬሽን ፈጽመው አገዛዙን እንኩትኩቱን ለማውጣት ነበር ፍላጎቱ። በእነ ማርሸት እንዝህላልነት፣ ያለመብሰል፣ በእነ እስክንድር እኔ ካልመራሁ ባይነት አንድነቱ ሊሳካ አልቻለም። በአስቸኳይ ይሄ ታርሞ ወደ አንድነት ከተመጣ ግን የዐማራ የመከራ ቀንበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይወልቃል። ውባንተን ያስገደለው እኮ በእስክንድር ስር አልገባም ማለቱ ነው። አሰግድም፣ ሌላውም ከተገደለ የሚገደልበት ዋናው ምክንያት ሌላ ሊሆን አይችልም። ብአዴን እስክንድርን ይዛ ፕሮሞሽን ሠርታለት በጎጃም ምድር ስታዞረው ከርማ ጫካ ግባና ተዋጋኝ ያለችው ለምን እንደሆነ የምታውቀው እሷ ናት። የፋኖ ወደ አንድነት ያለመምጣትን የተመለከተው አቢይ አሕድም ሰሞኑን "ክረምቱ እስኪወጣና በቂ ሎጀስቲክ እስክናሟላ ድረስ ጦራችንን ባለበት ቦታ እናክርም የሚል ውሳኔ ማስተላለፉን እና ሰሞኑን የአብይ አህመድ ጀኔራሎች ተሰብስበው ሲያወሩ መደመጡም ተነግሯል። ለዚህ ደግሞ ሚሊሽያ፣ ፖሊስና አድማ ብተና እየላክን ፋኖ ወደ ወታደራዊ ካምፖቻችን እንዳይመጣ የቅድመ መከላከል ማጥቃት እንደርጋለን። እስከዚያው በፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ሽብልቅ እየከተትን እነ እስክንድርን እየደገፍን እናጯጩኸው ነው የሚሉት ተብሏል። ይሄ በዚያ በኩል ያለ ዕቅድ ሲሆን…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ሰሞኑን ጩኸት የሚቀሙ የድል አጥቢያ አርበኞች ከዐማራ ፋኖ የትግል የፊት መስመር ላይ እንደ ጉንዳን፣ እንደ ቁጫጭ፣ እንደ በረሮ ሲርመሰመሱ፣ ውኃ እንደተጠማ የዱር እንስሳት ግርር ብለው ሲግተለተሉ እያየሁ ግርም ብሎኝ ነገርየውን ለማጣራት ፍጻሜውንም ለመመልከት ስል ጥጌን ይዤ ከዳርም ቆሜ በመታዘብ ላይ እገኛለሁ። እኔ የማየው፣ የምሰማው ሌላ፣ አዳሜና ሔዋኔ የድል አጥቢያ አርበኛ ሁላ የሚቦተረፈው ሌላ። ኦሆሆ ጉድ እኮ ነው እናንተው።
"…የዓድዋው ትግሬ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያው ስታሊን እንኳ ስለ ዐማራ ፋኖ አደረጃጀት፣ ጥንካሬና ድክመት ለማውራት ከ1:00 ሰዓት በላይ ዩቲዩብ ላይ ተጥዶ እብልዥቭዥቭኡቘፇኧቍ እያለ ሲንተባተብ ሳይ አምላኬ ሆይ ይሄንንማ በሕልምህ ነው በለኝ ብዬ ሦስት ጊዜ ሁላ ነው ያማተብኩት። "የፋኖን ትግል በ3 ደቂቃ የሚፈርስ ኢንዶሚን ነው" እያለ ሲሳለቅ የከረመው ሶዬ ዛሬ ዓይኑን በጨው አጥቦ ፋኖ፣ ፋኖ፣ ጀግናው እስክንድር አርበኛው ዘመነ ካሴ፣ ጋሽ አሰግድ፣ ምሬ ወዳጆ እያለ ሲደሰኩር ሳየው ዓይኔንም ጆሮዬንም ነው የተጠራጠርኩት። ደግሞ እኮ ልመናዋ አትቀርም። ክቡራን የሚዲያችን ተከታታዮች እንግዲህ ለዐማራ ትግል ለምናደርገው አስተዋጽኦ ሁላችሁም ያላችሁን በዜል፣ በካሽአፕና በዶነር ቦክስ ጣል ጣል አድርጉብን ሲል የዓይኑን ሽፋሽፍት እንኳ ለሰከንድ አያርገበግብም። አይ አማርኛ ለልመና ጊዜ ሁሉም አቁፋዳውን ይዞ ከች ይልብሻል። እነ ነውር ጌጡ። ኢመቺሽ ወለይ ነፍሴ።
"…የአዲስ አበባ ልጆች ወኪል። የብርቱው ሰው፣ የብረታ ብረቱ፣ የአይሰበሬው፣ የአይቀነጠሴው፣ የጀግናው፣ የፅኑው፣ የአለቱ፣ የጠንካራው፣ የአይበገሬው፣ የታላቁ እስክንድር ምክትል የባለ አደራው ጎምቱ ባለ ሥልጣን የነበረው የቀድሞው ኢህአዴግ፣ የኋላው ግንቦት 7፣ ቆይቶ ኢሳት፣ ከዚያ 360 አሁን ደግሞ የኮምፓሱ ባለቤት አማሪካዊው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ራሱ የፋኖ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ ያዥ ሆኖ ከፊተኛው የፋኖ ረድፍ ላይ ለቀድሞ አለቃው ለእስክንድር ነጋ ሽንጡን ይዞ ሲከራከር ሲሟገትለትም አይቼ ይሄማ ቅዠት መሆን አለበት ብዬ አስር ጊዜ ባማትብም እውነት ሆኖ አልለወጥ ብሎኝ ገርሞኝ፣ ገርሞኝ ነው እስከ አሁን ያለሁት።
"…የቲክቶክ መንደር የጎረምሶች ሽኩቻ፣ ድንፋታ፣ ዛቻ እና ግብግብ። የፌስቡክ መንደር ሁካታ፣ የዩቲዩብ ሰበር ዜናው ራሱ እኔ የማላቀው ነው የሆነብኝ። ፋኖዎቹ ሲሰበሰቡ በቅርብ እከታተለው የነበረውን የስብሰባ ሂደት በስብሰባው ላይ የሌሉና በሂደቱ ውስጥ ያልነበሩቱ አካላት ገሚሱ ዘመነን፣ ገሚሱ እስክንደርን ይዞ ሲጯጯህበት ሳይ ይሄ ነገር ብሔራዊ ቲአትር የሆነ ድራማ ለመሥራት ልምምድ እያደረጉ ይሆን እንዴ? ብዬ ለመጠየቅ ሁላ እየዳዳሁ ነው። መሬት ላይ ያለው እውነት እና አየር ላይ ያለው ሸቀጥ፣ ትርምስ አስደማሚ ነው። ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሶ ሌላ ዓለም ላይ ነው አዳሜ የካቶሊክና በፕሮቴስታንት ቀደምትነት እና መሪነት ጉዳይ ላይ ጭቅጭቅ ላይ ነው።
"…የመጀመሪያው ሐዋሪያዊ እምነት ኦርቶዶክስ ነው። ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ እምነት በኋላ የተከሰተ ድርጅት ነው። ቆይቶ ደግሞ ከካቶሊክ ፕሮቴስታንት ተገንጥሎ ወጣ። ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ከእምነት ፉክክር አልፈው በመንግሥታት የሚደገፉ ሆኑ። መንግሥታቱም የፖለቲካ ፖሊሲያቸው ማስፈጸሚያ አካል አድርገው ስለፈጠሩአቸው ግራና ቀኝ በደጋፊ መንግሥታት ታጅበው በዓለም ላይ የፕሮሞሽን ሥራውን ያጧጥፉት ነበር። የሮም ኢምፓየር የሮማን ካቶሊክ ይዛ ዓለምን አስገበረች። አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ፣ አውሮጳ፣ አሜሪካና ካናዳ፣ አውስትራሊያ ጭምር፣ እነ ካሪቢያን ደሴቶች ከካቶሊክ በቀር ሌላ ጥንታዊ እምነት የሌለ ተደርገው ነው የተሰበኩት። ኋላ ላይ ጴንጤዎቹም በፉክክሩ ገብተው በተለይ ከማርቲን ሉተር መምጣት በኋላ የተቃውሞ ጽሑፎቻቸውን በቶሎ ከሕዝብ ዘንድ ለማድረስ ሲሉ የጽሕፈት ማባዣ ማሽን ሁላ ፈልስመው ፕሮፓጋንዳውን አጦፉት። በመሃል የኦርቶዶክሱን ዓለም በእስላም አስቀጠቀጡት። አስወረሩት። እናም አሁን አንድ ካቶሊካዊ ወይም፣ ጴንጤ ስለጥንታዊ ሃይማኖት ብትጠይቁት ከካቶሊክና ከጴንጤ በቀር ሌላ እውነትም እምነትም እንዳለ አይነግራችሁም። ችግሩ የሰውየው ሆኖ አይደለም። ያልነገሩትን ከየት ያመጣዋል?
"…እኔም እላችኋለሁ ፋኖ ማለት በአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተንጠለጠለ አይደለም። በሻለቃ መሳፍንት እና በሻለቃ ባዬ፣ በምሬ ወዳጆና በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ በአቶ አሰግድ እና በመከታው ላይ ተቸክሎ የተቀፈደደ አይደለም። ኦርቶዶክስ የሚባል ጥንታዊ እምነት ከጀርባ ተሸፍኖ አለና የካቶሊክን እና የፕሮን ፍትጊያ እያየህ አንተ ፒፕሉ አትጀዝብ። ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ተያይዞ የመጣ ቀኖናዊ፣ ሐዋርያዊ፣ ዶግማዊ ሃይማኖት አለ። ራሳቸውን በግራ ቀኝ፣ በጠላት እና ወዳጅ በደጋፊ እና በተቃዋሚ ታጅበው በሚፈጥሩት ፍትጊያ የተሸፈኑ የትየለሌ ብፁዓን ፋኖዎች አሉና አትጩህ። ድምፅ ቀንስ ነው የምልህ። አሰግድ እና ምሬ ወደጆ፣ መከታው ፋንታሁን ሙሀባው፣ ባዬ እና ሀብቴ፣ ደረጄ፣ ሳሚ፣ ሰለሞን አጠናው፣ ጋሽ መሳፍንት፣ ደሳለኝ ብለህ እንደ ማስቲሽ እነሱ ላይ ብቻ ተለጥፈህ፣ ተጣብቀህም ዋይ ዋይ የምትልበት አይደለም የፋኖ ትግል። ዞር ዞር ስትል ከካቶሊክና ከፕሮው ጀርባ ድብቁ ግዙፍ እውነት የተሸከሙ ማስታወቂያ የማይሠሩ፣ ዶላር የማይቀፍሉ፣ ጀብድ የሚሠሩ ትንታግ ፋኖዎች አሉና አትንጫጩ። ሸቃጭ፣ ቲፎዞ፣ ግርግር፣ ውርውር የሌለባቸው፤ ሙያ በልብ ብለው ትኩረታቸውን ከትግሉ ላይ ብቻ ያደረጉ ተርቦች አሉ። እኔ የማየው እነዚያን ነው። የእነ ሀብታሙ አያሌው መከላከያ ተደመሰሰ፣ በገፍ እጅ ሰጠ፣ የነተበ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ላይ የማይሸቅጡ፣ የግንቦት 7፣ የባልደራስ፣ የእነ እስታሊን፣ የእነ ዋቅጅራን መንጠራዋዝ ከቁብ የማይቆጥሩ አሉና ተረጋጉ። አሁን ያለው የግራ ቀኝ ጫጫታ ትርፉ መላላጥ ካልሆነ በቀር የሚፈጥረው ነገር የለም።
"…ለትግል የሚላክ ዶላር እንደ አስቤዛ ፋኖ የሚሸምት። ለትግል የሚላክ ዶላር ኡጋንዳና ኬንያ ካፌና ሬስቶራንት የሚከፍት። ከኡጋንዳ ደቡብ ሱዳን ካሚዮን መኪና ገዝቶ የሚነግድ። ታጋዩ ቅማል እየበላው፣ ቂጣ አጥቶ በለስ እና ሙጫ እየበላ እያዩ እነርሱ ጊዜ ሰጥቷቸው የፋኖ መሪ ሆነው ስለተገኙ ቀን በቀን የብግና የፍየል ሙክት፣ በሬ ጥለው ሽንጥና ዱለት እየከኩ፣ ዝንጥ ብለው በፈረንካው በሸነና የሚሉትን ፌካፌክ በሚዲያ ሠራዊት ድጋፍ የሚንቀሳቀሱትን ገልቱዎች እውነተኛ ታጋዮች ሳያቃቸው ይቀር መስሏችሁ ነው? እህቱ የኦህዴድ ባለ ሥልጣን ያገባች የፋኖ አለቃ ዶላሩ በእህቱ በኩል ተልኮ በሸነና የሚለውን የፌክ ፋኖ ግሩፕ እውነተኛው ጠፍቶት መሰሎህ ነው? አሳምሮ ያውቃል። ጥያቄ ያያነሡ፣ ግምገማ ይደረግ ብለው ሓሳብ ያቀረቡ ታጋይ ፋኖዎችን መሣሪያ ገፍፈው የቁም እስረኛ፣ ሌላውን ደግሞ ጠርንፈው በጩቤ ጨቅጭቀው የገደሉ የፋኖ አለቆችን ታጋዩ ሳያውቅ ቀርቶ ይመስልሃል? አይደለም። ሁሉም ሁሉን ያውቃል። ዘራፊው፣ ገፋፊው ማን እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል። ባልየውን በመከላከያ አስገድለው ቤቱ ሄደው ገንዘቡን ሙልጭ አድርገው ዘርፈው ሲያበቁ ሚስትየዋን አንጠልጥለው ሰቅለው ሲያበቁ "ራሷን ሰቀለች" ያሉ ገፋፊ ሳዲስት የፋኖ አለቆች እንዳሉም ፋኖው አሳምሮ ያውቃል። ትግሉ ይዘገይ ይሆናል እንጂ በፍጹም አይቆምም። አሁን ግን እኔ ግን ጥጌን ይዤ ልመልከት። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 48፥22
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
“…ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ።” መዝ 84፥7
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉YouTube
https://www.youtube.com/live/W-w7yQ5WNh0?feature=shared
👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v56j2nm--ethiobeteseb.html
👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb
"…ሻሎም ! ሰላም !
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ልማት የሚጠላ የለም። ልማት ግን ሕዝብን አጥፍቶ አይደለም።
"…ዐማራ ብቻ ይሄን አረመኔ ፀረ ሰው አውሬ ቡድን ለመፋለም ነፍጥ ያነሣው። ዐማራ ብቻ ነው ከዚህ ልቡሰ ሥጋ ጋኔን ጋር ተናንቆ፣ እየተዋደቀ የሚገኘው። ዐማራ ብቻ ነው እምቢኝ ባርነት፣ እምቢኝ፣ በቃኝ ብሎ የተነሣው። ዐማራ ብቻ ነው የተሰባሰበው፣ እየተመካከረም ያለው። ዐማራ ብቻ ነው የአገዛዙን አሽከር ገረዶች እየቀነደሸ እያስበረገገ ያለው። ዐማራ ብቻ ነው አምባገነንነትን እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ ከዜሮ ተነሥቶ ዛሬ ሚልዮን ጀግና ያፈራው። ዐማራ ብቻ ነው ከፍቶኛል ወደ ሱማሌ፣ ኬንያ፣ ሊቢያና የመን ልሰደድ ሳይል ወደ ጫካ ወደ በረሃ ገብቶ እየተፋለመ ያለው። ዐማራ ብቻ ነው አልኩህ። ብራቮ ዐማራ። ሌሎቻችሁ እየተገደላችሁ፣ እየተፈናቀላችሁ፣ እየተሰደዳችሁ፣ እየለመናችሁ፣ እየተንከራተታችሁ፣ እያለቀሳችሁ፣ እየተራባችሁ ኑሩ። ዐማራ ያሸንፋል። ዐማራ ድል ያደርጋል። አሁን ከዚህ አውሬ አገዛዝ ጋር እየተዋጋ የሚሞት ዐማራ እንደሞተ አይቆጠርም። ገነት እንደገባ እንደ ሰማእት ነው የሚቆጠረው። በስደት ሲና በረሀ እና የመን በረሀ ውስጥ በውኃ ጥም ከመሞት ፋኖ ሆኖ ጥሎ መውደቅ በስንት ጣዕሙ።
• ዋሸሁ እንዴ…?
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።