zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተንፒሱ እስቲ…!

"…ከአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ በሚታሰብ ለሁለት ሰዓት ያህል እናንተ ደግሞ ተንፍሱ እስቲ…? ስለ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዝ ጭማሪ 300 እጥፍ አድርጌያለሁ ቀደዳም ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። 300 እጥፍ ማለት እኮ 300×1500=450,000ብር ማለት መሰለኝ። ማሞ ምህረቱ ጠበቃ ሆኖ የገንዘብ አለቃ ሲሆን፣ አቢይ አሕመድ ከ4ተኛ ኡኡ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆን እያየን በግድ ለምን Basic mathematical operation አልተማረም ማለት ያለብን አይመስለኝም አላለኝም አንዱ ጓደኛዬ።

"…ይሄ ከፋኖ ጋር ንግግር ጀምረናል ጭዌዋን ትቆየን እና ይሄ አቢይ አህመድ ጨመርኩ ያለው ደሞዝ 300 እጥፍ ነው ? ወይስ 300 % ለማለት ፈልጎ ነው? እኔም እኮ ተምታታብኝ። ሂሳብ የሚሉትን ትምህርት ከድሮ ጀምሮ ስጠላው ለጉድ ነው። 300 እጥፍ? 300%? 1500ው በ% ስንት ይመጣል ማለት ነው? እስቲ አስሉልኝ። ኤዲያ ደግሞ ስለዚህ ምን አገባኝ በናታቹ? ሥራው ያውጣው?

"…ይልቅ የለመደች ጦጣ…Convince እና Confuse ነው? ወፍ ኤለም… የሚለውን ጦማሬን እንዴት አያችሁት? ተንፒሱ እስቲ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የለመደች ጦጣ…
Convince እና Confuse ነው?
            ወፍ ኤለም…

"…ይልቅ ነፍጣችሁን አስቀምጣችሁ ከጫካም ወጥታችሁ ከአረጋ ከበደም ጋር ተነጋግራችሁ፣ ተደራደሩና በአሬ ስር ሆናችሁ ይቅርታ በአረጌ ስር ገብታችሁ ክልላችሁን በጋራ አበልጽጉ ብሎ ጽንፈኛ የተባለውን የፋኖን ኃይል እንደ ተራ ሽፍታ ቆጥሮ ባህርዳር በአባይ ድልድዩ ስር ቆሞ ከተናገረ፣ ከመከረም፣ ከደሰኮረም እኮ ገና ጥቂት ሳምንታት ናቸው ያለፉት። በጣም ጥቂት? እና ዛሬ ያውም በመንግሥት ደረጃ እየተደራደርን ነው የሚለው ማንን ለማጃጃል ነው የበሻሻው አራዳ? ሃኣ?

"…14 ሺ የፅንፈኛው ፋኖ ኃይል አባላት መንግሥት ያቀረበውን የምህረት ዐዋጅ ተቀብለው ከታች አርማጨሆ ወደ ላይ አርማጨሆ በመምጣት ለበድኑ የብአዴን መንግሥት በሰላም እጃቸውን አንከርፍፈው  ሰጥተው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ከጀመሩ ቆዩ፣ የተቀሩትም ቢሆን ሰሞኑን ለመንግሥት እጃቸውን አንከርፍፈው ለመስጠት መስቀልና ቁርዓን ጨብጠው ቃለመሀላ ገብተውልን እየጠበቅናቸው ነው በማለት አጅሬ አሚኮ (አቢይ አሕመድ ኮርፖሪሽን) በፎቶ ጭምር አስደግፎ የምልስ ፋኖዎችን ነፍ የትየለሌ ሚጢጢዬ ፎቶ ካሳየን እኮ ሳምንት አልሞላንም። ሃኣ…ኮንቪንሳም ሁላ።

"…ከአንዳንድ ኪስ ቦታዎች በቀር የክልሉን 97% ከፅንፈኛውና ከዘራፊው የፋኖ ኃይል አስለቅቀን፣ አፅድተን ከእግር ጥፍሩ ጀምሮ የተነቀለውን የክልሉን የመንግሥት አስተዳደርም መልሰን መትከል ከጀመርን ወር አለፈን ካሉን እኮ ገና መጪዋ የፊታችን ነሐሴ ልደታ አንደኛ ወራቸው ነው። ደግሞ ለጥንፈኛ የምን መደራደር ነው? ዐሞሌ ጨው ለሆነ ጅግሳ፣ ጃርት፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ፣ እርስ በእርሱ እየተናከሰ ላለ ጃዊሳ ቀበቶውን አስፈትተን ሱሪውንም እናስወልቀዋለን ካሉን ዓመት ሞላን አይደል? ወይ ኮንፊዩዝድ… የምን ድርድር ነው። ማነው የሚደራደረው?

"…አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣ ኮረኔል ታደሰ፣ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ አርበኛ መከታው ማሞ፣ በእስክንድር ነጋ የጋሪ ፈረስ ተሳፍረው በጨበራ የፌክ ምርጫ ሰበብ ከነፍሰበላው አቢይ አሕመድ ሥርዓት ጋር በአቋራጭ ተሞዳምደው፣ ተደራድረውም ገሌ ሆነው እኛን ለማምታታት ቢታትሩም እኔ ዘመዴ የቅሌታሞቹን የድምፅ ቅጂ በሃላል ይፋ አድርጌ ጉረሮአቸው ላይ በመቆሜ ሁሉ ነገር እንደ እንቧይ ካብ እንደፈረሰ ይታወሳል። የጎንደር እስኳድም የሰሊጥ ብሩን ሲልፍ ከርሞ ከተቀበረበት የመቃብር ጉድጓድ አፈሩን እያራገፈ ሳልሣዊ ብአዴንን በእስክንድር ነጋ በኩል ሊያዋልድ ሲንተፋተፍም አይተን ጉርንቦውን አንቀን የተፋትን የሴራ ቦለጢቃ መልሶ እንዲልሳት አድርገን መልሰን እንደቀበርነውም ይታወቃል። እና ከማን ጋር ነው ድርድሩ ጋሽ ኮንፊዩዝድ?

"…አሁን እኮ ነገሮች እየጠሩ ነው የመጡት። ጎጃም ውስጡን እያጸዳ ነው። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ ነው መኖር ያለበት በሚለው መርህ ምክንያት እነ አባ ዶላር ሹገር ዳዲ እስክንድር፣ እነ አውርቶ አደር ሀብታሙ አያሌው፣ ብሩክ ይባስ፣ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ቀፍለው ያታለሉት ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ተው ቢሉት አልሰማ ብሎ ጃስ ሲሉት በርግጎ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሀብቴ ወልዴ ዕዝ ወንድም ፋኖ ደረጀ ጋር ጎንደር ሸሽቶ ተደበቋል። ከዓባይ ድልድይ እስከ ጥግ ድረስ በምድረ ጎጃም ከዐማራ ፋኖ በጎጃም በቀር ሌላ የፋኖ አደረጃጀት አይኖርም ብሎም ሻለቃ ዝናቡ መወሰኑን እኮ ትናንት ሰማነ። በቃ ጎጃም ጎጄው መለኛው አመረረ፣ አመረረ። አለቀ።

"…ወሎም እንደዚያው፣ ሸዋም አርበኛ አሰግድን እነ መከታው ማሞ አሳልፈው ከሰጡት በኋላ አመዳቸው ቡን ብሎ፣ የሕዝብ ድጋፍ ርቋቸው፣ እስክንድርን ተሸክመው እሹሩሩ እንዳሉ ብቻቸውን ከሜዳ ላይ ቀሩ። ትግሉ ቀጥሏል። ጉባኤ ተጠርቶ ቋሚ መሪ እስኪመረጥ ድረስም በአርበኛ አቶ አሰግድ መኮንን ምትክ ኢንጂነር ደሳለኝ ተተኪ መሪ ሆኖም ተመረጠ። የቀረው ጎንደር ነበር። የሜጀር ጄነራል ውባንተ ልጆች እነሱ ነበሩ የቀሩት። በውስጣቸው የነበረውን፣ ለእስክንድር ነጋ የገበረውን። ከድርጅቱ ሓሳብና ፍላጎት ከመርህ ውጪ ሲንቀሳቀሱ የቆዩትን በሙሉ ጠራርጎ አብሯቸዋል። አሁን የዐማራ ፋኖ የሚገርም ቁመና ላይ ደርሷል። ከመቃብር አፈር አራግፈው የተነሡት የስኳድ ልጆችም መብረቅ እንደመታው እንጨት ፍርክስክስ ብለዋል። እኔ የለከፍኩት መቼም አይረባም ይኸው ዛሬ እነ ዶር ምስጋናው አንዷለምንም ጎንደር ወጊጂልኝ ብላ አብርራለች። ጎንደር ጎንደር ለባንዳ ለቀሳጢ፣ ለጠንቋይ ለአስማተኛ የማይመች የክርስቲያን ምድር። ጎንደር አባጃሌው። ጠርጎ ጣላቸው። የዛሬው የጎንደር ፋኖ መግለጫም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። እንዲያውም ሙሉ መግለጫቸውም ለምን እንደሚከተለው አላቀርብላችሁም። ሰሞኑን አንድ ጆሮ አመዳም፣ ወገበ ነጭ ሲሳይ አልታሰብ የሚባል ስኳድ፣ ከወዳጄ አያሌው መንበር ጋር እየተናበቡ ሲረግጡኝ አይቼ ስስቅ ነበር። አያሌው መንበር ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል በእኔ ቅሬታ ካለው ይጽፍልኛል፣ ይደውልልኛልም እንጂ እንዲህ አፉን ሲከፍትብኝ አይቼም አላውቅ። ይሄ የክፍለ ሀገር ልጅ ቆይ እመለስለታለሁ። አሁን ወደ መግለጫው።

"…በወቅታዊ ጉዳይ "ከዐማራ ፋኖ በጎንደር" የተሰጠ መግለጫ

ቀን ሐምሌ 26/2016 ዓም

"…በወቅታዊ ጉዳይ "ከዐማራ ፋኖ በጎንደር" የተሰጠ መግለጫ የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ መራሩን፣ በሴራ ጭምር የተተበተበውን የሥርዓቱን መንግሥታዊ ጉልበት ያፍረከረከ፣ በኅልውና አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ተስፋ ያለመለመ፣ የገዳዩን ሥርዓት ቅስም የሠበረ ለታሪክ የሚቀመጥ አኩሪ ገድል ነው። በማንነቱ ምክንያት በተወለደበት፣ ባደገበትና በሚሠራበት ቀዬ በሕይወት እንዳይኖር የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት መሆኑን ተከትሎ ተፈጥሯዊ "የአልሞት ባይ ተጋዳይነት" ትንቅንቁን በይፋ ከጀመረ ዓመት ሞልቶታል። ትግሉ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ በርካታ የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶችን በጥበብ ተሻግሮ ዛሬ የሚገኝበት ግዙፍ ቁመና ላይም ደርሷል። የተበታተኑ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ፣ ከጥቂት አደረጃጀቶች አውጥቶ ትግሉ ሕዝባዊና ተቋማዊ መሠረት እንዲኖረውና፣ ወታደራዊ ተቋማትም እንዲፈጠሩ የማድረግ ተግባርም የአጭር ጊዜ ስኬቱ ናቸው።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር" የዐማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ሂደት ካስገኛቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ተቋማችን በተለያዩ ቀጠናዎች ከሚገኙ ሐቀኛ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት ኅልውናን እንዲሁም ነጻነትና እኩልነትን የማረጋገጥ ሥራን በማከናወን ላይም
ይገኛል። መላው ሕዝባችን፣ መሬት ላይ የሚገኘው የትግል ጓድ እንደሚገነዘበው ትግሉ ጥቂት የማይባሉ ጓዶቻችንን በአርበኝነት የገበርንበት፣ ንጹሐን ወገኖቻችን በጅምላ የተጨፈጨፉበት፣ ሀብት ንብረት፣ መሠረተ ልማቶች የወደሙበት፣ በርካቶች የተፈናቀሉበት ቢሆንም ዘለቄታዊ ኅልውናችንን ለማረጋገጥ የሚከፈል መስዋዕትነት መሆኑን ይገነዘባል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው የዐማራ ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋርዮሻዊ የአንድ አታጋይ ተቋም የማዋለድ ሂደት ውስጥ የተፈጠረውን መደናገር ተከትሎ ከውስጥና ከውጭ ያሉ እንቅፋቶች የትግላችን መጽኛና ማጥሪያ በረከቶች እንጅ መርገሞች እንዳልሆኑ ተቋማችን በጽኑ ያምናል። ምንም እንኳ በሴራ ፖለቲካ እንደተካነ የሚነገርለት ሥርዓቱ አሉኝ የሚላቸውን የሤራ ጠበብቶች ተጠቅሞ ከመጨረሻው የውድቀቱ ደዌ ለማገገም ውዥንብሮችን እየፈጠረ ቢገኝም ሐሰቱና ሃሳውያኑ ጭምብላቸው እየተገፈፈ በባንዳነት ግብራቸው ሲገለጡ፣ በሐቅና በቅንነት የሚታገሉ👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።” አብድ 1፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …በራስህ እጅ ነው። እንደ ኬንያውያን ለመሆን ድጋሚ መፈጠርን ይጠይቃል። እንደዚያ ሁኑም ብዬ እኔም አልመክርም።

"…በነገራችን ላይ አለ አንድ ወዳጄ። በነገራችን ላይ ዘመዴ… አብይ አሕመድ ዐማራውን ማሸነፍ እንጂ መደራደር አይፈልግም። ምክንያቱም የዐማራ ጥያቄ በድርድር የሚፈታ ሳይሆን በብልፅግና መቃብር ላይ ብቻ የሚመለስ መሆኑን ስለሚያውቁ ነው። ህወሓትን ሳያጠፋ የተዋት ለዐማራ የጊዜ ፈንጅ (time bombing ) ብሎ ነበር። ህወሓት ከጠፋች ትግራይ እና ዐማራ ይታረቃሉ ብሎም ይሰጋል። ስለዚህ በተበደረው ሀገሪቱንም በሸጠበት ቢሊዮን ዶላሮች መሳሪያ እየገዛም መሆኑን እናውቃለን። በብሩ መሣሪያ ሲሸጡለት እዳው ለእኛው ይተርፋል እንጂ ገንዘቡ እንደሁ ተመልሶ እነሱው እጅ ነው የሚገባው። ቤተ መንግሥቱን ቢገነባበት የግንባታ ባለሙያው እና የግንባታው ጥሬ ዕቃም የሚሸመተው ከእነሱ ከራሳቸው ነው። ስለዚህ ገንዘቡ ዞሮ ዞሮ ከእነርሱ እጅ አይወጣም። ፍዳው ግን ለህዝቡ ሁሉ ነው የሚተርፈው። ነጮቹም በአፋቸው ድርድር ይበሉ እንጂ በልባቸው ማንበርከክን ተማምነው ነው መገደያችንን እንዲሸምትበት በገፍ ዶላሩን የሚያፈሱለት። ይሄን ሰይጣናዊ፣ አጋንንታዊ ሴራ ማክሸፍ የሚችለው የዐማራ ፋኖ ትግል ብቻ ነው። ስለዚህ የእኔ ምክር ዛሬም እንደትናንቱ ዐማራዬ ወጥር። መክት አንክት ማለት ብቻ ነው።

"…ረብሻ ከተፈጠረ ብለው በአቋራጭ የዐማራ ፋኖን ትግል ጠልፈው መንግሥት ለመሆን የተዘጋጁና በሀገረ አማሪካ ተሰባስበው የተከማቹ የቀድሞ አሮጌ ብአዴኖች፣ የወያኔ መስራቾች፣ የተቃዋሚ ባርቲ ሰዎችም የሚበላው ሳይኖር ለመብላት እጃቸውን ታጥበው በመጠባበቅም ላይ ናቸው። በእስክንድር ነጋ አድራሽ ፈረስነት ተንጠላጥለው በአቋራጭ አራት ኪሎ ለመግባት ያሰፈሰፉት ብቻ ናቸው ወገብ ዛላቸውን የተመቱት እንጂ በዚያኛው ወገን አሰፍስፈው የተቀመጡት የአማሪካንን ይሁንታም ፈቃድም አግኝተው ለሃጫቸውን በመጎምጀት እያንጠባጠቡ ሀገር ድብልቅልቁ እስኪወጣ የሚጠብቁም አሉ። የፈለገ ይሁን የፈለገ ግን መጪው ጊዜ ከዐማራ ፋኖ ውጪ ወደ ውጪ። አለቀ። በዚህ ቅር የሚልህ ካለ ጧ በል።

"…በሉ ለእረፍት ወደ ማደሪያ ስፍራዬ በባቡር እየሄድኩ ነው ይሄን በመሃል ጻፍኩላችሁ። ከእረፍት መልስ በሰፊው እስክንገናኝ ሰላም ቆዩኝ። 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የእረፍት ላይ "ርዕሰ አንቀጽ"

"…አሁን ያ ሊመጣ ያለውን አደጋ ለመሸፈን የምሽት የቡናቤት ዲምላይት መብራት የመሰለው የኮሪደር ልማት፣ ውኃ እና መብራት በሌላት ከተማ ውስጥ አዳነች አቤቤ በሌሊት እየተራወጠች የገነባቻቸው የፒፕሉ ማደንዘዣ የሚደንሱ የውኃ ፋውንቴኖች፣ ያልተኖረ የልጅነት ህልሙን የሚቀጨው የአጅሬ አቢይ አሕመድ ለአበዳሪዎቹ የወፈፊት መኖሪያነት የሚያዘጋጃቸው ቅንጡ መናፈሻዎችና ፓርኮች፣ ኢትዮጵያውያን የማይጠቀሙባቸው፣ በጦርነት ምክንያት ሀገር ጎብኚ የውጭ ሀገር ቱሪስት የማይመጡባቸው፣ የማያርፉባቸውም ፋይዳቢስ ፕሮጀክቶች፣ ሆስፒታልና ፋብሪካን የማይተኩ በውጭ ምንዛሬ በውድ ወጪ የተገነቡት ቅንጡ ሪዞርቶች ውበት የማይሸፍነው፣ የብልጽግና አክቲቪስቶችና ካድሬዎችም ዲስኩር የማይቋቋመው፣ የብልጽግና ወንጌል ፓስተሮች፣ የበዻዺና ሼኮችና ቄሶች "ትድኑ ዘንድ በብልፅግና አምናችሁ ተጠመቁ የሚለው አደንቋሪ ስብከትም የማይሸፍነው፣ የማይደብቀው፣ የማያድነውም። የኢቢሲ፣ የፋና፣ የዋልታ፣ የኦቢኤን እና የአሚኮ፣ የኢዜአም "እናንት ሾርት ሚሞርያም ምእመናን ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ" የሚለውና ከተለጠፈ በኋላ በቶሎ የተነሣው የምሥራች ዜናም እስከ አሁን ተለጥፎ ኖሮም ቢሆን የማይለውጠው ፍጥጥ ያለ እጅግ በጣም ከባድ አደጋ ከኢትዮጵያውያንም፣ ከብልግናውያን እና ከበዻዺናዎቹ ኦሮሙማዎችም ፊት ለፊት ድቅን ብሏል። ግመል ሰርቀህ አጎንብሰህ እንዴት ይሆናል? 

"…በዓለም ላይ እንደ እኛ እንደ ትናንት አንድ ሚልዮን ብር በባንክ ያስቀመጠ ሰው በማግስቱ 400 ሺ ብር ሟምቶበትና ኪሳራ ላይ ወድቆ የሚያድር ዜጋ ያለበት ሀገር ምንአልባት በዚምቡዋቤ ካልሆነ በቀር ሌላ ሀገር ሊኖር ይችላል እኔ ግን ሰምቼም አላውቅ። በጉዳዩ ላይ መጠነኛ ፈራ ተባ ያለ ፈሪ ምሑራዊ ትንተና የሰጡንን የዘርፉ ባለሙያዎችን ስንሰማ የትየለሌ አዳዲስ ደሀ እኮ ነው በአንድቀን ሌሊት ተፈልፍሎ ያደረው ያሉን። የአገዛዙ የብርን የመግዛት አቅም ማደክምን ተከትሎ ከወዲሁ በሀገሪቷ በዘይትና በዳይፐር፣ በዱቄት እና በወተት በሸቀጣሸቀጥ ምርቶች ላይ ከፍ ያለ ጭማሪ መታየቱ ነው የተሰማው። መቶ ኪሌ ጤፍ 19,000 ሺ ብር ገባ የተባለውም ዛሬ ላይ ነው። አሁን ነዳጅ በሊትር መቶ ምናምን ብር ይገባል። ነዳጁ ሲጨምር ደግሞ ነጋዴ ነፍሴው ደግሞ ሸቀጡን፣ ባለመሂናው ደግሞ የትራንስፖርት ዋጋውን ይጨምራል። በዚያውም የቤት ኪራይ ይንራል። የህክምና ወጪ፣ የትምህርት ቤት ወጪም አስቤዛውም ሁሉ በዚያው ልክ ይንራል። ደሞዙ ያው አምስት ሺ የነበረው የመንግሥት ሠራተኛ ምንአልባት አገዛዙ ሁለት እና ሦስት መቶ ብር ጨምርኩ ካለ እንኳ በማግሥቱ ከዚህ የባሰ ጭማሪ ይከተላል። ሚንስትሮች፣ ካድሬዎች፣ ፓስተሮችና ጳጳሳት የመጅሊሱ አመራሮችን ጭምር የማያገኘው የኑሮ ውድነትና ድቀት በሁሉም ቤት ይገባል። የሚመጣው ችግር እና የኑሮ ውድነት በሙዳየ ምጸዋት የሚተዳደሩ የሃይማኖት መሪዎችን፣ የመጅሊሱን ሼሆች፣ የብልጽግና ፓስተሮችን፣ ለአቅመ መስረቅና መዝረፍ የደረሱትን ሚንስትሮች ካልሆነ በቀር ጠኔው ሁሉንም ድብን አድርጎ ይዠልጣል። የሚምረውም የለም እየተባለ ነው። ምንአልባት ዘርፎ በሌ ሸኔ፣ እንዲሁም የትራፊክ ፎሊሶች፣ ጀነራሎች ካልሆኑ በቀር አዳሜና ሔዋኔን ሰሞኑን ሽግር አናቱን ያዞረዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሰሞኑን ተነጫናጭ ካድሬና ወታደሮችንም ጠብቁ።

"…የብር ምንዛሬ ጭማሪውን ተከትሎ ከዳያስፖራ እስከ ጉልት ነጋዴ ምን ሊውጠን ነው? ማለቱ የማይቀር መሆኑን የሚያውቀውና ከያንዳንዱ አደገኛ ሀገርና ሕዝብ አውዳሚ ተግባሮች ቀጥሎና ጎን ለጎን ከሲአይኤ የአጀንዳ የዳይቨርት መስደረጊያ ማንዋል ላይ የሚቀዳውን ትያትር በመሥራት የተካነው አብይ አሕመድም የጅማ የሀገሩን ልጅ የአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመን 4ኬ ካሜራ ጠምዶ በሰማይ በምድር እየዞረ በቶፕ ቪው ቀረጻ ሕዝቡን የሚያማልል ዶክመንተሪ በመቅረጽ ሊያደነዝዝ መሞከሩም አይቀር። ከአሁኑም እንደ አባባ ጃንሆይ ሰፈር ለሰፈር መኪና እያሽከረከረ ለአዲስ አበቤ ለፍቅረኛ ማቾች ማስቲካ ለምስኪኖች 100 ብር በመስኮት እየበተነ አዳዲስ ቲክቶከሮችን ሁሉ ማስናቅም ጀምሯል። ይሄ ቲክቶከራም።

"…ከአሁን ጭንቅ የገባት ብልፄ መጀመሪያ ከIMF ጋር ስትዋዋል ያላማከረችውን እንቅልፋሙንና የቀረበለትን አጀንዳ ሁሉ ሳይመረምር፣ ግራና ቀኝም ሳያይ ሳይመለከተም በእንቅልፍ ልቡ እጅ ወደላይ ቀስሮ በጭብጨባ ሁሉን ዐዋጅ አጽዳቂው የተነከሩት የባርላማ አባላት የታዛዦች ጥርቅም የሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተብዬ መንጋ የምክር ቤት አባላትም ለእረፍት ከሄዱበት መንደራቸው በአስቸኳይ ኑ ብሎ ለነገ ረቡዕ ጠዋት እንደጠራቸውም ተሰምቷል።

• ምን ሊያደርግ ?

~ አጀንዳ ሊሰጠን ነዋ የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

• ምን ዓይነት አጀንዳ…? 

~ ምንአልባትም ቀደም ብሎ ሳያማክራቸው በጓሮ በር የተደራደረበትን ጉድፈላ ጣጣ ያመጣበትን የብድር ስምምነት ፈርማችሁ አጽድቁና አብረን እንነካካ ሊላቸው ይችላል የሚሉም አሉ። ዛሬ ሚንስትር ተብዬ ደናቁርት የጂም ቤት ዳሌ አፈርጣሚ ቅልብ የሐረር ሰንጋ መሳይ ጉዶችን ሰብስቦ ይሄንኑ ነው መመሪያ ሰጥቶ አጽድቆ ወደ ፓርላማ የመራው። እነርሱም ነገ እጅ አውጥተው እንደለመዱት በርታ ብለው እሱ አፅድቆ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን ውጥንቅጥ ሊያጸድቁለት ይችላሉ።

• ሕዝቡስ ዝም ይላል? እንደ ኬኒያ ሊያምፅ ቢችልስ?

~ የትኛው ሕዝብ ነው የሚያምጸው? ትግሬ ለራሱ ሽግር ላይ ነው። ትግራይን ሳይሆን አሮጊቷን አሮጌዋን ህወሓት ከሞት በማዳን እና ባለማዳን መካከል ውጥረት ላይ ነው። የዓድዋ ትግሬዎቹ የስብሐት ነጋ ሥርወ መንግሥት ወራሴ መንግሥት የሆኑት እነ ሞንጆሪኖ እና ደፂ የወሎ ራያ ዐማራ የሆነውን ጌታቸው ረዳን ለብልፅግና አሳልፎ ሰጥቶናል ብለው ከሞት የታደጋቸውን ሶዬ ባንዳ ብለው ዘመቻ ጀምረውበታል። እናም ትግሬ አሁን በራሱ የውስጥ ችግር ተጠምዶ ቢሳካ ለኦሮሞ ተገርጄ ልኑር የሚልበት ጊዜ ላይ እንጂ ዐመጽን አይሞክራትም የሚሉም አሉ።

"…ዐማራ ካመፀ፣ በአገዛዙ ላይ ነፍጥ ካነሳ ዓመት ሞላው። ከባዶ ተነሥቶ ከምንሽር ወደ ዙ 23ም ተሸጋግሮ፣ ከሻለቃ ወደ ክፍለጦርም አድጎ እንደ ሕዝብ ይሄን ነቀርሳ አገዛዝ ቆርጦ ለመጣል ጉረምቦ ለጉረምቦ መተናነቅ ከጀመረም ዓመት ሞልቶታል። እናም ዓማራ ከሰላማዊ ሰልፍ ወደ ሰማያዊ ሰይፍ ከተሸጋገረም ዓመቱ ነው። ከአዲስ አበባ አፍንጫ ስር በደብረ ብርሃንና በጫጫም ስር አቅሙን እያሳየ ነው። ይሄ ቀውጢ እድል ሲገጥመው፣ ኑሮ ሁሉንም እኩል ሲዠልጥለት የነፃነት ቀኑን ያፈጥንለታል። ዓማራ ዛፉን ገዝግዞ፣ ገዝግዞ ሊጥለው ከጫፍ ደርሷል።

"…ኦሮሞ እንደ ሕዝብ አብዛኛው እየቸገረውም ቢሆን መንግሥቱ የእኔ የኦሮሞ መንግሥት ነው ብሎ ስለሚያምን እየራበው እየጠማውም ቢሆን ዝም ማለትን ነው የመረጠው። ይሄ መንግሥት ወድቆ ዐማራ ከሚገዛኝ ያቺ ህወሓት ተመልሳ መጥታ ብልቴ ላይ ሃይላንድ ብታንጠለጥልብኝ ይሻለኛል ብሎ ሂዊ ሞታ ተነሥታ ዳግም መምጣቷን ናፋቂ ሆኗል። ርምጦ ርምጥምጦ ኦነግ አንድ ቀበሌ ሳይዝ ፌስቡክ ላይ ብቻ እየጎረረ መደንፋቱን ንቆ ተስፋ ከቆረጠበት ቆየ። ኦነግን ራሱ ዐማራው ከመጣ ነፃ ያወጣው ይሆናል የሚሉ መተርጉማን አሉ። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወስላታ ምስክር በፍርድ ያፌዛል፥ የኀጥኣንም አፍ ክፋትን ይውጣል። ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር። ምሳ 19፥ 28-29

"…ባለጠጋ ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።” ምሳ 22፥7

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ከኢንተርኔቱ ዓለም ላይ ለእረፍት ከመውረዴ በፊት ለምን ይሄን ጉዳይ አላጠራውም በማለት ይሄን በሳሚ ላይ የተከፈተውን ክስ በተመለከተ ወደ እነሳሚ ዕዝ ጋር መልእክት አስቀምጬ ማብራሪያ እንዲሰጡኝ ጠይቄም ነበር። እናም ሳሚን ባላገኘውም ሳሚ ራሱ ይሄን ወሬ ሰምቶ በተለይ እነ አኪላና ዘርዓያዕቆብ የከፈቱበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰምቶ እንደነበርና ለማንኛውም ብሎ ከኮረኔል ጌታሁን ጋር ያወሩትን የስልክ መረጃ እንዳለ ገልጸውልኝ ያን መረጃም ልከውልኛል። እኔም ይሄንኑ በኮረኔል ጌታሁን እና በኮማንደር ሳሚ መካከል የነበረን የስልክ ልውውጥ አቀርብላችኋለሁ። እናንተም ሰምታችሁ ፍረዱ።

"…እኔን በተመለከተ ግን እጅግ በጣም በጣም በጣም ስለደከመኝ፣ እረፍት የለሽ ሌሊትና ቀኖችን አሳልፌ ስለናወዝኩኝ ወዲያውም ለጥቂት ቀናት ከቤተሰቦቼ ጋር ለማሳለፍ ስል ከማንኛውም የስልክም ሆነ የማኅበራዊ ሚዲያ ግኑኝነት ለመራቅ ወስኛለሁ። ማክሰኞ ቲክቶክ፣ ሐሙስ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ፣ እሑድ ደግሞ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር መርሀ ግብር አይኖረኝም። ቀሲስ ሳሙኤልንም፣ መረጃ ቲቪንም ፈቃድ ጠይቄ ፈቃዳቸውንም ሰጥተውኛል። እናም ስልኬን ውርውር አድርጌ እርፍ ልል ወስኛለሁ። በቶሎ እመለሳለሁ ብዬም አስባለሁ። እዚሁ ጀርመን ውስጥ ተራራ ያለበት ከተማና ስፍራ ፈልጌም በዚያ ለማሳለፍ ነው የወሰንኩት። ዋልድባ፣ ዙርአምባ፣ ዋልድቢት ባልሄድም አውሮጳ በበጋ ለምለም ነው። መንፈስን ለማደስ ይመቻል።

"…በተረፈ በርቱ። ግራና ቀኝ ተመልከቱ። ማንም የሚነዳችሁ መሂና፣ የሚያንሳፍፋችሁ ፊኛ አፉፋ፣ የገበቴ ላይ ውኃም አትሁኑ። መርምሩ። የሰማችሁትን፣ ያያችሁትን ሁላ ለመቀበል አትፍጠኑ። ግራና ቀኝ ተመልከቱ። ዓሣ እንደመብላት ቁጠሩት። ጥንቃቄ ይፈልጋል። አትቸኩሉ። ረጋ በሉ። ቶሎ አታልቅሱ፣ ቶሎም አትሳቁ። የረጋ ወተት ይባል የለ? አዎ ኢንዴዢያ ኖ። አትፍሩ። ሰላም እንትተኙ፣ ሰላማዊ እንቅልፍም እንዲወስዳችሁ እውነትን ተጋፈጡ። በይሉኝታ አትያዙ። እንደ ዜጋ ስለ ሀገራችሁ፣ እንደ አማኝ ስለሃይማኖታችሁ ለመመስከር አትቦዝኑ። ወደ ኋላም አትበሉ። በተረፈ እስክንገናኝ ሰላም ቆዩኝ።

• ከ30 ደቂቃ በኋላ የስልክ ውይይቱን እለጥፍላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲውም፣ አስነቀልቲውም ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።” ኢሳ 50፥4

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ይሄ ከባድ ነው።

"…አንድ ጋዜጠኛ ያውም ከደጀን ጎጃም የተገኘ ጋዜጠኛ። ከቅዱስ ሲኖዶስም በላይ ሆኖ የቅድስና ማእረግን ሲሰጥ ካየህ በቀጥታ ጸሎት ነው ማድረግ ያለብህ። እንዲህ ዓይነቱ አጋንንት በጾምና በጸሎት፣ ስግደት ጨምረህበት ያለ ግርማ መቁጠሪያ በማልቀስ ጭምር ካልጸለይ አይፋታህም።

"…ወግደረስስ ጎጃም ስላለ በቁጥጥር ስር አውለው አሁን ጠበልም፣ ምክርም ሰጥተው ያስተካክሉታል። ጌጥዬ እንዴት ይስተካከላል? ከማዶ ሀብታሙ አያሌው ዶላር እየላከ፣ አጠገቡ መከታው ማሞ በምስኪን ፋኖ እያስጠበቀ፣ ቅዱስ ጻድቅ እስክንድርን ዜና መዋዕሉን የሚከትብ ጋዜጠኛ ሸዋ አስቀምጠው ወይ ጻድቃኔ ማርያም ጠበልም ቢሆን በጊዜ ሳይወስዱት ቀርተው ይኸው ጌጥዬ ለቀቀ።

"…ሸዋ ቁጭ ብሎ የትውልድ ሀገሩ ጎጃምን ጓዳ ጎድጓዳ ስም እየጠራ ሲዘግብ ነው የሚያስቀኝ። ኔትወርክ በተዘጋ ጊዜ እንኳ ጌጥዬ ኢንተርኔት ሲጠቀም አይሳቀቅም። ድሮን ይመታኛል ምናምን የለም። ምክንያቱም የባሕታዊ ቅዱስ ጻድቅ እስክንድር ነጋ ጸሎት ከድሮን እይታ ይሰውረዋልና ነው።

"…ለማንኛውም የጻድቁ ቅዱስ እስክንድር ነጋ ጸሎት የመከታውን ጦር ይረዱ የነበሩትን የሸዋ መኳንንት አስቀረ። የፈረንካ ሰንዱቃቸውን ቆለፉ። መከታው ስንቅና ስንቅ እንዲጠርርበት አደረገ፣ አስደረገ። በአጠቃላይ የሸዋ የመከታው ጦር በአንድ እስክንድር ጦስ ሚልዮን ደጋፊዎቹን አጣ።

"…ከባድ ነው። በእነ መከታው የደረሰ መረገም በሀብቴና በኮሮኔል ፈንታሁንም ሙሀባውም ላይ ይድረስ አሜን። የኮቴ መናናው እስክንድር ነጋም መርገምት በላያቸው ይደር። 

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የተሰኘው የመረጃ ቴሌቭዥን የእሁድ ምሽት መርሀ ግብሬ በቴሌቭዥን እና በቲክቶክ ወደ እናንተ እስኪደርስ ድረስ እንዲህና እንዲህ እየዛግን እንቆያለን።

• አስነቀልቲው ዘመዴ ነቀለ አባ ንቀል ነኝ።😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ድሮ ድሮ የሠራኸው ግፍ በልጅ ልጅ፣ ወይም በልጅ፣ ወይ ቆይቶ ነበር የሚደርሰው። አሁን ግን በጣም ፈጣን ነው። 5ጂ በሉት። ግፍ ትሠራለህ ወዲያው ያናፍጥህሃል። በአናትህም ይተክልሃል።

"…የጋሽ አሰግድን በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ፣ መጀመሪያ አሰግድን ሊገድሉት ሲያሳድዱት የነበሩት ሀብታሙ አያሌው፣ መከታው ማሞና፣ ፋኖ ሀብቴ ወልዴ፣ እንዲሁም እስክንድር ነጋ ሲያሾፉበት፣ ለምን ጥይት አይጣጣምና አይሞትም ነበር እያሉ ሲያላግጡበት ነበር የከረሙት። ከእነዚህ አላጋጮችም መሃል ጎጃም ተቀምጦ ለሃብታሙና ለእስክንድር ይሠራ የነበረው ወግደረስ ጤናው አንዱ ነበር። ወግደረስ በፌስቡኩ እንዲህ ብሎ ነበር የጻፈው።

"...ንጋትና ጉድ እያደረ ይጠራል!!"

"አባ ዳምጠውም" እጅ ሰጥቷል።

በሃቀኛው የፋኖ አደረጃጀት ላይ ያ ሁሉ ዘመቻና ወከባ፣ ከማንና ለምን እንደሆነ ህዝቤ ሆይ ዛሬ የገባህ ይመስለኛል።

ዕውነት፤ዕውነት እላችኋለሁ፤ኪዳነምህረትን እኛ ግን እናሸንፋለን!!!!

ድል ለሃቀኛው ፋኖ!

"…እንግዲህ ወግደረስ ጤናው በመከላከያ እጅ ባለው በዕድሜም፣ በልምድም አባቱ በሚሆነው ጋሽ አሰግድ መኮንን ላይ ባሾፈ፣ እስክንድር ጽፎ የሰጠውንም መግለጫ በድምጽ አንብቦ ለዛራ ሚዲያ ለስታሊን ገብረ ሥላሴ በሰጠ በአምስተኛ ቀኑ ዛሬ በዕለተ እሑድ በሆቴል ቤት አልቤርጎ ውስጥ በፋኒት ትእግስት ጫኔ በቁጥጥር ስር ውሎ ገበያ ለገበያ እንደ ሌባ ሲያዞሩትና እኔን ያየህ ተቀጣ ሲያስብሉት ውለው በመጨረሻም ወደ ማረፊያ ስፍራ ወስደውታል።

"…ወዳጄ ዘንድሮ ግፍ አትስራ፣ ግፍ አትናገር። በልጅ ልጅህ፣ በልጅህ ሳይሆን በራስህ ላይ ነው የሚደርሰው። 5G በለው። ብራቮ ጎጄ ጎጄ መለኛው። ይቀጥላል… ✍✍✍

"…ዘመድኩን ነቀለ ነኝ (አስነቀልቲው) አባ ንቀል ከራየን ወንዝ ማዶ። 😂😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም… ርዕሰ አንቀጹ ከ13 ሺ ሰዎች በላይ እንደተነበበ የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት እያመለከተኝ ነው። እስከአሁን ከዚህ ልጥፍ በኋላ የሚጨመሩትን ሳይጨምር ወደ 10 ሰዎች አካባቢ ብው😡 ብለው በርዕሰ አንቀጹ መናደዳቸውን እያየሁ ነው። መቶ ሁለት መቶ የነበረው ተናዳኝ ወደ 10 እና 11 መውረዱም ትልቅ እመርታ ነው። ይሄ ለእኔ የአሸናፊነት ምልክቴም ነው።

"…በዐማራው ሊቅ ምሑር በአቻምየለህ ታምሩ ጦማር ላይ አነሰ ይምትሉት ካለ ጨምራችሁ፣ በዛ የምትሉት ካለም ቀንሳችሁ አስተያየት ለመስጠት ተዘጋጁ። ታዲ አስተያየት ስትሰጡ አዲስ ገቢዎች ሌላ ቦታ እንደለመዳችሁት አቦሬ አፋችሁን እከፍታለሁ ብትሉ እቀስፋችኋለሁ። ተቃውሞም ካለ በጨዋ ደንብ ይቅረብ። ሰምታችኋል።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ትይዩ ሊሆኑ ወደማይችሉበት ሚዛን እንዲቀመጡ እንደማድረግ ነው።

"…በአጭሩ እስክንድር እንደ ፋኖ አዛዥ ግምት ውስጥ ገብቶ እየተወዳደረ ያለው ያለውን የሚዲያና የገንዘብ ሞኖፖል በመጠቀም እንጂ በፋኖነት፤ ፋኖን በማደራጀት ባደረገው ጉልህ አስተዋጽኦና ጀብድ አይደለም። በስተመጨረሻም የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለኹ ብሎ ያወጀው ከሕዝብ የሰበሰበው መጠቀሚያ ገንዘብ ስላለው፣ ዝና አለኝ ብሎ ስለሚያስብ፣ በየቀኑ ስለሱ በሚያላዝኑ ተከፋይ ምላሶችና ጆሮዎች በመመካት እንጂ መልምሎ ባሰለጠናቸው ተዋጊዎች፣ ባደራጃቸው የፋኖ ብርጌዶችና በሰጠው በሳል አመራር ተመዝኖ አይደለም።

"…የምናውቀው የፋኖ ተጋድሎ ከተጀመረ ወዲህ እስክንድር ከጀምሩ ጀምሮ ይህንን ሁሉ በሕዝብ ገንዘብ የገዛውን የምላስና ጆሮ ተጎታች ጭኖ ሲንገታገት የከረመው የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት እንጂ ለዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ሊያውለው እንዳልሆነ ግልጽ ነበር። ለዚህም ነበር እውነተኞቹ የፋኖ አዛዦች የድኃ ገበሬ ልጅ እየመለመሉና እያሰለጠኑ የፋኖ ብድርጌዶችና ዕዞችን ለመመስረት ሲወጡና ሲወርዱ እስክንድር ግን የዐማራ የፋኖ መሪነት ጉዳይ አጀንዳ ሲሆን ከእውነተኛ የፋኖ አዛዦች ጋር በፍትሐዊ ሚዛን ሊቀመጥ እንደማይችል ስለሚያውቅና ከዐማራ ፋኖ መሪነት ያነሰ ሥልጣን ለመቀበል ዝግጁ ባለመሆኑ  በማናቸውን መንገድ የፋኖ መሪ ለመሆን የገንዘብ፣ የጆሮና ምላስ ኃይሉን ሲያደራጅና ሲያሰማራ የከረመው።  
"…ጊዜው ሲደርስም ያደራጀውን የጆሮና የምላስ ኃይል በማንሰሳቀስና ከሕዝብ በሰበሰበው ገንዘብ ደንገጡር በመግዛት እውነተኛ ፋኖዎች የፋኖ መሪ ለመሆን መሟላት አለባቸው ባሏቸው መመዘኛዎች ዙሪያ ያካሄዱት ጉባዔ ያለ ውጤት መበተኑን ተከትሎ የመላው ዐማራ ፋኖ መሪ ነኝ ብሎ መግለጫ አወጣ። ሳይመረጥ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ ሲል  ያወጣው ይህ መግለጫው የእስክንድርን የስልጣን ጥም በግልጽ ያሳየ ጉዳይ ነው። እስክንድር የዐማራ ትግል የኅልውና ተጋድሎ ነው ብሎ የሚያምን ቢሆን ኖሮ በኅልውና ተጋድሎው ስማቸው ከፊት የሚጠቀሱ ከአራት በላይ የፋኖ ዕዞች የዐማራ ፋኖ ጠቅላይ መሪ ለመሆን መሟላት ስላለባቸው መስፈቶች እያደረጉት የነበረውን ስብሰባ አቋርጠው ሲወጡና ራሳቸውን ከሒደቱ እናገልላለን ሲሉ፤ አንድም የፋኖ ዕዝ ከሒደቱ እንዳይወጣ ብሎ ጊዜ ተወስዶ ንግግሩ እንዲቀጥልና ያላግባባቸው ችግር እንዲፈታ ጥረት ያደርግ ነበር እንጂ ራሱን ሳይመረጥ የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር።

"…ምን ይኼ ብቻ! የአማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ በእስክንድር ምክንያት ከከሸፈ በኋላ አብዛኞዎቹ የፋኖ አደረጃጀቶች ሂደቱ አይወክለንም ብለው ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ የዐማራው ኅልውና ትግል ግድ የሚላቸው በውጭም በውስጥም የሚኖሩ ዐማራዎች ሁሉ በተፈጠረው ሁኔታ ብስጭታጨውን በተለያየ መንገድ እንደገለጹ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚሰጡትን አስተያየቶች መመልከቱ ብቻ በቂ ነው። በዚህ ሁኔታ አንድ ለዐማራው ትግል ቀናዊ ነኝ፣ ሓላፊነት ይሰማኛል የሚል አካል ቢኖር አንድ ሆነው ይወጣሉ ብሎ በጉጉት ለሚጠብቀው ሕዝብ ማድረግ የነበረበት ወደ አንድነት ለመምጣት የተሞከረው ድካም ባለመሳካቱ አዝኖ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቆ አንድነቱ ወደፊት ይሳካ ዘንድ ከሁሉም ጋር በወንድማማች መንፈስ በትጋት ለመሥራት ቃል ይገባ ነበር እንጂ ሳይመረጥ ራሱን ሹሞ በሕዝብ ላይ አይሰይምም ነበር። እስክንድር ግን ለዐማራው ካለው ንቀትና በሥልጣን ጥም መታወር የተነሳ የዐማራውን ጩኸትና ተቃውሞ እንደ ወፎች ዜማ ቆጥሮት እነ ዐቢይ እንደሚያደርጉት ዐይኑን በጨው አጥቦ በዲሞክራሲ አግባብ ተመርጫለሁ ብሎ የፋኖ መሪነቱን አወጀ።

"…እስክንድር ራሱን መሪ አድርጎ ሲሾም የሚታየው ድል ለዲሞክራሲ የሚለው ሕዝባዊ መዋቅር በተዘረጋበት አገር የሚታሰብ መፈክሩ እንጂ የዐማራ የኅልውና ተጋድሎ አይደለም። የፋኖ መሪ ሆኜ ተመርጫለሁ የሚለንም በዚህ ጭንቅላቱ እያጭበረበረ ነው። ሆኖም ግን የኅልውና ተጋድሎ አደረጃጀት ትልቅ ጥበብና ጥንቃቄ፣ ሀቀኛነት፣ ከራስ በላይ የሆነ ዓላማ መያዝ፣ መግባባትና ወንድማማችነት የሚጠይቅ እንጂ በዚህም በዚያም አማታትቶና ማጅራት መትቶም ቢሆን “በድል ለዲሞክራሲ” ተመርጫለሁ ተብሎ የሚታወጅበት አልነበረም። እስክንድር ግን ትኩረቱ ሥልጣኑ እንጂ የዐማራ የኅልውና ጉዳይ ስላልሆነ ይህ ሊታየው አይችልም።

"…እስክንድር የዐማራን የኅልውና ተጋድሎ እያወከው የሚገኘው ከላይ በቀረበው ተግባሩ ብቻ ሳይኾን የኅልውና ተጋድሎውን ዓላማና ግብ በማሳት ጭምር ነው። ከአሁን በኋላ በሚደረግ የኅልውና ተጋድሎው ማናቸውም እንቅስቃሴ በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ  ቅዱስ ዓላማ፣ መርኅና ግብ ላይ ጥርት ያለ አቋም ያስፈልጋል። ይህ ጥርት ብሎ አለመቀመጡ ለዐማራ ኅልውና የሚጋደሉ ፋኖዎች በእስክንድር ነጋ ፀረ- ዐማራ “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ዝባዝንኬ  ዙሪያ ድምጽ ለመስጠት እንዲቀመጡና ጉዳዩን የዐማራ አጀንዳ እንዲያደርጉት አድርጓቸዋል።

"…እስክንድር ነጋ ቀለብ የሚሰፍርላቸው ምላስና ጆሮዎቹ፤ ዐማራ ነኝ ማለት የሚቀፋቸውን የግንቦት ሰባት ጉግ ማንጉጎች፤ የእስክንድር ነጋን “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል ፀረ- ዐማራ ዝባዝንኬ ማዘውተራቸው ለምን ይሆን ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሲጀመር “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለው ፀረ- ዐማራ ማጭበርበሪያ የተፈለሰመው በእስክንድር ነጋም አይደለም። ማጭበርበሪያውን የፈለሰሙት የፋኖን ተጋድሎ ለመጥለፍ የተሰለፉ አሜሪካን አገር የሚኖሩ የምናውቃቸው የግንቦት ሰባት ጉግ ማንጉጎች ናቸው።

"…እነዚህ ጉግ ማንጉጎች በፋኖ በኩል በቀጥታ የዐማራን ተጋድሎ መጥለፍ ሳይቻላቸው ሲቀር ማጭበርበሪያውን ለእስክንድር ነጋ በማቀበል የዐማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ተሰማሩ። ለዚህም ነው ፀረ- ዐማራዎቹ የግንቦት ሰባት ኃይሎች ያቀበሉትን ፀረ- ዐማራ መፈክር እንደራሳቸው ሆኖ “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” እያለ ሲጃጃል በሚውለው እስክድር ነጋ ላይ ተሳፍረው የሙጥኝ የሚሉት። በአጭሩ  ፀረ- ዐማራው የግንቦት ሰባት ኃይል በእስክንድር ነጋ ላይ እንደ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ የሰፈረው “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለውን መፈክራቸውን አንጠልጥሎ ስለሚዞርላቸው ነው።

"…የዐማራ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በፋኖነት በመደራጀት እየተጋደለ ያለው ዐማራ በመሆኑ ብቻ በአቢይ አሕመድ አረመኒያዊ የጭካኔ አገዛዝ የዘር ማጥፋት ጦርነት ስለታወጀበት እንጂ በኢትዮጵያዊነቱ ጥያቄ ስላነሳ ወይም ከኢትዮጵያ ለመገንጠል አይደለም። ዐማራው የሚጋደለው የዘር ማጥፋት ያወጀውን የአቢይ አሕመድ አረመኔያዊ የጭፍጨፋ አገዛዝ አስወግጄና የኅልውና አደጋውን ቀልብሼ፣ ለሁሉ እኩል የሆነ መንግሥታዊ መዋቅር ተዘርግቶ፣ ዐማራውም እንደ ሕዝብ በኢትዮጵያ መንግሥታዊ ሥልጣን ውስጥ በእንደ ብአዴን ዓይነት ባንዳ በምስለኔ ሳይሆን በቀጥታ የመንግሥት ተጋሪ የምሆንበት መንግሥታዊ ሥርዓት እንዲዘረጋ ነው። ስለ ዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ዓላማ ከፋኖዎች የምንሰማው ቃል በቃልም ባይሆን ይህንን ነው። 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… የሀብታሙ አያሌው፣ ለዐማራ ፋኖ በተዋጣ ብር ደሞዝተኛ ሆኖ ለኢትዮ 360 ለሀብታሙ አያሌው ቅጥረኛ፣ የእስክንድር ነጋ በጎጃም የስለላ መዋቅሩ መሪ፣ የዓለም ብርሃን ጦረኞች የጦር መሪ፣ የግንቦት ሰባት፣ የግንባሩም፣ የሠራዊቱም አፈ ቀላጤ ሆኖ ሲሠራ የነበረው የጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው በቁጥጥር ስር መዋልን በተመለከተ ቆይቼ እመጣበታለሁ።

"…ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን በቁጥጥር ስር ያዋለችው ፋኒት ትግስት ጫኔ ናት። ጠዋት 1:15 አካባቢ ፈለገ ብርሃን አልጋ ቤት እያለ ነው ቀርጨም ያደረገችው። ትልቁ የሀብታሙ አያሌው የመረጃ ምንጭ ከስሩ እንዲከስም እየተደረገ ነው። ሸዋ መከታው ስር የሚገኘው ጎጃሜው የእስክንድር አምላኪ፣ ፍርዬ ኢንተርኔት በነፃ ሰጥታ እንዲደሰኩር የፈቀደችለት ጋዜጠኛ ጌጥየ ያለው ነው የሚቀረው። እርሱም አይቀርለትም። ይቀጥላል። ብራቮ ጎጄ። ጎጄ መለኛው። 😂💪💪🏿👌✊

"…አሁን በጉጉት በሚልዮኖች በጉጉት ወደሚጠበቀው ወደዛሬው "ርዕሰ አንቀጻችን" ብንሄድ ምን ይለናል? የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ የጻፈው እንደኔ የሐረርጌ መራታ ቆቱ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት እየተባለ የሚጠራ ለእኔ ደግሞ ወዳጄ የሆነ ጎምቱ ዐማራ ነው። ዛዲያስ እናንተስ ይሄን በራሱ በዐማራው ተወላጅ የተጻፈን ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

• አንድ 100 ያህል ሰው ዝግጁ ነነ ይበል እስቲ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።” ገላ 5፥12

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …አርበኞችም ሕዝባቸውንና ትግላቸውን ለዳግም ባርነት አሳልፎ ላለመስጠት በጥብዓትና በጽናት ለሕዝባቸው ቆመዋል።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር" እንደ ተቋም አንድ አማራዊ ድርጅት እንዲፈጠር ሂደቱ ላይ የነበረና በሂደቱ ውስጥ የነበሩ የአካሄድና የመርህ ጥሰቶችንም ጭምር እንዲስተካከሉ በመጠየቅ ግንባር ቀደሙ ከመሆን አልፎ ዛሬ ላይ የመጣው ውጤትም እንደሚመጣ የተነበዬ ተቋም ነው። ከምንም በላይ ለሥራ አሥፈጻሚው በሂደቶቹ ዙሪያ ግንዛቤዎችን እየፈጠረ፣ በሐቀኛ ዓላማ፣ መርኅና መታገያ ጉዳይ ተቃኝቶ
ለወንድማዊና ጓዳዊ አንድነት በርትቶ የሚሠራ፣ ሕዝባችን ለገጠመው የኅልውና ጥያቄ ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚሰጥ፣ በሕዝቡም በታጋዩም
ዘንድ ቅቡልነት ያለውን ተቋምና ሐቀኛ መሪዎችን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም ወገን በስክነት ለውይይትና ለአንድነት እንዲተጋ ተቋማዊ ጥሪ ማቅረቡም ይታወቃል።

"…ይህንን ተከትሎ የተለያየ የግልና ድብቅ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ከተቋማዊ አሠራርና መርኅ ባፈነገጠ መልኩ የተቋማችንን ኅልውና ለመናድ የሚከተሉትን መርሕ አልባና ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

1ኛ፦ ተቋማዊነትን ያልጠበቀና ከተቋም አቋም በተቃረነ መንገድ መግለጫ በተለያዩ ሚዲያዎችና የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በመስጠት የትግል መስተጋብርን ማበላሸት፤

2ኛ፦ ተቋማችን ከሦስተኛ ወገን ጋር የሚደርጋቸውን ግንኙነቶች መርኅና ተቋማዊ አሠራርን መሠረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት ተቋማችን ከሰየመው ግብረ ኃይል ውጭ ሌላ ግብረ ኃይል በሕገወጥ መንገድ በማዋቀር ከሦስተኛ ወገን ጋር ተቋምን ወክለው ንግግር ሲያደረጉ መገኘታቸው፤

3ኛ፦ ከላይ በተገለጡ ችግሮች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችን የተቋሙ መሪዎች ተደጋጋሚ የውይይት ጥያቄዎችን ቢያቀርቡላቸውም ከተቋማችን ጋር መቀጠል እንደማይፈልጉና ሌሎች ልዩ ልዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ትግላችንን ከመጎተት እስከ ተቋማዊ መስተጋብር ማበላሸት የዘለቀ የውስጥ ለውስጥ አካሄዶችን እየሄዱ ሠራዊቱን የሚከፋፈሉ ንግግሮችና ውይይቶችን አድርገዋል። አለፍ ሲልም በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ ተደጋጋሚ ግለሰባዊ አቋሞችን ተቋማዊ በማስመሰል የተሄዱ ሂደቶች እጅጉን አሳዝነውናል። የዐማራ ፋኖ በጎንደር ጉዳዩን ለረዥም ጊዜ በሰከነ መንገድ በውይይትና በሽምግልና ጭምር የልመና ያህል የሄዳቸው ሂደቶች ፍሬ ሳያፈሩ ቀርተው ዛሬ ላይ ለደረስንበት ተቋማዊ ውሳኔ ላይ ደርሷል። የተፈጠረው ችግር የአማራን እንዲሁም የጎንደርን ሕዝብም ሆነ በትግል ላይ የሚገኘውን አርበኛ የሚያሳዝን፣ የልዩነት አጀንዳን በማራገብ፣ አንድም በጎንደር ምድር ሌላ ሦስተኛ እዝ የማቋቋም ፍላጎትንም አንግበው መንቀሳቀሳቸው የሕዝባችንን ፍላጎትና ትግሉን ሳይሆን ግላዊ ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ መሆኑንም በግልጽ ተረድተናል። በዚህ መሠረት "ቅድሚያ ለተቋም ኅለውናና ለትግላችን" በሚል ብሂል የሚከተሉትን ግለሰቦች ከኃላፊነት እቀባ ማድረጋችንን እንገልጻለን።

1ኛ፦ኮሎኔል ታደሠ እሸቴ (ወታደራዊ አዛዥ የነበረ)
2ኛ፦ ፋኖ ጌታ አስራደ (የጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ)
3ኛ፦ ፋኖ እያሱ አባተ (ም/የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረ)
4ኛ. ዶ/ር ምስጋናው አንዱዓለም (ጊዜያዊ የውጭ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል የነበሩ) ግለሰቦችን ከአማራ ፋኖ በጎንደር ተቋም ኃላፊነት ማንሳታችንን እንገልጻለን።

"…በአጠቃላይ በ"ዐማራ ፋኖ በጎንደር" ውስጥ የምትገኙ ክ/ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሻለቃዎችና ሌሎችም አደረጃጀቶች ከላይ በከፊል ከተገለጡ እኩይ የሴራ አካሄዶች ራሳችሁንና ሠራዊታችሁን በመጠበቅ ከምንም በላይ በያላችሁበት በተቋማችሁ ጸንታችሁ በመቆም የአባቶቻችሁን፣ የተሰው የትግል ጓዶቻችሁን አደራ በመጠበቅ፣ የመለያየትና የአሉቧልታ አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ ከትግላችን ለማዘግየት የሚሠሩ
አካላትን በጽኑ እንድታወግዙ እንጠይቃለን። ከዚህ በተጨማሪም በየቀጠናው ከሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር ቀጠናዊ ትስስሮችን በማጠናከር ከተገለጠው ጠላት የብልጽግና ገዳይ ሠራዊት ጋር የሚካሄደውን እልህ አስጨራሽ ትግል አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ በታላቅ አክብሮት ተቋማዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። በመጨረሻም የሚዲያ አካላት ከላይ በስም በተገለጡት ግለሰቦች አማካይነት የሚሠራጩ መረጃዎችና መግለጫዎች የአማራ ፋኖ በጎንደር አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን።

"ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
የዐማራ ፋኖ በጎንደር
ጎንደር፣ ዐማራ፣ ኢትዮጵያ!!

"…ዘመነ ካሤን በግለሰብ ደረጃ በመጥላት ሰበብ ሙሉ ጎጃም ላይ የዘመተው የቲክቶኩ፣ የዩቲዩብ፣ የፌስቡኩም ግሪሣ የሀብታሙ አያሌው የትኋን ሠራዊትም ጥቂት ዲዲቲ ነፍተንበት በየፔጁ ተፈነጋግሎ መቅረቱንም አይተናል። ተስፋ አይቆርጤው የፌክ ኢትዮጵያኒስት ካምፑ ያረጀው የግንቦት 7 ሠራዊትም እንደ አሜባ ራሱን እየከፋፈለ እንደ ማያ ራሱን እየለዋወጠ መጥቶ፣ መጥቶ አሁን ኢትዮ 360 ን መልሶ ቢረከብም ግንቦቴዎች ግን ገና ሲናገሩ በድምጻቸው፣ ባይናገሩም በመልካቸው፣ በጠረናቸው፣ በሽታቸው ይታወቃሉና ሰሚ ያጣ ጩኸት ከመጮህ በቀር ምንም ሊያመጡ አልቻሉም። እኔ ግን ሰው በዚህ መጠን ሲሸት አይቼም፣ ሰምቼም አላውቅ።

"…አሁን መከራው በሁሉም ቤት ገብቷል። የችጋር ጅራፍ ሁሉንም መዠለጥ ጀምሯል። ገና ከአሁኑ ሁሉም እሪሪ ቁቁ ኡኡ እያለ ነው። ዐማራ በጅምላ ሲቀበር፣ ሲጨፈጨፍ፣ ሲሰደድ፣ ሲዘረፍ ቆሞ ያይ የነበረ ሁሉ የዐማራ እምባ እሳት ሆኖ እየለበለበው ነው። ድፍን ኢትዮጵያ ደም እንባ እያለቀሰ ነው። የመረጥከው፣ ሺ ዓመት ኑር፣ ግዛን ብሎ ሲለፋደድ የነበረው ሁላ አሁን አፈር ከደቼ ሊግጥ ነው። ምርቱን የሚያመርት ገበሬ ሲታረድ ዝም ያለ ሁሉ በቁሙ ቋንጣ ሆኖ ድፍት ሊል ነው። ድንጋይ ደቼ ትበላታለህ። አሁን ሁሉም ብቻውን ያወራታል። ይቅበዘበዛታል። የራበው ሕዝብ መሪዎቹን እንዴት እንደሚበላ አሁን በዓይንህ ታያታለህ።

"…ወዳጄ አሁን የታሽጓል ዜና አያድንህም። ስግብግብ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸው ተሰረዘ፣ በድብቅ የተከማቸው ንብረታቸው ተወርሶ ለሸማቾች ተከፋፈለ ብለህ ብትለፍፍ፣ ብትጮህ ሰሚ የለህም። የፓርክ መብራትና ውኃ አያደምቅህም። የኮሪደር ልማትም ምግብ አይሆንህም። ደሞዝ ጨምሬአለሁ፣ ነዳጅ ደጉሜአለሁ፣ ማዳበሪያ በነፃ አቅርቤአለሁ ብትል ወፍ የለም። ለምን ወርቅ መና አታዘንብም፣ ለምን ወርቅ አታነጥፍም፣ ከፊትህ የመጣውን መከራ ማምለጥም ማስመለጥም አትችልም። ዐማራ ብቻ ለምን ያንባ፣ ምን በወጣው ዘወትር ያልቅስ? ለቅሶ ኀዘን ለሁሉም በየቤቱ ይፍሰስ፣ ሁሉም ደም እንባ ያልቅስ። አልቅስ አልኩህ።

"…ቤተ መንግሥቴን ወደ ኮንዲሚንየም፣ ደሞዜን በነፃ አድርጌአለሁ ብትል ወፍ የለም አልኩህ። ማኔ ቴቄል ፋሬስን ታውቃለህ? በታላቁ መጽሐፍ ላይ አንብበኸዋልን? እንደዚያ ነው። "…የተጻፈውም ጽሕፈት፦ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላል። የነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው። ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው። ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። ዳን 5፥ 25-28

• እጄን ስለበላኝ ጻፍኩላችሁ እንጂ እኔማ እረፍት ላይ ነኝ።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• እንዴት ናችሁልኝሳ…?

"…ከተራራ ላይ ጉዞ፣ ከሸለቆ ለሸለቆ መንከራተት በኋላ አረፍ ስል እኔ አፍራሹ ዘመዳችሁ የሆነ ነገር ማፍረስ አማረኝ እና ብቅ አልኩላችሁ።

"…አዛኜን ሁሉም ነገር መስመር እየያዘ ነው። ዐማራን ነፍጥ ማንሣቱ እያስከበረው ነው። አጭቤው ኮንቪንስና ኮንፊዩዝድ ማድረግ ዛሬም አምሮት ቁማር ሊባለ "ከፋኖ ጋር ንግግር ጀምረናል አላለም" ኧረ ባኪ… ተባለ ኢንዴ? ስለሱም ልጽፍላችሁ ነኝ። እናንተ ግን ስጠፋ ጠፋችሁ እንዴ? አላችሁልኝ ወይ?

"…እስቲ አንድ 200 ያህል ሰው አለነ ዘመዴ ይበል። 😂😂 ከዚያ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ተናግሮ አናጋሪ ገጥሞኝ ድንገት እንዲህ በመሃል ብቅ እስካላልኩ ድረስ 1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን በሚለው የጠዋት፣ ጠዋት የእግዚአብሔር ሰላምታችን እንቆያለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አብዛኛው ሰው መብቱን መጠየቅ ፖለቲካ ነው ብሎ ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ በማለት በገዛ እጁ ፍርሃቱን በመደበቅ ዝቅተኛ፣ አነስተኛ የተባለ የራሱን መብት ከመጠየቅም ራሱን አሽሽቶ በድሀ ልጆች ሞት ከልያም ከሰማይ ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ ነፃ ይወጣ ዘንድ በጸሎት፣ በሱባኤና በዱዓ ነፃነትን የሚጠብቅ ራስ ውሸታም፣ አስመሳይ ራስ ወዳድ ስለሆነ ለነፃነቱ አያምጽም። እንደ ኬንያ ወጣቶች ለመሆን መጀመሪያ ፊደል መቁጠር፣ ቀለም ገብ መሆንን ይጠይቃል። አንድ መሆንንም ይጠይቃል። ቲክቶከራም፣ ሀሞተ ቢስ ስልብ ሆነህ ነፃነት ይናፍቅህሃል። የራሱን ቤት አፍርሶ ቆርቆሮ ለመሸጥ የሚጣደፍ፣ ከዚያ ቱቦ ውስጥ ለማደር የሚጋፋ ትውልድ ይዘህ ዐመጽ ያማይታሰብ ነው። መስሎ ማደር አራድነት ብልጥ መሆን፣ እንደ ዘመናዊነት በሚታይባት አዲስ አበባ ችግር አንቆ ወደ ሞት ሲመራው የችግሩን ምንጭ ታግሎ ማሸነፍ ሲችል ከችግሩ ሽሽት ወይ ሊቢያ በረሃ፣ የመንና ቀይ ባህር በመሸሽ፣ በፊኛ ጀልባ ላይ ውቂያኖስ ተሻግሮ ወደ አውሮጳ መሰደፍን ይመርጣል። በዚያም የዓሣ አንበሪ ቀለብ ይሆናል። ከከምባታ ተነሥቶ ሽግርን ሽሽት ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በእግሩ ኳትኖ ታንዛኒያ ጫካ ውስጥ ዘንዶ ይበላዋል እንጂ በሀገሩ ያለውን እባብ ረግጦ መብቱን ለማስከበር መድፈር አይሆንለትም። እናም አገዛዙ ሌላ ተአምር ካልተፈጠረ በቀር በአመጽ የመውረዱ ነገር አያሰጋውም።

•ነገ በፓርላማ ሌላስ ምን ዓይነት አጀንዳ ሊያመጣ ይችላል?

"…ባለፈው ከዓለም ባንክ ድርድር በፊት በፓርላማ ያጸደቀውን በጀት አሁን 1ቢልዮን ዶላር ብድር ስላገኘ ለመንግሥት ሠራተኞች እንዳያምጹ የ20 እና የ70 ብር የደሞዝ ጭማሪ በማድረግ አፋቸውን ሊያዘጋ በማቀዱ የበጀት ጭማሪ ሊከልስ እና ሊያስጨምር እንደሆነ የባሌው ተወላጅ በእናቱ ኦህዴድ፣ በአባቱ ሶማሌ የሆነው አህመድ ሺዴ ፓርላማውን ሊሰበስብ ነው የሚል መረጃም ወጥቷል። ዘንድሮ ቁርጥ ነው።

•ሌላው ቢሆን ተብሎ የሚጠበቅ አጀንዳም አለ ብለው የሚመኙ ወሬኞች አሉ።

"…የዐማራ ፋኖን በአሸባሪነት ፈረጅኩ" ብሎ ሊያውጅ ይችላል የሚሉም አሉ። በቲክቶክ፣ በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ላይ ያሰማራቸውን ግሪሳዎች በሙሉ ፈትቶ በመልቀቅ አጀንዳ ሰጠሁ ብሎ ሊደክምም ይችላል የሚሉም አሉ። ብዙ ቀዌ ስዩም ተሾመዎችም እስከ ሙላሊታቸው ድረስ በላብ ተጠምቀው አጀንዳውን ለማንጫጫት ሲራወጡም ይታዩ ይሆናል የሚሉም አሉ። ስለዚህ የፓርላማ አባላቱ ከእረፍታቸው ስፍራ ተጠርተው የመጡት ለአጀንዳ ዳይቨርቱ ድራማ ትወና አስፈልገው ሊሆንም ይችላል የሚሉ አሉ።

"…አቢይ አሕመድ ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የጠረረበትን ብር በመፈለግ ከመጓጓቱ የተነሣ ቀደም ሲል ማዘጋጀቱን ረስቶት ይሆናል እንጂ እንደልማዱ ከገንዘብ ማራከሱ ዜና ጋር ይህቺን የምክር ቤት ስብሰባ ድራማም ቀደም ብሎ ማድረግ ይችል ነበር። እሱ ድራማውን ቀድም ብሎ መሥራቱን ረስቶ "እንኳን ደስ አላችሁ" በሚል ቀሽም የኢቲቪ የምሥራች ድራማ ሊሸውደንም ፈልጎም ነበር። ነገር ግን የበሻሻው አራዳ ጭዌው ስላላዋጣውና ሕዝቡንም በሚፈለገው መልኩ ስላላረጋጋው፣ ወሬውም ከፍተኛ የሆነ መናጋት ካሁኑ እያመጣ ስለሆነ፣ ፓርላማውን በአስቸኳይ መጥራት የግድ ሆኖበታል የሚሉም መተርጉማን አሉ።

"…ይሄ ከፊታችን የመጣው ነገር ለዘገምተኛው፣ ተወዝፎ ነፃነት ጠባቂው፣ ሆዱን ብቻ አሳቢው ድቅድቅ ጨለማ ከፊቱ ሲገሽርበት፤ እንደ ዐማራ ላለው በመከራ በፍዳ ውስጥ ለከረመው ነገድ ደግሞ የሚደንቅ በረከት ይዞለት እንደሚመጣ ሊታወቅ ይገባል የሚሉም አሉ። በተለይ ደግሞ ይሄን አገዛዙ በገዛ እጁ ጎትቶ በራሱ ላይ ያመጣውን ፈተናና ችግር በሚገባ ከተጠቀመበት ለዐማራ ፋኖ አሸወይና ጌዜ ነው የሚሆንለት። አዳሜና ሄዋኔም በጣም ሆድ ስለባሰው የዐማራ ፋኖ ማድረግ የሚጠበቅበት ለዚህ ሆድ ለባሰው ፒፕል ማጭድ ማዋስ ብቻ ነው የሚሉም አሉ። አለቀ። እነ አባገዳ ሀብታሙ አያሌው እና እነ አይተ እስክንድር ነጋ ቀደም ብለው ስለተጋለጡ ስለ እነሱ ማቡካቱን ትቶ ይበልጥ በመጪው ጊዜ ላይ መሥራት አለበት የሚሉም አሉ።  አበበ በለውና ግምቦቴዎችም መክነዋል። ፋኖም ከምንግዜም በላይ ጠንክሯል። ከዕዝ፣ ከብርጌድ አልፎ ክፍለጦር ሁሉ አዘጋጅቷል። የኮማንዶ ሥልጠናው ተጠናቅቆም ምረቃ በምረቃ ሁሉ ሆኗል። እናም ይሄን የከሰረ፣ ሕዝብ እንደ መርገም ጨርቅ መንካት የቀፈፈው፣ እንደ አባቱ ገዳይም የጠላውን ነውረኛ አገዛዝ በግራ በቀኝ በመለብለብ ብቻ ግብዓተ መሬቱን ማፋጠን ይችላል ነው የሚሉት እንደ እኔ ሟርተኛ የሆኑ የአንድምታ ቦለጢቃ ሊቃውንት።

"…የዐማራ ፋኖ በነፃ ያለ ደሞዝ፣ ቆሎና ቅጠል እየበላ ነው የሚታገለው። የብራኑ ጁላ ወታደሮች ደግሞ የሚዋጉት ደሞዝ ተከፍሏቸው ነው። ቀለብና ስንቅ፣ ትጥቁም በአገዛዙ ወጪ ተሸፍኖላቸው ነው የሚዋጉት። በብድር የመጣው ዶላር ለቤተ መንግሥት ግንባታው፣ ለኮሪደር ልማቱና ለቅንጡ ፓርኮችና ሪዞርቶች ለነጮቹ ለራሳቸው መዝናኛ ለሚሆን ግንባታ ላይ የሚውል ስለሆነ በወታደሩም ቤት ችጋር መግባቱ አይቀርም። እናም ፋኖ አሁን ነው አንድነቱን አጠንክሮ ወደፊት መግፋት ያለበት። በተለይ ይሄን ክረምት ፋኖ በሚገባ ተጠናክሮ ካልተጠቀመበት እና በጋው ከመጣበት ምንም እንኳ ማሸነፉ ባይቀርም ነገር ግን በብዙ ይከብደዋል የሚሉም አሉ።

"…ፓርላማው የፈለገውን አጀንዳ ቢያመጣ ግን አዳሜና ሄዋኔ አጀንዳዬን አልቀይርም ነው ማለት ያለብህ። ጴንጤ ነህና አገዛዙ ጴንጤ ነው፣ መሪያችን የጌታ ሰው ነው ብለህ ለአቢይ አሕመድ ብትቦተልክለትም መራብህ እና በጠኔ መዳፋትህ እንደሁ አይቀርልህም። አቢይ ኦሮሞ ነው፣ አገዛዙ በዻዺና ነው እናም የኦሮሙማውን አገዛዝ ሺ ዓመት ያኑርልን ብለህ ስትፎክረለት፣ ስትጸልይለት ብትኖርም ከትናንትና ጀምሮ ከደጃፍህ የእሳት አለንጋ ይዞ የቆመው ችጋር ኦሮሞነትህ አያድንህም። እስላም ክርስቲያን ሁን፣ ትግሬ፣ ዐማራ፣ ወላይታ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ሐረሬ፣ ጉራጌ፣ ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ የፈለግከውን ሁን ጠኔው አይምርህም። አያልፍህም። ሊዠልጥህ፣ ሊያንገበግብህ ከደጃፍህ ቆሟል። እናም አጀንዳ አትቀይር።

"…ወዳጄ የአቢይን መናፈሻ አትበላው። ዳቦ የሚያበሉህ ፋብሪካዎች እኮ ተዘግተዋል። የዳቦ መግዢያ ዕውቀት የሚመግቡህ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ማእከላት እኮ ተዘግተዋል። አምስት ዓመት ኡንበርስቲ ተምረህ ስታበቃ ብራኑ ነጋ የመውጫ ፈተና ይሉት ነገር አምጥቶብህ ዲግሪህን ተከልክለህ የተማረ ነገር ግን ዲግሪ የተከለከለ መሃይም ሆነህ ሰፈር ለሰፈር የምትንከላወስ የወጣት ጦረተኛ አድርገውህ ካረፉ እኮ ቆዩ። ወደብ አገኘን እንኳን ደስ ያለህ ብሎ ያስጨፈረህ አገዛዝ እንኳን ወደብ ሊያመጣልህ እሱ ራሱ አደብ ገዝቶ፣ አንተ ላይ መደብ ሠርቶ ነው ከአናትህ ላይ ፊጢጥ ብሎ አርፎ የተቀመጠበህ። እንግዲህ መናፈሻውን አትበላው። ምን ተሻለህ? መብራት በኮሪደር ልማቱ አከባቢ እንጂ ሌላ ቦታም ሆነ በቤትህ የለ። እንደ ጎንደር የዝናብ ውኃ እየጠጣህ የብልፅግና መሪዎቻችንን "ክፉ አይንካብን" ብለህ ሰልፍ ብትወጣም ከችጋሩ አታመልጥ። ውኃም እንደዚያው ነው እንደ መብራቱ የለም። እናም የሚሻለው ሀገረ መንግሥቱን ከቸርች ተሰብስበው ከመጡ ፍንዳታ ጎረምሶች፣ ከፍንዳታም ወጠጤዎች አላቅቆ ምራቅ ለዋጡ ሰዎች ማስረከብ ብቻ ነው። አንድ ሰው ያውም የ4ተኛ ጨ ክፍል ተማሪ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የሚዘውራትን ሀገር ወደ ገደል ወደ ኢንቁፍቱ ተወርውራ ከመግባቷ በፊት መፍትሄው 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ስለ እንጀራው አላስተዋሉምና፤ ነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር።” ማር 6፥52

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የኮማንዶ ሳሙኤል ባለድል እና የኮረኔል ጌታሁን መኮንን የስልክ ውይይት ነው። እናንተም ውይይቱን ሰምታችሁ ፍረዱ። መልካም የእረፍት ጊዜ ለሁላችን ይሁን።

"…ሻሎም…! ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመሰናበቻ… ስለ ሁለት ነገር መጣሁ፦

"…አደጋው ከባድ ነው ብለው ኢኮነሚስቶች ሲያስጠነቅቁ ስለሰነበቱበት እና በአገዛዙ ካድሬዎች እና በአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን የእንኳን ደስ አላችሁ የምሥራች ዜና ሲበሠር የከረመውን የብር የመግዛት አቅምን መዳከም በተመለከተ ጥቅምና ጉዳቱን የዘርፉ ባለሙያዎች ይተንትኑት ዘንድ ለእነርሱ ትተን እኔ ግን ከከባዱ ፍልሚያ ማግስት ከእረፍት እስክመለስ ድረስ ለአሁን የመጨረሻዬ የሆነውን ጦማር በዚህ መልክ እለጥፍላችኋለሁ። በዛሬው ጦማሬ የኮሎኔል ጌታሁን መኮንንን የመጨረሻ ማረፊያ ስፍራ እና በኮሎኔል ጌታሁን እና በፋኖ ኮማንዶ ሳሙኤል ባለድል መካከል ተፈጠረ ተብሎ የተሰራጨውን ወሬ በተመለከተ የሁለቱን ሰዎች የስልክ ልውውጥ ትሰሙት ዘንድ ወደ እናንተ አቅርቤላችሁ እንለያያለን።

መረጃ፦ ፩

"…በቅድሚያ የኮረኔል ጌታሁን መኮንንን በተመለከተ ትናንት ለመከላከያ እጅ መስጠቱን ከስፍራው ያለ ለጊዜው ስሙን በሚዲያ የማልገልፀው የሁላችንም ወዳጅ የሆነ ተወዳጅ ወንድም የላከልኝን መረጃ እንደወረደ ማቅረቤን የመረጃው ባለቤት አስታውሶ ዛሬ ደግሞ ሌላ አዲስ መረጃ ልኮልኛል። ትናንት ከአራት ጠባቂዎቹ ጋር ሆኖ ከመከላከያዎቹም ጋር በስልክ ተገናኝቶ እጁን ሊሰጥ ወደ ሊበን ከተማ ለመሄድ መንገድ ጀምሮ እንደነበር እና ሽማግሌዎችን አሻፈረኝ በማለት እጁን ለመከላከያ ለመስጠት ስለተለየን ያን ምክንያት በማድረግ ነበር እጅ ሰጠ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሼ የነገርኩህ በማለት አስታውሶ ነገር ግን ከእኛ እንደተለየ እንደ ድንገት መንገድ ላይ ምን ሓሳቡን እንዳስቀየረው ሳይታወቅ ከመከላከያዎች ጋር ይድረስ አይድረስ፣ ይገናኝ አይገናኝ ሳይታወቅ "ሓሳቡን ቀይሮ ወደ ጃዊ አካባቢ ሄዷል የሚል መረጃ ደርሶን ቆይቷል። አሁን ግን ነገሮች ተለዋዋጭ ቢሆኑም ተለዋጭ ነገር ካለም መልሼ እስክነግርህ ድረስ ለጊዜው ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ለእስክንድር ነጋ ድጋፍ ከሰጠውና በአመለ ሸጋው ፋኖ ደረጀ ከሚመራው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ መግባቱም ተነግሯል። የተለየ ነገር ከተሰማ ብቻ በዚህ ጉዳይ እመለሳለሁ። ደግሞ መከላከያዎች አስረው ፈትተው ለምን ለቀቁት ምናምን እያላችሁ እንዳታዝጉኝ አደራ። ይሄን በተመለከተ እነ አበበ በለው፣ የጎንደር ስኳድ፣ ጎጤና እነ ጌትነት አልማው ይተነትኑላችኋል። ስለእሱ አይመለከተኝም።

መረጃ፦ ፪

"…ሁለተኛው መረጃ ፋኖ ሳሙኤል ባለድልን በተመለከተ ይሆናል። ሰሞኑን ሳይወለድ የሞተውና የጨነገፈው የእስክንድር ነጋው አዲሱ የጨበራ ጩሮራ ምርጫን መክሸፍ ተከትሎ በጎንደር ፋኖ ላይ ክፍፍል ለመፍጠር በሚመስል መልኩ በብዙ በደከሙት በእነ ዶ/ር ምስጋናው አንዷለም እና ሙሉነህ፣ በግንቦቴዎች፣ በግንባሩና በሠራዊቱ ግሪሳዎች መሪነት በኮማንዶ ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ላይ የተቀናጀ የስም ማጥፋት ዘመቻም ተከፍቶበት አይቻለሁ። ዘመቻው ልክ አርበኛ ፋኖ ሜጀር ጄነራል ውብአንተን ዘመቻ ከፍተው ሕይወቱ የተቀጠፈበትን መንገድ ይመስላል።

"…ውባንተ ከመሞቱ እና ከመሰዋቱ በፊት መጀመሪያ ስሙን ነበር ያጠፉት፣ ዘመቻ ከፋቾቹ ደግሞ በሀብታሙ አያሌው፣ በሀብታሙ በሻህ እና በሀብታሙ በቀለ ጉደታ የሚመራው የቲክቶክ ሠራዊት ነበር። ይሄ ሠራዊት ነበር ቅድሚያ የስም ማጥፋት በውባንተ ላይ የከፈተበት። አርበኛ ፋኖ መሳፍንት በበላይ ጠባቂነት የሚያዙት እና አርበኛ ፋኖ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው የጎንደር ዕዝ ደግሞ መግለጫ ጭምር ነበር ጽፎ በኢትዮ 251 ውስጥ ይሠራ ለነበረው ጋዜጠኛ ሙላት አድህኖ በመላክ ያንን መግለጫ በማንበብ ብቻ ሳይሆን መግለጫውን ለውይይት በማቅረብ በመረጃ ቲቪ ላይ በማሠራጨትም ስሙን አጥፍተው አዋክበው፣ አዋክበው ለሞት ያበቁት። በዚያው መንገድ ነው አሁንም ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ላይ የተቀናጀ ዘመቻ የከፈቱት።

"…በፋኖ ሳሙኤል ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ለየት የሚያደርገው በዘመቻው ላይ ሳሚ የሚደግፈውን የአቶ አሰግድን ግሩፕ ኮሚቴ ሁላ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ የዋን ዐማራዎቹ እነ አኪላና ዘርዓ ያዕቆብም ጭምር ለሳሚ "ቃየን" የሚል የወንድም ገዳይነት መጥፎ ብያኔ ያለው ስም ሰጥተው ሲጨፈጭፉት እንደነበርም መመልከቴ ነው። አርበኛ ጋሽ አሰግድ በደረሰበት ውክቢያ አገዛዙ እጅ ሲወድቅ እንዴት እንደወደቀ የሚያውቁት ዋን ዐማራዎች በሳሙኤል ባለድል ላይ የከፈቱት ዘግናኝ ዘመቻ ግን የማልደብቃችሁን ግርምት ፈጥሮብኛል። ዋን ዐማራዎች ዐማራ ነኝ ብለው እስከተነሡ ድረስ ለሚያነሡት መከራከሪያ ጣልቃ ገብቼባቸው የማላውቅ ቢሆንም በዚህኛው ግን በድፍረት ልክ አደላችሁም ልላቸው ወደድሁ። ለምሳሌ ከፋኖ አመራሮች መካከል ጋሽ አሰግድ እኔ ራሴ ተጋብዤ በተገኘሁበት አንድ የስልክ ውይይት መድረክ ላይ አኪላ የሚረዳኝ ልጅ ነው ብሎ የመሰከረለትን፣ ገንዘብ እንዲያስተባብር የፈቀደለትን ሰው እኔ ምንም አስተያየት ልሰጥበት አልችልም። ነገር ግን አኪላም ባለበትና አቶ አሰግድ በነበረበት አንድ መድረክ ላይ የተናገርኩትን ሁላቸውም ያስታውሱታል። አሁን ግን እነ አኪላ በኮማንዶ ሳሙኤል ባለድል ላይ የከፈቱት ቅጥያጣ የጥላቻ ዘመቻ፣ ከፖለቲካ ቅማንቴው፣ ከኦሮሙማው ፀረ ዐማራ ቡድን ጋር ስምም ሆኖ ስላገኘሁት የመጀመሪያውን ልክ አይደላችሁም የሚለውን የጭቃ ዥራፌን መልእክት አንሥቼ በስሱ ልዠልጣቸው ወደድኩ። ልክ አይደላችሁም።

"…ውባንተ ይገደል ሲል የከረመው የእነ ሀብታሙ አያሌው ገረድ ሳሚ ቅማንቴው በቲክቶክ መንደሩ በከፈተው ቤትም ውስጥ አሁንም ስለ ሳሚ ባለድል መገደል፣ መወገድ አንሥተው ሲወያዩ የነበረውን ውይይትም ለታሪክ ቀድቼ አስቀርቼ በእጄ ይዤዋለሁ። መጀመሪያ ውባንተ፣ ከዚያ አሰግድን፣ ከዚያ ዘመነን መግደል ይፈልግ የነበረው አደገኛ ግሩፕ ውባንተን በመግደል አሰግድን በማዋከብ አገዛዙ እጅ ላይ እንዲወድቅ ካደረገ በኋላ በቀጥታ የግድያ ዘመቻውን የከፈተው በዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ከሣሴ ላይ ነበር። ዘመነ ካሤን በቀላሉ መድፈር እንደማይቻል ካዩ በኋላ ደግሞ ፊታቸውን በቀጥታ ወደ ምሬና ወደ ባዬ ከማዞራቸው በፊት በቅድሚያ ወደ አርበኛ ፋኖ ሳሙኤል ባለድል ለይ ነበር። በዚህ ዘመቻ ላይ ተደብቀው ከርመው የነበሩት እነ ወንድም አያሌው መንበር ሁላ ናቸው ወደ አየር ሞገዱ የተመለሱት። እኔ ሳሚን አላውቀውም። እየተነሣበት ያለው ማዕበል ግን ወዴት እንደሚያመራ ስለሸከከኝ የግድ ጣልቃ ለመግባት ተገድጃለሁ።

"…ሳሙኤል እየተከሰሰ ያለው እነ አኪላ በከሰሱበት የትግሬነት ማንነት ላይ ሁላ ነው። በሸዋ የዐማራ ፋኖ ከምዕራብ ትግራይ ይውጣ ብሎ ሲታገል የከረመውን ሰሎሞን ወልደገሪማን አጨብጭቦ የተቀበለው ቡድን አሁን ሳሚን ከመሬት ተነሥቶ ማንነቱን ትግሬ አድርጎ ስሎ ነው ዘመቻ የከፈተበት። እንዲያውም ክፍለጦሩን ራሱ የዓድዋ ክፍለጦር ብሎ የሰየመው ሳሚ ትግሬ ስለሆነ ነው ሁላ ብለው የሚናገሩ ሰዎችን ሰምቻለሁ። መነሻቸው ደግሞ ኮረኔል ጌታሁን ወደ አርበኛ ባዬ ጋር ልለፍ ብሎ መንገድ ሲጀምር አታልፍም ብሎ መንገድ የዘጋበት ሳሚ ነው የሚል ክስም አቅርበውበት ነው ዘመቻውን የከፈቱበት። ኮረኔል ጌታሁን ሲያለቅስ ነው ተብሎ የተለቀቀውን ቪድዮም እኔም "ቢያለቅስ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ነው፣ ከውርደት ጋር አይያያዝም ብዬ ማቅረቤም ይታወቃል።👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻም…!

"…በጎጃም ዐማራ ፋኖ በጎጃም የሥራ አመራር ሓላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ ሳለ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ ማስረሻ ሰጤና እስክንድር ነጋ ከእናት ድርጅቱ ገንጥለው አስወጥተውት እናት ድርጅቱም በአንድ ቤት ሁለት አባወራ የለም። ንብረት አስረክብ፣ እጅህንም ስጥ ብለው ቢጠይቁት ሞቼ ነው ቆሜ ብሎ በሚዲያ እንዲፎክር ካደረጉት በኋላ በመጨረሻ በቁጥጥር ስር ሊያውለው የተንቀሳቀሰውን በጎጃም የዐማራ ፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት ሠራዊቱ ለጎጃም ፋኖ እጁን ሰጥቶ ነበር።

"…ኮረኔል ጌታሁን በሽማግሌ ግፊት ለመደምሰስ ከጫፍ ደርሶ ቢድንም አስቀድሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ለእነ ዘመነ እጅህን ከምትሰጥ እና ከምታዋርደን ሽጉጥህን ጠጥህ ሙት ቢሉትም እሱ ግን ጋሾላ ገዳም ውስጥ ከተወሰኑ ተከታይ ፋኖ ልጆቹ ጋር ቆይቶ ነበር። ሰው ቢላክበትም እምቢኝ ብሎ ቆየ። ልጆቹም ተበትነዋል። ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዐማራ ፋነለ በጎጃም እጅ ሰጥተው ተቀላቅለዋል። እሱ ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ግን አራት አጃቢዎችን ይዞ ወደ ሊበን ከተማ ወጥቷል። በይፋም እጁን ለመከላከያ ሰጥቷል።

"…ሀብቴ ወልዴ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ እስክንድር ነጋ በአርበኛ አሰግድ መኮንን በመከላከያ እጅ መውደቅ ሲሳለቁ፣ ኮረኔል ጌታሁንን ሲያጀግኑ፣ ሲያሞግሱ ቢቆዩም ኮረኔሉ ግን ጎመን በጤና ብሎ እጅ መስጠቱ ተሰምቷል። አበበ በለው፣ ሀብታሙ አያሌው አጀግነው አጀግነው ሰውዬውን አስበሉት። አለቀ በቃ።

• ጎጃም ጎጄ መለኛው ግን አንደኛ…!!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር አሁን ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ተከታተሉን።

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia

•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/Xx7nJiC45FQ

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከዓመት በፊት "እያናፈጠልን ነው" ብሎ አመስግኖኝ ነበር ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው። እኔ መቼም ወዳጅ አይበረክትልኝ በዚያ ላይ ሲያመኝ ጤና የለኝ አይደል? 😂 ቋሚ ወዳጅም ቋሚ ጠላትም የሌለኝ እኔ ዘመዴ ይኸው ዛሬ ደግሞ አለቃው እስክንድርን ጨምሮ ሁላቸውን አሯሩጬ በጭቃ ዥራፌ አናፍጣቸው ጀመር። ከምር እያናፈጥኳቸው ነው አይገልጸውም።

• እኔ ማለት ዘመድኩን ነቀለ ነኝ (አባ ንቀል)

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፋኒት ትእግስት ጫኔ…💪

"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም በግዛቱ ውስጥ የጠላትን ተልእኮ አንግበው፣ ከዐማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ውጪ ያሉትን የማጥራት ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል። በአንድ ቤት አንድ አባወራ በሚለው ዐማራዊ ይትበሃል መሰረት የዐማራ ፋኖ በጎጃም በጎጃም ውስጥ ሆነው በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ወደዱም፣ ጠሉም፣ በግድም በውድም ወደ አንድ ይመጡ ዘንድ መመሪያ አውርዶ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምሯል። እንዲያ ሲሆን ተጠያቂነቱም ከፍ ይላል።

"…በዚሁ መሠረት የጎጃም ፋኖ ከድርጅቱ የመልቀቂያ ሕጋዊ ደብዳቤ ሳይደርሰው፣ የድርጅቱን ንብረት፣ የጦር መሣሪያና የሰው ኃይል ይዞ በሀብታሙ አያሌው፣ በማስረሻ ሰጤና በእስክንድር ነጋ ሰበካ የጎጃም ፋኖን ከድቶ ድርጅት ቀይሬአለሁ ያለውን ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተንቀሳቅሶ አሁን የበዛው ሰራዊቱ ወደ እናት ድርጅቱ ተመልሶ ኮረኔሉ በጫካ ሆኖ በሽምግልና ተይዟል። ይሳካል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ሌላው ዜና ደግሞ ጠዋት የነገርኳችሁ የጋዜጠኛ ወግደረስ በጎጃም ፋኖ ቁጥጥር ስር መዋል ነው። ለመላው የዐማራ ፋኖ ከሕዝብ ከተሰበሰበው ዶላር ላይ በእስክንድር ነጋ እየተከፈለው በጎጃም የእስክንድር የምናብ ሠራዊት እና ለሀብታሙ አያሌው ቅዠት ኢትዮ 360 በጎጃም ምድር ቋሚ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል የነበረውን ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን የዐማራ ፋኖ በጎጃም በቁጥጥር ስር አውሎታል። ወግደረስን በቁጥጥር ስር ያዋለችው ደግሞ ፋኒት ትግስት ጫኔ ትባላለች። ዛሬ ጠዋት 1:15 አካባቢ ፈለገ ብርሃን አልጋ ቤት ውስጥ እያለ ነው ከእናት ድርጅቷ ከጎጃም ፋኖ አመራሮች በተሰጣት ትእዛዝ መሰረት ፋኒት ቲጂ ፋኖዎቿን አስከትላ ቀጨም ያደረገችው። አሁን የሀብታሙ አያሌውና የእስክንድር የመረጃ ምንጭ ከስሩ ከሰመ ማለት ነው።

• ብራቮ ቲጂ 👏👏👏 ብራቮ ጎጄ መለኛው

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው ይቀጥላል…✍✍✍ "…የዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ዓላማ ይህ በሆነበትና ዐማራው በኢትዮጵያዊቱ ላይ ጥያቈ ያነሳ ይመስል እስክንድር ግን አንጠልጥሎት የሚዞረው ጉዳይ የመኖር መብት የተነፈገው የዐማራ ሕዝብ ያነሳውን የኅልውና ጉዳይ ሳይሆን የግንቦት ሰባት ፀረ- ዐማራዎች የዐማራን የኅልውና ጥያቄ ወደ ዜግነት ጉዳይ አውርደው በዐማራው መቃብር ላይ የዜግነት ፖለቲካቸውን  ሊያራምዱ የሰጡትን “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል መፈክር ነው። በዚህ መፈክር መሰረት ለዐማራ ኢትዮጵያዊነት ከሆነ እድገት በኋላ የሚደርስበት ግብ ወይም መዳረሻ ነው።

"…በሌላ አነጋገር ዐማራው ዛሬ ላይ በእስክንድር አሳዳጊነትና ሞግዚትነት ጉዞ ላይ ስላለ የደረሰበት ግብ ወይም መዳረሻ የለውም። እስክንድር ነጋ ዐማራውን እንደዚህ ታሪክ የሌለውና ኮምፓሱ የጠፋበት መርከብ ለማድረግ ይኼን ያህል ርቀት የሄደበት ምክኒያት የምታወቀው “በኢትዮጵያዊነት ስታገል” ስለነበር ዐማራ መባል፣ በዐማራ መታገል እንደማነስ መስሎ ስለሚሰማውና እንዳይተወው በዐማራ ላይ ካልተረማመደ በስተቀር ከሥልጣን መድረስ እንደማይችል መስሎ ስለተሰማው ነው።

"…ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ከ ያ ትውልድ የተማሪ ፖለቲከኞች የተወረሰው ኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ሳትሆን በምኒልክ ቅኝ ግዛት የተሰባሰቡ ነጻ የነበሩ የአፍሪካ አገሮች የተሰባሰቡባት ኢምፓየር አድርጎ የማየት አባዜ ነው። እስክንድር “መነሻችን ዐማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ሲልም ይቺን በያ ትውልድ አእምሮ ኢምፓየር ሆና የተፈጠረችውን የነጻ አገሮች ስብስብ መሪ ከሆንሁ በኋላ ኢትዮጵያ ወደምትባል አገር አሳድጌ መዳረሻዬ አደርጋታለሁ እያለን ነው። እብደት ካልሆነ በስተቀር በዚህ የእስክድንር እንቶ ፈንቶ የሚስማማ ፋኖ ሊኖር አይችልም።

• ማጠቃለያ!

"…የፋኖ የኅልውና ተጋድሎ በአንድ ማዕከል ስር እንዲሰበሰብ ለማድረግ እሠራለሁ የሚል አካል ቢኖር የመጀመራያውና ቀዳሚው ተግባሩ መሆን ያለበት የፋኖ አንድነት እንዳይሳካና ሐዲዱን እንዲስት እያደረገ ያለው (The elephant in the room) እስክንድር ነጋ መሆኑን ዕውቅና ሰጥቶ ለጉዳዩ ዘለቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል።

"…በእኔ በኩል እስክንድር ነጋን በተመለከተ የሚታየኝ አንድ አማራጭ ብቻ ነው። እስክንድር ነጋ የፋኖ የኅልውና ተጋድሎ ችግር የሆነው የሥልጣን ፍላጎቱ ከቁጥጥር ውጪ አድርጎት ኅሊናው ሊወቅሰው ወደማይችል ግብዝ ፍጡር የለወጠው በመሆኑ ነው። ሆኖም ግን ዐማራው እያደረገ የሚገኘው የኅልውና ተጋድሎ በመሆኑ እስክንድር የኅልውና ተጋድሎው መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ ከሥልጣን ሽሚያና የዐማራውን ድምጽ ከፋኖ ከመጫረት ለጊዜው ገለል ብሎ እንዲቆይና የኅልውና ተጋድሎው መቋጫ አግኝቶ የፖለቲካ መድረክ ሲከፈት በፈለገው ፕሮግራምና ፓርቲ ስር ለምርጫ ድል ለዲሞክራሲውን ይዞ ቢወዳደር የተሻለ እንደኾነ፤ እስከዚያ ድረስ ግን በሞያው ተወስኖ አለኝ የሚለውን ተሰሚነት በመጠቀም የፋኖን የኅልውና ተጋድሎ እንዲረዳ ማግባባት የሚል ነው።

"…ከዚህ ውጭ የእስክንድር ጉዳይ ተለይቶ እልባት ሳይሰጠው ፋኖን አንድ ለማድረግ መሞከር በትግሉ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ከማድረስ ውጭ ዘላቂነት ያለው መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል መታወቅ አለበት። ነገር ግን የግል የስልጣን ፍላጎቱን ለማርካት ቆርጦ በተነሳው በእስክንድር ነጋና በተቀረው የኅልውና ተጋድሎ በሚያደርገው የአማራ ፋኖ መካከል መጠላለፍ ሳይፈጥር ሕዝብዊ ተጋድሎውን ወደፊት ማራመድ ይቻላል የሚል ሓሳብ ያለው ሰው ቢኖር ለመስማት ዝግጁ ነኝ። አበቃሁ!

• ተጻፈ በአቶ አቻምየለህ ታምሩ (ዐማራ ነው)

• አቅራቢ…

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

• ዐማራ አቀፍ የፋኖ አንድነት ለምን ከሸፈ? የሚፈለገው የፋኖ አንድነትስ እንዲመጣ ምን ሊደረግ ይገባዋል?

"…በየጠቅላይ ግዛቱ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶች አነሳሽነት እና በቅን አሳቢ ዐማራዎች ግፊት የዐማራ ፋኖን ወደ አንድ የተማከለ አደረጃጀት ለማምጣት በርካታ ጥረቶችና ሙከራዎች ተደርገዋል። ሆኖም ግን ጥረቶችና ሙከራዎች ሁሉ አንድ መሰረታዊ ችግር አለባቸው። ጥረቶቹና ሙከራዎቹ የተደረጉት በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ጣልቃ እየገባ ልዩነትና አለመግባባት እንዲሰፍን ያለ እረፍት የሚሠራ ችግር ጠማቂ ኃይል እንደሌለ በመቁጠርና የፈጠረውን ችግር በማለባበስ ነበር። “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” እንዲሉ በፋኖዎች መካከል የተፈጠረውን ችግር ምንጭ (root cause) በድፍረት ሳይመረምሩ በየጠቅላይ ግዛቱ  ወገን ለይተው የየራሳቸው አደረጃጀት የመሰረቱትን ፋኖዎች እንዲሰበሰቡ በማድረግ ብቻ ዘለቄታ ያለውና  እንደ ብረት የጠነከረ አንድነት ያለው የተማከለ የዐማራ አደረጃጀት እንዲፈጥሩ ማድረግ አይቻልም።

"…በየጠቅላይ ግዛቱ የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች አንድ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ጠላት እንዲተያዩና በጦር እንዲፈላለጉ በተደረጉበት ሁኔታ ከላይ የተንጠለጠለ መሪ በመሰየም የዐማራ ፋኖ አንድነት ሊመጣ አይችልም። በመሆኑም ዐማራ አቀፍ የፋኖ አንድነት ለመፍጠር በየጠቅላይ ግዛቱ በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች መካከል ጠንካራ ወንድማዊ አንድነት እንዳይፈጠርና በጠላትነት እንዲፈላለጉ ያደረጋቸው አካል መታወቅና መለየት አለበት።

"…የዐማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ የነበረው አሰግድ መኮንን ከይዞታው ከእስከንድር ነጋ ጋር በሚሠሩ ፋኖዎች ተባሮ ይንከራተት በነበረበት ወቅት መሆኑን ይመራው የነበረው ዕዝ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ይቻላል። በማኅበራዊ አውታሮች ሲዘዋወር ባዳመጥነው የአርበኛ አሰግድ ድምጽም አሰግድ በእስክንድር ነጋ በሚታዘዙ ፋኖዎች የደረሰበትን በደል እንባ እየተናነቀው በዝርዝር ሲናገር ሰምተነዋል።

"…መሪ ለመሰየም የተሰባሰቡ የየጠቅላይ ግዛቱ የፋኖ አዛዦች ይህን ችግር ተጋፍጠው መፍትሔ ማስቀመጥ ሲገባቸው ልክ ወንድማዊ ስምምነት በመካከላቸው ያለ ይመስል የፋኖ መሪ ለመሾም መስፈርት ዘርግተው ገመድ መጓተትና ምርጫ ለማድረግ ጥቆማ ውስጥ መግባት አልነበረባቸውም። ይልቁንም ሸዋ ላይ እስክንድር ነጋ የፈጠረው ችግር ምንድን ነው? ብለው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ቢሞክሩ ኖሮ ዛሬ ላይ በአርበኛ አሰግድ መኮንን ላይ የደረሰው መከራ ላይደርስ ይችል ነበር። በርግጥ የሸዋው ጎልቶ ስለወጣ እዚህ ላይ ተነሳ እንጂ እስክንድር ነጋ በረገጠው ምድር ሁሉ ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ በጎጃም፣ በጎንደርና በወሎም የፋኖን አንድነት እያመሰው ነው።

"…በአጭሩ መሪ ለመሰየም የተሰባሰቡ የፋኖ አዛዦች በየጠቅላይ ግዛታቸው አንድ ላይ መቆም ሳይችሉ ወይንም በጠላትንት እየተያዩ ወይም እንዲተያዩ ሚሊዮኖች እያፈሰሰ የሚሠራ ኃይል በመካከላቸው እያለ በዐማራ አቀፍ አደረጃጀት አንድ ላይ መቆም እንደማይችሉ ማሰብ ነበረባቸው። ምርጫ ተብየው ተሳክቶላቸውና አንድ ሰው መሪ አድርገው የመረጡ ቢሆን ኖሮ በመካከላቸው እንዲፈጠር የተደረገው በጠላትነት መተያየት በእርቅ ባልተፈታበት ሁኔታ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በወሎና በጎንደር የተደራጀውን ውሕዱን ፋኖ ማን ሊመራው ነበር? የሸዋውን ዕዝ የሚመራው አሰግድ ወይስ መከታው? የጎንደርሩንስ? የወሎውንስ? የጎጃሙንስ? ብለው አርቀው ሳያስቡ ዐማራ አቀፍ የፋኖ እውነተኛ አንድነት ለማምጣት መሞከራቸው ትልቅ ስህተት ነበር። 

"…በጉባዔ አንድ ሰው በመሪነት ስለተሰየመ ብቻ ጎራ ለይተው በጠላትነት እንዲፈላለጉ በተደረጉ የየጠቅላይ ግዛት አደረጃጀቶች መካከል የሰፈነው ጠላትነት ተንኖ ሊጠፋ አይችልም። በጠላትነት የሚፈላለጉ ቡድኖችን እርቅ ሳያወርዱ አንድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ውጤቱ አንዱ አንዱን ጥሎ ማለፍ ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ አንድነት ሊያመጣ አይችልም። በፋኖዎች ዘንድም የሆነ ይሄ ነው።

"…በአጭሩ በፋኖዎች ዘንድ ተገቢው ክብደት ተሰጥቶት ብቻውን ተለይቶ መታየት የነበረበትና ከፍ ብሎ ለታዩት ችግሮች ሁሉ መንስዔ የሆነው የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ሳይፈታ የፋኖ አንድነት ሊመጣ አይችልም። እስክንድር ነጋ እንደ ፋኖ አንድነት ዋናው የችግር ምንጭ ታይቶ የፈጠራቸው ችግሮች ቅድሚያ መፍትሔ እስካልተሰጣቸው ድረስ የአንድነት ጥረት ውጤቱ ወደፊትም ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ነው።

"…እስክንድር የዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ችግር የሆነው በፋኖዎች መካከል በሚፈጥረው መከፋፈል ብቻ አይደለም። ይልቁንም በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ እስክንድር ነጋ የሚባል አንድ ለዐማራ የኅልውና የሚጋደል የፋኖ አዛዥ ተደርጎ መቅረቡ ጭምር ነው።  እስክንድር ሕዝባዊ ግንባር፣ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ወዘተረፈ እያለ የፈጠራቸውና ከሱ በስተቀር ሌላ መስራች አባል የሌላቸው የውሸት ድርጅቶች ባለቤት መሆኑ ብቻ ሳይሆን የኋላ ታሪኩና በዐማራው የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ ሊያራምደው በሚሞክረው ፀረ ዐማራ እሳቤው ጭምር ተመዝኖ እንደየ ጠቅላይ ግዛቶቹ የፋኖ አዛዦች አንዱ ተደርጎ መቆጠር አልነበረበትም።

"…እስክንድር በዐማራ የኅልውና ተጋድሎ ላይ ያደረሰው ጥፋት ሁሉ ወደ ጎን ተብሎ እንደ አንድ የፋኖ መሪ ይቆጠር ቢባል እንኳን ለእውነተኛ ፋኖዎች ፍትሐዊ አይሆንም። እስክንድር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከዐማራው ማኅበረሰብ የሰበሰበ፤ የላቀ ገንዘብ እየከፈሉ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን እየገዙ ተጫዋች ሲያዘዋውሩ እንደሚውሉ የአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦች በየጠቅላይ ግዛቱ ከተሰባሰቡ የፋኖ አደረጃጀቶች ግለሰቦችን በረብጣ ብር እየገዛ ሲያዘዋውር የሚውል፤ በዐማራ ሕዝብ ትግል ስም የሰበሰበውን ገንዘብ የዐማራ ልጆች በሚከፍሉት መስዕዋትነት የሚሠራውን ገድል እየገዛ ያናወዘውን የሥልጣን ወልፉ ለማርካትና የዐማራን መስእዋትነት የሰልጣን መወጣጫና መፈንጫ አድርጎ የሚቆጥር በፍቅረ ሥልጣን የተለከፈ ሰው ነው።

"…እስክንድር የሥልጣን መዳረሻዬ ናት በሚላት ኢትዮጵያ ያነገበውን ርዕሰ መንግሥትነት ከዐማራ የኅልውና ተጋድሎና ከዐማራ በላይ በማድረግ ሌት ተቀን ሲያላዝኑለት የሚውሉ የብዙ ምላሶችና ጆሮዎች ባለቤት የሆነ ግለሰብ ነው። እነዚህ የእስክንድር መጠቀሚያ የሆኑ ምላስና ጆሮዎች ለኅልውና ተጋድሎ ተብሎ ከተሰባሰበው/ከሚሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ ቀለብ እየተሰፈረላቸው በየቀኑ ሲያቀርቡ የሚውሉት አቢይ አሕመድ በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚወርደውን መከራና ፍዳ ሳይሆን እስክንድር ነጋ በየቀኑ የሚነሳውን ፎቶና ተንቀሳቃሽ ምስል እያሳዩ እስክንድር መዳረሻው ለሆነችው ኢትዮጵያ ምን ያህል ከፈጣሪ የተሰጠ መሪ እንደሆነ በትወናና በመወድሰ የታበጀ የእስክንድር አምልኮ ነው።

"…ከእስክንድር ጋር ለውድርድር ቀረቡ የተባሉት እውነተኛ የፋኖ መሪዎች ደግሞ በዓላማ ከሚከተላቸው የድኃ ገበሬ ልጅ ውጭ ምንም የሌላቸው፤ በትክሻ ወይም በአህያ የተያዘ በሶ፣ ቆሎና ጥሬ እየበሉ፣ በወጣ ገባው አስቸጋሪ የአገራችን መልክዓ ምድር ሲወጡና ሲወርዱ የሚውሉ ምስኪኖች ናቸው። የሥልጣን ወልፉን ለማርካት ለእሱ የሚሠሩ ምላስና ጆሮ፤ እንዲሁም ለፍላጎቱ ማስፈጸሚያ የፋኖ ዕዝ ጭምር የሚገዛበት ረብጣ ገንዘብ ያለውን ግለሰብ ምንም ከሌላቸው ከወሎ፤ ሸዋ፤ ጎጃምና ጎንደር የፋኖ አዛዦች ጋር በአንድ መለኪያ መስፈር፤ እውነትኛ የፋኖ አዛዦችን ከፍ ባለ መለኪያና ፍትሐዊ ባልሆነ ሚዛን እየሰፈሩ፤ እስክንድርን ግን በጣም ዝቅ ባለ ልኬት በመመዘን

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የምስጋናው ፍጥነት እያስገረመኝ፣ እያስደነቀኝም ነው። 1ሺ ሰው ከምኔው አመስግኖ እንደሚሞላ ሳይም አምላኬን ደጋግሜ እያመሰገንኩትም ነው። በእውነት እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ሌላው በምስጋና መሃል ፀያፍ ቃል መጠቀም፣ መሳደብ፣ አዲስ አጀንዳ ጣልቃ ማስገባት፣ እኔን ጭምር ማመስገን፣ ማወደስ ያስቀስፋል ባልኩት መሠረት እንደምትመለከቱት በምስጋና መሃል ጣልቃ የሚገባ ሰው ጠፍቷል። የሚጻፈው ቃል በሙሉ እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ሆኗል። በእውነት መታደል ነው። ይሄ ሁሉ ሕዝብ በየቀኑ እግዚአብሔር ይመስገን እያለ ሲያመሰግንና ለምስጋና ሲጋፋ ማየት ምንኛ መታደል ነው? አመስጋኞች በረከታችሁ ይደርብኝ።

"…ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ የተጻፈው በእኔ አይደለም። በማን እንደተጻፈ ሰዓቱን ጠብቆ ይቀርብላችኋል።

"…ከዚያ በፊት ግን አሁን ከዐማራ ፋኖ በጎጃም የደረሰኝ ሰበር መረጃ አለ። ይኸውም በጎጃም የግንቦት7፣ የባልደራስ፣ ግንባሩና ሠራዊቱ የሚባሉት የእስክንድር ፍልፈሎች እየጸዱ መሆኑን ነው። ኮረኔል ጌታሁን ከወንድሙ ከዘመነ ጋር ይገናኛል፣ የግንቦቴዎችን ህልምም ይቀጫል የሚል ተስፋ ነው የሰጡኝ።

"…በዛሬው ዕለት ደግሞ የዐማራ ፋኖ በጎጃም በምሥራቅ ጎጃም አካባቢ የሠፈረውን ደርዘን አይሞሌ የእስክንድር የዶላር ሚሊሻን እጅ ለማሰጠትና ንብረት ለመረከብ ክፍለጦር ተልኮ ዘመቻ መጀመሩን ሰምቻለሁ።

"…በሌላ በኩል ጎጃም ተቀምጦ ለሀብታሙ አያሌው፣ ለ360 የዘገባ ሥራ ሲሠራ የከረመው የቀድሞው የባልደራስ የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ፣ የዓለም ብርሃን ሃይማኖት የጦር አደራጅ፣ የግንባሩና የሠራዊቱ አሁንም ሳይወለድ የሞተው የእስክንድር ድርጅት የፕሮፓጋንዳ ሓላፊ የነበረው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ለጎጃም ፋኖ እጅ መስጠቱ ተነግሯል።

• መጣሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ክቡራን ደንበኞቼ ሆዬ… ስላችሁ ወዬ አላችሁ? 😁

"…እህሳ… እኔ አስነቀልቲው ዘመዴ እንዴት ነኝ…?ብፌውስ እንዴት ነው? " …በእኔ በኩል ምን ጎደለ? ምንስ ልጨምር? ምንስ ልቀንስ…?

• እየኮመኮማችሁ ነው…?

Читать полностью…
Subscribe to a channel