zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…አሁን ደግሞ ስለዚ ሶዬ… በብሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምትክ አቢይ አሕመድ ቦታ እንደሚሰጠው ቃል እንደገባለት ዳንኤል ክብረት ለወዳጆቹ ሲናገር ስለተሰማው ስለ አባ ዶላር ዳዲ ስለ ፀረ ዐማራው፣ ስለ አባ ከፋፍሌ እስኬው የሆነ ነገር ልል ነኝ። መቼም እናንተ እንደ እነ እስክስ አበበ በለው፣ እንደ ሀፍታሙ አፍራሳ አይደላችሁም ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። የዛሬው የጥልያን እረፍቴን በደንብ ልጠቀምበት ብዬ ነው። ደግሞም…

"…በዚያውም እግረመንገዳችሁን ለሸዋው ፋኖ ለእስክንድር አምላኪው ለወደፊት ለክቡር ብሬዘዳንቱ የጥበቃ ሓላፊ ሆኖ ቃል ለተገባለት ለፋኖ መከታው ማሞ፣ ለጎንደሬዎቹ፣ ለእነ ጋሽ አባባ አርበኛ መሳፍንት፣ ለፋኖ ሀብቴ ወልዴ፣ እጅግ ለማከበረው ለፋኖ ደረጀ፣ ለፍሮፌሰር ጌታ አስራደ፣ ለኮረኔል ታደሰ፣ ለወሎዬው ለኮረኔል ለፈንታሁን ሙሀባው ታደርሱልኝማላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ልቀጥል አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከዚያ…

"…ጠቅላይ ሚንስትሯ… የበለጸገውን ባርቲያቸውንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ አደባባይ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥት ለመግባት የተሰባሰበውን ሱናሚ የሕዝብ ማዕበል ያስቆምላቸው ዘንድ በሀገራቸው አጠራር እንደ ኦሮሚያ ፎሊስ፣ እንደ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ እንደ አዲስ አበባ ፎሊስ፣ እንደ ፌደራል ፎሊስ፣ እንደ ጋቸነ ሲርና ያለ፣ እንደ መከላከያ ሠራዊት፣ እንደ ሰላም ሠራዊት፣ እንደ ደንብ ማስከበር፣ እንደ ሚሊሻ ያሉ የሀጋሪቱን የፀጥታ ተቋማት አዘዙ።

"…የሀገሪቱ የጸጥታ ተቋማትም የጠቅላይ ሚንስትሯን ትእዛዝ ተቀብለው። እንደ ብራኑ ጁላ፣ እነ አበባው ታደሰ፣ እንደ ደመላሽ ገበረ ሚካኤል የመሰሉ የባንግላዴሽ የጸጥታውና የወታደሩ ሊቃነ መናብርት በሉት ይሄን ሕዝብ ብለው አዘዙ። ወታደሩም ግራ ቀኝ ሳያይ የገዛ ወንድሙን፣ የአጎትና የአክስቱን ልጅ፣ በእጁ ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ያላዘን ሰላማዊ ዜጋ ግንባር ግንባሩን ይለው ጀመር። ወንዶች፣ ሴቶች እንደ አግአዚ ያለ ጦር በመሰሉ ጨካኝ ወታደሮች አናታቸው በስናይፐር እየፈረሰ በግራም በቀኝም ይወድቅ ጀመር። ሕዝቡ ግን የራበው፣ የመረረው፣ ራሱን እንደ ደባርቅ ነዋሪ መርዝ ጠጥቶና በገመድ ራሱን አንቆ ሞቶ በመንግሥተ ሰማያት ከሚኮነን በመንግሥት ሰይፍ ተሰይፌ ሰማእትነትን ልቀበል ብሎ በወደቁት አስከሬኖች ላይ እየተረማመደ ዋናውን ሰንኮፍ ለመንቀል ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመሄድ ወታደሮቹን ገትሮ ያዘ።

"…በመጨረሻም… ሆቴል ተቀምጠው፣ ቁርጣቸውን እየቆረጡ፣ ልጃገረድ ተማሪ ወጣቶች በጨረታ እየቀረቡላቸው የሚያመነዝሩት፣ በጠቅላይ ሚንስትሯ ኮንትሮባንድ እንዲሠሩ፣ እንዲዘርፉ፣ መሬትና ቪላ በነፃ እንዲታደላቸው የተፈቀደላቸው ጀነራሎች ፈሩ። ፈሩና ለወታደሮቻቸው መመሪያ ሰጡ አሉ። ግድያ አቁሙ፣ መንገዱን ልቀቁላቸው…

"…ከዚያ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ለእሁዱ የመረጃ ተለቭጅን ተናፋቂው "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" መርሀ ግብሬ ለመድረስ ስል ወደ ሀገሬ መመለሻ ድልድዩ በተሰበረብኝ ወቅት የክፉ ቀን መሸሸጊያዬ ወደሆነችው ወደ አጎት ሀገር ጀርመን መመለሻ ቀኔም ስለደረሰ ዛሬን በጥልያን ሮማ ከተማ ከሰዓት በኋላ በማረፊያ ቤቴ የእረፍት ሰዓት ይኖረኛል። በዚያን በእረፍት ሰዓቴ እስከ ምሽት እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ የልብ የልባችንን እናወጋ ዘንድም አስቤአለሁ። እናንተም በያላችሁበት በጨዋ ደንብ ለመወያየት ተዘጋጁ።

"…እስከዚያው ድረስ የሰላሌዋ ኦሮሞ ሚስቱ አባራው አሁን ከብሪጅእስቶን ጋር በቤልጂየም ብራስልስ ዓለሙን እየቀጨ ላለው ለባለ አንጓ ንቅሴው ለአባባ ሞጣና ለእማማ ብሪጅስቶን የዕለቱ የቲክቶክ ማሳመሪያ፣ ለግንቦቴ፣ ለግንባሩ፣ ለኦነግ እና ለሂዊ፣ ለብልፄ፣ ለፖለቲካው ቅማንቴና ለአገው ሸንጎ አክቲቪስቶች ራሳቸውን በራሳቸው ለስሜታቸው ማርኪያ ይሆን ዘንድ ይህቺን ፎቶ ከጥልያን ሮማ ልኬላቸዋለሁ።

"ሰበር ዜና"

"…አጭበርባሪው፣ ሌባው፣ ዱርዬው፣ ክፍትአፉ፣ እብድ ውሻው፣ ሰካራሙ፣ መራታው፣ ቀማቴው፣ ተሳዳቢው፣ አረም ነቃዩ፣ አያስዋሼው፣ አፍራሹ ዘመድኩን ነቀለ በጥልያን ሮማ ከተማ በፎሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ" ብላችሁ ትሸቅሉብኝ ዘንድ ይህችን ፎቶ ለጥፌላችኋለሁ። 😂😂😂

"…አዛኜን እኔ እኮ ለሚጠሉኝ እንኳ ለዕለት እንጀራ ይሆናቸው ዘንድ የሚያበላቸውን አጀንዳ በምስል አስደግፌ የማበረክት ደግ፣ ለጋስ፣ ቸርና ርህሩህ ነኝ። 😁 አይ ዘሙካ፣ ዘመዴ፣ ዘምነት፣ ዘሙ፣ ዘሜ፣ ዘምዬ፣ ዘመዳችን፣ ዘመድ ዘር…✍✍✍

"…አዳሜና ሔዋኔ ሆይ እንደ ንሥር ታድሼ እየመጣሁልሽ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻም…

"…ከብር የመግዛት አቅም መዳከም በኋላ በገበያው ላይ ምን ታዘባችሁ?

• ጤፍ በኪሎ ስንት ገባ…?
• 1 ኪሎ ሥጋስ
• ሽንኩርትስ?
• 1 ሊትር ዘይትስ?

"…ትራንስፖርት ጨመረ ወይስ በዚያው ነው። ከአዲስ አበባ ሀረር፣ ድሬደዋ፣ ከአዲስ አበባ መቀሌ፣ ደሴ፣ ጎንደር ባህርዳር የአውቶብስ የትራንስፖርት ዋጋ ስንት ገባ? ከአዲስ አበባ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ጋምቤላ በአውቶቡስ ይኬዳል ወይ? ከአዲስ አበባ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት፣ ደብረ ብርሃን፣ አምቦና ፎቼስ ስንት ገባ ትራንስፖርቱ?

"…አንድ ዳቦ ጨመረ ወይስ ቀነሰ? በየአይነቱ፣ ሽሮ ራሱ፣ ሻይና አንድ ተቆራጭ ኬክ ስንት ገባ? እኔ የምጠጣው ቅሽር ሻይ ስንት ደረሰ? ብርቱካን በኪሎ? አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ስንት ደረሰ?

"…ከአዲሱ ገበያ ፒያሳ ታክሲ እንደ ድሮው 3 ብር ነው ወይ? ከጊዮርጊስ ጎጃም በረንዳ 1ብር ከ50 ላይ ተጨመረ ወይ? ሸሚዝ፣ ካልሲ፣ ግልገል ሱሪስ ዋጋቸው እንዴት ነው?

"…የልጆች ትምህርት ቤት ዋጋ ጨመረ ቀነሰ? የደብተር ዋጋስ? የሰርቢስ ዋጋ? የህክምና ለካርድ እንደ ድሮው 30 ብር ነውን? ፊልም እና ቲያትር መግቢያቸው ስንት ሆነ? የቤት ኪራይስ? ደሞዝስ ጨመረ ቀነሰ?

• ኮሪደር ልማቱስ ምንሁኖ ነው መለስተኛ ሀይቅ የሆነው? የብሽክሊሊት መንጃው ቀዩ አፈር ምን አጠበው? እስቲ ትንሽ አጫውቱኝ። ለስላሳና ቢራስ በጠርሙስ ስንት ገቡ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አሁን እኮ እንደ ድሮ ብዙም የሚያስቸግር ነገር የለም። ሁሉም ነገር ጥርት እያለ ወደፊት እየመጣ ነው። ተኩላው ከበጉ፣ ብርሃን፣ ከጨለማ፣ ኃጥኡ ከጻድቁ፣ እውነት ከሐሰት እየተለየ ነው። የብዙዎች ሜካፕ እየለቀቀ የአፈር ገንፎ እየመሰሉ ነው። አሁን ያልነቃውን ሳይሆን የነቃውን ነው ቆጥረህ የማትደርስበት፣ ሁሉም ነገር መልክ መልኩን ይዟል።

"…አሁን እኮ ያ በሁሉም የተናቀው ፋኖ፣ የትም አይደርስም የተባለው፣ ባለ ሦስት ፍሬ ክላሽ ባለቤት፣ በሦስት ቀን ሱሪውን እናስወልቀዋለን፣ ጃዊሳ፣ አሞሌ ጨው፣ ጽንፈኛ፣ ሽፍታ፣ ዘራፊ የተባለው ፋኖ ዙ 23 መታጠቅ ጀምሯል። ክፍለጦር እያደራጀ ያለ እኮ ነው ፋኖ። ዕህእ።

"…እናም በፊት በፊት ብአዴንን አንበርክከህ ቅጣው፣ ዘር ማንዘሩንም አጥፋው፣ አቶ ግርማ የሺጥላ አሬሮ ኦሮሞ ነው። ከዐማራ ምድር መነቀል አለበት እያለ ሲደነፋ የነበረው የአፍራሳ የልጅ ልጅ ዛሬ ድንገት ተገልብጦ ብአዴኖች ለምን ተንበረከኩ? ይሄ እኮ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው በማለት ከብአዴን በላይ ብአዴን፣ ከብልፅግናም በላይ በልፅጎ የተንበረከኩትን ሰዎችን ሰብዓዊ ጥሰት ለማጣራት አሜሪካም ጦሯን ይዛ ትግባ ምናምን ካለህ በቃ ቲሽ እና ድር የመጨረሻ ተሸንፈዋል ማለት ነው። ማንቁርታቸው ላይ እንደቆምክ ዕወቅ።

"…ዘመነን በመጥላት ሰበብ ዘመነን መሸወድም፣ መግደልም ሲያቅትህ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ዘምተህበት ስታበቃ፣ አርበኛ ባዬ፣ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ላይ ይገደሉ፣ ይጥፉ ብለህ ካወጅክ በኋላ፣ ግዙፉን የምሬ ወዳጆን ጦር እያናናቅክ፣ አሰግድን አሳልፈህ መስጠትህ ሳያንስ የአሰግድን ይዞታ ለመከላከያ ለቀህ እየወጣህ፣ ከመከላከያ ጋር በመናበብ የሸዋ ፋኖ ላይ እየዘመትክ የፋኖ መሪ ነኝ አድምጡኝ፣ ተረዱኝ፣ እርዱኝ ስትል አለማፈርህ። ወዳጄ ዐማራ ሥራ ላይ ነው አልኩህ።

• አልቅስ 😭

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

•ቅዱስ ጴጥሮስ

"…ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ ከነገደ ሮቤል፣ በእናቱ ከነገደ ስምዖን ሲኾን፣ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ስምዖን" ነበር፡፡ ኋላ ላይ ጌታ "ጴጥሮስ" ብሎ ጠርቶታል፡፡ ትርጕሙም በግሪክ ቋንቋ ዓለት ወይም መሠረት ማለት ነው፡፡

"…ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ በዋና መዲናቸው በኢየሩሳሌም ፩ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን በዕጣ ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሮም ደርሶታል። በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣ በቀጳዶቂያና በቢታኒያም ዙሮ አስተምራል። በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በስሙ የተመዘገቡ ፪ መልእክታትንም ጽፏል።

•ቅዱስ ጳውሎስ

"…ቀዳሚ ስሙ ሳውል ነበር። ትውልዱም ከነገደ ቢኒያም ነው። የተወለደውም ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ሲሆን ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከገማልያል እግር ስር ሕገ ኦሪትን ተምሯል።

"…በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በስምንተኛው ዓመት ነበር። ለሐዋርያን የተመረጠውም ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ሲጓዝ የዓይኑን ብርሃን በሳጣው የጌታ ጥሪ በደማስቆ ሜዳ ላይ ነው። ስሙም ከሳውል ወደ ጳውሎስ ተቀይሮ ዓለምን ዙሮ ወንጌልን በብዙ ድካም አስተምሯል። ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

"…ታዲያ ሁለቱም ሐዋርያነ አበው በርትዕት ሃይማኖታቸው ምክንያት በ69 ዓም በጣኦት አምላኪው በሮሙ ንጉሥ ኔሮን ቄሳር በተሰጠ የሞት ፍርድ ቅዱስ ጴጥሮስን የቁልቁል ሰቅሎ፣ ቅዱስ ጳውሎስን ሰይፎ ሁለቱም በአንድ ቀን በሰማዕትነት አርፈዋል። በረከታቸው ይደርብን።

"…ለእኔ ሁለተኛዬ፣ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ የሆነው የጣሊያን ጉብኝታችን በሮማ ወዳጆቼ ክብካቤ በስኬት እየተጓዘ ነው። 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሊቀ መንበር እስክንድር ነጋ ምክትል ሊቃነ መናብርቶቼን መርጫለሁ ብሏል።

፩ኛ፦ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ከጎንደር (ዕዙ)
፪ኛ፦ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባ ከወሎ (ዕዙ)
፫ኛ፦ አርበኛ መከታው ማሞ ከሸዋ (ዕዙ)
፬ኛ፦ ኮረኔል ታደሰ እሸቴ ከጎንደር (ፋፍህዴን)
፭ኛ፦ ፍሮፌሰር ጌታአስራደ ከጎንደር (ፋፍህዴን)
፮ኛ፦ መስፍን አባተ (ከየት እንደሆነ እንጃ)
፯ኛ፦ አርበኛ ደረጀ በላይ ከጎንደር (ዕዙ)
፰ኛ፦ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከጎጃም (ዕዙ)
፱ኛ፦ መምህር ምንተስኖት ወንዳፈረ ከሸዋ (ዕዙ) ከኢዜማ ናቸው።

"…እንግዲህ የእነዚህ ሁሉ አለቃቸው ማን ሆነ? ጋሽ እስክንድር ነጋ። አዎ ጋሽ ሁሌ ሊቀመንበር አሁንም ሊቀመንበር ሆነዋል። በዚህ በጋሽ ሁሌ ሊቀመንበር ድርጅት ውስጥ ደግሞ ጎንደርን ወክለናል ያሉቱ በስፋት የሥልጣን ቦታ ሲያገኙ፣ ግዙፍ ጦር ያላቸው ከጎጃም እነ አርበኛ ዘመነ ካሤ፣ የጦሩ ሊቅ እነ ሻለቃ ዝናቡ፣ እነ ኢንጂነር ማንችሎት ጎጃሜ ስለሆኑ እግራችሁን ብሉ ተብለዋል።

"…ከዚያው ከጎንደር እነ አርበኛ ባዬ፣ እነ አርበኛ ፋኖ ሳሙኤል ባለድልና ሌሎቹም ጥፉ ከዚህ ድራሻችሁ ይጥፋ ተብለዋል። የምሥራቅ ዐማራው አብሪ ኮከብ፣ የጦሩ ገበሬ የዋርካው ምሬ ወዳጆም በባልደራሱ ሊቀመንበር በጋሽ እስክንድር አያስፈልግም ተብሏል። ሸዋ የአሰግድ ጦር፣ ኢንጂነር ደሳለኝ የሚመራው ጦር፣ ከሰም፣ ቡልጋ፣ አሳግርትን የመሰሉ ግዙፍ ጦር ያላቸው በጋሽ ዶላር ዕዝ ውስጥ አልተፈለጉም።

"…የጎንደሩ እስኳድ ከጎጃም፣ ከወሎ፣ ከራሱ ወንድሞች ከጎንደሮቹ፣ ከሸዋዎቹም ውጪ በእስክንድር መሪነት አራት ኪሎ ለመግባት ከአሁን ተሿሹመው ጨርሰዋል። ያለ ጎጃም፣ ያለ ወሎ፣ በዚያው በጎንደር፣ ደግሞም በሸዋ ስምም ሳትሆን ዝም ብሎ ድል ለዲሞክራሲ ብሎ በመፎከር 4ኪሎ መግባት አለ እንዴ?

• ቢመርም ደፈር ብላችሁ ተወያዩበት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሴትይዋ ላለፉት 15 ዓመታት ባንግላዴሽን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ሸክላ አድቅቀው የገዙ ናቸው ይሏቸዋል። ኑሮ ከበደ፣ የግለሰቧ ፈላጭ ቆራጭነት ቅጥአጣ፣ የፓሪቲ ሰዎች ብቻ የሌማት ቱሩፋቱም፣ የኮሪደር ልማቱም ተጠቃሚ ሆኑ። ሌላው የባንግላዲሽ ዜጎች በጠሚዋ ፈላጭ ቆራጭነትና በፓርቲያቸው አገዛዝ ተሰላቹ። መረራቸውም።

"…ከሳምንት በፊት በቁጥ ቁጥ ባንጋሊዎች ተቃውሞ ጀመሩ። ጠሚዋም ለማስደንገጥ በሪፐብሊካን ጋርዳቸው አንድ 200 ያህል ተቃዋሚዎችን ገደሉ። ደም ሲፈስ ደም ይፈላልና ሕዝቡም በአቋሙ ጸንቶ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ወጣ። በመጨረሻም ጠቅላይዋ እያየለ የመጣውን የሕዝብ ተቃውሞ ሰግተው እግሬ አውጪኝ ብለው ወደ ዱባይ ማነው ወደ ሕንድ ፈረጠጡ። 

"…አሁን እነዚያ ተቃዋሚዎች በተራቸው  ጠቅላይዋ ይኖሩበት ወደ ነበረው ቤተ መንግሥት በኃይል ሰብረው በመግባት በጠቅላይዋ መኖሪያ ቤት እንዳሻቸው እየፈነጩበት መሆኑም ተነግሯል።  ሪፐብሊካን ጋርዱ፣ መኴው፣ የኦሮሚያ ፎሊስ ጭምር ማነው የባንግላዲሽ ፎሊስ ማለቴ ነው ይቅርታ ከዳር ቆመው ከመመልከት በቀር ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም።

"…ለአንዲት ጥጋበኛ አምባገነን ሴትዮ ምቾት ብለን ሕዝባችን ላይ ለምን እንተኩሳለን? ሀገር ቀጣይ ናት፣ ፓርቲም፣ መሪም ይሄዳል ይመጣል ያሉት ወታደሮች ለበዓሉ ድምቀት 200 ያህል ሰው ከገደሉ በኋላ ከዚህ በላይስ ይበቃናል። “ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22 እንዲል መጽሐፍ እነርሱም የ200 ባንጋሊዎች ደም በከንቱ ካፈሰሱ በኋላ ሀገሪቷ ከጋንግሪኗ መገላገሏን እና ሕዝቡም እምነቱን ጥሎብን ሕዝባዊ መንግሥት እንዲመጣ አብረን እንሥራ ብሏል።

እኔ አረፍት ላይ ነኝ። ወደ ኋላ አንድ የፋኖ ዜና እለቅባችሁና ድጋሚ ወደ እረፍቴ እመለሳለሁ። እስከዚያው…በረከተ ባንግላዲሽ ይደርብን አሜን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ችግር ከትቢያ አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይበቅልም፤” ኢዮ 5፥6

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይስጣ…! ለምን ሰጠ ? አይባልም።

"…ምክኛቱም… በኦሮሚያ እኮ ብዙ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች አሉ። ብሮጀክቲቹም ነፍ የትየለሌ ናቸው። ለትራክተር መግዣ፣ ለውኃ መሳቢያ ሞተሮች መግዣ፣ ለገዳ ሲቲ ግንባታ፣ ለጫካ ፕሮጀክት፣ ለኦቦ ሽመልስ ቤተ መንግሥት መገንቢያ ወዘተ ብዙ ዶላር ያስፈልጋል። እናም ይስጣ ምን ክፋት አለው? አቤት ምንቀኝነት?

"…የገዳና የኦሮሚያ ባንክ ለ 1 ዶላር፣ 1ሺ ብር ቢሰጡስ ምን ያስመቀኛል? አቅም ካላቸው ለምን ሁለት ሺስ አይሰጡም? ምንቀኛ ሁላ።

• በርቱ። ተወዳደሩ። ተፎካከሩ። ቆይቼ ደግሞ ናይጄሪያ ሄጄ የታዘብኩትን እጽፍላችኋለሁ።

• እየዶለደራችሁ ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተንፒሱ እስቲ…!

"…ከአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ በሚታሰብ ለሁለት ሰዓት ያህል እናንተ ደግሞ ተንፍሱ እስቲ…? ስለ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዝ ጭማሪ 300 እጥፍ አድርጌያለሁ ቀደዳም ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። 300 እጥፍ ማለት እኮ 300×1500=450,000ብር ማለት መሰለኝ። ማሞ ምህረቱ ጠበቃ ሆኖ የገንዘብ አለቃ ሲሆን፣ አቢይ አሕመድ ከ4ተኛ ኡኡ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆን እያየን በግድ ለምን Basic mathematical operation አልተማረም ማለት ያለብን አይመስለኝም አላለኝም አንዱ ጓደኛዬ።

"…ይሄ ከፋኖ ጋር ንግግር ጀምረናል ጭዌዋን ትቆየን እና ይሄ አቢይ አህመድ ጨመርኩ ያለው ደሞዝ 300 እጥፍ ነው ? ወይስ 300 % ለማለት ፈልጎ ነው? እኔም እኮ ተምታታብኝ። ሂሳብ የሚሉትን ትምህርት ከድሮ ጀምሮ ስጠላው ለጉድ ነው። 300 እጥፍ? 300%? 1500ው በ% ስንት ይመጣል ማለት ነው? እስቲ አስሉልኝ። ኤዲያ ደግሞ ስለዚህ ምን አገባኝ በናታቹ? ሥራው ያውጣው?

"…ይልቅ የለመደች ጦጣ…Convince እና Confuse ነው? ወፍ ኤለም… የሚለውን ጦማሬን እንዴት አያችሁት? ተንፒሱ እስቲ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የለመደች ጦጣ…
Convince እና Confuse ነው?
            ወፍ ኤለም…

"…ይልቅ ነፍጣችሁን አስቀምጣችሁ ከጫካም ወጥታችሁ ከአረጋ ከበደም ጋር ተነጋግራችሁ፣ ተደራደሩና በአሬ ስር ሆናችሁ ይቅርታ በአረጌ ስር ገብታችሁ ክልላችሁን በጋራ አበልጽጉ ብሎ ጽንፈኛ የተባለውን የፋኖን ኃይል እንደ ተራ ሽፍታ ቆጥሮ ባህርዳር በአባይ ድልድዩ ስር ቆሞ ከተናገረ፣ ከመከረም፣ ከደሰኮረም እኮ ገና ጥቂት ሳምንታት ናቸው ያለፉት። በጣም ጥቂት? እና ዛሬ ያውም በመንግሥት ደረጃ እየተደራደርን ነው የሚለው ማንን ለማጃጃል ነው የበሻሻው አራዳ? ሃኣ?

"…14 ሺ የፅንፈኛው ፋኖ ኃይል አባላት መንግሥት ያቀረበውን የምህረት ዐዋጅ ተቀብለው ከታች አርማጨሆ ወደ ላይ አርማጨሆ በመምጣት ለበድኑ የብአዴን መንግሥት በሰላም እጃቸውን አንከርፍፈው  ሰጥተው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ከጀመሩ ቆዩ፣ የተቀሩትም ቢሆን ሰሞኑን ለመንግሥት እጃቸውን አንከርፍፈው ለመስጠት መስቀልና ቁርዓን ጨብጠው ቃለመሀላ ገብተውልን እየጠበቅናቸው ነው በማለት አጅሬ አሚኮ (አቢይ አሕመድ ኮርፖሪሽን) በፎቶ ጭምር አስደግፎ የምልስ ፋኖዎችን ነፍ የትየለሌ ሚጢጢዬ ፎቶ ካሳየን እኮ ሳምንት አልሞላንም። ሃኣ…ኮንቪንሳም ሁላ።

"…ከአንዳንድ ኪስ ቦታዎች በቀር የክልሉን 97% ከፅንፈኛውና ከዘራፊው የፋኖ ኃይል አስለቅቀን፣ አፅድተን ከእግር ጥፍሩ ጀምሮ የተነቀለውን የክልሉን የመንግሥት አስተዳደርም መልሰን መትከል ከጀመርን ወር አለፈን ካሉን እኮ ገና መጪዋ የፊታችን ነሐሴ ልደታ አንደኛ ወራቸው ነው። ደግሞ ለጥንፈኛ የምን መደራደር ነው? ዐሞሌ ጨው ለሆነ ጅግሳ፣ ጃርት፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ፣ እርስ በእርሱ እየተናከሰ ላለ ጃዊሳ ቀበቶውን አስፈትተን ሱሪውንም እናስወልቀዋለን ካሉን ዓመት ሞላን አይደል? ወይ ኮንፊዩዝድ… የምን ድርድር ነው። ማነው የሚደራደረው?

"…አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣ ኮረኔል ታደሰ፣ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ አርበኛ መከታው ማሞ፣ በእስክንድር ነጋ የጋሪ ፈረስ ተሳፍረው በጨበራ የፌክ ምርጫ ሰበብ ከነፍሰበላው አቢይ አሕመድ ሥርዓት ጋር በአቋራጭ ተሞዳምደው፣ ተደራድረውም ገሌ ሆነው እኛን ለማምታታት ቢታትሩም እኔ ዘመዴ የቅሌታሞቹን የድምፅ ቅጂ በሃላል ይፋ አድርጌ ጉረሮአቸው ላይ በመቆሜ ሁሉ ነገር እንደ እንቧይ ካብ እንደፈረሰ ይታወሳል። የጎንደር እስኳድም የሰሊጥ ብሩን ሲልፍ ከርሞ ከተቀበረበት የመቃብር ጉድጓድ አፈሩን እያራገፈ ሳልሣዊ ብአዴንን በእስክንድር ነጋ በኩል ሊያዋልድ ሲንተፋተፍም አይተን ጉርንቦውን አንቀን የተፋትን የሴራ ቦለጢቃ መልሶ እንዲልሳት አድርገን መልሰን እንደቀበርነውም ይታወቃል። እና ከማን ጋር ነው ድርድሩ ጋሽ ኮንፊዩዝድ?

"…አሁን እኮ ነገሮች እየጠሩ ነው የመጡት። ጎጃም ውስጡን እያጸዳ ነው። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ ነው መኖር ያለበት በሚለው መርህ ምክንያት እነ አባ ዶላር ሹገር ዳዲ እስክንድር፣ እነ አውርቶ አደር ሀብታሙ አያሌው፣ ብሩክ ይባስ፣ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ቀፍለው ያታለሉት ኮረኔል ጌታሁን መኮንን ተው ቢሉት አልሰማ ብሎ ጃስ ሲሉት በርግጎ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሀብቴ ወልዴ ዕዝ ወንድም ፋኖ ደረጀ ጋር ጎንደር ሸሽቶ ተደበቋል። ከዓባይ ድልድይ እስከ ጥግ ድረስ በምድረ ጎጃም ከዐማራ ፋኖ በጎጃም በቀር ሌላ የፋኖ አደረጃጀት አይኖርም ብሎም ሻለቃ ዝናቡ መወሰኑን እኮ ትናንት ሰማነ። በቃ ጎጃም ጎጄው መለኛው አመረረ፣ አመረረ። አለቀ።

"…ወሎም እንደዚያው፣ ሸዋም አርበኛ አሰግድን እነ መከታው ማሞ አሳልፈው ከሰጡት በኋላ አመዳቸው ቡን ብሎ፣ የሕዝብ ድጋፍ ርቋቸው፣ እስክንድርን ተሸክመው እሹሩሩ እንዳሉ ብቻቸውን ከሜዳ ላይ ቀሩ። ትግሉ ቀጥሏል። ጉባኤ ተጠርቶ ቋሚ መሪ እስኪመረጥ ድረስም በአርበኛ አቶ አሰግድ መኮንን ምትክ ኢንጂነር ደሳለኝ ተተኪ መሪ ሆኖም ተመረጠ። የቀረው ጎንደር ነበር። የሜጀር ጄነራል ውባንተ ልጆች እነሱ ነበሩ የቀሩት። በውስጣቸው የነበረውን፣ ለእስክንድር ነጋ የገበረውን። ከድርጅቱ ሓሳብና ፍላጎት ከመርህ ውጪ ሲንቀሳቀሱ የቆዩትን በሙሉ ጠራርጎ አብሯቸዋል። አሁን የዐማራ ፋኖ የሚገርም ቁመና ላይ ደርሷል። ከመቃብር አፈር አራግፈው የተነሡት የስኳድ ልጆችም መብረቅ እንደመታው እንጨት ፍርክስክስ ብለዋል። እኔ የለከፍኩት መቼም አይረባም ይኸው ዛሬ እነ ዶር ምስጋናው አንዷለምንም ጎንደር ወጊጂልኝ ብላ አብርራለች። ጎንደር ጎንደር ለባንዳ ለቀሳጢ፣ ለጠንቋይ ለአስማተኛ የማይመች የክርስቲያን ምድር። ጎንደር አባጃሌው። ጠርጎ ጣላቸው። የዛሬው የጎንደር ፋኖ መግለጫም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። እንዲያውም ሙሉ መግለጫቸውም ለምን እንደሚከተለው አላቀርብላችሁም። ሰሞኑን አንድ ጆሮ አመዳም፣ ወገበ ነጭ ሲሳይ አልታሰብ የሚባል ስኳድ፣ ከወዳጄ አያሌው መንበር ጋር እየተናበቡ ሲረግጡኝ አይቼ ስስቅ ነበር። አያሌው መንበር ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል በእኔ ቅሬታ ካለው ይጽፍልኛል፣ ይደውልልኛልም እንጂ እንዲህ አፉን ሲከፍትብኝ አይቼም አላውቅ። ይሄ የክፍለ ሀገር ልጅ ቆይ እመለስለታለሁ። አሁን ወደ መግለጫው።

"…በወቅታዊ ጉዳይ "ከዐማራ ፋኖ በጎንደር" የተሰጠ መግለጫ

ቀን ሐምሌ 26/2016 ዓም

"…በወቅታዊ ጉዳይ "ከዐማራ ፋኖ በጎንደር" የተሰጠ መግለጫ የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ መራሩን፣ በሴራ ጭምር የተተበተበውን የሥርዓቱን መንግሥታዊ ጉልበት ያፍረከረከ፣ በኅልውና አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ተስፋ ያለመለመ፣ የገዳዩን ሥርዓት ቅስም የሠበረ ለታሪክ የሚቀመጥ አኩሪ ገድል ነው። በማንነቱ ምክንያት በተወለደበት፣ ባደገበትና በሚሠራበት ቀዬ በሕይወት እንዳይኖር የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት መሆኑን ተከትሎ ተፈጥሯዊ "የአልሞት ባይ ተጋዳይነት" ትንቅንቁን በይፋ ከጀመረ ዓመት ሞልቶታል። ትግሉ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ በርካታ የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶችን በጥበብ ተሻግሮ ዛሬ የሚገኝበት ግዙፍ ቁመና ላይም ደርሷል። የተበታተኑ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ፣ ከጥቂት አደረጃጀቶች አውጥቶ ትግሉ ሕዝባዊና ተቋማዊ መሠረት እንዲኖረውና፣ ወታደራዊ ተቋማትም እንዲፈጠሩ የማድረግ ተግባርም የአጭር ጊዜ ስኬቱ ናቸው።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር" የዐማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ሂደት ካስገኛቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ተቋማችን በተለያዩ ቀጠናዎች ከሚገኙ ሐቀኛ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት ኅልውናን እንዲሁም ነጻነትና እኩልነትን የማረጋገጥ ሥራን በማከናወን ላይም
ይገኛል። መላው ሕዝባችን፣ መሬት ላይ የሚገኘው የትግል ጓድ እንደሚገነዘበው ትግሉ ጥቂት የማይባሉ ጓዶቻችንን በአርበኝነት የገበርንበት፣ ንጹሐን ወገኖቻችን በጅምላ የተጨፈጨፉበት፣ ሀብት ንብረት፣ መሠረተ ልማቶች የወደሙበት፣ በርካቶች የተፈናቀሉበት ቢሆንም ዘለቄታዊ ኅልውናችንን ለማረጋገጥ የሚከፈል መስዋዕትነት መሆኑን ይገነዘባል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው የዐማራ ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋርዮሻዊ የአንድ አታጋይ ተቋም የማዋለድ ሂደት ውስጥ የተፈጠረውን መደናገር ተከትሎ ከውስጥና ከውጭ ያሉ እንቅፋቶች የትግላችን መጽኛና ማጥሪያ በረከቶች እንጅ መርገሞች እንዳልሆኑ ተቋማችን በጽኑ ያምናል። ምንም እንኳ በሴራ ፖለቲካ እንደተካነ የሚነገርለት ሥርዓቱ አሉኝ የሚላቸውን የሤራ ጠበብቶች ተጠቅሞ ከመጨረሻው የውድቀቱ ደዌ ለማገገም ውዥንብሮችን እየፈጠረ ቢገኝም ሐሰቱና ሃሳውያኑ ጭምብላቸው እየተገፈፈ በባንዳነት ግብራቸው ሲገለጡ፣ በሐቅና በቅንነት የሚታገሉ👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።” አብድ 1፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …በራስህ እጅ ነው። እንደ ኬንያውያን ለመሆን ድጋሚ መፈጠርን ይጠይቃል። እንደዚያ ሁኑም ብዬ እኔም አልመክርም።

"…በነገራችን ላይ አለ አንድ ወዳጄ። በነገራችን ላይ ዘመዴ… አብይ አሕመድ ዐማራውን ማሸነፍ እንጂ መደራደር አይፈልግም። ምክንያቱም የዐማራ ጥያቄ በድርድር የሚፈታ ሳይሆን በብልፅግና መቃብር ላይ ብቻ የሚመለስ መሆኑን ስለሚያውቁ ነው። ህወሓትን ሳያጠፋ የተዋት ለዐማራ የጊዜ ፈንጅ (time bombing ) ብሎ ነበር። ህወሓት ከጠፋች ትግራይ እና ዐማራ ይታረቃሉ ብሎም ይሰጋል። ስለዚህ በተበደረው ሀገሪቱንም በሸጠበት ቢሊዮን ዶላሮች መሳሪያ እየገዛም መሆኑን እናውቃለን። በብሩ መሣሪያ ሲሸጡለት እዳው ለእኛው ይተርፋል እንጂ ገንዘቡ እንደሁ ተመልሶ እነሱው እጅ ነው የሚገባው። ቤተ መንግሥቱን ቢገነባበት የግንባታ ባለሙያው እና የግንባታው ጥሬ ዕቃም የሚሸመተው ከእነሱ ከራሳቸው ነው። ስለዚህ ገንዘቡ ዞሮ ዞሮ ከእነርሱ እጅ አይወጣም። ፍዳው ግን ለህዝቡ ሁሉ ነው የሚተርፈው። ነጮቹም በአፋቸው ድርድር ይበሉ እንጂ በልባቸው ማንበርከክን ተማምነው ነው መገደያችንን እንዲሸምትበት በገፍ ዶላሩን የሚያፈሱለት። ይሄን ሰይጣናዊ፣ አጋንንታዊ ሴራ ማክሸፍ የሚችለው የዐማራ ፋኖ ትግል ብቻ ነው። ስለዚህ የእኔ ምክር ዛሬም እንደትናንቱ ዐማራዬ ወጥር። መክት አንክት ማለት ብቻ ነው።

"…ረብሻ ከተፈጠረ ብለው በአቋራጭ የዐማራ ፋኖን ትግል ጠልፈው መንግሥት ለመሆን የተዘጋጁና በሀገረ አማሪካ ተሰባስበው የተከማቹ የቀድሞ አሮጌ ብአዴኖች፣ የወያኔ መስራቾች፣ የተቃዋሚ ባርቲ ሰዎችም የሚበላው ሳይኖር ለመብላት እጃቸውን ታጥበው በመጠባበቅም ላይ ናቸው። በእስክንድር ነጋ አድራሽ ፈረስነት ተንጠላጥለው በአቋራጭ አራት ኪሎ ለመግባት ያሰፈሰፉት ብቻ ናቸው ወገብ ዛላቸውን የተመቱት እንጂ በዚያኛው ወገን አሰፍስፈው የተቀመጡት የአማሪካንን ይሁንታም ፈቃድም አግኝተው ለሃጫቸውን በመጎምጀት እያንጠባጠቡ ሀገር ድብልቅልቁ እስኪወጣ የሚጠብቁም አሉ። የፈለገ ይሁን የፈለገ ግን መጪው ጊዜ ከዐማራ ፋኖ ውጪ ወደ ውጪ። አለቀ። በዚህ ቅር የሚልህ ካለ ጧ በል።

"…በሉ ለእረፍት ወደ ማደሪያ ስፍራዬ በባቡር እየሄድኩ ነው ይሄን በመሃል ጻፍኩላችሁ። ከእረፍት መልስ በሰፊው እስክንገናኝ ሰላም ቆዩኝ። 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከዚያ…

"…በታች በመስቀል አደባባይ በኩል፣ ከፒያሳ፣ ከሜክሲኮ፣ ከሽሮሜዳና ከመገናኛ አካባቢ በሚመስል መንገድ ወደ ቤተመንግሥቱ የተመሙት የባንግላዲሽ ዜጎች ቤተ መንግሥቱ ጋር ሲደርሱ በአጥሩ ላይ እየተንጠላጠሉ ውስጥ ድረስ ገቡ።

"…ጠቅላይ ሚንስትሯም የሕዝቡን ቢገደልም ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ ብሎ ግግም ማለቱን ባየች ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የቀረበላትን ምግብ ሳትቀምስ፣ ውኃ እንኳ ሳትጠጣ ብድግ ብላ ነው ወደ ዱባይ ማነው ወደ ሕንድ የተሰደደችው። 😂

"…ሕዝቡ ቤተ መንግሥት ሲገባ ባየው ነገር ተደመመ፣ እነ ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ፣ እነ ዳኒ ክብረት፣ እነ ጫልቱ ሳኒ፣ እነ ጌቾ ረዳ፣ እነ ግርማ ብሩ፣ እነ በለጠ ሞላ፣ እነ ብራኑ ነጋን የመሰሉ ባለ ሥልጣናት ሁለዜ በነፃ የሚቀለቡትንና ቦርጭ ያወጡበትን የቤተ መንግሥት ምግብ ተደርድሮ አገኙት። አገኙትናም ገሚሱ በቁሙ፣ ገሚሶቹ ተቀምጠው ይመገቡት ጀመር። አንዳዶቹም በጠቅላይ ሚንስትሯ አልጋ ላይ ጋደም ሁላ ብለዋል።

"…ወዳጄ ይሄን የሚያደርገው በጣም የራበው፣ የጨነቀው፣ ኑሮ የከበደው ሕዝብ ነው። በሴፍቲኔት መኖርን ጌጥ ያደረገ፣ ቀበሌ ሄዶ 2ኪሎ ዱቄትና 30 ብር አበል ስለተቀበለ ለአገዘዙ አቃጣሪ የሚሆን ዜጋ በፍጹም ሊደፍረው አይችልም። ሾካካ፣ አቃጣሪ፣ አስመሳይ፣ ፈሪ፣ ሽንታም ይሄን ሊያደርግ አይችልም።

"…በአገዛዙ የተዘረፈን የነጋዴ ንብረት በርካሽ መብላት የለመደ ሕዝብ ይሄን ሊያደርግ አይችልም። የአምባገነኖችን ቀንበር የሚሰብረው የተራበ፣ ፍትሕ የተጓደለበት፣ ኑሮ፣ በደል የከበደው፣ ጭቆና ያንገሸገሸው ሕዝብ ነው። ለአስመሳይ፣ አቃጣሪ፣ አስጠቋሪ፣ አውርቶ አደር፣ በወንድሙ ሞት እሱ ኗሪ ሕዝብ አይሞክረውም።

"…የዝናሽን ዳቦ ካገኘህ ምን ትፈልጋለህ? እኔ የጻፍኩት ስለ ባንግላዴሽ ሕዝብ ነው። ስለ አንተ አልተነፈስኩም። ሚልኢላልኢሄ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በባንግላዴሽ እንዲህ ነው የሆነው አሉኝ…

በመጀመሪያ…

"…በአገዛዙ ሹመኞች ያለቅጥ በሙስና መዘፈቅ፣ በአምባገነንነታቸው፣ ጨፍላቂና ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ ዜጎች በሕይወት ለመኖር በጣም ከበዳቸው አሉ። በየቤታቸው መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ የሚባሉት እንደ ሩዝ፣ ዘይት፣ ስኳር የመሳሰሉት ተወደው ከገበታቸው ላይ ጠፉባቸው አሉ። የቤት ኪራይ ጨመረ፣ የትራንስፖርት፣ የህክምና፣ የትምህርት ቤት ዋጋ ሰማይ ነካባቸው አሉ። እናም ወላጆች ልጄን ምን ላብላው? ምንስ ላጠጣው? እያሉ በየቤታቸው በጭንቀት በሽታ ላይ መውደቅ ጀመሩ አሉ። (እንደ ዳባት ጎንደር ራሳቸውን አንቀው የገደሉ፣ መርዝ ጠጥተው የሞቱ ስለመኖራቸው ግን አልሰማሁም።) ብቻ የወላጆቻቸውን ሰቆቃ ልጆቻቸው አዩ። ተመለከቱም አሉ።

"…ሰላማዊ ሰልፍ፣ መንግሥትን መቃወም በሚያስገድልበት ሀገር "የራባቸው ጥቂት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለምን ይሄን አምባገነን ገዳይ ዘራፊ መንግሥት በልተን አንገረስሰውም፣ እንብላውና እንቀደስ በማለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንቅስቃሴ ጀመሩ አሉ። ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው ነውና ከነተረቱ ሆድ የባሰው፣ የራበው፣ የጠማው፣ የጨነቀው ሁላ የወጣቶቹን ጥሪ ተቀብሎ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ወጣ። በቃ ወጣ።

"…ከዚያ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ሰዓሊ ለነ ቅድስት

"…ሰዓሊ ለነ ቅድስትን ቅዱስ ኤፍሬም አልተናገረውም። ይኸውም ሊታወቅ በሀገራቸው ከመጽሐፍ ቢፈልጉ በቃል ቢጠይቁ አይገኝም፡፡ ቅዱስ ያሬድ የዜማ መክፈያ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ እርሱም ከአፍኣ አምጥቶ ከልቡ አንቅቶ የተናገረው አይደለም። ከዚያው ከውስጥ ሰአሊ ካለው ሰአሊን ቅድስት ካለው ደግሞ ቅድስትን አምጥቶ ተናግሮታል፡፡ አንድም የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል።

"…ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በግብርናተ ዲያብሎስ ተይዞ የነበረ አዳምን ነጻ ያወጣው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ለብዎውን ሰላሙን ፍቅሩን በልቡናችን በአእምሯችን ሳይብን አሳድሪብን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እናንተስ አልታዘባችሁምን…?

"…ዐማራው በራሱ የቤት ሥራ መጠመዱን ያየሁት ዘንድሮ ነው። ከምር ከጉብኝት መልስ እንዲህ አረፍ ስል የዐማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬና የብልጽግና ፔጆችን ዞር ዞር ብዬ በወፍበረር ለማየት እሞክራለሁ።

"…ድሮ ድሮ የዐማራ አክቲቪስቶች መንደር ብዙ ዝብርቅርቅ ያለ ጫጫታ ነበር የምመለከተው። በተለይ እንደ ኦሎምፒክ አትነቱ ዓለምአቀፍ የስፖርት ውድድር ሲመጣ ዓይኑም፣ ጆሮውም እዚያው ተክሎ ፍጥጥ ብሎ ነበር የሚከርመው።

"…ዘንድሮ ግን አባቴ ወፍ የለም። ወርቅ ቀረ ብር ቀረ፣ ነሃስ የለ ሰርተፊኬት ትንፍሽ የሚል የለም። አስተያየት ሓሳብ አይሰጥ፣ አይተች፣ አይሞቀው አይበርደው። ዝም። ጭጭ።

"…እናቴ ዐማራው መነሻዬም መድረሻዬም ዐማራ ነው ብሎ ሥራ ላይ ነው። ትግል የጀመረበትን 1ኛ ዓመት ድምቅምቅ አድርጎ እያከበረ ፌስቡኩን በትግሉ ፎቶና ቪዲዮ ጥልቅልቅ አድርገው ነው የሰነበቱት። ቪቫ ዐማራ

"…የኮሪደር ልማቱ ጀልባ ሲያስፈልገው እያየ ዐማራ አይናገር፣ አይጋገር። መምህራን ደሞዝ አጡ፣ ጤፍ 20 ሺ ገባ፣ ሕወሓትና ሕወሓት ተጣሉ፣ አቶ ገዱ ይቅርታ ጠየቀ፣ ሀብታሙ እና እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጎጃም ይግባ ብለው እየዬ አሉ፣ ዶላር ጨመረ፣ ቀነሰ ዐማራው እሱ እቴ ዝም ጭጭ።

"…የዐማራ አክቲቪስቶች ገፅ ስገባ የማየው መረጃ ሲሰጡ፣ ፋኖ ሲያበረታቱ፣ ሲመክሩ፣ ሲመካከሩ ነው። ዐማራው ሌላ ደረጃ ላይ ደርሷል አባቴ ሌባውን ከደኅናው፣ አጭቤውን ከሰገጤው እየለየ ነው። ይሄ መታደል ነው። የኦሮሞ ፔጆች ለሲፈን ሲያሽቃብጡ ያውም በአማርኛ እኔ በሳቅ።

"…እናም እኔ ዘመዴ ከመደነቄ የተኗ የሮማ ጥልያን የእረፍት ቀኔ ውብ ሆኖልኛል። አሁን ዐማራን አጀንዳ ሰጥቼ አንጫጫዋለሁ አይሠራም። በዚሁ ከቀጠሉ እኔም ባለቤቶቹን ለማንቃት ብዬ እንደ እብድ ውሻ መጮሄን እቀንሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአሕፋድ ድፍረት

አፋሕድ፦ ሃሎ ብፁዕ አባታችን እንደምን አሉ? ቡራኬዎት ይድረሰን። ከኢትዮጵያ ነው የምንደውለው።

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ማን ልበል?

አሕፋድ፦ እኔ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፋኖ ሻለቃ መከታው፣ እስክንድር እና ወልደ ገብርኤል ነን።

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ እሸ ምን ልታዘዝ? በደህናችሁ ነው?

አሕፋድ፦ በደህና ነው ብፁዕ አባታችን። ያው በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የዐማራ ፋኖ አንድነት ዛሬ በዲሞክራሲያዊ መንገድ፣ በድምፅ ብልጫ አሳክተናል፣ አንድ መሪም መርጠናል። እናም ይሄን የምሥራች ነግረንዎ ጸሎተ ቡራኬ እንዲሰጡንና እኛም ቡራኬዎን ለመቀበል ነው የደወልነው።

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ መልካም ከጎጃምም፣ ከጎንደርም፣ ከወሎና ከሸዋ ከሁሉ ተስማምታችሁ ነው አንድ የሆናችሁ?

አፋሕድ፦ አዎ ብፁዕ አባታችን። ጋዜጠኛ እስክንድርን በድምጽ ብልጫ መሪ አድርገን መርጠነዋል። አሁን የእርሶ ቡራኬ ብቻ ነው የምንፈልገው።

"…መሸ ነጋ፣ ሁለተኛም ቀን ሆነ። እኔ ዘመዴ ምርጫ እንዳልተደረገ፣ ስብሰባው ዕጩ ሆነው በቀረቡት በአርበኛ ዘመነ ካሤና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ለእጩነት ለመቅረብ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላሉ ወይስ አያሟሉም በሚለው ላይ እየተነጋገሩ እንደነበር እና ይሄንኑ ሳይግባቡ አምስቱ ረግጠው ወጥተው አራቱ እንደቀሩ፣ እነዚህ የቀሩቱ በድብቅ በውሸት መሪ እንደመረጡ የስብሰባውን የድምፅ ቅጂ በመረጃ ቴሌቭዥን ለቅቄው በእነ አፍራሳ የልጅ ልጅ ሴራ ላይ ቀዝቃዛ በረዶ ቸለስኩበት። ብፁዕ አባታችንም ዝግጅቱን አይተው ደወሉልኝ። ጉድ ጉድ ተባብለንም ተለያየን። ሌባ ሁላ አለ ዘፋኙ። ድፍረታቸው ለጉድ ነው። ጭራሽ ጳጳስ ለመሸወድ መዳፈር።

• ጎዶኞቼ እኔ ሮም ጥልያን እረፍት ላይ ነኝ። አየሩ ይሞቃል። አረፍ ስል ነው ብቅ ብዬ የምጎበኛችሁ።

• አይገርሙላችሁም ግን?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ድንግል ሆይ! …ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ። ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ። መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ። ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ፡፡

"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን። እንኳን ለፆመ ማርያም (ፍልሰታ) በሰላም አደረሰን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኦቦ ቢቲኔም ሞተ አሉኝ።

"…በለንደኑ የኦሮሞ ምሁራን ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ማደሞክረስ ሳይሆን መደርመስ፣ መበታተን ነው ያለብን። ኦሮሞ ታጥቆ፣ ተዋግቶ ኢትዮጵያን መበታተን ነው ያለበት። የምትበታተን ኢትዮጵያን ስንፈጥር ብቻ ነው ኦሮሞ ሰላም የሚያገኘው፣ ኦሮሞም ነፃ የሚወጣው" ሲል የነበረው ኦቦ ቢቲኔ ኦቦ ሊበን ዋቆም ኢትዮጵያ ሳትሞት፣ ሳትበታተንም በፊት እሱ ቀድሞ ተበተነ፣ ሞተ፣ ከአፈርም በታች ተቀበረ አሉኝ።

"…እረፍት ላይ ሆኜ እኮ ነው ይሄን መርዶ የሰማሁት። የሚደንቀው ነገር ኢትዮጵያ ግን እስከአሁን አለች። ከነ ሕመሟ፣ ስቃይዋ፣ ከነ ቁስሏ አለች። እስከአሁን አልሞተችም። ወደፊትም አትሞትም። ገዳዮቿ ጆሮአቸው እየሰማ፣ አይናቸው እያየ እሷ ቆማ እነሱን እየቀበረች። ከአፈርም እየቀላቀለች፣ ወደፊት ትቀጥላለች።

"…እረፍት ላይ ብሆንም አንደዜ ልጸልይ እስቲ። አምላኬ ሆይ እባክህ ተለመነኝ፣ ደግሞ ሌላ አንድ ፀረ ኢትዮጵያ ገንድስልኝ። 🙏🙏🙏 እባክህ አምላኬ ሆይ ጸሎቴን ስማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሰኔ 15ቱ ቀውስ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ሰበብ ለረጅም ጊዜያት ወኅኒ ቤት ቆይተው የተፈቱትና መጀመሪያ ምሥራቅ ዐማራ ፋኖን ምሬ ጋር፣ ከምሬ ተለይተው ከኮ/ል ሞገስ ጋር፣ ከኮረኔሉም ተለይተው በደቡብ ወሎ ሲንቀሳቀሱ የቆዩትና ኋላላይ ከእናት ድርጅታቸው ጋር ተዋሕደው የዐማራ ፋኖ በወሎ ም/ል ወታደራዊ አዛዥ የነበሩት ኮ/ል ፈንታሁን ሙሀቤ በዛሬው ዕለት ከድርጅቱ መባረራቸው ታውቋል።

"…ነገርየው እየለየ መጥቷል። የዐማራ ፋኖ ሀገር ይበትናል ሲል የቆየውና በእነ ዶር ምስጋናው እና ሲሳይ አልታሰብ የሚታዘዘው ተገንጣዩ የጎንደር ፋኖ ቡድን ሦስተኛ አንጃ ሆኖ ተከስቷል። እስክንድር ነጋ ጋሽ መሳፍንትን አስምሎ፣ ጋሽ መሳፍንት ፋኖ ሀብቴ ወልዴን ወክሎ ከእስኬው ጋር ከተጣበቀ ወዲህ ለዚህ ታማኝነቱ እስክንድር ለ6ተኛ ጊዜ በፈጠረው ድርጅት የራሱ የእስክንድር ምክትል አድርጎ መርጦ ጮቤ አስረግጦታል።

"…ይሄ ስኳድ የተባለ የጎንደሩ ተገንጣይ ቡድን በአባ ዶላር እስክንድርን ነጋ መሪነት ከወሎ ኮ/ል ፈንታሁንን፣ ከሸዋ መከታው ማሞን በመያዝ በእነ አበባው ታደሰ ድጋፍ ሰጪነት በጎንደር በአርበኛ ባዬና በአርበኛ ሳሙኤል ባለድል ላይ፣ በወሎ በእነ የዋርካው ምሬ ላይ፣ በሸዋ በእነ ኢንጂነር ደሳለኝም ላይ ጦርነት ይከፍታል ተብሎም ይጠበቃል።

"…ስኳድ ተብዬው ጎንደር አሰዳቢ ቡድን በእነ ዶር አምባቸው ግድያ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበር ተብሎ የነበረውን ኮ/ል ፈንታሁንን አቅፎ ተጠርጣሪ ነው በተባለው አርበኛ ዘመነ ካሤ ላይ ልቅ ዘመቻ መክፈቱም አስገምቶታል። ስኳድ በዘመነ ስም ዘመቻ የከፈተው ጎጃምና የጎጃም ሕዝብ ላይ ሲሆን መከታውንና ኮረኔሉን ይዞም ጎጃምን ጦርነት ለመግጠም ሳያስብ ሁላ አይቀርም እየተባለም ነው።

• አታስመስሉ። አትፍሩም ደፈር ብላችሁ ተነጋገሩ። ስኳድንና እስክንድርን በግላጭ ሞግቱና ተፈወሱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤…” ዕብ 13፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የአቢይ አሕመዱ ብልፅግና የዛሬ ወር አካባቢ ፒፕሉን ሰብስቦ "ለምዕራባውያን ኃይሎች በእጅ አዙር ቅኝ አንገዛም" እያለ ሲፎገላ ናይጄሪያ ግን ለምዕራባውያኑ በሯን ከፍታ ምክረ ሓሳባቸውንም ተቀብላ ልክ አሁን አቡቹ አባ መላ እንዳደረገው የአንድ ዶላር ዋጋን በገበያው እንዲተመን ውሳኔ አሳልፋ የሀገራን መገበያያ የሆነውን ኒያራ የመግዛት አቅም ቀድሞ ከነበረበት ከእጥፍ በላይ አንኮታኩታ አንዱን ዶላር በ1,595 ኒያራ መመንዘር ጀመረች።

"…ያኔ ታዲያ የእኛው አቢቹ አባ መላ ለቀድሞ አሮጌ ሽማግሌ የናይጄሪያ ተጫዋቾች 90 ሚልዮን ነው 70 ሚልዮን ብር መድቦ አዲስ አበባ ድረስ አምጥቶ ከእነርሱ ጋር በሸነና ሲል ነበር። ሳይውል ሳያድር እነ ካኑ፣ እነ ኦሞካቺ በተመለሱ በወራቸው እኛም lIMF እጃችንን ሰጠን። ከኤርሚያስ አመልጋ በቀር ሌሎች ኢኮኖሚስቶች ስጋታቸውን ሲገልፁ ሳይ ጨነቀኝ እንጂ እኔ እንኳ አለ ሙያዬ፣ አለ ዕውቀቴ ሓሳብ የምሰጥበት ነገር አይደለም።

"…ናይጄሪያውያን ይኸው ዛሬ ባዶ መሶብና ድስት ሳይቀር ተሸክመው አደባባይ ወጥተው በመቃወም ላይ ናቸው። ነዳጅ ያላት ሀብታሟ ናይጄሪያ ያልቻለችውን የኢኮኖሚ ቀውስ እኛ ለምኖ አዳሪ የእኔቢጤዎቹ እንዴት እንሆን ይሆን? ሱቅ በማሸግ እየመጣ ያለውን ሱናሚ የሚያቆመው አይመስለኝም። የደከረተ ሰው ቲቪ ሶፋውን አውጥቶ እንደሚሸጥ አቢቹ አባ መላም የቤት ዕቃችንን እነ ቴሌን፣ የስኳር ፋብሪካዎች፣ አየር መንገዱንም ይሸጣል። ቀዳዳውን መሸፈን ግን ይቻል አይመስለኝም።

"…ይልቅ ድሉ እንዳለ ሆኖ በጎንደር ፋኖ እንደ አሜባ 3 ቦታ ተበጣጥሷል። እነ ምስጋናው አንዱዓለምም አዲስ ጎጃም ጠል ፋኖ አቋቁመዋል። ጋሽ መሳፍንትና መከታውም በእስክንድር ነጋ አዲሱ ባርቲ ሹመት አግኝተዋል። 😂። በሉ ተናግራችሁ አታናግሩኝ ወደ እረፍቴ ልመለስበት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!” መክ 10፥16

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …አርበኞችም ሕዝባቸውንና ትግላቸውን ለዳግም ባርነት አሳልፎ ላለመስጠት በጥብዓትና በጽናት ለሕዝባቸው ቆመዋል።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር" እንደ ተቋም አንድ አማራዊ ድርጅት እንዲፈጠር ሂደቱ ላይ የነበረና በሂደቱ ውስጥ የነበሩ የአካሄድና የመርህ ጥሰቶችንም ጭምር እንዲስተካከሉ በመጠየቅ ግንባር ቀደሙ ከመሆን አልፎ ዛሬ ላይ የመጣው ውጤትም እንደሚመጣ የተነበዬ ተቋም ነው። ከምንም በላይ ለሥራ አሥፈጻሚው በሂደቶቹ ዙሪያ ግንዛቤዎችን እየፈጠረ፣ በሐቀኛ ዓላማ፣ መርኅና መታገያ ጉዳይ ተቃኝቶ
ለወንድማዊና ጓዳዊ አንድነት በርትቶ የሚሠራ፣ ሕዝባችን ለገጠመው የኅልውና ጥያቄ ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚሰጥ፣ በሕዝቡም በታጋዩም
ዘንድ ቅቡልነት ያለውን ተቋምና ሐቀኛ መሪዎችን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም ወገን በስክነት ለውይይትና ለአንድነት እንዲተጋ ተቋማዊ ጥሪ ማቅረቡም ይታወቃል።

"…ይህንን ተከትሎ የተለያየ የግልና ድብቅ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ከተቋማዊ አሠራርና መርኅ ባፈነገጠ መልኩ የተቋማችንን ኅልውና ለመናድ የሚከተሉትን መርሕ አልባና ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

1ኛ፦ ተቋማዊነትን ያልጠበቀና ከተቋም አቋም በተቃረነ መንገድ መግለጫ በተለያዩ ሚዲያዎችና የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በመስጠት የትግል መስተጋብርን ማበላሸት፤

2ኛ፦ ተቋማችን ከሦስተኛ ወገን ጋር የሚደርጋቸውን ግንኙነቶች መርኅና ተቋማዊ አሠራርን መሠረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት ተቋማችን ከሰየመው ግብረ ኃይል ውጭ ሌላ ግብረ ኃይል በሕገወጥ መንገድ በማዋቀር ከሦስተኛ ወገን ጋር ተቋምን ወክለው ንግግር ሲያደረጉ መገኘታቸው፤

3ኛ፦ ከላይ በተገለጡ ችግሮች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችን የተቋሙ መሪዎች ተደጋጋሚ የውይይት ጥያቄዎችን ቢያቀርቡላቸውም ከተቋማችን ጋር መቀጠል እንደማይፈልጉና ሌሎች ልዩ ልዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ትግላችንን ከመጎተት እስከ ተቋማዊ መስተጋብር ማበላሸት የዘለቀ የውስጥ ለውስጥ አካሄዶችን እየሄዱ ሠራዊቱን የሚከፋፈሉ ንግግሮችና ውይይቶችን አድርገዋል። አለፍ ሲልም በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ ተደጋጋሚ ግለሰባዊ አቋሞችን ተቋማዊ በማስመሰል የተሄዱ ሂደቶች እጅጉን አሳዝነውናል። የዐማራ ፋኖ በጎንደር ጉዳዩን ለረዥም ጊዜ በሰከነ መንገድ በውይይትና በሽምግልና ጭምር የልመና ያህል የሄዳቸው ሂደቶች ፍሬ ሳያፈሩ ቀርተው ዛሬ ላይ ለደረስንበት ተቋማዊ ውሳኔ ላይ ደርሷል። የተፈጠረው ችግር የአማራን እንዲሁም የጎንደርን ሕዝብም ሆነ በትግል ላይ የሚገኘውን አርበኛ የሚያሳዝን፣ የልዩነት አጀንዳን በማራገብ፣ አንድም በጎንደር ምድር ሌላ ሦስተኛ እዝ የማቋቋም ፍላጎትንም አንግበው መንቀሳቀሳቸው የሕዝባችንን ፍላጎትና ትግሉን ሳይሆን ግላዊ ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ መሆኑንም በግልጽ ተረድተናል። በዚህ መሠረት "ቅድሚያ ለተቋም ኅለውናና ለትግላችን" በሚል ብሂል የሚከተሉትን ግለሰቦች ከኃላፊነት እቀባ ማድረጋችንን እንገልጻለን።

1ኛ፦ኮሎኔል ታደሠ እሸቴ (ወታደራዊ አዛዥ የነበረ)
2ኛ፦ ፋኖ ጌታ አስራደ (የጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ)
3ኛ፦ ፋኖ እያሱ አባተ (ም/የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረ)
4ኛ. ዶ/ር ምስጋናው አንዱዓለም (ጊዜያዊ የውጭ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል የነበሩ) ግለሰቦችን ከአማራ ፋኖ በጎንደር ተቋም ኃላፊነት ማንሳታችንን እንገልጻለን።

"…በአጠቃላይ በ"ዐማራ ፋኖ በጎንደር" ውስጥ የምትገኙ ክ/ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሻለቃዎችና ሌሎችም አደረጃጀቶች ከላይ በከፊል ከተገለጡ እኩይ የሴራ አካሄዶች ራሳችሁንና ሠራዊታችሁን በመጠበቅ ከምንም በላይ በያላችሁበት በተቋማችሁ ጸንታችሁ በመቆም የአባቶቻችሁን፣ የተሰው የትግል ጓዶቻችሁን አደራ በመጠበቅ፣ የመለያየትና የአሉቧልታ አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ ከትግላችን ለማዘግየት የሚሠሩ
አካላትን በጽኑ እንድታወግዙ እንጠይቃለን። ከዚህ በተጨማሪም በየቀጠናው ከሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር ቀጠናዊ ትስስሮችን በማጠናከር ከተገለጠው ጠላት የብልጽግና ገዳይ ሠራዊት ጋር የሚካሄደውን እልህ አስጨራሽ ትግል አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ በታላቅ አክብሮት ተቋማዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። በመጨረሻም የሚዲያ አካላት ከላይ በስም በተገለጡት ግለሰቦች አማካይነት የሚሠራጩ መረጃዎችና መግለጫዎች የአማራ ፋኖ በጎንደር አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን።

"ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
የዐማራ ፋኖ በጎንደር
ጎንደር፣ ዐማራ፣ ኢትዮጵያ!!

"…ዘመነ ካሤን በግለሰብ ደረጃ በመጥላት ሰበብ ሙሉ ጎጃም ላይ የዘመተው የቲክቶኩ፣ የዩቲዩብ፣ የፌስቡኩም ግሪሣ የሀብታሙ አያሌው የትኋን ሠራዊትም ጥቂት ዲዲቲ ነፍተንበት በየፔጁ ተፈነጋግሎ መቅረቱንም አይተናል። ተስፋ አይቆርጤው የፌክ ኢትዮጵያኒስት ካምፑ ያረጀው የግንቦት 7 ሠራዊትም እንደ አሜባ ራሱን እየከፋፈለ እንደ ማያ ራሱን እየለዋወጠ መጥቶ፣ መጥቶ አሁን ኢትዮ 360 ን መልሶ ቢረከብም ግንቦቴዎች ግን ገና ሲናገሩ በድምጻቸው፣ ባይናገሩም በመልካቸው፣ በጠረናቸው፣ በሽታቸው ይታወቃሉና ሰሚ ያጣ ጩኸት ከመጮህ በቀር ምንም ሊያመጡ አልቻሉም። እኔ ግን ሰው በዚህ መጠን ሲሸት አይቼም፣ ሰምቼም አላውቅ።

"…አሁን መከራው በሁሉም ቤት ገብቷል። የችጋር ጅራፍ ሁሉንም መዠለጥ ጀምሯል። ገና ከአሁኑ ሁሉም እሪሪ ቁቁ ኡኡ እያለ ነው። ዐማራ በጅምላ ሲቀበር፣ ሲጨፈጨፍ፣ ሲሰደድ፣ ሲዘረፍ ቆሞ ያይ የነበረ ሁሉ የዐማራ እምባ እሳት ሆኖ እየለበለበው ነው። ድፍን ኢትዮጵያ ደም እንባ እያለቀሰ ነው። የመረጥከው፣ ሺ ዓመት ኑር፣ ግዛን ብሎ ሲለፋደድ የነበረው ሁላ አሁን አፈር ከደቼ ሊግጥ ነው። ምርቱን የሚያመርት ገበሬ ሲታረድ ዝም ያለ ሁሉ በቁሙ ቋንጣ ሆኖ ድፍት ሊል ነው። ድንጋይ ደቼ ትበላታለህ። አሁን ሁሉም ብቻውን ያወራታል። ይቅበዘበዛታል። የራበው ሕዝብ መሪዎቹን እንዴት እንደሚበላ አሁን በዓይንህ ታያታለህ።

"…ወዳጄ አሁን የታሽጓል ዜና አያድንህም። ስግብግብ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸው ተሰረዘ፣ በድብቅ የተከማቸው ንብረታቸው ተወርሶ ለሸማቾች ተከፋፈለ ብለህ ብትለፍፍ፣ ብትጮህ ሰሚ የለህም። የፓርክ መብራትና ውኃ አያደምቅህም። የኮሪደር ልማትም ምግብ አይሆንህም። ደሞዝ ጨምሬአለሁ፣ ነዳጅ ደጉሜአለሁ፣ ማዳበሪያ በነፃ አቅርቤአለሁ ብትል ወፍ የለም። ለምን ወርቅ መና አታዘንብም፣ ለምን ወርቅ አታነጥፍም፣ ከፊትህ የመጣውን መከራ ማምለጥም ማስመለጥም አትችልም። ዐማራ ብቻ ለምን ያንባ፣ ምን በወጣው ዘወትር ያልቅስ? ለቅሶ ኀዘን ለሁሉም በየቤቱ ይፍሰስ፣ ሁሉም ደም እንባ ያልቅስ። አልቅስ አልኩህ።

"…ቤተ መንግሥቴን ወደ ኮንዲሚንየም፣ ደሞዜን በነፃ አድርጌአለሁ ብትል ወፍ የለም አልኩህ። ማኔ ቴቄል ፋሬስን ታውቃለህ? በታላቁ መጽሐፍ ላይ አንብበኸዋልን? እንደዚያ ነው። "…የተጻፈውም ጽሕፈት፦ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላል። የነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው። ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው። ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። ዳን 5፥ 25-28

• እጄን ስለበላኝ ጻፍኩላችሁ እንጂ እኔማ እረፍት ላይ ነኝ።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• እንዴት ናችሁልኝሳ…?

"…ከተራራ ላይ ጉዞ፣ ከሸለቆ ለሸለቆ መንከራተት በኋላ አረፍ ስል እኔ አፍራሹ ዘመዳችሁ የሆነ ነገር ማፍረስ አማረኝ እና ብቅ አልኩላችሁ።

"…አዛኜን ሁሉም ነገር መስመር እየያዘ ነው። ዐማራን ነፍጥ ማንሣቱ እያስከበረው ነው። አጭቤው ኮንቪንስና ኮንፊዩዝድ ማድረግ ዛሬም አምሮት ቁማር ሊባለ "ከፋኖ ጋር ንግግር ጀምረናል አላለም" ኧረ ባኪ… ተባለ ኢንዴ? ስለሱም ልጽፍላችሁ ነኝ። እናንተ ግን ስጠፋ ጠፋችሁ እንዴ? አላችሁልኝ ወይ?

"…እስቲ አንድ 200 ያህል ሰው አለነ ዘመዴ ይበል። 😂😂 ከዚያ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ተናግሮ አናጋሪ ገጥሞኝ ድንገት እንዲህ በመሃል ብቅ እስካላልኩ ድረስ 1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን በሚለው የጠዋት፣ ጠዋት የእግዚአብሔር ሰላምታችን እንቆያለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አብዛኛው ሰው መብቱን መጠየቅ ፖለቲካ ነው ብሎ ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ በማለት በገዛ እጁ ፍርሃቱን በመደበቅ ዝቅተኛ፣ አነስተኛ የተባለ የራሱን መብት ከመጠየቅም ራሱን አሽሽቶ በድሀ ልጆች ሞት ከልያም ከሰማይ ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ ነፃ ይወጣ ዘንድ በጸሎት፣ በሱባኤና በዱዓ ነፃነትን የሚጠብቅ ራስ ውሸታም፣ አስመሳይ ራስ ወዳድ ስለሆነ ለነፃነቱ አያምጽም። እንደ ኬንያ ወጣቶች ለመሆን መጀመሪያ ፊደል መቁጠር፣ ቀለም ገብ መሆንን ይጠይቃል። አንድ መሆንንም ይጠይቃል። ቲክቶከራም፣ ሀሞተ ቢስ ስልብ ሆነህ ነፃነት ይናፍቅህሃል። የራሱን ቤት አፍርሶ ቆርቆሮ ለመሸጥ የሚጣደፍ፣ ከዚያ ቱቦ ውስጥ ለማደር የሚጋፋ ትውልድ ይዘህ ዐመጽ ያማይታሰብ ነው። መስሎ ማደር አራድነት ብልጥ መሆን፣ እንደ ዘመናዊነት በሚታይባት አዲስ አበባ ችግር አንቆ ወደ ሞት ሲመራው የችግሩን ምንጭ ታግሎ ማሸነፍ ሲችል ከችግሩ ሽሽት ወይ ሊቢያ በረሃ፣ የመንና ቀይ ባህር በመሸሽ፣ በፊኛ ጀልባ ላይ ውቂያኖስ ተሻግሮ ወደ አውሮጳ መሰደፍን ይመርጣል። በዚያም የዓሣ አንበሪ ቀለብ ይሆናል። ከከምባታ ተነሥቶ ሽግርን ሽሽት ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በእግሩ ኳትኖ ታንዛኒያ ጫካ ውስጥ ዘንዶ ይበላዋል እንጂ በሀገሩ ያለውን እባብ ረግጦ መብቱን ለማስከበር መድፈር አይሆንለትም። እናም አገዛዙ ሌላ ተአምር ካልተፈጠረ በቀር በአመጽ የመውረዱ ነገር አያሰጋውም።

•ነገ በፓርላማ ሌላስ ምን ዓይነት አጀንዳ ሊያመጣ ይችላል?

"…ባለፈው ከዓለም ባንክ ድርድር በፊት በፓርላማ ያጸደቀውን በጀት አሁን 1ቢልዮን ዶላር ብድር ስላገኘ ለመንግሥት ሠራተኞች እንዳያምጹ የ20 እና የ70 ብር የደሞዝ ጭማሪ በማድረግ አፋቸውን ሊያዘጋ በማቀዱ የበጀት ጭማሪ ሊከልስ እና ሊያስጨምር እንደሆነ የባሌው ተወላጅ በእናቱ ኦህዴድ፣ በአባቱ ሶማሌ የሆነው አህመድ ሺዴ ፓርላማውን ሊሰበስብ ነው የሚል መረጃም ወጥቷል። ዘንድሮ ቁርጥ ነው።

•ሌላው ቢሆን ተብሎ የሚጠበቅ አጀንዳም አለ ብለው የሚመኙ ወሬኞች አሉ።

"…የዐማራ ፋኖን በአሸባሪነት ፈረጅኩ" ብሎ ሊያውጅ ይችላል የሚሉም አሉ። በቲክቶክ፣ በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ላይ ያሰማራቸውን ግሪሳዎች በሙሉ ፈትቶ በመልቀቅ አጀንዳ ሰጠሁ ብሎ ሊደክምም ይችላል የሚሉም አሉ። ብዙ ቀዌ ስዩም ተሾመዎችም እስከ ሙላሊታቸው ድረስ በላብ ተጠምቀው አጀንዳውን ለማንጫጫት ሲራወጡም ይታዩ ይሆናል የሚሉም አሉ። ስለዚህ የፓርላማ አባላቱ ከእረፍታቸው ስፍራ ተጠርተው የመጡት ለአጀንዳ ዳይቨርቱ ድራማ ትወና አስፈልገው ሊሆንም ይችላል የሚሉ አሉ።

"…አቢይ አሕመድ ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የጠረረበትን ብር በመፈለግ ከመጓጓቱ የተነሣ ቀደም ሲል ማዘጋጀቱን ረስቶት ይሆናል እንጂ እንደልማዱ ከገንዘብ ማራከሱ ዜና ጋር ይህቺን የምክር ቤት ስብሰባ ድራማም ቀደም ብሎ ማድረግ ይችል ነበር። እሱ ድራማውን ቀድም ብሎ መሥራቱን ረስቶ "እንኳን ደስ አላችሁ" በሚል ቀሽም የኢቲቪ የምሥራች ድራማ ሊሸውደንም ፈልጎም ነበር። ነገር ግን የበሻሻው አራዳ ጭዌው ስላላዋጣውና ሕዝቡንም በሚፈለገው መልኩ ስላላረጋጋው፣ ወሬውም ከፍተኛ የሆነ መናጋት ካሁኑ እያመጣ ስለሆነ፣ ፓርላማውን በአስቸኳይ መጥራት የግድ ሆኖበታል የሚሉም መተርጉማን አሉ።

"…ይሄ ከፊታችን የመጣው ነገር ለዘገምተኛው፣ ተወዝፎ ነፃነት ጠባቂው፣ ሆዱን ብቻ አሳቢው ድቅድቅ ጨለማ ከፊቱ ሲገሽርበት፤ እንደ ዐማራ ላለው በመከራ በፍዳ ውስጥ ለከረመው ነገድ ደግሞ የሚደንቅ በረከት ይዞለት እንደሚመጣ ሊታወቅ ይገባል የሚሉም አሉ። በተለይ ደግሞ ይሄን አገዛዙ በገዛ እጁ ጎትቶ በራሱ ላይ ያመጣውን ፈተናና ችግር በሚገባ ከተጠቀመበት ለዐማራ ፋኖ አሸወይና ጌዜ ነው የሚሆንለት። አዳሜና ሄዋኔም በጣም ሆድ ስለባሰው የዐማራ ፋኖ ማድረግ የሚጠበቅበት ለዚህ ሆድ ለባሰው ፒፕል ማጭድ ማዋስ ብቻ ነው የሚሉም አሉ። አለቀ። እነ አባገዳ ሀብታሙ አያሌው እና እነ አይተ እስክንድር ነጋ ቀደም ብለው ስለተጋለጡ ስለ እነሱ ማቡካቱን ትቶ ይበልጥ በመጪው ጊዜ ላይ መሥራት አለበት የሚሉም አሉ።  አበበ በለውና ግምቦቴዎችም መክነዋል። ፋኖም ከምንግዜም በላይ ጠንክሯል። ከዕዝ፣ ከብርጌድ አልፎ ክፍለጦር ሁሉ አዘጋጅቷል። የኮማንዶ ሥልጠናው ተጠናቅቆም ምረቃ በምረቃ ሁሉ ሆኗል። እናም ይሄን የከሰረ፣ ሕዝብ እንደ መርገም ጨርቅ መንካት የቀፈፈው፣ እንደ አባቱ ገዳይም የጠላውን ነውረኛ አገዛዝ በግራ በቀኝ በመለብለብ ብቻ ግብዓተ መሬቱን ማፋጠን ይችላል ነው የሚሉት እንደ እኔ ሟርተኛ የሆኑ የአንድምታ ቦለጢቃ ሊቃውንት።

"…የዐማራ ፋኖ በነፃ ያለ ደሞዝ፣ ቆሎና ቅጠል እየበላ ነው የሚታገለው። የብራኑ ጁላ ወታደሮች ደግሞ የሚዋጉት ደሞዝ ተከፍሏቸው ነው። ቀለብና ስንቅ፣ ትጥቁም በአገዛዙ ወጪ ተሸፍኖላቸው ነው የሚዋጉት። በብድር የመጣው ዶላር ለቤተ መንግሥት ግንባታው፣ ለኮሪደር ልማቱና ለቅንጡ ፓርኮችና ሪዞርቶች ለነጮቹ ለራሳቸው መዝናኛ ለሚሆን ግንባታ ላይ የሚውል ስለሆነ በወታደሩም ቤት ችጋር መግባቱ አይቀርም። እናም ፋኖ አሁን ነው አንድነቱን አጠንክሮ ወደፊት መግፋት ያለበት። በተለይ ይሄን ክረምት ፋኖ በሚገባ ተጠናክሮ ካልተጠቀመበት እና በጋው ከመጣበት ምንም እንኳ ማሸነፉ ባይቀርም ነገር ግን በብዙ ይከብደዋል የሚሉም አሉ።

"…ፓርላማው የፈለገውን አጀንዳ ቢያመጣ ግን አዳሜና ሄዋኔ አጀንዳዬን አልቀይርም ነው ማለት ያለብህ። ጴንጤ ነህና አገዛዙ ጴንጤ ነው፣ መሪያችን የጌታ ሰው ነው ብለህ ለአቢይ አሕመድ ብትቦተልክለትም መራብህ እና በጠኔ መዳፋትህ እንደሁ አይቀርልህም። አቢይ ኦሮሞ ነው፣ አገዛዙ በዻዺና ነው እናም የኦሮሙማውን አገዛዝ ሺ ዓመት ያኑርልን ብለህ ስትፎክረለት፣ ስትጸልይለት ብትኖርም ከትናንትና ጀምሮ ከደጃፍህ የእሳት አለንጋ ይዞ የቆመው ችጋር ኦሮሞነትህ አያድንህም። እስላም ክርስቲያን ሁን፣ ትግሬ፣ ዐማራ፣ ወላይታ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ሐረሬ፣ ጉራጌ፣ ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ የፈለግከውን ሁን ጠኔው አይምርህም። አያልፍህም። ሊዠልጥህ፣ ሊያንገበግብህ ከደጃፍህ ቆሟል። እናም አጀንዳ አትቀይር።

"…ወዳጄ የአቢይን መናፈሻ አትበላው። ዳቦ የሚያበሉህ ፋብሪካዎች እኮ ተዘግተዋል። የዳቦ መግዢያ ዕውቀት የሚመግቡህ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ማእከላት እኮ ተዘግተዋል። አምስት ዓመት ኡንበርስቲ ተምረህ ስታበቃ ብራኑ ነጋ የመውጫ ፈተና ይሉት ነገር አምጥቶብህ ዲግሪህን ተከልክለህ የተማረ ነገር ግን ዲግሪ የተከለከለ መሃይም ሆነህ ሰፈር ለሰፈር የምትንከላወስ የወጣት ጦረተኛ አድርገውህ ካረፉ እኮ ቆዩ። ወደብ አገኘን እንኳን ደስ ያለህ ብሎ ያስጨፈረህ አገዛዝ እንኳን ወደብ ሊያመጣልህ እሱ ራሱ አደብ ገዝቶ፣ አንተ ላይ መደብ ሠርቶ ነው ከአናትህ ላይ ፊጢጥ ብሎ አርፎ የተቀመጠበህ። እንግዲህ መናፈሻውን አትበላው። ምን ተሻለህ? መብራት በኮሪደር ልማቱ አከባቢ እንጂ ሌላ ቦታም ሆነ በቤትህ የለ። እንደ ጎንደር የዝናብ ውኃ እየጠጣህ የብልፅግና መሪዎቻችንን "ክፉ አይንካብን" ብለህ ሰልፍ ብትወጣም ከችጋሩ አታመልጥ። ውኃም እንደዚያው ነው እንደ መብራቱ የለም። እናም የሚሻለው ሀገረ መንግሥቱን ከቸርች ተሰብስበው ከመጡ ፍንዳታ ጎረምሶች፣ ከፍንዳታም ወጠጤዎች አላቅቆ ምራቅ ለዋጡ ሰዎች ማስረከብ ብቻ ነው። አንድ ሰው ያውም የ4ተኛ ጨ ክፍል ተማሪ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የሚዘውራትን ሀገር ወደ ገደል ወደ ኢንቁፍቱ ተወርውራ ከመግባቷ በፊት መፍትሄው 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…
Subscribe to a channel