"…ይቅርታ… አውቶሚክ ቦንቡ ያልኩት የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ዘገየባችሁ አይደል? መጣም ይቅርታ እጅግ አድርጌ ስቀምመው ስለቆየሁ ነው የዘገየሁባችሁ።
"…አሁን ጨርሼዋለሁ። ያበጠውን አፈነዳዋለሁ። ኤትአባቱንስና። ዛሬ ምሽት፣ ሌሊቱንም ሁሉ ስታነቡት ታድሩና እጅግ ረጅም እና ሊማሊሞን የመሰለ ርዕሰ አንቀጽ ስለሆነ፣ ደጋግማችሁ አንብባችሁ አስተያየት የምንሰጠው ነገ ከምስጋናው በኋላ ነው። በጠዋት የምስጋናውን መልእክት እለጥፍና አንድ ሺ ሰው ካመሰገነ በኋላ በቀጥታ በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ላይ በግልጽ እንወያየለን ማለት ነው።
"…የምጽፈው በስልኬ ነው። ሙቀቱ ሙቀት አይምሰላችሁ። እስከአሁን ምግብ በአፌ አልቀመስኩም። ውኃም አልጠጣሁም። በውስጥ በግልገል ሱሪ ነው ራቁቴን ርቃኔን ተቀምጬ የምጽፍላችሁ። አይኔ እንደዛሬ ተጨነባብሶ፣ እንባ በእንባ ተጨመላልቆም አያውቅም። የፈሰሰው ላቤን ውኃ ጠጥቼ ልተካ ነኝ። እስከዚያው እናንተ ግን መኖራችሁን አረጋግጡልኝ። መጠበቅ ሰልችቷችሁ ከጠፋችሁ ብዬ ነው መጠየቄ። ለነገሩ የት አባታችሁ ትሄዳላችሁ? 😂😂 አይደለም እንዴ?
• ልለጥፍ ነኝ አላችሁ ወይ…?
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ።
"…ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም። 1ኛ ሳሙ፥ 16፥13 …ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ …ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ …የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ምክሕነ” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.51/፡፡
"…እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.67፡7/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…እኔ ቋሚ ወዳጅ፣ ቋሚ ጠላትም የለኝም። እውነትን መሸቀጥ አይሆንልኝም። በገንዘብ የምንበረከክ ሰው አይደለሁም። ገንዘብ አቋሜን፣ እምነቴንም አያስቀይረኝም። መረጃ ቲቪን በነፃ ነው የማገለግለው። በነፃ አልኩህ። ራሱን የቻለ አንድ ግዙፍ ሚዲያ ያህል በቴሌግራም፣ በሚዲያ ግዙፍ የሚዲያ ሰው ሆኜ ሳለ እንደ አርቲስት አበበ በለው፣ እንደ ሀብታሙ አያሌው በየሀገሩ ዞሬ የጎፈንድሚ አቁፋዳ ተሸክሜ ለራሴ ገንዘብ አሰባስቤ አላውቅም። በሳምንት አንድ ቀን መረጃ ቲቪ ሰዓት መድረሱን ሳሳውቅ ከምለጥፋት የፔይፓል እና የዶነር ቦክስ ሊንክ ማስታወቂያ በቀር ተንፍሼም አላውቅም። የፈረንካ ጾር የተነቀለልኝ በመሆኑ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ። እናም እኔን በገንዘብም፣ በስድብም ልታንበረክከኝ አትችልም። በቤትህ እንጂ ቤቴ መጥተህም ልትሰድበኝ አትችልም። የእኔ የኮመንት መስጫ ሰንዱቅ ሁሌ ክፍት ነው። አፉን እንደለመደው እከፍታለሁ የሚል ይጎመዳል፣ ይቀሰፋል። በጨዋ ደንብ ተቃውሞን ማሰማት እንጂ ቤቴን አሳዳጊ በበደለው የባለጌ ስድአደግ ፀያፍ ስድብ ማግማማት፣ ማከርፋትም አይቻልም። አይፈቀድምም።
"…ቃሌን እጠብቃለሁ። ዐማራ መከራውን የሚቀለብስበትን የሥልጣን ቁልፍ ከእጁ እስኪያስገባ ድረስ ትግሌን አላቋርጥም። እንደ ኮሶ የሚመር እውነት እየጋትኩ የዐማራን ብሔርተኝነት ማቀጣጠሌን አላቋርጥም። ትግሬው ትግሬ ነኝ እያለ እየፎከረ፣ ኦሮሞ ኦሮሞ ነኝ እያለ እያቅራራ፣ ዐማራ ዐማራ ነኝ ሲል አዳሜና ሔዋኔ ለምን ለመታነቅ እንደሚፈልግ ስለገባኝ፣ በደንብ እያጓራ ነስር በነስር፣ ንፍጥና ለሃጩን አዝረብርቦ እስኪጨርስ ድረስ ዐማራ ዐማራ ነኝ ብሎ በዐማራነቱ እንዲሞግት እንደ ትግሬና ኦሮሞም እንዲከበር እሠራለሁ። የፌክ ኢትዮጵያኒስቶችን፣ ዐማራ ላይ የተጣበቁ አልቅቶችን የጭንቁስል ነው የምሆንባቸው። ፀረ ዐማራ የሆነ ሁሉ ጨጓራው እንዲላጥ በታማኝነት ነው አጥብቄ የምታገለው። የማነቃው።
"…በቀጣይ ጦርነቱ ከዐማራ ክልል የሚወጣበትን መንገድ በመፈለጉ ላይ በመትጋት እዳክራለሁ። ዐማራ የውስጥ ችግሩን እንደ ጎጃም ዐማራ፣ እንደ ወሎዬዎቹ ፈትቶ፣ የሚመከረውን መክሮ፣ የሚኮረኮመውን ኮርክሞ ጉዞ ወደ አራት ኪሎ በሚያደርግበት መንገድ ላይ መምከር እንጀምራለን። ጦርነቱ ከዐማራ ክልል መውጣት አለበት። እነ ዶር ምስጋናው አንዷለም ሰምታችኋል። ጦርነቱ ከዐማራ ክልል መውጣት አለበት። ሸዋ ላይ ያለው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዳይደረግ እግር ተወርች አስሮ የያዘው የእስክንድር ነጋ እና የመከታው ማሞ ጦርም አደብ ብትገዙ ይመረጣል። ከመከላከያ ጋር መዋጋት ትተህ ከወንድሞችህ ጋር አትዋጋ። አንድ ሁኑ። ትናንት የጎንደር ስብስብ ነን ብላችሁ በዙም የተሰበሰባችሁትንም እነ ዶክተር ምስጋናውን አንዷለምን ስሰማችሁ ነበር። እንዲያውም ቀድቼአችኋለሁ። ነፃነት የተናገረውንና አንድ ሁኑ ያለውን ደግማችሁ አስቡበት። "ጎንደሬ መራጭ ለምን ይሆናል፣ ጎንደሬ ተመራጭ መሆን አለበት" ያላችሁትንም ሰምቼ ደስ ብሎኛል። ታዲያ ለመመረጥ በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንጂ በማጭበርበር፣ ድፍን ጎጃምን በመስደብ፣ በመጥላት እንዴት ይሆናል? ነውር ነው። እናም አስቡበት። እኔ የትም አለሁ። የትም ጆሮዎች፣ ወፎች አሉኝ። ከእኔ እይታ አታመልጡም። እናም ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ። ጦርነቱ ከዐማራ ክልል መውጣት አለበት። ይሄን መፈክር በቅርቡ እናጮኸዋለን። መጨቅጨቅም እንጀምራለን።
"…ከ30 ደቂቃ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አስነቀልቲው፣ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"…ከዕለታት ባንድ ቀን ዕለቱ ሰኑይ (ሰኞ)፥ ጊዜው ነግህ (ጠዋት) ነው። ቅዱስ ኤፍሬም የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል። ከዚያም ላይ ሁና "ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም" ትለዋለች፤ እሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል። "ወድሰኒ" ትለዋለች እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራዊያን። (ምድራዊያን ጻድቃን ሰማዕታት ሰማያውያን መላእክት አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት።) "በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ ተናገር አለችው።"በተረቱበት መረታት ልማድ ነውና፤ እፎ ይከውነኒ ዝንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ ብትለው መልአኩ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ብሏት ነበርና።
"…ከዚህ በኋላ ለመንፈስ ቅዱስማ ይሳነዋል ብል ክህደት ይሆንብኝ የለምን ብሎ "ባርኪኒ እግዝእትየ መዝገበ በረከት" ይላታል፤ "በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅደር በላዕሌከ ትለዋለች።" ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል። ሲያመሰግናትም ደቀ መዝሙር ቅኔ ቈጥሮ እንዲቀኝ ድርሰት አስቦ እንዲያጽፍ አይደለም። ብልህ ደቀ መዝሙር ያጠናውን ቀለም ከመምህሩ ፊት ሰተት አድርጎ እንዲደርስ እንደዚያ ነው። ስታስደርሰውም ከሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች። ስለምን ቢሉ በሰባቱ ዕለታት መመስገን ፈቃዷ ስለሆነ።
“…የእመቤታችን፣ የአማላጃችን፣ የረዳታችን፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ አይለየን። ጣዕሟን በአንደበታችን፣ ፍቅሯንም በልባችን ይሳልብን፣ ያሳድርብን። የአባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በረከቱ በሁላችንም ይደር አሜን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያንም በምልጃዋ ትጎብኝልን፥ አሜን…!!
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ሲሆን በመረጃ ቴሌቭዥን የሳታላይት ቴሌቭዥን የተለመደውን "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘውን መርሀ ግብራችንን ይዤ ከች እላለሁ።
• አላችሁ አይደል…?
"…ቆይ እኔየምለው የዛሬው ውድድር የሴቶች ማራቶን ውድድር ነው አላላችሁኝም ነበር እንዴ? …ለምንድነው ኢትዮጵያዊቷን ልጅ የሚገፈትራት…? ነውር አይደለም እንዴ?
Читать полностью…"…ለምን ዝም ይባላል…?
"…ባለፈው ኦቦ በቴ ኡርጌሳ ኦነግ ናቸው ብሎ ኦህዴድ በምታዩት መልኩ እጃቸውን እንዲህ የፊጥኝ አስሮ በግፍ ገደላቸው። ያውም በራሳቸው ሀገር በመቂ ከሆቴል አውጥቶ ነው የገደላቸው። እስከአሁን የሟቹ ገዳዮች ለፍርድ አልቀረቡም።
"…አሁን ደግሞ ከጥልያን ሮማ እረፍት ስመጣ ጃል ፊጋን ኦነግ ራሱ በምታዩት መልኩ አስሮ ቶርች ሲያደርጋቸው አይቼ ዘገነነኝ። ለምንድነው ኦሮሞ እንዲህ ኦሮሞ ላይ የሚጨክነው?
"…እናንት ኢትዮጵያኒስቶችስ ብትሆኑ ዐማራ ክልል ብቻ የሆነ ነገር ኮሽ ሲል ብቻ ነው ወይ ኡኡ የምትሉት? ኦሮሞስ እንደ ኢትዮጵያዊ አታዩትም ወይ? እንዲህ ዓይነት ግፍ ስታዩ እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ሲሳይ አጌና፣ እነ ፋሲል የእኔዓለምስ ለምን ዝም ትላላችሁ? እነ አሉላ ሰሎሞን፣ እነ ወለይ እስታሊን ገብረ ሥላሴ ለምን ጭጭ ትላላችሁ? ትግሬ እና ዐማራ ላይ ብቻ ጉዳት ሲደርስ መጮህ ትክክል አይደለም።
"…እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እነ አበበ በለው፣ ተዉ ዝም አትበሉ እንጂ፣ ጎጃም ላይ ወግደረስን ዘመነ እጁን ሰበረው ለማለት እንደ ደፈራችሁት ይሄ ዜጋ እንዲህ ሲሰቃይ መዳረሻችሁ ኢትዮጵያ የሆናችሁ ሰዎች ለምን አታወግዙም?
"…ቶማስ ጃጀው፣ ጌትነት አልማው፣ ውብሸት ታዬ፣ ስዩም ተሾመ፣ ይሄን ሰቀቀን ለምን ዝም ትሉታላችሁ? ዳንኤል ክብረትስ ብትሆን እንዴት ይሄ ጭካኔ አስችሎህ አንድ ትርክት መተረክ አቃተህ? ሀብታሙ KMN፣ ፍሮፌሰር ሕዝቅኤል፣ ፀጋዬ አራርሳ፣ ጨካኞች ናችሁ በእውነት።
• ኦነጉ ሶዬ ምን ቢያደርግ ነው ግን እንዲህ ያንጠለጠሉት። ከዚህ በኋላ አረዱት? ወይስ በጥይት ደበደቡት? ከምር እኔ ለሰውየው አመመኝ።
• ሲዘገነን በማርያም…ኡፍ ወንድሜን…😭😭😭
"…ምን ቢያደርግ ነው ግን እንዲህ ለአሩስቶ እንደተዘጋጀ በግ ያንጠለጠሉት?
• የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ አይተውት ይሆን?
• እነ ሀብታሙ አያሌው፣ ጄሪና ጌጥዬ ዓይተውት ይሆን?
• እስክስ አበበ ገላው ዓይቶት ይሆን?
• ኢትዮጵያኒስቶቹ ይሄንን ግፍ ዓይተውት ይሆን?
• የሂዊና የኦነግ አክቲቪስቶችስ አይተውት ይሆን?
• መነሻዬ ዐማራ መዳረሻዬ ኢትዮጵያ እስክንድር ነጋ አይቶት ይሆን?
• ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራስ ዓይቶት ይሆን?
"…ከምር እኔ ሰውየው አሳዝኖኛል። ምን ቢያጠፋ ነው ግን? ኦሮሞን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ለኦሮሞ ነፃነት የሚታገልን ኦሮሞ ራሱ ኦሮሞ በኦሮሞ ምድር በኦሮሞ ነፃ አውጪዎች እንዲህ እንደ አሩስቶ በግ ማንጠልጠል አይሰቀጥጥም?
• ምን አጥፍቶ ይሆን…?
"…እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም ገብተናል…🙏🙏🙏
"…እኔ ምለው አሁን እኮ ነው የማየው። ኦነጉ ጃል ፊጋ ምን አድርጎ ነው ኦነግ ራሱ እንዲህ አድርጎ የሚቀጣው…? …ሲሰቀጥጥ… የፈጣሪ ያለህ !!
• እኔ ግን የስደት ሀገሬ በሰላም ገብቻለሁ።
"…ውዳሴ ዘቀዳሚት፣ ውዳሴ በቀዳሚት፣ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ይላል አንድ ነው ቃለ ጸሐፊ ነው። እርሱ ግን (ቅዱስ ኤፍሬም) "ንጽሕት ወብርህት" ብሎ ያመጣል። ይጀምራል። ከአባቱ ጋር ካስታረቀን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን።
"…ቅድስት አለ። ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ሲል ነው። ንጽሕትም አለ። ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም። እርስዋ ግን ከነቢብ ከገቢር ከሐልዮ ንጽሕት ናትና። "ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ እንዲል። ጽንዕትም አለ። ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው። እርሱዋ ግን፥ ቅድመ ጸኒስ፣ ጊዜ ጸኒስ፣ ድህረ ጸኒስ፣ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናትና። ክብርትም አለ። ሌሎችን ሴቶች ብናከብራቸው ጻድቃንን ሰማዕታትን ወለዱ ብለን ነው። እርሱዋን ግን ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና። ልዩም አለ። እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የተገኘች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና።
• ዓይኑ "ዓ" ቢሆን አዕምሮውን ለብዎውን ሳይብን።
• አልፋው "አ" ቢሆን ለምኝልን ማለት ነው። "…ልመናስ ከዚያ በኋላ ስንኳን በሱዋ በሌሎችም የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ የምታስምረን ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ። ይህን ሲጨርስ ባርካው ተነስታ ታርጋለች እርሱም እጅ ነሥቶ ይቀራል ይቆየን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…እነ አቢይ አመድ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ብራኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አረጋ ከበደ ወዘተ ይሄንንም እያዩ አሁንም ፋኖ አሞሌ ጨው ነው፣ ከክልሉ 97% ያህል አፅድተን የቀረን በኪስ ቦታ ላይ ያሉቱ ብቻ ነው። ፅንፈኛውን፣ ጃውሳውን፣ ቀማኛ፣ ዘራፊ ወዘተ ያሉትን የዐማራ ፋኖ ኃይል አጽድተነዋል፣ ቀበቶውንም አስፈትተነዋል ወዘተ ይሉ ይሆን…?
• የዐማራ ስብእናው የሚገርመኝ የጠላቱን አስከሬን ራሱ አክብሮ መቅበሩ… 👏👏👏
"…መከላከያን የምመክረው "…አባዬ ከሕዝብ ጋር ተዋግተህ ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም።"
"…ሽርሽር ላይ ሆኜ እኮ ብዙ ወሬ አምልጦኛል። ቆይ እኔምለው ሽርሽር ጥልያን ሮማ ከመሄዴ በፊት በአዲስ አበባ በብሽክሊሊት መንገድ ላይ በእግሩ የሚሄድ ሰው ብዙ ብር ይቀጣል አልተባለም ወይ…?
Читать полностью…"…እኔና ቤተሰቦቼ በጥልያን ሮማ ስናደርግ የነበረውን ቤተሰባዊ ጉብኝት ዛሬ አጠናቅቀናል። ነገ ወደ ማታ ላይ ወደ አጎት ሀገር ጀርመን ለመመለስ እንበርራለን። መቼም እንዴት ያለ ግሩም የቆይታ ጊዜ እንደነበረን በቃላት ልገልጽላችሁ አልችልም። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…በነገራችን ላይ የዶላር የምንዛሪ ዋጋ በብር ስንት ደረሰ ይሆን? ከወሬው ዓለም ስለራቅኩ በቃ ምንም ልሰማ አልቻልኩም።
"…አንድ ዶላር በሰማንያ ሁለት የኢትዮጵያ ብር መመንዘር ጀምሯል የሚባለው እውነት ነው ወይ…? በመንግሥት ሰማንያ ሁለት ብር ከሆነ በጥቁር ገባያው ስንት ደረሰ ማለት ነው?
በሉ ደኅና እደሩልኝ…
"…በጥልያን ሀገር በሮም ከተማ በዚህ ካቴድራል ውስጥ በዚህ ጠንካራ መስታወት ውስጥ ከሚታዩት ሁለቱ አንደኛው ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል ነው አሉኝ። አጭር አራት ማዕዘኗ ደግሞ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለው የክስ ጽሑፍ የተቀረጸበት ነውም አሉኝ። እዚያው ክፍል ውስጥ ክቡር ሥጋው ተጠቅልሎ ወደ መቃብር የወረደበት ጨርቅ ነው የተባለም ዋናውን ሳይሆን ቅጂውን በመስታወት አድርገው አስጎብኝተውናል።
"…ብርክክ ብዬ ዕለተ አርብን በማሰብ በዓይነ ህሊናዬ ኢየሩሳሌም ቀራንዮ አደባባይ ሄድኩኝ። ዞር ስል ሁለት ፈረንጆችም እንደኔው ብርክክ ብለው ይጸልዩ ጀመር። ለካ የበኩር ልጄ ጎረምሳው በስልኩ የካሜራ ዓይን ቀለብ አድርጎ አስቀርቶኝ ኖሯል።
"…በሉ ነገን በጥልያን ሮማ ቀሪ ቦታዎችንና የሜዲትራንያን ባህር ዳርቻዎችን ስንጎበኝ እንውልና ቅዳሜ አመሻሹን ወደ አጎት ሀገር ጀርመን በጢያራ በርረን እንገባለን። እስከዚያው እየተወያያችሁ ቆዩኝ። በጥባጭ ካለ ግን በመሃልም ቢሆን ገባ ብዬ ጆሮውን በመመልዘግ አደብ ማስገዛቴ አይቀርም። 😂
"…በሮም ፀሐይዋ ከነ ልጅ ልጆቿ ነው የወጣች የመሰለኝ። ምግባቸውም ጣፋጭ አይገልፀውም። የቤት ጠላ ነው ብለው ለውኃ ጥም መቁረጫ ይሁንህ ብለው ያጠጡኝ ደንበጃን ሙሉ ድራፍት ያሉት ጠላ መሳይ ነገርም በዓይነ ኅሊና አሸተን ማርያምን እና ዙር አምባ አቡነ አረጋዊን ነው የወሰደኝ። የቤት ጠላ የመሰለው ድራፍት ያሉኝ ነገር እዚህ ጀርመንስ ዞር ዞር ብልም የማጣው አይመስለኝም። እስቲ ጾሙ ይፈታና እማማ ብሪጅ እስቶንን ጠይቄ እሞክራለሁ። ሞጥዬ ብሊስ ብሪጅ ጠላ ቤቱን በመጠቆም እንድትተባበረኝ እርዳኝ። አደራ።
"…የሰማነውንና ያነበብነውን በልቦናችን ያሳድርልን፣ የተሰወረውን ምስጢር ይግለጥልን፣ የተኙትን ያንቃልን፣ ደኅና እደሩልኝ።
"…ሀብታሙ አያሌውና ተሾመ አፍራሳ እና እስክንድር ነጋ የብአዴን ገዳይ አስገዳዮች ለምን በእንብርክክ ተቀጡ? ስለዚህ አሜሪካ አጣሪ ኃይል ወደ ክልሉ ታስገባ፣ ጎጃሜዎች በአስቸኳይ ብአዴንን ከማሳደድ ይቆጠቡ፣ እምቢና አላርፍ ካሉ "…ከጎንደር ጋሽ አባባ መሳፍንትን፣ ሀብቴንና የምወደውን ደሬን፣ ከጎጃም ማስረሻ ሰጤን፣ ከደቡብ ጎንደር ፍሮፌሰርን ጌታአስራደን እና ኮረኔልን ታደሰን፣ ከወሎ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባን እና ፋኖ መከታው ማሞን ይዤ ነው የምዝምትበት፣ በብሮባጋንዳው አበበ በለው፣ ሀፍታሙ አያሎ፣ ብሩኬ፣ ጄሪ አሉልኝ፣ የሚል ድምጸት ያለው መግለጫ ሲሰጥ አሁን ሰምቼ የሆነ ነገር መጣብኝ እና እሱን ነገር ላሳያችሁ ወይስ ይቅር እያልኩ ነበር።
"…የእኔ ነገር ደግሞ ዶፍቶር ምስጋናው አንዱአለም፣ አመዶ ሲሳይ አልታሰብ፣ ማናት ጩጬዋ አያሌው መንበር ደግሞ ቅር እንዳይሰኙብኝ ብዬም ፈራሁ። እኔ ስፈራ መቼም እኮ ጤናም የለኝ።
"…እድሜ ለእኔ ለእኔ ለዘመዴ ይስጥልኝ እንጂ 😂 ሁሉም ዐማራ በጊዜ ነቃ እንጂ እነ አበበ በለው፣ እነ ሀፍታሙ አያሌው፣ እስኬ ብረቷም እኮ በአቅማቸው ፋኖን ሊከፋፍሉት ፍርግጥግጥ እኮ ነበር ያሉት። ከእንግዲህ ሀብታሙ ጮኸ፣ እስክንድር እሪሪ አለ፣ አባቴ ወፍ የለም። ወፍ የለም ስልህ።
"…ለማንኛውም ሁሉንም ነገር ለኦሮሙማውና ለትግርሙማው የሚያመቻቸው እስኬ ብረቷ፣ እስኬ ፌሮዋ በኦሮሙማው ላይ መጨከን ትታ ዘመነ ካሤ ንግሥናዬን አኮላሸብኝ በሚል ምክንያት እንዲህ ጎጃምን መጥመዱ ደስ ባይለኝም ፋኖን በዚህ መጠን ለመክሰስ መጋጋጥ የፈለገበትን ምክንያት የሆነች ቪድዮ ብለቅባችሁስ? 😂
"…አደራ የቦለጢቃው ቅማኔቴዎች፣ አገው ሸንጎ፣ ወነግ፣ ወዩ፣ ብልፄ እንዳትንጫጩብኝ። እኔ እናንተ እስክንደርን በተቸሁት ቁጥር ስትቆጡኝ እየተሳቀቅኩ ተሸግሬአለሁ።
• ልጠይቅ አይደል?
"…መልካም
"…እንደተለመደው ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው አንድ ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋናው ቀጥሎም እንደተለመደው በቀጥታ የምንሄደው ወደ ተናፋቂው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ርዕሰ አንቀጻችን ሥራዋን ዛሬ በይፋ ትጀምራለች።
"…የዛሬዋ ርዕሰ አንቀጻችን አደገኛ የሆነ አቶሚክ ቦንብ የሆነ አጀንዳ በማፈንዳት ነው የምትጀምረው። የዛሬዋ ርዕሰ አንቀጻችን ወደ ድል ማማ እያመራ ያለውን የዐማራ ፋኖ ትግል በአንገቱ ሸምቀቆ ከትቶ አላላውስ ያለውን ሾተላይ አካል ነጥሎ በመደብደብ ልፋለመው ቆርጬ የተነሣሁ መሆኔን የማውጅበት ርዕሰ አንቀጽ ነው።
"…ይሄ አዲስ ምዕራፍ ትግሌ ነው። እንደ ሁልጊዜው ዛሬም ከዚህ ርዕሰ አንቀጽ ንባብ በኋላ የማኅበራዊ ሚዲያው አዋራ ይጤሳል፣ ዛሩ ይንቀጠቀጣል፣ ከዚያ በቲክቶክ ፎቶዬ ተዘቅዝቆ፣ በፌስቡክ የስድብ መዓት ይዥጎደጎድብኛል፣ ከዚያ ቆይቶ በላብ መልክ ይወጣላቸዋል። እኔም እንደተለመደው አምላኬን ይዤ አሸናፊነቴን አረጋግጣለሁ። ይኸው ነው።
• ማሳሰቢያ… ማስታወሻ…ማስጠንቀቂያ
"…እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል 19 ዓመት አልፎኝ 50 ዓመት የሞላኝ ጎልማሳ ስለሆንኩ አንድም ሰው ለእኔ አግዞ እንዲከራከር፣ እንዲሟገት አልፈቅድለትም። አንድም ሰው አልኳችሁ። አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው መራታው ቆቱ የሀረርጌ ልጅ፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ምርጥዬ ልጅ ብቻዬን ድንግልን ይዤ እፋለማቸዋለሁ። አለቀ።
"…ርዕሰ አንቀጻችንም ደረጃው ከፍ ብሏል። እናስ ይሄን የመጀመሪያ ኮሶ የሆነ፣ መተሬ፣ መቅመቆ፣ ሰናፍጭ የበዛበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?
• ዘመዴ ሆዬ ወዬ… ዝግጁ ነነ በሉኝ እስቲ…
"…ተወዳጁና ተናፋቂው፣ እንደ ኮሶ ምርር ብሎ ገብቶ የሚያሽረው፣ እንደ መተሬ፣ መቅመቆ ያለው፣ ሰናፍጭ የበዛበት፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነው አስነፋጭ፣ አስነቃይ፣ ፍቱን የልብ አድርሴው፣ አንጀት አርሴው ተወዳጁ ርዕሰ አንቀጻችን ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተም እንደተለመደው አስደማሚ ሓሳባችሁን በጨዋ ደንብ ማስኮምኮም እንደምትሳተፉ በተስፋ እጠብቃለሁ። ተዘጋጁ።
"…ነገ ከውዳሴ ማርያም ትርጉም ሰላምታችን በኋላ አመስጋኙ አንድ ሺ ሰው ካመሰገነ በኋላ በሰፊው እንገናኛለን። እስከዚያው ደኅና እደሩልኝ።
ወቅታዊው የእኔ ድርጅቱ ዘመዴ
የአቋም መግለጫ
"…አሁን አሁን ሸክም እየቀለልኝ እየመጣ ስለሆነ ሳምንቱን ሙሉ እንደ አበደም፣ የሌባ ኮቴም እንደሰማ ምርጥ ታማኝ ውሻ 24/7 ኡኡኡ የምልበት ምክንያት እየቀነሰ እየመጣ ስለሆነ እንደበፊቱ አልካለብም። አሁን አሁን በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ያሉት፣ የነበሩትም የጉዳዩ ባለቤቶችም ከጥልቁ እንቅልፋቸው እየደበራቸውም ቢሆን፣ እየተነጫነጩም፣ እያጉረመረሙም ቢሆን ነቅተው ተነሥተዋል። የመጣባቸውን ጠላት፣ ሌባ ለመመከት በእጃቸው ያገኙትን መሣሪያ ይዘው ለራሳቸው ዘብ መቆም ጀምረዋል። በቲክቶክ ብትለው፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ብትለው በቴሌግራም አንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በየእውቀታቸው መጠን ግብረ መልስ መስጠት ጀምረዋል። አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆንን ተፀይፈው አጀንዳ አከፋፋይ ሆነዋል። ያውም ከእውቀት፣ ከውበት፣ ከደምግባት፣ ከፍጥነት፣ ከችሎታ ጭምር ነው በተናበበ መልኩ የጉዳዩ ባለቤቶች የተነሡት። እናም ታዲያ በዚህ ወቅት እኔ ውሻው ዘመዴ አረፍ ማለት ያስፈልገኛል።
"…በዚህ መሠረት ትናንት በመረጃ ቲቪ በተናገርኩት መሠረት ዘወትር በዕለተ ሰኞ አስገዳጅ ምክንያት ካልተፈጠረ በቀር ከቤተሰቤ ጋር እርፍ ብዬ ከራየን ወንዝ ዳር ሽር ብትን ብዬ ለመዋል ወስኛለሁ። ሰኞን ለእኔ ለዘመዴ የዶርዜ ማርያም ላደርጋት ወስኛለሁ ማለት ነው። የማይቋረጠው ጠዋት እግዚአብሔር ሰላምታው ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር ሰላምታ በኋላ ግን ሰኞ ሰኞ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር ሌላ ምንም አይነት ነገር ባልጽፍ እመርጣለሁ። ማክሰኞ በርዕሰ አንቀጽ የታጀበው የቴሌግራሜ መርሀ ግብሬ እንዳለ የሚቀጥል ሆኖ በ15 ቀን አንድ ቀን ምሽት ላይ ግን የተለመደውን የቲክቶክ መንደር አገልግሎቴን ለመስጠት ወደ ቲክቶክ መንደር እገባለሁ ማለት ነው። ረቡዕ ቴሌግራም፣ ሐሙስ ቴሌግራም እና የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዩቲዩብ መርሀ ግብሬ ከቀሲስ ሳሙኤል ጋር ይቀጥላል። አርብ ቴሌግራም፣ ቅዳሜ ቴሌግራም፣ እሁድ ቴሌግራም እና ምሽት ላይ በመረጃ ተለቭዥን ያለው መርሀ ግብሬ ይቀጥላል ማለት ነው።
"…እግዚአብሔር ረድቶች አይነኬ፣ አይሞከሬ የተባሉትን የዐማራ ጋንግሪኖች፣ የዐማራ ሾተላዮችን ብቻዬን እየተሰደብኩ፣ እየተረገምኩ፣ የማንም ክፍትአፍ፣ መደዴ የስድብ መሞከሪያ፣ የአፋቸው ክርፋት ማራገፊያ ሆኜም ቢሆን ወጥሬ ይዤ ጉረምቦ ለጉረምቦ በመተናነቅ ብዙዎችን የዐማራ ትግል ኮተቶች አራግፌአለሁ። በዐማራ ትግል ላይ የተጣበቁ ደም መጣጭ አልቅቶችን መንግዬ፣ መንግዬ ጥያለሁ። የዐማራ ትግል እንቅፋቶችን ከመንገዱ ላይ ብቻዬን ገለል እንዲሉ አድርጌአለሁ። እኔ የደብተራው ልጅ ዘመዴ ዘመዳችሁ አስማታቸውን፣ መተታቸውንም አክሽፌአለሁ። እንዲህ ብዬ ስጽፍ ታላቅ ኩራት ነው የሚሰማኝ።
"…ቢያንስ ዐማራ ዛሬ ለደረሰበት ራስን የመከላከል፣ የመደራጀት፣ አገዛዝን የመገዳደር ቁመና ላይ እንዲደርስ በሁሉ እየተሰደብኩ፣ እየተረገምኩ የራሴን አስተዋጽኦ አድርጌአለሁ። እሾም እሸለም ብዬ አይደለም እንዲያ ማድረጌ፣ ለነፍሴ ስል ነው። እጸድቅ ብዬ ነው ያደረግኩት። ዛሬ እኮ በማየው ነገር ከማንም በላይ የምረካው እኔ ነኝ። እኔ ነኝ ደስተኛ ሆኜ ጮቤ የምረግጠው። አምላኬ ምስክሬ ነው ነው እኔ ነኝ ደስተኛ ሆኜ የምፈነጨው። አይደለም እንዴ? መስክሩ እንጂ? ዋሸሁ እንዴ? እንደ እኔ ደስተኛ የሆነ የለም።
"…ዛሬ ትልቁን፣ ግዙፉን የመንግሥታዊ ተቋማት፣ አገዛዙ ያሰማራቸውን የተቃውሞ ጎራ ተዋንያን ከነሠራዊታቸው አሸንፌ፣ አምበርክኬ፣ የወያኔ፣ የኦነግ፣ የብልፅግናና የብአዴንን ኮተት አምጰርጵሬ፣ አይነኬዎቹን የግንቦት ሰባት፣ የባልደራስ፣ የግንባሩ፣ የፖለቲካው ቅማንት እና የፖለቲካውን አገው ሸንጎ አፈር ከደቼ አብልቼ ሳበቃ ተኝተው ከርመው ሲያበቁ፣ የዐማራ ፋኖ የትም አይደርስም ብለው በወልቃይት የሰሊጥ ብር ተስፋ አድርገው ተኝተው ሰኔ 15 ላይ ተቸንክረው የቀሩ ጥቂት ታላቁን ጎንደር የማይወክሉ ጥቂት የእንጭቅ ብአዴን በድኑ ልጆችን ጫጫታ ሰምቼ ለእነሱ ምላሽ ለመስጠት የምደክምበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። ይሰመርበት።
"…ዘመነን በመጥላት ሰበብ በጎጃም ሕዝብ ጥላቻ ላበዱት ለጩጬዋ ሚጢጢ ኩርማን አይሞሌዋ ተብታባ ለወሪት አያሌው መንበር እና ለጆሮ ቆረቆራሙ ድልብ ተቸንካይ ዐማራ ጠሉ የእስክንድር ነጋ የህዳር አህያ ለአቶ ሲሳይ አልታሰብ ጆሮዬን የምሰጥበት አንዳችም አይነት ምክንያት የለም። እርግጥ ነው አበበ በለውን እስኪታረም ድረስ እንደ ሞጣ፣ እንደ ብሪጅ እስቶን ሙድ እይዝበታለሁ። ቀድመው ከሚዲያ እስካልጠፉ ድረስ በኢትዮ 360 ዎች በሚሠሩት ፋውል እንዲሁ አልፎ አልፎ ለማላገጥ ስል ሙድ እይዝባቸዋለሁ። ፌክ ኢትዮጵያኒስቶችን እና ግንቦቴዎችንም እንዲሁ ሙድ እይዝባቸዋለሁ። እንጂ እንደ ድሮው ቆሜ ከሀብታሙ አያሌው፣ ከእስክንድር ነጋ፣ ከብሩኬ፣ ከጄሪ ጀሌዎች ጋር አፍላፊ አልካፈትም። ለራሳቸው ተቀስፈው እኔ የምጨመርበት ምንም ምክንያት የለም።
"…አሁን እኔ የማጥራት ሥራ ነው የምሠራው። ኡጋንዳ በስደት ስም የተሰባሰበውን ፀረ ጎጃም የጎንደር ስኳድ ቡድን ጊዜ ሰጥቼ ካልተመለሰ በተለመደው ብዕሬ አጣድፈዋለሁ። ፀጋዬ ነው። ወንበዴን፣ አስመሳይ ቀጣፊን መዠለጥ ፀጋዬ ነው። ኡጋንዳ የተሰበሰበውንና ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ሸዋ፣ ፀረ ወሎ ስብስብ እየመራ አጀንዳ እየቀረጸ ሚዲያ ላይ ያሉትን ልጆች ይሰበስባል የሚባለውን በጎንደር ስም ኡጋንዳ መሽጎ የዐማራ ፋኖን አንድነት ለመበታተን የሚንደፋደፈውንና በአቶ ሙሉዓለም ገብረመድህን የሚመራውንም ጎንደር አሰዳቢ ቡድን እንደአስፈላጊነቱ የጨበጣ ውጊያ በሚመስል መልኩ ፊትለፊት በብዕሬ እገጥመዋለሁ። ስለወልቃይት ብቻ እንጂ፣ አልፎ አልፎ ስለጎንደር ብቻ እንጂ ስለ ዐማራ ፋኖ ግድ የማይለውን ተቸንካሪ የጎንደር አሰደቢ ደቃቃ ቡድን እፋለመዋለሁ። ቃሌ ነው።
"…መሸነፋቸውን የማውቀው ስለ እኔ ጽፈው የኮመንይ መስጫ ሰንዱቃቸውን መዝጋታቸውን ሳይ ነው። ሚጢጢዋ የሰኔ 15 ተቸንካሪ አያሌው መንበር እንኳ ሰድባኝ፣ ሰድባኝ ስታበቃ ያደረገችው ነገር ቢኖር የኮመንት ሰንዱቋን መከርቸም ነው። ሉሲ ድንቅነሽ የኮመንት መስጫ ሰንዱቋን ጠርቅማለች፣ ሌሎችም እንደዚያው እያደረጉ ነው። ፈሪ ሁላ። ሉሲ ድንቅነሽ እነማን እንደሆናችሁ ሳላቅ ቀርቼ አይምሰላችሁ። ስለምታሳዝኑኝ ነው። አቅመቢስ ሁላ። እኔን ያስነሳኝ፣ የገለጠኝ የንፁሐን ዐማሮች ደም በከንቱ መፍሰሱን ማስቀረት የፈለገው ልዑል እግዚአብሔር ነው ባይ ነኝ። ሌላ ምንም ሊባል አይችልም። እና ለዚህ እኮ ነው ብቻዬን እንደ ሠራዊት የምፈራው፣ የምሠራው። አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ የተባልኩትስ ዝም ብሎ ይመስልሃል? ዶፍተር የለ ፍሮፌሰር፣ ኢንጅነር የለ ወታደር፣ ወዛደር ጫ ብሎ የሚሰማኝ በመልኬ ተደምሞ፣ በውበቴ ፈዝዞ፣ በትምህርት ወረቀቴ ተደንቆ መሰለህ እንዴ? እንደ በልአም አህያ፣ እንደ ቢታንያ ድንጋይ የምጮኸውን እኔን ሳትወድ በግድህ፣ ሳትፈልገኝ በውድህ እንድትሰማኝ የሚያደርገው ፈጣሪ መሆኑን መጀመርታ እመን።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር አሁን ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ተከታተሉን።
• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/0D_cyE20AhE
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሻሎም… ሰላም…!
ትዝብቴ ነው…!
"…እዚህ ሰፈርም፣ በተለቭዥን፣ በራዲዮም ብዙዎች አሼ አሸብርን ሲወቅጡት አያየሁ እየሰማሁም ነው። ለነገሩ ሰውየው ደግሞ ነውር ጌጡ ነገር ነው መሰል አይሞቀው አይበርደው። ይልቅ እኔ የገረመኝንና የታዘብኩትን ላንሳ።
"…አሸብር የኦሎምፒክ ኮሚቴው ሊቀ መንበር ነው። እሱ አትሌት አያመርት፣ አያለማምድ፣ አያሰለጥን። አትሌቶችን አምርታ የምታቀርበው እህቴም ወዳጄም ደራርቱ ቱሉ ናት። እናም መወቀስ ካለባትም መወቀስ ያለባት በግልፅ ደራርቱና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ሰዎች መሆን ሲገባቸው አሁን ግን ሁሉም ሰው አሼ ላይ ድንጋይ ማንሳቱ የሚያስተዛዝብ ነገር ነው።
"…አሸብር ኦሮሞ ቢሆን ኖሮ በዚህ መጠን ዱላ ይበዛበት ነበር? ሰውየው አላጠፋም አላልኩም። አሸብር ያለበት ቦታ ሁሉ ሽብር እንዳለ የታወቀ የተረዳ ነገር ነው። ቢያንስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በርካሽ እየተጠቀመ ቤተ ክርስቲያኒቱን በፓርላማ የሚያዋርድ ሰው ነው። እሱ ጥፋት ይኖርበታል። ግን ለይቶ ለብቻው መውገር ያስገምታችኋል።
"…ደሬ ደራርቱ ጀግና ናት። ለሀገሯ ብዙ ለፍታለች፣ ደክማለችም። እስከዛሬ መልካም ስትሠራ ሲጨበጨብላት ኖሯል። ወደፊትም ስትከበር፣ ሲጨበጨብላትም ይኖራል። ይሄ የሚሆነው ግን እስካልሳተች፣ እስካልተሳሳተች ድረስ ብቻ ነው። አሁን ግን የማታ እንጀራዬን ስጠኝ፣ አሟሟቴን አሳምርልኝ እያለች ልትጸልይ ይገባል። ፍጻሜው ካላማረ መጀመርማ ማንም ይጀምራል። ይሁዳ ሐዋርያ ሆኖ እኮ ነው የጀመረው፣ ሳጥናኤልም ሊቀ መላእክት ነበር ሲጀምር። መጨረሻቸውስ? ታውቁት የለ ምኑን እነግራችኋለሁ።
"…እናም ደሬ እህቴ ኦሮሞ ናት ብላችሁ፣ የሽመልስ አብዲሳ ጓደኛ፣ የአቢይ አህመድ ወዳጅ፣ የየብርሃኑ ጁላ፣ የደመላሽ ገብረ ሚካኤል የሰፈር ልጅ ናት ብላችሁ ፈርታችሁ አሼ ብቻ ላይ መጮህ ኢደብራል።
• ሚዛናዊ እንሁን ለማለት ነው።
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን
"…ሰንበተ ክርስቲያን አለ ሰንበተ አይሁድ አለችና ኪዚያ ሲለይ ነው። ያውስ ቢሆን እንዲያው በከንቱ ነውን? ሁለቱን በዓላት ቅዳሜና እሑድን የሚያከብር አንድ ክርስቲያን በሌላ ኃጢአት ተይዞ ወደ ሲኦል የገባ እንደሆነ አርብ በሠርክ ወደ ገነት ይወጣል፤ ሰኞ በነግህ ወደ ሲኦል ይወርዳል። አንዱን በዓል ዕለተ እሑድን የሚያከብር የሆነ እንደሆነ ግን ቅዳሜ በሠርክ ይወጣል ሰኞ በነግህ ይወርዳል። እንዲህ እያለ እስከ ዕለተ ምጽአት ይኖራል። እግዚአብሔርም ሰማይና ምድርን ለማሳለፍ የሚመጣው በዕለተ እሑድ ነውና በዚያው እንደወጣ ይቀራል። እስመ በዛቲ ዕለት ተፈጸመ ፍሥሓሃ ለቤተክርስቲያን በአማን ተፈጸመ እንዲል።
•
•
•
"…ክርክር በሰኞ ተፈጽሟልና "ባርክኒ" ይላታል እርሷም በረከተ ወልድየ ወአቡሁ መንፈስ ቅዱስ ይኅድር ትለዋለች። እርሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በአፍኣ ባሉ ንዋያት እየመሰለ ሲያመሰግናት ሰንብቶ ነበር። በዕለተ እሑድ ግን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባሉት ንዋያተ ቅድሳት በመሶበ ወርቅ፣ በተቅዋመ ወርቅ፣ በማዕጠንተ ወርቅ እና በበትረ አሮን እየመሰለ ያመሰግናታል።
"…ውዳሴ ዘሰንበተ ክርስቲያን፤ ውዳሴ በሰንበተ ክርስቲያን "ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት" ቢል አንድ ነው፣ ቃለ ጸሓፊ ነው። እርሱ ግን ነገሩን "ተሰመይኪ ፍቅርተ ብሎ ያመጣዋል። ቅድስት አለ ከሰባቱ ዕለታት ለይቶ አክብሯታልና።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…የተሰቀለውን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ልጅ እመለስበታለሁ። እኔምለው ይሄም ሶዬ… ይሄ Ethiopia out of Oromia እያለ እንጥሉ እስኪቆረጥ ይፎክር ያስፎክር የነበረው ቡሎ ሶዬ በቃ እንደ ቀልድ ኢትዮጵያዊ ሆነ ማለት ነው…?
• ቄሮ ተበላህ…! ጃዋር ነግሮን ነው ብለው እስከአሁን ሰማይ ላይ ከሚታየው ቀስተደመና በቀር ኦሮሚያ ውስጥ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ሲያዩ የሚነስራቸው ቄሮዎች ተሸወዱ።
• ቄሮ ግን ምስኪን ነው። ጉማ ሰቀታ፣ ዳንኤል ዻባ ወዘተረፈዎች አያችሁት ግን ይሄን Ethiopia out of Oromia ሶዬ። ምፅ…
"…ከምር የምን ዝምታ ነው…? እነ ሴቭ ኦሮሚያ፣ እነ ጉማ ሰቀታ፣ እነ ፍሪ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ባዮች፣ ኦሮሞን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ጫካ የገባን ነፃ አውጪ በእንዲህ ዓየነት ሰቅጣጭ ሆኔታ መቅጣት ግን አግባብ ነውን?
"…ኦሮሞ ኦሮሞን እንዲህ ይቀጣል እንዴ? ጃዋር መሀመድስ? ምነው ዝም አለ? በቀለ ገርባስ? KMN, OMN, ወዘተ፣ ዛራ ሚዲያ ስታሊንስ ምነው ዝም አለ?
"…በቤተሰብ ጠብ መካከል መግባት ባይገባም ይሄን ዘግናኝ ግፍ ግን ዓይቶ ዝም ማለት በፈጣሪም ዘንድ ያስጠይቃል። እናንተ ዝም ብትሉም እኔ ግን እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ የኦሮሞ ነፃ አውጪን ግፍ አጥብቄ ነው የምቃወመው።
• ኧረ ጉማ ሰቀታ የሆነ ነገር ተንፍስ…? 😭😭😭 ዘገነነኝ።
"…ቻዎ ቻዎ ጥልያን… ቻዎ ቻዎ ሮማ… ጉዞ ወደ ስደት ሀገር ወደ ራየን ወንዝ ማዶ ወደ አጎት አገር ጀርመን…!
"…በጢያራው ለመብረር፣ ሮጲላውን ለመሳፈር ሰከም፣ ሰከም እያል እየመጣን ነው…!
• እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ እሑድ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር እንገናኛለን።
እህም ነው ገና…
"…እኔ ዘመዴ ምኞቴ ይህ ነበር። ዝም ብሎ በብላሽ ታርዶ ከመሞት ቢያንስ ገዳይን መክቶም ከፍ ሲልም አንክቶ መሞት።
"…እንደ እብድ የጮህኩበት፣ እንደ ውሻ ያላዘንኩበት፣ በቄስ በሼኩ፣ በዶፍተር በፍሮፌሰሩ፣ በትግሬ በኦሮሞው፣ በፎለቲካው ቅማንት በአገው ሸንጎው፣ በወሃቢ በጴንጤው ስሰደብ የከረምኩት ዐማራን እንዲህ እንዲታጠቅ፣ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ወሳኝ፣ ፈራጅ፣ ለነገዱ ሞጋች ጠበቃ እንዲሆን በመቀስቀሴ ነበር።
"…አሁን ዐማራን በብላሽ መግደል፣ ማታለል፣ ማጭበርበርም አይቻልም። እየመጣ ያለው ዐማራ በመኖርና ባለመኖር መካከል ወስን ተብሎ ምርጫ ቀርቦለት በሕይወት መኖርን ምርጫው አድርጎ በመነሣት ይሄንኑ በተግባር እያሳየ ነው ያለው።
"…ዛሬ ላይ በዐማራ ክልል ትምህርት የለም። ዝግም ነው። የሥራ እንቅስቃሴም የለም። ታዲያ ዐማራ ይሄን የመከራ ጊዜ ወደ በጎ ነገር እየቀየረው ነው። አጋጣሚውን ተጠቅሞም ከትንሽ እስከትልቅ ራሱን በወታደራዊ ሥልጠና እየገነባ ነው።💪
"…ወዳጄ አኬር ይገለበጣል። ፍቅርም እንዲሁ ይገለባበጣል። ምንአልባትም አሁን ዐማራ ክልልን በጦርነት አድቅቀን ኦሮሚያን በልማት ሰማይ ላይ እንሰቅላታለን ብለው ቆምረው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አኬር ይገለበጣል። ዐማራ ደቅቆ፣ ትግሬ ወድሞ፣ አፋር ፈርሶ፣ ኦሮሚያ ብቻውን ገነት ሊሆን አይችልም። ተፈጥርአዊም አይደለም።
"…ቢዘገይም ዐማራ በአንድ ዓመት ውስጥ የደረሰበት የትግል ደረጃ በየትኛውም ዓለም ያለ የትጥቅ ትግል የሚያደርግ ድርጅት አሳክቶት አያውቅም። ያውም አሜሪካ ሳትረዳው፣ አረቦች ሳይደጉሙት፣ አውሮጳውያን ሳይደግፉት ከዜሮ ተነሥቶ ጀግና፣ ከባዶ እጅ ተነሥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ ባለ ዙ 23 ታጣቂ የሆነ ከዐማራ በቀር ሌላ ሰምቼም፣ ዓይቼም አላውቅም።
• አዛኜን የጮህኩለት ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።
"…ቆይ ደግሞ ሌላ ጥያቄ… ባለፈው ለታ የሆነ ቀን ላይ… ጠቅላይ አቡቹ አድማጭ ተመልካች አጨብጫቢ ሚንስቴሮችን ሰብስቦ… ሦስት ክላሽ ይዞ የብልጥግናን መንግሥት መቀየር አይቻልም አላለም ነበር እንዴ?
• እናስ ይሄ የማየው ነገር ምንድነው…?
• ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ አርብ።
"…ይዞትስ እንደመጣ ሰዱስ ቢል በቀና ነበር። ወደ ምስጢር ሄዶ አርብ አለ እንጂ። አርብ ማለት የፍጥረት መካተቻ ማለት ነው። ስድስቱን ቀን ሲፈጥር ሰንብቶ በሰባተኛው ቀን በዕለተ ቀዳሚት አልፈጠረም። "ወአእረፈ እግዚእነ እምኵሉ ዘአኀዘ ይግበር" እንዲል። አንድም መካተቻ ማለት ነው። ሰባቱን መና ሲያዘንብላቸው ሲለቅሙ ሰንብተው በስድስተኛይቱ ቀን በዕለተ ቀዳሚት አይዘንምም የቀዳሚቱን ዓርብ ደርበው ያገባሉና የመና መካተቻ ማለት ነው። አንድም የሥራ መካተቻ ማለት ነው ሠላሳ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በዚህ ዓለም የሰውነት ሥራ ሲሠራ ኖሮ በዚህ ቀን ሥራውን ፈፅሞ ዐርፏል።
"…ወአርበ ፋሲካሆሙ ለአይሁድ እንዲል። አለፈ ተከተተ ሲል ነው። በዚህ ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፣ የብርሃን ምንጣፍ ይነጸፋል፣ ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦ ፍቁርዬ ኤፍሬም ትለዋለች። እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል። ወድሰኒ ትለዋለች ክርክር በሰኞ አልቋልና ባርክኒ ይላታል። በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይህድር በላእሌከ ትለዋለች። እሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀመራል። ውዳሴ ዘአርብ ውዳሴ በአርብ ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በእለተ አርብ ይላል። ቃል ጸሐፊ ነው እሱ ግን ምስጋናዋን ቡርክት አንቲ ብሎ ይጀምራል።
"…በአዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ከፈጠረን ልጅሽ ፅንኢት በድንግልና እመቤታችን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…እጠይቃለሁ… ሁሌ ለምንድነው የትግራይ ነፃ አውጪዋ ወዩ እና የኦሮሞ ነፃ አውጪው ወነግ አክ እንቲፍስቶች እስክንድር ነጋ ለምን ይተቻል? ለምን ይነካል ብለው ጓ የሚሉት እል ነበር። በፊት በፊት ነው።
"…ሀብታሙ አያሌው ተሾመ አፍራሳን ሳይ፣ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራን ሳይ፣ በዚህ ላይ ብዙዎቹ በሚስት በኩል ትግሬና ኦሮሞ ማግባታቸውን ስመለከት፣ ዘራቸው ብቻ ሳይሆን ከቤትም ጫና ሊኖርባቸው ይችላልም ብዬ እል ነበር።
"…አርበኛ አሰግድን ሀብታሙ ሰድቦ፣ መከታው አዋክቦ ለመከላከያ አሳልፈው ከሰጡት በኋላ ማጀቴን የመከታው ማሞ ፈቄ ልጆች ተቆጣጥረው ቆይተው ነበር። እናም ዛሬ የመከታው ቡድን ለመከላከያ ማጀቴን ሁላ ለቅቆ ፈርጥጧል አሉኝ።
"…የመከታው ማጀቴን ለመከላከያ አስረክቦ መውጣት ያየው እስክንድር ነጋ ከኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባው ጋር ወደ ደቡብ ጎንደር ወደ ዶር አምሳሉ ሀገር በመሸሽ በዚያ አርበኛ ውባንተ በተሰዋበት ምድር ፋፍዴኖችን ሊቀላቀሉ ነው የሚል ጭምጭምታም ተሰምቷል። እነ ዶፍተር ምስጋናው አንዱአለም ከጎደር ዳያስጶራ ብር ለመሰብሰብ እየዳከሩ ነውም ተብሏል። ዶለር ግን ወፍ የለም።
"…አሁን ለዐማራው እጅግ ጥሩ ጊዜ ነው። ሁሉ ነገር በጊዜ መገለጡም ሸጋ ነው። ሸዋም በጊዜ ድክመቱን ከለየ በጊዜ ይጠነክራል። ጎጃም እንደሁ ከወዲሁ የብረት ግድግዳ ሆኗል። ጎንደር ተወዛግቧል። ዶላሩ እና መሃላው ወደ እስኬው አስጠግቶ ነበር። የሆነው ሆኖ እነ ፋኖ ደረጄ ይሄን ውርደት እንደ ጎንደር የሚቀበሉት አይመስለኝም። ወሎም ከወዲሁ ፈርጥሟል። እሾሁን ከመሃሉ ነቅሎ ጥሏል። የፈለገ ይሁን የደፈረሰው ነገር በጊዜ ጠርቶ ዐማራም በጥራት በኩራት ያሸንፋል።
• እኔ ዘመዴ የሚታየኝ እንዲህ ነው። ቦግ ብሎ የሚበራ የድል ችቦ ብቻ ነው የሚታየኝ። እንኳንም በጊዜ ተገለጠ።
• እስኬው ግን አይገርምላችሁም…?
አደራ፣ አደራ…አዳራ…
"…ይሄን ቪድዮ በእስክንድር ዶላር ለተንበረከኩት ለጎንደሬዎቹ ለእነ ጋሽ መሳፍንት ቡድን ለእነ ሀብቴ እና ለጎንደሬዎቹ ለፋፍዴኖቹ ቡድን ለእነ ፍሮፌሰር ጌታ አስራደ፣ ለሸዋው መከታውና ለወሎዬው ኮ/ል ፈንታሁን ሙሀባ አድርሱልኝ።
"…ዐማራ ባለመሆኑ ፋኖ ብሎ አስረግጦ መናገር የማይችለው እስኬው… ፋኖ የሚያስፈልገው ይላል…
1ኛ፦ ወያኔን ለመበተን
2ኛ፦ ጭፍጨፋውን ለማስቆም ብቻ ነው ይለናል።
"…ልብ በሉ አስታውሱም ድሮ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ ፋኖዎች ከደርግ ጋር ተዋጉና ወያኔን ከደደቢት በረሀ አውጥተው ተሸክመው 4ኪሎ አስገብተው እነሱ ተመለሱ።
"…ቀጠሉና የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ ፋኖዎች ከወያኔ ጋር ተናንቀው ሥርዓት ለወጡ፣ ዐማራ መስሏቸው ደመቀ መኮንን አንተ ምራ ሲሉት "እኔ እኮ ብአዴን ነኝ። እኛ ብአዴናውያን ስንፈጠር ለመሪነት አልተቀባንም፣ ስለዚህ ኦሮሞዎቹ ይምሩ ብሎ ሥልጣን አሳልፎ ሰጥቶ ዐማራ ባዶውን ተመለሰ።
"…እስኬ ብልጧ አሁንም ፈኖ እንደ ኩሊ፣ እንደ አጋሰስ መሆን ነው የሚያምርበት፣ ፋኖን መጠቀም ያለብን እንደ ጓንት፣ እንደ ኮንዶም ነው። ፋኖ እኛን ቤተ መንግሥት ካስገባ በኋላ እሱ ወደ ግብርናው መመለስ ነው ያለበት ነው የሚለው።
"…እሺ አረጋዊው ጎንደሬ ጋሽ መሳፍንትን፣ ሽማግሌው ኮረኔል ፈንታሁንን፣ ኡንበርስቲ ባለመበጠሳቸው ሀብቴንና መከታውን ዶላር አቅምሶ ሸወዳቸው ማለት በቃ ሌላውንም መሸወድ ይችላል ማለት ነው እንዴ?
"…አበበ በለው በእናቱ ትግሬ በአባቱ የፖለቲካ ቅማንት ነው አሉ፣ ሀብታሙ አፍራሳ፣ ብሩኬ ጉራጌ ናት፣ ጄሪ እንኳ እንጃ እነዚህን ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎጃም ኮተቶችን ይዞ ከሕዝብ በተሰበሰበ ዶላር ምኒልክ ብሎ ቲቪ ከፍቶ ዐማራን ማሞኘት ይቻላል ወይ?
•እንደ እስክንድር አባባል በእውነት ፋኖ ኮንደም ነው ወይ? ተወያዩ✍