"…ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፤ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፤ ለሰላም ሰው ቅሬታ አለውና። በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፤ የኃጢአተኞች ቅሬታ ይጠፋል። መዝ 37፥ 35-38
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ተቀበል…
• ሃሎ አዲስ አበባ… 😂
"…አይ ኦሮሞ አለ አቢይ አሕመድ… ቀኑ አልደርስ አላቸው እንዴ? መቼ ሊጀምሩት አስበው ይሆን…?
"…ቆይ ሙንኡኖው ኖው ግን…?
ተቀበል…
"…በዚህ ዘመን በቲክቶክ መንደር መኖር መመላለስ መንከላወስህ ካልቀረ በመንደሩ ውስጥ ማየት፣ መስማት፣ መከታተል የምትፈልጉትን መምረጥ መብቱ የእናንተ ነው። ማንም አያስገድዳችሁም።
"…ደስ የሚለው አሁን አሁን የሚገራርሙ ዐዋቂ ሲናገሩ አእምሮን የሚቆጣጠሩ፣ ሰቅዘው የሚይዙ አስደማሚ ዐማሮችን በመንደሩ ውስጥ እያየሁ ነው። እስከዛሬ ተደብቀው ከቆዩበት ጎሬ ወጥተው ሜዳ መንደሩንም እየተቆጣጠሩት ነው። እነዚህን አንደበተ ርቱዕ ዐማሮች ሲመጡ እንደኔ ያለው ተብታባ ማይም ሳይድ በግዱ ይደበቃታል።
"…ወዳጄ አባ አቢዲ እንደፍየል እንዲባልግብህ መፍቀድ መብትህ ነው። ያውም 2,400 ሰው እኮ ነው ዘጭ ብሎ የሚያየው። 😂… ማየት ብቻም አይደለም ለዚህ ለኢንተርኔት የቲክቶክ ላይ ጋለሞቶች ከክሬዲት ካርዱ ላይ የ500 ዶላር አንበሳ ጭሮ ሁሉ ያወርዳል። አባቴ… ቲክቶክ ላይ በዮኒ ማኛ አክሮባት መደመምም መብትህ ነው። በሞጣ ቀራንዮ ሽንጥና ዳሌ መረጣም መፍዘዝ፣ በሰገራ አፉም መግማት መግማማት መብትህ ነው። በእነ አኪላ ተኪላ ቮድካ ወሬ መስከርም፣ መጠንበዝም መብትህ ነው። መብትህ ነው አልኩህ።
"…ጭራሽ ዘመነ ሞተ፣ ፕሮፌሰር ሀብታሙን ልደቱ ከሰሳቸው፣ ጌታ አስራደ በዋና ጣናን አቋረጠ ተብሎ በእነ እስኳድ አቧራ ሲጨስ ዐማራ ሆዬ በቲክቶክ የሚገርም መረጋጋት ውስጥ ገብቶ ስለ ቀጣዩ የፋኖ አንድነት ነው የሚያወራው።
"…የገባኝ ነገር አሁን አሁን እንደ ድሮው በዐማራ ስም፣ በአማርኛ ቋንቋ ጎንደርና ጎጃምን ማጣላት፣ ወሎና ሸዋን ማባላት አይቻልም። ካካ ነው፣ እፉ ነው።
"…አሁንማ የትግሬ ነፃ አውጪዎች እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ሳይቀሩ በራሳቸ በትግርኛ ቋንቋ እና በላቲንኛ ቋንቋ መጻፍ፣ መደስኮር ትተው ሙሉ ሰበካቸውን በአማርኛ አድርገውት አረፈውታል። 😂
• አይገርምላችሁም…?
ተቀበል…
"…በይፋ ተጀምሯል።
• ግጥም ስጡት… አልችልም አትበሉ። ሞክሩ። ማንም በእናቱ ሆድ ግጥም ተምሮ ለምዶ የወጣ የለም። ሞክሩ…
…ያዝ እንግዲህ…
“…እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።” 1ኛ ተሰ 5፥11
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…ለእሁድ ምሽት የመረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ ካስቀረሁት በቀር ለዛሬ የራሴን ሓሳብ በርእሰ አንቀጽ መልክ ተንፍሼዋለሁ። ቀጥሎ እናንተ ደግሞ ለታሪክ የሚቀመጥ የበሰለ አስተያየታችሁን ትሰጡ ዘንድ ትጋበዛላችሁ።
"…ለወትሮ በምጽፈው ርዕሰ አንቀጽ ስር 😡 ብው ብለው ይናደዱ የነበሩ የፔጄ ላይ አልቅቶች በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ላይ እንጥላቸው እስኪታይ 😁 ሲገለፍጡ ታይተዋል። የሆነው ሆኖ የሚበሳጨውም የሚገለፍጠውም ሰው ቁጥር መቀነሱ በራሱ ግቤን እያሳካሁ መሆኔን አመላካች ነው። ችክ ምንችክ፣ ድርቅ፣ ድፍር ብዬ መጋተቴም ጠቅሞኛል።
"…እንቀጥላለን። በትግራይና በመሀል ሀገርም የተደፈራችሁ፣ ግብረ ሰዶም የተፈጸመባችሁ ዲያቆናትና ሕጻናትም ለማይቀረው ቤተ ክርስቲያንን የማዳን የመጨረሻ መንፈሳዊ ዘመቻ ተዘጋጁ። የምስልና ድምጽ መረጃዎችም እንደአሰፈላጊነታቸው ይቀርባሉ። እነ አማኑም ደፈር በሉ። ቀልድ የለም።
“…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥”ማቴ 24፥15። ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምንም አትሆንም። ምንም አልኳችሁ። በአገዛዙ ድጋፍ ነውረኞች ቤተ ክርስቲያኒቱ አናት ላይ እየተጸዳዱ ስታዩም አትጨነቁ፣ አትገረሙ። ለጥቂት ጊዜ ነው።
"…ጥቂቶች ደንግጠው እምነታቸውን ሊቀይሩ ይችሉ ይሆናል። ስለ ውባንተ ሞት የተናገርኩትን ቪድዮ ቆራርጠው፣ ዘመነ ሞተ ትላላችሁና ላይሞት ነው እንዴ የተፈጠረው? የምለውን ቪድዮ ቆርጠው ለጥፈው እሱን አይቶ ማገናዘብ የማይችለውን ሲያስለቅሱት እንደሚውሉት ዓይነት ሰዎች ጥቂት የዋሆችን ሊሸውዱ ይችሉ ይሆናል። አበደን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግን በሴረኞቹ እምብርት ላይ ሰንደቅ ዓላማዋን እየሰካች ጉዞዋን ወደፊት ትቀጥላለች። ይብላኝ ለወንድኛ አዳሪና ለዘራፊ ቀማኛ ሌቦች።
•1…2…3… ጀምሩ ✍✍✍
👆 ② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …በየቤታቸው ምሽቱን በመግባት እያንዳንዳቸውን ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት በማስፈራራት ልክ እንዳገቧቸውም ነው የተሰማው። ለዚህ ነው እሁድ በማሰማችሁ የበቃሉ ንግግር ላይ ስምዎን ይናገሩ ብለው የሲኖዶሱ አባላት ሲጠይቁት በቃሉ ነኝ የቦሌ መድኃኔዓለም ዋና ጸሐፊ ብሎ ሲመልስ ሙሉ ጉባኤው ከፍ ባለ ድምፅ ያጉረመረመው። ትሰሙታላችሁ። ትናንት ግን የጉደሩ ዳዊት ሮቶ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ሆኖ ማምሸቱ ነው የተነገረው። አይ ጊዜ…
"…የምሽቱ የመንግሥትና የጋንግስተሮቹ ወከባ በዚህ መልኩ ከተፈጸመ በኋላ በማግሥቱ ተበዳዮች ድምጻቸው እንዳይሰማ በተከለከለበት ጉባኤ ላይ የጎንደሩ ስኳድ ግርር ብለን ገብተን ውሳኔውን ማስቀልበስ አለብን ብሎ በሀገረ ስብከቱ ስብሰባ ላይ በተናገረው መሠረት በዳዮቹ በአለቃቸው በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፈቃድ ግርር ብለው እንዲገቡ ተደርጎ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ላይ የስድብ መዓት ሲያወርዱባቸው መዋላቸው ነው የተሰማው። በትግሬዎች ዘንድ የተለየ ክብር የሚሰጣቸውና ሰሞኑን በወይዘሮ እጅጋየሁ ከበደ አፍ ሁላ ሲንቆለጳጰሱ የከረሙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በፓትርያርኩና በምልዓተ ጉባኤው ፊት አንደዜ በጨዋ ደንብ ሌላ ጊዜ በነውጠኝነት ሲውረገረጉ፣ ሲዝቱ፣ ሲያስፈራሩ ሁሉ መዋላቸው ነው የተሰማው። እኔ የማሰማችሁ ትክክለኛ ጥያቄ የጠየቁበት የድምፅ ቅጂ ነው። በቀጥታ እኔ የደረሰኝ መረጃ ባይኖርም በሚዲያ ደረሰን ያሉ አካላት እንደተናገሩት እና እንደሰማነው ግን "ከዚህ በፊት ሥልጣነ ክህነታችንን ገፍፋችሁ፣ አዋርዳችሁ አባራችሁናል። በትግራይ ግን ያንን አላደረጋችሁም። አሁን ግን ያንን ማድረግ አትችሉም። አንፈቅድላችሁምም። እንዲያውም እኛ በተራችን እናንተን አባረን፣ ካስፈለገም አዲስ ፓትርያርክ መርጠን ልንቀጥል እንችላለን።" እስከማለት መድረሳቸው ነው የተነገረው። የአቡነ ሳዊሮስ ሹመኛው አቡነ ኤጲፋንዮስም "ዱላ ልንማዘዝ ሁላ ስለምንችል ተጠንቀቁ" እስከማለት መድረሳቸው ነው የተነገረው። ይሄ ሁላ ሲሆን ሊቃነጳጳሳቱም፣ የስብሰባው መሪ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ ጉባኤውን እንዲመሩ የተመደቡት አባ ያሬድ ሊያስቆሟቸው አልሞከሩም ተብሏል።
"…በጉባኤው ላይ ባለፈው የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን በመክፈል የተወገዙትና ኋላ ላይ በይቅርታ የተመለሱት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ፦ እናንት ተከሳሾችም ልክ እንደ ከሳሾቹ በመረጃ ስጡን። "በቃል ያለ ሳይሆን በጽሑፍ መረጃው ይሰጠን። እሱን አይተን ነው መፍረድ የምንችለው እንጂ እንዲሁ በቃል ብቻ ሰምተን መፍረድ የለብንም" ያሉ ሲሆን አቡነ ሳዊሮስም "የአቡነ ዜናማርቆስን ሓሳብ በመደገፍ እናንተም በቃል ሳይሆን ሰነዱን ስጡን እና አይተን እንፍረድ በማለት መልስ ሰጥተዋል። አቡነ ማርቆስም፣ ትናንት የቀረበውም ቢሆን ተከሳሾች ባልነበሩበት መቅረብ እንዳልነበረበት ተችተው አሁንም ተከሳሽ በሌለበት ከሳሽ ብቻ መደመጥ የለበትም። ሁለቱም ቀርበው ብለው ጠይቀዋል። ይጠየቁ። አቡነ ኤርሚያስም ተመሳሳይ ሓሳብ አንጸባርቀዋል። አቡነ ሉቃስ ደግሞ እኔ ጥያቄ ያለኝ ለእናንተ ነው በማለት ማፍያውን ግሩፕ የጠየቁ ሲሆን "ሁላችሁም ወጣ የተባለውን ሕግ አምርራችሁ ስትወቅሱት አይቻለሁ። እንደ እናንተ አበባል መተዳደሪያ ደንቡ ነው ጥፋተኛ ወይስ ከሕጉ ውስጥ ይሄና ያ አንቀጽ ይሻሻልልን የምትሉት አለ? ብለው የጠየቁ ሲሆን በግሩፑ በኩል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ አብርሃም፦ ለቀረበባቸው፣ ስድብ፣ ዛቻ፣ ዘለፋ አመስግነው ከሳሾቹ በሚቀጥለው ሲመጡ እንደ ቤት ሥራ ይዘው እንዲመጡ በአደባባይ በግልጽ ጥያቄ አቅርበዋል። "በእኔ ሥልጣን፣ በእኔ ፊርማ የእኔ የቤተሰብ አባል የተባለ በቃልም ይሁን፣ በጽሑፍ ቅጠሩ ብዬ ያዘዝኩት፣ የቀጠርኩት ካለ ይዛችሁ እንድትመጡ። ሌላው አላወቅነውም፣ ከሚዲያ ነው የሰማነው የምትሉትም የመዝገብ ቁጥር ይዞ፣ ቀንና ማኅተም ያረፈበት ደብዳቤ አልደረሰንም የምትሉም ከሆነ ይዛችሁ አቅርቡ። በተረፈ ለዛቻችሁና ማስፈራራቱ ቦታም አልሰጠው፣ ፍርዱንም ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ በማለት ንግግራቸውን ፈጽመዋል።
"…ብፁዕ አቡነ አብርሃምም ያ ብዙ ጊዜ በሁሉ ዘንድ የሚደነቅላቸውንና በሁሉም ዘንድ የሚታወቁበትን ስሜትን በመቆጣጠር ሁሉን እንደ አመጣጡ የማሳላፍ ፀጋቸውን በመጠቀም የትናንቱንም የትግሬዎቹን እና የኦሮሞዎቹን የተደራጀ አስደንጋጭ ሱናሚ የመሰለ የቁጣ ማእበል በትእግስታቸው ገስጸው በትህትና ማሳለፋቸው ነው የተነገረው። እኔ ባልሰማውም ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሰጡት የዛቻ የማስፈራራት መልስም "ግድ የለም የሚሰነብተውን እግዚአብሔር ያውቃል" በማለት ጉባኤውን ፀጥ ማሰኘታቸውም ነው የተሰማው። በነገራችን ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከዚህ በፊት መርካቶ ራጉኤል አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዜ ራጉኤሎች የሸሏማቸውን ወርቆች ለእኔ አይገባም በማለት በወቅቱ ፓትርያርክ ለነበሩት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደሸለሙ ይነገራል። አሜሪካ ተመድበው ሳለም ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአስቸኳይ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በቅዱስ ሲኖዶሱና በወቅቱ ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲታዘዙ፣ ኦሮሞው አቡነ ኤውስጣቴዎስ አልመለስም ብለው በዚያው ሲቀሩ ዐማራው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ግን "ይሄን ሥልጣን የሰጠችኝ እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፣ ወደዚህም የላከችኝ እሷው ናት፣ አሁንም ተመለስ ያለችኝም እናት ቤተ ክርስቲያን ናት። እናም ተመልሼ ሄጄ እሷ ይመጥንሃል ብላ በመደበችኝ ቦታ እሠራለሁ በማለት ብዙዎች ወቅቱ ጥሩ አይደለም ወደ ሀገር ቤት አይሂዱ፣ አይመለሱ ቢሏቸውም እምቢኝ ብለው ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ቁርጠኛ የቤተ ክርስቲያን አባትም ናቸው። አቡነ አብርሃም ወደ ሀገር ቤትም እንደተመለሱ በወቅቱ ምሥራቅ ሐረርጌ የተመደቡ ሲሆን በዚያም የልማት አርበኝነታቸውን አስመስክረው ኋላ ላይ አሁን ወዳሉበት ወደ ባሕርዳር ሀገረ ስብከት ተመድበዋል። እነ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስም በዝሙት ምክንያት ከተባረሩባት ሀገረ አሜሪካ ኦነግ ወደ ሀገር ቤት ሲገባ ከኦነግ ጋር አብረው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ገብተዋል። ከገቡም በኋላ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን በመቋቋም የጨረቃ ጳጳሳትን በመሾም በኦሮሚያ የብዙ ክርስቲያኖችን ደም አስፈስሰዋል። ቅዱስ ሲኖዶሱም ዘመኑ የኦሮሞ ነውና በማለት ለአቡኑ በውግዘት የተያዘውን ሥልጣነ ጵጵስናቸውን ከነሙሉ ክብሩና ማዕረጉ መልሶላቸዋል። አሁን ደም አስፈሳሹ ሊቀጳጳስ ምእመናንና ካህናትን እያቆረቡ፣ ሥልጣነ ክህነትም እየሰጡ ዘና ፈታ ብለው ደመ ወዛቸውን እየበሉ ፈታ፣ ዘና ብለው ይኖራሉ።
"…በመጨረሻም ከጉዳዩ ጋር በምንም መልኩ በማይገናኝ ሁኔታ ለብቻቸው ያስቀሯቸውን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን አቡነ ሳዊሮስ ምን እንደተሰማቸው ባይታወቅም መልሰው ከአቡነ ሄኖክ ጋር ታረቁ ብለው አሪፍ ካርታ ይዘው ቢመጡም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ግን እኔ የተጣላሁት ሰው የለኝም። እኔ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠኝን ሓላፊነት ነው በሕግና በመመሪያ እያስፈጸምኩ ያለሁት በማለት ነገሩን በተለመደው ትእግስታቸው በማሳለፍ ዛሬም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ክብር እንደ ቀድሞው ከግል ስሜት በጸዳ መልኩ ማስከበራቸው ነው የተሰማው። በብዙ ነገር ብበሽቅባቸውም በፅናታቸው ግን መደመሜን መካድ አልችልም። ነገሩ በዚህ ከተቋጨ እንግዲህ እኔ ዘመዴም አጥፊዎች በዚህ መልኩ ተደራጅተው ባለጊዜነታቸውን ማሳየት ከቻሉ፣…👇 ② ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍
መልካም…
"…በምዕራብ ሸዋው ማፍያ በጉደሩ ባለ ጊዜ በራሱ አነጋገር "ደፋር መደዴው" ዳዊት ሮቶ እጅ የወደቀችው የዘመናችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ሲያንቀጠቅጡ የዋሉበትን ሙሉ የድምፅ ሪከርድ እየሰማሁ ነበር ከትናንት ምሽት ጀምሮ ስደመም የቆየሁት።
"…ያ መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል ብለን ትናንትም፣ ዛሬ አሁንም፣ ነገም የምናምነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በተራ ማፍያና የዱርዬ ስብስብ እንዲህ ውጥንቅጡ ወጥቶ የጨበራ ተስካር ሲመስል እንደማየት የሚያቆስል፣ የሚያም ነገር ግን የለም። ከምር እኔ በጣም ነው ያዘንኩት።
"…ደርግ በመግደል፣ በመውረስ፣ ወያኔ በመክፈል፣ በመደብደብ፣ በመግደል፣ በመዝረፍ ያስቀጠለችውን ታላቋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማጥፋት ሴራ አሁን ደግሞ በአሕዛብና በመናፍቃን ጥርቅሙ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ ኢሊዩሚናቲ የኦሮሞ ብልፅግና በሃላል እንዲህ ተዋርዳለች።
"…እኔ በድምጽ ባለኝ መረጃ በትናንቱ የማፍያዎቹ ድንፋታ ላይ ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ፣ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤልያስ የአርባ ምንጩ፣ አቡነ ኤርሚያስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሚዛናዊ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ከሳሽም፣ ተከሳሽም ይቅረብ፣ ከሳሾች ትናንት በመረጃ፣ በማስረጃ እንዳቀረቡት ሁሉ ተከሳሾችም እንዲህ በጩኸት፣ በግርግርና በቃል ሳይሆን በጽሑፍ፣ በሰነድ መረጃቸውን ያቅርቡ ሲሉ ነው ያደመጥኳቸው።
"…ብፁዕ አቡነ አብርሃም በተለየ መልኩ በተቀደሰው ጉባኤ ፊት በማንም ሰካራም ዱርዬ ሲሰደቡ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለማስቆም አለመሞከሩን ስታዩም ታዝናላችሁ። ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ለመከላከል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን በቦሌው ጸሐፊ በጎንደሩ ስኳድ በበቃሉ አፍ በሲኖዶሱ ፊት ማሰደብ ግፍም፣ ነውርም ነው።
• ርእሰ አንቀጽ ይቀጥላል… እናንተስ ግን ዝግጁ ናችሁ አይደል…?
አሁንም ጥያቄ ነው…?
"…ጎንደር ደባርቅ ከተማ ዲዲቲ መርዝ ጠጥተው፣ እየተሰቀሉ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል የሚል ዜና አንብኤላሁ። አዲስ አበባም ከካድሬ በስተቀር ሌላው የአእምሮ ታማሚ ይበዛዋል፣ አማኑኤል ሆስፒታልም ታካሚው ከአቅሜ በላይ ነው እያለ ነው። ሁሉም እየዬ እያለ ነው።
"…በመርካቶም ቢሆን ኦሮሞውም፣ ጉራጌ፣ ዐማራና ትግሬ፣ ብሔር ብሔረሰቡ ሁላ ነው ገሚሱ ነግዶ፣ ገሚሱ ተሸክሞ፣ ገሚሱ ደልሎ፣ ሌባውም በለስ ከቀናው ሰርቆ ሆዱን ሞልቶ የሚኖርባት። እና መርካቶም ከወደመ። በክፍለሀገርም ተዟዙሮ መሥራት ካልተቻለ ምን ተሻለ?
"…እንደ ትግሬ በጅምላ አንዴ በመቶ ሺም ተገድለህ፣ እንደ ዐማራ በቁጥቁጥ በድሮን በወታደር ተጨፍጭፈህ፣ ከቤትህ፣ ከቀዬህ ተጠርገህ፣ በቁጥቁጥም ሞተህ፣ ተገድለህ ምኑ ነው የሚያስፈራው? መዋጮ አልሰጥ ካልክስ ምንድነው የሚያደርጉህ? ለኦሮሞ ሚሊሻ ዩኒፎርም አንተ ምን አገባህ? ለሚሊሻ በቆሎ አዋጡ ማለትስ ፌር ነው ወይ…?
• እንደ ትግሬ በጅምላ፣ እንደ ዐማራም በየተራ መገደሉ ካልቀረ አትግደሉን ብሎ እንደ ሕዝብ ወጥቶ ለመጠየቅ ዋናው ችግር የሆነው ነገር ምንድነው?
"…ሌላው ያልገባኝ ነገር እሺ እንደተባለው ኦሮሞው የኦሮሞ ቄሮ ጉራጌው፣ ዐማራና ትግሬ፣ ደቡቡ ተፈናቅሎ እሱ ሱቅም፣ ሆቴልም ገነባ፣ ወረሰም እንበል። ሌላውን አደህይቶ ማን በሆቴሉ ሊዝናናበት ነው? ሱቁስ ያፈናቀልከው ከደኸየ አንተ ኦሮሞው ታቅፈኸው ልትኖር ነውን? ሥራ አጥ ከበዛ ወታደር ይሆንልኛል ብሎ ሒሳብ መሥራቱስ እስከመቼ ነው የሚያዋጣቸው?
• ግን ምን ኦነው ነው?
"…ብለን ነበር እውነት ነው። ነገር ግን ከላይ መመሪያ ስላልወረደልን ከቻልን በሚቀጥለው ህዳር ወር ላይ እንደምንም ብለን እንሞክርላችኋለን ተብላችኋል አሉ።
"…እንደልቡ በነበረው የብር ኅተመቱ ጉዳይ ላይ የዓለም ባንክ ቆንጠጥ ያለ ቁጥጥር ማድረጉ አጣብቂኝ ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ብሪክስም ቶሎ ብድር የመስጠት ቁመና ላይ አልደረሰም። ለማንኛውም የመስከረምም፣ ጥቅምትም ወር ታሳቢ ተደርጎ ይከፈላል የተባለው ደሞዝ ለህዳር መቀጠሩን ነው የሰማሁት።
• የሰማሁትን ውሸት ያድርገው። 🙏🙏🙏
ደግሞ የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ
"…በነገዱ ስልጤ የመርካቶ የቦምብ ተራ ነጋዴ ነው። በአስቸኳይ ጉምሩክ ድረስ እንድትመጣ ብለው ይደውሉለታል። ተነሥቶ ይሄዳል። ጉምሩክ እንደደረሰ ቀጥል ብለው አፍነው ይወስዱታል። ከዚያ መጀመሪያ በእጁ ላይ የ1 ሚልዮን ብር ቼክ ነበረ ጻፍ አሉትና አጽፈው አወጡበት። ቀጥሎ 6 ሚልዮን ብር አምጣ አሉት። ለሚስቱ ነግሮ፣ ከጓደኞቹም ተለምኖ የተባለው ብር በባንክ ተላልፎ ተሰጣቸው። አፋኞቹ ከጉምሩክ ጊቢ አንድ ሰው አፍነው በአንድ ቀን ጀምበር 7 ሚልዮን ብር ቀምተው ከበሩ። ሰውየው ደግሞ በዚያው ቅፅበት የደሀ ደሀ ሆኖ አረፈው። ሰዎች ለምን ለፖሊስ አታመለክቱም ሲሏቸው ኧረ ድምፅ ቀንስ…።
"…ሌላ አንድ ልጨምርላችሁ። አሁንም ከወደ ጉራጌ ክልል የ1 ቤተሰብ አባላት የሆኑ አጎት አክስት ዘመድ ተጨምሮ ወደ 17 ያህል ሰው በኦነግ ሸኔ ታግቶ 17 ሚልዮን ብር ተጠየቀባቸው። ገንዘቡ እስኪሰባሰብ ድረስ ሁለት ሦስት ቀን ፈጀ። በመሃል አጋቾቹ ከታገቱት መሃል በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው የተባሉትን መርጠው አንድ ሦስቱን አረዱ። ሌሎቹ እንዳይታረዱ ቤተሰብ አጋቾቹን ጫካ ድረስ ሄደው አስረከቡአቸው። የሄዱት 4 ሰዎችም ታግተው ለእነሱም ተከፍሎ ተለቀው ወጡ።
"…የተለቀቁት በሙሉ ቀዬአቸውን ጥለው ወደ ተሰደዱ። ጉራጌው ለመፈናቀል 20 ሚልዮን ከፍሎ፣ ሦስት ሰው አሳርዶ ተሰደደ። አዲስ አበባ ለቅሶ ወደተቀመጡ የሟች ቤተሰቦች ጋር እኔ የማውቃቸው ሰዎች ለቅሶ ለመድረስ ሄዱ። የሟች ታላቅ ወንድም የብልፅግና አባል፣ የአቢይ አሕመድ የግል አምላኪ ነው አሉ። እናም ምን ቢል ጥሩ ነው። በቃ ኅዘን አናብዛ። ይሄ ሁላ የሚደረገው አቢይን እንዲጠላ ለማድረግ ነው። ዝም በሉ፣ ለሚዲያም አትናገሩ። ሃሌ ሉያ። ሌላም የምነግራችሁ የገረመኝ ነገር አለ። እቀጥላለሁ።
• ፍርሃታችን ግን የጤና ነው…?
"…ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ። ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፥ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ። ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤” 1ኛ ተሰ 5፥ 14-16 “…ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።” 1ኛ ቆሮ 14፥40
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…በዛሬው ርእስ አንቀጼ ላይ 3 ሰው ብቻ 😡 ብው ብሎ ሳይ የገመትኩት ግምት ትክክል እንደሆነ አረጋገጥኩ። የቀደመው የርእሰ አንቀጽ ማስታወቂያዬ ላይ ስለ ጎጃም ፋኖ ተግዳሮት በስሱ እጽፋለሁ ብዬ ከለጠፍኩ በኋላ ወዳጆቼ የምላቸው እንኳ በውስጥ መስመር መጥተው "ተው ዘመዴ ትንሽ ብታቆየው መልካም ነው" ብላ ብላ ብለው ስጋታቸውን ገልጸውልኛል። የስኳድን ጫጫታ አስታውሰው ፈርተው እኮ ነው። ደግሞም የጎንደሩን ስኳድ የባዶ በርሜል ቋቋታና ጩኸት አይተው ስለሆነ አይፈረድባቸውምም።
"…እኔ ግን ኬሬዳሽ። ጥፋ ከዚህ፣ አምልጥ ብዬ አብሪ ጥይቴን በጎጃም ፋኖ ውስጥ በተሰገሰጉት ሾተላይ የፖለቲካው አገው ሸንጎ ኃይል ላይ ተኩሻለሁ። የጎጃም ዐማራ ፋኖ ነን ብለው ከብአዴን ፖሊስነት በቀጥታ ፋኖ ሆነው በፋኖ ስም ዘረፋ ላይ የተሰማሩትን እንደማልፋታቸው አሳውቄአለሁ። የግለሰብ መኪኖችን ዘርፎ፣ ቀምቶ የሚያስለቅስና የዐማራ ፋኖን የሚያሰድብ ቆዳ የቀየረ የብአዴን ፋኖን ስፋታው ታየኝ እኮ።
"…የእኔ የፊልድ ማረሻው የዘመዴ ሓሳብ ይኽ ያነበባችሁት ነው። እናንተም ደግሞ የጎደለውን ሞልታችሁ፣ የጠመመውን አቅንታችሁ፣ የበዛ ካለ ቀንሳችሁ የራሴ የምትሉትን ሓሳብ ስጡበት… ✍✍✍
ተቀበል…
• ቪድዮውን ሳየው…
"…ከላይ ከኤርትራ፣ ከጎን ከሱዳንና ከግብፅ፣ ከኬኒያም፣ ከሱማሊያም፣ ከጅቡቲም፣ ራቅ ሲል ከኤምሬት፣ ከሳኡዲ፣ ከኢራንና ከቱርክ፣ ከእስራኤልም፣ ከቻይና፣ ከሩሲያ እና ከአሜሪካም ጭምር፣ ከጀርመንም፣ ከእንግሊዝም፣ ከስዊድንም፣ ከኖርዌይና ከፈረንሳይም፣ ከጣልያንም ምንም ዓይነት የድሮን፣ የስንቅም፣ የቁጢም፣ የትጥቅም ድጋፍ የማየገኝ፣ የማይሰጠውም የዐማራ ፋኖን ትግልን ይመስላል።
"…ጠልቆ ይወጣል። ወድቆ ይነሣል፣ ከላይ ከፈጣሪ፣ ከታች ከነፍጡ በቀር የሚተማመንበት፣ የሚመካበት አጋዥ፣ ደጋፊ የለውም። ከራሱ ጀግንነት፣ ስንቅና ወኔ፣ ትጥቁን ከጠላቱ ከወያኔና ከሸኔ፣ ተረክቦ ይፋለማል። በቃው ሞተ አበቃለት፣ ቀበርነው፣ አሰጠምነው ስሊቱ እሱ እቴ በጀርባው እየቀዘፈ በውኃው ላይ ፈልሰስ ብሎ ይሳንፈፋል።
"…በ56 ዓመቱ እናቱ ቤት ተጎልቶ እየተቀለበ የሚኖር የግብዳ ሕፃን ፈሪ፣ ሲያንኮራፋ ውይ ልጄን ቀስ በል የሚባለው ሁሉ እኮ ነው ዛሬ በዜሮ ተፍጨርጭሮ ተነሥቶ አገዛዙን ከዓመት በላይ የሚያንቀጠቅጠውን የዐማራ ፋኖ ለመተቸት የሚንጠራራው። መጀመሪያ ከእናትህ ቤት ውጣ። ራስህን ቻል።
"…ዐማራ በምድር የሚደርስለት እንደሌለ ስላወቀ ለህልውናው ሲል የዳንኤል ክብረትን የጊንጥ ስድብ ችሎ፣ የዳንኤል ክብረትን የጊንጥ ፍረጃ ተከትሎ ዐማራውን እንደ ሩዋንዳው በረሮ ለመጨፍጨፍ የተዘጋጁትን ሁሉ ለመመከት ቆርጦ የተነሣው።
ወዶ የገባ ሰው ከባህር ከውኃው
ዋኝቶ ይውጣት እንጂ ሌላ ማን ሊረዳው… አለ አዝማሪው።
"…ዐማራ ማለት እንዲህ ነው የሚታየኝ። ሳትደግፈው፣ ቤሳ ሳንቲም ሳትረዳው፣ ድምጽም ሞራልም ሳትሰጠው ልተችህ አትበለው። ዕድሜ ለአስታጥቄ።
• አይዞኝ ወጥር ዐማራ…! ጩጬው መጨረሻ ላይ ሲስቅ እይልኝማ። የመጨረሻውን ሳቅ የምንስቀው እኛ ነን ያለው ማን ነበር?
ተቀበል…
"…በዚህ ዘመን በቲክቶክ መንደር መኖር መመላለስ መንከላወስህ ካልቀረ በመንደሩ ውስጥ ማየት፣ መስማት፣ መከታተል የምትፈልጉትን መምረጥ መብቱ የእናንተ ነው። ማንም አያስገድዳችሁም።
"…ደስ የሚለው አሁን አሁን የሚገራርሙ ዐዋቂ ሲናገሩ አእምሮን የሚቆጣጠሩ፣ ሰቅዘው የሚይዙ አስደማሚ ዐማሮችን በመንደሩ ውስጥ እያየሁ ነው። እስከዛሬ ተደብቀው ከቆዩበት ጎሬ ወጥተው ሜዳ መንደሩንም እየተቆጣጠሩት ነው። እነዚህን አንደበተ ርቱዕ ዐማሮች ሲመጡ እንደኔ ያለው ተብታባ ማይም ሳይድ በግዱ ይደበቃታል።
"…ወዳጄ አባ አቢዲ እንደፍየል እንዲባልግብህ መፍቀድ መብትህ ነው። ያውም 2,400 ሰው እኮ ነው ዘጭ ብሎ የሚያየው። 😂… ማየት ብቻም አይደለም ለዚህ ለኢንተርኔት የቲክቶክ ላይ ጋለሞቶች ከክሬዲት ካርዱ ላይ የ500 ዶላር አንበሳ ጭሮ ሁሉ ያወርዳል። አባቴ… ቲክቶክ ላይ በዮኒ ማኛ አክሮባት መደመምም መብትህ ነው። በሞጣ ቀራንዮ ሽንጥና ዳሌ መረጣም መፍዘዝ፣ በሰገራ አፉም መግማት መግማማት መብትህ ነው። በእነ አኪላ ተኪላ ቮድካ ወሬ መስከርም፣ መጠንበዝም መብትህ ነው። መብትህ ነው አልኩህ።
"…ጭራሽ ዘመነ ሞተ፣ ፕሮፌሰር ሀብታሙን ልደቱ ከሰሳቸው፣ ጌታ አስራደ በዋና ጣናን አቋረጠ ተብሎ በእነ እስኳድ አቧራ ሲጨስ ዐማራ ሆዬ በቲክቶክ የሚገርም መረጋጋት ውስጥ ገብቶ ስለ ቀጣዩ የፋኖ አንድነት ነው የሚያወራው።
"…የገባኝ ነገር አሁን አሁን እንደ ድሮው በዐማራ ስም፣ በአማርኛ ቋንቋ ጎንደርና ጎጃምን ማጣላት፣ ወሎና ሸዋን ማባላት አይቻልም። ካካ ነው፣ እፉ ነው።
"…አሁንማ የትግሬ ነፃ አውጪዎች እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ሳይቀሩ በራሳቸ በትግርኛ ቋንቋ እና በላቲንኛ ቋንቋ መጻፍ፣ መደስኮር ትተው ሙሉ ሰበካቸውን በአማርኛ አድርገውት አረፈውታል። 😂
• አይገርምላችሁም…?
ተቀበል…
• ትዝብት
• ትዝብት ፩
"…ድሮ ድሮ የሆነ ቄስ ሲሰክር አየሁ ብሎ እምነቱን የሚቀይር በሽ ነበር። የትየለሌ። አሁን ግን ሞኝ የለም። ቆሻሻው ሰውየው እንጂ እምነቱ እንዳልሆነ በማወቁ ሰው አይሞቀው አይበርደው። ተናንቆ ልክ አግብቶ እምነቱን ያጸናል። ለሌባ ቄስ፣ ለዘራፊ እንትን መቅደሱን ትቶ የሚሰደድ የለም። ቀጥሎ ዥራፍ ነው።
• ትዝብት ፪
"…ድሮ ድሮ ዐማራን ለመሸወድ በጣም ቀላል ነበር። ፌስቡክ ላይ፣ ወይ ዩቲዩብ ላይ፣ አሁን ደግሞ ቲክቶክ ላይ በኤዲቲንግ መቀስ ኃይለኛ ቀዶ ጥገና የተደረገለት የሆነ አጀንዳ ትፈጥርና ነጠላ አዘቅዝቀህ ስታላቅሰው ትከርም ነበር። በጣም ቀላል ነበር። ዮኒ ማኛ እንዲህ ብሏል፣ ሞጣ ተናግሯል ብሎ የሚያመነዥከው የትየለሌ ነበር። አሁንስ? አሁንማ ወፍ የለም። የፈለገ አጀንዳ ቀርጸህ ብትበትን ዐማራ አይሰማህም። መልስ እንኳ አይሰጥህም።
"…ፕሮፌሰር ሀብታሙን በተመለከተ ሰሞኑን ለተነሣው አቧራ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አቀሳሳሪዎች እነ ተብታባው ሞገስ ዘውዱ ሳይቀሩ ለወሎዬው ልደቱ አያሌው ተጨነቀው ሲንበጫበጩ፣ ሲያቀሳስሩ ውለው ሲያድሩ ዐማራው ሆዬ ኬሬዳሽ ብሎ ምንም እንዳልተፈጠረ አጀንዳውን ኢግኖር ሲገጨው ነው የአየር ላዩ ዐማራ ፍጹም መቀየሩን ያረጋገጥኩት።
ልጨምርላችሁ…
"…እኔን በተመለከተ አንድ ለውባንተ ሞት ተጠያቂዎቹ ፋፍህዴን የጎንደር ስኳድ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ ናቸው ያልኩትን ቆርጠው፣ ሌላው ዘመነ ሞተ፣ ዘመነ ሞተ የምትሉት ዘመነ ቢሞትስ የሚቆም ትግል ያለ መስሏችሁ ነው ወይ? ዘመነ ሰው ነው አይደለም ውጊያ ላይ ያለ ታጋይ በትንታም ይሞታል ያልኩትን ይዘው ዘመነ ሞተ አለ ዘመዴ ብለው የበተኑትን ዐማራው ኢግኖር ገጭቶ ድካማቸው ላይ በረዶ ቸልሶ ሳየው ተደመምኩኝ። አጀንዳ ኖ? ኤለም።
• እናንተስ ምን ታዘባችሁ…?
ተቀበል…
ሰይፉ ይልማ
እንደ ዥዋዥዌ ሆኗል ነገሩ፣
ካይሮና ዱባይ ነው ውሎና አዳሩ፣
UNን ሲጠጋ ብሪክስ ይታየዋል፣
ብሪክስን ሲጠጋ UN ይታየዋል
ወይ ደሞዝ አልጨመረ ወይ ዝም አላለን
በመንታ ምላሱ አርጎ አወናበደን።
እኔ
እሱ ግራ ገብቶት እኛን ግራቀኝ አጋባን 😂
ተቀበል!
መልካም…
"…ዛሬ ዕለቱ ዕለተ ቀዳሚት ሰንበትም አይደል…? አዎ… እነደዚያ ነው። ቅዳሜ ከሰዓት ታዲያ በቤታችን በጉጉት በናፍቆት የሚጠበቅ ለየት ያለ መርሀ ግብር ነው ያለን። ግጥም፣ ቅኔ፣ ቀልድ፣ ነቆራ፣ ፉገራ የበዛበት ረሀ የሆነ መርሀ ግብር ነው።
• እሱም ምንድነው…?
"…የሜጀር ጀነራል ውብአንተ ልጅ የሜጀር ጀነራል ውብአንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ተመስገን ውብአንተ አባተ ይናገራል።
"…ውብአንተ የተሰዋበትን የዐማራ ፋኖ በጎንደርን ለእስክንድር ነጋ አሳልፎ በመስጠት በፋፍዴን ቁጥጥር ስር ለማድረግ ለሚዳክሩት ለአባቱ ገዳይ አስገዳዮችም መልእክት አለው።
"…የጎንደር ፋኖ ለምን መስቀል በደረቱ ላይ አደረገ ብሎ እያበደ ያለው የጠንቋዩ ልጅ ፓስተር ምስጌም እንዲያዳምጠው ላኩለት። ፍናፍንቱ አያሎ መንበሬም ቢሰማው አይከፋም። የወልቃይት የሰሊጥ ቦለጢቀኞች ስሁላውያን የፖለቲካው ቅማንት ዐማራ መሳይ ጆፌ ዐሞራ የትግሬ ዲቃሎችም ቢሰሙት ይፈወሳሉ።
"…ሙሉውን መልእክቱን እሁድ ምሽት በመረጃ ቴቪ ሳምንታዊ የነጭ ነጫ ብርግራሜ ጠብኡኝ። በነገራችን የቲክቶክ ዐማሮች እያኮራችሁኝ ነው። አጀንዳ መቀበል ቀረ። የጠንቋይ ልጆች ፀረ ዐማሮቹ ማዕተብ በጣሾቹ እነ ምስጌ ተላልጠው አጀንዳ ብለው ይመጣሉ አዳሜና ሔዋኔ ኢግኖር ገጭቶ ጭራሽ አስደማሚ የዐማራ ታሪክ በቲክቶክ ሌክቸር ይኮሞኩማል። ይሄ ነው መብሰል። ይሄ ነው አንደኝነት። ይሄ ነው መቅደም።
"…በዐማራ ስም አጁዛው ሁሉ ቢንጫጫ አትስሙት። መርካቶ ተቃጠለ፣ እስክንድር ተነነ፣ አፍራሰ መነነ፣ ዋቅጅራ ጎፈነነ፣ አኪላ ቀረነነ፣ አያገባህም። ኢግኖር ግጨው። ወዳጄ የራስህን አጀንዳ ፈጥረህ እንደ ዶክተር ሀብታሙ፣ እንደ ጋሽ ተክሌ ፒፕሉን አንጫጫ። አለቀ።
"…ሌሊቱን ይሄን እየሰማችሁ እደሩ። የነገ ሰው ይበለንና ከምስጋናው በኋላ መንደራችን እንቀውጠዋለን።
"…አንተ የሞትክ ደግሞ ናና "ዘመዴ ዘመነ ሞቷል ያልከው እውነት ነው እንዴ?" ብለህ አዝገኝ አሉህ። የማትረባ። የእኔ ልጆች፣ ጓደኞች፣ ወዳጆች በቲክቶክ መቀሶች አጀንዳ መደንገጥ ሳይሆን መሳቅ ነው የጀመርነው።
• እየሰማችሁ በሰላም እደሩልኝ። 🖐🖐🖐
👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ዛሬ ምንም ለውጥ ባናመጣ እኔም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ በቀጣይ በቴሌቭዥንም ሆነ በቴሌግራም ገጼ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ነውር፣ ዘረፋና ሌብነት፣ ሴሰኝነትም ሁሉ ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እጀምራለሁ። የሰው ልጅ እንዴት እንደሚሸጥም አሳያችኋለሁ። ሌሎች ሌሎች ነውሮችንም በይፋ በማቅረብ ሰው ባይቀጣቸው፣ እነሱ ባይፈሩ፣ ባያፍሩ ወዳጅ ዘመድ ያፍርባቸው ዘንድ በይፋ እንተጋተጋለን። ጥቂቶች እንዴት ምእመናን በሚሰጡት የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ በሸነና እንደሚሉ፣ ግንባታቸውን ሁሉ ከነ ሞዴላ ሞዴል መኪኖቻቸው እንደመምባቸዋለን። ትግሬና ኦሮሞ ገጥሟል። ዐማራ ፈዝዟል። እሱንም እናያለን።
•ትግራ -አክሱም
"…በትግራይ ከማእከላዊው መንግሥት የተገፋውን ህወሓትን ተከትሎ ጫካ ገብቶ የነበረው የትግራይ ቤተ ክህነትም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በይፋ መለየቱንና የራሱን የጨረቃ የጨበራ ሲኖዶስ ማቋቋሙንም በትናንትናው ዕለት በይፋ አሳውቋል። በኦሮሚያ አጋሮቻቸው ቀድሞ የተነሣውና ለጊዜው ደም አፋስሶ ሴራው የከሸፈበት ቡድን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ከተመለሰ በኋላ በዚያው በኦሮሚያው መንገድ ሄዶ የጳጳሳት መዓት በመሾም በትግራይ እንደ አሸን ያፈላውና ያፈሰሰው የትግሬው ከሳቴ ብርሃን መንበረ ሰላማ ቡድን እነ አባ ሰራቂን የመሰለ የኢትዮጵያና ዐማራ ጠል መናፍቅ ፀረ ማርያም ግለሰቦችን ይዞ የራሱን የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋሙን በመግለጫ ጭምር አረጋግጧል። ይሄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "ጣልቃ ገብነቷን ታቁምልኝ" ሁላ ብሎ ሲወበራና ትኩረት ፍለጋ ሲላላጥ ውሏል።
"…በፖለቲካው ቢሮክራሲ በኩል ከሀገረ ኢትዮጵያ ያልተገነጠለችውና አሁን ድረስ በጀት ከማዕከላዊው መንግሥት የሚመደብላት፣ ስልክና ባንክ፣ መብራትም፣ ደሞዝም ጭምር ከኢትዮጵያ የሚላክላት፣ ያለ እርዳታ ሕዝቧ መላወስ መቆየት የማይቻላት፣ ትርፍ አምራች ያልሆነችውን ትግራይን በሃይማኖቱ በኩል አዲሶቹ የትግራይ የጨረቃ ጳጳሳት ከፖለቲከኞቹ በፊት አስቀድመው በይፋ ትግራይን እንደ ሀገር በመቁጠርና በመጥራት በይፋ ከኢትዮጵያ መገንጠሏን እና መለየቷን ዐውጀዋል። ይሄን የሚቃወም አንድም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ የዋናው ሲኖዶስ ድምጽ የለም። ኦሮሞዎቹ ላይ እንደተያዘው አቋም በእነዚህኞቹ ላይ ግን አልተያዘም። እነ አቡነ ሳዊሮስ በአንድ በኩል እውነት አላቸው። የሚያስቀው ነገር ትግራይ ቤተ ክህነት ተብሎ በተቋቋመው አካል በኩልም አሁንም ድረስ ደሞዝ ከአዲስ አበባ የሚበሉ፣ እዚህ አዲስ አበባም ሆነው ደሞዝ የሚበሉ፣ ሁለት ቤት ያላቸው ሰዎች መኖራቸው ነው። ዐማራ ጉራጌ እና ሌላው ኦሮሞ ወላይታው በሚያዋጣው የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ እነ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ መሻኮታቸው ሳያንስ የትግሬ ነፃ አውጪዎችና ኦሮሞዎቹ በሃላል ሲራኮቱ እንደማየትም የሚያሳፍር ምን ነገር አለ? ቆይ ግን ምጸዋት መስጠቱ ቢያቆም ምን ሊውጣቸው ነው? ለካህናቱ የንስሀ ልጆቻቸው ደሞዝ እየከፈሉ ብሩ ቤተ ክህነት ሳይገባ አገልግሎቱ ቢቀጥል በምን ሊደባደቡ ነው? አስቂኝ እኮ ነው።
"…ይሳካላቸው አይሳካላቸው ባላውቅም ትግሬዎቹ እና ኦሮሞዎች አዲስ ሀገረ ግንባታ ላይ እንደሆኑ ይሰማኛል። በትግሬና በኦሮሞ ፅንፈኞች በኩል የሚታየው፣ የሚሰማውም ኢትዮጵያ ጠልነት፣ ሰንደቅ ዓላማ ጠልነት ወዘተ የመሳሰሉት ነገራት እየታዩም ቢሆን ዐማራውም ሌላውም ሕዝብ በዝምታ በአርምሞ መመልከቱን ቀጥሏል። የጎንደሩ ፀረ ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ፣ የፖለቲካው አገው ሸንጎ አፍቃሬ ኦሮሞ ወትግሬ ዲቃላው አገው ሸንጎ ዐማራውን እንደ ነገድ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደተቋም በሁለመናው ሽባ አድርገው ለአስገድዶ መደፈር እያዘጋጁ ይገኛል። በሩሲያና በዩክሬን ጦርነት እየተጎዱ ያሉት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። በሶሪያ ጦርነት የወደሙት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። በኢትዮጵያም ታርጌት የተደረገችው ታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። በጁንታው ጦርነት ከትግሬም፣ ከዐማራም የተፈጁት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። ደፈር ተብሎ መወያየት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልተጀመረ ነገርየው ደስስ አይልም። ትግሬው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና ኦሮሞው አቡነ ሄኖክ እኮ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያነሣን ከሆነ አዲስ አበባን ይዘን እንገነጠላለን እስከማለት የደፈሩት ከኋላ የልብ ልብ የሚሰጣቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ስላለ ነው።
"…እደግመዋለሁ ጳጳሳቱ ሁላ የሚጣሉት በምእመናኑ የአስራትና የሙዳየ ምጽዋት ብር በስለት ገንዘብ ጭምር ነው። ጠላ ጠምቃ፣ እንጨት ተሸክማ፣ አረብ ሀገር ተቃጥላ፣ ጉሊት ሽጣ፣ ከመንግሥት ደሞዙ፣ ከንግድ ሥራው ከልጆቹ ሆድ ቆጥቦ ለእግዚአብሔር በሚሰጠው ብር እኮ ነው እንዲህ የሚፎገሉት። እንዲህ የሚተራመሱት። ዘግናኝ ነው። የሲሲሊ ማፍያዎች እንኳ እንዲህ ጨካኝ ናቸው ማለት ያስደፍራል። ሦስት፣ ሁለት ቦታ ደሞዝ የሚበሉ። የቤተ ክርስቲያን መሬትና ሀብት በድፍረት የሚሸጡ፣ ቤተሰቦቻቸውን በየቦታው የሚቀጥሩ። ታሞ በፈቃድ ላይ ባለ ካህን ምትክ ሞቷል ብለው ማስታወቂያ አውጥተው የሥራ መደቡን በቁሙ የሚሸጡ፣ በዝውውር ሰበብ ሚልዮኖችን የሚሰበስቡ፣ ለቤተ ክርስቲያን ይሰጥልኝ የተባለ ኮንዶሚንየም ቀርጥፈው ሽጠው የሚበሉ፣ የራሳቸው ሙዳየ ምጽዋት ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ አስቀምጠው በኪሳቸው የሚያስገቡ፣ የሥዕለት ብርና ወርቅ ተሸክመው ወርቅ ቤት ለወርቅ ቤት ለመሸጥ የሚዞሩ። ባለ ፎቆች፣ ባለ ቪላዎች፣ ባለ ዘመናዊ የሚልዮን ብር የመኪና ባለቤቶች ሁሉ የሚጋደሉት በሙዳየ ምጽዋት ብር መሆኑ ነው።
"…የሚገርመው ግን ሁሉም ጤና የላቸውም። በቤታቸው ሰላም የላቸውም። ብሩን ዘርፈው አከማችተዋል ጤና ስለሌላቸው ግን ሀኪም እና ኪኒና ላይ ይጨርሱታል። የሙዳይ ምጸዋቱን ብር አይን አይኑን እንዳዩት ሳይበሉም፣ ሳይነኩትም እንዲሁ እንደ ጓጉ ያልፋሉ። ያርፋሉም። ሁሌ መድኃኒት እንደቃሙ ነው። መርፌ እንደተወጉ ነው። ችግር ድኅነት በስፍራው ላይ እንዳስቀመጣቸው ያውቃሉና ለሃይማኖት ብዙም ግድ የላቸውም። ዘወትር የቴዲ አፍሮን ካሴት እያስከፈቱ እያንጎራጎሩ የሚሄዱ አባት ቢያንስ አንድ ሃይማኖቱን የሚንቅ፣ ኋላም የሚመነፍቅ ነፍስ አፍርተዋል። አሁን ይሄን ሹፌር ዘፈን ኃጢአት ነው ብትሉት በምን ይሰማችኋል። እኒህ ሲሞቱ ወራሻቸው ሌላ ነው። የማይወልዱት፣ የማያገቡት፣ ሞቻለሁ ብለው የተገነዙት ገንዘቡን አከማችተው ይዘው በህጋዊ ጋብቻ በተቀደሰ ትዳር ልጅ አፍርተው የሚኖሩትን የካህናት ኑሮ አመሰቃቅለው፣ አመድ፣ አፈርም በትነውበት የሰበሰቡትን ብር ሳይበሉት ሴት ወይዛዝርቶች ተከፋፍለውት ያርፋሉ።
"…እኔ የምሰጋው፣ የምፈራውም በትግሬዎቹ አባቶች ጋጠወጥነት እያሳዩ ባለውም ድፍረት የተነሣ ዐማራውም እንደ ትግሬዎቹና ኦሮሞዎቹ ተማርሮ፣ መሰደብ፣ መገፋቱ በዝቶ፣ እኔም የራሴን ሲኖዶስ እመሰርታለሁ እንዳይል ብቻ ነው። አገዛዙም እየሠራ፣ እያበረታታ ያለውም እሱን ነው። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማስተሳሰር ከከረሙት ገመዶች መካከል ሁሉም ተበጣጥሶ አሁን የቀሩት በዋነኝነት ሁለት ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናቸው። አየር መንገዱም እየተንገታገተ አለ። ቤተ ክርስቲያኒቱም በትግሬና በኦሮሞ ፅንፈኞች እየተወቀረች አለች።
• ለዛሬ ይብቃኝ…!
•••
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 15/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!
"ርእሰ አንቀጽ"
"…በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ በትግራይ እና በአዲስ አበባ ሁለት ገራሚ ለአቅመ አጀንዳነት የሚበቃ ዜናዎች ሲንሸራሸሩ ውለዋል። የአዲስ አበባው የጉልበተኞች፣ የአገዛዙ ማፍያ ካድሬዎች፣ ዘመን መጣልኝ፣ አኬር ቆመልኝ ባይ ባለጊዜዎች በአምስት ኪሎ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጊቢ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የታየ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በትግራይ አክሱም ከተማ ራሱን አቴንሽን፣ ትኩረት ፍለጋ የሚያላልጠው የትግሬው "መንበረ ሰላማ" ወደ ሲኖዶስነት አድጌአለሁና ሀገር ይወቅልኝ ብሎ ሲንበጫበጭ የዋለበት ነው። ሁለቱንም በስሱ ለማየት እንሞክራለን። ሙሉ የድምጽና የምስል መረጃዎችን በዕለተ እሁድ ምሽት 2:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ላይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። አሁን ከአዲስ አበባው እንጀምር።
"…ጥቅምት 12/2017 ዓም በጸሎት የተጀመረው የወርሀ ጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ አዲስ ቅጥር፣ የሠራተኞች እድገት እና ዝውውር፣ ከመደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሌላ ወጪ እንዲቆም በመወሰን፦1.ቡፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ 2.ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስና 3.ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ከ4 ተጨማሪ ሊቃውንት ጋር በመሆን ችግሩን በዝርዝር በማጥናት ለግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲያቀርቡ በመወሰን የዕለቱን ስብሰባ ማጠናቀቁም ተነግሯል። ትናንት በቪድዮ የተደገፈ የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ከቀረበ በኋላ በእንባ፣ በቁጭት፣ በንዴት ሲላቀሱ ያመሹት ብፁዓን አባቶች መሽቶ ከነጋ በኋላ በዛሬው ዕለት በዝምታ ተውጠው ማሳለፋቸው ተሰምቷል። ዛሬ ለሲኖዶሱ መልስ እንሰጣለን ብለው በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሚመራ 19 የሀገረ ስብከቱ ሰዎች ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሄዱ የተነገረ ሲሆን 19ኙም ቢገቡ ቦታም ስለማይበቃ ተብሎ 14ቱ እንዲገቡ እንደተፈቀደላቸውም ተሰምቷል።
"…ከ7 ክፍለ ከተማ የተሰበሰበ ከቤተ ክህነቱ የወለድ ተቀማጭ የተወሰደ ነው የተባለ 20 ሚልዮን ብር ወጪ አድርገው ምሽቱን በየሊቃነ ጳጳሳቱ ቤት እየዞሩ ብር ለሚያስፈልጋቸው አባቶች ሲበትኑ እንዳመሹ የሚነገርላቸው የአዲስ አበባው የሀገረ ስብከቱ ማፍያ ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማው ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሩፋኤል አስተባባሪነት፣ በጎደሩ ባለ ጊዜ ኦሮሞ ነኝ ባይ ዳዊት ሮቶ፣ በሀገረ በቀለ፣ በሥራ አስኪያጁ የማነ፣ በቦሌ መድኃኔዓለሙ ስኳድ በበቃሉ እና በሸጎሌ ኪዳነ ምሕረቱ አለቃ አማካኝነት በግንባር ቀርበው ለቅዱስ ሲኖዶሱ ምላሽ መስጠታቸውን የደረሰኝ ሙሉ የድምጽ መረጃ ያመለክታል። ድሮ ድሮ በሁሉ ቦታ በእድር ዳኝነት፣ በታክሲ ተራ አስከባሪነት ሁሉ ከፊት ትግሬ ይቀድም እንደነበረው ሁሉ አሁን ደግሞ ጊዜው የኦሮሞ ነው በሚል ሁሉን የመቅደም መብት ለኦሮሞ ነኝ ባይ በመሰጠቱ በዚሁ አግባብ ከሁሉ ነገር ፊት ከፊት የሚቆመው ባለ ጊዜ ነኝ ባዩ የጉደሩ ዳዊት ሮቶ በድፍረት አፉን እየከፈተ እንደ ብራቅ በብልግና ጠባይ ሲጮህ መዋሉ ነው የተሰማው። አጀንዳው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የቀረበን የሙስና ጉዳይ አጣርቶ እንዲያቀርብ በሲኖዶሱ የተወሰነ ጉዳይ ቢሆንም ጋንግስተሮቹ ግን ወቅቱ ዐማራን የመውቀሻ፣ ከዐማራም ጎጃም ዐማራን የማዋረጃ ዘመን ነውና እንጠቀምበት በማለት በማይመለከታቸው ጉዳይ ባህርዳርን ከተማንና እና ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ሲያዋክቡ መዋላቸው ነው የታየው። በበቀደም ዕለቱ የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ ይታይ በነበረው ዶክመንተሪ እና የተጎጂዎች ምስክርነት በቪድዮ እያዩ ሲያለቅሱና ሲያዝኑ የነበሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም በትናንትናው ዕለት በነበረው የጋንግስተሮቹ የመልስ ምት ወቅት አንደበታቸው እንደ ዲዳ ተለጉሞ፣ በአርምሞ ጸሎት ላይ እንዳለ ባሕታዊ በዝምታ ተውጠው እንደ ቆረበ ሰው አፋቸውን ሸፍነው ማሳለፋቸው ነው የተነገረው። የተሰማውም።
"…በግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ እነ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል "በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰው እየተሸጠ ነው። ሙስናው ዘግናኝ ነው። ይሄ መንፈሳዊ ጉባኤ አንድ ውሳኔ ወስኖ ይውጣ" ብለው ሁሉም በሊቀጳጳሱ አቤቱታ ላይ ስምም ሆነው አጀንዳውን ለመያዝ ፈቃደኝነታቸውን ሲያሳዩ በወቅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ነበሩ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣናቸውን ተጠቅመው በአቡነ ሄኖክ የሚመራውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ "ሌላ ጊዜ እናየዋለን፣ አሁን በሌሎች አጀንዳዎች ላይ እንነጋገር" በማለት በአጀንዳው ላይ ቀዝቃዛ ውኃ ቸልሰው የሀገረ ስብከቱን መከራ እንዲራዘም ያደረጉት። ትናንት ግን ብፁዕ አቡነ አብርሃም ብቻቸውን ቀሩ። የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተጀመረ ዕለት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ "ቅራኔ ስላለን" ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጉባኤውን መምራት የለባቸውም። ጉባኤውን ቅዱስ ፓትርያርኩ ራስዎ ይምሩት ብለው ተቃውሞና ግርግር በማንሣታቸው ምክንያት ቅዱስ ፓትርያርኩም እኔ አርጅቻለሁ፣ ከመሩም ሥልጣኑ የአቡነ አብርሃም ነው። እንዴ ለምን ብለው? ለመሟገት ቢሞክሩም ጫናው ስለበዛ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከጉባኤው መሪነት እንዲገለሉ ተደርጎ በምትካቸው ቅዱስ ፓትርያርኩና አባ ያሬድ ጉባኤውን እንዲመሩ መደረጉም ነበር የተሰማው። ትናንት ግን የባሰ ባይተዋርነት እስኪሰማቸው ድረስ ሲዘለፉ መዋላቸው ከምር ብዙዎች ከጉባኤው በኋላ በግሌ ነግረውኛል። ለእኔ የምትነግሩኝን ለምን እዚያው አትናገሩም ስላቸውም "እዚያ ለመናገር ደግሞ ሌላ ችግር አለ" ነው መልሳቸው የብዙዎቹ።
"…ከትግራዩ ጦርነት መልስ በተካሄዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባዎች ላይ አቡነ አብርሃምን በግልጽ ፋኖ፣ ሌሎች ከዐማራ ወገን የመጡትንም በማንነታቸው በማሸማቀቅ ይታወቁ የነበሩት የጋምቤላው ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በትናንትናው ጉባኤ ላይ በአንፃራዊነት የሰከኑ እንደሆነ ሲነገር፣ በእሳቸው ምትክ ኦሮሞዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኦሮሞም የደራ አማራው እና በቅርቡ ኦሮሞ ነኝ ብለው በኦሮሙማ የተጠመቁት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጨረቃ ጵጵስናው ወቅት ሾመዋቸው ዕርቅ ሲፈጸም ውግዘታቸው ተነሥቶላቸው በፖለቲካዊ ውሳኔ ጵጵስና የተቸራቸው አዲስ ገቢዎቹ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና አቡነ ኤጲፋንዮስ ሲወበሩ መዋላቸው ነው የተሰማው። ከስብሰባው ቀደም ብሎ የኦሮሙማው የፌደራል ፖሊስ አዛዥ መርደረሩ ደምመላሽ ገብረ ሚካኤል ብፁዓን ሊቃነጳጳሳቱን ተራ በተራ ወደ ቢሮው እያስጠራ የሰው መሸጥ፣ መለወጥ፣ የባርያ ንግድ ክስ የቀረበባቸውን የወለጋ ተወላጁን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከቱን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ለማንሣት መሞከር ክፉኛ ከመንግሥት ጋር እንደሚያጣላቸው መናገሩና ማስፈራራቱም በሌሎች ሚዲያዎች ተዘግቦአል።
"…ይሄ ማስፈራሪያ በቂ አይደለም ያሉት የደቡብ ጎንደሩ የስኳድ ተወካይና የቦሌ መድኃኔዓለሙ ዋና ጸሐፊ አቶ በቃሉ ልክ በዘመነ ህወሓት ጊዜ ህወሓት ታደርገው እንደነበረው ሁሉ አሁንም እንደዚያው ማድረግ ይኖርብናል። ጳጳሳቱ ሲበዛ ራስወዳድና ፈሪ ናቸው፣ አንዳንዶቹ ልጆች አሏቸው፣ ለልጆቻቸው ሲሉ በሕይወት መቆየት የሚፈልጉ አሉ። በድህነት የኖሩ ስለሆነ አሁን ካሉበት የምቾት ዞን ሊወርዱ አይፈቅዱም። እምነት ያላቸው ጥቂቶች ናቸው። እናም በየቤታቸው ተገብቶ ፈሪውን በማስፈራራት፣ ደካማውን በማሸማቀቅ፣ ተገዳዳሪውን ከ20 ሚልዮኑ ላይ በመቦጨቅ፣ በጣም አክራሪውን ከፍ ሲል በመጎሸም ልክ እናግባቸው በማለት ከኦሮሞ ደኅንነቶች ጋር በዋዜማው…👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይደለምን? ” 1 ዜና 22፥18
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ሌላው…
"…ሌላው ደግሞ አሁን እየበለፀገችዋ ነው ተብሎ በሚነገረን አዲሲቷ ኦሮጲያ ኢትዮጵያችን "መዋጮ" የሚባል አዲስ ኪስ ማጠቢያ መቅሰፍት በዝቷል፣ መጥቷልም አሉ። ብዙ ሰው ትንሽ ትንሽ እየተማረረ ነውም አሉ። በተለይ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልሎች መዋጮ ጠያቂው እንደጉድ ነው የሚተራመሰው ሁላ አሉ። አንደኛው ቀበሌ እየጠየቀ ሌላኛው በር ላይ ቆሞ ተራ ይጠብቃል አሉኝ። ወረፋ ነው አሉ መዋጮ። 😂
"…ቦታው የት እንደሆነ ረሳሁት እንጂ አስፋልት ላይ ለቆመ የመንገድ መብራት ሁላ ከቀበሌ ነን ያሉ አካላት መጥተው "ለመብራቱ ክፈሉ" መዋጮም አውጡ ተብለናል ያለኝም ሰው አለ።
"…እምቢ ካልክ ደግሞ እዚያው ቆሞ "ቤትህን ኖ ማፈርሶ" ይልሃልም አሉ። ነጋዴው በተለይ መድረሻ ጠፍቶታልም ይላሉ አንዳንዶች።
• የመዋጮው ነገር እውነት ነው እንዴ?
• መዋጮው ለምን ለምንድነው…?
• ደረሰኝስ አለው…?
"…ለጠቅላላ እውቀት ብዬ ነው።
"…እሺ አሁን ደግሞ ሌላ ጨዋታ እናምጣ…
"…ታላቂቱን ሀገር እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ ጎትቶ እየፈጠፈጣት የሚገኘው የብልግናው አገዛዝ ከወርሀ ጥቅምት ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች በአዲሱ የደሞዝ ሥርዓት መክፈል እጀምራለሁ ብሎ ነበር አይደል…?
"ርእሰ አንቀጽ"
"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን በጥያቄ መልክ የሚቀርብ ነው። ጥያቄውም መጪውን ጊዜ በተመለከተ እንደ ሀገርም፣ እንደ መኖሪያ ክልላችሁም፣ እናንተ ጓደኞቼ የሚሰማችሁን ስሜት፣ ስጋትና ተስፋ ግምታችሁን በሙሉ የምታስቀምጡበት የመወያያ ርእሰ አንቀጽ ነው።
• እንደ ሀገር ኢትዮጵያን በተመለከተ
• እንደ ክልል መኖሪያ ክልላችሁን
• እንደ ከተማ መኖሪያ ከተማችሁን
• ወረዳችሁን፣
• ቀበሌአችሁን፣
• ሰፈራችሁን እና መኖሪያ ቤታችሁን ጭምር በተመለከ ወደፊት ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? እስቲ ስጋት ተስፋችሁን ጻፉ።
• ስለ ጋብቻ፣ ልጅ ወልዶ ማሳደግ፣ ቤት ሠርቶ፣ ሀብት አፍርቶ ስለመኖርስ ምን ዓይነት ተስፋ ይታያችኋል?
• በዚህ ሁሉ የኑሮ ውድነት ሳይጨነቅ፣ መጪው ጊዜም ሳያሳስበው ዘና፣ ፈታ እያለ የሚኖረው ጥቂት ሕዝብ የዚህ የደስታው ምንጩ ምንድነው? አደራ ኢየሱስ በቂው፣ አላህ በቂው ስለሆነ ነው እንዳትለኝ።
• ምንድነው የሚታያችሁ? ምንስ ነው የሚሰማችሁ…? ተስፋችሁንም፣ ስጋታችሁንም እስቲ ጻፉ። ወዴት እየሄድን ነው? የዚህ ምስቅልቅል መጨረሻውስ ምንድነው?
• ጻፉ እስኪ…✍✍✍
• በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የአምልኮ ያህል የግል ደጋፊ ናቸው በሚባሉት በሁለቱ አዲስ ገቢ ሊቃነጳጳሳት ከመስመር መውጣት ጉዳይ ጥቂት ማስታወሻ ልጻፍ አልጻፍ እያልኩ ተወዛገብኩ እኮ…?
"…ኧረ እረፉ በፈጠራችሁ። በምሽት በየቤቱ እየዞራችሁ መሳቂያ አትሁኑ። በአድማ የሚሆን ነገር የለም። ይሄ የኮሬ ነጌኛ ስብሰባ እኮ አይደለም? ኧረ ቀዝቀዝ። በቃ ዛሬ አጀንዳው ተሰማ አይደል? ጉዳዩ የሚመለከተው ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ሆኖ ሳለ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሰሙትና ባዩት ሪፖርት እንባ አውጥተው እያለቀሱ እያያችሁ እናንተ የምን እንዲህ መፈንዳት ልባችሁንም ማደደር ነው። ይሄ ምንም ከኦሮሞነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። በኦሮሞነት ከሄዳችሁም ኦሮሞዎቹ ሁሉ እኮ ናቸው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጋር የቆሙት። ምን አስባችሁ ነው ቆይ…? ተዉ ክፉ አታናግሩን እንጂ…?
"…እኔ የማክሰኞም፣ የረቡዕ የተያዘ የመረጃ መርሀ ግብሬን የሰረዝኩት እና ያዝ ያደረግኩት እኮ የጉባኤውን መንፈስ ላለመረበሽ ብዬ ነው። ሰአሊተ ምሕረትና ቦሌ መድኃኔዓለምን እንደ ማሳያ አሳያለሁ ያልኩትን ጉድ ማሰየቴ እንደሁ አይቀር። አንድ አለቃ ስንት ቪላ ቤት እንዳለሁ በቪድዮ ነው የማሳያችሁ። የሰው ልጅ እንደ ባሪያ የሚሸጥበትን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ እነ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል እንኳ ልብ ገዝተው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በቆሙበት በዚህ ወቅት የምን ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ መፈንዳት ነው? ውለታችሁን በሌላ መልክ መልሱ እንጂ የምን ፍየል ከመድረሷ ነው? ኧረ እንዲያው ሌላው ቢቀር መቼም ቤተ ክርስቲያንን ማስከበር ቀርቷል ብዬ ነው ለራሳችሁ ክብር እንኳ ትንሽ አስቡ።
"…አንጃ ፈጥራችሁ ግርግር ለመፍጠር የምትባክኑ ከሆነ እኔም አንጃም ግራንጃ ፈጥሬ ጓ ማለት እጀምራለሁ ማለት ነው።
• በእናታችሁ እረፉ…! አደብ ግዙ…! ሃይ…!
👆 ③ ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አቁም። ፋኖም ከአሁኑ እንደ ቻይኖ ኮሚኒስት ፓርቲ ሙሰኞችን በመረጃ ካረጋገጠ መስቀል አለበት ባይ ነኝ። እኔ አልፋታችሁም። ከነማስረጃው ነው የማሰጣችሁ። ተጠንቀቁ።
"…በእስቲበል ዓለሙ ከሚመራው የፋኖ አደራጀጀት በቀር ምሥራቅ ጎጃም አከባቢ ያለው የፋኖ ኃይል መሳሳት እንዳለበት ይነገራል። በተለይ ደግሞ በደጀንና አካባቢው ካለው የውጊያ ስትራቴጂክ ስፍራ መሆንና ወደ አዲስ አበባ ለመንደርደር ትልቅ ሥራ ተሠርቶ በርካታ የፋኖ ኃይል በአካባቢው ሊኖር ሲገባ የቀጠናውን ፋኖ እየበተኑ ከምሥራቅ ጎጃም ወደ ምዕራብ ጎጃም እየመጡ በዚያ መጠራቀምም በአስቸኳይ መታረም ይገባዋል። እንዲያውም የምሥራቅ ጎጃም የደጀንና አካባቢውን ፋኖ በትነው ወደ ምዕራብ ጎጃም ሸሽተው በዚያ ሥልጣንም ይሁን ሓላፊነት ላይ የተቀመጡ አካላት ይመርመሩ። የጠላት መግቢያ በር ከፍቶ መኝታ ቤት መከማቸት ምን የሚሉት ስልት ነው።
"…ይሄ የመጀመሪያ ስስ የጭቃ ዥራፌ ነው። በቶሎ የሚታረሙት ታርመው የጎጃም ፋኖ ከነ ግርማ ሞገሱ፣ ከነጀግንነቱ መቀጠል አለበት። ዕድሜ የሰጠው ሰው በቅርቡ የጎጃምና የጎንደር፣ የወሎና የሸዋ ፋኖዎች በአንድነት የሚፈጥሩትን ለማየት እንዲያበቃው መጸለይ ነው። ሥልጠናው ቀጥሏል። ጠላትን 1ሺ እጥፍ ቀድሞ ሴራ ማክሸፍ ተችሏል። የአገዛዙን አከርካሪ በመስበር በወንጀል እንዲዘፈቅ ማድረግ ተችሏል። በፋኖ ትግል ምክንያት የኦሮሞ ብልጽግና ሰዎች ቦርጫም፣ ተራው ዜጋ እስቴኪኒ ሆኖ እንዲታይ ተደርጓል። አዲስ አበባ ዜጋው እየሟሟ ካድሬው እየጠበደለ የመጣው የዐማራ ፋኖ አገዛዙ ብሩን ለካድሬ ሆድና ለጥይት ቦንብ መግዣ እንዲያውለው ስላስገደደው ነው። ይሄ ሁሉ ትርምስ የተፈጠረው በዐማራ ፋኖ መነሣት ምክንያት ነው። በተለይ የጎጃም ፋኖ ተጋድሎ አይዘነጋም።
"…ደግሞ ሰሞኑን በቲክቶክ ተንጫጫ አሉህ። ዘመዴ ጎጃምን ሰደበ በል አሉህ። ጎጃም ሆነ ጎንደር፣ ወሎ ሆነ ሸዋ እኔ ዘመዴ የሚመከረውን መምከር፣ የሚዠለጠውን መዠለጥ ነፃ ፈቃድ የተሰጠኝ ብቸኛው ሰው ነኝ። እናም እኔ በሆዴ እያጉረመረምኩ ነገር እያብሰለሰልኩ አልቀመጥም። የጨጓራ በሽተኛም፣ እንቅልፍም ማጣት አልፈልግም። ሌባውን እየዠለጥኩ፣ ሴረኛውን ሴራውን እያፈረስኩ፣ ጀግኖቹንና ሀቀኞቹን እያበረታታሁ ለሽ ብዬ እንቅልፌን እተኛለሁ። ጤነኛም ሆኜ እኖራለሁ። ሰምተሃል አይደል…? እየመከርኩህ ነው።
“…በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።” ምሳ 13፥10 …“…ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፤ መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል።” ምሳ 15፥22 … “…መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።” ምሳ 11፥14
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
•••
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 13/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!