zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እየሰማችሁ እደሩልኝ…!

"…አያሌው ኤርሚያስን ማድነቅ ሲጀምር ከስኳድ ጋር ተቀያየመ እንዴ ብዬ ገርሞኝ ነበር። አያሌው የእነ ረዳት ፍሮፌሰር ጌታ አስራደ በጎንደር ባንክ መስረቅ፣ መዝረፍ የደበረው ይመስላል። ስለሱ ጉዳይ ላለማንሳት መምህራን በሌሉበት፣ ወንዶች ሁሉ ጫካ በገቡበት ክልል ትምህርት ካልተከፈተ ብሎ ከዳንኤል ክብረት ጋር ተመሳሳይ አጀንዳ ይዞ እሱ ላይ ችክ ብሎ ቀርቷል። የደቡብ ጎንደሯ ዝርፊያ አንገቱን አስደፍታዋለች። አያሌው ወዳጄ ነው። ብዙ አብረን አሳልፈናል። በስሱ ዐውቀዋለሁ። ዝርፊያው አልተመቸውም። የፓስተር ምስጋናው ፋኖ እንዴት ዳዊት ተሸክሞ፣ መስቀል አንጠልጥሎ ይዋጋል የሚለውም ጉዳይ አፍ አውጥቶ አይናገር እንጂ ደብሮታል። አያሌው እስከአሁን ብአዴን ይሁን እንጂ ማዕተቡን የበጠሰ አይመስለኝም።

"…ኤርሚያስ ግን መቼ ነው ስለ ስኳድ እንዲህ ዓይነት ትንትና ትንትን አድርጎ ያቀረበው? አያሌው ኤርሚያስን አክብሮ፣ አድንቆ ሲጽፍ ጊዜ እስቲ ስለኤርሚ ሌላ ነገር ካለ ብዬ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ዞር ዞር ስል ነው ኤርሚ ዋቅጅራን ስለ ጎንደሩ ስኳድ የተነተነውንም ትንተና አግኝቼ የለጠፍኩላችሁ። መስማት አይጎዳም። ስኳድ አያሌው ያደነቀውን ኤርሚን ብትሰሙት ምንም አይደል።

• ወዳጄ አያሌው ግን ስለ ጥቆማህ ሳላመሰግንህ አላልፍም።

• እስቲ የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…9

• ምክር አፍላፊ ለሚናገሩ ትግሬዎች

"…የጦርነት ትርፉ ይኸው ነው። …ኀዘኑን፣ ህመሙን፣ ቁስሉንና ድቀቱን፣ በጭፈራ፣ በእስክስታ፣ በደርፊ፣ በአረቄ ውስጥ ደብቀህ አትሸፍነውም። ሸፍነህም አታልፈውም። ይሄ ሁሉ የትግሬ ወጣት ተቆምጦ፣ ተቆምጦ እንደማየት ሌላ ምን አንገት የሚያስደፋ ነገር አለ? በዚህ ላይ በትግሬም ምድር ፋብሪካው ወድሟል፣ ንግድ የለ፣ ሥራ የለ፣ ትምህርት የለ፣ እንቅስቃሴ የለ፣ ወያኔ ባመጣችው ጣጣ እንደከፍት በክልልህ በረት ውስጥ ታስረህ ተቀምጠህ ስትቆዝም መዋል ማደር ብቻ። በጣም ይከብዳል። ለመሰደድ እንኳ እግር ያስፈልጋል።

"…በባዶ ቤት አነ ተጋሩ፣ ባትጋሩኝ ማለት ምን ይጠቅማል? ስብራትን በፉከራና በጉራ እስከመቼ ተሸፍኖ ይዘለቃል? ደብረ ጽዮንና ጌታቸው ምን ሆኑ? ምናቸውስ ተጎዳ? የጻድቃን ገብረ ትንሣኤ ሚስትና ልጆች እኮ አማሪካ ናቸው። የሾቀው፣ እንደ ቅጠል የረገፈው፣ ተቆምጦ፣ ተቆምጦ ተጎንድሾ፣ አይኑ ፈርጦ የቤተሰብ ሸክም ሆኖ የቀረው ምስኪኑ የትግሬ ወጣት ነው። ወላጅ ያለ ጧሪ፣ ያለቀባሪ ነው የቀረው። ይመራል ግን ዋጡት።

"…ኀዘን ጭንቀት ቲክቶክ ላይ በመጨፈር፣ ዊኒጥ ዊኒጥ በማለት አይርቅም። እንደ ሴተኛ አዳሪ ብልጭልጭ ለብሶ፣ በቅባት ወዝቶ፣ ደስተኛ መስሎ በመጨፈር የውስጥ ቁስል አይሻርም። ፈጣሪ ፊት እንደማልቀስ፣ ንስሀ እንደመግባት ምንም እንዳልተፈጠረ በባዶ ሜዳ መፎከር፣ ማቅራራት ለማንም አይጠቅምም። በወጣትነት ያውም በከፋ ድኅነት ውስጥ እንዲህ ዊልቸር ላይ መዋል ምንም ደስ አይልም። ምንም።

"…አስተያየቱን የሰጠሁት አንዱ ትግሬ እኛ ተጋሩዎች እንዲህ ነን ብሎ ፎክሮ ስለላከልኝ ነው። ደግሞ ይሄን አልክ ብሎ የሚከፋው አይጠፋም። በአስተያየቴ ቅር የሚሰኝ ካለም ቅራሪ ይጠጣ…

• ተመልሼ እመጣለሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 7

ጥያቄ ነው።

"…አደህይቶ መግዛቱ እንደቀጠለ ነው። የሸገር ሲቲ መምህራን ከተማሪዎች እኩል ምሳ በምገባ ማዕከል መብላት ጀምረዋል።

• ራትስ?
• ሚስትና ልጆችስ ምን ሊበሉ ነው?

"…የውርደት ዘመን።

"…ተኝተው ከሚበሉት ከፓርላማ አባላት፣ ሸኔ ከሚዘርፈው ባንክ በጀት ተቀንሶ ለመምህራን ደሞዝ በመጨመር ራሳቸው ያማራቸውን ሠርተው እንዲበሉ ማድረግ ነው የሚሻለው ወይስ በየቀኑ ከህፃናቱ እኩል ፍርፍር እየሰጡ መምህር በመመገብ ሰበብ ማሸማቀቅ ነው?

• ከምር ያሳዝናል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

• አሁን ደግሞ የነቆራ ክፍለ ጊዜ ነው።

"…ዛሬ ወንዴዬ ፒኖክዮ ከኡጋንዳ በስንት መከራ ፎቶውን ቀይሯል። እንትኑ ግን ያው ነው። ምንም ለውጥ የለውም። ደግሞም በፍጹም ለማሳጠር አልተቻለውም። ወንዴ በምርቃና እየጎተተው እኮ ነው የዝሆን ኩምቢ ያሳከለው አላለኝም የአሸቦ ዕቃው ሲሳይ አልታሰብ አይ ስኳድ ክፉ ነህ የሥራህን ይስጥህ … 😂

• ከ50 ኮመንት በኋላ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

• የሙዚቃ ሰዓት ነው።

"…በድምጻዊ ብሬላላ ተደርሶ "ቻለው አሁን" በሚል መጠሪያ ሰሞኑን የተለቀቀውን አሪፍ ነጠላ ዜማን ሰምተን እንመለሳለን።

• አድማጭ ተመልካቾቻችን "ቻለው አሁን" በማለት ከክሊፑ ስር በመጻፍ አድናቆታችሁን ትጽፉለት ዘንድም ተጠይቃችኋል።

~ ቻለው አሁን…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… ተቀበል 1

"…ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን በይፋ ተጀምሯል። አዝማሪው የእናንተን ግጥም እየተጠባበቀ ነው።

• ተቀበል አዝማሪ…

… አበባየሆሽ…? 😂

~ ግጥም ይቀየር ተብሏል እስቲ እሷ ነገር ላይ የሆነች የሆነች ግጥም ለመግጠም ሞክሩ።

• በተለይ እንጨት ሰብሬ የሚለውን ትኩረት ስጡበት…

ችግኝ ነቅዬ… ለምለም
ስገባ ቤቴ… ለምለም
ጓ ይልብኛል… ለምለም
አብይ አጎቴ… ለምለም

አደዪ
የአብይ ወታደር ኮለል በዪ

"…ዓይነት ነገር… 😂 ጀምሩ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የነገ መርሀ ግብራችን ማስታወቂያ ነው።

"…በነገው የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን ከወዲሁ ብዙ ቁምነገሮችን እንዳስሳለን ብለን እንጠብቃለን። እናንተም ከወዲሁ ቀደም ብላችሁ ከአሁኑ ለዕለቱ መርሀ ግብራችን የሚመጥኑ ግጥሞችን፣ ቅኔዎችን፣ አጫጭር ቁምነገር ያላቸው ፈገግ እያደረጉ ቁምነገር የሚያስጨብጡ ቪድዮዎችን አዘጋጅታችሁ በውስጥ መስመር ላኩ።

• በሉ አባቢሌ ደናደሩ አባ ቦሌ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …አለሁ ለማለት፣ መኖሩንም ለማረጋገጥ፣ በዚያውም አጀንዳ ለመሆን ሀብታሙ አያሌው ፕሮፌሰር ሀብታሙን፣ የጎንደር ስኳዶቹ እነ አበበ በለው፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ ሰሎሞን ቦጋለ (ሃውልቴ) እኔ ዘመዴ ላይ ሲዘፈኑ ነው ያመሹት። ለከሰረ ጎጠኛ እኔ ዘመዴ ኬሬዳሽ።

"…የቀረው የአበበ በለው እና የስኳዱ ኦዲያንስ አሁን ያለው ውጭ ያለው ጥቂት ዳያስፔጰራ ነው። እነሱን ደግሞ የማገኘው በዚሁ በሶሻል ሚዲያው ነው። በተለይ ለአበበ በለው ገንዘብ የሚሰጡትን የዋሽንግተን ዐማራ ማህበር አባላትን የማገኘው በዚሁ በሶሻል ሚዲያው ላይ ነው። እነሱ ደግሞ እኔ የምጽፈው ጦማር ሱሰኞች ናቸው። አበበን ያሳበደው እኔ የመልሰበር ሆኜ በቴሌግራም አክቲቭ መሆኔ ነው። ሲግጣቸው የከረሙት የዐማራ ማኅበራት አባላት እኔን እንደሚያነቡኝ ስለሚያውቅ ኢጎው ተነክቷል። ለአበበ ማኅበር ዶላር መክፈል ያቆሙም አሉ። ነግረውኛል። መርቀውኛልም። ባለፈው እኔ ለምንድን ነው አበበ በለው ያለፉትን 30 ዓመታት የአዲስ ድምጽ እና በቅርቡም የዋሽንግተን የዐማራ ማኅበር ከተመሰረተ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተቀመጠው? ሰው ጠፍቶ ነው ወይ? ብዬ መጠየቄ ነው በለ ቴስላውን አበበ በለውን በድንጋጤ ያጫጨው። አሁንም እጠይቃለሁ ለምንድነው? ዐማሮች መልሱ። አሁን ቀንሰዋል እንጂ ወደ 322 የሚጠጉ አባላት ነበርሩት። በየወሩ እያንዳንዳቸው $30 ዶላር ይገብሩ ነበር። ይሄን ገንዘብ አበበ በለው የት እንደሚስገባው አይታወቅም ያሉኝ አባላቱ ራሳቸው ናቸው። እሱ የሚነዳው መኪና የገዛውን ቤት አይተን የባነነው አሁን ነው ነው የሚሉኝ አባላት የነበሩት። አበበ በለው አሁን በከተማው ውስጥ ተደብቋል። እንደ ድሮው መፏነን፣ እዩኝ እዩኝ ማለትም የለም። ዐውቃለሁ የአበበ ስስ ልብ ማኅበሩ ነው።  ማኅበሩ አበበን ቀይሮ በሌላ ዐማራ ካላስመራ እኔ ሁላቸውንም አልምራቸውም። ፀረ ዐማሮች አድርጌ ፈርጄ ስልካቸውን አስቀምጬ ነው የምቀጠቅጠው። ለፋኖ የተላከ ብር ከእስክንድር ጋር ተማክረው በልተው፣ ምኒልክ የሚባል ሳታላይት ቲቪ ከፍተው ሲያበቁ አሁን ደርሶ "ለፋኖ ፀረ ድሮን ልንገዛ ነበር ዘመድኩን ከለከለን ማለት ምንድነው? ሼም የለም እንዴ? ሌባ ሁላ። ሠርተህ ብላ።

"…ከምንም በላይ፣ ከእነ አበበ በላው በላይ ደግሞ ድራሽ አባታቸውን ያጠፋሁት የእነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ የእነ አያሌው መንበርን፣ የእነ ሰሎሞን ቦጋለ (ሃውልቴ) ን የስኳድ ቡድን ነው። ልብ ብላችሁ ከሆነ ባህርዳር እና ጎንደር ዘረፋ፣ ሰው ማገት የሚፈጽመው የጎንደር ስሁላዊ የስኳድ ቡድን ነው ብዬ እነ ሰሎሞን፣ እነ ሙላት አድኖ ባህር ዳር እና ጎንደር የሚሠሩትን የዘረፋ፣ (እገታ/ግድያ) ወንጀል ሚፈጽሙት ራሳቸው ናቸው ብዬ ካጋለጥኳቸው በኋላ፣ መረጃውንም በቪዲዮ ጭምር እንደ ማስረጃ አቅርቤ ከሠራሁ በኋላ፣ በሕፃን ፌቨን ምክንያት በጎጃምና በጎንደር መካከል ሊጭሩ ያሰቡትን እሳት ገና ከጅምሩ ካጠፋሁባቸው በኋላ፣ የወልቃይትን ጉዳይ አንሥቼ የዐማራ ፋኖ ወልቃይት መግባት አለበት፣ ደመቀ ዘውዱ የለየለት ፀረ ዐማራ ነው ብዬ አደባባይ በድፍረት ከወጣሁ በኋላ ነው የሞቱት።  የምር’ም ደግሞ አሁን ላይ እገታው እንደ ዱሮው አይደለም። ወንጀሉ በጣም ቀንሷል። አሁን አሁን አያሌው መንበር ራሱ እየወጣ 18 ሰው ላይክ በሚያደርገው ፌስቡኩ ላይ እየሞነጫጨረ ይሄ እገታ በእኔ ጥረት ነው የቆመው ብሎ መለጣጠፍ ጀምሯል።

"…በጎንደር እና በባህርዳር ሰዉ ስኳዶችን በጣም ነው የጠላቸው። በተለይ ደግሞ ገና የማወጣው የውርደት፣ የቅሌት ቪድዮን ሲያስቡት መግቢያ ነው የሚጠፋቸው። ጠብቀኝ። እኔ በአንዴ መረጃ አልለቅም። እነ የቁጩ ፕሮፌሰር እነ ኢያሱ ሲሰርቁ መረጃ ብልጭ አድርጌ ጥጌን ይዤ ነው የተቀመጥኩት። ስኳድ፣ እነ መሳይ መኮንን፣ ፀረ ፋኖ ሁላ ሱንጫጫ ዝም ነው ያልኩት። ብዙዎች እነ እያሱ አልሰረቁም ማለት ነው ብለው ለመወዛገብ ሲወዛገቡም እያየሁ ዝም ነው ያልኩት። አልተነፈስኩም። እነ ምስጋናው፣ እነ ሲሳይ፣ እነ ሳሚ ቅማንቴ ሲንጫጩ ጭጭ ነው ያልኩት። አያሌው መንበር ብቻ ነው በጋራ ጓደኛችን በኩል መልእክቴ ደርሶት በሌብነቱ ላይ ሳይጽፍ የተሸበለለው። አስተያየትም አልሰጠም። እንደ ቁጫጮቹ አልተንጫጫም። እንደ ጠንቋይ ልጆ እንደ ፓስተር ምስጋናውም አልተበጠረቀም። እሱ ሽብልል ብሎ ከዳንኤል ክብረት ጋር ተናቦ ህዳር ላይ የተማሪዎች አለመመዝገብ አሳስቦት ስለ ተማሪዎች ምዝገባ በመጻፍ ከእነ መሃይሙ ሳሚ ቅማንቴ ሓሳብ ተሸበለለ። ሌብነቱን አያሌው እስከአሁን አልደገፈም። ደግፎም አልጻፈም።

"…የእስክንድር የአክስት ነው የአጎት ልጅ የኡጋንዳው ወንደሰን ተክሉ እንዲሁ “የጀርመኑ ዘላን ዘመድኩን በዐማራ ጉዳይ ምን አገባው?” እያለ ሲጮህ ነው ያመሸው። አያሌው መንበር ሃውልቴው ሰሎሞን ቦጋለ፣ እነ ነጋ በፕሮፌሰሮቹ ስኳዶች ስለተዘረፈው የሕዝብ ገንዝብ ሌባውን ኢያሱን ደግፈው፤ ዘመነ ካሤን ሲሳደቡ፤ ዘመድኩንንም እነሱ ናቸው የቀጠሩት እያሉ ሲሳደቡ ሊያስቆማቸው አልፈለገም። በዋነኝነት ግን ትኩረታቸው ዘመነ ላይ ነበር። ኢያሱ ለሠረቀው ዘመነን መሳደብ ምን የሚሉት ቦለጢቃ እንደሆነም አልገባኝም።

"…ለማንኛውም ፀረ ዐማራ የውስጥ እሾሆችን እየነቀልኩ ነው። መሬት ላይ ያለው ትግል የግዱን ይሰተካከላል። እነ አኪላ፣ እነ ዘርዓ ያዕቆብ፣ እነ አመሀ ሙላውና እና እነ ሮቤል ረጅሙ እጇቸው ተቆርጧል። አሁን የሚያሲዙት የለም። በድሮን የሚያስመቱት የለም። የእነሱን ሳታላይት ስልክ ተሸክሞ አይደለም በድሮን ለምን በሚሳኤል አያስመቱትም። ለደንታው ነው። አሁን የሚያዘጉት ባንክ የለም። አሁን እንደድሮው ደውለው የሚበጠብጡት፣ መቶ ሺ ብር ሰጥተው የሚነዱት ፋኖ የለም። ወሎ ላይ፣ ሸዋ ላይ የነበረው ሴላቸው ተቆርጧል። ከጀርባቸው ያለው የወልቃይት ወያኔ ቅስሙም፣ ጅስሙም ተሰብሯል። እነ ዋን ዐማራ መሬት ላይ ያላቸው፣ በፋኖ ውስጥ የሰገሰጉት ተመንጥሮ መታሰር ጀምሯል። ፋኖ አምርሯል። ከባድ ምስጢር መምጣት ጀምሯል። በተለይ እሁድ መረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ ላይ የምትሰሙት፣ የምትመለከቱት ደግሞ ብትንትናቸውን ያወጣዋል።

"…ቀጣዩ የሚሆነው ይሄ ሲስተካከል ፋኖ ከሰፈሩ ወጥቶ ጨዋታውን ከክልሉ ውጪ ያደርገዋል። የወለጋ ሸኔ ሰሜን ሸዋ ውስጥ ከመጣ የጎንደር ፋኖ፣ የጎጃም ፋኖ ሱሉልታ የማይመጣው ለምንድነው? በሚለው ጉዳይ ላይ ማውራት እንጀምራለን። እስከዚያው ቸር እንሰንብት።

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 22/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆 ② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …መልኩ ወገቡን በነጠላ አስሮ እዬዬ ሲል የሚውል ነበር።
አሁንስ? አሁን ወፍ የለም። የዐማራ ሰው አጀንዳ መስጠት እንጂ አጀንዳ መቀበል ካቆመ ቆየ። ለዚህም እኔ ዘመዴ ዘመድኩን በቀለ የአንበሳውን ድርሻ እወስዳለሁ። "አጀንዳዬን አልቀይርም" የሚል መሪ መፈክር ያለማመድኩት፣ ለዐማራው የማኅበራዊ ሠራዊት ያስቀጸልኩት እኔው ዘመዴ ነኝ። እ… ምንአባክ ልትል ነው? እ…  ማነው ልትል ነው? እኔው ነኝ። ገገማ እንድትሆን የመከርከሁህ። ያስቀጸልኩህ። የትግሬና የኦሮሞን የሴራ አጀንዳ እንዴት እንደምትበጣጥስ ያሳየውህ።

"…እኔው ነኝ ትግሬን ኢግኖር ግጨው፣ የትግሬ የጨረቃ ጳጳሳ ልገነጠል ነው ሲልህ ለደንታህ በለው። መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ በለው። ስትገነጠል ግን ዕቃ አንተ ጋር አለኝ በለው። አክሱምን መልስህ ገደል ግባ በለው ያልኩህ እኔ ነኝ። ዐማራን ከአክሱም አባሮ ጎንደር የከተተውን ትግሬ መልሰህ የአባቶችህን ርስት እንደምትቀበል ንገረው ያልኩህ እኔ ነኝ። አጀንዳ እሰጥሃለሁ ሲል አንተ አጀንዳ ስጠው ያልኩህ እኔው ነኝ። አይደለህም እንዳትለኝ ብቻ…? አንተ እኮ አታፍርም። ኦሮሞው እስከ ራያ ካርታ ስሎ ወሎ፣ ጎጃም የእኔ ነው ብሎ አጀንዳ ሲሰጥህ አንተም ምን አሟገተህ እስከ ሀረር፣ እስከ ጅማ፣ ወለጋን በሙሉ አካልለህ ግብዳ ካርታ ሥለህ ይሄ ሁሉ አባት ሀገር ዐማራ ነው በለው ያልኩህ እኮ እኔ ነኝ። ለወራት ያንን እያሳየህ ዋይ ዋይ አስብለው ያልኩህም እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ተሳክቷል። እንዴት ከኦሮሞም ሆነ ከትግሬ አጀንዳ ፈብራኪዎች ጋር ተወዳድረህ አፈር ከደቼ እንደምታበላ የጠቆምኩህ እኔው ዘመዴ ነኝ። አለቀ።

"…ደግሞም መድኀኒቱ ይሄው ነው። ከመሬት ተነሥተው በበታቸኝነት፣ በዝቅተኝነት መንፈስ ለሚሰቃዩ። ዐማራ ባርያ አድርጎ ገዝቶናል፣ ነፍጠኛ ለ150 ዓመት ባርያው አድርጎ ጨቁኖን ነበር ብሎ ሳያፍር፣ ሳይሳቀቅ፣ በአደባባይ በአቢይ አሕመድ አፍ፣ በጃዋር መሃመድ አፍ፣ በአዳነች አቤቤ፣ በሽመልስ አብዲሳ፣ በለማ መገርሳ፣ ፈይሳ፣ በይልማ መርዳሳ፣ በሕዝቅኤል ጋቢሳ አፍ ደፍሮ ሲናገር ለምን ትከራከረዋለህ። ባርያ ነበርኩ ካለ ለባሪያ ልጅ በሚገባ ክብር ማነጋገር እየተቻለ የባርያን ልጅ ለምን ትለማመጠዋለህ። ወደ ቀልብህ ተመልሰህ በሚገባው ቋንቋ ማነጋገር ብቻ ነው መፍትሄው። ይደበለቃል፣ ከዚያ ይጠራል። ይደፈርሳል፣ ድብልቅልቁ ይወጣል ከዚያ ይጠራል። አለቀ። ጩቤ መቀመጫህ ላይ ሰክተህ አትዙር። የሰኩብህን ጩቤ ነቅለህ ታከም፣ አልያም የሰኩብህን ጩቤ ነቅለህ አንተም ሰካበትና ህመሙን እንዲሰማው አድርገው። መድኃኒቱም፣ መፍትሄውም እንደዚያ ነው። ያ ዐማራ ሲፈናቀል ሲስቅ የነበረው ትግሬ አሁን ተፈናቅሎ የመፈናቀልን ህመም አጣጥሞ ቀምሶት ልክ ገብቷል። ያ አማራ ሲፈናቀል አሁንም የሚስቀው፣ የሚያላግጠው የኦሮሞ ኤሊትም መቅመስ አለበት። ዘፈን እያወጣ አራት ኪሎ እያለ እየዘለለ እየፈረጠ በጥንባት አዳራሽ ማግማማት ብቻ አይደለም። ቁስሉን ሁሉም እኩል ሲቀምሰው ነው ነገር ልክ የሚመጣው።

"…አዎ አጀንዳ በዚህ መልኩ ነው መታየት ያለበት። የጎንደሩን የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ስኳድ እኔ ዘመዴ በድፍረት ባልላተመውና ባልጋፈጠው ኖሮ ማን አባቱ ነበር ደፍሮ የሚናገረው? ለዘመናት የዳበረ የሴራ ቦለጢቃ ባለቤት የነበረውን በጎንደር ዐማራ ላይ እንደ ሙጫ ተጣብቆ አልላቀቅ፣ እንደ አልቅት ተጣብቶት ደሙን መጥጦ በአጽም ያስቀረውን ስኳድ እኔ ባልደፍረው ኖሮ የትኛው ጎንደሬ፣ የትኛ ዐማራ ነበር የሚደፍራቸው? ንገር ሳትደብቅ። ሳትሸሽግ። እኔ ዘመዴ ነኝ ብትንትናቸውን ያወጣኋቸው። የዐማራ ነቀርሳ የሆነውን የጎንደር ስኳድ ድባቅ የመታሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ለጎንደር ዐማራ እፎይታ የሰጠሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ሌባውን፣ ነፍሰ ገዳዩን፣ አጭበርባሪውን አስኳድ አናት አናቱን በብእሬ በጦማሬ ቀጥቅጬ ፉዞ ያደረግኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። በጎንደር ዐማራ ስር ተሸሽጎ፣ ተደብቆ መርዙን ሲረጭ የነበረውን የትግሬ ዲቃላ ሁላ ገመናውን፣ ካባውን አውልቄ፣ ርቃኑን ያስቀረሁት እኔ ዘመዴ ነኝ።

"…እስቲ ቁጠሩልኝ፣ ከባህታዊ ገብረ መስቀል ጀምሮ፣ እነበጋሻው ደሳለኝን፣ እነ ትዝታው ሳምኤልን፣ እነ አሰግድ ሳህሉን፣ እነ ዘርፌ ከበደን ማነው ያሾቀው? ማነው የሞገተው? እየተሰደብኩ፣ እየታሰርኩ፣ እየተፈታሁ፣ እየተወገርኩ፣ ማን ነበር ተናገራ? እኔ ነኝ እኔ ዘመዴ፣ የሐረርጌው መረታ። አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ እኔ ዘመዴ ነኝ። እነ በጋሻውን፣ እነ አሰግድ ከቤተ ክርስቲያን ተወግዘው እንዲወጡ ፍዳ የበላሁት እኔ ነኝ። በዚህ እኮራለሁ፣ እንጠባረራለሁ። ከእኔ ጋር የታሰረ የለም። ከጥቂቶች በቀር ፍርድቤት አብሮኝ የቆመ የለም። ከእኔ ጋር የነበረው እግዚአብሔር ግን ሁሉን አስችሎኝ። የእነ በጋሻው ደጋፊ የአረብ ሀገር ሴቶችን ተቅማጥ የሚያስመጣ ስድብ አስችሎኝ፣ የፒያሳ ተራ አስከባሪዎችን ዛቻና ስድብም አስችሎኝ። የወያኔ ኢህአዴግን ፖሊሶች እስር አስችሎች። የደኅንነቶቹን ጫና እና ዛቻ አስችሎኝ፣ በወሮ ሳቤላ ቤት ተጠርቼ የስብሃት ነጋን ጫና እንድቋቋም አድርጎኝ፣ የትግሬዎቹን ዳኞችና ዐቃቢያነ ሕጎች ስድብ አስችሎኝ ሁሉን ተቋቁሜ በድል እንድወጣ ያደረገኝ እግዚአብሔር አምላክ ክብሩን ሁሉ ይውሰድ። አሜን።

"…ና ደግሞ እዚህ እኔ ተላትሜው የዳነውን ንገረኝ። እኔ ዘመዴ ለክፌው የዳነውን ንገረኝ። ከእኔ ከዘመዴ አፍ ገብቶ ሰው ሆኖ ቆሞ የሄደውን ንገረኝ። ንገረኛ። መጀመሪያ አጀንዳውን በስሱ ሳነሣ አፈር ከደቼ የምታበላኝ አንተ አይደለህ? አንቺ አይደለሽ? ቀድሜ ነገሮችን በተለየ መነጽር አይቼ እረፍ ብዬ ማስጠንቀቂያ ለአንዱ ስናገር ጠበቃ ሆነህ ስትለፋደድብኝ፣ አርቲክል ስትጽፍብኝ የነበርክ አንተ አይደለህ? ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስን ከእኔ በኋላ በስለት ሰይፍ ልትተች መጀመሪያ እንዴት ተወዳጁን አባታችንን ይናገራል ብለህ እሪሪሪ ቁምቡሪ ስትልብኝ የነበርክ አንተ አይደለህ? ኤርሚያስ ለገሰን ክፉ ሳልናገረው እረፍ ስላልኩት ብቻ አንተ ማን ስለሆንክ ነው? እኔ ፕሮፌሰር እገሌ፣ ዶክተር እገሌ ነኝ ብለህ ዋይ ዋይ ያልክብኝ አንተ አይደለህ? ታዲያ እኔ ኤርሚያስ ሰምቶኝ ሁለተኛ እንዳልናገረው አድርጎ ቃሌን ሲሰማ እስከዛሬ እኔ የተውኩትን ኤርሚያስ ዋቅጅራን ስትሰድበው የምትውለው አንተ አይደለህ? ንገረኝ እኔ ነክቼው የተረፈውን? በላ ንገረኝ።

"…ከኢትዮ 360 በላይ ሚዲያ ነበር እንዴ? የለም። ከሀብታሙ በላይ ተደማጭ ነበር እንዴ? አልነበረም። ከእስክንድር ነጋ በላይ የሚከበር ነበር እንዴ? አልነበረም። ከአበበ በለው በላይ የሚደመጥ ነበር እንዴ አልነበረም። እነዚህን በዳዊት ወንጭፍ ጎልያዶቹን ግንባራቸውን ብሎ ከዐማራ ትግል ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሡ ያደረገው ማነው? ከእኔ በላይ የምትጠቅሱትን ሰው አምጡልኝ? ዋን ዐማራ እነ አኪላን እንደ በግ ግልገል አቅርቦ፣ ጨው አልሶ፣ አደልቦ፣ አስብቶ ያረደ ማነው? ዛሬ አቅሏን እንደሳተች፣ እንዳበደች ውሻ አድማጭ አጥተው በባዶ እንደ በቀቀን እንዲለፈልፉ ያደረጋቸው ማነው? የሌባ ደጋፊ ሆነው እንዲንጫጩ፣ እንዲዋረዱ ያደረገ ማነው? አትፍራ ተናገር። አይነኬ ሆነው በዐማራ ትግል ላይ ሾተላይ የሆኑትን በሙሉ ጥግ ያስያዘ ማነው? በቴሌግራም ፎቶዬ ተዘቅዝቆ፣ ምሥሌ ተዘቅዝቆ፣ ዘርማንዘሬ እየተሰደበ፣ እየተረገምኩ የዐማራንም፣ የኢትዮጵያንም ጠላቶች ቤታቸው ድረስ ሄዶ የተጋፈጠ ማነው? ንገሩኝ፣ አትደብቁኝ። አዎ እኔ ዘመዴ ነኝ ሰንኮፉን…👇 ②  ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘመዴ ዛሬ ደግሞ ምሳም ሳትበላ የራት ሰዓት ደረሰብህ እኮ" የሚለው የባለቤቴ ንግግር በጆሮዬ ገብቶ እስኪያባንነኝ ድረስ አዛኜን ርእሰ አንቀጻችንን በተመስጦ እየጻፍኩ ነበር። እስከ ማክሰኞ ድረስ ርእሰ አንቀጽ ስለሌለን ለቅዳሜና እሁድ ጭምር የሚሆን እንዴት ያለ፣ ግሩም የሆነ ርእሰ አንቀጽ ነበር መስላችሁ ሳዘጋጅላችሁ የዋልኩት። እግዚአብሔር ምስክሬ ነው እንደ ዓባይ ወንዝ እንደወንዛችን ፍስስ ኩልል እያለ የሚወርድ፣ ግሩም የሆነ ርእሰ አንቀጽ በተመስጦ ውስጥ ሆኜ ነበር ስጽፍ የነበረው። ማርያምን የለሁም ነበር ማለት ይቻላል።

"…እናንተስ ይሄን ርእሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…? 100 ሰው ዝግጁ ነኝ ካለ እለጥፈዋለሁ።

• ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አሃ… ፓስተሪት ኦሮምቲቲ ናት ለካ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እስቲ በዚህ ደግሞ እየተወያየን እናምሽ…?

"…ሳስበው ሳስበው ይሄ ዘመነ ካሤ የሚባለው አርበኛ የጎጃም ዐማራ ፋኖ መሪ ቀጥሎ ከጎጃም የሚመጣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ይሆን እንዴ…?

"…ፓስተር ምስጋናው በፍናፍንቱ አያሌው በኩል በወንድ አንቀጽ ዘመነ ላይ ይንጫጫል። ሰሎምን ቦጋለ (አባቱ እስላም ነው ራሱ ነው የነገረኝ) እንትኑን እንደ አክሱም ሃውልት ቀጥ አድርጎ ቆሞ ዘመነ ካሴ አይነግሥም። ዘመነ ከነገሠ ሃውልቴ ይቆረጥ እያለ ሲምል ሲገዘት ያመሻል። የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ፣ የኦሮሞ የወሐቢይ እስላም፣ የብልጽግና ወጌንል አማኞች በሙሉ ዘመነ ዘመነ ብለው ሊሞቱ ነው። ይሄ ዘመነማ የሆነ ቅባትማ ሳይቀባ አይቅርም። ተንጫጩበት እኮ። የአጅሬ ጠቋር መንፈስ ስለ ዘመነ ምን ነግሯቸው ይሆን እነ መኔ ጫጫታውን እንዲህ ያበዙት…?

"…ሰሌማ ዘመድኩንን የቀጠረው ዘመነ ነው ብሎ አረፈው። ደግሞ እኮ ከሆነ ሰውዬ ጋር ሻወር ሊወስድ ነው አማሪካ። አይ ሰሌ ወንዳፍራሹ። 😂😂 …አይገርምላችሁም ግን…?

"…እስቲ ትንሽ እንወያይበት…? ይሄ የሴትየዋ ኢየሱስ ስለ ሚልዮን አራጁ አቢይ አሕመድ የማያሳያት ለምንድ ነው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉YouTube
https://www.youtube.com/live/TN8UeDAXUcc?feature=shared

👉በረንብል /Rumble

https://rumble.com/v5kwjrw--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡ / Facebook

https://www.facebook.com/share/PiDqX6Dbjq1wwfhY/

👉    በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram

/channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይ ይቀጥላል…✍✍✍ "…የሆነው ሆኖ አሁን አሁን በዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ የሚታይ ለውጥ አለ። ከምር ለውጥ አለ። እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ። ከወራት በፊት እኮ ማንም ሰው ደፍሮ ስለ እስክንድር ነጋ ትችት ማቅረብ አይደፍርም ሳይሆን አይሞክርም ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት ኢትዮ 360 ን እንደ ሚዲያ፣ ሀብታሙ አያሌውን እንደ ጋዜጠኛ ትንሽ እንኳ በስሱ ለመተቸት መሞከር ማለት እንዴት ያለ ከባድ ሱናሚ በራስ ላይ ሊያስነሣ እንደሚችል ሁሉ ሰው የሚያውቀው ሃቅ ነበር። እነ እስክስ አበበ በለውን ተቸህ ማለት እኮ አለቀልህ ማለት ነበር። በዲሲ ጎዳናዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያስነሣ የሚችል ማዕበል ሁላ ይቀሰቀስብህ ነበር። ይሄ እንግዲህ ከወራት በፊት የነበረ ጣጣ ነው።

"…ከወራት በፊት በጎንደር ውስጥ ችግር አለ። ስኳድ የሚባል የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ፀረ ዐማራ ቡድን አለ። ይሄ ቡድን በወልቃይት መሬት ሰሊጥ የደለበ፣ የገዢው ፓርቲም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ወሳኝ የሥልጣን ቁልፍ በእጁ የያዘ፣ በቁጥር ጥቂት ሲሆን እጅግ አደገኛ አደረጃጀት ነው ብሎ መናገር አይደለም ማሰብ ራሱ ሰማይና ምድርን የሚገለባብጥ የእንቁራሪቶችን ጩኸት ያስነሳ እንደነበር የታወቀ፣ የተረዳ ነገር ነው። በተለይ ከዐማራ ነገድ ውጪ ያለ ሰው ይሄንን አይሞክራትም ነበር። ጎጃሜ ነኝ፣ ጎንደሬ ነኝ የሚሉ የፖለቲካ ዲቃሎች ጎጃምንና ጎንደርን ለማጣላት ይንበጫበጩ ካልሆነ በቀር እውነተኛ ጎጃሜዎች እና እውነተኛ ጎንደሬዎች እንዲህ ያለ የዘቀጠ ተግባር ላይ አይገኙም ነበር። የትግሬ ነፃ አውጪዋ የህወሓት፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪው የኦነግ አክቲቪስቶች ነበሩ በዐማራ ስም ተደብቀው አንዱን የደገፉ መስለው አንዱን በመስደብ፣ ሌላውን በማንቋሸሽ ለመረበሽ ይሞክሩ የነበሩት። አሁን ሁሉም ረባሽ እንቁራሪቶች በሜካፕ፣ በፊልተር ያሉትም፣ ተደብቀው ባናና ሆነው የሚውሸለሸሉትም በሙሉ በስም ተለይተው ታውቀዋል። እና እነሱን አጥምዶ ማወቁ ላይ ነው መበርታት።

"…እስቲ ቲክቶክ ላይ ያሉ የዐማራው ትግል እንቅልፍ ነሺ ረባሽ እንቁራሪቶችን የምታውቁአቸውን ጥቀሱ። የማይደክማቸው፣ ለቀጠራቸው አካል፣ ዐማራን ለማባላት እንቅልፍ የሌላቸው። ሁለት ሁለት፣ ወይም ሦስት አራት ሆነው የሚያውኩ፣ ሲታዩ እንደ አኪላና ነቢዩ ብዙ ሺ ጦር የሚመስሉ እስቲ የኩሬውን እንቁራሪቶች በስም ጥቀሱ። የትም ይኑሩ የትም ኡጋንዳም ይኑሩ ጋይንት፣ ዳሞትም ይኑሩ ሳይንት፣ ይፋትም ይኑሩ ጂባት እስቲ ጥቀሷቸው። የእንቁራሪቶቹን ብዛት ማወቁ በጣም ወሳኝ ነው።

"…የቲክቶክ እንቁራሪቶች አብዛኞቹ ሁለት ሁለት ናቸው። እስቲ ተመራምራችሁ ድረሱባቸው። ሀገር ምድሩ ይወቃቸው፣ ያንብባቸው። ከዚያ ነው ወደ ቀጣዩ መፍትሄ መሄድ የሚቻለው። ሌባን በነገዱ ውስጥ የማይሸሽግ ትውልድ በመፈጠሩ ግን ኩራት እንደተሰማኝ ሳልደብቅ ማለፍ አልፈልግም። እንቁራሪቶች ሆይ ሁለት ሆናችሁ ሳለ እንደ ካምቦሎጆ የቅሪላ ገፊዎች ደጋፊ ሆሆሆ ብላችሁ አታደንቁሩን። አበቃሁ።

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 21/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እኔ ደግሞ ለወሬ ሱሴ፣ ለሀራራዬ የሚሆን ቁምነገርም አገኝበት እንደሁ ብዬ አራት ኪሎ ባርላማ አደራሽ የጩጬውን ምላሽ ለመስማት ተጎልቼ ማርፈዴ። ከምር እዚያ ተጎልቼ ነው ያረፈድኩት። ሰው እንዲህ እጅ እጅ ይላል በአዛኚቷ? እንዴት ያለ የኢኮኖሚ፣ የብልጽግና፣ የኑሮ ውድነቱን የሚያቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትንተና እሰማለሁ ብዬ ብሄድ፣ ተጎልቼ አይኔን አፍጥጬ ብጠብቅ ወፍ የለም። ከዸቱ ወዪ…😂

"…ኧረ ኤድያ ተዉኝ እስቲ። ይልቅ የዛሬው ርእሰ አንቀጻችንን ስለ እንቁራሪቶቹ መጻፍ አማረኝ እና ጻፍኩ። ከርእሰ አንቀጼ ንባብ በኋላ እናንተም ስለሳችሁ እንቁራሪቶች ትጽፉልኛላችሁ። እሺ በሉኛ። 😁

"…ለማንኛውም ስለ እንቁራሪቶቹ የሚያወሳውን የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

• አሁንም ለትግሬ ምክር ነው።

"…አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤" ገላ 6፥7

"…አስመሳይነት በሃይማኖት ካባ ሲያዩት ያስጠላል። ቋቅ ነው የሚለው። የመንደር ቦዘኔ፣ ቢፎግር፣ ቢሰርቅ፣ ቢቀልድ፣ ቢዋሽ ሙድ አለው ተብሎ ተስቆ ይታለፍለታል። የእነዚህ ግን ቋቅ ነው የሚለው። አስመሳይነት መስቀል ይዞ ያስጠላል።

"…እነዚህ የትግሬ የተወገዙ የጨረቃ "ጳጳሳት" ትናንትናና ዛሬ አየሩን ተቆጣጥረውት ሳይ፣ አንዳንዶች ቀድሞውኑ ሳይጣሉ የተጣሉ መስለው አየርና ሙድ ይዘው በትግሬ ጭንቅላት ቁማር የሚሠሩትን የትግሬ ነፃ አውጪ ድርጅት ጋንግስተሮች አስታረቁ ተብለው ሲመረቁ አይቼ በሳቅ ፈረስኩ። እንደ መጋቤ ሀዲስ አዕመረ አሸብር አይነቱ ፖለቲካውን የማይባንን ምስኪን የጎጃም ቄስ ጮቤውን ሲረግጥ የኦሮሞ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ድቤ ሲደቁ ሳይ ባሳቅ ፍረስ ፍረስ ነበር ያሰኘኝ።

"…እነዚህ ፍቅር የማያውቁ ጨካኞች፣ ሚልዮን ትግሬ ያስፈጁት ፖለቲከኞቹ ታርቀው ሲሸላለሙ እነዚህ የዲያብሎስ ታናሽ ወንድሞች፣ አስመሳይ ሰው መሳይ በሸንጎዎች ከፖለቲከኞቹ አንሰው ፓትርያርኩ ላይ የቤተ መቅደስ በር ዘግተው፣ አስለቅሰው የመለሱ የሰው ይሁዳዎች ዛሬ እንደ ሃይማኖት አባት አክት አድርገው ያልተጣሉ ፎጋሪ ትግሬዎችን አጨባብጠው ቅዱስ ቅዱስ ሊጫወቱ ይፈልጋሉ።

"…እነሰረቀ ሰራቂ የመናፍቅ ተሃድሶ ተወካይ፣ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ የተረገሙ፣ ቀልብም፣ ውቃቢም የራቃቸው፣ ታቦተ ጽዮንን ያረከሱ፣ ቀኖና የሻሩ፣ መንጋውን ለአውሬ ለመስጠት የቋመጡ አስታራቂ ሆነው ሲመጡ ሳይ በሳቅ ነው የምፈርሰው። ለራሱ አስታራቂ የሚፈልግ ኮተታም አስታራቂ ነኝ ሲል ያስቃል። ለማንኛውም ንስሀ ግቡ። ካለፈው የባሰ መከራ ውስጥ ለመዘፈቅ አትጣደፉ።

• ምክሬ ይጎመዝዛል ግን ዋጡት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…8

• ነቆራ ሁለት… 😂

"…የእስክንድር ነጋ የኡጋንዳ ተወካይ ወንዴ ሰልካኬ ድሮ ዘመነ ካሴን እንዳላወደሰች ዘመነ ለእስክንድር አልገረድ ሲል አዲስ አሽከር ማስረሻን ማደስ ጀመረ። እኔና አድማጭ ተከታዮቼንም አፍንጮበር ድረስ በሚሰማ ድምጽ ነው የሰደበን። ተው ግን ወንዴ? ወንዴ ሰልካካው።

• ከምር እንዲህ አበሳጭቼዋለሁ ማለት ነው እንዴ? እኔ እኮ ሲያመኝ ጤና የለኝም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…6

• የምክር እና የስብከት ሰዓት ነው።

"…የሚደንቀው ጠሹ እንዲህ ሲበጠር እነ ሬድዋን ሁሴን፣ ሙፈሪያት፣ አደም ፋራህ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ አረጋ ከበደ፣ ሙስጠፌ አቀርቅረው ሁሉም ማስታወሻ መያዛቸው ነው።

• ሙኖኖኖው ግን…? 🙏🙏🙏 ይቅር በለኝ አምላኬ። ባመመው ሰው ላይ ማላገጥ ግን ጥሩ አይደለም።

• ሙኖኖው ግን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…4

"…ሙኖኖኖው…? … እንደ ወንደሰን ተክሉ አፍንጫ ረዝሞባቸው መሰለኝ…

• መልሱላት… !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…2

"…የሆያሆዬና አበባየሆሽ ግጥም መቀየር አለበት… ብሏል… የዘንድሮ ሃኪሞች ግን ጨካኞች ናቸው። እንደ ድሮው በሽተኛ አይረዱም። ሙንሆኖነው ኖው ግን?

• ኢሾ ኢሾ… ኢሾ…

…እየገጠማችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን? አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን? በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን? በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ። ሮሜ 2፥ 21-24

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም …

"…1 ሰዓት ለንባብ በቂ ነው። በ1 ሰዓት ውስጥ 15 ሺ ሰው አንብቦ 12 ፍሬ ሰው 😡 ብው ብሎ መናደዱም ጤናማ ነው።

"…ቀጥሎ ደግሞ እኔ በዚህ ምሽት በራየን ወንዝ ዳር ወክ እያደረግኩ የእናንተን ኮመንት እየኮመኮምኩ ምሽቴን አሳልፋለሁ። እናም ተራው የእናንተ ነው። በጨዋ ደንብ አስተያየታችሁ ይስተናገዳል።

• 1…2…3… ✍✍✍ ጀምሩ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ሁሉ የነቀልኩልህ። አንበሳ ሆነው በሹል ጥርሳቸው ሊቦጭቁህ የነበሩትን ጥርሳቸውን የነቀነቅኩልህ እኔ ዘመዴ ነኝ። ነገርኩህ እኔ ዘመዴ ነኝ። የተነቃነቀ ጥርስ ማውለቅ ካቃተህ ለደንታህ ነው።

"…ከትናንትና ወዲያ ምሽት አንደኛው ጥርሱን ያረገፍኩለት የዐማራ ፋኖ እሾክ እስክስ አበበ በለው መረጃ ቲቪዎቸወ ለምንድን ነው ዘመድኩንን ከአየር ላይ  የማያወርዱት? የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ሆን ብለው ነው ይሄን የሚያደርጉት፤ ለመረጃ ቲቪ የዐማራ ማኅበራት ደብዳቤ ጻፉ። መረጃ ቲቪ ለመንግሥት የሚሠራ ነው። ይኸው እኛ ፀረ ድሮን ገዝተን ለፋኖ ማስገባት ያልቻልነው፣ ገንዘብ ለፋኖ መሰብሰብ፣ ሰልፍ ማዘጋጀት ያልቻልነው በዘመድኩን ነቀለ ምክንያት ነው። ዘመድኩን መሬት ላይ ብዙ ችግር እየፈጠረ ነው። ሰው እሱን እያየ እየተወዛገበ ነው ብሎ (ባለፈው ተመልካች የለውም፤ ተቀባይነት እንዳይኖረው አድርገነዋል ሲል የነበረውን ረስቶ እኮ)፤ መረጃ ቲቪ ላይ ያላችሁ ፕሮግራሞቻችሁን አቁሙ። አቋምም ያዙ፤ ወደ ምኒልክ ቲቪ ኑ፤ መረጃ ቲቪን በገንዘብ የምትደግፉ አስቡበት። አንዳንድ ፋኖዎች ለምንድን ነው ከእሱ ጋር የምትገናኙት? እሱ ፕሮግራሙን የሚሠራው ከእኛ ከውስጣችን ምስጢር የሚነግርው ስላለ ነው፤ የዐማራ ማኅበራትም ውዝግብ ሲኖር ለእርሱ አትንገሩት፣ እንዴት ፋኖዎች ዘረፉ ይላል? በራሳቸው ጥረት ያገኙትን እንዴት ይመልሳሉ? ብልጽግና እንኳን ተዘረፍኩ ሳይል እሱ ነው ዜና የሠራው። እሱ ከመረጃ ቲቪ እስከሚባረር ድረስ እንዲህ ዓይነት ፕሮግራም መሥራቴን አላቆምም። አንድ እብድ ማባረር ለምን ይከብዳል? ምንም ሥራ መሥራት ያልቻልነው በዘመድኩን ምክንያት ነው… እያለ ሲቆጣ፣ ሲጮህ ነው ነው ያመሸው። ያንኑ የፈረደበትን ”ምን እንደሚያናግረኝ አላውቅም” ያልኩበትን ቪዲዮ’ም ሲያጫውት ነበር ያመሸው። ኧረ ባለፈው’ም የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ቤት ሰልፍ እናካሂድ ሲል ሁላ ነበር።

"…አዎ ዥልጥ፣ ፋራ መስሎ የዐማራን ትግል ዐማርኛ ቋንቋ እየተናገረ አፈር ከደቼ ያበላውን አበበ በለውን እኔ ዘመዴ ነኝ ጆሮውን ቆንጥጬ እየመዘለግኩ እስክስ እያስባልኩ አደብ ያስገዛሁት። በጎንደሬነቱ ተማምኖ መሬት ላይ ያሉትን ፋኖዎች ጨው እያላሰ ደውሎ ስለሚያናግራቸው እነርሱን ማናገሩ ትክክልኛ፣ ሃቀኛ የሆነ ያስመስለው ዘንድ በእነሱ ሊያስፈራራኝ ይሞክራል። ፋኖ አርበኛ ደረጄ የደምቢያ ልጅ፣ የሰፈሩ ልጅ ስለሆነ እሱን አውቆት ስለሚያወራው በፋኖ ደረጀም፣ በፋኖ ሀብቴም ሆነ በሌሎች በኩል እኔን ጆሮዬን አስይዞ የሚያስቆመኝ ይመስለዋል። ደረጄም፣ ሀብቴም በሚያውቁኝ ያውቁኛል። ደውለውልኝ እንጂ ደውዬለት አላውቅም። ፋኖ ምክንያታዊ ነው። ያለ ምክንያት ተነሥቶ የሀገሬን ልጅ ነካኸው፣ ተቸኸው፣ ቀለብ የሚሠፍርልኝን ተቸህብኝ የሚል ማይም ፋኖ የለም። ቢኖርም ግድ አይሰጠኝም። እኔ የማውቀው ፋኖ ከፍ ያለ ስብዕናም አእምሮም የታደለ መሆኑን ነው። በአበበ በለው ምላስ ተሸውዶ፣ ለአበበ ተደርቦ ከእኔ ጋር የሚጣላ ያለ አይመስለኝም። ቅን ፈራጅ፣ ምክንያቱን የሚጠይቅ። ለሰፈሬ ልጅ ብሎ የማያደላ ነሆኑን ነው የማውቀው። አይ ለሰፈሬ ልጅ አድልቼ ለእሱ ተደርቤ ዘመዴን አስቀይመዋለሁ ብሎ የሚመጣ ካለ በማን እንደሚብስ ያነዜ እነየዋለን። ከከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ እንዴት አብሮ እንደሚወቀጥ አሳያቸዋለሁ። ማንም ሁን ማንም አልፋታውም። የሚሻለው በእኛ ጦርነት መሃል አለመግባት ነው። ሥራችን ያውጣን።

"…በዚህ ከእኔ ጋር ፀብ የአቤን ያክል ግን የተጎዳ የለም፤ እስቲ ፊቱን እዩት ገርጥቷል እኮ። ሲናገር ሊያለቅስ ምንም አይቀረውም እኮ። በደንብ ነው ኅብለ ሰረሰሩን ያወለቅኩለት። አበበ በለው ባለፈው ከመረጃ ቲቪ የወጣነው ፕሮግራማችን ስላልተላለፈ ነው ሲል እንደነበር ታስታውሳላችሁ። በፋኖ ስም ይቅማት የነበረችውን ስኳር ካቋረጥኩበት በኋላ ጉዳቱ ማሰቢያ አንጎሉን ሲሠርቀው ትናንት ደግሞ ከመረጃ ቴቪ የወጣነው ዘመድኩን ነቀለ በዚያ ስላለ ነው ሲል ነበር። ባለፈው መረጃን ዜሮ ስላስገባነው በድል ተወጥተነል፣ መረጃም ዘመድኩንም ተቀባይነት እንዳይኖራቸው፣  ፋኖዎች እንዳይገናኙት አድገናል እንዳላለ በዚህ ጉዳይ በድጋሚ አልመለሰም እንዳላለ ከትናንት ወዲያ ደግሞ ለምን እኔ ብቻ? ሌሎቻችሁም አብራችሁኝ ሁኑ እንጂ፤ አንድ ላይ ተባብረን እናባረው ሲል ነበር ያመሸው። እዬ ድራሚስት ስንኩል ፀረ ዐማራ የሳር ውስጥ እባብ የተከዜ ማዶ ልጅ ያላወቀው ነገር ከማን ጋር እንደሚጣላ ነው። እንደ አዲስ መጠቀም የፈለገው ስትራቴጂ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች የነበሩትን አሁን ግን በቦታው የሌሉትን ማሸማቀቅ በመሞከር ነው። በእሱ በኩል ወፍ የለውም። መረጃ ቴቬ የሕዝብ ነው። መረጃ ቴቬን በላቤ፣ በገንዘቤ ለምኜ አየር ላይ ያቆየሁት እኔ ነኝ። ኤልያስ ክፍሌ በለው ማንም በመረጃ ቲቪ ጉዳይ አያገባውም። ቅሬታ ካለህ ለእኔ ነው ማቅረብ። አለቀ።

"…የሚገርመው ነገር ከእንግዲህ በኋላ ለአበበ በለውም ሆነ ለሌሎች ቋንጃቸውን ሰብሬ ከዐማራ ትግል ላይ ያባረርኳቸውን ሰዎች ክብር ሰጥትቼ በመረጃ ቴቪ ላይ ለበዓሉ ድምቀት ሲባል አንዳንደዜ አልፎ አልፎ ለፈን ካልሆነ በቀር በቲቪ መስኮት መልስ አልሰጣቸውም። መልስ መስጠት ካለብኝ እኔ ደረጃዬ ስላልሆኑ፣ ስለማይመጥኑኝ እዚሁ ቴሌግራም ገጼ ላይ አነኩታቸወላሁ። የአበበ ኢጎው በጣም የሚነካው የት ላይ ሲነካ እንደሆነ አሳምሬ ነው የማውቀው። የአበበ መሃይምነት ልብ አድርጉ ማይም አላልኩም። መሃይም ነው ያልኩት። የአበበ መሃይምነት ወዳጁ ሀብታሙ አያሌው፣ ብሩክ ይባስ ቢሞቱ የእኔን ስም አያነሱም። ጨዋዎች ናቸው። ይገባቸዋል። የእዚህ ችግሩ ብሔራዊ ቲአትር መድረክ ላይ ያለ እየፎገረ ፒፕሉ የሚስቅለት ነው የሚመስለው። እናም ከእኔ ጋር መላተሙ የሚያስከትልበትን ሁለንተናዊ ጉዳት ልብ አይለውም። አይባንንም።

"…አበበ በለውን ያሳበደው እኔ በቴሌግራም ገጼ ላይ የእነ ዲያቆን የቁጩ ፕሮፌሰር ኢያሱን የባንክ ዘረፋ ቪድዮ በማውጣቴ ነው። የነ ኢያሱን ቪዲዮ ስለለቀኩ ነው የበሸቀው። ባለፈው ለፋኖ የተዋጣ ዶላር እነ ሕይወት በላቸው ለኢትዮ 360 በቼክ መስጠታቸውን ሳወጣው እነ ሀብታሙ ጭጭ ብለው ይሄ አዝማሪ ነው እወደድ ብሎ የፎገላው። ቀላዋጭ። ሳይነኩት ለሌባ እንዴት ጥብቅና ይቆማል? እንዴት ይሄ ከባድ ምስጢር ከመሀላችን ወጥቶ ለዘመድኩን ይሰጣል ብሎ ያበደው ቀጥሎ ወደ እሱ እንደምመጣ ስላወቀ ነው። እኔ ለአበበ ዛሬ የምመልስለት እሱ አሁን ተራ ዩቱበር መሆኑን እያወቅኩ ጭምር ነው። ለበዓሉ ድምቀት እና የደም ግፊቱን ለመጨመር ያህል ነው። የሰፋውን ኮት አስጠብቦ መልበስ የጀመረውን አቤን ካላረፈ እንዲደበቅ ነው የማደርገው። ሀብታሙም ትኩረት ፈልጎ ነው ለልደቱ አያሌው በወሎዬነት ሙድ አግዞ ፕሮፌሰር ሀብታሙን አታክ ሲያድርግ የነበረው። ሀብታሙ አያሌው እንዲህ አለ ተብሎ መነጋገርያ እንዲሆን፣ ሌሎችም አሉ ስሜን ጠርተው ተንኩሰውኝ መልስ ሰጥቻቸው ለመፈመስ የእኔን ትኩረት የሚፈልጉ። እኔ ምኔ ሞኝ ነው? እንደዜ ቀጥቅጬ፣ አናቱን ብዬ የቀበርኩትን ዘንዶ ከመቃብር አውጥቼ በጥንባቱ፣ በሽታው፣ በክርፋቱ ጤናዬን የማቃውሰው። እኔ ዘመዴ የዳዊት ጠጠሩ በስሱ ነክቼ የምጥለው አለ። በዝምታ የምጥለው አለ። ኒዩክለር ቦንብ የመሰለ ጦማር ለቅቅቤት ድራሽ አባቱን የማጠፋው አለ። ከጠፋ በኋላ…👇 ③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…በብዙ ነገር አጀንዳ ለመሆን የሚላላጡ ሁሉ ከባድ ኪሣራ ላይ ወድቀዋል። ከአቢይ አሕመድ ጀምሮ፣ እስከ እነ አበበ በለው፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ደፂ እና ጌቾ፣ ስኳድና አገው ሸንጎ፣ እስክንድር እና እስክናፋታ ድረስ ያሉ ሁላቸውም አጀንዳ በመሆን ለአፍታም ያህል ሕዝብን ለማንጫጫት አቅም አጥተዋል። ሕዝብ እንደ ሰጎን እንቁላል ትግሉን ከዐማራ ፋኖ ላይ አላነሣም ብሎ ገግሞባቸዋል። ለዚህ ደግሞ እኔ ዘመዴ ማይም አይደለሁ? በድፍረት እናገራለሁ የአንበሳውን ድርሻ የምወስደው እኔ ነኝ። ዐማራ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ መሆን የለበትም ብዬ አጀንዳ አለመቀበልን ያሳየሁ፣ የሰበክሁ፣ የጨቀጨቅኩ፣ የወተወትኩ እኔ ዘመዴ ነኝ። በዚህ ድብን አድርጌ እኮራለሁ። ደረቴን ነፍቼ ብጥርር ብዬ በሙሉ አፌም፣ አንደበቴም እናገራለሁ። ተቃዋሚ ካለ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል። አለቀ።

"…አቢይ አሕመድ አጀንዳ የሚሰጠው በሁለት ቦታዎች ላይ ነው። አንደኛው ፓርላማ ላይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሆነች ችግኝ ሲተክል፣ የሆነ ቦታ ልማት ብሎ ሲሄድ፣ ከአቡካዶ ዛፍ ስር፣ ቄጤማና ሳር ይዞ፣ የሆነ መጽሐፍ ምረቃ፣ አልያም የሆኑ አካላትን ሰብስቦ መልስ ሲሰጥ፣ አልያም ለብልጽግና ከብቶች የማያልቅ ሥልጠና ሲሰጥ ብቻ አንድ በቀለም የተቀባ ነገር ስር ቆሞ እሱ ብቻ በሚናገርበት መድረክ ላይ ይሁነኝ ብሎ፣ ተዘጋጅቶ፣ ከሲአይኤ የሥልጠና ማንዋል መካከል አንዷን ተንኳሽ አጀንዳ መርጦ ሕዝብ የሚነጋገርበት ቃል ስንቅር፣ ድንቅር አድርጎ ያስቀምጣል። ከዚያ ለፒፕሉ ያቺን እየቆራረጠ በሚዲያ ሠራዊቱ በኩል እንድትበተን በማድረግ ማኅበራዊ ሚዲያው አኞ ሥጋ የአጥንት ቅንጣቢ እንደተጣለት የቤትም፣ የሰፈርም ውሻ እሱኑ ሲያኝክ፣ ሲያላምጥ ይውላል፣ ያድራል፣ ይከርማልም። ለአቢይ አሕመድ ይሄ ስኬቱ ነው። ትልቅ ስኬቱ።

"…በትናንቱም የፓርላማ ውሎው ላይ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊ፣ በሀገሪቱ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር፣ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ሓሳብ ለመስጠት የዕውቀት ደሀ የሆነው አቢይ አህመድ ይሁነኝ ብሎ አጀንዳ ለመሆን የኦርቶዶክስ ክርስትናን ሲወቅስ፣ ለድህነታችን ተጠያቂ ሲያደርግ ነበር የመሸው። አጀንዳው በቂ ስላልመሰለው ለዐማራ ክልል እንደ አቢይ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ብልፅግናን ያመጣለት መንግሥት እንደሌለ ተበጠረቀ። እሱም ካልበቃ ብሎ "የአበባየሆች ግጥም መቀየር አለበት ብሎ ተበጠረቀ፣ ይሄ ሁሉ በማግስቱ አጀንዳ ለመሆን፣ ጸሐፍቶች፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች ወዘተ ርእስ ይዘው እንዲንጫጩለት እና ስሙ ሲጠራ ውሎ እንዲያድር ነበር። ይሄ ነበር ፍላጎቱ። ይህቺን ጨዋታ ከዳንኤል ክብረት ጋር ድሮ አብረን በደንብ ስለተጫወትናት አሳምሬ ዐውቃታለሁ። ዳንኤል ከእኔ ጋር ሆነን ለተሃድሶው ግሩፕ እንሰጥ የነበርነውን አጀንዳ የመስጠት ሴራ ነው ዛሬ አቢይን እያስቀጸለው ያለው። ከቃላት አጠቃቀሙ ጀምሮ አሳምሬ የማውቀው ዳኒ ዛሬ ላይ አቢይን እየተካው ነው ያለው። አስረግጬ ነው የምነግርህ። እንደዚያ ነው።

"…ሳር ብሉ። አጀንዳ ነው። ሙዝ በዳቦ ብሉ፣ አጅንዳ ነው። እኛ ሀገር ዶሮ የሚበላ የለም ሽንኩርት እንጂ፣ አጀንዳ ነው፣ የማንም ጭቃ ቤት ታሪካዊ ቤት ነው አትበለኝ አጀንዳ ነው። አረጋ ከበደ ከምኒልክና ከቴዎድሮስ ይበልጣል አጀንዳ ነው። ወዘተረፈ አጀንዳዎችን አቢይ አሕመድ ሲዘረግፍ ኖሮ አሁን አሁን ሰውየው ጠበል ወይ አማኑኤል የሚወስደው ዘመድ ያጣ ዕብድ መሆኑን ስላወቀ እንደ በፊቱ ጓ የሚል ፒፕል ቀንሷል። እንዲያም ሆኖ ግን አቢይ አሕመድ እብድም፣ ማይም መስሎ ጥፋቱ ግን ከባድ ነው። ሀገር በአፍጢሟ እየተከለ ነው። አደርገዋለሁ ብሎ ያለውን በሙሉ እያደረገ ነው። እነ ጃዋር በአንደዜ እንፈጽመው ብለው የተነሡለትን ትግል እሱ አይ እንደሱ አይደለም። ይሄን ሾርት ሚሞሪያም የኢትዮጵያ ሕዝብ በእናንተ መንገድ አፈር ደቼ ማብላት አይቻልም። ይሄንን ሕዝብ አፈር ደቼ ማብላት የሚቻለው በእኔ መንገድ ነው ብሎ በአቢይ አሕመድ መንገድ እሬቻውን እያበላው ነው።

"…የአቢይ መንገድ ከየ ብሔሩ ሆዳሞችን መርጦ፣ አቅርቦ መያዝ ነው። የአቢይ ካቢኔ ውስጥ ለመግባት ከዋሸሁ ልቀጣ በዘሩ በቤቱ የጠንቋይ ልጅ መሆን አለበት። መሰረተ እከካም ደሀ መሆን አለበት። በቤቱ ባዕድ አምልኮ የሌለው፣ ባለ አውልያ፣ ባለውቃቢ ካልሆንክ በአቢይ ካቢኔ አትመረጥም። ፕሮቴስታንት መሆን የመጀመሪያው መስፈርት ቢሆንም የጠንቋይ ዘር በዘሩ ውስጥ የሌለ ከአቢይ ጋር መሥራት አይችልም። ዘርዝራችሁ ጻፉ። ስማቸውን ይዛችሁ የእገሌ አባት፣ እናት፣ ወንድም ወይም እህት፣ ምንድነው ብላችሁ ጠይቁ። በሙሉ ጠንቋይ ሆነው ነው የምታገኙአቸው። የአቶ አረጋ ከበደ ወንድም በጎጃም እኔ ነኝ ያለ ጠንቋይ ነው። የዶር ይልቃል እናት እንዴት ያሉ የታወቁ ባለ ውቃቢ ነበሩ። በሙሉ ሌሎቹንም ጠይቁ። የደመቀ መኮንን ቤተሰብ እስከ አሁን የሚገበርለት ባለ አውልያ ናቸው። ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው መነኩሴ ሰውዬ ለሚንስትሩ ሁሉ ምን እንደሚሠራ ዓለሙ ሁሉ የሚያውቀው ነው። የዳንኤል ክብረት አባት፣ የአቢይ አሕመድ የሴት አያት፣ የአቢይ የራሱ እናት ምን እንደነበሩ ላስታ፣ ቡራዩ፣ አዲስ ዓለም ማርያምና በሻሻ ጠይቁ። የፓርስተሮቹ መመናፈስ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ለዚህ እኮ ነው ኢሬቻ፣ ዋቀ ጉራቻን መስቀል ላይ አምጥተው የጫኑት።

"…እናም ይሄ የአጋንንት መንፈስ፣ ደም መጠጣት ልምዱ የሆነ መንፈስ፣ የሰው ደም ግብሩ የሆነ መንፈስ፣ ሀገሪቷን ሽባ፣ ኦርቶዶክስን ዱቄት ለማድረግ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። የትግሬዎቹ እምነት ተሸርሽሯል። የወያኔ ሰይጣን በአቢይ ሰይጣን ተበልጧል። ትግራይ እነ አባ ሰረቀ የመሣሰሉ አጋንንቶች ተፈተው ተለቀውባታል። የትግሬ ሕዝብ አሁን ሥራ የለውም፣ ወጣቱ ተስፋ ቆርጧል። እየተሰደደም ነው። ትግራይ ወንጀል በርክቷል። ግድያ፣ በጩቤ መወጋጋት ልማድ ሆኗል። በትግራይ ቤተክርስትያን መናፍቃን እጅ ወድቃለች። እነ አባ ሰረቀ ብርሃን እጅ ወድቃለች። ነገሩን በቀላሉ የሚያየው በዝቷል። የጌቾና ደፂ መጣላት ድራማ ነው። መታረቅም ድራማ ነው። በዚህ አጀንዳ ሕዝቡ በመቀመጫው ላይ የተሰካውን ጩቤ ነቅሎ እንዳይታከም ቀልቡን መስረቂያ ነው። በግል ሳይሆን እንደ ክልል ልንጠፋ ነው። ጌታቸውና ደፂ ከተጣሉ ምን ሊውጠኝ ነው ብሎ ትግሬ ከመቀመጫው ላይ የተሰካበትን ሳንጃ ሳይነቅል ከነ ህመሙ እነሱን እያሰበ ችግሩን፣ ስቃዩን፣ ህመሙን እንዲረሳ ለማድረግ ነው። ለዚህ ነው አሁን አይታችኋል? ተፈናቃዮች ይመለሱ፣ የተራበ ሕዝብ ነፍ ነው፣ ሳር፣ ቅጠል እየበላ ነው፣ በራብ እየረገፈ ነው የሚል ዜና ከወደ ትግራይ ሰምታችኋል? አልሰማችሁም፣ አንሰማምም። ምክንያቱም ፒፕሉን ትግሬውን በሃይማኖት እና በደፂና በጌቾ ነፃ ትግል አጀንዳ ቀፍድደው ስለያዙት። እንዲህ ነው እየሆነ ያለው

"…ድሮ ድሮ አንድ አጀንዳ ሲፈበረክ "ማነሽ የብርጓል እስቲ ነጠላዬን አቀብይኝ" በማለት እንደ ቁጭራ ሰፈር ሴት አጀንዳውን ቀምቶ ማኅበራዊ ሚዲያውን ሲያጥለቀልቅ የሚውለው ዐማራው ነበር። ወሬ ሞቱ ነበር ድሮ ዐማራው። በማያገባው፣ በማይመለከተው ሁላ ገብቶ ፈትፋቹ ዐማራው ነበር። በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ሁላ ሲንጫጫ፣ ሲቀውጠው የሚውለው ዐማራው ነበር። የራሱን ጉዳይ ትቶ በተወረወረለት አኞ አጀንዳ ላይ ለሃጩን ሲያዝረበርብ የሚውለው ዐማራው ነበር። የዐማራ ወንድ አክቲቪስት፣ ከመንደር ነገረኛ ሴት በበለጠ…👇 ①… ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና። የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ። ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። ኤር 6፥ 13-15

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይሄን የፋኖ ጀግንነት እያየ ከኦሮሞ የወሃቢያ እስላምና ከደቡብ ጴንጤ በቀር ከአቢይ ወገን የሚቆም ወታደር ለመሆን የሚመኝ አንድም ኢትዮጵያዊ የለም። በአፈሳ ብትወስደው እንኳ ተኩስ ሳይጀመር ነው የሚማረክ።

"…በገንዘብ ዳጋፊዎቹ እነ ጣሊያን እነ ሳዑዲ አረቢያ፣ ድሮን እና ቦንብ አቅራቢዎቹ እነ ኢራን እና ኤምሬትስ እና ቱርክ ይሄን የዐማራ ጀግንነት ሲያዩ ምን ይሉ ይሆን…?

"…እነ ሱማሌ፣ እነ ግብጽና እነ ሱዳንስ ይሄን የመከላከያ ሠራዊት በዐማራ ፋኖ በዱላ መነዳት ሲያዩ ስለ ዐማራ ጀግንነት ምን ያስቡ ይሆን?

• እነ ሂዊ፣ እነ ኦኒ፣ እነ ብልጼ እንደሁ አይነግሯቸው። 😂

"…እግዚአብሔር ይርዳችሁ። ኃይሉን፣ ማሸነፉን፣ ሞገሱን ይስጣቹሁ። በርታ ዐማራ፣ ሃቅ አለህና ታሸንፋታለህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…4 ሰው ብው 😡 ብሎ የተናደደበት እና 13ሺ ሰው ያነበበው የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ቀጥሎ ደግሞ የእናንተን ሓሳብ ወደማስተናገዱ ያመራል።

"…እህሳ … ዛዲያስ እናንተስ ስለ አደንቋሪ እንቁራሪቶቹ ምን የምትሉት አለ? ጀምሩ… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Zemedkun Bekele:
"ርእሰ አንቀጽ"

"…ለፍቶ፣ ጥሮ፣ ደክሞ ባገኘው ሀብት ከተማ ላይ ጥሩ ቤት ገንብቶ፣ ትዳር ይዞ፣ ልጆች ወልዶ ይኖር ነበር አሉ አንድ ሰው። እየቆየ ሲመጣ የሀብቱም መጠን ሲጨምር የከተማው ግርግር መንፈሱን ይረብሸው ጀመር አሉ። እናም አንድ ውሳኔ ወሰነ። ውሳኔውንም ለክብርት ባለቤቱና ለውድ ልጆቹ አማከረ። "እንደምታዩት ነው። ብዙ ደክመን ሀብት ንብረት አፍርተናል። ቤትም መኪናም አስተማማኝ ድርጅትም አለን። ነገር ግን በከተማው መሃል ያለው የሕዝብ፣ የመኪና ጩኸት በእረፍት ቀኔ ማረፍ ብፈልግ እንኳ ሊያሳርፈኝ አልቻለም። እናም ለምን ከከተማ ወጣ ብለን ቤት ሠርተን በዚያ አንኖርም? ብሎ አማከራቸው አሉ። ቤተሰቡም በደስታ ሓሳቡን ተቀበለ።

"…ከጥቂት ዓመታት ድካም በኋላ የሚፈልጉት ዓይነት ቦታ፣ የመሬት አቀማመጥ፣ ፏፏቴው ቅርብ፣ ሜዳው፣ ወንዙ፣ ጨፌው፣ ጫካው ያማረ፣ ትንሽዬ ኮሬም በአቅራቢያው ያለ የቤት መሥሪያ መሬት አግኝቶ ቤቱን ገንብቶ ጨረሰ አሉ። ከዚያም ቤተሰቡ ሁሉ የከተማውን ኑሮ ትቶ ከከተማው ውጪ ወደተሠራው ወደ አዲሱ መኖሪያ ቤቱ ለመግባት ዝግጅቱን ጀመረ። የቤቱን ምርቃትም ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ቤተሰቡ ወደ አዲሱ ቤት በሚገባበት ቀን በእኩል ቀን እንዲመርቅ መርሀ ግብርም ተያዘለት። እናም እኩል በአንድ ቀን ምርቃቱም ተካሄደ፣ ቤተሰቡም ወደ አዲሱ ቤት ገባ። ፌሽታ ነበር። አድናቆትም ነበር። ይሄን ቦታ፣ ይሄን ስፍራ እንዴት አገኘኸው? አቤት ሶፋው ሲያምር፣ የቤቱ ቀለም ውብ ነው፣ አድናቆቱ፣ ሁካታው፣ ጭፈራው፣ መብል መጠጡ ሁሉ ልዩ ነበር አሉ። መርሀ ግብሩም ሲያልቅ ሁሉም ወደ ቤቱ ሲመለስ፣ ባለቤቶቹም ወደየመኝታቸው ሄዱ። ከድካም ብዛት እንዴት እንደተኙ ሳያውቁትም በየፊናቸው ተንጋለው ነጋላቸው። የዚያን ዕለት የመኪና ጡሩንባ የለ፣ ጩኸት የለ፣ አምቡላንስ የለ፣ ምንየለ ለሽ ብለው አደሩ።

"…መሸ ነጋ ሁለተኛ ቀን። ቤተሰብ ፀጥታ የሞላበት ሰላማዊ አየር እየማገ፣ እየተነፈሰም ዋለ። መምሸት አይቀርምና መሸ። ከራት በኋላም የግድ ነውና ወደ መኝታ ቤታቸው ገብተው ለመተኛት በሞቀው፣ በምቹው አልጋ ላይ ጋደም አሉ። እንቅልፍ ግን ከወዴት ይምጣ? ሰዎቹ ደክሟቸዋል፣ መተኛትም ፈልገዋል፣ እንቅልፍም እያዳፋቸው ነው፣ ነገር ግን እንዴት ይተኙ? የሆነ ድምጽ፣ ከዚህ በፊት ሰምተውት የማያውቁት ሰቅጣጭ፣ ረባሽ ድምፅ ይበጠብጣቸው ጀመር። የሚያውቁት ከከተማ ያስወጣቸው የመኪና ጥሩንባ አይደለም። ከቤተ ክርስቲያን የሚወጣ ማኅሌት፣ ቅዳሴም አይደለም። አዛንም አይደለም። አምቡላንስም፣ የእሳት አደጋ መኪና፣ የፖሊስ መኪናም ድምጽ አይደለም፣ ሞንታርቦ ከፍተው ካሴት የሚሸጡ፣ ለታመመ ሰው የሚለምኑም፣ ሰው ሞቶ የዕድር ጡሩንባ፣ ቆሻሻ አውጡም የሚሉ አይደሉም። ቆራሌው፣ ልዋጭ ልዋጭ፣ አለ ሱፍ ሲፍ አለ የሚሉም አይደሉም። ብቻ ጩኸት፣ ርብሽ ርብሽብሽ የሚያደርግ ጩኸት።

"…መስኮት በር በደንብ ቢዘጉም። ትራስ ጆሮአቸው ላይ ቢጠቀጥቁም፣ ጥጥም ጨርቅም በጆሮአቸው ላይ ቢወትፉም ኧረ እሱ እቴ። ወይ ፍንክች። በር ከፍተው አዩ፣ ሰቅጣጭ ጩኸቱ አላቆመም። የዚያን ቀን እንደምንም አደሩ። ነገ ይሻላል ብለውም በተሰፋም ዋሉ። በሁለተኛውም ቀን እንደዚያው። እየቆዩ ሲመጡ ነፍሳቸው እስክትወጣ ድረስ የወደዱትን ስፍራና አካባቢ እየጠሉት መጡ። የሚረብሻቸው ድምጽ ከተማውን የሚያስናፍቅ ሆነ። ቀን ቀን ቢፈልጉት አይሰማም። ሌሊት ግን እሪ ነው። ግራ ገባቸው። ከብዙ ድካም በኋላ ግን የችግሩን ምንጭ ደረሱበት። ችግሩ ያለው ከቤታቸው አጠገብ ካለው ኩሬ ውስጥ እንደሆነ ገባቸው። አዎ ኮሬው ውስጥ የሚኖሩ እንቁራሪቶች ነበሩ ሀገር ምድሩን ቀውጢ ያደረጉት። እናም እነዚህን እንቁራሪቶች ለማስወገድ እንቅስቃሴ ተጀመረ። የነጋዴ ነገር መቼም መላ አያጣምና አንድ መላ ዘየደ። ለምን እንቁራሪቶቹን አጥምጄ ለእነ እንትና ሬስቶራንት አልሸጥም ብሎ አሰበ፣ አሰበናም ወሰነ። ወሰነናንም ወደ ሬስቶራንቱ ባለቤቶች ዘንድ ሄዶም አነጋገረ።

"…እንዲያውም ወጋ ጨምረን እንገዛሃለን። የአቅርቦት ችግር ስላለብን እባክህ ፍጠን አሉት ባለ ሬስቶራንቶቹ። ሰውየው መንጠቆ ገዛ፣ ማጥመጃ መሣሪያዎችንም ሸመተ። ለገንዘቡም ብቻ ሳይሆን በዚያውም ልዝናና ብሎም አሰበ። ለሚያጠምዳቸው እንቁራሪቶች መያዣ፣ ማቆያም የሚሆን በርሜል ሁላ አዘጋጀ። እናም ወደ ኩሬው ሄዶ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ተሰየመ። ጠዋት የተቀመጠ እስከማታ ተጎልቶ ሁለት እንቁራሪት ብቻ አጠመደ። ቦታ እየቀያየረ ቢሞክር፣ ፀሐይ እየመታው ሲገላበጥ ቢውል ሌሎች እንቁራሪቶች ድርሽ አልል አሉ። ዓሣም እንቁራሪትም ማጥመድ ትእግስት ይፈልጋል ይባላል እና በትእግስት ቢጠብቅ ቢጠብቅ ከሁለቱ እንቁራሪቶች በቀር ወላ ሃንቲ ሀባ እንቁራሪት ጠፋ። የእነእንትና ሬስቶራንትም በጉጉት እየጠበቀ ነው። ሰውየውም ሲደክም ውሎ ሁለት እንቁራሪት ብቻ አጥምዶ ሲመሽ ወደ ቤቱ ገባ። የዚያን ቀን ሌሌት ቤተሰቡ ሳይረበሽ በሰላም ተኝቶ አደረ።

"…በሁለተኛው ቀንም እንቁራሪት ለማጥመድ ሰውየው ወጣ። እስከምሽት በኩሬው አጠገብ ውሎ ምንም እንቁራሪት አንድም ሳያጠምድ ወደ ቤቱ ተመለሰ። እሱ ወደቤቱ በምሽት ሲመለስ ቤተሰቡ በጊዜ ተኝቶ አገኘ። እሱም በጊዜ ተኛ። በማግስቱ ግን ከቤተሰቡ ጋር መከረ። የሚገርም ነው። እኒያን ሁሉ ቀናት እንቅልፍ አሳጥተው ከወደድነው፣ ደስም ካለን ሰፈራችን ሊነቅሉን፣ ሊያሰድዱን የነበሩት፣ ትራስ ስር የወሸቁን፣ በጆሮአችን ጥጥና ጨርቅ ያስወተፉን፣ በርና መስኮቱን ያስዘጉን፣ እንዲያ እረፍት የነሱን፣ የካምቦሎጆ ደጋፊ ድምፅ አውጥተው እንቅልፍ የነሱን እነዚህ ሁለት እንቁራሪቶች ብቻ እኮ ናቸው በማለት ከእኒያ ትናንሽ ሁለት ፍጥረታት የሚወጣ ድምጸፅ እንዴት የካምቦሎጆ የቅሪላ ደጋፊዎች ድምፅን ሊበልጥ ቻለ ብለው በመደነቅ ተነጋገሩ። ለእነ እንትና ሬስቶራንትም የሚያቀርቡትም ቀረ። ሁለቱን እንቁራሪቶች ከኩሬው አጥምደው ካወጡ በኋላም በሰፈሩ ሰላም ሰፈነ። 

"…አሁን ባለው የዐማራ ፋኖም ትግል የማየው እንደዚያ ያለ ነገር ነው። ጎንደርም፣ ጎጃምም፣ ወሎም ሆነ ሸዋ ላይ የሚታየው እንደዚያ ነው። የትግሉ ረባሽ እንቁራሪቶች ከሁለት ሦስት አይበልጡም። ይታወቃሉ። ድምጻቸው ግዙፍ ነው። ዓለም ይነቀንቃል። ጨክኖ እነሱን በብዙ ድካም ማጥመድ ከተቻለ ሰላም ይሆናል። መፍትሄው እሱ ብቻ ነው። እንዲያ ማድረጉ ላይ ነው መበርታት። የችግሩ ቦታ ኩሬው ከታወቀ። ኩሬው ውስጥ ሆኖ እንቅልፍም፣ ሰላምም የሚነሣው ነገር ከታወቀ፣ በቃ እሱን ችግር ፈጣሪውን ተሟሙተህ አጥምደህ ያዘው። ከያዝከው በኋላ መልሰህ ይበጠብጥህ ዘንድ በሽማግሌ ውትወታ አትልቀቀው። በእጅ ሰጥተህ በፈረስ ለፍለጋ አትድከምም። የጎንደር ዩኒቨርስቲው የአቢይ አምላኪው የዶር አሥራት አባት መምሬ አጸደወይን ቢመጡ እንኳ አትሞኝ። እሺ በጄም አትበል። ሌባ ይዞ ዱላ ይጠየቃል እንዴ? በስንት መከራ የያዝካቸውን እንቁራሪቶች መልሰህ ወደ ኩሬው ለቀህ ድጋሚ የምን እየዬ ነው? ተረበሽኩ፣ ተጨነቅኩ፣ ወየው ወየው ብሎ ለቅሶ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? …👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤” ምሳ 23፥17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel