zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች…። ” ማቴ 27፥64

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄ የለንደን ፋኖ ነው…!

"…እንደ እከደከን ማንችሎት፣ በብልጠትም ሆነ በጉልበት አበጀ ጥላሁን ጉግሣ ቤት ገብቶ ለሽ ብሎ ተኝቶ የነበረው ዐማራ የእንቅልፍ አዚሙ ተወግዶለት በመጨረሻው ሰዓት ከጥልቅ እንቅልፉ ነቅቶ በት በት እያለ ነው። እኔም ስለቴን ለለንደኗ ማርያም ላስገባ ነኝ ማለት ነው። የለንደኗ ማርያም አሁንም የቀረውን ዝንጉ፣ ዳተኛ፣ አለቅላቂ፣ ወሬኛ፣ ሸውከኛ፣ ፈሪ፣ አስመሳይ፣ ገተት፣ ሆዳም፣ ማይም፣ የወገኑ ስቃይ የማይሰማው፣ ራስወዳድ ዐማራን አዚሙን አስወግደሽ አንድ ላይ እንዲህ ካቆምሽው ስለቴን አስገባለሁ።

"…እነ አዲስ፣ እነ ወርቁ ብቻቸውን ይጮሁበት፣ እነ ያየሽህራድ ብቻቸውን ዋይዋይ ይሉለት የነበረው ዐማራ ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ጉያ በተአምራት ተፈልቅቆ ወጥቶ እንዲህ ሲቀውጠው እንደማየት ምን የሚያስደስት ሌላ ነገር አለ?

"…አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮጳ፣ አፍሪካም በሙሉ ይቀጥላል። ዐማራ ለመነሣት የፈጀውን ማገዶ ቢፈጅም መነሣቱ አይቀሬ እንደሆነ ዐውቅ ነበር። አሁንም ይቀራል። በዛሬ ምሽት የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ይሄም ይዳሰሳል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ…!✊✊✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄ መረገም ነው…

"…ደግነት መልክ ቢኖረው እሷን ነው የሚመስለው ተብሎ በያያ፣ ኢትዮጵያዊቷ ማዘርትሬዛ በፓስተር ምስጋናው አንዷለም ተብሎ ፕሮፓጋንዳ የተሠራላት፣ በእናቷ አዲስ ዘመን ግማሽ ቅማንቴ በአባቷ ኦሮሞ የደርግ ወታደር ልጅ እንደሆነች በሚነገርላትና ልክ እንደ እስክንድር ነጋ ስሟንም መልኳንም ፀረ ዐማራው ቡድን ቀባብቶ የዐማራ ሾተላይ አድርጎ ያዘጋጃት፣ የኢንተርኔት ላይ ማፍያዋ በተደራጁ የጎንደር ፀረ ዐማራ ኔትወርኮች አማካኝነት በተቸገሩ ዐማሮች ስም በቲክቶክ ወዘተ ዶላር ከዳያስጰራው በመግፈፍ ለተቸገሩት ዐማሮች ሳያደርሱ ይበሉ፣ ይሸቅጡ የነበሩት ቡድኖች በግፍ የሰበሰቡትን ብር ሳይበሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል።

"…በተለይ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ላይ ፈስሰው በቁማቸው ትል የሚረግፍባቸውን የዐማራ ተፈናቃዮች ታስታውሳላችሁ። እነ መማር አለባቸው እና በእሷ ጀርባ የነበሩት የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች 1ሚልዮን ብር ሰብስበው እንዳስቀሩባቸውም እንደነገርኳችሁ ታስታውሳላችሁ። ዋነኛው የመማር አለባቸው የጎንደር የዘረፋ ወኪልንም እነ አያሌው መንበር ለተፈናቃዮቹ መርዳትን እንደ ነውር ቆጥረው አፋቸውን በከፈቱብኝ ወቅት የጎንደሩን ወኪላቸውን ቢያንስ እግዚአብሔር ፍርዱን እስኪሰጥህ ዝም በል ማለቴም ይታወሳል።

"…ይህው ዛሬ በጎንደር የእነ መማርን ተወካይ በባንኩ ውስጥም ከ14 ሚልዮን ብር በላይ ዘጭ ብሎ፣ የተለያዩ መኪኖችንም በስሙ ገዝቶ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በተፈናቃይ ብቻ ሳይሆን በፋኖዎችም ስም የተሰበሰበ ገንዘብ አለና ፋኖዎችም ገንዘባችንን ስጠን እያሉት፣ ለድሆቹም የተዋጣውን ብር ሳይሰጥ ብሩ የአገዛዙ ቀለብ ሆነ።

• እነ ምስጋናው አንዷለም ሆይ…! አቦ እግዚአብሔር አምላክ የእጃችሁን ይስጣችሁ። በማታው የመረጃ ቴቬ የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ በሰፊው እመጣበታለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…9

"…በመጨረሻም…በመጨረሻም ያ ሞኝ መስሎ፣ ሀገር መውደዱ እንደ ፈሪም እንደ ፋራም፣ አንዳንዴም እንደ አድርባይ አስቆጥሮት፣ ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያን ይመራ ዘንድ ሕፃን መሆኑን ያልተማረ ማይም መሆኑንም እያወቀ፣ ጨቅላ ቢሆንም ግድየለም እየታገዘ ያድጋል፣ ይሁን ብሎ ድጋፍ ሰጥቶ፣ አንድም ኢትዮጵያን ስሟን እየጠራ፣ ሰንደቋን ለብሶ እየማለ እየተገዘ ቢያየው አያታለለኝማ አይሆንም፣ ግድየለም ጊዜ መስጠትም አይከፋም፣ አያስከፋም፣ ሽግርም የለውም፣ በማለት ለበሸሻሻው አራዳ ለአራጁ አቢይ አሕመድና ለአረመኔ ግሩፖቹ ዕድል የሰጠው፣ ያ በጊዜ አልነቃ ብሎ ጭራሽ እየሰደበኝ ጨጓራዬን ሲልጠኝ የከረመው ታላቁ የዐማራ ሕዝብ አሁን ትእግስቱ አልቆ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ማስታወቂያ ለጥፎ ቀጠሮ ይዞ ተነሥቷል።

"…ሰልፉ ዓለም አቀፍ ነው። ትግል ጠላፊ ግንቦቴ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ ግንባሩና ታፋና ጭኑም ግን ሰልፉን ሊመሩት አይገባም። አይፈቀድላቸውምም። ሰልፉን ዐማሮችን ይመለከታል፣ ዐማሮችም ይመሩታል። ለዐማራ ያዘኑ፣ ነግ በኔ ብለው ያሉም ቤርቤረሰቦች ግን በሰልፉ ላይ በመሳተፍ ለዐማራ ሕዝብ አጋርነታቸውን ያሳዩታል ተብሎም ይጠበቃል።

• መግደርደር የለም፣ ወጥር ዐማራ…! 💪💪🏿💪🏿👏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…6

"…ዐማራ እንዲህ ጥርሱን ነክሶ በባዶ እጁ ከቱርክ፣ ከሳዑዲ፣ ከኢራንና ከሳዑዲ አረቢያ በሚላክ የአቢይ አሕመድ ድሮን ጋር የሚዋጋው የሚሳፈጠው ለቄንጥ አይደለም። አሁን ተሰልፈህ ብትስቅበት፣ በቲክቶክ ስትሰድበው፣ ስትፎትተው ውለህ ብታድር መስሚያው ጥጥ ነው። ደንታውም አይደለም። አባቴ አሁን እሱ ጥርሱን ነክሶ፣ ወገቡን ታጥቆ ለይመለስ ተነሥቷል። የቀን፣ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው እንጂ እመነኝ ዐማራ ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።

"…አልሙት፣ አልፈናቀል፣ ደመከልብ አልሁን፣ አልዘረፍ፣ የዜግነት መብቴም የሕግ የበላይነትም ይከበር ብሎ በመጠየቁ እነ ትግሬው አባ ሰረቀ ሳይቀሩ "ዐማራ የሚባል ዘር የለም፣ ከዚያም ከዚህም ተለቃቅሞ የመጣ ልቅምቃሚ ነው ብለው ፍትህ ስለጠየቀ ብቻ ከፍ ዝቅ አድርገው በድፍረት አፋቸውን ሞልተው ሰደቡት። ተላገዱበት። ወዳጄ ያ "የለም" የሚሉትን ዐማራ ግን ቤቱ ድረስ ሄደው ሊያጠፉት ሲፈልጉ "ዐማራ የት ነው? ሂድ ወደ ክልልህ በማለት ሲጨፈጭፉት ይታያሉ። እንደ ጫጩት እኮ ነው የፈጁት። ይሄ አልበቃ ብሏቸው በሦስት ሳምንትም ሱሪውን እናስፈታዋለን ብለው ቤቱ ደጃፉ ድረስ ቢሄዱም ይኸው አጅሬው ዐማራ ለኅልውናው ሲል የእህቱን፣ የሚስት የእናቱን በግፍ መታረድ እያሰበ እንዲህ እንደከፍት እየነዳው ይገኛል።

"…የጊዜ፣ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ ማርያምን ስልህ ዐማራው ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• እየኮመታችሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…4

"…ዐማራ ማምረሩን አየህልኝ። ይሄ ዛሬ በአጎት ሀገር ጀርመን በፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ዐማራውያን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ጨካኝ፣ አራጁ፣ ነፍሰ ገዳዩ አረመኔው የኦሮሙማው አገዛዝ ያለ ርህራሄ በጅምላ ሕፃን፣ አረጋዊ፣ ነፍሰጡር ህመምተኛ ሳይል፣ በዓረቦች ቦንብ በድሮንና በጀት ለሚጨፈጭፋቸው ወገኖቹ ድምፁን ለማሰማት ግልብጥ ብሎ የወጣው ሕዝብ ነው።

"…እስከዛሬ ድረስ በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች አዚም ተተብትቦ ዐማራ ነኝ እንዳይል፣ ዐማራ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ ተውሎበት የነበረው ዐማራ አሁን አዚሙ እየተራገፈለት ይመስላል። ለኦሮሞ ሞት፣ ለትግሬ በኤርትራ ወረራ፣ በአጠቃላይ ዘር ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይመርጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ሲደርስ ግልብጥ ብሎ ድምጹን ሲያሰማ የነበረው ዐማራ ለእሱ ጊዜ ሲሆን ሌሎች ቢደበቁም እሱ እንኳን ለራሱ ለሌሎችም ሲተርፍ ነበር እና ይኸው ብቻውን ዐማራ ነኝ ብሎ ግልብጥ ብሎ መውጣት ጀምሯል። ይሄ ስኬት ጅማሮ ነው።

"…ያልነቃው ገተት ዐማራ ሲነቃ፣ ልክ እንደ ትግሬ፣ እንደ ኦሮሞ፣ ልክ እንደ ኦሮሞና እና እንደ ደቡብ ጴንጤ፣ ልክ እንደ ኦሮሞ ወሃቢያ በቃል ኪዳን፣ በዓላማ ጨከን፣ ቆረጥ፣ ኮምጨጭ ብሎ ሲነሣ አስቡት።

"…ዐማራ በዚህ መልክ ከተነሣ በቀጣይ ሾተላይ ዶላር ዩሮ የማያሳድድ፣ ከርሳም ለትውልዱ ለነገዱ የሚያስብ፣ 7 ወደላይ፣ 7 ወደ ጎን ተቆጥሮ ዐማራ የሆነ ድርጅት ያስፈልጋል። ልክ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ለነገዱ ታማኝ የሆነ ድርጅትም ያስፈልገዋል።

• ብራቮ ዐማራ…!

• ተቀበል። ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስዊድን፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ ወዘተ ያለህ ዐማራም አትሽኮርመም። እንደ ጀርመን ዐማራ ግልብጥ ብለህ ውጣ።

• እየኮመታችሁ…!


በዝህን ስዓት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…2

"…የቅዳሜ ከሰዓት ተቀበል መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው። አድማጭ ተመልካቾቻችንም ከያሉበት ሆነው ተዋዱጁን የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችንን እየተከታተሉ መሆናቸውን በሚያደርሱን የፎቶና የቪድዮ መረጃ እያሳወቁን ነው።

• ተቀበል… እየገጠማችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት በኋላው የተቀበል መርሀ ግብራችን አሁን በይፋ ጀምሯል። እንደተለመደው ለአዝማሪው ለባለመሰንቆው ግጥም በመስጠት መርሀ ግብራችንን እንጀምራለን።

"…ከእናንተ የተመረጠ ግጥም በመለጠፍ መርሀ ግብራችንን እንጀምራለን።

• ተቀበል…

• ግጥም ስጡት…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመርሀ ግብር ማስታወቂያ

• እንደ ተለብዥን ብሮግራም በጽሑፍ ብቻ ተወዳጅ እየሆነ የመጣው የእኔ የዘመዴ የቴሌግራም ቤጅ…😁 በነገው ዕለት ስለሚኖረው መርሀ ግብር ከወዲሁ ለአድማጭ፣ አንባቢ ተመልካቾቹ ያስታውቃል።

"…በቅድሚያ በእግዚአብሔር ሰላምታ ቀናችንን በምስጋና እንጀምራለን። 1ሺ ሰው ፈጥኖ "እግዚአብሔር ይመስገን" በማለት ተረባርቦ፣ ተሻምቶ ካመሰገነ በኋላ በቀጥታ ወደ አጫጭር መረጃዎች ወደማድረስ እንገባለን።

• በአንድ በእኔ በሀረርጌው መራታ በዘመዴ ጣቶች ተሰንዶ እንደ ግዙፍ ተቋም፣ ብዙ ሺ ሠራተኛ እንዳለው ጣቢያ በግሩም ሁኔታ ተዘጋጅቶ ወደ እናንተ የሚቀርበው ሳምንታዊው የቅዳሜ ከሰዓት የተወዳጁና የተናፋቂው "የተቀበል" የግጥም፣ የቅኔ መርሀ ግብራችንም ተሰናድቶ ወደ እናንተ ይቀርባል። ከወዲሁ እናንተም ግጥም፣ ቅኔያችሁን ጽፋችሁ ታዘጋጁ ዘንድ ትበረታታላችሁ። አልችልም አይባልም።

• በነገው መርሀ ግብራችን ሙግቶች፣ ክርክሮች፣ ውይይቶችም ይኖራሉ። ብቁ ሆነው የተገኙ ካሉና ለአቅመ ነቆራ የደረሱ ካሉም እንደተለመደው ያው 😡 የሚያደርግ የሚያስነቅል "ነቆራም" ይኖረናል። ጥያቄዎችንም በስፋት እንጠይቃልን።

• የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የእኔ ርእሰ አንቀጽ ተነብቧል። ቀጥሎ ደግሞ የእናንተ ተራ ነው። የጥቂት ሰዎችን አስተያየት እናነብና በቀጣይ ጊዜ ካለን ከጎንደር ዕዝ ፋኖዎች ከእነ ሀብቴ ግሩፕ የደረሰኝ ለሕዝብ ሁሉ አድርስልን የሚል መልእክት አስደምጣችኋለሁ።

"…አሁንም ጊዜ ካለን ዶር አምሳሉን፣ ወ/ሮ ሕይወትን፣ አቶ ሙልጌታንና አቶ ኤርሚያስን፣ እንዲሁም ኤርሚያስ ለገሰን፣ ወዳጄ መስፍን አማንና የእስክንድር ነጋ ባለቤት ወሮ ሰርካለም ፋሲል በኮሚቴነት የመሩትና ከሕዝብ የተሰበሰበ በመቶቪዎቸ የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደደረሰ መጠየቄን እቀጥላለሁ።

"…አበበ በለው ለምን የእስክንድር ሚስት ስም በገንዘብ ጉዳይ ስሟ ይነሣል ብሎ ለወቀሰኝ ወቀሳም ለምን እንደምጠይቅ የቪድዮ መረጃ ጭምር ይዤ እሞግታለሁ።

"…አንድ 50 ያህል ሰው በርእሰ አንቀጹ ላይ አስተያየቱን ከሰጠ በኋላ ምሽታችንን በጦፈ ክርክር፣ ሙግት እና ውይይት ደመቅ አድርገን እናሳልፋለን።

• ✍✍✍ ጀምረ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አይደለችም ነበር ያሉኝ። አያሌው ግን ነፍስህ አይማርም። ብቻ የጎንደር ጉዳይ ሳይወድ በግዱ እየጠራ ነው። በቅርቡም ተአምር ትሰማላችሁ። ዛሬ ማታም ከጎንደር ፋኖ የደረሰኝን አንድ ግሩም ቪድዮ እለቅላችኋለሁ። ከእስክንድር ነጋም ጋር በይፋ ይለያያሉ። የፓስተር ምስጋናው ፋፍዴንም ይከስማል። እነ ሀብቴና ባዬም ይታረቃሉ። ጎንደርም እንደ ጎጃም አንድ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ጎንደርን እነ እስክስ አበበ በለው አያዙትም። እጃቸውን ሳይታጠቡ ገብተው አይፈተፍቱበትም። አስሬ ለክቶ አንዴ የሚቆርጥ የጎንደር ዐማራ ተፈጥሯል። ወልቃይት አትገባም የተባለው የጎንደር ዐማራ ፋኖ መግለጫ ማውጣትም። ወልቃይት ገብቶ ማስተንፈስም ጀምሯል። አለቀ። እነ ምስጋናው ቢቃወሙትም እነ ሀብቴ በወልቃይት ጉዳይ መግለጫ ማውጣት ጀምረዋል።

"…እንደ ሁላችንም በእስክንድር ነጋ የአየር ላይ የስም ግንባታ የተሸወዱም ዐማሮች አሉ። እኔን ራሱ አንድ ወቅት ትዊተር ስፔስ ላይ ጋብዘውኝ የነበሩ ቅኖችን ዐውቃለሁ። ያኔ ቀርቦ ያወራኝ በጣም የማከብረው የሲያትሉ ወንድሜ መታገስ ነበር። እስከ አሁን ምንም ያልተቀየረ፣ የትም ቦታ በክፉ የማያነሣኝ፣ ባዘዘኝ ቁጥር ስታዘዘው የኖርኩት መታገስ ነበር የጋበዘኝ። እነ ሲሳይ ሙሉ ዋኘውም ቢሆን የሚጠሉኝ በጥቂት ነገር ነው። ሀብታሙ በቀለ ኦነግ እናቱን የገደለበት የሀረርጌ ዐማራ ነው። እነ አኪላ ናቸው ሰው ብሎ ተጠግቷቸው ከእነርሱ ጋር መሥራትም ጀምሮ ተንኮላቸው ኋላ ላይ ሲገለጥለት ስለተለያቸው "የአያቱን ስም ጉደታ" ብለው ኦሮሞ ነው ብለው ስሙን ያጠፉት እንጂ ክፋት የሌለው ሰው ነው የሚሉም አሉ። አይ እሱማ ኦነግ ነው የሚሉም አሉ። ሰውየው በሙያውም የተከበረ፣ እንደ ሌላው ቀፋይ ከትግሉ ሳንቲም ሊለቅም ያልመጣ፣ ቦይንግ ካምፓኒ የሚሠራ ዘጭ ያለ ገቢ ያለው ነው የሚሉት የሚያውቁት። ከፈለጋችሁ ስልኩን ለጥፌላችሁ ደውላችሁ ልታረጋግጡ ትችላላችሁ።

"…ሀብታሙ እኔን መስደብ፣ መጥላት የጀመረውም በእስክንድር ስለመጣሁበት እንጂ ምንም ምክንያት የለውም እኔን ለመጥላት። ኃይሌም ተራማጅ ጎንደሬ ነው። የጎንደር ዐማራ። እኔን አምርሮ ቢጠላኝም እነ ምስጋናውን በሚጠላበት የጥላቻ መጠን ግን እኔን አይጠላኝም። ሚዛናዊም ነው። ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለመላው ዐማራም ነው የሚሠራው። ለዚህ ደግሞ ከምርልጅ ተድላ ራሱ ምስክር ነው። እነ ምስጋናውን አምሮሮ ነው የሚጠላቸው። እነሱ በግምባሩ ምስረታ ወቅት ለእስክንድር ደም ሰጥተው ሲሟገቱ እነ ምስጋናው የሉም ነበር። ከሃዲው እስክንድር የለፉለትን እነ ሲሳይን፣ ሀብታሙን ትቶ በዶር አምሳሉ አስናቀ በኩል ፓስተር ምስጋናውን በላያቸው ላይ አምጥቶ በመሾም ነው ያሳበዳቸው። እነ ሲሳይ እና መታገስ እስከ አሁን ተስፋ አልቆረጡም። ከፓስተር ምስጋናው ጋር ቢጣሉም ድርጅቱንም ይደግፋሉ። የሐረርጌው መራታ ብላዘሬ ሀብታሙ በቀለ እንዲያውም ሰሞኑን እስክንድር ነጋን በግልጽ መተቸት ጀምሯል። ብራቮ የሀገሬ ልጅ። በርታ።

"…እስክንድር እንደ ቆንጆ ሴት ፉንጋ አስከትሎ በመሄድ ቆንጆ መምሰል፣ ደደብ ማይም ይዞ እየዞረ ሊቅ መስሎ መታየት ስለሚፈልግ እንጂ እነ ዲሲ ግብረ ኃይልን፣ እነ ሕይወት፣ ኤርሚያስን ይዞ የተንገታገተው በዚያ መንገድ ሄዶ ከሚሾቅ እነዚህ ፊደል የቆጠሩትን ቢቀርብ ኖሮ ባይተርፍም በጊዜ ሳይነጋ ፖለቲካዊ ሞት አይሞትም ነበር ብዬ እላለሁ። ሀብታሙ አያሌው ቀፋይ ነው። በብታሙ በቀለ ሲያትል ነው የሚኖረው ለቦይንግ ነው የሚሠራው። ቢሠጥ ቢለግስ አንጂ የተለገሰ አይነካም ብዬም አምናለሁ። ሲሳይ ኢፒዲሞሎጅስት ነው እሱም ሲያትል ነው የሚኖረው። አሁን ቴዲ ሀዋሳ ቤት ገብቶ ከነ በቀለ ወያ ከማይሞቹ ጋር ወርዶ ሲታይ የኡበር ሹፌር ነው የሚመስለው። ምንም ቢጠሉኝ አክብሮቴ ግን እንዳለ ነው። መታገስ ሆይ መልእክቱን አድርስልኝ። በጊዜ ቢነቁ ይፈወሳሉ። አለበለዚያ እነሱም አብረው ይከስማሉ።

"…እንዲህና እንዲያ እያለ የዐማራው ትግል ተንጦ፣ ተንጦ እንደ ቅቤ አናት ላይ መውጣቱ እንደሁ አይቀርም። የአየር ላይ ወሬኞችም መስመር መያዛቸው አይቀርም። የምድር ላይ ከፋፋዮችም መሸነፋቸው አይቀርም። የሰለቸውም ወደ አገዛዙ በእርቅ ስም መግባቱ አይቀርም። የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችም ለምዳቸው ቀስበቀስ መገፈፉ አይቀርም። ቀስበቀስ በዐማራ ጫንቃ ላይ የተጣበቁ አልቅቶችም መራገፋቸው አይቀርም። ይንጠባጠቧታል ስልህ። ዛሬ እኮ የኦሮሞ አክቲቪስቶችና የትግሬ አክቲቪስቶችን ገፅ ብትመለከቱ ታሪክ ተቀይሯል። ትግሬ እንደውም ፋኖን መደገፍ ጀምሯል። ኦሮሞም አፍሮ ነው እንጂ "ፋኖ ጋቸነ ቢያ" ብሎ ቢዘፍን አይጠላም። አዎ ጉልበት ያስከብርህሃል። ፋኖም ዐማራን ማስከበር ጀምሯል። ይሄ ለእኔ ትልቅ ለውጥ ነው። በተለይ አሁን አገዛዙ አንዲት ነፍሰጡር ከመግደል፣ የአንድ ደሀ ገበሬ በሬና ቤት ለመግደል የአንድ ሚልዮን ዶላር ቦንብ ሲጠቀምና ሲከስር እንደማየት የሚደንቅ ነገር የለም።

“…እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22። ነፃነት በነፃ፣ በብላሽ አይገኝም። ነፃነት የሚገኘው በላብ፣ በጨቀየ ደም፣ በአሰቃቂ መስዋእትነት ጭምር ነው የሚገኘው። መጀመሪያ ይሄ ይታወቅ። ደም መፍሰሱ ደም ስለሚያፈላም ለዐማራ ትግል ቆስቋሽ ቤንዚን ነው። አገዛዙ ንፁሐንን በጨፈጨፈ ቁጥር ቂም የሚቋጥረው ለትግሉም ነዳጅ የሚሆው ይበዛል። ዐማራም የዚያኑ ያህል ጀት ሆኖ ስለሚነሣ እጅጉን ይጠቅመዋል። አያስለቅስም። ዓለም የዚህን አረመኔ ገበናም እያየ ለፍርድ ስለሚያመቸው፣ በውጭ የተኛውንም የዐማራ ዳያስጶራ ስለሚያነቃው፣ እንደ በቀደሙ እንደ ዲሲው፣ እንደ ፍራንክፈርቱ፣ እንደ ትናንቱ እንደ ሲያትሉ ዐማራውን አንድ ላይ ስለሚያቆመው ለዐማራ ትግል ጥሩ ነው። ዛሬ በዐማራ ክልል ኦሮሙማው በድሮን የሚያፈርሳቸው ትምህርት ቤቶች ነገ ሌላ ቦታ አይፈርሱም ሟቾችም አይገድሉም ማለት አይደለም። በቀለኛ ትውልድ ነው እየተፈጠረ ያለው። በተለይ ተሸንፎ የሚሮጠው የኦሮሞ ጽንፈኛ ጴንጤና የወሃቢያ እስላም ወታደር እና የደቡብ ጴንጤ ወታደር ወንድ የተባለ ዐማራ መጨፍጨፉ የሌለ በቀል፣ የሌለ እልቂትም ፈጣሪ ነገር ነውና እነ ብራኑ ጁላ፣ እነ ብራኑ በቀለ በጊዜ ቢየስቡበት መልካም ነው። 👇 ③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…የህወሓት ጀነራል የነበረው ሓየሎም ዓርአያ የተባለው የተናገራት መልእክት ናት ተብላ የምትነገር ዝነኛ አባባል አለች። "ወደ ሕዝብ መተኮስ የጀመርክ ዕለት ውድቀትህ ይጀምራል። እኔም "አባባሏን እገዛታለሁ" ግሩም አባባል ናት። አንድ በሕዝብ የተመረጥኩ መንግሥት ነኝ የሚል አካል ወደሚያስተዳድረው ሕዝብ አፈሙዝ አዙሮ መተኮስ፣ በድሮንና በጀት ቦንብ ሕዝብ መፍጀት ሲጀምር የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውደቁን እንዳረጋገጠ ነው የሚያሳያው። ይሄ ተፈትኖ የተረጋገጠ እውነት ነው። ንፅት፣ ጽድት ያለ እውነት። ያውም ጥሬ ሃቅ። በዚህ መንገድ የተጓዙ አምባገነን መሪዎች የቆዩትን ጊዜ ያህል ሁሉ በተለያየ ዘዴ በሥልጣን ላይ ይቆዩ እንጂ የሆነ ቀን ከመኝታችን ስንነሣ ታሪካቸው ተቀይሮ እንደ ጋዳፊ ቱቦ ውስጥ፣ እንደ ሳዳም ሁሴን የአይጥ ጉድጓድ ውስጥ ተጥለው እናገኛቸዋለን። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ቀኑ ሲደርስ ኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ፣ የቶፕ ቪው ቀረጻ፣ የፋና ዶክመንተሪ፣ የዳንኤል ተረታ ተረት፣ ኮሪደር ልማት፣ መናፈሻና ሪዞልት አያድንህም።

"…ከትግራይ መልስ የኦሮሙማው አገዛዝ በቀጥታ ያመራው በጎጃም በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ከዐማራ ሕዝብና ከዐማራ ሠራዊቱ ፋኖ ጋር ነው ጦርነት የገጠመው። የዐማራ ክልሉ ጦርነት ለአገዛዙ ልክ እንደ ትግራዩ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያን ሕዝብ በውጭም፣ በሀገር ውስጥም አስተባብሮ አንድ ላይ ማዝመት አልቻለም። ኤርትራንና የሱማሌ ወታደሮችንም መጋበዝ አልተቻለም። የዐማራ ክልሉ ጦርነት በፍጹም ለኦሮሙማው ፕሮፓጋንዳ የሚመች አልሆነም። ልፕሮፕገንድ ቢል እንኳ የሚሰማ የለም። አይኖርምም። እንዲያውም በተቃራኒው የዐማራ ፋኖን ይንቅ፣ ያጣጥል የነበረው ሌላው ሕዝብ ሁላ አሁን አሁን የኦሮሙማው ዱላና በትር በአንድም በሌላም መልኩ ጀርባው ላይ ማረፍ ሲበረታበት፣ ኦሮሙማው እየዠለጠው ደም እንባ ሲያስለቅሰው "የፋኖን መምጫ ቀን እንደ ምጽአተ ክርስቶስ መናፈቅ ጀምሯል።" አዎ የዐማራ ክልሉን ጦርነት ሕዝብን አስተባብሮ፣ ሰንጋ አርዶ እና በሶ አስቋጥሮ፣ ወኔ ቀስቃሽ ክሊፕ እያሠራ በስሜት ወደ ዐማራ ክልል ጦርነት በገፍ የሚልከው ሰው የለም። ዳያስጶራውም እንኳ እንደ ትግሬ ጦርነቱ ጊዜ "ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን" እያለ ደረቱ ላይ እጁን ለጥፎ በእንባ ፍቅሩን እየገለጸ፣ ገንዘቡን እያዋጣ፣ በነጮቹ ጎዳና ላይ ከኤርትራውያን ጋር ፍቅር በፍቅር ሆኖ የድጋፍ ሰልፍ ለብልፅግና የሚያደርግ አንድም ሰው የለም። አንድም አልኳችሁ።

"…አቢይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት በአማርኛ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚያደነቁረን፣ ኦሮሞ በተሰበሰበበት ስፍራ ሁሉ ደግሞ ራሱ አቢይ አሕመድ በተገኘበት ሁሉ ንግግር ሲያደርግ "ኦሮሞ ከ150 ዓመት የነፍጠኛ ቅኝ ግዛት ነጻ መውጣቱን" ሳይሳቀቅ፣ ሳይፈራ፣ ሳያፍር ነው የሚሰብከው። በአዲስ አበባ ኦሮሞ ጠል ሕዝብ አለ ብሎ ሳይሳቀቅ ንግግሩ አቶሚክ ቦንብ መሆንን የማያውቅ ማይም ነው እኮ አሁን ያለው መንግሥት ተብዬ። በአማርኛ የኢትዮጵያ፣ በኦሮምኛ ግን የኦሮሞ መንግሥት መሆኑን በድፍረት የሚናገር ዘረኛ እኮ ነው። መንግሥታችን ተነካ ብለው ከሰንዳፋ፣ ከቡራዩ፣ ከሱሉልታ እየጎረፉ የነበሩ ኦሮሞዎችን በጥበብ አስቆምኩ ብሎ በገደምዳሜ እኔ ብነካ በአንድ ጀንበር መቶ ሺዎች እረዱ ብሎ ጥሪ የሚያስተላልፍ፣ በአደባባይ ያውም በፓርላማ የሚናገር አገዛዝ እኮ ነው ሀገር እየመራ ያለው። ማንም አያቆመንም፣ የ150 ዓመት የደም ውጤታችን ነው። አራት ኪሎ ሲያምርህ ይቀራል። ወዘተ እያሉ ክሊፕ የሚለቁለት ደጋፊዎች ፈትቶ የለቀቀ አገዛዝ እኮ ነው።

"…ወደ ዐማራ ክልል ዘማች ያጣው ዳግማዊ ደርጉ የኦሮሙማው አገዛዝ እንደ አባቱ እንደ ደርግ አፈሳ ጀምሯል። ከሚደርሱኝ የትየለሌ መረጃዎች መካከል አሁን አሁን የሚበዙቱ ልጄ ታፈሰ፣ አፈሱት ልጄን የሚል ነው። ዕድሜው 15 ነው፣ የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነው። ትንሽ ልጅ ነው ብንልም ሰሚ አጥተናል ነው የሚሉት ወላጆች። እንዲያውም አፋሾቹ አዲስ ቢዝነስ መጀመራቸው ነው የሚነገረው። ድሮ ድሮ በሊቢያና በየመን፣ በኦሮሚያም ሸኔ ነበር እያገተ ይሄን ያህል ብር ክፈሉ ይል የነበረው። አሁን ደግሞ ሚሊሻና ፖሊስ የተመደበበትን ኮታ ለማሟላት ሲል በጅምላ ያፍስና በታፈሱት ልጆች ላይ የማስለቀቂያ ብር ይመድባል። እንደ ቤተሰቡ የገቢ መጠን ከፍተኛው እስከ መቶ ሺ፣ ዝቅተኛው 25 ሺ መመደቡ ነው የሚነገረው። መክፈል የቻለ ይለቀቃል። መክፈል ያልቻለ ወደ ጦላይ ይላካል። በዚህ መንገድ ደርግም ሞክሮ አላሸነፈም።

"…የአሁኑን ለየት የሚያደርገው የአቢይ አሕመድን አገዛዝ መንግሥቴ ነው የሚሉ ባለ ድርሻ አካላት መብዛታቸው ነው። ከእነዚህ ባለ ድርሻ አካላት መካከል በዋነኝነት የኦሮሞ የወሀቢይ እስላም፣ የኦሮሞ ጽንፈኛ ጴንጤ እና ዋቄፈናዎች ዋነኛ መሪና መንግሥታችን ነው ብለው እሱ ከወደቀ ያልቅልናል በማለት የሚዋደቁቱ መሆናቸው ነው። አገዛዙ ቢሮክራሲውንም የሞላው በእነዚህ አካላት ነው። እነርሱ ሳይዘምቱ ነገር ግን ደግሞ እንደ ገረድ የሰበሰቧቸውን የደቡብና የዐማራ ታዛዦቻቸውን ይዘው መንግሥታቸው እንዳይወድቅ ይጋጋጣሉ። የጴንጤ ፓስተሮች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጴንጤ ምእመናኖቻቸው አገዛዙን መጠበቅ፣ ከአገዛዙ ተፋላሚ ፋኖዎች ጋር የብልፅግና ወታደር በመሆን መጋደል፣ መዝመት፣ መሞት እንዳለባቸው፣ ለዚህም "ጌታቸው በራእይ፣ እግዜራቸው በሕልም፣ መንፈሱ ደግሞ ተገናኝቶ እንደነገራቸው በመግለጽ የደቡብ ጴንጤንም በመስበክ ወደ ዐማራ ክልል ይሄን ምስኪን የደቡብ ጴንጤ እና ሙስሊም ወደ ሞት እየነዱት ይገኛሉ። ነፍስ ይማር።

"…እኔ በበኩሌ የቀን ጉዳይ እንጂ የዐማራ ክልሉ ጦርነት አሁን አሁን አያሰጋኝም። እንኳን አሁንና ድሮ ድሮ ከዓመት በፊት ባዶ እጁን በብላሽ በግሬደር ይቀበር የነበረ የዐማራ ሕዝብ እኮ ነው አሁን በባዶ ሜዳ በብላሽማ አልወድቅም። አልሞትምም በማለት ከአረመኔው አገዛዝ ጋር የገጠመው። እኔ በበኩሌ እመኝ፣ እንዲሆን እፈልግ የነበረው ነገር ነው የሆነልኝ። ስለቴ ነው የሰመረው። በሰለጠነ መልኩ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በአቤቱታ፣ ፍረዱልን፣ አትግደሉን፣ የመዘዋወር፣ የመማር፣ የመሥራት መብታችን ይከበርልን ብለው የጠየቁ ዐማሮች የማንም ሥርዓተ ቢስ መሳቂያ፣ ማሾፊያ ከመሆን አልፈው በአንድ ቀን 3ሺ አራት ሺ ዐማሮች ጨፍጭፈው "ለአስከሬናቸው ጥላ ይሆን ዘንድ ችግኝ እንተክልላቸዋለን" ብለው ሲያሾፉ የበገንኩትን ያህል አሁን ቢያንስ ጥሎ መውደቅ መጀመሩን በማየቴ ፈጣሪዬን አመስግኛለሁ። እንደ ትግሬ ነፃ አውጪ በትእቢት፣ በጉራ፣ በፉከራ፣ በማቅራራት፣ ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ እያለ በመፎግላት ሳይሆን፣ ይሄን የአረነኔውን የኦሮሙማውን ዕብደት ሊያስቆም የሚችለው ከዐማራው በቀር ሌላ ኃይል በዚያች ምድር እንደሌለ ቀኝ ትከሻዬን ይሸክከኝ ስለነበር ለዚያ ነበር እንቅልፍ አጥቼ፣ 24/7 ዐማራ፣ ተነሥ፣ ተሰባሰብ፣ ታጠቅ፣ ተዘጋጅተህ ተቀመጥ እያልኩ እንደ ዕብድ አቅሉን እንደሳተ ሰው ዋይዋይ እል የነበረው። አሁን ተሳክቷል። የተጀመረም ነገር መጠናቀቁ አይቀርም።

"…በወቅቱ የዐማራ ጴንጤዎች፣ የዐማራ የወሃቢ እስላሞች፣ የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች፣ በጎጃም ከሃዲዎቹ የፖለቲካው አገው ሸንጎዎች፣ በወሎም፣ በሸዋም ነፈዝ ጎጋ የበድኑ ብአዴን ገረዶች እንደ ጉድ ነበር የሚጮሁብኝ። የሚሰድቡኝ። በጎጃሜ ነን ባዮቹ በንቅሴው ሞጣ ቀራንዮ እና በስፐርም በፖስታ ላክልኝ ወሮ ትእግስት ብሪጅ ስቶን በኩል እንደ ጉድ ይወርዱብኝ ነበር። ትግሬዎቹ …👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ኢየሱስም መልሶ፡— ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፡ አላቸው። ዮሐ ፥ 11፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻም…!

"…ወዲህ ወዲያ እያልኩ ስዋከብ አንድ ታላቅ በአል አምልጦኝ ስናደድ ነው የዋልኩት። በአሉ ትናንት ነበር። ለወትሮው ፌስቡኩ፣ ቲክቶኩም ይቀውጠው ስለነበር ትዝ ይለኝ ነበር። ዘንድሮ ግን እንዲሁ ላይሞላ ነገር ስንጦሎጦል ረሳሁት። ከመቅረት መዘግየትም ይሻላል እንዲሉ አበው እና እመው እኔም ብዘገይም አሁን ሳስታውሰው ብቅ ብያለሁ።

"…በቀደም ዕለት "የታላቁ" እስክንድር ነጋ የዲሲ ሚኒሻዎች ሞቅ ደመቅ አድርገው ቁጥሩ ያልተጠቀሰውን የእስኬውን ልደት ሊያከብሩ እየተዘጋጁ ሳለ እኔ ቀዥቃዣም አይደለሁ? ያ አበበ አስክስ በነገር ጎንተል አድርጎኝ የእስክንድር ሚስት ከባሏ ጋር የሰበሰበችውን ዶላር የት እንዳደረሰችው ቀርባ ታስረዳ ስላልኩ ሲጮህብኝ ለምን ትጮህብኛለህ እያልኩ ከአቤ ጋር አንድ ሁለት ስንባባል ለካንስ የዲሲ ሚኒሻዎች ኬክ አዘጋጅተው ተዘጋጅተው ሳለ በእኔ ነቆራ ምክንያት ደንግጠው ሴቶቹ እየረገሙኝ ትተውት ነበር።

"…ኋላ ላይ ይሄማ ጥሩ አይደለም ብዬ፣ የኬክ መግዣ ለምኜላቸው፣ የሆነች ትንሽዬ ኬክ ይዘው ወደ ቀድሞው ኢትዮ 360 የአሁኑ የምኒሊክና የጣና ቲቪ ስቱዲዮ ሄደው የእስኬውን ልድት አክብረዋል። ሀብትሽና ብሩኬም 60 ሺ ዶላራቸውን እያስታወሱ ለ7 ደቂቃ ያህል እስኬውን ዘክረውት አምሽተዋል። በእውነት ገንዘብ ያዥዋ ሕይወት፣ ሽመልስ ጠሽ፣ ዱኒዬ፣ ኤርሚ ዲሲ ግብረ ኃይል ክር ይገባችኋል። የእስኬው ሚስት ሰርኬም "ፋኖ እስክንድር ነጋ" ብላ በቀየረችው የፌስቡክ ገጿ የባለቤቷን ፎቶ ለጥፋ እንኳን ተወለድክ ብላዋለች። ጎበዝ።

"…እነ ዘመነ፣ሀብቴ፣ ምሬ፣ ደሳለኝ፣ ባዬ፣ ሳሚ ቅር አይበላችሁ። የሆነ ቀን ይከበርላችኋል። እኔስ እሺ ስዋከብ ነው የታላቁን ልደት የረሳሁት። እናንተ ግን ምን ሆነን ነው የረሳነው ልትሉ ነው?

• የእነ ብሩኬ ድምጽ ግን ምነው ድክም ብሎ ሰለለብኝሳ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በትእግስት ጠብቁን…

"…መላቀቅ የለም ብለው ከሳታላይቱ ጋር እየታገሉ ነው ቴክኒሽያኖቹ። ወደ 2ሺ ሰው ዩቱዩብ ላይ እየጠበቀ ነው። ቀጥሎ የማቀርበው ነው ጣጣ ያመጣብኝ። ከዛሬ በኋላ መርሀ ግብሬን ቀድሞ ማስተዋወቅ አቆማለሁ።

• ወይ ንቅንቅ…💪 አላችሁ አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:30 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ግሩም ግሩም የሆኑ መርሀ ግብሮች ናቸው የሚጠብቋችሁ።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/f9fnW5M3AUk
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይገደል…✊✊✊

"…ይሄ ከወለጋ ናዝሬት ድረስ የመጣው የዋቃ ጉራቻ አራጅ ምን ዓይነት አሰቃቂና አረመኔያዊ ወንጀል ቢሠራ ነው የናዝሬት ሕዝብ እንዲህ አውራ ጎዳና ላይ ወጥቶ ይገደል፣ ይገደል፣ ይገደል ብሎ የሚጮኸው?

• የምሽት 2:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭቴ ምላሹን ይዞላችሁ ይጠብቃችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
🌹🌹🌹…🌹🌹🌹…🌹🌹🌹

"…ድንግል ሆይ…! ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፣ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።

"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…7

"…አየህልኝ ይሄን ጎንደሬ የቴዲ ልጅ…!

"…የሕዝብ ብዛቷ 2 ሚልዮን የማይሞላው የተባበሩት ኤምሬትስ አቢይ አሕመድን አቅፋ ደግፋ ድሮንና ቦንብ እየሰጠች የዐማራን ሕዝብ እያስፈጀችው ነው። ትግሬን አስፈጅታ ከጨረሰች በኋላ ወደ ዐማራው ነው የዞረችው።

"…ትናንት ዐመዳም ደሀ፣ የግመል ቂጥ ተከታይ የነበረ ሕዝብ ባለቤት የነበረችው ሚጢጢዋ አረብ ለኦሮሙማው አገዛዝ አግዛ በተለይ ጥንታዊውን እስልምናና፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት ቆርጣ የተነሣች ብር ልቧን የደፈነባት ሀገር ናት።

"…ይህቺ ሚጢጢ ደፋር ሀበሻን አትንኩ የሚልውን የነቢዩአን ቃል ችላ በማለት ሀገሬ ላይ ቦንብ ማዝነብ ከጀመረች ውላ አድራለች። ይሕቺን ጥገበኛ፣ ደፋር የአረመኔ አራጅ ደጋፊ ነው ለንደን ላይ ሁለት የለንደን ፋኖዎች እንዲህ ብጥብጥ ያደረጓት።

"…ተመልከት ዐማራን፣ ተመልከተው ልቡን፣ ተመልከተው ድፍረቱን፣ ተመልከተው ይሄን ግልብ ብር ልቡን የደፈነው ዊጢምጢማም ዓረብ መግቢያ ሲያሳጣው? አንበሳ የለንደን ፋኖ። 👏👏👏

"…እንግዲህ እኒህ ሁለት ዐማሮች ዐረቦቹን ለንደን ላይ እንዲህ ብጥብጥ ካደረጉ ለንደን ላይ የሚኖረው በመቶ ሺ የሚቆጠር ዐማራ ቢወጣ ብላችሁ አስባችሁታል?

"…አሁን ዶናልድ ትራምፕን በደንብ መጠቀም ነው። የታረዱ የዐማራ ቄሶችና፣ የታረዱ የዐማራ ሼኮችን፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ በቪድዮ ማሳያት ነው። አሁን ወደ ኋላ ማለት የለም። ገፋ ማድረግ ነው። ይሄን ኢትዮጵያ ዐማራ ገድሎ ዋሽንግተን ለሾፒንግ የሚመጣ የብልፅግና አራጁ እንዲህ ማንቆራጠጥ ነው።

• እስቲ በማርያም… ለለንደን ፋኖ ለአፄ ቴዎድሮስ ልጆች አንደዜ ሞራል። 👏👏👏👏👏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

"…ወንድ ከወንድ ጋር ሲገጥም፣ ገጥሞም ሲጥል፣ ወይም ሲወድቅ እኮ ተፈጥሮአዊ ነው። ወንድ ከወንድ ሲገጥም ገጥሞም ሲማርክ ወይ ሲማርክ ደንብ ነው፣ የቆየ ደንብ። የሚያስጠላ የሚደብረው መንግሥት ነኝ ብሎ፣ ባንክና ታንክ በእጁ ይዞ ሲያበቃ እንደ ወንድ ወንዶችን መግጠም ሲያቅተው፣ ገጥሞም ሲሸነፍ ሕፃን ሴት፣ አረጋዊ፣ ነፍሰ ጡር ሳይል የሚረሽነው ከንቱ ነው። ምርኮኛ የሚመራው ጦር ዕጣ ፈንታው መማረክ፣ እጅ መስጠት ብቻ ነው።

• በዐማራ ክልል የኦሮሙማን መከላከያ መፍራት ከቆመ ዓመት አለፈው…

• ቆይቼ ሲነዱት አሳያችኋለሁ። 💪💪🏿

• ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

"…ሲገድልህ፣ ሲጨፈጭፍህ ውሎ ጥይት ሲያልቅበት እጅ መስጠቱ ሳያንስ "ወተት ነው የምጠጣው። ወተት ስጡኝ ለሚል ምን ትመክራላችሁ… ወተት፣ ጮማ ስጡኝ ብሎ ያማርጣል እንዴ ምርኮኛ…?

• ሓሳብ ስጡበት…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 1
ከ~ GG

ጭንቅላቴ ጠቦ ሆዴ ከሚሰፋ፣
ለኔ ደስታ ብየ ሕዝብ ከሚከፋ፡
የገዛ ወገኔን  በእጄ ከማጠፋ፤
ይቅርብኝ መኖሩ ለሕዝቤ ስል ልጥፋ።
ታሪክ አላጠፋም  ደግሞ  እንደ ሚኒሻ፣
ወገኔን አልነክስም እንደአበደ ውሻ፣
አላጎነብስም አልሆንም ቅጥረኛ፣
አይደለሁም ፖሊስ የጥዋት መጋኛ፣
ለማተቤ ምሞት ፋኖ ነኝ ሀቀኛ:
ድል ለዐማራ ፋኖ!!

ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

…ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” 2ኛ ቆሮ 9፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በጎንደር ዝምታው ተሰብሯል።

" …የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊው ፋኖ አርበኛ መልካም ጣሴ ይናገራል። ከላይ የምታዩት መልከ መልካሙ ሸበላው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ምክትል የጦር ኣዛዥ ፋኖ ተሾመ አበባው ነው።

"…የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ እነ ጋሽ መሳፍንትን የመሳሰሉ 7 የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞች ስር ያለ እና አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዕዙ መሪ ሲሆን ነገር ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጋዜጠኛ እስክንድር ስር በመግባታቸው ምክንያት እንደ ጎንደር የብዙ ጎንደሬዎችን ቅስም ሰብረው ነበር። ነገር ግን ይኸው ዕዝ ሰሞኑን የሚያበሥረን የመሥራች እንዳለ ሆኖ በተለይ ሰሞኑን በወልቃይት ጉዳይ የሰጠው መግለጫ "ከዩጋንዳ እስከ አማሪካ፣ ከሙሉዓለም ገ/መድኅን እስከ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ድረስ ያሉትን ወፋፍራም ትግል ጠላፊ ስኳዶች በብርቱ እያንጫጫቸው ይገኛል። ጎንደር አዚሟ እየተገፈፈላት፣ አንድነቷም እየቀረበ ነው። መስቀልም አንጠልጥለው፣ ዳዊት እየደገሙ፣ ዱአም እያደረጉ ሶላት እየሰገዱ በነፃነት ነፃ የሚያወጡላት ልጆቿ ወደፊት እየመጡ ነው።

"…ሚኒሊክ ሚዲያ ባለቤቶች ለእነ ሀብታሙ አያሌው፣ ለእነ አበበ በለው፣ ለእነ ዶፍቶር አምሳሉ የቀረበ ጥያቄ ሲሆን እነ ዶፍተር ምስጋው አንዷለምም ጥያቄውን ሰምተው ምላሽ ቢሰጡበት መልካም ነው።

• አድምጡት። አድምጡትና ምኒልክ ቴሌቭዥኖች የሕዝብን አስተያየት ያነብባሉና አስተያየታችሁን እዚሁ ልጥፍ ስር አስቀምጡላቸው። ለስኳድም ጭምር ነው ታዲያ።

• ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ "…በሸዋ የእስክንድርና የመከታው ጦር እየተበተ ነው። ብዙዎች ወደ እነ ደሳለኝ እየተቀላቀሉ ነው። የመከታው የጦር አዛዥ ጫታሙ ሱሳሙ፣ መከታውን ያግዘው ዘንድ ከፌደራል ፖሊስ ወደ እነ መከታው የተቀላቀለው ኤርሚያስ ብቻ ነው አሁን ሕዝቡን እያስጨነቀ፣ የገበሬውን ፍየልና በግ እያነከተ፣ እየበላ ጫትና ሺሻውን እየማገ፣ የድህነት እድገቱን የሕዝብ ከብት አርዶ በመቀለብ፣ ሴቶቹን በመድፈር ዓለሙን እየቀጨ ያለው እንጂ ሌሎቹ በጊዜ ተሸብልለዋል። አቤ ጢሞም መውጫ ስላጣ እንጂ ከመሳይ መኮንን ጋር የባጥ የቆጡን የሚለፈልፈው ነዳጅ ጨርሷል። ሌሎች ብርጌዶችም መግለጫ ሁላ ማውጣት ጀምረዋል። እንዲያውም ከሰሞኑ ይሄ በሸዋ ይከሰታል ብለው የሚወራውን ልንገራችሁማ። ለምታውቁአቸውና በመከታው ማሞ ስር ለሚገኙ ፋኖዎችም ደውላችሁ ንገሩልኝ። አደራ።

"…ዘመዴ በጣም አስቸኳይ እና ጥብቅ መረጃ ነው ብለው ነው የመረጃ ምንጮቼ መረጃውን ያደረሱኝ። ከእስክንድር እንዳልለይ መጽሐፍ ቅዱስ አስይዞ አስምሎኛል ብሎ ሞቴን ከእስክንድር ጋር ያድርገው በማለት ሠራዊቱን ይዞ ገደል የገባው የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አዛዥ መከታው ማሞና በስሩ የሚመራው የሥራ አስፈፃሚ አባላት ከመንግሥት ጋር ተደራድረው ለመግባት መስማማታቸውን በዚያው በሚገኙ የውስጥ አርበኞች አማካይነት ሾልኮ የወጣው መረጃ ያረጋግጣል።

"…በአማራ ፋኖ የውስጥ አርበኞች አማካኝነት ሾልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚለው ለአቶ መከታው ማሞ ከጥቅምት 29/2017 ዓም እስከ ኅዳር 04/2017 ዓም ድረስ ባሉት ቀናቶች ውስጥ እሱ የሚመራቸውን የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የዐማራ ፋኖ አባላትን በይፋት ቀጠና ለስብሰባ በሚል ሽፋን ጥሪ ካስተላለፈ በኋላ በድሮን ለማስመታት መስማማቱ ነው ነው የተነገረው። ከመከታው እና ከሥራ አስፈፃሚ ቡድኑ ጋር የተስማሙት ጀነራል አበባው ታደሠ፣ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እና ዓለምሸት ደግፌ መሆናቸውም ታውቋል።

የስምምነቱ አካል የተደረጉት ነጥቦች :_

1. መከታው ማሞና ቡድኑ ያለ መከሰስ መብት፤
2. በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እና
3. በፈለጉት ሀገር ሄደው እንዲኖሩ የቪዛ ጭና ጉዞ ሰነድ ሁኔታን ማመቻቸትን ያጠቃልላል ሲሉ መረጃውን ያወጡት የዐማራ ፋኖ የውስጥ አርበኞች ገልጸዋል። ይህ መረጃ የደረሳችሁ የዐማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ ሴራውን እንዲከሽፍ እንድታደርጉ እናሳስባለንም ነው የሚለው መልእክታቸው። ለማንኛውም መጠንቀቁ አይከፋም።

"…በመጨረሻም ሰሞኑን በአሩሲና በጉራጌ ክልል የሰቆቃ ድምጽ እየተሰማ ነው። ግልገል ነፍጠኛ ብለው ለእርድ ያዘጋጁትንና ቀን የሚጠብቁለትን ጉራጌና ከጉራጌም ክርስቲያን ኦርቶዶክሱ ጉራጌንና በዚያ የሚገኙ የዐማራ ተወላጆች በከባድ ሰቆቃ ውስጥ መሆናቸውም እየተሰማ ነው። የዚህ አካባቢ ደግሞ ትንሽ ለየት የሚለው ጉራጌንና ዐማራን ከአካባቢው ለማጽዳት ኦሮሙማ ብቻዬን ለምን እጠቆራለሁ በማለት በፓስተሮቹ በኩል በተደረገ ቅስቀሳ አማካኝነት " የኩሽ ኅብረት" የሚል ጥምር ፈጥረው ሴማውያን ብለው የፈረጇቸውን በሙሉ የማጽዳት ሥራ እየሠሩ መሆናቸው ነው የተሰማው። ኦሮሙማው ትጥቅ አውርድ ሲልህ እንዳለቀልህ፣ ለእርድ እያዘጋጀህ መሆኑን ልታውቅ ይገባል። በጉራጌም የሆነው ይሄው ነው። መጀመርያ ቀደም ብለው ሙሉ በሙሉ የዐማራውን ገበሬ ትጥቅ አስወረዱ። ካስወረዱ በኋላም አሁን ላይ እነሱ በሚፈልጉት መልክ አዋራጅ የሆነ አሰቃቂ አገዳደል መግደል ጀመሩ። ከሁሉም ጀርባ ግን ኦህዴድ አለ ነው የሚለው ከስፍራው የወጣ መረጃ። የንስር ጋዜጠኛው "ለመከላከልስ ጥረት አላደረጋቹህም? ብለው ለጠየቁት  ጥያቄ የአካባቢው ኗሪዎች የሚከተለውን ምላሽ መስጠታቸውንም ዘግባዋል።

"…ጠቡ የተነሳው ከትናንት ወዲያ ሁዳድ 5 ቀበሌ አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከንባታ ሚኒሻ ታግቶ ነበር። ከዚያ እዚያ አከባቢ የነበሩ የዐማራ አንዳንድ ሽማግሌዎች ከንባታዎቹን ለመኑ። ከንባታዎቹ እንቢ አሉ። ትናንት ደሞ ያ የታገተውን ልጅ ብር አልከፍል ሲሉ በምላጭ ፊቱን ተለተሉት እና ማታ 1:30 አከባቢ ደግሞ ዳርጌ ላይ አንድ የከንባታ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ተገደለ። ይህን መነሻ በማድረግ ነው አሁን ዐማራን ቤት ለቤት መግደል እና ቤት ማቃጠል የጀመሩት። ሁሉም በደንብ ታጥቀዋል። በኦህዴድ ሰልጥነዋል። ዐማራዎች ለመከላከል ማንም አልሞከሩም። እንደሚታወቀው የዐማራ ትጥቁን የኦህዴድ እና የዞኑ አመራሮች አስቀድመው አሰቃይተው በግድ ተቀብለውታል። እንኳን ገበሬው የዐማራ ሚኒሻው ትጥቅ የለውም።

"…እነሱ ግን ሁሉንም ወጣቶች አደረጅተው በየ አዳራሻቸው እና ሰብስበውው "ፌስታል ይዛቹ ነው የመጣቹት ፌስቴል ይዛቹ ትሔዳላቹ" 1ከምባታ ቢሞት በጅምላ ዐማራ እንገድላለን" እያለ በስብሰባቸው ላይ ሊቀመንበሩ ይነግራቸው ነበር። ተብሏል። መከላከያና ፌድራል ፖሊስ አካባቢው ላይ እያሉ ቤት ሲቃጠል ንብረት ሲወድም ሕዝቡ ሲጨፈጨፍ አስቁሙሉን ብለን ብንማጸናቸውም ትዕዛዝ አልተሰጠንም በማለት ፊት ነሱን። ለመከላከልም አልፈለጉም ይላሉ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የወረዳው ነዋሪዎች። ለወረዳው ነዋሪዎች በጥቃቱ ምን ያህል ሰው ተጎዳ? አሁንስ ምንድነው ዋስትናቹህ ብሎ የቢዛሞ ሚዲያ ለጠዬቃቸው ጥያቄ ጥቃቱ አሁንም አልፎ አልፎ የቀጠለ በመሆኑ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልቻልንም ያሉት የቀበሌዋ ነዋሪዎች። ቤት ሲቃጠል አብረው የተቃጠሉትን ዐማራዎች እስከ አሁን አጽማቸዉን እንኳ ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ ተናግረዋል። አክለውም እስከ አሁንም ብንጮህ ሊደርስልን የቻለ የሕግ አካል የለም ያሉት ዐማራዎች አሁን ላይ በአንድ ቀን እንኳን ቢያልቁ ምንም ዓይነት የሕግም የኃይልም ዋስትና እንደሌላቸው እና በገዳዮቻቸው ተከበው እንዳሉ ነው ለቢዛሞ ሚዲያ የገለጹት።

"…የሩዋንዳው እልቂት የተፈጸመው የፕሬዘዳንት አውሮጵላን ተመትቶ በመውደቁ ነበር። አሁንም ኦሮሙማው ሁሉንም ብሔር አንድ ሰው ቢሞትብን እናንተን ነው የምንጨርሰው እንዲሉ እያስደረገ ከከምባታዎች የፈለገውን ገድሎ አርዶ በመጣል ይሄን ያደረገው ዐማራው ነው በማለት የዘር ጭፍጨፋውን ለማድረግ ይችላል የሚሉም አሉ። አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ዐማራና ኦርቶዶክስን መግደል፣ የዐማራ እስላምን መግደል በሕግ የማያስጠይቅ፣ በሥርዓቱ የሚያሸልም ስለሆነ ያልታጠቁ ዐማሮችና ኦርቶዶክሶች ላይ ትንሽ ጠንከር ከበድ ያለ ነገር ሊመጣ ይችል ይሆናል። የሆነው ሆኖ ግን ዐማራው በክልሉ ቢያረፍድም እንኳንም ቀደም ብሎ ታትጥቆ ውጊያ ጀመረ። ተወደደም ተጠላም፣ የፈጀውን ሰውና የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ዐማራው ከማሸነፍ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። ድርድር፣ ግርግር፣ ወላ ሃንቲ ነገር አያተርፈውም። ዐማራ መዳኛው ማሸነፉ ብቻ ነው። ከከሃዲው አቢይ ጋር ድርድር ማድረግ ማለት እንደ ትግሬ የአቢይ ገረድ፣ ባርያ፣ ጫማ ላሽ፣ ሰቀቀናም መሆን ብቻ ነው። ዐማራ ሦስት አማራጮች ናቸው ያሉት።

1ኛ፦ ማሸነፍ
2ኛ፦ ማሸነፍ
3ኛ፦ ማሸነፍ…  አለቀ። ከማሸነፍ በቀት ለዐማራ ሌላ ምርጫ የለውም። ያለበለዚያ ዐማራ እንደ ኩርድ ነው የሚጠፋው።

• በታሪክ የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ የለም። አኬር መገልበጡ እንደሁ ግን አይቀርም።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም….!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 29/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ዐማራው ከነቃ፣ ከታጠቀ መዳረሻውን ስለሚያውቁ ነገርየውን ለማኮላሸት አስቀድመው ዋይ ዋይ ይሉብኝ ነበር። ኦሮሞዎቹም ኦሮማራ በሚል ማደንዘዣ ያስተኙት ዐማራ በጊዜ ነቅቶ ጉዳችን ይፈላል ብለው ይወርዱብኝ ነበር። የደቡብ ፓስተሮች፣ ጴንጤዎች፣ የስልጤና የኦሮሞ፣ የወሎ የኦሮሞ ዲቃላ የወሃቢይ እስላሞች ስንትና ስንት ቪድዮ ሠሩብኝ? ወረዱብኝ? የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ እነ ቶማስ ጃጀው፣ እነ ዓምደማርያም ዕዝራ፣ ከጎጃም ወዶ ገቡ ገሌው ረዳት ፍሮፌሶር ጌትነት አልማው፣ ጉራጌው የደብረ ብርሃኑ ፍሮፌሰር፣ የአሩሲ ዐማራውና በግድ የወረመው ስዩም ተሾመ፣ የከንባታ ነው የሃድያው የመሃል ሜዳ ፓስተር ደሳለኝ፣ የሰው ነጋዴው ኮሮና ዳዊት፣ እስቲ ያልወረደብኝን ንገሩኝ? ከኦርቶዶክስ የወሎው ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጀምሮ ጓ ያላለብኝ አልነበረም። እኔ ግን ያየሁትን ስላየሁ ዋይዋይ ዐማራ ሆይ ግድየለህም ቢያንስ ተሰባሰብ፣ በጉዳዩ ላይ ምከር፣ ቀስብለህ ታጠቅ፣ ከዚያ መክት፣ በመጨረሻም አንክት ብዬ ወተወትኩኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ዐማራውም ሰማኝ። ሰማኝ እግዚአብሔር ይስማው። ተዘጋጀ፣ ቀኑን ጠብቆ ዛሬ ይኸው አዳሜና ሔዋኔን ወጥ በወጥ እያደረገ ይገኛል።

"…እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው። በጦርነት ደግሞ መውደቅ መነሣት፣ መሞት መመቁሰል፣ መማረክ፣ መማረክ፣ መክዳት መኮብለል፣ ባንዳነትም፣ ጀግንነትም የሚኖር ነው። ይሄ ተፈጥሮአዊ ነው። የሆነው ሆኖ ግን አሁን በተጀመረው የዐማራ ትግል የዐማራ ሕዝብ ለአፍታም ያህል ይሸነፋል ብዬ አስቤም አልሜም ዐላውቅ። እስከአሁን ጦርነቱ የተራዘመው፣ የተነዘዛውም ቆርጦ በሙሉ ልቡ ወደ ትግሉ የገባው ዐማራ በፐርሰንት ሲሰላ ገና 0. 11223 መሆኑ ነው። 1% ከመቶ እንኳ የሚሆነው ዐማራው ቆርጦ አልተነሣም። በዚህ ነው እንግዲህ ይሄው ቆርጦ የተነሣው ዐማራ ዓለምአቀፍ ንዝረት የፈጠረው። በዐማራ ተሸነፍኩ ማለት ውርደቱ ስለሆነ ዋጥ አድርጎት ነው እንጂ አገዛዙ በፋኖ ሽባ ሆኗል። ፋኖ አገዛዙን ሽባ አድርጎታል። ገንዘብ አሳጥቶታል። አድቅቆታል። ብቻውንም እያስወራው ነው። ዐማራው በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በዳያስጶራም ያለው ገና አልተነሣም። አዚሙ አልተገፈፈም። በግንቦት ሰባት፣ በፌክ ኢትዮጵያኒስቱ የተተበተበው ትብታብ አልረገፈለትም። ነቅቷል ግን ገና አልባነነም። አልተነሣም። ታጥቦ ኮተቱን አላስወገደም። ይሰማል ግን ዓይኑ አልተገለጠም። የሆነ ቀን መንቃቱ አይቀርም። እንግሊዝን በሚያህል ትልቅ ሀገር፣ በዚያ ያለው ዐማራ ሙሉ ለሙሉ ሳይነሣ እኮ ነው ሁለት ሦስት የለንደን ፋኖዎች ሚጢጢዬዋን ኤምሬትስን ድንብርብሯን ያወጧት። ክብር ለለንደን ፋኖዎች። በሁለት ሦስት ሰው ብቻ።

"…በሀገር ቤት እስክንድር ነጋም ሳንካ በመሆን ትግሉን አልጎተተም ማለት አይቻልም። ድብን አድርጎ ጎትቶታል። በዚህ ማመን አለብን። ከአሜሪካ መልስ ወደ ጫካ ገባሁ ያለውና ብአዴን አስሮ በመፍታት ያጀገነው፣ ውጋኝ፣ ደምስሰኝ ብሎ መርቆ ሸኝቶ የላከው፣ ወደ ጫካም የሸኘው እስክንድር ነጋ የቀደመ የጋዜጣ ላይ፣ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ የተገነባውንና በመታሰር በመፈታት "ታላቁ" የሚል ቅጽል ስም ያገኘው፣ ዕድሜ ልኩን ለኢትዮጵያዊነት ሲታገል የነበረው ሰው ድንገት ፋኖ ትጥቅ ትግል መጀመሩ የማይቀር መሆኑን ሲያውቅ ዘሎ ገብቶበት ትግሉን በጥብጦታል። እስክንድር ነጋ ብቻውን መንግሥት ያልቻለውን የዐማራ ፋኖን የመከፋሉን ሥራ እሱ አድርጎት አሳይቷል። ጎንደርን ሦስት ቦታ ከፋፍሎ አሁን ደግሞ ሀብቴንና ፋፍዴንን ወደራሱ አድርጓል። የውባንተ ልጆች እነ ባዬ፣ እነ ሳሚ ብቻ ናቸው ወጊድ እኛ የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ነን ብለው ኢግኖር የገጩት። በወሎም ሁለት ቦታ ነው የከፈላቸው። በምሬ ወዳጆ የሚመራው የዐማራ ፋኖ ወጊድ ሲለው በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ የሚመራው ፋኖ ለእስክንድር ነጋ ገብሯል። በሸዋም አሰግድንና መከታውን አጣልቶ ሸዋን ለሁለት ከፍሎ እሬቻቸውን አባልቷል። በጎጃም ብቻ ነው ያልተሳካላት። ጎጃም መሬው የእስክንድር ነጋን የጎጃም ሴል፣ ኔትወርኩን በሙሉ ቆራርጦ አንድ ወጥ አደረጃጀት በመፍጠር ድባቅ መትቶታል። እስክንድር ሾተላይ በመሆን የዐማራን ትግል አዘግይቶታል። በመጨረሻም ባዶውን በመቅረት አውላላ ሜዳ ላይ ተዘርፍጧል።

"…እስክንድር ነጋ የምድሩን ታጋይ ብቻ ሳይሆን የአየር ላይ ታጋዮችን ሳይቀር ነው እንደ አሜባ የበታተነው። ገንዘብ የሚገዛውን በገንዘብ፣ ሆዱን ያለ በሆዱ ጠልፎ ጥሏል። ከሁሉም ከሁሉም ዳያስጶራው በአንድ ልብ ትግሉን እንዳያግዝ አስቀድሞ የጉፈንድሚ ኮሮጆውን ይዞ በመዞር ብሩን ሰብስቦ በማቅለጥ ዳያስጶራው ፔኒ፣ ዲዱ፣ ጢና ሳንቲም እንዳይረዳ ደንቃራ ሆኗል። እስክንድር ለሰናይ ቲቪ ለመነ፣ ለባልደራስ ለመነ፣ ለግንባሩ ለመነ፣ ለምኖ ግን ብሩን እምጷ ቀሊጦ ነው ያደረገው። ሚስቱ ሠርካለም ምን ዓይነት ኑሮ እንደምትኖር የሚያውቅ የለም። እሷም የባልደራስ ገንዘብ አሰባሳቢ ነበረች። ወጥሬ ይዤአታለሁ የአደባባይ ሰው ስለሆነች ቀርባ እንድታስረዳን መወትወቴን እቀጥላለሁ። አበበ በለው አትንካት ስላለኝ አልምራትም። መጠየቅ ምን ችግር አለው? ደግሞም ጋዜጠኛ አይደለች እንዴ? እንደ ጉድ ትጠየቃለች። አዎ የዳያስጶራውን እርዳታ ያስቀረው የእስክንድር ነጋና የቲሙ ስግብግብነት ነው። 20 ሚልዮን ዶላር መሰብሰብ ሲችሉ በሁለትና ሦስት ሚልዮን ዶላር ለሃጫቸውን አዝረበረቡ። የደሀ ነገር። ግንባሩን አፍርሰው በሠራዊቱ ስም ለመለመን ሰንዳ ብለው ሲመጡ የጉረሮ አጥንት ሆንኩባቸው። ሕዝቡም ዳግም ከመጋጥ ታደግኩት። እነሱም ከስረው ቀሩ።

"…እነ ሻለቃ ዳዊትም ድርጊቱን ተቃውመው ወጡ። አክቲቪስት ጋዜጠኛው ሁሉ ተበጣጠሰ። የዳበረ የመከፋፈል ልምድ ያለው የጎንደሩ ስኳድ የፖለቲካው ቆማንት የትግሬ ዲቃላው ሁሉ ደንግጦ ግር ብሎ መጣ። በእስክንድር ጀርባ ታዝሎ ትግሉን ለመጥለፍ ይዳክር የነበረው መንጋም በገሀድ ተገለጠ። የጎንደር የዐማራ ጴንጤዎች፣ ጥቂት ፀረ ዐማራ አቋም ያላቸው የጎንደር የአይሁድ እምነት ተከታዮች፣ የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች፣ የጎንደር ፀረ ዐማራ የብአዴን የወሃቢይ እስላሞች ተሯሩጠው ግርር ብለው መጡ። ፓስተራቸውን ምስጋናው አንዷለምን ይዘው መንግሥታቸው ብልጽግናን ከመፍረስ ለማዳን ተገለጡ። የጎንደር ፋኖ መስቀል አድርጎ፣ ዳዊት እየደገመ ለምን ይዋጋል ? ብሎ የጠንቋይ ልጁ ዶፍተር በግልፅ ጓ አለ። ለእነ ውባንተ የተዋጣውን 60 ሺ ዶላር ቀርጥፈው በሉ። ወልቃይትን እንደ ነዳጅ ጉድጓድ የሚቆጠሩት ወልቃይቴ ነኝ ብለው በጎንደር ዐማራ ስም የሚነግዱት ነጋዴዎች በሙሉ ጫጫጫ ብለው ወጡ። እኔም አምላኬን ይዤ ብቻዬን ገጠምኳቸው። ገጥሜም አፈር ከደቼ አበላኋቸው።

"…ባይገርምላችሁ የጎንደሩ ጉዳዩ በመጨረሻ የሃይማኖት ሆኖ ተገለጠ። ይሄን ለማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ከቲክቶክ መንደር ሰባብሬ ያባረርኳቸው እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ትናንት ወደ ትዊተር ስፔስ ሄደው ያደረጉትን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ስፔሱን የከፈተችው ፈትለ ጴንጤ ናት አሉኝ የእነ አያሌው ቡድን ነው የሚነግረኝ። ማዕዶት ይሁዲ ናት አሉኝ። ናቫ አክራሪ ጴንጤ ናት ያሉኝ ሲሆን አይ ፈትሊ ድብልቅ ናት። ጴንጤ ብቻ አይደለችም ግራ የገባት ጴንጤም፣ ኦርቶዶክስም አይሁድም ናት። ዘመነ ካሤንና አንተን አምርራ ከመጥላቷ በቀር ብዙም ክፋት የለባትም። ትንሽ ጥራዝ ነጠቅነትም ያጠቃታል ነበር ያሉኝ። አልማዝ ኤርትራዊና ወልቃይቴ ናት። በዊድ የተበላሸች ጤነኛ… 👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የሳምንቱ የመጨረሻው ርእሰ አንቀጻችንን ሳዘጋጅ ነው የቆየሁት። ርእሰ አንቀጹ ሦስትና አራት ጉዳዮችን የዳሰሰ ነው። አረመኔው የአቢይ አሕመድ አገዛዝ የንጹሐንን ጭፍጨፋ በሰፊው ተያይዞታል። እሱንም እንዳስሰዋለን።

"…በዐማራ ፋኖ በወሎ ግንባር መጀመሪያ ተማርከው በወሎ የዐማራ ፋኖዎች ተሃድሶ ተሰጥቷቸው የተለቀቁ የምርኮኛው የብርሃኑ ጁላ ወታደሮች በድጋሚ አገዛዙ ልኳቸው አሁንም መማረካቸው ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያሳየው። እሁድ በመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ላይ በሰፊው በቪድዮ ጭምር እመለስበታለሁ። ጠብቁኝ።

"…ተመልከቱ ንፁሐንን ሲጨፈጭፍ የወለ አረመኔ የአረብ ተላላኪ የምርኮኛ ልጅ በዐማራ ፋኖ ሲማረክ "ወተት የለም፣ ወተት ስጡኝ" ነው የሚለው። ስሙት ገበሬውን "ወተት የለም" ብሎ ሲጮህ። ተማርኮም ወተት ስጡኝ። 😂 ወደው አይስቁም እኮ። "ወተት ስጡኝ አላለም" ይሄ ገዳይ ምርኮኛ ሰብስቦ በራብ ለሚሰቃዩት ለፋኖዎች የማያቀርቡትን ሰንጋ ጥሎ ፍሪዳ አርዶ አብልቶ፣ ወተትና እርጎ የማጠጣቱንስ ነገር እናንተ እንዴት ነው የምታዩት? የምትመለከቱትም? እስቲ በዚህ በምርኮኛ ጉዳይም ተወያዩበት።

• ርእሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቲሽ ኃይሌ በጠበጠው

"…ከቲክቶክ ዠልጬ ያባረርኳቸው ስኳዶች በሙሉ እንዳለ ነቅለው ወደ ቲዊተር ስፔስ ተሰደዋል። ለዶፍቶር ፓስተር ምስጋናው የገጽታ ግንባታ ተብሎ ራሷን የጎንደር ልዕልት ብላ በምትጠራው በፈትለ ቤት ነበር የተዘጋጀው። ፈትሊ ኃይለኛ የእስኬው ደጋፊ ናት። አቤት እኔንና ዘመነ ካሤን እንዴት አምርራ እንደምትጠላን አትጠይቁኝ። ዘመነ ካሤ የጎጃም መሪ መሆን የለበትም ብላም ቪድዮ ሠርታለች። እንደነገርኳችሁ ፕሮግራሙ ለፓስተር ምስጌ የገጽታ ግንባታ ነበር የተዘጋጀው። ውኃ በላው እንጂ። መጀመረያ ለእኔ ወፎች የተነገረው የተለያዩ ሰዎች መጥተው ምስጋናውን አድንቀው ጎንደር እንዴት እየተጠቃ እንዲያወሩ ነበር። በዚህ መሠረት አንዷ የጣና ቲቪ ሰው መጥታ የጎንደር ሕዝብ እንደ ሕዝብ እየተሰደበ፣ አዳዲስ ስም እየተሰጠው፣ ስኳድ ፋፍዴን እየተባባለ ብላ ረጅም ሰዓት አወራች። ፋፍዴን የሚባል የለምም አለች።

"…እዚህ ላይ ነው ኃይሌ የገባው። ኃይሌ በግሉ እኔ ዘመዴ ላይ ቅሬታ ቢኖረውም ለዐማራ ግን ከልቡ ነው የሚሠራው። የዲሲው ሠልፍ ላይ ራሱ በውጭ ሚዲያ ላይ ሁላ ቃለመጠይቅ ተደርጎለት ደስ ብሎኛል። ምን ፋፍዴን አላውቅም ትያለሽ? ፋፍዴን ማለት ከጎንሽ ያለው ምስጋናው ነው እሱን ጠይቂው። አታስመስሉ። በዚያላይ ጎንደርን የተናገረውን ሰው በግለሰብ ስም ጠርታችሁ መናገር ስትችሉ አንድ ሕዝብ ሌላውን እንደሰደበ አድርጋችሁ አታቅርቡ። ፋፍዴህን ጣና ምናምን ግን ምስጋናው ነው ሲላት ቀወጡት። ቤቱንም ዘጉት።

"…ኃይሌ የጎንደር ዕዝ ተወካይ የሲሳይ ጓደኛ ነው። ምስጋናው ደግሞ ሲሳይን አምርሮ ነው የሚጠላው። ቲሽ ሲያናድድ ደኅና እየቀዳኋቸው አቋረጡት። ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ ተመልሳችሁ ክፈቱና ሳልተኛ በፊት ልቅዳችሁ።

• በሉ በሉ የእንጀራ ገመዶቼ ተመልሰው መጡ ማዕዶት እየወቀጠችኝ ነው በሉ ልቅዳቸው። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቆይ ግን ዶፍቶር ሌባ ይባላል…?

"…የሄ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ የሆነ ሳሚ የሚሉት ልጅ እንዴት ያለ ደፋር ነው በናታቹ። እንዴት በስንት ልፋት በ12 ዓመቱ ዶፍተር የሆነን ቅማንቴ ስኳድ ሌባ ብሎ ይጠራል? በእውነት ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም። ልክም አይደለም። ግን ምን አገባኝ።

"…ምስጋናው የእነ ውባንተን 60 ሺ ዶላር ስለሰረቀ፣ ስለዘረፈ ሌባ መባል አለበት ግን? ምንሼ ነው? የደላው ስንት እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደነ ሀብታሙ አፍራሳ፣ እነደነ አቤ እስክስ ሚልዮን ዶላር ሃም አድርጎ ይሰርቃል ምስጌን 60 ሺ ዶላር ዘረፈ ብሎ ማማት፣ መሳደብ ነውር ነው። መሰለኝ።

"…ስኳድ ለእኔ እንጀራዬ ነው ስል በምክንያት ነው። እነ ወርቁ አይተነው፣ እነ ዘመነ ካሤም በቶሎ ክፍያኔ ጨምሩ፣ ጨምሩ ብያለሁ። ተናግሬአለሁ። ሳሚ ቅማንቴ አንተም ንገርልኝ። 🙏 ብሊስ…

"…የስኳድ ዶፍተርን ሌባ ማለት ግን አግባብ ነው? እስቲ እናንተም ፍረዱ። ምስጌ መመረቂያው ብርቧቅስ የመሰንቆ የአዝማሪ ወግ ነው አሉኝ።

"…ሳልረሳው No12 ናይጄሪያዊ የመሰለን ሸበላ የስኳድ ዶፍተር በአደባባይ ሌባ ብሎ መናገር አግባብ ነው ግን…? ሃቱ…😁

Читать полностью…
Subscribe to a channel