zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው። እኔ ኮሎኔል ደመከ ዘውዱን በግልጽ ጥያቄ ሳነሣበት ጎንደሬ ነኝ የሚል ዐማራውም፣ የትግሬ ዲቃላ ስኳዱም እሪሪ ብሎ ነበር የጮኸብኝ። ደመቀ ትግሬ ነው። ፕላን ቢ አድርገው ትግሬዎቹ ለክፉ ቀን ያስቀመጡት ልጃቸው ነው። ደመቀ ከወልቃይት ዐማራን ያጸዳ ሰው ነው። ወልቃይትን ጎንደሬ ዳግም ይበላል። መከላከያ ከወልቃይት እየተነሠሣ ነው የጎንደር ዐማራን የሚጨፈጭፈው። ደመቀ ዘውዱ ብልጽግና ነው። ደመቀ ዘውዱ አሳልፎ ወልቃይትን ለወያኔ ይሰጣል ብዬ ስለፈልፍ አፈር ከድሜ የምግጥ አይደለሁም እንጂ አፈር ከድሜ እኔን ለማስጋጥ የተሰለፈውን ሕዝብ ታስታውሳላችሁ። አይደል ምእመናን።

"…ይኸው ትናንት ዐማራው ጎንደሬ በወልቃይት ምክንያት የወጣውን ዜና ተመልክቶ ምንድነው ነገሩ? ምን ጉድ ነው የመጣብን? ምን ዓይነት ነገር ነው? what's going on, ምንድነው የምንሰማው ነገር፣ ምንድነው የምናየው ነገር በማለት ዋይዋይ ሲሉ ነው የዋሉት። የትግራይ አክቲቪስቶች እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውት "ተመዛበልቲ ወደ ገዛኦም ተመሊሳ" እያሉ ሲዘግቡ፣ በማይካድራ ጭፍጨፋ፣ በወልቃይት ጭፍጨፋ ተሳትፈው የነበሩ የወያኔ የጦር መኮንኖች አቢይ አሕመድ በላከላቸው አውሮጵላን ተሳፍረው ወልቃይት ሲደርሱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አውሮጵላን ጣቢያ ድረስ ሄዶ ሲቀበላቸው የተለቀቀው ፎቶ የጎንደርን ዐማራ ጆሮ ጭው ሲያደርግ ነው የዋለው።

"…ባይገርምላችሁ ጎንደሬ ሆነው ሁል ጊዜ ስለወያኔ ብቻ የሚጽፉ ፔጆች ላይ ሄድኩኝ። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ፔጅ ላይ ገባሁ ምንም ወፍ የለም። የወልቃይት ጉዳይ፣ የኮሎኔል ደመቀም ጉዳይ ቀይ መስመራችን ነው ብሎ በሚታወቀው ፉከራው የሚታወቀው ባህርዳር አድጎ ፀረ ጎጃሜ የሆነው የደቡብ ጎንደሩ አያሌው መንበር ፔጅ ገባሁ። እንደውም የዛሬ ስድስት ቀን የማይካድራን ጭፍጨፋ ከለጠፈ በኋላ ምን እንደሰማ አይታወቅም ድራሽ አባቱ ነው የጠፋው። ሙላት አድኖ ቤት ገባሁ ወፍ የለም። ሙላት የፈራ ይመለስ ዛሬም ጎጃሜን ነው የሚወቅሰው። አረጋ ከበደ ብራኑ ጁላን ሸለመው ብሎ ነው የሚያለቅሰው። ሲሳይ አልታሰብ የአሸቦ ዕቃው ወዳጄ ቤት ገባሁ። ወፍ የለም። ሙሉዓለም ገረ መድህን ኡጋንዳ ሆኖ ትንፍሽ አላለም። ብቻ what's going on የሚል ብቻ ነው የበዛው። ኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ እና አስፋው አብርሃ ብቻ ናቸው ደፍረው እንኳን በደኅና መጻዕኮም ኮሎኔሎታት ብጻይ አሐወይ ብለው የተነፈሱት።

"…የጎንደር የዐማራን ፋኖ ለ3 የከፈሉት ሁሉ ዛሬ ጮቤ እየረገጡ ነው። ወልቃይትን ነጻ ለማውጣት የሞቱ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ እና የጎንደር ዐማሮችን ነፍስ ይማር። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ ነው አይደል የሚባለው? ጎንደር ለዳግም ስደት ተዘጋጅ አልያም አንድ ሆነህ ጠላትን ለመጋፈጥ ተዘጋጅ። ባርነት ወይም ነፃነት ምርጫው የአንተው ነው። ዳግም ከመጡ ግን ለዘር አያስተርፉህም። ይሄን በደንብ ዕወቅ። ተረዳ። ወልቃይት ላይ አያቆሙም። ከአክሱም እንዳባረሩህና ጎንደር እንደወሸቁህ አሁን ከጎንደርም ድራሽ አባትህን ነው የሚያጠፉህ። አዲስ አበባና ኡጋንዳ መሰደድ አያዋጣም። ወደ አሜሪካና አውስትራሊያ፣ ወደ አውሮጳም መሰደድ አያዋጣም። ትግሬውን ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር ዐማራ ስም ሲሸውድህ ፋራ ዥል፣ ዥልጥ ሆነህ ከተሸወድክ በኋላ አሁን ማለቃቀሱ ዋጋ የለውም። የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም። በዚሁ ከቀጠለ በቅርቡ ወልቃይት የወያኔ ይሆናል። መዝግቡልኝ።

"…ስኳዶች አትደበቁ። ውጡና ተናገሩ። የእኔ ጦማር ያበሳጫል፣ ደም ያፈላል፣ ይጎረብጣል። ግን ኮሶ ነው ያሽራችኋል። ግን መድኃኒት ነው ይፈውሳችኋል። አትደበቁ። የማይነጋ መስሏችሁ ነው ቋት ውስጥ ያራችሁት እናንት በጠጣም ፀረ ጎንደሬ፣ ፀረ ዐማሮች። አሁን የት ትደበቁ? የት ትገቡ? ውጡና ተንፍሱ። ተናገሩ። በአፄ ቴዎድሮስ ስም እየማሉ፣ በጎንደር ሙዚቃ እየደነሱ፣ በፋሲል ግንብ እያጌጡ ወልቃይትን አደንዝዘው ያሳጧችሁን ለይታችሁ ውቀሱ። ጎንደሬዎች ትደነዝዙ ዘንድ የመገጭ ግድብ ይሠራላችኋል። የፋሲል ግንብ፣ የከተማዋ አውራ መንገድ በኮሪደር ልማት ቀለም፣ በመብራት ይሸቆጠቆጥላችኋል። እሱን እያያችሁ ወልቃይትን ይረከቡአችኋል። ይሄን ስላልኩ ፎክር፣ አቅራራ አሉህ አንት እስኳን ፀረ ጎንደር ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው። ፎክር።

"…በመጨረሻም ዐራቱም የዐማራ ፋኖ ዕዞች ወደ አንድ ለመምጣት የጀመሩትን ጉዞ ዐውቃለሁ። የወሎው በምሬ ወዳጆ፣ የጎንደሩ በባዬ ቀናው፣ የጎጃሙ በዘመነ ካሤ እና የሸዋው በኢንጂነር ደሳለኝ የሚመሩት ዕዞች ማለት ነው። ብዙ መንገድ ሄደዋል፣ ለፍተዋል፣ ደክመዋል። እየጣሩም ነው። ነገር ግን አሁን ላይ እነዚህ ዕዞች ወደ አንድነት እንዳይመጡ አንደኛው ዕዝ ላይ ሴራ እየተሴረ እንደሆነ እየሰማሁ ነው። ይኸውም ዕዝ የጎንደሩ የእነ ባዬ ቀናው ዕዝ እንደሆነም እየሰማሁ ነው። ይሄን ወደ አንድነት እንዳይመጡ የመጎተት ሴራው ደግሞ በጎንደሩ በእነ ባዬ ቀናው የጎንደር ፋኖ በኩል ይመስላል። ምክንያቱ ደግሞ አንድነቱን እያዘገየው ያለው በሴራ ነው ተብሏል። ሴራውም የተጎነጎነው የእነ ሀብቴ ወልዴ ቡድን ከእስክንድር ነጋ ድርጅት መውጣቱን በይፋ በግልፅ ሳይናገሩ፣ በጎን የጉንደር እዝ ወደ አንድ ልንመጣ ነው እያሉ የእነ ባየ ቀናው ዕዝ ከእነ ዘመነ፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ፣ ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ሊመሰርቱ ያሰቡት የፋኖ ኃይል ላይ እንቅፋት እየሆኑ መሆናቸው ነው የተሰማው። ለማንኛውም ጥንቃቄ ያስፈልጋል። እስር ቤት ያሉትም ከእስርቤት መልእክት እየላኩ አንድነቱን ባያዘገዩት ይመረጣል።

"…ለጊዜው ሊመጣ ከጫፍ የደረሰውን አንድነት አርበኛ ዘመነ ካሤን በመግደል ለማስተጎገል ታስቦ ነበር። እሱን እግዚአብሔር አከሽፎታል። ቀጣዩንም ሴራ እግዚአብሔር ያከሽፈዋል። ዝርዝሩን የምጽፈው ጉዳዩ አደገኛ አዝማሚያ ሲይዝ ብቻ ነው። መቼም የምለው ይገባችኋል። አለቀ።

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸዋለን…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 6/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው የምንሄደው። ዛሬ የሳምንቱ መጨረሻ የሥራ ቀን ነው። እኛም ርእሰ አንቀጽ እስከ ማክሰኞ ድረስ አይኖረንም። ለዛሬ ይሄ የመጨረሻው ርእሰ አንቀጻችን ነው ማለት ነው።

"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ሦስት አጀንዳዎችን መርጠን እንወያይበታለን። አንደኛው አጀንዳ
የእስክንድር ነጋ ድርጅት የመረጣቸው የፋኖ አደረጃጀቶች ፍርስርሳችው ሊወጣ ምልክት እየታየነ ስለመሆኑና በተለይ የነመከታው ፋኖ በየሚዲያ ብቅ እያለ "አንድ ነን፣ አንድነት ልንፈጥር ነው፣ ልዩነታችን የሓሳብ ነው፣ ተስማምተናል እያሉ ሲለፈልፉ የሚታዩት፣ ከአወነ ዘመነ፣ ከእነ ምሬ፣ ከእነ ባዬ እና ከእነ ደሳለኝ ጋር ልንስማማ ነው ብለው መለፍለፋቸው ከጤና አንጻር እንዴት ይታያል የሚለውን የዱፍትርና ልምዳችንን ተጠቅመን እንመረምረዋለን።

"…ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው እሱንም እንዳስሳለን። በመጨረሻም ዐራቱም የዐማራ ፋኖ ዕዞች ወደ አንድ ለመምጣት የጀመሩትን ጉዞ ዐውቃለሁ። ነገር ግን እነዚህ ዕዞች ወደ አንድነት እንዳይመጡ አንደኛው ዕዝ ላይ ሴራ እየተሴረ እንደሆነ እየሰማሁ ነው። የትኛው ዕዝ ነው እየተሴረበት ያለው የሚለውን ርእሰ አንቀጹ ላይ ለዛሬ ጠቆም አድርጌ አልፋለሁ። ሊመጣ ከጫፍ የደረሰውን አንድነት አርበኛ ዘመነ ካሤን በመግደል ለማስተጎገል ታስቦ ነበር። እሱን እግዚአብሔር አከሽፎታል። አሁን የሚዘገየው ለምንድነው? አብረን እናየዋለን።

"• ፊልድ ማረሻው ዘመዴ ነኝ። እህሳ ነጭ ነጯን ርእሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም እናንተም ሓሳባችሁን ለማካፈል ዝግጁ ናችሁ?

• 100 ፍሬ ሰው ዝግጁ ነኝ ይበል። ትእዛዝ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይ ስኳድ 😂              

"… በእኔ ጉዳይ ሊወያዩ ገብተው ጌታሰፋው እና ራስተፈሪ ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡላችሁ እኔ ልናገር እኔ ልናገር በሚል። በሉ ተስማሙና ቦጭቁኝ። 😂
ጌታስፋው ቀጥል።

"…ርእስ አመራረጣቸው ራሱ ገዳይ ነው። ዘመድኩንና ዘመነ ካሤ ይሉልሃል። አይ ዘመዴ ምኑ ጉደኛ ሰው ነህ። 😁

• እስቲ ልስማችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አቤ ጥሩ እያጫወተኝ ነው።

"…ዘመዴ ምላሽ አልሰጥህም እያለ ነገር ግን በቀን ሁለቴ ምላሽ እየሰጠኝ ነው… በመልስ አሰጣጡ ላይ ግን ጥሩ መሻሻል አሳይቷል። በዚህ ምላሹ ላይ ሌሎችን አግዙኝ፣ ፋኖ መግለጫ ያውጡልኝ፣ የዐማራ ማኅበራት ሰብሰብ ብለን መግለጫ እናውጣበት፣ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ዘመድኩንን አውሩዱልኝ ካልሆነ በቤታችሁ ሰልፍ ነው የምወጣው አላለም። አቤ ዐማራ ስላልሆነ የአማርኛ ፊደል ለምን ተሳሳተ ብዬ አላስጨንቀውም። የሆነው ሆኖ ለጠየቅኩት ጥያቄ ሳይወድ በግዱ በፈለገው መንገድ እየመለሰለኝ ስለሆነ አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው።

"…አቤ ያልመለሰልኝ ጥያቄዎችም አሉ። ኢትዮጵያውያን ሬስቶራንት ከተጠቀምክ በኋላ ለተጠቀምክበት ክፍያ የማትፈጽመው ለምንድነው? የሬስቶራንት ባለቤቶችን ለምን ታሳቅቃለህ? ሌሎች ሰዎች እንዲከፍሉልህ ለምን ትጠብቃለህ? ለሠራተኞች ቲፕ ለምን አትሰጥም? ዋ ከተቋቋመ ጀምሮ፣ አንተ ብቻ መሪ የሆንከው? በአንተ ሰምም ያስመዘገብከው ለምንድነው? 30 ዓመት ሙሉ አንተ ብቻህን የአዲስ ድምጽ ፕሬዝዳንት ለምን ሆንክ?

"…አቤ አሜሪካ ከመጣህ ጀምሮ ታክሲና ቁማር ቤት እየሠራህ ያልቀየርከውን ቶዮታ ፒረስ መኪና ዋን ባቋቋምክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የ80 ሺህ ዶላር ቴስላ መኪናና የሚሊየን ዶላር ቤት ገንዘብ ከየት አምጥተህ ገዛህ? የት ተምሮ ራሱን ጋዜጠኛ እያለ እንደሚጠራም አልነገረኝም። ስለዚህ የጠየቅኩትን ጥያቄ ካልመለሰ ግን እንዳመነ ይቆጠራል ማለት ነው። በቀጣይ ደግሞ ለነዚህ ምላሽ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ። እየመረጡ መመለስ አይቻልም። ገና ስለ ኦዲት፣ አደገኛውን ነገረ ጋብቻ አነሳለሁ። ኢየሩሳሌም የሄደበትን ብር አልከፍል ብሎ የጉዞ ወኪሉ ሀብታሙንና ኢየሩሳሌም ያሉ መነኮስ ሽምግልና ልከውበት ቀርጥፎ ክዶ ማስቀሩትም አልተነገረም።

አመድኩን ነቀለ ነኝ። ከመዶሻ ሰፈር።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉YouTube
https://www.youtube.com/live/43NenD_0Evk?si=Ly1zXFwqlbTSlP7_

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v5pa5f5--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡ / Facebook
https://www.facebook.com/share/14kUYY8QaG/ facebook.com/ethiobeteseb

👉    በቲውተር / Twitter
https://x.com/EBeteseb/status/1856174420647203066?t=OPJyziZjRHSXFW723OWVMQ&s=19

https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb

ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከእስክንድር ሌለ ሌላውን ፋኖ ጎጠኛ የሚሉት ወደው እኮ አይደለም። በጎንደር እነ ጋሽ መሳፍንት ለ30 ዓመት ጫካ ገብተው ሲታገሉ እስክንድር ፋኖ አልነበረም። (ጋዜጠኛ እንጂ በኋላም ታሰረ) በ2008 የጎንደር፣ የጎጃም እና የወሎ ወጣቶች ወያኔን ሲቃወሙ እና ሲታገሉ እስክንድር እስር ቤት ነበር። በወጣቶቹ ዐማሮች በአሁኖቹ ፋኖዎች ትግል እስክንድር ከእስር ተፈቷል። የትግራይ ጦርነት ከመጀምሩ ከወራት በፊት ጀምሮ ጦርነቱ እስከሚያልቅ ድረስ እስክንድር እስር ቤት ነበር። ፋኖ ግን ተደራጅቶ ለ2 ዓመታት ሲዋጋ ነበር። እስክንድር እስር ቤት እንጂ ፋኖን ሲያድራጅ አልነበረም። ሲፈታም ሸዋ፣ ጎንደር፣ ወሎ ጎጃም ሂዶ ፋኖዎችን አግኝቶ ዕውቅና ሰጥቻለው ነው ያለው። እስክንድር በየትኛው የውጊያ ልምዱ ነው እንግዲህ የፋኖ መሪ ነኝ። የፋኖ ፋይናንስ በእኔ በኩል ነው ማለፍ ያለበት ብሎ የሚወግመው? አሁን እኮ ፋኖን እየመሩ የሚገኙት ከእሱ በፊት ጫካ የገቡ፣ የውትድርና ሙያ ያላቸው፣ የጦርነት ልምድ ያላቸው፣ ተዋጊዎችን ሚያሰለጥኑ ናቸው። እስክንድርን ከእስር የታደጉት የዐማራ ክልል ተወላጆች እንጂ የአዲስ አበባ፣ የሐረር፣ የናዝሬት ወዘተ ልጆች አይደሉም። የአዲስ አበባ እና ሌሎች ከክልሉ ውጭ ያሉ እስከዛሬ ለምን እስክንድርን መሪ አድርገው አልተደራጁም? ለምን ባልደራስ ሲል አብረውት አልሆኑም ነበር? እኔ ዘመዴ ወያኔ በፈጠረው ክልል በሚለው የከብቶች ማጎሪያ አስተሳሰብ የማምን ሰው አይደለሁም፤ ሆኖም ግን የጨዋታው ሕግ የሚፈቅደው በዚያ መልክ ከሆነ የግድ ሁሉም በዚያ ሕግ መጫወት አለበት።

"…እስክንድር ግንባሩን ሲመሠርት ፋኖዎችን ወደ አንድ አመጣልሁ፣ ገንዘቡን አደርስላቸዋለሁ ብሎ እንጂ የእራሴን ፋኖ አቋቁምበታለሁ ብሎ አይደልም ገንዘብ የሰበሰበው። እስክንድር ላይ ብዙ ጊዜ የችሎታ እንጂ የታማኝነት ጥያቄ የማያነሱ ሰዎች ሁሉ አሁን ላይ በገንዘቡ እና በሚያደርገው ነገሮች ጥያቄ እያነሱበት ነው። ምን አልባት እስከዛሬ በገንዘብ ታማኝ ነው የተባለው ገንዘብ ስላልነበረው ነው የሚሉም መጥተዋል። በእኔ እስክንድር ፈተናውን ወድቋል። እስክንድር ሓላፊነት የሚሰጣቸው ሰዎች ሁሌም መጨረሻቸው አያምርም። ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ አሁን ላይ የዐማራ ብሔርተኝነት ተቃዋሚ እና የብልጽግና ደጋፊ ኦሮሞ ነው። ወ/ሮ ሰናይት ታደገ (የባልደራስ ሓላፊ የነብረች፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ያሳሰረች፣የምታሳስር ተብላ የምትከሰስ። እንዲያውም በአንድ ኢንተርቪዋ ላይ የሥርዓቱ ደጋፊ እና የፋኖ ትግል ተቃዋሚ መሆኗን ያሳየች። ኤርሚያስ እና ሰናይት ሁለቱም የባልደራስ አባል የነበሩ የዐማራ ተወላጆችን አሳስረዋል ተብለው የሚወቀሱ። ዶ/ር አምሳሉ ቤተሰቡ የብአዴን እና ወያኔ አባል። እስክንድር ሓላፊነት የሰጣቸው እነ ሕይወት ፋኖ ማርሸትን ስልክ ደውላ ሪከርድ በማድረግ የጎጃም ፋኖን ለመጥቃት የተጠቀመችበት። የእስክንድር ሰዎች ሰዎችን ያለ ፈቃዳቸው የሚሰልሉ እና ስልክ ደውለው የሚቀዱ ከሆነ ከአብይ አሕመዱ ኢንሳ በምን ይለያሉ?

"…ሰሞኑን ደግሞ በአንድ ወቅት እስክንድር ከማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኝቶ ስለሚያውቅ ዲፕሎማሲውን ይሠራዋል እያሉ ነው ተከታዮቹ። ሆኖም እስክንድር በአብይ የሥልጣን ዘመን አሜሪካ ሲመላለስ ከእስር ተፈቶ ከተገናኘው ውጭ ስንቴ ከሩቡዮ ጋር ተገናኝቶ ስለ ዐማራ ጀኖሳይድ ተናገረ? ሻለቃ ዳዊት በጀኖሳይድ እከሳለሁ ብለው ሲንቀሳቀሱ እሱም እኔም እከሳለሁ ብሎ አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ከማቅረብ ውጭ ምን አደረገ? እስክንድር አሜሪካ ሲመላለስ ማርኮ ሩቢዮን ጨምሮ ከሌሎች ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ስለ ዐማራ ጀኖሳይድ ከመናገር፣ ከመወያየት ይልቅ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በራፍ ላይ ሰልፍ ሲያደርግ ደብዳቤ ሲያስገባ ነበር። እስክንድር እንደ አብይ በሚፈልገው ጉዳይ ላይ በሚፈልገው ሚዲያ እሱ እንዲሰማለት የሚፈልገውን ጉዳይ ከመናገር ውጭ እንደ ሌሎች ፋኖዎች መቼ ነው ከተለያዩ ጋዜጠኞች (ከሀብታሙ አያሌው ውጭ) ተጠይቆ የሚያውቀው? እስክንድር ችሎታው ምንድን ነው? ሰው ማድራጀት? ፓለቲካ መሥራት? ዲፕሎማሲ መሥራት? ወታደር ማሰልጠን፣ መምራት? ፕሮፖጋንዳ መሥራት? ሰዎችን ማስማማት? ችግር መፍታት? ግፍ እና ጭፍጨፋዎችን ማጋለጥ? በየትኛው ነው ስኬታማ የሆነው? ንገሩኝ። እስክንድርን የዐማራን ችግሮች ቀውስ የመተንበይ እና ችግር የመፍታት እና ማኔጅ የማድረግ ክህሎቱ እጅግ በጣም ደካማ የሆነ ሰው ነው። ለዚህ ደግሞ አሁን ራሱ ያለበት ሁኔታ ምስክር ነው። ሁሌ ለድክመቱ ሰዎችን ተጠያቂ ከማድረግ ውጭ ሓላፊነት አይወስድም።

"…ይቀጥላል…ተወያዩበት። ገና ምኑንም አልነካሁትም። የዐማራ ማኅበራት ውስጣችሁን ፈትሹ። ፈትሹ ብያለሁ። ተናግሬአለሁ። አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ብሔረተኝነት፣ አዲስ አደረጃጀት፣ አዲስ አመራር፣ አዲስ፣ አዲስ፣ አዲስ…አከተመ።

"…በነገው ዕለት ይቀጥላል…አጀንዳዬን አልቀይርም። ታነቅ። ጧ በል። ፈንዳ…ኬሬዳሽ።

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸዋለን…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 5/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …
ያስፈልገዋል። እስከአሁን በዐማራነታቸው ከግንቦቴዎች፣ ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ዘንድ ነቀፌታ፣ ስድብ ሲወርድባቸው የነበሩትን የተገፉ ዐማሮች በሙሉ ወደፊት ማምጣት ያስፈልጋል። ጊዜው ከዚህ በፊት አንገታቸውን ያቀረቀሩ፣ እንዲሸማቀቁ ተደርገው የነበሩ ዐማሮች ነው። ጊዜው የዐማራን አጀንዳ በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ በኖሞር ጋንግስተሮች ሰልፍ ላይ አንስተው በፖሊስ ታስረው ተባረው የነበሩ ዐማሮች ነው። ጊዜው ግንቦቴና የኖሞር አጭበርባሪ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች አሁንም ቆዳ ቀይረው ዐማራ ሆነው ገንዘቡንም፣ ስንቁንም የሚያዙበት መሆን የለበትም። ዐማራ ለዐማራውያን። ፀረ ዐማራ ፌክ ኢትዮጵያኒስት በአናትህ ተተከል። ምድረ ዱቄታም።

"…በዐማራ ስም የተሰበሰበው ገንዘብ የት ሄደ? ከምንደረሰ? ብሎ መጠየቅ እንዴት አበበ በለውን እንደሚያሳብድ ተመልከት። እሱ በዐማራ ሰቆቃ ቴስላ ይነዳል፣ ዐማራ እዚያ አታላ ይደፋበታል። አበበ በለው እኔ በባልደራስ ገንዘብ ዙርያ ያነሳሁትን ጥያቄ ባልደራስን እና እስክንድርን በጊዜው አንተም ደግፈሃል በማለት ጥያቄውን ወደ ድጋፍ ሊቀይረው ይጋጋጣል። እስክንድርን በወቅቱ እስክንድርን በመደገፌ የማልቆጭ ባይሆንም በእስክንድር በመሸወዴ ግን መቆጨቴን ሳልደብቅ ስንቴ ቪድዮ እንደሠራሁ አላየም አልሰማም አቶ አበበ። አሁን ኡጋንዳ የወሰደው ኤዲተር ልጅ ቆራርጦ ከሚልክለት ቪድዮ በቀር የትኛውንም መርሀ ግብር በትግስት የመከታተል አቅምም እውቀትም ከሌለው ሰው ጋር ቢሆንም የምሟገተው ማገዶ ይፈጃታል እንጂ ማስተማሬ እና ማብሰሌ እንደሁ አይቀራትም። ጥያቄው ስለ ገንዘብ ነው። እዚህ ላይ አቤ የረሳው እና ሳያስብ ያጋለጠው ግን እስክንድርን ነው። እስክንድርን እኔን ጨምሮ ሌሎችም ምን ያህል እንደግፈው እንደነበር ነው። ሆኖም ግን እኛ ባልደራስ ግቡ እያልን የምንልካቸውን ሰዎች እስክንድር መምራት፣ ማስተዳደር አልቻለም። ይባስ ብሎ ሓላፊ ብሎ በሾማቸው በእነ ሰናይት እና ኤርሚያስ ለገሰ በተባሉ ሰዎች አማካኝነት ብዙ የአዲስ አበባ ተወላጆች እየተጠቆሙ እንዲታሰሩ ነው የተደረጉት። እስክንድር የአዲስ አበባ ተወላጆች አሰባሳቢ ፖለቲከኛ ሆኛለሁ ለዚህም መጀመርያ ባላደራ ምክር ቤት ከዚያም ባልደራስ ፓርቲ አቋቋምኩ አለ። በጎን ግን ኢትዮጲስ የሚባል ጋዜጣ አለኝ ብሎ እዚያ ላይ እየጻፍኩ ነው አለን። ይሄም አልበቃም ሰናይ ቴሌቪዥን የሚባል ለመክፈት አክሲዮን እየሸጥኩ ነው ከውጭ ደግሞ ገንዘብ እየሰበሰብኩ ነው አለን። እስክንድር እነ አምሳሉ፣ ሙሉጌታ፣ ኤርሚያስ፣ ሕይወት፣ ወንደሰን፣ ወዘተ ምን ዓይነት ውጤት ቢያመጡለት ነው ይህን ያክል ጊዜ እሱ በሚያቋቁማቸው ድርጅቶች ሁሉ ላይ ሓላፊ አድርጎ ሾሞ ያስቀመጣቸው? እስክንድር ባልደራስ የአዲስ አበባ ተወላጆች ፓርቲ ነው ካለ በኋላ አባል ለመሆን፣ ለማገዝ ወደ ባልደራስ የሄዱ የአዲስ አበባ የተማሩ ሰዎችን ተስፋ አስቆርጦ አላባረረም? የተራ አስከባሪ ሰብስቦ አዲስ አበባን እና የአዲስ አበባን ሕዝብ የወመኔ ምልክት አላደረገም። እነ ዶር ሰሎሞን፣ እነ ዶር መክብብ በይፋ የመልቀቂያ ደብዳቤ ጽፈው የለቀቁት እኮ እስክንድር የማይረባ አስመሳይ ሰው መሆኑን ስላወቁ ነው። ዶር መክብብ አሁን ካናዳ ያለው ወንድሜ ነው። ሲገባም አማክሮኝ ነው። ሲያየው ግን እስክንድር ለመርህ፣ ለደንብ የሚገዛ ሰው አይደለም። ከተማሩት ይልቅ ከስንታየሁ ጋር መወሰንን ያበዛል። ስሙ ሰማይ ስለነካወደ ምድር መውረድ አልቻለም። ከውጭ ሆነው የሚያዩት እስክንድር ሲቀርቡት ቢከፍቱት ተልባ ነው። እስክንድርን ያጎነው፣ ያገነነው፣ "የሞቀ ሚስቱን ትቶ፣ አሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ፣ የአሜሪካን ኑሮ ትቶ" ወዘተ የሚለው ታፔላ ብቻ ነው። አለቀ።

"…እስክንድር እነ አስቴርን፣ አስካለን፣ ስንታየሁን፣ ጌጥየን፣ ወግደረስን የተባሉ አጃቢዎች በሀቢባ 11 ሚልዮን አዘርፎ፣ እነሱኑ ነበር ይዞ ሲዞር የነብረው። እነዚህ ሰዎች አብን የሚባል የዐማራ ፓርቲ እያለ ነው ከዐማራ ፓርቲ ይልቅ ባልደራስ ይሻለናል ብለው የሄዱት። አስቴር ቀለብ ስዩም ከጎንደር አርማጨሆ መጥታ ስንት ፍዳ ስቃይ አስርና እንግልት ያየችበትን ግንቦት 7 ፓርቲን ትታ ነው ባልደራስ መጥታ የተቀላቀለችው። ከአርማጨሆ አዲስ አበባን ነፃ ለማውጣት እንደማለት ነው። ከስንታየሁ ውጭ ሌሎቹ አሁን ደግሞ ፋኖ ነን ብለው ልክ እንደ አለቃቸው ዐማራን እየበጠበጡ ነው የሚገኙት። እስክንድር የአዲስ አበባን ምሑራን ወደ ጎን ገፍቶ ነው እነ ገለታውን፣ እነ ቀለብን፣ እነ ስንታየሁንና አስካለን ይዞ እነዚህ ጎዳና ለጎዳና እየዞረ የፎቶ ቦለጢቃ ሲሠራ የከረመው። እነሱ ባልደራስ ብለው አዲስ አበባ ጎዳና ሲዞሩ ዐማራ በወለጋ፣ በመተከል፣ በማይካድራ፣ በጅጅጋ፣ በሃዋሳ፣ በሻሸመኔ፣ በአሩሲ…ሲጨፈጨፍ ነበር። ፋኖን እናደራጅ ብለው አልሄዱም፣ የሄዱትንም አልደገፉም። የጎጃም ፋኖው ቃላቀባይ የነበረው ማርሸት በአንድ ወቅት ወደ ባልደራስ ቢሮ ሄዶ እስክንድርን አግኝቶ "እስክንድር እባክህ ባላደራ፣ ባልደራስ ምናምን ብለህ የምትደክመውን ድካም ተወውና ያለህን ስም ተጠቅመህ የዐማራን ፋኖ ብታደራጅ ብሎ ሲጠይቀው በወቅቱ እስክንድር እንዴት እንዳበደበት፣ ከቢሮውም ገፍትሮ እንዴት እንዳስወጣው ራሱ ማርሸት ያጫወተኝ አይረሳኝም። አዎ ዐማራው ሲገደል እነሱ ለምርጫ ሲሯሯጡ ነበር። አሁን ሌሎች የሠሩትን ሥራ ገብተን ካልመራን ይላሉ። እስክንድር ተደራጅቶ የተሰጠውን ሕዝብ መምራት፣ ተሰብስቦ የተሰጠውን ገንዘብ ማስተዳደር አይችልም።

"…ሃቁን ዋጡት። የእስክንድር ሚስት ሰርካለም ፋሲል የኢሮብ ትግሬ ናት። በአንድ ጎን ከኤርትራ ትግሬነትም አላት ይባላል። አንድ በሉ። የማይቀየረው የእስክንድር ነጋ ገንዘብ ያዥ ዶር አምሳሉ አስናቀ ሚስቱም ትግሬ ናት። የሚገርመው ነገር ማመን አቅቶኝ እንጂ የእስክንድር ሚስት እና የዶክተር አምሳሉ ሚስት ሁለቱም ከትግሬነታቸው ባሻገር ታላቅና ታናሽ እህትማማቾች ናቸው አሉ። አሉ ነው እንግዲህ። መነን አካባቢ ያሉት ወዳጆቼ ናቸው ሹክ ያሉኝ። እውነት ከሆነ ተመልከት ፒፕሌ። 😂 እስክንድር በአንድ ወገን ደቡብ ጎንደሬ ነው። ዶር አምሳሉም ደቡብ ጎንደሬ ነው። ባለ ትግሬ ሚስቶቹ ደቡብ ጎንደሬዎች ለምን አንድ ላይ ገጠሙ አይባልም? ለምንድነው የማይለያዩት ብሎ መጠየቅም በሰው ፍቅር እንደመቅናት ያስቆጥራል። ጥያቄ መጠየቅ ግን ይቻላል። አይደለም እንዴ? አሁን ጣና ቴሌቭዥን ብለው የሚመጡት በሙሉ፣ በእስክንድር ስር የገቡት በሙሉ በአብዛኛው ጎንደሬ ማንነት ያላቸው ሰዎች ናቸው። የጎንደር ሁለት የፋኖ አደረጃጀትም በእስክንድር ስር ነው የገባው። የእነ ጌታ አስራደ እና የእነ ሀብቴ ቡድን ማለት ነው። የእነ ሀብቴ ሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ፋኖ ዮሐንስ ወይም ጆኒ የአክሱም ትግሬ ነው። ዋጡት። ከውባንተ ጋር በጋሼ መሰፋንት ፊት ዘር ተቆጣጥረው ውባንተ የጎንደር ዐማራ ዮሐንስ የትግሬ ልጅ ሆኖ ተገኝቷል። ጎንደሬው ውባንተ ተገድሎ ትግሬው ዮሐንስ የሀብቴ የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ሆኖ ተሹሟል። ሰሞኑን በወልቃይት ጉዳይ መግለጫ ሰጥቶ አዋራ ያስነሣው የሀብቴ ፋኖ የሕዝብ ግኑኝነት ሓለፊው ትግሬው ጆን ነው። ይሄንንም ዋጡት። ወልቃይትንም ዓይናቸው እያየ ባያስበሉት ምንአለ ዘመዴ በሉኝ።

"…እነዚህ ከትግሬ የተጋቡ፣ የወለዱና የዐማራ ፋኖን የሚመሩ ስሁላዊ አካላት እንዴት ዐማራውን ተብትበው እንደያዙት ተመልከቱ። ዐማራው ለእስክንድር ብሎ የሚያዋጣውን ገንዘብ በሙሉ የሚቆጣጠሩት ትግሬዎቹ እህትማማቾቹ የእስክንድርና የአምሳሉ ሚስቶች…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ይቅርታ ለአቤ በራሱ ሜዳ ሌክቸር የሰጠሁበትን ቪድዮ ስፈልግ ነው ያረፈድኩት። ሸዋን እግር ተወርች አስሮ ያደቀቀው ፀረ ዐማራው እስክንድር ነጋም ለአማሪካው አዲስ አስተዳደር እንኳን ደስ ያላችሁ የሚለውን መጋጫውን ለቋንቋ አስተማሪዬ ለሱሬ ሳስተረጉም ቆይቼ ነው የዘገየሁት። ትናንት የጀመርነውን ርእሰአንቀጽ ዛሬም ጠጠር አድርገን እንቀጥላለን።

"…ርእሰ አንቀጹ አእምሮ ውስጥ የሚቀመጥ ነው። ርእሰ አንቀጹ ባትፈልጉም በግድ ጥያቄ የሚያጭርባችሁ ነው። ርእሰ አንቀጹ ተኝታችሁ የሚያስቃዣችሁ ነው። ርእሰ አንቀጹ እያፋሸካችሁ፣ እየተንጠራራችሁ፣ እያንጠራራችሁም ቢሆን በግድ ለውይይት የሚጋብዛችሁ ነው። እኔ ደፍሬ፣ ጨክኜ ጽፌዋለሁ። ሓላፊነቴንም ተወጥቻለሁ። እናንተ ግን የራሳችሁ ጉዳይ።

"…ዛሬም እስክንድርና ቲሙን ነው የምጠይቀው። የምሞግተው። አበበ በለው ለበዓሉ ድምቀት እንደ ማባያ፣ ለጨዋታ ማሳመሪያ የማመጣው አሻንጉሊቴ እንጂ በቁምነገር ቦታ የምሰጠው ሰው ሆኖ አይደለም። በራሱ መድረክ ላይ ጋብዞኝ እስከ አፍንጫው እውነት ግቼው የተመለስኩ ሰው ነኝ እኔ ዘመዴ። ምስክሩም ያው ቪድዮው። ሙሉውን ሰሞኑን እለቅላችኋለሁ።

• እየጠበቃችሁኝ ነው ቤተሰብ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መርሀ ግብር ማስታወቂያ…

• ጠዋት እግዚአብሔር በማመስገን መርሀ ግብራችንን እንጀምራለን።

• 1ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ ከጨረሰ በኋለ ከዛሬ የተረፈው ርእሰ አንቀጽ ይቀጥላል።

"…በነገው ርእሰ አንቀጻችንም ብዙ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ። ሱፍ አድርጎ፣ በከረባት ታንቆ፣ ሰው መሳይ በሸንጎ፣ የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ በመሆን ዐማራን በማጭበርበር፣ በፊቱም ቲያትር በማሳየት፣ ኮመዲ በመኮመድ በትግሉም ላይ ደንቃራ፣ ሾተላይ መሆን እንደማይቻል አሳያለሁ። ኮተታሙን ሁሉ በመረጃና በማስረጃ እየሞገትኩ፣ ንስሀ የሚገቡም ካሉ የንስሀ ዕድል እየሰጠሁ የምኮረኩምበት ነው ርእሰ አንቀጽ ነው።

"…አቤ እስክስ በመረጃ ቴቪ ላይ ራምብል፣ ዌብሳይት ላይ በክብር ተለጥፎ ለታሪክ የተቀመጠን የእኔን የቀድሞ ንግግሮች እያመጣ ዋይዋይ እያለ ነው። ዘመዴ ሰውየውን ነርቩን ነክተህ አጨለልከው እያሉኝ ነው። ይሄ ትክክል አይደለም። እኔ አቤን ለማጨለል ሳይሆን ልክ ለማስገባት፣ እጁን ከፋኖ ብር ላይ እንዲያነሣ ለማድረግ እያስተማርኩት ነው። በእውነት ካወቀበት ይጠቀምብኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አይደለም እንዴ?

"…እኔ በሕይወቴ እንደ እስክንድር የሸወደኝ የለም ብዬ እኮ ተናገርኩ አቤ። በእስኬው የስም ግንባታም ላይ ግምበኛ ስለነበርኩ አሁን ግንቡ ሲጣመም የማስተካከል መብት አለኝም ብዬ ተናገርኩ እኮ። ስንቴ ልንገርህ አቢሻ። መስከረም ላይ ዘመድኩን ከስሯል፣ ከትግሉም አባረነዋል፣ ከእንግዲህ በዚህ ጉዳይ አልመለስበትም ካልክ በኋላ ማን እንዳይሰማኝ፣ ምን ተጽዕኖ እንዳልፈጥር ብለህ ነው የምትቧችረው? ካልተረጋጋህ በራስህ አፍ ከአንተ የተሻለ እንደምደመጥ፣ ተጽእኖ ፈጣሪነቴንም ጭምር በአደባባይ እየመሰከርክ መሆኑንም ዕወቅ።

• ደግሞ እንደ ወንድ ራስህን ችለህ ግጠም። እገዛ አትፈልግ፣ 3ኛ ወገን ጎትተህ ለማስገባትም አትድከም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…!

"…አሁን ደግሞ 15 ሰው አንብቦት 14 ፍሬ ሰው ብቻ 😡 ብው ብሎ የተናደደበትን ርእሰ አንቀጽ በእናንተ ወደማስተቸቱ እናመራለን። ተራው የእናንተ ነው።

"…ርእሰ አንቀጹ ረጅም ነው። በይቀጥላል ነው የቆመው። ነገ ጠዋት ካቆምንበት እንቀጥላለን። በደንብ እንተቻለን። አበጥረን እንመረምራለን። በድፍረት መወያየት እንጀምራለን። የሚበሳጭ እስክስ ማለት ይችላል። መብቱ ነው።

"…አበበ በለው ተነካብኝ፣ ተተቸብኝም ብሎ በጎጥ ተወሽቆ፣ የደንቢያ ልጅ ነኝም ብሎ፣ በዐማራነቱ ተሳስቦ በእኔ በሐረርጌው መራታ በዘመዴ ላይ ስህተት ካለብኝ እኔን ስህተቴን ከሚያርም ጨዋ አስተያየት በቀር ከመስመር ያለፈ ክፍት አፉን የሚከፍትብኝን፣ በአበበ ጭቅጨቃ ክፍት አፉን የሚከፍትብኝ የዐማራ ማኅበር ካለ እኔም በአፀፋው ምላሽ ለመስጠት የምገደድ መሆኔ ይታወቅልኝ።

• በሉ ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …የጉዳዩ ባለቤትም፣ መሪም፣ ተቆጣጣሪም፣ አዛዥም እስክንድር ነጋ ያለምንም ተቀናቃኝ ብቸኛው ሰው ሆነ። ጉራጌው ብርሃኑ ነጋ ዐማራን አልቦ፣ አልቦ፣ እጥብ አድርጎ ሲያበቃ፣ አናቱ ላይ ተጸዳድቶ ወደ አቢይ ዘንድ ገሌ ስለገባ፣ እነ ነአምን ዘለቀ፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እነ ኤፍሬም ማዴቦ፣ እነ ታማኝ በየነም የዐቢይ መንገድ ያዋጣናል ብለው በማሰብ በእስክንድር የስም ሽያጭ  የሚገኝን ዶላር ንቀው ዞር ከዚህ ዘራፊ ቡድና ክለብ ዞር ስላሉ ወደ አዲስ አበባ የታከለ ኡማ ኮንዲሚንየም ቃል ተገብቶለት ከተሸበለሉ ጥቂት የዲሲ ግብረ ኃይል አባላት የተረፉትን ይዞ እስክንር ወደ ግልጽ ዘረፋው ገባ። በዚህ ዘረፋ ላይ ሚስቱም ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በግልፅ ተሳታፊ ነበረች። ቪድዮው አለኝ። ባል እስክንድር ኢትዮጵያ ሆኖ፣ ሚስት አሜሪካ ሆና ይሄንን ምስኪን ዐማራ አለበቱ አይገልጸውም። አጠቡት። ለዘረፋ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ነው የሞለጩት።

"…ዘረፋው ሀ ተብሎ የተጀመረው በባላደራው ነው። ባላደራው ብዙም ሳይቆይ ባልደራስ ተብሎ ስሙን ቀይሮ ከች አለ። ሰናይ ቲቪም ምሥረታ ተብሎ፣ አክስዮን ሁሉ እንሸጣለን ብሎ እስክንድር ውርውር ብሎ ነበር። በእነዚህ ሁሉ ከላይ የጠቀስኳቸውን ጆፌ አሞሮች ሰብስቦ በአዲስ አበባ ስም ዳያስጶራውን በተስፋ እየሞላ፣ ለልመናው የሚሆን አጫጭር ቪድዮ እንደ ቲክቶከር እና እንደ ዩቱዩበር እሠራ እየላከ ይሄን ምስኪን ዳያስጶራ እንደ ጉድ ይሄን ዶላር ያልበው ጀመር። ኢትዮ 360፣ እኔን ጨምሮ፣ አበበ በለው፣ ፌስቡከርና ቲክቶከር፣ ዩቱዩበሩ ሁላ "ታላቁ እስክንድር" እያልን እንድንጮህ ተደረግን። እነ ኢሣት፣ እነ መሳይ፣ እነ ሲሳይ አጌና በተራቸው የቀድሞ እንጀራቸው የነበረውን እስክንድርን ይጠሉት፣ በግልፅም ይወርፉት ጀመር። ነገር ግን የኃይል ሚዛኑ ወደ እስክንድር መንደር ሰዎች ስላጋደለ ያኛው መንደር ተሸናፊ ሆነ። በተለይ የታከለ ኡማ አስተዳደር ቄሮዎችን ወደ እስክንድር ቢሮ እየላከ ሁከት በመፍጠር እስክንድር ነጋን ማጀገኑን ተያያዘው። ዳያስጶራውም፣ ሀገር ቤት ያለውም ሕዝብ እልህ ውስጥ ገባ። እስክንድር የኦሮሙማው አገዛዝ ብቸኛው ተቃዋሚ ሆኖ ወጣ። ቀድመው የነበሩት ተቃዋሚዎች በአቢይ አስተዳደር ውስጥ ተካተው ስለበለፀጉ፣ ቀድመው የነበሩት ተቃዋሚዎች እንደነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ እንደ ብራኑ ነጋ የመሳሰሉት የሥርዓቱ አጋር ስለሆኑ፣ እነ አብንም ተስፋ የሚጣልባቸው ስላልሆነ፣ እነ ልደቱ አያሌውም አፍቃሬ ወያኔ ናቸው ተብለው በሕዝቡ ዘንድ ስለተገመገሙ፣ የተቃዋሚው መንደር በተቃዋሚ መሪ እጦት እየተሰቃየ፣ እየቃተተ በነበረ ሰዓት ነው በወያኔ በተደጋጋሚ ታስሮ መፈታቱ እንደ ጥሩ ሪከርድ ተቆጥሮለት እሱ ራሱ ሳያስበው፣ ሳይጠብቀውም ያለምንም ተቀናቃኝ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሆኖ አረፈው።

"…ባላደራው ሲቋቋም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። አንድ በሉ። ባላደራው መፍረሱ ሳይነገር ባልደራስ ተቋቋመ። ባልደራስ ሲቋቋምም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ወሮ ሕይወት፣ አቶ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ባልደራስ ሳይፈረወስ እስክንድር ፈነንኩ ብሎ ጫካ ገባ። ጫካ ገባሁ ብሎም ግንባሩ የሚባል ድርጅት መመሥረቱን በይፋ ዐወጀ። አሁንም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ግንባሩ መፍረሱ ሳይነገር ሠራዊቱ የሚባል መቋቋሙ ታወጀ። አሁንም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ሠራዊቱ ተመሥርቶ ወር ሳይቆይ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የሚባል መመሥረቱ ታወጀ። አሁን ጭንቅ መጣ። ገንዘብ ያዦቹም ተደበቁ። ትናንት የዙም ማስታወቂያ ብሠራላቸውም ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡ ተደበቁ።

"…ለባልደራስ ተብሎ ሚልዮን ፈሪ ዶላር ተዋጣ። ያ በአሜሪካ ተሰብስቦ ወደ አዲስ አበባ ይላካል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ዶላር ወደ አዲስ አበባ ሳይላክ የእስክንድር ነጋ ሚስት በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠረችው በዚያው በአሜሪካ እንደ ጨው ሟሙቶ እንደ በረዶም ቀልጦ ቀረ። አዲስ አበባ የነበሩት የባልደራስ አመራሮችም ስለ ኦዲት፣ ስለ ተሰበሰበው ገንዘብ ሲጠይቁት አንድም መልስ ሳይሰጣቸው፣ ኦዲትም ሳይደረግ እስክንድር ነጋ እንደ ቦዘኔ፣ እንደ ዋልጌ ልጅ እንደወጣ ቀረ። እንዲያውም ከአሁን በኋላ ፋኖ ሆኛለሁ በቃ ብሎ ብጣሽ ወረቀት ለባልደራስ ጽሕፈት ቤት ለአስቴር (ቀለብ) ስዩም ልኮ እሱ ሰሜን ሸዋ ራሳ መከታው ጋር ሄዶ በዚያው ፈነነ። የነገው ቢሳካለት ሀገር ለመምራት የሚታትረው እስክንድር በትንሹ በባልደራስ ያልታመነ፣ ተመዝኖም የቀለለ ሰው ሆኖ ተገኘ። ይሄን አሁኑኑ ደፍረን ካልሞገትነው፣ ሕጋዊ ጥያቄውንም በድፍረት ካላነሣን አደጋ ነው። ይታያችሁ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆን ከአረመኔው አብይ አሕመድ የባሰ ዘራፊ፣ ነፍሰ ገዳይ ነው የሚሆነው። ልጓም የግድ ነው። ኋላ ላይ በሬ መስረቅ ጀምሮ ተይዞ ሊሰቀል ሲል ብናለቅስ እስክንድር የሚለን ምነው እናቴ በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ ነበር። የማይጠቅም፣ የማያድን ለቅሶ ነው የሚለን።

"…እስክንድር ነጋ በአሜሪካ ባልደራስን ሲያቋቁም ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራን ይዞ ነው። ኤርሚያስ ዋቅጅራ ደግሞ ኢህአዴግ ነው። እስክንድር ኢህአዴጉን ኤርሚያስ ለገሰን ከመረጠው በኋላ የተፈጠረው ቀውስ ቀላል አይደለም። እስክንድር የአዲስ አበባን ጉዳይ አጀንዳው ካደረገ በኋላ ብዙ የአዲስ አበባ ወጣቶች፣ ምሁራንም ባልደራስን ለማገዝ ተቀላቅለውት ነበር። የባልደራስ አባላት መብዛታቸው ሲታይ እንደተለመደው በኢትዮጵያ ፖሊስ፣ በወያኔም ጊዜ ሆነ በኦህዴድ ጊዜ ሲታሰር ጫፉን የማይነካው፣ ዝንቡ እሽ የማይባለው፣ በእስር ብቻ የሚጀግነው እስክንድር ነጋ የሀጫሉን ሞት ተከትሎ የእነ ጃዋር፣ የጓደኛው የበቀለ ገርባ ማባያ ተደርጎ ታሰረ። እስክንድር በእስር ዘመኑ ሃይላንድ በብልቱ ላይ  አልተንጠለጠለበትም። ጨለማ ቤት ገብቶም አልተሰቃየም። እንደሌላው የዓይኑን ብርሃንም፣ እግሩንና እጁንም አላጣም። ብቻ ይታሠራል። ይፈታል። ከተፈታ በኋላ የዶላር ማለቢያ ድርጅት ያቋቁማል። የአዲስ አበባ፣ በተለይ የፈረንሳይ ወጣቶች በመዝገቡ ተለቅመው ታሠሩ። ገሚሱ ተሰደደ፣ ገሚሱ ተገደለ።

"…እስክንድር ከእስር እንደተፈታ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ነው የሄደው። ድል ለዲሞክራሲ ሲል የነበረው እስክንድ አሜሪካ ከመሄዱ በፊት ግን ይመስለኛል በትግራዩ ጦርነት ጊዜ ከኢትዮጵያ ወገን ሆነው ለተዋጉ የፋኖና የአፋር ክልል መንግሥት ምስጋና ለማቅረብ የባልደራስ ቲምን አስከትሎ ሄዷል። እስክንድር በዚህ ጉዞው ፋኖ በሚገባ መዘጋጀቱን፣ ጦርነትም አይቀሬ መሆኑን ተረድቷል። የባልደራስ አባላትን ይዞ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋም የፋኖ አደረጃጀቶችን በተመስጦ ጎብኝቷል። ገምግሟልም። በጎንደር ጋሽ መሳፍንት ጋር በመሄድ ከጋሼ ጋር መክሯል። በውለታም፣ በመሃላም አስሮት ተመልሷል። በጎጃም ከኢንጂነር ይልቃል ጋር፣ ከነ ዘመነ እና ማስረሻ ሰጤ ጋር በመሆን መክሯል። የጎጃምን ፋኖ አደረጃጀት እና አያያዙንም ገምግሟል። ጎጃሜዎቹን ጋዜጠኞች ጌጥዬንና ወግደረስንም መልምሎ የባልደራስ አካል አድርጓቸዋል። ከዚያ ወደ ወሎ…👇②ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬም ቆሻሻ አመለካከት መጥረጊያዬን ይዤ፣ ወንፊትና ሰፌድንም ይዤ፣ ይሄን ዘራፊ፣ አጭበርባሪ የደም ነጋዴ ሁላ ልጠርገው፣ ለበጥረው፣ በዚያውም በጭቃ ዥራፌ እየዠለጥኩ፣ በእሳት አርጩሜ ብዕሬ እሸነቆጥኩ፣ በዐማራ ትግል ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው፣ እንደ አልቅት ደሙን እየመጠጡ ዐማራን ነጭ የአሸቦ ዕቃ አስመስለው ያስቀሩትን መዥገሮች ላራግፍ ነኝና ጮጋ ብላችሁ ጠብቁኝ።

"…ደጋግመው ፋውል የሠሩ፣ የዐማራ ትግል በገንዘብ እጦት እንዳይፋፋ፣ እንዳይመራ ሳንካ ሆነው ያስቸገሩ፣ እንደ ጋሬጣም የተጋረጡ፣ እንደ ሾተላይ የትግሉን ጽንስ ማጨናገፍ ቋሚ ሥራቸው ያደረጉ ሰው መሳይ በሸንጎዎችን ፋስ መዶሻ ሆኜ ልነቅል ነኝና ጫ ብላችሁ ጠብቁኝ።

"…እንደ ቴሌ የግድግዳ ስልክ ያለ ገንዘብ፣ ያለሳንቲም የማይሠሩ። እፍረት፣ ነውር፣ ሼም የሚባል ነገር የማያውቁ፣ አርጅተው በዳይፐር እየሄዱም እንኳ አሁንም ንስሀ ለመግባት ወኔ የሌላቸው የፖለቲካ ጋለሞቶችን ንስሀ እንዲገቡ ልሰብክ ነኝና ምእመናን ተዘጋጁ።

"…ይሄን ያፈጠጠና በጥቂት ግለሰቦች ተይዞ፣ በሕዝብ ትግል የግል ኑሮና ቤተሰብ የሚጦርበት፣ ከዳያስጶራው ተሰብስቦ ብልፅግና የሚቀለብበትን የአጭበርባሪ፣ የነውረኞችን የእንጀራ ገመድ በድፍረት ልበጥሰው ነኝና ተዘጋጁ። አዲስ ዐማራዊ ወጣት፣ አዲስ ዐማራዊ አስተሳሰብ፣ አዲስ ግልፅ የሆነ ተጠያቂነት ከሓላፊነት ጋር አስተባብሮ የያዘ ዘመናዊ ዐማራዊ አሠራር እንዲዘረጋ መጀመሪያ እነዚህን የዕድር ዳኞች፣ ዕቁብ ሰብሳቢዎች መቀየር፣ ከትግሉ ሜዳም ዞር ማድረግ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ወፍ የለም።

"…እህሳ የቲም እስክንድርን ነጋን የዶላር ዘራፊ ቡድን የዘረፋ ስልት ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይባልም…!

"…ለምን ዘመድኩን ቤት ሄዳችሁ ይባላል እንዴ? በፍጹም አይባልም። የኡጋንዳው ወንዴ አፍንጮ ግን ሲበዛ ክፉ ሰው ነው። አሽቆጠቆጣቸው እኮ። ይኸው እኔ ማሙሼ ጉልቻው ቤት ገብቼ እየሰማኋችሁ አይደል እንዴ? ሰው እኔ ቤት ገብቶ ቢያዳምጠኝ ምንድነው ችግሩ? በእውነት ትክክል አይደለም። ወንዴ የእስክንድር የአክስት ልጅ ነው ብለው ለምን እንዲህ እንደሚፈሩት ነው እኔ የሚገርመኝ።

"…ያፈነዳሁት የቲክቶክ ፈንጂ ስንቱን እንደረፈረፈ እየቃኘሁ ነው። በሁሉም ቤት ዘወር፣ ዘወር እያልኩ ሳይ በሁሉም ቤት አጀንዳው እኔ ነኝ። እኔ ዘመዴ እኮ በቃ ይሄን አይደል እንዴ የምፈልገው? አጥንት እወረውልሃለሁ እሱ ላይ ለሃጭህን እያዝረበረብክ ስትለፋ እኔ ጋደም ብዬ እየከለምኩህ ፈታ እላለሁ።

• እስቲ እነ ዳማከሴ ቤት ልግባ ደግሞ። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሉ ቤተሰብ… በርእሰ አንቀጹ ላይ አስተያየት እየሰጣችሁ ወደ ቲክቶክ መንደራችን እናምራ።

• እየሄዳችሁ ኮምቱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ግንቦት 7፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ኢህአፓ፣ ቅንጅት፣ ብአዴን፣ ወያኔ፣ ግንባሩ፣ ባልደራስ፣ ባላደራ፣ አፋህድ፣ አመድ ወዘተ ጋር የተነካኩትን እንደ ኢቮላ ቫይረስ ቆጥራችሁ ከአመራር እና ከገንዘብ ስፍራ አርቋቸው። የመርዝ ብልቃጥ ሕፃናት በማይቀመጡበት ስፍራ ነው መቀመጥ ያለበት። ተናግሬአለሁ።

"…አሁን ዘመኑ የወንፊት ዘመን ነው። የማበጠሪያ ዘመድ። ሰፌድ ላይ ትወጣለህ ትበጠራታለህ። ሚዛን ላይ የግድህን ትወጣለህ ትመዘናለህ ቀለህ ከተገኘህ ትወገዳለህ። እብቅ ነህ። መሬት ላይ ያሉት ፋኖዎች አሁን ችግር ላይ ናቸው አዎ ናቸው። ችግሩ እንደ ወንፊት ነው። ለሆዱ ብሎ የገባው ፋኖ ዶላሩ ሲቀር ወደ ዘረፋ፣ ከዚያ ወደ ቤቱ፣ አልያም ወደ ብልጽግና ይሄዳል። ለዓላማ የገባው ፋኖ ግን አፈር ደቼ እየበላ ተጋድሎውን በይፋ ይቀጥላል። የወሎ ዐማራ ፋኖ የእነ ምሬ ወዳጆ፣ የእነ ባዬ ቀናው የጎንደር ፋኖ፣ የእነ ዘመነ ካሤ የጎጃም ፋኖ፣ የሸዋው የእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ፋኖ እነደነ መከታው ፋኖ ዶላር አላገኘም። እነ መከታው እኮ እስከ 500 ሺ ዶላር በአጭር ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። አበበ በለው እኛ ምን ሠርተን እንብላ ብሎ እስኪያለቃቅስ ድረስ በጥበብ፣ ውስጥ ለውስጥ ተሠርቶ ነበር የደረሳቸው። እነሱ ግን የፂማቸውን ቁርጥ እያሳዩ ከመቀፈል በቀር ነቅነቅ አላሉም። ሥራ ፈት ጎሮምሳ ጫካ አስቀምጦ መቀለብ ደግሞ ግፍ ነው። ሳይረዱ፣ እርዱንም ብለው ሳይለምኑ ይኸው እነ ምሬ ጠላትን ይነዱት የለም እንዴ? ለእነሱ ቢረዳ እሺ። ሳይሠራ ምንአባቱ ስለሆነ ነው ግማሽ ሚልዮን ዶላር የሚቀለበው? ጥፋ በለው። ታነቅ። ስትሰድበኝ፣ መግለጫ ስታወጣብኝ ዋል። ሚልኢላል ኢሄ?

"…አሁን ምድር ላይ ያሉትን ፋኖዎች ትቼአለሁ። አሁን እኔ ሰቀቀን ውስጥ መክተት የምፈልገው የአየር ላዮቹን ጥቃቅን ቀበሮዎች ነው። ዋናዎቹ እዚያ አሜሪካ ያሉት ናቸው። እነ አምሳሉ አስናቀ፣ ምስጋናው አንዷለም፣ ሙሉጌታ አያሌው ደስታ፣ ኤርሚያስ እሹሹ ሽበሺ፣ ሕይወት በላቸው፣ ኢዮብ የቦስተኑ፣ ሃብታሙ ነጋሽ፣ ወንደሰን መኮንን፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው፣ ዱኒ ተስፋዬ፣ ክንፉ ወዳጄ፣ ዶ/ር ደረጀ ተሾመ፣ ዩሐንስ ሙሉነህ፣ እንግዳሸት፣ ገነት ረታ፣ ቴዎድሮስ ከበደ፣ የሺ ወንድሙ፣ ወሮ እቴነሽ እና ወሮ ሸዊት ናቸው። (ሸዊት ማለት እንዴት ያለች እናቴ ነበረች መሰለቻችሁ። እስክንድር ነው የለያየን። በእስክንድር ምክንያት ነው እኔን መደገፍ ሁላ ያቆመችው። በየወሩ መቶ ዶላር ነበር ሚዲያዬን የምትደግፈው። ዘመዴ እስክንድርን ስለነካህብኝ ከዛሬ ጀምሮ አቁሚያለሁ ሳትለኝ ነበር ቀጥ ያደረገችው) በሉ አንድ ሰው በወሮ ሸዊት ቦታ 100 ዶላር ይዞ ይቅረብ። እነዚህን የወይኑን እርሻ ሊያበላሹ የሚችሉ ቀበሮችን አጥሩን ልናጠብቅባቸው ይገባል።

"…ከባላደራው እና ባልደራስ ጀምሮ፣ በገንዘብ ስብሰባው ላይ የነበሩትን የእስክንድር ነጋ ባለቤት ከወሮ ሰርካለም እና መስፍንን ጀምሮ እነ አበበ በለው እንዴት በዙም ገንዘብ ይሰበስቡ እንደነበር በቪድዮ ይዤ እመጣለሁ። ከግምባሩ ሙልጌታ ጋር እንዴት ዶላር ሲቀፍል እንደነበረም አጋልጠዋለሁ። አበበ ፀረ ሸዋ ነው። አበበ ሸዋን እንደ ጉድፍ ነው የሚፀየፈው። አበበ እስክንድርን ይዞ አቅም የለውም እንጂ ሸዋን ለማድቀቅ የማይቆፍረው መሬት የለም። አለማፈሩ ለሸዋ ሰዎች እየደወለ ይዘበዝባል። በሙሉ የደወለላቸው እየደወሉ እንዲህና እንዲህ እያለን ነው ይሉታል።

"…አበበ በለው ከእስክስ ወጥቶ የዐማራን ትግል ማዳበሪያ ዶላር ክስክስ ነው ያደረገው። በዋ ዐማራ ማኅበር በኩል የዘረፈውን ፈጣሪ ይወቅ። ቤት ገዝቷል። ቶዮታ መኪናውን በቴስላ ቀይሯል። ከእስክንድር ተጠግቶ፣ ከእነ ሀብታሙ ተጠግቶ፣ ከግንቦቴም፣ ከባልደራስም፣ ከስኳድም ተጠግቶ ዋነኛ ዓላማው ቁጢ፣ ዶላሩ ላይ ነው። አበበ በለው እንደ ሴተኛ አዳሪ ለከፈለው ሁሉ የሚተኛ ነውረኛ ሰው ነው። አበበ በለው ሆቴል ገብቶ ሒሳብ እንደማይከፍል የሆቴል ባለቤቶች በምሬት የሚያወሩት ነው። አበበ በለው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር በዐማራ ስም በግልፅ እየሰበሰበ ሆቴል ገብቶ ለበላበት፣ ለጠጣው ሻይ የማይከፍል፣ ለአስተናጋጆች ጭምር ቲፕ የማይሰጥ ስቁንቁናም ነው። አስተናጋጆች እያሳሳቀን ሒሳብ ሳይከፍለን፣ ቲፕም ሳይሰጠን ነው የሚወጣው። እባክህ ዘመዴ ይሄን ሰው አንድ በልልን እስኪሉኝ ድረስ ነው ማፈሪያ የሆነው። አልፋታውም። ቪድዮ እየቆራረጠ የሚልክለት ልጅ አሁን ኡጋንዳ ገብቶ ሥራ አስጀምሮታል። ይሄም አያዋጣውም። እኔ በዐማራ ጉዳይ ድርድር፣ ቀልድ አላውቅም።

"…በመጨረሻም እላለሁ"…ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15። የምታስታውሷቸውን አሮጌም፣ ቀጭንም፣ ሽማግሌም፣ ወጣት፣ ጎልማሳ፣ ጥቃቅን ቀበሮችን ሁሉ እስቲ በስም ዝርዝር ጻፏአቸው። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ እስያ፣ አውሮጳ፣ እስራኤል፣ በአረቢያ ምድር፣ በአፍሪካም አዲስ አበባም እንዳለው እንደ ፌስቡከር ጥላሁን ጽጌ ዓይነት የፈትለ የጭን ገረድ ፍርፋሪ ለቃቃሚ የስኳድ ቀበሮ ዓይነቶቹን አጋልጡ። እናጋልጥ።

• ዛሬ ቲክቶክ ገባ ብዬ እወጣለሁ እና ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።

• ጥቃቅን ቀበሮዎቹን በጋራ እናጥምድ…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን ታዝባችሁልኝ ከሆነ በሸዋ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስር የሚተዳደረው የእነመከታው ፋኖ ቡድን በተደጋጋሚ ወደተለያዩ ሚዲያዎች እየወጣ ስለፋኖ አንድነት፣ ከአንድነት ውጪ ሌላ ምርጫና አማራጭም እንደሌለ፣ ሳይጠየቅ እየለፈለፈ ነው። ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር፣ ከእነ ዘመነ ካሤ ጋር፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ጋር በጋራ ለመሥራት እየተነጋገርን፣ በደንብ እየሄድንበት ነው የሚል መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። ይሄንኑ መግለጫም በጎንደሩ ስኳድ በፓስተር ምስጋናው ሚዲያና በመሳይ መኮንን ሚዲያ ላይ በመቅረብ አቤ ጢሞና መምህሩ ሲደሰኩሩም ተሰምቷል። አለቃቸው ፋኖ መከታውም በቪድዮ መልእክት ወጥቶ ከወንድሞቻችን ጋር በግድ ከመታረቅ፣ አንድ ከመሆን በቀር ሌላ አማራጭ የለንም ሲል ተሰምቷል።

"…ምኞቱ ጥሩ ነው። ጥሩም ነበር። ነገር ግን ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ታስሮ እንደተፈታ ሰው እንደ ግሪሳ ወፍ ከነ ወጥተው ዋይዋይ ያስባላቸው? ምን ሆነው? ምን አግኝተው ነው እንዲህ አደባባይ አውጥቶ የፍቅር፣ የአንድነት ሰባኪ ያደረጋቸው? ድንገቴው ነገር ምንድነው? ይሄንን ለመመርመር ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መልስ ግን እነርሱ ከሚያወሩት በእጅጉ የተለየ ነው። መሬት ላይ ያለው የኃይል አሰላለፍ ነው እነ መከታውን የአቡኤን መገበሪያ እንደበላ ሰው ያስለፈልፋቸው የጀመረው። ብዙ ሰዎች በሸዋ ጉዳይ የሸዋን ፖለቲካና የሸዋ ፋኖን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ አካላት ነገሩ በደንብ ይገባቸዋል። ለምን የእባብ መርዝ እንደቀመሰ ፍየል ማርከሻውን ፍለጋ እንደሚንጠራወዙ ይገባቸዋል።

"…እነመከታው በእስክንድር ምክንያት ደጋፊ አጥተዋል። በእስክንድር ምክንያት በሳምንት ይፈስላቸው የነበረውን 20 እና 30 ሺ ዶላር አጥተዋል። እነ መከታው ከተዋጊ ፋኖዎቻቸው በእስክንድር ጉዳይ ለሚነሳባቸው ጥያቄ ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠታቸው ከእነ መከታው የፋኖ አደረጃጀት የሚወጡ ብርጌዶች፣ ተዋጊዎች ዕለት ዕለት እየጨመሩ መምጣት፣ ክፍለ ጦሮችም ከጠቅላይ ዕዙ ለመለየት መግለጫ ማውጣት መጀመራቸው፣ እነሱ ተንፈላሰው ይኖሩበት የነበረው ቀጠና በተዋጊ ዕጦት መሳሳት መጀመሩ አሳስቧቸዋል። እስክንድርን ይዘው ሚልዮን ዶላሮችን ለማፈስ፣ እስክንድርን ይዘው በድርድር በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት በመጓጓት የሠሩት ስህተት ከባድ አርታኢሌ የሆነ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል። እናም ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ሳይጠየቁ መለፍለፍ፣ ሳይለመኑ የሰላም፣ የአንድነት ሰባኪ መሆን ብቻ ነው። ግን ረፍዷል።

"…እነመከታውን ነግሬአቸው ነበር። የሸዋ ተወላጅ ግማሽ ሚልዮን ዶላር የረዷቸው ሰዎችም ነግረዋቸው ነበረ። ከጎንደር ስኳድ ከፖለቲካው ቅማንት ከትግሬ ዲቃሎች ጋር ያላችሁን ግኑኝነትም አቁሙ ተብለው ነበረ። እስክንድርን ከመካከላችሁ አውጡት፣ ወይም በእናንተ ስር ገብቶ ይታገል፣ ሸዋ ተቀምጦ፣ በመከታው ጀሌ እየተጠበቀ፣ በሸዋ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ እያለ እንደ ኢንኪዩቤተር የፖለቲካ ጫጩት፣ ያውም የማያድጉ፣ ካካቸው የበዛ የፖለቲካ ድርጅት አይፈልፍል ቢባሉም አልሰሙም። ምክር ናቁ። በሽምግልናው ወቅት እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስን ነበር። እነ ደሳለኝ የወከሉት ደግሞ ዶር አብደላን ነበር። እነ ዶር አብደላ የጠየቁት አንዲት ጥያቄ ብቻ ነበር። እነ መከታው የወሰዱብንን አንዲት የግላችን ንብረት መልሱልን። እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስ ግን ስለዚህ ነገር የማውቀው ነገር የለም። እነ አሰግድ በእኛ ስር ከገቡ ይግቡ፣ ካልገቡ ግን አንለማመጣቸውም። እነሱን ለመደመስስ ግማሽ ሰዓት አይፈጅብንም ነበር ያለኝ። በሁለቱም በኩል መሬት ላይ የተመደቡትን ሽማግሌዎች ይሄ የእነ መከታው ፓስተር ነው አፈር ከደቼ ያበላው እና በትእቢት ነገርየውን እንዳይሆን ያደረገው። አሁን እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም የሸዋ ፖለቲካ የእነ መከታው ደጋፊ ሆነው ሲመጡ ነጥቦቹን ስገጣጥም ያገኘሁት ሥዕል የሚያሳየኝ የሸዋ፣ የእነ መከታው ትግል በብልፅግና ወንጌል ፓስተሮች ጭምር መጠለፉን ነው።

"…የሆነው ሆኖ የዐማራ ትግል የግዱን እየጠራ ይመጣል። በረሀ ወርጃለሁ ብሎ ጺምን ኦ እየተቆረጡ፣ ሁሌ ሥጋ፣ ሁሌ ፍየል እየበሉ፣ ስቴኪኒ ይዘው እየዞሩ፣ ሚስቶቻቸውን እና ገርል ፍሬንዶቻቸውን አቅፈው እየተኙ፣ አንዲት ከተማ ሳያስለቅቁ፣ የገበሬ ከብትና ፍየል፣ ሙክት ብግ ዳያስጶራ ደም ተፍቶ የሚልከውን በሸነና እያሉበት መቀጠል አይቻልም። እንደ ላስታ፣ እንደ የዐማራ ፋኖ በወሎ ልጆች ያለ ውጭ እርዳታ ሙጫና በለስ፣ አጋምና ቀጋ እየበሉ በመታገል ጠላትን ድል ማድረግ ይቻላል። እንደነመከታው እና እስክንድር ገጠር ተቀምጦ በዐማራ ፋኖ ትግል ቦርጭን አንዘርጥጦ ጽድት ብሎ መንገማሸር ፌር አይደለም። ሊወገዝ ይገባል። የህልውና ትግል ያለበት ፋኖ ዶላር ሲቀርበት ዋይዋይ አይልም። ፋኖነትን ለኑሮ ማሸነፊያ ማድረግ ስህተት ነው። ትልቅ ጥፋትም ነው። ደያስጶራው በዚህ በኩል ስሜታዊ፣ ደንታቢስ ሆኖ ሳይሆን መርምሮ፣ አጥንቶ፣ በዐማራ የፋኖ ትግል ውስጥ በተጨባጭ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚጨበጥ ትግል በማድረግ ላይ ያሉትን ፋኖዎች ለይቶ በማውጣት እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት። የሸዋ ተወላጅ የዐማራ ዳያስጶራዎች ያደረጉትም ይሄንኑ ነው። እነመከታውን ይረዱ፣ ይደገፉ ነበር። እነመከታው ጠገቡ፣ ወበሩ፣ የእስክንድርን ሚልዮን ብር ሊቀራመቱ ምራቃቸውን ዋጡ። ስለዚህ ቋሚ ደጋፊዎቻቸውን አሳዘኑ። የሸዋ ተወላጆችም እነመከታው ትእቢታቸው ጣሪያ ሲነካ ሽፍት አደረጉ። ወደ እነ ደሳለኝ ፊታቸውን አዞሩ። ወደከሰም፣ ወደ ቡልጋ ፊታቸውን አዞሩ። አሁን የእስክንድር የለመንለት ዶላር ሲጠር እነመከታው ኪሳቸው ባዶ ሲሆን፣ ሲራቆት፣ እነ ፓስተር ምስጋናውም ዱዲ ሳንቲም እንደማይሰጧቸው ሲያውቁ በየሚዲያው ወጥተው ከዘመነ ካሤ ጋር ልንታረቅ ነው። ከነ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ ልንሆን ነው፣ ከእነ ደሳለኝ ጋር ልንተቃቀፍ፣ ልንሳሳም ነው… ብላ ብላ…  ፓስተር ዮናስን ምን አልኩት። ታያለህ ዮኒዬ ኃይል የእግዚአብሔር ነው። እንዲህ እንደታበያችሁ ቀን መጥቶ ዘጭ ብላችሁ አፈር ደቼ ባትግጡ ምናለ ዘመዴ በለኝ ብዬ ነው እቅጩን የነገርኩት። የሆነውም የተናገርኩት ነው። ትእቢት እንዲህ ብርድ ብሎ ሲታይ ደስስ ሲል።

"…ከዚህ ሁሉ በኋላ በዛሬው ዕለት የእነ መከታው ቡድን በሸዋሮቢት ከመከላከያ ጋር እየተዋደቀ መሆኑን ይፋ አድርጎ በእነ መዓዛ መሀመድ ሮሀ ሚዲያ ሲዘገብ ታይቷል። በአካባቢው ምንድነው የሆነው? የእነ መከታው ጦር መከላከያ ላይ ለምን ተኮሳችሁ እያለ ፋኖዎችን የሚቀጣው ቡድን እንዴት ደፍሮ ተዋጋ ብዬ ወደ አከባቢው ደውዬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ የሚያሳየው እነመከታው እንዳልተዋጉ፣ ወደ መጨረሻው አካባቢ ሕዝቡ አስገድዶ ዲሽቃ እንዲሰጥ እንዳስደረገና፣ ቅር እያለው ዲሽቃ ይዞ የእነ መከታው ቡድን ወደ ስፍራው እንደሄደ ነው የተነገረው። የጦርነቱም መነሻ በአካባቢው ያለ የመከላከያ ኃይል በሸዋሮቢት ዙሪ ዝም ብሎ በዘፈቀደ የተኮሰው መድፍ አንድ ደገኛ የዐማራ ገበሬ ይገድላል። በሁኔታው የተበሳጨው የሸዋ ሮቢት ዙሪያ ገበሬ መከላከያን ባለው መሳሪያ ይገጥመዋል። ከዚያም መከላከያው ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ይገጥመዋል። መከላከያው ተረፈረፈ። ከዳር ቁጭ ብሎ የሚያየውም የመከታው ጦር በአስቸኳይ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ገበሬው አቀረበ። ሳይወዱ በግዳቸው ዲሽቃ ይዘው መጥተዋል። የሆነው ይሄው ነው ብለዋል የአካባቢው የመረጃ ምንጮቼ። …👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም እባርካለሁ። በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም። መዝ 145፥

"…እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ። 2ኛ ሳሙ 22፥ 2-4 “…ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” 2ኛ ቆሮ 9፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ በወልቃይ ጉዳይ ትንሽም እንኳን ቢሆን ይተነፍሳል ብዬ በየቤታቸው ብዘር ባፈጥ፣ ብሽከረከር፣ ምንም ወፍ የለም። ምንም አልኳችሁ። 😂

"…አያሌው ቀይ መስመር ቤት ገባሁ፣ የአሸቦ ዕቃው ሲሳይ አልታሰብ ቤት ገባሁ። ጭራሽ ትንፍሽ አይልም። ሙላት አድኖ የፈራ ይመለስ ሰፈር ሄድኩኝ ኧረ ምንም። ሚስተር ባናና ኢትዮጵያ ገብቶ ሰሞኑን ጭራሽ መቀሌ ነበር አሉ። ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ቤት ብገባ ጸሎትም፣ መዝሙርም የለም። በልሣን እንኳ አይናገረም። ምን ጉድ ነው?

"…አስፋው አብርሃና ርስተይ ተስፋይ ብቻ ናቸው ትንሽም ብትሆን ተጋግዘው ጫር ጫር ያደረጉት። ሙሉዓለም ገረመድህን ዝም፣ ጭጭ፣ ሰለሞን ቦጋለ (ሃውልቲ) ራሱ ዝም። እነ ፈትሊም ትዊተር ስፔስ ላይ ጭጭ ምን አስበው ነው ግን…?

"…ስኳድ የትግሬው ዲቃላ ጎጃምን ሲረግም፣ ዘመነ ካሤን ሲሳደብ፣ ሸዋ ገብቶ አሰግድ ሲያሳድድ፣ ወሎ ምሬ ላይ ሲያሟርት፣ ደቡብ ጎንደር ፍሮፌሰር ልኮ ባንክ ሲያዘርፍ ይውላል። የአዜብ መስፍን ዘመዶች አቢይ አሕመድ ሮጲላና ሂሊኮፍቶር ልኮ ወልቃይት አስገብቷቸዋል።

"…ከናዝሬት አዳማ የብልፅግና ሥልጠና መልስ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከህመሙ ጋር እየታገለ ሥራውን እየሠራ ነው። እኔ ደግሞ ምን አግብቶኝ ነው የምቀበጣጥረው። ስኳዶች ግን ተንፍሱ እንጂ። ያልገባን ነገር ካለም አስረዱን እንጂ። የምን ዝም፣ ጭጭ ነው? ሃኣ…?

"…ጠበቃ አስረስ ከወያኔ ጋር ይሠራል ብለው ዋይ ዋይ ሲሉ የነበሩት ሁሉ እኮ ናቸው ድራሽ አባታቸው የጠፋው። አይ ወልቃይት…

• ርስተይ ግን ያቀንአለኪ…!😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ይሄን 17 ሺ ሰው አንብቦት 9 ፍሬ ሰዎች ብቻ 😡 ብው ብለው የበሰጩበትን ርእሰ አንቀጽ ሳምንታዊው የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መርሀ ግብራችን እስኪጀምር ድረስ እናንተ ደግሞ ሓሳባችሁን በድፍረት፣ በእውቀት ማንሸራሸር ትችላላችሁ።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ናቸው። ይሄን የዋህ አይሉት ሞኝ ዐማራ ነው እንግዲህ እኔ ዘመዴ እንደ ፈረንጅ ላም ከመታለብ ያዳንኩት። አበበ በለው ድብን ያለ ፀረ ዐማራ ቅማንቴ ነው ሲባልም ሰምቻለሁ። እነ ምስጋናው አንዷለምን አይታችኋል። በረደድ ብሎ የዐማራ ገንዘብ ያዥ፣ ዋቅጅራ ብሎ የዐማራ ገንዘብ አሰባሳቢ እግዚአብሔር ያሳያችሁ። ደፍረህ ካልተናገርክ ያልቅልሃል ዐማራ። መጀመሪያ ተብትቦ የያዘህን መርገምት ከላይህ ላይ አራግፍ፣ በጣጥሰህም አስወግድ፣ ከላይህ ላይ አውርድ። ዓይንህን ግለጥ፣ አስብ፣ አሰላስል። ጨዋታው የዘር ከሆነ በዘርህ ተጫወት። ዘርህን ከፊት አሰልፍ። ስንቅና ትጥቅ ለትግሬ ሰጥተህ ስንቅና ትጥቅ አልደረሰኝም ብለህ አታለቃቅስ። ዋነኛውን የደም ስርህ ላይ ነው እስክንድርና አምሳሉ የቆሙት። ለዚህ ነው ከገንዘብ ያዥነቱ ቦታ አምሳሉ ቢሞት የማይነሣው።

"…የትግሬዎቹ ባሎች አምሳሉና እስክንድር መጀመሪያውኑ አዲስ አበቤ የሚል የሌለ ማንነት ፈጥረው በዋነኝነት የሸዋ ዐማሮችን ሲያዳክሙ እና ሲያወዛግቡ ነበር የከረሙት። አዲስ አበቤነት የሚባል ማንነት የለም። ልክ ባህርዳሬነት፣ ደሴነት፣ መቀሌነት፣ ሃዋሴነት፣ ናዝሬቴነት፣ ወዘተ የሚባል እንደሌለው) ማለት ነው። ሰኔ 15 እኮ እስክንድር በአዲስ አበባ ጉዳይ ባሕርዳር ሰልፍ ጠርቶም እኮ ነበር። ተመልከት። እስክንድር ከነ ጀሌዎቹ የአዲስ አበባ ጉዳይ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሸዋ ዐማሮች ይልቅ ወደ ባህር ዳር በተደጋጋሚ በመሄድ የአዲስ አበባን ጉዳይ እወያያለሁ ሲል ነበር። በወቅቱ ከአብን መቋቋም እና የዐማራ ብሔርተኝነት መጋጋል ጋር ባህርዳር የስበት ማእከል ነበር። እስክንድር የአዲስ አበባ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የሸዋ ዐማሮችን አነጋግሮ አያውቅም። ወደ ሸዋ ከተሞች (ደብረብርሃን፣ አጣየ፣ ምንጃር…) በጭራሽ አልሄደም። ከትግራይ ጦርነት በኋላ ከእስር ሲፈታ ግን ሂዷል፤ የዛኔ ደግሞ ፋኖ ተደራጅቶ ነበር። ፋኖ ከተደራጀና እሱም ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ግን  እስክንድር ለአዲስ አበባ ቀረብ ካሉት የሸዋ ከተሞች ከጎጃም እና ሸዋ በቀር ጎንደር ወይም ወሎ በፍጹም መሆን አይፈልግም። ለምን…? ሸዋን ለማፈን፣ ሸዋን አንቆ እንዳይላወስ ለማድረግ፣ ሸዋን ለመከፋፈል ነው። በሸዋ እኮ የመከታው ጦር ዋነኛው የጦር መሪ ትውልደ ጎንደሬ ነው። አሁን ያሉት አብዛኛው የአየር ላይ ጎንደሬዎች ደግሞ እንደምታዩት የእስክንድር ደጋፊ ሆነው ነው የተከሰቱት። በመከታው ጋር ብቻ ሳይሆን የመከታው የጦር አዛዥ ወንድሙ የእነ ደሳለኝ ጦር ጋርም ባለሥልጣን ነው አሉኝ። ዓሣ ስጎረጉር ያወጣሁት ዘንዶ ነው። ለምንድነው የትግሬ ባሎቹ ጎንደሬዎች ሸዋ ላይ የሰፈሩት? እኔ እጠይቃለሁ። እናንተም መልሱ። ሸዋ እየደቀቀ ነው። ሸዋ እየወደመ ነው። የሸዋ ገበሬ በአደባባይ በጥይት እየተረሸነ ነው። የሸዋ ፋኖን የሚመሩቱ ደግሞ የትግሬ ባሎች አብዛኛው ከደቡብ ጎንደር የሚመዘዙቱ ናቸው። እስቲ የጣና ቲቪ ስኳድ ዘገባን ተመልከቱ ፎከስ አድርገው የሚንቀሳቀሱት ደቡብ ጎንደርና ሸዋ ላይ ነው። የሸዋ ሰው ጎንደር ሄዶ የሚመራው ፋኖ የለም። ደቡብ ጎንደሬው እስክንድር አሰግድን ከሸዋ አዋክቦ ለኦህዴድ እንዴት እንደሰጠው ተመልከቱ። የሸዋ ዐማሮች ዶላራቸውን ለመከታው ነበር የሚልኩት። የሸዋ ፋኖን ከሚረዱት በሸዋዬነት ከተደራጁት ውስጥ በሚገርም ሁኔታ ጎንደር ያገቡ፣ ከጎንደር የተወለዱ ናቸው። አጋጣሚ አይመስለኝም። እስክንድር ነጋ የሚጠበቀው ከሸዋ ዐማሮች ለመከታው በሚላክ ዶላር ነበር። ተመልከቱ እንዴት ሸዋን ተብትበው እንደያዙት። ወያኔም ሸዋን ነበር ያደቀቀችው። ብአዴንም ከሸዋ ወደ ሥልጣን ያመጣው የለም። አሁንም ገና ፋኖ ማሸነፉ ሳይረጋገጥ ሸዋ ላይ የሚሠራው ሴራ ቀላል አይደለም። ለትግሬ ስስ ልብ ያላቸው እነ አኪላ እንኳን ሸዋን እንዴት እንዳመሱት አይታችኋል። ተመልክታችኋል።

"…እስክንድር ነጋን የምነቅፈው እሱ መስርቶት ከዳር ያደረሰው አንዳችም ድርጅት ስለሌለም ጭምር ነው። አብይ አህመድ ሥልጣን ከያዘ በኋላ እንኳ እስክንድር አቋቁሞ ከግብ ያላደረሳቸው እንመልከት። ሰናይ ሚዲያ ወፍ የለም። ባላደራው ምክርቤት የለም። ባልደራስ የለም። አብይ ቤተመንግሥት በራፍ ላይ የሰቀለውን ፒኮክ አስነሳለሁ ብሎ እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር ወፍ።  አብይን በጆኖሳይድ እከሳለሁ ብሎ እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር ወፍ። ሕዝባዊ ግንባር ሚልዮን ዶላሮችን ከትግሬ ሚስቱ እህት ባል ከአምሳሉ ጋር ሆኖ እምጷ ቀሊጦ። ሕዝባዊ ሠራዊት እሱ ላይ ነው እኔ ጣልቃ ገብቼ የገንዘብ መፍሰሻ ቱቦውን ጠርቅሜ የዘጋሁት። ሕዝባዊ ድርጅት አሁን የፈጠረው ነው። ምኒሊክ ቲቪ ወፍ የለም። አሁን ደግሞ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ የእነ ፓስተር ምስጋናው ጣና ቲቪ። የጣና ቲቪም የተመዘገበው በዶር አምሳሉ ነው። አይገርምላችሁም?
 
"…እስክንድር አቋቋምኩት ያለውን ባልደራስን የለቀቀበት መንገድ በጣም አሳፋሪ ነው።  ያሳፍራል። ሓላፊነቱን በሥርዓት ሳያስረክብ፣ ኦዲት ሳያስደርግ፣ ብጣሽ ወረቀት መልዕክት ልኮ ነው ከድርጅቱ የወጣው። የቤት ሠራተኞች እንኳን ከቤት ሲሰናበቱ በክብር ነው ሚወጡት። ከዚህ በፊት እየጀመረ ያላሳካቸው፣ መሥርቶ ያፈረሳቸው ተቋማትን በሚመለከት በተቋማቱ ስም ስለሰብሰበው ገንዘብ ተጥይቆ አያውቅም። እስከ አሁንም "ታላቁ፣ ብረቱ" በሚሉ መሸፈኛዎች ተከልሎ አልተጋለጠም ነበር። የአሁኑን ጉዳይ ለየት ሚያድርገው ግን ጉዳዩ የሕዝብ ህልውና ጉዳይ ስለሆነ ነው። የሰው ሕይወት የሚጠፋበት ትግል ስለሆነ ነው ጠንከር ያለ ጥያቄ የተነሣበት። እንደሌላ ጊዜው አድበስብሶ ታላቁ እስኬው በሚል ዳንኪራ አይታለፍም። ትፋት… ቱ… አድርጋት። የደም ነጋዴ ሁላ።

"…እስክንድር በተለያየ ጊዜ ከሕዝብ የሰበሰበውን ዶላር ማስተዳደር ካልቻለ እንዴት ነው በለስ ቀንቶት እንኳ ሀገር ምራ ቢባል ለሀገር በጀት ሚታመነው? እስክንድር ከሕዝብ እና ከደጋፊዎቹን ጭምር ለሚነሱበት ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ ካልሰጠ ነገ ሥልጣን ላይ ሲወጣ የሕዝብን ጥያቄ እንዴት ነው ሚያስተናግደው? 
ይሄ ብቻ አይደለም እስክንድር ነጋ የሾማቸው ውጭ ያሉ የሠራዊቱ ሰዎች ይህ ሁሉ ውዝግብ ሲነሳ አንድም ቀን ወጥተው ማብራርያ፣ ማስተባበያ ሰጥተው አያውቁም። ዶ/ር አምሳሉ የሚባለው ሰውየ ወንድሙ የብልጽግና ብአዴን የዐማራን ሕዝብ በድሮን የሚያስጨፈጭፍ፣ ፋኖን ገዳይ አስገዳይ ሁኖ ሳለ ወንድሙ እንዴት ነው የፋኖ ተወካይ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሚሆነው?
 
"…በዐማራ ክልል የተወለዱት ዐማሮች የጦርነቱ ቀጥታ ገፈት ቀማሾች ናቸው። የእስክንድር ደጋፊዎች ግን ትግሉን የአዲስ አበባ ልጅ ካልመራው ሌላው ጎጠኛ ነው ይላሉ። ሲጀምር ትግሉ የብሔር የጎጥ ነው። ሲቀጥል እስክንድር እራሱ በጎጥ ስለሚያምን ነው ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል ከርሞ አሁን በመጨረሻ ዐማራ ነኝ ከዚያም ወርዶ እናቴ ጎጃም፣ አባቴ ጎንደር ሲል የነበረው። አሁን ደግሞ ሸዋ ሲሄድ…👇③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

👆④ ከላይኛው የቀጠ…✍✍✍ …አዲስ አበባ ነው የተወለድኩት፣ አዲስ አበባ ደግሞ ሸዋ ነው የሚል ጨዋታ ያመጣው። ከዚያ ሲያልፍ ግን እስክንድር እና ደጋፊዎቹ ከፈለጉ ሥራ ያልተሠራባቸው የአዲስ አበባ፣ የናዝሬት፣ የሐረር፣ የሃዋሳ ሕዝብን/ፋኖዎችን ማደራጀት ይችላሉ እንጂ ሌላው የሠራውን ሥራ መንጠቅ ነውር ነው። የክልሉ የፋኖ እንቅስቃሴ ባለቤት አለው። ባለቤቱ አደሲ አበቤ ነኝ የሚለው እስክንድር አይደለም። እነ ጃል ሀብታሙ በሻህ እስክንድር ጎጠኛ፣ ዘረኛ ስላልሆነ እስክንድር ካልመራው ሞተን እንገኛለን የሚሉት፣

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ከዘመነ መፈታት በኋላ በጎጃም ችግርም ዕድልም ተፈጠረ። ሁለት ቦታ ተከፍሎ የነበረው የጎጃም ዐማራ ፋኖ ወደ አንድነት መጣ። በዝናቡ እና በዘመነ ይመሩ የነበሩ አደረጃጀቶችም ወደ አንድነት መጡ። እስክንድር በዝናቡ ላይ ኢንቨስት አድርጎ የነበረ ቢሆንም ጎጃሜዎቹ ተፋጭተው አንድ ሆኑ። ይሄ አንድነት ለእስክንድር ነጋና ለቡድኑ አልተዋጠለትም። ስለዚህ ትግል አቋርጦ የራሱን ኑሮ ይኖር የነበረን ማስረሻ ሰጤ የተባለን የእነ ዘመነን ጓደኛ ገንጥለው አመጡ። ኮሎኔል ጌታሁንንም የራሱ አደረገ። ጎጃም ግን ሁለቱንም ወደ መስመር ግቡ ብሎ አዘዘ። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ ብሎ ዐወጀ። ኮሎኔሉ ተዋግቶ ተሸነፈ። ማስረሻ ወደ ወሎ ፈረጠጠ። ጎጃም ብቻውን ወጥ አቋም ይዞ አመለጠ። የጎጃም ሲከሽፍ ጎንደርን ሦስት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ ከፈለ ታናሹ እስክንድር። የኦሮሙማው አገዛዝ ሊያደርግ የማይችለውን ነገር ነው እስክንድር ያሳካው። ፋኖ መሃል ሽብልቅ በመክተት፣ ፋኖ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን በማድረግ፣ ፋኖ ተዋጊ ኃይል ነው። ፖለቲካውን ይዘን ሥልጣን መያዝ ያለብን እኛ ጋዜጠኞቹ ነን በማለት የዐማራ ፋኖን አመሰው። ዳያስጶራው ባዋጣው ዶላር እስክንድር ነጋ ከፋፍሎት ቁጭ አደረገው።

"…ይቀጥላል… በማለት ነበር ትናንት ርእሰ አንቀጻችንን በይደር ያቆየነው። ዛሬ ካቆምንበት እንቀጥላለን።

"…እስክንድር ነጋ በሚኒሊክ ጋዜጣ ላይ ዐማራ ታሪኩን ያድሳል የምትል ለተወሰነ ጊዜ በጋዜጣው ላይ እንደ መፈክር ሆና ብልጭ ብላ ድርግም ካለች መፈከር በቀር ዕድሜ ዘመኑን የዐማራ ችግር አሳስቦት ለዐማራ ሕዝብ በዐማራ ስም ለመታገል የቆረጠ፣ የወሰነ ሰው አልነበረም። እስክንድር የፋኖ አደረጃጀት ጎምርቶ፣ አብቦ፣ ፍሬ ማፍራት ሲጀምር ነው ከኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ አፈንግጦ ወጥቶ ጭልጥ ብሎ ወደ ዐማራ ፋኖ ትግል የገባው። እስክንድር ሾተላይ ሆኖ የፋኖን ትግል ለማጨንገፍ የተላከ ሀሳዊ መሲህ ነው። እስክንድር ሲተች የሚያብዱት፣ የሚቆጡት፣ የሚንጨረጨሩት፣ ለሀጫቸውን የሚያዝረበርቡት እነማናቸው? እስቲ ተመልከቷቸው? ልብ ብላችሁ መርምሯቸው። እስክንድር ሲተች እንደ እብድ የሚያረጋቸው ግማሽ ዐማራዊ ደም ያላቸው፣ ሙሉ ዐማራ ሆነው እስከ አሁን ድረስ ግን ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ የሚሉ የዘግምተኛ አእምሮ ባለቤቶች ናቸው። የግንቦት ሰባት የጉራጌ ተወላጆች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ናቸው። አንድ እስክንድርን የሚደግፍ ሰው ካለ ዘሩን መርምረው። መልሱን ታገኘዋለህ። ከጎንደር እስክንድርን የሚደግፈው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው፣ ከጎጃም የአገው ሸንጎው፣ ከወሎ የትግሬ ዲቃላውና የኦሮሞ ዲቃላው፣ ከሸዋም እንደዚያው። እነዚህ ሁሉ በሙሉ ዐማራነት የሌላቸው የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ናቸው።

"…እስክንድር ከመጀመሪያው የሚስት ምርጫው ጀምሮ እስከ አሁን እስከ ዐማራ ፋኖ ብጥበጣው ድረስ በኮሚቴነት፣ በገንዘብ ያዥነት የሚሰበስበው ማንን ነው? ብላችሁ ብትጠይቁ መልሱን ታገኛላችሁ። ባለፈው እነ ሀብታሙ አውሮጳን ብር ለመጋጥ የገንዘብ አጠባ መርሀ ግብር ባዘጋጁ ጊዜ በየ አውሮጳ ከተሞቹ በሙሉ ሰብሳቢ ሆነው እነ ሀብታሙን ለመቀበል አሰፍስፈው የነበሩት እነማን ናቸው? እኔ አይሆንም፣ ይሄ አካሄድ ዐማራን መዝረፊያ ነው ብዬ እንቅፋት ስሆን ስልክ አንሥተው ዘመዴ ለምን ሳንካ ትሆናለህ ብለው የሞገቱኝ ኮሚቴዎች በአብዛኛው "የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማ፣ የቅንጅት የአውሮጳ ሰብሳቢ የነበሩቱ ናቸው። ከስዊድን የደወለልኝ እና ረጅም ሰዓት የሞገተኝ አቶ ጌራ ግንቦት ሰባት የነበረ ሰው ነው። መሬት ላይ የእነ ጋሽ አሰግድ ደጋፊ ነኝ አለኝ። አየር ላይ ግን ሀብታሙ አያሌውን ጠርቶ ዐማራን በስዊድን ያሉ ዐማሮችን ሊያዘርፍ የሚደክም ሰው ነበር። አቶ ጌራ እስክንድርን በአፉ አልደግፍም እያለ ነገር ግን ለአቶ እስክንድር ድርጅት ገንዘብ ሕዝቡ እንዲሰጥ ይወተውታል። ሕዝብ ሾርት ሚሞሪያም ተብሎ ስለተናቀ ምንም አይባነንም ብለው ነበር ይዳክሩ የነበረው። የአቶ አሰግድ ደጋፊ ነኝ እያለ አቶ አሰግድን በቁሙ ሙልጩን አውጥቶ የተሳደበውን ሀብታሙ አፍራሳን ስዊድን ድረስ ጠርቶ ዐማራን ሊያዘርፍ ይዳክራል።

"…የዐማራ ልጆች በጀርመን በፓርክ በመናፈሻ ውስጥ ተሰባስበው የዐማራ ማኅበር ይመሰርታሉ። ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው ማኅበሩን ፎርማል ለማድረግ ስብሰባ ይጠራሉ። የስብሰባው ቀን ብዙ ሰው መጣ። መሥራቾቹም ምርጫውን ቅቡል ለማድረግ ሰው እንምረጥ ብለው ምርጫው ይጀመራል። ወዲያው መጡኣ እነ አጅሬ፣ እነ ስም አይጠሬ፣ እነ ሾተላይ፣ ጥንብ ባለበት እንደማይጠፋ ጆፌ ዐሞራ ተሰብስበው፣ ተደራጅተው፣ ኔትወርክ ዘርግተው መጡ። ወዲያው ሰብሳቢው ግንቦቴ፣ ገንዘብ ያዥ ግንቦቴ፣ ፀሐፊው ግንቦቴ ሆኑ። የዐማራ ልጆች ይሄማ አይሆንም ብለው ሓሳብ አቀረቡ። ወረዱባቸው። በገዛ ዳቦአቸው ልብልቡን አጡት። በሠርጋቸው ላይ ሌሎች ተዳሩበት። ያ የዐማራ ማኅበር የግንባሩ ድጋፍ ሰጪ ነው ተብሎ ታወጀ። በቁማቸው ተዘረፉ። ተጠለፉ። ሴቶቹም፣ ወንዶቹም አልቅሰው፣ ተሰድበው፣ ተዋርደው አንገታቸውን ደፍተው ወጡ። ይሄ የሆነው እዚሁ ጀርመን እኔ በምኖርበት ሀገር ነው። እስቲ በየምትኖሩበት ሀገር አሁን የዐማራ ትግል መሪዎች ነን የሚሉትን ግለሰቦች የኋላ ታሪክ መርምሩ። በአብዛኛው ግንቦቴ ነው። እንዲያም ሆነው ፍጹም መለወጥን ተለውጠው ዘአማራ ሆነው ያገኘኋቸው እነ ወርቁን ነው። ለንደን ፋኖ።

"…የዐማራን ትግል ለማጨናገፍ እነዚህ ኃይላት ብቻ አይደሉም የሚዳክሩት። ኃያላኑ ሀገራትም በከፍተኛ በጀት ነው የሚደክሙት። ዐማራው ፍጹም ዐማራ ሆኖ ከመጣ ለኢትዮጵያ ያሰቡት ክፋትና ርኩሰት በሙሉ እንደሚጨነግፍባቸው ስለሚያውቁ አይተኙም። ዐማራው ከመጣ የትምህርት ፖሊሲው ላይ፣ ሃይማኖት ላይ፣ የሀገር ፍቅር ላይ፣ አርበኝነት፣ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ይዞት የሚመጣው ሓሳብ አይደለም ባንዳውን ኃያላኑን ሁላ ነው የሚያስጨንቀው። ለዚህ ነው በዐማራ ፋኖ ባለቤትነት ላይ ሽሚያ የበዛው። የዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ስለሆነ እየተነሣ ያለው ለምናልባቱ ፋኖ ካሸነፈም ፋኖ በራሱ መንገድ ሳይሄድ እኛው ቁጥጥር ስር አድርገነው እስክናፈርሰው ድረስ እንያዘው ነው ጨዋታው። ብአዴን በበኩሉ ፋኖ አለው። ትግሬዋ ወያኔም መመኘቷ አልቀረም። ኦሮሙማው ፋኖ ውስጥ አስርጎ ባሰገባቸው ጥቂቶች እሱም እየሞከረ ነው። እንዲህ ዓይነት አጓጊ የሆነ ልብ አንጠልጣይ ኩነት ባለበት ስፍራ ግብፅም፣ ሻአቢያም፣ ሲአይኤና ኤም16፣ የእስራኤሉም፣ የራሺያውም የስለላ መረብ በፋኖ ዙሪያ የለም፣ አይኖርም ማለት አይቻልም። የፈለገ ይሁን ግን ፋኖ ፊትለፊት በሚታዩትም፣ በማይታዩትም ልጆቹ አማካኝነት የጀመረውን ትግል ከዳር ማድረሱ አይቀርም። ድብቁ የፋኖ ሠራዊት ሥራ ላይ ነው። እንቅልፌን ለሽ ብዬ መተኛት የጀመርኩት ያየሁትን ስላየሁ ነው።

"…አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምለው አዲስ የዐማራ ወጣት አደረጃጀት ያስፈልጋል። ሰልፍ የሚመራ፣ ገንዘብ የሚያሰባስብ፣ እርዳታ የሚረዳ የዐማራ የዳያስጶራ ክንፍ ያስፈልጋል። ዲቃላ ያልሆነ። ዐማራነቱ የሚያንገበግበው፣ የሚቆጨው። ያ ሕዝብ የመከራው ቀን ይጠር፣ ስደት ጭፍጨፋው ይብቃው ብሎ የቆረጠ ፍጹም በዐማራነቱ የማይደራደር ትውልድ ያስፈልጋል። የቀደሙቱን ለእስከአሁኑ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ ከእነሱ እጅ መጫወቻ ካርታ፣ ገንዘብ ማለቢያ የሆነውን የዐማራነት ካርድ ፈልቅቆ አውጥቶ በራሱ ቁጥጥር ስር የሆነ፣ ራሱ የሚያዝበት ዐማራዊ የሆነ ድርጅት…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ። ማቴ 10 ፥11

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐማራ ፋኖ በወሎ… የዛሬ ውሎ

"…የብራኑ ጁላ ጦር በተደጋጋሚ በእግረኛ ሠራዊቱ ወደ ቃሊም ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ሠራዊቱን ከማስጨረስና ከማስመራክ በቀር ያገኘው አንዳችም ትርፍ እንደሌለው ያወቀው ሰው በላው መከላከያ ተብዬ በመጨረሻም ወልዲያ ተቀምጦ ወደ ቃሊም ከመድፍ ጀምሮ አለኝ ያለውን ከባድ መሳሪያ ሁሉ ያገኘውን ያግኝ በማለት ፍጹም ከጦርነት ሕግ ባፈነገጠ መልኩ ሕዝቡም ቢሆን ያው ፋኖ ነው በሚል ሒሳብ የመድፍ አረሩን እንደ ዶፍ ዝናብ ሲያዘንበው ውሏል። ይሄንን ተከትሎም።

"…አንድ ሰው ሲሞት በጣም ብዙ ሰዎች ቆስለዋል። እጅግ በጣም ብዙ ከብቶች፣ ፍየሎች እና የተለያዩ እንስሳቶችም ሞተዋል። ብዙ መኖሪያ ቤቶች በከባድ መሳሪያ ተመትተው ፈራርሰዋል። "እስራኤል በጋዛ ፍልስጤም ላይ እንደወሰደችው ዓይነት የማውደም እርምጃ የኦሮሞ ብልጽግናም ውጤቱ ምንም ይሁንምን በእስራኤል መንገድ ሄደን የዐማራን ሕዝብ እንደ ጋዛ ማውደም ነው ያለብን እያሉ ነው ተብሏል። ሕዝቡን እግዚአብሔር ጠብቆት ነው እንጂ እንደዛሬው ውሎ እና እንደ አገዛዙ እሳቤ የቃሊምን ሕዝብ የሚያልቀው ዘሬ ነበር ይላሉ ሲተኮስ የዋለውን እሳት ሲያዩ የዋሉ የዓይን ምስክሮች።

• በመጨረሻም ከፋኖ ምት ከሞት የተረፉት እና ጥይት የጨረሱት የምርኮኛው የጁላ አረመኔ ሠራዊት እንዲህ እንደከፍት በዐማራ ፋኖ ይነዳል።

"…የቀን ጉዳይ ነው ዐማራ ብቻውን ፈርሶ አይቀርም። መዝግብልኝ። የዐማራ በቀሉ፣ ቂሙ እየጨመረ ነው የመጣው። ሌላው ግን ጥጋብ፣ ትእቢት ላይ ስለሆነ አይታወቀውም። ይሄ ጥጋብ አንድ ቀን ይገለበጣል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ሄደ። በወሎም የወሎ ፋኖዎችን አግኝቶ ገምግሟል። በመጨረሻም ወደ ሸዋ በመምጣት በራሳ የነበሩትን የአሰግድ እና የመከታውን ፋኖ ጎብኝቷል። ገምግሟል። በነገራችን ላይ በወቅቱ አሰግድና መከታው አባትና ልጅ ሆነው አንድላይ ነበሩ።

"…እስክንድር ነጋ በአራቱም የዐማራ ግዛት የነበረውን የዐማራ ፋኖ አደረጃጀት ከገመገመ በኋላ ነው በቀጥታ ወደ አሜሪካ የበረረው። በአሜሪካም ለጥቂት ቀናት ከሚስቱም ጋር፣ በዚያ ካሉት ጓደኞቹም ጋር ሳይገናኝ የት እንደከረመ ሳይታወቅ ብቅ በማለት ከእነዚያው ከግንቦቴዎች ጋር መታየት ጀመረ። ለገጽታ ግንባታም አቶ ሙሉጌታንና አቶ ኤርሚያስን አስከትሎ በኢትዮጵያ ኤንባሲ ፊት ለፊት ለሦስት ሆነው መግለጫ ሰጥተው ሲያበቁ እስኬው በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። እስክንድር አሜሪካ በነበረ ጊዜ የዐማራ ፋኖ ቀድሞ ተደራጅቶ ቦታ ቦታውን በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። እስክንድር አሜሪካ በቆየ ጊዜ ለአሜሪካ መንግሥት የፋኖን አደረጃጀት፣ የሰው ኃይልና አቅም ሪፖርት ሳያቀርብ እንዳልቀረ የሚጠረጥሩ አካላትም አሉ። የአሜሪካ መንግሥትም ለኢትዮጵያው አገዛዝ ለእስክንድር እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር ሳያስገድዱት እንዳልቀረም ነው የሚነገረው። ለዚህ ነው እስክንድር አሜሪካ ሆኖ ለብዙ ሰው ከአሜሪካ እንደተመለሰ ወደ ትጥቅ ትግል እንደሚገባ ሲናገር አይፈራ የነበረው። እስክንድር ጫካ እገባለሁ እያለ እየሰማ አቢይ አሕመድም ምንም ዓይነት እንቅፋት ሳይፈጥርበት የድራማው አካል ሆኖ እስኬው ፈነነ።

"…በእስክንድር ግምገማ መሠረት ጎንደር መቀመጥን አልመረጠም። ሪሶርሱ ደካማ ነው ብሎ ነው የገመገመው። ከኤንባሲም የራቀ ነው። ከአሜሪካም፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲዎች ርቆ መቆየትን አልፈለገም የሚሉም አሉ። ወሎ ቤተ ዐምሓራም አስተማማኝ አልሆነለትም። ጎጃም ጠንካራ ነው። አደረጃጀቱ ያስፈራል። የተማረም ሰው ይበዛበታል። እንደ ሕዝብም ነው የጎጃም እንቅስቃሴ። እናም እስኬው በጎጃም መሆኑንም እንብዛም እንደማያዛልቀው ዐውቋል። ስለዚህ ምርጫው ሸዋ ሆነ። ሸዋ ለአሜሪካና ለእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቅርብ ነው። ሸዋ ላይ የፋኖ አደረጃጀት በወቅቱ እጅግ ደካማ ስለነበር፣ ብዙ የተማረ የሰው ኃይልም የሸዋ ፋኖን በወቅቱ ስላልተቀላቀለ፣ አቶ አሰግድና አቶ መከታውም በጋራ አንድላይ ስለነበሩ፣ የራሳና የይፋት ተኳሽ ፋኖዎች እንጂ ምሑራኑ በሙሉ እንደዛሬው በሸዋ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ ስላልነበር እስክንድር ሸዋን መርጦ ሸዋ ገባ። ሸዋ ከገባ በኋላ ደራሲና ጋዜጠኛ በውትድርናውም ዓለም ኮሎኔል የነበረውን አቶ አሰግድንና ማይሙን መከታውን እርስ በርስ አጋጭቶ አለያየ። አለያይቶም ሸዋን ከሁለት ቦታ ከፍሎ መከታውን ይዞ ተገንጥሎ ሄደ። በዚያውም ከአሜሪካ ማን እንደላከው ባይታወቅም የፋኖን አደረጃጀት ለሁለት መክፈሉን አሀዱ ብሎ በሸዋ ፋኖ ላይ ጀመረ። የሸዋ ፋኖን እንደ አሜባ ከከፈለ በኋላ ወደ ጎጃም እንዲገባ አጋጣሚውን አገዛዙ አመቻቸለት። ዘመነ ካሤ ታሠረ፣ እነ መስከረምም ታሠሩ፣ የጎጃም ፋኖን ብአዴን በታተነው። በዚህ ጊዜ እስክንድር ነጋ ጎጃም ምድር ላይ በሸነና ይል ጀመር። በነፃነት አንዴ ምሥራቅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ምዕራብ ጎጃም ሆኖ ይንሸራሸርበት ጀመር። በአንድ ወገን ጎጃሜ ስለሆነ ሜዳው ተመቸው። አቢይ አሕመድ ዘመነ ካሤን አሥሮ እስክንድርን የ3 ወር የእግር መንገዱን በግማሽ ቀን እያሳጠረለት በጎጃም ምድር እንዲምነሸነሽ አደረገው። እንዲያውም በደንብ ለማጀገን ሲልም ደንበጫ ላይ በቁጥጥር ስር ያዋለውን እስክንድር ነጋን ለመንግሥቱ አሸባሪ የተባለን አደገኛ ሰው እስከ ደጀን ከተማ ድረስ አዙሮት፣ በመላው ጎጃም ብቻ ሳይሆን በመላው ዐማራ ጀግና ጀግና አጫውቶት፣ በብቸና በሞጣ አዙረው ባህርዳር አስገብተው፣ በሕዝብ ትግል እንደተፈታ አስመስለው በመታወቂያ ዋስ ለቀውት ተመለስና ጫካ ገብተህ ውጋኝ ብለውም ለቀቁት። ስንታየሁን በካቴና አስሮ ከባህርዳር አዲስ አበባ በአውሮጵላን ያመጣው አገዛዙ የስንታየሁን አለቃ አጀግኖ መልሶ ወደ ጫካ ላከው። በእውነት በእስክንድር ነጋ ጉዳይ እንደ አቢይ አሕመድ ጻድቅ ከወዴት ይገኛል? እስኬውም ምኑ ሞኝ ነው ወዲያው ጎንደር በመሄድ ከዶር ወንደሰን ጋር በመገናኘት ተመለሰ። ዶ/ር ወንደሰንም ይኸው እስክንድርን አግኝቶት ከተመለሰ በኋላ ከርቸሌ ወረደ። በዚያውም ቀልጦ ቀረ።

"…እስክንድር ነጋ ዘመነ በታሰረበት ጎጃም እንዳሻው ሆነ። ዘመነ ሲፈታ ግን እስክንድር በግማሽ ቀን የእግር ጉዞ በተአምር ሸዋ ገባ ተባለ። እስክንድር ውሎ ያደረበት ቤት እስክንድር ከሄደ በኋላ በድሮን ይመታል። እስክንድርን የሚከተል ባጃጅ ተለይቶ ይመታል። እስክንድር እና መከታው ተሰብስበው ከሕዝብ ጋር የተመካከሩበት አዳራሽ፣ ትምህርት ቤት እስክንድር ዞር ካለ በድሮን ይመታል። ደብረ ኤልያስ የስላሴ ገዳም እስክንድር አለበት ተብሎ እንዴት እንደወደመ የምታውቁት እውነት ነው። አዎ እስክንድር እንዲያ ነው። በጎጃም አብሮት የታሰረው ልጅ ተገድሏል። እስክንድር ግን አለ። በጎጃም ግንባሩን ለእስክንድር ያደራጀው ልጅ ወሎ ስብሰባ ውሎ ሲመለስ ብቻውን በድሮን ተመትቶ ሞቷል። እስክንድር ለዚህ ልጅ ነፍስ ይማር እንኳ አላለም። እስኬው ከደንበጫ ሸዋ ለበረታ መንገደኛ ሁለት ወር፣ ወንዙን ለመሻገርም በጋ ተጠብቆ የሚፈጀውን መንገድ በግማሽ ቀን ሸዋ እየገባ አስደመመን። በአደባባይ መግለጫ እየሰጠ፣ ከራሳ ይፋትም በእግሩ እየተመላለሰ ምንም አይሆን። ይሄ የጸሎቱ ውጤት ነው አይደል?

"…ከዘመነ መፈታት በኋላ በጎጃም ችግርም ዕድልም ተፈጠረ። ሁለት ቦታ ተከፍሎ የነበረው የጎጃም ዐማራ ፋኖ ወደ አንድነት መጣ። በዝናቡ እና በዘመነ ይመሩ የነበሩ አደረጃጀቶችም ወደ አንድነት መጡ። እስክንድር በዝናቡ ላይ ኢንቨስት አድርጎ የነበረ ቢሆንም ጎጃሜዎቹ ተፋጭተው አንድ ሆኑ። ይሄ አንድነት ለእስክንድር ነጋና ለቡድኑ አልተዋጠለትም። ስለዚህ ትግል አቋርጦ የራሱን ኑሮ ይኖር የነበረን ማስረሻ ሰጤ የተባለን የእነ ዘመነን ጓደኛ ገንጥለው አመጡ። ኮሎኔል ጌታሁንንም የራሱ አደረገ። ጎጃም ግን ሁለቱንም ወደ መስመር ግቡ ብሎ አዘዘ። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ ብሎ ዐወጀ። ኮሎኔሉ ተዋግቶ ተሸነፈ። ማስረሻ ወደ ወሎ ፈረጠጠ። ጎጃም ብቻውን ወጥ አቋም ይዞ አመለጠ። የጎጃም ሲከሽፍ ጎንደርን ሦስት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ ከፈለ ታናሹ እስክንድር። የኦሮሙማው አገዛዝ ሊያደርግ የማይችለውን ነገር ነው እስክንድር ያሳካው። ፋኖ መሃል ሽብልቅ በመክተት፣ ፋኖ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን በማድረግ፣ ፋኖ ተዋጊ ኃይል ነው። ፖለቲካውን ይዘን ሥልጣን መያዝ ያለብን እኛ ጋዜጠኞቹ ነን በማለት የዐማራ ፋኖን አመሰው። ዳያስጶራው ባዋጣው ዶላር እስክንድር ነጋ ከፋፍሎት ቁጭ አደረገው።

"…በነገው ዕለት ይቀጥላል…

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸው…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

• ሃሎ…አበበ በለው ነኝ።
~ ሃሎ አቤ ሰላም ነው?
• ሰላም ነኝ እንዴት ናችሁ?
~ አለን፣ አለን እግዚአብሔር ይመስገን አቤ። ምን እንታዘዝ?
• ኧረ ይሄን ነገር እንዴት እያያችሁት ነው?
~ የቱን ነገር አቤ…?
• ይሄ የዘመድኩንን አካሄድ፣ እጅግ አደገኛ አካሄድ እኮ ነው እየሄደ ያለው። ፋኖዎች መሬት ላይ መግለጫ እያወጡበት ነው። ባለፈው ጎንደር አሁን ደግሞ ሸዋ እነ መከታው መግለጫ አውጥተውበታል። በጎጃምም፣ በወሎም እንዲሁ መግለጫ ሊያወጡበት ነው። እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት በዚህ ሰውዬ ላይ ዝምታችን እስከመቼ ነው? በቃ ዝም ብለን እያየነው ያፈራርሰን? ይሄ ለእኛ ትልቅ ውርደት ነው። እናም የእናንተም ማኅበር፣ የሌሎቹም ማኅበራት ሰብሰብ ብለን መግለጫ እናውጣበት። እኛ እንደ MDV በዋ ዐማራ በኩል መግለጫ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነን። እናም አስቡበት። እንወስን። በአቶ ዘመድኩን እና በመረጃ ቴሌቭዥን ላይ አቋም ልንይዝ ይገባል ይልልኛላ አቤ በለው በአንዳንድ የዐማራ ማኅበራት መሪዎች ስልክ ላይ እየደወለ። ይሄ ማለት ራሱ በለኮሰው እሳት ውስጥ ሌሎች እንዲገቡ እና አብረውት እንዲቃጠሉ ፈልጎ እያስጨነቃቸው ነው ማለት ነው። በእኔ በመረጃ ቲቪና፣ በኤልያስ መካከል እንዲገቡና እኔን ከአየር ላይ እንዲያስወርዱ ነው ፍላጎቱ። አበበም ሆነ ሌሎች ያልገባቸው ግን መረጃ ቲቪ የእኔም ላብ የፈሰሰበት፣ የእሁድ ምሽት አየሩ የግሌ የሆነ፣ ኤልያስ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች ጣልቃ የማይገቡብኝ፣ በምሠራው ሥራ ሓላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር አስተባብሬ በመያዝ አስሬ ለክቼ አንዴ የምቆርጥ መሆኑን ነው። ቅሬታ ያለው ወደ ኤልያስ ሳይሆን የቅሬታ ደብዳቤውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ወደ እኔ ነው ማቅረብ ያለበት። ኤልያስ ምንአገባው ስለእኔ ፕሮግራም? እነ አበበ፣ እነ ሀብታሙ መረጃ ቴቪ ላይ በነበሩ ጊዜ ኤልያስ እነሱ በሚሠሩት ፕሮግራም እንደማያገባው ሁሉ እኔም በምሠራው ፕሮግራም አያገባውም። ከምኔው ረሱት ግን?

"…አበበ በለውን ከሌሎች የዐማራ ተወላጆች፣ አክቲቪስቶች፣ አርቲስቶች፣ ኮሜዲያኖች፣ ጋዜጠኞች በተለየ መልኩ እንዲህ ያንገበገበው ምን ቢሆን ነው? የሚል ጠያቂ አይጠፋም። አበበ መሀይም ስለሆነ ነው እንጂ ሌሎቹ ጮጋ ብለው ተኩሱንም፣ ቅዝምዝሙንም ለጥ ብለው ሲያሳልፉ እሱ እንዲህ የሚያንቀዠቅዠው ተንኮሉ ነው። እስከዛሬ በዐማራ ትግልና ታጋዮች ላይ የሠራው ግፍ ነው። አበበ እኔን መጣላት የጀመረው እኔ ግንባሩ የተባለውን የእስክንድር የዶላር ማለቢያ ማሽን ግንባሩን ብዬ እንደ ጎልያድ ካጋደምኩት ጊዜ ጀምሮ ነው። እኔ ዘመዴ በገንባሩ ላይ ጥያቄ ሳነሣም ጥያቄውን የጠየቅኩት የግንባሩን የውጭ አስተባበሪ ሻለቃ ዳዊትን እና የግንባሩ ሊቀመንበር የሆነውን እስክንድር ነጋን ነው። መቼም ትልቅ ሰው ሁልጊዜ ትልቅ ነው። ቀለም የዘለቀው፣ ፊደል የቆጠረ፣ የተማረ ሰው አንዳንዴ ጥሩ ነው፣ የሥራ ልምድ፣ ዕድሜ፣ መሰልጠን ተጨምሮበት እንደ አንድ ግለሰብ ግንባሩን በተመለከተ ላነሣሁት ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ የሰጡኝ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው። እስክንድር ነጋ በጋዜጠኛ ጌጥዬ በኩል ለኤልያስ ክፍሌ ደውሎ ምላሽ እሰጣለሁ ካስባለ በኋላ ትንሽ ሰው ሁሌ ትንሽ ነውና ትንሹ እስክንድር በዚያው እልም ብሎ ጠፍቷል። እኔም ሻለቃ ዳዊትን አመስግኜ፣ እስክንደር ነጋን ግን እሞግተው ዘንድ ወስኜ ጥያቄዎቼን ይዤ ወደፊት ቀጠልኩ።

"…ጭራሽ የሚልዮን ዶላሩ ዶሴ ሳይዘጋ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በለው ወደ አዳራሽ መግቢያ ብቻ የሆነ መቶ ዶላሮች የተቆረጡበት ድል ያለ ዝግጅት በዋሽንግተን ከተማ አዘጋጅተው፣ ያንኑ ላሜ ቦራ የዐማራን ሕዝብ ወደ አዳራሹ ጠርተው የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚልም ማቋቋማቸውን ይፋ አደረጉ። የዚህ ድርጅት መቋቋምን ተከትሎ አሁንም የዚህ ድርጅት መሪ የሆኑት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና በውጪው ዓለም ደግሞ ሻለቃ ዳዊት ናቸው ተብሎ ታወጀ። የገንዘብ ያዡ ደግሞ ያው የማይቀየረው የእስክንድር ካዝና ተብሎ የሚገለፀው ዶር አምሳሉ አስናቀ መሆኑ ተነግሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችም በድጋሚ ያው የፈረደበትን ዐማራን እንደለመዱት ዶላር ሊግጡት ጥርሳቸውን አሹለው፣ ጥፍራቸውንም ሞርደው ተነሡ። እኔም መልሼ ቀላል ጥያቄ ጠየቅኩ። ሲጀመር ግንባሩ መፍሩሱን ሳትነግሩን እንዴት ሠራዊቱ ብላችሁ ተከሰታችሁ? የግምባሩ መሪም ሻለቃ፣ አሁንም የሠራዊቱ መሪ ሻለቃ ይሄ እንዴት ይሆናል? የበፊቱ ገንዘብ ሳይወራረድ፣ ኦዲት ሳይደረግ፣ እንዴት አሁን ደግሞ ሌላ ገንዘብ ትሰበስባላችሁ ብዬ ጥያቄ አቀረብኩ። ለዚህም ጥያቄዬ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ አሁንም ወዲያው ነው ፈጣን ምላሻቸውን የሰጡኝ። "ዘመዴ እኔ በአዲሱ ሠራዊቱ በሚባለው ውስጥ የለሁበትም። እንዲያውም ሠራዊቱ የሚባለው ሲመሠረት አበበ በለው እንዳትመጣ ብሎ ነው የከለከለኝ። ለገቢ ማሰባሰቢያ ብለው ባዘጋጁት ፖስተር ላይ ፎቶዬን መለጠፋቸውም አግባብ አይደለም ብዬ ተቃውሜአለሁ በማለት አሁንም ታላቅነታቸውን በሚያስመሰክር መልኩ ምላሻቸውን ሳይንቁኝ ሰጡኝ። እኔም የሻለቃን ምላሽ ለሕዝብ ይፋ አድርጌ ወደፊት ቀጠልኩ።

"…ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ ወደ ኋላ ሄጄ የእስክንድርን የኋላ ታሪክ ፋይሎች ከመዝገብ ቤት አውጥቼ መመርመር፣ ማገላበጥም ጀመርኩ። ታላቁ ያስባለው ነገር ምንድነው? እስክንድር እስከዛሬ ስንት ድርጅት መስርቶ አፈረሰ? የእስክንድር ስኬት ተብሎ የሚጠቀስ፣ የሚቆጠር ተግባሩ ምንድነው? በማለት ምርመራዬን ጀመርኩ። እናም በምርመራዬ እኔ ብቻ የደረስኩበትን ውጤት አገኘሁ። በውጤቱም፣ በግኝቴም መሠረት ከገንዘብ እና ድርጅት ፈጥሮ ከማፍረስ ጋር በተያያዘ የእስክንድር ነጋን እልል የተባለለት አፍራሽ፣ ሾተላይ፣ የተጨበጨበለት ዘራፊ፣ ሰርተፊኬት ያለው አጭበርባሪ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማሳያዎችን አገኘሁ። እስክንድር ነጋ ግንባሩ ጋር ሲደርስ እኔን ጣልቃ አስገብቶ በይፋ እግዚአብሔር ሰብሮ አጋለጠው እንጂ የኋላ ታሪኩ በሙሉ የሚያሳያው ትኩስ፣ አማላይ የሆነ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማና በኢትዮጵያ ስም የተጠቀለለ አጀንዳ በመፍጠር የዐማራ ዳያስጶራን ሙልጩን ሲያወጣ የኖረ ዘራፊ መሆኑን ደረስኩበት። እስክንድር ለዚህ ዘረፋው ብቻውን ሳይሆን በአሜሪካም የዘረፋው ተባባሪ ወኪሎች እንዳሉትም አረጋገጥኩ። ከእነዚህ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መሃልም ባለቤቱ ወሮ ሠርካለም ፋሲል እና አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ፣ የቅንጅቱ አቶ መስፍን አማን፣ እንዲሁም እነ አቶ ገለታው ዘለቀ እና አቶ ሙልጌታ የማይቀየረው ዶር አምሳሉ አስናቀንም አገኘኋቸው። ከሴቶች ያው ያለችው ሕይወት ናት።

"…በዚህ የገንዘብ ማሰባሰብ የተደራጀ የማፍያ ሥራ ዘረፋ ውስጥ አበበ በለው ከጀርባ ሆኖ በዙም ስብሰባ ወቅት ነጭ ላብ እስኪፈሰው ድረስ ያስተባብር ነበር። ቪድዮውም አለ። ከግንቦት 7 መፍረስና መክሰም በኋላ የዳያስጶራውን ኪስ ለማጠብ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ የተገኘው የአዲስ አበባ ጉዳይ ስለነበረ ለዚህ አጀንዳ ብቁ ነው የተባለው እስክንድር ነጋ መጀመሪያ ባላደራው የሚባል የገንዘብ ማለቢያ ድርጅት መሠረቱ። ቀደም ሲል እስክንድር ዘብጥያ እያለ በእስክንድር ፎቶ ሸቅሎ ገንዘቡን የበሉት ግንቦት 7ቶች ስለነበሩ አሁን ከግንቦት 7 መክሰም በኋላ በግንቦት 7 የዘረፋ ወቅት ከፍተኛ የዘረፋ ልምድ ያላቸው ዘራፊዎች ሙሉ ለሙሉ ተሰብስበው በእስክንድር ነጋ እግር ስር ተኮለኮሉ።…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።” ሉቃ 3፥9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የስብሰባ ጥሪ ነው…❗️

• እኔ ገብቻለሁ፣ እናንተም ግቡ። ገንዘቡን የት አደረሳችሁ ብላችሁ ጥያቄም ጠይቁ።

"…በቦስተን እና አካባቢው ለምትገኙ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አሕፋድ) የእስክንድር ነጋ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ የዐማራው የዘር ጭፍጨፋ ይቁም በሚል ሊካሄድ ስለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ለመወያየት ዛሬ ማክሰኞ 11/12/2024 በ 7:00 PM በዙም ስብሰባ ስለሚኖረን ከታች የተጠቀሰውን የዙም መግቢያ ሊንክ ወይም ስልክ ቁጥር በመጠቀም እንድትገኙሉን ስንል በአክብሮት ጠርተኖታል።

ድል ለፋኖ !
መነሻችን የአማራ ሕልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት !

በስልክ ለመግባት 
Phone Number: 646 558 8656
Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

Amhara Fano is inviting you to a scheduled Zoom meeting.

Topic: Stop Amhara Genocide
Time: Nov 12, 2024 07:00 PM Eastern Time (US and Canada)

Join Zoom Meeting
https://us06web.zoom.us/j/85635534107?pwd=LtpQqcYB5NiBXKo9yaRJhiDny2Ceuz.1

Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

---

One tap mobile
+13052241968,,85635534107#,,,,*039519# US
+13092053325,,85635534107#,,,,*039519# US

---

Dial by your location
* +1 305 224 1968 US
* +1 309 205 3325 US

Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

Find your local number: https://us06web.zoom.us/u/kdUbYSdW1A

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በርእሰ አንቀጻችን ላይ አስተያየት መስጠታችሁ እንደተጠበቀ ነው። ነገር ግን እኔ ደግሞ ተወት አድርጌው የነበረውን የቲክቶክ መንደሬን ሞቅ ለማድረግ፣ በዚያውም ጥቃቅን ቀበሮቹን ድባቅ ለመምታት ስል እንደ ቲክቶክ አንበሳ እያገሳሁ ወደ ቲክቶክ መንደራችን እየመጣሁ ነኝና እናንተም ከያላችሁበት ወደ መንደራችን በመሄድ አበባና ኮፍያ በማያዝ ገባ ገባ ብላችሁ እንደትጠብቁኝ እኔ ፊልድ ማረሻው ዘመዴ አዝዤአችኋለሁ።

• ሰምታችኋል አይደል…?

zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

"…ኣ… ላችሁ…  አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከመጀመሪያው ጀምሮ እስክንድርን ተጠግቶ እንደ አዝማሪ እስክስ እያለ ሆዱን፣ ቀፈቱን ሲሞላ የነበረው ከርሶ አበበ በለው እንዴት ሰርካለም ፋሲል ስሟን ዘመድኩን ያነሣዋል ብሎ ሲበጠረቅ የነበረው። እንዴት ገንዘቡን ሲሰበስቡ እንደነበር በቪድዮ ይዤ እቀርባለሁ።

"…አሁን የዐማራ የወይን እርሻ አብቧል። አጥሩም ጠባብቆ ስለታጠረ፣ በእሾህም፣ በጋሬጣም ስለታጠረ ወፋፍራሞቹም ጥቃቅኖቹም ቀበሮዎች መግባት አልቻሉም። ኢትዮ 360፣ አዲስ ድምጽ፣ ጣና ቲቪ የሚባለው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ቡድንም እንደፈለገ ቢዘበዝብ ወፍ የለም። ዐማራው አጥሩን አጠባብቆ ማጠር ጀምሯል። ዐማራ ለዐማራ ብቻ። ዐማራን መምራት ያለበት ዐማራው ብቻ። ከዚህ ቀደም በአንድም በሌላም መልኩ በኢትዮጵያም፣ በዐማራም ስም ኪስ የማውለቅ፣ የዐማራን ካዝና የማራቆት ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ቀበሮች በምንም ዓይነት መልኩ አሁን በዐማራው የደረሰ የወይን እርሻ ውስጥ በምንም መንገድ መግባት የለባቸውም። በምንም መልኩ አልኳችሁ። አትፍቀዱ። እናንተ ብትፈቅዱ እንኳ እኔ ለኅሊናዬ ሥር ቀበሮቹን እዋጋቸዋለሁ። አልምራቸውም።

"…ያለ ታማኝ በየነ፣ ያለ ግንቦቴው፣ ያለ ባልደራሱ፣ ያለ ግምባሩ የሰልፍ አስተባባሪነት ይኸው እኮ ዓለም አቀፍ የዐማራ ሰልፍ ማዘጋጀት ተችሏል። ክብር ለለንደኖች፣ ለዋሽንግተን፣ ለሲያትል ዐማሮች፣ ክብር ለፍራንክፈርት፣ ለደቡብ አፍሪቃ ዐማሮች ይኸው አሳዩ እኮ። አዲስ ሰው፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ አደረጃጀት ነው የሚያስፈልገው። የመርዝ ብልቃጦቹን አርቆ ማስቀመጥ ነው። ደቡብ አፍሪካ የእኔ ወንድም ደጉ ነው 600 ኪሎሜትር እየነዳ ባስ ሙሉ ዐማራ እስከ ፕሪቶሪያ ድረስ ይዞ ለሰልፉ የደረሰው። የዲሲው ሰልፍ በእነ መንጌ፣ በእነ ሰሌ የተመራ ነው። የለንደኑ፣ በእነ ወርቁ፣ በእነ አዲስ፣ የተመራ ነው። የፍራንክፈርቱም እንደዚሁ በአዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳ የተዘጋጀ ወይን ነው። አሮጌው አቁማዳ አዲሱን አቁማዳ ሊሸከመው አይችልም። ጥፋ በለው።

"…ቀበሮዎቹ አሁን ሌላ ዘዴ አምጥተዋል። ሁለት ነው ዘዴው። የመጀመሪያው ዋናውን ቀጩኑን ቀበሮ መደበቅ። ቀጭኑ ቀበሮ እስክንድርን መሸሸግ። በእስክንድ ምትክ ሰካራሙን ሀብታሙ ነው ያለው። ሰካራሙን ማስረሻ ሰጤን ወደፊት አምጥቶ በእሱ ስም ከዐማራው ላይ ማዳበሪያውን መግፈፍ ነው የፈለጉት። በጣና ቲቪ ሰበብ ከዐማራው ላይ ለመሰብሰብ የታቀደውን ገንዘብ እግር በእግር ተከታትዬ አድርቄዋለሁ። በመማር አለባቸው በኩል ያሰቡትን አይደለም ራሳቸውን መማር አለባቸውን አብሬ አሹቅ አድርጌያታለሁ። እነ ኪሩቤል ባለ ከበሮው፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ ዶፍቶር ደረጄ፣ እነ ሙላት አድኖ ወዘተ በቁማቸው ነው በረዶ ውስጥ የቀበርኳቸው። ዐማራን መጋጥ አይታሰብም። ከእንግዲህ ማንም እየተነሣ ኪሱን አያጥበውም። ጨርቅህን ጥለህ እበድ።

"…የሚገርመው አሁን አሁን ከብዙ ልፋት በኋላ ቀበሮዎቹ ጋር እኔም ራሴ ቀበሮ የመሰሉ የቀበሮ ቆዳ የለበሱ በግ ዐማሮችን፣ ጦጣ ዐማሮችን፣ ብልጥ፣ ንቁ የሆኑ ዐማሮችን አብሬ በማሰማራት አጀንዳቸውን በመቀማት፣ ምስጢራቸውን በመበዝበዝ ጥላቸውን እንዲጠራጠሩ አድርጌአቸዋለሁ። በየትኛውም የዙም ስብሰባቸው እኔ አለሁ። እኔ ባልኖር የእኔ ወፎች አሉ። እኔ በምተኛ ሰዓት እኔን ተክተው የሚሠሩ የትየለሌ ንስር ዐማሮችን አፍርቼአለሁ። በዚህ አምላኬን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ምስጋናው አንዷለም አሁን አሁን መናገር እስኪሳቀቅ ድረስ ነው የማስደነብረው። ስለምቀዳ መናገር ይቅርብኝ እስኪል ድረስ። የዐማራ ካባ ለብሰው ፋኖን ለምን መስቀል አንጠለጠለ? ለምን ዳዊት ደገመ? የሚሉትን ፓስተር ምስጋናው አንዷለምን ዛሬ ላይ ብቻውን እንዲያወራ ነው ያደረግኩት። ሚኪ ጠሽን ሰንደል ጆሮው ላይ ሰክቶ ፍራንክፈርት ባንሆፍ ላይ እንዲለፈልፍ ያደረግኩት እኔ ነኝ። ምስኪን ዐማራን ሲግጥ የከረመው ቀበሮው ሚኪ ዛሬ ብቻውን እያወራ የጆብ ሴንተር ጡረተኛ ሆኖ ዘርፏል። አልለቃቸውም። ሠርተህ ብላ።

"…እነዚህ ቀበሮዎች አሁን መገለጥ የፈለጉት ሌላው መንገድ ደግሞ ከአዲሱ የዐማራ ትውልድ ጋር ተመሳስሎ መቅረብ። አንድ ላይ እንስራ ብሎ መምጣት። ሰልፍ እናዘጋጅ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ኪስ አጠባው መሄድ ነው ያሰቡት። ሰልፍ መውጣት ይችላሉ ሰልፉን ግን መምራት አይፈቀድም። በፍጹም በጭራሽ አይፈቀድም። ከዚያ ገንዘብ ልሰብስብ ማለት በፍጹም፣ በጭራሽ አይታሰብም። ካካ ነው። እፉ ነው። እነዚህ የዐማራን የወይን እርሻ ማዳበሪያ ሌቦች ወደ እርሻው አካባቢ ማቅረብ በፍጹም አይሞከርም። ሲንጫጫ ውሎ ቢያድር ወፍ የለም። ቀበሮዎቹ ያላቸው አማራጭ ጎንደር ባሉ የጌታ አስራደ ታዛዥ ጥቂት ቀበሮ ፋኖ መሳይ ቀበሮዎች እኔን ማሰደብ ነበር። አደረጉት፣ ሞከሩት፣ ብሩክ ይባስ ሂርጶም ዜና አድርጎ፣ እስክክስ አበበ በለውም ለማጯጯህ ሞክረው ነበር። ነገር ግን አልተቻለም። ቀጥሎ ያደረጉት በሸዋ ፋኖ በማይሙ መከታውና በአበበ ጢሞ፣ በቀውሷ በኩል ነበር። እሱም አልተሳካም።

"…የሸዋ ተወላጅ ኮሚቴዎች ይፋት ተራራ መሽጎ የሚቀለበውን የእነ መከታውን እና የእነ እስክንድርን ጦር በሳምንት 10 ሺ፣ 20 ሺ፣ 30 ሺ ዶላር እየላኩ ደግፈውት ነበር። ከልባቸው መዋጋት የሚፈልጉ ቢኖሩም ነገር ግን ከብልፅግና ጋር የሚሞዳሞደው ስለሚበዛ አንዳች ነገር ጠብ ሳያደርጉ በሚላከው ዶላር በሸነና እያሉ፣ አንዲት የገጠር ቀበሌ ሳያስለቅቁ፣ ሳይዙ በይፋት ሸለቆ ውስጥ ሚስትና ገርልፍሬንዶቻቸውን፣ እቁባቶቻቸውንም ይዘው እየተምነሸነሹ፣ በስቴኪኒ ጥርሳቸውን እየጎረጎሩ፣ የፎቶ፣ የቪዲዮ ትርኢት እያሳዩ ሲቀፍሉ ኖረዋል። አሁን ያ የዶላር ማዳበሪያ ቀጥ ብሎ እንዲቆም ተደርጓል። መሬት ላይ በእነ መከታው በኩል ይሄድ የነበረው ዶላር ነጥፏል። ምን ይበላ? የገበሬ ፍየል፣ በግና በሬ እያረደ መብላትን የትግል ስልት አድርጎ የነበረው የሆድ ፋኖ ቡድን አሁን ፍርክርኩ ወጥቷል። ኩላሊቱ እየፈረጠ ለእነ መከታው ዶላር እየላከ እነ መከታው የቅቤ ቅል መስለው እያብለጨለጩ የሚኖሩበት አግባብ ላይመለስ ተቋርጧል። ከነመከታው ቡድን እንለያለን ላሉ በቀደም ዕለት ከተላከው 4ሺ ዶላር በቀር አንድም ዶላር ወደ ይፋት ጫካ ጎረምሶች መሄድ አቁሟል። 24 ሰዓት ሜካፗን ተለቅልቃ ትግል ላይ ነኝ እያለች ስትሳደብ የከረመችው ፎንፏኒትም የአሸቦ ዕቃ ወደ መምሰሉ ተቃርባለች። አለቀ። ለምን መግለጫ አይደለም ማጋጫ አያወጡም። እኔ መስሚያዬ ጥጥ ነው። በፎቶ ትርኢት ዐማራን መቀፈል ጊዜው አልፎበታል።

"…ባለፈው ባልደራስ ሲቋቋም ገንዘብ ያዥ የሆኑት በሙሉ በመላው ዓለም በፊት ግንቦት ሰባት፣ ቅንጅት የነበሩቱ ነበሩ። ጀርመን ፍራንክፈርት ተሯሩጠው መጥተው ቦታውን ያዙት። ግንባሩ ሲቋቋምም እነዚሁ ሰዎች ናቸው የመጡት። ቶሎ ብለውም ሊቀመንበር፣ ሰብሳቢ ነው የሚሆኑት። አሁንም ሰልፍ መዘጋጀት ሲጀምር እነዚሁ ሰዎች ናቸው ጥፍራቸውንም፣ ጥርሳቸውን አሹለው ከቻሳ ለማለት የመጡት። እስከአሁን ለንደኖች ነአዲስ ጉልበት፣ በአዲስ ኃይል ቀዳዳ ላለመክፈት እየጣሩ ነው። አሜሪካም እንደዚያው። የጀርመኖቹን ግን አላውቅም። በዐማራ አዲሱ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ የወይኑን እርሻ የሚያጠፉት ስመጥር ቀበሮዎች አሁንም ሰልፉን ከመሩት አደጋ ነው። ተመልሶ መንቦራጨቅ ነው። ስለዚህ በምንም ዓይነት መንገድ በአዲሱ የዐማራ ትግል አሮጌዎቹን የወይን መያዣ አቁማዳ መክተት አይገባም። ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ስለዚህ እነዚህን መርዞች፣ እነዚህን ቫይረሶች፣ እነዚህን የኋላ ታሪካቸው ደርግ፣ ኢህአዴግ፣

Читать полностью…
Subscribe to a channel