"…ተናፋቂዋ ደግሞ መጣይ…!
"…ከጄነራሎቹ ዘንዳ በአስቸኳይ ለዐማራ ክልል ሕዝብ እንዲደርስ የተባለ መልእክት ነው ይዛ የመጣይው። ቶሎ አክሽፈው ይላል መልእክቱ። ማክሸፍ አይደለም አፈርሰው።
• ቆይማ ልቀምመውና ልመለስ።
• ሊበላ…?
"…በዓለማችን ካሉ ቁጥር አንድ ሀብታሞች ተርታ በሚመደበው በአቶ ኤሎን መስክ ስም በተከፈተ የለገጣ፣ ሙድ መያዣ "Parody" የX ገጽ ላይ የዓይን ጥራትን በተመለከተ አንድ አላጋጭ የልግጫ ጥያቄ ይቀርባል። ጥያቄውን የመለሰ ደግሞ የ3 ሚልዮን ዶላር ሽልማት እንዳሚያገኝም ከጥያቄው ጋር አብሮ ተጠቅሷል።
"…ይሄን ጥያቄ ማን ያነበዋል? የዐማራ ወኪሉ የቆየው ብአዴን ሰው ቆይቶም በሰሊጥ ብር የበለጸገው ብልፅግናው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ነው ንግድ ሚንስቴር ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል። ሊበላ እኮ ነው። 😂 3 ሚልዮን ዶላር ሊልፍ። ሃኣ…? ቀልደኛ።
"…የጎንደር ፋኖ እዚያ በቀዬው የመጣውን የመላኩ አለበልን አለቆች ወራሪ ጦር አፈር ከደቼ ያበላል አጅሬው አያ መላኩ አለበል ደግሞ አዲስ አበባ ተቀምጦ 3 ሚልዮን ዶላር ሊበላ…?
• የዶላር ውይይቱ ቀጥሏል።
"…እስከ አሁን የተበሳጨ ሰው አላየሁም። የሆነው ሆኖ ተራው የእናንተ ሓሳብ የሚሰማበት ሰዓት ነው። ቀጥሉ።
• የማንን ራዕይ ማን ያስቀጥል…?
"…መልካም…
"…ዛሬ ሰኔ 6 አርባኛው ቀን ለበዓለ ዕርገት ደርሰን በዓሉን በያለንበት አከበርን። እንደልማዳችንም ከእኔ ጋር የትንሣኤውን ዐዋጅ ያውጁ ዘንድ የሚጠበቁት 1ሺ አመስጋኞች ዛሬም ሳይታክቱ፣ ሳይፈሩ፣ ሳይኮሩ፣ በደስታ አመስግነው የሚጠበቀው የአመስጋኝ ቁጥርም ሞልቷል።
• ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን በቪድዮ የተደገፈ ነው። ርዕሰ አንቀጽ በቪድዮ ለመመልከት እና እናንተም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?
• የ 100 ሰው ዝግጁነት ብቻ ነው የምጠብቀው። ዝግጁ…?
• ይደመጥ…!
"…የወሎ ዕዝ ፋኖዎች የአሳምነው ፅጌ ልጆች መልእክት ለኢትዮጵያ እናቶች…
• "ማይም" ግን እንደዚህ ከፍ ያለ የመጠቀ አእምሮ በለቤት ነው ማለት ነው? አይ ዐማራ…👌
እምሽክ ነው…!
ቅርብ ለቅርብ ነው ጎጃምና ጎንደር
ሲጫወቱ ውሎ ከመሸ ለማደር
"…አገኘሁ መስሎት ተግተልትሎ የገባው የኦሮሙማው አገዛዝ አራዊት በሙሉ በጎንደር ዐማሮቹ በአፄ ቴዎድሮስ እና በጎጃም ዐማሮቹ በበላይ ዘለቀ ልጆች አይሆኑ ሆኗል። የምርኮኛው ነገር ነው የጨነቀኝ። ወይ የሰው ልክ አለማወቅ?
"…አሁን ደግሞ የለብለብ የኮሪደር ልማቱን በተመለከተ ሪፖርተራችን ከአዲስ አበባ አጠናግሮ በቪድዮ ያደረሰንን ዘገባ ዓይተን እንመለስ።
Читать полностью…"…መልካም…
"…በርዕሰ አንቀጹ የተናደዱ የ5 ሰዎችን ኢሞጂ ከማየቴ በቀር 10 ሺ የተባለውን 15 ሺ ሰው አንብቦት፣ 300 ሰው የተባለውን 500 ሰው ላይክ አድርጎት ርዕሰ አንቀጹ በቲጂ መንደር ቤተሰቦቼ ተነብቧል።
"…ቀጥሎ ተራው የእናንተ ነው። የተናደዳችሁ 5 ታችሁንም ጨምሮ በተጻፈው ርዕሰ አንቀጽ ላይ የጎደለ ካለ ጨምራችሁ፣ የሚቀነስ ካለም ቀንሳችሁ እናንተ ደግሞ በተራችሁ ተንፒሱ። የአንድ የ120 ሰዎች አስተያየት ካነበብን ወዲያ ወደ ቀጣዩ መረጃ ወደመስጠቱ መርሀ ግብራችን እንገባለን።
• 1…2…3…ጀምሩ✍✍✍
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ሩጫው ከክረምቱ መግባት ጋር ነው። ትንቅንቁ ሰማይ ሳይጨላልም፣ ጉሙ ምድርን ሳይሸፍን የሆነ ነገር ለመፍጠር ነው። ግርግሩም ብልፅግና የለብለብ ሠራዊቱ እስኪደርስለት የመጨረሻዬ ያለውን ሠራዊቱን በዐማራ ምድር አሰማርቶ ለማሸነፍ ነው። እንደሚታወቀው ክረምቱም ከገባ ብልፅግና ከባድ መሳሪያ እንደፈለገው ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም። ለድሮንም አይመችም። ጦርነቱ የሚካሄደው ደግሞ ዐማሮቹ ምድሪቱን እንደ እጃቸው መዳፍ በሚያውቁትና በኖሩበት ምድር ነውና ለገብሱ የፈላ ሠራዊት ይቸግረዋል። ክረምቱ ለደፈጣ ውጊያም በጣም አመቺ ነው። ፋኖ የብልፅግና ጦር እሰፈረበት ካፕም ድረስ በመሄድ ጥቃት ሊያደርስ የሚችልበት፣ ሰኔ፣ ሀምሌ እና ነሐሴ ፋኖ ብልፅግናን እግር ከወርች አስሮ ወፌላላ የሚገርፍበትም ጊዜ ነው ክረምቱ። ተወደደም ተጠላም የማይካደው ሀቅ የብልፅግና ጦር ኃይሉ ተሸመድምዷል። ስለዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልፅግና ሳይወድ በግዱ ከማጥቃት ወደ መከላከል ይዞራል። እኔም ልክ እንደፋኖ ሽምቅ ልግባ አለ እኮ መኴ። ተግበስብሶ የገባውም ኃይል እንደ ኤሊፖፕ ተመጦ በትንሸ ጊዜ ውስጥ ያልቃል።
"…እንደ ብልፅግና ሓሳብማ አብይ ዐማራን በተራዘመ ጦርነት ማውደም፣ በኤኮኖሚም ማድቀቅ ነበር የፈለገው። ፋኖን በመናቅ ሳያሸንፈውም እዚያው እየተንከላወሰ ዐማራን ለማድቀቅ ነበር ፈልጎ የነበረው። በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ምክንያት ዐማራ አልተጎዳም ማለት አይደለም። ከዐማራ ይልቅ ግን ሀገሪቱ ራሷ የተጎዳችው ይብሳል።አገዛዙ ከዐማራ በኩል ማግኘት የነበረበትን ከፍተኛ ግብር ዘንድሮ አጥቷል። በኢትዮጵያ የመንግሥት ዙፋን የሚጸናው፣ ሥርዓተ መንግሥት የሚያውቀው ዐማራው በሚገብረው ግብር ነው። መንግሥቱ ኃይለማርያም አንድ ቁና ግብር ከትግሬ አስገብረን አናውቅም ያለው እኮ በቴሌቭዥን ነው። ግብር እየገበረ መንግሥት የሚያጸናው ዐማራው፣ የዐማራው አርሶአደር ነበር። ዘንደሮ ግን ግብር የገበረ ዐማራ በጣም ጥቂት ነው። ግብር ሰብሳቢዎች በሙሉ በፋኖ ታስረዋል። ገበሬ ለፋኖ ገብሯል። እንኳን ገበሬው ከተሜው "ሱቄን አሽጉት እንጂ ያልሸጥኩትን ከየት አምጥቼ ነው የምከፍለው" በማለት ግብር መገበር አልቻለም። አይደለም መንግሥት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፍተኛውን የአሥራት ፈሰስ ያገኝ የነበረው ከዐማራ ክልል በሚመጣ አሥራት ነበር።
"…አቢይ አመድ ዐማራ ክልልን በሰፊው ባካለለ መልኩ በቋሚነት ጦሩን በማስቀመጥ ትምህርትም፣ ንግድም፣ እርሻም በአጠቃላይ ክልሉ ከዚህ ቀደም ጎልቶ ይታወቅበት የነበረውን የጦፈ እንቅስቃሴ ለዓመታት በማዳከም፣ ልክ እንደ ትግሬ ሁሉ ዐማራንም በሻሻ የማድረግ ስትራቴጂ እየተከተለ ለመሆኑ እያንዳንዱ ከጦርነቱ በፊት እስከ ጦርነቱ መቀስቀስ ድረስ የወሰዳቸው እርምጃዎች ያሳብቃሉ። ይሄ ሁሉ ጦርነት እየተካሄደ ዐማራ ከቀዬው አልተሰደደም። አልተፈናቀለም። ቢፈናቀልም እዚያው ደጋ፣ ቆላ እያለ በክልሉ እንጂ እንደ ትግሬ ሱዳን እና ዐማራ ክልል አልተሰደደም። ይሄ ራሱ ተአምር ነው። ዐማራ ጿሚው በመብዛቱ ረሃብን የመቋቋም ተፈጥሮአዊ ፀጋም ያለው ሕዝብ ነው። ብልጽግና ዐማራን በመቆለፉ ትምህርት ቤት ተዘጋ። ትምህርት ቤት ሲዘጋ ደግሞ አስተማሪዎችና ተማሪዎች በሙሉ ፋኖን በገፍ ተቀላቀሉ። አገዛዙ ፋኖን በልጅ እንደ ህፃን እያየ፣ እየናቀ የነበረው አቢይ አመድ አሁን ፋኖ ራሱን በዘመናዊ የውትድርና ስልጠና እያዳበረ፣ ዘመናዊ የጦር መሳሪያም እየታጠቀ በመሄድ አስፈሪና ግዙፍ ደረጃ መድረሱን ሲያይ ገረጣ። ጭነቀቱ ከፒያሳ እስከ 4 ኪሎ ብስክሌት በመንዳት ሊያስተነፍስ ይጋጋጣል። ደግሞም ጦርነቱ ከሙሉ የዐማራ ሕዝብ ጋር በመሆኑ አገዛዙ በፍፁም ሕዝብን ሊያሸንፍ አይችልም። ጦርነቱ ዓመታትን፣ ወራትን፣ ሳምንታትን ሊፈጅ፣ ክፍለ ዘመናትንም ሊያስቆጥር ቢችል እንኳ "ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ" ነውና ከነተረቱ ከእንግዲህ ዐማራ አይመለስም። ፋኖ አገዛዙን ከማሸነፍ በቀር ሌላ ሁለተኛም፣ ሦስተኛም አማራጭም ምርጫም የለውም።
"…ይህ የዐማራ ክልል ጦርነት እንደ ትግሬዎቹ ጊዜ ጦርነት የመላውን ኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍም አላገኘም። አርቲስቱ በመዝሙር፣ በሙዚቃ በዘፈን ከጦሩ ጋር አልቆመም። ለባለሀብቱ አሁን ትናንት በተጻፈ ደብዳቤ እርዱን ብሎ በድብቅ የልመና ደብዳቤ ከመጻፉ በቀር አንድም ባለሀብት ለጦሩ በይፋ ድጋፍ አላደረገም። የሆነ ሰሞን የኦሮሞ ካድሬዎች ውርውር ብለው የድጋፍ ሰልፍ ቢጤ መሳይ ነገር ለማድረግ ዊኒጥ ዊኒጥ ከማለታቸው በቀር ወፍ የለም። በአጠቃላይ ጦርነቱ ሕዝባዊ ድጋፍ የለውም። ደቡብ ወሎ ያሉ ኦሮሞዎች ከለገሱት አራት ፍሬ በሬ ሌላ እንደ በፊቱ ሀገር ሙሉ ከፍት ለመኴ አልተጫነም። በየሰፈሩ በሶ የሚያዘጋጁ፣ ድርቆሽ የሚሠሩ፣ ለመከላከያ ሰንጋ የሚያዋጡም ሴፍቲኔታም ዜጎችም አልታዩም። የዚህ ጦርነት ውጤቱ ግን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ላይ አደጋን ደቅኖ ታይቷል። ትርፍ አምራች የሆነው የዐማራ ክልል በሰፊው የሚያመርታቸውን የምግብ እህሎች ለተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ማቅረብ ባለመቻሉ አሁን የአንድ ኪሎ ጤፍ ዋጋ በኪሎ እስከ 150 ብር መሸጥ ተጀምሯል። ክረምቱ ሲመጣ ደግሞ ይብስበታል።
"…በዐማራ ክልል የሚኖረው ሕዝብ በአሰፋፈር ሰብሰብ ብሎ በመኖሩ ለተቀረው የኢትዮጵያ ነጋዴ አመቺ የንግድ መደብርም ነበር። ሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴዎች በብዛት ምርታቸውን በገፍ የሚያራግፉበት ግዙፍ ወደብም ነበር ዐማራ። ትግሬ ከገበያው ከወጣ ወዲህ በአስመጪና ላኪነት ለተሰማሩት የኦሮሞና የስልጤ ነጋዴዎች ዋነኛ የገቢ ትርፍ መዛቂያቸውም የዐማራ ሕዝብ ነበር። አሁን ግን ወፍ የለም። መርካቶ ቀዝቃዛ ውኃ በረዶ እንደተቸለሰባት ነው የሚነገረው። ባንኮች ገንዘብ የላቸውም። ማበደርም አቁመዋል። ነጋዴ ደግሞ አብዛኛውን ቢዝነሱን የሚያሳልጠው በብድር ነው። አሁን ግን ብድር ወፍ የለም። አይደለም ባንክ በሃይማኖት ኃጢአት፣ በሕግ ወንጀል ነው የሚባለውን አራጣ እንኳ ለመበደር አልተቻለም ነው የሚባለው። ድሮስ 50 ሚልዮን ሕዝብ የሚኖርበት ክልል ላይ ጦርነት ከፍተህ ከኪሳራ በቀር ምን ልታተርፍ?
"…የየብስ ትራንስፖርቱ ከስሯል። መክሰሩንም ሚንስትሩ ዐውጇል። እንደ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ዓይነቱም ድርጅት ሕዝብን ታሳቢ አድርጎ ነበር የሚንቀሳቀሰው። አዳሜና ሔዋኔ ይታይህ 50 ሚልዮን ሕዝብ ኢንተርኔት መጠቀም ሲያቆም የሚደርሰውን ኪሳራ አስበው። አይደለም 50 ሚልዮን ዐማራ 5 ሚልዮን ትግሬ ከገበያው ከወጣ ችግር ነው። ትምህርት ሲዘጋ መምህራን እና ተማሪዎች መገኛቸው ፋኖ ጋር ሆነ። ይሄን ለማስቀረት ዘንድሮ የሰላም ሚንስቴር በተለይ የዐማራና የኦሮሚያ ተማሪዎች በእረፍት ሰበብ ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ተመልሰው ሲሄዱ ፋኖን እና ኦነግን እንዳይቀላቀሉ ሲባል በበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ስም ጠርንፎ ለመያዝ ምዝገባ በየዩኒቨርስቲዎቹ መካሄዱን ታውቋል። ቢቸግር።
"…እስቲ አንተንም አንቺንም ልጠይቃችሁ? ሥራ አለህ? ኪስህ፣ ቦርሳህ አልሳሳም? እንደ በፊቱ በቀን 3 ጊዜ ትበላለህ? ለልጆችህ አይደለም ለራስህ ጠግበህ ትበላለህ? ነዳጅ የተወደደው፣ የቤት ኪራይ የናረው፣ ትራንስፖርት ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ህክምናና መድኃኒት፣ የትምህርት ቤት ክፍያ ጣሪያ የነካው ለምን ይመስልሃል? በደቡብ ለመምህራን እና ለሀኪሞች ደሞዝ መክፈል ያቃተው ለምን ይመስልሃል? አንተን ለማደንዘዝ በቀለምና በመብራት ያበደ፣ የተሽቆጠቆጠ ከተማ፣ መናፈሻና ሆቴሎች ሠርቶ በሆሊዉድ የፊልም መሥሪያ ፕሮፌሽናል ካሜራዎች እየቀረፀ፣ በቴሌቭዥን፣👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ቆሮ 15፥ 21-22
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…በመቀጠል ደግሞ የBotox Cosmetic አጠቃቀምን የሚያሳይ አንድ ቪድዮ እለቅላችኋለሁ። Botox ሱ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነው። የጎንዮሽ ጉዳትም አለው። ሲበዛ ከንፈራችሁን ፈርፍሮ፣ ወዝ አሳጥቶ፣ የከንፈራችሁን የውስጥ ገበሩን ሊገለብጥባችሁ ይችላል። Botox እንዴት ወንዱ እና ሴቱን ሁላ ኡሙንዱኖኢሹ ዱንቡሽቡሽ ቦንቦሊኖ እንደሚያስመስልም አሳያችኋለሁ። በቪድዮው ትልቅ ትምህርት ታገኙበታላችሁ ብዬ አስባለሁ። እሺ የእኔ ማይሞች። 😂
• አልተኛችሁም አይደል…?
"…ከአንድ የኦሮሚኛ ሙዚቃ በኋላ ተመልሰን እንመጣለን።
• ማስታወሻ፦
"…የግንባሩ፣ የሞጣና የብሪጅ እስቶን፣ የግምቦቴና የሠራዊቱም ቲክቶከሮች ትንሽ ቀን ይንፈራገጡ ዘንድ፣ እርስ በእርሳቸውም እየተበጣበጡም ስለሆነ እኔ ከዳር ቁጭ ብዬ ሙድ ልይዝባቸውም ስለፈልግሁ ለዛሬ ቲክቶክ አልገባም። በሉ እኔ ላይ እያሟረታችሁ ተፈሳፈሱ። "ዘመዴን አባረነዋል፣ ድባቅ መተነዋል፣ ሁለተኛ ቲክቶክ ድርሽ አይላትም ወዘተረፈ እያላችሁ ራሳችሁን በራሳችሁ አፅናኑ። 😂 ዛሬ አየሩ መጣም መጣም ሸጋ ስለሆነ እኔ ምሽቴን ከራየን ወንዝ ዳር ሽርር ብትን እያልኩ ዓለሜን ልቅጭበት።
"…ምድረ መወቀኛ ሁላ… ለዘፋኙ የሚበተነውን ገንዘብ እያየህ ዓይንህ ይቅላ አሉህ ደግሞ። ባንክ ዘርፈው ነው፣ ብር አትመው ነው፣ ሰው አግተው ነው ምናምን እያልክ አውራ አሉህ። እኛ የባንክ ብድር አጥተን መነገድ አቃተን፣ የ3ወር ደሞዛችን እስከአሁን አልተከፈለንም፣ ኑሮ ተወደደ፣ የቤት ኪራይ ጨመረ፣ ዳቦ ሰማይ ነካ እያልክ ብቻ ተዘፍዝፈህ አላዝን። ይሄ ምንቀኝነት ነው። እና ታዲያ እንዲህ እንደ ወያኔ አቅሉን ካልሳተ ባለጊዜ መባሉ ምኑ ላይ ነው?
• በሉ አርፋችሁ እየተደነሳችሁ…!
የ4 ኪሎ መስመር…?
"…አቢይ ለኮሪደር ልማቱ ግምገማ ዐማሮችን ሰብስቦ ( ሦስት ከጎጃም፣ ሁለት ከወሎ፣ አንድ ጎንደር) ከፊት በማሰለፍ እንዲታይ የፈለገው ምን መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው? ብአዴን 😂
• እሺ ኦሮሞዎቹ እንኳ ከኋላም በብዛት ይኖራሉ። ሱማሌም አለ አደም ይታየኛል። ደቡቦችም አሉ ሲዘምሩ እያየኋቸው ነው። የእኔ ጥያቄ ከታረቁ በኋላ እንዴት አንድ ትግሬ ለአመል እንኳ በዚህ የ4 ኪሎ መስመር ጉብኝት ላይ አላካተተም? ምን ማለት ነው? ትግሬ በአዲስ አበባ እድገት ላይ ምንም አሻራ አላሳረፈም ወይ? ተዉ እንጂ። ይሄማ ግፍ ነው።
"…አዲስ አበባ ግን የማን ናት? 😂
"…መልካም…
"…ከእኔ ጋር ናችሁ አይደል?
• መቼም የእኔ ነገር በቶሎ አይገባቹም… ለማንኛውም እንደ ፍሮፌሰሩ እየተስተማራችሁ ጠብቁኝ።
• የ 777 ድፍረት ግን እስከ ጥግ ነው።
መልካም…
"…ከምስጋናችን ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀፃችን ነው ማለት ነው። የዛሬው እንደተለመደው ርዕሰ አንቀፁን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
• አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና ዝግጁ ነነ በሉትማ። 😂😂 አደራ ታክሲ ውስጥ ብቻ ትእዛዙን ፈጽማችሁ ፎሊስ ጣቢያ እንዳትውሉ።
ምከሩ እስቲ…
“…አሁን በገበያ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብር አሁን ካለበት ዋጋ በላይ ሊላሽቅ እንደሚችል እየተነገረ ነው። አንድ ዶላር በባንክ እስከ 90 የኢትዮጵያ ብር ሊዘረዘር ይችላልም ነው እየተባለ ያለው። ጂቡቲም የኢትዮጵያ ብር አፈር ደቼ ሊበላ ስለሆነ በእኛ ሀገር ኮሪደር ላይ እንደ መገበያያ መጠቀም አቁመናል” ማለቷም ተዘግቧል።
• ባለሙያዎች ሕዝቡን ምን ትመክሩታላችሁ?
፩ኛ፦ በባንክ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የሆነ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ብራቸው ቀልጦ እና ሟምቶ እንዳያድር ከወዲሁ ምን ያድርጉበት?
፪ኛ፦ የኦሮሞ ባለጊዜዎች እንደወርቅ እና መሬት፣ ቤት እየገዙ ያሉት፣ በዱባይ ቪላ እየሸመቱ ያሉት ከዚህ የብር መሾቅ ጋር ይያያዛል ወይ?
፫ኛ፦ 1ዶላር 90 ብር ተመነዘረ ሲባል ጮቤ የሚረግጥ፣ በቃ ሀብታም ልሆን ነው ብሎ የሚፈነጥዝ የትየለሌ ዳያስጶራ እንዳለ ይታወቃል። በእውነት ብር በዚህ መጠን መዘርዘሩ ያስፈነጥዛል ወይ…?
፬ኛ፦ በባንክ በዚህ መጠን የሚዘረዘር ከሆነ በጥቁር ገበያስ ምን ያህል ይዘረዘር ይሆን?
• እስቲ ሕዝባችሁን ምክር ለግሱ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የፓርኮቹና የሪዞርቶቹ መጨረሻ… የሚመጣው የኢትዮጵያ መንገሥት ምን ላይ ያተኩር ይሆን…?
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
“…አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።” መዝ 47፥5
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…የወሎ ዕዝ ፋኖዎች የላስታ የጻድቃን ዘር ፋኖዎች ለኦሮሞ፣ ለደቡብ፣ ለአፋር፣ ለሱማሌ እና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ እናቶች መልእክት አለን እያሉ ነው።
• አላችሁ አይደል…?
ደግሞ እንጠይቅ…!
"…ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚል ገንጣይ ስም ይዘው፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ሲሉ 17 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያን መንግሥት እየወጉ እጅና እግራቸው የተቆረጡ የትግሬ ነፃ አውጪዎችን ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲና ነፃነትን ለማምጣት ሲሉ ብሎ ማለት በምን ሒሳብ ነው ትክክል የሚሆነው?
"…የወያኔን የመከራ በአል አይተ ግንቦት 20ን ከኢትዮጵያ ምድር ያስቀረህ፣ ስም አጠራሩን የደመሰስክ አምላክ አሁንም ከትግሬ ጫንቃ ላይ ህወሓትን፣ ከዐማራ ጫንቃ ላይ ብአዴንን፣ ከኦሮሞ ጫንቃ ላይ ኦህዴድና ኦነግ የሚባሉ የኢትዮጵያ ነቀርሳዎችን፣ በአጠቃላይ ዘንዶ ብልፅግናን ደምስሰህ አጥፋልን። ዐማራ እንኳ ጥቂት ነው የቀረው። እየገነደሰው ነው ብአዴንን።
• ማይሞ’ችዬ… ቆይ ግን ይህቺን የመርዝ ብልቃጥ አንቀጽ 39 የሆነችን ጋለሞታይቱን ወያኔ ለኢትዮጵያ አንድነት ስትል ነው እጅ እግሯ የተቆረጠው ማለት አግባብ ነውን?
የበቴ ነገር…!
"…አንድ ሚልዮን ትግሬ ያስጨረሰውን፣ ያልተማረ 7ተኛ ጨ መሃይምነቱን፣ እብድነቱን፣ ጨካኝ፣ አረመኔ ዋሾ ቀጣፊነቱን ገልጦ በአደባባይ በቴሌቭዥን ሲሞልጨው የከረመውን አቶ ጌታቸው ረዳን አቅፎ እየደባበሰ፣ እንደኔው ወሎዬ እኮ ነው ብሎ እያሻሸ የራራለት አቶ አቢይ አሕመድ ምስኪኑን ኦሮሞውን አቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ለምንድነው የጨከነው? አሁን ከምር አቶ በቴ ኡርጌሳ በጭካኔ ከትግሬው አቶ ስብሃት ነጋ በልጦ ነው? አይመስለኝም። እርግጥ ነው…
• አቢይ አሕመድ የወሎ ዐማራ
• ዳንኤል ክብረት የወሎ ዐማራ
• ጌታቸው ረዳ የወሎ ዐማራ
"…ኦነግ እንኳ ስለ በቴ ኡርጌሳ እኮ ዝም ጭጭ ጀዺ ነው ያለው። የኦሮሞ አክቲቪስቶችም እንደዚያው ጮጋ ነው ያሉት። ጉማ ሰቀታማ የድሬደዋ መስተዳደር ማስታወቂያ ያሰራው ጀምሯል። የበቴን ቤተሰቦች እንኳ መርዳት ማገዝ አልፈለጉም። ምን ዓይነት ጭካኔ ነው ግን? ከምር እኔ በጣም እየገረመኝ እየደነቀኝም ነው።
"…እነዚህ 666 የሆኑ ሰዎች በቴ ኡርጌሳን ከሌሊቱ በ6 ሰዓት በ6 ፖሊሶች ከተኛበት ሆቴል ይዘው አውጥተውት፣ እጁን የፊጥኝ አስረውት በ6 ጥይትም ደብድበው ገድለውት፣ መግደላቸው ሳያንስ በቆሻሻ ገንዳ ላይ አስከሬኑን ለጅብ ጥለው የሄዱት አቶ በቴ ከንግግር ሌላ ምን ቢያደርጋቸው ነው ግን?
"…ወይም ደግሞ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው እንደቀሩት ልክ እስር ቤት እየበሰበሱ እንዳሉት እንደ ኦነግ አመራሮች በቴንም አስረው አዋሽ አርባ ቢያስቀምጡት ምን ነበረበት? የዚህ በግፍ የተገደለ ኦሮሞ ሰው ደም ግን እንዲሁ በከንቱ ፈስሶ መቅረቱም ያሳዝናል።
"…ጨካኝ እንሁን አለ ዳንኤል ክብረት። እውነትም ጨካኝ። እየቆየ ሲመጣ የዚህ ሰው የግፍ አሟሟት እንደ እግር እሳት እያንገበገበኝ ነው። ቤተሰቦቹስ እንዴት ሆነው ይሆን?
• ቆይቼ እመለሳለሁ።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …በዩቲዩብና በፌስቡክ ላይ በሚለቃቸው ፕሮፓጋንዳዎች ደንዝዘህ ችግር ቤቱን ላይህ ላይ እንዲሠራ እያደረገብህ ያለው ማን ይመስልሃል? የውኃ መውረጃ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ሳይሠሩ ያለ ጥናት በለብለብ የተሠራው እና በቀይና ጥቁር ቀለም የተዥጎረጎረው የከተማዋ አስፓልትም ወደ መዋኛ ሀይቅነት እየተቀየረ ነው። ይሄ ሁሉ ቅሸባ ሀገሪቷ እየደረሰባት ያለውን ኪሳራ ልትደብቅ ስላልቻለች እየተጋጋጡ ነው ገዢዎቿ።
"…እሰማለሁ በተለይ በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ በተለየ ሁኔታ መከራው መፅናቱ፣ ጫናው መብዛቱን። የኑሮ ውድነቱን ተተኸው አሁን በሰላም ወጥቶ መግባት ከባድ ሆኗል የሚለው የትየለሌ ሕዝብ ነው። የአዲስ አበባ ሕዝብ ቤቱ ሌሊት ሲበረበር ያድራል። ወርቅ ምናምን ካገኙም ላፍ ነው የሚያረጉት። ጠዋት ወይም ማታ ወደቤቱ ሲገባ በድጋሚ ይበረበራል። እንደውም ስልኩ ላይ የፋኖ ፎቶ ወይም አረንጎዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ካዩ የማርያም ጠላት አድርግው ወንድ ሴት ሳይሉ እንደ አህያ ባልበላ አንጀቱ ይነርቱታል። ዛሬ ሕዝቡን የሚደበድብ ሁሉ ነገም ብልፅግና የሚኖር ይመስለዋል። ጃንሆይን የሙጥኝ ብለው ሕዝብ የበደሉ በደርግ፣ ደርግን ያሉ በወያኔ፣ ወያኔን ያሉ በብልፅግና ታኝከው መተፋታቸውን የዛሬዎቹም አያስቡም። ነገ ኩርማን እንጀራ ከሕዝብ እየለመኑ እንደሚኖሩ አይረዱም።
"…ጃውሳ፣ ጃርት፣ አሞሌ ጨው፣ ደምሰሰነው አሁን በየቀበሌው የተንጠባጠበውን ፅንፈኛ እየለቀምነው ነው። የክልሉን 97% ከአሸባሪው ፋኖ ነፃ አድርገነዋል። አሁን ያለው አንፃራዊ ሰላም ማስቀጠል ያስፈልጋል ወዘተ ሲል የከረመው ብልፅግና ትናነት ተስፋ ሲቆርጥ "ማይም" ብሎ እስከ መሳደብ ደርሷል። ደግሞ ስድብ አይለጠፍ። መፍትሄው ቀላል ነው። ሥልጣኑን ለዐማራ ፋኖ መልቀቅ እና በፈቃደኝነት ለፍርድ መቅረብ ብቻ ነው። መሬት ያለ ሰው ይሄ የምጽፈው ነገር ብዙም ላይረዳው፣ ላይገባው ይችላል። EBS, EBC, ETV, FANA, WALTA ን አዘውትሮ የሚመለከት ሰው እንደ መረጃ ቲቪን ያሉትን ካላየ በቀር ፈረሱ ላይ የተቀመጠው ሰው እየደረሰበት ያለውን ፍዳ ሊያይ፣ ሊመለከት አይችልም። አይገባውምም። እንዲያውም ሲርበው ዓድዋ 00 ሙዚየም ጋር ሄዶ ረሃቡን ቀዝቃዛ አየር፣ ለብለብ ባለ ፀሐይ በመመገብ ሆዱን እያሻሸ ነፋስ ተቀብሎ ተቀብትቶ ቤቱ ይገባል። መቸም የማይም ነገር አይጣል ነው።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ፋኖ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም…
"…የሚጠበቀው ሺ አመስጋኝ በፍጥነት ሞልቷል። ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ተናፋቂው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም እንደወትሮው ነጭ ነጯን የሚዘረግፍ ነው። እንደ ኮሶ የሚያሽር ኮምጠጥ፣ መረር ያለ ሰናፍጭ የበዛበት ሚጥሚጣ በቃሪያ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ነው።
"…ክረምቱ እየመጣ ነው። እናስ የፋኖና የብልፅግና የዋንጫ ጨዋታ ምን ይመስላል የሚለውን ነው የሚዳስሰው ርዕሰ አንቀፁ። አጥፍቻለሁ፣ በድዬአለሁ ብላ ምርጫ ቦርድን ይቅርታ ስለጠየቀችው ዱቄት ህወሓት በሌላ አንቀጽ እንመለስበታለን። የጦር ዝግጅቷም ቪድዮ ደርሶኛል እንመለስበታለን። አሁን ግን ወደ ርዕሰ አንቀጻችን እንመለሳለን።
"…10 ሺ ሰው አንብቦት፣ 300 ሰው ላይክ ካደረገው የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ሓሳባችሁን ጽፋችሁ ጠብቁኝ።
• ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ አይደል?
"…ዌል እንግዲክ… ኡሙንዱኖኢሹ የእኔ ቦንቦሊኖ የሚያስመስለው ማነው Botox የሚሉት ይሄ ነው አሉኝ። መርፌው የተረሳ ቀን በቃ ማድያቱ ሁሉ ፍጥጥ ነው የሚል አሉ። አይጣል እኮ ነው። ከዚያ እነ እንትና ውይ የእኔ ጌታ ሲያምር፣ ስታምር ብለን ፍጥጥ ነው አሉ። 😂
• ማይሞችዬ… በሉ እየተ Botoxከሰካችሁ…!
"…አዪዪ መከራዬ… ! ዳኒ አሞሌ ጨው ነው ያለው ጃውሳው አሁን ደግሞ ምን አድርጎ ይሆን የዳኒ ድምጽ እንዲህ የተቀየረው…? ምቱ ይሆን እንዴ? አይ ጃውሳው የሥራህን ይስጥህ?
"…በ ፈረንጆቹ F ቃል መሳደብ እኮ ነው የቀረው። ኧረ ባባጃሌው። ዳኒዬ እንደ ሲንጋፖር መጨከን ነው የሚያስፈልገው። መጨከን ዳኒ። ጨከን በል።
• ቡቶክሶችዬ እየተማየማችሁ…!😁
"…ጥያቄ ነው…?
"…እሺ አቶ በቴን በዚህ መልክ በአሰቃቂ ሁኔታ ባይገድሉት ምንአለበት? በእውነት ግፍ ነው። አንዳንድ ኦሮሞዎች ይሄን ምስኪን ሰው ረስተው ኮሪደር ልማት እያሉ ሲጨፍሩ ሳይ ይገርሙኛል። እኔማ አቢይ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ብስክሌት የሚያሽከረክር ሁላ ነው የሚመስለኝ።
• ቆይ ከተማ የሚለማው ለማነው?
ጥያቄ ነው…???
"…የዐማራ ክልል ሕዝብ ጦርነት ላይ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሀገር ምን ዓይነት ጉዳት እየደረሰ እንዳለ ይሰማችኋል? የኢኮነሚስቶቹን ትንታኔ አቆዩና እስቲ እናንተው የሸቀጣ ሸቀጥም ሆነ የእህል ወዘተ ነጋዴዎች እና ሸማቾች የሆነ ነገር በሉን።
"…ይሄ ሁሉስ ጦርነት በምድሩ ላይ እየተካሄደ የዐማራ ሕዝብ ከቀዬው፣ ከመንደሩ፣ ከአድባር ከደብሩ ንቅንቅ የማይለው፣ ወደ ሱዳንም፣ ወደ ትግራይም የማይሰደደውስ ለምን ይሆን? አይገርምላችሁም?
"…ጦርነት የትም ይነሳ የት ሕዝብ መሰደዱ ግድ ነው። ዩክሬንን፣ ጋዛን ማየት ይቻላል። ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ አፍጋኒስታንንም አይተናል። ወንድሞቻችን ትግሬዎች ወደ ሱዳና ወደ ዐማራ፣ ኦሮሞዎች ከሱማሌ ወደ ሸዋ ሲሰደዱም አይተናል። ዐማራን በእሳት መሃል ተረጋግቶ እንዲራመድ ያደረገው ምንድነው ትላላችሁ?
• በቀለጠ ጦርነት መሐል ተረጋግቶ፣ ወዙ ጨፍ እንዳለ ሳይቀየር፣ ፈጣሪውን እያመሰገነ እንዲኖር ያደረገው ነገር ምንድነው? እንዲህ ዓይነቱ ተፈጥሮ ልዩ ጥበብን እና መሰጠትን ይጠይቃል ብዬ እኮ ነው።
• የጎጃም፣ የምንጃር ጤፍስ በምን ተተካ? በስንዴ?
• እናውጋ እስቲ…
"ርዕሰ አንቀጽ"
• ለፋኖዎች የሚጠቅም መረጃ ነው።
"…ከትላንት ወዲያ ጀምሮ ሱ-29 ጀት ልምምድ እያደረገ ነው። ከምርቃቱ በኋላ አንዴ ተነሥቶ ነበር። የአሁኑ ልምምድ ለህወሓት ጦርነት ጊዜ እንደተደረገው ዓይነት የውጊያ ልምምድ ነው። ይህን ማወቁ ለፋኖ ለጥንቃቄ ጥሩ ነው። ምንአልባት በድሮን ብቻ ሳይሆን በጀትም ድብደባ ሊኖር ስለሚችል ካሁኑ ጥንቃቄ ማድረጉ ጥሩ ነው። ባህርዳርን እንደበፊቱ ለድብደባ መነሻ ላያደርጉ ይችላሉ። ምንአልባትም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ጀቶቹ መነሻቸውን የአክሱም አየር ማረፊያን ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
"…ካለፈው አርብ ጀምሮ በአየር ኃይል ግቢ ከኦሮሞ ተወላጅ ውጪ ያለው እያጉረመረመ ነው የሚገኘው። የማጉረምረሙ ምክንያት ደግሞ በደብረዘይት አየር ኃይል ውስጥ አሁን በሥራ ላይ ያለ ወታደር የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ ብቻ በደብረ ዘይት የቤት መሥሪያ መሬት ይሰጠው ሌሎች ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ ወዘተ ደግሞ በክልላቸው መሬት ይውሰዱ በመባሉ ምክንያት ለምን የሚል ጥያቄ ተነሥቶ ለተነሣው ጥያቄም ከላይ የመጣ መመሪያ ነው፣ ይህንን ጥያቄ ክልላችሁን ጠይቁ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
"…ሌላው ጥያቄ የሆነው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ባሌም፣ ጅማ፣ ወለጋ፣ ሀረርጌ፣ አሩሲም ሆነ ከሚሴ የተወለደ ኦሮሞ እዚያው መሬት ሲሰጠው ደብረዘይት ተወልደው የደብረ ዘይት ልጅ የሆኑትስ ምን ይደረጉ ሲባል ኦሮሞ ካልሆነ አይሰጠውም የተባለ ሲሆን እነሱስ የት ይጠይቁ ሲባልም ወታደሩ መታወቂያ ወይም መዝገቡ ላይ ባስሞላው ብሔር ክልል ሄዶ ይሰጠው በመባሉ ነው አሉ ጉርምርምታው በዝቷል የተባለው። ይሄ ጉርምርምታ ወደፊት የሚኖር ግዳጅ ላይ በእርግጠኝነት ችግር መፈጠሩ አይቀርምና ይሄን ችግር ወስዶ ከወዲሁ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል የሚሉም አሉ። ሆድ ለባሰው ማጭድ ማዋስ ማለት ነው።
"…በሌላ በኩል ሰሞኑን በባህርዳር ሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና መምሪያ መግቢያ በር ላይ 3 ምሽጎች ተሠርተዋል። በፊት የነበሩት ስለፈረሱ ሰሞኑን እንደ አዲስ ነው የተሠሩት። ከዕዙ ውስጥም በጫካው ውስጥ የኮንክሪት ምሽግ ተሠርቶ መጠናቀቁም ተነግሯል።
"…ሌላው መረጃም ከላይ የመጣ ነው በተባለ መመሪያ መሠረት ሰሞኑን የስታፍ አባላት ሳይቀሩ ተመልምለው ለግዳጅ ከፋኖ ጋር ለመዋጋት እየሄዱ ያለበት ሁኔታ መኖሩም ተሰምቷል። የተወሰኑ የሠራዊት አባላትም የመጀመሪያ የህክምና ዕርዳታ ለመስጠት ተብለው ተመልምለው ተሰብስበው መግለጫ ከተሰጣቸው በኋላ የት እንደሆነ ባላይታወቅም ወደ ግዳጅ ወጥተዋል። ነፍስ ይማር።
"…ስለምን ጉዳይ እንደሆነ መጨረሻው ባይታወቅም ሰሞኑን በተከታታይ እየተሰበሰቡ ነው ያሉት። አሁን ለጊዜው እያወሩበት ያለው የስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ መከላከያ ራሱ የታክቲክ ለውጥ ለማድረግ ማሰቡን ነው የሚያመለክተው። ይሄም የታክቲክ ለውጥ ልክ እንደ ፋኖ እኛም የጉሬላ ውጊያ ካልገጠምን በቀር በዚህ አካሄዳችን ኃይል እንጨርሳለን እያሉ ነው። የህወሓት ጉዳይ የተጀመረውም የፋኖን ሓሳብ ለመከፋፈል፣ ሕዝቡን ከአገዛዙ ጎን ለማሰለፍ ጭምር ነው። ይሄም ከሽፏል። ይከሽፋልም። በቀጣይ ፋኖዎች በምድር ሲዋጉ ከላይ ሊመጣ የሚችለውን በማሰብ ልክ እንደ ጀት፥ ድሮን፥ ሚግ ... የመሳሰሉት ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸውም ተመክሯል። እናም ፋኖዎች ድል ካደረጉ በኋላ አንዳንድ ጊዜ በስሜት ተሰብስቦ መጨፈርም ለተለያዩ ጥቃቶች ያጋልጣልና ጥንቃቄ ይደረግም ተብሏል።
"…ሌላው ደግሞ የዐማራ ሚሊሺያ እና የዐማራ አድማ ብተናን በተመለከተ ቆስለው ሲመጡ ከመከላከያ ሆስፒታል ከወታደሩ እኩል እንዳይታከሙ፣ በቀጥታ ወደ ሲቪል ህክምና ተቋማት በሪፈራል መልኩ ለብቻቸው ይታከሙ የሚል ሓሳብ ተነሥቶ ለትግበራው ዝግጅት ይደረግም ዘንድ መመሪያ መውረዱም ተነግሯል። የቆሰሉ ሚሊሻዎችና አድማ ብተናዎች ብቻ ሳይሆኑ ሲቢሉ ሕዝብም ወታደሩ ቆስሎ ሲመጣ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሕክምና አቋርጠው የሆስፒታሉን አልጋ ለቆሰሉ ወታደሮች ለቅቀው እንዲወጡ መወሰኑም ተሰምቷል። ይሄ ደግሞ ለሚሰማ እና ለሚያገናዝብ ገረድ ብአዴናም ሁላ ብልፅግና ራሱ እንደ ሸንኮራ ተጠቅሞ እየጣላቸው መሆኑን ያመለክታል።
"…በቀጣይ መከላከያ ከፋኖ ጋር ሊያደርግ የሚችለው የመጨረሻ ውጊያ በከባድ መሳሪያዎች የተጋዘ ነው የሚሆነው። እንደ ታንክ፣ መድፍ፣ ዙ 23፣ ጀት፣ ድሮን፣ ሚግ ወዘተ ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ መልኩ ሊጠቀም ይችላል። ስለሆነም ፋኖም ለዚህ የሚሆን አሪፍ እና የተሻለ ታክቲክ ይዘው ቢጠብቁ መልካም ነው።
"…በመጨረሻም ለፋኖ የተለገሰ ምክር እንዲህ የሚል ነው። ከድል በኋላ ተሰብስቦ አለመጨፈር። የተማራኪ ወታደሮችን ትጥቅ ከችፕሶች አብጠርጥሮ መፈተሽ። የፋኖ መሪዎች ስልክ እንዳይጠቀሙ ማድረግ፣ የፋኖ አባላትን የእጅ ስልክም ጠርንፎ ማስቀመጥ። ምሽት የመኝታ ስፍራዎችን መቀያየር ወዘተ ይተግብሩ ተብሏል። ለምሳሌ መከላከያ አሁን የጀመረው የአንድን አካባቢ ፋኖ በተናጥል ማጥቃት ነው የያዘው። ይሄም ተተኳሽ ለማስጨረስ የተወሰነ ውሳኔ ስለሆነ በተቻለ መጠን ብዙ ስዓት የሚወስድ ውጊያ አለማድረግ። ቢቻል አጭር ተልዕኮ፣ በአነስተኛ የሰው ኃይል፣ በአጭር ጊዜ፣ በደፈጣ ማከናወን የተሻለ አማራጭ ይሆናል። ደፈጣ፣ የሽምቅ ውጊያ ሥርዓቱን በቁሙ አክስሮ የሚቀብር ፍቱን የውጊያ ሥልት ነው።
"…እስከዚያው እነ አቢይ አሕመድ አዲስ አበባን በቀለም እና በመብራት እያሳመሩ ሕዝቡን በባዶ ሆዱ ያጭበርብሩ። ፋኖም ሥራውን ይሥራ በሀገር፣ በቀዬ በሠፈሩ። ተብሏል። ለፋኖዎች አድርሷቸው።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"…መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 1ኛ ቆሮ፥ 3-4
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።