zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከጠዋቱ 20:: ሰዓት እስከ ምሽት የተካሄደን ንትርክ ኪስ ውስጥ በተያዘና በታፈነ ሁኔታ የተቀረጸን ስብሰባ ከድምጽ ወደ ጽሑፍ መገልበጡ እንዴት እንደሚያደክም በማርያም። ደግሞ ድምጹ እንዳይለቀቅ ቀራጮቹ ያወራሉ፣ ይስቃሉ፣ ይመክራሉ፣ በሰብሳቢዎቹ ያሾፋሉ። ለአደጋ እንዳይጋለጡ እሱን መለየቱም ሲበዛ አድካሚ ነው። አሳጥሬ ነገ አቀርብላችኋለሁ። አሁን እግሬንም ላፍታታ፣ የቀን የ10 ኪሜ እርምጃዬንም ላስነካው።

• እየሄዳችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትናንቱ ስብሰባ
     ክፍል ፪

"…አደገኛ መልክ ይይዝ የነበረው የእስላሞቹና የኦርቶዶክሶቹ ጦርነት በእንጭጩ ከተቀጨ በኋላ በቀጥታ የተገባው በክልሉ የተፈጠረው የኢኮኖሚ ድቀት እንዴት ይፈታ? የሚል ነበር።

"…በግርማ ብሩ ስር የተጠረነፉት የአቢይ ኔትወርክ የሆኑት የዐማራ ባለሀብቶች እነ አሥራት ሴንቸሪ፣ እነ በላይነህ ክንዴም መናገር ጀመሩ። "ወንድሙን በመመተት ሽባ አድርጎ በቤተ አሰቀምጣል እያሉ የሚያሙትና የንግድ ተፎካካሪዎቹን በሙሉ ቀርጥፎ በልቶ ከሌላኛው አባቱ መተተኛ ነው ከሚባለው ከሴንቸሪ ሞሉ ባለቤት ጋር አሁን የዐብይ ቀኝ እጅነቱን ያረጋገጠው የዐማራው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ እንዲህ በማለት መናገር ጀመረ።

"…በላይነህ ዐማሮቹን ዞርዞር በማለት በዓይኑ ከገረመማቸው በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ "አላሠራ አላችሁኝ! አላሠራ አላችሁኝ "አሁን እኔ በክልሉ ላይ 10ሺ ሥራአጥ የዐማራ ወጣቶችን መቅጠር ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ክልሉን ሰላም በማሳጣታችሁ ምክንያት ተረጋግቼ መሥራት አልቻልኩም። ስለዚህ ሰላም ወዳለበት ሌላ ክልል ሄጄ ልሠራ ነው። በክልሉ ገንዘባችን እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አልቻልንም። ምክንያቱም ክልሉ ሰላም ስላልሆነ። ስለዚህ በቶሎ እንምከር፣ እንዘክር፣ እነዚህ ጫካ የገቡ ሽፍታዎች (የዐማራ ፋኖን መሆኑ ነው) ከያሉበት ተለቅመው ይምጡ። ከዚህ ውጪ ሌላ መፍትሔ የለም በማለት ተናግሮ ሳይጨርስ እነ አሥራት የሴንቸሪ ሞል ባለቤት በጭብጨባ አጀቡት። ባለሀብቱም በሙሉ እነ አበባው ታደሰ እንዲያዩት እጁ እስኪቀላ ድረስ አጨበጨበ።

"…አሁን ሁሉም ተሰብሳቢ መቁነጥነጥ ጀምሯል። ይሄ የተቀበረ፣ በፍርሃት፣ በይሉኝታ የተሸሸገው ዐማራነት እየፈላ፣ እየተንተከተከ መምጣት ጀመረ። ትግሬው አበባው ታደሰም…

"…መተታም የጠንቋይ ልጅ ሁላ ግን ይገርማል። ዓይኔን እያሳረፍኩ እቀጥላለሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ትናንት ማታ ቡልጉው አረመኔው አቢይ አሕመድ አሊ ሊያስወግደው በኮሬ ነጌኛ አስከብቦት እንደ ዕድል አምልጧል ነው የሚለኝ አንዱ ወፌ። ምክንያት ስለው ምክንያቱማ "ገና ለገና ወልቃይትን ለትግሬ ለመስጠት እንቅፋት ይሆንብናል ብለው ሰግተው ነው። በዚያ ላይ የኮንደምነት ዘመኑም አልቋል። እንደሸንኮራ እኛም ትግሬዎቹም መጥጠን ጨርሰነዋል። ከእንግዲህ ለማናችንም አይጠቅመንም እና ይወገድ ነው የሚሉት አሉ። ይሄ ቢወገድ ዐማራዎቹም ቢደሰቱ እንጂ የሚያዝን አይኖርም። ስለዚህ ከሰኔ 30 በፊት ከወዲሁ ይወገድና የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን የሊቀ መንበርነት ቦታ ለሚመቸን ሰው እናስረክብ ተብሎ ነው የግድያ ሙከራ የተደረገበት ነው የሚሉት። መልአከ ሞት አቢይ አህመድ እንደሁ እሱ ከመወገዱ በፊት የሚምረው አንድም ሰው የለም። አንድም አልኳችሁ። አጥፍቶአቸው ነው የሚጠፋው።

"…ይቅርታ አናጥበውኝ እኮ ነው ወፎቼ። የጀመርኩትን የትናንቱን ደም የሚያሞቅ ስብሰባ ውሎ ልቀጥል ነኝ።

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በአቢይ አሕመድ ትእዛዝ በቀጥታ በግርማ ብሩ የተጠረነፉ፣ በዳንኤል ክብረት ስር የተጠረነፉ፣ ሽመልስ አብዲሳ እና አዳነች አቤቤም ጠርንፈው የሚመሯቸው ባለ ሀብቶች አሉ። በትናንትናው ዕለት በዐፄ ምኒልክ መናገሻ ከተማ በእቴጌ ጣይቱ ስም አውጪነት የዛሬውን ስሟን ባገኘችው በአዲስ አበባ ከተማ በአዲሱ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ሚዚየም ውስጥ የዐማራ ተወላጆችን ሰብስቦ ብልፅግና የመጨረሻ ኑዛዜውን በወታደሮቹ በኩል ሲንበጫበጭ ውሏል።

"…በዶር ሒሩት ካሣው፣ በአቶ ያያአዲስ የዐማራ ክልል ኢንቨስትመንት የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊና በሌባው አቶ ምትኩ የበረከት ስምኦን ሚስት ወንድም ተዘጋጅቶ፣ በአቢይ አሕመድና በዳንኤል ክብረት በተጠረነፉ የዐማራ ባለ ሀብቶች ስፖንሰር አድራጊነት የተጠራውን ስብሰባ ነው ዛሬ ከፋፍዬ በአጭሩ የማስኮመኩማችሁ።

"…ከአዳራሹ CCTV ካሜራ በቀር ሌላ ካሜራ በሌለበት፣ ማንኛውም ተሰብሳቢ የእጅ ስልኩን በመኪና ውስጥ ትቶ እንዲገባ ተደርጎ የተመረጡና የተጠረጠሩ ባለ ሀብቶች ስልክ መኪናቸው ተከፍቶ ፋይሎቻቸው የተሰረቁበት፣ ተናጋሪዎች ስማቸውን እንዳይናገሩ የተደረገበት፣ በእነ ሙጂብ አሚኖ እና በዳንኤል ከጎንደር ተመርጠው የመጡ የሃይማኖት አባቶች የተጣሉበት፣ ትግሬው አበባው ታደሰ እና ኮሚሽነር ዘላለም፣ ጀነራል በላይ ስዩም እያንቀላፉ እየዛቱ እየተማጸኑም የመሩትን ከባለሀብቶቹ በቀር ከሰዉ ኃይለኛ ድፍረት የታየበትን ስብሰባ አስኮመኩማችኋለሁ።

"…ለሰኞ ሌላ ስብሰባ ባህርዳር ተጠርቷል። ምንአልባትም ቀሽም፣ ደካማ፣ ሽባ፣ የማይረባ ተብሎ ሲሰደብ የዋለው ብአዴንን አፍርሰው ክልሉን ከ4 ክልል በላይ አድርገው በወታደሮች ስር ሆኖ ሊያቆዩት ይሆን የሚለውንም አብረን በስሱ እናያለን። ከማክሰኞ በኋላ ግን በየቤቱ የሚያብደውን ማየት ነው።

•ዝግጁ ናችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አይደለም እዚህች ቅርብ ሳዑዲ በቁም እስር ዘብጥያ ያለው አፍቃሬ ወያኔው ሼህ አሊ አላሙዲ ይቅርና ሌላም የፈለገ ቱጃር ዲታ ለምን ከማርስ ከጁፒተር አይመጣም። የዐማራን ትግል እንደሆን ከደረሰበት ወደኋላ የሚመልሰው አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለም። ነገርኩህ ዐማሮቹ አይሰሙህም። መስሚያቸው ጥጥ ነው።

• ኧረ አይሰሙህም…😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አቢይ አሕመድ እኮ አንዳንዴ አንጀቴን ነው የሚያርሰኝ። በተለይ ያመኑትን የሚከዳበት፣ ወዳጅ አድርጎአቸው ሲያበቃ በካልቾ ጠልዞ የሚያባርርበት፣ ፍላጎታቸውን፣ ደካማና ስስብልታቸውን አስቀድሞ አውቆ በፍላጎታቸው፣ በደካማው ስስብልታቸው በኩል ገብቶ፣ ለሆዳሙ ጭድ፣ ለከርሳሙ ፋጉሎ እየሰጠ፣ ከክብራቸው፣ ከማዕረጋቸው የሚያዋርድበት መንገድ እንዴት አንጀቴን እንደሚያርሰው አትጠይቁኝ።

"…አቢይ ጭምብል ገላጭም ነው። ፌካፌካም ኢትዮጵያኒስቱን ቡድን "በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይን" እየተረተ ወደ ገደሉ ጫፍ ወስዶ፤ ገፍትሮም ወደ ገደሉ ከትቶ ስብርብር፣ እንክትክት ባያደርጋቸው ኖሮ አስባችሁታል ፈተናው ዛሬ ለዐማራው በእነዚህ በኩል እንዴት ከባድ ይሆን እንደነበር?

"…አዎ በኢትዮጵያ ስም በኢትዮጵያ ካባ ተሸሽገው፣ ተደብቀው፣ እልል ያሉ መናፍቃን የነበሩትን ሁሉ አቢይ የሚባል ኬሚካል ነው ከለራቸውን አጥቦ ማንነታቸውን የገለጠው። አቢይማ በሞት ፍርድ ሲሰቀል በሕይወት ታሪኩ ላይ ከአረመኔነቱ ጎንለጎን የብዙዎቹን ጭምብል፣ ለምድ፣ ጎጋ፣ ቆዳም የገፈፈ ተብሎ ይጻፍለታል። የትየለሌ ፌካፌካም ኢትዮጵያኒስት መሳይ አስመሳዮችን በቂጣቸው እንዘጭ አድርጎ ያሰቀመጠ ባለውለታችን ነው አቢይ።

"…በቪድዮው ላይ ከምታዩዋቸው መካከል በቅርቡ ሳይለት ሙድ ላይ ከሚቀመጡት በቀር ሁሉንም ዱዳ አድርጎልናል። ስንቱን ዝም፣ ጭጭ፣ ጮጋ በማሰኘቱም አቢይን እደመምበታለሁ። ሲሳይ አጌናን አቢይ ባይመጣ እኮ ዐማራው እንዳጨበጨበለት ሊኖር ነበር። በቢአይካ ካርሎስ ቀበሮ በኩል ለስንቱ ወርሀዊ ድርጎ እየሰፈረ በሆዳቸው ይዞ እንዳይተነፍሱ ምላሳቸውን ለጎመልን።

"…ታማኝስ እሺ ዓለማዊ ነው። የጳጳሱ ነው የገረመኝ። የአብይን አረመኔነት የማይገልፅላቸውን አምላክ ነው እንዴ የሚያመልኩት? የሚያስመልኩትስ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጅሉ ሞሮ… ዘገምተኛ የሆነ ገሌ… "ትንሽ በደል ሲደርስብህ አላለም? ትንሽ በደል መገለጫው ምንድነው? ዐማራ አምልጧል። እስከዛሬ የጋጥከው፣ ያለብከውን፣ ያሞኘኸው ይበቃል? ይልቅ ወንድ ከሆንክ ዐማራ ከእጅህ ስለወጣ ኦነግ እየረገጠው፣ እየረፈረፈው፣ እየዘረፈው ያለውን ነገድህን ጉራጌን አትርፍ።

• ትንሽ በደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ምርኮኛን በተመለከተ እኔ የራሴን ሓሳብ ሰጥቻለሁ። ቀጥሎ ደግሞ እናንተ የራሴ የምትሉትን ሓሳብ የምትተነፍሱበት ሰዓት ነው።

• እናንተስ ምን ትላላችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የምርኮኛው ብራኑ ጁላ የአረመኔው ዘንዶ የአቢይ አህመድ ገረድ ጦር በሜዳ ላይ በዐማራ ፋኖ ሲቀጠቀጥ ወደ ከተማ በመግባት በመንግሥት ሥራ፣ በባንክ ሙያዎች፣ በነጋዴዎች፣ በሆቴል ቤት ሠራተኞች እና ተጠቃሚዎች፣ በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ባነበሩ ለቀስተኞች፣ በመቃብር ቆፋሪዎች፣ በአእምሮ ህሙማን እና በአብነት ተማሪዎች ላይ የርሸና ተግባር መፈጸሙን ቢቢሲን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው።

"…ለዚህ መፍትሄው ይሄን ሥርዓተ ቢስ፣ ከከብት ከእንስሳት ያነሰ፣ የጋርዮሽ ሥርዓት ዘበኛ፣ ገረድ፣ የአቢይ አሕመድ የግል አሽከር፣ ይሄን ነውረኛ የእንስሳ ስብእና የተላበሰ፣ የማይረባ፣ የማይጠቅም፣ ህሊናው የተሸጠ፣ የቀነጨረ ቅንጭር፣ ወገን የማይለይ ደናቁርት፣ በሆዱ የሚያስብ፣ አረመኔ ጨካኝ፣ በቤተሰቡ የተረገመ፣ ጭንቅላቱን ንፍጥ የሞላው፣ ማሰብ የተሳነው፣ ንፁሐንን መለየት የማይችል፣ ደደብ የደደብ ደደብ ምርኮኛ የሚመራው አራዊት የሆነ ሠራዊት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል የሚሉ መተርጉማን ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል።

"…በቤንዚል ይሻልሃል በጥይት? በየትኛው ልግደልህ ብሎ ሰብስቦ በአደባባይ ሕዝብን የሚረሽን አረመኔ ሰው በላ ቡልጉ ጭራቅ የሆነ አራዊት ማርኮ መቀለብ በራሱ በወገን፣ በንፁሐን ሞት እንደመቀለድ ነው። በውጊያ ላይ ወታደር ከወታደር ቢገዳደል ተፈጥሮአዊ ነው። ከውጊያ ቀጠና ውጪ ያሉትን ንጹሐን የሚደፍር፣ የሚረሽን፣ የሚገድል፣ የሚጨፈጭፍ አረመኔ በምርኮ ይዞ መለፋደድ ሲበዛ ነውር ነው። ኃጢአትም፣ ግፍም፣ ወንጀልም ነው።

"…አሁን ፋኖ ኮመጨጭ ያለ ሕግ ማውጣት አለበት። የመከላከያ ወታደሮች የሚለውን ስም መቀየር አለበት። አረመኔ፣ ፅንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ጨፍጫፊ የሚል ስም ሊሰጠው ይገባል። ከጦርነት ውጪ ንፁሐን በተገደሉ ሰሞን በንፁሐን ዐማሮች ምትክ የሚማርከው እንደሌለ ማወጅ አለበት። የብልፅግና ባለሥልጣናት በአቢይ አሕመድ ገረዶች በተገደሉ፣ በተረሸኑት ንጹሓን ምትክ ዋጋቸውን ማግኘት አለባቸው። በቀል በእጥፍ መጨመር አለበት። ንፁሐንን፣ እናቶችን፣ ሴቶችን፣ መምህራንን የሚጨፈጭፍ አራዊት ሠራዊት እሱም ያለ ምህረት ያለርህራሄ መጨፍጨፍ አለበት። ደምን በደም እያጠሩ መሄድ ነው።

"…ፋኖም በአራዊቱ ላይ ልክ እንደ አራዊቱ የጁላ ሠራዊት አረመኔ ካልሆነ በቀር እየቀለደቡት ሊኖሩ ነው። ጥይት የጨረሰ ምርኮኛ ምርኮኛ አይደለም። ንፁሐንን ሲጨፈጭፍ ውሎ ሲማረክ ተሳስቼ ነው የሚል አረመኔ ወታደር ይዞ መቀለብ እንደ ወንጀል መቆጠር አለበት። ኦሮሞ ስለሆነ፣ ደቡብ ስለሆነ፣ ፖለቲካ ለመሥራት ሲባል ዐማራን በመጨፍጨፍ ደክሞት የተማረከን ጨፍጫፊ አረመኔ ልቡሰ ሥጋ ጋኔል ነፍሰ ገዳይ አራጅ ሰዉነቱን አጥቦ፣ ልብስ ቀይሮ፣ አብልቶ እና አጠጥቶ፣ መታወቂያ አሠርቶ ፈትቶ መልቀቅ እንደገና ግደለን፣ ጨፍጭፈን ብሎ እንደ መላክ ያለ ነው። የፋኖ ዥልነት ይብቃ።

"…ሰሞኑን በሸዋ ከሞት ተርፈው የተማረኩ ወታደሮችን ቪድዮ ተልኮልኝ እያየሁ ነበር። ቆርጬ ዛሬ የለጠፍኩላችሁን ማለት ነው። ሙሉውን እሁድ በመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ እለቅላችኋለሁ። ወታደር የተባሉት በሙሉ ከየት ነው የመጣኸው ሲባል ከመተከል፣ ከምሥራቅ ጎጃም፣ ከወለጋ፣ ከሸዋ ከባኮ አካባቢ አካባቢ የመጡ ወታደሮች ናቸው። ንፁሐንን ጨፍጭፎ፣ ዘርፎ በውጊያ የሚገደለው ተገድሎ ከተማረኩ በኋላ ቀሪዎቹ እየለመኑ፣ እየተማጸኑ እጃቸውን ለዐማራ ፋኖ ሰጥተዋል። ምርኮኛው ራሱ የዐማራ ፋኖን እንክብካቤ ቃል በቃል "እንደ አየር መንገድ ያለ እንክብካቤ ነው" ሲል ነው የምታደመጡት። ፋኖ ማወቅ ያለበት ከስንት ጭቅጨቃ በኋላ አንድ ሁለት ተብሎ ተለምኖ ለፋኖ ቆሎ መግዣ ተብሎ የሚመጣን ዶላር አረመኔ አራጅ ለመቀለብ ከሆነ የሚያውለው ይሄ ልክ አይመጣም። ይታሰብበት።

"…የገዳዩ ወታደር በሥልጠና ወቅት የሚሰጠው መመሪያ እንዳለም ተሰምቷል። ዐማራን ጨፍጭፉት፣ ረሽኑት፣ ግደሉት፣ ዝረፉት፣ አሰቃዩት፣ አስመርሩት፣ በመንግሥት በኩል የሚጠይቃችሁ የለም። ምንአልባት በፋኖ በኩል እንደ አጋጣሚ ብትማረኩ እንኳ እናንተ መንግሥት አስገድዶን ነው፣ ተገድደን ነው፣ ተጸጽቻለሁ፣ ዐማራ ጀግና ነው፣ ፋኖ አደገኛ ነው፣ ከባድ ነው እያላችሁ አጃጅሏቸው፣ ፋኖ ለፖለቲካ ሲል ተንከባክቦ ይለቃችኋል ነው የሚባሉት አሉ። ሰምታችኋል። ጎጃሜ ነኝ ብሎ ሸዋ ላይ፣ ሸዋ ነኝ ብሎ ጎጃም፣ ጎንደሬ ነኝ ብሎ ወሎ፣ ወሎዬ ነኝ ብሎ ጎንደር፣ ብቻ ዐማራ ሆኖ ከዚህ አራጅ ፀረ ዐማራ አገዛዝ ጋር ተሰልፎ ሲወጋህ የምታገኘውን እንዴት ነው ማስተናገድ ያለብህ? በወለጋ ሲያርድህ የከረመውን አረመኔ ወሎ ላይ ቤትህ መጥቶ ሲገድልህ ውሎ ጥይት ሲጨርስ ተማረከ ነው የሚባለው? እህእ

"…ሸዋ ላይ ሲጨፈጭፍ ከርሞ የሸዋ ፋኖ ፈትቶ የሚለቀው የአቢይ አሕመድ ወታደር በሌላ ዙር ወደ ጎጃም ሄዶ የጎጃም ዐማራን ይጨፈጭፋል። ጎንደር ላይ የተለቀቀ ወሎ ላይ ተሰልፎ እንደ አዲስ ይጨፈጭፋል። ጎጃም ውስጥ ሁለቴ የተማረከ ኦሮሙማ አለ። ምን ማለት ነው እንዴ? ጅጋ ላይ ንፁሐንን የገደሉት፣ ሞጣ ላይ ዐማሮችን የረሸኑት ይሄኔ ከሸዋ፣ ከወሎ፣ ከጎንደር ተማርከው የተለቀቁ አረመኔዎች ይሆናሉ። ጦርነቱ በዐማራ ክልል እንዲረዝም ከሚያደርገው አንዱ የፋኖ ርህራሄ ነው። ፋኖ ቀልድ የያዘ ሁላ ነው የሚመስለው። ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ዓየነት አካሄድ ምንድነው? መከላከያው የቆሰለ ፋኖ ከሆስፒታል አውጥቶ እየረሸነ የፋኖ ጨፍጫፊ ገዳዩን ማርኮ ነጭ ጤፍ፣ ዳቦ እየመገበ፣ ጠላ እና ወተት ኮካኮላ እያጠጣ መቀለብ ይሄ ፋርነት እንጂ ሰብዓዊነትም አይደለም። በፍጹም።

"…ሁለት ነገር። ብአዴንን በጀመሩት መንገድ ማጽዳት። ንፁሐንን የገደሉ፣ የረሸኑ የብራኑ ጁላን አረመኔ ነፍሰ በላ አራዊትን በምርኮ ስም ይዞ አለመንከባከብ። ምርኮኛውን መንገድ ማሠራት፣ የገበሬ እርሻ ማሳረስ፣ አፈር ከደቼ ማብላት። አለቀ። ፍፁም እንደነሱ አረመኔ መሆን ነው። አንተ ተንከባከብከው አልተንከባከብከው በእሱ እንደሆን አትመረቅ፣ አትመሰገን፣ አትሸለም። ያው ስምህ ዐማራ ነው። ፅንፈኛ ነው። አሸባሪ ነው። ዘራፊ ነው። ፀረ ሰላም ነው። እና ምንአባክ ሆነህ ነው የእናትህን አራጅ፣ የወንድምህን ገዳይ፣ የእህትህንና የሚስትህን ደፋሪ አረመኔ ነውረኛ ዓለሙ የመሰከረለትን የቀን ጅብ የምትቀልበው? የምትንከባከበው? ምናባህ ሆነህ ነው አልኩህ ንገረኝ።

"…እስላሙ ፋኖ እንደ ሼክ የሚያደርግህን ነገር አቁም። ኦርቶዶክሱ ፋኖም ልክ እንደ ባህታዊ፣ እንደመናኝ የሚያጫውትህን አጉል መንፈሳዊነት አቁም። ጨከን በል። ዘርህን እየጨፈጨፈ፣ እየጨረሰ ካለ አረመኔ ጋር የምን መሞዳሞድ ነው? ከሆቴል ከሚመገቡበት ማእድ ላይ አንሥቶ ንፁሐንን ከረሸነ አረመኔ ጋር የምን ምርኮ፣ የምን እንክብካቤ ነው። በአደባባይ ንፁሐንን ያረደ አረመኔ ልብሱን ቀይረህ፣ ሰውነቱን አጥበህ፣ የጣመ የላመ መግበህ፣ መታወቂያ አውጥተህ፣ የኪስ ገንዘብ ሁላ ሰጥተህ የምትሸኘው አጉል ጻድቅ ለመሆን ነው? መሳቂያ መሳለቂያ ነው የምትሆነው። ራሱ ወታደሩ ይስቅብሃል። ምን ዓይነት የሌለ ዥልጥ ዥሎች ናቸው ነው የሚልህ። ማፈሪያ አትሁኑ።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ" ማር16፥19

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ልመጣ ነኝ…

"…ዕለቱ ማክሰኞም አይደል? አዎ ማክሰኞ ነው። በዕለተ ማክሰኞ ደግሞ ቀጠሮአችን በቲክቶክ መንደራችን መሆኑ ይታወቃል። እናም በቀጠሮአችን መሠረት እኔ ወደዚያው ወደ መንደራችን የሚወስደኝን መሂና እየጠበቅኩ ነው። ከጥቂት ደቂቃዎችም በኋላ እደርሳለሁ ብዬ አስባለሁ። እናንተም ጉዞ ጀምሩ። እዚያው እንገናኝ።

"…በተመረጡ ርዕሶች ዙሪያ ነጭ ነጯን እንነጋገራለን። እውነትን በድፍረት መናገርን እንለማመዳለን። የሚተች ያለ ምህረት ይተቻል። የሚመሰገንም ያለ ሰቀቀን ይመሰገናል። እኔ እንደሁ ቋሚ ወዳጅም፣ ቋሚ ጠላትም ስለሌለኝ በሚልዮኖች ፊት የልቤን ተናግሬ ተንፍሼ ያለ ጨጓራ ህመም ፏ ብዬ በጤና እኖራለሁ፣ የሰላም እንቅልፍም እተኛለሁ።

"…የምትሰድቡኝ፣ የምትወቅሱኝ፣ የምትዝቱ፣ የምታስፈራሩ፣ የምትፎክሩብኝ ሁላ ልክ አስገባችሁ ዘንድ፣ አስተነፍሳችሁ ዘንድ በቲክቶክ መንደሬ እንገናኝ። ያለ እናንተ እኔ ጀት አልሆንምና አትጥፉብኝ። የትግሬ ነፃ አውጪዋ የሂዊ፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ የኦህዴድ፣ የኦነግ፣ የኦፌኮ፣ የብልፅግና፣ የዐማራው ገተት ብአዴን፣ የኦሮሞ ወሃቢስቶች፣ የብልጽግና ወንጌል ሠራዊቶች ምላሳችሁን አሹላችሁ ጠብቁኝ።

👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …የመግዛት ሕልማቸው ይጨናገፍ እንዴ? አዎ ዐማራን ሊረዳ ይችላል ብዬ የማስበው አንድም ሀገር ምድር ላይ የለም። አክባሪም፣ ልነጠፍልህ ባይም የሚመጣው ራስህን ስታስከብር ብቻ ነው። ያለበለዚያ ስታለቅስ ሶፍት ስጠው ይልሃል ሽመልስ አብዲሳ።

"…ኤርትራም ትፈራዋለች። እስራኤል ዋነኛ የዐማራ ጠላት ናት። አሜሪካና አውሮጳን እያየህ ነው። እነ ራሽያ በኦርቶዶክስነቱ የመርዳት ፍላጎት ቢኖራቸውም ዐማራን ወክሎ የሚያናግራቸው የነበረው ፀረ ዐማራው አሮጌ ጅቡ ደመቀ መኮንን ነው። አሁን እንኳ በሩሲያ ብልፅግና ወክሎ የላካቸው ሱማሌውን አደም ፋራህ፣ ኦሮሙማውን ኦቦ አዲሱን እና ኩሻንኩሽ አገው ሸንጎ የወያኔ አድራሽ ፈረሱን አቶ ሰማ ጥሩነህን ነው። በየት በኩል ዐማራውን ያግኙት? ዐማራ ላይ ወጥመዱ ከባድ ነው። ነገር ግን ትናንት እንዳሸነፈው ዛሬም ያለ ጥርጥር ያሸንፋል። የሚያስከብርህ ነፍጥህ ነው። አልቃሻን ማንም አያከብረውም። ሁሉ ነው የሚንቀው። ስለዚህ ለመከበር ፈርጠም ብሎ ገግሞ መመከት እና ማሸነፍ ብቻ ነው።

"…የዐማራ ልጆች በኢትዮጵያዊነት ቅመም የተሠሩ ናቸው። ሳይንቲስት ቢሆን፣ ምን ፕሮፌሰር፣ ኢንጂነር ቢሆን፣ ቱጃር ዲታ ኢንቬስተር ቢሆን የዐማራ ሰው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ እስቲ እኔም እንደ ትግሬው ቴዎድሮስ አድሃኖም ለሚጨፈጨፈው ወገኔ ዐማራ ነኝ ብዬ ድምጼን ላሰማ አይልም። በዚህ ጠባዩና ዐመሉ ምክንያት የበግ ለምድ በለበሱ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ እንደ ግንቦቴዎች ባሉ ጨበርበርቱ ሁላ ሲጭበረበር ይኖራል። ይሄን ዐማራ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እያሳዩ ይገርፉታል። ይወቁታል። ያልቡታል። ኪሱን ያረቁቱታል። እናም ይሄን ለዐራጁ ቢለዋ መግዣ የሚያዋጣ ዐማራ ዐማራ ለማድረግ ማገዶ ይፈጃል። ብዙ ማገዶ ነው የሚፈጀው። ይሄ ዐማራ እንደ ትግሬና ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች በራሱ ነገድ መኩራትና ነገዱን ከተጋረጠበት አደጋ ለማላቀቅ ከጉራጌው ብራኑ ነጋ፣ ከኦሮሞው አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከደቡቤው ኤፍሬም ማዴቦ፣ ከእነ ዮናስ ብሩ፣ ከትግሬው ነአምን ዘለቀ ወዘተረፈ ለማላቀቅ ብዙ ጸሎት ከስግደት ጋር፣ ምህላና ሱባኤ ከጸበል ጋር ሁላ ያስፈልጋል። ዐማራነቱን አድኖ የትም የማትሄድበትን ኢትዮጵያን መታደግ ሲችል ዘሩን አይኑ እያየ እንደ ጨው ሲሟሟ ይመለከታል። አቢይ አህመድ ራሱ እኮ አሁንም ኢትዮጵያ ሲለው መቅኔው ፍስስ የሚልበት ዐማራ የትየለሌ ነው። ይሄ ሁሉ ዐማራ ወደ ቀልቡ ተመልሶ ልክ እንደ ትግሬና ኦሮሞ በአንድ መምከር ሲጀምር አስባችሁታል? አይደለም ለዐማራ ለአፍሪቃ ይተርፋል ባይ ነኝ።

"…እናም የዐማራ ፋኖን በገንዘብ፣ በጸሎት፣ በሓሳብ፣ በሞራል፣ ስንቅና ትጥቅ ሳትረዳው እህ ብለህ አምጠህ ድል ውለድ ማለት ተገቢ አይደለም። ከዳር ቁጭ ብለህ የክረምት ጫማ፣ የዝናብ ልብስ ሳትገዛለት እንዲሁ አሜሪካ፣ አውሮጳ እና አዲስ አበባ የሞቀ ቤትህ ውስጥ ተቀምጠህ አስተያየት ለመስጠት መላላጡ አይነፋም። የግል ፋኖ አቋቁሞ መንግሥት ለመሆን የሚላላጥ ዐማራ ነኝ ባይ አሞራ ባለበት ሀገር። ፋኖን ከፋኖ እያበላለጠ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች ለመግዛት ጎፈንድሚ የሚከፍት ዐማራ ነኝ ባይ ሰገራ በበዛበት ዓለም የዐማራን ፋኖን፣ በራስ አቅም በፈጣሪና በጥቂት ልበ ብርሃን፣ አርቆ አሳቦ ዐማሮች ድጋፍ እዚህ የደረሰውን ትግል ማጣጣል አይገባም።

• ተወደደም ተጠላም። ተፈለገም አልተፈለገም ዐማራ ያሸንፋል። የግዱን ያሸንፋል። ወዶ ሳይሆን ተገድዶ ያሸንፋል። አለቀ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በአካልም ሆነ በሥነ ልቦና በሚገባ ተዘጋጅቶ፣ ሠልጥኖ እየገሰገሰ ወደፊት በመምጣት ላይ ያለው የዐማራ ትግል እጅግ አስፈሪም ልብ የሚያሞቅም ነው። ከብዙ ትእግስት በኋላ የተቀጣጠለው የዐማራ ትግል ላይበርድ ግለቱን ጨምሮ መሰረቱን በማጠንከር እየገዘፈ በመገለጥ ላይ ነው። የዚያኑ ያህል ደግሞ በመረጃ እጦት ሳይሆን በዳተኝነት፣ በስንፍና፣ በአድርባይነት፣ በባንዳነት ቀሽም እንቅልፋም ዳተኛ በመሆኑ እየመጣ ላለው ዐማራ መር ሀገራዊ ለውጥ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በኦሮሞ ነፃ አውጪ እግር ስር የትግሬ ነፃ አውጪን ፕሮፓጋንዳ እየተጋተ ዝፍዝፍ ብሎ የተቀመጠው ዐማራም ደግሞ የትየለሌ ነው። ይሄኛው ዓይነቱ ዐማራ በጊዜ ካልነቃና ካልተዘጋጀ በቀር ገሀነመ እሳትን የሚያስንቅ መጪ ጊዜ ከፊቱ ይጠብቀዋል። አሁን በዐማራ ፋኖ የቆሰለው አውሬ ፍላጎቴን ማሳካት ካልቻልኩማ የምወጋውን ፋኖ፣ ብረት ያነሣብኝ ዐማራ መደምሰስ ካቃተኝማ፣ በክልሌ ውስጥ ያለውንና በእጁ ማረሻ እና ቀንበር ይዞ አፈር ገፍቶ ኗሪውን ድምጥማጡን አጠፋለሁ በማለት ሩዋንዳ ተመላልሶ ባገኘው ልምድ መሠረት የኦሮሞን ልዩ ኃይል የመከላከያ ልብስ በማልበስ ጭፍጨፋውን ያከበደዋል። ስለዚህ ዳተኛው ዐማራ ከዚህ ጭፍጨፋ ለመዳን መፍትሄው የግድ መዘጋጀት ነው።

"…በባለፈው አንድ ዓመቱ የዐማራ ትግል እና ጉዞ ብዙ አመርቂ ድሎች ተገኝተዋል። ተመዝግበዋልም። ስህተት እየታረመ፣ እየወደቀ እየተነሣ ዐማራው ዓለም አቀፍ ትኩረት የሚስብ ትግል አካሂዷል። ቢያንስ ቢያንስ ዜጎች በሙሉ የዐማራ ተዋጊ የሌለበት፣ የዐማራ ሕዝብ ድጋፍ የሌለው መከላከያ እግሩ ቄጤማ፣ ዓይኑ ጨለማ እንደሆነም አሳይቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ የብረት አጥሩ ዐማራው እንደነበረም ዓለም ሁሉ መስክሯል። ዐማራም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ እስቲ መከራዬን ቢያቀልልኝ በማለት እንደነሱ እኔም መብቴን ያላከበረልኝን መንግሥት ተብዬ ኮተታም አራጅ ነፍሰ ገዳይ አረመኔ ላይ ልተኩስና ልሞክረው ብሎ ተኩሶ ሞክሮም ጣፋጩን የድል ፍሬ ቀምሶ አጣጥሞታል። ኦቦ ብራኑ ጁላ እና አበባው ታደሰ የናቁት፣ በሳምንት ውስጥ ቀበቶውን እናስፈታዋለን ብለው ያቅራሩበት ዐማራ ጭራሽ እንኳን ቀበቶ ሊፈታ እነሱኑ ሽንት በሽንት፣ ቅዘን በቅዘን አድርጎ ፍርክርካቸውን አውጥቶታል።

"…የተበታተነው፣ ፍላጎተ ብዙው፣ መሪ አልባ የነበረው የዐማራ ትግል በጊዜ ሂደት ወደ አንድነት እየመጣ ነው። መሪ አልባው ትግልም በእሳት የተፈተኑ መሪዎችን አምጦ እየወለደ ነው። መሪ መሳይ ፌካ ፌካም አስመሳይ አርቴፊሻል መሪ ነን ባዮችን እንኳ የሚለይበት መነፅር አጥልቆ በድፍረት መሪዎቹን ለይቶ ማየት እየጀመረ ነው። ባጣ ቆየኝ የነበረው ዐማራ አሁን እንደዚያ የሚሆን ክበብ መፍጠሪያ ቦታ ለማንም ለመተው የማይችል፣ የማይፈቅድም ሆኖ ነው የተገኘው። መከበር በከንፈር፣ ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል እያለ ዕድሜ ዘመኑን ሲተርት የነበረው ዐማራ ነፍጠኛ እያሉ ክፍት አፋቸውን ይከፍቱበት የነበሩትን ንፍጣሞችን በነፍጡ ማናፈጥ፣ ቅዘናሞችን ማስቀዘን፣ ሽንታሞችን ሽንት በሽንት ማድረግ መጀመሩን ሁሉም ዐውቋል። ጃዋር እንኳ ቢጨንቀው በዐማራ ክልል ያለውን እብደት በቶሎ አስቁሙ እስከማለት አስደርሷል። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ስለ ዐማራ ምንአባቱ አገባው?

"…ልጅ ያሬድ የተባለ ክፍት አፍ እና ፓስተር ከፍያለው የተባለ ገተት ዘብጥያ ወርደው ከመጡ በኋላ በርቶላቸው ኦርቶዶክስን እንደ ሃይማኖት፣ ዐማራን እንደ ነገድ አክብረው ሳይሳቀቁ መናገር መጀመራቸውን በማየቴ አምላኬን አመስግኘዋለሁ። ምንአለበት እስር ቤት ሳንገባ ይሄ መገለጥ ቢሆንል ኖሮ፣ ለሁለት ሦስት ሰዎች መልስ እንሰጣለን ብለን ታላቁን፣ የተከበረውን የዐማራ ሕዝብ በማዋረዳችን፣ በመስደባችን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለው ሲጸጸቱ እንደማየት ምን የሚያስደስት ነገር አለ? አንገቱን የደፋው ዐማራ በሙሉ አንገቱን ቀና ማድረግ የጀመረው አሁን በፋኖ ትግል ነው። ትግሬ በወያኔ፣ ኦሮሞ በኦነግ እንደሚመካው ሁሉ ዐማራም በስተመጨረሻ ከላይ ከሰማያት ባለው በፈጣሪው በምድር ደግሞ በልጆቹ ክንድ በነፍጠኞቹ ፋኖዎች መመካት ጀምሯል። ተመስገን ነው ዐማራም እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ወጉ ደርሶት አንተ ማነህ? ሲባል ዐማራ ማነህ? ዐማራ ነኝ ማለት ጀምሯል።

"…እስቲ ትናንት አንድ አስተያየት ሰጪ በእኔ ፔጅ ላይ ያነሣውን ሓሳብ እዚህ ጋር ላምጣውና ርዕሰ አንቀጼን ላድምቅበት። አስተያየት ሰጪው "ቢታሰብበት መልካም ነው" በማለት ነበር ሓሳቡን ያካፈለን። ስለቀጣይ የዐማራ ትግል እንዲህ ቢሆን ብሎ ነበር ጥቆማም፣ ምክርም የራሴ ነው ያለውን ሓሳብ የለገሰው። እሱን እያየን እንቀጥል። 

1.የዐማራ ሕዝብ ትግል አንድ ዓመት ሙሉ የኦህዴድን አጀንዳ ለማክሸፍ ከመሮጥ ያለፈ አጀንዳ ሰጪና ውስብስብ የውጊያና የስለላ ዕቅዶችን በማውጣት ለኦህዴድ ራስ ምታት መሆን ያልቻለው ለምንድነው?፥ የኦህዴድ ሰራዊት ባለፈው አንድ ዓመት ብዙ ወታደራዊ ስልት ተጠቅማል(የፈጠራ ወሬ ተጠቋሟል፥ዐማራ እርስ በርሱ የሚያደርገውን የምቀኝነት አባዜ ተጠቅሞ ብዙ ፕሮፓጋንዳ ሠርቷል፥ በስልክ ትራክ በማድረግ ጥቃት ፈጽሟል፥ ዐማራ የሴት ሱስ አለበት በማለት ሴት ሰላዮችን አሰማርቷል፥ ከድተው የመጡ መስለው የፋኖ መሪዎችን እንዲገድሉ የራሱን ቅጥረኞች አስርጎ ለማስገባት ሞክሯል፥ የፋኖ ቤተሰብ ናቸው የተባሉትን አግቷል፥ ገድሏል፥ ዘርፏል፥ በሌሊት ኔትወርክ አጥፍቶ ጥቃት መሰንዘር ጀምሯል፥ ከትልልቅ፥ ከተሞች ወደ ገጠር ቀበሌዎች በመሄድ መዋጋት ጀምሯል። ዛሬ ላይ እንደ ራሽያው መሪ ቪላድሚር ፑቲን ዐማራ ሆዳም ነው ከሚለው አስተሳሰብ ተነሥቶ በቢልቃጥ መርዝ የያዙ ሰላዮችን በየምግብ ቤቱ አሰማርቷል። ይህ ተሞክሮ ህወሓት በስምንት ወራቱ ጦርነት በኦህዴድ ሰራዊት ላይ ተጠቅሞታል ሲባል ነበር። ኦህዴድ ከመምህሩ ትምህርት በሚገባ የወሰደ ይመስላል። በአንጻሩ የዐማራ ታጋዮች የኦህዴድ ሰራዊት ወዳሉበት ሲሄድባቸው ከመዋጋት ያለፈ ይህ ነው የሚባል አንድም የውጊያ/የስለላ/የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲያደርጉ አልታዩም። የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

"…አስተያየት  ሰጪው ያሉት ሁሉ እውነት ነው። ነገር ግን የዘነጉት ነገር ባለ ቢልዮን ዶላር በጀት ባለቤቱን፣ ባለ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ባለቤቱን፣ ባለ ቢሮክራሲው በሙሉ በእጁ ያለውን አገዛዝ እና ገና እንደተወለደ ሕጻን ከዚያም ከዚህም ተጠረቃቅሞ አገዛዙን በዲሞፍተር፣ በምንሽር፣ በክላሽና በፍልጥ፣ በድንጋይ የገጠመውን ፋኖ በዚህ መጠን ይሄን ይሄን አላሳካህም ተብሎ ሊወቀስበት የሚችል ምክንያት እንደሌለ ዘንግተዋል። ተዋጊው ፋኖ ዐማራ ይሁን አይሁን ማጣራቱ በራሱ ፍዳ እኮ ነው። ለዘር ቦለጢቃው አዲስ የሆነው ዐማራ እንደ ትግሬና ኦሮሞ ዘረኞች በዘረኝነት ፐርፌክት እስኪሆን ጊዜ እንደሚወስድበት ሊታወቅ ይገባል። ወታደራዊ ሥልጠና ገና አሁን ነው እየተሰጠ ያለው። ዐማራ ሀገራዊ ቁመና ያለው ተዋጊ ለመፍጠር ገና አሁን ነው ፍዳውን እየበላ ያለው። በተፈጥሮው ቃታ ስቦ መተኮስ የማያቅተው  ዐማራ አሁን ገና ነው መተኮስ ብቻውን አዋጭ አይደለም ብሎ ሳይንሳዊ ውትድርና ለዐማራ ወጣቶች በሙሉ መስጠት የጀመረው። ይህን ሲያደርግ በአንድ እጁ እያረሰ፣ በሌላው እየሰለጠነ፣ በሌላው የኦሮሙማውን ጦር እየመከተ ነው። ይሄ ዘላለመዓለሙን እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ስለመገንጠል ሳያስብ ኢትዮጵያን እያለ የኖረ ነገድ በአንድ ጊዜ ከተደራጁት ጋር ማነፃፀሩ ተገቢ አይደለም። 👇ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    መልክአ  ኢየሱስ

"…ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ
ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ
ኢየሱስ ከርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ
ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ
ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰከ ፈኑ ። "

ትርጉም…

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
ምጥቀቱ ለማይመረመር ዕርገትህ ሰላምታ ይገባል በአባትህ ቀኝ ለመቀመጥህም ክብር ይገባል
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ
በአንተ ለሚያምኑና ለሚተማመኑ ሁሉ
የተቀደሱና ንጹሓን ይሆኑ ዘንድ እንደ በረዶ የሚያነፃ  እንደ ውኃ የሚያጠራ ካንተ ዘንድ የሚገኝ መንፈስህን ላክላቸው።

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትናንቱ ስብሰባ
     ክፍል ፬

"…አሁን ሁሉም ተሰብሳቢ መቁነጥነጥ ጀምሯል። ይሄ የተቀበረ፣ በፍርሃት፣ በይሉኝታ የተሸሸገው ዐማራነት እየፈላ፣ እየተንተከተከ መምጣት ጀመረ። ትግሬው አበባው ታደሰም ብዬ ነበር ያቆምኩት እቀጥላለሁ። "…ትግሬው አበባው ታደሰም አለ "ዛሬ የምንወያየውን እኔ ራሴ የመወሰን መብትም ሥልጣንም አለኝ። እናንተም ነጭ ነጯን ሳትፈሩ ተናገሩ ብሎ በመናገሩም ሊፈትኑት በሚመስል መልኩ አንደኛው ዐማራ ተነሣ። ተነሣናም ስሙ አለ… ስሙ የዚህ ሁሉ በክልሉ ዋነኛ ችግር ተጠያቂው አንደኛው ከፊት ለፊታችን ያለኸው ራስህ ጄነራል አበባው ታደሰ ነህ።

"…ሁለተኛው የክልላችን ችግር ደግሞ አለ ተናጋሪው ከአንተ ጋር በክልሉ ዙሪያ የሚሠሩ ፖለቲከኞች ናቸው። ተነሥ ታጠቅ፣ ዝመት፣ ዘምተህ የማረከውን ታንክም ቢሆን ለግልህ ትወስደው ዘንድ ታውጇል ያለውን ሰው ሥልጣን ሰጥታችሁ፣ ወደ ፌደራል አምጥታችሁት ስታበቁ የምን መሣሪያ ፍቱ ብሎ እየዬ ነው? ወልቃይት ከተነካ ሽጉጤን እጠጣለሁ ያለው ሰው አሁን የት ነው ያለው? የክልሉ መሪ ፖለቲከኞችም ልምሻ የያዘው፣ ልፍስፍስ፣ በራሱ የማይቆም ሽባ የሆነ ነው። ሆድአደር፣ ድሮ እነዚያን ሲሸከም የኖረ፣ አሁንም አሁን ያሉትን የሚሸከም፣ የሚሸከመው በመብዛቱ የተነሣ ቁጥራቸው በዛበት መሰለኝ…  ብሎ ሲናገር አዳራሹ በሳቅ ተሞላ።

"…ከተናጋሪው ንግግር በኋላ አበባው ታደሰም መዘገበው። ደመራው ወዴት እየወደቀ እንደሆነም ገባው። ሌላኛው የሴት እሳተ ነበልባል የሆነች እህት ተነሣች። ተነሣችናም በድፍረት መናገር ጀመረች። የፋኖን ስም ማጠልሸት ወንጀል ነው። የፋኖን ስም ማጠልሸትን ልንፈቅድ አይገባም። ፋኖነት የዐማራ የተከበረ እሴት ነው። ፋኖ ከጣልያን ጊዜ ጀምሮ ሀገር የታደገ ነው። አሁን እንኳ በትግሬዎቹ በተከበባችሁ ጊዜ ደርሶ የታደጋችሁ ነው። ነፍሳችሁን ያተረፈ ነው። ከመከላከያ ጋር ዘምቶ ድል ያደረገ ነው። ጀግንነቱን ስትመሰክሩ የነበራችሁ ናችሁ። ፋኖን ጫካ እንዲገባ ያደረጋችሁት እናንተው ናችሁ በማለት ቀወጠችው።

"…የዐማሮቹ ወደ አንድ አቋም መጥቶ በድፍረት መናገር መድረኩ ላይ ያሉትን አደነባበራቸው። ወደ አዲስ አበባ ለመግባት አንድ ሚልዮን ሁለት ሚልዮን ክፈል ሲባል የነበረ ሕዝብ፣ ሻሸመኔ ሲታረድ፣ ወለጋ ሲጨፈጨፍ፣ መተከል በአንድ ጉድጋድ በግሬደር ሲቀበር የት ነበራችሁ? በደኖ አልቀረ፣ አርባባ ጉጉ አልቀረ ዐማራ ሲታረድ የኖረ እኮ ነው። ቡራዩ ላይ የጋሞጎፋ ልጆች፣ የጉራጌና የደቡብ ልጆች ሲታረዱ የት ነበራችሁ? ዐማራ ብዙ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቆ ሲለምናችሁ፣ ይሄ የመጨረሻ ሰልፋችን ነው አልያ ሰልፍ ሳይሆን ሰይፍ ነው የምናነሳው ሲል ምነው አላወያያችሁ? ደግሞስ በሳምንት ውስጥ ትጥቁን እናስፈታዋለን ብላችሁ ስታበቁ በአንድ ዓመትም ማስፈታት ሲያቅታችሁ እኛን ሰብስባችሁ ምን አድርጉ ነው የምትሉን? በማለት ወጥረው ያዙ… አይ ዐማራ…

"…ለሽንት መውጣት የለ፣ መድኃኒት ልውሰድ ማለት የለ፣ ወይ ፍንክች። ጀነራሎቹ ደም ሥራቸው እየተገታተረ፣ የሴንቸሪ ሞል ባለቤት እየበሰጨው፣ እነ በላይነህ ክንዴ እየነደዳቸው፣ ዶር ሂሩት ፊቷ በርበሬ እየመሰለ መጣ። በዚህ መሃል የወልድያው ተወላጅ፣ የሼህ አላሙዲን ጓደኛ ዶር አረጋ ንግግር ለማድረግ ዕድል ስለተሰጣቸው ተነሡ።

"…ትግሬው አበባባው ታደሰም አይኑን አፍጥጦ ወደታች መመልከቱን ቀጠለ… አረፍ እያልኩ እቀጥልላችኋለሁ። መጣሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትናንቱ ስብሰባ
     ክፍል ፪

"…ያየህ አዲስ እና ምትኩ በየነ፣ ሌሎችንም በስም የምጠቅሳቸውን ስልካቸውን እና ፎቶአቸውን ብናገኘው መልካም ነበር። ዐማራ ደውሎ ምነው? ምነው? ምነው ምን በደልናችሁ ብሎ በጨዋ ደንብ እየደወለ እንዲያናግራቸው ብዬ ነው። ተባበሩኝ እና ላስተዋውቃቸው። ወደ ስብሰባው እንግባ።

"…በእነ ሙጂብ አሚኖ የሚመሩት እስላሞችና በእነ ዳንኤል ክብረት የሚዘወሩት ኦርቶዶክሶች ሁለት ፅንፈኛ የብልፅግና ቢንዚን አርከፍክፎ እሳት አንዳጆች መጥተዋል። በግራና በቀኝም ተሰድረዋል። ትግሬው ጀነራል አበባው የመናገር እድል የሚሰጠው ደግሞ ለሚፈልገው ሰው ነው። ያውም ስም እየጠራ። ለዐማራ ትግሬ ዳኛ ሲሆን ፈጣሪ ያሳያችሁ።

"…የመጀመሪያው ተናጋሪ ከጎንደር የመጣው ፀረ ዐማራ የእነ ሙጂብ አሚኖ እስላም ሺኪ ሆኑ። ስማቸው የማይነገረው ሼኪ ቀጠሉ ቀጠሉና የዐማራ ሰላም የደፈረሰበትን፣ ክልሉ ሰላም ያጣበትን ምክንያት መናገር ጀመሩ። "ይሄ ችግር በዋነኛነት የመጣው እስላም በክልሉ አይኑር ተብሎ፣ መስጊድ ፈርሶ ተቃጥሎ፣ የሃይማኖት መሪዎቻችንና ሙኢሚኖቻችን ተገድለው፣ በቀብር ቦታዎቻችን ላይ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ ስንትና ስንት ግፍ ስለተሠራብን " እኛ እስላሞች በዱአችን፣ በጸሎታችን ወደ አላህ አልቅሰን ነው ይሄ ሁሉ መከራ፣ በላ በክልሉ ላይ የወረደው። ይሄን ሁላ መዓት ያመጣው የእኛ የእስላሞች ዱአ ነው ብለው ተናገሩ። አዳራሹ በስሱ አጨበጨበ። መድረኩን የሚመሩት ትግሬው አበባው ፈገግ አለ።

"…ከእነ ዳንኤል ክብረት በኩል የሆኑቱ የጎንደር ፅንፈኛ የብልፅግና ኦርቶዶክሶች ደግሞ ተነሡ። "ይሄ እስላሙ ሼክ የተናገረው ንግግር ፍፁም ከሃቅ የራቀ ነው። ፀብ አጫሪነት ነው። እስላሞቹ እንደሚቀሰቅሱት እኛም ብንቀሰቅስ፣ ሕዝቡንም ብናሰልፍ የሚፈጠረው ነገር ጠፍቷችሁ አይደለም። የዐማራ ክልልን ቀውስ እኛ በጸሎት ያመጣነው ነው የምትለው እናንተ የት ተቀምጣችሁ ነው? እንግዲያው ስሙ እንንገራችሁ፣ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት አለቀ። የምታመጡትን እናያለን አለ የዳንኤል ክብረት ኔትወርኩ ጎንደሬ። አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፣ ቀለጠ፣ ደመቀ። ሼኩም፣ ትግሬው አበባው ታደሰም ያለጠበቁት መቅረብ ወረደባቸው። ከስክሪፕቱ ውጪ የሚተውኑ ድንገቴ ተዋንያን ተፈጠሩ።

"…ጎንደርም፣ ሞጣ ጎጃምም በእስልምና ወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ድርጊት በማን እንደተፈጠረ የምናውቀው ሃቅ ነው። አቢይ አሕመድ፣ ዳግማዊት ሞገስ በእኩለ ሌሊት ተነሥተው በቲዊተር ገፃቸው ላይ ያቀጣጠሉትን ያጠፋው የዐማራ አምላክ ነው። ዐማራ ልበሰፊ፣ ብልህ፣ ጥበበኛ ባይሆን እኮ ዶግ አመድ አድርገውን ነበር። አሁንም የያዘ ይዟቸው ነው እንጂ የወሎን የከሚሴን እስላም ከጊጃም እና ከጎንደር ፅንፈኛ እስላሞች ጋር አቀናጅተው "የዐማራ ፋኖ እኮ ክርስቲያን ነው" የሚል ፕሮፓጋንዳ ሲሠሩ የሚውሉት እነዚሁ ፅንፈኛ የኦሮሞ ወሀቢያ እስላም ገረዶች ናቸው።

"…በወለጋ ያሁሉ የወሎ እስላም ሲጨፈጨፍ፣ መስጊዶች ሲቃጠሉ፣ የአረብ ስም በዝቷል ብሎ ሽመልስ አብዲሳ በአደባባይ ሲደነፋ፣ በሸገር ሲቲ ከ30 በላይ መስጊድ ፈርሶ ገና ሌላም እናፈርሳለን ሲባል ተለጉመው ዐማራ ክልል ግለሰቦች ቢጣሉ እንኳ፣ በባህርዳር የቢሮ አጥር ተናደ ብለው ጉዳዩን ወደ ሃይማኖት ግጭት አዙረው ዐማራን በሚዲያ ጭምር ሳይቀር ለማበጣበጥ እንዴት እንደ ሚሠሩ እኮ እናውቃለን ባዮች ናቸው የጎንደር የዳንኤል ክብረት ኔትወርኮቹ። ነገርየው እውነት አላቸው።

"…ትግሬው አበባው ታደሰ በረገገ። ነገርየው ከእጁ ሊያመልጥ ሆነ። እስላሞቹ ሲናገሩ ኦርቶዶክሶቹ ሼም ይዟቸው ነገርየው በእስላሞቹ አስፈራሪነት ይጠናቀቃል ብለው አስበው የነበረ ቢሆንም ራሳቸው እስላሞቹ ከመጀመሪያው የጨው ሃውልት አድርጎ እንደ ሎጥ ሚስት የሚያስቀር መዓት ከጎንደሬዎቹ ኦርቶዶክሳውያን ስለወረደባቸው የቁማሩን ካርታ ተበሉ። ነገርየው ከቀጠለ መመለሻ ስለሌለው ትግሬው አበባው ታደሰ ማሳሰቢያ ሰጠ። የሃይማኖት ነገር አይነሣም። ጭብጨባም አይኖርም። ተረኛው የውይይት ርዕስ ኢኮኖሚ ነው። እናም በኢኮኖሚው ዙሪያ እንወያያለን በማለት ዕድሉን ወደ ተሰብሳቢዎቹ አዞረ።

"…አቶ በላይነህ ክንዴ ተነሣ… ተነሣና ዐማራ ላይ ይደነፋ ጀመር…

"…10 ሺ ሰው ካነበበው በኋላ እቀጥላለሁ… መጣሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትናንቱ ስብሰባ
     ክፍል ፩

"…ምዕራባውያኑ የዐማራ ክልሉ ጉዳይ ከብልፅግና እጅ እንደወጣ ተርደተዋል። አገዛዙ ሽባ አቅመቢስ በአፍ ጅዶ እንደሚተዳደርም ገብቷቸዋል። ወጧ እንዳማረላት ሴት ወደ አዲስ አበባና መቀሌ ከሚመላለሰው ከአማሪካው መልእክተኛ ከአቶ ማይክ ሐመር እና ከፈረሰችው ከሊቢያ እና ከደቡብ ሱዳን ከጅቡቲ በቀር አይደለም በመንግሥታት ደረጃ ዝቅተኛ የፖለቲካ አመራሮች እንኳ የአዲስ አበባውን አገዛዝ ንቀውት ወደ ሸገር መምጣት ካቆሙ ቆዩ። እንዲያውም የካቡት፣ ሳይሠራ ኖቤል የሸለሙት የምዕራባውያን ሚዲያዎች መውደቁን ስላዩ ሙልጭ አድርገው መስደብ ከጀመሩም ውለው አድረዋል።

"…ይሄ በእንዲህ እንዳለ ነው የጨነቀው ብልፅግና የዐማራ ተወላጆችን ለትናንት ሐሙስ እና ለዛሬ አርብ ለሁለት ቀን ስብሰባ የጠራው። ስብሰባው የተጠራው በአእምሮ ስልቧ በገሌዋ ሒሩት ካሳው፣ በአቶ ያያ አዲስ እና አቢይ እንደመጣ የጥረት ኮርፖሬሽንን ሙልጭ አድርጎ ዘርፏል ተብሎ ታስሮ በነበረው የበረከት ስምኦን የሚስት ወንድም በአቶ ምትኩ አማካኝነት ነው። ስብሰባውን ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኘችበት፣ ኤታማዦር ሹሙ ብራኑ ጁላ፣ አዳነች አቤቤና የብአዴን ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት በመገኘት ይመሩታል ተብሎ የነበረ በሆንም ነገር ግን በትናንቱ ስብሰባ ላይ የትግሬና የአገው ድቅሉ አበባው ታደሰ እና ሌላኛው ዐማራ ጠል እኩለ ሌሊት ድቅድቅ ጭለማ ሳዲስት ፊቱ ጄነራል በላይ ስዩም ከኮሚሽነር ዘላለም ጋር ሆነው መርተውታል።

"…ተሰብሳቢዎቹ በሙሉ በኔትወርክ ተስበው የመጡ ሲሆን፣በአቢይ አሕመድ መስመር በኩል በኦሮሞው በአቶ ግርማ ብሩ ተጠርንፈው የሚንከላወሱት ባለ ሰፊ ጃንሜዳ ሆዶቹ የጎጃም፣ የሸዋና የጎንደር ባለሀብቶችም ተገኝተዋል። ባለሀብቶቹ ከመገኘትም አልፈው የተሰብሳቢውን ምሳ ስፖንሰር አድርገዋል። በስብሰባው ላይም ንግግር አድርገው የገዛ ወገናቸውን ዐማራውን አስፈራርተው ታይተዋል። የሁሉንም ስልካቸውን ከነ ንግግራቸው አስቀምጥላችኋለሁ። የሚገርም ነው ፋኖ ማሸነፉ ላይቀር እንዲህ መስገብገባቸው የሚገርም ነው። በተለይ ሁለቱ ያስቁኛል። ግርማ ሞተ፣ ተገደለ ብሎ ዐማራ ከድርጅቱ ጠርጎ ያባረረው የሴንቸሪ ሞል ባለቤት በሰይጣናዊ ተግባር በአባቱ ኮተት ሀብት እንዳፈራ የሚታወቀው አሥራት መንገሻ እና ወንድሙ መስፍን መንገሻ፣ ከበላይነህ ክንዴ፣ ካርሎስ ቀበሮ ቢአይካ ጋር ሆነው እንዴት እንዴት እንደሚያደርጋቸውም በሰፊው አወጋችኋለሁ።

"…በአቶ መላኩ ፈንታ በኩል ከጎንደር የመጡ የዐማራ ወጣቶች ማኅበር ቡድኖች ስብሰባውን በጭብጨባ ለማወክ ከፈፀሙት ግርግር በቀር ባልተጠበቀ ሁኔታ ስብሰባውን የእግዚአብሔር መንፈስ የዐማራ አምላክ ተቆጣጥሮት ሰብሳቢዎቹን እና ሴረኞቹን አሳፍሯል። ከመደንገጣቸውም የተነሣ ለሁለት ቀን የተቀጠረው ስብሰባ ከምሳ በኋላ በቋ እንቋጨው ተብሎ በአጭር ተቀጭቷል። በዳንኤል ክብረት በኩል ተመርጠው የገቡ ጎንደሬዎች እና በእነ ሙጂብ አሚኖ፣ በጣሂር ኢብራሂም፣ በእነ አህመዲን በኩል ተመርጠው የገቡት የሃይማኖት አባቶች ገና ስብሰባው ሳይጀመር በፈጠሩት ሁከት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያን ጎንደሬዎቹ እስላም ጎንደሬዎቹን "አሁንስ አበዛችሁት፣ ዝም ስንላችሁ ጥሬ ካካችሁን በአናታችን ልትዘፈልሉ ያምራችኋል? በሚል መንፈስ "አዎ ምን ታመጣላችሁ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" በማለታቸው አዳራሹ በጭብጫ በመናጋቱ ሰብሳቢዎቹ ጭብጨባ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞም አስተያየቶች እንዳይሰጥ ማሳሰቢያ እስከመሰጠትም የተደረሰበት ስብሰባ ነበር።

"…የስብሰባው ርዕስ ስለ "ሰላም" ነበር። ጸሎት እና ከዐማራ በቀር ኦሮሞና ትግሬ የማይዘምረውን ትግሬ ያወጣውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ከተዘመረ በኋላ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሩ በቅርቡ ትቀውሳለች ተብሎ በምትጠበቀው በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተጀመረ። ያው የተለመደውን "የቆሸሸ ሰፈር አሳመርልናችሁ፣ ብልፅግና የጽዳት ፓርቲ ነው፣ የሥራ ፓርቲ ነው" ወዘተ የሚለውን ዲስኩር ካሰማች በኋላ አዳራሹ በጭብጨባ ተናግቷል ተብሏል። አዳነች ደስኩራ መድረኩን ለውይይት ከፍታ ሌላ የፅዳት ሥራ ሥላለብኝ እኔ ልሂድ፣ እናንተ ዐማሮቹ ራሳችሁን አፅዱ፣ ለሆዳችሁ ምሳ አለ ብላ ነካችው ተብሏል። የምግብ መኖር ሲታወቅ የብአዴን አባላት ሂሩት ካሳውን ጨምሮ ምራቃቸውን እየዋጡ በጉጉት ስብሰባውን ለመከታተል ፍላጎታቸው መጨመሩ ነው የተነገረው።

"…ወዲያው ስብሰባውን ይመሩ ዘንድ በአባቱ ትግሬ፣ በእናቱ የሰቆጣ አገው ልጅ በዐማራ ኮታ የሚንቀሳቀሰው አበባው ታደሰ፣ ሌላኛው ፀረ ዐማራ በስብሰባው ላይ ፋኖን ተሳድቦ፣ ተሳድቦ ሲያበቃ ደክሞት እንቅልፉን የለጠጠው ብርጋዴር ጄነራል በላይ ስዩም እና ጎተራው ኮሚሽነር ዘላለም መድረኩን ተረከቡ። ዋና ሰብሳቢው የትግሬው ልጅ ፀረ ዐማራው አበባው ታደሰ "ሀገራችን ታማለች፣ ክልላችን ታሟል፣ በዛሬው ስብሰባ የተጠራችሁ ዐማሮች "ነጭ ነጯን" ንገሩን እና መፍትሄ እንፈልግ። ያለበለዚያ ጊዜ የለንም ብሎ ጀመረ። ወደ ሕዝቡም አጀንዳውን ወረወረ።

"…ስብሰባውን በዋናነት ያዘጋጀው አቶ ያያ አዲስ የባህርዳር ከንቲባ የነበረ፣ የዐማራ ሰፖርት መሪም የነበረ፣ አሁን የዐማራ ኢንቨስትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ተጠሪው ቀደም ብለው ከጎንደር በእነ ሙጂብ አሚኖና በእነ ጣሂር የተዘጋጁትን ጽንፈኛ እስላሞች እና እነዚህን ፅንፋኛ እስላሞች የኃይል ሚዛን ያዳክሙ ዘንድ በእነ ዳንኤል ክብረት ተዘጋጅተው የመጡ ሁለት ብልፅግና ወለድ ፅንፈኛ ክርስቲያን ዐማሮች ስብሰባውን ሞቅ ያደርጉት ዘንድ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ይናገሩ ዘንድ ተራ በተራ አበባው ፈቀደላቸው። ቅድሚያ የመናገር ዕድሉን ያገኙት ተሰብሳቢ ዐማሮቹን በሃይማኖት ስም ያሸብሩ፣ ያስዶክኩም፣ አንገትም፣ ቅስምም ይሰብሩ ዘንድ ወደተዘጋጁት የዐማራ ክልል በተለይ የጎንደር ዐማራ እስላሞች ነን ለሚሉት በቅድሚያ የመናገር ዕድሉ እንዲሰጥ ተደረገ። ይቀጥላል…✍✍✍ 100 ሰው 👍 10ሺ ሰው እንደነበበው…

"…ቆይቼ ክፍል ሁለትን ይዤ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ፥ ደግሞም ለዓመፀኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ።” መዝ 68፥18

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነዘረኝ…!

"…ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…

• ለዐማራ ከማሸነፍ በቀር ሌላ ምርጫም፣ አማራጭም የለም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በዕለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉በዩቱብ /YouTube
https://www.youtube.com/live/4DNwO-Cf77c?si=7SZvGniswdqIXQA2

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v52pbp6--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡክ/Facebook
https://www.facebook.com/share/Kg7w3KdGW5jwDPTX/?mibextid=oFDknk

👉በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም/ Telegram
♦/channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።” መዝ 47፥5

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ነው…??

"…የገበሬ ከብት፣ የገበሬ እህል አስገድዶም መብላት እየቻለ፣ አቅሙም እያለው ልታገልለት ብዬ ከወጣሁለት ሕዝብ ላይ አስገድጄ አልበላም በማለት እንዲህ ሙጫ ከዛፍ ላይ እየበላ የሚታገል ፋኖ እያለ…  በጥላቻ ተሞልቶ፣ ዐማራን አጠፋለሁ፣ እደመስሳለሁ፣ ባርያም አደርገዋለሁ ብሎ የመጣን አረመኔ፣ ከፍት፣ ከእንስሳ በታች የሆነ አውሬ የኦሮሙማ ጦር፣ ያውም ገድሎ ገድሎ ጥይት ጨርሶ አማራጭ ሲያጣ የተማረከን ነፍሰ በላ ነጭ ማኛ የጤፍ እንጀራ መቀለብ አግባብ ነው ወይ?

"…ፅንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ዘራፊ፣ ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ ሰላም ብሎ ፈርጆህ ሲያበቃ የራስህ የፖለቲካ ተወካይ ነኝ ባለው በበድኑ ብአዴን ትከሻ ተጭኖ መጥቶ ሚስትህን፣ እህትህን፣ እናትህን አስገድዶ ደፍሮ፣ ንፁሐንን አንበርክኮ ጨፍጭፎ ሲያበቃ በመጨረሻ ጥይት ጨርሶ እጅ ሰጥቼ ምርኮኛ ነኝ የሚለውን ነፍሰገዳይ ወንበዴ ሰውነቱን አጥበህ፣ ልብስ ቀይረህ፣ አብልተህ፣ አጠጥተህ፣ እናት አባቱ ያልሰጡትን እንክብካቤ ሰጥተህ፣ ተንከባክበህ መታወቂያ አሠርተህ፣ ከዚያም በላይ ለእጁ ሳንቲም ሰጥተህ ስንቅ ቋጥረህ የምትሸኘው በየትኛው መንፈሳዊም፣ ዓለማዊም ሕግ ነው? በየትኛው ዓለምአቀፍ ሕግ ነው?

"…እየፎከረ፣ እየፎገላ፣ ዐማራ መጣሁልህ እያለ መጥቶ ጨፍጭፎህ ሲያበቃ ጥይት ሲጨርስ ተገድጄ ነው፣ አቢይ አሕመድ ሌባ ነው፣ ብርሃኑ ጁላ እንዲህና እንዲያ ነው። ፋኖ አንበሳ ነው፣ ነብር ነው ስላለ ገዳይን አንቀባርሮ መሸኘት ወንጀል ነው።

"…ለፋኖ ተብሎ የሚዋጣው ብር ፋኖ እየተራበ ይሄን በአረብ ብር፣ በኢትዮጵያ በጀት ደሞዝ እየተቆረጠለት ሆዱ ሳይጎድልበት ዘር እየጨፈጨፈ ለሚኖር አራጅ መቀለቡ መቆም አለበት።

• ገዳይ መገደል ነው ያለበት። አለቀ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ምርኮኛ ማለት የጥይት ካዝናው እንደሞላ እጅ የሚሰጥ ነው። ምርኮኛ ማለት አዛዡን፣ ጄኔራሉን፣ አስተኳሹን በጭንቅላቱ ቆጥሮበት፣ በግንባሩ ደፍቶት እጅ የሚሰጥ ነው። ጥይት ጨርሶ የሚማረከው ምርኮኛ እና ታዲያ ከመማረክ በቀር ሌላ ምን አማራጭ አለው? ለምንድነው ፋኖ ቆስሎ ላለመማረክ እዚያው ጥይት ጠጥቶ የሚሞተው? አዎ አገዛዙ ከማረከው ቆራርጦ እንደሚበላው ስለሚያውቅ አይደለም እንዴ? ዓለም አቀፍ የእስረኛ አያያዝ ለማያውቅ አውሬ የጋርዮሽ ሠራዊት አንተ የሰለጠነ ለመምሰል ለምንድነው የምትጋጋጠው? ፋኖ ሞላ ወልድያ ላይ ቆስሎ ሆስፒታል ቢገባ እኮ አረመኔው የጁላ ሠራዊት ከሆስፒታል አውጥቶ በጭንቅላቱ ላይ መኪና ነድተው ፈጭተው እኮ ነው ጨፍልቀው በሚዘገንን ሁኔታ የገደሉት። እና ለዚህ አረመኔ ዐማራ ጠል ለሆነ ልጋጋም ጋጠወጥ መከላከያ ተብዬ አሳፋሪ መንጋ ነው የምትራራው?

"…በመጪው እሁድ ምሽት በመረጃ ቲቪ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው የቴሌቭዥን ዝግጅቴ ላይ በሸዋ ውጊያ ላይ ስለተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የብሔር ተዋጽኦ አሳያችኋለሁ። ከየት ነህ ሲባል ከጎጃም ነኝ፣ ከጎንደር ነኝ፣ ከወሎ ነኝ ሲል እንዴት ደም እንደሚያፈላ አትጠይቁኝ። ዐማራ ሆነው ዐማራውን ለመጨፍጨፍ ለመጡ ደደብ፣ መሃይም፣ ባዶ ጭንቅላት፣ ነፈዝ፣ እከካም የዐማራ ተወላጅ ነኝ ባይ የአቢይ ገረድ ወታደር ለየት ያለ አያያዝ ከወዲሁ መታወጅ አለበት። መረር ማለት ነው ፋኖ ያለበት። ኮምጨጭ ነው ማለት ያለበት። ሚሪንዳ መሆን የለበትም። ኮሶ፣ መተሬ፣ በረኪና ነው መሆን ያለበት። ተናግሬአለሁ። የሰማችሁ ላልሰሙ አድርሱልኝ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ትናንት ማታ ቲክቶክ ላይ ተጥጄ ሱፐር ሶኒክ ሚሳኤሌን ስተኩስ አምሽቼ ወደ መኝታዬ በመሄዴ ዛሬ ከመኝታዬ አርፍጄ ነው የተነሣሁት። ከወትሮው ባረፍድም ግን የጌታ ትንሣኤ ዐዋጅ የአምላክ ምስጋናው አልተቋረጠም። ዘወትር በቤቴ ፈጣሪን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው የአመስጋኝ ቁጥርም ከመሙላትም በላይ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። ታዲያ ከምስጋና ቀጥሎ እኔ ዘመዴ በቀጥታ የማልፈው ወደተለመደው እና ወደ ተናፋቂው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…ዛሬ ከመኝታዬ ስነሣ ስለ ዐማራ ፋኖ የምርኮኛ አያያዝ ጉዳይ ዘመዴ ጻፍ ጻፍ ብሎ ቀኝ ትከሻዬን ቢሸክከኝ ጊዜና ጻፍኩት። የዐማራ የምርኮኛ አያያዝ ጉዳይ የበዛ፣ ጅልነትና የዋህነት የተሞላ ስለመሰለኝ ጻፍኩት።

"…በጅጋ፣ በሞጣ፣ በደቡብ ጎንደር በሸዋ ቤት ለቤት እየዞረ ምስኪኖችን የሚረሽን፣ የሚጨፈጭፍ፣ የሚያርድ፣ የሚገድልን አረመኔ የአቢይ አሕመድ ገረድ የሆነን ወታደር ሰውነቱን አጥቦ፣ ልብስ ቀይሮ፣ ጠላና እርጎ እያጠጡ፣ መታወቂያ አውጥተው መልሶ መላክ የሚለውን የፋኖን የባህታዊ መንገድ ከልሰን እንድናየው ፈልጌ ጻፍኩት።

• ጦማሩ ትንሽ መረር ያለ ነው። እናንተ ለማንበብ፣ አንብባችሁም አስተያየታችሁን ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ? የአንድ መቶ ሰው ዝግጁነት ካየሁ በኋላ እለጥፍላችኋለሁ።

• ዝግጁ ናችሁ…? 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ልመጣ ነኝ…

"…ዕለቱ ማክሰኞም አይደል? አዎ ማክሰኞ ነው። በዕለተ ማክሰኞ ደግሞ ቀጠሮአችን በቲክቶክ መንደራችን መሆኑ ይታወቃል። እናም በቀጠሮአችን መሠረት እኔ ወደዚያው ወደ መንደራችን የሚወስደኝን መሂና እየጠበቅኩ ነው። ከጥቂት ደቂቃዎችም በኋላ እደርሳለሁ ብዬ አስባለሁ። እናንተም ጉዞ ጀምሩ። እዚያው እንገናኝ።

"…በተመረጡ ርዕሶች ዙሪያ ነጭ ነጯን እንነጋገራለን። እውነትን በድፍረት መናገርን እንለማመዳለን። የሚተች ያለ ምህረት ይተቻል። የሚመሰገንም ያለ ሰቀቀን ይመሰገናል። እኔ እንደሁ ቋሚ ወዳጅም፣ ቋሚ ጠላትም ስለሌለኝ በሚልዮኖች ፊት የልቤን ተናግሬ ተንፍሼ ያለ ጨጓራ ህመም ፏ ብዬ በጤና እኖራለሁ፣ የሰላም እንቅልፍም እተኛለሁ።

"…የምትሰድቡኝ፣ የምትወቅሱኝ፣ የምትዝቱ፣ የምታስፈራሩ፣ የምትፎክሩብኝ ሁላ ልክ አስገባችሁ ዘንድ፣ አስተነፍሳችሁ ዘንድ በቲክቶክ መንደሬ እንገናኝ። ያለ እናንተ እኔ ጀት አልሆንምና አትጥፉብኝ። የትግሬ ነፃ አውጪዋ የሂዊ፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ የኦህዴድ፣ የኦነግ፣ የኦፌኮ፣ የብልፅግና፣ የዐማራው ገተት ብአዴን፣ የኦሮሞ ወሃቢስቶች፣ የብልጽግና ወንጌል ሠራዊቶች ምላሳችሁን አሹላችሁ ጠብቁኝ።

• አላችሁ አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ በ15 ተኛ ቀናችን በቲክቶክ መንደር እንገናኛለን። እናም የቲክቶክ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በርዕሰ አንቀጹ ላይ እየተወያየን እንቆያለን።

• ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…የዐማራው ፋኖ ኦህዴድ ያለበት ጋር ሄዶ ለመዋጋት መጀመሪያ በቤቱ ያለውን ብአዴን ማጽዳት ይጠበቅበታል። እንዲያው ኦሮሙማው ስላስመረረን፣ ስላንገሸገሸን፣ ፋኖን በገንዘብ፣ በስንቅ፣ በትጥቅም ሳያግዙ፣ ሳይረዱ ዝም ብሎ ተአምር እንዲሠራ መጠበቅ ልክ አይደለም። በባዶ እጅ እንዲህ አገዛዙን ሽባ ያደረገ ኃይል ከልብ ማገዝ፣ እውነተኛ ሒስና ትችት ማቅረብ፣ በዚህ ጀግንነታቸው ላይ ከፍ ያለ ድል እንዲያስመዘግቡ በኃይለኛው ማገዝ እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ "የተወለደው ሕጻን ዛሬውኑ ይደግ፣ ይመደንግ" ማለቱ ተገቢ አይመስለኝም።

"…አስተያየት ሰጪው ይቀጥላሉ።

2. ኦህዴድ በዚህ ወር ከዓለም ባንክ ኃላፊዎች ጋር ከሚያደርገው የገንዘብ ልመና ስብሰባ በፊት የዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ ትኩረት ለማግኘት ያለምንም ምክንያት ያሰራቸውን ሰዎች እየፈታ ይገኛል። ይህን የማደናገሪያ ስልት በመጠቀም ኦህዴድ ከእነዚህ ተቋማት ገንዘቡን ካገኘ የዐማራ ሕዝብ የሚገጥመውን መከራ ማሰቡ የሚከብድ አይመስለኝም። ይህ ከመሆኑ በፊት በየትኛውን የዓለም ክፍል ያላቹህ ኢትዮጵያውያን ኦህዴድ ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዳያገኝ ጫና ማድረግ ይገባችኋል። በማለት ሓሳብ ይሰጣሉ።

"…ብር አይዋጋም። ዶላር አይዋጋም። ኔቶና የተባበሩት መንግሥታት፣ ዓለም ሁሉ ጦሩን ስላዘመተብህ ትሸነፋለህ ማለትም አይደለም። ቬትናም አልተሸነፈችም። ኢትዮጵያም በፋሽስት አልተሸነፈችም። አፍጋኒስታንና ሱማሌያንም ማየቱ በቂ ነው። አሁንም እነ ቱርክ፣ ኢራን፣ ኤምሬትስ፣ ሳዑዲአረቢያ በጦር መሣሪያ፣ ምዕራባውያን በፕሮፓጋንዳ፣ በዝምታ፣ ባላየ ባልሰማ በማለፍ ዐማራውን ቀደም ሲል ከትግሬ ነፃ አውጪው ጋር፣ አሁን ደግሞ ከኦሮሙማው ጋር በመሆን ወግተውታል። ዐማራው የጦር መሣሪያ የሚያገኘው በድኑ ብአዴን ለውጊያ የተሰጠውን መሣሪያ ይዞ ሲሄድ ነው። እናም የዓለም ባንክ ሰጠው አልሰጠው የሚቀየር ነገር የለም። የሚለወጥም ነገር የለም። ዐማራ እየታገለ ያለው ሀቅን ይዞ ነው። ሃቅን የያዘ ደግሞ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ አሸናፊ ነው።

3. ኦህዴድ ከእስር እየፈታቸው ያሉ ንጽሃን ዜጎችን፥ ምንም ባልታጠቁ ንጽሃን ዐማራዎች ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት መሸፈኛ እንዲሆን አድርጎ እየሠራበት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ጅጋ ላይ 30 ዐማራዎች በጠራራ ፀሐይ ይረሸናሉ፣ ለዚል መሸፈኛ ኦህዴድ ሁለት የፖለቲካ እስረኞችን ፈታሁ ብሎ ለዓለም ያስወራል። ይህን ፓተርን ተረድቶ መፍትሄ መፈለግ ብዙ ዐማራዎችን በሕይወት ለመታደግ ይጠቅማል።

"…በዚህ ሓሳብ እስማማለሁ። አፍቃሬ ወያኔ የሆነው በቃሉ አላምረው በመፈታቱ አይከፋኝም። በቃሉ በመፈታቱ ጮቤ የረገጡት ግን ትግሬዎች መሆናቸውን ስታይ ትገረማለህ። ትደነቃለህም። ዐማራ ሆነው ለትግሬ ለተገረዱ ቦታ ሰጥተህ የራስህን አጀንዳ ረስተህ መጮህ የለብህም። በላይ ማናየን እንኳን ተፈታ የሚል ትግሬ አላየሁም። ምክንያቱም በላይ ዐማራ ነዋ። የሆነው ሆኖ አገዛዙ ፈታ፣ አሰረ ለደንታው ነው። የፈታቸውን በማግስቱ ማሰር ይችላል። ማን ከልካይ አለበት። ትግሉ እኮ ይሄን በዘፈቀደ እንደ ግል ከፍቶችህ በፈለገው ጊዜ ኦሽሽ እያለ እየነዳህ ወስዶ እንደ በረት ዘብጥያ አክርሞህ፣ ፍርድ ቤት ሳያቀርብህ የሆነ ቦታ የሆኑ ንፁሐን ዐማሮችን ከፈጀ፣ ከጨፈጨፈ በኋላ በመሃል ለዓመል ጠብ እያደረገ እየፈታ ጮቤ በማስረገጥ አጀንዳ ማስቀየሻ መሆን የለበትም ዐማራ። በዚህ ሓሳብ እስማማለሁ።

4. ዐማራ ታጋዮች ስለኦህዴድ ሠራዊት ያላቸው አመለካከት በጣም የተዛባ ይመስለኛል። ፋኖዎች በየሚድያው ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ "መከላከያ እያሉ ነው የሚጠሩት" በእኔ እምነት ይህ በጣም ስህተት ነው። (ፋሽስት፥ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ፥ ወንበር ጠባቂ) እያሉ መጥራት ሲገባቸው ከስምንት ወር ህፃን እስከ 80 ዓመት አዛውንት ያለርህራሄ የሚጨፈጭፍን ዘረኛ ሠራዊት መከላከያ እያሉ የሚጠሩት ለምን እንደሆነ እስካሁን አልገባኝም።

"…በዚህም 100% እስማማለሁ። የምጨምርበትም አስተያየት የለኝም።

5.የዐማራ ታጋዮች በምርኮኛ ጉዳይ ካለፈው ስህተታቸው ትምህርት ወስደው የተሻለ መንገድ መከተል አለባቸው። ለምሳሌ የኦህዴድ ሠራዊት አባላት ወላጅ አልባ፥ በሥራ አጥነት ተማረው ተስፋ የቆረጡ፥ ከየመንገዱ የታፈሱ፥ በዐማራ ጥላቻ የሰከሩ ዘረኞች (ከኦሮሚያ የሚመለመሉትን ይመለከታል) ወላጅ ቢኖራቸውም ማሳደግ አቅቶት ከቤት ያስወጣቸው ወጣቶች ስብስብ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፥ ሁልጊዜ የዐማራ ታጋዮች የማረክናቸውን ወደ ወላጆቻቸው ላክናቸው ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ፈጽሞ የተሳሳተ አካሄድ ነው፥ መጀመሪያ የኦህዴድን ፋሽስታዊ ሠራዊት ስሪቱ ምን ዓይነት እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው። ወላጅ አልባ፥ ከየመንገዱ የታፈሰ ሥራ አጥ፣ በብሔር በጥላቻ የሰከረ አራዊታዊ ስብስብ ገንዘብ ተሰጥቶ የሚሸኝበት ወላጅ የለውም። ያሉትንም ሓሳብ እንደ ሓሳብ እቀበለውና ግን ምርኮኛን ዐማራ የሰለጠነ ማኅበረሰብ ስለሆነ ከዓለም አቀፍ የምርኮኞች አያያዝ በተጻራሪ እንዴት እንዲይዘው እንደሚችል ተጨማሪ ሓሳብ ቢያቀርቡ ጥሩ ነበር። ነገር ግን አላቀረቡም። በውጊያ ላይ እጅ ያልሰጠው እየተደመሰሰ ነው። እጅ የሰጠውን ግን ሌላ ዓይነት የምርኮኛ አያያዝ ካለ ቢያስረዱን ጥሩ ነበር።

6.የዐማራ ሕዝብ ትግል ባለፈው አንድ ዓመት በትጥቅ ደረጃ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አላሳዬም። ዛሬም ከኦህዴድ ፋሽስታዊ ሠራዊት ትጥቅ ማረኮ በመታጠቅ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ አካሄድ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ነው። ይህ እየሆነ ያለው ዐማራ ህልውናውን ለማስከበር የሚጠቅመው ዓለም አቀፍ ድንበር እያለው መሆኑን ስናይ በጣም ያሳዝናል። ዐማራ ከሀገር ሀገር ተንቀሳቅሰው የውጭ ግንኙነት የሚሠራለት አንድ ዐማራ ማጣቱ በጣም ያስገርማል። ከዛሬ ስድሳና ሰባ ዓመት በፊት የትግራይና የኤርትራ ነጻ አውጪዎች ከሰሜን አሜሪካ እስከ ምዕራብ አውሮጳ፥ ከሱዳን እስከ ሱማሊያ ተንቀሳቅሰው የውጭ ግንኙነት በመፍጠር የሕዝባቸውን መከራና ስቃይ ለማሳጠር የሚሮጡ ወጣቶች ነበሯቸው። በሚሊዮን ከሚቆጠረውና በውጭ ሀገር ከሚኖረው ዐማራ አንድ እንደ ስዩም መስፍን ከሀገር ሀገር ተንቀሳቅሶ ለዐማራ ሕዝብ በድንበር በኩል ትጥቅ የሚያቀርብ ዐማራ ማጣት ያስገርማል። እናም እባካቹህ ከኦህዴድ መሃይምና አራዊት ስብሰብ የተሻለ በማሰብ፥ በፍጹም  የዐማራን ሕዝብ መከራና ስቃይ ለማሳጠር እንሩጥ። በማለት አስተያየታቸውን ይቋጫሉ። እኔም በዚህ ላይ የራሴን ሓሳብና አስተያየት በመስጠት ርዕሰ አንቀጼን ልቋጭ።

"…የዐማራ ትግል ለውጥ አላሳየም የሚሉትን አልቀበለውም። ከዚህ በላይ ምን ለውጥ ያምጣ? በባዶ እጅ ተነሥቶ ክፍለ ጦር እየመሠረተ ያለ ዐማራ ከዚህ በላይ ምን ዓይነት ለውጥ ያምጣ? በሀገራት ደረጃም፣ በግለሰብ ደረጃም የሚረዳው ሳይኖር በራስ አቅም ከዜሮ ተነሥቶ እዚህ የደረሰውን ዐማራ ከዚህ በላይ ምን ተጠብቆ ኖሯል? ወያኔና ሻአቢያ ከሶማሊያ እስከ ሱዳን ቢሯሯጡ ኢትዮጵያን ቀብድ አስይዘው ነው። ወያኔ እኮ ሥልጣን ላይ ሲወጣ የዐማራን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ሰጥቶ ነው። ዓረቡም፣ ምዕራባውያንም ትግሬና ኦሮሞ ነፃ አውጪዎችን የሚረዱት ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ጥንታዊው የዐማራ ሙስሊም ስለሆኑላቸው ነው። ዐማራን ማን ይርዳው? ሲያለቅሰ የኖረን ዐማራ ማን ይርዳው። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ሲባክን የኖረን ጥርስ የተነከሰበትን ዐማራ ማን ይርዳው? ሱዳን ዐማራን ረድታ ለም የዐማራን መሬት ትመልስ እንዴ? ዐረቦቹ አቢይን እየረዱ ያገኙትን አዲስ አበባን የመውረስ፣ ኢትዮጵያን👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1 ሺ ሰው ሞልቷል። የዘገየሁት እንዲያው ንሽጥ አድርጎኝ ሊማሊሞ የመሰለ የዐማራ ፋኖን ጉዳይ በርዕሰ አንቀጽ መልክ ስጽፍ ነበር። አፉ በሉኝ ቤተሰቦቼ።

"…ዐማራ ሌላ ዓለም ላይ ነው ወዳጆቼ። ዐማራም ልክ እንደ ትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓት እና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ ብልፅግና ኦህዴድ የዘር ፖለቲካውን ጥቅም ለመሞከር ደፋ ቀና እያለ ነው። በጥቂት ጊዜም ከኋላቸው ተነሥቶ ከላይ ከማማው ላይ ሊቀመጥ ነው።

"…እስከዛሬ ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈስ፣ አጥንቱን ይከሰክስ የነበረው ዐማራ ትግሬና ኦሮሞ ብልጥ ሆኖ ዐማራውን በኢትዮጵያ ስም ዘሩን ማጥፋት አለማቆማቸው ከጥልቅ እንቅልፍ አንቅቶት ብትት ብሎ ዐማራ ዐማራነቱን ከምድረ ገፅ ሳይጠፋ በቶሎ ለመታደግ የቤት ሥራውን በሚገባ እየተወጣ ነው።

"…ጻፍኩት አይገልፀውም። እናንተስ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ። አንብባችሁም የራሳችሁን ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?

• አሳዩኝ እስቲ ዝግጁ ነታችሁን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐማራ ፋኖ ትግል…

"…ብዙ ሰዎች የዐማራ ፋኖ ትግል ቀጥ ብሎ የሚገለጠው መቼ ነው? የታረቁት ሁለቱ የጎንደር ፋኖ አደረጃጀቶች መቼ ነው ቀጥ ብለው ወጥ የሆነ አደረጃጀት የሚፈጥሩት? የታረቁት ሁለቱ የሸዋ ፋኖ አደረጃጀቶችስ መቼ ነው ቀጥ ብለው ወጥ ወደ ሆነ አደረጃጀት የሚመጡት? ጎጃም ላይ ያለው አደረጃጀት የተፈጠረበትን ሳንካ እንዴት ነው የሚሻገረው? የወሎ ፋኖ ከሁሉም ኋላ ተነሥቶ ወደ አንድነት የመጣበትን ምስጢር ሌሎቹ ለምን ለመቀጸል ተቸገሩ? እስክንድር ሠራዊቱ እያለ በራሱ መስመር ለምን የፋኖ አደረጃጀት ይረብሻል? ወዘተ የሚል ጥያቄ ይነሣል።

"…የዐማራ ፋኖ ትግል በብዙ ጠማማ ሓሳብ ባላቸው ዐማራ መሳይ አሞሮችም የተሞላ ስለሆነ በመሠረታዊ ትግሉ ላይ አንዳች ሽግር ባይፈጥሩም ጊዜ መውሰዱ ግን አልቀረም። ግንቦቴ የሚባል ጥንብ አንሳ ራሱን ችሎ የማይቆም የዐማራ አልቅት የሆነ ግሩፕ፣ በድኑ ብአዴን ላዩላይ ተዘፍዝፎ የዐማራ ፋኖን ትግል ጎባጣ፣ ጎርባጣ መምሰሉ አልቀረም።

"…የዐማራን ትግል ቀጥ ያለ እንጨት አድርጎ ለማውጣት እንዲህ እንደጎባጣው እንጨት በመከራ ውስጥ ተገላብጦ ማለፍ አለበት። ዐማራ ቀጥ ያለ ወጥ ሓሳብ ይዞ እንዲወጣ ግራ ቀኙ እንዲህ ፍቅፍቅ፣ እሽት፣ ውቅጥ፣ ፍግፍግ መደረግ አለበት። እንዲህ ሲደረግ ነው የዐማራ ትግል ወዶ ሳይሆን በግዱ፣ የግዱን ቀጥ ያለ እንጨት የሚወጣው። የዐማራን ትግል ያጎበጡ፣ ያጣመሙ ሁሉ በጊዜአቸው ተራግፈው ሰጋቱራ ይሆናሉ። ሰጋቱራ።

"…የተያዘው የዐማራ ትግል የህልውና ትግል ስለሆነ ጎባጣውን የትግሬ ወረራ፣ የኦሮሞ ጭፍጨፋ፣ የሱዳን ገፈፋ፣ የብአዴን ዘለፋ፣ የግንቦቴ፣ የግንባሩ፣ የሠራዊቱም ቅፈላ አያስቆመውም። ወዶ ሳይሆን በግዱ የዐማራ ትግል ቀጥ ብሎ ይገለጣታል። ይንፈራገጣል ግን ደግሞ ይስተካከላታል።

• በጦማሬ ቅር የሚልህ ካለህ ለደንታህ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel