zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የመከታው ቀኝ እጅ ናት። ከ8ንት ነው ከ10ኛ ክፍል ማለፍ ሲያቅታት ወደ አረብ ሀገር ትሄዳለች። እዚያ ጂኒ ይለክፋትና የሸዋ ዐማሮች ሳንቲም አዋጥተው ለጠበል ወደ ሸዋ ይልኳታል። በሸዋ ጠበል እየተመላለሰች መከታውን ታገኘዋለች። መኬ ቁመናዋን ሲያይ ወሴ ነገር ናትና የሴቶች ጦር ሓላፊና የሸዋ የመከታው ጦር ሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ማለት ነው።

"…መቅደስ ወይም በትግል ስሟ ባርች ነፃ የኢንተርኔት የአየር ሰዓት ኦህዴድ ይሰጣትና እስክንድር እየጻፈ የሚሰጣትን እንድትለጥፍ ይደረጋል። ቲክቶክ ከፍታም ቀኑን ሙሉ እንድትጣድም ይደረጋል። ልጅቷ የሰፈረባት አጋንንት ከእስክንድር አጋንንት ጋር ተዳምሮ ሸዋን ማመስ፣ እኔንም እስኬው በእሷ ላይ አድሮ መስደብ ይጀምራል።

"…በጎንደር ሀብታሙና እስክንድር ውባንተ በእናንተ ስር አልገባም ስላለ አዋክበው እንዳስመቱት ሁሉ በሸዋም አሰግድ እንቅፋት ስለሆነባቸው ቦርከና ሚዲያ ላይ ፕሮፌሰሩ እንደከተበው መነሻዬ ዐማራ፣ መድረሻዬም ዐማራ የሚሉት ይመቱ እንዳለው እስክንድርና መከታው አሰግድ ይመታ ዘንድ ይወስናሉ። ከዚያም በዚህች ልጅ በኩል ነውረኛ ቃላት ተጠቅመው አሰግድን ያዋርዱታል። ሊገድሉት ሲሄዱ አሰግድን ሕዝቡ ያሸሸውና እንደ ውብአንተ ሳይሞት ይቀራል።

"…አሁን ጀነራል ተፈራ ማሞን እንዴት ትላንት እንደተጫወቱበት እንደሸወዱት ማርያምን ዛሬ ማታ በመረጃ ቴሌቭዥን አሳያችኋለሁ። በጣም ነው የተናደደው። ዘመዴ "ምን አለ?" ያሉት ፋኖዎች በሙሉ ዘመዴ ጓ ማለቴን ሲያዩ ኮሎኔል ሙሀባውም ሸርተት፣ የጎንደሩም ኮሎኔል ታደሰ እኔ አልመረጥኩም ማለቱ ተሰምቷል። የመከታው ጦር ወደ ሌላ ይገባል። ምስኪኑ መከታውም ከፋኒት ባርች ጋር እያዘንኩለት ሜዳ ላይ ከእስኬው ጋር ይቀራል። ባርች ግን እንደ ማርሸት ሳልገባላት ቀድማኝ ተፈጠፈጠች።

• ማርያምን ዐማራ ግን በዝርራ ያሸንፋል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘመነ መልእክት ነው

"…የብልጽግናን ሠራዊት እንኩትኩቱን የጎጃም ዐማራ ፋኖን አግልለህ እንዴት ነው እድሜ ልኩን ድል ለዲሞክራሲ እያለ ሲያዝገን የነበረ፣ ፖርቲ እየፈለፈለ በማምከን የሚታወቅ ሰው፣ የዐማራ ሕዝብ በነፍጤ ነው ለውጥ የማመጣው፣ ነፃነቴን የምቀዳጀው ብሎ ጫካ ሲገባ ተከትሎ ገብቶ፣ ተኩሶ የማያውቅ፣ ድሮኗ እየጠበቀችው፣ እሱ ሰው መስሏቸው የረዱት በሙሉ በድሮን እየተጨፈጨፉ፣ ከደንበጫ ሸዋ ድረስ በእግር 3 ወር የሚፈጅ መንገድ በግማሽ ቀን ገባ እየተባለ 😂 ብአዴንና ብልጽግና አድራሽ ፈረስ አድርገው የሚጋልቡት ሰው በዚህ መጠን የዐማራ ትግል ላይ ይቀልዳል?

"…የሌሎቹን የጋራ መግለጫ እየጠበቅኩ ነው። ምስጋናው አንዷለምን ጨምሮ ይሄን ትግል ለመጥለፍ ብአዴናዊ ጠባያቸውን ይዘው የገቡት ሁሉ ከሠራዊቱ ውክልና ይሰናበታሉ ብዬ እጠብቃለሁ። የዐማራ ፋኖ ትግል እሳት ለብሶ፣ እሳት ጎርሶ እንደ ንሥር ታድሶ ይወጣል።

"…አገዛዙ ኢንተርኔቱን የከፈተው ለዚህ ተግባሩ ነበር። ጄነራል አበባው ታደሰ ሰሞኑን የምሥራች ጠብቁ ፋኖን ለሁለት እንከፍለዋለን አለ ተብሎ የተነገረውም ይሄንኑ ለማለት ነው። የሚከፈል ፋኖም የለም። ተዋጊ አርበኞቹ ከቦታቸው ዝንፍ ሳይሉ እንዳሉ ናቸው። በስብሰባው ላይ ሻለቃ ዝናቡ የተናገረው ነገር አስደማሚ ነው። በመረጃ ቲቪ ሰምታችሁ ትፈርዳላችሁ። የበለጠ ነው ያከበርኩት። ዝናቡን የእነ አስረስና የእነ ዘመነ ካሴ እንዝህላልነት፣ የባህታዊ ፖለቲካ ቀፍድዶ ባያስረው ኖሮ ከዚህም በላይ በጀግንነት ተአምር መሥራት የሚችል ነበር። ኮሎኔል ጌታሁን ከዘመነ ካሴ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው ከእስክንድር ስር እንዲለጠፍ ያደረጉት ከዘመነ በታች ያሉ ኮተታሞች ናቸው። እሱም ይሰተካከላል ብዬ አምናለሁ።

• የዘመነ የእጅ ጽሑፍ ያልተነበባችሁ በኮመንት ሰንዱቁ ውስጥ ታነቡት ዘንድ አስቀምጥላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” ማቴ 7፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኦነጎቹ ምነው አበዱብኝሳ…?

"…የግንቦቴው፣ የግንባሩ፣ የሠራዊቱ፣ የአገው ሸንጎው፣ የወየንቲው፣ የፖለቲካው ቅማንት፣ የኦሮሙማው ብልጽግናዎች እኔ ላይ መጮሃቸው የተለመደ ነው። ኦነጎቹ ምናቸውን ብነካው ነው እንዲህ ዋይ ዋይ ብለው የሚጮሁብኝ?

"…ለማንኛውም ወያኔ እስክንድርን በማሰር በመፍታት አጀገነችው። አቢይ ሲመጣ እኔ ነኝ የምነግሰው ሲል እስክንድር በአቋራጭ ለንግሥና ደብረ ኤልያስ ሄዶ ሊቀባና ሳልሣዊ ቴዎድሮስ ሆኖ ሊመጣ ከጫፍ ሲደርስ አቢይ ተመስገን ጥሩነህን አስልኮ እንዳይቀቡት ቢልም ይነግሣል ብለው የፈሩት እነ አቢይ ደብረ ኤልያስን አወደሙት። ብአዴን የያዘውን እስክንድርን አጀግኖ ተዋጋኝ ብሎ ለቀቀው።

"…የዐማራ ፋኖን የገንዘብ ምንጭ ያደረቀው እስክንድር ነጋ ዛሬ አዲሱን ድርጅቱን ከማወጁ በፊት ያለፈው እሁድ የሥላሴ ዕለት ብልፅግና በዐማራ ክልል ኢንተርኔት ለቀቀ። ከ3 ቀን በኋላ ዛሬ ደግሞ ምሬ ወዳጆ፣ ዘመነ ካሴን፣ ባዬ ቀናው፣ አሰግድ መኮንን፣ እነ ኢንጅነር ደሳለኝ በሌሉበት፣ ኮሎኔል ሙሀባው ጋር ባለ በመስፍን ወይም ተስፋሁን በተባለው ሰብሳቢ ከኮንፈረስ ኮል ስብሰባው ተባረው በሀብቴ፣ በመከታውና በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው አማካኝነት እስክንድር ነጋ በዓመት ውስጥ ሦስተኛውን ድርጅቱን ፈጥሮ መሪ ሆኖ ከቺሳ ብሏል። 😂😂😂

"…አንድም ቦታ ሳይዋጋ በመከታው ጦር ሲጠበቅ የከረመውና የዐማራ ፋኖን መርቼ ካልነገሥኩ ሞቼ እገኛለሁ ባዩ እስክንድር ነጋ አሁን በዐማራ ፋኖ ስም ሊደራደር አስፍስፎ መጥቷል። ነገር ግን አይቻልም። አጭቤ ሁላ እፋታህ መስሎሃል።

"…ሙሉ የስልክ ኮንፍረንሱን ትስቁ ዘንድ እለቀዋለሁ። ሁሉም ነገር እንዲህ እየጠራ መምጣቱ ሸጋ ነው። ግቦቴም፣ ኦነጌም ወየንቲም ተንጫጫብኝ። ዐማራ እንደሁ ድብን አድርጎ ያሸንፋል። ቃሌ ነው ሴራውም ሁሉ እንደ እንቧይ ካብ ይፈርሳል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ለቅቆ እነ አኪላን ዝምበሉ ማለትም ልክ አይሆንም። የግንባሩ፣ የፒለቲካው ቅማንቴ፣ የፖለቲካው አገው ሸንጎ፣ የኦሮሙማው እና የትግሬው የሚዲያ ሠራዊት የእነ አሰግድ ፋኖ ላይ ተቀናጅቶ ከብልጽግና ሠራዊት ጋር እየዘመተባቸው እያየሁ እነ አኪላን ከተጀመረው ብሽሽቅ ራሳችሁን አግልሉ ማለት አይቻልም። ብሽሽቅ ብሽሽቅ ነው። አንዱ አብሻቂ እንደፈለገው በጀት ተመድቦለት ሌላኛውን ያብሽቅ፣ ሌላኛው ግን ዝም ይበል ይባላል እንዴ? እነ አኪላን መመከር መገሰጽ ያለብኝንም በነገው ዕለት በይፋ በርዕሰ አንቀጼ እመጣበታለሁ። ይሰሙኛል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ይሄኛው ርዕሰ አንቀጽ እንደ መንደርደሪያ ነው። እንደ መግቢያ ማለት ነው። አፒታይዘር በሉት። ዋናው ይከተላል። እኔ የሓሳብ ነጋዴ ነኝ። ኮሶ የሆነ ሓሳብ ሻጭ ነኝ። የሆድህን ፀረ ዐማራ ትላትል ከአእምሮህ ሁላ ፍቄ የማወጣልህ የማሽርህ ኮሶ ነጋዴ ነኝ። አይስክሬም መብላት እንጂ መሸጥ አይሆንልኝም። አልታወቅበትም። ዕጣ ክፍሌም አይደለም። ነጭነጯን ዘርግፌ አዳሜና ሔዋኔ መስቀል እንዳየ አጋንንት፣ ፀበል እንደነካው ሰይጣን ሲያጓራ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም። እንደ ዘመነ አይነቱ ስተቸው፣ እንደ ምሬ፣ አይነቱ ስተቸው እልል ብሎ ትችቱን ተቀብሎ ወደፊት ይስፈነጠራል። እንደ እስክንድር አይነቱ አቦ አቦ፣ ጎሽ ጎሽ የለመደ የባርያ ጠባይ ያለው ደግሞ ጀግንነቱ በመዋጮ፣ በድርጅት የመጣ ስለሆነ ሲተች ይደናበራል። ከትችቱ ለመራቅ ቅጥረኛ ገዝቶ ያሠማራል። እኔ ደግሞ ወይ ፍንክች፣ ወይ ንቅንቅ እስከመጨረሻው ውግም።

“…ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤” ኢሳ 40፥4

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!

• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ዐማራስ? ዐማራማ ዐማራ ነኝ ማለት ከጀመረ ራሱ ስንት ሳምንቱ ነው? ቁጠሩት። ዐማራማ ትግሬና ኦሮሞ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ከኢትዮጵያ ነፃ ለመውጣት ሲባትቱ እሱ ከእነዚህ ነፃ አውጪዎች ጋር ለምን? እንዴት እያለ ነፍሱን ሲገበር ነው የኖረው። የዐማራ ስሪቱ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ተሰናስሎ የተሠራ በመሆኑ ዋጋ ሲከፍል ነው የኖረው። ሰፊ ሕዝብ ነው ቢሞትም ምንም ዓይደል፣ ቢፈናቀል፣ ቢጨፈጨፈም ምንም አይደል እየተባለ ዛሬ የዐማራን ትግል ለመጥለፍ ባሰፈሰፉ ዐማራ መሳይ ጆፌ ዐማሮች ሳይቀር ሲጎተት የኖረ ነው ዐማራ። ዐማራ በራሱ ብአዴን በተባለ ትግሬ ሠራሽ ፍጡር መከራ ፍዳውን የሚያይ ነው። ትግሬ ለህወሓት ኦሮሞ ለኦነግ የሚያደርገውን ድጋፍ ብአዴን ለዐማራ ፋኖ እንዳይሰጥ የተደረገውም በብዙ ምክንያት ነው።የዐማራን ትግል ፈጠነ፣ ዘገየ፣ እዚህና እዚያ ደረሰ ለማለት መጀመሪያ ተግዳሮቶቹን በመመርመር መፍትሄ ማበጀት ይቀድማል ባይ ነኝ። መፍትሄውን ለማምጣት ሥራና ትግል አቁሞ ሳይሆን በአንድ እጅ እየታገሉ፣ በሌላኛው እጅ መስመር ማስያዝ የግድ ነው። በአንድ እጅ እያመረቱ፣ በሌላኛው እጅ መተኮስ እንደማለት ነው። የዘመናት የዐማራ መርግ በሳምንታት አይፈታም። ግን መፈታቱ አይቀርም።

"…የዐማራ ፋኖን ትግል ዘረኛ ትግሬዎችና ዘረኛ ኦሮሞዎች ሲተቹት የዓይናቸው ሽፋሽፍት እንኳ አይርገበገብም። ዐማራ ዘረኝነት አያምርበትም እንደሚል የትግሬና የኦሮሞ ዘረኛን እንደመስማት የሚያስቅ ሌላ ምን ይኖራል? ትግሬና ኦሮሞ ላይ ያማረ ዘረኝነት ዐማራ ላይ አያምርም ሲሉ ጤንነታቸውን ብትጠራጠሩ አይፈረድባችሁም። ይሄን ይዘው ነው የግንቦት7 ዲቃላዎችና የእስክንድር ባልደራስ ግንባሩ ሰዎች በዐማራ ትግል ገብተው የሚፈተፍቱት። አንዳቸውም ኦሮሞና ትግሬ ካምፕ ውስጥ ገብተው ለመታገል አይደፍሩም። አይሞክሩምም። ክፍቱ ቤት የዐማራው ነው ብለው ነው ዘው ብለው ሊጣዱበት የሚከጅሉት። አንዳንዴም ገብተው ሁላ ፍትፍት በቆማጣ እጃቸው ይፈተፍቱበታልም። እሱ ነገር ነው አሁን ደም አፋሳሽ ትግል እየተደረገበት ያለው። ይሄንንም ዐማራ አሳምሮ ያሸንፈዋል።

"…ሌላው የዐማራ ትግል እንቅፋት ሆኖ ለጊዜው የተገኘው ዐማራ ነን የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ስማቸው የአማርኛ መሆን ጭምር ነው። አንድ ሰው አማርኛ ከተናገረ፣ ስሙም የዐማራ ነው ከተባለ አለቀ በቃ በዐማራ ትግል ውስጥ ገብቶ ለመፈትፈት ሰፊ ዕድል ነው የሚያገኘው። የዐማራ ገንዘብ አፈላላጊ አደረጃጀት ውስጥ ፈጥነው ገብተው ወሳኝ ቦታ የሚይዙት፣ ከያዙም በኋላ ንቅንቅ የማይሉት ወይ የትግሬ፣ ወይ ደግሞ የኦሮሞ ድቅል፣ ውህድ ማንነት ያላቸው፣ አልያም ህወሓት ወያኔ ወለዱ የፖለቲካው ቅማንት አልያም አገው ሸንጎ ነው የሚሆኑት። እንደዚያም ሆነው አልያም በድብቁ የአማርኛ ስም ለተሸፈነው ለትግሬ ማንነታቸው፣ አልያም በአማርኛ ስም ለተደበቀው፣ ለተሸፈነው ለድብቁ ለኦሮሞ ማንነታቸው ሲታትሩ ነው የሚታዩት። ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ፣ ዐማራ ይውደም የምትል የጽንፈኛ ወያኔ ትግሬ ሚስቱን ታቅፎ እየተኛ የዐማራ ፋኖ ገንዘብ ያዥ ሆኖ ሲያስተባብር ዐማራው ለምን ብሎ አይጠይቅም። በቃ ሰውዬው ዐማራ ከሆነ አይመራመርም። ጭንቅላቱን ለማሠራት አይሞክርም። ትግሬ ቢሆን እንደዚያ ያደርጋል ወይ? ኦሮሞስ ቢሆን?  አያደርግም። ዐማራ አግብተሻል ፍቺው? ዐማራ አግብተሃል ፍታት ተባብለው ስንቱ ትግሬና ኦሮሞ ነው ትዳሩን፣ ተቋሙን ያፈረሰው። ዐማራ እንደዚያ ያድርግ ማለት ሳይሆን የዘር ትግል ላይ የሚገቡ በተለይ ገንዘብ የሚያሰባስቡ ሰዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል ባይ ነኝ። ትግሉን ይበሉታል። ያዘገዩታልም።

"…ምሳሌ እናምጣ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ሀብታሙ አያሌው፣ በግድ ዐማራ ዐማራ እንዲሸት እስክናደርጋቸው ድረስ እንደ አበበ በለው ኢትዮጵያኒስቱ ካምፕ ውስጥ ነበሩ። ከእነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ነአምን ዘለቀ፣ ከእነ አበበ በገላው ካምፕ ውስጥ ነበሩ። አንዳንዶቹ ለብአዴንም ለፖለቲካው ቅማንትና ለፖለቲካው አገው ሸንጎም ስስ ልብ የነበራቸው ሁላ ነበሩ። ዐማራ የሆኑት በቅርቡ ነው። ይሄ ውሸት አይደለም። እስክንድር ሚስቱ ሰርካለም ትግሬ ስለሆነች የእነ እስታሊን፣ የእነ አሉላ ሰሎሞን ድጋፍ ስላለው እኔ ተቃውሞ የለኝም። እስክንድር ባልደራስን ሲያቋቁም የሰበሰባቸው ሰዎች የግንቦት ሰባት ሰዎች ስለሆኑም ችግር የለብኝም። እነዚያ ግንቦቴዎች ከባልደራስ ወደ ግንባሩ፣ ከግንባሩ ወደ ሠራዊቱ አብረውት ሳይቀየሩ ስለመጡም ችግር የለብኝም። መብቱ ነው። የእኔ ችግር እስክንድር በባልደራስ ስም አዲስ አበባን አሻግራለሁ በማለት የሰበሰበውን የዐሜሪካ ዶላር ለባልደራስ ሳያስረክብ እዚያው በአሜሪካ አቅልጦ፣ አስምጦ መቅረቱ ላይ ነው። የባልደራስን ሂሳብ አወራርድ ሲሉት ባልደራስን በአፍጢሙ ደፍቶ ወደ ግምባሩ ተሸበለለ። ግንባሩም ላይ ሲመጣ እነዚያኑ ግንቦቴዎች ገንዘብ ያዥ አድርጎ መምጣቱ ሳያንስ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር በዐማራ ፋኖ ስም ከሰበሰበ በኋላ ገንዘቡን ለፋኖዎቹ አከፋፍል ሲባል ልክ ባልደራስን በአፍጢሙ ደፍቶ ፋኖ ነኝ ብሎ እንደተከሰተው ወዲያው ነበር ሠራዊቱ ነኝ በማለት የተከሰተው። ባልደራስን በብጣሽ ወረቀት ያፈረሰው እስክንድር ግንባሩን እንዴት እንዳፈረሰው እንኳ ሳይናገር ነው በሦስት ደቂቃ ቪድዮ ዶር አምሳሉ የተባለ የደቡብ ጎንደር ፀረ ዐማራ ትግሬ ሚስት ያለው ወንድሙ የብአዴን ሓላፊ የሆነ ሰው ገንዘብ ያዥ አድርጎ በዐዋጅ የተከሰተው። ይሄ ነገር ምን ፈጠረ? የዐማራ ሕዝብ የማምነው አጣሁ ብሎ የፋኖን ትግል በሙሉ ኃይሉ በገንዘብ እንዳይረዳው ዕንቅፋት ፈጠረ። ዝለት ሕዝቡ ላይ ፈጠረ። 20 ሚልዮን ዶላር በ4 ወር ሊሰበስብ የተነሣው ስብስብ በ2 ሚልዮን ዶላር ወገብ ክንፉን ተመትቶ ቆመ። ይሄን ያደረገው እስክንድር ነጋን የተጣበቀው ፓራሳይት የግንቦቴ ስብስብ ነው። እስክንድር በሁላችን የተገነባ፣ አይነኬ ቅዱስ፣ ክቡር ስሙን ከፊት አስቀምጦ እርኩሳን መናፍስቶቹን ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ ሾተላይ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶችን በጫንቃው ተሸክሞ አጋብሶ አምጥቶ በተጀመረው ገነት ወደ ሆነው ወደ ቅዱሱ የዐማራ ትግል ውስጥ አምጥቶ ለዘፈዘፋቸው ነው የሚዳክረው። አሁን ችግር ለመፍጠር የሚንበጫበጩት እነዚህ ፓራሳይቶች ናቸው።

"…የዐማራ ትግል ከጨቅላነቱ ደግሞም ለብሔርተኝነት አዲስ ከመሆኑ የተነሣ በብዙ ተግዳሮቶች የተሞላ ነው፣ የታጀበም ነው። የዐማራ ትግል ግን አይነኬ የሚመስሉ ጉዳዮችንም፣ ግለሰቦችንም፣ ተቋማትንም እየነካ ከኃይል ወደ ኃይል እየተሸጋገረ መጥቷል። መጀመሪያ በስሜት የተያዘው የዐማራነት ትግል አሁን በዕውቀት እና በስሌት የሚመሩት፣ የሚሞቱለትም ተፈጥረዋል። የዐማራ ታጋዮች አሁን ሁሉን ወለል፣ ግልፅ አድርጎ የሚያሳያቸው መነፅርም አድርገው ሁሉን በሚገባ እያዩ ማን ምን እንደሆነ እየለዩ እየገመገሙም ነው። አሁን የዐማራ ትግል በአንዳርጋቸው ፅጌ ዲስኩር፣ በእስክንድር ነጋ ድል ለዲሞክራሲ መፈክር፣ በግንባሩና በግንቦቴ ግርግር አይቆምም። እንደ ወንፊት እያንገዋለለ፣ እንደ ሰፌድ እያበጠረው ገለባውን፣ ስንዴ መሳይ እንክርዳዱን እየለየ ወደፊት ይገሰግሳል። የዐማራ ትግል የፀረ ዐማራውን የወያኔን ድጋፍ በፍጹም አይፈልግም። ትግሬ ልብ ገዝቶ ትንኮሳውን ትቶ ባለመረበሽ ፀባይ አሳምሮ አርፎ በመቀመጥ ብቻ ካገዘው እሰየው በቂው ነው። ወያኔን የመሰለ አጋንንት የሚያመልክ ትግሬ ቅዱስ የሆነውን የዐማራ ትግል ሊያረክስ አይገባም። ዐማራ ግን ማንንም አይሰማም።👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"
     ክፍል ፩

“…ከኃይል ወደ ኃይል መሄድ።” መዝ 84፥7

"…ከመንግሥት ተብዬው የኦሮሙማው አገዛዝ ጋር በመታኮስ ነፍጥ በማንሣት ልክ የዛሬ ዓመት የተጀመረው የዐማራ ፋኖ ትግል ከትንሽ ኃይል ወደ ግዙፍ ኃይል የደረሰው በአንደዜ አይደለም። ደግሞም የዐማራ ትግል አስቀድሞ ታስቦበት፣ ቀመር ወጥቶለት፣ በጀት ተይዞለት፣ አመራር መርጦ፣ ቃለ ጉባኤ ይዞ፣ አጀንዳ ቀርጾ፣ ሠራዊት መልምሎ፣ ስንቅና ትጥቅ አደራጅቶ በጥራት የተጀመረ አይደለም። ትግሉ የተጀመረው በስንት ጉትጎታና ከብዙ ትእግስት መሟጠጥ በኋላ ነው። ትግሉን የጀመሩት ዐማሮችም እንደ ደራሽ ጎርፍ ድንገት ግልብጥ ብለው መጥተው ነው። የአገዛዙ ጭቆና እና ብሶት ናላውን ያዞረው፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማዱ በጅምላ ተጨፍጭፎበት ከሞት የተረፈ፣ የንግድ መኪናው፣ ድርጅቶቹን፣ የደረሰ የእህል ክምሩን አቃጥለውበት፣ መኖሪያ ቤቱን በላዩ ላይ አፍርሰውበት፣ ከሥራ አፈናቅለው፣ ከመንገድ አፍሰው በማጎሪያ ከምፕ ያጎሩት፣ እህቱን፣ ሚስቱን፣ እናቱንና አባቱን አስገድደው ደፍረውበት፣ እርሻውን አውድመው፣ ጎተራ ሙሉ እህሉን አቃጥለው፣ ከብቱን ነድተውበት፣ እሱን አግተው ጥሪቱን ዘርፈው ወስደውበት፣ መሄጃ መድረሻ አሳጥተውት፣ አዲስ አበባ ለመግባት በሰው ሚልዮን ብር አስከፍለው መክፈል ያቃተውን እንደከብት ሲያርዱት ማየትና መስማት የሰለቸውና የመረረው በደል ያንገሸገሸው፣ ነግ በእኔ ነው ከአሁኑ ይሄን ነገር ልመከት ያለና በበቀል የተንተከተከ ብአዴናዊ ያልሆነ አዲስ አስተሳሰብ የያዘ ያነገበም የዐማራ ትውልድ ድንገት ብድግ ብሎ ተነሥቶ ከየሥፍራውም ተሰብስቦ ነው እግሩ ወደመራው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ በመግባት ትግሉ የተጀመረው።

"…ዐማራ የሆነ ሁሉ ዶክተሩም ከሆስፒታል ከጤና ጣቢያው፣ ወዛደሩም ከፋብሪካው፣ ኢንጂነሩም፣ አናጺውም፣ ግንበኛውም ከሥራ ቦታው፣ ገበሬውም ከእርሻው፣ ወታደር፣ ፎሊሱም፣ ሚሊሻውም ከተቋማቱ፣ ኦርቶዶክሱም ከመቅደሱ፣ እስላሙም ከመስጊዱ፣ ወንድ ነህ፣ ሴት ነሽ፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ነጋዴ የለ፣ መምህር ከነ ተማሪ፣ ሹፌሩ የመኪናውን ቁልፍ ለቤቱ አስረክቦ ወዘተ ከዚህም ከዚያም ተጠረቃቅሞ ነው በቁጭት፣ በእልህ፣ በወኔ የዐማራ ፋኖን ትግል የጀመረው። ጥይት ተኩሶ የማያውቅ ብቻ ሳይሆን ጥይት ሲተኮስ ሸምቅቅ፣ ድንግጥ የሚለው ሁላ እኮ ነው ለቀጣዩ የዐማራ ትውልድ ዛሬ ላይ እርሱ ሞቶ ሌላውን ነፃ ለማውጣት መስዋእት ሆኖ ለመታገል ሲል ወደ ጫካ ግርር ብሎ የገባው። ቀደም ብለው በሽፍትነት፣ ኋላም በወያኔ ጦርነት ጊዜ በዘመነ ጁንታ የሀገር መከላከያውን ለመርዳት በዐዋጅ ተጠርተው ለትግል የወጡት በጁንታው ጦርነት ጊዜ በሰበሰቡት ጥቂት መሳሪያ ነው የዐማራ ፋኖን ትግል አሀዱ ብለው ያስጀመሩት። ታጋዮቹ ሁላቸውም አንዱ ከአንዱ አይተዋወቁም ነበር። የፋኖ ትግል እንደ እንደ ደራሽ ጎርፍ ድንገት ነው ምድሪቱን ያጥለቀለቀው። ግብስብስ ብሎ ነው እየተገማሸረ ድንገት ከተፍ ያለው የፋኖ ትግል።

"…ከዓመት በፊት ለሸዋ ቅርብ የሆነ እና በሸዋ መታገል የሚፈልግ የጎንደር ወይ የጎጃም ወይ የወሎ ዐማራ ሸዋ ሄዶ ለመታገል ይቸገር ነበር። ሸዋም ያለው፣ ጎንደርም ያለው፣ ጎጃምም ወሎም ያለው እንደዚያው ይቸገር ነበር። በአገዛዞች አስቀድሞ በተዘራ ዐማራን በጎጥ የመከፋፈል መንፈስ ዐማራ ሆኖም በዐማራ አደረጃጀት ውስጥ በፈለገው የዐማራ ግዛት ውስጥ ለመታገል እጅግ አስቸጋሪም አስፈሪም ነበር። ደቡብ ጎንደሮች እና ጎጃሞች ተስማምተው በአንድ ላይ ለዐማራ ይታገላሉ ብሎ የገመተም፣ የጠበቀም አልነበረም። ወሎና ሸዋ፣ ጎጃምና ሸዋ፣ ጎንደርና ጎጃም፣ ወሎና ጎንደር አንድ ላይ ይቆማሉ ብሎ የገመተም አልነበረም። አገዛዙዝም የተሸወደው እዚህ ላይ ነበር። ከሰኔ 15 በፊትም ከሰኔ 15ም በኋላ በመንግሥታዊ ሴራ፣ በመንግሥታዊ በጀት፣ በመንግሥታዊ የፕሮፓጋንዳ የሚዲያ፣ የካድሪና የባለሥልጣናት ፕሮፓጋንዳ ጎጃምና ጎንደር በተለይ ተስማምተው አንድ ላይ ይቆማሉ ብሎም አላሰበም። ግርማ የሺጥላን አስገድሎ በሸዋ መካከል ሽብልቅ አስገብቶ ሸዋን እከፋፍላለሁ ብሎ ያሴረው ሴራም ለአገዛዙ ግርማ የሺጥላን ደመ ከልብ ከማድርግ ውጪ የፈየደለት ነገር የለም።

"…እንዲህና እንዲህ ሆኖ የጀመረው የዐማራ ትግል መጀመሪያ በየሰፈሩ፣ በየጎጡ፣ የሚተዋወቁ፣ የሚግባቡ ተሰባስበው ነው አገዛዙን መግጠም የጀመሩት። አገዛዙዝም ይሄን በጎጥ፣ በሰፈር ያለ አደረጃጀት በመግጠም ማሸነፍም አያቅተኝም በማለት ነው በብራኑ ጁላ፣ በአበባው ታደሰ መሪነት በሳምንት ሱሪያቸውን አስወልቃለሁ፣ እናጸዳቸዋለን በማለት በንቀት፣ በፉከራ ዘለው የገቡበት። ዘሎ የገባውም የጁላ ሠራዊት ጭዳ ነበር የሆነው። እነ እስታሊን ገብረ ሥላሴ፣ እነ አሉላ ሰሎሞን፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ የብልጽግና አክ እንትፍስቶች ሁሉ በዐማራ ፋኖ ጉዳይ ስምም ሆነው የመጡት አይሰበሬውን ዐማራ ካዩት በኋላ ነው። በሎም እያለ የትግሬን ሠራዊት ሲያስወቃ የነበረው ናትናኤል መኮንን፣ ወያኔ ትግሬ ለማጥፋት አስር ቦንብ በቂ ነው ያለውን ዳንኤል ክብረት ዐማራን ጃዊሳ በማለቱ ከጣሪያ በላይ ተደስቶ ለናቲና ለዳኒ ላይክና ሼር የሰጡት የትግሬና የኦነግ አክቲቪስቶች የታዩት የዚያን ሰሞን ነበር። ዐማራ ላይ በተደረገው ዘመቻ ሄሮድስና ጲላጦስ ፅዋ አንስተው ቺርስ እስከመባባል ነበር የደረሱት። የመጀመሪያው ቀን። አሁንስ ወፍ የለም። ጉማ ሰቀታ በፌስቡክ ገጹ፣ በቴሌግራም ገፁ የድሬደዋ መሬት አስተዳደርን ማስታወቂያ ነው የሚሰራው፣ የአዋሳው ትግሬው ዳዊት መሪጌታ መዝግቡና ላኩልኝ ላስገድል ወደማለት ገብቷል። የኦሮሞ አክቲቪስቶች በቁቤ ማውራት፣ መጻፍ ትተው በአማርኛ ሆኗል ሽለላ ለቅሷቸው። ዳኒ ጮጋ ብሏል። ይሄን ምን ፈጠረው ያልከኝ እንደሆን ምቱ ነው። የፋኖ ምት።

"…ባልተቀናጀ፣ ባልተደራጀ፣ በዐማራዊ ሥነ ልቦና ብቻ ትግልን ሀ ብሎ የጀመረው ዐማራ የሺ ዘመናት የአራሽ፣ ቀዳሽ፣ ተኳሽ የጦረኝነቱን ልምድ፣ በደሙ ውስጥ ያለውን የማሸነፍ እና የመደራጀት ጥበብ ተጠቅሞ ነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ልዩነቱን አጥብቦ፣ ፈታቶም በሚገርም ሁኔታ አስቀድሞ በተበታተነ መልኩ የነበረውን አደረጃጀት ቀስ በቀስ ወደ ሁለት ሦስት ዝቅ ወደማድረግ በምጣት አሁን ዝሆን ያከለው።  በጎንደር ውስጥ በእነ ጋሽ መሳፍንት ስር የመጡ የግንባሩ፣ በእነ ሻለቃ ባዬ ስር የገቡ ፋፍዴን በመባል የሚታወቁ ወንድሞች ነበሩ። ፋፍዴኖች ድርጅታቸውን አክስመው በእነ ሻለቃ ባዬ እዝ ሥር ተጠቃለው ሲገቡ ጎንደር ከብዙ የፋኖ አደረጃጀት ወደ ሁለት ነው የመጣው። አሁን የማንነካካው የወልቃይቱ የደመቀ ዘውዱ ሠራዊት ሳይጨመር ማለት ነው። ይሄ ለጎንደሮች ድል ነው። አሁንም ሌት ተቀን በር በመዝጋት ጎንደሮች ወደ አንድ ለመምጣት እየተሟገቱ፣ እየተጨቃጨቁ፣ እየተከራከሩ ነው። ይሄ ደግሞ ጤናማም፣ ተፈጥሮአዊም፣ የሥልጡን ሕዝብ ባህሪም ነው። ከብዙ ወደ ሁለት ቀርበው ከሁለት ወደ አንድ ለመምጣት አሰልቺ፣ ቋቅ የሚል ግን የማይተው ሙግት፣ ክርክር፣ ውይይት እያደረጉ ነው። በቅርብ የማውቀውን ነው የምነግራችሁ።👇ከታች ይቀጥላል ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤” ኢሳ 40፥4

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከዚህ የመሸጋገሪያ መልእክት በኋላ እንመለሳለን… 😂😂😂

"…ባንዲራው የሰይጣን ነው ብለው ለባንዲራው ደሙን የሚያፈሰውን ሶዬ ባንዲራው ላይ አስቁመው አስካዱት። ይሄ ባንዲራ የሰይጣን ባንዲራ ነው" በል አሉት ኦነግ ሸኔውም ግጥም አድርጎ ይሄ ባንዲራ የሰይጣን ባንዲራ ነው ብሎ አረጋገጠላቸው። ይሄ ባንዲራ አያሻግርም፣ ይሄ ባንዲራ አያበለፅግም😂 ይሄ ባንዲራ ሀገር አጥፊ ነው በል አሉት ሸኔውም አለላቸው።

"…በመጨረሻው ዘመን ቤተሰብ ለቤተሰብ አንዳንዴ ይጣላል የተባለው እውነት ነው ለካ። የራስህ ጉዳይ…

• ቆይቼ ተመልሼ እመጣለሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… ወደ ሁለተኛው ጥያቄ እናልፋለን።

"…ለመጀመሪያው ጥያቄዬ "አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ አዳኝም ጠባቂም ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…? ለሚለው ጥያቄ መቶ ሰዎች ይመልሱልኝ ብዬ ብጠይቅም በደቂቃዎች ውስጥ ከ400 በላይ ሰዎች በድፍረት፣ በወኔ፣ በእውነት እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው መልሱ ፋኖ ነው በማለት መልሰዋል። ግሩም ነው። ዕጹብ ድንቅ ነው።

• ሁለተኛውን ጥያቄ እቀጥላለሁ።

"…አሁንም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ (የነገድ አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ከሆነ፣ የኦነግ ሸኔ ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው እንላለን…?

• ይሄንንም ሳትዘበዝብ፣ ሳትቸከችክ፣ ሳታንዛዛ መልስልኝ።

• ከአንድ 100 ሰው መልስ በኋላ ከች እላለሁ።

"…እደግመዋለሁ። "…የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ነው ካልን፣ የኦነግ ሸኔም ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ይሄ ሩቅ ዓባይ ማዶ አይደለም። ተከዜም፣ ራስ ደጀንና መተማ፣ ቋራም አይደለም። ደምበጫም፣ አዲስ ዘመን፣ ነፋስ መውጫ፣ ደብረታቦር ጋይንትም አይደለም። የዋግሹሞቹ ሀገር ላስታ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎም አይደለም። እዚህ ነው አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ሸዋ ክፍለ ሀገር። አዎ እዚሁ ቅርብ ነው።

ከጥንት እስከ ዛሬ ቃሉን የጠበቀ
ፋኖ ነው ዘላለም ሱሪ የታጠቀ

"…ይሄ የምታዩት የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ነው። ዐማራ በታሪኩ በመንግሥት ላይ ተቆጥቶና አኩርፎ ነፍጥ ሲያነሣ ይሄ ዘመን ዘመነ አቢይ የመጀመሪያው ነው። ዐማራ ዳር እስከዳር "መዳኛችን ነፍጣችን" ብሎ ሲወስንም ይሄ ዘመን የመጀመሪያው ዘመን ነው። ያውም ማነቆ ባንዳዎች፣ ሆዳም ዐማሮች፣ የጠላት ቅጥረኞች፣ ሾተላይ ሰላዮች በውስጡ ተሰግስገው፣ በላዩም ተከምረው ተጣብቀውበት ሁሉን ጣጥሎ ከባዶ እጅ፣ ከድንጋይና ሽመል ተነሥቶ እንዲህ ዘጭ ያለው በአንድ ዓመት ውስጥ ነው። ይሄ በአንድ ዓመቱ እዚህ ቁመና ላይ የደረሰው የዐማራ ነገድ እንደ ትግሬ ነፃ አውጪዋ ወያኔና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪው ኦነግ ከ50 እና 60 ዓመት ጀምሮ ብሎ አለማሰቡ ይሻላል። ይሄኔ በምሥራቅ አፍሪካ ራሱን የቻለ ልዕለ ኃያል ነበር የሚሆነው።

"…የዐማራ ትግል አሁን ቁርጥ ሆኗል። አደረጃጀቱም በመንግሥት ቁመና ነው እየተደራጀ ያለው። በስመ ፋኖ መንቀሳቀስ። መዘባረቅ አይቻልም። ፋኖ ባለቤት አለው። የ10 ኛ ክፍል ወዳቂ እና መውደቂያ፣ ገዢ ያጣ ፖለቲካ ይዞ የሚዞር የቦለጢቃ ነጋዴ ሁላ በስሙ የሚነግድበት አይደለም። ሸዋ እንዲህ የሆነ ጎጃም፣ ጎንደር፣ እና ወሎን ማሰብ ነው። መንደሩ ሁሉ ወታደራዊ ሥልጠና ላይ መሆኑም አስደሳች ነው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከዝክር መልስ…

ከጥያቄ 27 - 60

"…ዛሬ ደስ ብሎኝ ነበር ያመሸሁት። በሀገረ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጅ ከዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን የሐምሌ ሥላሴን አከበረን። ኢትዮጵያን ነው ያስታወሰኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከመኝታ በፊት ግን ይህን ልበል። እንግዶቼን ከሸኘሁ በኋላ አስቀድሞ ወጣ በተባለው በፈተናው ጉዳይ ዘመዴ ይሄ የለጠፍከው ያልተፈተኑት ነው የሚል ሓሳብ ሰጪ በዝቶ አግኝቻለሁ። ጥያቄው የማኅበራዊ ሳይንስ ቢሆንም ከሰብጀክት ኮድ በስተቀር አይመሳሰልም። ለምሳሌ፦ ፔጅ ነምበር፣ ቡክሌት ኮድ፣ ምርጫ ኮድ በአጠቃላይ ጥያቄው ገና ያልተፈተኑት ነው የሚልም አስተያየት እያየሁ ነው።

"…የሆነው ሆኖ እኔን ምን አስጨነቀኝ? ምንስ አጨቃጨቀኝ? ተማሪዎቹ ቀድመው ተፈትነውት ከሆነ እሰየው ቀድመው ያልተፈተኑት እና ወደፊት የሚፈተኑት ከሆነም ከሆነም እሰየው፣ የተፈተኑት ከሆነ እንዲያውም ክለሳ ይሆንላችኋልና ለምን ሙሉውን አልለጥፍላችሁም ብዬ በማሰብ ሙሉውን ለጥፌላችኋለሁ። ተማሪዎች ቀድመው የተፈተኑት ከሆነ መልካም ነው መልሰው ቢያጠኑት ምናቸው ይጎዳል? ምንም። ያልተፈተኑት ከሆነም አገዛዙ ተሰርቆ ወጥቶበት ከሆነ ይጠነቀቅበታል። አለቀ። ተማሪዎች ግን አጥኑ። ሳትዘናጉ ወጥራችሁ አጥኑ።

• ደኅና እደሩልኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የለጠፍኩትን የፈተና ወረቀት በተመለከተ ሌሎችም መምህራን ያደረሱኝ ሲሆን። ይሄ የፈተና ወረቀት የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች የተፈተኑት የፈተና ወረቀት ነው። እናም አሁን በመጪው ሳምንት የሚፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ የሚፈተኑት አይደለም የሚሉ መረጃዎች ደርሰውኛል።

"…ምስጋና በቀጥታ የስልክ መስመር ጭምር ደውላችሁ እኔ ራሴ ፈተናውን በኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ክልል ወዘተረፈ ፈትኜዋለሁ ብላችሁ መልሳችሁ ለላካችሁልኝ ይሁን። ልጃችሁ ይዞት መጥቶ አይሆንም እውነት ከሆነም መንግሥት እርምት ይውሰድበት ብላችሁ ጥያቄውን ለላካችሁልኝ ቤተሰቦች ይሁን።

"…የሆነው ሆኖ የፈተና ወረቀቱ ቀደም ብሎም ይውጣ አይውጣ ጉዳዩ ላሳሰባችሁና ለተጨነቃችሁ በሙሉ እንደ ዜጋ ነገሩ አሳስቦን ጥያቄውን ሳነሣና ለውይይት ሳቀርብ ፈጣን ምላሽ ለሰጣችሁኝ ወንድም እህቶቼ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለማንኛውም እኔ ወደ ወደ ዘኬ ለቀማዬ ልመለስ ቢሆንም ፈተና ወረቀት የተባለው ቢሆንም፣ ባይሆንም ብታጠኑት አይጎዳችሁም እና እኔ እንደሚከተለው አድርጌ ለጥፌላችኋለሁ።

• ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ተፈተኑ። መልካም የፈተና ሳምንት ይሁንላችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"
         ፩

• የኢንርኔት መለቀቅን በተመለከተ።

"…50 እና 60 ሚልዮን ሕዝብ በሚኖርበት የዐማራ ክልል ውስጥ ዓመት ሙሉ ኢንተርኔት ዘግቶ ጦርነት ሲያካሂድ፣ የዘር ማጥፋት ሲፈጽም የከረመው የኦሮሙማው አገዛዝ ሰሞኑን በእሜቴ ፍርዬ ታምሩ በኩል ከፓርላማው ዘንዳ ቀርቦ በዐማራ ዘንድ ብከስርም በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ግን ትርፍ በትርፍ ሆኛለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይሄው ትርፋማ ሆኛለሁ ብሎ የተቦተረፈው የፍርዬው ቴሌኮም ካምፓኒ ነው ታዲያ በዛሬው ዕለት በተመረጡ የዐማራ ክልል ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍት ማድረጉን ያወጀው። ይሄን በማስመልከትም የዐማራ አንቂዎች ስጋታቸውን፣ ጥቅምና ጉዳቱንም ጭምር አስመልክተው አጭር የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል። ተጠቀሙበት።

ሀ፦ ጥንቃቄ እና አደጋው

፩ኛ፦ አንዳንድ የዐማራ ወጣት ፋኖዎች ልክ እንደ እንደ እስክንድር ፋኖ እንደ ፋኖ ባርች ሌላኛውን ፋኖ ለመስደብ፣ ለመከፋፈል እና ሰሞኑን የተራገበውን የብልፅግና ሰዎች የሚጮሁበትን የምኞት የክፍፍል ዜና በስፋት በቲክቶክና በፌስቡክ ጭምር በቪዲዮና እና በፎቶ ጭምር ቁርቋሶውን ቢያሰፋልን ብለው በማሰብ በዚያውም የወጣቶቹን ማንነትና መገኛ ስፍራ፣ አደረጃጀት ወዘተ በማነፍነፍ የመሪዎችን መገኛም ለማወቅ ሊሆን ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ ተብላችኋል።

ለ፦ ጥቅሙ እና መልካም አጋጣሚው

፩ኛ፦ አገዛዙ ለተንኮሉም ይሁን የኪሳራው ጉዳት አሳስቦት የከፈተውን ኢንተርኔት መላው የዐማራ ሕዝብ ደግሞ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ቶሎ ቶሎ መረጃ እንዲለዋወጥበት ይደረግም ተብሏል። ለምሳሌ እንደ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ዓይነቱን መልእክት ተለቭዥን ለሌለው ለሁሉም የዐማራ ሚሊሻና አድማ ብተና አባላት እንዲደርስ ማድረግ

፪ኛ፦ በአገዛዙ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን ቶሎ ቶሎ ለታማኝ ሚዲያዎች በመላክ ወዲያው ግን የኢንተርኔት አጠቃቀምን በራስ ላይ ማዕቀብ በመጣል ጭምር ገደብ መጣል ያስፈልጋል ተብሏል።

፫ኛ፦ ከወትሮው በተለየ መልኩ የፋኖ አባላት ስልክ እንዳይጠቀሙ መጠርነፍ፣ መከልከል። ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ፣ ለፍቅረኛ ወዘተ ለመደወል መሯሯጥ ቢቀርም ተብሏል። ወዳጄ ፋኖ ድምጽህን አጥፋ። እንደ እነ ፋኖ ባርች በመንግሥት የተፈቀደልህን የመከፋፈል ፈቃድ ይዘህ  ኢንተርኔት ላይ ተጥደህ አትደስኩርም ተብለሃል።

"…የማትሪኩን የፈተና ወረቀት በተመለከተ ከ30 ደቂቃ በኋላ ሓሳቤን በመረጃና በማስጃ እሰድላችኋለሁ። መጀመርታ ይሄኛውን ተጠቀሙበት።

• ቆይቼ እመለሳለሁ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን። ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።

…በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። 2ኛ ቆሮ፥ 13፥ 9 -14

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ያዝ እንግዲህ…😂

"…ዳግማዊ አቢይ አሕመድ አንድ እብድ፣ አንድ ወፈፌ ታላቁን የዐማራ ሕዝብ እንዲህ ሊጫወትበት ሲፍጨረጨር እያየሁማ ዝም አልልም።

"…አጅሬ እስክንድር ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ጉብኝት በሚል ሰበብ ሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር ይሄዳል። ከጎንደር የጋሽ መሳፍንትን አማኝነት ያያል። በዚያ መንገድ ገባባቸው፣ አስማላቸው፣ ጎንደሬ ለማዕተቡ ሟች ነው ይኸው እነ ሀብቴን የመሰሉ ጀግኖችን አፍዘው፣ አደንግዘው የእስክንድር ባሪያ አድርገዋቸው ቀሩ። እስክንድር የጋሽ መሳፍንትን የቆሰለ ልጅ አዲስ አበባ ድረስ ወስዶ አሳክሞ፣ አሜሪካ የያዘችው ገንዘብም ሲለቀቅልኝ እሰጣችኋለሁ ብሎም ነው አስሮ የያዛቸው።

"…እስክንድር ዘመነ ጋር ሲሄድ ዘመነ የተማረ ቢሆንም ሁሉን አማኝ፣ ፎልፏላ፣ ሆደ ቡቡ፣ ሃይማኖተኛ፣ አስሬ ለክቶ አንዴ የማይቆርጥ መሆኑን በደንብ አየ። ሳያርቅ ሳያቀርበውም በሃብታሙ አያሌው በኩል ማርያምን እኔና እስክንድር አንለያይም እያስባለው ለጉሞት ቆየ።

"…እነምሬ ጋር ሲሄድ እነምሬ አድንቀውት ግን እንደ ጎንደርና ጎጃም ልባቸውን ሳይከፍቱለት ሸኙት። ከወሎ መልስ ሸዋ መጣ። በሸዋ ያገኘው በአንድነት የነበሩትን አሰግድና መከታው ነበር። እስክንድር እንደ አቢይ አህመድ የተማረ ሰው ጠልና ሰብሳቢ ነውና አሰግድ ፊደል የቆጠረ፣ በውትድርናውም ውስጥ ኮማንደር የሆነ፣ ደራሲና ሀያሲ ብስል ፖለቲከኛ መሆኑን አየ። መከታው ከሁለተኛ ክፍል ይበሉኝ ከ8ተኛ ክፍል ትምህርቱን ያቋረጠ ምስኪን መሆኑንም ተመለከተ።

"…በመጨረሻ ታናሹ ማረፊያው መከታው ጋር እንዲሆን ወሰነ። መከታው ጋር ሆኖ መጀመሪያ አሰግድንና መከታውን ለያየ። ጎጃም ተሻግሮ ዘመነ ላይ አሳመፀ፣ ጎንደርን ለ2 ከፈሎ አገዳደለ፣ ይኸው ወሎን ሰነጠቀው። እኔ ዘመዴ ከነከስኩ ነከስኩ ነው ሳላደማማ መፋታት መች ዐውቅና።

💪 አይደለም እንዴ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ከወትሮው በተለየ ዛሬ ሁኔታ በፍጥነት ሞልቷል። 😂 እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ይህ የምታዩት ፎቶ ደቡብ አፍሪካ በሄድኩ ጊዜ ኔልሰን ማንዴላ ታስሮበት የነበረውን የሮቢን ደሴት ከጎበኘሁ በኋላ በኬፕታውን ከተማ አናት በቴብል ማውንቴን ላይ የተነሣሁት ፎቶ ነበር። ካሜራ ማኖቹ ተሼና አባ ነበሩ።

"…ፎቶውን ስነሣ በአንደበቴ እናገር የነበረውን ቃል አሁን ድረስ አልረሳም። በህወሓት ኢህአዴግ፣ በጥልቁ ዓለም ሰዎች ይደገፉ ከነበሩትና በወቅቱ በሕዝብ ዘንድ ቅቡል ከነበሩት ከእነ በጋሻው፣ ዘርፌ፣ አሰግድና ትዝታው ምድረ ተሃድሶ ጋር ብቻዬን ጉረንቦ ለጉረንቦ ተናንቄ እፋለም የነበረበት ወቅት ስለነበረ እንደማሸንፋቸው እርግጠኛ መሆኔን እየተናገርኩ የተነሣሁት ፎቶ ነበር። ሁል ጊዜ የአሸናፊነት ስሜት ሲሰማኝ ፈልጌ የማየው ይሄን ፎቶ ነው።

"…ትናንት ብዙ ሰዎች በቲጂ ፔጄ ላይ በአፋቸው እንዲያስታውኩና እንዲጸዳዱ ፈቅጄ ከዳር ቆሜ ሲበለሻሹ እያየሁ ነበር። የብልፅግና፣ የወያኔ፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት፣ የባልደራስ፣ የግንባሩ፣ የሠራዊቱ፣ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱ፣ የዓለም ብርሃን ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ቅማንት፣ የአገው ሸንጎ፣ የብአዴን ሰዎችና ደጋፊዎች እንደ ግሪሳ ሲሰፍሩብኝ እያየሁ አሸናፊነቴን እያስታወስኩ እስቅ ነበር። ለዚያ ነው ያስታውኩ ዘንድ የፈቀድኩላቸው። ዛሬ ግን እንዳያችሁት በምስጋና ሰዓት ማስታወክ ስድብም ካካ እፉ ሆኖ ስለማይፈቀድ ቀስፌ ቤቴን አጽድቼዋለሁ።🔥🔥

"…እኔ ዘመዴ ሳልጋበዝ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ ነበርኩ። ጄ/ል ተፈራ ማሞ በደስታ ሲቦርቅ፣ ሙሀባው፣ መከታው፣ ኮ/ል ታደሰ ሲደሰቱ፣ ዝናቡ ሲቆጣ ሁሉንም ቀድቻቸዋለሁ። እናንተም ትፈርዱ ዘንድ በመረጃ ቴቪ ሙሉውን እለቅላችኋለሁ። ጠብቁኝ።

• ማርያምን ሴረኞችን ብቻዬን አሸንፋቸዋለሁ።  

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አቋሜን ስለማሳወቅ…

"…እኔ ዘመድኩን በቀለ አክሊለ ገብርኤል የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የሐረርጌው መራታ፣ የምሥራቁ ሰው፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ፣ አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ የዐማራ የነፍጠኛው ወዳጅ ወድጄና ፈቅጄ ማንም ሳያስገድደኝ እነዚህ በምሥሉ ላይ ከሚታዩአቸው የዐማራ ሕዝብ ፋኖዎች ጎን የምቆም መሆኔን በታላቅ ወኔና በታላቅ ድፍረት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

"…የኮመንት ሳጥኔን ክፍት ያደረግኩት አውቄ ነው። ዝንቦቹን ለማጥመድ ስለፈለግኩ ነው። የወያኔ፣ የግንቦት ሰባት፣ የግንባሩ፣ የፖለቲካው ቅማንት፣ የአገው ሸንጎ፣ የብአዴን፣ የብልጽግና፣ የዓለም ብርሃኖች፣ ኦነጎች፣ ዲቃላዎች ስለተንጫጩ ንቅንቅ አልልም። እነዚህን በምሥሉ ላይ የምታዩአቸውን በገንዘብ ያልተገዙ፣ ከነ ድክመታቸው እና ከእነ ስህተታቸው አብሬአቸው የምቆም መሆኔን አረጋግጣለሁ።

"…በስድስት ዓመት ውስጥ ከዛሬው ጋር 5 ድርጅት መሥርቶ ሲያፈርስ ከነበረ አፍራሽ ግለሰብ ጎን የማልቆም መሆኔንም አረጋግጣለሁ። 1- የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት ሊቀመንበር፣ 2- የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበርነ፣ 3- የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ሊቀመንበር፣
4 -የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት ፋኖ ሊቀመንበር፣
5- የዛሬው ራሱን በራሱ የመረጠውን የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሊቀመንበ ተብዬውን ሌላው አቢይ አሕመድ እብዱ፣ የወደቀው መላክ እስክንድር ነጋ አጥብቄ በመቃወም የምሞግት መሆኔንም አረጋግጣለሁ።

"…በጥዋቱ ጥቅስ አቋሜን እቋጫለሁ። “…ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤” ኢሳ 40፥4

"…አዛኜን ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል። ተንጫ ምድረ በጭባጫ ሁላ። ማርያምን እኔ ዘመዴ ብቻዬን ክፍለጦር ነኝ። አዛኜን እንቅልፍ ነው የማሳጣችሁ። እናትማ እኔን ወለደች። 😂😂😂✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

😂 ሳንቀደም እንቅደም መሆኑ ነው። 😂

"…የፖለቲካ ፓርቲ ኢንኪዩቤተሩ እስክንድር ነጋ እኔ ገና ተናግሬ ሳልጨርስ በዓመት ውስጥ ሦስተኛውን ድርጅት ዛሬ መሠረተ። የእስክንድር ሚስት የሥጋ ዘመድ ነው የሚባለው የዛራ ሚድያው የዓድዋው ትግሬ እስታሊን ገብረ ሥላሴና የሀብታሙ አያሌው ኢትዮ 360 ሚዲያም ይኸው በሰበር ዜና ከች አሉ።

"…ያው እንደተናገርኩት ነው የሆነው። ጎንደር የጋሽ መሳፍንት ግሩፕ በእነ ሀብታሙ አያሌውንና በሌሎች ሚዲያ በኩል ስሙን ካስጠፉት በኋላ ሜጀር ጀነራል ውብአንተ ተገደለ። ውብአንተ እኔ የሀብታሙ አያሌው ወታደር አልሆንም እንዳለ ነው የተገደለው።

"…የዛሬ ሳምንት ደግሞ እስክንድር ተጠግቶት ያለው የመከታው ፋኖ የሸዋ ፋኖውን መሪ አቶ አሰግድ ለመግደል ሰራዊት ተልኮ ዐማራ ለዐማራ ከሚጫረስ ብሎ አቶ አሰግድ ማጀቴን ለቅቆ አፈገፈገ።

"…እስክንድር ነጋ ዘመነን ለመገልበጥ ወንድሙን ማስረሻ ሰጤን አምጥቶ የጎጃም ፋኖ ላይ ሽብልቅ ከተተ፣ ኮሎኔል ጌታሁንን ከጎጃም ፋኖ በብዙ ሚልዮን ብር ወደራሱ ገንጥሎ ወሰደ።

"…እስክንድር አንድ የሆነውን የወሎ ፋኖን በብር ኃይል ለ2 ከፈለ። ከፈለናም በብአዴን እርዳታ፣ በብልፅግና ድጋፍ፣ በእነ እስታሊን ና በእነ ናትናኤል መኮንን በግንቦቴና በግንባሩ ሰዎች ግርግር በዛሬው ዕለት የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሚል መስርቶ ራሱንም ሊቀመንበር አድርጎ ከች አለ። እስታሊንም የተላከለትን የድምጽ ቅጂ በሰበር ዜናው ለቀቀው።

"…እስክንድርን አስራው ጀግና ያደረገችው ወያኔ፣ እስክንድርን ባህርዳር ይዞት ተነጋግሮ ተስማምቶ የፈታው ብአዴንና ብልጽግና የዐማራ ትግል የተጠለፈ፣ ፕሮፌሰር አሥራት ዛሬ ድጋሚ የተገደሉ እስኪመስሏቸው ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸው። 😂 ወዳጄ እነ አኪላ ለምን እንደሚጠሉ ዛሬ ገባችሁ አይደል?

• እህሳ ምን ታስባላችሁ? እስቲ ተንፕሱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ "…ዐማራ የዘመናት ጋግርቱን ብአዴን የተባለን መርግ ከላዩ አሽቀንጥሮ የጣለ ቀን ነው ነፃ የወጣው። ኦሮሞ ኦነግን፣ ትግሬ ወያኔን መቅደስ ሠርተው ሲያመልኩ ዐማራ ነው ወያኔ ሠራሹን ብአዴን የተባለ የሀገርም፣ የዐማራ ነቀርሳ ዘንዶ ገርስሶ የጣለው። ዐማራ አሁን ቀጣዩ እርምጃው ድርጅታዊ ተቋም መመሠርት ነው። ማጠናከር ነው። ወታደራዊ ቁመናውን ማሳደግ ነው። ለገዳይ ወያኔም ኦነግም የሚያስፈራ፣ የሚበቀል፣ እረፍት የማይሰጥ፣ ትንታግ የሆነ በቂም በቀል የሰከረ፣ ዐማራን መንካት ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚያረጋግጥ፣ የትም ገብቶ የትም እርምጃ የሚወስድ፣ ትንታግ ሠራዊት መመሠረት ነው። እሱን እየሠራ ነው። የተጀመረው የዐማራ የህንነት ተቋም ማደግ አለበት፣ የዐማራ ሚዲያ ማደግ አለበት። ዘፈኑ፣ ሙዚቃው በጥራት ዐማራ ዐማራ እየሸተተ መፈብረክ፣ መመረት አለበት። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች የአማርኛ ለቅሶ ላይ እየሳቀ፣ እየገለፈጠ፣ ሙድ እየያዘ ወደፊት መግፋት አለበት። ዐማራን የሚያድነው ከእንግዲህ ቆራጥ፣ ጨካኝ፣ የቄስና የሼህ ስብከት ሸብረክ የማያደርገው፣ ቁማር በላሁት፣ ወዘተ የማያደነዝዘው ሀሞተ ኮስታራ መሆን ብቻ ነው የሚያሳድገው።

"…በሽዋ፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በጎንደር የዐማራ ፋኖ አደረጃጀት በአቅሚቲ በጥሩ ቁመና ላይ ነው የሚገኘው። ተቋማዊ ለማድረግ እየተፍጨረጨሩ ነው። ከግለሰብ ኢጎ ለማውጣት እየተንደፋደፉ ነው። በሰው ትከሻ፣ በግለሰብ ምላስ ላይ ከመንጠልጠል እየወጡ ነው። ብልጦች ቆዳ ቀይረው፣ ሜካፕ ተቀብተው እንደፈለጉ በፈለጉት ጊዜ መጥተው የሚዘውሩትም አይደለም። አሁን የዐማራ ፋኖ የሚገርም ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው ያለው። አሁን እኮ የዐማራ ፋኖ የብልጽግና አክቲቪስቶች ከጠፋ፣ ተደመሰሰ ወጥተው ቢሆንልን፣ የበሬው ቆ*ጥ ቢወድቅልን ብለው አሰግድና መከታው ተጣሉ፣ መከታው አሰግድን ገደለው፣ ደመሰሰው፣ ዘመነ እና እስክንድር ተጣሉ። ሙሀባው ለእስክንድር አገዘ፣ ሀብቴ ከእስክንድር ጋር ቆመ፣ ማርሸት ሀብቴን ሰደበው፣ እገሌ እገሌን እንዲህ አደረገው እያለ የመንደር ወሬ፣ ሀሜት በኪሱ ይዞ ሲቸረችር ነው የሚውለው። ይሄ ራሱ ትልቅ ለውጥ ነው። እንዲያውም አንዳንዴ ተመካክሮ እንዲህ አጀንዳ መወርወር ጥሩ ነው። ሁለቱ የጎንደር እዞች ሰሞኑን በአንድ ተጣምረው አንድላይ ተሰልፈው ነው በአንድነት የጁላን አራዊት ሠራዊት ፍዳውን ያሳዩት። ሁለቱ ወደ አንድ እዝ እስኪመጡ እንዲህ መረዳዳታቸው የግድ ነው። በወሎም፣ በሸዋና በጎጃምም እንዲሁ ነው። ዐማራ ያሸንፋል።

"…አሁን ግልጽ ክርክር ተጀምሯል። ይሄ ግማታም የበሰበሰ አገዛዝ መውደቁ አይቀሬ በመሆኑ ለሥልጣን መፎካከርም ተጀምሯል። ይሄ ደግሞ ጤነኛ ነው። ተፈጥሮአዊ ነው። ዐማራና ዐማራ እኔ ልምራ፣ እኔ ልምራ ቢሉ መብታቸው ነው። ትግሬን፣ ኦሮሞን ምንአግብቶት፣ ምን ጥልቅ አድርጎት ነው እንዴት አሁን እንዲህ ይላሉ ለማለት የሚዳዳቸው። ግንቦት ሰባት ምንአባቱ አግብቶት ነው ዘመነ አይመራም፣ እስክንድር ይሻላል ብሎ አስተያየት የሚሰጠው። የዐማራ ጉዳይ መፈታት ያለበት በዐማራ ነው። ቢላቀሱ፣ ቢደሰቱ በራሳቸው በዐማሮች ነው የሚያምረው። እናም ጥፋ ጎጠኛ፣ ወሬኛ፣ ምቀኛ፣ ሸረኛ፣ መጋኛ፣ ጌኛ ሁላ። ተውላቸው፣ ገለል በልላቸው። እንደ ፓራሳይት፣ እንደ አልቅት አትጣበቅባቸው። የራስህን መስመር ፈልግ። የራስህን ተቋም ገንባ። አታቃጥር። ምድረ ቃጥራ አውርቶ፣ አጋጭቶ አደር ወሬኛ ሁላ። እንደ ጋለሞታ ነገር ከዚህ ከዚያ አታመላልስ።

"…ተቋማዊ ድርጅቱ ማደጉን ያየሁት የጎጃም የዐማራ ፋኖ የደረሰበትን ደረጃ ሳይ ነው። ከነ ችግሩ የጎጃም ፋኖ ተመንድጓል። ተመንጥቋል። ማርሸት ፀሐዩ የመሰለን ልጅ ላይ አቋም ወስዶ ከኃላፊነት ማንሳት ማለት ለሌሎች በዙህ ወቅት አይቻላቸውም። ማርሸት ፀሐዩ ለእኔ ጀግናዬ ነው። የሥራ ሰው ነው። የሥራ ሰው ደግሞ ይሳሳታል። ሥህተቱን እንዲያርመው ሰፊ እድልና ጊዜ ተሰጥቶታል። ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ሊጠቀምበት አልቻለም። ልጁ እየተወደደ ነገር ግን መወደዱ በድርጅቱ ላይ ከባድ አደጋም፣ ኪሳራም እንደሚያመጣ ሲታወቅ ድርጅቱ ተሰብስቦ ማርሸትን ከሥልጣኑ ላይ አነሣው። እናም ይሄን በማድረጉ አሰፍስፎ የነበረው የግንቦት ሰባት፣ የብልፅግና፣ የኦሮሙማውና የወያኔ ግሩፕ በአንድ ቀን ተለጎሙ። አፋቸው ተሸበበ። የጎጃም የዐማራ ፋኖ በዝረራ ሁሉንም አሸነፈ። ማርሸትም ራሱን አዋርዶ ዐማራንና የጎጃም ፋኖን አስከበረ። እንዲህ ነው ተቋም የሚገነባው። አንድ ተቋም አደረጃጀቱ እያደገ ሲመጣ ያስታውቃል። የሕዝብ ግኑኝነት ያዋቅራል። የሚዲያ ክፍል ያዋቅራል፣ የደህንነት ክፍል፣ የሎጀስቲክ ክፍል ወዘተ ያዋቅራል። ከሞላ ጎደል ሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ላይ ይሄ እየታየ ቢሆንም የጎጃም ፋኖ ግን ይለያል። ኔትወርክ ከጎረቤት ክልል እየጫኑ እየመጡ ሥራ የሚሠሩ ናቸው የወሎና የጎጃም ፋኖዎች። ጎንደርና ሸዋም ላይ ምርጥ ጅማሮዎች አሉ።

"…ለሸዋ ፋኖ ፈተና ወደ ሆነው እና ወደፊት አደጋ ስለሚፈጥረው ነገር ነገ እመለስበታለሁ። ሸዋ ላይ የዋህነት፣ የበዛ ሃይማኖተኝነት ትግሉን ግንቦቴዎች እንዳይጠልፉት ስጋቴን እገልጣለሁ። ሻለቃ መከታው ማሞ የሚመራው ግዙፍ ጦር ጦሩ ምንም ባይሆን በመስራቹ በመሪው እንዝህላልነት ወይም ደግሞ የሀዋሕነት፣ አልያም አለማወቅ፣ ወይም ደግሞ ሆን ብሎ በተንኮል ውሳኔ ባለመወሰን በሸዋ ዐማራ ላይ ስለደቀነው አደጋም ለብቻው እጽፋለሁ። መከታው ለዐማራ እታገላለሁ ብሎ ወጥቶ ባለማወቅና ባለመንቃት በብአዴንና በኦነግ መንገድ በመጓዝ ጭራሽ ለጠላት መግቢያ በር እንዳይሆንም እሰጋለሁ። በዚህ ልጅ እጅ ያለውን የሸዋ ፋኖ አደረጃጀት በስህተት፣ በእንዝህላልነት ልፋት ድካሙ አፈር ከደቼ እንዳይበላም እሰጋለሁ። የሸዋ የመከታው ፋኖ በራሱ በጠቢቡ የሸዋ ሰው መጠበቅና ከተኩላ መከለል ካልቻለ አደጋው ከፍ ያለ ነው። መከታው ከእስክንድርና ከሠራዊቱ መምረጥ ያለበት ሰዓት አሁን ነው። ሸዋዎች ከመከታውና ከእስክንድር አንዱን መምረጥ ያለባቸውም ሰዓት አሁን ነው። አንድ ሰው ለማሰናበት የግድ ባንዳ መሆን የለበትም። እንዲያውም ከባንዳ ይልቅ እጅግ አላዋቂና ዳተኛ መሃይም መሃይም የሚጫወት እርሱ በጣም አደገኛ ነው። አንጃ በተቋሙ ውስጥ የሚፈጥርን ሰው ወታደር ጠባቂ መድቦ እያስጠበቀ ሸዋን እመራለሁ ማለት አደጋ አለው። የጎንደሩ ፋኖ ደጀ በላይ ካድሬውን የብልፅግና ተላላኪ የቄስና የሼክ መንጋ ጥፋ ከዚህ ብሎ በእግሩ የነዳው እኮ ደረጄ በላይ የክህነቱና የሽክናው ክብርና ሞገሱ፣ ሰዎቹም የተከበሩ የፈጣሪ አገልጋይ መሆናቸው ጠፍቶት አይደለም። በቄሱ እና በሼኩ አለማወቅ በኩል ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ፋኖ ደረጀ በላይ አስቀድሞ በመረዳቱ ነው እኮ ነው መስቀልና ታቦት ተሸክመው የመጡበትን ካድሬዎች የቁም አስረኛ አድርጎ ሴራውን ያከሸፈው።

"…ነገ በሰፊው የሸዋ ፋኖ ላይ ለይቼ የእነ መከታው ግሩፕ ላይ የጭቃ ዥራፌን አናሳለሁ። እንደ ጎጃም ፋኖ በከፋፋይዋ ፋኖ ባርች ወይም መቅደስ ላይ የእርምት እርምጃ ይወስዳል ወይስ ጥሞት ይቀጥላል? እሱን እተቻለሁ። እነ ማዕረግ ጉራጌው፣ እነ ሳሚ ቅማንቴው፣ እነ ሀብታሙ ጉደታ ኦሮሞው፣ እነ ሀብታሙ በሻህ ኦሮሞ ግንቦት ሰባቴዎቹ የቲክቶክ ሠራዊት መከታውንና እስክንድርን ደግፈው የሚንጫጩት ጫጫታ እነ አኪላ ደግሞ በሌላው ወገን ሆነው እነ አሰግድን አግዘው የሚንጫጩት ጫጫታ መሬት ላይ በስሱም ቢሆን ችግር አይፈጥርም ማለት ባይሆንም ግን ይለይላቸው ብሎ ማየቱም ደግ አይመስለኝም። እነዚያን…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ጎጃምም እንደዚያው ከብዙ የፋኖ አደረጃጀት ወደ አንድ ለመምጣት የተኬደበትን መንገድ ሁላችሁም የምታውቁት ነው። እንዲያም ሆኖ የጎጃም ፋኖን አሁንም ሁለት ሦስት ቦታ ለመሰንጠቅ እየተሄደበት ያለ መንገድ አልቀረም። ነገር ግን ጎጄ መለኛው የዋዛ ባለመሆኑ በጥበብ እያከሸፈው እየመጣ እንጂ በተለይ ውጫዊ ግፊቱ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የእስክንድር ነጋ በጥባጭነት፣ ለጎንደርም፣ ለወሎና ለሸዋ፣ ለጎጃምም ፈተና መሆኑ አልቀረም። የወሎም ከብዙ ወደ አንድ፣ የሸዋም ከብዙ ወደ ሁለት ነው የመጣው። ይሄ ሁሉ የሆነው በአንድ ዓመት ውስጥ መሆኑ ሲታይ ደግሞ የዐማራ ትግል ከኦነግና ከወያኔ አንጻር ሲታይ እጅግ አስደማሚ ነው የሚሆነው። እንደ ወያኔ ትግል በአረቡ ዓለም እና በምዕራባውያን የሥንቅ እና ትጥቅ አቅርቦት የሌለው፣ እንደ ኦነግ መንግሥታዊ የሥንቅ እና ትጥቅ ድጋፍ የሌለው የዐማራ ትግል በራስ አቅም፣ በራስ ሀብት ተደራጅቶ የዐማራን ግዛት ነፃ አውጥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ፍርስርስ ማድረጉ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በ60 ዓመት የኦነግ ትግል ውስጥ አንድ ቀበሌ ማስተዳደር ካልቻሉት ጋርማ ፈፅሞ ሊወዳደር አይችልም። ከ17 ዓመት መቶ ሺ ትግሬዎች መርገፍ በኋላ በ17 ተኛው ዓመት ወደ ድርድር የተጠራውን ወያኔና በ9 ወር ትግል እባክህ፣ ባባትህ፣ በናትህ እንደራደር የተባለውን የዐማራ ፋኖ ትግል ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ትክክል አይደለም። የዐማራ ትግል ልዩ ነው።

"…ያውም ይሄ የዐማራ ትግል ችግር የሚፈጥሩበት ከውጭ ብቻ አይደለም። የዐማራ ትግል ችግር ፈጣሪዎቹ ከውስጥ ጭምር መሆኑ ነው አደጋው። የወያኔ እና የኦነግ ጠላትነት የተገለጠ የታወቀም ነው። ሁለቱም ከጥንት ጀምሮ በተፈጠረባቸው የበታቸኝነት ስሜት በዐማራ ላይ የካንሰር በሽታ ስለሆነባቸው ተኝተው አያድሩም። ወያኔማ ኦሮሞን ሃውልት ተክላ፣ የዐማራን ጥላቻ እንደ እናት ጡት ስትግተው ከርማ በማሳደጓ እሷ አቅም ባይኖራት እንኳ ያን የጥላቻ መርዝ ግታ ያሳደገችው "አይ ኦሮሞ ብሎ አቢይ ያሾፈበትን" ኦሮሞን ተጠቅማ ዐማራ ላይ ጓ ማለቷን አትተውም። ህወሓት እስከአለች ድረስ ዐማራና ትግሬ እስራኤልና ፍልስጤም፣ ህንድና ፓኪስታን፣ ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ ሆነው መዝለቃቸው የማይቀር ነው። ተጋብተዋል፣ ተዋልደዋል፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ባህል ነው ያላቸው የሚለው ዲስኩር አይሠራም። ፆምና ጸሎት የማይፈታው ችግር እንደሌለ ባምንም አጋንንት ወያኔና ጋኔሉ ልጇ ብአዴን እስካሉ ድረስ ትግሬና ዐማራ ሰላም አይሆኑም። አራት ነጥብ።

"…በዚህና ይህን በመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ የዐማራ ጥላቻ በተከበበ ዓለም ውስጥ የሚገኘው የዐማራ ፋኖ ትግል ከላይ ፈጣሪውን፣ ከታች ነፍጡን ተማምኖ ነው ጠላቶቹን እየወቃ፣ እያደቀቀ፣ እያሸነፈ የሚገኘው። ጎንደር አንድ ሆኖ እንዳይቆም ህወሓት አስቀድማ የፈጠረችው የፖለቲካ ቅማንት ሾተላይ ሆኖ ከጉድጓዱ የሚወጣውን የዐማራ ትግል ተረከዝ ይዞ ይጎትታል። ጎጃምም እንዲሁ ህወሓት የሠራችው የአገው ሸንጎ ተብዬ የፖለቲካ አገው፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ ኩሽ ነኝ እንዲል ያደረጉት የፖለቲካው አገው ሸንጎ ይፍጨረጨራል፣ በወሎም ኦሮሞ ነኝ እንዲል ያደረጉት አካል እግር ይጎትታል። በሸዋም እንዲሁ ከአዲስ አበባ የሄደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጭራሽ "ድል ለዲሞክራሲ ከሚል መፈክሩ 360 ዲግሪ ተጠምዝዞ የዐማራ መሪ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ በማለት እግር ይጎትታል። ድል ለዲሞክራሲ ሲል የከረመ ታጋይ ወንድም አሁን ደግሞ መነሻዬ ዐማራ፣ መድረሻዬ ኢትዮጵያ በማለት ሌላ ሽብልቅ በፋኖ መካከል ከትቶ ትግሉን ለማመስ ይጥራል። ልብ በሉ ዐማራ ይሄን ሁሉ ተቋቁሞ ነው በእሳት ውስጥ ነጥሮ ወርቅ ሆኖ ለመውጣት እየታተረ የሚገኘው። እኔ በዐማራ አሸናፊነት ለሰከንድ ተስፋ የማልቆርጠው የዐማራን የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ጠንቅቄ ስለተረዳሁ ነው።

"…የዐማራ ትግል እንደ ትግሬም እንደ ኦሮሞም ጥርት ያለ የዘር ትግል አልገጠመውም። ትግሬ የሆነ አንድ ታጋይ በእናቱ ወይ በአባቱ ዐማራ ቢሆን የሚመርጠው ፅንፈኛ ትግሬነቱን ነው። ኦሮሞም እንደዚያው። እንደውም እነዚህ ውህድ ማንነት፣ ድቅሎች ከዋናው ኦሮሞም፣ ከዋናው ትግሬም፣ በእናቱም፣ በአባቱም ትግሬ፣ ኦሮሞ ከሆነው ይልቅ ጨካኞች ናቸው። በግማሽ ማንነት ባገኙት ነገድ ውስጥ ገብተው በዚያ ነገድ ውስጥ ተቀባይነትን ለማግኘት፣ ከብሔረሰቡ በላይ ብሔሩን ወዳጅ፣ አፍቃሪ መስለው ለመታየት ሲሉ አረመኔ፣ ጨካኝ ነው የሚሆኑት። ጃዋር መሀመድን ተመልከቱት። ጃዋር መሀመድ በእናቱ ሰሜን ሸዋ ዐማራ፣ ኦርቶዶክስ፣ በአባቱ አሩሲ ኦሮሞ የሆነ ሰው ነው። አንገቱን በሜንጫ፣ ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ እስኪል ያደረሰው ግን ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን ከመጋጋጥ የመጣ ነው። ጃዋር እንደዚያ ሆኖ በመተወኑ ይሄው ዲታ፣ ሚሊንየር በመሆን እየሟሸሸ ወደ ሞት እያመራም ዘጭ ብሎ ተቀማጥሎ ይኖራል።

"…የዐማራ ትግል እንደ ትግሬዎች እና ኦሮሞዎችም በሙሉ ዐማሮች የሚደገፍ አይደለም። ትግሬ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ምሥራቅ፣ ማዕከላዊ ትግራይም ይኑር፣ ትግሬ ጎንደርም፣ ወሎና ጎጃም፣ ሸዋና አዲስ አበባ ይኑር፣ ትግሬ አፋር፣ ሶማሊ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያና ጉምዝ ይኑር፣ ትግሬ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ይኑር፣ ትግሬ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውሮጳ፣ እስራኤል፣ እስያ፣ አውስትራሊያና ዓረብ ሀገር ይኑር፣ የትም ይሁን የትም፣ አረናም ይሁን ወያኔ፣ ቄስም ይሁን ሼክ፣ ፓስተርም ይሁን ዳስተር፣ ለምን ሴተኛ አዳሪም ወንድኛ አዳሪም አይሆንም በትግሬ ጉዳይ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢልም አንድ ናቸው። ኦሮሞም እንደ ትግሬ ባይሆንም እንደዚያው ነው። በመሃላቸው ሰው አያስገቡም። ለመግባትም አይመችም። እነሱ በመሃላቸው ሌላ እንዳይገባ በዐማራ ላይ ግን ሌላው እንዲፏችር አድርገውም ነው ለዘመናት ሲሠሩበት የኖሩት። የሆነ ጊዜ እንደውም መለስ ዜናዊን እንዲህ አሉት አሉ። "ዐማራን ለማዳከም ለምን ቅማንትን እና አገውን ክልል አታደርግም? ለምን ወሎን ክልል አታደርግም አሉት አሉ። መለስም መለሰ እንዲህም አለ። "ቅማንትን፣ አገውን፣ ወሎን ክልል ካደረግኩ ዐማራ ብቻውን ቀረ ማለት ነው። ዐማራ ላይ ዐማራን ሾምን ማለት በገዛ እጃችን በራሳችን ላይ የመጥፊያችንን ፈንጂ አፈነዳን ማለት ነው። የሚሻለው ክልሉ እንዳለ ሆኖ፣ ቢሮክራሲውን፣ ፖለቲካውን እና ኢኮኖሚውን የአገው ሸንጎ፣ የፖለቲካው ቅማንት እና የከሚሴ ኦሮሞ እንዲመራው ማድረግ ነው። አለ አሉ። እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዐማራ በዐማራ ክልል ነግሦ፣ ተሹሞ አያውቅም። አሁን ወባ እንደያዘው ሰው ወያኔና ኦሮሙማ ሚልዮን ሰው አስፈጅተው ሁለት ቆማጦችን የሚያስተቃቅፍ ፍቅር የመጣው ከድንጋጤ የተነሣ ነው። ዐማራ ተነሣ፣ አገሣ፣ ሊነግሥ፣ ራሱን በራሱ ሊመራ ከች አለ። ደነበሩ። እንዲያውም ዐማራን 5 ክልል ሁላ እናድርገው እያሉ ነው አሉ እነ ሽመልስ አብዲሳ። 😂😂😂 እንዲያ ከሆነ ደግሞ ኦሮሚያ 85 ቦታ ትሸነሸናለች ማለት ነው።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እንደተለመደው እግዚአብሔር ይመስገን ባዩ ሕዝብ ቁጥሩ ሞልቶ አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። ያው እንደሁል ጊዜው ከምስጋና ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን እንደ ጥቅሱ የዐማራን ሸለቆ ሁሉ ከፍ የሚያደር፥ ተራራውና ኮረብታ የመሰለውን ሁሉ ዝቅ የሚያደርግ፣ ጠማማውንም የሚያቀና፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል ብሎ ዐማራውንና የዐማራውን ትግል የሚደግፉትን ሁሉ በተስፋ የሚሞላ መራር እውነት የያዘ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ” ኢሳ 40፥4

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ዛሬ ተጀምሮ ዛሬ የሚያልቅ አልሆነም። ስጽፈው ራሱ እየተቃጠልኩ፣ በተስፋ እየተሞላሁ የጻፍኩት ስለሆነ ብዙ አናግሮኛል። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚያልቅ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ከእኔ ርዕሰ አንቀጽ እንደ መንደርደሪያ ተነሥታችሁ እናንተም በራሳችሁ እይታ ልታዳብሩትም ትችላላችሁ። የዛሬው ርዕሰ አንቀጼም እንደ ወትሮው ሰናፍጭ የበዛበት፣ መተሬም፣ እንቆቆም ያለበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የበዛበት ርዕሰ አንቀጽ ነው። ሰብሰብ ብላችሁ የምታነቡት ነው።

"…እኔ ርዕሰ አንቀጼን ቋጭቼ ወደ እናንተ ለትችት እስከመጣው ድረስ እስከዚያው በእዚህ ቁርስና ምሳ እራትም በሆነ የፋኖዎች አቋም እየተደመማችሁ ቆዩኝ። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ተአምር እየተሠራም ነው።

• ወደ ኩሽናዬ ተመልሼ ርዕሰ አንቀጹን ልቀምምላችሁ አይደል? 😂 እስኪ እናንተም ለምሳም ለእራት ለቁርስም የሚሆናችሁን ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችሁ እስክመጣ ድረስ እነዚህን የእሳት ላንቃ የሆኑ ነበልባል የዐማራ ፋኖዎችን ሞራል እየሰጣችሁ፣ አጋርነታችሁን እየገለጻችሁላቸው፣ እየመረቃችኋቸውም ጠብቁኝ።

"…አንዳንድ ቦታ ኔትወርክ ስለተለቀቀ መልእክታችሁን ያነብቡታልና በማርያም ሞራል ስጡአቸው። 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የነገ ርዕሰ አንቀጼ ነው።

"…በአርበኛ ዘመኔ ካሴ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ይመሰገናል፣ ይበረታታል፣ ደግሞም ከእኔ ከምሥራቁ ሰው ከሐረርጌው ቆቱ ከመራታው ዘመዴ ከሥላሴ ባርያ ከድንግል አሽከር ከባለ መዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ ከነፍጠኛ ወዳጁ ከአክሊለ ገብርኤል  ተጨማሪ ነጭ ነጯን የሆነ ወንድማዊ ማር ማር የምትል የጭቃ ዥራፌን ምክር እሰጣለሁ። አርበኛ ማርሸት ፀሐዩን አመሰግናለሁ። ድርጅቱንም የዐማራ ፋኖ በጎጃም ከምክር ጋር አከብረዋለሁ። የነገ ሰው ይበለን።

"…በአንጻሩ በሻለቃ መከታው እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጋራ የሚተዳደረውንና የሚመራውን የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ፋኖን መከታውን ጨምሮ በውስጡ ስላሉት ወንድሞች ስል የማርያም መንገድ የሚሰጥ የጭቃ ዥራፌን ምክር እና ጥቆማም እሰጣለሁ። መቼ ነገ ጠዋት በርዕሰ አንቀጼ ማለት ነው።

"…የጎጃማ ዐማራ ፋኖዎች የሕዝባችሁን አስተያየት ስለሰማችሁ ሰምታችሁም ማስተካከያ ስላደረጋችሁ በታላቁ የዐማራ ሕዝብ ስም ሳመሰግናችሁ ቅሽሽ አይለኝም። ያውም ቆሜ ነው የማጨበጭብላችሁ። ቀሪ ጎዶሎአችሁም እንዲሁ ይሰተካከላል ብዬም አምናለሁ።

"…ሻለቃ መከታው እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም አብራህ የተቀመጠችውንና በሕግ ያልተሰጣትን የዐማራ ፋኖ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ይመስል የሌለ ከፋፋይ አጀንዳ እያነሳች ሕዝብ ላይ ምታስታውከውን በመደዴነትም በሸዋ ሕዝብ ላይ ቅርሻቷን እንድታቀረሽ የቴሌ ኢንተርኔት አሰጥታችሁአት የምታስለፈልፋትን የአጣዬ ወረዳ በርግቢ አካባቢ ተወላጇን በትግል ስሟ ፋኒት ባርች ወይም በመዝገብ ስሟ መቅደስ አድማውን በተመለከተ እሷን እንደ ተናግሮ አናጋሪ በመቁጠር ልክ እንደ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የግል ትችቴን አቀርባለሁ። መቼ? ነገ ጠዋት።

• ማርያምን አዛኜን ዐማራ ግን ድብን አድርጎ ያሸንፋል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ግሩም ነው…!

"…ለመጀመሪያው ጥያቄ ማለትም "አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…? ለሚለው ጥያቄ አንድም የሳተ ሰው ሳይኖር ፋኖ በማለት መልሷል።

"…ቀጥሎም በሁለተኛ ደረጃ ለቀረበው "የወያኔ ባለቤቱ ትግሬ ነው ካልን፣ የኦነግ ሸኔም ባለቤቱ ኦሮሞ ነው ካልን የፋኖ ባለቤቱ ማነው…? ለሚለው ጥያቄም እንደ ቀደመው ጥያቄ አንድም የሳተ ሰው ሳይኖር በብዙ ሰው የሚደንቅ ተሳትፎ ዐማራ በማለት ተመልሷል።

"…አሁንም እጠይቃለሁ… ወያኔን የሚመራው፣ መሪውንም የሚመርጠው ትግሬ ከሆነ፣ ኦነግ ሸኔንም የሚመራው መሪውንም መሪ ሁነን ብሎ የሚመርጠው ኦሮሞ ከሆነ ፋኖን ለመምራት የፋኖን መሪም መምረጥ፣ መሾም፣ መሻርም ጭምር ያለበት ማነው?

• አንድ 100 ሰው ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በጥያቄ እንጀምር…?

"…አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገድ (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…?

"…መዘብዘብ የለም። ጥያቄው ቀላል ነው ብሎ መናቅም የለም። መጎረር፣ መፎከርም የለም። ከዚህ ምላሽ በመቀጠል ወደ ሌላ ጥያቄ እና መልስ ስለምንሄድ ያለምንም ገተታ መልሱን ብቻ ቁጭ።

"…እደግመዋለሁ… አሁን ባለው የኢትዮጵያ ቦለጢቃ የነገዶች (አዳኝም ጠባቂም) ትርጓሜ መሠረት ለትግሬ ወያኔ፣ ለኦሮሞ ወነግ ሸኔ ካልን ለዐማራ ማን እንላለን…?

~ 100 ሰው ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።” ኢሳ 30፥26

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከዝክር መልስ…

ከጥያቄ 1 - 26

"…ዛሬ ደስ ብሎኝ ነበር ያመሸሁት። በሀገረ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጅ ከዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን የሐምሌ ሥላሴን አከበረን። ኢትዮጵያን ነው ያስታወሰኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከመኝታ በፊት ግን ይህን ልበል። እንግዶቼን ከሸኘሁ በኋላ አስቀድሞ ወጣ በተባለው በፈተናው ጉዳይ ዘመዴ ይሄ የለጠፍከው ያልተፈተኑት ነው የሚል ሓሳብ ሰጪ በዝቶ አግኝቻለሁ። ጥያቄው የማኅበራዊ ሳይንስ ቢሆንም ከሰብጀክት ኮድ በስተቀር አይመሳሰልም። ለምሳሌ፦ ፔጅ ነምበር፣ ቡክሌት ኮድ፣ ምርጫ ኮድ በአጠቃላይ ጥያቄው ገና ያልተፈተኑት ነው የሚልም አስተያየት እያየሁ ነው። አይ እገሌ ነኝ ይሄንን በእገሌ ዩኒቨርሲቲ ፈትኜዋለሁ የሚሉም ታይተዋል።

"…የሆነው ሆኖ እኔን ምን አስጨነቀኝ? ምንስ አጨቃጨቀኝ? ተማሪዎቹ ቀድመው ተፈትነውት ከሆነ እሰየው ቀድመው ያልተፈተኑት እና ወደፊት የሚፈተኑት ከሆነም ከሆነም እሰየው፣ የተፈተኑት ከሆነ እንዲያውም ክለሳ ይሆንላችኋልና ለምን ሙሉውን አልለጥፍላችሁም ብዬ በማሰብ ሙሉውን ለጥፌላችኋለሁ። ተማሪዎች ቀድመው የተፈተኑት ከሆነ መልካም ነው መልሰው ቢያጠኑት ምናቸው ይጎዳል? ምንም። ያልተፈተኑት ከሆነም አገዛዙ ተሰርቆ ወጥቶበት ከሆነ ይጠነቀቅበታል። አለቀ። ተማሪዎች ግን አጥኑ። ሳትዘናጉ ወጥራችሁ አጥኑ።

• ደኅና እደሩልኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ቀጥሎ የምጽፈው ርዕሰ አንቀጽ ለፍሮፌሰር ብራኑ ነጋ ተቋም ለሆነው ለትምህርት ሚንስቴር ነው። ይሄ በስሱ አለፍ አለፍ አድርጌ የለጠፍኩት ፈተና የእናንተ ተቋም ለመጪው ረቡዕ ያዘጋጀው የፈተና ወረቀት ነው ወይ? ከሆነስ አስቀድሞ ተበትኗል እና ለማስተካከል ምን አስባችኋል? ካልሆነም በመረጣችሁት መንገድ አትጨነቅ አትሰብ በሉኝ ለማለት ስል ይህን ርዕሰ አንቀጼን ቀጥዬ እለጥፋለሁ።

• ፌክ ከሆነ ግን እለፉት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ይጠበቅ የነበረው 1ሺ አመስጋኝ በቶሎ ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ሰሞኑን በነገርኳችሁ መሠረት ዛሬ በቤቴ ከባባድ እንግዶች ይመጡብኛል። እኔና ቤተሰቤም የቅድሥት ሥላሴን፣ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስንና ቅዱስ ጴጥሮስን፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዝክር በአንድነት ልንዘክር ተፍተፍ እያልን ነው። እናም ዛሬ ሰፊ ርዕሰ አንቀጽም ሆነ ዛሬ ማታ በመረጃ ተለቭዥን ነጭነጯን ከዘመዴ ጋር አይኖረንም። በፈረንሳይኛ ዛሬ ዘኬ ለቀማ ላይ ነኝ ማለት ነው። ገባችሁ ኣ…?

"…ለማንኛውም ግን በዐማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በይፋ ሳይነሣ በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተነሣውን የኢንተርኔት እገዳ አስመልክቶ የቅድመ ጥንቃቄና አንዳንድ መልእክቶችን…

"…የፊታችን ሐምሌ 10 የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ፈተናን በተመለከተ ለትግሬና ለኦሮሞ ተማሪዎች አስቀድመው መልሱን ሠርተው ይዘጋጁ ዘንድ ነው ተብሎ የወጣን ሙሉ የፈተና ወረቀት ለልጃቸው ደርሶ ነገር ግን ድርጊቱን ተቃውመው ሕዝቡም መንግሥትም ድርጊቱን አውግዘው ያርሙም ዘንድ ከአንድ ለነፍሳቸው ካደሩ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለ ማዕተብ ቤተሰብ የተላከልኝን ሙሉ የሒሳብ የፈተና ወረቀት በተመለከተም ለትምህርት ሚንስቴርና ለኢትዮጵያው አገዛዝ ጥቆማ ከነምልክቱ ለመስጠት ብቅ ለማለት እሞክራለሁ።

"…አገዛዙ ስህተቱን የሚያርም ከሆነ በተመቸው መንገድ ያሳውቀኝ። ዝም ጭጭ ብሎ ባላየ ባልሰማ ለማሳለፍ የሚሞክር ከሆነ ግን ዛሬ እስከ ማታና እስከ ነገ ጠዋት የማያሳውቀኝ ከሆነ ትግሬና ኦሮሞ ብቻ ፈተናውን የሚሠራበት ምክንያት የለም ብዬ ዐማራ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጉራጌና ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ጉምዙ፣ ጋምቤላው ሁሉም ተዘጋጅተው ይገቡ ዘንድ ሙሉውን የፈተና ወረቀት ለመለጠፍ እገደዳለሁ።

• እንግዶቹ ሳይመጡ አጭሯን ርዕሰ አንቀጽ ልጻፍላችሁ አይደል? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ ጽፌ ከለጠፍኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ወርሀዊው የማኅበር ጸሎት ስፍራ ነበር የሄድኩት። የቴሌግራም መንደር የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም ክፍት አድርጌ ነው እኔ ስልኬን ዘግቼ የጸሎት መርሀ ግብሬን ስከታተል ያመሸሁት።

"…ከጸሎት መልስም ከካህናት አባቶቼና ከወንድም እህቶቼ ጋር ስጫወት አምሽቼ ከሁሉም ጋር ከተለያየን በኋላ ነው ቆይቼ ወደ ቴሌግራም መንደሬ የገባሁት። ወደ መንደሬ ስገባ እማመይ ድረሽ መንደሩ በአስተያየት ጨቅ ብሎ ነው የጠበቀኝ። አንድም ሳይቀረኝ ሙሉ በሙሉ ነው አስተያየቶቹን ያነበብኳቸው።

"…ግንባሩና ሠራዊቱ ቲክቶክ ላይ በአፋቸው የሚጸዳዱ የሴትና የወንድ ክፍት አፎችን እንደለመዱት ወደ እኔ የቴሌግራም መንደር ልከው የለመዱትን ጥንባታም፣ ግማታም፣ ክርፋታም፣ ሸታታ የተለመደ አሳቃቂ የስድብ ናዳ የሚያወርዱ ልማደኞች እንደሌላው ቤት መስሏቸው በለመዱት መንገድ ወደ ቤቴ መጥተው ቤቴን ቁናስ በቁናስ ሊያደረጉ የሞከሩ ጥቂት ክፍት አፎችን በማግኘቴ እነሱን ከቤቴ ጠራርጌ ወደ ጋርቤጅ ከትቼ ነው ገና አረፍ ማለቴ ነው። እንዴት ናችሁልኝ? እንዴት አመሻችሁ?

"…ደፈር ብሎ መነጋገር መጀመሩ አስደስቶኛል። የዛሬው አብሪ ጥይት ነው። ስስ የጭቃ ዥራፌም ነው። ወፈር ያለው የጭቃ ዥራፌ እንደ ሁኔታው እየታየ ወደፊትም ይቀጥላል። በድፍረት በእውነት እና በእውቀት መወያየት ያጸድቃል። ገነት ነው የሚያስገባው።

"…እኔ አይስክሬም ነጋዴ ወይም ሻጭ አይደለሁም። እኔ ኮሶ ነጋዴ ነኝ። መቅመቆ መተሬ ሻጭ። ስታነበው ሱሩር ይልሃል። ይቀፍሃል። ያንገሸግሽሃል። እንደምንም እያንዘረዘህ፣ እያንቀጠቀጠህ ጨክነህ መጨለጥ ነው።

• ደና ናቹ…?

Читать полностью…
Subscribe to a channel