zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያለምንምንም ተናዳጅ 😡 ሰው እስከአሁን ርዕሰ አንቀጻችንን 14 ሺ ሰዎች ማንበባቸውን የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት በግድግዳዬ ላይ ተለጥፎ ይታያል። ይሄን ከለጠፍኩ በኋላ 😡😡😡 ብው ያሉ ሰዎች ቢግተለተሉ አይገርመኝም። የሚጠበቅም ነው።

"…እንግዲህ ቀጥሎ ደግሞ እስከ መኝታችን ሰዓት ድረስ የእናንተ ሓሳብ የሚደመጥበት ሰዓት ነው። ርዕሰ አንቀጹ ላይ ጎደለ የምትሉት ነገር ካለ መጨመር መብታችሁ ነው። የበዛ ነው የምትሉት ካለም መቀነስ መብታችሁ ነው። እኔ የታየኝን፣ የመሰለኝን ጽፌአለሁ። እናንተም እንደዚያው።

"…እንደ ማሳሰቢያ በዚህ ርዕሰ አንቀጽ ላይ ጥቅማችን ተነክቷል። በደል ደርሶብናል የምትሉም ካላችሁ ደግሞ በጨዋ ደንብ መወያየት፣ መሞገትም የተፈቀደ ነው። በተለይ የግንባሩ፣ የሠራዊቱ፣ የግለሰቦች ፍቅር ከትግሉ በላይ እንደ አምልኮ የተጠናወታችሁ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን መግለጽ ትችላላችሁ። የቦርኮ ስድብ ግን አልታገስም። ቦዘኔ ጥግህን ያዝ። አልያም ክፍት አፍህን እከፍታለሁ ብትል አጠናግሬ አሳርፍህሃለሁ። ሰምተሃል።

"…ይሄ ስስ፣ ቀጭን የጭቃ ዥራፌ ነው። ጸሎቴ ተሰምቶ ተናግሮ አናጋሪ ካገኘሁ ግን ከዚህ የባሰ፣ ወፈር ያለ ርዕሰ አንቀጽ እንደምንም ብዬ በትበት ብዬ ላዘጋጅላችሁ እሞክራለሁ።

• 1…2…3… ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

✍✍✍

👆ከላይኛው የቀጠለ… ሙሉ ሲጠራቸው አቤት፣ ሲልካቸው ወዴት የሚሉ ሰዎችን ነው የሚሰበስበው። ሲሾማቸው እሺ፣ ሲሽራቸው እሺ የሚሉትን ነው የሚሰበስበው። እስክንድርም እንደዚያው ነው። በብዙዎች ተስፋ የተጣለበትን ባልደራስን እኮ ያፈረሰው አቅም ያላቸውን ዶክተሮች፣ ምሁራን ድራሽ አባታቸውን አጥፍቶ የተራ አስከባሪ፣ ሊስትሮና የጥበቃ ሰዎችን ሰብስቦ ነው አፈር ከደቼ ያበላው። በባልደራስ ስም በአሜሪካ የተሰበሰበ ዶላር እዚያው አሜሪካ ነው ቀልጦ የቀረው። የተራ አስከባሪ የባልደራስ አባላት፣ ሊስትሮዎች ይሄን ሊጠይቁ አይችሉማ። ኦዲት ሳይደረግ ነው ተቀርጥፎ የቀረው። እስክንድር ሸዋ ላይም እንደዚሁ ነው ያደረገው። መጀመሪያ ሁሉንም በአራቱም የፋኖ ግዛት ዚሮ ተመለከተ። ገመገመ። የኃይል ሚዛናቸውን፣ የሰው ሀብታቸውንም ገመገመ። አማኞቹን በመሀላ ቀፈደደ፣ ምርጫውን ግን ሸዋ ከመከታው ጋር አደረገ። መከታው እንደ እስክንድር ፈጣሪውንም ያከብር አይመስለኝም። የመከታውን ስስ ብልት እስኬው በደንብ ነው ያገኘው።

"…እስክንድር ገንዘቡ በእጁ፣ ፕሮፓጋንዳውን በሀብታሙ አያሌው በኩል አድርጎ ኢትዮጵያኒስቱን በእነ አበበ በለው ታጅቦ በሸዋ አሰግድና መከታው እንዳይስማሙ፣ እንዳይታረቁ አድርጎ ሽብልቅ ገባላቸው። እስክንድር በደረሰበት ስፍራ ሁሉ ድሮኗ ከእስክንድር ኋላ የሚሄድ ወሳኝ ዐማራ እየበታተነች ስትገድል ኖራለች። ደብረ ኤልያስ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ የተካሄደው በእስክንድር ነጋ ምክንያት ነው። በሸዋም እንደዚሁ። እስክንድር ኢንተርኔት ይጠቀማል። የአገዛዙ ስጋት የለበትም። እስክንድር እነ ባርች የተባሉ የ10ኛ ክፍል ወዳቂ፣ የአረብ ሀገር ተመላሽ ህመምተኛ ከአጠገባቸው አድርገው ሸዋ ላይ ክፍፍል ይፈጽማሉ። በእነ አቶ አሰግድ ጋርም ጥፋት የለም እያልኩ አይደለም። ጥፋቱ ግን በንግግር የሚፈታ እንጂ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚያስነሣም አይደለም። የሆነው ሆኖ እስክንድር የፋኖን ትግል ቢያዘገየው እንጂ ሊያስቆመው አይችልም።

"…አሁን ጉዳቱ ለእነ መከታው ጦር ነው። የመከታው በግል ከእስክንድር ነጋ ጋር መጣበቅ የመከታውን ጦር ዓለምአቀፍ የሸዋ ተወላጆችን ድጋፍ አሳጥቶታል። መድኀኒት፣ የሴት ታጋዮች የንፅህና መጠበቂያ ቁስ ሳይቀር ይረዱ የነበሩት አሁን ቀጥ አድርገዋል። ለአቶ አሰግድ አግዘው አይደለም ያቆሙት። የእስክንደር ነጋ ሴራ ስለገባቸው ነው ያቆሙት። የመከታው የጦር አዛዦችም ለመከታው አማራጭ እያቀረቡ ነው። ወይ ከእኛ ወይ ከእስክንድር ብለውት አጣብቂኝ ውስጥ ከትተውታል። የእስራኤል የስለላ ቡድን ድጋፍ እንዳለው የሚነገርለት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባለው ቡድን ከእስክንድር ነጋ ጀርባ መኖር ደግሞ እስክንድር የገንዘብ ምንጩ ይነጥፍበታል ተብሎ እንደማይገመት የሚናገሩም አሉ። እስክንድር ገንዘብ እስካለው ድረስ ትንቢት የተነገረልኝ የፋኖ መሪ ነኝ ባዩ እስክንድር ነጋ የፋኖን ትግል ማተራመሱን ይቀጥላል። ሰሞኑን አይታችሁ እንደሆነ የኦሮሞና የትግሬ አክቲቪስቶች፣ የግንቦቴና የግንባሩ ሰዎች ሳይቀር ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸው። የመከታው ጦር የሚባለው የአቶ አሰግድ መኖሪያ ነው የተባለን ቤት ወርረው በቪድዮ ተቀርጸው የለቀቁት ምስል እስክንድር ነጋ ሁሌ ዙሪያው የሚያሰፍረው ጋጠወጥ መደዴ መረን የለቀቁ፣ የዐማራን ስብዕና የማይወክሉ ግለሰቦችን እንደሆነ ነው። እኔ መከታውን ጨምሮ እነ አቤ ጢሞን፣ እነ ዮናስን የመሰሉ ሰዎች እንዴት እንዲህ ዓይነት ጋጠወጥ ወጠጤዎች መሪ ሆነው እንደተቀመጡም ገርሞኛል። 

"…ዳግማዊ ቴዎድሮስ ነኝ፣ በጳጳስ ተቀብቼ ነግሻለሁ፣ ትንቢት የተነገረልኝ ቀጣዩ ንጉሥ ነኝ የሚሉ ቅዠታም ድንባዣም አእምሮቢስ ሰገጤዎችን በዚህ ትግል ውስጥ ማየቱም እንብዛም አይገርመኝም። በተለይ የታላቁ እና የታናሹ እስክድር አጠቃላይ የዐማራ ፋኖ መሪ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ ብሎ የሙጥኝ ማለት በፋኖ ውስጥ ቀውጢ እየፈጠረ ነው። ይሁን እሺ አንግፋው ብለው ቢያቀርቡትም አንጃ ለመፍጠር ከመወተርተር አልቦዘነም። በጎጃም ማስረሻ ሰጤን እና በወሎ የኮለኔል ሞሀባውን ክንፉ በመዘወር የሥልጣን ግብግብ እንዲያደርጉ የሚገፋፋው ደግሞ ሀብታሙ አያሌው ነው ተብሏል። የእነ ዘመነ ካሴ ድክመት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ሀብታሙም የወሎ ዐማራ ነኝ በማለት የሸዋ የቱለማ ኦሮሞዎችን በእነ መከታው በኩል በማስተባበር፣ አሰግድንና መከታውን በማመታት፣ በመጨረሻ አሰግድን በማስገበር እስክንድርን ይዘን ወደፊት መምጣት አለብን ነው የሚሉት። ገና አራት ኪሎ ሳንገባ ካላነገሣችሁኝ የሚል የሥልጣን ጥም ያለባቸው አንድ አንድ ሰዎች ቢያስቸግሩንም ግን ዘመዴ ሙት አሳምረን እናሸንፋለን የሚሉኝ ፋኖዎች መኖራቸውን ሳይ ደግሞ ተስፋዬ ሺ እጥፍ ይለመልማል።

"…የእስክንድር አካሄድ አይሳካም። እኔ ሲመስለኝ በሻዋ ጠንካራ ዲሲፒሊን ያለው እስከአሁንም አድፍጦ ሲሠራ የነበረ፣ እዩኝ፣ እዩኝ የማይል አዲስ ግርማ ሞገስ ያለው ጦር ይፈጠራል። በቅርቡም ሁሉንም ውጦ ሰልቅጦ ወደ አንድ የሸዋ አደረጃጀት ያመጣቸዋል። አሁን ራሱ በመከታውም በአሰግድም ጦር ስር ያሉት ታጋዮች ከነ ብርጌዳቸው ወደዚያ የፋኖ አደረጃጀት ለመግባት ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የመከታውም ጦር ከመከታው ይለያል። የማውቀውን ነው የምነግራችሁ። የአሰግድም ጦር እንደዙያው። መስማማት፣ መነጋገር፣ መወየያት፣ ልዩነትን መፍታት የማይችል የዐማራ ፋኖ ትግልን አያሻግርም። ትግሉ የህልውና ትግል ነው። በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለም አይደከም። እየወደቀ፣ እየተነሣም ይሻገራል። የሚገርመው በጎንደር ሁለት አይነት የፋኖ አደረጃጀቶች ቢኖሩም ውጊያ ሲመጣ ሁለቱም ልዩነታቸውን ትተው አንድ ላይ ሆነው ነው የሚታገሉት። የሚዋደቁት። ይሄ ማለት ጠንካራ፣ ቅን፣ እውነተኛ ሽማግሌ ቢኖር ጎንደር አንድ ይመጣል። ሸዋም እንደዚያው። እንደ እስክንድር አይነት እኔ ካልመራሁ ባይ የዳያስጶራ ገንዘብና የኢትዮጵያኒስቱ ካምፕ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ ካምፕ የሆነ ሰው እያለ ግን ትግሉ ይዘገያል። ይዘገያል እንጂ ድሉ እንደሁ አይቀርም።

"…የሚያናድደው ነገር እስክንድር እና እነ ሀብታሙ አያሌው ከሥልጣን ጥም የተነሣ ባይበጠብጡ ኖሮ በዚህ ክረምት ወደ አንድ መጥተው በጋራ አመራር የተሳካ ኦፕሬሽን ፈጽመው አገዛዙን እንኩትኩቱን ለማውጣት ነበር ፍላጎቱ። በእነ ማርሸት እንዝህላልነት፣ ያለመብሰል፣ በእነ እስክንድር እኔ ካልመራሁ ባይነት አንድነቱ ሊሳካ አልቻለም። በአስቸኳይ ይሄ ታርሞ ወደ አንድነት ከተመጣ ግን የዐማራ የመከራ ቀንበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይወልቃል። ውባንተን ያስገደለው እኮ በእስክንድር ስር አልገባም ማለቱ ነው። አሰግድም፣ ሌላውም ከተገደለ የሚገደልበት ዋናው ምክንያት ሌላ ሊሆን አይችልም። ብአዴን እስክንድርን ይዛ ፕሮሞሽን ሠርታለት በጎጃም ምድር ስታዞረው ከርማ ጫካ ግባና ተዋጋኝ ያለችው ለምን እንደሆነ የምታውቀው እሷ ናት። የፋኖ ወደ አንድነት ያለመምጣትን የተመለከተው አቢይ አሕድም ሰሞኑን "ክረምቱ እስኪወጣና በቂ ሎጀስቲክ እስክናሟላ ድረስ ጦራችንን ባለበት ቦታ እናክርም የሚል ውሳኔ ማስተላለፉን እና ሰሞኑን የአብይ አህመድ ጀኔራሎች ተሰብስበው ሲያወሩ መደመጡም ተነግሯል። ለዚህ ደግሞ ሚሊሽያ፣ ፖሊስና አድማ ብተና እየላክን ፋኖ ወደ ወታደራዊ ካምፖቻችን እንዳይመጣ የቅድመ መከላከል ማጥቃት እንደርጋለን። እስከዚያው በፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ሽብልቅ እየከተትን እነ እስክንድርን እየደገፍን እናጯጩኸው ነው የሚሉት ተብሏል። ይሄ በዚያ በኩል ያለ ዕቅድ ሲሆን…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን ጩኸት የሚቀሙ የድል አጥቢያ አርበኞች ከዐማራ ፋኖ የትግል የፊት መስመር ላይ እንደ ጉንዳን፣ እንደ ቁጫጭ፣ እንደ በረሮ ሲርመሰመሱ፣ ውኃ እንደተጠማ የዱር እንስሳት ግርር ብለው ሲግተለተሉ እያየሁ ግርም ብሎኝ ነገርየውን ለማጣራት ፍጻሜውንም ለመመልከት ስል ጥጌን ይዤ ከዳርም ቆሜ በመታዘብ ላይ እገኛለሁ። እኔ የማየው፣ የምሰማው ሌላ፣ አዳሜና ሔዋኔ የድል አጥቢያ አርበኛ ሁላ የሚቦተረፈው ሌላ። ኦሆሆ ጉድ እኮ ነው እናንተው።

"…የዓድዋው ትግሬ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያው ስታሊን እንኳ ስለ ዐማራ ፋኖ አደረጃጀት፣ ጥንካሬና ድክመት ለማውራት ከ1:00 ሰዓት በላይ ዩቲዩብ ላይ ተጥዶ እብልዥቭዥቭኡቘፇኧቍ እያለ ሲንተባተብ ሳይ አምላኬ ሆይ ይሄንንማ በሕልምህ ነው በለኝ ብዬ ሦስት ጊዜ ሁላ ነው ያማተብኩት። "የፋኖን ትግል በ3 ደቂቃ የሚፈርስ ኢንዶሚን ነው" እያለ ሲሳለቅ የከረመው ሶዬ ዛሬ ዓይኑን በጨው አጥቦ ፋኖ፣ ፋኖ፣ ጀግናው እስክንድር አርበኛው ዘመነ ካሴ፣ ጋሽ አሰግድ፣ ምሬ ወዳጆ እያለ ሲደሰኩር ሳየው ዓይኔንም ጆሮዬንም ነው የተጠራጠርኩት። ደግሞ እኮ ልመናዋ አትቀርም። ክቡራን የሚዲያችን ተከታታዮች እንግዲህ ለዐማራ ትግል ለምናደርገው አስተዋጽኦ ሁላችሁም ያላችሁን በዜል፣ በካሽአፕና በዶነር ቦክስ ጣል ጣል አድርጉብን ሲል የዓይኑን ሽፋሽፍት እንኳ ለሰከንድ አያርገበግብም። አይ አማርኛ ለልመና ጊዜ ሁሉም አቁፋዳውን ይዞ ከች ይልብሻል። እነ ነውር ጌጡ። ኢመቺሽ ወለይ ነፍሴ።

"…የአዲስ አበባ ልጆች ወኪል። የብርቱው ሰው፣ የብረታ ብረቱ፣ የአይሰበሬው፣ የአይቀነጠሴው፣ የጀግናው፣ የፅኑው፣ የአለቱ፣ የጠንካራው፣ የአይበገሬው፣ የታላቁ እስክንድር ምክትል የባለ አደራው ጎምቱ ባለ ሥልጣን የነበረው የቀድሞው ኢህአዴግ፣ የኋላው ግንቦት 7፣ ቆይቶ ኢሳት፣ ከዚያ 360 አሁን ደግሞ የኮምፓሱ ባለቤት አማሪካዊው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ራሱ የፋኖ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ ያዥ ሆኖ ከፊተኛው የፋኖ ረድፍ ላይ ለቀድሞ አለቃው ለእስክንድር ነጋ ሽንጡን ይዞ ሲከራከር ሲሟገትለትም አይቼ ይሄማ ቅዠት መሆን አለበት ብዬ አስር ጊዜ ባማትብም እውነት ሆኖ አልለወጥ ብሎኝ ገርሞኝ፣ ገርሞኝ ነው እስከ አሁን ያለሁት።

"…የቲክቶክ መንደር የጎረምሶች ሽኩቻ፣ ድንፋታ፣ ዛቻ እና ግብግብ። የፌስቡክ መንደር ሁካታ፣ የዩቲዩብ ሰበር ዜናው ራሱ እኔ የማላቀው ነው የሆነብኝ። ፋኖዎቹ ሲሰበሰቡ በቅርብ እከታተለው የነበረውን የስብሰባ ሂደት በስብሰባው ላይ የሌሉና በሂደቱ ውስጥ ያልነበሩቱ አካላት ገሚሱ ዘመነን፣ ገሚሱ እስክንደርን ይዞ ሲጯጯህበት ሳይ ይሄ ነገር ብሔራዊ ቲአትር የሆነ ድራማ ለመሥራት ልምምድ እያደረጉ ይሆን እንዴ? ብዬ ለመጠየቅ ሁላ እየዳዳሁ ነው። መሬት ላይ ያለው እውነት እና አየር ላይ ያለው ሸቀጥ፣ ትርምስ አስደማሚ ነው። ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሶ ሌላ ዓለም ላይ ነው አዳሜ የካቶሊክና በፕሮቴስታንት ቀደምትነት እና መሪነት ጉዳይ ላይ ጭቅጭቅ ላይ ነው።

"…የመጀመሪያው ሐዋሪያዊ እምነት ኦርቶዶክስ ነው። ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ እምነት በኋላ የተከሰተ ድርጅት ነው። ቆይቶ ደግሞ ከካቶሊክ ፕሮቴስታንት ተገንጥሎ ወጣ። ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ከእምነት ፉክክር አልፈው በመንግሥታት የሚደገፉ ሆኑ። መንግሥታቱም የፖለቲካ ፖሊሲያቸው ማስፈጸሚያ አካል አድርገው ስለፈጠሩአቸው ግራና ቀኝ በደጋፊ መንግሥታት ታጅበው በዓለም ላይ የፕሮሞሽን ሥራውን ያጧጥፉት ነበር። የሮም ኢምፓየር የሮማን ካቶሊክ ይዛ ዓለምን አስገበረች። አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ፣ አውሮጳ፣ አሜሪካና ካናዳ፣ አውስትራሊያ ጭምር፣ እነ ካሪቢያን ደሴቶች ከካቶሊክ በቀር ሌላ ጥንታዊ እምነት የሌለ ተደርገው ነው የተሰበኩት። ኋላ ላይ ጴንጤዎቹም በፉክክሩ ገብተው በተለይ ከማርቲን ሉተር መምጣት በኋላ የተቃውሞ ጽሑፎቻቸውን በቶሎ ከሕዝብ ዘንድ ለማድረስ ሲሉ የጽሕፈት ማባዣ ማሽን ሁላ ፈልስመው ፕሮፓጋንዳውን አጦፉት። በመሃል የኦርቶዶክሱን ዓለም በእስላም አስቀጠቀጡት። አስወረሩት። እናም አሁን አንድ ካቶሊካዊ ወይም፣ ጴንጤ ስለጥንታዊ ሃይማኖት ብትጠይቁት ከካቶሊክና ከጴንጤ በቀር ሌላ እውነትም እምነትም እንዳለ አይነግራችሁም። ችግሩ የሰውየው ሆኖ አይደለም። ያልነገሩትን ከየት ያመጣዋል?

"…እኔም እላችኋለሁ ፋኖ ማለት በአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተንጠለጠለ አይደለም። በሻለቃ መሳፍንት እና በሻለቃ ባዬ፣ በምሬ ወዳጆና በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ በአቶ አሰግድ እና በመከታው ላይ ተቸክሎ የተቀፈደደ አይደለም። ኦርቶዶክስ የሚባል ጥንታዊ እምነት ከጀርባ ተሸፍኖ አለና የካቶሊክን እና የፕሮን ፍትጊያ እያየህ አንተ ፒፕሉ አትጀዝብ። ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ተያይዞ የመጣ ቀኖናዊ፣ ሐዋርያዊ፣ ዶግማዊ ሃይማኖት አለ። ራሳቸውን በግራ ቀኝ፣ በጠላት እና ወዳጅ በደጋፊ እና በተቃዋሚ ታጅበው በሚፈጥሩት ፍትጊያ የተሸፈኑ የትየለሌ ብፁዓን ፋኖዎች አሉና አትጩህ። ድምፅ ቀንስ ነው የምልህ። አሰግድ እና ምሬ ወደጆ፣ መከታው ፋንታሁን ሙሀባው፣ ባዬ እና ሀብቴ፣ ደረጄ፣ ሳሚ፣ ሰለሞን አጠናው፣ ጋሽ መሳፍንት፣ ደሳለኝ ብለህ እንደ ማስቲሽ እነሱ ላይ ብቻ ተለጥፈህ፣ ተጣብቀህም ዋይ ዋይ የምትልበት አይደለም የፋኖ ትግል። ዞር ዞር ስትል ከካቶሊክና ከፕሮው ጀርባ ድብቁ ግዙፍ እውነት የተሸከሙ ማስታወቂያ የማይሠሩ፣ ዶላር የማይቀፍሉ፣ ጀብድ የሚሠሩ ትንታግ ፋኖዎች አሉና አትንጫጩ። ሸቃጭ፣ ቲፎዞ፣ ግርግር፣ ውርውር የሌለባቸው፤ ሙያ በልብ ብለው ትኩረታቸውን ከትግሉ ላይ ብቻ ያደረጉ ተርቦች አሉ። እኔ የማየው እነዚያን ነው። የእነ ሀብታሙ አያሌው መከላከያ ተደመሰሰ፣ በገፍ እጅ ሰጠ፣ የነተበ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ላይ የማይሸቅጡ፣ የግንቦት 7፣ የባልደራስ፣ የእነ እስታሊን፣ የእነ ዋቅጅራን መንጠራዋዝ ከቁብ የማይቆጥሩ አሉና ተረጋጉ። አሁን ያለው የግራ ቀኝ ጫጫታ ትርፉ መላላጥ ካልሆነ በቀር የሚፈጥረው ነገር የለም።

"…ለትግል የሚላክ ዶላር እንደ አስቤዛ ፋኖ የሚሸምት። ለትግል የሚላክ ዶላር ኡጋንዳና ኬንያ ካፌና ሬስቶራንት የሚከፍት። ከኡጋንዳ ደቡብ ሱዳን ካሚዮን መኪና ገዝቶ የሚነግድ። ታጋዩ ቅማል እየበላው፣ ቂጣ አጥቶ በለስ እና ሙጫ እየበላ እያዩ እነርሱ ጊዜ ሰጥቷቸው የፋኖ መሪ ሆነው ስለተገኙ ቀን በቀን የብግና የፍየል ሙክት፣ በሬ ጥለው ሽንጥና ዱለት እየከኩ፣ ዝንጥ ብለው በፈረንካው በሸነና የሚሉትን ፌካፌክ በሚዲያ ሠራዊት ድጋፍ የሚንቀሳቀሱትን ገልቱዎች እውነተኛ ታጋዮች ሳያቃቸው ይቀር መስሏችሁ ነው? እህቱ የኦህዴድ ባለ ሥልጣን ያገባች የፋኖ አለቃ ዶላሩ በእህቱ በኩል ተልኮ በሸነና የሚለውን የፌክ ፋኖ ግሩፕ እውነተኛው ጠፍቶት መሰሎህ ነው? አሳምሮ ያውቃል። ጥያቄ ያያነሡ፣ ግምገማ ይደረግ ብለው ሓሳብ ያቀረቡ ታጋይ ፋኖዎችን መሣሪያ ገፍፈው የቁም እስረኛ፣ ሌላውን ደግሞ ጠርንፈው በጩቤ ጨቅጭቀው የገደሉ የፋኖ አለቆችን ታጋዩ ሳያውቅ ቀርቶ ይመስልሃል? አይደለም። ሁሉም ሁሉን ያውቃል። ዘራፊው፣ ገፋፊው ማን እንደሆነ አሳምሮ ያውቃል። ባልየውን በመከላከያ አስገድለው ቤቱ ሄደው ገንዘቡን ሙልጭ አድርገው ዘርፈው ሲያበቁ ሚስትየዋን አንጠልጥለው ሰቅለው ሲያበቁ "ራሷን ሰቀለች" ያሉ ገፋፊ ሳዲስት የፋኖ አለቆች እንዳሉም ፋኖው አሳምሮ ያውቃል። ትግሉ ይዘገይ ይሆናል እንጂ በፍጹም አይቆምም። አሁን ግን እኔ ግን ጥጌን ይዤ ልመልከት። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር።” ኢሳ 48፥22

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ።” መዝ 84፥7

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉YouTube
https://www.youtube.com/live/W-w7yQ5WNh0?feature=shared

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v56j2nm--ethiobeteseb.html

👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ልማት የሚጠላ የለም። ልማት ግን ሕዝብን አጥፍቶ አይደለም።

"…ዐማራ ብቻ ይሄን አረመኔ ፀረ ሰው አውሬ ቡድን ለመፋለም ነፍጥ ያነሣው። ዐማራ ብቻ ነው ከዚህ ልቡሰ ሥጋ ጋኔን ጋር ተናንቆ፣ እየተዋደቀ የሚገኘው። ዐማራ ብቻ ነው እምቢኝ ባርነት፣ እምቢኝ፣ በቃኝ ብሎ የተነሣው። ዐማራ ብቻ ነው የተሰባሰበው፣ እየተመካከረም ያለው። ዐማራ ብቻ ነው የአገዛዙን አሽከር ገረዶች እየቀነደሸ እያስበረገገ ያለው። ዐማራ ብቻ ነው አምባገነንነትን እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ ከዜሮ ተነሥቶ ዛሬ ሚልዮን ጀግና ያፈራው። ዐማራ ብቻ ነው ከፍቶኛል ወደ ሱማሌ፣ ኬንያ፣ ሊቢያና የመን ልሰደድ ሳይል ወደ ጫካ ወደ በረሃ ገብቶ እየተፋለመ ያለው። ዐማራ ብቻ ነው አልኩህ። ብራቮ ዐማራ። ሌሎቻችሁ እየተገደላችሁ፣ እየተፈናቀላችሁ፣ እየተሰደዳችሁ፣ እየለመናችሁ፣ እየተንከራተታችሁ፣ እያለቀሳችሁ፣ እየተራባችሁ ኑሩ። ዐማራ ያሸንፋል። ዐማራ ድል ያደርጋል። አሁን ከዚህ አውሬ አገዛዝ ጋር እየተዋጋ የሚሞት ዐማራ እንደሞተ አይቆጠርም። ገነት እንደገባ እንደ ሰማእት ነው የሚቆጠረው። በስደት ሲና በረሀ እና የመን በረሀ ውስጥ በውኃ ጥም ከመሞት ፋኖ ሆኖ ጥሎ መውደቅ በስንት ጣዕሙ።

• ዋሸሁ እንዴ…?

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እግዚአብሔር ይመስገን። ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ሞልቶ ተትረፍርፏል። ከምስጋናው በመቀጠል ደግሞ ያው እንደተለመደው ወደ ርዕሰ አንቀጽ ንባባችን እንሄዳለን ማለት ነው።

"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ደግሞ ስለ ኮሪደር ልማቱ ፀጋ እነ ቱሩፋት ስላመጣውም በረከት፣ በውበት እያማረች፣ እየተዋበች፣ እያሸበረቀች ስላለችው፣ ስደተኛ እየጎረፈባት ስላለችው አዲስ አበባችን ጻፍ ጻፍ አሰኘኝ። እናም በተለመደው ኮምጣጤ የጦማሬ አጻጻፌ ርዕሰ አንቀጼን መጻፍ አምሮኝ አዘጋጀሁላችሁ።

• እህሳ እናንተስ ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የታገቱትን ተማሪዎች በተመለከተ…

• ኦቦ ኃይሉ ጎንፋ (ኮሬ ነጌኛ)

~ የታገቱት 167 ተማሪዎች ናቸው። 160 ውን ተዋግተን አስለቅቀናል። የቀሩን 7 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። አረጋገጡ ነው የሚለው የአሻም ዜና።

• የኦሮሚያ ክልል ደግሞ ያው (ሽመልስ አብዲሳ ዋናው ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ብልፅግና ማለት ነው) እንዲህ አለ።

~ ስለታገቱ ተማሪዎች ምንም መረጃ የለኝም። አላቅም። ስለምን እገታ ነው የምታወሩት? እንዲያውም እኔ ራሴ እናቴን አግተውብኝ 10 ሚልዮን ብር ለምኜ ነው ከፍዬ ያስፈታኋት።

• የታገቱት ልጆች ቤተሰቦች

~ የተፈቱ፣ የተለቀቁም ልጆች የሉም። እንዲያውም አጋቾቹ በሰው 1 ሚልዮን አጠቃላይ 167 ሚልዮን ብር ክፈሉ ብለውናል። ልንከፍል ሕዝብ መለመን ስንጀምር ደግሞ መንግሥት ተብዬው መጥቶ ልመና መለመን አይቻልም ብሎ ይከለክለናል። አሁን ልጆቻችን ከሰላሌ ወደ ደምቢዶሎ ሳያዘዋውሩአቸው አልቀረም።

• እሜቴ አሜሪካ…

"…የታገቱት ተማሪዎች ከ100 በላይ ናቸው። በጣም ያሳዝናል። ምፅ ምን ይደረግ? (የታገቱት ዐማራ ስለሆኑ ነው እንጂ ትግሬ ቢሆኑ ነጠላ ዘቅዝቃ ታለቅስ ነበር) ብለው የሚያሙ ሐሜተኞች ግን አሉ።

• የብልጽግና አክቲቪስቶች

~ አዲስ አበባ ዱባይ መስላለች። ኮሪደር ልማቱ ዋው ነው። ባይበላስ፣ ባይጠጣስ ቢቀርም ያሰኛል። አቢቹ ችግኝ ተከለ፣ ቅሪላ ገፋ፣ በሎጬ አለፈ። በሺ ዓመት አንዴ የሚታይ ፔናሊቲም አስቆጠረ። ሃሌሉያ…

"…የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

~ ኢትዮጵያ ቡና ዋንጫ በላ። የስቴዲየም ወንበር ዲቻዎች ሰበሩ። የቢራ ዋጋ መጨመሩ ፌር አይደለም። እናስይዝ የዘንድሮውን የአውሮጳ ዋንጫ ቬንዝዋላ ይበላዋል። ቡርኪነፋሶ በሁለተኝነት ያጠቃልላል ብለው ሙግት ላይ ናቸው አሉ። ኮሪደር ልማት።

• ይሄ በእንዲህ እንዳለ አቶ ንጉሡ ጥላሁንስ ምን ብለው ይሆን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጄነራሉ ጥሪ…!

"…ከአረጋዊው ሊቀጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቀጥሎ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በዛሬው ዕለት ከበረሃ ከዐማራ ፋኖ የትግል ሜዳ ሆነው በቪድዮ በምሥል የታገዘ መልእክት ለተለያዩ አካላት በይፋ የትግል ጥሪ አቅርበዋል። ጥሪ ያቀረቡላቸው አካላትም የሚከተሉት ናቸው።

፩ኛ፦ ለዐማራ ሕዝብና ለዐማራ ሕዝብ ደጋፊዎች

፪ኛ፦ ለዐማራ አድማ ብተናና ለዐማራ ሚሊሻዎች

፫ኛ፦ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙሉ

፬ኛ፦ ለዐማራ ዳያስጶራ በሙሉ

፭ኛ፦ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል።

"…ለትግል ቀድመው ጫካ የገቡ የዐማራ ፋኖ አደረጃጀቶችም በሙሉ ወደ ትግል ሜዳ እየጎረፈ የሚመጣውን አዳዲስ ፋኖ በአግባቡና በተደራጀ መልኩ ደግሞም በጥንቃቄ እንዲቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል።

"…የእኔ ጀግኖች እነ ወጣት እገሌ በድንጋይና በፍልጥ በባዶ እጃቸው የጀመሩት የዐማራ ፋኖ ትግል ይኸው ዛሬ ልክ በዓመቱ ፍሬ አፍርቶ ኮሎኔል እና ጄነራሎች ተቀላቅለው የሚታገሉበት የኅልውና ትግል ሆነ። ዐማራ ተራራው ያለ ምንም አጋዥና ድጋፍ ፈጣሪውን እና ነፍጡን ይዞ በአንድ ዓመት ውስጥ ከዜሮ ተነሥቶ ይኸው ከዚህ በሽበሽ ላይ ደረሰ። ከእንግዲህ በኋላ ዐማራው ጥቂት ሳምንታት ከቆየማ አለቀ ማለት ነው።

"…ዐማሮችዬ አሁንም ጥንቃቄ ሳይለያችሁ። ዓሣን በብልሃት እየበላችሁ ወደፊት ብቻ። ወደፊት ዐማራ 💪💪🏿✊

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ሞት ለብልጽግና…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል። የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።”
ምሳ 27፥ 5-6

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተባራሪ ወሬ ነው…

"…ኦቦይ ስብሃት ቀደም ብሎ ወጥቶ አማሪካ ገብቶ በዚያ ከትሟል። እሱን ተከትለው መጀመሪያ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ቀጥሎ የገዱ አለቃና ፈጣሪው አቶ በረከት ስምኦን ወደ አማሪካ ተሻግረዋል።

"…እነሱን ተከትሎ ጄነራል ጻድቃን በዚያ አለ ቢባልም ሌሎች ወሬኞች ደግሞ በጻድቃን ላይ እንዲህ የሚል ሟርት የሚመስል ወሬ ሲበጠረቁበት እንደነበርም ተሰም ል።  "ለሥራ ጉዳይ ከመከላከያ ሚንስትሯ ኢንጅነር አይሻ ጋር አፈር ሄደው ሚንስትር አይሻ ወደ መሀል ሀገር ስትመለስ ጻድቃን ግን በኤርትራ ኃይሎች ተጠልፎ ወደ ኤርትራ ታፍኖ ተወስዷል ብለው ሲሿከቱ የከረሙ ቢሆንም አሁን ግን ጻድቃን መቼና እንዴት እንደሄደ ባይታወቅም በአክስት ሀገር አሜሪካ እንደሚገኝ ጭምጭምታው ተሰምል።

"…አሜሪካ እየተከካ፣ እየተቦካ ያለ ነገር እንዳለ ሁሉም ሰው ይሰማዋል። ለዚሁ ቡኮ፣ ለጥንስሱ ጌታቸው ረዳ ያስፈልጋል ተብሎም የእሱ መምጣት እየተጠበቀም ነው ተብሏል።

"…ይህ በእንዲህ እንዳለ የዐማራ ጀነራሎች ጓ ማለት መጀመራቸው ያሰጋው አቢይ አህመድ የሆነ ቀን እንደሚበላ ቆሌው ሳይነግረው አይቀርምና "መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉብኝ ነው" ብሎ የጠረጠራቸውን ሁሉ ሳይቀደም ለመቅደም ሥራ መጀመሩም ተነግሯል። በመጨረሻም ዳኒንም ሊበላት ነው መሰል።

"…ዛሬ ወይ ነገ አሜሪካ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀውን አይተ ጌታቸው ረዳን ወይም በቅጽል ስሙ ሎቕማፅምን የአቢይ አገዛዝ እሺ በጀ ብሎ ያሳልፈዋል ወይ የሚሉ አሉ። ስብሃት ነጋ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ እስኬው ነጋ፣ አቢቹ ነጋ ነጋ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጼ መነበቡን የቴሌግራም ሰሌዳዬ እየነገረኝ ነው። ይበሰጭብኛል 😡 ብዬ የጠበቅኩትም ሰው እምብዛም እስከዚህም ነው የሆነብኝ። ለማንኛውም ተራው የእናንተ ነው። ተንፒሱ።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ ✍✍✍ …ሻሸመኔ፣ አሩሲ፣ ጅማ የሆነውን ታውቃላችሁ፣ በጋንቤላም እየሆነ ያለውን ትመለከታላችሁ። አዎ ኢትዮጵያን ሰብረህ አፍርሰህ ኦሮሚያን ገንባ ነው የደናቁርቶቹ ፍልስፍና። እስቲ ተራ በተራ እንመልከት በኦሮሙማው ፍርስርሱ ለመውጣት እየዳከረ ያለውን የኢትዮጵያ ክልል።

• ትግራይ፦

"…ኦሮሙማው ከወያኔ ጋር ተጠቃቅሶ በስሱ ምታኝና የመለስን ኔትወርክ እናጽዳ ብለው ተማምለው የጀመሩትን ልፊያ ኦሮሙማው አጋጣሚውን ተጠቅሞ፣ ክልሎችን በሙሉ አስተባብሮ ትግሬን አደቀቀው። አወደመው። ከሚልዮን በላይ ትግሬን ጨፍጭፎ ከአፈር በታች ደባለቀው። አሁን ትግሬ ደካማ፣ በራሱ የማይቆም፣ ያለፈውን ጊዜ እያሰበ የሚቆዝም፣ ትግራይ የወንጀለኞች መናሃሪያ፣ የድህነት፣ የራብ ተምዳሌት፣ ጭንቀት፣ ጥበት የሞላባት፣ ትግሬዎች ዙሪያቸው በእሳት የታጠረ፣ በየትኛውም ክልል ተዟዙረው መሥራት የማይችሉ። በከተማ የሞሉ ለማኞች አድርገዋቸዋል። እያንዳንዱ ትግሬ አሁንም እንደምንም ኦሮሞን አጭበርብሬ፣ ጀግና፣ ጎበዝ ብዬ ተጠግቼ ተመልሼ ያለፈውን ዘመኔን እመልሳለሁ ብሎ ነው የሚያስበው። ዐማራን በመጥላት እስከ አጥንቱ ድረስ የዘለቀ ነቀርሳ የሆነ ህመም እንዲታመም ስላደረጉት ወያኔዎቹ ወደፊትም በኢሮሙማው የተደገሰለትን የጥፋት ድግስ ቢያወቅም ዐማራ ጋር ከምሆን ኦሮሞ ይጨፍጭፈኝ ብሎ ለመጨፍጨፍ ፈቃደኛ ሆኗል። ለዚህ ነው የትግሬ አክቲቪስቶች ለኦሮሙማ ከኦሮሞ አክቲቪስቶች በላይ ግርድናቸውን ፕሮፌሽናል ያደረገቱት።

• አፋር፣ ትግሬ፣ ሱማሌ

"…ኦሮሙማው አፋርና ትግሬ ደም አቃብቶአቸዋል። ትግሬዎቹ ለዚህም የአፋሩን ፕሬዘዳንት እንጂ ተጠያቂ የሚያደርጉት የኦሮሙማውን ሴራ ንክች አያደርጓትም። አወል አርባ እንዲህ አድርጎ፣ እንዲያ ፈጥሮ ነው የሚሉት። አሁንም የሆነ ቀን ሊያፋጃቸው እንደሚችል እያወቁም ለመፍትሄው ከመባጀት ይልቅ ሌላ ዓለም ላይ ናቸው ትግሬዎቹ። አፋርና ሱማሌም እየተፋጀ ነው። ኦሮሞ ከዳር ቆሞ እየሳቀ ነው። እሳቱ የሚነካው አይመስለውም። ብልጠቱ የተነቃ፣ የሆነ ቀን አፈር ከደቼ እንደሚበሉ አይገምቱም። አያስቡም። ኦሮሚያን ለመገንባት ሌላውን ማፋጀት በሚለው መርሀቸው መሠረት እያስኬዱት ነው። እያስቀጠሉትም ነው።

"…ደቡብን እንደ ከረሜላ ቁርጥ ከፋፍፈለው በዳጣ ሊበሉት አዘጋጅተው ጨርሰዋል። እነ ነጭ ሳር ሁሉ ኦነግ ገብቶ እንዲሰፍርባቸው ተደርገዋል። እነ ጥቁር ውኃ፣ ሲዳሞ ሃዋሳ ጭምር ኦሮሙማው ሊከረሽማቸው አጣጥቦ፣ አድርቆ ቀን እየጠበቀላቸው ነው። ጉራጌ ሊዋጥ አንድ ሀሙስ ነው የቀረው። በአጠቃላይ ደቡብ በጃዋር መሀመድ ቀውጢ፣ በአባዱላ ገመዳ ፕላን፣ በኦሮሙማው ፕሮጀክት ጣጣው ያለቀ ተሰልቃጭ ሆኖ አፈር ከደቼ ሊያበሉት በዝግጅት ላይ ናቸው። ኦሮሙማ በቃኝ አያውቅም። ኦሮሙማ ከምድር አልፎ ሰማዩ፣ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ፣ አረብ፣ ሜዲትራኒያንን ተሻግሮ ሲሲሊ ሁላ የእኔ ነው ባይ ነው። ጥንታውያን ግብፆች እኛ ነን የሚሉትም የቀልዳቸውን አይደለም። ኤርትራ፣ ትግራይ በሙሉ የኦሮሞ ግዛት ነው። አክሱም አካሱማ፣ ቅዱስ ያሬድ የመደባይ ኦሮሞ ነገድ አባል ነው። የሚሉትም ጆክ እንዳይመስልህ። መቀሌ መስቀለኛ መንገድ ነው። መተማ ሞቱማ ነው። ዋልድባ ወልዱባ ነው። ሌማሊሞ ለማለማ ነው የሚለው እየቀለደ ከመሰለህ ተሳስተሃል።

"…ሀረሪ ተውጧል። አስተዳደሩ ከላይ ሲቀር ከታች በሙሉ ኦሮሞ ሆኗል። ድሬደዋ ከሱማሌው እጅ ፈልቅቀው አውጥተው ኦሮማይዝድ አድርገውታል። አዲስ አበባን እናንተው መስክሩ። በጉልበተኛ ጎረምሳ ስር እንዳለች ሴተኛ አዳሪ ቀለም ቀባብተው ለገበያ እንድትታይ አድርገው ወንዱ ሁሉ የቤቱን ችግር ረስቶ ለሃጩን እንዲያዝረበርብባት እያደረጓት እያያችሁ ነው። በቤቱ መብራት አሳጥተውት በጀነሬተር እንደሚሠራ ቡናቤት አደባባዩን ብቻ በዲም ላይት አንቆጥቁጠው፣ በቶፕ ቪው የድሮን ቀረጻ በቴሌቭዥን እያስኮሞኮሙ ራሱን በራሱ እንዲያረካ ያደርጉታል። ውኃ በቤቱ ከመጣች ወር የሆነው አዲስ አበቤ የአዳነች አበቤን የጎዳና ላይ ፋውንቴን ከነግማቱ፣ ከነ ክርፋቱ፣ ከነ ጥንባቱ ወጥቶ በማድነቅ ራሱን ሸውዶ ወደ ቤቱ በባዶ ሆዱ ይሄዳል። ዋሸሁ እንዴ? ይሄ ይገርምሃል ገና ለአደባባዩ መብራት የአዲስ አበባ ነዋሪ የመብራት ታሪፍ ተጨምሮበት ይከፍላታል። ኦሮሚያ እስክትለማ ሌላው ሀገር ይደማታል።

"…ጋምቤላና ቤኒሻንጉል። ጋምቤላ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሀገር ከሆነች ሰነበተች። የኦነግ ሸኔ መቀመጫም፣ መፈንጫም ከሆነች ቆየች። ጋንቤላ የሆነ ቀን የመሃል ሀገር ሰዎች ሩዋንዳ እንደሚሆኑ አትጠራጠሩ። ቤኒሻንጉል እየጸዳ ነው። ከዐማራው፣ ከጉምዙ፣ ከአገው፣ ከበርታው እየጸዳም ነው። ቤንሻንጉል ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመጠቃለል አንድ ሀሙስ ነው የቀራት። አዲስ አበባ፣ ደቡብ፣ ድሬደዋና ሀረር የሆነ ቀን ከመኝታችሁ ስትነሡ ወርመው ልታገኟቸው ትችላላችሁ። አሁን ቤኒሻንጉል መብራት የለም። በምድር ትራንስፖርት ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ባህርዳርና ወደ ሌላውም ክልል መሄድ አይሞከርም። የቤንሻንጉል ጫካዎች በሙሉ በኦሮሙማው በአቢይ አህመድ ፕላን ቢው ኦነግ ሽሜ ነው የተሞሉት። ሆስፒታሎች በመብራትና ውኃ እጦት ሥራ አቁመዋል። የህዳሴው ግድብ መገኛ ቤኒሻንጉል ጭለማ ላይ ናት። በአሶሳ ትምህርታቸውን የጨረሱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ወደ ክልላቸው በትራንስፖርት መመለስ ስላልቻሉ፣ ዩኒቨርሲቲዎችም እናንተን ማቆየት ስለማልችል ጥፉልኝ በማለት ከደጅ አፍስሷቸዋል። አዳሜና ሄዋኔ ግን ይህን አላይም ብሎ የኮሪደር ልማት እያየ ራሱን በራሱ እያረካ ነው የሚገኘው።

"…እንግዲህ ለኦሮሙማው እቅድ ስኬት እንቅፋት፣ ሳንካ፣ ደንቃራ የሆነው አንድ ክልል ብቻ ነው። አንድ ነገድ። እሱም ዐማራ ይባላል። ዐማራው ብቻ ነው የኦሮሙማው አካሄድ ዘግይቶም ቢሆን ገብቶት ቀድሞም ተረድቶት ጓ ብሎ ከፊቱ እንደ ቅዱስ ዳዊት ወንጭፍ በጠጠር ይዞ ከጎልያዱ ኦሮሙማ ፊት የተገሸረበት። አዎ ጎልያድ ሁሉን ውጦ ውጦ ዐማራው ጋር ሲደርስ ቆሟል። ትግሬን አንጠባጥቦ ዱቄት እንዳደረገ የነገረን ጎልያድ ኦሮሙማው ዐማራው ከፊቱ መቆሙን ባወቀ ጊዜ ሳቀ፣ ተሳለቀም። ትግሬ ዐማራን ባዶ እጁን አስቀርቶ ዐማራው በምንሽር ብቻ ነው ያለው፣ በሳምንት ውስጥ ሱሪውን አስወልቄ ገርፌ ልክ አገባዋለሁ ብሎ የተነሣው ጎልያድ ኦሮሙማ ወደ ቅዱስ ዳዊት ዐማራው ዘንድ ሸለፈታሙ እየፎከረ ገባ። ገባናም በዳዊት ወንጭፍ በዐማራው ጠጠር ጎልያዱ ተጋደመ። አዎ ዐማራ ነው አሁንም የእስራኤል ኢትዮጵያን መርገም ሸለፈታሙን ፍልስጤማዊ ጎልያድ የኦሮሙማን ትእቢት የሚያበርደው። እስራኤል ኢትዮጵያንም የሚታደገው ይሄው ዳዊት እረኛው ቅዱሱ ዐማራው ነው። አከተመ።

"…ቢያንስ ቢያንስ አሁን ዐማራው ፈተናዎች ቢኖሩበትም እንደ ትግሬ ዱቄት የሚሆን ሕዝብ አለመሆኑን አስመስክሯል። ዐማራ ከዜሮ ተነሥቶ ሂሮ፣ ከባዶ እጅ ተነሥቶ ከባድ መሣሪያ እስከመታጠቅ ደርሷል። ዐማራ ግብር ለፋኖ ለልጆቹ መገበር ጀምሯል። በአንድ ዓመት ውስጥ ከነችግሮቹ ከከፍታው ማማ ላይ ወጥቶ ጉብ ብሎ ተቀምጧል። ከእንግዲህ ኦሮሙማው ሊያደርግ የሚችለው እንደ መንደር ሴተኛ አዳሪ ደጃፉ ላይ ቆሞ ለመከፋፈል ከመሳደብ እና ከመውረግረግ በቀር ሌላ አቅም ይኖረዋል ብዬም አላስብም። ክልሎችን አጠፋለሁ በማለት ዐማራን ራሱ አስር ትንንሽ ለማድረግ ሕግ እያወጣ እንደሆነ እየተሰማ ነው። አገውና ቅማንትን ክልል፣ ጎንደርን 4 ቦታ፣ ጎጃምን 3 ቦታ፣ ወሎን 5 ቦታ፣ ሸዋን በኦሮሞ ስር በማድረግ ለመዋጥ መዘጋጀቱ ነው የሚነገረው። ዐማራ ግን ወይ ፍንክች።…👇 ከታች ይቀጥላል ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አመስጋኙ ጨምሯል። 1ሺ ስጠብቅ ስድስት መቶ ጭማሪ አሳይቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋናችን በመቀጠል የምንሄደው ወደ ተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ከወትሮው ትንሽ መረር ያለ ሃቅ የያዘ ነው። ከወዲሁ ጓ የሚሉብኝ አካላቶችም በአይነ ህሊናዬ እየታዩኝ ነው። ዛሬ ርዕሰ አንቀጼን መጻፍ የፈለኩትና ያማረኝም በ…

የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጂ
የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ

በሚል ስሜት የተጻፈ ነው። እንደ ሬት፣ እንደኮሶ፣ እነደ ሆምጣጤና እነደ ሰፈነግ ያለ ርዕሰ አንቀጽ ነው። መረር ይላል። እኔ ራሴ ሳዘጋጀው ቋቅ እያለኝ ነው። ያው በል በል ሲለኝ፣ አልፎ አልፎም ትከሻዬን ሲሸክከኝ በወንድ አቅሜ በስተ እርጅና በትበት ብዬ ያዘጋጀሁላችሁ ርዕሰ አንቀጽ ነው።

"…ውኃ በሰፈራችሁ ካለች ትንሽ ውኃ በብርጭቆ አዘጋጅታችሁ ብታነቡት እመክራለሁ። ፐ እኔ እኮ አልተንትን? አዛኜን ትን እስኪልህ አይደል እንዴ የምተነትነው። 😂 ጽፌ ስጨርስ ራሴን እጠይቃለሁ። አንተ ዘመዴ ግን ከየትኛው የአማሪካ ወይ የእንግልጣር ኡኒበርስቲ ነው የበጠስከው እለዋለሁ። ለነገሩ ተፈሪ መኮንን እየተማርኩ እኔ ባልገባበትም እንኳ በበራፉ ሳልፍ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስንት ዓመት ጠጠር ወርውሬአለሁ እኮ። ማን ያውቃል ተንታኝ የሆንኩት እኔ ኡንበርስቲ ባልገባም የወረወርኩት ጠጠር መግባቱ ታይቶ ቢሆንስ። አሜን ነው? አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና፣ ሆኖልሃል በል በሉት። ኡንበርስቲ በጥሰሃል በል በሉት። ነካ አድርጉትና… 😂😂😂

"…ቀልዱ ቀልድ ነው ለማንኛውም ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… በዚህኛው በኩል ደግሞ ይሄን ነፍሰ ገዳይ አረመኔ ሥርዓት ለመንቀል ለሕይወታቸው ሳይሳሱ በድንጋይና በዱላ ሳይቀር ፊት ለፊት ከጠላት ጋር እየተናነቁ የአገዛዙን ሠራዊት እያባረሩ ትጥቅ የሚማርኩ ጀግኖችን ስናይ ደግሞ ተስፋችንን ይበልጥ ያለመልመዋል። እንኳን አሁንና አድማ ብተናው፣ ሚሊሻው ግልብጥ ብሎ ወደ ፋኖ ትግል እየገባ፣ እንኳን አሁን እና ኮሎኔል ጄነራሉ ወደ ፋኖ ትግል እየተመመ ይቅርና በፊትም ቢሆን ገና በጨቅላ በልጅነት ጊዜ በፋኖ ትግል አፍሬ አላውቅም። ይደፈርሳል። ከዚያ ደፍርሶም ይጠራል። ገፈቱ፣ አተላው ይወገድ እና ንጹሑ የጠራቀው ፋኖ ያቸንፋል። አለቀ። ይሄው ነው።

"…ሁለት ሦስት እንቁራሪቶች በጩኸት በሚረብሹት ውቅያኖስ ውስጥ ስንትና ስንት ፀጥ ብለው ሥራቸውን የሚሠሩ ግዙፍ ግዙፍ ሻርኮችና ዓሣ አንበሪዎች እንዳሉ ማወቅ ተገቢ ነው። እንዴት ሰው ከኦሮሙማውና ከትግርሙማው አክቲቪስት እኩል እንዲህ ወርዶ በራሱ መሪዎች ላይ ይደነፋል? እናም ወዳጆቼ በእንቁራሪቶች ጩኸት አትረበሹ ለማለት ነው። እንቁራሪታም…

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አንድ ሰሞነኛ ጀብዱ ላጫውታችሁ። ሰሞኑን ነው።  10 መኪና ሙሉ የሰለጠነ የብራኑ ጁላ መከላከያና የአቢይ አህመድ ሪፐብሊካን ጋርድ ከባህር ኃይልና ከኮማንዶ ጋር ተሰባጥረው በአንድነት የተዘጋጁ ልዩ ኦፕሬሽን ሠሪ ናቸው የተባሉ ወታደሮችን የያዘ ጦር ለተባለው ልዩ ኦፕሬሽን ወደ አንድ የፋኖ ቀጠና እየተመመ ይሄዳል። ያ የፋኖ ሠራዊትም እየተመመ ወደ ቀለበቱ ውስጥ የሚመጣውን ጦር ጠብቆ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር ይደመስሰዋል። ፋኖዎቹ ሦስቱን መኪና ወታደር ይቀብሩና የ7ቱን መኪና አስከሬን ግን ሕዝቡን ቅበሩ ብለው ያዝዛሉ። ሕዝቡም በጡሩንባ ወጥቶ ወታደሮቹን ከነቀዩ ቆብ ልብሳቸው እያለቀሰ ቀበራቸው። ተተኳሽ ጥይት፣ በግመል፣ በአህያ፣ በበቅሎም ተግዞ አላልቅ ነበር ያለው። ሁሉ ነገር በፎቶም፣ በቪድዮም ተቀርጿል። ነገር ግን ለአንዳቸውም የሚዲያ አካላት አልተላከም። ፕሮፓጋንዳም አልሠሩም። ሃቀኛ ሠራተኛ እንዲህ ነው። አይለፈልፍም። እወቁኝ፣ እዩኝ፣ ተመልከቱኝም አይልም።

"…ሰሞኑን በጎጃም እና በጎንደር የተደረገ አንድ ከፍተኛ ሰቅጣጭ የሆነ የጦርነት ቪድዮ እያየሁ ነበር። በጦርነቱ ላይ በተፈጸመ ተጋድሎ ምክንያት በፋኖ ኃይሎች የተጨፈጨፉ የአገዛዙን የመከላከያ ሠራዊት አባላት እያየሁ ነበር። የፋኖ ኃይሎቹ ከድል በኋላ በአስከሬኖቹ ዳር ቆመው ሲያለቅሱ ሁላ ነው ያየሁት። ለአንድ አቢይ አህመድ ለተባለ እብድ ሰው ብለው እንደ ጭዳ እየተጨፈጨፉና እያለቁ ስላሉ የኦሮሞና የደቡብ ወጣቶች ቆመው ሲያለቅሱ ነው ቪድዮው የሚያሳየው። "ጨርሱን፣ ግደሉን፣ ግደሉን" የሚሉና ከወገብ በታች ተጎምደው የሚያቃስቱ፣ በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ የሚቃትቱ ነፍሳትን እያየሁ መፈጠሬን ነበር የጠላሁት። ከጎረቤት ሀገር ጠላት ጋር፣ ከውጭ ከመጣ ወራሪ ጋር አይደለም ጦርነቱ። ጦርነቱ ከራስ ሕዝብ ጋር፣ ከራስ ወገን ጋር ነው። እናም ዘግናኝ ነው። ይሄን ጀብዱ የሚፈጽሙ የዐማራ ፋኖዎች ግን ሚዲያው አያውቃቸውም።

"…በዚያው ልክ የበሰሉ የዐማራ ፋኖ ትግል የገባቸው፣ አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ ያልሆኑ የዐማራ ሚዲያዎችንም እያየሁ ነው። የማይሞቃቸው የማይበርዳቸው። በግንቦት ሰባት፣ በባልደራስ፣ በግንባሩና በሠራዊቱ ዝባዝንኬ ላይ ሓሳብ የማይሰጡ፣ እንደ ዋቅጅራ ልጅ፣ እንደ ስታሊንና ሀብታሙ የመሳሰሉ የሰይጣን ጥንቸሎችን ለመያዝ የማይሯሯጡ ጎበዝ የዐማራ ሚዲያዎችን እያየሁ ነው። ሥራ ብቻ ላይ የተጣዱ። ይሄ ራሱ የዐማራ ፋኖ የደረሰበትን ከፍታ የሚያሳይ ነው። ቆሜ ነው የማጨበጭብላቸው። አከበርኳችሁ። መከታውን እንግደለው፣ አሰግድን ድፋው፣ ዘመነን አስወግድ፣ ሀብቴ ድራሹ ይጥፋ፣ ምሬ እንደዚህ ነው የማይሉ። ትግሉ የገባቸው። የጠላትን አጀንዳ የማያስፈጽሙ። በወሬ የሌለ ፍሬ የማይለቅሙ። የአባቶቻቸው ልጆችን እያየሁ ነው። ዝንፍ እንዳትሉ አንበሶቼ።

"…የዐማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ከዐማራው ይልቅ ለምን አማሪካ፣ ብርሃኑ ጁላና ብአዴን እነ ህወሓት ሁላ እንደፈለጉት አልገባኝም። የብልፅግና አክቲቪስቶችም በአንድነቱ ላይ ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ እየተጉ ነው። አንድነቱ ባይጠላም በእርግጥ ለአንድነቱ እንቅፋት እየሆኑ ያሉ በጣት የሚቆጠሩ በእነ ሀብታሙ አያሌው በኩል የሚዘወሩ አደረጃጅቶችም እንዳሉ እሙን ነው። በእነ ሀብታሙ በኩል ብቻ ሳይሆን በጎጃም በእነ ማርሸት በኩልም በዚህ በዘመነ ቴክኖሎጂ ጊዜ ድምፁ እንደሚቀዳ እየታወቀ ሆን ተብሎ ለጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው ከፋፋይ መረጃ መስጠት ለምን እንደተፈለገም የሚያወረቁት ሴራውን የፈጠሩ አካላት ናቸው። እንደ ምናላቸው ዓይነት ጎምቱ ጋዜጠኛም ለፋኖ የማይጠቅም የወረደ ተርኪ ምርኪ መረጃ መለቃቀም እና እንደነ ሀብታሙ አያሌው የፋኖ ትግል ውስጥ ገብቶ ማቡካካትን ለምን እንደመረጠ አላውቅም። ሀብታሙ አያሌው ሸዋን፣ ወሎን፣ ጎንደርና ጎጃም ላይ ራሱ ዘልቆ ገብቶ እያተራመሳቸው ነው። ምንአላቸው ደግሞ የሰፈሩን ልጅ ይዞ ሀብታሙን ለመገዳደር እየታተረ ነው። በሀብታሙና በምናላቸው፣ በግዮን ቲቪና በኢትዮ 360 ፉክክር ፋኖዎች በሁሉም እየታዘቡ ይስቃሉ።

"…በቅርበት እንደማውቀው በአንድነት ጉዳይ ሰፊ ሥራ እየተሠራበት ቢሆንም ልዩነቱን በማስፋት በጎጣቸው እና በአካባቢያቸው ለመወሸቅ የሚሠሩ ታጋይ መሳይ ብዙ ባንዳዎችም ተፈልፍለውም እየታዩ ነው። ፀቡ ባለፈው እንደገለጥኩት በፋኖ አደረጃጀት አለመስማማትና ሁሉም የመሪነት ሥፍራውን ቦታ ለመያዝ መሽቀዳደም ላይ ነው የተጠመደው። አሁን ላይ የብርሃኑ ጁላን ሠራዊት ከመመከት ባለፈ በአንድነቱ ላይ እየመከሩ ቢሆንም ልዩነቶች እየሰፉ ስለመጡ በዚህ ከቀጠሉ እመኑኝ በቅርቡ እርስ በእርስ ይጣለዙና ትልቁ ዓሣ ትንሹን ዓሣ ቀርጥፎ በመብላት አሸናፊ ሆነው ለመከሰት ይላላጣሉ። ይሄ አስፈሪ ነው። መካሰሱ፣ ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከሚቢያው ላይ ቁምቢጥ ልበል ባዩም በዝቷል።

"…ወደ ሰሞነኛው የአንድነት ጉባኤ ስንመጣ የዋቅጅራ ልጅ እንደሚያወራው አይደለም። ሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ተገናኝተው ተሰባስበዋል። ሕግም አውጥተዋል። በሕጉም ላይ ቃል በቃል ተናብበው አስተያየትም፣ እርማትም ሰጥተው ቃላቸው እንደፊርማ ተቆጥሮ ተመዝግቦ አልፎ ጸድቋል። ከዚያ ወደ ጥቆማ ነው የተሄደው። የሚጠቆመው ሰው ከተጠቆመ በኋላ በሥሩ ስላለው የኃይል አሰላለፍ፣ ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያ፣ የእዝ፣ የብርጌድ ብዛት፣ ወዘተረፈ ማስመዝገብ አለበት። እናም በዚህ መሠረት ነው ስምም ሆነው ወደ ምርጫው የገቡት። የመጀመሪያውን ዕጩ ተመራጭ ሻለቃ ዝናቡ ጠቆመ። የጠቆመውም አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ነበር። ከጥቆማው በኋላ በሕጉ መሠረት አርበኛ ዘመነ ካሴ ስለሚመራው ጦር አጠቃላይ መረጃ ከነጦር መሣሪያው ዘርዝሮ አቀረበ። አለቀ። የዘመነ እንደተሰማ ቀጣዩ ጥቆማ እና ተጠቋሚ ቀረበ። የተጠቆመው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነበር። መልካም በሕጉ መሠረት ስለምትመራው ጦር፣ ስላለህ የኃይል ብዛት፣ ከነጦር መሣሪያህ አቅርብ ተባለ። እስክንድር አላቀርብም አለ። አንተን ሳንገፋህ ወደዚህ ኅብረት ያመጣንህ ለዐማራ ስንል ነው። እናም በጨበጣ ማለፍ የለም። የምትመራውን ጦር አስጽፍ ተባለ። በስንት ውትወታ ኮሎኔል ጌታሁን የእኔ ነው። ጎጃም ጋር ማስረሻ አለ። ጎንደርና ወሎም አለኝ አለ። ጎንደር የት? ወሎስ እነማን ብለው አፋጠጡት። አልናገርም አለ። እገሌ ጋር ሁለት ስናይፐር፣ አንድ ሞርታር አለኝ ሲል ጉባኤው በሳቅ ፈረሰ። በቃ ስብሰባው ተቋረጠ። እርግጥ ነው ከወሎ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባው፣ ከሸዋ መከታው፣ ከጎጃም ኮሎኔል ጌታሁን፣ ከጎንደር እነ ጋሽ መሳፍንት፣ የማከብረው ሀብቴም ወደ እስክንድር ነው የሚያደሉት። በጉዳዩ ላይ የፋፍዴን እና የቀደመው ጎህልማ ቡድን፣ የፒለቱካው ቅማንት እና የፖለቲካው አገው ሸንጎ፣ ግማሽ ኦሮሞ የሆኑቱ የሸዋ ሰዎችም፣ የዜጋ ፖለቲካ አራማጆችም አንድ ያለን ተስፋ እስክንድር ነው በማለት ከእስኬው ጋር እየተንደፋደፉ ነው። ግን በብዙ ምክንያት አይሳካላቸውም ባይ ነኝ።

"…እስክንድር መሪ መሆን አይችልም። እስክንድር ከዳር ያደረሰው አንድም ድርጅት የለም። እስክንድር የተማረ ሰው ፀር ነው። እስክንድር ሁል ጊዜ ሁላችን በገነባንለት ስሙ ላይ ተንጠላጥሎ ድርጅት ከመሠረተ በኋላ ገንዘብ በመሰብሰብ ወደ ድርጅቱ የተማሩ ሰዎች፣ መርህ ይከበር የሚሉ ሰዎች አጠገቡ እንዲደርሱ አይፈልግም። እስክንድር ነጋና አቢይ አሕመድ ለእኔ ተመሳሳይ ባሕሪ ነው ያላቸው። አቢይ አሕመድም በዙሪያው የሚሰበስበው አቅመ ቢስ ደካሞችን ነው። እሱ ሲናገር የሚያጨበጭቡ። ስድስት ዓመት 👇ከታች ይቀጥላል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ምስጋናችን ሰፍቷል። አመስጋኙም በዝቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋናው በኋላ በቀጥታ የምንገባው እንደተለመደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው።

"…ትናንት በክብርት ባለቤቴ ትዕዛዝ ሁላችን የቤተሰቡ አባላት በቤት ሥራ ተጠምደን በማምሸታችን ምክንያት እንደወትሮው ርዕሰ አንቀጻችን ሊቀርብ አልተቻለም። የእናንተ ርዕሰ አንቀጽ ይቀራታል እንጂማ የ30 ዓመት ባለቤቴን ትእዛዝ አልሽራትም። እንደዚያ ብዬ ነው ከግድግዳ ግድግዳ እንደ ፌንጣ እየዘለልኩ መስታወት ሳጸዳ ያዋልኩት። አቤት እንዴት እንደመረቀችኝ። አይነገርም። በሚስታችሁ መመረቅን የመሰለ ነገር የለም። ባረከችኝ በሉት።

"…ዛሬ ከድካም አገግሜ፣ እስትራፖው  ለቅቆኝ😂 እንደምንም ተከስቻለሁ። በዛሬው ርዕሰ አንቀጼ እነዚህን ወንድሞቼን የጭቃ ዥራፌን አንስቼ እየሸነቆጥኩ፣ መራር ኮሶ፣ መተሬ ሰናፍጭ የበዛበት ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ሸንቆጥ፣ ብትት፣ ነቃ የምታደርግ ጦማር በርዕሰ አንቀጽ መልክ ላቀርብላቸው ወደድኩ። ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ምክር ልመክራቸውም ፈለግኩ። ደግሞስ ምክር ነው ምንአባታቸው ያመጣሉ? ምንም ምንም አያመጡም።

"…እ… እንዴት ነው ምን ታስባላችሁ? ልምከራቸው ልተዋቸው።  ባላየ ባልሰማ ልዝለላቸው? እናንተስ ርዕሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?

• ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በካቶሊክና በፕሮቴስታንቶች የፕሮሞሽን ብዛት ስለተሸፈነው ጥንታዊውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በተመለከተ እንዴት ያለ ክሽን ጥፍጥ ያለ ርዕሰ አንቀጽ አዘጋጅቼ ነበር መሰላችሁ።

"…ሰሞኑን እንግዶች ስለሚመጡ መኖሪያ ቤታችን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ይጽዳ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ከክብር ቀዳማዊት እመቤት እሜይቴ ሚስት ቀጭን ትእዛዝ ስለወረደ እኔም ከቤተሰቡ በአቅሜ እሠራው ዘንድ የቤቱን መስታወት የተባሉ ጉዶች አፀዳ ዘንድ የወደቀብኝን ዕጣ አንሥቼ እንደ ወፍራም ወደል ዝንጀሮ ከጣሪያ ጣሪያ ከግድግዳ ወደ ግድግዳ ስዘል ቆይቼ ገና አሁን መሬት መንካቴ ነው። የማዳም ቅመሞች ድካም፣ የሚስቶች፣ የእህቶችም የቤት ጽዳት ድካምን ዛሬ አይደል እንዴ ያየሁት። የመድኃኔዓለም ያለህ።

"…አሁን ደግሞ የወደቀብኝን ዕጣ ጉዳይ ጨረስኩ ስል ቤተሰቡ አድሞ አዬ ወዴት ወዴት በል በል የምን ስልክ ላይ መጣድ ነው? አባው አልጨረስክም። አሁን ደግሞ የቤቱን ደረጃና የቤቱን ምንጣፎች ታጸዳ ዘንድ ሁለተኛው ዕጣ የወደቀው አንተ ላይ ነው። እናም ፅዳቱን የሚያግዝህ ማሽን ቢሆንም ሥራው ግን የሚጠብቀው አንተኑ ነው ተብዬ ወደዚያው ልነካው ነው።

"…ዛሬ ብዙ የምሥራች፣ ቁንጥጥ፣ ልምዝግ የሚያደርግም ጦማር ለማዘጋጀት በትበት ብዬ መጣም፣መጣም ዝግጁ የነበርኩ ቢሆንም የቤተሰብ ጉባኤው ፍርድ ግን አላላወሰኝም።

"…ዳይ ወደ ጥግረራዬ… ጊዜ፣ ፋታ ካገኘሁ እመለሳለሁ። እስከዚያው በፋኖ ፍቅር የወደቀው የወለይ ስታሊን እና የዐማራ ፋኖ ቃለ የስብሰባ ጉባኤ ያዥ ሆኖ የተከሰተው የባለአደራው፣ የባልደራሱ የአዲስ አበቤው የእስክንደር ነጋ የአማሪካ ተወካይ የነበረው ኤርሚ ኤል ዋቅጅራን ዘገባ እየሰማሁ ልጠግረር። 😂😂😂

• 🖐🖐🖐

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ…!

"…አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እስከአሁን ርዕሰ አንቀጹ በ17 ሺ ሰው መነቡብን እያየሁ ነው። ቆይቶ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ እስከ አሁን በርዕሰ አንቀጹ የተበሳጨም ሰው 😡 አላየሁም። ከርዕሰ አንቀጹ ቀጥሎ የሚቀርበው ደግሞ ርዕሰ አንቀጹን ተከትሎ ከእኔ የጎደለው የሚሞላበት፣ የበዛው የሚቀነስበት የእናንተው ሓሳብ የሚንሸራሸርበት መድረክ ነው።

"…ዛሬ ከወትሮው ከተለመደው ሰዓታችን 1 ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርበው የዕለተ ሐሙሱ የኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ ዝግጅታችን እስኪደርስ ድረስ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ሓሳብ እየሰጠን እንቆያለን።

• 1…2…3…ጀምሩ…!✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አቅም ያለው በአውሮጵላን፣ መለስ ያለው በመሂና፣ ሌላው በእግሩ ወደ አዲስ አበባ እየጎረፈ ነው። ጦርነቱን፣ ራቡን፣ እገታውን፣ ግድያውን፣ አስገድዶ መደፈሩን ሽሽት ዜጎች በሙሉ ወደ ሸገር አዲስ አበባ እየፈለሱ ነው። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ከትግራይ፣ ከዐማራ፣ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ፣ ከሱማሌ፣ ከጋምቤላ፣ ከሲዳማ፣ ከጉምዝ ተሰዶ ተከማችቷል። አፋር ብቻ ስለ መሰደዱ አልሰማሁም እንጂ በሙሉ አዱ ገነት ከትሟል አሉ።

"…ዜጎች አዲስ አበባን ለስደት ተመራጭ ያደረጓት ደግሞ ቀሽሙ የኦሮሞ ብልጽግና ራሱን በራሱ ለማርካት ሲል በፈጠረው ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ነው ተብሏል። በክልሎች ትምህርት ቤት ተቋርጧል። በአዲስ አበባ ግን እየተማሩ ነው። ስለዚህ ፍለሰት ወደ አዲስ አበባ እንደጉድ ነው። ቴሌቭዥኑ ሲከፈት አዳነች አበቤና አቢይ አህመድ በአውሮጳ ስታይል ከተማዋን ገነት እንዳስመሰሏት በስሎው ሞሽን፣ በቶፕ ቪው የድሮን ቀረጻ፣ የዲም ላይት የኮሪደር ልማቱን ደጋግመው ሲያሳዩ ዜጎች በበሳሶ፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በየመን በቀይባህር፣ በኬንያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ምን አሰደደን በማለት ነው ወደ መሃል ሃገር እየፈለሱ የሚገኙት።

"…አዲስ አበባ ደግሞ አብዛኛው ነዋሪዎቿ መንገድ ዳር በሚከፍቱት ሱቅ ውስጥ በሚሠሩት ሥራ ነበር ሚልዮኖች የዕለት እንጀራቸውን የሚበሉ የነበረው። አሁን በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ጥርግ፣ ሙልጭ ተደርገው ፍርስርሳቸው ወጥቷል። ፒያሳ የሺዎችን ኑሮ ደግፎ የሚኖር ስፍራ ነበር። አራት ኪሎም እንደዚያው። ከአራት ኪሎ እስከ መገናኛ፣ ከፒያሳ እስከ ቄራ፣ ወዘተረፈ ሚልዮኖች ኑሮአቸውን የሚገፉበት ስፍራ ነበር። አሁን ሱቅ የሚባል በሙሉ ፈርሷል። የቀን ሠራተኛው፣ ተሸካሚ ወዛደሩ፣ ተሯሩጦ አዳሪው በሙሉ መዋያ የለውም። አጨብጭቦ ቀርቷል። ከባድ ነው የሚሰማው።

"…መንገድ ላይ ሚዛን አስቀምጠው የሚሠሩ ህፃናት ሳይቀር ሚዛናቸውን ተቀምተው እየተባረሩ ነው። አሁን ለአረቦች እንተሸጠች በሚነገረው አዲስ አበባ ውስጥ  በአነስተኛና በመካከለኛ ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች እሮሮ እየተበራከተ መጥቶአል። ያለምንም ምክንያት ንብረት ተወስዶባቸው ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነን እባካችሁ አታስርቡን ቢሉም የሚሰጣቸው ምላሽ ገና በደንብ ትራባላችሁ የሚል ሆኗል። የብልፅግናው አገዛዝ ይዞ የተነሳው መሪ ቃል ድህነትን ለማጥፋት መጀመሪያ ደሀን ማጥፋት አለብህ የሚል እንደሆነ የተገነዘበ ነዋሪ ግን ያለ አይመስልም።

"…የአራዳ ክፍለ ከተማ ሕዝቡን ሰብስቦ ፒያሳዎች በሦስት ወር ውስጥ ቤታችሁ ስለሚፈርስ ተዘጋጁ ይሏቸዋል። ሕዝቡም እሺ ግን የት እንውደቅ ብሎ ይጠይቃል። አላውቅም ነበር መልሱ ክፍለከተማው። አቢይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው የተባሉትን ጠራ፣ ሰበሰበ። ከዚያም ማንም የጠፈጠፈው ጭቃ ሁሉ ታሪክ ነው ተብሎ አይቀመጥም። ይፈርሳል። ይጠረጋል። በፍርድ ቤት የሚቆም የለም። ለልማት አፍርሰው ብሎ ዐወጀ። በማግስቱ የአራዳ ክፍለከተማ አስተዳዳሪ ቤቶቹን አፍርስ ተባለ። አላደርገውም ለ3 ወር በል ተብዬ አልነበረም ወይም አለ? አሰሩት አሰሩትና እና እነሱ ከኦሮሚያ ፎሊስ አምጥተው አካባቢውን አጥረው ናዱት። ናዱትና ድራሹን አጠፉት። አዲስ አበባ ሽንታም ነው ነው የሚሉት። ሌላም የወረዳ ይሁን የክፍለ ከተማ አመራር ባላረጋግጥም በልደታ ክፍለ ከተማ እንዴት ብዬ ነው ቤታችሁን ልቀቁ ላፈርሰው ነው የምለው? ቢያንስ የመዘጋጃ ጊዜ እንስጣቸው ያለ አመራር በአዳነች ፖሊሶች ተይዞ ከታሰረ ወራቶች ተቆጥረዋል።

"…አዳነች አቤቤና አብይ አህመድ በሌሊት እየዞሩ የግለሰቦችን ቤት ተደብቀው ያያሉ አሉ። ለዓይናቸው ያላማረ ቤትና ግቢ ካዩ በቃል ነው ለአፍራሽ ግብረ ኃይሉ የሚነግሩት አሉ። 😁 ብስቅም መረጃው የእውነት ነው። ወደ አንዱ ሰፈር ወይም ቤት ሌሊት ጎራ ይላሉ። "ይሄን እስከዚህ አፍርሱት። ይሄኛውን ቤት ተውት አይደብርም" ብለው እዚያው ትእዛዝ ሰጥተው ይሄዳሉ። ከቀናት በኋላ ተመልሰው ይሄዳሉ። አሁንም ለአይናቸው ያላማረ ነገር ካዩ "ይሄንም አፍርሱት" ብለው ይሄዳሉ።አፍራሽ ግብረ ኃይሉ "ክብርት ከንቲባ የዚህኛው ግቢ ባለቤት እኮ አጥሩ እንጅ ቤቱ እንደማይፈርስ ተነግሮት አጥሩን አስተካክሎ አጥሮ ጨርሷል። አዳነች አቤቤ " አይ ይፍረስ ይፍረስ አፍርሰው" በቃ ይፈርሳል።

"…ኦሮሙማ ሆዳሙን የአዲስ አበባ ሕዝብ አስተሳሰብ በሚገባ የተረዳ እጅግ በሳል በጥበብ የተሞላ አካሄድ ነው እየተከተለ ያለው። ለምሳሌ አስፋልቱን ሲጨርሱ ወደ ውስጥ ገባ ማለት ጀመሩ። ቤቱ የፈረሰባቸው ያለቅሳሉ። ከእነርሱ ቀጥሎ ያሉ ጎረቤቶች ደግሞ ይስቃሉ ይደሰታሉ። ከፊት ያለው ቤት ሲፈርስ "የእኛ አይፈርስም ተብሏል። እንግዲህ እግዜር ያውቃል። እንዲያውም የእኛ ቤት አስፋልት ፊት ስለወጣ ለቢዝነስ ያመቻል በማለት ጮቤ ይረግጣሉ። በጎረቤቱ እምባ የራሱን ተስፋ እያዬ ፈገግ ይላል። ቆዬት ብሎ አጅሬው ተስፈኞችን በዶዘር ይጎበኛቸዋል። ቀስ በቀስ ሁሉም ሰፈሩን ለቅቆ ይሄዳል። አሁንም በአዲስ መልክ እዬቀጠለ ነው። ከፒያሳ ያልተማረ ከማን ይማራል?የቀደሙት በግርግር በጥድፊያ ተደናብረው የእውነት ልማት ብሎ በማሰብም እያለቀሱ ሄደዋል። የፈረሰው ላይ ሳርና ቅጠል ሲጎዘጎዝ እያዩ ያሉ ናሪዎች ግን ምን ነክቷቸው ይሆን? አንዳንዱ የቀበሌ ቤት ነዋሪማ ጭራሽ የእኛ ቤት ፈርሶ ኮንዶሚንየም የሚሰጠን መቼ ነው ብሎ ይጸልያል አሉ። ከዚያ ይመጣና አቢይ ይንድበትና ድራሽ አባቱን አጥፍቶ ይገላግለዋል።

"…የብልፅግናን አገዛዝ ወይም አቢይ አህመድ አሊ በሥልጣን ከቀጠለ እነዚህ ሕጎች አብረው ይቀጥላሉ። መፍረስ፣ መጽዳት፣ መፈናቀል፣ መታገት፣ መደፈር፣ መዘረፍ፣ መከፋፈል እና መገደል ይቀጥላሉ። ይሄን ሕግ የሳዲስቶች ሕግ ለማስቆም ከፈለግህ ደግሞ መጀመሪያ መንቃት፣ ከዚያ መደራጀት፣ መሰልጠን፣ ከዚያ መመከት፣ በመጨረሻም ለማነከት የፋኖን እና የጀነራሎቹን መንገድ መከተል። ያለበለዚያ በቁምህ ትቃዣለህ፣ በቁምህም ሟምተህ ታልቃለህ። አሁን በየቀኑ በኑሮ ምክንያት የሚያብደው ሰው በመብዛቱ ምክንያት ታንቆ ከሚሞተው፣ መርዝ ከሚጠጣው የተረፈው ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚጎርፈው ብዛቱ ይሄ ነው አይባልም የሚል ዘገባ እየወጣ ነው።

"…ትናንት ነዳጅ ጨምሯል። ደሞዝ የለም። ኑሮ ሰማይ ይነካል። አዳነች አበቤ ፋብሪካ ሳይሆን 33 ቢልዮን ብር ወጪ አድርጋ ሱቆች፣ መንደሮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መኖሪያ ቤቶች አፍርሳ አበባ ነው የተከለችልህ። በቤትህ መብራት ከጠፋ እና በዳፍንት መኖር ከጀመርክ ስንት ዘመንህ። ውኃ በቤትህ በስንት ቀን ነው የሚመጣው? እየሸትክ፣ እየገማህ፣ እየራበህ፣ እየጠማህ መኖርን ለለመድክ ለአንተ እነ አቢይ አህመድ ተመችተሃቸዋል። ሚልዮን ትግሬ ገድሎ ፈታ ብሎ የሚኖር አቢይ ለሚልዮን አዲስ አበቤ መራብ ደንታውም አይደል። አንተን ውኃ አሳጥቶ እሱ አስፓልት ያጥብበታል። አንተን ጨለማ ውስጥ አሳድሮ እሱ የኮሪደር ልማቱነረ ዲም ላይት ያንቦጎቡግበታል። 👇 ከታች ይቀጥላል ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።” ሉቃ 3፥9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጥርሳችሁ ይርገፍ እቴ¡¡…አሁን ይሄ ምኑ ያስቃል?

"…ሰኩሪቲ ካሜራ ከመሬት ሥር ቀብረናል ማለት እንዲህ ያስቃል? እንዲህስ ያስገለፍጣል? በቃ ሁሉ ነገር በፈረንጅ ሀገር በዚያው እንደ ፈረንጆቹ ባህል ሰኩሪቲ ካሜራ በህንጻ ላይ፣ በግድግዳ ላይ ካልተሰቀለ ካሜራ የተሰቀል አይመስላችሁም አይደል? ምን ዓይነቶቹ ነጫጭባዎች ናቸው በጌታቸው?

"…እኛ እኮ ሀበሾች ነን።አይደለንም እንዴ? የራሳችን ባሕል ያለን፣ ደግሞ ልንገራችሁ አይደል እናንት ንገሩን ባዮች። በእኛ ሀገር ትሪ እና ሻሸመኔ ላይ ሰው እንጂ የሚሰቀለው ካሜራ አይሰቀልም። ካሜራ ክቡር ነው። ካሜራ ይቀበራል እንጂ አይሰቀልም። ከተሰቀለማ ይሞታል። በዚያውስ ካሜራ ቢሰቀል ሌባው መች አንድ ቀን ያሳድረዋል? ወዲያው ነው የሚወስዱት።

"…ደግሞ በሀበሻ እንደዚያ ነው የሚባለው። አያ ጅቦ መጣልህ ሲባል አያ ጅቦ የሚባል ነገር አለ? የለም። ግን ይባላል። በዉነት ምሽቴን ነው ያጨለሙብኝ። ጥርሳችሁ ይርገፍ እቴ። አሁን በእነሱ ቤት በ33 ቢልዮን ብር የተገነባ የኮሪደር ልማት፣ የተቀበረ የሴኪዩሪቲ ካሜራን ጉዳይ ሰምተው ክብሪት ከንቲባችን ላይ ሙድ መያዛቸው ነው። ጥርሳችሁ ይርገፍ አልኳችሁ። አድዬ በርቺ። ዝም ብለሽ ቅበሪ። የአዳሜንና የሔዋኔን የጫማ ቁጥር ሳይቀር በተቀበረው ካሜራ ቅረጪ። ነገርኩሽ ማንመኘንም አትስሚ። ቅበሪ አድዬ።

• ጥርሳችሁ ይርገፍ። ከምር በሰጨኝ። 😡😡😡

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጎዶኞቼ ሆይ እንደምን ዋላችሁ…?

"…በቶሎ የምንመለስ መስሎን ለቀጭን ቤተሰባዊ ጉዳይ ወጥተን በቶሎ መመለስ ባለመቻሌ የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ወደ እናንተ ሊደርስ አልቻለም።

"…መጀመሪያ የታከለ ኡማ አባት በሸኔ ታገቱ ተባለና ድራማ ተሠራ። ከዚያ ለታከለ ኡማ አባት ለኦቦ ኡማ በንቲ ማስለቀቂያ የወርቅ ሚንስትር የነበረው ሊጃቸው ታኬ 10 ሚልዮን ብር መዥረጥ አድርጎ ከፈላቸውና ተለቀቁ ተባልን። የሚገርመው ደግሞ የታከለ ኡማን አባት ያገቱት የታኬ አብሮአደግ የሰፈሩ ልጆች እና የራሱ የታኬ የአጎትና የአክስት ልጆች ሁላ ነበሩበት ተብሏል። መቋቋሚያ ተሰጣቸው አትሉም አፋኞቹ። አቶ ኡማ ተፈተው ወደቤታቸው የተመለሱ ጊዜ አፋኞቹ አረቄ፣ ውስኪና ሙክት ሁላ ይዘው እንኳን ደስ አልዎት ብለዋቸው ነበር አሉ። 😂 በዚህ የደበረው አቢይም ታከለን ወደ አሜሪካ ንካው አለው አሉ።

"…ቀጥሎ ደግሞ የአየር ኃይሉ አለቃ የኦቦ የይልማ መርዳሳ ቤተሰቦች በሸኔ ታገቱ ተባለ። ከዚያ ጄኑ ይልማ መጀመሪያ ጓ ብለው ለመፋለም ሞክረው ሸኔ አንድ ሁለት የቤተሰብ አባላቸውን ሲያርድ ወዲያው "ተተኳሽና ጥይት በብዛት ሰጠተዋቸው ቤተሰቦቻቸው ተለቀቁላቸው ተባለ።

"…ዛሬ ደግሞ የኦሮሞ ፕሬዘዳንት የዋናው አሳራጅ የኦቦ ሽመልስ እናትን የሽሜ አብሮአደግ ልጆችና የአክስት የአጎቱ ልጆች አግተዋቸው 10 ሚልዮን ብር አስከፍለው ለቀቁአቸው ብለው ከጥይት የተረፈውን ሕዝብ በሳቅ ሲገድሉት እያየሁ ነገር ግን መተንፈስ፣ መናገር የማልችልበት ቦታ ስለነበርኩ ተለጉሜ ውያለሁ። አሁን ገና ነው ቤቴ ስገባ አለሁ ለማለት ብቅ ያልኩት።

• ጀነራል ተፈራ ማሞም ከበረሃ የላኩት የቪድዮ ደርሶኛል። አይቼው እለጥፍላችኋለሁ።

• ታጋቾችዬ ግን እንዴት ናቹ? እንደምን ናቹ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከተጠራሁ ከተጋበዝኩመ እመጣልሻለሁ…!

"…ባርች ትባላለች የማከብረው ወንድሜ የእነ ሻለቃ መከታው ሠራዊት አባል ናት። ኢንተርኔቷ ሁል ጊዜ ክፍት ነው። ቲክቶክ Live ነው የምትጠቀመው። እነ አቤ ጢሞ፣ እነ መከታው፣ እነ ዮናስ አለቆቿ እንኳ በስንት ውጣውረድ ተራራ ቧጥጠው ወጥተው፣ ዛፍ ላይ ተስቅለው፣ ስንትና ስንት ወንዝ አቋርጠው ነው የሚያገኙኝ። ይህቺ በህመም ምክንያት በመዋጮ ከዓረብ ሀገር ተመላሽ ወጣት ግን ጭብጨባ ሲበዛባት ህመሟን ረስታ አፈላች።

"…በእሷ ቤት ለእስክንድር ነጋ አግዛ አባቷ የሚሆነውን ቢያጠፋ እንኳ በእንዲህ ዓይነት ዐማራዊ ባልሆነ ሥነ ምግባር አቶ አሰግድን ማዋረዷ ነው። ስህተት ሁሉም ጋር አለ። እነ ባርች ማረክን ብለው እኛ ሁሉ በመረጃ ቲቪ ያሳየነውንና ማረክን ያሉትን የብልጽግና የአድማ ብተና ኮሎኔል ራርተው በነፃ ለቀውት የዐማራ ፋኖ የሸዋ ዕዝ የኦፕሬሽን ሓላፊ የነበረውን ጀግና ዐማራ ወንድማቸውን ፋኖ አርበኛ ወንድወሰን አበበን ለ15 ቀን አቆይተው  በጭካኔ እንደገደሉት ድፍን ሸዋ ቂም ይዞ እንደተቀመጠ አጥታው አይደለም።

"…አበደን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በእነ ባርችም ሆነ በማከብረው በሻለቃ መከታው በኩል አያሸንፉኝም። ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ባርችዬ ፍልሚያውን እንጀምረዋለን። ያዥ እንግዲህ። እኔ የማንም ደጋፊ እንዳልሆንኩ ግን አለቆችሽን እነ አቤ ጢሞን፣ እነሻለቃ መከታውን ጠይቂ። ለማንኛውም ዐማራ ያሸንፋል። የሸዋ ፋኖ በዚህ መልክ መዋረዱ፣ የሕዝብ ግኑኝነት ሥራም የሚሠራ አንድ ምራቅ የዋጠ ባለሙያ መጥፋቱ በእውነት ያሳዝነኛል። ሸዋን የመሰለ ትልቅ ዋርካ እንዲህ በውስጥ ማለቅ የሚችልን ጉዳይ አደባባይ በሚያወጡ፣ እነ መከታው ራሱ ቢጣሉ በዚህ መልክ የማያዋርዱትን ሰው የሚያዋርዱ መደዴ ታጋዮች መፈጠራቸው ያሳዝናል።

"…አምላኬ ሆይ ተናግሮ አናጋሪ አታሳጣኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የኢትዮጵያም ሰዎችም የፓስተረሩን ግሩም የሆነ ዲስኩር በሰሙ ጊዜ “…እርስ በርሳቸውም፦ ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው? ተባባሉ።” መሳ 6፥29

"…መቼም የፓስተሩ ዲስኩር ግሩም ነው። ተሰምቶም አይጠገብም። ጥያቄው ግን "በእውነት ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው?" የሚለው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ "…በተለይ ዐማራ ለኢትዮጵያዊነት ሲታገል የቆየውን እስክንድር ነጋን ለኢትዮጵያዊነት እንዲታገል ገሸሽ አድርጎት፣ ዐማራን ለዐማራውያን ብሎ ትግሉን ከቀጠለ በቅርቡ አሸናፊነቱን ያረጋግጣል። እስክንድር አዲስ አበቤን ይዞ ዐማራን ለዐማሮቹ ጥሎ፣ ለቅቆ፣ እነ ግንቦት ሰባትንና ባልደራስን፣ መኢአድን፣ ኢዴፓ፣ ብልፅግናን ይዞ ቢቀጥል አዋጭ ይሆንለታል። የዐማራን ትግል ጥቂት ሊያዘገየው የሚችለውም የእስክንድር ነጋ የትግል ስልት ብቻ ነው። አሁንም እኔ ልምራ እኔ አስብሎ እየጎተታቸው ያለው እስኬው ነው። እስኬው ከሸዋ የጦር መሪዎቹ ባልተስማሙበት መከታውን በብቸኝነት፣ ከጎጃም ማስረሻን፣ ከጎንደር እነ ወንድም ሀብቴን፣ ከወሎም በይፋ ያልወጡ ግን እነ ወንድም ኑረዲንን መያዙ እየተነገረ ነው። ብልፅግናም በዚህ ቀመር መሠረት በፕሮፓጋንዲስቶቿ አማካኝነት ለእስክንድር ጠበቃ ሆነው የፕሮፓጋንዳ እንዲሠሩለት እያስደረገችም ነው። እናም ዐማራው ይሄን የእስክንድርን አካሄድ በጥበብ ካለፈው፣ እስክንድርም በሚያምርበት፣ በሚታወቅበት በኢትዮጵያኒስት ካምፕ ውስጥ ቢጠቃለልና በዚያ መታገል ቢጀምር የመከራ ያጥራል ብዬ አምናለሁ። መንግሥት ከአሁኑ የጋሽ አሰግድን ሠራዊት ለሚያዋርዱ ለሻለቃ መከታው የሴት ፋኖዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጥቶ የመከታው ሴት ታጋዮች ቲክቶክ ላይ ተጥደው ከትግል ሜዳ መከፋፈል ጀምረዋል። መከታውና ሠራዊቱም ከዳያስጶራ የሸዋ ዐማሮች የሚያገኘው ድጋፍ ቀጥ ብሎ ቆሟል። የመከታው ከእስክንድር ጋር መጣበቅ በሰራዊቱ መካከል ልዩነትን ፈጥሯል። ይሄን በሰፊው እመለስበታለሁ።

"…ለማንኛውም ይሄ ሁሉ ቀውጢ በዌስት ባንክ ኢትዮጵያ፣ በጋዛ ሠርጥ ኢትዮጵያ እሳት እየነደደ ታላቋ ኦሮሚያ በኮንዲሚንየሟ ኢትዮጵያ ላይ ሁሉም የቤት ቁጥሮች እሳት በእሳት ተያይዘው በቤት ቁጥር 004 ውስጥ ያለችው ኦሮሚያ በ2016 ዓም የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ አዘጋጅታለች ተብላችኋል። ቆማጢትም፣ ገጣቢትም፣ ጎባጢትም፣ አንካሲትም፣ አይነ እውሪትም እልል በይ።

"…ታስታውሱ እንደሆን አቢይ አህመድ ከዚህ በፊት ዐማራን ለመዉጋት ገና እያሟሟቀ ሳለ ጣሊያን ሄዶ 50 ሚሊየን ፓውንድ ተችሮት መጣ። ያንን ብር ይዞ ወደ ሱዳን ሮጦም ሄደ። በዚያ ዩሮ ለአልቡርሃን ከፍሎ ዐማራን ሊወጥር ነበር ፍላጎቱ። ነገሩ በዕለታት ውስጥ ተገልብጦ አራጁ ልቡሰ ሥጋ ጋኔሉ አቢይ አሕመድ ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ ሱዳን ሲኦል ሆና አደረች። መልአከ ሞት ነውና ሱዳኖች ረገፉ።  እርስ በእርሳቸዉኘም ተባሉ። አቢይም ሴራው ከሸፈበት። አሁንም አቢይ ለኦሮጲያ ግንባታ ዐማራን በሻሻ ለማድረግ ያግዝ ዘንድ ለሱዳን ያልተከፈለ የመብራተወ 90 ሚሊየን ዶላር አልተቀበለም። በዚያ ሌላም ከኤምሬትስ ተቀብሎ ለሁለቱም እየሰጠ እንጨምርላችሁለን እያለ በርታ ጠንከር ብለው ወደ ዐማራ እንዲገፉለት እየባከነ ነው። ለዚሁም ዛሬ ፖርት ሱዳን ገብቷል። በቀጣይ በመላው ኢትዮጵያ አሁን አሁን ኔትውርክም ችግር ሆነ ዳታም ያስፈራል።

"…የእስክንድር ነጋ ኪስ ፋኖ መግዣ ዶላር እንደማያጣው ሁሉ ኦሮሚያም ለጊዜው የገንዘብ ችግር የለባትም። በቀደም እለት ኦሮሚያ ለትግራይ ክለቦች መልሶ ማቋቋሚያ መቶ ሚልዮን ብር አካባቢ መለገሷ በዜና ተነግሯል። አንዱ ወዳጄ ደውሎ ዘመዴ ብሩ ከየት ነው የሚመጣው ሲለኝ ጠብቅ ሰሞኑን ዐማሮች በአቢይ ሽመልስ ትእዛዝ ይታገታሉ። ኦሮሚያም ያወጣችውን ወጪ በአንድ ቀን ገቢ ታደርጋለች ብዬ ነግሬው ነበር። ይሄ ጥቁር ምላሴ የነካው መቼም መፈጸሙ አይቀርም ወዲያው ውሎ ሳያድር ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚሄዱ ተማሪዎችን ሰላሌ ላይ በማገት አሁን በአንድ ተማሪ አንድ ሚልዮን ብር በመጠየቅ በአንድ ቀን መቶ ሚልየን ለትግሬ ክለብ ያወጣውን የዐማራን ልጆች በማገት ሊያስመልስ ነው። አቢይ አሕመድ ማለት እንዲህ ያለ አውሬ ነው። በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሀገሪቱን ካዝና ለጦርነትና ለቢልዮን ብሮች ቤተመንግሥት ግንባታ እያዋለ እየረጨ የጨረሰው ዕብድ መሪ፣ የጎርፍ ማስወገጃ የሌለው የመንገድ ዳር ልማት፣ የቡና ቤት አምፖል መትከያ ገንዘብ የጠረረበት አራጅ ኮሎኔል አብይ አህመድ የገዛ ሕዝቡን ከመግደል፣ ከማሰር፣ ከማጋዝ፣ በተጨማሪ ይኸው ተማሪ እያገተ የሚረካው ሳዲስቱ ካገታቸው ተማሪዎች በቀናት ውስጥ መቶ ሚልዮን ብር በመሰብሰብ ሪከርድ ሊሰብር ነው።

"…በሰሜን ተዋግተው ያላሸነፉትን ዐማራ፣ ከሰሜኑ ድል በኋላ ሊበሉት ተዘጋጅተውለት የነበረውን ዐማራ አሁን አላስችል ብሏቸው በትግሬ አክቲቪስቶች ጉትጎታና በኦሮሞ አክቲቪስቶች ጉትጎታ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በተለይ በከፋ ሰሞኑን ዐማራን ለማጽዳት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል። ቴሌግራም ገፆቻቸውን ተመልከቱ። አሩሲም እየወደመ ነው ዐማራው። በወለጋ እንደ አዲስ እያረዱት ነው ያልነቃውን ዐማራ። መከላከያው ነው ቆሞ የሚያሳርደው። በጅማም ዐማራውን መሳሪያውን ገፍፈው ለእርድ እያዘጋጁት ነው። ከሩዋንዳ የተማርነው በአንድ ቀን ሚልዮኖችን አርደን ቀንሰን ከዚያ በሃገር በቀል በእርቅና ምክክር ኮሚሽን በቄስና በሼክ በፕሮፓጋንዳ በእርቅ እንዘጋዋለን ነው የሚሉት። የኦሮሞ ቄሮ ሰው እያገተ ሕንፃ እየገነባ ነው። ከዋሸሁ ልቀጣ። መጨረሻቸውን ብቻ ማየት ነው የናፈቀኝ። አየህ ይህቺ ኦሮሚያ ናት በ2016 ዓም የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ አዘጋጅታለች ብለው የሚሳለቁብህ።

የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጂ
የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ … በልልኝማ አንተው።

• ደርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በኦሮሚያ ክልል በ2016 ዓም የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል። መንግሥት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋትና ተደራሽ የማድረግ ሥራዎችን በተገባደደዉ የበጀት ዓመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሠራ ቆይቷል። ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓም ይላሉ ትናንት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሲሲራጭ የዋለው ዘገባ። የእኔ ጥያቄ የሚመጣው ቀጥሎ ነው።

"…እነዚህ በ2016 ዓም ብቻ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለምረቃ የተዘጋጁባት ኦሮሚያ በየትኛው የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችው ኦሮሚያ ናት። እንዲህ ለብቻዋ በጀቷ ሳይሰረቅ፣ በሌቦች ሳይበላ፣ የመላእክት ስብስብ ካልሆኑ በቀር ባልተለመደ ሁኔታ ለ21 ሺ ፈሪ የቀረው ፕሮጀክቶች ሠርተው የሚያጠናቅቁት ምን ዓይነት የተለዩ ፍጡራን ቢሆኑ ነው ? ይሄ መመርመር አለበት ባይ ነኝ።

"…በውኑ ይሄ የምናውቀውና ዓለሙ ሁሉ የመሰከረለት ሕገ ወጥነት የነገሠበት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የምድር ሲኦል የኦሮሚያ ክልል ነው ይሄን አስደማሚ የልማት እየፈጸመ ያለው? ሌሎቹ ክልሎች ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደሞዝ አጥተው በሰቀቀን እየኖሩ እንዴት ነው ኦሮሚያ ለብቻዋ ወጥታ እንደ ዱባይ ለመሆን አክት እያደረገች ያለችው? እንደ ሀገር የዩኒቨርስቲ መምህራን ኑሮ ከብዷቸው የማስተማር ሂደቱን አስተጓጉለው የባጃጅና የታክሲ ሹፍርና ሥራ እየሠሩ ባለበት ሀገር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ሀኪሞች ደሞዝ አጥተው ከሆስፒታል ሥራ ወጥተው የቀን ሥራ ለመሥራት በሚሯሯጡበት ሀገር የዚህ ሁሉ ቀውስ ጠማቂው ክልል እንዴት እንደ ጃፓን ለብቻው ተነጥሎ መበልፀጉን ለማወጅ ደፈረ?

"…ለእኔ እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ ማለት እንደ አንድ ኮንዲሚንየም ቤት ህንፃ ነው የማያት። በኮንዲምንየም ቤት ህንፃ ላይ ብዛቱ የታወቀ መኖሪያ ቤት ይገነባል። በእነዚያ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ደግሞ ሰዎች ይኖራሉ። ህንፃው የጋራ ህንፃ ነው። የህንፃው መሠረት አንድ ነው።  ምሰሶውም የሁሉንም በህንፃው ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ደግፎ የሚይዝ ነው። በህንፃው ላይ የሚኖሩት ነዋሪዎች በራሳቸው በተሰጣቸው የቤት ቁጥር ነው የሚኖሩት። ከቤት ቁጥር 001 እስከ ቤት ቁጥር 086 ድረስ ያሉት ቤቶች በኗሪዎቹ የተያዙ ናቸው። ሁሉም ነዋሪዎች በጤና፣ በደስታ በህንፃው ላይ መኖር የሚችሉት አጠቃላይ የህንፃው ነዋሪዎች በየቤታቸው በሰላም ሲኖሩ ብቻ ነው። በየቤቱ ቆሎም፣ ጎመንም፣ ቂጣም፣ ጮማም በልቶ ሊያድር ይችላል። ዋናው ግን ሰላሙ ነው።

"…በኮንዲሚንየም ህንጻ ላይ ነዋሪ ስትሆን የምትጠነቀቀው ለራስህ ሰላም ብለህ ነው። ፎቶ፣ ስዕል ለመስቀል በግድግዳህ ላይ የምትመታው ሚስማር የወዲያኛውን የግድግዳህን ተጋሪ ሊረብሸው ይችላል። እናም ማስፈቀድ፣ ማሳወቅ ግድ ይልሃል። ህንፃው ላይ የሰካራም ረብሻ፣ የባልና ሚስት ፀብ፣ የኀዘን፣ የደስታ ድምጾች ሁሉ ሌላውን አሳታፊ ናቸው። እሳት በአንዱ የቤት ቁጥር ቢነሣ ሁሉም ናቸው የሚረበሹት። የሚታወኩት። አንዱ ቤት የተነሣው እሳት ህንፃውን ሙሉውን ነው የሚያወድመው። የሚያቃጥለው። እነ እንቶኔ ቤት የተነሣው እሳት እኔ ጥግ ላይ፣ ዳር ላይ ስላለሁ አይነካኝም አይባልም። እሳቱንም የምታጠፋው በጋራ ተረባርበህ ነው። ሰዎቹን ልትወዳቸውም፣ ልትጠላቸውም ትችላለህ። እሱ ለደንታህ ነው። ነገር ግን እሳቱን ለራስህ ስትል ዋጋ ከፍለህ ታጠፋለህ። ለማጥፋት ትረባረባለህ።

"…አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ግን ተአምረኛ ኢትዮጵያ ናት። መሃንዲሶቿ በሀገረ እንግሊዝ ለንደን ላይ ነው ዲዛይኗን የቀየሱት። ለኦሮሞ ብቻ የምትመች ኢትዮጵያን እንሠራለን ብለው ነው የወሰኑት። ቤድሩሟን፣ ሳሎኗን፣ ኩሽናዋን ሁሉ በምንፈልገው መልኩ ነው የምንሠራውና የምንገነባው ብለው ነው የወሰኑት። በውሳኔአቸው መሠረት ደግሞ ኦሮሚያ እንድትለማ፣ ኦሮሚያን ዲሞክራሲያዊት ለማደርገ ኢትዮጵያን መሰባበር፣ ማፈራረስ ያስፈልጋል ነበር ያሉት። የሞተች፣ የታመመች፣ የደከመች፣ የፈራረሰች ኢትዮጵያ ላይ ነው ኦሮሚያን የምንገነባው ነበር ያሉት። ኢትዮጵያ ካልወደመች፣ ካልፈረሰች ኦሮሚያን ኢንሌሊስቱ፣ በዻዺኒ ኢንጂሩ ነበር ያሉት። እናም እየሆነ ያለው እንደዚያ ነው።

"…ትግራይ እስክትለማ ኢትዮጵያ ትድማ ብሎ በመፈክር ኢትዮጵያን አደህይቶ፣ ግጦ፣ እልብ አድርጎ በአጽሟ ያስቀራት የትግራዩ ጁንታ ብዙ እጁን የጁንታው መሪዎች ሲማግጡበት፣ ሲምነሸነሹበት ከርመው፣ ፋብሪካም፣ መንገድም፣ መሠረተ ልማትም ሲዘረጉ ከርመው፣ ሌላውን ክልል እና ነገድ ፀረ ልማት፣ ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ እድገት፣ አሸባሪ፣ ፅንፈኛ፣ ጠባብ፣ የግብፅ ተላላኪ፣ የሻአቢያ ቅጥረኛ፣ የአልሸባብ ፈረስ ሲሉ ከርመው፣ እኛ ወርቅ ሕዝቦች ነን። እኛን መግፋት ግድግዳ እንደመግፋት ነው ሲሉ ከርው፣ ለጥጋባቸው ለከት ማበጀት አቅቷቸው፣ የሚያደርጉት የሚሠሩት አሳጥቷቸው ቅብጥብጥ ብለው። ሌላውን ክልል አደንቁረው፣ አተራምሰው ለጊዜው እነሱ የሰላም ምልክት፣ ሰላማውያን ሕዝቦች፣ ሰው የማይታገትበት፣ ሴቶች የሚደፈሩበት ግን ዋጥ፣ ጭጭ ብለው የሚኖሩበት፣ ነዳጅ እንዳወጣ ሀገር በሸነና በበሸነና የሆኑበትን ሥርዓት ፈጥረው ነበር። ኮንዲሚንየሙ ታውኮ፣ ተረብሾ ነገር ግን የኮንዲሚንየሙ ነዋሪና የቤት ቁጥር 001 ነዋሪዎች እየሳቁ፣ እየፈነጠዙ፣ በሌሎች እየቀለዱ ይኖሩ ነበር። ሽንቴ ሚሪንዳ ነው የሚሉ እንጀራ በወርቅ ካልበላን የሚሉ ሁላ ነበሩ። ዛሬስ የቤት ቁጥር 001 ነዋሪዎች በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? መልሱን ለእናንተው።

"…አሁን ተረኛውን የቤት ቁጥር 004 ነዋሪዎችን እንመልከት። አየሩንም፣ ምድሩንም፣ ባንኩንም ታንኩንም ተረክበው ሳለ ተቃዋሚም ሳይኖርባቸው የኮንዲሚንየሙን ሰላም ጠብቀው አስጠብቀው በሰላም ማስተዳደርም አብሮ መኖርም ሲችሉ እነሱም ከቤት ቁጥር 001 ነዋሪዎች አወዳደቅ ትምህርት መውሰድ አቅቷቸው የሌለ አፈሉ። 001 ኦች ያደርጉ የነበረውን በእጥፍ፣ በዘግናኝ ሁኔታ መፈጸም ጀመሩ። ይሉኝታ፣ ሼም የሚባል ነገር የማያውቁ፣ ጨካኞች፣ አረመኔዎች ሆኑ። ፅንስ አርደው የሚበሉ ጨካኞች። አንገት ወግተው ደም የሚጠጡ ቫንፓየሮች፣ ዘራፊ፣ ገፋፊዎች ሆኑ። እህልና ከብት የሚያወድሞ፣ የሚያቃጥሉ፣ ሼክና ቄስ የሚያርዱ፣ ቤተ ክርስቲያን እና መስጊድ የሚንዱ፣ የአይሁድ እና የአረብ ስም በዝቷል ብለው በሜንጫ የሚቀንሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርዓን የሚያቃጥሉ፣ ለሀገር፣ ለእሴት፣ ለታሪክ፣ ለባህል ደንታ የሌላቸው ሆነው አረፉት። በዚሁ መሠረት ለንደን ላይ በወሰኑት ውሳኔ መሠረት ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ኢትዮጵያን አፈራርሰው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ኦሮሚያ የምትባል ገነት የሆነች ምድር ለመመሥረት ደፋ ቀና ይሉ ይዘዋል።

"…አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የኦሮሙማ መንግሥት መጀመሪያ ሥልጣን ላይ ሲወጣ ማረድ፣ መፍጀት የጀመረው ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ከሀረርጌ ምድር ላይ ነው። ሶማሌ ክልል የሚኖሩ ዐማሮች እና ኦርቶዶክሳውያን የቤት ቁጥር 003 ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ፣ በማረድ ነበር እነሱን በመሰዋት ኢትዮጵያን ማፈራረስ ሀ ብሎ የተጀመረው። ከዚያ በኋላ ያለውን እናንተ ቁጠሩት። ቤንሻንጉል፣ መተከል፣ አዲስ አበባ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ሙሉ ኦሮሚያ፣ ጌዲኦ፣ ሀረር፣ ድሬደዋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ወለጋ፣ ኧረ ሥንቱ ተጠርቶ፣ ይዘለቃል። እነ ሲዳማ ሳይቀሩ ኦርቶዶክስ፣ ጉራጌና ዐማራን አረዱ፣ ለኢየሱስ አየዘመሩ ካህናትን በቤንዚን አቃጥለው ደፉ፣ ገደሉ።👇ከታች ይቀጥላል✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ክፉ ለማድረግ የሚያስብ ተንኰለኛ ይባላል።” ምሳ 24፥8

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel