zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ለዚህ ሁሉ ጦስ የዳረገችንን ሂዊን ከዚህም በላይ አለ የተባለ ምር በላውን ሁሉ ፈጣሪ ያውርድባት። አይደለም መከፋፈል ለምን አስር ትንንሽ አትሆንም። እህዕ እና እኔ ምን አገባኝ… 😂

• ከምር እውነቴን እኮ ነው ያገባናል እንዴ? ይመለከተናልስ ወይ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…18 ሺ ሰው አንብቦት 29 ሰዎች 😡 ብው ያሉበት የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ መነበቡን የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት ያመለክታል። ከንባብ ቀጥሎ የጎደለ ካለ የሚሞላበት፣ የበዛ ካለም የሚቀነስበት፣ በጨዋ ደንብ እናንተ ደግሞ የምትተነፍሱበት መርሀ ግብር ነው የሚከተለው። ለመተንፐስ ተዘጋጁ።

"…እኔ እንደሌሎቹ እንደነ ዳንኤል ክብረት ራሴ ተናግሬ ሌላው እንዳይናገር በር አልቆልፍም። እኔ ዲሞክራት ነኝ። ያለ ፀያፍ ስድብ ሓሳባችሁን፣ ተቃውሞአችሁን መስጠት ትችላላችሁ።

ሁለት ማስታወሻ፦

፩ኛ፦ ዘወትር ሐሙስ እኔና ቀሲስ ሳሚ በጋራ የምናቀርባት ተወዳጇ የዕለተ ሐሙስ መርሀ ግብራችን ቀሲስን አስፈቅጄ ለዛሬ እረፍት ስለተሰጠኝ አንመጣም ማለት ነው።

፪ኛ፦ በእነ ናሁሰናይ ጉዳይ ላይ የጀመርኩትን ጥያቄ ለጊዜው መብረቁን ብልጭ አድርጌ ያዝ አደርገዋለሁ። በተለይ የመከታው ዕዝ ነብር አየኝ ይበል።

"…በተረፈ ሁላችሁም ተንፍሱ፣ በጨዋ ደንብ ተወያዩ። ነገር ግን ከርዕሰ አንቀጹ ውጪ ለማስቀየስ የምትመጣ ካለህ፣ ዘመዴን አትከተሉት፣ አትስሙት ብለህ በገጼ ላይ አንተ ልትቀመጥ አልፈቅድልህም። አይረባም ዘመዴ ብለህ እየነገርከኝ ምንአባክ እንድታደርግ አስቀምጥህሃለሁ። ለቀልድ ብለህ በንዴት ቦልከኝ ብለህ ስትጽፍም ፍላጎትህን ሳሟላልህ ሰከንድ አልጠብቅም። አንተ ንቁ፣ ሊቅ ሆነህ አድማጭ ተከታታይ አንባቢዎቼን በመንጋ ስትሳደብ ምህረት የለኝም። እቀስፍህሃለሁ። ሁለት እድል ነው ያለህ በጨዋ ደንብ መወያየት፣ አልያም ጮጋ ብሎ እያረሩ ከዳር ቆሞ መንገብገብ። ይኸው ነው።

"…1…2…3…በሹገር ዳዲው ርዕሰ አንቀጼ ላይ ሓሳብ መስጠት ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ጫካ ወይም ደን የምንለው የዛፎች ስብስብ ነው። ሰዎች ዛፍን መቁረጥ፣ ደንን መመንጠር ሲፈልጉ ለመቁረጥ ከዛፎች ሁሉ ጠማማውን ዛፍ መርጠው ያን ጠማማ ዛፍ የመጥረቢያ እጀታ ያደርጉትና የምሳር ወይም የመጥረቢያ እጀታ ይሆናል። በላዩ ላይ ስለት ይገጠምለትና ስለቱም ከመጥረቢያው ላይ እንዳይወድ በምስማር ወይም በእንጨት ይጠባብቅና ከዚያ ጓዶቹን ትንሽ ትልቅ ሳይል የገዛ ወገኖቹን እየቆረጠ ይኖራል። ያ ወገን ቆራጭ በመሆን ሲያገለግል የከረመው መጥረቢያ ማርጀቱ አይቀርምና ሲያረጅ ከሰው ከቆራጩ ትከሻ ላይ ወርዶ ስለቱም ወጥቶ እጀታው ወደ እሳት ወደ ምድጃ ይወረወራል፣ ይከስላል፣ አመድም ይሆናል። ባንዳም ልክ እንደ እጀታው እንደመጥረቢያው እንጨት ያለ ነው። በመጨረሻም የጊዜ ጉዳይ እንጂ የእጁን ያገኛል።

"…የዐማራ ቦለጢቃ አሁን ጠማማ ሓሳብ ባላቸው የራሳቸው ዘሮች በሆኑ ጥቂት ባንዳዎች በመሞላቱ ለጊዜው ገጭ ገርገጭ የሚል ይመስላል። የዐማራ መቁረጫ መጥረቢያ ሆነው የሚያገለግሉት ደግሞ ዶላር የተባለ ማጥበቂያ ተገጥሞላቸው የሚንቀሳቀሱ እጀታዎች ናቸው። ምሳሩን ማጥበቂያ ዶላር የተባለው ሽብልቅም መውለቁ አይቀርም። ወልቋልም። እናም ያነዜ እጀታ ሆነው ይንቀሳቀሱ የነበሩ መጥረቢያዎች በሙሉ ያረጃሉ፣ ያርጣሉ። ወደ እሳትም ይጣላሉ።

"…የትኛውም እንቅስቃሴ ያለ ገንዘብ አይሆንም። ገንዘብ አስፈላጊ ነገር ነው። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ትርጉሙ በሮጲላ ስለመሄድ አይደለም። በሂሊኮፍተር፣ በመንኮራኩር፣ በጀት ስለመብረር አይደለም። በሰማይ መንገድ አለ ማለት ገንዘብ ያለው ገንዘቡን ከመጸወተ፣ ድሆችን ከረዳ፣ አሥራት በኩራቱን ካወጣ ይጸድቃል፣ ገነት መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው። ገንጸብ በአግባቡ ከተጠቀሙበት የጽድቅ መንገድ ይሆናል ማለት ነው። ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሥር የሚሆንበትም አግባብ እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

"…ገንዘብ ከሠሩበት እንደሚያጸድቅ ሁሉ ገንዘብ በተቃራኒው ለሲኦልም ይዳርጋል። መኖሪያህን ገሀነመ እሳት ሊያደርግብህ ይችላል። በገንዘባችን ዝሙት ሥንሠራ የሚጠብቀን ገሀነመ እሳት ነው። ገንዘብ ስላላቸው ብቻ ገንዘብ አጥተው የተቸገሩ ነፍሳትን እየደለሉ የሚያነውሩ፣ በዝሙት የሚያረክሱ ሹገር ዳዲዎች፣ ጀነራል ኮሎኔሎች፣ ኢንቨስተር ዳያስጶራዎች፣ ባለ ሥልጣናት ወዘተ ገንዘብ ስላላቸው ብቻ የስንቱን ሕይወት አጨለሙ። ስንቱን ለበሽታ፣ ላላስፈላጊ እርግዝና ዳረጉ። ስንቱን ሕይወት ኑሮውን በጠበጡ። አዎ ገንዘብ ያጸድቃል ሲዖልም ያገባል።

"…ገንዘብን እንደ መስኖ ውኃ የሚጠቀሙበት አሉ። ልማት ላይ የሚያውሉ። ገንዘቡን በጤናማ መስመር ካመጡ በኋላ ሹገር ዳዲም፣ ሹገር ማሚም ሳይሆኑ፣ ለፍትወታቸው ማርኪያ ብልት የሚከራዩ፣ የሚሸምቱ ሳይሆን ገንዘቡን እንደ መስኖ ውኃ ቦይ እየከፈቱለት አንዴ ሕንጻ፣ ፋብሪካ፣ እርሻ፣ ሱቅ፣ ዳቦቤት፣ ትራንስፖርት፣ ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት ወዘተ ላይ እያዋሉት በበጎ ሥራ ስማቸው ሲታወስ፣ ሲወደስ የሚኖሩ አሉ። ገንዘብ ያጸድቃል ያስኮንናልም። ዋናው አጠቃቀሙ ነው።

"…ለዐማራ ፋኖ ትግል ገንዘብም ወሳኝ ነው። ገንዘቡ የሚመጣው ደግሞ ጥቂት ከሀገር ውስጥ፣ ብዙው ከሀገር ውጪ ነው። ትግሉ ከጀመረ ገና አንድ ዓመቱ ስለሆነ እስከአሁን ገንዘብ ይረዳ የነበረው በጎጥ፣ በሰፈር፣ በትውውቅ ነበር። ይሄ ደግሞ አድካሚም ውጤታማም አይደለም። አይሆንምም።  ከዚያ ይልቅ እንደ ዐማራ አንድ ግዙፍ ተቋም ቢቋቋም እና በዚያ ተቋም በኩል ቢረዳ የተሻለም ይሆን ነበር። በዚያ መንገድም ተሞክሮ ብዙም አላዋጣም። አላስኬደምም። ተግዳሮቶቹም በዙ። ሕዝብ በሰበሰበው ገንዘብ ፋኖ የሚገዛ ኮሚቴ ተገኘ። ጉድ እኮ ነው።

"…ከሁሉም የተሻለው የገንዘብ አሰባሰብ ስልት ግንባሩ ተብሎ በእስክንድር መሪነት የመጣው ድርጅት ነበር። ግንባሩ የተባለው የእስክንድር ድርጅት እንደ ጥላ ሆኖ ገንዘብ በማሰባሰብ ለሁኑም የፋኖ አደረጃጀቶች ገንዘብ እንዲደርሳቸው የሚል ነበር እሳቤው። ለዚህም ነው የሁሉም ክፍለ ሀገራት ፋኖዎች ፎቶ ተለጥፎ ሚልዮን ዶላሩ በሦስት በአራት ቀን የተሰበሰበው። ሕዝቡ ገንዘቡን ሲሰጥ። እስክንድር የተገነባለትን ስም አምኖ፣ በትክክልም ገንዘቡን ለሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ይደርሳቸዋል በሚል እምነት ነው። በ4 ወር እስከ 20 ሚልየን ዶላር ሊሰበስብ የተነሣው ኮሚቴም በእስክንድር በጥባጭነት፣ በግንቦቴዎች ስግብግብነት በአጭሩ ተቀጨ።

"…እስክንድር ለሁሉም ፋኖዎች የተሰበሰበውን ገንዘብ ጠማማ ሓሳብ ይዞ መጥቶ ገንዘቡን ፋኖ መግዣ አደረገው። የራሱን ድርጅት መሥርቶ መንቀሳቀስ ጀመረ። በአጭሩ እስክንድር የዐማራ ፋኖ ሹገር ዳዲ ሆኖ ተከሰተ። የቸገራቸው፣ ገንዘብ ያጠራቸው ፋኖዎች ነውር፣ ኃጢአት መሆኑን ቢያውቁም ዶላር በእጁ ላይ ላለው ሽማግሌ፣ ሹገር ዳዲው እስክንድር ቅድስናቸውን አርክሰው ተኙለት። ገበሩለት። ልክ በከተማ ያሉ የቸገራቸው ምስኪን የደሀ ልጆች ለቆርማዳ፣ ለአረጀ፣ ለሼባ ክብራቸውን ለችግራቸው መሸፈኛ ሲሉ እንደሚሸጡት ብዙ የፋኖ አደረጃጀቶችም የተለመነ ዶላር እና  ገንዘብ ላለው ለእስክንድር ገበሩለት፣ ተገዙለት። ገንዘብ ይናገራል፣ ያናግራልም አይደል?

"…በልመና ለመጣው ለሹገር ዳዲው እስክንድር ዶላር ክብራችንን አንሰጥም። አንተኛለትም። አንገረድለትም ያሉም ቅድስናቸውን የጠበቁ ጀግኖችም ነበሩ። ለምሳሌ እንደ ጀግናው ሜጀር ጄነራል ውብአንተ አይነት የጎንደር ዐማራ በሻለቃ ዳዊት ስብከት፣ በሀብታሙ አያሌው ዛቻ፣ በእስክንድር ነጋ ማስፈራራት ከአቋሙ ዝንፍ ሊል አልወደደም። አልፈለገምም። ለሹገር ዳዲ የሚያስተኛኝ ስብዕና የለኝም። ገንዘብ፣ ሀብቱን እንደሆን ትቼው ነው የወጣሁት። እኔን በገንዘብ መግዛት አይሞከርም። አይቻልም ብሎ ነበር እስከመጨረሻው ህቅታው ድረስ እነ ሀብታሙንና እነ እስክንድርን ሞግቶ ያለፈው። እነ ጋሽ መሳፍንት ተስፉ፣ እነ ሀብቴ በሚዲያ ስሙን አጥፍተው አካልበው ሲሞት ከነ ክብሩ ነው ያረፈው።

"…በሸዋም፣ በወሎም፣ በጎጃምም ሹገር ዳዲው እስክንድር እኛው በለመነውና ባሰባሰብነው ገንዘብ ሊያነውራቸው የሚችላቸውን ነውረኞች ሲሸምት ነው የኖረው። ያውም ባህታዊ፣ ቄስ መነኩሴ መስሎ። ጿሚ ጸሎተኛ፣ ጥሬ ቆርጣሚ፣ መሬት የሚተኛ መስሎ። መቅጠኑን እንደ መንፈሳዊ ፅናት እንዲቆጥሩለት ራሱን ሽጦ ተለሳልሶ ነው በልመና ገንዘብ ሹገር ዳዲ ሆኖ የሚተኛቸውን፣ የሚያቆሽሽ የሚያዛቸውን ምስኪን ድሆችን የሸመተው። እናም የዐማራን ትግል በገንዘብ ገዝቶ ሊያዘገየው የሞከረው። አሁን ግን ሁሉም በመንቃቱ፣ የልመናው ገንዘብም በመመናመኑ በጨበራ ምርጫ ወደ አዲስ አበባ በድርድር ስም ለመሻገር ያደረገው ሸፍጥም በዐማራ ንቃተ ሕሊና ከፍ ማለት የተነሣ ከሸፈ። አከተመ።

"…አሁን በጎጃም ምን እየሆነ ነው። በጎጃም ሹገር ዳዲው በገንዘብ የገዛው ምስኪኑ ኮሎኔል ጌታሁን በራሳቸው በጎጃሜዎቹ እጅህን ስጥ ተብሏል። ለኮሎኔል የተሰጠው 2 ሚልዮን ብር አትሞላም። ሁለት ሚልዮን ብር ማለት አንድ የኦሮሞ አርቲስት ለአንድ ቀን አዳር ተጫርቶ ሴተኛ አዳሪ በአዲስ አበባ የሚሸምትበት ብር ማለት ነው። ኮሎኔሉ በዚህ ብር ነው ሹገር ዳዲው እስክንድር የገዛው። ሀብታሙ አያሌውና ብሩክ ይባስ የሹገር ዳዲው ደላሎች ናቸው። ሹገር ዳዲው እስክንድር ሊተኛቸው፣ ሊያረክሳቸው የሚፈልጋቸውን የወሎ፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋ ጋለሞቶችን እና የቸገራቸው ምስኪኖችን በሚዲያ ጭምር የሚደልሉ ደላሎች ናቸው። ግን ይዋረዳሉ። በተለይ ብሩክ ይባስ👇 ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ስለ ሹገር ዳዲ የሆነች አጠር ብላ ረዘም ያለች፣ ቀጠን ብላ ወፈር ያለች ትንሽዬ ርዕሰ አንቀጽ እያዘጋጀሁላች ስለሆነ ነው የጠፋሁት። ተፍተፍ እያልኩ ነው። ጠብቁኝ እሺ… ማጣሎ። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለነገ…

"…እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና የነገ ሰው ቢለን ስለ ናሁሰናይ እና አቤኔሬር አሟሟት መሸፋፈኑን ትተን ደፈር ብለን መነጋገር እና መጠየቅ ብንጀምርስ ብዬ አስባለሁ። አንዳንድ ጥያቄዎችን ባነሣና አብረን ብንጠይቅስ ምን ይላችኋል?

• በዚህ ጉዳይ ደግሞ የኢትዮ 360 ዎቹ አክተሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና ወሮ ጄሪም የምታውቁት ነገር ካለ ጀባ ብትሉን መልካም ነው። እኔ የሚያሳዝነኝ ብሩኬ ብቻ ነው። ብሩክ ይባስ ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ሆኖበት እንጂ ወደፊት የሚመጣበትን ጣጣ አላወቀም። ብሩኬ ምንም ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ።

"…የሸዋ ጠቅላይ ግዛቱ ዕዝ የፋኖ መከታው ቡድን ማለት ነው እነ አበበ ጢሞና እነ ኢሳያስም በእነ ናሁ አሟሟት ላይ የምታውቁትን ብትነግሩን መልካም ነው። ጎንደሬዎቹ ሞተው የእናንተ ልጅ እና ኢየሩሳሌም መኪና እያሽከረከሩ ይፋት የገቡት ምን አይነት አክተር ቢሆኑ ነው? ሁለቱን አስገድለህ ስታበቃ አንተን ካስመለጠችህ ከዐማራ ክልል ጋዜጠኛዋ ኢየሩሳሌም መኮንን ጋር በሚዳ ኦሮሞ ተደብቀህ ያለኸው ፀረ ዐማራው ስኳድ ፋኖ ታምራት ይርጋም ብቅ በልና ተንፍስ። እንግዲህ ነገሩ በደንብ ይጥራ ከተባለም ፋኖ ሀብቴ ወልዴም አስተያየት ካለው ጠይቁት።

"…የናሁ እና የአቤኔዘር ደማቸው እንዲህ በከንቱ ፈስሶ ደመ ከልብ ሆነውማ አይቀሩም። የእነ መከታው ቡድን ግን ፈጣሪ ገና በምድር ሲኦላቸውን ያሳያቸዋል ጠብቀጀ። በሉ ወጣ ወጣ ብላችሁ ተናገሩ። ተንፒሱ አልኳችሁ።

~ የነገ ሰው ይበለን…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይሄም የኮሪደር ልማቱ ውጤት ነው ተብያለሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዲስ አበባ…

"…አርበኛ ፋኖ እነ ናሁሰናይ አንዳርጌ በተሰዉ ወቅት በሟቾቹ ላይ ሲሳለቅ የነበረው የፖሊስ  አዛዥ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ፍየል ቤት በሚባለው አካባቢ ብላክ  ጭፈራ ቤት ውስጥ "ደም በደም ይጠራል በሚለው ሕግ መሠረት" ፎሊስ አዛዡ ከእነ አጃቢዎቹ በአዲስ አበባ በቆንጆዎች እስከወዲያኛው መሸኘቱን ከሸገር የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

“…ክፉ ሰው እጅ በእጅ ሳይቀጣ አይቀርም፤ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።” ምሳ 11፥21

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ፊት… … ፋኖ… 💪🏿

• ኋላ… ብልጽግና…💀

• ድል ለዐማራ ፋኖ…✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1ኛ ቆሮ 5፥13 “…እነሆ። ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ አድርጌሃለሁ አለኝ።” ኤር 1፥10

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ያፈረስኩትን የጠላትን ሴራ የቀብር ሥነ ሥርዓት እፈጽም ዘንድ ዛሬ ምሽት 3:30 ላይ በመረጃ ቲቪ ነጭ ነጯን እነግራችሁ ዘንድ ከተፍ ብዬ እመጣለሁ። በሴራ የተሞላውንና በዐማራ ጠላቶች ዘንድ ጮቤ ያስረገጠውን በ6 ዓመት ውስጥ አምስተኛውን ሳይወለድ የሞተውን የእስክንድር ነጋን ፀረ ዐማራዊ ጭምብልም እንገላልጠዋለን።

• አርበኛ ጋሽ አሰግድን በተመለከተም እንነጋገራለን።

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia

•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 YouTube: https://youtu.be/ippclXNonM4

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዘመድኩን ነቀለ ማለት…😂

“…እነሆ። ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ አድርጌሃለሁ አለኝ።” ኤር 1፥10

• አሜን ነው…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጹን 25ሺ ሰው አንብቦት 25 ግለሰቦች እንደተበሳጩብኝ 😡 ብው ብለው እንደተናደዱብኝ የቴሌግራም ካምፓኒ ሪፖርት ያመለክታል። ብው ባዮቹ ከዚህም በላይ ሊበዙ እንደሚችሉ ሪፖርቱ ያመለክታል። ከ25 ሺ ሰው 25 ሰው ከበሰጨብኝ እጅግ አትራፊ፣ እጅግም ስኬታማ ነኝ ማለት ነው።

"…ዛሬ ማታ ደግሞ በመረጃ ቲቪና በቲክቶክ ገጼ ሌላ አስደማሚ ጉድ አሳያችኋለሁ። አርበኛ አሰግድ መኮንን እንዴት እንደተያዘም የተገኘውን መረጃ አሳያችኋለሁ። ወንበዴው የእነ መከታውና የእነ ፋኖ ድርሳንን፣ የፋኖ የቁማር ድርጅት ባለቤቱን የግርማ የሺጥላ ሚዜ፣ እስክንድርን ጎትቶ ይፋት የከተተው የእነ ፋኖ አበባው ሰሎሞንን ሌብነት እና ጉድ፣ የእነ ዳንኤል መንፈስን፣ ወንድሙ የደኅንነት መሥሪያቤት ሓላፊ የመከታው ቁልፍ የደኅንነት ሓላፊውን የኢሳያስን፣ የሸዋው ዕርቅ እንዳይሳካ ያደረገውን የመከታው ቀኝ እጅ የፓስተር ዮናስን ጉድ እዘረግፈዋለሁ። የሸዋው ሽምግልና እንዴትና በማን ፈረሰ? የመናገሪያ ጊዜው አሁን ነው። የአቢይ አህመድ የመከታው ቢሮ ወኪል የፋኖ የፓስተር ዮናስን ፎቶ ያላችሁ ወዳጆች ካላችሁ ላኩልኝማ።

"…ዛሬም የዋንጫ ጨዋታ ነው። ያለመረጃና ያለማስረጃ ትንፍሽ አልላትም። በፔጄ ላይ መሳደብ ክልክል ነው። እኔ የዐማራ ጠላቶችን እበትን፣ አበሳጭ፣ ጭራና ቀንድ አስበቅል፣ ጨጓራና ጣፊያ አቃጥል ዘንድ የተላኩ የዳዊት ጠጠር ነኝ። ዐማራ ተቀበለኝ አልተቀበለኝ ለደንታው ነው። እኔ የቆምኩት ከእውነት ጋር ነው። የብልፄንም፣ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱንም ሴራ ብጥስጥሱን ነው የማወጣው።

• ስሜ ማነው…?

~ አፍራሽ…😂

• በሉ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና ሴራው ፈረሰ፣ ተሰበረም፣ እንኩትኩትም አለ በሉት።😁

… በሥነ ሥርዓት ነቃ፣ ቀና፣ ቆፍጠን ብላችሁ አስተያየታችሁን መጻፍ ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር ጠዋት ጠዋት ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ከሞላ በኋላ በቲጂ መንደር ቤተሰቦቼ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ መርሀ ግብር አለ። የዚህን መርሀ ግብር ስም ጥቀስ።

• ✍✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከመኝታ በፊት…

• አንተ ማነህ…?
• አንቺስ ማነሽ…?

• ቀና በል… ነቃ ነቃ… አንተ ማነህ…? ጻፈው። ድብልቅልቁን ዐውጣው። አንተ ማነህ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!” መክ 10፥16

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አመቻች ኮሚቴው በደቡብ ወሎ…

"…በቀይ ያከበብኩበት በመስፍን ስም የገባው፣ ማርሸት ፀሐዩ ሰብሳቢው ሲባረር በምትኩ በምክትል ሰብሳቢነት የተሾመ ሰው ነው። ኮሎኔል ፋንታሁን ደግሞ የሕዝባዊ ሠራዊቱ ደጋፊ፣ የእስክንድር ነጋ አፍቃሪ፣ የሀብታሙ አያሌው ታዛዥ ናቸው።

"…አንድ የጋራ ወዳጃችን ደውሎ ስለነበረው ሁኔታ ሲጠይቃቸው ኮሎኔሉ እንዲህ አሉት። "በምርጫው ላይ አልነበርኩም ነገር ግን እስክንድር በመመረጡ ችግር የለብኝም። እኔም ኮሎኔሉን አልኳቸው "እርስዎ ሃይማኖት አልዎት፣ በአላህ ያምናሉ፣ ያልተደረገን ምርጫ ተደርጓል ሲሉ አይቀሉም ወይ? እድሜዎትስ እንዴት ነው የፈቀደልዎት። ከእንግዲህስ ማን ያምንዎታል?

"…ጎጃም2፣ ጎንደር 1፣ ወሎ1፣ ሸዋ1፣ አጠቃላይ 5 ድምጽ ውድድሩን አቋርጦ ወጣ። ከጎንደር ሀብቴ፣ 1፣ ከወሎ ኮሎኔል ሙሀባው 1፣ ከሸዋ መከታው 1 ድምጽ ለእስክንድር ከሰጡ ውድድሩ ሳይደረግ እኮ እስክንድር በዝረራ ተሸንፏል። ሀብታሙ አያሌው እንደ ወርቅና ገበዮ እና አባዱላ ገመዳ ቁጥር ላይ ኔፓ ነው እንዴ?

"…ለማንኛውም ስብሰባው ይሄን ይመስል ነበር። ለኔትወርኩ ጥራት ምስጋና ለፍርዬ … እኔም ጀርመን ሆኜ በዚህ መሠረት ነው የተሳተፍኩት።

• መቀለድ፣ ማጭበርበር፣ ድሮ ቀረ። አሁን ወፍ ኤለም።

"…እስክንድር ነጋና ሀብታሙ አያሌው ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ፣ ሀብቴ ወልዴና መከታው ማሞ ድፍን ዐማራን አጭበርብረዋል። ዋሽተዋል። ቀጥፈዋል። በአስቸኳይ ይቅርታ ጠይቁ። ጨበርበርቱ ሁላ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …እየተሸማቀቀ
በሆነ አስገዳጅ ምክንያት ለሀብታሙ አያሌው ልክ እንደ ኢየሩስ መገረዱ በጣም ይበሰጨኛል። ስለ ብሩክ ይባስ ስጽፍ ትንፋሼ እየተቆራረጠ፣ እጄ እየተንቀጠቀጠ ነው የምጽፈው። ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ ሆኖብኝ ተቸገርኩ። ምንም ማድረግ አልችልም።

"…በሹገር ዳዲ እስክንድር ሌብነት፣ ከፋፋይነት ምክንያት ዳያስጶራው አሁን ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት መላክ ቀጥ በሚባል መልኩ አቁሟል። የዐማራ ፋኖዎች ሌላ አማራጭ በማየት በመንቀሳቀስም ላይ ይገኛሉ። ጠንካራ የሚባሉ የፋኖን እንቅስቃሴ የሚረዱ በሸዋ የመከታው፣ በጎጃም የእነ ዘመነን የሚረዱ እንዳሉ መረጃው ነበረኝ። የጎጃሞቹ ከምን እንደደረሱ ባላውቅም የሸዋዎቹ ግን የመከታው ማሞ ከሹገር ዳዲው እስክንድር ነጋ ጋር መጣበቅ በስጭቷቸው፣ ለምነው አስለምነው፣ ተለይ ከዚህ ሰው ብለው መክረው አስመክረው ያልተቋረጠ የገንዘብ ድጋፍ ያደርግለት የነበረው የሸዋው የዳያስጶራ ረጂ ቡድን ለመከታው ለራሱ ሹገር ዳዲህ ይርዳህ በማለት ግኑኝነታቸውን አቋርጠው አሁን ባዶ እጁን እንዲቀር አድርገው ምንጩን ቆልፈው ደፍነውበታል። የመከታው ሠራዊት አሁን ጭንቅ ውስጥ ነው ያለው። መከታውም ሠራዊቱ ለሚያነሣበት ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻለም። እንዲያውም የመከታው ዘር ይጣራልን ማለት የጀመሩም አሉ። አያቱ ከኦሮሞ ስም ጋር ይገናኛል እና ይጣራልን ማለት ጀምረዋል። መከታውም ከእስክንድር ጋር እስከሞት አንለያይምን እየዘፈነ መሆኑም ተሰምቷል። በሌላ በኩል እኔ ዘመዴ ዘመድኩን ነቀለ ነቃዩ፣ መዶሻ አፍራሹ የሕዝባዊ ሠራዊቱን የገንዘብ ምንጭ በመብረቅ ስለመታሁት ሹገር ዳዲ እስክንድርም ቤሳቤስቲን ሊረዳቸው አልቻለም። ኤትአባክ።

"…ወደ መፍትሔው ስመጣ…

"…በሹገር ዳዲ እስክንድር ምክንያት የተፈጸመውን ክህደት፣ በእነ አበበ በለው ምክንያት የፈረሰውን እምነት፣ በሀብታሙ አያሌው፣ በኢየሩሳሌም ምክንያት የተፈጠረውን ነውር ላለማየት፣ ለለመስማት ወስነን እንዴት የፋኖዎችን ችግር ለመቅረፍ እንንቀሳቀስ በሚለው ላይ ብንመክር መልካም ነው። ሁለት ሚልዮን ዶላሩን እንደ ኪሳራ ሳይሆን ቢያንስ ትምህርት እንደተወሰደበት ቆጥረን (የሁለት ሚልዮን ዶላር ትምህርት ይታያችሁ) አሁን እንዴት ለፋኖዎቹ እንድረስ የሚለውን መንገድ እንመልከት። በተለይ አሁንም እነ ኮሎኔል ፋንታሁን ወደ አንዳንድ የወሎ ፋኖዎች በመደወል አንዳርጋቸው ጽጌ ይረዳናል፣ የግል ሬድዮ፣ የሳታላይት ስልክ፣ ዲሽቃና መትረየስ እንሰጣችኋለን፣ ሬሽንም አለን፣ ጥይትም አለን። ከእኛ ጋር ስሩ። ለእስክንድር ገብሩ የሚሉትን ለማስቆም ፋኖዎቹን መርዳት ያስፈልጋል።

"…ለመከታው 60 እና 70 ሚልዮን ዶላር ይልክ የነበረው ጠንቀካራው የሸዋ ቡድንም የሸዋ ዕዝ ተጠናክሮ ከወጣ ፊታቸውን ወደዚያው ማዞራቸው አይቀርም። አሁን ትግሉ እየጠራ ነው። ልፋታችንን እግዚአብሔር አየቆጠረልን ነው። መከታው ማሞ የሚመራው ፋኖ ላይ ከፍተኛ የሆነ መተራመስ ተፈጥሯል። እኛን ሳታማክር ሸጥከን የሚለው ሰራዊት ቁጣውን በአደባባይ መግለጽ ጀምረዋል። ከአሁን በኋላ እስከንድር የሚባል ሹገር ዳዲ ሰው በአደረጃጀታችን ውስጥ ማየት አንፈልግም ብለው በግልጽ ጥያቄ አቅርበዋል። እኛ እንዲመራን የምንፈልገው ዘሩ በአራቱም ዐማራ የሆነ ዐማራ ብቻ ነው። አስክንድ የብሔር ተዋፆ እያለን ስለሆነ ከኛ ድርጅት ላይ በአስቸኳይ ለቅቆ ይሂድልን። ፋንታሁን ሙሀቤ ወሎ፣ ሀብቴና ጋሽ መሳፍንት ጎንደር፣ ማስረሻ ሰጤ ጎጃም ይቀበሉት። አስካሁን ያበጣበጠን፣ ከወንድሞቻችን ደም ያቃባን ይበቃል በማለት ኃይለኛ ትችት አቅርበዋል። በዚህ የተደናገጡት አመራሮች ዛሬ ኦፕሬሽን አንሠራለን ብለው ባልተጠና መልኩ ድንገት በማጋፈጥ ከመከላከያ ጋር ተነጋግረው ሊያስመቷቸው እንደወሰኑም ተሰምቷል።

"…እስቲ እናንት የዳያስጶራ ወሎዬዎች፣ ጎጃሜና ጎንደሬዎች፣ ሸዋዎችም እናንት ዐማራዎች ተወያዩ። ተነጋገሩ፣ ተመካከሩ። ተመካከሩናም ወስኑ። በወር 7200 ዶላር፣ በአጠቃላይ ለኢትዮ 360 በወር 50 እና 40 ሺ ዶላር ለሀብታሙ አያሌውን ለሹገር ዳዲ እስክንድር ነጋ ከምትፈጨፍጩ ተመካከሩና፣ ልብ ገዝታችሁ፣ ምራቅ የዋጡ ዐማሮችን መርጣችሁ በአስቸኳይ ለፋኖዎች ድረሱላቸው። ድረሱላቸው አልኳችሁ። ጠማማው ዛፍ በራሱ ጊዜ ያረጃል። ይወልቃል። ደኑ ዐማራም ጠማመነት ከመሃሉ ሲወጣ በሰላም ይኖራል። ጭንብላሙም፣ ለምድ ለባሹም በሙሉ ይገለጣል። ዐማራ እንደሁ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

"…አይታችሁልኛል እሜቴ አሜሪካም የእነ ሀብታሙ አያሌውን፣ የእነ አበበ በለውን ዩቲዩብ ማውረዱን ተወች። ዐማራን አፍራሽ ሆነው ሲመጡ እነሱን መንከባከብ ጀመረች። ገጥመናል፣ ገጥመናል አንድ ሺ ሰብስክራይብ እስኪሞላ ሰብስክራይብ አድርጉ ማለትም ቀረ። ተመልካች ግን ከየት ይምጣ? ወፍ የለም። ግም 7 ትና፣ የግምባር ሠራዊት አሽቃባጭ ሹገር ማሚዎች ካልሆኑ በቀር በዚያ አካባቢ ዝር የሚል የለም። አስቱካ ከሃረር፣ ሄለን፣ ሚሚ፣ ሚጡ፣ ሰላም የሚባሉ ሹገር ማሚዎች ብቻ ሆነዋል ኮማቾቹ እንኳ። ሕዝብ ከነቃ ነቃ ነው። ደረጄ ሀብተወልድ እስክንድር እስክንድር እያለ እየዬውን ተያይዞታል። ሊበላ። ወፍ የለም። እስክንድርን አዝለኸው ዙር አለው ዐማራ። እናም አሁን ሹገር ዳዲ እስክንድር ያበላሸውን የፋኖን መርጃ መንገድ እንዴት እናድሰው። የላስታም፣ የምሬም፣ የሸዋም፣ የጎጃምና የጎንደር ፋኖዎች ቢያንስ በዚህ በክረምት ከዝናብ የሚጠለሉበት የላስቲክ ልብስ ያስፈልጋቸዋል። እስቲ ምከሩበት? ምን እናድርግ?

"…ዐማራ በቁጥር ብዙ ነው። በረቱ እንደጠፋበት ጥጃና ግልገል ያለ በረቱ ገብቶ እየተጣደ ኪሳራ ላይ ወደቀ እንጂ ዐማራማ ታላቅ ሕዝብ ነው። የአሜሪካ የስፖርት ውድድር፣ የአውሮጳው ጭምር አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቁን ይዞ የሚሄደው በብዛት ማነው? ዐማራው አይደለምን? ደፈር በሉ። ጨከን በሉ። እናንት በውጭ ያላችሁ ዳያስጶራዎች ደረጀ ሀብተወልድን አምናችሁ ለመከላከያ ሠራዊቱ ዩሮ ስታሸክሙ የነበራችሁ። ለማንኛውም መንገደኛ በስመ ኢትዮጵያዊ አማርኛ ስለተናገረ፣ ዐማራ ነው ብላችሁ ገንዘባችሁን ስትገፈገፉ ለኖራችሁ። ለእስክንድር ይደርሳል ብላችሁ ለዶር አምሳሉና ለተጋሩ ሚስቱ ስትገፈግፉ ለኖራችሁ፣ እስቲ አሁን ደግሞ ጨከን ብላችሁ የተከበሩ ዐማሮችን ሰብስባችሁ ተአምር ሥሩ። ተወያዩ፣ ተሰባሰቡ፣ ተነጋገሩ።

• አስነቀልቲው ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እንደምንም በትበት ብዬ ደረሰልኝ። ስለ ሹገር ዳዲ የጻፍኩት ርዕሰ አንቀጽ ደርሶልኛል። አንብቡትና ጨው ካነሰው እጨምርበታለሁ።

"…እናስ ስለ ሹገር ዳዲ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ? አንብባችሁስ አስተያየት ለመጻፍ ዝግጁ ናችሁ? እስቲ አንድ መቶ ያህል ሰው ዝግጁ ነነ ይበል። 100 ሰው በቂ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ…።” ነሀ 4፥14

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይ ጉማ ሰቀታ…

"…የሱ-27 ሮጲላ ፎቶ ከጉግል አውርጄ የለጠፍኩትን በእሱ ቤት ተመራምሮ መሞቱ ነው በድሮን ነው ወይ ፎቶው የተላከልህ ብሎ ገሌ የሆነበትን የወያኔና የገገሜክስ የኦነግ ደጋፊዎቹን ጮቤ ያስረግጣል።

"…የድሬደዋ መሬት አስተዳደር ማስታወቂያ እየሠራ ለብልፅግና እያቃጠረ እንዲኖር ድርጎ የተጣለለት የሀጫሉ ሁንዴሳ አስገዳይ አፍቃሬ ትግሬው የደርግ ወታደሩ የድሬደዋው ልጅ ዮናታን (ጉማ ሰቀታ) ሰሞኑን እኔው የቤት ሥራ ሆኜበታለሁ።

"…ተንቀሳቀስ ጉማዬ። የአንተን ልጥፍ አንብበው ኦነግሶክቹና ወያኔክሶቹ ፎቶው ትክክል አይደለም እያሉኝ ነውና በናትህ ከብቶችህን ሰብስብልኝ። በናትህ ባባትህ። 😂

• ለጉማ አንድ ጊዜ እምቧ በሉለት እስኪ…? በናታቹ… አንድ ጊዜ ብቻ እ…ም…ቧ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጠየቅኩ…

"…ሶዬው ምንኡኖ ነው? ምንስ ኢያደረጋ ኖ? ብዬ ጠየቅኩ።

መለሰልኛ…

~ በሰፈራቸው ውኃ ከጠፋች 26 ቀኗ ነው። እና ይጠንባልህ እንዴ? አላለኝም። ይሞታል ወይ ይሞታል ወይ ታዲያ… እህዕ

• ካልሲ የሚያጥቡ፣ ውኃ በኃይላንድ የሚቀዱ፣ ህጻናት ልጆቻቸውን ሳሙና ቀብተው የሚያጥቡ ሁላ አሉ ነው የሚለኝ ሶዬው። መብራት የማይጠፋው ኮሪደር ልማቱ ጋር ስለሆነ ደብተራቸውን ይዘው መጥተው የሚያጠኑ አሉ ያለም ሰው አጋጥሞኛል።

• እየታጠባችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መረጃ ለፋኖ…

"…ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ወደ ጎጃም አቅጣጫ ሲያጓራ የዋለው ሱ -27 የሚባለው የውጊያ አውሮጵላን ነው። አውሮጵላኑ ተነስሥቶ ልምምድ እንዲያደርግ ነበር የታዘዘው። ለድብደባ መሆኑ ነው። ፋኖ ጥንቃቄ ያድርግ። በ27 ቀኑ የፋኖ ስብሰባ የእነ መከታው፣ የእነ ኮሎኔል ሙሃባው ስልክ ኦፕሬት ሲደረግ የነበረው በብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት ስለነበር የስለላ ሥራ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል። ወዲያው እነ እስክንድር ነጋና እነ መከታው አቶ አሰግድን አዋክበው አቶ አሰግድ አገዛዙ እጅ ላይ እንዲወድቅ አድርገዋል። እናም ከጋሽ አሰግድ ስልክም ላይ መረጃ ሊሰበስቡም ይችላሉ። እናም።

• ፋኖዎች ካምፓቸውን እንዲቀያይሩ
• ስልካቸውን ከነ ሲም ካርዱ እንዲያስወግዱ።
• የደፈጣ ውጊያው ላይ እንዲበረቱ
• ሰብሰብ ብለው እንዳይሄዱ፣ እንዳይቀመጡ ይሁን ተብላችኋል።

"…በተቀረ ሮጲላዎቹ ቦንብ ጭነው ከተነሡ ወዲያው እንነግርሃለን ብለዋል የመረጃ ምንጮቼ፣ ወፎቼ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በላለዴንጣ…

"…ግባ በለው።

"…እንኳን ወደ ቅዱሱ የዐማራ ፋኖ ትግል በሰላም በደኅና  መጣችሁ።

"…ተወደደም ተጠላ፣ ተፈለገም አልተፈለገ፣ ተቀበልክ አልተቀበልክ፣ አመንክም አላመንክም መጬው ጌዜ የዐማራ ፋኖ ዘመን ነው። ዐማራ ማንንም ሳይለማመጥ፣ የማንንም እርዳታ ሳይፈልግ፣ የትኛውንም ምድራዊ ሴራ እየበጣጠሰ፣ ከኃይል ወደ ኃይል ይሸጋገራል። ጠላት ዓይኑ እያየ፣ ጆሮ እየሰማ ዐማራ ያሸንፋል። ቃሌ ነው።

"…እንደ ሁልጊዜው ዛሬም እደግመዋለሁ። የዐማራ ትግል ቅዱስ ትግል ነው። የዐማራ ትግል ፍጥጥ ያለ ከተራራ የገዘፈ ሃቅ አለው የዐማራ ትግል ሕዝባዊ ሆኗል። ሕዝብን ማሸነፍ ደግሞ በፍጹም አይቻልም። በታሪክ መንግሥታትን ያሸነፈ ሕዝብ እንጂ ሕዝብን ያሸነፈ መንግሥት የለም።

"…የዳንኤል ክብረት ጃዊሳ፣ ጃርት፣ አሞሌ ጨው፣ ጽንፈኛ፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ወዘተ ስድብ፣ የናቲ አንደግምም ወይ፣ የቶሜ ጃጀ፣ የጌትነት አልማው ማቃጠር፣ መገረድ፣ የሲሳይ አጌና መንበጫበጭ፣ የብራኑ ጁላ ደንፉ፣ የአቢይ አሕመድ ጉራ መንበጣረር፣ የፋና፣ የኢቲቪ፣ የኦቢኤን፣ የዋልታ ፕሮፓጋንዳ የዐማራን ትግል አያቆመውም።

"…ይህ የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በጌምድር ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሸርብ አቸነፍ የሚመራ ጦር ነው። ግባ በለው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ዐማራ በግድ ያሸንፋል። አከተመ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ። 😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማስታወቂያ…

"…ለዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላቀርበው የነበረው ነጭ ነጯን ከዘመዴ የተሰኘው መርሀ ግብራችን በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት 1 ሰዓት ወደፊት ተገፍቶ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ የሚቀርብ መሆኑን ለመግለጥ እወዳለሁ። 3:00 ላይ ጠብቁኝ።

"…እስከዚያው ድረስ ግን በፊት ኬንያ፣ አሁን ኡጋንዳ ሆኖ ጋሻ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ብሎ በመክፈት አዝግ ሥራዎችን ሲሠራ የሚውለው የታናሹ እስክንድር የወንድም ይሁን የእናቱ ልጅ የሆነው ወንደሰን ተክሉ የዘመድኩን ነቀለን ተከታይና ደጋፊዎችን ማንነት ገላጭ ስድስት ወሳኝ ነጥቦችን በተመለከተ ያስቀመጣቸውን ምሁራዊ ትንታኔዎች እያነበባችሁ ትጠብቁ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ።

"…ወንዴ ጓ የሚልብኝ የአክስቱ ልጅ የሆነው አይተ እስክንድር ነጋን አጅሬ ሆዬ ዘመዴ ንግሥናውን አስቀረበት ብሎ ነው የሚንጨረጨርብኝ። ኧረ እጨጌ ዘመንበረ ጋኔልም ብሎኛል። ኦሆሆይ ደግሞ ምንዓይነት አዲስ ስም ነው ይሄ? ይሁን ግድየለም። እኔ መቼም የማልችለው የለም። 😂😂😂

"…ወንዴ ስለ ዘመድኩን ነቀለ አማኞች ማንነትና ምንነትም በእስክንድር የሥጋ ዘመድ መንፈስ ተምርቶ ጥልቅ የሆነ ትንታኔም በሚገባ ሰጥቷል። በእውነት የሚገርም ዕይታ ነው።

"…በአንድ ወቅት ከአበበ በለው ጋር… በነገራችን ላይ ወንዴ ማለት ከአቤ በለው ፊት የተገሸረው ራሰ በራው እሁድ ማግስት ሰኞ ጠዋት ዝናብ ዘንቦ ፊቱ የሚመስሉት ሶዬ ናቸው ልል ብዬ ከአፌ ነው የመለስኩት። አምልጦኝ ነበር። 😂

• አምላኬ ይቅር በለኝ። ዘንድሮማ ከምር መንቀሌ ነው። ለትንሽ ሰውየውን እኮ ሰድቤው ነበር። 

"…እየነቀላችሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ስትዘቀዝቀኝ ውለህ ብታድር እኔ እንደሁ ኬሬዳሽ…!

"…ልጁ ሳሚ ይባላል። የፖለቲካው ቅማንቴ ነው። መኖሪያው ሀገረ ኢንግሊዝ ነው። ቅማንቴው ሳሚ በወያኔ የዘር ፖለቲካ ተለክፎ ያደገ ፀረ ዐማራ ነው። እኔ በፊት ሳውቀው ጎንደር የቅማንት እንጂ የዐማራ አይደለም የሚል የወያኔ መንፈስ ሰፍሮበት ሲያጓራ ነው።

"…ሳሚ የፖለቲካው የወያኔው ቅማንቴ የጎንደሩን ሀብቴን በመደገፍ እነ ዘመነ፣ አሰግድ፣ ባዬና ምሬ ወዳጆም ላይ የዘመተ ነው። ሳሚ የዐማራ የጭን ቁስሉ የሀብታሙ አያሌውም ቅጥረኛ ነው።

"…የቲክቶክ ቤቱን ከፍቶ ሲሰየም በፊት በፊት ጉራጌው የጀርመን ስደተኛ፣ ጀርመን አልቀበል ብላው እነ ሀብታሙ አያሌው በሜክሲኮ አሜሪካ እናስገባሃለን ብለው ፍርፋሪ እየሰጡ የሚያስለፈልፉት እነ ማዕረግም ይገቡለት ነበር። ሊያላቅሱት ማለት ነው። አሁን ሁሉም ሲቀሩ የቅማንቷ ንግሥት እና የአገው ሚድያ አጅበውት ያላቅሱታል። ፈንዳ፣ ጧ በል። 😂😂😂

"…ትናንት ሀብታሙ አያሌው ጋሽ አሰግድ ከምን እጅ ሰጠ፣ ለምን ራሱን አያጠፋም እያለ ሲሳደብ ሳይ አፈርኩለት። መቀመጫው ላይ ኪንታሮት ወጥቶበት ከትግሉ የሸሸ ሰው እንደዚህ ጨካኝ ይሆናል ብዬም አላሰብኩም ነበር። ወዲያው ለቅማንቴው ደውሎ ይህን አጀንዳ አድርገው ብሎት የጎንደሩ ተብታባ ፀረ ዐማራና ፀረ ቅማንቱ የባንዳ ልጅ ጋሽ አሰግድን ሲሰድባቸው ዋለ። ስድቡን ማታ በቴሌቭዥን አሳያችኋለሁ።

"…ዐማራ ደገፈኝ አልደገፈኝ ለደንታው ነው። እንዲያውም የዐማራን ድጋፍ አልሻም። ብቻዬን ግን አምላኬን ይዤ እንዳችኋለሁ። ፍርስርሳችሁን ነው የማወጣው።

• ወጥር ዘመዴ… እበድ ጧ በል ፀረ ዐማራ…💪🏿💪💪🏿

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…እንዲህ አሰብኩ። አሰብኩ አሰብኩና ፎልፏላው ዘመዴን፣ በመዝገብ ስሙ ሁለገቡን መምህር፣ ደራሲ፣ አሸበርቲው ዘመድኩን በቀለን፣ የመረጃ ቴሌቭዥኑን አክ እንቲቪስቱን ዘመዴ ነጭ ነጯን፣ አቡነ ናትናኤል የሚጠሩት ዘመድዘርን፣ ወዳጆቹ፣ የቅርቦቹ የሚጠሩት ዜዶን፣ ዘሙን፣ ዜድዬን፣ ዘሜን፣ እንደ ገና ደግሞ ያ የምታውቁትን ሃቅ እንቅ አለቅሙን፣ ደሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብሎ ዋይዋይ ባዩን፣ ከእውነት ጋር ላይፋታ የቆረበውን የምሥራቁን ሰው የሐረርጌውን ቆቱ፣ መራታው ዘመዴን፣ የሥላሴ ባርያ፣ የድንግል አሽከሩን ባለ ማዕተቡን ምርጥዬ የተዋሕዶ ልጅ አክሊለ ገብርኤልን ከያሉበት ስብሰባ ጠርቼ ረጅም ሰዓት የፈጀ ውይይት ተወያይተን ከውሳኔ ላይ ደረስን።

"…በስብሰባችን ላይ ተወያይተን ከደረስንበት ነገሮች አንዱ የዐማራ ትግል ወደ ሚገርም ከፍታ መሸጋገሩን ነው። የአክቲቪስቶቹ የመረዳት፣ የማስረዳት እድገት ገራሚ መሆኑን። ዐማሮች እንደ ድሮው አጀንዳ ሲሰጣቸው ያንን አጀንዳ ተቀብለው የሚያራግቡ የዐማራ አክቲቪስቶች አሁን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አለመኖራቸው። አርበኛ አሰግድ እጅ ሰጠ፣ አርበኛ አሰግድ በቁጥጥር  ስር ዋለ፣ አርበኛ አሰግድ እንዲህና እንዲያ ሆነ እየተባለ በብልፅግናው ሰፈር ጮቤ ሲረገጥ ራሱ የዐማራ ሚድያዎች ሌላ ተአምር ነበር ይጽፉ የነበረው። በመተማ አምስት መኪና ሙሉ መከላከያ ከነ ሙሉ ትጥቁና ስንቁ መማረኩን፣ ብልጽግና ወደ ፋኖ ዘንድ የላካቸውን ካቢኔዎች ፋኖዎቹ በእንብርክክ ሲነዷቸው፣ ጭራሽ እጅ ሰጠ ብለው ብልፄዎች አታሞ የሚመቱበትን ለአርበኛ አሰግድ መኮንን "እናመሰግናለን ጋሼ" ብለው ግጥም ሲገጥሙለት ነው የዋሉት። አይ ዐማራ። ተአምረኛ የሆነ ነገድ እኮ ነው። እነ ጉማ ሰቀታ ዋይዋይ ይላሉ እሱ ሌላ ዓለም ላይ ነው።

"…ከምር ይሄ መባረክ ነው። ይሄ የዐማራ ትግል በዚህ ፍጥነት የደረሰበትን ከፍታ የሚያሳይ ነው። መሪ ቢሞት፣ መሪ ቢከዳ፣ መሪ ቢሰዋ፣ መሪ ቢበነድድ፣ መሪ ቢደክም፣ መሪ ቢዝል እንኳ ትግሉ እንደማይቆም ነው ያየሁበት። እንዲያውም በአስተማማኝ ሁኔታ እልፍ ቆራጥ መሪዎች ከዐማራ ማኅፀን መውጣታቸውን ነው ያየን የተረዳንበት። በቃ የዐማራ ትግል በፕሮፓጋንዳም፣ በመድፍና በድሮንም ንቅንቅ እንደማይል ነው የተረዳነው። በፊት በፊት አንዳንድ የዓረብ ሀገር ሴት እህት ዐማሮች የሆነች ኮሽታ በሰሙ ቁጥር አየሩን በሙሉ በፍርሃት፣ በስጋት፣ በጩኸት፣ በእንባ፣ በልቅሶ ነበር ድብልቅልቁን ሲያወጡ ይውሉ ያመሹ የነበሩት። አሁን ግን ወፍ የለም። የጀግና ዘር።

"…በዐማሮች ገንዘብ ሕይወቱን የሚገፋው የውጭ ሀገሩ ፀረ ዐማራ የሚድያ ክንፍ የፀረ ዐማራ እንቅስቃሴ መሪው የእነ ሀብታሙ አያሌው ኢትዮ 360 ራሱ ልሣኑ ነው የተዘጋው። የሕዝቡን ንቃተ ኅሊና በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ መያቱ ብቻ ራሱ በቂ ነው። የትግሬና የፖለቲካው ቅማንቴ ድቅል ነው የሚባለውና ራሱም ፈላሻ ነኝ ብሎ ሲናገር ተምቷል የሚባለው ባለ እስክስታው አዝማሪ አበበ በለውም ለጊዜው ዝም ጭጭ፣ ምጭጭ፣ ጮጋ ነው ያለው። የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞና የብልጽግና ልሣናት እንዴት ጓ ሲሉብኝ እንደዋሉ መመልከቱ በራሱ በቂ ነው። እናም ዐማራው ድብን አድርጎ አሸንፏል። ተኩላዎቹንም የለበሱትን የበግ ለምድ አስወልቋል። ዐማራው በአንድ ዓመት የትግል ዘመን ውስጥ ስንዴውን ከአንክርዳዱ ለይቷል። ብርሃን ከጨለማም ለይቷል። የብርሃን መልአክ መስለው በስሙ የተገለጹትን የጨለማው ዓለም አበጋዞች መንጥሮ አውጥቷል። ብቻ ምንም ቃላት የለኝም።

"…መሬት ላይ ደግሞ ተአምር እየተሠራ ነው። በቅርቡ ዐማራው የጦር መሣሪያ በዐማራ ምድር ሲያመርት የሚያሳይ ተአምር ልታዩ ትችላላችሁ። እኔ ያየሁትን ጉድ ነው የምነግራችሁ። ከመቼውም ጊዜ በላይ ዐማራው ወታደራዊ ሥልጠናውን አጧጡፎታል። የሴራ ፖለቲካውን ከእነርሱ በባሰ መንገድ መሥራቱንም ተያይዞታል። በቃ ምንአለፋችሁ ዐማራ አዚሙ ለቆታል። ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ አፀፋዊ ምላሽ በሚሰጡ ልባም የዐማራ ልጆች ተሞልቷል። ዐማራ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ቁመና የሚያስከነዳ ቁመና ፈጥሮ ቁጭ ብሏል። ታዘቡኝ ከጥቂት ሰሞኑን ትግሉንና የትግሉን ወሬ መስማት ከጀመሩ ጥቂት ሰዎች በቀር ሌላው ዐማራ የብልፅግና ካድሬዎች ፈብርከው ሻሞ ያሉትን አጀንዳ ከቁብም አልቆጠረው። ዳይ ወደፊት።

"…እናም ነገር በሦስት ይጸናል ነገርም ትምህርትም በአይን ይገባልም እንዲሉ። የዛሬ ሳምንት ረቡዕ የእነ ታናሹ የበግ ለምድ የለበሰ አጋንንት እስክንድር ነጋን፣ መከታው፣ ሀብቴና ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባውን፣ የሀብታሙ አያሌውንና የኢትዮ 360ን የአበበ በለውን የእንጭቅ ልጅ የጅል ሁላን ሴራ በድማሚት መፈራረሴ ይታወቃል። ከረቡዕ ዕለት የድማሚት ወቀጣ በኋላ ደግሞ ሌላ ሱፐር ሶኒክ ሚሳኤል የሆነ መርሀ ግብር ዕሁድ ዕለት ለቅቄ ምደረ ሰገጤ የጅል አራዳውን ቀፋይ አጭበርባሪ ሁላ ብትንትኑን አውጥቼ መድረሻ አባቱን ማሳጣቴም ይታወቃል።

"…እናንላችሁ ዛሬም በርዕሰ አንቀጽ ፈንታ የመረጃ ቲቪን የማኔጅመንት አባላት አስፈቅጄ ምሽት ሁለት ሰዓት ከአርበኛ አሰግድ መኮንን ጋር የተያያዘውን ነጭ ነጯን መረጃና ሌሎች የቀሩ መረጃዎችን በመረጃ ቴሌቭዥንና በራሴ ቲክቶክ ላፈነዳው ወሰንኩ። ውሳኔዬንም ለእነ ዘመዴ፣ ዘመድዘር፣ ዘመድ፣ ዘመድኩን፣ አክሊለ ገብርኤል አሳወቅኩ። እነርሱም ልክ እንደ ኢህአዴግ፣ እንደ ወያኔ፣ እንደ ብልጽግና፣ እንደ እስክንድር ነጋ የጨበራ መርጫ ያለ አንዳች ተቃውሞና ያለ አንዳች ድምጸ ተአቅቦ በዲሞክራሲያዊ መንገድ 100% በሓሳብህ ተስማምተናል አሉኝ። እናም ዛሬ ማታ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በመረጃ ቴቪ እና በቲክቶክ መንደሬ ጠብቁኝ። ከተፍ ነው ብዬ የምመጣው።

"…አርበኛ ሀብቴን ከጎንደር፣ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባውን ከወሎ፣ ድርሳን፣ ፋኖ አበባው ሰሎሞን፣ መሀይሙ መከታውን ከሸዋ፣ እስኬ አጭቤውን፣ ከፋፋይ ባንዳ ሀብታሙ አያሌውን፣ እስክስ አበበ በለውንም፣ የግንቦቴ፣ የኦነጌ፣ የወዩወያኔወያኒት፣ የብልፅግና ገረዶች፣ የግንባር፣ የሠራዊት አራዊቶች ሁላችሁ ጫ ብላችሁ ጠብቁኝ። የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ይሄን ይመስላል። ዐማራ ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወዲያውም ገና ሲናገር ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ። …መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና፦ መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ብሎ ሳመው፤ እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት። …ኢየሱስም መልሶ፦ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ አላቸው። ሁሉም ትተውት ሸሹ። ማቴ 14፥ 43-50

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሻሎም… ሰላም…!

"…ያለፉትን ሳምንታት እሰከ ሌሊቱ 8 እና 9 ሰዓት ድረስ ዋይዋይ እያልኩ ሳመሽ መቆየቴ ይታወቃል። የነበርንበት ጦርነት እንዲህ በቀላሉ የሚታይም አልነበረም። በትናንትናው ዝግጅቴ ላይ ግን "ስለ ደከመኝ ዛሬ ከእግዚአብሔር ሰላምታው ቀጥሎ ሺ ሰው ካመሰገነ በኋላ እርፍፍ ብዬ እውላለሁ" ብዬ መናገሬም ይታወሳል። በእርግጥም ዘሬ እርፍፍ ብዬ ነው የዋልኩት።

"…በዐማራ ክልል ሚልዮን ድሎች ሲመዘገቡ እንደዋሉ እያየሁ ነው። ሰዉ ሁሉ ግን በጋሽ አሰግድ ጉዳይ ላይ ብቻ ሲነታረክ እየተመለከትኩም ነበር። ስለ ሁኔታው እኔ ያለኝን መረጃና የደረስኩበትን "ቀኝ ትከሻዬን ከሸሸከከኝ" በነገው ዕለት አልያም በማግስቱ ነጭ ነጯን ከጭቃ ዥራፌ ጋር እያጮህኩ እለጥፍላችኋለሁ።

"…አሁን እኔ የሚታየኝ ዐማራ ማሸነፉ ነው። የዐማራ አናት እልፍ ጀግኖችን የወለደች ማኅፀነ ለምለም ናት ። በግለሰብ ላይ ላይ የተመሰረተ ትግል አልተጀመረም። ግለሰብ ይደክማል፣ ይሰዋል፣ ይቆስላል፣ ይማረካል፣ ይከዳል። ይሄ ሃቅ ነው። እውነትም ነው። በተለይ ወታደር ሆኖ ጫካ የገባ ሞት በአናቱ ተሸክሞ ነው የሚገባው። ይሄን ማመን አምኖም መቀበል ያስፈልጋል። ግድ ነው። ግዴታ።

"…የዋልኩት ሠራዊቱ ጋር ነበር። ምንም የተፈጠረባቸው ክፍተት የለም። ዝርዝር መረጃውን ነገ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።

"…በምንም ይሁን በምን አሁን አርበኛ አሰግድ መኮንን በአገዛዙ እጅ ነው። አገዛዙ ደግሞ እንክብካቤ እያሳየው ነው። 😂 አቶ ስብሃት ነጋን ሲይዝና አቶ ክንፈ ዳኘውን በቁጥጥር ስር ሲያውል እንዳዋረዳቸው ጋሼን አላዋረደውም። ምንአልባትም አቶ አሰግድን ሹመት ሁላ ሊሰጠው ይችላል። 😂 እንደ አያያዙ ማለቴ ነው። እናም ይሄ መልእክት ለሌሎች ፋኖዎች ሌላ ነው።

"…የደፈረሰው ሁሉ ይጠራል። ዐማራ ግን ማርያምን ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…
Subscribe to a channel