መልካም…
"…1ሺ የክርስቶስን ትንሣኤ የሚያውጅ ሕዝብ እስኪመጣ ነበር የቆየሁት። አሁን ግን የሚጠበቀው አመስጋኝ ሕዝብ ሞልቷል። በነገራችን ላይ ርዕሰ አንቀጹ የሚፈጥነውና የሚዘገየውም በዚህ ምክንያት ነው። ከምስጋናው ቀጥሎ የምናመራው ወደ ተወዳጁ የቤታችን ርዕሰ አንቀጽ ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የሚያተኩረው በወያኔና በአብይ ስምምነት ምክንያት በአፍሪካ ቀንድ እየመጣ ያለውን ከባድ ጦርነት የሚያውቁት አሜሪካኖቹ ይፈጠራል ብለው ለሚገምቱት ከባድ ዕልቂትና ስደት ድንገት ከመሬት ብድግ ብለው ጎረቤት ሀገር ኬንያን የቀጣናው አረጋጊ ሃገር አድርገው ስለሾሙበት እና "ዶሮን ሲያታልሏት የሚፈላው ውኃ ለገላሽ ማጠቢያ ነው አሏት" ዓይነቱ ስለ ሩቶ እና ስለ የአሜሪካ አቀባበሉም አይደለም። እሱን ራሱን በቻለ አንቀፅ እመጣበታለሁ።
"…ደግሞም ዐማሮቹ ገርስሰው ሳይጥሉኝ ራያንና ወልቃይትን ልስጥሽና አንቺ ደግሞ ዐማራን በመውጋቱ እርጂኝ፣ በዚያውም ዐማራን በጋራ ወግተን ከጣልን በኋላ ጠላትሽ ኤርትራን አብረን እንወጋዋለን ተባብለው በራያ አካባቢ ስለሚያሳዩት ትርኢትም አይደለም የምጽፈው።
"…የአሜሪካ ኤምባሲ ማንን ለማብሸቅ እንደሆነ በሚታይ መልኩ የጃንሆይን ፎቶ ለጥፎ ጃንሆይን በክብር ተቀብሎ ሲያበቃ ጃንሆይ ከአሜሪካ እንደተመለሱ በኦሮሙማው ደርግ አገዛዝ በኩል የዘውድ ሥርዓቱን ገርስሶ ጥሎ፣ ንጉሠ ነገሥቱንም አፍኖ ገድሎ ሲያበቃ አስከሬናቸው ላይ ቢሮ ሠርቶ እንዲቀመጥ ስላደረጉት አማሪካኖች አይደለም የምጽፈው። በኤርትራ፣ በወያኔና በኦሮሙማው መካከል ስለተደገሰው ጦርነትም አይደለም።
"…እኔ ዛሬ መጻፍ የፈለግሁትን ጽፌአለሁ። እናንተስ የጻፍኩትን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ? ዝግጁ ነነ ብልቻችሁ ደብለቅለቅ አድርጉት እስቲ…!
• አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ።
• አሁንም እጠይቃለሁ?
"…እስክንድር ጦር ሠራዊት አለው ወይ? ካለው አለው ብሎ መመለስ የአባት ነው። ከሌለው ደግሞ የለውም ብሎ መመለስ እንጂ የምን ነገር መጠምዘዝ ነው?
"…እስክንድር ባለ አደራ ብሎ ሲያቋቁም አይተናል። ባለ አደራን አፍርሶ ባልደራስን ሲመሠርትም ቢሮ ነበረው፣ ከምርጫ ቦርድም ፈቃድ፣ ለዚህ እኔም ምስክር ነኝ። እስክንድር ሰላማዊ ትግል አዋጭ አይደለም ብሎ የዐማራ ፋኖን ትግል ሲቀላቀል መጀመሪያ መግለጫውን ልኮልኝ ያነበብኩለት እኔው ነኝ። መጀመሪያ ሸዋ ከዚያ ጎጃም ሄዶ መከራ ፍዳውን ሲበላም የማገኘውም እኔው ነበርኩ። እስክንድር መነሻዬ ዐማራ መድረሻዬ ኢትዮጵያ ብሎ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ሲመሠረትም ሁላችንም እኩል ነው የሰማነው። ቆይቶ ግንባሩን አፍርሶ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ ሲመጣም አሁንም አብረን ነው የሰማነው።
"…እና አሁን የጎንደር፣ የወሎ፣ የጎጃም ዐማራም ወደ አንድ መጥቷል። የሚቀረው የሸዋው ነው። የሸዋውም እርቅ አውርደው የሚቀረው በጣም ትንሽ የአፈጻጸም ነገር ነው። እሱንም መሬት ላይ ያሉ ሽማግሌዎች እየሠሩበት እየደከሙበትም ነው። ከፍጻሜም ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የእኔ ጥያቄ የሚመጣው እዚህ ጋር ነው።
• እስክንድር ከዐራቱ የዐማራ ግዛቶች በየትኛው የፋኖ አደረጃጀት ስር ነው የታቀፈው? ቀላል ጥያቄ እኮ ነው?
• መፍረሱ፣ መክሸፉ በይፋ የተነገረለትን የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል ስም እዮተጠቀመ በሸዋና በጎጃም በወሎና በጎንደር መካከል ለምን ሽብልቅ ይከታል? ሠራዊት አለው? ካለ የት ነው? መልስ
• ይሄ ቀላል ጥያቄ ሲጠየቅ ግንቦቴዎች ዘው ብላችሁ መጥታችሁ አኪላ የሚባል አንድ አክቲቪስት እየጠቀሳችሁ መዘብዘብ ምንድነው? በቲክቶክና በዩቲዩብ አየር ላይ ያለው አኪላ ነው ወይስ ምድርና ቴቪ ላይ ያለው እስክንድር ነው ትግሉን የሚጎዳው?
አልገባኝምና ብትመልሱልኝ 🙏🙏🙏
"…የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ዐፄ ዳዊት ክፍለጦር እና የዐማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ እስክንድር ነጋ ክፍለጦር የጋራ የአቋም መግለጫ የሚል ቪድዮ ከወዳጄ ኑረዲን ዘንድ ደርሶኛል።
"…የእኔ ጥያቄ እስክንድር ነጋ ያለው ሸዋ ነው። የሚጠበቀውም በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በእነ ሻለቃ መከታው ነው በእነ አቤ ጢሞ ነው። ይሄን ያዙልኝ። ዐጼ ዳዊት ክፍለ ጦርም በእነ ሻለቃ መከታው ስር ያለ ክፍለ ጦር ነው። የእስክንድር ነጋ ክፍለ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ጦር ደግሞ በወሎ ዕዝ ስር ያለ ክፍለ ጦር ነው ተብሏል። ይሄንንም ያዙልኝ።
"…እሺ ምንም ዓይነት ጦር የሌለው እስክንድር ነጋ በሻለቃ መከታው ጦር በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ስር የግል ጠባቂ ተመድቦለት ደኅንነቱ እየተጠበቀ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ እስክንድር ሰሞኑን ለአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ሰጠ በተባለው መግለጫ እና እሱን መግለጫ ተከትሎ የእስክንድር የግል ደጋፊዎች እስክንድር እንግሊዝኛ ይችላል ብለው ባንቆለጳጳሱት መግለጫው መጨረሻ መደምደሚያ መዝጊያ ላይ "የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ" በማለት መቋጨቱ አደናጋሪ ነው የሆነብኝ። ሠራዊቱ ሠራዊት አለው ወይ? አበበ በለው እና ሀብታሙ አያሌው ሠራዊቱ የሚሉት ከጎጃሙ ከማስረሻ ሰጤ ቀጥሎ ይሄንን የሸዋ ጠቅላይ ዕዝና የወሎ የእስክንክንድር ነጋን ጦር ነው ወይ?
"…የእኔ ጥያቄ እስክንድር ነጋ በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ስር ሆኖ፣ በጠቅላይ እዙ ጋርዶች እየተጠበቀ፣ ድሮኗ ጠባቂዎቹን፣ ከኋላ የሚከተሉትን ባጃጆች ብቻ እየተከተለች እየገደለች እንዴት አንድ ሰው ብቻውን ፓርቲ ሆኖ በእንግድነት ተጠግቶ ባለበት ሥፍራ እንደ ባለቤት ባለቤት ሆኖ መግለጫ ይሰጣል? በሌለ ነገር?
"…እስክንድር ሸዋ ተቀምጦ በጎጃም ካፒቴን ማስረሻን ቆስቁሶ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ በተመሰረተ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ላይ ተደራቢ አድርጎ ማምጣቱስ ልክ ነው ወይ? በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር እና በወሎ መካከል የሆነ ሽብልቅ ለመክተት የታሰበ ነገር አይመስልም ወይ…?
"…ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሰሞኑን በእነ ሻለቃ መከታው እና በእነ ኮማንደር አሰግድ ጦር መካከል ግጭት መፈጠሩ ይታወቃል። እኔ ፈጽሜ ካቆሙኩበት የቀጠሉ ሽማግሌዎች እየደከሙበት እንደሆነም ዐውቃለሁ። የሆነው ሆኖ የእስክንድር ቡድኖች ሀብታሙ አያሌውም ሆነ ሀብታሙ በሻህ ለእነ ሻምበል መከታው ቡድን አግዘው እነ ኮመንደር አሰግድንና እነ ኢንጅነር ደሳለኝን በፕሮፓጋንዳው መቀጥቀጣቸው ምንን ያመለክታል? እነ ኮማንደር አሰግድ መኮንን የእስክንድር ነጋ በሸዋ መኖር እንደ ሸዋ ገና ያፋጀናል የሚሉትስ እውነት ይሆን እንዴ?
"…የመጨረሻ ልጨምር። እስክንድር ነጋ ክፍለጦር የተባለው እና በወሎ ዕዝ ስር ያለው ኃይልስ ከወሎ ዕዝ ከእነ ኮሎኔል ፋንታሁን እና ከእነ የዋርካው የምሬ ወዳጆ እውቅና ውጪ በእነ ሻለቃ መከታው ዕዝ ስር ነኝ ካለው የዐፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ጋር በግል በዘፈቀደ መፈራረም ይችላሉ ወይ? በእነ መከታውና በወሎ የዐማራ ፋኖ መካከል ግጭትና ቁርሾስ አይፈጥርም ወይ…?
"…ለእነዚህ መልስ ካገኘሁ እኔ ብዙ ጥያቄዎች ይኖሩኛል። ይሄ የዛሬው ጥያቄዬ አባቶች አብርደው ካሉኝ ጉዳይ ጋር በፍጹም አይያያዝም። እሱም ቢሆን በዝምታዬ የሚጠፋው ጥፋት ከበረታብኝ ዝምታዬን ሰብሬ ለመውጣት መገደዴን ለመግለጽ እፈልጋለሁ።
"…ጋሽ አሰግድ እና ሻለቃ መከታውም እባካችሁ ተረጋጉ። ተደማመጡ። በመሃላችሁ ነፋስ አታስገቡ። እንደ አባቶቻችሁ ጠቢባን ሁኑ። ስክንም በሉ። በነፍሱ ተጠያቂ ናችሁ እና በእናንተ ስህተትና አለመደማመጥ ምክንያት አንድም ቢሆን የሚሞት የሸዋ ፋኖ አይኑር። ሽማግሌዎችን አድምጡ። ለሽማግሌዎቻችሁም ቃል ተገዙ። ደግሜ እላለሁ ተደማመጡ። ይቅር የማይባል ታሪካዊ ስህተት ከመፈጸምም ተቆጠቡ።
• ጥያቄዬ የገባችሁ አስረዱኝ።
"ርዕሰ አንቀፅ"
"…ከ No More እስከ No Go…
"…የሸንኮራ ጥቅሙ ወይ በጥርስህ ትልጠዋለህ፣ አልያም ከድጋይ ከዛፍ ታጋጨውና ትሰብረዋለህ፣ አልያም በካራ ትሸነሽነዋለህ። ከዚያ በጉንጭህ ልክ አፍህ ውስጥ ከተህ በጥርስህ እያኘክ፣ እያላመጥክም ጣፋጩን ጨምቀህ መጥጠህ ትውጥና ቀሪዉን ተፍተህ ትጥለዋለህ። የአገዳ ጭማቂ ወይ ለከብት መኖ ይሆናል አልያም ደግሞ ለእሳት ራት ማገዶ ይሆናል። አለቀ። የኮንደምም አገልግሎቱም ተመሳሳይ ነው።
"…አንድ የሃይማኖት አባት ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምርጫ የተሾመ አገልጋይ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን ማገልግል ትቶ ከፓርቲው አባላት በበለጠ እወደድ ባይነት ከሃዲ፣ አረመኔ፣ ለነፍሰ ገዳይ ዲዮቅልጢያኖስ የመሰለ አገዛዝ ለማገልገል ከባከነ መጨረሻው No Go ነው።
"…ማገልግለስ “ ለዘላለም የማይጥለውን ጌታ፤” ሰቆ. 3፥31 …ማገልገልስ ሕዝቡን የማይጥለውን፣ ርስቱንም የማይተወውን እግዚአብሔርን" መዝ 94፥14 የተባልነውም “አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፤ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።” ዘዳ 10፥20 ነው። አለቀ።
"…በእያንዳንዱ ቤት፣ ሰፈር፣ ድርጅት፣ መስሪያቤት፣ መንደር፣ ጎጥ መከራው ይገባል። የፈለገ ብታሽቃብጥ፣ የፈለገ ብትገረድ፣ አይቀርልህም። አንተ ባልጠበቅከው፣ ባልገመትከው፣ ይሆናልም ብለህ ባላሰብከው መንገድ በመከራ በትር ትዠለጣለህ፣ የመከራ ቀንበርም ላይህ ላይ ይወድቃል። የፈለገ አልኩህ እልል እያልክ ብታሽቃብጥ ወገብ ዛላህን ቆምጦ ሳይለንት ሙድ ላይ ቆልፎህ እያለህ ድራሽ አባትህን ያጠፋሃል።
"…ይልቁኑ በቶሎ ንስሐ ግቡ…“አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።” ዘዳ 13፥4። ወደ ልባችሁ ተመለሱ። ንስሐም ግቡ።
• No Go…
"…ከዐማራ ፋኖ ጋር ለመዋጋት ወደ ዐማራ ግዛት ለሚገቡ ለብርሃኑ ጁላ እና ለአቢይ አሕመድ ወንበር አስጠባቂ ወታደሮች ነገርየው እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ ገና ወደ ዐማራ ክልል ነው የምትሄዱት ተብሎ ሲነገራቸው ቀድሞ እንዳይሞክሩት በሼክም በቄስም በወዳጅ በዘመድ በቤተሰብ በጓደኛም ቀድሞ ማስረዳቱ መልካም ነው። አቢይ እና ድርጅቱ በቅርቡ መትነኑ ላይቀር ምስኪን የደሀ ልጆች ያውም በአንድ ወር ለብ ለብ ሥልጠና ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ጥይት ሲሰማ፣ ባሩድ ሲያሸት፣ ከግሪሳ ወፍ መሃል ለይቶ በጥሶ በጥይት ከሚመታ የዐማራ ፋኖ ጋር ማጋጠሙ ልክ አይደለም። ደግሞም መማረክ፣ እጅ መስጠት የሚባል ነገርም እኮ አለ።
"…የአረጋ ከበደን 97% ክልሉን ነፃ አድርገነዋል ዲስኩር፣ የዳንኤል ክብረትን ወተት፣ ጨው፣ ጃርት፣ አሞሌ ጨው ተረት፣ የጄነራሉን ደመሰስናቸው፣ የብራኑ ጁላን እየመነጠርን፣ እየለቀምናቸው ነው አጉል ዝብዘባ መስማት ትተው እኛን ቢሰሙ መልካም ነው። ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ያወገዙት፣ የገዘቱት፣ የረገሙት ሠራዊት ከማለቅ በቀር ሌላ ዕጣ ፈንታ አይኖረውም። ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ የመረቁት፣ የባረኩት ሠራዊት ደግሞ ከማሸነፍ በቀር ሌላ ምንም አማራጭ የለውም።
"…ዐማራ ከወደቅኩም ጥዬ ነው የምወድቀው ስላለ መከባበሩ ይበጃል። ዐማራ ስላመረረ በቀላሉ ይፈታል ብሎ ማሰብም አይቻልም። የአንድ ሀገር ልጆች በአንድ ጦሰኛ፣ ዘረኛ፣ መሃይም ምክንያት እንዲህ ሲገዳደሉ ማየት አሳዛኝ ቢሆንም ሕዝብን ማሸነፍ ግን አይቻልም። ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ለሚልዮኖች ሞት ምክንያት የሆነውን አረመኔውን አቢይ አሕመድን ከነ ግብረአበሮቹ በአደባባይ ለስቅላት ፍርድ ማዘጋጀት ብቻ ነው።
“…እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉በዩቱብ /YouTube
♦https://www.youtube.com/live/31eQROXj1qg?si=0iR4ij2WCG-F2Tto
👉በረንብል /Rumble
♦ https://rumble.com/v4wypmk-no-go-ethiobeteseb.html
👉በፌስቡክ/Facebook
♦https://www.facebook.com/share/rMAfC1osyZU7n7pF/?mibextid=oFDknk
👉በቲውተር / Twitter
♦https://twitter.com/EBeteseb
👉 ቴሌግራም/ Telegram
♦/channel/ethiobeteseb
"…ሻሎም ! ሰላም !
“…እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።” ፊል 3፥10-11
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
ምን አገባኝ…!
"…የአንድ ድሮን ዋጋው እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር ነው እየተባለ፣ ለ UV ድሮን እና ድሮንበስተር 30,000 ዶላር ብቻ ያስወጣል እየተባለ፣ ዩኒቨርስቲ ዘግቶ ቦንብ የሚገዛው ብልፅግና በአንድ ቀን ይሄ ሁሉ ዶላር ወድሞበት በወለጋ ምድር ኪሳራ ደረሰበት የሚል ጮማ ወሬ እያለ ምን አገባኝና ነው አየር መንገዱ አጥር ስር የነበሩ የካርቶን ቤቶች ተቃጠሉ ብዬ የምንጫጫው?
"…ስለ ድሮኑ ውድመት እንዳይወራ አየር መንገዱ ጋር ሄደህ ሰሞኑን የሚፈርስ የካርቶን ቤት ታቃጥልና የፒፕሉን ቀልብ ዳይቨርት ለማስደረግ ትጋጋጣለህ። ዥል…
"…በቃ ዝም ብላችሁ የድሮኑን ዋጋ በብር ምቱት። 😂 …በጎንደር የወደመውን የጁላ ጦር ስለ እሱ አውሩበት። አጥር ስር የተሠራ የፎሊስ ማረፊያ የካርቶን ቤት ተቃጠለ አልተቃጠለ ለደንታው ነው። ምን አገባኝ።
"…ሲሰድበኝ የሚውል የብልጽግና ሠራዊት በሙሉ ዘመዴ እያለ ያልጠየቅኩትን መረጃ እንደ ጎርፍ አጥለቅልቆ ሲልክልኝ እኮ ነው የምባንነው። 😂😂😂
"…የሐረርጌን ውኃ ቀምሰህ… በዚያ ላይ አራዳ ደጃች ውቤ ውቤ በረሃ ስታድግ በቀላሉ በበሻሻ አራዶች አጀንዳ አትሸወድም። ያሳቁኝም አሉ። የትግሬ አክቲቪስቶች ከምር አስቀውኛል። የትግሬ አክቲቪስቶች ያ በጁንታው ጦርነት ጊዜ እንደ ሽንኩርት የከታተፋቸው ድሮን… የድሮኑ መውደቅ ሳይሆን ዐማሮቹ አልጣሉትም ነው ሙግታቸው። 😂። ዐማራ አይደለም ለምን አሞራ አይጥለውም። እህእ ምን ያበሳጫቸዋል? 😂 የመድኃኔዓለም ያለህ። ጥላቻ ግን ክፉ ደዌ ነው በማርያም።
• በቃ ድሮን ወድቋል። ወድቋል። አከተመ።
"ርዕሰ አንቀፅ"
• ሰበር ርዕሰ አንቀፅ ነው። የዘገየሁትም የፎቶው መረጃ እስኪደርሰኝ ነበር። ቪድዮውም መንገድ ላይ ነው።
"…በዛሬው ዕለት በቀን 14/2016 ዓም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ አዋሳኝ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉጋና ቀበሌ ልዩ ስፍራው ጫንጮ አቦ እና ሥላሴ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም አሰሳ ላይ የነበረች ቱርክ ሠራሽ ድሮን በወለጋ አናብስቶች በአንገር ክፍለ ጦር በወለጋ ዐማሮቹ ፋኖዎች ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ተመትታ ተከስክሳለች። 💪💪🏿💪
"…ድሮኗ የተከሰከሰችው እዚሁ ደንጎሮ ወረዳ አሩሲ ቀበሌ ላይ ሲሆን ከአሁን ቀደም 27 ንጹሐን ዐማሮች በድሮን በጅምላ የተጨፈጨፉበት አካባቢ መሆኑም ተነግሯል። ያው መቸም ብድር በምድር ነውና ተገድዶ ከዘር ጨፍጫፊው ኦነግ ብልፅግና ራሱን መከላከል የጀመረው የወለጋ ዐማራ በዛሬው ዕለት በውድ የውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ዐማራን ለመጨፍጨፍ ሥራ ላይ ካዋሉት ዓረብ ሠራሽ የወሓቢይ እስላም ሀገር ድሮኖች መካከል አንደኛውን ድሮን ድባቅ በመምታት ጥለው በግዳዩ ላይ ቆመው የፎቶ መረጃ ከሥፍራው ልከውልኛል። "ዘመዴ እናሸንፋለን። ለዐማራ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ በልልንም ብለውኛል።" ገዳይን መግደል እንዲህ ነው።
• የመረጃ ምንጩ፦ የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ደኅንነት ክንፉ ነው። ይኸኛው ፎቶ ነው። ቪድዮው እንደደረሰኝ እለጥፍላችኋለሁ። እስከዚያው…
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
ስሙኝማ
"…ነገርየው የሃይማኖት ጉዳይ ነው። ከብልፅግና፣ ከብአዴን፣ ከህወሓት፣ ከኦነግ፣ ከኦህዴድም ወዘተም በላይ ነው። ለሰሚ ሁሉ ቀላል አይምሰለው። እነርሱ በተዘጋጁበት ልክ ሳይሆን እጥፍ አስበልጠን፣ እነሱ በአቀዱት ልክና መጠን ሳይሆን ከዚያም በላይ እጥፍድርብ አድርገን መዘጋጀትና መግጠም ነው። በዘመናችን ተዋሕዶ ሃይማኖታችን የማንም መሳቂያ፣ መጫወቻ፣ መቀለጃ ሆና እንድትታይ አንፍቀድ። ሞት እንደሁ አይቀር።
"…ፋኖም በዚያው በያዘው መንገድ ይቀጥል። በኦሮሙማ የተገፋው የዐማራ እስላምም የሃጂ ሙፍቲን መገፋት፣ መዋረድም በቅርቡ ይክሳል። ክርስቲያን ፋኖም እንደዚያው። በሀገር መከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በሚሊሻም ይሁን በደህንነት መሥሪያ ቤቶች የምትገኙ ባለማዕተቦችም ከወዲሁ ተዘጋጁ። ቀልድየለም ስልህ።
"…በጥቂት ሆዳም፣ ስግብግብ፣ ነውረኛ ግለሰቦች የተነሣ ዓይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ ጥንታዊቷና ብሔራዊቷ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማርከስ ሲንበጫበጩ ዝም ብለን ማየት የለብንም። እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን በሙሉ ኃይላችን እንገጥማቸዋለን። እነዚህን ጥቂት ቆሻሻ፣ ወራዳ፣ ኮተታም ዘረኛ እበት መሳይ እበቶች ወደ መስመርም እናስገባቸዋለን። ሁሉም ሰው ለማዕተቡ ሲል ይዘጋጅ። ምድረ በጭባጫ ቅዘናም ሁላ አይቀልድብንም። በሃይማኖት ቀልድ የለም። ስም ጠርተን፣ ፎቶ ለጥፈን በስልካቸው ላይ ደውለን ነው የምንገጥማቸው።
"…እኔ ዘመዴ በበኩሌ እንደተለመደው እንደነ ይቴ ይታገሱ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጊዜው ምን ጉድ ነው? ብለህ አዳሜና ሔዋኔ እስክታፍርብኝ ድረስ ፍጹም ባለጌ ባለጌ፣ ስድም፣ እብድ እብድም መጫወቴን በይፋ ነው የምጀምረው። በዚህ ትግል የምምረው አንድም ሰው አይኖርም። ትህትና፣ ጨዋነት የሚባሉት ቃላት ለተወሰኑ ቀናት በመዝገበ ቃላቶቼ ውስጥ አይኖሩም።
• እናንተስ…?
👆…ከላይኛው ይቀጥላል… ✍✍✍
•••
"…እኔ ግን እላለሁ ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ!ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ ትክዳኝም። ባላስብሽ እና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።
"…ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
"…ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት።+49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር እና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 12/2016 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
• ብዬ መሃላዬን እጀምራለሁ ማለት ነው።
መልካም…
"…ቃል ቃል ነው። የሚፈለገው፣ በዘመነ ትንሣኤ በጌታ ትንሣኤ ወራት የጌታን ትንሣኤ ያውጁ ዘንድ የሚጠበቁት 1ሺ አመስጋኞች ሞልተዋል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…በመቀጠል የምናልፈው ትፈርስ ዘንድ በኦሮሙማው አገዛዝ የተፈረደባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በተመለከተ የተደገሰላትን የጥፋት ድግስ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ወፎቼ አጠናቅረው የላኩትን መረጃ በርዕሰ አንቀጽ መልክ አቀርብላችሁና በእሱ ላይ ወደ መወያየቱ እንገባለን። እንሄዳለንም።
"…እህሳ… ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁን?
"…በመጨረሻ ይሸነፋሉ እንጂ የኦሮሙማዎቹ አያያዝ ሲያዩት ጫን ያለ ነው የሚመስለው…
"…ብፁዕ አቡነ አብርሃምን እና አባ ወልደየሱስ ሰይፈ (አባ ህፃን) ያላቸው ንብረት እንዲጣራ ፌደራል ፖሊስ የአዲስ አበባ ክፍለከተሞች ካዘዘው ትእዛዝ በተጨማሪ ከፌደራሉ ፍርድቤት ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በቁጥጥር ስር ለማዋል የፍርድ ቤት የመያዣ ወረቀት በእጁ ማስገባቱ ተሰምቷል።
"…ዘገባውን እየቀሸርኩት ነው። አዳነች አቤቤና ትግሬው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የጀመሩት የስልክ ሴራም ደርሶኛል። ወፎቼም በሙሉ አቅማቸው ሥራ ጀምረዋል። የአራራት ሆቴል የሴራ ጉባኤም፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንሱ የአቶ ወርቁ ጋቸናም ጣልቃ ገብነት፣ በቅርቡ በወሊሶ በሚዶለተው የሴራ ጉባኤም ላይ ወፎቼ በአካልም በስልክም ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ሳበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ወዳጄ የመስመር ስልኩን ትተህ በኋትስአፕ ማውራቱ አያድንህም። እድሜ ለወፎቼ አሰጣልሃለሁ።
• የደረሰኝን መረጃ አንብቤም፣ አይቼም ጨርሻለሁ። የማጣሪያ ውይይት ላይ ነኝ። አጥርቼው ከደረሰ አሁን ካልደረሰልኝ ርዕሰ አንቀጽ አድርጌ ነገ ጠዋት እለጥፍላችኋለሁ። ለአሁኑ አስሬ ለክቼ አንዴ ልቁረጥማ። ጉድ ነው ዘንድሮ።
• መጣሁ…!
“…ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።” 1ኛ ጴጥ 1፥3-5
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ ይዘራል፥ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል፥ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፥ በኃይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። 1ኛ ቆሮ 15፥ 42-44
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…የጠፉ ናቸው ብለው ራሳቸውን ያጠፉ የኦሮሞ በጎች ሰበሰበና… የተሰበሰቡትን የዐማራ በጎች ድራሻችሁ ይጥፋ ብሎ No Go አለላችኋ… ጉድ እኮ ነው… 😂
"…የዱባይዋ ፋጢማም፣ አቢይ የፈለገውን አጀንዳ ያምጣ፣ ምክክር ኮሚሽኑም በ21 አጀንዳ ስብሰባ ይጀምር፣ የፈለገ የፈለገውን ይሁን አባቴ ይሙት አበደን ከዘንድሮው የቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ዓይናችንን አናነሣትም።
"…ባለ ማዕተብ የሆንክ የተዋሕዶ ልጅ ተዘጋጅ ብዬሃለሁ። ነግሬሃለሁ። እኔ በሙሉ ኃይሌ ነው ሰተት ብዬ የምገባው። የሌለ ፍፁም የለየለት ባለጌ ሁላ ነው የምሆነው። በኃይለኛው ነው እብድ እብድ ሁላ የምጫወተው።
• በጎች ሰምታችኋል…! 😂
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…በወልቃይት እና ጠለምት መሬቶች ጉዳይ በኦሮሞ ብልፅግና እና በህወሓት መካከል ልክ እንደ ወሎው ራያ ምድር አይነት ስምምነት ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም። የመጣው ይምጣ ብሎ የኦሮሞው ብልጽግና ከህወሓት ጋር ተደርቦ የወልቃይትን መሬት አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ ግን የሚፈጠረው ትርምስ አካባቢውንም፣ ቀጠናውንም ያተራምሳል ተብሎም ይታሰባል። እናም ለክፉም ለደጉም ብለው የሰፈጉት የዐማራ ብልጽግና ሰዎች በራያ ጉዳይ የመወሰን አቅም እንዳጡ የገባቸውና በማንኛውም ሰዓት አየር ላይ እንደሚንሳፈፉ፣ ከሕዝባቸውም ከአገዛዙም ማረፊያ እንደሌላቸው የገባቸው ደደብ ብአዴኖች የራያ ጉዳይ ከታወቀ ወዲህ በጎንደር እና በወሎ በተለየ ሁኔታ የፖለቲካው ምህዳር በፍጥነት መቀየሩ እየተነገረም ነው።
"…የኦሮሞ ብልጽግና ህወሓትን ከመቀሌ አምጥቶ ራያን ማስወረሩ ለወሎ ቤተ ዐማራ ፋኖዎች ያልታሰበ በረከት ነው ያወረደላቸው። ከሁለት ተከፍሎ የነበረው የወሎ ፋኖ ወደ አንድ ዕዝ የመጡበት ወቅትም ስለነበር በሺ የሚቆጠሩ የዐማራ ሚሊሻና የዐማራ አድማ ብተና ኃይላት የትኛው ጋር እንቀላቀል ብለው ሳይቸገረ ከነሙሉ ትጥቃቸው ነው የወሎን ፋኖን የተቀላቀሉት። በጎንደርም እንደዚያው ነው። እነ ኮሎኔል ደመቀ የሚያስተዳድሩት ወልቃይቴ ለጥቂት ጊዜ ፈጥሮት የነበረውን ዳተኝነት በፍጥነት በማረም ከጎንደር የዐማራ ፋኖዎች ጋር በሚገባ መናበብ ጀምሯል። የብልፅግናን ከሃዲነት፣ የብአዴንን ከጅብ አያስጥሌነት የተረዳው በተለይ የጎንደር ብልፅግናው ቡድን በአንድም ይሁን በሌላም ምክንያት በኦሮሙማው ብልፅግና የመካድ ስሜት ስለተፈጠረበት ወደ ኩርፊያ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ፋኖ በረካ ሳይወርድለት አይቀርም የሚል ስሜትም ይሰማኛል። የሰሞኑ የጎንደር ጀብዱ፣ ድል፣ በገፍ የሚቀላቀሉት ሚሊሻዎችና የአድማ ብተና አባላት ጉዳይም ምስጢሩ ሌላ መሆኑን ለመገመት ኢዩ ጩፋን መሆን አይጠበቅብህም።
"…ሌላው ፋኖዎቹም ሆነ ብልፅግና በመጪው ክረምት የሞት ሽረት ፍልሚያ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ናቸው። ብልጽግናም ክረምቱ ሳይገባ ፋኖዎቹ በሙሉ ኃይላቸው ወጥተው እንዲገጥሙት ይፈልጋል። ፋኖ ወጥቶ ፊትለፊት ካልገጠመው እና በዚህ ሁኔታ ክረምቱ ከገባ ከባድ ኪሳራ እንደሚገጥመው የተረዳው የኦሮሙማው ብልጽግና እንቅልፍ አልባ እቅዶችን በማውጣት እየዳከረ ይገኛል። ሸዋ ላይ ያለው የሁለቱ እዞች ግጭትም በጊዜ ካልበረደ እና ሁለቱም ጎሮምሶች ሃይ የሚላቸው ሽማግሌ ካልተገኘ ለኦሮሙማው ብልፅግና ዕድሜ ማራዘሚያ በጣም ማዳበሪያ የሆነ አሸወይና እድል ነው። ወሎም፣ ጎጃምም፣ ሸዋና ጎንደር በንግግር፣ በስምምነት፣ በውይይት ወደ አንድነት መጥተው ሸዋዎች ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ መመርመር ያስፈልጋል። በተለይ የግንቦት 7፣ የግንባሩና የባልደራስ ግሪሳ ሁሉ ከአንደኛው ቡድን ጋር ቆሞ ሌላኛው ላይ እንዲዘመት መቀስቀስ ኪሳራው በትሪሊዮን ገንዘብ የሚገመት አይሆንም። ቢታሰብበት መልካም ነው።
"…ሌላው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ስለሚማረኩ፣ የሚንስትሮች እና የባለሥልጣናት መኪኖች ጉዳይ ነው። ሰሞኑን የአቶ ተመስገን ጥሩነህ የፕሮቶኮል መኪና በፋኖ ሓይሎች ተማረከች መባልን ተከትሎ የመጣ ምክርም አለ። መማረኩ ሸጋ ሆኖ ሳለ ማራኪ ፋኖዎቹ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ ግን ተመክረዋል። ምናልባትም ይላሉ ስጋቱ የገባቸው ተጠራጣሪዎች ምንአልባትም መኪናዎቹን ዐውቀው እንዲማረኩ ካደረጉ በኋላ የፋኖ አመራራሮች መጠቀም ሲጀምሩ መኪናዋ ውስጥ ሰውር ካሜራ፣ የድምጽ መቅጃና ሌሎች መረጃ ማስተላለፊያ መሳሪያዎች የተገጠመላቸው ሊሆኑ ይችላል። አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ የጸጥታ ሓላፊ በድብቅ ሲነጋገሩ የነበረውን መረጃ ወደ አንድ ቋት ይዞ በማስተላለፍ በማዕከል እንዲደመጥ በማድረግ አቶ ለማ መገርሳ እና የጸጥታ ሓላፊው ሲያወሩ የነበረውን ሁሉ ሰብስቦ እነርሱን ለማስወገድ የተጠቀመው በዚህ መንገድ ነው። እናም በምንም በማንም አልያዝ አልጨበጥ ያለውን የዐማራ ፋኖን ምስጢራዊ አስተደዳር መኪና ማረክን ብለው ለድሮን ሲሳይ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ያድርጉም ይላሉ መካሪዎቹ።
"…ዛሬ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ኋላ ላይ እንገናኛለን። እስከዚያው በዚህኛው ርዕሰ አንቀጽ ላይ እየተወያያችሁ ጠብቁኝ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"…የቦንቡን፣ የመለዋወጫውን፣ የኦፕሬተር የሠራተኞቹንና የትራንስፖርቱን ሳይጨምር በጥቁር ገበያ ተዘርዝሮ ድሮኑ ብቻ 240 ሚልዮን ብር ነው የሚሸመተው እየተባልክ። እየተነገረህ፣ እየሰማህ፣ እያየህ፣ እዚህ መጥተህ ዩኒቨርሲቲ እኮ ለተማሪ የሚቀርብ ምግብ ጠፋ፣ በወላይታ ለመምህራን ደሞዝ መክፈል ቀረ፣ መድኃኒት በገበያ ላይ የለም፣ ነዳጅ ተወደደ ትላለህ።
"…አርፈህ እንደ ኦሮሞ ብልጽግና አትበልጽግና ችግር አውራ። አይደለም ደሞዝ ገና የራስህ ደም አይኖርህም። ደም ነው የሚያጥርህ።
"…ባለ ጊዜ ማለት እንዲ ኖ…
አሁናዊ መረጃ…!
"…ከፌደራል የተላከ የቴክኒክ ቡድን በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራው እንዳቀናና በቱሉጋና ከተማም እንዳረፈ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ድሮኗ የተሸከመቻቸው ያለፈነዱ ቦንቦች ከድሮኗ ስር ስላሉ ድሮኗን ለማቃጠልም ሆነ ለመነካካት አለመቻሉን ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያመለክተው።
"…በተያያዘ ዜናም የኦነግም ሆነ የተጂ አክቲቪስቶች ሳይወዱ በግዳቸው እኔው የለጠፍኩትን መረጃ መልሰው ለመለጠፍ መገደዳቸውም ተመልኳቷል። የሀብታሙና የፀጋዬ አራርሳው ኩሽ ሚዲያማ "የፈጣሪ ቁጣ ነው" አላለም።
"…የአንድ ድሮን ዋጋና የአንድ የድሮን ቦንብ ዋጋ በዶላር ስንት ይሆን? የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚመገቡት ምግብ አጥተው ዩኒቨርሲቲዎች ሊዘጉ ነው የሚል ዜና በሚሰማበት ሀገር መሃይሙ አቢይ አሕመድ የቱርክን ድሮን በመሸመት ኤርዶጋንን ይጦራል። የሚደንቀው ሁላቸውም ይጠፋሉ። ተንነው ይጠፋሉ። ብን ነው የሚሉት።
"…በጎንደር የዐማራ አድማ ብተና ኃይሉ እና የዐማራ ሚልሻ ምን ሰምቶና ዓይቶ ነው በገፍ የዐማራ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለው። የሆነማ ነገር አለ። እየፈለፈልኩት ነው። የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች አልተቻሉም። የብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ከሞት የተረፈው ወደ ሱዳን ነካው አሉኝ።
• የጨነቀለ’ት…ድል ለዐማራ ፋኖ…!
"…ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤” 1ኛ ቆሮ 15፥ 13-14
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
ውጊያው ተጀምሯል…!
"…አቢይ አሕመድ አውግዘውኛል፣ ሠራዊቱም እንዲገድለኝ ቀስቅሰውብኛል ያላቸውን ብፁዕ አቡነ ሉቃስን በፍርድ ቤት ከስሶ የ9 ዓመት ጽኑ እስራት እንዳስፈረደባቸው ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአውስትራሊያ ወደ አሜሪካ የሄዱትን ብፁዕ አቡነ ሉቃስን የዋሽንግተንና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከእነ ቀሲስ ዘበነ እና ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና ጋር በመሆን በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱ፣ እንዳይቆርቡ መከልከላቸውን ራሳቸው ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከጋዜጠኛ አዲሱ አበባ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ገልጸዋል።
"…አሁን ደግሞ ከብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጋር ይቀራረባሉ ተብለው ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዓለሙ የሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሲኖዶስ አባል፤ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያና አካበባቢው ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የሲኖዶስ አባል በተገኙበት ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትእዛዝ እንደወጣባቸው የአገዛዙ ልሣናት መለፈፍ ጀምረዋል። ሁለቱም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአሁን ወቅት በአሜሪካ ሀገር የሚገኙ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሲል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ማዘዙንም አያይዘው ገልጸዋል።
"…መዘጋጀት ነው እንጂ አይደለም መከሰስ፣ መታሠር 7ተኛውን የኦሮሞ ፓትርያርክ ለማሾም እስከ ማረድ ሊደርሱ እንደሚችሉ ይገመታል። የዘሪሁን ሙላትና የዳንኤል ክብረት ምክረ ሓሳብ እስከዚህ መድረሱም ተሰምቷል።
"…ይሄ ከወዲሁ ሌሎቹን ማሸማቀቂያ መንገድ መሆኑ ነው። አስቀድሞ ተጠንቀቁ፣ አይቀርላችሁም እና ከሕዝብ ጋር ሁኑ ብንላቸው አልሰማ ቢሉንም አሁን በመጨረሻ እያስፈራራቸው አይኑን አፍጥጦ፣ ጥርሱንም አግጥጦ መጥቶባቸዋል። ከላይ ጀምሮ ሊዠልጣቸው ነው። አዛኜን ድብልቅልቁም ሊወጣ ነው።
• ይደፈርሳል ግን ይጠራል።
መልካም…
"…ምስጋና ለወፎቼ ይድረስ እና ሁላችሁም ርዕሰ አንቀፁን በሚገባ በጥሞና እንዳነበባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ቀጥሎ የሚሆነው በርዕሰ አንቀፁ ላይ መልስ ለመስጠት፣ አስተያየታችንም ለማቅረብ ጉዳዩ ያገባናል፣ ይመለከተናልም የምትሉ ብቻ አስተያየታችሁን እንድትሰጡ ትጋበዛላችሁ። ነገርየው የማይመለከታችሁ ግን በቃ ባላየ፣ ባልሰማ ጮጋ፣ ዝም፣ ጭጭ ብትሉ ይመከራል።
"…ጀምሩ…
"ርዕሰ አንቀፅ"
…የወፎቼ ደብዳቤው ሲከፈት…
"…የመጪው የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በኦሮሙማው አገዛዝ ከፍ ያለ አጀንዳ ተይዞለታል ነው የሚሉት ወፎቼ። የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገቡ ተከልክለዋል። መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ አፋር በረሃ ተወርውሯል። የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን አስቀድመው በማሰር አሸማቅቀዋል። የተለያዩ ማኅበራት አመራሮችን ከወዲሁ ወደ ዘብጥያ አውርደዋል። ኦሮሙማዎቹ።
"…አሁን የሚቀረው ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንደራሴ፣ በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ምትክ የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ፣ በመሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ምትክ ጸሐፊ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን አንሥቶ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሾም ብቻ ነው የሚቀረው ነው የሚለው የወፎቼ መረጃ። ይሄንን ከፍ ያለ የኦሮሙማ ሴራ ከወዲሁ በመንቀዥቀዥ ሊያሰናክሉ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ አንድ መነኩሴ (በአባ ህፃን) ላይ እና ምን አልባትም ወንጀል የተገኘባቸው እንደሁ ተብሎ በአንድ ሊቀጳጳስ (በብፁዕ አቡነ አብርሃም) ላይ የእስር ማዘዣ ከፍርድ ቤት አስወጥተው በፖሊሶች እጅ እንዲቆይ መደረጉም ታውቋል። አስቀድሞ በሌብነቱ የታሰረው ቀውሲ በላይ መኮንንም ትናንት በፍርድ ቤት የዋስትና መብት መከልከሉ እና እንደ ዐማሮቹ አዋሽ አርባ ሳይሆን ማታ ማታ ከሚስቱ ጋር እያደረ ቀን ቀን በፎሊስ ጣቢያ እንዲውል መደረጉም እነ አቡነ አብርሃምን እና ሌሎችንም አባቶች ሁሉ ለማሰር ዝግጅት ማለቁን ጭምር ያመለክታል ነው የሚሉት ወፎቼ።
"…ከአቡነ ሩፋኤል ጋር በመገናኘት ይሄን ሴራ ለመጎንጎን በዳንኤል ክብረት በኩል ተጠቁሞ ነገሩን ያሳልጥ ዘንድም የሱሉልታው ነዋሪ ሥራ አጡ፣ ተደብቆ የሰቀቀን ኑሮ ኗሪው፣ ኮፍያውና ጫማው በላዩ ላይ የከረፋው የብልጽግና አቃጣሪ ትግሬንና የዓባይ ማዶ ሰዎችን ሳልበቀል ብቀር ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ ባዩ ዶፍቶር ሰውበሰው ተጫነ ወይም ዶሮ ዘሪሁን ሙላትን የቤት ኪራይ፣ የምሳና የራት ተችሎት የተመደበ ሲሆን ሥልጣኑ ከትግሬና ከአባይ ማዶ ሰዎች ወጥቶ ለሸዋና ለወለጋ ኦሮሞ መሰጠት እንዳለበት መወሰኑም ነው የሚሰማው። ከመንግሥት ለአቡነ ሩፋኤል የአርቴፍሻል ኢንተለጀንሱ አቶ ወርቁ ጋቸና ቪ8 መኪና የመደበላቸው ሲሆን ለአቡነ ሩፋኤል የተመደበው የመኪና ታርጋም የተባበሩት መንግሥታት ታርጋ፣ የእርዳታ ድርጅት ታርጋ፣ የቀይ መስቀል፣ የመንግሥትና አንዳንዴም ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የሚጠቀምባቸው ታርጋዎች እንደሚሰጣቸው ታውቋል። አቡነ ሩፋኤል እና ዶፍቶር ዘሪሁን ሙላት ኮተቤ መዳረሻ በሚገኘው አራራት ሆቴል እየተገናኙ እንዲመክሩ መመቻቸቱ እና በዚያም እየተገናኙ እየመከሩ እንደሆነ ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያሳየው።
"…በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የቅዱስነታቸው እንደራሴ፣ እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን ራሳቸው ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልና በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ ባሳዩት አቋም እና በወሰኑት ውሳኔ መሰረት በአገዛዙ ልብ ሞገስን ያገኙትና "ልትፈርስ፣ ልትሞት 50 ዓመት ለቀራት ቤተ ክርስቲያን ምንድነው እንደዚህ መጨነቅ?" አሉ ተብሎ በሚነገረው ዝነኛ ንግግራቸው የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ዘአሜሪካም በተጠባባቂ እንደራሴነት እንዲያዙ መወሰኑም ተሰምቷል። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የታጩ ሲሆኑ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ራሱ አቡነ ሩፋኤል መታጨታቸው ነው የሚሰማው። አቡነ ሩፋኤል ግን እነደራሴነቱን ካጡ በዋና ጸሐፊነት ሳይሆን ለኮቴ ብቻ 45 ሺ ብር አበል ወደሚያስገኘው የአዲስ አበባ ዋና ሥራ አስኪያጅነት ይመደቡ ዘንድ በሚገፋፉ የአዲስ አበባ ማፍያዎች መንታ መንገድ ላይ መቆማቸው ነው የሚነገረው። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሊቀጳጳስነት አበሉ ብቻ 45ሺ ብር ነው። ይሄን ዘረፋም አይገልጸው።
"…የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ይሄው ዕቅድ ተግባራዊ እንደሚሆን የተወሰነ ሲሆን በአርተፊሻል ኢንተለጀንሱ አቶ ወርቁ ጋቸና አጋዥነት አቡነ ሩፋኤል በሁሉም አባቶች ቤት እየዞሩ እንዲያስፈራሩ ሙሉ ሥልጣን እንደተሰጣቸውም ነው የተሰማው። ከአቡነ ሩፋኤል በተጨማሪ በስም የተጠቀሱ 7 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቅጥረኛ የሆኑ ዋና ጸሓፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆችና የአድባራት አስተዳዳሪዎችም ወደ ቅስቀሳ ሥራው እንዲገቡ የተደረጉ ሲሆን በቅርቡም በአቡነ ሳዊሮስ ሃገረ ስብከት በወሊሶ ለምክክር እንደሚሄዱ ለዚህ ሴራ ከተመረጡት አንደኛው በስካር መንፈስ ሲበጠረቅ ቀድተውት መረጃውን አድርሰውኛል። ይሄ እንግዲህ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ለእያንዳንዱ ብፁዓን አባቶች በየማረፊያ ቤታቸው አንዳንድ በግ በፖስታ ከታሸገ 25 ሺ ብር የሰጡትን የደጅ መጥኛ ብር አይመለከትም። አቡኑ እንደራሴነቱ ካልተሳካ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዳይነሱ አዳነች አበቤ ከየማነ ጋር ዋጋ እንደሚከፍሉም ተነግሯል።
"…ሌላው የአዲስ አበባ አስተዳደር ከፌደራል ፖሊስ በተላከለት እና በደረሰው "አስቸኳይ" የሚል ማኅተም ባረፈበት ደብዳቤ መሰረት ክፍለ ከተሞቹ በሙሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና አባ ህጻን በስማቸው የተመዘገበ መሬትም ሆነ ህንፃ ካለ መረጃው ይላክለት ዘንድ አዟል የሚል ደብዳቤ መበተኑም ተመልክቷል። ሌሎቹን ሁሉ ለማስደንገጥ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ማሸማቀቅ እና ቢቻል ወንጅሎ ማሰር አማራጭ የሌለው አትራፊ መንገድ እንደሆነ አውቆና ተገንዝቦ አገዛዙ እንደ ደርግም፣ እንደ ወያኔም ደፈር፣ ጨከን ብሎ እንዲወስን በዶፍቶር ዘሪሁን ሙላት ሰውበሰው ተጫነ ምክረ ሀሳብ እንደቀረበለትም ነው የሚነገረው።
"…እንግዲህ እነርሱ በዚህ መጠን ተሰልፈው ለዘመቻ ከተነሡ፣ እኔ ዘመዴም ደግሞ ለጊዜው ትቼዋለሁ ብዬ ያልኩትን የቤተ ክርስቲያኔን ነገር መለስ ብዬ ለማየት እገደዳለሁ። ያው እንደተለመደው ባለጌ ባለጌም መጫወት እጀምራለሁ ማለት ነው። ባለጌ ብቻ አይደለም እንደ እብድ ስድ ሁሉ ነው ሆኜ የምተውነው። ይሄን ምድረ ሸርሙጣ፣ እምነት የለሽ ዘራፊ ጋንግስተር ሌባ ወንድኛ አዳሪ ጋለሞታ ሁሉ በድፍረት በሙሉ ኃይሌ ወደ መግጠምም እመለሳለሁ ማለት ነው። ወፎቼም በሙሉ ኃይላቸው ሥራ ይጀምራሉ። እኔም እንደዚያው እጀምራለሁ። ይሄን የተቀደሰ እምነት ለማርከስ የሚንቀሳቀሱ ሉጤ ወሴ ወራዳ ቀላጩን ሁላ እጋፈጠዋለሁ። አሸማቅቀዋለሁ። መድረሻ ቦታም አሳጣዋለሁ። በብዕሬ ብቻ እፋለመዋለሁ። የደበቅኩላቸውን፣ ለንስሀ ይጠቅማቸዋል ብዬ የያዝኩትን ሁሉ እንደየአስፈላጊነቱ እለቀዋለሁ። የማንንም እገዛና እርዳታ አልፈልግም። ብቻዬን እኔው አምላኬን ይዤ እፋለማቸዋለሁ። በመረጃ በመሳተፍ የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል መሆን የምትፈልጉም እኔን መቀላቀል መብታችሁ ይሆናል። መንፈሳዊ ፋኖ መሆን የሚፈልግ ከአሁኑ ይቀላቀለኝ። አለቀ።
"…ያን የምታወቅበትን የዘመናት መሃላዬንም ከፍ ባለ ድምፅ በድጋሚ ማሰማት እጀምራለሁ። አዛኜን በሃይማኖቴማ ቀልድ የለም። ሌባ ሁላ። አባቴ ይሙት እበትንህሃለሁ። አሸማቅቅህሃለሁ። መድረሻ ነው የማሳጣህ ምድረ ፈዳላ ኮተታም ግማታም፣ ጥንባታም ሁላ። ተሳደብክ በለኝ አሉህ ደግሞ።… 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
“…እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤” መዝ 78፥65
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
ደብዳቤው ዝርዝር አለው።
"…አርክቴክት ተደርጎ የተሾመው ሰው በሰው ተጫነ ነው የሚለው። የፓትርያርኩ እንደራሴ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከእነዚህ 3 ሊቃነ ጳጳሳት እንዳያልፍ። ሥልጣን ከትግሬና ከዐማራ እጅ እንዲወጣ፣ ከአባይ ማዶ የሚመጡ በሸዋ ኦሮሞና በወለጋ እንዲተኩ ነው የሚለው የርግቦቼ መረጃ።
• በአንድ ሊቀጳጳስና በአንድ መነኩሴ ላይ ፌደራል ፖሊስ የበተነው ደብዳቤም ደርሶኛል። ቆይ እየቀሸርኩት ነው ጠብቁኝም። ደብዳቤውንም እለጥፍላችኋለሁ።
• መጣሁ።