"…አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"1ኛ ቆሮ15፣20
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
• ትዊተር 👉 Twitter: https://twitter.com/MerejaMedia
• በራምብል 👉 Rumble: https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=5Sg_s6sj7M0
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
"…ልብ በሉ…አስተውሉም።
"…የጋሻ ሚድያ ባለቤቱ አቶ ወንደሰን ተክሉ ነው። አቶ ወንደሰን ተክሉ ደግሞ በፎቶ ላይ የምታዩት ከአበበ በለው ፊት ያለው በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀስ ሶዬ ነው። አሁን ሰውዬው ከኬኒያ ወደ ኡጋንዳ እንዲዘዋወር ተደርጓል። አቶ ወንደሰን የእስክንድር ነጋ የእህት ወይም የወንድም ልጅ ነው። የሚደጎመውም በህዝባዊ ሠራዊቱ መሪ በቦስተኑ ዶር አምሳሉ ቡድን ነው።
"…ደግሜ እላለሁ።ጎጃም ውስጥ መኖር ያለበት አንድ የዐማራ የፋኖ አደረጃጀት ብቻ ነው። እስክንድር ነጋም ለዐማራ ለመታገል ከሆነ የወጣው ገብቶ መታገል ያለበት በአንድ የዐማራ የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ እንጂ ፋኖን ለሁለት ወደሚከፍል አጀንዳ ውስጥ መግባት የለበትም። ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለውም የሚፎክሩት ይሄንኑ አንድ የፋኖ አደረጃጀት ለሁለት የመክፈል አቅም እንዳላቸው ሆነው ነው።
"…ደጋግሜ ተናግሬአለሁ አሁንም እናገራለሁ በየትኛውም የዐማራ ክልል ውስጥ ፋኖና ፋኖ ከተተኳከሰ ተጠያቂዎቹ እስክንድር ነጋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው እና ኢየሩስ ናቸው። ግንቦት ሰባቶች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው።
• ፋኖን አትከፋፍሉት። እረፉ። ደግሞ ናና እንዲህ ለምን ትላለህ ብለህ ስደበኝ አሉህ። ሌባ ሁላ…😂
መልካም…
"…ዘወትር የምንጠብቀው አንድ ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። ከምስጋናው በመቀጠል በቀጥታ የምንሄደው እንደ ልማዳችን ወደ ርዕሰ አንቀጽ ነበረ። እሷ ዛሬ አትኖርም። በዚሁ ወደ መወያየቱ እንገባለን።
"…የእስክንድር ጉዳይ ዛሬም ማጨቃጨቁን እንደቀጠለ ነው። ወያኔው ፓስተር ኤድሞንድ እነ ሀብታሙ በሻህን ሰብስቦ ሲያላቅሳቸው ውሏል። ዩሪ ታደሰ አስተያየት ሊሰጥ ቢፈቀድለትም ማእረግና ግንቦቴው ሀብታሙ በስድብ አጥረግርገው ሊያሸማቅቁት ሞክረዋል። ፓስተሩ ይናገር ብሎ ሲከራከርለትም ታይቷል።
"…የእስክንድርም ሆነ የግንቦቴዎቹ መዳኛቸው ዐማራውና የዐማራው ትግል ብቻ ነው። እስክንድርና ግንቦቴዎቹ መመራት ያለባቸው በዐማራው ፋኖ ሥነልቦና መመሪያና ሕግ ነው። በዐማራ መሬት ላይ ለዐማራ ነፃነት ይታገል ዘንድ የሚፈቀድለት የዐማራ ፋኖ ብቻ ነው። አይ አልፍልግም እኔ የምታገልበት መርህ አለኝ የሚል ካለ ወደ ሙከጡሪ፣ አዲዳዕሮ፣ ዳውሮ፣ ጅባትና ሜጫ ጫካ ገብቶ መታገል ይችላል። በዐማራ ቤት፣ በዐማራ ትከሻ ላይ ሌላ ደባል ትግል በዐማራ ሀብት እና ኪሣራ መታገል አይቻልም። እርምህን ታወጣለህ።
"…አይደለም ፓስተር ኤድመንድ ወያኔው ጋር አብይ አህመድ ስር ብትለጠፍ፣ ከቤት ቤት፣ ከጣሪያ ጣሪያ ስትዘል ውለህ ታድራለህ እንጂ ወፍ የለም። ይልቅ በቶሎ ንስሐ ግቡ።
"…እደግመዋለሁ። በዐማራ ምድር አንዲት ደም በወንድማማቾች መሐል ቢፈስ ከአበበ በለው እና ከሀብታሙ አያሌው ራስ አይወረድም። በዚህኛው የሠራዊት ምስረታ ላይ ቀደም ብዬ እስክንድር ነጋ እንደሌለበት የተናገርኩትን ትናንት ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከአበበ በለው ጋር በነበረው ቆይቷ አረጋግጦልናል። ይሄ ማለት እስክንድር ወጥቶ መግለጫ እስካልሰጠ ድረስ ብቻ ነው እንደ ንጹሕ የሚቆጠረው። አለቀ።
"…ለማነሣው ሓሳብ ምላሽ መስጠት እንጂ መሳደብ ትርፉ ኪሳራ ነው።
ልጠይቅ ነኝ…!
…የካንሳስ እና ሚዙሪ አካባቢ ነዋሪዎች በሻለቃ ዳዊት እና በጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ታጋዩ ኋላ ፋኖ በሆነው በታጋይ እስክንድር ነጋ ለሚመራው የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር በከተማቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ኢቨንት አዘጋጅተው ከ60 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ አሰባስበው በተሰጣቸው መንገድ ብሩን ገቢ ያደርጋሉ።
"…ቆይተው የካንሳስና የሚዙሪ ነዋሪዎች ይህን የተሰበሰበ ገንዘብ በምን አገልግሎት ላይ እንደዋለ ንገሩን በማለት ዶክተር አምሳሉን ይጠይቃሉ። ዶክተር አምሳሉ ምን ቢል ጥሩ ነው "ዝም ብላችሁ እመኑን፣ አትጠይቁን። ይላል። ይባላል እንዴ?
"…ሕዝቡም ይህን መልስ ሲሰማ ጥያቄውን ይዞ በከተማቸው ዐማሮችን ሰብሳቢ አቶ ጌታነህ ዓለምን ይጠይቁታል። እሱም ጉዳዩ አሳስቦት የግንባሩን ሰዎች ብሩ የት ገባ ይላቸዋል። አጥጋቢ መልስ ሲያጣ የከተማውን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ከማኅበሩ ይለቃል። የለቀቀበትም ምክንያት ምንድነው ብዬ ስጠይቅ ያገኘሁትን መልስ እንካችሁ።
• አቶ ጌታነህ፦ "…በዶነር ቦክስ የተሰበሰበው ገንዘብ የት ገባ?
• ገንዘብ ያዧ ወሮ ሕይወት አድማሴ ፦ "ይቅርታ በስህተት ወደ አንድ የቻይና ካምፓኒ ገብቶብን ነው።"
"…የእኔ ጥያቄ ለፋኖ ተብሎ አሜሪካን ሀገር የተሰበሰበ ገንዘብ በምን አግባብ ነው ወደ ቻይና ካምፓኒ ባንክ የሚገባው? ይሄ ሐሰት ከሆነ ወጥተው ይሞግቱኝ። ኦዲት አስደርጉ ሲባልስ ታንቀን እንገኛለን ብሎ ጓ ማለት ምን ማለት ነው? ሀብታሙ አያሌው እየመጣሁ ነው ጠብቀኝ። አበበ በለውም እንደዚያው።
•ማርያምን አልፋታችሁም አዛኜን አልኳችሁ…! ቆይ ቻይና ምን አገባት በግንባሩ ገንዘብ…?
"…መልካም…
"…የቪድዮዎቹ ማብራሪያ ወደ በኋላ ጊዜ ሲገኝ ይኬድበታል። ኮማንደር ሀብታሙ ግን ዛቻና ቂጣቸው ገንፍሎ ወጥቷል። በሠራዊታቸው የዐማራ ፋኖን ሊውጡ መዘጋጀታቸውን አልደበቁም። የዌልስ ፋርጎው ባንክ ዶላር እና የባንክ ኦፍ አሜሪካው ዶላር በደንብ እያንዘረዘራቸው ነው።
"…ትናንት ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጋር ይገናኛል ብሎ ያጥረገረገው ሰውዬ ዛሬ ያንኑ ሰካራም ያለውን ሰው የሕዝባዊ ሠራዊቱ መሪ ነህ ብሎ ሲክበው ይታያል። በጎጃም ምድር ደም ከፈሰሰ ተጠያቂው ራሱ ሀብታሙ አያሌው ነው። እስክንድር ነጋም በቶሎ ማብራሪያና መግለጫ ካልሰጠ ከመጠየቅ አያመልጥም።
"…ውይይታችን ይቀጥላል። የበቅሎ ልጆች ተረጋጉ። 😂 …ሓሳብ በጨዋ ደንብ ይንሸራሸር። ተንፒሱ።
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍…ሰርሰሬ አሳር አብልቼ ደም ሳይነካኝ የምወጣ ነኝ እኔ ዘመዴ። አሁንም ያደረግኩት እንደዚያ ነው።
"…አሁን አሸናፊነቴ ታውጇል። የቀሩት ጥቂት በቀቀኖች ናቸው። 100 እና ሁለት መቶ ሰው ቲክቶክ ላይ ሰብስበው ዋይ ዋይ የሚሉ ምስኪኖች ናቸው የቀሩት። ለምሳሌ ከእነዚህ ከቀሩት ውስጥ የተለየ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር የማልነካቸው አሉ። በጣም ሲበዛ ወዳጆቼ የሆኑ አፍቃሬ እስክንድር የሆኑ ናቸው የቀሩት። ለምሳሌ እስራኤል የነበረው እና አሁን ካናዳ ያለው ወንድሜን ዮሴፍ ይጥናን እንዲች ብዬ አንዳች ነገር አልናገረውም። አሱ ለዐማራ ትግል ያበረከተውን አስተዋጽኦና ተጋድሎ የማውቀው እኔ ነኝ። ሰሞነኛ ታጋይ አይደለም። እኔ ሕዝብ ይሰማኛል፣ መቀደድ፣ መበጥረቅ እችላለሁ ብዬ አፌን ልከፍትበትም አልሻም። ብዙዎቻችሁ እየሰደበህ ነው ብላችሁ ቆርጣችሁ የላካችሁልኝን አይቼዋለሁ። ነገር ግን እኔ የሚገባኝ ነገር ይገባኛል። ዮሴፍ ይጥና እስክንድር ነጋን ከልቡ የሚወድ፣ የሚያከብር ሰው ነው። እና እኔን ደውሎ ቢያናግረኝ ምላሽ የሚያገኘውን በስሜት ወጥቶ ሆድ ለባሰው ማጭድ አውሰው እንዲሰድበኝ አደረጉት እንጂ ሌላ ጉዳይ የለውም። እስክንድር ወጥቶ መግለጫ ሲሰጥ ሁሉ ነገር ያቆማል።
"…ሀብታሙ በሻህ ከስሯል። አይ አም ፕራውድ ጋላ ነኝ ብሎ በገዛ እጁ ተበጥርቆ አሁን የፈለገ ነገር ቢል ማን ሊሰማው? ማን ሊያዳምጠው? ሱሬ ይሄን ዓይነቱን ሰው " He's already dead" ሲል ሰምቻለሁ። የሞተ፣ ያበቃ፣ ያለቀለት ሰው ነው እንደማለት መሰለኝ። ሌላኛው ሀብታሙ የሚባል የሀረርጌ ኦሮሞም አለ፣ ከሳሚ ቅማንቱ ጋር ሆኖ ዋይ ዋይ የሚል። ሀብትሽ ፈሪ ኦሮሞ ነው፣ እንደ ቅማንቴው ሳሚ መገለጥ አይፈልግም። ሌላኛው የካዛንችሱ ማእረግ ነው። ምስኪን የጀርመን ስደተኛ ወንድሜ ነው። ምንም ቢል የማልቀየመው ምስኪን ተብታባ ወንድሜ ነው። ምስጢረኛዬ፣ የመረጃ ምንጬ፣ እናም አፍቃሬ እስክንድር ስለሆነ እሱም የፈለገውን ቢል አልቀየመውም። የአዲስ አበባ የሸገር ልጅ አይደል? እስክንድር መግለጫ ሲሰጥ፣ ሥርዓት ሲይዝ አብረው ሥርዓት የሚይዙ ስለሆነ በእነዚህ የአዲስ አበባ የአራድዬ ልጆች የሚቀየም ልብ የለኝም። ይንበጫረቁ።
"…እርግጠኛ ሆኜ መናገር ባልችልም ትናንት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ሰጠ በተባለው የሕዝባዊ ሠራዊት በጎጃም መግለጫ ላይ የእስክንድር ነጋ እጅ ያለበት አይመስለኝም። አይመስለኝም ነው ያልኩት። ምክንያቱም እስክንድር ነጋ ሌላ ግሩም ውሳኔ ላይ መድረሱን እና ማዕበሉን ሁሉ ፀጥ የሚያሰኝ ውሳኔ ለመወሰኑን መወሰኑን በቅርብ ስለማውቅ፣ ስለሰማሁም ነው። እስክንድር በሸዋ የደረሰበት ውሳኔ ያስደነገጣቸው ብአዴኖች ናቸው የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ዘመድ፣ ከስድስት ወር በፊት አየር ኃይል ለፓይለቶች ስልጠና ይሰጥ የነበረውን ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን፣ ብአዴን ሚሽን ሰጥቶ የሌለ እና ጎጃምን ለሁለት ይከፍልልናል ብለው ያሰቡትን መግለጫ እንዲሰጥ ያስደረጉት። ከትግሉ ወጥቻለሁ ብሎ፣ በቅርቡ ታምሞ የተኛን፣ እድሜ ማራዘሚያ የሚወስድ ሕመምተኛን ሰው ከአልጋ አስነሥተው መግለጫ ያሰጡት ሆን ብለው ነው የሚሉም አሉ። ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ሁሉን ይመረምራል እንጂ በነገሩ እስክንድር ያለበት አይመስለኝም። ቢኖርበትም ግን ታሪኩ ይበላሻል እንጂ ምንም አይፈጠርም። በዚህ ምክንያት ለሚፈሰው ደም ግን ኃላፊነቱን የሚወስደው እስክንድር ይሆናል። ይመርራል ግን ዋጠው።
"…የእነ ዘመነ ካሴ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ቢሆን በፊት እነ ሻለቃ ዝናቡ ይሄዱበት በነበረው ፍጥነት እስካልሄዱና የባህታዊ፣ የቅዱስ ቅዱስ፣ የሚድያ ላይ ፕሮፓጋንዳ ላይ ብቻ ተወስነው ከቀሩ አይደለም በብአዴን ድጋፍ በማስረሻ ሰጤ ስም የሚመጣው ሕዝባዊ ሠራዊት አይደለም የራሱ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ለለውጥ ይነሣባቸዋል። በተለይ ደግሞ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ላይ ከሕዝብ የሚጎርፉ ቅሬታዎች በአመራሩ በጊዜ ካልታረመ በቅርቡ ከሩቅ በሚመጣ ኃይል ሳይሆን ከውስጥ በሚነሣ ኃይል ችግር ይገጥመዋል። ግብርን፣ ያለ አግባብ እስርን፣ በቂም በቀል፣ በድሮ ፀብ፣ የሓሳብ ልዩነትን ባለማስተናገድ፣ ጥቂት አምባገነናዊ ባሕሪን በተላበሱ ግለሰብ አመራሮች ስህተት ችግር ይገጥማቸዋል። ሆደ ሰፊ፣ ዲሲፒሊናቸው የተመሰከረላቸው፣ መጡልን እንጂ መጡብን የመይባሉ መሆን አለበቸው። በጎጃም በዐማራ ፋኖ ስም ጠላት ያሰማራቸው ወንበዴዎች እንዳሉ ሁሉ በራሱ በጎጃም ፋኖ አማካኝነት የሚፈጸሙ ስህተቶች፣ አንባገነንነቶች አደጋ እንዳይፈጥሩበት እሰጋለሁ። ይሄ በጎጃም ብቻ ሳይሆን በጎንደርም፣ በወሎና በሸዋም ካለ በፍጥነት ታርሞ ወደፊት መገስገስ ያለበት አለበት ባይ ነኝ። አሁን የእነ ዘመነ ፋኖ ቆፍጣና፣ ወታደር ካልመሰለ፣ እንደ ወታደርም ቆራጥ መሆን ካልጀመረ፣ በውይይት ማመን ትቶ ጥያቄ የሚጠይቁትን ወደ ማሰር ከገባ ስንዝር፣ ጋት አይራመድም። አኩራፊ ይነሣበታል። ችግር ይፈጠራል። በፍጥነት እርማት ይወሰድ።
"…ትግሉ ቀጥሏል። የእነ መሳይ መኮንን አንከር ሚዲያና የእነ ሀብታሙ አያሌው ምኒልክ ሚዲያ በመረጃ ቴሌቭዥን ላይ የሚጠቀሙ ጋዜጠኞችን በሙሉ "ከእኛ ጋር ሥሩ" እያሉ መወትወት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ስደቱን፣ ትግሉን ከእስክንድር ጋር የጀመረ፣ ውጣውረዱን፣ ስቃዩን አብሮ ከእስክንድር ጋር የተጋፈጠ፣ ከእስክንድር ጋር እስከ ቀራንዮ ብሎ የወሰነ ስለሆነ በእሱ ላይ ምንም የከፋ ጥያቄ የለኝም። እንዲህ ዓይነት ቆራጥ፣ ቀን አይቶ የማይከዳ፣ ደግሞም ለጥያቄዎች ሁሉ በትሁት አንደበት፣ በእርጋታ የሚመልስ፣ ምንም ይሁን ምንም በጽናት እስከ መጨረሻው ሓሳቡን የማይቀይር፣ የማይወላውል ቀጥ ያለ የማይልመጠመጥ ሰው ለእኔ ጀግናዬ ነው። የፈለገ የስህተት መንገድ ላይ ቢሆን ወጥ አቋም ያለው ሰው ለእኔ ጀግና ነው። አከብረዋለሁ። በኡጋንዳም ያሉት ከመረጃ እንዲወጡ ያለተደከመ ድካም የለም።
"…ትናንት ሀብታሙ አያሌው የግንባሩ ገንዘብ የበሉ ካሉ ይጠየቁ። አብረን እንጠይቃለን ሲል ተደምጧል። ዌል እንግዲክ እንዲል አትሌት ኃይሌ ዌል እንግዲክ እኛም ወደ መጠየቁ እንገባለን። በኢትዮጵያ ትንሣኤ ማኅበር ለግንባሩ የተሰበሰበ ከዌልስ ፋርጎ፣ እና ከሌሎችም የግንባሩ ባንኮች ወደ ኢትዮ 360ዎች የባንክ አካውንት በተጨባጭ እስከ 200 ሺ ዶላር መግባቱ ተረጋግጧል። አልገባም ካሉ ወጥተው ይናገሩ። ሻለቃ ዳዊትም ያስረዳ። ይሄን ብር አውጥተው አይደለም ጋዜጠኛ ፋኖስ እየገዙበት አይደለምን? እሱን ስለገንዘቡ የአሜሪካ መንግሥት ይጨነቅበት። አቶ ኃይሌ የተባለ ሰው ከሂውስተን የላኩት 100 ሺ ዶላር የት ገባ? እነ አቶ ኃይሌ ከሂውስተን የላኩት መቶ ሺ ብር ወደ ቻይና ካምፓኒ የተላከው ለምን እንደሆነም የእስክንድር ገንዘብ ያዥ ወ/ሮ ሕይወት አድማሴ ትጨነቅበት። ሻለቃ ዳዊት የግንባሩ ገንዘብ የተሰበሰበው በኢትዮ 360 የባንክ አካውንት ላይ ነው ብለው አስቀድመው የተናገሩትንም እሱንም አይአርኤስ ይጨነቅበት። በባንክ ኦፍ አሜሪካ የታገደው አንድ ሚልዮን 28 ሺ ዶላርም ይለቀቅ አይለቀቅ የሚታወቅ ነገር የለም። ከተለቀቀም የት እንደደረሰ የማስረዳት ሓላፊነቱ የሚወድቀው በአቶ ሙልጌታ እና ወ/ሮ ሕይወት አድማሴ ጫንቃ ላይ ነው። በዚህ በግንባሩ ገንዘብ የተገዙ ፋኖዎች መገዳደል ከጀመሩ አደገኛ ነገር ነው። ማስረሻ ሰጤን ትናንት የጋሻ ሚዲያ ባለቤቱ የእስክንደር የአክስት ነው የአጎት ልጅ አቶ ወንደሰን ተክሉ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
መልካም…
"…ዛሬ አርፍጄ አምሽቼ፣ አርፍጄ ተኝቼ፣ አርፍጄ በመነሳቴ የምስጋና ሰዓታችንን አርፍደን ለመጀመር ተገድደናል። ሆኖም ግን እንደተለመደው የጌታንም ትንሣኤ ያውጅ ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወዴት ነው? አዎ ወደ ርዕሰ አንቀጻችን።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የሚመለከተው ሰሞኑን እንወጣው ከማይመስለው ከከባዱ ሱናሚ ወደ የቧንቧ ውኃ ጠብታ ነጠብጣቦች መሸጋገራችንን የምንመለከትበት፣ አይነኬ አድርገው፣ በሌለ ከፍታም ላይ ራሳቸውን አስቀምጠው የቆለሉትን፣ እንደ ጭድ ክምር፣ እንደ እምቧይ ካብ የናድነበትንና እነዚያ ቀናትም አልፈው ዛሬ ውርውር የሚሉ ድንቢጦችን የምናይበት ሰዓት ላይ መድረሳችንን የምናይበት ነው።
"…በሀብታሙ አያሌው አዲሱ የሕዛባዊ ሠራዊቱ ካርታ ላይ እስክንድር ነጋ አለበት ወይ? የሚል ጥያቄም የምናይበት፣ ምን አልባትም እነ ሀብታሙ እስክንድር ከእጃቸው ሊወጣ ሲል ትናንት አረቄያም ብሎ የሰደበውን ማስረሻ ሰጤ የእድሜ ማራዘሚያ እየወሰደ ሕመሙን ከሚያስታምምበት አልጋ ላይ አምጥቶ ያስለፈለፈው ያለምክንያት አይደለም የሚሉ መተርጉማንም ትርጓሜም እናያለን።
"…በጎጃምም ይሁን በሸዋ፣ በጎንደርም ይሁን በወሎ የሕዝባዊ ሠራዊት በሚባል ቡድን ምክንያት ፋኖዎች ቢመታቱ፣ ደምም ቢፋሰሱ የዚህ ተጠያቂው በዋነኝነት ሀብታሙ አያሌው ሲሆን የእሱ የግል አሽከር አገልጋዩ ወሮ ኢየሩሳሌም ተ/ጻድቅም ተጠያቂ ናት።
"…ጋዜጠኛ ወግደረስ የመረጃ ቲቪ የዐማራ ክልል ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን ለጋዜጠኛው መረጃ ቴቪ ከነ አጃቢዎቹ በወር ደሞዝ ይከፍለው ነበር። እሱን ነው ሀብታሙ አስኮብልሎ የወሰደው። መረጃም ውሉን አቋርጧል።
• ይሄንና ይሄን የመሰለ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
"…እድሜ ለወፎቼ የገዳዬን 😂 …ሙሉ አድራሻ፣ ለነ ሙሉ ስሙ። ዕድሜው፣ ወቅታዊ ስልኩ ጭምር አግኝቼዋለሁ። እሱ ከቀረ እኔ ራሴ እሄድለታለሁ። ለአስተርጓሚነት ሱሬን አስቸግረዋለሁ።
"…ወደ ዋናው ቁምነገር እንምጣ።
"…እርግጥ ነው ለዘመናት የማይነካ ስፍራን ነክቻለሁ። እንደ ታቦት፣ እንደ መቅደስ የሚታዩ ግለሰቦችና ቡድኖችን አደባባይ አስጥቼአቸዋለሁ። ማፍያው ቡድን ሃይማኖት የለውም። አብዛኛው በሀገሩ ላይ ቂም የያዘ እልኸኛና በቀለኛ ስደተኛ ነው። ሀገሩን በአፉ የሚጠራ ግን በልቡ የሚረግማት ጨካኝ ነው ሲባል ጭካኔው እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም።
"…ይሄ ቡድን ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ ሲቃወም የመጣ ቡድን ነው። ኔትወርክ አለው። ሲፈልገው ቅንጅት ይሆናል። የልደቱ አያሌው ቲፈዞም ይሆናል። የበየነ ጴጥሮስ፣ የመራራ ጉዲናም ደጋፊ ይሆናል። በቀለ ገርባን፣ ጃዋር መሀመድን አዝሎ ለመሮጥ ሁኔታዎች ብቻ ነው የሚጠብቀው። አቢይ አሕመድ እግር ስር ለመደፋት ሰከንድ አያስብም። ወያኔን ብቻ እየረገመ ለወያኔ አባት ለሻአቢያ ሲገረድ ቅሽሽም አይለው።
"…ኑሮው በቅፈላ ላይ የተመሰረተ ነው። ሳይሠሩ፣ ምንም ዓይነት የሥራ ታሪክ የሌላቸው ግን አሁን የሪልስቴት ባለቤት የሆኑ አሉ። ቀሪ እድሜአቸውን በኢትዮጵያ ድሆች፣ በተፈናቃይና በጦርነት፣ አሁን ደግሞ በዐማራ ስም ዘርፈው ያስቀመጡትን ለመብላት እንኳ ሆዳቸው በቃኝ አያውቅም። ፔርሙዳ ሆድ ሁላ።
"…አሁን ደግሞ አምና ኖሞር ላይ ሰልፍ የወጡትን ዐማሮች ፖሊስ ጠርተው ያሳሰሩ ገተቶች ዓይናቸውን በጨው ታጥበው በዐማራ ፋኖ ስም በእስክንድር ነጋ ስር ተኮልኩለው ብቅ አሉ። እኔ እነዚህን የሰው ቡልጉ ጭራቆች ነው የመታኋቸው። 95% ደብድቤአቸዋለሁ። ከዚያ በመቀጠል በፋኖ ስም ሀብታም የሆኑትን፣ ኤክስቫተር ገዝተው፣ ቪላ ሰርተው ያሉትን ወደ መቀንደሹ እሄዳለሁ።
•✍✍✍
መልካም…
"…አሁን ደግሞ በርዕሰ አንቀጹ ላይ የተሰማችሁን ስትፈልጉ ተችታችሁ የመተንፈስ ተራው የእናንተ ነው። ግን በጨዋ ደንብ።
• 1…2…3…ጀምሩ…
“ርዕሰ አንቀጽ”
"…ሲጀመር እኔ ዘመዴ ከሀብታሙ አያሌውም ሆነ ከአበበ በለው ጋር፣ ከእስክንድር ነጋም ሆነ ከማስረሻ ሰጤ ጋር ከሌሎችም ጋር ቢሆን የግል ጠብ የለኝም። አይኖረኝምም። በሚስትም፣ በርስትም የሚያጣላን ነገር የለም። የሓሳብ ልዩነት መቼም ይፈጠራል፣ የሓሳብ ልዩነቱ አንዳንዴ በውስጥ ይፈታል፣ በውስጥ ለመፍታት ያልተቻለው ደግሞ እንዲህ አደባባይ ይወጣና ሕዝብ አዳም ፊት ለአድማጭ ተመልካቹ ይቀርብ እና የቀረበው ሓሳብ ደጋፊና ተቃዋሚ አፍርቶ ከሁለት ጎራ ይቆሙና እነዚያ ኃይላት በዚያ በቀረበ ሓሳብ ላይ ተጠዛጥዘው ባሻቸው መልክ ወቅጠው፣ ፈትገው፣ ፈጭተው፣ ዱቄት አድርገው፣ አቡኩተው ይጋግሩታል። አለቀ። የቀረበው ሓሳብም እንዲሆን የተፈለገው ዳቦ ወይ እንጀራ ሆኖ ለአቅመ መብል እንዲደርስ ነው።
"…የእኔ ሰሞነኛ አጀንዳዎች ምንድናቸው? ያልን እንደሆነ በጣም ግልፅና ግልጽ ናቸው። እስቲ አንዳንዶቹን ከብዙ በጥቂቱ ተራ በተራ እንመልከታቸው።
፩ኛ፦ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ የሚገኙ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች የየራሳቸው አንዳንድ የፋኖ አደረጃጀት ይኑራቸው። ሌላ አምስተኛ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ የሚባል አደረጃጀት መኖር የለበትም። አራቱ ጠቅላይ ግዛቶች መጀመሪያ ሁለት ሦስት የነበረውን አደረጃጀቶቻቸውን ወደ አንድ ካመጡ በኋላ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲደርስ ደግሞ አራቱም ጠቅላይ ግዛቶች በጊዜአቸው ወደ አንድ የፋኖ ማእቀፍ ውስጥ ይገባሉ። ወደ ግዙፉ የዐማራ ፋኖ። ስለዚህ አምስተኛው ግንባር፣ ድድ፣ ጥርስና አገጭ የሚባለው አደረጃጀት ጣልቃ የገባ ነውና ወደ አንዱ ይጠቃለል ነው ያልኩት።
• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን ከመሬት ተነሥተው ፎገሉ። ይሄ የእኔ ሓሳብ ምኑ ተጠልቶ እንዲህ ጓ እንዲሉ እንዳደረጋቸው ግን ጌ"ጌታቸው" ይወቅ።
፪ኛ፦ ለዐማራ ፋኖ ተብሎ የሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ የእስከዛሬው ሚልዮን ዶላር በኪሳራ ይታይ እና ከዚህ በኋላ ያለው አካሄድ ግን ተጠያቂነትን በሚያመጣ መልኩ ይሁን። ደግሞም ከእንግዲህ በኋላ ራሳቸው የፋኖ አመራሮች በሚወክሉት ሰውም ሆነ ቡድን በኩል ገንዘቡ ይሰብሰብ እንጂ ማንም እየተነሣ በዐማራ ስም ገንዘብ እየለመነ የእከኩ ማራገፊያ አያድርግ፣ ሥርዓት ይበጅለት። 70 የዐማራ ማኅበራት ፈርሰው አንድ ብቁ የዐማራ ማኅበር ይመሥረት ነው ያልኩት።
• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን ይሄም ጉዳይ ሲነሣ እንደ እብድ ነው ያደረጋቸው። እንዲያውም አንደኛው በላተኛ፣ ኑሮውን በዐማራ ችግር ላይ የመሠረተ፣ ሲያዩት፣ ሲሰሙት የዐማራ ተቆርቋሪ የሚመስል ሰው በድፍረት ምን ቢል ጥሩ ነው። "እሺ እንዲህ ከሆነ እኛ ምን ሠርተን ልንበላ ነው?" ሠርተህ ብላ ኦንድሜ። ድንጋይ አፈር አባህ ያስበላህ የአባቴ አምላክ። አንተ በዐማራ ስም የዐማራን መከራ እያራዘምክ ከዚያ በምታገኘው ገንዘብ ፏ ሽር ብትን ብለህ ያለ ስጋት አማሪካ ትኖራለህ። የዐማራ ችግር ከተፈታ ጦምህን እንደምታድር ነው የሚሰማህ። ኧረ ወዲያ ያንተስ ነገር። ስትንበጫበጭ ውለህ ታድራለህ እንጂ የዐማራ ትግል ከግለሰብ አናት ወርዶ ተቋማዊ ይሆናል። የእናንተን ምላስ ፈርተው ከጓሮ የተደበቁ ምርጥ የዐማራ ልጆችም እናንተ ገለል ስትሉላቸው ወደፊት መጥተው ሥራቸውን ይጀምራሉ። እኔ ደግሞ በብዕሬ እናንት ሾተላዮቹን እጠርጋችኋለሁ።
፫ኛ፦ ለግንባሩ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ከምን ደረሰ? ግንባሩ ተቋቋመ ተብሎ በታወጀ ማግስት ገንዘቡ ተሰብስቦ ሲያበቃ የግንባሩ መፍረስ ሳይነገረን እንዴት በአበበ በለው እና በሀብታሙ አያሌው አማካኝነት ሠራዊቱ የሚል አደረጃጀት መጣ? አበበ በለው የግንባሩን ሰው ሻለቃ ዳዊትን ለምን አባረረ? የአበበ በለው ሥልጣን እምን ድረስ ነው? የግንባሩም ሆነ የሠራዊቱም መሪ እንዴት እስክንድር ነጋ ሆኖ ተመረጠ? ማነውስ የመረጠው? የግንባሩም ሆነ የሠራዊቱ ሠራዊታቸው የት ነው ያለው? አንድ ሰው ብቻውን እንዴት ሰራዊትም፣ ግንባርም ሊሆን ይችላል? ወዘተረፈ የሚል ጤናማ ጥያቄ ነበር ያነሣሁት።
• ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግን የሌለ ጓ አሉ። ስለ ገንዘቡም ሆነ ስለ ግንባሩ አንተ ምን አገባህ? አበበ በለውን፣ ሀብታሙ አያሌውን፣ እስክንድር ነጋን አትናገርብን። እነሱ ዐማሮች ናቸው። የፈለጉትን ያድርጉ። አንተ የሐረርጌ ቆቱ ነህ አያገባህም ወዘተ የሚል ለፍዳዳ ዘጊ ቃል ይዘው ወደ አደባባይ ወጡ። ማን እንደሆንኩ የት አባህ ታውቀኛለህ? ምደረ እንቦጭ ሁላ። እኔማ አንተ ዐማራነትን ተፀይፈህ ስትንበጫበጭ በነበረ ጊዜ ዐማራ በዐማራነቱ ይደራጅ ብዬ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ስጮህ ነበር። የሆነው ሆኖ ስለ ግንባሩ መምከን፣ ስለ ሠራዊቱ መፈጠር የሚተነፍስ፣ የሚያስረዳም፣ የሚያብራራም ጠፋ። "ጭራሽ ትግሬው እስታሊን ነፍሴ ለዐማራ ለፋኖ ጠበቃ ሆኖ ከች አለ። እስክንድር የአሜሪካ የሞቀ ቤቱን ጥሎ ነው በረሀ የገባው። እስክንድርን መሪ አድርጎ የማይቀበል ዐማራ፣ ዐማራ አይደለም" ብሎ እርፍ አለ ወለይ። እኔ ግን በጥያቄዬ ቀጠልኩ። የእነ GGጂጂግግ እና የእነ TGቲጂትግ መንበጫበጭ ለአፍታም ያህል ከጉዞዬ አላቆመኝም።
፬ኛ፦ ሌላው ያነሣሁት ጥያቄ ምኒልክ ቴቪን ለመመሥረት መረጃ ቲቪን ለማፍረስ የእስክንድር ጠበቃ ነን፣ እስክንድር አማላጃችን ነው። የዐማራ መዳኛ መንገዱ፣ ሕይወቱም በእስክንድር ነጋ እጅ ነው የሚሉት የግንባሩ ሰዎች እና እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እየሩስ ተክለ ጻድቀ እና አበበ በለው የሄዱበት ያረፈደ የድሮ ስግጥ ያለ መሰሪ አካሄድን ነው የተቃወምኩት። ሚዲያ መቋቋሙ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ ገና ለገና የዩቲዩብ ሱፐርቻት ገቢ ስለሌለን የራሳችንን ጣቢያ ከፍተን ገቢ እንፍጥር ብለው ላወጡት ፕሮጀክት ሲባል በነፃ በነፃነትም ያቀርቡበት የነበረውን ፕላትፎርም ተመራርቆ፣ መለያየት ሲቻል አዋርዶ፣ አፍርሶ፣ አኮስሶ መሄድ ነውር ነው ያልኩት።
• በዚህም ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ጓ ነው ያሉት። ኤልያስ ክፍሌን፣ ግርማ ካሣን እና እኔ ዘመዴን የሌለ ሞለጩን። አዋረዱን። ሰደቡን። በተለይ ሽመልስ የተባለ ጎጋ እንደ ቁራ ሲያንቋርር የሚውል ሞኝባገኝ እና አቶ ወንደሰን ተክሉ የእስክንድር ነጋ የእህት ነው የወንድም ልጅ ነው የተባለ እና በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀስ ደባል ሱሳም የትልቅ ትንሽ ቅሌታም ሰው ከፊት አድርገው፣ እነ ወዳጄና ከምር እናቴ ወሮ ሸዊት፣ በኒውዮርክ አስተናጋጄ፣ ተቀባዬ ወሮ ማርታ፣ እነ ዶክተር አምሳሉ፣ እነ አቶ ክንፉ በሚወረውሩለት ዶላር እንደ አበደ ውሻ ሲጮህብን ከረመ። ሰውን በማሸማቀቅ ከእውነት ለማውጣት፣ ለማራቅ ይሄዱበት የነበረው የድሮ መንገድ ለዘንድሮ አላዋጣም። በተለይ አቶ ሽመልስ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶችን በፎቶ አውጥቶ የሠራው ነውር እጅግ ቀፋፊ ነበር። የለንደን ፋኖ የመወያያ ግሩፕም የእነ ጆፌ አሞሮቹ የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞቹ እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ግሩፖች መጠራቀሚያ ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ነውሮች በፔጃቸው ሲለጠፉ አለመታገሳቸውን ሳላደንቅ አላልፍም። ከስር ከስር እግር በእግር እየተከታተሉ ነው ሲደልቱ የማየው። ይሄም አንድ ለውጥ ነው። በተለይ 40 ዓመት አሜሪካ ኖሮ ዘንድሮም ላልሰለጠነ ሰገጤ መቶ ኪሎ ፋራ ይሄ መንገድ ቅስም ሰባሪ ነው የሆነው።…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
የትንሣኤ ማግስት ዓርብ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።
"…ዓርብ ማለት የሥራ መክተቻ፣ ምዕራብ፣ መግቢያ ማለት ነው። ይህች ዕለትም እንደ ዕለተ ሐሙስ ሦስት ስያሜዎች አሏት፡፡ ይኸውም፡- አንደኛው ከሆሳዕና ቅዳሜ በፊት ያለችው ዓርብ የጌታችን ጾም የሚፈጸምባት፤ የጾመ ድጓው ቁመትም የሚያበቃባት፣ በመሆኗ በቤተ ክርስተያን "ተጽዒኖ" ስትባል፤ በሕዝቡም ዘንድ በሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤው ከባዱን ሥራ ስለሚያቆምባት "የወፍጮ መድፊያ፣ የቀንበር መስቀያ" ትባላለች፡፡ ሁለተኛውም በመጀመሪያ የሰው አባትና እናት አዳምና ሔዋን ስለተፈጠሩባት፣ ኋላም በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለቤዛ ዓለም መከራ ተቀብሎ ስለተሰቀለባትና የማዳን ሥራውን ስለፈጸመባት "ዕለተ ስቅለት አማናዊቷ ዓርብ" ትባላለች። ሦስተኛው ደግሞ የዛሬዋ ዓርብ በሰሙነ ትንሣኤው ያለችው "ቤተ ክርስቲያን" ትባላለች።
"…ጌታችን ከልደቱ እስከ ሞቱ ያደረገው የማዳን ጉዞ በሙሉ የተፈጸመው ዓርብ ነው። “ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ” እንዲል። ዓርብ የቤተ ክርስቲያን ሁለመናዊ ምስጢር የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች። ማለትም ዓርብ ለቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑ ዋና ዋና ምስጢራት ተሟልተዋል። ለምሣሌ የመስቀል አዳኝነቱ ከእርግማንነቱ ተለይቶ ታውቋል፤ የሕንጻዋ መሠረት ቀራኒዮ ተተክሎላታል፤ ሥጋ መለኮት የምትፈትተው በቀራኒዮ ተቆርሶላታል፤ ልጆቿን ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ ፈስሶላታል። ስብከት፣ ትምህርት፣ ተአምራት፣ ትንሣኤ ተደርጎላታል። ይህንን ሁሉ ምሥጢር ያገኘችው በዕለተ ዓርብ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ተባለች።
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
ለልጥፉ መልስ…
"…ዛሬ ብዙ ሰዎች ይሄንን ልጥፍ ሲልኩልኝ ውለዋል። ይመስለኛል ከዛሬ ጋር በዚህ ገጽ ላይ ስሜ ወጥቶ ሰዎች ሲልኩልኝ ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። እኔ የመሰለኝን ግለሰብም ሆነ ቡድን በገባኝ መጠን እንደምተቸው ይሄም ሰው ሆነ ቡድን በእኔ ላይ የፈለገውን ነገር የፈለገውንም ሓሳብ በፈለገው መልኩ ቢጽፍ አልቃወምም። የፈለገውን መጻፍ፣ መተቸት ይችላል። ሙሉ መብቱም የተጠበቀ ነው። ከእኔ የሚጠበቀው ለአቅመ መልስ መስጠት ብቁ ከሆነ መልስ መስጠት ብቻ ነው። እናም በገጼም ላይ ለጣፊው ስለበዛ ለዚህም አጭር መልስ እሰጣለሁ ማለት ነው።
"…መምህርት መስከረም አበራ ፈልጋ ያገኘችኝ ራሷ ናት። እኔ እስከሚገባኝ፣ እስከምረዳው ድረስ "ዘመዴ" ብለው ፈልገውኝ የሚመጡ ጴንጤዎች የዐማራ ትግል እንቅፋት ይሆናሉ ብዬ አላምንም። ለምሳሌ መዓዛ መሀመድ፣ ጌታቸው በየነ፣ እና መስከረም አበራ "በጌታ" ስለሆኑ ለአቢይ አሕመድ ያደሉ ይሆን የሚል ስጋት ቢኖርብኝም ከአቶ ጌታቸው በቀር ሌሎቹ ለዐማራ ዋጋ ሲከፍሉ ነው ያየሁት። ኦርቶዶክስም እስላምም ሆነው ለዐማራ ትግል እንቅፋት የሚሆን የለም ማለቴ እንዳልሆነ ግን ይታወቅልኝ። ለዐማራነት ብዙ ዋጋ የሚከፍሉ ጴንጤዎችንም ዐውቃለሁ።
"…አንድ ቀን በስደት ባለሁበት ሀገር ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ተቀምጬ ሳወጋ ለእኔ የደወለችልኝም፣ የጻፈችልኝም ራሷ መስኪ ናት። ረጅም ሰዓት አውርታኝ ዓይን ገላጭ ምልከታም የሰጠኋት እኔው ዘመዴ ነኝ። ከዶክተር ወንደሰን ጋር እየሠራሽ ከሆነ አለቀልሽ ያልኳትም ራሴው ነኝ። ሁለት ቀን ደውሎልኛል እንጂ በአካል አላገኘሁትም ያለችኝም ራሷ መስኪ ናት። ያልኩት አልቀረም እነ ትንግርቱ በቦሌ ወጥተው እነ መስኪ ከርቸሌ ገቡ። የሆነውም እኔ ያልኩት ነው።
"…አሁን ከቴዲ ርዕዮት ጋር የሚሠራው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ እና ጋዜጠኛ ዳዊት እኮ የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው ከእስር ቤት ወጥተው ነበር። ፖሊስ ድንገት የዶር ወንደሰንን ኮምፒዩተር ሲመረምር የጋዘኛ ዳዊትና የዶር ወንደሰንን የስልክ ልውውጥ ዶ/ሩ ቀድቶ ካስቀመጠው ኮምፒዩተር ላይ አግኝተው ተሯሩጠው የዋስትና መብቱን ቴዲን ፈትተው እሱን እስከ አሁን በእስር ላይ የሚያማቅቁት። ይሄን ይት አባቱ ያውቃል መንጋው?
"…መስኪንም የተቃወምኳት ከላይ ባስቀመጥኩት ንግግራ ነበር። እንዴት ፋኖን ከቄሮ ጋር እኩል በኢ መደበኛነት ትፈርጃለሽ? ነበር ያልኳት? መስከረም የዩኒቨርሲቲ መምህርት ናት። እኔ ደግሞ ሀ ገደሉ የማይገባኝ ተማሪዋ ነኝ። ተማሪ ደግሞ መምህሩን መጠየቅ የቆየ ልማድ ነው። እና እኔ የምታወቀው ተማሪ መምርቷን ለጠየቅኩት ማንነቱ የማይታወቅ ምንአልባትም ጎጤ ብአዴን ወይም ራሷ ወያኔን ሊሆን የሚችል ማንነቱ የማይታወቅ አካል አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ዋይ ዋይ ቢል እንዴት እሰማዋለሁ። ያውም መዓዛ መሀመድን ተቸህ የሚለኝ፣ መዓዛ እኮ ብተቻት አልተቀየመችኝ። እህቴ ናት። የገባት ናት። ደውላ ነው የምታስረዳኝ። ቴዎድሮስ ትርፌንና እነ ትሪፕል AAA ን ተቸህብን የሚል ሰው ግን ጤናማነቱ ያጠራጥራል። የፕሮፌሰሩን ስም አሟልቶ አጥርቶ እንኳን የማያውቅ ተደብቆ የሚተኩስ ልፈራ ይቅርና ሚሳኤል የተሸከመ አገዛዝ መቼ ፈራሁ አባቴ።
"…የእኔ ተግባር እየሠራሁት ያለው ሥራ ወደዳችሁም ጠላችሁም ፍሬ እያፈራ ነው። ከሰሞኑ ብዙ የምሥራቾችን ትሰማላችሁ። እናም እኔ ሥራ ላይ ነኝ። ማንም አየር ላይ ቢለፈልፍ መስሚያዬ ጥጥ ነው። የእኔ ግኑኝነት ምድር ላይ ካሉት አናብስት ከሁሉም ጋር ነው። ጎበዝ ጥያቄና ጥላቻ እየለየን እንጂ። እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግ ግን እጃችሁን ከፋኖ አመራር ጣልቃ ገብነት አውጡ ነው። ይሄ ጥያቄዬ የሚያስወቅሰኝ ከሆነ ግደለኝ። አልሰማህም።
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጼ እንደተነበበ እያየሁ ነው። ይህ የእኔ የዘመዴ ሓሳብ ነው። እኔ ተንፍሼ፣ ተገላግዬ፣ ጤናማ እንቅልፍ ሲወስደኝ፣ እናንተ ሳትተነፍሱ ቀርታችሁ እየተብሰከሰካችሁ በሽተኛ ሆናችሁ እንዳትቀሩ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።
"…በርዕሰ አንቀጹ ብትበሳጩ እንኳ እነ GGጂጂግግ እና TGቲጂትግ እንደ ዘመነ ኢህአፓ ኢድዩ፣ ደርግ መኢሶን ገዜ በጉልቤ፣ በደንፉ፣ እንደ ኦነግና ወያኔ በስድብ በነውር ቃል አትምጡ። ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ በጨዋ ደንብ ሞግቱኝ። የተመልካች አይን አታቆሽሹ።
"…ቀንተህ ነው፣ ፈንድተህ ነው፣ ምንጥስዮ፣ ቅብጥርስዮ ብትል ፍንድት አባክ ያድርግህና አልሰማህም። ሥነ ሥርዓት ይዘህ ሞግተኝ። አይችልም፣ መሃይም ነው ምናምን ብላ ብላ በትለኝም እልህሃለሁ መሃይም ቤት ምንአበህ ትሠራለህ? እደግመዋለሁ ሥነ ሥርዓት ይዘህ ተቃውሞ እንኳ ቢኖርህ ለ400 ሺ ሰው በነፃ ሓሳብህን ሽጥ። ያለበለዚያ ብሎክባን በሚባል በቴሌግራም ሰይፌ ወገብ ዛላህን ቆምጬ ነው የምገላግልህ። በዙህ አባባሌ ብትበሳጭም እንኳ ትእግስትን ተለማመድ።
"…1…2…3…ጀምሩ…!
ጉድ ፈላ…
"…ጽንፈኛው ኃይል፣ ዘራፊው፣ አሸባሪው፣ ጃዊሳው የምትለዋ ቃል ተዋጠች። ተዋጠች እና "ስለ ዐማራ ተቆርቁራችሁ ጫካ የገባችሁ" በሚል ቃል ተተካች።
• ወጥር ፋኖዬ…!💪🏿💪✊
እደግመዋለሁ…በደንብ ይደመጥ…!
"…በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በወሎ ፋኖዎች እርስ በእርስ ከተታኮሱ፣ ከተገዳደሉ፣ ደም ከፈሰሰ ተጠያቂዎቹ በዋነኝነት ሀብታሙ አያሌው ሲሆን፣ እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው እና ኢየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ ናቸው። ኢትዮ 360 ሚዲያም እንደ ተቋም የዚህ ቆሻሻ ታሪክ ባለቤት ይሆናል ማለት ነው።
"…የሙያ ሥነ ምግባር ጠብቀው፣ ከዲክታተሩ ሀብታሙ አያሌው ስር ያሉትን ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስን፣ ይድኔን እና ልዩን አይመለከትም። በተቋም ደረጃ በሀብታሙና በጄሪ ምክንያት በሚመጣው ዳፋ ካልተጠየቁ በቀር በግል የሉበትም። ዋነኛው ተጠያቂ ሀብታሙ አያሌው ነው።
"…አሁንም ወደ ገደለው ነገር አልገባሁም። እነ አበበ በለው በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋና በጎንደር ያዘጋጁትን የደም ማፋሰስ ፕላን ኦሮሙማውም ሆነ ወያኔ አላዘጋጁትም። ሕዝብ ለፋኖ ብሎ በሰጠው ገንዘብ ፋኖ ገዝቶ ፋኖን ለመከፋል፣ ለማገዳደል መጣር ወንጀል ነው።
"…እኔ መንጋ ጎጋ ግንቦቴና ግንባሩ፣ ጥርሱ፣ ብብቱ የሚባል ኮተት አልፈራም። የሀብታሙ በሻህና የማእረግ መንተባተብን ከቁብ አልቆጥርም። እኔ ምድር ላይ እነ ሀብታሙ እየፈጠሩ ያሉትን አደገኛ ጥፋት እንድታስቆሙ እየወተወትኩ ነው። ሀብታሙ አያሌውን ሰከን እንዲል፣ አቅሙን ዐውቆ እንዲቀመጥ ምከሩት እያልኩ ነው። ሀብታሙም፣ አበበ በለውም አሁን በትንሹ መተንፈስ ጀምረዋል። ወደ ጫወታው ሲገቡ እኔም ወደዚያው እገባለሁ። እስከዚያው ግን እረፉ በሏቸው።
"…ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ይሄን ሳላደማ ሌላ አጀንዳ አላመጣም። አዛኜን ሌላ አጀንዳ አላመጣም። አበደን…!
የትንሣኤ ሳምንት እሑድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል።
"…በቀዳሚው ትንሣኤ በሳምንቱ በሚውለው በዛሬዋ ዕለተ እሑድ የሚውለው ቀን "ዳግም ትንሣኤ" ወይም በተለምዶ ዳግማይ ትንሣኤ ተብሎ ተዘክሮ ይውላል። በዚህ ቀን በትንሣኤው ዕለት ማታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ ቤት ሳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ በመካከላቸውም ተገኝቶ "ሰላም ለዅላችሁ ይኹን" በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው በወቅቱ ሐዋርያው ቶማስ በስፍራው አልተገኘም ነበር፡፡ከሔደበት ሲመጣ ግን የጌታን ትንሣኤ እና ለእነሱም መገለጡን በነገሩት ጊዜ "እናንተ አየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ሰምቼአለሁ" ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? በፍጹም አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም" አለ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን አይቶ እንዲያምን ሲል ነው ጌታ በትንሣኤ ሳምንት በ8 ተኛው ቀን ሐዋርያቱ በዝግ ቤት ሳሉ ዳግም ተገልጾ ቅዱስ ቶማስንም "ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ" ብሎ አሳይቶ፣ እርሱም አይቶና ዳስሶ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎም የመሰከረበት እለት በመሆኑ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ ይዘከራል። ዮሐ 20፥ 24-30
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
• እኔ የምለው…
"…በአንደበቴ የምናገረው፣ በጣቶቼ የምጽፋቸው ሓሳቦች ቆይቶም ቢሆን እየገባችሁ ነው አይደል…?
"…ካልገባህ ደጋግሜ ስግትህ ይገባሃል። አንተ ብቻ ተሳድበህ ከመቀሰፍህ በፊት በትእግስት ከዳር ቁመህ በጥሞና ተከታተል።
"…ተሳድበህ ቀስፌ ካባረርኩህ በኋላ ቆይተህ ሲገባህ በጓሮ በር መጥተህ ብትለፋደድብኝ አልሰማህም። ይሄን ዕወቅ።
• የምለው ገብቷችኋል…ኣ…? 😁
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …ይዞ መምጣቱ ሌላ ትኩሳት መፍጠሩም እየታየ ነው። ሀብታሙ አያሌው በኢየሩስ ተክለጻድቅ በኩል በትናንትናው ዕለት ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን አነጋግራ ስለ ሕዝባዊ ሠራዊቱ እንዲናገር ወትውታ ያሰጠችው ቃል በጎጃም በእነ ዘመነ ካሴ በኩል ቁጣን ቀስቅሷል። ጋዜጠኛ ወግደረስ አቅም ያለው ጋዜጠኛ ሲሆን መረጃ ቴሌቭዥን የዐማራ ክልል ዳይሬክተር አድርጎ የቀጠረው በወር ከፍተኛ ደሞዝ እየተከፈለው በእሳት ውስጥ እያለፈ የሚያገለግል ጀግና ጋዜጠኛ ነበር። ይህን ጋዜጠኛ ነው እንግዲህ ሀብታሙ አያሌው ስንት ብር ጨምሮ ከፍሎ እንደወሰደው ሳይታወቅ በትናንትናው ዕለት ወደ ሚድያ መጥቶ ጎጃምን የሚከፋፍል መረጃ ሲያሰራጭ የታየው። ለዚህም ሓላፊነቱን የሚወስዱት እንደ ተቋም ኢትዮ 360 ሲሆን፣ በግለሰብ ደረጃ ከእነ ዘመነ ካሴ ጋር የግል ፀብ ውስጥ የገባው ሀብታሙ አያሌው እና ወይዘሮ ኢየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ ናቸው። ዋጋ ቲከፍላሎ አለ ኦሮሞው አዝማሪ። የጎጃም ዕዝ ተብሎ የተቋቋመው ሠራዊትም ጫካ ውስጥ ሆኖ መግለጫ ሲሰጥ ታይቷል። ቪድዮውም ደርሶኝ አይቼዋለሁ።
"…ሌላው መልካሙ ዜና እኔ አውቶሚክ ቦንብ የሆነውን አጀንዳዬን ካፈነዳሁ በኋላ እነ ዶር አምሳሉ በፋኖ ስም ገንዘብ መሰብሰቡን አቁመዋል። በተለይ አሜሪካማ ቀጥ ነው ያለው። ካናዳም ወፍ የለም። ነገር ግን ሰሞኑን የጀርመኑ ማዕረግ በካናዳ 100 ሺ ዶላር በሠራዊቱ ስም ሰብስበናል ሲል ተደምጧል። በእውነት ተሰብስቦ ከሆነ ለየትኛው ሠራዊት ነው የተሰበሰበው? እንጠይቃለን። በየ እስቴቱ የተቋቋሙ የዶላር ማለቢያ ቻፕተሮች አንዳንዶቹ በይፋ ነው ነው ከእነ ሀብታሙ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያቆሙት። በፈረንሳይ ሀብታሙ አያሌውን እና ሽመልስ አበራን ጠርተው ገንዘብ ሊሰበስቡ የነበሩት የዐማራ ማኅበራት በፍጥነት ነው የሽሜንና የሀብታሙን ስም አውጥተው ውሳኔ የወሰኑት። ጀርመን ሙኒክ ሁለት ቦታ ተከፍለው እየተወያዩ መሆናቸውን ሰምቻለሁ። በሙኒኩ የእነ ሀብታሙ አያሌው ስብሰባ ላይ ከኢትዮጵያ ጭምር መጥተው ሀብታሙን የሚያገኙት የብአዴን ሰዎች እንዳሉ ነው የሰማሁት። የሸከከኝ ነገር የጀርመኑ አጀንዳ ጎንደር ላይ ትኩረት አድርጎ እንዴት ጎንደሮችን ማበጣበጥ እንደሚቻል ለመምከር ነው የሚሉ መተርጉማን አሉ። ሜጀር ጀነራል ውብአንተን "በእስክንድር ዕዝ ስር አልገባም" ስላለ ብቻ እንዴት እነ ሀብታሙ አያሌው እሱ እኮ ብአዴን ነው ብለው አዋክበው፣ ስሙን አጥፍተው፣ አዋርደው፣ ለሞት እንደደረሰም አይተናል። ውብ አንተ ከተሰዋ በኋላ የአዞ እንባ አፍሳሾቹም እነሱው ሆነው ነው የገኙት። እናም ሀብታሙ አያሌው ከዐማራ ፋኖ የውስጥ ጉዳይ እጁን ካላነሣ ዐማራ ፍዳው ይበረታበታል።
"…በሀብታሙና በእስክንድር ደጋፊዎች እኔ ዘመዴ የምከሰሰውም ዐማራ አይደለም። እሱ የሀረር ቆቱ ነው። ስለዚህ ከቆቱው ዘመዴ ይልቅ ዐማሮቹ እነ ሀብታሙ አያሌው የፈለጉትን ያድርጉን የሚል መሃይም ደናቁርቶች ንግግር እሰማለሁ። ሲጀመር እኔ ዐማራ አይደለሁም። ኦሮሞም ጉራጌም፣ ትግሬም ነኝ አላልኩም። እኔ የሐረርጌ ቆቱ ነኝ አልኩ በቃ። እኔ አለኝ ያልኩትን ከተናገርኩ በኋላ በግድ ወስዶ ነኝ ያላልኩት ብሔር ላይ መለጠፉ ነውር ነው። እኔ ዐማራም አልሁን ለምን ኡዡንቡራዊ አልሆንም ስህተት ነው ያልኩትን መተቸት ማን አባቱ ነው የሚከለክለኝ? ዘመዴ ቆቱ ስለሆነ አያገባውም እነ ሀብታሙ ዐማራ ስለሆኑ ያገባቸዋል ማለት ዘመዴ አያገባህም ብአዴን ግን ዐማራ ስለሆነ ያገባዋል ከማለት በምን ይለያል? ፋኖ ብአዴንን ዐማራ ሆኖ የሚጠርገው ለዐማራ በጠላትነት፣ በባንዳነት፣ በጨቋኝነት ከዘመዴ ይሻለናል ተብሎ ታልፏል እንዴ? እናም የሀብታሙ ዐማራነት ለዐማራ ጥፋት የሚያመጣ ከሆነ ያው ብአዴን ነው። ጧ በል፣ ፈንዳ።
"…ነገሮች እየጠሩ ነው። ጫጫታው እየቀነሰ ነው። የለንደን ፋኖ የመወያያ ግሩፕ ኮተት ልጥፎችን አድሚኖቹ እያጸዱ፣ ባን እያደረጉ ስለሆነ እጅግ ደስ አሰኝተውኛል። የአውሮጳም የመወያያ ግሩፕ የሽመልስ እና የአቶ ወንደሰን ትውከት ማስመለሻ ከመሆን ጸድተው ስላየሁ እጅግ ደስ ብሎኛል። እነ ሀብታሙም የገንዘብ ምንጩ ቀጥ ሲል ማበጣበጣቸውም በዚያው ቀጥ ይላል። የፋኖዎቹ አንድነት በመሬት ላይ እጅግ ደስ ይላል። በቅርቡም ብዙ የምሥራቾችን እንሰማለን። ጎጃሞችም በጥበብ ነገሮችን ይፈቱታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እነ ሀብታሙም ወደ ቀልባቸው ይመለሳሉ፣ ታላቁ እስክንድር ነጋም ግንባር፣ ሠራዊት የሚለውን በይፋ አፍርሶ ወደ አንዱ ዕዝ ስር ተጠቃልሎ በይፋ መግለጫ እንደሚሰጥም እጠብቃለሁ። ያን ጊዜ እነ ግግጂጂትግ ድባቅ ይመታሉ። መንጋውም ጮጋ ይላል ሌባ ሁላ።
ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
~ ከ1:00 ሰዓት በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍተዋለሁ። እስከዚያው ርዕሰ አንቀጹ በጥሞና ይነበብ። ያነበባችሁ ሓሳባችሁን ጽፋችሁ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ስድብ ያስቀስፋል። አመሰግናለሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…ለዘመናት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አይነኬ፣ አይደፈሬ መስለው የከረሙትን፤ እንደ ታቦት፣ እንደ ቤተ መቅደስ የሚፈሩት፣ የሚከበሩትን እኔ ዘመዴ በድፍረት ነክቼአቸዋለሁ። ክንብንባቸውንም ገልጬ ለዓለሙ ሁሉ ገመናቸውን አሳይቻቸዋለሁ። ብዙዎች እንደ ዖዛን የምቀሰፍ፣ ደርቄም የምቀር መስሏቸው መፍራታቸውን ዐውቃለሁ። የማይነኩ ነካ አሁን ገና ዘመዴ ተሳሳተ ብለው የሰጉልኝም ነበሩ። ውለው ሲያድሩ ግን አሸናፊነቴ ሲታወጅ የቀደመ ፍርሃታቸውን ሳይሸሽጉኝ ጽፈውልኛል፣ ገልጸውልኛልም። የሆነው ሁሉ የሆነው ሁሉን ማድረግ በሚችለው በልዑል እግዚአብሔር አጋዥነት ነው። ዘወትር ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ የምላት ወላዲተ አምላክም በምልጃዋ ስላልተለየች ነው። ክብሩን ሁሉ እግዚአብሔር ይውሰድ።
"…እኔ ይሄ ግሩም ከባድ ቅዱስ የሆነው የሳይበሩ ዓለም ትግል የትርፍ ጊዜ ሥራዬ አይደለም። 24/7 365 ቱንም ቀናት ሌት ተቀን፣ ክረምት ከበጋ፣ ዓመት እስከ ዓመት ያለማቋረጥ፣ ያለመሰልቸት እንደ ሰጎኗ ከእንቁላሉ ላይ ዓይኔን ሳላነሣ በትኩረት የምሠራው ሥራ ነው። እንዲያው ሲደብረኝ፣ መሄጃ ሳጣ፣ ዝም ብዬ ቲክቶክ ገብቼ የምቀደድ፣ ቴሌግራም ላይ የምበጠረቅ፣ ያለ መረጃ በትርፍ ጊዜዬ የምዘባርቅም ሰው አይደለሁም። አስሬ ለክቼ አንዴ የምቆርጥ፣ በአቆራረጤም ፍፁም የሆነ የቆረጣ ስልትን የምከተል፣ ልዩ ጥበብንም የምጠቀም ሰው ነኝ። ይሄን ከድሮ ጀምሮ ስከተለው የኖርኩት የትግል መርህ እና መንገድ ነው። ወደፊትም በዚሁ አግባብ ይቀጥላል።
"…ሸከከኝ ስል ቀድሜ ስለማውቀው ነገር ነው እንጂ ስለሚታየኝ ራእይ አይደለም። ቀድሜ የማውቀው ነገር፣ ደግሞም ሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ስፍራ ግሩም ግሩም የሆኑ ረቂቃን ወፎች ስላሉኝም ጭምር ነው። ሌላ ምንም የተለየ ተአምር የለውም። ለአንድ ነገር ትኩረት ሰጥተህ፣ ጊዜ ሰጥተህ፣ መዳረሻ ግብ አስቀምጠህ፣ አስሬ ለክተህ አንደዜ የመቁረጥ ልማድን ካዳበርክ በኋላ የምትደርስበት ራሱን የቻለ ተፈጥሮአዊ ማእረግ አለ። እኔ አሁን እዚያ ማእረግ ላይ ደርሻለሁ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በጥባጭ የት እንዳለ ከልምድ ዐውቄአለሁ። በጥባጩ ወይም በጥባጮቹ እንዴት እንደሚዠለጡም ከልምድ ዐውቄአለሁ። ከዚያ እንዴት አደብ እንደሚገዙም እንዲሁ ከልምድ ዐውቄአለሁ። ስለዚህ አሸናፊ ነኝ።
"…አሁን በተነሣው የግንባሩ፣ የሠራዊቱና የግንቦቴዎች ጉዳይ ብዙ አስቤበት፣ ከራሴው ጋር ብዙ መክሬበት፣ ስብሰባ፣ ጉባኤ ተቀምጬበት፣ በጸሎት የሚያግዙኝ በጸሎት እንዲያግዙኝ አስደርጌ የገባሁበት ነው። ሦስቱም ልምድ ያላቸው፣ ገንዘብ ያላቸው፣ በገንዘባቸው ተሳዳቢ፣ አሸማቃቂ፣ አሳቃቂ፣ አስፈራሪ፣ አስዶካኪ ግሪሳ ሠራዊት ያላቸው በጥፋት፣ በተንኮል ጥርሳቸውን የነቀሉ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ የሰውም ርህራሄ የሌላቸው፣ ሳዲስቶች፣ ማታለልን እንደ ሙያ የሚቆጥሩ፣ ከስማቸው ፊት ያለውን ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ አቶ፣ ወሮ፣ ጋዜጠኛ፣ ኢንጂነር ወዘተ የሚለውን ስም እንደ የቡዳ መድኃኒት፣ የመብረቅ መከላከያ አድርገው የሚጠቀሙ፣ ሁለት ጠጉር ያበቀሉ፣ መላጣ፣ በምርኩዝ ሁላ የሚሄዱ ስለሆነ እነሱን መንካት እንደሚያስቀስፍ ነገር ስለሚቆጠር ማንም የማይደፍራቸውም ነበሩ እስከ ዛሬ። እኔ ዘመዴ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ ደፈርኳቸው። አፈራረስኳቸውም።
"…አሁን ጫጫታው ቀንሷል። ዋነኛው የገንዘብ ምንጫቸውም ደርቋል። የጥፋት የግኑኝነት መስመራቸውም ተቋርጧል። ድንጋጤ ኀዘን ወርሷቸዋል። ማንንም ማታለል፣ መቀፈል እንዳይችሉ ተደርገው ተደቁሰዋል። ቁጥራቸው እንደ ቀይ ቀበሮ ቀንሷል። እንደ ምኒልክ ድኩላ በስንት ጊዜ አንዴ ብቅ ብለው የሚታዩም ሆነዋል። የቀሩትም እንዲሁ ይደመሰሳሉ። ብቻ ከእኔ የሚጠበቀው እስክንድር ነጋን እየጠበቅኩ በእሱ ዙሪያ የከበቡትን ጆፌ አሞሮች፣ የጥንብ አንሣ ፖለቲከኞች ደጋግሜ መውቀጥ፣ መቀጥቀጥ ነው። ደጋግሜ መውገርም ነው። አሣር ፍዳቸውንም ማሳየት ነው። በመረጃና በማስረጃ ድራሽ አባታቸውን ማጥፋት ነው። አለቀ።
"…እኔ ሁላችሁም እንድታውቁልኝ የምፈልገው የምሠራው ሥራ በምድር ላይ ያሉት ታጋዮች፣ የፋኖ መሪዎች የነገሩኝን፣ ያዘዙኝን ብቻ ነው። ሀብታሙ አያሌውን ከትግላችን ውስጥ እጁን አስወጡልን ያሉት የፋኖ አለቆቹ ናቸው። በጠበጠን፣ አወከን፣ ለያየን፣ ሰደበን፣ አዋረደን፣ ከፋፈለን፣ ሊበትነን ነው፣ እንደ አለቃችን አክት ያደርጋል፣ አልታዘዝ ስንለው በሚዲያ ባለው ተደማጭነት ስማችንን ያጠፋዋል። ፈላጭ ቆራጭ ልሁን ባይ ነው። የአንዳችንን ትግል ወስዶ ሌላው እየሰጠ ይከፋፍለናል። አንተ የምልህን ካልሰማህ ብአዴን ነህ ብዬ አሳየህሃለሁ ይለናል። ከአበበ በለው ጋር ሆነው ማኒፌስቶ አዘጋጅተው በዚህ ተዳደሩ፣ እስክንድርን መሪ አርጋችሁ ምሩጡ ይለናል። እረፍ ስንለው መዓቱን ያወርድብናል። እባካችሁ ይሄን ሰው አንድ ነገር አድርጋችሁ ከትግላችን አስወጡልን። ይሄ ነበር የፋኖ አመራሮች ዋነኛ ጩኸት። የፈለገ ሰው ደውሎ ያጣራ።
"…እናም እኔም ይሄን የአርበኞች ጩኸት፣ ጥሪ ሰምቼ ነው የመጣሁት። ዋነኛው ችግሬም ሀብታሙም ሆነ አበበ በለው የተጠለሉት በእስክንድር ነጋ ስር መሆኑ ነው። እነሱ ሲነኩ እስክንድርም የግድ መነካቱ አይቀርም። እስክንድር ሲነካ ደግሞ የሀብታሙ አያሌው፣ የአበበ በለው፣ እንደ ተቋም የአዲስ ድምጽ እና የኢትዮ 360 ደጋፊዎች ግንባር ፈጥረው መንጫጫታቸው አይቀርም። የሚጠበቅም ነው። እነሱ ሲንጫጩ ደግሞ መንጋው፣ ጎጋው፣ ግራና ቀኝ የማያገናዝበው፣ ነገሩ እስኪጠራ ከዳር ቆሜ ልታዘብ የማይለው፣ አእምሮ ስልቡ፣ ስሜታዊው ግሪሳም ወጀቡን ተቀላቅሎ እንደሚመጣም የታወቀ ነው። የሚጠበቅም ነው። እሱን በአግባቡ ማኔጅ ማድረግ ነው ከእኔ የሚጠበቀው።
"…ይሄም ብቻ አይደለም እኔ እዚህ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት የመሰለ ትግል ውስጥ ስገባ ቀን የሚጠብቁልኝ፣ ጊዜ የሚጠብቁልኝ፣ መቼና እንዴት ባገኘነው የሚሉ ፖለቲካ ወለዶቹ፣ የወያኔ ጥፍጥፍ ቅማንቴና አገው ሸንጎው ስታዲየም ሙሉውን መንጋው ሁላ ግር ብሎ የሚመጣበት ነው። አታዩም ትግሬዋ ወያኔ ሳትቀር ዘመዴን አገኘሁት ብላ ለእስክንድር ደጋፊ ሆና እኔን ተቃዋሚ መስላ ዐማሮች ይሄን ልጅ ከትግላችሁ አርቁት፣ አስወጡት እስከማለት ስትደርስ። ትግሬ ብቻ አይደለም ይሄን አጋጣሚ ካገኘንማ እኛም አለን በማለት ኦነግ፣ የዐማራው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ኦፌኮና ብልፅግና በሙሉ ግር ብሎ ስታዲየሙን ሞልቶ ይጮህብኛል። በዚህ ላይ አንዳንድ የወሎ የወሀቢይ እስላም ዐማሮች፣ ሙሉ የኦሮሞ ወሀቢይ እስላሞች፣ የጎጃም ቅባት ሃይማኖቶች፣ የዓለም ብርሃኖች፣ የደቡብ እና የወለጋ ጴንጤዎች፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማፍረስ የባከኑት የተሃድሶ ቡድን አባላት፣ የመምህር ግርማ ካዳሚዎች በሙሉ የዘመቻው አካል ነው የሚሆኑት። በዚህ ግርግር ነው እንግዲህ ዘመዴን መጣያው አሁን ነው ብለው እነ ጂጂግግትግ ሁሉ አንድ ላይ ቆመው እንውረድበት ብለው የሚመጡት።
"…የእኔ ተግባር እንደ ማር ቆራጭ ሆኖ መዘጋጀት ነው። በጭስ ለሚሸሹት ጭሱን እየለቀቅኩባቸው፣ ሌላውን ጓንትና መሸፈኛ አጥልቄ በጥንቃቄ ማሩን ብቻ ቆርጬ ወደ ቦታዬ መመለስ ነው። ለእዚህ ዓይነቱ ትግል ልምድ ስላለኝ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሃኪምም ነኝ። መርፌ፣ መቀስ፣ ፋሻ፣ ምላጭ በቀደድኩት ሆድ ውስጥ የማልረሳ፣ ጉበት ላክም ብዬ ጣፊያ ቆርጬ የማልወጣ፣ ለምጥ የመጣችውን የሬሳ ማድረቂያ፣ ለግርዛት የመጣውን የምጥ መርፌ የማልወጋ፣ ታርጌቴን፣ ኢላማዬን ሳልስት ቱ ዘፖይንት እንዲል ሱሬ የነገሩን ብልት ህብለ ሰረሰሩን…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
የትንሣኤ ሳምንት ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ትባላለች፦
"…ሴቶች የሚታወሱበት፣ የሚዘከሩበት ዕለት ነው። ዓለም ማርች 8 ብሎ ሴትን ሁሉ መታሰቢያ ቀን ሰጥቶ እንደሚያከብር ያለ ሳይሆን በዕለተ ትንሣኤ ሌሊቱን ወደ ጌታ መቃብር ሲመላለሱ ያደሩ ሴቶች የድካማቸውና ጌታን የመሻታቸው ዋጋ መታሰቢያቸው ይሁን ብላ ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኑን የሰየመችው።
"…ጌታ ከከሚከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ ያህል ሕዝብ መሃከል የመረጠው 12 ሐዋርያት፣ 72 አርድዕት፣ 36 ቅዱሳት አንስት መርጦ ነበር። ከተመረጡት 120 ቤተሰብ መካከል 36 ቱ ሴቶች ናቸው። ስማቸውና የመታሰቢያ ወርሐዊ በዓላቸውም በቤተ ክርስቲያን ይከበራል። በተለይ የትንሣኤ ሌሊት ትንሣኤውን ሽተው ወደ መቃብሩ ሲመላለሱ ቅዱሳን መላእክትን ያዩበት የተደነቁበትና በመቃብሩ ያለውን መዓዛ ትንሣኤ አሽትተው የተመሰጡበት ዕለት ስለሆነ እንዲሁም ድካማቸው ከንቱ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነው።
"…አንድም ጌታችን አስቀድሞ ለእነርሱ ለሴቶቹ ታይቶ ትንሣኤውን ያረጋገጠበት ስለሆነ እነርሱ ከአምላክነቱ ግርማ የተነሳ ረቡኒ ብለው ያደነቁበት ዕለት መታሰቢያ ስለሆነ። አንድም በጠቅላላው ከሕማማቱ እስከ ትንሣኤው ብዙ የእንባ መሥዋዕት ያቀረቡ እናቶች የሚታሰቡበት ስለሆነ አንስት አንከራ ተብሎም ይጠራል የዛሬው ቅዳሜ።
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍስሐ ወሰላም።
የገዳይና ሟች ውይይት፦
• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በ +14707670531 ስልክ ቁጥሩ ደውሎ ነው ቀጠሮ የሚይዝልኝ። አንተ ቆሻሻ ሰላም ብትገዛ ይሻላል እሰከነቤተሰቡ ነው የማጠፋሀ። ብታርፋ ይሻላል። አንተ የሀረር ጅብ።
~ ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦ መልካም ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ። መቼ ነው እኔንም ቤተሰቤንም የምታጠፋው። ተዘጋጅተን እንጠብቅህ ወይስ ድንገት እንደ ክርስቶስ ነው የምትመጣው? እስቲ ይሄንኑ ለሕዝቡ ሁሉ ከነ ስልክህና ስምህ ይፋ አደርገዋለሁ።
• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በጣም ጥሩ አንተ ከብት።
~ ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦ "…ናልኝ እንጂ ወርቄ። ና ጋሽ ወርቅነህ። ወይስ አንተ ከደመህ እኔ ቤተሰቦቼን ይዤ ልምጣና ታጠፋን ይሆን? ላቅልል ብዬ ነው። 😁
• ገዳዬ ጋሽ ወርቅነህ ተስፋዬ፦ በቅርብ ቀን አንተ ደብተራ።
• ሟች እኔ ዘመድኩን በቀለ፦"…እጠብቃለሁ። በማለት ተለያየን እላችኋለሁ። ቆይቼ እመለሳለሁ። አቶ ወርቅዬ ግን ማናቸው?
👆…ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…አሁን እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ምን ቀራቸው? ምንም ምንም አልቀራቸውም። የእስክንድር የአክስት ልጅ ከኬኒያ ወደ ኡጋንዳ የሄደውና በጫት ጭማቂ የሚንቀሳቀሰው የትልቅ ትንሽ የጋሻ ሚዲያ ባለቤትም አሁን ሰሞኑን ሸከከኝ ያልኳችሁን የጎጃምን ካርድ መዝዞ ከመንዘባዘቡ በቀር ምንም ሊያመጡ አልቻሉም። በግንባሩ ገንዘብ ያዥ በሕይወት በላቸው አማካኝነት እነ ማርሸት፣ ዝናቡ ላይ የተቀነባበረው የእነ GGጂጂግግ አጀንዳ ሰሚ አጥቶ ነው የከሸፈው። አሁንም በተመስገን ጥሩነህ ዘመድ በካፒቴን ማስረሻ በኩል አዲስ አጀንዳ ብለው ይዘው የመጡት በሙሉ ፉርሽ ይሆናል። መና ይቀራል። ሰሞኑን እስክንድር ነጋም የምሥራች ያሰማናል ብለን እንጠብቃለን። የሸዋ ጉዳይ በድል ሲጠናቀቅ የእስክንድር ግንባርና ሠራዊት ነገርም አብሮ ነው መቋጫ የሚያገኘው። እስክንድርም ከሸዋዎች ቃል እንደማይወጣ ተስፋ አለኝ። የሚከስሩት እነ GGጂጂግግ እና እነ TGቲጂትግ ብቻ ናቸው።
"…ሀብታሙ አያሌውም ልክ ይገባል። መስመርም ይይዛል። እጁን ከፋኖዎች ውስጥ ሳይወድ በግዱ ይሰበስባል። አበበ በለውም እንደዚያው። ሌሎቹም እንደዚያው። መተቸት፣ አቅጣጫ መጠቆም የአባት ነው። ከዚያ በዘለለ ግን የአንዱን ድል ለሌላው ሰጥቶ መዘገብ ከዚህ በኋላ አይሞከርም። ደውሎ የፋኖ አመራሮችን ማስፈራራት፣ ከእስክንድር ስር ካልሆናችሁ ስማችሁን ነው የምናጠፋው እያሉ ማስፈራራት፣ እንደ ባለጌ አግድም አደግ በቆሻሻና በወረዱ የስድብ ቃላት የፋኖ አመራሮችን መስደብ፣ በገንዘብ ማስኮብለል ወዘተ አይሠራም። ይሄም በቅርቡ መቋጫ ያገኛል።
"…ምድረ ኮተት፣ አውርቶ አደር፣ ተሳዳቢ መንጋ ሁላ ሥርዓቱን ሳይወድ በግዱ ይይዛል። በእስክንድር ነጋ ጀርባ ታዝለው ወደ ዐማራ ፋኖ ትግል ዘው ብለው ለመግባት አዳዲስ ከረባትና ሱፍ አዘጋጅተው የነበሩ ድልብ፣ አቀንጭራ የዚያ ዘመን ሰዎችም አደብ ይገዛሉ። ይሄኛው ትውልድ እሳት የላሰ ትውልድ ነው። ደፋር ጠያቂም ነው። በኢህአፓ፣ በደርግ፣ በወያኔ፣ በግንቦት ሰባት እና አሁን በኢዜማ ተከስተው የዐማራን ትግል ቀርጥፈው ሲበሉ የነበሩ ሾተላዮችን የማይታገስ ትውልድ ተፈጥሯል። አሁን በዐማራ ትግል ፊት ለፊትም ሆነ ከጀርባ ነገር መጎንጎን አይቻልም። አይሞከረምም። የነቃ ጠያቂ የዐማራ ትውልድ ነው የተፈጠረው።
"…ዓሥራት ቲቪን ላቋቁም ብለህ ከዐማራው ላይ ዶላር ገፈህ ያስፈረስክ፣ ኢሣት የተባለ ዐማራን እሳት ሆኖ ላስፈጀ ገዳይ ድርጅት በኢትዮጵያዊነት ስታስግጠው የከረምክ። ለዐብን ተብሎ የተዋጣ ገንዘብ ለራስህ ቀርጥፈህ በልተህ ስታበቃ አሁንም ጎንደርን ለሁለት ለመክፈል የዓይናርህን በውኃ ሳታብስ ዓይንህን በጨው ታጥበህ የተደነሰርክ፣ በግንባሩ ስም፣ በትሪፕል ኤ፣ በዋፋ፣ በወፏ ስም ወዘተ ዐማራን ኪሱን ስታራቁት የኖርክ ፕሮፌሽናል ሌባ ሁላ አሁን ታርፋታለህ። ዶክተር ሁን ኢንጂነር፣ ፕሮፌሰር ሁን ወዛደር፣ ቄስ ሁን ሼክ፣ ኡስታዝ ሁን ሰባኪ መምህር ለደንታህ ነው። የማይነካ፣ የማይተች ታቦት የመሰለ ስም ያለው የለም። ሁልሽም ትዠለጫለሽ። አለቀ። ጋዜጠኛ ነኝ ብለህ ሚድያ ይዘህ ብትለፋደድ፣ እሱ ከባድ ነው እንዴት እንናገረዋለን የሚል ትውልድ አሁን የለም። የኅልውና ትግል ነው ወዳጄ። ሚዲያ ላይ ወጥተህ ብትለፈልፍ በሚዲያ መልስ እሰጥሃለሁ። በቲክቶክ ብትመጣ በቲክቶክ እቀነድብህሃለሁ። አለቀ።
"…ፈረንሳዮች ግን ክበሩልኝ ነገሩ ገብቷችሁ ሀብታሙ አያሌውን እና ሽመልስ አበራ ጆሮን ለገንዘብ ማሰባሰቡ ጠርታችሁ ስታበቁ በሁለቱ ላይ ጥያቄ ሲነሣ ተሰባስባችሁ ሁለቱም እንዳይገኙ መወሰናችሁ ያስመሰግናችኋል። ጀርመን በተለይ ብአዴኖች ሁላ ከኢትዮጵያ መጥተው እንደሚሳተፉ ሰምቻለሁ። በተለይ በጎንደር መሃል ቅርቃር በመክተት አሁንም ጎንደርን ለመበጣጠስ፣ ወሎንም፣ ጎጃምንም፣ ሸዋንም ለመበታተን ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተደከመ መሆኑን ተጨባጭ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። ነገር ግን ይሞከራል እንጂ አይሳካም። እናም በአውሮጳ ያላችሁ የዐማራ ማኅበራት ብትታገሱ ነው የሚሻለው። እኔን ያናገረኝ አንዱ የማኅበር መሪ ሀብታሙ አያሌው የሚጠላቸውን እነ አሰግድን እየደገፈ እነ መከታውን እንደሚጠላ ነው የታዘብኩት። የተምታታ ነገር። የዐማራ ማኅበር ነኝ ብሎ አንዱን ፋኖ ወድዶ ሌላውን ፋኖ መጥላት ማለት ይሄ ራሱ ብልግና ነው። አስቡበት።
"…የእኔ ዓላማ ግልጽ ነው። የዐማራ ፋኖን ትግል ለዐማራ ፋኖ ተዉለት። የዐማራ ፋኖን ትግል በገንዘብ ለመርዳት ከተፈለገም የዐማራ ፋኖዎች በሚሰጡት ውክልና እና ሓላፊነት ብቻ አክብሮ መመራት ነው። ይኸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ወደፊት ያሰብኩት አንድ ነገርም አለ። እሱን ነገርም በሸዋ ዐማሮች እጀምራለሁ። ይኸውም ምንድነው የሸዋ ዳያስጶራ በተለይ ተደማጭ የሶሻል ሚዲያ አንቀሳቃሾች የሆኑ የሁለቱም ደጋፊዎችን በጋራ አወያይቼ ልዩነታቸውን አጥብበው በአንድ እንዲሰለፉ ለማድረግ ፈልጌአለሁ። ሁለቱንም አካላት አውርቼ ፈቃደኞች ናቸው። በዝግ ቤት ተነጣጥሰው፣ ተገማግመው፣ ስህተታቸውን ተራርመው አንድ ላይ እንዲሰለፉ ለማድረግ መንገድ ጀምሬአለሁ። ምድር ላይ ያሉት አንድ እንደሆኑት ሁሉ በአየር ላይ ያሉትም አንድ መሆን አለባቸው። ከዚያ ወደ ጎጃም፣ ወሎ፣ ጎንደርም እንዘልቃለን። ሌባ ሌባው ግን እንደ አጋንንት ራሱ ጩሆ ይወጣል። ጤነኛው መንጋ ግን በሰላም በጋጣው ይኖራል።
"…ይሄን ሁሉ በራስ ተነሳሽነት ከፈጸምኩ በኋላ፤ የዐማሮችን ጉዳይ ለዐማሮች ትቼ እኔ ወደ ዐውደ ምህረቴ እመለሳለሁ። እስከዚያው ግን ፈንዳ ጧ በል እንጂ ንቅንቅ የለም። ስትሳደብ፣ ስታቅራራ ብትውል አልሰማህም። ነገርኩህ የማይተች አንድም ሰው የለም። ሁሉም ይተቻል። የዐማራ ትግል ንፁሕ ወርቅ ነው። መጀመሪያ ጭቃ የሆነ ወርቅ። እሳት ውስጥ ገብቶ ተቃጥሎ የወጣ ወርቅ ነው የዐማራ ፋኖ ትግል። እድፋም፣ ኮተታም፣ ነውረኛ ለዐማራ ትግል አስፈላጊ አይደለም። ሌባ፣ የደም ነጋዴ፣ ውሸታም እንዲሁ አስፈላጊ አይደለም። ምንም ብትለኝ አልሰማህም። እኔ የማዳምጠው ፈጣሪዬን እና በምድር ከስቃዩ ስፍራ ላይ ያሉትን አባቶቼን ብቻ ነው። ድሮም ቡሆን ቲክቶከራም ቲክቶከራም ነው። ምን አባቱ ያመጣል? ስድብ እንደሆነ ቀለቤ ነው። ልብሴ ነው። ስትሰድበኝ ውለህ ብታድር አይሞቀኝ አይበርደኝ። ጭራሽ ብሎ ብሎ ስታሊን እኔን ከዐማራ ፋኖ ትግል ይውጣ ይበለኝ? እሱስ እሺ እነ ጂጂግግ ግን ምን ነክቷቸው ነው ስታሊን ልክ ነው ዘመድኩን የምትባል ሰይጣን የሰይጣን ቁራጭ ከዐማራ ትግል ውጣልን የሚሉት። እኔ ኬሬዳሽ። ይኸው ነው።
ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም…
"…ያመሰግን ዘንድ፣ ትንሣኤውንም ያውጅ ዘንድ የሚጠበቀው 1ሺ ሰው ሞልቷል። በምስጋና መሃል ኮተት ሓሳብ የሚደነቅሩ ባን ይደረጋሉ ብዬ ቃል በገባሁላችሁ መሠረት ወደ 33 የሚጠጉ በምስጋና መሃል የራሳቸውን ኮተት ይዘው መጥተው ሊዘበዝቡ የሞከሩ ሰዎች ተቀስፈዋል። አለቀ። ይህ የቤቴ ህግ ነው። በምስጋና ሰዓት ሌላ ወሬ መዘብዘብ ያስቀስፋል።
"…ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ተለመደው ሰናፍጭ ወደ በዛበት፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም ልክ እንደ ትናንቱ ብቻዬን አንድም ምድራዊ አጋዥ፣ ተደርቦ የሚሟገት፣ የሚከራከርልኝ ሳያስፈልገኝ ሓሳቤን በአደባባይ ለሽያጭ አቀርባለሁ። ሓሳቤን የወደደ ይገዛዋል፣ ይሸምተዋል። ሓሳቤን ያልወደደው ይነካዋል። ሱቄ በራፍ ላይ ቆሞ ስድስድ መጫወት ከባድ የመቀሰፍ አደጋም ያመጣበታል። ተናግሬአለሁ።
"…ሰሞኑን ባነሣሁት ሓሳብ፣ በተፈጠረ ፍትጊያ ይሄ ነው ተብሎ የማይገለጽ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር ወደ መስተካከል መጥቷል። ጫጫታውም እየበረደ ነው። የሸከኩኝ ነገሮች ሁሉ ፍጥጥ ብለው እየወጡ ነው። በጎጃም የፈራሁት እና ስጽፈው የቀወጡ ሁሉ ዛሬ ሲንበጫበጩ ሳይ በሳቅ ነው የምፈርሰው። ግራቀኝ የማያይ፣ ነገር የማይመረምር፣ ቲክቶክ ስላገኘ ብቻ የሚበጠረቅ ሰው አግኝተው የሚጦዙ ሰዎች ለእኔ መዝናኛዬ ናቸው። ታስቁኛለሽ ነገር ማለት ነው።
"…ወዳጄ ብቻህንም ብትቆም ከመንጋው ጋር ልክ ባልሆነ ልዩነት አንድ ለመምሰል አትላላጥ። አሁን ይሄ ሁላ ጥቁር ዣንጥላ ውስጥ አንድ ቀይ ዣንጥላ መኖሩ በራሱ ውበት አይደል እንዴ? ልዩ እኮ ነው። የሌለ ውብ እኮ ነው። እኔ ዘመዴ ማለት ቀዩ ዣንጥላ ማለት ነኝ። አላምርም…? 🎷🎷🎷😂
"…ከነከስኩ ሳላደማ አልመለስ አይደል? እናም ፒፕሉን ላንጫጫ ልመጣ ነኝ። ዝግጁ ናችሁ?
"…አሁን ለአስተያየት ክፍት ነው። ከፀያፍ ስድብ በቀር አስተያየት መስጠት መብት ነው። የተቃውሞም ቢሆን የተፈቀደ ነው። መሳደብ ግን እፉ ነው። ያስቀስፋል። አስተያየት ያልሰጠ ወላጅ ያመጣል ስላላልኩ ካልገባህ ዝም በል።
Читать полностью…"…ሟች ከመሞቱ በፊት ከመልአከ ሞት ጋር ይተሻሽ ነበር አሉ። ከአስብቶ አራጅ፣ ከሰር ውስጥ እባብ፣ ከሸማቂ ጓደኛ ከቁማርተኛ ወዳጅ ዘመድም ይሰውራችሁ።
• የእነ ዶር አምባቸውን፣ ጄነራል ሰዓረ መኮንንም ነፍስ ይማር…!
• አሜን… 🙏🙏🙏
👆ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍
ጎበዝ…
"…ገንዘብ ባለበት ስፍራ የማይጠፉትን፤ እንደ ጥንብ አንሳ፣ እንደ ጆፌ አሞራ ተወርውረው የሚሰፍሩትን፣ ግንቦቴ እና ግንባሮችን እያባረርን የዐማራ ፋኖ አመራሮች በወከሏቸው ሰዎች በኩል ብቻ ለሰብአዊ ጉዳት የሚውል ገንዘብ እና ዶላር መሰብሰቡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
• ጆፌ አሞሮቹን በጋራ እንከላከል።
• የጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች ይውደሙ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።