መልካም…
"…የሚጠበቀው ሺ አመስጋኝ በፍጥነት ሞልቷል። ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ተናፋቂው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም እንደወትሮው ነጭ ነጯን የሚዘረግፍ ነው። እንደ ኮሶ የሚያሽር ኮምጠጥ፣ መረር ያለ ሰናፍጭ የበዛበት ሚጥሚጣ በቃሪያ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ ነው።
"…ክረምቱ እየመጣ ነው። እናስ የፋኖና የብልፅግና የዋንጫ ጨዋታ ምን ይመስላል የሚለውን ነው የሚዳስሰው ርዕሰ አንቀፁ። አጥፍቻለሁ፣ በድዬአለሁ ብላ ምርጫ ቦርድን ይቅርታ ስለጠየቀችው ዱቄት ህወሓት በሌላ አንቀጽ እንመለስበታለን። የጦር ዝግጅቷም ቪድዮ ደርሶኛል እንመለስበታለን። አሁን ግን ወደ ርዕሰ አንቀጻችን እንመለሳለን።
"…10 ሺ ሰው አንብቦት፣ 300 ሰው ላይክ ካደረገው የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ሓሳባችሁን ጽፋችሁ ጠብቁኝ።
• ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ አይደል?
"…ዌል እንግዲክ… ኡሙንዱኖኢሹ የእኔ ቦንቦሊኖ የሚያስመስለው ማነው Botox የሚሉት ይሄ ነው አሉኝ። መርፌው የተረሳ ቀን በቃ ማድያቱ ሁሉ ፍጥጥ ነው የሚል አሉ። አይጣል እኮ ነው። ከዚያ እነ እንትና ውይ የእኔ ጌታ ሲያምር፣ ስታምር ብለን ፍጥጥ ነው አሉ። 😂
• ማይሞችዬ… በሉ እየተ Botoxከሰካችሁ…!
"…አዪዪ መከራዬ… ! ዳኒ አሞሌ ጨው ነው ያለው ጃውሳው አሁን ደግሞ ምን አድርጎ ይሆን የዳኒ ድምጽ እንዲህ የተቀየረው…? ምቱ ይሆን እንዴ? አይ ጃውሳው የሥራህን ይስጥህ?
"…በ ፈረንጆቹ F ቃል መሳደብ እኮ ነው የቀረው። ኧረ ባባጃሌው። ዳኒዬ እንደ ሲንጋፖር መጨከን ነው የሚያስፈልገው። መጨከን ዳኒ። ጨከን በል።
• ቡቶክሶችዬ እየተማየማችሁ…!😁
"…ጥያቄ ነው…?
"…እሺ አቶ በቴን በዚህ መልክ በአሰቃቂ ሁኔታ ባይገድሉት ምንአለበት? በእውነት ግፍ ነው። አንዳንድ ኦሮሞዎች ይሄን ምስኪን ሰው ረስተው ኮሪደር ልማት እያሉ ሲጨፍሩ ሳይ ይገርሙኛል። እኔማ አቢይ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ብስክሌት የሚያሽከረክር ሁላ ነው የሚመስለኝ።
• ቆይ ከተማ የሚለማው ለማነው?
ጥያቄ ነው…???
"…የዐማራ ክልል ሕዝብ ጦርነት ላይ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሀገር ምን ዓይነት ጉዳት እየደረሰ እንዳለ ይሰማችኋል? የኢኮነሚስቶቹን ትንታኔ አቆዩና እስቲ እናንተው የሸቀጣ ሸቀጥም ሆነ የእህል ወዘተ ነጋዴዎች እና ሸማቾች የሆነ ነገር በሉን።
"…ይሄ ሁሉስ ጦርነት በምድሩ ላይ እየተካሄደ የዐማራ ሕዝብ ከቀዬው፣ ከመንደሩ፣ ከአድባር ከደብሩ ንቅንቅ የማይለው፣ ወደ ሱዳንም፣ ወደ ትግራይም የማይሰደደውስ ለምን ይሆን? አይገርምላችሁም?
"…ጦርነት የትም ይነሳ የት ሕዝብ መሰደዱ ግድ ነው። ዩክሬንን፣ ጋዛን ማየት ይቻላል። ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ አፍጋኒስታንንም አይተናል። ወንድሞቻችን ትግሬዎች ወደ ሱዳና ወደ ዐማራ፣ ኦሮሞዎች ከሱማሌ ወደ ሸዋ ሲሰደዱም አይተናል። ዐማራን በእሳት መሃል ተረጋግቶ እንዲራመድ ያደረገው ምንድነው ትላላችሁ?
• በቀለጠ ጦርነት መሐል ተረጋግቶ፣ ወዙ ጨፍ እንዳለ ሳይቀየር፣ ፈጣሪውን እያመሰገነ እንዲኖር ያደረገው ነገር ምንድነው? እንዲህ ዓይነቱ ተፈጥሮ ልዩ ጥበብን እና መሰጠትን ይጠይቃል ብዬ እኮ ነው።
• የጎጃም፣ የምንጃር ጤፍስ በምን ተተካ? በስንዴ?
• እናውጋ እስቲ…
"ርዕሰ አንቀጽ"
• ለፋኖዎች የሚጠቅም መረጃ ነው።
"…ከትላንት ወዲያ ጀምሮ ሱ-29 ጀት ልምምድ እያደረገ ነው። ከምርቃቱ በኋላ አንዴ ተነሥቶ ነበር። የአሁኑ ልምምድ ለህወሓት ጦርነት ጊዜ እንደተደረገው ዓይነት የውጊያ ልምምድ ነው። ይህን ማወቁ ለፋኖ ለጥንቃቄ ጥሩ ነው። ምንአልባት በድሮን ብቻ ሳይሆን በጀትም ድብደባ ሊኖር ስለሚችል ካሁኑ ጥንቃቄ ማድረጉ ጥሩ ነው። ባህርዳርን እንደበፊቱ ለድብደባ መነሻ ላያደርጉ ይችላሉ። ምንአልባትም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ጀቶቹ መነሻቸውን የአክሱም አየር ማረፊያን ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
"…ካለፈው አርብ ጀምሮ በአየር ኃይል ግቢ ከኦሮሞ ተወላጅ ውጪ ያለው እያጉረመረመ ነው የሚገኘው። የማጉረምረሙ ምክንያት ደግሞ በደብረዘይት አየር ኃይል ውስጥ አሁን በሥራ ላይ ያለ ወታደር የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ ብቻ በደብረ ዘይት የቤት መሥሪያ መሬት ይሰጠው ሌሎች ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ ወዘተ ደግሞ በክልላቸው መሬት ይውሰዱ በመባሉ ምክንያት ለምን የሚል ጥያቄ ተነሥቶ ለተነሣው ጥያቄም ከላይ የመጣ መመሪያ ነው፣ ይህንን ጥያቄ ክልላችሁን ጠይቁ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
"…ሌላው ጥያቄ የሆነው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ባሌም፣ ጅማ፣ ወለጋ፣ ሀረርጌ፣ አሩሲም ሆነ ከሚሴ የተወለደ ኦሮሞ እዚያው መሬት ሲሰጠው ደብረዘይት ተወልደው የደብረ ዘይት ልጅ የሆኑትስ ምን ይደረጉ ሲባል ኦሮሞ ካልሆነ አይሰጠውም የተባለ ሲሆን እነሱስ የት ይጠይቁ ሲባልም ወታደሩ መታወቂያ ወይም መዝገቡ ላይ ባስሞላው ብሔር ክልል ሄዶ ይሰጠው በመባሉ ነው አሉ ጉርምርምታው በዝቷል የተባለው። ይሄ ጉርምርምታ ወደፊት የሚኖር ግዳጅ ላይ በእርግጠኝነት ችግር መፈጠሩ አይቀርምና ይሄን ችግር ወስዶ ከወዲሁ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል የሚሉም አሉ። ሆድ ለባሰው ማጭድ ማዋስ ማለት ነው።
"…በሌላ በኩል ሰሞኑን በባህርዳር ሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና መምሪያ መግቢያ በር ላይ 3 ምሽጎች ተሠርተዋል። በፊት የነበሩት ስለፈረሱ ሰሞኑን እንደ አዲስ ነው የተሠሩት። ከዕዙ ውስጥም በጫካው ውስጥ የኮንክሪት ምሽግ ተሠርቶ መጠናቀቁም ተነግሯል።
"…ሌላው መረጃም ከላይ የመጣ ነው በተባለ መመሪያ መሠረት ሰሞኑን የስታፍ አባላት ሳይቀሩ ተመልምለው ለግዳጅ ከፋኖ ጋር ለመዋጋት እየሄዱ ያለበት ሁኔታ መኖሩም ተሰምቷል። የተወሰኑ የሠራዊት አባላትም የመጀመሪያ የህክምና ዕርዳታ ለመስጠት ተብለው ተመልምለው ተሰብስበው መግለጫ ከተሰጣቸው በኋላ የት እንደሆነ ባላይታወቅም ወደ ግዳጅ ወጥተዋል። ነፍስ ይማር።
"…ስለምን ጉዳይ እንደሆነ መጨረሻው ባይታወቅም ሰሞኑን በተከታታይ እየተሰበሰቡ ነው ያሉት። አሁን ለጊዜው እያወሩበት ያለው የስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ መከላከያ ራሱ የታክቲክ ለውጥ ለማድረግ ማሰቡን ነው የሚያመለክተው። ይሄም የታክቲክ ለውጥ ልክ እንደ ፋኖ እኛም የጉሬላ ውጊያ ካልገጠምን በቀር በዚህ አካሄዳችን ኃይል እንጨርሳለን እያሉ ነው። የህወሓት ጉዳይ የተጀመረውም የፋኖን ሓሳብ ለመከፋፈል፣ ሕዝቡን ከአገዛዙ ጎን ለማሰለፍ ጭምር ነው። ይሄም ከሽፏል። ይከሽፋልም። በቀጣይ ፋኖዎች በምድር ሲዋጉ ከላይ ሊመጣ የሚችለውን በማሰብ ልክ እንደ ጀት፥ ድሮን፥ ሚግ ... የመሳሰሉት ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸውም ተመክሯል። እናም ፋኖዎች ድል ካደረጉ በኋላ አንዳንድ ጊዜ በስሜት ተሰብስቦ መጨፈርም ለተለያዩ ጥቃቶች ያጋልጣልና ጥንቃቄ ይደረግም ተብሏል።
"…ሌላው ደግሞ የዐማራ ሚሊሺያ እና የዐማራ አድማ ብተናን በተመለከተ ቆስለው ሲመጡ ከመከላከያ ሆስፒታል ከወታደሩ እኩል እንዳይታከሙ፣ በቀጥታ ወደ ሲቪል ህክምና ተቋማት በሪፈራል መልኩ ለብቻቸው ይታከሙ የሚል ሓሳብ ተነሥቶ ለትግበራው ዝግጅት ይደረግም ዘንድ መመሪያ መውረዱም ተነግሯል። የቆሰሉ ሚሊሻዎችና አድማ ብተናዎች ብቻ ሳይሆኑ ሲቢሉ ሕዝብም ወታደሩ ቆስሎ ሲመጣ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሕክምና አቋርጠው የሆስፒታሉን አልጋ ለቆሰሉ ወታደሮች ለቅቀው እንዲወጡ መወሰኑም ተሰምቷል። ይሄ ደግሞ ለሚሰማ እና ለሚያገናዝብ ገረድ ብአዴናም ሁላ ብልፅግና ራሱ እንደ ሸንኮራ ተጠቅሞ እየጣላቸው መሆኑን ያመለክታል።
"…በቀጣይ መከላከያ ከፋኖ ጋር ሊያደርግ የሚችለው የመጨረሻ ውጊያ በከባድ መሳሪያዎች የተጋዘ ነው የሚሆነው። እንደ ታንክ፣ መድፍ፣ ዙ 23፣ ጀት፣ ድሮን፣ ሚግ ወዘተ ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ መልኩ ሊጠቀም ይችላል። ስለሆነም ፋኖም ለዚህ የሚሆን አሪፍ እና የተሻለ ታክቲክ ይዘው ቢጠብቁ መልካም ነው።
"…በመጨረሻም ለፋኖ የተለገሰ ምክር እንዲህ የሚል ነው። ከድል በኋላ ተሰብስቦ አለመጨፈር። የተማራኪ ወታደሮችን ትጥቅ ከችፕሶች አብጠርጥሮ መፈተሽ። የፋኖ መሪዎች ስልክ እንዳይጠቀሙ ማድረግ፣ የፋኖ አባላትን የእጅ ስልክም ጠርንፎ ማስቀመጥ። ምሽት የመኝታ ስፍራዎችን መቀያየር ወዘተ ይተግብሩ ተብሏል። ለምሳሌ መከላከያ አሁን የጀመረው የአንድን አካባቢ ፋኖ በተናጥል ማጥቃት ነው የያዘው። ይሄም ተተኳሽ ለማስጨረስ የተወሰነ ውሳኔ ስለሆነ በተቻለ መጠን ብዙ ስዓት የሚወስድ ውጊያ አለማድረግ። ቢቻል አጭር ተልዕኮ፣ በአነስተኛ የሰው ኃይል፣ በአጭር ጊዜ፣ በደፈጣ ማከናወን የተሻለ አማራጭ ይሆናል። ደፈጣ፣ የሽምቅ ውጊያ ሥርዓቱን በቁሙ አክስሮ የሚቀብር ፍቱን የውጊያ ሥልት ነው።
"…እስከዚያው እነ አቢይ አሕመድ አዲስ አበባን በቀለም እና በመብራት እያሳመሩ ሕዝቡን በባዶ ሆዱ ያጭበርብሩ። ፋኖም ሥራውን ይሥራ በሀገር፣ በቀዬ በሠፈሩ። ተብሏል። ለፋኖዎች አድርሷቸው።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
"…መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 1ኛ ቆሮ፥ 3-4
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ከሚመሳሰሉ፣ ከሚግባቡአቸው፣ ነገርየው የገባቸውን ሰብስቦ፣ የሆነ የተለየ ግሩፕም ከፍቶ ለመወያየት እንዲህ ያለው ልጥፍ እጅግ ጠቃሚ ነው።
"…እንደምን አደራችሁ ለሚል ልጥፍ እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ ለመመለስ ትምህርት አይጠይቅም። ማንኛውም ሰው 12 ፊደላት ያሉትን ቃል ተጠቅሞ ሊመልስ ይችላል። ሺ ሰዎች በሰዓት ውስጥ ፔጄን ሊያጥለቀልቁ ይችላሉ።
"…በፎቶና በአጭር ቪድዮ ስር መልእክቱ የሚያስቅ ከሆነ ለመሳቅ፣ የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስም ከሆነ "አቤቱ አምላክ ሆይ ለምን ተውከን" ብሎ ለመጸለይ የኮመንት መስጫ ሰንዱቁ ላይ ማንም ሊሰለፍ ይችላል። የሆነ አካል ለማብሸቅ፣ ለመፎተት፣ ለመፎገር፣ ለማጀገን ተብሎ በተለጠፈ ልጥፍም ላይ ኮማቹ ይበዛል። ከበድ የሚለውና አብዛኛው ወገቤን የሚለው ግን የዚህ የዛሬው ዓይነቱ ልጥፍ ላይ ነው።
"…የዛሬውን ርዕሰ አንቀፅ 36 ሺ ሰው፣ አስተያየታችሁን ስጡ የሚለውንም እንደዚያው ከ20 ሺ ሰው በላይ አንብቦታል። ያነበበው ገብቶት በሚገባ በሥነ ሥርዓት አስተያየቱን የሰጠው ሰው ግን ቁጥሩ 60 ቤት ነው። እዚሁ ላይ ለቧልት፣ ለፌዝ፣ ለቀልድ የመጡትን ኮመንታቸውን አንስቼባቸው ማለት ነው 60 ቤት ሰዎች የተገኙት።
"…አሁን እኔ እዚህ መንደር የኢትዮጵያ ፖለቲካ የገባቸው እንደልቤ የሆኑ በጣም ጥቂት ሰዎችን አግኝቻለሁ። ተደብቀው የሚያነቡኝ እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። ስለዚህ ለጀማው ገብስ ገብሱን እያቀረብኩ ጠንከር ጠንከር ለሚለው ራሱን የቻለ ሌላ የውይይት፣ አዳዲስ መረዳትና ሓሳብ ያላቸውን ሰዎች የያዘ ግሩፕ መፍጠር እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው። ደግሞም አደርገዋለሁ።
"…ከዚህ ልጥፍ መልስ ራያ እወስዳችኋለሁ። የእኔ ሥራ ኦሮሙማው እንዴት በህወሓት ስግብግብነት፣ በብአዴን ጀዝባነት ዐማራና ትግሬን እንደሚያፋጇቸው ማሳየት፣ መጠቆም ብቻ ነው።
• አይደለም እንዴ?
"ርዕሰ አንቀፅ"
ሀ፦ አገዛዙ ከወያኔ ጋር በጋራ እየሠራ ወያኔ ራያን ወረረች ወልቃይትም አይቀርለትም የሚል ወሬ እንዲወራ ለምን የፈለገ ይመስላችኋል?
ሁ፦ ይህን እያለ ያለው ደግሞ በሸገር ራድዮ ለአዲስ አበባና ለአካባቢው ሕዝብ፣ በአሚኮ በኩል ለዐማራ ሕዝብ ብቻ መሆኑስ ምን ይጠቁማችኋል?
ሂ፦ እና አብይ ከCIA ማንዋል በተዋሰው የተለመደ አሰራር ጦርነት ወያኔ ከፍቶ እሱ አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ እንዲመክን ማድረጉ፣ የንክክር ኮሚሽን፣ የኮሪደር ልማት ጉብኝት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት በየክልሉ ሁሉ መሆኑ እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የለብ ለብ ሠራዊት ወደ ክልሉ ልኮ በመወጠር መሆኑን ስታይ ፋኖ አይ በቃኝ ልደራደር ይለኛል ሊል ፈልጎ ነው ወይስ የዐማራ ሕዝብ ከፋኖ ይነጠልልኛል ብሎ በማቀድ ?
ሃ፦ ይህ ባይሆን የህውሓትን ወረራ በአሚኮ በኩል አያስነግርም ነበር። ምክንያቱም ሚሊሻና አድማ በታኝ እንዲሁም ብአዴኖችን በገፍ ወደ ፋኖ እንዲቀላቀሉ ከማድረግ ገበሬውና ሕዝቡ ወያኔን ከላከብንማ በሚል ንቅል ብሎ ፋኖን ይደግፍበታል። እንዲያ ከሆነ ደግሞ ምን አገኝ፣ ምን አተርፍ ብሎ ነው? እስቲ እይታችሁን አካፍሉኝ።
"…አብይ አህመድ መቼም ቢሆን ወልቃይት ወይም ራያን የትግራይ ወይም የዐማራ ነው ብሎ በይፋ አይናገርም። በይፋ የትግራይ ነው ማለት ይቅር እና በዝምታ ለህወሓት ቢሰጣት እንኳን የሚፈጠረውን ያውቃል። አሁንም በምዕራባውያንና በአረቦቹ ቀመር የሚመራው የኦሮሙማው ጨዋታ ያልገባው አንዳንድ ጎጋ ደነዝ ሆዳም ዐማራና አብይ አህመድ የእውነት ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ የሚያምን ነፍ ጄኔራል ጭምር እንደሚነሳበት ያውቃል። ምኑ ሞኝ ነው የበሻሻው።
ሄ፦ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱስ የሚከተለው መንገድ ለታክቲክ ነው እየተባለ እሱ ያላለውን ሌሎች እሱን ሆነው የሚወረቱንስ እስከመቼ እንታገሳቸው? ደመቀ ሚሊሻ አሰልጥኖ ፋኖን የወጋውስ ለታክቲክ ብለን አሁንም እንመን?
ህ፦ በመጀመሪያው ጦርነት አብይ ለራሱ ህልውና ሲል ወልቃይት ላይ ያለ የሌለ ኃይሉንና የወልቃይትን ሕዝብ ተጠቅሞ ቦታውን ገድግዶ አጥሮ ይዞ እንደነበር ይታወቃል። አሁንስ አቢይ በወልቃይት በኩል ለአገዛዙ ስጋት አለብኝ ብሎ ያስባል ወይስ አያስብም። ካሰበ ምን ሊያድርግ ይችላል? ምክንያታችሁ ይጻፍ።
ሆ፦ ጭራሽ የወልቃይት በህወሓት መያዝ ለእሱ ትልቅ የዋንጫ ጨዋታ ነው የሚሆንለት፣ በፊት ጎንደሬውን እስከ ጥግ አስተባብሮ ወልቃይት እንዳይያዝ የተጣጣረውን ያህል አሁን ደግሞ በተቃራኒው ነው የሚጫወተው የሚሉም አሉ። እናንተስ ሓሳባቸውን ትጋራላችሁን?
ለ፦ ህወሓት ወደ ወልቃይት እና ራያ የምትመጣው እንደበፊቱ በአማሪካ እና በሱዳን በኩል በሚመጣ አቅም ነውን ወይስ በራሳችን በኢትዮጵያ በአየር መንገዳችን በኩል በፌደራል መንግሥቱ በኩል እስከ ጥግ እስከ አፍንጫዋ ታጥቃ…?
ሉ፦ እንበልና ህወሓት በዚህም በዚያም ብላ ቦታውን ከያዘች በኋላ ወደ ሌሎች የዐማራ ግዛቶች ውልፍት አትልም የሚሉ አሉ። ምክንያቱ ደግሞ ቀሪው ዐማራ ወደኔ ካልመጣች በሚል ስሜት ቆሞ እንዲያይ ለማድረግ ይረዳቸዋል የሚሉ አሉ። እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ሉ፦ ህወሓት ቶሎ ብላ ቦታዎቹን እንድትይዝ ይደረግና፣ ቦታዎቹን እንደያዘች ከተረጋገጠ በኋላ ይሄ ጌታቸው ረዳን ያስፈነጠዘው የምክክር ኮሚሽን ተብዬውን አብይ አመድ ሪፈረንደም በማለት አፈጣጥኖ ጉዳዩን ሕጋዊ መልክ አስይዞ በድል ላይ ድል ይቀዳጃል። ከዚያም ሁለት አንድ ዓይነት ሕዝብ ናችሁ። ምንድን ነው በቁራጭ መሬት መጣላት? ተስማምታችሁ ኑሩ አልያ ስትቦጣቦጡ ኑሩ ብሎ ፋይሉን ሊዘጋው ይችላል የሚሉም አሉ? እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ሊ፦ የጎንደር ፋኖ ህወሓት በዘመናዊ የጦር መሳሪያና የበሕዝባዊ ማእበል የተዋጊ ኃይል ወደ ወልቃይት እንደምትመጣ፣ በተዘዋዋሪም በትግራይ በኩል ዩኒፎርም ለብሶ ወልቃይት ለመግባት የተዘጋጀ "ኦሮሙማ የመከላከያ" ጦር እንዳለስ ያውቃሉን? ለዚህስ ዝግጅት እያደረጉ ነው?አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ያዥው በሚል የሚመጣውን ኃይል በዐማራዊ ኃይል ብቻ ለመመከት ወስነው በዚያ ልክ እየተዘጋጁ ነው? ወይስ አሁንም የወልቃይትን ጉዳይ ለኮሎኔሉ የተከዜ ዘብ፣ አለፍ ሲል ለጎንደሬ ብቻ ትተው ዘጭ ብለው ተቀምጠዋል?
ላ፦ ፋኖን ያገለለው ታክቲከኛው ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ😁 ለወያኔ ጦር ምን ዓይነት ታክቲክ ሊጠቀም ይሆን?
ሌ፦ ኮሎኔሉ በአብይ አህመድ የሚታዘዘው የኦነግ ጦር የእሱንም ትእዛዝ የሚቀበል መስሎት ይሆን?
ሎ፦ የኮሎኔል ደመቀ ጦር ከወልቃይት ውጣ ሲባል ይወጣል? ወይስ አልወጣም ብሎ ከመሪ ድርጅቱ ብልፅግና፣ ከአለቃው አቢይ አሕመድ ጋር ይጋጫል? ያኔስ ከረፈደ በኋላ አብይን ሊከሰው ነው? የመክሰሻ ጊዜ ይቅርና ጉዳዩን ለሕዝብ የማድረሻ ዕድልስ ይኖረው ይሆንን?
ሐ፦ አቢይ አሕመድ ወልቃይት የትግሬ ነው ካለስ? ምን አስቧል ጎንደሬ?
ሑ፦ ህወሓት ተሳክቶላት አንዴ ወልቃይትን ከያዘች በኋላ አስለቅቃለሁ በሚል ከቀሪው የዐማራ ክፍል የሚንቀሳቀስ ፋኖ ካለ በአብይ በድሮን እየመታ፣ አለኝ የሚለውን መሳሪያ ሁሉ በህወሓት በኩል በመተኮስ "ህወሓት ናት፣ በሱዳን በኩል ድሮን ስላስገባች" ብሎ ይገግማል የሚሉ አሉ። እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ሒ፦ አቢይ በደመቀ ዘውዱ በኩል ከመከላከያ ጋር ሆኖ ወልቃይትን እንደተቆጣጠርኩት አሁንም ህወሓት ወልቃይት ብትገባም በመከላከያ ሠራዊቴ ወልቃይትን አስጠብቃለሁ ብሎ አስቦ ነው የሚሉ አሉ? በጄኖሳይድ ይካሰሱና ጸብ ላይ የነበሩ ሁለቱ ኃይሎችን እንዲህ ያጣበቃቸው ምን ዓይነት አዲስ የታክቲክ ፍልስፍና ይሆን?
ሓ፦ ህወሓት ወልቃይት ላይ በምታደርገው ፍልሚያ ሕዝቡ ፋታ አግኝቶ እንዳይከታተልና አብይ አህመድንም ህወሓትን በመደገፍ እንዳይጠረጥረው እንዲሁም አብይ በቃኝ ብሎ እንዳይቆርጥ ለማወዛገብ እንደተለመደው ከወዲሁ ታላላቅ አጀንዳዎችን መፍጠሩ አይቀርም። እናስ ከፊታችን ብልፅግና እና ህወሓት በምዕራባውያኑ የማደናገሪያ ማንዋል ላይ ከተጻፉት ታላላቅ አጀንዳዎች መሃል ይመጣሉ ብላችሁ የምትጠብቋቸውን አስቀያሽ አጀንዳዎች እስቲ የቻላችሁትን በጽሑፍ ግለፁ። ከኮሪደር ልማት፣ ከሚሞት አርቲስት፣ ከንክክር ኮሚሽኑ ወዘተረፈ ሌላ የምትጠረጥሩትን አጀንዳ ጥቀሱ።
ሔ፦ ሰኔ 30 ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?
ሕ፦ ህወሓት እንደ ራያ ወልቃይትንም ከወረረች የዐማራ ብልልግና ብአዴን ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል?
ሖ፦ በመከላከያ ውስጥ ያሉ ዐማሮችስ ምን የሚወስኑ ይመስላችኋል?
"…ለዛሬ በዚህ ይብቃኝ። የእናንተን ምላሽ ዓይቼ ካነሰ እያየሁ እጨምራለሁ። ከመጠይቆቹ ውስጥ ሁሉንም የመመለስ ግዴታ የለባችሁም። ከጥያቄዎቹ መሃል ደስ ያላችሁን ብቻ መርጣችሁ መመለስ ትችላላችሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
“…እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤” መዝ 78፥65
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሁድ ምሽት በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው መርሀ ግብራች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወደ እናንተ ይቀርባል።
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/vlpZjPys7LM
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
"…ወያኔን ወይም ጁንታውን ለመደምሰስ፣ አባይ ጸሐዬን፣ ስዩም መስፍንን፣ ዓባይ ነፍሶን ለመገንደስ፣ 1.2 ሚልዮን ትግሬን ለመቀነስ፣ ፋብሪካውን ነቅሎ አውድሞ ለመመለስ ወደ ትግራይ ከዘመቱት 15 ጀነራሎች መካከል 13ቱ ኦሮሞ ሆነው ሲገኙ የሚሰማህ ስሜት እንዲህ ነው የሚያደርግህ። stockholm syndrome አለ ሱሬ።
Читать полностью…"…እንደተናገረ ተነሥቶአል ! ማቴ 28፣6
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
አባትና ልጅ ተገናኝተዋል…!
• ፎቶውም የዛሬ ነው። በግምት 11:30 ሰዓት አካባቢ።
"…የሸዋዎቹ ፈርጦች አርበኛ፣ ደራሲ፣ ኮማንደር ፋኖ ጋሽ አሰግድ መኮንን እና አርበኛ ፋኖ ሻለቃ መከታው የዛሬ ወር የግንቦት ልደታ በዕለተ ልደቷ ለማርያም በስልክ ባወሩ፣ በመከሩ፣ በተወያዩ ዛሬ ደግሞ ሰኔ 1 መልሶ በዕለተ ልደቷ ለማርያም በእመቤታችን በልደቷ ዕለት በሽማግሌዎች አማካኝነት በአካል ተገናኝተው፣ ተወያይተው፣ አውግተው የሸዋን አንድነት በታላቅ ፍቅር ወደ አንድ ለማማጣት መወሰናቸው ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ሙሉ ዝርዝር መረጃውን በነገው ዕለት በሰፊው እመለስበታለሁ።
"…ወዳጄ ሸዋ ባላመጠ በዓመቱ ይውጣል የሚባለው ብሂል እኮ እውነት መሆኑ ይኸው ታየ። ከመለያየት፣ ከመነጣጠል፣ ከማወሳሰብ፣ ከማጣላት፣ ከማራራቅ፣ በወንድማማቾች መሃል ሽብልቅ ከመክተት ይልቅ እንዲህ በማቀራረብ አንድ ማድረግ ያጸድቃል። የደም ነጋዴዎች እርማችሁን አውጡ።
"…አሁን ጎጃም ወደ ፩ ፋኖ፣ ወሎም ወደ ፩ ፋኖ፣ ሸዋም ፩ ወደ የፋኖ አደረጃጀት መጥቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። የጎንደሩም እርቁ የኪዳነምህረት ዕለት ተፈጽሞ የወረቀት ሥራው ነው ያደከመን እንጂ የሆነ ቀን አንድነቱ ከፍጻሜ ደርሶ አንድ ሆነው እንዲህ ሰበር የምሥራች መስማታችን አይቀርም።
• እልልልል በል ዐማራ…!💪💪🏿✊
"…መልካም…
"…ርዕሰ አንቀፁን እንዳነበባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ፋኖን በቄስ፣ በሼህ በሽማግሌ ለምናችሁ አምጡልን፣ ያመጣችሁትን ሰው ደግሞ እንኳን ልንገድለው በጥፊ አንመታውም። እነሱ እናንተን ይጠብቃሉ እኛ ደግሞ ወልቃይትን እና ራያን እንጠብቃለን አላለም። 😂 በፊት ራያንም ነበር የሚሉት። እሱን ካስበሉ በኋላ አሁን ደግሞ የሚደናገር ብናገኝ ብለው ነው የሚዘበዝቡት።
"…በወልቃይት ጉዳይ ጦርነቱ አይቀሬ ከሆነ የወንድ ዘር በ10 ሺ ብር አይደለም በ100 ሺብርም የሚገኝ አይመስለኝም። የሆነው ሆኖ ርዕሰ አንቀፄ ላይ ጓ ማለት መብት ነው። የበዛ ካለ ቀንሳችሁ፣ የአነሰም ካለ ጨመር አድርጋችሁ አስተያየታችሁን መስጠት ትችላላችሁ።
• 1…2…3…ጀምሩ።
"…ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ቆሮ 15፥ 21-22
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
"…በመቀጠል ደግሞ የBotox Cosmetic አጠቃቀምን የሚያሳይ አንድ ቪድዮ እለቅላችኋለሁ። Botox ሱ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነው። የጎንዮሽ ጉዳትም አለው። ሲበዛ ከንፈራችሁን ፈርፍሮ፣ ወዝ አሳጥቶ፣ የከንፈራችሁን የውስጥ ገበሩን ሊገለብጥባችሁ ይችላል። Botox እንዴት ወንዱ እና ሴቱን ሁላ ኡሙንዱኖኢሹ ዱንቡሽቡሽ ቦንቦሊኖ እንደሚያስመስልም አሳያችኋለሁ። በቪድዮው ትልቅ ትምህርት ታገኙበታላችሁ ብዬ አስባለሁ። እሺ የእኔ ማይሞች። 😂
• አልተኛችሁም አይደል…?
"…ከአንድ የኦሮሚኛ ሙዚቃ በኋላ ተመልሰን እንመጣለን።
• ማስታወሻ፦
"…የግንባሩ፣ የሞጣና የብሪጅ እስቶን፣ የግምቦቴና የሠራዊቱም ቲክቶከሮች ትንሽ ቀን ይንፈራገጡ ዘንድ፣ እርስ በእርሳቸውም እየተበጣበጡም ስለሆነ እኔ ከዳር ቁጭ ብዬ ሙድ ልይዝባቸውም ስለፈልግሁ ለዛሬ ቲክቶክ አልገባም። በሉ እኔ ላይ እያሟረታችሁ ተፈሳፈሱ። "ዘመዴን አባረነዋል፣ ድባቅ መተነዋል፣ ሁለተኛ ቲክቶክ ድርሽ አይላትም ወዘተረፈ እያላችሁ ራሳችሁን በራሳችሁ አፅናኑ። 😂 ዛሬ አየሩ መጣም መጣም ሸጋ ስለሆነ እኔ ምሽቴን ከራየን ወንዝ ዳር ሽርር ብትን እያልኩ ዓለሜን ልቅጭበት።
"…ምድረ መወቀኛ ሁላ… ለዘፋኙ የሚበተነውን ገንዘብ እያየህ ዓይንህ ይቅላ አሉህ ደግሞ። ባንክ ዘርፈው ነው፣ ብር አትመው ነው፣ ሰው አግተው ነው ምናምን እያልክ አውራ አሉህ። እኛ የባንክ ብድር አጥተን መነገድ አቃተን፣ የ3ወር ደሞዛችን እስከአሁን አልተከፈለንም፣ ኑሮ ተወደደ፣ የቤት ኪራይ ጨመረ፣ ዳቦ ሰማይ ነካ እያልክ ብቻ ተዘፍዝፈህ አላዝን። ይሄ ምንቀኝነት ነው። እና ታዲያ እንዲህ እንደ ወያኔ አቅሉን ካልሳተ ባለጊዜ መባሉ ምኑ ላይ ነው?
• በሉ አርፋችሁ እየተደነሳችሁ…!
የ4 ኪሎ መስመር…?
"…አቢይ ለኮሪደር ልማቱ ግምገማ ዐማሮችን ሰብስቦ ( ሦስት ከጎጃም፣ ሁለት ከወሎ፣ አንድ ጎንደር) ከፊት በማሰለፍ እንዲታይ የፈለገው ምን መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው? ብአዴን 😂
• እሺ ኦሮሞዎቹ እንኳ ከኋላም በብዛት ይኖራሉ። ሱማሌም አለ አደም ይታየኛል። ደቡቦችም አሉ ሲዘምሩ እያየኋቸው ነው። የእኔ ጥያቄ ከታረቁ በኋላ እንዴት አንድ ትግሬ ለአመል እንኳ በዚህ የ4 ኪሎ መስመር ጉብኝት ላይ አላካተተም? ምን ማለት ነው? ትግሬ በአዲስ አበባ እድገት ላይ ምንም አሻራ አላሳረፈም ወይ? ተዉ እንጂ። ይሄማ ግፍ ነው።
"…አዲስ አበባ ግን የማን ናት? 😂
"…መልካም…
"…ከእኔ ጋር ናችሁ አይደል?
• መቼም የእኔ ነገር በቶሎ አይገባቹም… ለማንኛውም እንደ ፍሮፌሰሩ እየተስተማራችሁ ጠብቁኝ።
• የ 777 ድፍረት ግን እስከ ጥግ ነው።
መልካም…
"…ከምስጋናችን ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀፃችን ነው ማለት ነው። የዛሬው እንደተለመደው ርዕሰ አንቀፁን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
• አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና ዝግጁ ነነ በሉትማ። 😂😂 አደራ ታክሲ ውስጥ ብቻ ትእዛዙን ፈጽማችሁ ፎሊስ ጣቢያ እንዳትውሉ።
ፌደራል ፎሊሱን ተመልከቱት…
"…በመላ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ሰልፍ ክልክል ነው። ገና ስታስብ ነው ፌደራልም፣ መከላከያም ቆመጥና መትረየስ ይዘው የሚበትኑህ። በካድሬ የተመረጡ ሰዎች አቢይ አሕመድንና ብልፅግናን ለመደገፍ የተጠና ሰልፍ ሲያደርጉ ካልሆነ በቀር አይፈቀድም። ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይስፈን የሚል ሰልፍ ያዘጋጁ ሰዎች ገና መግለጫውን አንብበው ሳይጨርሱ ነው አዋሽ አርባ ተወስደው የተለበለቡት። ይሄንን ያዙልኝ።
"…ጌታቸው ረዳና አቢይ ለትግሬና ለዐማራ ምን እንዳሰቡ ፈጣሪ ይወቅ። ጎጋው የሂዊ ደጋፊ ትግሬም ምን እንደተደገሰለት ሳያውቅ በሬ ሆይ በሬ ሆይ የሚለውን ተረት እየተረቱበት ዐማራን ያበሸቀ መስሎት ዓይኑን ወልቃይትና ራያ ላይ ተክሎ እንደ በግ ወደ ቄራ እየተነዳ ነው። እንዲያውም አንዳንዶቹ ትግሬዎችማ አጋራቸው የሆነውን ኦነግሸኔን ሁላ መውቀስ ጀምረዋል።
"…ይሄ የምታዩት የራያው ሰልፍ ነው። ይሄን ፎቶ ሳይ በራያ ተገደለ የተባለውን ልጅ ትግሬዎቹ ለመግደላቸው ማረጋገጫ አይኖረኝም። ፌደራል ፖሊስ አዛዡ ኦሮሞ ነው። ፖሊሶቹም አብዛኞቹ ኦሮሞዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ሙሉ የተከለከለ ሰልፍ መጀመሪያ በራያ ብቻ እንዴት ፈቀዱ? እሺ ይፍቀዱ ፈቀዱ እንበል ፌደራል ፖሊሱን አያችሁት? 😂
"…ፌደራል ፖሊሱ ሰልፍ ሲያስተባብር አያችሁ? 😂 በሁለት ስልክ ሰልፉን ቀድቶ፣ የራያ ዐማራ ትግሬን ሲያወግዝ ቀርፆ ለማን ሊልክ ይመስላችኋል? ትናንት የብልፅግናዎቹ እነናቲ አንደግምም ወይ ን ጨምሮ፣ ከብአዴን ጋር ንኪኪ አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ አክቲቪስቶች በሙሉ የራያውን ሰልፍ ያለምንም ኢንተርኔት መቆራረጥ ነበር የደረሳቸው። እኛም ከእነሱ ነው የወሰድነው። አሚኮ ራሱ እዚያው ነበር።
"…የእኔ ጥያቄ የፌደራል ፖሊስ ቡሁለት ስልክ የተቃውሞ ሠልፍ የሚቀርጸው ለማን ለመላክ ነው?
• ደግሞ ስደቡኝ አሏችሁ…!
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀፁን በሚገባ ጊዜ ወስደን አንብበናል። ቀሪው ሰዓት ደግሞ የእናንተ ሓሳብ የሚኮመኮምበት ነው። ከተጠቁት ጥያቄዎች መሃል ያሻችሁን መርጣችሁ መልሱ። ከተጠየቀው ጥያቄ ውጪ ሌላ አስተያየት ለዛሬ አልቀበልም። አነሣዋለሁ። መለወስ ብቻ።
"…ዛሬ ምሽት እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ ይህንኑ እያወጋን እንቆያለን እንጂ በዚህ መሃል እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ሌላ ነገር በፍጹም አናወራም።
• የጋሽ ሰባተኛ ጨን የፎግረህ ብላን ግጥም እየሰማችሁ አስተያየት መስጠታችሁን 1…2…3… ጀምሩ…!
መልካም…
"…የሚጠበቀው 1 ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው በቀጥታ ወደ ርዕሰ አንቀፃችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችንም በራያ፣ ወልቃይት እና አዲስ አበባ ላይ ለመወያያ የሚሆን ጥያቄዎችን ማንሣት ነው ያማረኝ። የሸከኩኝን ጉዳዮች በጥያቄ መልክ ብናንሳና ብንወያይ ምን ይመስላችኋል?
• ዝግጁ ናችሁ…?
"…አሁን አሚኮን እያየሁ ነበር። ይሄን ዜና ካየሁ በኋላ ግን የሆነ ነገር ጠረጠርኩ። ኦህዴድ፣ ብአዴንና ህወሓት የመከሩ ይመስለኛል። ለሰልፉ ገፊ መነሻ የሚሆነውን ምክንያት ህወሓት ፈጥራ እንድት ተውን ሓላፊነቱን ወሰደች። ወሰደች እና አንዱን የራያ ወጣት በጥይት በታትና ገደለች። ከዚያ ይህን ምክንያት አድርገው ብአዴኖች ሰልፉን እንዲያስተባብሩ አዘዘች። ኦህዴድኦነግ ብልፅግና ደግሞ ለሰልፍ የሚወጣው ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማ ሳይይዝ ድምፁን ብቻ ወጥቶ እንዲያሰማና ፎክሮ ወደ ቤቱ እንዲገባ ጥበቃ እንዲያደርግ ተመደበ።
"…ሰልፉ የሕዝቡን ሙቀት መለኪያ እና ማስተንፈሻ ስለነበር በሚፈለገው መጠን ተቀሰቀሰ። ተፎከረ፣ ተሸለለ፣ ተጮኸ። በመጨረሻም የሰልፉ አስተባባሪ ሰውዬ ወደ መድረኩ ወጥቶ እንዲህ አለ። "እኛ ሕግ አክብረን ትጥቅ እንደፈታን ሁሉ አለ የሰልፉ አስተባባሪ የአላማጣው ወጣት። እኛ ሕግ አክብራን ትጥቅ እንደፈታን ሁሉ መንግሥት "ከቻለ" ከራያ መሬት ጠቅልሎ እንዲያወጣልን በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀናል። 😂😂 ብልፅግናን እኮ ነው መንግሥትን የሚለው። ቀልድ።
"…አስቂኙ ነገር የሚመጣው ደግሞ ከዚህ በኋላ ነው። መሳሪያና ትጥቃቸውን ፈትተው ከእኛ ጋር መኖር የሚፈልጉ ከሆነ ግን እኛ ራያዎች እንኳን ትግሬ ሌላውንም አቃፊ ነንና እንቀበላቸዋለን። አላለም። የት ልታሰፍራቸው ነው የምትቀበለው ወንድምዓለም ? 😂
"…ከዚያ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ብአዴን በአሚኮ በኩል ዜና ሠርቶ እዩልኝ ህወሓት የምትሠራብኝን ግፍ ፍረዱኝ ብሎ እዬዬ። እንዴት ዓይነት ቀልድ እንደተያዘ እኮ። ከዚያ ፋኖ ባይወጋኝ ኖሮ እኮ… ሊል ነው።
"…አይ ሰኔ 30 መቼም የማታሳየን ጉድ የለም።
"ርዕሰ አንቀፅ"
"…የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ያልለጠፈ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው የተባለ አንድ ነጭ አውሮጵላን ዛሬ ወደ አክሱም ከተማ በረራ መጀመሩ ተነግሯል። የመቀሌው ከጀመረ ቆየ። ወያኔ በወልቃይት ውጊያ ልትጀምር ነው። አሁን ሎጀስቲኩ አይቸግራትም። በቀጥታ በአየር መንገዱ ስንቅና ትጥቅ ወታደርም በሽሬ፣ በአክሱምና በመቀሌ ይራገፍላታል። አለቀ።
"…የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከአሁን ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አላቋረጠም። ከአዲስ አበባ አስመራ፣ ከአስመራ አዲስ አበባ ሽር ብትን እየተባለ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤንባሲ ተዘጋ ብለው የወያኔና የኦነግ አክ እንትፊስቶች ለምን እንደሚጮሁም አልገባኝም።
"…ሌላው ራያ የገባው የወያኔ ሠራዊት አንድ የራያ ዐማራ የሆነ የመብራት ሠራተኛ ተኩሰው ገድለዋል በሚል በራያ አላማጣ ምድር ቁና ሆናለች። አሳዛኙ ነገር ግን ራያ ባዶ እጁን መሆኑና እስከ አሁን "መንግሥት" ብሎ ብልፅግናን አምኖ የተቀመጠ ምስኪን ሕዝብ መሆኑ ነው። የመከላከያና የሂዊ ወታደሮች በጋራ ቢራ እየጠጡ፣ ሲጋራ ተቀባብለው እያጨሱ በራያዎች ይሳለቁባቸዋል።
"…ወያኔን ሌባ፣ ዘራፊ ብለህ በስሟ ስለጠራሃት አትሰማህም። በጠበልም በጸሎትም አትወጣልህም። ምሷ ጥይት ነው። ያውም ሰንደቅ ዓላማ ሳትይዝ በሰላማዊ ሰልፍ። ኧረ ራያዎች አትቀልዱ። ወልቃይቶች ነቃ ሰንዳ በሉ።
"…በዚህ ምድር ላይ እንደወያኔ ገገማ አይቼም ሰምቼም አላውቅ። ግግም በቃ። ራያ ትግሬ ነው ይልሃል። ሕዝቡ ደግሞ ትግሬ አይደለንም እኛ የወሎ ዐማሮች ነን ብሎ ይቀውጠዋል። የፕሪቶሪያው ስምምነት ይባልልኛላ። ፕሪቶሪያም ሁላ። የትኛውን ሕዝብ ልታስተዳድር ነው የምትመጣው? ከ5ሚልዮን ወደ 3ሚልዮን ከመቀነስ በቀር ትርፋችሁ አይታየኝም።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸብርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
የፈለገ ቢረሳ እኔ እንደሁ አልረሳት…!
"…አይ እስታሊን… ጥቂት ሆዳም ዐማራ፣ አቃጣሪ፣ ባንዳ የባንዳ ልጅ የሆነ ጥቂት ዐማራ፣ ሰገጤ ፋራ፣ ደንታ ቢስ፣ ሞራለ ቢስ፣ ሰጎን ጭንቅላት ቀሽም ሾርት ሚሞሪያም ዐማራ መሳይ ዐሞራ አለና፣ እንደፈለግኩ ልጫወትበት እችላለሁ ብለህ አስበህ፣ አንተ ተብታባ ገመድ አፍ አንተም ከሰው ተቆጥረህ፣ አንት የሰው ግማሽ አንት ወያኔው፣ ፀረ ኢትዮጵያው ገንጣይ የገንጣይ ልጅ ወንበዴ ከእኔ ይልቅ አንተ ለእስክንድር ነጋ አዝነህ ዛሬ "እስክንድርን የማይቀበል ዐማራ ከትግሬ ጋር እንዴት አንድ ልሁን ብሎ ይመኛል? ብለህ በድፍረት ትናገር…? ጉድ እኮ ነው።
"…ማነህ ከዘመድኩን ይልቅ ወለይ እስታሊን ይሻለናል ያልከው የግንባሩ ተሟጋች ግንቦቴ ያው ናና የስታሊንን ትውከት ጥረግለት። ዳይፐሩን ቀይርለት።
"…እኔ ግን እስክንድርን አከብረዋለሁ። ያልገባኝን እጠይቀዋለሁ፣ ያልተስማማሁበትን እሞግተዋለሁ፣ እስከምችለው ድረስ እሟገተዋለሁ። ከእስክንድር ጋር ብጋጭ በሃሳብ ብቻ ነው። በአካሃድ ብቻ። የፈለገ ነገር ቢሆን ግን እንደ እስታሊን እስኬውን በዚህ መጠን አፌን አልከፍትበትም።
"…እኔማ ሾርት ሚሞሪያም አይደለሁም። ጎጋህን እዚያው ግንቦቴና በድኑ ብአዴን መንደርህ ፈልግ።
"…እስክንድር መሬት ላይ ካሉት ወንድሞቹ ሓሳብ አይለይም። ከመስመራቸውም አያፈነግጥም፣ ዝንፍም አይልም።
• የዐማራ ነፃነት እስኪረጋገጥ እኔ ዘመዴ ወይ ፍንክች።
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…የህወሓት ጦር ማለት ዐማራን ሁሉ መጨፍጨፍ እየፈለገ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ሕግ ላለመጠየቅ ሲል እየተደበቀ እንደሚገለው የአብይ ጦር አይደለም። ህወሓት ማለት በአብይ የተጫነለትን ከባድ መሳሪያ ሁሉ ተጠቅሞ መላው ዐማራን ፊት ለፊት እየገደለ እየረሸነ የሚጓዝ ጦር ነው። ይሄን ስል በስታሊን ፉገራ የደነዘዘው ዐማራ ሊሰድበኝ ይችላል። ለደንታህ ነው። ህወሓት ዘር አጥፊ፣ ጨፍጫፊ ናት። ድሮን ገብቶላቸው ከሆነ ደግሞ አስቡት። አብይ አህመድም የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት የሚለውን ተጠቅሞ ዐማራን በግላጭ የሚያገኝበት ጊዜ አሁን ነው። ግማሽ ጦሩን ለህወሓት ሰጥቶ ግማሽ ጦሩን ደግሞ ለዐማራ የወገነ አስመስሎ እንደከዚህ ቀደሙ አፈግፍጉ እያለ ሁለት ስለት ምርጥ ቢላዋ እየተጠቀመ መሸክሸክ ነው። ለትግሬ ኤርትራን ጋብዞ እንዳስፈጃት ለዐማራ ደግሞ ሱዳንን ጋብዞ ሊያስጨፈጭፍ ይችላል።
"…የዐማራ ፋኖ እንደከዚህ ቀደሙ ኦነግን እያጠቃ ከከተማ የሚወጣበት ጊዜ የሚያበቃ ይመስለኛል። የህወሓት እና የኦነግ ወረራ መላውን የዐማራን ህዝብ ለማንቀሳቀስ ለፋኖ በር ይከፍትለታልም ብዬ እጠብቃለሁ። ደመቀ ዘውዱ ከህወሓት ጋር ስለመሥራቱ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ከአብይ ጋር ፀረ ዐማራ ሆኖ ለአንዲት አካባቢ ነጻነት እንደሚሠራ ግን ራሱም በአደባባይ የነገረን ቅሽሽ ሳይለው ነው። ደግሞም በተግባሩም ተረጋግጧል። ሁሉንም ነገር በቅርቡ የምናየው ይሆናል። አብይ አህመድ ሰይጣን ነው። ህወሓትን በጎን ወረራ ያስጀምረውና በደመቀ ዘውዱ በኩል በወልቃይትና በቀሪው ጎንደር ያለውን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ ይሞክራል። ህወሓት ወረራ ስትጀምር እነ ደመቀም ከኦነግ መከላከያ ጎን ሆነን ህወሓትን እንመክት የሚል ጥሪ ያቀርባሉ። የዐማራ ክልል ገዢው ስደተኛው ብአዴንም የእርስ በእርስ ትግላችንን ትተን ህወሓትን እንመክት የሚል መሰል ጥሪዎችን ያቀርባሉ። ፋኖ ለደመቀ ዘውዱም ለአቢይ አህመድም፣ ለብአዴንም መልስ አልሰጥ ብሎ በአቋሙ ገግሞ መከላከያን ከገጠመው "በህወሓት ተወረን እንኳን የማይራሩ ጨካኞች፣ ህወሓት የወረረችን እኛ ከፋኖ ጋር ስንዋጋ ነው" የሚል ይዘት ያለው ፕሮፓጋንዳ በፋኖ ላይ ይከፍታል። ስለዚህ ዐማራ በተለይ ጎንደሬው ህወሓት መጣ በተባለ ቁጥር እንደ ፈሪ ከኦነግ ጋር ሄዶ የሚጣበቀውን ነገር ካልመረመረ የእስከዛሬው የፋኖ ድል በዜሮ የተባዛ ይሆናል ማለት ነው።
"…እንደ መፍትሔ ከታየ የጎንደር ፋኖ በግርግርና በጦርነት መሃል ተሰሚነቱ ከመቀነሱ በፊት በወልቃይት ላይ ያለውን አቋም ለሕዝቡ ይፋ ቢያደርግ ሸጋ ነው። አሁን በዐማራ ምድር ብቻውን የቀረው የአብይ ፈረስ ቢኖር ደመቀ ዘውዱ ብቻ ነው። የጎንደር ፋኖ ከሰውየው ጋር ይገናኛል ይመክራል? አቋሙን አውቀውታል? በዐማራነት ላይ ተግባብተው አብረው እየሠሩ ነው? ከሆነ ጥሩ ነው። ሙያ በልብ ብሎ ዝም ማለት ነው። ካልሆነ ግን ካልሆነ ግን እደግመዋለሁ ካልሆነ ግን የደመቀ እና የጓደኞቹ አቋም በተቃራኒው ከሆነ የጎንደር ፋኖ ሳይመሽበት፣ ሳይረፍድ፣ ጀንበር ሳትጠልቅ ከወዲሁ ለሕዝቡ አቋሙን ይፋ ማድረግም ይጠበቅበታል። እነርሱም እንደኛ ምንም ፍንጭ ከሌላቸው ለእነ ደሜ ቡድን በአደባባይ ጥሪ ያቅርቡለት። የጎንደር ሕዝብ ህወሓት መጣ ሲባል ከኦነግ ጎን የሚሸጎጥ ከሆነ አስር ወር ሙሉ ታንክና ድሮን እስከሚዘንብበት ለምን ጠበቀ? ውባንተስ ለምን ከሞቀ ቤቱ ወጥቶ ተሰዋ? ለማንኛውም አረረም መረረም፣ በቦሌም ሂድ በባሌም ና የወልቃይት ዐማራ ትግል የሚወሰነው በደመቀ ዘውዱ ነው። ወይ ከዐማራ ፋኖ ጎን ይሰለፋል አልያም በዐማራ ጠላቶች ተበልቶ የዐማራ ፋኖ መላውን ዐማራ ሁለት እኩል ጠላቶች እንዳሉት አሳምኖ ያለ አንዳች የኦነግ አብይ ተለጣፊነት ለአንድ ዓላማ ይንቀሳቅሳል። አከተመ።
"…ህወሓቶች ይፈሩታል፣ ይጠሉታል። ለጠላት በር ላለመክፈት ሲባል ደመቀን አንናገረው የሚል ጥሬ ንግግር የዋህነታችሁን እና የፖለቲካ ዳተኝነታችሁን ከማሳየት የዘለለ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም።
ህወሓትን፣ ኦህዴድንና ብአዴንን ተወት አድርጎ ቤትን ዘግቶ የራስን ስሌት ሠርቶ ጨርሶ በር መክፈት ነው ውጤት የሚያመጣው። ድሮም እንዲህ አድርጎህ እኮ ነበር። ቀድመህ ባለመወሰንህና የጠላት አሰላለፍን ተረድተህ ራሳህን ሳትችል በመቀመጥህ ምክንያት ህወሓት መጣችብኝ ብለህ በድንጋጤ ከብአዴን ጎን የተሰለፍክበትን ጊዜ ማስታወሱ ብቻ ለአንተ ለዐማራው በቂ ነው። ብአዴኖች ህወሓት በፋኖ እንደተመከተች ከተረጋገጠ በኋላ ነው ፋኖን በየቤቱ እየገባ መግደል የጀመረው። አሁንም እደግመዋለሁ ፋኖ ለመላው ጎንደሬ በተለይም ለወልቃይት ሕዝብ ጥሪ አቅርቦ የደመቀን ጉዳይ ማሳካት ከቻለ፤ የዐማራና የትግሬ ጦርነት በፍቅር ይቋጫል። በጦርነትም ከተባለ በፋኖ ይቋጫል። አለቀ።
"…የኤርትራን አቋም በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። የሻአቢያ ገረድ፣ የበግና የፍየል እረኛ ሆነው፣ መንገድና ግድብ፣ እርሻ ሲያሠሯቸው ዘመናዊ ባሪያዎቹ የኦነግ አክቲቪስቶች እና ሻአቢያን እንደፈጣሪያቸው የሚያዩት የወያኔ አክቲቪስቶች አዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ኤርትራ ዘጋች እያሉ ነው። ለደንተዋ ነው። ኢሳያስና አቢይ በኮሪያ አልተገናኙም ወዘተ የሚለውም ለደንታቸው ነው። እስከ አሁን ግን የኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ወደ አስመራ እየበረረ ነው። ቢሆንስ ብለን የኤርትራን እና የኬንያን ሚና በሌላ ጊዜ እናወራለን። ኔቶ ናይሮቢ፣ የእነ ሩሲያ ኃይል አስመራ ቢገቡስ ብለን ደግሞ የአቅሚቲ የቢሆንስ፣ የቀኝ ሽከካ ትን የሚያስብል ትንታኔአችንን ለመስጠት እንሞክራለን። ማን እንደተማረ ነው የፖለቲካ ሳይንስ የምንማረው? ከመሬት ተነሥቶ ማንም 777 You is my president ሆኖ ቦለጢቀኛ ተብሎ ቦለጢቃን ከተነተነ እኔ ከየኔታ ጉረሮ ጠጅ ይንቆርቆር እያልኩ ፊደል ስቆጥር የኖርኩት ዘመዴ ምን ያንሰኛል? ደግሞ ይሄን አለ ዘመዴ ብላችሁ ጓ በሉብኝ አሏችሁ። እኔ እንደሆንኩ ኬሬዳሽ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!