"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ዘወትር እሁድ ምሽት በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው መርሀ ግብራች አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወደ እናንተ ይቀርባል።
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaMedia
•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/6UtwNk7BQag
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
"…ሻሎም ! ሰላም !
"ርዕሰ አንቀፅ"
"…ሰሞኑን ይሄን ርዕስ አንስተን በሰፊው ስንወያይ ነበር። ስለ መንግሥታዊው የዘር ጭፍጨፋ፣ አርቴፊሻል ራቡን፣ ስለ ቤት ኪራይ፣ ስለ ልጆች ትምህርት ቤት፣ አስቤዛ፣ ህክምና፣ የትራንስፖርት ወጪን ውድነት አንስተን ስንወያይ ነበር።
"…ከእኛ ውይይት በኋላ አገዛዙ ራሱ በፓርላማ በተጠሪው በኩል የኑሮ ውድነቱን አስመልክቶ የመከረውን ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬ ዕትሙ ይዞት ወጥቷል። በተለይ የመንግሥት ሠራተኞችን በተመለከተ "በምሳ ሰዓት የሚበሉት ስለሌለ በቤተ እምነቶች እያሳለፉ እንደሆነ፣ ቤት የሌላቸው ደግሞ በዚያው በመሥሪያ ቤቶች ውስጥ ውለው እያደሩ መሆኑን ዘግቧል። ሌላም ሰው እንዲህ ብሎኛል።
• መምህር እና የልጆች አባት የሆነ ሰው አመሻሽ ላይ ራቅ ያለ ሰፈር ለልመና እንደሚቆም።
• ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ ሚስቱን ለሴተኛ አዳሪነት ሸኝቶ ጠብቆ ወደ ቤቱ የሚመልስ ባልም እንዳለ ሰምቻለሁ። ሌላውን እናንተ ጨምሩበት።
"…ብልፅግና ግን መስሚያዬ ጥጥ ነው ብሎ ለጦርነቱ ከሚሸምተው ድሮን፣ ጠብመንጃ፣ ጥይትና ቦንብ በተጨማሪ በ10 ቢልዮን ዶላር ወጪ እኔ ነኝ ያለ ቤተ መንግሥት ከነስማርት ሲቲው እያስገነባ ነው። ለግንባታው ግብር የዜጎች ደም በከንቱ እየፈሰሰ ንፁሐን እየተጨፈጨፉም ነው። ትናንት ብቻ በወለጋ ከ200 በላይ ዐማሮችን መጨፍጨፉን መከላከያ በኩራት ገልጿል።
"…በውስጥ ከሚደርሱኝ የሰዎች ችግርና ሰቆቃ ብዛት የተነሣ ምንም ማድረግ ባለመቻሌ የማልደብቃችሁ እኔ ራሴ የሌለ ጭንቀት ውስጥ እየገባሁ ነው። ለይቶለት በግልፅ ለማኝ ሆኖ ጎዳና የወጣ ሰው እኮ ዕድለኛ ነው። የሚያስጨንቀው ሰውነትህ እንዳማረበት ማጠፊያው ሲያጥርህ ነው። አማኑኤል ሆስፒታልም ሞልቶ መቀበል አቁሟል አሉ። አቢይ አሕመድ ግን ይሄ ሁሉ በቂ አይደለም ገና ለመሠዋት እንዘጋጅ እያለ ነው።
• ኡፍፍ ይጨንቃል…
አንዳንድ ጊዜ…
"…ደመና፣ ዝናብና ጭጋግ በሚበዛበት በአውሮጳ ምድር ላይ… በጋ ሆኖ በጉጉትና በናፍቆት ተጠብቃ ለጥቂት ወራት የምትገኘዋን ፀሐይ በዚህ መልክ ስታገኝ አንዳንዴ ስልክህን ጥፍትፍት አድርገህ፣ በምድር ላይ ያለ ገነት በመሰለ፣ በጥበበኞች እጅ በተሠራ፣ በአበቦች ባጌጠ ደን ውስጥ ሲያሰኝህ በዝግታ እርምጃ እየተራመድክ፣ ከፈለግክ አረንጓዴ ምንጣፍ በመሰለው መስክ ላይ ጋደም ብለህ አእምሮህን እየመገብክ ታድሳለህ።
• ያውም ቅዳሜ ሆኖ ይሄን የመሰለ ብሩህ ቀን በከንቱ ማሳለፍ ይቆጫል። ለነገ የመረጃ ቲቪ ዝግጅቴ እንዲህ እንዲህ ያለ ቦታ በመሄድ ነው የምዘጋጀው።
• አመሻችሁልኝ…?
👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ከሻአቢያ ጋር ሁላ እሠራለሁ እያለ ነው። የጌታቸው ረዳን ጠባቂዎች ፌደራል መንግሥቱ ቀይሮለታል የሚባለው እዚያ አካባቢ ካለ ትርምስ የመነጨ ነው።
"…አሁን የፋኖ ትግል ጠንከር ሲል የሸዋ ኦሮሞዎች ግግም ብለው አዳነች አቤቤን ጠቅላይ ሚኒስትር እናደርጋለን ብለው በውስጥ ለውስጥ መክረው ጨርሰዋል። በእነሱ ቤት የአርሲ ሰው መምረጣቸው ነው። እሷ ግን ከሸዋ ወደ አሩሲ ከሄዱ ቤተሰቦች የተገኘች ሸዋዬ ነች። በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ባለሀብቱንም ሌላውንም ይዛለች፣ በዚያ ላይ ደፋር ሴት ነች ተብሎ ነው እሷን ይዘው መንቀሳቀስ የፈለጉት። አዲስ አበባ ምሽት ምሽት ዓድዋ ሚዚየም ጋር ወለጋ፣ አሩሲ፣ ጅማና ሸዋ ፉክክር ውስጥ ገብተው ሲያቀልጡት ታያለህ። ወደ ኋላ እንመለስና ታንዛኒያ እንሂድ። ታንዛኒያ ስንሄድ ሬድዋን ሁሴንን እና ጌታቸው ጉዲናን እናገኛለን። ብልፅግና እና ኦነግ ሸኔ በታንዛኒያ ድርድር ሲያደርጉ አቢይ የላከው እነርሱን ነበር። ከታንዛኒያ መልስ የጠቅላዩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የነበረው ሬድዋን ሁሴን በተመስገን ቦታ ተተክቷል። ሬድዋን በህወሓትም፣ በአቢይም ለመወደድ የሚሠራ ስልብ ባሪያ ነው። ጌታቸው ጉዲና ከጃል መሮ ጋር ከተደራደረ ወዲህ በየትኛውም የመከላከያ ዜና ላይ ጠፍቶ ነበር የቆየው። አቢይ ጌታቸው ጉዲናን ለድርድር የላከው ከሸዋ ኦሮሞ መጥቶብኛል የሚለውን ስጋት ለመሻገር ጌታቸው የወለጋ ሰው ስለሆነ በእሱ በኩል ነገሩን መያዝ ስለፈለገ ነው። የሸዋዎች መፈርጠም አቢይን ጌታቸው ጉዲና ላይ እንዲጣበቅ አደረገው። ለዚህ ነው የሪፐብሊካኑ አለቃ እና የመከላከያ መረጃ ደህንነቱ አለቃ የአብይ ደህንነት ስላሰጋቸው እንደገና ጥበቃውን የሚያጠናክር ሌላ ጋርድ ያስመረቁት።
"…የዐማራ ፋኖ በጀመረው ይቀጥል። ሥልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥል። የሀብት ስብሰባው ከጥገኝነት ወጥቶ ከፌደራል መንግሥት ሀብቶች መካፈል ይጀምር። መጪው ክረምት ነው። ክረምት በተፈጥሮው ጭለማ ነው። ሠራዊቱም ከቀን ይልቅ በጨለማ ለመዋጋት የሚፈልግ ይመስላል። ስለዚህ በጨለማ ለሚመጣ መከላከያ ሠራዊት መድኃኒቱ የቀን እንቅልፍ በመተኛት ሌሊቱን ቀን ማድረግ እና ሌሎች ወታደራዊ ስልቶችን መጠቀም ነው። የእንቅልፍ ሰዓቱም ተገድቦ በተቆራረጠ መልኩ በፈረቃ ማድረግ እና ለጥቃት ላለማጋለጥ ጥረት መደረግ አለበት። ይሄን ማድረግ ሁለት ዓይነት ጥቅም አለው።1ኛ፦ ራስን ከጥቃት ታድናለህ፣ ሲቀጥል ወታደሩ ባላሰበው መልኩ በማያዉቀው ቦታ ጥቃት ሲደርስበት ያለ ቁጥጥር ተበታትኖ እንዲጠፋ እና ተበትኖ እንዲቀር በማድረግ ትጥቁን ለፋኖ አስረክቦ እንዲሸነፍ ያደርገዋል። ስለዚህ ክረምቱን የመጨረሻ አድርጎ መዘጋጀት ያስፈልጋል።
"…ነጮቹም የሰሙትን እንጃ ደጋግመው ብልፅግናው ላይ ጓ ማለት አብዝተዋል። አሜሪካም፣ የተባበሩት መንግሥታትም፣ የአውሮጳ ኅብረትም፣ እንደ ካናዳ ያሉ መንግሥታት ሳይቀር በግልፅ ጓ እያሉበት ነው ያለው። ፋኖ በአንድ እጁ እያለማ፣ እያሰለጠነ፣ እያመረተም፣ በሌላኛው እጁ መዋጋቱን ይቀጥል። ድርድር፣ መፈንቅለ መንግሥት ብላ ብላም አይመለከተውም። ኦሮሞዎቹ ፕላን ቢ አድርገው የሚንቀሳቀሱት እሱኑ ነው። የፋኖን ማሸነፍ እነ ጃዋር መሀመድንም፣ እነ ስታሊንንም እኩል እያስጮኸ ነው። ምንአልባት ፋኖ እየገፋ ከመጣ አስቀድመው ሸኔንም አዲስ አበባ በማስገባት አዲስ አበባን በውድመት በማስፈራራት ፋኖን ወደ ድርድር ሊያመጡት ይሞክሩ ይሆናል። ለፋኖ ግን ያለው ምርጫ ሦስት ብቻ ነው። አንደኛው ምርጫ ያው የታወቀ ነው ማሸነፍ ነው። ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ማሸነፍ ነው። ሦስተኛው ምርጫ ግን ሌላ ምርጫ ስለሌለው ማሸነፍ ብቻ ነው።
"…አጀንዳዎች እየበዙ ይመጣሉ። ሸዋና አሩሲን እረፍት ለመንሣት በዚያ የሚገኙ ዐማሮች ላይ አዲስ ስደት፣ ሞት፣ መፈናቀል፣ የመሬት መቀማት፣ የከብት፣ የንብረት ዘረፋ፣ የቤት ውድመት፣ እርድና ጭፍጨፋም ይኖራል። ብዙ ታዋቂ ሰዎችን በመግደል ጉዳዩን በፋኖ ላይ ለማላከክ ዝግጅትም ተጀምሯል። ህወሓት ለፍታበት የነበረው የፖለቲካው ቅማንት እና የዐማራ ፋኖ አንድ ላይ መሆን ዐማራውን ሲያበረታ አገዛዙን አላስደሰተም። በጎጃም አገውና ዐማራ፣ ጉምዝና ዐማራ አንድ ላይ መሆናቸውም ያበሳጨው አገዛዙ ያን ጨፍጫፊ የጉምዝ መሪ ዳግም በእርቅ ሰበብ አስገብቶታል። ዐማራና አካባቢውንም ለመበጥበጥ ኩሽ ነን የሚሉ ኃይሎች በገፍ እየታጠቁ አካባቢውን ለማወክ እንቅስቃሴ ይጀምራሉ። የህወሓት ኃይልም አርፎ አይተኛም። እናም ስለዚህ ዐማራው አንድነቱን በማጠንከር፣ ልዩነቱን በማቀራረብ፣ አንድ ሆኖ ወደፊት መሄድ ብቻ ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ፋኖም ሳይመጣ እርስ በራሳቸው በቅርቡ ይለይላቸዋል። ይሄ ይመዝገብ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።
መልካም… የሚጠበቀው አመስጋኝ ከአንድ ሺም አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። ከምሥጋና ቀጥሎ የሚቀርበው ያው የተለመደው ርዕሰ አንቀጻችን ነው።
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ከወደ ጀነራሎቹ አካባቢ በወፎቼ በኩል ትናንት የመጣ ወሬ ነው። ወሬው የሚገባው ለቦለጢቀኞቹ እና ጉዳዩን በቅርበት ለሚያውቁት ብቻ ነው። እኔ ግን ጦማሩ ለታሪክ በገፄ ላይ ይቀመጥ ዘንድ በዚህ መልክ አስፍሬዋለሁ።
"…እህሳ ጉበዝ… ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?
"…ድንቄም ጠቅላይ ሚንስትሪት…😂
"…ኧረ ጉድ ነው። …ሸዋ፣ ጅማ፣ ወለጋ…?🤜👊🤛 …አሁንም ከወፎቼ ማብራሪያ እየጠበቅኩ ነው። ለዛሬ ከደረሰ ደረሰ፣ ካልደረሰ ነገ ጠዋት ያገናኘን።
"…ምርኮኞች ለቤተሰቦቻቸው መልእክት እያስተላለፉ ነው። ደቡብ እና ኦሮሞዎች በጎንደር እና በጎጃም በሸዋም ምድር ላይ እንደ ቅጠል ረገፉ።
• ምንም ማድረግ አይቻልም።
ዘመዴ ጉድ ስማ ይለኛል…
"…አንዱ ወዳጄ እኮ ነው ዘመዴ ጉድ ስማ፣ ያየህ ሰው ሽመልስ አንድ እንግልጣራዊ ጋዜጠኛ አቢይ አሕመድ አሁን በስሙ የሚጠራባቸው አቶ አህመድ አሊ ወላጅ አባቱ አይደለም ብሎ መጽሐፍ ጻፈ፣ አንተ ወሎዬ ነው ስትል እንግሊዛዊው ደግሞ ጉራጌ ነው ብሏልም ይለኛል። 😂
"…እርግጥ ነው አቢይን ድሮ የኢትዮጵያ ኦዲዮቪዥዋል ዋና ጸሐፊ በነበርኩ ጊዜ፣ እሱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ሆኖ ሳውቀው የጉራጌ ተክለ ሰውነት ያለው ስለሚመስል እኔም ጉራጌ ይመስለኝ ነበር። ኋላ ነው በሻሻ ድረስ ሰው ልኬ የአቢይ እናቱም፣ አባቱም ወሎዬ እንደሆኑ ተረድቼ በቀደመው ፌስቡኬም፣ በቴሌግራምና በዩቲዩብ፣ እንዲሁም በመረጃ ተለቭዥን ያጋለጥኩት።
"…እነያየህ ሰው ሽመልስ የአቢይን የትምህርት ደረጃ፣ ዲግሪውን እንዴት እንዳገኘ፣ ግብጻዊው ፕሮፌሰር፣ የምክክር ኮሚሽኑ ዶር ዮናስ አዳዬ፣ የህወሓት ሰዎች በስም በፎቶ የምጠቅሳቸው እንዴት እንዳ ዶከሩት ይፋ ስላላወጣሁ እሱን የማወጣበትን ቀን እየጠበቁ ነው። እኔ ደግሞ ጊዜ እየጠበቅኩለት ነው።
"…በተረፈ የአቢይ አባት ወሎዬ ነው። እናቱም የላስታ ጠዳ ሴት ናቸው። የአቢይ እናትና አሳዳጊ አባቱ አቶ አሕመድ አሊ ተጣልተው፣ ወሮ ትዝታ ወልዴ እዚያው በሻሻ ጠጅ ቤት ከፍተው ሳለ፣ በግድግዳ የሚጎራበቷቸው ወሎዬው አቶ መሀመድ አቶ አህመድ አሊንና ወሮ ትዝታን ለማስታረቅ ብዙ ደክመው ስላልተሳካላቸው፣ ኋላ ላይ ለንብረት ለማካፈል ወደ ጠጅ ቤቷ ይመላለሱ የነበሩት አቶ መሀመድ ዋሴ ከወሮ ትዝታ ወልዴ ጋር በፍቅር ይወድቃሉ። አቶ አህመድ አሊና ወሮ ትዝታ ወልዴ ከተፋቱ በኋላ በ1968 ዓም አቢይ ተወለደ። ለዚህ ነው አቶ አህመድ አሊ አቢይን እንደ ልጆቼ ነው ያሳደግኩት ብለው ቃላቸውን በሰጡ በወሩ የሞቱት። የአቢይ የአባት ልጆች ተደብቀው ነው ያሉት።
• መጣሁ…!
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…አገዛዙ ለሚቀጥለው ዓመት ለ2017 ዓም ግድብና፣ ዩንቨርሲቲ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለመንገድ እና ሆስፒታል ለመገንባት ምንም ዓይነት በጀት የለኝም ብሏል። 87% የሀገሪቱ በጀት ተጠቅልሎ ወደ ሥርአቱ ወንበር ጠባቂ ወደሆነው የመከላከያ ኃይል ገብቷል። ይህ ሥርዓት ከመጣ ወዲህ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለከተማ ልማት እና ለሴፍቲኔት የሚመደበው በጀት አንድ ላይ ተደምሮ ለሥርቱ ወንበር ጠባቂ ወታደር የሚበጀትለትን በጀት አይደርስበትም። እንደጉድ ነው የሚቀረጥፈው።
"…የብልፅግናው ወንበር ጠባቂው ይሄን ሁሉ በጀት እየቀረጠፈ፣ ቦንብና ጥይት የሚተፋ፣ አውዳሚ መሳሪያም እየሸመተ፣ እንደ በጀት አበላሉ በየትኛውም ዐውደ ውጊያ አሸንፎ ያለማወቁ ነው። በትግራይ የትግሬ ሴቶች ሚጥሚጣ ዓይኔ ላይ በተኑብኝ ብሎ ሁላ ነው ሩጦ የወጣው። በሱማሊያ አልሸባብ ከ7 ሺ በላይ ወታደሮችን መግደሉን እየተወራ ነው። ኦነግና ኦነግ ሸኔ በየጊዜው መከላከያውን እንደ በግ እየነዱት፣ እንደ ጭዳ ዶሮ እየጨፈጨፉ ፎቶ ተነሥተው እየለቀቁት ነው። ኤርትራ እንኳ በአቅሟ የመከላከያው አዛዥ ከሆነች ሰነባበተች። ደቡብ ሱዳን ጅንካ ድረስ፣ ሰሜን ሱዳን ጎንደር መግባት ነው የቀራቸው። እንደ ዘመነ አቢይ አሕመድ የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ እንዲህ ተዋርዶ አያውቅም።
"…በሰላም አስከባሪነት በአፍሪካ ሀገሮች ተመራጭ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር አሁን ከዳርፉር፣ ከደቡብ ሱዳን ከአቢዬ ግዛት እየወጣ ነው። ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ላይቤሪያ ዘምቶ ምስጉን የነበረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አሁን በሁሉ የተናቀ፣ የተዋረደ ሆኖ ተገኘ። ቢያንስ ዶላር ለሀገር በማስገባት የውጭ ምንዛሪ ያመጣ የነበረው መኴ አሁን ግን ወፍ የለም። ሱማሌ እንኳ ከአቅሟ አልሸባብ ይፈንጭብኝ፣ ያፈንዳኝ እንጂ የኢትዮጵያ ጦር ከሀገሬ ይውጣልኝ ብላ ቀነ ገደብ እስከማስቀመጥ ደረሰች። ይሄ ሁሉ ሀገር ሕጻን እጅ ስለወደቀች የመጣ ነው።
"…ከሁሉ የሚከፋው ከወያኔም፣ ከሱዳንም፣ ከደቡብ ሱዳንም፣ ከኦነግ እና ከአልሸባብም ጋር አነጻጽሮ የዐማራ ፋኖን ንቆ በአንድ ሳምንት ሱሪውን አስወልቀዋለሁ ብሎ አስቦ የገባበት ጦርነት ነው። ዐማራን ይዞ ሻአቢያን፣ ሱማሌን፣ ሱዳንን የሚያሸንፈውን ዐማራ፣ በገበሬ ጭምር ሱዳንን የሚያደባየውን ዐማራ ንቆ ከወያኔ በታች ቆጥሮ ዘው ብሎ መምጣቱ አስቂኝ ነገር ነበር። ዐማራ ሀገረ መንግሥቱን አክብሮ እንደ ወያኔና እንደ ኦነግ መንግሥት ላይ አልተኩስም ማለቱ ነበር በኦሮሙማው ያስናቀው። ዐማሮቹ አልተደራጁም፣ አይስማማሙም፣ አይግባቡም። ያላቸው መሣሪያም ኋላቀር ነው። እኛ በሠራዊት ብዛት፣ በድሮንና በጀት፣ በታንክም እናንበረክከዋለን ብለው ነበር ንቀውት ወደ ጦርነት የገቡት።
"…እውነት ነው ዐማራ መሣሪያ የለውም ነበር። ነገር ግን ምርኮኛው ብራኑ ጁላ ተማራኪ ሟች ሠራዊቱንና በኢትዮጵያ ዕዳ የተገዛን የሀገር የትየለሌ መሳሪያም ተሸክሞ እያንጋጋ የፋኖ አፈሙዝ ራት በመሆን ጭምር ፋኖን እስከ አፍንጫው አስታጠቀው። በአንድ ዓመት ጦርነት የዐማራ ፋኖ የሥርዓቱን ኢኮነሚ ሸምድምዱን አወጣው። አራት ኪሎና ፒያሳ በቡናቤት መብራት ስለተንቆጠቆጠ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ መውደቅ አይሸፍነውም። በሀገሪቱ መብራት የለም። ውኃ የለም። ፒያሳ ላይ ፋውንቴን እያሳዩ የከተማውን ነዋሪ ውኃ ጥም መደበቅ አይቻልም። እንዲያውም አሁን የመብራት ታሪፍ ዝቅተኛ ስለሆነ መጨመር አለበት ብለው አሁን የመብራት ዋጋ በመጨመር ሕዝቡን ሊያሳብዱት ነው።
"…አሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ካየነው ሥርዓቱ ለጦር መሳሪያ ግዢ የሚያወጣው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በቀጥታ ወደ ፋኖ እጅ እየገባ ነው። ይህ ደግሞ ብልፅግና ፋኖን በአንድ ዓመት ውስጥ በመሳሪያ የደረጀ ኃይል እንዲሆን አድርጎታል። የዐማራ ፋኖ የአባቶቹን ቆመህ ጠብቀኝ፣ አልቤን፣ ምንሸር፣ ቤልጅግ ወዘተ… እየወለወለ በክብር ያኖራል፤ በእሱ ፈንታ ዘመናዊ ራሺያ ሠራሽ መሳሪያ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ ይታጠቃል። ስለዚህ ዕድሜ ለብልፅግና በትንሽ ጊዜ ውስጥ በአፍሪካ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ማኅበረሰብ ቢኖር ዐማራ ይሆናል። በትንሽ ጊዜም ውስጥ በአፍሪካ ምድር አስፈሪ ኃይል ሆኖ ይወጣል።
"…የተበታተነ ሓሳብ የነበረው የዐማራ ነገድ አሁን ሳይወድ በግዱ ወደ አንድነት እየመጣ ነው። ለጎጃምና ለጎንደር፣ ለሸዋና ለወሎ በጠላት ተዘጋጅቶ የነበረው ሴራ በሙሉ ተበጣጥሶ ወድቋል። ጎንደር ጎጃም ተሻግሮ፣ ጎጃም ጎንደር ተሻግሮ መተጋገዝ ተጀምሯል። ሸዋ ወሎ ሄዶ፣ ወሎ ሸዋ መጥቶ በአንድነት ቆመው ከጠላት ጋር መፋለም ጀምረዋል። በውጭ ያለው ዳያስጶራም እንደ ድሮው በመንገደኛው ሁላ መሸወዱን አቁሟል። በዐማሮች መካከል ያሉ፣ የነበሩ ልዩነቶች ሁሉ በፀብም፣ በጭቅጭቅም እየጠበቡ መጥተዋል። አንድ ላይ ቆሞ ገቢ ማሰባሰብ ተጀምሯል። ጅማሬዎቹ ሲያድጉ አንድነቱም አብሮ ይመጣል። ደፋር ተሟጋቾች እያየሁ ነው። ልፍስፍስ ዐማራ እየጠፋ ነው። ቀበቶውን ያጠበቀ፣ ሱሪውን የታጠቀ ዐማራ አሁን በሽ ሆኗል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…በግሬደር ተቀብሮ ማልቀስ ቀርቷል። ዐማራን እንደፈሪ ማየት ቀርቷል። የፋኖን ስም ሁሉም ናፋቂ እየሆነ መጥቷል። ወታደሩ ወደ ዐማራ ክልል ሳይዋጋ እጅ ለመስጠት ተሰላፊ ሆኗል። ለሥልጠና ተመልምሎ ወደ ብርሸለቆ የሚሔድ ምልምል ወታደር በኦሮሚያ ፖሊስ ተጠብቆም እንኳ በጎጃም ከካምፕ እየሸሸ ፋኖን ከመቀላቀል ወደ ኋላ አላለም። የዓለም መንግሥታትም ሳይወዱ በግዳቸው ለፋኖ ጆሮ መስጠት መጀመራቸውም ሌላኛው የዐማራ ድል ነው። መከበር በከንፈር ይሉት ተረት በዐማራ እየታየ ለመምጣቱ ሁሉም ምስክር ነው።
"…ቀጥሎ የሃይማኖት ጦርነት በብልፅግና ይሞከራል። በወሎና በኦሮሚያ ይሞክራል። ነገር ግን እሱም ይከሽፋል። የጎንደሩ የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ መንገድ ዝግ በመሆኑ ሰላም ወርዷል። የመተከሉ አገው ሸንጎ ግን በኦሮሚያ ባጀት እና ድጋፍ፣ በኦኤምኤን ሰበካ እና ፕሮፓጋንዳ በቄስ ስንታየሁ የኔአባት መሪነት ከዐማራ ፋኖ ጋር ለመዋጋት ሥልጠናውን ጨርሶ ወደ ውጊያ ሊገባ እየዳከረ ነው። የአገው ልጆች ዕጣ ፈንታችን ከዐማራ ጋር ነው ያሉ አገዎች ተደራጅተው ራሱን አገው ሸንጎ ተብዬውን እየመከቱት ይገኛሉ። ግዙፉን መከላከያ ልክ ያስገባ ለኩሽ ህልመኞች ቦታ ይሰጣል ማለት አይታሰብም።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ፋኖ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
“…እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።” ሉቃ 24፥50-51
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…የዐማራ ክልሉ ጦርነት ሸፍኖት ነው እንጂ አፋር እና ሱማሌ ደም አፋሳሽ ውጊያ እያደረጉ ነው ተብሏል። ኦሮሙማው ለወደብ፣ ለውኃው ለመቅረብ ዕድሜ ካገኘ ቀጥሎ የሚያባላው ሱማሌና አፋር ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ።
• ትግራይ… ዐማራ… ????? በሻሻ ማድረጉ ይቀጥላል።
የጄነራሎቹ መልእክት…!
"…ሰላም ዘመዴ እንዴት አለህ? ጊዜ የለም ወደ ገደለው እንግባ። ይሄን መልእክት በተለመደው መንገድ ቀድመህ ለሕዝቡ አድርስ። ይፍጠን ዘመዴ።
"…ይኸልህ ዘመዴ። በዐማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት መንግሥት እየተሸነፈ መሆኑን በግልፅ እየተረዳው ነው። ለዚህም ማሳያው ብርሃኑ ጁላ እኛን የዐማራ ተወላጅ ጄኔራሎችን ሰብስቦ ነበር። ጁላ የሚለው ኮስተር ብሎ "ክልላችሁን አድኑ፣ አትርፉ።" የሚል ትእዛዝ ነው የሰጠን። የዐማራ ጄነራሎች በተለይ አዲስ አበባ ያሉት ከቢሮሥራ ወጥተን በየትውልድ ቀዬአችን እና ዞናቸው ሄደን መጀመሪያ እዚያ ካለው አመራር ጋር እንድንወያይ፣ ቀጥሎ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሕዝቡ ጋር እንንወያይ ያስጠነቀቀን። ይህንን እንዲከታተል ደግሞ አበባው ታደሰን ጥብቅ መመሪያ ሰጥቶታል።
"…እናልህ ዛሬ አበባው ታደሰ ወደ ክልል ሄዳችሁ ተወያዩ የተባልበውን የዐማራ ጀነራሎችን በሙሉ ሰብስቦ ምን መደረግ እንዳለበት ከላይ ከጠሚው የተሰጠውን ትእዛዝ ጭምር ሲነግረን ውሏል። ለምሳሌ ጎጃም የተወለደ ጄነራል ወደ ጎጃም፣ ጎንደሬው ወደ ጎንደር ወሎዬው ወደ ወሎ፣ ሸዋየው ወደ ሸዋ እንድንሄድ ነው የነገረን። ስለዚህ ሰሞኑን በሁሉም የዐማራ ዞኖች የውይይት የሚመስል ነገር ግን ሕዝቡን የሚያስፈራራ ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር በየመድረኩ በእኛ አማካኝነት ይተላለፋል። "ፋኖ ሕዝቡን እየጎዳው እንደሆነ፣ መንግሥትም አቅሙን ያልተጠቀመው ሕዝቡን አክብሮ እንጂ ፋኖን መደምሰስ አቅቶት እንዳልሆነ፣ ከዚህ በኋላ ግን ሙሉ አቅሙን እንደሚጠቀም፣ ሕዝቡም ፋኖን አምርሮ መጥላት እንዳለበት የሚያሳስብ ሓሳብ አንሸራሽሩ ተብለናል። ሕዝቡ እንዲረበሽ የሚያደርግ ነገር እንድትፈጥሩ ነው የታዘዝነው። እኛ ጄነራሎቹ ይህን ካላደረግን ግን የመጣው አደጋ እንደማይምንም ነው የነገሩን። አንዳንድ የምዕራባውያን መንግሥታትም አገዛዙ እንዳበቃለት በግልፅ መናገር ጀምረዋል። አገዛዙ አብቅቶለታል።
"…ሌላው በአዲስ አበባ ያሉ ዐማራ ባለ ሀብቶችም ለብቻቸው እንዲሁ ይሰበሰባሉ ተብሏል። ከአሁን በፊት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሰብስቦአቸው ያለውጤት የተበተነውን አሁን ደግሞ ጄነራሎቹ ሰብስበው እንዲያስፈራሩአቸውም፣ በዚያውም ለፋኖ ድጋፍ የሚያደርግ ባለሀብት ቢኖር ወዮለት የሚል ማስፈራሪያም ለመስጠት ሲባል በአስቸኳይ መድረክ ይዘጋጅ ዘንድም ታዟል። የአዲስ አበባውን ባለሀብቶች ሰብስቦ እንዲያስፈራሩ መድረኩንም እንዲመሩ የተመደቡት ደግሞ ትግሬው አበባ ታደሰ እና ሌተናል ጄነራል በላይ ስዩም ናቸው።
"…ባለሀብቶቹ አማራጭ የላቸውም። የዐማራ ሕዝብ ግን እኛ በምንመራው መድረክ ላይ ከተቻለ ባለ መገኘት። የፋኖ ኃይሎችም እንደ በቀደሙ የደቡብ ጎንደሩ ስብሰባ ስብሰባውን እንዳይካሄድ አደጋ በመጣል፣ ከዚህ አልፎ በስብሰባው ላይ የሚገኝም ሕዝብ የፋኖን ሓሳብ ብቻ እንዲያንሸራሽር አሳስብ። ዘመዴ መንግሥት ይህን ስብሰባ የሚያደረገው እየተሸነፈ መሆኑን አውቆ፣ ተረድቶ እንደሆነ ለሕዝቡም ለፋኖዎችም አድርስ።
• ያው አድርሻለሁ…! እሑድ በቴሌቭዥንም አደርሳለሁ።
ምከሩ እስቲ…
“…አሁን በገበያ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብር አሁን ካለበት ዋጋ በላይ ሊላሽቅ እንደሚችል እየተነገረ ነው። አንድ ዶላር በባንክ እስከ 90 የኢትዮጵያ ብር ሊዘረዘር ይችላልም ነው እየተባለ ያለው። ጂቡቲም የኢትዮጵያ ብር አፈር ደቼ ሊበላ ስለሆነ በእኛ ሀገር ኮሪደር ላይ እንደ መገበያያ መጠቀም አቁመናል” ማለቷም ተዘግቧል።
• ባለሙያዎች ሕዝቡን ምን ትመክሩታላችሁ?
፩ኛ፦ በባንክ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የሆነ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ብራቸው ቀልጦ እና ሟምቶ እንዳያድር ከወዲሁ ምን ያድርጉበት?
፪ኛ፦ የኦሮሞ ባለጊዜዎች እንደወርቅ እና መሬት፣ ቤት እየገዙ ያሉት፣ በዱባይ ቪላ እየሸመቱ ያሉት ከዚህ የብር መሾቅ ጋር ይያያዛል ወይ?
፫ኛ፦ 1ዶላር 90 ብር ተመነዘረ ሲባል ጮቤ የሚረግጥ፣ በቃ ሀብታም ልሆን ነው ብሎ የሚፈነጥዝ የትየለሌ ዳያስጶራ እንዳለ ይታወቃል። በእውነት ብር በዚህ መጠን መዘርዘሩ ያስፈነጥዛል ወይ…?
፬ኛ፦ በባንክ በዚህ መጠን የሚዘረዘር ከሆነ በጥቁር ገበያስ ምን ያህል ይዘረዘር ይሆን?
• እስቲ ሕዝባችሁን ምክር ለግሱ።
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…የፓርኮቹና የሪዞርቶቹ መጨረሻ… የሚመጣው የኢትዮጵያ መንገሥት ምን ላይ ያተኩር ይሆን…?
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
“…አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።” መዝ 47፥5
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።
“…እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” 1ኛ ጢሞ 3፥16
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።
መልካም…
"…ርዕሰ አንቀጹ መነበቡን እያየሁ ነው። ዛሬም እስከአሁን ድረስ በርዕሰ አንቀጹ ላይ በኢሞጂም ቢሆን 😡 የተናደደ፣ የበገነም ሰው አላየሁም። ቀጥሎ ደግሞ የ100 ያህል አንባቢዎችን ሓሳብ እንቀበልና ከዚያ ወደ ሌሎች መረጃዎች እናልፋለን።
"…ዐማራ ቢሸነፍለት አቢይ ቀጥሎ ከአፋር እና ከደቡብ በፊት ሱማሌን ነበር ለጥብስ ያዘጋጃት። ከሱማሌ በፊት ግን የሸዋ ኦሮሞ መመታት እንዳለበት በድንገቴ መወሰኑ ነው የሚሰማው።
"…ሸዋዎች መሬትም፣ ሰውም ሽጠው፣ ዘርፈው በኢኮኖሚ ፈርጥመዋል። አቢይ አሁን በቀላሉ ሽመልስን ከሥልጣን ለማውረድ አይቻለውም። አዳነችንም እንደዚያው። ሊያደርግ የሚችለው አንድ ነገር ብቻ ነው። በወለጋ ጴንጤና፣ በኦሮሞ ወሃቢይ እስላም መቀጥቀጥ፣ ከዚያ ቀዳዳ ካገኘ በሙስና አዋክቦ ማስወገድ። ከቻለ ነው እሱንም።
"…አቢይ የወሃቢያ እስላምንም አሁን ይጠቀምበት እንጂ ኋላላይ እነሱንም መብላቱ አይቀርም የሚሉ አሉ። ኤምሬትስ ወሀቢይን እየጠረገች ስለሆነ ከሀገሯ፣ ሳዑዲም ወሀቢይን ከሀገሯ አባርራ ወደ አፍሪካ ነው የገፋቻቸው። እዚህ እንዲረብሹ ማለት ነው። አቢይ ወሀቢይ አሁን ከፈረጠመ በኋላ ላይ ልቆጣጠረው ቢል ይከብደዋልም ነው የሚሉት ታዛቢዎቹ።
"…ዐማራና የዐማራ ፋኖ ወግሞ ያዘ እንጂ አቢይ ሁሉንም በሻሻ አድርጎ ህልሙን ለመኖር ቋምጦ ነበር። ጃልመሮን ሲደራደር፣ ሸዋ የእኛስ ጃልሰኚ? ከጃል ሰኚ ጋርስ ማነው የሚደራደረው? ብለው ነበር። 😀 ሁሉም የራሱ ሸኔ ስላለው ማለት ነው።
"…የፖለቲካው ቅማንት ከፋኖ ጋር መዋሃድ መጀመሩ ያሳበዳቸው ብልፅፄና ሂዊ አገው ሸንጎ ላይ መሥራት ጀምረዋል። ፋኖ ከአገው ማበሩ፣ ከጉምዝም ጋር መታረቁን ሲያዩም የቤንሻንጉል ነፃ አውጪ ነው የተባለውን በእርቅ ሰበብ አምጥተውታል። በጅማ ዐማራን ትጥቅ ለማስፈታት እየሞከሩ ነው።
• ፋኖዬ ወጥር 💪💪🏿✊
ርዕሰ አንቀጽ"
"…ታስታውሱ እንደሆን ከዛሬ ስድስት ወር በፊት በወርሀ ህዳር ሪፐብሊካን ጋርድ የሚባሉትና የቤተ መንግሥት ዙሪያውን ጥበቃ የሚካሂዱት ወታደሮች አንድም ሳይቀሩ ወደ ደብረዘይት ተወስደው በሥልጠና ሰበብ ግምገማ አካሂደው ነበር። ሥልጠናው የተካሄደው በቢሾፍቱ አየር ኃይል ግቢ ሲሆን ስለ ሥልጠናው ሁኔታ ሪፖርት ያቀረቡት የሥልጠናው አስተባባሪ ኮሎኔል ወንዴ ወልዱ እንደነበሩ ነበር በወቅቱ የተገለፀው። ኮሎኔሉ ሙያዊ የክብር ሰልፍ ዓይነቶች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ወታደራዊ ስልት በተያዘው ዕቅድ መሰረት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል ሲል መረጃውን ልኮ በመከላከያ ገጽ ላይ የዘገበው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ቡድን እንደነበር ይታወሳል።
"…የሪፐብሊካን ጋርዱን በስብሰባ፣ በውይይት እና በሥልጠና ሰበብ ደብረ ዘይት ከወሰዱት በኋላ በስፍራው ተካሂዶ የነበረው ሥልጠና ሳይሆን ግምገማ ነበር ነው የሚሉት ሁኔታውን በንቃት የሚከታተሉ ኃይላት። እንዲያውም ከብልፅግና ግምገማ በፊት የተደረገው ግምገማ ይሄ ነበር ነው የሚባለው። "ይመቱኛል" ብሎ አብይ በመፍራቱ ነው በወቅቱ ወታደሮቹ እርስ በራሳቸው ተገማግመው ይጥሩ ተብሎ ወደ ደብረዘይት የተወሰዱት። በእጅ ስልኩ ላይ በሚያዳምጠው ዘፈን፣ በስልኩ ላይ ሴቭ ባደረጋቸው ቪድዮዎችና ምስሎች፣ በግሩፕ ውይይት፣ በተናጥል ውይይት ወቅትም ወታደሮቹ ያላቸው አመለካከት ተጠንቶ፣ ተገምግሞ፣ ለተጨማሪ ተሃድሶ የሚፈለጉት ለሌላ ሥልጠና ሲወሰዱ አደገኛ ናቸው ተብለው በግምገማው ወቅት የተጠረጠሩት ደግሞ ከስብሰባው በኋላ ገሚሱ ለግዳጅ ተብሎ ወደ እሳቱ የዐማራ ጦርነት ውስጥ ተማግዶ ሲወገድ ቁጥራቸው ያልተገለፁትን ደግሞ የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም።
"…ይህን ሁሉ ስጋት የፈጠረው መፈንቅለ መንግሥት ነው። አቢይ መፈንቅለ መንግሥት ይገጥመኛል ብሎ ፈርቷል። በአፍሪካ ምድር እየተደጋገመ የመጣው ዕጣ ለእሱም እንዳይወድቅበት፣ ህወሓትም እግር እየተከለች ስለሆነ ትበላኛለች ብሎም ሰግቷል። ደግሞም ይቀርለት አይመስልም። እንዲያውም ዶር ዳኛቸው "ያቆሰለህን ግደለው፣ አትማረው" እያለ የሚወተውተው የሚመጣው ነገር ስላሰጋው ነው። የወያኔ ሚዲያዎች በሙሉም ዳኛቸው እንዲህ በማለቱ ከዘር ማጥፋት ጋር አያይዘው እየወረዱበት ይገኛሉ። አሁንም ከስድስት ወር በኋላ በትናንትናው ዕለት በወጣው የመከላከያ ዜና ላይ ደግሞ "የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት እያከናወነ ያለውን የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደት አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በዛሬው ዕለትም የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ሁሉን አቀፍ ውሰብስብ ግዳጆችን በአንድ ጊዜ መወጣት የሚችሉ የልዩ ኃይል አባላትን አሰመርቋል የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል።
"…ይሄ ዜና የሚያሳየው የመፈንቅለ መንግሥቱ ሁኔታ አሁንም እንዳለ የሚጠቁም ነው። በትናንቱ ምረቃ ሥነ ሥርዓት በተባለው ዝግጅት ላይ የተገኘቱት ደግሞ የመከላከያ መረጃ በእጁ ላይ ያለው ጄነራል ጌታቸው ጉዲና እና የአቢይ አሕመድ ዘመድ እንደሆነ የሚነገርለት የጅማ ተወላጁ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አብዱሮ ከድር ናቸው። የትናንቱ ዜና ሲሠራ ምረቃው በአብይ የጥበቃ ኃላፊ እና በመከላከያ ደህንነት ኃላፊ የተደረገ ሲሆን "ልዩ ተልዕኮ" ተብሎ የተገለፀ ነው። ልዩ ተልእኮው ምንድነው? ሌላውን ዝብዘባ ትተን እዚህ ላይ ነው ማስመር። ልዩ ተልዕኮ። አቶ ተመስገን ጥሩነህ ወደ ጠቅላዩ ቢሮ ከመሄዱ በፊት ነው ጌታቸው ጉዲና የደህንነት መሥሪያ ቤቱን ከነ ቢሮዎቹ የወረሰው። ተመስገን ስላልታመነ ነው እንደዚያ የተደረገው። አሁን አዲስ አበባ የምትመራው በመከላከያ ደህንነት ነው።
"…መጀመሪያ የቤተ መንግሥቱ ልዩ ጥበቃ የነበረው ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ነበር። ብርሃኑ በቀለ ሸዋ ነው። አቢይ ደግሞ ሸዋዎቹን እንደ ስጋት ዓይቶ ጅማና ወለጋን ይዞ መንቀሳቀስ ጀምሯል። ስለዚህ ብርሃኑ በቀለን ከሪፐብሊካን ጋርድ ኃላፊነት አነስቶ በሀገሩ ልጅ ያውም በዘመዱ ተካው። ብርሃኑን ጎንደር ላከው። ከሞትክም፣ ከኖርክም ሥራህ ያውጣህ ብሎ ነው የላከው። ብርሃኑም ከሽመልስ አብዲሳ ጋር ሆኖ የሲሚንቶ ንግዱን ያጣድፋል። የዐማራን ልጃገረዶችን ያለ ምህረት ይገለሙታል። በነገራችን ላይ አብይ የጅማና የወለጋን ኤሊት እያቀናጀ ነው። ወደ ራሱ የሚያቀርበው ጅማን ሲሆን የወለጋውን ደግሞ ሸዋ ነው የመታህ እያለ ቦታ እየሰጠ እርስ በእርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ እያደረገ ነው። አዲስ አበባ ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ በጅማ እና በወለጋ መሙላት ከጀመረ ሰነባበተ። እንዲያውም አሩሲ አላሠራ አለን፣ ጅማ እንዲህ አደረገ፣ ወለጋ ሀገሩን ሞላው ተባብለው መነቻቸፍም ጀምረዋል።
"…ከስድስት ወር በፊት የቤተ መንግሥት ጥበቃዎች ደብረዘይት ላይ ሲገመገሙ ገምጋሚ የነበረው የአብይ ጥበቃ ኃላፊ የጅማ ልጅ አብድሮ ከድር አሁንም ከጌታቸው ጉዲና ጋር መኖሩ የጥበቃዎቹ ተልዕኮ ሰፊ እንዳልሆነ ያሳያል። ሰፊ ካልሆነ ሥልጠናው የአቢይን መንግሥት ከመፈንቅለ መንግሥት እንዴት እንጠብቀው ነው የሚመስለው። በነገራችን ላይ ከተወሰኑ ወራት በፊት ብርሃኑ ጁላ የተወሰኑ ጀኔራሎችን ሰብስቦ "የአገር ጉዳይ ከእኛ ከመከላከያ ትክሻ ላይ ወድቋል" ማለቱን እነ አቢይ እንደ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው የወሰዱበት። አሁን አቢይ የመጨረሻ ተስፋ ያለው በጅማዎች እና በወለጋዎች ላይ እንደሆነ ነው ነገሮች የሚጠቁሙት።
"…ሌላው በመፈንቅለ መንግሥቱ ህወሓትም ሌላ ስጋት ናት። ወደ ፌደራል መንግሥት ዳግም ተስባ ለመምጣት ያላት ቀሪ አማራጭ መፈንቅለ መንግሥት ነው። መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ ደግሞ መፈንቅለ መንግሥቱን ሊያካሂዱ የሚችሉት ሁለት አካላት ናቸው። ብርሃኑ ጁላና ጌታቸው ጉዲና። የህወሓቱ ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ብርሃኑ ጁላ በጣም የቅርብ ወዳጆች ናቸው። ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ዳግም ስምምነት የተደረገው የኬንያ ናይሮቢ ነበር። በዚያ ውይይት ላይ ብርሃኑና ታደሰ በጦርነት ሚልዮኖችን እንዳስፈጀ ሳይሆን እንደተነፋፈቀ ሰው ነበር ሲተቃቀፉ የነበሩት። እናም ሁለቱ ለጌታቸው ረዳና ለአብይ አሕመድ እንደ ስጋት ነው የሚታዩት። ታደሰ ወረደ የጊዜያዊ አስተዳደር አካል ሆኖም ከዓድዋው ህወሓት ጋር ነው አሰላለፉ። የብልፅግና አክቲቪስቶች ሁልጊዜ እየኮነኑ ይጽፉበታል። ብርሃኑ ደግሞ ከታደሰ ጋር ወዳጅ ነው። ህወሓት መሰል ነገር ከፈለገ ሊጠቀም የሚችለው የእነ ብርሃኑ ጁላን ጀኔራሎች ነው።
"…ሌላው አቢይ በቶሎ እርምጃ የወሰደበት አብርሃ በላይን ነው። አብርሃ በላይ ህወሓት ወደ መሃል መምጣቷ አይቀርም እናም ያኔ ትበቀለኛለች አትለቀኝም የሚል እምነት ነበረው። ስለዚህ በትግሬ ላይ ለደረሰው ውድመት፣ ፍጅት የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶት ህወሓትን ለመካስ ከእነ ብሬ ጁላ ታደሰ ወረደም ጋር መዋል ማደርም ጀምሮ ነበር። በወልቃይት እና በራያ ላይም እያሳየ የነበረው እልህ ይሄንኑ ለንስሀ መግቢያና ዐማራን እጅ መንሻ አድርጎ በማቅረብ ከትግሬ ወገኑም ጋር ለመቀራረብ ይፈልግ ነበር። ሁኔታው ስላላማረው አቢይ በቶሎ አንስቶ የቆላ ዝንብ ጠባቂ ሚንስትር አድርጎ ከመከላከያ አንሥቶ ወረወረው። በዚህ ላይ ልብ ብለን የእነ ታዬ ደንድአን፣ የእነ ጃዋርን ጉዳይና አጠቃላይ የሸዋውን ኦሮሞ እንቅስቃሴ ካየን አብይ የመፈንቅለ መንግሥት ስጋት ገጥሞታል ማለት ይቻላል። በትግራይ ያለው ሁለት መንግሥት ነው። በብልፅግና የሚደገፈው ጌታቸው ረዳና የእነ ሞንጆሪኖ መንግሥት። በሁለቱ መካከል የአንድነት መስመር የለም። አንደኛው የወያኔ ቡድን እንዲያውም 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
"…ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ" ማር16፥19
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።
ወፌ ደግሞ መጣይ…!
"…ወፌ ወፊቱ ርግቢቱ ዛረም የጄነራሎቹን መልእክት ነው ይዛ የመጣችው። ቆይ በደንብ ላጣራው፣ በዚያም ላይ ነገርየው ከበድ ስለሚል ማብራሪያም ልጠይቅ። ወይም ደግሞ የበዛውን መልእክት አጠር አድርገው ይስደዱልኝ፣ አልያም እኔው አሳጥሬ ልጻፍ።
• ወለጋ የሊጠ ቢፍቱ ዸጋን ጊቤ ኮንኮላቴ… አለ አዝማሪ ማን አብተው… ኢጆሌ ጂማ፣ ኢጆሌ ሸዋ፣ ሸዋ ሊጣ… 😂
• ራሳቸው ካፈጣጠኑት እሰየው። እኔ ግን ማብራሪያ ስለምፈልግ ማብራሪያውን እስካገኝ ድረስ ጄኔራሎችዬ ትንፍሽ ሳልላት ወደ ሌላ ወግ እሸጋገራለሁ። ኦኦ…
• መጣሁ…
"…በሥራ ላይ ሆኜ የጻፍኩትን ርዕሰ አንቀጼን እንዳነበባችሁልኝ ቴሌግራም እየነገረኝ ነው። ይህን ከተናገርኩ በኋላ ካልገጠሙኝ በቀር እስከአሁን ዛሬም እንደትናንቱ በኢሞጂ እንኳ የተናደደ ሰው ፊት አላየሁም።
"…ቀጥሎ ደግሞ የእናንተ የአድማጭ፣ የአድፋጭ፣ ተመልካቾቻችን ሓሳብ የሚሰማበት ሰዓት ነው። ተራው የእናንተ ነው። የአንድ የመቶ ያህል ሰዎችን ሓሳብ ከተቀበልን በኋላ ወደ ሌሎች መረጃዎች፣ እና ውይይቶች እናልፋለን።
"…አባቴ ቴሌግራምን እንደኔ የተጠቀመባት ማን አለ? ማንአለ አልኩህ? ማኅበራዊ ሚዲያን በጨዋ ደንብ ከተጠቀሙ አይቀር እንደ ዘመዴ አላለም አንዱ ወንድሜ ጓዴ…!😂 ስንቱን ሙጢ፣ ተናጋሪ፣ ለፍላፊ አደረግኩት እኮ። እኔ መሃይም ብሆንም ስንቱን ሊቅ ዘጭ አድርጌ ሥነ ሥርዓትም፣ መረጃም አስያዝኩት አስጨበጥኩት እኮ። አፌን እከፍታለሁ የሚል ሲኖር አጠናግሬ እየለቀቅኩ ልክ አስገባሁት እኮ። በነፃነት… በጨዋም ደንብ ተንፒሱ። ተወያዩ፣ ተመካከሩ፣ ተከራከሩ።
• በሉ ተንፒሱ… 1…2…3 ጀምሩ…
"…ዛሬ ሚጢጢዬ የግል ጉዳይ ነበረኝ። እናም በዚያ ምክንያት በጠዋት መነሣት ስለነበረብኝ ማታም በጊዜ ነው የተኛሁት። ዛሬ 9 ቀን እየቀረን የዘመነ ትንሣኤውን ሰላምታ እንኳ ዘንግቼ በዘወትር ሰላምታችን ነው የተከሰትኩት። እሱ ነገ ይስተካከላል።
"…ሌላው ርዕሰ አንቀጻችን ነው። ማታ ጀምሬው ሳልፈጽመው ነበር የተኛሁት። የምስጋና ሰላምታችን ይቆያል ብዬ አስቤ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በመፍጠኑ ተረጋግቼ እጽፈዋለሁ ብዬ አስቤ የነበረው ሳላስበው ፈጥኖብኝ ወደ እናንተ ለማድረስ ዘገየሁ። የሆነው ሆኖ በውጥረት ውስጥ ሆኜ ሥራዬን፣ ጉዳዬንም ስለፈጸምኩ አሁን የተለመደውን ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነውን ርዕሰ አንቀጼን ልለቅባችሁ ነኝ።
• እናንተስ ለማንበብ፣ አንብባችሁም ሓሳባችሁን ለማካፈል ዝግጁ ናችሁ…?
"…አንድ የሚያስቅ ቀልድ ልንገራችሁማ…😂😂 …አላለም…? ……… እና ዜናውን እንደሰማሁ በሳቅ ነው ፍርፍር ያማረኝ…! ከምር ጁላማ አይቀልድ… አንዴ ቀልድ ከጀመረ የምን ክበበው ነሽ፣ የምን ፍልፍሉ…? … ታስቁኛለሽ…አለ።
• መኴ ኦሬክስ
• ሸኔ ኦሬክስ
• ኦህዴድ ኦሬክስ
• ብልጼ ኦሬክስ
• 😂😂😂
"…ተናፋቂዋ ደግሞ መጣይ…!
"…ከጄነራሎቹ ዘንዳ በአስቸኳይ ለዐማራ ክልል ሕዝብ እንዲደርስ የተባለ መልእክት ነው ይዛ የመጣይው። ቶሎ አክሽፈው ይላል መልእክቱ። ማክሸፍ አይደለም አፈርሰው።
• ቆይማ ልቀምመውና ልመለስ።
• ሊበላ…?
"…በዓለማችን ካሉ ቁጥር አንድ ሀብታሞች ተርታ በሚመደበው በአቶ ኤሎን መስክ ስም በተከፈተ የለገጣ፣ ሙድ መያዣ "Parody" የX ገጽ ላይ የዓይን ጥራትን በተመለከተ አንድ አላጋጭ የልግጫ ጥያቄ ይቀርባል። ጥያቄውን የመለሰ ደግሞ የ3 ሚልዮን ዶላር ሽልማት እንዳሚያገኝም ከጥያቄው ጋር አብሮ ተጠቅሷል።
"…ይሄን ጥያቄ ማን ያነበዋል? የዐማራ ወኪሉ የቆየው ብአዴን ሰው ቆይቶም በሰሊጥ ብር የበለጸገው ብልፅግናው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ነው ንግድ ሚንስቴር ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል። ሊበላ እኮ ነው። 😂 3 ሚልዮን ዶላር ሊልፍ። ሃኣ…? ቀልደኛ።
"…የጎንደር ፋኖ እዚያ በቀዬው የመጣውን የመላኩ አለበልን አለቆች ወራሪ ጦር አፈር ከደቼ ያበላል አጅሬው አያ መላኩ አለበል ደግሞ አዲስ አበባ ተቀምጦ 3 ሚልዮን ዶላር ሊበላ…?
• የዶላር ውይይቱ ቀጥሏል።
"…እስከ አሁን የተበሳጨ ሰው አላየሁም። የሆነው ሆኖ ተራው የእናንተ ሓሳብ የሚሰማበት ሰዓት ነው። ቀጥሉ።
• የማንን ራዕይ ማን ያስቀጥል…?
"…መልካም…
"…ዛሬ ሰኔ 6 አርባኛው ቀን ለበዓለ ዕርገት ደርሰን በዓሉን በያለንበት አከበርን። እንደልማዳችንም ከእኔ ጋር የትንሣኤውን ዐዋጅ ያውጁ ዘንድ የሚጠበቁት 1ሺ አመስጋኞች ዛሬም ሳይታክቱ፣ ሳይፈሩ፣ ሳይኮሩ፣ በደስታ አመስግነው የሚጠበቀው የአመስጋኝ ቁጥርም ሞልቷል።
• ቀጥሎ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን በቪድዮ የተደገፈ ነው። ርዕሰ አንቀጽ በቪድዮ ለመመልከት እና እናንተም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?
• የ 100 ሰው ዝግጁነት ብቻ ነው የምጠብቀው። ዝግጁ…?
• ይደመጥ…!
"…የወሎ ዕዝ ፋኖዎች የአሳምነው ፅጌ ልጆች መልእክት ለኢትዮጵያ እናቶች…
• "ማይም" ግን እንደዚህ ከፍ ያለ የመጠቀ አእምሮ በለቤት ነው ማለት ነው? አይ ዐማራ…👌