zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።

• ትዊተር 👉 Twitter: https://twitter.com/MerejaMedia

•በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

• ዩቲዩብ 👉 YouTube: https://www.youtube.com/watch?v=zly-QY5YNmU


"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ”

• ትግራይ፦

"…በፌደራል አገዛዙ፣ በመከላከያ ዕርዳታ ሙሉ ራያን በመውረር አሁን ደግሞ ወደ ላስታ ተራሮች እያቀኑ መሆኑ ተነግሯል። አቢይ አሕመድ በፕሮፓጋንዳ ሳታጮሁት እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወልቃይትንም በዚሁ መልክ ትረከባላችሁ ብሎ ቃል እንደገባላቸውም ተነግሯል። አንድም የትግሬ አክቲቪስትም ሆነ ሚዲያ በዚህ ዙሪያ እንዳይዘግብ መደረጉም ተሰምቷል። የዐማራ ብልፅግና ነኝ ባዩ በድኑ ብአዴን የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶም መቀባጠር ጀምሯል።

• ዐማራ፦

"…በመንገደኞች አውሮጵላን፣ በመኪና፣ በእግረኛ ጭምር የሀገሪቱ መከላከያ፣ የጸጥታ ኃይል የተባለ በሙሉ ክተት ዐውጆ ወደ ክልሉ ገብቶ ከዐማራ ፋኖ ጋር የሞት ሽረት ከባድ ጦርነት ከፍቷል። መከላከያው ለተዋጊ ወታደሮቹ በሰጠው መመሪያ መሰረት። "…ተዋጉ፣ ግደሉ፣ አውድሙ፣ ድፈሩ፣ ዝረፉ። ጥይት ስትጨርሱ ለፋኖ እጅ ስጡ። ከዚያም ተገደን፣ ሳንፈልግ ነው የገባነው፣ ወደ ቤተሰቦቻችን ላኩን ብቻ በሉ። ፋኖም ተንከባክቦ መታወቂያ አሠርቶ ይፈታችኋል በማለት እንደሚያሰማራቸው ታውቋል። ፋኖ ማርኮ ፈትቷቸው ድጋሚ የተማረኩ እንዳሉም እየተነገረ ነው። በአጠቃላይ የዘንድሮው ክረምት ሳይገባ በሚል የዐማራ ክልል ዐውዳሚ የጦርነት ጊዜን በመጋፈጥ ይገኛል።

• ኦሮሚያ፦ ልማት ላይ ነው። ክልሎች ሁሉ በሻሻ ከሆኑ በኋላ እንደ ኒውዮርክ ያለ የነጻነት ሐውልት በአምቦ ከተማ ላይ እስኪገነባ ድረስ ኦሮሚያ ልማት ላይ ናት። የኦሮሞ እስላሞች በኦነግ ሠራዊት ውስጥ ሆነው ይሣተፋሉ እንጂ በክልሎች ውጊያ ላይ ከአዛዥነት ባለዘለለ በገፍ እንዳይሳተፉም መደረጉ እየተነገረም ነው። በኦሮሞስም የኢትዮጵያን ሥልጣን የያዘው አካል ኢትዮጵያን የማፈራረስ ምቹ ጊዜ ላይ እንዳለ እየተሰማው መሆኑም እየታየ ነው።

• ኦሮሙማ አውዳሚ ነው። ካላመንከኝ ኪስና ጓዳህን ተመልከት።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በዚህ እንሰነባበት…!

"…በመጨረሻም የጅቡቲ የ100 ዓመት ኮንትራት አልቆ እንደ ጋምቤላ እና ኦጋዴን ወደ እናት ሀገሯ ለመመለስ ጥቂት ዓመታት ሲቀሯት ደርግ የተባለ ኦሮሙማ ፈጥራ ንጉሣዊ ዘውዳዊ ሥርዓቱን አፍርሳ፣ አስፈርሳ አይደለም ጅቡቲን ወያኔና ሻአቢያን አሰልጥና ኤርትራን ከነውኃችን ቅፍፍ አድርጋ አስገንጥላ ስታበቃ ወያኔ ራሷ ደደቢት በረሃ ገብታ ማክበር ያቆመችውን፣ አቢይ አሕመድም ደብሮት የተወውን፣ ከካላንደር ላይ ራሱ ሊፋቅ ቀጠሮ የተያዘለትን ግንቦት 20ን አሜሪካ ሆዬ።ሞቼ ነው ቆሜ ምን ሲደረግ እኔ ግን ድብን አድርጌ ነው የማከበረቅ ብላ እርፍ።

• አለ ማርያም ምን ነበር ያለው? መልካም ግንቦት 20 በዓል ለአማሪካ… 😂😂😂

"…ሱሬ ሆይ ይኸው ድካምህ መና አልቀረም። በአንተ እንግልጣርኛ ማወቄም ይኸው በደንድብ አድርጎ እየጠቀመኝ ሳይሆን አይቀርም። ወደፊት እንደውም በእንግሊዝ አፍ ነው የምጦምረው። አከተመ። 😁

• በድጋሚ መልካም Downfall of Derg ✍✍✍😂🎷🎷

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አቶ ደመቀ ሞተ አልሞተ፣ ገደሉት አልገደሉት እኔ ምን ያገባኛል? ይልቅ ይሄን ቀጥሎ የምጽፍላችሁን አይታችሁልኛል?

"…ይህቺ የአቢይ አሕመድ ገሌ አማካሪ አለማሪያም ተብዬዋ ወሴ ሰውዬ ጠፍጥፋ ሰው ያደረገቻትን አሜሪካን መሸሞር ደግሞም የአሜሪካውን አምባሳደር በጥቁርነቱ እንዴት አድርጎ እንደሚገልፀው፣ እንደሚሰድበው አያችሁልኝ?

"…በነገራችን ላይ እንደ ሀብትሽ አያሌው የደረቀ ንፍጥ ወይም ምራቅ የመሰለ አገጭ ላይ የተለጠፈ ሳይሆን የሀበሻ ወንድ ለአመል ታህልም ቢሆን ትንሽዬ ጢም ማስቀረት ነውር አይደለም። ኧረ ደግሞ ስለ ጢሙ ምን አገባኝ? ምን ጉድ ነኝ? እኔም ደህና ጢም እንዳለው ሰው ሌላውን ልፎትት ስነሣ አለማፈሬ። ጉድ እኮ ነው።

"…M ass inga ማለት ግን የአለማርያም አገላለፅ እንደ ስድብ መሰለኝ። የሱሬ ያለህ? ኧረ የተርጓሚ ያለህ? በአሜሪካ ጥቁር ለጥቁር እንዲህ ቢሰዳደብ ምንም አይደል? ጥቁርን ግን ሌላ ሰው እንዲህ ቢሰድበው በግንባሩ ላይ ነው ጥይት የሚቆጥርበት የሚሉም መተርጉማንም አሉ።

"…M ass inga ??? ምን ማለቱ ነው አለ ማርያም። ሆሆይ …M ass inga አላለም ይሄ የትልቅ ትንሽ የሆነ ሰው። ኧረ ወዴት እየሄድን ነው ጎበዝ? ፍሮፌሰርም ሆኖ M ass inga ብሎ መሳደብ አግባብነት አለው ወይ?

• M ass inga

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሮጲላም ሄዱ፣ በኮንኮላታ፣ በቶቢሲም ሄዱ፣ በእግራቸውም ገቡ በፈረስ በበቅሎ የእናት አባታቸው ጸሎት የረዳቸው ትረፉ ያላቸው ብቻ በሕይወት ይማረካሉ። ቀን የጨለመባቸው ደግሞ የኅልውና ትግል ነውና ይደመሰሳሉ። ዐማራ ማለት የሚደንቅ ሃይማኖተኛ ሕዝብ እኮ ነው። ሊገድለው የመጣን ጠላት ራስን በመከላከል መክቶ ከገለው በኋላ ለጠላቱ እያለቀሰ መልሶ በክብር የሚቀብር፣ አፈር የሚያለብስ፣ የጠላቱን አስከሬን እንኳ አክብሮ የሚቀብር ሕዝብ ነው። ከነ ልብሳቸው አክብሮ ይቀብራቸዋል። ሌላው ቢሆን ብላችሁ አስቡት።

"…በተለይ ይሄኛው ዙር ለዐማራም፣ ለኦሮሙማም ሆ፣ ለወያኔም ጭምር የመጨረሻ የዋንጫ ጨዋታ ነው የሚሆነው። ዐማራ አሁን በአገዛዙ ተመልምሎ ሠልጥኖ ተመርቆም በገፍ ወደ ዐማራ ወደ ክልሉ የሚገባውን አዲስ ምልምል የብልፅግና ጦር መክቶ ከደመሰሰ ነገር ሁሉ ያበቃል። ሁሉም ነገር መቋጫውን ያገኛል። ያከትምለታልም።

"…መጪዎቹ ሁለት ሦስት ወራት የዐማራን ትንሣኤ የሚያፋጥኑ ወይም የዐማራን ትንሣኤ የሚያዘገዩ ይሆናሉ። በተለይ ኦሮሙማው ክረምት ሳይገባ በማለት ህፃናትን ሳይቀር አፍሶ ወደ ማሰልጠኛ እያጎረ ነው። ክረምቱ ከገባ ፋኖ ድራሽ አባቱን ነው እንደሚያጠፋው በደንብ ተረድቷል። እናም ደፈጣ። ደፈጣ ነው አገዛዙን ኪሳራ ላይ የሚጥለው። መቀጥቀጥ ነው። መግቢያ መውጫ ማሳጣት ነው።

"…እመኑኝ አንድም ወንጀለኛ ከምድሪቱ አያመልጥም። ብልፅግና የተባለ ኮተት ዘር አጥፊ ጄኖሳይደር በሙሉ ከነደጋፊዎቻቸው በግልጽ የሚዳኙበት ጊዜም በጣም ቅርብ ነው። በጣም ቅርብ ጊዜ አልኳችሁ። መዝግቡልኝ። ለዚህ ለፈሰሰው ነፍስ ሁሉ እያንዳንዱ ይጠየቃታል። አልሰማሁም፣ አሽከር ተላላኪ ነበርን ይቅርበሉን አይሠራም።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…በፋኖዎች ስም፣ በሌለው ሠራዊት ገንዘብ አይለምንም። አይለምንም ማለት ለምን የግንቦት ሰባት ሰዎችን ብቻ ያናድዳቸዋል? በእንግሊዝኛ ሌላ በአማርኛ ሌላ መግለጫ ማስነበብ ለምን ፈለገ እስክንድር? እንደ ወያኔ ሕዝብን ማጭበርበር ለምን ፈለገ እስክንድር? የእስክንድር ሠራዊት የት ነው ያለው? በጎጃም ለምን ክፍተት መፍጠር፣ መወሎ ቀዳዳ ማበጀት ለምን ፈለገ? ለምንድነው በሸዋ መከታው ጋር ተጠግቶ ከሌሎች ጋር እነመከታው እንዲታኮሱ የሚያደርገው? እስክንድር በደረሰበት ቦታ ሁሉ ውድመት፣ ሞት ሳያንስ አሁን ደግሞ ቢያንስ መከታውንና አሰግድን አባትና ልጅን ያለውን ስም ተጠቅሞ እንደማስታረቅ ለምንድነው ሲታኮሱ ዝም ብሎ የሚያየው። እንዲህ ብሎ መጠየቅ እስክንድርን መጥላት የሚሆነው በምን ስሌት ነው?

"…መወያየት ደግ ነው። አሰግድና መከታው ቢገዳደሉ ተጠያቂው ከእስክንድር ጀርባ ያሉት አንዱን ወደው፣ አንዱን ጠልተው፣ አንዱን አቅርበው፣ አንዱን አርቀው፣ አንዱን አጀግነው፣ አንዱን አኮስምነው ፕሮፓጋንዳ የሚሠሩት እነ ሀብታሙዎች ናቸው። አሰግድን ሰድበህ፣ መከታውን አሞግሰህ የምታመጣው ለውጥ የለም። መከታውን አኮስምነህም አሰግድን አጀግነህ የምታመጣው ለውጥ የለም። ሸዋ ቢገዳደል ቤተሰባዊ ቁርሾ ነው የሚፈጠረው። የአጎት፣ የአክስት ልጅ ነው የሚገዳደለው፣ በጠላት ከጠላት ጋር ተዋድቆ መሞት የሚገባው የሸዋ ፋኖ በመከታውና በአሰግድ ስር ተለያይቶ መዋጋት መገዳደል የለበትም።

"…እኔ የማውቀውን ሓላፊነቴን በሚገባ እየተወጣሁ ነው። አንተ ብትንጫጫ አያገባኝም። ተላላቅ ሰዎች በሁለቱ መሃል ግቡ። ግቡና በቶሎ መፍትሄ አምጡ። በጎጃም አንድ ፋኖ እና የፋኖ አደረጃጀት እንጂ እስክንድር የሚመራው ሌላ የፋኖ አደረጃጀት መኖር የለበትም። በጎንደር፣ በወሎና በሸዋም እንደዚያው። እስክንድር በፋኖ ስም መግለጫ አውጣ ያለው ሳይኖር ማውጣት የለበትም። የዐማራ ትግል ባለቤት አለው። የፋኖ ትግል ባለቤት አለው። እስክንድር ሠራዊት የለውም። ውክልናም የለውም። የእስክንድር እንግሊዝኛ ቋንቋ ማወቅ ሌላውን ፋኖ።መናቅ ነው። እኔ እንኳ የማውቃቸው፣ እስክንድርም የሚያውቃቸው በረሃ የከተሙ ፕሮፌሰሮችን መናቅ ነው። ለድርድርም፣ ለመግለጫም ሥነ ሥርዓት። ነው ያልኩት። አይ መብቱ ነው አይሠራም።

"…ይሄ የሰካራም ድግስ አይደለም እስክንድር እንደፈለገ ገብቶ የሚፈተፍትበት ቡኮ አይደለም። እስክንድርን ታዝለህ፣ በእስክንድር ስር ተጠልለህ የመጣህ ወንበዴ፣ ሌባ ግንቦቴና ፌክ ኢትዮጵያኒስ፣ ጨበርበርቱ ወዪ፣ ሃስመሳይ ሌባ ሁላ አደብ ትገዛለህ። ዐማራ አሁን ዐማራ ነኝ እያለ ነው እየታገለ ያለው። በዐማራ ትግል ላይ ግንቦቴና ግንባር ባልደራስ ወዘተ እጃችሁን አንሡ። ዐማሮቹ ሲፈልጉ ተደባድበው፣ ተጣልተው፣ ተጨቃጭቀው፣ ተሟግተው ቤታቸውን ያጽዱ። እንደፈለጉ ይሁኑ። በዐማራ ፋኖ ትግል ላይ ያንዣበብክ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ ሁላ አርፈህ ተቀመጥ። ምን አባህ ታመጣለህ? ምንም።

"…ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ቃላት አርማችሁ፣ በጨዋ ደንብ ለመወያየት ተዘጋጁ። ከፔጄ የሚባረረው እናትን የሚሰድብ ስድአደግ ባለጌ ብቻ ነው።

• በዚህ መልኩ መወያየት እንልመድ። አይደለም እንዴ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…ለምን? እንዴት? ማን? ወዴት? ብሎ ጠያቂ፣ ግራና ቀኝ ተመልካች ተጠራጣሪ፣ አገላብጦ የሚያይ ተመራማሪ፣ እንደወረደ የማይቀበል፣ አላምጦ የሚውጥ፣ ማንም ተነሥቶ ጎትቶ እንደ ፈለገ እንደ ህዳር አህያ የማይጭነው እሳት የላሰ ሞጋች ትውልድ ተፈጥሯል። እኔ በዩቲዩብ መንደር ባልኖርም በፌስቡክና ቲክቶክ መንደር እንኳ የሚገርምና የሚደንቅ ለውጦች እያየሁ ነው። በተለይ በቴሌግራም ያውም በእኔ በዘመዴ ቤት የሚታየው ደግሞ ይበል የሚያሰኝ ነው።

"…በፊት በፊት ጊዜ ፖለቲካም፣ ሴራም የሚሰማው፣ የሚታየው፣ የሚነበበው፣ የሚቀመረውም በመንግሥታዊ ልሳኖች እና በአገዛዞች ካድሬዎች አመካኝነት ነበር። አጀንዳ የሚሰጠውም በዚያ በኩል ብቻ ነበር። እነ አዲስ ዘመን፣ ኢቴቪ፣ በሪሳ፣ ሠርቶ አደር፣ የኢትዮጵያ ራዲዮ ወዘተረፈ አንድ ለእናቱ ሆነው ያለተገዳዳሪ የኦሮሙማው ደርግ ንጉሣዊ ሥርዓቱን ገርስሶ በምትኩ እሱ ራሱ የፕሮፓጋንዳ ቅርሻቱን በዜጎች አእምሮ ላይ የሚደፋበት ዋነኛ ፋብሪካዎቹ ነበሩ። በዚያን ጊዜ ፌስቡክ የለ፣ ኢንተርኔት የለ፣ ዩቲዩብ የለ፣ ቴሌግራም የለ፣ ቲክቶክ የለ፣ ከመንግሥቱ ቅርሻት በቀር ሌላ የሚሰማ፣ የሚታይ፣ የሚነበብ አማራጭም አልነበረም። ድንገት እንደነ በዓሉ ግርማ ዓይነት ደራሲያን ብቅ ብለው ከአገዛዙ የተለየ ሓሳብ በመጽሐፍ መልክ ሲያቀርቡ ወዲያው እፍን፣ ግድል፣ እርድ፣ ቅብር። አለቀ እንዲያ ነበር። ይሄን ነፃነት የተነፈጉ ደግሞ ብረት አነሡ፣ ጫካ ገቡ።

"…ቆይተው በትግሬ ነፃ አውጪዎች የሚመራው ኢህአዴግ የተባለ ስብስብ የኦሮሙማውን መንግሥት ደርግን ጥሎ መንበረ ሥልጣኑን ያዘ። በቀድሞዎቹ ሚድያዎች ላይም እነ ፋናና ዋልታ የሚባሉ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ተጨመሩ። ነፃ ፕሬስም እንደ ጉድ ፈሰሰ። ወያኔ ጥይት እንጂ ብዕር፣ መተኮስ እንጂ መጻፍ፣ ወታደር እንጂ ደራሲ ብሎ ነገር አይገባትምና ነፃ ፕሬሱን አፍና አንቃ ሲጥ አድርጋ ገደለችው። በመጨረሻም የምትቆጣጠረው ዩቲዩብ፣ የማትቆጣጠረው ፌስቡክ የተባለ ገደብ የለሽ የግለሰብ ነፃነት የሚንጸባረቅበት ነፃ መድረክ ተፈጠረባት። ብዙም ሳትቆይ ኦሮሙማውን ኮሎኔል መንግሥቱን ገርስ በዳግማዊው ደርግ በኦሮሙማው አገዛዝ በኮሎኔል አብዮት አሕመድ ቋንጃዋ ተሰብሮ፣ ወገብ ዛላዋ ተቆምጦ፣ ሽባ ሆና ወደ ደደቢቷ ተመለሰች። ቆይቶ ዱቄት በሻሻ ያደረጋት ኦሮሙማው አቢይ ከዐማራው ጋር ለገባበት ቅርቃር ብትረዳኝ፣ ብታግዘኝ ብሎ እንደምንም አፈር አስልሶ ራያ አስገብቷቷል። የወያኔንም የኦሮሙማውንም መጨረሻቸውን ማየት ነው።

"…ዳግማዊው ደርግ የአቢይ ኦሮሙማው አገዛዝ ላለፉት 60 ዓመታት የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት ለመናድ፣ የሀገር መከላከያዋን ለማፍረስ የደከመውን ድካም፣ የለፋውን ልፋት ብአዴን በተባለ የዐማራ በድን ተባባሪነት ከጫፍ ደርሶለት መጨረሻውን ለማየት በጉጉት እየተጠባበቀ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። አሁን ጨዋታው በቴሌቭዥን ብቻ አይደለም። አሁን ጨዋታው የትየለሌ ሜዳዎች ነው ያሉት። በአለቅነት የማትቆጣጠራቸው ነፍ ሜዳዎች ነው ያሉት። ካድሬ የማይደርስባቸው እንደ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም የመሳሰሉ የግለሰብ ሚዲያዎች ናቸው ምድሪቱን የሞሉት። በጨዋነት እንኳ ብትሞግት ለምን ብሎ የሚገድልህ አረመኔ አገዛዝ  ባለበት ሀገር ማቅረብ የማትችለውን ሓሳብ መብቱ ነው ብሎ የመናገር ነፃነትህን በሚያከብር ሀገር ላይ ቁጭ፣ ጉብ ብለህ በነፃነት ሓሳብህን ታንሸራሽራለህ። ሰሚም በየቤቱ፣ በየኪሱ ወጣ አድርጎ ይኮመኩምህሃል። እኔም እያደረግኩ ያለሁት ያንኑ ነው።

"…በእኔ የቴሌግራም ገጽ ብቻ። በኢትዮጵያ ከእኔ ገፅ በቀር ቴሌግራምን በዚህ መልክ የሚጠቀምበት አይቼ አላውቅም። አሁንማ ዕለት ከዕለት በቴሌግራም መንደሬ ላይ የሚቀርቡ ሓሳቦቼን የሚደግፉም፣ የሚቃወሙም በጨዋ ደንብ መወያየትን ባህል አድርገው መታየት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አንድ የተለየ ሓሳብ ማንሣት ልክ እንደ አምባገነን አገዛዞቹ ሁሉ የግለሰብ አምባገነኖችም ለምን ሓሳቡ ተነሣ ብለው በመወያየት ፈንታ እምቧ ከረዩ እሪቋቀምበጭ ሲሉም ይታያል። ይሄን የግሪሳዎች እሪታ በመፍራት፣ በመሸማቀቅ ብዙዎች ሓሳብ አንሸራሽረው፣ አስተችተው፣ አወያይተው፣ አከራክረው፣ አሟግተው ብዙ ለውጥ ማምጣት ሲችሉ የባለጌ፣ የስድአደጎችን ስድብ ፈርተው ተሸማቅቀውም በአጭር ቀርተዋል። እንደ እኔ ዓይነቱ ገገማ መስሚያው ጥጥ የሆነ የሀረርጌ ቆቱ ደግሞ ለተንበጫባጭ አሸማቃቂዎች ቦታ ሳይሰጥ ከቁብም ሳይቆጥር "ውሾች ይጮሃሉ ግመሏ ጉዞዋውን ቀጥላለች" የሚለውን የአፋሮች ተረት እየተረተ፣ ጠላትን በብዕሩና በምላሱ እየነረተ ወደፊት ብቻ መጓዝን ይቀጥላል። ኢንዴዢያ ነው።

"…በፔጄ ላይ የሰው ቁጥር ይጨምራል። ደግሞም ይቀንሳል። በፍርሃት፣ በንዴት እና ስድአደግ ፀያፍ ስድብ ተሳዳቢ ይጠረግና ተቀስፎ ከፔጄ ተባርሮ ይቀንሳል። መንግሥት በስልኩ ላይ የዘመዴ የቴሌግራም ፔጅ የተገኘበትን ሰው ስለሚቀጣ ይቀንሣል። እኔም አበረታታለሁ። ሌሎች ደግሞ አኩርፈው፣ ለምን ተነካን ብለው የሚቀነሱም አሉ። ጡርግ ለምን አትልም ለደንታህ ነው። ወዳጅም እንደዚያው ነው። የሆነ ወቅት ወዳጄ ይጨምራል ከዚያ የሆነ ቀን ወዳጄ ይቀንሳል። ወዳጆቼ የሚቀንሱት የሆነ ቀን የእነሱ መስመር ስህተት ሆኖ ሳገኘው ስዠልጣቸው ነው ብን ብለው የሚጠፉት። ሌላው ሲወቀስ፣ ሲዠለጥ እንጂ ደስ የሚላቸው እነርሱ ሲነኩ አይወዱም። የቀጠሩኝ ሁላ ይመስላቸዋል። እንደ ባሪያ፣ እንደበቀቀን ሊያዩኝ የሚፈልጉም የትየለሌ ናቸው። እኔ ዘመዴ ቋሚ ወዳጅ፣ ቋሚ ጠላትም እንደሌለኝ አይረዱም፣ ቢረዱም ማመን አይፈልጉም። አምላኬን አስቀድሜ እሱን ብቻ በመፍራት ሌላውን የምምረው ሰው የለኝም። ያጠፋህ መስሎ ሲታየኝ ብዙ ዕድል ሰጥቼ አፈር ከደቼ አበላሃለሁ። እኔንም ልክ አይደለም የሚለኝ ሲዠልጠኝ ይውላል። መብታቸውም ነው። አለቀ ያጠፋን ባንዳ ከሀዲን ሱሪውን ዝቅ አድርጎ በሳማ መግረፍ ይሄ የእኔ ጠባይ ነው። መመሪያም ነው።

"…ትናንት በእስክንድር ነጋ ዙሪያ የጀመርኩት ጥያቄም እንዲሁ ሲያፈታፍት መዋል ማደሩን ነው ያየሁት። እኔም ይሁነኝ ብዬ ሰው ሁሉ በድፍረት እንዲጠይቅ፣ እንዲወያይ በማለት የአስተያየት መስጫ ሰንዱቄን እንኳ ሳልዘጋው ክፍቱን ነው ያሳደርኩት። የሆነው ሆኖ እንደዚያም ሆኖ አንድ ሰው ብቻ ነው ከእንቅልፌ ስነቃ ባለጌ ፀያፍ ስድብ ሲሳደብ ያገኘሁት። እሱንም ቀስፌ ከፔጄ አባርሬዋለሁ። ሌላው ግን በሚገርም መልኩ ነው ሲወያይ፣ ሲሟገት፣ ሲከራከር ያየሁት። ይሄ ነገር መለመድ አለበት። ይሄ መንገድ አጥብቀን ልንከተለው ይገባል። መወያየትን የመሰለ ይችግሮች ሁሉ መፍትሄ በዓለም ላይ የለም። ከጸሎት በተጨማሪ ምድራችን የምትፈወሰው በምክክርና በውይይትም ነው። ዐማራ ግን የሚያሸንፈው በነፍጡ ብቻ ነው። ወያኔ ደርግን፣ የመጀመሪያውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች ባደረጉት አስገዳጅ ውል ዓይነት መንገድ ነው የሚያሸንፈው። ለዐማራ አሁን ድርድር ሳይሆን ድል ብቻ ነው አሸናፊም፣ ዘሩንም እንዲተርፍ የሚያደርገው። አለቀ። 👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።” 1ኛ ጴጥ 1፥3-5

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የገባችሁ አሁን መልሱልኝ።

• አመሰግናለሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

🙏…ስለዚህ ቪድዮ የተብራራ መልስ ስለፈልግሁ ልጠይቅ ነኝ። ትፈቅዱልኛላችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ ይዘራል፥ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል፥ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፥ በኃይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። 1ኛ ቆሮ 15፥ 42-44

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የጠፉ ናቸው ብለው ራሳቸውን ያጠፉ የኦሮሞ በጎች ሰበሰበና… የተሰበሰቡትን የዐማራ በጎች ድራሻችሁ ይጥፋ ብሎ No Go አለላችኋ… ጉድ እኮ ነው… 😂

"…የዱባይዋ ፋጢማም፣ አቢይ የፈለገውን አጀንዳ ያምጣ፣ ምክክር ኮሚሽኑም በ21 አጀንዳ ስብሰባ ይጀምር፣ የፈለገ የፈለገውን ይሁን አባቴ ይሙት አበደን ከዘንድሮው የቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ዓይናችንን አናነሣትም።

"…ባለ ማዕተብ የሆንክ የተዋሕዶ ልጅ ተዘጋጅ ብዬሃለሁ። ነግሬሃለሁ። እኔ በሙሉ ኃይሌ ነው ሰተት ብዬ የምገባው። የሌለ ፍፁም የለየለት ባለጌ ሁላ ነው የምሆነው። በኃይለኛው ነው እብድ እብድ ሁላ የምጫወተው።

• በጎች ሰምታችኋል…! 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በወልቃይት እና ጠለምት መሬቶች ጉዳይ በኦሮሞ ብልፅግና እና በህወሓት መካከል ልክ እንደ ወሎው ራያ ምድር አይነት ስምምነት ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም። የመጣው ይምጣ ብሎ የኦሮሞው ብልጽግና ከህወሓት ጋር ተደርቦ የወልቃይትን መሬት አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ ግን የሚፈጠረው ትርምስ አካባቢውንም፣ ቀጠናውንም ያተራምሳል ተብሎም ይታሰባል። እናም ለክፉም ለደጉም ብለው የሰፈጉት የዐማራ ብልጽግና ሰዎች በራያ ጉዳይ የመወሰን አቅም እንዳጡ የገባቸውና በማንኛውም ሰዓት አየር ላይ እንደሚንሳፈፉ፣ ከሕዝባቸውም ከአገዛዙም ማረፊያ እንደሌላቸው የገባቸው ደደብ ብአዴኖች የራያ ጉዳይ ከታወቀ ወዲህ በጎንደር እና በወሎ በተለየ ሁኔታ የፖለቲካው ምህዳር በፍጥነት መቀየሩ እየተነገረም ነው።

"…የኦሮሞ ብልጽግና ህወሓትን ከመቀሌ አምጥቶ ራያን ማስወረሩ ለወሎ ቤተ ዐማራ ፋኖዎች ያልታሰበ በረከት ነው ያወረደላቸው። ከሁለት ተከፍሎ የነበረው የወሎ ፋኖ ወደ አንድ ዕዝ የመጡበት ወቅትም ስለነበር በሺ የሚቆጠሩ የዐማራ ሚሊሻና የዐማራ አድማ ብተና ኃይላት የትኛው ጋር እንቀላቀል ብለው ሳይቸገረ ከነሙሉ ትጥቃቸው ነው የወሎን ፋኖን የተቀላቀሉት። በጎንደርም እንደዚያው ነው። እነ ኮሎኔል ደመቀ የሚያስተዳድሩት ወልቃይቴ ለጥቂት ጊዜ ፈጥሮት የነበረውን ዳተኝነት በፍጥነት በማረም ከጎንደር የዐማራ ፋኖዎች ጋር በሚገባ መናበብ ጀምሯል። የብልፅግናን ከሃዲነት፣ የብአዴንን ከጅብ አያስጥሌነት የተረዳው በተለይ የጎንደር ብልፅግናው ቡድን በአንድም ይሁን በሌላም ምክንያት በኦሮሙማው ብልፅግና የመካድ ስሜት ስለተፈጠረበት ወደ ኩርፊያ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ፋኖ በረካ ሳይወርድለት አይቀርም የሚል ስሜትም ይሰማኛል። የሰሞኑ የጎንደር ጀብዱ፣ ድል፣ በገፍ የሚቀላቀሉት ሚሊሻዎችና የአድማ ብተና አባላት ጉዳይም ምስጢሩ ሌላ መሆኑን ለመገመት ኢዩ ጩፋን መሆን አይጠበቅብህም።

"…ሌላው ፋኖዎቹም ሆነ ብልፅግና በመጪው ክረምት የሞት ሽረት ፍልሚያ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ናቸው። ብልጽግናም ክረምቱ ሳይገባ ፋኖዎቹ በሙሉ ኃይላቸው ወጥተው እንዲገጥሙት ይፈልጋል። ፋኖ ወጥቶ ፊትለፊት ካልገጠመው እና በዚህ ሁኔታ ክረምቱ ከገባ ከባድ ኪሳራ እንደሚገጥመው የተረዳው የኦሮሙማው ብልጽግና እንቅልፍ አልባ እቅዶችን በማውጣት እየዳከረ ይገኛል። ሸዋ ላይ ያለው የሁለቱ እዞች ግጭትም በጊዜ ካልበረደ እና ሁለቱም ጎሮምሶች ሃይ የሚላቸው ሽማግሌ ካልተገኘ ለኦሮሙማው ብልፅግና ዕድሜ ማራዘሚያ በጣም ማዳበሪያ የሆነ አሸወይና እድል ነው። ወሎም፣ ጎጃምም፣ ሸዋና ጎንደር በንግግር፣ በስምምነት፣ በውይይት ወደ አንድነት መጥተው ሸዋዎች ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ መመርመር ያስፈልጋል። በተለይ የግንቦት 7፣ የግንባሩና የባልደራስ ግሪሳ ሁሉ ከአንደኛው ቡድን ጋር ቆሞ ሌላኛው ላይ እንዲዘመት መቀስቀስ ኪሳራው በትሪሊዮን ገንዘብ የሚገመት አይሆንም። ቢታሰብበት መልካም ነው።

"…ሌላው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ስለሚማረኩ፣ የሚንስትሮች እና የባለሥልጣናት መኪኖች ጉዳይ ነው። ሰሞኑን የአቶ ተመስገን ጥሩነህ የፕሮቶኮል መኪና በፋኖ ሓይሎች ተማረከች መባልን ተከትሎ የመጣ ምክርም አለ። መማረኩ ሸጋ ሆኖ ሳለ ማራኪ ፋኖዎቹ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ ግን ተመክረዋል። ምናልባትም ይላሉ ስጋቱ የገባቸው ተጠራጣሪዎች ምንአልባትም መኪናዎቹን ዐውቀው እንዲማረኩ ካደረጉ በኋላ የፋኖ አመራራሮች መጠቀም ሲጀምሩ መኪናዋ ውስጥ ሰውር ካሜራ፣ የድምጽ መቅጃና ሌሎች መረጃ ማስተላለፊያ መሳሪያዎች የተገጠመላቸው ሊሆኑ ይችላል። አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ የጸጥታ ሓላፊ በድብቅ ሲነጋገሩ የነበረውን መረጃ ወደ አንድ ቋት ይዞ በማስተላለፍ በማዕከል እንዲደመጥ በማድረግ አቶ ለማ መገርሳ እና የጸጥታ ሓላፊው ሲያወሩ የነበረውን ሁሉ ሰብስቦ እነርሱን ለማስወገድ የተጠቀመው በዚህ መንገድ ነው። እናም በምንም በማንም አልያዝ አልጨበጥ ያለውን የዐማራ ፋኖን ምስጢራዊ አስተደዳር መኪና ማረክን ብለው ለድሮን ሲሳይ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ያድርጉም ይላሉ መካሪዎቹ።

"…ዛሬ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ኋላ ላይ እንገናኛለን። እስከዚያው በዚህኛው ርዕሰ አንቀጽ ላይ እየተወያያችሁ ጠብቁኝ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የቦንቡን፣ የመለዋወጫውን፣ የኦፕሬተር የሠራተኞቹንና የትራንስፖርቱን ሳይጨምር በጥቁር ገበያ ተዘርዝሮ ድሮኑ ብቻ 240 ሚልዮን ብር ነው የሚሸመተው እየተባልክ። እየተነገረህ፣ እየሰማህ፣ እያየህ፣ እዚህ መጥተህ ዩኒቨርሲቲ እኮ ለተማሪ የሚቀርብ ምግብ ጠፋ፣ በወላይታ ለመምህራን ደሞዝ መክፈል ቀረ፣ መድኃኒት በገበያ ላይ የለም፣ ነዳጅ ተወደደ ትላለህ።

"…አርፈህ እንደ ኦሮሞ ብልጽግና አትበልጽግና ችግር አውራ። አይደለም ደሞዝ ገና የራስህ ደም አይኖርህም። ደም ነው የሚያጥርህ።

"…ባለ ጊዜ ማለት እንዲ ኖ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አሁናዊ መረጃ…!

"…ከፌደራል የተላከ የቴክኒክ ቡድን በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራው እንዳቀናና በቱሉጋና ከተማም እንዳረፈ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ድሮኗ የተሸከመቻቸው ያለፈነዱ ቦንቦች ከድሮኗ ስር ስላሉ ድሮኗን ለማቃጠልም ሆነ ለመነካካት አለመቻሉን ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያመለክተው።

"…በተያያዘ ዜናም የኦነግም ሆነ የተጂ አክቲቪስቶች ሳይወዱ በግዳቸው እኔው የለጠፍኩትን መረጃ መልሰው ለመለጠፍ መገደዳቸውም ተመልኳቷል። የሀብታሙና የፀጋዬ አራርሳው ኩሽ ሚዲያማ "የፈጣሪ ቁጣ ነው" አላለም።

"…የአንድ ድሮን ዋጋና የአንድ የድሮን ቦንብ ዋጋ በዶላር ስንት ይሆን? የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚመገቡት ምግብ አጥተው ዩኒቨርሲቲዎች ሊዘጉ ነው የሚል ዜና በሚሰማበት ሀገር መሃይሙ አቢይ አሕመድ የቱርክን ድሮን በመሸመት ኤርዶጋንን ይጦራል። የሚደንቀው ሁላቸውም ይጠፋሉ። ተንነው ይጠፋሉ። ብን ነው የሚሉት።

"…በጎንደር የዐማራ አድማ ብተና ኃይሉ እና የዐማራ ሚልሻ ምን ሰምቶና ዓይቶ ነው በገፍ የዐማራ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለው። የሆነማ ነገር አለ። እየፈለፈልኩት ነው። የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች አልተቻሉም። የብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ከሞት የተረፈው ወደ ሱዳን ነካው አሉኝ።

• የጨነቀለ’ት…ድል ለዐማራ ፋኖ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አንዳንድ ቀን አለ አልፎ አልፎ ምሳ ቀመስ ካደረግክ በኋላ የዓለሙ ሁሉ ጢራሞና ዲራሞ እንቅልፍ በላይህ ላይ የሚከመርበት። ምሳ በልቼ ዓይኔን መግለጥ እስኪያቅተኝ እንቅልፍ አላዳፋኝም። ሲጣፍጥ ደግሞ ምን አይነት እንቅልፍ ነው።

"…የመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በርዕሰ አንቀጻችን ላይ ብናወራስ…?

• ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤” 2ኛ ጢሞ 2፥8

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በመጨረሻው ዘመን…!

"…በኢሰመጉ ላይ መንግሥት እየፈጸመ ያለው ከፍተኛ ጥቃትና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል! ሲል ራሱ የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በይፋ ገልጿል።

"…ዜጎች ተበደሉ፣ ተገደሉ፣ ተፈናቀሉ ብሎ ከመጮህ የዘለለ በመንግሥት ላይ ይሄን ያህል ጉዳት የማይፈጥረውና ዘገባ ከማውጣት የዘለለ፣ መንግሥት አጥፊዎችን ለፍርድ ያቅርብ እያለ ከመወትወት ያለፈ ሥልጣን የሌለው ኢሰመጉ በመጨረሻ ራሱ ለራሱ አስጊ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መግለጫ አውጥቶ ሁሉም ይወቅልኝ ብሏል።

• መከራውማ ሁሉም ቤት መግባቱ ግድ ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ምን ማለት ነው?

"…ቆይ ይይ አየር መንገዱ አሰልጥንልኝ ብሎ ለአየር ኃይሉ የላከው ሆስተሶቹን ኮማንዶ አድርግልኝ ብሎ ነው ወይስ እንዴት ነው ነገሩ ተዘበራረቀብኝሳ።

• እነዚህ በሮፐጲላ ተጭነው ወደ ዐማራ ክልል በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጓጓዙት የወንድ ሆስተሶች ይሆኑ እንዴ? 😂 ግራ ቢገባኝ ትፈርዱብኛላችሁ እንዴ?

• አየር ወለዲት ሆስተስ ማነሽ ደናነሽ እንዴት ነሽ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…13 ሺ ሰው አንብቦት 6 ሰዎች 😡 የተናደዱበት ርዕሰ አንቀጻችን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ለአንባቢዎች አስተያየት ሰንዱቁ ክፍት ይሆናል። እናትህ እንዲህ ትሁን ከሚል ፀያፍ ስድብ በቀር እና ከተጻፈው አጀንዳ ውጪ ካልሆነ በቀር አስተያየት መስጠት ከአሁን ሰዓት ጀምሮ የተፈቀደ ነው።

• 1…2…3…✍✍✍ ጀምሩ… እኔም ቁጭ ብዬ አስተያየቶችን ልኮምኩም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ሌላው የታዘብኩት ነገር በፔጄ ላይ አስተያየት የሚሰጠው ሕዝብ ቁጥር መጨመርና የአስተያየታቸው ማስደመም፣ የሓሳባቸው ጥራት እና ውበት ነው። በቃል ማውራት እንጂ በጽሑፍ ማውራት እምብዛም ባልተለመደበት ማኅበረሰብ ውስጥ የተፈጠርን እኛ የዛሬዎቹ ሓሳባችንን በጨዋ ደንብ በጽሑፍ ማስፈራችን በራሱ መታደል ነው። ይሄ ራሱ አንድ እድገት ነው። በእድር ላይ፣ በማኅበር ላይ፣ በጽዋ ላይ፣ በሠርግ ላይ፣ በኀዘን በልቅሶ ላይ፣ በድርጅት፣ በመሥሪያ ቤት ስብሰባ ላይ በእርቅ በሽምግልና ላይ ጽሑፍ ለፊርማ፣ ለውል ማሰሪያነት እንጂ ለመግባቢያነት መጠቀምን ከነገሥታቱ ዘመን ከነገሥታቱ ደብዳቤ ወዲህ የቀረውን አሁን በእኔ ዘመን በቴሌግራም ገጼ ላይ በጽሑፍ ሓሳብን በጨዋነት የመግለጽ ልምድን እያዳበርን መገኘታችን የሚበረታታ ነው። በእውነት በዚህ ልትኮሩ ይገባል። ቀላል ነገርም አይምሰላችሁ። በእውነት እጅግ ልዩ ነገር ነው።

"…የእኔ ፔጅ እንደ ድሮው ዐማራ ተገደለ፣ ተጨፈጨፈ፣ ተረሸነ ተብሎ አይለቀስበትም። የእኔ ፔጅ ዐማራ ምንም ዓይነት ምላሽ በማይሰጥበት ዘመን ብቻዬን ዐማራን ለማነሣሣት፣ ዐማራን ለማንቃት፣ ዐማራን ለማደራጀት፣ ከተኛበት ለመቀስቀስ ይፈጸምበት የነበረውን ግፍ እየዘረዘርኩ እጽፍ የነበርኩት ዘመን አሁን አልፏል። አሁን በፔጄ ላይ የምጽፈው ከፍ ስላለ ነገር ብቻ ነው። ዐማራ እንዴት ሀገር አልባ ከመሆን ተርፎ ባለሀገር እየሆነ እንዳለ ነው የምጽፈው። አሁን እኮ ርዕሰ አንቀፅ ነው የሚተነተነው። የዐማራ ጉዳይ ከላይ ጨረቃ ላይ ተሰቅሏል። የዐማራ ጉዳይ የኳስ የእሳት አሎሎ ሆኗል። ዐማራ ዐማራነቱን አስመስክሯል። አሁን የሚታየው የዐማራ ትግል እንደውም ክረምቱ እስኪያልፍ በቶሎ የሚበላው ጎመኔ ነው። ዋናው ዘር፣ ዋናው እህል ከፊታችን ነው። በጎመኔው እያዘገምን በእህሉ ዘመን በሸነና እንላለን።

"…አሁን እኔ የምነካው አይነኬ የሆኑትን እና በዐማራ ስም የተሰበሰቡትን፣ የዐማራን ትግል በአንድም በሌላም አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ ብዬ የምሰጋባቸውን ነው የምነካው። እንደ ታቦት የሚፈሩትን፣ አይነኬ፣ አይተቼ፣ አይዳሰሴ የሆኑትን ነው የምነካው። ስነካ ደግሞ በሥነ ሥርዓት በጨዋ ደንብ ነው የምነካው። የምተቸው። ለምን ነካህብኝ፣ ለምን ተቸህብኝ ማለት አይሠራም። ነውር ነው። ወንጀልም ነው። ኃጢአትም ነው። በዐማራ ስም ተሰብስቦ የዐማራን ትግል የበግ ለምድ ለብሶ ሊያመክን የሚፈልግ ካለ ቁርጡን ይወቅ እፋለመዋለሁ። እዋጋዋለሁ። አልፋታውም። የእኔ ውጊያ እኮ ደግሞ ወይ በጣቴ በምጽፈው በጦማሬ ነው፣ አልያም በምላሴ ነው የምለፈልፈው። ከብዕሬና ከምላሴ ማለፍ ያቃተው የዐማራ ትግል ጠላፊ ዕድሉ ነው። ለምን በአናቱ አይተከልም።

"…አርበኛ መሳፍንት፣ እርበኛ ደረጀ፣ አርበኛ ባየ፣ አርበኛ ዘመነ፣ አርበኛ ዝናቡ፣ አርበኛ ምሬ፣ አርበኛ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ አርበኛ አሰግድ፣ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ፣ አርበኛ መከታው፣ አርበኛ አበበ ጢሞ፣ አርበኛ እስክንድር ነጋ ሁላቸውም ለእኔ ወዳጆቼ ናቸው። ሲደውሉልኝና እና ሲያዙኝ የምታዘዛቸው አክባሪያቸው የሆንኩ ልጃቸው ነኝ። እንዲያም ሆኖ ግን ከእነዚህ መሃል አንዳቸውም ከዐማራ ሕዝብ ፍላጎት ውጪ ቢንቀሳቀሱ አልፋታቸውም። እንደ ታቦት የሚፈሩ፣ እንደ መቅደስ፣ እንደ መስጊድ የሚከበሩ ቢሆኑም የባንዳነት፣ የሌብነት፣ የዘራፊነት፣ የቀማኛነት፣ የትግሉን ሻጭነት መንፈስ ካየሁባቸው፣ በተግባርም ሲንቀሳቀሱ ካገኘኋቸው አልምራቸውም። ያው በተለመደው ጦማሬና በተለመደው ምላሴ እሸነቁጣቸዋለሁ። አለቀ።

"…አንተ ዐማራ አይደለህ ምን አገባህ? የሚል ገተት አይጠፋም። ዐማራ አልሁና፣ ዐማራ ጓደኛ፣ ዐማራ ቤተሰብ፣ ዐማራ የሃይማኖት አባት ካለኝስ መብቴ አይደለም እንዴ? ለምን ቆቱ አይደለም ኳለሏሏምፑራዊ፣ ከኡዡንቡራ አልሆንም። ዋናው ነገር እኔ የማነሣው ነገር እውነት ነው ወይስ ሐሰት የሚለው ነው። እኔ የማነሣው ነገር ለዐማራ ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም የሚለው ነው። ከጠቀመና ገዢ ካገኘሁ እሰየሁ። ካልጠቀመና ገዢ ካጣሁ የምከስረው እኔው ነኝ አንተን ምን አስጨነቀህ? እኔ የዐማራን ትግል ልምራው ብዬ አላውቅም። መምራትም አልችልም፣ አቅምም የለኝ። የዐማራን ትግል የማገዝ ግን ሙሉ መብት አለኝ። አንተ ስለፈልግክ ስላልፈለግህ ሳይሆን እንዲሁ መብት አለኝ። እኔ ዘመዴ በዐማራ ትግል የገንዘብ ፍሰት ውስጥ የለሁበትም። በዐማራ በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲና አደረጃጀት ውስጥ የለሁበትም። እኔን በግሌ የሚያዘኝ ግለሰብ፣ ማኅበርም ሆነ ድርጅት የለም። አለሁ የሚል ካለ በአናቱ ይተከል። በአናቱ አልኳችሁ። ካለ ዱቄታም በሉት። እኔ ራሴን የቻልኩ ድርጅት ነኝ። እኔ ራሴ ብቻዬን አሁን ተቋም ሆኛለሁ። በእኔ የሕይወት ጉዞ ውስጥ ጣልቃ የሚገባ ድርጅትም፣ ማኅበርም፣ ተቋምም ሆነ ግለሰብ የለም። ሰምታችኋል። 

"…ስለዚህ አሁን የእኔ ሥራ የበሰበሰው፣ ሊወድቅ አንድ ሳምንት የቀረው የአቢይ አህመድ የብልቅጥና አገዛዝ ሳይሆን የሚያስጨንቀኝ እኔን የሚያስጨንቀኝ ሌላ ነው። እርሱም የዐማራ ትግል እዚህ ደረጃ ሲደርስ መጥለፍ የለመዱ ሾተላይ ጠላፊዎች ትግሉን ለመጥለፍ የሚያንዣብቡትን ጆፌ አሞሮች መበተን፣ ላባቸውን መነቃቀል፣ ክንፋቸውንም መስበር ነው የእኔ ሥራ። ፌክ ኢትዮጵያኒስቱን፣ ግንቦቴና ግንባሩ ተብዬ አጭበርባሪ የፖለቲካ ጋለሞታዎችን እየዠለጥኩ አደብ ማስገዛት ነው። በእባብ ላይ ተዋሕዶ ገነት የዐማራ ትግል ላይ እንደ ሰይጣን ዘው ብሎ መግባት አይቻልም። ይሄ ካካ ነው። እፉ ነው። ስትፈልግ ተንጫጫ፣ እበድ፣ ስትፈልግ እሪሪሪ በል። አልፋታህም። ደግሞስ ምንአባህ ታመጣለህ።

• በዐማራ ፋኖ ስም የሚዘርፉ፣ የሚያግቱ፣ የሚገድሉ
• በዐማራ ፋኖ ስር የማይታቀፉ፣ የማይመሩ፣ የማይታዘዙ
• በዐማራ ፋኖ ላይ ሌላ አደረጃጀት የሚፈጥሩ
• በዐማራ ፋኖ ስም ገንዘብ የሚዘርፉ፣ የሚሰበስቡ
• በዐማራ ፋኖ ስም መግለጫ የሚያወጡ፣ የሚደሰኩሩ
• በዐማራ ፋኖ ስም የሚሸቅጡ፣ ሸቀጣሞች፣ የዐማራ ፋኖን የማይወክሉ፣ ከዐማራ ፋኖ በላይ ፋኖ ነን የሚሉ፣ የሚከፋፍሉትን አይማረኝ ብምራቸው። አለቀ።

"…እጠይቃለሁ። ዛሬ ያልተተቸ፣ ዛሬ ተተችቶ በእሳቱ ውስጥ ቀልጦ ያላለፈ የዐማራ ታጋይ ነገ ወርቅ ሊሆን አይችልም። ዛሬ ለምን እተቻለሁ፣ ለምን እወቀሳለሁ ብሎ መንጋ ተሳዳቢ ሠራዊት የሚያሰማራ የዐማራ ፋኖ አመራር እድል ቀንቶት ነገ በትረ መንግሥቱን በጨብጥ ከመንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ከመለስ ዜናዊ፣ ከአቢይ አህመድ የበለጠ ቡቸር ነው የሚሆነው። ጨፍጫፊ አረመኔ ነው የሚሆነው። ከአሁኑ ነው መሪዎቹን ልክ ማስገባት። መስመር ማስያዝ። ነገ ይከብዱናል። ከመስመር የወጣ፣ ቲፎዞ አለኝ፣ ደጋፊ አለኝ፣ ተሳዳቢዬ ነፍ ነው አይሠራም።

"…እስክንድርን በተመለከተ መጠየቄን እቀጥላለሁ። ገና ያልተነኩ ጥያቄዎች አሉኝ። እስክንድር ጋዜጠኛ ነው። ጋዜጠኛ ሆኖ ሲጠይቅ፣ ሲሞግት ነው የኖረው። ይሄ ትክክል አይደለም። ያኛው ተሳስቷል ሲል ነው የኖረው። አሁን እስክንድር ታጋይ ነው። እስክንድር ወታደር ነው። እስክንድር ጠላትን ተኩሶ ሊገድል፣ እሱም በጠላት ሊገደል ፈርሞ በነፍሱ ተወራርዶ ጫካ የገባ ነው። እስክንድር የሞቀ ቤቱን ጥሎ ነው የወጣውና አይጠየቅም፣ አይተችም ብሎ ነገር የለም። ሌሎቹ በረዶ፣ የቀዘቀዘ ቤታቸውን ጥለው ነው እንዴ በረሃ የገቡት። ቀልደኛ። እናንተ ብቻማ አራዳ አትሁኑ።👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…1ሺ የክርስቶስን ትንሣኤ የሚያውጅ ሕዝብ እስኪመጣ ነበር የቆየሁት። አሁን ግን የሚጠበቀው አመስጋኝ ሕዝብ ሞልቷል። በነገራችን ላይ ርዕሰ አንቀጹ የሚፈጥነውና የሚዘገየውም በዚህ ምክንያት ነው። ከምስጋናው ቀጥሎ የምናመራው ወደ ተወዳጁ የቤታችን ርዕሰ አንቀጽ ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን የሚያተኩረው በወያኔና በአብይ ስምምነት ምክንያት በአፍሪካ ቀንድ እየመጣ ያለውን ከባድ ጦርነት የሚያውቁት አሜሪካኖቹ ይፈጠራል ብለው ለሚገምቱት ከባድ ዕልቂትና ስደት ድንገት ከመሬት ብድግ ብለው ጎረቤት ሀገር ኬንያን የቀጣናው አረጋጊ ሃገር አድርገው ስለሾሙበት እና "ዶሮን ሲያታልሏት የሚፈላው ውኃ ለገላሽ ማጠቢያ ነው አሏት" ዓይነቱ ስለ ሩቶ እና ስለ የአሜሪካ አቀባበሉም አይደለም። እሱን ራሱን በቻለ አንቀፅ እመጣበታለሁ።

"…ደግሞም ዐማሮቹ ገርስሰው ሳይጥሉኝ ራያንና ወልቃይትን ልስጥሽና አንቺ ደግሞ ዐማራን በመውጋቱ እርጂኝ፣ በዚያውም ዐማራን በጋራ ወግተን ከጣልን በኋላ ጠላትሽ ኤርትራን አብረን እንወጋዋለን ተባብለው በራያ አካባቢ ስለሚያሳዩት ትርኢትም አይደለም የምጽፈው።

"…የአሜሪካ ኤምባሲ ማንን ለማብሸቅ እንደሆነ በሚታይ መልኩ የጃንሆይን ፎቶ ለጥፎ ጃንሆይን በክብር ተቀብሎ ሲያበቃ ጃንሆይ ከአሜሪካ እንደተመለሱ በኦሮሙማው ደርግ አገዛዝ በኩል የዘውድ ሥርዓቱን ገርስሶ ጥሎ፣ ንጉሠ ነገሥቱንም አፍኖ ገድሎ ሲያበቃ አስከሬናቸው ላይ ቢሮ ሠርቶ እንዲቀመጥ ስላደረጉት አማሪካኖች አይደለም የምጽፈው። በኤርትራ፣ በወያኔና በኦሮሙማው መካከል ስለተደገሰው ጦርነትም አይደለም።

"…እኔ ዛሬ መጻፍ የፈለግሁትን ጽፌአለሁ። እናንተስ የጻፍኩትን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ወይ? ዝግጁ ነነ ብልቻችሁ ደብለቅለቅ አድርጉት እስቲ…!

• አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አሁንም እጠይቃለሁ?

"…እስክንድር ጦር ሠራዊት አለው ወይ? ካለው አለው ብሎ መመለስ የአባት ነው። ከሌለው ደግሞ የለውም ብሎ መመለስ እንጂ የምን ነገር መጠምዘዝ ነው?

"…እስክንድር ባለ አደራ ብሎ ሲያቋቁም አይተናል። ባለ አደራን አፍርሶ ባልደራስን ሲመሠርትም ቢሮ ነበረው፣ ከምርጫ ቦርድም ፈቃድ፣ ለዚህ እኔም ምስክር ነኝ። እስክንድር ሰላማዊ ትግል አዋጭ አይደለም ብሎ የዐማራ ፋኖን ትግል ሲቀላቀል መጀመሪያ መግለጫውን ልኮልኝ ያነበብኩለት እኔው ነኝ። መጀመሪያ ሸዋ ከዚያ ጎጃም ሄዶ መከራ ፍዳውን ሲበላም የማገኘውም እኔው ነበርኩ። እስክንድር መነሻዬ ዐማራ መድረሻዬ ኢትዮጵያ ብሎ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ሲመሠረትም ሁላችንም እኩል ነው የሰማነው። ቆይቶ ግንባሩን አፍርሶ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ ሲመጣም አሁንም አብረን ነው የሰማነው።

"…እና አሁን የጎንደር፣ የወሎ፣ የጎጃም ዐማራም ወደ አንድ መጥቷል። የሚቀረው የሸዋው ነው። የሸዋውም እርቅ አውርደው የሚቀረው በጣም ትንሽ የአፈጻጸም ነገር ነው። እሱንም መሬት ላይ ያሉ ሽማግሌዎች እየሠሩበት እየደከሙበትም ነው። ከፍጻሜም ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የእኔ ጥያቄ የሚመጣው እዚህ ጋር ነው።

• እስክንድር ከዐራቱ የዐማራ ግዛቶች በየትኛው የፋኖ አደረጃጀት ስር ነው የታቀፈው? ቀላል ጥያቄ እኮ ነው?

• መፍረሱ፣ መክሸፉ በይፋ የተነገረለትን የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል ስም እዮተጠቀመ በሸዋና በጎጃም በወሎና በጎንደር መካከል ለምን ሽብልቅ ይከታል? ሠራዊት አለው? ካለ የት ነው? መልስ

• ይሄ ቀላል ጥያቄ ሲጠየቅ ግንቦቴዎች ዘው ብላችሁ መጥታችሁ አኪላ የሚባል አንድ አክቲቪስት እየጠቀሳችሁ መዘብዘብ ምንድነው? በቲክቶክና በዩቲዩብ አየር ላይ ያለው አኪላ ነው ወይስ ምድርና ቴቪ ላይ ያለው እስክንድር ነው ትግሉን የሚጎዳው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አልገባኝምና ብትመልሱልኝ 🙏🙏🙏

"…የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ዐፄ ዳዊት ክፍለጦር እና የዐማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ እስክንድር ነጋ ክፍለጦር የጋራ የአቋም መግለጫ የሚል ቪድዮ ከወዳጄ ኑረዲን ዘንድ ደርሶኛል።

"…የእኔ ጥያቄ እስክንድር ነጋ ያለው ሸዋ ነው። የሚጠበቀውም በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በእነ ሻለቃ መከታው ነው በእነ አቤ ጢሞ ነው። ይሄን ያዙልኝ። ዐጼ ዳዊት ክፍለ ጦርም በእነ ሻለቃ መከታው ስር ያለ ክፍለ ጦር ነው። የእስክንድር ነጋ ክፍለ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ጦር ደግሞ በወሎ ዕዝ ስር ያለ ክፍለ ጦር ነው ተብሏል። ይሄንንም ያዙልኝ።

"…እሺ ምንም ዓይነት ጦር የሌለው እስክንድር ነጋ በሻለቃ መከታው ጦር በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ስር የግል ጠባቂ ተመድቦለት ደኅንነቱ እየተጠበቀ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ እስክንድር ሰሞኑን ለአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ሰጠ በተባለው መግለጫ እና እሱን መግለጫ ተከትሎ የእስክንድር የግል ደጋፊዎች እስክንድር እንግሊዝኛ ይችላል ብለው ባንቆለጳጳሱት መግለጫው መጨረሻ  መደምደሚያ መዝጊያ ላይ "የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ" በማለት መቋጨቱ አደናጋሪ ነው የሆነብኝ። ሠራዊቱ ሠራዊት አለው ወይ? አበበ በለው እና ሀብታሙ አያሌው ሠራዊቱ የሚሉት ከጎጃሙ ከማስረሻ ሰጤ ቀጥሎ ይሄንን የሸዋ ጠቅላይ ዕዝና የወሎ የእስክንክንድር ነጋን ጦር ነው ወይ?

"…የእኔ ጥያቄ እስክንድር ነጋ በዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ስር ሆኖ፣ በጠቅላይ እዙ ጋርዶች እየተጠበቀ፣ ድሮኗ ጠባቂዎቹን፣ ከኋላ የሚከተሉትን ባጃጆች ብቻ እየተከተለች እየገደለች እንዴት አንድ ሰው ብቻውን ፓርቲ ሆኖ በእንግድነት ተጠግቶ ባለበት ሥፍራ እንደ ባለቤት ባለቤት ሆኖ መግለጫ ይሰጣል? በሌለ ነገር?

"…እስክንድር ሸዋ ተቀምጦ በጎጃም ካፒቴን ማስረሻን ቆስቁሶ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት ብሎ በተመሰረተ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ላይ ተደራቢ አድርጎ ማምጣቱስ ልክ ነው ወይ? በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደር እና በወሎ መካከል የሆነ ሽብልቅ ለመክተት የታሰበ ነገር አይመስልም ወይ…?

"…ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሰሞኑን በእነ ሻለቃ መከታው እና በእነ ኮማንደር አሰግድ ጦር መካከል ግጭት መፈጠሩ ይታወቃል። እኔ ፈጽሜ ካቆሙኩበት የቀጠሉ ሽማግሌዎች እየደከሙበት እንደሆነም ዐውቃለሁ። የሆነው ሆኖ የእስክንድር ቡድኖች ሀብታሙ አያሌውም ሆነ ሀብታሙ በሻህ ለእነ ሻምበል መከታው ቡድን አግዘው እነ ኮመንደር አሰግድንና እነ ኢንጅነር ደሳለኝን በፕሮፓጋንዳው መቀጥቀጣቸው ምንን ያመለክታል? እነ ኮማንደር አሰግድ መኮንን የእስክንድር ነጋ በሸዋ መኖር እንደ ሸዋ ገና ያፋጀናል የሚሉትስ እውነት ይሆን እንዴ?

"…የመጨረሻ ልጨምር። እስክንድር ነጋ ክፍለጦር የተባለው እና በወሎ ዕዝ ስር ያለው ኃይልስ ከወሎ ዕዝ ከእነ ኮሎኔል ፋንታሁን እና ከእነ የዋርካው የምሬ ወዳጆ እውቅና ውጪ በእነ ሻለቃ መከታው ዕዝ ስር ነኝ ካለው የዐፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ጋር በግል በዘፈቀደ መፈራረም ይችላሉ ወይ? በእነ መከታውና በወሎ የዐማራ ፋኖ መካከል ግጭትና ቁርሾስ አይፈጥርም ወይ…?

"…ለእነዚህ መልስ ካገኘሁ እኔ ብዙ ጥያቄዎች ይኖሩኛል። ይሄ የዛሬው ጥያቄዬ አባቶች አብርደው ካሉኝ ጉዳይ ጋር በፍጹም አይያያዝም። እሱም ቢሆን በዝምታዬ የሚጠፋው ጥፋት ከበረታብኝ ዝምታዬን ሰብሬ ለመውጣት መገደዴን ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

"…ጋሽ አሰግድ እና ሻለቃ መከታውም እባካችሁ ተረጋጉ። ተደማመጡ። በመሃላችሁ ነፋስ አታስገቡ። እንደ አባቶቻችሁ ጠቢባን ሁኑ። ስክንም በሉ። በነፍሱ ተጠያቂ ናችሁ እና በእናንተ ስህተትና አለመደማመጥ ምክንያት አንድም ቢሆን የሚሞት የሸዋ ፋኖ አይኑር። ሽማግሌዎችን አድምጡ። ለሽማግሌዎቻችሁም ቃል ተገዙ። ደግሜ እላለሁ ተደማመጡ። ይቅር የማይባል ታሪካዊ ስህተት ከመፈጸምም ተቆጠቡ።

• ጥያቄዬ የገባችሁ አስረዱኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…ከ No More እስከ No Go…

"…የሸንኮራ ጥቅሙ ወይ በጥርስህ ትልጠዋለህ፣ አልያም ከድጋይ ከዛፍ ታጋጨውና ትሰብረዋለህ፣ አልያም በካራ ትሸነሽነዋለህ። ከዚያ በጉንጭህ ልክ አፍህ ውስጥ ከተህ በጥርስህ እያኘክ፣ እያላመጥክም ጣፋጩን ጨምቀህ መጥጠህ ትውጥና ቀሪዉን ተፍተህ ትጥለዋለህ። የአገዳ ጭማቂ ወይ ለከብት መኖ ይሆናል አልያም ደግሞ ለእሳት ራት ማገዶ ይሆናል። አለቀ። የኮንደምም አገልግሎቱም ተመሳሳይ ነው።

"…አንድ የሃይማኖት አባት ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምርጫ የተሾመ አገልጋይ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን ማገልግል ትቶ ከፓርቲው አባላት በበለጠ እወደድ ባይነት ከሃዲ፣ አረመኔ፣ ለነፍሰ ገዳይ ዲዮቅልጢያኖስ የመሰለ አገዛዝ ለማገልገል ከባከነ መጨረሻው No Go ነው።

"…ማገልግለስ “ ለዘላለም የማይጥለውን ጌታ፤” ሰቆ. 3፥31 …ማገልገልስ ሕዝቡን የማይጥለውን፣ ርስቱንም የማይተወውን እግዚአብሔርን" መዝ 94፥14 የተባልነውም “አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፤ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።” ዘዳ 10፥20 ነው። አለቀ።

"…በእያንዳንዱ ቤት፣ ሰፈር፣ ድርጅት፣ መስሪያቤት፣ መንደር፣ ጎጥ መከራው ይገባል። የፈለገ ብታሽቃብጥ፣ የፈለገ ብትገረድ፣ አይቀርልህም። አንተ ባልጠበቅከው፣ ባልገመትከው፣ ይሆናልም ብለህ ባላሰብከው መንገድ በመከራ በትር ትዠለጣለህ፣ የመከራ ቀንበርም ላይህ ላይ ይወድቃል። የፈለገ አልኩህ እልል እያልክ ብታሽቃብጥ ወገብ ዛላህን ቆምጦ ሳይለንት ሙድ ላይ ቆልፎህ እያለህ ድራሽ አባትህን ያጠፋሃል።

"…ይልቁኑ በቶሎ ንስሐ ግቡ…“አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።” ዘዳ 13፥4። ወደ ልባችሁ ተመለሱ። ንስሐም ግቡ።

• No Go…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከዐማራ ፋኖ ጋር ለመዋጋት ወደ ዐማራ ግዛት ለሚገቡ ለብርሃኑ ጁላ እና ለአቢይ አሕመድ ወንበር አስጠባቂ ወታደሮች ነገርየው እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ ገና ወደ ዐማራ ክልል ነው የምትሄዱት ተብሎ ሲነገራቸው ቀድሞ እንዳይሞክሩት በሼክም በቄስም በወዳጅ በዘመድ በቤተሰብ በጓደኛም ቀድሞ ማስረዳቱ መልካም ነው። አቢይ እና ድርጅቱ በቅርቡ መትነኑ ላይቀር ምስኪን የደሀ ልጆች ያውም በአንድ ወር ለብ ለብ ሥልጠና ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ጥይት ሲሰማ፣ ባሩድ ሲያሸት፣ ከግሪሳ ወፍ መሃል ለይቶ በጥሶ በጥይት ከሚመታ የዐማራ ፋኖ ጋር ማጋጠሙ ልክ አይደለም። ደግሞም መማረክ፣ እጅ መስጠት የሚባል ነገርም እኮ አለ።

"…የአረጋ ከበደን 97% ክልሉን ነፃ አድርገነዋል ዲስኩር፣ የዳንኤል ክብረትን ወተት፣ ጨው፣ ጃርት፣ አሞሌ ጨው ተረት፣ የጄነራሉን ደመሰስናቸው፣ የብራኑ ጁላን እየመነጠርን፣ እየለቀምናቸው ነው አጉል ዝብዘባ መስማት ትተው እኛን ቢሰሙ መልካም ነው። ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ያወገዙት፣ የገዘቱት፣ የረገሙት ሠራዊት ከማለቅ በቀር ሌላ ዕጣ ፈንታ አይኖረውም። ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ የመረቁት፣ የባረኩት ሠራዊት ደግሞ ከማሸነፍ በቀር ሌላ ምንም አማራጭ የለውም።

"…ዐማራ ከወደቅኩም ጥዬ ነው የምወድቀው ስላለ መከባበሩ ይበጃል። ዐማራ ስላመረረ በቀላሉ ይፈታል ብሎ ማሰብም አይቻልም። የአንድ ሀገር ልጆች በአንድ ጦሰኛ፣ ዘረኛ፣ መሃይም ምክንያት እንዲህ ሲገዳደሉ ማየት አሳዛኝ ቢሆንም ሕዝብን ማሸነፍ ግን አይቻልም። ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ለሚልዮኖች ሞት ምክንያት የሆነውን አረመኔውን አቢይ አሕመድን ከነ ግብረአበሮቹ በአደባባይ ለስቅላት ፍርድ ማዘጋጀት ብቻ ነው።

“…እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉በዩቱብ /YouTube
https://www.youtube.com/live/31eQROXj1qg?si=0iR4ij2WCG-F2Tto

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v4wypmk-no-go-ethiobeteseb.html

👉በፌስቡክ/Facebook
https://www.facebook.com/share/rMAfC1osyZU7n7pF/?mibextid=oFDknk

👉በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም/ Telegram
♦/channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።” ፊል 3፥10-11

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ምን አገባኝ…!

"…የአንድ ድሮን ዋጋው እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር ነው እየተባለ፣ ለ UV ድሮን እና ድሮንበስተር 30,000 ዶላር ብቻ ያስወጣል እየተባለ፣ ዩኒቨርስቲ ዘግቶ ቦንብ የሚገዛው ብልፅግና በአንድ ቀን ይሄ ሁሉ ዶላር ወድሞበት በወለጋ ምድር ኪሳራ ደረሰበት የሚል ጮማ ወሬ እያለ ምን አገባኝና ነው አየር መንገዱ አጥር ስር የነበሩ የካርቶን ቤቶች ተቃጠሉ ብዬ የምንጫጫው?

"…ስለ ድሮኑ ውድመት እንዳይወራ አየር መንገዱ ጋር ሄደህ ሰሞኑን የሚፈርስ የካርቶን ቤት ታቃጥልና የፒፕሉን ቀልብ ዳይቨርት ለማስደረግ ትጋጋጣለህ። ዥል…

"…በቃ ዝም ብላችሁ የድሮኑን ዋጋ በብር ምቱት። 😂 …በጎንደር የወደመውን የጁላ ጦር ስለ እሱ አውሩበት። አጥር ስር የተሠራ የፎሊስ ማረፊያ የካርቶን ቤት ተቃጠለ አልተቃጠለ ለደንታው ነው። ምን አገባኝ።

"…ሲሰድበኝ የሚውል የብልጽግና ሠራዊት በሙሉ ዘመዴ እያለ ያልጠየቅኩትን መረጃ እንደ ጎርፍ አጥለቅልቆ ሲልክልኝ እኮ ነው የምባንነው። 😂😂😂

"…የሐረርጌን ውኃ ቀምሰህ… በዚያ ላይ አራዳ ደጃች ውቤ ውቤ በረሃ ስታድግ በቀላሉ በበሻሻ አራዶች አጀንዳ አትሸወድም። ያሳቁኝም አሉ። የትግሬ አክቲቪስቶች ከምር አስቀውኛል። የትግሬ አክቲቪስቶች ያ በጁንታው ጦርነት ጊዜ እንደ ሽንኩርት የከታተፋቸው ድሮን… የድሮኑ መውደቅ ሳይሆን ዐማሮቹ አልጣሉትም ነው ሙግታቸው። 😂። ዐማራ አይደለም ለምን አሞራ አይጥለውም። እህእ ምን ያበሳጫቸዋል? 😂 የመድኃኔዓለም ያለህ። ጥላቻ ግን ክፉ ደዌ ነው በማርያም።

• በቃ ድሮን ወድቋል። ወድቋል። አከተመ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

• ሰበር ርዕሰ አንቀፅ ነው። የዘገየሁትም የፎቶው መረጃ እስኪደርሰኝ ነበር። ቪድዮውም መንገድ ላይ ነው።  

"…በዛሬው ዕለት በቀን 14/2016 ዓም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ አዋሳኝ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉጋና ቀበሌ ልዩ ስፍራው ጫንጮ አቦ እና ሥላሴ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም አሰሳ ላይ የነበረች ቱርክ ሠራሽ ድሮን በወለጋ አናብስቶች በአንገር ክፍለ ጦር በወለጋ ዐማሮቹ ፋኖዎች ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ተመትታ ተከስክሳለች። 💪💪🏿💪

"…ድሮኗ የተከሰከሰችው እዚሁ ደንጎሮ ወረዳ አሩሲ ቀበሌ ላይ ሲሆን ከአሁን ቀደም 27 ንጹሐን ዐማሮች በድሮን በጅምላ የተጨፈጨፉበት አካባቢ መሆኑም ተነግሯል። ያው መቸም ብድር በምድር ነውና ተገድዶ ከዘር ጨፍጫፊው ኦነግ ብልፅግና ራሱን መከላከል የጀመረው የወለጋ ዐማራ በዛሬው ዕለት በውድ የውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ዐማራን ለመጨፍጨፍ ሥራ ላይ ካዋሉት ዓረብ ሠራሽ የወሓቢይ እስላም ሀገር ድሮኖች መካከል አንደኛውን ድሮን ድባቅ በመምታት ጥለው በግዳዩ ላይ ቆመው የፎቶ መረጃ ከሥፍራው ልከውልኛል። "ዘመዴ እናሸንፋለን። ለዐማራ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ በልልንም ብለውኛል።" ገዳይን መግደል እንዲህ ነው።

• የመረጃ ምንጩ፦ የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ደኅንነት ክንፉ ነው። ይኸኛው ፎቶ ነው። ቪድዮው እንደደረሰኝ እለጥፍላችኋለሁ። እስከዚያው…

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…
Subscribe to a channel