zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወያኔን ወይም ጁንታውን ለመደምሰስ፣ አባይ ጸሐዬን፣ ስዩም መስፍንን፣ ዓባይ ነፍሶን ለመገንደስ፣ 1.2 ሚልዮን ትግሬን ለመቀነስ፣ ፋብሪካውን ነቅሎ አውድሞ ለመመለስ ወደ ትግራይ ከዘመቱት 15 ጀነራሎች መካከል 13ቱ ኦሮሞ ሆነው ሲገኙ የሚሰማህ ስሜት እንዲህ ነው የሚያደርግህ። stockholm syndrome አለ ሱሬ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እንደተናገረ ተነሥቶአል ! ማቴ 28፣6

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አባትና ልጅ ተገናኝተዋል…!

• ፎቶውም የዛሬ ነው። በግምት 11:30 ሰዓት አካባቢ።

"…የሸዋዎቹ ፈርጦች አርበኛ፣ ደራሲ፣ ኮማንደር ፋኖ ጋሽ አሰግድ መኮንን እና አርበኛ ፋኖ ሻለቃ መከታው የዛሬ ወር የግንቦት ልደታ በዕለተ ልደቷ ለማርያም በስልክ ባወሩ፣ በመከሩ፣ በተወያዩ ዛሬ ደግሞ ሰኔ 1 መልሶ በዕለተ ልደቷ ለማርያም በእመቤታችን በልደቷ ዕለት በሽማግሌዎች አማካኝነት በአካል ተገናኝተው፣ ተወያይተው፣ አውግተው የሸዋን አንድነት በታላቅ ፍቅር ወደ አንድ ለማማጣት መወሰናቸው ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ሙሉ ዝርዝር መረጃውን በነገው ዕለት በሰፊው እመለስበታለሁ።

"…ወዳጄ ሸዋ ባላመጠ በዓመቱ ይውጣል የሚባለው ብሂል እኮ እውነት መሆኑ ይኸው ታየ። ከመለያየት፣ ከመነጣጠል፣ ከማወሳሰብ፣ ከማጣላት፣ ከማራራቅ፣ በወንድማማቾች መሃል ሽብልቅ ከመክተት ይልቅ እንዲህ በማቀራረብ አንድ ማድረግ ያጸድቃል። የደም ነጋዴዎች እርማችሁን አውጡ።

"…አሁን ጎጃም ወደ ፩ ፋኖ፣ ወሎም ወደ ፩ ፋኖ፣ ሸዋም ፩ ወደ የፋኖ አደረጃጀት መጥቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። የጎንደሩም እርቁ የኪዳነምህረት ዕለት ተፈጽሞ የወረቀት ሥራው ነው ያደከመን እንጂ የሆነ ቀን አንድነቱ ከፍጻሜ ደርሶ አንድ ሆነው እንዲህ ሰበር የምሥራች መስማታችን አይቀርም።

• እልልልል በል ዐማራ…!💪💪🏿✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…ርዕሰ አንቀፁን እንዳነበባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ፋኖን በቄስ፣ በሼህ በሽማግሌ ለምናችሁ አምጡልን፣ ያመጣችሁትን ሰው ደግሞ እንኳን ልንገድለው በጥፊ አንመታውም። እነሱ እናንተን ይጠብቃሉ እኛ ደግሞ ወልቃይትን እና ራያን እንጠብቃለን አላለም። 😂 በፊት ራያንም ነበር የሚሉት። እሱን ካስበሉ በኋላ አሁን ደግሞ የሚደናገር ብናገኝ ብለው ነው የሚዘበዝቡት።

"…በወልቃይት ጉዳይ ጦርነቱ አይቀሬ ከሆነ የወንድ ዘር በ10 ሺ ብር አይደለም በ100 ሺብርም የሚገኝ አይመስለኝም። የሆነው ሆኖ ርዕሰ አንቀፄ ላይ ጓ ማለት መብት ነው። የበዛ ካለ ቀንሳችሁ፣ የአነሰም ካለ ጨመር አድርጋችሁ አስተያየታችሁን መስጠት ትችላላችሁ።

• 1…2…3…ጀምሩ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…ዶር ጫልቱና ስለ ፌካሙ የቁጩ ቢልየነር ዶላር አጣቢው መንሱር ጀማል ለአንድ ሳምንት ተጋብተው ተፋቱ። ዐማራ ስለጫልቱና ስለ መንሱር ምንአገባው? ግርርርር። የሚያገባው ስንትና ስንት አጀንዳ በቤቱ ሞልቶ ፈስሶ እያለለት የጫልቱና የመንሱር የ1 ሳምንት የፌክ የጋብቻ አጀንዳ አስጨንቆት ይራኮታል። አሁን ዐማራ እንደ ሰጎኗ ዓይኑን ከእንቁላሉ ላይ ሳያነሣ አፍጥጦ ትኩረት ሰጥቶ በራሱ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚያደርግበት ጊዜና ወቅት እንጂ ጫልቱ፣ ገመዳ፣ መንሱር፣ ከምሱር እያለ በጨበርበርቱ አጀንዳዎች የሚሸወድበት ወቅት አይደለም መሆን ያለበት።

"…ዐማራ ስማኝ ካለፈ ስህተትህም ተማር። አጀንዳ ስጥ እንጂ አጀንዳ አትቀበል። ህወሓት ልትወርህ፣ አቢይ ሊያስወርርህ ሲፈልግ አዳዲስ አጀንዳ ነው አምጥቶ የሚዘረግፍብህ። ያለ ፍትህ፣ ያለፍርድ በግፍ የታሰሩት እና በወህኒ ቤት የሚማቅቁትን ጋሽ ታዲዮስ ታንቱን ሳይፈቱ ተፈቱ ብሎ ማወጅ። ይሄ አጀንዳ ነው። ትግሬው ሊላይ ኃይለ ማርያም ተቀጥቅጦ ታሰረ። ለምን ዘልዝለው አይበሉትም። ምን አገባህ። ሰማያዊ ፓርቲን ጨፍልቆ መስዋእት ያቀረበው የኢዜማው አቶ የሽዋስ አሰፋ ታሰረ። ለምን አይቀፈድም። የኦሮሙማው አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ ብሎ ሠራዊቱን ወደ ዐማራ ክልል ባስገባ ጊዜ ከትግሬው ወረራ ጋር አቻ ለማድረግ እና ዐማራ ቢሆንም ሚዛናዊ ሰው ነው ተብሎ ለመታየት ሲል "…ይህ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ነው፤ መንግሥት ሕግን ማስከበር ይኖርበታል" ያለን ባንዳ ዐማራ ነኝ ባይ ሰውዬን እሰይ ባትል እንኳ አዎ "መንግሥት ሕግ እያስከበረብህ ነው" ብለህ እንደማለፍ እንደ ጃዋር ነሐመድ ወጥተህ አቶ የሺዋስ አሰፋ ይፈቱ ምናምን የምትል ዐማራ ጤንነትህ ያጠራጥራል። ድሮ የህወሓት ትግሬ አሁን ደግሞ የብአዴን ዐማራ ነኝ ባዩ የአቶ ሽባባው ልጅ ባል የጌታቸው ረዳ ዘመድ ዛድግ አብርሃ ከቦንብ ጥቃት አመለጠ። ጌታቸው ረዳ ራሱ በመቀሌ ከቦንብ ከግድያ አመለጠ፣ ይሄ ሁሉ የግድያ እና የተፈቱ፣ ታሰሩ የቦንብ ጥቃት ወሬ ለምን ዓላማ እንዲሰራጭ እንደተደረገ ታዘብ። ወያኔ ዐማራን ሊወር መሆኑ በግልፅ እየነገረህ ነው።

"…ነገሩን ስንመረምረው አብይ አመድ በመከላከያውም፣ ታፍሶ በሚላከው ቄሮም ተስፋ እንዳጣና ወያኔ ሆይ አድኚኝ ብሎ እየለመነ ያለ ይመስላል። በዚህ ሁሉ የአቅጣጫ ማስቀየርያ የወሬ ፋብሪካዎች ላይ አብይ ምን ዓይነት ሙታንታ እንዳጠለቀ አበጥራ ምታውቀው ኃያሏ ሀገር አማሪካም የዐማራውን ችግር አስረዱኝ ምን ይሆን ስትል የዐማራ ትግል አንቂ የተባሉ ግለሰቦችን ስብሰባ ጠርታ እያጃጃለች ትገኛለች። በጣም የደነቀኝ እስከ ዛሬ 5 ወር ኦሮሙማን ሲደግፍ እና ድንገት 360 ዲግሪ ታጥፎ ዐማራ የሆነው ስልክልክ፣ ቅልስልስ ሴታ ሴት ተለማማጬ ፋሲል የኔዓለም እንኳ ጌታቸው ረዳ ከግድያ ማምለጡ ብቻ ሳይሆን ጠባቂው ሳይቀር ቆስሎ መትረፉን፣ ወያኔዎች በ2 ቀናት ልዩነት የወረደባቸው መዓት እና ጥይትም ቦምብም የማይነካቸው ዩፎ መሆናቸውን ያስመሰከሩበት ሆኖ አልፏል። ታየኝ እኮ ግንቦቴው ፋሲል የኔዓለም በተለይ ለዐማራ ሲቆረቆር።

"…ትናንት ከመሬት በተሰማው ዜና ሰሞኑን ሙቀት ለመለካትና ገዢ መሬቶችን ለመቆጣጠር እንደ በር መክፈቻ የጎንደር ዐማሮችን የገደለው፣ ህፃናቱን በእሳት ያቃጠለው፣ ህወሓት በመከላከያ ሠራዊቱ ታጅቦ የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ የዋልድባንና የማይጠምሪን ወረዳዎች መውረሩ ተነግሯል። የህወሓት አርሚ 1 ተከዜን ተሻግሮ በማይዳጉሳ በኩል በኢንሲያና በተከዜ መገጣጠሚያ በኩል ወደ ዋልድባና ማይጠምሪ ገብቷል። አርሚ 11ኛ፣ 17ኛ እና 44ኛ ደግሞ በሌላኛው አቅጣጫ ተከዜን ለመሻገርና ወልቃይትን ለመውረር ተጠግተዋል። በአካባቢው ያለው የመከላከያ ኃይል ምንም ዓይነት ምላሽ አይሰጥም። እነ ደመቀ ዘውዱና የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴዎችም ዝም ጭጭ ነው። ይሄ ሁሉ ኮተት እያለ ዐማራ ኢትዮ ፎረም ከበለጠ ካሣ የቴሌግራም ገፅ ላይ እየቃረመ በሚያወጣው ዜና ደንዝዞ፣ ስለ ጫልቱና መንሱር ሲሟገት፣ አቤት ቅሌት እያለ ሲቀደድ ይውላል።

"…ስለ ወልቃይት ለመጻፍ ስትነሣ፣ ለመተቸት ስትነሣ፣ የኮሎኔሉ የግል አድናቂ ጎንደሬ ነን ባዮች ጓ ስለሚሉ የእሱን ጉዳይ ጊዜ ይፍታው ብዬ ከተቀመጥኩ ቆይቻለሁ። ደመቀ ዘውዱ ብልፅግና ነው። ከብልፅግና እሳቤ አይወጣም። ደመቀ ዘውዱ የራያና የመከተል፣ የደራም ጉዳይ አያገባንም ብሎም የዐማራ ታጋይ ነው የሚለው ኃይል ሰውየው ሲወቀስ ጓ ስለሚል መጨረሻውን አይተው ወየው ወየው ወይም እሰይ እሰይ እስኪሉ መጠበቅ ነው። ደመቀ ዘውዱ አሳምነው ፅጌን ሲሰድብ፣ ደመቀ ዘውዱ ለኢትዮ ፎረም ጋዜጠኛ ለአበበ ባዩ ፋኖ መከላከያ ላይ መተኮስ አልነበረበትም ብሎ በአደባባይ ቃለመጠይቅ ሲሰጥ ግድየለም ተሳስቶ ነው አንውቀሰው ባይ ጎንደሬ ነኝ የሚለው እንደ አሸን ስለሚፈላ ዝም ማለት አማራጭ አልነበረውም። ሄዶ ሄዶ ግን የተረገዘው በተፈጥሮ ምጥም፣ በመርፌ ምጥም፣ በቀዶ ጥገናም መወለዱ አይቀር። በቆሎ ዘርቶ ጦጣን ጤፍ ነው የዘራሁት ብሎ መሸወድ እኮ አይቻልም። ይታይ የለ እንዴ ኋላ፣ ታሞ ከመማቀው አስቀድሞ መጠንቀቅ።

"…አሁንም የወልቃይት ነገር እንዴት ነው? ብሎ መጠየቅ አይከፋም። ማንም ስለ ወልቃይት ሲያወራ አይደመጥም። ህወሓትስ እንዴት በአደባባይ ሳይቀር በእርግጠኝነት ሰኔ 30 ወልቃይት ነኝ ሊል ቻለ? ከውስጥ የተማመኑበት አደረጃጀት ይኖራል ወይ? አሁን ባለው ሁኔታ "መከላከያ ሠራዊቱ" ከህወሓት ጋር ሰላም ነው። ስለዚህ እሱ ራሱ ነው መንገድ ከፍቶ የሚያስገባቸው። ደመቀ ዘውዱ ደግሞ ከሳምንታት በፊት ከመከላከያ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ድግስ ላይ ነበር። እንዴት ህወሓትም እነ ደመቀም ሁለቱም መከላከያን በጋራ ተሞዳሞዱት? ተወዳጁት?

"…በሌላ ዜና ደግሞ የወልቃይትን የኮሙኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ ስናይ ደግሞ ብአዴናዊ ዜናው እንደቀጠለ ነው። "የጓሮ አትክልት" "ችግኝ" ወዘተ እያለ ነው። ሰው የታረደበት፣ ከብት የተነዳበትም አይመስልም። የጎንደር ፋኖ የደምለውንና የደመቀን የእስከ ዛሬ እንቅስቃሴ ሲከታተል ነበር ወይ ብሎ መጠየቅ አሁን ላይ መልስ ይኖረው ይሆን? ደመቀ ዘውዱ አንድ ሰው ነው ምንም አያመጣም ከሚል የዋህነት ቢወጣ መልካም ነበር ግን አልሆነም። ደመቀ የወልቃይት አደረጃጀት እጁ ላይ ነው። ለህወሓት እየሠራ ቢሆንስ ብሎ መጠየቅ በዚያ አካባቢ እንደ ኦሪት ሕግ በኮሜንታተሮች የስድብ ናዳ ሊያስቀጠቅጥህ ይችላል። እንደዚያ ከሆነ ህወሓት በቀናት ወልቃይትን ተቆጣጥሮ ከእነ ደመቀ ጋር በመሆን እምቢኝ የሚለውን የወልቃይት ታጣቂ ማፈንና ማጥቃት አይቻላትም ማለትም አይቻልም። ህወሓት እና አቢይ ተስማምተው፣ ደመቀን ጨምሮ ወልቃይትን ያዙ ማለት ከዚያ በኋላ የዐማራ ትግል በዜሮ ተባዛ ማለት አይደለምን?

"…የህወሓት ጦር አንዴ ወልቃይት ከገባ በኋላ ዐማራ እንደ አብይ መከላከያ በሽምቅ ነው የሚያጠቃው? የህወሓት ጦር እንደ አብይ መከላከያ አይደለም። ሕዝባዊ ጦር ነው ተብሎ ስለሚታወቅ በግልጽ ሕዝብ እየጨፈጨፈ አንድን ቦታ ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀስ ኃይል ነው። ይሄ ለአብይ ጦር አሸወይና ነው። ከእነርሱ ጋር በመቀላቀል እንደፈለገ የታጠቀውንም ያልታጠቀውንም የዐማራ ሕዝብ መጨፍጨፍ ይችላል። ምክንያቱም በሕወሓት አሳብቦ ዐማራን ይጨፈጭፋል። ህወሓትን ደግሞ እነ አሜሪካ ስላሉላት ዘር ጨፈጨፈች አይባልም። የተባበሩት መንግሥታት በቴዎድሮስ አድኀኖም አንባ በወር 6 ጊዜ አይሰበሰብም። ማይካድራ፣ ጭና ምን ተፈጠረ? ምንም።👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ15 ፣ 3-4

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአፈሳ ዜና…!

"…ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናት ልጆቻችን ታፍሰው በግዳጅ ወደ ውትድርና ተወስደውብናል ያሉ የታዳጊ ታፋሾ ልጆች ወላጅ የሆኑ የኦሮሞ አባቶችን ራሱ የዓረብ ስም በዝቷል ያለው የሽመልስ አብዲሳ መንግሥት አገልጋይ የሆነው የኦሮሚያ ፍሊስና የኦሮሚያ ሚሊሻ ወላጆቹን እንዲህ እንደምታዩት ቆምጦ፣ ቆምጦና ወግሮ ለቅቋቸዋል።

• የውሻ ቁስል ያድርግላችሁ። ሌላ ምን ይባላል?

• አፈሳው ግን አልቆመም ማለት ነው?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እሷም ፋኒት ልክ እንደ ወንድሟ ስለገባት ነው…

• አራት ነጥብ።

• ክብር ለዐማራ ፋኖ… 💪🏿💪✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከርዕሰ አንቀፁ ንባብ በኋላ የሚከተለው መርሀ ግብር ደግሞ ያው እንደተለመደው የእናንተ አስተያየት በሃላል የሚሰማበት፣ የሚነበብበት፣ የሚደመጥበት ሰዓት ነው።

"…ጓ በሉብኝ እንግዲህ። ጀምሩ። ተንፒሱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…የዐማራ ትግል የት እንደደረሰ ተመልከት። ከአንድ ዓመት በፊት እንዲህ ብሎ ለመናገር፣ ለመፎከር፣ በአደባባይ ቃል ለመግባት ይታሰብ ነበር ወይ? ያውም ይሄ እኮ ጎንደር ላይ ነው። ያውም እኮ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዐማራ በወራሪው የጁላ ጦር በሚፈተንበት ጎንደር በኃዘንተኞቹ በእነ ናሁሰናይ ቤተሰቦች ድንኳን ውስጥ ነው። ያውም እኮ ተመልከት ጧፍ እያበሩ በቁጭት ቃል የሚገቡት የጎንደር ዐማራ እናቶች እና ሴቶች ጭምር ናቸው። ሴቶች ያመኑበት ትግል ደግሞ ውጤታማነቱ አያጠያይቅም። ከጥቂት ዓመታት በፊት ዐማራ ነኝ ብሎ መናገር እኮ ራስን ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ የማድረግ ያህል ተቆጥሮ እንደ ክብረ ነክ ነገር ተደርጎ የሚታይ ነገር ነበር። ዐማራ ዐማራነቱን ጠልቶ አልነበረም ዐማራ ዐማራነቱን ወደ ኋላ አድርጎ ዐማራ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ዘር ለገበሬ ነው። ምንድነው ከሀገር አንሶ፣ ወርዶ በዘር፣ በጎሳ፣ በጎጥ መጠራት ይል የነበረው ዐማራነቱን ጠልቶ፣ አፍሮበት ሳይሆን ኢትዮጵያን ከነፍሱ፣ ካንጀቱ፣ ከልቡ ስለሚወዳት፣ ስለሚያፈቅራት፣ ደግሞም ስለሚሳሳላት እንጂ።

"…አሁን ዘመን ተቀይሯል። አሁንም ቢሆን ዐማራው እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞው 100% ዐማራውም ዐማራ ነኝ ብሎ እኮ አልተነሣም። አይደለም 100ቱ 50% ቱም እኮ ዐማራ ነኝ ብሎ አልተነሣም። 50% ብዙ ነው 10% ቱ ዐማራ ዐማራ ነኝ ብሎ ገና አልተነሣም። አሁን ዐማራ ነኝ ብሎ ዐማራነቱን ለማዳን ቆርጦ ውድ እና አይተኬ ሕይወቱን ለመገበር ወስኖ ወደ ትግል የገባው ዐማራ በፐርሰን ከመቶኛ ሲሰላ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው። አዚሙ የተገፈፈለት፣ ከድባቴው የወጣ፣ አስማቱ የከሸፈለት ዐማራ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው። በጣም ጥቂት አልኳችሁ። ይሄ ጥቂቱ ነው አሁን ተአምራት እየሠራ ያለው። ይሄ ጥቂቱ ነው ከሱዳን፣ ከትግሬ ነፃ አውጪ፣ ከጉምዝ ታጣቂ፣ ከኦነግ ሠራዊት፣ ከኦሮሙማው መከላከያ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ የገባው ይሄ ጥቂቱ ኃይል ነው። ይሄ ኃይል ነው አገዛዙን ሽባ አድርጎ ከምበል ደፋ፣ ቀና ወዝወዝ እያደረገው ያለው።

"…በቆመህ ጠብቀኝ፣ በነፍስ ወከፍ መሣሪያ፣ በክላሽ ጠብመንጃ በድንጋይና በክትክታ ዱላ ብቻ ይሄን በድሮን፣ በአየር ኃይል ጀትና ሂሊኮፍተር ታግዞ ከላይ ቦንብ የሚያዘንበውን፣ በምድር በቢኤም፣ በታንክ፣ በሞርታር፣ ዲሽቃ እና ብሬን እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀውን፣ በኢትዮጵያ በጀት፣ በዐማራ ግብር እና ታክስ የሚጦረውን የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን የገጠመው እና እንደ ቤርሙዳ ውጦ ያስቀረው ይሄው በአነስተኛ ቁጥር ወስኖ የተንቀሳቀሰ የዐማራ ፋኖ ኃይል ነው። ይሄ ኃይል ነው ከዚህ ሁሉ ግዙፍ ጦር ጋር ግብ ግብ ገጥሞ ፍዳውን እያበላው ያለው።

"…የዐማራን ትግል ዐማራ ነን የሚሉ ዐማሮች ልክ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ 100% አይደለም 10 እና 15% ቱ ዐማራ ወስኖ ይሄን ቀድሞ ወስኖ ትግሉን የተቀላቀለውን  ጥቂት ኃይል ቢቀላቀል አይደለም የኢትዮጵያ ጉዳይ የምሥራቅ አፍሪቃ ነገር ይስተካከላል። ገና ነው ዐማራ አልተነሣም። የሚያወራው ይበዛል። ቀባጣሪው፣ አውርቶ አደሩ ይበዛል። ወላዋዩ፣ አቃጣሪው ይበዛል። መስሎ አዳሪው፣ ጆተኒው ይበዛል። ያልወሰነው መሃል ሰፋሪው አጃኳሚው ይበዛል። ሰነፉ፣ ዋሾ፣ ቀጣፊው ይበዛል። ገና ነው መረጃው አለው ነገር ግን ዳር ቆሞ የደመራው እሳት ወዴት እንደሚወድቅ የሚጠባበቀው ይበዛል። ደሀው ሞቶለት እሱ ከመንገሥ የቋመጠው ይበዛል።

"…አሁን በዐማራ ትግል መረጃ የሌለው ሰው የለም። ሁሉም መረጃ አለው። ዐማራ ምን እያደረገ መረጃ የሌለው የለም። አይደለም ዐማራው፣ ትግሬው አሳምሮ ያውቃል። ኦሮሞው አሳምሮ ያውቃል። ጉራጌው፣ አፋሩ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ ጉራጌው፣ ጋምቤላው ወዘተረፈ አሳምረው ያውቃሉ። ቤር ቤረሰቦች ብቻ አይደሉም፣ ጀዝባው የአፍሪቃ ኅብረት፣ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ዐማራ አቋም ያላቸው የዐረብ ሊግ፣ የአውሮጳ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ የወያኔ የጡት እናት አማሪካም በደንብ ነው የምታውቀው። ሁላቸውም አሳምረው ያውቃሉ። የሚመጣው ዐማራ ሰውነትን አስቀድሞ ለነፃነት የሚመጣ ስለሆነ ግን አሻንጉሊት ስለማይሆንላቸው አይፈልጉትም። ይፈሩታል። ይጠሉታል። አይናቸው እያየ ያሸንፈፈቸዋል።

"…ትግሬ ምድር እንቅፋት የመታው ሰው የሚዘግቡት፣ ትን ሲለው እኔን የሚሉት፣ ሲያስነጥስ ይማርህ የሚሉት የምዕራባውያን ሚዲያዎች፣ እነ ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ ወዘተረፈ የሆኖት ሚዲያዎች አሁን በዐማራ ክልል ስለሚፈጸመው የንፁሐን ጭፍጨፋ ሲዘግቡ ሰምታችኋልን? በዓመት 12 ጊዜ ስለ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ነፍስ ተጨንቆ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ይወተውት የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሁን አለ? በዐማራ ክልል እየተደረገ ስላለው ጭፍጨፋ መረጃ ሳይኖረው ቀርቶ ነው? አይደለም። በዐማራ ጉዳይ ዳተኞች፣ የጥፋቱ ተባባሪዎች ስለሆኑ ብቻ ነው። እናም ዐማራ የሚገጥመው፣ የሚያሸንፈውም እነዚህን አካላት በሙሉ ነው። ውጊያው የመንፈስ ውጊያ ነው። ውጊያው ዓለምአቀፋዊ ጣልቃ ገብነት ያለበት ነው። ውጊያው መጠነ ሰፊ እጆች የሚሳተፉበት ውጊያ ነው። ይሄን ውጊያ ነው በጣም ጥቂቶች የቆረጡ ዐማሮች ወስነው ለመፋለም ፈጣሪንና ክንዳቸውን ተማምነው የገቡበት። ሃቅ ስላላቸው ነው ገትረው ገዝግዘው አፈር ከደቼ እያበሉት የሚገኙት።

"…በአሜሪካ ብቻ ያለውን የዐማራ ተወላጅ ዳያስጶራ ቁጥሩን እስኪ ገምቱ? የተማረውን የዐማራ ብዛት ገምቱ? በንግድም፣ በኑሮም ተሳክቶለት ያለውን ዐማራ እስቲ ገምቱ? ገምታችሁ ስታበቁ ስንቱ ነው እየመጣ፣ እየሆነ ያለው ነገር ገብቶት ለነገሩ፣ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እንቅልፍ አጥቶ እየታገለ ያለው? ልክ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ በአይን ጥቅሻ የሚግባባው ዐማራ ስንቱ ነው? ፕሮፌሰሮቹ የት ናቸው? አዕምሮአቸውን በነጭ ፍልስፍና ራጥበው፣ ሆዳቸውን በቢራ ቆዝረው፣ እንደ ድርስ ነፍሰጡር ተቀብትተው ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩ፣ እንደ ሀረር ሰንጋ ሻኛ በማጅራታቸው፣ ላት በአንገታቸው፣ እንደ ሁዳድ እርሻ ዳሌአቸውን አስፍተው ደንታ ቢስ ሆነው ኖረው፣ ደንታ ቢስ ሆነው የሚሞቱት ስንት ናቸው? የሌላውን ሳልጨምር የአሜሪካ ዐማራ ብቻ ቢሰባሰብ፣ ሥራዬ ብሎ ቢታገል አስባችሁታል? ግን ወዶ ሳይሆን በግዱ መንቃቱ አይቀርም።

"…በአንድ ዓመት ውስጥ በጥቂቶች እዚህ የደረሰው የዐማራ ትግል ትግሉ የገባቸውና የወሰኑ፣ የቆረጡ ጥቂቶች ቢቀላቋሏቸው ደግሞ አስቡት። ትግሉን ዐማሮቹ ከልብ ገብተው ቢመሩት፣ ቢይዙት፣ ጋዜጠኞች የጦር መሪ ልሁን ብለው ባልተላላጡ ነበር። ዐማሮች ትኩረት ሰጥተው ትግሉን ተረክበው ቢመሩት ኖሮ የዲሲ ጋንግስተሮች በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ የግል ፋኖ መግዛትና ማደራጀት ባልጀመሩ ነበር። ዐማራው ኮምጨጭ ብሎ ትግሉን ቢቀላቀል ኖሮ በዐማራ ስም ግለሰቦች ሚልዮን ዶላሮችን ባልቀፈሉ ነበር። እናም ዐማሮች ሆይ በተለይ ዳያስጶራው ትግሉን ተቀላቀል። ፋንቅለህ ቅርፊትህን ሰብረህ ውጣ። አግዝ ተሳተፍ። የቲክቶክና የዩቲዩብ ዜና እያሳደድክ አነፍንፈህ እየተመገብክ ተደብቀህ አትቀመጥ። ወሬኛ፣ መንደሬ፣ ሾካካ አትሁን። ፊትለፊት ውጣና …👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ቆሮ 15፥ 21-22

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~እምይእዜሰ
• ኮነ
~ፍስሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉YouTube

https://www.youtube.com/live/uq1i-NRnX-c?si=FgqNJHbmVWRyMRmd

👉በረንብል /Rumble

https://rumble.com/v4zyd0k--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡ / Facebook

https://www.facebook.com/share/hKVNPSW6CdKwdpTk/?mibextid=oFDknk

👉    በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram

   /channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ሌላውን እሁድ በመረጃ ቲቪ በሰፊው እመጣበታለሁ። አንድ የምሥራቅ ጎጃም የ92 ዓመት ሽማግሌ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ደብረ ብርሃን የተፈናቀለ ስንትና ስንት ዐማራ እያለ መቀሌ ትግራይ ድረስ ሄደው እርዳታ ረዱ ሲባል የነበረውን አስቂኝ ጽድቅ የሌለው ተግባርም እንመለከታለን። ከጎጃም ዳንግላ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሞቶ፣ ተዋግቶ ያስፈታቸው የትግሬ ኮሎኔሎችንም እሁድ በሰፊው እናነሣቸዋለን። እነዚያ የትግሬ የጦር መኮንኖች አሁን የት ናቸው? በራያ በኩል ዘምተው ዐማራን እየገደሉ ነው? ወይስ በጎንደር በኩል አዲአርቃይ ገብተው ዐማራን እያረዱ ነው? በእግር ሰዶ በፈረስ ፍለጋ ይደብራል? ይገባኛል ነገርየው ለፖለቲካ ትርፍ የተደረገ ቢሆንም ወያኔ ሃይማኖት የላትም። ይሄን ማወቅ አስፈላጊ ነው። በገዛ እጅህ ለአራጅህ ቢለዋ ስለህ ማቀበል ምን የሚሉት ዥልጥነት ነው? ምን የሚሉት ፋርነት ነው?

"…ተናግሬአለሁ። መጪው ክረምት ከበድ ይላል። አሁንም ደፈጣ፣ የደፈጣ ውጊያ አገዛዙዝን ድምጥማጡን ነው የሚያጠፋው። አሁንም የብአዴን አቃጣሪዎችን መኮርኮሙ አዋጭ መንገድ ነው። ግብር ተሰብስቦ ለፋኖ ነው መስጠት። ግብር ሰብሳቢ ነኝ ብሎ ብአዴን ልኮት ገጠር የሚመጣውን እዚያው ለፋኖ ግብር ማሰብሰብ ነው። መከላከያ ተብዬውም በየቀኑ አመራሩን በሞት እያጣ ነው። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በርክቷል። መከላከያ እስከመቼስ የብአዴን ሹመኞችን እያገዘ፣ እያጀበ ዐማራ ክልል እየተንገዋለለ ይቀመጣል? እስከመቼ? ኪሳራውንስ አስባችሁታል? ዐማራ መከላከያን ሲወጋው እውነት አለው። ሃቅ አለው። መከላከያው ዐማራን ሲወጋው ግን ምንም ሞራላዊም፣ ሕጋዊም፣ ፖለቲካዊም መሠረት የለውም። ስለዚህ መከላከያው ይሸነፋል። ዐማራው ያሸንፋል። መጨረሻ ላይ የሚሆነውም ይሄ ነው። አሁን የትግሬ ነፃ አውጪዋ ወያኔና የኦሮሞ ብልፅግና ኦነግም ያልተቀደሰ ጋብቻ የሚፈጽሙት የሚወለደውን የዐማራ የነጻነት ንጉሥ ሳይወለድ ገድለው ለመቅበር ነው። የዐማራ የነጻነት፣ የድል፣ የሃቅ ንጉሥ ከዐማራ ልጆች ማኅፀን ሁሉም እያየው ይወለዳል። ብርሃኑም ለመላው ኢትዮጵያ ያበራል። ዐማራ ከላይ በፈጣሪ፣ ከታች በልጆቹ ክንድና ኃይል በነፍጡ ጠላትን አናፍጦ አሳምኖ፣ አሳምሮም ያሸንፋል። ይኸው ነው።

• ዋንጫው የዐማራ ነው። አለቀ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ፋኖ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸባርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የሚጠበቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። እንዲያውም አልፏል። እግዚአብሔር ይመስገን። አሁን በቀጥታ የምንገባው ወደ ተለመደችዋ ቃሪያ በሚጥሚጣ ወደሆነችዋ ርዕሰ አንቀፃችን ነው።

"…ርዕሰ አንቀፃችን ዛሬ የሚመለከተው ለዋንጫ ጨዋታው ለማለፍ እየተደረገ ስላለው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነው የሚያወሳው። ደርግን አጭበርብሮ ለ27 ዓመት ሻምፒዮና ሆኖ የነበረውን የትግሬ መር ኢህአዴግ ቡድንን ከዚህ ቀደም አጭበርብሮ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና የሆነው ቡድን፣ በመቀጠልም ያንኑ ማጭበርበሩን ቀጥሎ መላውን የኢትዮጵያ ደጋፊ ሰብስቦ ወደ ትግራይ በመግባት ከሂዊ ጋር ተጋጥሞ ጊዜአዊ ድል አግኝቶ ቆስሎ የመጣው የኦሮሙማ በልፃጊ ቡድን አሁን በመጨረሻም ያንኑ የማጭበርበር ልማዱን ይዞ ከዐማራ ቡድን ከፋኖ ጋር ለመግጠም ቢመጣም አልተሳካለትም። የለመደች ጦጣ ሁል ጊዜ ሸምጥጣ አለ አጎቴ ሌኒን።

"…እናስ ወገኖቼ የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ሳምንታዊው የዕለተ ሐሙስ ዝግጅታችን እስኪደርስ ድረስ ርዕሰ አንቀፁን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

•የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዘገባ ነው።

"…እጅግ ዘግናኝ ነው! ትህነግ በዐማራ ላይ ሌላ ፍጅት ፈፀመ! ህፃናትን ገድሎ አስከሬናቸውን አቃጠለ። ወርቃይኑ ተብሎ በሚጠራው የትህነግ ጀኔራል የተላኩ የትህነግ ታጣቂዎች ዐማራ ክልል ሰርገው ገብተው አንድ መንደር ሙሉ በሙሉ አውድመው፣ በሺህ የሚቆጠሩ  ንፁሃንን አፈናቅለው በርካቶችን ገድለዋል። ከእነዚህ መካከል ህፃናትን ገድለው በእሳት አቃጥለዋል።

"…ትህነግ ሰሞኑን በፌስቡክ "ሰኔ 30" የሚል ዘመቻ የከፈተ ሲሆን ወደ ወልቃይት እንገባለን ብለው ያሰቡበትን ቀንን ነው የዘመቻው አካል ያደረጉት። ዘመቻውን ግን በፌስቡክ ብቻ አይደለም። በተግባርም ወደ ወልቃይት ቢገቡ ሊያደርጉ የሚችሉትን አዳርቃይ ላይ ፈፅመውታል።

"…ትህነግ ወደ ዐማራ ግዛቶች ቢገባ ሊፈፅመው የሚችለውን ትናንት ሌሊት በፈፀመው ጭፍጨፋ ጠቁሞናል።

•የእኔ ምልከታ ይቀጥላል።

"…ሰሞኑን በርዕሰ አንቀፄ እንደጠቆምኳችሁ የትግራይ ነፃ አውጪዋ ወያኔ ያለ ጦርነት መኖር አትችልም። ሚካኤል ስሁል የሚባል አረመኔ ከትግሬ ተነሥቶ ጎንደር ቤተ መንግሥት ተጠግቶ የፈጸመውን ብታነቡ ይሰቀጥጣችኋል። ዐፄ ዮሐንስ ዓለም በቃኝ ብለው ገዳም የገቡትን ንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስን ከገዳም አውጥተው ዓይናቸውን በጋለ ብረት አውጥተው እንዴት የሳዲስትነት ተግባር እንደፈጸሙም አይተናል።

"…በትግል ወቅት ወያኔ እንዴት የተንቤን ባላባቶችን ፊውዳል ናቸው ብላ መሬት ውስጥ አበስብሳ አትልታ እንደገደለች፣ አንድ የወያኔ መሪ ሁለት እህትማማቾችን ተኝቶ አድሮ ጠዋት ግንባራቸው ነድሎ እንዴት እንደረሸናቸው፣ ፀለምት ላይ በደርግ ተከበው የሚበሉት ቢያጡ ታጋዮቹ ዕጣ ተጣጥለው ዕጣው የወጣበትን የራሳቸውን ሰው አርደው በልተው ያን ክፉ የሚሉትን ዘመን እንዴት እንዳለፉት የነገሩንም ራሳቸው ናቸው።

• ክረምቱ እየመጣም አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ያልለጠፈ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው የተባለ አንድ ነጭ አውሮጵላን ዛሬ ወደ አክሱም ከተማ በረራ መጀመሩ ተነግሯል። የመቀሌው ከጀመረ ቆየ። ወያኔ በወልቃይት ውጊያ ልትጀምር ነው። አሁን ሎጀስቲኩ አይቸግራትም። በቀጥታ በአየር መንገዱ ስንቅና ትጥቅ ወታደርም በሽሬ፣ በአክሱምና በመቀሌ ይራገፍላታል። አለቀ።

"…የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከአሁን ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አላቋረጠም። ከአዲስ አበባ አስመራ፣ ከአስመራ አዲስ አበባ ሽር ብትን እየተባለ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤንባሲ ተዘጋ ብለው የወያኔና የኦነግ አክ እንትፊስቶች ለምን እንደሚጮሁም አልገባኝም።

"…ሌላው ራያ የገባው የወያኔ ሠራዊት አንድ የራያ ዐማራ የሆነ የመብራት ሠራተኛ ተኩሰው ገድለዋል በሚል በራያ አላማጣ ምድር ቁና ሆናለች። አሳዛኙ ነገር ግን ራያ ባዶ እጁን መሆኑና እስከ አሁን "መንግሥት" ብሎ ብልፅግናን አምኖ የተቀመጠ ምስኪን ሕዝብ መሆኑ ነው። የመከላከያና የሂዊ ወታደሮች በጋራ ቢራ እየጠጡ፣ ሲጋራ ተቀባብለው እያጨሱ በራያዎች ይሳለቁባቸዋል።

"…ወያኔን ሌባ፣ ዘራፊ ብለህ በስሟ ስለጠራሃት አትሰማህም። በጠበልም በጸሎትም አትወጣልህም። ምሷ ጥይት ነው። ያውም ሰንደቅ ዓላማ ሳትይዝ በሰላማዊ ሰልፍ። ኧረ ራያዎች አትቀልዱ። ወልቃይቶች ነቃ ሰንዳ በሉ።

"…በዚህ ምድር ላይ እንደወያኔ ገገማ አይቼም ሰምቼም አላውቅ። ግግም በቃ። ራያ ትግሬ ነው ይልሃል። ሕዝቡ ደግሞ ትግሬ አይደለንም እኛ የወሎ ዐማሮች ነን ብሎ ይቀውጠዋል። የፕሪቶሪያው ስምምነት ይባልልኛላ። ፕሪቶሪያም ሁላ። የትኛውን ሕዝብ ልታስተዳድር ነው የምትመጣው? ከ5ሚልዮን ወደ 3ሚልዮን ከመቀነስ በቀር ትርፋችሁ አይታየኝም።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸብርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የፈለገ ቢረሳ እኔ እንደሁ አልረሳት…!

"…አይ እስታሊን… ጥቂት ሆዳም ዐማራ፣ አቃጣሪ፣ ባንዳ የባንዳ ልጅ የሆነ ጥቂት ዐማራ፣ ሰገጤ ፋራ፣ ደንታ ቢስ፣ ሞራለ ቢስ፣ ሰጎን ጭንቅላት ቀሽም ሾርት ሚሞሪያም ዐማራ መሳይ ዐሞራ አለና፣ እንደፈለግኩ ልጫወትበት እችላለሁ ብለህ አስበህ፣ አንተ ተብታባ ገመድ አፍ አንተም ከሰው ተቆጥረህ፣ አንት የሰው ግማሽ አንት ወያኔው፣ ፀረ ኢትዮጵያው ገንጣይ የገንጣይ ልጅ ወንበዴ ከእኔ ይልቅ አንተ ለእስክንድር ነጋ አዝነህ ዛሬ "እስክንድርን የማይቀበል ዐማራ ከትግሬ ጋር እንዴት አንድ ልሁን ብሎ ይመኛል? ብለህ በድፍረት ትናገር…? ጉድ እኮ ነው።

"…ማነህ ከዘመድኩን ይልቅ ወለይ እስታሊን ይሻለናል ያልከው የግንባሩ ተሟጋች ግንቦቴ ያው ናና የስታሊንን ትውከት ጥረግለት። ዳይፐሩን ቀይርለት።

"…እኔ ግን እስክንድርን አከብረዋለሁ። ያልገባኝን እጠይቀዋለሁ፣ ያልተስማማሁበትን እሞግተዋለሁ፣ እስከምችለው ድረስ እሟገተዋለሁ። ከእስክንድር ጋር ብጋጭ በሃሳብ ብቻ ነው። በአካሃድ ብቻ። የፈለገ ነገር ቢሆን ግን እንደ እስታሊን እስኬውን በዚህ መጠን አፌን አልከፍትበትም።

"…እኔማ ሾርት ሚሞሪያም አይደለሁም። ጎጋህን እዚያው ግንቦቴና በድኑ ብአዴን መንደርህ ፈልግ።

"…እስክንድር መሬት ላይ ካሉት ወንድሞቹ ሓሳብ አይለይም። ከመስመራቸውም አያፈነግጥም፣ ዝንፍም አይልም።

• የዐማራ ነፃነት እስኪረጋገጥ እኔ ዘመዴ ወይ ፍንክች።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አንድ የምሥራች አብሥሬኤቸሁ ደስስ ብሎን ብናድርስ…? ሃኣ…?

• የምሥራች ዐማራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…የህወሓት ጦር ማለት ዐማራን ሁሉ መጨፍጨፍ እየፈለገ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ሕግ ላለመጠየቅ ሲል እየተደበቀ እንደሚገለው የአብይ ጦር አይደለም። ህወሓት ማለት በአብይ የተጫነለትን ከባድ መሳሪያ ሁሉ ተጠቅሞ መላው ዐማራን ፊት ለፊት እየገደለ እየረሸነ የሚጓዝ ጦር ነው። ይሄን ስል በስታሊን ፉገራ የደነዘዘው ዐማራ ሊሰድበኝ ይችላል። ለደንታህ ነው። ህወሓት ዘር አጥፊ፣ ጨፍጫፊ ናት። ድሮን ገብቶላቸው ከሆነ ደግሞ አስቡት። አብይ አህመድም የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት የሚለውን ተጠቅሞ ዐማራን በግላጭ የሚያገኝበት ጊዜ አሁን ነው። ግማሽ ጦሩን ለህወሓት ሰጥቶ ግማሽ ጦሩን ደግሞ ለዐማራ የወገነ አስመስሎ እንደከዚህ ቀደሙ አፈግፍጉ እያለ ሁለት ስለት ምርጥ ቢላዋ እየተጠቀመ መሸክሸክ ነው። ለትግሬ ኤርትራን ጋብዞ እንዳስፈጃት ለዐማራ ደግሞ ሱዳንን ጋብዞ ሊያስጨፈጭፍ ይችላል።

"…የዐማራ ፋኖ እንደከዚህ ቀደሙ ኦነግን እያጠቃ ከከተማ የሚወጣበት ጊዜ የሚያበቃ ይመስለኛል። የህወሓት እና የኦነግ ወረራ መላውን የዐማራን ህዝብ ለማንቀሳቀስ ለፋኖ በር ይከፍትለታልም ብዬ እጠብቃለሁ። ደመቀ ዘውዱ ከህወሓት ጋር ስለመሥራቱ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ከአብይ ጋር ፀረ ዐማራ ሆኖ ለአንዲት አካባቢ ነጻነት እንደሚሠራ ግን ራሱም በአደባባይ የነገረን ቅሽሽ ሳይለው ነው። ደግሞም በተግባሩም ተረጋግጧል። ሁሉንም ነገር በቅርቡ የምናየው ይሆናል። አብይ አህመድ ሰይጣን ነው። ህወሓትን በጎን ወረራ ያስጀምረውና በደመቀ ዘውዱ በኩል በወልቃይትና በቀሪው ጎንደር ያለውን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ ይሞክራል። ህወሓት ወረራ ስትጀምር እነ ደመቀም ከኦነግ መከላከያ ጎን ሆነን ህወሓትን እንመክት የሚል ጥሪ ያቀርባሉ። የዐማራ ክልል ገዢው ስደተኛው ብአዴንም የእርስ በእርስ ትግላችንን ትተን ህወሓትን እንመክት የሚል መሰል ጥሪዎችን ያቀርባሉ። ፋኖ ለደመቀ ዘውዱም ለአቢይ አህመድም፣ ለብአዴንም መልስ አልሰጥ ብሎ በአቋሙ ገግሞ መከላከያን ከገጠመው "በህወሓት ተወረን እንኳን የማይራሩ ጨካኞች፣ ህወሓት የወረረችን እኛ  ከፋኖ ጋር ስንዋጋ ነው" የሚል ይዘት ያለው ፕሮፓጋንዳ በፋኖ ላይ ይከፍታል። ስለዚህ ዐማራ በተለይ ጎንደሬው ህወሓት መጣ በተባለ ቁጥር እንደ ፈሪ ከኦነግ ጋር ሄዶ የሚጣበቀውን ነገር ካልመረመረ የእስከዛሬው የፋኖ ድል በዜሮ የተባዛ ይሆናል ማለት ነው።

"…እንደ መፍትሔ ከታየ የጎንደር ፋኖ በግርግርና በጦርነት መሃል ተሰሚነቱ ከመቀነሱ በፊት በወልቃይት ላይ ያለውን አቋም ለሕዝቡ ይፋ ቢያደርግ ሸጋ ነው። አሁን በዐማራ ምድር ብቻውን የቀረው የአብይ ፈረስ ቢኖር ደመቀ ዘውዱ ብቻ ነው። የጎንደር ፋኖ ከሰውየው ጋር ይገናኛል ይመክራል? አቋሙን አውቀውታል? በዐማራነት ላይ ተግባብተው አብረው እየሠሩ ነው? ከሆነ ጥሩ ነው። ሙያ በልብ ብሎ ዝም ማለት ነው። ካልሆነ ግን ካልሆነ ግን እደግመዋለሁ ካልሆነ ግን የደመቀ እና የጓደኞቹ አቋም በተቃራኒው ከሆነ የጎንደር ፋኖ ሳይመሽበት፣ ሳይረፍድ፣ ጀንበር ሳትጠልቅ ከወዲሁ ለሕዝቡ አቋሙን ይፋ ማድረግም ይጠበቅበታል። እነርሱም እንደኛ ምንም ፍንጭ ከሌላቸው ለእነ ደሜ ቡድን በአደባባይ ጥሪ ያቅርቡለት። የጎንደር ሕዝብ ህወሓት መጣ ሲባል ከኦነግ ጎን የሚሸጎጥ ከሆነ አስር ወር ሙሉ ታንክና ድሮን እስከሚዘንብበት ለምን ጠበቀ? ውባንተስ ለምን ከሞቀ ቤቱ ወጥቶ ተሰዋ? ለማንኛውም አረረም መረረም፣ በቦሌም ሂድ በባሌም ና የወልቃይት ዐማራ ትግል የሚወሰነው በደመቀ ዘውዱ ነው። ወይ ከዐማራ ፋኖ ጎን ይሰለፋል አልያም በዐማራ ጠላቶች ተበልቶ የዐማራ ፋኖ መላውን ዐማራ ሁለት እኩል ጠላቶች እንዳሉት አሳምኖ ያለ አንዳች የኦነግ አብይ ተለጣፊነት ለአንድ ዓላማ ይንቀሳቅሳል። አከተመ።

"…ህወሓቶች ይፈሩታል፣ ይጠሉታል። ለጠላት በር ላለመክፈት ሲባል ደመቀን አንናገረው የሚል ጥሬ ንግግር የዋህነታችሁን እና የፖለቲካ ዳተኝነታችሁን ከማሳየት የዘለለ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም።
ህወሓትን፣ ኦህዴድንና ብአዴንን ተወት አድርጎ ቤትን ዘግቶ የራስን ስሌት ሠርቶ ጨርሶ በር መክፈት ነው ውጤት የሚያመጣው። ድሮም እንዲህ አድርጎህ እኮ ነበር። ቀድመህ ባለመወሰንህና የጠላት አሰላለፍን ተረድተህ ራሳህን ሳትችል በመቀመጥህ ምክንያት ህወሓት መጣችብኝ ብለህ በድንጋጤ ከብአዴን ጎን የተሰለፍክበትን ጊዜ ማስታወሱ ብቻ ለአንተ ለዐማራው በቂ ነው። ብአዴኖች ህወሓት በፋኖ እንደተመከተች ከተረጋገጠ በኋላ ነው ፋኖን በየቤቱ እየገባ መግደል የጀመረው። አሁንም እደግመዋለሁ ፋኖ ለመላው ጎንደሬ በተለይም ለወልቃይት ሕዝብ ጥሪ አቅርቦ የደመቀን ጉዳይ ማሳካት ከቻለ፤ የዐማራና የትግሬ ጦርነት በፍቅር ይቋጫል። በጦርነትም ከተባለ በፋኖ ይቋጫል። አለቀ።

"…የኤርትራን አቋም በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። የሻአቢያ ገረድ፣ የበግና የፍየል እረኛ ሆነው፣ መንገድና ግድብ፣ እርሻ ሲያሠሯቸው ዘመናዊ ባሪያዎቹ የኦነግ አክቲቪስቶች እና ሻአቢያን እንደፈጣሪያቸው የሚያዩት የወያኔ አክቲቪስቶች አዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ኤርትራ ዘጋች እያሉ ነው። ለደንተዋ ነው። ኢሳያስና አቢይ በኮሪያ አልተገናኙም ወዘተ የሚለውም ለደንታቸው ነው። እስከ አሁን ግን የኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ወደ አስመራ እየበረረ ነው። ቢሆንስ ብለን የኤርትራን እና የኬንያን ሚና በሌላ ጊዜ እናወራለን። ኔቶ ናይሮቢ፣ የእነ ሩሲያ ኃይል አስመራ ቢገቡስ ብለን ደግሞ የአቅሚቲ የቢሆንስ፣ የቀኝ ሽከካ ትን የሚያስብል ትንታኔአችንን ለመስጠት እንሞክራለን። ማን እንደተማረ ነው የፖለቲካ ሳይንስ የምንማረው? ከመሬት ተነሥቶ ማንም 777 You is my president ሆኖ ቦለጢቀኛ ተብሎ ቦለጢቃን ከተነተነ እኔ ከየኔታ ጉረሮ ጠጅ ይንቆርቆር እያልኩ ፊደል ስቆጥር የኖርኩት ዘመዴ ምን ያንሰኛል? ደግሞ ይሄን አለ ዘመዴ ብላችሁ ጓ በሉብኝ አሏችሁ። እኔ እንደሆንኩ ኬሬዳሽ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

• አመስጋኙ ከፈጠነ ርዕሰ አንቀፁም ይፈጥናል። አመስጋኙም ከዘገየ ርዕሰ ዘንቀፁም ይዘገያል። 20 ሺ ሰው አንብቦ ለማመስገን ከፈራ 1ሺ ደፋር አመስጋኝ እስከሚጣ መጠበቅ የግድ ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀፃችን ወልቃይት ነው የሚያሽከረክረን። ዛሬም በወልቃይት ጉዳይ ጓ የሚልብኝ አይጠፋም ብዬ እጠብቃለሁ። የሆነው ሆኖ ለስለስ ያለ ዶሮ ማታ ዶሮ ማታ የመሰለ ኮሶ ልግትህ ነኝና ጠብቀኝ። ጎንደሬ ነኝ ብለህ ጓ ብትል ለደንታህ ነው። ትግሬ ነኝ ብለህ ብትንጣጣም ለደንታህ ነው። ኦሬክስ ነኝ ብለህ ብትንበጫበጭም ለደንታህ ነው። እኔ ግን ስጋቴን ጨምቄ እፅፍልሃለሁ።

"…እናስ ጎዶኞቼ ከእኔ ጋር ወልቃይት ሄዳችሁ ትውላላችሁ ወይስ ስለመንሱርና ጫልቱ የአንድ ቀን ጋብቻ ትበጠረቃላችሁ። ወይስ ጌታቸው ረዳ ከጥይት ከቦንብ ናዳ ተርምኔተርን ሆኖ አመለጠ ከሚል የጅል ገንፎ አጀንዳ ጋር ትቆያላችሁ?

"…ወይስ ፋኖ እጁን ከሰጠ እኛ ወልቃይትና ሁመራን እንጠብቅላችኋላን ከሚለው የተበለጠለጠ የኑግ ቡኮ የቀትር ጋኔን ከመሰለው ሶዬ ጋር ትቆያላችሁ። ወይስ የጀግናውን የውባንተን መንፈስ ተከትላችሁ ከእኔ ጋር ወልቃይት ታረፍዳላችሁ? ደፈር ብለን ብንነጋገርስ?

• ዛዲያሳ ርዕሰ አንቀፁን ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ? እስቲ አንድ 100 ያህል ሰው ዝግጁ ነነ ይበል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሱሬ ግን continuity ነው የሚባለው አይደል እንዴ ያልከኝ…? …ኮንቲኒቲም ይባላል እንዴ? …ብቻ ሱሬ የእንግሊዝ አፍ አስተምርሃለሁ ብለህ እያሳሳትከኝ እንዳይሆን።

"…አንተ continuity ትለኛለህ። የዓለም ሎሬት፣ ኮሎኔል ዶክተር ጠቅላይ ሚንስትር ደግሞ ኮንቲኒቲ ነው የሚሉት። ግራ ገባኝ እኮ ጎበዝ። ቆይ የማንኛችሁን ልያዝ? continuity ወይስ ኮንቲኒቲ…?

• እስቲ ነፃና ገለልተኛ የሆናችሁ የንክክር ኮሚሽኖች ካላችሁ በቅንነት መለስ ስጡኝ።

• የተማረ ይግደለኝ አባቴ። 777 ያለህ። ተወዛገብኩ እኮ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሳቅቼ ልሞት ነው።

"…ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝትም፣ ለስብሰባም የሚመጣ ሲጠፋ፣ ጎንደርም፣ ባህርዳርም፣ ደሴም የሚጓዝ የሚጎበኝ ቱሪስት ሲጠፋ፣ ነዳጅ አቃጥለው ኮልኮሌዎቹ የክልል መንግሥታት ነኝ ባይዎች ራሳቸው ጉብኝቱን ጀመሩት? 😂

"…ደግሞ እኮ የኮሪያው መሪ የመጡ ይመስል ደስታ ዴላሞን ገቡ ወጡ ይባልልኛል። ይሄ ሁሉ ጭንቀት ዐማራ ክልል ሰላም ነው ለማሰኘት እንደሆነም ይገባኛል። ማን ይሙት አሁን ማንን ለመሸወድ ነው? ኧረ ሼ…

"…ልብ ብዬ አስተውዬ ሳይ ባህርዳር የሄዱ ብልፅግናዎች አንዲት ድልድይ ይጎበኛሉ። ቦታው አይቀየር፣ ፎቶ አንሺው ራሱ አንድ ሰው ነው የሚመስለኝ። ጎንደር የሚሄዱት ደግሞ አንድ ከተጀመረ 17 ዓመት የሞላው የማያልቅ መንገድ ይጎበኛሉ። 😂። ኧረ እዳዬ እናንተው። ኮምቦልቻ የሚሄዱት ደግሞ ሁለት ፋብሪካዎች አሉ። እነ አህመዲንን ሲመጡ ዘበኛው ራሱ ሰልችቶት አሉ ለምን እዚሁ እንዳኛ አይቀጠሩም አለ ብለው ሲያስቁኛለሽ ነበር። የሚጎበኘውም፣ ጎብኚዎቹም አይቀየሩም።

"…ወላይታ የመምህራን ደሞዝ መክፈል አቅቶት ሰዉ ሰልፍ ወጥቶ ኧረ የመንግሥት ያለህ ይላል ዴሌሞ ዐማራ ክልል ገባ፣ ጎበኘ ይባልልኛል። ኮምቦልቻ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማው ምን ታስቦ ነው? ማን ሊሞት ነው ደግሞ?

• አይ እነ ገቡ ገቡ… በሉ ቶሎ ውጡ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ስለገባው እኮ ነው።

"…እንዳንተ ፕራንክ እየሠራ፣ እየቀፈለ፣ ቲክቶክ መንደር እየተውሸለሸለ መኖር አቅቶት መሰለህ? ስለገባው ነው በረሀ መውረዱ፣ እንዲህ ላቡን ማፍሰሱም። መጪውን የዐማራን ፍዳና መከራ ከወዲሁ መቀልበስ እንዳለበት ወስኖ ነው እሱ እንደ ሻማ በርቶ ለመጪው ትውልድ ማብራት የፈለገው።

"…የመልኩን ማማር፣ ቁመናውን ዕዪ። የፊቱን ቅላት፣ የደረቱንም ስፋት፣ ጡንቻውንም ተመልከቺ፣ ወንዳወንድነቱን አየሽው አይደል? አዎ ሹገር ማሚ፣ ጨው ማሚ እያለ ቀሚስ መከተል፣ በነውር እያጌጠ፣ እየቀፈለ፣ እፎተተም መኖር አቅቶት ይመስልሻል በረሃ የወረደው? ይሄኔ ይሄን የመሰለ መልክ ይዞ ምን ነክቶት ነው በረሃ የወረደው? ብለሽ በልብሽ ትደሰኩሪ ይሆናል። በረሃ የወረደውማ ለነገው የዐማራ ነፃነት ሲል ነው። ሰማሽ ሹገር ማሚ።

"…ቢራ ገልብጦ መጠጣት፣ ፓርቲ፣ ጭፈራ መውጣት አቅቶት ይመስልሃል? ለአርሰናልም፣ ለማንችስተርም መደገፍ፣ ለቡናና ለጊዮርጊስም መጨፈር፣ ከአበበ ጊደይ፣ ከመንሱር አብዱልቀኒ፣ ከፍቅር ይልቃል እኩል መተንተን አቅቶት መሰለሽ፣ ፋሽን መልበስ፣ መደነስን አጥቶት፣ ቢያንስ ቢያንስ ሥራ ቢጠፋ እንኳ ሰፈር ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ መቀፈል፣ ነውጠኛም ከሆነ ማጅራት መትቶ ቀምቶ፣ ሰርቆ መብላቱ ጠፍቶት መሰለሽ? አይደለም እሱ የመረጠው ዛሬን ሞቶ የነገውን ዐማራ በሕይወት ማኖር ነው።

"…እንደ አንተ ፋኖ የት ደረሰ? ፋኖ ለምን ቆየ? አይመጡም እንዴ? ደብረ ብርሃንን ቢይዙ፣ በሞጆ በኩል ቢመጡ፣ ኮምቦልቻ ቢገቡ፣ ባሕርዳር፣ ጎንደርን ቢቆጣጠሩ፣ ሱዳንን ቢመክቱ፣ ወያኔን ቢያነክቱ፣ ኦነግን ቢደመስሱ፣ እንዲያና እንዲህ ቢያደርጉ እያለ ፌስቡክ ላይ ኮመንት፣ ቲክቶክ ላይ መንቶክቶክ አቅቶት እኮ አይደለም። እሱ የመረጠው አንድያ ነፍሱን ሰጥቶ የነገውን ዐማራ ነፃ ማድረግ ነው።

• ክብር ለዐማራ ፋኖ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ተጋፈጥ።

"…አየህ ትግሉ የት እንደደረሰ? አየህ የጎንደር እናቶች፣ ሴቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች በአደባባይ ቃል ሲገቡ፣ ሻማ እያበሩ ሲማማሉ። አየህ ጎንደሬ የፖለቲካ ነቢያት ማፍለቂያ ምድር ነው። ጎንደሬን በአገኘሁ ተሻገር፣ በመላኩ አለበል አትለካው፣ በጣሂር መሃመድ አትመዝነው። አየህ ጎንደሬ አማኝ ሕዝብ ነው። በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ውስጥ ሆኖ በአደባባይ አገዛዙን እንደሚበቀለው፣ እንደሚደመስሰው እርግጠኛ ሆኖ ይማማላል። ተሸሽጎ እኮ አትደለም። ተደብቆ እኮ አይደለም። እዚያው አደባባይ ላይ እኮ ነው የሚምለው። የሚፎክረውም።

"…ይሄን ጦማር የምታነብ አንተን፣ አንቺን፣ እርስዎን ልጠይቅዎ፣ ልጠይቃችሁ? የት ጋር ነው የቆማችሁት? ትግሉ የት ደረሰ? ምነው ዘገዩ እያላችሁ እንደ ታዛቢ ከዳር ቆማችሁ እየገመገማችሁ ነው? የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶችን ፔጆች እያነበባችሁ በእነሱ ውሸት ተመስጣችሁ እየተንበጫበጫችሁ ነው? በገንዘብ፣ በሞራል፣ በጸሎት እያገዛችሁ ነው? እስቲ ለዚህ ለዐማራነት ትግል ምን አይነት አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ ነው? ከጠላት ጎራ ተሰልፋችሁ ከጠላት በላይ ዐማራን እየሰደባችሁ፣ እያዋረዳችሁ፣ እያብጠለጠላችሁ ነው ወይ? አሁንም በግንቦት 7 ፀረ ዐማራ ድርጅት እየተቀፈላችሁ፣ እየተበዘበዛችሁ፣ ተደናብራችሁ፣ ተወዛግባችሁ ነው ወይ ያላችሁት? ጥገኝነት ለስደት እንጂ ጥገኝነት በፖለቲካ ላይ እኮ ተውሳክ ነው። ከስታሊን ጋር፣ ከሀብታሙ በሻህ ጋር፣ ከኤድመንድ ጋር እኔን እየሰደባችሁ ነው? እያብጠለጠላችሁ ነው? የት ናችሁ?

"…ዐማራ እያሸነፈ ይመጣል። የብራኑ ጁላ መከላከያ ይበተናል። ዐማራ ወደድክም ጠላህም ሕልውናውን 4ኪሎ ገብቶ አረጋግጦ ዘሩን ይታደጋል። 5 ሚልዮን ትግሬን ከኢትዮጵያ ገንጥዬ ሀገር እሁናለሁ ባዩን ገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴም ይደመሰሳል። ራሱ የትግሬ ሕዝብ እነ ደብረፅዮንን በአደባባይ ጎትቶ ይሰቅላቸዋል። መዝግቡልኝ። ኦሮሞን ገንጥዬ እፏላለሁ የሚለውን ደነዝ ዱር ቤቴ የሆነውን ኦነግንም ከጫንቃው ላይ አራግፎ ይደመስሳል። ይሄንንም መዝግቡልኝ። ዐማራ የተባለ ሁሉ በቁጥሩ፣ በወርዱ፣ በስፋቱ፣ በታሪኩ፣ በቁመቱ ልክ ይከበራል። አናሶች፣ ሰፊውን ሕዝብ፣ ታላቁን ሕዝብ በድጋሚ ባርያ፣ ገረድ አድርገው አይበዘብዙትም፣ አይጫወቱበትም፣ አይፈነጩበትም፣ አበደን ዳግም ጥሬ ካካቸውን አናቱ ላይ አይዘፈልሉበትም። የፈለግከውን በለኝ። እንደፈለግከው ስደበኝ። እንደፈለግክ ክፍት ቡሃቃ አፍህን፣ አፍሽን ክፈቺብኝ፣ ዐማራን አታልሎ፣ አጭበርብሮ ዳግሞ ለባርነት ማዘጋጀት አይቻልም። ዐማራ ከእንግዲህ ፋጣሪን ከላይ፣ ክንዱንና ነፍጡን በልጆቹ ላይ አሳርፎ ነፃነቱን ይቀዳጃል።

"…የዐማራ ፋኖ አንድነትም በጊዜው ይከወናል። ያለ ጊዜው የሚሆን ነገር ውብ አይሆንም። ስለዚህ ነገር ጠቢቡ ሰሎሞን እንዲህ ነው የሚለው። “ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤" መክ 3፥11። በጊዜው ለሚሆን ነገር አንዳንዶቻችሁ ከጣሪያ በላይ አትበጥረቁ። በሸዋ ብቻ ከ20 እና 30 በላይ የነበረው የፋኖ አደረጃጀት ወደ ሁለት ወርዷል። በወሎ የነበረው ወደ አንድ መጥቷል። የጎጃምም እንደዚሁ ወደ አንድ መጥቷል። የጎንደርም ወደ ሁለት መጥቷል። ሸዋና ጎንደርም ወደ አንድ ለመምጣት እየተጉ፣ እየሠሩ፣ እየተነጋገሩ ነው። አንድ ባይሆኑም እየተረዳዱ ነው። እየተጋገዙም ነው። እናም የሆነ ቀን አንድነቱ ይመጣል። እስከዚያው ሰካሾች አትሰክሱ። ከፋኖ ትግል ላይ እጃችሁን አንሱ። አንድነቱን በምድር ላሉት ፋኖዎች ተዉላቸው። አይሳካላችሁም እና የሆነ ቡድንና የሆነ ግለሰብ መርጣችሁ ለማንገሥ አትሞክሩ። የዐማራ ትግል ግለሰብ ለማንገሥ እየተደረገ ያለ ትግል አይደለም። እናም ጊዜውን ጠብቁ።

"…መጽሐፍ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤
ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። መክ 3፥ 1-8 አይደል የሚለው። ጊዜውን እንጠብቅ። ጊዜውን እንዋጅ። አንድ ዕዝ ስር መሆኑ ጥሩ ነው። ባይሂኑም እስኪሆኑ እየደገፉ መጠበቅ እንጂ አንድ የማትሆኑ ከሆነ አንረዳችሁም ማለት ዥልጥነት ነው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የጌታን ትንሣኤ ያውጅ ዘንድ የሚጠበቀው 1 ሺ ሰው ሞልቶ እንዲያውም ከዚያም አልፏል። ከምስጋና በኋላ የምንሄደው በቀጥታ ወደተለመደው ርዕሰ አንቀፃችን ነው።

"…የዛሬው ርዕሰ አንቀፃችንም ከዐማራው ትግል ላይ ዓይኑን አያነሣም። እዚያው ነው እኝኝ፣ ችክ ምንችክ የሚለው። የዐማራ ትግል እንዴት ከዜሮ ወደ ሂሮ እንዳደገ የምትመለከቱበት ነው። የዐማራን ትግል የዐማራ እናቶች እንዴት በይፋ በአደባባይ እንደተቀላቀሉት ነው። አውይ ዐማራ እኮ አይወስን ከወሰነ መመለሻም የለው። እሱን እናያለን። እንመለከታለን።

"…የመጀመሪያው ቪድዮ ጎንደር በአርበኛ ናሁሰናይ የኀዘንተኞች ድንኳን ውስጥ የጎንደር የዐፄ ቴዎድሮስ ልጆች የሰማዕታቱን አደራ ከዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ሲገቡ ነው። እንዴት ልብ እንደሚያሞቅ።

"…ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ የዐማራ ትግል እንዴት from zero to hero እንዳደገ የሚያሳየን ነው። ከቆመህ ጠብቀኝ፣ ከክላሽ ማደጉን የሚያመላክት ነው።

"…ሦስተኛው ቪድዮ ባሌ ሮቤ ኦሮሞ ልጁን መርቆ፣ ለእርድ ወደ ዐማራ ክልል ሲሸኝ ነው። ግዳጅ፣ አፈሳ ሊኖር ይችላል። ግን ደግሞ ደስታውም እንዳለ ነው ተመልከቱት። ኦሮሞ ዐማራ ምድር ላይ ጭዳ እየሆነ ነው።

"…የዛሬዋ ርዕሰ አንቀፄ አጠር፣ ቆፍጠን ያለች ነች። ማርያምን እኔ አይሰለቸኝም። በማየው ለውጥ፣ በማየው እድገት ጭራሽ እንቅልፋም ሁሉ እየሆንኩ ነው። ታዲያ ይሄን ስል የዐማራ ትግል ሳንካ የለውም እያልኩ አይደለም። "…ዘእንበለ ድካም ኢይትረከብ ፀጋ" ያለ ድካም ፀጋ አይገኝም አባቴ። ያለፈተና ወጤት፣ ያለ ጾም ፋሲካ የለም። No free lunch ይለኝ ነበር ሱሬ ራሱ እንግልጣር ሲያስተምረኝ።

"…እናስ የዛሬውን ርዕሰ አንቀፅ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከወንድ ጋር ገጥሞ እንዲህ መሸነፍ የአባት ነው። ተፈጥሮአዊም ነው። በጦርነት ውስጥ የሌሉ ህጻናት እና ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የቤት እንስሳትን መግደል ግን አረመኔነት ነው።

"…ወንድ ሱሪ ያጠለቀውን ከከተማ፣ ከመንደር ወጥተህ ከሜዳው ላይ ግጠም። ገጥመህ ከቻልክ አሸንፈው። አሸንፈህም ስትፈልግ ገረድ፣ ባሪያ ሆኖ ይገዛልህ። ውጣና ግጠም አልኩህ።

"…ለጁላ ሠራዊት ዐማራ ቤርሙዳ ሆኗል። እህቱ፣ እናቱ፣ ሴት ልጁ፣ አባቱ፣ ወንድሙ የተደፈረበት፣ የተገደለበት፣ ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ነው የምትገጥመው። ሂድ ሞክረው። ግጠመው አልኩህ።

"…የምትገጥመው ሃቅ ያለው፣ እውነት ያለው፣ ምክንያት ያለው ዐማራን ነው። የአቢይ ሠራዊት ዐማራን የሚዋጋበት ምንም ምክንያት የለውም። ስለዚህ ይሸነፋል። ይደቅቃል። እንደከብትም ይነዳል።

• ፋኖ ንዳው…💪

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ሳምንታዊው የዕለተ ሐሙስ የኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ መርሀ ግብራችን እስኪጀምር ድረስ ጥቂት ደቂቃዎች ይኖሩናል። እስከዚያው ድረስ በርዕሰ አንቀጻችን ላይ የእናንተን ቃል በመቀበል፣ አስተያየታችሁንም በማንበብ እንቆያለን።

• 1…2…3…ጀምሩ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀፅ"

"…ከተማ ሙሉ ሕዝብ ወጥቶ እየጨፈረ፣ እልልል እያለ በጭብጨባ የሚሸኙ የኦሮሞ አዲስ ገቢ ወታደሮችን የጫኑ አውቶቢሶች ከባሌ ሮቤ ተነሥተው ወደ ጦር ግንባር ሲተምሙ በቪድዮ እያየሁ እየተገረምኩ ነበር። እንደ ጉድ ነው የሚገቡት። ሁሉም ነገር እንደምታዩት ነው። እብደቱ ከመጠን በላይ በዝቷል። ከላይም፣ ከታችም ትንኮሳው በዝቷል። እሳትም፣ በረዶም እየዘነበ ነው። ትግሬም ለሰኔ 30 ቀውጢ ለመፍጠር ቀጠሮ ይዞ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው። ሰኔ 30 ካለፈ የሚከተለው ውርደት ቢያስፈራም ነውር፣ ውርደት ጌጧ የሆነው ወያኔም የሆነ ምክንያት ሰበብ ፈጥራ ዕድሜዋን ለማርዘም መጣሯም አይቀርም። ማይክ ሐመርንም ቢሆን መግለጫ ስጥልኝ ብላ ለሐምሌ 30 ዳግም ልትቀጥር ሁላ ትችላለች። መጪውን ክረምት ጠብቆ በትግሬም በኩል ወደ ዐማራ ክልል ለመግባት ሲባል ዉጊያ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። የትናንቱ የአዲአርቃይ ወረዳ የትግሬ ታጣቂዎች በዐማራ ሕጻናት ላይ የፈጸሙት ዘግናኝ ጭፍጨፋም ለመጪው ጊዜ ክፉ ምልኪ እንደሚሆን አመላካች ነው።

"…መንግሥት ሆኖ ሀገር የሚመራው ኦሮሞም መንግሥታዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ በሀገር መከላከያ በኩል ዐማራን ለማንበርከክ የሞከረው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ አሁን መከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የዐማራ አድማ ብተና፣ የዐማራ ፖሊስ እና የዐማራ ሚኒሻን፣ የክልል ልዩ ኃይልና ወታደሮችን ይዞ ያቃተውን የዐማራ ፋኖ ሙሉ ኦሮሞን ንቀል፣ ክተት ብሎ ወደ ዐማራ ክልል ኦሮሞም አንዳንድ ቦታ እየመረቀ፣ እየጨፈረ፣ በሌላ ቦታ ደግሞ እያለቀሰ፣ እየተደበደበ ልጆቹን ወደ ዐማራ ቤርሙዳ እየሸኘ ነው። አሁን ላይ ትግሬ እንድታግዘው የፈለገውም ለዚህ ነው። የሮማ ካቶሊክ እና የጴንጤ እምነት ተከታይ ምዕራባውያ፣ አረቦችና እስላማዊ የውጭ መንግሥታት በሙሉ ከኦሮሙማውና ሂዊ ጎን መቆማቸውም የታወቀ፣ የተረዳ ነው።

"…ዐማራስ?

"…ዐማራማ ገራሚ ፍጥረት ነው። ዐማራማ ብቻውን በእሾህ መሃል እንደ በቀለ ፅጌረዳ አበባ ለተመልካች ዓይን እንጂ ለመቀጠፍ የማይመች ሆኖ ተገልጿል። እንደ ገና ዳቦ ከላይ እሳት፣ ከታችም እሳት እየነደደበትም ቢሆን ከላይ ከፈጣሪ ከታችም ነፍጡን ይዞ ለመመከት አልፎም ለማነከት ተነሥቷል። ከላይ ከፈጣሪ በምድር ከነፍጡና ከእውነቱ እና ከሃቁ በቀር ምድራዊ አድናቂ እንጂ ምድራዊ ደጋፊ የሌለው ዐማራ ያለምንም የውጭ እርዳታ ነገሩን ሁሉ በፈጣሪ እርዳታና በልጆቹ ክንድ እየመከተ፣ እያነከተም ድል በድል ላይ ደራርቦ ከዚህ ደርሷል። የሚጠራው ሁሉ እየጠራ ነው። የዐማራ ትግል ወደ ኋላ ላይመለስ ወደፊት መስፈንጠሩን ቀጥሎ ሁሉንም እያስደመመም ነው። "ዘራፊው ኃይል፣ ፅንፈኛው ኃይል፣ አሸባሪው ብድን" የሚለው ለዐማራ ፋኖ የተሰጠው ቅጽል ስምም በይፋ በኃያሏ አማሪካ ጭምር "የዐማራ ፋኖ" ተብሎ በክብር ስሙ ተጠርቷል። የታጠቀ፣ ጫካ የገባ የሚለውም ስድብ ቀርቷል። ወረዳ፣ ዞን እና ከተማ እያስተዳደረ የምን ጫካ ነው?

"…አሁን ወደ 5% የሚሆነው ዐማራ የመጣበት አደጋ እንዳለ ገብቶት ያን የመጣበትን አደጋ ወደ መቀልበሱ ገብቷል። ዐማራ ሆኖ አሁን አሁን በቲክቶክም ሆነ በፌስቡክ ቧልት የሚያወራ አልገጠመኝም። ሁሉም በገባው መጠን ልክም ሆነ አልሆነ ስለትግል፣ ስለፋኖ፣ ዘሩን ስለማዳን እያወራ ነው። ዛሬ ላይ ትንሽ ዝብርቅርቅ ቢልም እየዋለ ሲያድር ግን እየጠራ ይመጣል። መረዳታቸውም ከፍ ይላል ብዬ አምናለሁ። የዐማራ ቲክቶከሮች፣ ዩቲዩበሮችም ሁሉ አሁን ከበፊቱ ንዝህላልነታቸው እየወጡ ንቁ እየሆኑ ነው። መከራው በየቤታቸው ገብቶ ምዝልግ ሲደረጉ፣ መከራው በደጃፋቸው አልፎ ሳሎናቸው ውስጥ ሲገባ ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ቢሆንባቸውም አሁን አሁን ነቃ ነቃ ማለት ጀምረዋል።

"…እነ ኢትዮ 251፣ እነ ባህርዳር ዊኪሊክስ፣ እነ በለጠ ካሣ፣ እነ ሉሲ ድንቅነሽ፣ እነ ፋኖ ዋልታ፣ ኧረ ስንቱን ልጥቀስ የሚደንቁ፣ የሚገራርሙ መረጃ ሰጪዎች መጥተዋል። ኢትዮ ፎሮም እንኳ ከእነ በለጠ ካሣ መረጃ ግልብጥ አድርጎ ወስዶ ለትግሬ እያለቀሰ እንጀራውን እንዲገፋ አድርገውታል። ዐማራ ሳይበሩንም መቆጣጠር ጀምሯል። አዎ ዐማራ የተኛውን ያህል አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንደ ትግሬና ኦሮሞ ባይነቃም በነቁት ልጆቹ ግን ገራሚ ሥራ እየሠራ እንደሆነ ይሰማኛል። እኔ ዘመዴም እያረፍኩ ነው። እኔም ሸክም እየቀለልኝ ነው። አዎ ዐማራ ዐማራ መሽተት ጀምሯል። ዐማራ ዐማራነቱን ማስመስከር፣ ማሳየት ጀምሯል። እየተደመምኩበት ነው። ዐማራ እስኪግል፣ እስኪፈላ፣ እስኪፍለቀለቅ ድረስ ነበር ማገዶ የሚፈጀው እንጂ ከጋለ ወዲህ መመለሻ፣ ማብረጃም እንደሌለው ይታወቃል። እየሆነ፣ እየተመለከትን ያለውም እሱ ነው።

"…መሬት ላይ ያለው ከሚጠበቀው፣ ከሚገመተው በላይ ነው። መሬት ላይ ያለው እንደ ማዕበል የገነፈለ፣ የተጠለቀለቀ የታጋይ ጎርፍ ነው የሚታየው። በዚህ ሱናሚ መካከል ተፈጥሮአዊ የሆኑ ጥቃቅን ልዩነቶች ይኖራሉ። እሱንም ቢሆን በጥበብ መፍታት ነው። የዐማራ ጋዜጠኞች ወደ አንድነት ለመምጣት ሲሽኮረመሙ እያየሁ ነው። እንደዚያ ነው እየሆነ ያለው። አሁን በአየር ላይ ሆኖ የዐማራን ትግል ማጠልሸት አይታሰብም። አይሆንምም፣ አይቻልምም። በጭራሽ። አየር ላይ አንዱን አንግሠው ሌላውን ፋኖ በድፍረት የሚያጠለሹ፣ የሚሳደቡ፣ ከማቀራረብ ይልቅ ለማራራቅ የሚጥሩ ቲክቶክ ላይ 24 ሰዓት እንደ ሞጣ ተዘፍዝፈው የሚቀመጡ ግንባራም ልጆች ቢኖሩም እነርሱም ባትሪአቸው ሎው እያለ ነው። በቅርቡ ቻርጅ ዘግተው ይጠፋሉ። የግል ፋኖ አምራቾችም ቁርጣቸውን እያወቁ መጥተዋል። አንተ ስንት የግል ፋኖ አለህ? እየተባባሉ በዋሽንግተን ዲሲ ጎዳናዎች የሚፎጋገሩ ጋንግስተሮችም አሁን አደብ እየገዙ መጥተዋል። ለዐማራ ፋኖ እየተባለ በሕገወጥ መንገድ ከዐማራ ላይ ትግሬ ሚስት ያላቸው የዐማራ ባሎች የሚሰበስቡት ገንዘብም አሁን ነጥፏል። ምንጩም ደርቋል። ራሳቸው ምድር ላይ ያሉት ፋኖዎች"በእነ እገሌ በኩል ብር ላኩልን" ማለት ጀምረዋል። እሺ እኛስ ምን ሠርተን እንብላ ይሉ የነበሩ ቀፋዮችም ኡበር ሠርታችሁ ብሉ ተብለዋል። በሕገወጥ መንገድ ለግለሰብ የሚሄደው ብር ሲቆም መሬት ላይ ያለው የግዱን ሥርዓት ይይዛል። ልክም ይገባል። አለቀ። ምድር ላይ ያለውን ፋኖ የሚከፋፍለው የግል ፋኖ ደላላ ከአሜሪካ ለግሉ ተሰብስቦለት የሚሄደው ፈራንካ ሲነጥፍ እርሱም ፀባይ አሳምሮ ትግሉን ብቻ ይታገላል።

"…አሁን ከዐማራ በኩል የሚቀረው እንደ ትግሬ ነፃ አውጪዋ ወያኔና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪው ኦህዴድና በፖለቲካው በኩል ኦነግ ጨካኝ፣ አረመኔ መሆን ብቻ ነው። እሱ ብቻ ነው የሚቀረው። ዐማራ ቆፍጠን፣ ኮምጠጥ ማለት ከጀመረ ሁሉም ነገር ያበቃል። ይሄ ተግተልትሎ የሚገባውን ወራሪ ጦር በፈሪሀ እግዚአብሔር፣ ባህታዊ ባህታዊ በመጫወት አለመቅለስለስ። ቆፍጠን፣ ኮምጠጥ ማለት። አለቀ። ሊያርደው እየፎከረ የሚመጣውን ወራሪ የምን እሹሩሩ ነው? የምን ወንዲሜ፣ ኢሂቴ ብሎ መሽለጥለጥ ኖ። አርዶህ፣ ደፍሮህ፣ ከብትህን ሳይቀር የጨፈጨፈን አራዊት የምን ትኩስ እንጀራ አቅርቦ መቀለብ ነው? በቃ ውጊያ ላይ ለመማረክ አለመዋጋት። ጣጣውን ሁሉ እዚያው በውጊያ ላይ መጨረስ አለቀ። ተኩሶ፣ ተኩሶብህ ጥይት ሲጨርስ የተማረከው ሁሉ ምርኮኛ አይመስለኝም። ጥይት ጨረሰ እኮ በቃ። እና ምን እንዲሆንልህ ፈለግክ? እህዕ…👇 ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።” ፊል 3፥10-11

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጋዜጠኛ በለጠ ካሣ ይሄን ዘግቧል።

"…ከትግራይ ደብረ ዓባይ ተከዜን የተሻገሩ የህወሓት ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር አዳርቃይ ወረዳ አሌ በተባለ ቦታ አሰቃቂ የንፁሃን ጭፍጨፋ ፈጽመዋል።

"…ከአርሚ 11 በጀኔራል ወርቃይኑ የተላኩት ታጣቂዎች አራት ሕፃናትን እሳት ውስጥ በመጨመር አቃጥለዋል። 11 ሰዎችን በጥይት ደብድበው ገድለዋል። 17 ሰዎችን አፍነው ወስደዋል። 27 መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል። 534 የቁም ከብቶችን ዘርፈዋል። 1478 ሰዎች እንዲፈናቀሉ አድርገዋል። ከ40 በላይ ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም።

"…የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የፀጥታ አካላት ወደ ቦታው ደርሰው ያጣሩት መረጃ ነው። ታጣቂዎች ተጨማሪ ኃይል ከትግራይ ወደ ዋልድባ በኩል ተከዜን እያሻገሩ ነው። ግንቦት 27/2016 ዓም በማለት በቪድዮ የተደገፈ መረጃ አቅርቧል።

"…በመቀሌ የዘፈን አይዶል ውድድር የሚያደርገው ትግሬ የሱዳን ዘፈን አድንቆ ከራያ የመጣ ተወዳዳሪ በአማርኛ ስለዘፈነ ለምን ብለው ዳኞቹ ጓ ያሉበትን ስታይ ምን ያህል በዐማራ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው ነው የሚያሳየው። ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው። የህወሓት ሰዎች ጋር ሲደርስ ግን ሙዚቃ ራሱ ጠቦ ጠቦ ትግሬ ብቻ ይሁን ብለው ግግም ይላሉ። እና የዐማርኛ ሙዚቃ ተወዳዳሪ አንሰማም ያሉ ሰዎች በወልቃይት አማርኛ ዘፈን የከፈተ፣ በአማርኛ የሚነጋገር ሰው ይገድሉ ያስሩ የነበሩ ሰዎች አሁንማ ዐማራውን እንዲህ ጨፍጭፈው ቢጨርሱት ደስታቸው ነው።

"…የትግሬ ነፃ አውጪ ሆይ ብታርፊ አይሻልሽም። ይሄን አይተው ቢያጨበጭቡልሽ የኦሮሞ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ብቻ ናቸው። መከራ በራሳችሁ ላይ ባትጠሩስ? አሁን ይከብዳችኋል። አትሞክሩት። በእጥፍ የሚመልስ ትውልድ ነው የተፈጠረው።

• ዐማራን ማረድ በጎንደር በኩል ወያኔ ጀመረችው ማለት ን ። እንግዲህ ሥራሽ ያውጣሽ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel