መልካም…
"…በመቀጠል ደግሞ ይሄን የሳምንቱ መጨረሻ እና እስከአሁን 13 ሺ ሰዎች አንብበውት 12 ፍሬ ሰዎች ብው 😡 ብለው የተናደዱበትን የዕለተ አርብ ርእሰ አንቀጻችንን በእናንተ ደግሞ የጉደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ቀንቶ፣ የበዛው ምልከታ ተቀንሶ በዚያ ባመረ ብዕራችሁ በጨዋ ደንብ እንደ ጅረት ወንዝ ኩልል ብሎ ወደሚፈሰው አስተያየታችሁ እናልፋለን።
"…1…2…3 ✍✍✍ ጀምሩ
👆③ ✍✍✍ …ለመቅበር ቢሞክሩም ግን ይኸው መደበቅ፣ መሸሸግ አልተቻለም። ሽንፈታቸው ፈንቅሎ እየወጣባቸው ነው። ውስጥ ውስጡን በልቶ፣ በልቶ የጨረሳቸው ፋኖ አሁን ገርስሶ ሊጥላቸው ከጫፍ ደርሷል።
"…የዐማራ ፋኖ ትግል በዳንኤል ክብረት ተረት፣ እርግማን ጭምር አልፈረሰም። የላካቸው ጠንቋዮች ሳይቀሩ በፋኖ እጅ መውደቃቸው ነው የተነገረው። ሱፍ ለብሶ፣ በሜካፕ ተብለጭልጮ፣ የባህርዳር ስታዲየምንና ድልድዩን፣ የጎንደርን የፋሲል ግንብ፣ የኮምቦልቻ ሁለት ፍሬ ፋብሪካ፣ የደብረ ብርሃን መጋዘን ተመላልሶ በመጎበኘት፣ በሂሊኮፍተር ቦታው የማይታወቅ ምናልባትም ኦሮሚያ አርሲ ሊሆን ይችላል የስንዴ ማሳ ውስጥ በመቆም ሰላም ነን፣ ምርታማ ሆነናል በማለት በመደስኮር የሚሚጣ ለውጥ የለም። ዐማራ ነው ነገዱ። ዐማራ አይጀምር እንጂ ከጀመረ በኋላ ሳይቀብርህ አይመለስም። ልትጨፈጭፈው፣ ልታወድመው ትችላለህ። ጭፍጨፋውን እንደ መቀስቀሻ፣ እንደ ቤንዚን ተጠቅሞ ግን ቆረጣጥሞ ይበላሃል። ያወድምህሃል። ዐማራ ሳያሸንፍ አበደን ወደ ኋላ የለም። ንቀውት ስለጀመሩ እንዴት እንዋረዳለን ብለው ነው እነ ማይሙ አቢይ አሕመድ ሀገር ቁልቁል በአናቷ እየተከሉ የሚገኙት።
"…በሌላ በኩል የዐማራ ፋኖ አንድነት ከምንግዜውም በላይ አየጠራ መጥቷል። በተለይ በጎንደር አባት አርበኞቹ "ጎንደር ሆይ ሚናህን" ለይ ዐዋጅ ካወጁ በኋላ በጎንደር ትርምስ ነው የተፈጠረው። በዚህ በኩል ነገ የምነግራችሁ አዲስ መረጃ ይኖረኛል። የጎንደር ዕዝ ስር የነበሩ በወልቃይቱ ደመቀ ዘውዱ ከጀርባ ይዘወሩ የነበሩ ከ300 በላይ ፋኖ ነን ብለው የነበሩ ጉደኞች ከአባት አርበኞቹ መግለጫ በኋላ በቀጥታ እጃቸውን ለብልፅግና ሰጥተዋል። ጎንደር እየጠራ ነው። እነ ዶክተር አምሳሉ ዶላሩን እንዴት እንደተጫወቱበት አሳያችኋለሁ። ሰሞኑን በዐማራ ቴሌቭዥን እጅ ሰጠ የተባለው ሰውን ጨምሮ ከመጀመሪያው በእነ ስኳድ የደመቀ ዘውዱ ጓርድ ፋኖን ተቀላቀለ ሲባል የትኛው የጎንደር ፋኖ ስንል የሀብቴ ወልዴን ሲሉን፣ አይ እሱማ ጀርባው ሌላ ነው ስንል የተሰደብነውን ታስታውሳላችሁ? አዎ ያ የደመቀ ጋርድ የወልቃይትና የፀገዴ ተወላጅ ብቻ የሆኑ ፋኖ መሳይ ቀፋይ የስክንድር ነጋው ድርጅት የሀብቴ ወልዴን ልጆች ይዞ ወደ ብልጽግና ተቀላቅሏል። ተመልከቱ ጎንደርን ብቻ ሳይሆን ዳያስጶራውን እንዴት አድርገው እንዳከሰሩት። 300 ፋኖ ዝም ብሎ ሲቀለብ፣ በሚልዮን በሚቆጠር ብር መሣሪያ ተገዝቶ ተሰጥቷቸው አሁን የቁርጡ ቀን ሲመጣ ጎንደር በአባት አርበኞቹ የማንቂያ ደወል ሲነቃ የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ ተንጋግተው ወደ ብአዴን ብልፅግና ከነመሳሪያ፣ ከነ ተተኳሻቸው ገቡ። ሙሉ መረጃ ነው ያለኝ። አሁን ሲሳይ ወስኗል። ረባሹ አንተነህ፣ የእስክንድር ቅጥረኛ መውጫ ነው ያጣው፣ ሀብቴ ወልዴ ሦስት አማራጮች ቀርበውለታል። ሠራዊቱም ወደ አባት አርበኞች እና ወደ እና ባዬ ቀናው እየተመመ፣ እየተቀላቀለ ነው። ደሬ የምወደው ደረጄ በላይም ከእስክንድር መለየቱን ሊያውጅ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሰሞኑን በነበረው ግምገማ የእኔም ስም በሠራዊቱ በኩል ተነሥቶ "መምህር ዘመዴ የተናገረው በሙሉ ዓይናችን እያየ ተፈጽሟል። አሁን ምክንያት መደርደሩን ትተን በዳያስጶራ ላይ የተንጠለጠለውን ትግል ትተን ጎንደሬ የጎንደር ዐማራ ሆነን፣ እንደ ዐማራ እንታገል ወደሚል መም ታቸውን ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያሳየው። የጎንደር ጉዳይ ሊጠራ ጥቂት ሰከንዶች ናቸው የቀሩት።
"…እንዲያም ሆኖ፣ እስክንድር ነጋ የዐማራን ትግል በፍጥነት እንዳይሄድ፣ እንዳይራመድ ሰቅዞ ይዞ፣ የጎንደር ስኳድ የፖለቲካው ቅማንት በትግሬ ዲቃሎች ተተብትቦም ቢሆን ጎንደር ከእስራቱ፣ ከድግምቱ፣ ከተዋለበት መተት እየተፈታ ነው። ሸዋም ነቅቷል። ወሎም ከጫፍ ደርሷል። ጎጃም ስለጎጃም ምን ይነገራል። የውጩ መርገምት እነ እስክስ አበበ በለው ፈስቶባቸዋል። የእነ ሀብታሙ አያሌው ፖለቲካም ከሽፏል። እነ ኤርሚያስ ዋቅጅራ የሚመሩት የዐማራ ፋኖ ትግል አሁን ላይ የለም። ዲቃሎች፣ የዐማራን ትግል አንቀው የያዙ መርዘኞች ከገንዘቡም፣ ከመሪነቱም ሥፍራ እየፈረጠጡ ነው። የዐማራ ፋኖ ቢቀረውም ውስጡን እያጠራ፣ እየታገለም፣ እያሸነፈም፣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። የዐማራ ፋኖ ባዶ እጁን ጀምሮ የሀገሪቱን አገዛዝ የገንዘብ ያለህ እያስባለው ነው። የዐማራ ፋኖ ትግል ኦህዴድ ብልፅግናን ከልጁ ከኦነግ ሸኔ ጋር እንታረቅና አንድ ሆነን ዐማራን እንውጋው እያስባለው ነው። የኦሮሙማው መንግሥት አጀንዳዎቹ በሙሉ አልቀው የቀረው እንደ ሩዋንዳው የሆነ ትልቅ ስም ያለው ኦሮሞ ገድሎ በዐማራ ላይ ሙሉ በሙሉ በሚሊዮኖች ለመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ዐዋጅ በሚዲያ ማወጅ ብቻ ነው። ይሄ ነው የቀረው። እሱን እየሞከረ ነው። የፈጣሪ ሥራ ሆኖ በደራ የፈጸመው የእርድ ድራማ በራሱ በኦሮሞዎቹ ነበር የከሸፈው። በዚህም ብልፅግና አብዷል። ጨልሏል። የጠበቀውን ግብረ መልስ አጥቷል። የሆነው ሆኖ ዐማራው በደንብ ነቅቶ መዘጋጀት አለበት።
"…ኦሮሞ ብቻ ለምን ይታፈሳል? ለምን ኦሮሞ ብቻ ወታደር ሆኖ ይሞታል? ሌላውስ ለምን አይዘምትም የሚል ጫና በመብዛቱ ምክንያት ከደቡቦች ቀጥሎ አሁን ደግሞ ከዚያው ከዐማራ ክልል ከደቡብ ጎንደር በብዛት፣ ከቀወት ወረዳ በግዳጅ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ የዐማራ ሥራ ያለውም፣ ተማሪና ሥራ አጡን ሁላ በማፈስ ወደ ወታደር ማሠልጠኛ ጣቢያ መውሰድ ማጋዝ ጀምረዋል። የደነገጠ ፊት ያላቸው ምስኪን ሴቶች ሁላ ናቸው እየተጋዙ ያሉት። ይሄም አያድነውም። ለዳንኤል ክብረት ቅርበት ያለው አንድ የጋራ ወዳጃችን እንዳጫወተኝ ከሆነ አሁን ከዐማራ ክልል በግዳጅ የታፈሱት ወታደሮች ተመልሰው ወደ ዐማራ ክልል የሚዘምቱ ሳይሆን ወደ ዐማራ ክልል ዘምተው የተዋረዱትን የኦሮሞ ወጣቶች ለማካካስ ኦነግ ሽሜ ወዳለበት የኦሮሚያ ክልል ተመድበው ገሚሱ እንዲገደል፣ ገሚሱ ደግሞ ከየት ነው የመጣኸው እያሉ ራቁታቸውን እየቀረጹ ለማዋረድ እንደሆነም ሲናገር መስማቱ ተሰምቷል። የፈለገ ይሁን የፈለገ፣ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ፣ የፈለገው ሀብትና ንብረት የሰው ሕይወትም ይቀጠፍ፣ ዐማራው እንደሰው ለመቆጠር፣ ለህልውናው ሲል በሃቅ ላይ የተመሰረተው ትግሉ በድል ይቋጫል። የእነ እስክንድር፣ የፖለቲካው ቅማንት፣ የአገው ሸንጎው የትግሬ ዲቃሎቹ ሴራም ይከሽፋል። ዐማራ አሳምሮ፣ አሳምኖ ያሸንፋል። ሀገረ መንግሥቱንም ከውርደት፣ ከውድቀት ይታደጋል። ማርያምን እውነቴን ነው። ዐማራ ያሸንፋል።
"…የብልፅግና ወንጌል የጴንጤዎቹ ድንፋታ፣ ስድብ፣ ርግማን ዐማራን አያስቆመውም። የብልፅግና ወንጌል ከሳዑዲ ተባርረው አፍሪካን እንዲያተራምሱ የተላኩት የኦሮሞ የወሃቢይ እስላሞች ዛቻና ጉራም ከመንገዱ አያስቀረውም። የፈለገህን ዛት፣ የፈለገህን የቦንብ ናዳ አቅርድ፣ የፈለገህን ጨፍጭፍ ከመሸነፍ አታመልጥም። አትድንምም። የዐማራ ፋኖ ትግል ሰዉን ሁሉ ዐመዳም፣ ግርጣታም፣ ጭንቀታም አድረጎታል። የዐማራ ፋኖ ትግል አገዛዙን ለኪሳራ ዳርጎ ዳቦ 15 እንጀራ ደረቁ 40 ብር እንዲሸጥ አድርጎታል፣ የዐማራ ፋኖ ትግል ጤፍ እንደ ሜሪኩሪ እንዲቆጠር፣ ሥጋን ባለ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ብርቅ ምግብ እንዲሆን አድርጎታል። የዐማራ ፋኖ ትግል አገዛዙ ማሳ ለማሳና በመናፈሻዎች ውስጥ ስለ ልማት፣ ስለ እድገት እንዲለፈልፍ አስደርጎታል። የዐማራ ፋኖ ትግል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግር፣ ጭንቀት እንዲቆነጥጠው አስደርጎታል። የዐማራ ፋኖ ትግል የዘወትር የኢትዮጵያ ዜና ከመሆን አልፎ የኦሮሞ ተማሪዎች አደባባይ ወጥተው ፋኖ፣ ፋኖ፣ ፋኖ እያሉ…👇③✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…የሚጠይቅ ባይኖርም እውነታው ግን ይኸው ነው። ከመስከረም 2017 ዓም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ይከፈላል የተባለው የደሞዝ ጭማሪ ወርሀ ህዳር ገብቶ ወርሀ ታህሳስ ቢመጣም ወፍ የለም። ምክንያቱም ገንዘብ የለማ። ቦንብና ጥይት ተገዝቶበት አልቋል። አይደለም የሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በደቡብ ክልል አገዛዙ ያችኑ አነሥተኛ ወርሀዊ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ መምህራን የማስተማር ተግባራቸውን አቁመው ቤታቸው መቀመጥ፣ የቀን ሥራ መሥራት ከጀመሩ ወራቶች ተቆጥረዋል። ገንዘቡ ቦንብና ጥይት ተገዝቶበት ደሞዝ ከየት ይምጣልህ? የትግራዩ ክልል ጦርነት ቢያንስ የኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነበረው። ዳያስጶራው ሳይቀር ዶላር አዋጥቶ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ለአገዛዙ ገቢ በማድረግ ይደጉም ነበር። ክልሎችም እንዲሁ በሃላል ገንዘብም፣ ወታደርም ያዋጡ ነበር። ድርቆሽ፣ በሶ፣ በሬ፣ በግ እያዋጡም አገዛዙን ያግዙ ነበር። ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች በይፋ ጦርነቱን ይደግፉ ነበር። በተለይ የዐማራና የአፋር ክልሎች በጀታቸው ሳይቀር ለቆሰሉ ወታደሮች ህክምናና ማገገሚያ ይውል ነበር። አሁን ግን ወፍ የለም።
"…አንድ ትሪልዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለ2017 ዓም ዓመታዊ በጀት አጽድቆ ገና በሦስተኛ ወሩ ተጨማሪ በጀት ያስፈልገኛል በማለት አምስት መቶ ቢልዮን ብር ጨምሮ አንድ ነጥብ አምስት ትሪልዮን ብር አጽድቋል ትናንትና። ይሄንንም በወሩ ይጨርስና ምን እንደሚሆን አብረን እናየዋለን። ከኮሪደር ልማት ተብዬው ብልጭልጭ የታይታ ፕሮጀክት በቀር የማኅበረሰቡን ዕድገት ከፍ የሚያደርግ፣ የኑሮውንና የጤናውን ሁናቴ የሚያሻሽል ፕሮጀክቶች በሌሉበት፣ እንደ መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የመስኖ፣ የኃይል ግድቦች፣ በግብርናው ላይ የተያዘ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሳይኖሩ፣ አዳዲስ ፋብሪካዎች ተከፍተው የሥራ አጡን ቁጥር ለመቀነስ ሙከራ ሳይደረግ በባዶ የበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት ሳይፈጸም ተጨማሪ በጀት መጠየቁ ከምን የመነጨ ይመስልሃል። መልሱ የዐማራ ክልሉ ጦርነት እጅግ ከባድ መሆኑን ያሳይሃል። ይነግርሃል።
"…ማመን ያለብህ አባዬ የዐማራ ክልሉ ጦርነት የአብይን አገዛዝ የገንዘብ በጀት አከርካሪውን ሰብሮታል። እንቁሽቁሹን ነው ያወጣው። በበጀቱ የመከላከያውን ዓመታዊ በጀት በእጥፍ ጨምሮታል። ግዙፍና ውድ ወታደራዊ ማጓጓዣ አይሮፕላን ገዝቷል፣ ከዓረቦቹ ሶማሌና ሱዳን ላይ ላይተኩስ ፈርሞ ለዐማራና ለሀገር ውስጥ ሕዝብ መጨፍጨፊያ ብቻ አስገዳጅ ውል የገባበትና የፈረመባቸውን ድሮኖቾ ከነ ተተኳሻቸው በውድ ዶላር ገዝቷል። ሁለትና ከዚያ በላይ ሄሊኮፕተር፣ አዳዲስ ሞርታሮች፣ ወታደራወዊ ቁሳቁሶችን ገዝቷል። የድሮን ባለሙያዎቹ ዓረቦች፣ ቱርኮችና ነጮች ደሞዝ የሚከፈላቸው በዶላር ነው። አንድ ድሮን ለአንዴ አንዲት ነፍሰጡር ለመግደል ሲል ዓየር ላይ ለሚቆየው የሚወጣው ወጪ ከባድ ነው። የሚወረውረው ቦንብም በሚልዮን የሚቆጠር ብር ነው የሚፈጀው፣ ወታደራዊ ጀነራሎቹ፣ አመራሮቹ የሚጠቀሙት ሄሊኮፍተር ወጪው ከባድ ነው። አዳራቸው አዲስ አበባ ስለሆነ በምልልሱ ወጪው አደገኛ ነው። ከበድ ነው።
"…አጅሬው IMF በለቀቀለት ብድር ወዲያው የጦር መሳሪያ ገዝቶበት ብሩን ጨርሶታል። ያለ ውጤት በግዳጅ እያለቀሰ ወደ ፋኖ ግንባር የሚሄደው የወታደሩ ሆድም የሚቻል አይደለም። ለዚህም ነው በግልጽ ዐማራን ዘርፈህ ብላ የተባለው። ወታደሩ በብድር ተገዝቶ የመጣውን መሣሪያ እንዳንከረፈፈ ነው ወደ ፋኖ በምርኮ የሚጋዘው። ይሄም ለአገዛዙ ኪሣራ ነው። ከባድ ኪሳራ። የዐማራ ክልል ቀረጥ፣ ግብር ገቢ ወደ ፌዴራል መንግሥቱ አይሄድም። ጤፉ፣ በቆሎው፣ ገብሱ እንደበፊቱ ለገበያ ከክልሉ አይወጣም። ይሄ ሁሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን አስወጥቶታል። በትግራይ ጦርነት ደመወዝ መክፈል ያላቃተው መንግሥት አሁን በዐማራ ክልሉ ጦርነት ካዝናው የተንቆሻቆሸ ባዶ በመሆኑ ለሠራተኛው የሚከፍለው ብር አጥቷል። በደቡብ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ደሞዝ ከተከፈላቸው ወራት ተቆጠሩ። አዲስ አበባም መዘግየት፣ በዐማራ ክልልም አንዳንድ ቦታ ላይ መክፈል አቁሟል። ጦርነት ይሄው ነው ትርፉ። በተለይ ሀገር በአርቲስት ስትመራ፣ ሀገር በማይም ስትመራ፣ ሀገር በኮሜዲያን ስትመራ፣ ሀገር በካድሬዎች ስትመራ ውጤቱ አሁን የምናየው ነው የሚሆነው።
"…የሩሲያንና የዩክሬንን ጦርነት እንመልከተው። ሩሲያ ኃይል ሀገር ስለሆነች፣ የተፈጥሮ ሀብትም፣ የጋዝ ክምችትም ስላላት፣ ሕዝቧ ጦሙን ባያድርም በሩሲያም ቢሆን ኑሮው ከባድ እኮ ነው እየሆነ ያለው። የዩክሬን ደግሞ ይብሳል። የዩክሬን ሕዝብ በመላው አውሮጳ ስደተኛ ሆኖ ተበትኗል። ሀገሪቷ ወድማለች። ሙሉ አውሮጳ፣ አሜሪካም ዩክሬንን በመደገፍ፣ በማገዝ ያፈሰሱትን ዶላር ሰምታችኋል። ዩዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት በዩክሬንና በሩሲያ ሕዝቦች ላይ ብቻ ተጽዕኖ ፈጥሮ አልቀረም። ኃያሏ አሜሪካን ጨምሮ መላው አውሮጳ ላይ የዋጋ ጭማሪ ነው በኑሮ ላይ የፈጠረው። ከሁለት ዓመት በፊት ባለሁበት ሀገር የነበረው የወተት ወጋ ዛሬ በቦታው የለም። ሱፐርማርኬቶች በዋጋ ጭማሪ ተጥለቅልቀዋል። የጦርነት ወላፈኑ እንዲህ ነው። የምድራችንን ከፍተኛ የምግብ ፍጆታ ትሸፍን የነበረችው ስንዴ አምራቿ ዩክሬን ጦርነት ላይ ስለሆነች በተለይ ደሀ ሀገራት ወላፈኑ እየጠበሳቸው ነው። እንግዲህ ኃያላኑን ሀገራት ጦርነት እንዲህ ከነቀነቃቸው እኛ መናጢ ደሀዎቹን እንዴት አድርጎ አይንጠን? አያንዘፈዝፈን። አራግፎ ነው የሚጥለን።
"…ዶላር ከ56 ብር ምንዛሬ ወደ 123 ብር የገባውና ሀገሩን የነቀነቀው ተዛብቶም ሀገር ያዛባው በዐማራው ክልል ጦርነት ነው። የአቢይን ያለቅጥ የተለጠጠ ተስፋና ህልም ያጨለመው የዐማራው ክልል ጦርነት ነው። አቢይ ሁልጊዜም ምነው በዐማራ ክልል ጦርነት የጀመርኩበትን እጄን በቆረጠው እያለ እጁን እየነከሰ እንደሚውል አልጠራጠርም። ሰውዬው ሓሳቡ፣ ዕቅዱ እኮ ረጅም ነበር። ኤርትራን አስገብሬ፣ አሰብን በቁጥጥሬ ስር አድርጌ፣ ቀይ ባህር ላይ ባህር ኃይል አቋቁሜ፣ ወደብ ያስመለሰ መሪ ተብዬ፣ በቀጠናውም በዓለምም ፈላጭ ቆራጭ ተጽእኖ ፈጣሪ ተብዬ፣ በሕዝቤ ተከብሬ ተዘክሬ፣ በአዲሱ ቤተ መንግሥቴ ያለ ምንም ኮሽታ ሀገሩን ሰጥ ለጥ አድርጌ ረጅም ዘመን እገዛለሁ ነበር ህልሙ። ነበር ሆኖ ቀረ እንጂ። ዐማራ ታሊባን ሆነበትና በቃ ህልሙን፣ ምኞቱን ሁሉ እንዳይሆን አድርጎ አጨቀየበት። መና ከንቱ አድርጎ አስቀረበት። ይኸው ዛሬ አቢይ አሕመድ ቤት እየቀያየረ የሚያድር፣ ዓይኑን ስታዩት ራሱ እንቅልፍ የራቀው፣ በእንቅልፍ እጦት የተጠቃ፣ ዓለምም አፍሪካም የናቀውና ያኮሰመነው ተራ መሪ ሆኖ ቀርቷል። እና የዐማራ ክልሉ ጦርነት ሰውየውንም አገዛዙንም ኪሶቹ ተቦጭቀው እስኪበተኑ ድረስ እጥብ ነው ያደረገው። ሙልጩን ነው ያወጣው።
"…ከህዳር በኋላ ደግሞ ይብስበታል። ኑሮው ሁሉ አሁን ካለበት እጥፍ ይጦዛል። ከቲክቶከር፣ ከካድሬ በቀር ሌላው ጨርቁን ጥሎ ያብዳል። አገዛዙ ከአሁኑ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል ካቃተው በቅርቡ ከአሁኑ የበለጠ ሁሉ ነገር ይጦዛል። ሕዝቡ ሽንታም፣ ፈሪ፣ በጭባጨ መሆኑ ስለታየ ይጨመራል የተባለው የደሞዝ ጭማሪ የውኃ ሽታ ሆኖ ይቀራል። በዛሬው ዕለት እንኳ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከ10 ብር ወደ 20 ብር መጨመሩ ታውጇል። ሁሉ ነገር ይጨምራል። መምህራን ማመጽ፣ ሀኪሞች ሥራ ማቆም ጀምረዋል። በመርካቶ፣ በንግድ ሱቆች ላይ እሳት እየለኮሰ፣ ለሳርና ለብሽክሊሊት መሄጃ ብሎ ከፒያሳ እስከ መገናኛ በካሳንችስ ያወደማቸው የንግድ ድርጅቶች፣ በንግድ ድርጅቶቹ…👇① ✍✍✍
"…እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል። የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ። ኢሳይ 41፥ 10-12
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉YouTube
https://www.youtube.com/live/atatOKCdA8w?feature=shared
👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v5u0iz2--...-ethiobeteseb.html
👉በፌስቡ / Facebook
https://www.facebook.com/share/15MbDC3h6c/ facebook.com/ethiobeteseb
👉 በትዊተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb
👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb
ሻሎም…! ሰላም…!
"ርእሰ አንቀጽ"
• ጥያቄ ፩
"…የፌዴራል መንግሥት ተብዬው የ "ሀ ገደሉ" ማይም ወጠጤ ዱርዬ ስብስብ ባለፈው ሰኔ ላይ በምክር ቤት አቅርቦ የ2017 ዓም 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት መጸደቁ ይታወቃል። መልካም…
"…ታዲያ ይሄ የተበጀተ በጀት መስከረም ወር ላይ ይጨመራል ለተባለው ደሞዝ እንኳ ሳይጨመር፣ ከኮሪደር ልማቱ መብራትና የብሽክሊሊት ማሽከርከሪያ መንገድ በቀር ሌላ ምንም ዕቅድ በሌለበት ገና በወርሀ ህዳር ተጨማሪ 583 ቢልዮን ብር ያስፈልገኛል በማለት በትናንትናው ዕለት ማስጨመሩ ይታወቃል።
"…በዐማራ ክልል የኦሮሚያ አምባሳደር ዶር ለገሰ ቱሉም በፌስቡክ ገጹ ላይ "የፌዴራል መንግስት የ2017 አጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊየን ብር ደረሰ። በትላንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል። ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ እያለች ነው።" በማለት ተሳልቋል።
"…ወደ ኋላ ሄደን በ2015 ዓም በጀት 786.6 ቢሊዮን ብር ወይም 14.64 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2016 ዓም ጭማሪ አሳይቶ 801.65 ቢሊዮን ብር ወይም 14.2 ቢሊዮን ዶላር፣ ዘንድሮ በ2017 ዓም 971 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር ሆኖ ከጸደቀ በኋላ ወዲያው አነሰኝ በማለት 582 ቢልዮን ብር አስጨምሮ 1.5 ትሪልየን ብር አጽድቋል። ይሄንንም በወቅቱ ምንዛሬ በዶላር ስንመታው 12 ቢሊዮን ዶላር ይመጣል ብለው የጻፉ አይቻለሁ።
"…እሺ በ2015~ 14.64 B$፣ በ2016~14.2 B$ ከሆነ የዘንድሮ…የዘንድሮው የ2017~12 B$ ዶላር ከመጣ ለስሙ 1.5 ትሪልየን ብር ተባለ እንጂ በወቅቱ ምንዛሬ በዶላር ሲመታ ከ2015 እና ከ2016 ዓም በጀት ያነሰው የዘንድሮው የ2017 ዓም ዓመታዊ በጀት እንዴት ቢሆን ነው "ምእመናን እልል በሉ ኢትዮጵያ አደገች፣ ከፍ ከፍም አለች" ተብሎ በመንግሥት አፍ በድፍረት የሚነገረው…? በቃ እነዚህን ደናቁርት የማይም ስብስቦችን ሃይ የሚል ወንድ ጠፋ ማለት ነው? ሀገሩን እንዴት ቢንቁት ነው ግን እንዲህ የተጸዳዱበት…? ከምር እንዴት ያለን ሾርት ሚሞሪያም እንደሆን አድርገው ቢቆጥሩን እንዲህ የሚያላግጡብን።
"…እነዚህ ማይም፣ ደናቁርት ትሪልዮን በጀቱ ገና በህዳር ወር ምን ቢያደርጉት ነው ያነሳቸው? በምንስ ነው የጨረሱት? ታህሳስና ጥር፣ ሚያዚያና ግንቦት ሲመጣስ ምን ሊሆኑ ነው? ኧረ ሌላው ይቅር ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ አለች እልል በሉ የሚያሰኘው የምሥራች ምኑ ላይ ነው?
• መልሱልኝ… ሁለተኛው ጥያቄዬ ሌላ ሦስተኛ ጥያቄ ስለወለደ እንዲሁ እየቆየሁ እጠይቃለሁ። ምሑራን መልሱልኝ በማርያም፣ በናታቹ፣ ባባታቹ…?
"…ኢየሱስም መልሶ፡— ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፡ አላቸው። ዮሐ 11፥ 9-10
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…ይሄን 16 ሺ ሰው አንብቦት 3 ሰው ብቻ ብው 😡 ብሎ የበሰጨበትን ርእሰ አንቀጽ እናንተ ደግሞ በተራችሁ በሰላው ብዕራችሁ እስቲ ሂዱበት… ✍✍✍
👆② ✍✍✍ …መንጋ እጅግ የተራበ፣ በጨለማም በቀንም የሚሰማራ አደገኛ የጅብ መንጋ ነው። ጅቦ ከአንበሳው ዐማራ ጋር ነው አሁን እየተፋለመ ያለው። ውጤቱን አብረን እናየዋለን።
"…አሁን የብዙ ሰላላ ውሾችን ጩኸት እየሰማሁ ነው። የጅቡ አድናቂ የሰው ውሾችም እየተንጫጩ ነው። ሰብሮ፣ ሰብሮ ለእኛም ትርፍራፊ ቢያተርፍልን ብለው ጅቡን ከመጀመሪያ ቀን ጀምረው ዝም፣ ጭጭ ብለው እየደገፉ ያሳለፉት ሁላ አሁን አያ ጅቦ ከተደላደለ በኋላ ወደ እነርሱም ዞሮ መንከስ ስለጀመረ እየዬም ዋይ ዋይም እያሉ ነው። ጅቡ ከወፈረ፣ ከፈረጠመ በኋላ ምንም የማይፈይዱ፣ የሰለሉ፣ የቀጠኑ የውሾች ጩኸት አየሩን እየሞላው ነው። ጅቡ ከሄደ፣ ካወደመ፣ ከሰበረ በኋላ ጩኸት ምን ሊረባ? ምን ሊጠቅም? ጅቡን ማስቆም፣ መግታት የሚቻለው በኅብረት፣ በአንድነት ሲቆም ነበር። ጊዜ የሚባልም ነገር እኮ አለ ሲባሉ ያልሰማ ሁላ አሁን እሪሪ ቋቀምበጭ ይሉልኛላ። ጅቡ እኮ ያው የቀደመው የጅብ ልጅ ነው። ደግሞም የጅብ ቆንጆም፣ የጅብ ደኅናም የለውም። በጊዜ መላ ቢበጅለት ይሻላል ብለን ጥቂቶች ስንጮህ ማን ይስማን? ከጅቡ ጋር በፍቅር የወደቁ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ፣ ከአውሮጳና ከዓረቡ ዓለም፣ ከአፍሪቃም ጭምር እየጎረፉ ወደ ጅቡ ጎሬ ተመሙ። ለጅቡ መንጋም አጋርነታቸውን አሳዩት። አይዞህ በርታ ብለው አበረታቱት። ከጅቡ ጋር አብሮ ለመሥራት ለመሸቀል ብለው ከነቦርጫቸው ከአሜሪካ ከአውሮጳ ዶላርና ዩሮአቸውን ተሸክመው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ቦርጫም ውሾች በሙሉ በስድስተኛው ወር ከስተው፣ ከስረው፣ ጠውልገው፣ ከንፈራቸው ደርቆ፣ ኮታቸው በላያቸው ሰፍቶ፣ ብራቸውንም፣ ቀልባቸውንም ተዘርፈው፣ በስንት መከራ፣ ከልጅነት እስከ ዕውቀት በስደት ያፈሩትን የመጦሪያ ገንዘባቸውን ለተራበ ጅብ አስረክበው እያጨበጨቡ ለዳግም ስደት ወደመጡበት ተመለሱ። ኧረ ተዉ አትቸኩሉ ሲባሉ አልሰማ ብለው ዋጋቸውን አገኙ። ኤትአባህ…
"…ጅቡ እንደ አክተር ማያም ያደርገዋል። አንዳንዴ ቆንጅዬ እባብም ሆኖ ይገለጻል። ሊፒስቲክ ተቀብቶ፣ ቋቋ ታኮ ጫማ አድርጎ፣ መርዙን በምላሱ ስር ደብቆ ይገለጣል። አንዳንዴ በየፓርኩ ወዲያ ወዲህ ሲል ላየው አቤት ሲያምር! ይሄን በሜካፕ ያበደ ቆንጅዬ እባብ ወተት እያጠጡ አፋፍተው ተንከባክበው ያሳደጉት፣ ለእባቡ በቀን አንድ ዩሮ፣ በቀን አንድ ዶላር ሁላ እያዋጡ የለገሱለት የትየለሌ ናቸው። እባቡም ፋፋ፣ ወፈረ፣ አደገም። ኧረ ተዉ እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም ቢባል ማን ይስማ? የእባቡም፣ የጅቡም አድናቂው ከመብዛቱ የተነሣ የአደጋ ጊዜ ደወል ደዋዮቹን ድምፅ ማን ይስማ? እንዲያውም የእባቡንና የጅቡን ቲሸርት አሠርተው ለብሰው የሚተኙ፣ ጅቡ ምን በላ? እባቡስ ምን ጠጣ የሚሉ ሴቶች ምድሪቱን ሞሉ። ወሴዎችም እንደዚያው። የጅብና የእባብ አድናቂ በዛ። ቀይቶ ያው እባባቸው እያዩት ዘንዶ ሆነ። ዘንዶውም በቁመት ረዘመ፣ ወደጎንም ሰፋ፣ ጉልበትም ጨመረ። አባቴ አሁን ዘንዶዬ እገሌ ወእገሌ ሳይል መልክና ቀለም ሳይመርጥ፣ ጾታና ብሔር፣ ሃይማኖትም ሳይመርጥ አዳሜና ሔዋኔን ከነቆዳው ከነልብሱ ይወጥ፣ የቆረጥመው ጀመር። ታዲያ አሁን የምን መንጫጫት ነው? ቻለው እንግዲህ አለ ብራኑ ጁላ።
"…ይኸውልህ ኦገኔ ስማኝማ ዛሬም ሳልሰለች ልንገርህ። እነሱ ሥራ ላይ ናቸው። ብልፅግና የሚሉትን ለመተከል ስንት ሚልዮን ሕዝብ መቀነስ እንዳለበት ወስነው ነው የሚሠሩት። አስቀድመው ያቀዱትን ዕቅድ ነው እየፈጸሙ ያሉት። ህልማቸውንም እየኖሩ ነው። በጀቱ ከውጭ ነው። እናንተ ፍጁት ባላየ ባልሰማ እናልፈዋለን፣ ለዚህ ድካማችሁ እንደ ኤርትራ የኦሮሚያ ሪፐብሊክን መሥርታችሁ በሸነና ትላላችሁ ስለተባሉ ማይሞቹ ጮቤ እየረገጡ ሀገር እያወደሙ ያለው ለዚያ ነው። የኦሮሚያ ሪፐብሊክን የመመስረት ዋዜማው አልፎ ሀገር ለማዋለድ ከጫፍ መድረሳቸውን ሽሜ ቡቡ ሰሞኑን መተንፈሱም እየተነገረ ነው። አስቀድሞ በለማ መገርሳ የተጀመረው አዲስ አበባን የማወረም፣ የፊንፊኔ አካል የማድረግ፣ የዲሞግራፊ ለውጡንም አገባድደው ወደ ማጠናቀቁ ደርሰዋል። ሀገር አፍራሾቹ የቀን ጅቦች ለዚህ ማደናገሪያ የኮሪደር ልማት በሚል ሰበብ ፈጥረው እየፈጸሙ ያሉትን ድብቅ ሴራ ማንም ሰው በትኩረት እያየም አይደለም። ምን እየተሠራ እንደሆነ የገባውም ሰው ያለ አይመስልም። ማታ ማታ በሚበራው የቡና ቤት መብራት ምክንያት ዓይኑ የተጭበረበረ፣ የደነዘዘ ሰው ድሮስ እንዴት ይንቃ። ከተራበ የቀን ጅብ ጋር የተፋቀረ፣ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ያለ እንዴት ይባንን? ሌላ አማራጭ የለውም። በጅቡ ከመበላት፣ በዘንዶው ከመዋጥ በቀር ሌላ አማራጭ የለውም።
"…አንድ ወዳጄ በላከልኝ መልእክት ላይ የኮሪደር ልማት የሚል የዳቦ ስም ስለተሰጠው የጥፋት ፕሮጀክት ዋና ዓላማውን ሲገልጽልኝ እንዲህ በማለት ነው። የኮሪደር ልማቱ ዋና ዓላማው የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር የተደረገ የፖለቲካ ሴራ ነው። ያለ ምንም ጦርነት ያለ ምንም ግርግር አዲስ አበባን የራሳችን እናደርጋለን በሚል አስቀድመው የመከሩትን ምክር እየተገበሩ ነው። ያለቀው ይለቅ፣ የሞተው ይሙት፣ የሚሰደደው ይሰደድ፣ የራሱ ጉዳይ ብቻ ይሄን ወርቃማ ጊዜ ዳግም ላናገኘው ስለምንችል በዚያም፣ በዚህም ብለን ዕድሉን እንጠቀምበት" በማለት ነው ተረባርበው እየሠሩ ያሉት። እያፈረሱህ፣ እየነቀሉህ ያሉት። አንተ ብታብድ፣ ገመድ ገዝተህ ብትሰቀል፣ በረኪና፣ የአይጥ መርዝ ብትጠጣ፣ ባህር ጠልቀህ፣ ገደል ገብተህ ብትሞት ጆቦቹ ደንታቸው አይደለም። አንተው ወተት እየጋትክ ያሳደግከው እባብ፣ ተው ይቅርብህ ስትባል መልኩ ያምራል፣ ቆንጅዬ ነው፣ ገር፣ የዋህ ነው ያልከው እባብ አድጎ ዛሬ ቆንጅዬ ዘንዶ ሆኖ ሲውጥህ መቻል ነው። ጅቡ ከሄደ በኋላ የውሻ ጩኸት ነው የሚገርመኝ።
"…ጅቦቹ መጀመሪያ ላይ የመሀል ከተማው ሕዝብ እንዲፈራቸው፣ ሽንታም፣ ቦቅቧቃ፣ ፈሪ እንዲሆን የዳር ከተማውን ነዋሪ በሃላል አረዱት፣ ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሀዲያ፣ ዐማራውን ቡራዩ፣ ከታ፣ አስኮ ላይ ሰብስበው አረዱት። ጨፈጨፉት። የመሃል ከተማው ሰው ያንን ሲያይ ደነገጠ፣ ምን ጉድ ነው የመጣብን ብሎ አደብ ገዛ። ጭጭ ምጭጭም አለ። ትንፋሽ ሁላ አጠረው። የመሃል ሀገሩ ሕዝብ እንዲዶክክ የዳር ሀገሩን ገበሬ አርደው፣ ጨፍጭፈው አጸዱት። ጅቦቹ በሰዎቹ ጭፍጨፋ ሲዝናኑ የመሃል ሀገሩ ሰው ተብረከረከ። ዓይቶም ሰምቶም ስለማያውቅ ምን ጉድ ነው የመጣብን ብሎ ሰው ሁሉ ጨለለ። ሰውን እንደ በግ አጋድሞ የማረድ በሰይፍ ቀንጥሶ መግደል የዓረብን ግብር አለማመዱን፣ አሳዩን። ጅቡ በኦሮሚያ በአስር ሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ሲገድል የደነገጠው የመሃል ሀገር ሕዝብ በህወሓት ጥጋብ የጅብ መንጋው ትግራይ ገብቶ ሚልዮኖችን ሲቆረጥም፣ ቀርጥፎም ሲበላ ዓይቶ መገረም አቆመ። ዳንኤል ክብረት በግልፅ ወጥቶ መቶ ሚልዮን ቢሞት እንኳ "እስቲል" 30 ሚልዮን ሕዝብ አለ። እናም እሱ መኖር ይችላል ብሎ እስከመናገር ደረሰ። እናም አሁን ያን ቁጥር ለማምጣት እንደሚሠሩ የሚያውቅ በጣም ጥቂቱ ነው።
"…ሸገር ከተማ ብለው አዲስ አበባን በቀለበት ውስጥ ከትተው አስቀመጡት። ከዚያ ውስጥ ከኦሮሞ ውጪ ያለውን ነገድ በሕገወጥ ግንባታ ሰበብ አወደሙት። አፈረሱት። አጸዱት። ገሚሱ ወደ ደብረ ብርሃን፣ ገሚሱ ወደ ደቡብ፣ ገሚሱ ወደ ሌላሌላ ክልል ተሰደደ። በሸገር ከተማ ውስጥ ቤቱ ለፈረሰበት በተለይ ዐማራ ለሆነ ሰው የሚያከራይ ኦሮሞ ቤቱም እንደሚፈርስ፣ 50 ሺ ብርም እንደሚቀጣ መመሪያ አወጡ። ዐማራው መሪ፣ ተከራካሪ ስላልነበረው፣ የሚጮህለት የፖለቲካ ፓርቲም ስለሌለው፣ ብአዴንም አብንም…👇② ✍✍✍
አላችሁ አይደል…?
"…በርእሰ አንቀጹም ላይ ሓሳብ እየሰጣችሁ የቲክቶክ መንደራችንንም ሞቅ፣ ደመቅ፣ መቅመቅ እያደረግን እናመሻለን።
• እየጠበቅኳችሁ ነው። ገባ ገባ በልልኝማ…
👆④ ✍✍✍ "…ኢትዮ 360 ገነነ። ሁለቱ የኢህአዴግ ልጆች አባትና ልጆቹ ኤርሚያስ ለገሰ እና ሀብታሙ አያሌው በዐማራው ኪሱም፣ ቦርሳውም ላይ ናኙበት። ዋኙበት፣ አጠቡትም። ወዲያው የዋቅጅራ ልጅ ያሳደገውን ሀብታሙን ተለይቶ ኮምፓስ ብሎ ወጣ። ኤርሚያስን ተከትሎ ምናላቸው ስማቸው ወጣ። ኢትዮ 360 በፍራሳ ልጅ በሀብትሽ፣ በኦሮሞዋ ቡሩኬ፣ በተክለጻድቅ ልጅ በጄሪ እጅ ወደቀ። ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ የመጣችው መዓዛ መሀመድ ሮሀ ብላ ከች አለች። እስከአሁንም አለች። ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ አማሪካና አውሮጳ የሚኖር ዐማራን ታሳቢ አድርገው ሁላቸውም ዐማራውን ያወዛግቡት ጀመር። በዚህ ሁሉ መፍረስ መሠራት ላይ ገንዘብ ከምታወጡ፣ ለሳታላይት መቶ ሺ ዶላሮችን ከምታፈስሱ ፕላትፎርም ላክፈትላችሁና በነፃ አየር ሰዓት ወስዳችሁ አገልግሉ በማለት የመረጃ ቲቪ ያመጣውን ዕድል መጠቀምን ችላ አሉ። ምክንያቱም ሕዝቡን እንዴት አድርገው የሳታላይት ወጪ ኪራይ ብለው ይጋጡት? ተተራመሱ። ኢኤም ኤስ ለሁለት ተከፈለ። ሲሳይ አጌናም በመጨረሻ በዐማራ ገንዘብ ቤተሰቡን ሲመራ ከርሞ አቢይ አሕመድ የተሻለ ሲከፍለው በልፅጎ አዲስ አበባ ገብቶ አረፈው።አመድ አፋሹም ዐማራ በመጨረሻ አጥንት የሚሰብር ስድብ በሚሰድበው ሲሳይ አጌና ይሰደብ ጀመር። ይዋረድ ጀመር።
"…የጎንደር እስኳዶቹ በሙሉ ወደ ኡጋንዳ ነው የሸሹት። ኡጋንዳ ሸሽተው የከፈቱት ሚዲያዎችን ነው። የወልቃይት ሰሊጥ ሽያጭ እየተሰፈረላቸው ነው የተቀመጡት። አሁን ሁሉም ፀረ ጎንደር፣ ፀረ ዐማራ መሆናቸው ታውቆ ያ የተለመደ የዐማራ ገንዘብ ቀጥ ብሎ ደርቆባቸው የሚሆኑት ጠፍቷቸዋል። 360 ዎች በኢሳት መንገድ ሄደው ዓለም ላይ ያለውን ዐማራ ኪሱን ሊያጥቡት ቢፈልጉም እኔ ደንቃራ ሆኜ አላስበላ አልኳቸው። አውሮጳ የያዙት መርሀ ግብር በሙሉ ታጠፈ፣ ተሰረዘም። በአሜሪካ፣ በካናዳ የተሞከረው የገቢ ማሰባሰቢያም ነጠፈ። የግምባሩም ዶላር አለቀ። የባልደራስም አለቀ። አሁን ጎንደሬዎችንና ሸዋዎችን ብናገኝ ብለው በፓስተር ምስጋናው አንዷለም በኩል ጣና ብለው ቢመጡም እምቦጭ ውጧቸው ቀሩ። ከዐማራ ምንም ነገር ቤሳ ቤስቲን ዱዲ ጢና ሲያጡ፣ እንደማያገኙም ሲያውቁ በግልጽ "ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል" እንደሚባለው ይኸው መሳደብ ጀመሩ። ማስፈራራት፣ መዛት ሁላ ጀመሩ። ወዳጄ ወፍ የለም።
አሁን ምን ይደረግ…?
"…እነዚህን ፀረ ዐማራ መሳይ ሚዲያዎች በራሳቸው ጊዜ ፈጥጠው በመገለጣቸው መዝግቦ መያዝ። የሚዲያ ዋናው አንቀሳቃሽ ገንዘብ ነውና ገንዘቡ ደግሞ የሚወጣው ከዐማራ ኪስ ነውና የሚወጣው እሱን አድርቆ ገድቦ መያዝ። እነ ሀብታሙ አያሌው ምንአልባትም ሊያደርጉ የሚችሉት ከዚህ በፊት በሰላሙ ጊዜ ቀድተው የያዙትን ሪከርድ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ በፋኖ በኩል መተማመን እንዳይኖር ማድረግ ነው። ከዚህ የዘለለ ምንም ሊያደርጉ አይችሉም። እንዲያውም የአሁኑን የአበበ በለውን እና የሀብታሙ አያሌውን በግልፅ በሪከርድ ማስፈራራታቸውን ሳይ እስከ አሁንም ድረስ ለመንግሥት የድምጽ ቅጂ መረጃ የሚሰጡት እነሀብታሙ አያሌውና አበበ በለው ናቸው ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል። በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ስለሆነ ኦሮሙማው ገንዘብ ከበጠሰላቸው ችግር የለባቸውም ብንል አንሳሳትም። ስለ ፋኖ በእጃችን አለን የሚሉትን መረጃ ሁሉ ይለቁለታል። ያልጠረጠረ ተመነጠረ። ጠርጥር አይጠፋምና ከገንፎ ውስጥ ስንጥር።
ሀ፦ ፋኖዎች፦
"…ከእነ አበበ በለው፣ ከሀብታሙ አያሌው ጋር ስታወሩበት የነበረውን ስልካችሁን አሁኑኑ ቀይሩ።
"…ከዚህ ቀደም ሪከርድ ተደርጋችሁ የእነ ዋን ዐማራ፣ የእነ አመሀ ሙላው፣ የእነ ሮቤል፣ የእነ አኪላና ዘርሽ እስረኛ የነበራችሁ በሙሉ እንዳትሸማቀቁ። እንዳታፍሩ። ከእስራታችሁ ፈትናችኋል፣ ነፃም አውጥተናችኋል። እንደ ጎጃሙ ፋኖ ማርሸት ወጊድ ብላችሁ በፅናት ቁሙ።
ሁ፦ የዐማራ ሕዝብ፦
"…ከሀብታሙ አያሌው፣ ከአበበ በለውና ከራሴ ከዘመድኩን በቀለም ቢሆን የፋኖን ትግል የሚበታትን አፍራሽ የድምጽ ቅጂ ቢለቀቅ "ደግ፣ እሰይ፣ እንኳን፣ ደግ አደረጉ ብላችሁ ኩም አድርጉን። አደራ ወሽመጣችንንም፣ ቅስምና ጅስማችንንም ስብርብር አድርጉት። በሰላም፣ በብሶት ጊዜ በምስጢር የተወራን ጉዳይ ፋኖን ለመከፋፈል መጠቀም ነውር መሆኑን አስመስክሩ። ምንም ብትሰሙ ጥፋ ከዚህ ብላችሁ አውጁ። አለቀ። ይህን ስታደርጉ አጀንዳው ሳይወለድ ሞተ ማለት ነው።
በአፒታይዘሯ እንቋጭ…
"…ይሄ የአዝማሪ አኳማሪ እስክስተኛ በዐማራ ችግር የራሱን ችጋር አራጋፊ፣ በስተመጨረሻ ገርፌ፣ ገርፌ ርቃኑን አስቀረሁት። የበግ ለምዱንም ገላልጬ አደገኛ ፀረ ዐማራ ተኩላነቱን አሰጣሁት። ጨርቁን ጥሎ ሊያብድ ነው። አሁን ማድረግ የሚችለው ምንአልባት በቀረው ዶላር ሀብቴንና ደረጀ በላይን አታልሎ አባት አርበኞቹ ላይ የተቃውሞ መግለጫ ማስወጣት ነው። መዝግቡልኝ። የምወደው አርበኛ ደረጀ የሠፈሩ ልጅ ስለሆነ ካላገዘው በቀር መሬት ላይ ታሪክ ተቀይሯል። ጎንደር ወደ አንድነት መምጣቱ የግድ ነው።
"…ሀብታሙም ከእንግዲህ የሚበጠብጠው፣ የሚያምሰው የዐማራ ፋኖ ትግል የለም። ዘመነ ካሤ ከሀብታሙ ወጥመድ አምልጧል። እነ አርበኛ መሣፍንት፣ ምሬ ወዳጆ፣ ደሳለኝ፣ ባዬ ቀናው እነሻለቃ ዝናቡ፣ እነማንቼ ከወጥመዱ ካመለጡ ቆዩ።
"…በሀብታሙ ወጥመድ የተያዘው ኮሎኔል ሙሀባው ወጥመድ ሰብሮ ለመውጣት እየጣረ ነው። ማስረሻ ሰጤ፣ መከታው ማሞ፣ አበበ ጢሞ በወጥመዱ ተይዘው መንቀሳቀስ ያልቻሉ የሀብታሙ ቆቅ ዥግራዎች ናቸው። ኮሎኔል ጌታሁን፣ አሰግድና ውባንተ ተበልተዋል። አሁን ወላ ሃንቲ ወፍ የለም።
"…አይደለም የድምጽ ቅጂ የቪድዮ ቅጂ ልቀቅ። ውርደቱ ለአንተ እንጂ ለፋኖ መሪዎች አይደለም። blackmail በማድረግ እስከዛሬ ብዙዎቹን አፈር ከደቼ አብልታችኋል። ለblackmail ለለblackmailማ እኛስ blackmail ማድረግ ያቅተን ይመስሏችኋልን? ጀምሩት እንጀምረዋለን። blackmail ግን የፋኖን ትግል ቅንጣት አያስቆመውም። አያ አቤ በሀብታሙ እጅ ያለው blackmail ፑቲን እጅ ያለ አቶሚክ ቦንብ አስመሰለው እኮ። በብራኑ ጁላ ድሮን ያልፈረሰ የዐማራ ትግል ነው በሀብታሙ blackmail የሚፈርሰው? ደነዝ። ወቅጅራም አልቅስ…
ሌባ ሁላ ሌባ ሁላ
ኡበርም ቢሆን ሰርተህ ብላ
"…እያየሁ እጨምራለሁ። ዛሬ ቲክቶክ በጊዜ ስለምገባ እዚያ ላይ ደግሞ በስሱ እናወራለን። እስከዚያው በዚህ አዝግሙ።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሕዳር 17/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆②…✍✍✍ …የከሰሩ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ ፀረ ዐማራም ኃይላት ሁሉ አሁን በይፋ መሸነፋቸውን ባያምኑም ነገር ግን ውስጥ ለውስጥ መንደፋደፋቸው አይቀርም። ግን ሁሉም መንገድ ዝግ ነው።
"…በስፋት ሳልተነትነው ለዛሬ የፋኖ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረስ እና የፋኖ አንድነት በይፋ ሊረጋገጥና ሊታወጅ ከጫፍ መድረሱ ሲታወቅ እየተገላለጡ ስላሉ ጭምብላሞች ጥቂት ልበል። ጆሮና ዓይናችሁን ክፈቱልኝማ።
፩ኛ፦ የእነ እስክስ አበበ በለው ጭምብል መውለቅ…
"…የጎንደር ፋኖ የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞች የሆኑት እነ አርበኛ ሻለቃ መሳፍንት ያፈነዱት ፈንጅ ከጎንደር አልፎ አዲስ አበባ በለሆሳስ፣ ኡጋንዳ በጅምላ፣ አሜሪካ በችርቻሮ ጉዳት ማድረሱን እያየን ነው። ስማቸው ያልተጠራ ሁላ ከየጎሬው ወጥተው ኡኡ፣ እየዬ ተቃጠልን እያሉ እየለፈለፉ ነው። በተለይ አዝማሪ አበበ በለው የሌለ እንቅጥቅጥ እስክስታ እየወረደ ነው። ሀብታሙ አያሌውም ምክሬን ሰምቶ ከደርጉ ክንፉ ወዳጄነህ የኮረጃትን የደረቀ ንፍጥ በከንፈሩ ስር ያለ የሚያስለውን የጺም አቆራረጥ አስተካክሎ ቢመጣም በነ ጋሼ ግን የሌለ እያበደ ነው። እነ ሲሳይ ሙሉን የመሰሉ የቦለጢቃ ድኩማን ማይም የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎችም ዋይ ዋይ እያሉ ነው። እነ ፓስተር ምስጋናውም አብደዋል። በተለይ ኑሮውን በዐማራ ፋኖ ትግልና በዐማራ ሕዝብ ችግር ላይ የመሠረተው አዝማሪ አበበ በለው ይሄ የፖለቲካው ቅማንቴ የትግሬ ዲቃላ የሆነ ግለሰብ የሌለ ነው የተንጨረጨረው። ያበደው።
"…መረጃ ቲቪን፣ ABC ቲቪን እና ሮሀ ቲቪን እንደ ጉድ እየከሰሱ ነው። የአርበኞቹን ዜና የሠራው የABC ቴሌቭዥን ሆኖ ሳለ እነሱ ከኤቢሲ ላይ ዜናውን ወስደው የዘገቡትን እኔን ጨምሮ ሮሀ ቴሌቭዥንን እንደ ብራቅ፣ እንደ ቁራ እየጮሁበት ነው። በተለይ አበበ በለው ጨርቁን ጥሎ ማበዱ ነው። ዜና መሥራትም ክልክል ሊሆን ነው ማለት ነው። የሚዲያ ሞኖፖሊ ይዘው በሚዲያ ብቻ በብቸኝነት ሊዘውሩት የነበረው የዐማራ ትግል አሁን ከጊዜ ጊዜ ራሳቸውን እያረሙ የሚሄዱ የዐማራ ሚዲያዎች መጥተው እነ አበበ በለውን ጦም ሊያሳድሩ ነው። የአፍራሳ የልጅ ልጅ የሚመራው የዐማራ ትግል አሁን የለም። ዐማራ በገዛ ልጆቹ ነው መመራት ያለበት። በዐማራ ስም የዐማራን ኪስ ማጠብ አይቻልም። ካካ ነው። እፉ ነው።
"…እነ ጋሽ መሳፍንት በነፃ ደማቸውን የሚያፈሱ ታጋዮች ናቸው። ሀብታሙ አያሌው ታዝሎ፣ አበበ በለው ከደርጉ ኪነት ጋር ተንዘላዝሎ በነበረ ጊዜ ነው ትግል የጀመሩት። 200 ሺ ዶላር ለኢትዮ 360 የተሰጠው እኮ በቅርቡ ነው። ስድሳ ምናምን ሺ ዶላርም ለ360 ከፋኖ ካዝና ተዝቆ የተሰጠው እኮ በቅርቡ ነው። ሀብታሙ 7 ሺ ዶላር በወር የሚበላው በዐማራ ደም እኮ ነው። ሦስት ሰዓት ደስኩሮ ከዶክተሮች፣ ከፕሮፌሰሮች በላይ ዶላር የሚግጠው በዐማራ ደም እኮ ነው። እነ ጋሽ መሳፍንት ከዐማራ ፋኖ ትግል ያተረፉት ልጆቻቸውን መገበር ነው። አሱ ልጆቹን በዐማራ ደም እያሰደገ፣ እነ ጋሽ መሳፍንትን ሊያዋርድ አይገባም። ወቀሳ፣ አስተያየት መስጠት፣ ትችት ይፈቀዳል። አሳያችኋለሁ፣ ትግሉን አፈርደቼ አበላዋለሁ ማለት ግን ድፍረት ነው። በዐማራ ዳያስጶራ የተለመነ ዶላር ሕይወትን እየገፉ የዐማራን ትግል በብላክሜይል አፈራርሳለሁ ማለት ድድብና ነው።
"…የትናንቱን ምሽት የአበበ በለውን እንጭርጭር ፕሮግራም እያየሁ ነበር። አበበ ይህን ፕሮግራም ሊሠራ እንደነበርም ቀድሜም ዐውቅ ነበር። እሱ ሰሞኑን የተለያዩ ሰዎች ጋር ስልክ በመደወል ጆሮው ሊደፈን ነው። የሚገርመው እሱ የሚደውልላቸው ሰዎች በሙሉ ደግሞ አንዳንዶቹ ቀድተውት ሁላ ነው የሚልኩልኝ። በተለይ የዐማራ ማኅበራቱን ጨቅጭቆ ሊገድላቸው ነው። "ዘመድኩን ከትግሉ እንዲወጣ እናድርግ፣ መግለጫ እናውጣ፣ አግዙኝ እንጂ እያለ ነው የሚወተውታቸው። መሬት ላይ ያሉትም ፋኖዎች እንዲሁ ነው ቁምስቅላቸውን እያወጣ የሚገኘው። አበበ በለው እንደ ወንድ ብቻውን አይገጥምም። አበበ አጃቢ ይፈልጋል። ፋኖዎች መግለጫ አውጡልኝ። የዐማራ ማኅበራት መግለጫ አውጡልኝ፣ የመረጃ ቲቪን ሰብስክራይበሮች አንሰብስክራይብ አድርጉ፣ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ሆይ ዘመድኩንን ከመረጃ ቲቪ ከነጭ ነጯን አውርዱልኝ፣ የዘመድኩን ተከታዮች ዘመድኩንን በቲክቶክ አትከትለት። በቲክቶክ አትመልከቱት። አሁን አሁን ደግሞ ቲክቶከሮች ሆይ እባካችሁ አግዙኝ፣ ዘመድኩን ላይ ዘመቻ ክፈቱልኝ እያለ ነው። አላወቀኝም ይሄ እስክስ። አንዴ ከነክስኩ ሳላደማ እንደማልለቅ አላወቀኝም። እንኳን ለቲክቶከር ለሞርታር እንደማልደነግጥ የት ያውቃል። በይፋ ክራር ይዘህ እስክስ በልና፣ ያለ ቦታዬ ነው የገባሁት በልና፣ ሁለተኛ አይለመደኝም በልና ያነዜ እተውሃለሁ። የአንተን ጠብ 3ኛ ወገን ገብቶ እንዲፋለምልህ አትፈልግ። ራስህን ችለህ ግጠመኝ። ሕዝቡ ይዳኘን።
"…ጋሽ አቤ በጣም በጣም ደደብ ስለሆነ ነው እንጂ እኔ ከዐማራ ትግል እኔን የማስወጫ መንገዱን፣ መፍትሄውን ጭምር ነግሬው እንኳን አይገባውም። እኔ ዘመዴን ከዐማራ ትግል ለማስወጣት ወንድ መሆንን ይጠይቃል። ሱሪ መታጠቅ፣ ማንበብ፣ መጻፍ፣ ሃይማኖት ጭምር ያስፈልጋል። እኔ ዘመዴ የምደውልለት ፋኖ የለም፣ ሲደውሉልልኝ ግን አነሳለሁ። እናንተ በርትታችሁ ለፋኖ መሪዎች ዘመድኩንን አታግኙ ብላችሁ ንገሩአቸው፣ አሳስቧቸው፣ አስጠንቅቋቸው መፍትሄው እሱ ነው እያልኩ ስንቴ ነግሬው አይገባውም። የመረጃ ቲቪ ሰዎች አቶ ግርማ ካሳን ጨምሮ የቀድሞ ባለቤቶቹን፣ ኤልያስ ክፍሌን ጨምሮ በመስደብ፣ በማዋረድ፣ በማንጓጠጥ፣ በማጥፋት እኔን ማውረድ እንደማይቻል እየነገርኩት አይገባውም ደደብ ነው። አበበ እልም ያለ ባለጌ ሰው ነው። ይሄንኑ ነው በሠራው ቪዲዮ ሊያቀሳስር የሞከረው። አበበ የሚለው ቢያጣ ሌላው በጣም አስገራሚ ነገር ተናገረ። መረጃ ቲቪ ከአረመኔው የ ብልፅግናው መንግሥት ገንዘብ ወስዷል ዓይነት ክስ አቀረበ። አሁን ሰብስክራይበሮቹ ስለቀነሱ ከየት አምጥተው ይከፍላሉ ሁላ እያለ ነበር? ባለፈው ለመረጃ ቴቪ ባዘጋጃችሁት ፕሮግራም ከቀነሰው በላይ አዳዲስ አባል አግኝተናል። እኔ ዘመዴ አስተባብሬ የማይሳካ ነገር እንደሌለ እኮ ያውቀዋል። የመረጃ ቲቪ ሰዎች የአበበ በለውን እከክ ያራገፉ፣ የመሥሪያ ቢሮ ከፍተው የሰጡት ቢሆንም ይሄ በልቶ ካጅ፣ የበላበትን ወጪት ሰባሪ ነውረኛ ሰው ዛሬ በአደባባይ ይሰድባቸዋል።
"…አበበ በዚህ ሐሜቱ ምክንያት ብቻ እንኳን እኔ የማውቃቸው የታዘቡት ብዙ የሸዋ ሰዎች አሉ። ሁሉንም የመረጃ ቲቪ ሰዎች የሚያውቁ እና ሁሉም ገንዘብ ከበቂ በላይ ያላቸው፣ ለተለያዩ ጉዳይ አምጡ ሲባሉ የሚሰጡ እንደሆን እንኳን ለእራሳቸው ቲቪ ገንዘብ ቸግሯቸው ከመንግሥት ሊወስዱ ለራሱ ለአበበ የሚተርፉ ስብስቦች ናቸው። ሲቀደድ ሰው ይታዘበኛል እንኳ አይልም። አቤ የመረጃ ቲቪ ሰዎች አይመጥኑህም። ከእግራቸው ጫማ ስር እንኳ ቦታ የለህም። እነሱ አንተ ስትለፈልፍ ንቀው ትተውሃል። የምትናገረው ግን ወንጀል ነው፣ ስም ማጥፋት ነው። አንተ የምትደውልላቸው ሰዎች እንዴት እንደሚታዘቡህ ብታውቅ መደበቂያ ታጣ ነበር። ዛሬ ሃይማኖታቸውን ጠቅሶ ለማሸማቀቅ የሚሞክረው ያኔ ያኔ መረጃ ቲቪ ላይ በነበርክ ጊዜ አታውቀውም ነበርን? በየሆቴሉ እንደ ውሻ እየተከተልክ ሆድህን ስትሞላ ያኔ አታውቃቸውም ነበርን? ደግሞስ ባለፈው ዘመድኩንን እንዳትሰሙት አድርጌአለሁ። በድል ተወጥቻለሁ በዘመድኩን ጉዳይ አልመለሰበትም ብለህ የደሰኮርከውን ረስተህ ነው እንዴ አሁንም መጥተህ ዘመድኩንን አትስሙት እያልክ የምትንጨረጨረው? አበበ በለው የተቋም ፀር ነው።👇②
አፒታይዘር… appetizer
"…ይሄ የአዝማሪ አኳማሪ እስክስተኛ በዐማራ ችግር የራሱን ችጋር አራጋፊ፣ በስተመጨረሻ ገርፌ፣ ገርፌ ርቃኑን አስቀረሁት። የበግ ለምዱንም ገላልጬ አደገኛ ፀረ ዐማራ ተኩላነቱን አሰጣሁት። ጨርቁን ጥሎ ሊያብድ ነው። አሁን ማድረግ የሚችለው ምንአልባት በቀረው ዶላር ሀብቴንና ደረጀ በላይን አታልሎ አባት አርበኞቹ ላይ የተቃውሞ መግለጫ ማስወጣት ነው። መዝግቡልኝ። የምወደው አርበኛ ደረጀ የሠፈሩ ልጅ ስለሆነ ካላገዘው በቀር መሬት ላይ ታሪክ ተቀይሯል። ጎንደር ወደ አንድነት መምጣቱ የግድ ነው።
"…ሀብታሙም ከእንግዲህ የሚበጠብጠው፣ የሚያምሰው የዐማራ ፋኖ ትግል የለም። ዘመነ ካሤ ከሀብታሙ ወጥመድ አምልጧል። እነ አርበኛ መሣፍንት፣ ምሬ ወዳጆ፣ ደሳለኝ፣ ባዬ ቀናው እነሻለቃ ዝናቡ፣ እነማንቼ ከወጥመዱ ካመለጡ ቆዩ።
"…በሀብታሙ ወጥመድ የተያዘው ኮሎኔል ሙሀባው ወጥመድ ሰብሮ ለመውጣት እየጣረ ነው። ማስረሻ ሰጤ፣ መከታው ማሞ፣ አበበ ጢሞ በወጥመዱ ተይዘው መንቀሳቀስ ያልቻሉ የሀብታሙ ቆቅ ዥግራዎች ናቸው። ኮሎኔል ጌታሁን፣ አሰግድና ውባንተ ተበልተዋል። አሁን ወላ ሃንቲ ወፍ የለም።
"…አይደለም የድምጽ ቅጂ የቪድዮ ቅጂ ልቀቅ። ውርደቱ ለአንተ እንጂ ለፋኖ መሪዎች አይደለም። blackmail በማድረግ እስከዛሬ ብዙዎቹን አፈር ከደቼ አብልታችኋል። ለblackmail ለለblackmailማ እኛስ blackmail ማድረግ ያቅተን ይመስሏችኋልን? ጀምሩት እንጀምረዋለን። blackmail ግን የፋኖን ትግል ቅንጣት አያስቆመውም። አያ አቤ በሀብታሙ እጅ ያለው blackmail ፑቲን እጅ ያለ አቶሚክ ቦንብ አስመሰለው እኮ። በብራኑ ጁላ ድሮን ያልፈረሰ የዐማራ ትግል ነው በሀብታሙ blackmail የሚፈርሰው? ደነዝ። ወቅጅራም አልቅስ…
ሌባ ሁላ ሌባ ሁላ
ኡበርም ቢሆን ሰርተህ ብላ
• መጣሁ…
መልካም…
"…ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ነው። በቤታችን ደግሞ ከምስጋና በኋላ መቅብ የሚጀምር የጦማር ቡፌ አለ። ያውም በጉጉት፣ በናፍቆት የሚጠበቅ። መልካም… ይሄ በናፍቆት የሚጠበቀው ከምስጋና ቀጥሎ የሚቀርበው የእኔ የዘመዴ ቤት የጦማር ቡፌ ምን ይባላል?
• ከምስጋናችን ቀጥሎ በእኔ በዘመዴ ቤት የምትጠብቁት ምንድነው? ፊደሉን ሳይቀር ሳትስቱ አስተካክላችሁ ጻፉልኝ አስቲ…
👆④ ✍✍✍ …እንዲያለቃቅሱ አስደርጓል። የዐማራ ፋኖ ትግል ሚንስትሩን ሁሉ አክስቷል፣ አቢይ አሕመድን እንቅልፍ አልባ፣ ዳንኤል ክብረትን ተራጋሚ፣ ሽመልስ አብዲሳን ሸኔን ተለማማጭ አድርጎታል። የዐማራ ፋኖ ትግል እነ ጃዋርን፣ እነ ሕዝቅኤልን አደብ አስገዝቷል። እነ ስታሊንን ወደው ሳይሆን በግዳቸው ጀግንነቱን እንዲመሰክሩ አስገድዷል። የዐማራ ፋኖ ትግል መንግሥትን ኪሱን አራቁቶ ደሞዝ የሚከፍለው እንዲያጣ አስደርጎታል።
"…የዐማራ ግዛት በጣም ግዙፍና ሰፊ ነው። የዐማራ ሕዝብ እንደ ታሊባን ሕዝብ አይደለም ከካድሬ ስብስብ ከምድረ ደናቁርት የወያኔ ምርኮኞች ከሚመሩት ከምርኮኛ የኦሮሙማ ሠራዊት ጋር አይደለም መቶ ዓመት ከኃያላኑ ጋር ሊዋጋ ይችላል። ነልክአ ምድሩ አመቺ ነው። ሰፊ ነው። ግዙፍ ነው። እንደ ትግሬ ከላይ በኤርትራ፣ ከታች በዐማራና በአፋር ዘግተህ የምትቀጠቅጠው አይደለም። አይቻልም። ዐማራ አሁን በአፋር በኩል፣ በሱዳን በኩል፣ በኤርትራም በኩል በሩ ከጎረቤት ሀገራት ጋር መገናኘት ይችላል። ዐማራውን ከመንግሥት ቢሮክራሲ ማጽዳት አይቻልም። ግዙፍ ሕዝብ ነው። ዐማራው ኦሮሚያ ክልል ስለተወለደ ኦሮሞ መስሎ፣ ኦሮሞ ሆኖ አሁን አድጎ በኦሮሞ ኮታ ሥልጣንና ሀብት አግኝቶ ያለ አለ። ዐማራውን ማሸነፍ አይቻለም። አቢይ አሕመድ በእናቱ ዐማራ ነው፣ በሚስቱም ዐማራ ነው። አጠገቡ ያሉት ሆዳም ቢሆኑም ዐማሮች ናቸው። የጦር መኮንኖቹ ብቻ የአገው ተወላጅ የአገው ሸንጎ፣ ቅማንቴ የሆኑ ናቸው እንጂ ዐማራ ይበዛዋል። የዐማራ ቢሮክራሲን ከኢትዮጵያ መበጠስ፣ መለያየት ፈጽሞ አይቻልም። በፍጭራሽ።
"…አሁን ደግሞ ሌላው የምሥራች በፊት በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ተጠልፎ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ዘር ለገበሬ፣ ብሔሬን አልናገርም፣ ዘረኛ አልሆንም፣ ዐማራ ነኝ ግን ከኢትዮጵያዊነቴ ወርጄ እንደ ትግሬና ኦሮሞ አልሆንም እያለ ይለፋደድ፣ ትለፋደድ የነበረችው ሁላ አሁን አዳሜና ሔዋኔ መከራው ሁሉ እየተሳበ፣ እየተጎተተ መጥቶ በቤቷ ሲገባ፣ የኀዘን ድንኳን ከግቢዋ አልነቀል ብሎ ሲከርምባት፣ ኢትዮጵያዊነቷ ሳይሆን ዐማራዊነቷ፣ ዐማራዊነቱ እሳት እያዘነበበት እንደሆነ ሲገባው፣ ሲገባት ጨርቄን፣ ማቄን ሳትል ዓይኗን በጨው ታጥባ "የሌለ ዐማራ" ሆና ተከስታለች። ለመጀመሪያ ጊዜ የዐማራ ዳያስጶራ ዐማራ ነኝ ብሎ በፌክ ኢትዪጵያኒስቶች፣ በፀረ ዐማራ ዐማራ መሳይ አሞሮች ሳይመራ በምዕራቡ ዓለም አደባባይ ስቶፕ ዐማራ ጄኖሳይድ በማለት አደባባይ ወጣ። ታዲያስ ይሄ ትልቅ ድል አይደለም እንዴ ለዐማራው። መሬት ላይ ያለው ዐማራ ከእን እስክንድር ሴራ፣ ኮተት ከራቀ፣ ካመለጠ፣ 5% ፐርሰንት ዐማራው እንኳ እንቢኝ፣ ብሎ ከተነሣ የሁሉ ነገር መቋጫው፣ ፍጻሜው ይቀርባል።
"…አገዛዙ ደህይቶ፣ ደክርቶ ይወድቃል። ይገነደሳልም። አገዛዙ ሲወድቅ ግን ሕዝቡንም አደክርቶ፣ አደህይቶ፣ ብቻውን አስወርቶ፣ ጨርቁን አስጥሎ፣ አጠውልጎ፣ አመንምኖ፣ አፈናቅሎት ነው የሚወድቀው። አገዛዙ ይወድቃል ብቻውን ግን መውደቅ አይፈልግም። ሰፊ የዘር ጭፍጨፋ አካሂዶ፣ ሰፊውን ሕዝብ ከርስቱ አፈናቅሎ፣ ነቅሎ፣ ሕዝቡን ሁሉ ደም አቃብቶ፣ ሃይማኖት ከሃይማኖት አባልቶ፣ አናክሶ ነው የሚወድቀው። እንደዚያ ነው የሚያደርገው። ይወደቃል ግን ብዙ ሰው ይጥላል። መምህራን፣ ሀኪሞች ደሞዝ አልተከፈለንም ብላችሁ፣ ራበን ጠማን ብላችሁ በገምድ ታንቃችሁ፣ በረኪና፣ የአይጥ መርዝ ጠጥታችሁ መሞታችሁን አቁሙ። ይሄን ያህል ሞትን የማትፈሩ ከሆነ ገመድ ላይ ከመንጠልጠል፣ መርዝ ጠጥቶ ክልትው ከማለት የኢትዮጵያን ርግማን፣ አንዱን ሰው በላ ጥላችሁ አትሞቱም። ሰነፍ፣ ታንቀህ ሞተህ፣ መርዝ ጠጥተህ ሞተህ ሁላ ፍትሃት እንኳ አይደረግልህም። ፈሪ፣ ደፈር ብለህ ሚልዮኖችን ለጦርነት የዳረገ አረመኔውን መርጠህ ይዘህ ውደቅ። ምንድነው በ10 ብር ገመድ ታንቆ መሞት። በዚያ ላይ አስከሬናችሁ በሽንትና በሰገራ ተጨመላልቆ ተዋርዳችሁ፣ መሳቂያ፣ መሳቀቂያ ሆናችሁ በወርደት ከምትሞቱ እንደ ወንድ ሁኑ። የሀገሪቱን መርገም ጥሎ ማለፍ በታሪክም ያስመሰግናል።
"…በገጠር ቤተሰቦቹ በድሮን፣ በጀት፣ በወታደር እያለቁበት እሱ ሚንስትሩን፣ ጄነራሉን አጃቢ ሆኖ ከርሱን ይሞላል። ቤተሰቦቹ ተፈናቅለው ጉዳና ላይወጥተው እሱ ፖሊስ ሆኖ ሥርዓቱን ያገለግላል። ይሄ ነውር ነው። የሆነው ሆኖ የዐማራ ፋኖ ያሸንፋል።
"…አሁንም ዐማራው ሦስት አማራጮች ብቻ ናቸው ያሉት።
1ኛ፦ ማሸነፍ
2ኛ፦ ማሸነፍ
3ኛ፦ ማሸነፍ… አለቀ። ለዐማራው ከማሸነፍ በቀር ሌላ ምንም አማራጭም ምርጫም የለውም። አለበለዚያ ዐማራው የሚጠብቀው ምርጫው እንደ ኩርድ ሕዝብ ሀገር አልባ መሆን ብቻ ነው።
• ደግሞም በየትኛውም የዓለም ታሪክ የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ ኖሮ አያውቅም። አኬር እንደሁ መገልበጡ አይቀር።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
•••
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 20/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!
👆② ✍✍✍ …ውስጥ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች በሙሉ ዛሬ ሥራ አጥ ሆነዋል። ቤተሰብ ተበትኗል። አገዛዙ የገቢ ምንጩ ነጥፏል። እሳት እየለኮሰ በማንደድ፣ አዳዲስ አጀንዳ በመፍጠር ለማስቀየስ መንደፋደፉ አላዛለቀውም፣ አላዋጣውምም። ኪሳራ በኪሳራ ነው የዘፈዘፈበት። ነጋዴው ከአቅም በላይ ግብር መጠየቁ ሌላ ፍጥጫ እየፈጠረ ነው። ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በወንዝ ዳር የከተማ ግብርና ላይ ተሰማርተው የጓሮ አትክልት ያመርቱ የነበሩት በቀደም አቁሙ ሲባሉ እንደ ሌላው ጊዜ እሺ ብለው አቁመው አንገት ደፍተው አልሄዱም። ለምን ብለው ጠየቁ። አቁም፣ አቁም ነው የምንአባህ ጥያቄ ነው? የሚል መልስ ነው ከኦሮሙማው የተሰጣቸው መልስ። አንነሣም ብለው ተናነቁ። ጥለው ወደቁ። በራብ ከመሞት በሰይፍ መሞት ይሻለናል ብለው ነው የወንድ ሥራ የሠሩት። ይሄ ጅማሮ ነው። እነዚህ የቦሌ ሩዋንዳ ነዋሪዎች ቄራ ላይ የተፈጸመውን ዓይተዋል። የቄራዎች ዕጣ ወደ እነሱ እየመጣ እንደሆነም ተረዱ። እንደ ፒያሳና እንደ ካዛንቺስ ልጆች ጨፍረው ወደ ሞት መሄድን አልፈቀዱም። ቢያንስ ለምን ብለው ጠይቀው ምላሹ ኃይል ሲሆን ርቦኝ ከምሞት በጥይትህ ግደለኝ ብለው የጀግና ሥራ ሠርተዋል። አኩርፎ በገመድ ታንቆ፣ መርዝ ጠጥቶ ከመሞት ይሄ በስንት ጣዕሙ። ቄራዎች ምንድነው የሆኑት ትናንት ከደረሰኝ አንድ አስተያየት ያገኘሁትን ላካፍላችሁ።
"…በቅድሚያ አክብሮቴን እገልጻለሁ። ብዕርህ አይንጠፍ በማለት ነበር አስተያየት ሰጪው አስተያየቱን የጀመረው። በጻፍከው ላይ ለመጨመር ሳይሆን፥ በአዲስ አበባ ላይ የወደቀው አዚም ሁሌም እየገረመኝ አለሁ። በፈረሳው ጉዳይ፥ ለስንት የሚበቃ አለ የተባለ ዱርዬ ቁጢጥ ብሎ ሲያለቅስ ስታይ የድንዛዜውን ጉልበት ትመለከታለህ። መቼም ትልቁ Prison ፍርሃት ነው። ከስደት፣ ከዘብጥያና በስውር ከመገደል የተረፈው አብዛኛው የአዲስ አበባ ወጣት፥ በዚህ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ መገኘቱ፥ ለሰሚም ግራ ነው። ለምሣሌ የቄራን አካባቢ ጉዳይ ላንሣ። የቄራ ልጆች መተዳደሪያቸው የቄራዎች ድርጅትና የከብቱ መሸጫ በረት ነው። የልጅ ልጅ ልጅ የታየበትም ሥፍራ ነው። በዚህም በቀላሉ ገቢ መፍጠር የቻሉ ሀብታሞችን ያፈራ አካባቢም ነው። ሆኖም የኦሮሙማው ጅብ ቀኑን ጠብቆ ከጎሬው ከመውጣቱ በፊት የቄራ ልጅ መንግሥትን በመደገፍ አይታማምና በትግራይ ለተደረገው ጦርነት ለመከላከያ ሁለት አይሱዙ በሬ መስጠቱ የሚታወቅ ነው። በድንገት ግን ማንም ምንም ባልጠበቀው ቅፅበት ተናዳፊው እባባዊው ሥርዓት (የዕባብ ብልጥነት መሽሎክሎኹ ይመስለኛል) ዚግዛግ እየሠራ መጥቶ ቄራን መናድ ጀመረ። መጀመሪያ ከጎፋ ጋር በሚዋሰነው ገባር አስፓልት መንገድ ሰበብ በረቱን ቆርሶት አለፈ። በመቀጠል ወሳኝ የነበሩ ምልክቶች የተባሉ የሠፈሩ ታሪኮችን መሸራረፍ ቀጠለ። በየተራ እያላጋው ያ ሁሉ ለሺህ የሚተርፍ የቄራ ልጅ አይደለም ጉልበቱ ልሳኑ ተዘግቶ አጃምባና ጣፎ ገብቶ ሠፈረ። እንደ ብስባሽ ደረጃውን ባልጠበቀ ከባቢ አራርቆ ቀበራቸው።
"…ቀጣዩ ዕጣ ፈንታቸው ያሳሰባቸው ቄራዎች ጥቂት ጓ ብለው ደንቦችና ፖሊሶችን መሰባበር ሲጀምሩ አገዛዙ የብሔር ካርድ ስቦ ከች አለ። የኦሮሞ ተወላጅ የቄራ ልጆችን ለብቻ በወረዳ አዳራሽ ሰብስቦ Lobby በማድረግና አግዙን፣ አብረን እንሥራ፣ ኦሮሞ ተበድሏል በማለት የቀረውም የቄራ በረት ልጅ አንድ ሆኖ እንዳይቆም ብልጽግና ቁማሩን በላቸው። ስግብግቡ የጭቅና ሥጋ ሳይቀር ለአየር መንገድ፣ ለሸራተንና ለትልልቅ ሆቴሎች እያቀረበ ዲታ የነበረው፣ በሰላሙ ዘመን ገንዘቡን ባንክ ጨቅ አድርጎ እርድና መስሎት ፋሽን እያባረረ፣ ሴት ሲለዋውጥ የኖረው ማጋጭ ዘማዊውም (ሰብሰብ ብሎ አምሰት አምስት እየሆነ የጋራ አፓርታማ ገንብቶ እንኳ ይህን ክፉ ቀን ማለፍ ሲችል) ከተወለደበት ከእናቱ ቤት በጉልምስናው ዘመኑም ሳይወጣ፤ ባንክ ያለው ገንዘቡም ዋጋውን አጥቶ፣ በቀጣይ የሚሠፍርበትን አካባቢ ዕጣ ለማውጣት ይጠባበቃል። ፍርሃትን ራሱ የሚፈራው ስም ጥሩ የቄራ ልጅ እንዲህ ሞተሩ እወረደ መኪና ዘጭ ብሎ ተገኘ።
በዋናነት የቄራ ልጅን በጅቡ መንግሥት ጥርስ ውስጥ የከተተው ቀናኢ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ መሆኑ ነው። በአካባቢውም ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል፣ ጎፋ ቅድስት ኪዳነ ምህረት፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ከርቸሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ይገኛሉ። የድሮ ከርቸሌ በተለምዶ (እስረኛው ሚካኤል) ቡልጋሪያ ያለው በጥር 12 ደምቆ የሚያልፈው በቄራ በኩል ነው። ከከተራ ጀምሮ ከአምሰት ያላነሰ በሬ ታርዶ ካህናት፣ ምእመናንና ነዳያን ሁሉ ይመገባሉ። በታቦቱም ፊት አማኙ ስዕለቱን አስገብቶ አካባቢውን ባርኮ ያልፋል። ይህ ለኦሮሙማው የእግር እሳት ሆኖበት ቆይቷልና ተበቀላቸው። ይሄ በሁሉም ቦታ ይቀጥላል። ከመቆጨት በቀር ምንም ማምጣት አልተቻለም። ዐማራ ይሄን ፍርሃት ነው የሰበረው። እንደ ቄራ፣ እንደ ካዛንችስና እንደ ፒያሳ ልጆች ጃንቦ እየለጋ እሱ በካልቾ ተለግቶ እንጨቆረር አልገባም። ዐማራ ግን ጀግና ነው።
"…ዛሬ የዋዜማ ራድዮን ዜና እያየሁ ነበር። ዜናው እንዲህ ይላል። ለቸኮለ! ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓም የዋዜማ ዕለታዊ ዜና፦"…አገር አቋራጭና መካከለኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ምልምሎችን በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ጣቢያዎች እንዲያመላልሱ እየተደረጉ መኾኑን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከበላይ አካል የተሰጠ ትእዛዝ ነው በማለት ተሽከርካሪዎቹ ከባለንብረቶቹ ፍቃድ ውጪ ምልምሎችን ወደተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንዲያመላለሱ እያደረጉ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የትራንስፖርት ማኅበራትም ይሁኑ የግለሰብ ንብረት የኾኑ ተሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎችን መንገድ ላይ እንዲያወርዱ ከተደረጉና ታርጋቸው ከተፈታ በኋላ፣ በጸጥታ ኃይሎች መሪነት ምልምሎች ወደሚገኙባቸው ማዕከላት ተወስደው ምልምሎቹን የማጓጓዝ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚገደዱ ዋዜማ ሰምታለች። በርካታ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቻቸው ለግዳጅ እንዳይያዙባቸው በመስጋት፣ ለሳምንትና ከዚያ በላይ ደብቀው ለማቆም እንደሚገደዱና፣ ይህን ድርጊት ፈጽመው ሲገኙ ደሞ ፍቃዳቸውን እስከመነጠቅና እስከመታሠር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ምንጮች ጠቁመዋል ይላል ዜናው።
"…አያችሁ የዐማራው ክልል ጦርነት ምን ያህል ክብደት እንዳለው? ሁሉም የትራንስፖርት ተሽከርካሪ እኮ ነው በግዴታ ምልምል ሟች ወታደር እንዲያጓጉዝ የተፈረደበት። እንዲህ ሲሆን የሚፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ተመልከቱ። ያውም ተሳፋሪ ጭኖ የወጣ መኪና መሀል መንገድ ላይ አስቁመው ሻንጣ አስወርደው፣ መኪናውን ከነሹፌሩ ወደ ግዳጅ ይወስዱታል። ለምን ሲባል መልሱ ከላይ የታዘዘ ነው። መንገድ ላይ የወረዱት መንገደኞች ይዘረፋሉ፣ ይደረፈራሉ፣ የሃኪም ቀጠሮ፣ የፍርድ ቤት፣ የኤምባሲ ቀጠሮ፣ የውጭ ሀገር ጉዞ ያለባቸው የሚደርስባቸውን መንገላታት እና ኪሳራ አስቡት። ይሄ ሁሉ በዐማራ ክልል አገዛዙን ምንድነው የገጠመው? ከዳር ዳር የመኪና ያለህ እያለ ሁሉንም ለግዳጅ አምጣ አስረክብ እያለ ያለው ምን ቢደርስበት ነው ብሎ የሚጠይቅ ባይኖርም የዐማራ ክልሉ ጦርነት ኦሮሙማውን ርቃኑን እያስቀረው ነው። ገራዥ የደበቀውን መኪና ባለንብረቱን ቀጥቅጠው በግድ እየወሰዱበት እኮ ነው። በትግራዩ ጦርነት ወቅት የሀገሪቱ መኪና በዚህ ልክ በግዳጅ ተንቀሳቀስ አልተባለም። በዐማራ ክልል የገጠማቸውን ጉድ ግን ከምዕራባዊያን እና ከዓረቦቹ አለቆቻቸው ጋር ተጋግዘው በማፈን👇…② ✍✍✍
መልካም…
"…በወንድ አቅሜ፣ በጉልምሳና ዘመኔ፣ ጣቴ እስኪደነዝዝ፣ ዓይኔ እንባ እስኪያቀረዝዝ ድረስ ተፍ ተፍ፣ በት በትም ብዬ እስከ ማክሰኞ ድረስ የማይነበብ የማይገለጸውን የሳምንቱን መጨረሻ የዕለተ አርብ ርእሰ አንቀጻችንን ረዘም አድርጌ፣ ቅመማ ቅመሞቹን ሁሉ ጨማምሬ፣ በጨው አጣፍጬ፣ ግሩም፣ ጣፋጭ አድርጌ አዘጋጅቼ ላችኋለሁ።
"…እህሳ…! ቤተሰብ… ርእሰ አንቀጹን አንብባችሁ ባነበባችሁትም ላይ እኔም በጉጉት የምጠብቀውን አስተያየታችሁን ልታስኮመኩምኝ ፈቃደኞች ናችሁ ወይ…?
• ዝግጁ ቤተሰብ…?
መልካም…
"…ዘወትር ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርበው ሳምንታዊው መርሀ ግብራችንን እስክንጀምር ድረስ ይህን 15ሺ ሰዎች አንብበውት 12 ፍሬ ሰዎች ብው😡 ብለው የተናደዱበትንና በዛሬው ርእሰ አንቀጻችን የጠየኩትን ጥያቄ ምላሽ በማንበብ እቆያለሁ።
"…በጀቱን ምን በላው? መልሱልኝ።
መልካም…
"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ጥያቄ እንዲሆን ነው የፈለግሁት። ጥያቄዎቼ ሁለት አጫጭር ጥያቄዎች ናቸው። እኔ ልጠይቅ የምታውቁ ሰዎች አስረዱኝ። እንደኔ ያልገባችሁ ጮጋ፣ ዝም፣ ጭጭ በሉ። በጉዳዩ ላይ በቂ ዕውቀት ያላችሁ ግን ሳትሰስቱ በዚህ ሚልዮኖች ዓይናቸው ተክለው አፍጠው በጉጉት በሚከታተሉት ፔጅ ላይ ዕውቀታችሁን አጋሩን።
"…የአንደኛው ጥያቄ ኢኮኖሚስቶችን ይመለከታል። ሁለተኛው ጥያቄ ግን ሁሉም ሰው በገባው፣ በተረዳው መልኩ ሊመልስልን ይችላል። ስትመልሱም በዚህ መልክ ቢሆን ሸጋ ነው።
• ዘመዴ ጥያቄ አንድን ልመልስ
• ዘመዴ ጥያቄ ሁለትን ልመልስ
"…በማለት ጥያቄዎቹን ለይታችሁ ቢሆን ይመረጣል። ሁለቱንም ጥያቄዎች የምትመልሱ ሰዎች ግን የመጀመሪያውን ዕወቀት ተኮር ጥያቄ የመመለስ አቅምያላችሁ ሰዎች መሆን አለባችሁ እላለሁ። ሁለተኛው ጥያቄ ግን "በትከሻዬን ሸከከኝ" ማዕቀፍ ማንኛችሁም ልትመልሱት የምትችሉት ጥያቄ ነው። ቤተሰብ ተግባባን አይደል?
• መልካም ጥያቄዬን ልጠይቅ ነኝ…?
ይድረስ ለዐማራ ታጋዮች…
"…እስክስ እውነቱን ከመናገር ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። በግድ አቢይን ከስሩ ነቅሎ እንዲታገል ለምን እንደምትጨቀጭቁት አልገባኝም። በግድ ይሆናል እንዴ? የቡርቧክስ ፕሮፌሰር የኪነት ችሎታውን እንደ ኪሎ መቀነስ ያለ አንዳንድ አይዲያውን እሱ እንዳለው ውሰዱለት። በተረፈ ግን ለዋ ማኅበሩ ዶላር ማዋጣታችሁን አታቁሙ እንጂ አቢይን ከስሩ ለመመንገል እንዲታገል አታስገድዱት።
"…ወ/ሮ ልቅሜ ኪዳኑ የአበበ በለው እናት ናቸው። ያውም የተከዜ ማዶ ምርጥ ትግራዋይ እናት። በአባቱ ግማሽ ቤተ እስራኤላዊ ነው አቤ። እናም በግድ ዐማራ ሁን ብላችሁ አትጨቅጭቁት። ዶላር ብቻ ስጡት እንጂ ትን እስኪለው ይሄን እስክስታ ያስነካላችኋል። አይደል አቤ?
ለአቤ ቴስላ
ለዐማራ አተላ
አለ የኦነጉ ቀጄላ
አቤን ካልተወገደ አትበሉት
ዶላሩን ብቻ በትኑለት
"…እየኮመታችሁ…✍✍✍
👆③ ✍✍✍ …አሽከር፣ ገሌም ስለሆኑ ሰሚ አጥቶ ባከነ፣ ባዘነ፣ ልጆቹ ትምህርት አቋረጡ፣ ትዳሩ ፈረሰ። ራብና ሰቆቃ በረታበት። ጉራጌውም፣ ከምባታውም ምድር ጠበበችው። በቀላሉ አጸዱት። ነፃ አደረጉት። ይሄ ሁላ ሲሆን አቅም ያላቸው ወደ መሃል አዲስ አበባ ተመልሰው ቤት ተከራይተው፣ መኖር ጀመሩ። ጅቡ ይሄን አየ። ተመለከተ። ስለዚህ መሃል ከተማውን በምን፣ እንዴት ላጽዳው ብሎም ወሰነ። አዎ የኮሪደር ልማት ብዬ አነሣዋለሁ። አጸዳዋለሁ ብሎ ወሰነ። ማንም አቡክቶ የለጣጠፈውን የጭቃ ቤት ሁላ ታሪካዊ ነው ምናምን ብሎ ማስቆም አይቻልም። ፍርድቤትም በዚህ በኩል አያገባውም። ይነሣሉ፣ ይጸዳሉም ብሎ ወሰነ። ለጥቂቶች ቤት ሰጥቶ ፕሮፓጋንዳውን ነዛው። ልማቱን የጠላ ባይኖርም አነሳሡ ግን ዘግናኝ ሆነ።
"…የፒያሳ ልጆች ፓርቲ አዘጋጅተው ነው ጨፍረው መሃል ከተማውን ለቅቀው የወጡት። ካዛንችሶች ጭራሽ ባንድ አቁመው፣ ቢራና ውስኪ አውርደው፣ ሰንጋ ጥለው ነው ከከተማ ዳር የተደፉት። ደባል ናችሁ የተባሉትን ሁሉ ውኃ ነው የበላቸው። አየር ላይ ነው የቀሩት። አንድ ሰው ትንፍሽ እንዳይል ተደርጓል። ሰው ተነቅሎ ሳር ተተክሏል። ከቤት ከድርጅት፣ ከፋብሪካ የመብራት ኃይል ተቋርጦ ለብሮባጋንዳው ፍጆታ የመንገድ ዳርና ሕንፃው ሁሉ በቡና ቤት መብራት ተጥለቅልቋል። ፋፏቴው ውኃ በወር የሚመጣባት አትመስልም። ይሄን ሁላ ታዲያ ዜጎች ላይ ተጨምሮ ለኮሪደር ልማት ለበራው መብራት፣ ለፈሰሰው ውኃ ይከፍላል። ያውም በእጥፍ። የት ልረፍ ይሉ የነበሩ ሁላ አሁን ጥያቄ እንኳ ቢጠይቁ ከልማቱ አትበልጥም፣ ድራሽህ ይጥፋ ጥፋ ከዚህ እንደሚባሉም ተሰምቷል። አጅሬው የአንድ አሮጊት ቤት ገንብቶ የመቶ ሺ አሮጊቶችን ቤት ይንደዋል። በቴሌቭዥን የሚታየው የአንዲቷ ለሳምፕል የተሠራች የአሮጊቷ ቤት ናት። የፈረሰው መቶ ሺ የአሮጊቶችን ቤት ማን ይመለከተዋል። እንዲህ ዓይነት ነገር ነው የገጠመን።
"…በኮሪደር ልማቱ ሥራ ላይ የተሠማሩትን ኮንትራክተሮች ብሔር ዓይተው የሚያብዱ ሁላ ገጥመውኛል። እና ራሴን ልጥቀም ብሎ ከአባቱ ከህወሓት ዓይቶ ኮርጆ ቀጽሎ የመጣው ኦህዴድ ከዚህ የዘለለ ምን እንዲያደርግልህ ነበር የፈለግከው? ኮንትራክተሮቹም፣ ሠራተኞቹም ከ95% በላዩ ኦሮሞ የሆነው እኮ በምክንያት ነው የሚል መልስ ነው የምታገኘው። ምነው በትግሬዎቹ ጊዜ አልተናገራችሁ? ዛሬ እኛ በደማችን ያመጣነውን ለውጥ በረከቱን እንዳናጣጥም ነው የምትፈልጉት? 5% የቀን ሠራተኛ ከሆንክ አነሰህ? በዚህ እንኳ ትኩሳትህን አብርድ ትባላለህ። አብርድ። ከአዲስ አበባ ያለጦርነት ትጸዳለህ ነው ጨዋታው። እያጸዱትም ነው። መርካቶ ይቃጠላል፣ ይታጠራል፣ መሀል ከተማው ይፈርሳል። የንግድ ድርጅቱም፣ በቅናሽ የሚበላ ምግብ መሸጫ የኮንቴይነር ሽሮቤትም ይፈርሳል፣ የግንባታ ሥራ ይቆማል፣ በቀን ሥራ የሚተዳደረው አብዛኛው ሰው ሥራ አጥ ስለሚሆን ሥራ ፍለጋ ያለምንም አስገዳጅ ጣጣ፣ አንጃ ግራንጃ ከተማዋን ለቅቆ ሙልጭ ብሎ ወደ ገጠር ይመለሳል፣ አልያም እግሩ ባመራው ሥፍራ ወደ ስደት ይቆሰቁሰዋል። ሥራ አጣሁ ብለህ መንገድ ዳር ቆመህ ብትገኝ፣ እለምናለሁ ብለህ ወዲያ ወዲህ እላለሁ ብትል ትታፈሳለህ፣ ወይ ወደ ዘብጥያ አልያም በፋኖ እጅ አልያም በሸኔ እጅ ትገደል ዘንድ ወደ እሳት ትላካለህ።
"…አሁን በዘመነ ብልፄ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲም፣ ተማሪም የለም። ትግሬ መማር ካቆመ ቆየ። ትምህርት ቤቶቹም ወድመዋል፣ መምህራኑና ተማሪዎቹም በጦርነቱ ወይ ሞተዋል፣ አልያም ተሰደዋል። የቀሩትም ሴት ደፋሪ፣ ቆዛሚ፣ ባለዊልቸር ሆነዋል። ዐማራም በአቢይና ደፂ ጥቅሴ ጦርነት ወቅት ትምህርት ቤቱ ወድሟል፣ አሁንም እየወደመ ነው። በሰሜን ትምህርት የሚባል እንዳይኖር አድረጓል ኦሮሙማው። በድሮን፣ በእሳት ሁላ ነው እያወደሙት ያለው። ወዳጄ ትምህርትን እየተማሯት፣ ሥራን እየሠሯት ያሉት ባለጊዜዎቹ ናቸው። ተረኞቹ። አዲስ አበባ ከተማ ለሸገር ሲቲ የኦሮሞ ተማሪዎች ዩኒፎርም የማሟላት ግዴታም አለበት። በቀደም በደራ በግፍ አንድ ሰው ታረደ ብለው በየዩኒቨርሲቲው ሰልፍ የወጡትን የኦሮሞ ተማሪዎች ብዛት ስታይ ኦሮሞና ትግሬ ትቀናለህ፣ ትቃጠላለህ፣ ሌላ ምርጫ የለህማ። ለመጪው ጊዜ ምን እየታሰበ እንደሆነም ይገባሃል። አሁን ኦሮሚያ እስክትለማ ሌላው ክፍል ይድማ የሚለው መፈክር በሃላል ተግባር ላይ ውሏል። ከእንግዲህ ካሣ ምናምን ብሎ ነገር የለም። ተነሥ አልነሣም ብሎ ክርክርም የለም። ዝም ብለህ እሳት ትለቅበታለህ። አንሱ አታንሱ ብሎ ግብ ግብም የለም፣ በሂሊኮፍተር እሳቱን ልናጠፋው እየሞከርን ነው ብለህ ዜና ትሠራለህ። የእሳት አደጋው እንዳያጠፋው ግን ታሰለጥነዋለህ። ከዚያ አለቀ ድራሽ አባትህን ያጠፉታል።
"…መከራው በአዲስ አበባ ብቻ አያቆምም። ይከተልሃል ገጠር ድረስ፣ አዲስ አበባ ዱባይን፣ ፓሪስን መሰለች፣ አቤት ስታምር ብሎ ሀረርጌ ላይ፣ ሱማሌ አፋር፣ ሲዳማ ላይ፣ ደሴ፣ ባህርዳር ነቀምት ጎንደር ላይ ሆኖ ምራቅ የወጣ ሁሉ የኮሪደር ልማቱ በረከት እየገሰገሰ ከደጁ ከች ይልለታል። ፋብሪካ፣ ትምህርት ቤት መመኘት ሲኖርብህ የቡና ቤት መብራት ተመኝተሃልና የተመኘኸው በረከቱ ለሁልህም ይደርስሃል። ጅማ አካባቢ ይመስለኛል ኦሮሚያ ውስጥ በኦሮሚኛ ቋንቋ ተሰብስበው ደም እንባ የሚያለቅሱ ሰዎች እያየሁ ነበር። ግሬደሩ ቤታቸውን፣ ቡናቸውን ሲንድ፣ ደሴም እንደዚያው። ደቡብ መምህራን ደሞዝ ከተከፈላቸው ቆየ አሉ። የብልፅግና ጽሕፈት ቤት ግንባታን በተመለከተ የመንግሥት ሠራተኞች ከደሞዛቸው ይቆረጥ ተብሎ በመወሰኑ እምቢ ያሉት ወደ ዘብጥያ ገብተው እየተነረቱ ነውም ተብሏል። ደቡብ መዋጮ፣ ኦሮሚያና ዐማራ አፈሳ፣ አዲስ አበባና በከተሞች ፈረሳው ጦፏል። በዚህ ላይ ነው እንግዲ እስላምና ክርስቲያን፣ ብሔር ከብሔር ይጫረስ ዘንድ ሩዋንዳን የሚያስንቅ መንግሥታዊ የሞት ቅስቀሳ እና ዐዋጅ እየተጠናከረ የመጣው።
"…እባቡን ተንከባክባችሁ፣ በሞራል፣ በጸሎት፣ በገንዘብ፣ በፕሮፓጋንዳ ደግፋችሁ ዘንዶ አሳክላችሁት አሁን ዘንዶው እየዋጣችሁ ጅቡም እየቆረጠማችሁ ያላችሁ የተከበራችሁ ቤርቤረሰቦችዬ ደና ናቹ? እንደምን ናቹ? ትምህርት የለ፣ ሥራ የለ፣ ደሞዝ የለም። የጅቡ መከራ በሁሉም ቤት ገባ። ዘንዶው ሁሉንም እየዋጠ ነው። ተራ በተራ ይሰልቅጥሃል።
"…ታዲያ ምን ይሻላል…? አትበለኝ…! እንጃልህ…! እኔ ምን ዐውቅልህ። ትልና ዓይንህን፣ ቀልብህን፣ ተስፋህን ፋኖ ላይ ጣል ታደርጋለህ።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሕዳር 18/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ጅቡ የልቡን ፈቃድ አድርሶ ከሄደ በኋላ የውሾች ጩኸት ምን ሊረባ? ምንስ ሊፈይድ? በቃ ሄደ እኮ። በረቱን ሰብሮ፣ ከጋጣው ገብቶ፣ መንጋውን እየነከሰ፣ እየገደለ፣ ዘንጥሎ ዘንጥሎ ቦጫጭቆህ ሽባ ካደረገህ በኋላ ምን የሚሉት ጩኸት ነው? የረፈደበት የውሾች ጩኸት ምን ሊፈይድ? ምን ሊረባን ነው? ከንቱ ጩኸት። እንደ ዐማራ ጅቡን ገትሮ፣ እባብ ዘንዶውን ቀጥቅጦ ካልተፋለመው መጨረሻህ ዓይንህ እያየ፣ ጆሮህ እየሰማ መቆርጠም፣ መዋጥ፣ መሰልቀጥ ነው ዕጣ ፈንታህ። ጠበቃ አንዷለም ቡካቱ ገዳ ትናንት የጻፈው አንድ አሳዛኝ ገጠመኝ የማኅበራዊ ሚዲያውን አየር ሞልቶት ባየው ጊዜ ነው ይሄን ርእሰ አንቀጼን በዚህ መልክ ለመጻፍ ተነሳሣሁ። ጠበቃ አንዷለም የጻፈው ታሪክ በዚህ መልኩ ነበር የከተበው።
"…ቅስም ይሰብራል። በማለት ነበር ጠበቃው የጀመረው። "…አርብ ዕለት ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ አትክልት በማምረት ሥራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው ቢሮዬ መጡ። ሰፈሩ ለልማት ሊነሣ ነው እየተባለ ነው። ከወላጆቻችን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ለ73 ዓመታት ቆይተናል። ድንገት ተነሡ ብንባል ምን ይዋጠን!?' አሉኝ። "መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማመቻቸት የመንግሥት ግዴታ ነው። ያ ሳይሆን ለማስነሣት እንቅስቃሴ የሚደረግ ቢሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቤ እግድ እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ!' ብያቸው ተለያየን። ቅዳሜ ጉዳዩ የሚታይበትን አግባብ ሳዘጋጅ ዋልኩ። እሁድ ጠዋት ደወሉልኝ። ከቤተ ክርስትያን ስንመለስ ቤታችን እየፈረሰ አገኘነው አሉ። (ልብ በሉ ከቤተ ክርስቲያን ሲመለሱ ነው)
"…ከባልደረባዬ ጋር ሄድን። አይዟችሁ ብለን መትረፍ የሚችለውን ለማስቆም እንሞክራለን አልናቸው። እስከ ማታ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት የሕግ አቤቱታዎችን ስናዘጋጅ አመሸን። ሰኞ ጠዋት ኮሚኒቲው ሕጋዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር ያላቸው በመሆኑ በማኅበራቸው ስም ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ኑርጋ ውክልና እንዲሰጡን ተነጋገርን። ትላንት ከሰዓት ሊቀመንበሩ የጠበቃ ውክልና ለመስጠት የማኅበሩን የመመስረቻ ጽሑፍ ስላጡት ለማክሰኞ ጠዋት እንደሚሰጡን ተነጋገርን። ዛሬ ጠዋት አቶ ዱላ ከቤታቸው ሲወጡ የማኅበሩ አባላት ሰፈር ውስጥ ለማፍረሻ የመጣ ዶዘር ቆሟል። ሌሎች አባላቶች ለኛ ውክልና ለመስጠት ውልና ማስረጃ እየጠበቋቸው ነው። አብራቸው ከቤት የወጡትን ባለቤታቸውን "መጣሁ እየሄድሽ ጠብቂኝ" ብለዋት ወደ ቤት ተመለሱ። በአንዲት ቀጭን ሲባጎ ራሳቸውን አንጠልጥለው ተገኙ።
"…ዛሬ ጠዋት 3:00 ላይ እኔ አቤቱታዬን ይዤ የአቶ ዱላን ስልክ ስጠብቅ ከሌሎች አባላቶች ተደወለልኝ። ከዛ ወዲህ ያለው ቢነገርም ጥቅም የለውም። ሰፈሩ መፍረሱ እና መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰዓት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው። አቶ ዱላ ለ20 ዓመት በሊቀመንበርነት ያገለገሉትን፣ ከ70 ዓመት በላይ በአንድ ቦታ የቆየውን ለፍቶ አዳሪ ማኅበረሰብ "ፌይል አደርጌያቸዋለሁ" ብለው ራሳቸውን አጥፍተዋል። እኔም ያንን ኮሚኒቲ ፌይል አድርጌዋለሁ። ትላንት አቤቱታውን ባስገባ ምናልባት ሊቀመንበሩ ከውሳኔው ይቆጠብ ይሆን?! ከጠዋት ጀምሮ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ።
ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል። ነብሳቸውን ፈጣሪ ይቀበላት። በማለት ታሪኩን ቋጭቷል። የሚገርመው የዚህ ጠበቃ ጓደኞች የሆኑ እነ ቶማስ ጃጀው ታሪኩን ሼር በማድረግ እንኳ አላገዙትም።
"…ይሄ በግልፅ የተነገረ ነው። ያልተነገረውን ቤት ይቁጠረው። በሌላ ዜና ትናንት ራሱ አሻም ቲቪም የሆኑ የእናቶች "መልካችንን ሳታሳዩ ብሶታችንን ቅረጹና ለመላው ዓለም አስተላልፉልን" በማለት ቤታቸው ያለ ተለዋጭ ስፍራ በላያቸው ላይ የፈረሰባቸው እናቶች ተሰብስበው ሲያለቅሱ ዓይቻለሁ። ከራብ፣ ከጦርነት ሌላ ብዙ ሰው በድንጋጤ እየሞተ ነው። አንድ ሰው ከልማት አይበልጥም እየተባለ በአንድ ሰው ሞት ምክንያት የሚበተነው የቤተሰብ ብዛት፣ የሚፈጠረው ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሃገሩን እያጫጨው ነው። ሙሉ ፒያሳ እስከ መገናኛ ድረስ መንገድ ዳር የነበሩ ሱቆች፣ የንግድ ድርጅቶች በሙሉ በአስቸኳይ ፈርሰዋል። በቦታው ላይ ደግሞ ገሚሱ ታጥሯል፣ ገሚሱ የብሽክሊሊት መንጃ መንገድ ሆኗል። ልማቱ ይሄ ሆኗል። በእነዚያ በፈረሱ ሱቆች ውስጥ፣ በፈረሱት ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ዜጎች በሙሉ አሁን በአንድ ጀንበር የደሀ ደሀ ሆነው ተገኝተዋል። ከድንጋጤ የተነሣ ታማሚው መብዛቱ አማኑኤል ሆስፒታል የአእምሮ ህሙማን መቀበል ሁላ አቁሟል እየተባለ ነው። ዓረቦች ሀገሪቱን ገዝተዋል። ዓረብ ሀገር ለዓረብ ገረድ ሆነው ለፍተው ሲደክማቸው ወደ ሀገሬ ልግባ ብለው ለዓመታት ፈግተው ጥረው ግረው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በላባቸው የሠሩት ሕጋዊ ቤት ፈርሶ ለዓረቦች እየተቸበቸበ ነው። በዚህ ምክንያት ገሚሶቹ ታንቀው፣ መርዝ ጠጥተው ሞተዋል፣ ቀሪዎቹም ፀበል ለፀበል መንከራተት ይዘዋል። ነገርየው ከባድ ነው።
"…አሁን ከመንጋው ይልቅ ጁቡ ነው ጉልበት ያለው። በተለይ አዲስ አበባ ላይ ጅቡ ያለው ጉልበት ከበድ ያለ ነው። ጅቡ እጅግ ርኅራሬ የሌለው ጨካኝ፣ አረመኔ አደገኛ ጅብ ነው። ቀደም ብለው ጅቡን በጊዜ መላ በሉት ይሉ የነበሩትን ድምጾች አንሰማም፣ አናዳምጥም ይሉ የነበሩ፣ እንዲያውም ለጅቡ በራቸውን ከፍተው ሌጦ ቆዳም አንጥፈው እዚህ ተኛ፣ እዚህ አረፍ በል ይሉት የነበሩ፣ ኧረ ተዉ ይነክሳችኋል፣ ይሄ ጅብ ልጅ እግር ስለሆነ ነው እንጂ አባቱ እኮ ህወሓት የተባለው ያ የቀን ጅብ ብላችሁ ያባረራችሁት የዚያ የጅብ ልጅ ነው ስንል ኧረ ማን ሰምቶን? እንዲያውም ይሄኛውን ጅብ እና ያኛውን ጅብ በምን ሒሳብ ነው የምታነጻጽሩት? ሁላ ብለው የወረፉን፣ የወረዱብን ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ይሄኛው ጅብ ቆንጅዬ ነው። ሞገሱ ራሱ ይከይፋል። አንደበቱም ጣፋጭ ነው። በዚያ ላይ ሃይማኖቱም እስላምና ክርስቲያን ነው። ቢዋሸንም ልጅ ስለሆነ ነው። ደግሞም ሀገሩን ኢትዮጵያን እኮ ይወዳታል። ከአፉም አይለያትም። ሴቶችንና ሚስቱን ወላጅ እናቱንም ሁሉ በፓርላማ በአደባባይ ያከበረ እኮ ነው። በፍጹም ይሄኛው ጅብ ከዚያኛው ጅብ ጋር መነጻፀር የለበትም። ምቀኛ፣ ሴረኛ፣ ቅናታም፣ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ሕዝብ፣ የወያኔ ተላላኪ ወዘተ ስለሆናችሁ እንጂ ይሄኛው ጅብ የማታ ጅብ ነው ነበር የጅቡ አድናቂዎች መልሳቸው። አያ ጅቦ ይኸው አሁን ሲፈልግ አድናቂዎቹን፣ ሲያሻው ተቃዋሚዎቹን ያለ ከልካይ ተራ በተራ ይቆረጣጥማቸው ይዟል። ይበልህ።
"…ይሄ የማታም የቀንም የሆነ ሰዓት የማይመርጥ ጅብ አሁን የጅብ መንጋ ሆኗል። ባንክና ታንኩን ተቆጣጥሯል። መንጋው በተለይ አዲስ አበባ ላይ ተቆጪ፣ ገልማጭ፣ ቀጪም የለውም። የጅብ መንጋው ከዚህ ቀደም ትግራይን አድቅቆ ቆረጣጥሞ ዘጭ አድርጓታል። ጅቦ በትግራይ ሲበላ፣ ጠብሶ ሁላ ነው የበላው። ከብቱን አላስቀረም፣ ሙልጭ አድርጎ ነው የበላው። አሁን በትግራይ የትግሬ ገበሬ ወንዱ አልቆ ሴቷ ናት የቀረችው። ከብት ጠፍቶ ሰው ጠምዳ ታርሳለች በትግራይ የትግሬ ሴት። ይኸው እስከአሁን ትግራይ አላገገመችም። የጅብ መንጋው አፋርን፣ ሶማሌን፣ ደቡብን፣ ጋምቤላን ያለከልካይ ተራ በተራ እያማረጠ ነው ሃም፣ አኝ እያደረገ እየበላ ያለው። የጅብ መንጋው ዐማራ ክልልን ከአባቱ ከወያኔ ጋር በልቶ አልጠግብ ብሎ አሁን ደግሞ ለብቻዬ ልብላው ብሎ ወደ ዐማራ ክልል ገብቷል። በዚያ ብቻ ነው ጅቡ ከባድ የመከላከል ፈተና የገጠመው። ዐማራ ከጅብ መንጋው ጋር ሲገጥም ሌላው ከዳር ቆሞ እያየ ይስቃል። ይሄኛው የጅብ…👇 ① ✍✍✍
“…ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።” ፊል 3፥2 “…ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።” ራእ 22፥15
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
በቲክቶክ መንደራችን ልመጣ ነኝ…!
"…ከቲክቶክ ካምፓኒ ባገኘሁት ምክረ ሀሳብ መሠረት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ቲክቶክ መግባት ካለብኝ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት12 ጀምሮ የምገባ መሆኔን እገልጥላችኋለሁ።
"…ሌላው ቲክቶክ ገብቼ ጸሎቱን በመጀመሪያዎቹ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ እንዳደርግም ተመክሬአለሁ። ከዚያ በኋላ በቀጥታ ወደ መርሀ ግብሬ። አለቀ።
"…በመጨረሻም የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ እያነበባችሁ ወደ ቲክቶክ መንደሬ በታክሲም፣ በቶቢሲም፣ በሼሼንቶም፣ በጋሪም፣ በእግርም ብቻ በፈለጋችሁት የመጓጓዣ ዘዴ በሮጲላም ቢሆን ሄዳችሁ በዚያ እንገናኝ። ነጭ ነጯን መስማት የሚፈልግ ከቤቴ ይምጣ…
በላሌዴንጣ… አዲጭ…
• ወደ መንደሬ የመግቢያ ካርዱ ይኸው
👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
👆③ ✍✍✍ …የጎንደሩ እነ አያሌው መንበር አስራት ቲቪን፣ የጎንደሩ እነ ሙሉቀን ተስፋው አብኔትን፣ እንዳፈረሱት ሁሉ የጎንደሩ አበበ በለው ደግሞ መረጃ ቲቪን ለማፍረስ ይፍጨረጨራል። መቼም ልብ አይሞት? እሱ አብሯቸው የሚሠራው እነ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም እኮ እንኳን ሚዲያ ዙም መምራት እንደማይችሉ አሳዩን። ሰው ምን ያህል እንዳሰለቸ ብታውቁ ጥሩ ነው። አበበ በለው የሬስቶራንት ባለቤቶች፣ የሬስቶራንት አስተናጋጆች የሚደውሉልኝ ስለሰለቸሃቸው እኮ ነው። በቃ ከበላ ከጠጣ ብር ይክፈለን፣ መተደዳሪያችን ቲፕ መሆኑን እያወቀ ጭራሽ እኛ አስተናጋጆች እንድንከፍልለት ሁላ ይፈልጋል። በጣም ሰገጤ እልም ያለ ገጀራ ፋራ ነው። የዐማራ ማኅበራት ሰዎች ደውለው ለእኔ ስለአንተ ደደብነት የሚነግሩኝ ስለሚበሳጩብህ ነው። የጣና ቲቪው አመራሮች ሚስጥራችሁን አውጥተው የሚነግረኝ ተንኮላችሁ ቢያንገሸግሻቸው ነው። የዋ አባላት የሚደውሉልኝ አንተን ቢታዘቡህ ነው። እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ ውስጥ አለሁ። የዲሲ ሰው አምርሮ ተበሳጭቶብሃል። ሰው ጠፍቶ ነው ወይ የአዲስ ድምጽም፣ የዋ’ም መሪ የሆንከው? ሰው እየታዘብህ ነው። ቁማር ቤት እየሠራህ እና ታክሲ ሹፌር ሁነህ ቴስላ እና የሚሊየን ዶላር ቤት መግዛትህን የዋ አባላት ናቸው ግራ ቢገባቸው በትዝብት የነገሩኝ። ብዓዴን እንደሆንክ እና ባህር ዳር ቤት እንደሰጡህ የነገረኝ ጓደኛህ ወንደሰን ተክሉ ነው። በቪዲዮም አለ።
"…ማይይም ስለሆንክ እንጂ አንተ የምትለጣጥፈውን ቪድዮ ያሳየሁት የኦሮሞ ፔጆች ላይ ነው ያገኙሁትን ነው። ትናንት ያጫወትከው ቪዲዮ የኦሮሞ ገጾች ላይ አለ ከፈለክ ሊንኩን እልክልሃለሁ። አንተ የፋኖ ሚስቶች ደወሉልኝ የምትለው ሰርካለምን እንደሆነ 100% አፌን ሞልቼ እናገራለሁ። ሠርካለም ፋሲል ባሌን ፋኖ ጋዜጠኛ እስክንድርን አድኑልኝ ብላ እንደጠየቀችው እሷ ደግሞ ስትጠየቅ እራሷ መጥታ ምላሽ ትስጥ። ዘመድኩን ፀረ ጎንደር ነው ብለው ያን ሁሉ ፕሮፖጋንዳ ሰርታችሁ ስለከሰራችሁ እንደበሸቃችሁ ዐውቃለሁ። ጧ በል። ከዚያ ሁሉ ፕሮፖጋንዳ በኋላ የቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች እኔ ጋር መደወላቸው፣ እነ ጋሽ መሳፍንት እና ሌሎች ፋኖዎችም እኔ ጋር መደወላቸው፣ ያች ቧሏ የተሰዋበት የጎንደሯ የፋኖ ሚስት ከነ ልጆቿ ዘመዴ እርዳኝ ብላ እኔ ጋር የደወለችው እኮ እኔ እንደ አንተ ፀረ ጎንደር የእናት ጡት ነካሽ እንዳልሆንኩ ስለምታውቅ ነው። እርምህን አውጣ። እንደ ደርጉ ክንፉ ወዳጄ የደርግ ሕዝብ ለሕዝብ እስክስተኛ ስለሆንክ በሰው ተቋም ማዘዝ፣ አምባገንን መሆን፣ መሆን ትፈልጋለህ። አንተ ዶላር አፍሳለሁ ብለህ መረጃ ቲቪን ለቅቀህ ስትወጣ እነ ሙሉጌታ አንበርብር የመረጃ ቴቪን ፕራይም ታይም ወስደው እምብርትህ ላይ ቆሙ። ተቃጠል። እናም አሁን አንተ በቁምህ የሞትክ ፀረ ዐማራ የሆንክ፣ የዐቢይ አሕመድ አሽከር ስለሆንክ በጊዜ ዞር ብትል ለጤናህም መልካም ነው። አንድ የምነግርህ ነገር ግን ሀብታሙ አያሌው አያዋጣህም። ውባንተን አቃጥሎ የገደለው ሀብታሙ አንተንም አብሮ እያዋረደ ታሪክህን በቆሻ ብዕር ይደመድምልሃል። ቲስላምዬ ስማኝ። አንድ በሉልኝ…
"…ዜና ዜና ነው። ዜና ሲገኝ ደግሞ ዜናውን መርጠው የሚያቀርቡት የፓርቲ ሚዲያዎች ናቸው። ጋዜጠኞች ደግሞ ወገናዊነት ቢያሳዩ እንኳ ዜናውን በስሱ መሥራት ግዴታቸውም ነው። ዜናውን የትግሬ እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ፣ የብልፅግናም ጋዜጠኞች ባይሠሩት እንኳ እሺ በዐማራ ስም ምለው እየተገዘቱ፣ ከዐማራው ሕዝብ ላይ ገንዘብ እየሰበሰቡ፣ እየቀፈሉ ኑሮአቸውን በዐማራ ደም እየገፉ፣ የዐማራ ችግር ቸርችረው እየሸጡ የኑሮአቸው ቋሚ መተዳደሪያ ያደረጉ የዐማራ ሚዲያ ነን ባዮች ዝምታ ግን ገራሚም አስደንጋጭም ሆኖ ነው ያገኘሁት። የጎንደር አባቶች በእስክንድር ነጋ ተጭበርብረናል የሚለውን ድምጻቸውን ከማፈን አልፈው አበበ በለውና ሀብታሙ አያሌው እነዚህን ሰዎች እስከመሳደብና ማስፈራራት ድረስ መድፈራቸውንም ስታይ ትደመማለህ። ለወትሮው በሰበር ዜና ሲያጨናንቁን የነበሩት ሁሉ እኮ ናቸው ድራሽ አባታቸው የጠፋው። ኢትዮ ፎረም እንኳ እሺ አፍቃሬ ወያኔ ነው፣ ወያኔ ደግሞ ጋሽ መሳፍንትን አምርሮ ነው የሚጠላቸው፣ እርሱ አይዘግብ ሌሎቹን ምን በላቸው? ኡጋንዳ ያሉት ኢትዮ ኒውስ፣ ኢትዮ 251 ወዘተ ዝም ጭጭ፣ ምጭጭ ነው ያሉት። ጎንደሬው በለጠ ካሣ፣ ከረንት አፌር ደመቀ ዘውዱንና የባንክ ሌቦቹን የፋፍዴኖችን ዋሽቶ እነሱ የተዘረፈ ባንክ እንዳስመለሱ አድርጎ የዘገበው ሶዬ አሁን የእነ ጋሽ መሳፍንት ቢዘግብ ነበር የሚገርመው።
"…የቀድሞ ኢሳት፣ ግንቦት ሰባቶቹ እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ደረጄ ሀብተወልድ እኮ ድራሻቸው ነው የጠፋው። ጣናማ ጣና ነው ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ይዘግበዋል ተብሎም አይጠበቅም። የሆነው ሆኖ የሁሉም አስመሳይነት በመገለጡ በእጅጉን ነው ደስስ ያለኝ። እነ ጋሽ መሳፍንትን ከመስደብ አልፈው ጭራሽ ሚዲያዎቹን ወደ መስደብ ነው የገቡት። እንዴትና ለምን የእስክንድርን ስም እና ድርጅት የሚያዋርድ መረጃ ትለቃላችሁ ብለው ነው ያበዱት። መረጃው ትክክል ነው አይደለም ብሎ መሞገት የአባት ነው። መረጃውን ያቀረቡትን ሚዲያዎች እነ ABC Tv፣ እነ ሮሀ ሚዲያን እና የእኔውኑ መረጃ ቲቪን ማበሻጥ፣ ማዋረድ ገራሚ ነበር። በተለይ አበበ በለው አቅሉን ነው የሳተው። የጎንደሮች የሽምግልና ዜና በተነገረ ጊዜ ያኔ ቅድሚያ ወጥቶ አርበኛ ደረጀን በሚዲያው አቅርቦ ያጣጣለው አበበ በለው ነበር። እርር፣ ትክን ብሎ ነበር ሲያጣጥል የነበረው። አሁንም አብሮአደጉን ደረጄን ይዞ ሊንገታገት ይችላል። ደረጄን ሊሸውድ ይችላል። በሰፈር ልጅነት፣ በአብሮ አደግነት ሊያታልለው ይችላል። ሀብቴ ወልዴም ወደ ወልቃይት ፋፍድሄኖችና ደመቀ ዘውዱ ጋር ሊሄድ ይችላል። ይሄን የሚያወራው ራሱ የእነ አበበ በለው ቡድን ነው። ነገር ግን የጎንደር ፋኖ አንድ ከመሆን የሚያግደው ነገር የለም። ማርያምን ስልህ። ተመልከቱ የእነ ጋሽ መሳፍንት ቦንብ እኮ አዲስ አበባን ከእስክንድር ነጋ ጋር አሳልፎ የሰጠው የዋቅጅራ ልጅ ኤርሚያስ ለገሰ ጭምር እኮ ከተደበቀበት ጎሬ ነው ወጥቶ አደባባዩን የሞላው። ዋቅጅራ በምን ሞራሉ ነው ጋሽ መሳፍንትን ከሀዲ የሚለው? አስባችሁታል ግን?
"…በቀጣይ የዐማራ ጉዳይ ይዘው ያሉ፣ በዐማራው ገንዘብ የሚተዳደሩ ሚዲያዎችን ወደ መመርመሩ መሄድ ሳያስፈልገኝ አይቀርም። ከኢሳት እንጀምር። ኢሳት ዐማራውን በኢትዮጵያ ስም ሙልጭ ሲያደርግ የኖረ የሚዲያ ድርጅት ነው። በመጨረሻ ዐማራውን ሽጦ ኦሮሙማው ስር ገሌ ገባ። የኢሳት ጋዜጠኞች በዐማራው ደም ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ኖሩ። ቆይቶ ኢሳቶች ለዐራት ተከፈሉ። እነ ሀብታሙ፣ ኤርሚያስ፣ ብሩክ፣ ልዩ፣ ምናላቸው እና ባለቤቱ ጄሪ አንድ ወገን ሆኑ። አንድ ወገን ሆነው ዐማራውን ይግጡት ጀመር። እነ ሲሳይ አጌና፣ ጴጥሮስ፣ ወንድማገኝ፣ ፋሲል የእኔዓለምና ጋሽ ማናቸው ጋሽ ግዛው አንድ ላይ ሆነው ኢኤምኤስ ብለው መጥተው ዐማራውን እየሰደቡም፣ እየሞገቱም ገትገት ብለው ጋጥጋጥ አድርገውት ለመታየት ሞከሩ። በወዲያ በኩል ደግሞ አበበ ገላው ከአንድ ጋዜጠኛ ጓደኛው ጋር ወጣ። አልቆየም ተጣሉና ተለያዩ። ጎንደሬው የታማኝ ወንድም ተቦርነና የኦቦ ዓለሙ ልጅ ርእዮት ደግሞ ተገንጥለው ወጥተው ባልና ሚስቱ ሚድያ ከፈቱ። ደረጀ ሀብተወልድ ለብቻው ዋይ ዋይ ይል ጀመር። በሙሉ አሜባ ሆኑ። ተከፋፈሉ። ዐማራውን ተቀባብለው ስም እየቀየሩ ጎፈንድሚ ከፍተው ያጥቡታል።👇 ③✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ከዕለተ ሰኞ ማግስት በዕለተ ማክሰኞ ተጀምሮ በዕለተ አርብ ፍጻሜውን የሚያገኘው የእኔ የዘመዴ የዘመዳችሁ የግል ምልከታ የሆነው ተወዳጁና ተናፋቂው ርእሰ አንቀጻችን አሁን ይጀምራል። ተከታተሉት።
"…በመጀመሪያ ሰሞኑን እየሰማን ባለነው ጠፍተው የነበሩት የቅድስት እናታችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጆች የነበሩና ኋላ ላይ ሌላ ቅልውጥ አመል አበጅተው በመታየታቸው ስንቆጣቸው ቱግ ብለው አኩርፈው ግርር ብለው ተከታትለው ወጥተው ከስንዱዋ እመቤት ከተዋሕዶ ቤት ሸሽተው እንደሄዱት ሁሉ አሁን ደግሞ በተከታታይ ግርር ብለው እየመጡ ወደ ቀደመ ቤታቸው እየተመለሱ እንደሆነ የሚያሳይ ዜና እያየሁ በመሆኑ እግዚአብሔርን በማመስገን እጀምራለሁ። ያኔ በዚያን ጊዜ እነርሱ በውስጥ ከእኛ ጋር ሆነው፣ እኛኑ መስለው እኛኑ እንዳይበጠብጡን፣ የበግ ለምድ ለብሰው ተኩላ ሆነው እንዳይጎዱን ፊትለፊታቸው ቆሜ በድፍረት ብቻዬን እንደገጠምኳቸው፣ እንደሞገትኳቸው፣ እንደተፋለምኳቸውም ሁሉ ዛሬ ላይ ምድሩ ሁሉ ከእኔ ጋር ቆሞ ሳይም አምላኬን አምሰግነዋለሁ። እኔ ያኔ ሀብት ንብረቴን ሀገሬን ጭምር ያጣሁባቸው፣ በእነርሱ ተከስሼ በፖሊስ ቦክስ እና በጥፊ እየተወገርኩ ወደ ወኅኒ እስከመወርወር የደረስኩበት ጉዳይ በስተ መጨረሻ በእኔ አሸናፊነት ከቤተ ክርስቲያን እቅፍ ከክርስቲያን ኅብረት መለየት መውጣታቸው አሸናፊነቴን እንዳረጋገጥ አድርጎኝ ደስስ እንዳሰኘኝ ሁሉ አሁን ደግሞ በሄዱበት ስፍራ ወይ አልመቻቸው ብሎአቸው፣ ወይም ደግሞ የቀደመ ሕይወታቸው ናፍቋቸው፣ አልያም ድብቅ አጀንዳ ተሸክመውም ይሁን ከልብ ተጸጽተው ብቻ በእንባ፣ በንስሀ፣ በይቅርታ ተመልሰናልም ብለው የሆነው ይሁን ጊዜ የሚፈታው፣ የሚገልጠው ቢሆንም ለአሁኑ ግን ተፀፅተን ተመልሰናል እያሉ አልቅሰው ሲናገሩ ሳይ ከሁሉ በላይ እኔው ዘመዴ በደስታ፣ በፍቅር ልቀበላቸው ይገባል በማለት እጄን ዘርግቼ ልቀበላቸው ይገባል። እንዲያ ነው።
"…ያነዜ ሀገር ምድሩን አነቃንቄ፣ እኔ በሌላው ተነቅንቄ፣ አርማጌዶን ጦርነት ከፍቼባቸው፣ በወዳጆቻቸውም በጠላትም ተሰድቤ፣ ተገፍቼ፣ ተደብድቤ፣ ተዋርጄ ፊትለፊት እንደተፋለምኳቸው ሁሉ አሁን ደግሞ አሸናፊነቴ ተረጋግጦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ድምፄን፣ ጩኸቴን ሰምታ በውግዘት የለየቻቸው ወንድም እህቶቼ በይቅርታ፣ በንስሀ ተመልሰናል ሲሊ ሳይ የጠፋው ልጅም ሲገኝ ከሁላችሁ በላይ ልደሰት፣ እልልል ብዬም ልቀበላቸው የሚገባው እኔን ዘመዴን ነውና የጠፋችሁ ወንድም እህቶች በመመለሳችሁ ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለትም እወዳለሁ። አይደለም ትናንሾቹን ዓሣዎች እነ ሐዋዝ፣ ዕዝራንና ጽጌሬዳን ገና እኔ ግዙፍ ሻርኮቹን እነ በጋሻውንና ትዝታውን፣ ዘርፌንም ቢሆን በናፍቆት እጠብቃቸዋለሁ። በተለይ ትዝታው ሳሙኤል ከሆነ ግለሰብ ጋር ተቀያይሞ እንጂ በእውነት ወንጌል ሳይገባው ቀርቶ ስቶ አይመስለኝም። እናም የሆነ ቀን የምሥራች እንሰማም ይሆናል። እኔ ተስፋ አልቆርጥም። ታዲያ እኔ ዘመዴ እንዲሁ ዝም ብዬ ከአበደው ጋር የማብድ አይደለሁም። ሳላላምጥም አልውጥም። ይሉኝታ፣ ሼምም የሌለበት ለሁላችን የሚጠቅም፣ አመላለሳቸውን በተመለከተ ሕግና ሥርዓቱን፣ ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ ነው የተመለሱት፣ ወይስ ሌላ የተደገሰልን ድግስ አለ የሚለውን እመረምራለሁ። የሆነ የሚሸተኝ ነገር አለ፣ ቀኝ ትከሻዬን የሚሸክከኝ እሱንም በግልፅ አውጥተን እንነጋገራለን። ተመለሱ የተባሉትስ ወንድም እህቶች በቀጣይ በምን ዓይነት መንገድ ነው መጓዝና መኖር የሚገባቸው? እንዴት ባለ ሁናቴ ነው ሊያዙ የሚገባው? የሚለውን ነጭ ነጯን የሆነች መራር ግን ፈዋሽ እውነትም መነጋገር ይኖርብናል። ሚስቶቻቸው፣ ባሎቻቸውስ አብረው ተመልሰዋል ወይ? እንጠይቃለን። ለሆነ ማኅበር የሚሠራ ፕሮሞሽን እያየሁ ጥርጣሬዬም እየጎላ ነው። የግብረ ሰዶማዊነት ልምምድ ውስጥ ገብተው የነበሩና አሁን ተመልሰናል የሚሉ ቢኖሩ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው መቀበል የሚኖርብን? እንዴት ነው የሚስተናገዱት? እኔ ዘመዴ አሁንም ቢሆን በደስታዬ መሃል ማንንም የማይጎዳ ለጥንቃቄ የሚሆን ጥያቄ፣ ስጋትና ተስፋም አለኝ። ይሄንን ጥያቄ፣ ስጋትና ተስፋም ደግሞ ዛሬ በቲክቶክ መንደሬ በስሱ፣ በዕለተ ሐሙስ የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ሳምንታዊ መርሀ ግብሬ ላይ ደግሞ በሰፊው እመለስበታለሁ። የሐሙስ ሰው ይበለን። ይሄን እዚህ ላይ እንዝጋውና ወደ ተለመደው ሀገራዊ አጀንዳችን እንመለስ።
"…የዓለም ሁናቴ እንደምትመለከቱት፣ እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ነው። እንደ አየር ጠባይ ተለዋዋጭ የሆነው የዓለም ቦለጢቃ አሁን ላይ እያበደ ነው። ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ እየፈጠነ ያለው የዓለም ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እየሆነም ነው። ሁሉም በራሱ መንደርና ቀዬ ችግሮች ስለተወጠረ የዚያ ማዶን ሰፈር ችግርና ሰቆቃ አያይ አይመለከትም እንጂ ዓለም ሁሉ ጭንቅ ላይ ነው ያለው። ሁሉም ሀገር፣ ከኃያላኑ እስከ የደሀ ደሀው ድረስ በውሳጣዊና በውጫዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ችግሮች እየተናጡ ነው። አንዳንዶች ጋር ዘርና ሃይማኖት ተጨምሮ እየጦዘ ነው። ለአፍሪካውያን ብቻ የተፈረደ ይመስል የነበረው የጦርነት ቀጠና አሁን በአውሮጳ ሩሲያንና አውሮጳን፣ አሜሪካንም እያፋጠጠ፣ በተለይ ዩክሬንና ሩሲያን እያጨፋጨፈ ነው። ነጩም፣ ጥቁሩም ሁሉም በያለበት እያለቀሰ ነው። እየሰጋም፣ እየተጨነቀ ነው። ቄለም ወለጋ፣ አዲጉደም፣ ደምበጫ፣ ታች አርማጨሆ፣ ይፋትና ራያ ብቻ አይደለም እየተጨነቀ ያለው። ዓለሙ ሁሉ ጭንቅ ላይ ነው። የእኛ የሚብሰው በማይም፣ ባልተማሩ፣ ሜካፓም ዱርዬዎች መመራታችን ብቻ ነው። የእኛ የሚያሰጋው እነዚህ ማይሞች የሆነ ቀን ማታ ወይ ንጋት ላይ በቴሌቭዥን እና በራዲዮ ቀጥታ ስርጭት ቀርበው እንደ ሩዋንዳ ጭፍጨፋ "ጀምሩ" ብለው ሚልዮኖችን እንዳያጨፉጭፉንና ጉድ እንዳያደርጉን ብቻ ነው። ይሄን ስጉልኝ። እንጂ ዓለሙ ሁሉ በራሱ ጭንቅ ላይ ነው።
"…በዚህ ሁሉ ጭንቅ መሃል ግን አሁን አሁን ቅዱሱ የዐማራ ፋኖ ትግል ጉዳይ እንደ ጥሩ ምንጭ ውኃ ኩልል ብሎ እየጠራ መጥቷል። ድንግዝግዙ ጨላማ የመሰለው ሁሉ ወደ ብርሃን እየወጣ ነው። የፋኖ ትግል ጥራቱ በቃ፣ አለቀ፣ ፍጹም ነው ምንም ዓይነት ተግዳሮት የለበትም የሚያስብልም እንደዚያም ማለትም አይደለም። የከፋ አደጋ የለውም እንጂ በፋኖ ገና የውስጥ ትግል የሚጠይቁ ተግዳሮቶችም ይጠብቁታል። ጊዜው የተለያዩ ኃይላት ፍላጎታቸውን በፋኖ ትግል ላይ ለመጫን የሚራኮቱበት ወቅትም ነው። ማሸነፉ አይቀሬ መሆኑ የታወቀው የዐማራ ፋኖ የእነዚህን ኃይላት ፍላጎት እና ስሜት ማራገፊያ ላለመሆን እያደረገ ያለው ትግል፣ ፍትጊያና ፍልሚያም የሚደነቅ ነው። ፋኖ የትጥቅ ትግል በጀመረ በአንድ ዓመት ውስጥ ግዙፉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከባዶ እጅ ተነሥቶ አራግፎ ባዶውን ማስቀረቱ ሲታይም በዚህ ከመደመም በቀር ሌላ ምንም አማራጭ አይኖረንም። ያለምንም የውጭ ኃይሎች ርዳታ አንድ ፍሬ ጥይት በ2 የአሜሪካን ዶላር እየሸመተ፣ ቀሪውን ከመከላከያ ሠራዊቱ በሚያገኘው ምርኮ እየሰበሰበ፣ ቀድሞ በተፈጥሮ በነፍስ ወከፍ ካለው በሚልዮን የሚቆጠር የጦር መሣሪያ በተጨማሪ አሁን በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በመቶ ሺ የሚቆጠር የዐማራ ወጣት ሰልጥኖ አዳዲስ ዘመናዊ መሣሪያ ከራሱ ከአገዛዙ እጅ በመንጠቅ የታጠቀው የዐማራ ፋኖ ኃይል አሁን አይደለም የክልሉና የሀገሩ አስተማማኝ የቀጠናው ኃያል ኃይል ወደ መሆን ተሸጋግሯል። ይሄ በእጅጉ የሚያኮራና የሚያስደስት ነገር ነው። ድቃቂ የዶላር ሳንቲም ሰጥተው እንደ ህዳር አህያ ሊጋልቡት ፈልገው የነበሩ 👇①
"…እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።…እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። …ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል…። ሉቃ15፥ 7-32
"…ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።” 1ኛ ቆሮ 14፥40
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼