zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የብርድ ልብስ ሪፖርት…

"…የሚያስፈልገው የብርድ ልብስ ብዛት 1200 ነበር። 5 መጠባባቂያ ይዤ ማለት ነው። የአንዱ ብርድ ልብስ ዋጋ 600 የኢትዮጵያ ብር ነው። ስንት ዶላር፣ ዩሮ፣ ወይ ፓውንድ እንደሆነ አላውቅም። የሆነው ሆኖ ግን እስከአሁን ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ ሰዎች እያንዳንዳቸው አቅማችን ይችላል የሚሉትን በማዋጣት በቀበሮ ሜዳ ጎንደር የብርድ ልብሱ መግዣ አዋጥተው አጠናቅቀውታል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ለጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ለብርድ ልብስ መግዣ የሚሆን ያበረከቱ ደጋግ ሰዎች በቁጥር 40 ናቸው። አርባ ሰዎች ናቸው 1205 ተፈናቃዮችን ብርድልብስ ያለበሱት። እያንዳንዳቸው የሚችሉትን ያህል የገዙትን ብርድ ልብስ ብዛትም አያይዤላችኋለሁ። ልብበሉ 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለ50 ሰው ጌጡ ማለት ይሄ ነው። በቁጥር 40 የሆኑ ሰዎች ናቸው የስደተኞቹን ብርድ ለብስ የዘጉት። ይሄን በብር ስናሰላው 1,205×600= 724.197 ብር ነው የመጣው። ወዳጄ እጅህን ለመፍታት መመረጥ፣ እግዚአብሔር መፍቀድ አለበት። እነሆ የተፈቀደላቸው ይህን አድርገዋል። እነርሱም…

      ስም           ብዛት
1.ሆቤ ተስፋዬ~ 120
2.ቲጂ ~              83
3.አቤል~             83
4.ከፍያለው~        83
5.ምሥራቅ ~        83
6.ጋሽ ኃይሉ ~      83
7.ቢኒ ከለንደን ~   80
8.ሎዛ ~              60
9.ፍርዬ~              50
10.ሰሎሞን          40
11.ገኒ~               33
12.የዓለም ልጅ~   30
13.ሃይማኖት ~      30
14.ተክለ መስቀል~ 30
15.ሳሚ ከአዲስ አበባ~ 30
16.ዴቭ ሪች ~              30
17.መሰረት ከቤሩት ~    30
18. ኤልሳ በቀለ~          28
18.ሙሉ ~                    20
19. ትሪስተ~                 20
20.ማይክ ከሰውዝ አፍሪካ ~ 16
21.ወንዴ ~                         16
22.የኔነሽ ካናዳ~                  15
23.ስንታየሁ ከደቡብ አፍሪካ ~ 15
24.ወለተ ወሀና ~                   14
25.ሂሩት ከሊባኖስ ~               10
26.አበባ ከአሜሪካ ~              10
27.ገዛኸኝ ~                          10
28.ቤዛ ~                              10
29.ገነት ~                               8
30.ወድነህ~                            8
31.ሄኖስ ~                              5
32.አሜን ዳኒ~                        5
33.መክሊት~                         5
34.ቤዛ ~                              2
35.ጌታመሳይ ~                     2
36.ክንፈ ~                            2
37.እንዳወቅ~                       2
38.ምስጋናው~                      2
39.ሳሙኤል~                       1
40.ወለተ ሰንበት~                 1

"…ብርድልብሱን ያሟሉ ዘንድ እግዚአብሔር የፈቀደው ለእነዚህ ደጋግ ቅን ልብ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ብርድልብስ መግዢያ ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ። አለቀ። ተፈጸመ፣ ተጠናቀቀ። እግዚአብሔር ይመስገን። የሚቀረኝ አንሶላና ፍራሽ ነው። እሱላይ ተሻሙ።

• የ1 ብርድ አንሶላ ዋጋ 500 ብር ነው።
• የአንድ ፍራሽ ዋጋም 3500 ብር ነው።

"…የስደተኞቹ መከራ፣ ሰቆቃ፣ ከሰውነታቸው የሚወጣው ትል ያሳቀቃችሁ ወገኖች የምትችሉትን ያህል አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል አንሶላና ፍራሽ ለመግዛትና ከወደቁበት አፈር ላይ ለማንሣት ተረባረቡ። በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓውንድ በጣም ብዙ ነው። ዳያስጶራ ግድየለህም ተሳተፍ። አንሶላው ላይ እንረባረብና እሱን እናጠናቅቀው። አንድ አንሶላ በ500 ብር አባዝታችሁ የምትችሉትን ቃል መግባት ትችላላችሁ።

• 👉🏿 +49 1521 5070996 የእጅ ስልኬ ነው። ይሄን ስልክ ሴቭ አድርጉትና ወይ በኋትስአፕ፣ አልያም በቴሌግራም ቃላችሁን ስጡ። እኔም ወዲያው የስደተኞቹን የባንክ አካውንት እልክላችኋለሁ። አመሰግናለሁ። ፍጠኑ።

• ለአንሶላው ደግሞ ስንት ሰው ይሆን የሚያስፈልገው አምላኬ። ፍጠኑ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የፋኖ ዜና የሚኖረኝ፣ ርእሰ አንቀጽም የሚጻፈው ከማክሰኞ እስከ አርብ ድረስ ብቻ ነው። እሱም ቢሆን እንደ ድሮው ዋይ ዋይ እሪሪ ቁቁቁ ኡኡኡም የለበትም። በቃ ለስለስ ያለ አንጀት አርስ፣ አናት ቀዝቀዝ የሚያደርግ ለጋ ቅቤ የመሰለ ዜና ብቻ ነው የማቀርበው። አለቀ።

"…አሁን የዐማራ ትግል ከባዱን ማዕበል፣ ወጀብ፣ ሞገድ እያለፈ ነው። እየተሻገረም ነው። የተጸነሰው የነጻነት ልጁ ሊወለድ ከጫፍም ደርሷል። ጩኸቱም የምጡ ድምጽ ነው። ህመሙም የምጥ ህመም ነው። የምጥ ህመም ደግሞ ጩኸቱ እርግጥ ይረብሻል፣ ቀበቶ ያስፈታል፣ ማርያም ማርያም ያስብላል፣ ለተመልካች ለሰሚ ይጨንቃል እንጂ እንደ ራስ ምታት፣ እንደ አሜባ፣ ወስፋት፣ ኮሶ የመሰለ የበሽታ የሆድ ቁርጠት፣ አይደለም። በቃ ልጅ ሊወለድ ነው። ደምም፣ ውኃም ቢፈስ፣ ልጄን፣ እናቴን፣ ውይ እህቴን የእኔ ደም ይፍሰስልሽ ተብሎ ደረት የሚያስደቃ፣ የሚያስለቅስ አይደለም። ምጥ ነው። ልጁ ሲወለድ ጠብቆ ምጡን እርሺው ልጁን አንሺው ማለት ብቻ ነው።

"…ይልቅ ለመልሶ ግንባታ ከወዲሁ ተዘጋጁ። በወለጋ በኦሮሚያ ወላጆቻቸው የታረዱ የትየለሌ የዐማራ ሕፃናትን ለማሳደግ፣ ለማስተማር ተዘጋጁ፣ በኦሮሙማው እና በትግርሙማው የወደሙ አብያተ ክርስቲያናትና ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታል ጤና ጣቢያዎችን መልሶ ለመገንባት ተዘጋጁ። እኔ የምዘጋጀው ለእሱ ነው። ድሉ ወዶ ሳይሆን በግዱ አፈር ልሶ፣ ደቼ በልቶ ይመጣታል። ለነገው ዛሬ መስጠትን ልመዱ።

"…መርዳት አሁን ጎንደር በቀበሮ ሜዳ ስደተኞች ጀምረናል። የምትችሉትን በውስጥ ጻፉልኝ እና የባንክ አካውንታቸውን ውሰዱ። ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ ነው አሁን የምፈልገው።

• 1 ፍራሽ በ3500 ብር
• 1 ብርድልብስ በ600 ብር
• አንሶላ በ500 ብር

• ቀጥሎ እስከአሁን ስንት ሰው እንደለገሰ እለጥፍላችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።” ምሳ 19፥17  …“ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና።” ምሳሌ 22፥9  …“ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፤ ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።”
ምሳ 28፥27 "…እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና። ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፥ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን። ምሳ 3፥ 26-27

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:05 ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ በሚገኙ ስደተኞች ካምፕ ነው የምናመሻው። በዚያም እያለቅስንም፣ እየሳቅንም አብረን እያወጋን እናመሻለን። 

• ቲክቶክ 👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

• ትዊተር 👉https://twitter.com/MerejaTV

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/mmnEIicMuZQ

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም… ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እልልልል እያላችሁልኝ።

"…ይሄን ፍራሽ አቃጥለን በአዲስ ፍራሽ እንተካዋለን።

ፍራሽ

ዝናሽ ከቤሩት ~ 2000 ዶላር
60 ፍራሽ
ሀይል ጊዮርጊስ ~ 1000 ዶላር
30 ፍራሽ


ብርድ ልብስ

ከፍያለው~ 83
ሃይማኖት ~ 30
ሂሩት ከሊባኖስ ~ 10
ስንታየሁ ከደቡብ አፍሪካ  ~ 15
አበባ ከአሜሪካ ~ 10
ገዛኸኝ ~ 10
ወለተ ወሀና ~ 14
ሳሙኤል ~ 1
ክንፈ ~ 2

• አንሶላ
ሳሚ ሲያትል~ 30
ፍሰሃ ከሊቨር ፑል~ 25
መዓዛ ~ 20
ያሬድ ከአሜሪካ~ 12
መስፍኔ ከአሜሪካ~ 10
ሰሎሞን ~ 10
ጋሻው እስራኤል ~ 6
ክንፈ ሚካኤል ከናዝሬት፣~ 2
ዋሴ ~ 1 አንሶላ

"…እግዚአብሔር ይስጥልኝ። አግኝታችሁ አትጡ። ቃላት የለኝም። እንዲያው ዝም፣ ጭጭ ብቻ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዘመቻ ፍራሽ ተጀምሯል
ያዙ እንግዲህ ሻሞ…

"…የድምፅ መልእክቴን ሰምታችሁታል። የሚያናድድ፣ የሚያበሳጭ ነገር ባልናገርም ነገር ግን የሆኑ ሰዎች 😡 ብው ብላችሁ ትታዩኛላችሁ። ምህረቱን ይላክላችሁ። እኛ ግን ሥራ ላይ ነን። እንቀጥላለን።

"…አንድ የተባረኩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ዶክተር ፍራሹን በተመለከተ ባህርዳር ላይ ያለ ግሬስ የሚባል ፋብሪካ አለ የሥራ አስኪያጁ ስልክ አልሠራ ስላለኝ ነው ከዚያው በፋብሪካ ዋጋ እንዲገዛ እናደርጋለን ብለው ተስፋ ሰጥተውኛል። የአንሶላና የብርድልብስም የምታውቁ አገናኙኝ። እኔ እማፀናቸዋለሁ።

የሚያስፈልገው የፍራሽ ብዛት 1200
                የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር

የሚያስፈልገው የብርድ ልብስ ብዛት 1200
                የአንዱ ብርድልብስ ዋጋ 600 ብር

የሚያስፈልገው የአንሶላ ብዛት 2400
                  የአንዱ አንሶላ ዋጋ 500 ብር

"…ከላይ መርጣችሁ ልባችሁ የፈቀደውን ለሟሟላት ጀምሩ። ጻፉልኝ። የባንክ አካውንታቸውን እሰጣችኋለሁ። እስከማታ ድረስ እስከ መረጃ ቲቪ ነጭነጯን ከዘመዴ ጋር ድረስ ከጨረስን መልካም በቀጥታ ወደ ተማሪዎች ዩኒፎርም እንሄዳለን። ካልጨረስን ግን በነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ ዋይዋይ ስል አመሻለሁ ማለት ነው።

"…1…2…3 ጀምሩ…✍✍🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጀመሪያ ትሉን እናጠፋለን…

"…ትሉ የመጣው ከመኝታው ንፅሕና ጉድለት ነው። 3 ዓመት ሙሉ አፈር ላይ መተኛት ያመጣው ነው። የሕክምና ባለሙያዎች ትሉ በዝንብ የሕይወት ዑደት ያለ የዕጭ ደረጃ ነው ይላሉ። በሕክምና በሽታው Myiasis ወይም "ዱቅንዱቅ" ተብሎ የሚጠራ ሲኾን ሕክምናውም ዕጩ በአለበት አካባቢ ዙሪያውን ቫዝሊን በመቀባት አየር በማጣት እንዲሞቱ ማድረግ አሊያም ነቅሶ ማውጣት፤ እንዲኹም በጣም የቆሰለ ከኾነ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር መድኃኒት መጠቀም ይቻላል ነው የሚሉት። በዋነኝነት ግን መሬቱን ሲሚንቶ መለሰን፣ ፍራሽና የፕላስቲክ ምንጣፍ ማንጠፍ፣ ንፁሕ ጽዱ ከባቢን መፍጠር።

"…እኔ ዛሬ ያሰብኩት መጀመሪያ መኝታቸውን ማስተካከል ነው። ቅድሚያ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ ካሟላንላቸው በኋላ መሬቱን ሊሾ ለማድረግ አልቸገርም። ቅድሚያ ግን በእናቶቻችን፣ በአባቶቻችንና በሕፃናቱ ሰውነት ውስጥ የሚራባውን ትል ማጥፋት ይኖርብናል። ትሉን ለማጥፋት ደግሞ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብሱን ማሟላት አለብን። ባለ ፋብሪካ ወይም በጅምላ የሚያከፋፍል ነጋዴ ካለ ብትጠቁሙኝ መልካም ነው።

"…ፍራሽ የሚፈልገው የሰው ብዛት፣ የሚፈለገው የፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ ብዛት ከነዋጋው ጭምር ከቀበሮ ሜዳ ኮሚቴዎች ደርሶኛል። እሱን ነው የማቀርብላችሁ። በግል፣ በቤተሰብ፣ በማኅበር መግዛት ትችላላችሁ። ይሄን ነገር አንድ በካናዳ፣ በአሜሪካ፣ በእስራኤል፣ በኢትዮጵያ፣ በአውስትራሊያ፣ በደቡብ አፍሪካና በአውሮጳ የሚገኝ ባለፀጋ ሀብታም ጎንደሬም ሊዘጋላቸው ይችላል። ጎንደሬው አያገባኝም ቢል እኔ ሐረሬው ለጎንደር ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለምኜ ማሟላት አያቅተኝም። እነታማኝ በየነ፣ አበበ በለው፣ ጎንደር ኅብረት፣ ስኳድ እያሉ እኔ በቁማቸው ትል ለሚበላቸው ወገኖቼ በመለመኔ አላፍርም።

• ዋጋ ልለጥፍ ነኝ። ለመረባረብ ዝግጁ ናችሁ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ። ዘካ 7፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተናግሬ ሳልጨርስ…

"…ለአዲስ ዓመት በዓላቸው ፈታ ብለው ስቀው እንዲውሉ ግማሽ ሚልዮን ብር ጠዋት ያስገባላቸው ያደግ ሰው አሁን ደግሞ ዘመዴ ለህጻናቱ ትምህርት ቤት የሚጎድለውን ንገረኝ። እኔ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ቆርቆሮ ገዝቼ አሠራላቸዋለሁ ብሎ አስደስቶኛል ብቻ ሳይሆን በረዶ እንደፈሰሰበት ሰው አደንዝዞ አስቀርቶኛል።

"…ጋሼ ኧረ በሚልዮኖች የሚቆጠር ብር ሊያስወጣህ ይችላል ብለውም ታዲያ ይሄ ሁሉ ሕፃን መሃይም ሆኖ ይቅር እንዴ? የራሱ ጉዳይ ያስወጣኝ። አንተ ብቻ ወጪውን በባለሙያ አሠርተህ አስልክልኝ እኔ ማቴሪያሉን ገዝቼ እልካለሁ ብሎኛል። በቅርቡ አልቆ ትምህርት መጀመር አለባቸው ብሎኛል።

"…እኔ ዘመዴ ገና ለገና በነገ ዕለት ምሽት በመረጃ ቴሌቭዥን ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው መርሀ ግብሬ ላይ ድንጋይ ተሸክሜ ሕዝብ እለምናለሁ ብዬ ዕቅድ የያዝኩት ሰውዬ ዛሬውኑ ተሳክቶልኝ የምሆነው ጠፍተኛል። የባንክ ደብተራቸውን ሳልለጠፍ በጥቂት ሰዎች ልገሳ ብቻ ዓለሜን እያየሁ ነው። በእውነት ከእኔ በላይ በዚህ ምድር ማን ዕድለኛ አለ?

• አሁን ቆይ ላልቅስ…? ወይስ ልሳቅ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የድግሱ ፍጻሜ…!

"…ለድግሱ የሚያስፈልገው ሁሉ ተሟልቷል። በመዋጮው ላይ የተሳተፉትም ቁጥራቸው 4 ሰዎች ብቻ ናቸው። ልብ በሉ ጎፈንድሚ የለው። ኮሚቴ የለው። በዘመዴ በኩል አያልፍ። ብሩ የሚገባው በቀጥታ ለእነሱ ነው። ቲክቶክ ላይ ተጥዶ አንበሳ አውርዱልኝ የለ። ኮሚሽን የለ። ምንየለ ምን የለ።

"…5 ሰንጋ፣ 5 ፍየል፣ ለስላሳ፣ ቢራ፣ ውኃ፣ ጨው፣ በርበሬ የቻለው አንድ ሰው ብቻ ነው። 5 ኩንታሉን ጤፍ የቻሉት የተባረኩ ባልና ሚስት ናቸው። ቅቤውን ከነ ማገዶ እንጨቱ የቻለው የእኔው ወዳጅ ጆኒና ባለቤቱ ወይኒ ናቸው። የሚቀረው ወንበርና ድንኳን ነው እሱንም ተከራዩ አልኳቸው። እሺ አሉ ዋጋ ጠየቁ። እየፈሩ ነገሩኝ። 50 ሺ ብር አካባቢ ይመጣል አሉኝ። ይሁና አልኩ። ይሁና ምንአባቱ። ደግሞ ለ50 ሺ ብር።

"…ደወለላችሁሃ አንዱ ቀዥቃዣ። ቀዥቃዣ ወዳጄ ነው። አሮን ይባላል ከካናዳ። ዘመዴ አንድ በሬ ልቻል አለኝ። የምንአባክ በሬ ነው? በሬ ተቀድመሃል አልኩት። እና ምን ተሻለኝ አለ። የሚሻልህማ በበሬው ፈንታ፣ ድንኳኑን፣ ወንበሩን፣ ጎላ ድስቱን፣ ጭልፋ ሰሀኑን፣ ተከራይላቸው ብዬ የባንክ አካውንታቸውን ላኩለት። አለቀ።

"…ማርያምን አዛኜን የበዓሉ ዕለት አዝማሪም አይቀረኝ። ሀሴት በሀሴት ነው የማደርጋቸው። እናትዋ ጎንደር፣ እህልዋ ጎንደር እያሉ በሸነና ይበሉ።

"…የጨረስነው የድግሱን ነው። ለዚህ ለእስከአሁኑ  እግዚአብሔርን አመስግኑልኝና ሌላውን ደግሞ ቆይቼ እቀጥላለሁ።

"…የበዓሉን ድግስ አንዳችሁም ሳትሳተፉበት 5 ወዳጆቼ ብቻ ዘግተውታል። እናም ጓደኞቼ እኔ ዘመዴ ያልተደሰትኩ ማን ይደሰት? በደስታ ያላበድኩ ማን ይበድ?

• ወደ ዋናው ችግር መቅረፊያ መርሀ ግብሬ ልመጣ ነኝ። ይሄኛው ማሟሟቂያ ነው። ይሄኛው ሙቀት መለኪያ ነው።

• ደስ አይልም በማሪያም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

"…ቀጣዩን የምሥራች እስክነግራችሁ እስኪ ግጠሙ። ቅኔ ዝሩ። ደስታ በደስታ፣ ፌሽታ ይሁን ዛሬ ቅዳሜአችን።

"…ግማሽ ሚልዮኑ ብር በባንካቸው ገብቷል። ሪሲቱ ደርሶኛል። እሱንም ቆይቼ እለጥፍላችኋለሁ።

"…ትል ከላያቸው ላይ ሲረግፍ፣ ከሰውነታቸው ተቀዶ ሲወጣ እያየሁማ ዝም ብዬ አልተኛም። ፍራሹን በአዲስ፣ ከነ አንሶላው። አፈሩን በሲሚንቶ ነው የምቀይርላቸው። ብርድልብስ አይቀረኝ ሳንበሸብሻቸው።

"…ተመልከቱ የባንክ ደብተሩን ሳልለጥፍ እኮ ነው እስከአሁን ሁለት ሰዎች ብቻ አንጀታችንን ያራሱን። ጮቤም ያስረገጡን።

"…ትክክለኛ ሰው ጠፋ፣ ሁሉ ሌባ ሆነ እንጂ የሚረዳማ ነፍ ነው። የትየለሌ ነው። ለሰጪ እግዚአብሔር ይስጠው። ለመስጠት አቅም ያጠራችሁን ደግሞ የምትሰጡት ይስጣችሁ።

• የምሥራች ይዤ እስክመለስ እስኪ ለተቀበል፣ ለባለ።መሰንቆው ግጥም ስጡት። 😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከእንጀራ እንጀምር…!

"…ቀበሮ ሜዳ የሚገኙት ተፈናቃይ የጎንደር ዐማሮች መንግሥት በየወሩ የሚሰጣቸው 15 ኪሎ በቀሎ ነው። እሱን አስፈጭተው፣ ንፍሮ አድርገው ሕይወታቸውን የሚገፉት። እናም በዘላቂነት ቦታ እስኪያገኙ እሱ ይቀጥላል።

"…እኔ ግን ቢያንስ ሌላው ቢቀር አዲሱን ዓመት አንደኛ ደረጃ ነጭ ማኛ ጤፍ ተገዝቶ እሱን እንጀራ ቢበሉ ብዬ ከኮሚቴዎቹ ጋር ተነጋገርኩ። ኮሚቴዎቹም እጅግ ደስስ አላቸው። ስንት ኩንታል ያስፈልጋል ስላቸው 4 በቂ ነው። አሉኝ። ቆይተው ከራሳቸው አልፈው ለሌላ ማሰብ ጀመሩ። በጎንደር ከተማ ውስጥ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው የሚረዱ አሉ። ለእነሱ እናካፍላቸዋለን አሉኝ። አይ ጎንደር። አይ ባለ ማዕተብ ሕዝብ አስደናቂ እኮ ነው። ግድየለም የእናንተ እንዳለ ሆኖ አንድ ኩንታል ጨምሬ ለእነሱ ታስረክቡልኛላችሁ አልኳቸው። እሺ አሉኝ። ከዚያ በቀጥታ ወደ ሂሳብ ሥራው ነው የገባነው።

"…አንድ ኩንታል ጤፍ ከነ ማስፈጫው ከነምናምኑ ጨምሬ ኪሎውን በ125 ብር ከፍፍፍ አድርጌ አስልቼ ያዝኩት። ይትረፍረፍ ብዬ። አምስቱ ኩንታል 62,500 ብር መጣ። የሌሎቹንም በዝርዝር በዚህ መልኩ አወጣን። አወጣንና ገና ሳልናገረው ሁለት ደጋግ ባልና ሚስቶች ጻፉልኝ። ጤፉን እኛ እንቻል ብለው ጻፉልኝ። ቻሉት አልኳቸው። ስመ ክርስትናቸው ወልደ ገብርኤል እና ትርሲተ ሚካኤል የተባሉ ደጋግ እኔ የማላቃቸው እነርሱ የሚያውቁኝ ቻሉት። አበቃ። የእንጀራው ነገር ተያዘ።

"…ቀጥሎ ወደ ሰንጋው ነው የምንሄደው። አምስት ሰንጋና አምስት የፍየል ሙክት። ስለሱ ደግሞ እነግራችኋለሁ። ጠብቁኝ።

• 100 ሰው እልልልልልል ካለ በኋላ ቀጣዩን የምሥራች እነግራችኋለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ውሎ ከስደተኞች ጋር

"…ዛሬ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ወደ ጎንደር ሄደን ቀበሮ ሜዳ በተባለ አሰቃቂ የጎንደር ዐማራ ተፈናቃይ የስደተኛ ካምፕ ነው የምውለው። ቀበሮ ሜዳ ከሚገኙ ተፈናቃይ የጎንደር ዐማራ ስደተኞች ጋር ነው የምንውለው። ከወለጋ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከወልቃይት፣ ከትግራይ በግፍ ተፈናቅለው ባዶ እጃቸውን ቤሳቤስቲ ሳይዙ ተባረው ከመጡ የጎንደር ዐማራ ስደተኞች ጋር ነው የምንለው።

"…ተፈናቃይ ስደተኞቹ በነበሩበት ስፍራ ሀብት ንብረት አፍርተው የነበሩ። በረታቸው በከብት፣ ጋጣቸው በበግና በፍየል። ወተት፣ አሬራ፣ እርጎ፣ ቅቤ፣ እንቁላሉ ከማዕዳቸው የማይጠፋ፣ ማሳቸው ያማረ፣ ጎተራቸውም ማዕዳቸውም ሙሉ የሆነ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ባማረ አልጋ ላይ ንፁሕ አንሶላና ፍራሽ ላይ የሚተኙ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ፍሪዳ አርደው የሚያስተናግዱ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ነበሩ። ግን ዐማራ ስለሆነ ተፈናቀሉ። ተባረሩ። በአንድ ጀንበር የደሀ ደሀ ሆኑ።

"…ዛሬ ከእነዚህ ስደተኞች ጋር ነው የምንውለው። ነገም በመረጃ ቲቪ የሚጎድላቸውን በሙሉ ድንጋይ ተሸክሜ እናንተን እየለመንኩ ሳሟላላቸው ነው የምውለው። ብዙም ሰው የሚያስፈልገው አልነበረም። በጥቂት ሰዎች ብቻ የሚሟላ ነገር ነው ጉድለታቸው። እሱን ስናሟላላቸው እንውላለን። ማርያምን ትል ከሰውነታቸው ውስጥ ሲወጣ አሳያችኋለሁ። መፈጠራችሁን ነው የምትጠሉት። መፈጠራችሁን አልኳችሁ። ጎንደር በዚህ ልክ ሲሰቃይ ማየት ያማል።

"…ተፈናቃዮቹ ሕጋዊ የባንክ ደብተር አላቸው። ያውም በመንግሥት የተፈቀደ የባንክ ደብተር። በእሱ ላይ ነው በቀጥታ የምናስገባላቸው። ከእኔ ጋር አይነካካም። ከዚህ በፊት እንደማደርገው ሁሉ ነው አሁንም የማደርገው። ዘመዴ ብሩን በላው እንዳትሉኝ ሳይሆን የሚሉ ስላሉ የእነሱንም አእምሮ ከመጠበቅ አንፃር እኔ በእኔ በኩል በግሌ ሰብስቤ ስለማላውቅ አሁንም በቀጥታ ከተጎጂዎቹ ጋር ነው የማገናኛችሁ። ባንኩ ስዊፍት ኮድም ስላለው ካላችሁበት ሀገር ቀጥታ በባንክም ትልኩላቸዋላችሁ ማለት ነው። አለቀ።

"…በመጀመሪያ ዛሬ የምናደርገው መጪውን አዲስ ዓመት ደስስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ በዓሉን እናሳምርላቸዋለን። ቀጥሎ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ በቋሚነት የጎደላቸውን እናሟላላቸዋለን። ለምሳሌ እንደትምህርት ቤት ያለውን እንገነባላቸዋለን። ሰሞኑን ከኮሚቴዎቹ ጋር ስለዚህ ጉዳይ ነበር በዝርዝር ስንወያይ የከረምነው። ሁሉንም በባለሙያ አስጠንተው ልከውልኛል። አንዱም አይቀረኝ ሁሉንም ለምኜ አሟላላቸዋለሁ። በቅድሚያ ግን አዲሱ ዓመት በደስታ የሚያሳልፉበትን ነው የማስቀድመው።

"…መንግሥት ለወር ብሎ 15 ኪሎ በቆሎ ነው ለስደተኞቹ የሚያድለው። 15 ኪሎ በቆሎ። እሱን ነው በልተው የሚኖሩት። በቆሎው በዚያው ይቀጥል። እኔ ግን ለአዲስ ዓመት ለቅዱስ ዮሐንስ ለእንቁጣጣሽ ነጭ ማኛ አንደኛ ደረጃ ጤፍ አስፈጭቼ ነው ሰንጋ ጥዬ፣ ለስላሳ፣ ውኃ ገዝቼ አንበሽብሼ የማውላቸው። ጥብሱን፣ ቁርጡን ነው የማማርጣቸው። በደስታ ነው ሳስለቅሳቸው የምውለው። የትአባቴንስና።

"…ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸው በዝርዝር ተነግሮኛል። እነሱ 3 ሰንጋ ይበቃናል ነው ያሉት እኔ ግን ለመጠባበቂያ 4 አደርግላቸውና አምስተኛ ሰንጋም እጨምርበታለሁ። አምስተኛውን ሰንጋ ደግሞ እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ልጆችን የሚረዱ አሉ ለእነሱ እናበረክትላቸዋለን። በጤና ምክንያት የበሬ ሥጋ ለማይበሉና እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ለሚገኙ ለሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ደግሞ 5 ሙክት ፍየል ያስፈልገናል ብለዋል። እሱን እኔ ራሴም ቢሆን ከራሴ ጦሜን አድሬ አሟላላቸዋለሁ። የሚረዳኝ ካገኘሁ መልካም ነው። ከሌለም እሱ አያቅተኝም።

"…50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ለ50 ሰው ግን ጌጥ ነው። እንደምታስቡት አይደለም። የነገው መርሀ ግብሬ ላይ ላይ በዛ ያለ ሰው ያስፈልገን ይሆናል እንጂ ለዛሬው መርሀ ግብሬ በጣም ጥቂት ሰው ነው የሚያስፈልገኝ። በጣም ጥቂት ሰው። ቃል ትገባላችሁ። ያን ቃላችሁን ትልኩልኛላችሁ። እኔ ደግሞ የባንክ አካውንታቸውን እልክላችኋለሁ በዚያ ቀጥታ ታስገቡላቸዋላችሁ። በነገው ዕለት ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአቅሙ ይሳተፍ ዘንድ የባንክ አካውንታቸው በይፋ በቴሌግራም ገፄም፣ በመረጃ ቴሌቭዥንም ይለጠፋል።

• ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁኝ መጣሁ። ከጤፉና ከሰንጋው ነው የምንጀምር።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተዘጋጅታችሁ እደሩ።

"…ነገ ቅዳሜ ጠዋት ከዘወትር የእግዚአብሔር ምስጋና በኋላ ርእሰ አንቀጽ አይኖረንም። በርእሰ አንቀጹ ፈንታ እስከ ተቀበል የግጥም፣ የቅኔ ሰዓታችን ድረስ ሁላችሁንም ይዤ በሓሳብ ፈረስ ወደ ጎንደር በቀበሮ ሜዳ ትል ከላያቸው ላይ ወደሚረግፍባቸው ስደተኛ የጎንደር ዐማሮች አሰቃቂ መጠለያ ጣቢያ ሄደን እንደርስላቸዋለን። እሁድ ደግሞ በመረጃ ቲቪ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው መርሀ ግብሬ ላይ ከነገ የሚቀር፣ የሚጎድል ጎዶሎአቸውን ሁሉ እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል ድንጋይ ተሸክሜ ለምኜ እሞላላቸዋለሁ።

• ተፈናቃዮቹ ሕጋዊ የባንክ አካውንት አላቸው። ስዊፍት ኮድም ጭምር ስለወጣላቸው የምንለግሰውን ገንዘብ በቀጥታ በባንክ ነው የምናስገባላቸው። የምትለግሱት ገንዘብ ከእኔም ጋር ሆነ ከሌላ ከማንም ጋር ንኪኪ አይኖረውም።

• ለአዲስ ዓመት መግቢያ ለቅዱስ ዮሐንስ 5 ሰንጋ እንገዛላቸዋለን።

• እስከዛሬ መንግሥት ለወር 15 ኪሎ በቆሎ ብቻ ነበር ሰጥቶአቸው የሚበሉት። አሁን ግን አግኝተው ያጡ ናቸውና ባይሆን ለበዓሉ ማኛ የጤፍ እንጀራ እንዲበሉ አንድ 5 ኩንታል ጤፍ እገዛላቸዋለሁ።

• ሽንኩርት፣ በርበሬና ቅቤና ዘይትም እንገዛላቸዋለን።

• በስደተኛ ጣቢያው ውስጥ ላሉ ሕፃናት ተማሪዎች ቦርሳ፣ ደብተር፣ ዩኒፎርም እናሟላላቸዋለን።

• የተጀመረ ትምህርት ቤት አለ እሱን የጎደላቸውን ሲሚንቶ ብረት አጠናቀን ህፃናቱን ትምህርት እናስጀምራቸዋለን።

"…የካሊድን ግማታም ሸታታ ፍራሽ አስወግደን አዲስ ፍራሽ ከነአንሶላው ገዝተን ከአፈር ላይ እናነሣቸዋለን።

• ከሰውነታቸው የሚወጣውን ትል ብታዩ መፈጠራችሁን ነው የምትጠሉት። ማርያምን አዛኜን እኔ ዘመዴ እናንተን ይዤ እደርስላቸዋለሁ።

• የእኔ የሆናችሁ ጓደኞቼ ፈቃደኞች ናችሁ አይደል? የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለዐማራ ነው የጻፍኩት…!

"…ይሄ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የተባለ የጎጃም ዐማራ ሰው ይሄን በተናገረ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ነው ልቤን ብሎ አጣጥሮ የሞተው። ደፉት። እሱንም ቆርጥመው በሉት።

"…እርጉዝ፣ ድርስ ነፍሰጡር የዐማራ ሴት ሆዷ ተሰንጥቆ ጽንሱ በሚጥሚጣ በዳጣ በበርበሬ እየተጠቀሰ መበላቱን እኮ ራሱ ብአዴን እንዲህ ያምናል። ግን አንዴ ለመናፍስቱ ስለፈረመ ሳት ብሎት ስለዐማራ ችግር ቢናገር ሆዴን ብሎ ወዲያው በቁርጠት፣ ልቤን ብሎ በድካም ይወገዳል።

"…ከዚህ ዘሩ በመረሸን፣ በመታገት አይደለም ታርዶ በመበላት አላልቅ ካለ ነገድ ተወልዶ ለዚህ አራጅ መንግሥት ተገርዶ አሁንም በገዛ ቀዬው ከጠላት ጎን ቆሞ የሚገድልህን ዐማራ ማርከህ "ከየት ነው የመጣኸው? ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎ፣ ከሸዋ እያስባል ማስደስኮር አይከይፍም። የፋኖን ውጊያ እንዴት አየኸው? ከተማረክ በኋላስ አያያዛችን ምን ይመስላል? እስቲ ለሕዝቡ ግለፅ እያሉ ማናዘዝ ኢደብራል።

"…አሁን ደግሞ ሱማሌ ልዝመት፣ ለእናት ሀገሬ ይፈሳል እንባዬ እያለ ሄዶ በሴራ በጥቅሴ አፈር ከደቼም ሊበላ ይችላል ያልነቃው እከ የሆነው ዐማራ። ወዳጄ ልትጠፋ ያለች ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አይሰማ ነው የሚባለው።

"…በዐማራ ክልል ለሚካሄደው ጭፍጨፋ ዝምታን የመረጠ ቤርቤረሰብ ለምን በላ አይወርድበትም። መብረቅ ለምን አይፈጀውም። አይደለም መሬት መንሸራተት ገና መሬት ተከፍታ ትውጠናለች። እሳት ነው የሚነድብን። ዐማራ ላይ ለተፈጸመው ግፍ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአንድም በሌላም ይቀጣሉ። በራብ፣ በኑሮውድነት፣ በሰላም ማጣት በጭንቀት ይቀጣሉ። እንቅልፍ አይወስድህም። ነገርኩህ።

"…ግብፅ አትመጣም እንጂበግብፅም ብትመጣ ኦሮሙማው ከፈጸመብህ የባሰ ምንም አታመጣብህም። አለቀ።

• ዐማራ ቤትህን ሥራ። አለቀ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እግዚአብሔር ይመስገን። የብር ድልብስ ሪፖርት ላቀርብ ነኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬ የዕረፍት ቀኔ ነው። ዕለተ ሰኞን ለእኔ የዶርዜ ማርያም በሏት። የእሁድ ጩኸቴን፣ መወራጨቴን፣ ላቤን፣ ልፍለፋዬን ዕለተ ሰኞን በማረፍ ላካክሰው ከወሰንኩ እነሆ ዛሬ ሁለተኛ ሳምንት ሆነኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ሆኖም በጎንደር በቀበሮ ሜዳ ላሉት ወጎኖቻችችን የጀመርነውን ሥራ በቶሎ ጨርሰን ለሌሎቹ በደብረ ብርሃን፣ በወሎ፣ በደቡብ ለሚገኙ እንደርስ ዘንድ የጀመርነውን መጨረስ ስላለብን በመሃል የደረስንበትን ላስታውሳችሁ ብቅ እላለሁ።

"…እንደሚታወቀው አቶ ወርቁ አይተነው ትልቁን ሸክማችንን አቅልሎልኛል። ግማሽ ሚልዮን ብር በመለገስ መጪውን አዲስ ዓመት ተፈናቃይ ስደተኞቹ ደስ ብሏቸው እንዲውሉ ሰንጋውን፣ ፍየሉን፣ ውኃና የለስላሳ መጠጡን ለግሶልናል። አንድ ባልና ሚስቶች አምስት ኩንታል ማኛ የሆነ ነጭ ጤፍ አቅረበውልናል። ወድሜ ጆኒ ቅቤውንና ማገዶውን ችሏል። ማባያ፣ ሚጥሚጣ፣ በርበሬ፣ ሽንኩርቱ ሁሉ በአንድ ወንድም ተችሏል። ድንኳን፣ ወንበር፣ የኩሽና ዕቃም በአንድ ወንድሜ ተችሎ ብሩ ገቢ ሆኗል። በ6 ሰው የግብዣው ነገር ተጠናቅቋል።

"…አሁን የሚቀረን እነዚያን ህጻናቱን ትል የሚያወጣባቸውን የመኝታቸውን ጉዳይ በአዳዲስ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ መቀየር ነው። እሱን እየተረባረባችሁበት ነው። የደረስኩበትን ቀጥዬ እለጥፍላችኋለሁ። እሱን እንደጨረስን ትምህርት ቤታቸውን አቶ ወርቁ እኔ እፈጽመዋለሁ ስላለ እኛ ደግሞ ለተማሪዎቹ ሕፃናት ዩኒፎርም፣ ጫማና ካልሲ፣ ቦርሳ፣ ደብተር፣ እርሳስና እስክሪብቶ እናሟላላቸዋለን። በቅድሚያ ግን የጀመርነውን እንፈጽማለን።

"…ይሄን በቶሎ እንደጨረስን በቀጥታ ከጳጉሜ 1-5 በደብረ ብርሃን፣ በወሎ፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአፋር የሚገኙትን ሌላው ቢቀር ሰንጋ በማቅረብ እንጎበኛቸዋለን። የዚያ ሰው ይበለን።

• የምትችሉትን ጻፉልኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ነጭ ነጯን ጀምረናል…

• አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እስከ አሁን…

"…412 አንሶላ፣ 260 ብርድልብስ፣ 170 ፍራሽ ተችሏል።

"…ዝናሽ ከቤሩት ~ በ2000 ዶላር 60 ፍራሽ፣
ኃይል ጊዮርጊስ ከካናዳ ~ በ1000 ዶላር 30 ፍራሽ፣ ኖሐ ከአሜሪካ በ1000 ዶላር 30 ፍራሽ ብዙ በመግዛት ይመራሉ። የሰፈሬ ልጆች ቢኒ ከደጃች ውቤ ከሀገረ ለንደን 80 ብርድልብስ ከፌ የደጃች ውቤ ከሜሪላንድ 83 ብርድልብስ ችለውኛል። አንተነህ ከለንደን በ150 ሺ ብር ለ300 አንሶላ መግዣ ለግሷል። ሳሙኤል 1 ብርድልብስ፣ ሃኒም 1 ብርድ ልብስ ለግሰዋል። እግዚአብሔር ለሁላችሁ ይስጥ።

የአንዱ ፍራሽ ዋጋ 3500 ብር ነው
የአንዱ ብርድልብስ ዋጋ 600 ብር ነው
የአንዱ አንሶላ ዋጋ 500 ብር ነው።

"…በጎንደር በቁማቸው ትል በላቸው ወገኖች እርዱ። አንዳንድ ቪ ዶላር፣ አምስትም ሦስትም ሺ ዶላር፣ አቅም ያላችሁ እጃችሁን ዘርጉላቸውና በትል ከመበላት ታደጉአቸው።

• እንዲሰጥህ ስጥ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እልል በሉልኝማ…

• እስከአሁን ያገኘሁትን ልንገራችሁማ። 

ከአንሶላ ልጀምር…

አንሶላ… 3 ወዳጆቼ ገዝተዋል።

አንተነህ ከለንደን ~   300
ሰለሞን ፈለቀ ባህርዳር ~ 5
ሃኒ ~ 1
ድምር = 306

ብርድ ልብስ
• ቢኒ ከለንደን ~ 80 ብርድልብስ
• አሜን ዳኒ~ 5
ድምር=  85

ፍራሽ
• ኖህ አሜሪካ በ 1000 ዶላር
34 ፍራሽ
• ዶር ወዳጄ ሽመልስ~ 10
አመሊታ~ 10
ቲጂ ~ 20
ብርሃነ መስቀል ~4
ኤልሳ~6
ድምር 80 ፍራሽ


• ይቀጥላል። የብርድልብስና የአንሶላ ፋብሪካውን ባለቤቶች አግኝቻለሁ። እነሱንም ቀጥቼ፣ አስቀንሼ አግዛለሁ። በዚያ ላይ ጎንደሬዎች ናቸው። አከተመ

• እንረባረብ…🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የ 39 ደቂቃ የድምፅ መልእክት ናት። ሰብሰብ ብላችሁ አድምጡልኝማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አንድ ሺ አመስጋኝ እግዚአብሔር ይመስገን ካላለ በቀር ወደ ሌላ ሥራ እንደማልገባ ይታወቃል። ዛሬ እኔም ነጋ አልነጋ እያልኩ ሌሊት ነው የተነሣሁት። እናንተም በጊዜ ነው 1ሺውን ምስጋና የሞላችሁት። እንግዲህ ከምስጋናው ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ዛሬው አጀንዳችን ነው።

"…የዛሬው አጀንዳችንም ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ነው የሚወስደን። እነዚህ በምሥሉ ላይ የምታዩአቸው የጎንደር ዐማራ ሕፃናት በቁማቸው የትል መፈልፈያ የሆኑ ሕፃናትን የመታደግ ዘመቻ ላይ ነው ተሰልፈን የምንውለው።

"…ለስደተኞቹ 50 ሎሚ ለ 1 ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ግን ጌጡ ነው እንደሚባለው ሁሉ ሲያዩት ለአንድ ሰው የሚከብደው ለብዙ ሰው ይቀለዋልና በዚያ መንገድ ችግራቸውን ተረባርበን እንፈታዋለን።

"…እኔ ለራሴ እንጂ የማልሆነው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለአባቶቼ ገዳማውያን፣ ለስደተኞች፣ ለተቸገረ፣ ለተጨነቀ ሰው ለምኜ አፍሬ አላውቅም። እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ተዘጋጁ። የእርዳታ አሰጣጡን ቀጥዬ እጽፍላችኋለሁ። በተለይ፣ በዶላር፣ በዩሮ፣ በዲናር፣ በፓውንድ የምትሰጡ ሰዎች የብዙዉን ቀዳዳ ትሸፍናላችሁ። ለመስጠትም እኮ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ። በተለይ ሕፃናት ልጆች ያላችሁ አግኝቶ ከማጣት ፈጣሪ ይጠብቃችሁ።

• የእኔዎቹ ዝግጁ ናችሁ አይደል…? አንድ 100 ያህል ሰው ፈቃደኝነቱን ካሳየኝ ማብራሪያዬን እቀጥላለሁ። አያችሁ እግዚአብሔር ሲፈቅድ በቴሌግራም ጽሑፍ ብቻ ያለምንም ጩኸት እግዚአብሔር ሥራውን ሲሠራ…?

• ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ለነገ እነዚህን አስፈላጊ ቁሳቁሶች ለጎንደር ለቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች ለሟሟላት እያሰባችሁ ተዘጋጅታችሁ እደሩ።

"…በህፃን በዐዋቂዎቹ ገላ ውስጥ የሚርመሰመሰውን ትላትል ለማጥፋት መሬቱን በሲምንቶ እንቀይረዋለን። ፍራሽም አንሶላም እናሟላላቸዋለን። ጽዱ አካባቢ ስንፈጥር ትላትሉ ይጠፋል። አለቀ።

"…ህፃናቱ ትምህርት ቤቱ ከተሠራላቸው ይማራሉ። ሲማሩ ደግሞ መሃይም ሆነው አይቀሩም። ለዚህ ደግሞ ለሁሉም ሕጻናት የትምህርት መርጃ መሣሪያ እናሟላላቸዋለን።

"…ነገጠዋት የእያንዳንዱን ዋጋ እጽፍላችኋለሁ። ለአንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ወጪም እጽፍላችኋለሁ። እናንተ መሻማት ነው። መረባረብ ነው።

"…ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸውን ቁሳቁሶች በፋብሪካ ዋጋ የሚሸጥልኝ ካገኘሁ እመርቀዋለሁ። አገናኙኝ፣ ወይ ደግሞ ጠይቁልኝ። አደራ፣ አደራ። አደራ። በማርያም።

• ፍራሽ
• ብርድ ልብስ
• አንሶላ
• ደብተር
• እስክሪፕቶ
• እስራስ
• ሸራ ጫማ
• ዩኒፎርም
• ሲሚንቶ
• አሸዋ
• ቆርቆሮ

"…ይሄን ወዳችሁ ሳይሆን በግዳችሁ በነገው ዕለት ተረባርባችሁ የምታጠናቅቁት ይመስለኛል። ኮሚቴ የለ፣ ጎፈንድሚ የለ፣ አንበሳ አውርዱልኝ የለ። በቃ በጥቂት እግዚአብሔር በፈቀደላቸውና በተመረጡ ሰዎች ይጠናቀቃል። ደኅና እደሩልኝ። የነገ ሰው ይበለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አልጨረስኩም ገና ምኑ ተነካና…

"…ወደ ዋናው አጀንዳችን እየተንደረደርኩ ነው። የሕጻኗ የመራቢያ አካል ለለሚታይ ሙሉ ፊልሙን አላሳያችሁም። ነገር ግን ይሄ በፌስታል ውስጥ የምታዩት መኮሮኒ የሚያካክል ትል ከሰውነቷቸው ውስጥ ተለቅሞ፣ ሰውነታቸው ተቀድዶ የሚወጣ ትል ነው።

"…አፈር ላይ ስለሚተኙ፣ ፍራሽ ብርድልብስ ስለሌላቸው ነው። መሬቱን በሲምንቶ ቀጭን ፍራሽም ብንገዛላቸው ከዚህ ሁሉ ስቃይ ይድናሉም ይወጣሉም።

"…ማርያምን ጎንደር ሰው አጥታ የሰው ደሃም ሆና አይደለም። ዕድሜ ለመላኩ ተፈራ እሱን ሽሽት ከሁሉ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ ከሀገር የወጣው የተሰደደው ጎንደሬ ነው። ነገር ግን ማን ያስተባብረው? ማን ይሰብስበው። የጎንደር አክቲቪስቱም ሲበዛ ራስ ወዳድ ጉረኛም ነው። በቤቱ ያለውን ገመና ሳይሸፍን በውጭ በሌላ በማያገባው የሚደክም ጉረኛ ይበዛዋል። ያ ሆኖ ነው እንጂ ጥቂት ጎንደሬዎች ለዚህ በቂ ነበሩ።

፩ኛ፦ ለተማሪዎቹ ትምህርት ቤት ያስፈልጋቸዋል። የተጀመረ ትምህርት ቤት አለ እሱን አጠናቅቅላቸዋለሁ። ወንበር፣ ሰሌዳ ሳይቀር አሟላላቸዋለሁ።

፪፦ 3,500 ሕፃናት ሙሉ ዩኒፎርም፣ ሸራ ጫማ፣ ደብተርና ቦርሳ እገዛላቸዋለሁ። ይሄንም አደርገዋለሁ።

፫ኛ፦ መሬቱን ሲሚንቶ፣ መኝታቸውን ፍራሽና አንሶላ ብርድልብስም እንዲኖራቸው አደርጋለሁ። ወላዲተ አምላክ ትረዳኛለች አደርገዋለሁ። አሁን ከእነዚህ ላይ 1 ሚልዮን ብር ይሠረቃል? ይወሰዳል? ነውር ነው።

"…ለጎንደር እኔ ዘመዴ ብቻዬን እበቃታለሁ። ሾተላይዋን እነቅለዋለሁ። መርገምቶቿን አርቃለሁ። የጎንደር ዐማራን ስንፍናም ለዓለም እገልጠዋለሁ። እወቅሳቸዋለሁ። በጭቃ ዥራፌ እዠልጣቸዋለሁ።

• ተራ በተራ እያሟላን እንሄዳለን። እግዚአብሔርም ይረዳናል። ልጁን የሚወድ ከእኔ ጎን ይቆምና የእነዚህን ህፃናት ሰቆቃ ያስወግዳል።

• አዛኜን አላለቅስም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ደጋግሞ ደወለ። ሰዓቴን አየሁ። አሜሪካ ስሔድ ከቀሲስ ሳሚ ጋር ተጨቃጭቆ ከቤቱ አድሬአለሁ። በደወለበት ሰዓት እሱ ጋር ሌሊት ነው። ለምን እንደደወለ ገባኝ። እኔ ደግሞ ከግማሽ ሚልዮኑ ብር ለጋሽ ጋር እያወራሁ ነበር። ስጨርስ እደውልለታለሁ ብዬ ዝም አልኩ። ቆይቼ የምጥልበትንም ዕዳ የማሸክመውንም ሸክም እያሰብኩ ደወልኩለት።

እ…አልኩት… ምን ፈልገህ ነው?

~ እዘዘኛ ዘመዴ። ከበረከቱ ልሳተፍ።

• ቅቤ አለ። ቅቤውን ውሰድ።

• ስንት ኪሎ ነው?

• 5 ኪሎ፣ ኪሎው በ950

• 4,750 ብር ብቻ

~ አዎ።

• ኧረ አልቀበልም ጨምር።

• ማገዶ አለ። 30 ሺ ብር

~ ሌላም ጨምር።

• በቃ ይበቃሃል ጆዬ፣ ውዷ ባለቤትህን ወይኒን ሰላም በልልኝ። ሌላውን እንዲሁ እነግርሃለሁ።

~ እሺ የጎደለ ነገር ካለ ንገረኝ። ይሄ ግን ያንሣል።

• በል ጥፋ ድራሽ አባክ አይጥፋና ጥፋ።

"…የማገዶው ነገር ተጠናቅቋል። ቅቤውም ተትረፍርፏል። በሉ አሁን ደግሞ ከዚያው ከአሜሪካ የሌላ ወዳጄ ስልክ መጥቶብኛል። ምን ልትለኝ ይሆን ደግሞ።

• እልልልል እያላችሁ ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰንጋና የፍየሉ ነገር…

"…የእንጀራውን ጉዳይ ከዘጋን በኋላ ቀጣዩ ሰንጋ ነበር። አንዱን ሌላ ቦታ ላሉ የአእምሮ ውስንነት ላለባቸው ተረጂዎች ልክ እንደ ጤፉ ነበር ለማካፈል የፈለጉት። እንግዲያውስ 3 በሬ ይበዛ ይሆን አሉኝ። 4 አድርጌላችኋለሁ አልኳቸው። በአጠቃላይ 5 ሰንጋ ማለት ነው። ምድር ቀውጢ ሆነች በቀበሮ ሜዳ።

"…ይሄን ጉዳይ እኮ ገና ወደ እናንተ አምጥቼ  ዋይዋይ እሪ ኡኡም ቁቁም ብዬ ድንጋይ ተሸክሜ ልለምን ነው። ድፍረቴ ግን አይጣል ነው። ሰው በሰው ኪስ እርግጠኛ ሆኖ እንዴት በሙሉ ልብ ደረቱን ነፍቶ ቃል ይገባል? ልክ እንደራሴ ኪስ መዝረጥ አድርጎ እንደሚሰጥ እኮ ነው የምጎርረው። 😂 አይ ዘመዴ እውነትም መራታ የሀረርጌ ቆቱ እኮ ነኝ።

"…ዋጋ ንገሩኝ አልኩ። ነገሩኝ። የአንዱን በሬ ዋጋ በጎንደር 50 ሺ፣ የፍየሉ 3ሺ×5=15 ሺ አጠቃላይ 265ሺ ብር። ካላስ ሽግር የለም ፍጥጥ ብዬ መለመን ነው አልኩኝ።

"…ቆይቶ ስልኬ ላይ ተደወለ። አነሣሁ። ስሜ ይቆይ አሁን የለጠፍከውን የቀበሮ ሜዳ ስደተኞች ጉዳይ ሰምቼ ነው አሉኝ። እናስ አልኳቸው። እናማ እዘዘኝ። ለበዓሉም፣ ከበዓሉም ውጪ አሉኝ። ለበዓሉ ጤፍ ተችሏል። አሁን 5 ሰንጋ እና 5 ፍየል ነው የምፈልገው። እርስዎ ደስ ያልዎትን ይምረጡና አንዱን ይግዙ አልኳቸው። የአጠቃላዩ ዋጋ ስንት መጣ ማለት ነው አሉኝ። 265ሺ አልኳቸው። በቃ የባንክ ሂሳባቸውን ላክልኝ። ስደተኞቹ በዓልን ሁሉ ተሟልቶላቸው ተደስተው መዋል አለባቸው አሉኝ። ማንልበል ጌታዬ? እገሌ ነኝ። ኡኡኡኡኡ። እርስዎ ነዎት። መልካም ብዬ የባንክ ቁጥሩን ከነደብተሩ ላኩላቸው።

"…ግማሽ ሚልዮን ብር ይደርሳቸዋል። ንገራቸው አሉኝ። 500 ሺ ብር ማለት ነው? አልኩኝ ጆሮዬን እየተጠራጠርኩ። አዎ አሉኝና ሰላም ሁን፣ በርታ ብለው ስልኩን ዘግተው ተሰናበቱኝ።

• እቀጥላለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተመልሼ መጣሁ…

"…ይሄን ፎቶ ታስታውሱታላችሁ አይደል? አሜሪካ ከሚገኙት ወንድሞቼ ማኅበረ ካህናት ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ከጭፍጨፋ ለተረፉ ወጎኖቻችን እስከዛሬ ፊልሞ ተቆርጦ የምሰደብበትንና እያለቀስኩ፣ እያለቀስንም ዕርዳታ ሳስተባብርላቸው በነበረ ጊዜ የተነሣሁት ፎቶ። በቤቴ ኢንተርኔት ስለሌለኝ አንድ ወዳጄ ቤት ሄጄ፣ ኢንርኔት ሰጥቶኝ ሳስተባብር። አስተባብሬም ከጨረስኩ በኋላ በእኩለ ሌሊት በመቃብር ስፍራ አልፌ፣ ጫካና ወንዝ አቋርጬ፣ ከቀሲስ ሳሙኤል፣ ቀሲስ ሱሬና ቀሲስ ያሬድ ጋር በቪድዮ እያወራሁ ወደቤቴ የምሄድበትን ጊዜና ዘመን ነው ያስታወሰኝ። አሁን ግን ኢንተርኔትም ማረፊያ ቤትም አለኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…አሁን በቀጥታ ወደ ሥራችን ነው የምንገባው። ደግሞም የምሥራችም አለኝ። ገና ልመና ሳልጀምር ወዳጆቼ መተንፈሻ አሳጥተውኝ ጉድ ሆኜአለሁ። በፈረንጅ ሀገር እኔ ባለሁበት የምረብሸው ጎረቤት ስለሌለኝ ነው እንጂ እልልታዬ ና ጩኸት ጭፈራዬን የሰማ ሰው ቢኖር ፖሊስ ወይ አምቡላስ ሳይጠራብኝ ይቀራል ብላችሁ ነው? ደስ ብሎኛል።

"…ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ገና ምኑም ሳይጀመር በደስታ እየቀወጡት ነው። ከምር እኔ ዘመዴ እኮ ዕድለኛ ነኝ። የጎንደርን በድል ስጨርስ ደግሞ ወደ ሌላ ስፍራም አቀናለሁ። በወር በወር ቢያንስ እንዲህ ዓይነት የበጎሥራ መሥራትም አለብን። እናደርገዋለንም። ስትሰጡ ደግሞ በደስታ ስጡ። ከጉድለታችሁ ስጡ። ስደተኛን መርዳት፣ አግኝቶ ያጣን ሰው መርዳት ለጤናም እጅግ ጠቃሚ ነው። ምርቃቱም ቢሆን ለልጅ ልጅ ነው የሚተርፈው።

• ልጀምር ነኝ። ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤ እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፤ እውነትን ለዘላለም የሚጠብቅ፤ ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታል፤ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድሀ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል፤ የኃጢአተኞችንም መንገድ ያጠፋል። እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ። መዝ 146፥ 5-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከጨነቀው ከአትክልተኛው አቢይ አሕመድ ብሮባጋንዳ አልፈው አይመጡም አይሞክሯትም እንጂ ግብጽና ሶማሊያ ቢመጡ እንኳን ዐማራን ብቻ መርጠው እንደ ኦሮሙማው እንደዚህ ይጨፈጭፉታል ብላችሁ ታስባላችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዛሬውን ትን የሚያስብል ትንታኔ የተንፀባረቀበትን ርእሰ አንቀጻችንን 20 ሺ ሰው አንብቦት ምንም ብው ብሎ የተናደደብኝ ሰው እንደሌለ ነው የቴሌግራም ካምፓኒያችን ሪፖርት የሚያሳየኝ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሚናደደብኝ ሰው እያጣሁ ወይም የሚናደድብኝ ሰው ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ ቅሬታ እንደገባኝ፣ እያዘንኩም እንደሆነ ሳልገልፅ አላልፍም።

"…መልካም እንግዲህ እኔ ዘመዴ የደብተራው ልጅ በቀኝ ትከሻዬ ሽከካ መሠረት የሸከከኝን ነገር፣ የተሰማኝንም ስሜት በርእሰ አንቀጽ መልክ ተንፍሻለሁ። ቀጥሎ ደግሞ ተራው የእናንተ ነው። በገባችሁ በተረዳችሁ መጠን በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን የምትገልጹበት ሰዓት ነው። እኔ ደግሞ እስከማታ ድረስ የእናንተን አስተያየት እየኮመኮምኩ ምሽቴን ደማቅ አድርጌ አመሻለሁ።

"…1…2…3…ጀምሩ…

Читать полностью…
Subscribe to a channel